You are on page 1of 11

ዲያቆንያ የሥነ መለኮት ኮሌጅ ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ

የድህረ ምረቃ መርሃ ግብር

አረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን አገልጋይ መሪነት አስተሳሰብ


ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው በእግዚአብሔር ቃል አኳያ እንዴት ይታያል?

ጥናታዊ ጽሑፍ

አለማየሁ ካሣ

አማካር

ዶ/ር ወንጌላዊ ተስፋዬ በላቸው

2013 ዓ.ም

ወላይታ ሶዶ

1
ምዕራፍ አንድ

1.1 መግቢያ
አገልጋይ መሪነት አብዛኛውን ጊዜ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚያያዝ ቃል ወይም ሐረግ ነው፡፡ አገልጋይ

መሪነት ምን ማለት እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ከተተገበረው ልምድ ማግኘት እንችላለን፡፡ ሰለአገልጋይ

መሪነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት መማርና ከዛሬው የቤተሰቦቻችን፣ የቤተክርስቲያን፣ የማህበረሰብና

የድርጅቶች ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ማዛመድ ከባድ ተግዳሮት ነው፡፡ ይህንን ጥናታዊ ጽሑፍ ለማዘጋጀት ይህ

የመጀመሪያው አነሳሽ ምክንያት(Motivation) ነበር፡፡ ይህንን ጥናታዊ ጽሑፍ ለማዘጋጀት ከመጀመሬ በፊት

ራሴን የጠየኳቸው ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ አንደኛ፣ በዛሬው አውድ አገልጋይ መሪነትን የምንረዳው እንዴት ነው?

ሁለተኛ፣ የአገልጋይ መሪነትን ባህሪያት በዕለት ተዕለት ኑሮዬ እንዴት እያዛመድኳቸው ነው?

አገልጋይ መሪ ለመሆን እየተማርን በእያንዳንዱ ቀን ኑሯችን የበለጠ ወደ እርሱ ወደ ክርስቶስ መቅረቡን

እንማራለን፡፡ የአገልጋይ መሪነት መሰረትና ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን

በመሪነት የሚያገለግሉ ሁሉ በትህትናና እግዚአብሔርን እየሰሙ የሚሄዱ የጌታ ደቀ መዝሙር ስለሆኑ

በሁሉም ኑሯቸውንና አካሄዳቸውን ለክርስቶስ ለመኖርና ለእግዚአብሔር ክብር ሁሉን ለማድረግ የተጉ ይሆኑ

ዘንድ ነው፡፡ ይህ ይሆን ዘንድ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት በሕይወታችን ቅድሚያ ያለው መሆን አለበት፡፡ አገልጋይ

መሪ ቃሉ እንደሚለው ትዳር በሚገኝበት ንግድ የግል ኑሮ ትርፍ፤ ዕድገት ወይም ጥቅም ፍለጋ ውስጥ

የተጠላለፈና በዚያ የተገዛ መሆን የለበትም፡፡ ከዚያ ይልቅ የጌታውን ትዕዛዝ ሰምቶ የሚታዘዝ በመንፈስ ቅዱስ

ምሪት በየዕለቱ የሚጓዝ መሆን አለበት፡፡ በሰዎች ሕይወት ውስጥ እንደተለመደው ምድራዊ ክብር ለመፈለግና

የራስን ጥቅም ለመሻት በመባዘን ላይ ያሉ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ለይቶ ለማወቅ፤ ለመስማትና

ለመታዘዝም አደጋችና ፈታኝ ይሆንባቸዋል፡፡ ለጌታ ለመታዘዝ ፈቃደኛ የሆኑ በምድር ላይ በተሰጣቸው ዘመን

ዘላለማዊ የሆነውን የጌታን ፈቃድ የሚፈጽሙ ይሆናሉ፡፡ የመሪዎች የአገልጋይነት አመራርና ሕይወት ለዛሬም

ሆነ ለነገዋ ቤተክርስቲያን ዕድገት መንፈሳዊ ጤንነትና ተልዕኮ አፈጻጸም ብርቱና ጉልህ የወሳኝነት ሚና

ይኖረዋል፡፡

አረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት የተመሰረተው በኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን

ህብረት ዕውቅና መሰረት ሲሆን ከሃያ ዓመት በላይ ዕድሜ አስቆጥሯል፡፡ የተመሰረተበትም ዓላማ በአረካ

ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ከቤተ እምነቶች ጋር በአንድነት ወንጌልን ለመስራት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ይህ የአብያተ

