You are on page 1of 8

የወላይታ ሰክሰስ አካዳሚ

የ 2014 ዓ.ም የትምህርት አመራር እና አሰራር ሂደት እቅድ

አላማችን ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ለትውልዱ ማሸጋገር ነው፡፡

መስከረም 2014 ዓ.ም


መግቢያ

ትምህርት በሀገራችን እድገት ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫውት ዘርፍ መሆኑን በማመን ትምህርት ቤታችን ወላይታ ሰክሰስ
አካዳሚ ለትምህርት እድገት ከፍተኛ ስራ ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሁለንተናዊ ስብእናው የተሟላ በዕውቀት
፤በክህሎትና በአመለካከት እንዲሁም በመልካም ስነ-ምግባርና በዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የታነፀ ብቁ ዜጋ ለማፍራት የሚያስችል
የትምህርት ስልጠና አሰራር ቀርፆ ወደ ተግባር በመግባት በስራ ላይ ለማዋል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ትምህርት
ቤታችን እቅዱንም ተግባራዊ ለማድረግ ከየትኛውም ጊዜ ትኩረት ሰጣቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የትምህርት አሰጣጥንና
ተደራሽነትን ፤ፍትሃዊነትን ፤ውጥታማነትን በተሻለ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ለማቅረብ በተቀረፁ እቅድና የስራ ሂደት በማዘጋጀት
ወደ ተግባር እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ፍትሃዊነት እንደማረጋገጥ ቆጥሮ የገባው ትምህርት ቤታችን በተጨማሪ በአጠቃላይ በሀገሪቱ
ያለውን የትምህርት ጥራት ችግር እንደ አንድ ቁልፍ ጉዳይ በመውሰድ በ 1999 ዓ.ም በአጠቃላይ ትምህርት ጥራት
ማረጋገጫ ፓኬጅ መሰረት ትምህርት ቤታችን የህንን ፓኬጅ ለመተግበር ከፍተኛ ሲያደርግ ቆይቷል ፡፡ የህም ፓኬጅ የሀገራችንነ
ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ከመፍታት አንፃር ከፍተኛ የሆነ ሚና ይጫወታል፡፡ ስለሆነም ትምህርት ቤታችን ሀገራችንን
ከፍተኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማስመደብ ጥራት ያለው ትምህርት ከፍተኛ የሆነ የማይተካ ድርሻ እንደሚጫወት
ትምህርት ቤታችን አምኖ ይህንን የትምህርት ጥራት ፓኬጅ ለመተግበር ወደ ስራ ከገባ አመታትን አስቆጥሯል ስለሆነም ይህ
የትምህርት ቤታችን እቅድ ይህንን የትምህርት ጥራት ፓኬጅ በተቻለ የአቅም ግንባታ ለመተግበር በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ
የተዘጋጀ ነው፡፡

በዚሁ መሠረት ትምህርት ቤታችንፓኬጁን ተግባራዊ በማድረግ ለቀጣይ የትምህርት ደረጃዎች ድልድይ የመሆን መሰረት
የመጣል ሚናችንን በአግባቡ ለመወጣት እስከ አሁን እያስመዘገብን ያሉትን ውጤት በማሻሻል እና ተቋማዊ ለውጥ
በማምጣት እንደ ተቋም በትምህርቱ ዘርፍ የተቀመጡ ግቦችን በተቀመጠው እቅድ መሠረት ትምህርት ቤታችን የላቀ ደረጃ
ለማድረስ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት እና ወደ ተግባር ለመግባት ከወዲሁ ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡

ይህ የትምህርት ቤታችን የትምህርት አመራር እና አሰራር ሂደት እቅድ አላማ ፣ አስፈላጊነት፣ ከወትሮ በላይ ስለሆን በውሥጡ
ስለ እቅዱ ሙሉ በሙሉ በመተንተን እቅዱን ያሰቀምጣል፡፡

