You are on page 1of 53

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የፈተና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1/2015

ሚያዚያ 30/2015

አዲስ አበባ

0
መግቢያ
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በማቋቋሚያ ደንቡ 260/2004 በተሰጠው ስልጣን
እና በሀገሪቱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ መሠረት ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን አዘጋጅቶ የሚሰጥና
በየትምህርት እርከኑ ማጠቃለያ ላይ የትምህርት ቅበላ ጥናቶችንም የሚያደርግ ተቋም ነው፡፡
በዚህም የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን በማዘጋጀትና በማስተዳደር ሂደት የፈተና ደህንነትን
ማስጠበቂያ የአሰራር ሥርአቶችን በመከተል በከፍተኛ ጥንቃቄና በተደራጀ አሰራር ከማዕከል
እስከ ትምህርት ቤት (የፈተና ጣቢያ) ድረስ ሁሉንም የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ፈተናዎችን
ሲያዘጋጅና ሲያስተዳደር ቆይቷል፡፡

ሀገር አቀፍ ፈተናን ሚስጥራዊነቱና ደህንነቱ ተጠብቆ እንዲሰጥ በማድረግ ሂደት ውስብስብ
የፈተና ደህንነት ስጋቶች በየወቅቱ መከሰት፣ የተፈታኞች ቁጥር በየአመቱ በከፍተኛ ሁኔታ
እየጨመረ መምጣት እና የፈተና አስተዳደር ሂደቱ በቴክኖሎጅ አለመደገፍ ስራውን ከፍተኛ
ውጥረት የተሞላበት እንዲሆን አድርጎታል። በተለመደው የፈተና አሰጣጥ ሂደት ፈተናን በት/ቤት
ደረጃ ለመስጠት የማስችሉ አስገዳጅ ሁኔታዎች በመፈጠራቸው አገልግሎቱም ችግሩን
ለመፍታት የሚያስችል የአደረጃጀት ለውጥ በማድረጉ እና የፈተና እተዳደር ሂደቱን ከት/ቤት
ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሰባሰብ ፈተናው ሚስጥራዊነቱና ደህንነቱ ተጠብቆ እንዲሰጥ
በማስፈለጉ በ2012 ዓ.ም ተዘጋጅቶ የነበረውን የፈተና አስተዳደር መመሪያ እንደገና አሻሽሎ
ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡

በመሆኑም በፈተና አስተዳደር ስራ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ የተፈታኞች ምዝገባ አስፈጻሚዎችን፣


የፈተና አስፈጻሚዎችን፣ የፈተና አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት ለመወሰን፤
የፈተና ደንብ ጥሰትን ለመከላከል የሚያስችሉ የአሰራር ስርአቶችን፣ የፈተና ማዕከላትን
አደረጃጀትና አሰራር ለመወሰን እና በየደረጃው የሚካሂደው የፈተና አስተዳደር አስፈጻሚዎች
ምልመላ፣መረጣና ምድባ ግልጽ በሆነ መስፈርትና የአሰራር ስርአት መፈጸም እንዲቻል ዘንድ
ይህ የፈተና አስተዳደር መመሪያ በአገልግሎቱ ተዘጋጅቷል፡፡

1
ክፍል አንድ
ጠቅላላ ድንጋጌዎች
1. አውጪው ባለስልጣን
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 260/2004
አንቀጽ 9 (2) በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

2. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ “የፈተና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1/2015” ተብሎ ይጠቀሳል፡፡

3. መሰረታዊ የቃላት ፍቺ እና የፆታ አገላለጽ


የቃሉ ወይም የሀረጉ ፍቺ ሌላ ራሱን የቻለ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ሰነድ
ለሚገለጹ ይዘቶች እና በፈተና አሰጣጥ ሂደት በሚሳተፉ ፈተና አስፈፃሚዎች መካከል ለሚኖር
የጋራ መግባባት ከታች የተቀመጡ ቃላት ወይም ሀረጋት የሚከተለው ትርጓሜ ይኖራቸዋል፡-
3.1 ”አገልግሎት” ማለት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተቋም ነው፡፡
3.2 “ልዩ ወረዳ” ማለት ከዞን ትምህርት መምሪያ አደረጃጀት ጋር አቻ የሆነ አደረጃጀት ያለው ሆኖ
በልዩ ወረዳው የትምህርት ሥራን በበላይነት የሚመራ የልዩ ወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ነው።
3.3 “ፈተና አስተዳደር” ማለት ከተፈታኞች ምዝገባ እስከ ፈተና አስፈፃሚዎች ምልመላና ስምሪት፣
የፈተና አሰጣጥ፣ እርማት፣ ውጤት ማጠናቀርና መግለጽ፣ የምስክር ወረቀት መስጠትን ያካተተ
የአሰራር ሥርዓት ነው፡፡
3.4 “የትምህርት ማስረጃዎች (Educational Documents) አጣሪ ቡድን” ማለት በትምህርት ጽ/ቤት እና
በትምህርት ቤት ደረጃ ለፈተና የሚቀመጡ ተመዝጋቢዎችን የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት
ለማጣራት የተቋቋመ ቡድን ነው፡፡
3.5 “የፈተና ደንብ መተላለፍ” ማለት በቅድመ ፈተና፣ በፈተና አሰጣጥ እና በድህረ ፈተና አስተዳደር
ስራዎች ላይ በቡድንም ሆነ በግል የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ተግባራትን የሚያካትት ነው።
3.6 “ሀገር አቀፍ ፈተና” ማለት በኢትዮጵያ ደረጃ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጥ የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ
ትምህርት ማጠቃለያ (12ኛ ክፍል) ሀገራዊ ፈተና ነው።
3.7 “የፈተና ጉድኝት ማዕከል (Exam Cluster Center)” ማለት ከአንድ በላይ የሆኑ የፈተና ጣቢያዎችን
ፈተና በሚሰጥበት አካባቢ ወይም ዩኒቨርስቲ ውስጥ የተዋቀረ የፈተና አሰጣጥ አደረጃጀት ነው፡፡
3.8 “መፈተኛ ክፍል” መፈተኛ ክፍል ማለት በአንድ የፈተና ጣቢያ እስከ 36 (ሰላሳ ስድስት)
ተፈታኞችን የሚይዝ ለፈተና አሰጣጥ ምቹ የሆነ አንድ መፈተኛ ክፍል ነው፣

2
3.9 “የፈተና አስፈጻሚዎች” ማለት በፈተና አሰጣጥ ሂደት በጉድኝት ማዕከል ኃላፊነት፣ በጉድኝት ማዕከል
አስተባባሪነት፣ በጣቢያ ኃላፊነት፣ በሱፐርቫይዘርነት፣ በፈታኝነት፣ በአንባቢነት፣ በመልስ ወረቀት
ቆጣሪነት፣ በፈተና ኮረጆ ተረካቢና አስረካቢነት ወዘተ በመሰል ሥራዎች የሚሳተፉ ሰዎች ነው።
3.10 “የፈተና ጉድኝት ማዕከል ኃላፊ” ማለት በፈተና ማዕከሉ ስር ያሉትን የፈተና ጣቢያዎች የፈተና
አሰጣጥ ሂደት በበላይነት የሚመራ የፈተና አስፈጻሚ ነው፡፡
3.11 “የፈተና ጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ” ማለት በማዕከሉ ስር ያሉትን የተለያዩ የፈተና ጣቢያዎችን
የሚያስተባብር ተጠሪነቱ ለፈተና ጉድኝት ኃላፊ የሆነ የፈተና አስፈጻሚ ነው፡፡
3.12 “የፈተና ጣቢያ ኃላፊ” ማለት በአንድ የፈተና ጣቢያ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ የመፈተኛ
ክፍሎችን እና ፈተና አስፈፃሚዎችን የሚመራ፣ ተጠሪነቱ ለፈተና ጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ የሆነ
የፈተና አስፈጻሚ ነው።
3.13 “ሱፐርቫይዘር” ማለት በአንድ የፈተና ጣቢያ የአራት መፈተኛ ክፍሎችን የፈተና አሰጣጥ ሂደት
የሚመራ እና ተጠሪነቱ ለፈተና ጣቢያ ኃላፊ የሆነ የፈተና አስፈፃሚ ማለትነው።
3.14 “ፈታኝ” ፈታኝ ማለት በአንድ የፈተና ጣቢያ በአንድ መፈተኛ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ብዛታቸው
እስከ 36 (ሰላሳ ስድስት) ድረስ የሆነ እና ዓይነ ስውር ተፈታኝ ያልሆኑ ተፈታኞችን የፈተና አሰጣጥ
ሂደት የሚመራና የሚቆጣጠር ተጠሪነቱ ለሱፐርቫይዘር የሆነ የፈተና አስፈጻሚ ማለት ነው።
3.15 “አንባቢ / ረዳት ጸሐፊ” ማለት በአንድ የፈተና ጣቢያ ለሚገኝ የዓይነ ስውር ተፈታኝ የፈተና
ጥያቄዎችን የማንበብ እና የመልስ ወረቀት መረጃዎችን የመፃፍ / የእጅ እንቅስቃሴ ችግር ላለበት
ተፈታኝ የመልስ ወረቀት መረጃዎችን የመፃፍ አገልግሎት የሚሰጥና ተጠሪነቱ ለሱፐርቫይዘር የሆነ
የፈተና አስፈፃሚ ነው፣
3.16 “የመልስ ወረቀት ቆጣሪ” ማለት በአንድ የፈተና ጣቢያ የመልስ ወረቀት የመቁጠር እና የመልስ
ወረቀቶቹን የማደራጀት አገልግሎት የሚሰጥ የፈተና አስፈፃሚ ነው፣
3.17 ክዘና(storing)፡- ማለት የፈተና ግብአቶችን ሚስጥራዊነታቸውና ደህንነታቸው(confidentiality
and security) ተጠብቆ የሚቀመጡበት ቦታ/ክፍል ነወ፡፡
3.18 “ሴሽን (Session)” ማለት አንድ የትምህርት ዓይነት ፈተና የሚሰጥበት የጊዜ ቆይታ ነው፡፡
3.19 “የሴሽን ክፍያ” አንድ የፈተና አስፈጻሚ በፈተና አስፈፃሚነት ስራ ሲሳተፍ የሚከፈል የሙያ
አገልግሎት ክፍያ ነው።
3.20 አነጋገሩ ግልጽ በሆነ መልኩ ካላመለከተ በስተቀር በወንድ ጾታ የተቀመጠ አገላለጽ ሁሉ ለሴት
ጾታም ያገለግላል፡፡

4. የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠቃለያ ሰርተፍኬት (12ኛ ክፍል)
ፈተና እንዲሁም ሌሎች ሀገር አቀፍ ፈተና አስተዳደር በተመለከተ በምዝገባ አፈፃፀም፣ በፈተና

3
አሰጣጥ፣ በግብዓትና መሰረተ ልማት አጠቃቀም፣ ውጤትን በማጠናቀር እና በመግለጽ ሂደቶች
ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

5. ዓላማ
የተፈታኞች ምዝገባን፣ የፈተና ግብዓትና መሰረተ ልማት አቅርቦት፣ ድልድል፣ ስርጭትና ከዘና፤
የፈተና አሰጣጥ፣እርማት እና ውጤት መግለጽ ሂድት ውስጥ የፈጻሚዎችና የባለድርሻ አካላት
ሚና በግልጽ በመለየት ጥራትና ደህንነቱ የተጠበቀ የፈተና አስተዳደር ሥርዓት እንዲኖር
ማድረግ ነው፡፡

ክፍል ሁለት
የተፈታኞች ምዝገባ አፈጻጸም
6. ለምዝገባ ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶች
6.1 መደበኛ ተማሪዎች 8ኛ ክፍል ተፈትነው ያለፉ፤ ከ9ኛ አስከ 11ኛ ክፍል ተከታታይ

አመት “ትራንስክርቢት” ማቅረብ የሚችሉ እና 12ኛ ክፍል በመደበኛው ፕሮግራም


በመማር ላይ ያሉ መሆን አለባችው፤
6.2 ተመዝጋቢዎቹ መንግስታዊ ያልሆኑ መደበኛ ትምህርት ቤት ተማሪ ከሆኑ ዕውቅና

በተሰጣቸው ትምህርት ቤቶች 8ኛ ክፍል ተፈትነው ያለፉ፤ ከ9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል
ተከታታይ አመት “ትራንስክርቢት” ማቅረብ የሚችሉ እና በዘመኑ የ12ኛ ክፍልን
በመማር ላይ ያሉ መሆን አለበቸው፤
6.3 ከላይ 6.1 እስከ 6.2 የተጠቀሱት ዓመታት ተከታታይ ካልሆኑ ያቋረጠበትን ምክንያት

ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፤


6.4 በማታ ክፍለ ጊዜ ትምህርታቸውን ተከታትለው ለኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ

ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚመዘገቡ የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያለፉ እና
ከ9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ከአራት ዓመት ተኩል በፊት ያጠናቀቁ የ12ኛ ክፍልን
የመጀመሪያ “ተርም” አጠናቀው የሁለተኛውንና የሦስተኛውን ተርም በማታው
የትምህርት ክፍል በመማር ላይ ያሉ መሆን አለባቸው፤
6.5 በርቀት ወይም በበይነ መረብ መስመር(online) መርሃ ግብር ትምህርታቸውን
ተከታትለው የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና
የሚመዘገቡ ከላይ ከአንቀጽ 6.1 እስከ 6.3 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ትምህርት

4
ሚኒስቴር ለርቀትና ለበይነ መረብ ትምህርት ፕሮግራም ያስቀመጠውን የትምህርት
ጊዜ አጠቃቀም ያሟሉ መሆን አለባቸው፤
6.6 ከላይ በ6.5 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የርቀት ትምህርት ተፈታኞች ከሌሎች

ፕሮግራምች ጋር ሳይቀላቀሉ በተማሩበት ት/ቤት ስምና ኮድ መመዝገብ አለባቸው፤


6.7 በግል በድጋሚ ፈተና ለመውሰድ ለሚያመለክቱ ተመዝጋቢዎች ቀደም ሲል
የተፈተኑበትን ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ
ያላሟሉ መሆን አለባቸው፤
6.8 የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ (12ኛ) ክፍል ለመፈተን ተመዝግበው በአሳማኝ ምክንያት

ሳይፈተኑ ከቀሩ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ያጠናቀቁበትን ትራንስክሪፕትና ፈተናውን


ላለመፈተናቸው ከተማሩበት ት/ቤት በሚቀርብ መረጃ መሰረት በቀጣዩ አመት በግል
ለመፈተን ይመዘገባሉ፤
6.9 የስም ለውጥ ያደረጉ ተመዝገቢዎች ከምዝገባ በፊት ስማቸውን ያስለወጡበትን የፍርድ

ቤት ውሳኔ ማስረጃ በማቅረብ በተለወጠው ስማቸው ለፈተናው መመዝገብ የሚችሉ


ሲሆን ከምዝገባ በኋላ ለተደረገ የስም ለውጥ ማስተካከያ አይደረግም፣
6.10 በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም ከኢትዮጵያ ውጭ በራሳቸው ስርዓተ ትምህርት
በሚሰጡ ትምህርት ቤቶች የተማሩ እስከ 12ኛ ክፍል ማጠናቀቃቸውንና በኢትዮጵያ
ስርዓተ ትምህርት አቻ ግመታ በማሰራት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
6.11 ማንኛውም ተመዝጋቢ ለምዝገባ የሚያቀርባቸው የትምህርት ማስረጃዎች ሁሉም
ዋናው (ኦርጅናል) መሆን አለበት፣
6.12 የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት (12ኛ ክፍል)
ፈተና ተፈትነው በተፈተኑበት ዓመት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያገኙ
እንደገና ሊመዘገቡ አይችሉም፤
7. የተመዝጋቢዎች መብትና ግዴታዎች
7.1 . አገልግሎት መስሪያ ቤቱ በሚሰጠው ፈተና ለመፈተን የሚያስችል ከ6.1 እስከ 6.11
የተመለከቱትን መስፈርቶች አሟልተው የሚቀርቡ አመልካቾች ለፈተናው የመመዝገብ
መብት አላቸው፣
7.2 ተመዝጋቢዎች በተቀመጠው ጊዜ ገደብ መሰረት ማንኛውንም ከምዝገባ ጋር
ተያያዥነት ያላቸው ስህተቶች ከተፈጠሩ የምዝገባ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት
በተመዘገቡበት ጣቢያ ማስተካከያ የማድረግ መብት አላቸው፣

5
7.3 . የግል (Private)፣ የርቀት (Distance)፣ የበይነመረብ መስመር (Online) አመልካቾች
በአካል በመቅረብ ለየትምህርት ዓይነቱ የሚከፈለውን የመመዝገቢያ ክፍያ እና
አስፈላጊ የትምህርት ማስረጃዎችን በማሟላት መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን የሚያቀርቧው
የትምህርት ማስረጃዎች ዋና (ኦርጅናል) መሆን አለባቸው፣
7.4 . ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ሲቀርቡ ኮፍያ፣ ሻሽ እንዲሁም ሌሎች ጀሮን የሚሸፍኑ
አልባሳት ማድረግ የለባውቸም፤ ሆኖም እንዳስፈላጊነቱ ሃይማኖታዊ አለባበሶች ሙሉ
የፊት ገጽታና ሁለቱም ጆሮ ሳይሸፈን መነሳት አለባቸው፤
7.5 . የስም ለውጥ ለማድረግ የሚፈልጉ ተመዝጋቢዎች ከምዝገባ በፊት በህግ ያስቀየሩበትን
የፍርድ ቤት ውሳኔ በማቅረብ በተቀየረው ስማቸው መመዝገብ ይኖርባቸዋል፣
7.6 . ምዝገባ ከተፈፀመ በኋላ የሚቀርቡ ማንኛውም አይነት የስም ለውጥ ጥያቄ ተቀባይነት
የለውም፣
7.7 . ተመዝጋቢዎች የፈተና መግቢያ (addmision) ካርድ በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት
በተመዘገቡበት ጣቢያ በአካል ቀርበው መፈተኛ ካርዳቸውን መውሰድ ይኖረባቸዋል፤
የፈተና መግቢያ ካርድ የሌለው ተፈታኝ ለፈተና አይቀመጥም፡፡
8. የምዝገባ አስፈጻሚዎች ተግባርና ኃላፊነት
8.1 የአገልግሎቱ ምዝገባ አስፈጻሚ(EAES Administrator)ተግባርና ኃላፊነት
8.1.1 የበይነ መረብ ምዝገባ ሂደቱን (online registration) በበላይነት ይመራል፤
ያስተዳድራል፤ይከታተላል፣
8.1.2 ከምዝገባ መተግበሪያው አልሚ ድርጅት(software development team) ጋር
በመነጋገር እንዳስፈላጊነቱ የማሻሻያ እና ማስተካከያ ሥራ እንዲሰራ ያደርጋል፣
8.1.3 በምዝገባ ሂደት ለክልል የምዝገባ አስፈጻሚዎች ኃላፊነትና የምዝገባ
አስፈጻሚነት መለያ(account & user name) እንዲሰጥ ያደርጋል፤
አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣
8.1.4 በስሩ ላሉት የስራ አስፈጻሚው ዴስኮች ባላቸው የስራ ድርሻ መሰረት ኃላፊነት
እና የምዝገባ አስፈጻሚነት መለያ(account & user name)ይሰጣል፤
አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤
8.1.5 በማዕከል ለክልል ምዝገባ አስፈጻሚዎች እና ባለድረሻ አካላት የአሰልጣኞች
ስልጠና ይሰጣል፤አፈጻጸሙንም ይከታተላል፡፡

