You are on page 1of 29

Contents

1. ማኔጅመንት/አመራር ትርጉም................................................................................................................................2
2. ክርስቲያን ማኔጅመንት/አመራር.........................................................................................................................2
2.1 የቤተ ክርስቲያን አመራር አላማው.................................................................................................................2
2.2 የአመራር ነገረ ምክንያት.................................................................................................................................3
2.3 የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን መዋቅርና መሪነት ንድፍ...................................................................................3
2.4 መጥፎ የመሪነት ልምምዶች..........................................................................................................................4
3. አስተዳደር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?.........................................................................................................................4
3.1 የቤተ ክርስቲያን አመራር ለምን አስፈለገ.......................................................................................................4
3.2 ማኔጅመንት/አመራር እና መሪነት...................................................................................................................5
4. የማኔጅመንት/አመራር ደረጃዎች............................................................................................................................5
4.1 የማኔጅመንት ክህሎት....................................................................................................................................6
4.2 የማናጀር/አመራር ሚናዎች............................................................................................................................6
4.3 የማኔጅመንት/አመራር ተግባራት....................................................................................................................7
4.4 የእቅድ አይነቶች.............................................................................................................................................8
4.5 የእቅድ መርሆች.............................................................................................................................................8
4.6 ስትራቴጂያዊ/ስልታዊ/ እቅድ:-.......................................................................................................................8
4.7 ማደራጀት....................................................................................................................................................10
4.8 ስታፊንግ......................................................................................................................................................12
4.9 መቆጣጠር....................................................................................................................................................13
5. የግጭት ማጅመንት/ conflict management/..........................................................................................................13
6. የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር...................................................................................................................................15
6.1 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አስተዳደር ምን ይላል...................................................................................................15
7. የቤተ ክርስቲያን ዲስፕሊን/ Church Discipline....................................................................................................16
7.1 ቤተ ክርስቲያን ዲስፕሊንን መተግበር ያለባት ለምንድነው...........................................................................16
8. በጀት ዝግጅት........................................................................................................................................................16
8.1 የበጀት እቅድ አላማው.................................................................................................................................17
8.2 የበጀት አዘገጃጀት ሂደቶች............................................................................................................................17
8.3 የበጀት አዘገጃጀት መርሆች..........................................................................................................................17

የቤተ ክርስቲያን አመራር

1
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
በቤተክርስቲያን ውስጥ ይሁን ከዛን ውጪ ባሉ ተቋማት የብቁ አመራር አለመኖር የሚፈጥረው ችግር በጣም ሰፊ ነው፡፡

ይህም ኃላፊነትን ካለመወጣት፣አትኩሮት ያለመስጠት እና ኃላፊነትን የመወጣት አቅም ወይም ክህሎት ችግር ነው፡፡ ቤተ

ክርስቲያን በክርስቶስ ወደ ታየላት መልክ እንድትደርስ ከተፈለገ የእግዚአብሔርን ቃል መሠረት ያደረገ መልካም አመራር

ያስፈልጋታል፡፡

ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን በተጻፈበት ቁንቋ በግሪኩ ኤክሌሲያ የሚለውን ይጠቀማል፡፡ ትርጉሙ

ተጠርተው የወጡ ወይንም ጌባኤ የሚለውን ሃሳብ ይይዛል፡፡ ሐዋ 7፡38

መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ ትርጉሙን ስንመለከት የአማኞች ህብረት ወይንም ጉባኤ በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ

የተመሰረተች ክርስቶስ ራስ የሆናት እርሷም አካል እና ሙላቱ የሆነች ናት፡፡ ኤፌ 1፡22-23፣1 ቆሮ 1፡2፣ገላ 1፡13

 ቤተ ክርስቲያን መቼ ተጀመረች! በዚህ ዙሪያ ያሉትን አመለካከቶች በጽሑፍ ሠርታችሁ አስገቡ

1. ማኔጅመንት/አመራር ትርጉም

ሰዎችን ለመምራት ስጦታ የተሰጣቸውና በሰዎች የሚታመኑ ሰዎች የሚሰሩት ክንውን ነው፡፡

ማኔጅመንት ሂደት ሲሆን ማቀድ፣ማደራጀት፣ማበረታታት፣መምራትና መቆጣጠርን የድርጅት

ንብረትን በመጠቀም ወደ ተፈለገው ግብ ለመድረስ የሚደረግ ሂደትን የሚቃኝ ነው፡፡

ማናጀር ማለት የአንድ ድርጅት/ቤተ ክርስቲያንን ለመምራትና ውሳኔ ለመስጠት ስልጣን የተሰጠው ሆኖ

የተቋሙን ንብረትና ሃብት በመጠቀም ወደ ታሰበለት አላማና ግብ ለማድረስ የሚሰራ ወይንም ሃላፍትና

የተሰጠው ግለሰብ ነው፡፡

የሰው ሃይልን ተጠቅሞ ስራን ማከናወን ወይንም ማቀላጠፍ ነው፡፡ ይህ ትርጉም ከሶስት ነገሮች

ይይዛል፡፡

 የምጣኔ ሃብትን

ሃብትን በአግባቡ ከማስተዳደር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ያለን ሃብት ውስን ነው ነገር ግን የሰው ልጅ

ፍላት ደግሞ ገደብ የለሽ ነው ስለሆነም ሁለቱን ያጣጣመ ምጣኔ


2
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
 የስልጣን ስርዓት/ዘዴ

የሰው ልጅ የሚመራበት እና ሰዎችን ተጠቅመን ስራዎችን ለማከናወን ሰውን የምንይዘበት፣

የምንመራበት ዘዴ ወሳኝ ነው፡፡

 የእውቀት ምሁራንን፣መደብን ይይዛል

እውቀት የሰው ልጅ ስጦታ ነው፡፡ ሰውን በአግባቡ ካሊያዝን ከሰዎች የሚፈለገውን ማግኘት

አንችልም፡፡ ምሁራን ያላቸውን እውቀት፣ክህሎትና አቅም ለያዝነው እቅድ ግብ መድረስ

ወሳኝ ናቸው፡፡

የግል አመራር ማለት

 መልካም መሆን

አመራር ለሌሎች መልካም ማንነቱን ከማሳየቱ በፊት በግል ህይወቱ መልካም ማንነት ወይንም

የእግዚአብሔርን ህይወት የተላበሰና የክርስቶስ ልብና አስተሳሰብ ያጎለበተ መሆን አለበት፡፡

 በመልካም ማገልገል

አገልግሎት በአዲስ ኪዳን ከፍቅርና ከባላደራነት መንፈስ የመነጨ እንጂ ማትረፊያና ቁስ መሰብሰቢያ አይደለም፡፡ 1 ቆሮ

4፡1

 በመልካምነት መጨረስ ናቸው

አገልግሎት ባላደራነት ነው፡፡ የምንጀምረው ተቀብለን በመሆኑ በእኛ ሚሰራው መንፈሱና ጸጋው ስለሆነው በታማኝነት

የተቀበልነውን አደራ መጨረስ ልክ ጳውሎስ ሩጫውን ጨርሻለው እንዳለው ማለት ነው፡፡

የግል አመራር የሚከተሉትን ይይዛል

አመራር ከግል ህይወት ይጀምራል፡፡ ለዚህ ነው ጳውሎስ ለጢሞቲዎስና ለቲቶ በጻፈው መልዕክቱ ኤጲስ ቆጶስ እንደ

እግዚአብሔር መጋቢ እንደዚ ሊሆን ይገባዋል ይለናል፡፡ ጤናማ የግል ህይወት አመራር በዋናነት የሚከተሉትን ያካትታል፡፡

 ከአግዚአብሔር ጋር ያለንን ህብረት

3
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
ሰው እግዚአብሔር ለህበረት ስለፈጠረው ጤናማ አመራር ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛና ቅዱስ የሆነ ህብረት

