You are on page 1of 13

Daniel Fikadu Law Office

በኢ.ፌ.ዱ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃሊይ ትምህርት


ዘርፍ የትምህርት ቤቶች ፈቃዴ አሰጣጥ እና እዴሳት
መመሪያ ቁጥር 992/2016

Daniel Fikadu Law Office


መመሪያ ቁጥር 992/2016
በኢ.ፌ.ዱ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃሊይ ትምህርት ዘርፍ
የትምህርት ቤቶች ፈቃዴ አሰጣጥ እና እዴሳት መመሪያ

በሀገራችን በአጠቃሊይ ትምህርት ዘርፉ ስር ከተሰማሩ በውጭና በአገር ውስጥ


ባሇሃብቶች የሚቋቋሙ፣ በላልች ሀገሮች ያለ የኢትዮጵያ ማሀረሰብ ትምህርት ቤቶች
እና በሀገር ውስጥ ያለ የወጪ ሀገር ማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች የእውቅና ፈቃዴና
እዯሳት እንዱሁም ላልችም ተያያዥ የሆኑ አገሌግልት ሇመስጠት የሚያስችሌ
የአሰራር ስርአት ሇመዘርጋት፤ የትምህርት ጥራትን እንዱሁም ተዯራሽነትን ሇማረጋገጥ
አስፈሊጊ በመሆነ፤

ሇሀገሪቱ እዴገት የበኩሊቸውን አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ፥ በትምህርቱ መስክ


ሇመሰማራትና መዋእሇ ንዋያቸውን በዘርፉ ሇማዋሌ ሇሚፈሌጉ ሰዎችና የተሇያዩ
አካሊት ምቹ ሁኔታ ሇመፍጠር፣ ሇተሇያዩ ዜጎችም አማራጭ የትምህርት እዴሌ
ሇመፍጠር እና የእውቀት ሽግግር እንዱኖር ማዴረግ በማስፈሇጉ፣

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር የፌዯራሌ አስፈጻሚ አካሊትን ስሌጣንና ተግባርን


ሇመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2013 አንቀጽ 34 (1) (ሇ እና ሸ) እና 19(4)
መሰረት ይህንን መመሪያ አውጥቷሌ ፡፡

ክፍሌ አንዴ

ጠቅሊሊ ዴንጋጌ

1. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ “የአጠቃሊይ ትምህርት ዘርፍ የትምህርት ቤቶች ፈቃዴ አሰጣጥ እና
እዴሳት መመሪያ ቁጥር 992/2016” ተብል ሉጠቀስ ይችሊሌ፡፡

2. ትርጓሜ
የቃለ አገባብ ላሊ ትርጉም የሚያሰጠው ካሌሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፤