2|Page
የትምህርት ቤቱ ዓላማዎች
አጠቃላይ ዓላማ
 ƒ ትምህርት ቤታችን ወጥነት ባላቸው መስፈርቶች/ስታንዳርዶች መሰረት እንዲሄድ ማድረግና ወደ ሚፈለገው የጥራት
ደረጃ መድረስ ነው፡፡
ዝርዝር ዓላማዎች
 ትምህርት ቤታችን ወጥነት ባላቸው መስፈርቶች/ስታንዳርዶች መሰረት እንዲመራ ማድረግና ጥሩ ውጤት ላይ
እንዲደርሱ ማድረግ፣
 በትምህርት ቤታችን የሚገኙትን ጉድለቶች በመለየት ወደ ሚፈለገው የብቃት ደረጃ ማድረስ፤
 በደረጃው ካሉ ትምህርት ቤቶች መካከል የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ ማድረግ፣
 ትምህርት ቤቱ ሶስቱን የልማት ሰራዊት አቅሞች/ የድርጅት፣ የመንግስትና የህዝብ ክንፎች/ በመጠቀም በተደራጀና
በተቀናጀ መልኩ በመስራት የት/ቤታችንን ውጤታማነት ደረጃ ለማሳደግ ማስቻል፣
የትምህርት ቤቱ እቅድ አስፈላጊነት
 በሀገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ቤት እቅድ ሥርዓት ተዘርግቶ ስራ ላይ መዋል የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኛል
 ወጥ በሆነ እቅድ የትምህርት ጥራትን በሀገርአቀፍ ደረጃ ያረጋግጣል፣
 ትምህርት ቤቱን ከግብአት፣ ሂደት እና ውጤት አኳያ ጥሩ ደረጃ ለመድረስ ያግዛል፣
 ከትምህርት ቤቶች ሁሉ በመለየት በማደግ የተሻለ አፈፃፀምና ውጤት በማግኘት ለበለጠ ስኬት
እንዲደርስ ማድረግ፣
 ከዚህ በፊት ለተገኘው የትምህርት ቤቱን ዝቅተኛ አፈፃፀምና ድክመቶች በግልፅና በማያሻማ መንገድ
እንዲሻሻል ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ፣
 የተጠያቂነት ስርአት በየደረጃው ለማስፈን፣
 ትምህርት ቤታችን ያሉበትን የአፈፃፀምና የውጤት ደረጃ የሚያሣይ መረጃ ለባለድርሻ አካላትና
ለህብረተሰቡ ለመስጠትና የተደራጀ የመረጃ ስርዓት ለማስፈን፡፡
እቅድ 1
 ትም/ቤቱ የመማሪያና አገልግሎት መስጫ ህንፃዎች በተቀመጠላቸው እቅድ መሰረት ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ባካተተ
መልኩ(በቂ ብርሃን፣ስፋት፣ወለል መሰረት አገልግሎት እንዲሠጡ ማድረግ፡፡
 ትምህርት ቤቱ የተማሪ-ክፍል ጥምርታ የመምህሩ/ሯ መምሪያ እና አጋዥ/ ማጣቀሻ መጽሐፍትን ማሟላት ፤
 ትምህርት ቤቱ በስታንዳርዱ መሠረት ቤተ-መጽሃፍት፣ቤተ-ሙከራ፣ የትምህርት ማበልጸጊያ ማዕከል፣ አሟልቶ መገኘት፤
 ትምህርት ቤቱ ሀገር አቀፍ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ፣ ገዥ መመሪያዎች፣ አገራዊና ክልላዊ ፕሮግራሞችና
ማእቀፎች፣ ህገ-መንግስት ወዘተ እንዲሁም ተያያዥነት ያላቸው መመሪያዎችና የት/ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ ማሟላት

