You are on page 1of 19

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስተዳደር የዉስጥ መመሪያ

ቁጥር 08/2014

ጥር 2014 ዓ.ም.

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
ማዉጫ
መግቢያ......................................................................................................................................................................3

ክፍልአንድ፡-................................................................................................................................................................4

አንቀጽ 2፡ ትርጓሜ......................................................................................................................................................4

አንቀጽ 3፡ የተፈጻሚነት ወሰን.......................................................................................................................................5

ክፍል ሁለት.................................................................................................................................................................5

አንቀጽ 4፡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ድልደላ..........................................................................................................................5

አንቀጽ 5፡ የመኖሪያ ቤት ድልደላ መስፈርት....................................................................................................................5

አንቀጽ 6፡ የድልድላ መስፈርቱ የሚይዘው ነጥብ ዝርዝር...................................................................................................6

ክፍል ሦስት..............................................................................................................................................................10

አንቀጽ 7፡ በትምህርት ላይ ያሉ መምህራን....................................................................................................................10

አንቀጽ 8፡- የቤቶች ደረጃ አሠጣጥ...............................................................................................................................10

አንቀጽ 9፡ የውድድር ሂደትና የቤት አደላደል..................................................................................................................11

ክፍል አራት...............................................................................................................................................................12

አንቀጽ 10፡ መብትና ግዴታዎች...................................................................................................................................12

አንቀጽ 11፡- የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኮሚቴ ስለማቋቋም...................................................................................................15

አንቀጽ 12፡ የዩኒቨርሲቲውን ልዩ ዉሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮችና የመወሰን ስልጣን....................................................................16

አንቀጽ 13፡ የቤት ደልዳይ ኮሚቴ አውቃቀር..................................................................................................................16


አንቀጽ፡-14 ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች.......................................................................................................................................17
አንቀጽ 15፡ መመሪያዉን ስለማሻሻል.................................................................................................................................17
አንቀጽ 16፡ ተፈጻሚነት የማይኖራቸው መመሪያዎች..........................................................................................................17
አንቀጽ 17፡ አባሪ.......................................................................................................................................................17

አንቀጽ 18፡ መመሪያ ስለማጽናት................................................................................................................................17

2
መግቢያ
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ያስቀመጠዉን ራዕይ ከማሳካት አንጻር በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማህበረሰብ

አገልግሎት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር በርካታ ፋይዳ ያላቸዉን ተግባራት እየሰራ የሚገኝ ተቋም ሲሆን የትምህርት ሥራ

በአንድ በተወሰነ ወቅት ተከናውኖ የሚያበቃ ሳይሆን የተከታታይነት ባህርይ ያለው ሥራ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዉ አሁን

ባሉትም ሆነ ወደፊት በሚያስገነባቸው የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለመምህራን በህግ ላይ ተመስርቶ

በመደልደል፤

ሀ) እየናረ በሚሄደዉ የቤት ኪራይ ወጪ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በማድረግና የተረጋጋ ኑሮን በመፍጠር ህይወታቸውን

ለመምራት ለማስቻል፤

ለ) የመማር ማስተማር፣ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎችን በይበልጥ

ለማጎለበትና ለማሳለጥ፤

ሐ) ለተማሪዎች ትምህርታዊ የምክር አገልግሎት ለመስጠትና በቅርብ የተማሪዎችን ችግር በጋራ ለመፍታት፤

መ) በመምህራን መካከል መቀራረብን፤ መማማርንና የጋራ ተግባቦትን በመፍጠር የሚያጋጥሙ ማህበራዊ ችግሮችን

በጋራ የመፍታትን ሁኔታ ለመፍጠር፤

ሠ) በወርክ ሾፕ፣ በላቦራቶሪ የሚደረጉ ረጅም ሰዓት የሚወስዱ ሥራዎችን ተረጋግተዉ እንዲሰሩ ለማገዝ፤

ረ) የዩኒቨርሲቲውን የመማር ማስተማር፣ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራ ቀልጣፋ፣

ጥራትና ብቃት ያለው እና የሥራ ሂደቱን የተሳካ ለማድረግ ከሚያስችሉ አበይት ተግባራት መካከል የመምህራን የጋራ

መኖሪያ ቤት ችግር ደረጃ በደረጃ በመቅረፍ የሥራ ተነሣሽነትን ማሳደግ አንዱ በመሆኑ፣ ዩኒቨርሲቲው በሶዶ ከተማ

የጋራ መኖሪያ ቤት ህንፃዎችን በራሱ ወጪ በመገንባት እና በመግዛት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለመምህራን ለመደልደል

የሚያስችሉ መመሪያዎችን በ 2006 ዓ.ም፣ 2007 ዓ.ም፣ 2011 ዓ/ም አዘጋጅቶ እየሰራ የቆዬ ብሆንም በአፈጻጻም ላይ

ክፍተቶች የታዩ በመሆናቸዉ ነባሩ መመሪያ እንዲሻሻል ከመምህራን በተለያዩ ጊዚያት ጥያቄዎች በመቅረባቸዉ

ምክንያት፤

 ዩኒቨርሲቲው 225 ቤቶችን የያዘ 15 የጋራ መኖሪያ ቤት ህንፃዎችን በሁለት ሳይቶች ከቤቶች ልማት ኤጀንሲ

የገዛቸውን፣

 96 ቤቶችን የያዙ ሁለት መንቲያ አዲስ እየተገነቡ ያሉ ዘመናዊ ህንጻዎችን፤

 አሁን በቴክኖሎጂና በኦቶና ካምፖሶች አገልግሎት እየሰጡ ያሉ 48 ቤቶችን የያዙ ሁለት ዘመናዊ ህንጻዎችን፣

እና

 ዩኒቨርሲቲዉ በቀጣይ የሚገነባቸዉን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ግልፅና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ድልድል ለማድረግ

እንዲያስችል ነባሩ መመሪያ ተሽሮ በዚህ መመሪያ ተተክቷል፡፡

3
ክፍልአንድ፡-
አንቀጽ 1፡ አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤት ድልደላ አፈጻጸም የዉስጥ መመሪያ ቁጥር
08/2014 ተብሎ ይጠቀሳል፡፡

