You are on page 1of 48

የአዲስ አበባ ከተማ

አስተዳደር የበጎ ፈቃድ


5/20/2013 አገልግሎት አሰራር
መመሪያ ቁጥር
1/2013

የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ

አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

መመሪያ ቁጥር 1/2013

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር መመሪያ ቁጥር 1/2013

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ የበጎ ፈቃድ


አገልግሎት አሰጣጥ በተደራጀና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመምራት፣ የከተማው
ህብረተሰብ የበጎ ፈቃደኝነት ባህል እንዲጎለብት ፣ ዜጎች በአካባቢያቸው ጉዳይ ላይ
በራሳቸው ተነሳሽነት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ፣ በከተማዋ ዘላቂ ልማትና ዕድገት
ለማምጣት በሚደረገው ርብርብ በጎ ፈቃደኞች ሚናቸውን አንዲወጡ ለማስቻል
እንዲሁም ተጠያቂነት እና ሃላፊነትን በአግባቡ መወጣት የሚያስችል የበጎ ፈቃድ
አገልግሎት አሰራር ስርዓት ማበጀት በማስፈለጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ
አካላትን እንደገና ለማቋቋም ባወጣው አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀፅ 29 ከንዑስ አንቀፅ
14-18 በተሰጠው ስልጣንና ሃላፊነት መሰረት ይህን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር
መመሪያ አዘጋጅተዋል፡፡

[Type the company name]| 1


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ማውጫ
ክፍል አንድ.................................................................................................................................. 4
1. ጠቅላላ ድንጋጌ .................................................................................................................................. 4
1.1 አጭር ርዕስ .......................................................................................................................... 4
1.2 ትርጓሜ .......................................................................................................................................... 4
1.3 የተፈፃሚነት ወሰን ................................................................................................................. 8
ክፍል ሁለት ................................................................................................................................ 9
2.1 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዕቅድ ............................................................................................. 9
2.2 ምዝገባ ................................................................................................................................ 11
2.3 የበጎ ፈቃደኞች ምልመላና መረጣ .......................................................................................... 14
2.3.1 ተቋሙ በጎ ፈቃደኞችን የሚመለምልበት ስርዓት ................................................................ 14
2.4 ግንዛቤ መፍጠር/ Cognition/ ............................................................................................ 15
2.5 ገለፃ / Oreintation / ....................................................................................................... 15
2.6 ስልጠና / Training / ........................................................................................................... 16
2.7 ስምሪት ............................................................................................................................... 17
2.8 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ክትትል፤ ድጋፍና የምዘና ስርዓት ...................................................... 18
2.8.1 ክትትልና ድጋፍ............................................................................................................... 18
2.8.2 ምዘና .............................................................................................................................. 19
ክፍል ሶስት................................................................................................................................ 21
3.1 የበጎ ፈቃድ መርሆዎች፣ መብትና ግዴታዎች እና ስነ - ምግባር ............................................. 21
3.1.1 የበጎ ፈቃድ መርሆዎች ..................................................................................................... 21
3.1.2 የበጎ ፈቃደኞች መብት...................................................................................................... 22
3.1.3 የበጎ ፈቃደኞች ግዴታ ...................................................................................................... 23
3.2 በጎ ፈቃደኞችን የሚያሳትፉ ተቋማት መብትና ግዴታዎች ................................................... 24
3.2.1 በጎ ፈቃደኞችን የሚያሳትፉ ተቋማት መብት ...................................................................... 24
3.2.2 በጎ ፈቃደኞችን የሚያሳትፉ ተቋማት ግዴታዎች ................................................................ 25
3.3 ስነ ምግባር .......................................................................................................................... 26
3.4 የስነምግባር ጥሰቶች ......................................................................................................... 27
3.5 ይግባኝ ............................................................................................................................ 30
ክፍል አራት ............................................................................................................................... 31

[Type the company name]| 2


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

4 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ግብዓት አቅርቦት ...................................................................... 31


4.1 የበጎ ፈቃደኞች የስራ መለያ .................................................................................................. 31
4.2 የቢሮው አርማና መሪ ቃል ............................................................................................... 32
4.3 የበጎ ፈቃደኞች መታወቂያ ................................................................................................ 32
4.4 ወጪ መተካት /Reimbersment/ ......................................................................................... 33
4.4.1 ትራንስፖርት ክፍያን አፈፃጸም .......................................................................................... 33
4.4.2 የግንኙነት ማሳለጫ ወጪዎች .......................................................................................... 34
4.4.3 ለአደጋ መከላከያ የስራ ላይ አልባሳት ወጪ መተኪያ ........................................................... 35
4.4.4 የስልጠናና ልዩ ኮርሶች ወጪ መተኪያ.................................................................................. 35
4.4.5 ከሃገር ውጪ/ ከከተማ ውጪ ለሚደረጉ ጉዞዎች የወጪ መተኪያ....................................... 36
4.4.6 ከግማሽ ቀን በላይ ለሚሹ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የሚከናወን ወጪ መተኪያ .................... 36
4.5 የበጎ ፈቃደኞች መድህን ዋስትና ........................................................................................ 36
4.5.1. የበጎ ፈቃደኛ የጤናና የህይወት መድህን ዋስትና ሽፋን ክፍያ .............................................. 38
ክፍል አምስት ............................................................................................................................ 39
5.1 የእዉቅና፣ ማበረታቻ እና ሽልማት አሰጣጥ ስርዓት ............................................................ 39
5.1.2 ዕለታዊ እውቅናና ማበረታቻ አይነቶች ................................................................................ 41
5.1.3 መካከለኛ የእዉቅና የሽልማት አሰጣጥ................................................................................ 42
5.1.4 ዋና የእውቅናና ማበረታቻ ሽልማት.................................................................................... 42
5.1.5 ልዩ ማበረታቻና እና ሽልማት............................................................................................ 43
ክፍል ስድስት ............................................................................................................................. 46
6. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች .............................................................................................................. 46
6.1 ትስስራዊ የተግባር አፈጻጸም አግባቦት ................................................................................ 46
6.1.1 ለጋሽ በጎ ፈቃደኛ ፣ተቋም እና አስተባባሪ የመመሪያዉ አተገባበር ......................................... 46

[Type the company name]| 3


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ክፍል አንድ
1. ጠቅላላ ድንጋጌ
1.1 አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራርን በተደራጀና
ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመምራት የተዘጋጀ መመሪያ ቁጥር 1/2013 ዓ.ም; ተብሎ
ሊጠቀስ ይችላል፡፡

1.2 ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-

1 "በጎ ፈቃደኛ" ማለት ያለማንም አስገዳጅነት በራስ ተነሳሽነት ግዜውን፣


ጉልበቱን፣ ዕውቀቱን ወይም ሃብቱን ከስጋ ዝምድና ውጪ ላለ
አካል፤ህብረተሰብ የሚሰጥ ግለሰብ ማህበር፣ ስብስብ፣ ተቋም፣ ወ.ዘ.ተ ነው፡፡
2 "በጎ ፈቃደኝነት" ማለት በፍፁም ነፃ ፈቃድ ፣ያለማንም አስገዳጅነትና ከክፍያ
ነፃ ግዜን፣ ጉልበትን ፣ ዕውቀትን ወይም ሃብትን ለማህበረሰብ እና ለሌሎች
አካላት ጥቅም የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡
3 "የበጎ ፈቃድ አገልግሎት" ማለት በጎ ፈቃደኞች በዕውቀታቸው፣
በጉልበታቸው፣ በሃብታቸው፣ በጊዜያቸው፣ በክህሎታቸው ወ.ዘ.ተ
ለማህበረሰብ፣ ለተቋም ወይም ለሌሎች ከክፍያ ነፃ በሆነ መልኩ
የሚያከናወኑት ተግባር ነው፡፡
4 "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር" ማለት በኢፈድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 49
በአዲስ አበባ ቻርተር የተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡
5 "የአዲስ አበባ ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ " ማለት በአዲስ አበባ
ከተማ አስተደደር አስፈፃሚ አካላትን ለማቋቋም በተደነገገው አዋጅ 64/2011
መሰረት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን እንዲመራ፣ እንዲያስተባበር እና ምቹ
ሁኔታ እንዲፈጥር ስልጣን የተሰጠው ተቋም ነው፡፡

[Type the company name]| ክፍል አንድ 4


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

6 "የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት" ማለት በክ/ከተማና ወረዳ ደረጃ


የሚገኙ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን የሚመራ፣ የሚያስተባበር እና ምቹ ሁኔታ
የሚፈጥር ተቋም ነው፡፡
7 "መደበኛ የበጎ ፈቃድ ማህበር " ማለት ሁለትና ከዛ በላይ ዓባላት ያሉት
ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ሰውነት ያለው ማህበር ነው፡፡
8 "መደበኛ ያልሆነ የበጎ ፈቃድ ማህበር" ማለት ሁለትና ከዛ በላይ ዓባላት ያሉት
የግል ፍላጎታቸውን መሰረት ያደረገ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት
የተሰባሰቡ እና ከራሰቸው ውጪ የማንም አካል እውቅና የሌላቸው ማህበራት
ናቸው፡፡
9 "በጎ ፈቃደኛ ግለሰብ" ማለት ያለማንም አስገዳጅነት በራስ ተነሳሽነትና
ያለምንም ክፍያ ግዜውን፣ ጉልበቱን፣ ዕውቀቱን ወይም ሃብቱን ከስጋ ዝምድና
ውጪ ላለ አካል፤ህብረተሰብ የሚሰጥ ግለሰብ ነው፡፡
10 "ሞያተኛ በጎ ፈቃደኛ " ማለት ያለማንም አስገዳጅነት በራስ ተነሳሽነት ከክፍያ
ነፃ ሙያውን፣ ዕውቀቱን፣ ግዜውን ለህብረተሰብ ጥቅም የሚያውል ግለሰብ
ነው፡፡
11 "ጡረተኛ በጎ ፈቃደኛ" ማለት ከመደበኛ ስራቸው በእድሜ ወይም
በአገልግሎት ከስራ በጡረታ የተገለለ ያለማንም አስገዳጅነት በራስ ተነሳሽነት
ግዜውን፣ ጉልበቱን፣ ዕውቀቱን፣ ሙያውን፣ ልምዱን ወይም ሃብቱን ከስጋ
ዝምድና ውጪ ላለ አካል፤ህብረተሰብ የሚሰጥ ግለሰብ ነው፡፡
12 "ህፃናት በጎ ፈቃደኛ" ማለት እድሜያቸው እስከ 14 አመት ሆኖ በወላጅ
ጠባቂነትና ፈቃድ ግዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ዕውቀታቸውን ለበጎ ፈቃድ
አገልግሎት የሚያውሉ ህፃናት ናቸው፡፡
13 "ወጣት በጎ ፈቃደኛ" ማለት እድሜያቸው ከ15 እስከ 29 አመት ሆኖ
ያለማንም አስገዳጅነት፣ በራስ ተነሳሽነት ከክፍያ ነፃ ግዜውን፣ ጉልበቱን፣
ዕውቀቱንና ሙያውን ወይም ሃብቱን ከስጋ ዝምድና ውጪ ላለ
አካል፤ህብረተሰብ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶች ናቸው፡፡
14 "ዓለምአቀፍ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት" ማለት ያለማንም አስገዳጅነት በራስ
ተነሳሽነት ግዜን፣ ጉልበትን፣ ዕውቀትንና ሙያን ወይም ሀብትን ለመስጠትና

[Type the company name]| 1.1 አጭር ርዕስ 5


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ለማገልገል ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር ድንበር አቋርጦ የሚከናወን የበጎ


ፈቃድ ተግባር ነው፡፡
15 "ወሰን የለሽ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት" ማለት ያለማንም አስገዳጅነት በራስ
ተነሳሽነት ግዜን፣ጉልበትን፣ዕውቀትንና ሙያን ወይም ሀብትን ለመስጠትና
ለማገልገል በአንድ አገር በሚገኙ የአስተዳደር ወሰኖች ውስጥ ከአንድ አካባቢ
ወደ ሌላ አካባቢ የሚደረግ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር ነው፡፡
16 "ወሰን የለሽ በጎ ፈቃደኛ" ማለት ያለማንም አስገዳጅነት በራስ ተነሳሽነት
ግዜውን፣ጉልበቱን፣ዕውቀቱንና ሙያውን ወይም ሀብቱን ለመስጠትና
ለማገልገል በአንድ ሀገር ከሚገኙ የአስተዳደር ወሰኖች ውስጥ ከአንድ ቦታ
ወደ ሌላ ቦታ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ጉዞ በማድረግ የሚሳተፍ በጎ
ፈቃደኛ ነው፡፡
17 "የብሄራዊ አገልግሎት በጎ ፈቃደኛ " ማለት ያለማንም አስገዳጅነት በራስ
ተነሳሽነት ግዜውን፣ ጉልበቱን፣ ዕውቀቱንና ሙያውን ወይም ሀብቱን በሀገር
አቀፍ ደረጃ በሚደረግ ሃገራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጥሪ ላይ የሚሳተፍ በጎ
ፈቃደኛ ነው፡፡
18 "ወጪ መተካት " ማለት በጎ ፈቃደኞች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት
በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውስጥ ከኪሳቸው የሚያወጡት ህጋዊና የተረጋገጠ
ወጪን ለመተካት የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡
19 "የበጎ ፈቃድ የመድህን ሽፋን/ኢንሹራንስ " ማለት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት
ለተሰማራ በጎ ፈቃደኛና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለሆነ ለሶስተኛ ወገን የሚገባ/
የሚከፈል የመድህን ዋስትና ነው፡፡
20 "የስነ ምግባር ጥሰት " ማለት በከተማዉ አስተዳደር የሚንቀሳቀስ ግለሰብም
ሆነ ተቋማዊ የበጎ ፈቃድ ሰጪ አካል በዚህ መመሪያ ክፍል ሶስት
የተዘረዘሩትን የበጎ ፈቃድ መርሆዎችና እና እሴቶችን በአግባቡ መከተል
፣መፈጸምና መተግበር ሳይችል የቀረ እና ያመነ ወይም ሆን ብሎ፣ፈልጎ
፣ተዘጋጅቶ ፣አስቦበት አልያም ሃላፊነትን ቸል በማለት እና በግዴለሽነት
እናም ይህን ማድረጉ የሚያስከትለዉን መዘዝ በምክንያታዊነት አለመረዳት
ጭምር የስነምግባር ጥሰት ነው፡፡

[Type the company name]| 1.1 አጭር ርዕስ 6


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

21 "የበጎ ፈቃድ መርህ " ማለት የወጣቶችና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ


ቢሮ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር መመሪያ 1/2013 ክፍል 3
የተቀመጡትና በጎ ፈቃደኞች ሊያከብራቸው ሊጠብቋቸው የሚገቡ መሰረታዊ
እሳቤዎች ናቸው፡፡
22 "የበጎ ፈቃድ ዕውቅና" ማለት ለበጎ ፈቃደኞች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ
ላደረጉት ተሳትፎ በቃል፣ በፅሁፍ ወ.ዘ.ተ የሚሰጥ ዕውቅና ነው፡፡
23 "የበጎ ፈቃድ ማበረታቻ " ማለት ለበጎ ፈቃደኞች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት
ላደረጉት አስተዋፅኦ እና ላስመዘገቡት ውጤት የሚሰጥ ማበረታቻ ነው፡፡
24 " የበጎ ፈቃድ ሽልማት " ማለት በጎ ፈቃደኞች ላስመዘገቡት የላቀ የበጎ ፈቃድ
አገልግሎት የሚሰጥ ሽልማት ነው፡፡
25 " የበጎ ፈቃደኛ መብት " ማለት በህግ ፣በሞራል ፣ በአሰራር ተቀባይነት
ያላቸው ለበጎ ፈቃደኞች የሚሰጡ ጥቅሞች ናቸው፡፡
26 " የበጎ ፈቃደኛ ግዴታ " ማለት ከህግ፡ ከሞራልና አሰራር አንፃር ከአንድ በጎ
ፈቃደኛ እንዲተገበር የሚጠበቅ ሃላፊነት ነው፡፡
27 "የበጎ ፈቃድ ተቋም መብት" ማለት የአዲስ አበባ ወጣቶችና በጎ ፈቃድ
ማስተባበሪያ ቢሮ በህግ ፣ በሞራልና በአሰራር ከበጎ ፈቃደኞች ማግኘት
የሚፈልገዉ አገልግሎት ነው፡፡
28 "የበጎ ፈቃድ ተቋም ግዴታ" ማለት የአዲስ አበባ ወጣቶችና በጎ ፈቃድ
ማስተባበሪያ ቢሮ ከህግና ከሞራል አንፃር ለበጎ ፈቃደኞች እንዲያሟላው
የሚገደድበት/የሚጠበቅበት ተግባር ነው፡፡
29 "የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስተባባሪ" ማለት ቢሮው በየደረጃው ለሚያከናውነው
በጎ ፈቃድ አገልግሎት የክትትል፣ድጋፍ፣ቁጥጥርና ምዘና የሚያከናውኑ
ባለሙያዎች ናቸው
30 "በጎ ፈቃደኛ አስተባባሪ " ማለት በአንድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ -
ግብር ውስጥ የተሰባሰቡ በጎ ፈቃደኞች የሚመርጧቸው ተግባሩንና
አገልግሎቱን ከተቋማችን ጋር በመናበብ ለማከናወን የሚያግዙ አስተባባሪዎች
ናቸው፡፡

[Type the company name]| 1.1 አጭር ርዕስ 7


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

31 "ከፍተኛ የማኔጅመንት ኮሚቴ"፡- ማለት በየደረጃው በሚገኘው የወጣቶችና በጎ


ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ/ፅ/ቤቶች ውስጥ ያለው የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ አካል
ነው ፡፡

የፆታ አገላለጽ

በዚህ መመሪያ ውስጥ በወንድ ፆታ የተደነገገው የሴትንም ፆታ ያካትታል፡፡

1.3 የተፈፃሚነት ወሰን


ይህ መመሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ባሉ ወረዳዎችና ክፍለ ከተሞች እንዲሁም
ከቢሮው ጋር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሚያከናውኑ አካላት ላይ ሁሉ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

[Type the company name]| 1.3 የተፈፃሚነት ወሰን 8


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ክፍል ሁለት
2. የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ አመራር ስርዓት
2.1 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዕቅድ
2.1.1 በቢሮው የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በሙሉ የታቀዱ
መሆን ይኖርባቸዋል
2.1.2 ቢሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ሲያቅድ የታላሚ ቡድኖችን
መሰረት በማድረግ ከዕድሜ አንፃር /የህፃናት፣ የወጣቶች፣ የጎልማሶችና
የጡረተኞች/ ፣ ከግዜ አንፃር የአጭር የመካከለኛ እና የረዥም ግዜ የበጎ
ፈቃድ አገልግሎቶች፣ ከአገልግሎት ወሰን አንፃር/ አካባቢያዊ፣
ክልላዊ፣አህጉራዊና ዓለማአቀፋዊ/፣ ከሙያዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት
አንፃር፣ አገልግሎቱን መስጠት ከሚፈልጉ በጎ ፈቃደኞች አንፃር/
በግል፣በቡድን፣በቤተሰብ / ወ.ዘ.ተ በማቀድ ወደ ተግባር ሊያስገባ ይችላል
2.1.3 በተራ ቁጥር 2.1.2 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ የአጭር ግዜ
የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የቆይታ ግዜ እስከ 4 ወር የሚፈጅ ሲሆን ፣
የመካከለኛ ግዜ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ከ6 ወር እስከ 8 ወር የሚቆዩ
እንዲሁም 1 አመትና ከዛ በላይ የሚቆዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች
የረዥም ግዜ አገልግሎቶች በመባል የሚታቀዱ ይሆናል፡፡
2.1.4 በቢሮው የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ዕቅድ የከተማው
ህብረተሰብ ያለበትን የአገልግሎት ክፍተት መነሻ በማድረግ በቢሮው በራሱ
የሚታቀዱ እንዳሉ ሁሉ ከማንኛውም በጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት
ከሚፈልግ በጎ ፈቃደኛ ግለሰብ፣ መደበኛና መደበኛ ያልሆነ ማህበር፣ ተቋም
ወ.ዘ.ተ በሚቀርቡና ጠቀሜታቸው በተረጋገጠ ዝክረ ተግባሮችም
የሚከናወን ይሆናል፡፡
2.1.5 በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዕቅድ ዝግጅት ወቅት የበጎ ፈቃድ
አገልግሎት ስራው ለየትኛው የልማት አጀንዳ ስኬት አስፈላጊ እንደሆነ
ከሚመለከተው አጋር/ባለድርሻ አካል ጋር በመሆን በጥናት የተለየ እና
ማህበረሰባዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑ መረጋገጥ ይጠበቅበታል
[Type the company name]| ክፍል ሁለት 9
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

2.1.6 በሴክተር መስሪያ ቤቶች ውስጥ በመደበኛነት የሚቀረጹ የበጎ


ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች ከሴክተሩ ዓላማና ተልዕኮ ጋር የሚሄዱ፣
የሴክተር መስሪያ ቤቱን አገልግሎት አሰጣጥ ችግር የሚቀርፉና በዚህም
ሴክተሩን የሚመራው አካልና በውስጡ ያሉ ሰራተኞች ያመኑበት መሆን
ይገባዋል፡፡
2.1.7 በተ.ቁጥር 2.1.6 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ በሴክተር መስሪያ
ቤቶች ውስጥ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት የተቀረፁ ፕሮግራሞች
ተግባራዊነት የሚመራው ተቋማቱ በሚፈራረሙት የጋራ ስምምነት ሰነድ
እና የከተማ አስተዳደሩ ለየተቋማቸው በሰጠው የስራ ባለቤትነት መሰረት
ይሆናል፡፡
2.1.8 አንድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ወደ ተግባር ከመግባቱ
በፊት የስራው አይነት፣ የት እንደሚሰራ፣ ለስራው የሚያስፈልጉ የበጎ
ፈቃደኞች አይነትና ብዛት፣የስራ መደቡ ስያሜ፣ መደብ ቁጥር፣ የስራው
ዝርዝር ተግባር፣ የበጎ ፈቃደኞች መመልመያ መንገድ፣ ለስራው አስፈላጊ
የሆኑ ግብዓቶች፣ የክትትል ድጋፍና ምዘና መርሃ ግብር እና ከስራው
የሚጠበቅ ውጤት ምን እንደሆነ በግልፅ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
2.1.9 ቢሮው ከሌሎች ተቋማት ጋር በሚያደርገው የበጎ ፈቃድ
አገልግሎት የስራ ግንኙነት በጎ ፈቃደኞችን በማሰማራት ፣የስራውን
ውጤት በመመዘን እና እውቅናና ሽልማት ሂደትን በተመለከቱ ጉዳዮች
ዙሪያ የበጎ ፈቃደኞች ፍላጎት ጥያቄ መቀበያ እና የተዘጋጁ በጎ ፈቃደኞችን
የማስረከቢያ እንዲሁም የስራውን ውጤታማነት የመመዘኛ አካሄድ
አሰራሮችን መከተል/መጠበቅ ይገባዋል፡፡
2.1.10 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞች ውጤታማነትን
ከማረጋገጥና የሃብት ብክነትን ከመቀነስ አኳያ በአብዛኛው የሚታቀዱት
በቢሮ ደረጃ ቢሆንም ከፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ነባራዊ ሁኔታቸውን
ባገናዘበ መልኩ በቢሮው ከታቀዱ ፕሮግራሞች ጋር ተናባቢ
ያልሆኑ/የማይመሳሰሉ የአጭር፣የመካከለኛና የረዥም ግዜ የበጎ ፈቃድ

[Type the company name]| የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዕቅድ 10


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

አገልግሎት ፕሮግራሞችን በማቀድና በለቢሮው እንደ ፕሮግራም


እንዲታወቅ በማድረግ ወደ ስራ ማስገባት ይችላሉ፡፡
2.1.11 ከላይ ከራ ቁጥር 2.1.1 እስከ ተ.ቁ 2.1.10 ድረስ ከተገለፀው
አግባብ ውጪ የሚታቀዱ የበጎ ፈቃድ ፕሮግራሞች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
2.2 ምዝገባ
2.1.12 ከቢሮው ጋር የሚሰራ ማንኛውም በጎ ፈቃደኛ በምዝገባ ስርዓት
ውስጥ ማለፍ ይኖርበታል፡፡
2.1.13 የቢሮው የበጎ ፈቃደኞች ምዝገባ በሁለት ዓይነት የሚከናወን
ይሆናል ይህም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሚያስተባብሩ ወረዳዎች በአካል
በመገኘትና በማንኛውም ግዜና ወረዳዎች ፣ከየትኛውም የአለም ክፍል
በቀጥታ/ኦንላይን ተቋሙ በሚያወጣው መደበኛ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት
የስራ ዘርፎች ማንኛውም በተቋሙ መደበኛ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት
መሰማራት የሚፈልግ ግለሰብ፣ማህበር፣ተቋም፣ ስብስብ ወ.ዘ.ተ ምዝገባ
ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡
2.1.14 ማንኛውም መደበኛ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ምዝገባ የሚከናወነው
ይፋ የሆነ ማስታወቂያ በማውጣት ሲሆን በጎ ፈቃደኛው እራሱ በተቋሙ
የበጎ ፈቃደኞች መመዝገቢያ ድረ-ገፅ ውስጥ በመግባት የሚመዘገቡ
ይሆናል፡፡
2.1.15 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ማስታወቂያ የሚወጣባቸው
መንገዶች የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ማስታወቂያዎች፣የተቋሙ ድህረ ገፅ፣
የማህበራዊ ትስስር ገፆች፣ ህትመት ሚዲያዎች፣ በራሪ ወ.ዘ.ተ፣
ኤስ.ኤም.ኤስ፣ ሌክትሮኒክ ኒውስ ሌተር/ኢ- ኒውስ/፣ ሰዎች በሚበዙባቸው
ቦታዎች የሚደረግ ቅስቀሳ፣ እርስ በርስ መልዕክት በማስተላለፍ
የመሳሰሉት
2.1.16 የበጎ ፈቃደኛ ፕሮግራም ማስታወቂያ አየር ላይ የሚቆየው ለ 10
የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
2.1.17 በተራ ቁጥር 2.1.17 የተቀመጠው እንደተጠበቀ ሆኖ ሰው ሰራሽ
እና ተፈጥሮአዊ አደጋ ወይም ፈታኝ ወቅታዊ ሁኔታ በአስተዳደሩ/ቢሮው

[Type the company name]| 2.2 ምዝገባ 11


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ቢገጥመው ለተጨማሪ/ለተለዋጭ የስራ ቀናት የማስታወቂያ ጊዜውን


ሊያራዝም ይችላል፡፡
2.1.18 የበጎ ፈቃደኞች ምዝገባ በሚከናወንበት ወቅት ተመዝጋቢው
ማንነቱን የሚገልፅ ማስረጃ ሊያቀርብ ይገባል፡፡
2.1.19 ከምዝገባ በኋላ በተቋሙ ተቀባይነትን ላገኙ ግለሰብ በጎ ፈቃደኞች
መታወቂያ፡፡እንዲሁም ለተቋማት፣ማህበራት፣ ክበባት፣ ስብስብ ወ.ዘ.ተ
ከተቋሙ ጋራ ስለሚያከናውኑት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ብቻ የሚውል
የምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
2.1.20 የተመዘገቡ በጎ ፈቃደኞች መረጃ በቢሮ ደረጃ በአንድ ማዕከል
የመረጃ ቋት /Web Based Data Base System/ የሚደራጅ ሲሆን የበጎ
ፈቃደኞች መታወቂያ ቁጥር እና የዕውቅና ምስክር ወረቀት መለያ
ቁጥሮች ጭምር ወጥ በሆነ መንገድ ከዚሁ ማዕከል የሚሰጥ ይሆናል፡፡
2.1.21 ለበጎ ፈቃደኞች የሚሰጥ መታወቂያ በየአመቱ በቢሮው እድሳት
የሚደረግለት ሲሆን ለኦንላይን ተመዝጋቢዎችና የመታወቂያ ዕድሳት
አድራጊዎች /Web Based Data Base System/ በመጠቀም
በኢ -ሜላቸው በኩል ኦንላይን ላይ የመታወቂያ መስጠትና የእድሳት
አገልግሎት ይሰጣቸዋል፡፡
2.1.22 የግለሰብ በጎ ፈቃደኞች ፣ ማህበራት ፣ስብስቦች ፣ ክበባቶች
ወ.ዘ.ተ ምዝገባ የሚከናወነው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በሚከናወንበት
የወረዳው የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ ቤት ይሆናል፡፡
2.1.23 በተ.ቁ 2.1.23 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ በበጎ ፈቃድ ስራ
ላይ መሰማራት የሚፈልጉ ተቋማት ምዝገባ የሚከናወነው በቢሮ ደረጃ
ይሆናል፡፡
2.1.24 አንድ በጎ ፈቃደኛ በቢሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሳተፍ
የሚችለው በሚፈልገውና በረጠው 2 የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ብቻ ነው፡፡
2.1.25 በተራ ቁጥር 2.1.25 እንደተጠበቀ ሆኖ ሰፋ ያለ ህዝባዊ ተሳትፎ
የሚሹና ሙያ ነክ ያልሆኑ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ ለመሳተፍ ግን ገደብ
የለውም