Daniel Fikadu Law Office


1/ “ፈቃዴ” ማሇት በአጠቃሊይ ትምህርት ዘርፍ ሇሚሰማሩ ተቋማት የሚሰጥ
የትምህርትና ሥሌጠና የሥራ ምዝገባ ነው፤

2/ “እውቅና” ማሇት ተቋማዊ ኢንስፔክሽን በማካሄዴ በሚገኘው ውጤት መሠረት


ሇአጠቃሊይ ትምህርት ተቋማት የሚሰጥ የጥራት ማረጋገጫ ነው።

3/ “ባሊስሌጣን” ማሇት የትምህርትና ስሌጠና ባሇስሌጣን ነው ፤


4/ “ፈቃዴ እዴሳት’’ ማሇት በዚህ መመሪያ የትምህርት መርሃ ግብሩ እንዱቀጥሌ ባሇው
ወቅታዊ አፈጻጸም መሰረት በማዴረግ ሇተቋሙ የሚሰጥ የፈቃዴ እዴሳት ነው፤
5/ “ፈቃዴ መሰረዝ’’ ማሇት በተሰጠው ፍቃዴ መሰረት ተቋሙ ያሇመስራቱ
በባሇስሌጣኑ ሲረጋገጥ የሚወሰዴ አስተዲዯራዊ እርምጃ ነው፤
6/ “የዯረጃ ማሳዯግ ፈቃዴ” ማሇት ትምህርት ቤቱ በሚያቀርበው ጥያቄ መነሻነት እና
በተቋሙ ያሇውን ነባራዊ ሁኔታ መሰረት በማዴረግ የሚሰጥ የትምህርት እርከን ማሳዯግ
ነው፤
7/ “የማስፋፊያ ፈቃዴ” ማሇት ትምህርት ቤቱ በሚያቀርበው ጥያቄ መሰረት በተቋሙ
ያሇውን ነባራዊ ሁኔታ እና እንዲስፈሊጊነቱ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ፈቃደን
መሰረት በማዴረግ የሚሰጥ የቅርንጫፍ ጭማሪ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት
ነው፤
8/ “ወሊጅ፣ ተማሪ፣ መመምህር ህብረት” ማሇት የወሊጅ፣ ተማሪና መምህራንን ያካተተ
ሇትምህርት ስራው አጋዥ የሆነ አዯረጃጀት ነው፤
9/ “ሌዩ ፍሊጎት” ማሇት በአካሌ ጉዲተኝነት፣ ሌዩ ተሰጥኦ ያሊቸው ወይም በላልች
ሁኔታዎች ሌዩ ዴጋፍ የሚያስፈሌጋቸው ተማሪዎች ነው፤
10/ “በኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ማህበረሰብ ትምህርት ቤት” ማሇት በኢትዮጵያ የሚኖሩ
የአንዴ ላሊ ሀገር ዜጎች ሌጆቻቸውን በሀገራቸው ስርዓተ ትምህርት ሇማስተማር
የሚያቋቁሙት ትምህርት ቤት ሆኖ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሇ በዚያ ሀገር ኤምባሲ ወይም
ቆንስሊ ፅ/ቤት ባሇቤትነት ወይም እውቅና የተቋቋመ ነው፡፡
11/ “በውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት” ማሇት በውጭ ሀገር የሚኖሩ
ኢትዮጵያውያን ወይም ትውሌዯ ኢትዮጵያውያን ተቋቁሞ በኢትዮጵያ ስርዓተ
ትምህርት መሰረት የትምህርት አገሌግልት የሚሰጥ ነው

Daniel Fikadu Law Office


12/ “ዓሇምአቀፍ ትምህርት ቤት” ማሇት በኢትዮጲያ ውስጥ የሚቋቋም ዓሇም አቀፍ
ምዝገባ፣ ሥርዓተ ትምህርት፣ ምዘና እና የጥራት ቁጥጥር ያሇውና ተግባራዊ የሚያዯርግ
ሆኖ በኢትዮጵያ ውስጥ የትምህርት አገሌግልት ሇመስጠት አግባብ ካሇው አካሌ ፍቃዴ
የተሰጠው ትምህርት ቤት ነው፡፡
13/ “የውጭ ባሇሃብት” ማሇት የውጭ ካፒታሌ ወዯ ኢትዮጵያ በማስገባት ኢንቨስት
ያዯረገ የውጭ ሀገር ዜጋ ወይም ሙለ በሙለ በውጭ ሃገር ዜጋ ባሇቤትነት የተያዘ
ዴርጅት ወይም ከሃገር ውስጥ ባሇሃብት ጋር በቅንጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በተቋቋመ
ዴርጅት ኢንቨስት ያዯረገ የውጭ ሀገር ዜጋ ወይም ዴርጅት ሲሆን እንዯ ውጭ
ባሇሃብት መቆጠር የፈሇገ መዯበኛ ነዋሪነቱ በውጭ ሃገር የሆነ ኢትዮጵያዊን
ይጨምራሌ፡፡
14/ “በውጭ ባሇሃብት የተቋቋመ ትምህርት ቤት” ማሇት በዚሁ አንቀጽ ንአስ አንቀጽ13
መሰረት የውጪ ባሇሃብት የተቋቋመ ትምህርት ቤት ነው፡፡
15/ "የበጎ አዴራጎት ትምህርት ቤት" ማሇት በሲቪሌ ማህበረሰብ ዴርጅቶች አዋጅ
ቁጥር 1113/2011 መሰረት በተቋቋመ በጎ አዴረጎት ዴርጅት የሚቋቋም ትም/ቤት
ሲሆን ሇጠቅሊሊ ህዝብ ወይንም ሇሶስተኛ ወገን መስራትን አሊማ አዴርጎ የተቋቋመ
ትምህርት ቤት ነው፡፡
16/ "ሇትርፍ ያሌተቋቋሙ ትም/ቤት" ማሇት ሇትርፍ ያሌሆነ በግሇሰብ ወይም
ማህበራት ወይም በህብረት ስራ ማህበራት ወይም በንግዴ ማህበራት ወይም አግባብነት
ባሇው ህግ የተመሰረተ ወይም በውጭ ሀገር ተመስርቶ በኢትዮጵያ ውስጥ ፈቃዴ
አግኝቶ የሚንቀሳቀስ የትምህርት ተቋም ነው፡፡
17/ "የትምህርት ቤት ክፍያዎች" ማሇት በተሇምድ ሇተማሪዎች ሇተሇያዩ
አገሌግልቶች፣ መገሌገያዎች ወይም የትምህርት ግብአቶች በትምህርት ተቋማት
የሚከፈለ የገንዘብ ክፍያዎች የሚመሇከት ሆኖ እነዚህ ክፍያዎች የትምህርት ፣
የምዝገባ፣ የሊብራቶሪ ፣ የመማሪያ መጽሀፍ ፣ የመጓጓዣ ክፍያዎች እና ላልች
በትምህርት ቤቱ በሚቀርቡ ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ሊይ ከመሳተፍ ጋር የተያያዙ
ክፍያዎችን ይጨምራለ።
18/‘‘ሚኒስቴር ወይንም ሚኒስትር” ማሇት የትምህርት ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው፤
19/ በወንዴ ጾታ የተመሇከተው የመመሪያው አገሊሇጽ የሴትንም ጾታ ይጨምራሌ ።