እቅድ 2
 ትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማሻሻል ላቀዳቸው ቅድሚያ ለሚሰጣቸው
ተግባራት ማስፈፀሚያ የሚያገለግል የፋይናንስ ሃብት ማሟላት ፣
 ትምህርት ቤቱ የውስጥ ገቢን በማመንጨት የፋይናንስ አቅሙን ማጎልበት፣
እቅድ 3
 ትምህርት ቤቱ ለደረጃው የሚመጥኑ ርእሳነ መምህራን፣ መምህራን እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በስታንዳርዱ መሰረት
ማሟላት ፡፡
ምቹ የመማሪያ አካባቢ መፍጠር
እቅድ 4
 ትምህርት ቤቱ ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ምቹ፣ የማያሰጋ እና ደህንነታቸውን የሚያረጋግጥ የመማር-
ማስተማር አካባቢ መፍጠር፣
3|Page
 ትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደትን ከሚያውኩ ሁኔታዎች የፀዳ ማድረግ፣
 በትምህርት ቤቱ በቂ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ መፀዳጃ ቤቶች ከውሃ እና ሳሙና ጋር ማሟላት ፡፡
 ትምህርት ቤቱ ንፁህና የታከመ ለመጠጥ የሚያገለግል የውሃ አቅርቦት ማሟላት፣
እቅድ 5
 ትምህርት ቤቱ የተደራጀ የትምህርት ልማት ሰራዊት መፍጠር ፣
 በትምህርት ቤቱ ዓላማዎችና ተልዕኮዎችን ለመተግበር የሚያስችል ግብዐት፣አደረጃጀትና የአሰራር ስርዐት
መፍጠር
 በትምህርት ቤቱ የተቀመጡ ዓላማዎችና ግቦችን ተልዕኮዎችን የተገነዘበና ለመፈፀም ዝግጁ የሆነ የትምህርት ልማት
ሰራዊት መፍጠር ፣
 በትምህርት ቤቱ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ሙያዊ ክህሎትና የአመራር ብቃት መፍጠር ፣
የትምህርት ቤቱ ራእይ፣ ተልእኮ፣ እሴቶችና ዕቅዶች
 ትምህርት ቤቱ የጋራ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች ማዘጋጀት
 ትምህርት ቤቱ አሳታፊ የት/ቤት መሻሻል እቅድ ማዘጋጀት
 ትምህርት ቤቱ ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ መለየት

-
መማር ማስተማር

እቅድ 6
 የተማሪዎች መማርና ማስተማር ተሳትፎ ማጎልበት
 ተማሪዎች የተሰጧቸውን ሥራዎች በትጋት ማሰራት ይህ ሃላፊነት በመምህራኖች ላይ የሚጣል ይሆናል፣
 ተማሪዎች ጥያቄዎችን ለመጠየቅና መልሶችን ለመመለስ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማድረግ
 ተማሪዎች በ 1 ለ 5 (ኔትወርክ) አደረጃጀት ተደራጅተው በትምህርታቸው እንዲከታተሉ ማድረግ
 ተማሪዎች በተለያዩ ክበባት በመደራጀት ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ማበረታታትና ሁኔታዎችን ማመቻቸት
 ተማሪዎች በህፃናት ፓርላማና በተማሪ ካውንስል ተደራጅተው በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ውሳኔ በመስጠት ተሳትፎ
እንዲያደርጉ ማድረግ ፣

እቅድ 7
 ተማሪዎች በትምህርት አቀባበላቸው መሻሻል እንዲያሳዩ ማድረግ ፣
 ተማሪዎች የትምህርት ጊዜያቸውን ሳያባክኑ በአግባቡ እንዲጠቀሙ ማድረግ፣
 ተማሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት አዲስ ነገር መፍጠር፣መመራመርና የራሳቸውንና የአካባቢያቸውን ችግሮች መፍታት
እንዲችሉ ማድረግ፣
 ተማሪዎች በፈተና/ምዘና ፣ የሚፈፀም ኩረጃ ጸያፍ መሆኑን ማስገንዘብ
 ተማሪዎች ለትምህርት ቤታቸው በጎ አመለካከት እንዲኖራቸው ማድረግ
 ተማሪዎች ትምህርት ቤቱ በሚሰጣቸው አገልግሎት እንዲረኩ ማድረግ ፣
 ት/ቤቱ ለሚያከናውኗቸው ሥራዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ማድረግ፣
 ተማሪዎች ለት/ቤቱ ማህበረሰብ ተገቢውን አክብሮት እንዲሰጡ ማድረግ ፣
 ተማሪዎች የት/ቤቱን ህግና ደንቦች ተቀብለው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማድረግ፣

