You are on page 1of 18

በታደሰ ሁሪሳ

መንፈሰዊ መሪነት

በመጋቢ ታደሰ ሁሪሰ

ሀዋሰ 2008 ዓ/ም

1
በታደሰ ሁሪሳ

ማዉጫ

1.የመሪነት ትርጉም
2. መንፈሰዊ መሪ

3. የመሪ የስልጣን ምንጭ

4. የመሪዎችተግባራት

5. የመንፈሰዊ መሪ መልክ

6. መሪ ከየት ይገኛል

7. የእዉነተኛ መሪ መለየዎች

8. የመሪ ተግደሮቶች

9. መሪዎች የሚሰሩአቸዉ ስህተቶች

10. መሪነት የሚያስከፍለዉ ዋጋ

11. መሪ ሊያድግበቸዉ የሚገበቸዉ አቅጠጨዎች

12. መንፈሰዊ መሪነት በቡልይ ኪደን

13. አድስ ኪደናዊ የመሪ ስየሜዎች

14. የአመራር ዘይቤዎች

15. መሪዎች በመሪነት አገልግሎታቸዉ ዉጤታማ ለመሆን

1. የመሪነት ትርጉም ፡- የተለያዩ ፀሐፊት የሰጡት ትርጉም

2
በታደሰ ሁሪሳ

-- መሪ ማለት ሰዎችን ለአንድ የጋራ ዓላማ የማስተባበር ችሎታና ቆራጥነትያለው በአባላቱ መካከል
የመተማመንና የተስፋን ስሜት የውጤትና የትጋትን መንፈስ መፍጠር የሚችል ነው፡፡

 የጋራ ዓለማ
 የማስተባበር ችሎታ
 ቆራጥነት
 በአበለቱ መከከል የመተማመንና የተስፈን ስሜት መፍጠር
 የዉጤታማነትንና የትጋትን መንፈስ መፍጠር

-- መሪ ማለት መንገዱንና አቅጣጫውን የሚያውቅና ወደግራም ወደቀኝም የማይወናበድ ወደፊት ቀጥብሎ


የሚሄድና ሌሎችንም በዚያ አቅጣጫ የሚስብ ነው፡፡

---መሪ ሰዎች ሊሰሩትና ሊያደርጉት የሚተክተቸውን ነገር እንዲወዱትና እንዲሰሩት የሚያደርግ ነው ፡፡ ጄ


ኦስዋልድ ሰንደርስ

----- መሪነት ስራዎች በሰዎች እንዲከናወኑ የሚያደርግ ኪነጥበባዊ ችሎታ ነው፡፡

--- መሪነት ሀሳቦችን ሰዎችን ገንዘብን ጊዜያትንና እምነትንም በመገናኘት የተተለመውን

ሥራ ከግብ የማድረስ ችሎታ ነው ፡፡

---- መሪነት በሰዎች ላይ በጎ ተፅዕኖ ማሳደርና የሌሎችን ዝንባሌ እርሱ ወደሚያምንበት አቅጣጫ መለወጥ
ነው ፡፡

---- መሪነት ሰዎች የእርሱን ሀሳብ ተቀብለው የሚሰጣቸውን ትዕዛዝ ለመፈፀም ዝግጁ እንዲሆኑ እምነት
የሚጣልበት ሆኖ የመገኘት ብቃት ነው፡፡ ቺተር ዊቸርክ

መሪነት

1. ዲሲፕሊን ነው

 በመጠን መኖር
 ህይወትን በጥንቃቄና በዕቅድ መምራት መቼ ምን እንደምንሰራ አስቀድሞ ማወቅ
 ዝርክርክ የሆነ ህይወት ለመሪነት አይበጅም ፡፡

2. ራዕይ ነው መሪ ከህዝቡ ቀድሞ ማየት መቻል አለበት --- እግ/ር የሚያየውን ነገር እግ/ር በሚያይበት
እይታ ማየትና ለእግ/ር ክብርና ለሰዎች ጥቅም ማዋል ነው ፡፡ራዕይ ያለዉ መሪ ይጨናቃል ያስበል ያያል
ያምናል ያሰምናል ያቅደል ያስተበብረል ወደአየዉ ግብ ይደርሰል

