You are on page 1of 23

በታደሰ ሁሪሳ

የደቀመዝሙርነት

ትምህርት ማስተማሪያ

በመጋቢ ታደሰ ሁሪሳ

መስከረም 2002

ማውጫ

1
በታደሰ ሁሪሳ

1. በደስታ እግ/ርን ማምለክ

1.አምልኮ ምንድነው

2. አምልኮ እንዴት ይቀርባል;

3. አምልኮ መቼና የት ይቀርባል;

4. የአምልኮ ውጤትና ጥንቃቄው ምንድነው;

II. በፀሎት ከእግ/ር ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት ማድረግ

1. ፀሎት ምንድነው

2. ፀሎታችን ምን ምን ልያካትት ይገባዋል;

3. የፀሎት ምክንያቶች ምንድናቸው;

4. የፀሎት መንገድና መልሱ

5. የፀሎት አይነቶች

6. ለፀሎት በእግ/ር ፊት እንዴት እንቅረብ;

7. ፀሎት መቼና የት ማድረግ አለብን;

8. የፀሎት መመሪያና ውጤት

9. ፆምና ፀሎት

1. የፆም ትርጉም

2. የፆም አላማው

3. የፆም ፀሎት የጊዜው ርዝመት

4. በፆም ፀሎት ጊዜ ልናደርጋቸው የሚገቡ ነገሮች

III. ቅድስና

1. የቅድስና ትርጉም

2. በአለባበስ መቀደስ

3. የቅድስና አስፈላጊነት

4. ቅድስናን እንዴት መጠበቅ ይቻላል;

IV.አገልገይና አገልግሎት

1. አገልግሎት

ሀ. የአገልግሎት ትርጉም

ለ. የምናገለግለው ለምንድነው ;

ሐ. የአገልግሎት አላማው ምንድነው

2
በታደሰ ሁሪሳ

መ. የምናገለግልበት የአገልግሎት ዘርፍ ከመምረጥ በፊት

ሠ. የምናገለግልበት ዘርፍ ለመምረጥ

2. አገልጋይ

ሀ. የአገልጋይ ምንነት

ለ. አገልጋይ መሆን ያለበት ማነው ;

ሐ. አገልጋይ ለአገልግሎቱ የሚጠቀምባቸው መሣሪያዎች

V. ወንጌል መመስከር

1. የወንጌል ምስክርነት ቸል ማለት የሌለብን ለምንድነው;

2. ወንጌል መመስከር ያለበት ማነው;

3. የክርስቶስ ምስክሮች ለመሆን የሚያበቃን ምንድነው;

4. ለወንጌል ምስክርነት ስንወጣ ከማን ጋር ነው የምንሰራው;

5. በምስክርነታችን ውጤታማ ለመሆን ሊኖረን የሚገባ የህይወት አቋም ምንድነዉ

6. ወንጌል እንዳንመስክር ሰበብ የሚሆኑብን ነገሮችን ምንድናቸው;

7. ለመመስከር ስንወጣ ልንከተላቸው የሚገቡን እርምጃዎች

8. ለምስክርነት ስንወጣ ምን አይነት ሰዎች ያገጥሙን ይሁን;

9. መመስከር ቢፈለግ ሰዎችን የት አገኛለሁ;

1. በደስታ እግዚአብሔርን ማምለክ

1. አምልኮ ምንድነው; ዮሐ 4፡23-24

አምልኮ ለአምላካችን ብቻ የሚሰጥ አገልግሎት ነው ዘፀ 20፡1-3

 አምልኮ ስግደትን ውዳሴን ፣አክብሮትን፣መገዛትን ፣ፀሎትን ፣መሰዋዕትን መልካም ሥራን ፍራሃትንና ፍቅርን
ያጠቃልላል ፡፡

3
በታደሰ ሁሪሳ

አምልኮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ


 ከሙሴ በፊት ወይንም ከሕግ በፊት የቤተሰብ ራስ የሆነው ወንድ በየቦታው መሰዊያ ሠርቶ መስዕዋትን
በማቅረብ እግ/ርን ያመልኩ ነበር ዘፍ 4፡3-4 .8፡20-21 12፡7-9
 ከሙሴ እስከ ክርስቶስ በሕጉና በሥራዓቱ መሠረት በመገናኛ ድንኳን በቤተመቅደስ ከዚያም በምኩራብ በካህናት
በኩል የአምልኮ ሥርዓት ይፈፀም ነበር
 በግል እያንደንዱ ሰዉ ህጉን የመጣበቅ፤እግዚአብሄርን መዉደድና ለእግዚአብሄር የመገዛት ግዴታ አለበት፡፡
 በአድስ ኪደን በፀሎት የህጉን ቃል በማንባብ በመዝሙር በትንቢትና በልሳን መናገር ምፅዋትን መስጠት
የጥምቀትና ቅዱስ ቁርባንን ሥርዓት መፈፀምን ያጠቃልላል
እነዚህ ሁሉ በአምልኮ ፕሮግራሞች ላይ የሚደረጉ ነገሮች ሲሆኑ እውነተኛ አምልኮ ግን
ሀ. አምላክነቱን አውቆ ለእግ/ር በደስታ መገዛት ነው ፡፡ መዝ 100፡1-5
ለ. እግ/ርን በፍፁም ልብ በፍፁም ነፍስ በፍፁም ኃይል መዉደድና ባልንጀራን
እንደራስ መውደድ ነው፡፡ ማር 12፡28—33 1 ኛ ዮሐ 1-5 2፡9-11 3፡15 4፡20-21
ሐ. መስዋዕትን ማቅረብ ነው ፡፡መዝ 95፡1-7 51፡16—17
በአዲስ ኪደን ምን አይነት መስዋዕት ነው መቅረብ የሚጠበቅብን ;
 ሰውነታችንን ሮሜ 12፡1-2
 ምስጋናችንን ዕብ 13፡15 መዝ 50፡14—23
 ገንዘባችንና መልካም ሥራችንን ዕብ 13፡16 ያዕቆብ 1፡27

መ. ለእግ/ር ብቻ የሚቀርብ የዘላለም ሥርዓት ነው ፡፡

ዘዳ 4፡15—19 መዝ 96፡1—10 ኢሳ 42፡8 መዝ 145፡1፡13 ዕብራ 7፡9-15

2. / አምልኮ እንዴት ይቀርባል; /

አምልኮ ፈቃድን ስሜትንና አካል አጠቃሎ በሰው ሁሉንተን የሚፈፀም ድርጊት ነው፡፡

ሀ. በቃል ይቀርባል ፡- ዝማሬ እልልታ ምስጋና 2 ኛ ዜና 5፡11-14

ኤፌ 5፡19-20 ቆላ 3፡15-17

ለ. በድርጊት ይቀርባል፤ ስግደት ሽብሸባ ጭብጨባ የሙዚቃ መሳሪያ ፣መስጠት

2 ኛ ሳሙ 6፡5 1 ኛ ዜና 13፡8 15፡25—28 2 ኛ ዜና 29፡25—30 መዝ 150፡1—6

ሐ. በመንፈስና በእዉነት በውስጣዊ ስሜት በመነሳሳት ይቀርባል ዮሐ 4፡23-24

መ. አምልኮ በንጹህ ልብና በተቀደሰ ዓላማ ይቀርባል ዘሌዋ 10፡8—11 ነህ 12-30

2 ኛ ዜና 5፡11 አሞፅ 5፡21 –24 ያዕ 1፡26—27

3. አምልኮ መቼና የት ይቀርባል;

 አምልኮ በቦታና በጊዜ በሁኔታ ሳይወሰን ሁልጊዜ በሁሉ ቦታ በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ለእግ/ር ልቀርብ ይገባል ፡፡
 አምልኮ በግልና በቅዱሳን ህብረት ልቀርብ ይችላል
 የህብረት አምልኮ በግለሰብ መኖሪያ ቤት በቤተመቅደስ ለፀሎት በተመደቡ ቤቶች ልደረግ ይችላል
መዝ 149፡1 -2 መዝ 134፡1-2 135፡1 150፡1 ማር 14፡26 ሐዋ 12፡12 ሐዋ 13፡13

4. የአምልኮ ውጤትና ጥንቃቄዉ

ሀ. ውጤቱ
1. እግ/ር ራሱን ይገልጣል / ድምፁን ይሰጣል /
2 ኛ ዜና 5፡13 14 1፡5-7 ሐዋ 10፡1-8
2. የሰው ህይወት እግ/ን ለማምለክና ለማገልገል የተዘጋጀ ይሆናል ሐዋ 1፡4 13፡1-4
3. በጠላቶቻችን ላይ ድልን ይሰጠናል 2 ኛ ዜና 20፡20 -30 መዝ 50፡23

4
በታደሰ ሁሪሳ

ለ. ጥንቃቄዉ
1. በአምልኮ ጊዜ ስሜታዊ ብቻ ከመሆን መጠበቅ
2. አምልኮ ስርዓት መፈፀም ብቻ እንዳናደርገው እንጠንቀቅ
3. አምልኮ ከማቅረባችን በፊት ንሰዓ በመግባት የህይወታችንን ቅድስና ማረጋገጥ ዘሌዋ 10፡1-7 አሞፅ 5፡21
-27 ማቴ 5፡23-24

II. በፀሎት ከእግ/ር ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት ማድረግ

1. ፀሎት ምንድነው; ሉቃ 11፡1

ሀ. የልብን ሀሳብ ገልጾ ከእግ/ር ጋር መነጋገር ነው 1 ኛ ሳሙ 1፡9—16 ፊል 4፡4-7


2 ኛ ነገ 19፡14—19
ለ. ለአማኞች የደስታ ስፍራ ነው /በእግ/ር መደሰት ነው/ፊል 1፡3-4 ኢሳ 56፡6-7
 ሀዘተኛ የሚፅናናበት
 ሐጢያተኛ ምህረት የሚያገኝበት / የሚቀበልበት
 የደከመ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ የሚበረታበት
 በሽተኛ የሚፈወስበት

2. ፀሎታችን ምን ምን ልያካትት ይገባዋል;

ሀ. የምስጋናና የአምልኮ ፀሎት ስለአምላክነቱና ስለተደረገልን


ዳን 6፡10 ሉቃ 10፡10፡21 ኤፌ 1፡15 -17 ፊል 1፡4-5 ቆላ 1፡3-5
ለ. ኑዛዜና ንሰሃ
 ሀጢያታችንን የምንነዘዝበትና ደግመን ላለማድረግ ቃል የምንገባበት ፀሎት ነህ 9፡1-3
መዝ 51፡1-10 ዳን 9፡3-4-20

