You are on page 1of 4

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ለአምደ ተዋሀህዶ ሰ/ት /ቤ አባላት እና አመራሮች በሙሉ

የሰንበት ት/ቤቱ አገልግሎት ለጊዜው መቃረጡን ምክንያት በማድረግና በሽታውና የወረርሺኙን ስርጭጽ
አሳሳቢነት ግምት ውስጥ በማስገባት የቀረበ የስራ አመላካች ፕሮፖዛል

በመጀመሪያ በሰንበት ት/ቤ አመራር የተወሰነው ውሳኔ ትክክልና ወቅቱን የጠበቀ እንዲሁም የአባቶችን መመሪያ ወይም
ትዛዝ ተግባራዊ ያደረገና የሚጠበቅም ነበር ተብሎ የሚታሰብ ነው በተጨማሪም አባሉን እንዲሁም ምእመኑን ከዚህ
ወረርሺኝ ለመታደግ በፅ/ቤቱ ደረጃ የተኬደውን እርቀት እጅግ የሚበረታታና እንደ አባልም በእግዚአብሐር ስም ትልቅ
ምስጋና ማቅረብ እንፈልጋለን ፤፤

በተለያዩ ሚዲያ እንዲሁም ድኸረ ገፆች እንደሰማችውትና እንደምታውቁት በአሁኑ ወቅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ
በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ስጋት የሆነና የብዙዎችን ነብስ በመቅጠፍ ላይ የሚገኝ እንደሆነ ይታወቃል ፤፤

ቫይረሱ ወደ ሀገራችን ከገባበት ቀን ጀምሮ ቁጥሩ እየጨመረ ከባለፈው ሳምንትም ቁጥሩ 12 የነበረ ሲሆን በትናትናው
እለት ወደ 16 መግባቱን የተለያዩ ሚዲያዎች ገልፀዋል ብዙዎችም በጥርጣሬ ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልፃል

በዚህም መሰረት እንደ መንግስት እየተሰራ ያለ ስራ ቢኖርም እንደ ቤተ-ክርስቲያንም የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት
በቅዱስ ሲኖዶሱ የመተላለፊያ መንገዶችን በዝርዝር በመጥቀስ እና መከላኪያወንም እንደዚህው በመጥቀስ የተለያዩ
ክልከላዎችን እንዲተገበርም መመሪያ ማስተላለፉ የሚታወቅ ሲሆን ነገር ግን ማህበራት እንዲሁም ህዝበ ክርስቲያኑ
በቸልታ እንዲሁም ጥንቃቄንና እምነትን ባምታታ መልኩ ትክክል ያልሆነ አስተሳሰብ ምክንያት እነዚህ በቅዱስ
ሲኖዶስ የተላለፉ መመሪያዎች እና መከላኪያ መንገዶች ተብለው የተዘረዘሩትን ነገሮች ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር
ከፍተኛ ክፍተት እየተፈጠረ ነው ይህንም በእኛው ቤተ-ክርስቲያን በቅዳሴው መረሀ-ግብር ወቅት ለማየት ችለናል ፤፤

ስለሆነም የሰንበት ትምህርት ቤቱ የስራ አመራር እነዚህ የጥንቃቄ እርምጃዎች ለማስፈፀም መዋቅራዊ ግዴታም አለብም
በዚህም መነሻነት እንደ ሰንበት ትምህርት ቤት ከነዚህ ጉባያት ወይም መረሀ-ግብርና አንዳንድ የመንግስትም ሆነ የግል
መስሪያቤቶች መቋረጥ እና በፈረቃ መሆን ጋር ተያይዞ የተለያዩ አቅጣጫዎች ማስቀመጥ ቢቻል ለነዚህም መነሻ ሀሳብ
ይሆን ዘንድ እንደሚከተሉት ለመጥቀስ እንሞክራለን

1. የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት ብሎም በሽታውን ለመከላከል ለሚወሰዱ እርምጃዎች የሚፈጠረውን


ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅህኖ ለመፍታት ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል የተወጣጣ ጊዜያዊ ኮሚቴ
ማዋቀር ቢቻል እንዴት እናዋቅር የሚለውን ስራ አመራሩ ( ስራ አስፈፃሚ) ሰፋ ባለ መልኩ ቢወያይበት
እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ማቋቋም ቢቻል ፤፤

 በዚህ ኮሚቴ ውስጥ መካተት ያለባቸው ባለድርሻ አካላት


• የሰንበት ት/ቤቱ አመራር
• ከሰበካ ጉባዪ
• ማህበረ ካህናት( ካህናት )
• የወጣቶች ማህበራት
• የፅዋ ማህበራት
• ከምህመኑ ( ከህዝበ ክርስቲያኑ ) በዚህ መልኩ መዋቀር ቢቻል
ምክንያቱም ከዚህ በሽታ ጋር የተያያዙ የተለያዩ ስራዎችን በምንሰራበት
ወቅት እክል ወይም እንቅፋት እንዳይገጥመን በዚህ መልኩ መዋቀሩ
የተሻለ ነው ተብሎ ይታሰባል ካልሆነ ግን በሰንበት ት/ቤቱ ደረጃ በክፍላት
ማዋቀር ቢቻል ፤፤