1
ክርስቲያናት ህብረት ከሃያ ዓመት በላይ ያስቀጠረ ሲሆን እንደ ዕድሜው ታማኝ አገልጋይ መሪዎችን

በማፍራት አልዳበረም፡፡ አጥኚው በዚህ ህብረት ውስጥ እንደ አባል እና እንደ ትርፍ ሰዓት አገልጋይ ለሰባት

ዓመታት ያህል መሻሻል የሚሹ የተለያዩ ችግሮችን አስተውሏል፡፡ አጥኚው በህብረት ውስጥ በሚገባ የታጠቁ

እና ታማኝ አገልጋዮችን ለማየት በመጓጓቱ በጥናቱ ለእነዚህ ችግሮች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መፍትሄ ለመፈለግ

እና ለመጠቆም ሞክሯል፡፡

1.2. የጥናቱ አደረጃጀት


ጥናቱ አምስት ምዕራፎች አሉት፡፡ ምዕራፍ አንድ የጥናቱ መግቢያ፣ የጥናቱ ዳራ፣ አነሳሽ ምክንያት፣ የጥናቱ
ዓላማ፣ የምርምር ጥያቄዎች፣ የችግሩ መገለጫ፣ የጥናቱ ጠቀሜታና ወሰን ያካትታል፡፡ በምዕራፍ ሁለት ደግሞ
ክለሳ ድርሳን በሚል ርዕስ በጥናቱ ርዕስ ዙሪያ የተለያዩ ፀሐፍት የሰጡትን ንድፈ ሐሳብና ቀደምት ጥናቶች ካሉ
የሚቃኙበት ነው፡፡ በምዕራፍ ሦስት ጥናቱ የሚከተለውን ዘዴ የሚብራራበት ሲሆን ምዕራፍ አራት ለጥናቱ
የተሰበሰቡ መረጃዎች ትንተናና የውጤት ማብራሪያን ይዟል፡፡ በመጨረሻም በምዕራፍ አምስት በተገኘው
የጥናት ውጤት መሰረት የድምዳሜ ማጠቃለያና የአጥኚውን አስተያየት ወይም የመፍትሔ ሃሳብ በማቅረብ
ይቋጫል፡፡

1.3. የጥናቱ ዳራ

አገልጋይ መሪ በማንኛውም ቦታ በህዝብ ተወካይነትም ሆነ በድርጅት እንዲሁም በቤተክርስቲያን ውስጥ

ሊሰራ የሚችል እውነተኛና አገልጋይ የሆነ የመሪ ባህሪይ የሚታይበት ነው፡፡ አገልጋይ (servant= በግሪክ

Diakonos) ማለት እንጂ ባሪያ (Slave/ Bondsman or Dulos) የሚለው ማለት አይደለም፡፡ አዳዲስ ሰዎች

አገልጋይ መሪ በቤተክርስቲያን ብቻ መታየት ያለበት ሊመስላቸው ይችላል፡፡ ይህ በርግጥ በሁሉም ስፍራ

ሊታይ የሚገባው የአገልግሎት ሰጪነት አመራር ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዚህ ስልት ዋነኛ ሞዴልና

አራማጅ ነው፡፡ የራሱን ክብርና ዝና የማያዳምጥ ራሱን ለሰው የሰጠ እንዲህ ያለ መሪ በቀላሉ ለማግኘት

ያስቸግራል በማለት (ተሾመ፣2007፣106) ገልፀዋል፡፡ የአገልጋይ መሪነት መሰረትና ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ

ነው፡፡ መሪነት ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶች አንዱ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ

አገልጋይ መሪነት ያስተማረው በሎሌነት ማገልገል ነው፡፡ “በእናንተ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም

ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፤ ከእናንተ ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የእናንተ

ባሪያ ይሁን፡፡” (ማቴዎስ 20፡26-28)፡፡ አገልጋይ መሪነት ማለት ሰዎችን በሰዎች አማካይነት የማከናወን ጥበብ

ነው። እንዲሁም የታሰበውን አላማ ለማሳካት ሃሳቦችን፣ ሰዎችን፣ ነገሮችን፣ ጊዜን እና እምነትን የማዋሃድ

ጥበብ ነው፡፡
2
ግሪንሌፍ (1977/2002) “አገልጋይ መሪ በመጀመሪያ አገልጋይ ነው፡፡” አጀማመሩ ራሱ የአገልጋይነትን መንፈስ

በመያዝ ከመሆኑም በላይ፤ በቅድሚያ ሌሎችን ለማገልገል እንጂ ለመገላገል ከመፈለግ አንጻር አይደለም፡፡

አገልጋይ መሪ የሚያገለግለው ሕዝብ ፍላጎቶችን ለማሟላት በከፍተኛ ደረጃ ቅድሚያው አድርጎ ይወስዳል፡፡

የአገልጋይ አመራር(Servant Leadership) ዋና መለኪያው (የራሱን የአገልጋይ መሪነት) ለመገምገም አስቸጋሪ

ቢሆንም ለሚከተሉት ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ በመስጠት እንደሆነም ያምናል፡፡ የማገለግላቸው ሰዎች