ሐ. የልመና ፀሎት

 የሚያስፈልገንን የምንጠይቅበት ጊዜ
ቆላ 1፡9 1 ኛ ሳሙ 1፡26 –29 ኤፌ 1፡16-18 6፡18-20

መ. የምልጃ ፀሎት

 ስለሌሎች ሰዎች በእግ/ር ፊት የምንማልድበት ጊዜ ዘፍ 18፡22—23 ዘኀ 14፡13-19 ፊል 4፡6


1 ኛ ጢሞ 2፡1-4
ሠ. የተቃዉሞ ፀሎት ከሰይጣንና ከመላዕክቱ ጋር ጦርነት የሚደረግበት ጊዜ

ያቆ 4፡7-8 ኤፌ 6፡10-11 2 ቆሮ 10፡3-6

3. የፀሎት ምክንያቶች ምንድናቸው; /ለምን እንፀልያለን;/

ሀ. ፍላጎት፤ፀሎት የእግ/ርና የሰው ፍላጎት ስለሆነ

 ሰዎች የልባቸውን ሃሳብ በመግለፅ እንዲናገሩት እግ/ር ሁሉ ጊዜ ፀሎት ለመስማት ይፈልጋል


፡፡ መዝ 34፡15 50፡14-15 ኤፌ 29፡12—14 33፡3
 የልባቸውን መሻትና ምስጋና ለማሰማት ሰዎች ዘወትር ወደ እግ/ር መፀለይ ይፈልጋሉ ፡፡
መዝ 65፡2 102፡1 27፡8 1 ዜና 20፡5-13 ዕብ 4፡16

ለ. ትዕዛዝ፤እግ/ር እንድንፀልይ በቃሉ አዞናል

ሉቃ 11፡9 ለምኑ ሉቃ 21፡36 ስትፀልዩ ትጉ 1 ተሰ 5፡17 ሳታቋርጡ ፀልዩ

ስለሚከተሉት ጉዳዮች እንድንፀልይ ታዘናል

5
በታደሰ ሁሪሳ

1. ስለግል ህይወታችን ሉቃ 21፡34 -36 ይሁዳ 20፡21

2. ስለ አማኞች ኤፌ 6፡18 ያዕ 5፡13-18

3. ስለ እግ/ር ሥራና ስለ አገልጋዮች ማቴ 9፡36 –38 2 ኛተሰ 3፡1-2

4. ስለ ተቃዋሚዎችና ስለሚጠሉን ሰዎች ማቴ 5፡4-3-48

5፤ ስለሀገር መሪዎችና ስለሰዎች መዳን ኢሳ 62፡6-7 1 ኛ ጢሞ 2፡1-2

 በአጠቃላይ እያንዳንዱ ክርስቲያን ዘወትር በትጋት እንዲፀልዩ መፅሐፍ ቅዱስ ያዘናል ሉቃ 18፡1-18
ሮሜ 12፡12

4. የፀሎት መንገዱና መልሱ

ትክክለኛውን የፀሎት መልስ ለማግኘት ትክለኛውን የፀሎት መንገድ መጠቀም እንደሚያስፈልግ የአምላካችን ቃል
ያስተምረናል ፡፡

ሀ. የፀሎት መንገድ

1. በመናዘዝ መፀለይ 2 ኛ ዜና 7፡14 ነህ 1፡4 –6 ኢሳ 1፡15 –18 ዳን 9፡3 ኢሳ 59፡1-2

2. የእግ/ር ፈቃድ በማወቅና በመከተል መፀለይ 1 ኛ ዮሐንስ 5፡14—15 ማር 10፡35-41

3. የተስፋ ቃሎችን መሠረት በማድረግ መፀለይ ነህ 1፡7—11 ሉቃ 11፡9—13 ዮሐ 15፡7

4. በእምነት መፀለይ ማቴ 21፡21 –22 ማር 11፡20 -24 1 ኛ ዮሐን 5፡15 ያዕ 1፡5-8

5. በመስማማት መፀለይ ማቴ 18፡19

6. በጌታ ኢየሱስ ስም መፀለይ ዮሐ 14፡13—14 16፡23 –24

ለ. የፀሎት መልስ

አንደ እግ/ር ፈቃድ የሚፀለይ ፀሎት ሁሉ መልስ አለው የፀሎት መልሶች ሶስት ሲሆኑ እነርሱም

1. ወዲያውኑ የሚመለስ 1 ኛ ነገስት 18፡36—38 ዳን 9፡20—23

2. በቆይታ የሚመለስ መዝ 40፡1 ማቴ 15፡22—28

3. የሚከለከል መልስ ዘፀ 33፡17 -23 ማቴ 20፡20-28

በጸሎታችን እግ/ርን መለመንና መሰሰብ እንጂ እግ/ርን መስገደድ ስለማይቻል እግ/ር የሚሰጠንን መልስ ሁሉ የእግ/ርን
ሁሉ አዋቂነትና መልካምነት በማመን በደስታ መቀበል ይኖርብናል ፡፡

5. የፀሎት አይነት

ሀ. የግል ፀሎት

 ሰው ለብቻው ከእግ/ር ጋር የሚገናኝበት ጊዜ ነው


 በጓዳ በስውር የሚደረግ የግል ፀሎት ነው
 የልብን ሀሳብ ለእግ/ር ለመንገር ምቹ ጊዜ ነው
 ከእግ/ር መልዕክትን ለመስማት / ለመቀበል / ምቹ ጊዜ ነው ማር 1፡35 ዳን 6፡10 ማቴ 6፡5—6 ማቴ 16፡18
ሉቃ 5፡15 –16 ሐዋ 10፡9-30 ሉቃ 18፡9 –14 ራይ 1፡9-11

ለ. የቡድን ፀሎት

6
በታደሰ ሁሪሳ

ጥቂት ሰዎች በጋራ ሆነው በመስማማት በተመሳሳይ የፀሎት ርዕሶች ላይ የሚፀልይበት ፀሎት ነው ማቴ 18፡19-
20 ዳን 2፡17-18 ሐዋ 13፡1-3

ሐ. የጉባኤ ፀሎት

ብዙ ሰዎች በጋራ በአንድ ሰው መሪነት ወይም ሁሉም በአንድነት የሚፀልዩበት ፀሎት ነው ሐዋ 12፡5-12 ሐዋ 4፡
24-31 2 ዜና 20፡1—13

6. ለፀሎት በእግ/ር ፊት እንዴት እንቅረብ

ሀ. ውስጣዊ አቀራረብ

1. ራስን በእግ/ር ፊት በማዋረድ መቅረብ 2 ኛ ዜና 7፡14 1 ኛ ጴጥ 5፡6 ማቴ 23፡12

ያቆ ቁ 10

2. በፍፁም ልብ መቅረብ ኤር 29፡12—14 ያዕ 1፡6-8

3. በመፀፀትና በእንባ መቅረብ ኢዮኤል 2፡12—17 ያዕ 1፡8-10

4. በእግ/ር መንፈስ ቁጥጥር ስር ሆኖ መቅረብ ይሁዳ 20፡21 ኤፌ 6፡18

ሮሜ 8፡26—27

በመንፈስ ሆነን ስንፀልይ

 የእግ/ርን ፀሎት እንፀልያለን ዮሐ 16፡13


 የእግ/ር ስሜት ይሰማናል ሉቃ 22፡39—44
 የእግ/ን ሀሳብ እናስባለን 1 ቆሮ 2፡10

5. በትህትና ጨዋ በሆነ እግ/ርን በሚፈራ መንፈስ መቅረብ መዝ 51፡17 ምሳ 15፡8 -29 ዮሐ 9፡31

ለ. ውጫዊ አቀራረብ

1. ተንበርክኮ መፀለይ ዳን 6፡10 ሉቃ 22፡41-42 ሐዋ 21፡5 ኤፌ 3፡14 -15

2. ቆሞ መፀለይ ማር 11፡25 1 ኛ ነገ 8፡22 2 ዜና 20፡5 -13 ዘፍ 18፡22

3.ተቀምጦ መፀለይ 2 ሳሙ 7፡18 ነህ 1፡4

4. ተደግፎ መፀለይ ዘኀል 16፡22 ኢያ 7፡6 -10 ማቴ 26፡36 –39

5. እጆችን ዘርግቶ መፀለይ 1 ኛ ነገስ 8፡54 1 ጢሞ 2፡8

6. በፀጥታ በልብ መፀለይ ሰቆቃ ኤር 3፡40 -41 ዕዝ 9-5 1 ኛ ሳሙ 1፡10-13

7. ድምጽን በመስማት መፀለይ ነህ 9፡1 -4 ሐዋ 4፡24

8. በአንድ ሰው መሪነት መፀለይ 2 ኛ ዜና 20፡5-13

9. ሁሉም ሰው በአንድነት መፀለይ ሐዋ 4፡24-31

10. ተኝቶ መፀለይ ኢሳ 38፡1-5

 ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት አቀራረቦች ሁሉ መፀለይ የሚቻል ቢሆንም እግ/ርን በማክበርና በማምለክ ለመፀለይ
ተንበርክኮ መፀለይ ይመረጣል ፡፡

7
በታደሰ ሁሪሳ

7. ፀሎት መቼና የት ማድረግ አለብን;

ሀ. የፀሎት ቦታ

1. ለፀሎት በተመደበ ቤት ውስጥ / በፀሎት ቤት / ሉቃ 2፡36 -38

2. በክርስቲየሰኖች መኖሪያ ቤት ውስጥ ሐዋ 12፡12 ዳን 6፡10 ሐዋ 1፡12—14

3. በሠራ ቦታ ነህ 2፡4

4. በሜዳ ላይ ዘፍ 24፡11—14 ሐዋ 16፡13

ለ. የፀሎት ጊዜ ፣

ዘወትር ሳታቃርጥ ፣ በትጋት ፣ሁልጊዜ

1. በማለዳ መዝ 55፡17 ማር 1፡35

2. በቀን መዝ 55፡17 ሐዋ 10፡9 -30

3. በማታ መዝ 55፡17 ዳን 6፡10

4. ለሊቱን በሙሉ ሉቃ 6፡12-13 1 ሳሙ 15፡11

 ፀሎት በጊዜ በቦታና በሁኔታዎች ስይወሰን ሁልጊዜ መፀለይ ይችላል ዋናው ነገር በመንፈስ ቁጥጥር ስር በመሆን
እንደ እግ/ር ፈቃድ መፀለያችን ነው ፡፡

