You are on page 1of 3

የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት

የተማሪዎች ምረቃ እና ዓመታዊ በዓል መልዕክት

ትጉ" ፪ኛጴጥ ፩፥፲


"መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ"

ሰንበት ት/ቤታን በ፶፱ ዓመታት አገልግሎቱ በርካታ ወጣቶች፣ ጎልማሶች፣ እናት እና አባቶችን መሠረታዊ
ትምህርተ ሃይማኖት (ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት)፤ ሥርዐተ ቤተክርስቲያን እንዲሁም የግዕዝ ቋንቋ፣ ሥነ
ምግባር እና ታሪክ በማስተማር በተማሩት እና በተረዱት እንደ ቀደምት አባቶቻቸው ሃገራቸውን በቅንነትና
በታማኝነት ማገልገል የሚችሉ ብቁ ዜጎች በማፍራት፤ ለቅድስት ቤተክርስቲያንም በተለያየ ዘርፍ በገዳማት እና
አድባራት በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ በልማት እና ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት እና ከዚህ ላቅ ሲልም
ከዲቁና እስከ ጵጵስና ማዕረጋት የበቁ እንደ እነ ብጹዕ አቡነ ገብርኤል፣ በቅስና እነ ቀሲስ ነፀረ ታዬ፣ ተመስገን
ፍቅሬ፣ ወንድወሰን መገርሳ፣ ሕብረት የሺጥላ፣ ጥላሁን ጉደታ፣ . . . እና ሌሎች በርካታ ትጉህ ኖላውያንን
እንዲሁም በርካታ ዲቆናት፣ ሰባኬ ወንጌል እና የደብር ጸሐፊ እና ልዩልዩ ሠራተኞች በማፍራት የድርሻውን
በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

ውድ የሰንበት ት/ቤታችንን ጥሪ አክብራችሁ በዚህ በዓል የታደማችሁ አባቶቻን ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደብር
አለቆች፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፣ ክቡራን እና ክቡራት እንግዶቻችን እንዲሁም የት/ቤታችን
አባላት እና ተማሪዎች፤ ይኽ ዘመን ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በብዙ ተግዳሮቶች እየተፈተነች ያለችበት
ነው፡፡ በመሆኑም ቤተክርስቲያናችን የተጋረጡባትን ፈተናዎች በድል አድራጊኒት እንድታልፍ ልጆቿ
አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት

. . . ወንድሞች ሆይ መጠራታችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ . . . ፪ ጴጥ ፩፥፲

. . . ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑ ንዋጁ . . . ኤፌ ፮፥፲፬-፲፭

ብለው እንዳትማሩን የቤተክርስቲያን ልጆች ሁላችን በተለይም ደግሞ የሰንበት ት/ቤት አባላት እና ተማሪዎች
ቅድስት ቤተክርስቲያንን እየደረሰባት ካለው ችግር ለመታደግ እንደ እንደቀደምት ሐዋርያን አበው አንድ ልብ
መካሪ፣ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነን በመተባበር በትዕግሥት እና በጽናት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን መቆም፣
ቤተክርስቲያን የምታስተላልፈውን መልዕክት ብቻ በመስማት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች
እንዳስተማረው ኤፌ ፮፥፲፬-፲፭ ወገባችንን በእውነት ታጥቀን፤ የጽድቅንም ጥሩር ለብሰን፤ የሰላምን ወንጌልም
ተጫምተን በጽናት መቆም ምዕመናንን ከምንጊዜም በተሻለ በማስተማር፣ በማስተባበር እና በመምራት ዘመኑን
ለሚዋጅ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ሁሉ ብቁ ሆነን በመገኘት የድርሻችንን መወጣት ይገባናል፡፡

ውድ የሰንበት ት/ቤታችን አባላት እና ተማሪዎች ዛሬ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየደረሰ ያለው መከራ


መነሾ ጊዜው በተመቻቸው ምድራውያን ተጽዕኖ ብቻ ሳይሆን በእኛ ልጆቿ መንፈሳዊ ዝለት ምክንያት በመሆኑ
ቤተክርስቲያናችንን ወደ ቀደመ ክብርና ልዕልናዋ እንድትመለስ ሁላችን በሃገራችን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና
ማኅበራዊ ጉዳዮች ሁሉ ቀጥታ ተሳታፊ በመሆን በሕዝብና መንግሥታዊ ኃላፊነቶች ተገቢውን ኃላፊነት እና
ድርሻ በመቀበል ፍትሃዊና ርቱዕ ሃገራዊ አገልግሎቶች በማስፈን የሕዝብን እንባ ልናብስ እንዲሁም ሃገራዊ እና
መንፈሳዊ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባናል፡፡

ለዚህ ደግሞ በዚህ ዘመን በሰንበት ት/ቤታችን በመማር፣ በማስተማር፣ በማስተባበር እና በመምራት የምንገኝ
አባላት እና ተማሪዎች የቀደሙት አባላት (እናቶች፣ አባቶች እና ወንድሞቻችን) እንደዛሬ ባልተመቸ ሁኔታ
ውስጥ እያገለገሉ ለዛሬ የሰንበት ት/ቤታችን ዕድገት ደረጃ መሠረት ጥለው ያለፉ አባላት የተቀበልነውን
የቤተክርስቲያን አገልግሎት፣ ዘመኑን በዋጀ የአገልግሎት ደረጃ በማሳደግ እና ለነገው ትውልድ ለማስረከብ
ሰንበት ት/ቤታችን የቅድስት ቤተክርስቲያንን ወቅታዊ ውጫዊና ውስጣዊ ችግሮችን በመዳሰስ ከተዘፈቅንበት
ጥልቅ ችግሮቻንን ለመውጣት ያዘጋጀውን የሦሥት ዓመታት ሥልታዊ ዕቅድ ለመተግበር ያጋጠሙን የአገልጋይ
እጥረት፣ የእቅም ውሱኑነት እና ዝግጁነት ተግዳሮት በመቅረፍ በምልዐት እንዲተገበር ከምንጊዜም በላይ
በንቃት እንድትሳተፉ በቅድስት ቤተክርስቲያን ሥም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ውድ የሰንበት ት/ቤታችን አባላት እና ተማሪዎች ቤተክርስቲያንስ በክርስቶስ ደም የተዋጀት ቅድስት