እንደግለሰብ አድገዋል? ባገለገልኳቸው ዘመናት ሁሉ የበለጠ ጤነኞች፤ ነጻ የሆኑና በእግራቸው መቆም

የሚችሉ እና ራሳቸውም አገልጋዮች ለመሆን የበቁ ሆነዋልን? በተለያዩ የኑሮ ሁኔታዎች ዝቅተኛ ዕድል

የነበራቸው ሰዎች ከነበሩበት ሁኔታ ወደ ተሻለ ኑሮ ተሸጋገረዋል ወይንስ ወደ ባሰ ድህነት አሽቆልቁለዋል?

ካለኝ አመራር ተጠቃሚ ሆነዋል፤ ወይንስ ለእርከን መወጣጫ፤ መጠቀሚያ አድርጌአቸዋለሁ? ግሪን ሊፍ

ያቀረበውን የአገልጋይነት አመራር እሳቤ ለመረዳት እንዲያስችል ላረስ ፒርስ የሚባል በአስር ጉዳዮች

ቋጭቶታል፡- “መስማት፤ መረዳት፤ ርህራሄ፤ ፈውስ፤ የላቀ ንቁነት፤ ማራክ አቅራቦት፤ እሳቤ ማስተዋል፤ አርቆ

አሳቢነት፤ ባለአደራነት፤ ለሕዝብ ዕድገት ቅድሚያ መስጠትና ሕብረተሰቡን ማሳደግ ናቸው፡፡” ግሪን ሊፍ

ያመጣውን “የአገልጋይነት አመራር” (servant leadership) ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባለው ዓለምም ይሁን

በቤተክርስቲያን በሥራ ሲተረጎም ለመዋጥ የሚያስቸግር ከባድ እውነት ስለሆነ ብዙ መሪዎች ሃሰቡን

ለመቀበል ይቸገራሉ፡፡ ከዚህ ይልቅ የለመዱት የሚመሩትን ሕዝብ በኃይልና በግዴታ መምራት ይቀናቸዋል፡፡

ስቴኤል እና ቦምሌጅ (2004) መሪነትን ስግለጹ፡- መሪነት፣ርዕስ፣ወይም ሁኔታ አይደለም፡፡ ከፍተኛ ቦታን
መቆጣጠር ብቻ አይደለም። እንዲሁም ሀብት ለማከማቸት መሣሪያ አይደለም።ግን አንድ የጋራ ግቡን ሲመታ
ሌሎች ሙሉ አቅማቸውን እንዲደርሱ ማስቻል ነው፡፡ከላይ የቀረበው የስቲል እና ቦምሌጅ መሪነት
በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት እራሱን የሚመራ ሲሆን ከዛም በዛ ቃል ሌሎችንይመራሉ። መሪነት
ሰዎችን መሄድ ወደ ሚፈልጉበት ቦታ መውሰድ ብቻ አይደለም፡፡ መሄድ ወደ ማይፈልጉበት ቦታም ይወስዳል።
መሪነት አመራሮች ከሚመሩበት እና ለሰዎች የመሪነት ስሜት ከሚሰማቸው ስሜት በላይ ነው፡፡ የአገልጋይነት
አመራር የአንድን ሰው እንደ ሎሌ ወይም አገልጋይ ለሌላው በማስረከብ የሚገለጽ ርምጃ አይደለም፡፡ የሀገር
መሪነት በራስ የመተማመን መንፈስን የሚያነቃቃ ባሕርይ ጋር ተያይዞ የአገልጋይ ለጋራ ጥቅም መሪ ለሆኑ
ሰዎች ግብ በቅንዓት እንዲሰሩ ማሳደረ ነው (ሃንተር 2004)፡፡ ስቲቨን ኮቭ እንዳሉት የአገልጋይ መሪነት 'አየር እና
'ውሃ' ለሰብዓዊ መንፈስ ይሰጣል (ስፒርስ፣1998)፡፡ እሱ ከታች እየመራ ነው፣ከላይ ላይም ወይም ከላይ
አይደለም።በሥልጣን ብቻ ሳይሆን ከልብ የሚመነጭ ነው፡፡ ከላይ ባሉት ትርጓሜዎች መሠረት ተመራማሪው
የአገልጋይ መሪነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የአገልጋይ መሪን አምሳል ፍጹም በሆነ መልኩ ያሳየው
እውነተኛ መሪ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩ እና አሁን ያሉ በዓለም ውስጥ ያሉ መሪዎች ሁሉ