6
8.2 የክልል ምዝገባ አስፈጻሚ(Regional Administrator) ተግባርና ኃላፊነት
8.2.1 የአስመዝጋቢ ትምህርት ቤቶችን መረጃ በመለየት በምዝገባ መተግበሪያው
ላይ እንዲጫን ያደርጋል፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣
8.2.2 በምዝገባ ሂደት ለዞን ምዝገባ አስፈጻሚዎች ኃላፊነትና የምዝገባ አስፈጻሚነት
መለያ(account & user name) እንዲያገኙ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙንም
ይከታተላል፣
8.2.3 በክልል ደረጃ ለዞን /ክፍለ ከተማ የምዝገባ አስፈጻሚዎች እና ለባለድርሻ
አካላት አስፈላጊውን ስልጠና ይሰጣል፣
8.2.4 የምዝገባ ግብዓት እና መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ ክትትል እና ድጋፍ
ያደርጋል፤ መሟላቱን ያረጋግጣል።
8.3 የዞን ምዝገባ አስፈጻሚ(Zonal Administrator) ተግባር እና ኃላፊነት
8.3.1 የአስመዝጋቢ ትምህርት ቤቶችን መረጃ በምዝገባ መተግበሪያው ላይ
እንዲጫኑ በወቅቱ ለይቶ ያቀርባል፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል
8.3.2 በምዝገባ ለሚሳተፉ መዝጋቢዎች አካውንት እና የመለያ ስም (account and
user name) ይፈጥራል፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣
8.3.3 በተፈታኞች ምዝገባ ለሚሳተፉ መዝጋቢዎችና ባለድርሻ አካላት ስልጠና
ይሰጣል፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣
8.3.4 የምዝገባ ግብዓት እና መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ ክትትል እና ድጋፍ
ያደርጋል፤ መሟላቱን ያረጋግጣል፣
8.3.5 የግል፣የማታ፣ የርቀትና የበይነ መረብ መስመር(online) ትምርት ፕሮግራም
ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ብቁ ሆነው መመዝገባቸውን ይከታተላል፤
የዶክመንት ምርመራም እንዲካሄድ ያደርጋል፣
8.3.6 የምዝገባ ሰነዶችንና ሪፖርቶችን አሰባስቦና አደራጅቶ ለአገልግሎቱ
ያስረክባል፣
8.4 የመዝጋቢ ተግባርና ኃላፊነት
8.4.1 ለምዝገባ የተመቻቸለትን የምዝገባ ቦታ ዝግጁ በማድረግና ለተመዝጋቢዎች
የምዝገባውን ሂደት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ገለጻ በመስጠት ምዝገባ
ያካሂዳል፤
8.4.2 በበይነ መረብ (Online) የተመዘገቡትን ተመዝጋቢዎች ሙሉ ዝርዝር መረጃ

7
ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲለጠፍ እና ተመዝጋቢዎች እንዲያረጋግጡ
ከር/መምህሩ ጋር የማመቻቸት ስራ ይሰራል፤
8.4.3 የት/ቤቱ ተመዝጋቢዎች ሙሉ በሙሉ መመዝገባቸውን ከር/መምህሩ ጋር
በመሆን ያረጋግጣል፣
8.4.4 ምዝገባው እንደተጠናቀቀ የምዝገባ ቀሪ ቀናት ሳይጠብቅ የተመዝገቢዎችን
ዝርዝር በጥንቃቄ በመያዝ ለሚመለከተው ያስርክባል፤
8.4.5 መዝጋቢው ሲስተም ውስጥ ባሉት ት/ቤቶች እና በተሰጠው የተመዝጋቢዎች
ዝርዝር በተፈጠረለት አካውንት ብቻ ይመዝግባል
8.4.6 በበይነ መረብ (Online) የተመዘገቡትን ተመዝጋቢዎች የምዝገባ ሰነድ
አጣርቶና አረጋግጦ ለትምህርት ቤቱ ር/መምህር በመፈራረም ያስረክባል፣
8.4.7 የግል፣ የርቀትና የበይነመረብ ፕሮግራም ተመዝጋቢዎችን ለምዝገባ
አገልግሎት ሲመጡ ለምዝገባ ብቁ መሆናቸዉን በማረጋገጥ ይመዘግባል፡፡
8.5 የትምህርት ማስረጃ አጣሪ ተግባርና ኃላፊነት
8.5.1 የተመዝጋቢዎችን ዝርዝር መረጃ ከወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ይረከባል፤
8.5.2 በመመሪያው መሰረት ዶክመንቶችን በመመርመርና በማጣራት የተጣራውን
የተመዝጋቢዎች ዶክመንት በማረጋገጥ ተቀባይነት ያገኙትን ለዞን ትምህርት
መምሪያ ኃላፊ ያቀርባል፣
8.5.3 በዶክመንት ማጣራት ወቅት ውድቅ የተደረገባቸው ተመዝጋቢዎች ተቀባይነት
ያላገኙበትን ምክንያት በመግለጽ በወረዳ ፈተና ክፍል ኃላፊዎች አማካኝነት
ተመዝጋቢዎች እንዲያውቁ ያደርጋል፤
8.5.4 ለዶክመንት ምርመራ የተሰበሰበው ኦርጅናል ዶክመንት በአግባቡ በመያዝ
ለወረዳ ት/ጽ/ቤት በጥንቃቄ ያስረክባል፤ የወረዳ ት/ጽ/ቤትም ለተመዝጋቢዎቹ
ይመልሳል፡፡
9. የተፈታኞች ምዝገባ ጊዜና ቦታ
9.1 የየትምህርት ዘመኑ የተፈታኞች ምዝገባ መደበኛ ትምህርት በተጀመረ በአንድ
ወር ጊዜ ውስጥ እንዲካሄድ ይደረጋል፣
9.2 የመደበኛና የማታ ተመዝጋቢዎች በሚማሩበት ትምህርት ቤት በርዕሳነ
መምህራን ኃላፊነት መመዝገብ አለባቸው፣
9.3 የግል (Private)፣ የርቀት (Distance)፣የበይነ መረብ መስመር (Online)

8
ፕሮግራም ተፈታኞች ምዝገባ በክፍለ ከተማ ፤ በልዩ ወረዳ እና በወረዳ ትምህርት
ጽሕፈት ቤቶች ይካሃዳል፡፡

ክፍል ሦስት
10. የፈተና ማዕከላት አደረጃጀትና አሰራር
10.1 የፈተና ጣቢያቢያዎች አደረጃጀትና አሰራር
10.1.1 የፈተና ማዕከላት የሚደረጁት የመንግስት መደበኛ ትምህርት ቤቶችን መሰረት
በማድረግ ይሆናል፣
10.1.2 የግል ትምህርት ቤቶች፣ የማታ፣ የድጋሚ ተፈታኞች፣ የርቀትና የበይነ መረብ
ትምህርት ፕሮግራምችም አቅራቢያቸው ባሉ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ስር
በፈተና ጣቢያነት እንዲደራጁ ይደረጋል፣
10.1.3 የፈተና ጣቢያዎችን በቀላሉ ለመለየትና ለመጠቀም የሚያስችል የፈተና ጣቢያ
መለያ ቁጥር(group number) እንዲሰጥ ይደረጋል፣
10.1.4 ለፈተና አሰጣጡ የሚያስፈልጉት መሰረታዊ የፈተና ጣቢያ መረጃዎች
የሚሰበሰቡት በትምህርት ቤት ደረጃ በተናጠል ሳይሆን በ10.2 እንደተጠቀሰው
በፈተና ጣቢያ ደረጃ ያሉት ትምህርት ቤቶችና የትምህርት ፕሮግራምችን ታሳቢ
በማድረግ በጥቅል ይሆናል፣
10.1.5 ለእያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ የሚመደበው የፈተና ግብዓት፣ በጀትና የሰው ኃይል
መሰረት የሚያደርገው በፈተና ጣቢያ ደረጃ በጥቅል የቀረቡ መስረታዊ የፈተና
ጣቢያ መረጃዎችን ታሳቢ በማድረግ ይሆናል፣
10.1.6 የፈተና ጣቢያ ኃላፊ የሚመደበው በተፈታኝ ቁጥር መሰረት ሲሆን ከፍተኛ
የተፈታኝ ቁጥር ያላቸው የፈተና ጣቢያዎች ከአንድ በላይ የፈተና ጣቢያ
እንዲኖራቸው ይደረጋል፣
10.1.7 የፈተና ጣቢያው የተፈታኝ ብዛት ሰላሳ ስድስት እና ከዚህ በታች ከሆነ የጣቢያ
ኃላፊው የሱፐርቫይዘር እና የፈታኝነት ኃላፊነትን ደርቦ ያስተዳድራል፡፡
10.1.8 ሱፐርቫይዘር በአንድ የፈተና ጣቢያ የመፈተኛ ክፍሎችን መሰረት በማድረግ
የሚመደብ ሲሆን አራት የመፈተኛ ክፍሎችን የሚመራ አንድ ሱፐርቫይዘር
ይመለመላል፣ ይመደባል፣

9
10.1.9 በ10.1.8 እንደተጠበቀ ሆኖ በአንድ ፈተና ጣቢያ የመፈተኛ ክፍሎች ከአራት
በታች ከሆኑ ሱፐርቫይዘር መመደብ ሳያስፈልግ በጣቢያ ኃላፊ የሚመሩ ይሆናል፡

10.1.10 በአንድ የፈተና ጣቢያ ለአንድ ዓይነ ስውር ተፈታኝ አንድ አንባቢ መምህር
ይመለመላል፣ ይመደባል፣
10.1.11 የእጅ እንቅስቃሴ ችግር ያለበት መሆኑ በክልሉ በኩል በሚቀርብ ደብዳቤ ጥያቄ
መሰረት አንድ ረዳት የመልስ ወረቀት ማጥቆር የሚሰራ ፈታኝ ይመለመላል፣
ይመደባል፣ በዚህ ኃላፊነት የሚመደብ ፈተና አስፈጻሚ እንደማንኛውም ፈታኝ
ፈተና አስፈጻሚ ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ርቆ ሊመደብ ይችላል።
10.1.12 አንድ የፈተና ጣቢያ የተፈታኘች ቁጥር ከ 500 በላይ ከሆነ በማንዋሉ ላይ
በተቀመጠው ዝርዝር አፈፃፀም መሰረት የመልስ ወረቀት ቆጣሪ ይመደባል።
10.2 የፈተና ጉድኝት ማዕከላት አደረጃጀትና አሰራር
10.2.1 የፈተና ጉድኝት ማዕከል የፈተና ጣቢያዎችንና የተፈታኞችን ብዛት መሰረት
በማድረግ ለፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ
ይደራጃል፣
10.2.2 በ10.2.1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በአንድ የፈተና ጉድኝት ማዕከል ሥር
የሚኖሩ የተፈታኞቹ ቁጥርም ከ5000 እንዳይበልጥ ተደርጎ ይደራጃል፤ከ2000
ተፈታኝ ቁጥር ያላቸው የፈተና ማዕከላት የጉድኝት አስተባባሪ ሳያስፈልጋቸው
በፈተና ማዕከል ኃላፊው እንዲመራ ይደረጋል፡፡
10.2.3 የፈተና ጉድኝት ማዕከላት የፈተና አስፈጻሚዎችን በቅርበት በመከታተልና
በመደገፍ ውጤታማ የፈተና አሰጣጥ ሂደት እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል
ግብአት፣ በጀትና የተሟላ የሰው ኃይል እንዲኖራቸው ይደረጋል፣
10.2.4 ለፈተና ጉድኝት ማዕከል አስተባባሪነት የሚመደቡ ባለሙያዎች በፈተና አስጣጡ
ሂደት ባሉ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ አተኩረው እንዲሰሩ፣ በቂ ክትትልና ድጋፍ
እንዲያደርጉ ይደረጋል፣
10.3 የፈተና ማዕከላት አደረጃጀትና አሰራር
10.3.1 በየክልሉ የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት/ካምፓሶችና ኮሌጆች
የፈተና ማእከላት ሆነው እንዲያገለግሉ ይደረጋል፣

10
10.3.2 እንደ አስፈላጊነቱ በየክልሉ የሚገኙ የክልል የመምህራንና ሌሎች የትምህርት
ተቋማት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስር ሆነው በፈተና ማእከልነት እንዲያገልግሉ
ይደረጋል፣
10.3.3 ተፈታኞች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ
አቅራቢያቸው ባሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲመደቡ ይደረጋል፣
10.3.4 በፈተና አሰጣጡ ወቅት ለፈተና አሰጣጡ ደህንነትና ሚስጠራዊነት ሲባል
ከሚመለከታቸውና ለፈተና አሰጣጡና ተጓዳኝ ሥራዎች ከተመደቡት የከፍተኛ
ትምህርት ተቋማት ሰራተኞች ውጪ ወደ ግቢ እንዳይገቡ ይደረጋል፣
10.3.5 እያንዳንዱ የፈተና ማእከል(ከፍተኛ ትምህርት ተቋም) በዩንቨርስቲው ፕሬዘንዳንት
የሚመራ ግብረ ኃይል ያቋቁማል፤
10.3.6 በፈተና አሰጣጥ ወቅት ለተፈታኞች ተገቢውን የምግብ፣ የመኝታና፣ የጽዳትና የጤና
አገልግሎቶችን ሊያስተባብር የሚችል በአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዘዳት
የሚመራ ንዑስ ግብረ ኃይል እንዲያቋቋም ይደረጋል፤
10.3.7 በፈተና አስጣጥ ሂደት ተፈታኞችና ፈተና አስፈጻሚዎች ተገቢውን የፈተና አሰጣጥ
ሂደት ገለጻ አግኝተውና በቂ ግንዛቤ ጨብጠው ፈተናው ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ
መስጠት እንዲቻል በዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዘዳንት የሚመራ ንዑስ
ግብረ ኃይል አቋቁሞ እንዲሰራ ይደረጋል፣
10.4 የፈተና ማዕከላት ግብአትና መሰረተ ልማት አቅርቦት፣ ድልድል፣ ስርጭትና ክዘና
አፈጻጸም
10.4.1 የፈተና አስተዳደር ግብአቶችና መሰረተ ልማቶች በማዕከል ደረጃ እንዲሟሉ
የሚደረግ ቢሆንም በማዕከል ደረጃ ያልተሟሉትን በባለድርሻ አካላት በተዋረድ
እንዲሟሉ ይደረጋል፤
10.4.2 የፈተና አስተዳደር መተግበሪያ ግብአቶችና መሰረተ ልማቶች ከተለያዩ ሀገራት
ወይም አቅራቢ ድርጅቶ ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ ተገዝተው ሲቀርቡ
በሚመለከተው የደህንነት ተቋም እንዲረጋገጡ ይደረጋል፤
10.4.3 የፈተና ጥራዝ ህትመቱን ጥራት ለማሰጠብቅ የሚደረግ የማረጋገጫ ንባብ ወይም
ንክኪ በማሰቀረት ዘመናዊና ጥራቱን በጠበቁ ማሽኖችን እንዲታተም ይደረጋል፤

11
10.4.4 የፈተና ግብአት አቅርቦት፣ ድልድል፣ ስርጭት እና ክዘና ስራዎችን በአግባቡ
ለመምራት የሚያስችል የተሟላ የአሰራር ስርአት ማንዋል በማዘጋጀት በየደረጃው
ተግባራዊ እንዲሆን ይደረጋል፣
10.4.5 በፈተና ግብአትና መሰረተ ልማት ድልድል ወቅት ለየፈተና መስጫ ማእከል
የሚደለደሉ ግብአቶች የደህንነት መጠበቂያ መለያ (barcode) እና መግለጫ(lable)
የተሟላላቸው ሆነው እንዲዘጋጁ ይደረጋል፣
10.4.6 ለፈተና አስተዳደር በማዕከል ደረጃ የሚገዙ እና የሚሰራጩ ንብረቶች በየደረጃው
ባሉ የትምህርት መዋቅሮች በህጋዊ ሰነድ ርክክብ ይፈፀማል፤ በተገቢው ቦታ
እንዲከዘኑ በማድረግ ለታለመለት ስራ ብቻ እንዲውል ክትትል ይደረግበታል፤
10.4.7 የፈተና ግብአትና መሰረተ ልማቶችን ከማዕከል ሆኖ ለመከታተል እና ለማስተዳደር
የሚያስችል የፈተና ግብአትና መሰረተ ልማት አስተዳደር መረጃ ቋት እንዲለማ
በማድረ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለፈተና ማዕከላት ለመስጠት የሚያስችል የአሰራር
ሥርአት ይቀየሳል፤
10.4.8 አገልግሎቱ በሚያቋቁማቸው የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የፈተና ግብአትና መሰረተ
ልማት ክትትልና ድጋፍ ባለሙያዎችን በመመደብ የፈተና ማእከላት ተገቢውን
ክትትልና ድጋፍ እንዲያገኙ ይደረጋል፣
10.4.9 የፈተና ግብአት ሥርጭት እና ክዘና ሥራው በሶስትዮሽ አሰራር (የጉዞ መስመር
ተወካዮች፣ አጃቢ ፖሊሶች እና ትራንስፖርት አቅራቢዎች) ተረክበው ደህንነቱ
በተጠበቀ የትራንስፖርት አማራጭ በሰአቱ እንዲጓጓዝ፣ እንዲከዘንና በቂ ጥበቃ
እንዲያገኝ ይደረጋል፤
10.4.10 እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በፈተና ቴክኖሎጅ ፈተና ለመስጠት ማስቻሉን
የሚያረጋግጥ የኢንስፔክሽን ቡድን እንዲደራጅ፣ የማረጋገጥ ሥራ እንዲሰራ
በግኝቱም ላይ ተመስርቶ አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ይደርጋል፡

ክፍል አራት
የፈተና አስፈጻሚዎች ተግባርና ኃላፊነት
11.1 የጋራ ተግባርና ኃላፊነት
የፈተና አስፈፃሚዎች እንደ ፈተና አስፈፃሚነታቸው የኃላፊነት ተዋረድ የሚኖራቸው ኃላፊነትና
ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት አለባቸው፤
12
11.1.1 በፌደራል ደረጃ ከአገልግሎቱ ስለ ተፈታኞች ምዝገባና ፈተና አስተዳደር ሁኔታ
የሚቀርብለትን አጠቃላይ ገለፃ እና የስራ ትዕዛዝ ይከታተላል፣ ይቀበላል፣ በተዋረድ
ለሚመለከታቸው አካላት ገለፃ ይሰጣል፤
11.1.2 የፈተና አስተዳደር አፈፃፀም ሂደት በተመለከተ የተዘጋጁ መመሪያዎችን እና
የአሰራር ማንዋሎችን በመከተል ስራ ላይ ያውላል፤
11.1.3 በተሰጠው ገለፃ መሰረት በተመደበበት ቦታ (የፈተና አስፈፃሚነት ወሰን መሰረት)
የፈተና አስፈፃሚዎች እና ቦታው ለፈተና ስራ ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣
ስራውን በአግባቡ ይፈፅማል፣ ያስፈፅማል፤
11.1.4 ተፈታኞች በፈተና ወቅት ወደ ፈተና አዳራሽ ከመግባታቸው በፊት እና በሂደት ላይ
ህጋዊ ተፈታኝ ስለመሆናቸው በመግቢያ(addmision) ካርድ ያረጋግጣል፣
11.1.5 የተሰጠውን ኃላፊነት በመፈፀም እና በማስፈፀም ሂደት ስራው በአግባቡ ስለመካሄዱ
ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ በተዋረድ ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፣
11.1.6 ተፈታኞች ልዩ ፍላጎት ያላቸው ወይም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ተገቢውን
ሁኔታ በማመቻቸት ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣
11.1.7 . በፈተና አስተዳደር ወቅት በተፈታኞችም ሆነ በፈተና አስፈፃሚዎች እንዲሁም
በሌሎች አካላት የፈተና አስተዳደር ደንብ መተላለፍ ችግር እንዳይከሰት ተገቢውን
ክትትል ያደረጋል፣ ችግር ተከስቶ ከተገኘ በተዋረድ ለሚመለከተው አካል በሪፖርት
ያሳውቃል፤
11.1.8 በስራው አጋጣሚ የሚያገኘውን ሚስጢሮች በመጠበቅ በትጋትና በታማኝነት
ይሰራል፣ ኃላፊነታቸውን የማይወጡ የፈተና አስፈፃሚዎች ካሉ በተዋረድ
ለሚመለከተው አካል የማሳወቅ ግዴታ አለበት፤
11.1.9 የፈተና አስፈፃሚዎች የምድብ ቦታ አመዳደብ መመሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ በምድብ
ቦታው የሰው ኃይል ክፍተት ሲኖር በተዋረድ የሚሰጠውን ኃላፊነት እና ተግባር
ተቀብሎ ይተገብራል፤
11.1.10 የፈተና አስተዳደር ተግባራትን አፈፃፀም ሪፖርት ያዘጋጃል፣ በጋራ ይገመግማል፣
ግብረ መልስ በመቀበል ለቀጣይ ስራዎች እንደግብዓት ይጠቀማል፡፡