አንቀጽ 2፡ ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ፡ -
2.1. ዩኒቨርሲቲ፡ ማለት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማለት ነዉ፡፡
2.2. ከፍተኛ አመራር ማለት ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ማለት ነዉ፡፡
2.3. መምህር ማለት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ በተለያዬ ደረጃ ያሉ ተማሪዎችን በቋሚነት በማስተማር፣
በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራ ላይ የሚገኝ የዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚክ ሰራተኛ
ማለት ነዉ፡፡
2.4. መካከለኛ አመራር ማለት ዳይሬክተሮች፣ የካምፓስ ዲኖች፣ የኢንስቲትዩት ዋና ኃላፊዎች፣ የኮሌጆች ወይም
ትምህርት ቤቶች ዲኖች እና ሌሎች በተመሳሳይ ማዕረግ የሚሰየሙ ኃላፊዎችን ያካትታል፡፡
2.5. መሠረታዊ አመራር ማለት የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ ተባባሪ ዲኖች፣ ምክትል ዲኖች፣ ተባባሪ
ሬጅስተራሮች፣ ረዳት ሬጅስትራሮች፣ አስተባባሪዎች እና ሌሎች በተመሳሳይ ማዕረግ የሚሰየሙ ኃላፊዎችን
ያካትታል፡፡
2.6. የጋራ መኖሪያ ቤት ማለት ለማንኛውም የአካዳሚክ ዘርፍ ኃላፊ ወይም ባለሙያ (መምህር) ለመኖሪያነት
በውድድር ተደልድሎ የሚሠጥ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤት ማለት ነው፡፡
2.7. ልዩ ቤቶች ማለት ለሌሎች የማይሰጡ ያለዉድድር በፕሬዚዳንትነት እና በምክትል ፕሬዝዳንትነት ለሚሾሙ
መምህራን የሚሰጥ መኖሪያ ቤት ማለት ነዉ፡፡
2.8. የአገልግሎት ዘመን ማለት በወላይታ ሶዶ ዪኒቨርሲቲ ወይም በአቻ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ወይም የመንግስት
ኮሌጆች በመምህርነት ያገለገሉበት እና በተቋማቱ የሰው ሀብት ጽ/ቤት ማህተም የተረጋገጠ ህጋዊ ማስረጃ የቀረበ
የሥራ አገልግሎት ማለት ነው፡፡
2.9. ጋብቻ ማለት አግባብነት ያለው የሀገርቱ ቤተሰብ ህግ ዕዉቅና ከሰጣቸዉ የጋብቻ አፈፃፀም ሥነ-ሥርዓቶች
በአንዱ መሠረት የተፈጸመ ጋብቻ ቢሆንም በወሳኝ ኩኔት ጽ/ቤት የተረጋገጠ ሆኖ በግልጽ የሚታይ የጥንዶች ፎቶ
ግራፍ ያለበት፣ ያረጋገጠዉ የወሳኝ ኩነት ጽ/ቤት ኃላፊ ፊርማ ያለበት እና የወሳኝ ኩነት ጽ/ቤት ማህተም ያረፈበት
የጋብቻ ሰነድ ማለት ነው፡፡

4
2.10. የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤት ደልዳይ ኮሚቴ ማለት በዚህ መመሪያ አንቀጽ 13 ላይ የተዘረዘሩትን
የሚያጠቃልል ነዉ፡፡

2.11. ቤተሰብ ማለት ለዚህ መመሪያ ዓላማ ሲባል በዩኒቨርሲቲዉ የጋራ መኖሪያ ቤት በሚኖር መምህር ስር የሚተዳደሩ
ሰዎች ማለት ነዉ፡፡

2.12. አካል ጉዳተኞ ማለት የአካል ወይም የአዕምሮ ጉዳተኛ ሆነው ማየትና መስማት የተሳናቸዉ፣ በተሽከርካሪ ወንበር
ወይም በክራንች የሚሄዱ ወይም የከፋ የአካል ጉዳት ያለባቸውና ጉዳቱ በዓይነቱ ለረዥም ጊዜ /በዘላቅነት/ የዕለት
ተዕለት ተግባራቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያደርስ ማለት ነው፡፡

2.13. ፆታ በዚህ መመሪያ በወንድ ፆታ የተገለጹ አንቀፆች ለሴትም ፆታ ያገለግላሉ፡፡

አንቀጽ 3፡ የተፈጻሚነት ወሰን

3.1 ይህ መመሪያ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በሚገኙ በሁሉም ካምፓሶች ተመድቦ ወይም ተቀጥሮ ለሚሰራ
የአካዳሚክ ዘርፍ ኃላፊ እና ባለሙያ (መምህር) ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለት

አንቀጽ 4፡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ድልደላ

4.1 የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ የሚደለደሉት በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እና በቴክኖሎጂ
ሽግግር ሥራ ላይ በዩኒቨርሲቲዉ ዉስጥ በቀጥታ በመሳተፍ ላይ ለሚገኙ መምህራን ወይም ቤተሰብ ያላቸው
በትምህርት ላይ ለሚገኙ መምህራን ይሆናል፡፡

አንቀጽ 5፡ የመኖሪያ ቤት ድልደላ መስፈርት

5.1. በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለመምህራን ቤት የሚሰጠው ምንም ዓይነት አድሎ በሌለበትና አንድ ወጥ ሥርዓትንና
አፈጻጸምን በተከተለ መልኩ ብቻ ይሆናል፡፡

5.2. መምህራን የዩኒቨርሲቲውን ዓላማ በማስፈጸም ረገድ ቀጥተኛ ሚና የሚጫወቱ በመሆናቸው የመኖሪያ ቤት
የማግኘት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

5
5.3. የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ድልደላ በዋናነት የአካዳሚክ ማዕረግ እና ደረጃ፤ የአገልግሎት ዘመን፣ የሥራ ኃላፊነትን እና
ህጋዊ ጋብቻን እንደ መሰረታዊ መስፈርት በማድረግ ሌሎች ተጨማሪ ነጥቦች የሚሰጡበት መስፈርቶች ታክለውበት
በውድድር የሚፈጸም ይሆናል፡፡

አንቀጽ 6፡ የድልድላ መስፈርቱ የሚይዘው ነጥብ ዝርዝር


6.1. ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ድልደላ የሚደረግባቸዉ አራቱ መሠረታዊ መስፈርቶች ከመቶ የሚይዙት
ነጥብ
እንደሚከተለው የተሰላ ሲሆን በልዩ ሁኔታ የተቀመጡ ነጥቦች በተጨማሪነት የሚሰጡ ይሆናሉ፡፡
ሀ. የትምህርት ደረጃና እና የአካዳሚክ ማዕረግ …. 55%
ለ. የአገልግሎት ዘመን …….....……………………25%
ሐ. የሥራ ኃላፊነት …..…..…………….………….10%
መ. የጋብቻ ሁኔታ ……….…………….…………..10%
6.2. በልዩ ሁኔታ (በተጨማሪ የሚሰጡ ነጥቦች)
ሀ. ለአካል ጉዳተኛ መምህር/ርት ……….………….10%
ለ. ለሴት መምህራን ………………...……..……..…7%
ሐ. ልጅ ያላዉ መምህር በእያንዳንዱ ልጅ ….….…..1%
6.3. ከ 6.1 (ሀ-መ) ያሉ መሠረታዊ መስፈርቶች ከ 100% የሚያዙ ሲሆን በልዩ ሁኔታ የሚያገኘው
ነጥብ በመምህሩ አጠቃላይ ዉጤቱ/ቷ ላይ የሚደመር ይሆናል፡፡
6.4. የአካዳሚክ ማዕረግ እና የትምርት ደረጃ ነጥብ አሠጣጥ
የትምህርት ደረጃ እና አካዳሚክ ማዕረግ 55 ነጥብ የሚይዝ ሆኖ በየማዕረግ መካከል ያለው
ልዩነት 5 (አምስት) ነጥብ ይሆናል፡፡ ዝርዝሩ እንደሚከተለው ተተንትኗል፡፡
ሀ. ፒ.ኤች.ዲ /ስፔሻሊቲ/ሳብ ስፔሻሊቲ ደረጃ እና ኘሮፌሰር ……..……55
ለ. ፒ.ኤች.ዲ /ስፔሻሊቲ/ሳብ ስፔሻሊቲ ደረጃ እና ተባባሪ ኘሮፌሰር…... 50
ሐ. ፒ.ኤች.ዲ /ስፔሻሊቲ/ሳብ ስፔሻሊቲ ደረጃ እና ረዳት ኘሮፌሰር……..45
መ. ማስተርስ ዲግሪ/ዲቭ ኤም/አጠቃላይ ሀኪም እና ተባባሪ ኘሮፌሰር....45
ሠ. ማስተርስ ዲግሪ/ዲቭ ኤም/አጠቃላይ ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር ....40
ረ. ሌክቸረር ………..………………………..………….…………........ 35
ሰ. ረዳት ሌክቸረር ……….………...…………………………………..…30
ሸ. ረዳት ምሩቅ II ……………………………….….………………….…25
ቀ. ረዳት ምሩቅ I …………………………………………….………...…20
ነጥብ የሚሰጥ ይሆናል

