You are on page 1of 28

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን

ሦስተኛ ክፍል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች


ማደራጃ መምሪያ የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰንበት ት/
ቤቶች አንድነት የተዘጋጀ 2015 ዓ.ም
ያግኙን

Email
office@eotc-gssu.org
YouTube
https://www.youtube.com/channel/
UC83LE1vp0FBsV2TEfcpSmUg
Facebook
http://facebook.com/EOTC.GSSU
Telegram
https://t.me/EOTCNSSU
Website
https://eotc-gssu.org/a/

Copyright ©
2015 E.C
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና
ሥራ አስኪያጅ እና የባህርዳር
ሁገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ


በሰንበት ትምህርት ቤቶች
ማደራጃ መምርያ የበላይ
ሊቀጳጳስና የሰሜን ሸዋ ሀገረ
ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ
ሲኖዶስ አባል
ማውጫ
ምዕራፍ አንድ
፩.፩ ሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን መግቢያ በጥያቄና መልስ...................................... ፪
፩.፪ ስለ አፈጻጸማቸው በጥያቄና መልስ .............................................................. ፫
፩.፫ ምስጢረ ጥምቀት በጥያቄና መልስ.................................................................፬
፩.፬ ለምን በውኃ እንጠመቃለን? በጥያቄና መልስ ............................................... ፭

ምዕራፍ ሁለት
፪.፩ ምስጢረ ሜሮን በጥያቄና መልስ........................................................................ ፯
፪.፪ ምስጢረ ቁርባን በጥያቄና መልስ ...................................................................... ፰

ምዕራፍ ሦስት
፫.፩ ምስጢረ ክህነት በጥያቄና መልስ.......................................................................... ፲፩
፫.፪ ምስጢረ ንስሐ በጥያቄና መልስ............................................................................. ፲፪
፫.፫ ምስጢረ ቀንዲል በጥያቄና መልስ........................................................................... ፲፫

ምዕራፍ አራት
፬.፩ ምስጢረ ተክሊል በጥያቄና መልስ ........................................................................ ፲፮
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

ምዕራፍ አንድ

ሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን

የምዕራፉ ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ
፩ .ስለ ሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን ትርጉም ያውቃሉ፤
፪. ምስጢራቱን እና ማን እንደሚፈጽማቸው ይረዳሉ፤
፫. በቤተ ክርስቲያን በመገኘት ምስጢራቱን ይከታተላሉ ፤ የምስጢራቱም ተካፋዮች ይሆናሉ።


የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን
• ልጆች ምስጢር ማለት ምን ማለት ነው?
፦ ስውር ሽሽግ የተደበቀ ለቅርብ ወዳጅ ለሚያምኑት የሚነገር
• ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ለምን ምስጢር ተባሉ?
፦ ለሚያምኑ የተገለጡ ለማያምኑ ደግሞ የተሰወሩ ስለሆኑ
፦ በሚታይ አገልግሎት የማይታይ ጸጋን ስለሚያስገኙ
• ምስጢራቱ ስንት ናቸው?
፦ ሰባት ናቸው
• ምን ምን ይባላሉ?
፩. ምስጢረ ጥምቀት
፪. ምስጢረ ሜሮን
፫. ምስጢረ ቁርባን
፬. ምስጢረ ንስሐ
፭. ምስጢረ ክህነት
፮. ምስጢረ ተክሊልና
፯. ምስጢረ ቀንዲል ናቸው።

፩.፪ ስለ አፈጻጸማቸው
• ልጆች ሰባቱ ምስጢራት በአፈጻጸም ደረጃ በስንት ይከፈላሉ?
፦ በሁለት
• ምን ምን ተብለው?
፦ የሚደገሙ እና የማይደገሙ እንዲሁም ለሁሉ የሚፈጸሙ እና ለሁሉ የማይፈጸሙ
• የሚደገሙ የሚባሉት ምስጢራት የትኞቹ ናቸው?
፦ ምስጢረ ቁርባን
፦ ምስጢረ ንስሐ
፦ ምስጢረ ቀንዲል ናቸው።
• የማይደገሙ የሚባሉትስ?
፦ ምስጢረ ጥምቀት
፦ ምስጢረ ሜሮን
፦ ምስጢረ ክህነት
፦ ምስጢረ ተክሊል ናቸው።
• ላመኑ ሁሉ የሚፈጸሙ ምስጢራት የትኞቹ ናቸው?
፦ ምስጢረ ጥምቀት
፦ ምስጢረ ሜሮን
፦ ምስጢረ ቁርባን
፦ ምስጢረ ንስሐ ናቸው።
• ልጆች ለሁሉ የማይፈጸሙ ምስጢራት የሚባሉት እነማን ናቸው?
፦ ምስጢረ ክህነት
፦ ምስጢረ ተክሊል
፦ ምስጢረ ቀንዲል ናቸው።


የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን
፩.፫ ምስጢረ ጥምቀት

• ልጆች ጥምቀት ማለት ምን ማለት ነው?


