You are on page 1of 21

ምዕራፍ ሁለት

፫.ማህበራዊ ክርስትና
‹‹ ቢቻላችሁስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ ሮሜ 12 ፤ 18 ››

፫.፩ የማህበራዊ ኑሮ ጠቀሜታ እና አስፈላጊነት


የማኅበራዊ ህይወት መሰረቶች
ክርስትና ማኅበራዊ ህይወት ነው:: መንፈሳዊነትም ለሌሎች መኖር ነው፡፡

 ይህንንም ጌታችን በተወለደ ጊዜ በቤተልሔም ያየነው ክስተት ለኛ ትልቅ


ትምህርት ነው፡፡ ይኸውም ተለያይተው የነበሩትን ሰባቱን መስተጻርራን
ጌታችን ሰው በመሆኑ አንድ ማድረጉ ነው፡፡
 ከዚህም በተጨማሪ አምላካችን ሰው በሆነ ጊዜ ለዘመናት የተለያዩትን
አይሁድ እና አህዛብን፣ሳምራውያንን እና አይሁድን አንድ አድርጓል፡፡እነዚህ
ቡድኖች በሃይማኖት በርዕዮተ ዓለም፣ በባህል በቋንቋ፣ በቦታ እና
በመሰለውም ሁሉ የተለያዩ ነበሩ:: ክርስትና ሁሉን አንድ አድርጋ ክርስቲያን
አሰኘቻቸው፡፡ከአንድ ዘር ከእግዚአብሔር ቃል የተወለዱ ሆኑ ልዩነት ጠፋ
የኃጢአት ድልድይ ተሰበረ፡፡ ይህ በመሆኑም ክርስቲያናዊ ህይወት በብዙ ነገር
ልዩ ከሆኑ ሰዎች ጋር በሰላም እና በፍቅር መኖር ነው፡፡ ይህ የሚጀምረው
ደግሞ ከቤት ውስጥ ነው፡፡
 ቤተሰብ የማኅበረሰብ መሰረት ነውና ፡፡
— 1 ኛ ተሰሎንቄ 5፥12-13
“ወንድሞች ሆይ፥ በመካከላችሁ የሚደክሙትን በጌታም የሚገዙአችሁን
የሚገሥጹአችሁንም ታውቁ ዘንድ፥ ስለ ሥራቸውም በፍቅር ከመጠን ይልቅ
ታከብሩአቸው ዘንድ እንለምናችኋለን። እርስ በርሳችሁ በሰላም ሁኑ።”
ኤፌ 2፤15፣
“እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም
የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤
ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም
ያደርግ ዘንድ፥”

ቆላ 1፤20፣1 ተሰ 5፤13፣2 ጢሞ 2፤22፣ዕብ 12፤14፣1 ጴጥ 3፤11 ዘሌ 26፤6፣መዝ 4፤


8፣መዝ 34፤14፣37፤11፣38፤3፣፣118፤165 ኢሳ 26፤12 መዝ 48፤22፣ኢሳ 52፤7፤ኢሳ
57፤21፣ዘካ 8፤19፣
ከዚህም በተጨማሪ የማኅበራዊ ህይወት መሰረቶች ከሆኑት መካከል የሚከተሉት
ተጠቃሾች ናቸው
 ቃለ እግዚአብሔር
 የሰው ተፈጥሮ
 የቤተክርስቲያናችን ቅዱስ ትውፊት

የማኅበራዊ ኑሮ ጠቀሜታ
1. ችግርን ለማስወገድ ለመጽናናት ለመረጋጋት ዲድስቅልያ አንቀጽ 8 አንዱ
የአንዱን በደል ይቅር ይበል
2. ሀሳብ ምክር ለመለዋወጥ
3. ደስታን ለመጋራት ሀዘንን ለማቅለል
ሮሜ 12፤ ¹⁴ የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ።¹⁵ ደስ
ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።
4. መንፈሳዊ በረከትን ለመቀበል ምሳሌ እንግዳን መቀበል
5. በኑሮ መሻሻል እና እድገትን ለማምጣት መክ 4፤9
መክብብ 4 ⁹ ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት
መሆን ይሻላል።
¹⁰ ቢወድቁ አንዱ ሁለተኛውን ያነሣዋልና፤ አንዱ ብቻውን ሆኖ በወደቀ ጊዜ
ግን የሚያነሣው ሁለተኛ የለውምና ወዮለት።
¹¹ ሁለቱም በአንድነት ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ አንድ ብቻውን ግን እንዴት
ይሞቀዋል?
6. መልካም ቤተሰባዊ ህይወትን ለመመስረት
7. እቅድን ለማሳካት
8. የምጣኔ ሀብት እድገት ለማምጣት
9. ለመንፈሳዊ ህይወት ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎችን ለማግኘት
10. ቅዱስ ትውፊትን ለመከተል

፫.፪ የክርስቲያኖች የህብረት ኑሮ (ማኅበራዊ ኑሮ) በተለያየ


ዘመናት
 በህገ ልቡና ማኅበራዊ ኑሮ በህገ ልቡና የሚኖሩ አበው ከቤተሰባቸው ጋር
በልባቸው በተጻፈላቸው ህግ እየተመሩ መልካም ማኅበራዊ ሰላማዊ ኑሮን
ይኖሩ እንደነበረ ብዙ ምስክሮች በቅዱሳት መጻህፍት ተጽፈውልናል ምሳል
አብርሃምና ሎጥ በኅብረት ይኖሩ እንደነበረ ዘፍ 13፤
 በህገ ኦሪት እስራኤላውያን በአጠቃላይ የእስራኤል ጉባኤ የእግዚአብሔር
ማኅበር እየተባሉ ይጠሩ ነበር መሪያቸውም ሊቀ ነብያት ሙሴ ነበር
— ዘኍልቁ 10፥3 ፤“ሁለቱም መለከቶች በተነፉ ጊዜ ማኅበሩ ሁሉ ወደ
አንተ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይሰብሰቡ።”
 በህገ ወንጌል (በዘመነ ሀዋርያት) ክርስትናን እና ማኅበረ ክርስትናን በስሙ
የመሰረተው ለስም አጠራሩ በቃል ለመነገሩ በኅሊና ለመዘከሩ የክብር ክብር
ይግባውና ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
1 ማኅበርተኞቹም መጀመሪያ ሐዋርያት
— ዮሐንስ 1፥37“ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን
ተከተሉት።”
2 ከዚያ ሰባ ሁለቱ አርድእት እና ሰላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት
አጠቃላይ 120 ቤተሰብ የክርስትና የመጀመሪያዎቹ ማኅበርተኞች ነበሩ፡፡
በኋላ በነቅዱስ ጴጥሮስ እና እስጢፋኖስ ስብከት ከ 120 ወደ 8000 አደገ
ያም በዓለም ተበትኖ በዓለም አሁን ያለነውን የክርስቲያኖች ማኅበር ወለደ