3
ከኢየሱስ የአመራር ቁርጠኝነት ጋር ሲወዳደሩ፣ተከታዮቻቸውን በሙሉ ለእነሱ እንዲሞቱ ልከው ነበር፡፡ ግን
ለሕዝቡ የሞተው ብቸኛው መሪ እና የተከታዮቹን እግር ያጠበ መሪ ኢየሱስ ነው፡፡ ተመራማሪው አሁን ያሉት
የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በዛሬው አማኞች ላይ በጎ ተጽዕኖ ለማሳደር ራሳቸውን መስዋት ማድረግ
እንዳለባቸው ያምናል፡፡ የዛሬዎቹን አማኞች እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የሰጠውን ዓላማ ለማምጣት
መሪዎቹ የአገልጋይነት መሪሆችን አስፈላጊ ባህሪዎች መከተል አለባቸው፡፡

እነርሱም፡ -

 ሌሎችን መውደድ እና ማክበር


 ሞገስ፣ታዛዥነት፣ታማኝነት እና መስዋትነት
 በትኩረት ማዳመጥ፣የሌሎችን ስሜት መረዳት እና አለመተው
 ጉዳት የደረሰባቸውን መፈውስ
 በኃይል ከመገፋት ይልቅ አማኞችን በፍቅር መያዝ
 ሰዎችን መንገድ ማሳየት እንጂ ከእነርሱ አለመራቅ
 ከፍ ከማድረግ ይልቅ ሌሎችን መገንባት
 ለሌሎች እድገት እና ፍጻሜ መስራት

 ግሪንሌፍ "አገልጋይ መሪ በመጀመሪያ አገልጋይ ነው አለ፡፡” ማለቱ የመገልገል ፍላጎት “የአገልጋዩ ልብ”

መሰረታዊ የአገልጋይ መሪ ባህርይ ነው፡፡ እሱ አገልጋይ መሆን ሳይሆን እሱ ሌሎችን ለመርዳት ስለመፈለግ

ነው። ይህ የሥራ ባልደረቦችን፣ ደንበኞችን እና ማህበረሰቦችን ፍላጎቶች መለየት እና ማሟላት ነው፡፡

የአገልጋይነት መነሻ ወይም ምንጭ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነትና ጥሪ ነው፡፡የቤተክርስቲያን የመሪነት

አገልግሎት በሚታይና በሚጨበጥ ሁኔታ በታማኝነት በቅንነትና በትጋት መፈጸም አለበት፡፡ የጌታ ደቀ

መዝሙር ሆነን የእርሱን ሕዝብ ለማገለገል የተመረጠን የእግዚአብሔር ዕቃዎች ሆነን እግዚአብሔር በእኛ

መስራት ይፈልጋል፡፡ የላቀ አገልግሎት መሰረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ የአገልጋይነት መጀመሪያውና

መጨረሻውም ከእግዚአብሔር ጋር ደቀ መዝሙሩ ያለው ሕያው የሆነ ጤናማ ግንኙነት ነው፡፡ የአገልጋይነት

ማንነት መነሻው ይህ ነው፡፡ ይህ በሥጋዊ አስተሳሰብና በአእምሮ ጡንቻ ለመፈጸም ቀላል አይደለም፡፡ በአንድ

ቀን ፍጹም የሚሆን ጉዳይ አይደለም፡፡ የነፍሳችን ትኩረት በየዕለቱ የእግዚአብሔር ሀሳብ መሆን አለበት፡፡

አገልጋይነት ራስን ሳይሆን ሌሎችን የሚጠቅም ሥራ ለመፈጸም ራስን፣ ጊዜን፣ ሁለንተናን መስጠት ነው፡፡

ከጌታ የተሰጠን ኃይል፤ ስልጣን፤ ዕውቀት፤ ክህሎት ለሌሎች ጥቅምና ዕድገት እንዲሆን ነው፡፡ መሪነት ኃይል

4
ያለው ግንኙነት ነው፡ በቤተክርስቲያን ለታቀደለት ዓላማ መዋል አለበት፡፡ ዓላማ የሌለው ኃይል ምንም ፋይዳ

የለውም፡፡

መሪነት ተጠያቂነት ጨምሮ ያለበት መሆኑን በመገናዘብና በማወቅ አገልግሎቱ መፈጸም ይገባቸዋል፡፡

ለአገልጋይ መሪ የጉልበት ምንጮች የእግዚአብሔር ቃል፤ የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት፤ የአዲስ ኪዳን ፀጋና

