You are on page 1of 5

1

ዲያቆናት

ዲያቆናት በቤተ ክ/ን ዉስጥ ችግርን በመቅረፍና ሁሉንም በባርነት (ዝቅ ብሎ በነፃ) በማገልገል
ማዕድ/ ገበታን ( የሚለዉ ቃል አስፈላጊ አቅርቦቶችን ያጠቃልላል ሮሜ 16፡1-2) በማደል
አንድነትን የሚገነቡ አገልጋዮች ናቸዉ፡፡ ሐዋ 6፡ 1-7

1. ትርጉም፡

Diakonos (deacon) የሚለዉ የግሪክ ቃል ማገልገል፤ ማከፋፈል፤ በፍትሐዊነት ማዳረስ


ወይም መርዳት ማለት ሲሆን ዲያቆን ማለት አለቃ ሳይሆን ባርያ አገልጋይ (ነፃ አገልግሎት
ሰጪ) ደጋፊ ማለት ነዉ፡፡ 1ጢሞ 5፡17 መሪዎች በመልካም እንዲያስተዳድሩ በመስበክና
በማስተማር ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ዲያቆናት ሜዳዉን የሚያመቻቹ ፍትህን የሚያነግሱ፤
ደካሞች እንዳይጎዱና አስፈላጊዉን አቅርቦት እንዲያገኙ የሚያገለግሉ መሪዎችን የሚደግፉ
አገልጋዮች ናቸው፡፡

2. የዲያቆናት አገልግሎት አጀማመር


ሐዋ 4፡32-35 በመጀመርያ ያመኑትም አንድ ልብና አንድ ሀሳብ ነበራቸዉ ያላቸዉም ሁሉ
የጋራ ነበር፤ በመካከላቸዉም ደሃ አልነበረም፤ ለሚያስፈልገዉም ሰዉ በፈለገዉ መጠን
ይሰጠዉ ነበር ነገር ግን ሰዉ ሲበዛና በግሪክ በሚናገሩ አይሁዶች እና እብራይስጥን በሚናገሩ
አይሁዶች መካከል በምግብ ክፍፍልና በእኩልነት አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ልዩነት በመታየቱ
ማጉረምረምና ኩርፍያ በመፈጠሩ በመካከላቸዉ ፍትህን ለማንገስ ዲያቆናት ተሾሙ፡፡ ሰው
ሲበዛ የአቅርቦት ማነስና ትኩረትን የሚያጡ ቡድኖች ስለሚኖሩ በሰዎች መካከከል መከፋፈል
ሊፈጠር ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡ 1ቆሮ 3፡1- 1ቆሮ 11፡18-27 በጌታ እራት ጊዜ አንዱ ሲጠግብ
ሲሰክር ሌላው ሲራብ ነበር፡፡

3. ምርጫ፡ እና መስፈርቶች፡-
ሐዋ 6፡3 ዘጸ 31፡3 መልካም ምስክርነት፤ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ፤ ጥበብ የሞላባቸው(
ጥበብ ማለት እግዚአብሔርን መፍራት ወይም እዉቀትና ልምድ ላይ ያለንን ጥልቅ ግንዛቤ/
ማስተዋል በመጠቀም ችግርን የመፍታት ብቃት) የሚለዉ እንደተጠበቀ ሆኖ የጸሎት ሰዎችና
በወንጌል ስርጭት የሚሳተፉ ስለሆነ ጳዉሎስ ከችሎታና አስተዳደራዊ ክህሎት ይልቅ ሰብአዊና
መንፈሳዊ ባህሪይን እንደ ቁልፍ ክራይቴርያ ይወስዳል፡፡ 1ጢሞ3፡ 8-13 ምክንያቱም እነዚህ