[Type the company name]| 2.2 ምዝገባ 12


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

2.1.26 ማንኛውም በጎ ፈቃደኛ ግለሰብ ፣ ማህበር ፣ተቋም፣ ክበብ፣


ስብስብ ወ.ዘ.ተ ከሚኖርበት አካባቢ ውጪ ባለ በየትኛውም የከተማዋ
አካባቢ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማከናወን የሚችል ሆኖ ምዝገባ ማድረግ
ግን የሚችለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን በሚያከናውንበት የወረዳ
አስተዳደር ክልል ውስጥ ብቻ ነው፡፡
2.1.27 ከአንድ ቦታ/አካባቢ/ ውጪ በላይ መስራት የሚፈልጉ በጎ
ፈቃደኞች ባላቸው/ቀድሞበተሰጣቸው የምዝገባ ቁጥር የሚቀጥሉ ሆነው
የስራ ቦታቸው ዝርዝር ግን በመረጃ ቋት ውስጥ የሚደራጅበት አግባብ
ይኖረዋል፡፡
2.1.28 በአንድ ቦታ ላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረ
ግለሰብ፣ማህበር፣ስብስብ፣ክበብ ወ.ዘተ ወደ ሌላ አካባቢ በመዘዋወር የበጎ
ፈቃድ አገልግሎት መስጠት የሚችል ሲሆን የዚህም የምዝገባ ስረዓት
የሚከናወነው የምዝገባ ቁጥሩ ሳይቀየር አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ ግን
በተዘዋወረበት አካባቢ የመረጃ ማደስ ተግባር በመረጃ ቋት ውስጥ
ይደረግለታል፡፡
2.1.29 ማንኛውም በጎ ፈቃደኛ ግለሰብ ከአንድ በላይ በሆነ የበጎ ፈቃድ
አገልግሎት ፕሮግራም ለመሳተፍ ሲያመለክት ምዝገባው የሚከናወነው
አንዴ ብቻ ሲሆን ለመረጣቸው ፕሮግራሞች የሚሰጠው መለያ ቁጥር
አንድ ብቻ ይሆንና የሚሳተፍባቸውን የአገልግሎት መስኮች የሚያደራጅበት
የመረጃ ቋቱ አሰራር ይኖረዋል፡፡
2.1.30 ከላይ በተራ ቁጥር 2.1.30 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ
ተጨማሪ የስራ መስኮቹ የሚከናወኑት ቀድሞ ምዝገባ ከተደረገበት ወረዳ
ውጪ ከሆነ ቀድሞ በወሰደው የምዝገባ ቁጥርና አድራሻ ይጸናና ተጨማሪ
አገልግሎት በሚሰጥበት ወረዳ እንዲጠናቀር የመረጃ ቋቱ በአሰራር
ይፈታዋል
2.1.31 ማንኛውም ግለሰብ በጎ ፈቃደኛ በተለያዩ ቦታዎች የበጎ ፈቃድ
አገልግሎት መስኮች ቢሰማራም ከአንድ ምዝገባ ቁጥር በላይ አይሰጠውም፡፡

[Type the company name]| 2.2 ምዝገባ 13


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

2.1.32 አንድ በጎ ፈቃድ አገልግሎቱን በሚያቆምበት/በሚያቋርጥበት ግዜ


በማመልከቻ ለተቋሙ በማሳወቅ በምዝገባ ወቅት የወሰዱትን
መታወቂያ/የምዝገባ ካርድ እና ሌሎች ለስራ የወሰዷቸው የተቋሙ
ቁሳቁሶች እንዲመልሱ በማድረግ ከምዝገባው የሚሰረዙ ይሆናል፡፡

2.3 የበጎ ፈቃደኞች ምልመላና መረጣ


2.3.1 ተቋሙ በጎ ፈቃደኞችን የሚመለምልበት ስርዓት
2.3.1.1 የበጎ ፈቃደኞች ምልመላና መረጣ እኩልነትን፣ግልፅነትን፣አሳታፊነትንና
ብዝሃነትን በተቻለ መጠን በየደረጃው የጠበቀ ስለመሆኑ ይረጋገጣል፡፡
2.3.1.2 የተቋሙ በጎ ፈቃደኞች ምልመላ የሚከናወነው በሰነድ ማጣራትና በቃለ -
መጠይቅ ብቻ ይሆናል፡፡
2.3.1.3 የሰነድ ማጣራት እና ቃለ - መጠይቆች በአካል መቅረብ
ለማይጠበቅባቸው በኦንላይን መፈፀም ይቻላል፡፡
2.3.1.4 የበጎ ፈቃደኞች ውጤት አሞላል የሚሆነው 40% በሰነድ ማጣራት እና
60% በቃለ መጠይቅ የሚገኘው ተደምሮ ይሆናል፡፡
2.3.1.5 የበጎ ፈቃደኞች የሰነድ ማጣራት ሲከናወን የሚታዩ መስፈርቶች ተፈላጊ
የትምህርት ደረጃ፣ የስራ ልምድ/የበጎ ፈቃድ የስራ ልምድን ጨምሮ፣
ተጨማሪ ችሎታ እና ለአንዳንድ የስራ መስኮች እንደ አስፈላጊነቱ
ከወንጀል ነፃ መሆኑና የጤና ሁኔታ ማረጋገጫ የሚጠየቅ ይሆናል፡፡
2.3.1.6 የበጎ ፈቃደኞች ቃለ መጠይቅ ለማከናወን ከተቋሙ የስራ ክፍሎች
የሚወከሉ ባለሙያዎችና የስራ ሃላፊዎች ከ 3-5 ዓባላት ያሉት የቃለ
መጠይቅ ቡድን በማደራጀት የሚከናወን ይሆናል፡፡
2.3.1.7 በበጎ ፈቃደኞች ቃለመጠይቅ ወቅት ሊነሱ የሚገባቸው ጥያቄዎች እራስን
ማስተዋወቅ፣ ስለበጎፈቃደኝነት ያለ አመለካከት፣ ከተቋሙ ጋር ለምስራት
ለምን እንደፈለገ፣ ከስራው የሚጠብቀው ነገር ካለ እና ሙያ ነክ ለሆኑ
መደቦች ሙያዊ ጥያቄዎች በቡድኑ ዓባላት ሊጨመሩ የሚችሉ ይሆናል፡፡

[Type the company name]| 2.3 የበጎ ፈቃደኞች ምልመላና መረጣ 14


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

2.3.1.8 የተመረጡ በጎ ፈቃደኞች ያመጡት ውጤት እንደየቅደምተከተላቸው


ተዘጋጅቶ በተቋሙ የማኔጅመንት አካል እንዲፀድቅ ይደረግና ለሁሉም
አካል ግልፅ በሆነ ቦታ ላይ ይለጠፋል፡፡be onlinim yigeletsal
2.3.1.9 የበጎ ፈቃድ ምልመላና መረጣ ሂደት ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም አካል
ውጤቱ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ አምስት የስራ ቀናት
ውስጥ ቅሬታውን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
2.3.1.10 ለቀረቡ ቅሬታዎች ምላሽ የሚሰጠው በዚህ መመሪያ ክፍል 3 አንቀፅ
በተዘረዘረው መሰረት ይሆናል፡፡
2.3.1.11 የምልመላና መረጣ ሂደቱን ያለፉ ተፈላጊ በጎ ፈቃደኞች የስራ ስምሪት
ውል እና እንደአስፈላጊነቱ ቃለ - መሃላ እንዲሞሉ ይደረጋል፡፡
2.3.1.12 ለእያንዳንዳቸው የተመረጡ በጎ ፈቃደኞች የግል ማህደር የሚከፈትላቸው
ሆኖ ምልመላና መረጣ የተከናወነባቸው ሰነዶች በሙሉ በማህደራቸው
ውስጥ እንዲደራጅ ይደረጋል፡፡ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ የማህደሩ
ሚስጥራዊነት የተጠበቀ ይሆናል፡፡

2.4 ግንዛቤ መፍጠር/ Cognition/


ሁሉም በጎ ፈቃደኛ ተመሳሳይ የሆነ ገለፃ / Oreintation / ይደረግለታል ነገር ግን
እንደሚመደብበት የበጎ ፈቃድ ዘርፍ የተለየ ስልጠና የሚሰጠው ይሆናል፡፡

2.5 ገለፃ / Oreintation /


2.5.1 በጎ ፈቃደኞች ወደ ስራ ከመሰማራታቸው በፊት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
2.5.2 ገለፃ ስብሰባና ወርክሾፕ በማዘጋጀት፣ በበራሪ ፅሁፎች፣ በቃለመጠይቅ ወቅት፣
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መመሪያ መፃህፍትን በማዘጋጀት፣ በተንቀሳቃሽ ምስል
ወ.ዘ.ተ ማከናወን ይቻላል፡፡
2.5.3 የገለፃ መድረኮች የሚዘጋጁት ከ 2 እስከ 3 ሰዓት በሚፈጅ የግዜ ገደብ ውስጥ
ይሆናል፡፡

[Type the company name]| ግንዛቤ መፍጠር/ Cognition/ 15


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

2.6 ስልጠና / Training /


ስልጠና እንደ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፉ የሚዘጋጅ ሲሆን በተቋሙ የሚሰጡ
ስልጠናዎች

2.6.1 በጎ ፈቃደኞች የሚሰማሩባቸውን የስራ ዘርፎችን መሰረት በማድረግ


የሙያና የክህሎት ስልጠና በሚፈልጉ መስኮች እንደ የህክምና፣የስነልቦና
ማማከርና ድጋፍ አገልግሎት፣ የአይ.ሲ.ቲ፣ ሹፍርና፣ የህግ ድጋፍ፣ የድንገተኛ
አደጋዎች kidme መከላከል ወ.ዘ.ተ በመሳሰሉት የሙያ ዘርፎች ተቋሙ በራሱ
ወይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ስልጠናው ለበጎ ፈቃደኞች
እንዲሰጥ ያመቻቻል፡፡

2.6.2 በስራ ላይ ለሚገኙ በጎ ፈቃደኞች የማትጊያ ስልጠናዎች በህይወታቸው ላይ


ተጨማሪ ዕውቀት ለመቅሰም የሚረዳቸው የአኗኗር ዘይቤያቸውን
ለማስተካከል የሚረዷቸው አመለካከትን/አስተሳሰብን የሚያዳብሩ እንደ
የህይወት ክህሎት፣ የስራ ፈጠራ፣ የንግድ ክህሎት፣ የአመራር ጥበብ፣
የተግባቦት ክህሎት ወ.ዘ.ተ ልዩ ስልጠናዎችን የሚሰጥ ይሆናል፡፡
2.6.3 ከስራ ስምሪት በኋላ በማበረታቻ፣ዕውቅናና ሽልማት መልክ የሚሰጡ
የአጭር እና የረዥም ግዜ ስልጠናዎች የቴክኒክና ሙያ በደረጃና
በዲፕሎማ፣የመጀመሪያና የሁለተኛ ድግሪ እንዲሁም የሶስተኛ ድግሪ
የትምህርት እድሎችን በሀገር ውስጥና ከሃገር ውጪ ካሉ የትምህርት
ተቋማት ጋር በመተባበር በዓመት አንድ ግዜ ለተመረጡ በጎ ፈቃደኞች
የሚያመቻች ይሆናል፡፡
2.6.4 የተቋሙ የበጎ ፈቃደኞች ስልጠና ሂደት የተጠና፣ የተደራጀ እና ውጤቱ
የሚለካ መሆኑን ማረጋገጥ የሚጠበቅበት ሲሆን ስልጠናዎች በተቋሙ
በራሱ ወይም በተባባሪ አካላት በኩል ሊሰጥ ይችላል፡፡
2.6.5 ከላይ በተ.ቁጥር 2.6.4 የተቀመጠው እንደተጠበቀ ሆኖ በተባባሪ አካላት
የሚሰጠው ስልጠና በበላይነት ማስተባበር እና ስልጠናው ያመጣውን
ለውጥ መመዘን የተቋሙ ሃላፊነት ይሆናል፡፡

[Type the company name]| 2.6 ስልጠና / Training / 16


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

2.6.6 ለበጎ ፈቃደኞች የሚሰጡ የስልጠና ዓይነቶች፣ይዘቶች፣ መጠንና


የተደራሽነት ወሰን እንደየስልጠናው ባህሪና ከስልጠናው እንደሚጠበቀው
ውጤት ሊሰፋና ሊጠብ የሚችል ሲሆን ዝርዝር አፈፃፀሙ በስልጠና
ማስፈፀሚያ ማኑዋል የሚተነተን ይሆናል፡፡

2.7 ስምሪት
2.7.1 የበጎ ፈቃደኞች የስራ ስምሪት ሂደት የሚከናወነው በጎ ፈቃደኞች
እንዳላቸው ምርጫ፣ ችሎታና ልምድ ብቻ ነው፡፡
2.7.2 በስራ ስምሪት ላይ እያለ በጎ ፈቃደኛው ከአቅም በላይ የሆነ እክል
ቢገጥመው ከስራ መቅረቱን ለቅርብ ሃላፊው የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡
2.7.3 ማንኛውም በጎ ፈቃደኛ በስራ ስምሪት ወቅት በዚህ መመሪያ በመደበኛነት
የፀደቀውን የተቋሙን የስራ መለያ ልብስ መልበስና እና የበጎ ፈቃደኝነት
መታወቂያ መያዝ ግዴታ አለበት፡፡
2.7.4 በጎ ፈቃደኞች ወደ ስራ ሲሰማሩ እንደአስፈላጊነቱ የስራ ላይ ግብአቶች
ቁሳቁሶች ሊሟሉላቸው ይገባል፡፡
2.7.5 ማንኛውም በጎ ፈቃደኛ በስራ ስምሪት ወቅት በታማኝነትና በቅንነት
የማገልገል ግዴታ አለበት፡፡
2.7.6 በስራ ስምሪት ወቅት ሁሉም በጎ ፈቃደኞች ከተቋሙ የተሰጣቸውን የስራ
መመሪያ/ የስራ መዘርዝር ማክበርና መተግበር ይጠበቅባቸዋል፡፡
2.7.7 በጎ ፈቃደኞች የስራ ስምሪት ሲሰጣቸው የሚሰሩበት የስራ መደብ የስራ
ዝርዝር፣በጎ ፈቃደኛው ያለው የሥራ ሃላፊነት፣የተመደቡበት
መደብ፣የቅርብ ተቆጣጣሪውን ወ.ዘ.ተ ማክበርና መተግበር
ይጠበቅባቸዋል፡፡

[Type the company name]| 2.7 ስምሪት 17


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

2.8 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ክትትል፤ ድጋፍና የምዘና ስርዓት

2.8.1 ክትትልና ድጋፍ


2.8.1.1 ቢሮው በጎ ፈቃደኞች ወደ ስራ ከተሰማሩ በኋላ እንደየስራው ባህሪና
ስፋት ወጥና የተደራጀ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡
2.8.1.2 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞች ክትትልና ድጋፍ ዓላማ መሰረት
ማድረግ የሚገባው በጎ ፈቃደኞቹ የተጣለባቸውን ኃላፊነቶች በአግባቡ
እየተወጡ ስለመሆናቸው፣ በጎፈቃደኞቹ በስራቸው በሚያጋጥማቸው
ችግሮች ዙሪያ ለመወያየት ፣ለበጎ ፈቃደኞች አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን
በወቅቱ ለማቅረብ፣ በጎ ፈቃደኞች ለተቋሙ የእኔነት/ባለቤትነት ስሜት
እንዲያዳብሩና በተነሳሽነት የማገልገል አቅማቸውን ለማጎልበት፣ የበጎ
ፈቃደኞች ዕውቅና፣ ማበረታቻ እና ሽልማት አሰጣጥ የአገልግሎት ወይም
የስራ ብቃትን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን ለማስቻል ነው፡፡
2.8.1.3 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ክትትልና ድጋፍ የሚደረግላቸው አካላት የበጎ
ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞች እና በማዕከል፣ በክ/ከተማ እና በወረዳ
የሚገኙ የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤቶች የበጎ ፈቃድ
አገልግሎት አሰራር ሂደት ይሆናል፡፡
2.8.1.4 በቢሮው በክትትልና ድጋፍ ሂደት ውስጥ በዋነኝነት የሚከናወነው ተግባር
ከበጎ ፈቃድ ፕሮግራሞች የሚፈለገው ውጤት ስለመምጣቱ መረጃ
የመሰብሰብና የመመዝገብ ሂደት ይሆናል፡፡
2.8.1.5 የክትትልና ድጋፍ መረጃ የማሰባሰብ፣ የመመዝገብ፣የመተንተንና
የማጠናቀር ስራው የሚከናወነው ቢሮው ባዘጋጃቸው ወጥ የመረጃ
መሰብሰቢያ እና ሪፖርት ማጠናቀርያ ቅፃ ቅፆች፣ የግዜ ሰሌዳዎች ወ.ዘ.ተ
ይሆናል፡፡
2.8.1.6 በክትትልና ድጋፍ በዋነኝነት የሚሰበሰቡና የሚመዘገቡ መረጃዎች የበጎ
ፈቃደኞች ብዛት፣ የበጎ ፈቃደኞች አጠቃለይ ግላዊ መረጃ፣ የበጎ
ፈቃደኞች ተሳትፎና የአገልግሎት ዘመን፣ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉበት የበጎ