 የዚህ ኮሚቴ የስራ ተግባር ምንድ ነው


 በሁሉም የቤተ-ክርስቲያን መግቢያና መውጫ በሮች ላይ የእጅ ሳሙና ፤ ሳኒታይዘር ፤ ወይም አልኮሎችና
ውሀዎችን እንዲሁም የእጅ መታጠቢያ ከበጎ አድራጊዎች ጋር በመተባበር ማዘጋጀት ፤፤
 በውጪ በሮች እና በቤተ-መቅደስ መግቢያው ላይ በሁሉም በሮች ምእመናንን እጃቸውን በአልኮል እና
በሳኒታይዘር እንዲያፀዱ ከሰንበት ት/ቤቱ አባላት ጋር በመተባበር ተግባራዊ ማድረግ ፤፤
 በቤተ መቅደስ ውስጥ የሚገኙ የአገልግሎት መገልገያ ንዋየ ቅዱሳን ማለትም ግልፅ ለማድረግ ያክል ወንበር ፤
መቋሚያ የመሳሰሉትን በእጅ የሚነካኩ እቃዎችን ከቅዳሴ በፊት በአልኮል ማፅዳት
 በቤተ-መቅደስ ውስጥ ፤ በፀበል ቦታ ፤ በቤተ-ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ በሚያስቀድሱበት ወቅት እና
በሚጠመቁበት ወቅት ምመናን ርቀታቸውን እንዲመብቁ ማስተባበር እና የመሳሰሉትን ስራዎችን ማከናወን
ለዚህም ተግባራዊነት ብዙ የሰው ሀይል ያስፈልጋል ለዚህም አባላቶች እራሳችንን ለዚህ አገልግሎት
እንድናዘጋጅ እና አመራሩም ጥሪ ማቅረብ ይኖርበታል እንዲሁም መወያየት ይኖርብናል
 በተለይ በቤተ-መቅደስ ውስጥ የሚኖረውን መጨናነቅ ለመቀነስ ቆራቢ ብቻ ወደ ውስጥ እንዲገቡ ማድረግና
ይሀንንም ማስተባበር እና ማቀናጀት
 ሌላው ለህዝበ ክርስቲያኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ማዘጋጀት ለምሳሌ በተለያዩ ድረ ገፆች በዚህም ተደራሽ
ለማይሆኑ ሕዝበ ክርስቲያኖች ሞንታርቦዎች በማዘጋጀት መኪናዎችን ከበጎ አድራጊዎች በመተባበር በየሰፈሩ
ውስጥ እየዞሩ ግንዛቤ መስጠት በዚህ ጉዳይ ላይ የሰንበት ት/ቤታችን የጤና ባለሙያዎች ትልቅ ድርሻ
ይወስዳሉ ለምሳሌ ዶ/ር ኤርሚያስ አብርሀም
ዶ/ር ሳምሶን ተፈሪ