8. የፀሎት መሳሪያነትና ውጤቱ

ሀ. የፀሎት መሳሪያነት / ጥቅሙ/

 ፀሎት ታላላቅ ውጤቶች ያሉት መንፈሳዊ መሳሪያ ነው ፡፡


 ፀሎት የሚያስፈልገን በረከቶች ሁሉ ለመቀበል ወደ እግ/ር የምንዘረጋው የእምነት እጅ ነው ፡፡
 ወደ ምስጋናው አደባባይና ወደ በረከቱ ጓዳዎች እንድንገባ እግ/ር የከፈተው የበረከት ደጅ ነው ፡፡
 ፀሎትን ለሚከተሉት ጉዳዮች እንደ መሳሪያ ልንጠቀምበት እንችላለን ፡፡
1. ለግል ሕይወታችን
ሀ. ከእግ/ር ጋር ህብረት ለማድረግ 1 ዮሐ 1፡1—7 2 ጴጥ 1፡4 ሐዋ 12፡2
ለ. የሚያስፈልገንን ጠይቆ ለመቀበል / ምህረት ፀጋ ኃይል የእለት
እንጀራ/ ሉቃ 11፡9-13 ማቴ 7፡7 -11 ዕብ 4፡16
ሐ. ሁል ጊዜ የእግ/ርን መንፈስ ለሞሞላት ሐዋ 10፡1—6—9፡20
ሐዋ 4፡31 – 19፡6—7 8፡15 –17
መ. ከተፅዕኖ በላይ ለመኖር ዳንኤ 2፡12—24 ሐዋ 12፡1-17 ዘፀ 2፡23-24
2. ቅዱሳንን ለመደገፍ
ሀ. በህይወታቸው እንዲባረኩ ኤፌ 6፡18 ቆላ 1፡9 -12-4፡12
ለ. በፈተና ድልን እንዲያገኙ ገላ 6፡2 ዕብ 13፡3 1 ጴጥ 3፡8
ሐ. የታመሙ እንዲፈወሱ ያዕ 5፡13-18 ማር 16፡17
3. የወንጌል ስራ ለመደገፍ
ሀ. አገልጋዮች እንዲነሱ ማቴ 9፡36—38
ለ. አገልጋዮች ለአገልግሎታቸው ብቁ እንዲሆኑ ኤፌ 6፡19—20 ቆላ 4፡2-4
ሐ. አገልጋዮች እንዲጠበቁ ሮሜ 15፡30—33 2 ተሰ 3፡1-2
መ. ሰዎች በወንጌል አምነው እንዲድኑ 1 ጢሞ 2፡1—4
ሠ. ሰዎች በድፍራት ወንጌልን እንዲመሰክሩ ሐዋ 4፡24 –31

8
በታደሰ ሁሪሳ

4. የእርኩሳን መናፍስት ስራ ለማፍረስ ኤፌ 6፡10-13 1 ጴጥ 5፡6-11 ያዕ 4፡7-8 2 ቆሮ 10፡3-6

ለ. የፀሎት ውጤት

1. የሰዎች መንፈሳዊ ህይወት መለወጥና ማደግ ሐዋ 16፡25 –34 2 ቆሮ 10፡3 -6

2. የህሙማን ፈውስ ማር 16፡18 7፡31-37

3. ከመከራ ድልን አግኝቶ መውጣት 2 ዜና 20፡1—31 መዝ 50፡15 አስቴር 4፡15-17፤9፡1 ሐዋ 12፡1—11

4. ለሰዎች ጥያቄ መልስ መገኘት 1 ሳሙ 1፡12 -28 2 ዜና 7፡11—16 ዮሐ 16፡23-24

ማቴ 15፡22—25 ዮናስ 2፡1-3

5. የሚስጥሮች መገለጥ ኢያሱ 7፡10-21 ዳን 2፡17—23

“እንግዲህ ፀሎት ታላለቅ ውጤቶች የሚያመጣ መሆኑን ተገንዝበን ጊዜ ሰጥተነው አክብረነው


ልንለማመደውና ከውጤቱ ልንጠቀም የሚገባን ጌታ የሰጠን ተግባር ነው፡፡

ፆምና ፀሎት

ሀ. የፆም ትርጉም

 በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሠረት መፆም ማለት ከምግብና ከመጠጥ መከልከል ወይንም
አለመመገብና አለመጠጣት ነው አስቴ 4፡15-17 ዘካ 7፡4—6 ሉቃ 4፡1-2 ሐዋ 27፡33—34
 ለእኛ ለክርስቲያኖች ፆም ከፀሎት ተለይቶ ለብቻው የሚፈፀም ሥርዓት አይደለም ምክንያቱም ፆም
የፀሎት መጠናከሪያ ወይም ራስን በእግ/ር ፊት የበለጠ አዋርዶ ለማቅረብ የሚደረግ የአቀራረብ
መንገድ ነው ፡፡ ዕዝ 8፡21 -23 ነህ 1፡4 መዝ 35፡13-14 ነፍሴንም በጾም አደከምኳት

ለ. የፆም ፀሎት አላማ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግ/ር ሰዎች ፆምን ለሚከተሉት ነገሮች ተጠቅመው ምሳሌ ሆናዉናል

1. ከእግ/ር ጋር ለመገናኘት ወይም ለበረከት ሐዋ 13፡1-3

2. ዕርዳታንና ኃይልን ከእግ/ር ለመጠየቅ 2 ዜና 20፡9 አስቴር 4፡15-17

3. ምሪት ከእግ/ር ለማግኘት ዕዝ 8፡21-23 ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረቶችንም የቀናውን መንገድ እንለምን ዘንድ

4. በፀፀትና በእንባ ወደ እግ/ር ቀርቦ ምህረትን ለመቀበል 1 ሳሙ 7፡1—6 ዕዝ 10፡3-6 ኢዮኤል 2፡12—18 ዮናስ 3፡
5-10 ዳን 9፡3-10

5. የፈውስ ሃይል ከእግ/ር ለማግኘት 2 ሳሙ 12፡15-23 ማቴ 17፡21

6. አገልጋዮችን ለእግ/ር ለማስረከብ ሐዋ 13፡2-3

ሐ. የፆም ፀሎት የጊዜ ርዝመት

1. አርባ ቀን ማቴ 4፡1-2 ዘፀ 34፡28 ዘዳ 9፡9

2. ሃያ አንድ ቀን ዳን 10፡1

9
በታደሰ ሁሪሳ

3. ሰባት ቀን 2 ሳሙ 12፡16-20

4. ሶስት ቀን አስቴር 4፡15—17

5. አንድ ቀን ዕዝ 10፡5-6 መሳ 20፡26

መ. በፆም ጊዜ ልናደርጋቸው የሚገቡ ነገሮች ኢሳ 58፡1 ማቴ 6፡1—18

1. መፀለይ

2. ከበደልና ከአመፅ ራስን መጠበቅ ኢሳ 58፡3-4

3. መልካሙን ነገር ሁሉ ማድረግ ኢሳ 58፡6—12

 በደልን እስራት መፍታት ምህረትን ማድረግ


 የተገፉትን መርዳት
 እንጀራን ለተራበ መቁረስ
 የታረዘውን ማልበስ
4. ለታይታ ከማድረግ መጠበቅ

III. ቅድስና

 አማኞች በኢየሱስ በማመን ይቀደሳሉ ኤፌ 1፡4 1 ጴጥ 1፡1 1 ቆ 1፡2


 አማኞች በኢየሱስ ካመኑ በኃላ ከሐጢአት በመጠበቅ ይቀደሳሉ
1 ጴጥ 1፡15 ፣16 1 ተሰ 4፡3-6 ዕብ 12፡14 ኤፌ 4፡22 -27
 አማኝ በጌታ ቤት እየኖረ ኃጢያት ሠርቶ ቢገኝ ንሰሃ በመግባት በኢየሱስ ደም ይቀደሳል 1 ዮሐ 17—9

1. ምንነት/ትርጉም/

ከአለም ማለት ከሥጋ ምኞት ከአይን አእምሮትና ስለገንዘብ ከመመካት በመለየት የኢየሱስ ክርስቶስ መልክን በመምሰል
ማድግና የመለኮት ባህሪይ ተካፋይ መሆን ነው ፡፡ 1 ኛ ዮሐ 2፡15 1 ኛ ጴጥ 1፡4 ዕብ 9፡11-14 ዕብ 12፡10

ሀ. ከአለም ክፉ ምኞት መለየት

1 ዮሐ 2፡15 ዘፀ 33፡16 ላይ “በምድር ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ህዝብህ የተለየን እንሆን ዘንድ “

 በተግባር ከሌለው ሕዝብ ዓለማዊ ከሆኑ ኑሮ በመለየት ለእግ/ር የክብር ዕቃ መሆን ነው ፡፡ ሮሜ 12፡14 2 ኛ
ጢሞ 2፡21 ዘሌ 20፡26 ኢሳ 52፡11
 ዓላማዊነት በእግ/ር ቃልና በፀሎት ካልተሸነፈ አዳማዊ ማንነታችን ከውስጣችን የሚወጣ ክፉ ባህሪይ ነው፡፡
ማር 7፡14—23 ገላ 5፡18-21
መጽሐፍ ቅዱስ አንድንለያቸው የሚያዘን አለማዊነቶች ወይም የሥጋ ሥራዎች የሚከተሉት ናቸው ፡፡

1. ዝሙት ፡- ከትዳር ጓደኛ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያመለክታል ፡፡

 ዝሙትን የሚሠረ በራሱ ሥጋ ላይ ሐጢያትን ይስራል


 የቅዱስ እግ/ር መንፈስ ማደሪያ የሆነውን ሥጋውን የሐጢያት ማደሪያ ያደርገዋል ፡፡ 1 ቆሮ 6፡12-20 3፡16-17
 ዝሙት እዉነተኛ ያልሆነውን ለባዕድ / ለጣዖት / የተደረገ የአምልኮ ሁኔታንም ይገልጣል ፡፡ ኤር 3፡9 ማቴ 12፡39

