You are on page 1of 3

መግቢያ

ትምህርት ለአንድ ሀገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍትህና ዲሞክረራሲያዊ ስርአት እንዲሁም ለመልካም
አስተዳደር መስፈን የሚጠበቅበትን ድርሻ በደንብ መጫወት ይችል ዘንድ የሚሰጠውንም ትምህርት ጥራት የማስጠበቅ
አለ የማይባል ጉዳይ ነው፡፡ በየክፍል ደረጃው የሚሰጠው ትምህርት ጥራቱ ተጠብቆ የተማሪዎች ውጤት መሻሻል
እንዳለበት ከባለ ድርሻው አካላት ከፍተኛ ጥራት ይጠበቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል ሁኔታና
የሁሉንም የትምህርት ውጤት በማሻሻልና ለኢኮኖሚው ቁልፍ ሚና መጫዎት የሚችል ዜጋ ለማፍራት የሚያስችሉ
ስልቶችን በመቀየስ መንቀሳቀስ አማራጭ የማይገኝለት ተግባር ነነው፡፡ በመሆኑም ሕይወተ ጽዮን አካዳሚ ት/ቤት
የተጀመረው አጠቃላይ የትምህርት ጥራት ፓኬጅ ለ 2011 ዓ.ም ትምህርት ዘመን አጠናክረን ቀጥለናል፡፡

/
ት ቤቱ አላማ

ሕይወተ ጽዮን አካዳሚ ትምህርት ቤት በመማር ማስተማሩ ሂደት ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን የት /ቤቱን ፈጣን
እድገት ማምጣት፡፡

ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በት/ቤቱ በመስጠት በእውቀት በክህሎትና በአመለካከት የተስተካከለና ለልማት፣ ለፍትህ፣
ለሰላም፣ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ትውልድ መቅረፅ፡፡
ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ ተመራማሪና አገር ገንቢ ዜጋ መፍጠር
በችሎተታው የዳበረ ትምህርቱን ከተጨባጭ መረጃዎች ጋር ማገናዘብና ውጤታማ ማድረግ የሚችል ዜጋ ማፍራት
የት/ቤቱ ውስጥ የሚገኙ የትምህርት መስኮችን በተመለከተ መምህራን የማስተማር ስልታቸውን ተማሪ ተኮር የሆነ
የማስተማር ስነ-ዘዴ እንዲከተል ማድረግ ከአካባቢ ጋር ተያይዞ መሻሻል የሚገባቸውን ስርአት ትምህርት ይዘቶች
በመለየት ለሚመለከተው አካል ግብር መልስ በመስጠት እንዲሻሻል ማድረግ
የተማሪዎችን በራስ የመተማመን መንፈስ በማዳበር ሀሳብን በማፍለቅ፣ የፈጠራ ስራዎችን በማለማመድ እንዲሁም
የመመረራመርና ችግርን የመፍታት ችሎታ እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡

ሃላፊነትና ተጠያቂነት የሚሰማው ዜጋን መፍጠር፣

ዕውቀትን፣ ክህሎትን፣ አመለካከትን በተሟላ መልኩ ለሚያስረዱ በመማር ማተማሩ ሂደት ጥራት ያለው ትምህርት
በመስጠት የደንበኞችን ፍላጎት የሚያረካ ዜጋ ማፍራት ነው፡፡
ግብ
የመማር ማስተማሩ ሂደት በብቃትና በጥራት የትምህርት አሠጣጥ በማግኘታቸው የረኩ ደንበኞችን ማየት
ትምህርት ለልማት መሳሪያ እንዲሆን የትምህርት ተሳትፎ ጥራት፣ ተገቢነትና ፍትሃዊነት አሰጣጥ ሂደትን ማረጋገጥ፡፡

የመደበኛ የትምህርት አገልግሎት ክፍያን ንጽጽር በሚከተለው ሰንጠረዥ መሰረት ይቀርባል፡፡

ተ.ቁ የክፍል ደረጃ በዚህ ዓመት በወር በቀጣይ ዓመት በወር ተሰልቶ ልዩነት (ጭማሪው)
ተሰልቶ እያስከፈለ ሊያስከፍል የታሰበው
ያለው
በገንዘብ በገንዘብ በመቶኛ በገንዘብ በመቶኛ
1 ቅድመ መደበኛ 520.00 ብር 720.00 ብር 28% 200.00 ብር 28%
ሕይወተ ጽዮን አካዳሚ ለ 2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመማር ማስተማሩ ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ
ያስችለው ዘንድ የተለያዩ የትምህርት ግባቶችን ለምሳሌ ወንበር፣ ጠረጵዛ፣ የተማሪዎች የውጪና የውስጥ መጫወቻ
ጥገናዎች፣ የፅህፈት መሳሪያ የኮፒውተር፣ ፕሪተር ቀለም፣ ቾክ፣ እስኪብሪቶ፣ ወረቀት የመሳሰሉትን ግብአት
በማሟላት ትምህርቱ የተሳካ እንዲሆን የሚረዳ ዝግጅት ለማድረግ፡፡

ትምህርት ቤቱ የትምህርት ጥራት ፓኬጅን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር ለት/ቤቱ
መሻሻል እንደ ግብዓት በመጠቀም ቀደም ሲል ከተሰሩት ስራዎች ባሻገር በኢንስፔክሽንና እውቅና ፍቃድ እድሳት ወቅት
በግብረ መልስ በታዩት ክፍተቶች ዙሪያ

ለምሳሌ፡- ክፍል ማስፋት፣ የጎደሉ ግብአት፣ የመጀመሪያ እርዳታ ክፍል፣ ግብዓቶች፤ ትምህርት መርጃና የማበለፀጊያ
ክፍል ግብአቶች፤ በመማሪያ ክፍል የጎደሉ ግብአቶችን እና ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቷቸው በት/ቤቱ መተግበር
የሚገባቸው ጉዳዮች በተገቢው ሁኔታ ለሟሟላት፡፡

የት/ቤቱ ባለቤት ስም ወ/ሮ ራሔል አባተ

ቀን 05/07/2011 ዓ.ም

ፊርማ

ቁጥር ሕ/ጽ/አ/ቁ 55/11

ቀን 5/07/2011 ዓ.ም

ጉዳዩ፡ - 2012 ዓ.ም የመደበኛ ክፍያን ጭማሪ አስመልክቶ ከት/ቤቱ ወ.መ. ጋር የተደረገ ውይይትን
ይመለከታል፡፡

ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው ሕይወተ ጽዮን አካዳሚ በቀን 15/06/2011 ዓ.ም ወላጅ ኮሚቴ

በመሰብሰብ የመደበኛ ክፍያ ጭማሪ መጠን ለመወሰን አወያይቶ ቃለ ጉባኤ ይዟል፡፡ ለዚህም በቀጣዩም

------------------- ገፆች አያይዘን ልከናል፡፡

ከሠላምታ ጋር
ህይወተ ጽዮን አካዳሚ

You might also like