Daniel Fikadu Law Office


3. የተፈጻሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ በአጠቃሊይ ትምህርት ዘርፉ ስር በተሰማሩ ትምህርት ቤቶች ሊይ
ተፈጻሚ ይሆናሌ፡፡
4. የመመሪያው አሊማ
ሁለንም በአጠቃሊይ ትምህርት ዘርፉ ስር የተሰማሩ ትምህርት ቤቶችን ወጥነት ባሇው
የአሰራር ስርአት እንዱመሩ በማዴረግ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ነው፡፡

ክፍሌ ሁሇት
የተማሪዎች ቅበሊ እና ስርዓተ ትምህርት

5. በውጪ ሀገር የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት


1. በውጪ ሀገር የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት በውጭ ሀገር በኢትዮጲያ
ኢምባሲ የሚቋቋም ሆኖ በዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተማሪዎችን፤ የሚያስተምር
ትምህርት ቤት ነው፤
2. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 የተመሇከተው እንዯተጠበቀ ሆኖትምህርት ቤቱ
በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት ሇመማር የሚፈሌጉ በትውሌዴም በዜግነትም
ኢትዮጵያውያን ያሌሆኑ ተማሪዎችን መቀበሌ ይችሊሌ፡፡

6. በኢትዮጵያ የውጪ ሀገር የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች


1. የሀገራቸውን ዜጎች፣

2. የውጭ ሀገር ዜግነት ያሊቸውን ተማሪዎች እና


3. በውጭ ሀገራት ተምረው የመጡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎችን፤
4. በትምህርት ቤቱ የሚማሩ እህት ወይም ወንዴም ያሊቸውን ተማሪዎችን፤
5. ነፃ የትምህርት እዴሌ የሚያገኙ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ተቀብል
ማስተማር ይችሊሌ፡፡

7. ዓሇም ዓቀፍ ትምህርት ቤቶች

በኢትዮጵያውያን ወይም በላሊ ሀገር ስርአተ ትምህርት የተማሩ የውጪ ዜጎችን እና


ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ተቀብል ያስተምራሌ፡፡

Daniel Fikadu Law Office


8. በውጭ ባሇሃብት የተቋቋሙና በኢትዮጵያ ስርዓተ- ትምህርት የሚያስተምር ትምህርት
ቤት

ሀ. ኢትዮጵያውያንን ተቀብል ያስተምራሌ፣


ሇ. የውጭ ሀገር ዜግነት ያሊቸውን ተማሪዎች ተቀብል ያስተምራሌ፣
ሐ. የውጭ ሀገር ዜግነት ያሊቸውን ተማሪዎችን አግባብ ባሊቸው አካሊት የተሰጠ የጉዞና
የመኖሪያ ፈቃዴ እነዱሁም የአቻ ግመታ ማረጋገጫ እንዲሊቸው በማረጋገጥ ተቀብል
ያስተምራሌ፡፡
6. ስርዓተ ትምህርት አተገባበር

