You are on page 1of 16

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ

Higher Education Relevance and Quality


Agency

በድህረ ምረቃ ደረጃ በመደበኛ መርሃ ግብር የእዉቅና ፈቃድ ግምገማ

ማጠቃለያ ሪፖርት

አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ


2014 ዓ.ም
ማዉጫ
መግቢያ 1
I. አጠቃላይ መረጃ 1
II. የግምገማ ማጠቃለያ ሪፖርት 1
III. ዝርዝር ሪፖርት 3
1. ህንጻና አካባቢያዊ ሁኔታ........................................................................................................................................................3

2. አመራርና አደረጃጀት.........................................................................................................................................................3

3. ተቋማዊ ሰነዶች (ፖሊሲዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች)........................................................................................3

4. ስርዓተ ትምህርት.....................................................................................................................................................................4

5. ቤተ-መጻሕፍት እና ግብዓቶች.........................................................................................................................................4

6. የአካዳሚክ መምህራንና የምርምር አማካሪዎች......................................................................................................5

7. መማሪያ ክፍሎች................................................................................................................................................................7

8. ቢሮዎችና የተቋሙ ፊዚካል ግብዓቶች..................................................................................................................................7


9. የሰርቶ ማሳያ ክፍሎች እና ግብዓቶች....................................................................................................................................7

10. የተማሪ ቅበላና ሬጂስትራር.............................................................................................................................................8

11. የጥራት ማረጋገጥ ስርዓት................................................................................................................................................8

12. የጥናትና ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት.......................................................................................................9

i
መግቢያ

አፍሪካ የድህረ ምረቃ ኢንስቲትዩት በጅግጅጋ ካምፓሱ ባቀረበዉ የእውቅና ፈቃድ ጥያቄ መሰረት ከከፍተኛ ት/ት
አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ 3 ባለሙያዎች እንዲሁም ከጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ተባባሪ ባለሙያ በጋራ ያከናወኑት
የሰነድ ምርመራና የመስክ ምልከታ ግምገማ ዝርዝር ሪፖርት እንደሚከተለዉ ቀርቧል።

1. አጠቃላይ መረጃ
1. የተቋሙ ስም፡- አፍሪካ የድህረ ምረቃ ኢንስቲትዩት

2. ካምፓስ፡- ጅግጅጋ

3. አድራሻ፡ ካምፓሱ የሚገኝበት ክልል፡- ሱማሌ ከተማ፡- ጅግጅጋ የቦታው ልዩ መጠሪያ፡-

4. ቀደም ብሎ በካምፓሱ እዉቅና ፍቃድ ያገኘባቸዉ ፕሮግራሞች፡- የለም

5. እውቅና የጠየቀበት ቀን፦ 29/06/2021 እና የደብዳቤ ቁጥር፦ AIGS/007/21

6. እውቅና የጠየቀባቸው የትምህርት መስኮች፦ ፕሮጀክት ማኔጅመንት እና ኤም ፒኤች ኢን


ኒውትሪሽን
7. ትምህርቱ የሚሰጥበት ደረጃ፡ ድህረ-ምረቃ

8. ትምህርቱ የሚሰጥበት አግባብ/ዘዴ/፡ በመደበኛ፣ የመጀመሪያ ማመልከቻ

2. የግምገማ ማጠቃለያ ሪፖርት


1. ህንፃና ከባቢያዊ ሁኔታ
ተቋሙ ያዘጋጀዉ ህንጻ የመደበኛ ትምህርት አገልግሎቱን በቀጣይነት ለመስጠት የሚያስችል፣ አስፈላጊ ግብዓቶች
የተሟሉለት እንዲሁም ከባቢያዊ ሁኔታዉ ለመማር ማስተማር ምቹ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
2. አመራርና አደረጃጀት
የአሰራር ስርዓት የዘረጋና በአደረጃጀቱ መሰረት ተገቢ የሆነ የሰው ሀይል የመደበ ቢሆንም ተቋማዊ መዋቅር
የሌለው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
3. ተቋማዊ ሰነዶች
በመደበኛ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ በድህረ ምረቃ ደረጃ ትምህርትን ለመስጠት የሚያግዙ የአሰራር ሰነዶችን
አዘጋጅቷል፤ በአደረጃጀቱ መሰረት በሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ስራ ላይ ማዋሉን ለማረጋጥ ተችሏል፡፡
4. ስርዓተ ትምህርት
የስርዓተ ትምህርት አዘገጃጀት፣ ግምገማና ክለሳ ስርዓት ያልዘረጋ፤ የስርዓተ የትምህርቱ አስፈላጊነትና አግባብነት
በፍላጎት ዳሰሳ ያልተረጋገጠ መሆኑና ሰርዓተ ትምህርቱ ትምህርት ለማስጀመር በሚያስችል መልኩ ያልተዘጋጁ
መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
5. ቤተ-መጸሀፍትና ግብዓት

1
የቤተ መጽሀፍቱ ስፋት በቂ የሆነ፤ ሳይንትፊክ ጆርናሎችን ለማግኘት የሚያስችለውን ስርዓት የዘረጋና
ባለሙያዎችን የመደበ ቢሆንም ፤ አስፈላጊ ግበአቶች የልተሟሉለት፣ ወቅታዊ የሆኑ የመማሪያና የማጣቀሻ
መጽሀፍትን በቁጥርና በአይነት ያላደራጀ፣ ሳይንትፊክ ጆርናሎችን ውል ያልፈፀመ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
6. የአካዳሚክ መምህራን
ተቋሙ መምህራንን የሚያስተዳድርበት ስርዓት ያልዘረጋ፤ ለሁለቱም የትምህርት መስኮች ትምህርቱን ለማስጀመር
የሚያስችል የመምህራንን ቁጥርና ስብጥር ያላሟላ እንዲሁም የመመረቂያ ጽሁፍ ሊያማክሩ የሚችሉ በቂ