ነርስ በረከት እና የስነ ልቦና ባለሙያ ካላችው የማናውቃችው ትልቅ ድርሻ


ትወስዳላችው እንደሚታወቀው በመንግስትም ደረጃ የጤና ባለሙያዎች እና ተማሪዎችም ብሔራዊ ግዴታ
እንደተጣለባችው ይታወቃል ፤፤

 ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ምን ላይ ማተኮር አለበት


• ኮሮና በሽታ መነሻው ምንድ
• የኮሮና በሽታ ምልክቶች ምንድ ናቸው
• የኮሮና በሽታ እንዴት ይተላለፋል
• የኮሮና በሽታን እንዴት መከላከል እንችላለን
• እንደ ቤተ-ከርስቲያን ምን ምን አይነት መፈትኤዎችን መውሰድ አለብን
በሚል ዙሪያ ላይ ከጤና መመሪያዎችና ከሳይንሳዊ መርሆች ጋር
በማይጋጭ መልኩ የተብራራ በሆነ መልኩ ቢዘጋጅ
 ልክ እንደ ሰንበት ት/ቤቱ የወጣቶች ማህበራት ፤ ፅዋ ማህበረሰብ ለጊዜው መረሀ-ግብር እንዲያቀርጡ
ግንዛቤ መፍጠርና ማንኛውንም አገልግሎት እንዳያደርጉ ክትትል ማድረግ
 ካህናትን በማስተባበር በቤተ-ክርስቲያን ዙሪያ እና በየአካባቢው መአጥንቱን ይዘው የማጥንትን መረሀ-ግብር
እንዲካሄድ ጥረት ማድረግ በዚህም መሰረት ህዝበ ክርስቲያኑን በፍረሀት ውስጥ የገቡትን እና የስነ ልቦና
ቀውስ የገጠማቸውን ክርስቲያኖችን እንዲረጋጉ ማድረግ
 በመጨረሻም በሽታው አሳሳቢ ደረጃ ሊደርስ ስለሚችል ቤተ-ክርስቲያኒቱ ላይ ሊደርስ የሚችለውን አስከፊ
ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ዝግጁ መሆን ምእመኑንም በዚህ ደረጃ ዝግጁ
እንዲሆን ማድረግ ለምሳሌ መንግስት በበኩሉ የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ነው የትምህርት
ተቋማትን ከመዝጋት ጀምሮ የመንግስት እና የግል መስሪያቤቶች በከፊል መዝጋት ጀምሩዋል ፤፤
በቀጣይ የበሽታው ስርጭት እና ተዛማችነቱ እየከፋ የሚመጣ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴዎች እና ከቤት
ያለመውጣት ገደቦች ሊታወጁ ይችላል በዚህም መሰረት ለሚፈጠሩ ኢኮኖማዊና ማህበራዊ ቀውስ እንደ
ሰንበት ት/ቤት በቅፅረ ቤተ-ክርስቲያን የሚገኙ እንዲሁም ገዳማት እና በአካባቢያች የሚኖሩ ዝቅተኛ እና
ምንም ገቢ የሌላቸው ደጅ ጠኚ ካህናት እንደ ክርስቲያን ሰበዓዊ እና መንፈሳዊ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ
ስለሚገኝ የተለያዩ ቁሳቁሶችን የፅዳት መጠበቂያዎችን ፤ ደረቅ ምግቦችን ፤ ማዘጋጀት እና እንዲሰበሰብ
ማብረግ

 ለዚህም የሚያስፈልጉ የምግብ አይነቶች


 ፓስታ
 ሩዝ
 ማካሮኒ
 ዘይት
 ፉርኖ ዱቄት
 የቦቆሎ ዱቄት
 ምስር ክክ
 በሶ
 ቆሎ
 ደረቅ ብስኩቶች
 የንህፅህና መገልገያ የሚያስፈልጉ የንህፅህና መጠበቂያ ግብአቶች
 ሶፍት
 ሳኒታይዘር
 ፈሳሽ ሳሙና
 ግላቭ
 በረኪና
 አልኮል
 የአፍ መሸፈኛ

እነዚህንና የመሳሰሉትን ነገሮችን ከበጎ አድራዚዎች እና ከምእመኑ ማሰባሰብ የሚቻልበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት
የኮሚቴው ዋና ተግባራት ሲሆን ይህንን ከላይ የገለፅናቸውን ዝርዝር ነገሮች ኮሚቴው በሚገባ ተወያይቶበት
እያንዳነዱ ስራዎቹን በመከፋፈልና አባላትን በማደራጀት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደስራ መግባት ይኖራባቸዋል ፤፤
የሰንበት ት/ቤቱ አባላትም ለዚህ ቅዱስ ዓላማ አይ ይህ የኔ ክፍል ስራ አይደለም ብሎ ቦክስ ውስጥ መታጠር ትተን
አስከፊውን ጊዜ ለማለፍ ሁላችንንም የበኩላችንን የምንወጣበት ጊዜ መሆኑን በመረዳት የበኩላችንን ድርሻ መወጣት
አለብን፤፤

ይህንን ስራዎችን ወደ ተግባር እንዴት መለወጥ እንችላለን

1. ከሰንበት ት/ቤታችን ንስሐ አባት ከሆኑት እና የቤተ-ክርስቲያናችን አስተዳዳሪ ከሆኑት አባታችን ጋር በሰፊው
ውይይት በማድረግ

2. ከሰበካ ጉባዩ ጋር በመወያየት


3. ከላይ ከተገለፁት ከባለድርሻ አካላት ጋር ማለትም ከሰንበት ት/ቤቱ አመራርና አባላት ፤ ወጣቶች ማህበራት ፤ የፅዋ
ማህበራት ፤ ከበጎ ፍቃደኛ ምዕመናት ጋር በጥልቀት በመወያየት

4. በተለይ ከሚያስፈልጉ የተለያዩ ግባዓቶች ጋር ተያይዞ በአውደ ምህረት ላይ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር


5. በጎ አድራጊዎችን በመጠየቅና ክርስቲያን የሆኑ ባለሀብታሞችን በመፈለግና በመጠየቅ
6 .በተጨማሪም ምዕመኑንም ሀሳቡን በሚገባ በማስረዳት የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ በማድረግ

ስራ አመራሩም ተጨማሪ ሃሳቦችንም አካቶ ከወዲሁ ወደ ስራ መግባት የምንችልበትን ሁኔታዎችን ብናመቻች እንደ
ክፍል እና እንደ ሰንበት ት/ቤቱ አባልም ሃሳብ እናቀርባለን ፤፤

ወስብሓት ለእግዚዓብሔር

አዘጋጅ አምደ ተዋህዶ ሰንበት ት/ቤት ጥናትና ስልጠና ንውስ ክፍል


ቀን 19-07-2012

You might also like