፦ በውኃ መዘፈቅ መነከር ማለት ነው።
• ጥምቀትን ማን መሠረተው?
፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ፴ ዘመኑ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ
• ጥምቀት መቼ ይፈጸማል?
፦ ለህፃናት ለወንዶች ከተወለዱ በ፵ ቀናቸው ለሴቶች ደግሞ ከተወለዱ በ፹ ቀናቸው።
• ስንጠመቅ በማን ስም እንጠመቃለን?
፦ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
• በጥምቀት ምን እናገኛለን?
፦ የሥላሴን ልጅነት
• የክርስትና ስማችሁ ማን ይባላል?

፦ መምህር የራስዎን ክርስትና ስም በመንገር ተማሪዎችም ተራ በተራ እንዲናገሩ እድል ይስጡአቸው።

• ጥምቀትን ማን ይፈጽማል ወይም ማን ያጠምቃል?


፦ ቀሳውስትና ጳጳሳት
• ምስጢረ ጥምቀት የት ይፈጸማል?
፦ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን

ሥዕል ፩ ምስጢረ ጥምቀት አፈጻጸም የሚያሳይ ሥዕል


የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

፩.፬ በውኃ ለምን እንጠመቃለን ?


• ጥምቀት በምን ይፈጸማል?
፦ በውኃ
• ለምን በውኃ እንጠመቃለን?
፦ ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በውኃ ስለሆነ
፦ ውኃ በሁሉ ይገኛል ምስጢረ ጥምቀትም ለሚያምን ሁሉ በቀላሉ ለመፈጸም።
፦ ውኃ እድፍን ያጠራል ጥምቀትም እንዲሁ የኃጢአት ሥርየትን ያሰጣልና።

የተግባር ልምምድ
ልጆች በዚህኛው ምዕራፍ የተማራችሁትን ለወላጆቻችሁ ተናገሩ

የመልመጃ ጥያቄዎች
ትዕዛዝ አንድ:- በተማራችሁት መሠረት ትክክለኛውን መልስ መልሱ
፩ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን ስንት ናቸው?
፪ ምስጢረ ጥምቀት የት ይፈጸማል?
፫ ምስጢረ ጥምቀትን ወንድ በ...... ሴት ደግሞ በ....... ዓመታቸው ይጠመቃሉ።
፬ ለምን በውኃ እንጠመቃለን?
፭ ምስጢረ ጥምቀትን ማን መሠረተው?


የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

ምዕራፍ ሁለት

ምስጢረ ሜሮንና ምስጢረ ቁርባን

የምዕራፉ ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ
፩. ስለ ምስጢረ ሜሮን ይገነዘባሉ፤
፪. ስለ ምስጢረ ቁርባን ተረድተው ይቆርባሉ፤
፫. በምስጠራቱ ስለሚገኘው ጸጋ ያውቃሉ፤


የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

፪.፩ ምስጢረ ሜሮን


• ሜሮን ማለት ምን ማለት ነው?
፦ ቅዱስ ቅብዓት ማለት ነው።
• ማን ያዘጋጀዋል?
፦ ብጹአን አባቶች ወደ እግዚአብሔር ጸሎትን በማድረግ ያዘጋጁታል።
• ማን መሠረተው?
፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
፦ ቅዱሳን ሐዋርያት
• መቼ ይፈጸማል?
፦ ከጥምቀት በኋላ
• ለማን ይፈጸማል?
፦ ክርስትና ለተነሱ ሁሉ መንፈስ ቅዱስን በተጠማቂዎች ላይ ለማሳደር።
• የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ለመቀበል ምን ያስፈልጋል?
፦ ቅብዓ ሜሮንን መቀባት
• ስንት ቦታ እንቀባለን?
፦ ፴፮ ህዋሳቶቻችን ላይ
• ማን ይቀባናል?
፦ አባቶች ቀሳውስትና ጳጳሳት
• ከጥምቀት ውጪ መቼ ይፈጸማል?
፦ ምስጢረ ክህነትና ምስጢረ ተክሊል ሲፈጸም
• በአገልግሎትስ?
፦ አዲስ ቤተክርስቲያን ይከብርበታል እንዲሁ ንዋያተ ቅድሳት ይቀደሱበታል።

