You are on page 1of 4

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በካራቆሬ መ/ም ቅዱስ ፋኑኤል ሐመረ ኖኅ ሰ/ት አባላት ግንኙነት ክፍል የተዘጋጀ

ቀን፦19/6/15
ለሚመለከተው ሁሉ
ጉዳዩ፦ በተድጋጋሚ ጥፋተኛ የሆኑ አባላት ላይ የተወሰደ የእርምት እርምጃን
በተመለከተ

በቅድሚያ እንኳን ለታላቁ ዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ እያልን ከላይ


በርዕሱ እንደገለጽነው በሰንበት ት/ት ቤታችን ነባር አባላት ሆነው እያገለገሉ ያሉ
ነገር ግን ከፍላችን ለ 6 ወራት ባደረገው ክትትል መሰረት በሕገደንባችን አንቀጽ 34
ላይ በግልጽ ከሰፈሩት የአባላት ግዴታዎች መካከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህግና
መመሪያዎች በተደጋጋሚ በመጣስ፣
አንቀጽ 34.2.3
አንቀጽ 34.2.17
አንቀጽ 34.2.24
አንቀጽ 34.2.6
አንቀጽ 34.2.14
ከዚህም አልፎ በተደጋጋሚ በታላላቅ የሰት/ት ወንደሞችና እህቶች፣ በተለያዩ
ክፍላት፣ በኮርስ መምህራኖቻቸውና ከደብሩ ጋር በመነጋገር በምክረ ካህን ይታገዙ
በሚል አባት በመመደብ ጭምር ቢረዱና በግንኙነት ክፍሉ በርካታ አባላት
እንደወንድም እንደእህት ተመክረው ሊመልሱ ባለመቻላቸው እና ከዛ ይልቅ
በሚመክሯቸው፣ በሚያዟቸውና ለአገልግሎት በሚጠሯቸው አባላት ላይ አጸያፊ
ስድቦችን፣ ፌዝና ስላቆችን እንዲሁም ለጸብና ቅጣት የሚጋብዙ ስርዐት አልባ
ምላሾችን በተደጋጋሚ በመስጠታቸው ግንኙነት ክፍሉ ከመዝሙር ክፍል ጋር
በመነጋገር የነዚህን ጥቂት አባላት ስነልቦና ለመጠበቅና አብረዋቸው ከሚያገለግሉና
አርዓያ ከሚሆኗቸው አባላት ተምረው ወደልቦናቸው ይመለሱ በማለት ለ 3 ወራት
መላው የአዳጊ ክፍል አባላትን ከእሑድ ጠዋት አውደምሕረት አገልግሎት
ማቀባችን ይታወሳል::
ነገር ግን በዚህ ሁሉ ሂደት እነርሱን እያረመ ሳይሆን መልካም
ስነምግባር የነበራቸውን አባላት እየሸረሸረ፣ በምዕመናን ዘንድ ተደጋጋሚ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በካራቆሬ መ/ም ቅዱስ ፋኑኤል ሐመረ ኖኅ ሰ/ት አባላት ግንኙነት ክፍል የተዘጋጀ

ወቀሳዎች እያስተናገደ፣ አዳዲሰ አባላት እንዲሰናከሉና ሰት/ቱን እንዲርቁ


ምክንያት መሆኑ ስለተረጋገጠ በአጠቃላይ
 የሰንበት ት/ቱ ቋሚ መርሐግብራትና የሰንበት ቅዳሴ ላይ በቸልተንኝነት
ባለመሳተፍ
 ሰንበት ት/ቱ በሚመድባቸው ልዩ ልዩ አግልግሎቶች ላይ ሆን ብሎ
ባለመሳተፍ
 በቤተክርስቲያኒቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሰርክ ጉባኤ፣ በቅዳሴ፣
በአውደምሕረትና በሰንበት ት/ቱ መደበኛ መርሐግብራት ወቅት በቡድን
በመሰብሰብ ፣ስልኮችን በመጠቀም፣ የማይገቡ ሳቅና ስላቆችን ምዕመናንን
ጭምር በሚረብሽና የሰንበት ት/ቱን ገጽታ በሚያጎድፍ መልኩ በማሳየት
 ሰው አክባሪነት፣ታዛዥነት፣ትህትና፣ አርዓያንተና ና መሰል የስነምግባር
እሴቶች ፈጽሞ የሌላቸውና ለሌሎች ወንድም እህቶች አሰናካይ
በመሆናቸው ምክንያት
የሰንበት ት/ቱን ሕገደንብ በቀጥታ ጥሰው በተገኙ የሰንበት ት/ታችን 9 ነባር
የአዳጊ ክፍል አባላት ላይ ግንኙነት ክፍላችን ጥፋተኞችን ያርማል፣ሌሎችን
ያስተምራል፣ሕገደንቡን በማስከበር ለቤተክርስቲያንና ለሐገር የሚጠቅሙ
አባላት ለማፍራት ያግዛል በማለት ከዚህ በታች ያለውን ውሳኔ ወስኗል።