1/ የውጭ ሃገር ወይም የኢትዮጵያን ስርዓተ ትምህርት ሇመተግበር ፍቃዴ የወሰዯ


ትምህርት ቤት ስርዓተ ትምህርቱ የሚጠይቀውን ሁለ ይተገብራሌ፤
2/ ትምህርት ቤቱ በዚህ መመሪያ መሰረት ሇዯረጃው የሚገባ የትምህርት ማስረጃ
ይሰጣሌ፤
3/ በትምህርት ቤቱ የሚሰጡ ትምህርቶች ከማንኛውም የሀይማኖትና የፖሇቲካ
አመሇካከት ነፃ የሆነ፣ የሀገሪቱን ባህሌ እና ሌማዴ የማይፃረር መሆን አሇበት
4/ ኢትዮጵያ ውስጥ የተመዘገበ የውጭ ሀገር ማኅበረሰብ ትምሕርት ቤቶትና ዓሇም
አቀፍ ትምሕርት ቤት የሚገሇገሌበት ሥርዓተ ትምህርት ስራ ሊይ ከማዋሌ አስቀዴ
ከሚኒስትሩ ማረጋገጫ ማግኘት አሇበት
5/ የውጪ ስርአተ ትምህርት በመከተሌ ኢትዮጵያውያንን የሚያስተምር ትምህርት
ቤት ከፌዯራሌ የሥራ ቋንቋዎች መካከሌ እንዯ ነባራዊ ሁኔታው የሚመርጡትን ቋንቋ
እንዯ አንዴ የትምህርት አይነት የመስጠት፣ የማህበራዊ ሳይንስ እና የግብረ-ገብ
ትምህርቶችን ማካተት አሇበት፤

ክፍሌ ሶስት
የትምህርት ግብዓት እና አዯረጃጀት

7. መምህራን በተመሇከተ
1/ ትምህርት ቤቶች የሚቀጥሯቸው መምህራን ሇተመዯቡበት የትምህርት እርከን
የሚመጥን የትምህርት ዝግጅት፣ መሰረታዊ የማስተማር ስነዘዳ እውቀት ያሊቸውና
የማስተማር ሙያ ፍቃዴ የተሰጣቸው መሆን አሇባቸው፤

Daniel Fikadu Law Office


2/ ትምህረት ቤቶች የሚቀጥሯቸው የውጭ ሀገር መምህራን በመምህርነት ሙያ
ሇመቀጠር የሚያስችሌ እውቀት ያሊቸው፤ ህጋዊ የመኖሪያ እና የስራ ፍቃዴ ያሊቸው፤
አግባብነት ያሇው የትምህርት ማስረጃና የሞያ ብቃት ምዘና ምስክር ወረቀት ማቅረብ
የሚችሌ መሆን አሇበት ፤
3/ በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት የሚቀጠሩ የውጪ ሀገር መምህራንን
ሇመቅጠር የሚቻሇው፡-
ሀ. ተፈሊጊውን የትምህርት ዯረጃና የትምህርት መስክ የሚያሟሊ መምህር
በሀገር ውስጥ አሇመገኙቱን ማረጋገጥ ሲቻሌ፤
ሇ. የሀገሪቱን የጡረታ መውጫ እዴሜን ጣሪያ መሰረት በማዴረግ እና
ሐ. ከውጭ ሀገራት የተገኙ የትምህርት ማስረጃዎች ከመጡበት ሀገር
ትክክሇኛነት በሚመሇከተው አካሊት ህጋዊነቱ ተረጋግጦ ሲቀርብ ነው፤
4/ በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3(ሇ) የተዯነገገው ቢኖርም በውጭ ሀገር በጡረታ
መውጫ እዴሜ ጣሪያ የተገሇለ መምህራን በበጎ ፈቃዴ ከመምህርነት ውጪ
በአስተዲዯር ስራዎች አገሌግልት መስጠትን አይከሇክሌም፡፡
5/ በዚህ አንቀጽ የተቀመጡትን ቅዴመ ሁኔታዎች በማሟሊት የሚቀርቡ የበጎ ፍቃዴ
መምህራንን ትምህርት ቤቶች ተቀብሇው ማሰማራት ይችሊለ፡፡

