You are on page 1of 40

0 | ገፅ

VISION:

 WODA envisions transformed Wolaitta from backwardness and poverty.

MISSION STATEMENT:

 The purpose of WODA is to provide services via human capital development,


sustainable livelihood security and integrated health to vulnerable, needy and poor
people of Wolaitta.

THEMATIC AREAS
 Human Capital Development.
 Sustainable Livelihood Security.
 Integrated Health services.

ADDRESS
 Tel፡+251465512188 / 1632 / 2474 / 3692 / 5242
 Fax፡+251465510037
 P.O.Box፡ 001: Wolaitta Soddo
 e-mail፡ wda@ethionet.et / wolaitta@gmail.com
 website፡ www.wolaittada.org
 Other social network sites www.facebook.com/wolaittadevelopmentassociation,
www.youtube.com/WODA2001

1 | ገፅ
ማውጫ

ርዕስ ገጽ

መልዕክቶች……………………………………………………………………………

መግቢያ……………………………………………………………………………….

የትምህርት ልማት……………………………………………………………………

ግብርና እና አካባቢ ጥበቃ…………………………………………………………….

የተቀናጀ ጤና ልማት………………………………………………………………….

ሪሶርስ ሞቢላይዜሽን……………………………………………………………………

የሰው ሃብት…………………………………………………………………………….

ክትትል ምዘና እና ኢንፎርሜሽን………………………………………………………..

2 | ገፅ
የወላይታ ልማት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ መልዕክት

3 | ገፅ
የወላይታ ልማት ማህበር ዋና
ዳይሬክተር መልዕክት

እጅግ የተወደዳችሁና
የተከበራችሁ የወላይታ ልማት
ማህበር አጋሮች፣ ደጋፊዎችና
ወዳጆች እንዲሁም አባላት
ከሁሉ አስቀድሜ ወልማ አሁን
ላለበት
ደረጃ እንዲበቃ ላደረጋችሁት
ድጋፍ እና ላሳያችሁት
አለኝነታችሁ የተሰማኝን ጥልቅ
ክብርና ደስታ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡ ሁላችሁም እንደምታዉቁት ወላይታ ልማት ማህበር
ከሀገር ዉስጥ ደጋፊዎችም ሆነ ከሌሎች የዉጭ አጋሮች የሚያገኘዉን ሀብት በአግባቡ
በመጠቀም የወላይታ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ለማቃለል ያለአንዳች መሸራረፍ
ህዝቡን ተጠቃሚ በሚያደርግ ሥራ ላይ በማዋል የተሻለ ለዉጥ ለማምጣት ሲተጋ ቆይቷል፡፡
ወልማ ዳግም ከተመሰረተበት ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ከ3 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተስፋ
ሰጪ የልማት ተግባራትን አከናዉኗል፡፡ እ.አ.አ 2013 እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በትምህርት፣
በተቀናጀ ጤና፣ በግብርናና አከባቢ ጥበቃ እና በቢዝነስ ልማት የሥራ ዘርፎች ትኩረት
በመስጠት አመርቂ ዉጤት የተመዘገበበትን ሥራ እየሠራ ከርሟል፡፡ ታዲያ ለዚህ ሁሉ ስኬት
የጀርባ አጥንት የሆናችሁ እናንተ ናችሁና ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይገባችኋል ለማለት
እወዳለሁ፡፡
ይህ ማለት ግን የወላይታ ህዝብ ችግር ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል ማለት አይደለም፤ ከወላይታ
ልማት ማህበርም ከእናንተም ብዙ ሥራ መስራት ይጠበቃል ብል ማጋነን አይሆንም፡፡ ለዚህም
ልማት ማህበሩ አዲስ ስትራተጂክ ዕቅድ በማዘጋጀት በተሻለ ወኔና ተነሳሽነት ለመሥራትና
የህዝቡን እዉነተኛ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
በመጨረሻም ለዚሁ ስኬት የዘዉትር ድጋፋችሁና ትብብራችሁ እንደማይለየን ተስፋ እያደረኩ
ለማህበሩ በሁለት እግር መቆም ለሚታበረክቱት አስተዋጽዖ በድጋሚ በቃላት ለመግለጽ
የሚከብድ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ ለሁላችሁም መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ፡፡ እጅግ
አመሰግናለሁ፡፡

4 | ገፅ
መግቢያ
ወላይታ ልማት ማህበር (ወልማ) መንግስታዊ ያለሆነ፣ ለትርፍ ያልቆመ እና ህዝብንና
ደጋፊዎችን በማስተባበር የተለያዩ የልማት ሥራዎችን የሚሰራ የልማት ድርጅት ሲሆን
በ1993 ዓ.ም ዳግም ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እየሰራ ለህዝቡ
እያደረሰ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በ2005 ዓ.ም (2013) በአራት የትኩረት አቅጫዎችን
ማለትም በሥነ-ምህዳራዊ ላይ የተመሰረተ የምግብ ዋስትና፣ የትምህርት ተደራሽነትና
ጥራት፣ የተቀናጀ የሥነ-ህዝብ፣ የጤና አገልግሎትና አከባቢ ጥበቃ እና የሪሶርስ
ሞብላይዘሽንና ቢዝነስ ልማት መሰረት በማድረግ እንደየአስፈላጊነቱ እቅዱን እየከለሰና
ከወቅቱና ከየጊዜዉ ጋር ለሚሄዱ ጉዳዮች ቅድሚያ እየሰጠ ህዝቡን ተሳታፊ እና ተጠቃሚ
ያደረጉ የተለያዩ ሥራዎችን ሠርቷል፡፡
ዉድ አንባብያን በመጽሄቱ ዉስጥ የተካተቱ ዝርዝር ሀሳቦችን በቀላሉ መረዳት
እንዲትችሉ ብሎም ለሚቀጥለዉ ንባብ ጭብጥ እንድትይዙ አበይት ነጥቦችን በመግቢያችን
ልናሰፍር ወደድን፤ መልካም ቆይታን ከልብ ተመኘን፡፡
ወልማ በትምህርት ዘርፍ ለወላይታ ሊቃ ትም/ ቤት የተለየ ትኩረት ከመስጠት ባሸገር
የመጀመሪያ ደረጃ የትምህርት ጥራት እና በአልፋ (Aclerated Learning For Africa)
የመጀመሪያ ደረጃ የት/ት ፕሮጀክቶች የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በበጀት ዓመቱ ሰፊ
ሥራ እየሰራ ቆይቷል፡፡ በዚህም መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁስ
መስጠት፣ደሀ የሆኑና ለችግር የተጋለጡ ሕፃናትን መርዳት፣ የራስ አገዝ ቡድን ማደራጀት፣
ልጅ ለልጅ ፕሮግራም እና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በማከናወኑ አመርቂ ዉጤት
ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
ወልማ በስነ-ምህዳራዊ ግብርና ላይ የተመሰረተ የምግብ ዋስትና ስራ ላይ በተለያዩ
ወረዳዎች የፊዚካል አፈርና ወሃ ጥበቃ ሥራ፣ ኩሬዎች ቁፋሮ፣ እንዲሁም የተጎዳዉን
መሬት በሥነ- ህይወታዊ ሥራዎች ለመሸፈን የተለያዩ የሣር ዘሮች እንዲተከሉ በማድረግ
አከባቢዉ እንዲያገግም አድርጓል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የተለያዩ የዝንጅብልና የካሳቫ ዘሮች
ለአርሶ አደሮች ተሰራጭተዉ ስለአጠቃቀምና አተካከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና
እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡
ወልማ በጤናዉ ዘርፍ አካል ጉዳተኞች ማህበራዊ አገልግሎት፣መድኃኒት አገልግሎት፣
የተለያዩ ቀዶ ጥገና መደበኛ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እንዲሁም በተቀናጀ ስነ-

5 | ገፅ
ተዋልዶ፣ ጤናና አከባቢ ጥበቃ ሥራ ላይ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠናዎች እንዲሰጥ
ተደርጓል፡፡
በሪሶርስ ሞብላይዘሽን ዘርፍም ተጨማሪ አባላት ማፍራት፣ ገቢን አሟጦ መሰብሰብ፣
የወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብን ማጠናከር፣ ቅርንጫፎችን የመደገፍ፣ በቢዝነስ ልማት ላይ
የተለያዩ ስልጠናዎችንና መነሻ ካፒታል የመስጠት እና ወዘተ ሥራዎችን ሰርቷል፡፡
ዉድ የመጽሄታችን ታዳሚዎች በእስካሁኑ ቆይታችሁ ወልማ እ.አ.አ በ2013
ያከናወናቸዉን የልማት ተግባራት የሚያስገነዝብ ጭብጥ እንደያዛችሁ እምነታችን ነዉ፤
ከዚህ በማስከተል ደግሞ የበጀት አመቱን የልማት ጉዞ በዝርዝር የሚያስረዳዉን ጽሑፍ
እየጋበዝን በድጋሚ መልካም ንባብ ተመኘን፡፡

የትምህርት ልማት
ወላይታ ልማት ማህበር በበጀት አመቱ ከህዝቡ እና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች የሚያገኘዉን
ድጋፍ መሰረት በማድረግ በትኩረት ሲሰራ ከቆየባቸዉ ስራዎች በዋናነት የሚጠቀሰዉ
የትምህርት ዘርፍ ነዉ፡፡ ትምህርት ለወላይታ ህዝብ የህልዉናዉ ጉዳይ መሆኑን በማመን
ሁሌም ወልማ ከሚሰራቸዉ ስራዎች ሁሉ የላቀ ስፍራ ይሰጠዋል፡፡ በመሆኑም እንደ ከዚህ
ቀደሙ ሁሉ እ.አ.አ በ2013 ይህንን ዘርፍ በቀኝ እጁ ይዞ ሲሰራ መክረሙን በሚያሳይ መልኩ
የሚከተለዉን ተግባር አከናዉኗል፡፡

የትም/ ቤቶች ግንባታ እና እድሳት፣ የትም/ት ቁሳቁስ አቅርቦት፣ የትም/ ቤቶች አቅም
ግንባታ ስልጠና ወዘተ በትምህርት ልማት ዘርፍ በበጀት ዓመት ከተሰሩ ስራዎች በዋናነት
የሚጠቀሱ ናቸዉ፡፡ በዚህ ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች ፕላን ኢንተርናሸናል፣ ኢሶብ ፋዉንዴሸን፣
ጀኔቫ ግሎባል፣ ሚንስ ፎር ላይፍ፣
ዶን ቦስኮ ከተሰኙ አጋር ድርጅቶች
እንዲሁም ከተለያዩ ገቢ ምንጮች
የተገኘ ብር 14,747,616 (37%)
ወጪ ተደረጎ ተተግብረዋል፡፡

ወልማ ከፕላን ኢንተርናሽናል


ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በቦሎሶ ሶሬ
ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ

Figure 1፡ ለመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ከተሰራጩ የኮምፒውተር እና ፎቶኮፒ ማሽኖች በከፊል

6 | ገፅ
የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተለያዩ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ በፕሮጀክቱ ከተከናወኑ
ስራዎችም አብዛኛዎቹ የአመለካከት ለዉጥን በማስፋት የትምህርት ጥራትን እዉን ሊያደርጉ
የሚችሉ የአቅም ግንባታ ሥራዎች ናቸዉ፡፡
በትምህርት ቤቶች ላይ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ
በሚደረገዉ ጥረት የተስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት የምክር አገልግሎት ለሚሰጡ የቡድን
አባላት፣ ከሴቶች ክበብ እና ከሥርዓተ ፆታ ክበባት ለተወጣጡ 62 (ወ 59 ሴ 3) አባላት
ስልጠና የተሰጣቸዉ ሲሆን በስልጠናዉ ያገኙትንም እዉቀት በመጠቀም ለዉጥ ማስመዝገብ
ችለዋል፡፡

በሌላም በኩል ለ72 (ወ 60 ሴ 12) ወላጅ መምህራን ሕብረት ሰብሳቢዎች፣ ስልጠና ቦርድ
አባላት፣ መንግስት መ/ቤቶች ተወካዮች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች
በትምህርት ቤትና ከትምህርት ቤት ውጭ ላሉ ሴቶች ትምህርት በማመቻቸት እና በአካል
ጉዳተኞች ድጋፍና እክብካቤ ፅንሰ ሀሳብ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ይህም በተለያዩ ምክንያቶች
ጫና ደርሶባቸዉ ወደኋላ የቀሩ ሴቶችና አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን በመታደግ ረገድ ከፍተኛ
ፋይዳ አበርክቷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በት/ቤቶች በተደረገው ምልከታ በታዩ ክፍተቶች ላይ
ያተኮረ ከተለያዩ ት/ቤቶች ለተወጣጡ ለ46 የሴቶች መማክርት ቡድን፣ ለሴቶች ክበባት እና
ለሥርዓተ ፆታ ጉዳይ ተወካዮች ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ስልጠናዉን ያገኙ አካላት በየትም/
ቤታቸዉ ተግባር ላይ በማዋላቸዉ በሴት ተማሪዎች ላይ የሚደርሱ ችግሮችን በመፍታት
መልካም አጋጣሚ መፍጠር ተችሏል፡፡

በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በሚገኙ 22 ትም/ ቤቶች የተቋቋሙ የትም/ ቤት ክበባትን ለማጠናከርም 40


(ወ 9 ሴ 31) ክበባቱን ለሚመሩ መምህራን በክበባት ማኑዋልና በተማሪ ስነ-ምግባር ላይ
ያቶከረ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ለ22 (ወ 4 ሴት 18) የሴት ተማሪዎች
ክበብ መሪዎች በክበብ አመራርና ችግሮች አፈታት ላይ እንዲሁም ለ72 (ወ 25 ሴ 47) ጎበዝ
ተማሪዎችና ለ4 የትም/ ባለሙያዎች በሕይወት ክህሎት ላይ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይህም
ክበባትን የመምራት እዉቀት እንዲያዳብሩ የረዳቸዉ ሲሆን በህይወት ክህሎት ላይ የወሰዱት
ስልጠናም በግል ህይወታቸዉ ላይ ጭምር ለዉጥ እንዲያመጡ አስችሏቸዋል፡፡

