You are on page 1of 11

በታደሰ ሁሪሳ

የአሰበበክ ዘዴ/HOMILETICS/
በዚህ ኮርስ የምንመለከተቸዉ ርዕሶች

1. የስብከት ምንነት
2. የስብከት አስፈላጊነት/ጠቀሜታ/
3. በስብከት አገልግሎት የእግ/ርና የሰዉ ድርሻ
4. የሰባኪ የብቃት መስፈርቶች
5. የስብከት ዓይነቶች
6. የስብከት አወቃቀር ብልሀት
7. የስብከት አቀራረብ

1. የስብከት ምንነት 1 ቆሮ 1፤18-23 2 ጢሞ 4፤1-5


ስብከት ከእግ/ር የሚሰጥ ጸጋ ወይንም ስጦታ ሲሆን የእግ/ርን መልዕክት በንግግር፤በጽሁፍና በተግባር ለሰዎች ማድረስ
ወይንም ማስተላለፍ ነዉ፡፡

ስብከት በአደበበይ ለማያምኑ ሰዎች የሚታወጅ የወንጌል የምስራች አዋጅ ነዉ፡፡ /Heralding/bringing good
news/public proclamation/

ስብከት ስጦታ ብቻ ሰይሆን ስልቶችንና ዘዴዎችን ስለምጠቀም ሳይንስና ጥበብም ነዉ፡፡

- ስጦታ ነዉ ስንል መለኮታዊ ጥሪና ጸጋ ነዉ ማለታችን ነዉ፡፡


- ሳይንስ ነዉ ስንል ሰባኪዉን ዉጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ ተጨባጭ መርሆዎችን በመማርና በማጥነት ይገኛል
ማለታችን ነዉ፡፡
- ጥበብ ነዉ ስንል የስብከቱን መርህ ወደ ተግባር መቀየርና ዉበት ያለዉ እንዲሁም ትርጉም የሚሰጥ ሆኖ
በሰባኪዉ አማካኝነት ማቅረብ ይኖርበታል ማለታችን ነዉ፡፡

2. የስብከት አስፈላጊነት/ጠቀሜታ/
ስብከት ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ሲሆን ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸዉ

ሀ. የእግ/ርን ማንነትና ባህርይ ለመግለጥ

ለ. ለወንጌል ስርጭት

ሐ. የእግ/ርን መልዕክት ለሰዎች ለማድረስ

መ. ለመንፈሳዊ ዕድገት

- ቅዱሳን በእምነታቸዉ እንድያድጉ


- ቅዱሳንን ለአገልግሎት ለማሳደግ
- ከሀሰት ትምህርት ለመጠበቅ

1
በታደሰ ሁሪሳ

ሠ. መለኮታዊ ጥሪን ለማከናወን ይጠቅማል

ረ. የሰዎችን ችግርና እንቆቅልሽ ለመፍታት ይጠቅማል

3. በስብከት አገልግሎት የእግ/ርና የሰዉ ድርሸ


የእግ/ር ድርሻ

- ሰባኪዉን መጥራት

-መለኮታዊ ጸጋ መስጠት

-መልዕክት መስጠት

-በስብከቱ የሰዎችን ህይወት መለወጥ

-ቃሉን በድንቆችና በተአምራቶች ማጽናት

የሰዉ ድርሻ

-ራሱን ለአገልግሎቱ ማዘገጀት /በጸሎት፤ቃሉን በማጥናት፤በቅድስና/

-የአሰባበክ ዘዴንና ስልቶችን መማር

-በጊዜዉም አለጊዜዉም ቃሉን በቃልና በኑሮ ለመስበክ ዝግጁ መሆን

4. የሰባኪ የብቃት መስፈርቶች ቲቶ 1፤3 2 ጢሞ 2፤14-19


ሀ. በኢየሱስ አምኖ የሐጢየት ይቅርታ አግኝቶ የዳነ/የሚሰብከዉን ቃል የማዳን ኃይል በህይወቱ የተለማመደ/ ሉቃ 7፡
36-51 ቲቶ 1፡3 2 ጢሞ 2፡14-19