እቅድ 8
4|Page
 መምህራን የትምህርት እቅድ የሚያስተምሩትን ትምህርት አላማ፣ ይዘት፣የማስተማር ስነ ዘዴ… ወዘተ በአግባቡ
እንዲያካትቱ ማድረግ
 መምህራን የመማሪያ ማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎችን በማዘጋጀት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ
 መምህራን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግ ተማሪዎቻቸው የአካባቢ ቁሳቁስ ተጠቅመው የፈጠራ
ስራዎችን እንዲያከናውኑ የማበረታታት ሂደት ፣
 መምህራን ተማሪዎቻቸው በትምህርታቸውና በውጤታቸው እንዲሻሻሉ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት እገዛ
እንዲያደርጉ ማድረግ፣

እቅድ 9
 መምህራን የሚስተምሩትን የትምህርት ይዘት ጠንቅቀው እንደሚያውቁ ማረጋገጥ
 መምህራን በሚያስተምሩት ትምህርት ይዘት በቂ እውቀትና ክህሎት እንዳላቸው ማረጋገጥ፡፡
 መምህራን ለተማሪዎች በሚመጥን ቋንቋ እና አቀራረብ ይዘቱን ቀለል አድርገው እንዲያቀርቡ ማድረግ፣
 መምህራን በትምህርቱ ውስጥ ያሉ ቁልፍ ጽንሰ ሃሳቦችን ለተማሪዎች በግልጽና አብራርተው እንዲቀርቡ ማድረግ

እቅድ 10
 የት/ቤቱ አመራርና መምህራን ለሁሉም ተማሪዎች ተስማሚና ዘመናዊ የማስተማር ስነ-ዘዴዎችን በመጠቀማቸው
የሁሉም ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ ማጎልበት፣
 መምህራን ተማሪዎችን በትምህርታቸው ተመራማሪ፣ ፈጣሪ፣ ችግር ፈቺ እና ራሳቸውን የሚመሩ እንዲሆኑ
ልዩ ልዩ አሳታፊ ዘዴዎችን እንዲያዘጋጁ ማድረግ፣
 የትምህርት ቤቱ አመራር ዘመናዊና አሳታፊ የመማር-ማስተማር ስነ ዘዴ በት/ቤቱ እንዲተገበር ምቹ ሁኔታዎዎችን
መፍጠር፣
 የትምህርት ቤቱ አመራር ዘመናዊና አሳታፊ የመማር-ማስተማር ስነ ዘዴ በት/ቤቱ እንዲተገበር ምቹ ሁኔታዎችን
መፍጠር፣
 መምህራን ተማሪዎችን እንደ አስፈላጊነቱ በጥንድ፣ በቡድን እና በግል ትምህርታቸውን እንዲማሩ ማድረግ፣
 መምህራን ለሴት ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ እንዲሰጡ ማድረግ፣
 መምህራን ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ እንዲሰጡ ማድረግ፣
 መምህራን የመማር ማስተማሩን ችግር ለመፍታት የተግባር ምርምር እንዲያካሄዱ ማድረግ፣

እቅድ 11
 ትምህርት ቤቱ ለሴቶችና እና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች አስፈላጊውን መረጃ ይይዛል፣ ልዩ ድጋፍ እንዲያድግ
ማድረግ፣
 ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን የተመለከቱ መረጃዎች ትምህርት ቤቱ መዝግቦ እንዲይዝ ማድረግ፣
 ትምህርት ቤቱ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን የትምህርት ውጤት ለማሻሻል እና ለማሳደግ ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ
ማድረግ፡፡
 ትምህርት ቤቱ የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ውጤት ለማሻሻል እና ለማሳደግ ልዩ ድጋፍ መስጠት፣

