You are on page 1of 20

የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት ባለሙያዎች መመሪያ

መመሪያ ቁጥር………/2012

ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

መስከረም/2011 ዓ.ም

0
ክፍል አንድ

1. አጠቃላይ ድንዳጌዎች
1.1 አጭር ርዕስ፡-
ይህ መመሪያ #በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳት ባለሙየሳዎች
መተዳደሪያ መመሪያ ቁጥር----/2012; ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፤
1.2 አውጭው አካል፡-
ይህ መመሪያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1152/2011
አንቀፅ 35/2 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሚኒስትሩ የወጣ ነው፡፡
1.3 ትርጓሜ
በዚህ መመሪያ ውስጥ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር፡-
ሀ. #የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት; ማለት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በማስተማሪያ ሆስፒታሎች
በሚገኙ በላብራቶሪ፣ በፋርማሲ፣ በወርክሾፕ እና በመስከ የተግባር ትምህርት ለመስጠት እንዲሁም
የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራን በሙያው ለማገዝ የተቀጠረ ነው፡፡
ለ. #የተግባር ትምህርት; ማለት በቤተሙከራ (በወርክሾፕ) እና በመስክ ትምህርት ለተማሪዎች የሚሰጥን
ትምህርት ያጠቃልላል፡፡
ሐ. #ቤተሙከራ; ማለት ለተፈጥሮ ሳይንስ፣ ማህበራዊ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ትምህርት በአንድ ክፍል
በተደራጁ መሳሪያዎችን በመጠቀም በሳይንሳዊ ምርምር ሙከራዎች የሚደረግበት ክፍል ነው፡፡
መ. #የመስክ ትምህርት; ማለት የተፈጥሮ ሳይንስ፣ የማህበራዊ ሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ትምህርት
በተግባር በመታገዝ በመስክ የሚሰጥ ትምህርት ነው፡፡
ሠ. #ወርክሾፕ; ማለት የተለያዩ መሳሪያዎችንና ማሽኖችን በያዘ ክፍል ውስጥ የተግባር ትምህርት
የሚሰጥበት ማለት ነው፡፡
1.4 የጾታ አገላለጽ
 በዚህ መመሪያ በወንድ ጾታ የተገለጸው ለሴት ጾታ ያገለግላል፡፡

1.5 ተፈጻሚነት ወሰን


 ይህ መመሪያ በሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በምርምር ጣቢያዎችና በልህቀት
ማዕከላት እና በማስተማሪያ ሆስፒታሎቸ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
1.6 ዓላማ
1
ሀ. በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መስኮች ላይ ያተኮረው የከፍተኛ ትምህርት ሰፊ የተግባር
ትምህርትን የሚያካትት በመሆኑ፣ በዚህ ረገድ ተማሪዎች የተሻለ የተግባር ትምህርት የሚያገኙበትን
መንገድ ለማመቻቸት፡፡

ለ. የተግባር ትምህርት የሚሰጡ ባለሙያዎች የሚኖራቸውን መብት ተግባር እና ሃላፊነት እንዲሁም ማግኘት
የሚገባቸውን የደረጃ እድገት ደሞዝ እና ጥቅማ ጥቅም ለመወሰን፡፡

ሐ. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚኖረውን የወርክሾፖች፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የኢንደስትሪ ትስስሮች፣


የልህቀት ማዕከላት፣ የመስክ የተግባር ትምህርት፣ ምርምሮችና የማህበረሰብ አገልግሎቶችን ለማሻሻል
ውጤታማ ለማድረግና ከስራው ባህሪ አንፃር የባለሙያዎችን ተጠቃሚነትና መብት ለማረጋገጥ፣

1.7 መርህ
ሀ. በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥ የሆነ የአስራር ስርዓት ለመዘርጋት፣
ለ. የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳት ባለሙያን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፤
ሐ. በከፍተኛ ትመህርት ተቋማት የሚሰጡ ተግባር ትምህርትንና የምርምር ስራን ጥራን
ለማስጠበቅ፡፡

ክፍል ሁለት

2. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት ባለሙያዎች ተግባርና ኃላፊነት፣መብትና ግዴታዎች እና ሙያው የሚጠይቀው


ዕውቀትና ክህሎት፤

2.1. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት ባለሙያዎች ተግባርና ኃላፊነት


ሀ. የቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የተግባር ትምህርት በሙያው መደገፍ፤
 ተማሪዎች ፕሮጀከት ለመስራት እንደ መነሻ ሃሳብነት የሚያገለግሉ የተለያዩ ናሙና

ፕሮጀክቶችን ሰርቶ ያቀርባል፤

 የተግባር (የቤተ-ሙከራ/የመስክ) ትምህርት በሚሰጥባቸው በቅድመ ምረቃ እና በድህረ

ምረቃ የሚሰጡ ትምህርቶችን የስተባብራል፤

 ለተግባር ትምህርት የሚያገለግሉ የተለያዩ አይነት ማንዋሎችን በጥራት አዘጋጅቶ ጥቅም

ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ የተዘጋጁ ማንዋሎችን ይገመግማል፣ ማስተካከያ ይሰጣል፤