ለ. በቅድስና ህይወት የሚመላለስ/በሚሰብከዉ ወንጌል የተለወጠ/ 1 ቆሮ 9፡27 ዕብ 4፡12-13 ፊል 3፡12-16


1 ጢሞ 4፡12-16 ሮሜ 2፡17-24

ሐ. የኢየሱስ ክርስቶስን ጌትነት በግሉ የሚያምን

-ጌትነቱን በተግባራዊ ህይወቱ ያስመሰከረ ማቴ 7፡21-23

-መኖሩም ሆኖ መሞቱ ለጌታ ክብር ሊሆን እንደተገባ የተረዳ ሮሜ 14፡1-9

መ. ከመንፈስ ቅዱስ ኃይልን የተቀበለ መሆን ይኖርበታል፡፡ 1 ተሰ 1፤5 ሉቃ 24፡47-49 ሐዋ 1፡8 1 ቆሮ 2፡4-5
ሮሜ 15፡18-19

 ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ሊሆነን ከስብከት አገልግሎቱ በፊት የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ተቀበሎ ነበር፡፡ ማቴ 3፡
16 ማር 1፡9-15
ሠ. ቃሉን ለመስበክ ከፍተኛ ፍላጎት ያለዉ
-ለሰዎች መዳንና የህይወት ለዉጥ ሸክም ያለዉ
-ቃሉ የሚሰራዉን ሥራ አዉቆ ለዉጤቱ የሚገገ
2
በታደሰ ሁሪሳ

ረ. ጌታ ኢየሱስንና የሚያገለግላቸዉን ሰዎች የሚወድ


ሰ. የሰባኪነት ግልፅ ጥሪ ያለዉ
-የዳነ ሁሉ ወንጌልን ለመስበክ ተጠርቶአል 1 ጴጥ 2፡9
-ለወንጌል ሰባኪነት በተለየ ፀጋና ጥሪ የተጠሩ አሉ ማር 3፡13-14 ኤፌ 4፡11
ሸ. የእግዚ/ር ቃል እዉቀት ያለዉ
-በግልና በቡድን ቃሉን በማጥናት
-በቤተክርስቲያን ከሌሎች እግር ሥር ተቀምጦ በመማር
-መፅሐፍ ቅዱስ ት/ቤት ገብቶ በመማር
ቀ. የሚያገለግለዉን ህዝብ ዓይነትና የተሰበሰበበትን ዓላማ የሚያዉቅ
-ፆታ፤ዕድሜ ፤ት/ት ደረጀ
-ሠርግ፤ልደት፤ትንሳኤ፤ቀብር፤ሀዘን
5. የስብከት አዘገጃጀትና አይነቶች
1. አዘገጃጀት
ሀ. ለዝግጅት የሚረዱ ነገሮች
1. መፅሐፍ ቅዱስ
2. መንፈሳዊ መፅሐፍት /የተመረጡ የስነ መለኮት መፅሐፍት/
3. የቤተክርስቲያን ታሪኮች የተጻፉባቸዉ መፅሐፍት
4. መዝገበ ቃለት
5. የዓለም ካርታዎች
ለ. የስብከት ዝግጅት ደረጃዎች
1. የማሰስ ደረጃ----ዋናዉን ሀሳብ መምረጥ/ማዋቅ/ማግኘት/--ኃጢአት
2. የማገናዘብ ደረጃ---የምንባቡን ክፍል መምረጥ---ሮሜ 3፡23
3. አቅጣጫ የማስያዝ ደረጃ---የትኩረት አቅጣጫ መወሰን---የሐጢአት ዉጤት
4. የቅንጅት ደረጃ---ስብከትን ማዋቀርና ቅርፅ መስያዝ
5. የማስፋፋት ደረጃ---ስብከቱን በሀሳቦች መሙላት
6. የመፈተን ደረጃ---የተሰራዉን ሥራ ማየት
7. የመተየብ ደረጃ---ቃል በቃል በማስታወሻ ደብተር ላይ መፃፍ