--- ራዕይ ያለው መሪ / እይታ / አዳዲስ እርምጃዎችን መውሰድ አይፈራም

3. ጥበብ ነው

--- ጥበብ እውቀትን በተገቢው መንገድ መጠቀም ነው

--- ጥበብ ሚዛናዊ እንዲንሆን ያደርገናል

3
በታደሰ ሁሪሳ

4. ውሳኔ የመስጠት ችሎታ ነው

--- መሪ ለውሳኔ የሚቸኩልም ውሳኔ ለመወሰን የሚፈራም መሆን የለበትም ነገር

ግን በትክክለኛ ጉዳይ ላይ በትክክለኛ ጊዜ ውሳኔ መስጠት መቻል ይኖርበታል ፡፡

5. ድፍረት ነው

--- ድፍረት አላማንና ለምን እንደምንኖር ከማወቅ ይመነጫል

---- ጳውሎስ ፤ለሞትም ቢሆን በድፍረት ወደ ፊት ሄዶአል

--- ነህምያ፤ የማይቻል የሚመስል ጉደይ ይቻለል ብሎ አምኖ ሄዶአል

6. ትህትና ነው

መሪነት ድፍረት ቢሆንም ትዕቢተኝነት ግን አይደለም

መሪ በእግ/ርም በሰውም ፊት ትሁት መሆን አለበት

---- እግ/ር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሁታን ግን ፀጋዉን ይሰጠል

---- ሙሴ ትሁት ሰው ነበር

---- ኢየሱስም ትሁት ነበር

7. ተግባብነት ነው

--- በቀላሉ ከሁሉም አይነት ሰዎች ጋር መግባባት የመቻል ችሎታ ነው

--- መግባባት ካልቻለ ሰዎችን ማስከተልና ለሥራ ማሳተፍ ይቸግረዋል ፡፡

8. ትዕግስት ነው

ትዕግስት ለሰዎችም ለነገሮችም ጊዜ መስጠት መቻል ነው

---- ቶሎ አለመቆጣት

---- ቶሎ ተስፋ አለመቁረጥ

---- ትዕግስተኛ ሰው ነገ የተሸለ ቀን እንደሆነ ተስፋ ያደርጋል ሰዎችም ሆኑ ነገሮች

ነገ ወደተሸለ ነገር ልለወጡ እንደሚችሉ ተስፋ ያደርጋል ፡፡

9. የመነሣሣትና የመነቃቃት ችሎታ ነው ነህ 2፤17-18

10. መቆጣትም ነው

መሪ አስፈላጊና እግ/ርን በሚያስቆጣ ነገር ላይ መቆጣት መቻል አለበት ነገር ግን

4
በታደሰ ሁሪሳ

ቦታን ጊዜንና ሁኔታን ማስተዋል አለበት


--- ቁጣው የራሱን ክብርና ጥቅም ለማስጠበቅ መሆን የለበትም የሰዉ ቁጣ የእግ/ርን ጽድቅ አይሰረምና፡፡
11. ተፅዕኖ ፈጠርነት ነዉ

2. መንፈሳዊ መሪ

1. በእግ/ር የተጠራ ነው
ዘፀ 3፤ ሙሴ ሐዋ 9፤ ጳውሎስ ነህምያ ኢያሱ
2. በእግ/ር የተላከ ነው
3. የሚሰራውን ሥራ ከእግ/ር የተቀበለ ነው
4. የባለስልጣንነት ሳይሆን የአገልጋይነት ባህርይ ያለው ነው
ማር 10፡42/ ማቴ 20፡25---28
5. በምሳሌያዊ ህይወቱ ሁልጊዜ የሚቀድም ነው
1 ጢሞ 3፡1—7
 ለመንፈሳዊ መሪ ማንነቱ /ባህርይው/ ወሳኝ ነው ፡፡