2. መዳራት፡- ወደ ዝሙት የሚያመራ አላስፈላጊ የሆነ የተለያዩ ፆታዎች ንክኪ ወይም ጨዋታን ያመለክታል ፡፡

 ወንድና ሴት በዝሙት ሀሳብ ተነድተው ሲጫወቱ


 ያለአግባብ የሆነ መተሻሸትና መሳሳም ገላ 5፡20

10
በታደሰ ሁሪሳ

3. ክርክር ፡- ጥቅም የሌለው ወደ ጥል የሚያመራ ከልክ ያለፈ ንግግር

 የራስን ሃሳብ አክርሮ ከመያዝ ይመነጫል ፡፡


 ከዚህ ዓለም እርኩሰት በመለየት ፅድቅን በማድረግ ነው
 ክርክር ፍቅርና ህብረትን ይጎዳል ያበላሻል
 ክርክር የሥጋ ሥራ ነው 1 ቆሮ 3፡3
 የእግ/ር ሰው ከክርክርና ከጭቅጭቅ ነፃ መሆን አለበት 1 ጢሞ 3፡1-4

4. ቅንዓት፡- ጥቅም ወይም ፍቅር ወደ ሌላ ሲያልፍ መቆጣት መበሳጨትን ያመለክታል

 ለሌላ ሰው የሆነውን ለራስ መፈለግ


 ቅንዓት ከቀናው የእግ/ር መንገድ ያስታል መዝ /73/1፡3 ሮሜ 13፡13 1 ቆሮ 13፡4 2 ቆሮ 12፡20 ፊል 1፡15
1 ጢሞ 6፡4-5 1 ጴጥ 2፡1 ማቴ 27፡18 ሐዋ 13፡45 17

“ ቅንዓት ጤናማና ጤናማ ያልሆነ ልሆን ይችላል ፡፡

 ሰው ለሰውና ለእግ/ር ሥራ መልካም የሆነ ቅንዓት ልቀና ይችላል፡፡” የቤትህ ቅናት በልታኛለችና “1 ኛ ነገ 19፡10-
14 2 ኛ ቆሮ 11፡2
 እግ/ር ለክብሩ ይቀናል ዘፀ 20፡4—6 34፡14 ዘዳ 4፡23-24 5፡9

5. አድመኝነት፡- ሰዎችን አስተባብሮ በእውነት ላይ ጠብን ክርክርን መለያየትና አመፅ ማነሳሳት ሮሜ 2፡8 2 ቆሮ 12፡20
ያዕ 3፡16 ዘኅልቁ 12፡1-8

6. ስካር ፡- በመጠጥ ብዛት ከአእምሮ ወጪ መሆን ነው ፡፡ የእግ/ር ሰዎች መጠጥ እንዳይጠጡና እንዳይሰክሩ ተከልክለዋል ፡፡
ዘዳ 21፡18—21 ምሳ 23፡29-35 ዘሌ 10፡8-10 1 ቆሮ 5፡11 6፡10 ኤፌ 5፡18

ኖህ ሰከረ --- እራቁትን ሆነ ልጁንም ረገመ ዘፍ 9፡20 ---25


ሎጥ ሰከረ --- ከገዛ ልጆች ወለደ ሞዓብና አሞን ተገኙ ዘፍ 19፡30-38
ናባል ስከረ -- ምናምቴ ሰው ነበረ 1 ሳሙ 25፡25—36

“እስራኤል ይጠቀሙበት የነበረው ወይን መልካም ተግባርም ነበረው፡፡

የእግ/ር በረከት ምልክት ነበር ዘፍ 27፡28


መሥዋዕት ይሆን ነበር ዘፀ 29፡40
ሰውን ደስ ያሰኘ ነበር መዝ 105 ፡15 ምሳ 31፡6 መክ 10፡19
ኢየሱስ ወይንን ጠጣ ውሃንም ወደ ወይን ጠጅ ለወጠ ዮሐ 2፡1-11 ማቴ 11፡19
ለአዲስ ኪዳን ሥራዓት ወይንን ስጠ / የጌታ እራት / ማቴ 20፡27 –29 ሉቃ 22፡7 –20
ወይን መድሐኒትም ይሆን ነበር ሉቃ 10፡34 1 ጢሞ 5፡23

7. ጣዖትን ማምለክ ፡- በእግ/ር ፈንታ የሚመለከ የሚሰገድለትና የሚወደድ የተለያየ ቅርፃ ቅርፆችን ወይንም ምስሎችን
ወይንም ፍጡሮችን / ሰውን እንሰሳን ፀሐይንና ጨረቃን ያመለክታል ዘዳ 4፡15---19 ዘፀ 20፡3-6 ሮሜ 20—25 መዝ 113
፡12-16 1 ቆሮ 8፡4 ኢሳ 40፡18—20

8. ምዋርት ---ጋኔን ፣ጥንቆላ ፣ መተት በአጋንት ሃይል የሚሰራ ክፉ መንፈስ ዘዳ 18፡10 1 ሳሙ 6፡2 1 ነገ 17፡17 ኢሳ 44 ፡
25 ሐዋ 16፡16 -18

9. መናፍቅነት፤ ከእውነተኛ ከእግ/ር ቃል ትምህርት መራቅ ወደ ስህተት ትምህርት መሄድና

ይህንንም ትምህርት ለሌሎች ማስተማር / ማሳፋፋት /

10. ምቀኝነት ፡- ለስዎች ከሚሆነው መልካም ነገር የተነሳ አለመደሰትና በእርሱ ላይ ክፉን ማሰብ መናገርና ማድረግ
ቲቶ 3፡3

11
በታደሰ ሁሪሳ

11. ዘፋኝነት፡- በቅኔና በግጥም ከልዩ ልዩ መሳሪያዎች ጋር የሚቀርብ ሲሆን ባዕድ አምልኮናንና ዝሙትን የሚያስከትል
ድርጊት ነው ፡፡

 በቡሊይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን መካከል በቃሉ አጠቃቀም ልዩነት አለ እስራኤል ለእግ/ር የሚቀርብን ዝማሬና
አምልኮን ዘፈን ብሎ ሲጠራው በአዲስ ኪዳን በአብዛኛው ዘፈን የተባለው ቃል ለእግ/ር ላልሆነ ነገር ጥቅም ላይ
ውሎአል ፡፡ ማር 6፡2 -28
ሮሜ 13፡13 ገላ 5፡19-21 ዘፀ 32፡6
በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ
 በልደት ቀን ኢዮብ 21፡11,-12 ማቴ 1፡4-6
 በሠርግ ቀን ኤር 31፡4 ማቴ 11፡17
 በድል ቀን ዘፀ 15፡20-,-21 መሳ 11፡34 1 ሳሙ 18፡6
 መንፈሳዊ በዓል ቀን 2 ሳሙ 6፡12—23
 በተለያዩ የደስታ ቀኖች ሉቃ 15፡25 ይዘፍኑ ነበር

ነገር ግን ባዕድ አምልኮና ዝሙትን የሚያስከትል ዘፈን አልተፈቀደላቸውም ነበር ዘፀ 32፡6-19

ለ. የመለኮቱ ባህርይ ተካፋይ በመሆን የልጁን መልክ መምሰል ነው

2 ኛ ጴጥ 1፡4

 ቅድስና ከክፉ ምኞት መለየት ብቻ ሳይሆን ተለይቶ ልጁን መምሰል / የመለኮት ባህርይ ተካፋይ መሆን / ነው
ቅድስና --መለየት +መምሰል፡፡ ሮሜ 8፡29-30
 እግ/ር መምሰል እርሱን በማወቅ በእርሱ ማደግና የባሕርይው ተካፋይ መሆን ነው ማቴ 5፡48
 እግ/ርን መምሰል ለምድራዊ ሕይወትና ለዘላለማዊ ሕይወት ይጠቅማል ፡፡
1 ጢሞ 4፡7-8
 እግ/ርን መምሰል ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት በመራቅ የእግ/ር ማደሪያ የሆነውን ሥጋችንን ከእርኩሰት
መጠበቅ ነው ፡፡ 1 ጴጥ 2፡11 1 ቆሮ 6፡19 1 ጢ 4፡7-4
1 ቆሮ 3፡16-17

2. በአለባበስ መቀደስ

 የክርስቲያኖች አለባበስ በሕብረተሰቡ ዘንድ በክፉ ሥራቸው ወይም በሐጢያት መንገዳቸው ከሚታወቁት
ሰዎች አለባበስ የረቀና የተለየ መሆን አለበት ምሳ 7፡10 ላይ “የጋለሞታ ልብስ የለበሰች ነፍሳትን ለማጥመድ
የተዘጋጀች ይላል “፡፡ ከክርስቲያን ከእንዲህ አይነት አለባበስ የሚቆጠብ መሆን አለበት ፡፡
 ቤተክርስቲያን ባለችበት ሠፈርና አካባቢ የሚኖረው ህብረተሰብ ስለ አለባበስ ያለው አስተሳሰብ ማወቅና በዚህ
ህብረተሰብ ውስጥ ለክርስቲያን “የሚገባ ልብስ “በመልበስ የእግ/ር ስም እንዳይሰደብ ሰዎችንም ለፈተና
ከመገለጥ መጠበቅ ይገበናል ፡፡
 እንደ ክርስቲያን ሰዎችም በእኛ እንዳይሰናከሉ መጠንቀቅ ይኖርብናል ፡፡
 አለባበሳችን በውስጥ ህይወት ያለውን እግ/ር መፍራት ወይም አለመፍራታችንን የሚያሳይ ገፅታ አለው ፡፡
 አለባበስ ራስን የመግዛት ኑሮ አመልካችም ነው 1 ጢሞ 2-9-10
 የሚገባ ልብስ ካለ የማይገባ ልብስ መኖሩን ያመለክታል / መረዳት ያስፈልጋል/
 በቡሉይ ኪዳን ራስን መሸፈን / መከናነብ / የጋለሞታ ምልክት ነበር በዘፀ 38፡14-15 በአዲስ ኪዳን በቆሮንቶስ
የነበሩ ጋለሞቶች ደግሞ ፀጉራቸውን ባለመሸፈን የታወቁ ስለነበር ጳውሎስ ሴቶች በቤተክርሲያን ፀጉራቸውን
እንዲሸፍኑ መከረ 1 ቆሮ 11፡2-16
 ስለዚህ በምንኖርበት ህብረተሰብ መካከል ተቀባይነት ያለው አለባበስ በመልበስ ራስንና ሌላውን ከፈተና ጠብቆ
እግ/ር ማክበር ያስፈልጋል