7 | ገፅ
ሚኒ-ሚድያን በማጠናከር ተማሪዎች በትምህርት ስራ ላይ ያላቸዉን ተሳታፊነት እንዲያጎለብቱ
ብሎም ተስጧቸዉን ይበልጥ እንዲጠቀሙ ለማድረግ ስለሚኒ-ሚድያ ጠቀሜታ እና አሰራር
ከተማሪዎች፣ ከመምህራንና ከትምህርት ባለሙያዎች ለተወጣጡ 60 (ወ 32 ሴ 28)
ተሳታፊዎች ስልጠና ከመስጠት ባለፈ ክበባቱን በቁሳቁስ ለማጠናከር ሜጋፎን፣ የመኪና ባትሪ፣
ወዘተ ዕቃዎች ከነመለዋወጫዉ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በመሆኑም በአሁን ወቅት በሁሉም ትም/
ቤቶች የተጠናከረ የሚኒ-ሚድያ ስራ እየተሰራ ያለ ሲሆን ትም/ ቤቶቹም ለተማሪዎች
ማስተላለፍ የሚፈልጉትን መልእክት በተለይም የትምህርት ጥራት ጉዳይን እያዝናኑ
በሚያስተምሩ ፕሮግራሞች በማቅረባቸዉ በስራዉ ላይ ለዉጥ ሊመጣ ችሏል፡፡
በሌላ በኩል ለ40 (ወ 30 ሴ 10) የቀበሌና ወረዳ ትምህርት ስልጠና ቦርድ አመራሮችና ወላጅ
መምህር ህብረት አባላት በወረዳ መስክ ጉብኝት ወቅት በትምህርት ጥራት በታዩ ክፍተቶች ላይ
የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ በተለይም በትምህርት አስተዳደር እንዲሁም በገንዘብና ንብረት
አስተዳደርና አያያዝ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያትም ለ69 (ወ 51 ሴ 18)
መም/ራን የትም/ ጥራት ለማስጠበቅ አቅምን ከመገንባት አንጻር ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ
ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡
በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከሚሰራባቸዉ 22 ት/ቤቶች ለተወጣጡ 73
(ወ 40 ሴ 33) መምህራን፣ 7 (ወ 4 ሴ 3) የወረዳ ትም/ ባለሙያዎች በትምህርትና
ኅብረተሰብ፣ በካሪኩለም ማሻሻል፣ አተገባበርና ግምገማ እንዲሁም በትምህርት መሪነት
አስተዳደር ላይ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡ በክላስተር ትም/
ቤቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርና ልምዳቸውን በማካፈል እንዲማማሩ ለማድረግም
ጉብኝትና ውይይት ተደርጓል፤
በፕሮጀክቱ አፈፃፀምና በተገኙ
ልምዶች ላይም ከተለያዩ
የመንግስት አካላትና
መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች
ከተወጣጡ ተሳታፊዎች ጋር
ወርክሾፕ ተካሂዷል፡፡ በዚህም
መልካም ተሞክሮ የሚሆን
ልምድ መለዋወጥ ተችሏል፡፡

Figure 2: በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ዘርፍ ከተካሄዱ ሥልጠናዎች በከፊል

8 | ገፅ
በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፕሮጀክቱ በሚያካትታቸዉ ትም/ ቤት ሴት ተማሪዎች ፎረም
በተማሪዎች የሴሜስተር ውጤት እና በዓመቱ በታዩ ክፍተቶች ላይ በ45 ተሳታፊዎች (ወ 13
ሴ 32) ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት ተደርጓል፤ በሩብ ዓመት አፋጻጸምም ላይ ምክክር
ተደርጓል፡፡ በተደረገዉ ዉይይትና ምክክር ለታዩ ክፍተቶችና ችግሮች መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ
አማራጮችን ማግኘት ተችሏል፡፡ የሞዴስ አገልግሎት ለ5400 ሴት ተማሪዎች፤ ደብተር፣
እስክርብቶና ጫማ ለ263 (ወ 131 ሴ 132) ተማሪዎች ተሰጥቷል፡፡ ከትምህርት ገበታቸው
በተለያዩ ምክንያት የቀሩ 390 (ወ 184 ሴ 206) ተማሪዎች ወደ ትም/ ቤት እንዲመለሱ እና
ትምህርታቸዉን እንዲቀጥሉ ተደርጓል፡፡

በሌላም በኩል በተለያዩ ጫናዎች ሳቢያ ዉጤታቸዉ ዝቅ ያለባቸዉ በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በሚገኙ
12 ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የቲቶሪያል ትምህርት ሲሰጥ
ቆይቷል፡፡ በዚህም በ1 ለ5 አደረጃጀት በ20 ጎበዝ ተማሪዎች አማካኝነት ለሴቶችና ውጤታቸው
ዝቅተኛ ለሆነባቸው ተማሪዎች በ5,310 ቲቶሪያል ፕሮግራም ተዘጋጅተዉ በአጠቃላይ 40,858
(ወ 20,891 ሴ 19,967) ተማሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ በትም/ ቤቶቹ የሚገኙ መምህራንና
ሱፐርባይዘሮች በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታቸው የሚቀሩ ተማሪዎችን በተለይም
ሴቶችን ለመደገፍና የምክር አገልግሎት ለመስጠት ባደረጉት ቤት ለቤት ክትትል በአጠቃላይ
1,926 (ወ 809 ሴ 1,117) ወላጆች እና 1,792 (ወ 851 ሴ 941) ተማሪዎች የምክር
አገልግሎት አግኝተዋል፤ በዚህም በቤታቸዉ ቀርተዉ የነበሩትን ተማሪዎች ወላጆቻቸዉ ወደ
ትምህርት ቤት የላካቿቸዉ በትም/
ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ የት/ት


ጥራት ፕሮጀክት ትኩረት
በሚያደርግባቸዉ ትም/ ቤቶች የተለያዩ
ማጣቀሻ መፃሐፍት በቤተ-መጻህፍት
በመሟላታቸዉ የተማሪዎች የማንበብ
ባህልና የትምህርት ውጤት መሻሻሉን
በመስክ ምልከታ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
Figure 3፡ የተማሪዎች ቤተ-መጻሕፍት
በእነዚህ ትም/ ቤቶች በ2005ዓ.ም

9 | ገፅ
የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ 36 ሞዴል ሴት እና በክላስተር ደረጃ የጥያቄና መልስ ውድድር
ተደርጎ አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎች የማጣቀሻ መፃሐፍ፣ የተማሪ ቦርሳ፣ ደብተር ወዘተ
እንዲሸለሙ ተደርጓል፡፡

በከፍተኛ ጫና ዉስጥ አልፈዉ በርትተዉ በመማር በተለያዩ የመንግስት መስ/ ቤቶች እየሰሩ
የሚገኙ ሴቶች፣ የዩንቨሪሲቲ ሴት መምህራን እና የወላይታ ሊቃ ትመወ/ ቤት ሴት
ተማሪዎች ተሞክሯቸውንና የህይወት ልምዳቸዉን ለሴት ተማሪዎች በፋና ኤፍ.ኤም 99.9
ወላይታ ሶዶ ሬዲዮ ፕሮግራም አማካኝነት እንድያካፍሉ ተደርጓል፤ በትምህርት ጥራት ላይም
የተለያዩ ፕሮግራሞች በሳምንት ሁለት ጊዜ በወላይትኛና በአማርኛ ቋንቋዎች ተዘጋጅተዉ
እንዲተላለፉ በማድረግ የህዝቡን ንቃተ ህሊና ማሳደግ ተችሏል፡፡
በሌላም በኩል በወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ ባለሙያዎች አማካኝነት በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በሚገኙ
በተመረጡ ትም/ ቤቶች በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ጥናት ተካሂዶ በመማር ማስተማር
ላይ ለሚስተዋሉ ክፍተቶችና ችግሮች የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠቁሙ የጥናት ውጤቶችም
በትም/ ቤቶች ተግባራዊ እንዲሆን ተደርገዋል፡፡
ተማሪዎች በፈጠራ ሥራ ላይ ጠንካራ ተሳትፎ እንዲያደርጉ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሥራዎች
በቅርበት እንዲተዋወቁና የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችና የፈጠራ ሥራዎች በሌሎች ትም/
ቤቶችም እንዲተገበሩ ለማድረግ በጉሩሞ ኮይሻ የመጀመሪያ ደረጃ ትም/ ቤት የሳይንስና
ቴክኖሎጂ ሥራዎች ኤግዚቢሽን 191 (ወ 110 ሴ 81) ከተለያዩ ባለድርሻ አካላትና የወረዳ
ተማሪዎች ፎረም አባላት በተገኙበት ተካሄዷል፡፡ ተማሪዎችም ከተለያዩ የወዳደቁ ነገሮች
የተሰሩትን የፈጠራ ስራዎች ለተሳታፊዎች በማቅረባቸዉ ተሳታፊዎቹ ለአካባቢያቸዉ የተሸለ
ልምድ ቀስመዉ በስራ ላይ በማዋል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ለሴት
ተማሪዎች ማንበቢያና የምክር
አገልግሎት የሚሰጥባቸዉን
ክፍሎች በስድስት ትም/ ቤቶች
በመጠገን በተለያዩ አስፈላጊ
ቁሳቁሶች ማለትም 60
ጠረጴዛዎች፣ 120 ወንበሮች እና
18 መደርደሪዎች አንዲሟሉ

Figure 4፡ ለተለያዩ ት/ቤቶች ከተደረጉ ኮምባይንድ ዴስኮች በከፊል

10 | ገፅ
በማድረግ 10,337 (ወ 5,501 ሴ 4,836) ተማሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ በዚህም
በሴቶች ዉጤት ላይ መሻሻል ሊገኝ ችሏል፡፡
በሌላ በኩል በወረዳው ት/ጽ/ቤት በቀረበው ጥያቄ መሠረት ከፍተኛ የወንበር ችግር ያለባቸው 7
ት/ቤቶች 383 ኮንባይንድ ዴስኮች በመሰጠታቸዉ 2,298 (ወ 964 ሴ 1,334) ተማሪዎች
ከመቀመጫ ችግር እንዲላቀቁ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም 6 ት/ቤቶች መፀዳጃ ቤት የሌላቸውና
የሴት ተማሪዎች መፀዳጃ ቤቶች ላልተለያቸዉ ትም/ ቤቶች አዲስ መጸዳጃ ቤቶች
በመገንባታቸዉ ተማሪዎቹ በተሻለ ሁኔታ እየተጠቀሙባቸዉ ይገኛሉ፡፡
በ4 ክላስተር ትም/ ቤቶች የሚገኙ ሴት ተማሪዎች እየተዝናኑ እንዲማሩም ለማድረግ
የመጫወቻ ሜዳ በማደራጀት እና ቁሳቁሶችን ማለትም የስፖርት ልብስ፣ የተለያዩ ኳሶችና
ሌሎችም በመግዛት ለማዕከላት እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ የክላስተር ማዕካላትን ለማጠናከር
ለጉሩሞ ኮይሻ ት/ቤት አንድ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ 3 ኮምፕተርና ሌሎች የቴክኖሎጂ
ቁሳቁሶችን እንዲጠቀሙባቸዉ በመደረጉ ለረጅም ጊዜ ይታይ የነበረዉን የተክኖሎጂ እጥረት
ችግር በመቅረፍ ከፍተኛ ፋይዳ ማበርከት ተችሏል፡፡

በፕሮጀክቱ ለተካተቱ ትም/ ቤቶች


የተለያዩ የሳይንስ ትምህርቶች ላቦራቶሪ
ዕቃዎችና (kits) ኬሚካሎች ተገዝተዉ
እንዲሰራጩ ተደርጓል፤ ለመምህራንና
ተማሪዎች ስለዕቃዎችና ኬሚካሎች
በተሰጣቸዉ ስልጠና መሰረት የተግባር
ትምህርት ማጠናከር ችለዋል፡፡
በዳሞት ወይዴ ወረዳ በቶራ ዉልሾ
Figure 5፡ የላቦራቶሪ ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው ት/ቤቶች በአገልግሎት ላይ
ቀበሌ 400 ተማሪዎችን ተጠቃሚ
የሚያደርግ ትምህርት ቤት ተጠግኖ ለመማር ማስተማር ሥራ ምቹ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
በጃፓን ኤምባሲ ገንዘብ ድጋፍ በወላይታ ሊቃ ትም/ ቤት አንድ አዲስ ሕንጻ ተገንብቶ 15
ጠረጴዛዎችና 86 ወንበሮች ተሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ከጃፓን ኤምባሲ በተገኘው ገንዘብ
በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በሶሬ ሆምባ አንደኛ ደረጃ ትም/ ቤት አንድ ባለ 4 ክፍል መማሪያ ሕንጻና
መጸዳጃ ቤት ተገንብቷል፤ የተለያዩ ፈርኒቸሮችም ተሰጡ፡፡ ለዚሁ ትም/ ቤት አንድ የወላይታ

11 | ገፅ
ተወላጅ በራሳቸዉ ተነሳሽነት አንድ መደርደሪያና በርካታ መጻሕፍት በስጦታ አበርክተዋል፡፡
እንደዚሁም በኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ለዜቦ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 35 ጠረጴዛዎች፣ 12 የጥቁር
ሠሌዳዎች፣ 64 ወንበሮች እና 200 ዴስኮች ተሰጥቷል፡፡ በመሆኑም በየትም/ ቤቶች ይስተዋል
የነበረዉ የመማሪያ ህንጻ እና ቁሳቁስ እጥረት ሊቀረፍ በመቻሉ ተማሪዎች ተረጋግተዉ
በመማር ለተሸለ ዉጤት እንዲተጉ ማድረግ ተችሏል፡፡
በሌላም በኩል ወልማ ለ125 ወላጅ አጥ እና ድሃ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እያስተማረ ይገኛል፡፡