አዎንታዊ እይታ አሉታዊ እይታ

--- የአንዲት ሚስት ባል --- የማይሰክር


--- ልከኛ --- የማይጨቀጨቅ
--- ራሱን የሚገዛ --- የማይከራከር
--- እንደሚገባው የሚሰራ -- ገንዘብን የማይወድ
--- እንግዳ ተቀባይ -- አድስ ክርስቲያን ያልሆነ
---ለማስታረቅ የሚበቃ
--- ገር የሆነ
--- ልጆችን በጭምትነት እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር
6. ብስለትና ብቃት ያለው ነው
--- በማስተማር ብቃቱ የላቀ ሆኖ መገኘት ይገባዋል
--- በማስተዋልና በሁሉ አቀፍ እውቀቱም ተሸሎ መገኘት ይጠበቅበታል
--- የሀሰትን ትምህርትን የመቃወም / በእውቀት / ብቃት ያስፈልገዋል
--- 1 ጢሞ 1፡3—4 1 ጢሞ 4፡6 11—16 ቲቶ 1፡5 1 ጢሞ 5፡17
7. መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ የሆነ ሰው ነው ፡፡

5
በታደሰ ሁሪሳ

 መንፈሳዊ መሪነት የኢየሱስን ምሳሌነት መከተል ነው እርሱ መልካም እረኛ ስለነበረ


ነፍሱን ስለበጎቹ በመስጠት መራቸው ጠበቃቸው አስመራቸው
መሪነት-- ገንዘብን፣ ጊዜን፣እውቀትን፣ በደስታ ለሌሎች መስጠት ነው
8. በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚደግፍ ነው
9. ተጠየቅነቱ ለእግ/ር ነው
10. የአገልግሎቱ ትኩረትና ግብ የእግ/ር አጀንዳ ነው
 የእግ/ር ክብር፣የሰዎች ማዳንና መታነፅ ለይ ትኩረት ያደርጋል

3. የመሪ የስልጣን ምንጭ


ሀ. መንፈሳዊ ያልሆኑ መሪዎች የስልጣን ምንጫቸው
1.ማንነት
2. ሹመት
3. ትምህርት
ለ. የመንፈሳዊ መሪ የስልጣን ምንጭ
 እውነተኛ ጥሪ
 የእግ/ር አብሮነት በእግ/ር መጠራታቸው ፣በእግ/ር መለካቸውና የእግ/ርን ሥራ
መሥራታቸው እግ/ር ከእነርሱ ጋር እንደሆነ ያደርገዋል ፡፡ የገባውን “ከእናንተ ጋር
እሆናለሁ “ ቃል ያከብርላቸዋል
ዘፀ 3፡12 ኢያሱ 1፡1—9 ዘፍ 12፡1—4 ማቴ 28፡18—20
 ጥሪዉን ለማስፈፅም የተሰጠዉ የእግዚአብሄር ፀጋ

4. የመሪዎች ተግባር
1. ህዝብን ካለበት ሥፍራ እግ/ር ወደሚፈልግበት ሥፍራ መምራት
2. በሰዎች ላይ አዎታዊ ተፅዕኖ በመፍጠር መምራት / Influence /
በአላማችን የተነሱ መሪዎች ከሌለዉ ህዝብ የለየቸዉ ቁልፍ ነገር በህይወተቸዉ፤ በአከሄደቸዉ ፣
በንግግራቸው እና በሥራቸው በተከታዮቻቸው ዘንድ ያመጡት ተፅዕኖ ነው፡፡
3. ውሳኔ በመስጠት መምራት / Decision making /
መሪ ተገቢውን ውሳኔ ተገቢውን ሥፍራ ሰዓትና ሁኔታ መሰጠት ይኖርበታል ፡፡
4. ችግሮችን እየፈቱ መምራት / problem solving /
-- መሪ ከግጭትና ከአለመግባባቶች ነፃ ልሆን አይችልም ስለዚህ ሁል ጊዜ