3. መቀደስ ለምን አስፈለገ

1. የጠራን እግ/ር ቅዱስ ስለሆነ ዘሌ 11፡441 ጴጥ 1፡15

2. የተጠራነው ለቅድስና ስለሆነ ሮሜ 1፡7 1 ተሰ 4፡7 1 የሐ 2፡6

12
በታደሰ ሁሪሳ

3. ቅድስና የእግ/ር ፈቃድ ስለሆነ 1 ተሰ 4፡3

4. አለመቀደስ ቅጣት ስላለው 1 ተሰ 4፡6 ኤፌ 5፡3-6

4. ቅድስናን እንዴት መጠበቅ ይቻላል;

1. በፀሎት ማቴ 26፡41 ሉቃ 22፡46 21፡34-36

2. የእግ/ር ቃል በማወቅና በመታዘዝ ያዕ 1፡22-23 መዝ /119/፡11

3. እግ/ርን በመውደድና በመፍራት መዝ 111፡10 ምሳ 1፡4-27 ምሳ 19፡23 ዮሐ 14፡15

4. ንሰዓ ገብቶ በክርስቶስ ደም በመንፃት 1 ዮሐን 1፡7-9

IV አገልጋይና አገልግሎቱ

I አገልግሎት

ሀ. ምንነቱ ---የአገልግሎት ትርጉም

1. የጌታ ሥራ ነው 1 ቆሮ 1፡58 1 ጢሞ 4፡5

የጌታ ስራነው ስንል

13
በታደሰ ሁሪሳ

ሀ. ጌታን እንደግል አዳኛቸው አድርገው የተቀበሉ ሰዎች ከእግ/ር ፀጋና ምህረት የተነሳ እንዲሰሩ የተሰጣቸው መንፈሳዊ
ስጦታ ማለታችን ነው 2 ቆሮ 4፡1

ለ. በቅዱሳን በጎ ፍቃደኝነት ላይ ተመስርቶ የሚሰራ መንፈሳዊ ተግባር ነው 1 ዜና 29፡5

ሐ. አማኝ በረከት ፍለጋ ሳይሆን ስለተባረከ የሚፈፅመው መልካም ተግባር ነው

2. የአገልግሎቱ ባለቤት ታማኝ አድርጎ በቆጠራቸው ቅዱሳን ላይ የሚያኖረው ውድና ክቡር

መንፈሳዊ አደራ ነው ፡፡ 2 ጢሞ 1፡14

3. አገልግሎት ተግባር ብቻ ሳይሆን ሕይወትም ነው ፡፡ ስለዚህ እግ/ር በእኛ ውስጥ ባኖረው በመንፈስ ቅዱስ የሚከናወነው
ሥራ ነው፡፡ 1 ቆሮ 2፡13 4-5

4. አገልግሎት ጌታ ብቻ የሚሰጠው ሃላፊነት /ሹመት/ነው፡፡ 1 ጢሞ 1፡12 ሐዋ 1፡15-26 ሐዋ 20፡28 ዘኅ 4፡16

ለ. የምናገለግለው ለምንድነው; /የአገልግሎት ምክንያቶች ምንድናቸው

 ለመንፈሳዊ ሰው የአገልግሎት ምክንያት መለኮታዊ ፍቅር ብቻ መሆን እንዳለበት ከመጽሐፍ ቅዱስና ከጌታ
ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት እንማራለን 1 ጢሞ 1፡5-7
2 ቆሮ 2፡4

1. አምላካችንን እግ/ርን ስለምንወድ

ዘዳ 6፡5 ዮሐ 21፡15 ሮሜ 8፡35-39 2 ቆሮ 5፡14-15


ማንኛውም ክርስቲያን ወደ አገልግሎት ለመምጣት ሲያስብ ዋናው ምክንያቱ የእግ/ር ፍቅር ብቻ መሆኑን
እርግጠኛ መሆን ይኖርበታል ፡፡

2. የእግ/ርን ህዝብ ስለምንወድ

 አገልጋይ በሁለተኛ ደረጃ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ በእግ/ር ተወደው ልድኑ በተወሰኑት ሕዝብ ፍቅር በመነካት ወደ
አገልግሎት መምጣት ይኖርበታል 2 ቆሮ 2፡4 1 ቆሮ 16፡24 1 ጴጥ 4፡7-8 1 ዮሐ 4፡10-12 ያዕ 2፡1-4
 ፍቅር የእግ/ር የመሆናችንን ምልክት ስለሆነ ለሰዎች ያለን ፍቅር በግልጽ መታወቅና መታየት አለበት 2 ቆሮ 2፡
12 ሉቃ 10፡27
 ክርስቶስ ራሱን የሰጠው ሰለ ሰዎች ነው እኛም የምናገለግለው ዋጋ የምንከፍለውና የምንደክመው ስለሰዎች
መዳንና ጥቅም በፍቅር ሲሆን ይገባል ፡፡ ሐዋ 7፡58-60
ሮሜ 5፡6-112 ቆሮ 4፡11-15

3. በተሰጠን ፀጋ የምናገለግለውን አገልግሎት ስምንወድ

አገልጋይ በተጠራለትና በአደራ በተቀበለው አገልግሎትም ፍቅር መነካት አለበት ፡፡ ምክንያቱም አገልግለታችንን ወይም
የተሰጠንን ፀጋ ሳንወድና ሳንቀበለው ውጤታማ የሆነ ሥራ መስራት ያስቸግረናል ፡፡ ነገር ግን የሚነዳንና የሚያንቀሳቅሰን
የአገልግሎት ፍቅር ብቻ እንዲይሆን መጠንቀቅ አለብን ፡፡ ሮሜ 11፡13-14

 ሰው የሚወደውን ነገር ያከብራል ለሚወደው ነገር ይጠነቀቃል ጊዜውንና ያለውን ሁሉ በፈቃደኝነት


ይሰጣል ፡፡

ሐ. የአገልግሎት አላማው ምንድነው;

1. እግ/ርን ማክበር ፊል 1፡9

2. ሌሎች እግ/ርን እንዲያከብሩት መርዳት

3. ከእግ/ር የተቀበልነውን መልዕክት ለሰዎች ማስተላለፍ

14
በታደሰ ሁሪሳ

መ. አገልጋይ የሚያገለግልበትን የአገልግሎት ዘርፍ ከመምረጡ በፊት ማወቅ ያለበት ነገሮች

1. አገልግሎቶች ሁሉ በእግ/ር ፊት እኩል አክብሮት ተፈላጊነትና ዋጋ

እንዳላቸው ማወቅ አለበት

2. በአንድ የአገልግሎት ዘርፍ ውስጥ የምናገለግለው ዘርፉን ስለምንወድ ወይም

ቀላል መስሎን ስለታየን ሳይሆን ፀጋ ስለተሰጠ መሆኑን ማወቅ አለበት

3. የአገልግሎት ስምሪት መቀበል ያለበት ከራሳችን ፍላጎት ወይም ከሌሎች

ሰዎች ሳይሆን ከእግ/ር መሆኑን መረዳት አለበት

4. አገልግሎቶቹ ሁሉ የሚከናወኑት ወይም የሚሰሩት በአንዱ በመንፈስ ቅዱስ

ፀጋ እንጂ በሰው ኃይልና ብቃት እንዳልሆነ ማወቅ አለበት

ሠ.የምናገለግልበትን ዘርፍ ለመለየት የሚረዱ ሃሳቦች

1. በፀሎት በእግ/ር ፊት መቆየት ከእግ/ር ምሪትን መቀበል ፀጋን ለይቶ ማወቅ

2. ከአገልግሎት በፊት ስለ አገልግሎቱ ምንነት ትምህርት መማር

3. የአገልግሎት ዘርፍ ለሚጠይቃቸው ጊዜ እውቀት ፀጋ ምላሽ ለመስጠት

ዝግጁ መሆናችንን ማረጋገጥ

4. ልናገለግል በምናስብበት ዘርፍ ከእግ/ር የተቀበልናቸው አሁን በህይወታችን

መታየት የጀመሩ ነገሮች መኖራቸውን ማረጋገጥ

5. ፀጋ ተቀብያለሁ ብለን በምናስብበት ዘርፍ ዙሪያ እንቅስቃሴዎች መጀመርና

ፀጋን በተግባር ማሳደግ

6. የአገልግሎቱን ፍሬ በጥቂቱ መገምገም

7. የቀደሙትንና የሚያውቁንን አገልጋዮች ምክርና እርዳታ በመጠየቅ እንደ

እግ/ር ቃል የሆነውን ምክራቸውን ተግባራዊ ማድረግ

II. አገልጋይ

ሀ. ምንነቱ

 ጥሬ ቃሉ በአማርኛ መዝገብ ቃላት ባሪያ ፣ተዘዥ ፣አሽከር


 ክርስቲያን አገልጋይ ለእግ/ር 1 ሳሙ 15፡22 ኢያሱ 1፡8 1 ጴጥ 2፡13-16 ለመንግስት
ቲቶ 3፡1-2 ለቤ/ክ ዕብ 13፡17 ለወላጆች ኤፌ 6፡1 1 ኛ ጴጥ 5፡5 ቆላ 3፡20 ነው፡፡ ፊል 1፡1 ቲቶ 1፡1 2 ጴጥ 1፡1 ያዕ 1፡
1 ይሁዳ 1 ዕብ 5፡8 መተዘዝ ይኖርበታል፡፡
 በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ይህንኑ ትርጉም መሠረት አድርጎ እንዲህ ይገልጸዋል

1. በእግ/ር የተመረጠና በጌታ መንፈሳዊ ሥራ ላይ የተወከለ መንፈሳዊ ሰው ማለት ነው ፡፡ ዮሐ 15፡16 ኤር 1፡1 ማር 3፡15
ማቴ 12፡18 -21

15
በታደሰ ሁሪሳ

2. የእግ/ር ሃሳብ ዓላማና ፕሮግራም የሚከናወንበት መጠቀሚያ ዕቃ ማለት ነው ፡፡ሐዋ 9፡15

3. ጌታ ለእርሱ የከፈለውን መስዋዕትነት አስቦ ጌታ የሚያዘውን በታማኝነት ለመታዘዝ ራሱን የሰጠ ማለት ነው ፡፡
1 ጢሞ 1፡12 2 ጢሞ 4፡6