6.5. የአገልግሎት ዘመን ነጥብ አሠጣጥ

6
6.5.1. የአገልግሎት ዘመን ከፍተኛው 25 ነጥብ የሚይዝ ሆኖ በሚከተለው መልኩ ተተንትኗል፡፡

6.5.1.1. በወላይታ ሶደ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ላገለገሉበት ለእያንዳንዱ አንድ ዓመት አገልግሎት ሁለት
ነጥብ አምስት (2.5) ነጥብ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
6.5.1.2. በትምህርት ሚኒስቴር ሥር ባሉ በሌሎች የመንግሥት አቻ ዩኒቨርሲቲዎች ለተሰጠ አገልግሎት
ለእያንዳንዱ ዓመት አንድ ነጥብ አምስት (1.5) ነጥብ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
6.5.1.3. በመንግሥት ኮሌጆች ለተሰጠ አገልግሎት ለእያንዳንዱ ዓመት አንድ (1) ነጥብ የሚሰጥ
ይሆናል፡፡
6.5.1.4. በእነዚህ ሁኔታዎች ረዥም አገልግሎት ላበረከተ መምህር የሚሠጠው ትልቁ ነጥብ 25 ብቻ ይሆናል፡፡
በዩኒቨርሲቲዉ ሰኔት ሌጅስሌሽን አንቀጽ 42.7 እና በስቭል ሰርቭስ አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አፈጻጸም መመሪያ
2011 አንቀጽ 58(7) ስር በተደነገገዉ መሠረት ለሁሉም መምህራን በትምህርት ላይ የነበሩበት ዓመት የሥራ
ልምድ ሆኖ አያገለግልም፡፡ ይሁን እንጂ በሥራ ላይ ሆኖ ትምህርቱን ለተከታተለ መምህር ትምህርት ላይ የቆዬዉ
ዓመት ህጋዊ ማስረጃ ሲቀርብ የሥራ ልምድ ሆኖ ይያዛል፡፡

6.6. በዚህ መመሪያ መሠረት ቴክኒካል ረዳቶች ለጋራ መኖሪያ ቤት መወዳደር አይችሉም፡፡

6.7. የሥራ ኃላፊነት ነጥብ አሠጣጥ


6.7.1. ከመደበኛ የማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራቸው በተጨማሪ በሥራ
ኃላፊነት ተመድበው ለሚሰሩ መምህራን የሚሠጠው ከፍተኛው ነጥብ 10 ሆኖ አሠራሩ እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡
6.7.2. በመካከለኛ አመራርነት ደረጃ በኃላፊነት ለሚያገለግል መምህር

6.7.2.1. በፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ስር ያሉ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች፤

6.7.2.2. በአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ስር ያሉ ካምፓስ/ኮሌጅ /ት/ቤትዲኖች

እና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች፤

6.7.2.3. በምርምራና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ስር ያሉ ዳይሬክቶሬት

6.7.2.4. በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ስር ያሉ ዳይሬክቶሬት

ዳይሬክተሮች፤

6.7.2.5. በቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ስር ያሉ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች እና

በተመሣሣይ ደረጃዎች ለሚያገለግሉ ኃላፊዎች ለተጨማሪ የሥራ ኃላፊነታቸው 10

ነጥብ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

6.7.2.6. በሌላ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ በየትኛዉም የኃላፊነት ደረጃ ያገለገለ መምህር ላገለገለበት ለአንድ ዓመት 1.5

ነጥብ የሚሰጥ ሲሆን በአጠቃላይ የአሥር ነጥብ 80% (8 ነጥብ) የሚያገኝ ይሆናል፡፡ በሌላ የመንግስት ኮሌጅ

7
በየትኛዉም የኃላፊነት ደረጃ ያገለገለ መምህር ለአንድ ዓመት 1 ነጥብ የሚሰጥ ሲሆን ትልቁ ነጥብ የአሥር ነጥብ

70% (7 ነጥብ) ይሆናል፡፡ ዳይሬክተሮች፤


6.7.3. በመሠረታዊ አመራርነት ደረጃ በኃላፊነት ለሚያገለግል መምህር
6.7.3.1. በፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ስር ያሉ አስተባባሪዎች፤
6.7.3.2. በአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ስር ያሉ ኮሌጅ ወይም ትምህርት ቤት ተባባሪ/ምክትል
ዲኖች፣ ትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ ተባባሪ ሬጅስትራሮች፣ ረዳት ሬጅስትራሮች፣ ፕሮግራም አስተባባሪዎች፤
6.7.3.3. በምርምራና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ስር ያሉ ፕሮግራም አስተባባሪዎች፤
6.7.3.4. በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ስር ያሉ ፕሮግራም አስተባባሪዎች፤
6.7.3.5. በቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ስር ያሉ አስተባባሪዎች እና በተመሣሣይ ደረጃዎች
ለሚያገለግሉ በመሠረታዊ አመራርነት ደረጃ ኃላፊዎች ለተጨማሪ የሥራ ኃላፊነታቸው 7 ነጥብ የሚሰጥ ይሆናል፤
6.7.3.6. በሌላ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ በየትኛዉም የኃላፊነት ደረጃ ያገለገለ መምህር ላገለገለበት ለአንድ ዓመት 1.25
ነጥብ የሚያገኝ ሲሆን በአጠቃላይ የሰባት ነጥብ 80% (5.6 ነጥብ) የሚያገኝ ይሆናል፡፡ በሌላ የመንግስት ኮሌጅ
በየትኛዉም የኃላፊነት ደረጃ ያገለገለ መምህር ለአንድ ዓመት 0.75 ነጥብ የሚሰጥ ሲሆን ትልቁ ነጥብ የሰባት ነጥብ
70% (4.9 ነጥብ) ይሆናል፡፡
6.8 ከዚህ ቀደም በኃላፊነት ላገለገሉ መምህራን ማለትም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ

የኃላፊነት ቦታዎች ላገለገሉ መምህራን እያንዳንዱ ዓመት 3 ነጥብ የሚሰጠው ይሆናል፡፡

6.8.1. በመካከለኛ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ መምህራን ለምሳሌ፡- ዲኖችና ዳይሬክተሮች ወይም

በእነዚህ ደረጃዎች በኃላፊነት አገልግለው ለነበሩ ኃላፊዎች ለእያንደንዱ ዓመት ሶስት (3) ነጥብ

የሚሰጥ ሆኖ በአጠቃላይ ለአንድ ዙር ዘጠኝ (9) ነጥብ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

6.8.2 በመሰረታዊ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ መምህራን ለምሳሌ፡-ለትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፤

አስተባባሪዎች፤ ተባባሪ/ምክትል ዲኖች፤ ረዳት ሬጅስትራርና በተመሳሳይ ደረጃዎች በኃላፊነት

አገልግለው ለነበሩ ለእያንዳንዱ ዓመት ሶስት (3) ነጥብ የሚሰጥ ሆኖ በአጠቃላይ ለአንድ ዙር

ስድስት (6) ነጥብ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

6.9 ከዚህ ከላይ በንዑስ አንቀጽ 6.7.2 እና 6.7.3 የተጠቀሱ ኃላፊዎች በተከታታይ ለሁለት ዙር (terms) ያገለገሉ ከሆነ

የሚያዘው ነጥብ የሁለቱም ዙር ሆኖ መካከለኛም ይሁን መሠረታዊ ኃላፊነት ቦታ ላይ ያገለገሉበት ትልቁ ነጥብ ከ 10
መብለጥ የለበትም፡፡
6.9.1 በሌላ በኩል ከአሁን በፊት በኃላፊነት ቦታ ላይ አገልግለው የነበሩና አሁንም በኃላፊነት

ላይ ያሉ መምህራን በአንቀጽ 6.10.1 እና 6.10.2 ከተመለከተው የኃላፊነት አገልግሎት የተሻለዉ

ነጥብ ይያዛል፡፡ ነገር ግን ከዚህ በፊት ያገለገለበት የኃላፊነት ቦታ አሁን ካሉበት የተሻለ ከሆነ የበፊቱ የኃላፊነት ዉጤት

የሚያዝ ይሆናል፡፡

8
6.10. አሁንም ይሁን ቀድሞ በመካከለኛ ወይም በመሠረታዊ የሥራ ኃላፊነት ቦታ/ዎች ላይ አገልግሎ የነበረ መምህር

የአገልግሎት ጊዜዉ ከአንድ ሴሚስተር በታች ከሆነ የኃላፊነት አገልግሎት ዉጤት አያገኝም፡፡
6.11. ህጋዊ ጋብቻ ለፈጸሙ መምህራን የሚሠጥ ነጥብ
6.11.1. በአንቀጽ 2.9 መሠረት ህጋዊ ጋብቻ ስለመፈጸሙ በህጋዊ ማስረጃ የተረጋገጠ መምህር 10 ነጥብ ይሰጣል፡፡
በወሳኝ ኩነት ያልተረጋገጠ የጋብቻ ሰነድ ለጋራ መኖሪያ ቤት ዉድድር ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
6.11.2. ጋብቻ ፊቺ የፈተመ/ች መምህር የጋብቻ ዉጤት አይሰጠዉም፡፡
6.11.3. በዉድድር ወቅት አጠራጣሪ የሆነ የጋብቻ ሁኔታ ከተገኘ የጋራ መኖሪያ ቤት ደልዳይ ኮሚቴ በህጋዊ መንገድ
የሚያጣራ ሆኖ ጋብቻዉ ስህተት መሆኑ ከተረጋገጠ ከዉድድር ዉጪ ሆኖ በመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤት የዉስጥ
አስተዳደር ደንብ/መመሪያ መሰረት የሚቀጣ ይሆናል፡፡
6.11.4. ባልና ሚስት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መምህር ሆነው ለውድድር ሲቀርቡ የሚወሰደው ከሁለቱ የአንደኛው
ከፍተኛ ነጥብ ብቻ ይሆናል፡፡
6.11.5. ቤተሰብ ያለው መምህር ለትምህርት ቢሄድ ቤተሰቡ ማለትም ባለቤቱ እና ልጆች በተሠጠው ቤት እንዲኖሩ
ይደረጋል፡፡
6.12. በልዩ ሁኔታ የሚሰጥ ነጥብ
6.12.1. አካል ጉዳተኛ መምህር በዉድድር ጊዜ በአራቱ መሠረታዊ መስፈርቶች (አንቀጽ 6.1(ከሀ-መ)) ተወዳድሮ
ከመቶ በሚያኘዉ ነጥብ ላይ አካል ጉዳተኛ በመሆኑ 10 (አሥር) ነጥብ ይጨመራል፡፡
6.12.2 ይህ ተደምሮ በአጠቃላይ አካል ጉዳተኛ ተወዳዳር መምህር ባገኘዉ ነጥብ ልክ ለድልድል ከወጡ ቤቶች ዉስጥ
ልያገኝ ከሚችለዉ ተመሳሳይ ቤት ደረጃዎች መካከል ለራሱ የሚመቸዉን የመምረጥ ዕድል ይሰጣዋል፡፡
6.12.3 ሴት መምህሪት በዉድድር ጊዜ በአራቱ መሠረታዊ መስፈርቶች (አንቀጽ 6.1(ከሀ-መ)) ተወዳድራ ከመቶ
በሚታገኘዉ ነጥብ ላይ ሴት በመሆኗ ብቻ ተጨማሪ 7 (ሰባት) ነጥብ ይጨመርላታል፡፡ ነገር ግን ሴት መምህሯ አካል
ጉዳተኛ ከሆነች ከሁለቱ ተጨማሪ ነጥቦች ከፍተኛ ነጥብ የያዘዉ 10 ነጥብ ይያዝላታል፡፡
6.12.4. መምህሩ ህጋዊ ማስረጃ ሲያቀርቡ በአንድ ልጅ 1 ነጥብ የሚያገኙ ሆኖ የጉዲፈቻ ልጅ ወይም የእንጀራ ልጅ
ያለዉ መምህር ህጋዊ ሰነድ ሲያቀርብ የተጠቀሰዉን ነጥብ ያገኛል፤
6.12.5 ባልና ሚስት በዩኒቨርሲቲዉ መምህራን ከሆኑ ከሁለቱ አንዱ ባላቸዉ ልምድ እና የትምህርት ዝግጅት ዉጤት
መሠረት ተወዳድረዉ ቤት የሚያገኙ ሆኖ ከሁለቱ አንዱ የቤት አበል ያገኛል፡፡

9
ክፍል ሦስት

አንቀጽ 7፡ በትምህርት ላይ ያሉ መምህራን

7.1. በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ዪኒቨርሲቲዎች በትምህርት ላይ ያሉ መምህራን በተረጋጋ ሁኔታ ተምረውና
ተመልሰው ዩኒቨርሲቲውን እንዲያገለግሉ ለማበረታታት ሚስቱ/ባሏ ወይም ህጋዊ ልጅ/ የዉድድር ሰነድ ይዘዉ
በመቅረብ ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡

7.2. በሥራ ላይ ሆኖ የሚማር የዩኒቨርሲቲያችን መምህር በቀጥታ በመማር ማስተማር፤ ምርምርና ማህበረሰብ
አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራ ላይ የሚሳተፍ ስለሆነ መወዳደር ይችላል፡፡

አንቀጽ 8፡- የቤቶች ደረጃ አሠጣጥ


8.1. በአሁኑ ጊዜ ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤቶች 21 ብሎኮችና 369 ቤቶች አሉት፡፡
ቤቶቹ በአራት ሳይቶች ማለትም፡-
1 ኛ) በላይኛዉ የሠራተኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ በር ፊት ለፊት ያለዉ፤
2 ኛ) በታችኛው የሠራተኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ በር ፊት ለፊት ያለዉ፤
3 ኛ) በቴክኖሎጂ እና በኦቶና ካምፓሶች ያሉ ሳይቶች ናቸዉ፡፡
ሀ) የታችኛው ሳይት T4 Blocks ሲባል 30 ባለሁለት መኝታና 45 ባለአንድ መኝታ በድምሩ 75
ቤቶች አሉት፡፡
ለ) የላይኛዉ የሠራተኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ በር ፊት ለፊት ያለዉ ሳይት 12 ብሎኮች
ሲኖሩት 6S2 Blocks፣ 4M2 Blocks እና አዲስ ሁለት ዘመናዊ ህንጻዎች ሲሆኑ በአጠቃላይ
198 ቤቶች አሉ፡፡
ሐ) በቴክኖሎጂ ካምፓስ አዲስ ሦስት (አንድ ህንጻ መምህራን እየኖሩበት ያለዉ ሲሆን ሁለቱ
በግንባታ ላይ ያሉ) ዘመናዊ ህንጻዎች እና በኦቶና ካምፓስ አዲስ አንድ ዘመናዊ ህንጻ ያሉ
ሲሆን በአጠቃላይ 96 ቤቶች አሉ፡፡
መ) ይህንን መረጃ መሠረት በማድረግ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚከተሉት ደረጃዎች ተዘጋጅተዋል፡፡
8.1.1 የቤቶች ደረጃ ማውጫ መስፈርቶች፡-
ሀ). የመኖሪያ ቤቶች መኝታ ቤት ቁጥር/ብዛት፤

ለ). ቤቶቹ የሚገኙበት ወለል/የፎቅ ደረጃ ሲሆኑ በእነዚህ መሥፈርቶች መሠረት የሚከተሉት ደረጃዎች

ወጥቶላቸዋል፡፡
8.2 የመኖሪያ ቤቶች መኝታ ቤት ቁጥር/ብዛት፡-
ለመምህራን የሚደለደሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ካላቸው የመኝታ ቤት ብዛት አንጻር የሚከተለው ደረጃ ወጥቶላቸዋል፡፡
8.2.1. ባለ 3 መኝታ ቤቶች ………………… ደረጃ አንድ

10
8.2.2. ባለ 2 መኝታ ቤቶች ………………… ደረጃ ሁለት
8.2.3. ባለ 1 መኝታ ቤቶች ……………… ደረጃ ሦስት እና
8.2.4. ስቱዲዮ ቤቶች ……………….. ደረጃ አራት በመሆን ደረጃ ተሠጥቷቸዋል፡፡

8.3 በአንጻራዊ የብሎኮች ንጽጽር

1 ኛ) አዲስ ዘመናዊ ህንጻዎች በላይኛዉ የሠራተኞች መግቢያ በር ፊት ለፊት ላይ ያለዉ፤ አዲስ ዘመናዊ ህንጻ
ቴክኖሎጂ ካምፓስ እና አዲስ ዘመናዊ ህንጻ ኦቶና ካምፓስ፣

2 ኛ) 4M2 ብሎኮች፤

3 ኛ) 6S2 ብሎኮች እና

4 ኛ) 5T4 ብሎኮች ተብሎ ደረጃ ወጥቶላቸዋል፡፡


8.4. ቤቶቹ የሚገኙበት ወለል/የፎቅ ደረጃ
8.4.1. በአንጻራዊ የወለል ንጽጽር ሁሉም ብሎኮች ማለትም፡- አዲስ የተገነቡ ስድስት ዘመናዊ ህንጻዎች (አራት ያለቁ
/ኦቶና አንድ፣ በቴክኖሎጂ ካምፓስ አንድ፣ ትልቁ የሠራተኛ መግቢያ በር ፊት ለፊት ያሉ ሁለት እና በቴክኖሎጂ
ካምፓስ እየተገነቡ ያሉ ሁለት ህንፃዎች፣ 4M2 ብሎኮች፤ 6S2 ብሎኮች እና 5T4 ብሎኮች አንደኛ፣ ሁለተኛ እየተባለ
እስከ 5 ኛ ወለል እና መሬት ተብሎ ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ በቅደም ተከተል ደረጃ ወጥቶላቸዋል፡፡

አንቀጽ 9፡ የውድድር ሂደትና የቤት አደላደል


9.1. የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤት ፈላጊ መምህር ለውድድር አሰፈላጊውን መረጃ ከነሙሉ አባሪ ጋር የቤቶች
ውድድር ቅጽ በመሙላት ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያቀርባሉ፡፡
9.2. የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ባላቸው የመኝታ ክፍል ብዛትና ወለል (ደረጃ) መሠረት አሸናፊዎች ከመቶ ባገኙት ነጥብ
ቅደም ተከተል ይደለደላል፡፡
9.3. በጣም ከፍተኛ ነጥብ ያገኙ ተወዳዳሪዎች በሁሉም ህንፃዎች ለዉድድር የወጡትን ባለ 3 መኝታ ቤት ደረጃ-1
ያገኛሉ፡፡
9.4. ቀጥሎ ባለ ሁለት መኝታ ቤቶችን የሚያሸንፉ መምህራን በሁሉም ህንፃዎች ለዉድድር የወጡትን ባለ ሁለት
መኝታ ቤቶችን በነጥባቸው ቅደም ተከተል ያገኛሉ፡፡
9.5. ቀጥሎም በሁሉም ህንፃዎች ለዉድድር የወጡትን ባለ አንድ መኝታ ቤቶችን በነጥባቸው ቅደም ተከተል ያገኛሉ፡፡
9.6. በየደረጃው ባሉ ቤቶች ተወዳዳሪዎች እኩል ነጥብ ካገኙ በፆታ፣ በትዳር፣ ባላቸዉ የልጆች ብዛት እና በትምህርት
ደረጃቸዉ እየታየ ቅድሚያ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ይህ ማለት አንድ ሴት መምህርትና ወንድ መምህር ባላቸዉ የቤተሰብ
ብዛት፣ የጋብቻ ሁኔታ እና በትምህርት ደረጃቸዉ እኩል ከሆነ ቅድሚያ ለሴቷ ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም ባለትዳርና ልጅ
ላላቸዉ ቅድሚያ የሚሰጥ ሆኖ ባለትዳር ሆነዉ ልጅ ለሌላቸዉ ሁለተኛ ደረጃ እና ባለትዳር ላልሆኑ ቀጥሎ የሚሰጥ

