You are on page 1of 5

የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት

የ 2009 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ዕቅድ


ቁልፍ ተግባር:- የተደራጀ የት/ት ልማት ሠራዊት መፍጠር 70%

- በ 2009 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት ልማት ሰራዊት በመገንባት የአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ
ፓኬጅን በውጤታማነት በመፈፀም ሁሉም ተማሪዎች በሁሉም የክፍል ደረጃዎችና የትምህርት አይነቶች 50 እና
በላይ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ማድረግ፡፡

- በሂደት ደረጃ የ 1 ለ 5 ዕቅድ ተዘጋጅቶ በሂደቱ አባላት የጋራ በማድረግ ወደ ተግባር ማስገባት፣

-ሁሉም ትምህርት ቤቶች የተደራጀ የትምህርት ልማት ሰራዊትን ያካተተ ዕቅድ አዘጋጅተው ወደ ስራ እንዲገቡ
ማድረግ፣

-በሁሉም ትምህርት ቤቶች የተማሪና የመምህራን የ 1 ለ 5 ና የልማት ቡድን አደረጃጀት ማደራጀት፤-ወመህ እና


ቀትስቦ ት/ቤቶችን በባለቤትነት መንፈስ እንዲመሩ ግንዛቤ በመፍጠር፣ በተግባርና በየሃላፊነታቸው የአቅም ማጎልበቻ
አጫጭር ስልጠና በመስጠት በየወሩ እየተገናኙ ት/ቤቶችን እንዲመሩ ማድረግ፡፡

1. የትምህርት አመራር አሰራርና አደረጃጀት ማሻሻያ መርሃ-ግብር

-በት/ቤቶች አጠቃላይ የት/ት ጥራት ማስጠበቂያ ኘሮግራምና የምዕተ ዓመቱን ግብ አቀናጅቶ የሚፈፅም የትምህርት አመራር
ሀይል በየደረጃው መፍጠር፡፡

- ፣ ከጉድኝት እስከ ት/ቤት ድረስ የተጠናከረ ተቋማዊ የውድድር ስርዓት ፣በማዘጋጀትና ተግባራዊ በማድረግ መ/ራንና የት/ት
አመራር አካላት በውጤታማነት እንዲወጡ ማድረግ፣ በት/ቤቶች የሴቶችን የአመራር ተሳትፎ አሁን ካሉበት የአመራር አቅም
ወደ ተሻለ ተሳትፎ በማሳደግ አቅማቸውን ማጠናከር፡፡

-ት/ቤቶች በብቁና ለደረጃው በሚመጥኑ፣በአግባቡ በተመረጡና በሰለጠኑ ር/መ/ራንና ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም በሌሎች ልዩ
ልዩ አደረጃጀቶች እንዲመሩ ማድረግ

- ከ 1-8 ባሉ ት/ቤቶች 63 የክላስተር ዲፕሎማ መምህራን፣10 ር/መ/ራን፣5 ሱፐርቫይዘሮችና ለ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች 6 ድገፍ
ሰጭ ሰራተኞችንና 6 ቅድመ መደበኛ መ/ራን በአዲስ ቅጥር በመፈፀም በወቅቱ እንዲመደብላቸው ማድረግና ት/ቤቶች
የተፈለገውን ግብ እንዲመቱ ማድረግ፣

- ሁሉም ሱፐርቫይዘሮችና ር/መ/ራን ከዞን በሚመጣ በወረዳ ደረጃ በሚዘጋጅ የአጭር ጊዜ ልዩ ልዩ ስልጠና እንዲያገኙ
ማድረግ፣

2.የመምህራን ልማት መርሃ-ግብር


-በክልሉ መ/ራን ትም/ኮሌጆች የሚሰጠውን የመጀመሪያ ደረጃ መምህራን ቅድመ ስራ ለማሰልጠን በሚሰጠን ኮታ መሰረት
መፈፀም፡፡

-መ/ራን በተግባር መሳሪያዎች ቋት የሙያ ማሻሻያ ኘሮግራም ስልጠና ሂደት በማሳተፍ አካዳሚያዊ እውቀታቸውንና ሙያዊ
ስነ-ምግባራቸውን በማሻሻል ሀላፊነታቸውን የሚወጡና በራሳቸው እንዲተማመኑ ማስቻል፡፡