13
11.2 የፈተና ጉድኝት ማዕከላት ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት
ከት/ት ሚኒስቴር፣ ከአገልግሎቱ እና እንደ አስፈላጊነቱ ከሌሎች የፌዴራል ተቋማት
የትምህርት ባለሙያዎች የሚመለመልና በአገልግሎቱ የሚመደብ ሲሆን ተጠሪነቱም
ለአገልግሎቱ ይሆናል፤
11.2.1 ከስሩ የተመደቡትን የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪዎችን በኃላፊነት ይመራል፤
ይከታተላል፣ ይደግፋል
11.2.2 ለተመደበበት የፈተና ማዕከል የተፈታኞችን ቁጥር ታሳቢ ያደረገ የጥያቄ ቡክሌት
ከነመጠባበቂያው የያዘ፣ በአግባቡ ታሽጎ የተቆለፈ፣ በሸራው ላይ ለመለያነት የተጻፈ
ጽሑፍ ትክክልና ግልጽ ሆኖ የተጻፈ፣ ያልተቆረጠ፣ ያልተበሳ፣ እርጥበት ያልነካውና
ያልበሰበሰ ሸራ (ኮሮጆ) መሆኑን አረጋግጦ ከአገልግሎቱ ይረከባል፤
11.2.3 የተረከባቸውን ፈተና እና የመልስ ወረቀት የያዙ ሸራዎችን ዝርዝሩ ቀድሞ በተሰጠው
የጸጥታ አካላት በማሳጀብና ተገቢው የደህንነት ጥበቃ መደረጉን በማረጋገጥ ወደ
ተመደበበት ፈተና መስጫ ማዕከል በኃላፊነት ያጓጉዛል፤
11.2.4 ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲደርስም ደህንነቱ ቀድሞ ተፈትሾ በተረጋገጠና የጦር መሳሪያ
የታጠቀ በቂ የሰው ኃይል በቀን የ24 ሰዓት ጥበቃ ለማድረግ በተመደበበት አዳራሽ
ውስጥ ፈተናውን ያስቀምጣል፣ አዳራሹን በራሱ ቆልፎ ቁልፉን ይይዛል፣ ከጥበቃዎቹ
ጋር ይፈራረማል፤
11.2.5 ፈተናው በሚሰጥበት ዕለት የዕለቱን ፈተና እና የመልስ ወረቀት የያዙ ሸራዎችን
ለጉድኝት ማዕከል አስተባባሪዎችና ለጣቢያ ኃላፊዎች ያስረክባል፤
11.2.6 እንደአስፈላጊነቱ በማዕከሉ የተመደቡ ተፈታኞችንና የፈተና አስፈጻሚዎችን ታሳቢ
በማድረግ ረዳት በአገልግሎቱ ሊመደብለት ይችላል፡፡
11.2.7 የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪዎችን ያሰለጥናል፣ ወደ ስራ ያስገባል፣ ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፣
11.2.8 በተመደበበት ማዕከል የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት
ይመራል፣
11.2.9 በፈተና አስተዳደር ዙሪያ ከአገልግሎቱ የሚሰጠውን ማናቸውም የአሰራር ስርዓት
ይቀበላል፣ ይተገብራል፣ ፈተና አፈጻጸሙን በተመለከተ ለአገልግሎቱ ሪፖርት
ያቀርባል፣

14
11.2.10 ተፈታኞች በፈተና ማዕከል ቆይታቸው ተገቢውን የምግብ፣ የመኝታ፣ የጤናና
መሰል አገልግሎቶች በትክክክል ስለማግኘታቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር
በቅንጅት ይሰራል፡፡
11.2.11 የ ፈተና አስፈጻሚዎች በፈተና አሰጣጥ ቆይታቸው ስለሰጡት አገልግሎት የቆይታ
እና የሙያ አገልግሎት ክፍያ በመመሪያው መሰረት እንዲከፈላቸው ከሚመለከታቸው
አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡
11.2.12 የመልስ ወረቀት የያዙ ፖስታዎችን አሰባስቦ፣ በአግባቡ መደራጀታቸውን
አረጋግጦ ከማእከል አስተባባሪው ቆጥሮ በመረከብ ለአገልግሎቱ ቆጥሮ ያሰረክባል፣
11.2.13 የተሰጠውን ሥራ አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ በጽሑፍ ከአገልግሎቱ
ይወስዳል፡፡
11.3 የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ ተግባርና ኃላፊነት

ከክልል የትምህርት አመራር፣ ባለሙያዎችና መምህራን የሚመለመሉ ሆነው


ተጠሪነቱ ለጉድኝት ማዕከል ኃላፊ ይሆናል፤
11.3.1 ፈተና በሚሰጥበት ዕለት በማዕከል ለሚያስተባብራቸው የፈተና ጣቢያዎች
የሚያስፈልገውን ፈተና የያዙ ፖስታዎችና ተዛማጅ ቁሳቁሶች በአግባቡ ከማዕከል
ኃላፊው ተረክቦና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ በየእለቱ ለፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች
እንዲሰራጭ ያደርጋል፣
11.3.2 ስለ ፈተና አስተዳደር ሂደት አጠቃላይ ሁኔታ ከማዕከል ኃላፊው ጋር ውል ይዋዋላል፣
የፈተና ሥራን በተመደበበት የጉድኝት ማዕከል (ቦታ) በበላይነት ይመራል፣
ይከታተላል፣
11.3.3 ለፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች አስፈላጊውን የፈተና አሰጣጥ ገለፃ ይሰጣል፣
11.3.4 የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ሲጠናቀቅ ፈተናው የተፈታኞችን የመልስ ወረቀት እና
ሌሎች ለፈተና ስራ አገልግሎት የተሰጡ ቁሳቁሶችን ከፈተና ጣቢያዎች በመሰብሰብ
ለማዕከል ኃላፊ ያስረክባል፣
11.3.5 የተፈታኞች ብዛት ታሳቢ ያደረገ የጥያቄ ቡክሌት የያዘ፣ በአግባቡ የታሸገና የተቆለፈ፣
በሸራው (ኮሮጆ) ላይ ለመለያነት የተጻፈ ጽሑፍ ትክክል የሆነ ሸራ እንዲሁም ኮሮጆው
ያልተቆረጠ፣ ያልተበሳ፣ እርጥበት ያልነካውና ያልበሰበሰ ሸራ (ኮሮጆ) መሆኑን
አረጋግጦ ከማዕከል ኃላፊው ጋር ያደራጃል፡፡

15
11.3.6 ፈተና በሚሰጥበት ዕለት ለፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች የዕለቱን ፈተና ቡኩሌቶችን የያዘ
ሸራና የመልስ ወረቀት የያዙ ሸራዎችን የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
11.3.7 ለጣቢያ ኃላፊዎች ስልጠና ይሰጣል፣ ወደ ስራ ያስገባል፣ በስሩ ያሉ ጣቢያ ኃላፊዎችን
ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፡፡
11.3.8 የመልስ ወረቀት የያዙ ፖስታዎችን አሰባስቦ፣ በአግባቡ መደራጀታቸውን አረጋግጦ
ከፈተና ጣቢያ ኃላፊው ቆጥሮ በመረከብ ለማዕከል ኃላፊው ቆጥሮ ያስረክባል፣
11.3.9 ከማዕከል ኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
11.3.10 የተሰጠውን ሥራ አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከማዕከል ኃላፊው በጽሑፍ
ይወስዳል፡፡
11.4 የፈተና ጣቢያ ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት

የፈተና ጣቢያ ኃላፊ ተጠሪነቱ ለጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ ሆኖ የሚከተሉት


ኃላፊነትና ተግባራት ይኖሩታል
11.4.1 የፈተና አስፈጻሚዎችና የፈተና ጣቢያው ለፈተና ስራ ዝግጁ መሆናቸውን
ያረጋግጣል፤
11.4.2 ለሱፐርቫይዘሮች፣ ፈታኞች፣ አንባቢዎች፣ መልስ ወረቀት ቆጣሪዎችና ተፈታኞች
በፈተና ጣቢያ ደረጃ አስፈላጊውን የፈተና አሰጣጥ ገለፃ ይሰጣል፣
11.4.3 በተለያዩ ምክንያቶች አድሚሽን ካርድ ይዘው ባለመምጣታቸው ወደ ፈተና አዳራሽ
እንዳይገቡ ለሚከለከሉ መደበኛ ተፈታኞች ከአገልግሎቱ ከተላከው ዝርዝር
ማረጋገጫ (master list & photo album) ተማሪዎች ስለመሆናቸው ተገቢውን
ማረጋገጫ እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ፈተና ክፍል እንዲገቡ ያደርጋል፣
11.4.4 በጣቢያው ውስጥ ያሉ ፈተና አስፈጻሚዎችን ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣
በወቅቱ መፍትሔ በሚሹ ጉዳዮች ላይ አፋጣኝ ውሣኔ ይሰጣል፡፡ ከአቅም በላይ
ከሆነም ከማዕከል አስተባባሪው ጋር በመነጋገር የጽሑፍ ሪፖርት ያቀርባል፤
11.4.5 ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል
እንዳይገባ፣ ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል እንዳይወጣ እና
ለፈተናው የተፈቀደው የጊዜ ገደብ ሳይጠናቀቅ የተሰጠውን የጥያቄ ወረቀት ይዞ
እንዳይወጣ መደረጉን ይቆጣጠራል፤
11.4.6 የፈተና ወረቀት የሚያሰራጭበት፣ ሥራውን የሚያከናውንበት እና የፈተና የመልስ
መስጫ ወረቀቶች የሚሰበሰብበት ደህንነትና ምስጢራዊነት የተጠበቀ ጊዚያዊ ቢሮ

16
እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ በዚህ ረገድ በራሱ የጥንቃቄ ጉድለት ለሚከሰት ማንኛውም
ችግር ኃላፊነት አለበት፡፡ በፈተና ወቅት በአካባቢው በመንቀሳቀስ እገዛ ለሚሹ
ሱፐርቫይዘሮችና ፈታኞች ድጋፍ ይሰጣል፤
11.4.7 ማናቸውንም ከፈተና አሰጣጥ ጋር በተጓዳኝነት የሚሞሉ ቅፃቅጾችን በአግባቡ
በማስሞላትና በመሙላት ለማዕከል አስተባባሪው ከመልስ ወረቀት ጋር ያስረክባል፤
11.4.8 በፈተና አሰጣጥና በልዩ ልዩ የፈተና የሥነ ሥርዓት ጉድለት ከፈተና ስለሚታገዱ
ተማሪዎች በፈታኝና በሱፐርቫይዘር በግልና በቡድን የፈተና ደንብ መተላለፍ
ችግሮች ሪፖርት ማቅረቢያ ቅጾች ላይ ተሞልተው በሚቀርቡለት ሪፖርቶች መሠረት
ውሣኔ ያስተላልፋል፤
11.4.9 የመልስ ወረቀት ቆጣሪዎች የርክክብ ስራውን በአግባቡ መስራታቸውን ይከታተላል፤
በታሸገው ፖስታ ላይም ይፈርማል፤ የታሸጉት ፖስታዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ
ሁኔታ እንዲከማቹ ያደርጋል፤
11.4.10 የኮሌጅ ዲን/ትምህርት ክፍል ኃላፊ ወይም ተወካይ በፈተና አሰጣጥና በመልስ
ወረቀት ርክክብ ወቅት የማህተም፣ የቢሮና የጠቅላላ አገልግሎት ሥራ በመሥራት
ለፈተናው ሥራ መሳካት አስተዋፅኦ እያዲያበረክቱ ያደርጋል፤
11.4.11 ለዓይነ ስውር ተፈታኞች በደንብ ማንበብና መልስ ማጥቆር የሚችሉ ፈታኞችን

ወይም የእጅ እንቅስቃሴ ችግር ላለባቸው ተፈታኞች የተመደቡ ረዳት ጸሐፊዎችን


ትክክለኛነታቸውን አረጋግጦ ይመድባል፤ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ማስተካከያዎች
እንዲደረጉ ያደርጋል፤
11.4.12 በፈተና አሰጣጥ ወቅት በቀጥታ በፈተና አሰጣጡ ሂደት ከሚሳተፉ ሰዎች በስተቀር
ወደ ፈተና ጣቢያው ቅጥር ግቢ ወይም መፈተኛ አካባቢ ማንም ሰው እንዳይገባ
ያደርጋል፤
11.4.13 እያንዳንዱን ፈተና በመጀመሪያ ሰዓቱ ያስጀምራል፤ ሰዓቱ ሲያበቃም ተፈታኞች
መስራት እንዲያቆሙ ያስደርጋል፤
11.4.14 በፈተና ጣቢያ የመልስ ወረቀት ከተቆጠረ፣ ከቀሪ መቆጣጠሪያ ጋር ተገናዝቦ
የርክክብ ቅፅ ከተሞላ በኋላ የመልስ ወረቀቶቹና የስም መቆጣጠሪያው ቅፅ በአንድ
ላይ በመልስ ወረቀት ማሸጊያ ፖስታ ውስጥ ተከተው እንዲታሸጉ ያደርጋል፤
በታሸገው ፖስታ ላይም የየኒቨርሲቲው ወይም የካምፓሱ ማህተም እንዲያርፍበት
ያደርጋል፤

17
11.4.15 በፈተና ጣቢያው ውስጥ የተሰራባቸው የመልስ ወረቀቶች በጉዞ ወቅት
እንዳይበላሹ ሆነው መታሸጋቸውን ይቆጣጠራል፤
11.4.16 የመልስ ወረቀት የያዙ ፖስታዎች የታሸጉበትን ሸራ እና የሸራው ቁልፍ
የታሸገበትን ፖስታ እንዲሁም ባዶ ሸራዎችንና የተረከባቸውን ቁልፎች በሙሉ
ለማዕከል አስተባባሪው ወይም በአገልግሎቱ ለተመደበው የኮማንድ ፖስት ተጠሪ
ወይም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መተማመኛ አስፈርሞ ያስረክባል።
11.4.17 በፈተና መስጫ ግቢ እና ክፍል ውስጥ በፈተና አሰጣጥ ወቅት በተፈታኞች እና
በፈተና አስፈፃሚዎች በግልም ሆነ በቡድን የሚፈጸሙ የፈተና ደንብ መተላለፍ
መረጃዎችን በደንብ መተላለፍ ቅጽ ላይ በማስሞላት ከፈታኝና ሱፐርቫይዘር ጋር
ተፈራርሞ ለማዕከል አስተባባሪ ያሰረክባል።
11.4.18 የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ሲጠናቀቅ የተፈታኞችን ለፈተና ስራ አገልግሎት የተሰጡ
ቁሳቁሶችን ለማዕከል አስተባባሪ ያስረክባል፣
11.4.19 በአንድ የፈተና ጣቢያ የተፈታኞች ቁጥር 36 እና በታች ሲሆን ፈታኝና
ሱፐርቫይዘር ሳያስፈልገው ራሱ ይፈትናል፡፡
11.4.20 በፈተና ጣቢያው የፈተና አስፈጻሚዎችን አሰራር ሂደት ክትትል እና ድጋፍ
በማድረግ ተፈታኞችን በአግባቡ እንዲፈተኑ ያደርጋል፣ በፈተና አስተዳደር ዙረያ
ከማዕከል አስተባባሪው የሚሰጠውን ማናቸውም የአሰራር ስርዓት ይቀበላል፣
ይተገብራል፣ ፈተና አፈጻጸሙንም በተመለከተ ሪፖርት ያቀርባል።
11.4.21 የጣቢያው ውስጥና ዙሪያው ተገቢው የደህንነት ፍተሻ የተደረገለት መሆኑን
ያረጋግጣል
11.4.22 ማንኛውም የተከለከሉ ቁሳቁሶች/ዕቃዎች በጣቢያው የሌሉ ወይም ተፈትሸው
የተወገዱ መሆኑን ያረጋግጣል
11.4.23 ተፈታኞች ወደ ፈተና ጣቢያው ሲገቡ በአግባቡ መፈተሻቸውን ይከታተላል፣
ጉድልት ሲኖር እንዲስተካከል ከሚመለከታቸው ጋር ይሠራል
11.4.24 ለሱፐርቫይዘሮች፣ ለፈታኞች፣ ለአይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢዎች እና መልስ
ወረቀት አደራጆች ስልጠና ይሰጣል፣ ወደ ስራ ያስገባል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡
ማስተካከያዎችን ያደርጋል፡
11.4.25 የመልስ ወረቀት በአግባቡ መደራጀታቸውን አረጋግጦና አሰባስቦ ለጉድኝት
ማዕከል ኃላፊ ያስረክባል።

18
11.4.26 የተሰጠውን ሥራ አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከጉድኝት ማዕከል
አስተባባሪ በጽሑፍ ይወስዳል።
11.5 የሱፐርቫይዘር ተግባርና ኃላፊነት

ሱፐርቫይዘር ተጠሪነቱ ለጣቢያ ኃላፊ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፣

11.5.1 የመፈተኛ ክፍል ፈታኞች እና አንባቢዎች ለፈተና ስራ ዝግጁ መሆናቸውን


ያረጋግጣል፤
11.5.2 ከጣቢያ ኃላፊው ጋር በመተባበር ፈተናው በሥነ ሥርዓት እንዲከናወን የማድረግ
ኃላፊነት አለበት፤
11.5.3 የጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን የፈተና አሰጣጥ መመሪያ ተግባራዊ ያደርጋል፤
11.5.4 አንድ ሱፐርቫይዘር በአማካይ 144 ተፈታኞችን ወይም ከአራት ያላነሱ የመፈተኛ
ክፍሎች የመቆጣጠርና የመከታተል ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም እንደየአካባቢው
ተጨባጭ ሁኔታና እንደመፈተኛ ክፍሎችና አዳራሾች የመያዝ አቅምና የመቀራረብ
ሁኔታ በአማካይ ከተገለፀው የተለየ ምደባ ቢካሄድ ምደባውን ይተገብራል፤
11.5.5 ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል
እንዳይገባ፣ ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል እንዳይወጣ እና
ለፈተናው የተፈቀደው የጊዜ ገደብ ሳይጠናቀቅ የተሰጠውን የጥያቄ ወረቀት ይዞ
እንዳይወጣ መደረጉን ይቆጣጠራል፤
11.5.6 ተፈታኞች በሚቀመጡባቸው ወንበር መካከል በተቻለ መጠን በቂ ርቀት መኖሩን
ያረጋግጣል፤
11.5.7 ተፈታኞች ጎን ለጎን ተመሳሳይ የቡኩሌት ኮድ አለመያዛቸውን ያረጋግጣል፡፡
11.5.8 በፕሮግራሙ መሠረት የተመደበ ሱፐርቫይዘር በተመደበበት ጣቢያ ፈተናው
ከመጀመሩ አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ በመገኘት ሥራውን ያከናውናል፤
11.5.9 የጣቢያ ኃላፊው ሁሉንም የመልስ ወረቀቶች ተረክቦና አደራጅቶ እስኪጨርስ ድረስ
የጣቢያ ኃላፊውን በመርዳት በጣቢያው መቆየት ይኖርበታል፡፡
11.5.10 አንድ ሱፐርቫይዘር ፈተናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የተመደበባቸውን
ክፍሎች በማስተባበር ፈታኞችና ተፈታኞች ተግባርና ግዴታቸውን በአግባቡ
መወጣታቸውን በቅርበት ይቆጣጠራል፤
11.5.11 በእያንዳንዱ መፈተኛ ክፍል በየትምህርት አይነቱ የሥም መቆጣጠሪያ በአግባቡ
መወሰዱን፣ ተፈታኞችም በሚፈተኑት የፈተና አይነት ቡክሌት ኮድ መሠረት በስም

