You are on page 1of 2

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ትምህርት ቢሮ

የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዋና የሥራ ሂደት


የ 2008 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ

ጥቅምት 2007 ዓ.ም

1. የ 2008 ዓ.ም በጀት ዓመት የ SMASEE ቁልፍ ተግባር

 ስማሴን በተጠናከረ መልኩ በሁሉም የመንግሰት ት/ቤቶች በቁርጠኝነት እንዲተገበር ከተማ አቀፍ የንቅናቄ መድረክ
በመፍጠር የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ
1.1.የቁልፍ ተግባሩ አጠቃላይ ዓላማ

1. የሒሳብና ሳይንስ ትምህርቶችን አሰጣጥ ጥራት በማሻሻል ተማሪዎች የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ
ማስቻል
1.1.1.የቁልፍ ተግባሩ አጠቃላይ ግቦች
 የመምህራንን አቅም ማሳደግ፣

 የክፍለ ከተማ ስማሴ አስተግባሪ ባለሙያዎቸንና የወረዳ የመምህራን ልማት አቅም ማሳደግ

 የስማሴን መርሐ-ግብር ከ 5 ኛ - 8 ኛ የክፍል ደረጃዎች ማስፋፋት

 የሂሳብና የሳይንስ ትምህርቶች ተማሪ ተኮር እንዲሆኑ ማስቻል፣

 በሳይንስና ሒሳብ ትምህርቶች ዙሪያ ለሕብረተሰቡና ለወላጆች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማዘጋጀት፣

 የሂሳብና የሳይንስ ትምህርቶች በተግባር የተደገፉ እንዲሆኑ ማስቻል፣

 ተማሪዎቸ ለሳይንስና ለሂሳብ ትምህርቶች የተሻለ ዝንባሌ እንዲኖራቸው ማስቻል፣

ቁልፍ ተግባር- በትምህርት ሴክተሩ የተሟላ ቁመና ያለዉ የትምህርት ልማት ሰራዊት በመገንባት ስኬታማ
ተሞክሮዎችን በማስፋፋትና የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓከጅ ተግባራዊ በማድረግ የትምህርት ጥራትን
ማረጋገጥ
ግብ.1 በየደረጃው ባሉ ተቋማት ሁሉም ህብረተሰብ በትምህርት ስራ ላይ ሙሉ በሙሉ ተሳታፊ እንዲሆን ማድረግ
1. ከክፍለ ከተማ የስማሴ ባለሙያዎች ጋር የጋራ ዕቅድ በማዘጋጀት ተናቦ መስራት
2. ከመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ወተመህ አባላት ጋር በተማሪዎች የሳይንስና ሂሳብ ውጤት መሻሻል ዙሪያ ማወያየትና ለተግባራዊነቱ የራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ ድጋፍ ማድረግ
ግብ 2 .በስራ ሂደቱ የመረጃ ሽፋን፣ጥራትና ተደራሽነትን 100% ማድረስ
1. የተሟሉና ጥራት ያላቸው መረጃዎችን በሙሉ ማሰባሰብ ፣ ማደራጀት፣ ለተገልጋይ ዝግጁ ማድረግና ማሰራጨት፣
2.የስማሴን እንቅስቃሴ ለባለድርሻ አካላት በሚዲያ፣ በብሮሸር፣ በመጽሔት፤ በድረ-ገጽ ወዘተ በሰፊው ማስተዋወቅ
3. በኮተቤ መምሀራን ኮሌጅ ሊቋቋም የታቀደውን የከተማ አቀፍ የሳይንስና ሂሳብ ማዕከል ህንፃ ግንባታ መከታተል
4. እቅድና ሪፖርት ማዘጋጀትና ማሰራጨት
5. በስልጠና ጣቢያ ቤተሙከራዎች ውስጥ የሚገኙ ቁሣቁሶችን መዝግቦ መያዝ
ግብ 3 . የህዝብ ንቅናቄና ኮሙኒኬሽን አሰራር ማሳደግ
1. የህዝብ ንቅናቄ ፕሮግራም በማዘጋጀት ከባለድርሻ አካላት ጋር መወያየትና በኮሙኒኬሺን ጉዳዮች አማካኝነት ፕሬስ ሪሊዝ ማድረግ
በብሮሸር ፣ በመፅሄትና በሬዲዮ የስማሴን መርሃግብር ማስተዋወቅ
ግብ 4፡- የድጋፍ፣ ክትትል ፣ግምገማና ግብረ-መልስ አሰራርን በማጠናከር በሁሉም የትምህርት ተቋማት ተግባራዊ ማድረግ.

1.በየተቋሙ የተጠናከረ የክትትልና ድጋፍ አሰራር ስልት መዘርጋትና ተቋማዊ ማድረግ


2. ለተቋማት የተሰጠውን ግብረ መልስ በመጠቀም የሚታየውን ክፍተት ማሻሻላቸውን ማረጋገጥ
3. በየደረጃው ላሉት ተቋማት በአካል ወርዶ ድጋፍ መስጠት
4. በክትትልና ድጋፍ ስራ ባለድርሻ አካላትን በየደረጃው ማሳተፍ

ግብ 410 ፡-የ SMASEE ፕሮግራምን ተግባራዊ በማድረግ የ 7 ኛና 8 ኛ ክፍል ተማሪዎችን የሂሳብና የሳይንስ ውጤት በማሻሻል
1. ለመምህራን፣ ለሱፐርቫይሮችና ለ SMASEE ባለሙያዎች ተከታታይና ውጤታማ የሆነ ስልጠና መስጠት
2. ከክፍለ ከተሞችና ከወረዳዎች ከተመደቡ የመምህራን ልማተ ባለሙያዎች ጋር የጋራ ዕቅድ በማዘጋጀት ተናቦ መስራት
3. ከትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን፣ ከጉድኝት ማዕከላት ሱፐርቫይዘሮች፣ ከ SMASEE ተወካይ ባለሙያዎችና ከክ/ከተማ ትምህርት አመራሮች ጋር የ 6 ወርና
የ 1 ዓመት የ SMASEE አፈጻጸምን መገምገም
4. ጥሩ እንቀስቃሴ ያላቸውን ት/ቤቶች ተሞክሮ በመቀመር ወደ ሌሎቸ ት/ቤቶች እንዲሰፋፉ ማድረግ
5. በየሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ሥራዎችንና ፕሮግራሙ ያለበትን ሁኔታ መገምገምና ሪፖርት ማድረግ

You might also like