6
በታደሰ ሁሪሳ

በጥበብ በማስተዋልና በትዕግስት የሚነሡ አለመግባባቶችን መፍታት ይጠበቅበታል


5. የህብረትን አስተዋዕኦ በመጠቀም መምራት
--- ሁሉንም አይነት ሰውና ፀጋ / ክህሎት / መጠቀም አለበት
6. ሃላፍነትን በማሰራጨትና በማስተላለፍ መምራት
--- ከተገቢው በላይ የሆነ የሥራ ሃላፊነት መደራረብ ውጤታማነትን ይቀንሣል ጤናን ይጎዳል ፡፡
--- መሪ ሃላፊነትን ለሌሎች መስጠት ሌሎችን ማመን አለበት
--- ተተኪን በማፍራት ላይ ጊዜ ሰጥቶ መስራት አለበት ---
7. የጋራ ዕቅድ ማዘጋጀት ማስፈፀምና መገምገም
key leadership function - planning --Initiating--
controlling--- supporting --Informing---Evaluating
8. የአሠራር ሥርዓትን ማዘጋጀት
9. ለለውጥና ለዕድገት ምክንያት መሆን
10. በቃልና በኑሮ ምሳሌ ሆኖ መምራት

5. የመንፈሳዊ መሪ መልክ ማር 10፤35 –45 ማቴ 20፡ 20---28


መሪዎች ሁለት መልክ አላቸው
1. ተገልጋይ መሪነት
--- በሌሎች ለመጠቀም መሪ መሆን
--- ሌሎችን ለመግዛት መሪ መሆን
--- በሌሎች ላይ ለመሰልጠንና ለመግዘት
--- በሌሎች ለማገልገል መሪ መሆን
2. አገልጋይ መሪነት
--- ሌሎች ለማገልገል መፈለግ
--- ነፍሱን ለሌሎች እስከመስጠት መፍቀድ
--- በህይወት ምሳሌነትና በመሥዋዕትነት ለመገልገል መፍቀድ

7
በታደሰ ሁሪሳ

--- ባሪያ ሆኖ ለማገልገል ማዘጋጀት

6. መሪ ከየት ይገኛል ;
1. ይወለዳል ---በተፈጥሮ
2. ይጠራል --- በእግ/ር
3. ይሠራል --- በትምህርት፤ በሥራና በሌሎች
4. ይሾማል --- በሌላ ባለስልጣን

7. የእውነተኛ መሪ መለያዎች
1. እረፍት የሌለው / Restless /
--- የእግ/ር ሀሰብ እስኪፈፀም ድረስ ማረፍ አይሆንለትም
--- ለመሄድ ፣ ለማድረስ፣ ለማደግ ፣ ለለውጥ ጉጉቱ አይቋረጥም
2. ጨለምተኛ ያልሆነ / 0ptimism—optimistic /
ሮሜ 8፡28,32 ዕብ 6፡9
---- ነገሮች በእግ/ር መልካም ፍፃሜ እንደሚኖራቸው የሚያምን
----ነገ የተሸለ ቀን እንደሚሆን የሚያምን
3. ራሱን የሚገዛ / self control /
--አንደበቱን
--ስሜቱን
ገላ 5፡22 1 ቆሮ 6፡12

