You are on page 1of 96

መንፈሳዊ ስጦታዎችና አጠቃቀማቸው

ምዕራፍ 1

አጠቃላይ ዳሰሳ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 12
መንፈሳዊ ስጦታዎችና ተፈጥሯዊ ችሎታዎች. . . . . . . . . . . . . . .
መንፈሳዊ ስጦታዎችና ስላሴ
ተገቢውን አተረጓጎም በተግባር ማዋል . . . . . . . . . . . . . . . . .19

ምዕራፍ 2
በ1ኛቆሮ 12 የተገለጡት መንፈሳዊ ስጦታዎችና አጠቃቀማቸው፡፡
የመገለጥ ስጦታዎች. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 22
2.1. የእውቀት ቃል.
2.2. የጥበብ ቃል
2.3. መናፍስትን መለየት

የኃይል ስጦታዎች. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .41


2.4. እምነት
2.5. የፈውስ
2.6. ተአምራት

የማነቃቂያ ስጦታዎች. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .59


2.7. ልሣናት
2.8. ልሣናትን መተርጎም
2.9. የትንቢት ስጦታ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 1


ምዕራፍ 3
በሮሜ 12፡3-7 የተገለጡት መንፈሳዊ ስጦተዎችና አጠቃቀማቸው

ሮሜ ላይ የተገለጡ ስጦታዎች. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .68


3.1 መምራትና ማስተዳደር
3.2 እርዳታ/ አገልግሎት
3.3 መምከር
3.4 መስጠት
3.5 ምህረት የማድረግ.

ምዕራፍ 4
በኤፌ 4፡7-11 የተገለጡት መንፈሳዊ ስጦታዎች
የአገልግሎት ሰጦታዎች. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .76
4.1 ሐዋርያነት
4.2 ነቢይነት
4.3 ወንጌላዊነት
4.4 እረኝነት (መጋቢነት)
4.5 አስተማሪነት.
ማጠቃለያ. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 89

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 2


መንፈሳዊ ስጦታዎችና አጠቃቀማቸው

ምዕራፍ 1

አጠቃላይ ዳሰሳ

መንፈስ ቅዱስ ኃጢአተኛው የሰው ልጅ ክርስቶስን እንዲያምን


ይወቅሰዋል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ወቀሳና ልዩ ረድኤት ወደ ክርስቶስ
የመጣው ኃጢአተኛ አዲስ ጅማሬን ይለማመዳል፡፡ አማኙ በጀመረው
መንገድ በክርስቶስ ፍቅር እንዲያድግ የመንፈስን ቅዱስ ሥራ ወሳኝ
ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለአማኙ አቅሙን ያገናዘበ ሥልጠና ይሰጠዋል፡፡
ይህንንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ልዩ ልዩ አገልጋዮች
በመጠቀምና በአማኙ ግላዊ ሕይወት ውስጥ በመንቀሳቀስ
ያከናውነዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሚከተሉትን አገልግሎቶች በአማኙ
ሕይወት ውስጥ ይፈጽማል፣

(1) ያስተምራል ዮሐ 14፡26


ጌታ ኢየሱስን የገለጠልን መንፈስ ቅዱስ በእኛ በአማኞች ውስጥ እየኖረ
የጌታን ፈቃድ በማድረግ ለመራመድ ለምንፈልግ ለሁላችንም ወቅታዊ
መንፈሳዊ ማዕድ ያዘጋጅልናል፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስን አዳኛችንና
ጌታችንን በሙላት ይገልጠዋል፡፡ የትምህርቱም አድማስ እግዚአብሔርን
ለመምሰል የሚያግዝ ተፈጥሮ አለው፡፡ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን
መማር አቅምን ገንብቶ ማንነትን ቀይሮ የሙያ ክህሎት ሰጥቶ ስያሜን
እንደሚቀይር ሁሉ ከአስተማሪው መንፈስ ጋር ቆይተው የተማሩ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 3


በሙሉ የእግዚአብሔርን የልጁን መልክ እንዲመስሉ ይቀየራሉ፡፡
በውስጣችን የሚኖረው ቅባቱ ሁሉንም በተመለከተ ሚዛን የጠበቀ
ትምህርት ይሰጠናል፡፡ በማንኛውም መንገድ ከሚመጣው፣ በጆሮ
የሚሰማ ትምህርት በላቀ መንገድ ልንገነዘበው በምንችል መንገድ
ነዋሪው ቅባት የመለኮትን እውነት ገሃድ ያደርግልናል፡፡ እግዚአብሔር
በመንፈሱ በኩል የሰማይ ውበቱን ከመንፈሱ ጋር በስምምነት ጎዳና ላይ
ለሚራመድ አማኝ ይገልጣል (1ኛ ቆሮ 2፡9)፡፡
መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ልብ ውስጥ ሊያድር የገባው ለዘላለም
ነው፡፡ ይሁን እንጂ አያሌ አማኞች ለመንፈስ ቅዱስ ትኩረት የሚሰጡት
እነርሱ ሲፈልጉ ብቻ ነው፡፡ እርሱ በጊዜውም አለጊዜውም ውስጣቸው
መኖሩን የሚያስታውሱና ትኩረት የሚሰጡት ጥቂቶች ብቻ መሆናቸው
ያስደነግጣል፡፡ የጌታ መንፈስ በአማኙ ውስጥ ያለማቋረጥ እያለ ትኩረት
ቢነፈገውም፣ መረሳቱ ቅር ቢያሰኘውም እንደሌለ ተቆጥሮ የሚሰራው
አመጽ ግን የበለጠ ቅዱሱን መንፈስ ያሳዝነዋል፣ ያስመርረዋልም (ኢሳ
63፡10 ኤፌ 4፡30)፡፡ የከበረ መንፈሳዊ እድገት በአማኙ ውስጥ
በተግባር የሚታየው አማኙ መንፈስ ቅዱስን እያስተናገደ፣ በውስጡም
የሚኖረው ቅዱሱ መንፈስ እንዳስተማረው እየኖረ እንዲሁም እየጸለየና
እያገለገለ ለመኖር ራሱን የሰጠ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው
ነገር የመረጃ ክምችት ብቻ እንጂ የሕይወት ለውጥን የሚያመጣ
ትምህርት አይሆንም፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠን ትምህርት የባሕሪን
ለውጥ በሕይወታችን ሥር ነቀል በሆነ መንገድ ከማምጣቱም ባሻገር
ጌታን የመምሰል ናፍቆትን በውስጣችን ያጎለብታል፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ
ሳይማር ኃይማኖታዊ እውቀትን በሚሰበስብ ግለሰብ የሚያስገርም
የመረጃ ክምችት ልናይ እንችላለን፡፡ ይሁን እንጂ መንፈስ ቅዱስ
የሚሰጠውን ልደት ተቀብለው ከእርሱ ካልተማሩ የሕይወት ለውጥ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 4


አይመጣም፡፡ ያለኑሮ የሆነን እውነት መለፈፍ ግብዝነት እንደሆነ ሁሉ
እውነት በተገቢው መንገድ ከእኛነታችን ጋር ሳናዋህድ እንለማመደዋለን
የምንለው መንፈሳዊነት ደግሞ መንፈሳዊ ድንቁርና ከመሆን አልፎ ዓይን
ያወጣ ድርቅና ነው፡፡ ይህ መንፈስ ቅዱስ ያልገራው ሕይወት ዓይነተኛ
መግለጫ ነው፡፡

(2) ይመሰክራል ሮሜ 8፡16


የእግዚአብሔር ልጅነታችን ጉዳይ በእኛ በራሳችን ይጠየቃል፣
በዲያብሎስ በራሱ ይጠየቃል፡፡ እንኳን እኛ በብዙ ጉድለታችን
የምንታወቀውና ከፍጥረታችን የቁጣ ልጅ የሆነውን ይቅርና ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነቱን በሚያጠያይቅ
ሁኔታ እንዲመለከት ጥያቄ ቀርቦለት የለ? ለመሆኑ ልጅነታችን ላይጠየቅ
እኛ ማን ነን? እኛ ራሳችን እንኳን ስለራሳችን ሲደበላለቅብን፣ ሕይወት
ሲመሳቀልብን እንጠይቃለን፡፡ ሌሎች የእኛ ጉዳይ ግራ ያጋባቸው ሰዎች
ደግሞ ስለ እኛ ይጠይቃሉ፡፡ መጠየቅ በሰለቸንና ግራ በገባን ጊዜ
ማምለጫችን አንድ ብቻ ነው፡፡ እርሱም እግዚአብሔር በመንፈሱ
አማካኝነት የሚያቀብለን ልዩ እገዛ ነው፡፡ ጥያቄ ናላችን ሲያዞረው
አቅም ስናጣ የመንፈስ ቅዱስ እገዛ ወደ እኛ ይመጣል፡፡ እንዴት? በዚህ
ጊዜ ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን
ጋር ይመሰክራል።›› (ሮሜ 8፡16)
ሌሎች ስለእኛ የእግዚአብሔር ልጅነት በሂደት ከፍሬያችን
ያውቃሉ (ማቴ 7፡16-18 ሉቃ 6፡44-45)፡፡ እኛ ግን ሰለ ራሳችን ሁነኛ
የሆነ ነገር የምንገነዘበው የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን
በሚሰጠን ማረጋገጫ ነው፡፡ የጌታ ሞት ለእኛ መሆኑን ተገንዝበን፣
ኃጢአታችንን ተናዝዘን ራሳችንን ለአምላካችን ስንሰጥ የእርሱ ወገን

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 5


የሚያደርገን መንፈሱ ወደ ውስጣችን መጥቶ ይቀመጣል(ሮሜ 8፡9)፡፡
ይህ ዓለም የማያየውና የማይቀበለው መንፈስ በእኛ ውስጥ ሆኖ
የእግዚአብሔር ልጅነታችንን ይመሰክራል (ዮሐ 14፡16 ሮሜ 8፡16)፡፡
የምድር ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ከሚሰጡን ተጨባጭ ማረጋገጫ
የሚበልጠውና የተሻለው ከውስጣችን የምንሰማው አስተማማኝ
የመንፈስ ቅዱስ ማረጋገጫ ነው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ልዩ እገዛ የተነሳ
እርግጠኝነት ውስጣችን ይፈስሳል፡፡ የአምላክ ልጅነታችንን ጥያቄ
ውስጥ በማስገባት በተቃዎሞ የሚያጣድፉን ቢበዙ እንኳን የተረጋጋን
እንሆናለን፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሰጠን ውስጣዊ ማረጋገጭ ልባችንን
ይደግፍልናልና፡፡
ማርቲን ሉተር የተባለው የተሃድሶ መልእክተኛ ጽድቅን በሥራ
ለማግኘት ለዓመታት ደከመ፡፡ ይሁን እንጂ የድርጊቱ ብዛት ተስፋ
አስቆረጠው እንጂ እርግጠኛነት እንዲሰማው አላደረገም፡፡ ከአያሌ
ዘመናት ልፋት በኋላ ከጌታ ጋር በእምነት ተዋወቀ፡፡ የእግዚአብሔር
ልጅነቱን የሚያስረግጥ ተጨባጭ ነገር በመንፈስ ቅዱስ ልዩ ረድኤት
አማካኝነት በውስጡ ፈሰሰ፡፡ ይህንን እርግጠኛነቱን ለመንጠቅ
መረዳቱን በሚቃወሙ ተቃዋሚዎቹ የተሰነዘረ ብዙ ዛቻ ሰማ፡፡
እንደውም ሊያስፈራሩት ከሞከሩት መካከል ቀንደኛ የነበሩት ጳጳሱ
እንዲህ ሲሉ መልእክት ላኩበት ‹‹ሉተር ዓለም በሞላ ተቃውማሃለችና
ብትጠነቀቅ ይሻላል›› አሉት፡፡ ከብዙ ሰዎችም ሆነ ከጳጳሱ ከራሳቸው
ይህንን የተቃውሞ ድምጽ የሰማው ሉተር ሊፈራና ሊደነግጥ ይገባው
ነበር፡፡ ጳጳሱም ይህንን መልእክት የላኩበት ዋናው ምክንያት
የተቃውሞውን ግዝፈት አይቶ በመፍራት ከገባው እውነት ያፈገፍጋል
በሚል ተስፋ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ማርቲን ሉተር ለዚህ ግዙፍ ተቃውሞ
ሲመልስ ‹‹እንግዲያው እኔም ዓለምን ተቃውሜያታለሁ›› አለ፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 6


ይህንን በመሰለ እርግጠኝነት የሚሞላ የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ
ነው፡፡
(3) ይመራል ሮሜ (8፡14)
መንፈሳዊ እርምጃ የብልሃት አይደለም የምሪት ነው፡፡
በሕይወታችን እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበትን እኛም የምንታነጽበትን
ነገር የማድረጉ ጉዳይ የጉልበት አይደለም የረድኤት ነው፡፡ነገራችን
በተቀላጠፈ መንገድ ሕይወታችን የሰመረ እንዲሆን የሚያስፈልገን የሰላ
አእምሮ ሳይሆን ከመንፈስ ቅዱስ የሚለቀቅ ምሪት ነው፡፡ በብሉይ
ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን የጌታ ምሪት በብዙ መልኩ የጌታን ልጆች
ትክክለኛውን ነገር በትክክለኛ ጊዜና ቦታ በማድረግ እንዲመላለሱ
ለማድረግ የሚረዳ ምሪት በመስጠት መንፈስ ቅዱስ ፈቃዱን ሲገልጥ
ይስተዋላል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ትኩረታችንን በሚያገኝበት መንገድ
ለልባችን ይናገራል፡፡ ፈቃዳችንን አይጥስም፡፡ በሚገባን መንገድ ተናግሮ
ወደ ፈቃዱ ይመራናል፡፡ ጌታ ኢየሱስም ይህንን በተመለከተ ሲናገር
‹‹የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ
አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።›› (ዮሐ 8፡12)፡፡ መንፈሳዊ ሕይወት
የጌታን ፈቃድ አውቆ በእርሱ መመራት ነው፡፡ ክርስትና ጌታን መከተል
ነው፡፡ የእርሱን ፍላጎት በተግባር በሕይወት በተግባር ላይ ማዋል ነው፡፡
ሰው ከሕያው ብርሃን ከጌታ ኢየሱስ ጋር ሕያው ግንኙነት ሲኖረው
ሚዛናዊ፣ የተረጋጋ ልበ ሙሉ፣ ጤነኛ የሕይወት አቋም ውስጥ
ይሆናል፡፡ የማያየው ነገር ባለመኖሩ ነገሮችን እንደ አመጣጣቸው
ያስተናግዳቸዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ ሥጋት የራቀው ኑሮ ለመኖር
ይታደላል፡፡ ያለ ብርሃን ማየት የሆነለት ማን ነው? አካላዊ ብርሃን
ሲገለጥ ሌላውን መመልከት ከባድ አይሆንም፡፡ ማየት የቻልነው
ዓይናችንና ውጫዊው ብርሃን በተገቢው መንገድ ስለተቀናጁ ነው፡፡ ያለ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 7


ሚዛናዊ ቅንጅታቸው ማየት ከባድ ነው፡፡ ልክ እንዲሁ መንፈሳዊውን
ነገር ለማየት ከጌታ ጋር ትክክለኛ ሕብረት መፍጠር አለብን፡፡ ጌታ
ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈሳዊ ብርሃን ይለግሰናል ‹‹በእኔ የሚያምን ሁሉ
በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፡፡›› ዮሐ
12፡46፡፡ ብሏልና፡፡

(4)ይወቅሳል ዮሐ 16፡7-8
‹‹እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን
እልክላችኋለሁ።እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም
ዓለምን ይወቅሳል፡፡›› (ዮሐ 16፡7-8) ወቀሳ አሌ የማይባል ማስረጃን
በታራሚው ኃጢአተኛ ፊት በማቅረብ ተገቢውን ብያኔ መስጠት ነው፡፡
መንፈስ ቅዱስ ኃጢአተኛው ቅጣት የሚገባው ምርጫ የለሽ ጥፋተኛ
መሆኑን አሳይቶ ፊቱን ወደ ምህረት ጌታ እንዲያዞር የፍቅር ግብዣ
ያደርግለታል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ኃጢአተኛው ፊቱን ወደ መንፈሳዊ ነገር
እንዲያዞርና ለመንፈሳዊነት ትኩረት እንዲሰጥ ገና ከጅማሬው የወቀሳ
ሥራውን በመሥራት ትክክለኛውን ጎዳና ያመለክታል፡፡ መንፈስ ቅዱስ
ይወቅሳል፣ (ዮሐ 16፡7-8)፡፡ ከእግዚአብሔር ከአምላካችን ተለይተን
የምንሄድበትን መስመር አክሳሪነትና ያለጌታ ያለውን ሕይወት ብልሹነት
ገሐድ በማድረግ የሞራል ብያኔ አስተላልፎ ጥፋተኝነትን ያሳውቃል፡፡
የተሰበከልንን፣ የሚሰበክልንን ወይም ብቻችን ሳለን ያነበብነው ሕያው
ቃል በመጠቀም አንተ(ቺ) ወይም እናንተ ኃጢአተኞች ናችሁ
የሚለውን ውሳኔ በውስጣችን እንድንሰማውና ያለንበት ሰባራ ሁኔታ
ወለል ብሎ እንዲታየን ያደርጋል፡፡ እንዲህ ላለው የመንፈስ ቅዱስ
የወቀሳ ድምጽ አዎንታዊ ምላሽ ስንሰጥ በዚያው ቅጽበት ጌታን በማመን
ራሳችንን ለፈጣሪ ፈቃድ ሰጥተን ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 8


በስምምነት እንድራመድ ያደርጋል፡፡ አማኙንም መንፈስ ቅዱስ
ይወቅሳል፡፡ ለመንፈስ ቅዱስ ማንም የቅርብ ዘመዱ አይደለም፡፡
ስለሆነም መንፈስ ቅዱስ አያመቻምችም፡፡ ስህተታችንንም እያየ ከእኛ
ጋር ስላለው ቅርበት ብሎ በይሉኝታ አያልፈንም፡፡ ወቀሳዎቹ እንደ
አቃቤ ሕግ ፋይል ከፍቶ የተወነጀልንበትን ጭብጥ ይዞ ተራ በተራ
ክሱን መደርደር ሳይሆን ጨዋ በሆነና ልንረዳው በምንችል
በማናስተባብልበት መንገድ ይወቅሳል ፡፡ ለውስጣችንም በሚታወቀን
መንገድ በምልክት በእኛ እንቅስቃሴ የተበላሸውን ነገር ያሳየናል፡፡
ቀጥተኛ በሆነ በሚገባን መንገድ ስለሚናገር ወቀሳው ያለብዙ ውትወታ
ፍንትው ብሎ ይታየናል፡፡ የመንፈስ ቅዱስን ወቀሳ የሰማ ሰው
ከሚሄድበት ጠማማ መንገድ ይመለሳል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ባሳየውም
መንገድ ይጓዛል እንደዚያ ሲሆን መንፈሳዊነቱ ይጎለብታል፡፡

(5)ያዝዛል ሰዎችንም አቅጣጫ ያሳያል (የሐዋ 8፡29)

ይህንንም በሐዋርያት ሥራ ላይ እንዲህ በሚል መልኩ ተመዝግቦ


እናገኛለን ‹‹የጌታም መልአክ ፊልጶስን። ተነሥተህ በደቡብ በኩል
ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ
ሂድ አለው።›› (የሐዋ 8፡26) የታዘዘውን ፈጽሞ በጣቢያው በተገኘ ጊዜ
መንፈስ ተከታይ ምሪት ሰው እንዲህ ሲል ‹‹መንፈስም ፊልጶስን።
ወደዚህ ሰረገላ ቅረብና ተገናኝ አለው።›› መንፈስ ቅዱስ ልዩ ልዩ
መንገድን በመጠቀም ትዕዛዝን ያስተላልፋል፡፡ ለምሳሌ የፊሊጶስና
የጃንደረባው ግንኙነት መንፈስ ቅዱስ በሰጠው ትዕዛዝ የተከናወነ
ነበር፡፡ ምስኪኑ ኃይማኖተኛ በደረቅ ንባብ በተዳከመ ጊዜ የሚያነበውን
ለማስተዋል የሚሆን ምሪት እንዲቀበል መንፈስ ቅዱስ ረጂና ተረጂን

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 9


በማገናኘት ፈጸመ፡፡ መሪ ፈላጊው መሪውን ሲያገኝ መሪው ደግሞ
ተገልጋዩን አገኘ፡፡ ይህም ሁሉቱን ባገናኘው መልአክ አማካኝነት
ተፈጸመ፡፡ ሁለቱም ተፈላልገው መገናኘት የሚችሉበት ሁኔታ
ውስብስብ ነበር፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ተአምራዊ ምሪት መፈጸም
በሚችለው መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ተገናኝተው የጌታን ደስታ
ተለማመዱ፡፡ ጃንደረባው ደስ እያለው እንደሄደ ፊሊጶስም የጌታን
ትዕዛዝ በመፈጸሙ ደስታው ታላቅ እንደነበር መገመት አያስቸግርም፡፡
መንፈስ ቅዱሰ‹‹ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን። እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥
ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሣብህ የለምና አትፍራ፥ ነገር ግን ተናገር
ዝምም አትበል፤ በዚህ ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉኝና
አለው።በመካከላቸውም የእግዚአብሔርን ቃል እያስተማረ ዓመት
ከስድስት ወር ተቀመጠ።›› (የሐዋ 18፡9-11) ከጌታ ትዕዛዝ
እንደምንረዳው ጳውሎስን ስጋት ውስጥ የጨመረ ሁኔታ ነበር፡፡
ከፍርሃትም የተነሳ ዝም ከማለቱ ባሻገር አካባቢውን ለቆ ለመሄድ ፈተና
ውስጥ እንደነበር መገመት አያስቸግርም፡፡ ባይፈራ አትፍራ አይባልም፡፡
ላለመናገር ውሳኔ ውስጥ ባይሆን ደግሞ ዝምም አትበል አይባልም
ነበር፡፡ ሥጋቱ የመነጨው ሰዎች በጭካኔያቸው ሊያደርሱበት
የሚችሉትን ከመፍራት ጋር ይያያዝ ነበር፡፡ ጌታ የሚነሳብሕ የለም ሲል
አረጋጋው፡፡ እንደውም ቦታው የጠላት መንደር ሳይሆን ጌታ
የሚያድናቸው ሕዝቦች ያሉበት ቦታ ነው፡፡ ጳውሎስ በዚያ ሥፍራ
ለበርካታ ወራት እንዲቆይ የጌታ መንፈስ ድፍረትን ሰጠው፡፡

(6)ሰዎችን ለመንፈሳዊ አገልግሎት ይጠራል (የሐዋ 13፡2)


‹‹ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ። በርናባስንና ሳውልን
ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ።››

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 10


መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን በመጠቀም ሰዎች ለአገልግሎት እንዲለዩ
ይጠራል፡፡ ይህ መልእክት በምን መልክ እንደመጣ ክፍሉ ግልጥ
አያደርግም፡፡ ‹‹መንፈስ ቅዱስ … ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ›› ግን
መልእክቱ ከማን እንደ መጣ፣ ስለ እነማን እንደሆነ፣ ለማን እንደሆነ
በቀጥታ ገሐድ የሆኑ ነገሮች አሉ፡፡

(7) ሰዎችን ለመንፈሳዊ አግልግሎት ይልካል (የሐዋ 8፡29-36፤ 13፡4)


‹‹በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ›› (13፡4)
መንፈስ ቅዱስ ፊሊጶስን ወደ ‹‹ሠረገላው ቅረብ›› ብሎ የሚያነበውን
ለማስተዋል ወደ ተቸገረ ሰው ላከው፡፡ የተላከው ፊሊጶስ ጀንደረባውን
እውነትን ሊረዳ በሚችል አስተምሮ ከጌታ ጋር እንዲታረቅ አድርጎ
አጠመቀው፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት ማከናወን ያስቻለው ላኪና
ተቀባይን ያገናኘ መንፈስ ነበር፡፡ ወደ ‹‹ሠረገላው ቅረብ›› እንዲሁም
‹‹ተልከው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ›› የሚሉት አረፍተ ነገሮችን በቅርበት
ስንመለት መንፈስ ቅዱስ ሥምሪት በመስጠትና ልጆቹ በማሰማራቱ
ሥራ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደነበር አንስተውላለን፡፡ መልእክተኞ ልኮ
ስምሪት የሚሰጣቸው ጌታ ያስፈልጋቸዋል ወዶ ዘማቾች አይደሉምና፡፡

(8) ለቅዱሳን ይማልዳል (ሮሜ 8፡26)


ሐዋርያው በሮሜ 8፡26 ልዩ ስለሆነው የመንፈስ ቅዱስ እገዛ
ይናገራል፡፡ በመቃተት መማለድ መንፈስ ቅዱስ አማኙ ውስጥ በመሆን
ለአማኙ የሚሰጠው በቃል ሙሉ ለሙሉ ሊገነዘበው የማይችል
አገልግሎት ነው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ‹‹..በቃላት ሊገለጥ በማይችል
መቃተት ለእኛ ይማልዳል›› (ሮሜ 8፡26) መንፈስ ቅዱስ በአማኙ
ውስጥ በተፈለገውና ወሳኝ በሆነው ሰዓት የሚያከናውነው ይህ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 11