፫.፫ የክርስቲያኖች የህብረት ኑሮ በዛሬይቱ ቤተክርስቲያን


በማኅበራዊ ኑሮ ለመንፈሳዊ ህይወታችን የሚያስፈልጉን ነገሮች
ምንድናቸው
1. ዓላማ፤ ዓላማ የህይወት መርሕ ነው ለምን እንዴት እንደምንኖር
የሚያሳየን የህይወት መልህቅ ነው፡፡ዓላማ የሌለው ሰው ማንም
እንደወደደ የሚነዳው በሌላው ፈቃድ፣ ሐሳብ የሚኖር ነው፡፡
በመንፈሳዊ ህይወት ስንኖር ከሚያስፈልጉን ዋና ነገሮች አንዱ
ዓላማ ነው ዓላማችንም እግዚአብሔር እና ከእርሱ ጋር መኖር ብቻ
ነው ሊሆን የሚገባው
2. በጎ ኅሊና ሊኖረን ይገባልነገሮችን በቅንነት ልንረዳ የምንችለው እና
ደስተኞች ከሰዎች ጋር ተግባቢ መሆን የምንችለው በጎ ኅሊና
ሲኖረን ብቻ ነው፡፡
3. ትጋት በስራችን በህይወታችን በኑሮዋችን ሀኬት እና ስንናን አርቀን
ተግተን ከሰራን በሁሉ የምንወደድ እና የምንፈለግ ተወዳጆች
እንሆናለን፡፡
4. ግልጽነት(ቅንነት) አበው ቅንነት ለሰው ውስብስብ አለመሆን ነው
ይላሉ፡፡
5. ትህትና እና ርኅራሄ እነዚህ ነገሮች የመንግስተ ሰማያት
ድልድዮችናቸው ከሰው ሁሉ ጋር በፍቅር የሚያኖሩን ምግባራትም
ናቸው
6. እምነት ተስፋ ፍቅር ሊኖረን ይገባል
7. ታጋሾች ልንሆን ይገባናል

፫.፬ ክርስቲያናዊ ስነምግባር በየት ቦታ ይፈጸማል?

3.4.1. መንፈሳዊ ኑሮ በቤታችን ውስጥ ክርስትና (መንፈሳዊ ህይወት) እና


ቤተሰባዊ ህይወት
የማኅበረሰብ መገኛ ቤተሰብ ነው፡፡ የቤተሰብ ጥንቱ ደግሞ ትዳር ነው፡፡
እግዚአብሔር ያለበት ትዳር የጥሩ ቤተሰብ መገለጫው ነው ጥሩ ቤተሰብ ደግሞ
የበጎ ማኅበረሰብ መገኛ ነው፡፡የየትኛውም ሰብእና ግንባታ መጀመሪያው ቤተሰባዊ
ኑሮ ነው፡፡