2. የስብከት አይነቶች

1. ርእሳዊ ስብከት

ርዕሳዊ ስብከት ያለመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ ከስብከቱ ማዕከላዊ ሐሳብ መርጦ በመዉሰድ የሚመሰረት ሆኖ ዋና
ዋና ክፍሎቹም እያደጉ የሚሄዱት ማዕከላዊ ሀሳቡን በማጠናከር ነዉ፡፡
-ርዕሱን ከአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አዉጥቶ ዋናዉን ሀሰብ ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሊያዘጋጅ
ይችላል፡፡
ርዕሳዊ ስብከት ያለ ጥቅስ መነሻ ርዕሱን ማዘጋጀት የሚችል ቢሆንም ስብከቱ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ታራቂ
የሆነ እያንዳንዱ ክፍል በእግዚአብሔር ቃል መሰረት የተጠነከረ መሆን ይኖርባታል፡፡
ምሳሌ፤ ፀሎት የማይመለሰዉ ለምንድነዉ;
1. በተሳሳተ ልመና ምክንያት ያዕ 4፡3
2. በልብ ውስጥ ባለ ኃጢአት ምክንያት መዝ 66፡18

3
በታደሰ ሁሪሳ

3. የእግ/ርን ቃል በመጠርጠር ያዕ 1፡6-7


4. በከንቱ ዉዳሴ ምክንያት ማቴ 6፡7
5. ለእግ/ር ቃል ባለመታዘዝ ምሳ 28፡9
 ልናስተዉለዉ የሚገባን ነገር በአንድ ርዕሳዊ ስብከት ጊዜ አንድ ዋና ሀሳብ ብቻ ማንሳት የሚገባዉ መሆኑን
ነዉ፡፡
 መልስ ስላጣ ፀሎት እንጂ ስለ ፀሎት ትርጉም ወይንም ስለ ፀሎት ጥቅም አለነሳንም፡፡
የርዕሳዊ ስብከት ጠንካራ ጎን
1. አንድነትና ወጥነት ያለዉ ነዉ
2. ለዝግጅት ቀላል ነዉ
3. በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መልዕክት ለማቅረብ ይመቻል
4. ዉጤት ላይ ያተኮረ ስለሆነ የሰሚዎችን ስሜት በመቆጣጠር ተፅዕኖ ለመፍጠር ያስችላል፡፡
የርዕሳዊ ስብከት ደካማ ጎን
1.ያለ ዝግጅት ለመስበክ የተገለጠ ነዉ
2. የግል ሀሳብን በሰዎች ላይ ለመጫን የተገለጠ ነዉ
3. ለተነበበዉ የእግ/ር ቃል ታማኝ እንዳይሆኑ ይፈታተነል
4. ሰባኪዉ ክብርን ወደ ራሱ እንዲጎትት ያነሳሳዋል፡፡ የተለየ መገለጥ የመጣለት በማስመሰል ራስን ከሌሎች
አልቆ ለማሳየት ለሚደረግ ክብር ፍለጋ የተገለጠ ይሆናል፡፡

2. አዉደ ምንባባዊ ስብከት

- ዋና ሐሳቡ መዉጣት ያለበት ከተመረጠዉ የምንባብ ክፍል ብቻ ነዉ፡፡

- የአዉደ ምንባባዊ ስብከት ዓላማ ማብራሪያ መስጠት ነዉ፡፡

- የአዉደ ምንባባዊ ስብከት አስተዋዕዖ ቃላቶቹም ሳይቀሩ መወሰን ያለባቸዉ በምንባብ ክፍሉ መሰረት ነዉ፡፡

- አለማችን በምንባብ ክፍሉ ያለዉን እዉነት አንጥረን በማዉጣት ለሰሚዎቹ ግልጽ ማድረግ ነዉ::

