You are on page 1of 2

የብርሃን ሶሻል ዴቨሎፕመንት ትሬይኒንግ ኤንድ ኮንሰልቴሽን ሴንተር የማኔጅመንትና ዴቨሎፕመንት

ም/ ፐሪንሲፓል፣ ወ/ሮ ሉልአበሻረታ፣ ግንቦት 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ለተመራቂዎች ያስተላለፋት


መልዕክት

 የተከበሩ አቶ ቦንሳ ባይሳ፣ የብርሃን ሶሻል ዴቨሎፕመንት ትሬይኒንግ ኤንድ ኮንሰልቴሽን ሴንተር ቦርድ
ሊቀመንበርና እንዲሁም የዕለቱ የክብር እንግዳ፣
 ውድ ተመራቂዎች፣
 የተከበራችሁ የተመራቂ ቤተሰቦች፣
 ጥሪ የተደረገላችሁ የማህበረሰብ ተወካዮች፣
 ተጋባዥ እንግዶችና
 የድርጅቱ ኃላፊዎችና ሠራተኞች

በብርሃን ሶሻል ዴቨሎፕመንት ትሬይኒንግ ኤንድ ኮንሰልቴሽን ሴንተር ስር የሚተዳደረው ብርሃን ሶሻል
ዲቨሎፕመንት ኮሌጅ በዛሬው ዕለት ትምህርታቸውን በየደረጃው አጠናቀው ለሚመረቁ ሰልጣኞች
ባዘጋጀው የምረቃ በዓል ላይ መልዕክት እንዳስተላልፍ ሲነገረኝ በአንድ በኩል የላቀ ደስታ የተሰማኝ ሲሆን
በሌላ በኩል ደግሞ የዚህ ድርጅት መሥራች፣ ፕሪንሲፓልና ዕርዳታ አሰባሳቢ የነበሩት ዶ/ር ጀምበር ተፈራ
ሁልጊዜም በየዓመቱ በሰልጣኞች ምረቃ ላይ እየተገኙ መልእክት ያስተላልፉ እንደነበርና ዘንድሮ ግን
ባልተጠበቀ ሁኔታ ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለዩን አብረውን አለመኖራቸህውን ሳስብ ጥልቅ ሀዘን
ተሰምቶኛል፡፡ ሆኖም ግን የሰው ልጅ መጨረሻው ይኸው መሆኑን ተገንዝበን የሳቸውን ሌጋሲ ለማስቀጠል
ቃል በመግባት ሥራችንን መቀጠል ይኖርብናል፡፡

ከሁሉ አስቀድሜ እናንተን ተመራቂዎችን እንኳን ለዚህ የምረቃ ዕለት አበቃችሁ፣ እንኳንም ደስ አላችሁ
በማለት ልባዊ ደስታዬን እገልጻለሁ፡፡ ትምህርት ሁልጊዜም ቢሆን ዉጤቱ ጣፋጭ ቢሆንም ብዙ ድካምንና ዉጣ
ውረድን የሚጠይቅ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በተለይም ካለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ በዓለማችንና በአገራችንም
ጭምር የተከሰተው ከባድ የወረርሺኝ በሽታ፣ ማለትም ኮቪድ--19፣ ያስከተለውን የተለያዩ ተግዳሮቶች ሁሉ
ተቋቁማችሁ የጀመራችሁትን ትምህርት ለማጠናቀቅ በመብቃታችሁ ደስታችሁ፣ እንዲሁም ደስታችን እጥፍ
ድርብ ነው፣ መምህራኖቻችሁንና በአጠቃላይ የኮሌጁን ማህበረሰብም አኩርታችኋል፡፡ በተጨማሪም ይህንን
መልካም ዉጤት እንድታገኙ ድጋፍ ላደረጉላችሁ ቤተሰቦቻችሁና ወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጭምር እንኳን ደስ
አላችሁ እላለሁ፡፡

ይህ ኮሌጅ ከቀድሞው በሙሉ በተቀነባበረ ዘዴ የከተማ ልማት ፕሮጀክት ተወልዶ ከራሱ ከፕሮጀክቱና
ከመሰል መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ልምድ በመነሳት የከተማ ድህነትን ለመቅረፍ የሚያስችል
ፕሮገራምን በመዘርጋትና በመተግበር አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ የተቋቋመ በመሆኑ የተጀመረውን
መልካም እንቅስቃሴ በየጊዜው በቲቬት የሚሰጠውን መመሪያ በማከል ሥልጠናውን አጠናክሮ በመቀጠል
ላይ ይገኛል፡፡
ውድ ተመራቂዎች፤ ከኮሌጁ ያገኛችሁትን እውቀትና ክህሎት በስራ ለመተርጎም የሚቻላችሁን ጥረት
በማድረግ አገራችን ካለችበት የድህነት አረንቋ ለማውጣት በሚደረገው የልማት እንቅስቃሴ ከፍተኛ ድጋፍ
እንደምትሆኑ እምነቴ የፀና ነው፡፡

በተጨማሪም ለዚህ እንድትበቁና ጥረታችሁና ድካማችሁ ውጤታማ እንዲሆን ከጎናቸሁ ሳይለዩ


ሁኒታዎችን በማመቻቸት ሲረዷችሁ የቆዩትን መምህራን፣ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ እንዲሁም
የዛሬውንም በዓል በማዘጋጅት ረገድ የተሳተፉትን ሁሉ በኮሌጁና በራሴም ስም ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

ውድ ተመራቂዎች፤ ትምህርት ቀጣይ ሂደት በመሆኑ በአገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ራሳችሁን በበለጠ


በማሻሻል ለሀገርና ለህዝብ የሚጠቅም ሥራ እንድትሠሩና ለወደፊትም መልካም ዕድል እንዲገጥማችሁ
ምኞቴን በመግለጽ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ፤

ስላዳመጣችሁኝ ከልብ አመሰግናለሁ

You might also like