ቤተሰብ የመጀመሪያ ትምህርት ቤትም ነው፡፡ ጌታችን መልካም ዛፍ መልካም


ፍሬ ያፈራል ክፉ ዛፍ ክፉ ፍሬ ያፈራል ብሎ እንዳስተማረን
ከጥሩ ቤተሰብ መጥፎ ልጅ ከመጥፎ ቤተሰብ ጥሩ ልጅ በብዛት አይገኝም ከስንት
አንዱ አምልጦ እና ሾልኮ የሚወጣ ግን አይጠፋም ይህም ሌሎች ተጽእኖዎች
የበዙበት ሲሆን ነው፡፡ የቤተሰብ መገኛው ባልና ሚስት በመሆናቸው በኑሮዋቸው
ሁሉ በጎ ክርስቲያናዊ ህይወትን ተለማምደው በሱ መኖር ካልቻሉ የሚወልዷቸው
ልጆቻቸው ለቤተሰብም ለሀገርም ጠር ይሆናሉ፡፡
1. ባልና ሚስት የሚከባበሩ ከሆኑ ልጆቻቸው ሰውን ሁሉ የሚያከብሩ ይሆናሉ
2. በቤተሰብ ውስጥ መደማመጥ ካለ ልጆች ሰውን ሁሉ የሚሰሙ ይሆናሉ
3. በቤተሰብ ውስጥ መወያየት ካለ በውይይት የሚያምኑ ኅብረተሰብ ይበዛሉ
4. በቤተሰብ ውስጥ ፍቅር ካለ ልጆች ሰውን ሁሉ የሚወዱ ርኅሩሀን ይሆናሉ
5. በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ቤተሰብ በትእግስት የሚፈታ
ከሆነ ልጆች አለመግባባቶችን በትእግስት በፍቅር የሚፈቱ ይሆናሉ
6. በቤተሰብ ውስጥ የቤተክርስቲያን ፍቅር ካለ ልጆች ስለሃይማኖታቸው
ስለቤተክርስቲያናቸው አንገታቸውን ለሰይፍ ለስዕለት ይሰጣሉ
7. ባልና ሚስት ተከባብረው ተዋደው ሲኖሩ ያዩ ልጆችከባልንጀሮቻቸው እና
ከጎረቤቶቻቸው ጋር በፍቅር እና በሰላም መኖር ይችላሉ፡፡
8. ቤታቸችን ውስጥ ቃለ እግዚአብሔር የሚሰጥበት የሚሰማበት ከሆነ
ልጆችበዛ ተቀርጸው ያድጋሉ
9. ገድለ ቅዱሳን በቤታችን የሚነገር ከሆነ ልጆቻችን በቅዱሳን አሰረ ፍኖት
የሚሄዱ ይሆናሉ
10. በቤታችን ዘወትር ጸሎት የምንጸልይ ከሆነ ልጆች በህይወታቸው
አስቸጋሪ ነገር ሲገጥማቸው በጸሎት ይፈታሉ
11. የገጠመንን የደረሰብንን በግልጽ ለልጆቻችን ምንነግራቸው ከሆነ
ልጆቻችን የደረሰባቸውን ምንም ሳይፈሩና ሳያፍሩ ይነግሩናል ግልጽነትን
ቅንነትን ይማሩልናል፡፡
12. ቤታችን ውስጥ የምናያቸው የምንሰማቸው በመገናኛ ብዙኃን
የሚለቀቁ ነገሮች ልጆቻችንን በበጎም በመጥፎም ቀርጸው ሊያወጡዋቸው
ይችላሉ
13. በቤታችን ዝማሬ መዘመር እና ማድመጥ ከለመድን ትንሷን
ቤተክርስቲያን ለልጆቻችን እናለማምዳቸዋለን
14. በቤታችን ቅዱሳንን ስንዘክር ትምህርተ ቤተክርስቲያንን ትውፊተ
አበውን በልጆቻችን አዕምሮ እንቀርጻለን
15. በቤታችን በዝግታ መኖርን ከለመድን ልጆቻችን የተረጋጋ ማንነት
እናላብሳቸዋለን፡፡
16. በቤተሰብ ውስጥ የስራ ድርሻ ተከፋፍለን ከሰራን የልጆቻችንን በጎ
ሰብእና ከፍ ማድረግ እንችላለን
17. በመርሐ ግብር ቤተሰቦቻቸችንን የምንጠይቅ ከሆነ ለልጆቻችን
የቤተሰብ ፍቅር እናሳድርባቸዋለን
18. ለችግረኞች ምጽዋት ስንሰጥ ልጆቻችንን ወስደን ካሳየናቸው
ከሚያገኙት እና ካላቸው ምጽዋት መመጽወትን እናስተምራቸዋለን
19. ቤተክርስቲያ መጥተን ስናስቀድስ ልጆቻችንን አምጥተን
ካቆረብናቸው የቤተክርስቲያንን ሱታፌ እናለማምዳቸዋለን
20. በቤተክርስቲያን በማገልገል ስለ አገልግሎት ምንነት እና ፍቅር
ለልጆቻችን በጎ አርአያ እንሆናቸዋለን፡፡
21. እንግዶችን በመቀበል እና እግር በማጠብ ለልጆቻችን ክርስትናን
በተግባር እናስተምራቸዋለን
22. ከአበ ንስሐችን ጋር ስንነገገር በማሳየት ከካህናት ጋር ማውራት
መወያየት እንዳለባቸው እናለማምዳቸዋለን
23. የመታዘዝን ዋጋ በምስጋና እናሳያቸዋለን
24. ሌሎችንም አንድ ክርስቲያን በቤቱ ሊያደርግ የሚገባውን ጸሎቱን
፣ጾሙን ፣ስግደቱን፣ ምጽዋቱን፣አስራቱን፣ በኩራቱን ሁሉን በደረጃ ማሳየት
የተገባ ነው፡፡ እንዲህ ካደረግን ቤታችንን ትንሻቤተክርስቲያን ማድረግ
እንችላለን፡፡

መንፈሳዊ ሰው በቤቱ ውስጥ ምን ሊሆን ይገባዋል


1. ለቤተሰቡ የሚያስብ፣ቤተሰብ አክባሪ፣ ታጋሽ፣ታዛዥ፣ትሁት ሊሆን
ይገባዋል፡፡
2. ለቤተሰቡ አርአያ የሚሆን፣ በእግዚአብሔር ቃል የሚመራ መሆን ይገባዋል
3. የተማረውን ክርስቲያናዊ ህይወት በተግባር ማሳየት ይገባዋል
4. ቤት ውስጥ የማይገቡ ነገሮች ሲደረጉ መክሮ አስተምሮ የሚለውጥ፣ ተግሳጽ
የሚፈልጉ ጥፋቶችን ገስጾ የሚያስተካክል፣ ትእዛዛተ ወንጌልን የሚፈጽም፣
ራሱንም ቤቱንም ለእግዚአብሔር የሚያሥገዛ፣ ቃለ እግዚአብሔርን
የሚያነብ፣ ክርስትናን በተግባር የሚኖር(የሚጾም የሚጸልይ የሚሰግድ)፣
እግዚአብሔርን የሚፈራ ጸሎት የሚያደርስ ነው፡፡

5. ቅን የሆነ ቤተሰብን የሚያከብር፣ ስለ ሃይማኖት እና ምግባር የሚወያይ፣


መልካም ንግግርን የሚናገር
6. ቤተሰቦቹን የሚያስተምር፣የሚመክር ከክፉ ነገሮች የሚጠብቅና የሚመልስ
ነው
7. የቤተሰብ ሥርዓት ሊኖረው ይገባል
8. ዘወትር ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሄድ፣ በቤት ውስጥ ጸሎት የሚያደረስ፣
በቤት ውስጥ ከቤተሰቡ ጋር በሰላም የሚኖር፣ ቤተሰቡን የሚወድድ መሆን
ይገባዋል፡፡
9. ማንኛውንም ስራ ከቤተሰቡጋር በጋራ ሊሰራ ይገባዋል
10. ለአመጋገቡ ሥርዓት (ከምግብ በፊት እና በኋላ ሊጸልይ ሊያመሰግን
ይገባዋል) ና ለአለባበሱ ጸጉር አቆራረጡ ሥርዓት ሊኖረው ይገባል
11. ለቤተሰብ ችግር ደራሽ መሆን አለበት እንዲሁም ግልጽ መሆን
ይገባዋል
12. የተማረውን ትምህርት ለቤተሰቡ የሚያስተማር ና በማስተዋል እና
በመግባባት አብሮ የሚኖር ሊሆን ይገባዋል