19
መቆጣጠሪያ ቅፅ ላይ መፈረማቸውን፣የመልስ ወረቀቶችን ከተፈታኞቹ የምዝገባ
ቁጥር አንፃር በትክክል በማገናዘብና በቅደም ተከተል መቀመጡን፣ተጓዳኝ ቅፃቅጾች
በአግባቡ መሞላታቸውን በማረጋገጥና ከፈታኞች በመረከብ ለጣቢያ ኃላፊው
ያስረክባል፤
11.5.12 ፈታኝ በተጓደለበት ሁኔታ በፈታኝነት ተመድቦ የሚሰራ ሲሆን ክፍያው ግን
በሱፐርቫይዘር ስሌት ይፈፀምለታል፤
11.5.13 በተመደበባቸው ክፍሎች በመዘዋወር በተፈታኞች መልስ ወረቀት አናት ላይ
ፈታኙ የመዘገበው የቡክሌት ኮድ ቁጥር ተፈታኙ ከተሰጠው የፈተና ቡክሌት ኮድ
ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ሆኖም ግን ስርዝ ድልዝ ካለበት ፈታኙን
በመጠየቅና በማረጋገጥ ትክክለኛ ሆኖ ሲያገኘው ፈታኙ በመልስ ወረቀቱና በስም
መቆጣጠሪያ ቅፁ ላይ በፃፋቸው ቡክሌት ኮዶች ጐን በፊርማ እንዲያረጋግጥ
ያደርጋል፤
11.5.14 የመፈተን ተግባርና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ ፈታኞች ሲያጋጥሙ
ወዲያውኑ ለጣቢያ ኃላፊው ሪፖርት ያደርጋል፤
11.5.15 የፈተና ሥነ ሥርዓት ጉድለት የፈፀሙ ተፈታኞች ሲያጋጥሙ እንደአስፈላጊነቱ
የግል ወይም የቡድን የተፈታኞች የፈተና ደንብ መተላለፍ ሪፖረት ማቅረቢያ
ቅጾችን ከፈታኙ ጋር በመሙላትና በመፈረም ወዲያውኑ ለጣቢያ ኃላፊው ያቀርባል፤
11.5.16 በፈተና አሰጣጥ ሂደት ወቅት ከተፈታኞች በፈታኞች አማካይነት የሚቀርቡለትን
ችግሮች ማስታወሻ ይዞ ለጣቢያ ኃላፊው ያቀርባል፤
11.5.17 ማንኛውም በፈተና ስራ ላይ በሱፐርቫይዘርነት የተሰማራ ግለሰብ ተንቀሳቃሽ
ስልክ /ሞባይል/ ይዞ ወደ ፈተና ክፍሎች ውስጥ መግባትም ሆነ በአካባቢው መዘዋወር
በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን በመገንዘብ ሞባይሉን ሌላ ቦታ አስቀምጦ የመግባት
ኃላፊነት አለበት፤
11.5.18 የሱፐርቫይዘርነት አገልግሎቱን ለሠራበት የአገልግሎት ክፍያ(session)
በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ላይ ይፈርማል፣ ለቆየበት የውሎ አበል መፈረሚያ ቅጽ
በእስክሪብቶ በትክክል መቀመጡን በማረጋገጥ በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ላይ የባንክ
አካውንቱን ትክክለኛነት አረጋግጦ ይፈርማል፡፡

20
11.5.19 የጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተጓዳኝ ተግባራት ያከናውናል፡፡ በፈተና
አሰተዳደር ዙሪያ ከጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን ማንኛውም የአሰራር ስርዓት
ይቀበላል፣ ይተገብራል፣ ፈተና አፈፃፀሙንም በተመለከተ ሪፖርት ያቀርባል፤
11.5.20 መፈተኛ ክፍሎችና ዙሪያቸው ተገቢው የደህንነት ፍተሻ የተደረገላቸው መሆኑን
ያረጋግጣል፣ እንዲሆኑም ይሠራል፣
11.5.21 የተከለከሉ ቁሳቁሶችና መሣሪያዎች በመፈተኛ ክፍሎች ውስጥና ዙሪያ
እንዳይኖሩ ከሚመለከታቸው ጋር ይሰራል፣ ይከላከላል።
11.5.22 የፈተና ደንብ ጥሰትን ይከላከላል፣ ሲከሰቱም ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት
ይሰራል፣ ፈርሞ ሪፖርት ያደርጋል።
11.5.23 ፈተና በሚሰጥበት ዕለት ከጣቢያ ኃላፊ የተረከባቸውን የታሸጉ የዕለቱን ፈተናና
የመልስ ወረቀት የያዙ ፖስታዎችን ለፈታኞች ያስረክባል፣ ይከታተላል፡፡
11.5.24 ፈታኞችን፣ አይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢን እና መልስ ወረቀት አደራጆችን
ያስተባብራል፣ ወደ ስራ ያስገባል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
11.5.25 የመልስ ወረቀት በአግባቡ መደራጀታቸውን አረጋግጦና አሰባስቦ ለመልስ
ወረቀት ቆጣሪ ያሰረክባል፡፡
11.5.26 የተሰጠውን ሥራ አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከጣቢያ ኃላፊ በጽሑፍ
ይወስዳል፡፡
11.6 የፈታኝ ተግባርና ኃላፊነት

ፈታኝ ተጠሪነቱ ለሱፐርቫይዘር ሲሆን የሚከተሉት ተግባራትና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡-

11.6.1 የፈተና ሥራን በተመደበበት የፈተና ጣቢያ የመፈተኛ ክፍል በበላይነት ይመራል፣
ይከታተላል፣ የመፈተኛ ክፍል እና ተፈታኞች ለፈተና ስራ ዝግጁ መሆናቸውን
ያረጋግጣል፤
11.6.2 ፈታኙ በሚፈትንባቸው ቀናት ሁሉ ፈተናው ከመጀመሩ አንድ ሰዓት በፊት ለፈተና
ጣቢያ ኃላፊው ሪፖርት ያደርጋል፡፡ በሰዓቱ ተገኝቶ ሪፖርት ካላደረገ በቅርብ ኃላፊ
በኩል በሚቀርበው ሪፖርት መሰረት በሚመለከተው አካል እርምጃ እንዲወሰድ
ይደረጋል፤
11.6.3 አንድ ፈታኝ በአማካይ 36 ተፈታኞችን የመቆጣጠርና የመፈተን ግዴታ አለበት፡፡
ሆኖም እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታና እንደ መፈተኛ ክፍሎችና አዳራሾች
የመያዝ አቅም ከአማካኙ የተፈታኝ ቁጥር በላይ ሊፈትን ይችላል፤

21
11.6.4 ተፈታኞችን በሚፈተኑበት ክፍል/አዳራሽ በር ላይ በምዝገባ ቁጥራቸው ቅደም
ተከተል በማሰለፍ እና የምዝገባ መታወቂያ /Admission Card/ በማየት መቀመጫ
ያስይዛል፡፡ በተጨማሪም መፈተኛ ክፍል ውስጥ ከገቡ በኋላ የተፈታኞችን ማንነትና
የምዝገባ ቁጥር ያረጋግጣል፤
11.6.5 ተፈታኞች በምዝገባ ቁጥራቸው ቅደም ተከተል መሠረት መቀመጫቸውን ከያዙ
በኋላ የመልስ ወረቀቶችን ያድላል፣ በመልስ ወረቀት ላይ ያሉትን መረጃዎች
በትክክል መፃፍና ማጥቆራቸውን እየተዘዋወረ ይቆጣጠራል፣ በአግባቡ ያልሞሉና
ያላጠቆሩ ተፈታኞች ካሉ እንዲሞሉና እንዲያጠቁሩ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
11.6.6 ተፈታኞች ከእርሳስ፣ ከላጲስ፣ ከእርሳስ መቅረጫና ከማስመሪያ በስተቀር ሌሎች
የተከለከሉ ነገሮችን ማለትም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች /ሞባይልና ካልኩሌተር/
የመሳሰሉትን ወደ ፈተና ክፍል ይዘው እንዳይገቡ ይቆጣጠራል፤
11.6.7 በመልስ ወረቀቶች ላይ ያለው መረጃ በጥንቃቄ መሞላቱን ካረጋገጠ በኋላ የጥያቄ
ወረቀት የያዙ ፖስታዎችን በተፈታኞች ፊት በመክፈትና የቡክሌት ኮዶችን
መሠረት በማድረግ ወረቀቶችን ለተፈታኞች እንደ አቀማመጣቸው ያድላል፤
በትርፍነት የቀሩ የጥያቄ ወረቀቶችን ወዲያውኑ ሰብስቦ ለሱፐርቫይዘሩ ይሰጣል፤
11.6.8 የጥያቄ ወረቀት በሚታደልበት ጊዜ ጐን ለጐን እንዲሁም ፊትና ኋላ የተቀመጡ
ተፈታኞች አንድ አይነት ቡክሌት ኮድ እንዳይደርሳቸው ጥንቃቄና ጥብቅ ክትትል
ያደርጋል፡፡ በመልስ ወረቀት አናት ላይ በተሰጠው ቦታ ለተፈታኙ የተሰጠውን
የፈተና ቡክሌት ኮድ በእስክሪፕቶ ይጽፋል፤
11.6.9 የፈተናውን የጥያቄ ቅርጽና ይዘት አስመልክቶ ከተፈታኞች የሚቀርብ ማንኛውንም
ጥያቄ ማስታወሻ ይዞ በሱፐርቫይዘሩ አማካይነት ለጣቢያ ኃላፊ ከማቅረብ ባለፈ
ለተፈታኞች የመሰለውን ማስተካከያ መስጠት ፈፅሞ የተከለከለ ነው፤
11.6.10 ማንኛውንም ዓይነት የፈተና ደንብ የተላለፈ ተፈታኝ ሲገጥመው ከሱፐርቫይዘሩ
የግል የፈተና ደንብ መተላለፍ ችግሮች ሪፖርት ማቅረቢያ ቅፅ በመውሰድ ሞልቶና
ፈርሞ ለሱፐርቫይዘሩ ያቀርባል፡፡ በቡድን የተፈፀመ የፈተና ደንብ መተላለፍ ችግር
ሲገጥመው ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀውን ቅፅ በመሙላትና በመፈረም ለሱፐርቫይዘሩ
ያቀርባል፤
11.6.11 የየፈተናውን መጀመሪያና ማጠናቀቂያ ሰዓት ያስከብራል፤

22
11.6.12 እያንዳንዱ ተፈታኝ የተመዘገበበትን የት/ዓይነት ለመፈተኑ በተዘጋጀው
መቆጣጠሪያ ቅፅ (Attendance Sheet) ላይ የጻፈው የምዝገባ ቁጥርና የፈተናው
ወረቀት /ቡክሌት/ ኮድ ትክክለኛነት በተፈታኙ ስምና ፊርማ እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤
11.6.13 በፈተና ወቅት ተፈታኞችን ከመቆጣጠርና የፈተና አሰጣጥ ደንብ ከማስከበር
ውጭ በፈተና ክፍል ወይም አዳራሽ ውስጥ ፈተና ማንበብ ወይም ሌላ ሥራ
መሥራት በፍፁም አይፈቀድም፤
11.6.14 ተፈታኞች የሚያጋጥማቸው ችግር ሲኖር ወዲያውኑ መፍትሔ እንዲያገኙ
በቅርብ ላለው ሱፐርቫይዘር ወይም ለጣቢያ ኃላፊው ሪፖርት ማድረግ ይኖርበታል፤
11.6.15 ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ዘግይተው የሚመጡ ተፈታኞች ወደ ፈተና
አዳራሽ አንዳይገቡ፣ ፈተናው ከተጀመረ 45 ደቂቃ ሳይሞላ እንዳይወጡ፣
የመጨረሻው ደወል ከመደወሉ በፊት የሚወጡ ተፈታኞች ካሉ የፈተና ወረቀቱን
ይዘው እንዳይወጡ እና ለፈተናው ከተፈቀደው ጊዜ በመጨረሻው 15 ደቂቃ ውስጥ
መውጣት ስለማይፈቀድ የፈተና ወረቀቶች በሙሉ እስከሚሰበሰቡ ድረስ ተፈታኞች
መልስ መስጫ ወረቀታቸውን ገልብጠው በማስቀመጥ በቦታቸው በፀጥታ ተቀምጠው
እንዲጠብቁ ያደርጋል፤
11.6.16 ተፈታኞች በፈተና ክፍል ውስጥ ሲጋራ ማጨስና፣ ማስቲካ ማኘክ፣ ቆብ ማድረግ፣
ልብስ መከናነብ፣ ዕቃ መዋዋስና የመሳሰሉትን ተግባራት እንዳይፈጽሙ ይከላከላል፣
ይቆጣጠራል፤
11.6.17 በጣቢያ ኃላፊው በታወቀ ምክንያት የጊዜ ገደብ ለውጥ ካልተገለጸ በስተቀር
በጥያቄ ወረቀት የሽፋን ገጽ ላይ ለእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት በተፈቀደው ጊዜ
መሠረት ፈተናው እንዲካሄድ ያደርጋል፤
11.6.18 ፈተናው ተጀምሮ አስኪጠናቀቅ ድረስ ተፈታኞች የቀራቸውን ጊዜ በየ30
ደቂቃው ያስታውሳል፤
11.6.19 ሕጋዊ ምዝገባ አካሂደው ፈተናው ሲሰጥ ያልተገኙ ተፈታኞችን በትክክል
በማረጋገጥ የምዝገባ ቁጥራቸውን በተፈታኞች መቆጣጠሪያ ቅጽ (Attendance
Sheet) ግርጌ በተዘጋጀው ቦታ ላይ ያሰፍራል፤ ፊርማውንም ያኖራል፤
11.6.20 ፈተናው እንደተጠናቀቀ የመልስ ወረቀቶችን በእያንዳንዱ ቡክሌት ኮድ
በመለየትና በምዝገባ ቁጥር ቅደም ተከተል በማስተካከል፤ በተፈታኞች መቆጣጠሪያ

23
ቅፅ (Attendance Sheet) እና በስተግርጌ ከተፃፈው የቀሪዎች የምዝገባ ቁጥር ጋር
በማገናዘብ ለሱፐርቫይዘሩ ወዲያውኑ ያስረክባል፤
11.6.21 ማንኛውም በፈተና ስራ ላይ በፈታኝነት የተሰማራ ግለሰብ ተንቀሳቃሽ ስልክ
/ሞባይል/ይዞ ፈተና ክፍል ውስጥ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን በመገንዘብ
ሞባይሉን ሌላ ቦታ አስቀምጦ የመግባት ኃላፊነት አለበት፤
11.6.22 የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ሲጠናቀቅ የተፈታኞችን እና ሌሎች ለፈተና ስራ
አገልግሎት የተሰጡ ቁሳቁሶችን ከተፈታኞች በመሰብሰብ ለሱፐርቫይዘር ያስረክባል፣
11.6.23 የፈታኝነት አገልግሎቱን ለሠራበት የአገልግሎት ክፍያ(session) በተዘጋጀው
መቆጣጠሪያ ላይ ይፈርማል፣ ለቆየበት የውሎ አበል መፈረሚያ ቅጽ በእስክሪብቶ
በትክክል መቀመጡን በማረጋገጥ በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ላይ የባንክ አካውንቱን
ትክክለኛነት አረጋግጦ ይፈርማል፡፡
11.6.24 መፈተኛ ክፍሉ ተገቢው የደህንነት ፍተሻ የተደረገለት መሆኑንና ፈተና
ለማስፈተን ዕውቅና የተሰጠው መሆኑኑ አረጋግጦ ይረከባል።
11.6.25 በህግ ከተፈቀደለት ተፈታኝና ቁሳቁሶች ውጭ ማንኛውም በፈተና ክፍል
የተከለከሉ ቁሳቁሶች ወይም መሣሪያዎች ቀድመው በክፍሉ ውስጥ በማንኛውም ቦታ
አለመቀመጣቸውን እና ተፈታኞችም አለመያዛቸውን ያረጋግጣል፣
11.6.26 መፈተኛ ክፍል የገቡ ሁሉም ተፈታኞች የተፈታኞች መቆጣጠሪያ(attendance)
መፈረማቸውን እና የፈረሙት እያንዳንዳቸው የመልስ ወረቀት መመለሳቸውን
ያረጋግጣል።
11.6.27 የመልስ ወረቀትና የተፈታኞች መቆጣጠሪያ(attendance) በአግባቡ አደራጅቶና
ቆጥሮ ለሱፐርቫይዘር ያሰረክባል፡፡
11.6.28 የጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተጓዳኝ ተግባራት ያከናውናል፡፡
11.6.29 የተሰጠውን ሥራ አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከጣቢያ ኃላፊ በጽሑፍ
ይወስዳል፡፡
11.7 የዓይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢ ተግባርና ሃላፊነት

የዓይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢ ተጠሪነቱ ለሱፐርቫይዘር ሲሆን የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች
ይኖሩታል፡-

24
11.7.1 ለአንባቢነት የሚመለመው መምህር ወይም የልዩ ፍላጎት ትምህርት ባለሙያ
የተፈታኞችን የግል መረጃዎች (personal information) በከፍተኛ ጥንቃቄ መሙላት
ይኖርበታል፤
11.7.2 አንባቢው የፈተና ጥያቄዎችን ብዛትና የተመደበውን ሰዓት ለተፈታኞች ማሳወቅ
አለበት፤
11.7.3 አንባቢው ተፈታኙ ተደግሞ እንዲነበብለት በጠየቀ ጊዜ የተመደበውን ሰዓትና
ቀጣዩን ፈተና ግምት ውስጥ በማስገባት ደጋግሞ ማንበብ ይኖርበታል፤
11.7.4 አንባቢው አሻሚ የእንግሊዝኛ ድምጽ ያላቸው ቃላት ሲገጥሙ የትርጉም ልዩነት
ሊፈጥሩ ስለሚችሉ የእንዳንዱን ፊደል (spelling) ስም በመጥራት ለተፈታኞች
ማንበብ አለበት፤
11.7.5 አንባቢው አገልግሎት የሚሰጠው ዓይነ ስውር ተማሪ ተገቢ ባልሆኑ የመፈተኛ
ሥፍራ (በረንዳ፣ መተላለፊያ ኮሪደር ወዘተ) ላይ ሆኖ መፈተን እንደሌለበት ግንዛቤ
ሊኖረው ይገባል፤
11.7.6 በፈተና ስራው የተመደቡበት ኃላፊነት የዓይነ ስውራን ተፈታኞች አንባቢ ከሆነ
ተፈታኙ በሚረዳው አግባብ በእርጋታ እና በትዕግስት ያነባል፣ ከተፈታኙ የተሰጠውን
መልስ በመልስ መስጫ ወረቀት ላይ ያጠቁራል፤
11.7.7 አንባቢው ተፈታኙ ለእያንዳንዱ የፈተና ጥያቄ የሚሰጠውን መልስ በከፍተኛ
ጥንቃቄ በፈተና ጥያቄዎቹ ላይ ምልክት እያደረገ ወደ መልስ መስጫ ወረቀቱ
መገልበጥ የሚጠበቅበት ሲሆን ፈተናው እንደተጠናቀቀ በትክክል መልሶቹ
መገልበጣቸውን ያረጋግጣል፡፡
11.7.8 የአንባቢነት አገልግሎቱን ለሠራበት የአገልግሎት ክፍያ(session) በተዘጋጀው
መቆጣጠሪያ ላይ ይፈርማል፣ ለቆየበት የውሎ አበል መፈረሚያ ቅጽ በእስክሪብቶ
በትክክል መቀመጡን በማረጋገጥ በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ላይ የባንክ አካውንቱን
ትክክለኛነት አረጋግጦ ይፈርማል፡፡
11.7.9 የዓይነ ስውር ተፈታኝ ተማሪ መፈተኛ ቦታ ተገቢው የደህንነት ፍተሻ የተደረገለት
መሆኑንና ፈተና ለማስፈተን ዕውቅና የተሰጠው መሆኑኑ አረጋግጦ ይረከባል።
11.7.10 የዓይነ ስውር ተፈታኝ በተሰጠው የስም ዝርዝር እና የፈተና አዳራሽ መግቢያ
ካርድ መሠረት ያስቀምጣል፣