ቤተክርስቲያን በየዘመኑ የሚያጋጥሟትን ተግዳሮቶች ሁሉ እያሸነፈች እስከ ሙሽራዋ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት
ትኖራለች፡፡ በመሆኑም ሁላችን ይኽንን በመረዳት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅ እንደ አባቶቻንን
ሰማዕታት በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ክብርና እንድናገኝ ሐዋርያው ቅዱስ ጵጥሮስ . . . መንግሥተ ሰማይ
በጭንቅ ልንገባ ይገባናል፡፡ . . . ፩ኛ ጴጥ ፬፥፩፰

ውድ የሰንበት ት/ቤታችንን ጥሪ አክብራችሁ በዚህ በዓል የታደማችሁ አባቶቻን ቅዱሳን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ክቡራን
እንግዶቻችን፣ ሰንበት ት/ቤታችን ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመሥጠት የሚያስችል ሕንጻ፤ በደብራችን
ፈቃድና የገንዘብ አስተዋጽዎ እንዲሁም በምዕመናንና በሰንበት ት/ቤታችን አገልጋዮችና አባላት ተሳትፎ ገንብቶ
በአስፈላጊው ቁሳቁስ በማሟላት ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጓል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከሰባቱ የሰ/ት ት/ቤቱ ዋና
የአገልግሎት ክፍሎች በተጨማሪ፤ መሠረታዊ የአብነት ትምህርት (በትምህርትና ስልጠና ዋና ክፍል ውስጥ) እና
የአይሲቲ እና የሚዲያ ክፍሎችን በማዋቀር፤ ቤተክርስቲያንን ሚያስቀጥሉ የአብነት ተማሪዎችን በማፍራት፤
የሰ/ት/ቤቱን መንፈሳዊ ትምህርቶች ለመላው ሕዝበ ክርስቲን ለማዳረስ የሚያስችል የመረጃና የቴክኖሎጂ
ግብአቶችን በማሟላት አገልግሎቱን ለማዳረስ ዝግጁ ሆኗል፡፡ ይህን አገልግሎቱን የበለጠለ ማስፋትና ተደራሽ
ለማድረግ የደብራችን ሰበካ ጉባኤና የአስተዳደር ላደረገልንና እያደረገልን ላለው አስተዋጽዎ ምስጋናችንን
እያቀረብን፤ ይህን ድጋፉን ወደ ፊትም እንደማይለየን ተስፋ በማድረግ ነው፡፡በተጨማሪም፤ አገልግሎቱን
ምዕመናን፤ ተማሪዎች በእውቀታችሁ በገንዘባችሁ ይልቁንም በጸሎታችሁ ታስቡ ዘንድ ጥሪያችንን በባለራዕዩ
ብጹዕ አባታችን ጎርጎርዮስ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፍላችኋለን፡፡

ዛሬ ከአራት ዓመታት በኋላ፤ በሰ/ትቤታችን ለምረቃ የበቃችሁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም የተመራቂ
ቤተሰቦች እንኳን ለዚህ ዕለት አበቃችሁ፤ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን እኛም የደስታችሁ ተካፋይነታችንን
ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ ተመራቂዎች፤ ከቤተክርስቲያን ትምህርት፤ እፍታውን በጭልፋ እንዳገኛችሁ
ተገንዝባችሁ፤ ሃዋርያው ለላቀው መንፈሳዊ አገልግሎት ትጉ እንዳለ ቤተክርስቲያንን በበለጠ ማዕርግ ለማገልገል
የሚያስችላችሁን፤ ተጨማሪ ትምህርት ከአባቶች እግር ስር በመሆን ወደ ጥልቁ ውቅያኖስ እንድትገቡ
እያበረታታን፤ በሰንበት ት/ቤቶች፤ በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤያት እንዲሁም በልዩ ልዩ አገልግሎት፤
በቤተክርስቲያንን ያላችሁን ሱታፌ በመጨመር፤ ከማይጠገበው በረከቷ እንድትቋደሱ፤ጥሪ
እናስተላልፍላችኋለን፡፡

እንግዲያውስ ሐዋርያው ሥራ የሞላበት ትልቅ በር ተከፍቶልኛልና ተቃዋሚዎችም ብዙናቸው (1 ኛ ቆሮ 16፡9)


እንዳለ፤ የሰንበት ት/ቤትአባላት፤ የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎች፤ እንዲሁም በየዘርፉ በተለያየ የቤተክርስቲያን
አገልግሎት ሱታፌ ያለን ምዕመናን ሁላችን፤ እስካሁን ካደረግነው ይልቅ እጅግ ተግተን ቤተክርስቲያንም
ያለባትን ተግዳሮትተገንዝበን፤ የምንሠራው ሥራ ብዙ አለና ወገባችንን በእውነት ታጥቀን የጽድቅንም ጥሩር
ለብሰን በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችን ተጫምተን መቆም ይገባናል (ኤፌ 6፡14-15)፡፡ ይህንንም
እንድንፈጽም፤ የእናታችን የቅድስት ድንግልማርያም ምልጃ የቅዱሳን ጸሎት፤ እንዲሁም የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ
ጊዮርጊስ ፈጣን ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

You might also like