ሥዕል ፪ ምስጢረ ሜሮን ከጥምቀት በኋላ ሲፈጸም የሚያሳይ ሥዕል


የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን
፪.፪ ምስጢረ ቁርባን
• ቁርባን ማለት ምን ማለት ነው?
፦ አምኃ፣ መባ፣ ነጻ ስጦታ ማለት ነው።
፦ መቅረቢያ መቀራረብያ መገናኛ ማለት ነው።
፦ የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም መቀበል ማለት ነው።
• ማን መሠረተው?
፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
• መቼ መሠረተው?
፦ በጸሎተ ሐሙስ
• ምን ብሎ አዘዘን?
፦ ቅዱስ ሥጋየን ብሉ ቅዱስ ደሜን ጠጡ ብሎ።
• ለመቁረብ ምን ያስፈልጋል?
፦ መጾም ንስሐ መግባት ማስቀደስ
• ቅዳሴና ቁርባን ምን አገናኛቸው?
፦ ቅዳሴ ቅዱስ ቁርባን የሚዘጋጅበት ጸሎት ስለሆነ።
• ከመቁረብ በፊት ምን እናድርግ?
፦ ገላችንን እንታጠብ ንጹሕ ልብስ እንልበስ።
• በምንቆርብበት ጊዜስ?
፦ ተራችንን መጠበቅ፣ በትህትና መቁረብ፣ ጠበል መጠጣት
• ከቆረብን በኋላስ?
፦ ልብሳችንን አለማውለቅ፣ ምራቅ አለመትፋት? ከቤት አለመውጣት።
• ምን መብላት የለብንም?
፦ የሚተፉ ምግቦች
• መቼ እንቆርባለን?
፦ በሰንበት፣ በአፅዋማትና በበዓላት ቀን
• የማንን ሥጋና ደም እንቀበላለን?
፦ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
• ስንቆርብ ምን እናገኛለን?
፦ የዘለዓለም ህይወት

የተግባር ልምምድ
ልጆች በዚህ ምዕራፍ የተማራችሁትን ለጎረቤቶቻችሁ ተናገሩ


የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

ሥዕል ፫ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጢረ ቁርባንን ሲመሰርት የሚያሳይ

የመልመጃ ጥያቄዎች
በተማራችሁት መሠረት ትክክለኛውን መልስ ስጡ
፩. ለቅዱስ ቁርባን የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶችን ዘርዝሩ
፪. ምስጢረ ሜሮንን የመቀባት ሥልጣን ያለው ማነው?
፫ .አንድ ሰው ከቆረበ በኋላ የሚጠበቅበትን ጥንቃቄ ዘርዝሩ?
፬. ቅዱስ ቁርባንን ማን መሠረተው?
፭ . ምስጢረ ሜሮን ከጥምቀት ውጪ መቼ ይፈጸማል?


የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

ምዕራፍ ሦስት

ምስጢረ ክህነት፤ ንስሐና ቀንዲል

የምዕራፉ ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ
፩ ምስጢረ ክህነትንና የክህነት ደረጃዎችን ይረዳሉ።
፪ ስለ ምስጢረ ንስሐ ምንነት ያውቃሉ።
፫ ስለ ምስጢረ ቀንዲል ምንነት በእድሜያቸው ይረዳሉ።


የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

፫.፩ ምስጢረ ክህነት


• ክህነት ማለት ምን ማለት ነው?
፦ ተክህነ ከሚለው ቃል የወጣ ሲሆን መሾም ማገልገል ማለት ነው።
• እንዴት ይፈጸማል?
፦ በአንብሮተ እድ/ እጅ በመጫን
• ማን መሠረተው?
፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
• ማንን በመሾም?
፦ ቅዱሳን ሐዋርያትን
• ሲሾማቸው ምን ሥልጣን ሰጣቸው?
፦ በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ ነው
፦ በምድርም የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ነው።
• በብኪይ ኪዳን ክህነት ነበረ?
፦ አዎ ነበረ
• በብሉይ ኪዳን ከነበሩ ካህናት ጥቂቶቹን ጥሩ?
፦ ካህኑ አሮን ፣ ካህኑ መልከጼዴቅ፣ ካህኑ ዘካርያስ፣ ሌዋውያን ካህናት
• የክህነት መዓርጋት ስንት ናቸው?
፦ ሦስት ናቸው
• ስማቸው ማን ይባላል?
፦ ፩ኛ ዲያቆን
፪ኛ ቀሳውስት
፫ኛ ኤጲስቆጶሳት

• ክህነት ለማን ይሰጣል?