3.4.2.መንፈሳዊ ኑሮ በአካባቢያችን
አካባቢያቸችን ከግቢያችን ከመኖሪያ ህንጻችን ይጀምራል፡፡በዚያም
መንፈሳዊነታችንን በተለያዩ መንገዶች ልንገልጥ ይገባናል እንደ ምሳሌ
1. ስንገባ እና ስንወጣ ለጎረቤቶቻችን ሰላምታ መስጠት
2. ለችግሮቻቸው ፈጥነን መፍትሄ መስጠት
3. ሊረዳ የሚገባውን ለይተን የምንረዳ፣ የግጭት ምክንያቶችን የምናጠፋ፣
ግጭቶች ከተከሰቱ ደግሞ ፈጥኖ ይቅርታ የምንጠይቅ እና በትህትና ነገሮችን
የምናረግብ መሆን ይገባል
4. አካባቢያችን የሚጠይቀንን ማንኛውም ዓይነት ማኅበራዊ ተሳትፎ ማድረግ
ምሳሌ ጽዳት፣ እድር፣… እንዲሁም አካባቢያችንን በንጽህና መጠበቅ፣
በደስታ እና በሀዘን ጊዜ መረዳዳት፣ ቤታችን ጠርተን ዝክሩን ተበል ጠዲቁን
ማድረስ፣ ሻይ ቡና ተጠራርቶ ስለ ህይወታቸው ማውራት፣ በተቻለን መጠን
በሁሉ ነገር በጎ አርአያ መልካም አብነት ሆኖ መገኘትና ሌሎቸችንም ከእኛ
የሚጠበቁ ነገሮችን ማድረግ ይገባል፡፡

3.4.3. መንፈሳዊ ኑሮ በመስሪያ ቤት


ክርስቲያን ያለምንም ምክንያት ስራ ፈቶ ሊቀመጥ አይገባውም በመጽሐፍ ሊሰራ
የማይወድ አይብላ ተብሏልና 2 ተሰ 2፤3
አዳምን ሲፈጥረው ፈጣሪ ስራም አብሮ አዘጋጅቶለት ነበር ያበጃጃት ይጠብቃት
ዘንድ በኤደን ገነት አኖረው በማለት ዘፍ 1፤28 እንደተጻፈው ክርስቲያን የሆነ ሁሉ
ከኃጢአት በቀር በአቅሙ የሚችለውን ስራ ሊሰራ እና ሊያድር ይገባዋል፡፡ ለሰው
የከበረ ሀብት ትጋት ነውምሳ 12፤27 ይኸውም የእለት ጉርስ የዓመት ልብስ
ስለማግኘት ሊሆን ይገባል፡፡ በዚህ ሂደት አንድ መንፈሳዊ ሰው በመስሪያ አካባቢው
በሚሰራው ስራ ሊያሳያቸው የሚገቡ ክርስቲያናዊ ጠባይዓት አሉ፡፡ በሚችለው
ሁሉ እነዚህን ነገሮች ሊያደርግ ይገባዋል፡፡
1. ለአለቆቹም ሆነ ለስራ ባልደረቦቹ መታዘዝ ሮሜ 13፤1
2. ከስርቆት ከግቦ እና ከመሳሰለውም መራቅ
3. በሰዓት ገብቶ በሰዓት መውጣትን መልመድ
4. የተሰጠንን ስራ በትጋት መከወን መፈጸም
5. ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ የወጣ የስራ ትእዛዝን አለመፈጸም
6. በስራ ትጋት ለሌሎች በጎ አርአያ መልካም አብነት በመሆን ለሁሉም ፍጹም
የሆነ ትህትናን ማሳየት
7. የመስሪያ ቤታችንን ንብረት ለመስሪያ ቤታችን አገልግሎት ብቻ ማዋል
8. ስለ እግዚአብሔር ብለን ተገልጋዮችን በቅንነት ማስተናገድ
9. በእምነት ከማይመስሉን ጋር በፍቅር በመኖር
10. ለሰሩት ስራ ዋጋ በመስጠት

ስራና መንፈሳዊ ህይወት ምን ሊመስል ይገባል፡፡


ስራ በራሱ መንፈሳዊ አምላካዊ ትእዛዝም ህግም ነው፡፡ 2 ተሰ 3፤10 ከኃጢአት እና
ወደ ኃጢእት ከሚያደርስ ስራ በቀር ልንንቀው ልንተወው የሚገባ ስራ ሊኖር
አይገባም አዳም ወደ ገነት ገብቶ እንዲሰራ ታዞዋልና፡፡ዘፍ 2፤ መንፈሳውያን የሆኑት
መንፈሳዊነትን በተሰማሩበት ማንኛውም የስራ መስክ የሚገልጡ ናቸው፡፡
1. ትጉ ሰራተኞች ልንሆን ይገባናል ምሳ 12፤27
2. ከክፋት የራቅን ቅንነት በተግባር የምናሳይ ሊሆን ይገባል
3. በፍቅር ልንሰራ ይገባናል
4. ያልተገባ ጥቅምን መራቅ ይገባናል
5. ትሁት እና ሰላማዊ ልንሆን ይገባናል
6. ሰዓት አክባሪ በጎ አርአያ ልንሆን ይገባናል
ክርስቲያናዊ አገልግሎት በሰንበቴ ማኅበር፣
ሰንበቴ የሚለው ቃል ሰንበተ አረፈ ሰንበት እረፍት ማለት ሲሆን ሰንበቴ እረፍቴ
የዕረፍት ቀኔ በዓሌ ማለት ነው፡፡
ማኅበር ኀብረ አንድ ሆነ ኅብረት አንድነት ጉባኤ ሸንጎ ማለት ነው፡፡ማኅበር
ብዙዎች ተሰባስበው በአንድ ልብ የሚመክሩበት በአንድ ቃል የሚናገሩበት እርስ
በእርስ የሚረዳዱበት እና የሚተጋገዙበት ብዙዎች አንድ የሚሆኑበት ኅብረት ነው፡፡
ለማኅበር ጥቅም ጥሩ ምሳሌ የራሳችን ሰውነት ነው 1 ቆሮ 12፤12 በሌላ በኩል
ማኅበር ቤተክርስቲያን የሚል ትርጉም አለው የእስራኤል ጉባኤ ጉባኤ
እግዚአብሔር በሐዲስ ኪዳን አቅሌስያ ተብሏል፡፡ ስለዚህ የማኅበር ምንጭ መገኛዋ
ቤተክርስቲያን ናት፡፡ስለ ማኅበር ጌታችን ሁለት ወይም ሶስት በስሜ ብትሰበሰቡ እኔ
በመካከላችሁ እገኛለው ብሎ ቃል ገብቶልናል ማቴ 18፤19 ፣ ቅ.ዳዊት
በመዝሙር 132፤1 ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ መልካም ነው እነሆም ያማረ
ብሎ አስተምሮናል ቅዱስጳውሎስ ደግሞ በዕብ 10፤25 ላይ መሰባሰባችንን አንተው
ብሎናል፡፡