[Type the company name]| 2.8 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ክትትል፤ ድጋፍና የምዘና ስርዓት 18
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ፈቃድ አገልግሎት አይነት፣ የበጎ ፈቃደኞች አስተዋፅኦ ከማህበራዊና


የኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አንፃር፣ በበጎ ፈቃደኞች የተሸፈነ የሀብት መጠን እና
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማስተባበር የወጡ ወጪዎች ግብዓቶችን ጨምሮ
ወ.ዘ.ተ ያካተ የህብረተሰብ ክፍሎች ያሳተፈ ስለመሆኑ፣ ከእቅድ አንፃር
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሙ ውጤታማነት፣ በክትትልና ድጋፍ
የተገኘውን ክፍተት መነሻ በማድረግ ስለተወሰዱ/መወሰድ ስለሚገባቸው
የእርምት እርምጃዎች፣ በተገኙ ክፍተቶች ላይ በጎ ፈቃደኞች በማሳተፍ
የጋራ ውይይት ማድረግና አስፈላጊውን የማስተካከያ ውሳኔ የማሳለፍና
ይጠበቅባቸዋል፡፡
2.8.1.7 የክትትልና ድጋፍ ሂደቱ ያስገኘውን ፋይዳና ውጤታማነት sileka
ለመለካት ግልፅ፡ የሚለካ፡ የሚደረስ፤ እውነተኛና የጊዜ ገደብ ያለው
መሆን ይጠበቅበታል፡፡
2.8.1.8 የቢሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ክትትልና ድጋፍ የሚከናወነው በከተማ ፣
በክ/ከተማና በወረዳ ደረጃ የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ የክትትልና
ድጋፍና ምዘና የስራ ክፍል ይሆናል፡፡
2.8.1.9 ክትትልና ድጋፍ የየእለት ተግባር ቢሆንም የበጎ ፈቃድ ፕሮግራሞችን
ዕቅድ መነሻ በማድረግ ቢሮውና በተዋረድ የሚገኙ ተቋማት የረዥም ጊዜ
ፕሮግራሞች በአመት ለ4 ጊዜ እንዲሁም እንደ የአስፈላጊነቱ ለአጭርና
መካካለኛ ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞች በማጠቃለያ ምእራፍ
ላይ የሚደረግ ይሆናል፡፡

2.8.2 ምዘና
2.8.2.1 ቢሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞችን እንቅስቃሴ፣ ባህሪ
ዉጤታማነትና ፋይዳ በቂ መረጃ በመሰብሰብና በመተንተን በጥልቀት
የሚገመገምበት የምዘና ስረዓት ያካሄዳል፡፡
2.8.2.2 ቢሮው በአጠቃላይ በምዘና ስርዓት በጎ ፈቃደኞች በተለያዩ ፕሮግራሞች
ታቅፈዉ ባከናወኗቸዉ ተግባራት ለህብረተሰቡ ብሎም ለሃገር ያለዉ
ጠቀሜታ ወይም ፋይዳ ይለካል፡፡

[Type the company name]| ምዘና 19


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

2.8.2.3 ቢሮው የበጎ ፈቃድ ፕሮግራሞችና በጎ ፈቃደኛውን ለመመዘን ሂደታዊ


ምዘና፣ግብ ተኮር ምዘናና ዉጤት ተኮር የምዘና ዓይነቶችን ይጠቀማል፡፡
2.8.2.4 በቢሮው የሚከናወኑ የአጭር እና የመካከለኛ ግዜ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት
ፕሮግራሞች ምዘና የሚካሄደው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞች
ማጠቃለያ ላይ ሲሆን ለረዥም ግዜ የበጎ ፋቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞች
እንደየግዜ እርዝማኔያያቸው በ2 ዓመት ተኩል እና በየአምት ዓመት የግዜ
ዑደት ይሆናል፡፡
2.8.2.5 በቢሮው ለሚካሄዱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞች ምዘና ወጥና
የተደራጀ የመረጃ መሰብሰቢያ መመዝገቢያ ፣መተንተኛ መቀመሪያና
ሪፖርት ማቅረቢያ ቅፆች ብቻ ይሆናል፡፡

[Type the company name]| 20


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ክፍል ሶስት
3.1 የበጎ ፈቃድ መርሆዎች፣ መብትና ግዴታዎች እና ስነ - ምግባር
3.1.1 የበጎ ፈቃድ መርሆዎች
በከተማችን አዲስ አበባ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ግለሰቦች፣ማህበራት እና ተቋማት
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ሊያሟሏቸዉ የሚገቡ ዓለም ዓቀፍ ፣አካባቢያዊ
ወጎችና ባህሎችና እሴቶችን መጠበቅ የሚያስችሉ የበጎ ፈቃድ መርሆዎች፣ መብትና
ግዴታዎች እና ስነ - ምግባር በዚህ ምዕራፍ ተብራርተዉ ተደንግጓል፡፡

3.1.1.1 ቢሮውና በስሩ የሚሰማሩ በጎ ፈቃደኞች የሚከተሉትን የበጎ ፈቃድ


አገልግሎት መርሆዎችን መከተልና መተግበር ግዴታ አለባቸው፡፡
3.1.1.2 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማህበረሰቡም ሆነ ለበጎ ፈቃደኛዉ የሚሰጠው
ፋይዳ የጎላ ነው፡፡
3.1.1.3 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ክፍያ የለዉም፡፡
3.1.1.4 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሁልጊዜ በራስ ምርጫና ተነሳሽነት፤ ያለማንም
አስገዳጅነት የሚከናወን ነዉ፡፡
3.1.1.5 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለትርፍ ባልተቋቋሙ ብቻ ዘርፎች/ተቋሞች
የሚፈፀም ተግባር ነዉ፡፡
3.1.1.6 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በቋሚ/ግዜያዊ ቅጥር ሰራተኝነት የማይሰራ
ተግባር ነው፡፡ግ
3.1.1.7 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመንግስት ጡረታ ወይም የአበል/ክፍያ
በምትኩ ለማግኘት የሚከናወን ተግባር አይደለም፡፡
3.1.1.8 በጎ ፈቃደኞች በመደበኛነት በክፍያ ለሚሰሩ ሰራተኞች ምትክም ሆነ
ስጋት አይደሉም
3.1.1.9 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጎ ፈቃደኞች የሰዉ ልጆችን፣የአካባቢንና
የማህበረሰብ ፍላጎቶችን ለሟሟላት የሚችሉበት ተመራጭ ማንቀሳቀሻ
መንገድ ነው፡፡

[Type the company name]| ክፍል ሶስት 21


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

3.1.1.10 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዜጎች በማህበረሰባቸዉ ውስጥ በሚከወኑ


ተግባራቶች በቀጥታ ተሳትፎ ለማድረግ የሚያስችል ህጋዊ መንገድ
ነዉ፡፡
3.1.1.11 በጎ ፈቃደኞች የሌሎችን ባህል፣ መብት፣ እኩልነትንና አመለካከትን
ያከብራሉ፡፡
3.1.1.12 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማንኛዉንም የህብተሰብ ክፍል፣ ብሄር
፣ሃይማኖት ፣ ፆታ፣ የአካል ጉዳት፣ የቆዳ ቀለም ወ.ዘ.ተ ሳይለይ
ያሳትፋል፡፡
3.1.1.13 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘላቂ ልማት ለማምጣት አጋዥ መሳሪያ ነው፡፡

3.1.2 የበጎ ፈቃደኞች መብት


በጎ ፈቃደኞች የሚከተሉት መብቶች ይኖራቸዋል፡፡

3.1.2.1 ከአድሎ ነፃ በሆነ መንገድ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት


የመመዝገብ፣ የመመልመል/መመረጥና የመሳተፍ መብት የማግኘት
3.1.2.2 በጎ ፈቃደኞች በተቋሙ አመራርና ሰራተኞች፣ አገልግሎት
በሚሰጡባቸው ቦታዎች እንዲሁም በሌሎች በጎ ፈቃደኞች የመከበር
መብት አላቸው
3.1.2.3 ቢሮው ስለ በጎ ፈቃደኞች ግላዊ መረጃ ተገቢ ማጣራት ለማድረግ
ሲፈልግ ፍቃደኝነታቸው የመጠየቅ መብት
3.1.2.4 በጎ ፈቃደኞች በሚፈልጉት/በመረጡትና በሚችሉት የስራ መስክ ብቻ
የመመደብ
3.1.2.5 ስለስራቸውም ሆነ ስለተቋሙ አሰራር የማወቅ፣ ግልፅ የሆነ የበጎ
ፈቃድ መርሃ ግብር የስራ መዘርዝር የማግኘት
3.1.2.6 የቅርብ ተቆጣጣሪያቸውን የማወቅና ክትትልና ድጋፍ የማግኘት
3.1.2.7 ተገቢ ስልጠናና የስራ ቁሳቁስና ግብአት የማግኘት
3.1.2.8 ጤናማና ምቹ የስራ አካባቢ የማግኘት
3.1.2.9 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት ሂደት ከኪሳቸው ላወጡት
አግባብነት ያለው ወጪ የወጪ መተኪያ የማግኘት

[Type the company name]| የበጎ ፈቃደኞች መብት 22


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

3.1.2.10 በአደጋ ጊዜ ተገቢ የሆነ የጤና/የህይወት መድን ዋስትና የማግኘት


3.1.2.11 ተገቢ ዕውቅናና ማበረታቻ የማግኘት
3.1.2.12 በጎ ፈቃደኞች ለሚያቀርቡት ቅሬታ ተገቢ ምላሽ የማግኘት

3.1.3 የበጎ ፈቃደኞች ግዴታ


3.1.3.1 በጎ ፈቃደኞች ከአቅም በላይ በሆነ ችግር በስራ ላይ መገኘት
በማይችሉበት ጊዜ ለቅርብ ተቆጣጣሪያቸው አስቀድመው ማሳወቅ
አለባቸው፡፡
3.1.3.2 የተቋሙን፣ የሌሎች በጎ ፈቃደኞችንና የተጠቃሚዎችን /የበጎ ፈቃድ
አገልግሎት ተቀባዮችን/ ሚስጥር የመጠበቅ
3.1.3.3 በተግባር ወቅት በሌሎች ሰዎች ተግባር ዉስጥ ጣልቃ መግባት
የለባቸዉም
3.1.3.4 በበጎ ፈቃድ ስራ ወቅት በጎ ፈቃደኞች የተቋሙ አምባሳደር ሆኖ
የማገልገል
3.1.3.5 ከተቋሙ ጋር በገቡት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የስራ ውል ስምምነት
አግባብ መሰረት የመፈፀም
3.1.3.6 የመኖሪያ ወይም የስልክ አድራሻ ሲቀይሩ የማሳወቅ
3.1.3.7 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ላይ በሚሆኑበት ወቅት ተገቢውን
አለባበሰ መተግበር ፣ የባህሪ እና የሙያ ስነ ምግባሮችን ማክበር
3.1.3.8 ለተሰማሩበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር በሃላፊነት፣ በቅንነትና
በታማኝነት የማገልግል
3.1.3.9 የተቋሙን ፖሊሲ፣ህግ፣ደንቦችና እሴቶችን የማክበር
3.1.3.10 አገልግሎት ለሚሰጡት ተቋም/የህብረተሰብ ክፍል ባህል ፣ዕምነት፣
አመለካከትን ማክበር
3.1.3.11 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራው የሚፈልገውን ተገቢ እውቀት መያዝ
እንዲሁም ለስራው አጋዥ የሆነ ስልጠና ሲሰጣቸው የመሳተፍና
የመከታተል ግዴታ አለባቸው
3.1.3.12 የቅርብ ተቆጣጣሪያቸውን መልዕክትና ትዕዛዝ ማክበር

[Type the company name]| የበጎ ፈቃደኞች ግዴታ 23


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

3.1.3.13 በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ወቅት በቸልተኝነት/እንዝህላልነት


ከሚደርስ አደጋ እራሳቸውን የመጠበቅ
3.1.3.14 በአገልግሎት ወቅት ለሚደረስ አደጋ ተገቢውን የመጀመሪያ ደረጃ
የህክምና እርዳታ በወቅቱ የመውሰድ እና አደጋው ስለመድረሱ
የማሳወቅ ግዴታ አለበት
3.1.3.15 ለቡድን አጋሮቹ አስፈላጊውን ድጋፍና ክብር መስጠት አለበት
3.1.3.16 ከግል ህይወት ጋር አብሮ የማይሄድ/ የማይችሉት/የማይፈልጉት የስራ
መርሀ ግብ፣ የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም መምረጥ የለባቸዉም

3.2 በጎ ፈቃደኞችን የሚያሳትፉ ተቋማት መብትና ግዴታዎች


3.2.1 በጎ ፈቃደኞችን የሚያሳትፉ ተቋማት መብት
3.2.1.1 ከበጎ ፈቃደኞች ጋር በገቡት የስራ ውል መሰረት አገልግሎት የማግኘት
መብት
3.2.1.2 በተቋሙ ለመስራት ካመለከቱት መካከል የተሻለ አመልካችን leyito
አስፈላጊዉን ማጣራት እና ቃለመጠይቅ በማድረግ መምረጥ፡፡
3.2.1.3 ሰራተኞች ከተቋሙ አሰራር ሁኔታ እንዳይወጡ እና የስራ
ዝርዝራቸዉን ተግባራዊ እንዲያደርጉ የመከታል፣ የመደገፍና
የመቆጣጠር
3.2.1.4 ለበጎ ፈቃደኞች በተዘጋጀ ስልጠና ላይ በጎ ፈቃደኞች እንዲሳተፉ
የማድረግና የመከታተል
3.2.1.5 የተሻለ በጎ ፈቃደኞችን መመደብ ላይ ዉሳኔ የመስጠት
3.2.1.6 ደከም ያሉ በጎፈቃደኞችን በተመለከተ አቅም የመገንባት፣ ሃሳብ
የመስጠት
3.2.1.7 ግልጽና ክፍት የሆነ ንግግርና ዉይይትን ለበጎ ፈቃደኞች የማድረግ
3.2.1.8 የስራ ውል ስምምነት የማድረግ የመፈፀም
3.2.1.9 አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጎ ፈቃደኞችን የማሰናበት

