You are on page 1of 1

-የተከበራችሁ ተጋባዥ እንግዶች -ውድ ተመራቂዎች

-የተከበራችሁ የተመራቂዎች ቤተሰቦች -እንዲሁም የኮሌጁ


ማህበረሰብ በሙሉ
በዛሬው የምረቃ በዓል ተገኝቼ መልዕክት እንዳስተላልፍ ዕድሉን በማግኘቴ የተሰማኝን ደስታ እየገለጽኩ
ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ፡፡
አንድን ማህበረሰብ ወደ ተሻለ ሕይወት ለማሸጋገር አመለካከቱን መለወጥ ዋናና አስፈላጊ ጉዳይ ሲሆን
የሰዎችን አመለካከት መለወጥ የሚቻለው ደግሞ በትምህርትና ሥልጠና መሆኑ የማይታበል ሃቅ ነው፡፡
ይህ ኮሌጅ ማህበረሰብን ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገርና ለአገር ዕድገት አስተዋጽዖ ማድረግ የሚያስችል የሶሻል
ዎርክ ትምህርት ለወጣቶች በጥራት እየሰጠ ከደረጃ 1 እስከ 4 አሰልጥኖ ዛሬ ለ 12 ኛ ጊዜ እያስመረቀ የሚገኝ
ተቋም ነው፡፡ ከዚህ ተቋም የተመረቁ በሙሉ ሥራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ
የተቋሙ መረጃ ይጠቁማል፡፡ ስለሆነም ሁሉም የሚመለከታቸው ድርጅቶች፣ የመንግስት አካላትና ግለሰቦች
ይህ ተቋም ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን እንዲወጡ አደራ እንላለን፡፡
ውድ ተመራቂዎች በተቋሙ ያገኛችሁትን ዕውቀትና ክህሎት ይዛችሁ ወደማህበረሰቡ ሄዳችሁ አርኪ
አገልግሎት እንደምትሰጡ ኮሌጁ ይተማመንባችኋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ራሳችሁን ከወቅቱ ጋር
እየለወጣችሁና እያሻሻላችሁ ሁሌም አገርንና ማህበረሰብን በለውጥ ጎዳና ለመምራት ዝግጁ ሆናችሁ
እንድትገኙ አደራ ጭምር እናሳስባችኋለን፡፡
የሰው ልጅ የስኬት ጎዳና ሁሌም ቀጥታ መንገድ አይደለም፡፡ ብዙ ውጣ ውረዶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡
በጉዞአችሁ አንዳንድ መሰናክሎች ቢያጋጥማችሁ ደጋግማችሁ ጥረት በማድረግና መሰናክሎችን በማለፍ ወደ
ምትመኙት የስኬት ዳርቻ መድረስ እንደመምትችሉ መጠቆም እወዳለሁ፡፡
በመጨረሻም የዚህ ተቋም አሰልጣኞችና ሠራተኞች እነዚህን ሠልጣኞች አሰልጥነው ለምርቃት ብቁ
በማድረጋቸው ታላቅ ምስጋና አቀርባለሁ
ተመረቂዎች የወደፊት ህይወታችሁ ሁሉ ብሩህ እንዲሆን እመኛለሁ
አመሰግናለሁ

You might also like