አገልግሎት ምልጃ የሚል ስያሜ እንደ ተሰጥቶታል፡፡ መማለድ ማለት
ምን ማለት ነው በአጭሩ ሲገለጥ መማለድ ማለት በሌላው ፈንታ
መገኘት ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ደግሞ መማለድ ማለት ተተክቶ
ማማጥ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ሆኖ በሚገባን አረፍተ
ነገር ሳይሆን ጌታችን ጋ መልእክቱ በሚደርስበት ኮድ የወቅቱን ሁኔታ
በትክክል ለሰማይ ያስተላልፋል፡፡ አንዳንዱን የመንፈሳዊ ዓለም
ምስጢር ለፍጡር እንደሚገባ አድርጎ መናገር ያስቸግራል፡፡ ለምሳሌ
ዳንኤል ጸሎቱ የተሰማው ገና በመጀመሪያው ቀን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ
ለመዘግየቱ ምክንያት ጌታ አለመስማቱ ሳይሆን መልሱን ይዞ
የሚመጣውን የአምላክ መልእክተኛ የተቋቋሙ ኃይላት በመንገድ ላይ
በፈጠሩት እንቅፋት ነበር (ዳን 10፡1-21)፡፡ ለእግዚአብሔር ሰው
መልእክቱን ለማድረስ ጉዞው ምንያህል ቀናት እንደፈጀ መጽሐፍ ቅዱስ
በገልጽ ያስቀምጥልናል፡፡ ይህ ተጨባጭ ምሳሌ ገሃድ የሚያደርግልን
እውነታ መንፈሳዊው ዓለም ከምናስበውና ከምንገምተው በላይ
ውስብስብ መሆኑን ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ ያለረዳት መወጣት
ስለማንችል እግዚአብሔር ወኪል ሳይሆን ራሱን ሰጠን፡፡ መንፈስ
ቅዱስና አብ ያለቃላት ይገናኛሉ፡፡ መርማሪው መንፈስ የጌታን ሃሳብ
ያውቃል አእምሮም አለው፡፡ ቃላትን በመጠቀም ማብራሪያ ሳይሰጡ
መናበብ መቻል ጥልቅ እውቀትን የምናገኘበት ምሳሌነት ነው፡፡ በዚህ
ሥፍራ አብና መንፈስ ቅዱስ የሚያሳዩንም ይህንን ታላቅ የሕይወት
ምስጢር ነው፡፡ አብና መንፈስ ቅዱስ በመሐላቸው በሚፈሰው ሕይወት
ተሳስረዋልና አንዱ መናገር ሳያስፈልገው ሌላው ይረዳዋል(ሮሜ
8፡26)፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 12


(9) እምቢተኛን … ይለያል (ዘፍ 6፡3 ኢሳ 63፡10፣ ኤፌ 4፡30)

‹‹መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፥ እርሱ ሥጋ ነውና››፡፡


(ዘፍ 6፡3)
መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን ተገቢውን እንክብካቤ በመስጠት ደስ
የሚሰኘውን ያህል በጎነቱን ባልተረዱለትና ሆን ብለው በሚያምጹ
ልጆቹ ያዝናል፤ ይመረራልም፡፡ በብሉይ ኪዳን ከመመረሩ የተነሳ
ትቷቸው ለመሄድ ይገደድ ነበር፡፡

ከላይ በመጠኑ እንደተገለጸው አማኝ ውስጥ የሚኖረው መንፈስ


ቅዱስ በጥቂቱ የተዘረዘሩት ዓይነተኛ አገልግሎቶች አሉት፡፡ በዚህ
አገልግሎቱ ሁሉም አማኞች እኩል እንደማይጠቀሙ የቅዱሳን
ተግባራዊ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ በውስጣቸው ኖሮ ሥራውን
እንደሚሠራ የሚገነዘቡ ጥቂቶች ቢኖሩም፣ አያሌ አማኞች ከመንፈስ
ቅዱስ ጋር በስምምነትና በብስለት መቀናጀት አይሆንላቸውም፡፡
የቆሮንቶስ አማኞች የወደቁበት ፈተና ዛሬም በዘመናችን ብዙ
አማንያንን ሲያስቸግር ይስተዋላል (1ኛቆሮ 6፡19)፡፡ መንፈስ ቅዱስ
የሰማያዊ አባታችንን ባሕሪ በአማኙ ውስጥ ሊገነባ ይኖራል፡፡ ይሁን
እንጂ አያሌ አማኞች ለዚህ ተልእኮው ንቁ አይደሉም፡፡ ሐዋርያው
ጳውሎስ በዚህ መሰሉ የግዴለሽ ኑሮ የታወቁትን የቆሮንቶስ አማኞች
እንዲህ ሲል ይጠይቃል ‹‹የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲኖርባችሁ
አታውቁምን›› (1ኛቆሮ 3፡16) የዚህ ጥናት መሠረታዊ ዓላማ
መንፈሳዊ ስጦታዎችንና አጠቃቀማቸውን በተመለከተ በአማኞች ዘንድ
በቂ ግንዛቤ እንዲገኝ እንጂ ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነትና አገልግሎት

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 13


የተብራራና ጥልቀት ያለው ትምህርት መስጠት አይደለም፡፡ በርዕሰ
ጉዳዩ ጥልቀት ያለው ትምህርት ለማግኘት ሌሎችን ከመንፈስ ቅዱስ
ማንነትና አገልግሎት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን መመልከት ተገቢ
ነው፡፡ የዚህ ጥናታችን ትኩረት ግን መንፈሳዊ ስጦታዎችና
አጠቃቀማቸውን ይመለከታል፡፡
ቅዱሳን መንፈሳዊ ስጦታን አስመልክቶ በሚሰጡት ፍቺ ሁለት
ቦታ ይመደባሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ መንፈሳዊ ስጦታዎች መሠረት ጣይ
ስለነበሩ መሠረቱም የሚጣለው አንዴ ብቻ ስለሆነ በዛሬው ዘመን
እንደ አዲስ ኪዳን ዘመን መንፈሳዊ ስጦታዎች አይሰሩም፡፡ በእነዚህ
ቅዱሳን እይታ ስጦታዎች አብቅቶላቸዋል፡፡ ሃሳባቸውንም ለመደገፍ
(ኤፌ 2፡18-22፣ ዕብ 2፡2-4፣ 1ኛቆሮ 13፡8) በመጥቀስ ማስረጃ
ያቀርባሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ መንፈሳዊ ስጦታዎች በቤተ ክርስቲያን
የጅማሬ ዘመን ብቻ ሳይሆን ጌታ መጥቶ እስኪወስደን ድረስ ቅዱሳንን
ያጽናናሉ እንዲሁም ያንጻሉ፣ በማለት ይከራከራሉ፡፡ ይህንን
ሃሳባቸውን ለመደገፍ የሚከተሉትን ክፍሎች እንደ ማስረጃ ያቀርባሉ
(1ኛቆሮ 12፡8-9፣28፣ሮሜ 12፡4-7፣ኤፌ 4፡111ኛጴጥ 4፡10-11)
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው በአዲስ ኪዳን የጸጋ ስጦታዎችንና
አሠራራቸውን በዝርዝር የሚገልጡ አራት ክፍሎች አሉ፡፡ አንዳንድ
የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች በ1ኛቆሮ 12፡8-9 የተገለጡትን የጸጋ
ስጦተዎች ላይ ብቻ በማትኮር ስለ ዘጠኙ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች
ብቻ መናገርና ማስተማር ይቀናቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ለመጽሐፍ ቅዱስ
ትምህርት ታማኝ እንሁን ካልን የጸጋ ስጦታዎችን በእነዚህ ብቻ
መገደብ ሚዛናዊነት እንደሚጎድለው እንገነዘባለን፡፡ ስጦታዎችን
በዘጠኝ ገድቦ ለማስተማር በተመረጠበት ክፍል እንኳን የስጦታዎቹ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 14


መዘርዝር ከዘጠኝ በልጦ እንመለከታለን፡፡ በአራቱ ክፍሎች
የተጠቀሱት የጸጋ ስጦታዎች መዘርዝር፣

ሠንጠረዥ አንድ የሥጦታዎች መዘርዝር በአዲስ ኪዳን


ስጦታቸው በተገለጡበት ክፍልና ዓይነታቸውን ያሳያል፡፡

1ኛቆሮ 12፡8-9፣28 ሮሜ 12፡4-7 ኤፌ 4፡11 1ኛጴጥ 4፡10-11


ጥበብ ትንቢት ሐዋርያ የሚናገር
እውቀት አገልግሎት ነቢይ የሚያገለግል
መናፍስትን መለየት ማስተማር ወንጌላዊ
እምነት መምከር እረኛ
ፈውስ መስጠት አስተማሪ
ታምራት ማድረግ መግዛት
በልዩ ልሳን መናገር ምህረት
ልሳን መተርጎም
ትንቢት
ሐዋርያት
ነቢያት
አስተማሪ
እርዳታ
አገዛዝ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 15


መንፈሳዊ ስጦታዎችና አመዳደባቸው
መንፈሳዊ ስጦታዎችን ከሚሠሩበት መሠረታዊ ባህርያት
ጋር በማስተሳሰር በቡድን መክፈልን የማስተማር መንገዳቸው
አድርገው የሚወስዱ ቅዱሳን ብዙ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ
አገልግሎትን ለማቀላጠፍ የሚረዱ ስጦታዎችና ለቤተ ክርስቲያን
በስጦታ መልክ የሚሰጡ ሰዎችን መለየት ተገቢ ነው ይላሉ፡፡
በሚሠሩበት መንገድ በመመደብ ማጥናት

በንግግር የሚገለጡ በተግባራዊ በተአምራዊ ኃይል


አገልግሎት የሚገለጡ
የሚገለጡ
ጥበብ ልግስና ፈውስ
እውቀት ማስተዳደር ተአምራት ማድረግ
ልሳንና ትርጉሙ ምህረት ማድረግ እምነት
ትንቢት ሌሎችን ማገልገል መናፍስትን መለየት
ወንጌላዊነት
አስተማሪነት
መምከር
ሐዋርያነት
እረኝነት

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 16


የስጦታዎች ዓላማ የእግዚአብሔርን ረቂቅ ጥበብ በአማኞች
መተናነጽ ለትእይንቱ ተመልካቾች በተግባር በማሳየት ሰዎች ለጌታ
አክብሮትን እያሳዩ ፍጹም መገዛትን እንዲለማመዱ ነው፡፡ እነዚህ
መንፈሳዊ ስጦታዎች በአምላክ ረቂቅ ጥበብ ተሳስረው ለአንድ
ታላቅ ግብ ሲሰሩ ትኩረትን የሚስብ ውበት ይገለጣል፡፡ ሐዋርያው
ጳውሎስ ይህንን ሁኔታ በኤፌ 3፡10 ላይ ይገልጸዋል፡፡ ይህ ቃል
(ፓሉፓይኪሎስ) በአብዛኛው ጥቅም ላይ ውሎ የምናገኘው
የጥበብ ሥራዎችን ለመግለጽ ነው፡፡ አበቦችን፣ ዘውድን እንዲሁም
በልዩ ቅንብር የተሠራ ሥጋጃን ለመግለጽ ያገለግላል፡፡ ልክ እንዲሁ
ጌታ በልጆቹ ውስጥ ባኖረው ልዩ ልዩ ጸጋ በሚደረግ የሕብረት
አገልግሎት የአምላክ ረቂቅ ጥበብ ይገለጣል፡፡ ከልዩ ልዩ ቀለሞች
በጥንቃቄና በተጠና ቅንብር የሚሠሩ የጥበብ ሥራዎች አይንን
እንደሚማርኩ ሁሉ ከእግዚአብሔር ልግስና እና ባለጠግነት የተነሳ
ለአማኞች የተሰጡት መንፈሳዊ ስጦታዎች ተገቢ ቅንጅታቸውን
ጠብቀው ሲያያዙ የአምላካችንን አስገራሚ ጥበብና ውብ አሠራሩን
በገሃድ ለማሳየት የየበኩላቸውን የብርሃን ጮራ ይፈነጥቃሉ፡፡
የሁላችንም ፈጣሪ የሆነው የሰማይ አምላክ ከቸርነቱ የተነሳ
ይህንን የጸጋ ሥራውን በመካከላችን እውን ያደርጋል፡፡

መንፈሳዊ ስጦታዎችና ተፈጥሯዊ ችሎታዎች


የመንፈሳዊ ስጦታዎችና የተፈጥሯዊ ችሎታዎች ጉዳይ በቅዱሳን
መሐል አነጋጋሪ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ሲደባልቋቸው ሌሎች ደግሞ
ነጣጥለው ያይዋቸዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ መነጋገር ሰንበት ብሏል
ቅዱሳን የተመቻቸውን እየያዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ያሉትን
እየተቀበሉ የሚያምኑትን ለማስታወቅ ጥረዋል፡፡ ለእኛም ያለን

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 17


ምርጫ ይኸው ነው፡፡ ቅዱሳን አንድ ናቸው የተለያዩ ናቸው
በሚለው ቦታ ላይ ናቸው፡፡
አንድ ናቸው
አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች ተፈጥሮአዊ ችሎታዎችና
መንፈሳዊ ስጦታዎች ምንም ልዩነት የላቸውም የሚል አቋም
አላቸው፡፡ ለዚህም መነሻ የሚያደርጉት መጽሐፍ ቅዱስ
ተፈጥሮአዊ ችሎታዎችንና መንፈሳዊ ስጦታዎችን ከፋፍሎ
ያስቀመጠበት ግልጽ ማስረጃ ባለመኖሩ ሁለቱን መነጣጠሉ የተገባ
አይደለም በማለት ይከራከራሉ፡፡

የተለያዩ ናቸው
መንፈሳዊ ስጦታዎችና ተፈጥሮአዊ ችሎታዎች የሚመሳሰሉበት ነገር
ቢኖርም አንድ ዓይነት ግን አይደሉም፡፡ ወንዶችና ሴቶች
በተፈጥሮአቸው እንደሚለያዩ ሁሉ ተፈጥሮአዊ ችሎታዎችና
መንፈሳዊ ስጦታዎች ራሱን የቻለ ልዩነት አላቸው፡፡ እርግጥ ነው
የሁለቱም ምንጭ እግዚአብሔር ነው፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ
ሊመሳሰሉ የሚችሉበት ሁኔታ አለ፡፡ ይሁን እንጂ ተፈጥሮአዊ
ልደትና ዳግም ልደት እንደሚለያዩ ሁሉ መንፈሳዊ ስጦታዎችና
ተፈጥሮአዊ ችሎታዎች የዚያኑ ያህል ይለያያሉ፡፡ ባመኑትና
ባለመኑት መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ የሚያስገነዝቡን
መንፈሳዊ ስጦታዎች ናቸው፡፡ መንፈሳዊ ስጦታዎች ያመነ ሰው
እድል ፈንታ ናቸው፡፡ መንፈሳዊ ስጦታዎች ለአማኙ በክርስቶስ
አካል ውስጥ ሥፍራን ይሰጡታል፡፡ ያለእነዚህ ስጦታዎች አማኝ
የተጣለበትን አደራ በቀላሉ አይገነዘብም፡፡ ስለ ልዩነታቸው እንዲህ
ብንናገርም የሚገናኙበት ሁኔታ የለም ማለት ግን አይቻልም፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 18


ግንኙነታቸው
1ኛ. የሁለቱም ምንጭ እግዚአብሔር መሆኑ፣ እግዚአብሔር
በተፈጥሮአችን ውስጥ ለተቀመጡ ልዩ ልዩ ችሎታዎቻችን ምንጭ
ነው፡፡ ማንም ለራሱ ያንን ማድረግ አይቻለውም፡፡ ተፈጥሮአዊ
ችሎታዎቻችን በስልጠና ቢዳብሩም በምርጫችን የኛ
ልናደርጋቸው አንችልም፡፡ ድምጻችንን፣ በባሕሪያችን ውስጥ
የተቀመጡ ልዩ ልዩ የማንነቶቻችን መግለጫዎች የመነጩት
ከሰጪው ነው፡፡
2ኛ. ተፈጥሮአዊ ችሎታዎች ለበጎ ምግባር የሚውሉ መሆናቸው፣
በተፈጥሮ ችሎታችን ውስጥ የተቀመጡ አንዳንድ ተሰጥኦዎች
እግዚአብሔር በአማኙ ውስጥ ለሚሠራው ሥራ አመቺ ሁኔታን
ይፈጥራሉ፡፡ ለምሳሌ ድምጻቸው መረዋ የሆኑ ሰዎች ዘፋኝ ሆነው
ያገለገሉትን ያህል ዘማሪ ሆነው ሊያገልገሉ የሚችሉበት ሁኔታ
መፈጠሩ፣ በባህሪያቸው ለጋስ የሆኑ ሰዎች የምህረት አድራጊነት
ጸጋ በውስጣቸው ሊሠራ መቻሉ፣ ተናጋሪና ፀሐፊ የሆኑ ሰዎችን
ሰባኪና መምህራን ለመሆን መቻላቸው ከብዙ በጥቂቱ
ይጠቀሳሉ፡፡

መንፈሳዊ ስጦታዎች
የጸጋ ስጦታዎች ስማቸው እንደሚያመለክተው እግዚአብሔር
ከርህራሄው የተነሳ ቅጣት ለሚገባቸው ሰዎች ያደረገው ልግስናዎች
ናቸው፡፡ ሁሉም አማኞች የዚህ እድል ፈንታ ተካፋይ ናቸው፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 19


ይሁን እንጂ ስጦታውን የሚቀበሉና በአግባቡ የሚያስተናግዱ ብዙ
አይደሉም፡፡ መንፈሳዊ ስጦታዎች ለተቀባዩ ጥቅምና መታነጽ
የተሰጡ ቢሆንም አውራ ግባቸው የክርስቶስን አካል ማነቃቃትና
መገንባት ነው፡፡ ስለ ስጦታ በተጠቀሰባቸው አራቱ የአዲስ ኪዳን
ክፍሎች ወደ ሃያ የሚሆኑ ስጦታዎች ተዘርዝረው እንመለከታለን፡፡
በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ሁለት አውራ ስህተቶች አሉ፡፡
እነርሱም እግዚአብሔር ግልጽ ትእዛዝና መመሪያን ሳይሰጠን
በእርሱ ስም መናገርና ግልጽ ትእዛዝና መመሪያ ከሰጠን በኋላ
ደግሞ በስሙ አለመናገር ናቸው፡፡ ሁለቱም አደገኛ ናቸው፡፡
ከእንዲህ ዓይነቱ ክፋት ጋር የሚመሳሰለው ነገር ደግሞ
የእግዚአብሔር የሆነውን ለሰይጣን መስጠት የሰይጣን የሆነውን
ደግሞ የእግዚአብሔር ነው ብሎ በመቀበል ከባድ ስህተት መፈጸም
ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች በዛሬው ዘመን አዘውትሮ የሚያጋጥሙ
ፈተናዎች መሆናቸው በተደጋጋሚ የታየ ፈታኝ ሁኔታ ነው፡፡

መንፈሳዊ ስጦታዎችና ስላሴ


በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች በተነሳባቸው
ምንባቦች ሁሉ ሥላሴያዊ አገላለጾችና ማብራሪያዎች አብረን
እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ በሮሜ 12፡5-8 ባለው ክፍል ተዘርዝረው
የምናገኛቸው ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስጦታዎች ከእግዚአብሔር አብ
ጋር ተያይዘው መገለጣቸውን እንመለከታለን፡፡ ይሁን እንጂ
እነዚህን ስጦታዎች የእግዚአብሔር አብ ብቻ አድርጎ መመልከት
ሚዛን ይጎድለዋል፡፡ በኤፌ 4፡11 ላይ ተጠቅሰው የምናገኛቸው
አምስቱ የአገልግሎት ቢሮዎች ከክርስቶስ ጋር ተያይዘው
ተጠቅሰዋል፡፡ እነዚህ በቀጥታ ከክርስቶስ የሚሰጡ መሆኑን ክፍሉ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 20


በማያሻማ መንገድ ገሃድ ያደርጋል፡፡ ይሁን እንጂ ስጦታዎቹን
የክርስቶስ ብቻ ማድረጉ አግባብ አይሆንም፡፡ በ1ኛቆሮ 12፡8-9
በተገለጡት ስጦታዎች ዙሪያ ሰፊ የትኩረት ድርሻ ተሰጥቶት
የምናየው ለመንፈስ ቅዱስ በመሆኑ ስጦታዎችን ከመንፈስ ቅዱስ
ጋር ብቻ አያይዘው የሚያስተምሩ አማኞች አሉ፡፡ ይሁን እንጂ
ክፍሉ በቅርበት ስናጠና ለእንዲህ ዓይነቱ አካሄድ ሙሉ ድጋፍና
መረጃ አናገኝም፡፡ ይልቁንም የስጦታዎቹን ሥላሴያዊ ገጽታ በቁ
4-6 ባለው ክፍል በግልጥ እንመለከታለን፡፡ ከዚህ የተነሳ መንፈሳዊ
ስጦታዎች በባህሪያቸው ስላሴያዊ ናቸው የሚለው ድምዳሜ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው እንላለን፡፡ በዚህ ጥናታችንም የመንፈስ
ቅዱስ ስጦታዎች ከማለት ይልቅ መንፈሳዊ ስጦታዎች ማለቱ
የተመረጠ መሆኑ ከዚህ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ልናስገነዝብ
እንወዳለን፡፡ እናስተውል! ቀደም ብለን እንዳስገነዘብነው የመንፈስ
ቅዱስ ስጦታዎች ዓላማ ምእመናን ማነጽ (1ቆሮ14፡4) እና
የስጦታዎች ሁሉ ምንጭ የሆነውን ሕያው አምላክ ማክበር ነው፡፡

ተገቢውን አተረጓጎም በተግባር ማዋል


አጠቃላይ የስነ አፈታት መርሆን የተከተለ ንባብና ትርጉም
ግንዛቤያችንን ሚዛናዊ ያደርጋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስናነብ ክፍሉን
(ምንባቡ) በቅደሚያ መገንዘብ፣ ቀጥሎ አውዱ ክፍሉን (ምንባቡን)
ለመተርጎም ፍንጭ ይሰጥ እንደሆነ እናጢን፡፡ ከዚያም ከምእራፉ
ጋር ያለው ተዛምዶ ከግምት እናስገባ፡፡ ከመጽሐፉ ሃሳብ ጋር
ያለውን ትስስር ልብ እንበል፡፡ በመጨረሻ ክፍሉ ከጠቅላላው
የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት አኳያና ከድኅነት ታሪካችን ጋር
ያለውን ተዛማጅነት በውል በመገንዘብ ለክፍሉ ፍቺ እንስጥ፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 21


ይህንን ስናደርግ ሚዛን ያልጎደለው የአፈታት ጥበብን በተግባር ላይ
እናውላለን፡፡ በክፍሉ ተገልጸው የምናየው የስጦታዎቹን መዘርዝር
እንጂ የአሠራር ባህሪያቸውን ባለመሆኑ አጠቃቀማቸውን
ለማብራራት ከሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ምሳሌዎችንና
ማብራሪያዎችን መውሰድ ግድ ነው፡፡ ስለ ሁሉም ስጦታዎች
መጽሐፍ ቅዱስ በልዩ ልዩ ክፍሎች የሚሰጣቸውን ማብራሪያዎች
በማስተሳሰር ለመረዳት እንሞክራለን፡፡

ምዕራፍ 2
በ1ኛቆሮንቶስ 12 የተገለጡት መንፈሳዊ ስጦታዎችና
አጠቃቀማቸው፡፡
የመገለጥ ስጦታዎች
የመገለጥ ስጦታዎች ስያሜቸው እንደሚያመለክተው ከአምስቱ
ስሜተ ሕዋሳት መረጃና ድጋፍ ሳይመረኮዙ አንድን እውነት
በትክክለኛ ገጽታው በመገንዘብ ጠቃሚና የሚያንጽ መመሪያን
ለማስተላለፍ የሚገለጡ የመለኮት እገዛ ናቸው፡፡

2.1. የእውቀት ቃል (1ኛቆሮ 12፡8-9)

በመሠረታዊው ፍቺ ቅዱሳን ሁለት ዓይነት አመለካከት አላቸው፡፡


አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን እውቀት የሚለውን የዚህ
ክፍል ሃሳብ ጥልቅ ከሆነው የእግዚአብሔር እውቀት ጋር
በማዛመድ ይረዱታል፡፡ ስለሆነም አንድን እውነት በጥልቀት
ከመገንዘብና ከማወቅ ከሚነሳው የማብራራት ሃሳብ ጋር

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 22


ያያይዙታል፡፡ ለዚህም በም 2፡11-16 ያለውን አውዳዊ ማስረጃ
ያቀርባሉ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ወቅቱን ያገናዘበ
መንፈሳዊ እውነት የገለጸበትን ሁኔታ እንደ እውቀት ቃል
(መልእክት) በምሳሌነት ያቀርባሉ፡፡ ከዚህ የተነሳ የሰውን ወቅታዊ
ፍላጎት የሚደርስ ብርሃን ለጋሽ የሆነ ማብራሪያ ለማስገንዘብ
ይሞክራሉ፡፡ ክፍሉ ግን ፍቺው ይህ ብቻ ነው የሚል ድምዳሜን
አይሰጠንም፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ዛሬም ይሠራሉ
የሚለውን እውነታ የሚቀበሉ ብዙ አማኞች ግን ከላይ የተገለጠው
አማራጭ ፍቺ እንደ ተጠበቀ ሆኖ፣ የእውቀት ቃል መንፈስ ቅዱስ
ሲፈቅድ እርሱ ራሱን ለመግለጥ የሚሰጠው ወቅታዊ ብርሃን ነው
የሚለው የበለጠ ይመቻቸዋል፡፡ ለእኔም ይህንን ክፍል በተመለከተ
ይኸኛው ይስማማኛል፡፡ እወቀት የሚለውን ቃል መዝገበ ቃላት
ሲፈታው በመስማትና በማየት የሚገኘውን እውነት በማካበት
የአንድ ተሰጥኦ ባለቤት መሆን ነው፡፡

የእውቀት ቃል ያልሆነው
 የሰውን ጥረት ጠግኖ በማረም አሻሽሎ ማቅረብ አይደለም
 የአስተዋዮች ቅደመ ትንበያ፣ ግምገማና ምክር አይደለም
 በምርምር የሚገኝ ግኝት አይደለም
 ቃሉን በማጥናት የሚገኝ ብርሃንም ሆነ አስደናቂ የቃሉ
እውቀት አይተካውም
 በእድሜና በልምምድ የሚደረስበት ብልህነት የተሞለባት
ድምዳሜ አይደለም