እቅድ 12
 መምህራን፣ ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ መርሃ-ግብር /CPD/ ተግባራዊ እንዲያደርጉ
ማድረግ፣

5|Page
 ነባር መምህራን፣ ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የትምህርት ቤቱን የመማር ማስተማር ችግር ለመፍታት
የሚያስችል ችግሮችን በቅደም ተከተል ለይተው ሞጁል አዘጋጅተው ቢያንስ በዓመት ለ 6 ዐ ሰዓት በተከታታይ
ሙያ ማሻሻያ መርሃግብር ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማድረግ፣
 አዲስ ጀማሪ መምህራን አማካሪ መምህራን ተመድበውላቸው የሙያ ትውውቅ መርሃ ግብር/Induction
Course/እንዲ ወስዱ ማድረግ፣

እቅድ 13
 የትምህርት ቤቱ አመራር፣ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በልማት ሠራዊት በመደራጀት በቡድን ስሜት እንዲሰሩ
ማድረግ ፣
 የትምህርት ቤቱ አመራር፣መምህራን፣ተማሪዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ተደራጅተው
የትምህርት ልማት ሰራዊት በመገንባት ስራቸውን ውጤታማ በሆነ መልክ ተወጥተዋል፣ በውሳኔ አሰጣጥ ላይ
እንዲሳተፉ ተደርጓል እርስ በእርስም በውስጥ ሱፐርቪዥን አማካኝነት እንዲገነቡ ማድረግ፣
 የትምህርት ቤቱ አመራር፣መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በጥሩ ስነ ምግባር የታነፁ፣ ለሙያቸው ተገቢ ክብር
ያላቸው፣ትምህርት ቤቱን ለማገልገል ቁርጠኛ እንዲሆኑ ማድረግ፣
ሥርዓተ ትምህርት
እቅድ 14
 ሥርዓተ ትምህርቱ ትርጉም ያለው ፣ አሳታፊ እና የተማሪዎቹን የእድገት ደረጃና ፍላጎቶች ያገናዘበ መሆኑን መምህራን
ይገመግማሉ፣ግብረ መልስ እንዲሰጡና እንዲያሻሽሉ ማድረግ፣
 መምህራን በሥራ ላይ ያለውን ሥርዓተ ትምህርት ጠንቅቀው እንዲያውቁ ማድረግ፣
 መምህራን የሚያስተምሩት ትምህርት በአገር አቀፍና በክልል የተዘጋጁ ሥርዓተ ትምህርቶችን ያገናዘበ እንዲሆን ማድረግ፣
/
ምዘና ፈተና
እቅድ15
 ተማሪዎች በትክክል ተመዝነዋል፣ አስፈላጊው ግብረመልስ እንዲሰጣቸው ማድረግ፣
 በትምህርት ቤቱ የሚዘጋጅ ምዘና ስርአተ ትምህርቱን መሰረት ያደረገ በቢጋር /Table of
Specifications/ የተዘጋጀ አድንዲሆን ማድረግ፣
 ተማሪዎች በክልል/ከተማ አስተዳደር፣በዞን/ክፍለ ከተማ በወረዳና በጉድኝት ማዕከል በሚዘጋጁ ፈተናዎች እንዲመዘኑ
ማድረግ፣
 መምህራን የተማሪዎችን ውጤት ለመለካት በተቀመጠው ዝቅተኛ የመማር ብቃት /MLC/ መሠረት የንድፈ ሃሳብና
የተግባር ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ ተከታታይ ምዘናን እንዲጠቀሙ ማድረግ፣
 መምህራን የተማሪዎችን ውጤት በመተንተን ድጋፍ እንዲሠጡ ማድረግ፣
 መምህራን ተማሪዎች ውጤታቸውን እንዲያሻሽሉ ግብረ-መልስ በመስጠት ድጋፍ እንዲያደርጉ ማድረግ፣
 ትምህርት ቤቱ የተማሪዎችን ውጤት ለወላጆች በማሳወቅ ግብረ መልስ እንዲቀበሉ ማድረግ፣