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 1


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት

- በወረዳው ውስጥ ያሉ መ/ራን የስልጠና ፍላጐታቸውንና ያሉባቸው የአቅም ክፍተት ተለይቶ ወቅታዊ አጫጭር ስልጠና
በመሰጠት ተጨማሪ አቅም መፍጠር፡፡

-በሁሉም ደረጃ የሚገኙ መለስተኛና በመምህር ደረጃ ያሉ መምህራንን መመዘን፡፡

-የይዘትና የፔዳጎጅ ምዘና ለወሰዱ ጀማሪ መምህራን የተግባር ምዘና ይሰጣል፡፡

2.የትምህርት ቤት ማሻሻያ መርሃ-ግብር


-በትምህርት ቤት መሻሻል መርሀ ግብር ላይ ያለውን የአመለካከት የክህሎትና የግብዓት ችግሮችን ለመቅረፍ
የሚያስችል በየደረጃው ላሉ አካላት ግምገማ ነክ ስልጠና በመስጠት የተሻለ ፈፃሚና አስፈፃሚ ሀይል መፍጠር፡፡

-የትምህርት ቤት ማሻሻያ ፕሮግራም በወረዳው ውስጥ ተቋማዊ የሆነ የአሰራር ስርዓት እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡
-50/90 የት/ቤት ኮሌጅ ግንኙነት ውስጥ በሆነ መንገድ በት/ቤት ማሻሻያ መርሀ- ግብር እንዲሆን ማድረግ፣

- ትምህርታዊ የጥናትና ምርምር ፅሁፎችን ውጤት ማሳተም፣ግብረ-መልስ መስጠት ፣ማሰራጨትና ከሚመለከታቸው አካላት
/መምህራን፣ወላጆች፣ተማሪዎችና የትምህርት ባለሙያዎች ጋር ተገቢውን ውይይት ማካሄድ፣

-የት/ቤትና ህብረተሰብ ግንኙነት በታቀደና በተደራጃ መልኩ በማጠናከር ህብረተሰቡም የተማሪዎች ውጤት
የማሻሻሉን ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ማድረግ፡፡

-በክፍል ውስጥ መማር-ማስተማር ሂደቱን በአዲስ የትምህርት ቤት ማሻሻል ማዕቀፍ መሰረት እያሻሻሉ በመሄድ
የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል፡፡

-ተማሪዎች በዓመቱ ውስጥ በሙሉቀን የሚማሩት 1075፡30 ሰዓት በፈረቃ የሚማሩበት ደግሞ 820 ሰዓታት ትምህርት
ያገኙ መሆኑን ማረጋገጥ በበቂ ምክንያት ለሚቀሩ መምህራን የተተኪ መምህራንን ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ ማድርግ፣

-በአጠቃላይ በወረዳው ውስጥ የሚገኙ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤቶች የቤተ-ሙከራ አጠቃቀም በአግባቡ ተቃኝቶና
ተጠንቶ የሳይንስ ትምህርት ቤቶች የቤተ-ሙከራ አጠቃቀም በአግባቡ ተቃኝቶና ተጠንቶ የሳይንስ ትምህርት በተሸለ
መልኩ ለመስጠት የሚያስችል ስልት ቀይሶ ተግባራዊ ማድረግ

-በየደረጃው
ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት በአዲሱ ክልላዊ ስታንዳርድ ወሳኝ የሆኑ ግብዓቶችን በማሟላት ምቹና
ማራኪ በማድረግ የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል፡፡