ከወልማ በአዲስ መልክ ስምምነት


ተፈራርሞ በ2013 ስራ በጀመረዉ
የተፋጠነ ትምህርት ለአፍሪካ
‘Accelerated Learning for Africa
program (ALFA)” በሚባለዉ
ፕሮጀክት በተለያዩ ምክንያቶች
እድሜያቸዉ ገፍቶ ትምህርት
ያልጀመሩ ወገኖች በአንድ ዓመት

Figure 4፡ የተፋጠነ ትምህርት ለአፍሪካ በተሰኘው ፕሮግራም የታቀፉ ተማሪዎች በትመህርት ገበታ ሦስት የክፍል ደረጃዎችን ተምረዉ
ላይ
እንዲያጠናቅቁ እያደረገ ይገኛል፡፡
ይህንን ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድረግ የተቀጠሩ 128 የፕሮጀክቱ ሠራተኞችም በበጀት አመቱ
ስለፕሮጀክቱ አተገባበር ስልጠና እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡

በአጠቃላይ በዚሁ አዲስ ፕሮጀክት 3,000 (ወ 1,528 ሴ 1,472 ) ትምህርት ቤት ያልገቡ


ልጆች በአራት ወረዳዎች (ሁምቦ፣ ኪንዶ ኮይሻ፣ ዱጉና ፋንጎ እና ዳሞት ወይዴ) ከእያንዳንዱ
30 ማለትም በአጠቃላይ በ120 ማዕከላት ትምህርታቸዉን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ ለመጀመሪያ
ዙር አስፈላጊ ከሆኑ የትም/ ቁሳቁሶች 40 ፓኬት ማርከር፣ 3120 ዶሲ፣ 800 ደርዘን ደብተር፣
80 ፓኬት እስክብርቶ፣ 260 ፓኬት እርሳስ፣ 3120 ላጲስ፣ 3000 የእርሳስ መቅረጫዎች እና
ሌሎች የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች እንዲዳረሱ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ለማዕከላቱ 115
ጠርጴዛዎች፣ 1,800 ወንበሮች፣ መለማመጃ ሠሌዳዎች ለ14 ትም/ ቤቶች በመሰራጨት
የፕሮጀክቱን ግብ ለማሳካት እየተሰራ ይገኛል፡፡

12 | ገፅ
ሌላዉ ከአልፋ ፕሮግራሞች
አንዱ በኅብረተሰቡ ዉስጥ
የቁጠባን ባህል ማስረጽ በመሆኑ
ለዚህም ተግባር በ120 የአልፋ
ማዕከላት 120 ቁጠባ ቡድኖች
ተቋቁመዉ ለእያንዳንዱ ቡድን
10,000 ብር ለመስጠት
ከመስከረም 2006 ዓ.ም ጀምሮ
እንደየቡድኑ ዉሳኔ ከ2 ብር እስከ
5 ብር በየቀበሌዉ በሚገኘዉ ኦሞ Figure 5፡Figure 6፡ የተፋጠነ ትምህርት ለ አፍሪካ በተሰኘው ፕሮግራም የታቀፉ ተማሪዎች
በትመህርት ገበታ ላይ
ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም
እንዲቆጥቡ ተደርጓል፡፡
ለእነዚህ ለተደራጁትና ለቆጠቡት እናቶችም ብር 1,200,000 በብድር ተሰጥቷቸዉ
እንደየፍላጎታቸዉ እና ዝንባሌያቸዉ በተለያዩ ሥራና ንግድ ዘርፎች ተሰማርተዉ የለዉጥ
እንቅስቃሴ እንዲጀምሩ ተደርጓል፡፡
በአልፋ ፕሮጀክት አፈጻጻም ላይ ከፍተኛ አስተዋእጾ ለሚኖራቸዉ ፕሮጀክቱ በሚያቅፋቸዉ
ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት ማለትም ር/መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች፣
ለቀበሌ አመራሮች በአራቱ አልፋ ዋና ዋና ተግባራት ማለትም በአልፋ ክፍል፣ የመጀመሪያ
ደረጃ ትም/ ቤቶች አቅም ግንባታ፣ ልጅ ለልጅ ፕሮግራም እና ራስ አገዝ የቁጠባ ቡድን ላይ
ለ120 (ወ 119 ሴ 1) የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም
ፕሮጀክቱ ከሚያቅፋቸዉ ትም/ ቤቶች ለተወጣጡ 280 (ወ 239 ሴ 41) ተሳታፊዎች ስለ
አልፋ ፕሮጀክት በቀበሌ ደረጃ ሥልጠና ተሰጥቷቸዉ ግንዛቢያቸዉ እንዲያድግ እና
ለስኬታማነቱ የበኩላቸዉን እንዲያበረክቱ ተደርጓል፡፡
ፕሮጀክቱ በሚያቅፋቸዉ ወረዳዎች ልጅ ለልጅ ፕሮግራም እንዲጠናከር በአጠቃላይ 200 (ወ
167 ሴ 33) የሚያስተምሩ አቻ ተማሪዎች በማዘጋጀትና በየሰፈራቸው 1000 ሕፃናት
እንዲመዘገቡ ተደርጎ ፊደል ማሰተማር ጀምረዋል፡፡

13 | ገፅ
የአልፋ ክፍል የመጀመሪያ ዙር በጥሩ ሁኔታ ተጠናቅቆ የሁለተኛ ዙር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ለሁለተኛ ዙር ትምህርት ሂደት የተለያዩ የመማሪያና ማስተማሪያ ቁሳቁሶች
እንዲሰራጩ በመደረጉ ተማሪዎቹ በጥሩ ሁኔታ እየተማሩ ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል ፕሮጀክቱ ተግባራዊ በሚሆንባቸዉ ትም/ ቤቶች ለአልፋ ተማሪዎች ድጋፍ
እንዲሆንና ለት/ቤቶቹም አስፈላጊ ጉዳዮች መንቀሳቀሻ እንዲሆን ለ40 ትም/ ቤቶች ብር
120,000 ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር በትምህርት ዘርፍ ከሚያከናዉናቸዉ አበይት የልማት ተግባራት


መካከል የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ሥራ በዋናነት የሚጠቀስ መሆኑ እሙን ነዉ፡፡
በመሆኑም ማህበሩ ይህንን ተቋም በመጠቀም ወደፊት ለወላይታ ብሎም ለኢትዮጵያ እድገት
ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ በየትኛዉም መድረክ ተወዳዳሪ የሚሆኑ ዜጎችን ለማፍራት
ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በ2004 ዓ.ም የተገኘውን ውጤት መሠረት በማድረግና የተገኙ


ልምዶችን በመቀመር በ2005 ዓ.ም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ጠንክሮ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
ትምህርት ቤቱ ለ2005 ዓ.ም በዓመቱ መጀመሪያ ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል 253 (ወ 213 ሴ
40) ወላጅ አጥና ድሃ እንዲሁም የትምህርት፣ የምግብ፣ የመኝታ ወጪዎችን እና ሌሎች
አገልግሎቶችን በመሸፈን የሚያስተምራቸዉ ተማሪዎችና 332 (ወ 214 ሴ 118) ወጪያቸውን
በመጋራት የሚማሩ በአጠቃላይ 585 (ወ 427 ሴ 158) ተማሪዎችን ተቀብሎ አስተምሯል፡፡

የ2005 ዓ.ም የተማሪዎችን የክፍል ውጤት ስንመለከት 2.7% ተማሪዎች ከ96-100%፣


40.7% ተማሪዎች ከ86-95%፤ 47.3% ተማሪዎች ከ73-85% ውጤት ሲያመጡ 53
ተማሪዎች (9.3%) ከ73% በታች ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ በአጠቃላይ 90.7% ተማሪዎች
ከመነሻ ማርክ በላይ ውጤት አምጥተዋል፡፡

ትም/ ቤቱ በበጀት አመቱ ከወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ 3,516ና ከቦዲቲ ከተማ 453
የተለያዩ የክፍል ደረጃዎች የተማሪ መጻሐፍትን በድጋፍ መልክ አግኝቷል፡፡ ይህም በዉስጡ

14 | ገፅ
የሚስተዋለውን የተማሪ መጽሐፍ እጥረት ችግር በመቅረፍ የተማሪ መጽሐፍ ጥምርታን
ከእንግልዝኛ መጽሐፍ በስተቀር 1፡1 እንዲሆን አድርጓል፡፡

የትም/ ቤቱን ክበባት ማጠናከርና ለሚሠሩ ሥራዎች ቼክ ሊስት ማዘጋጀት፣ 20 ተንቀሳቃሽና


ተንቀሳቃሽ ያልሆኑ የማስተማሪያ ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት፣ ቲቶሪያል ትምህርት ለ8ኛ፣ 10ኛ እና
12ኛ ክፍሎች መስጠት እና ተከታታይ የመምህራን ሙያ ማሻሻያ (CPD) ፋይል የማዘጋጀት
ሥራዎች በበጀት አመቱ የተከናወኑ ተግባራት ናቸዉ፡፡ በሌላም በኩል በትም/ ቤቱ የወላጅ፣
የተማሪና የት/ቤቱ ግንኙነት ማጠናከር፣ በትምህርት ቤቱ የተማሪ ውጤት መነሻ
(Benchmark) ሰይሞ መንቀሳቀስ፣ የተማሪዎች ምግብ አገልግሎት (ቁርስ፣ ምሳ፣ እራት)
ሳይጓደል እንዲቀርብ ማድረግ፣ ዩኒፎርም፣ ትራንስፖርት፣ ህክምና፣ የትምህርት ቁሳቁስና
የመኝታ አገልግሎት በወቅቱ፣ በጥራትና በበቂ ሁኔታ ማቅረብም በበጀት አመት በት/ቤቱ
የተከናወኑ ሥራዎች ናቸው፡፡
የትምህርት ቤቱን የ2005 ዓ.ም ብሔራዊና ክልላዊ ፈተና ዉጤት ስንመለከት፡-
ሀ. 8ኛ ክፍል (የተማሪዎች ብዛት 96)
 26 (26.53%) ተማሪዎች በአማካይ 90 እና ከዚያ በላይ፣
 67 (68.36%) ተማሪዎች በአማካይ 80 እስከ 89.9፣
 3 (3.06%) ተማሪዎች በአማካይ 75 እስከ 79 በመሆኑም በት/ቤቱ
እንደታቀደው 100% የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች አማካይ ዉጤት ከ75 በላይ
አስመዝግቧል፡፡
ለ. 10ኛ ክፍል (የተማሪ ብዛት 86)
 81 (94.2%)ተማሪዎች 4.00 (21 ተማሪዎች ሁሉንም ትምህርት “A”)፣
 5 (5.8%) ተማሪዎች 3.86 አስመዝግቧል፡፡
ሐ. 12ኛ ክፍል (የተማሪ ብዛት 58)
 51 (87.9%) 413 - 549 ዉጤት
 7 (12.1%) 550 - 595 ዉጤት አስመዝግቧል፡፡
በዚሁ መሠረት ከአጠቃላይ 58 ተማሪዎች፤
 44ቱ (75.86%) ሜዲካል ፣
 9ኙ (15.51%) ምህንድስና እና

15 | ገፅ
 5ቱ (8.62%) በሌሎች ጤና መስክ ተመድበዉ ወደተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች
ሄደዋል፡፡

ት/ቤቱ በ2006ዓ.ም የት/ት ዘመን ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል 526 (ወ 382 ሴ 144) ነባርና
አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም 216 (ወ 186 ሴ 30)
ተማሪዎች በወልማ ድጋፍ የሚማሩ ሲሆን 310 (ወ 197 ሴ 113) ወጪ በመጋራት የሚማሩ
ናቸዉ፡፡
ዉድ አንባቢያን ወልማ በበጀት አመቱ በትምህርቱ ዘርፍ ያከናወናቸዉ አበይት ተግባራት
እስካሁን ያየናቸዉን ይመስሉ ነበር፤ እስኪ አሁን ደግሞ ወደ ግብርናዉ ዘርፍ እናምራ እና
የተሰሩ ስራዎችን እናስቃኛችሁ፡፡ በድጋሚ መልካም ንባብ፡፡

ከአደጋ የተረፈች ነፍስ….. በቦሎሶ ሶሬ


ተማሪ ብርሃነሽ አንጁሎ ትባላለች፤ የ15 ዓመት ቁመተ ለግላጋ የደስደስ ያላት ወጣት ናት፤
ብርሃነሽ፡፡ ገና በልጅነቷ አባቷን በሞት የተነጠቀችው ብርሃነሸ በችግር ምክንያት የእድሜዋን
ያክል በትምህርት ሳትገፋ ቆይታ በ15 ዓመቷ ከጓደኞችዋ ወደኋላ ቀርታ ገና የ5ኛ ክፍል
ተማሪ ልትሆን ተገዳለች፡፡
ይህች ወጣት የቋጥኝ ያህል የከበዳትን ኑሮ ተቋቁማ ትምህርቷን በመጨረስ የህክምና
ባለሙያ የመሆን ራእይንም ሰንቃ ነበር የምትጓዘው፡፡
#የዘወትር ህልሜ ትምህርቴን ስጨርስ ሀኪም ሆኜ በቅድሚያ ተቸግረው ያሰተማሩኝን
ቤተሰቦቼን ከዛ ደገሞ ለአከባቢዬ እና ለመላው የሀገራችን ህዝብ ሙያዬ የሚፈቅደውን
አቅሜ የቻለውን ሁሉ ማድረግ ነው፡፡; በማለት ነበር ውሰጣዊ ህልሟን ያጋራችን፡፡
ነገር ግና ተምሮ የመለወጥ ብሎም ለወገን ዘመድ የመድረስ ትልሟን የሚያጨፈግግ፤
ህይወቷን የሚያናጋ እና ለመከራና ሰቆቃ የሚዳርጋት አንድ ደንቃራ ከፊቷ ተደቀነ፡፡
ነገሩ እንዲህ ነዉ፤ ለጥቃቅን ጥቅም ወገኑን አሳልፎ የሚሰጥ በርካቶችን በህገወጥ መንገድ
ወደአረብ ሀገር የሚልክ ደላላ ወጥመዱን በዚች ምስኪን ወጣት ላይ አነጣጠረ፤ መግቢያ
መውጫዋን አድፍጦ በመከታተል ልቧን አሸፍቶ ሃሳቧን ለማሰቀየርም ጊዜ አልፍጀበትም፡፡
በሚያማልል ምላሱ #በዚህ በወጣትነትሽ በችጋር የሚትጠበሽው ለምንድነው፤ አረብ አገር
ብትሄጂ በአጭር ጊዜ ውስጥ ረብጣ ብር አግኝተሽ የራስሽንም ሆነ የቤተሰቦችሽን ህይወት
የሚቀይር ታሪክ መፍጠር ትችያለሸ፤ ገና በልጅነት በእጦት እና በችግር መማቀቅ ምን