የአዉደ ምንባብ ስብከት ምሰሌ፤

የምንባብ ክፍል፤ ዕዝራ 7፡10

ዋና ሀሳብ/ርእስ/ የዕዝራ የልብ ዝግጅት

ዋና ዋና ክፍሎች

1. የእግ/ር ቃል ለማዋቅ ተዘጋጅቶ ነበር

2. ለእግ/ር ቃል ለመታዘዝ ተዘጋጅቶ ነበር

3. የእግ/ር ቃል ለማስተማር ተዘጋጅቶ ነበር

የአዉዳዊ ስብከት ጠንካራ ጎን

1. የመጽሐፍ ቅዱስ መልዕክት ብቻ ማስተላላፉ

4
በታደሰ ሁሪሳ

2. የሰባኪዉን ታማኝነትና ብቃት የሚያሳድግ መሆኑ

3. ሰሚዎችን የተሻለ የእግ/ር ቃል እዉቀት እንዲኖራቸዉ ማድረጉ

4. ሰባኪዉ ትክክለኛዉን የአተረጎጎም ሥርዓት እንዲከተል መርዳቱ

5. ሰሚዎቹ መልዕክቱን ለረዥም ጊዜ እንዲያስታዉሱት መርዳቱ

6. ሰሚዎቹ እግ/ር እየተናገራቸዉ እንደሆነ በቀላሉ ይረዳሉ

7. የምናነበዉና የምንሰብከዉ ቃሉ ስለሆነ ትንቢታዊ መልዕክት ሊተላላፍ መቻሉ

የአዉዳዊ ስብከት ደካማ ጎን

1. ሰባኪዉ በማብራሪያዎቹ ዉስጥ የራሱን ሀሳብ ሊያስገባ ይችላል

2. ሰባኪዉ በቃሉ ዉስጥ የሌላን ትርጉምና ፍልስፍና ሊሰጥ ይችላል

3. ለሰሚዎቹ ጠቀሜታ የማይሰጥ ከንቱ ሐተታ ልያበዛ ይችላል

3. ገላጭ ስብከት

ሀ. የገላጭ ስብከት ትርጉም፤

የሮቢንሰን ትርጉም

መጽሐፍ ቅዱሳዊዉን እዉነት ትክክለኛዉን የአተረገገም ዘዴ ተከትሎ በማዉጣት ማለትም


ታሪካዊዉን፤ሰዋሰዋዊዉንና ሥነ ጽሁፋዊዉን አዉድ አጥንቶ በማዉጣት መጀመሪያ ከራስ ህይወት ጋር በማዛመድ
በመቀጠል ከሰሚዎች ጋር በማዛመድ ማስተላለፍ ነዉ፡፡

ከዚህ ትርጉም ዉስጥ አራት ዋና ዋና ሀሳቦች ይወጣሉ

1. መጽሐፍ ቅዱሳዊ እዉነትን ማስተለላፍ

2. መጽሐፍ ቅዱሳዊዉ እዉነት የሚወጣዉ ከምንሰብከዉ ክፍል ነዉ

3. እዉነቱ መጀመሪያ የሚዛመደዉ ከሰባኪዉ ህይወት ጋር ነዉ

4. ቀጥሎ እዉነቱ ከሰሚዎች ህይወት ጋር መዛመድ አለበት

የራሜሽ ሪቻርድ ትርጉም

የአንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ማዕከላዊ ሀሳብ ትክክለኛ የአተረገገም ስርዓትን ተከትሎ በማግኘትና ማዕከለዊ ሀሳቡን
ከወቅቱ ጋር በማዛመድ ወይንም በማገናዘብ ዉጤታማ በሆነ የሀሳብ ግንኙነት የአማኞችን አእምሮ መረዳት ለማሳደግ
ልባቸዉን ለማቅናትና ባህርያቸዉ እግዚ/ን ወደ መምሰል እንድያድግ መርዳት ነዉ፡፡