8
በታደሰ ሁሪሳ

4. በኃይል ለመሥራት የተነቃቃ / Energetic /


--- ራሱን የማይቆጥብ
--- ሰነፍ ያልሆነ ኤፌ 5፡16 ዮሐ 9፡9 ገላ 6፡9 1 ቆሮ 15፡10, 58
5. ነቀፋን የሚታገስ / Thick skin /
-- ለምን ተነካሁ የማይል --ለምን ስሜ ተነሳ የማይል
2 ቆሮ 4፡8,16 ገላ 1፡10
6. አርቆ አሳብ / A hard thinker /
7. በግልፅነት መናገር የሚችል / Articulate /
8. ለማስተማር የሚበቃ / Able to Teach / 1 ጢሞ 3፡2
9. በመልካም በህርይ የተመሰከረለት
10. ጥበብን የተሞላ ቆላ 4፡5—6 ምሳ 25፡11
11. የማስተባበሪና የማስተደደር ብቃት ያለው
--ሰዎችን
--ገንዘብን
--ንብራትን
--ፀጋዎችን
12. ፅናት ያለው / perseverant /
ማቴ 24፡13 ገላ 6፡9
13. የቤተሰቡ መሪ የሆነ 1 ጢሞ 3፡4-5
14. በአምላኩ ማረፍን የሚያውቅ/Rest full/
መዝ 127 1፡2 ማር 6፡31 ዘፀ 20፡9---10
15. በልክ መኖርን የሚያውቅ --- በምኞት የማይነዳ ከአቅሙ በላይ መኖር የማይፈልግ
16. የጊዜ አጠቃቀምን የሚያውቅ
--- በዕቅድ የሚሠራ
--- የመጣ ሁሉ ይዞት የማይሄድ

9
በታደሰ ሁሪሳ

8. የመሪ ተግዳሮት
1. ዝሙት
2. ገንዘብ
3. ዝና--ትዕቢት
4. አንባገነንነት --- ሁሉን መቆጣጠሪ መፈለግ / ዋና መሪ የመሆን ፍለጎት/
5. የበታችንት ስሜት

9. መሪዎች የሚሠሩአቸው ስህተቶች


 ትላልቅ መሪዎች ትላልቅ ስህተቶችን ይሠራሉ፡፡ወ/ዊ እንደለ/ዶ/ር/
1. የሚመሩትን ህዝብ ወደታች የማየት ሁኔታ
/ ምንም እንደማየውቅ / ምንም ማድረግ እንደማይቻል መቁጠር /
--- አንባገነንነት በሀገራችን የተለመደ የመሪ በህርይ የሆነበት ምክንያት
-- በህላችን ያስተማረን መሆኑ
-- በጠም ቀላል መሆኑ / ምንም ዋጋ አለመስከፈሉ /
-- የሰው ውድቀት ውጤት መሆኑ

10
በታደሰ ሁሪሳ

2. ሰዎችን ከመስራት ይልቅ ለወረቀት ሥራ ቅድሚያ መስጠት


--- የአገልግሎታችን ግቡ ክርስቶስን የሚመስል ሰው ማዘገጀት መሆኑን መርሳት
3. ለሌሎች አገልጋዮች እውቅና አለመስጠት
--- ሰዎች ለሠሩት ነገር ምስጋናና እውቅና ይፈልጋሉ
4. በውሳኔ አሰጣጥ ላይ አግባብ ያልሆነ ተፅዕኖ ማሰየት
5. አግባብነት ያለው የሥራ ክፍፍል አለማድረግ
6. የግንኙነት / ተግባቦት / ቀውስ
--- ሰዎች ማወቅ የሚገባቸውን ነገር በጊዜው አለማስወቅ
7. ስኬትን የግል ጥረት ውጤት አድርጎ መቁጠርና መግለፅ
8. አለመሳካትን በሰዎች ላይ ማሳበብ
--- የራስን ጥፋት / ጉድለት / ድካም / አለማመን / አለመቀበል

10. መሪነት የሚያስከፍለዉ ዋጋ


1. ራስን መስዋዕት ማድረግ ብዙ ነገርን ማጣት
2. ብቸኝነት 2 ጢሞ 1፡15
3. ሥራው የሚያመጣው ድካም
4. ነቀፋና ትችት
5. መናቅና መገለል

11. መሪ ሊያድግባቸው የሚገባ አቅጣጫዎች 1 ጢሞ 4፡15


1. በባህሪይ --- ድካምንና ጉድለትን እያረሙ ማደግ
--- ማንነት
--- ሥነምግባር
2. በችሎታ --- የሥራችን አፈፃፀም ማሳደግ
--- ብቃትን
--- ክህሎትን
--- ጤናማ ድፍረትን / confidence / ማሰደግ
3. በእውቀት / መረዳት /