አማካሪ መምህራን ያልመደበ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡


7. መማሪያ ክፍሎች
ተቋሙ ለሁለት የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ያዘጋጃቸው የመማሪያ ክፍሎች ቁጥር በቂና ተገቢውን አገልግሎት
ለመስጠት አስፈላጊ ቁሳቁሶች የተሟሉላቸው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
8. ቢሮዎችና ፊዚካል ግብዓቶች
ለተቋሙ የድህረ ምረቃ አስተባባሪዎች ፣ለትምህርት ክፍል ሀላፊዎች፣ ለመምህራንና ለድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች
በተገቢው ቁሳቁስ የተደራጁ ቢሮዎችን አላአዘጋጀም፡፡
9. የኮምፒውተር ማዕከል
ተቋሙ አስፈላጊ በሆኑ ግብዓቶች የተደራጀ የኮምፒውተር ማዕከል ያላዘጋጀና አጋዥ ባለሙያዎችን ያልመደበ
መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
10. የተማሪዎች ቅበላና ሬጂስትራር
ለስራ ክፍሉ ተገቢ የሆነ ባለሙያ የመደበና የአሰራር ስርዓት የዘረጋ ቢሆንም፤ የሬጂስትራር አገልግሎትን
ለመስጠት የሚያስችል በቂ የሆኑ ግብዓቶች ያልተሟሉለት ክፍል ያደራጀ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
11. የጥራት ማረጋገጥ ስርዓት
ተቋሙ የዉስጥ ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ያልዘረጋ፣ ለስራ ዘርፉ ተገቢ የሆነ ባለሙያ
ያልመደበ መሆኑና በአስፈላጊ ግብዓቶች የተደራጀ ቢሮ ያላዘጋጀ መሆኑ ተረጋግጧል።
12. ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት
ለጥናትና ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎትን ለማካሄድ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት የዘረጋ፣ ለስራ ዘርፉ
ተገቢ የሆነ ባለሙያ የመደበ መሆኑንና በአስፈላጊ ግብዓቶች የተደራጀ ቢሮ ማዘጋጀቱ ተረጋግጧል።

2
3. ዝርዝር ሪፖርት
1. ህንጻና አካባቢያዊ ሁኔታ
ተ.ቁ. መስፈርት መለኪያዎች ተሟልቷ በከፊ አልተሟላ
ምርመራ
ል ል ም
የህንጻ የባለቤትነት ሰነድ ወይም ከ 3 ዓመት በላይ √ የህንጻ የክራይ ውል የቀረበ
የሚያገለግል በሕግ ፊት የጸና የኪራይ ውል ቢሆንም፤ ውሉ ለ 3 ዓመት
ማስረጃ ቀርቧል፡፡ የሚፀና መሆን ይገባል፡፡
የክራይ ውል ሰነድ የአማርኛ
ወይም የእንግሊዘኛ ትርጉም
ሊደረግለት ይገባል
የህንጻው ሁኔታ (ሙሉ በሙሉ ዝግጁ የሆነ ፣
ከባቢዉ ከጎርፍ፣ ከከባድ ንፋስ፣ከፍሳሽና ድምፅ √ በመስክ ምልከታ ተረጋግጧል
ብክለት) የጸዳ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
ተቋሙ በተከራያቸው /በባለቤትነት በያዛቸው
ወለል/ሎች ሌሎች የንግድ ተቋማት አለመኖሩ √ በመስክ ምልከታ ተረጋግጧል
ተረጋግጧል፡፡
የመብራት፣ የኢንተርኔት አገልግሎትና መጸዳጃ
ቤቶች (ለወንድና ሴት ተማሪዎች፣ መምህራን እና √ በመስክ ምልከታ ተረጋግጧል
አስተዳደር ሰራተኞች) ተዘጋጅቷል፡፡
ህንጻው ለመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ
መስጫ አግልግሎት የሚዉሉ ግብአቶችና √
የመዝናኛ ክበብ አቅርቦት አለዉ፡፡

2. አመራርና አደረጃጀት
ተ.ቁ. መስፈርት መለኪያዎች ተሟልቷ በከፊል አልተሟላ
ምርመራ
ል ም
2.1. ግልጽ የሆነ ተቋማዊ ራዕይ፣ ተልእኮና ዕሴት √
ተቋማዊ ማዋቅር ሊዘጋጅ
ያለውና ተጠያቂነትን ያመላከተ ተቋማዊ መዋቅር
ይገባል
አዘጋጅቷል፡፡
2.2. መሰረታዊ አደረጃጀት (የበላይ ሀላፊ፣ የትምህርት
ክፍል ሀላፊዎች፣ የድህረ ምረቃ አስተባባሪ፣
የውስጥ ጥራት፣ የጥናትና ምርምር እና

ማህበረሰብ አገልግሎት፣ ሬጅስትራር፣ የቤተ-
መጸሀፍት ሀላፊ፣ የሰው ሀይል አስተዳደርና
የፋይናንስ እና የመሳሰሉትን) አደራጀቷል፡፡
2.3. ለእያንዳንዱ የስራ ክፍል ለደረጃው ብቁ የሆነ √

3
የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ያላቸው
ባለሙያዎች በቋሚነት ቀጥሯል፤ የሥራ
ድርሻቸው (መዘርዝር) በጽሁፍ የተደገፈ ሰነድና
የቅጥር ደብዳቤ በማዘጋጀት እንዲየውቁት
ተደርጓል፡፡
2.4. ኃላፊዎችን፣ መምህራንንና ባለሙያዎችን √
ብቃትን መሰረት ያደረገ የምልመላ፣ የእድገትና
መሰል አስተዳደራዊ ማስተካከያዎችን ለመውሰድ
የሚያስችል ስርዓት ዘርግቷል፡፡