ሰንበቴ ማኅበር እና የአገልግሎቱ ኂደት


በዕለተ ሰንበት ብቻ የሚደረግ ማኅበር ማለት ነው፡፡ ሰንበቴ ማኅበር ክርስቲያኖች
በየሳምንቱ በቤተክርስቲያን በመሰብሰብ መንፈሳዊ ትምህርት እየተማሩ ነዳያንን
እየመገቡ መንፈሳዊ ነገርን እየተወያዩ ያሳልፉ ነበር፡፡ይህ የሰንበቴ ማኅበር
ከእብራውያን የተወሰደ ይመስላል ሲሉ ካህሳይ ግብረ እግዚአብሔር በባህል እና
ክርስቲያናዊ ትውፊትመጽሐፋቸው ገጽ 247 ላይ ገልጸዋል፡፡እብራውያን በዕለተ
ሰንበት በቤተክርስቲያን በመሰብሰብ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት ምግብ
አዘጋጅቶ በመብለት ያሳልፉ ነበርና፡፡ በሐዲስ ኪዳንም የመጀመሪያዎቹ
ክርስቲያኖች ይህንን መንፈሳዊ ባህል በህይወት ይኖሩት እንደነበረ ግብረ ሐዋርያት
ምዕ 1 እና 2 ይነግረናል 1 ቆሮ 11፤27
በሀገራችንም በቀደመው ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጣው ሁሉ ይቆርብ ነበር፡፡
በጊዜው እናቶች ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ቆሎውን ዳቦውን፣ቂጣውን
እንጀራውን አነባበሮ የቻለ ጠላ ይዘው ይመጡና በአንድ ላይ ያስቀምጡታል
ምዕመኑ ቅዳሴ አስቀድሶ ሲወጣ በካህናት አስባርከው ያመጡትን ለምዕመኑ
ያድሉታል ከዛም እሱን በልተው በመምህራን አማካይነት ትምህርት ይሰጣል ከዛም
ስለ ማኅበራዊ እና መንፈሳዊ ህይወታቸው ይወያያሉ ችግር ያለበት መፍትሄ
ሰጠዋል፡፡በድህነት ለሚቸገሩ ገንዘብ እና እህል እንዲዋጣ በማድረግ ይረዱታል፡፡ቤት
የፈረሰበት ካለ እንጨት እና ድንጋይ በማሰባሰብ በጉልበትም ጭምር ረድተውቤቱን
ይሰሩለታል፡፡የተጣሉ ካሉ እንዲታረቁ ይደረጋል፡፡ ምጽዋት ያዋጣሉ ሐዋርያት
የኖሩትን ኑሮ በሰንበቴ ማኅበር ይኖሩታል፡፡ገንዘብ ብቻ ሳይሆን እህል ላጣውእህል
ጉልበት ላነሰው ለታመመው ለደከመው በጉልበት ስራውን ይሰሩለታል፡፡ሰንበቴው
እንደአጥቢያው ምዕመን ብዛት እና ማነስ እንደዚሁም እንደበሀተክርስቲያኑ ቅርበት
እና ርቀት በሳምንት ወይም በወር የሚደረግ ነው፡፡
በቀድሞው ጊዜ የነበረው የሰንበቴ ማኅበር ማኅበርተኞቹ ከመብላት
ከመጠጣጣታቸው በፊት ችግረኞች ያበሉ ያጠጡ ነበር የማኅበሩ ዋና ዓላማውም
ድሆችን መርዳት ነውና፡፡ምዕመናን የሰንበቴ ማኅበራቸውን በሁለት ቦታ ያካሂዱት
ነበር አንደኛ ከቤተክርስቲያኑ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ባለው በር ነው ይህ በር ደጀ
ሰላም የሰላም ደጅ ይባላል፡፡ በኋላ የምዕመኑ ቁጥር እየጨመረ መጥቶ ደጀሰላሙ
የማይበቃሲሆን ደጀ ሰላም የካህናቱብቻ ሆነ፡፡በሌላም በኩል በቀደመው ጊዜ
ሰንበቴውን ህዝብ በሚተላለፍበት ጎዳና፣ዛፍ እና ዋርካ ስርም ያደርጉት ነበር፡፡
ይህንን የሚያደርጉት የአብርሃምን ፍለጋ ለመከተል ነው፡፡በአጠቃላይ በሰንበት ቀን
የሚደረገውን ዝክር እና ሰንበቴ ማኅበር ከስጋ ወደሙ ቀጥሎ ምዕመኑ የበረከት
ምንጭ ነው ብሎ ስለሚያምን ለመቀበል ይሽቀዳደም ይጓጓ ነበር፡፡ ይህም
እንዳይቀርበት ምዕመኑ በሰንበት ዕለት ከቤተ ክርስቲያን አይቀርም ነበር፡፡ማንም
ሰው ለምን ቀረህ ብሎ የሚቀጣው ባይኖርምማንምከሰንበቴ ማኅበር አይቀርም
ነበር፡፡ምክንያቱም ሰንበቴ ማድረግ እና መካፈል መንፈሳዊ ግዴታቸው እንደሆነ
ያምኑ ነበርናካህናቱም ልጆቻቸው መምጣትአለመምጣታቸውን የሚከታተሉት
በሰንበቴ ማኅበር ነበር፡፡የህዝበ ክርስቲያ ቁጥር እየበዛ ሲሄድ ግን ህዝቡ በየቡድኑ
እየተደራጀ በሶስትምበአምስትም ቦታ የሰንበቴ ማኅበር ማቋቋም ጀመረለዚህ
አሰራር ይረዳ ዘንድም ህዝቡ በየጎጡ መደራጀት ጀመረበዚያውም ድግስ አሰራሩም
ተለወጠእንደሌላው ማኅበር ሁሉ አባላት ተራ ገብተው ድግስ መደገስ ጀመሩ ለዚህ
አሰራር ይዳ ዘንድም ማኅበሩ አመራር አስፈለገውበመሆኑም የማኅበሩ አባላት
የሚመራ እና የሚያስተናብር ሙሴ ይመርጣሉ እንደማኅበሩ አባላት ብዛት በአንድ
ቀን ከአንድ በላይ ሰው ሊደግስ ይችላል፡፡ዛሬ ሰንበቴ ማኅበር ዓላማውን እየሳተ
ይመስላል ቀድሞ ድሆች መጀመሪያ በልተው የተረፈውን አባላቱ ለበረከት
ይቃመሱት ነበር ዛር ከአባላቱ የሚተርፈውን ለድሆች ለመስጠት ከባድ ሆኖባቸዋል