4. በጌታ ቤት ወይም በቅዱሳን መካከል የጌታ ስራ እንዳይቀዘቅዝና እንዳይቃረጥ የተቻለውን ጥረት የሚያደርግ የጌታ
ባሪያ ማለት ነው ቆላ 4፡17 ዕብ 3፡5

5. ሰዎች ከመንፈሳዊ ህይወት አንፃር የሚኖርባቸውን ሸክም ድካምና ጉድለት ለመርዳትና ለመደገፍ ባለአደራ የሆነ ሰው
ማለት ነው ፡፡ 2 ጢሞ 1፡14

ለ. አገልጋይ መሆን ያለበት ማነው;

1. በክርስቶስ አምኖ የተለወጠ መንፈሳዊ ህይወት ያለው ሰው 1 ጴጥ 2፡9-12

2. በጌታው ፈቃድ ፍፁም ለመመራት የተሸነፈ ሕይወት ያለውና የወሰነ ሰው ሐዋ 9፡6 ዕብ 10፡9 3፡6—39

3. በቅድስና ህይወቱን ጠብቆ ለመኖር የወሰነና የሚኖር ሰው ዕብ 12፡3-14 ኢሳ 52፡11 ዘጸ 39፡30

4. ምሳሌነት ያለውን ሕይወት የሚኖር ሰው 1 ተሰ 2፡9-12 1 ጢሞ 4፡11-12

ሀ. በአነጋገር ምሳሌ መሆን ቲቶ 2፡7-81 ጢሞ 1፡6-7

ለ. በአኗኗር ምሳሌ መሆን ማቴ 2፡3-3 5፡19 ኤፌ 4፡25-29

ሐ. በፍቅር ምሳሌ መሆን ገላ 6፡1-2 ዮሐ 13፡34 -35 ሉቃ 10፡26

መ. በእምነት ምሳሌ መሆን 2 ጢሞ 1፡12 1 ጢሞ 6፡6 ፊል 3፡17 1 ቆሮ 11፡1

ሠ. በቅድስና ኢሳ 52፡11 ዘፀ 39፡30 2 ቆሮ 6፡14-18

5. አምላኩንና ቃሉን የሚያውቅ ሆሴ 4፡6 ቆላ 7፡16

4. ሌሎችን ለአገልግሎት ማዘጋጀት

ሐ. አገልጋይ ለአገልግሎት የሚጠቀምባቸው መሳሪያዎች

ምንድናቸው;

 አገልግሎት ትልቅ የጌታ ሥራ ስለሆነ አገልጋይ ለሥራው ማስፈፀሚያ የሚጠቀምበት መሳሪያዎች


ማወቅ ይኖርበታል ፡፡ ብዙ መሳሪያዎች ቢኖሩም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

1.ፀሎት

 ለማንኛውም የአገልግሎት እንቅስቃሴ ግንባር ቀደሙና ወሳኙ ለአገልግሎት ካሰማራን የስራው ባለቤት ጋር ጊዜን
በማሳለፍ ለሥራው መልዕክትና ምሪት መቀበል ተገቢ ነገር ነው ፡፡
 አገልጋይ ልፀልይባቸው ከሚገቡ ርዕሶች መካከል
ሀ. ስለሚያስተላልፈው መልዕክት
ህዝቡ የእግ/ር ስለሆነ ለሕዝቡ የሚያስፈልገውን የሚያውቅ እግ/ር ብቻ ነው
ስለዚህ መልዕክቱን ከእርሱ መስማት ያስፈልጋል ፡፡
ለ. ስለሚያገለግላቸው ሰዎች ፡-
የሕዝቡ ልብ አስቀድሞ በፀሎት ማዘጋጀት ያስፈልጋል ፡፡ ኤር 3፡14-19
1 ሳሙ 12፡23 ሕዝ 22፡30 ሉቃ 5፡15
ሐ. ስለራሱ ስለቤተሰቡና ስለአገልግሎቱ
 እግ/ር ማመስገን

16
በታደሰ ሁሪሳ

 አገልግሎቱ ለእግ/ር ክብር ለሰዎች ጥቅም እንዲሆን


 የክፉ መንፈሳዊ ሠራዊት ሥራ በማፍረስ ጠላትን ማሰር “ጠላትን ሥራ መቃወም 2 ቆሮ 10፡3-
6 ማቴ 26፡41 “ሃይለኛውን ሳያስር ወደ ሃይለኛው ቤት ገብቶ -----››

2. የእግ/ር ቃል /መጽሐፍ ቅዱስ /

አገልጋይ በአገልግሎቱ ፍሬያማ ለመሆን የእግ/ርን ቃል ለመማር የተዘጋጀ ልብ

ልኖረው ይገባል ፡፡ 1 ሳሙ 15፡22 ኢሳ 48፡17 መዝ 85፡8 1 ሳሙ 3፡10

 አገልጋይ የእግ/ር ቃል ለአገልግሎቱ እንደመሳሪያ ለመጠቀም


ሀ. ቃሉን ማወቅ አለበት know ማቴ 22፡29 ሕዝቄ 1፡4 ቆላ 3፡16 መዝ/119/፡140 ኢሳ 1፡7-9
ለ. ቃሉን ማመን አለበት Belieue አገልጋይ እግ/ርቃል ኃያል፣ታላቅ ፈውሽ፣ እውነተኛ፣
የሚያስፈራ፣ መሆኑን አምኖ መኖር አለበት
ሐ. ቃሉን መታዘዝ / ማክበር/ አለበት obey አገልጋይ ለተረዳው ለእግር ቃል ታዛዥና ተገዢ
በመሆን ለሚያገለግላቸው ሰዎች በቃልና በሕይወት ጥሩ አስተማሪ መሆን ይጠበቅበታል ማቴ 7፡
24 ያዕ 1፡22-25
መ. ቃሉን ማስተማር /ማስተላለፍ / አለበት Teach 2 ጢሞ 2፡1-2
ዕዝ 7፡10

3. መንፈስ ቅዱስ

 መጽሐፍ ቅዱስ ስናጠና ጌታ ኢየሱስ ለአገልጋዮች የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሳይቀበሉ ለአገልግሎት
መውጣት እንደሌለባቸው ሲያስጠነቅቃቸው እናገኛለን ሉቃ 24፡49 ሐዋ 1፡8 ኤፌ 5፡18
 መንፈስ ቅዱስ ለአገልጋዩ የራዕይ የድፍረት ፣የብቃትና፣የስኬት፣ ምንጭ ነው፡፡ ሕዝ 37፡1-7
ሐዋ 10፡38 ዘካ 4፡6
 መንፈስ ቅዱስ በፀጋ ስጦታዎች የተሰወረውን በመግለጥ ታላቅ ታአምራቶችን በማድረግ
የአገልጋዩን አገልግሎት ይደግፋል ቃሉን ያፀናል ፡፡
 የመንፈስ ፍሬን እንዲያፈሩ በመርዳት አገልግሎታቸው ምሳሌነት ባለው ህይወት እንዲደገፍ
ያደርጋል ፡፡ሮሜ 12፡6-8 1 ቆሮ 12፡4-11 ገላ 5፡22

4. ታማኝነት፡- 1 ቆሮ 4፡2 ዕብ 3፡5-6 1 ጢሞ 1፡12

---- ለእግ/ር

----- ለሰዎች

----- ለአገልግሎት

5. ትጋት

ምሳ 12፡241 ቆሮ 16፡13 ምሳ 21፡5 ዕብ 6፡10-12

6. ትግስትና ፅናት

1 ቆሮ 15፡58 2 ጢሞ 4፡2-5 ያዕ 5፡8-10

V. ወንጌል መመስከር

2 ነገስት 7፡9

መልካም አላደረግንም ዛሬ የመልካም የምስራች ቀን ነው እኛም ዝም ብለን እስኪነጋ ድረስ ብንቆይ በደለኞች እንሆናለን
ኑ እንሂድ ለንጉሱ ቤተሰብ እንናገር ተባባሉ ሉቃ 2፡10—11

17
በታደሰ ሁሪሳ

ወንጌል ምንድነዉ ሮሜ 1፤1-3 ፤ሉቃ 4፤18-19 ኢሳ 61፤1-3

ወንጌል ፤-የምስራች ነዉ

፤-መልከም ዜና

፤-የእግዚ/ር የማደን ሐይል ነዉ

ይህ ወንጌል

1.ለድሆች የምስራች ነዉ

ድሆች፤-በመንፈሰዊ ህይወታቻዉ ራሃብና ጥመት የጠቀቸዉ

፤-እዉነትን ለማዋቅና ለመከተል የተጠሙ

፤-በዉስጠቻዉ የነፍስ ጩኃት ለለበቸዉ

፤-በነብሰቸዉ የሚቅበዘበዙና የሚንከረተቱ

፤-የህይወት ትርጉም የጠፈበቸዉ

ማቴ 5፤3-6 “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፅአን ናቸዉ መንግስተ ሰማየት የእነርሱ ናትና”

“ጽድቅን የሚረቡና የሚጠሙ ብፅአን ናቸዉ ይጠግበሉና”

2.ለታሰሩት መፈተትን የሚሰጥ ነዉ/የተጨቆኑትን ነፃ የሚየወጠ ነዉ/

 በመንፈሰዊዉ ዓለም ሁለት መንግስት አለ


የእግዚ/ር መንግስትና የሰይጠን መንግስት ሰዉ የግድ ከሁለቱ መንግስት ለአንዱ ይገዘል ለአንዱ በፍቅርና
በዉዴታ ለሌለኛዉ በግዱታ
 የእግዚ/ር መንግስት የነፃነት፤የሰለም፤ የደስታ፤የጽድቅና የዘላለም ህይወት መንግስት ነዉ፡፡
 የሰይጠን መንግስት የባርነት፤የጨለማ፤የጭንቅ፤የርኩሰት፤ሰለምና ደስታ የሌለበት ሞት የነገሰበት መንግስት
ነዉ፡፡
ወንጌል ከሰይጠንና ከሐጢአት ባርነት ነፃ ያወጠል፡፡