8. የትምህርት ቤት አመራር
1/ የቅዴመ አንዯኛ ዯረጃን የሚያስተባብር ሃሊፊ በአጸዯ-ህጻናት ትምህርት ሙያ
የሰሇጠነ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያሇው መሆን አሇበት፤
2/ የአንዯኛ ዯረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር በትምህርት አስተዲዯር በመጀመሪያ
ዱግሪ /በመምህርነት ሙያ የሰሇጠነ ሆኖ የርእሰ መምህርነት መምርነት ስሌጠና የወሰዯ
እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያሇው መሆን አሇበት ፤
3/ የሁሇተኛ ዯረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር በትምህርት አስተዲዯር በሁሇተኛ
ዱግሪ /በመምህርነት ሙያ የሰሇጠነ ሆኖ የርዕሰ መምርነት ስሌጠና የወሰዯ እና
የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያሇው መሆን አሇበት፤
4/ የውጪ ሀገር ርዕሰ መምህር መቅጠር ሲያስፈሌግ ተፈሊጊው የትምህርት ዯረጃና
የትምህርት መስክ የሚያሟሊ በሀገር ውስጥ አሇመገኙቱን ማረጋገጥ አሇበት፤

Daniel Fikadu Law Office


5/ ከውጭ ሀገራት የተገኙ ርእሳነ መምህራን ህጋዊ የመኖሪያ እና የስራ ፍቃዴ ያሊቸው
እና የትምህርት ማስረጃዎች ከመጡበት አግባብ ካሇው ባሇስሌጣን ስሇ ትክክሇኛነታቸው
ተረጋግጦ መቅረብ አሇበት፣

9. ዴጋፍ ሰጪ ሰራተኞች

በትምህርት ቤቱ የአስተዲዯር ዴጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ቅጥር አግባብ ባሇው ህግ መሰረት


ተፈጻሚ ይሆናሌ፡፡

10. የትምህርት ቤት መሰረተ ሌማት

1/ ትምህርት ቤቱ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነዴ ወይንም የ5 ዓመት የኪራይ ውሌ ማቅረብ


ይጠበቅበታሌ፤
2/ ሇመማር ማስተማር ስራው ምቹና አስፈሊጊ የሆኑ የመሰረተ ሌማቶች፣ የመማሪያ እና
አገሌግልት መስጫ ክፍልቹ በተቀመጠ ስታንዲርዴ መሰረት በግብዓት ቢያንስ 75%
መሟሊት አሇበት፤
3/ ሇየዯረጃው የሚመጥንና የተሇያየ የትምህርት ቤት ግቢ ( ሇአፀዯ ህጻናት፣ ሇአንዯኛ
ዯረጃ፤ መከሰከሇኛ እና ሇሁሇተኛ ዯረጃ ማዘጋጀት፤
4/ የትምህርት ቤቱ የመማሪያ ህንጻው እና ግቢው ሌዩ ፍሊጎት ያሊቸው ተማሪዎችን
ያማከሇ መሆን አሇበት፡፡

11. የትምህርት ክፍያ

1/ ሇመመዝገቢያ የሚጠይቀው የገንዘብ መጠን ከወርሃዊ ክፍያ 25% መብሇጥ


የሇበትም፤
ትምህርት ቤቶች የማስመዝገቢያ ክፍያን ተግባራዊ ከማዴረጋቸው በፊት ሇተቆጣጣሪው
መስሪያ ቤት አቅርበው ይሁንታ ማግኘት አሇባቸው አሇባቸው፤
2/ የትምህርት ዘመኑ ከተጀመረ በኋሊ ትምህርት ቤት ማንኛውንም ክፍያ ጭማሪ
ማዴረግ አይችሌም፤