1
2

አገልጋዮች የማገዝ ስራቸዉ በመንፈሳዊም ስራ ላይ ሊሆን ስለሚችል ነዉ፡፡ የሐዋ 6፡8


እስጥፋኖስን፤ 21፡8 ወንጌላዊዉን ፊሊጶስን ማየት እንችላለን፡፡

እዚህ ላይ ጳዉሎስ 9 ተፈላጊ ብቃቶችን ይጠቅሳል፡፡1ጢሞ3፡ 8-13

ቁ8 ጭምትና የተከበረ/ች፤ ቁ8 በ2 ቃል የማይናገሩ የታመኑ/ ውሸታም ያልሆኑ፡ ቁ8


የመጠጥ ሱስ የሌላቸዉ የማይሰክሩ/ አባካኝና ተሳዳቢ ያለሆኑ፡ ቁ9 ገንዘብ የማይወዱ/ ገንዘብ
ላይ ስለሚሰሩ እንደ ይሁዳ እንዳይፈተኑ፤ ቁ9 በንጹህ ህሊና የሐይማኖትን ሚስጢር(
በውስጡ ድካምም ቢኖር) የሚይዙ 1ጢሞ 3፡16፤ ቁ10 የተፈተኑና ያለ ነቀፋ የሆኑ ጥሩ ስም
ያላቸዉ/ ነቀፋ ካለ ሰው ቤተ ክ/ንን ስለሚሸሽ፤ ቁ11 ሚስቶቻቸዉ/ባሎቻቸው የማያሙ
ጭምቶች ልከኞች የታመኑ የሆኑ 1ጢሞ5፡10፤
ቁ12 የአንዲት ሚስት ባል ወይም የአንድ ባል ሚስት/ መጥፎ ምሳሌ እንዳይሆኑ፤ ቁ12
ልጆቹንና ቤተሰቡን በሚገባና በመልካም የሚያስተዳድር/ የምታስተዳድር
4. ሀላፊነቶች፡- (የዲያቆናት የስራ ድርሻ)
ለወንጌል ስራ አከባቢንና ሁኔታዎችን የሚያመቻቹ አካላዊ፤ ማህበራዊና አስተዳደራዊ
ስራዎችን በሙሉ ለመስራት ተፈጠሩ፡፡( ከፕሮ. ቤንጃሚን ሜርክሌ፣ ዌክ ፎርሰት ሴሚነሪ
ኖርዝ ካሎሪና)
1) ፋስሊቲ፡ የአምልኮ ቦታ ዝግጂት፤ጽዳት፤ ሳዉንድ ሲስተም፤ ቅዱስ ስርአቶች (ጥምቀትና
የጌታ እራት፤ የጋቢቻና የሰርግ፤ ለቅሶና የቀብር) ህሙማንን መጠየቅ እንዲጸለይላቸዉና
እንዲታከሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፡፡

- ንብረቶችን ወንበሮችን፤ ወለሉንና ግድግዳዉን በንጽህና እንዲያዙ ማገዝ፡፡ ቆሻሻ በቤተ ክ/ን
ዉስጥ እንዳይጣልና ሰዉ ሁሉ ድርሻዉን እንዲወጣ መምከርና ማስተማር፡፡ - የቤተ ክ/ን ግቢ
ንጹህ የማረና አረንጓዴ ማድረግ፡፡ - በቂ ብርሃንና አየር መኖሩን ማረጋገጥ፤ የሚረብሹ
ንፋሶችና ሙቀቶች፤ ከዉስጥም ሆነ ከዉጪ የሚወጡ ድምጾችን አጣርቶ እንዲሰተካከሉ
ማድረግ፤ ለምሳሌ፡ ሞንታረቦ ፊትለፊት የሚቀመጡ ሰዎች ለጆሮአቸዉ ምቾት እንዳላቸዉና
እንደሌላቸዉ ማጣራትና እንዲመች ማስመጠን፡፡ - ቅዱስ ስርአቶች ሲደረጉ ከወንጌል ሰዎች
ጋር ሆኖ ሁኔታዎችን የማመቻቸቱን ስራ በዋናነት መስራት፡፡ ለህሙማን የሚጸልዩና ህሙማን
እንዲጸለይላቸዉ ማገዝና ማዳናቸዉን በመከታተል ሲድኑም ለምስክርነት ማዘጋጀት፡፡ -
በሀዘንና በለቅሶ በቀብር ሥነ ስርዓት የሚሰሩ የዕድርና ባልትና አገልግሎትን ማደራጀት