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 23


የእውቀት ቃል ማለትም እግዚአብሔር ብቻ የሚያውቀውን
እውነት በእርሱ እገዛ ለማወቅ ታድሎ መመሪያ ለመስጠት፣ ችግርን
ለመፍታት፣ አቅጣጫ ለማስያዝ የሚያስችል ልዩ የመንፈስ ቅዱስ
ረድኤት ነው፡፡ መገለጥ ማለት እግዚአብሔር ብቻ የሚያየውን
ማየት ሲሆን፣ እግዚአብሔር ምን ያያል ብንባል እርሱ እኛ
የማናያቸውን ሁሉ ያያል፡፡
ይህ ስጦታ ከአምስቱ ስሜተ ሕዋሳት መረጃና ድጋፍ ውጭ፣
የሆኑትን፣ እየሆኑ ያሉትን ነገሮች በትክክል ማወቅ ነው፡፡ ይህ ልዩ
እውቀት ሁሉን አዋቂ ከሆነው ጌታ ዘንድ ለተጨባጩ ሁኔታ
የሚሰጠን ወቅታዊ የመለኮት ብርሃን ነው፡፡ ይህ ብርሃን
በባለስጦታው ተቆጣጣሪነት ሥር አይደለም፡፡ ይህ ልዩ ማወቅ
በእግዚአብሔር ፈቃድና ውሳኔ ብቻ የሚመራ እንጂ በባለስጦታው
ትጋትና ንቃት ላይ የሚመረኮዝ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ፈቅዶ
በዚህ ስጦታ ሰዎች ማገልገል ሲጀምሩ የሚያውጁት እግዚአብሔር
ሰርቶ የጨረሰውን ስለሆነ ለመልእክቱ የሩቅ ጊዜ ቀጠሮ
አያሻውም፡፡ መልእክተኛው እንደ ተናገረ መልእክቱ እዚያው
በተግባር ይፈጸማል፡፡

ስለ እውቀት ቃል ጠቀሜታ ተግባራዊ ምሳሌዎች

የእውቀት ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በልዩ ልዩ ተግባራዊ


ሁኔታዎች ውስጥ ጥቅም ላይ ውሎ እንመለከታለን፡፡ ስለ ስጦታው
ጠቀሜታ የመከተሉትን ምሳሌዎች

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 24


2.1.1. ክፉው ከሚያስከትለው ጉዳት ሕዝቡን ማትረፍ (2ኛ ነገ
6፡9-12)
ነቢዩ ኤልሳእ ከጌታ በተቀበለው ብርሃን ለሕዝቡ ከለላ ይሰጥ
ነበር፡፡ በአደባባይ ከተቀመጡት ፖለቲከኞች ይልቅ በጓዳው
የተቀመጠው ይህ የእግዚአብሔር ሰው ሕዝቡን ከአደጋ ያተረፈ
ትልቅ አገልግሎት እንዳከናወነ መጽሐፍ ቅዱስ ይነገረናል፡፡
መልእክቱ አመጣ መልእክቱም ወዲያው በተግባር ላይ ዋለ፡፡
ካንጃበበ አደጋ ሕዝቡን ለማስጣል አምላክ ብዙ ጊዜ ባሪያዎች
በዚህ ብርሃን ደግፏል፡፡ በዘመናችንም በዚህ መልኩ እንክብካቤን
ያገኙ አማኞች ብዙ ናቸው፡፡

2.1.2. የመዳንን ወንጌል ግልጽ በሆነ መንገድ ለማቅረብ (በዮሐ


4፡18-19)
የእልከኛ ሰዎች ልባቸው ተረትቶ ለጌታ ራሳቸውን
እንዲሰጡ ከክፋት መንገዳቸው እንዲመለሱ የሚያስችል መልእክት
ለማስተላለፍ ያግዛል፡፡ ከላይ በተጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ውስጥ የጌታ መልእክት ውጤታማ በሆነ መንገድ ወደ
መልእክተኛው የደረሰው ወቅታዊ በሆነ መልኩ ልቧን የሚረታ
የወንጌል ብርሃን ስለ በራላት ነው፡፡ ጆን ዊንበር የተባለ የወንጌል
መልእክተኛ በአንድ ወቅት በነበረው የአውሮፕላን ጉዞ የአንድ ሰው
ፊት ትኩር ብሎ ተመለከተ፡፡ በጊዜው ዝሙት የሚል ብልጭታ
ግምባሩ ላይ አንብቦ ነበር፡፡ በዚያ ሲደነቅ መንፈስ ቅዱስ
የሴትዮዋን ስም ገለጠለት፡፡ ጉዳዩን ለሰውየው ነገረው፡፡ ሰውየውና
ባለቤቱ ንስሃ ገቡና ሕይወታቸውን ለጌታ አስረከቡ፡፡ እኔም በግሌ
ይህንን የመሰለ ታሪክ ገጥሞኝ ያውቃል፡፡ ከተሰጠኝ ብርሃን የተነሳ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 25


የወንጌል ጠላት የነበሩ ሰዎች ራሳቸውን ለወንጌል እውነት
አስገዝተዋል፡፡

2.1.3. ቅድስናን ለማጎልበት ርኩሰትን ለመከላከል (2ኛ ነገ 5፡26)


የረከሰ የአመጽ እንቅስቃሴ ቆሞ የጌታ ልጆች በአምላክ
ፍርሃት ውስጥ እንዲራመዱ በእውቀት ቃል አማካኝነት ወቅታዊው
ብርሃን ተላለፏል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ስለሆነ ርኩሰት
ያሳዝነዋል፡፡ የእውነት መንፈስም ስለሆነ በግብዝነት የተሸፈነ ኑሮ
አይቀበልም፡፡ ከዚህ የተነሳ ቅድስናን ለማጎልበት አስመሳይነትን
ወደ ብርሃን በማውጣት በእውቀት ቃል በኩል ይዘልፋል፡፡
አታላዩና አስመሳዩ ግዓዝ የታረመው ያ ክፋት በጌታ ሥራ
እንዳይቀጥል ነበር፡፡ ሐዋርያው ጴጥሮስ ሀናንያንና ሰጲራን
የዘለፈበት ታምራዊ አገልግሎቱ የእውቀት ቃል ጸጋን ያካተተ ነበር
(የሐዋ 5)፡፡

2.1.4. ምሪት ለመስጠት (1ኛሳሙ 10፡22)


ጌታ ላቀደው ዓላማ ልጆቹ ንቁ እንዲሆኑ ሲሻም ሆነ፣ ልጆቹ
ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ምሪቱን ሲሹ እውን የሚሆን ጸጋ ነው፡፡
እግዚአብሔር በዚህ ጸጋ አማካኝነት ብርሃን ይልክላቸዋል፡፡
የእስራኤል ሕዝ ከእግዚአብሔር ምሪትን በፈለጉ ጊዜ ትክክለኛ
ሁኔታውን ገለጸላቸው፡፡ ለእኛም በለት ተለት ጉዳያችን እርሱ
ሲፈልግ ይህንን የመሰለ ምሪት ሊሰጠን ይችላል፡፡ አብዛኛውን
ጊዜ በዚህ መልኩ የሚላከው ብርሃን በጭለማ ውስጥ ስናሽከረክር

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 26


በምንጠቀምበት ብርሃን ይመሰላል፡፡ የምናየው ከፊታችን ያለውን
ብቻ ነው፡፡ የሚለቀቅልን ብርሃን የረጅም ርቀት እይታን የሚሰጥ
ሳይሆን አካባቢው አጥርተን እንድንቀሳቀስ የሚያግዝ ነው፡፡

 አማኞችን ማስተሳሰር፣ መንፈስ ቅዱስ በሐዋ 9፡11-17


ሁለት ሊቀራረቡ የማይችሉ ሰዎችን ያስተሳሰረው ለሁለቱም
በተላከ ወቅታዊ ብርሃን ነበር፡፡ አዲሱ አማኝ ጳውሎስ ቀጣይ
የህይወቱን ምእራፍ እንዲያቅ፣ በሳሉ አማኝ ሐናንያ በጌታ ሥራ
እንዲደነቅ፣ በዚህ ጊዜ ከመለኮት የተላከው ብርሃን ጠቀሜታው
ድንቅ ነበር፡፡ የእውቀት ቃል ያለ ብዙ ውይይት ልብና ልብን
የሚያቆራኝ ሥራ ይሠራል፡፡ ይህ ታምራዊ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ
ነው፡፡
 ለሚሠራው መንፈሳዊ ሥራ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
(ማር 14፡13-15)፡ ለጌታ የፋሲካ ማእድ የተዘጋጀበት ሁኔታ በዚህ
ጸጋ አማካኝነት ተግባር ላይ የዋለ ነበር፡፡ በዘመናቸንም
ከማይፈልጉን ጋር ትግል ከመግጠም ጌታ በሚሰጠን ብርሃን
ወቅታዊ ሁኔታችንን የሚመጥን ምሪት ካምላክ በዚህ መልኩ
ልንቀበል እንችላለን፡፡ መለኮታዊ ብርሃን አምላክ ሲፈቀድ
የሚለቀቅ ነው፡፡ ጊዜውን መወሰን ሁኔታውን መምረጥ የፍጡር
ሳይሆን የፈጣሪ ነው፡፡ እንዲመራንና ምቹ ሁኔታውን እንዲያሳየን
በፊቱ መቆየት ልባምነት ነው፡፡

2.1.5. ጌታን በእውን ማንነቱ ለመባረክና ለመግለጥ (ሉቃ 2፡26)

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 27


ጌታን በትክክለኛ ማንነቱ መገንዘብ በፍጡር ንቃት ላይ
የተመሠረተ አይደለም፡፡ ይህ እንዲሆን ገላጭ ያስፈልጋል፡፡ አንተ
ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ የሚለውን ቃል
ለማውጣት የጴጥሮስ ንቃት ሳይሆን የአምላክ ረድኤት በጉዳዩ
እንዳለፈት ጌታ ኢየሱስ ተናገረ (ማቴ 16፡17)፡፡ ከጴጥሮስ ንቃትና
ችሎታ ይልቅ የአምላክ ብርሃንና ችሮታ ወሳኝ እንደ ነበር
አስገነዘበ፡፡ በጌታ የተቀባውን ሳያይ እንደማይሞት የተረዳውም
ስምኦን በዚህ ልምምድ ውስጥ የታደለ ነበር፡፡ ጌታን በተለየ
ማንነቱ አየው፡፡ ከዚያ ማየት ጋር የተያያዘ አምልኮና ስግደትን
ለአምላኩ አቀረበ፡፡ የእውቀት ቃል በአማኞች መሐል በሙላት
እውን ሲሆን በእውነትና በመንፈስ የሆነው አምልኮ ከአማኞች
እሩቅ አይሆንም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ወደ ጌታ ሃሳብ ሲያመጣን
በፍጡር ቃል ሊገለጥ የማይቻል ደስታ ውስጥ እንገባለን፡፡ ይህ
ጸጋ በአማኞች መሐል በተግባር ሲታይ አማኞች እርካታ ከራቀው
እርባናቢስ ኑሮ ይላቀቃሉ፡፡

2.1.6. መልእክቱ እንዴት ይመጣል


የእውቀት ቃል እንደ ተቀባዩ ሁኔታና እንደ መልእክቱ ይዘት በልዩ
ልዩ ቅርጽ ለመልእክተኛው ይደርሳል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
በልዩ ልዩ መንገድ እንደ ተገለጠም እናስተውላልን፡፡ ከብዙ ቅርጾች
መሐል የሚከተሉትን ለአብነት እናነሳለን፡፡
1. ለልብ በሚሰማ ድምጽ
2. በሕልም
3. በራእይ
4. በሰማያዊ መልእክተኛ እገዛ (መልአክ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 28


5. ተቀባዩ ብቻ በሚገነዘበው ምልክት

2.1.7. ስጦታው በአማኞች መሐል በተግባር ሲውል ሊደረግ


የሚገባ ጥንቃቄ
1. በእውቀት ቃል ጸጋ የሚያገለግል ግለሰብ መልእክቱ ሲቀበል
አሻሚ ከሆኑ ነገሮች ጽዱ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡ ከዚያም
መልእክቱን በጥበብ ማስተላለፍ አለበት፡፡ አዳማጮች በእርጋት
እንዲያዳምጡ የበኩሉን ማስተዋል የተሞላበት ርምጃ መውሰድ
አለበት፡፡
2. መልእክቱን የሚቀበሉ ሰዎች በእርጋታ በማዳመጥ እውነትነቱን
መፈተሸና የጌታ መሆኑን የሚገነዘቡበት የተጨበጠ ነገር ሲያዩ
ለጌታ አክብሮትን መስጠት፡፡

2.2. የጥበብ ቃል (1ኛቆሮ 12፡8-9)


የጥበብ ቃል እንደ እውቀት ቃል ተመሳሳይ በሆነ መልኩ
ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ይረዱታል፡፡ ጥበብ ማለትም
መንፈሳዊ እውነት ለመገንዘብ የሚያስችል የልቡና አብርሆት
አድርገው ይገነዘቡታል፡፡ እውነትንም የሰዎችን ትኩረት በሚስብ
ወቅቱንና ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ከማብራራት ጋር
ያያይዙታል፡፡ መሠረተ እምነትን (መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮን)
ጥልቅ እውነትን ለሰው ሁሉ በሚገባ መልኩ መግለጽ እንደ ጥበብ
ቃል ይመለከቱታል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስም በም 2፡6
የሚያደርገው ይህንኑ ነው ይላሉ፡፡ ይህ እውነት እንደ ተጠበቀ ሆኖ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 29


የጥበብ ቃል መንፈስ ቅዱስን ከመገለጥ ጋር በተያያዘ አሠራሩ
ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ወቅታዊ መለኮታዊ መመሪያ ነው፡፡
ጥበብ የሚለውን ቃል መዝገበ ቃላት ሲፈታው
በትምህርት የተካበተውን ችሎታ በተገቢው የተግባር ጣቢያ
መግለጥ ነው፡፡ ስለሆነም የጥበብ ቃል ማለት የገጠመን ወይም
የሚገጥምን የተወሳሰበ ሁኔታ ለመፍታት የሚያስችል መለከታዊ
ብርሃን ነው፡፡ ይህም ስጦታው በሚሠራበት ሰው የሚገለጥ ነገርን
በተቀላጠፈና በማያዳግም ሁኔታ ለማከናወን የሚያስችል ልዩ
ብቃት ነው፡፡ የእውቀት ቃልና የጥበብ ቃል ስጦታዎች ለመለየት
እስኪያስቸግር ድረስ በአሠራራቸው የተሣሠሩ ናቸው፡፡
እግዚአብሔር ለሰዎች የሚሰጠው ወቅታዊ ስልት ነው፡፡

የጥበብ ቃል ያልሆነው
 የአእምሮ ብሩህነትና ብልጥነት አይደለም፡፡
 አንድን እውነት እየፈለቀቁ የማሳየት ልዩ ተስጥኦ አይደለም፡፡
 አስተዳደራዊ የአመራር ብልሃት አይደለም
 የነገሮችን አዝማሚያ እያዩ የሚሰጥ በብልሃት የተሞላ
አይደለም

የጥበብ ቃል የሆነው
የጥበብ ቃል ለአስፈላጊው መንፈሳዊ ሥራ መንፈስ ቅዱስ
በሚመርጠው ጊዜና ቦታ የሚላክ የመለኮት ልዩ ድጋፍ እንጂ
የሁልጊዜ ንቃት አይደለም፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 30


ስለ ጥበብ ቃል ጠቀሜታ ተግባራዊ ምሳሌዎች

2.2.1. ከዘመኑ ችግር ለማምለጥ የሚያስችል ብርሃንና ምሪትን


ለመቀበል (ዘፍ 6፡13-20፣ ዘፍ 41፡28)

ጊዜው ከሚያመጣውና ካመጣው ችግር ለማምለጥ መንገዱ


ከአምላክ የተሰጠ ጥበብ ነበር፡፡ ኖህና ቤተሰቡ ከጥፋት ውኃ፣
ዮሴፍ ያገለገላቸው እስራኤላውያን ግብጻውያን ከርሃብ የተረፉት
እግዚአብሔር በጊዜው በላከላቸው መለኮታዊ ጥበብ ነው፡፡
ፈርኦንም እንዳንተ ያለ አስተዋይና ጠቢብ የለም ሲል በመደነቅ
የተናገረው በዮሴፍ ሕይወት ውስጥ ከተመለከተው ጥበብ የተነሳ
ነበር፡፡ ዛሬም ይህ የጥበብ ቃል በአማኞች መሐል እውን ሲሆን
ከብዙ ጉዳት ማምለጥ ይቻላል፡፡

2.2.2. ወሳኝ የሆነውን መንፈሳዊ አገልግሎት እንደ ጌታ ፈቃድ


ለማከናወን (ዘጸ 31፡1-4)

ባስልኤልና ጓደኞቹ የመገናኛውን ድንኳን ሥራ እግዚአብሔር


በሚፈልገው መንገድ እንዲሠሩት ከጌታ ዘንድ ጥበብ ተስጥቷቸው
ነበር፡፡ ልክ እንዲሁ መንፈሳዊን ሥራ በተፈለገው መንገድ
ለማከናወን ከመለኮት የሚሰጥ ብርሃን ኣስፈላጊ ነው፡፡ ዛሬም

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 31


መንፈስ ቅዱስ በጊዜው መከናወን ያለበት መንፈሳዊ ሥራ ጌታ
በሚፈልገው መንገድ እንዲፈጸም ጥበቡን ያደላቸው ሰዎች በቤቱ
ያስቀምጣል፡፡ መፍትሔ እነዚያን ሰዎች ጌታ ለመሪዎች
እንዲያሳይና እነዚያም ሰዎች ጥበባቸውን በተገቢው የተግባር
ጣቢያ መግለጥ አለባቸው፡፡ ባጭሩ ለመንፈሳዊ ሥራ ብቃትን
ለመለገስ ያገለግላል ማለት ነው፡፡

2.2.3. የተወሳሰበ ችግርን ለመፍታትና አወዛጋቢ ጉዳይን ለመዳኘት


(1ኛ ነገ 3፡11-28፣ የሐዋ 6፡3)
የእግዚአብሔርን ሕዝብ በአግባቡ ለመዳኘት ጥበብ የለመነው
ሰሎሞን የጥበብ ቃል ተሰጥቶት የተወሳሰበ ችግር የፈታበት
መንገድ ጥንት ብቻ ሳይሆን በአስገራሚነቱ እንደምሳሌ ይነሳል፡፡
ወስብሱን ችግር ለመፍታት አንድ የጥበብ ቃል ብቻ ነበር
ያስፈለገው፡፡ ሰይፍ አንጡልኝ፡፡ ያ ቃል ግልጽ፣ አጭርና
የማያዳግም ቃል ነበር፡፡ መንፈስ በጊዜው የሚያመጣው ቃል
በባሕሪው እንዲህ የማያዳግም ነው፡፡ መፍትሔው ግን ሁሉንም
እኩል ደስ ያሰኛል ማለት ግን አይደለም፡፡ በሐዋርያት
የመጀመሪያው የማእድ አገልግሎት ችግር ተመሳሳይ ጥበብን ጠይቆ
ነበር፡፡ ሁላችን አንደምናስታውሰው ጊዜው ምግብ የማከፋፈሉ
ሥራ በቅዱሳን መካከል ትርምስን ያመጣበት ሁኔታ ነበር፡፡ ይሁን
እንጂ ችግሩን ለመፍታት ጥበብና መንፈስ ቅዱስ የሞላባቸው
ሰዎች አስፈልጎ ነበር፡፡ ያንን ጉዳይ ሐዋርያት የፈቱት በጥበብ
የሚያገለግሉ ሰዎች በቦታው ላይ በማኖር ነበር፡፡
 ከወጥመዱ ለማመለጥ (ሉቃ ማቴ22፡21 20፡22-25)፣

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 32


ተንኮለኞች በሻጥር፣ ግፈኞች በጭካኔ፣ አመጸኞች በምህረት
የለሽነት የሚያመጡትን ጣጣ ማምለጥ የሚቻለው ከላይ በሚሰጥ
ጥበብ ነው፡፡ ጌታን ማጥመድ የፈለጉት ሰዎች በጥበቡ ተገርመው፣
በማስተዋሉ ተደንቀው፣ በተገለጠው ብርሃን ደንግጠው ከፊቱ
ገለል ለማለት ተገደዱ፡፡ አላስፈለጊ ጥያቄም በተጠየቀ ጊዜ ቀጥተኛ
መልስ ሳይሰጥ ማበረሪያ የሆነውን ጥያቄ ጠየቀ፡፡ ማምለጫውን
ለእኛም ሲያሳየን መንገዱ ከጌታ ዘንድ የሚመጣ ጥበብ ነው፡፡
ስለሆነም የምናመልጠው በትንተና እና በሙግትና ሳይሆን ጌታ
በሚያቀብለን አጭርና ግልጽ የሆነ የማያዳግም ብርሃን ነው፡፡
የጥበብ ቃል ሲመታ ከወጥመዱ በቀላሉ እናመለጣለን፡፡

 ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆነው ሳሉ የብርሃኑን መምጫ


ለማሳየት (የሐዋ 27፣ ሉቃ 21፡12-15)
ከተራራው ባሻገር ያለውን ሜዳ ለማየት፣ የብርሃን ፍንጭ
በሌለበት ቦታ መምጫውን ለማመላከት፣ ሞት ጥላውን ባጠላበት
ቦታ ሕይወት ለማሳየት፣ጭንቀት በነገሰበት ቦታ እፎይታ ይኸውና
ብሎ በሚገባ ለማሳየት፣ ዙሪያውን ገደል በሆነበትና አራቱም
ማእዘን ግድግዳ በሆነበት መውጫውን ለማሳየት፡፡ ተስፋ
በጠፋበት ሥፍራ ምግብ ለመመገብ እንደ ምሳሌ በፊታቸው
ያደረገው ነገር ስለ ጥበብ ቃል አሠራር የሚያስገነዝበን ተግባራዊ
ምክር አለው፡፡ ሰዎቹም ተጸናንተው መልእክቱን ሙሉ ለሙሉ
በተግባር አዋሉት፡፡

2.2.4. ቅይጡን ነጥሎ ለማውጣት (መሣ 12፡6)

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 33


ወዳጅና ጠላት፣ እውነተኛና ውሸታም፣ ሐቀኛና
አስመሳይ፣ ገንቢና አፍራሽ አንድ ላይ ያሉበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡
ሁሉም ተመሳሳይ ስለነበሩ ይህንን ጉዳይ በእስራኤልና በምድያም
መካከል ነጥሎ ማውጣት ቀላል አልነበረም፡፡ ይሁን እንጂ በጊዜው
የመነጠያው መሣሪያ ተገኘና ማን ማን እንደሆነ ተለየ፡፡ ሕዝቡም
ከጌታ ዘንድ የተገኘ ድሉን ጠበቀ፡፡ ዛሬም አስመሳዩ የአማኞችን
ቋንቋ ተክኖ፣ በብዙ ነገሮቻቸው ተመሳስሎ፣ ያለ ገደብ አታሎ
እንዳይኖር ይህ ጸጋ አስፈላጊ ነው፡፡ ቅይጡ የሚለየው ከጌታ ዘንድ
በሚገኝ ጥበብ ጭምር ነው፡፡

2.2.5. ምስኪኖችን ለመታደግ (ዮሐ 8፡1-12)


በፍርደ ገምድል ዳኝነት ጉዳት ሊያስከትሉ እርሱንም
ለማጥመድ የተሰለፉ ሰዎችን ጌታ ገደብ ያሲያዘው ፋይል ከፍቶ
የጠለቀ ማስረጃ አቅርቦ ከካሳሾቿና ከከሳቾቹ ጋር በመሟገት
አልነበረም፡፡ ይልቁንም አንዲት አረፍተ ነገር በመናገር ነበር፡፡
በመጣው ጥበብ የተሞላ መለኮታዊ ብርሃን እርሱ ከተነኮላቸው
አመለጠ፡፡ የምስኪኗንም ሕይወት ታደገ፡፡ እኛም ከብዙ ወጥመድ
የምናመልጠው ሌሎችን ለመታደግ መሣሪያ ሆነን የምናገለግለው
በዚህ ጸጋ ስንባረክ መሆኑ ሊጠፋን አይገባም፡፡

2.2.6. በጠማማ ባሕል የታሠረ ልባችንን ለመግራት (የሐዋ 10፡9-


16)
በጠንካራ ወግ የታሠረው ጴጥሮስ ወደ ልቡ የሚገባ
የጥበብ መልእክት ተላከለት፡፡ ለጴጥሮስ ከተሰጠው ራእይ
የምንረዳው ጌታ ይህንን ሰው በሚያሸንፍበት ብርሃን ማግኘቱን

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 34


ነው፡፡ ከስይጣን በባሰ መንገድ ያሠረውን ባሕል የበጣጠሰው
በሚገባው መንገድ ካነጋገረው በኋላ ነው፡፡ ባሕል አስሮ ሲጎትት
ከሰይጣን ይብሳል፡፡ ከጌታ ጋርም በድፍረት ያሟግታል፡፡ ይሁን
እንጂ የጥበብ ቃል ሲመጣ ጴጥሮስን ገራው፡፡ እኛንም እንዲሁ
እግዚአብሔር ካሠረን ባሕላዊ ወግ በረቂቅ ጥበቡ ይፈታናል፡፡

2.2.7. ለእለታዊ ርምጃችን ብርሃንን በመፈንጠቅ (ቆላ 4፡6፣ ያዕ


1፡5)
ወጥንቅጧ በወጣው በዚህች ዓለም ውስጥ ስንኖር የጌታን
ፈቃድ እየለየንና ከጌታ ጋር እየተስማማን እንድራመድ የጥበብ ቃል
ልዩ እገዛን በመልቀቅ ይገለጣል፡፡ የጥበብ ቃል አገልግሎት በመከራ
ውስጥ ተገቢውን መንፈሳዊ አቋም እንድናገኝ በመደገፍም
ይገለጣል፡፡ (ያዕ 1፡5)