2
 የቴክኖሎጅ እድገትና መሻሻልን በመከተል የላቦራቶሪ እና የመስክ ትምህርት የላቀ፤ ቀልጣፋና

ውጤታማ ያደርጋል፤

 የላቦራቶሪ እና የመስክ የስራ በሀላፊነትን ይመምራል፣ የተግባር ትምህርት የሚወስዱ

ተማሪዎችንም ያስተባብራል፤

 በላቦራቶሪና በመስክ የሚሰሩ ማንኛውንም የተግባር ትምህርት ውጤቶች ትክክል

መሆናቸውን ያረጋግጣል፤

 የተለያዩ የላብራቶሪ /የመስክ፣ የወርክ ሾፕ መሳሪያዎችን መግጠም፣ መፍታት፣ ማደራጀት፣

ብቃታቸውን በማረጋገጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣

 ከሌሎች የሚመለከታቸው መምህራን እና ተመራማሪዎች ጋር በመተባበር የተለያዩ

ላብራቶሪ (ወርክ ሾፕ ) እንዲደራጁ ያደረጋል፤


 የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎችን በቤተ-ሙከራ /በመስክ የሚወስዱትን የተግባር
/የመስክ ትምህርቶችን ዓለማቀፋዊ ደረጃውን በጠበቀ መልክ እንዲማሩና እንዲመራመሩ
ያመቻቻል፣
 ከቤተ- ሙከራ/ከመስክ ስራ የሚገኙ ማንኛውንም የልኬት ወይም የምልከታ ውጤቶች
ትክክል መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
 ቤተ-ሙከራ እና የቤተ ሙከራ መሳሪያዎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ
ተሟልተው እንዲቀርቡ ሙያዊ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤
 አዲስ ቤተ-ሙከራ ለማቋቋም የሚያስችል በጥናት ላይ የተመሰረተ ምከረ-ሃሳብ (ፕሮፖዛል)
ሰርቶ ያቀርባል፤ ሲፈቀድም ተከታትሎ ያስፈጽማል፤
 አመታዊ የስራ እቅድ ከመምህራንና ከተመራማሪዎች ጋር በቅንጅት ያወጣል፣ የተግባር

ትምህርት ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል፤


 ኢንዱስትሪዎችን የሚደግፍ የተግባር ሞዴል ዲዛይን ለፋብሪካዎችና ተዛማጅ ሴክተሮች
ይሰራል ፤ሙያዊ ድጋፍም ይሰጣል፣
 ጥናትና ምርምር ለሚሰሩ አካላት የላቦራቶሪ እና የመስክ ስራዎችን የማመቻቸት

ውጤቶችን የመተንተን ስራ ይሰራል፤

3
 ኢንዱስትሪዎችን የሚደግፍ ቴክኖሎጂ በማላመድ የአሰራር ሲስተሞች በመዘርጋት

ለፋብሪካዎች እና ለመሳሰሉ ተዛማጅ ሴክተሮች ሙያዊ ድጋፍ ይስጣል፣

 በጥናትና ምርምር ዙሪያ የተገኙ ውጤቶችና መረጃዎችን በማጠናከር በጥንቃቄ ይይዛል፤

እንደ አስፈላጊነቱ ውጤቱንም ለጥናትና ምርምር ማዕከል ሪፖርት ያደርጋል፤


 የተግባር (የቤተ-ሙከራ/የመስክ) ትምህርቱን ወይም የምርምር ስራውን ውጤታማ
ለማድረግ ለማንዋሎች ዝግጅት የሚረዳ የዳሰሳ ጥናት ያደርጋል፣ የተዘጋጁ ማንዋሎችን
ይገመግማል፣ ማስተካከያ ይሰጣል፤
 ለተግባር (የቤተ-ሙከራ/ወርክሾፕ፣የመስክ) ትምህርትና ምርምር ስራ መማሪያ የሚሆኑ
ማንዋሎችን በየደረጃው ያዘጋጃል፣
 ተማሪዎች ፕሮጀከት ለመስራት እንደ መነሻ ሃሳብነት ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ የተለያዩ
ንድፈ ሃሳብ ፕሮጀክቶችን የሚሰሩበትን ቅድመ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
 የተግባር (የቤተ-ሙከራ/ወርክሾፕ፣የመስክ) ትምህርት ወይም ምርምር የስራ ሁኔታውን
ከግብ ለማድረስ አዳዲስ የጥናት ሃሳቦችን ያቀርባል፤
 የተማሪዎች የመመረቂያ ፕሮጀክቶች እና ሌሎች ስራዎች ላይ ሙያዊ የድጋፍና የምክር
አገልግሎት ይሰጣል፤
 በተቋሙ ያሉት የምርምር ውጤቶች ከተመራማሪው ጋር በመቀናጀትና ሙያዊ ድጋፍ

በማድረግ ወደ ማህብረሰቡ እንዲወርዱ ያደርጋል፤


 ተማሪዎች ተግባራዊ ልምምድ በሚያደርጉበት ወቅት ለማህረሰቡ የሚጠቅም ምርምር

እንዲያካሂዱ እገዛ ያደርጋል፤

 ከቤተ ሙከራ/ወርክ ሾፕ ጋር በተያያዘ በአካባቢ ላይ ከሚደርሱ ተጽዕኖ በጸዳ ሁኔታ

የሚሰራበትን የተለያየ ዘዴዎችን በመቀየስ ተግባራዊ እንዲሆኑ የበኩሉን አስተዋጽኦ

ያደረጋል፤

 ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ የተለያዩ ሙያዊ ስራዎችን ይሰራል፤

2.2. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት ባለሙያ መብቶች፤

 የአካዳሚክ ነጻነት ከዩንቨርስቲው ተልእኮ መሰረት ባደረገ መልኩ ይተገብራል፤

 የአጭርና የረጂም ጊዜ ትምህርትና ስልጠ የማግኘት መብት ይኖረዋል፤


4
 ለከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመምህርነት ባለው የማስተማር ክፍት ቦታ በውስጥ የእርስ

በዕርስ ውድድር ተወዳድሮ መምህር የመሆን፤

 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚሰጡዋቸው አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ከሚያገኙዋቸው

ተጨማሪ ስራዎች የአካዳሚ ቴክኒክ ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎችን ስራው የሚያሳትፍ

በሚሆንበት ጊዜ ፍትሃዊ የሆነ ጥቅም የማግኘት፤

 ከመንግስት ሰራተኞች የመደበኛ የስራ ስዓት ውጭ ለሰሩት ስራ ክፍያ የመጠየቅ፤

 በሁለት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በአካዳሚ ቴክኒክ ድጋፍ ሰጭ ባለሙያው መካከል

በሚደረግ ስምምነት መሰረት የመዛወር፤

 ፍትሃዊና መመሪያን መሰረት ያደረገ አስተዳደራዊ ጥቅማ ጥቅም፤ ደመወዝና የደረጃ

ዕድገት፤ ማበረታቻ የማግኘት፤

 በዩንቨርስቲው የአካዳሚክ ስራዎችን በሚመለከት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን

የማቀድ እና ስራዎችን የመገምገም ተሳትፎ፤

 በዩኒቨርስቲው በሚወሰኑ ውሳኔዎች ውስጥ እንደማንኛውም የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ

የመሳተፍ መብት ይኖረዋል፤

 የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት በስራው ምክንያት ለሚደርስበት የጤና መዛባት፣ የአካል ጉድለት፣