2
3

አገልጋዮቹንም ማገዝ፡፡ የግቢ ዉስጥ አካል ጉዳተኛን በማሰብ መንገድ ማበጀትና ማስታወቅያ
መለጠፍ/ቢልቦርድ ማቆም

2) እርዳታ፡ ለባልቴቶችና አረጋዊያን፤ ወላጅ ላጡ ህጻናትና ስደተኞች እንዲሁም ድሆች

ያዕ 1፡ 27፡- ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤


ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ
ሰውነቱን መጠበቅ ነው። 1ጢሞ5 ፥16 ባልቴቶች ያሉት የሚያምን ቢሆን ወይም የምታምን
ብትሆን፥ ይርዱአቸው፥ ቤተ ክርስቲያንም እውነተኞችን ባልቴቶች እንድትረዳ አይክበዱባት።
ገላ 2፡10 ድሆችን እናስብ ዘንድ ብቻ ለመኑን፥ ይህንም ደግሞ ላደርግ ተጋሁ።

በቤተ ክ/ን ያሉ በኑሮ የሚቸገሩ ምዕመናንን በመለየት ስራና ገቢ እንዲያገኙ ት/ትና ስልጠና
እንዲያገኙ ሰርተዉ ራሳቸዉን እንዲችሉ፤ ስራን ሳይንቁ እንዲሰሩ እርስ በርስም እንዲረዳዱ
በመደራጀት በመንግስትና ሲቪል ማህበራት አከባቢ የሚገኘዉንም ዕድል እንዲጠቀሙ መምከር
ማስተዋወቅ ማበረታታት፡፡ ወገኖችን በመቅረብና በማቅረብ የግል ኑሮአቸዉን ቤታቸዉን
በመረዳት ልብስና ምግብ የሌላቸዉን ካላቸዉ በማሰባሰብ ማከፋፈል፤ እቤታቸዉ የፈረሰባቸዉና
በተለይም ክረምት በጎርፍና በዝናብ የሚጎዱ አረጋዊያንን አስቀድሞ በመለየት ምዕመናንን
በማስተባበር መርዳት፡፡ ወላጅ ያጡ ህጻናትን፤ በጦርነትና በተፈጥሮ አደጋ የተፈናቀሉ ፤
እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የታሰሩ ወይም በሞት የተለዩን የቤተሰብ መሪዎች ቀሪ
ወገኖችን በመለየት በሚያስፈልጋቸዉ መደገፍ፡፡ እየተማሩ ያሉ ግን በእርዳታ ማጣት
ምክንያት ት/ታቸዉን አቋርጠዉ ላልተፈለገ ህይወት የተጋለጡ ወጣቶች ካሉ መከታተልና
ከዲያብሎስ ወጥመድ ማስመለጥ፡፡

3) ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር፡- አስራትና ስጦታዎችን መሰብሰብ፤ መቁጠር፤


መመዝገብ፤ ፈንድ ሬይዝ፤ ንብረቶች በአግባቡ እንዲያዙ እየተጨመሩ እንዲሄዱም መስራት

2ቆሮ 12፡9 የዚህ ረድኤት አገልግሎት ለቅዱሳን የሚጎድላቸውን በሙሉ የሚሰጥ ብቻ


አይደለምና፥ ነገር ግን ደግሞ በብዙ ምስጋና ለእግዚአብሔር ይበዛል፡፡ ቤተ ክ/ን የተለያዩ
የወንጌል ስራዎች በሚኖራት ጊዜ የገንዘብና የማቴርያል እጥረት እንዳያጋጥም ጊዜ ያላቸዉን
ወገኖችን በመለየት ገቢ ማግኛ ስራዎችን ማሰራት ፤ ቤተ ክ/ንቷ የልማት ክንፍ ኖሮአት ት/ት
ቤት፤ የእርሻ ስራ፤ የግንባታና የሚከራዩ ፎቆች፤ ፋብሪካ ወዘተ ቢኖራት ጠንካራና የሚሮጡ
የወንጌል እግሮች ኖሮአት የእግዚ/ን መንግስት የሚታሰፋ የዲያቢሎስን መንግስት የሚታፈርስ
3
4