[Type the company name]| በጎ ፈቃደኞችን የሚያሳትፉ ተቋማት መብትና ግዴታዎች 24


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

3.2.2 በጎ ፈቃደኞችን የሚያሳትፉ ተቋማት ግዴታዎች


3.2.2.1 የመ/ቤቱን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አጠቃላይ አሰራር የማዘጋጀትና
የማሳወቅ
3.2.2.2 የበጎ ፈቃደኞች፣ የሱፐርቫይዘሮች፣ የአጋርና ባለድርሻ አካለትን አቅም
የመገንባት
3.2.2.3 በጎ ፈቃደኞች የተሰጣቸውን ተግባር ውጤታማ በሆነ መንገድ
ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ስልጠና የማዘጋጀት
3.2.2.4 ለስራ የሚዉሉ አስፈላጊዉን የተቋሙን መለያ ደንብ ልብስ እና ግበዓት
የማቅረብ
3.2.2.5 ለበጎ ፈቃደኞች እዉቅና፣ማበረታቻ እና ሽልማት የመስጠት
3.2.2.6 በሁሉም የፕሮግራም ዝግጅት ፤የልማት ዕቅድ ትግበራና የስራ ግምገማ
የበጎ ፈቃደኞች ሃሳብና አስተያየት በደማቅ ሁኔታ መታየቱንና
መተግበሩን ማረጋገጥ
3.2.2.7 ለበጎ ፈቃደኞች አስፈላጊዉን የወጪ መተካትና የጤና/የህይወት
መድህን ዋስትና የመስጠት
3.2.2.8 የበጎ ፈቃደኝነትን ስራ በተከፋይ ሰራተኞች የሚሰራዉን የማይሸፍንና
ተከፋይ ሰራተኞችን የማያፈናቅል መሆኑን ማረጋገጥ
3.2.2.9 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስተባበሪና ተቆጣጣሪዎች በጎ ፈቃደኞች
ያስመዘገቡትን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የፈጀዉን ሰዓት፣ቀን እና ጊዜ
መዝግቦ መያዝ አለባቸው
3.2.2.10 ለበጎ ፈቃደኞችና ለተገልጋዮች የማይሆን ተስፋና ቃል ከመግባት
መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡

[Type the company name]| በጎ ፈቃደኞችን የሚያሳትፉ ተቋማት ግዴታዎች 25


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

3.3 ስነ ምግባር
 ቢሮው በጎ ፈቃደኞች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ላይ ሲሰማሩ ሊከተሏቸው
የሚገቡ የስነምግባር ደንቦች እንደሚከተለው አዘጋጅተዋል ተዘርዝሯል፡፡
3.3.1 የቢሮው በጎ ፈቃደኞች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት የተሰጣቸውን
ኃላፊነት ለግል ጥቅማቸው ወይም ለዘመዶቻቸው ጥቅም ወይም ለጓደኞቻቸው
ጥቅም በማዋልና ሥልጣናቸውን ያለአግባብ መጠቀም የለባቸውም፤
3.3.2 የቢሮውን ሀብት፣ መረጃ ወይም የቢሮውን በጎ ፈቃደኝነታቸውን ለሌላ ሶስተኛ
ወገን ጥቅም ማዋል አይኖርባቸውም፤
3.3.3 ለስራ የተሰጣቸውን ማንኛውም ዓይነት የቢሮው ንብረት/ቁሳቁሶች ለቢሮው የበጎ
ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ብቻ መጠቀም አለባቸው፤
3.3.4 በኃላፊነታቸው ምክንያት ያወቁትን የቢሮውን/የሰራተኞችን/የሌሎች በጎ ፈቃደኞችን
መረጃዎች ሚስጥራዊነት የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው፤
3.3.5 የበጎ ፈቃድ ስራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት ለስርዓተ-ፆታ ጉዳዮች ትኩረት
መስጠትና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከማንኛውም ዓይነት ፆታዊ ትንኮሳ ድርጊቶች
ከመፈፀም መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል፤
3.3.6 ለህብረተሰቡና ለስራው ተስማሚ የሆነ የአለባበስ ሥርዓት በመጠበቅ በቢሮው
አጋሮችና በህብረተሰቡ ዘንድ መልካም ገጽታ መገንባት ይጠበቅባቸዋል፤
3.3.7 ከቢሮው ጋር በሚሰሩበት ወቅት ከፍተኛ የተአማኒነትና ኃላፊነት መንፈስ
ሊኖራቸው ይገባል፤
3.3.8 በቢሮው በሚሰሩበት ጊዜ አለምዓቀፉን እንዲሁም የተቋሙን የበጎ ፈቃደኞች
እንቅስቃሴና መርሆዎቹን ወክለው እንደሆነ ማስታወስ አለባቸው፤
3.3.9 ማንኛውንም ተግባር ሲያከናውኑ በቢሮው የአሰራር ደንቦችና መርሆች መሰረት
መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው፤
3.3.10 ምንግዜም ቢሆን የሌሎች ሰዎችን ፍላጎት በንቃት መጠበቅ አለባቸው፤
3.3.11 የቢሮውን ዓርማ አጠቃቀም ደንብ ማክበርና ምንጊዜም ቢሆን ያለአግባብ የሆነ
አጠቃቀምን መከላከል አለባቸው፤

[Type the company name]| 3.3 ስነ ምግባር 26


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

3.3.12 የቢሮውን ዓላማዎች ተግባራዊ ሲያደርጉ ያልገባቸው ነገር ካለ ውሳኔ


ከመስጠታቸው በፊት የቅርብ ተቆጣጣሪያቸውን ምክረ ሃሳብ ማግኘት (መጠየቀ)
አለባቸው፤
3.3.13 ሰዎች እራሳቸውን በራሳቸው መርዳት በሚችሉበት መንገድ ማገዝ አለባቸው፤
3.3.14 ደረጃውን የጠበቀ የበጎ ፈቃደ ተግባር (ጥራቱን የጠበቀ) ስራ ለማከናወን
የሚችሉትን ሁሉ ማድረግ አለባቸው፤
3.3.15 የሚረዷቸውን አገልግሎት የሚሰጣቸውን የሚደገግቸውን ሰዎች ሚስጥር መጠበቅ
ይኖርባቸዋል፡፡
3.3.16 የሚስሩለትን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚያደርጉትን ህብረተሰብ ሁኔታ
መገንዘብና ባህሉን መጠበቅ ያስፈልጋቸዋል፡፡
3.3.17 ለህብረተሰቡ ፍላጎት ምላሸ ሲሰጡ በሰብዓዊነትና በፍቅር መሆን አለበት፤
3.3.18 አገልግሎት ለመስጠትና ሁልጊዜም ተደራሽ ለመሆን ዝግጁ መሆን አለባቸው፡፡

3.4 የስነምግባር ጥሰቶች


3.4.1 የስነ ምግባር ጥሰት ማለት የበጎ ፈቃድ መርሆዎችና እና እሴቶችን መተግበር፣
በአግባቡ መከተልና መፈጸም ሳይችል የቀረ ወይም ሆን ብሎ፣ፈልጎ ፣ተዘጋጅቶ
፣አስቦበት አልያም ሃላፊነትን ቸል በማለት እና በግዴለሽነት እናም ይህን ማድረጉ
የሚያስከትለዉን መዘዝ በምክኒያታዊነት አለመረዳት ጭምር በዚህ መመሪያ የስነ
ምግባር ጥሰት ተብሎ ይወሰዳል፡፡
3.4.2 የስነምግባር ጥሰቶች ዓይነትና ዝርዝር የግድ በዚህ የአሰራር ማዕቀፍ (መመሪያ)
የተጠቀሱት ዕንኳ ብቻ ባይሆንም
3.4.2.1 በማወቅ ወይም ባለማወቅ እና በግዴለሽነት የሚፈጸሙ
ስርቆት፣ማጭበርበር፣የሀሰት ሰነድ መጠቀም
3.4.2.2 አደገኛ አደንዛዥና አነቃቂ እጾችን መሸጥ ይዞ መገኘት ብሎም ፣ይዞ
መገኘትና ለሌላ ወገን ማስተላለፍ
3.4.2.3 ፆታዊ ትንኮሳ መመኮርና መፈፀም
3.4.2.4 ከአሰራር ማዕቀፍ ወጪ የሆነ የተጋነነ የወጪ መተኪያ ክፍያ
መጠየቅ

[Type the company name]| የስነምግባር ጥሰቶች 27


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

3.4.2.5 ገንዘብ ብክነት /የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን ለማከናወን ከሚወጣው


የግዜ፣የእውቀት፣የጉልበትና የሃብት መጠን በላይ ያለአግባብ ጥቅም
ላይ ማዋል/
3.4.2.6 በሃሰት ሌላዉን መወንጀል እና አሉባልታ መንዛት
3.4.2.7 የበጎ ፈቃድ ተግባር የሚመለከት መረጃ፣ ሰነድ ወይም ዶሴ/ፋይል
ያለአግባብ መጠቀም፣ ማጥፋትና አሳልፎ ለሶስተኛ ወገን መስጠት
3.4.2.8 ያለአግባብ የተቋሙን ሃብት፣ ንብረትና ግብዓቶችን ያለአግባብ
መጠቀም፣ ማበላሸት፣ መበዝበዝ፣ መዉሰድ፣ አለመመለስና ማጉደል
3.4.2.9 በሌላዉ ላይ አስገዳጅ /የፖለቲካ፣የእምነት፣ የባህል፣ የአስተሳሰብ
ወ.ዘ.ተ/ ሰብዕናን ማሳየትና መጫን
3.4.2.10 ለበጎ ፈቃድ ተግባር መደበኛ ክፍያ መጠየቅ
3.4.2.11 ለገጠመ የአሰራር(አፈጻጸም) ችግር ሃይል ተጠቅሞ ለመፍታት
መሞከር
3.4.2.12 ሌሎችን ምቾት የሚነሳና ስነ ምግባር የጎደለዉ አለባበስ በስራ ላይ
መልበስ
3.4.2.13 በንግግር ወቅት አስነዋሪ እና ፀያፍ ቃላትን እንዲሁም ምልክት
መጠቀም
3.4.2.14 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሚሰጥበት ስፍራ አምባጓሮ/ፀብ መፍጠርና
ድብድብ ማካሄድ
3.4.2.15 የበጎ ፈቃደኞችን፣ የቢሮው፣ ወይም የተገልጋዮችን ሚስጥር
ማውጣት/አሳልፎ መስጠት
3.4.2.16 ቢሮው የስነ ምግባር ጥሰት ስለመከሰቱ ጥቆማ ሲደርሰው፣ሙከራ
ሲደረግና ተፈፅሞ ሲገኝ የሚያጣራበትና ውሳኔ የሚሰጥበት ሂደት
የሚኖረው ሲሆን ይህም በየደረጃው ባለ የቢሮው መዋቅር የዲስፕሊን
ኮሚቴና ማስፈፀሚያ ደንብ በማዘጋጀት የሚፈታው ይሆናል፡፡
3.4.2.17 በዚህ መመሪያ የተፈጻሚነት ወሰን በሙሉ የሚታዩ፣ የተጠረጠሩ፣
ሪፖርት የተደረጉ፣ የተጠቆሙ እና የተረጋገጠ የስነ ምግባር ጥሰቶች
ተጠያቂነት ይኖራቸዋል

[Type the company name]| የስነምግባር ጥሰቶች 28


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

3.4.2.18 በዚህ መመሪያ የስነ ምግባር ጥሰት ተፈፅሞ ሲገኝ የሚከናወን


የማጣራት ሂደት የሚከተሉት ይሆናሉ

ሀ. ለሚመለከተዉ አካል ለጥያቄ መቅረብን

ለ. ለዉይይት መጠራትን

ሐ. መመርመርን ያካትታል

3.4.2.19 በዚህ መመሪያ ተፈፅመው ለተገኙ የስነ ምግባር ጥሰቶች መፍቻ


መንገዶች ተደርገው የሚቆጠሩት

ሀ. ግልግል

ለ. ሽምግልና

ሐ. ሙግት/ክርክር

መ. ለፍርድ ማቅረብን ያካትታል

3.4.2.20 በዚህ መመሪያ ተፈፅሞ ለተገኘና ለተረጋገጠ የስነምግባር ጥሰት


ሊወሰን የሚችል የቅጣት ደረጃ

ሀ. የቃል ማስጠንቀቂያ

ለ. የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

ሐ. የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

መ. እግድ

ሠ. የስራ ዉል ስምምነት መሰረዝ/ማቋረጥ

ረ. ስንብትን ያካትታል

[Type the company name]| የስነምግባር ጥሰቶች 29


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

3.5 ይግባኝ
3.5.1 ማንኛውም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ከቢሮው ጋር ዉል ወስዶ እየሰራ
ላለ አካል ለተወሰደበት እርምጃ ከተወሰደበት ዕለት አንስቶ በሚኖሩ አምስት የስራ
ቀናት ለቢሮው ከፍተኛ የማኔጅመንት ኮሚቴ ይግባኙን በጽሁፍ ማቅረብ
ይኖርበታል፡፡ይግባኙም የሚመራዉ በቢሮ ሃላፊው ሲሆን ዉሳኔዉ የመጨረሻ ነዉ
ነገር ግን የይግባኙ ሰሚ አመራር የስነ ምግባር ጥሰት ዕርምጃ ዉሣኔ ካሳለፉት
ከፍትኛ የማናኔጅመነት ኮሚቴዎች ውጪ መሆን አለበት፡፡
3.5.2 በዚህ መመሪያ በቢሮው አሰራር እና አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ ለሚቀርቡ
ቅሬታዎችና አቤቱታዎች የቅሬታ አቀራረብ፣ ቅሬታን ማጣራት እና ለቀረቡ
ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት የሚከናወነው ቢሮው ባለው
መደበኛ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት ይሆናል፡፡

[Type the company name]| ይግባኝ 30


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ክፍል አራት
4 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ግብዓት አቅርቦት
4.1 የበጎ ፈቃደኞች የስራ መለያ
4.1.1 በቢሮው የሚሰማሩ መደበኛ በጎ ፈቃደኞች በስራ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ

የሚጠቀሙባቸው አልባሳት/የስራ መለያ ይኖራቸዋል፡፡

4.1.2 የቢሮው የበጎ ፈቃደኞች መለያ አልባሳት ቀለም መደቡ --------------

ይሆንና የጨርቁ አይነት በሀገር ውስጥ መመረት የሚችሉ ማንኛውም ከጥጥ፣

ከላይነን፣ ከካኪ፣ ከፖሊስተር፣ ሳተን፣ አቡጀዲ፣ ገበርዲን ወ.ዘ.ተ የጨርቅ

አይነቶችን በመጠቀም ማዘጋጀት ይሆናል፡፡

4.1.2 ቢሮው ከላይ በተመረጠው የቢሮው የበጎ ፈቃደኞች አልባሳት መለያ ቀለምና
የጨርቅ አይነት በመጠቀም የመለያ አልባሳቱ እንደየ በጎ ፈቃድ ፕሮግራሞቹ
ምቹነት በሰደርያ፣ በሽርጥ፣ በሸሚዝ፣ በቲ - ሸርት፣ በቱታ፣ በኮፊያ መልክ
የተለያየ የአልባሳት ዲዛይኖችን ይጠቀማል፡፡
4.1.3 የቢሮው የበጎ ፈቃደኞች የስራ ላይ መለያ አልባሳት ግዥና ስርጭት ማከናወን
የሚቻለው በቢሮ ደረጃ ብቻ ነው፡፡
4.1.4 በቢሮ ደረጃ የተዘጋጁ የበጎ ፈቃደኞች የስራ ላይ አልባሳት ስርጭት የሚከናወነው
በቢሮ፣ በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ በመደበኛ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት
ለመሰማራት በተመዘገቡና በመረጃ ቋት ውስጥ በተደራጀ የበጎ ፈቃደኞች መረጃ ላይ
ብቻ የተመሰረተ ይሆናል፡፡
4.1.5 የበጎ ፈቃደኞች የሥራ ላይ አልባሳት በየደረጃው ላለ አስፈፃሚ አካል ስርጭት
የሚከናወነው በመንግስት የግብዓት ወጪና ገቢ ስረዓት አፈፃፀም ይሆናል፡፡
4.1.6 በተራ ቁጥር 4.1.6 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ
ለበጎ ፈቃደኞች የሚሰጥ የስራ መለያ አልባሳት ሲኖር ክፍለ ከተማው/ወረዳው