11
ይሆናል፡፡ ከዚያም የትምህርት ደረጃቸዉ ይታያል፡፡ በዚህም ሁሉ ተመሣሣይ ከሆኑ አሸናፊው በዕጣ ተለይቶ ቤቱን
ያገኛል፡፡
9.7. ዉድድር የሚደረገዉ ቤቶች በተለቀቁ በ 15 ቀናት ዉስጥ ቤቶቹን ከሚያስተዳድረዉ ክፍል ሪፖርት ከቀረበ በኋላ
ማስታወቂያ በማዉጣት በየሩብ ዓመት ይደረጋል፡፡

ክፍል አራት

አንቀጽ 10፡ መብትና ግዴታዎች


10.1. ተወዳድሮ ቤት የሚያኘ መምህር መብት፡ -
10.1.1. በዉድድር ባገኘዉ ቤት ያለማንም ጣልቃ ገቢነት በተቀመጠዉ ጊዜ ገደብ የመግባትና የመዉጣት መብት፤
10.1.2. ተወዳድሮ በህጋዊ መንገድ ባገኘዉ ቤት ከነቤተሰቦቹ መኖር፤
10.1.3. በመኖሪያ ግቢዉ ዉስጥ በየኒቨርሲቲዉ የተፈቀደዉን የትኛዉንም አገልግሎት የማግኘት፤
10.1.4. በመኖሪያ ግቢዉ መተዳደሪያ መመሪያ መሠረት በተፈቀደዉ ሰዓት የመግባትና የመዉጣት መብት አለዉ፡፡

10.1.5. በዩኒቨርሲቲው የመምህራን መኖሪያ ቤት ውስጥ የሚኖር መምህር ለሌላ የተሻለ ቤት የመወዳደር መብቱ
የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም አዲስ የተወዳደረውን ቤት ካላሸነፈ ቀድሞ ሲኖርበት የነበረውን ቤት እንዲለቅ አይገደድም፡፡

10.1.6. በመኖሪያ ቤት ድልደላ ሂደትና አፈጻጸም ቅሬታ ያለው መምህር ውጤቱ በተገለጸ አምስት (5) የሥራ ቀናት
ውስጥ ቅሬታውን በማመልከቻ ለዩኒቨርሲቲዉ አስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
የማቅረብ መብት አለዉ፡፡
10.2. ተወዳድረው ቤት የሚያገኙ መምህራን ግደታ
10.2.1. በውል ከዩኒቨርሲቲው የተረከቡትን ቤት ለሌላ መምህር ማስተላለፍ አይቻልም፡፡
10.2.2. ቤቱን በውድድር ያገኘ መምህር የቤቱን ወለል፤ ግድግዳ፤ በርና ሌሎች መሠረታዊ ክፍሎች በጥንቃቄ
መገልገልና መጠበቅ አለበት፡፡ ነገር ግን በጥንቃቄ ጉድለት የተበላሸ ወይም የተሰበረ ዕቃ የማጠገን ወይም በአዲስ
የመተካት ግዴታ አለበት፡፡
10.2.3. መምህሩ ተወዳድሮ ያገኘውን ቤት ጡረታ ሲወጣ ለአንድ ዓመት እንዲኖር ይፈቀዳል፡፡ ነገር ግን አንድ ዓመት
ጊዜ እንደተጠናቀቀ ቤቱን ያስረክባል፡፡ አንድ መምህር ዩኒቨርሲቲዉን በዝውውርም ሆነ በሌላ ምክንያት ሲለቅ በ 1 ወር
ጊዜ ውስጥ ቤቱን እንዲለቅ ይደረጋል፡፡
10.2.4. ቤቱን ተወዳድሮ ያገኘ መምህር ቤቱ ላይ ጉዳት ማድረስ አይችልም፡፡ ነገር ግን በቤቱ ላይ ማሻሻያ ወይም
ማናቸውንም ዓይነት ለውጥ ካደረገ ያሻሻለበት ወይም የለወጠበት ክፍያ ገንዘብ እንዲመለስለት መጠየቅ አይችልም፡፡
10.2.5. መምህሩ ለትምህርት ሲሄድ የቤት ዉክልና መስጠት የሚችለዉ በቤቱ ውስጥ ለሚቀሩ ለባል ወይም ለሚስት
ሆኖ በልዩ ሁኔታ ለአቅመ አዳም/ሄዋን ያልደረሱ ልጆች የሚኖሩበት ከሆነ በዩኒቨርሲቲዉ ዕዉቅና በፍርድ ቤት ወይም
በሌላ ህጋዊ አካል ዉክልና የተሰጠዉ አካል ቤቱን ሊያስተዳድር ይችላል፡፡

12
10.2.6. መምህሩ ከተቋሙ ውጭ ርቆ የሄደ ከሆነና ራሱ ቤቱን ማስረከብ በማይችልበት ሁኔታ ላይ ከሆነ የእሱ ተወካይ
ቤቱን ማስረከብ ይችላል፡፡
10.2.7. የመኖሪያ ቤት በውድድር ያገኘ መምህር ከአስተዳደር ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ፈቃድ ሳያገኝ በራሱ ፈቃድ ቤቱን (የቤቱ ደረጃ ተመሳሳይ ቢሆን እንኳን) መቀያየር ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
በተጨማሪም ቤቱን ከወሰደ በኋላ ከሌላ ቦታ ቤተሰብ በማስመሰል ሌላ ሰዉን አምጥቶ ማስገባትም ሆነ አከራይቶ
መጠቀም አይቻልም፡፡
10.2.8. የቤት ድልድሉ ውጤት በአስተዳደርና ተማሪዎች ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ጸድቆ በግልጽ ማስታወቂያ
ሰሌዳ ላይ ተለጥፎ ደብዳቤ ለአሸናፊዎች እስኪገለጽ ድረስ ማንኛውም መምህር በተደለደለበት ቤት ዉስጥ መግባት
አይችልም፡፡ ተወዳድረዉ ቤት ያገኘ መምህር ውጤቱ በተገለጸ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በተደለደሉበት ቤት ካልገባ
አስ/ተ/አገ/ም/ፕ/ጽ/ቤት ቤቱን ለሚቀጥለው ተጠባባቂ መምህር ይሰጣል፡፡
10.2.9. ማንኛውም መምህር የመኖሪያ ቤት ሻወር ቤት ውስጥ ልብስ ማጠብ አይችልም፡፡
10.2.10. መምህራን የሚኖሩበትንም የጋራ መኖሪያ ቤት ግቢ ሆነ የአካባቢውን ጽዳት የመጠበቅና የማስጠበቅ ግዴታ
አለባቸዉ፡፡
10.2.11. የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤት ግቢ ዉስጥ የሚኖር መምህር በሚኖሩበት ህንጻ ወይም ሌሎች ግቢ ዉስጥ
ባሉ ህንጻዎች የሚኖሩ ሌሎች መምህራንና ቤተሰቦችን የሚያዉክ ወይም የመኖር መብታቸዉን የሚጎዳ ማንኛዉንም
ድርጊት ራሱ ወይም ቤተሰቡ መፈጸም የተከለከለ ነዉ፡፡
10.2.12. ማንኛውም መምህር አብረው ለሚኖሩ ቤተሰብ አባላት ዩኒቨርሲቲዉ የሚሰጠዉን መታውቂያ እንዲይዙ
ማድረግ ይኖርበታል፡፡
10.2.13. ማንኛውም መምህር በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ንግድ መንገድ፤ እንስሳትን ማርባትና የነዋሪውን ሰላምና ደህንነት
የሚያውኩ ማናቸውንም ተግባራት መፈጸም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