-ተጨማሪ ክፍሎችን በመገንባት የተማሪ ክፍል ጥምርታን 1-4 1፡50 ና 5-8 1 ለ 45 ማድረስ፣

- የተማሪ መምህር ጥምርታን 1-4 1፡50 ና 5-8 1 ለ 45 ማድረስ፣ - የተማሪዎችን የማንበብ ልምድ
በማዳበር ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ፣ከ 1—4 የመማሪያ ክፍል ደረጃ ሞባይል ቤተ-መፅሀፍት ማዘጋጀት ከ 1-4 ት/ቤት ንባብ
ቤቶችን ማዘጋጀት ከ 5—8 ና ከ 9—10 ቤተ-መፅሀፍት 100% እንዲኖራቸው ማድረግ
- ሁሉም ተማሪዎች 100% ደረጃቸውን በጠበቁ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበርና ዴስክ መቀመጥና መማር
መቻላቸውን ማረጋገጥ፣

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 2


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት

-ደረጃቸውን የጠበቁ የትም/ት ተቋማት ግንባታን ጥያቄ ከየቀበሌዎች በቀረበው መሠረት ተለይቶ አመች ሁኔታ መፍጠርና
ሁሉም የተገነቡት የትም/ት ተቋማት በበቂ መጠንና ጥራታቸውን የጠበቁ በስታንዳርዱ መሠረት የክፍል ተማሪ ጥምርታ
እንዲኖር በማድረግ የደንበኞችን እርካታ መጨመር፡፡በወረዳችን በሚገኙ ሁሉም ት/ቤቶች ደረጃቸውንና ጥራታቸውን የጠበቁ የት/ት
መሳሪያዎችን ማቅረብ፣በወረዳችን ባሉ የት/ት ተቋማት ወቅቱን የጠበቀ የት/ት መሳሪያዎች ጥገናና ዕድሳት ጥያቄ ወቅታዊ
ምላሽ እንዲያገኝ ማድተግ

-የክፍል፣የጉድኝነትና የወረዳ እንዲሁም የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ትንተና ለተማሪዎች ውጤት ማሻሻያነት በግብዓትነት
የመጠቀም የአሰራር ስርዓት ተጠናክሮ ተግባር ላይ እንዲውል ማድረግ፡፡

4. የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት መርሃ-ግብር


-የስነ--ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት ከምንግዜውም በላይ በተሻለ ሁኔታ የሚሰጥበትን ስርዓት አጠናክሮ በመቀጠል
የሀገራችን ማህበራዊ እሴቶች በትምህርት ቤት ውስጥና ውጭ ማስረፅ፡፡

-ትምህርቱን በይበልጥ ለማስረፅ ሌሎች ተጓዳኝ ተግባራትን አጠናክሮ ተማሪዎች ላይ በመስራት የትምህርት አሰጣጥን
በማጠንከርና በበቂ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ፡፡-የተጠናከሩ የክፍል ውስጥ የክበባትና የአደረጃጀት ስርዓቶች ተከታታይነት ባለው
መልኩ መዘርጋትና ተግባር ላይ በማዋል የተማሪዎችን ዲሲሰፕሊን ማሻሻል፡፡

-በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሰንደቅ ዓላማና መዝሙር ስነ-ስርዓት በአግባቡ እንዲከበር በማድረግ የተማሪዎችን የሀገር ፍቅር ስሜት
ማጎልበት፡፡

-ተማሪዎች በትምህርት ቤትና ከትምህርት ቤት ውጭ በንድፈ ሀሰብ የቀሰሟቸውን እሴቶች የተላበሱ መሆኑን የሚያረግጡባቸው ተግባራዊ
ስራዎች በማከናወን ተጨባጭ ውጤታማ ለውጥ ማሳየት፡፡

5.የስርዓተ-ትምሀርት ማሻሻያ መርሃ-ግብር


-የስርዓተ ትምህርቱን ትግበራ ለመደገፍ መካተት የሚገባቸውን ወሳኝ ተጓዳኝ ተግባራት በየትምህርት ቤቱ ማስፈፀም፡፡
-በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጣውን የስርዓተ ትምህርት መነሻ በማድረግ ክልላዊ ስትራቴዎች ተዘጋጅተው በዝግጅትና