የህይወት ዋስትና የማግኘት፤

2.3. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት ባለሙያ ግዴታዎች

 በተቋሙ ተልዕኮ፣ እሴቶች እና ሥርዓት መሰረት የተግባር ትምህርት፣ ምርመርና ማህበረሰብ


አገልግሎቶችን የመደገፍ ስራ ይሰራል፣
 ለተግባር ትምህርት የሚያገለግሉ የተለያዩ አይነት ማንዋሎችን በጥራት አዘጋጅቶ ጥቅም
ላይ እንዲውሉ የማድረግ፤ የተዘጋጁ ማኑዋሎችን የመገምገም ብሎም ማስተካከያ መስጠት
አለበት፤
 ተማሪዎች ፕሮጀከት ለመስራት እንደ መነሻ ሃሳብነት የሚያገለግሉ የተለያዩ ናሙና
ፕሮጀክቶችን መስራት አለበት፤

5
 ለተግባር ትምህርት የተገዙ ቁሳቁሶችን ተማሪዎች በጥንቃቄ እንዲጠቀሙ የማድረግ፤
ማስተካካልና ትክክለኛ ያልሆኑትን በማሻሻልና በማጠናከር በጥንቃቄ የመያዝና እንደ
አስፈላጊነቱም በጥናትና ምርምር ዙሪያ የተገኙ ውጤቶችና መረጃዎችን ስህተትና ችግር
ያለባቸውን ለይቶ ውጤቱንም ለጥናትና ምርምር ማዕከል ሪፖርት ማድረግ አለበት፤
 ተማሪዎች ያላቸውን የተግባር እውቀት ክፍተት ለመሙላት ሳይንሳዊ እና ተግባራዊ ድጋፍ
ማድረግ አለበት፤
 የተማሪዎችን የተግባር ትምህርት ምዘና ውጤት ምስጥራዊነቱን መጠበቅ፤ የተጀምሩ
ወይም ያላለቁ ስራዎች የተለያዩ አይነት ጥናቶችን እና ተገቢ ባልሆኑ ሰዎች እጅ
እንዳይወድቁ በኃላፊነት መጠበቅ፤
 ተማሪዎች የተቋሙን ተልዕኮ መሪ እሴቶችና የከፍተኛ ትምህርት ዓላማዎችን እንዲያውቁ
የማገዝና የመርዳት፤ ሙያዊ ምክር አገልግሎት የመስጠት፣ በተግባር የተማሩትን
ተማሪዎችን የመመዘን እና ውጤት የመስጠት፣ የተማሪዎችን ቅሬታዎችንና አቤቱታዎችን
የማስተናገድና በአጠቃላይ የሚጠበቅበትን ሙያዊ ስነ ምግባር መወጣት አለበት፤
 የከፍተኛ ትምህርት ዓላማዎችንና ተቋሙ የሚመራባቸውን እሴቶች የማክበር፤
የመተግበርና በሙያዊ ስነ ምግባርና አግባብነት መወጣት ይኖርበታል፤
 ለመንግስት ሰራተኞች የመደበኛ ጊዜ የስራ ስዓት መሰረት በማድረግ በቀን 8 ስዓት
የመስራት፤
 ልዩ ፍላጎት የሚሹ ተማሪዎችን የመደገፍ እና የማብቃት ሃላፊነት አለበት፤

2.4. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት ባለሙያዎች የሚጠበቁ ክህሎት እና እውቀት


 ተግባርና ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት የሚያስችለው የትምህርት ዝግጅት እና ክህሎት

ያለው ባለሙያ ሊሆን ይገባል፤

 በተናጠል እና በቡድን መስራት የሚያስችለው ተግባቦት ክህሎት (communication skill)

ይኖረዋል፤

 በላብራቶሪ ወይም ወርክሾፕ የሚገኙ ሳይንሳዊ መሳሪያዎችን የመጠቀምና ሌሎችን

የመምራትና የማሳየት ክህሎት ይኖረዋል፤

 መሰረታዊ የኮምፒውተር የመጠቀም ክህሎት ያለው መሆን አለበት፤

 የተግባር ትምህርትን የማቀድና ሪፖርትን የማዘጋጀት ችሎታ ይኖረዋል፤


6
 የላብራቶሪ/የመስክ ማኑዋሎችን በማዘጋጅት የተግባር ትምህርት ፕሮግራም ማዘጋጀት

አለበት፤

 የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት በስራው ዘርፍ ለሚነሱ ቴክኒካዊ ለሆኑ ችግሮች ወቅታዊና

አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣል፣

ክፍል ሦስት
3. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳቶች ደረጃ፣ ጥቅማጥቅምና የደሞዝ ስኬል

3.1. ደረጃ ዕድገት አፈፃጸም


ለሁሉም የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት ደረጃቸውን በጠበቁና የትምህርት ዝግጅታቸውን መሠረት
ያደረገ ቅጥር የሚፈጸም ሲሆን ትምህርቱን በማሻሻሉ፣ በአገልግሎቱ እና የሥራ አፈጻጸሙ ታይቶና
ተመዝኖ ወደ ቀጣዩ የእድገት መሰላል ይሸጋገራል። ስለሆነም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳቶች እያንዳንዳቸው ሶስት ደረጃ ያለው ሶስት ተዋረድ ያለው
የዕድገት መሰላል ይኖረዋል፡፡ እነሱም፡-

ሀ. ደረጃ አንድ፡- የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት I፣ II እና III፣


ለ. ደረጃ ሁለት፡- ሲኒየር የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት I፣ II እና III እና
ሐ. ደረጃ ሦስት፡- ቺፍ የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት I፣ II እና III ተብለው ይጠራሉ።

3.2. በንዑስ አንቀፅ 3.1 የተዘረዘሩት ሦስት ዋና ዋና የዕድገት መሰላሎች እያንዳንዳቸው በሦስት ተዋረዶች ወይም

እርከኖች የተከፋፈሉ ሲሆን የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳቶች ደረጃቸውን ማሻሻል የሚችሉት የትምህርት
ዝግጅታቸውን መሰረት አድርጎ ይሆናል፡፡ በዚሁም መሰረት፡-

ሀ. የመጀመሪያው ሶስት ተዋረድ/እርከን የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት ዲፕሎማ ወይም