3.3 ክርስቲያናዊ አገልግሎት በጽዋ ማኅበር፣


ጽዋ ማለት፡-
አለቃ ኪዳነ ወልድ በመዝገበ ቃላታቸው ገጽ 747 ላይ በቁሙ ስተረጉሙት ጥዋ ፣
ኩባያ፣ ዋንጫ፣ የመጠጥ መሳሪያ ከሸክላ ከእንጨት፣ ከቀርከሃ ከማዕድን የሚሰራ
የተጠሩ ሰዎች የሚጠጡበት ነው ብለዋል ተርጉመዉታል በሌላ መልኩ ደግሞ
ጽዋ መከራ ይሆናል ጌታችን በዕለተ ሐሙስ ይህች ጽዋ ከኔ ትለፍ እንዳለው
ማቴ 26፤39 ማቴ 20፤22 ዮሐ 18፤11

አንድም የከበረ ንዋይ ነው (ከንዋያተ ቅድሳት አንዱ ነው) ዘጸአ 37፤20


፣2 ኛነገሥት 12፤14

አንድም ዕጣ ፈንታ እድል መዝ 10፤6 መዝ 15፤5 መዝ 74፤8

አንድም ቁጣ ኢሳ 51፤22 ህዝ 23፤33 ራዕ 16፤1


አንድም ዝክረ ቅዱሳን ጽዋ ይባላል ማቴ 10፤42 ማር 9፤41 1 ኛ ቆሮ 10፤16

አንድም ስጋ ወደሙ 1 ኛ ቆሮ 11፤26-ሉቃ 22፤20 ማር 14፤23 ማቴ 26፤27 ጽዋ


ይባላል፡፡

ማኅበር ኀብረ አንድ ሆነ ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ማኅበር ኅብረት አንድነት
ማለት ነው፡፡ዘሌ 4፤13

ጽዋ ማኅበር፡- ተጠራርተው በኅብረት በአንድነት ቅዱሳንን የሚዘክሩበት፤ ስለ


ማኅበራዊ ህይወታቸው የሚነጋገሩበት፣ በአንድነት የሚበሉ የሚጠጡበት
የሚያበሉ የሚያጠጡበት የክርስቲያኖች ኅብረት ወይም አንድነት ነው፡፡

የጽዋ ማኅበር ሥርዓት


አባላቱ በቁጥር አስራ ሁለት እና ሀያ አራት ነው ብዙ ጊዜ የሚሆኑት ከዚያ ሊበዙም
ሊያንሱም ይችላሉ፡፡አስራ ሁለት መሆናቸው የአስራሁለቱ ሐዋርያት ሀያ አራት
መሆናቸው የሀያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ምሳሌ ነው፡፡ ማኅበርተኞቹ በወር በወር
የሚዘከር ሲሆን አንድ ሰው የሚደርሰው በዓመት ነው፡፡

ሙሴ
 ሙሴ የእስራኤል ነቢይ መስፍንም ነበር ህዝቡን በመልካም መርቶ ወደ
ምድረ ርስት ያደረሰ ነው፡፡
 የሚመረጠውም ሙሴ የሚባለውም ሰውን በህይወት፣ በትምህርት፣
በትሩፋት እና በአመራሩ ህዝቡን መርቶ ለመንግስተ ሰማያት ማብቃት
ይገባዋል፡፡ ሙሴ የሚመረጠው በጸሎትና በእጣ ነው፡፡ወንድም ሴትም ሊሆኑ
ይችላሉ፡፡ለሴቶች ማኅበር ሴት ለወንዶች ደግሞ ወንድ ይሆናል፡፡
 ሙሴው ለማኅበርተኞቹ በማንኛወም ችግራቸው ወቅት ፈጥኖ
የሚደርስላቸው በበጎ አጠባበቅ የሚጠብቃቸው መሆን አለበት
 ሙሴው በሶስት ይከፈላል
 ሙሴ ሁሉን የሚያከናውን ለሁሉ ተጠሪ ሲሆን
 ደርገ ሙሴ ደግሞ የአገልግሎት ተባባሪው ነው፡፡
 ግልገል ሙሴ ሙሴው በሌለበት ወቅት ሙሴውን ሆነው የሚያስተናብሩ
የሚያስተናግዱ ናቸው፡፡

የሙሴ ተግባር
1.አዲስ አባል ወደ ማኅበሩ ሲመጣከማኅበሩ ጋር መክሮ ፈቃድ ይሰጣል

2.ከማኅበሩ አባል አንዱ እክል ቢገጥመው ቢታመም ቢቸገር ለማኅበሩ ነግሮእርዳታ


ሰብስቦ ያስታምማል ይረዳል
3.አብረውት ከሚያገለግሉት ከደርገ ሙሴ እና ግልገል ሙሴ ጋርበመሆን ማኅበሩን
ያስተናብራልሥነ ሥርዓት ያስይዛል ማኅበሩን ይመክራል
4.በየወሩ ማኅበርተኞች ሲሰበሰቡ አደግድጎ ያስተናብራል

