You are on page 1of 3

የተግባር ዕውቀት አልባ አድርጎ የቃል ዕውቀት የሚያንበሸብሸው የት/ት ስርዓታችን

የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት በፌደራልና በክልሉ መንግስት ቁጥጥር ይመራል፡፡ በህገ-መንግስቱ ለውጥ
ከተደረገ በኋላ አንዳንድ ጉዳዮች በክልል በኩል እንዲወሰኑ ተላልፏል፡፡ የፌደራል መንግስት የክልል የት/ት ፖሊሲ
አያወጣም እንደህጉ፡፡ ነገር ግን በፌደራልና በክልል የስርዓት ልዩነት የለም፡፡

መንግስት የት/ት ስርዓት አግባብነቱንና የዓለም አቀፍ እስታንዳርን ጠብቆ ለውጥ ሊያደርግ ሲገባ በየጊዜው
ያለምክንያት ይለዋወጣል፡፡ አንድ ሰሞን አስር ሲደመር ሶስት አለ፣ በሌላ ጊዜ ሌቭል ሦሥት እና አራት አለ፣
እንደገና ከአስረኛ ክፍል የጨረሱት የብቃት ችግር ስለሚታይባቸው የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ያስፈልጋቸዋል
አለ፣ የዲግሪ ፕሮግራሞች አንዳንድ ዓመታት ይቀነስባቸው አለ፣ ተማሪ ተኮር ስርዓት አለ፣ በፕላዝማ ከ 7-12
ያሉ ተማሪዎች ይማሩ አለ፣ የተማሪ መምህራን ተዋፅዖ 1 ለ 17 ይሁን አለ፣ የመምህራን ግምገማ ያስፈልጋል
በደንብ እንዲያስተምሩ አለ፣ ለመምህራን አጫጭር ስልጠና ያስፈልጋቸዋል አለ እና የመሳሰሉትን አለ፡፡

ስለዚህ የትምህርት ሥርዓቱ አነዚህን ችግሮቸ እንዲያስተካክል ስርዓቱ ከፖለቲካ ነፃ ሆኖ በትምህርት ዘርፍ ያሉ
ምሁራን የአለም አቀፍ እስታንዳርድን ጠብቀው ሊሚሩ ይገባል፡፡ ጠንካራ ዕውቀት የሌላቸው ዜጎች ሲበዙ ከ 2-
3 ትውልድ ለዕውቀት ዕጦት ሠለባ ይዳረጋል፡፡ ከታች የቀረቡት በሥርዓቱ ላይ የሚታዩ ችግሮችንና የመፍትሄ
ሃሳቦችን ይጠቅሳሉ፡፡

በመንግስት ትምህርት ተቋማት የሚታዩ ችግሮቸ

1. በአንድ የመማሪያ ክፍል 2 እና 3 ጎበዝ ተማሪዎች ብቻ መኖር…. ትኩረት የማያደርጉ ሰነፍ


ተማሪዎች መብዛት

2. የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚ ተማሪዎች ቁጥር መብዛት

3. ከተበላሸው የት/ት ስርዓት የተወራረደ የመምህራን ብቃት መውረድ

4. በፖለቲካዊ አስዳደር ስር መውደቅ

5. በአንድ የመማሪያ ክፍል ብዙ ተማሪዎችን ማጎር

6. ተማሪ-ተኮር በሚል ፖሊሲ መምህራን ተማሪዎችን በደንብ እንዳያስተምሩ ማድረግ

7. የመምህር አመላመል ያለበቂ መስፈርት ማድረግ

8. የስነ-ምግባር ደንብ በማውጣት ተማሪዎችን በስነ-ምግባር አለማነፅ…..ፀጉር ማንጨባረር፣ ልቅ


አለባበስና የሱስ ተጠቂ መሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪነት መገለጫ አድርጎ መውሰድና
በተከታዩ ትውልድ መቀበል

9. የት/ት ሙስና መበራከት……በፈተና፣ በውጤትና በነጥብ ሙስና መጨመላለቅ

10. ጠንካራ የተግባር መለማመጃ አሰራር አለመኖር


11. በየጊዜው ያለምክንያት የት/ት ፖሊሲ እስታንዳርዱን ያልጠበቀ ለውጥ ማድረግ

12. በተቋማት ዙሪያ የሚገኙ የአደንዛዥ ዕፅ ማቀጣጠያ ቤቶችን አለማስቆም

13. በተቋማት ዙሪያ የሚገኙ ሴት ወጣቶች ለጅብ ወንዶች የሚደልሉ ሰዎችንና ቤቶችን አለማስቆም

14. በተቋማት ዙሪያ የምሽት ክበቦች እንዳይፈቀዱ አለማድረግ

15. ጥራት ካለው ምሩቃን ይልቅ ብዛት ያለውን ምሩቃን በማስመረቅ ማመን

16. የት/ት ጥራትን በግምገማ ለማስተካከል መሞከር….ብዙ ውስጣዊ ችግሮች እያሉ

17. የት/ት ጥራትን ከመምህራን የት/ት ደረጃና ተዋፅዖ ጋር ብቻ ማገናኘት….50% ዲግሪ፣ 40%
ማስተርስ እና 10% ፒኤቸዲ በሚል