16 | ገፅ
የሚሉት ሞኝነት ነው፤ ኋላ እንዳይቆጭሸ ፈጥነሸ እድልሸን ተጠቀሚ; እያለ በቅቤ ምላሱ
አቋሟን እንደተፈታተናት ነገረች፡፡
የሩቅ ህልም ሰንቃ የምትጓዝ ብርቱ ወጣት የደላላው የሰላ ምላስ የሚያዘንበውን የቅዠት ሀብት
እና ብር የማካበት ስብከት መቋቋም ተሳናት፤ እንደምንም የደላላውን ፍላጎት አሟልታ ብር
ወደሚዛቅበት፤በቅዝበት ከበርቴ ወደሚኮንበት ተብየዉ አገር ወደ አረቡ ምድር ለማምራት
ወሰነች፡፡
እናም ጉዳዩን ለእናቷ በማማከር ለመላው ቤተሰቡ እንደ ብቸኛ ሀብት እና ቅርስ የሚታየውን
መሬት በማሸጥ አረብ አገር ለመሄድ ሽር ጉዱዋን ቀጠለች፡፡
በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ በህገወጥ መንገድ ለመሰደድ ሲሸረብ የቆየው ሴራ ይፋ የወጣው፡፡
እናቷ ስለ ጉዳዩን ክፋት ከኋላ ሲሰሙ ልባቸው ተሰበረ፤ እጅጉን አዘኑ፤ በአስቸኳይ ለት/ቤቷም
አሳወቁ፡፡ እንደመታደል ሆኖ ብርሃነሽ የሚትማርበት የመጌ ጢዮ 1ኛ ደረጃ ት/ ቤት ወልማ
ከፕላን ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ
ብሎም የሴት ተማሪዎች ተሳትፎ ለማጎልበት ከሚሠራባቸው 22 ት/ቤቶች መካከል አንዱ ነበር
እና ጉዳዩን የፕሮጀክት አስተባባሪው ይሰሙታል፡፡
እንደ ብርሃነሽ አይነት አግጦ እና አፍጦ የወጣ ከባድ ችግር ይደርሳል ብሎ በማሰብ ብቻ
ሳይሆን በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት የሚቀሩ ሴት ተማሪዎችን ለመደገፍ ወልማ በሰጠው
ስልጠና እንዲሁም ድጋፍ እና ክትትል አማካኝነት በትም/ ቤቱ የተቋቋመው የተማሪዎች
ካውንስሊንግ አገልግሎትም ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡
ብርሃነሽን ከጥፋት ለመታደግ ስለ ስደት አስከፊነት መምከር እና የደላላው አፈቀላጤነት
ሊደርስባት ከሚችለው ተገዶ መደፈር፣ በኤች አይ ቪ መጠቃት ብሎም ለሌሎች መከራ እና
ሰቆቃዎች ሊያተርፋት እንደማይችል በሚገባ እንድትረዳ ማሳመን ተጀመረ፡፡ ነገር ግን በባዶ
ተስፋ የነሆለለው ልቧ በቀላሉ ሊመለስ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም የነበረባትን ችግር አጉልቶና
የሌለ ተስፋ ሰጥቶ ደለላዉ ልቧን ክፉኛ አሸፍቷልና፡፡
ጉዳዩን በጽናት ይከታተል የነበረዉ የመጌ ጢዮ 1ኛ ደረጃ ትም/ ቤት ርዕሰ መምህር አቶ
መንግሥቱ መና ስለጉዳዩ እንዲህ በማለት ያስረዳሉ፡፡
‹‹ብርሃነሽ በስደት ልትሄድ እንደሆነ ሲሰማ በጣም ደነገጥኩ፣ ወደ ወላጅ እናቷም ሄጄ ስለጉዳዩ
ተወያየን፣ እናቷ ለአፍታ እንኳ እንድትለያት እንደማይፈልጉ ነግረውኝ ልጃቸውን
እንድታደጋት ተማጸኑኝ፡፡ እናም ከወልማ ተልከው ት/ቤታችን ሲደግፉ ከቆዩ ፕሮጀክቱ

17 | ገፅ
አስተባባሪ ጋር በመሆን ጉዳዩን ለሴቶች ጉዳይ፣ ለፖሊስ እና ፍርድ ቤት አሳውቅን፤ አቅማችን
የቻለውን ሁሉ አደረግን፡፡››
ክፉ ደጉን ለይታ የማታውቅ ይህች ወጣት አደጋ ላይ ስትወድቅ ማየት እጅጉን ሊጸጽታቸው
እንደሚችል የተረዱት የት/ቤቱ ዳይሬክተር፣ የተማሪዎች ካውንሲል አባላት እንዲሁም የወልማ
ፕሮጀክት አስተባባሪ ተስፋ ሳይቆርጡ ያደርጉት እልህ አስጨራሽ ጥረትም ፍሬ የሚያስገኝበት
ፍንጭ ሰጠ፡፡ በተደጋጋሚ ከነዚህ አካላት የሚሰጣት ምክር ብርሃነሽን ሃሳቧን እንድትቀይር
አደረጋት፡፡
ብርሃነሽም #ደላላው ሲያግባባኝ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ገንዘብ እንደማገኝ እና ከራሴ አልፌ
ለቤተሰቦቼ መትረፍን ሳስብ ልቤ ሸፈተ፤ ያለውን አማራጭ ሁሉ ተጠቅሜ ትምህርቴንም
በማቆም ወደ አረብ አገር ለመሄድ ወስኜ ነበር፡፡ የትም/ ቤታችን የካውንስሊንግ አባላት፣
ዳይሬክተራችን እንዲሁም የወልማ ፕሮጀክት አስተባባሪ በተደጋጋሚ በለገሱኝ ምክር ከደላላው
የተነገረኝ ሁሉ ባዶ ውሸት መሆኑን ተረዳሁ፡፡ በዚህም በችግር ምክንያት አርፍጄ የጀመርኩትን
ከምንም በላይ የወደፊት ተስፋዬ የሆነው ትምህርቴን በሙሉ ልብ ለመማር እና ከዚህ የስደት
ጉዞ ለመቅረት ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡ በአሁን ወቅት ተረጋግቼ ትምህርቴን በመማር ላይ ሲሆን
ከወላይታ ልማት ማህበር በተደጋጋሚ የሚሰጡኝ የተለያዩ ስልጠናዎች እንዲሁም የትምህርት
ቁሳቁስ ድጋፎች የበለጠ በትምህርቴ ላይ ትኩረት እንዳደርግ ረድቶኛል እና እግ/ሔር ይሰጥልኝ
ለማለት እወዳለሁ፡፡; አለች፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር ከፕላን ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ


ብሎም የሴቶችን ትምህርት ተሳትፎ ለማጎልበት በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በሚገኙ 22 ትም/ ቤቶች
ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ መድቦ እየሰራ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ እንደብርሃነሽ ያሉ በርካታ ሴት
ተማሪዎችን በመደገፍ እና ተስፋቸዉን በማለምለም ተጨባጭ ለዉጥ ማምጣት የቻለ ሲሆን
መንግስት፣ ህብረተሰቡ እና መላዉ የትምህርት ቤት ማህበረሰብ አባላት የሚያደርጉትን
ሁለንተናዊ ተሳትፎ አጠናክረዉ የሚቀጥሉ ከሆነ የተሸለ ለዉጥ ማምጣት ይቻላልና አብረን
እንሥራ እያልን ቆይታችን ቋጨን፤ መልካም ጊዜ ፡፡

2.የግብርናና አካባቢ ጥበቃ ልማት


ግብርና እና አካባቢ ጥበቃ ዘርፍ ወልማ እንደቁልፍ የትኩረት አቅጣጫ የሚያየዉ እና
የአርሷደሩን ህይወት ለማሻሻል ለሚደረገዉ ጥረት ከመንግስት ጎን በመቆም የአንበሳዉን ድርሻ

18 | ገፅ
ሰጥቶት ከሚሰራባቸዉ ዘርፎች አንዱ ነዉ፡፡ ለዚህም ሥራ በዋናነት የሚጠቀሱ አጋሮች
ኮንሰርን ወርልድዋይድ ኢትዮጵያ፣ አዉሮፓ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ልማት
ፕሮግራም (UNDP)፣ የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት/ፓካርድ
ፋዉንዴሽን ሲሆኑ ኦፋ፣ ሁምቦ፣ ዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ፑላሳ፣ ዳሞት ሶሬ እና ሶዶ ዙሪያ
ወረዳዎች ደግሞ ፕሮጀክቶቹ የተከናወኑባቸዉ አካባቢዎች ናቸዉ፡፡
በመሆኑም ወላይታ ልማት ማህበር በበጀት አመቱ በዘርፉ የግብርና ግባዓቶችን ማቅረብ፣
ማህበራትን ማደራጀትና ማጠናከን፣ ለአርሶ አደሮች የመነሻ ካፒታል በተዘዋዋሪ ብድር
ማቅረብ፣ የአፈርና አከባቢ ጥበቃ ስራ ማካሄድ፣ የዘር ማባዣ ጣቢያዎችን ማጠናከር የመሳሰሉ
ተግባራትን አከናዉኗል፡፡ ወልማ በኦፋ ወረዳ በበጀት ዓመቱ የተለያዩ የአፈርና ውሃ ጥበቃ
ሥራዎችን አከናናዉኗል፡፡ ከነዚህም መካከል በማንቻ ጎጋራ፣ በዋጭጋ ኤሾ እና ኮዶ ቀበሌያት
በ37.75 ሄ/ር መሬት ላይ 14.4 ኪ.ሜ የአፈር ካብ፣ 11 ኪ.ሜ ድንጋይ ካብ፣ 8.5 ኪ.ሜ
ክትር ስራ፣ 10 ኪ.ሜ አጥር ሥራ፣ 2500 ግማሽ ጨረቃ እርከን ሥራዎች በዋናነት
የሚጠቀሱ ናቸዉ፡፡ እንደዚሁም እንስሳት ውሃ የሚጠጡባቸዉን እያንዳንዳቸዉ 2,913 ሜ.
ኩብ ውኃ የመያዝ አቅም ያላቸዉን ሦስት ኩሬዎች ቆፊሮ ለህብረተሰቡ በማስረከቡ ከዚህ ቀደም
በአካባቢዉ ጎልቶ የሚስተዋለዉ የእንስሳት ዉሃ እጥረት ሊቀንስ ችሏል፡፡ በሌላም በኩል ከነዚህ
ቀበሌያት የድሃ ድሃ የሆኑ 400 ሰዎች ከላይ በተጠቀሱ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ
በመሳተፍ የሰፍቲኔት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ እነዚህን የተጎዱ አካባቢዎችን በስነ-ሕይወታዊ
ሥራዎች ለመሸፈን እና ቶሎ እንዲያገግሙ ለማድረግ የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን 18 ኩንታል
እርግብ አተር፣ 60 ኪ.ግ ሮዳስና 60 ኪ.ግ ዲሰሞዲየም የሣር ዘሮች ተገዝተው በዋጭጋ ኤሾ፣
ማንቻ ጎጋራና ኮዶ ቀበሌ ተፋሰስ ቦታዎች ላይ እንዲዘሩ በመድረግ የተጎዳውን መሬት የማገገም
ሥራ ተሠርቷል፡፡

በኦፋ ወረዳ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት መሠረት በውስን መሬት ብዙ ማምረት እንዲቻል የተሸለ
ዝርያ ያለዉ 270 ኩንታል ቮልቮ ዝንጅብል ዝርያ ከዋጭጋ ኤሾ፣ ቡሻ፣ ዎሽዎቻ ደቃያ
ቀበሌዎች ለተመለመሉ 196 (ሴ 79 ወ 117) ተጠቃሚዎች የተሰጠ ሲሆን ይህም ለእያንዳንዱ
ተጠቃሚ 1 እስከ 1.5 ኩ/ል እንዲደርስ ተደርጓል፡፡ ወልማ ከአረካ እርሻ ምርምር ጋር
በመተባበር በኦፋ እና በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳዎች በሦስት የዝንጅብል ዝርያዎች በ20 አርሶ
አደሮች ላይ ጥናት ሲደረግ የቆየ ሲሆን በ20 አርሶ አደሮች ማሳ የተተከለው የቦዛቢ፣ ያሊና
ቮልቮ ዝርያ ዝንጅብል ምርቱ ደርሶ እንዲሰበሰብ ተደርጓል፡፡