10.2.14. ማንኛውም መምህር ለውድድር ትክክለኛ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

10.2.15. በዩኒቨርሲቲዉ የጋራ መኖሪያ ቤት ዉስጥ የሚኖር መምህር በመኖሪያ ቤቱ ዉስጥ ያሉ ንብረቶችን
(መብራት፣ ዉሃ፣ ወዘተ) በአግባቡ የመጠቀምና የመንከባከብ ኃላፊነት አለበት፡፡

10.2.16. ቤቱን ተወዳድሮ ያገኘ መምህር ከዩኒቨርሲቲው ጋር ውል ሳይገባ ቤቱን መረከብ አይችልም፡፡

10.2.17. አንድ መምህር ወይም ማንኛዉም ሰዉ ወደ መምህራን መኖሪያ ግቢ በሚገባበት ጊዜ በሚመለከተዉ አካል
ሲጠየቅ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ማሳየት አለበት፡፡ እንዲሁም ንብረት ይዞ ሲገባም ሆነ ሲወጣ በሚመለከተዉ
አካል ሲጠየቅ ማሳየት አለበት፡፡
10.3 የዩኒቨርሲቲዉ ግዴታ
10.3.1. ዩኒቨርሲቲው የራሱን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን 24 ሰዓት ጥበቃ መድቦ የማስጠበቅ ግዴታ አለበት፡፡
10.3.2. የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በእርጅና ወይም በዝናብና ሌሎች ተፈጥሯዊ በሆኑ ምክንያቶች እድሳት ወይም ጥገና
ስለሚያስፈልጋቸው ዩንቨርሲቲዉ ዓመታው የጥገና ሥርዓት በመዘርጋት ማሳደስ/ማስጠገን አለበት፡፡
10.3.3. ዩኒቨርሲቲው የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን ዙሪያ አጥር ደረጃውን በጠበቀ አጥር ማሳጠር አለበት፡፡

13
10.3.4. የመኖሪያ ቤቶቹ በልዩ ልዩ አትክልቶች የተዋቡ፣ ለመኖር ማራኪና ምቹ እንዲሆኑ የዉበት ዛፎችንና
አትክልቶችን ያስተክላል፤ አትክልተኛን ይመድባል፡፡
10.3.5. ከነዋሪዎች ከተመረጡ ኮሚቴዎች ጋር በመነጋገርና አቅጣጫ በመንደፍ ቆሻሻ በዘመናዊ መንገድ
የሚወገድበትን ስልት ይነድፋል፡፡ ለአፈጻጸሙም አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡
10.3.6. ለጋራ መኖሪያ ቤቶች የውሃ ታንከሮችን፤ የጋራ ኩሽናዎችን፤ የጋራ ልብስ ማጠቢያ ገንዳዎችን ሁሉን
ተጠቃሚዎችን ባማከለ ሁኔታ ያዘጋጃል፡፡
10.3.7. የመማር መስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎች ወቅትን የተከተለ እና ሁል ጊዜ አዳዲስ
መረጃዎችን የሚፈልግ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የዋይ.ፋይ (WI-FI) አገልግሎት ያሟላል፡፡
10.3.8. ዩኒቨርሲቲው ለመምህራን ቤት ሲያከራይ ሙሉ ጥገና ወይም እድሳት በማድረግ በሮች ከተሟሉ ቁልፎቻቸው
ጋር ሙሉ መሆናቸዉን፤ የበርና የመስኮት መስተዋቶች ያልተሰበሩ፤ የኤሌክትሪክና የውሃ መስመሮች የተሟሉ፣
ያልተበላሹ እንዲሁም ግድግዳና ወለል ንጹህ መሆናቸውን አረጋገግጠዉ በጋራ ስምምነት ውል ላይ በግልጽ ተጠቅሶ
በሚደረግ የውል ስምምነት የቤት ኪራዩን የማከናወን ግዴታ አለበት፡፡
10.3.9. ለመምህራን አመቺ የመኖሪያ አካባቢን ለመፍጠር የሚያስችሉ ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

አንቀጽ 11፡- የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኮሚቴ ስለማቋቋም


11.1. በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በሁሉም የኮንዶሚኒየም ሳይቶች ለመምህራን መኖሪያነት በሚያገለግሉ ቤቶች
ተወዳድረዉ አሸንፈው ከሚኖሩ መምህራን መካከል በዩኒቨርሲቲው አሰተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል
ፕሬዝዳንት /ጽ/ቤት ኃላፊነት ኮሚቴ ይዋቀራል፡፡
11.2. የኮሚቴውም ዋና ተግባር ከላይ በአንቀጽ 10 (ንዑስ አንቀጽ 10.1 እና 10.2) የተገለጹትን የመምህራን መብትና
ግዴታዎች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን ግዴታ (ንዑስ አንቀጽ 10.3) ከንብረትና ፋሲሊት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቡድን ጋራ በጋራ በመሆን ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤ ይገመግማል፤
ለአሰተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕ/ጽ/ቤት ሪፖርት ያደርጋል፡፡
11.3. በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የሚፈጠሩ መሰረታዊ ችግሮችን በጥናት በመለየት ለመምህራኖቹ ምቹ የመኖሪያ
አካባቢን ለመፍጠር ይሰራል፡፡ ተጠያቅነት ያለበትን አሰራር ይዘረጋል፤ መመሪያዎችን በማዉጣትና ጥሰቶችን በመለየት
ከሚመለከተው የበላይ አካል ጋር በመወያየት አስፈላጊዉን እርምጃ ይወስዳል፡፡
11.4. የዋና ኮሚቴ አባላት ብዛት ከሰባት የማይበልጥ ሆኖ አንድ ሰባሳቢ ከኮሚቴው አባላት የሚመረጥ ሲሆን
የዩኒቨርሲቲው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቡድን መሪ ፀሐፊ ይሆናል፡፡ በየሳይቱ በኮንዶሚኒየሞቹ ብዛት ልክ (ከየህንፃው)
የተመረጡ ንዑሳን ኮሚቴዎች ይኖራሉ፡፡ ንዑሳን ኮሚቴዎች ተጠሪነታቸዉ ለዋናው ኮሚቴ ሆኖ የአንድ ንዑስ ኮሚቴ
አባላት ብዛት ሶስት ይሆናሉ፡፡