በጥፋተኛ አባላት ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች


1. ለስድስት ወራት ከሰንበት ትምህርት ቤቱ መደበኛ አባልነት እንዲታቀቡ
2. ሰንበት ት/ቱን ወክለው ምንም አይነት የአፍኣ አገልግሎት ከመስጠት
እንዲቆጠቡ
 የውስጥና የውጭ መድረኮችና አውደምህረት ላይ
መርሐግብር የመምራት፣የማስተማር፣ዝማሬያትንና
ወረቦችን ከማቅርብና ልዩ ልዩ ኪነጥበባዊ ስራዎችን
ለአባላትና ለምዕመናን ከማቅረብ
 በዐቢይና ንዑስ ክፍላት ላይ ከአባልነት ውጪ የክፍል
ተጠሪ ሆኖ ከማገልግል
 መንፈሳዊ ጉዞዎችን፣መርሐግብራትን፣ምድብ
ስራዎችንና መሰል እንቅስቃሴዎችን ከመዘርጋትና
በአዘጋጅነት፣ በኮሚቴነትና በአስተባባሪነት ከማገልገል
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በካራቆሬ መ/ም ቅዱስ ፋኑኤል ሐመረ ኖኅ ሰ/ት አባላት ግንኙነት ክፍል የተዘጋጀ

 ከተለያዩ የአጋር አካላትና አጥቢያ ሰንበት ቤቶች ጋር


የግንኙነት ስራዎችን ከመስራት እንዲቆጠቡ
3. በተለየ ሁኔታ የቅዳሴ የሰንበት ት\ት ቤቱ ቋሚ መርሐግብራት ላይ
እንደአባል ማሟላት የሚገባቸውን ቁሳቁስ፣ የአልባበስ ስርዓት ፣
ስነምግባራት በሙሉ አሟልተው የመገኘትና ከአቅም በላይ ከሆነ
በአንቀጽ 34.2.17 መሰረት በማመልከቻ ሲያሳውቁ ብቻ የመቅረት ፍቃድ
እንዲሰጣቸው
4. በሚያገልለግሉበት የአገልግሎት ክፍል ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉና
የሚታዘዟቸውን ተግባራት በሚጠበቅባቸው ልክ እንዲፈጽሙ
5. በቤተክርስቲያኒቷ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተንቀሳቃሽ ስልክና መሰል
ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በግልም ሆነ በቡድን ይዞ ከመምጣትና
ከመጠቀም እንዲቆጠቡ
6. ሕገደንቡ ለመደበኛ አባላት የሰጣቸውን ልዩ ልዩ መብቶች ለስድስት
ወራት እንዲነፈጋቸው ወስነናል።
የአፈጻጸም ቅደም ተከተል
1. ውሳኔው ከጸደቀበት ዕለት አንስቶ አባላቱንና ወላጆቻቸውን በአካል ጠርቶ
የማናገር ስራ በሰንበት ት/ቱ ጽ\ቤትና ግንኙነት ክፍል ማከናወን
2. የአባላቱን ዕለተዕለት የመርሐግብር ሱታፌ፣ የስነምግባር ለውጥ፣
የትምህርትና የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን
በቅርበት የሚከታተሉና ለውጡን የሚያግዙ 4 የግንኙነት ክፍል አባላትን ስራ
ማስጀመርና የአባላቱን የእርምት ደረጃ በየሳምንቱ ለግንኙነት ክፍል ጽ\ቤት
እንዲዘግቡ ማድረግ
3. የዚህን ውሳኔ ግልባጭ ለሚመለከታቸው የአገልግሎት ክፍላት ሁሉ በማድረስ
ውሳኔዎቹ በሰንበት ት/ቱ አጠቃላይ ክፍላት ዘንድ ተግባራዊ መሆኑን
መከታትልና ጥሰው በሚገኙ ክፍላት ተጠሪዎች ላይ ተገቢውን የእርምት
እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ወስነናል።
የእርምት እርምጃ የተወሰደባቸው አባላት ስም ዝርዝር
1. ናታን ሰርጸ
2. ቴዎድሮስ ኦኬ
3. ዳዊት ሙሉጌታ
4. ናሆም ደጀኔ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በካራቆሬ መ/ም ቅዱስ ፋኑኤል ሐመረ ኖኅ ሰ/ት አባላት ግንኙነት ክፍል የተዘጋጀ

5. ቃልኪዳን ጋሻው
6. ቅድስት ንቁ
7. በረከት ቢያዝን
8. በቃሉ ምስጋናው
9. ሰላም ሰለሞን
የአባላቱን ለውጥ የሚያግዙ ተከታታዮች
1. አደራው ካሳሁን
2. ሰላም መለሰ
3. ጸጋነሽ ዘነበ
4. የአብስራ ደረሰ
የአፈጻጸም ሂደቱ ተከታታዮች
1. አሰቴር አባተ
2. ቃልኪዳን እሸቱ
ሠላማዊት በቀለ አዱኛ
የአባላት ግንኙነት ክፍል ተጠሪ
ሠላመ እግዚአብሔር አይለያችሁ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

You might also like