3. ተቋማዊ ሰነዶች (ፖሊሲዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች)


ተ.ቁ. መስፈርት መለኪያዎች ተሟልቷ በከፊል አልተሟላ
ምርመራ
ል ም
3.1 የተማሪ ቅበላን፣ ምዝገባን፣ መልሶ መቀበልን፣
የትምህርት ጊዜን ኮርሶችን፣ የሴሚስተር ጫናን፣
ምዘናንና ለምረቃ የሚያበቁ ሁኔታዎችንና √ በሰነድ ምርመራ ተረጋግጧል
የመሳሰሉትን በማካተት አካዳሚክ ህገ-ደንብ
ተዘጋጅቷል፡፡
3.2 የተማሪዎች መብትና ግዴታን የያዘ የተማሪዎች

ሰነድ (ስቱደንት ሀንድ ቡክ) ተዘጋጅቷል፡፡
3.3 የመምህራን የቅጥር ሥርዓት፣ መብትና ግዴታ

የያዘ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡
3.4 የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር √
የሚያወጣቸው ሕጎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣
ፖሊሲዎችና ሌሎችን የያዘ ሰነድ በማካተት
ተዘጋጅቷል፡፡
3.5 የአምስት አመት ስትራቴጅክ እቅድና አመታዊ
√ በሰነድ ምርመራ ተረጋግጧል
እቅድ የያዘ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡
3.6 ህጋዊ የሆነ የንግድ ምዝገባ እና የንግድ ፍቃድ ለ 2013 ዓም የታደሰ የንግድ

መረጃ ቀርቧል፡፡ ፈቃድ ቀርቧል
3.7 ሌሎች ለተቋሙ አገልግሎት አስፈላጊ የሆኑ
ፖሊሲዎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና ማንዋሎች √
ተዘጋጅቷል፡፡

4. ስርዓተ ትምህርት
ተ.ቁ. መስፈርት መለኪያዎች ተሟልቷ በከፊል አልተሟላ
ምርመራ
ል ም
4.1. የስርዓተ ትምህርት አዘገጃጀት፣ አተገባበር፣ √
ግምገማና ክለሳ የሚከታተልና ግብረመልሶችን

4
በመሰብሰብ በቀጣይነት የሚያሻሽል ተገቢ
አደረጃጀትና ስርዓት ተዘርግቷል፡፡
4.2. አዲስ የትምህርት ዓይነት ለመክፈት በቂ ፍላጎት √
ለስረአተ ትምህርቱ ግምገማ
መኖሩን የሚያረጋግጥ የዳሰሳ ጥናት ፣ በስርዓተ
ከተካሄደለት በኋላ ተቋሙ
ትምህርቱ አግባብነት ዙሪያ ባለድርሻ አካላትን
የተሰጡትን ሀሳቦች
ያካተተ ዐውደ ጥናትና የተሰጡ አስተያየቶችን
አስተካክሎ አላቀረበም
ያካተተ ማስረጃ ቀርቧል፡
4.3 ስርዓተ ትምህርቱ ለእያንዳንዱ ኮርስ የተሟላ √
ዓላማ፣ መግለጫ (course description) ፣
ለስረአተ ትምህርቱ ግምገማ
የማስተማሪያና የምዘና ዘዴዎችን፤ የውጤት
ከተካሄደለት በኋላ ተቋሙ
አሰጣጥ፤ የመማሪያና ማጣቀሻ መጽሐፍት
የተሰጡትን ሀሳቦች
ዝርዝር ፤ የአብይ ኮርሶች ከጠቅላላው ክሬዲት
አስተካክሎ አላቀረበም
ሃወር በአማካይ 66 በመቶ ባላነሰ መልኩ
ተዘጋጅቷል፡፡
4.4 በየሴሚስተሩ (16 ሳምንት የፈተና ጊዜን √
ሳይጨምር) በመደበኛ መርሃ-ግብር የሚሰጠው ለስረአተ ትምህርቱ ግምገማ
የክሬዲት ሃወር መጠን ከ 12-15 ክሬዲት ሃወር ከተካሄደለት በኋላ ተቋሙ
መሆኑንና 6 ክሬዲት ሃወር ለጥናትና ምርምር የተሰጡትን ሀሳቦች
እንዲሁም ባጠቃላይ ከ 36 ክሬዲት ሃወር አስተካክሎ አላቀረበም
ያልበለጠ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
4.5 ለመማር ማስተማር በሚመች መልኩ በቀላሉ √ ለስረአተ ትምህርቱ ግምገማ
የተደራጀና የትምህርቱ ጥራት በማይጓደልበት ከተካሄደለት በኋላ ተቋሙ
ሁኔታ ሊሰጥ የሚችል ይዘትያለዉ ስርዓተ የተሰጡትን ሀሳቦች
ትምህርት ተዘጋጅቷል፡፡ አስተካክሎ አላቀረበም

5. ቤተ-መጻሕፍት እና ግብዓቶች
ተሟልቷ በከፊ አልተሟላ
ተ.ቁ. መስፈርት መለኪያዎች ምርመራ
ል ል ም
የተቋሙ አጠቃላይ እውቅና በሚቆይበት ወቅት ተቋሙ ለየድህረ ምረቃ ት/ት
በአጠቃላይ ሊኖሩት የሚችሉትን የተማሪ መስክ 70 ተማሪዎችን መያዝ
ቁጥር ቢያንስ 25 ከመቶ በአንድ ጊዜ የሚችል የድህረ ምረቃ ቤተ-
5.1. ማስተናገድ የሚችልና በተማሪ 1.5 ካ. ሜ መጽሀፍት አደራጅቷል። ይህም