ሊኖረን ያስፈልጋል፡፡

 ከቤተሰባችን ጋር ያለንን ግንኙነት

አመራር የሚጀምረው ከግል ህይወት በመሆኑ በቤተሰባችን ውስጥ መልካም የሆነ ለሰዎች ምስክርነት ያለው

ግኝኑነት ሊኖረን ይገባል፡፡

 ቅንነታችንን

አመራር ሁሌም የሰዎችን ሃሳብ የሚቀበል፣ሰዎችን በመልካም ጎን የሚረዳ፣ መልካም እይታ እና ለመፍረድ

የማይቸኩል መሆን አለበት፡፡

 መነሳሳታችንን

አመራር ሁሌም የተነቃቃ እና የተነሳሳ ልብ ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡ ሰዎች ላይ ተጽኖ ያለው አመራር እንዲኖረን

ከተፈለገ በግል ህይወታችን የተነቃቃን በመንፈስ የምንቀጣጠል ሁሌ ንቁ ሆነን የመንፈስን ሃሳብ የምንቀበል

መሆን አለብን፡፡

 ማንነታችንን

ማንነታችን የተገነባበት መረዳት እና ስለ ራሳችን ያለን ግንዛቤ ለአመራርነት ወሳኝ ነው፡፡ ማንነታችንን

የተረዳነው የእግዚአብሔር ቃል ከሚለው ውጪ ከሆነ በዚህ አለም ባሉ የፍልስፍና አስተምህሮቶች

ስለምንወሰድ አደለም ለሌሎች ለራሳችን መሆን አንችልም፡፡ ሁሌም ማንነታችን እግዚአብሔር ከሚለው

ውጪ መረዳትም ሆነ መገንዘብ አያስፈልግም፡፡

 ስሜታችንን የምናስተናግድበትን መንገድ

ምሳ 16፡32 ስሜቱን የሚገዛም ከተማን ከሚይዝ ይበልጣል ይላል አገልጋይ ወይም አመራር ከምንም በላይ ስሜቱን

የሚገዛ፣ እራሱን በስሜት ከመነዳት፣ከመወሰን የሚታደግ፣ልከኛ፣ በመንፈስ የሚመራ መሆን አለበት፡፡

 ባህሪያችንን

በግል ህይወት ምልልስ አማኝ ባህሪው ክርስቶስን የሚገልጥ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን መሆን አለበት፡፡ 1 ጢሞ 4፡11

ለሚያምኑት በንግግርና በኑሮ፣በፍቅር፣በእምነትና በንጽህና አርዓያ ሁንላቸው፡፡ መልካም ባህሪ ለአማኝ ወሳኝ ነገር ነው፡፡

4
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
መልካም ባህሪ የማይታይበት አገልግሎት፣ የግል ህይወት ለአማኝ ትልቅ ውድቀት ነው፡፡ ምንም እንኳን የዳነው መልካም

ባህሪ ስላለን ባይሆንም የዳነ ሰው መልካም ባህሪና ስነ መግባር በአለምና በጨለማ ላለው ክርስቶስን የሚገልጥ ህይወት

ሊኖረን ይገባል፡፡

 ባላደራነታችንን

አማኝ በግል ህይወቱም ይሁን በህብረት የክርስቶስ አደራ አለበት፡፡ ገላ 2፡7፣1 ጢሞ 6፡20 ኤፌ 2፡10 መልካሙን

ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ተፈጠርን፡፡ ሁሌም አማኝ በየትኛውም ቦታ ሲንቀሳቀስ የክርስቶስን ተልዕኮ

ለመፈጸም ዝግጁ መሆን አለበት፡፡

2. ክርስቲያን ማኔጅመንት/አመራር

የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መንፈሳዊውንና መዋቅራዊ የሆነውን ሃሳብ በአንድ ላይ ያዋሃደ ነው፡፡ ቤተ

ክርስቲያን መንፈሳዊ አካል ያላት በመሆኑዋ የሚከተሉትን ታቅፋለች፡-

 የጀርባ አጥንት

 Doctrine/ዶክትሪን

 Holiness/ቅድስና

 Authority/ስልጣን

 Internal system/ውስጣዊ ውቅሯ

 Muscle/ጡንቻዋ

 Flesh/መግለጫዋ

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምልከታ በቤተክርስቲያን አመራር

የእምነት ተቋም እንደ መሆኑዋ መጠን ቤተክርስቲያን ከሌሎች አለማዊና ማህበራዊ ተቋማት በምስረታዋ፣

በህብረትዋ፣ በተልኮዋና አላማዋም ይለያል፡፡ ቤተክርስቲያን እምነት ላይ የተመሠረተ ተቋም እንደመሆኑዋ

ከአመራር ሳይንስ ጋር የሚያገናኝ እና ምትከተለው መርህ ይኖራል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ከሚገኙ መርሆች

5
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
ማለትም የተቋሙ መዋቅር፣ ተግባራት፣ተቋም እና ከተልዕኮው በተጨማሪ በውጭው ማህበረስብ፣

አመለካከት፣ ህሳቤ እና ልማድ የታጠረነው፡፡ ሆኖም ከውጭ ካሉት ተቋማት ጋር የጋራ የሆነ ነገር ይኖራታል፡፡

የሚያለያይ ተቋማዊ ባህሪም አላት፡፡ ስለሆነም በተገቢውና በሚጠበቅባት ልክ መመራትና መተዳደር

ይኖርባታል፡፡

የአመራር ሳይንስን መርሆችና ክህሎቶችን በቤተክርስቲያን ውስጥ ለመተግበር በመጽሐፍ ቅዱስ መደገፍ

ይኖርበታል፡፡ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን አመራርና አስተዳደርን በተመለከተ ብዙ ህሳቤና ተግባራትን

መገንዘግ እንችላለን፡፡

አመራር በአዲስ ኪዳን

ዘፍ 1፡28 ሰው በመጀመሪያ ሲፈጠር ጀምሮ እንዲገዛ አንዲያስተዳድር ነው፡፡ ማስተዳደር ወይንም መምራት የሚለው

ሃሳብ ጽንሰ ሃሳቡ በአዲስ ኪዳን የሚነሳዉ ከባለአደራነት ጋር ተያይዞ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል በመሆኑዋ

በክርስቶስ ህይወትና መንፈስ ነው ምትመራው፡፡ ጳውሎስ በ 1 ቆሮ 4፡1 ሰው ሁሉ እኛን እንደ ሎሌዎች እና እንደ

እግዚአብሔር ሚስጥር መጋቢዎች ይቁጠረን ይላል፡፡

በሁለት የአዲስ ኪዳን ክፍሎች አመራር እንዴት እንደተገበረ ማየት እንችላለን፡፡

• Matthew 24:45: “A faithful, sensible servant is one to whom the master can give the

responsibility of managing his other household servants and feeding them.”

• 1Timothy 3:5: “but if a man does not know how to manage his own household, how will he

take care of the church of God?”