ተመጣጣኝ የሆነ የትምህርት ዝግጅት ሊኖረው ይገባል፣

ለ. ሲንየር የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው፣

ሐ. ቺፍ የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት ሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ዝግጅት የሚጠይቅ ይሆናል።

3.3. ዝርዝር የሙያ መሰላሉም የሚከተለው ቅርፅ ይኖረዋል፡-

7
ሀ. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት I
ለ. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት II
ሐ. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት III
መ. ሲንየር የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት I
ሠ. ሲንየር የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት II
ረ. ሲንየር የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት III
ሰ. ቺፍ የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት I
ሸ. ቺፍ የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት II
ቀ. ቺፍ የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት III

3.4. የደሞዝ ስኬልና ደረጃ


የአካዳሚክ ቴክኒክ ድጋፍ ባለሙያ የደመወዝ ደረጃ እና ደመወዝ ስኬል በስራ ምዘና የደረጃ ጥናት
መሰረት ይሆናል፤

3.5. ለየደረጃው የተሰጠው የስራ ዝርዝርና የሚጠበቅ ውጤት

ሀ. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት በሥራ መደቡ በመማር ማስተማር የሚጠበቁ ተግባራት፡-

 ተማሪዎችና መምህራን በመማር ማስተማር፣ ጥናትና ምርምር ሲያደርጉ ማገዝና

ማስተባበር፣

 ለተግባር ትምህርት ወደ ወርክሾፕ የሚመጡ ተማሪዎች በአካላቸው ላይ ጉዳት

እንዳይደርስባቸው መሠረታዊ የቅድመ ጥንቃቄ ትምህርት ይሰጣል፣

 ለተግባራዊ ትምህርቶችና የምርምር ስራዎች የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝግጅት ያደርጋል፤

አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም የምርምርና የመስክ ስራውን ያግዛል፣ያስተባብራል፤

 ተማሪዎች በቤተ-ሙከራና በመስክ ወቅት የሚጠቀሙበትን በተዘጋጀ ማኑዋል (የተግባራዊ

ትምህርት ማስተማሪያ ጽሑፍ/መጽሓፍ ቀድሞ የተዘጋጀውን ለተማሪዎች እንዲደርስ

ያደርጋል)፣
 ተግባራዊ የሙከራ ትምህርቶች በሚሰጡበት ጊዜ ቀድሞ ወደ ቤተ ሙከራ በመግባት

በእለቱ ለሚሰጠው ተግባራዊ ትምህርት ቤተ-ሙከራውን ለስራ ዝግጁ ያደርጋል፣


8
 ተማሪዎች ተግባራዊ ሙከራ ሲያደርጉ በመከታተል በሙከራ መሳሪያዎችም ሆነ
በራሳቸው ላይ ጉዳት ሳያደርሱ ስራቸውን በአግባቡ እንዲጨርሱ ክትትልና ድጋፍ

ያደርጋል፣

 ለተማሪዎች ከትምህርት ክፍል ውጭ ሙያዊ እገዛ ያደርጋል፣

 ተማሪዎች ፕሮጀክት ሲሰሩ እንዲሁም መምህራንና ሰራተኞች ቤተ-ሙከራውን

ለአጫጭር ስልጠናዎችና ልምድ ልውውጥ ሲፈልጉት የመስክ ትምህርት ሲኖር

አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል፤

 በመምህሩ የተዘጋጀውን የተግባርና የጽሁፍ ፈተና ይፈትናል፣

 ተማሪዎች በየቡድናቸው ሆነው የተዘጋጀውን ቁሳቁስ (materials) ተጠቅመው የተግባር

ትምህርታቸውን እንዲማሩ ተግባራዊ ጽንሰ ሀሳብ በመስጠት ይሳተፋል፣

 የመማር ማስተማር እቃዎች በአግባቡ ያደራጃል፣ ለተማሪዎችና ለተቋሙ ድጋፍ ሰጪ

ሰራተኞች ስልጠናዎች ሲሰጡ ድጋፍ ያደርጋል፣

 የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸውና የተበላሹ ዕቃዎችንና መሳሪያዎች እንዲጠገኑ

ወይም እንዲሰሩ ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ያደርጋል፣

 ስልጠና ለሚያስፈልጋቸው የዩኒቨርሲቲው ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች አጫጭር ስልጠናዎች

ሲሰጡ ያግዛል፣

 ተማሪዎች በክፍልና በቤተ-ሙከራ ውስጥ የተማሩትን በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የተግባር

ጉብኝት እንዲያገኙ ሃሳብ ያቀርባል በጉብኝት ወቅትም ይደግፋል፣

 የቤተ-ሙከራና የመስክ መርጃ መሳሪያዎች በአስፈላጊ ቦታዎችና ሁኔታ መቀመጣቸውን

የቤተ-ሙከራ እቃዎች እንዳይጎዱ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ያደርጋል፣

 ቤተ-ሙከራዎች ለምርምር አገልገሎት ምቹ እንዲሆን ያደርጋል፣

 የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለትምህርት ክፍል ኃላፊ ያቀርባል፣

9
ለ. የሥራው ክብደት (ውስብስብነት)

 ስራው ተማሪዎችና መምህራን በመማር ማስተማር፣ ጥናትና ምርምር ሲያደርጉ ማገዝ፣

የመማር ማስተማር እቃዎች በአግባቡ ማደራጀት፣ ለተማሪዎችና ለተቋሙ ድጋፍ ሰጪ

ሰራተኞች ስልጠናዎች ሲሰጡ እገዛ ማድረግ፣ የተዘጋጁ የጽሁፍ ፈተናዎች መፈተን፤

 በክንውን ጊዜው ስራው የቴክኖሎጂ መለዋወጥ፣ የተለያዩ የትምህርት አቀባበል ደረጃ

ያላቸው ተማሪዎች መኖር፣ ተማሪዎች የሚሰሩት ፕሮጀክቶችም ሆነ ፈተናዎች ከሌሎች

ተማሪዎች መገልበጥ፣ ተግባራዊ የሆኑ በቂ መረጃ ያለማግኘት፣

 የቴክኒክ ባለሙያው ወቅቱን የጠበቀ የተለያዩ ቴክኖሎጂ መጠቀም፣ የእውቀት ክፍተት

ላለባቸው ሰፊ ጊዜ ሰጥቶ በመርዳት፣ በፈተናም ሆነ ፕሮጀክቶች ሲሰሩ ጥብቅ ቁጥጥር

በማድረግ መከታተል፣ ተማሪዎች በተግባር ወደ ህብረተሰቡ ወርደው መረጃ በማምጣት

የሚፈቱ ችግሮች ናቸው፡፡


 ተማሪዎችና መምህራን በመማር ማስተማር፣ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት
ሲሰሩ ማገዝ፣ የመማር ማስተማር ቁሳቁሶች በአግባቡ ማደራጀት፣ ለተማሪዎችና ለተቋሙ
ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ስልጠናዎች ሲሰጡ ድጋፍ ማድረግ፣