5.ማኅበርተኞቹ ወደቤታቸው ከመሄዳቸው በፊት እስከ ሶስት ወር ድረስ ያሉትን


ባለተራዎች ያሳውቃል

ለማኅበር በሚሰበሰቡበት ወቅት የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናሉ


1.በኅብረት ጸሎት ያደርሳሉ ለቀረ ለታመመ ለተቸገረ ይጸልያሉ

2.ሰአልናከ በኅብረት ይቀምሳሉ በአንድ ጽዋ ይጠጣሉ

3. ቃለ እግዚአብሔርን ይማማራሉ

4.ስለ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ህይወታቸው ይወያያሉ

5. ነዳያንን ጠርተው ያበላሉ ከነዳያኑ የተረፈውን በፍቅር ይበላሉ

6. ቅዱሳንን ይዘክራሉ

7.የተጣላ ያስታርቃሉ
8. ችግረኛ ካለ እንደቆሮንቶነስ ምዕመናን እርዳታ አሰባስበው ይጠይቃሉ 1 ቆሮ 8፤
ሰአልናከ
ሰአልናከ ማለት ለመንህ ማለት ሲሆን ይህ በቤተክርስቲያናችን ደወል ተደውሎ
የኅብረት ጸሎት ደርሶ ማኅበሩ የሚበላው የሚጠጣው ነገር ሰአልናከ ይባላል
ከጸሎት ከልመና በኋላ የሚደረግ በመሆኑ ይህ መደረግ የሚገባው ምንም ምግብ
ሳይበላ ነው ምክንያቱም አንድ ነን ልባችን አንድ ነው ሲሉ ነው እንዲህ
የሚያደርጉት የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በአንድ ልብ ይኖሩ እንደነበር፡፡የሐዋ 2፤
ቅዳሜና እሁድ በዓለ ሃምሳ ሲሆን በጠዋት ነው ማኅበሩ የሚሆነው፡፡ይህ ከስጋ
ወደሙ ጋር የሚገናኝ አይደለም አንዳንዶች እንደዛ የሚያስቡ አሉ፡፡

ከጽዋ ማኅበር ሊስተካከሉ የሚገባቸው ነገሮች


1.ከነዳያን በፊት መብላት

2.አቅምን ያላገናዘበ ድግስ መደገስ

3.ዘፈን እና ስካርን ማብዛት መጣላት

4.ያለ ካህን ምስክርነት ማኅበሩን ማካሄድ

5.በማይታወቅ ሰባኪና እና መምህር መማር

6.ከማኅበርተኛ ጋር ተራክቦ ማድረግ

7.ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን መውጣት


2.6. መንፈሳዊ ኑሮ በማኅበራዊ ህይወት በሰርግ በለቅሶ በጉርብትና በሌላውም
ሁሉ
በጉርብትና እና በማኅበራዊ ህይወታችን ከምናገኛቸው ማኅበራዊ ኩነቶች መካከል
ሰርግ እና ለቅሶ ዋና ዋናዎቹ ናቸው ሰርግም ለቅሶም ግቦም ሞትም ልደትም
የፈጣሪ ስራ ናቸው በዚህ ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ በእግዚአብሔርስራ ተባባሪ
መሆን ነው ህገ እግዚአብሔርን ቃለ ሐዋርያትን የጌታችንን ህይወት መከተልም
ነው፡፡ነቢያቱ ስለ ጋብቻ ክብር ቅድስና አስተምረዋል ዘፍ 2፤18፣ዘፍ 7፤13፣ሚል 2
በሐዲስ ኪዳን ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ በአካል ሰርግ ቤት
ተገኝቶ የጋብቻን ክብር ገልጧል፡፡የመጀመሪያውንም ተዐምራት በእነቱ በድንግል
ማርያም ምልጃ በሰርግ ቤት አድርጓል ቅዱሳን ሐዋርያትም በመልእክታቸው እኛስ
ጋብቻ ንጹህ እንደሆነ ልደትም ርኩሰት እንደሌለበት እንናገራለን ብለው
ለተከታዮቻቸው አስተምረዋል፡፡
በለቅሶ ቤትም ተገኝተን ያዘኑንትን ማጽናናት እንደሚገባን ነቢያቱ ወደግብዣ ቤት
ከመሄድ ወደ ለቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል እርሱ የሰው ሁሉፍጻሜ ነውና
መክ 7፤2 ብለው አስተምረዋል ጌታችን አልአዛር ባረፈ ጊዜ ወደ ለቅሶ ቤትመጥቶ
አልቅሶ ወደመቃብሩ ሄዶ አልአዛርን ከሞት አስነስቶታል፡፡ቅዱሳን ሐዋርያትም
በሮሜ 12፤15 ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ
ብለው ማኅበራዊ መንፈሳዊህይወትን አስተምረውናል፡፡ በጉርብትናም በመልካም
አኗኗር መኖር እንደሚገባን መቅዱሳት መጻህፍት እንደዚህ
ተቀምጧልሩት 4፤17፣2 ነገ 4፤3 ሉቃ 15፤6 ዘጸአ 3፤22 መዝ 31፤1፣44፣13
ስለዚህ አንድ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ህይወት ሲመላለስ በማኅበራዊ ህይወቱ
እንዲህ ሊሆን ይገባዋል
1. አንድ ክርስቲያን በተቻለው ሁሉ ለጎረቤቱ ቅን እና መልካም ሊሆን ይገባዋል
2. ጎረቤቱን በችግሩ ጊዜ ፈጥኖ ሊረዳው ይገባዋል
3. ከጎረቤት ጋር የሚፈጠርን ችግር በእርጋታ በሰላማዊ መንገድ ሊፈታ
ይገባዋል
4. በለቅሶ ቤት በመገኘት በቃለ እግዚአብሔር ሀዘንተኞችን ማጽናናት ይገባዋል
5. በሠርግ ቤት በመገኘት በስራ በማገዝ የደስታቸው ተካፋይ ሊሆን ይገባዋል
6. በሰርግ ቤት በመገኘት በመብላት በመጠጣት ባለመዝፈን ክርስቲያንነቱን
ሊሳይ ይገባዋል
7. በሁሉም ቦታ ከእሱ የሚጠበቀውን በጎ ምግባራት ማከናወን ይገባዋል
8. ጎረቤት ያሉ ወገኖቹን ሲጣሉ መክሮ ማስታረቅ ይገባዋል
9. ክርስቲያን የሆኑትን በንስሐ በስጋ ወደሙ እንዲኖሩ መምከር ይገባዋል
10. መልካም ጉርብትናን በህይወቱ ሊያሳያቸው እና አርአያ ሊሆናቸው
ይገባል
ትዳር እና መንፈሳዊ ህይወት
ትዳር የማኅበራዊ ኑሮ መሰረት ነው፡፡ በመሆኑም ኦርቶዶክሳዊ የትዳር ህይወት
የትክክለኛ መንፈሳውያን መገኛ ምንጭ ነው በመሆኑም ለትዳር ህይወት ትልቅ
ቦታ ልንሰጠው ልንጠነቀቅለት እና ልንንከባከበው የሚገባን ህይወት ነው፡፡ጋብቻ
ሁለት ለአቅመ አዳም እና ለአቅመ ሄዋን የደረሱ ወጣጦች ተፈቃቅደው
የሚመሰርቱት ግቢ ሲሆን ጋብቻ የሚባለው የሁለቱ አንድነት ሲሆን እሱም
የሚደረገው በቤተክርስቲያን በክርስቶስ ስጋ እና ደም ነው ጋብቻውን የማወጃ
በዓሉ ሰርግ ሲባል በጋብቻ አንድ የሆኑ ምዕመናን፣በሰርግ ግቢያቸውን ያወጁ
የሚኖሩት ኑሮ ትዳር ይባላል፡፡ጋብቻ ክቡር ነው ለመኝታውም ርኩሰት የለበትም
ዕብራውያን 13፤4