የተመጠነ የቦታ ስፋት ያለው ቤተ-መጸሀፍት የቤተ-መጽሃፍቱ በአንድ ጊዜ 25%
ተደራጅቷል፡፡ ተማሪዎችን መያዝ የሚያስችል
መሆኑን በመስክ ምልከታው
ተረጋግጧል።
5.2. ቤተ መጽሀፍቱ ከፍተኛ ትምህርትን የሚመጥኑ √ በመስክ ምልከታ ተረጋግጧል
የወንበርና የጠረንጴዛ ግብዓቶች ዝግጅት፣

5
የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ብርሃንና አየር ማስገባት
በሚያስችል ሁኔታ ተደራጅቷል፡፡
5.3. ከትምህርት መስኮቹ ጋር አግባብነት ያላቸው በቤተ መፅሀፍት ውስጥ ማጣቀሻ
የቅርብ ጊዜ (በ 10 ዓመት ውስጥ) የታተሙ መፅሀፍት ለኤም ፒኤች
የመማሪያና የማጣቀሻ መጻሕፍትና አለመኖሩ ታውቋል ለምሳሌ ያህል
የኤሌክተሮኒክስ ቅጅዎችና ሳይንሳዊ ጆርናሎች Essential niutrition,
ክምችት አለዉ፡፡ Epidemiological niutrition, እና
ሌሎችም፡፡ ለፕሮጀክት
√ ማኔጅመንት፡- project
management, project evaluation,
project design, qualitative &
quanitative data analysis, project
risk &disaster management,
operational behivior and Encart
እና ሌሎችም መፅሀፍት ሊዘጋጁ
ይገባል
5.4. የኤሌክትሮኒክ መጽሐፍትና ጆርናሎች፤ በላይብረሪ ውስጥ ምንም
መጠቀም የሚያስችሉና የኢንተርኔት ኮምፒውተር አልተዘጋጀም፡

አገልግሎት ያላቸው ከአምስት ያላነሱ የኢንተርኔት አገልግሎትም
ኮምፒዩተሮች አሉት፡፡ አልተዘረጋም
ለሙያው ተዛማጅ የትምህርት ዝግጅትና
5.5. ልምድ ያለው የቤተመጻሕፍት ባለሙያና √
ረዳቶች መድቧል፡፡
ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ እስከ ምሽቱ ሁለት የቤተ መጽሃፍት አሰራር ስርዓት
5.6. ሰዓት ድረስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል √ ን በተመለከተ ምንም የቀረበ
የቤተ መጽሃፍት አሰራር ስርዓት ዘርግቷል፡፡ ሀሳብ የለም
መዝገበ ቃላት፣ ፒሪዮዲካልስ፣ ጋዜጦች እና
5.7. ወዘተ ክምችት እንዲሁም መጽሃፍትና ሌሎች

ግብዓቶች የካምፓሱ ስለመሆናቸው የሚያሳዩ
መለያዎች አሉት፡፡
5.8 አግባብነት ያላቸውን ሳይንቲፊክ ጆርናል √ በመስክ ጉብኝት ወቅት በት/ት
ተደራሽ ሊያደርግ የሚያስችል አለም አቀፍ መስኮቹ አግባብነት ያላቸውን
ኦንላይን ጆርናል ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ ሳይንቲፊክ ጆርናሎች አገልግሎት
አገልግሎት ስለማገኘቱ እና አገልግሎት ስለማገኘቱ ለማረጋገጥ ተችሏል።
ነገር ግን የውል ስምምነት
መስጠት መቻሉ ተረጋግጧል፡
አልቀረበም፡፡

6. የአካዳሚክ መምህራንና የምርምር አማካሪዎች


ተ.ቁ. መስፈርት መለኪያዎች ተሟልቷል በከፊ አልተሟላ ምርመራ
ል ም

6
6.1 ተቋሙ መምህራንን
የሚመለምልበት፣የሚያሳድግበትና √ በቂ መረጃ አልቀረበም
የሚያስተዳድርበት ስርዓት ዘርግቷል፡፡
6.2 በመደበኛው ክፍለ ጊዜ የእያንዳንዱ ቋሚ
መምህር ሳምንታዊ ጫና ከ 15 ክሬዲት ሃወር √ በቂ መረጃ አልቀረበም
ያልበለጠ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
ተቋሙ የእውቅና ፈቃድ ጥያቄ ሲያቀርብ
6.3 ሁለት ረዳት ፕሮፌሰር ማእረግ
በእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት ለአብይ (Major
ያላቸው ቋሚ መምህራን
Courses) ኮርሶች በሙያው ሁለት የሦስተኛ ዲግሪ √
ለእያንዳንዱ ፕሮግራም
ወይም ሁለት ረዳት ፕሮፌሰር ማእረግ ያላቸው
ተመድበዋል
ቋሚ መምህራን ለአንድ ክፍል ምጣኔ መድቧል፡፡
የቋሚና የጊዜያዊ መምህራን የትምህርት በሁለቱም የድህረ-ምረቃ ት/ት
6.4. መስኮች ለተመደቡ መምህራን
ማስረጃዎች (የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያም በላይ
ወቅታዊ
ያሏቸው የትምህርት ማስረጃዎቻቸው
መልቀቂያ፣መተማመኛ
ከነትራንስክሪፒታቸው) ፣ የቅጥር ደብዳቤ፣
ቅፅ፣የውል ስምምነት
ከተቋሙ ጋር የገቡት የስራ ስምምነት ውል፣
የሚያረጋግጡ ሰነዶች
የመተማማኛ ቅጽና ወቅታዊ መልቀቂያ √
አልቀረቡም
የሚያረጋግጡ ሰነዶች ቀርቧል፡፡
ለፕሮጀክት ማኔጅመንት
የቀረበው አንዱ መምህር
የትምህርት ዝግጅቱ
ከፕሮግራሙ ጋር ተዛማጅ
አይደለም
ከኢትዮጵያ ውጭ ከሚገኝ የከፍተኛ ትምህርት የሁለት መምህራን ከውጭ
6.5.
ተቋም የተገኙ የመምህራን የትምህርት የተገኘው የትምህርት ዝግጅት