በሁለቱም ክፍሎች እንደምናየው ማስተዳደር/መምራት እንዲሁም ቤተሰብ የሚለውን ሃሳብ እናገኛለን፡፡

አመራር/ማስተዳደር የሚለውን ሃሳብ የግሪኩ ቃል ማስተዳደርና ቤተሰብን በያዘ መልኩ የሚያብራራው ሲሆን

ይህም (oikonomos) አይኮኖሞስ የሚለውን ቃል ይጠቀማል፡፡

6
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
አይኮኖሞስ የሚለው ቃል “Oikonomos” cognates from አይኮስ “oikos” and “nemo” ኒሞ ከሚለው ቃል

የተወሰደ ነው፡፡አይኮስ ማት ቤት/ ቤተሰብ ማለት ሲሆን ኒሞ ማለት ማስተዳደር/ መምራት የሚለውን

የሚይዝ ሲሆን ባጠቃላይ የቤት አመራር ወይንም አስተዳደር ማለት ነው፡፡

በአዲስ ኪዳን (oikonomos) አይኮኖሞስ የሚለውን ቃል በተለያየ ቦታና ህሳቤ ጥቅም ላይ ውልዋል፡፡ እሱም

ባላአደራ፣አገልጋይ፣የሚመራ፣ገዢ፣የቤት አስተዳዳሪ የሚሉ ትረጉሞችን ይዟል፡፡

Luke 12:42; 1 Corinthians 4:2; Galatians 4:2.

ቤተሰብ በመጽሐፍ ቅዱስ የአማኙን ማህበረስብ ህብረት ወይንም የአማኞች ህብረት በሚል ተገልጻል፡፡ (Gal

6:10, Eph 2:19, 1 Pet 4:17, 1 Tim 3:12 and 1 Tim 3:15)

የቤተስብ አመራር ወይንም አባላቱ 3 ሃላፊነት አለባቸው፡-

 የቤተክርስቲያን ራስ ለሆነው ለኢየሱስ ክርስቶስ

 ለሌሎች ቤተክርስቲያን አካላት

 ከቤተክርስቲያን አካል ውጭ ላሉት ማህረስብ

የአመራር ወይንም አስተዳደር ብቃት

በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ አመራርነት እና አስተዳደር የራሱ የሆነ መለኪያ እና ብቃት መመዘኛ አለው፡፡ ለምሳሌ

1 ጢሞ 3፡1-7

 መልካም ባህሪይ (1 Tim 3:2-3)

 በቃልና በኑሮ

7
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
 በፍቅር

 በእምነት

 በንጽህና

 በትምህርት ደህንነት

 ጭምትነት

 ጤናማ የማይነቀፍ ንግግር

 ቤቱን/ቤቱዋን በመልካም ማስተዳደር (1 Tim 3:4-5).

 ክህሎትና ብቁ እድሜ ላይ የደረሰ (1 Tim 3:6).

 በሰዎች ዘንድ ምስክርነትና ቅቡልነት ያለው (1 Tim 3:7).

የሚከተሉትን አብራራ

ዲያቆን- Greek word diakoneo or diakonia meaning “service (Rom 12:7, Rom 12:8, 1 Cor 12:28,

2 Cor 8:19).

ቤተክርስቲያን በአመራር ሳይንስ ላይ ለምን ተዘናጋች

የአመራር እና አስተዳደር መርሆች እና ክህሎት በቤተክርስቲያን ተቋማት ውስጥ ሲተገበሩና ጥቅም ላይ

ሲውሉ አይታይም፡፡ ብዙ ነገረ መለኮት ትምህርቶች የቤተክርስቲያን አመራርና አስተዳደር እንደ ዲስፕሊን

አይሰጥም ይህም ለአመራር ያላቸውን ክፍተት ያሳያል፡፡ ቤተ ክርስቲያን በአመራርና አስተዳደረ በአለም ካሉት

ተቋማት የተሻለ አፈጻጸም እና ምልከታ ሊኖራት ያስፈልጋል ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስለሆነ፡፡ የቤተ

ክርስቲያን አመራርን በተመለከት ሁለት አሉታዊ አመለካከቶች ይንጸባረቃሉ፡፡

 ቤተክርስቲያን ልዩ ተቋም ናት እና በመንፈሳዊ መርሆች ነው ምትመራው


8
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
 አገልጋዮች መሪዎች ናቸው እና አስተዳዳሪ ወይንም አመራሮች አይደሉም

የአመራርን ሳይንስ ጥቅምን ለቤተክርስቲያን ለማሳየት አሉታዊ ምልከታዎች እና መረዳች በመጽሐፍ

ቅዱሳዊ ቤተ ክርስቲያን አመራር እሳቤዎች መመርመር አለበት፡፡

 ቤተ ክርስቲያን ተቋም አይደለችም የክርስቶስ አካል ናት ስለሆነም በመንፈሳዊ መርህ እንጂ በአመራር

ጥበብ ልትመራ አይገባም ይላሉ፡፡

2.1 የቤተ ክርስቲያን አመራር አላማው

 ለመንፈሳዊ አገልግሎት፣ ለጋራ ተልኮ፣ ባለ አደራነት. መተባበርና በጋራ ለመስራት ምቹ ሁኔታን

ይፈጥራል፡፡

 እስከ ፍጻሜ በጽናት እንድናገለግል

 አባላትን የአግዚአብሔር ቤተሰብ አድርገን እንድናስብና እንድንሰራ ያደርጋል

 ሰው ተኮር እና አሳታፊ ነው

 መተባበርና የቡድን ስራ ላይ ያተኩራል

 አካላትን ወደ ክርስቶስ መልክ መስራት ላይ ያተኩራል

 ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት፣ጸሎት፣እምነት፣ መታዘዝ እንድንማር ያደርገናል

 በሁለተኛ ጢሞቲዎስ 2፡1-7 ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ በጻፈው መልዕክት ላይ በሶስት ነገረ ጋር እያነጻጸረ

ሲናገር እናያለን፡፡ ወታደር፤አትሌትና ገበሬ፡፡ ይህን በክፍል ውስጥ ተወያዩበት

የክርስቲያን አመራር ሰዎችን በትህትና ማገልገልና በእውቀት፣በባህሪና በህይወት ምልልስ በጎ ተጽኖ ማሳደርና

ወደ ተፈለገው ግብ ማድረስ ነው፡፡

2.2 የአመራር ነገረ ምክንያት

 ሰዎች/ተከታይዎች
9
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
ቤተ ክርስቲያን አመራር ያስፈለጋት አንዱ መንስኤ ህብረቱ የሰዎች ስብስብ በመሆኑ የሰው ልጅ

ደግሞ ትልቅ ሃብት ነው፡፡ ወደ ተፈለገው ግብና ስኬት ለመድረስ ያለንን የሰው ሃብት እንደ ሥጦታ

ቆጥረን በአግባቡ መምራትና ማቀናጀት ይጠበቃል፡፡ የሰው ልጅ ደግሞ በተለያየ መረዳት፣ባህል፣ቋንቋ

የሚኖረ በመሆኑ አመራር ያስፈልገዋል፡፡

 መሪ

መሪ ለቤተ ክርስቲያን ከሚሰጥ ስጦታ አንዱ ነው፡፡ ባለ አደራነት ወይንም የእግዚአብሔር ሚስጥር

መጋቢነት ስጦታ ነው፡፡ ስለሆነም ስጦታ ሚሰጠው አስፈላጊ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን የተሰጣትን

ተልዕኮ ለመወጣት መሪ አስፈላጊ ነው፡፡

 አከባቢ/ሁኔታ

አከባቢ ከሁለት መንገድ ይታያል፡፡ አንደኛው ውስጣዊና ውጫዊ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከውስጥም ሆነ