ከዚህ ትርጉም ዉስጥ ሰባት ዋና ዋና ሀሳቦች ይወጣሉ

1. የመጽሐፍ ቅዱሳዊዉ ክፍል ማዕከላዊ ሀሳብ

5
በታደሰ ሁሪሳ

የመጀመሪያዉ ፀሐፊ ለመጀመሪያዎቹ ሰሚዎች ሊያስተላልፍ የፈለገዉ ሀሰብ

2.መተርጎም

መፅሐፍ ቅዱሳዊ የአተረገገም ጥበብን ተከትሎ የሚሰራ

3. ከጊዜዉ ጋር ማገናዘብ

የጥንቱን ለአሁን እንዲሆን ማድረግ

4. ግንኙነት

ትክክለኛ አተረገገም ከመጀመሪያዎቹ ፀሐፊና ሰሚዎች ጋር የሚያገናኝ ሲሆን ግንኙነት ግን ከአሁኑ ሰሚዎች ጋር
ያገናኛል

ዉጤታማ ግንኙነት የሚኖረዉ ሰባኪዉ አድማጮቹን በተገቢዉ መንገድ ሲያዉቃቸዉ ነዉ


ባህላቸዉን፤ቐንቐቸዉን፤አስተሳሰባቸዉን፤ዋጋ የሚሰጡትን ነገር

5. አዕምሮን መመገብ ፤እዉቀትን ማካፈል

6. ልብን ማቅናት ፤ዉሳኔን እንዲወስኑ መርዳት

7. በሰሚዎች ፀባይ ላይ ተዕጽኖ ማሳደር

ለ. የገላጭ ስብከት አስፈላጊነት

1. የእግዚ/ን መንጋ በእግዚ/ር ቃል መመገብ

2. ለሰባኪዉም ሆነ ለሰሚዎቹ የጠለቀ የእግዚ/ር ቃል እዉቀት እንዲኖራቸዉ ያደርጋል

3. ምዕመናን የእግዚ/ርን ቃል ለማንበብና ለማጥናት እንድነሳሱ ያደርገል

4. ለስብከታችን ስልጣንን ይጨምራል

5. አንድ ዋና ሀሳብ ብቻ እንድንሰብክ በመርዳት ሰሚዎችን ከግራ መጋባት ይጠብቃል

6. የቃሉ ኃይል ይገልጣል

7. የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ይገልጣል

8. ስብከትን በተለየ ሰዉ ወይንም ቡድን ላይ ያተኮረ እንዲሆን የማድረግ ዝንባሌን በማስወገድ ከአንዳንድ ግለሰቦች
ወቀሳ ያድነናል