ማስረጃዎች በኤጀንሲው የአቻ ግመታ በኤጀንሲው የአቻ ግምት
ተሰርቶላቸዋል፡፡ አልተሰራም
የመመረቂያ ጽሁፍ ሊያማክሩ የሚችሉ ረዳት በሁለቱም የድህረ-ምረቃ ት/ት
ፕሮፌሰርና በላይ መምህራን 1፡8 ጥምርታ መስኮች ለእያንዳንዳቸው በ 1፡8
መሠረት የተገባ የውል ሰነድና የትምህርት ጥምርታ ተማሪዎችን
6.7. ማስረጃ አቅርቧል √ የመመረቂያ ጽሁፍ ሊያማክሩ
ከሚችሉ አማካሪዎች ጋር የተገባ
የውል ሰነድና የትምህርት
ማስረጃ አልቀረበም

ተቋሙ የእውቅና ፈቃድ በጠየቀበት ፕሮጀክት ማኔጅመንት እና ኤም ፒኤች ኢን ኒውትሪሽን የትምህርት መስክ ስልጠናውን
ለመጀመር በቋሚነት የተቀጠሩ የመምህራን ብዛትና ስብጥር እንደሚከተለው ተጠናቅሮ ቀርቧል።
የትምህርት ደረጃና የቅጥር ሁኔታ ምርመራ
የስልጠና መስክ

7
ፕሮግራም የመምህሩ ሁለተኛ ዲግሪ/ ረዳት የቅጥር የውል መልቀቂያመተማመኛ
ሥም ሦስተኛ ድግሪ ፕሮፈሰር ደብዳቤ ስምምነት ቅጽ
ለ 2 ተኛ እና ለ 3 ተኛ
አሊ ሙሀመድ ኢኮኖሚክስ አፍሪካን ኢኮኖሚክስ √ X X X ዲግሪ አቻ ግምት
ፕሮጀክት አልተሰራም
ማኔጅመንት አብድወህብ ወተር ኤንድ ሄልዝ ከተጠየቀው ፕሮግራም
ሀሼ ስፔሻላይዜሽን ወተር ኤም ፒኤች ኢን √ X X X ጋር ተዛማጅ የትምህርት
ኤንድ ፐብሊክ ሄልዝ ኢፒድሞሎጂ
ዝግጅት አይደለም
ኤም ፒኤች ኢን አብዲላሂ ዩሱፍ ብሄቬርያል ሄልዝ ሳይንስ ፐብሊክ ሄልዝ ኢን  X X X ለሶስተኛ ዲግሪ አቻ
ኒውትሪሽን ሪፕሮዳክቲቭ ሄልዝ ግምት አልተሰራም

ረሺድ አብዲ ሄልዝ ሳይንስ ኢፒድሞሎጂ X X X

ከላይ በቀረበው ማስረጃ መሰረት ተቋሙ በፕሮጀክት ማኔጅመንት እና ኤም ፒኤች ኢን ኒውትሪሽን ትምህርቱን ለማስጀመር
የሚያስችል የመምህራንን ቁጥርና ስብጥር አላሟላም።

7. መማሪያ ክፍሎች
ተሟልቷ በከፊ አልተሟላ
ተ.ቁ. መስፈርት መለኪያዎች ምርመራ
ል ል ም
7.1. በአንድ ተማሪ 1.2 ሜትር ካሬ ምጣኔ ከ 35- 2 የመማሪያ ክፍሎች ያዘጋጀ ሲሆን
እያንዳንዳቸው 30 እና 40 ተማሪዎችን
45 ተማሪዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ 
መያዝ የሚችሉ መሆኑን በመስክ ምልከታ
የሚችሉ የመማሪያ ክፍሎች አሉት፡፡ ታውቋል
7.2. የእውቅናው ፍቃድ በሚቆይበት ጊዜ ያህል
ሊኖሩት የሚችሉትን ባቾችና ሌሎች
እውቅና ያላቸውን የትምህርት መስኮች 
ሊያስተናግዱ የሚችሉ የመማሪያ ክፍሎች
አሉት፡፡
7.3. የመማሪያ ክፍሎች በቂ ብርሃንና በመማሪያ ክፍል ውስጥ የተለያዩ
ቬንትሌሽን ያላቸው፣ ደረጃቸውን በጠበቁ ግብአቶች ተዘጋጅተዋል ፡- ነጭ
ቁሳቁሶች (ነጭና ጥቁር ሰሌዳ፣ ኤልሲዲ ሰሌዳ፣ አንድ ኤልሲዲ
ፕሮጀክተር፣የመምህራን ማረፊያ ወንበር፣ 
አርምቼር፣ ወዘተ) የተደራጁ እና ለመማር
ማስተማር ሂደት ምቹነትን በሚያረጋግጥ
ሁኔታ ተደራጅቷል፡፡

8. ቢሮዎችና የተቋሙ ፊዚካል ግብዓቶች


ተ.ቁ መስፈርት መለኪያዎች ተሟልቷ በከፊል አልተሟላ ምርመራ
. ል ም
ለድህረ-ምረቃ አስተባባሪ፣ ለእያንዳንዱ  ለድህረ ምረቃ አስተባባሪ፣
የትምህርት ክፍል ኃላፊ (Department Head) ለትምህርት ክፍል ሀላፊ እና