3.6. ሲኒየር አካዳሚክ ቴክኒካል ረዳቶች (Senior Technical Assistant)

ሀ. ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት

 ማንዋሎችን በማዘጋጀት ለቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የተግባር ትምህርት ከኮርሱ መምህር

ጋር በመተባበር ያሳያል፣ የተለያዩ ምርምሮችን ያግዛል፣

 የተግባር (የቤተ-ሙከራ/የመስክ/ዎርክሾፕ) ትምህርት ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል በእቅዳቸው

መሰረት እንዲሰሩ ያደርጋል፣

 ተማሪዎች በቤተ-ሙከራ/በመስክ/ዎርክሾፕ ስራ የሰበሰቡትን የልኬት/የምልከታ መረጃ

ተመልክቶ ያረጋግጣል፣ በመረጃው መሰረት የሚጽፉትን ሪፖርት ስብስቦ ያርማል

ውጤታቸውንም ያስተላልፋል፣

10
 የተግባር (የቤተ-ሙከራ/የመስክ/ዎርክሾፕ) ትምህርት በሚሰጥባቸው በቅድመ ምረቃ

በቅድሚያ በሚሰጡ (Introduction) የተግባር ትምህርቶችን ገለጻ (Orentation) እንዲሰጥ

ያደርጋል፤

 የተግባር (የቤተ-ሙከራ/የመስክ/ዎርክሾፕ) ትምህርት ከመምህራን ጋር በመሆን በየደረጃው

የተግባር ፈተናዎችን እንድዘጋጁና እንድፈተኑ ውጤታቸውም እንድጠናቀር ያደርጋል፤

 የተግባር (የቤተ-ሙከራ/የመስክ/ዎርክሾፕ) ትምህርት መርሃ-ግብሮችን ያዘጋጃል፤ ስራዎችን

በዕቅዳቸው መሰረት መስራታቸውንም ይከታተላል፡፡

 የተግባር (የቤተ-ሙከራ/የመስክ/ዎርክሾፕ) ትምህርቱን/ምርምሩን ውጤታማ ለማድረግ

ለማንዋሎች ዝግጅት የሚረዳ የዳሰሳ ጥናት ላይ እገዛ ያደርጋል፣

 ለተግባር (የቤተ-ሙከራ/የመስክ/ዎርክሾፕ) ትምህርትና ምርምር ስራ መመሪያ የሚሆኑ

ማንሎችን ያዘጋጃል፣

 በቤተሙካራና በወርክሾች ለጥናትና ምርምር የሚሆኑ መረጃዎችን ለሚፈልጉ ባለሙያዎች

መረጃ ያሰባስባል፣ ትብብርም ያደርጋል፣

 መምህራን እና ሰራተኞች አጫጭር ተግባራዊ ስልጠና እና ልምድ ልውውጥ ሲያደርጉ ቤተ-

ሙከራውን መጠቀም ሲያስፈልጋቸው አስፈላጊዉን ሙያዊ እገዛ ያደርጋል፡፡

 ቤተ-ሙከራውን ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ እና ስለመሳሪያዎች አጠቃቀም ኦረንቴሽን

ይሰጣል፡፡

 የተለያዩ ኬሚካሎችንና የሙከራ መሳሪያዎችን ለስራ ዝግጁ በማድረግ ቅድመ ሙከራ

ያደርጋል፣

 በቤተ-ሙከራ ውስጥ ስለሚገኙ የተለያዩ አይነት መሳሪያዎች አጠቃቀም እና መመሪያዎች፤

ደንቦችና ህግጋት ለተማሪዎች ያስጨብጣል፣ በጥንቃቄ እንዲሰሩ ያደርጋል፣

 ለተግባር (ለቤተ-ሙከራ/ለመስክ/ዎርክሾፕ) ትምህርት/ምርምር የሚያስፈልጉ የተለያዩ

ቁሳቁሶች እንዲሟሉ ያደርጋል፤

 ለቤተ-ሙከራ/ለመስክ/ዎርክሾፕ የሚያስፈልጉ የተለያዮ ቁሳቁሶችን እንዲገዙ የግዥ ፍላጎት

ያቀርባል፤

11
 የመሳሪያዎችን የተግባር ልኬት (Calibration) ያስተካክላል፣ በልኬታቸው መሰረት

መስራታቸውንም ለቤተ ሙከራ /ለመስክ /ለዎርክሾፕ  ተግዝተው  የተበላሹ መሳሪያዎችን 

ይፈትሻል፣ ብልሽቶችንም መዝግቦ በመያዝ ሪፖርት ያደርጋል፣ ይገመግማል አስፈላጊውንም

ክትትል ያደርጋል፣

 ለቤተ-ሙከራ /ለመስክ /ለዎርክሾፕ የተገዙ እቃዎችን በተጠየቀው መሰረት መገዛታቸውን

ፈትሾ ያረጋግጣል አስፈላጊውንም ማስተካከያ እንዲደረግበት ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፤

 የቤተ-ሙከራ /ለመስክ /ለዎርክሾፕ የሚያገለግሉ እቃዎችን ሲበላሹ ቀላል ጥገና ያደርጋል፣

ለ. የሥራው ክብደት (ውስብስብነት)

 ስራው ተማሪዎችን የተግባር ትምህርት መምራትና እና እንዲመዘኑ የማድረግ፤

ለዩኒቨርሲቲው ሰራተኞችና መምህራን አጫጭር ስልጠናዎችን ማመቻቸት፤

የመሳሪያዎችን የትግባር ልኬት (Calibration) ማስተካከል ብሎም በልኬይታቸው መሰረት

መገኘቱን የመገምገም፤ የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን ማገዝ፤ ተግባራዊ በሆኑ በማህረሰብ