[Type the company name]| ክፍል አራት 31


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ሚፈልገውን የአልባሳት ብዛትና አይነት ከበጎ ፈቃድ አገልግሎት የስራ እቅድና


በስራው ላይ የሚሰማሩ የበጎ ፈቃደኞች ብዛት ለቢሮው በማቅረብ እንዲዘጋጅለት
ማድረግ ይኖርበታል፡፡
4.1.7 የበጎ ፈቃደኞች የሥራ ላይ መለያ አልባሳት በአጠቃቀም ወቅት ቢቀደድ፣ቢበላሽ
ወይም ቢጠፋ በምትኩ እንዲተካላቸው በቅርባቸው ላለ አስፈፃሚ አካል ማመልከት
ይጠበቅባቸዋል፡፡
በጎ ፈቃደኞች ከቢሮው ጋር ያላቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሥራ ስምምነት
ውል በማንኛውም መልኩ ሲጠናቀቅ የወሰዱትን የስራ ላይ መለያ አልባሳት
መመለስና ከቢሮው ንብረት ነፃ መሆናቸውን ማረጋገጫ/ክሊራንስ/ መውሰድ
ይጠበቅባቸዋል፡፡

4.2 የቢሮው አርማና መሪ ቃል


4.2.1 ቢሮው የተቋቋመበትን ዓላማና ከበጎ ፈቃድ አገልግሎት አንፃር ሊያሳካ ያሰበውን
ግብ የሚያመላክት ሎጎ/ዓርማ እና መሪ ቃል ያለው ሲሆን ይህም ------------------

4.2.2 ቢሮው በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ አርማ እና ሞቶውን መጠቀም የግድ


ሲሆን ይህም ከተቋሙ በሚወጡ ደብዳቤዎች ላይ፣ በበጎ ፈቃደኞች አልባሳት ላይ፣
ቢሮው በሚያዘጋጃቸው ማንኛውም የማስታወቂያ መድረኮችና መንገዶች ላይ
ወ.ዘ.ተ ይሆናል፡፡
4.2.3 በዚህ መመሪያ ለቢሮው የፀደቀው አርማና ሞቶ ማንኛውም ሶስተኛ ወገን
መጠቀምም ሆነ ይዘቱንና ቅርፁን መቀየር አይችልም፡፡

4.3 የበጎ ፈቃደኞች መታወቂያ


4.3.1 ቢሮው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሚሰማሩ በጎ ፈቃደኞች ወጥነት ያለው እና

ከየትኛውም ሲስተም ጋር ተናባቢ ሊሆን የሚችል ልዩ መለያ ቁጥር የተሰጠው

መታወቂያ እና የምዝገባ ካርዶችን አዘጋጅቶ ይሰጣል፡፡

[Type the company name]| የቢሮው አርማና መሪ ቃል 32


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

4.3.2 በቢሮው የሚሰጡ የበጎ ፈቃደኞች መታወቂያና የምዝገባ ካርዶች፣ ህትመት


የሚከናወነው በአንድ ማዕከል በተደራጀው የመረጃ ቋት መሰረት በቢሮው ብቻ
ይሆናል፡፡
4.3.3 ማንኛውም በጎ ፈቃደኛ የወሰደውን መታወቂያ ወይም የምዝገባ ካርድ ከቢሮው
ጋር ያለው የስራ ውል ስምምነት በማንኛውም ሁኔታ ሲቋረጥ መመለስ
ይጠበቅበታል፡፡
4.3.4 ቢሮው ለበጎ ፈቃደኞች የሰጠው መታወቂያ ወይም የምዝገባ ካርድ ቢጠፋ
፣ቢቀደድ ወይም ቢበላሽ በቅርብ ላለ ተጠሪ አስፈፃሚ አካል በማሳወቅ ምትክ
እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡
4.3.5 በቢሮው የሚሰጠው መታወቂና እና የምዝገባ ካርዶች ስርጭት አጠቃቀም

አመታዊ የኦዲት ቁጥጥር ይደረግላቸዋል፡፡ማንኛውም በጎ ፈቃደኛ በቢሮው የወሰደውን የበጎ


ፈቃድ አገልግሎት አጋዥ ግብዓትም ሆነ ቁሳቁስ በተቻለ መጠን በንፅህና ጠብቆ መያዝና
መጠቀም ይኖርበታል፡፡

4.4 ወጪ መተካት /Reimbersment/


በዚህ መመሪያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት በቢሮው ቀጥታ ስምሪት ለሚሰጣቸው
መደበኛ በጎ ፈቃደኞች አገልግሎቱን በመስጠት ሂደት ውስጥ ከኪሳቸው የሚያወጧቸው
ወጪዎች ለተቋሙ በሚያቀርቡት ተገቢ ማስረጃ መሰረት እንደአስፈላጊነቱ ወጪን
የመተካት አሰራር ይኖረዋል፡፡

4.4.1 ትራንስፖርት ክፍያን አፈፃጸም


4.4.1.1 አንድ በጎ ፈቃደኛ በሚኖርበት ወረዳ ክልል ውስጥ ለሚያከናዉናቸዉ
የበጎ ፈቃድ ተግባራት የትራንስፖርት ወጪ መተካት አይደረግለትም፡፡
4.4.1.2 ከላይ በተራ ቁጥር 4.4.1.1 እንደተጠበቀ ሆኖ ከወረዳ - ወረዳ ፣ከወረዳ -
ክ/ከተማ እና ከክፍለ ከተማ - ክፍለ ከተማ ለሚደረግ የበጎ ፈቃድ
እንቅስቃሴ የሚሄዱበት የቦታ ርቀት ታሳቢ ያደረገ የትራንስፖርት ወጪ
የሚተካ ይሆናል፡፡

[Type the company name]| 4.4 ወጪ መተካት /Reimbersment/ 33


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

4.4.1.3 የቢሮው የትራንስፖርት የወጪ መተካት ስርዓት የሚከናወነው ቢሮው/


በየደረጃው ያለው ተቋም ከአንበሳ አውቶቡስ ወይም ከሸገር የብዙሃን
ድርጅት ብቻ የጉዞ ፓኬጅ በመግዛትና ትኬቱን በመስጠት ይሆናል፡፡
4.4.1.4 የበጎ ፈቃደኞች ወጪ መተካት አሰራርን ውጤታማና ቀልጣፋ በሆነ
መንገድ ለማስፈፀም በየደረጃው ያለ አካል ለበጎ ፈቃደኞች የትራንስፖርት
ወጪ አስፈላጊ የሆኑባቸውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብሮችን
አስቀድሞ በማቀድና ለግዥ ጥያቄ በማቅረብ ይሆናል፡፡
4.4.1.5 በጎ ፈቃደኛዉ በእግረ መንገድ ለሚያከውነው ግላዊ፣ ቤተሰባዊ እና
የንግድ ጉዳዮች ወጪ መተካት አይከናወንለትም
4.4.1.6 ቢሮው ከተቋማት/ማህበራት/ስብስቦች ወ.ዘ.ተ ጋር በጋራ በሚያከናውነው
መደበኛ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚኖሩ የወጪ መተኪያ ክፍያዎች
ተፈፃሚ የሚሆኑት ቢሮው ከተቋማቶቹ ጋር በገባው
የሁለትዮች፣ሶስትዮሽ እና ከዛ በላይ በሆኑ የአጋርነት የስራ ስምነት ውል
ይሆናል፡፡

4.4.2 የግንኙነት ማሳለጫ ወጪዎች


4.4.2.1 የግንኙነት ማሳለጫ ወጪዎች ለስልክ፣ለፖስታ፣ ለኮፒ፣ጽሁፍ፣
ኢንተርኔት፣ስካን፣ ፋክስ ወ.ዘ.ተ ቢሮው ከበጎ ፈቃደኞች ወይም በጎ
ፈቃደኞች ከቢሮው ጋር የስራ ግንኙነት ለማድረግ የሚወጡ ወጪዎች
ናቸው
4.4.2.2 በዚህ መመሪያ ስራውን ለማሳለጥ የሚረዱ የግንኙነት ወጪዎች በተቻለ
መጠን ወቅቱን የዋጁ እንዲሆኑ የኢንተርኔትና ዲጂታል ቴክኖሎጂን
እንዲጠቀም ማድረግና የነዚህም ወጪዎች የወጪ መተካት ሂደት
የሚፈፀመው ተቋሙ ከኢትዮ ቴሌሌኮም የድምፅ፣ የመልዕክትና፣
የኢንተርኔት ጥቅሎችን በመግዛትና የሚቀርቡ ወጪዎችን
እንደአስፈላጊነቱ በመመደብ ይሆናል፡፡

[Type the company name]| የግንኙነት ማሳለጫ ወጪዎች 34


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

4.4.2.3 የግንኙነት ማሳለጫ የወጪ መተኪያ ስርዓት ተጠቃሚ የሚሆኑት


የመደበኛ በጎ ፈቃድ አገልግሎት በጎ ፈቃደኛ አስተባባሪዎች ብቻ
ይሆናሉ፡፡
4.4.2.4 በተራ.ቁጥር 4.4.2.3 ተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ የሚተኩ የግንኙነት
ወጪዎች በወር ለአንድ ግዜ ብቻ እንደየሚያስተባብሩት ስራ የግንኙነት
መጠንና ስፋት ዝቅተኛው የ 25 ብር የአየር ሰዓት ሲሆን ከፍተኛው
100 ብር የአየር ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡

4.4.3 ለአደጋ መከላከያ የስራ ላይ አልባሳት ወጪ መተኪያ


4.4.3.1 ቢሮው እንደአስፈላጊነቱ ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞች የስራ ላይ
መለያ እና የአደጋ መከላከያ አልባሳትን የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
4.4.3.2 በተራ.ቁጥር 4.4.3.1 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ የአደጋ መከላከያ
አልባሳትን ስራውን በጋራ ሚያከናውኑ አጋር ተቋማት በኩል እንዲሸፈን
ማድረግ ይችላል፡፡
4.4.3.3 ከላይ በተራ ቁጥር 4.4.3.1 እና 4.4.3.2 ከተገለፀው ውጪ ውስን በሆኑ
እና በጣም ልዩ ባህሪ ላላቸው የበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ ለሚሰማሩ በጎ
ፈቃደኞች የአደጋ መከላከያ የስራ ላይ አልባሳት ከኪሳቸው በማውጣት
ገዝተው ለሚጠቀሙ በጎ ፈቃደኞች የሚያቀርቧቸውን ህጋዊ ሰነዶች
መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ የወጪ መተካት ይፈፅማል፡፡

4.4.4 የስልጠናና ልዩ ኮርሶች ወጪ መተኪያ


4.2.4.1 ቢሮው በስራ ስምሪትና በማትጊያ መልክ በየደረጃው በሚያዘጋጃቸው የበጎ
ፈቃደኖች ስልጠና ወይም ልዩ ኮርሶች ለሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች የስልጠና/ልዩ ኮርስ ወጪ
የሚተካው በከተማ ውስጥ ለተዘጋጀ ስልጠና/ልዩ ኮርስ ከተማ አስተዳደሩ በስልጠና/ስብሰባ
ወቅት እንዲከፈል ባስቀመጠው የክፍያ አሰራር ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ
ለሚዘጋጅ ስልጠና/ልዩ ኮርስ በፌደራሉ የፋይናንስ ክፍያ አሰራር መሰረት የሚፈፀም
ይሆናል፡፡

[Type the company name]| የግንኙነት ማሳለጫ ወጪዎች 35


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

4.4.5 ከሃገር ውጪ/ ከከተማ ውጪ ለሚደረጉ ጉዞዎች የወጪ መተኪያ


4.4.5.1 ከሃገር ውጪ/ ከከተማ ውጪ ለሚደረጉ ጉዞዎች ወጪ መተኪያ ማለት
ከከተማ አስተዳደሩ ወደ ሌላ የሃገሪቱ አካባቢዎች ወይም ከሃገር ውስጥ
ወደ ሌሎች ሃገራት ከ አንድ ቀን በላይ ለሚፈጁ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት
ስራዎች ለሚመጣ ወይም ለሚሄድ በጎ ፈቃደኛ የትራንስፖርት፣
የምግብ፣የመኝታ፣ የቪዛ ክፍያዎች ቢሮው የወጪ መተኪያ ክፍያዎችን
ይፈፅማል፡፡
4.4.5.2 ከሃገር ውጪ/ ከከተማ ውጪ ከአንድ ቀን በላይ ለሚደረጉ የበጎ ፈቃድ
አገልግሎት ጉዞዎች የሚወጡ የትራንስፖርት፣ የምግብ፣የመኝታ፣ የቪዛ
ክፍያዎች ወጪ መተኪያ የሚፈፀመው በከተማ አስተዳደሩ ወይም
በፌደራሉ የፋይናንስ ክፍያ አሰራር መሰረት ይሆናል፡፡

4.4.6 ከግማሽ ቀን በላይ ለሚሹ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የሚከናወን ወጪ


መተኪያ
4.4.6.1 ከግማሽ ቀን በላይ ለሚሹ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የሚከናወን ወጪ
በመደበኛ የበጎ ፈቃድ ስምሪት ወቅት ከግማሽ ቀን በላይ ወይም ምሽት፣
ሌሊትንና ጥዋትን ጭምር ለመስራት የሚያስገድዱ የበጎ ፈቃድ
አገልግሎቶች ሲገጥሙ የሚከናወኑ የምግብና የመኝታ ወጪ
መተኪያዎችን የሚፈፅም ይሆናል፡፡
4.4.6.2 በተራ ቁጥር 4.4.6.1 የተገለፁት ወጪዎችን መተካት የሚፈፀምው
በከተማ አስተዳደሩ የመስተንግዶ አሰራር ወይም ለእንደዚህ አይነት
ወጪዎች በተወሰነው የክፍያ አፈፃፀም አሰራር መሰረት ይሆናል፡፡

4.5 የበጎ ፈቃደኞች መድህን ዋስትና


4.5.1 የበጎ ፈቃደኞች መድህን ዋስትና በበጎ ፈቃድ ስራ ወቅት በበጎ ፈቃደኞችና
በተቋሙ ደንበኞች ላይ ለሚያጋጥም አደጋ እንደአስፈላጊነቱ ቢሮው የሚሰጠው
የህይወትና የጤና መድህን ዋስትና ነው፡፡

[Type the company name]| ከሃገር ውጪ/ ከከተማ ውጪ ለሚደረጉ ጉዞዎች የወጪ መተኪያ 36
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