2.2.8. የጥበብ ቃል እንዴት ይመጣል


የጥበብ ቃል ወደ መልእክተኛው በልዩ ልዩ መንገድ ይፈስሳል፡፡
ሁሉንም በዚህ ሥፍራ ማብራራት እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ መጽሐፍ
ቅዱስም ውስጥ በየሥፍራው ተበትነው ምሳሌዎችን እናገኛለን
እንጂ በቀጥታ ስለዚህ ያስተምራሉ በሚል ለእኛ እንደሚመቸን
ተኮልኩለው አናገኛቸውም፡፡ ጥቂት ምሳሌዎች ከብሉይ ከዳንም
ከአዲስ ኪዳንም እናያለን
1. በአባባል ይመጣል፣ በሁለት በሚመሳሰሉ በተዛመዱ ሕዝበች
መካከል ጦርነት ተነስቶ ማንም ማንን መለየት ባልቻለ ጊዜ
መለያ መንገድ ተገኝቶ ወገንና ጠላት ‹‹ሺቦሌት›› በሚለው
ቃል ተለየ ( (መሳ12፡6) ጌታ ኢየሱስም ያቺን በምንዝር

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 35


የተያዘች ከከሾቿ ያዳናት ፋይል ከፍቶ ጭብጡን አስረድቶ
ሳይሆን አንድ ቃል ብቻ በመናገር ነበር ፣ ‹‹ኃጢአት
የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው›› (ዮሐ
8፡7)
2. በአረፍተ ነገር ‹‹የጴጥሮስ ባሕላዊ እስራት የተፈታው
እግዚአብሔር ያነጻውን አታርክሰው … አርደህ ብላ›› (የሐዋ
10፡13-15) በሚለው አረፍተ ነገር ነው፡፡
3. ሥዕላዊ ምሳሌን በመጠቀም፣ ጌታ ኢየሱስ በተፈተነ ጊዜ
ጥበብ ለበስ ምሳሌ በመጠቀም መለሰ ‹‹ይህች ፎቶ ጽህፈቲቱስ
የማነው?›› (ሉቃ 20፡24) ጳውሎስ በመርከቡ ላይ የወሰደው
ምግብን የመመገብ እርምጃ ሌሎችን በብሉልኝ ከመለመን በጎ
ተጽእኖ ነበረው (የሐዋ 27)፣ የንጉሥ ሰለሞን የሰይፍ
አንጡልኝ ጥያቄ ሐቀኛ ወላጅ ማን እንደነበር ወሳኝ ነበር (1ነገ
3)፡፡
4. በተግባራዊ ድርጊት የታየ መንፈሳዊ ጥበብ፣ በዮሴፍ የሕልም
ፍቺ በጥጋቡ ዘመን ብልሃት የርሃቡ ዘመን ታለፈ፣ ባስልኤልና
ጓደኞቹ ከሰማይ በመጣ ጥበብ የመገናኛውን ድንኳን ዕቃዎች
ሠሩ (ዘፍ 41 እና ዘጸ 31)

የጥበብ ቃል ከሰው ተፈጥሮአዊ ችሎታ ልቆ የሚገኝ የመለኮት


መገለጥ ነው፡፡ ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔር ሞኝነት ስለሚጠበብ
አማኞች በሙሉ ከዚህ የመለኮት ስጦታ በመጠቀም መታነጽ ቢሹ
እንዲጸልዩ መጽሐፍ ቅዱስ ያደፋፍራል (ያዕ 1፡5)፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 36


2.3. መናፍስትን መለየት (1ኛቆሮ 12፡8-9)
መስለውና ተቀይጠው በሕዘቡ ላይ አደጋ ለመጣል የተሰናዱትን
ኃይላት ሴራ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው፡፡
ርኩስ ሆነው የተቀደሱ፣ ዋሾ ሆነው ሐቀኛ፣ ምንደኛ ሆነው
መልእክተኛ፣ ከክፉው ወግነው፣ ቅዱሳንን አታለው፣ በቅኖች
መሐል ተሰግስገው ለመኖርና ለማደናገር የተሰለፉትን ነጥሎ
የሚያወጣው የአምላክ እጅ ነው፡፡ የስጦታው ዓይነተኛ ባሕሪ
ቅዱሳን በተቀደሰው መስመር ከመምራት ይልቅ ማምታት
የሚቀናቸው መመንጠር ነው፡፡ ለዚህ ስጦታ አንዳንድ ቅዱሳን
በቤተ ክርስቲያን ዘብ የቆመ ተቆጣጣሪ የሚል ቅጥያ ስም
ሰጥተውታል፡፡
አማኞችንም ሆነ አስመሳዩን ተተግነው የሚሠሩት
አታላይ መናፍስት ከሚፈጥሩት አደጋ ሕዝቡን ለመጠበቅ ይህን
እንክብካቤውን ለአማኞች ሰጥቷል፡፡ መናፍስት በድብቅ
ተንኮላቸው፣ በረቀቀ ወጥመዳቸው ሰርገው መግባት ቢችሉም
አንዳንድ ጊዜ የአማኙ የሳተ አቋም እንዲሁም መራራ ድርጊት
ለሰይጣን አሠራር ምሽግ ሊሆነው እንደሚችል ሊጠፋን
አይገባም፡፡ በሉቃስ 9፡55 ላይ የነጎድጓድ ልጆች በመባል
የሚታወቁት ደቀ መዛሙርት ከተበሳጨና ከሳተ መንፈሳቸው
በወጣ ቁጣ አሣፋሪ የስንፍና ንግግር አደረጉ፡፡ ርህራሄ የጎደለው
የጭካኔ ብያኔአቸውን ጌታ በሰማ ጊዜ ‹‹ምን ዓይነት መንፈስ
እንደሆነላችሁ አታውቁም›› ሲል ገሰጻቸው፡፡ በሌላ ጊዜ በራሱ
ፈቃድና ፍላጎት የታወረው ጴጥሮስ በቅርቡ ብቻ ያለውን በማየት
ታውሮ በመናፍስት አሳች ወጥመድ ወደቀ፡፡ በዚህም ሁኔታ ጌታን
ማረም ሲቃጣው፣ ጌታ ኢየሱስ የነገሩን ትክክለኛ ምንጭ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 37


በመረዳት ጴጥሮስ ለሰይጣን ትርፍ በሚጠቅም ሁኔታ ራሱን
አመቻችቶ በማቅረቡ ‹‹ሂድ አንተ ሰይጣን የሰውን እንጂ
የእግዚአብሔርን አታስብም›› ሲል ገሰጸው (ማቴ 16፡33)፡፡
እንደግዲህ ይህ ስጦታ፣ መንፈሳዊ ሥነስርዓት
በእግዚአብሔር ቤት እንዲጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
በእግዚአብሔር ቤት የዚህ ስጦታ ብልፅግና ሲበዛ ከትርምስና
ከተምታታ እርባናቢስ እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያን ጠርታ፣ የነጠረና
የጠራ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እውን ሆኖ አማኞች ይታነጻሉ፡፡

መናፍስትን መለየት ያልሆነው


 አስገራሚ የስነ አእምሮ እውቀት አይደለም
 የሰዎችን አእምሮ ማንበብ አይደለም
 የሌሎችን ስህተት አድኖ ማግኘት አይደለም
 ንቁ ጥርጠራ አይደለም

መናፍስትን የመለየት ጸጋ ጠቀሜታው ተግባራዊ ምሳሌዎች

2.3.1. የሚታየውንና የማይታየውን የክፉ ኃይላት ሥራ መግታት


(ማቴ 12፡22፣ማር 5፡5፣ ሉቃ 9፡39)
የመናገርና የማየትን ኃይል ከበስተኋላ ሆነው የነጠቁትን ድብቅ
ኃይላት ማቆም በአዲስ ኪዳን በተደጋጋሚ የሚታይ አገልግሎት
ነበር (ማቴ 12፡22)፡፡ ይሁን እንጂ የመስማትና የማየት ችግር
ምክንያቶች ክፉ ኃይላት ብቻ ናቸው ብሎ መደምደም ትልቅ
ስህተት ነው፡፡ በልምምድ የተገኙ ብዙ ማስረጃዎች እንዳረጋገጡት

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 38


በተደጋጋሚ ማማከር አገልግሎትና በልዩ ልዩ መንፈሳዊ እርዳታ
መፍትሔ ያልተገኘለት ችግር አብዛኛውን ጊዜ ሰይጣናዊ ተፈጥሮ
አለው፡፡ መናፍስትን መለየት ጸጋ የተሰጠው አማኝ ባለበት ሥፍራ
ራሳቸውን መሠወር ስለማይችሉ መረታታቸውን በገሃድ ያሳያሉ
(ማር 5፡5፣ ሉቃ 9፡39)፡፡

2.3.2. የጌታን ሥራ ለማደናቀፍ በስውር የሚሠሩትን ኃይላት


ለመምታት (የሐዋ 13፡9-10፣16፡16)
ሐዋርያው ጳውሎስ ያከናውን የነበረውን የወንጌል ተልእኮ
ለማደናቀፍ የተሰለፈው መሠሪ የክፋት ኃይል የተመታው ጌታ
በጳውሎስ ውስጥ ባኖረው ጸጋ ነበር፡፡ በሌላ ጊዜ ጳውሎስ
የሰጠውን አገልግሎት በኃይማኖታዊ ቡራኬ ማደናቀፍ የፈለጉት
ክፉ ኃይላት የተገቱት ጳውሎስ መንፈሱን ነጥሎ ገለል እንዲል
ትዕዛዝ በሰጠ ጊዜ ነበር፡፡ ይህ ጸጋ በውስጡ ይሠራ ስለነበር
በግልጥም ሆነ በድብቅ የጌታን ሥራ ለማደናቀፍ የተሰለፉ ኃይላት
አልተከናወነላቸውም፡፡ መንፈሳቸው ተለየ ሥራቸው ፈረሰ፡፡

2.3.3. የሃሰት ትምህርት ለማጋለጥ(1ኛጢሞ 4፡ 1-2)

በርካታ የሃሰት ትምህርቶች ምንጫቸው ክፉ ኃይላት ናቸው


(1ኛጢሞ 4፡ 1-2)፡፡ በተለየ መንገድ በዚህ ጸጋ ጌታ የባረካቸው
ቅዱሳን የስህተት ትምህርት ሰንኮፉን በመንቀል ቅዱሳንን በእውነት
የሚያስታጥቁት፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በዚህ ጸጋ የተባረከ ነበር፡፡
የጻፋቸው መልእክቶቹ ለዚህ ተጨባጭ ማስረጃዎች ናቸው፡፡
የሚበዙቱ ሐሰትን በማረም ቅዱሳንን የማጽናት ዓይነተኛ ባህሪያት

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 39


ነበራቸው፡፡ ማራኪ በሆነ የአነጋገር ለዛ እንዲሁም ትኩረትን
በሚስብ ጽሁፍ ብዙዎችን የሚያሳስቱን ነጥለው በማየት እውነትን
መግለጥ የሚችሉት በዚህ ጸጋ የተባረኩ ናቸው፡፡

2.3.4. በሰይጣን በመታገዝ አስመሳይ ተአምራትን የሚያደርጉትን


ለማጋለጥና ለማስቆም (2ተስ 2፡9)
በዓለማችን በብዙ ሥፍራ በሰይጣናዊ ተአምራት ተጠልፈው
ከእውነተኛው መንገድ የወጡ ብዙ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ
አሠራር ምእመናንን እንዳያሳስት የዚህ ጸጋ ጠቀሜታ ይህ ነው
አይባልም፡፡ ቅዱሳንን ከአስመሳይ ተአምራት ተጽእኖ ለማስጣል
መናፍስትን የመለየት ጸጋ ተፈላጊ ነው፡፡ ምእመናንን ለማደናገር
አስመሳይ ኃያላት በታላቅ ጭካኔ በምድር ተሰማርተዋል፡፡ ከዚህ
ክፉ ኃይላት ወረራ እንዲጠበቁ ምእመናን መናፍስት
ከእግዚአብሔር ሆነው እንደሆነ መርምሩ ተብለዋል፡፡ መንፈስን
ሁሉ አትመኑ በሚለው ቃል ምክር፣ ትዕዛዝና ማሰጠንቀቂያ
በሚዛናዊ ቅንጅት ተቀምጠዋል፡፡ አትመኑ የሚለው ማስጠንቀቂያ
ከክፉ ቀን ለመጠበቅ የሚያስችል በጎ ምክር ነው፡፡ ይሁን እንጂ
አንዳንዱ የጠላት ሥራ ከመልካሙ የመንፈስ አሠራር ጋር
ስለሚመሳሰል በዚህ ጸጋ የተባረኩ አማኞች አገልግሎት መታገዝ
ከሰይጣን ጥቃት ከመጋለጥ ያድናል፡፡ ክፉው ቅዱሳንን በተአምራዊ
ድርጊቱ ለማደናገር ሲሞክር እንቅስቃሴውን ለመግታትና ለማጋለጥ
ይህ ጸጋ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 40


2.3.5. መናፍስትን ለመለየት የሚሆነው መረዳት እንዴት
ይመጣል
1. ለልብ በሚሰማ ድምጽ
2. ተቀባዩ ብቻ በሚገነዘበው ምልክትና ልዩ ብርሃን
3. በራእይ
4. በሰማያዊ መልእክተኛ እገዛ (መልአክ
5. በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን አማካኝነት

የኃይል ስጦታዎች

በዚህ ስያሜቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቀጥታ ተጽፈው


አናገኝም፡፡ ይሁን እንጂ ስጦታዎቹ በአማኞች የዕለት ተዕለት
ልምምድ የማናያቸውን ትንግርት የሚባሉ አስደናቂ ድርጊቶችን
እውን በማድረግ ስለሚገለጡ የኃይል ስጦታዎች የሚለው ስያሜ
ይስማማቸዋል፡፡ ስጦታዎቹ ራሳቸውን በተግባር በሚገልጡበት
ባህሪያት ሰይሞ ማጥናት እውነቱን በሚዘልቅ መንገድ ለማቆየት
ይመረጣል፡፡ አያሌ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቸ መንፈሳዊ
ስጦታዎቹን በልዩ ልዩ ቅርጽና አደረጃጀት ማጥናቱን
እንደሚመርጡ ቀደም ብለን ለማሳየት ሞክረናል፡፡ የዚህ ጽሁፍ
አቅራቢ ይኸኛው ቅርጽ የተሻለ እንደሆነ ያስባል፡፡

2.4. የእምነት ስጦታ (1ኛቆሮ 12፡9)


መንፈስ ቅዱስ ስጦታውን ባካፈለው አማኝ ውስጥ
የሚገልጠው፣ በእግዚአብሔር ላይ የሚታይ ልዩ መደገፍ ነው፡፡
ይህ እምነት በማይቻሉ ሁኔታዎች ውስጥ ተከቦ ከሚታየው ጭንቅ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 41


ባሻገር ያለውን መፍትሔ በማየት መረጋጋትን በተግባር የሚገልጥ
ነው፡፡ ያላዩትን እንዳዩ፣ የሌለውን እንዳለ፣ ያጡትን እንዳገኙት፣
ኃያሉን እንደ ደካማ፣ ከባዱን እንደ ቀላል በመቁጡር ሁሉን
በሚችለው ጌታ መተማመን ነው፡፡

የእምነት ስጦታ ያልሆነው

 እምነት አቅጣጫ የሌለው እንቅስቃሴ አይደለም


 እምነት መፍዘዝ ወይም መደንዘዝ አይደለም
 እምነት ተላላነት አይደለም
 እምነት ስንፍናን መሸፈኛ አይደለም
 እምነት ሽንገላ አይደለም
 ሌላውን አማኝ በመገፋት የሚወጣ ኃይለ ቃል አይደለም

በመሠረቱ እምነት ማለት ፍጹም በእግዚአብሔር


በመታመን፣ በመደገፍ፣ በማረፍ ያለየነው እንደሚሆንና እንደሆነ
ማመን ሲሆን ሽልማቱም ያመንነውን በገሐድ ማየት ነው፡፡ እንዲህ
ዓይነቱ እምነት ቃል ኪዳኑን ሳይሆን ቃል ኪዳን ሰጪውን
በጥልቀት ይገነዘባል፡፡ ይደገፋልም፡፡ እምነት ከፍጡር የሚመነጭ
ሳይሆን ፈጣሪ የሚያድለው ጸጋ ነው፡፡
የእምነት ጸጋ ጠቀሜታውና ተግባራዊ ምሳሌዎች

2.4.1.ነገንና ሩቅ ዘመናትን አሁን እዚህ ለማየት የሚያስችል ልዩ


አቅም ይሰጣል (ዘፍ 27፣ ዘፍ 49)

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 42


የእምነት ጸጋ የሚመጡትን ዘመናት እንቅስቃሴና እጣ
የሚወስን ድርጊት በአሁኑ ሁኔታ ውስጥ ማከናወንን በተግባር
ይገልጣል፡፡ እምነት ወደ ፊት አይልም፣ ወደ ፊትን እዚሁ
ያየዋልና፡፡ ይስሐቅም ሆነ ያእቆብ ልጆቻቸውን ሲባርኩ የሆነው
ነገር ይህ ነበር፡፡ የየልጆቻቸውን ድርሻ በእምነት ቡራኬ ሲሰጡ
ያሉት ነገር እንደሚሆን ምንም ጥርጥር አልነበራቸውም፡፡ የሚሉት
ነገር ደግሞ ከንቱ ልፍለፋ፣ ትርጉም የለሽ የቃላት ድርድር ሳይሆን
ይልቁንም የወደፊትን እጣ የሚወስን እውን ክስተት ነበር፡፡ ድንቅ
የሆነው ከብዙ ዘመን በኋላ የሚመጣውን እነርሱ በአሁን ጊዜ
ማየታቸው ነበር፡፡ እምነታቸው እይታንና እርግጠኝነትን
ውስጣቸው ስለሠራው ምንም ሳይደናገሩ ነገን በፍጹም
እርግጠኝነት ዛሬ ይናገራሉ፡፡ የእምነትን ጸጋ ለመረዳት ይስሃቅ
በልጁ በያእቆብና በኤሳው መሐል የፈጸመው የምርቃት ሥነ
ሥርዓት ጥሩ ምሳሌ ሆኖ ያገለግለናል፡፡ ኤሳው ሲመለስ
ወንድምህን በአንተ ላይ ጌታ አደረግሁት የሚለው ነገር ገዥ መሆኑ
ምንም የሚያጠራጥር አልነበረም፡፡ ከታሪኩ ወዲህ ማዶ ያለን
ሰዎች ይህ ተፈጽሞ ስናይ ሁኔታው በእርግጥ የሚገርም እንደ ነበር
እንገነዘባለን፡፡ የአባቱን እምነት በተግባር የተለማመደው ያዕቆብ
በዮሴፍ ልጆች በምናሴና በኤፍርም ያደረገውን እናስታውሳለን፡፡
ከብዙ ዘመን በኋላ ጉዳዩ እርሱ እንዳለው እንደነበር
እናስተውላለን፡፡ ምርቃቱ ምርቀት እንደሆነ ሁሉ የተግሳጽና
የማረሚያው በትርም ያንኑ ያህል ውጤት ያመጣ ነበር፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ ቅዱሳንን በሚያዋርድ ምርጫ በሄደው
ወንድም ያደረገው ይህንን መሰሉን የእምነት ርምጃ ያካትት ነበር፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 43


ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘው ግለሰብ የወደፊት እጣ ላይ በአሁን ሁኔታ
ወሰነ (1ኛቆሮ 5፡1)

2.4.2. የማይቻለውን የሚያስችል ብቃት በማጎናጸፍ (2ኛ ነገ 4፡1)

እምነት አበቃለት አይልም፡፡ እምነት አለቀለት አይልም፡፡


ይልቁንም ጸጋው ሲገለጥ በሰው አእምሮ የማይገመቱ ነገሮች ሆነው
እንመለከታለን፡፡ ነቢዩ ኤልሳዕ መጥረቢያውን በውኃ ለሰጠመበት
ሰው የሰጠው መፍትሄ ለብዙ ዘመናዊያን አእምሮ አይመችም፡፡
መንስፋፍ የነበረበት እንጨቱ መሆን ነበረበት ብረቱ ግን
ተንሳፈፈ፡፡ የኤልሳዕ ዓይን ብረቱ የሚወጣበትን መንገድ አይቶት
ስለነበር መፈትሄውን አመለከተ፡፡ የማይቻለው ተቻለ፡፡ በዚህ ጸጋ
የተባረኩ ሰዎች የሌለው እንዳለ አድርጎ የማየት አቅም አላቸው፡፡
ተስፋ የለውም ከተባለ ነገር ባሻገር የሚያይ አይን አላቸው፡፡
ለእነርሱ ተጨባጭ የሆነውን ነገር እርግጠኛ ሆነው ሲናገሩ
ብዙዎች አይረዷቸውም፡፡ ቢሆንም እምነት ተጨፍኖ መጎተት
ወይም ዝም ብሎ መነዳት ሳይሆን በተከፈተ ዓይን ጌታ ያየውንና
እንዲሆን የፈቀደውን አይቶ መራመድ፣ ከጌታ ሃሳብ ጋር መቀናጀት
ነው፡፡ ጸጋው በትክክል የሚሠራባቸው ሰዎች በእምነት ይሆናል
ያሉት ሆኖ ስንመለከት እኛም በመገረምና በመደነቅ እንሞላለን፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 44


2.4.3. አሻግሮ ለማየት የሚያስቸል ልዩ እገዛን እውን ያደርጋል
(ሐዋ 27፡26)

የእምነት ጸጋ ችግር ከነገሰበት የአካባቢ ሁኔታ በላይ የሚያደርግ


ስሜትን እንዲሁም ተስፋን በአገልጋዩና በዙሪያው ባሉት ላይ
ይፈጥራል፡፡ በእምነት የሚወሰደው ተግባራዊ እርምጃ ባካባቢው
ሆነው የሚመከቱትን ሰዎች የሚያጽናና ሆኖ ሲገለጥ
እናስተውላለን፡፡ የመዳን ተስፋ ባጡ ሰዎች መሐል ክፉ ዕጣን
የሚቀይር ተስፋና ብርሃን ይፈነጥቃል፡፡ ከላይ በተጠቀሰው
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጳውሎስ ምንም አትሆኑም ብቻ ሳይሆን
የተነገረው ነገር በተግባር የሚፈጸም መሆኑን አምናለሁኝ በማለት
አስገነዘበ፡፡ ሁኔታውም እንደ ቃሉ ተፈጸመ፡፡

2.4.4. ጌታ የሰጠውን ቃል ኪዳን ለመቀበል የሚያስችል ብቃትን


ይለግሣል (ዕብ 11፡11-12)

አይቻልም በተባለበት ሁኔታ ውስጥ ጌታ ያለውን ከማመን የተነሳ


ኪዳኑ እንደ ቃሉ የተፈጸመው የኪዳኑ ተቀባይ ባለው እምነት
ጭምር መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ለሞተው ሕይወት
ለአረጀው መታደስን የሚሰጥ ሕያው እምነት ቃል ኪዳኑን
በተግባር ለማየት የሚያስችል ኃይልን ይፈጥራል፡፡
2.4.5. ከክፉ ኃይላት ጋር የፊት ለፊት ውጊያ ለመግጠም (ዕብ
11፡32)

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 45


ከሚታየው ክፋትና የብልግና ንግግር በስተኋላ የጨለማ ኃይላት
መኖራቸው አይጠረጠርም፡፡ የክፋት እንቅስቃሴያቸውን ለማፍረስ
የእምነት ጸጋ ጠቀሜታ ታላቅ ነው፡፡ የጭለማ ኃይላት ቅዱሳን
ለማስጨነቅ የሚወረውሩት ልዩ ልዩ ፍላጻ የሚመክነው የእምነት
ጋሻን ባነገቡ ንቁ ቅዱሳን ትጋት እና ምከታ ነው፡፡ ከዚህ ጸጋ
አሠራር አኳያ እያንዳንዱ አማኝ በተግባራዊ ሕይወቱ የዚህ ጸጋ
ተካፋይ እንዲሆን መጸለይ አለበት፡፡ ይህንንም መጽሐፍ ቅዱስ
ያደፋፍራል፡፡ በዚህ ጸጋ ስጦታ የተባረኩ ሰዎቸ አስገራሚ የጸሎት
ጸጋ አላቸው፡፡ ያለ ጸሎ ሕይወት ይህንን ስጦታ እንለማመዳለን
የሚሉ ሰዎች በቅርበት መታየት አለባቸው፡፡ የስጦታው ባሕሪ
ጸሎተኛነትን ያከትታል አልን እንጂ ስጦታው የሚሰጠው
ለጸሎተኞች ነው አላልንም፡፡

2.4.6. የእምነትን ጸጋ ለመለማመድ የሚሆነው መረዳት እንዴት


ይመጣል
1. ለልብ በሚሰማ ድምጽ
2. ተቀባዩ ብቻ በሚገነዘበው ምልክትና ልዩ ብርሃን
3. በተቀባዩ ሕይወት በሚፈስ ልዩ እርግጠኝነት
4. በሰማያዊ መልእክተኛ እገዛ (መልአክ
5. በተለመደው የሰው አመለካከት ተቀባይነት ካለው
ሁኔታ ባሻገር እንድናይና ሌሎች ሰዎች የማይቀበሉትን ጉዳይ
እንደንቀበል በሚያደርግ አቅምና ሕይወት ውስጥ በመገኘት፡፡
2.5. የፈውስ ሥጦታዎች (1ኛቆሮ 12፡8-9)
የፈውስ ስጦታ እንደ ሌሎቹ ስጦታዎች የመንፈስ ቅዱስ ተአምራዊ
እርዳታ የሚያመለክት ነው፡፡ በተለያየ ደዌ የደቀቁትን

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 46


ሕመምተኞች ጤና ለማድረግ የሚገለጥ ልዩ የእግዚአብሔር ጣት
ነው፡፡ ለእያንዳንዱ የፈውስ ስጦታ ምንጩ ፈጣሪ እንጂ ፍጡር
አይደለም፡፡ በዚህ ስጦታ የሚያገለግለው ሰው ለጌታ ፈቃድ
መተላለፊያ መሣሪያ እንጂ የስጦታው አደላዳይ አይደለም፡፡
ሥጦታው የሚሠራው በባለሥጦታው ትጋትና ንቃት ሳይሆን
በአንድዬ ፈቃድና ሥልጣን ነው፡፡ ተፈዋሹንና ጊዜውን መምረጥ
የመለኮት ብቻ ነው የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ
በተለየ መንገድ ክብሩን ሲገልጽ ሰዎች ከልዩ ልዩ ደዌ ነጻ
ይሆናሉ፡፡