አገልግሎቶች ላይ መሳተፍ እና መተግበር ነው፣

 በክንውን ጊዜው ስራው የተግባር እና የቴክኖሎጂ ሁኔታው ተለዋዋጭ መሆኑ፣ ትምህርትን

በአቀባበል ደረጃቸው የተለያዩ ተማሪዎች መኖራቸው፣ ተማሪዎች የሚሰሩት

ፕሮጀክቶችም ሆነ ፈተናዎች ከሌሎች ተማሪዎች የመኮራረጅ፣ ተማሪዎች ተግባራዊ የሆኑ

በቂ መረጃ ያለማግኘት፤ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን ማህበረሰቡ ቶሎ ያለመረዳት፤ ለተግባር

ትምህርት የሚገዙ እቃዎች ከካምፓኒዎች በቂ የአጠቃቀም ስልጠና ያለማግኘት፣

 ተማሪዎችን ተግባራዊ እውቀት ለማስጨበጥ አስፈላጊ የጥናትና ምርምር እውቀቱን

ማሳደግ፣ የእውቀት ክፍተት ላለባቸው ተማሪዎች ሰፊ ጊዜ ሰጥቶ የተለያዮ ዘዴዎችን

በመጠቀም፣ በፈተናም ሆነ ፕሮጀክቶች ሲሰሩ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ መከታተል፣

ተማሪዎች በተግባር ወደ ህብረተሰቡ ወርደው መረጃ በማምጣት፤ ከማህበረሰቡ ጋር

ውይይት ማድረግ፤ ከካምፓኒዎች ጋር የጠበቀ ግንኙንተ በመፍጠር የሚፈቱ ችግሮች

ናቸው፡፡

12
3.7. ቺፍ አካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት

ሀ. በሥራ መደቡ መማር ማስተማር ላይ የሚጠበቁ ተግባራት

 የተግባር ትምህርትና ስልጠና ማንዋሎችን በማዘጋጀት ለቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ

ተማሪዎች የተግባር ትምህርት ማስተማርና ተግባራዊ ስልጠናዎችን ይሰጣል፤


 የተግባር (የቤተ-ሙከራ/የመስክ/ወርክሾፕ) ትምህርት ያስተምራል፤
 ተማሪዎች በቤተ-ሙከራ/ በመስክ/ ወርክሾፕ የሚወስዱትን የተግባር ወይም የመስክ
ትምህርቶችን ዓለም አቀፋዊ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ እንዲማሩና እንዲመራመሩ
ያደርጋል፤
 የተግባር (የቤተ-ሙከራ/የመስክ/ወርክሾፕ) ትምህርት በሚሰጥባቸው በቅድመ ምረቃ

(Advanced) ትምህርቶች እና በድህረ ምረቃ (Introduction) የተግባር ትምህርቶችን

ያስተምራል፤
 የተግባር (የቤተ-ሙከራ/የመስክ/ወርክሾፕ) ትምህርት ላይ ተማሪዎችን ይመዝናል፣ የተግባር
ፈተናዎችን በደረጃው አዘጋጅቶ ይፈትናል፣ ውጤታቸውንም ሪፖርት ያደርጋል፤
 ከቤተ-ሙከራ/ከመስክ/ወርክሾፕ ስራ የሚገኙ ማንኛውንም የልኬት /የምልከታ/ ውጤቶች
ትክክል መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
 በቤተ-ሙከራ/በመስክ/በወርክሾፕ ተማሪዎች የተግባር ልምምድ የሚያደርጉበትን ሁኔታ
ያመቻቸል፤
 ከተግባር ትምህርት ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ችግር ፈቺ የሆኑና የተለያዩ ወቅቱን የጠበቁ

ጥናትና ምርምሮችን ያደርጋል፤


 የተግባር ትምህርቱን (የቤተ-ሙከራ/የመስክ/ወርክሾፕ)/ምርምሩን ውጤታማ ለማድረግ
ለማንዋሎች ዝግጅት የሚረዳ የዳሰሳ ጥናት ያደርጋል፣ የተዘጋጁ ማንዋሎችን ይገመግማል
ማስተካከያም ይሰጣል፤
 ለተግባር (የቤተ-ሙከራ/የመስክ/ወርክሾፕ) ትምህርትና ምርምር ስራ መማሪያ የሚሆኑ
ማንዋሎችን በደረጃው ያዘጋጃል፤
 ተማሪዎች ፕሮጀከት ለመስራት እንደ መነሻ ሃሳብነት ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ የተለያዩ
ናሙና (Sample) ፕሮጀክቶችን የሚሰሩበትን ቅድመ ጥናትና ምርምር ያደርጋል፤

13
 የተግባር(የቤተ-ሙከራ/የመስክ/ወርክሾፕ) ትምህርት/ምርምር የስራ ሁኔታውን ከግብ
ለማድረስ ክህሎቱን እና እውቀቱን ያበረክታል፤
 ጥናትና ምርምር ለሚሰሩ ተማሪዎችም ሆነ መረጃ ለሚፈልጉ የቤተ-ሙከራ አግልግሎትና
ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
 በጥናትና ምርምር ዙሪያ የተገኙ ውጤቶችና መረጃዎችን በማጣራት ስህተትና ችግሮች
ያለባቸውን ለይቶ ያስተካካል፣ ትክክለኛ የሆኑትን በማሻሻልና በማጠናከር በጥንቃቄ ይይዛል፤
እንደአስፈላጊነቱ ውጤቱንም ለጥናትና ምርምር ማዕከል ሪፖርት ያደርጋል፤
 የጥናትና ምርምር ደረጃን ለማሳደግ ከተለያዩ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት ያሉ
የምርምር ማዕከሎች ጋር የግንኙነት መረብ በመፍጠርና በማጠናከር የስራ ትብብርና የመረጃ
ልውውጥ ስርዓት ይፈጥራል፤
 ነባር ቤተ-ሙከራዎች የቤተ-ሙከራ መሳሪያዎችን በሟሟላት ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን
የጠበቁ እንዲሆኑ ጥረት ያደርጋል፤
 አዲስ ቤተ-ሙከራ ለማቋቋዋም የሚያስችል በጥናት ላይ የተመሰረተ ምከረ-ሃሳብ
(ፕሮፖዛል) ሰርቶ ያቀርባል፤ ሲፈቀድም ተከታትሎ ያስፈጽማል፤
 በስሩ ካሉ ሰራተኞች ጋር በጋራ መግባባት ላይ መሰረት ያደረገ እቅዶችን በማውጣት
ተግባራዊ ያደርጋል፤
 ኢንዱስትሪዎችን የሚደግፍ የተግባር ሞዴል ዲዛይን ለፋብሪካዎችና ተዛማጅ ሴክተሮች
ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
ለ. የሥራው ክብደት (ውስብስብነት)
 ስራው የተግባር ትምህርትና ስልጠና ማንዋሎችን በማዘጋጀት የቅድመ ምረቃና የድህረ