ክትትልና ግምገማ
እቅድ 16
 የትምህርት ቤቱ አመራር የልዩ ልዩ አደረጃጀት ተጠሪዎች ያቀዷቸው እቅዶች በተያዘላቸው ጊዜ፣ ጥራትና
መጠን መሰረት መፈጸማቸውን መከታተል፣
እቅድ 17
 ትምህርት ቤቱ የሰው ፣ የገንዘብ እና የንብረት ሃብት አጠቃቀም ስርአት ዘርግቶ ተግባራዊ እንዲያደርግ ማድረግ፣
 መምህራን በሰለጠኑበት የትምህርት አይነት ተመድበው እንዲያሥተምሩ ማድረግ
 ርዕሰ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ተመድበው እንዲሰሩ ማድረግ፣

6|Page
 በት/ቤቱ ያሉ ህንፃዎች፣ ፋሲሊቲዎች እና ተጨማሪ ግብዓቶች በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣
 የት/ቤቱ በጀት ቅድሚያ ለተሰጣቸው የትምህርት ቤት መሻሻል እቅድ ላይ በተቀመጡና አግባብነት ያላቸው
አካላት በወሰኑት መሠረት በተገቢ መንገድ ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣

የትምህርት ቤት፣ የወላጆችና የማህበረሰብ አጋርነት

እቅድ 18
 ትምህርት ቤቱ ከተማሪ ወላጆችና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ጠንካራ ግንኙነት እነዲኖራቸው ማድረግ ፣
 ትምህርት ቤቱ ወላጆች በመማር ማስተማሩ ስራ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማበረታታት፤ በትምህርት ቤትና በክፍል
ደረጃ ወላጆች ትርጉም ያለው ተሳትፎ በተደራጀ መልኩ እንዲያደርጉ ማድረግ፣
 ትምህርት ቤቱ በየወቅቱ ለወላጆችና ለአካባቢው ማህበረሰብ በተማሪዎች የትምህርት አቀባበልና ውጤት፣ ባህርይ፣
የፋይናንስ አጠቃቀም እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ላይ መረጃ እንዲሰጥና ግብረ መልስ እንዲቀበል ማድረግ፣
 ወላጆች ልጆቻቸው በቤት ውስጥ በትምህርታቸው እንዲበረታቱ ማገዝ፣
 ወላጆች በወላጅ፣ተማሪ፣ መምህር ህብረት(ወመህ/ወተመህ) እንቅስቃሴ ላይ ንቁ ተሳትፎእንዲያደርጉ ማድረግ፣
 ትምህርት ቤቱ ለአካባቢው ማህበረሰብ በአንጻራዊነት የልህቀት ማዕከል በመሆን እንዲያገለግል ማድረግ፣
 ወላጆች በትምህርት ቤቱ የሥራ አፈፃፀም መርካታቸውን ማረጋገጥ