3.ለተወሩት ማየትን የሚሰጥ ነዉ

የሰዉን የመንፈስና የአእምሮ ጨለማ የሚያበራ ወንጌል ብቻ ነዉ፡፡


2 ቆሮ 4፤3-6 “የእግዚ/ር ምሰሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንደያበረለቸዉ የዚህ ዓለም አምለክ
የማየምኑትን አሰብ አሰወረ--“
“--በክርስቶስ ፊት የእግዚ/ርን የክብሩን እዉቀት ብርሃን እንድሰጥ በልበቸዉ ዉስጥ የበራ በጨለማ ብርሃን
ይብራ የለ እግዚ/ር ነዉና፡፡”
 ሰይጠን ያጨልማል ወንጊል ያበራል፡፡

4.ወንጌል የእግዚ/ር የማደን ኃይል የሚገለጥበት መንገድ ነዉ፡፡1 ቆሮ 1፤18-25 ሮሜ 1፤16

--ከመንፈሰዊ ሞት የሚደንበት

--ከሰይጠን ባርነት ነፃ የሚወጠበት

--ከኃጢአት ኃይል የሚንፈተበት

--ከበሽታ የሚንፈወስበት

18
በታደሰ ሁሪሳ

“ለሚየምን ሁሉ የእግዚ/ር ኃይል ለማደን ነዉ፡፡”

‹‹ እነሆ ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምስራች እነግራችኃለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱ
ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኃልና፡፡››

የወንጌል ቃል ዛሬ መነገር ያለበት ሰዎችን ከሞት ከሀዘን ከሐጢያትና ከጭንቀት የሚያድን የምስራች መልዕክት ነው ፡፡

ይህ የምስራች ለሰዎች ለማድረስ ሰዎች የተለያዩ አይነት የወንጌል ስርጭት ዘዴን / የአመሰካከር ዘዴን / ይጠቀማሉ
ሁሉም የራሳቸው ጠቀም ጎን አላቸው ከሁሉም ዘዴዎች በጣም ምቹና ውጤታማ የሆነው ዘዴ በነፍስ ወከፋ ወይንም
አንድ ለአንድ ወንጌልን የመመስከር ዘዴ ነው ፡፡

ይህ ዘዴ ተመራጭ የሆነባቸው ምክንያቶች ፡-

ሀ. ወንጌልን መመስከር የክርስቲያን ሁሉ ሃላፊነት ስለሆነ ይህ

ሁሉንም የሚያሰትፍ በመሆኑ

ለ. የተመሰከረላቸውን ክትትል ለማድረግ ስለሚመች

ሐ. የተመሰከረለት ሰው ለመጠየቅና የበለጠ ለመረዳት ዕድል ስለሚሰጠው

መ. በጊዜያዊ ስሜት ሳይገፋፉ አስበው ለመወሰን ስለምያስችል

ሠ. በአጭር ጊዜ ብዙ ሰዎች ለማድረስ ስለማያስችል

ረ. ጊዜንና ገንዘብን ስለሚቆጥብ ሰው ሁሉ በራሱ ጊዜ የሥራና

የመኖሪያ ሠፈር ልሠራው ይችላል ፡፡

1. ወንጌል መመስከር ያለብን ለምንድነው;

ሀ. የጌታ ትዕዛዝ ስለሆነ

 አንድ ትዕዛዝ ከባድ የሚያደርገው ትዕዛዙን የሰጠው ሰው ያለው ስልጣን ነው ፡፡ ኢየሱስ ስልጣን ሁሉ በሰማይና
በምድር ተሰጠኝ አለ ማቴ 28፡18—20 ማር 16፡15-20 ዮሐ 20፡21 ሉቃ 24፡42-48
ለ. ጌታ ህይወቱን የሰጠበት ጉዳይ ስለሆነ የሐ 3፡14-15 ሮሜ 3፡6-10
ሐ. የሰዎችን ህይወት ከሲሆል የማዳን ጉዳይ ስለሆነ ዮሐ 5፡24 3፡17-18

መ. ከደህንነታችን ጋር የተያያዘ ስለሆነ 1 ጴጥ 2፡9 ሮሜ 10፡8 -10

ማቴ 10፡32 -33

ሠ. የአጥቢያ ቤተክርሲቲያን ህልውና የተመሰረተው በወንጌል ስርጭት ላይ ስለሆነ

ወንጌልን የማትመሰክርና የማትበዛ ቤተክርሲቲያን ትሞታለች ፡፡

“ በምዕራብ አለም / አውሮፓና አሜርካ / ያሉ አብያተክርሲቲያናት እየሞቱ ያሉት ወንጌልን መመስከር ስላቆሙና
የወንጌልን አገልግሎት ለተወሰኑ አገልጋዮች በመተዋቸው ነው ፡፡

2. ወንጌል መመስከር ያለበት ማን ነው;

“በጌታ አምነው ብርሃን የበራላቸው የኃጢአት ይቅርታ ያገኙ፣ የእግ/ር ልጆች የሆኑ የእግ/ር ሕዝብ በሙሉ ኢሳ 43፡10”

እናንተ የመረጥሁት ባሪያዬ ምስክሮቼ ናቸው “1 ጴጥ 2፡9 ሮሜ 10፡8-10 ማቴ 5፡4 -16 ፊል 2፡14-16

3. የክርስቶስ ምስክሮች ለመሆን የሚያበቃን ምንድነው;

19
በታደሰ ሁሪሳ

ሀ. ክርስቶስን እንደሚገባ ማወቅ

ስለእርሱ ሳይሆን እርሱን ማወቅ ሐዋ 4፡20 5፡27-32 ዮሐ 15፡26

ለ. ማዳኑን በህይወታችን ማየታችን

 የሐጢያት ይቅርታ / የነፍስ ደህንነት / አግኝተናል


 ከብዙ መከራ ጭንቀት ድነን ሰላም አግኝተናል
 ከሥጋ ደዌ ተፈውሰናል ዮሐ 9፡1-14

ሐ. የእግ/ር ቃል ሙላት ቆላ 3፡16 ኤር 23፡28 -30 ሕዝ 11፡19-20 36፡26

ዕብ 4፡12

መ. ለሰዎች ያለን ፍቅር

 ክርስቶስ የሞተው ሰዎችን ስለሚወድ ነው/ የሰዎችን ጥፋት ስለማይወድ ነው / ዮሐ 3፤16-17


 እኛም ለሰዎች ካለን ፍቅር በመነሳት መመስከር ይገባናል 1 ዮሐ 4፡8-21
ሠ. የመንፈስ ቅዱስ ኃይል መቀበላችን ሐዋ 1፡8
 ለየትኛውም አገልግሎት ብቃትን የሚሰጥ መንፈስ ቅዱስ ነው 2 ቆሮ 3፡5-6
“ ብቃታችን ከእግ/ር ነው እንጂ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳች እንኳን ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም እርሱ
ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን ፡፡”

 የመንፈስ ቅዱስ መሰጠት ከወንጌል ምስክርነት ጋር በግልፅ ተያይዞ ተፅፎዋል


ሐዋ 1፡8 ዮሐ 16፡14 ሉቃ 12፡12

4. ለወንጌል ምስክርነት ስንወጣ ከማን ጋር ነው የምንሠራው;

ሀ. ከእግ/ር አብ ጋር

 የመጀመሪያው ወንጌላዊ ሰው ፍለጋ የወጣ እግ/ር ራሱ ነው ዘፍ 3፡1


 ለሰው ልጆች ኃጢአት ልጁንም የሰጠው እግ/ር ነው ዮሐ 3፡6
 ከጌታ ከኢየሱስ ጋር ሠርቶአል
 ከአማኞች ጋርም ሠርቶአል ይሠራልም 1 ቆሮ 3፡6-9
ለ. ከጌታችን ከኢየሱስ ጋር ማቴ 28፡20 ማር 16፡19-20

ሐ. ከመንፈስ ቅዱስ ጋር

 መንፈስ ቅዱስ መስካሪዎችን ይልካል ሐዋ 13፡1-5


 ከጌታ የሆነውን ወስዶ ይናገራል ዮሐ 16፡14-16
 ምሪትን ይሰጠናል ሐዋ 10፡19-20 16፡6-7
 የጥበብን ቃል ይሰጠናል ሉቃ 21፡15 12፡11-12
 ሐይልን ይሰጠናል ሐዋ 1፡8
መ. ከቅዱሳን መልአክት ጋር
መላእክት በወንጌል አገልግሎት ትልቅ ድርሻ አላቸው
 የጌታን መፀነስ ያበሰሩ እነርሱ ናቸው ለዮሴፍ ማቴ 1፡20 ለማርያም ሉቃ 1፡26 -30
 የጌታን መወለድ ለእረኞች የተናገሩት እነርሱ ናቸው ሉቃ 2፡8-15
 የጌታን ትንሳኤ ለእነ ማርያም ያበሰሩ እነርሱ ናቸው ሉቃ 24፡1-4
 እርገቱንና ዳግም ምፅአቱን ለደቀመዘሙርት የገለጡ ሐዋ 1፡10
 መዳን የሚወርሱትን ለማገዝ ይልካሉ ዕብ 1፡13-14
 የሚድኑትን ያዘጋጃሉ ሐዋ 10፡3—6
 የሚያገለግሉትን የእግ/ርን መልዕክት ይነግሩአቸዋል ሐዋ 16፡26-37

20
በታደሰ ሁሪሳ

5. በምስክርነታችን ውጤታማ ለመሆን ሊኖረን የሚገባ የህይወት አቋም

ሀ. በስርዓት የታነፀ ህይወት / Disaplined / 2 ጢሞ 2፡3-6

 እንደ ወታደር ተዘጋጅቶ መኖር


 በውድድር እንደ ሚሳተፍ ሰው ልምምድ ሠርቶ እንደሚገባ መታገል
 እንደ ታታሪ ገበሬ የምገባውን ሠርቶ በእምነት መዝራት
ለ. በፅኑ ውሳኔ የሚኖር ህይወት
 ጌታን ሁል ጊዜ ለመከተል የወሰነ
 ምሳሌነት የለው ህይወት ለመኖር 1 ጢሞ 4፤11-16
 ሳየቐርጡ ለመመስከር ሰዎችን ወደ እግ/ር መንግስት ለማምጣት የወሰነ ሉቃ 9፡61-62

“ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኃላ የሚመለከት ለእግ/ር መንግስት የተገባ አይደለም