ከውጭ የሚገጥማትን ጉዳይ ለመጠቀምም ሆነ ለመከላከል አመራር ወሳኝ ነው፡፡

 ተግባቦት

አመራር ያለ ተግባቦት ውጤት አልባ ነው፡፡ ከውስጥም ሆነ ከውጭ በሚፈለገው መንገድና ክህሎት

ተግባቦት በመፍጠር ቤተ ክርስቲያን የራስዋን ሚና መወጣት አለባት፡፡ ጤናማ የሆነ የተግባት ሥርዓት

የዘረጋችና እንደ እግዚአብሔር ባለ አደራ የምትመራ ቤተ ክርስቲያን ውጤታማ ነች፡፡

2.3 የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን መዋቅርና መሪነት ንድፍ

እግዚአብሔር የሁከት አምላክ አይደለም፡፡ 1 ቆሮ 14፡33 የተፈጥሮው አለም አደረጃጀት፣ዲዛይን፣መዋቅር

እግዚአብሔር አምላክ ሁሉን ነገር በስርዓትና ቅደም ተከተል እንደሰራው ያስረግጣል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ

እንደሚናገር አግዚአብሔር የስርዓት አምላክ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያንንም በስርዓትና መዋቅር እንድትመራ

አድርጎ ነው የመሠረታት፡፡

10
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
በዓለም ዙርያ በቤተክርስቲያናት ዘንድ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ አመራር ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት

የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ወደሚቀጥለው የእድገት እርከን የሚያሸጋግሯቸውን ወጣትና ጠንካራ አዳዲስ

መሪዎችን በማበረታታትና በማሰልጠን መርሀ ግብሮች ተጠምደዋል፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ነገር በአሁኑ ወቅት

በሚገኙት በአብዛኞዎቹ አብያት ክርስቲያናት ውስጥ የሚንጸባረቀው የአመራር ሥርዓት በመፅሐፍ ቅዱስ

ውስጥ ከተገለጠው አመራር ፍጹም የተለየ ነው፡፡

ኢየሱስ የቤተ ክርስቲያን እራስ ነው፡፡ ኤፌ 1፡22-23 ኢየሱስ በሰማይና በምድር ስልጣን እንደተሰጠው

መጽሐፍ ይነግረናል፡፡ ማቴ 28፡18 በሰው ሚዛን፣ወግና ባህል ቤተ ክርስቲያን አትመራም፡፡ ስለሆነም

በእውነተኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀትና መንፈስ ነው ቤተ ክርስቲያን ምትመራውና ምትተዳደረው፡፡ ቤተ

ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ስትሆን በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ በእግዚአብሔር አብ ስልጣን ፍቃድ

የተመሰረተች ቲኦክራቲክ አመራርን የምትከተል ነች፡፡ ስለሆነም የቤተ ክርስቲያን አመራር/አስተዳደር

ማጥናት/መማር አስፈላ ነው፡፡

2.4 መጥፎ የመሪነት ልምምዶች

ገንዘብ ነክ ጉዳዮች

ማቴ 6፡24 ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም

1 ቆሮ 5፡10፣ 1 ጢሞ 6፡10 ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነው፡፡

ስልጣንን ያለ አግባብ መጠቀም

2 ቆሮ 13፡10 ስልጣን የተሰጠን ቤተ ክርስቲያንን እንድንጠቅም፣ቅዱሳንን እንድናንጽ ለክርስቶስ

ለመስራት እንጂ ሰዎችን ለመጉዳት ለግል ጥቅም ለመጠቀም አይደለም፡፡

መጥፎ የግለሰብ ህይወት መመላለስ

የህይወት ምልልስ በእግዚአብሔር ቃል ካልተፈተሸ፣የቅዱሳን ምስክርነት ከሌለው ለመሪነት ብቁ

አይደለም፡፡ መልካም ሥነ ምግባር ወይንም መንፈሳዊ ፍሬ ከድርድር የማይገባ ጉዳይ ነው፡፡ ሰዎች

11
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
በዚህ ዘመን የልባቸውን የሚፈጽሙበት፣ ለአማኙ የማይጠነቀቁ፣ጨካኞች፣ እራስ ወዳዶች

ናቸው፡፡ ስለሆነም የተቀበልነውን ህይወት የሚመጥን ኑሮ ከእኛ ይጠበቃል፡፡ የመሪነት አንዱ

መመዘኛ መልካም የህይወት ምስክረነት ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን የተለያየ ጸጋ ስጦታ ያላቸው

ሰዎች የባህሪ/የህይወት ምልልስ ችግር አለባቸው፡፡ በዚ ዘመን በጣም ሊሰመርበት እና ሊሰራበት

የሚገባ በመሆኑ መሪዎች ባላ አደራ መሆናቸውን አውቀው ሊሚመሩት ህዝብ ዋጋ መስጠት

አለባቸው፡፡

3. አስተዳደር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?

Stewardship/መጋቢነት/ ከእግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን

አመራር/አስተዳደር ባይኖራት ውጤቱ ምን ሊሆን ይችላል፣

ዘፍ 1፡28፣ ሉቃ 12፡42፣1 ቆሮ 4፡1፣ኤፌ 3፡2፣ቆላ 1፡25፣1 ጵጥ 4፡10

3.1 የቤተ ክርስቲያን አመራር ለምን አስፈለገ

 የቤተ ክርስቲያን ሀብት ስላላት እሱን ለማስተዳደር

 ሃላፍትና/ባለአደራነት ስለ ተሰጣት

 ሰዎችን ማበረታቻ

 የጊዜ አጠቃቀም ለማስተማር፣ለመገምገም

 የቤተ ክርስቲያን ህብረት ቁጥር ብዛት መጨመር

 የአገልግሎት ውጤታማነት ላይ ያለውን አስተዋጾ በመገንዘብ

 ሰዎችን ወደ ለውጥ ለመምራትና ለፍሬ ለማብቃት

የግለሰብ አስተዳደር/ማኔጅመንት ምን ማለት ነው፡ አመራር ከግል ይጀምራል፡፡ ቤቱን ያልመራ ቤተ ክርስቲያንን

ሊመራ አይችልምና፡፡ እራሱን የሚመራ መሪ፡

12
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
 በመልካም ማንነት መጀመር

 በመልካምነት ማገልገል

 በመልካም ማንነት መጨረስ

3.2 ማኔጅመንት/አመራር እና መሪነት

 አስተዳደር መጠበቅ፣አቅጣጫ መስጠት፣ ጥቃቅን ነገሮች የሚመለከተው እና አስተዳደራዊ ነው፡፡

አስተዳደር ብቃትን የሚፈልግ ነው፡፡ ስራ ተኮር ነው፡፡

 መሪነት ቪዥነሪ፣ለውጥ ተኮር፣የሚያነቃቃና ሂደታዊ ነው፡፡ መሪነት ውጤት ላይ ያኩራል፡፡ ሰው ተኮር፣

ሰዎችን በማነቃቃት፣ ማበረታታት ራዕይውን ከግብ ለመድረስ ነው፡፡

4. የማኔጅመንት/አመራር ደረጃዎች

ማናጀር/አመራሮች በስራ ድርሻቸውና በድርጅት ውስጥ ባላቸው ሃላፊነት በመነሳት በሁለት ይከፈላሉ፡፡

ማናጀር ማነው?