ሐ. የገላጭ ስብከት ግብ

የገለጭ ስብከት ግብ ትክክለኛ፤ግልፅና ጠቃሚ ህይወት ሊለዉጥ የሚችል ስብከት መስበክ ነዉ፡

/accurate clear and relevant/

6
በታደሰ ሁሪሳ

1. ትክክለኛ ስብከት

የመጀመሪያዉ ፀሐፊ ማስተላለፍ የፈለገዉን ሀሳብ አግኝቶ እርሱን ማንፀባረቅ;ቃሉን ብቻ መናገር፡፡

2. ግልፅ ስብከት

ሰሚዎቹ ሰባኪዉ ሊል የፈለገዉን በትክክል ማግኛት ሲችሉ

ግልፅነት የሰሚዎችን ደረጀ፤ባህላቸዉን፤አዉደቸዉንና በበቂ ዝግጅት መልዕክተችንን በማወቅ የሚመጣ ነዉ፡፡

3. ጠቃሚ ስብከት

ሰሚዎች ከሉበት ሁኔታና ከችግረቸዉ ጋር የሚዘመድና ምን እርምጀ መዉሰድ እንደለበቸዉ የሚያሰይ ነዉ፡፡

ለተግባራዊ እርምጀ የሚያነሰሳ ነዉ፡፡

ለችግሮችና ለጥያቄዎች መፍቴሔን የሚጠቁም ነዉ፡፡

መ. የገለጭ ስብከት ተግደሮት

የገለጭስብከት ተግደሮት በዋናናት ሁለት ናቸዉ እነርሱም፤

1. ታላቅ የሆነዉን ቅዱስ የሆነዉንና ዉስን የልሆነዉን እግዚ/ርን ዉስን ፤ኃጢአተኛና ዝቅተኛ ከሆነ ከሰዉ ጋር
መገነኘት

2. በጥንቱ የመፅሐፍ ቅዱስ በህልና ቐንቐ ዉስጥ የሚኖረዉን መልዕክት አሁን ከለዉ ዘመናዊ ሰዉ ጋር መገነኘት

 ትክክለኛ መልዕክት ለመግኘት እንቅፈት ከሚሆኑብን ነገሮች መከካል


1. በህል
2. ቐንቐ
3. ጊዜ
4. የቦታ ርቀት/መልከዓ ምድር/
5. የፀሐፊዉ አለመኖር

6. የሰባኪ ዝግጅት
ዉጤታማ ስብከት የመለኮትና የሰባአዊ ጥምረት ዉጤት ነዉ፡፡ሁለቱም ያስፈልገሉ፡፡1 ቆሮ 3፤9

ሀ. ከመድረክ አገልግሎት በፊት

1.ግልፅ የሆነ ዓላማና ግብ መያዝ

2. ከመናገር በፊት ማወቅ

3. ለምያገለግለዉ ህዝብ ሸክም ያለዉ መሆን

4. ምሳሌያዊ ህይወት መኖር

7
በታደሰ ሁሪሳ

5. የመንፈሳዊ ህይወትና የግንኙነትን ጤንነት መጠበቅ

6. አካላዊ ጤንነትና ንፅህናን መጠበቅ

7. በቂ የፀሎትና የቃል ጥናት ዝግጅት ማድረግ

8. ሁል ጊዜ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆን

ለ. በመድረክ አገልግሎት ወቅት

1. በራስ ማንነት ቃሉን ማስተለለፍ

2. በተገቢዉ መንገድ ለብሶ መቅረብ

3. መልዕክቱን ግልፅና ቀለል አድርጎ መስበክ

4. ጊዜን በተገቢዉ መንገድ መጠቀም

5. ለጉባኤዉ አክብሮት በመስጠት መስበክ

6. የምንጠቀማቸዉን ቃላት መርጦ መነገር

ሐ. ከመድረክ አገልግሎት ቦኃላ

1. የህዝቡን ምላሽ መስማት

2. ለሰሚዎች መፀለይ

3. አገልግሎትን መገምገም

4. ለተሻለ አገልግሎት መዘጋጀት

5. በሰበከዉ ቃል ለመኖር ጥረት ማድረግ

6. ስኬት የበለጠ ትሁት እንድያደርገን እንጂ እንዳያስተቢየን መጠንቀቅ

7. የስብከት አወቃቀር ብልሀት


አንድን የስብከት ዓይነትና የመፅሐፍ ቅዱስ የመነሻ የምንባብ ክፍል ከመረጥን ቦኃላ ቅደም ተከተል ያለዉ የአወቃቀር
ሥርዓቱን መከተል ይገባል፡፡አወቃቀሩ ከሚያካትታቸዉ ቅደም ተከተሎች መከከል

1. የንባብ ክፍል

2. ርዕስ

3. መግቢያ/የንባብ ክፍለችንን አዉድ ለማሰየት ጥረት ማድረግ/

4. ዋና ሀሳብ/የንባብ ክፍላችንን መዋቅር ሠርቶ አንድ ዋና ሀሰብ መዉጣት/

5. ማጠቃለያ/ከክፍሉ ስለ ክርስቶስ በመስበክ ከሰሚዎቹህይወት ጋር በማዛመድ ማጠቃለል/


8
በታደሰ ሁሪሳ

ርዕስ

የስብከት የመጀመሪያ ስራ የርዕስ ስያሜ መስጠት ነዉ፡፡ርዕስ ቀጥሎ የሚተነተነዉን ዋና ትምህርት ቀድሞ
የሚያስተዋዉቅና የሚናገር ወይንም መሠረት የሚጥል ነዉ፡፡

ርዕስ ስብከቱን ከማስተዋወቅ፤ለስብከቱ ፍላጎት እንድያሳዩ የአድማጮችን ልብ ከማነሳሳት በተጨማሪ የስብከቱን


ወጥነትና አንድነት ይጠብቃል፡፡

የርዕስ አሰያየምና ባህርያት

1. የአድማጮችን ፍላጎትና ቀልብ የሚስብ ሊሆን ይገባል

2. ግልፅና ይዘቱን አመልካች መሆን ይኖርበታል፡፡

3. የሚያነሳሳ፤እዉነተኛነት ያለዉ፤ታማኝነትን ማዕከል ያደረገ ሊሆን ይገባል፡፡

መግቢያ

በስብከት ዉበት ዉስጥ አስቀድሞ የተመልካችን ትኩረት ለመሳብና አስተማማኝ ሁኔታ ለመፍጠር የሚረዳ እንዲሁም
የምንባብ ክፍሉን፤ርዕሱን፤መንደርደሪያዉን እና ዋና ክፍሉን ቀድሞ ማስተዋወቅ የሚቻልበት አንድ ክፍል ነዉ፡፡