19 | ገፅ
Figure 8፡Figure 6፡ የቮልቮ ዝንጅብል ከ ስርጭት እስከ ምርት አሰባሰብ

የካሳቫ ምርት በስፋት ከሚመረትበት ኦፋ ወረዳ ዎሽዎቻ ደቃያ፣ ዋጭጋ ኤሾና ኮዶ ቀበሌያት
ለተመለመሉ 40 (ሴ 16 ወ 24) ተጠቃሚዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና ስልጠና ከተሰጠ በኋላ
40 የካሳቫ መክተፊያ ማሽን ተሰጥቷቸዋል፤ በዚህም ማሽን በመጠቀም ምርታቸዉን
በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲያቀርቡ ተደርጓል፡፡

20 | ገፅ
በቀበሌያቱ የሚገኙ የተፋሰስ ቦታዎችን በቀጣይነት ለማልማት የተፋሰሱ ተጠቃሚ ህብረተሰብን
በማህበር በማደራጀት የተለያዩ ግንዛቤ ማስጨበጫና አቅም ግንባታ ስልጠናዎች

Figure 9፡ በተፋሰስ ልማት መልሰው ባገገመ መሬት ተደራጅተው ንብ በማነብ ስራ ከተሰማሩ አርሷደሮች ምርት በከፊል

ተሰጥቷቸዋል፡፡ ስልጠናዉን ከወሰዱ በኋላም ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ይሆንላቸዉ ዘንድ


ከየቀበሌያቱ ለተደራጁ 40 የማህበራቱ አባላት በድምሩ 160 (ሴ 64 ወ 96) ተጠቃሚዎች
የተሻሻለ ዘመናዊ የንብ ቀፎ ከነሙሉ ቁሳቁሱ ጋር የተሰጠ ሲሆን በዋጭጋ ኤሾ ተፋሰስ የንብ
ማነቢያ ቤትም ተሰርቶላቸዉ ስራ እንዲጀምሩ ተደርጓል፡፡

በኦፋ ወረዳ ሲገነባ የቆየዉ የዎዮ


ድልድይ ግንባታም በበጀት ዓመቱ
የተጠናቀቀ ሲሆን ይህም ከ10 ሺህ
በላይ ወገኖችን በማስተሳሰር የዕለት
ዕለት ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ
ግንኙነታቸዉን እንዲያጠናክሩ ጉልህ
ድርሻ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

በሌላም በኩል በግብርና እና አካባቢ


Figure 10፡ ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀው በኦፋ ወረዳ የሚገኘው የወዮ ድልድይ
ጥበቃ ሥራዎች ተጠቃሚ የሆኑ
አርሶ አደሮች ግንዛቤና ክህሎታቸዉን ማሳደግ ይቻል ዘንድ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ
ሥልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡ በዚህም 151 (ወ 114 ሴ 37) 2 ሕብረት ሥራ ኮሚቴ አባላት፣
የእድርና ኃይማኖት መሪዎች፣ የቀበሌ አስተዳደሮችና የልማት ጣቢያ ባለሙያዎች በአበላ

21 | ገፅ
ሲፓና ሆብቻ ቦርኮሼ ቀበሌ በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ፣ በእሴት ግንኙነት (Value chain) ፅንሰ
ሀሳብ ስልጠና እንያገኙ ተደርጓል፡፡ 92 (ሴ 39 ወ 53) ተሳታፊዎች ደግሞ በፍራፍሬ ምርት
ላይ፣ 17 በንብ ማነብ ሥራ ላይ፣ 60 ተጠቃሚዎች (ወንድ 51 ሴት 9) በካሳቫ አመራረት እና
አመጋገብ ላይ፣ 38 ተጠቃሚዎች (ወንድ 33 ሴት 5) በዝንጅብል አመራረት ላይ፣ 32 (ወንድ
25 ሴት 7) የእህል ባንክ ተጠቃሚዎች ማህበር ኮሚቴ አባላት በብድር አያያዝ፣ አመዘጋገብ
እና በእህል ግዥና ሽያጭ እንዲሁም በገበያ ጥናት ላይ ስልጠና ያገኙ ሲሆን እነዚህ
በስልጠናዎቹ ያገኙትን እዉቀት ተግባራዊ በማድረግ አመርቂ ለዉጥ ማስመዝገብ ችለዋል፡፡

በሁምቦ ወረዳ አምፖ ኮይሻ ቀበሌ በሚገኘውን የዘር ማባዣ ጣቢያ ላይ 0.25 ሄክታር መሬት
በመለየት የተሻሻለ የሙዝ ዘር እና 1.5 ሄክታር መሬት ላይ ካሳቫ ተተክሎ እየለማ ያለ ሲሆን
ከደረሰው ሙዝ ሽያጭም 11 ድሃና አካል ጉዳተኛ ወገኖች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡

Figure 11፡ የአምፖ ኮይሻ የሚገኘው የተሻሻለ የሙዝ ዝርያ ምርት ለአቅመ ደካማ እና የአካል ጉዳተኛ ቤተሰቦች ሲሰራጭ

ወልማ በበጀት አመቱ በአዲስ መልክ ስምምነት የተፈራረመዉን የተባበሩት መንግሥታት


የልማት ፕሮግራም /UNDP/ የተባለዉን አዲስ ፕሮጀክት ህብረተሰቡ በሚገባ አዉቆ
ተሳታፊነቱን ያጠናክር ዘንድ ፕሮጀክቱ
ከሚተገበርባቸዉ አካባቢዎች በሁምቦ
ወረዳ አበላ ሲፓ እና ሆብቻ ቦርኮሼ
ከተወጣጡ 54 ተጠቃሚዎች ጋር
ኅብረተሰብን ያማከለ ተፋሰስ ልማት፣
እንዲሁም ቁጠባ እና ብድርን
Figure 12፡ ከአርሷደሮች ጋር ከተደረጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች በከፊል

22 | ገፅ
በተመለከተ ውይይት ተደርጓል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ከ28 የቀበሌ አመራሮች ጋር የሚለሙ
አካባቢዎችን የመለየት ስራና አጠቃላይ በፕሮጀክቱ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በተመሳሳይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተሻለ ግንዛቤ ኖሯቸዉ ከፍተኛ ለዉጥ እንዲመዘገብ
የወረዳው ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ፣ የህብረት ሥራ ማህበር፣ የወረዳ አስተዳደር እና የወረዳው
መሬት አስተዳደር በተሳተፉበት በፕሮጀክት ዓላማ እና ግብ ላይ ምክክር ከማድረግ ባለፈ
በአበላ ሲፓ እና ሆብቻ ቦርኮሼ ቀበሌያት ሁለት ማህበረሰብ አቀፍ ህብረት ሥራ ማህበራት
እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ከአበላ ሲፓ 72 አባላት ከሆብቻ ቦርኮሼ 143 አባላት በራሳቸዉ ዉሳኔ
የመመዝገቢያ ክፍያ ከፍለዉ በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ መቆጠብ ጀምረዋል፡፡ በማህበረሰብ
ሕብረት ሥራ ማህበራቱ አማካኝነትም ወልማ በአበላ ሲፓ 40.84 ሄክታርና በሆብቻ ቦርኮሼ
ደግሞ 24.85 ሄክታር የተጎዳ መሬት ለማልማት ከወረዳው መሬት አስተዳደር ጋር በመሆን
የመለየት ሥራ ሰርቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ 10 ሰዎች (ወ 6 ሴ 4) በጓሮ አትክልት ሥራ ላይ ስልጠና እንዲያገኙ


በማድረግ የተለያዩ የጓሮ አትክልት ዘሮች ተሰጥቷቸዉ በማምረት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
እንደዚሁም ከወረዳዉ ግብርና ጽ/ ቤት ጋር በመሆን 30 (ሴ 8 ወ 22) አርሶ አደሮች
ተመልምለዉ በበግ እና በፍየል እርባታ ላይ እንዲሰለጥኑ ከተደረገ በኋላ ለ15 (ሴ 8 ወ 7)
ሰዎች 23 በጎችና 25 ፍየሎች ተገዝተዉ ተሰጥቶላቸዉ ወደ ስራ ገብተዋል፡፡

ወልማ እያንዳንዱ ተጠቃሚ የሥርዓተ ፆታ እና የኤች አይቪ ኤድስ ግንዛቤያቸዉ ያድግ


ዘንድም ጎን ለጎን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ሲሰራ ቆይቷል፤ በዚህም ለዉጥ ሊመዘገብ
ችሏል፡፡

ተማሪዎች በአየር ንብረት ለዉጥ እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ ያላቸዉ ግንዛቤ አድጎ የበኩላቸዉን
ማበርከት ይችሉ ዘንድ በሁምቦ ወረዳ አበላ ሲፓ እና ሆቢቻ ቦርኮሼ ትምህርት ቤቶች የአካባቢ
ጥበቃ ክበብ እንዲጠናከር ተደርጓል፡፡ የክበቡ አባል ተማሪዎች ለሌሎች ጓደኞቻቸዉ የግንዛቤ
ማስፋት ስራ የጀመሩ ሲሆን ወቅቱን ጠብቀዉ ችግኝ ለመትከል ተዘጋጅተዋል፡፡

እንደ እድር እና ማህበር ያሉ ማህበረሰብ አቀፍ ተቋማት በአካባቢ ጥበቃ ላይ ያላቸዉ ተሳትፎ
ይጎለብትም ዘንድ 450 የተለያዩ የእርሻ መሳሪያዎች የአፈር እና ዉሃ ጥበቃ ስራ እንዲሰሩ
ተሰጥቷል፡፡ በዚህ ማህበረሰብ አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ስራ ከእቅድ እስከ ትግበራ ድረስ

23 | ገፅ
ህብረተሰቡ በንቃት እንዲሳተፍ ተደርጓል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በፕሮጀክቱ የወላይታ ዞን
የተፈጥሮ ሀብት እና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት እንዲሁም የሁምቦ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በሙሉ
ተነሳሽነት ተሳትፈዋል፡፡

ወልማ ይህን ፕሮጀክት ለመተግበር ከሁምቦ ወረዳ ጋር በገባዉ ስምምነት መሰረት በአበላ ፋረቾ
ለሚገኘዉ የችግኝ ማፊያ ጣቢያ ከ500 በላይ ኪሎ ግራም የሚመዝን የአካሺያ ሰለጊና፣
ግራቪሊያ እንዲሁም ዋንዛ፣ ቢሳና፣ ዝግባ፣
ወይራ፣ ኮሽም እና ሌሎች ዘሮችን ሰጥቷል፡፡

ወልማ በራሱ የቢዝነስ ልማት ባለሙያ


የህብረት ስራ ማህበር አባላትንም በጥቃቅን
ንግድ ዘርፍ አሰልጥኗል፡፡ ስልጠናዉን
ከወሰዱ 40 (ሴ 16 ወ 24) አባላት የተሻለ
የንግድ እቅድ ያቀረቡ 10 ሰልጣኞችን
Figure 12፡ አርሷደሮች በተፋሰስ ልማት ስራ ላይ
በመመልመል ለእያንዳዳቸዉ ብር 2,000
በመስጠት በንግድ ሥራ እንዲሰማሩ የተደረገ ሲሆን በአሁን ወቅት ሁሉም በተሰማሩበት
የንግድ ዘርፍ ዉጤታማ ሆነዉ ኑሯቸዉን በማሻሻል ላይ ይገኛሉ፡፡

ወልማ በበጀት አመቱ በግብርናና አከባቢ ጥበቃ ዘርፍ ያከናወናቸዉ ተግባራት ከላይ ያየናቸዉ
ሲሆኑ በዚህም በርካታ ወገኖች ተጠቃሚ ሆነዋል:: ከዚህ በመቀጠል የምንመለከተዉ ማህበሩ
በተቀናጀ ጤና አገልግሎት ዘርፍ ያከናወናቸዉን ተግባራት ይሆናል፤ እነሆ ብለናል፡፡

3. የተቀናጀ ጤና ልማት

ጤና ለሁሉም የልማት ተግባራት መሰረት በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ተግባር ነዉ ቢባል
ማጋነን አይሆንም፡፡ ይህንንም በመረዳት ወልማ በበጀት አመቱ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ
ሲሰራ ከርሟል፡፡ ለነዚህ ተግባራት ስኬት የሚዉል በገንዘብም ሆነ በቴክኒክ በመደገፍ ከፍተኛ
አስተዋእጾ ያበረከቱት ድርጅቶች ደግሞ ሲ ቢ ኤም ኢትዮጵያ፣ የክርስቲያን በጎ አድራጎትና
ልማት ማህበራት ህብረት/ ፓካርድ ፋዉንዴሽን እና ፒ ኤቺ ኢ ኢትዮጵያ ኮንሰርቲዬም ሲሆኑ
ዳሞት ሶሬ፣ ሶዶ ዙሪያ፣ ሁምቦ፣ ዳሞት ፑላሳና ዳሞት ጋሌ ደግሞ ፕሮጀክቶቹ
የተተገበሩባቸዉ እና በዘርፉ በተሰሩ ስራዎች ተጠቃሚ ከሁኑት ወረዳዎች መካከል በዋናነት
የሚጠቀሱ ናቸዉ፡፡

24 | ገፅ
ወልማ በዚሁ ዘርፍ የማህበረሰብ አቅም ግንባታ፣ የስነ-ተዋልዶ ጤና፣ ስነ-ህዝብ፣ጤናና አከባቢ
ጥበቃ ክበባትን ማደራጀትና ማጠናከር፣ የፈዉስ ህክምና አገልግሎት መስጠት እና ሌሎች
ሥራዎችን በእቅዱ መሰረት ሲሰራ ቆይቷል፡፡