ምረቃ ትምህርትንና የጥናትና ምርምር ስራዎችን የመደገፍ፣ ተማሪዎች በቤተ-

ሙከራ/በመስክ/ወርክሾፕ የሚወስዱትን የተግባር /የመስክ ትምህርቶችን ዓለም አቀፋዊ

ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ እንዲማሩ እና እንዲመራመሩ የማድረግ፤ የተግባር (የቤተ-

ሙከራ/የመስክ/ወርክሾፕ) ትምህርት ላይ ተማሪዎችን የመመዘን፣ የተግባር ፈተናዎችን

በደረጃው አዘጋጅቶ የመፈተንና ውጤታቸውን ሪፖርት የማድረግ፤ ከቤተ-

ሙከራ/ከመስክ/ወርክሾፕ ስራ የሚገኙ ማንኛውንም የልኬት /የምልከታ ውጤቶች ትክክል

መሆናቸውን ማረጋገጥ፤ የተግባር ትምህርቱን (የቤተ-ሙከራ/የመስክ/ወርክሾፕ)/ምርምሩን


14
ውጤታማ ለማድረግ ለማንዋሎች ዝግጅት የሚረዳ የዳሰሳ ጥናት ማዘጋጀትና ማንዋሎችን

የመገምገምና የማስተካከል ስራ ነው፡፡

 በክንውን ወቅት የጥናትና ምርመር፣የማህበረሰብ አገልግሎትና የመስክ ትምህርት

የሚሰጥበት ሁኔታ የተራራቀና ጊዜ የሚፈጂ በመሆኑ፣የቤተሙከራዎችና ወርክሶፖች

ግብአት ደረጃውን የጠበቀ አለመሆን፣በተማሪዎች ምዘና ወቅት ከተማሪዎች ቁጥር መብዛት

ጋር በተያያዘ ሁሉንም ተማሪ ለመመዘን የጊዜና የግብአት እጥረት ማጋጠም፣የልኬት

ውጤቶችን ትክክለኛ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የዘመናዊ ቴክኖሎጅ ግብአትና አጠቃቀም

ውስንነት ሊኖር ይችላል፡፡

 የተግባር ትምህርት ማዋሎችን ደረጃውን ጠብቆ በማዘጋጀት፣የቤተሙከራዎችና

ላብራቶሪዎች ስታንዳርዱ በሚጠይቀው መጠን እንድሟሉና እንድዘጋጁ

በማድረግ፣ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት በምን ደረጃ እደጨበጡት ለማረጋገጥ የምዘና

ሂደቱን ዘመናዊና በበቂ ግብአት የተሟላ በማድረግ፣ከተግባር ትምህርቱ ጋር በተያያዘ

ውጤታማ መሆኑን በዳሰሳዊ ጥናት በማረጋገጥና በመተግበር የሚከናወን ይሆናል፡፡

3.8. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳቶች ባለሙያዎች የትርፍ ስዓት ክፍያና ጥቅማ ጥቅም፤

ሀ. የትርፍ ሰዓት፡-
 የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት፡- በስዓት 30 ብር
 ሲኒየር የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት በስዓት 40 ብር እና
 ቺፍ የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት በስዓት 50 ብር በሰሩት ትርፍ ስዓት ተሰልቶ
ይከፈላል፡፡
ለ. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳቶች በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች ለዩንቨርሲቲው በሚጠቅምና
ደረጃውን በሚመጥን መልኩ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ይደረጋል። እንዲሁም በራሳቸው
የትምህርት ዕድል አፈላልገው ሲያገኙ የትምህርት ዕድሉን የሚጠቀሙበት ሁኔታ ይመቻቻል፣
ሐ. በሥራ ባህሪያቸው የተነሳ ለጤና ጎጂ ለሆኑ ንጥረ ነገሮች (chemicals)፣  ከጨረራዎች
(radiation)፣ ኤሌክትሪክ አደጋዎች(electric shock) ሽታ፣ ትናኝ እና ብናኝ ጋር ተያያዥ
በሆኑ ቦታዎች መደበኛ ሥራ የሚሠሩ የአካዳሚክ ቴክኒካል አሲስታንቶች በወር 150 ብር
ለወተት ይሰጣል።

15
መ. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳቶች የስራ ቦታን አደጋን ለመከላከል ሲባል ቱታ በዓመት ሁለት ጊዜ፣
አጭር ቡትስ ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጊዜ፣ የጥንቃቄ ጫማ በዓመት አንድ ጊዜ፣ ከቆዳ
የተሰራ ጉርድ ሽርጥ በዓመት ሁለት ጊዜ፣ ከቆዳ የተሰራ የእጅ ጉዋንት በዓመት አንድ ጊዜ፣
የፊት፣ የጆሮ፣ የአፍና አፍንጫ ማስክ እንደየስራ ባህሪይ የሚሰጥ ይሆናል።
ሠ. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳቶች በሥራ ላይ ለሚደርስ አደጋ በሲብል ሰርቪስ መመሪያ መሰረት
ዋስትና ያገኛል።
ረ. በቤተ-ሙከራ/መስክ/ወርክሾፕ ከሚሠሩ ከማናቸውም በምርምር ስራዎች ሲሳተፉ
አስፈላጊውን ጥቅም እንዲያገኙ ይደረጋል።
ሰ. በዩኒቨርስቲው ሊከናወኑ በታሰቡ የመማር ማስተማር፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎቶች
የዕቅድ ክንውን ሌሎች ውይይቶችና ጥናቶች ላይ እንዲሳተፉ ይደረጋለ።
ሸ. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳቶች ተገቢውን የእድገት መሰላል ትምህርታቸውን ሲያሻሽሉና
የአገልግሎት ዘመናቸውን ታሳቢ በማድረግ ተገቢ የሆነ የደረጃ እድገት ወቅቱን ጠብቆ
እንዲሰራ ይደረጋል።
ቀ. በማማከር፣ በጥናትና ምርምር ስራዎች ተመርኩዞ የሚገኙ ጥቅማጥቅሞች ላይ የአካዳሚክ
ቴክኒካል ረዳቶች እንደ ተሳትፏቸው ታስቦ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፤