8
ለብቻ እንዲሁም ለቋሚ መምህራንን (Staff) ለቋሚ መምህራን የሚሆን
8.1.
በየትምህት መስኩ በተገቢው ቁሳቁስ ቢሮዎች አልተደራጁም፡፡
(ወንበርና ጠረጴዛ፣ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ እንዲሁም ለጊዜያዊ መምህራን
የኢንተርኔት አገልግሎት፣ ፋይል ካቢኔት፣ ማረፊያ ቦታ አልተዘጋጀም፡፡
ሼልፍ፣ ወዘተ) የተደራጁ ቢሮዎች አሉት፣
በተጨማሪም ለጊዜያዊ መምህራን ማረፊያ
ቦታ አዘጋጅቷል፡፡
ለተቋሙ የበላይ ሀላፊዎች፣ ለትምህርት ለጥናትና ምርምርና ማህበረሰብ

ጥራት ማረጋገጥ፣ ለጥናትና ምርምርና አገልግሎት፣ ለተቋሙ የበላይ ሀላፊ
ማህበረሰብ አገልግሎትና ለተማሪዎች ድጋፍ እና የሬጅስትራል ቢሮ ብቻ
8.2. አገልግሎት ክፍሎች ለእያንዳንዳቸው ራሱን የተዘጋጀ ሲሆን ሌሎች ቢሮዎች
የቻለ ቢሮ በተገቢው ቁሳቁስ (ወንበርና አልተደራጁም
ጠረጴዛ፣ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ፋይል
ካቢኔት፣ ሼልፍ፣ ወዘተ) እንዲሁም ለድጋፍ
ሰጪ ሰራተኞችና ለቴክኒካል ረዳቶች ቢሮ
ተዘጋጅቷል፡፡

9. የሰርቶ ማሳያ ክፍሎች እና ግብዓቶች


ተ.ቁ. መስፈርት መለኪያዎች ተሟልቷ በከፊል አልተሟላ ምርመራ
ል ም
9.1. መሰረታዊ የኮምፒውተር ኮርስ ለመስጠት  ተቋሙ ለድህረ-ምረቃ ፕሮግራም
አገልግሎት የሚሰጥ 6
የተማሪዎችን ቁጥር ግምት ውስጥ ያስገባና
ኮምፒውተሮች ያሉት አንድ
እርስ በእርስ የተገናኙ (Server based
የኮምፒውተር ማዕከል ያለው
network) የኢንተርኔት አገልግሎት
ቢሆንም፤ የኮምፒውተር ቁጥር
የተገጠመላቸው 15 ኮምፒውተሮች ያሉት
በመጨመር 15 እና ከዛበላይ
የኮምፒውተር ማዕከል ተደራጅቷል፡፡
ማዘጋጀት እና የኢንተር ኔት
አገልግሎት ሊዘረጋ ይገባል
9.2. ለትምህርት መስኩ አስፈላጊ በሆኑ
ግብዓቶች የተደራጁ በተማሪ 3.0 ካሬ ሜትር ለተጠየቁት ፕሮግራሞች አስፈላጊ
ቤተ-ሙከራና የዲሞንትሬሽን ክፍል፣ 5.0 መለኪያ አይደሉም
ካሬ ሜትር የድሮዊንግ ክፍል እና 6.0 ካሬ
ሜትር ስፋት ያለው ወርክሾፕ ዝግጅት እና
ለሜንቴናንስና ጥገና የተዘጋጀ ክፍል
ተዘጋጅቷል፡፡
9.3. ለተግባር ኮርሶች በአንድ ቤተሙከራ፣
ወርክሾፕ፣ ወዘተ የተማሪዎች ቁጥር ከ 30 ለተጠየቁት ፕሮግራሞች አስፈላጊ
ባልበለጠ መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡ መለኪያ አይደሉም

9
9.4. ለቤተሙከራ፣ ወርክሾፕ እና ዲሞንስትሬሽን
ክፍሎች ከሥልጠናው ጋር ቀጥተኛ ለተጠየቁት ፕሮግራሞች አስፈላጊ
ግንኙነት ያለው ረዳት ቴክኒሺያን መለኪያ አይደሉም
ተመድቧል፡፡
9.5. ለሕክምና፣ ለጤና ሣይንስ፣ ለቴክኖሎጂ፣
ለግብርናና ወዘተ ፕሮግራሞች ልምምድ ለተጠየቁት ፕሮግራሞች አስፈላጊ
ከሚካሄዱባቸው ተዛማጅ ድረጅቶች ጋር መለኪያ አይደሉም
ሊያሰራ የሚችል የስምምነት ሰነድ ቀርቧል፡፡