ወልማ በበጀት ዓመቱ በሁምቦ፣ በዳሞት ሶሬና ዳሞት ፑላሳ በሚገኙ 21 ቀበሌዎች 317
(ወንድ 148 ሴት 169) የተለያዩ አካል ጉዳት ላለባቸው ሕፃናት የሜድካል፣ የትምህርት እና
የቤት ለቤት እንክብካቤ በመስክ ሠራተኞች እንዲሰጥ አድርጓል፡፡ ለአካል ጉዳተኛ ሕፃናት ቤት
ለቤት ክብካቤ ከማድረግ በተጨማሪ ለፈዉሳቸዉ የሚረዳ በህክምናዉ አጠራር ፓራለል ላይን
እና ኮርነር ወንበር (parallel line and corner chair) የተሰኙ ቁሳቁሶች ተበርክቶላቸዋል፡፡
ህጻናቱም ቁሳቁሶችን በሚገባ እንዲጠቀሙ በሲ ቢ አር (የማህበረሰብ አቀፍ ተሃድሶ) የመስክ
ሰራተኞች ክትትል እንዲያደርጉ በመደረጉ ጤናቸዉ ላይ ከፍተኛ መሻሻል ሊታይ ችሏል፡፡

በሌላ በኩል ወልማ 370 (ወ 200 ሴ


170) በዝሆኔ እና በሚጥል በሽታ
ለተጠቁ ወገኖች የግንዛቤ ማስጨበጫ
ስልጠና ሰትቻዋል፡፡ ከስልጠናዉም በኋላ
የሚጥል በሽታ ላለባቸዉ መድሃኒት፣
የዝሆኔ በሽታ ላለባቸዉ ደግሞ ጫማ
እና ሌሎች ቁሳቁሶችን በመስጠት
Figure 13፡ በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ ከተደረጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች በከፊል ጤናቸዉ እንዲሻሻል ጥረት አድርጓል፡፡
እንደዚሁም ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ከሚሆንበት ወረዳዎች ለተወጣጡ 43 ተሳታፊዎች (ወ 11 ሴ
32) ማለትም የማህበረሰብ ተቋማት ተወካዮች በጤና፣ በትምህርት እና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ
ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ 200 (ወ 107 ሴ 93) ወገኖች ደግሞ የወባ በሽታ መከላከያ አጎበር
እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም የህብረሰቡ አመለካከት ከመለወጡ ባሻገር ወባን በመከላከሉ
ረገድ ተጨባጭ ለዉጥ ሊገኝ ችሏል፡፡

የአካል ጉዳት ያለባቸዉን ወገኖች በመርዳትም


ረገድ በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ 12 (ወንድ
5 ሴት 7) የእግር ችግር ያለባቸው ሕፃናት
ወደ አዲስ አበባ ኪዩር ሆስፒታል ተልከዉ
የእግር ቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎላቸው

Figure 14፡ ለዝሆኔ በሽታ ተጠቂዎች ከተደረጉ የድጋፍ እና ክብካቤ ሥራዎች በከፊል

25 | ገፅ
የኦርቶፒድክ ጫማ እንድወስዱ በመደረጉ
በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ፡፡ በተመሳሳይ
መልኩ 351 (ወ 189 ሴ 162) የሚጥል
በሽታ ያለባቸው ሕፃናት በወላይታ ሶዶ
ሆስፒታል የሕክምናና የመድሃኒት አገልግሎት
እንዲያገኙ ተደርጓል፤ በህክምናዉም
Figure 15፡ ለዝሆኔ በሽታ ተጠቂዎች ከተደረጉ የድጋፍ እና ክብካቤ
ሥራዎች በከፊል
አማካኝነት ወደቀድሞ ጤንነታቸዉ ተመልሰዉ
የእለተለት እንቅስቃሴያቸዉን ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ከተለያዩ ወረዳዎች የተወጣጡ 9 ( ወ 6 ሴ
3) የከንፈር ስንጥቅ ችግር ያለባቸውን ወገኖችንም ወደ አዲስ አበባ ዘንባባ አጠቃላይ ሆስፒታል
ተልከዉ ቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎላቸዉ አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሌላዉ ወልማ በበጀት ዓመቱ በጤናዉ ዘርፍ ከሰራቸዉ ስራዎች በዋናነት የሚጠቀሰዉ የማየት
ችግር ያለባቸዉን ወገንች መርዳቱ ነዉ፡፡ በዚህም 421 (ወ 212 ሴ 209) የማየት ችግር
ያለባቸው ሰዎች በወላይታ ሶዶ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን
217 ሰዎች መድሃኒት እንዲሁም 93 ሰዎች ደግሞ የዓይን መነፅር እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
ሌሎች 111 ሰዎች የካታራክት ቀዶ ጥገና
ህክምና ተደርጎላቸዉ በጥሩ ሁኔታ ላይ
የሚገኙ ሲሆን 30 (ወ 18 ሴ 12) ማየት
ለተሳናቸው ሰዎች ለመራመድ የሚያግዛቸዉ
በትር (cane) ተሰጥቷቸዋል፡፡
Figure 15.1 ፡ ከ አካል ድጋፍ ልገሳ ስራዎች በከፊል ሁለት የእንቅስቃሴ ችግር ያለባቸው ወንዶች
ከሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ባለ 3 እግር
ብስክሌት 22 (ወ 11 ሴ 11) አካል ጉዳተኞች ደግሞ ከሐዋሳ ቺሸር ሰርቪስ ኢትዮጵያ ዊልቼር
አግኝተዉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም ወልማ ከቺሺያር ሰርቢስ


ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ከወላይታ ዞን
12 ወረዳዎች የተመለመሉ በአካል ጉዳት
ሳቢያ የመንቀሳቀስ ችግር ያለባቸዉ
1199 (ወ 831 ሴ 368) ወገኖችን ልዩ

Figure 16፡ የመስማት ችግር ላለባቸው ሕፃናት ከተደረጉ የሕክምና ሥራዎች


በከፊል
26 | ገፅ
ጫማ፣ ብሬስ እና የተለያዩ የአካል ድጋፍ ቁሳቁሶች ልገሳ አድርጓል፡፡ እንደዚሁም 11 (ወ 9 ሴ
2) የእጅ ጉድለት ያለባቸው ሰዎችም ሰው ሰራሽ እጅ ተተክቶላቸዋል፡፡ ከዳሞት ፑላሳና ሁምቦ
ወረዳ የተመለመሉ 483 (ወ 256 ሴት 227) የጆሮ ችግር ያለባቸው ሕፃናትም የሕክምና
አገልግሎት እንዲያገኙ በመደረጉ ከበሽታቸዉ ተላቀዉ መስማት ችለዋል፡፡

ህብረተሰቡ በአካል ጉዳተኝነት ላይ ያለዉ ግንዛቤ አድጎ ለለዉጡ አስተዋጽዖ ያበረክት ዘንድ
በተካሄዱ የንዛቤ ማስጨበጫ ዉይይቶች 6,972 (ሴ 2922 ወንድ 4050) ተካፋይ እንዲሆኑ
ተደርጓል፡፡ በተመሳሳይ በ21 ቀበሌያት 504 የማህበረሰብ ውይይት ፕሮግራም 1470
ተሳታፊዎች (ሴት 735 ወንድ 735) በተሳተፉበት የተካሄደ ሲሆን ተሳታፊዎችም የአካል
ጉዳተኛ ክብካቤና በቤተሰብ ዕቅድ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት እንዲያደርጉ ተደርጓል፡፡

የአካል ጉደተኞችን የኑሮ ደረጃ ለመለወጥም 1060 (ወንድ 504 ሴት 556) አካል ጉዳተኛ
ወገኖች በገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ እንዲሳተፉ በ21 ቡድን ተደራጅተዋል፡፡ እነዚህ በዳሞት ሶሬ፣
ዳሞት ፑላሳና ሁምቦ ወረዳዎች የተደራጁ 21 የራስ አገዝ የቁጠባ ቡድን አባላት በገቢ ማስገኛና
በቁጠባ ላይ ሥልጠና ከተሰጣቸው በኋላ ብር 47,857 በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም
ቆጥበዋል፡፡ ከቡድኖችም መካከል 10 ቡድኖች በቆጠቡት ገንዘብ በግ ገዝተዉ ማርባት
ጀምረዋል፡፡

ከዳሞት ፑላሳና ሁምቦ ወረዳዎች የተወጣጡ 21 መምህራንና 3 ሱፐርቫይዘሮች በአካቶ


ትምህርት፣ ልዩ ፍላጎትና ምልክት ቋንቋ ላይ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርገዋል፡፡ በተመሳሳይ 21
የመስክ ሠራተኞች፣ 21 የጤና ኤክስቴሽን ሠራተኞችና 4 የፕሮጀክቱ ሠራተኞች በአካል
ጉዳተኝነትና ክብካቤዉ ላይ ሰልጥነዉ እዉቀታቸዉ እንዲሰፋ ተደርጓል፡፡

2ኛ ዙር የተቀናጀ ስነ-ሕዝብ
ጤናና አከባቢ ጥበቃ ፕሮጀክት
ከመጀመሩ በፊት ፕሮጀክቱ
በሚተገበርበት አከባቢ የሚገኙ
ባለድርሻ ማለትም የመንግስትና
ማህበረሰብ አካላት የፕሮጀክቱ
Figure 17፡ ከማህበረሰብ ወይይት ተሳታፊዎች ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ከተደረጉ የግንዛቤ
ማስጨበጫ ውይይቶች በከፊል ዓላማ፣ አጠቃቀምና አተገባበር
ላይ በተለያዩ ቦታዎች ውይይት ከተደረገ በኋላ የወረዳና የቀበሌ አማካሪ ኮሚቴ ምርጫ
ተደርጎ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ በዚህም 60 (ወ 30 ሴ 30) የማህበረሰብ አመቻቾች በማህበረሰብ

27 | ገፅ
ውይይት ፅንሰ-ሀሳብና አካሄድ ላይ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ በሌላ በኩል 100 (ወ 50 ሴ
50) አቻ ለአቻ ዉይይት አስተባባሪዎችና አመቻቾች በተቀናጀ ስነ-ሕዝብ፣ ጤናና አከባቢ ጥበቃ
ላይ በ20 ቀበሌያት 1800 (ወ 900 ሴ 900) ሰዉ የተሳተፈበት የማህበረሰብ ዉይይት
በተቀናጀ ጤና፣ በአከባቢ ጥበቃ በኤች አይ ቪ ኤድስና፣ በአላስፈላጊ እርግዝና፣ ያለዕድሜ
ጋብቻ፣ በቤተሰብ ምጣኔ፣ ወዘተ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና ተሠጥቷቸዋል፡፡ በተጨማሪም
በማዳበሪያ አዘገጃጀት ላይ ለ60 (ወ 58 ሴ 2) ሞደል አርሶ አደሮች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ከሶዶ ዙሪያ፣ ከዳሞት ሶሬ፣ ከዳሞት ጋሌና ከዳሞት ፑላሳ ወረዳ ት/ቤቶችና ከት/ቤት ዉጪ
ለተወጣጡ 120 (ወ60 ሴ 60) ለስነ ተዋልዶ፣ ጤናና አከባቢ ጥበቃ (Population, Health
and Environment /PHE/) ክበብ መሪዎች የአመራርነት ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህም
ተሳታፊዎች ስለ ስነ ተዋልዶ፣ ጤናና አከባቢ ጥበቃ የተለየ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል፡፡

በሌላም በኩል ልማት ማህበሩ በጤና


ዘርፍ አገልግሎትን በማስፋት
ከጉልጉላ፣ ከጋቸኖ፣ ከቢቢሶ ኦሎላ
እና ከጉኑኖ ጤና ጣቢያ ጋር
በመተባበር ለ2,910 (ወ 1,553 ሴ
1,357) ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ
(mobile VCT service)

Figure 18፡ ከግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች በኋላ ተማሪዎች በፈቃደኝነት የኤች አይ ቪ /


ኤድስ የደም ምርመራ ሲያካሂዱ
በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የኤች አይ ቪ ምርመራና የምክር አገልገሎት በስፋት አከናዉኗል፡፡

ወልማ በበጀት አመቱ በጤናዉ ዘርፍ ያከናወናቸዉ ተግባራት ከሞላ ጎደል ከላይ ያየናቸዉ
ሲሆኑ በዚህ በርካታ ወገኖች ተጠቃሚ ሆነዋል:: ከዚህ በመቀጠል የምንመለከተዉ ደግሞ
ማህበሩ በሪሶርስ ሞብላይዜሽን እና ቢዝነስ ልማት ዘርፍ ያከናወናቸዉን ተግባራት ይሆናል፤
እነሆ ብለናል፡፡

............. አካል ጉዳተኞች እንደማንኛዉም ዜጋ ሰርተዉ መለወጥ ይችላሉ........