3.9. የስራ ቦታ ዝውውርና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች፤

ሀ. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳቱ ተጨባጭ የሆነ ማህበራዊና የቤተሰብ እንዲሁም ሌላ ተዛማጅ


ችግር ሲገጥመው ለጤናው ወይም ለቤተሰቦቹ ምቹ ወደ ሆኑ ዩኒቨረሲቲዎች፣ በምርምር
ጣቢያዎች የያዘውን ደረጃና ደመወዝ ሳይለቅ ተዘዋውሮ የመስራት መብት ይኖረዋል።
ነገርግን ዝውውሩ በሁለቱ ተቋማትና በግለሰቡ ስምምነት የሚፈጸም ይሆናል፡፡
ለ. ለከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመምህርነት ለመቀጠር የወጣውን መስፈርት ካሟላና በተመደበት

የአካዳሚ ቴክኒክ ድጋፍ ሰጭነት ቺፍ ቴክኒካል ረዳት III ደረጃ የደረሰና ቺፍ የአካዳሚክ ቴክኒካል

ረዳትነት 2 ዓመት ያገለገለ ባለው የማስተማር ክፍት ቦታ በውስጥ የደረጃ እድገት ተወዳድሮ

በሌክቸረር ደረጃ መምህር የመሆን፤

16
ክፍል አራት

4. የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳቶች የቅጥር አፈፃጸም


4.1 የቅጥር ደረጃ
ድረጃ ተፈላጊ ችሎታ
የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት I ከፍተኛ ዲፕሎማ እና ዜሮ አመት የስራ ልምድ ወይም
ዲፕሎማና ተመሳሳይ ደረጃ ያለው/ያላት እና 2 አመት
አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ያለው/ያላት
የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት II ከፍተኛ ዲፕሎማ እና 2 አመት የስራ ልምድ ወይም
ዲፕሎማና ተመሳሳይ ደረጃ ያለው/ያላት እና 4 አመት
አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ያለው/ያላት
የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት III ከፍተኛ ዲፕሎማ እና 4 አመት የስራ ልምድ ወይም
ዲፕሎማና ተመሳሳይ ደረጃ ያለው/ያላት እና 6 አመት
አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ያለው/ያላት
ሲኒየር የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት I የመጀመሪያ ድግሪ እና 2 አመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት
ሲኒየር የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት II የመጀመሪያ ድግሪ እና 4 አመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት
ሲኒየር የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት III የመጀመሪያ ድግሪ እና 6 አመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት

ቺፍ የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት I ሁለተኛ ድግሪ እና 4 አመት የስራ ልምድ ወይም የመጀመሪያ
ድግሪ እና 8 አመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት
ቺፍ የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት II ሁለተኛ ድግሪ እና 6 አመት የስራ ልምድ ወይም የመጀመሪያ
ድግሪ እና 10 አመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት
ቺፍ የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት III ሁለተኛ ድግሪ እና 8 አመት የስራ ልምድ ወይም የመጀመሪያ
ድግሪ እና 12 አመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት

17
ጥናቱ ላይ የተሳተፉ አካላት

NO Name Email Addres Universty/Institute/MoSHE Phone No Remark

miki.abel.gezish@gmail.com/
ArbaMinch University 251-920978527
1 Gezahagn Zerihun gezahagn.zerihun@yahoo.com  

2 Mihret Hadgu mihretnahom11@gmail.com Mekelle Universty 251-914019912  

3 Kumela Dabesa kume.dabesa@gmail.com AMBO University 251-91067123  

4 Dereje Dadi derejedadi21@yahoo.com Jimma University 251-917026083  

5 Samuel Mengistie samuelemengistie4@gmail.com BDU/Bahir Dar University 251-918018716  

6 Adinew Bezabh adinewbezabh4@gmail.com ArbaMinch University 251-926110397  

DBU/Debire Birhan
menilek.ay@gmail.om 251-932807089
7 Menilek Ayalew University  

251-911654185/
kassayeng@yahoo.com AAU/AAiT
8 Kassaye Negash 011232414  

9 Engidasew W/kidan enawsed@yahoo.com MoSHE 251-913040799  

0914709903/0945074
yonasfitsum4@gmail.com Mekelle Universty
10 Yonas Fitsum Reta 430  

TAFESSE Afework
taf.afework@gmail.com Ambo University 251-939230460
11 Beyene  

Teshome Boja
tasheboja@gmail.com Jimma University 251-916892293
12 Mekonnin  

13 Tolera Bedada Etana tolerabedada@gmail.Com Jimma University 251-917614613  

14 Gezahagne Asmare gezah12345@gmail.com Bahir Dar university 251-913933361  

15 Bamlaku Amente bage2003@gmail.com Addis Ababa University 251-911415722  

16 Dr.Nejib Mohammed nejib.mohammed@amu.edu.et ArbaMinch University 251-924457531  

17 Semahegn Abayneh sehegn@yahoo.com Addis Ababa University 251-913350031  

DBU/Debire Birhan
argawtesfaye17@gmail.com 251-961107479
18 Argaw Tesfaye University  

19 Ato Getachew Tefera dessiegetachew58@gmail.com Moshe 911522905  

18
20 Yibeltal Ayalew (PhD) yaab63@gmail.com Moshe 911168053  

21 Tegegn Dagne tegegndagne@yahoo.com Moshe 251-911419278  

22 Tewedros Ferede rehobot.tewo@gmail.com Moshe 911958038  

23 Chane Adefrs chane.adefris@gmail.com Moshe 251-911167250  

24 Defaru Anteneh antedefar@gmail.com Moshe 913949676  

25 Atala Wube   Moshe 943543805  

26 Mekonen Tadesse   Moshe 911984036  

27 Haile Habte hailehbt@gmail.com Moshe 251-911956213  

19

You might also like