10. የተማሪ ቅበላና ሬጂስትራር


ተሟልቷ አልተሟላ
ተ.ቁ. መስፈርት መለኪያዎች በከፊል ምርመራ
ል ም
የተቋሙ የሬጅሰትራር አሠራር
ሥርዓት፣ የውጤት አመዘጋገብና
አገላለጽ ሥርዓት፣ የምረቃና የትምህርት
መረጃ ዝግጅት፣ በሬጅስትራሩ ሥር የሚኖሩ
10.1  በሰነድ ምርመራ ተረጋግጧል
የተለያዩ የሥራ ክፍሎችን ተግባርና ኃላፊነት
የሚገልጽና ጠቅላላ የሥራ ክፍል ዝርዝር
አሠራሮች የሚመሩበት ማኑዋል
ተዘጋጅቷል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
በየዓመቱ የሚያወጣውን የከፍተኛ የተማሪ ቅበላ መመሪያ፣ ሌሎች
ትምህርት መግቢያ መስፈርት ማዕከል አስፈላጊ ማንዋሎችና
10.2 
አድርጎ የተዘጋጀ የተማሪ ቅበላ መመሪያ፣ የማስፈጸሚያ ቅጻቅጾች ሊዘጋጁ
ሌሎች አስፈላጊ ማንዋሎችና ይገባል
የማስፈጸሚያ ቅጻቅጾች አሉት፡፡
ተገቢ የሙያ ዘርፍና ልምድ ያለው
አንድ የሬጅስትራር ባለሙያ
10.3 የሬጅስትራር ሀላፊና ረዳት ሬጅስትራር 
ተመድቧል
ተመድቧል፡፡
ደህንነቱ የተረጋገጠና አስፈላጊ ግብዓቶች የሬጅስትራል ቢሮ የተዘጋጀ
(ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ስልክ ወንበር፣ ቢሆንም ቢሮ በተለያዩ የቢሮ
10.4 
ጠረንጴዛ፣ ሸልፍ፣...) የተሟሉለት ግብአት ፡- ሼልፍ እና መሰል
ሬጅስትራር ተደራጅቷል፡፡ ሊሟላ ይገባል

11. የጥራት ማረጋገጥ ስርዓት

ተሟልቷ አልተሟላ
ተ.ቁ. መስፈርት መለኪያዎች በከፊል ምርመራ
ል ም

10
የኤጀንሲውን አስር የትኩረት መስኮችን በሰነድ ምርመራ ተረጋግጧል
11.1 ያካተተ የውስጥ ጥራት ማስጠበቂያ 
መመሪያ ወይም ፖሊሲ ተዘጋጅቷል፡፡
ባለሙያ የተመደበ ቢሆንም
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልምድ
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
11.2 ያለውና ስለውስጥ ጥራት አጠባበቅ በቂ 
ልምድ ስለመውሰዱ በቂ መረጃ
ስልጠና የወሰደ ባለሙያ ተመድቧል፡፡
አልቀረበም
የክፍሉ አመታዊ እቅድና በጀትን የሚያሳይ አመታዊ አቅድ ና በጀትን
11.3 ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡  በተመለከተ የጥራት ማረጋገጥ
ክፍል ሊያዘጋጅ ይገባል
በቂ ግብዓት የተሟላለት ራሱን የቻለ ቢሮ እራሱን ችሎ በተገቢ ግብአት
11.4 
ተደራጅቷል፡፡ የተደራጀ ቢሮ አልተዘጋጀም

12. የጥናትና ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት


ተሟልቷ አልተሟላ
ተ.ቁ. መስፈርት መለኪያዎች በከፊል ምርመራ
ል ም
የተቋሙን የጥናትና ምርምር እና የማህበረሰብ
12.1. አገልግሎት ባግባቡ ለመምራት የሚያችል መመሪያ  በሰነድ ምርመራ ተረጋግጧል
ወይም ፖሊሲ ተዘጋጅቷል፡፡
ባለሙያ የተመደበ ቢሆንም
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
12.2. በከፍተኛ ትምህርት ተቋማ ልምድ ያለውና 
የጥናትና ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ልምድ ስለመውሰዱ በቂ መረጃ
በቂ ስልጠና የወሰደ ባለሙያ ተመድቧል፡፡ አልቀረበም
የክፍሉ አመታዊ እቅድና በጀትን የሚያሳይ አመታዊ አቅድ ና በጀትን
ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡ በተመለከተ የጥናትና ምርምር እና
12.3. 
የማህበረሰብ ክፍል ሊያዘጋጅ
ይገባል
አስፈላጊ ግብዓት የተሟላለት ራሱን የቻለ ቢሮ ቢሮ የተዘጋጀ ቢሆንም ቢሮ
ተደራጅቷል፡፡
12.4.  በተለያዩ የቢሮ ግብአት ፡- ሼልፍ
እና መሰል ሊሟላ ይገባል

11
አፍሪካ የድህረ ምረቃ ኢንስቲትዩት በጅግጅጋ ከተማ ጅግጅጋ ካምፓስ የእውቅና ፈቃድ (Accreditation) ጥያቄ
አስመልክቶ የተዘጋጀ ሪፖርት ላይ የተደረገ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ

የስብሰባ ቦታ፡ ከትአጥኤ ቢሮ ቁጥር፦ 116

የስብሰባ ቀን፡ 09/03/2014 ዓ.ም


የስብሰባ ሰዓት፡ 9፡00-09-30
በስብሰባው ላይ የተገኙ የቡድን አባላት
በስብሰባው ላይ የተገኙ ፡

1. ስማቸው አስሬ ሰብሳቢ

2. አበባው ደፈርሻ አባል

3. ማህሙድ ሽኩር ፀሐፊ እና አባል

አጀንዳ
1. አፍሪካ የድህረ ምረቃ ኢንስቲትዩት በድህረ ምረቃ ደረጃ በፕሮጀክት ማኔጅመንት እና ኤም ፒኤች ኢን

ኒውትሪሽን የትምህርት መስክ የዕውቅና ፈቃድ ጥያቄ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፤


2. በሌሎች በሚነሱ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
አጀንዳ ቁጥር 1

12
በአጀንዳው መሠረት በሰብሳቢው አጠር ያለ መግለጫ ከተሰጡ በኋላ ሪፖርቱ ቀደም ብሎ ለአባላቱ የተሰጠና

የተነበበ በመሆኑ ጥያቄ፣ ማብራሪያ ወይም ሌሎች የሚነሱ ጉዳዮች ካሉ ውይይት እንዲደረግባቸው ባሳሰቡት

መሠረት ውይይቱ እንደሚከተለው ተካሂዷል።

አፍሪካ የድህረ ምረቃ ኢንስቲትዩት በጅግጅጋ ከተማ ጅግጅጋ ካምፓስ ለጠየቀው የዕውቅና ፈቃድ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት
ከኤጀንሲው ሶስት ባለሙያዎች እንዲሁም ከጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ተባባሪ ባለሙያ በአጠቃላይ አምስት