፦ ንጽሕና ድንግልና ለጠበቀ
፦ ቃለ አግዚአብሔር ለተማረ
፦ እግዚአብሔር ለመረጠው
• ክህነት በማን ይሾማል/ ይሰጣል?
፦ በጳጳሳት
• የካህናት ሥራ ምንድን ነው?
፦ ምእመናንን መጠበቅ
፦ ምስጢራትን መፈጸም
፦ ወደ እግዚአብሔር ሰውን ማቅረብ

፲፩
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

ሥዕል ፬ የክህነት ደረጃዎችን የሚያሳይ ሥዕል

፫.፪ ምስጢረ ንስሐ

• ንስሐ ማለት ምን ማለት ነው?


፦ መጸጸት፣ በሠሩት ኃጢአት ከልብ ማዘን ማለት ነው።
• ንስሐ መግባት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ሰው ነው?
፦ የሚሰርቅ፣ የሚሳደብ፣ ኃጢአት የሚሠራ...
• ንስሐ የሚገባው ማን ጋር ነው?
፦ ንስሐ አባቶቻችን ጋር
• ንስሐ ስንት ሂደቶች አሉት?
፦ ሦስት
• ምን ምን ናቸው?
፦ ኃጢአትን መናዘዝ
፦ ቀኖና መቀበል
፦ ቀኖና መፈጸም
• ንስሐ ከሚገባ ሰው ምን ይጠበቃል?
፦ ከልብ መመለስ፣
፦ የታዘዘውን ቀኖና መፈጸም፣
፦ እግዚአብሔርን መለመን
• በንስሐ ምን ይገኛል?
፦ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ

፲፪
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

ሥዕል ፭ በካህን ፊት ምስጢረ ንስሓ የምትፈጽም እህት

፫.፫ ምስጢረ ቀንዲል


• ቀንዲል ማለት ምን ማለት ነው?
፦ መብራት
፦ ቅዱስ ቅብዓት ማለት ነው።
• ማን መሠረተው?
፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
• እንዴት ተመሠረተ?
፦ ህሙማንን ለመፈወስ ለሐዋርያት ሥልጣንን ሰጥቶ ( ማር ፮፥፲፫ ይመልከቱ)
• እንዴት ይፈጸማል?
፦ የታመመ ሰው ካህናት እንዲጸልዩለት በመጠየቅ
• ምን ያደርጉለታል?
፦ ንስሐ ያስገቡታል፣ ቅዱስ ቅባት ይቀቡታል ( ያዕ ፭፥፲፬ ይመልከቱ)
• የታመመው ሰው ምን ያገኛል?
፦ ኃጢአቱ ይቅር ይባላል
፦ ከህመሙ ይፈወሳል
• ቅብዓ ቅዱስ ማን ይቀባል?
፦ ቀሳውስት ብቻ

፲፫
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

ሥዕል ፮ ካህናት ለታመመ ሰው ምስጢረ ቀንዲል ሲፈጽሙ

የተግባር ልምምድ
ልጆች በዚህ ምዕራፍ የተማራችሁትን ለጎረቤቶቻችሁ ተናገሩ

፲፬
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን
የምዕራፉ መልመጃ ጥያቄዎች
ትክክለኛውን ዓረፍተ ነገር እውነት ትክክል ያልሆነውን ዓረፍተ ነገር ሐሰት በሉ፡፡
፩. የካህናት ሥልጣን የሚያገለግለው በምድር ብቻ ነው፡፡
፪. ዲያቆን ከክህነት ማዕረጋት መካከል አንዱ ነው፡፡

ትክክለኛ መልሱን ምረጡ


፫. ከክህነት ማዕረጋት መካከል ትልቁ የቱ ነው?
ሀ. ቅስና ለ. ጵጵስና
ሐ. ድቁና መ. መሪጌታ
፬. ቤተ ክርስቲያን ለህመምተኞች የምትፈጸመው ምስጢር የትኛው ነው?
ሀ. ምሥጢረ ንሰሐ ሐ. ምሥጢረ ክህነት
ለ. ምሥጢረ ቁርባን መ. ምሥጢረ ቀንዲል
፭ .በብሉይ ኪዳን ከነበሩ ካህናት ጥቂቶቹን ጥሩ?
ሀ ካህኑ አሮን ለ ካህኑ መልከጼዴቅ፣
ሐ ካህኑ ዘካርያስ መ ሁሉም መልስ ነው

፲፭
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

ምዕራፍ አራት

ምስጢረ ተክሊል

የምዕራፉ ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ
፩ የምስጢረ ተክሊል ምንነትን በእድሜያቸው ግንዛቤ ያገኛሉ።

፲፮
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

• ተክሊል ማለት ምን ማለት ነው?