11
በታደሰ ሁሪሳ

--- በትምህረት / Formal and informal Education /


--- የእይታ
--- የአመለካከት
4. በግንኙነት
--ከሥራ ባልደረባ ፣ ከበላይ ሃላፊዎች እኛ ከሚነዛቸው ሰዎች ጋር ከህዝብ
ጋር ጤናማ ተግባቦትን መፍጠር
-- ከሰው ሁሉ ጋር በተቻለ መጠን ወዳጅነትን መፍጠር

12. መንፈሳዊ መሪነት በብሉይ ኪዳን


በቡልይ ኪዳን ዘመን ሦሥት የአመራር አይነቶች በዋናነት ተይተዋል
1. መለኮታዊ አገዛዝ / Theocracy / ዘፀአት
--- ቀጥተኛ የእግ/ር ጥሪ የሚታይበትና መሪ በእግ/ር የሚመረጥበት አመራር ነው ፡፡
ዋና መሪው እግ/ር ነው ድርጊቶቹ በእግ/ር የሚወሰኑና የሚደረጉ ናቸው
 ሙሴ ፣ እያሱ ፣ዳዊት
--- ሙሴ በእግ/ር እየተመራ እንደ ፖለቲካ መሪ ፣ እንደ ነፃ አውጪ
እና እንደመካከለኛ /ከህን/ መንፈሳዊ መሪ ሆኖ አገልግሎ ነበር ፡፡
/ ነብይነት ፣ ክህነትና ንጉስነት / ፈራጅነት //
--- እግ/ር ራዕይ ሰጪና የሥራው ባለቤት ሆኖ ሙሴ ደግሞ ረዕይ አስፈፅሞ አገልጋይ ሆኖ ይሠራ ነበር
2. መሳፍንታዊ አገዛዝ / Anarchy / መሳፍንት
--- የነገድ መሪዎች ሆነው ጠላት በሚመጣበት ጊዜ ሀገሩን ሁሉ እየመሩ ጠላትን ይዋጋል
 የጦር መሪና መንፈሳዊ መሪም ሆነው አገልግለዋል
--- እስከ ሳሙኤል መነሳት የዘለቀ ሲሆን ሳሙኤል በመሳፍታዊ አገዛዝና በዘውደው አገዛዝ መካከል
ድልድይ ነበር
3. ዘውዳዊ አገዛዝ / Monarchy / ሳሙኤል ፣ነገስትና፣ ዜና/

12
በታደሰ ሁሪሳ

 በህዝብ ጥያቄ የተጀመረ ሲሆን የመጀመሪያው ንጉስ ሳኦል ነበር ነገር ግን አልቀጠለም
በሳኦል አለመታዘዝ ተከላከለና እግ/ር ንጉስ ዳዊትን ሾመላቸው ከዚያ በኃላ ንግስና
በዘር የሚወረስ ሆኖ
 በዘውዳዊ አገዛዝ ጊዜና በመሳፍታዊ የአገዛዝ ጊዜ የነበረው የነገድ ግለኝነት ቀርቶ
እስራኤል እንደሀገር ቆማ ፡፡የሰለሞን ዘመን አብቅቶ እስራኤል ለሁለት
እስከተከፈልበት ጊዜ ድረስ