በዓለማችን የተለያዩ የጋብቻ ዓይነቶች አሉ


1.መንፈሳዊ ጋብቻ

2.ባህላዊ( ልማዳዊ ጋብቻ)

3.ብሔራዊ( ሲቪል)
መንፈሳዊ ጋብቻን ሰው እንደየ እምነቱ የሚፈጽመው ሲሆን
ባህላዊ ጋብቻ ማኅበረሰቡ እንዳደገበት አካባቢ ባህል የሚፈጽመው ነው
ብሔራዊ የሚባለው መንግስታዊ የሆነ እና ይህንን ጉዳይ ለማስፈጸም በተዘጋጀ
አካል የሚደረግ የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ ቅዱስ ተርቱሎስ ከቤተክርስቲያን እውቅና
ውጭ የሚደረግ ግቢ ሁሉ የዝሙት መንገድ ነው ብሎ አስተምሯል በመሆኑም
በባህላዊ እና በብሔራዊ ( ማዘጋጃዊ) ግቢ የፈጸሙ ሁሉ ጋብቻቸውን በህገ ቤተ
ክርስቲያን ሊያጸኑት ይገባል፡፡

የክርስቲያናዊ ጋብቻ ዓላማዎች


1. ለመረዳዳትዘፍ 2፤18
2. ዘር ለመተካትዘፍ 1፤28
3. ከዝሙት ለመጠበቅ ነው 1 ቆሮ 7፤1
ክርስቲያናዊ ጋብቻ በምንም ምክንያት የማይፋቱበት እርስ በእርስ ተከባብረው
ተዋደው የሚኖሩበት ህይወት ነው

ወደ ትክክለኛ የትዳር ህይወት ለመድረስ መጀመሪያ ሊያደርጉ


የሚገባቸውን ነገሮች እነዚህ ናቸው
1. የመንፈሳዊ ህይወት ብስለት መንፈሳዊ ብስለት በመንፈሳዊ ህይወት በማደግ
ሚገኝ የመንፈስ ቅዱስ ሀብት ነውዮሐ 3፤6 በቃለ እግዚአብሔር በነገራተ
ቤተክርስቲያን በምስጢራትዋም እየበረቱ ሲሄዱ የሚገኝ ነው
2. ሥነ ልቡናዊ ብስለት በትዳር ህይወት ለሚገጥሙን ማንኛውም ችግሮች እና
መሰናክሎች ቀድመን ተዘጋጅተን ከገባን ችግር ቢፈጠር እንኳን አንደነግጥም
የጠበቅነው በመሆኑ ሳንበረግግ እንቀበለዋለን መፍትሄ እንፈልግለታለን
ምክንያቱም ቀድመን በሥነ ልቡና ተዘጋጅተንባታልና
3. አካላዊ ብስለት ልጅ አርግዞ አምጦ ለመውለድ ወንዶ ለማሳደግ አካላዊ ብስለት
ሊኖረን ይገባል ማት እድሜያችን እና ሰውነታችን ልጅ ወልደን ለማሳደግ የተዘጋጀ
እና የተገባ ሆነን መገኘት ይገባናል
4. አእምሮአዊ ብስለት ይህ እውቀት ተኮር እድገት ሲሆን ስለትዳር ስለጋብቻ ስለ
ሰርግ ስለ ማኅበራዊ ኑሮ በአጠቃላይ ስለጋብቻ ያለንን እውቀት የምንፈትሽበት
እናእዛ ላይ ደርሻለው ብለን ስናስብ የምንገባበት ነው
5. ምጣኔ ሀብታዊ ብስለት አንድ ወደ ትዳር ለመግባት የሚያስብ ሰው ስለሚበላው
እና ስለሚያበላው ስለሚለብሰው እና ስለሚያለብሰው፣ ስለሚኖርበት ሊያቅድ
ለዛም ሊዘጋጅ ይገባዋልየእለት ጉርሱን የዓመት ልብሱን ለዛም የሚሆነውን ማቀድ
ይገባዋል ለዛም መዘጋጀት አለበት
ከትዳር አጋራችን ጋር ዘወትር በመመካከር ራሳችንን ለካህን እያሳየን መንፈሳዊ
ህይወታችንን እየመረመርን በስጋ ወደሙ ተወስነን ልንኖር ይገባናል::

በጋብቻ ህይወት ስንኖር መንፈሳዊነታችንን የምንገልጥባቸው


መንገዶች ደግሞ በጥቂቱ የሚከተሉት ናቸው፡-
1. በንስሐ ህይወት መመላለስ
2. እርስ በእርስ በስራ መተጋገዝ
3. እንግዶችን መቀበል እግር አጥቦ መማስተናገድ
4. ቤተክርስቲያን ዘወትር በመምጣት መጸለይ ቤት ውስጥም በኅብረት መጸለይ
5. ቤተክርስቲያንን ማገልገል
6. ህመምተኞችን እና ችግረኞችን መጎብኘት
7. እርስ በእርስ መመካከር ውሎን መነጋገር
8. ምንም ዓይነት ክፍተት አለመፍጠር
9. ለሌሎች በጎ አርአያ መልካም አብነት መሆን

You might also like