4.5.2 ቢሮው በጎ ፈቃደኞች በስራ ወቅት በድንገት ለሚደርስባቸው አደጋ/ጉዳት


እንደአስፈላጊነቱ የበጎ ፈቃደኞች የጤና/የህይወት መድህን ዋስትና ሽፋን
ይሰጣል፡፡
4.5.3 በጎ ፈቃደኞች ቢሮውን ወክለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት
በተጠቃሚዎች ላይ በድንገት ለሚያደርሱት ጉዳት/አደጋ እንደአስፈላጊነቱ
የጤና/የህይወት መድህን ዋስትና ይሰጣል፡፡
4.5.4 በጎ ፈቃደኞች በስራ ላይ ባሉበት ወቅት ለሚደርስ ማንኛውም የድንገተኛ አደጋ
በከተማ አስተዳደሩ ስር ፍቃድ አውጥተው የሚንቀሳቀሱ ሁሉም የግልና
የመንግስት የጤና ተቋማት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና
እርዳታ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡
4.5.5 ከበጎ ፈቃድ አገልግሎት የስራ ስምሪት ቦታና ሰዓት ውጪ በበጎ ፈቃደኞች ላይ
ለሚደርሱ ጉዳት/አደጋዎች ቢሮው ምንም አይነት የጤና/የህይወት መድን
ዋስትና ሽፋኖችን አይሰጥም፡፡
4.5.6 በሀገሪቱ እና በከተማው አስተዳደር ውስጥ በሚተገበሩ የኢንሹራንስ ህጎች
ለሚሸፈኑ የጉዳት /አደጋዎች ቢሮው ተጨማሪ የጤና/የህይወት መድን ዋስትና
አይሰጥም፡፡
4.5.7 በተጠቃሚዎች ላይ ለሚደርስ ጉዳት/ አደጋ የሚሰጠው የጤና/የህይወት መድን
ዋስትና የሚሸፈነው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር የሚከናወንለት ተጠሪ
ተቋም ጋር በተደረገው የሁለትዮሽ፣ የሶስትዮሽና ከዛ በላይ ስምምነት ላይ የበጎ
ፈቃደኞች የጤና/የህይወት መድን ዋስትና ሽፋንን አስመልክቶ በተደረሰ
የአፈፃፀም ስምምነት መሰረት ይሆናል፡፡
4.5.8 ቢሮው የሚሰጠው የጤና/የህይወት መድን ዋስትናዎች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት
ስምሪት ግዜና ቦታ ላይ ለደረሰ ድንገተኛ አደጋ/ጉዳት ሆኖ በክስተቱ ወቅት
ወይም በወቅቱ በደረሰ የድንገተኛ አደጋ/ጉዳት ሳቢያ ውሎ አድሮ የሚመጣ
የጤና/የሕይወት እክል መሆኑ በተገቢው አካል ሲረጋገጥ ነው፡፡
4.5.9 በቢሮው የሚሸፈኑ የጤናና/የህይወት መድን ዋስትናዎች ተፈፃሚ ለማድረግ
አደጋው በደረሰበት ቅፅበት የተቋሙ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስተባባሪና
የበጎፈቃደኞች አስተባባሪ በጣምራ ስለ ጉዳቱ ግዜ፣ ሁኔታና መጠን ተቋሙ

[Type the company name]| የበጎ ፈቃደኞች መድህን ዋስትና 37


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ባዘጋጀው ቅፅ ----- አረጋግጠው ማስረጃ ማቅረብና በየደረጃው ላለ የተቋሙ


ሃላፊዎች ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4.5.10 ቢሮው አጣርቶና አረጋግጦ አስፈላጊነታቸውን ያመነባቸውን የጤና መድን
ሽፋን ዋስትናዎች ተፈፃሚ የሚያደርገው በከተማ አስተዳደሩ ባሉ የመንግስት
የጤና ማዕከላት/ ጤና ጣቢያዎች፣ ሆስፒታሎች/ ውስጥ ብቻ ይሆናል፡፡

4.5.1. የበጎ ፈቃደኛ የጤናና የህይወት መድህን ዋስትና ሽፋን ክፍያ


4.5.1.1 አጠቃላይ የድንገተኛና የተመላላሽ ህክምና ለአንድ በጎ ፈቃደኛ በአመት
10‚000 ብር የጤና መድህን ዋስትና ይሸፈናል፡፡
4.5.1.2 በጎ ፈቃደኞች በበጎ ፈቃድ ስራ ላይ ተሰማርተው ሳለ ለሚደርስ የሞት
አደጋ ለአንድ በጎ ፈቃደኛ 40‚000 ብር የሞት መድህን ዋስትና ሽፋን
ያገኛል፡፡

[Type the company name]| 4.5.1. የበጎ ፈቃደኛ የጤናና የህይወት መድህን ዋስትና ሽፋን ክፍያ 38
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ክፍል አምስት
5.1 የእዉቅና፣ ማበረታቻ እና ሽልማት አሰጣጥ ስርዓት
5.1.1 ቢሮው በበጎ ፈቃድ ተግባር ላይ ለተሰማሩ በጎ ፈቃደኞች የዕውቅና፣ ማበረታቻ እና
ሽልማት ይሰጣል፡፡
5.1.2 ቢሮው የበጎ ፈቃደኞች ዕውቅና፣ ማበረታቻ እና ሽልማት የሚሰጠው በጎ ፈቃደኞቹ
በምዝገባ ወቅት የሞሉት ፎርም ላይ ባሰፈሩት የዕውቅና አይነት ይሆናል፡፡
5.1.3 ቢሮው የዕውቅና ፣ማበረታቻ እና ሽልማት ስርዓት ሲፈፅም የሚከተላቸው
የዕውቅና አሰጣጥ ደረጃዎች በጀማሪ፣ በመካከለኛ እና ከፍተኛ ተብለው ይለያሉ፡፡
5.1.4 ቢሮው የዕውቅና ፣ማበረታቻ እና ሽልማት ስረዓት ሲፈፅም የሚከተላቸው
የዕውቅናና ሽልማት አይነቶች ዕለታዊ፣ መካከለኛና፣ ዋና ተብለው ይለያሉ፡፡
5.1.5 ቢሮው ለሁሉም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለተሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ዕውቅና ይሰጣል
5.1.6 ቢሮው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፈው የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ላበረከቱ በጎ
ፈቃደኞች ማበረታቻ ይሰጣል፡፡
5.1.7 ቢሮው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፈው የጎላ/የተለየ አስተዋፅኦ ላበረከቱ በጎ
ፈቃደኞች ሽልማት ይሰጣል፡፡
5.1.8 ቢሮው ለበጎ ፈቃደኞች የሚሰጠው ማበረታቻና ሽልማት ደረጃዎች የሚወሰነው በጎ
ፈቃደኞቹ በአገልግሎት ወቅት ባስመዘገቡት የስራ ሰዓት፣ የሃብት፣ የጉልበት፣
የሙያ/ዕውቀት መጠን፣ የአገልግሎት ቆይታ ዘመን እና በስራ ላይ በነበራቸው
ስነ-ምግባር/ዲስፕሊን መሰረት ይሆናል፡፡
5.1.9 ቢሮው ለበጎ ፈቃደኞች የሚሰጠው ዕውቅና ማበረታቻ እና ሽልማት ይኖራቸዋል
ተብሎ የተለዩ ደረጃዎች እና አይነቶች እንደ በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ባህሪ አንደኛው
ከሌላኛው የሚዋረሱት ደረጃና አይነቶች ይኖራል፡፡
5.1.10 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዕውቅና የሚሰጠው በየዕለቱ/በየወቅቱ ይሆናል ፤
5.1.11 ማበረታቻ የሚሰጠው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ወቅት እና ፕሮግራም
ማጠቃለያ ላይ ነው፡፡
5.1.12 ሽልማት የሚሰጠው በዓመት አንድ ግዜ በቢሮ ደረጃ በሚዘጋጅ የዕውቅና
ማበረታቻ እና ሽልማት መርሃ ግብር ነው፡፡
[Type the company name]| ክፍል አምስት 39
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

5.1.13 ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ለበጎ ፈቃደኞች መስጠት የሚችሉት የእውቅናና


ማበረታቻ ብቻ ነው፡፡
5.1.14 በደብዳቤ እና በምስክር ወረቀት መልክ ለበጎ ፈቃደኞች የሚሰጡ የእውቅና
ማበረታቻ የሚዘጋጁ በአንድ ማእከል በቢሮው ሲሆን በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ
ላሉ በጎ ፈቃደኞች የሚሰጡ ደብዳቤዎና የምስክር ወረቀቶች ቢሮው በሚሰጠው
የደብዳቤና የምስክር ወረቀት ቁጥር ብቻ ይሆናል፡፡
5.1.15 ከደብዳቤና የምስክር ወረቀት በስተቀር በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ የሚሰጡ የበጎ
ፈቃደኞች ዕውቅናና ማበረታቻ አይነቶች ነባራዊ ሁኔታቸውን ባገናዘበ መልኩ
ከቢሮው ጋር በመናበብ የሚሰጡ ይሆናሉ፡፡
5.1.16 ለአጭርና የመካከለኛ ግዜ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብሮች በደብዳቤ መልክ
ለበጎ ፈቃደኞች የሚሰጠው ዕውቅና ማበረታቻ እና ሽልማት በፕሮግራሙ
ማጠቃለያ ላይ የሚሰጥ ሲሆን በረዥም ግዜ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሚሳተፉ በጎ
ፈቃደኞች በዕውቅና ማበረታቻ እና ሽልማት መልክ የሚሰጥ ደብዳቤ መፃፍ
የሚችለው በጎ ፈቃደኛው በፕሮግራሙ መሳተፍ ከጀመረ ጀምሮ 3 ወር ሲሞላው
ነው፡፡
5.1.17 ቢሮው በአመት አንድ ግዜ በሚያዘጋጀው ሽልማት ፕሮግራም ተሸላሚ የሚሆኑ
አካላት በቢሮው በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ተሳትፈው የጎላ አስተዋፅኦ
ላበረቱ በጎ ፈቃደኞች እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ወይም በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ
በግላቸው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፍ በመሰማራት ሃገራዊ ፋይዳ ያለው
አስተዋፅኦ ላበረከቱ ታዋቂ ግለሰቦች የሚሰጠው የክብር ሽልማት ይሆናል፡፡
5.1.18 በዓመት አንድ ግዜ ለሚዘጋጀው የሽልማት ፕሮግራም እጩ ተሸላሚዎች
ምልመላና መረጣ የሚከናወነው ቢሮው በሚያቋቁመው የሽልማት አመቻች ኮሚቴ
እና ለዚሁ ሲባል በሚዘጋጅ ማስፈፀሚያ አሰራር ስርዓት ይሆናል፡፡
5.1.19 ቢሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለፈፀሙ፣ለተሳተፉ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ
ላደረጉ እና ልዩ ልዩ አስተዋፅኦ ላበረከቱ በጎ ፈቃደኞች በከተማ አስተዳደሩ
የተፈፃሚነት ወሰን እና መዋቅራዊ አደረጃጀትን ታሳቢ ያደረጉ ከ 80 በላይ የተለዩ
የእውቅና የማትጊያና ማበረታቻ ሽልማቶችን ቅድሚያ በመስጠት እየለዩ መስጠትን
ታሳቢ ያደርጋል፡፡

[Type the company name]| የእዉቅና፣ ማበረታቻ እና ሽልማት አሰጣጥ ስርዓት 40


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

5.1.20 በዚህ መመሪያ መሰረት በቢሮው የሚሰጡ እለታዊ ፣ መካከለኛና ዋና የዕዉቅናና


የሽልማት አይነቶች እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡

5.1.2 ዕለታዊ እውቅናና ማበረታቻ አይነቶች


ሀ. የቃል ምስጋና "እናመሰግናለን" ማለት
ለ. እጅግ መልካም ነገር እንደሰሩ ለበጎ ፈቃደኞች መናገር
ሐ. በጎ ፈቃደኞች ሻይ/ቡና አብረዉን እንዲጠጡ መጋበዝ
መ. ሃሳባቸዉ/አመለካከታቸዉን እንዲያጋሩ መጠየቅ
ሠ. በጎ ፈቃደኞች ጠዋት ሲመጡ ሠላምታ ማቅረብ
ረ. በግል ምርጫቸዉ /ፍላጎታቸዉ /ዙሪያ ፍላጎታችንን ማሳየት
ሰ. ስናያቸዉ ፈገግ ማለት
ሸ. በሃላፊዎች አካባቢ ሲመጡ ስለመልካም ስራቸዉ ማዉራት
ቀ. አጭር የምስጋና ማስታዎሻ መለጠፍ
በ. ከበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር በኋላ በጋራ አብሮ መዝናናት
ቨ. በግል ስብዕናቸዉ ላይ ያላቸዉን ጠንካራ ጎን በማመልከት አዎንታዊ ነገር መናገር
ተ. ለበጎ ፈቃደኞች እነርሱ እስከመጡበት ጊዜ ድረስ ተቋሙ ምን ሁኔታ ላይ እንደነበር
መናገር

ቸ. ለአጋር አካላት የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ በጎ ፈቃደኞችን መጋበዝ

ኀ. የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡበት አካባቢዎችን በስም ወይም በልደት ቀናቸዉ


ማስዋብ
ነ. ሃላፊዎች የምስጋና ደብዳቤ እንዲጽፉ ማድረግ
ኘ. አንዳንድ በጣም ልዩ በሆነ ስብሰባዎች ላይ በጎ ፈቃደኛዉ ተቋሙን ወክሎ እንዲገኝ
ማድረግ
አ. ልዩ የተባለ የበጎ ፈቃደኛ ተግባርን መዘከር ማክበር
ከ. ምስላቸዉን በልዩ ሁኔታ በአስተዳደሩ ልዩ ልዩ የማስታወቂያ ስፍራዎች መለጠፍ
፣ዜና ማቅረብ እና ፕሮግራም መስራት
ኸ. ከቢሮዉ ሃላፊዎችና አመራሮች ጋር መደበኛ ያልሆነ የጭውውት ጊዜ ማመቻቸት

[Type the company name]| 5.1.2 ዕለታዊ እውቅናና ማበረታቻ አይነቶች 41


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

5.1.3 መካከለኛ የእዉቅና የሽልማት አሰጣጥ


ሀ. የምሳ ግብዣ ማድረግ
ለ. የበጎ ፈቃድ ስብሰባዎች ላይ ምግብ፣ሪፍሬሽመንት ማቅረብ
ሐ. በጎ ፈቃደኞች ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባበረከቱት ምርት/ፈጠራ ስራ ላይ ስማቸውን
እንዲያኖሩ መፍቀድ
መ. በሃላፊዎች የተጻፈ "ለሚመለከተዉ ሁሉ" የሚል የድጋፍ/የዕውቅና ደብዳቤ
መስጠት
ሠ. በጎ ፈቃደኞችን በልዩ ልዩ የኮሚቴ ስራዎች ዉስጥ ማስገባት/ማሳተፍ
ረ. የሳይክል፣የሞተር ሳይክል እና የመኪና ማቆሚያ ትኬት ፓኬጅ ገዝቶ በነጻ መስጠት
ሰ. የወሩ ምርጥ በጎ ፈቃደኞችን ስምና ምስል ግልጽ በሆነ ቦታ ላይ መለጠፍ
ሸ. የበጎ ፈቃድ ስራቸዉን በልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ስራዎች ማዉራት/መዘከር እና
እያሳዩት ያለዉን ጥረት በተንቀሳቃሽ ምስል ለእይታ ማቅረብ
ተ. ለበላይ ሃላፊዎች በሚደረጉ ሪፖርቶች ዉስጥ ዋና ዋና አሰተዋጽኦ ያደረጉ ሰዎችን
ስም ጠቅሶ መላክ
ቸ. በጎ ፈቃደኞች የስራ ዉጤታቸዉን ለበላይ ሃላፊዎች እንዲያቀርቡ መጋበዝ እና
ዕድል ማመቻቸት
ኀ. ከቢሮዉ ዉጪ ልዩ ልዩ ሴሚናሮች ጉባዔዎች ፣ፓናሎች እና ሙያዊ ስብሰባዎች
ላይ እንዲሳተፉ ማመቻቸት እና ፈቃድ መስጠት
ነ. ስለሰሩት ስራ በጋዜጣና በመጽሄት ርዕሰ አንቀፅ መፃፍ