ትምህርት ቤቱና ተማሪዎች ያስመዘገቡት ውጤት


እቅድ 19
 ትምህርት ቤቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ የትምህርት ተሳትፎና የውስጥ ብቃት/Internal efficiency/
የትምህርት ልማት ዘርፍ መርሃ ግብር ግቦችን እንዲያሳካ ማድረግ፣
 በትምህርት ቤቱ አካባቢ የሚገኙ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ሁሉ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ማድረግ፣
 ትምህርት ቤቱ የጥቅል ተሳትፎ ዕቅዱን እንዲያሳካ ማድረግ፣
 የትምህርት ቤቱ የተማሪዎች ጾታዊ ምጣኔ ዕቅዱን እንዲያሳካ ማድረግ፣
 የትምህርት ቤቱ መጠነ ማቋረጥ እንዲቀንስ ማድረግ፣
 የትምህርት ቤቱ መጠነ መድገም እንዲቀንስ ማድረግ፣
 ሁሉም ተማሪዎች በክፍል ፈተና በእያንዳንዱ የትምህርት አይነት ውጤታቸው 50 ፐርሰንት እና በላይ እንዲያስመዘግቡ
ማድረግ፣
 ትምህርት ቤቱ ለሁሉም ሴት ተማሪዎች ባደረገው ልዩ ድጋፍ በክፍል ፈተና በእያንዳንዱ የትምህርት አይነት
ውጤታቸው 50 ፐርሰንት እና በላይ እንዲሆኑ ማድረግ፣
 ትምህርት ቤቱ ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ባደረገው ልዩ ድጋፍ በክፍል ፈተና በእያንዳንዱ የትምህርት አይነት
ውጤታቸው 50 ፐርሰንት እና በላይ እንዲሆን ማድረግ፣
 የተማሪዎች የክልልና የብሄራዊ ፈተና ውጤቶች በትምህርት ቤቱ ዕቅድ መሰረት ማሳካት፣

-
የተማሪዎች ግለ ስብዕና

7|Page
እቅድ 20
 ተማሪዎች በስነ ስርዓት የታነጹ፣ መልካም እሴቶችና ባህልን የተላበሱ፣አካባቢን
 የመንከባከብ ሃላፊነት የሚሰማቸው መሆኑ በተግባር ንዲያረጋግጡ ማድረግ፣
 ተማሪዎች በስነ ምግባር የታነጹ፣ የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ የሚያከብሩ፣እርስ በርስ የሚከባበሩ፣ የሚተጋገዙና ኪራይ
ሰብሳቢነትን የሚታገሉእንዲሆኑ ማድረግ፣
 ተማሪዎች የትምህርት ቤቱን ንብረት እንዲከባከቡ ማድረግ፣
 ተማሪዎች የትምህርት ቤቱን እሴቶች፣ደንቦችና መመሪያዎችን አውቀው ስራ ላይ በማዋል ተጨባጭ ውጤት እንዲያመጡ
ማድረግ፣
 በትምህርት ቤቱ ተማሪዎች መካከል የመቻቻልና ልዩነትን በውይይት የመፍታት ባህል ማዳበር፣
 ተማሪዎች ትምህርት ቤታቸውንና አካባቢያቸውን እንዲከባከቡ ማድረግ፣

የመምህራንና የትምህርት አመራር ግለ - ስብዕና


እቅድ 21
 በትምህርት ቤቱ መምህራን፣ አመራርና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች መካከል ጥሩ ተግባቦት እና መስተጋብር
ተፈጥሯል፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን የመታገልና የተጠያቂነት ስሜት ማዳበር፣
 የትምህርት ቤቱ መምህራን ፣ አመራርና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ተማሪዎችን የሚያከብሩና ተግባቢ በመሆን
የተማሪዎችን የመማር ፍላጎት ማጎልበት፣
 በትምህርት ቤቱ መምህራን፣ አመራርና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች መካከል ጤናማ የሥራ ግንኙነትና በትብብር የመስራት
ባህል ማዳበር፣
 የትምህርት ቤቱ መምህራን፣ አመራርና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባርን የሚታገሉና
የሚፀየፉ፣ በተጠያቂነት መንፈስ እንዲሰሩ ማድረግ፣

የወላጆችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፎ


እቅድ 22
 ትምህርት ቤቱ ከወላጆች፣ ከአካባቢው ማህበረሰብና ከአጋር ድርጅቶች ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠሩ ትምህርት ቤቱ
ድጋፍ እንዲያገኝ ማድረግ፣
 ትምህርት ቤቱ ከወላጆች ፣ ከአካባቢው ማህበረሰብና አጋር ድርጅቶች ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠሩ ድጋፍ
እንዲያገኙ ማድረግ፣
 ወላጆችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፎ በመጨመሩ ትምህርት ቤቱን በባለቤትነትስሜት የመምራት ልምድ
እንዲያዳብሩ ማድረግ፣

8|Page

You might also like