ትግበራ ሂደት በስኬታማነት መፈፀም፡፡


- የቅድመ-መደበኛ ትምህርት የማስተማሪያ መፅሐፍት/ደረጃ አንድ፣ሁለትና ሶስት/ማሰራጨት፣

- የክልሉን የአጠቃላይ ትምህርት አፈፃፀም በቀጣይነት እያሻሻሉ ለመሄድ እንዲቻል የትምህርት ጥናትና ምርምር
ባህልን አጠናክሮ ተግባራዊ ማድረግ፡፡

-የስርዓተ ትምህርትን ለማሻሻልና ለማጎልበት የሚያስችሉ ምዘናና ተግባርን በውጤታማነት መፈፀም፡፡

-የመጀመሪያ ትምህርት ማጠናከሪያ ፈተና፣የተማሪዎች ምዝገባ፣የፈተና ህትመት ስርጭት፣የፈተና አስተዳደርና


ውጤትን ማሳወቅ፣

6. የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ አገልግሎትን የማስፋፋት መርሃ-ግብር


ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 3
የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት

-የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት የማስፋፋት ፕሮግራምን ተቋማዊ የሆነ አሰራር ስርዓት እንዲኖር
ማድረግ፡፡

- አዲስ በተሸሻለው መደበኛና መደበኛ ያልሆውን ትምህርት በመደገፍ የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ፡፡

-የሬዲዮ ስርጭት ለማይደርስባቸው ት/ቤቶች ሚሞሪ አስጭነዉ ት/ቤቶች እንዲጠቀሙ ማድረግ፣

-የት/ቤት ሚኒ-ሚዲያ ክበባትን ለማጠናከር ለ 110 መምህራንና ተማሪዎች በሚኒ-ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ስልጠና
መስጠት፣

- የሬዲዮ ፕሮግራም የጊዜ ሰሌዳ ተዘጋጅቶ ለመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ፣

አብይ ተግባር ፡ የትምህርት ሽፋንን ማሳደግ 25%


-በወረዳው ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት በሙሉ ትምህርት ቤት ገብተው እንዲማሩ ማስቻል፡፡

-በወረዳው እድሜያቸው ሰባት ዓመት የሞላቸው ሁሉም ህፃናት ትምህርት ቤት የሚገቡበት ቅድመ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣
 ወ 2600 ሴ 2636 ድ 5236 ተማሪዎች እድሜያቸው ሰባት ዓመት የሞላቸውን መቀበልና የአንደኛ ክፍል ጥቅል
ቅበላን ወ 3389 ሴ 3435 ድ 7324 ማድረስ
 የአንደኛ ደረጃ ጥቅል የትምህርት ሽፋንን ወ 17975 ሴ 15685 ድ 32763 ማድረስ
 በሁለቱ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎችን የትምህርት ሽፋንን 750 ማድረስ

 በ 4 የአፀደ-ህፃናት ተቋም የትምህርት ሽፋንን ወ 825 ሴ 751 ድ 1576 ማድረስ


 የልዩ ፍላጎት ትምህርት ተሳትፎ ሽፋንን በማሻሻል ወ 76 ሴ 74 ድ 150 ተማሪዎችን ማስተናገድ
 የ 2009 ዓ.ም የቅድመ-መደበኛ የት/ት ተሳትፎን ወ 3257 ሴ 2865 ድ 6122 ማድረስ
 በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ወ 651 ሴ 887 ድ 1538 ማድረስ
-በየደረጃው የሚሰጠውን የትምህርት አቅርቦትና ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስፈልጉ ወሳኝ ግብዓቶች እንዲሟሉ ማድረግ፡፡
ለዚህም የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ይከናወናሉ፡፡
-5 አዲስ ግንባታና በ 35 ት/ቤቶች ተጨማሪ መማሪያ ክፍሎችን መገንባት፣በ 102 ት/ቤቶች መማሪያ ክፍሎች ጥገና፣3 ፈፅሞ
የተጎዱትን ት/ቤቶች አፍርሶ የመገንባት ስራ ማካሄድ
-በወረዳ ደረጃ 3 የልዩ ፍላጎት ዩኒት ማዕከል መገንባት
-በዚሁ የት/ት ዘመን በሁሉም የክፍል ደረጃዎችና የትምህርት አይነቶች የመማሪያ መፃህፍትን ለሁሉም ተማሪዎች በነፍስ
ወከፍ ማዳረስ
-ከህብረተሰቡ፣ከረድዔት ሰጭ ድርጅቶችና ከአካባቢው ተወላጆች ወዘተ ሀብትን በማሰባሰብ ወደ አንድ ቋት ማስገባትና ይህን
ከተለያዩ ምንጮች የተገኘን ሀብት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ድልድል መፈፀም
ተግባር ሶስት