፦ መከለል፣ መጋረድ፣ መቀዳጀት (አክሊል ማድረግ) ማለት ነው።
• ማን መሠረተው?
፦ ልዑል እግዚአብሔር
• መቼ መሠረተው?
፦ አባታችን አዳምንና እናታችን ሔዋንን ሲፈጥር
• ከምን ይከላከላል?
፦ ከኃጢአት ከዝሙት
• ዝሙት ምንድን ነው?
፦ እግዚአብሔር የሚጠላው ኃጢአት
• ተክሊል ለማን ይፈጸማል
፦ በንጽሕና በድንግልና ለኖሩ ወንዶችና ሴቶች
• መቼ ይፈጸማል?
፦ በጋብቻ ወቅት
• ሠርጋቸው ላይ ማን ይገኛል?
፦ ልዑል እግዚአብሔር
፦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
፦ ቅዱሳን መላእክት
፦ ቅዱሳን ሐዋርያት
• በድንግልና ቢቆዩ ምን ይጠቀማሉ?
፦ እግዚአብሔር ይወዳቸዋል
፦ የክብር አክሊል ያደርጋሉ

ሥዕል ፯ በስርዓተ ተክሊል


የሚያገቡ ሙሽሮች

፲፯
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

የተግባር ልምምድ
ልጆች በዚህ ምዕራፍ የተማራችሁትን ለእኅትና ለወንድሞቻችሁ ተናገሩ

የማጠቃለያ ጥያቄዎች
ትዕዛዝ አንድ፦ በተማራቸሁት መሠረት ትክክለኛውን መልስ ምረጡ።
፩. ምስጢረ ተክሊልን ማን መሠረተው?
ሀ) አዳም ለ) ልዑል እግዚአብሔር
ሐ) ሔዋን መ) መልስ የለም
፪. ለታመመ ሰው የሚቀባ ቅብዓት ምን ይባላል?
ሀ) ቅብዓ ነገሥት ለ) ቅብአት
ሐ) ቅብዓ ቀንዲል መ) መልስ የለም
፫. ንስሐ ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ) መጸጸት ለ) በሠሩት ኃጢአት ከልብ ማዘን
ሐ) ሀእናለ መ) መልስ የለም
፬ ለመቁረብ ምን ያስፈልጋል?
ሀ) መጾም ለ) ንስሐ መግባት
ሐ) ማስቀደስ መ) ሁሉም መልስ ነው
፭. ከሚደገሙ ምስጢራት መካከል አንዱ የትኛው ነው?
ሀ ምስጢረ ጥምቀት ለ ምስጢረ ንስሐ
ሐ ምስጢረ ቁርባን መ ለ እና ሐ መልስ ናቸው

ትዕዛዝ ሁለት፦ በተማራችሁት መሠረት እውነት ሐሰት በሉ


፮. ቅዱስ ቁርባን ከተቀበልን በኋላ ልብሳችንን ማወለቅ እንችላለን?
፯. ቅብዓ ቅዱስን መቀባት የሚችሉት ካህናት ብቻ ናቸው?

ትዕዛዝ ሦስት፦ በተማራችሁት መሠረት ትክክለኛውን መልስ ጻፉ።


፰ ............. ከማይደገሙ ምስጢት መካከል አንዱ ነው።
፱. ምስጢረ ጥምቀትን ማን መሠረተው?
፲ ንስሐ የሚገባው ማን ጋር ነው?

፲፰
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሦስተኛ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን
ዋቢ መጻሕፍት
፩. ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ
፪ .ሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን
፫. ሰባቱ የሕይወት ምሰሶዎች መርጌታ ሰናይ

፲፱
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሰንበት ት/ቤት አመራር እና መምህራን እንዲሁም ተማሪዎችና ወላጆች
በመጽሐፉ ላይ ያላችሁን ማንኛውም አስተያየት እና ግብዓት በሚከተለው
አድራሻ ላኩልን

office@eotc-gssu.org
https://t.me/GSSUCurriculum_bot

You might also like