25
11.7.11 በህግ ከተፈቀደለት ተፈታኝና ቁሳቁሶች ውጭ ማንኛውም በፈተና ቦታ የተከለከሉ
ቁሳቁሶች ወይም መሣሪያዎች ቀድመው አለመቀመጣቸውን እና ተፈታኙም
አለመያዙን ያረጋግጣል፣
11.7.12 የፈተና መጀመሪያና ማቆሚያ ሰዓትን ይቆጣጠራል፣ ተጨማሪ የተፈቀደላቸውን
በአንድ ሰዓት ውስጥ 20 ደቂቃ እንዲጠቀሙ ያደርጋል፡፡
11.7.13 በመፈተኛ ቦታ የፈተና ደንብ ጥሰትን ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል፣ ተከስቶ ሲገኝም
በአግባቡ መዝግቦ ይዞ በተሰጠው ቅጽ መሠረት ሞልቶና ፈርሞ ሪፖርት ያደርጋል፡

11.7.14 ተፈታኙ አቴንዳንስ መፈረሙን እና የመልስ ወረቀት መመለሱን ያረጋግጣል
11.7.15 መልስ ወረቀቱን ለሱፐርቫይዘር ቆጥሮ ያስረክባል፡፡
11.7.16 የጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተጓዳኝ ተግባራት ያከናውናል፡፡
11.7.17 ሥራውን አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከጣቢያ ኃላፊ በጽሑፍ
ይወስዳል፡፡
11.8 የመልስ ወረቀት ቆጣሪ ተግባርና ኃላፊነት

የመልስ ወረቀት ቆጣሪ ተጠሪነቱ ለጣቢያ ኃላፊ ሲሆን የሚከተሉት ኃላፊነት ተግባራት
ይኖሩታል፡-

11.8.1 በየፈተና ወቅቱ መጨረሻ የመልስ ወረቀቶችን ከሱፐርቫይዘሮች ቆጥሮ ይረከባል፤


11.8.2 ከፈተና ጣቢያ ኃላፊው፣ ከኮሌጅ ወይም ትምህርት ክፍሉ ተወካይ ጋር በመሆን
የመልስ ወረቀቶችን በየፈተናዎቹ አይነት፣ ኮድና በተፈታኞች የምዝገባ ቁጥር ቅደም
ተከተል በማደራጀት በፖስታ ያሽጋል፤
11.8.3 በታሸጉት ፖስታዎች ላይ ይፈርማል፣ ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ እንዲቀመጡ
በማድረግ ለጣቢያ ኃላፊው እገዛ ያደርጋል፤
11.8.4 በታሸገው ፖስታ ላይ በተፃፈው ቁጥርና በፖስታው ውስጥ ባለው የመልስ ወረቀት
ብዛት መካከል ልዩነት ከተፈጠረ ተጠያቂ ይሆናል፤
11.8.5 አንድ መልስ ወረቀት ቆጣሪ እስከ 1000 የመልስ ወረቀቶች በሴሽን ቆጥሮ
የመረከብ ኃላፊነት አለበት፤
11.8.6 በፈተና ጣቢያው ውስጥ የተሰራባቸውን የመልስ ወረቀቶች የያዙትን ፖስታዎች
ውሃ እንዳያበላሻቸው በላስቲክ ጠቅልሎ በጥንቃቄ በሸራ ከረጢት ውስጥ በመክተት

26
የሸራውን አፍ በካቦ አስሮ ይቆልፋል፡፡ የተቆለፈበትን ቁልፍም በወረቀት ጠቅልሎ
ያሽጋል፤
11.8.7 የሸራው/ዎቹ ቁልፍ/ቁልፎች በአንድ ፖሰታ ውስጥ ተከተው ፖስታው ይታሸጋል፡፡
ፖስታው ሊከፈትባቸው በሚችልባቸው ቦታዎች ላይ የት/ቤቱ ማሕተም
እንዲመታበት ያደርጋል፤
11.8.8 የተረካቢነት አገልግሎቱን ለሠራበት የአገልግሎት ክፍያ(session)በተዘጋጀው
መቆጣጠሪያ ላይ ይፈርማል፣ የባንክ አካውንቱን ትክክለኛነት አረጋግጦ ይሰጣል፡፡
11.8.9 የጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተጨማሪ ስራዎች ያከናውናል፡፡
11.8.10 የመልስ ወረቀቶችን ተፈታኞች ከፈረሙት የተፈታኞች
መቆጣጠሪያ(attendance) ፊርማ ጋር ያመሳክራል፣ እኩል መሆናቸውን ቆጥሮ
ያረጋግጣል።
11.8.11 የዓይነ ስውር ተፈታኝ ተማሪ መልስ ወረቀት ይሰበስባል፤ ያደራጃል።
11.8.12 የመልስ ወረቀቶች ያልተቀደዱ፣ ያልተቦጨቁ፣ ያልተቆረጡ፣ ያልተበሱ እና
እርጥበት ያልነካቸው መሆናቸውን ያረጋግጣል። እንደዚህ ዓይነት ነገር ሲከሰትም
ለፈታኝ ሪፖርት ያደርጋል፡፡
11.8.13 የመልስ ወረቀቶችን ያደራጃል፣ ለፈታኝ ያሰረክባል።
11.8.14 በአግባቡ የተደራጀውንና የተቆጠረውን የመልስ ወረቀትን ለጣቢያ ኃላፊ
ያሰረክባል።
11.8.15 ሥራውን አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከጣቢያ ኃላፊ በጽሑፍ
ይወስዳል፡፡
11.9 የፈተና አስፈፃሚዎች መመልመያ መስፈርት

11.9.1 የመጀመሪያ ድግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያለው፣ በመምህርነት ወይም
በትምህርት ባለሙያነት፣ትምህርት አመራርነት ያገለገለ ሆኖ ለጉድኝት ማዕከል
አስተባባሪነት 10 ዓመት፣ ለጣቢያ ኃላፊነት 7 ዓመት፣ ለሱፐርቫይዘር 5 ዓመት፣
ለፈታኝነት 02 ዓመት እና ከዚያ በላይ አገልግሎት ያለው ፤
11.9.2 የስራው ባህርይ በሚፈለገው አግባብ ተንቀሳቅሶ ለመስራት የአካል እና የአእምሮ
ዝግጁነት ያለው፤ ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ የፈተና ቁሳቁስ ተረክቦ ማስረከብ
የሚችል፤ ከማንኛውም ደባል ሱስ ነፃ የሆነ፤

27
11.9.3 ቀደም ሲል በፈተና አስፈፃሚነት ሰርቶ የሚያውቅ ከሆነ ምንም ዓይነት የስነ ስርዓት
ደንብ መተላለፍ (ጥፋተኝነት) መረጃ ያልተያዘበት መሆን ይገባዋል ወይም
ማስረጃ/ሪከርድ/ ተይዞበት ከሆነ እንደጥፋቱ ሁኔታ የውሳኔ ወይም የይቅርታ ጊዜ
ገደቡ የተጠናቀቀ መሆን አለበት፤
11.9.4 የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሚመድበው በየትኛውም የፌዴራል
መንግስት ክልል በሚገኙ የፈተና መስጫ ማዕከል፣ ጣቢያ ወይም መፈተኛ ክፍል
ኃላፊነቱን ተቀብሎ በቦታው በሰዓቱ በመገኘት ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ፤
11.9.5 በስራው አጋጣሚ የሚያገኛቸውን ሚስጥሮች የመጠበቅ እንዲሁም የፈተና ደንብ
መተላለፍ ከመፈፀሙ በፊት ሁኔታውን የሚከላከል፣ ተፈጽሞ ከተገኘም ሁኔታውን
በተዋረድ ለሚመለከተው አካል ለማቅረብ የሚችል፣ ለዚህም በቅርብ ኃሊፊው ወይም
በስራ ባልደረቦቹ ምስክርነት የተሰጠው፤
11.9.6 በስሩ ያለ የፈተና አስፈፃሚዎችን ሰርቶ የማሰራት እና የመምራት ብቃት ያለው
ስለመሆኑ ቅርብ ኃላፊው እና በስራ ባልደረቦቹ ምስክርነት የተሰጠው፣
11.9.7 ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ የመልስ መስጫ ወረቀቶችን እንዲሁም የፈተና ቁሳቁስ
ከፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ተረክቦ ለቅርብ ተጠሪው ማስረከብ የሚችልና ፈቃደኛ
የሆነ፡፡
11.9.8 ለዓይነ -ስውራን ተፈታኞች በአንባቢነት መምረጫ መስፈርት ከፈታኞች ጋር
ተመሳሳይ ሆኖ ጥሩ የማንበብ ልምድ ያለው፣ ታጋሽ የሆነ፣ ለረጅም ጊዜ መቆየት
የሚችል ቢሆን ይመረጣል፤
11.9.9 ለዓይነ-ስውራን አንባቢነት ለመመደብ አመልካች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን
የተከታተለ ወይም መሰረታዊ የልዩ ፍላጎት ዕወቀትና ክህሎት ስልጠና የተከታተለ
ከሆነ ቅድሚያ የማግኘት መብት አለው፤
11.10 በልዩ ሁኔታ የፈተና አስፈፃሚዎችን ስለመመደብ
11.10.1 ከላይ ከ11.9.1 እስከ 11.9.9 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በፈተና አስተዳደር ስራ
እንደፈተና ጣቢያው የተፈታኞች ብዛት እና ስፋት አንፃር በመመልከት በፈተና ስራ
አስፈፃሚነት የሚመለመሉ ተሳታፊዎች በተዋረድ የሚገኘው የፈተና አስፈፃሚ ተሳታፊዎች
ምልመላ እና ምደባ ኮሚቴ ለአገልግሎቱ በማቅረብ ሲፈቀድለት የራሱን የመመልመያ
መስፈርቶችን በማዘጋጀት ሊመለምል እና ሊመድብ ይችላል፡፡

28
11.10.2 የፈተና ስራ አስፈፃሚዎች ምልመላ አደራጃጀት በተዋረድ እንደሚገኘው የትምህርት
ስራ አስፈፃሚ አካል የሚወሰን ሆኖ በሁሉም ተዋረድ በሚቋቋም ኮሚቴ የመሰረታዊ
መምህራን ማህበር ኃላፊ ወይም ተወካይ በአባልነት ያካተተ መሆን አለበት፡፡
11.10.3 የፈተና አስፈጻሚዎች ምደባ በማእከል በተዘጋጀ የምደባ መተግበሪያ አማካኝነት
በአገልግሎቱ የሚከወን ሲሆን የምደባ ውጤቱም በአጭር የጹሑፍ መልእክት
ለእያንዳንዱ ፈጻሚ እንዲደርሰ ይደረጋል፣
11.10.4 በውጪ ሀገራት ለሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ከላይ ከ11.9.1 እስከ 11.9.9 የተጠቀሰው
እንደተጠበቀ ሆኖ የተሻለ የፈተና አስተዳደር ልምድ ያላቸው የአገልግሎቱ
ባለሙያዎች በውድድር እንዲመደቡ ይደረጋል፤ ዝርዝር አፈጻጸሙም በማንዋሉ
የሚገለጽ ይሆናል፡፡

ክፍል አምስት
የፈተና አስፈጻሚዎችና ተፈታኞች መብትና ግዴታ
12. የፈተና አስፈጻሚዎች መብትና ግዴታዎች
12.1 የፈተና አስፍጻሚዎች መብት
12.1.1 ማንኛውም የፈተና አስፈጻሚ ከፈተና አስተዳደር ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ጠይቆ
የመረዳት መብት አለው፡፡
12.1.2 በህጉ የተፈቀደለትን የውሎ አበልና የአገልግሎት ክፍያ(session) ክፍያዎችን
በወቅቱ የማግኘት መብት አለው፡፡
12.2 የፈተና አስፈጻሚዎች ግዴታ
12.2.1 በተመደደበት የፈተና ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) እንዲገኝ በተወሰነው ሰዓት፣ ቀንና ቦታ
የመገኘትና የተሰጠውን የፈተና አስፈጻሚነት ተግባር የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡
12.2.2 የፈተና ደንብ ጥሰትን የመከላከል እና ተከስቶም ሲገኝ ፈርሞ ሪፖርት የማቅረብ
ግዴታ አለበት፡፡
12.2.3 የተፈታኞችንና ፈተና አስፈጻሚዎችን መብት የማክበር ግዴታ አለበት፣
12.2.4 በተዋረድ የጥያቄና የመልስ መስጫ ወረቀቶችን የመረከብና በአግባቡ አደራጅቶ
የማሰረከብ ግዴታ አለበት።
12.2.5 ለፍትህ አካላት በተለይም ለፌዴራል ፖሊስ የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡

29
12.2.6 ተፈታኞች በአግባቡ መፈተሻቸውን፣ የተከለከሉ ነገሮችን አለመያዛቸውንና
አለመጠቀማቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለበት፡፡
12.3 ለፈተና አስፈጻሚዎች የተፈቀዱ ነገሮች

12.3.1 የማዕከል ኃላፊ፣ የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ እና ጣቢያ ኃላፊ ፡- ስልክ ከመፈተኛ
ክፍል ውጪ እንዲይዙና እንዲጠቀሙ
12.3.2 ቀድሞ ምንም ያልተጻፈበትን ማስተወሻ ደብተር እና አስክርብቶ እንዲጠቀሙ
የተፈቀደ ነው፡፡
12.3.3 ማንኛውም የፈተና አስፈጻሚ በሐኪም የተፈቀደለትን መነጽር ሊጠቀም ይችላል፡፡
12.4 ለፈተና አስፈጻሚዎች የተከለከሉ ነገሮች

12.4.1 ማንኛውም ማዕከል ኃላፊ፣ የጉድኝንት ማዕከል አስተባባሪ፣ ጣቢያ ኃላፊ፣


ሱፐርቫይዘር፣ ፈታኝ፣ የዓይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢ፣ የመልስ ወረቀት ቆጣሪ እና
ሌሎች የፈተና ግብረ ኃይል አባላት በሙሉ ወደ መፈተኛ ክፍል እና አካባቢ ስልክ፣
ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት እና ሌሎች ማንኛውንም ፎቶ፣
ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን መያዝና መግባት
ክልክል ነው፡፡
12.4.2 ማንኛውም ፈታኝና ሱፐርቫይዘርና የመልስ ወረቀት አደራጅ ማንኛውንም ዓይነት
መጽሐፍ፣ መጽሔት፣ ጋዜጣ፣ በመፈተኛ ክፍል ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም
የተከለከለ ነው፡፡
12.4.3 ማንኛውም ፈታኝና ሱፐርቫይዘርና የመልስ ወረቀት አደራጅ የጆሮ ጌጥ፣ የጸጉር
ጌጥ፣ የአንገት ሐብል ወይም ጌጥ፣ የእጅ አምባር፣ የጣት ቀለበት ይዞ መገኘትም ሆነ
ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የጋብቻ ቀለበት የተፈቀደ ነው፡፡
12.4.4 ማንኛውም ፖሊስ በልዩ ሁኔታ በጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ ወይም በጣቢያ ኃላፊ
ህግ ለማስከበር ተጠይቆ ካልሆነ በስተቀረ መፈተኛ ክፍል መግባት የተከለከለ ነው፡

12.4.5 ከፖሊስ በስተቀረ ማንኛውም የፈተና አስፈጻሚ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ፣
ስለት ያለው ወይም ሹል ብረት/ፕላስቲክ በፈተና ማዕከል ይዞ መገኘትም ሆነ
መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

30
12.4.6 ማንኛውም ፖሊስ (የጸጥታ አካል) በህግ የተፈቀደውን ዓይነት ዩኒፎርም በአግባቡ
ሳይለብስ በፈተና አስፈጻሚነት በፈተና ማዕከል መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
12.4.7 በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ማስቲካ ማኘክ የተከለከለ ነው፡፡
13. የተፈታኞች መብትና ግዴታ
13.1 የተፈታኞች መብት
13.1.1 ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት
አለው፡፡
13.1.2 በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና
ትራስ የማግኘት መብት አለው፡፡
13.1.3 ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ
ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣
የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አለው፡፡
13.1.4 የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው፡፡
13.1.5 በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ
ጠረጴዛ የማግኘት መብት አለው፡፡
13.1.6 ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ የማግኘት መብት አለው፡፡
14. 1 የተፈታኞች ግዴታ
14.1.1 ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን የመፈተኛ ካርድ(admission card)
ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት፡፡
14.1.2 ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት
መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት፡፡
14.1.3 ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ለሚካሄደው
ሙሉ አካላዊ ፍተሻ ለጸጥታ አካላት ትብብር የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
14.1.4 ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ
ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን መያዝ የለበትም።
14.1.5 ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት፤
14.1.6 ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት፡፡

31
14.1.7 ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና
አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን
ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
14.1.8 ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ
አለበት፡፡
14.1.9 ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን
ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት፡፡
14.1.10 ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድልብስና
የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።
14.2 ለተፈታኞች የተፈቀዱ ነገሮች
ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡ ይዘው እንዲመጡ እና ግቢ ውስጥ እንዲጠቀሙ
የተፈቀዱ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡
14.2.1 አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማርና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበረ ማስታወሻ ደብተር፣
የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት ደረቅ
ምግቦች ወይም ቶሎ የማይበላሹ ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)
14.2.2 ገንዘብ (ብር)፣ የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ
14.2.3 የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ፣ የጥርስ ብሩሽ፣
የጥርስ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣
የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)
14.3 ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች
በፈተና ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) እና መፈተኛ ክፍሎች ውስጥ የተከለከሉ ነገሮች
የሚከተሉት ናቸው፡፡
14.3.1 ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ፣ ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና
ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
14.3.2 ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም
ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል
የግል ዕቃ/መሳሪያ /ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣
ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች
ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን

32
በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ
ነው፡፡
14.3.3 በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣
ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም
መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
14.3.4 ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሐኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት
(በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም
የተከለከለ ነው፡፡
14.3.5 ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡

14.3.6 ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ
አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት
በስተቀረ)
14.3.7 ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ
45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡
14.3.8 ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን
ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡
14.3.9 በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ
ነው
14.3.10 በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ
ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡
ክፍል ስድስት