-የአካቶ ትምህርትን በየደረጃው በመስጠት የትምህርት አቅርቦትን ማስፋፋት፣

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 4


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት

-በወረዳው የአካቶ ት/ት ባሉት ት/ቤቶች በሚማሩ ተማሪዎች ጥናት በማካሄድ ፕሮጀክት በማዘጋጀት የሃብት ማፈላለግ
ማመንጨት ተግባር መፈፀም፣
-መሠረታዊ የጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም በሁሉም የወረዳው ቀበሌዎች በመጀመር የጎልማሳውን አቅም ማጠንከር፣ወ
7293 ሴ 5737 ድ 13030 አዲስና ወ 4844 ሴ 3829 ድ 8673 ነባር ጎልማሶችን መመዝገብ
-በ 130 ጣቢያዎችና በ 115 አመቻቾች ትምህርቱን መስጠት(በሁሉም ቀበሌዎች)፡፡ይህን የሚያስተባብሩ 3 ባለሙያዎችም
ተቀጥረዋል፡፡
ተግባር ሁለት

-ወረዳዊ የህዝብ ንቅናቄ ሰነድ በማዘጋጀትና ከወረዳ እስከ ቀበሌ በማስተዋወቅ ግንዛቤ መፍጠር፣
-ማንበብ፣መፃፍና ማስላት የማይችሉ ወጣቶችና ጎልማሶችን መረጃ በየደረጃው አጠናቅሮ መያዝና
ለሚመለከተው ክፍል ማሳወቅ፣
የትምህርት ፍትሀዊነትን ማስጠበቅ፡፡

-በየደረጃው በሚገኙ የትምህርት ፕሮግራሞች የስነ-ፆታዊ ክፍተትን/Gender Disparity/ የሚያጠቡ ተግባራትን መፈፀም፡፡
ለዚህም ለ 2009 ዓ.ም የሴቶችን የት/ት ተሳትፎ ለማጎልበት 15685 ለማድረስ ዕቅድ ተይዟል፡፡

-በከተሞችና በገጠር መካከል ያለውን የትምህርት አቅርቦት ልዩነት/urban-Rural inequity/ ለማጥበብ በገጠርና በኋላቀር
አካባቢዎች የትምህርት ተቋማት በተጠናና በተጠናከረ ሁኔታ ማስፋፋት፣
-ዝቅተኛ የተማሪ ተሳትፎ ባላቸው ቀበሌዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ተሳትፎን የሚያጎለብቱ የተለያዩ
ተግባራትን መፈፀም፣
የትምህርት ብቃትን ማሻሻል፡፡

-በ 2009 ዓ.ም በጀት ዓመት በመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች የመማሪያ ሴክሽን ተማሪ ጥምርታ በስታንዳርዱ መሠረት ማድረግ፣
-በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ተቋማት የተማሪዎችን መድገምና ማቋረጥ ምጣኔን የሚያሻሽሉ ተግባራትን
በውጤታማነት መፈፀም፣የመድገም ምጣኔን 3% በታች ማድረስ፣የማቋረጥ ምጣኔን ከ 2% በታች ማድረስና የእርከኑን
ማጠናቀቂያ ምጣኔ ማሻሻል
በወረዳችን በሚገኙ በሁሉም ት/ቤቶች ደረጃቸውንና ጥራታቸውን የጠበቁ የትም/መሳሪያዎች ማቅረብ፡፡

-በማንኛውም መንገድ ማለትም በግዥ ወይም በዕርዳታ የሚገኙ የትም/መሳሪያዎችን በፍትሀዊነት በወቅቱ በየተቋማቱ እንዲደርስ ማድረግ፣

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 5

You might also like