ተማሪ ታረቀኝ ዛዛ ይባላል፡፡ የ20 ዓመት ወጣት ነዉ፡፡ ገና ከተወለደ በ3 ወሩ የአካል ጉዳት
እንደደረሰበት ነገር ግን መንስኤዉ ምን እንደሆነ እነደማያቁ የነገሩን እናቱ ናቸዉ፡፡ ታረቀኝ
በ2002 ዓ.ም ከወልማ ጋር ሲገናኝ የ6ኛ ክፍል ተማሪ ነበር፡፡ ይህ ወጣት የአካል ጉዳት

28 | ገፅ
ይኑርበት እንጂ መንፈሰ ጠንካራ ወጣት በመሆኑ ለሌሎች ምሳሌ ሊሆን የሚችል እምቅ ሃይል
ያለዉ ነበር፡፡ ወልማም ለዚህ ወጣት ድጋፍ ቢያደርግ የተሸለ ደረጃ ላይ እንደሚደርስ በማመን
1500 ብር ለመንቀሳቀሻነት በተዘዋዋሪ ብድር ይሰጣል፤ ወጣቱም የተሰጠዉን ብድር በመጠቀም
ያለምንም ብክነት ስራ ላይ አዉሎ ካገኘዉ ትርፍ ብድሩን በአግባቡ መክፈል ቻለ፡፡ መገለል
እና መድሎ ሳይበግረዉ በጠንካራ መንፈስ የሚጥረዉን ወጣት ብርታት ያየዉ ወልማም
የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረጉም በላይ የአካል ድጋፍ ዊልቸር እንዲያገኝ በማድረግ
ይረዳዋል፡፡
ወጣቱ አሁንም ጥረቱን ቀጥሏል…. በአንድ በኩል ንግዱን በሌላ በኩል ደግሞ ትምህርቱን
በሚገባ በብልሃት ማስኬድ ቻለ፡፡ ይህ ብርታቱ ይጠናከር ዘንድም ወልማ ስልጠናዎችን
በመስጠት እንዲሁም የቅርብ ክትትል እና ድጋፉን ሲያጠናክርለት የበለጠ ተነሳስቶ ለስኬት
መብቃቱን ወጣቱ እንደሚከተለዉ ያስረዳል፡፡
#ገና ከልጅነቴ ጀምሮ ሰርቶ የመለወጥ እና የማደግ ህልም ነበረኝ፡፡ ነገር ግን ያሰብኩትን
ለማሳካት መነሻ የሚሆነኝን ብር ማግኘትን ግን እጅጉን ይከብደኝ ነበር፤ ይህ ችግር ደግሞ
በአካል ጉዳቴ ላይ ተደምሮ እንዴት ሊከብድ እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡ በአንድ በኩል
መገለል እና መድሎዉን ተቋቁሜ በሌላ በኩል ችግሬን እያታመምኩ ተስፋ ሳልቆርጥ
ትምህርቴን መግፋት ቀጠልኩ፡፡ ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ 6ኛ ክፍል ስደርስ ወልማ
ደረሰልኝ፡፡ እዉነት ለመናገር ሁሌም ተስፋ የማልቆርጥ መንፈሰ ጠንካራ ነኝ ብዬ አስባለሁ፡፡
በዚህም ወልማ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጠኝን ብር1500 በአግባቡ ተጠቅሜ በዉላችን መሰረት
በአመቱ ብድሩን መለስኩ፡፡ ወልማ በዚህ ብቻ አልተወኝም፤ የትምህርት ቁሳቁስ እና ዊልቸር
ሰጠኝ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም በህይወቴ ላይ ትልቅ ለዉጥ እንዳመጣ ስልጠና እንዳገኝ ረዳኝ፡፡
እናም ከወልማ ጋር ስንገናኝ ትንሽዬ የገጠር ሱቅ ነበረችኝ አሁን ግን በአስር ሺዎች ካፒታል
የሚንቀሳቀስ የከተማ ሱቅ አለኝ፣ በተጨማሪም የግል መኖሪያዬን ከተማ ዉስጥ ሰርቼያለሁ፤
በትምህርቱም መስክ 10ኛ ክፍል ደርሼያለሁ፡፡;
ታረቀኝ የግል ህይወቱን ብቻ በመቀየር አላበቃም፤ ለሌሎችም መኖርን የሚሻ ቅን ልብ ያለዉ
በመሆኑ ወንድም እና እህቶቹን ባገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ እንደሚረዳቸዉ ይናገራል፡፡
ታረቀኝ #በአሁን ወቅት ለኔ ሁሉም ነገር ተስፋ ሰጪ ነዉ፤ ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል ከግል
ህይወቴ አይቻለሁ፤ እኔ ገና 10ኛ ክፍል ብሆንም ወንድሜን 10+3 አስተምሬ አስመርቂያለሁ፤
ስራም ጀምሮ ህይወቱን መለወጥ ችሏል፡፡ እንደዚሁም እህቴን በ10+3 እየደገፍኳት
በማስተማር ላይ ነኝ፡፡ እናም ይህንን ከራሴ አልፌ ወንድም እና እህቶቼን መርዳት የቻልኩት

29 | ገፅ
ወልማ ባደረገልኝ መነሻ ድጋፍ መሆኑን ሳስብ ሁሌም ከልቤ አመሰግነዋለሁ፡፡ ሌላዉ ከወልማ
ያገኘሁት እንደኔ አካል ጉዳተኛ የሆኑ ወገኖችን ባለኝ እዉቀት እና አቅም ሁሉ መርዳት እና
መደገፍ የሚያስችል ትልቅ ዕዉቀት ነዉ፡፡ ይህ ሲሆን አካል ጉዳተኞች እንደማንኛዉም ዜጋ
ሰርተዉ መለወጥ ይችላሉ፤ ከራሳቸዉም አልፈዉ ሌሎችን መርዳት ይችላሉ ብዬ እስባለሁ፡፡
ለዚህ ደግሞ ዋናዉ ማሳያ እነዉ ነኝ፡፡ በመጨረሻም ወልማ ላደረገልኝ ድጋፍ ሁሉ ከልብ
የመነጨ ምስጋናን አቀርባለሁ፡፡; ብሏል፡፡

4. ሪሶርስ ሞብላይዜሽንና ቢዝነስ ልማት

ይህ ዘርፍ ማህበሩ የቆመለትን ዓላማ እውን ለማድረግ ሀብት በማሰባሰብና አባላትን በማፍራት
ብሎም አደራጅቶ በመምራት ረገድ ከፍተኛ ስራዎችን የሚሰራበት ዘርፍ ነዉ፡፡

በመሆኑም ወልማ በበጀት አመቱ ሀብት የማሰባሰብ፣ አባላትን የማደራጀትና


የማንቃት፣ ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብን የማጠናከር፣ የንግድ ክህሎት ስልጠናዎችን
የመስጠት፣ ለድሃ እና ዝንባሌ እንዲሁም ፍላጎት ላላቸዉ ሴቶችና ወጣቶች ብድር
የሚያገኙበት ሁኔታ በማመቻቸት የሥራ ዕድል እንዲፈጠር የማድረግ፣ የገቢ ማስገኛ
ተቋማትን የማደራጀትና የማጠናከር፣ የተለያዩ የልዩ ገቢ ማሰባሰቢያ ፐሮግራሞችን የማካሄድ
ሥራዎችን አቅዶ ሲተገብር ከርሟል፡፡ ተግባራቱንም በዝርዝር እንደሚከተለው እንመልከት፡፡

4.1 አባላት ልማትና ሀብት አሰባሰብ

ይህ ዘርፍ በተገባደደዉ በጀት አመት አባላቱንና ደጋፊዎችን በማስተባበር ብሎም ከለጋሽ


ድርጅቶች እና ከራሱ ተቋማት ለመሰባሰብ ካቀደው ሀብት 81% ተሳክቷል፡፡ በሃዋሳ፣
ሻሸመኔና ወላይታ ሶዶ ላይ ለማካሄድ የታቀደዉ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተከናዉኗል፡፡
ከቅርንጫፎቹ ጋር ውይይት በማደረግ፣ ኮሚቴ በማዋቀርና የሥራ ድርሻቸውን ለይቶ
በመስጠት እንዲሁም ገቢ የማሰባሰብ ስልት በአዲስ መልክ ተነድፎ እንቅስቃሴ በመደረጉም
ሥራዎች እንዲቀላጠፉ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም በሀዋሳ በተደረገዉ የገቢ ማሰባሰብያ በአጠቃላይ
1,406,873 ብር ቃል ተገብቷል፤ ቃል ከተገባዉም 1,041,755 ብር ተሰብስቧል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በሻሻመኔ ከተማ በተዘጋጀዉ የገቢ ማሰባሰብያ 412,161 ብር ቃል ተገብቶ


305,201 ብር ማሰባሰብ ተችሏል፡፡ ቀሪዉን ገንዘብ የማሰባሰብ ስራም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

30 | ገፅ
በወላይታ ሶዶ ከተማ በተካሄደዉ ወላይታ
ኤክስፖ 2006 ደግሞ ከ100 በላይ ነጋዴዎችን
በማሳተፍ ብሎም 3 ድርጅቶች ማለትም ሃዋሳ
ችፑድ ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና
ደቡብ ግሎባል ባንክ ስፖንሰር በመሆን
አጋርነታቸዉን እንዲያሳዩ በማድረግ
Figure 19፡ ወልማ ሻሸመኔ ቅርንጫፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ከፊል
ገጽታ
በአጠቃላይ 987,608 ብር ሊሰበሰብ ችሏል፡፡
ከዚሁ ጎን ለጎን የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች ከመንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ
ተቋማት ጋር በጥምረት በማካሄድ ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብን ለማጠናከር የምሳ ግብዣ እና
ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራች ተደርገዋል፡፡ በዚህም 8.5 ሚሊዮን ብር ማግኘት ተችሏል፡፡
ለዚህ ፕሮግራም ስኬትም የወላይታ ዞን 7 ሚሊዮን፣ የደቡብ ክልል መንግስት 300 ሺህ፣
ሙለጌ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር 100 ሺህ፣ ወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ 100 ሺህ በመለገስ
አለኝታነታቸዉን አስመስክረዋል፡፡ ሌሎች ድርጅቶችና ግለሰቦችም አቅማቸዉ የቻለዉን ያክል
በመለገስ ለማህበሩና ለክለቡ ያላቸዉን ክብርና ፍቅር በይፋ ማሳየት ችለዋል፡፡

በሌላ በኩል የወልማ አባላትን በማደራጀት ዘርፍ በበጀት አመቱ 17,635 አዲስ አባላትን
ማፍራት የተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት ልማት ማህበሩ 486,593 አባላት
እንዲኖሩት ማድረግ ተችሏል፡፡

መደበኛዉ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በደማቅ


ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን በጉባኤም የማህበሩ
የ2012 ክንውን ሪፖርትና የ2013 ዕቅድ
ቀርቦ ዉይይት ከተደረገበት በኋላ
እንዲጸድቅ ተደርጓል፡፡ የማህበሩ ሥራ
አመራር ቦርድ ማሟያ ምርጫም ተካሂዷል፡፡
የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ቅርንጫፎችን Figure 20፡ የወልማ 2013 እ.አ.አ ጠቅላላ ጉባዔ ከፊል ገጽታ

ለማበረታታትም በተያዘዉ እቅድ መሰረት በጉባኤዉ


ላይ የተሸለ ዉጤት ያስመዘገቡ 5 ቅርንጫፎች 2
ሞተር ብስክለቶችን፣ 2 ኮምፕዉተሮችንና 3

Figure 21፡ የወልማ ዲላ ቅርንጫፍ ዓመታዊ ጉባዔ ከፊል ገጽታ

31 | ገፅ
ፕሪንተሮችን በሽልማት መልክ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

በሌላም በኩል የጠቅላላ ጉባኤ ቀንን ለማድመቅ ብሎም ሕዝቡ የማህበሩን ሥራ በግልፅ
እንዲያይ ለማድረግ የተለያዩ ፎቶዎችን የያዘ ባነር በማሳተም የጉባኤዉ ተሳታፊዎች
እንዲያዩ ተደርጓል፡፡ ለጉባኤዉ ቀንም ልዩ ቲ-ሸርትና ኮፍያ ታትሞ እንዲሰራጭ በማድረግ
ተሳታፊዎች ለብሰዉ እለቱን እንዲያደምቁት ተደርጓል፡፡

በየቅርንጫፉ የሚካሄደዉ ጠቅላላ ጉባኤም በታቀደዉ መሰረት በ12 የወልማ ቅርንጫፎች


የተካሄደ ሲሆን በጉባኤውም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ማለትም የቅርንጫፍ ዕቅድ አፈጻጸምና
የቀጣይ ዓመት ዕቅድ፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን ማጠናከር እና የጎደሉ የቅርንጫፍ ኮሚቴዎች
መተካት ላይ በሰፊዉ በመወያየት መፍትሄ እንዲበጅ እና የተሻለ ዉጤት እንዲገኝ ለማድረግ
ተደርጓል፡፡

በየቅርንጫፉ የሚካሄደዉ ጠቅላላ


ጉባኤዎቹም በታቀደዉ መሰረት በሶዶ፣
ዲላ፣ አዲስ አበባ፣ ቦዲቲ፣ ዳ/ጋሌ፣
ኪ/ዲዳዬ፣ ኪ/ኮይሻ፣ ቦ/ሶሬ፣ ኦፋ፣
ሀዋሳ፣ ሻሽማኔና አርባምንጭ የወልማ
ቅርንጫፎች የተካሄደ ሲሆን በጉባኤውም
በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ማለትም
የቅርንጫፍ ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ Figure 22፡ የወልማ አርባምንጭ ቅርንጫፍ ዓመታዊ ጉባዔ ከፊል ገጽታ

ዓመት ዕቅድ፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን ማጠናከር እና የጎደሉ የቅርንጫፍ ኮሚቴዎች መተካት


ላይ በሰፊዉ በመወያየት መፍትሄ እንዲበጅ እና የተሻለ ዉጤት እንዲገኝ ለማድረግ በስፋት
ተመክሮበታል፡፡

4.2 ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ

በበጀት አመቱ በስፖርቱ ዘርፍ ከተከናወኑ አበይት ተግባራት መካከል የወላይታ ድቻ እግር ኳስ
ቡድንን ማጠናከር የሚጠቀስ ነዉ፡፡ በዚህም 10 አዲስ እና 14 ነባር ተጫዋቾችን ለዋናው
እግር ኳስ ቡድን የማስፈረም፣ የወንድ መረብ ኳስ ቡድንን የማጠናከርና የሴት እግር ኳስ
ቡድንን የማደራጀት የበጀት አመቱ አብይት ተግባራት ነበሩ፡፡ የ‘B’ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን
ማጠናከርም ማህበሩ ትኩረት ሰጥቶ ያከናወነዉ ተግባር ነበር፡፡

32 | ገፅ

Figure 23፡ ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ (የወንዶች እግር ኳስ ቡድን አባላት)