የፈተና ደንብ መተላለፍ እና የስነ ስርዓት እርምጃ አፈፃፀም


15. የተፈታኞች የፈተና ደንብ መተላለፍ እና የስነ ስርዓት እርምጃ አፈፃፀም
15.1 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተግባራት የፈፀመ ተፈታኝ የተፈተናቸው እና የሚፈተናቸው
ፈተናዎች ውጤት ሙሉ በሙሉ ይሰረዝበታል፡፡
15.1.1 ከተሰጠው ምዝገባ ቁጥር ውጪ በሌላ ተፈታኝ ምዝገባ ቁጥር ሌላ ሰው (ተፈታኝ)

ሲያስፈትን፣ ለሌላ ተፈታኝ ሲፈተን ወይም ሲሰራ የተገኘ ወይም እነዚህን


ስለመፈፀሙ በመረጃ የተረጋገጠበት ከሆነ፤

33
15.1.2 በመፈተኛ ግቢ ወይም በፈተና ክፍል ውስጥ በግሉ ወይም ሌሎች ተፈታኞችን
በማሳደም የፈተና አስፈፃሚዎችን የሰደበ፣ የደበደበ፣ መጥፎ ስራ ለመስራት የዛተ
ወይም የሞከረ ወይም የፈተና ጣቢያውን ያወከ ወይም እነዚህን ደንብ መተላለፍ
ተግባራት ስለመፈፀሙ በመረጃ የተረጋገጠበት ከሆነ፣
15.1.3 በፈተና ክፍል ውስጥ ሌላውን ተፈታኝ ተረጋግቶ ፈተናውን እንዳይሰራ ያወከ፣
የፈተና ወይም የመልስ ወረቀት የቀማ ወይም ማንኛውንም ዓይነት የኃይል ወይም
የጉልበት ተግባር በሌላ ተፈታኝ ላይ የፈፀመ፤
15.1.4 የፈተና ጥያቄ ወረቀት ከፈታኙ ከተቀበለ በኋላ ወደ ውጭ እንዲወጣ ለማድረግ
የሞከረ ወይም ያወጣ ወይም ከውጭ የመጣ የፈተና ወይም የመልስ ወረቀት
ወይም ሌላ ለፈተና ደንብ መተላለፍ አገልግሎት የሚሰጥ ቁስ(መሳሪያ) የተቀበለ፣
በቁሱ የፈተና መልስ የሰራ፤
15.1.5 በመፈተኛ ግቢ ወይም በፈተና ክፍል ውስጥ ሞባይል ስልክና ሌሎች
ኤሌክትሮኒኪስ መሳሪያዎችን ይዞ የተገኘ ወይም መልዕክት በመቀበል፣ በመላክና
በመጠቀም ሂደት ላይ የተገኘ ወይም በተዛማጅ መሳሪያ ደንብ መተላለፍ
ተግባራት ስለመፈፀሙ በማረጃ የተረጋገጠበት ከሆነ፤
15.1.6 በሚፈጽመው ቀላል ደንብ መተላለፍ ምክንያት በፈታኙ የሚሰጠውን ምክርና
ተግሳፅ ባለመቀበል በአንድ የፈተና ክፍለ ጊዜ ተደጋጋሚ ጥፋቶች የፈፀመ ወይም
ለመፈፀም የሞከረ ከሆነ፤
15.1.7 ከፅህፈት መሳሪያ ውጪ ሌሎች ያልተፈቀዱ ቁሶችን በተለይም የስለት መሳሪያ
እና ሰውን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮች ይዞ መፈተኛ ግቢ ወይም ክፍል ለመግባት
መሞከር፣ መግባት፣ ለመጠቀም መሞከር፣ መጠቀም፤
15.1.8 የዘመኑን የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሳያጠናቅቅ ለፈተና የተቀመጠ፤ በሀሰተኛ
የትምህርት ማስረጃ የተማረ ወይም የተመዘገበ ስለመሆኑ ሪፖርት የቀረበበት፤
ቀደም ሲል ፈተናውን ተፈትኖ የዘመኑን ማለፊያ ነጥብ አግኝቶ እያለ በፈተና
ላይ ተቀምጦ የተገኘ ከሆነ፤
15.1.9 ከአንድ በላይ በሆነ የፈተና ወረቀት ወይም የመልስ ወረቀት ለመፈተን የሞከረ
ወይም ሲፈተን የተገኘ ከሆነ፤

34
15.2 በፈተና አሰጣጥ ወቅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተግባራት የፈፀመ ተፈታኝ ጥፋት
የፈጸመባችው የፈተና አይነት ወይም ውጤቶች ብቻ ይሰረዝበታል፡
15.2.1 ከሌላ ተፈታኝ ለመኮረጅ ወይም ስለትምህርቱ ይዘት የተፃፈበት የተቆራረጠ
ማስታወሻ (ብጣሽ ወረቀት)ወይም በሰውነት ክፍሉ ወይም በልብሱ በመያዝ መልስ
ለመስራት የሞከረ፣
15.2.2 የፈተና ወረቀት ወይም ሌላ የመፈተኛ ቁስ እንዳያገለግል አድርጎ ያበላሸ ከሆነ
ወይም ለማበላሸት የሞከረ ከሆነ ወይም ስለማበላሸቱ በማስረጃ የተረጋገጠበት ከሆነ፤
15.2.3 የፈተና አስተዳደር ስራን ሊያውክ የሚችል አለባበስ (ስካርቭ፣ ባርኔጣ፣ ቆብ፣ ሻሽ
፣ መጠኑ የበዛ አለባበስ) አድርጎ በመምጣት ፈተናውን ለማወክ የሞከረ
15.2.4 ከሌላ ተፈታኝ ለመኮረጅ ወይም ስለትምህርቱ ይዘት የተፃፈበት የተቆራረጠ
ማስታወሻ (ብጣሽ ወረቀት)ወይም በሰውነት ክፍሉ ወይም በልብሱ በመያዝ መልስ
ለመስራት መሞከር የፈተና
15.2.5 የፈተና ወረቀት ወይም ሌላ የመፈተኛ ቁስ እንዳያገለግል አድርጎ ያበላሸ ከሆነ
ወይም ለማበላሸት የሞከረ ከሆነ ወይም ስለማበላሸቱ በማስረጃ የተረጋገጠበት ከሆነ፤
15.2.6 የፈተና መልስ ወረቀት ማስረከብ ሲገባው በማወቅም ሆነ ባለማስተዋል ሳያስረክብ
ከመፈተኛ ክፍል የወጣ ከሆነ፣ ከመልስ ወረቀት በተጨማሪ ሌላ መመለስ ያለበት
ቁስ መመለስ ሲገባው ሳይመልስ ከመፈተኛ ክፍል የወጣ ከሆነ፤
15.2.7 ፈታኙ የሰጠውን የፈተና ወረቀት /ቡክሌት ኮድ ከሌላ ተፈታኝ ጋር ካቀያየረ፤
የተፈታኞች መቆጣጠሪያ(attendance) ላይ ወይም በመልስ መስጫ ወረቀት ራስጌ
ላይ ከተፃፈው ቡክሌት ኮድ ጋር ሲመሳከር ልዩነት ካሳየ፤
16. የፈተና አስፈጻሚዎች ደንብ መተላለፍና የስነ ሥርአት እርምጃ አፈጻጸም
16.1 በፈተና መስጫ ግቢ ወይም መፈተኛ ክፍል ውስጥ ከተፈቀደለት ፈተና አስፈፃሚ

(የፈተና ጣቢያ ኃላፊ) በስተቀር ማንኛውም ሰው ሞባይል ስልክና ሌሎች ኤሌክትሮኒክስ


መሣሪያ መያዝ አይፈቀድም ይዞ ከተገኘም ከፈተና አስፈፃሚነቱ ይሰናበታል፣ አግባብነት
ባለው ሕግም ይጠየቃል፤
16.2 ከላይ በተራ ቁጥር 15.1 የተደነገገውን የተላለፈ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደተጠበቀ
ሆኖ 5 ዓመት ከፈተና አስፈፃሚነት ይታገዳል፤
16.3 በፈተና ስራ አስፈፃሚነት የተሳተፈ ይህንን መመሪያ በሚፃረር ተግባር ውስጥ
የተሳተፈ፣ ያስፈፀመ አግባብ ባላው ህግ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፤

35
16.4 ሀሰተኛ መረጃ የሰጠ አስፈፃሚ አግባብ ባለው ህግ ተጠያቂ ይሆናል፤
16.5 ማንም አስፈፃሚ በስራ አጋጣሚ ያወቀውን ሚስጥር ይፋ ያደረገ እንደሆነ አግባብ
ባለው ሕግ ተጠያቂ ይሆናል፤
16.6 በፈተና ስራ አስፈፃሚነት ተመድቦ ተፈታኞችን እንዲኮራራጁ የፈቀደ ወይም የፈተና
ሂደቱን ያስተጓጎለ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደተጠበቀ ሆኖ 5 ዓመት ከፈተና አስፈፃሚነት
ይታገዳል፣ አግባብ ባለው ሕግም ተጠያቂ ይሆናል፡፡
16.7 በፈተና ስራ አስፈፃሚነት ተመድቦ በፈተና ወቅት ያለበቂ ምክንያት ወይም ፍቃድ
የቀረ፤ በተደጋጋሚ ያረፈደ፤ ወዲያውኑ ከፈተና አስፈፃሚነት ይታገዳል፣
16.8 በፈተና ስራ አስፈፃሚነት ተመድቦ የተፈታኞችን መብት ያላከበረ፣ ያንጓጠጠ፣ የሰደበ
ያሸማቀቀ መሆኑ በማስረጃ ከተረጋገጠ 2 ዓመት ከፈተና አስፈፃሚነት ይታገዳል፣
16.9 አንድ የፈተና ስራ አስፈፃሚ ከቅርብ ሀላፊው የሚሰጠውን የስራ ትዕዛዝ ባለመቀበሉ
ወይም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ተባብሮ ባለመስራቱ ምክንያት የፈተና ስራው እክል
ቢገጥመው፤ ይህም በማስረጃ ከተረጋገጠ ከፈተና አስፈፃሚነት ይታገዳል፣
16.10 የመልስ ወረቀቶችን እና የተለያዩ ኣስፈላጊ ቅጻቅጾችን በአግባቡ አደራጅቶ
ለሚመለከተዉ አካል ያላስተላለፈ ከሆነ ይህም በማስረጃ ከተረጋገጠ ከፈተና አስፈፃሚነት
ይታገዳል፣
17. ፈተናን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ስለመሰረዝ

17.1 በፈተና አሰጣጥ ወቅት የሥነ ሥርዓት ጉድለት እንደተፈፀመና ፈተና በሕገ ወጥ
መንገድ በግል፣ በቡድን፣በክፍል ደረጃ ወይም በፈተና ጣቢያ ደረጃ እንደተሰራ
የሚጠቁም መረጃ ከተገኘ ወይም በፈተና ውጤት ግሽበት ወይም መናር መነሻ ምክንያት
መሆኑ ሲረጋገጥ አገልግሎቱ የተፈታኞችን ውጤት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ
መብት አለው፤
17.2 ከላይ በተራ ቁጥር 16.1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ድርጊቱን የፈጸሙት በፈተና
ስራ አስፈፃሚነት የተመደቡ ባለሙያዎች ወይም ሌሎች አካላት መሆኑ ከተረጋገጠ
አስተዳደራዊ ቅጣት እንደተጠበቀ ሆኖ 5 (አምስት) ዓመት ከፈተና አስፈፃሚነት
ይታገዳሉ አግባብነት ባለው ሕግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

36
ክፍል ሰባት
17. የፈተና አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት
17.1 የክልል ወይም የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ተግባርና ኃላፊነት

17.1.1 የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት (12ኛ ክፍል) ፈተና


ከምዝገባ ጋር የተያያዙ ስራዎች በአግባቡ መከናወናቸውን ያረጋግጣሉ፤
የማስተካካያ እርምጃም ይወስዳሉ፤
17.1.2 በተፈታኞች ምዝገባ ወቅት ቦታዎች እንዲመቻቹ እንዲሁም አስፈላጊ ግብዓት
እንዲሟሉ ድጋፍ ያደርጋል፤
17.1.3 መዝጋቢዎች የሚመዘግቡበት ት/ቤቶችን በክልሉ ተጨባጭ ሁኔት በመለየት
የምዝገባው ሂደት በአግባቡ እንዲከናወን ያደርጋል፤
17.1.4 በተዋረድ ለዞን፣ለወረዳ ፣ለልዩ ወረዳ፣ ለከተማ አስተዳደር እንዲሁም ለት/ቤት ርዕሳነ
መምህራን የምዝገባው ሂደት በተገቢው መንገድ እንዲከናወን የቅድመ ዝግጅት
ስራዎችን በአግባቡ እንዲሰሩ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል ፤
17.1.5 የምዝገባ ማስተግበሪያ ቴክኖሎጅ መሳሪያ ወይም አስፈላጊ ግብአቶች መኖራቸውን
በማረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል.
17.1.6 በፌደራል ደረጃ የተዘጋጀውን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ
ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና የፈተና አሰጣጥ ማስፈጸሚያ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ስለ
አፈጻጸሙም ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ለአገልግሎቱ ሪፖርት ያደርጋል፤
17.1.7 በትምህርት ዘመኑ ነባር እና አዲስ ፈተና የሚያስፈትኑ ትምህርት ቤቶችን
አጠቃላይ የቅድመ ፈተና መረጃ እና የተፈታኞች ብዛት መረጃ ለአገልግሎቱ
በወቅቱ ያሳውቃል፤
17.1.8 በተፈታኞች ምዝገባ እና ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ይከታተላል፣
በተዋረድ ይሰጣል፣ አፈፃፀሙን በተመለከተ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
17.1.9 የፈተና አስፈፃሚዎችን ይመለምላል፣ ያሰማራል፣ አፈፃፀሙ ሰላማዊ እና ከፈተና
ደንብ መተላለፍ የፀዳ እንዲሆን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ ችግር ሲፈጠር
አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ የፈተናው ስራ እንዲቀጥል ያደርጋል፤

37
17.1.10 በቅድመ ፈተናና ድህረ ፈተና ወቅት ተፈታኞችን ወደ ፈተና ማዕከላት ወይም
ዩኒቨርስቲ የማድረስና የመመለስ ስራ እንዲሰሩ ዞኖችን ከክልል ትራንስፖርት
ቢሮ ጋር በመቀናጀት ያግዛል፣ ያስተባብራል፣ ይከታተላል፤
17.1.11 በክልል እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ የተዘጋጀውን የፈተና አስተዳደር
ማስፈፀሚያ በጀት መነሻ በማድረግ በተዋረድ ለሚመለከተው አካል እንዲደርስ
ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን በተመለከተ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ ሰነዱን ለገንዘብና
ኢኮኖሚ በማቅረብ በወቅቱ ያወራርዳል፤
17.1.12 በክልሉ ወይም በከተማ አሰተዳደሩ የፈተና አስተባባሪ ግብረ ኃይል ያቋቁማል፣
አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፣ በፌደራል ደረጃ ለሚቋቋመው ግብረ ኃይል ስራውን
በተመለከተ ግብዓት ይሰጣል፡፡
17.1.13 የክልሉ ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያደርጉትን ጉዞ የትራንስፖርትና
ሎጀስቲክስ ቢሮ ከክልሉ መንግስትና ከሚመለከታቸው ጋር ሆኖ ያመቻቻል፡፡
17.1.14 የክልሉ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች በሚደረገው ምደባ አገልግሎቱና እና
በክልሉ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቅርበት ይሠራል፣ ያመቻቻል፣ ይተባበራል፤
17.1.15 የአስፈጻሚዎች ምደባ ሲታወቅም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንዲሄዱ ጥሪ
ያስተላልፋል፣ መሄዳቸውን ይከታተላል፣ ተመድበው ያልሄዱ ሲገኙም እንደ
አስፈላጊነቱ እርምጃ ይወስዳል፣ ያስወስዳል፤
17.1.16 ከባለድርሻ አካላት ጋር በፈተና ደህንነት መረጋገጥና ደንብ ጥሰት መከላከል ላይ
ውይይት ያደርጋል፣ ግንዛቤ ይፈጥራል፣ ጸረ ኩረጃ ንቅናቄ ያደርጋል፤

17.2 የዩኒቨርስቲ ተግባርና ኃላፊነት


17.2.1 የፈተና ማዕከሉን (የዩኒቨርሲቲውን /ከምፓሱን /ኮሌጁን) የፈተና ስርዓት የሚመራ
የተለያየ ግብረ ኃይል ያቋቁማል፣ አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፣
17.2.2 ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ጋር የተማሪዎችን ትራንስፖርት
(የማድረስና የመመለስ) ስራ እና ምደባን በሚመለከት በቅርበትና በቅንጅት
ይሠራል፤ ይተባበራል፡፡
17.2.3 እንደ አስፈላጊነቱ ከክልል ወይም ከከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ አመራር፣
የክልል /የከተማ አስተዳደር የፍትህ አካላት (ፍርድ ቤቶችና የጸጥታ አስተዳደር
አካላት) እንዲሁም የአከባቢው የመንግስትና የጸጥታ አስተዳደር ጋር ጥምር ግብረ

38
ኃይል ሊያቋቁም፣ ለትምህርት ሚኒስቴር አሳውቆ ተግባርና ኃላፊነት ሊሰጥ ይችላል፡

17.2.4 በክልል እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ለተቋቋመው ግብረ ኃይል ስራውን
በተመለከተ መረጃ ይለዋወጣል፤ የፈተናው ሂደት ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ
በየቀኑ አፈፃጸሙን ይገመግማል፣ ይከታተላል፣
17.2.5 በፈተናው ሂደት ውስጥ የሚገጥሙ ችግሮችን ፈጣን የሆነ ምላሽ በመስጠት
ይፈታል፣
17.2.6 የፈተናውን አፈፃጸም ከግብረ ኃይሉ ጋር በየዕለቱ በመገምገም የሚታዩ ክፍተቶችን
እንዲሟሉ ያደርጋል፣
17.2.7 ለፈተና ጉዳይ የተመደበውን በጀት ከፋይናስ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር
ለሚፈለገውና ለተፈቀደለት የሰው ኃይል እንዲውል አቅጣጫ ይሰጣል፤
ያስተባብራል ይመራል፤
17.2.8 የፈተና አስተዳደር አፈፃፀሙ ሰላማዊ እና ከፈተና ደንብ መተላለፍ የፀዳ እንዲሆን
ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል.፤ ችግር ሲፈጠር በተዋረድ ሪፖርት ያደርጋል፣
አስፈሊጊውን እርምጃ በመውሰድ የፈተናው ስራ እንዲቀጥል ያደርጋል፤
17.2.9 የፈተና አስተዳደር ማስፈፀሚያ በጀት መነሻ በማድረግ የፈተና አስፈፃሚዎች
የክፍያ ሰነድ በማዘጋጀት ክፍያ ይፈፅማል፣ ሂደቱን በተመለከተ ክትትልና ድጋፍ
ያደርጋል፣ ሂሳቡን በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያወራርዳል፤
17.2.10 በቅድመ ፈተና እና በፈተና አሰጣጥ ሂደት ከስራው ጋር በተያያዘ የመፈተኛ
ጣቢያዎች የፈተና አስተዳደር እና ለተፈታኞች ዝግጁ መሆናቸውን በተዋረድ
ሱፐርቪዢን በማድረግ ያረጋግጣል፣ አስፈሊጊውን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
17.2.11 የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ከፈተና ደንብ መተላለፍ ነፃ ሆኖ በሰላማዊ እና በተረጋጋ
ሁኔታ እንዲካሄድ አስፈሊጊውን ሁሉ ያደርጋል፣ ያልተጠበቁ ችግሮች ሲከሰቱ
አፊጣኝ ምላሽ በመስጠት የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ እንዲቀጥል ያደርጋል፡፡
17.2.12 ተፈታኝ ተማሪዎች ግቢ ከመግባታቸው በፊት የመኝታ ክፍሎች፣ አልጋ፣ ፍራሽ፣
ትራስና የተለያዩ ቁሳቁሶች እንዲሟሉ ያደርጋል፣ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ
መሆናቸውን ያረጋግጣል፣ ድልደላ ያካሂዳል፤ ተፈታኞች የህክምና አግልግሎት
እንዲያገኙ ያደረጋል፣ አገልግሎቶች በሚጠበቀው ደረጃ መኖሩን ያረጋግጣል፣