ከመሆንዋም በላይ ለምዕመናን ወገኖችዋ የስራ ዕድልንም ትከፍታለች፡፡ ለዚህም ዓላማ


የመሪዎችና የዲያቆናት ድርሻ የጎላ ይሆናል፡፡ ይህም እንዲሳካ መጸለይና አብሮ በመፍሰስ ሌተ
ቀን መስራትን ይጠይቃል፡፡

ቤተ ክ/ን ያላት ሀብት (ገንዘብና ንብረት) የእግዚ/ር እና የህዝቡ የምዕመኑ ስለሆነ በተለይ
ዲያቆናት በሀላፊነት ንብረት ሳይባክን ሳይሰበር ሳይሰረቅ በንጽህናና በጥንቃቄ ተጠብቀዉ
ለረጂም ጊዜ እንዲቆዩ አገልግሎት እንዲሰጡ ልዩ የእንክብካቤና የጥበቃ ሀላፊነት ላይ
በመሰራት በዚህ ጉዳይ ከሚሰሩ ምዕመናን ወይም ሰራተኞች ጋርም በመቀናጀት ወይም
በትብብር መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

4) መስተንግዶ፡ ጉባኤዉንና እንግዶችን ማስተናገድ፤ማቴርያሎችን ማከፋፈል


diakonos (dee-ak'-on-os) የሚለው ቃል አስተናጋጅ ፤ አገልጋይ ባርያ፤ ፓስተር፤ ሰባኪ፤
አስተማሪ ማለትም ይሆናል፡፡ በቤተ ክ/ንና በኮንፈራንስ ቦታዎች ማስተናገድ እንደተጠበቀ ሆኖ
ወደ ቤተ ክ/ንቱ ከሌላ ቦታ ተዛዉረዉ የሚመጡ እንግዶች አማኞችን ሀገር ፤ በአምልኮ ጊዜ
ማስተናገድ ስንል መንፈስን ጠብቆ እያመለኩ ለእንግዶች ቦታ መስጠት፤ ያለስጋትና ረብሻ
ንብረቱ ተጠብቆ አምልኮ ወደ ቤቱ እንዲመለስ ከሚበጠብጡ ዱሪየዎች፤ ሌቦችና የአጋንንት
ሁከቶች ፤ እንዲሁም በመነቃቃት ጊዜ የሚወድቁና የሚወራጩ ሰዎች ሲኖሩ እነሱን፤
ህጻናትንና ደካሞችን ማገዝ
5) ሎጂስትክስ፡ የጉዞ ትራንስፖርት ማቴርያሎችንና ግብአቶች፤ለቤተ ክ/ን ለሚገዙ
የግንባታም ሆነ የአገልግሎት ዕቃዎች ማጓጓዝ ማጫንና ማዉረድን ከእቅድ እሰከ ስቶር ወይም
ስራ ላይ ማዋል ያሉትን ሂደቶች፤ ለሚያድሩ እንግዶች ትራንስፖርት ፤ማደርያዎችን፤
ምግብና ልብስ አልጋ ወዘተ ማመቻቸት፡፡ ይህ አገልግሎት ለሚጋበዙ አገልጋዮች ብቻ ሳይሆን
የቤተ ክ/ን አገልጋዮች ወይም የምዕመናን ልዩ የጋራ ጉባኤ በተለይም ወጣ ባለ ከተማ ወይም
የአምልኮ ስፍራ በሚከናወንበት ጊዜ ከቤተ ክ/ንቱ የዝግጅት ኮሚቴ ጋር በመቀናጀት የሚሰራ
ስራ ነው፡፡ በተለይም በጀማ የወንጌል ስብከት ጊዜ ወይ ም በአደባባይ ኮንፈራንስ በሚደረግበት
ጊዜ የዲያቆናት ድርሻ በጣም ብዙ ነው፡፡