በአጠቃላይ ክለቡን ለማጠናከር ከሚሰጠዉ ስልጠና ባሻገር አስፈላጊ የሆኑ የተለያዩ የስፖርት
ቁሳቁሶች እንዲሟሉ ተደርገዋል፡፡ በአጠቃላይ ለሁሉም ቡድኖች የተሟላ የምግብና የሕክምና
አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ የወንድ እግር ኳስ ክለብ በብሔራዊ ሊግ ጨዋታ በአጠቃላይ 36
ነጥብ በማሰባሰብ በምደቡ አንዴም ሳይሸነፍ 1ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ ተጉዞ በጥሎ
ማለፍ ዉድድር ሻምፒዮን ሆኖ ዋንጫ በማግኘት የኢትዮጵያን ፕሪሜየር ሊግ የተቀላቀለዉም
በዚሁ በጀት አመት ነበር፡፡ ቡድኖች አሸንፈዉ ሲመለሱም የመረብ ኳስ ቡድኑን ጨምሮ

Figure 24፡ ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ ሻምፒዮን በመሆን ፕሪሚየር ሊጉን በተቀላቀለበት ወቅት
የስፖርት አፍቃሪዎች አቀባበል በከፊል
33 | ገፅ
የገንዘብ ማበረታቻ ሽልማት ለእያንዳንዱ ተጨዋች እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡

የወላይታ ድቻ መረብ ኳስ ቡድን አሰልጣኝና ቡድን መሪን ጨምሮ 13 አባላትን በማቀፍ


ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀለው በጥር ወር 2005 ዓ.ም ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉ 3ኛ በመሆን
የውድድር ዓመቱን አጠናቅቋል፡፡ በ2006 ዓ.ም የወንድ እግርና መረብ ኳስ ቡድኖች ለፕሪሚየር
ሊግ ውድድር በቂ ዝግጅት በማድረግ በዓመቱ ውድድርም በመልካም ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

በሌላም በኩል የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በአዲስ መልክ ተደራጅቶ 20 አባላት እና 2


አሰልጣኞችን እንዲሁም ቡድን መሪን አካትቶ ዉድድር ማድረግ ጀምሯል፡፡

Figure 25፡ ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ መረብ ኳስ ቡድን አባላት መረብ ኳስ ቡድኑ በጨዋታ ላይ

(በ2005 ዓ.ም ቡድኑ የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ በ3ኛ ደረጃ አጠናቀወቋል፡፡)

Figure 26፡ ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ (የሴቶች እግር ኳስ ቡድን አባላት)

34 | ገፅ
4.3 ቢዝነስ ልማት

በተለያዩ ፕሮጀክቶች ተዘዋዋሪ ብድር እና መነሻ ካፒታል የሚሰጣቸዉ ወገኖች የስራ ፈጠራ
ክህሎታቸዉ እንዲያድግ እና የገንዘብ አያያዝ ብሎም የቢዝነስ ክህሎታቸዉ እንዲጎለብት
ስልጠናዎችን መስጠት በዓመቱ ከታቀዱ
ተግባራት አንዱ ነዉ፡፡ በመሆኑም በበጀት
አመቱ በዚሁ ዘርፍ ለተሳተፉና ለሚሳተፉ
ተጠቃሚዎች የተለያዩ ስልጠናዎች
ተሰጥቷል፡፡ በዚህም ከዳሞት ሶሬ፣ ከዳሞት
ፑላሣና ሁምቦ ወረዳዎች ከ21 ቀበሌዎች
ለተመለመሉ 175 ተጠቃሚዎች በብድርና
ቁጠባ አገልግሎት ላይ ስልጠና
Figure 26፡ ተደራጅተው በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎች ለተሰማሩ የሕብረተሰብ
ክፍሎች ከተሰጡ ሥልጠናዎች በከፊል አግኝተዋል፡፡ ተጠቃሚዎቹ ከሥልጠናው
በኋላ በመረጡት የስራ ዘርፍ እንዲደራጁ ተደርገዉ ለ100 ተጠቃሚዎች 250,000 ብር በብድር
በመስጠት ወደ ስራ ገብተዋል፡፡

በሌላም በኩል በምግብ ዋስትና ፕሮግራም ለታቀፉ ሶስት ማህበራት (አትክልትና ፍራፍሬ
ማህበር፣ ሁለገብ ህብረት ሥራ ማህበር እና ንብ አናቢዎች ማህበር) በሂሳብ አያያዝ ላይ
ስልጠና ከተሠጣቸው በኋላ 621,530 ብር በብድር እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ በአጠቃላይ ከላይ
በተጠቀሱት 3 ማህበራት ዉስጥ ተካትተዉ የሚገኙ 462 አባላት የተሰጣቸዉን መነሻ ካፒታል
በመጠቀም በየተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ጥናት ቡድን ጋር ሲካሄድ የነበረው በቁጠባ ባህል ላይ የሚደረግ


ጥናት ሙሉ መረጃዎች ተሰብስቦና ተጠናቅሮ የጥናት ቡድኑ የመጀመሪያ ዙር ውጤቱን
አውጥቶ በተሰጠው አስተያየት መሰረት የቀጣዩን እርማት ሥራ እንዲጀመሩ ተደርጓል፡፡

ለወላይታ ጉታራ ሥልጠና ማዕከል እና ለወላይታ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ ድርጅት


በአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ጉዳይ፣ ታክስ አከፋፈልና መመሪያ እንዲሁም በተለያዩ ርዕሰ
ጉዳዮች ላይ ክትትልና ሙያዊ ድጋፍ እንዲሰጥም ተደርጓል፡፡

35 | ገፅ
5. ቢዝነስ ተቋማት

5.1. ወላይታ ጉታራ ሥልጠና ማዕከል

የወላይታ ልማት ማህበር በስሩ ከሚያስተዳድራቸዉ የቢዝነስ ተቋማት መካከል አንዱ


የወላይታ ጉታራ ሥልጠና ማዕከል ነዉ፡፡ ይህ ማዕከል ለአካባቢዉ ህብረተሰብ ብሎም
ለእንግዶች የተለያዩ አገልግሎቶችን ከመስጠት ባሻገር የወላይታ ህዝብ ማንነት ማለትም ወጉ
እና ባህሉ የሚገለጽበት ቦታ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ ማዕከሉ የካፍቴሪያ፣ የአዳራሽ
ኪራይ፣ የመኝታ እና ሌሎች አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡

5.2 የወላይታ ቤትና ቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ ድርጅት

ወላይታ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ ድርጅትም እንደ ወላይታ ጉታራ ሁሉ


የወላይታ ልማት ማህበር ከሚያስተዳድራቸዉ ተቋማት አንዱ ነዉ፡፡ ይህ ተቋም ከዚህ በፊት
በማህበሩ ተቋማትና በማህበሩ ለሚተገብሩ ፕሮጀክቶች ሥራ ብቻ የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን
በማምረት ስራ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ ቆይቶ ነበር፡፡ በበጀት አመቱ ግን ራሱን ችሎ
እንዲደራጅ በመደረጉ፣ የሰው ኃይልና አስፈላጊ ግብአቶች ተሟልቶለት የማህበሩንም ሆነ
የሌሎች ተቋማት እንዲሁም የግለሰቦችን ትእዛዝ እየተቀበለ በጥራት የማምረት አገልግሎት
እየሰጠ ከርሟል፤ እየሰጠም ይገኛል፡፡

Figure 27፡ ወላይታ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ ድርጅት

34 | ገፅ
6. የሰው ሀብት አስተዳደር

የወላይታ ልማት ማህበር እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ 446 (ወ 351 ሴ 95)
ሰራተኞችን ይዞ ስንቀሳቀስ ነበር፡፡ ከእነዚህም መካከል 186ቱ በበጀት አመቱ በአዲስ መልክ
በቋሚና በጊዜያዊ ኮንትራት የተቀጠሩ ናቸዉ፡፡

Figure 28፡ የወልማ ዓመታዊ የሠራተኞች ቀን በዓል አከባበር ከፊል ገጽታ


በ2012 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ሠራተኞች ለመሸለም በታቀደው መሠረት
በየሥራ ዘርፍ በየክፍሉና በተቋማት ተከፋፍሎ እንዲለዩ በማድረግ በአጠቃላይ 20 ሠራተኞች
በሠራተኞች ቀን ከየክፍሉና ከየተቋማቱ ከ1ኛ እስከ 3ኛ የወጡ ሠራተኞች እንዲሸለሙ
ተደርጓል፡፡ ዓመታዊ የሠራተኞች ቀን በዓል አጠቃላይ ሠራተኞች በተገኙበት በወላይታ ጉታራ
ሥልጠና ማዕከል በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

7. ክትትል፣ ግምገማና የሕዝብ ግንኙነት

ወልማ በክትትል፣ ምዘናና ኢንፎርሜሽን ማኔጅመንት ስራ ዘርፍም በበጀት አመቱ በርካታ


ስራዎችን እየሰራ የቆየ ሲሆን ዋና ዋናዎቹም በሚከተለዉ መልኩ ቀርበዋል፡፡

35 | ገፅ
7.1. ክትትልና ግምገማ

በዚህም መሰረት የክትትል እና ግምገማ ስራ ዘርፍ የማህበሩ የስራ ክፍሎች በየክፍላቸው


ሳምንታዊ የክትትልና ግምገማ እቅዶችን ተከትለው በየስራ ክፍሎቹ በየሳምንት ውጤቱን
እየገመገሙ እንዲሰሩ ሲያደርግ ከርሟል፡፡ እንደዚሁም የዕቅዱ አፈጻጸም በየወሩ በማኔጅመንት
ኮሚቴ ደረጃ በመስክ እየተጎበኘና እየተገመገመ ሥኬታማ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በሌላ በኩል
የማህበሩ ሥራ አመራር ቦርድ በየሩብ ዓመት የተሠሩ ሥራዎችን ከዕቅዱ ጋር እያነጻጸረ
በመገምገም አቅጣጫ እያስቀመጠ ሥራው በታቀደው ልክ እንድሄድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ
አበርክተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በየፕሮጀክቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በየሶስት ወሩና በየስድስት ወሩ


የየፕሮጀክቱ አፈጻጸም እየተገመገመ የጋራ ውሳኔ ሲተላለፍና በዚያው መሰረት ማስተካከያ
እርምጃ በመውሰድ የዓመቱ ሥራ በመልካም ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ተደርጓል፡፡

የተቀናጀ ልማት ፕሮግራም፣ የማህበረሰብ አቀፍ ተሃድሶ ልማት ፕሮጀክት እና የምግብ


ዋስትና ፕሮጀክት ለሶስትና አራት ዓመታት ለመስራት የታቀዱት በማጠናቀቃቸው በማለቂያ
ጊዜ ግምገማ እንዲካሄድም ተደርጓል፡፡ ግምገማውም በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
መሪነት ከክልል፣ ከዞንና ወረዳዎች በተውጣጡ ፈራሚ መንግስት መሥሪያ ቤቶች ተወካዮች
አማካይነት እንዲካሄድ ተደርጓል፡፡

የማህበሩ ሀብትና ንብረት በተገቢው ሁኔታ ለማህበሩ አገልግሎት እንዲውል አስፈላጊ የሆነ
የውስጥ ቁጥጥር ሲካሄድ ነበር፡፡ የማህበሩ የውስጥ ቁጥጥር የቅርንጫፎችን ጨምሮ የሂሳብና
ንብረት አሰራር፣ አያያዝና አጠቃቀም በፕሮግራምም ሆነ በድንገት ባጠቃላይ 18 ጊዜ ምርመራ
ተካሂዷል፡፡ እንደዚሁም የማህበሩ 2012 ሂሳብ በውጪ ኦዲተር ተመርምሮ ለ12ኛው ጠቅላላ
ጉባኤ ቀርቦ እንዲጸድቅም ተደርጓል፡፡ በውስጥና በውጪ ኦዲተሮች የተሰጡ አስተያቶችንም
መነሻ በማድረግ የአሰራር ክፍተቶች እንዲታረሙም ተደርጓል፡፡

7.2 የሕዝብ ግንኙነት ሥራ

ወላይታ ልማት ማህበር የሚያከናውናቸው ሥራዎችን ሕዝቡ እንዲያዉቃቸዉ እና ድጋፉንም


እንዲያጠናክር ለማድረግ በደቡብ ቴሌቭዥን እና ሬድዮ 12 ፕሮግራሞች የአየር ሽፋን
እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በየሣምንት አንድ ጊዜ በወላይትኛ 52 ፕሮግራሞች በተለያዩ ርዕሰ
ጉዳዮች በሬዲዮ እንዲተላለፉ ተደርገዋል፡፡ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 99.9 ወላይታ ሶዶ

36 | ገፅ
ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር በሣምንት ሁለት ጊዜ በአማርኛና በወላይትኛ ቋንቋዎች በሴቶች
ትምህርት እንዲሁም በአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ላይ አስተማሪ ፕሮግራሞች እንዲተላለፉ
ተደርጓል፡፡ የተለያዩ የማህበሩን ሥራን የሚያበስሩ ሰበርና መደበኛ ዜናዎች በተለያዩ
ሚድያዎች እንዲተላለፉ ተደርጓል፡፡

የ2012 በጀት ዓመት ሥራዎችን የሚገልፁ 1500 ኮፒ ዓመታዊ መጽሔት በማሳተም ለሕዝቡ
እንዲደርስ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ወላይታ ኤክስፖ 2006 መጽሄትና የወላይታ ሊቃ ት/ ቤት
12ኛ ክፍል ተማሪዎች ምረቃን በተመለከተ መጽሔት ታትሞ ተሰራጭቷል፡፡

የወልማን ድረ ገጽ በየጊዜው በተለያዩ መረጃዎች የማደስ ሥራ ተሰርቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ


ቀድሞ www.wolaitta-da.org.et በሚል አንድ ላይ የነበረውን የወላይታ ልማት ማህበር እና
የወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ ድረ ገጽ በአዲስ መልክ ለያይቶ ለሁለት በመክፈል
www.wolaittada.org እና www.wolaittadsc.org በሚል ራሱን የቻለ ሁለት ድረ ገጽ
እንዲኖር የማድረግ ሥራም በጅምር ላይ ይገኛል፡፡

37 | ገፅ

You might also like