 ማናጀር ማለት የአንድ ድርጅት/ቤተ ክርስቲያንን ለመምራትና ውሳኔ ለመስጠት ስልጣን የተሰጠው

ሆኖ የተቋሙን ንብረትና ሃብት በመጠቀም ወደ ታሰበለት አላማና ግብ ለማድረስ የሚሰራ ወይንም

ሃላፍትና የተሰጠው ግለሰብ ነው፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ማናጀሮች፡- የሰራተኞችን ሥራ የሚቆጣጠርና ሃላፊነት ያለበት ነው፡፡

 የየእለት ስራዎችን የሚያቅዱ

 ሥራዎችን የሚያከፋፍሉ

 በሰራተኛው አፈጻጸም ላይ የሚያተኩር

 ሪፖርቶችንና መረጃዎችን ለበላይ ኃላፊ የሚልክ

 ከበታች ሰራኛ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውና የሚገመግሙ

የመካከለኛ ደረጃ ማናጀር


13
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
የከፍተኛ ደረጃ ማናጀር

የሃላፊነት ተግባራን በመመርኮዝ

ፋንክሽናል ማናጀር፡- የክፍል ስራ ሂደት ሃላፊ ወይንም የሆነ ክፍልን በተቋሙ ውስጥ የሚመራ ማለት

ነው፡፡

ጄነራል ማናጀር፡- አጠቃላይ ድርጅቱን በበላይነት የሚመራ ሲሆን ሁሉም የክፍል ስራ ሃላፊዎች

ለጠቅላላ የበላይ ሃላፊ ተጠሪ ናቸው፡፡

4.1 የማኔጅመንት ክህሎት

ቴክኒካል ክህሎት/technical skills/፡- የኮምፒውተር አጠቃቀም፣ጽሁፍ፣የድርጅቱን መረጃ

ማጠናቀር፣የዲዛይን መፍጠር፣ኪቦርድ ማስተካከል፣

ሰዋዊ ክህሎት /human skills/፡- ከሰዎች ጋር ባለ ግንኙነት አብሮ የመስራት ክህሎት ነው፡፡

ተግባቦት፣መልካም አስተሳሰብ፣ሰዎችን ማበረታታት

ኮንሰፕችዋል ክህሎት/conceptual skills/፡- የድርጅቱን ትልቅ እይታ/ምልከታ የማየት ክህሎት፣ ውሳኔ

የመስጠት፣

4.2 የማናጀር/አመራር ሚናዎች

 ከሰው ጋር የተያያዘ/ኢንተርፐርሰናል

 ወካይነት- ድርጅቱን በመወከል በተለያዩ ልዩና ድርጅቱን ገጽታ ግንባታሊጠቅሙ በሚችሉ

ፕሮግራሞች/ጉዳዮች ላይ መወከል፡፡ የዶክመንት ፊርማ፣ ጎብኚዎችን መቀበል

 ሊይዘን፡- ከድርጅቱ ውጪ ከሆኑ ሰዎች ጋር ተግባብዎት መፍጠር፣ የግንኙነት መረብ መሆን

 የመሪነት ሚና፡- ሰራተኞችን በመመልመል፣መቅጠር፣ማሰልጠን፣ማበረታታትና ዲሲፕሊን

በማድረግ ተገቢውን ስራ እንዲሰሩ የማድረግ ሚና

 ኢንፎርሜሽናል/ መረጃን የማጠናቀር ሚና

14
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
 መረጃን የማጠናቀር፣ማሰራጨት፣ገለጻ የመስጠት

 የሞኒተሪንግ ስራ

 ውሳኔ የመስጠት ሚና

 አዲስ ነገሮችን የመፍጠር ሚና

 ችግሮችን የመፍታት

 ንበረትን የማደላደል

 የማግባባት ስራ

4.3 የማኔጅመንት/አመራር ተግባራት

አመራር አራት እና ከዛ በላይ የሆኑ ተግባራት አሉት፡፡ እነርሱም ማቀድ፣ማደራጀት፣ስታፊንግ፣መመዘንና

መቆጣጠር ናቸው፡፡

1. ማቀድ

ይህ ውሳኔ የመስጠት ሂደት የሚያካትት ሲሆን ተልኮንና አላማን በትክክል በመምረጥ ተቋማት አሁን

ያሉበትንና የወደፊቱን የሚያስተሳስር ነው፡፡ ስራዎች ምን ይሰራ፣እንዴት ይሰራ፣ለምንድነው

ሚሰራው፣መቼ ይሰራና ማን ይስራው ይወስናል፡፡

በእቅድ ማውጣት ሂደት ውስጥ የመጀመሪያው ስራ የተቋሙን አላማ ማስቀመጥ ነው፡፡ ከዛም በድርጅቱ

ስር ላሉት የሥራ ክፍሎች አላማ በማውረድ ሰልታዊ በሆነ መንገድ ለማሳካት ፕሮግራም መቅረጽ ነው

ቀጣዩ ስራ፡፡

እቅድ የሚሰራው በላኛው የተቋም ሃላፊዎች ሲሆን የታችኛው ደረጃ ማናጀሮች በየሥራ ክፍላቸው

የሚመለካታቸውን እቅድ ከድርጅቱ እቅድ ላይ ያዘጋጃሉ፡፡

15
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
እቅድ ማዘጋጀት የማናጀሪያል ተግባር እንደመሆኑ መጠን የወደፊት የተቋሙን ክንውኖች በማጠናቀር ነገን

በመሳል፣ በማሳየት እንዲሰሩና እንዲያከናውኑ ይረዳል፡፡

እቅድ ሲዘጋጅ የራሱ የሆነ ሂደት አለው፡-

 ችግሮችን መለየትና መተርጎም/ማብራራት

 ግልጽ የሆነ አላማ ማዘጋጀት

 የእቅዱን መንስኤ ማስቀመጥ

 አማራጭ ሊሆኑ የሚችሉ መፍትሄዎችን መለየት

 አማራጭ መፍትሄዎችን መገምገም

 ምቹ የሆነውን አማራጭ/መፍትሄ መምረጥ

 ግኙቱን ወደ እቅድ መለወጥ

 እቅዱን ወደ አሃዝ መቀየር

እቅድ ሲዘጋጅ የራሱ የሆነ ክህሎትና ልምድ ይፈልጋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ወሳኝ የሆኑት ትንበያ/የግምት

እውቀትና ውሳኔ መስጠት ናቸው፡፡

4.4 የእቅድ አይነቶች

እቅድ በአንድ ተቋም ውስጥ በተለያየ የጊዜ ገደብ ይዘጋጃል፡፡ ከዚህ በመነሳት ሶስት አይነት እቅድ ይዘጋጃል፡-

 የአጭር ጊዜ እቅድ፡- ለአንድ አመት ባልበለጠ ጊዜ የሚዘጋጅ ነው፡፡

 የመካከለኛ ጊዜ እቅድ፡ ከአንድ አመት እስከ አምስት አመት ለሚፈጅ ጊዜ የሚዘጋጅ ነው፡፡

 የረጅም ጊዜ እቅድ፡- ከአምስት አመትና ከዛ በላይ ለሆነ ጊዜ የሚዘጋጅ ነው፡፡

4.5 የእቅድ መርሆች

16
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
ጥሩና ችግር ፈቺ እቅድ ሲዘጋጅ ደረጃዎችን በግልጽ የተከተለና ስኬታማ መፍትሄ የሚያመጣ ነው፡፡

ሂደቱም የሚከተሉትን መርሆች የተከተለ መሆን ይኖርታል፡-

o አቃፊና ሀሉን ያገናዘበ መሆን አለበት

o ብቁ መሆን አለበት

o ሁሉን ባለድርሻ አካል ያወያየ መሆን አለበት

o በሚመለከታቸው አካላት የሚታወቅና ውጤቱም የታመነበት

o ያዋሃደ

o ምክንታዊ

o ግልጽ

4.6 ስትራቴጂያዊ/ስልታዊ/ እቅድ:-

ስትራቴጂይ የሚለው ቃል ከግሪክ “ሰተራቴጂኦስ” ከሚለው ቃል የተወሰደ ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ የሠራዊት