13. አዲስ ኪዳናዊ የመሪ ስያሜዎች


--- በብሉይም በአዲስ ኪዳንም መሪን ለህዝቡ የሚሰጥ ህዝቡን የሚመራ እግዚአብሔር ነው፡፡
--- በአድስ ኪዳን ጌታ ኢየሱስ ከአገልግሎት ትኩረቶቹ መካከል አንዱ መሪዎችን መጥራት ፣ ማሰልጠንና
መሾም ነበር፡፡
የአድስ ኪዳን መሪዎች ኤፌ 4፡11
1. ሐዋርያት
--- ከሙሉ ስልጣን ጋር የተላከ መልዕክተኛ ማለት ነው፡፡
 ኢየሱስ ሐዋርያ ተብሎአል በአባቱ ተልኮ ወደ ዓለም ስለመጣ
 አሥራ ሁለቱ ደቀመዘሙርት ሐዋርያት ተብለዋል -- የበጉ ሐዋርያት
 ማቲያስ ሐዋርያ ተብሎአል
 ጳውሎስ ሐዋርያው ተብሎአል
 በርናባስ ጢሞቴዎስ ፣ ሌሎችም ሐዋርያ ተብለዋል
--- ወንጌልን መስበክ ፣ አብያተክርስቲያናትን መትከልና ማደራጀት፣ ድንቅና ታአምራትን በማድረግ
የእግ/ርን መንግስት መስፋፋት ዋና አገልግሎታቸውን ነበር፡፡
2. ነብያት ሐዋ 13፡1—3
--- ነብያት የእግ/ር አፍ ናቸው ያለፈውን አሁን ያለውንና የሚመጣውን ከእነርሱ ሰብአዊ እውቀት ውጭ
በሆነ እውቀት የሚናገሩ ናቸው
--- የአድስ ኪዳን ነብያት በአመራሩና በማስተማሩ አገልግሎትም ድርሻ ነበረቸው
ሐዋ 11፤28,21፤10 አጋቦስ
ሐዋ 15፡32 ይሁዳና ሲላስ
ሐዋ 21፡19,13,19 የፊልጶስ ልጆች

13
በታደሰ ሁሪሳ

3. እረኛ
እረኛ ፣ መጋቢ፣ አጳስቆጳስ ፣ ጳጳስ፣ ሽማግሌ ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ለአንድ አገልግሎት የተሰጡ
ስያሜዎች ናቸው
--የመምራት፣ የማስተማርና የማስተዳደርን ሥራ በዋናነት ይሠራሉ

እረኛ ይጠብቃል
ይመግባል ያስተዳድራል
ያሰማራል
4. የወንጌል ሰባኪዎች ---ወንጌላዊያን
---- በዋናነት የደህንነት ወንጌል ለማያምኑ ሰዎች በመሰበክ ያመኑትን ደቀመዝሙር በማድረግ
የሚያገለግሉ ናቸው
ሐዋ 8፡5,21,፡8—9 2 ጢሞ 1፤10-11
5. አስተማሪዎች
--- መሠረታዊ የሆነ የእምነት ዶክትርኖችን ከመፅሐፍ ቅዱስ ጋር
በመገነዘብ አብራርተው የሚያስተምሩ ናቸው
---- ሕዝቡን በአስተምህሮ ከሀሰት ት/ት ይጠብቃሉ
---በመፅሐፍ ቅዱስ ት/ት ቤቶች ያስተምራሉ
---እዉቀትን ማስጨበጥ ለይ ያተኩረሉ

14
በታደሰ ሁሪሳ

14. የአመራር ዘይቤዎች


በአለም ላይ በጣም ብዙ አይነት የአመራር ዘይቤዎች አሉ አሁን ለእኛ ትምህርት
በአራቱ ላይ ብቻ ትኩረት እናደርጋለን 1.Transactional
1. ቢሮክረት 2.Transformational
--- ህግንና ሥርዓትን የሚያስጠብቁ የመንግስት 3.charismatic
ባለስልጣናትን የያዘ መዋቅር ማለት ነው 4.Task oriented
--- ጠባብ ና ቀጥ ያለ አመለካከትን ተከትለው 5.people oriented
የሚሠሩ ሰዎች ያመለክታል 6. servant
 መለያ በህርያቸው 7. Autocratic
---ሰው ሁሉ የወጣውን ደንብና ህግ ተከትሎ 8. Democratic
መሥራት አለበት ብለው የምናሉ 9. Bureaucratic
--- ማንኛውንም ጉደይ ከጊዜ ጋር ከመገናዘብ ይልቅ ካለው 10. Laissez-faire
ህግና መማሪያ ጋር መገናዘብን ይመርጣሉ
--- አዳድስ ሀሳቦችን ከመቀበልና ከማስተናገድ ይልቅ የወጣው ሕግና ደንብ
ማስከበር ይመርጣሉ
2. አውቶክራት
--- አንድ ወጥ የሆነ አገዛዝ ማለት ነው
--- አንድ ሰው ፍፁም የበላይነት ሥልጣን ኖሮት ብቻውን መወሰ የሚችልበት የአገዛዝ ሥርዓት ነው
 መለያ በህርያቸው
--- ከሰው ይልቅ ለሥራው ክብደት ይሠጣሉ
--- ጠንካራ አቀም ያላቸው በሚወስኑአቸው ውሳኔዎች የሚተማመኑ ናቸው
--- ለሁኔታዎች ፈጣን የሆኑ እርምጃ ይወስዱ ሥራን አየጓትቱም