5.1.4 ዋና የእውቅናና ማበረታቻ ሽልማት


ሀ. ልዩ ልዩ ብርጭቆ ፣በቢሮው መለያ አልባሳት ቀለም የተዘጋጀ ካኔቴራ ፣ቀበቶ፣ኮፊያ
፣ፒን፣ የቁልፍ ማንጠልጠያ፣ የኪስ ቦርሳ ወ.ዘ.ተ በማዘጋጀት ለበጎ ፈቃደኞች
በመስጠት ማወደስ (ማክበር)
ለ. በጎ ፈቃደኞች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራቸዉ ስላሳኩት ስራ ርዕሰ አንቀጽ
እንዲጽፉ ማበረታታት
ሐ. የትምህርት ቤት ክፍያ ድጋፍ መስጠት

[Type the company name]| መካከለኛ የእዉቅና የሽልማት አሰጣጥ 42


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

መ. የሚታወስ ዕቃ ገዝቶ ማበርከት

ሠ. በጋዜጦችና በመጽሄቶች የፊት ገጽ የበጎ ፈቃደኛዉን ፎቶ ልዩ ተግባርን አስመልክቶ

መለጠፍ/ማሳተም/ማሰራጨት

ረ. ለበጎ ፈቃደኛዉ ተጨማሪ ሃላፊነትና መስጠት እና አዲስ የስራ ማዕረግ መስጠት


ሰ. ለበጎ ፈቃደኞች ምስጋና ማቅረብያ የጋዜጣ አምድ መከራየት
ሸ. ዋና የተገኙ ዉጤቶችን የሚያወድሱ የበጎ ፈቃደኞችን ምስል የያዙ ባነሮች መስቀል
ቀ. በስልጠና ስፍራ እና በሌሎች ስፍራ የበጎ ፈቃደኞችን ስም ዝርዝር
መጥቀስ፣መለጠፍ፣መጥራትና ማስጠራት
በ. በከተማ አስተዳደሩ ዓመታዊ የልማት ዕቅድ ዝግጅትና የአፈፃፀም ግምገማ መድረኮች
በጎ ፈቃደኞችን ማሳተፍ
ሸ. በስራ ውድድር ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልምድ እንደ አቻ የስራ ልምድ
ወይም በተጨማሪ ነጥብነት መያዝ
ተ. ወቅታዊ የምርት ማሰባሰቢያ ስራ ባላቸው የማምረቻ ፋብሪካዎች፣ እርሻ ዎች
ወ.ዘ.ተ ግዜያዊ የስራ ዕድል
ቸ. ታዋቂ በጎ ፈቃደኞች የለበሱትን የስራ መለያ ለሌሎች በጎ ፈቃደኞች መሸለም

5.1.5 ልዩ ማበረታቻና እና ሽልማት


ሀ. ከመደበኛ ብድር ባነሰ ወለድ የብድር አገልግሎት በመስጠት ማበረታታት
ለ. የብድር መመለሻ የጊዜ ወቅትን በማራዘም ማበረታታት
ሐ. የኢ - መደበኛ ትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ
መ. ከኮስት ሼሪንግ እዳ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት መክፈል የሚያስችል አሰራር ማበጀት
ሠ. በልዩ ልዩ የባህልና ቱሪዝም ዝግጅቶችና መርሃ ግብሮች መግቢያ ትኬት፣ ነጻ
የፊልም ትኬት፣ የትያትር ትኬት፣የኮንሰርት ትኬት፣የቅርስ ሙዚየም እና ታሪካዊ ቦታ
ጉብኝት በሃገር ዉስጥና በዉጪ ለበጎ ፈቃደኞች በመስጠት ማትጋት
ረ. በጎ ፈቃደኛዉ ለ1 ቤተሰብ የተመደበለትን የወርሃዊ ፍጆታ መጠን ከሸማቾች ማህበር
በ 2 ቤተሰብ መጠን ለ 3 ወር መግዛት እንዲችሉ ዕድል በመስጠት ማበረታታት፡፡
ሰ. ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማበረታቻነት የ 3 ወር የውሃ ክፍያን ማንሳት

[Type the company name]| ልዩ ማበረታቻና እና ሽልማት 43


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ሸ. 1 ዙር ነጻ የመፀዳጃ ቤትና የፍሳሽ መምጠጥ አገልግሎት መስጠት


ቀ. ለበጎ ፈቃደኞች ልዩልዩ የዉሃ ግድቦችና ዉሃ ማጣሪያ ማዕከላትን የማስጎብኘት
ማበረታቻ መስጠት
ሰ. የ 3 ወር የመብራት ፍጆታ አገልግሎት ተጠቃሚ አድርጎ ማበረታታት
ሸ. ልዩ ልዩ የሃይል ማመንጫዎችና የኢንዱስትሪ መንደሮችን የመጎብኘት ዕድል
በማመቻቸት ማበረታታት
ቀ. ነጻ የቪ. ዐይ. ፒ ትኬት ለዓለም ዓቀፍ አህጉራዊ እና ሃገር አቀፍ እና የተዋረድ ልዩ
ስፖርታዊ ዉድድሮች በሃገር ዉስጥ እና በዉጭ እንደአስፈላጊቱ ሙሉ ወጪ ሸፍኖ
በመስጠት ማበረታታት
በ. ልዩ ተግባር ለፈጸሙ በጎ ፈቃደኞች ነጻ የህክምና ምርመራ አገልግሎት፣ ሪፈራል
አልጋ በሃገር ዉስጥና በዉጪ መስጠት
ቨ. ልዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት ረዥም ርቀት የተጓዘ ተቋምና ግለሰብ ወይም
ስብስብ ላሰበዉ ግንባታ እና ማስፋፊያ ዕቅድ አጋዥ የሆነ የነፃ ዲዛይንና የንድፍ ስራ፣
የነፃ እደሳ ስራ፣ የነጻ የምክር አገልግሎት ስራ፣ የነፃ የግንባታ አቅርቦት ስራ መሰልና
ወዘተ ማበረታቻዎችን በሽልማት መልክ መለገስ
ተ. ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማበረታቻነት ታሳቢ የሆነ፣ ነጻ የመገናኛ ብዙሓን የዜናና
የፕሮግራም ሽፋን፣ ነጻ የአየር ሰዓትና አምድ፣ ነጻ የዉይይት መድረክ፣ ነጻ የስቱዲዮ
ጉብኝት፣ ልዩ ልዩ የተመረጡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብሮችን ሆስት አድርጎ
በማቅረብ በጎ ፈቃደኞች ማበረታታ
ቸ. በከተማዉ ባሉ የኩነት አገልግሎቶች የነጻ የኩነት አገልግሎት /መታወቂያ፣ ያገባ
፣ያላገባ ፣የጋብቻ፣ ፍቺ፣ የልደት እና ሞት/ በጎ ፈቃደኛዉ ለአንድ ግዜ ብቻ ተጠቃሚ
ማድረግ
ኀ. በከተማችን በሚገኙ የአጭርና የረዥም የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ፣ የ 1
ሳምንት፣ የ15 ቀን የ 1 ወር ፣ የ 1 ዓመት እና የዕድሜ ልክ ነፃ የትራንስፖርት
አገልግሎት በመስጠት ማበረታታት
ነ. በከተማችን በሚገኙ ሆቴሎች ሙሉ መስተንግዶ / ነጻ ምሳ፣ አልጋ፣ ምግብ
መጠጥ፣ አዳራሽ ከቡናና ሻይ ጋር፣ ኮክቴል፣ ዉሃ፣ ስቲምና ማሳጅ ወ.ዘ.ተ

[Type the company name]| ልዩ ማበረታቻና እና ሽልማት 44


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ኘ. የሙያና ቴክኒክ እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ የክህሎት ስልጠናዎችን የሚማርበትን


ዕድል መሥጠት
አ. የበጎ ፈቃደኛዉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መፍትሄ የንድፈ ሃሳብ በነጻ በቴክኒክና
ሙያ ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች ነጻ ተግባራዊ ሙከራ እንዲያገኝ ማድረግ
ከ. ከሚመለከተዉ በየደረጃዉ ካለ ተቋምና አመራር እጅ ለበጎ ፈቃደኛዉ
የቤት፣የመኪና፣ ሳይክል እና የሞተር ቁልፍ በሽልማት መልክ መስጠት
ኸ. እጅግ ልዩ በጎ ፈቃድ ለፈጸሙ ግለሰቦች ስብስብ እና ተቋማት የመሬት ይዞታ ፣
የመንገድ ስያሜ ፣የአደባባይ ስያሜ ፣የወጣት ማዕከላት ስያሜና የልማት ተቋም ስያሜ
በግላቸዉና በተቋሙ እንዲያገኙና እንዲሰየምላቸዉ ማድረግና ማበረታታት
ወ. ሙሉ የብሄራዊ እና የከተማ ልዩ ልዩ ፌዴሬሽኖች ተጫዋቾቻቸዉን
የሚያስታጥቁትን ትጥቅ በሽልማት መልኩ በመስጠት ማትጋት
ዐ. ለተለየ ተግባርና ለበዛ አደጋ ተጋላጭነት ለነበረዉ የበጎ ፈቃድ ተግባር ለፈጸሙ ልዩ
ጥበቃ እና ልዩ የፖሊስ ማዕረግ በመስጠት ማሸለቅ

[Type the company name]| ልዩ ማበረታቻና እና ሽልማት 45


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

ክፍል ስድስት
6. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
6.1 ትስስራዊ የተግባር አፈጻጸም አግባቦት
6.1.1 ለጋሽ በጎ ፈቃደኛ ፣ተቋም እና አስተባባሪ የመመሪያዉ
አተገባበር
6.1.1.1 የተቋሙን አጠቃላይ ህልዉና በማያናጋ ሁኔታ
በሁለትዮሽ፣ሶስትዮሽ እና ከዚያም በላይ በሆነ ትስስራዊ
የአጋርነት ዉል ተፈራርሞ ወደ ተግባር ሲገባ የለጋሽ አካሄድ
ልግስናዉን የሚቀበለዉ ተቋም ዉስጣዊ አሰራርና የአሰራር
አፈጻጸም መመሪያን አክብሮ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
6.1.1.2 ለጋሽ የበጎ ፈቃደኛ ዓለም አቀፍና ሃገር በቀል ተቋም የበጎ
ፈቋድ ልግስና ተቀባይ ተቋም፣ማህበር ኔትዎርክ፣ፎረም፣ቡድን
ወይም ግለሰብን የአእምሮ ንብረት፣የህጋዊ ተደራሽነት
ወሰን፣የተቋም መመሪያ ፣ደንብና ስርዓት ብሎም የተቋሙ
የዉስጥ አሰራር፣የስነ ምግባር አፈጻጸም መመሪያና አሰራር
አክብሮ መንቀሳቀስ ይጠበቅበታል፡፡
6.1.1.3 የአዲስ አበባ ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ
በየደረጀዉ ለአንድ ዓላማ በሚያሰልፋቸዉና ፣በትብብር
እንዲሁም በጋራ አብሮ ለመስራት እሺታዉን ያሳያቸዉ
ወይም በአስተባባሪነት አብሮ ለመስራት ዉል የተዋዋላቸዉን
የበጎ ፈቃድ ቡድኖች ፣ተቋማት እና አጋሮች ላይ ህጋዊ
አሰራራቸዉንና የተቋቋሙበትን ዓላማ በጠበቀና ባከበረ ብሎም
በማይቀረን አሰራር በትብብር መንፈስና በአሳላጭነት
(አስተባባሪነት) ብቻ ሊሰራ የገደዳል፡፡
6.1.1.4 እንደየአስፈላጊነቱ በዚህ መመሪያ ክፍል ሶስት በክትትልና
ድጋፍ የተቀረፀና የፀደቁ ቅፃቅፆች ለአሰራርና ለአፈፃፀም

[Type the company name]| ክፍል ስድስት 46


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰራር 2013
መመሪያ ቁጥር 1/2013

እንዲያመቹ በየጊዜዉ በቢሮ ደረጃ ሊለወጡ እና ሊቀየሩ


ብሎም ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
6.1.1.5 በዚህ መመሪያ መርሃ ግብር (የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር)
እንጂ በየደረጃዉ ተቋም አይመዘንም፡፡ይልቁንም ተቋሙ
በመደበኛ ተቋማዊ የምዘና ስርዓት ይፈፀማል፡፡
6.1.1.6 ለዚህ መመሪያ ተፈጻሚነት አጋዥ የሆኑ እና የሚረዱ ልዩ
ልዩልዩ አስፈላጊ የማስፈፀሚያ መመሪያ ይዘጋጅለታል፡፡
6.1.1.7 ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረኑ ማናቸውም ልማዳዊ
አስራሮችና ተግባሮች በዚህ መመሪያ ውስጥ በተሸፈኑ ጉዳዮች
ላይ ተፈፃሚነት አይኖራቸውም፡፡
6.1.1.8 በየደረጃው የሚገኝ ፈፃሚ አካል ማለትም ኃላፊ/አስተባባሪ/
ወይም ባለሙያ በዚህ መመሪያ ክፍል አምስት የተዘረዘሩትን
የዕውቅና ማበረታቻና ሽልማት ለግሉ/ለዘመድ/ ያለአግባብ
አውጥቶ ቢገኝ በቀጥታ በፍርድ ሂደት ይዳኛል፡፡
6.1.1.9 በዚህ መመሪያ የተፈፃሚነት ወሰን ውጪ በሚኖሩ ዓለም
አቀፍ ተቋማት፣ የፌደራል መንግስት፣ ክልሎችና የከተማ
አስተዳደሮች ብሎም የከተማዋ እህት ከተሞች ጨምሮ
አስተዳደሩ ተጋብዞ የሚፈፅማቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና
ተግባራት በሁለትዮሽ፣ በሶስትዮሽ እና ከዚያ በላይ በሚደረግ
ከፍተኛ ድርድርና ውይይት የዚህን መመሪያ ህጋዊ
ህልውናነት በማይነሳ መልኩ ጠብቆ መፈፀምና ማስፈፀም
አለበት፡፡
6.1.1.10 ይህ መመሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መደበኛ ምክር
ቤት …../……/……ዓ.ም ፀድቋል፡፡
6.1.1.11 መመሪያው በተግባር እየተፈተሸ እንደአስፈላጊነቱ በየጊዜው
የሚሻሻል ይሆናል፡፡

[Type the company name]| 6.1.1 ለጋሽ በጎ ፈቃደኛ ፣ተቋም እና አስተባባሪ የመመሪያዉ አተገባበር 47

You might also like