የመግቢያ ተግባራት፤

1. የሰሚዎችን ትኩረት መሳብ

2. በስብከቱ ርዕስና በምንባብ ክፍሉ መካከል ያለዉን ግንኙነት በጥሩ ሁኔታ መመስረት

3. የስብከቱን ዋና ክፍል ለማስተዋወቅ ይጠቅማል

የመግቢያ ልዩ ባህርያት

1. ተስማሚና በትክክል የተዘጋጀ ሊሆን ይገባል

2. ያልተንዛዛና ቀጥተኛ ዓለማ ያለዉ ሊሆን ይገባል

3. በጣም ቀላልና የማይደጋገም ሊሆን ይገባል

4. በእዉነተ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት

5. በአዎንታዊና በተረጋጋ ስሜት መቅረብ ይኖርበታል

ማጠቃለያ

ስብከትን ወደ ፍፃሜ ለማምጣት የሚያስችል ወሣኝና የስብከት የመጨረሻ ክፍል ነዉ፡፡ያለ መደምደሚያ የሚቀርብ
ስብከት ያለ ጣሪያ ክዳን እንደሚቀር ቤት ነዉ፡፡ማጠቃለያ የስብከት ማዕከላዊ ሀሰብ ግቡን እንድመታ የሚረዳና አድማጭ
ወደ መታዘዝ እንዲመጡ የሚጋብዝ ነዉ፡፡

ማጠቃለያ በሚሰጥበት ጊዜ

9
በታደሰ ሁሪሳ

1. የስብከቱን ማዕከላዊ ነጥቦች በአጭሩ በግልጥ ማስቀመጥ

2. ሰዎች የሰሙትን የእግዚአብሔርን ቃል በህይወታቸዉ ተግባራዊ ለማድረግ መታዘዝ እንዲጀምሩ አቅጣጫ ማሳየት

3. አጠቃላይ የስብከቱን ዓላማ በአንድ አረፍተነገር ማስቀመጥና መናገር

መደምደሚያ ስንሰጥ ልናደርግ የሚገባን ጥንቃቄ

1. ከድንገተኛ አጨረራስ መጠበቅ

2. መደምደሚያዉን ተናግሮ ሳይጨርሱ መጽሐፍ ቅዱስን ማጣጠፍና ማስተዋሻ መሰብሰብ

3. ማጠቃለያ ሰጥተዉ ከጨረሱ ቦኃላ ሌላ ወሬ መጀመር

8. የስብከት አቀራረብ
1. ግልፅ የሆነ የቐንቐ አጠቃቀም

2. አካለዊ ሁኔታ

-አቐቐም

-እንቅስቃሴ /ተገትሮ አለመቆም ፤ መድረክ ላይ አለመሮጥ/

-አለባበስ አግባብነት ያለዉና መድረኩን የሚመጥን አለባበስ መጠቀም

-የድምፅ አጠቃቀም በጣም አለመጮህ በጣም ዝቅተኛ ድምፅ አለመጠቀም ድንገት አለመጮህ

-የዓይን እይታ አንድ ቦታ ለይ አለመቆየት ሜዳ ሜዳ/ጣሪያ አለማየት

3. እየሰበኩ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር መሆን ወይንም መነጋገር

4. ስብከትን በፅሁፍ ይዞ መቅረብ

5. አግባብነት ያላቸዉና ግልፅ ትርጉም ያላቸዉን ምሳሌዎች ብቻ መጠቀም

6. ለሰሚዎች አክብሮትን በመስጠት መቅረብ

7. በማጠቃለያ ሰዎችን ለተግባራዊ ዉሳኔ መነሳሳትና ማስወሰን

8. ከድንገተኛ አጨራረስ መጠበቅ

10
በታደሰ ሁሪሳ

11

You might also like