ሉቃ 9፤61-62

“ወንጌልን አደራ ይሰጠን ዘንድ እግ/ር የታመንን ሆነን እንድንገኝ መጠን እንዲሁም እንናገራለን 1 ተሰ 2፤4

ሐ. ለክርስቶስ መከራን ለመቀበል የተዘጋጀ ህይወት ፊል 1፡27-30

ማቴ 16፡24 -27 2 ጢሞ 3፡12

 ክርስቶስን ማገልገል ብቻ ሳይሆን መከተል ዋጋ ያስከፍላል


 በትክክል ጌታን የሚከተል ሰው መስቀሉን ተሸክሞ ነው የሚከተለው
 የጌታን ክብር የምንካፈለውም መከራውንም አብረን ስንካፈል ነው
ሮሜ 18፡17

6. ወንጌልን እንዳንመሰክር ሰበብ የሆነብን ነገሮች ምንድን ናቸዉ

 ሰበብ ምክንያት አይደለም

 ስለክርስቶስ መመስከር አስፈላጊነት በደንብ ከገባን ለመመስከር ሰበብ እንጂ ምክንያት ከቶውን
ሊኖረን አይችልም ፡፡
 ሰዎችን ለዘላለም እሳት ከማውጣት የበለጠ አንገብጋቢና አስቸኳይ ሥራ ልኖር አይችልም
ሰበቦቸችንን አውቀን እንድናስወግዳቸው እግ/ር ይፈልጋል

ሀ. አጓጉል ፍርሃት

 ጤናማ ፍርሃት አለ ሰው፣ ሞትን ፣እንሰሳን ፣እሳትን ፣ መኪናን ፣ ይፈራል


 ነገር ግን መኪናን ፈርቶ ከቤት አለመውጣት አጓጉል ፍርሃት ነው
 ወንጌል መመስከር ከሚያስፈራሩን ነገሮች መካከል አንዱ ሰው ነው መጽሐፍ ቅዱሳችን ደግሞ ሟች የሆኑትን
ሰዎች እንደሳር የሚጠወልጉትን የሰውን ልጆች ለምን ትፈራለህ; ይላል ኢሳ 51፡12 ደግሞም በማቴ 10፡28
ላይም ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ ይልቁንም ነፍስንም ሥጋንም
በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ ብሎ ይናገረናል
ለ. የሌሎች ሰዎች ሥራ አድርጎ ማየት
 ወንጌልን የመመስከር ስራ ለወንጌል አገልግሎት ሙሉ ጊዜአቸውን ለሰጡ ሰዎች እና በቤተክርስቲየን
ለተቐቐማ የምስክርነት ቡድን ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉም አማኞች አገልግሎት ነው

ሐ. ጊዜ የለኝም ብሎ ማመካኘት

 ብዙ ጊዜ የለኝም የሚሉ ሰዎች ብዙ ሥራ የሌላቸው ሰዎች ናቸው


 ጊዜ የለኝም የሚሉ ሰዎች በዕቅድ የማይመሩ ስለሆነ ያገኘ ሁሉ የሚወስዳቸው ሰዎች ናቸው
 በዕቅድ የማይኖር ሰው የጊዜም የገንዘብም እጥረት ያጋጥመዋል ፡፤

21
በታደሰ ሁሪሳ

 ወንጌልን ለመመስከር የተለየ ጊዜ አያስፈልገንም ወደ ስራ ስንሄድ በሥራ ቦታችን ላይ ከሥራ ስንመለስና


በመኖሪያ ስፍራችን ውስጥ ልንመሰክር እንችላለን ፡፡

መ. አስፈላጊነቱን አለማመን
 አንዳንድ ሰዎች እግ/ር የምህረት አምላክ ስለሆነ ሰዎች ወደሶኦል አያወርድም ሁሉንም ያድናል ብለው ያስባሉ
ሠ. አልችልም / አልበቃም / በሚል የዝቅተኝነት/ የበታችነት/ ስሜት መያዝ በእውቀት በእድሜ በፆታ በበታችነት
ሀሳብ መያዝ

 ምስክርነት ያየነውንና የገባንን የተደረገልንን ለሌሎች መነገር እንጂ ጠለቅ ወዳለ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ገብተን
ማብራሪያ የሚሰጥበት አይደለም
ረ. ምቹ ጊዜ መጠባበቅ
 አንዳንድ ሰዎች ጌታን ማገልገል እንዳለባቸው ያምናሉ ነግር ግን ጊዜው አሁን አይደለም ይላሉ ይህ ሲሟላ እዚያ
ስደርስ ይላሉ ዛሬ ለአንድ ሰው መመስከርን ሳይደፍሩና ሳይለማመዱ በትላልቅ መድረኮች ላይ ቆመው
ለመመስከር ያልማሉ
 እግ/ር ስርዓት ባለው ዕድገት ያምናል
“በጥቂቱ የታመነ በብዙ ይሾማል “ማቴ 25፡21
 ወንጌል ለመመስከር ከዛሬ የተሸለ ቀን አይመጣም በደርግ መንግስት ጊዜ ብዙ ሰዎች ይህ የመከራ ጊዜ ሲያልፍ
በደንብ እንመሰክራለን ይሉ ነበር ነገር ግን ነፃነቱ ሲመጣ ባሰ መመስከር የማንችልበት ሁኔታ ውስጥ ገባን
 ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ምንም ሊሰራ የማይችልበት ሌሊት ትመጣለች ዮሐ 9፡4 ወገን ሆይ
ከዛሬ የተሸለቀን የለም አይመጣምም ዛሬን ተጠቀምበት

ሰ. ውጤት ባላገኝ ብሎ መስጋት / ሰዎች በይሰሙኝ/

 ገበሬ በእመነት በእርሻው ላይ ዘርን ይዘራል ማሳውም ዘሩን ያበቅላል ነገር ግን የዘሪሁት ባይበቅልስ ብሎ
የሚያስብ ከሆነ መዝራት አይችልም
 ነገር ግን ምንም እንኳን ዘሩን በእምነት ብዘራም ማሳውን መለስለሱን እውቀቱን መለየቱን ግን አይረሳውም
 የተዘራው ዘር ሁሉ እንደማይበቅል ግልፅ ነው ወፎች የሚለቅሙትን በጭንጫ መሬት ላይ የሚወድቅና
አረም የሚውጠው አይጠፋም ፡፡ የእኛ ድርሻ አስቀድሞ መፀለይና የሰዎችን ልብ መንፈስ ቅዱስ በቃሉ
እንዲያዘጋጅ ጊዜ በመውሰድ ቃሉን በእምነት መዝራት ነው የሚያሳድግ እግ/ር ነው
 እኛ ለሰዎች የእግ/ርን መልዕክት ማድረስ እንጂ ሰዎችን ማሳመን አንችልም ፡

7. ለመመስከር ስንወጣ ልንከተላቸው የሚገቡ እርምጃዎች ምንድናቸው

ሀ. በመንፈስ ቅዱስ ላይ መደገፍ

 በምስክርነት ወቅት ዋናው ሠራተኛ መንፈስ ቅዱስ ነው እኛ የሚጠበቅብንን ዝግጅት አድርገን


በሥፍራው መገኘት ነው ፡፡ ማር 13፡11
 በዚያ ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና “
ሉቃ 21፡15
ወደረኞቻችሁ ሁሉ ሊቃወሙና ሊከራከሩ የማይችሉት አፍና ጥበብ እሰጣችኃለሁ
ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ እያሳበብን ዝግጅቱን ቸል ብንል / መፀለይና ማንበብን/ ውጤቱ ጥሩ አይሆንም
መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ካለው መዝገብ አውጥቶ ነው የሚሠራው

ለ. የት ጀምረን የት መጨረስ እንዳለብን ማወቅ

 የእግ/ር ፍቅር ዮሐ 3፡16


 የሰው ኃጢአተኝነት ሮሜ 3፡23
 የኢየሱስ ብቸኛ አደኝነት ሐዋ 4፡12
 ንሰሃ ገብቶ በጌታ ማመን

ሐ. ስንመሰክር ብዙ ጥቅስ አለማብዛት

22
በታደሰ ሁሪሳ

መ. የሌሎችን እምነት ከመንቀፍና የድፍረት ቃላትን ከመጠቀም መጠበቅ

ሠ. የምስክርነታችን ዋና ነገር ክርስቶስ ማድረግ

ረ. የተመሰከረለት ሁሉ መዳን አለበት ብሎ መለመጨነቅ

ሰ. አለባበስን በስርዓት ማድረግ

ሸ. ቢቻል ሁለት ሁለት መሆን አለበት አለዚያ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት ብንመሰክር ከተለያዩ ፈተናዎች እንጠበቃለን

8. ለምስክርነት ስንወጣ ምን አይነት ሰዎች የገጠሙን ይሆን

ሀ. ፍላጎት እያላቸው የሚቀሰቅሳቸውን ሰው የሚፈልጉ

ለ. ፍላጎት እያላቸው የሚጠረጠሩ ሰዎች

ሐ. ፍላጎት እያላቸው የሚከራከሩ ሰዎች

መ. ፍላጎት እያላቸው በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓት የተያዙ

ረ. መስማት የማይፈልጉ ከሃዲዎች

ሰ. አማኞች ላይ ጉዳት ማድረስ የሚፈልጉ በልዩ ልዩ ሃይማኖት ቀናተኞች የሆኑ

ሸ. የሀሰት አስተማሪዎች

ቀ. ንሳሃ ለመግባት የተዘጋጁ ሰዎች

በ. ከኃጢአትና ከሰይጠን ፈተናዎች የተነሰ ተስፋ የቆረጡ ሰዎች

9. መመስከር ቢፈልግ ሰዎችን የት አገኛለሁ;

ሀ. ቤተሰብና ቤተዘመድ

ለ. ጎረቤትና ጓደኛ

ሐ. በሥራ ቦታና በት/ት ቤት የምናገኘችው ሰዎች

መ. በእግ/ር ጉዞ ወቅት / በመኪና / በአውሮፕላን ጉዞ

ሠ. በሆስፓታሎችና በማረማ ቤቶች

ረ. ሆን ብሎ ለመመስከር ወደ ሰዎች መሰብሰቢያዎች፣መኖሪያ ቤቶች ፣የመኪናፌርማታዎች በመሄድ

23

You might also like