ምህረት እንዲሁም ለጥሪው ፈጽሞ መሰጠት ናቸው፡፡ እውነተኛ የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀ መዝመር መሆን

ኢየሱስ ክርስቶስን ሞደል አድረጎ መከተል ነው፡፡ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ባለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት

የለውጥ ሐዋርያትና ማህበረሰቡን ለበጎ የሚያዘጋጁ የዓለም ጨውና ብርሃን ሆነዋል (ማቴ. 5፡13-14)፡፡ በአዲስ

ኪዳን ዘመን በሕብረተሰብ ተቀባይነት የነበረውን ባህል የሚለወጥ ትምህርት ኢየሱስ አስተምሯል፡፡ የአገልጋይ

መሪነትን ማንነት ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያላቸውን ሥነ መለኮታዊ ትምህርቶችንና

የአስተምህሮ ፍልስፍናዎች ማጥናት የሚጠቅምና እጅግ አስፈላጊ አካሄድ ነው፡፡ ኢየሱስ ለሁላችን የሰጠን

ትዕዛዝ “እኔ እንዳደረግሁላችሁ እናንተም እንደዚሁ እንድታደርጉ ምሳሌ ትቼላችኋለሁ፡፡” ዮሐ. 13፡

15 /አመት/ የሚል ነው፡፡ ይህ ትዕዛዝ በአገልግሎታችን አካሄድ ድርሻችንን እንድናውቅ የሚረዳ ነው፡፡ የሥራው

ባለቤት እግዚአብሔር ነው፡፡ ሕዝቡ የእግዚአብሔር ነው፡፡ አለቃው እርሱ ነው፤ ትዕዛዝ ከእርሱ ሳይቀበሉ

እርሱን ሳይሰሙ የጌታን ሕዝብ ለመምራት አይቻልም፡፡ አገልጋይ መሪነት የጌታ ደቀ መዛሙር ስለሆነን

በሌሎች ዘንድ የተናቀ የሚመስለውን ቦታ በትዕግስት በእርጋታ ያለማንጎራጎር ለመቀበል ፈቃደኝነት ነው፡፡

አገልጋይ መሪ የጌታው አገልጋይ እንጂ የራሱ የሆነ ጥቅም፤ ክብርና ዝና ፈላጊ አይደለም፡፡አገልጋይ መሪ

ለሌሎች የሚኖር፥ የራሱ የሆነውን የማይመለከት፥ ከራሱ ዕድገት ይልቅ የጋራ ብልጽግናን የሚመኝ፥

የእያንዳንዱን ሰው ድካምና ብርታት በመረዳትና በቅርብ በመከታተል ለክርስቶስ ሙላት ለማድረስ የሚጥር

ነው፡፡ ተሾመ (2007፣ 110) ጎት ፍሬድ ኦሲሜንሳን ጠቅሶ አገልጋይ መሪ ራሱን ከህብረተሰቡ ነጥሎ የማያይ

መሆን አለበት፥ በተለይ አፍሪካዊ መሪ ግን ሁል ጊዜ ራሱን በህብረተሰብ ውስጥ ነው የሚያየው፡፡

አገልጋይ መሪነትን እጅግ አስቸጋሪ የሚያደርገው አንዱ ስልጣንና ጉልበት የለሌውና በትህትና የሚሰጥ

አገልግሎት የመሆኑ አካሄድ ነው፡፡ ራስን ዝቅ አድርጎ የማገልገል ግባችን ጌታን መምሰል ስለሆነ በሕይወታችን

የምናደርገውን ለሎች ያደርጉ ዘንድ ማሰልጠን አለብን፡፡ ስለዚህ እንደ ክርስቶስ ለራሳችንን በመሞት

በመሥዋዕትነት የምናገልገል መሆን አለብን፡፡

5
ለቤተክርስቲያን ተልዕኮ በተገቢው መንገድ በትጋትና በታማኝነት መፈጸም የመሪዎች የአገልጋይነት ሚና

ብርቱና ግንባር ቀደም ድርሻ አለው፡፡ የአምላካችን የእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ እጅግ ሰፊ ነው፡፡ ሥራውን

ለመፈጸም ታማኝ፣ ትጉ፣ ቅን፣ ለአገልግሎቱ በቃሉ መሰረት ሁለንተናቸውን መሰዋዕት አድረገው የሰጡ

አገልጋዮች ያስፈልጋሉ፡፡

የአንድ አገልጋይ መሪ አስተሳሰብ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ላይ መጎልበት ለአንድ ቤተ ክርስቲያን ታማኝ

ለሆኑ አገልጋዮች እድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህም ሊታይ የሚቻለው በጸሎት፣ ቀጣይነት ያለዉን