ዋና አዛዥ/ጀነራል፣ ይህም ከጦርነት ጋር ተያይዞ ጥቅም ላይ ይውል ነበር፡፡

የተቋምን የረጅም ጊዜ ችግሮች ለመፍታት በበላይ ሃላፊዎች የሚዘጋጅ ሲሆን የሚከተሉትን ያካተተ ነው፡፡

ማን ተጠያቂ እንደሆነና በምን ሃብት የተሰጠውን አላማ/ግብ ማከናወን እንዳለበት ይመልሳል፡፡

ተልዕኮ፡- ድርጅቶች የተቋቋሙበት ምክንያት፣መሰረት ነው፣ ምሳ. ወንጌል ለማድረስ፣

አላማ፡- ወደፊት ሊደረስበት የታሰበው ውጤት ነው፡፡

ስትራቴጂ/ስልት፡- የታሰበውን አላማና ግብ ለማናወን የሚያስፈልግ ዘዴዎች ናቸው፡፡

ግብ ሲዘጋጅ ሁል ጊዝ መመዘን ይኖርበታል፡፡ ለዚህም የሚሆኑ 5 መስፈርቶች አሉት፡፡ እነርሱም፡

የተወሰነ/በቀጥታ

በግልጽ የተለየ/የተቀመጠ፣ ሊሰራ/ ሊደረስበት ያለውን ግብ ወስኖ ማስቀመጥ፡፡


17
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
የሚመዘን

ልንደርስበት ያቀድነው ግብ ባስቀመጥነው ስታንዳርድ ወይም መስፈርት መመዘን የሚችል/

የሚለካ መሆን አለበት፡፡

ሊደረስበት የሚችል

ያምናቅደው ግብ ማከናወን የምንችለው፣ በአቅማችን ጋር የተዛመደ መሆን አለበት፡፡

አግባብነት ያለው/ታማኝ

የምናቅደቅ ግብ በውስጥና በውጭ ባሉ ሰዎች ሁሉ ታማኝ የሆነ አሳማኝ እና አስፈላጊ የሆነ

መሆን አለበት፡፡

በጊዜ ገደብ የተወሰነ- ለምናቅደው ግብ የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ ግዴታ ነው፡፡ ያቀድነውን ግብ

ባስቀመጥነው ስታንዳርድ ጊዜ መሰረት ማከናወን አለብን፡፡ ካልሆነ ግን ግባችን ስኬታማ

አይሆንም፡፡

ስትራቴጂክ እቅድ ለማዘጋጀት የሚከተሉት ሂደቶችን መከተል ወሳኝ ነገር ነው፡፡

1. የተቋሙን የአሁን ጊዜ ተልዕኮ፣አላማና ስልት መለየት

2. ውጫዊ ዳሰሳና ምዘና መስራት

3. ውስጣዊ ዳሰሳ መስራት

4. ስትራቴጂ መመስረት

5. ስትራቴጂውን መተግበር

6. መገምገም፣መመዘን

እንደ ክርስቲያን መህበረሰብ ስትራቴጂክ እቅድ ሲዘጋጅ

 ምርመራ፣ትንተና እና ጸሎት ማድረግ፡- እንዴት እንስራው፣ደስተኛ ነን ወይ፣ ወዴት ነው ለመድረስ

ያሰብ ነው

 ውስጣዊ ዳሰሳ መስራት


18
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
 ውጫዊ ዳሰሳና ምዘና መስራት፣ ጥንካሬ፣ድክመት፣አማራጭና ስጋት እንዲሁም መመሪያ፣ስነ

ተግባር፣ስምምነቶች ማዘጋጀት፣በጀት ማዘጋጀትና መግለጫ መሠራት

በጀት ሁለት ማዕቀፍ አለው፡ ገቢና ወጪ ናቸው፡፡ ሶስት አይነት በጀቶች አሉ፡- እነርሱም

1. ጠቅላላ በጀት፡- ለአንድ አመት የተመደበ ፈንድ በየጊዜው የሚወሰድ

2. ካፒታል በጀት፡- ለግዢ የሚመደብ ፈንድ

3. የተሰየመ ፈንድ፡- ከጠቅላላ በጀት ላይ ለአስፈላጊ ጉዳይ የሚመለስ ሆኖ በውሰት የሚወሰድ ነው፡፡

አላማ፣ተልኮ፣መመሪያ፣ፖሊሲ ምን እንደሆኑ በግልጽ አብራራ???

አንድ ተቋም ተልዕኮ ወይንም አላማ ባይኖረው ውጤቱ ምንድነው???

4.7 ማደራጀት

ይህ ከታቀደው እቅድ መሰረት በማድረግ ለሰራተኛው አፈጻጸም ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ሂደት ነው፡፡

የማደራጀት ሂደት የሚከተሉትን ያካተተ ነው፡-

ተግባራትን መለየት

ተግባሮችን ወደየ ስራ ክፍሎች መመደብ

ሃላፍትናን ለእያንዳንዱ የሥራ ክፍል ከበቂ ሰልጣን ጋር መመደብ

የድርጅት ውስጥ ግንኙነት መረብ መዘርጋት

የማደራጀት ሂደት የራሱ የሆነ ደረጃዎች አለው እነርሱም፡

 አላማን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ተግባራትን መወሰን/መለየት

 የስራ መደቦችን መፍጠር፣ተግባራቸውንና ኃላፊነታቸውን መለየት

 ተግባራትን ለሥራ አፈጻጸም እንዲመች በሥራ ክፍል ማዋቀር

 ሥልጣንና የክትትል ግንኙነትን ማስፈን

19
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
 ስልጣንን መስጠት

ጠቃሚ የማደራጀት ሂደት መሰረታዊ ዉጤቶች

 የሥራ ክፍል መመስረት

 ውክልና፣እንደራሴ

 የስልጣን ተዋረድ ከላይ ወደ ታች ማሰራጨት

ተቋማት ሁለት አይነት መዋቅር ይጠቀማሉ፡

 ግድም /horizontal/

 ከላይ ወደ ታች /vertikal/

ተቋም ወይንም ድርጅቶች ሲመሰረት በሁለት አይነት መንገድ ነው

 መደበኛ፡ ግልጽ የሆነ አላማና ግብ ተቀምጦላቸው በመመሪያና ደንብ በህጋዊ መንገድ፣በማኔጅመንት

መዋቅር የሚተዳደር ነው፡፡

 መደበኛ ያልሆነ፡ በአጋጣሚ የሚቋቋሙ፣የቡድን፣ማህበረስ አላማና ግብ ለማሳካት፣ጊዜያዊ ችግር

ለመፍታት ነው፡፡ ጥብቅ የሆነ መመሪና ሥርዓት የላቸው በባህላዊ መንገድ መልኩ የመተዳደር ነገር

የዘነብላል፡፡

 ማደራጀት የራሱ የሆነ ጥቅም አለው፡፡ ጥቅሙን ተወያዩበትና በግሩፕ አስገቡ

 መልካምና ብቁ የሆነ አስተዳደር ይኖራል

 የሃብት አጠቃቀም ከብክነት ይከላከላል

 ግልጽ የሥራ ድርሻ እንዲኖር ያደርጋል

 ሥአ ሥርዓት ያለው የመረጃና ተግባቦት አካሄድ ይኖራል

 ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን ያሰፍናል

 መስፋትና እድገትን ያመጣል

20
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
 በአለማችን ላይ የቤተ ክርስቲያን አመራር መዋቅር በተለያዩ 4 አይነት ሲተገበር ይታያል፡፡