Daniel Fikadu Law Office


3/ ሇቀጣዩ የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ ሇማዴረግ የሚያስገዴዴ
ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ካጋጠመ የትምህርት ዘመኑ ከመጠናቀቁ 3 ወራት ቀዯም ብል
ሇወሊጆች ማሳወቅ አሇበት፤
4/ ትምህርት ቤቱ የትምህርት ክፍያ ጭማሪ ማዴረግ ያስፈሇገበትን ምክንያት በዝርዝር
በማቅረብ ከወሊጅ ኮሚቴዎች እና ቢያንስ ከ51% ከሚሆኑ ወሊጆች ጋር በመወያየት
የተዯረሰበትን የስምምነት በቃሇጉባኤ የተዯገፈ ሰነዴ ሇባሇስሌጣኑ ወይም ባሇስሌጣኑ
ሇወከሇው አካሌ በፅሁፍ ማሳወቅ አሇበት።

ክፍሌ አራት
ስሇ ፈቃዴ
12. ፈቃዴ ስሇመስጠት

ፈቃዴ ጠያቂው ትምህርት ቤት በዚህ ክፍሌ የተዘረዘሩትን ቅዴመ ሁኔታዎች አሟሌቶ


ሲገኝ ባሇስሌጣኑ ፈቃዴ ይሰጣሌ፡፡

13. በኢትዮጵያ የውጪ ሀገር የማህበረሰብ ትምህርት ቤት


1/ አግባብ ካሇው የመንግስት ተቋም አንዱሁም ከየአገሮቻቸው ኤምባሲዎች
በማህበረሰቡ ስም ስሇሚቋቋመው ትምህርት ቤት የተሰጠ የእውቅና ማረጋገጫ፣
2/ ከውጪ ጉዲይ ሚኒስቴር ጋር የተዯረገ የስምምነት ሰነዴ እና የትምህርት ቤቱን
ዯረጃ የሚመጥን ግብአቶችን ማሟሊት፤
3/ የሰው ሃብት ቅጥር፣ እዴገትና ስንብት፣ መረጃዎች እና አስፈሊጊ ሰነድች፤
4/ ሇትምህርት ቤትነት የሚመጥን አካዲሚያዊና አስተዲዯራዊ አዯረጃጀትን የሚያሳይ
ሰነዴ እና የትምህርት ቤቱ መተዲዯሪያ ዯንብ፣ የመመስረቻ ሰነዴ እና የራሳቸው
የትምህርት ካሊንዯር ሲያቀርብ ፍቃዴ የሚሰጥ ይሆናሌ፡፡

14. በውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት

1/ ትምህርት ቤቱ ከሚቋቋምበት ሀገር ጋር የተዯረገ የስምምነት ሰነዴ እና የትምህርት


ቤቱን ዯረጃ የሚመጥን ግብአቶችን ማሟሊት፤
2/ ሇዯረጃው የሚመጥን አካዲሚያዊና አስተዲዯራዊ አዯረጃጀትን የሚያሳይ ሰነዴ፤

Daniel Fikadu Law Office


3/ የትቤቱ መተዲዯሪያ ዯንብ እና የመመስረቻ ሰነዴ ሲቀርብ እውቅና የሚሰጥ
ይሆናሌ፡፡

15. ዓሇም ዓቀፍ ትምህርት ቤት


1/ የኢንቨስትመንት ፍቃዴ፤
2/ የንግዴ ፍቃዴ፤ ወይንም የስራ ፍቃዴ
3/ ስርዓተ-ትምህርቱ ከተዘጋጀበት በአገሪቱ ስርአተ ትምህርት መሰረት ሇማስተማር
የተሰጠ ፍቃዴ ወይንም ስምምነት፤
4/ የትምህርት ቤቱ መተዲዯሪያ ዯንብ እና መመስረቻ ሰነዴ፤
5/ ሇትምህርት ቤት የሚመጥን አካዲሚያዊና አስተዲዯራዊ አዯረጃጀትን የሚያሳይ ፤
ስሇተማሪዎች የትምህርት ክፍያ መምህራን ሉያሟለት ስሇሚገባው አነተስኛ መመዘኛ፥
ነጻ የትምህርት እዴሌ ስሇሚሰጡበት ሁኔታ፣ የመምህራን እንዯዱሁም የተማሪዎች
መብትና ግዳታ፣ የተማሪዎችን የቅበሊ ስርዓት የሚመሇከት ይዘት ያሇው መተዲዯሪያ
ዯንብ፤
6/ የትምህርት ቤቱን ዯረጃ የሚመጥን የትምህርት ቤት ግቢና አስፈሊጊ ቁሳቁሶችን
ማዯራጀቱን ሲረጋግጥ ፍቃዴ የሚሰጥ ይሆናሌ፡፡