የፈውስ ጸጋ ያልሆነው
 ክርስቶስን የማይገልጠው የተለምዶ አደራረግ
 በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያልተቀመጠ እንግዳ ልምምድ
 ላለመፈወስ ስህተቱ (የአለማመን ችግር) በሕመምተኛው
ላይ ብቻ የሚያሳብበው

አብዛኛውን ጊዜ እንዲህ ዓይነቱ ፈውስ በጉባኤ እውን የሚሆነው


ሰዎች የጌታን ክብር አይተው ከእርሱ ጋር ኅብረት እንዲያደርጉ
ነው፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በምእመናን መካከል ሲሠራ ጌታን
የሚያውቁ ለበለጠ መሰጠት ይነቃቃሉ፡፡ ጌታን የማያውቁ
እንግዶች ደግሞ ባዩት የአምላክ ክብር ተነክተው ከአዳኛቸው ጋር
የሚታረቁበት እድል ይፈጠራል (የሐዋ 4፡29-33)፡፡ የፈውስ
ዋነኛው ዓላማ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ሕያው መሆኑን

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 47


ማስረገጥ ነው (የሐዋ 3፡15-16)፡፡ የፈውስ በረከት ለአማኝ በተለያየ
መንገድ ይመጣል፡፡
የፈውስ ጸጋ ጠቀሜታውና ተግባራዊ ምሳሌዎች
2.5.1. ይህ ጸጋ ሲሰራ ለመታወክ ምክንያት የሆነው የስቃይ ምንጭ
ይወገዳል (ዘፍ 20፡17፣ ማቴ 8፡14)
አብርሃም ጸለየ አግዚአብሔር አቤሜሌክና ቤተሰቡን
ፈወሰ ከሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ የስቃዩ ምንጭ
መወገዱን እንመለከታለን(ዘፍ 20፡17)፡፡ የበሽታው ዓይነት ምንም
ይሁን ምን ይህ ጸጋ ባለው ሰው የችግሩ ምንጭ ተወግዶ
ታማሚው ጤና ይመለስለታል፡፡ የጴጥሮስ አማት ንዳድ ለቋት
ወዲያው በመደበኛ ሥራ ላይ ተሰማራች (ሉቃ 4፡38-41)፡፡

2.5.2. ፈውስ የማያምኑ ሰዎች ወደ ጌታ ለማምጣት መሣሪያ ሆኖ


ያገለግላል (ማር 16፡ 15-20፣ የሐዋ 8፡6-7)

ፈውስ ለተፈዋሹ የጤንትን በረከት በማምጣት እጹብ ድንቅ ደስታ


መለሰጉ ታላቅ ድርጊት ቢሆንም ከዚያ የሚልቀው ተልእኮው የጌታ
ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በማስረገጥ ኃጢአተኞችን ወደ ምህረቱ
መጣራት ነው (የሐዋ 3፡15-16)፡፡ የኢየሱስን ጌትነት የማያስረግጥ
በጸሎት የሚገኝ ፈውስ ወደ ባሕላዊ ሕክምና ዝቅ ይላል፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 48


2.5.3. ፈውስ ምእመናንን በመደነቅና በአምልኮ እንዲሞሉ
ያደርጋል (ማር 2፡12፣ ሉቃ 5፡-24-26)

በሕመም የተሰቃዩ እፎይታ ሲያገኙ፣ አካላቸው የጎደለበቸው ሙሉ


ሲሆኑ እነርሱና ስለ እነርሱ የተጨነቁና ግራ የገባቸው አካላት
ፈዋሹን በማድነቅና በማምለክ ይሞላሉ፡፡ የትኛውም የጌታ ቸርነት
በእርሱ ደግነት እንድንገረም ካላደረገን የጌታን ልብ ያሳዝናል (ሉቃ
17፡17) አሥሩስ አልነጹምን ዘጠኙስ ወዴት አሉ (ሉቃ 17፡17)
ለፈውሳቸው ተገቢውን አክብሮት ስለ ነፈጉ ሰዎች የተጠየቀ ጥያቄ
ነው፡፡
2.5.4 ፈውስ እንዴት ይመጣል

ፈውስ በልዩ ልዩ መንገድ ለተቀባዮቹ መድረሱን መጽሐፍ ቅዱስ


በልዩ ልዩ ክፍሎች ያስታውቃል፡፡ ፈውስ
1. በመንካት (ማር 1፡41)
2. የስልጣን ቃል በመናገር (ሉቃ 7፡6-10)
3. መንፈስ ቅዱስ በጊዜው በመረጠው መንገድ ይገለጣል (የሐዋ
19፡11)፡፡ ፈውስን በተመለከተ በተደጋጋሚ የሚስተዋል ስህተት
አለ፡፡ ይህም ስህተት ያለመፈወስን ችግር ከሚጸለይላቸው ሰዎች
ጋር ብቻ ማያያዙ ነው፡፡ ሰዎች ከእምነት ማነስ የተነሳ
የማይፈወሱበት ጊዜ ቢኖሩም ሁሉም ሰውና ሁልጊዜ
ላለመፈወሳቸው ብቸኛ ምክንያት ግን ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ከዚህ
የተነሳ የፈውሱ ጸጋ አለው የተባለው ግለሰብ እርግጠኝነትም
በውል መጤን አለበት፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 49


2.5.5.እምነትና ፈውስ

እምነትና ፈውስ በልዩ ልዩ መንገድ ተቆራኝተው እናያለን፡፡


ለምሳሌ የሚሆነን አጠር ባለ መልኩ እንደሚከተለው
እንመልከት፡፡
1. ስለ ሌላው በመማለድ በተግባር የሚታይ እምነት (ማር 2፡5)
2. ታማሚው ፈውሱን ለመቀበል የሚያበቃው የእምነት ሁኔታ
(ማቴ 9፡22)
3. ታማሚው ራሱን መርዳት ባልቻለ ጊዜ የሚገለጥ የአገልጋዩ
እምነት (የሐዋ 28፡7-9)
4. ጸሎተኛውና የሚጸለይለትን ሰው ግድ የሚል እምነት (ማቴ
9፡28-29)
5. ጌታ በቸርነቱ በርህራሄው የሚሰጠው ፈውስ (ዮሐ 5፡1-9)
6. እምነት በሌለ ጊዜ ፈውስ ሊዘገይ ወይም ላይኖር ይችላል
(ማቴ17፡14-21፣ማር 9፡14-29)
ሆኖም በተደጋጋሚ ልናይ እንደሞከርነው በዚህ ስጦታ ያገለገሉ
ሰዎች ለጸለዩላቸው ሁሉ ፈውስ አላስገኙም፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ
ስጦታው ቢኖረውም የወንጌል አጋሩን አፍሮዲጡንም
አልፈወሰውም፡፡ ይልቁንም በጌታ ጊዜ በሂደት ማገገሙን
ሲያስገነዝብ ጌታ ማረው ሲል ተናገረ (ፊሊጵ 2፡25)፡፡
ጢሞቲዎስንም ሕመሙ የሚቀንሰበትን መንገድ ሲመክረው እንጂ
ሲፈወሰው አናይም (1ኛጢሞ 5፡23)፡፡ እነዚህ ሁለት ተጨባጭ
ድርጊቶች የሚያመለክቱን የፈውስ ጸጋ ያላቸው ሰዎች የጸለዩለት
ሁሉ እንደማይፈወስ ነው፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 50


2.6. ተአምራት የማድረግ ስጦታ (1ኛቆሮ 12፡9፣

መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ የተአምራት ታሪኮች የተሞላ መጽሐፍ


ነው፡፡ ክህደትንና ጥርጣሬን የሕይወታቸው መርሆ ያደረጉ ሰዎች
የመጽሐፍ ቅዱስ የተአምር ታሪኮችን መስማትም ሆነ ማንበብ
አይወዱም፡፡ ይሁን እንጂ ያለ እነርሱ ማረጋገጫ መጽሐፍ ቅዱስ
መልእክቱን የተቀበሉ ምእመናን እያነጸ ሁሉን አሳልፎ ለዘለቄታው
ይኖራል፡፡ ተአምር የእግዚአብሔርን ክብር፣ የክርስቶስን ማዳን
የገለጠባቸው አማኞች በመገረምና በመደነቅ ተሞልተው
አምላካቸውን የባረኩበትንና ከፍ ከፍ ያደረጉበቸውን ሁኔታዎች
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዙ ሥፍራዎች እናያለን፡፡
ከጌታ ኢየሱስ ረድኤትና ከመንፈስ ቅዱስ እገዛ የተነሳ
ታምር በአማኞች ሕይወት ሲገለጽ የታበየ ይዋረዳል፣ አመጸኛ
ይቀጣል፣ የማያምን ደግሞ ስንፍናው ገሃድ ሆኖ ይገለጣል፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ ‹‹ለአንዱም ታአምራት ማድረግ..›› በሚለው
አገላለጹ ማስገንዘብ የፈለገው በዚያ ዘመን በተግባር የታየውን
የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው፡፡

ተአምራት ያልሆነው
 በፍጡር ብልሃት የሚከወን ምትሃት አይደለም
 የአምላክን ክብር የማይገልጽ የፍጡር ትንግርት አይደለም
 ከእውነተኛ አምልኮ የሚያርቅ ብርቅ ነገር አይደለም
 ፍቅር የራቀው ኃይል አይደለም
ተአምራት የማድረግ ጸጋ ጠቀሜታውና ተግባራዊ ምሳሌዎች

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 51


2.6.1. የእግዚአብሔር ሕዝብ ከጨካኝ ኃይላት ለማላቀቅ (ዘጸ 4-14፣
የሐዋ 12፡1-19)
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጨካኝ ኃይላት የጌታን ልጆች
ርህራሄ በጎደለው መንገድ ሲጎዷቸው ሊያስጥላቸው የጌታ እጅ
ሲንቀሳቀስ ብዙ ጊዜ ታይቷል፡፡ ተአምሩ ልዩ ልዩ ገጽታ ለብሶ
ተገልጧል፡፡ በሙሴና አሮን አገልግሎት የታዩት ታምራቶች
አላማቸው ሕዝቡ እግዚብሔር ለማገልገል ነጻ እንዲወጣ ነበር፡፡
ተአምር ሲከናወን ሁልጊዜም ወደ አድራጊው ይጠቁማል፣
የተደረገለት ደግሞ ወድቆ ይሰግዳል፡፡ አድራጊውንም ይባርካል፡፡

2.6.2. የጌታ ሕያውነትና አሸናፊነት እንዲታይ ነው (1ኛ ነገ 17-19፣


2ኛ ነገ1፣ ከም3-ም7፣ የሐዋ 3፣ 9፣ 14፣ 19፡19)
በብሉይ ኪዳን ከተአምር ጋር የተያያዙ አያሌ ታሪኮች
አሉ፡፡ ሁሉም እግዚአብሔር ሕያውና አሸናፊ መሆኑን አማኞች
ተገንዝበው ለእርሱ ሙሉ ለሙሉ እንዲገዙ የተከናወኑ ነበሩ፡፡
የኤልያስም ሆነ የኤልሳዕ የአገልግሎት ታሪኮች በቅደም ተከተል
የሚያስገነዝቡን ይህንን መለኮታዊ እውነታ ነው፡፡ የባዕድ አማልክትን
ከንቱነት የእግዚአብሔርን ብቸኛ ጌትነት ለማስረገጥ ውርርድ የገጠመው
ኤልያስ ፍጥረት ሊሰግድለት የሚገባው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን
በሕይወቱ ባለፈው ታአምር አስገነዘበ፡፡ የጌታ ኢየሱስ አገልግሎት
በብዙ ተአምራት የተሞላ ነበር፡፡ ጥቂቱን አተረፍርፎ መመገብ፣
ወኃውን ወደ ወይን መቀየር፣ ለሙት ትንሳኤ መስጠት፣በውኃ ላይ
መራመድ፣ ማዕበሉን ጸጥ ማሰኘት በአገልግሎቱ ከታዩ ታአምራት
ጥቂቶቹ ነበሩ፡፡ እነዚህ በሙሉ በዓላማ የተከናወኑ የአምላክ ሥራዎች

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 52


እንጂ ፍጡር ለማስደሰት የቀረቡ ድራማዎች አልነበሩም፡፡ በሐዋርያት
አገልግሎትም ቃላቸው፣ ልብሳቸው፣ ጥላቸው የጌታን ክብር በሚያሳይ
መንገድ የጌታን ተአምራዊ ኃይል እያሳየ ታላላቅ አገልግሎት ይከናወኑ
ነበር፡፡ ታምር የአዲስ ኪዳን አገልግሎት መታያ መሆኑን የእብራውያን
ጸሐፊ በማያሻማ መንገድ ያስረዳል (ዕብ 2፡4)

2.6.3. አማኞች በተቀደሰ ሕይወትና በፈሪሃ እግዚአብሔር


እንዲመላለሱ ለመርዳት (ዘሁ 12፡1 2ሳሙ 6፣ የሐዋ 5
ተአምራት በተደረገበት ሥፍራ ሁሉ ፈሪሃ እግዚአብሔር በሕዝቡ
ላይ ይወድቃል፡፡ የማይፈሩት መንፈሳዊ ድንቁርና የተጫነው ብቻ
ናቸው፡፡ በሐዋ 5 ግብዝነት በንጹኋና በጨቅላዋ ቤተ ክርስቲያን አስርጎ
በማስገባት ገና በትንሽነቷ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ ለመበረዝ
የተደረገውን ሙከራ መንፈስ ቅዱስ በተአምር እንዲቆም አደረገ፡፡
ይህንን ልብ ብሎ የተመለከተ አንድ የእግዚአብሔር ሲናገር እንዲህ አለ
‹‹መንፈስ ቅዱስ እንደ ሐዋርያት ዘመን ዛሬም የሚሠራ ሆኖ ቢሆን ቤተ
ክርስቲያን የምህረት ቤት የፈውስ ቤት መሆኗ ቀርቶ የሬሳ ቤት ትሆን
ነበር›› ሲል ተናገረ፡፡

2.6.4. የወንጌልን እንቅፋት በማስወገድ ቃሉን በተአምር


ለማጽናት(የሐዋ 13፡11-12)
መንፈስ ቅዱስ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ አገልጋዮች
በወንጌል ዘመቻ ላይ ተሠማርተው ሳሉ የቃሉን አዋጅ በታምር
አጸናላቸው (የሐዋ 13፡11-12)፡፡ ጳውሎስ የወንጌሉን እውነት ይዞ ወደ
አገረ ገዥው በሄደ ጊዜ የኃይላት ውጊያ ተካሄደ የጌታም አሸናፊ ጣት
ተገለጠች፡፡ አገረ ገዥውም ከጌታ ልዩ መገኘት የተነሳ አመነ፡፡ ዛሬም

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 53


ተአምራት አገልግሎት ለማጽናት ተፈላጊ በሆነ ቦታ ሁሉ ይገለጣል፡፡
የተአምራት ዓለማው አማኞችን ማዝናናት ሳይሆን የጌታን ታላቅነት
ማስተጋባት ነው፡፡ ክብሩን የሚቀናቀኑ ኃይላት ባሉበት ቦታ ልጆቹ
ቆመው መገኘቱን ሲናፍቁ ምንጊዜም ከተፍ ይልላቸዋል (ማር 16፡15-
20፣ ዕብ 2፡4)፡፡
የኃይል ስጦታዎች በሚል ርዕስ ልናጠናው የሞከርናቸው
እነዚህ መንፈስ ቅዱስን የሚገልጡ ሥጦታዎችን ሥራ የሚወስነው ራሱ
መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ዓላማውም እርሱ በመረጠው መንገድ በመሥራት
ራሱን መግለጥ ሰዎች በእግዚአብሔር ልጅ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ
አምነው ራሳቸውን ሙሉ ለሙሉ እንዲሰጡት ለማድረግ ነው፡፡ ሰዎች
የሚድኑበት ጊዜና ሁኔታ መምረጥ የመንፈስ ቅዱስ ግላዊ መብት ነው፡፡
ስጦታው የሚሠራበት ሰው እንኳን እያንዳንዱን ሁኔታ ምን እንደሆነ
ለመግለጽ አይቻለውም፡፡ ሁሉን አለማወቅ የሰውነት መለዮአችን እንጂ
ጉድለታችን ሆኖ መታሰብ የለበትም፡፡

2.6.5 ተአምራት የማድረግ ጸጋ እንዴት ይገለጣል

1. ጸጋው የተሰጠው ሰው በሚረዳው ልዩ ምልክት (መንካት፣ የስልጣን


ቃል፣ ወዘተ..
2. የተለየ ኃይልን እውን በማድረግ (ኤልሳዕን መላጣ ብለው
በተሳደቡት ብላቴኖች የመለኮት ፍርድን ጠየቀ እንዳለውም ሆነ 2 ነገ
2፡23-24)
3. ከሰው ግንዛቤ በላይ የሆኑ ክስተቶችን በመግለጥ፣ ጊዜው የተዋሰውን
መጥረቢያ ያጣበት ሁኔታ ነበር፡፡ እንጨት ሲንሳፈፍ እንጂ ብረት

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 54


ሲንሳፈፍ አናውቅም፡፡ ይሁን እንጂ ለማመን የሚያስቸግር ነገር አደረገ
ነገሩም ችግሩን በሚፈታ መንገድ ተከናወነ፡፡ (2 ነገ 6፡6)

የማነቃቂያ (የመናገር ፣ የልሣናት ስጦታዎች)


በዚህ ክፍል ሥር የምንመለከታቸው ስጦታዎች ከመናገር ጋር በጥብቅ
ተሣስረዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ስጦታው ያካፈላቸውን አማኞች ተጠቅሞ
ሲሠራ ምእመናን የሚያንጽ ጸጋ ይለቀቃል፡፡ በዚያን ጊዜ ምእመናን
ይታነጻሉ፣ ይነቃቃሉ፣ ጌታን ለማምለክና ለማገልገል ይበረታታሉ፡፡
ስህተት ሠርተው ከሆነ ይመለሳሉ፣ አዝነው ከሆነ ልባቸውን የሚደግፍ
ፀጋ በዚህ ስጦታ አማካይነት ሲደርስላቸው ይፅናናሉ፣ በእልኸኝነትና
በአመጸኝነት ለመጓዝ አስበውና ወስነው ከሆነ ደግሞ ይህ ስጦታ ሲሠራ
በሚላከው ተግሣጽ አማካኝነት ይታረማሉ፡፡ እነዚህ ስጦታዎች
አሠራርና ባሕሪ በቅደም ተከተል ለመመልከት እንሞክር፡፡

2.7. የልሣናት ሥጦታ (በልሣን የመናገር) ስጦታ(1ኛቆሮ 12፡8-9)


በልምምድ እንዲሁም በትምህርት ባልተገኘ ቋንቋ መናገር ሲሆን ይህም
በዚህ ምድር ሰዎች በሚጠቀሙበት አሊያም መንፈስ ቅዱስ ብቻ
በሚያውቀው ሰማያዊ ቋንቋ ለመናገር መታደል ነው፡፡

የልሳን ስጦታ ያልሆነው


 በልማድ የተገኘ ቋንቋ መጠቀም አይደለም
 የተለየ ተሰጥኦ ያለውን አማኝ ጸጋ መኮረጅ አይደለም
 ትርጉም የለሽ ቃላትን መደጋገም አይደለም
 በድምጽ ቅኝት ማንጎራጎር አይደለም

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 55


መንፈስ ቅዱስ ለአማኙ ይህንን ቋንቋ ሰጥቶት አማኙ መናገር ሲጀምር
አብዛኛውን ጊዜ በተናጋሪው አዕምሮም ሆነ በአዳማጮቹ ጆሮ
መልእክቱን መገንዘብ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ስጦታው አንድን ቋንቋ
አበጥሮ ማወቅና ከዚያም በኋላ በቋንቋው መጠቀም መቻል
አይደለምና፡፡ ይህ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የሚሠራው በአማኞች
አእምሮ ላይ ሳይሆን በአማኞች አንደበት ላይ ነው፡፡ አማኞች ይህንን
ቋንቋ ለመጸለይ ሲጠቀሙበት አንደበታቸውም ሲተጋና
መልእክታቸውን ማለትም (ንስሃን፣ ልመናን፣ ምስጋናን፣ ምልጃን) ወደ
ሰማይ ሲያስተላልፉ የአማኞች አእምሮ ይህንን አስገራሚ የመንፈስ
ቅዱስ ሥራ በገለልተኛ ተመልካቸነት ያስተናግደዋል፡፡ አማኞች
በአእምሮአቸው ሲጸልዩ እንደሚያደርጉት ቃላትን መምረጥ ማቀናጀት
ላይ አይሳተፍም፡፡ በዚህ ጊዜ አእምሮ ተችሎት የሚያደርገው ነገር
ቢኖር የድምጽ መጠንን መጨመርና መቀነስ ነው፡፡

በልሳን የመናገር ጸጋ ጠቀሜታውና ተግባራዊ ምሳሌዎች


በልሳን የመናገር ጥቅሞች ብዙ ናቸው፡፡ እነርሱንም ከዚህ በሚከተለው
መልክ እንቃኛለን፡፡

2.7.1. አማኞች በልሳን ሲናገሩ ራሳቸውን ያንጻሉ (1ኛቀሮ 14፡4)


በልሳን የሚናገሩ መንፈስ ቅዱስ በሰጣቸው በዚህ ቋንቋ ሲጠቀሙ
ይታነጻሉ፣ ይገነባሉ እንዲሁም በመንፈሳዊነት ያድጋሉ፡፡ ይህንን ጸጋ
ሲለማመዱ አእምሮአቸው ቃላትን በመምረጥ እንዲሁም ትኩረትን
በሚስብ መልኩ እንደ ሰንሰለት ማያያዝ ሊገልጣቸው የማይችላቸውን
ፍላጎቶች መንፈስ ቅዱስ ለመልእክቱ ተቀባይ ያደርስላቸዋል፡፡
የምንለውን እንደሚገባን አለማለት ብዙዎቻችን የሚሞግት ፈተና ነው፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 56


በልሳን የመናገር ጸጋ ካለን ግን ይህ ችግር ሳይገጥመን መንፈስ ቅዱስ
በሰዋዊ አንደበታችን ስሌትም ሆነ በምንፈልገው መንገድ ልንገልጸው
የማንችላቸውን እውነቶች በቀጥታ ለእግዚአብሔር ይነግርልናል፡፡ ይህ
የአማኞችን ልብ የሚደግፍ የጌታ ቸርነት ነው፡፡

2.7.2. ማኅበሩ (ጉባኤው) ይታነጻል (1ኛቆሮ 14፡5)


በልሳን በመጸለይ በግላዊና በማኅበራዊ ሕይወታቸው የታነጹና የተገነቡ
አማኞች ውለው አድረው ማኅበሩን ለማነጽ መሣሪያ ሆነው
ያገለግላሉ፡፡ ማኅበር የግለሰቦች ድምር ውጤት እንደ መሆኑ በልሳን
የታነጹ አማኞች ማኅበራቸውን ለማነጽ ስጦታቸውን ይገለገሉበታል፡፡

2.7.3. ጌታን ከልብ በሆነ መሰጠት ለማመስገንና በፊቱ ለመጸለይ


ይጠቅማል

በመንፈስ መጸለይና መዘመር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ አማኝ ጌታን


ለማመስገንና በፊቱ ለመጸለይ እንዲሁም ጌታን ከልብ በመነጨ በጎነት
ለመባረክ ይህ ጸጋ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ይሁን እንጂ በልሳን
የማይጸልዩ በመንፈስ አይጸልዩም የሚለው የአንዳንድ አማኞች
መደምደሚያ ግልጥ ያለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም፡፡ የዚህ
ጽሁፍ አቅራቢ በልሳን የማይናገሩ ግን በመንፈስ የሚጸልዩ እንዳሉ
ያምናል፡፡ ሌሎቻችንም ብንሆን በልሳን ሳይናገሩ የመንፈስ ፍሬዎችን
በሕይወታቸው እያሳዩ በአስገራሚ መሰጠት ጌታን የሚያገለግሉና
የሚባርክ ሕይወት ያላቸው ብዙ አማኞች እናውቃለን፡፡ በልሳን
ስላልተናገሩ በመንፈስ አልተሞሉም የሚለው መደምደሚያ ሚዛን

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 57


ይጎድለዋል፡፡ ስለዚህ ሁሉን እንደማናውቅ ተገንዘበን የኛን
መደምደሚያ ከመስጠት ተቆጥበን እንድንመላለስ አሳስባለሁ፡፡

2.7.4 በልሳን የመናገርን ስጦታ በአግባብና በስርዓት መጠቀም

 የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴን በሚቀበሉ አማኞች ዘንድ በብዛት


የሚታይ መንፈሳዊ ስጦታ ነው፡፡ ይህ ጸጋ በኅብረት ስብሰባዎች ላይ
ጥቅም ሊይ ሲውል ታላቅ ጥንቃቄን ይጠይቃል፡፡ ራስን መግዛትና
የሌላውን ስሜት ባገናዘበ መልኩ ስጦታውን መጠቀም ለግልና
ለማኅበር ያለው እገዛ ልዩ ነው፡፡ ራስን ከመግዛት ውጭ የሆነ
ስሜታዊነት ለግልና ለማኅበር ሰለማዊ ግንኙነት ጠንቅ ነው መጠንቀቅ
ተገቢ ነው፡፡ ጥንቃቄ በጎደለው መንገድ በአማኞች መሐል
የሚስተዋለውን ትርምስ ሐዋርያው 1ኛቆር 14፡32 ይኮንናል፡፡
 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጥንቃቄ ጠበቅ ያለ ማሳሰቢያ ቢሰጥም ሚዛን
እንድንጠብቅ ሲመክረን በልሳን ከመናገር አትከልክሉ በማለት ግልጥ
ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም በስጦታው ራሳችንን እንድናንጽ
ያደፋፍረናል (1ኛቆሮ 14፡39)፡፡
 የልሳንን ስጦታ በጥንቃቄ እንድንጠቀም መመሪያ የሚሰጠን
መጽሐፍ ቅዱስ፣ በቤተ ክርስቲያን አማኞች በኅብረት ባለንበት ሥፍራ
በትርጉም መልክ የማይተላለፍ ልሳ ጮክ ብሎ መናገር የማይገባ
መሆኑን ይናገራል (1ኛቆሮ 14፡28፣19)፡፡