39
የድንገተኛ ህክምና ክፍሎችን ያዘጋጃል፣ ክሊኒኩ 24 ሰዓት አገልግሎት እንስዲሰጥ
ያደርጋል፤
17.2.13 በግቢ ውስጥ የመብራት፣ የሱቆች፣ ሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ ጸጉር ቤቶች፣
ካፍቴሪያዎች ኖረው ተፈታኞች እንዲጠቀሙ ያደርጋል፤
17.2.14 የመኝታ፣ የሻውርና የመጸዳጃ ክፍሎችን የንብረት አያያዝና አጠቃቀም ስርዓት
ግንዛቤ ይሰጣል፣ አፋፃጸሙን ይቆጣጠራል፣
17.2.15 የግቢውን አጠቃላይ ደህንነት ለመጠበቅ ከጸጥታ አካል ጋር በመቀናጀት የሰዓት
ዕላፊ ገደብ ህግ በማውጣት ያሳውቃል፣ ይከታተላል፣
17.2.16 ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆነ የማደሪያና መፀዳጃ ቦታዎችን ለይቶ ያዘጋጃል፣
እንደአስፈላጊነቱ ድጋፍ የሚሰጡ ሰዎችን ይመድባል፤
17.2.17 በየኮሌጁ/በየካምፓሱ/ የተመደቡ ተፈታኝ ተማሪዎች ቁጥር ልክ በየሰዓቱ የቁርስ፣
የምሳና እና የእራት አገልግሎት የተሟላ እንዲሆን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
ያልተሟሉ ግብአቶችን በወቅቱ በመለየት እንዲቀርቡ ያደርጋል፣
17.2.18 አስፈላጊ የሆኑ የውሃና የመብራት አገልግሎቶች በቅድመ ዝግጅት የክንውን ጊዜ
ውስጥ እንዲሟሉ ያደርጋል፤ ሲቋረጡም አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣል፤
17.2.19 የፈተና አስፈጻሚዎችን ክፍያ በተዘጋጀው መመሪያ የክፍያ ማስፈጸሚያ ተመን
(breakdown) መሰረት አዘጋጅቶ ክፍያ እንዲፈጸም ያደርጋል፣ ይከታተላል፣
ይደግፋል፡፡ የሂሳብ ማወራረድ ሂደትን ያስፈጽማል፣
17.2.20 በየካምፓሱ ለፈተና ደህንነት ጥበቃ ምቹ የሆኑ የፈተና መከዘኛዎችን ያዘጋጃል፤
17.2.21 ፈታኝ፣ የዓይነ ስውር ተፈታኞች አንባቢ እና የመልስ ወረቀት አደራጅ
ይመለምላል ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያሳውቃል፡፡
17.2.22 በተመደቡለት የተፈታኝ ተማሪዎች ቁጥር ልክ መፈተኛ ክፍሎችን ያዘጋጃል፣
በቂና ለፈተና ምቹ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
17.2.23 ለፈተና የተመደቡ ሱፐርቫይዘሮችን፣ ፈታኝ መምህራንና የአይነ ስውራን
አንባቢዎችን በየፈተና ክፍሉ ከጣቢያ ኃላፊ ጋር በመሆን ይደለድላል፣ ለስራው
ውጤታማነት ይተባበራል፤

40
17.2.24 ከፈተና አሰጣጥ ስራ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ቁሳቁሶችን ከአገልግሎቱ ይረከባል፣
ምስጥራዊነቱና ደህንነቱን ባስጠበቀ መልኩ ልዩ ጥበቃ ያስደርጋል፣ ስራው ሲጠናቀቅ
ተመላሽ በማድረግ ለአገልግሎቱ እንዲደርስ ያደርጋል፤

17.2.25 ተፈታኞችን በፈተና ጣቢያና በተፈታኞች መለያ ቁጥር ቅደም ተከተል


የሚፈተኑበትን ክፍል በመመደብ ያሳውቃል፣ ወደ መፈተኛ ክፍል በአግባቡ
ተፈትሸው እንዲገቡ ያደርጋል፤

17.2.26 የመልስ ወረቀቶችን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን በትምህርት ቤት እና


በተፈታኝ አይነት፣ በተፈታኞች መለያ ቁጥር (Reg. No) ቅደም ተከተል
እንዲሰበሰብ፣ ተቆጥሮ እንዲታሸግና ርክክብ እንዲደረግ ይተባበራል፣

17.2.27 የዩንቨርስቲው ግብረ ኃይል አመራርና አባላት በፈተና ወቅት ወደ መፈተኛ


ክፍል ከ50 ሜትር ርቀት ውስጥ መግባትና ወደ ክፍል ውስጥ መግባት የተከለከለ
ነው፡፡

ለተፈታኞች ለፈተና አሰጣጡ የሚያስፈልጉ የጽህፈት መሳሪያዎችንና የተለያዩ


ግብአቶችን በወቅቱ እንዲቀርቡ ያደርጋል፣

17.3 የዞን እና የክፍለ ከተማ ትምህርት መምሪያ ወይም የልዩ ወረዳ ጽ/ቤት ተግባርና
ኃላፊነት

17.3.1 ትምህርት ዘመኑ ነባር እና አዲስ ፈተና የሚያስፈትኑ ትምህርት ቤቶችን እና


አጠቃላይ ቅድመ ፈተና መረጃ እና የተፈታኞች ብዛት መረጃ ለክልሉ ያሳውቃል፣
ከመረጃው ጋር ተያይዞ የሚዘጋጁ ሰነዶችን ትክክለኛነት ያረጋግጣል፤
17.3.2 ለወረዳ ት/ጽ/ቤት ለምዝገባ የተለዩ ት/ቤቶችን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው
ለምዝገባ ዝግጁ እንዲሆኑ መመሪያ ይስጣል፤
17.3.3 የግል፤ የማታ፤ የርቀትና የበይነ መረብ መስመር (Online) ተፈታኞች የቅድመ
ዶክመንት ምርመራ ለምዝገባ ብቁ በሚያደርጉ መስፈርቶች መሰረት ዝግጁ ሆነው
እንዲጠብቁ ያደርጋል፤
17.3.4 የመዝጋቢዎችን የመመዝገቢያ ላፕቶፕ እና እንተርኔት አክሰስ እንዲሁም አስፈላጊ
ግብአቶች መኖራቸውን በማረጋገጥ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
17.3.5 በዞኑ ምዝገባ ሲጠናቀቅ የማረጋገጥ ስራን ይሰራል፤ተፈላጊ መረጃዎችንና ሰነዶችን
አደራጅቶና አጣርቶ ለአገልግሎቱ እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

41
17.3.6 የማታ፣ የግል፣የርቀት፣የበይነ መረብ መስመር (Online) እና መንግስታዊ ያልሆኑ
መደበኛ ተመዝጋቢዎች የክፍያ ዝርዝር ለአገልግሎቱ ገቢ የተደረገበትን የባንክ
ደረሰኝ እና ሌላ ክፍያ የተፈፀመባቸውን የሂሳብ ሰነዶች በመመሪያው መሰረት
ለሚመለከተው ያስረክባል ሂሳቡም ተመርምሮ እንዲወራረድ ያደርጋል
17.3.7 ፈተና አስፈፃሚዎችን በተሰጠው ኮታና መመልመያ መስፈርት መሰረት
ይመለምላል፣ ለክልሉ ያሳውቃል፤ በተመደቡበት የፈተና ማዕከል እንዲሄዱ
ያሳውቃል፤
17.3.8 በቅድመ ፈተናና ድህረ ፈተና ወቅት ተፈታኞችን ወደ ፈተና ማዕከላት ወይም
ዩኒቨርስቲ የማድረስና የመመለስ ስራ እንዲሰሩ ወረዳዎች ከዞን ትራንስፖርት
መምሪያ ጋር በመቀናጀት ያግዛል፣ ያስተባብራል፣ ይከታተላል፤
17.3.9 የፈተና አስተዳደር ማስፈፀሚያ በጀት መነሻ በማድረግ ለፈተና አስፈፃሚዎች
የክፍያ ሰነድ በማዘጋጀት ክፍያ ይፈፅማል፣ ሂደቱን በተመለከተ ክትትልና ድጋፍ
ያደርጋል፣ ሂሳቡን በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያወራርዳል፤
17.3.10 በተዋረድ የፈተና አስተባባሪ ግብረ ኃይል ያቋቁማል፣ አፈጻጸማቸውንም
ይከታተላል፣ በክልል እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ለሚቋቋመው ግብረ ኃይል
ስራውን በተመለከተ ግብዓት ይሰጣል፤
17.4 የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት

17.4.1 በትምህርት ዘመኑ ነባር እና አዲስ ፈተና የሚያስፈትኑ ትምህርት ቤቶችን እና


አጠቃላይ ቅድመ ፈተና መረጃ እና የተፈታኞች ብዛት መረጃ ለዞን ትምህርት
መምሪያ ያሳውቃል፣ ከመረጃው ጋር ተያይዞ የሚዘጋጁ ሰነዶችን ትክክለኛነት
ያረጋግጣል፤
17.4.2 ለምዝገባ አስፈላጊ ግብዓቶችና መሰረተ ልማቶችን ት/ቤቶች አዘጋጅተው
እንዲያቀርቡ ያደርጋል
17.4.3 የግል፣ የማታ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ መደበኛ ት/ቤቶች፣ የርቀትና የበይነ መረብ
መስመር (Online) ተፈታኝ ተማሪዎች ለምዝገባ ብቁ በሚያደርጉ መስፈርቶች
መሰረት ዶክመት አጣርቶ ያቀርባል ፤
17.4.4 ምዝገባ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ ለተመዝጋቢዎች ስለ ምዝገባው እና ስለ አፈጻጸም
መርሃ ግብሩ ተገቢውን መረጃ እና ገለጻ እንዲሰጣቸው ያደርጋል፤

42
17.4.5 የምዝገባ ሂደቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ እንዲሰራ ክትትልና ድጋፍ
ያደርጋል
17.4.6 በቅድመ ፈተናና ድህረ ፈተና ወቅት ተፈታኞችን ወደ ፈተና ማዕከላት ወይም
ዩኒቨርስቲ የማድረስና የመመለስ ስራ ይሰራል፣ የጉዞ ደህንነታቸውን ይከታተላል፤
17.4.7 በተዋረድ የፈተና አስተባባሪ ግብረ ኃይል ያቋቁማል፣ አፈጻጸማቸውንም
ይከታተላል፣ በዞን እና ክፍለ ከተማ ደረጃ ለሚቋቋመው ግብረ ኃይል ስራውን
በተመለከተ ግብዓት ይሰጣል፤
17.5 የትምህርት ቤት (የፈተና ጣቢያ) ተግባርና ኃላፊነት

17.5.1 የትምህርት ቤቱን ተፈታኞች መረጃ አዘጋጅቶ ለወረዳ ትምህርት ጽፈት ቤት


ይልካል፤
17.5.2 የት/ቤቱ ሁሉም ተመዝጋቢ ተማሪዎች ስለመመዝገባቸው ያረጋግጣል፤
17.5.3 የትምህርት ቤቱን የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ምዝገባ በአግባቡ እንዲካሄድ ምቹ
ሁኔታ ይፈጥራል፤ ለትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ስለ ምዝገባ ገለፃ ይሰጣል
17.5.4 የተፈታኞችን ዝርዝር በተመዝጋቢ አይነት መደበኛ እና የማታ (regular, night)
ለይቶና አረጋግጦ ለመዝጋቢው ያቀርባል፤
17.5.5 እንደተመዝጋቢው ብዛትና እንደ ምዝገባ መርሃ ግብሩ መሰረት በቀን ምን ያህል
ተመዝጋቢ መመዝገብ እንዳለበት ለይቶ በማደራጀት ተመዝጋቢዎች ዝግጁ
እንዲሆኑ ያደርጋል፤
17.5.6 የተመዘገቡት ተማሪዎች ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ከመዝጋቢው ቅጂ ወስዶ
በማስታወቂያ ቦርድ ላይ በመለጠፍ ተመዝጋቢዎች እንዲያረጋግጡ ያደርጋል፤
17.5.7 ምዝገባው ሲጠናቀቅ በተሰጠው ሮስተር መሰረት ምዝገባው ስለመከናወኑ
ትክክለኛነቱን ከመዝጋቢው ጋር ማረጋገጫ በመፈራረም፤ የተመዝጋቢዎችን ዝርዝር
መረጃ በሚገባ አደራጅቶና አረጋግጦ ለአገልግሎቱ እንዲደረስ ለሚመለከተው ክፍል
ያስረክባል፤
17.5.8 የመደበኛ ተፈታኞችን አጠቃላይ መረጃ ለሚመለከተው አካል በህጋዊ ደብዳቤ እና
በወቅቱ በሚፈለገው መረጃ የማስተላለፊያ መንገድ በተዋረድ ያቀርባል፤
17.5.9 የትምህርት ቤቱን የዘመኑን ተፈታኞች ግለ ታሪክ በሚፈለገው የጥራት ደረጃ
አጠናቅሮ ይይዛል፤

43
17.5.10 ተፈታኞች እና ት/ቤቱ ለፈተና አሰጠጥ ሂደቱ ዝግጁ እንዲሆኑ በቅድመ ፈተና
ወቅት አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፣ ያልተሟሉ ሁኔታዎች ካሉ እንዲሟሉ
ያደርጋል፤
17.5.11 ለትምህርት ቤቱ ተፈታኞች የሚያስፈልጉ የፈተና ማስተግበሪያ ቴክኖሎጂዎችን
ይረከባል፣ ደህንነታቸውን ይጠብቃል፤ ተደራሽነት ያለው ስለመሆኑ ያረጋግጣል፤

17.6 የፌደራል የጽጥታና የደህንነት ተቋማት ተግባርና ኃላፊነት

ከፌደራል ፖሊስ የሚመለመሉና ከተመደቡት መካከል አንድ ኃላፊ በመወከል


ይመራል፣ ተጠሪነቱ ለፌደራል ፖሊሲ ሆኖ በየፈተና ማዕከላቱ ራሱን በቻለ አንድ
የአመራር ሰንሰለት በአጃቢነትና በፈታሽነት የሚሰሩ ይሆናል፡፡
17.6.1 ከማእከል የተመደቡ የፌደራል ፖሊስ አባላት ፈተናውን ከህትመት ጀምሮ እስከ
ፈተና መስጫ ጊዜ ድረስ የ24 ሰዓት ጥበቃ ያደርጋል፣ በስርጭት ጊዜ አጅቦ ወደ
መፈተኛ ማዕከል ያደርሳል፤
17.6.2 ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ለፈተና ጥያቄ ወረቀቶችና በየቀኑ
በተፈታኞች መልስ ለተሰጠባቸው የመልስ መስጫ ወረቀቶች ማስቀመጫ የሚሆን
ደህንነቱ የተጠበቀ ምቹ ክፍል መሆኑን ያረጋግጣል፣ ለክፍሉም የ24 ሰዓት ጥበቃ
ያደርጋል፤
17.6.3 የፈተና ማስቀመጫው ክፍል በሚከፈትበትና በሚዘጋበት ወቅት ሁሉ የፈተና
አሰጣጡን ሥራ ከሚመሩት አካላት ጋር በመሆን የፈተናውን ደህንነት ይቆጣጠራል፤
17.6.4 የፈተና ጥያቄ ወረቀቶች ወደ መፈተኛ ክፍል ሲጓጓዙና ተፈታኞች መልስ
የሰጡባቸው የመልስ መስጫ ወረቀቶች ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ ሲጓጓዙ አስፈላጊውን
እጀባ ያደርጋል፣
17.6.5 የመልስ ወረቀቶችን በእጀባ የመመለስ እና የስርቆት ወይም ጉዳት የማድረስ ወንጀል
እንዳይፈጸም የመከላከል እና የመጠበቅ ግዴታ ይወጣል፤
17.6.6 የፖሊስ አባላት ተገቢውን ዲስፕሊን ጠብቀው እየሠሩ መሆናቸውን ይከታተላል፣
እንደ አስፈላጊነቱ የእርምት እርምጃ ይወስዳል፡፡
17.6.7 ማንኛውም ተፈታኝና ፈተና አስፈጻሚ ወደ ፈተና ማዕከልና መፈተኛ ክፍል ይዞ
እንዳይገባና እንዳይጠቀም የተከለከሉ ነገሮችን አለመያዙንና አለመጠቀሙን
ያረጋግጣል። አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡

44
17.6.8 ማንኛውም ተፈታኝና የፈተና አስፈጻሚ መብቱ እንዲከበርና ግዴታዉን እንዲወጣ
ከሚመለከታቸው ጋር በትብብር ይሰራል፣ መፈጸማቸውንም ይከታተላል፣
አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፣ እንዲወሰድም ያደርጋል።
17.6.9 በፈተና ማዕከል ደረጃ ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርስቲ ሲገቡ እና ወደ መፈተኛ ክፍል
ሲገቡ በእጅና በመፈተሻ መሳሪያ (Metallic Detector) በአግባቡ ይፈትሻል፡፡
ስልክን ጨምሮ ማንኛውን ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ይዘው እንዳይገቡ ያደረጋል፣
17.6.10 በፈተና ጣቢያ በመገኘት ከመፈተኛ ክፍል ውጭ /በፈተና ጣቢያ ግቢና በዙሪያው/
ያለውን ለፈተና አሰጣጡ ሂደት አዋኪ የሆነ ማንኛውንም አይነት እንቅስቃሴ
ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊ ከሆነም ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፤
17.6.11 ከፈተና ጣቢያ ኃላፊና ሱፐርቫይዘሮች የሚቀርቡለትን የደንብ ማስከበር
ጥያቄዎች ተቀብሎ አስፈላጊ ከሆነም የጣቢያ ኃላፊው ጥያቄ ሲያቀርብ ብቻ ወደ
መፈተኛ ክፍል በመግባት ሥርዓት አልበኞችን ይቆጣጠራል፤
17.6.12 በፈተና አስፈጻሚነት ለሚሳተፉ የትምህርት ባለሙያዎች የፈተና አሰጣጡ ሂደት
እስከሚጠናቀቅ ድረስ በፈተና ጣቢያ ግቢም ሆነ ውጭ አስፈላጊውን ክትትልና
የደህንነት ጥበቃ ያደርጋል፤
17.6.13 የፈተና ጣቢያ ኃላፊው በወሰነው ቦታ በመሆን ተገቢውን ስነ ስርዓት የማስከበር
ተግባር ያከናውናል፤ ለልዩ እርዳታ ካልተፈለገ በቀር ወደ መፈተኛ ክፍሎች
መግባትና መጠጋት አጥብቆ የተከለከለ ነው፤
17.6.14 አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከክልል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት የፈተና ማዕከሉን የጸጥታ
ሁኔታ ያስከብራሉ፣
17.7 የክልል ፖሊስ ተግባርና ኃላፊነት
ከክልል ፖሊስ የሚመለመሉና ተጠሪነታቸውም ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ይሆናል፤
17.7.1 ከፈተና ማዕከላት ግቢ ውጭ እና በአካባቢው ተፈታኞችን ሊረብሹ የሚችሉ
ይከላከላሉ፤ እርምት ይወስዳል፣ ለሚመለከተው ሪፖርት ያደርጋል፤
17.7.2 ተፈታኞች በመሄጃና በመመለሻ ጊዜ የሚገጥሟቸውን የጸጥታ ችግሮች በማጣራት
አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋሉ፤
17.7.3 ከፌደራል የተመደቡ አጃቢና ፈታሽ ፖሊስ እገዛቸውን ሲፈልጉ በመነጋገር ድጋፍ
ያደርጋሉ፤