15
በታደሰ ሁሪሳ

--- የተሻለ አመራጭ ራሱ ካገኘና ካመነበት ሃሳቡን መለወጥ አይቸገርም


--- በሥራው ውጤት ማርካት ይፈልጋል
--- ለብዙሃኑ ሀሳብ ወይም ፍላጎት በሩ ዝግ ነው ፡፤
3. ዲሞክራት
--- ሕዝባዊ አገዛዝ ማለት
--- ሕዝብ የበላይነት ኖሮት ህዝብ በወከላቸውና በመረጣቸው የመተዳደር
ሥርዓት አቀንቃኞች ናቸው
 መለያ ባህርያት
--- ከሥራ ይልቅ ለሰዎች ክብደት ይሠጣሉ
---- ሁኔታዎችን ለውሳኔ በመመቻቸት ሌሎች በውሳኔ እንዲሳተፉ ያደርጋሉ
--- ብዙ ሥራዎች ውሳኔ በጊዜ ስለማይሰጣቸው ይወዘፋሉ ህዝብም ይመራራል
4. ሌይስዝ ፌር ---- ነፃ አገዛዝ ማለት ነው
--- ሰዎች ደስ እንዳላቸው መሥራት እንዲችሉ የሚፈቅድ የአገዛዝ ፍልስፍና ነው
 መለያ በህርያቸው
---- በሥሩ ያሉ መሪዎች በመሰላቸው መንገድ እንዲሰሩ ይፈቅዳሉ
--- መማሪያ ሲሰጥና የሥራ ቁጥጥር ሲያደርግ አይታይም
--- እንዲህ አይነት ዘይቤ በሚታመንበት ስፍራ ድርጅታዊ መዋቅር ወይም
መሪ መኖሩ ጎልቶ አይታይም
--- ሥራው መሠረቱ ሳይሆን ሰው ሁሉ ደስተኛ መሆኑን ትኩረት ይሰጣሉ

16
በታደሰ ሁሪሳ

15. መሪዎች በመሪነት አገልግሎታቸው ውጤታማ ለመሆን ማር 1፡35-45


1. ለእግዚአብሔር መገኛት
--- በፀሎት
---በቃል
----በመተዘዝ
2. ለሰዎች መገኘት
---- በችግር ጊዜ ----እውቀት/ ምክር ---በብቻኝነታቸው ጊዜ
--- በደስታ ጊዜ ---- ገንዘብ --- በኃጢያት በወደቁ ጊዜ
--- ነገር በተበላሸባቸው ጊዜ
3. ሚዛናዊነት
--- በሰዎች መካከል
---- በአገልግሎቶች መካከል
---- በሀሳቦች መካከል
4. ራስን ማዋቅና ራስን ለማሳደግ ጥረት ማድረግ
---- ብርቱና ደካማ ጎንን ማወቅ
--- መሥራት የሚንችለውንና የማንችለውን ነገር ማወቅ
5. በፍቅር ህይወት መኖር
--- ለእግዚአብሔር
--- ለሰዎች ለማይቀበሉን / ለሚቀየሙን
ክፉ ለሚያስቡብንና ለሚያደርጉብን
---ለአገልግሎት
6. ሥራችንን / አገልግሎታችንን / በእውቀት ተዘጋጅተን መሥራት
--- ስንፀልይ

17
በታደሰ ሁሪሳ

--- ስንሰብክ
--- ስንመክር
7. ጠቃሚ ሆኖ መገኘት

18

You might also like