ስልጠና በመስጠት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ የቡድን መሪ ጊዜ በመስጠት፣ ለአመራሮች ግንዛቤ በማስጨበጥ

እና በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ አገልጋይ መሪዎችን በማፍራት ነው፡፡

1.4. የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት


የአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ህብረት ላለፉት ሃያ ዓመታት የሚሆን ጊዜ ያስቆጠረ አንጋፋ

የመንፈሳዊ ህብረትና ለከተማው ህብረተሰብ እንዲሁም ለአከባቢው፤ ለአገር፤ ለአህጉርና ለዓለም የሚጸልይ

የቤተ እምነቶች አንድነት ወይም ህብረት ነው፡፡ ይህ ሁሉም ቤተ እምነቶች በአንድነት የሚያመልኩበትና

ወንጌልን ለማስፋፋት አብሮ የሚሰሩበት አንዱ መንገድ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ባለው ሁኔታ ይህ ህብረት

ሙሉ በሙሉ ባይጠፋም መቀዛቀዝ ሁኔታ ይታይበታል፡፡ ለዚህ ምክንያት ይሆናሉ ብዬ የማምናቸው አንደኛ

በእግዚአብሔር የተመረጠና አደራን ተቀብሎ መስራት፣ ማስቀጠል፣ ለተተኪው ማስተላለፍና ማስፈጸም

የሚችል አገልጋይ መሪ ባለመኖሩ፤ ሁለተኛ በአከባቢው ያሉ አንዳንድ ቤተ እምነቶች አብሮ ከመቀጠል ይልቅ

ለብቻቸው ለማደግ መፈለጋቸው፤ ሶስተኛ ከአንድነት ይልቅ የየራሳቸውን ቤተ እምነት ለማገነን

መፈለጋቸው፤ አራተኛ የክርስቶስን ፈለግ በመከተል ዝቅ ብሎ ከማገልገል ይልቅ ስልጣንና ሹመት መፈለግ፤

አንዱ ቤተ እምነት የሌላውን ቤተ እምነት ፀጋ አለመቀበል… ወዘተ ችግሮቹን በማየት ከሥነ መለኮት

ትምህርት ቤት ባገኘውት ዕውቀት ምክንያት ጉዳዩን ተጠግቼ የማጥናት ፍላጎት አደረብኝ፡፡ በአገልጋይ መሪነት

(Servant Leadership) በተለያየ ቦታ ጥናት ቢደረግም በአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን አገልጋይ
መሪነት አስተሳሰብ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸውን በእግዚአብሔር ቃል አኳያ እንደት ይታያል በሚል በዚህ
ርዕስ ላይ በመጀመሪያም ሆነ ሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ ከዚህ በፊት የተጠና ጥናት አለማግኘቴ ዋነኛ አነሳሽ
ምክንያት ነው፡፡
በተጨማሪም የአገልጋይ መሪዎች አስተሳሰብ ከቦታ ቦታ፤ ከቤተ እምነት፤ በቤተ እምነት ልለያይ የሚችል
በመሆኑ እና የመሪዎችና የአገልጋዮች ማህበራዊና መንፈሳዊ ሕይወት የዕለት ተዕለት ውሎ ምን እና ማንን

6
እንደምመስል መግለጽ አለበት በሚል እምነት ጥናቴን በአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት
አገልጋይ መሪነት አስተሳሰብ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸውን በእግዚአብሔር ቃል አኳያ መለየት በሚል ርዕሰ
ጉዳይ ላይ ለማድረግ ተነሳስቻለሁ፡፡

1.5. የጥናቱ ዓላማ


አጠቃላይ ዓላማ፡- በአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን አገልጋይ መሪነት አስተሳሰብ ችግሮችና
መፍትሔዎቻቸውን በእግዚአብሔር ቃል መፈተሸ፡፡ በዚህ ዓቢይ አላማ ስር የሚካተቱ ንዑሳን ዓላማዎች
ደግሞ፡-
1. በአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን አገልጋይ መሪነት አስተሳሰብ ምን እንደመመስል መለየት፡፡

2. የአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን አገልጋይ መሪነት ችግሮችን መለየት፡፡


3. የአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ለአገልጋይ መሪነት ችግሮች መፍትሔዎቻቸውን መለየት፡፡

1.6. የጥናቱ መሰረታዊ ጥያቄዎች


1. በአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን አገልጋይ መሪነት አስተሳሰብ ምን ይመስላል?
2. የአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን አገልጋይ መሪነት ችግሮች ምን ምንድናቸው?
3. የአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ለአገልጋይ መሪነት ችግሮች መፍትሔዎቻቸው ምን
ምንድናቸው?