የግል ት/ት ተቋማት ችግሮች


1. የተማሪዎች ምልመላ የት/ት ሚኒስቴር መስፈርትን ያልጠበቀ መሆን

2. መምህራን ምልመላ የት/ት ሚኒስቴር መስፈርትን ያልጠበቀ መሆን

3. ጠንካራ የተግባር መለማመጃ አሰራር አለመኖር

4. የመማሪያ ማስተማሪያ ማቴሪያሎች አለማሟላት

5. በትምህርት ሙስና መጥለቅለቅ

የትምህርት ስርዓት ለውጥ የሚደረግባቸው ጉዳዮች

1. ዓለም አቀፍ እስታንዳርድን የጠበቀ ወጥነት ያለው የትምህርት ስርዓት ለውጥ ማድረግ
2. በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የወጪ መጋራትን አሰራር ለጊዜው ማስቀረት
3. የትምህርት ስርዓቱ ከ 0I, 0II, 0III, 1, 2, 3,……,12 ክፍል ቢደረግ…..ዜሮ ክፍል እንደ አፀደ-ህፃናት
ትምህርት ተወስዶ ህፃናት 0a-በአምስተኛ ዓመታቸው፣ 0b-በስድስተኛ ዓመታቸው እና አንደኛ
ክፍልን በሰባተኛ ዓመታቸው ላይ እንዲማሩ ቢደረግ…..ፕሪፓራቶሪ ትምህርት በዋናው ስርዓት ተካቶ
ቢቀር
4. የአስረኛ ክፍል ስርዓት በማስቆም የቴክኒክና ሙያ ትምህርቶች አስራ ሁለተኛ ክፍል ላጠናቀቁ
ተማሪዎች ቢደረግ
5. የብቃት ማረጋገጫ ፈተናዎች የትምህርት ፕሮግራም ማብቂያ ላይ ቢደረጉ
6. በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የት/ት ዓይነት አመዳደብ ተማሪዎቸ ባላቸው ሀገር-ዓቀፍ ፈተና
ውጤትና ዝንባሌ ቢደረግ…ያለፍላጎቱ የገባ ተማሪ በጥሩ ሞራል ስለማይማርና ወደፊትም በሞራል
በተማረው ት/ት ህዝቡን ስለማያገለግል
7. በየሁሉም የት/ት ተቋማት የካውንስሊንግና ጋይዳንስ ባለሙያ ተመድቦ የተማሪዎችን ዝንባሌ
ተከታትሎ በዝንባሌያቸው እንዲበረቱ ማስደረግ
8. የዲግሪ ፕሮግራሞች እንደ ት/ት ዓይነቱ ሆኖ አራትና ከአራት ዓመት በሚበልጥ የት/ት ዘመን ቢደረግ
9. ዓለም አቀፍ እስታንዳርድ ስር የሌሉ የት/ት ዘርፎችን ማቋረጥ
10. ሁሉም የዲፕሎማ ፕሮግራም ሦሥት ዓመት የት/ት ዘመን ቢደረግ
11. በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የየት/ት ኮርሶች እስታንዳርድ ማስተማሪያ ሞጁሎች እንደዘጋጅ
ቢደረግ
12. የትምህርት ስርዓቱ ከፖለቲካው ሙሉ ለሙሉ እንዲነጠል ቢደረግ
13. ብቃት የሚያንሳቸው መምህራን በተማሩት ት/ት ወደ ሌላ የሥራ ዘርፎች ተዘዋውረው እንዲሰሩ
ቢደረግ
14. ከፍተኛ ነጥብ፣ ፍላጎት፣ የንግግርና የቋንቋ ክህሎት ያላቸው ምሩቃን በመምህርነት ከ 1 ኛ ከፍል
ጀምሮ ባለው የትምህርት ዕርከን ቢመደቡ…….የሚያውቀውን ለሌላው መግለፅ የማይችል መምህር
ሊሆን አይችልም
15. የሙያ ትምህርቶች ላይ በሙያው የሰሩ ምሁራንን መምህራን ማድረግ…ህክምና፣ መህንድስና፣……
16. የሌቭል ፕሮግራምን ሙሉ ለሙሉ መሰረዝ
17. አንዳንድ አግባብነት የሌላቸው የትምህርት መስኮች ላይ የስያሜ ለውጥ ቢደረግ….ሌቭል ወደ
ዲፕሎማ
18. የብቃትና የዕውቀት ክፍተት ያለባቸውን ከኮሌጅና ከዩኒቨርስቲ ለተመረቁ ምሁራን አጫጭር
ስልጠናዎችን በመስጥት ክፍተቱን መሙላት
19. የርቀት ት/ት ፕሮግራምን ለጊዜው ማስቀረት
20. እንደ ጤናና ምህንድስና ያሉ የሙያ መስኮች በመደበኛው የት/ት ፕሮግራም ብቻ እንዲሰጡ
ማስደረግ…ክረምት፣ ምሽትና ሻንዲውች ፕሮግራሞች ላይ ፈፅሞ ባይሰጥ
21. የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ልዩ ጥናት ተደርጎ ጥራት ያላቸውና ሀገራዊ ኃላፊነት
የሚሰማቸውን ብቻ ለይቶ ማስቀጥልና በጥብቅ መከታተል
22. የመንግስትና የግል የትምህርት ተቋማትን የሚከታተል ገለልተኛ የት/ት ጥራትን የሚከታተልና
የሚቆጣጠር ድርጅት ማቋቋም
23. የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በስነ-ምግባር እንዲታነፁ የስነ-ምግባር ደንብ በማውጣት መስራት

ከበላይ አበራ

You might also like