16. በውጭ ባሇሃብት የሚቋቋም ትምህርት ቤት

1/ የኢንቨስትመንት ፍቃዴ ፤
2/ የንግዴ ፍቃዴ ፤
3/ የትምህርት ቤቱ መተዲዯሪያ ዯንብ እና መመስረቻ ሰነዴ፤
4/ የትምህርት ቤቱን ዯረጃ የሚመጥን ግብአት፤
5/ አካዲሚያዊና አስተዲዯራዊ አዯረጃጀትን የሚያሳይ ፣ ስሇተማሪዎች የትምህርት
ክፍያ አከፋፈሌ ሁኔታ፣ የመምህራን የቅጥር፣ የዯረጃ እዴገትና ስንብት፣የተማሪዎች
ቅበሊ፣ የመምህራንንና የተማሪዎችን መብትንና ግዳታ የሚያሳይ ይዘት እንዱኖረው
ተዯርጎ የተዘጋጀ የመመስረቻ ሰነዴ አሟሌቶ ሲያቀርብ ፍቃዴ የሚሰጥ ይሆናሌ፡፡

17. ፈቃዴ ስሇማዯስ

Daniel Fikadu Law Office


1/ ፈቃዴ አግኝቶ ሲሰራ የነበረ ትምህርት ቤት የፈቃዴ ዘመኑ ሲያሌቅ የእዴሳት
ጥያቄ ሇባሇስሌጣኑ የፈቃዴ ጊዜው ከማሇቁ ሶስት(3) ወራት ቀዯም ብል ማመሌከት
አሇበት።
2/ ማመሌከቻውም በዚህ መመሪያ በተሰጠው ፈቃዴ ሇማውጣት መሟሊት ያሇበት
ቅዴመ ሁኔታዎች መሰረት መተግበራቸውን የሚያረጋገጥ እና ትምህርት ቤቱ የ5
ዓመት እቅዴና የ2 ዓመት አፈጻጸሙን ሪፖርት ማቅረብ አሇበት፤
በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 2 የተመሇከተው የሪፖርቱ ይዘትም፦
ሀ) የትምህርት ግብዓቶችን የሚገሌፅ ፣
ሇ) መምህራን የትምህርት ዝግጅትና ላልች መረጃዎች የሚያመሇክት፣
ሐ) የተማሪ መማሪያ ክፍሌ፣ የመምህር ተማሪ እና የተማሪ መፅሃፍ ጥምርታን
የሚያሳይ፣
መ)የተማሪዎችን ብዛት በዜግነት እና የጾታ ስብጥር የሚያሳይ መሆን ይኖርበታሌ ፣