አንቀጽ 12፡ የዩኒቨርሲቲውን ልዩ ዉሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮችና የመወሰን ስልጣን


12.1. ለፕሬዚዳንት እና ለም/ፕሬዚዳንቶች እንደተሾሙ በዩኒቨርሲቲዉ የተዘጋጁ ልዩ ቤቶች የሚሰጣቸዉ ሆኖ ከስልጣን ሲነሱ
ባለሦስት መኝታ ቤት የሚሰጣቸዉ ይሆናል፡፡ ለካምፓስ ዲኖች እና የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች ዲን ባለሁለት መኝታ ቤት እንደተሾሙ
የሚሰጣቸዉ ሲሆን ከኃላፊነት ቦታቸዉ ሲነሱ ሌላ ተመጣጣኝ ቤት ይሰጣቸዋል፡፡

14
12.2. በጋራ መኖሪያ ቤቶቹ አስተዳደራዊ ጉዳዩች፤ ዲሲፒሊንና ሌሎች ተያያዥ ነገሮችን ዩኒቨርሲቲው የመወሰን መብት አለው፡

አንቀጽ 13፡ የቤት ደልዳይ ኮሚቴ አውቃቀር

13.1. በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉትን ቤቶች ሁሉ ሁሉም ካምፓሶች ደረጃ ቤት ደልዳይ ኮሚቴ በሚከተለው ሁኔታ
ይዋቀራል፡፡

1. አካ/ፕ/መ/ል/ዳይሬክተር …………………………………………...… ሰብሳቢ

2. የትምህርት ጥራት ማጎልበቻና ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር… አባል

3. የሥርዓተ-ጾታ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ……………………….….….አባል

4. የሰው ሀብት ልማት አስተዳደርዳ ይሬክቶሬት ዳይሬክተር ………….. አባል

5. የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር …………….…..…….. አባል

6. የአካል ጉደተኞች ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር……..አባል

7. የንብረትና ፋሲሊቲ አሰተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ….አባልና ፀሐፊ

8. መምህራን ልማት ቡድን መሪ …...…………………………………….አባል

9. የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ ……………………………....አባል

13.2. የዩኒቨርሲቲው የበላይ አካል በሴኔት ሌጅስሌሽን መሠረት የቤት ደልዳይ ኮሚቴ በማዋቀር የቤት ድልደላ ሂደቱን
የማስፈጸም ግዴታ አለበት፡፡

ክፍል አምስት

15
አንቀጽ፡-14 ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

14.1. የህግ ተጠያቂነት

14.1.1. በዚህ መመሪያ ላይ የተገለጹትን ግዴታዎችን ተላልፎ የሚገኝ መምህር ይህንን መመሪያ ለማስፈጸም
በሚወጣዉ በዩኒቨርሲቲዉ የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስተዳደራዊ ልዩ መመሪያ መሰረት ተጠያቂነት አለበት፡፡

አንቀጽ 15፡ መመሪያዉን ስለማሻሻል

15.1. የአፈጻጸም ክፍተቶች ሲኖሩ ወይም ለሚመለከተው አስተዳደር አካል ጥያቄ ቀርቦ ሲወሰን ይህ መመሪያ ሊሻሻል ይችላል፡፡

አንቀጽ 16፡ ተፈጻሚነት የማይኖራቸው መመሪያዎች

16.1. ይህንን መመሪያ የሚቃረኑ ማንኛቸውም ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመኖሪያ ቤቶች ጋር የሚገናኙ አሠራሮችና ቀደምት
መመሪያዎች በዚህ መመሪያ ስለተተኩ ተፈጻሚነት አይኖራቸዉም፡፡

አንቀጽ 17፡ አባሪ


17.1. በጋራ መኖሪያ ቤት ጠያቂ መምህራን የሚሞላ የማመልከቻ ቅጽ እና ተወዳድረው ያሸነፉ መምህራን
የሚሞሉት ውል በአባሪነት ከመመሪያዉ ጋር ተያይዟል፡፡
17.2. በጋራ መኖሪያ ቤት ጠያቂ መምህራን የሚሞላ የማመልከቻ ቅጽ ከማስረጃዎች ጋር ተያይዞ የማይቅረብ ከሆነ
ዋጋ አይኖረውም፡፡

አንቀጽ 18፡ መመሪያ ስለማጽናት


ይህ መመሪያ ከዛሬ ከ 04/05/2014 ዓ/ም ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

ፊርማ-------------------
ፕሮፌሰር ታከለ ታደሠ
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
ፕሬዝዳነት

16
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማመልከቻ ቅጽ፤

1. ስም ከነአያት _______________________________

2. ፆታ፡- ወንድ_____ ሴት _____


3. የትምህርት ደረጃ
3. አካዳሚክ ማዕረግ _________________________________________________

4. የአገልግሎት ዘመን አጠቃላይ፡_

 በዩኒቨርሲቲው (ወሶዩ)___

 በሌላ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ______

 በመንግሥት ኮሌጅ____

5. ሥራ፡-

 የሚያስተምሩበት ትምህርት ክፍል _________________________________

 አሁን በኃላፊነት ካሉ ይገለጽ______________________________________

 ከዚህ በፊት የኃላፊነት አገልግሎት ዘመንና ቦታ_________________________

6. የጋብቻሁኔታ

 ያገባ _____

 ያላገባ _____

 የልጆችብዛት_____

7. ያገቡ ከሆነ ባለቤትዎ የዩኒቨርሲቲው መምህር(ት) ናቸው? አዎ_____ አይደሉም _____

8. አካል ጉዳተኛ ከሆኑ ብቻ ምልክት ያድርጉ

9. የጉዳቱ ዓይነት ይገለጽ_______________________________________________

አመልካች የሥራ ክፍል ኃላፊ

ስም_____________________ ስም _____________________

ፊርማ________________ ፊርማ ________________

ቀን______________ቀን________________ ማህተም

ማሳሰቢያ፡-

 የአገልግሎት ዘመን ሲሞሉ ቀን፣ ወርና ዓ.ም ይጥቀሱ፣

 ቅጹ በሚሞላበት ወቅት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፣

 ትክክለኛመረጃ ብቻ ይሙሉ፣

17
 በትምህርት ላይ የቆዩበት ጊዜ በአገልግሎት ዘመን ውስጥ አይካተትም፣

 ከላይ ለሚሰጡ ምላሾች አባሪ ማስረጃዎች መያያዝ አለባቸው፡፡

አዘጋጆች

1. መ/ር ሀርቆ ሀላላ


2. ዶ/ር መብራቱ በለጠ
3. ዶ/ር ጌታቸዉ ጌኖ
4. መ/ርት ንግስት አበበ
5. ወ/ሮ አታክልት ጌታቸዉ
6. አቶ እሸቱ ፋንታ

ማጠቃቃሻ የተጠቀምናቸዉ

 የከፍተኛ ትምህርት ተቋም አዋጅ 1152/11


 የዩኒቨርሲቲዉ ሌጅስሌሽን
 የቀድሞዉ የዩኒቨርሲቲዉ የጋራ መኖሪያ ቤት መመሪያ
 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
 ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ
 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

18
19

You might also like