እነዚህ ከላይ የጠቀሱት 5ቱ አገልግሎቶች ከቃልና ከጸሎት የተለዩ ቢሆኑም ሁሉም የማዕድ
ሳይሆኑ መንፈሳዊና የቤተ ክርስትያን አካላዊ አስተዳደራዊ ፤ማህበራዊና የአምልኮ ስርዓቶች
ናቸዉ፡፡ መልዕክት/ደብዳቤ ወይም

4
5

ዕቃዎችን ማድረስና በመቀበል ወደ ቤተ ክ/ን በማምጣት የመላላክ ስራዎችን መስራት፡፡


5. አደረጃጀት
ዲያቆናት በኮሚቴ መልክ እንዲደራጁ የሚል ሀሳብ አለ፡ አያስፈልግም በጭቅጭቅ ጊዜ
ይገላሉ በያንዳንዱ የተለያዩ ውስን ስራዎች ላይ የተለያዩ ዲያቆናት ይሾሙና ራሳቸዉን
ችለዉ ይሩጡ የሚሉም አሉ፡ ግን እንደሁኔታዉ መሪዎች ይወስናሉ፡፡ ለመመካከርና
ለጸሎት ህብረት ጥሩ ነው፡፡ አንድነታቸዉን ጠብቀው የሚያስተባብሩ የቡድን መሪዎች
ግን ግድ ነዉ፡፡ 1ነገ 10፡5 የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም አሠራር
አለባበሳቸውንም፥ ፥ ‹‹‹‹ ባየች ጊዜ ነፍስ አልቀረላትም። ዲያቆናት ለእግዚ/ር ክብር
የሚገባ አለባበስ ዩኒፎርም ሊኖራቸቸዉ ይገባል፡፡ አሰላለፋቸዉና አለባበሳቸዉ የእግዚ/ርን
ክብር የሚገልጥ የነገስታትን የክብር ዘበኞች የሚመስሉ የቤተ ክ/ንን ዉበት የሚገልጡ
የክብር እቃዎች አደርጎ መቅረጽ፡፡
6. የአገልግሎት መርሆዎች
1. የምናገለግለዉ እግዚአብሔርን፤ የቤተ ክርስትያን መሪዎችን እና ምዕመናኑን ስለሆነ
የ3ቱንም ፍላጎት አድራሻና እንዴት የት ምን ማድረግ እንዳለብን ማወቅና ሀሳባቸዉን
ለማገልገል መዘጋጀት( ፍጹም ታዛዥ ትሁትና ሁልጊዜ ዝግጁ ሆኖ መገኘት) ሳኦልን
እናስታዉስ 1ሳሙ 15
በሐዋርያት ዘመን ምዕመናን አንድ ላይ ነበሩ፡፡ አገልግሎቱም እዚያዉ አንድ ቦታ
ነበር፡፡ አሁን ግን ሰዉ ቤቱም ኑሮዉም ለየብቻ ነዉ፡፡ ማህበራዊና አካላዊ ችግሮቹም
በየቤቱ በየሰፈሩ ሊሆን ስለሚችል የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት የምዕመናኖቻችንን
አድራሻ እና ኑሮአቸዉን በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
2. የምናገለግለዉ በቡድን በመሆኑ እርስ በርስ መተዋወቅ መግባባበት መቀባበል
መተባበርን መፍጠር ሮሜ 15 አንዱ ያንዱን ሙሉ አድራሻ ማወቅና አገልግሎቱን
ከራስ መጀመር
3. ደመወዛችን አና ብድራተችን ከጌታ ዘንድ ብቻ መሆኑን በማወቅ ያለመሰልቸት
ሁልጊዜ ቢመችም ባይመችም ማገልገል ዕብ 11 ፡25-26፤ 2ጢሞ 4፡2
4. ጸጋዉ እነዲበዛልን ሁልጊዜ በፀሎት መትጋት ሮሜ 15፡31-32 ፤ ኤፌ 6፡18

You might also like