አባላትን ያካተተ የባለሙያዎች ቡድን የሰነድ ምርመራና በተቋሙ በመገኘት የመስክ ምልከታ በማድረግ ማጠቃለያውን
እንደሚከተለው አቅርቧል።

ተቋሙ፦

 ተቋሙ ያዘጋጀዉ ህንጻ የመደበኛ የትምህርት አገልግሎቱን በቀጣይነት ለመስጠት የሚያስችል፣


አስፈላጊ ግብዓቶች የተሟሉለት እንዲሁም ከባቢያዊ ሁኔታዉ ለመማር ማስተማር ምቹ መሆኑ፣
 በመደበኛ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ በድህረ ምረቃ ደረጃ ትምህርትን ለመስጠት የሚያግዙ የአሰራር ሰነዶችን
አዘጋጅቷል፤ በአደረጃጀቱ መሰረት በሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ስራ ላይ ያዋለ መሆኑ፣
 ተቋሙ ለሁለት የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ያዘጋጃቸው የመማሪያ ክፍሎች ቁጥር በቂና ተገቢውን አገልግሎት
ለመስጠት አስፈላጊ ቁሳቁሶች የተሟሉላቸው መሆኑ፣
 ለጥናትና ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎትን ለማካሄድ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት የዘረጋ፣ ለስራ ዘርፉ ተገቢ
የሆነ ባለሙያ የመደበ መሆኑንና በአስፈላጊ ግብዓቶች የተደራጀ ቢሮ ማዘጋጀቱ ተረጋግጧል።
ነገር ግን፦
 የአሰራር ስርዓት የዘረጋና በአደረጃጀቱ መሰረት ተገቢ የሆነ የሰው ሀይል የመደበ ቢሆንም ተቋማዊ መዋቅር የሌለው
መሆኑ፣
 የስርዓተ ትምህርት አዘገጃጀት፣ ግምገማና ክለሳ ስርዓት ያልዘረጋ፤ የስርዓተ የትምህርቱ አስፈላጊነትና አግባብነት
በፍላጎት ዳሰሳ ያልተረጋገጠ መሆኑና ሰርዓተ ትምህርቱ ትምህርት ለማስጀመር በሚያስችል መልኩ ያልተዘጋጁ
መሆኑ፣
 የቤተ መጽሀፍቱ ስፋት በቂ የሆነ፤ ሳይንትፊክ ጆርናሎችን ለማግኘት የሚያስችለውን ስርዓት የዘረጋና ባለሙያዎችን
የመደበ ቢሆንም ፤ አስፈላጊ ግበአቶች የልተሟሉለት፣ ወቅታዊ የሆኑ የመማሪያና የማጣቀሻ መጽሀፍትን በቁጥርና
በአይነት ያላደራጀ፣ ሳይንትፊክ ጆርናሎችን ውል ያልፈፀመ መሆኑ፣
 ተቋሙ መምህራንን የሚያስተዳድርበት ስርዓት ያልዘረጋ፤ ለሁለቱም የትምህርት መስኮች ትምህርቱን ለማስጀመር

የሚያስችል የመምህራንን ቁጥርና ስብጥር ያላሟላ እንዲሁም የመመረቂያ ጽሁፍ ሊያማክሩ የሚችሉ በቂ

አማካሪ መምህራን ያልመደበ መሆኑ፣

13
 ለተቋሙ የድህረ ምረቃ አስተባባሪዎች ፣ለትምህርት ክፍል ሀላፊዎች፣ ለመምህራንና ለድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች
በተገቢው ቁሳቁስ የተደራጁ ቢሮዎችን ያላዘጋጀ መሆኑ፣
 ተቋሙ አስፈላጊ በሆኑ ግብዓቶች የተደራጀ የኮምፒውተር ማዕከል ያላዘጋጀና አጋዥ ባለሙያዎችን ያልመደበ መሆኑ፣
 ለስራ ክፍሉ ተገቢ የሆነ ባለሙያ የመደበና የአሰራር ስርዓት የዘረጋ ቢሆንም፤ የሬጂስትራር አገልግሎትን ለመስጠት
የሚያስችል በቂ የሆኑ ግብዓቶች ያልተሟሉለት ክፍል ያደራጀ መሆኑ፣
 ተቋሙ የዉስጥ ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ያልዘረጋ፣ ለስራ ዘርፉ ተገቢ የሆነ ባለሙያ
ያልመደበ መሆኑና በአስፈላጊ ግብዓቶች የተደራጀ ቢሮ ያላዘጋጀ መሆኑ ተረጋግጧል። በመሆኑም የሚከተለዉ
የዉሳኔ ሀሳብ ተሰጥቷል፡፡

የውሳኔ ሐሳብ

የግምገማው ውጤት እንደሚያመለክተው ተቋሙ የዕውቅና ፈቃድ በጠየቀበት በፕሮጀክት ማኔጅመንት እና ኤም

ፒኤች ኢን ኒውትሪሽን የትምህርት መስክ በድህረ ምረቃ ደረጃ ተማሪዎችን ለማሰልጠን ለደረጃው የተቀመጠውን
አነስተኛ የደረጃ መለኪያ (Minimum Standard) ያላሟላ በመሆኑ የጠየቀው የዕውቅና ፈቃድ ሊሰጠው እንደማይገባ
ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

አጀንዳ፡ 2፦

ሌሎች ጉዳዮች አልተነሱም በመሆኑም ስብሰባው ተጠናቋል።

14

You might also like