1.7. የችግሩ መግለጫ

መንፈሳዊ አገልጋይ መሪነት በሁሉም ቤተ እምነቶች ዉስጥ ለፈጣን እድገት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ በአረካ

ከተማ ቤተ እምነቶች ውስጥ አገልጋይ መሪነት ላይ ክፍተት አለ፡፡ በቤተ እምነቶች ውስጥ የመሪነት ሚና

እየተጫወቱ ባሉ የአንዳንድ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን መሪዎች መካከል የተለመደ የተሳሳተ የአስተሳሰብ

ግንዛቤ አለ፡፡ እነዚህ የተሳሳቱ አመለካከቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡- ወደ መሪነት የመጣነዉ በክብር፣

በስልጣን እና በማዕረግ ብሎ ያስባሉ ነገር ግን የአገልጋይ መሪነት መሰረትና ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

ከነዚህም ችግሮች በተጨማሪ እንደ መሪ ከቀድሞ መሪዎቻቸው እና ከሌሎች ከጎለመሱ ክርስቲያኖች

ስህተታቸውን ለመቅረጽ የሚያደርጉትን አስተያየቶች አይቀበሉም፡፡ ደግሞም እነሱ የሚመሯቸውን የሰዎች

የልብ ትረታ አይሰሙም። ነገር ግን ውሳኔያቸውን ብቻ እንዲስማሙ በኃይል ለማስገደድ ይሞክራሉ፡፡ እነሱ

መሪነትን በባህላዊ መንገድ ብቻ ማለትም በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ መሠረተ ባልሆነ ሁኔታ በራሳቸው

አስተሳሰብ ይለማመዳሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ቤተ እምነቶች ማለትም አንዳንድ ቤተክርስቲያን መሪዎች እና

7
ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ህብረት ላይ ታማኝነት እየመነመነ ነው፡፡ አሁንም

ችግሩ መፍትሄ አላገኘም ሌላ ጥናት የሚፈልግ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህ እና ሌሎች በ ወንጌላዊያን አብያተ

ክርስቲያን ህብረት ውስጥ ያሉ ዋና ዋና ችግሮች መሻሻል ያስፈልጋቸዋል፡፡ አጥኚው ይህንን ከግምት ውስጥ

በማስገባት ጥናቱን በአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ህብረት አገልጋይ መሪነት ውስጥ ጥናት

አካሂዷል፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮች የተከሰቱት በሚገባ የክርስቶስን ፈለግ በመከተል ራሳቸውን ዝቅ የሚያረጉ

ትህትህናን የተላበሱ ለተተክ መሪዎች ተምሳለት የሚሆኑ መሪዎች ባለመኖር፣ የህብረቱን ፋይናንስ ያለ

አግባብ በመጠቀም፣ ለውጥ ለማምጣት በመሪዎች መካከል አለመግባባቶች እና መሪዎች እራሳቸውን

ለማዘጋጀት ዝግጁ አለመሆኑ ወዘተ… ምክንያት ነው፡፡ ሌላም ደግሞ ውጤታማ አገልጋይ መሪ እንዴት መሆን፣

ምን መስራት፣ ማንን መምሰል፣ መቼና የት መስራት እንዳለበት አለመረዳት ነው፡፡ እንደ ህብረቱ አገልጋይ ይህ

ሁሉ ችግር ሊቀረፍ የሚቻለዉ በእግዚአብሄር ቃልና በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ነዉ ብዬ አምናለሁ!!

1.8. የጥናቱ ጠቀሜታ

ጥናቱ የሚከተሉትን ፋይዳ ያስገኛል ተብሎ ይገመታል፡፡

ሀ. በአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ለአገልጋይ መሪነትነት አስተሳሰብ ለውጥ አዲስ ሀሳብን
ያበረክታል
ለ. ከዚህ በኋላ በዚህ ርዕስ ዙሪያ ለሚደረጉ ሌሎች ጥናቶች መነሻ የሚሆኑ ሀሳቦቹን በመጠቆም ረገድ
አስተዋጾ ሊያደርግ ይችላል
ሐ. በአጠቃላይ ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ በአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን የህብረት መሪዎቹን፤
የእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ/ያን ሙሉ ጊዜ አገልጋዮቹን፤ መጋቢዎቹን፤ የወጣቶች መሪዎቹንና ለሎቹንም
የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ይረዳል የሚል እምነት አለኝ

1.9. የጥናቱ ወሰን


ይህ ጥናት ዋነኛ ትኩረቱ በአገልጋይ መሪነት አስተሳሰብ ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ ሲሆን ጥናቱ