1. ኢኩሜኒካል/ecumenical ፡- የተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት በአንድ አይነት ዶክትሪን፣የሚመሩ ሆነው በወካይ

አማካኝነት የሚመራ ህብረት ወይም ሲኖዶስዊ የሚመሩ ናቸው፡፡ ካቶሊክ፣ሉተራን፣ሜትዲስት፣

2. ሪፓብሊካን፡- ይህ ደግሞ የተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት በተወሰነ አከባቢ ላይ ያላቸው ስብስብ ነው፡፡

3. ኮርፖሬት ሞዴል፡- ይህ በቦርድ የሚመራ ሲሆን ቦርዱ የበላይ ባለ ስልጣን ነው፡፡

4. ኢንተርፕሪነር ሞዴል፡- ይህ በፓስተር ወይም በባለ ራዕይ የሚመራ ሲሆን ሁሉን ለማድረግ ስልጣን ያለው

ፓስተሩ ወይነም ባለ ራዕይው ነው፡፡

4.8 ስታፊንግ

ይህ ሂደት ክፍት የስራ መደቦችንና ሰራተኛውን ለሚፈለገው ስራ መቅጠርና ብቁ የማድረግ ነው፡፡ የስታፊንግ

ሂደት የሚከተሉትን ቅደም ተከተል ይይዛል፡፡

1. የሚያስፈልግ ሰው ሃይል ማቀድ

2. መመልመል

3. መቅጠር

4. ገለጻ መስጠት፣ድርጅቱን ማስተዋወቅ

5. ስልጠና መስጠትና ማልማት

6. አፈጻጸምን መመዘን

7. እድገት፣ዝውውር፣ የደረጃ ቅጣት ማከናወን

8. ማቋረጥ

ኢየሱስ በአገልግሎቱ ደቀመዛሙርትን ለመምረጥ የተጠቀመው ስታፊንግ ሂደት አለ፡፡ እርሱም የሚከተለው

ነው፡፡

 መምረጥ

21
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
 አብርሆት፣ህብረት መፍጠር

 መለየት

 ጸጋ ማካፈል፣ማጋራት

 ሞክሮ ማሳየት

 መወከል፣ስልጣን መስጠት

 ክትትል፣ቁጥጥር ማድረግ

 ማባዛት፣ ተተኪ ማፍራት

ሊዲነግ/በቀዳሚነት መምራት

ይህ ሰዎችን በበጎ ተጽኖ፣በማበረታታትና አቅጣጫ ሰጥቶ በመምራት ለተቋሙ አላማና ግብ የበኩላቸውን

ከፍተኛ አስተዋጾ እንዲያደርጉ ማድረግ ነው፡፡ ይህም 3 ነገሮችን ይይዛል፡ መበረታታት/ማነቃቃት፣ የመሪነት

ዘይቤ እና ተግባቦትን የካተተ ነው፡፡

መሪነት በተለያያ ዘዴ በአለማችን ላይ ይንጽባረቃል፡፡ ከነዚህም መካከል፡

 አምባገነን

 ዲሞክሪያሳዊ እና ሊይዘስ ፌር/ነጻ የሆነ አስተሳሰብ አለው

4.9 መቆጣጠር

ይህ ሂደት ከማኔጅመንት ተግባራት አንዱ ሲሆን የክንውን ስራዎችን ከእቅድ አንጻር መመዘን እና ማረምን

የሚያካትት ነው፡፡ ትክክል የሆነ አፈጻጸም ሲገኝ እርምጃ መውሰድን ያካትታል፡፡

የቁጥጥር ሂደት የራሱ የሆነ ሶስት ደረጃዎች አሉት፡አነሱም፡-

 ስታንዳርድን ማውጣት/ማስቀመጥ

 አፈጻጸምን መገምገም

22
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
 አፈጻጸምን ከእቅድ ጋር ማነጻጸር

 ትክክለናውን እረምጃ መውሰድ

5. የግጭት ማጅመንት/ conflict management/

ይህ የአመራር ክህሎት አለመግባባት በግለሰብ፣በድርጅት ሰራተኞች መካከል ሲፈጠር የሚፈታበት ሲሆን ጉዳት

በመቀነስ ጥቅሙን የማጉያ መፍትሄ ነው፡፡ ይህም ማናጀሮች የግል ታክቲክና ክህሎትን በመጠቀም በማግባባትና

የፈጠራ ሃሳብ በመጠቀም የሚካሄድም ጭምር ነው፡፡

 ግጭት በተለያዩ ምክንያች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይከሰታል፡፡ መንስኤዎቹ ላይ ተወያዩ

 ደካማ የመግባባት አቅም

 የማገናዘብና የማመዛዘን ችግር

 የልተሟላ ፍላጎት

 አለመቻቻል

 ሰዎችን መጉዳት

 የግል ፍላጎት

 አላዋቂነት

 የስልጣን ጥማት

 እራስ ወዳድነት

 አጉል ግምት/ምክንያታዊ ያልሆነ ግምት

አምስት አይነት የግጭት አፈታት መንገዶች አሉ፡፡ እነርሱም

 Accommodating/ አቃፊ

የራስን ፍላጎት ለሰዎች በመተው በጉዳዩ ያለመጨነቅ አይነት ስሜት በመፍጠር ሰላምን በመፈለግ ብቻ

ከጉዳዩ ይልቅ ሰላምን ለመፍጠር ተፈለግ የሚደረግ መንገድ ነው፡፡

23
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
 Avoiding/ማስወገድ

ይህኛው መንገድ ችግር ፈጣሪዎቹን፣መንስኤ የሆነውን አካል ሁሉንም ወይንም በከፊል በማስወገድ

ወይንም ወደ ሌላ ክፍል በማዘዋወር የሚፈታ ነው፡፡

 Compromising/አስታራቂ ሀሳብ

ይህ ሁለቱን ወገን ፍላጎታቸውን አንዲተውና ወደ መፍትሄ እንዲመጡ በማድረገ ሁለቱነም ተጠቃሚ

የሚያደረግ፣ ትንሽ ነገር በመተው ወደ መግባባት አንዲመጡ በማድረግ የሚፈታ ነው፡፡

 Competing/ ውድድር

ይህ ዘዴ የማስታራቅ ሃሳብና የሌሎችን ሃሳብ የማያስተናድ ሲሆን ትክክለኛ ሃሳብና አመላካከት ነው

ያለኝ ሌላኛው ቡድን የሱን ሃሳብ እዲቀበል የማስገደድ አይነት ሆኖ በችኮላ የሚደረግ ነው፡፡

 Collaboration/መተባበር

የሁሉም አካል ፍላጎትና ሃሳብ የሚሰማበት ሁሉንም የማከለ መፍትሄ የሚሰጥበት ነው፡፡ ነገር ግን አስቸጋሪና ጊዜ

የሚወስድ ነው፡፡ ሆኖም ዘላቂ መፍትሄ የሚመጣበት ነው፡፡

6. የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር

የበተ ክርስቲያን አስተዳደር ማለት የቤተ ክርስቲያን መዋቅሩ/አገዛዙ የተቀመጠበትን የሚያመለክት ነው፡፡

የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መሠረቱ አግዚአብሔርን የማክበር፣ ሰዎች ላይ ያተኮረ ነው፡ የተለመዱት

የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አይነቶች፡-

 Congregationalist፡- ራስ መር አስተዳደር ሲሆን የራስን ጉዳይ በራስ የመወሰን፣ በራስ የማስተዳደር

ስልጣን ያለው በሌሎች ላይ የማይደገፉ ናቸው፡፡

 Elder-led፡- ከህብረቱ ውስጥ የተወሰኑ ሰዎችን በመምረጥ እነርሱን በመወከል ውሳኔ መስጠትና

ማስተዳደር ሥራን ያከናውናሉ፡፡ ባፕቲስት፣ፕሪስቢቴሪያን

 Denominational፡- ይህ ደግሞ አንድ ወይንም የተወሰኑ ሰዎችን በመምረጥ በሥሩ የሚገኙትን ቤተ

ክርስቲያን/ህብረቶች የሚመራና ሚያስተዳድር ውሳኔ ሚሰጥበት አይነት ነው፡፡ ሉተራን፣አንጀሊካን

24
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
6.1 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አስተዳደር ምን ይላል

በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥

 እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።

እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት

እንናገር፤ አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ፤ የሚያስተምርም ቢሆን በማስተማሩ

ይትጋ፤የሚመክርም ቢሆን በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር

በደስታ ይማር። ሮሜ 12፡4-8

ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን

እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤ ቲቶ 1፡5

እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም

አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥

የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል። 1 ቆሮ 12፡28

እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና

አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ

ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን

አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ። ኤፌ 4፡12-13

25
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
7. የቤተ ክርስቲያን ዲስፕሊን/ Church Discipline

 ሶስት አይነት ዲስፕሊን በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጾ እናያለን፡፡ እነዚህም፡-

1. Formative discipline:- በምክር፣ በቁጣ በቃል በመንገር፣ የሚታረም ነው፡፡

2. Corrective discipline ፡- ይህ ሰዎች በየትኛውም በደልና ኃጢያት ቢገኙ ከመንገዳቸው አንዲመለሱ

በየዋህነት ማቅናት፣ህይወታቸውን ከአለም እድፍ እንዲጠብቁ ማስተማር እንዲሁም በንሰሃ እንዲገቡ

በማድረግ የሚወሰድ እርምጃ ነው፡፡

ገላ 6፡1፣ ኤፌ 5፡11፣ ቲቶ 3፡10፣ 1 ቆሮ 5፡1-13

26
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
3. Preemptive discipline: - ይህ የአካሉን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል በደለኛውን ከህብረት በማገድ

እራሱን በቤቱ እንዲያርም በማድረግ የሚወሰድ ዲስፕሊን ነው፡፡ ሐዋ 8፡17-27,ዩሐ 2፡9-10

7.1 ቤተ ክርስቲያን ዲስፕሊንን መተግበር ያለባት ለምንድነው

 መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው

የቀደመችው ቤተ ክርስቲያን የስነ ምግባር ችግር ያለባቸውን አማኝም ይሁን አገልጋዮች እንዴት

እንዳረሙ እንደፈቱ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የነበረው ችግር እንዴት

እንደተፈታ፣ ጳውሎ በነሱ መካከል የነበረውን የስነ ምግባር ጉድለት በተለያየ መልክ ሲፈታ እናያለን፡፡

 የክርስቶስን ስምና መልክ ለመጠበቅ

አገልጋይ ይሁን አማኝ በስነ መግባር ወይንም በመልካም ባህሪ መመላለስ ያለበት ለተቀበለው ህይወት

ታማኝ መሆን ስላለበት እንዲሁም የክርስቶስን መልክና ስም ለመጠበቅ ነው፡፡

 ለወንጌል ጠቃሚ ስለሆነ

ወነጌል በቃል ብቻ ሳይሆን በኑሮም የሚኖር ህይወት ነው፡፡ ይህንን ደግሞ ጳውሎስ ጢሞቲዎስን

ሲመሰክርለት እናያለን፡፡ የምንኖረውን የምንናገር፣የተናገርነውን የምንኖር መሆን አለብን፡፡ ወነጌል

በእኛ እንዳይሰደብ መጠንቀቅ፣ አካሄዳችን መፈተሽ አለብን፡፡

 ለቤተ ክርስቲያን ጤንነት ስለሚጠብቅ

ሌላው ደግሞ መልካም ሥነ ምግባር የህብረትን ጤኔነት ይጠብቃል፡፡ የአካሉን ህብረት ካጠበቅን እጅ

ሲታመም ሙሉ አካሉ እንደሚጎዳ መገንዘብና የአካል መንፈስ ይዘን መመላለስ አስላጊ ነው፡፡

27
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
 ለአለም ምስክርነት ስለሚሆነ

መልካ ሥራችሁነ አይተው የሰማይ አባታችሁን ያመሰግኑ ዘንድ እንደሚል ቅዱስ ቃሉ ህብረት ሁልጊዝ

በመልካም ሥራ፣ በፍቅር፣ ሰዎችን በመርዳት፣በቅድስና ክርስቶስን በሚያከብር ነገር ሁሉ መታወቅ

አለባት፡፡

 በደለኛውንና ጥፋተኛውን ለማረም፣ለማቅናት - ቤተ ክርስቲያን ደካማውን በማቅናት፣የሳተውን

በመመለስ፣ በማረም፣ ሰዎችን ለክርስቶስ በመስራት የሁል ጊዜ ሥራዋ መሆን ይገባዋል፡፡

8. በጀት ዝግጅት

ብቁና መልካም የሆነ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ስትራቴጂይ ቤተ ክርስቲያን ከግቡዋ በተፈለገው ጊዜ

እንድትፈጽም ይረዳታል፡፡ ይህም የሚሆነው ቤተ ክርስቲያን የእቅድ ማዘጋጀት፣የአደረጃጀት ሥራዎችና

የፋይናንስ እቅድ በሚፈለገው አይነት አዘጋጅታ ስትመራ ነው፡፡ በጀት ማለት የታቀደውን እቅድ፣ግብና

የማኔጅመንት አላማ ወደ አሃዝ/ቁጥር በመቀየር በሚያስፈልገው ጊዜና ተግባራት ዝርዝር ማስቀመጥ ነው፡፡

በጀት የፋይናንስ እቅድ ሲሆን ለሚፈለግበት ጊዜ በብዛት የአመት ሊያዝ የታሰበውን ፈንድ መመጠንና

መመደብ ነው፡፡

8.1 የበጀት እቅድ አላማው

 ገቢና ወጪን ለመገመትና ለመመዘን

 የአፈጻጸሙን ፋይናንስ ውጤት ከእቅዱ ጋር ለማወዳደር

 ወጪ በተያዘለት መሠረት ለፕሮጀክት፣ፕሮግራምና ተግባራት እንድናወጣ ያስገድደናል

8.2 የበጀት አዘገጃጀት ሂደቶች

በጀት ሲዘጋጅ ለንከተለው የሚገባ ቅደም ተከተል ወይንም ሂደት ነው፡፡


28
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ
1. በጀት ማዘጋጀት/ማቀድ

2. በጀት ማጸደቅ

3. በጀቱን መተግበር/መልቀቅ

4. ሪፖርት ማድረግ/በጀት ግመግማ

8.3 የበጀት አዘገጃጀት መርሆች

 የበላይ ማናጀሮች ድጋፍና ክትትል

 የሰራተኛው ተሳትፎ

 የድረጅቱ/ቤተ ክርስቲያኒቱ ግብ መግለጫ

 ኃላፊነትን መወጣት

 የድርጅቱ መዋቅር

 ተለዋዋጭ

 ውጤቱን ለበላይ አመራር ሪፖርት ማድረግ

 ተገቢውን የአካውንቲንግ ሲስይስተም መተግበር

29
የቤተ ክርስቲያን አመራር አዘጋጅ፡- ሙሉነህ ጳውሎስ

You might also like