ስጦታው እንዴት ይመጣል


 እኛ በግላችን ስንጸልይ በልሳን ልንናገር እንችላለን

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 58


 ሌሎች ስለ እኛ ሲጸልዩ በሕብረት ቦታ ልንናገር እንችላለን
 መንፈስ ቅዱስ በመረጠው ሰዓት ሁኔታ ሲሰጠን

2.8. በልሳን የተነገረውን የመተርጎም ስጦታ (1ኛቆሮ 12፡9)

መንፈስ ቅዱስ በወቅቱ እንዲተላለፍ የሚፈልገውን መልእክት


በልምምድና በመማር ባልተገኘው ቋንቋ ካስተላለፈ በኋላ የመተርጎም
ጸጋ የተሰጠው ግለሰቡ ወይም ሌላው አማኝ ፍቺ ይሰጣል፡፡ እንዲህ
ባለው ሁኔታ የሚተላለፈው መልእክት ቅንጅትን ይጠይቃል፡፡ በልሳን
መናገር ለተናጋሪው ተአምራዊ የሆነውን ያህል መልእክቱን ለመፍታት
በመንፈስ ቅዱስ መመራት ተአምራዊ ነው፡፡ አንድን ቋንቋ በሌላ ቋንቋ
ሆህያት ማስቀመጥ (Translation) ብለን በተለምዶ የምናውቀው
እውነታ፣ ፍቺ ከመስጠት ወይም ከመተርጎም (Interpretation)
በጥብቅ የለያያል፡፡ ፍቺ መስጠት ወይም መተርጎም(Interpretation)
መንፈስ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ እንዲተላለፍ የሰጠውን መመሪያ ፍልቅቅ
(በሚገባ መንገድ ግልጥልጥ) አድርጎ ከማቅረብ ወይም ደግሞ
መልእክቱን የሚሰሙ ሰዎች በተግባራዊ ሕይወታቸው እውነቱን
ማዋሃድ የሚችሉበት አቅጣጫ ነው፡፡
በልሳን የመተርጎም ስጦታ ያልሆነው
 በልማድ የተገኘን ቋንቋ በአዋቂ ማስተርጎም አይደለም
 የአንድ ለአንድ የቃል ግኙነትን መጠቀም አይደለም

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 59


ልሳንን የመተርጎም ጸጋ ጠቀሜታውና ተግባራዊ ምሳሌዎች
2.8.1 ተአምራዊ የአምላክ ሥራ በማየት አማኞች ይታነጻሉ (1ኛቆሮ
14፡19)
ከልሳን ይልቅ በልሳን የተነገረውን መተርጎም አድማጮች ላሉበት ሁኔታ
የሚጠቅም መልእክትን ያስተላልፋል፡፡ በዚህም ቅዱሳን በሰሙት
መልእክት ስተው ከሆነ ይታረማሉ፣ ያሉበትን ሁኔታ ላገናዘበው
መልእክት በገባቸው መንገድ ምላሽ በመስጠት ከአምላክ ጋር ኅብረት
ይፈጥራሉ፡፡ ባጠቃላይ በዚህ መስመር ወደ እነርሱ ከሚፈስሰው
የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት የተነሳ ምእመናን ይታነጻሉ፡፡

2.8.2 በእግዚአብሔር አሠራር የሚደነቁበት ሁኔታ ውስጥ ይመጣሉ


በበዓለ ሃምሳ ቀን ቋንቋውን የማያውቁ ሰዎች የእግዚአብሔር ድንቅ
ሥራ ለሰሚዎቹ እንደ ተረኩ ሁሉ በዚህ ረቂቅ የመንፈስ ቅዱስ አሠራር
መልእክት ሲተላለፍ አማኞችም ሆነ የማያምኑ በመገረምና በመደነቅ
ይሞላሉ፡፡ ጸጋው ያላቸው አማኞች ይህንን ስጦታ በተግባር ሲያውሉ
ማለትም የራሳቸውንም ሆነ የሌሎቹን ልሳን ሲተረጉሙ አእምሮአቸውን
በመጠቀም ቃል እየመረጡ አይሆንም፡፡ ይህ ድንቅ የመንፈስ ቅዱስ
ሥራ የሚታይበት ሁኔታ እንጂ የፍጡር ብቃትና ችሎታ የሚታይበር
መድረክ አይደለም፡፡ ስለሆነም መንፈስ ቅዱስ ጸጋው ያላቸው አማኞች
ሊገነዘቡት፣ ሊለዩት በሚችል መንገድ ምልክት ከሰጣቸው በኋላ
መልእክቱን ያስተላልፋል፡፡ በዚኅ ጊዜ ሰሚው የእግዚአብሔር አእምሮ
ለሕዝቡ እንደ ተከፈተ ያስተውላል፡፡ ጸጋው የተሰጣቸው አማኞችም
እኩል በመደነቅ ጌታ የሚለውን እያስተላለፉ ይታነጻሉ፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 60


ልሳንን የመተርጎም መልእክት እንዴት ይመጣል
 የትንቢት መልእክት በሚመጣበት ሁኔታ ይመጣል፡፡

2.9. የትንቢት ስጦታ


ትንቢት የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ናባ የሚለውን ሥያሜ ሲይዝ
መፍለቅለቅ፣ በቀስታ መንጠባጠብ መፍሰስ ማለት ነው፡፡ ይህም ማር
ከሰፈፉ ወደ መሰብሰቢያው፤ ዘይት ደግሞ ከመጨመቅያው ወደ
ማጠራቀሚያው ከሚፈስበት ሁኔታ ጋር ያለውን መመሳል በመውሰድ
የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ ልክ እንዲሁ የትንቢት መልእክት ከዋናው
ምንጭ ከእግዚአብሔር በመልእክተኛው በኩል ወደ ሕዝቡ ስለሚፈስ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ለትንቢት የተሰጠው የግሪኩ ሥያሜ
‹‹ፕሮፌት›› የሚለው ሲሆን የቃሉ ትርጉም ደግሞ ሌላውን ተክቶ
መናገር፣ የሌላው አፍ መሆን ማለት ነው፡፡
ትንቢት ማለት በመለኮት ብርሃን በወቅቱ ያለውን እና ሊሆን ያለውን
መልእክት በመንፈስ ተነድቶ ማስተላለፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር በህዝቡ
መካከል ፈቃዱንና ዓላማውን የሚገልጥበት መሣሪያ ነው፡፡ በተለምዶ
ትንቢት የመንፈስ ቅኔ እየተባለ ይጠራል፡፡ እንደዚህ የተሰየመበት ዋናው
ምክንያት መልእክቱ በሚተላለፍበት ወቅት፣ የመልእክት አስተላላፊው
የቋንቋ አጠቃቀምና ከውስጡ የሚፈልቁት ቃላት የተሸከሙት የሃሳብ
ጥልቅነት ከመልእክት አስተላላፊው ወቅታዊ ይዘት ጋር ሲወዳደር እጅግ
የጠለቀ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡ ልሳን በልምምድ ባልተገኘ ወይም
ተናግሪው በደንብ በማያወቀው መንፈስ ቅዱስ በሚሰጠው መለኮታዊ
ቋንቋ መናገር እንደሆነ ሁሉ የትንቢት መልእክት ደግሞ ወደ ፊትም ሆነ
በዚያው ቅጽበት ሊሆን ያለ የመለኮት መልእክት በተለመደ ቋንቋ
ማስተላለፍ ነው፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 61


ትንቢት ያልሆነው
 የሰውን ሁለንተና የሚነካ ልዩ ስብከት አይደለም
 ስሜትን የሚመስጥ ትኩረትን የሚስብ ወቅታዊ ትምህርት
አይደለም
 ትንቢት የአእምሮ ቅምር ውጤት አይደለም

ትንቢት የመናገር ጸጋ ጠቀሜታውና ተግባራዊ ምሳሌዎች

2.9.1 ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ያገለግላል (1ኛቆሮ 14፡3)

የትንቢት መለእክት በትክክለኛ ሁኔታ ጠቀሜታ ላይ ሲውል


የአማኞችን በጌታ ማደግ ያፋጥናል፡፡ ዋናው ተልእኮ ቤተ ክርስቲያንን
ለመገንባት ነው፡፡ ስጦታው በእውነተና ገጽታው በተግባር ላይ ሲውል
ምእምናን በእውነትና በታማኝነት ላይ የተመሠረተ ጠንካራ ኅብረት
ውስጥ ይገባሉ፡፡

2.9.2 ምእመናንን ለመምከርና ለማበረታትይረዳል (1ኛቆሮ 14፡3)


መምከር የሚለው ቃል (ፓራካሌሲስ ) በልዩ መፈቃቀድ
መጠጋጋትን ሲያመለክት በመጠጋት ማበረታታት ማለት ነው፡፡ በብዙ
ውስብስብ ነገር በተሞላች ዓለም ውስጥ አማኝ በብዙ ፈተና እና የኑሮ
ውጣ ውረድ ውስጥ ማለፉ የታወቀ ነው፡፡ ሁኔታዎች ተዘበራርቀው
አማኞችን ግራ ሲያጋቧቸው፡፡ በዚህ ስጦታ አማካኝነት ያሉበትን
ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ ላሉበት ሁኔታ ግልጽ የሆነ መፍትሔንና
መጽናናትን ከሰማይ ሲያገኙ ምእመናን ይጽናናሉ፡፡ በዚህ ጸጋ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 62


አማካኝነት ይረጋጋሉ፣ ይበረታታሉ፡፡ መምከር እውነትን በትዕዛዝ
መልክ መንገር ሳይሆን ይልቁንም የፍቅር ግብዣ ማቅረብ ነው፡፡ ግላዊ
የማማከር አገልግሎት ብለን ከምንጠራው የዛሬው ዘመን አገልግሎት
ጋር ተመሣሣይነት ያለው ቢሆንም አንድ አይነት ግን አይደለም፡፡
ማማከር በማደመጥ መፍትሄ ማፈላለግ ሲሆን ወቅቱን ጠብቆ የሚፈስ
የትንቢት መልእክት ግን አማኞች ካሉበት ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ
የሚገለጥ ከጌታ በቀጥታ የሚላክ ድምጽ ነው፡፡ በዚህ ወቅት አማኞች
ጌታ ሁኔታቸውን እንዳየ፣ በወቅቱም እንደ ደረሰላቸው የሚረዱበትና
የሚደነቁበት ሁኔታ ውስጥ ስለሚገቡ ይነቃቃሉ ይበረታታሉም፡፡

2. 9. 3 ምእመናን ተፋላሚ ሁኔታን ተቋቁመው እንዲጸኑ ያግዛል


(14፡3፣31)
ግራ በሚያጋባ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ገብተው የሚይዙትና
የሚጨብጡት ሲጠፋቸው በመንገላታታት ብዛት ሲዋልሉ፣ ቅዱሳንን
ከጌታ ጋር ለማጣበቅ የሚገለጥ የጌታ ድጋፍና እገዛ ነው፡፡ በብዙ ሰቀቀን
ውስጥ ያለፉ፣ በትልቅ መከራ ውስጥ ተዘፍቀው የተንገላቱ ቅዱሳን
ከከበደ ልብ ተላቅቀው እንዲጸኑ ይህ ጸጋ ያግዛል፡፡ አማኞች ጌታ
እንዳያቸውና እንደሚደርስላቸው ሲገነዙ በጊዜው አለጊዜው
የሚጸኑበትን መልካም ልብ ያተርፋሉ፡፡

2. 9. 4. የማያምኑ ሰዎች ወደ ጌታ እንዲመጡ ያግዛል (1ኛቆሮ 14፡24-


25)
የማያምኑ ሰዎች በልባቸው የደበቁት ምስጢር ሲገለጥ ይደነቃሉ
ይደነግጣሉም፡፡ ይህ ጸጋ በትክክል በአማኞች መሐል ሲሠራ
ኃጢአተኞች በንስሃ ለጌታ የሚማረኩበት እድል ይመቻቻል፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 63


ስጦታው ኃጢአተኛውን ስለ ኃጢአቱ ከመውቀስ ባሻገር የማያምኑ
ሰዎች የእግዚአብሔርን ረቂቅ አሠራር እንዲገነዘቡ እድል
ይሰጣቸዋል፡፡

2. 9. 5 አማኞች ስለ እግዚአብሔር የሚማሩበትን እድል ይሰጣቸዋል


(1ኛቆሮ 14፡31፣ 39)
የሚበዙት አማኞች ግንዛቤ የትንቢት መልእክት ወደ ፊት
ከሚገጥማቸው ሁኔታ ጋር የተያያዘ እውነታ አድርገው ይገነዘቡታል፡፡
ይሁን እንጂ የወደፊቱን በማስገንዘብ ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡
እንደውም አብዛኛውን ጊዜ አማኞችን ከማስተማርና ወደ ብስለት
ለማሻጋገር የሚረዳ መሣሪያ ሆኖ ተገልጧል፡፡ እግዚአብሔር
አምለካችን ወቅቱን ያገናዘበ ለጊዜው የሚሆን በጎነቱን ሲገልጥ ስለ
ድንቅ አሠራሩና ስለ አምላካችን ማንነት የከበረና የጠለቀ እውነትን
በዚህ ስጦታ አማካኝነት እንማራለን፡፡

2. 9. 6 አማኞች ሊወስዱት ስለሚገባ ጥንቃቄ ብርሃን ይሰጠናል


(የሐዋ 11፡ 27-30)
የወደፊቱን ሁኔታ አመላካች መልእክት በዚህ ስጦታ አማካኝት
ሲተላለፍ በወቅቱ ልንወስደው የሚገባንን እርምጃ እንድንወስድ
ያዘጋጀናል፡፡ በሐዋርያት ሥራ ውስጥ አጋቦስ የተባለው ነቢይ ወደ ፊት
ስለሚያጋጥም ነገር የተናገረው ትንቢት የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን
ያስተናገደችበት መንገድ እንድናስተውል የተወልን ምክር አለ፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 64


2. 9. 7 ነቢይነትና የትንቢት ስጦታ
ብዙ አማኞች ነቢይነትንና የትንቢት ሥጦታን አምታተው
ይገነዘቡታል፡፡ ነቢያት ትንቢት ይናገራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ትንቢት
የተናገሩ ሁሉ ነቢያት አይደሉም፡፡ ልዩነታቸውን እንደሚገባ አለመረዳት
በቤተ ክርስቲያን የተወሳሰበ ችግር ከመፍጠሩም በላይ ሁኔታዎችን
የማመሳቀል አደጋ ማምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡ ይህ እንዳይሆን
የሚመሳሰሉበትንና የሚለያዩበትን መንገድ እንመልከት፣

ሀ) ልዩነታቸው
 የነቢይነት ቢሮ ከሚያገለግሉት ቅዱሳን ማንነት ጨርሶ የተለየ
አይደለም፣ የትንቢት ስጦታ ግን መሣሪያ ነው (1ቆሮ 12፡ 10) ስጦታው
የነብይነት ምልክት ሳይሆን የአገልግሎት መሣሪያ ነው፡፡ ነቢይ
የሚያሰኘው ነገር የላቀ የመለኮት እጅ ይጠይቃል፡፡ በ1ኛቆሮ 14፡1
ፍልጉ የተባልነው ስጦታውን እንጂ ቢሮውን አይደለም፡፡
 የነቢይነት አገልግሎት በመገለጡ እጅግ የላቀ ስለሆነ፣ ያለፈውን፣
የዛሬውንና የወደፊቱን በተለየ መንገድ ማየት መቻልን ይጠይቃል
እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ በ1ኛቆሮ 14፡1 ሁላችሁም ፈልጉት ከተባለው
ስጦታ ጋር በፍጹም ይለያል፡፡ በሌላ በኩል የትንቢት ስጦታ ከልሳን ጋር
ተወዳድሯል፡፡ ይህም መሣሪያነቱን ብቻ ያመለክታል (1ኛቆሮ 14፡5)፡፡
 ነቢይነት መሪነትን የሚያካትት ሲሆን የብሉይም ሆነ የአዲስ ኪዳን
የመጀመሪያዎቹ ነቢያት አመራር በመስጠት አገልግለዋል፡፡ በተለይ
የብሉይ ኪዳን ነቢያት የፓለቲካ አመራር ጭምር እስከ መስጠት
ያገለገሉበትን ሁኔታ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እንመለከታለን፡፡
በአዲስ ኪዳን ግን የትንቢት መልእክት የሚያመጡ ሰዎች መልእክቱን

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 65


ካስተላለፉ በኋላ መልእክታቸው እንዲመረመር ለመሪ አገልጋዮች
ወይም ለጉበኤው ሥፍራቸውን ይተዋሉ (1ቆሮ 14፡29)፡፡

ለ) ትንቢትን በሚመለከት ልብ ልንላቸው የሚገቡ እውነቶች


 ይህንን ስጦታ በብርቱ እንድንፈልግ ታዘናል (1ኛቆሮ 14፡1)
 በልሳን የተነገረው እስካልተተረጎመ ድረስ ትንቢት የተሻለ ነው
(1ኛቆሮ 14፡5)
 አማኞች መንፈስ ቅዱስን ተሞልተው ወዲያው ትንቢት
ሊናገሩ ይችላሉ (የሐዋ 19፡6)
 ስጦታው በአማኙ ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል
መተካት የለበትም (1ኛቆሮ 13፡8፣ 1ጴጥ 1፡25)
 የመልእክቱ እውነተኛነት መፈተሸ አለበት በማስፈራሪያ
መታለፍ የለበትም (ሕዝ 13፡1-9፣ 1ቆሮ 14፡29 1ተስ 5፡20)
 አጠቃቀሙን በተመለከት አማኞች ኃላፊነት እንዳለባቸው
ማወቅ አለባቸው (1ኛቆሮ 14፡32)
 ስጦታው በአገባብና በስርዓትመጠቀም አለብን እንጂ ትርምስ
መፍጠር የለብንም (1ኛቆሮ 14፡29)

የትንቢት መልእክት ወደ መልእክት አስተላላፊው እንዴት ይመጣል


 ለልብ በሚሰማ ድምጽ
 መልእክተኛ ሊያነባቸው በሚችል መልኩ የሚታይ ራእይ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 66


 የመንፈስ ቅዱስን ልዩ መገኘት አመልካች የሆነ ሁኔታ አንድ
ቃል ይሰጣቸውና በዚያ ሲጀምሩ ሌላው ይከተላል፡፡
መልእክቱም ሲያበቃም የማቆሚያ ምልክት ይሰጣቸዋል፡፡
የጸጋ አሠራር አገልጋዩንም ተገልጋዩንም የማነጽ፣ የመገንባትና
የማሳደግ የሁለትዮሽ ውጤት አለው፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 67


ምዕራፍ 3
በሮሜ 12፡3-7 የተገለጡት መንፈሳዊ ስጦተዎችና አጠቃቀማቸው

ብዙ ጊዜ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ትምህርት ሲሰጥም ሆነ


ውይይት ሲደረግ በዚህ ክፍል የተጠቀሱት እነዚህ ስጦታዎች ወይ
በቂ ትከሩት ሳይሰጣቸው ይታለፋሉ ወይም ደግሞ ዝቅተኛ ግምት
ይሰጣቸውና በአሰሳ መልክ ይዳሰሳሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን
ይህንን ሚዛን የጎደለው አደራረግ እንድንለማመድ አያደፋፍረንም
እንደውም ይኮንናል ቢባል ተገቢ አባባል ነው፡፡ ስለሆነም እነዚህን
ስጦታዎች በቅደም ተከተል ለመመልከት እንሞክራለን፡፡

3.1 የመምራትና ማስተዳደር ስጦታ (ሮሜ 12፡8፣ 1ቆሮ 12፡28)


የመምራትና የማስተዳደር ስጦታ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ
ፍላጎቶችና ግብአቶቻቸውን የማገናኘት ልዩ ጸጋ ነው፡፡ አቅጣጫ
ለማስያዝ ፣ ሥርዓት ለማስፈን የሚያስችል ልዩ ተሰጥኦ ነው፡፡
በልዩ ልዩ መንገድ የሚከሰቱ ፍላጎቶችንና ፈላጊያቸውን በአግባቡ
ለማገናኘት የሚቻልበት መንገድ ሲጠፋ በጸሎት ቤት ውስጥ
ጨኸት ይበረክታል፡፡ ይህ ጩኸት እንዲወገድ የመምራትና
የማስተዳደር ጸጋ ያላቸው ቅዱሳን ጠቀሜታ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
በእነርሱ በኩል በሚገለጽ ጸጋ ጩኸት ይቆማል፣ ትርምስ
ይወገዳል፣ መልካም ሥርዓት ይሰፍናል፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 68


መምራትና ማስተዳደር ያልሆነው
 ሰዎችን በቲፎዞና በቡድን አደራጅቶ ወገናዊነትን ማጎልበት
አይደለም፡፡
 ከመስዋእትነት ይልቅ መታየትን የሚፈልግ ሁኔታን
ማነሳሳትአይደለም
 አለመግባባትና የሃሳብ ልዩነትን በጉልበት ለመፍታት መጣር
አይደለም
መምራትና ማስተዳደር የሚለው ቃል ቀጥተኛ ትርጉም መርከብን
በትክክል ከመንዳት(መምራት) ከሚለው ስዕላዊ ሁኔታ የተወሰደ
ሃሳብን ይይዛል፡፡ ይህም በቤተ ክርስቲያን አመራር (ሽምግልና)
ለማገልገል የተሰጠን ጸጋ እንደሚያመለክት ይታመናል፡፡ ሽማግሌ
ሆነው እንዲያገለግሉ የሚጠየቁ ሰዎች ይህ ጸጋ እንዲኖራቸው
ይጠበቃል (1ኛጢሞ 5፡17፣ ሮሜ 12፡8)፡፡ በዚህ ስጦታ
ለአገልግሎት የሚለዩ በሙሉ የማያቋርጥ ትጋት፣ ያላሰለሰ ጥረት፣
እንዲሁም በማስተዋል ማቀድ ዓይነተኛ ባህሪያቸው ነው፡፡ ይህ
በመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ የተለየ ብቃት ከሰዎች ተፈጥሮአዊ ችሎታ
ጋር ተወራራሽነት ስላለው ተአምራዊነቱን በቅጽበት ለማየት
ብስለትንና ጊዜን ይጠይቃል፡፡ በዚህ ጸጋ አማካኝነት በባህሪያቸው
አብሮ መሆን ከባድ የሚሆንባቸውን ጸባየ ብዙ ሰዎች አስተሳስሮ
ለመሄድ የሚያስችል ልዩ ብቃት ይታያል፡፡ ይህንን ከጌታ የሚሰጥ
ብቃት በተአምራዊነቱ ከሌሎች ያነሰ አድርጎ መመልከት አግባብ
አይሆንም፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 69


ይህ ጸጋ እንዴት ይገለጣል
 የጸጋው አሠራር በባህሪው በቅጽበት ተግባር ላይ የሚውል
ባለመሆኑ ጸጋው በተሰጠው ሰው የሕይወት እርምጃ ውስጥ
የለት ተዕለት ጥረቱን፣ ለጌታ ሥራ የሚያደርገውን ልፋቱን
በማሳካት ይገለጻል፡፡
 ፈታኝ በሆኑና በተወሳሰቡ ሁኔታዎች ውስጥ በሚደረግ
የአመራር ጥበብ ይገለጣል፡፡
 ትክክለኛውን ነገር፣ በትክክለኛ ጊዜና ቦታ ላይ በማድረግ
ይገለጣል

3.2 እርዳታ/ አገልግሎት (1ኛቆሮ 12፡28፣ ሮሜ 12፡7፣ 1ኛጴጥ 4፡11 ኤፌ


4፡12)

ተግባራዊ የሆነውን አስፈላጊ እገዛ ለተረጂዎቹ በወቅቱ የማድረስ ጸጋ


ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እንዲህ ዓይነቱ አገልግሎት ሲኖር ብቻ ሳይሆን፣ ረጂው
ሳይኖረውም በመስዋእትነት የራስን ሙሉ ምቾት ትቶ ተረጂዎችን
ለመድረስ የሚያስችል ብቃት ማግኘት ነው፡፡ አዲስ ኪዳን በተጻፈበት
በግሪክኛው ቋንቋ ዲያቆን (διάκονος) የሚለው ቃል የሚያመለክተው
ችግር ላለበት ክፍል ፈጥኖ መድረስን የሚመለከት ሁኔታ ነው፡፡
አገልግሎት፣ ይህ ጸጋ መደረስ ያለበትን ፍላጎት በአምላክ እገዛ መድረስ
ነው፡፡ ምንም ማካካሻ (ሽልማት) ሳይጠበቁ ሌላውን ለመሽከም
የሚያስችል ከመለኮት የሚሰጥ ልዩ ትከሻ ነው፡፡ በዓይነቱ ልዩ ልዩ
ልብሰፊነትና ደግነትና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ያቀናጀ ስጦታ ነው፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 70


እርዳታ ያልሆነው
 ለመመጻደቅ የሚሰጥ ምጽዋት ወይም እርጥባን አይደለም
 ከእዩልኝ የግብዝነት ልግስና ጋር አይቆራኝም
 እርዳታው የሰጪውን ሰበራነት ወይም ጉድለቱን ለመሙላት
የሚደረግ ሙከራ አይደለም ወይም ከበደለኝነት የሚመነጨውን
ኃይማኖታዊ ወግ ለመፈጸም የሚደረግ ሙከራ አይደለም፡፡

የእርዳታ ጸጋ ጠቀሜታ
የታመሙ እንዲታወሱ፣ የተራቡ እንዲጎርሱ፣ያጡ እንዲታሰቡ፣
ብቸኞች እንዲከበቡ፣ የተራቆቱ እንዲለብሱ ያለቀሱ እንዲዳሰሱ የዚህ
ስጦታ ጠቀሜታ እጅግ የጎላ ነው፡፡ ይህንን የሚያደርጉት በችሎታ
ሳይሆን ከመንፈስ ቅዱስ በሚገኝ ስጦታ ነው፡፡ ይህንን ስጦታ በተፈጥሮ
ከሚገኝ ገራገርነት ርህሩህነት ጋር በማጣመር የጸጋውን ተአምራዊ
ተፈጥሮ ማሳነስ ተገቢ አይሆንም፡፡