የሚካሄድባቸው በአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ህብረት ከሚገኙት አሥራ ሶስት ቤተ

እምነቶች መካከል በአራቱ ቤተ እምነቶች ላይ አተኩሯል፡፡ እነርሱም ሙሉ ወንጌል፤ መሠረተ ክርስቶስ፤ መካነ

8
ኢየሱስ እና ሕይወት ቃል ናቸው፡፡ ይህ ከተማና እነዚህ ቤተክርስቲያናት የተመረጡበት ምክንያት አጥኚው

ካለው የጊዜና የገንዘብ እጥረት የተነሳ መረጃ ለመቀበልና ለመሰበሰብ ምቹ በመሆናቸው ነው፡፡

ሰለዚህ ይህ ጥናት በአረካ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን አገልጋይ መሪነት አስተሳሰብ ችግሮችና
መፍትሔዎቻቸውን በእግዚአብሔር ቃል መፈተሽና በአራቱ በተመረጡ ቤተ እምነቶች ብቻ ይገደባል
ሌሎችን አይመለከትም፡፡

ዋቢ መጻሕፍት (REFERENCES)

1. Biehl, Bobb. Masterplanning: The Complete Guide for Building a


Strategic Plan for Your Business, Church, or Organization. Nashville:
Broadman & Holman Publishers, 1997.
2. Fairbanks, E. LeBron. “Servant Leadership for a Servant Community.”
http://www.mvnu.edu/facstaff/admin/presidentsoffice/speeches.html.
3. Greenleaf, R.K. (1991). The servant as leader. Indianapolis, IN: The
Robert K.Greenleaf Center. [Originally published in 1970, by Robert K.
Greenleaf].
4. Greenleaf, R.K. (1996). On becoming a servant-leader. San Francisco:
Josey-Bass Publishers.
5. Greenleaf, R.K. (1998). The Power of Servant-Leadership; San Francisco:
Berrett-Koehler Publishers.
6. Greenleaf, R.K. (2002). Servant Leadership: A Journey into the Nature of
Legitimate Power and Greatness. Mahwah, NJ: Paulist Press, 2002.
7. Hunter, J.C. (2004). The world’s most powerful leadership principle: how
to become a servant leader. New York: Crown Business.
8. The Holy Bible, New International Version. Grand Rapids: Zondervan,
1973.
9. Lloyd, B. (1996). A new approach to leadership. Leadership &
Organization Development Journal, 17(7), 29-32.
10. Reed, Harold. The Dynamics of Leadership: Open the Door to Your
Leadership Potential. Danville, IL: Interstate Printers and Publishers,
1982.

9
11. Sarkus, D.J. (1996). Servant-leadership in safety: advancing the cause
and practice.Professional Safety.
12. Sendjaya, S., and Sarros, J.C. (2002). Servant leadership: its origins,
development, and application in organizations. Journal of Leadershiop
and Organization Studies.
13. Smith, B.N., Montagno, R.V., and Kuzmenko, T.N. (2004). Journal of
Leadership and Organizational Studies, 10(4), 80-91.
14. Stone, A.G., Russell, R.F., and Patterson, K. (2003). Transformational
versus servant leadership: a difference in leader focus. Leadership &
Organization Development Journal, 25(4), 349-361.
15. Spears, L. (1996). Reflections on Robert K. Greenleaf and servant-
leadership. Leadership & Organization Development Journal, 17(7), 33-
35.
16. Spears, L.C., and Lawrence, M. (eds.). (2004). Practicing servant-
leadership:
17. Spears, L.C. Character and servant leadership: Ten characteristics of
effective, caring leaders. J. Virtues Leadersh.
18. Spears, Larry C., editor. Insights on Leadership: Service, Stewardship,
Spirit, an Servant-Leadership. New York: Wiley, 1998.
19. Spears, Larry C., Lawrence, Michelle (et al); Practicing Servant
Leadership: Succeeding through Trust, Bravery, And Forgiveness.
Jossey-Bass, San Fransisco, CA. 2004.
20. Spears, Larry C.; Diary of Alpha Kappa Psi (article: Servant-Leadership).
Gary L. Epperson, CAE. Spring 2008.
21. Tate, T.F. (2003). Servant leadership for schools and youth programs.
Reclaiming Children and Youth, 12(1), 33-39.
22. ደቀ መዝሙር አድራጊ መሪዎች፡ መጽሐፍ ሁለት፡ ኢሳያስ ኤርሳቦ.
23. የአመራር ሌጋሲ የክርስቶስን ሌጋሲ መከተል! ፓስተር ዶ/ር አሳየኸኝ በርኸ ገ/ሥላሴ (እ. እ. አ. 2014).

10

You might also like