45
17.8 የፈተና መሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ተግባርና ኃላፊነት
17.8.1 አስፈታኝ ትምህርት ቤቶች በምዝገባ ወቅት አስፈላጊውን ያልተቆራረጠ
የመብራትና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣
17.8.2 አስፈታኝ ትምህርት ቤቱ በፈተና ወቅት ያልተቆራረጠ የመብራትና እንደ
አስፈላጊነቱ ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣
17.8.3 ለአስፈታኝ ትምህርት ቤቶች የሚያስፈልጉ ደህንነታቸው የተጠበቀ ሌሎች
መሰረተ ልማቶች በየደረጃው እንዲሟሉ ማድረግ፣
17.9 የሙያና የብዙሃን ማህበራት ተግባርና ኃላፊነት
17.9.1 በየደረጃው በሚካሄዱ የፈተና አስፈጻሚዎችም ምልመላ፣ መረጣ እና ምደባ ሂደት
ላይ በንቃት በመሳተፍ ብቃት ያላቸው የፈተና አስፈጻሚዎችን ወደ ምዘና
ሥርአቱ እንዲመጡ ማድረግ፣
17.9.2 የአካል ጉዳት ያለባቸውን ተፈታኞች ዝርዝር መረጃ በምዝገባ እና ከፈተና
አሰጣጥ በፊት በየትምህርት ቤቶቹ እንዲሰባሰብ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ
የአወንታዊ ድጋፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፣
17.9.3 በተገልጋዮች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በየደረጃው ለሚገኙት የትምህርት
መዋቅሮች በማቅረብ ወቅታዊ ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ፣
17.9.4 በአገልግሎቱ የሚወጡ ፕሮግራሞችን፣ የአፈጻጸም መመሪያዎችንና የተለያዩ
መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች በወቅቱ በማጋራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፣
ክፍል ስምንት
19. የፈተና እርማትና ውጤት አገላለፅ ሂደት
19.1 የፈተና እርማት ሂደት
19.1.1 የተፈታኞች መልስ ወረቀትና የቀሪ ተፈታኞች መቆጣጠሪያ ለእርማት በሚያመች መልኩ
በትምህርት ቤት እና በተፈታኝ አይነት በተፈታኞች መለያ ቁጥር (Reg. No) ቅደም
ተከተል ተሰብስቦ፣ ተቆጥሮና ታሽጎ ርክክብ ይደረጋል፣
19.1.2 የተፈታኞች የመልስ ወረቀት በማንበቢያ ማሽኖች(optical mark readers)ተነበው
ያለምንም ንክኪ ወደ መረጃ ቋት ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲገቡ ይደረጋል፤
19.1.3 በእርማት ሂደት የሚከናወኑ የመረጃ ማጥራት ሥራዎች በቀሪ ተፈታኞች፣ የፈተና
ደንብ ጥሰት በፈጸሙ ተፈታኞችና የትምህርት ቤት መለያ ቁጥር አሳስተው በተፈተኑ
ተፈታኞች ላይ ብቻ በማተኮር እንዲሰራ ይደረጋል፣

46
19.1.4 የፈተና እርማት የሚካሄድበት ክፍል በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በመታገዝ እና
በደህንነት መጠበቂያ መሳሪያ ጭምር የ24 ሰዓት ጥበቃና ሌሎች የደህንነት መፈተሻ
ሶፍትዌሮችን በመጠቀም የእርማት ስራው በአስተማማኝኝ ሁኔታ እንዲካሄድ
ይደረጋል፣
19.1.5 የፈተና እርማት በሚሰራበት ክፍል ውስጥ ማንኛውም ባለጉዳይ መግባት አይቻልም፤
የክፍሉም ሰራተኞች ማንኛውንም አይነት ሞባይልና የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ይዞ
መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
19.1.6 በተፈታኞ ምዝገባና ውጤት ጥንቅር የተመደበ ባለሙያ ስራውን ለመስራት ወደ
ሲስተሙ ለመግባት ከተሰጠው የመግቢያ ስምና የራሱ የይለፍ ቃል(password) ውጭ
መጠቀም አይቻልም፤
19.1.7 ዝርዝር የሆኑ የእርማት ሂደት አፈጻጸሞችን በማንዋል ተዘጋጅተው በምዝገባና
እርማት መተግበሪያው ላይ እንዲጫኑ ይደረጋል፤ ከእርማት መተግበሪያውና ክፍሉ
ውጪ ማሳተም፣ ወደ ውጪ ማውጣትና ሌላ አካል ማስተላለፍ አይቻልም፤
19.1.8 ወደ እርማት ክፍል ውስጥ የገባ የተፈታኞች መልስ ወረቀት በማንኛውም ምክንያት
ከክፍሉ ተመልሶ ሊወጣ አይችልም፤
19.1.9 በእርማት ወቅት እና ከእርማት በኃላ የፈተና መረጀ ደህንነት ለመቆጣጠር
የሚያስችል ስርአት (Exam Log Management Audit) በመዘርጋት ተግባራዊ
ይደረጋል፣
19.1 የፈተና ውጤት አገላለፅ
19.1.1 ፈተናው የተሰጠው በበይነ መረብ መስመር (Online) ወይም በቴክኖሎጂ በተደገፈ
ከሆነ ውጤት የሚገለፀው የመጨረሻው ፈተና በተጠናቀቀ በአምስት የስራ ቀናት
ይሆናል፤
19.1.2 ፈተናው የተሰጠው ወረቀትን መሰረት ያደረገ ከሆነ ውጤት የሚገለፀው የመጨረሻው
ፈተና በተጠናቀቀ በ45 ቀን ጊዜ ውስጥ ይሆናል፤
19.1.3 የእርማት ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የተፈታኞች ውጤት በአጭር የጽሁፍ መልዕክት
እና በአገልግሎቱ ገጸ ድር(website) ይገለጻል፡፡
19.1.4 ከተፈታኞች ውጪ የፈተና ውጤቱን የሚጠየቁ ባለድርሻ አካላት ተፈታኞች
ውጤታቸውን ተመልክተው ቅሬታ ለማቅረብና ምላሽ ለመሰጠት የተሰጠው ጊዜ
ከተጠናቀቀ በኃላ በኃላፊነትና በተጠያቂነት ፈርመው እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡

47
ክፍል ዘጠኝ
20. የፈተና አስተዳደር ልዩ ልዩ ክፍያዎች አፈፃፀም
20.1 ውሎ አበል
20.1.1 የቀን ውሎ አበል ክፍያ በሲቪል ሰርቪስ የመንግስት ሰራተኞች የሀገር ውስጥ
የቀን ውሎ አበል ክፍያ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2012 መሰረት ተፈፃሚ
ይሆናል።
20.1.2 የፈተና አስፈፃሚዎች የመስክ ላይ ቆይታ እንደተሰጣቸው ኃላፊነት የሚወሰን
መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ዝርዝር የቆይታ ቀን እና የክፍያ አሰራር በማንዋል
በተቀመጠው አግባብ ይፈፀማል።
20.1.3 የፈተና አስፈፃሚዎች በፈተና አሰጣጥ ወቅት በዩኒቨርሲቲው የመኝታ
አገልግሎት የሚያገኙ ከሆነ በሲቪል ሰርቪስ መመሪያ መሰረት ከቀን ውሎ አበል
ክፍያ ተመን ላይ አርባ በመቶ ተቀናሽ ሆኖ ቀሪው ስድሳ በመቶ የቀን ውሎ
አበል ተከፋይ ይሆናል።
20.1.4 የፈተና አስፈጻሚዎች የመኝታ አገልግሎት በራሳቸው የሚሸፍኑ ከሆነ ሙሉ
የቀን ውሎ አበል ክፍያ የሚከፈለው ይሆናል፣
20.1.5 በሱፐርቪዥን እና በማዕከል ደረጃ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ፈተናውን
በማስፈፀም ሂደት ለሚሳተፉ የአገልግሎቱ ባለሙያዎች የቀን ውሎ አበል
አከፋፈል መመሪያ መሰረት ክፍያው ተፈፃሚ ይሆናል።
20.2 የአገልግሎት (ሴሽን) ክፍያ
20.2.1 የአገልግሎት (ሴሽን) ክፍያ በትምፈአ ረቂቅ ሰነድ ተዘጋጅቶ በሚመለከተው
የመንግስት ከፍተኛ አካል በፀደቀ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
20.2.2 አንድ የፈተና ክፍለ ጊዜ በሁለት የአገልግሎት (ሴሽን) ክፍያ የሚገለጽ መሆኑ
እንደተጠበቀ ሆኖ የፈተና አስፈፃሚዎች የሰሩበትን የፈተና አሰጣጥ ክፍለ ጊዜ
ፊርማ ብዛት መሰረት በማድረግ ይከፈላል፣
20.2.3 በሱፐርቪዥን እና በማዕከል ደረጃ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ፈተናውን
በማስፈፀም ሂደት ለሚሳተፉ ተሳታፊዎች በማንዋሉ በተቀመጠው ዝርዝር
የአገልግሎት (ሴሽን) ተመን መሰረት ክፍያው ተፈፃሚ ይሆናል።

48
20.3 የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ
20.3.1 የፈተና አስፈፃሚዎች እና ተፈታኞች ከፈተና አስተዳደር ስራ ጋር በተያያዘ
የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚጠቀሙ ይጠበቃል። ይህን መሰረት በማድረግ
የአገልግሎት ክፍያ በመንገድ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የመንገድ ትራንስፖርት
አገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ተሳቢነት ተፈፃሚ ይሆናል።
20.3.2 በመንግስት የተቀመጠው አፈፃፀም ሂደት ተፈፃሚ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ
በየብስ ወይም / እና በአየር መንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ደረሰኝ ሲቀርብ
ክፍያው ተፈፃሚ ይሆናል።
20.3.3 ባህላዊ የመጓጓዣ አገልግሎት የሚጠቀም ፈተና አስፈፃሚ እንደአካባቢው
ተጨባጭ ሁኔታ በፈተና አስፈፃሚ ግብረ ኃይል በሚወሰን ውሳኔ ክፍያ ተፈፃሚ
ይሆናል።
20.3.4 ተፈታኞች ከሚኖሩበት ወረዳ ወደ መፈተኛ ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) እንዲሁም
ከመፈተኛ ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) ወደሚኖሩበት ወረዳ ያለው ርቀት ታሳቢ ተደርጎ
የሚሰራ ቢሆንም ወጪው እንደ አስፈላጊነቱ በክልሎች ወይም በተፈታኞች
እንዲሸፈን ይደረጋል ።
20.4 የመረጃ ልውውጥ አገልግሎት ወጪ ክፍያ
20.4.1 ፈተና አስፈፃሚዎች ካላቸው የስራ ኃላፊነት እና ተደጋጋሚ የመረጃ ልውውጥ
አስፈላጊነት አንፃር በማንዋል ላይ ባለው የካርድ ተመን ወይም የጥቅል
አገልግሎት ዝርዝር አፈፃፀም መሰረት የመረጃ ልውውጥ አገልግሎት ወጪ ክፍያ
ተፈፃሚ ይሆናል።
20.4.2 ክፍያው ለተጠቃሚው በቀጥታ የአየር ሰዓት ካርድ በመግዛት ወይም የድምጽ፣
የመልዕክት እና የኢንተርኔት አገልግሎት ጥቅል በመግዛት የሚፈፀም ይሆናል።
20.5 የጉልበት ሰራተኛ አገልግሎት ክፍያ
20.5.1 በቅድመ ፈተና እና በድህረ ፈተና አሰጣጥ ወቅት በሚኖረው የፈተና ግብዓት
ከቦታ ቦታ ማጓጓዝ ሂደት በስራው ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ የጉልበት ሰራተኞች
የአገልግሎት ክፍያ ቀደም ሲል በሚደረግ የስራ ውል ስምምነት ተፈፃሚ
ይሆናል። ከላይ በተገለፀው አግባብ

49
ሀ/ በቅድመ ፈተና አሰጣጥ ወቅት የተፈታኞች የመፈተኛ ካርድ ስርጭት ሲካሄድ፣
ለ/ በፈተና አሰጣጥ ወቅት ከምስጢራዊ ፈተና ህትመትና ተጓዳኝ ስራ ጋር
በተያያዘ እና
ሐ/ በድህረ ፈተና አስተዳደር ስራ ወቅት የተፈታኞች የመልስ ወረቀት ርክክብ፣
ወደ ትምፈአ ማድረስ እንዲሁም የተፈታኘች ውጤት ካርድ ወደ ክልል ለመጓጓዝ
በሚደረግ ሂደት የጉልበት ስራ ለሚሰሩ ሰራተኞች የጉልበት ሰራተኛ አገልግሎት
ክፍያ ይከፈላል።
20.6 የትርፍ ሰዓት ስራ አገልግሎት ክፍያ
20.6.1 በቅድመ ፈተና አስተዳደር የተፈታኞች ምዝገባ፣ የፈተና ጣቢያዎች መረጃ
ስብሰባ፣ የምስጢራዊ ፈተና ህትመትና ተጓዳኝ ስራዎች፣ የፈተና ወረቀት
መሰብሰብና የእርማት ስራዎች በጥቅል ለሚሳተፉ ባለሙያዎች፣ የፌደራል ፖሊስ
አባላት እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ከአገልግሎቱ ልዩ የስራ ባህሪ አንጻር በሲቭል
ሰርቪስ በተፈቀደው የክፍያ ሥርአት መሰረት ይከፈላል፣
20.6.2 በፈተና አሰጣጥ ወቅት ከተፈታኞች ጠቅላላ አገልግሎት ስራዎች ጋር በተያያዘ
በድጋፍ ሰጭነት የሚሳተፉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች
በሲቪል ሰርቪስ የትርፍ ሰዓት ስራ መመሪያ መሰረት ከመደበኛ ስራ በተጨማሪ
ለሚሰሩ ስራዎች የትርፍ ሰዓት ስራ አገልግሎት ክፍያ ተፈፃሚ ይሆናል።
20.7 የተፈታኞች የምገባ አገልግሎት
20.7.1 የተፈታኞች የምግብ ምገባ አገልግሎት የገንዘብ ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት
ተማሪዎች በአንድ ተማሪ በተመነው ተመን ክፍያ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት
ተፈፃሚ ይሆናል።
20.7.2 የክፍያ ተመኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ተፈታኞች በዩንቨርስቲ ለፈተናው
የሚቆዩበትን ቀን ታሳቢ ተደርጎ ክፍያውን በማስላት በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል
የሚተላለፍ ይሆናል፣
20.8 የፈተና አስተዳደር የመጫኛ እና ማውረጃ ክፍያዎች(loading unloading)
20.8.1 ለፈተና አስተዳደር የተለያዩ ግብአቶች የመጫኛና ማውረጃ ክፍያዎች የጭነቱን
ክብደትና የሚወርድባቸውንና የሚጫንባቸውን ቦታዎች ብዛት ታሳቢ በማድረግ
ተሰልቶ የሚመደብ ይሆናል፣

50
20.8.2 ክፍያው የሚፈጸመው የፋይናንስ መመሪያ በሚያዘው ለዚሁ በተዘጋጀው
የአፈጻጸም ማንዋል መሰረት ይሆናል፤
20.9 የተፈታኞች ምዝገባ፣ መረጃ ማጣራትና ተዛማጅ አገልግሎት ክፍያ
20.9.1 የተፈታኞች ምዝገባ፣ የትምህርት ማስረጃ ማጣራት፣የፈተና እርማት መረጃ
ማጥራት(key correction) እና ተዛማጅ አገልግሎት ጋር በተያያዘ
የተመዝጋቢዎች/የተፈታኞች ሰነዶች ብዛትን መሰረት በማድረግ በሚተመን
የቁርጥ ክፍያ አፈፃፀም መሰረት ክፍያ ይፈፀማል።
20.9.2 እያንዳንዱ ተሳታፊ በዚህ መመሪያ ዝርዝር ማስፈፀሚያ ማንዋል መሰረት
በተለያዩ ስራዎች በሚኖረው ኃላፊነት በሚተመነው ተመን ክፍያ የሚከፈል
ይሆናል።
20.9.3 የተፈታኞችን ምዝገባ ለማካሄድ በክልል እና በዞን ደረጃ ለሚካሄዱ ሥልጠናዎች
የስራ ማስኬጃ ወጪዎች በክልል/በዞን/በወረዳ እንዲሸፈኑ ይደረጋል፣
20.9.4 በማእከል ደረጃ ለሚደረጉ የአስልጣኞች ስልጠና፣ የዶክመንት ምርመራና ርክክብ
ስራዎች ወጪ በአገልግሎቱ የሚሸፈን ይሆናል፤

ክፍል አስር
ልዩልዩ ድንጋጌዎች
21.1 የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት
21.1.1 በተፈታኞች ምዝገባ እና በፈተና አሰጣጥ ወቅት ለሚቀርቡ ማናቸውም ቅሬታዎች
የሚስተናገዱት በአገልግሎቱ ድረ ገጽ (Online) ወይም ለአቤቱታ ማቅረቢያ
በተዘጋጀ ድህረ ገጽ ብቻ ይሆናል፤
21.1.2 ለቅሬታ አቅራቢዎች በቀረበው ቅሬታ መሰረት አገልግሎቱ ቅሬታ በቀረበለት
በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በአገልግሎቱ ድረ ገጽ (Online) ወይም ለአቤቱታ
ማቅረቢያ በተዘጋጀ ድህረ ገጽ ምላሽ ይሰጣል።
21.1.3 ቅሬታ የሚያቀርብ ግለስብ ለቅሬታ መነሻ የሆነውን ጉዳይ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ
በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በአገልግሎቱ ድህረ ገጽ (Online) ወይም ለአቤቱታ
በተዘጋጀ ድህረ ገጽ ማቅረብ አለበት፣ ከአንድ ሳምንት በኋላ ለሚቀርብ ቅሬታ
አገልግሎቱ ምላሽ አይሰጥም
21.1.4 የቀረበውም ቅሬታ በሚመለከታቸው አካላት ተመርምሮ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ
ይሆናል፤
51
21.2 የአገልግሎት ክፍያ ተመን
21.2.1 አገልግሎቱ ለሚሰጣቸው የፈተና አስተዳደር አገልግሎቶች የማታ፣ የግል እና
መንግስታዊ ያልሆኑ መደበኛ ተመዝጋቢዎች በመንግስት በሚፀድቀው ተመን
መሠረት የአገልግሎት ዋጋ ያስከፍላል፤
21.3 መመሪያ ስለማሻሻል
21.3.1 አገልግሎቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ይህን መመሪያ ሊያሻሽል ይችላል፡፡
21.3.2 መመሪያውን መሰረት አድርጎ የአፈፃፀም ማንዋሎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡
21.4 የተሻሩ ህጎች
በ1998 ዓ.ም የወጣው ጊዜያዊ የፈተና አስተዳዳር መመሪያ፤ በመጋቢት 2007 ዓ.ም
የወጣው ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና ፈተናዎች ኤጀንሲ የፈተና አስተዳደር መመሪያ
እና ጥቅምት 2004 ዓ.ም የወጣው የምዝገባ አፈፃፀም ማንዋል እና የካቲት 2007 ዓ.ም
የወጣው የፈተናዎች አሰጣጥ ማንዋል እና 2012 ዓ.ም የወጣው የፈተና አስተዳደር መመሪያ
ቁጥር 1 በዚህ መመሪያ ተሽረዋል፤
21.5 ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም አሰራር በዚህ መመሪያ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ
ተፈፃሚነት አይኖረውም፤
21.6 ይህ መመሪያ በሚኒስትሩ ተፈርሞ ከወጣበት ከ------ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡

52

You might also like