የእርዳታ ጸጋ እንዴት ይታወቃል


 ለተረጂዎች ፈጥኖ በመድረስ በሚያሳዩት ትጋት
 ምንጊዜም ተረጂዎች ባሉበት ቦታ ይህ ጸጋ የተሰጣቸው ወገኖች
አሉ፡፡
 ከሚያገኙት ይልቅ ስለሚሰጡት ነገር ቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡ ምላሽ
ሳይጠበቅ የሚደረግ ልግሥናን በተግባር በማሳየቱ፣
 ያላቸውን ለማካፈል ፈጣኖች ሲሆኑ ስለ ሌላቸው ነገር ቢኖረኝ
ብለው አይጨነቁም፡፡ ችሮታቸውን በተገቢው ጊዜ በመስዋዕትነት
ያቀርባሉ፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 71


 ስለ መብዛትና ማነስ ሳይጨነቁ የሚችሉትን በማድረግ ይተጋሉ፡፡
በእነርሱ እይታና አቅም የተረጂውን ችግር የሚቀርፍ በጎነት
ይፈጽማሉ፡፡

3.3 የመምከር ጸጋ (ሮሜ 12፡8)

መምከር አማኞችን የማበረታታት የማጽናናት አገልግሎት ነው፡፡


አማኞችን ለማስጠንቀቅና ሊገጥማቸው የሚችለውን ሁኔታ በደንብ
በማሳየት አቅጣጫ መጠቆምን ይጨምራል፡፡

መምከር ያልሆነው
 መስበክ አይደለም፣ በስብከት ጊዜ በአብዛኛው ሰባኪው
ሰሚው የሚሰበከውን እውነት እንዲቀበል መገፋፋት
ይፈጸማል በምክር ጊዜ አውራው ማሳመን ሳይሆን አማራጭ
ማሳየት ነው፡፡
 ትዕዛዝ መመሪያ መስጠት አይደለም፣ በድንጋጌ የተሞላ
አይደለም ከተመካሪው ችግር ጋር ራስን ማቆራኘት ነው፡፡
 ማስተማርና ነገሮችን መተንተን አይደለም፣ የተመካሪው
ዓለም ውስጥ በመገኘት አብሮ ነገሮች ለማየት መሞከር ነው
 መገሰጽም አይደለም፣ የተሳሳተን ሰው ብርሃን በመስጠት
ለማረም ጥረት ማድረግ አይደለም፡፡ ይልቁንም ራሱን
እንዲያይ መስተዋት ሆኖ ማገልገል ነው፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 72


የመመከር ጸጋ ጠቀሜታ

መምከር ከትንቢት ስጦታ ጋር በብርቱ ይቆራኛል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ


የትንቢት ስጦታ ያላቸው ምእመናን የመምከርም ጸጋ አላቸው፡፡
መምከር ከጉሮሮ ይልቅ ለጆሮ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ የመምከር ጸጋ
የተሰጣቸው አማኞች በአብዛኛው አዳማጮች ናቸው፡፡ በተመካሪው
ዓለም ውስጥ ለአስፈላጊው ጊዜ ይቆያሉ፡፡ ከዚያም የሌላውን ስሜትና
የልብ ስብራት ይጋራሉ፡፡ ይህን ካደረጉ በኋላ ሁኔታውን የሚመጥን
ምክር ይሰጣሉ፡፡ በተጨማሪም ተመካሪው ካለበት ሁኔታ
የሚወጣበትን ብርሃን ይፈነጥቃሉ፡፡ በአብዛኛው መምከር ሰዎች ጌታ
የሚፈልግባቸውን በማድረግ እንዲጸኑ የሚገለጥ ጸጋ ነው፡፡ ተመካሪዎች
ከመካሪው በሚያገኙት ብርሃን የክርስቶስን ፈቃድ ለመፈጸም ጉልበት
ያገኛሉ፡፡ መምከር የደከመውንና የቆሰለውን እንዲበረታታ ማነሳሳት
ነው፡፡

የመምከር ጸጋ ያላቸው እንዴት ያውቃሉ


 ማንም የማይቀርባቸውን የማቅረብና የመሸከም ጸጋ
ይታይባቸዋል፤
 ተነጥሎና ተገልሎ መቆየት የሚቀናቸውን ማቀፍ ይሆንላቸዋል
 ብዙ ብቸኞችን ጓደኛ የማድረግ ልዩ ተሰጥኦ አላቸው
 ሰዎችን ለማዳመጥ ቅድሚያ ስለሚስጡ በችግረኞች ይከበባሉ
 በየትኛው ጊዜ ምክርን ለሚሹ ሰዎች አጀንዳቸው ክፍት
በመሆኑ ይለያሉ፤

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 73


3.4 የመስጠት ጸጋ (ሮሜ 12፡8)

በደግነት፣ በመስዋእትነት እና በደስታ ያላቸውን ነገር ለሚያስፈልጋቸው


ማካፈል ነው፡፡ ከእርዳታ ጋር በብዙ ይቆራኛል፡፡ እርዳታ ተረጂን
ቀዳሚ ሲያደርግ፣ መስጠት ግን የሰዎችን ፍላጎት የሚደርስ፣ የሌላውን
ሰው ሁከት ቀንሶ መረጋጋትንና ደስታ በሚያበዛ መልካምነት የሚገለጽ
ትጋት ነው፡፡

መስጠት ያልሆነው
 አባካኝነት አይደለም፣ ጥሪትን ፍላጎትን ባላገናዘበ መንገድ
መበተን አይደለም፤
 ማባበያ አይደለም፣ የሰጪውን አጀንዳ ለማስፈጸም የሚውል
ገጸ በረከት አይደለም፡፡
 የታይታ ትእይንት አይደለም፣ አድራጊውን ሳይሆን ፈጣሪን
ብቻ ለማሳየት የሚውል ድርጊት ነው እንጂ ሰዎች አንቱ
እንዲሉን የሚከናወን የእዩልኝ እንቅሰቃሴ አይደለም፡፡

የመስጠት ስጦታ ጠቀሜታ


መስጠት ለተገቢው ፍላጎት የሚደርስ ከታይታ ጽዱ የሆነ ልግስና ነው፡፡
አብዛኛውን ጊዜ በዚህ ጸጋ የተባረኩ ሰዎች በመስዋእትነት በደስታና
በታላቅ ጉጉት ያላቸው ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በሙሉ በተገቢው
ሰዓት በማድረስ ይተጋሉ፡፡ የመስጠት ጸጋ ያላቸው ሰዎች አጋጣሚውን
ፈልገው ማድረግ ያስደስታቸዋል፡፡ ፍላጎት ኖሮ የሚሰጡትን ባጡ ጊዜ
ስቃያቸው ይበዛል፡፡ የሚበዛውን ጊዜ ጸጋቸው ፍላጎት ካለበት ሁኔታ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 74


ጋር ያገናኛቸዋል፡፡ ባለ መስጠት ከመሳሳት በመስጠት መሳሳትን
ይመርጣሉ፡፡ ምንጊዜም የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ታዞ ርምጃ
ለመውሰድ አይሰንፉም፡፡ በእንዲህ ዓይነቱ ጸጋ እግዚአብሔርን
የሚያገለግሉ አማኞች ሲተርፋቸው ብቻ ሳይሆን ከጉድለታቸው እንኳን
ለመስጠት የሚያስችል ልዩ ጸጋ አላቸው፡፡ በዚያው ልክ ብዙዎች
የሰጡትን ያህል ይባረካሉ፡፡ ለመባረክ ብለው ግን አይሰጡም፡፡

የመስጠት ጸጋ እንዴት ይታወቃል

 ምንጊዜም ምላሽ ሳይጠብቁ ይሰጣሉ


 ከሚያገኙት ይልቅ ስለሚሰጡት ነገር ቅድሚያ ይሰጣሉ
 ስለ መብዛትና ማነስ ሳይጨነቁ የሚችሉትን በማድረግ
ይተጋሉ፣

3.5 ምህረት የማድረግ ሥጦታ (ሮሜ 12፡7-8)


ይህ ጸጋ ከእርዳታና ከመስጠት ጸጋ ጋር በጥብቅ ይቆራኛል፡፡ የምህረትን
ጸጋ ለየት የሚያደርገው በባሕሪው ሁለንተናዊ መሆኑ ነው፡፡ እንዲህ
ዓይነቱ ጸጋ በሌሎች የደረሰውን በራስ እንደ ደረሰ አድርጎ ያ ችግር
እስኪቃለል ደርስ ሌላውን ለማገዝ እንዲተጉ የሚያደርግ ጸጋ ነው፡፡
ሰው ጎዶሎ ሆኖ ከተገኘበት ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ እስኪላቀቅ የሚሰጥ
እንክብካቤ በመስጠት መትጋትን እውን የሚያደርግ አገልግሎት ነው፡፡
በአብዛኛው ምህረት ማድረግ ከዕርዳታና ከመስጠት ጋር ስለሚቆራኝ
በዚያ ሥር ያነሳናቸው እውነቶች ከምህረት ሥጦታም ጋር
መገናኘታቸውን እናስተውል፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 75


ምዕራፍ 4
በኤፌ 4፡7-11 የተገለጡት መንፈሳዊ ስጦታዎች

መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚያስተምረን ጌታ ኢየሱስ ወደ አባቱ


ካረገ በኋላ የእርሱ አገልግሎት በሙላት እንዲቀጥል የእርሱን አዳኝነት፣
ጌትነትና ታላቅነት የሚያውጁ ሰዎችን ለቤተ ክርስቲያን
ሰጥቷል፡፡የወንጌል ሠራተኛነት ‹‹አገልግሎት›› ከሌሎች ሙያዎች
የሚለየው ለአገልግሎት የሚለዩት ሰዎች እንዲያደርሱ የተላኩት
መልእክት የተሰጣቸው መሆናቸው ነው፡፡ ለወንጌል ጥሪ የደረሳቸው
ሰዎች መልእክተኞቸ ናቸው፡፡ ዳሩ ግን ሳይላኩ የሚሰብኩ
መልእክተኞች ወይም ሰባኪዎች ሳይሆኑ ራሳቸውን ያሰማሩ ወዶ
ዘማቾች ናቸው፡፡ ወዶ ዘማችነት ሲመች የራስን ገድል ለመተረክ
የሚተጉበት፣ ሳይመች ደግሞ ምንቸገረኝ በማለት መንጋውን ለአውሬ
የሚሰጡበት የምንደኝት ሕይወት ነው (ዮሐ 10፡12-13)፡፡ ምንደኞች
መስዋዕትነትን በሚያስከፍል ሁኔታ ውስጥ ለመንጋው በመስዋእትነት
ራሳቸውን ከመስጠት ይልቅ ለእነርሱ መትረፍ ጠቃሚ የሆነውን
የመትረፊያ አማራጮቻቸውን ይመለከታሉ፡፡
ከጌታ ኢየሱስ አነጋገርም ሆነ ከጳውሎስ መልእክት
እንደምንገነዘበው የምሥራች አብሳሪዎች መልእክት አሲዞ የሚልካቸው
ጌታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ አለበለዚያ በፈጠራ ሥራ ላይ የተሰማሩ ወሬኞች
ይባላሉ እንጂ መልእክተኞች አይባሉም፡፡ ከልተላኩ የወንጌል
መልእክተኛነት ስለማይሰምር የወንጌሉ አዋጅ ነጋሪ በዚህ የመላላክ
መስመር ውስጥ የገባ መሆኑ ከየትኛውም ጉዳይ
ይቀድማል፡፡አገልግሎት አግድምና ወደ ላይ የሆነ ገጽታ አለው፡፡
አገልግሎት ልዩ ልዩ ገጽታዎች አሉት የሚባለው በአንድ ጊዜ ሰማይንና

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 76


ምድር ያሳተፈ በመሆኑ ነው፡፡ ከሰማይ መቀበልን ለምድር ደግሞ
ማቀበልን እውን በማድረጉ አገልግሎት ሁለቱንም ነው ቢባል ማጋነን
አይሆንም ፡፡ ሁለቱንም የሚያስተሳስራቸው የአገልጋዩ ታዛዥነት ነው፡፡
አገልጋይ በላኪ ና ተቀባይ መካከል ያለ መካከለኛ ነው፡፡ ጥሪ በባሕሪው
ዓይነቱን፣ ተቀባዮቹን እንዲሁም ቦታውን የማካተት ተፈጥሮ አለው፡፡
የአገልግሎትን ዓይነትና ሥፍራውን አለማወቅ ብዥታን ይፈጥራል፡፡
አገልግሎትን በፍሬ ለመለካትም እንቅፋት ይሆናል፡፡ እንዲያገለግሉ
የተጠሩ በሙሉ ቦታውን፣ የአገልግሎታቸውን ዓይነትና የተገልጋዮቹን
ማንነት ገሐድ ያደርጋል፡፡ ሙሴ ባሮቹን፣ ሕዝቅኤል አመጸኞቹን፣
ሐዋርያት ደግሞ አይሁድና አሕዛብን ለማገልገል መጠራታቸው
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይፋ ሆኖ ተቀምጧል፡፡
አገልግሎትን ከስጦታዎች ነጥሎ ማየት አይቻልም፡፡
ቀደም ብዬ እንዳልኩት ጥሪው ዓይነቱን፣ ተገልጋዮቹንና ቦታውን ገሐድ
ያደረገ የመለኮት ግብዣ ነው፡፡ ያለ እነዚህ ስጦታዎች ጌታን
አገለግላለሁ ብሎ መነሳት ምናምንቴነት ነው፡፡ ስለሆነም አገልጋይ ጌታ
እንደጠራው ሲናገር ምን ዓይነት ጥሪ እንደተሰጠው የሚለየው
ከተሰጠው የጸጋ ስጦታ አኳያ ነው፡፡ በእነዚህ ስጦታዎች ምእመኑን
ለማነጽ እድል ያልተሰጠው አገልጋይ ተልእኮውን በጥልቀት መርምሮ
ለእንደዚህ ዓይነቱ ሁኔታ የማይበጀውን የእርሱን ሁኔታ ለማስተካከል
ተገቢውን ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ለወንጌል አገልግሎት የተሰጡን
የጸጋ ስጦታዎች መንፈሳዊ አገልግሎትን ፍሬ የሞላበት ለማድረግ
ጠቀሜታቸው አሌ አይባልም፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 77


የአገልግሎት ሰጦታዎች
ቀደም ብለን ያየናቸው ስጦታዎች አገልግሎት ለማከናወን
የሚያግዙ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ እነኚህኞቹ ግን ሰዎቹ ራሳቸው ቋሚ
ስጦታዎች ናቸው፡፡ ማንም ሰው የተለየ ጸጋ ቢሰጠውም ክርስቶስ
ያገለገለውን አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ሊተካ አይችልም፡፡ ስለሆነም
ክርስቶስ የእርሱ ሥራ ሕያው ሆኖ እንዲቀጥል ለዚህ ጉዳይ የሾማቸው
ሰዎች ለቤተ ክርስቲያን ሰጠ፡፡ እነዚህ ስጦታዎች ሰው ጸልዮ
የሚሆናቸው፣ ልሁን ብሎ መርጦ የሚያገኛቸው አይደሉም፡፡ የቤተ
ክርስቲያንን ፍላጎት የሚያውቀው ጌታ እርሱ የመረጠላቸውን ቦታ
እንዲይዙ እነዚህ ሰዎች ሰጥቷል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ድርሻዋ እነዚህ
አገልግሎቶች በቤተ ክርስቲያን እወን ሲሆኑ መለየትና ተገቢወን
የአክብሮት ቦታ መስጠት ነው፡፡ አንቅፋት እየደነቀሩ የሚቋቋሟቸው
ቢበዙም እንኳን በዚህ ጸጋ እግዚአብሔር ያስነሳቸው ሰዎች ከእርሱ
በሚመጣ ድጋፍ በታማኝነት አገልግሎታቸውን ያከናውናሉ፡፡
የአገልግሎት ስጦታዎች ሁልጊዜ ከሰዎቹ አይነጠሉም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ
የሐዋርያነት፣ የነብይነት፣ የወንጌላዊነት ስጦታ ተሰጥቶኛል እንድንል
አያደፋፍርም፡፡ በኤፌ 4፡11 እንደምንመለከተው አገልጋዮቹ ራሳቸው
ከክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡ ናቸው፡፡

4.1 ሐዋርያ (ኤፌ 4፡11)

የቃሉ ትርጉም የተላከ ማለት ሲሆን ጠቅለል ባለ መልኩ ስንመለከተው


እያንዳንዱ ክርስቲያን ወደ ዓለም ስለተላከ ሐዋርያ ነው ማለት
ይቻላል፡፡ ሚሲዮናዊ የሚለው የላቲን ቃል አቻ ፍቺ ሐዋርያ ማለት
ስለሆነ ሚሲዮናዊ ሐዋርያ ነው ማለት እንችላለን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 78


ውስጥ ሐዋርያ የሚለው ቃል ለሌሎች አገልጋዮች የዋለበት ሁኔታ
እናያለን፡፡ ይሁን እንጂ ከበጉ ሐዋርያት ጋር በቀጥታ
አያመሳስላቸውም፡፡

የበጉ ሐዋርያት ዓይነተኛ መለያዎች፣


 ሁሉም በጌታ ኢየሱስ በቀጥታ የተመረጡ ነበሩ (ማቴ 10፡1-5፣
ማር 3፡13፣ሉቃ 6፡13፣ ሮሜ 1፡1)
 የትንሳኤው ምስክር የነበሩና ከእርሱም ተልእኮን በቀጥታ የተቀበሉ
ነበሩ (የሐዋ 1፡21-26፣5፡32፣ ሉቃ1፡1-4፣ 1ኛቆሮ 9፡1-2፣ 15፡8፣ ገላ 1፡1)
 ቃሉን በሙሉ የመለኮት ውክልና መናገርና መጻፍ(2ጴጥ 3፡2፣
1ቆሮ 13፡3፣ 1ተስ 2፡13፣ 4፡15፣ 3፡6) እንደ ቃላቸው የማይሄድ
ከጉባኤው ይገለላል፡፡
 በመጪው ዓለም በአሥራ ሁለቱ ዙፋኖች ላይ የሚቀመጡት
እነዚህ ሐዋርያት ናቸው (ራዕ 21፡12-14)
 አገልግሎታቸው በድንቅና በተአምራት የተሞላ ነበር (የሐዋ 5፡12፣
2ቆሮ 12፡12) ተግባራዊ አገልግሎታቸውም ወንጌል መስበክ (ማር
16፡20፣ ሮሜ 15፡19-20፣ ሐዋ 14፡23) ማስተማርና የሐሰት ትምሀርትን
መከላከል (ሐዋ 2፡41-42፣ ቆላ 1፡28) መምራት (ሐዋ 6፡1-6፣8)
 አስገራሚ የሆነ የመስዋዕትነት የምሳሌነት ሕይወት 2ቆሮ 12፡12

የበጉ ሐዋርያት በባሕሪያቸው መሠረት ጣይ ናቸው፡፡ የአዲስ ኪዳን


መገለጥም የተላለፈው በእነርሱ አማካኝነት ነው፡፡ እነርሱ ዛሬም በዚህ
ዘመን ላለነው ክርስቲያኖች ሁሉ ሐዋርያት ናቸው፡፡ በመልእክታቸውም
ያንጹናል፡፡ በምክራቸውም የእለት ተእለት እርምጃችን ይገራል፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 79


ድኅረ ትንሳኤ ሐዋርያት አህዛብ በወንጌል እንዲደረሱ የጎላ አስተዋጽኦ
አድርገዋል፡፡ በእነዚህ አብያተክርስቲያናትም ገንቢ ሚና
ተጫውተዋል፡፡

ሐዋርያት በዘመናችን አሉ ወይ


ይህን ጥያቄ ብዙ ቅዱሳን ያነሳሉ፡፡ አንዳንዶች ይህንን ጥያቄ
አሉታዊ በሆነ ገጽታው ማስተናገድ ይቀናቸዋል፡፡ ለዚህ አቋማቸው
መደገፊያ የሚያቀርቡት ቤተ ክርስቲያን ለማነጽና ለማዘጋጀት
የሚሆነው መገለጥ ሙሉ ለሙሉ በበጉ ሐዋርያት የተላለፈ ስለሆነ ነው
ይላሉ (ኤፌ 2፡18-22፣ 3፡5፣ 4፡11)፡፡ በተቃራኒው ሐዋርያት
በዘመናችን አሉ በማለት የሚከራከሩት ደግሞ ጥቂቶች አይደሉም፡፡
እርግጥ ነው፣ ሁሉም የበጉ ሐዋርያትን በመሰለ መለኮታዊ ስልጣን
የተላኩ ሐዋርያት በዘመናችን የሉም በሚለው አጠቃላይ መደምደሚያ
ይስማማሉ፡፡ ይሁን እንጂ በአዲስ ባሕል ውስጥ ሰንጥቀው ገብተው
ወንጌል ላልደረሳቸው ሰዎች ክርስቶስን የሚያውጁ ሐዋርያት ዛሬም
አሉ በማለት አያሌ ቅዱሳን ይከራከራሉ፡፡ ከጥቂቶች በስተቀር ብዙዎች
በዚህ ስም ለመጠራት ጉጉትና መሻት ሲያድርባቸው ግን አልታየም፡፡
ቅዱሳን የሐዋርያን አገልግሎት በተመለከተ

የድኅረ ትንሳኤ ሐዋርያት ዓይነተኛ ምልክቶች

1. ተከታታይነት ያለው በድንቅና ታምር የሚገለጥ አገልግሎት


 ቀጣይነት ያለው በድንቅና በተአምር የታጀበ አገልግሎት ይህ
አገልግሎት ወቅታዊና እየሰነበተ የሚመጣ አይደለም፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 80


 በጎ ተጽእኖውም በውስን ቀበሌ ላይ ብቻ ያተኮረና የተገደበ
ሳይሆን ሰፊ ክልልን በሚሸፍን አገልግሎት የሚገለጽ ነው፡፡
 ክርስቶስ ተኮር የሆነ የወንጌል አዋጅ ዓይነተኛ መለያው ነው
(ሮሜ 15፡20፣ 2ቆሮ 10፡16)

2. በርካታ ሰዎች ለወንጌል እንዲማረኩ ያደረገ አገልግሎት


 ቀዳሚ ትኩረቱ በወንጌል ያልተደረሱ ሕዝቦችን ወንጌልን
ማድረስና ሰዎች ለክርስቶስ መማረክ በዚህ ጥረትም ስኬታማ
ነው፡፡ (የሐዋ 2፡43፣ 4፡30፣ 5፡12፣ 14፡3፣ ዕበ 2፡2-4)
 ክርስቶስን የምታውጅ ቤተ ክርስቲያን ተክሎ የሚመሯትን
መሪዎች ወደ ብስለት አምጥቶ መሰየም
 ተጽእኖው በአገራዊነት ብቻ የተገደበ ሳይሆን ክፍለ አህጉራዊ
አድማስ ያለው ነው

3. አስገራሚነትን የተላበሰ ምሳሌያዊ ሕይወት


 ከቃል ለመግለጫ በላይ የሆነ የመስዋእትነት ሕይወት
2ቆሮ 11፡18-28፣ ፊሊጵ 2፡30
4. እግዚአብሔር መሰል መንፈሳዊ ርምጃ (Moral)
 ለሚመለከታቸው በሙሉ ገሐድ የሆነ ክርስቶሳዊ ባሕሪ (2ቆሮ
12፡12)
ውሸተኞች ሐዋርያት
 ለሌላው ከመትረፍ ይልቅ በመለፈፍ ይታወቃሉ (ራዕ 2፡2)
 ከፍሬያማነት ይልቅ ግብዝነት የቀደመበት ሕይወት የሚያሳይ
አገልግሎት ነው (2ቆሮ 11፡13)

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 81


ከታሪካዊ ስነ መለኮት አኳያ ቤተ ክርስቲያን ከበጉ ሐዋርያት በኋላ
በእነርሱ ሞት ሌሎች እንደተተኩ የሚናገር ማስረጃ አናይም፡፡
ቤተክርስቲያን በጨለማው ዘመን በተዋጠች ጊዜ ሁሉም የአገልግሎት
ቢሮዎች የተዳፈኑበት ጊዜ ነበር፡፡ በዘመነ ተሃድሶ ለእግዚአብሔር ቃል
ስልጣን ተገቢው ቦታ ከተሰጠ በኋላ ሁኔታዎች እያገገሙ መጡ፡፡ ጆን
ዌስሌ ‹‹ኃጢአትን የሚፈሩ ፍላጎታቸው እግዚአብሔር ብቻ የሆነ 11
ሰዎች ስጡኝ ዓለምን በለውጥ ማእበል እንንጣታለን ሲል ተናገረ፡፡››
ይህ ሰው ለ 43 ዓመታት ያለማቋረጥ በቀን 2 ሰዓት ሰብኮ ነበር፡፡
በምድር ዙሪያ በፈረስ ጀርባ 225000 ማይሎች ተጉዞ ከመቶ ሚሊዮን
በላይ ለሚደርሱ ሰዎች ወንጌል ሰብኳል፡፡ ይሁን እንጂ ሐዋር ያ በሉኝ
ሲል አልተሰማም፡፡ ወች መኒ በብዙ የመስዋዕትነት ሕይወት ኖሮ ታላቅ
ምሳሌነት ትቶልን አልፏል፡፡ ይሁን እንጂ ድኅረ ትንሳኤ ሐዋርያ ነኝ
ለማለት አልዳዳውም፡፡ ዎች መኒ ሚሲዮናውያን የሚባሉ ከ200 በላይ
መልእክተኞች በቻይና አስማርቶ ቻይና አቀፍ የወንጌል አገልግሎት
ሰጥቷል፡፡ የሚደንቅ የመስዋእትነትን ኑሮ ስለ ወንጌል ኖሯል፡፡ የዚህ
ተቃራኒ ኑሮ እየኖሩ፣ ከተማ ውስጥ በተንጣለለ ቪላ እየተንፈላሰሱ፣
ከአንዱ ቦታ አፍሰው ሌላ ቦታ ስለ ከመሩ ሐዋርያ በሉን ማለት
የሚቀናቸው ወገኖች ትልቅ ሚዛን ይጎድላቸዋል፡፡ ከላይ እንደገለጽነው
ሐዋርያ ሁሉ በሁሉ ነው፡፡ በውስጡ የሚሠራው ኃይልም ሰሞናዊ የሆነ
የመለኮት ጣትን ሳይሆን ዘመናትን ዘልቆ የሚሻገር በጎ ተጽእኖ ከቀበሌ፣
ከከተማ፣ ከአገርና ከክፍለ አህጉር አልፎ ዓለም አቀፍ ተጽእኖ
የሚያመጣ ጉልበት ያለው አገልግሎት እውን የሚያደርግ ነው፡፡
የሐዋርያው አገልግሎት ፈረጀ ብዙ ነው፡፡ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 82