3/ በዚህ አንቀጽ የተመሇከቱት መረጃዎች ተሟሌተው ሲቀርቡ እና የትምህርት ቤቱ


አፈጻጸም በቂ ሆኖ ሲገኝ ፈቃደ ሇሁሇት አመት ይታዯሳሌ፤
4/ በዚህ አንቀጽ የተመሇከቱት መረጃዎች ጉዴሇቶች ያለበት መሆኑ ከተረጋገጠ በሶስት
ወራት ውስጥ እንዱያስተካክለ በማሳወቅ ሇአንዴ አመት የሚቆይ የፈቃዴ እዴሳት
ይሰጣሌ፤
5/ ትምህርት ቤቱ የታዩ ጉዴሇቶችን በ3 ወራት ውስጥ የማያሻሽሌ መሆኑ ከተረጋገጠ
ሇሚቀጥሇው አመት ፈቃደ እንዯማይታዯስ ዯብዲቤ በመስጠት ሇትምህርት ቤቱ
ያሰውቃሌ።
18. የማስፋፊያ ፈቃዴ
1/ ፈቃዴ ተሰጥቶት በስራ ሊይ ያሇ የዓሇም ዓቀፍ እና በውጭ ባሇሃብት የተቋቋመ
ትምህርት ቤት ዯረጃውን ማሳዯግ ሲፈሌግ የኢንቨስትመንት ፈቃደን መሰረት አዴርጎ
ሇባሇስሌጣኑ ሲያመሇክት የትምህርት ዓመቱ ከመጀመሩ ከ3 ወራት በፊት አስፈሊጊው
ምሌከታ ተዯርጎሇት ጥያቄው አሳማኝ ሆኖ ሲገኝ የዯረጃ ማሳዯግ ፈቃዴ ይሰጣሌ፤
2/ ፈቃዴ ተሰጥቶት በስራ ሊይ ያሇ የማህበረሰብ ትምህርት ቤት ዯረጃውን ማሳዯግ
ሲፈሌግ የትምህርት ዓመቱ ከመጀመሩ ከ3 ወራት በፊት ሇባሇስሌጣኑ በሚያቀርበው

Daniel Fikadu Law Office


ጥያቄ መሰረት የትምህርት ቤቶች የሱፐርቪዥን ቡዴን አስፈሊጊው ምሌከታ ተዯርጎ
ጥያቄው አሳማኝ ሆኖ ሲገኝ የማስፋፊያ ፍቃዴ ይሰጣሌ።
19. ስሇ ፈቃዴ መሰረዝ
1/ በዚህ መመሪያ መሰረት የተሰጠ ፈቃዴ የሚሰረዘው፡-
ሀ. በወቅቱ ባሌታዯሰ የስራ ፈቃዴ እየሰራ ሲገኝ፤
ሇ. ከተፈቀዯሇት ዯረጃ ውጪ እየሰራ ሲገኝ፤
ሐ. በዕውቅና ፍቃዴ እዴሳት ምዘና ከሚጠበቀው መስፈርት በታች ሆኖ ሲገኝ
መ. ህጋዊ የመኖሪያ እና የስራ ፍቃዴ በላሊቸው የውጪ ሀገር መምህራንና
ሰራተኞች ሲያሰራ ሲገኝ፤
ሠ. ስርዓተ ትምህርቱን ጥሰው ሲገኙ የዕውቅና ፍቃደ የሚሰረዝ ይሆናሌ፤
2/ በዚህ አንቀጽ መሰረት የትምህርት ቤቱ ፈቃዴ የሚሰረዝ ከሆነ ትምህርት ቤቱ
ሇተማሪ ወሊጆች አዱሱ የትምህርት ዘመን ምዝገባ ሳይከናወን ቢያንስ ከ1 ወር በፊት
የማሳወቅ ግዳታ አሇበት፡፡
20. ፈቃዴ ስሇመመሇስ
1/ ፈቃዴ የተሰረዘበት ወይም ስራውን ያቋረጠ ትምህርት ቤት ሲሰራበት የቆየውን
የፈቃዴ ሰነዴ ሇባሇስሌጣኑ መመሇስ አሇበት፤
2/ ትምህርት ቤቱ የተሰጠውን ፍቃዴ ሇማሳዯስ ጊዜው ያሇፈበትን ፍቃዴ መመሇስ
አሇበት፡፡

ክፍሌ አምስት

ሌዩ ሌዩ ዴንጋጌዎች
21. የመሸጋገሪያ ዴንጋጌ

ይህ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት የተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ይህ መመሪያ


ያስቀመጠውን መስፈርት አሟሌተው አስከተገኙ ዴረስ ባሊቸው ፈቃዴ መሰረት
ስራቸውን መከናወን ይችሊለ።

22. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ

Daniel Fikadu Law Office


ይህ መመሪያ በፍትሕ ሚኒስቴር ተመዝግቦ በሚኒስቴሩ እና በራሱ በፍትሕ ሚኒስቴር
ዴረ-ገፅ ከተጫነበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናሌ፡፡

ብርሃኑ ነጋ /ፕሮፌሰር/

የትምህርት ሚኒስትር

የካቲት 29 ቀን 2016ዓ.ም

Daniel Fikadu Law Office. https://t.me/lawethiopiacomment

Daniel Fikadu Law Office

Daniel Fikadu Law Office

You might also like