መትከል፣ ማደራጀት፣ ማሳደግና ለተልእኮ ማብቃት በአገልጋዩ ሕይወት
ይፋ የሆነበት ልምምድ ተግባራዊ ነው፡፡
በታሪክ ውስጥ በውርስ የሚተላለፍን ሐዋርያዊ ተልእኮን
የሚቀበሉ አብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያ ከአንድ አጥቢያ በላይ
ለሚቆጣጠር ማንነት ማደል ይቀናቸዋል፡፡ የተሃድሶ አማኞች ከቃሉ
ባለስልጣንነት ያፈነገጠውን ልምምድ አያደፋፍሩም፡፡ የቃሉን
ማእከላዊነት ገሸሽ ያደረገው አመለካከትና ልምምድ ለቤተ ክርስቲያን
ጤናማነት አስጊ ነው፡፡ በእኛ አገር ሙሉ ጊዜያቸውን ለወንጌል
አገልግሎት የሰጡትን አገልጋዮች ወንጌላዊ በሚለው መጠሪያ ለዘመናት
ስንሰይም ቆይተናል፡፡ ባለፉት ሃያ ዓመታት ሰዎችን በአገልግሎት
ስጦታቸው መሰየም እየተለማመድን መጥተናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን
በመትከል የፋና ወጊነቱን ተልእኮ ለተወጡ ሰዎች ስያሜው ቢሰጥ ቅር
አያሰኝም፡፡ በቅርብ ጊዜ ጉዳዩን ከአገልግሎት ስጦታነት ይልቅ ወደ
ሹመትነት እየቀየሩ የመሄድ አዝማሚያዎች እየታዩ በመምጣታቸው
ጉዳዩ በብዙ ጥንቃቄ መታየት ያለበት ይመስለኛል፡፡ እርግጥ ነው
ሐዋርያ የሚለውን ስያሜ ሚሲዮናዊ በሚል አቻ ፍቺው መጠቀም
ስህተትነት የለውም፡፡ ዳሩ ግን እንደ በጉ ሐዋርያት ዓይነት ቦታ ፈልጎ
ከተጠቀሙበት ግን አግባብ አይደለም እንደውም መናፍቅ ወደ መሆን
የሚወስደንን በር ይከፍታል፡፡

4.2 ነቢይነት

ነቢይነት የቃሉ ትርጉም በመንፈስ እየተነዳ የሚናገር ማለት ነው፡፡


ነቢይነት መስበክን ቢያጠቃልልም እጅግ የላቀ ነው፡፡ ነቢይ ያለ አንዳች
ዝግጅት እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚያመለክተውን በቀጥታ

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 83


ያስተላልፋል (ኤፌ 3፡5)፡፡ የትንቢት ስጦታ አጥቢያዊ ሲሆን የነቢይነት
ስጦታ በአብዛኛው ዓለማአቀፋዊ ይዘት አለው፡፡ የብሉይ ኪዳን ነቢያት
ይተነብያሉ፣ ይመራሉ፡፡ በአዲስ ኪዳን የትንቢት መልእክት የሚያመጡ
አገልጋዮች መልእክት አቅርበው መልእክቱ እንዲመረመር ለጉባኤው
ወይም ለሚመለከተው ክፍል ይተዋሉ፡፡ አዲስ ኪዳን ምእመናንን
ለማነጽ አማኞች ሁሉ የትንቢት ስጦታን (ሮሜ 12፡6፣ 1ቆሮ 11፡4-5፣
12፡10፣ 13፡2፣ 8-9፣ 14፡1-6፣ 20-33፣37፣ 1ተስ 5፡20
የሚለማመዱበትን ሁኔታ ያደፋፍራል፡፡
ልክ እንደ ሐዋርያ ይህም ስጦታ የማይደገም መሠረት ጣይ ስጦታ
ስለሆነ ነቢያት በዘመናችን የሉም ብለው የሚከራከሩ የመጽሐፍ ቅዱስ
ተማሪዎች አሉ (ኤፌ 2፡20፣ኤፌ 3፡4-5)፡፡ መሠረት የመጣሉም ሥራ
በመጠናቀቁ እንደዚህ ዓይነት ነቢያት ዛሬም የሉም፡፡ ይሁን እንጂ
በመልእክታቸው ከአንድ አገር የሚዘል ተሰሚነት ያላቸው ታላላቅ
አገልጋዮች ዛሬም ሊኖሩ ይችላሉ የሚሉ በሌላኛው ጽንፍ አሉ፡፡ ቤተ
ክርስቲያንን በነቢይነት የሚያገለግሉ ቅዱሳን ሊኖሩ መቻላቸው እንደ
አማራጭ ሊታይ ይችላል፡፡ እገሌ የሚባል ሰው ግን እስካአሁን
አልታየም፡፡ ቃል የሚያካፍሉ ሁሉ ሰባኪ እንደማይባሉ፣ የሚመስክሩም
ሁሉ ወንጌላዊ እንዳይደሉ የትንቢት መልእክት የሚያመጡ ነቢያት ብሎ
መጥራት ተገቢ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ በእኛ እይታ ውስጥ ስላልታዩ
ሙሉ ለሙሉ የሉም ብሎ መደምደም ሚዛን ይጎድለዋል የሚሉ
ብዙዎች ናቸው፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 84


4.3 ወንጌላዊነት

ወንጌላዊነት የቃሉ ትርጉም መልካሙን የምሥራ አብሣሪ ማለት ነው፡፡


በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከሁሉም አገልግሎት በተሻለ ግንዛቤ ያለን
በዚህኛው አገልግሎት ላይ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ለብዙዎቻችን
የወንጌላዊ አገልግሎት በቤተ ክርስቲያን ያለው ቦታና የአገልግሎት
ድርሻው ጥርት ብሎ አይታይም፡፡ ወንጌላዊ የሐዋርያውን ወይም ደግሞ
የእረኛውን ሥራ ሊሠራ ጨርሶ አይችልም፡፡ ለዚህ ግልጽ የሆነው
ምሳሌ የሚሆነን ፊሊጶስ ነው፡፡ በሐዋ 8፡1- በሰማርያ ወንጌል በሰበከ
ጊዜ ብዙዎች የሰበከውን ቃል አመኑ፡፡ አገልግሎቱን የሚያጸና ብዙ
ድንቅና ተአምራት ታየ፡፡ ሆኖም ፊሊጶስ በስብከቱ የዳኑትን ነፍሳት
ለሐዋርያት እንክብካቤ ሰጥቶ ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የወንጌሉን
መልእክት ለማቅረብ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ተቀብሎ ሄደ፡፡ ከዚህ
እንደምንረዳው ወንጌላዊ ሒያጅ እንጂ ተቀማጭ አለመሆኑን ነው፡፡
ጥሪውን ያላገናዘበ የወንጌል መልእክተኛ ችግር ይገጥመዋል፡፡
ወንጌላዊ በአንድ ሥፍራ የጀመረው አገልግሎት ለየት ባለ ሁኔታ
ሲባረክ በተቀበሉትና እርሱን በባረኩት ሰዎች መካከል ሰፊ ጊዜውን
ሰጥቶ ለመኖር ይፈተናል፡፡ ይህንን የምቾት ፈተና ማለፍ ከተሳነው
የሚከተሉት ችግሮች ይፈጠራሉ፡፡

 ወንጌላዊ ጸጋውን ይዞ በአንድ ሥፍራ ሲቀመጥ ሌሎች ወንጌል


ጨርሶ ያልሰሙ ህዝቦች ሊተላለፍላቸው የሚገባው የሕይወት ቃል
ይቀርባቸዋል፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 85


 ሒያጅ የነበረው የወንጌላዊ የአገልግሎት ተፈጥሮ በሌላው አገልጋይ
ሥራ ላይ እንቅፋት ይፈጥራል፡፡ ሥፍራውን ለሌሎች መልቀቅ ሲገባው
ያለቦታው ተቀምጦ ስለሚያጣብብ ችግር ይፈጠራል፡፡ ምእመናንም
ከእርሱ የሚጠብቁትን መስጠት ስለማይሆንለት እሮሮና ችግር ተፈጥሮ
አገልግሎቱ ችግር ውስጥ ይወድቃል፡፡
ባጠቃላይ ስንመለከት ወንጌላዊ የክርስቶስን ፍቅር፣
የማዳኑን እውነት በማወጅ ይህችን ጨለማ ዓለም ለመድረስ የተዘረጋ
የክርስቶስ ክንድ ነው፡፡ የእርሱ አገልግሎት ወንጌል ሰብኮ ነፍሳትን ወደ
አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እንዲጨመሩ ማገዝ ነው፡፡ ከወንጌላዊው
የወንጌል አዋጅ የተነሳ ሙታን ካንቀላፉበት የጭለማው መንደር በታላቅ
ርሃብ ይነቃሉ፡፡ ርሃባቸውን የሚያስታገስ መንፈሳዊ ማእድ የማዘጋጀት
ጸጋ የተሰጠው ለመጋቢው ነው፡፡ ወንጌላዊው እነዚህ
ርሃበተኞች በአስቸኳይ ለመጋቢው ማስተላለፍ አለበት፡፡

4.4 እረኝነት (መጋቢነት)


እረኝነት መጋቢነት የሚለው ቃል የተወሰደው ፓዮመን ከሚለው
የግሪክ ቃል ሲሆን ፍቺውም የእግዚአብሔር መንጋ የሚመግብና
የሚንከባከብ ማለት ነው፡፡ አገልግሎቱ በአብዛኛው ከሽማግሌ ጋር
ሲመሳሰል ልዩነቱ ግን ሽማግሌ በተወሰኑ የመጸሐፍ ቅዱስ መመዘኛዎች
ሲመረጥ (1ኛጢሞ 3፡1፣ ቲቶ 1፡5-9) እረኛው (መጋቢው) ግን
የክርስቶስን አካል ብልት እንዲያገለግል የሚሰጥ ስጦታ ነው፡፡ እረኝነት
ማእረግ ሳይሆን አገልግሎት ነው፡፡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት የቤተ
ክርስቲያን ሠራተኛ እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እረኛ ለማግኘት
አልታደሉም፡፡ በፋብሪካ ሞዴል ትላልቅ ቤተ ክርስቲያናትን ውስጥ
የሚሠሩ መደበኛ የቅጥር እረኞች ቢኖሩም መልካም እረኞች ግን

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 86


አይደሉም፡፡ መልካም እረኛ እንደ ቃሉ መንጋውን በመጠበቅ ከእረኞች
አለቃ ፈቃድ በታች በታማኝነት የሚኖር ነው፡፡ መጠበቅ የሚለው ቃል
ከእረኝነት አኳያ ፈረጀ ብዙ ነው፡፡ በውስጡ አራት አገልግሎቶች አሉ፡፡
እነርሱም መንከባከብ፣ አቅጣጫን ማመልከት፣ መምራት፣ ናቸው፡፡
መንከባከብ (Caring)፣ የደከሙትን ማበረታት ተስፋቸው እንዲታደስ
ማበርታት፣ አማኙ ያለበትን ሁኔታ ያገናዘበ ምግብ መመብን፣
ታማሚዎችን እንዲፈወሱ ምቹ ሁኔታ መፍጠርን፣ የተሰበሩ መጠገንን
ይመለከታለ
አቅጣጫን ማመልከት (GUIDING)፣ ምእመናን የሚያተኩሩበትን
ሁነኛ ቦታ ማመላከትን፣ የጠፋውን ፈልጎ ማግኘትን እንዲሁም
የባዘነውን በትክክለኛው መስመር ውስጥ እንዲገባ የመደገፍን
አገልግሎት ይመለከታል፡፡

3. መምራት(LEADING )፣ ከአብሮ ተጓዥ ቀደም ብሎ በዓላማ ወደ


ታቀደ ግብ ምእመናንን ማስከተት ነው፡፡
እረኛ ፊት ፊት እየሄደ እንዲከተሉት ምሳሌነትን የሚያሳይ እንጂ የሚነዳ
አይደለም፡፡ ሰዎቹን የሚወስድበት ቦታ በውል ተረድቶ በቃሉ
ምእመናን አቋም እንዲይዙ ያደርጋል፡፡ አካባቢውንም ሲለቅ ለጸጋው
ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ ይላል፡፡
4. መከላከል (PROTECTING) ከአጥቂ መጋረድን ወይም ጥቃት
ፈጻሚን እንዲመክቱ ምእመናንን ማዘጋጅትን ይመለከታል፡፡ እረኛ
መንጋውን ከበላተኛ መጠበቅ በጥበቃ ሥራው ላይ የሚከሰት ቀዳሚ
ተልእኮው ነው፡፡ አያሌ የሃሰት ትምህርቶች ትኩረት መንጋን ማጥቃት
ነው፡፡ እረኛ አደጋን ቀድሞ ያሸታል ከዚያም ተገቢውን እርምጃ
ይወስዳል፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 87


4.5 አስተማሪነት
አስተማሪ በግሪኩ አጠራር ዲዳሰቃሎስ ማለት ሲሆን ፍቺው መመሪያ
ሰጪ ማለት ነው፡፡ አስተማሪ ሊደረጉ የሚገባቸውን ነገሮች ግልጥልጥ
አድርጎ የሚያስረዳ ነው፡፡ መጋቢነትና አስተማሪነት ጥብቅና ጥልቅ
ግንኙነት አላቸው፡፡ እንደውም አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ
አስተማሪዎች አንድ አድርገው ይረዷቸዋል፡፡ ሆኖም እንደ መጽሐፍ
ቅዱስ አገላለጥ አንድ አይደሉም፡፡ ቢሆንም በመደጋገፍና በመያያዝ
በአጥቢያ ያለውን የእረኝነት ሥራ ያከናውናሉ፡፡ ምእመናን
በእግዚአብሔር እውነት ታንጸው እንዲያድጉ የእግዚአብሔርን ቃል
በጥልቀት ያስተምራሉ፡፡ አስተማሪነት መንፈሳዊ እውነትን የመግለጥ
የተለየ ተሰጥኦ ነው፡፡ አስተማሪ ለቃሉ ዘብ መቆም ዓይነተኛ ባሕሪው
በመሆኑ ከሸቃጮች፣ አታላዮችን እንዲሁም ከአሳቾች ጋር በሚደረግ
ትንንቅ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ
አስተማሪ ልዩ ልዩ ጥቃቶች ይደርስበታል፡፡ ይሁን እንጂ የገባቸው
እውነት ስለሚደግፋቸው ጌታም የተለየ ጸጋውን
ስለሚያበዛላቸው በጽናት ይቆማሉ፡፡

የአገልግሎት ስጦታዎች ዓላማ


 የክርስቶስን ሥራ ከእውነተኛ ግቡ ማድረስ
 ቅዱሳን ፍጹማንና ምሉአን ሆነው በሁሉም ነገር ብቃት
ያላቸውን ሆነው እንዲገኙ
 የክርስቶስ ህንጻ፣ የአካል ብልቶች እርሰ በርሳቸው
ተቀናጅተው ተያይዘው ፍሬ ባለው ሁኔታ እንዲያድጉ መርዳት
ከዓላማዎቹ አንዱ ነው፡፡

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 88


ማጠቃለያ
እንደሚታወቀው በውትድርና ሙያ ለሐገር መከታ የሆነው ሠራዊት
ከመዋቀሩ በፊት ሠራዊቱን የሚመሩ መኮንኖች አስቀድመው
ይሠየማሉ፡፡ የእነርሱ መሰየምና መሰልጠን ተዋጊ፣ ጠንካራ ተፋላሚ
ሠራዊት በመመልመል በሁሉም መልኩ ብቁ የሆነ ጦር ለመፍጠር
ነው፡፡ ልክ እንዲሁ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን የሚያንጹና ቤተ
ክርስቲያንን በዚህ ሁኔታ የሚያዘጋጁ፣ የሚያስታጥቁ ሰዎች ለቤተ
ክርስቲያን ሰጥቷል ከእነርሱም ትጋት የተነሳ በየአጥቢያው ያሉ
ምእመናን እርስ በርስ ለመተናነጽ ይበቃሉ፡፡ ሁሉም አማኞች
የአገልግሎት ስጦታ ባይኖራቸውም ሁሉም ግን በክርስቶስ አካል ውስጥ
አንድ አንድ ብልት ሆነው በተቀመጡበት ሥፍራ ቤተ
ክርስቲያን(አካሏን ) በመገንባትና በማሳመር ሥራ ላይ የየበኩላቸውን
ግልጋሎት የሚያበረክቱበት የሥራ ድርሻ አላቸው፡፡ ስለሆነም ከትንሽ
እስከ ትልቅ በተገቢው መንገድ ሠርተን የእግዚአብሔር ሥራ መቀናት
የበኩላችንን መወጣት እንድንችል ጌታ ይርዳን፡፡

ምዕራፍ 1
የውይይት ጥያቄዎች
1. በዚህ ክፍል ከተጠቀሱት ሌላ ከማንነቱ ጋር በሚያያዝ
መንገድ መንፈስ ቅዱስ ያደርጋቸዋል የሚባሉት ነገሮች ምን
ምን ናቸው?
2. በእናንተ እይታ የተፈጥሮአዊና የመንፈሳዊ ስጦታ ልዩነት
መመሳል ምኑ ላይ ነው?

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 89


3. መንፈሳዊ ስጦታዎችን ከአንዱ የስላሴ አካል ጋር ብቻ ማያያዝ
አደጋው ምን ላይ ነው?
4. መንፈሳዊ ስጦታዎች አብቅቶላቸዋል የሚሉ ክፍሎች
ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሻችን ምንድነው?
5. መንፈሳዊ ስጦታዎችን በአግባቡ ለመረዳትና ለመለማመድ
አተረጓጎም ወሳኝ የሚሆነው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 2
የውይይት ጥያቄ
የመገለጥ ስጦታዎች
1. የመገለጥ ስጦታዎችን በዚሕ ሥም እንዲጠሩ ያደረጋቸው ነገር
ምንድነው? ትክክለኛ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?
2. በዕውቀት ቃልና በጥበብ ቃል መካከል ያለው ልዩነትና
ተመሳሳይነት ምንድነው?
3. በእውቀት ቃል አማካኝነት ለሚመጡ ፈውሶች የሩቅ ጊዜ
ቀጠሮ አያሻቸውም ሲባል ምን ማለት ነው? ሰዎች
ባልተፈወሱ ጊዜ ስላላመናችሁ ነው የሚባለውን ማብራሪያ
እንዴት ታዩታላችሁ?
4. መናፍስትን መለየት የአጋንንት ዓለም ከመረዳት ጋር ብቻ
ማያያዝ ምን ዓይነት አደጋ አለው?
5. እነዚህ ጸጋዎች በቤተ ክርስቲያን በሙላት እንዲታዩ ምን
መደረግ አለበት?

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 90


የኃይል ስጦታዎች
1. ሰዎች ለመፈወሳቸው ሁልጊዜ ማመን አለባቸው? ሳያምኑ
የሚፈወሱ ካሉ ለመፈወስ በግድ ማመን የሚያስፈልግበት
ምክንያት ምንድነው?
2. እነዚህ ስጦታዎችን ለብቻቸው የኃይል እንዲባሉ ያደረጋቸው
ምንድነው?
3. ከተፈወሱ በኋላ ሰዎች ፈውሳቸውን ሊያጡ ይችላሉን?
ለምን?
4. በኃይል ስጦዎች በኩልና በእውቀት ቃል በኩል የሚመጡ
ፈውሶች ልዩነታቸው ምንድነው?
5. የተአምራት ጸጋ በዘመናችን ብርቅ የሆነው ለምንድነው?
የምንሰማቸው ፈውሶች የውስጥ ደዌ ላይ ያነጣጠሩበት
ምክንያት ምንድነው?

የማነቃቂያ ስጦታዎች
1. ልሣን አብዛኛው የሚለማመደው ሆኖ ሌሎች ጸጋ በብዛት
አለመታየታቸው ችግሩ ከምን የመነጨ ነው?
2. ቀጥታ ትንቢት መናገርና ልሣን ተርጉሞ መልእክት ማምጣት
ልዩነታቸው ምንድነው?
3. ትንቢትና እውቀት ለወደፊት መልእክት ሲተላለፍባቸው
አንዱን ካንዱ ለመለየት የሚቻለው እንዴት ነው?
4. ትንቢት ከወደፊት ጋር የተያያዘው ከመናገር ጋር የተሳሰረ ነው
የሚለውን አባባል እንዴት ታዩታላችሁ?

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 91


ምዕራፍ 3
የውይይት ጥያቄዎች
1. መምራትና ማስተዳደርን እንደ ሌሎቹ የጸጋ ስጦታዎች
አለማየት ችግሩ ምኑ ላይ ነው?
2. እርዳታ/አገልግሎት ከጸጋ ስጦታዎች እኩል ያልተተኮረባቸው
ለምንድነው?
3. በመምከር፣ በስብከትና በትንቢት መካከል ያለው ልዩነት
ግንኙነት ምንድነው?
4. መስጠትና አባካኝነት የሚመሳሰሉትና የሚለያዩት ምን ላይ
ነው? ሰጪን አባካኝ ለሚሉ ምን መልስ አለን?
5. በፕሮቴስታንቱ መካከል ምህረት የማድረግ አገልግሎት
በስፋት የማይታየው ለምንድነው?

ምዕራፍ 4
የውይይት ጥያቄዎች
1. ሐዋርያት በዘመናችን አሉ? ካሉስ የት? መለያቸውስ ምንድነው?
2. ነቢያት በዘመናችን አሉ? ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ መገለጫቸው አኳያ
ከቤተ ክርስቲያን አድማስ ያለፈ ተጽእኖ አላቸው ? ካሉስ የት?
3. በወንጌላዊነት የረጅም ጊዜ አገልግሎት ወደ መጋቢነት የማደጉ
ልምምድ አደጋው ምንድነው? ከአንዱ ጸጋ ወደ ሌላው ይታደጋል?
4. በእረኛውና በአስተማሪው ጸጋ መካከል ያለው ልዩነት
ምንድነውከአንዱ ጸጋ ወደ ሌላው ይታደጋል? አስተማሪ እረኛ
ሊሆን ይችላል? እረኛስ አስተማሪ?

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 92


5. የአገልግሎት ጥሪ እድሜ ልክ ወይስ በጊዜ የተገደበ? አገልግሎት
የማዕረግ ቦታ (ፓዚሽን) ሳይሆን ተልእኮ መከወኛ (ፈንክሽን)
የሚለውን አባባል እንዴት ትረዱታላችሁ?

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 93


ዋቤ መጻሕፍት Bibliography
Cole, Graham A. He Who Gives Life: The Doctrine Of The
Holy Spirit. Wheaton: Crossway, 2007.
David Ewert. The Holy Spirit in the New Testament.
Scottdale, Pa.: Herald, 1983.
Erickson, Millard J. Christian Theology. Grand Rapids:
Baker Book House, 1985
Fee, Gordon D. God’s empowering presence the Holy Spirit
in the letters of Paul. Massachusetts: Hendrick son
publisher, Inc, 1994..
Green, Michael I Believe in the Holy Spirit. Grand Rapids:
William B. EerdmansCompany, 1975.
Grudem, Wayne Systematic Theology. Grand Rapids:
Zondervan Publishing House, 1994.
Horton, Stainly M. What the Bible Says About the Holy
Spirit Springfield Missouri: Gospel Publishing House,
1995.
Johnson, Alan F. & Webber Robert E. What Christians
Believe. Grand Rapids: Zondervan Publishing House,
1989.
McGrath, Alister E. Christian Theology An Introduction.
Oxford: Blackwell, 1994.
Packer, J.I. Concise Theology: A Guide to Historic Christian
Beliefs. Wheaton: Tyndale, 1993.

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 94


________Keep in Step with The Spirit New Jersey: Fleming H.
Revel Company, 1984.
Pinnock, Clark H. Flame of Love. A Theology of the Holy
Sprit. Downers grove, Illinois: IVP, 1996.
Pinnock, Clark. The Scripture Principle. San Fransisco:
Harper, 1984.
Ryrie, Charles C. Basic Theology. Illinois: Victor Books,
1986.
Schreck, Allan Hearts of flame. The Spirit at the heart of
christian life today Michigan: Servant Publications, 1995.
Smith, Billy B. The Holy Spirit and His gifts Texas: Billy B.
smith ministiesPublications, 1991.
Spurgon, charles. Holy Spirit power. New kensington:
whitaker house, 1996.
Stott, John R.W. Baptism and fullness. The work of the Holy
Spirit. Illinois: IVP, 1977.
Sumkall, Lester. The gifts and ministries of the Holy Spirit.
New Kensington: Whitaker house, 1993
Swindoli, Charles R. Flying closer to the flame Dallas: Word
Publishing, 1993
Turner, Max The Holy Spirit and Spiritual Gifts then and
Now. Great Britain: Bidd Ltd. 1996
William Fitch. The Ministry of the Holy Spirit. Grand
Rapids: Zondervan, 1974.

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 95


William, Rodman J. Renewal Theology (Systematic Theology
from a Charismatic Perspective). Grand Rapids:
Zondervan Publishing House, 1996.
መለሰ ወጉ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ማወቅና በአግባቡ መጠቀም
ዮርክ፡ የኢትዮጵያውያን አገልግሎት፣ 2000.

ፓ/ር ኃይሉ ቸርነት( ዶ/ር) ሎስ አንጀለስ ሴፕቴምበር 2013 Page 96

You might also like