You are on page 1of 19

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤ ፀሐይና ብርሃን ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ፥


ደመናትም ከዝናብ በኋላ ሳይመለሱ፤” መጽሐፈ መክብብ 1 ፥ 12

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ _____ሕብረት መተዳደሪያ ደንብ

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጽያ

መስከረም ፳፻፩፮ ዓ.ም

0|Page
ማውጫ
መግቢያ .........................................................................................................................................................................1
ደንብ አንድ፤ ስያሜ .......................................................................................................................................................2
ደንብ ሁለት፤ ትርጓሜ ....................................................................................................................................................2
ደንብ ሶስት ፤ የሕብረቱ ዓላማና ተግባር ........................................................................................................................2
ደንብ አራት ፤ የሕብረቱመዋቅር ....................................................................................................................................3
ደንብ አምስት ፤ የአባልነት መመዘኛ ..............................................................................................................................3
ደንብ ስድስት ፤ የአባላት መብትና ግዴታ ......................................................................................................................3
6.1 መብት ..................................................................................................................................................................3
6.2 ግዴታ ...................................................................................................................................................................4
ደንብ ሰባት ፤ የጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣንና ተግባር ...........................................................................................................5
ደንብ ስምንት ፤ የሥራ አመራር ጉባዔ ሥልጣንና ተግባር ..............................................................................................5
ደንብ አሥር ፤ በሥራ አመራር ጉባዔ የሰብሳቢ የሥራ ድርሻ ..........................................................................................7
ደንብ አሥራ አንድ ፤ በሥራ አመራር ጉባዔ የምክትል ሰብሳቢ የሥራ ድርሻ ..................................................................8
ደንብ አሥራ ሁለት ፤ በሥራ አመራር ጉባዔ የጸሐፊው የሥራ ድርሻ ..............................................................................8
ደንብ አሥራ ሦስት ፤ በሥራ አመራር ጉባዔው የሒሳብ ክፍል እና ንብረት ተቆጣጣሪ ድርሻ..........................................9
ደንብ አሥራ አራት ፤ በሥራ አመራር ጉባዔ የልማት፣የንድረክ ዝግጅትና የመርሐ ግብር ክፍል የሥራ ድርሻ...............10
ደንብ አሥራ አምስት ፤ በሥራ አመራር ጉባዔ የስልጠና ክፍል የሥራ ድርሻ .................................................................10
ደንብ አሥራ ስድስት ፤ በሥራ አመራር ጉባዔ የመዝሙርና የሥነ-ጥበብ ክፍልየሥራ ድርሻ ........................................11
16.3 የመዝሙር ክፍል ................................................................................................................................................11
16.4 የሥነ-ጥበብ ክፍል ..............................................................................................................................................12
ደንብ አሥራ ሰባት ፤ በሥራ አመራር ጉባዔው የግንኙነት ክፍል የሥራ ድርሻ ..............................................................13
ደንብ አሥራ ዘጠኝ ፤ በኃላፊነት ሊመረጡ የሚችሉ አባላት መመዘኛ ነጥቦች .............................................................13
ደንብ ሃያ ፤ የቅጣት ደረጃዎች ......................................................................................................................................14
ደንብ ሃያ አንድ ፤ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎት ...........................................................................................................................15
21.1 ሥርዓተ-ትምህርት .............................................................................................................................................15
21.2 መምህራን .........................................................................................................................................................15
21.3 መዝሙርና የመዝሙር መሣሪያዎች ....................................................................................................................15
21.4 የንብረት አያያዝ .................................................................................................................................................16
21.5 የሒሳብ ክፍል ....................................................................................................................................................16
21.6 የስብሰባ ጊዜ ......................................................................................................................................................16
ደንብ ሃያ ሁለት ፤ ደንቡ የሚጸናበት ............................................................................................................................16
ደንብ ሃያ ሦስት ፤ ስለደንቡ መሻሻል ............................................................................................................................16
ደንብ ሃያ አራት ፤ የደንቡ የበላይነት ............................................................................................................................16
መግቢያ
መንፈሳዊ አገልግሎት ‹‹መንፈሳዊ (Spiritual)›› እና ‹‹አገልግሎት (Service)›› የሚሉትን ቃላቶች የያዘ
ሲሆን ‹‹መንፈሳዊ›› የሚለው ገላጭ የአገልግሎቱን ዓላማና መሪ የሚያሳይ ነው፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት
ዓላማው የሰው ልጆች ድኅነት ነው፡፡ መሪውም መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ በአጠቃላይ የሰው ልጆች ለመንግስተ
ሰማያት እንዲበቁ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ‹‹መንፈሳዊ አገልግሎት›› ሊባል ይችላል፡፡ ይህም
የሕይወትን ቃል ያላወቁ ወገኖች እንዲያውቁና እንዲያምኑ ማድረግ፣ ያመኑት ደግሞ እንዲጸኑና መንፈሳዊ
ትሩፋትን እንዲሠሩ ማድረግን ያካትታል፡፡

የመንፈሳዊ አገልግሎት መሰረቱ በቅዱሳት መጻሕፍት የተገለጠው የእግዚአብሔር ፈቃድና ፈቃዱን


ለመፈጸም የሚያተጋን አምላካዊ መመሪያ ነው፡፡ ከዘመነ አበው ጀምሮ፣ በዘመነ ኦሪትም በቅዱሳን
አባቶችና ነቢያት አድሮ የመንፈሳዊ አገልግሎት ተልዕኮንና መመሪያን የሰጠው በፍፁም አንድነትና በልዩ
ሦስትነት የሚመሰገን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስም ከሦስቱ አካላት አንዱ
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ተወልዶ፣ ግዕዘ ህፃናትን
ሳያፋልስ በትህትና አድጎ፣ መንፈሳዊ አገልግሎት ምን መምሰል እንዳለበት በተግባር አስተምሮ ለቅዱሳን
ሐዋርያት አብነት የሆነ የአገልግሎት ተልዕኮና መመሪያ ሰጥቷቸዋል፡፡ አብነት የሆነው ተልዕኮ ‹‹እኔ እንደ
በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ›› የሚለው ሲሆን መሪ መመሪያው ደግሞ ‹‹ስለዚህ እንደ እባብ
ልባሞች እንደ ርግብ የዋሆች ሁኑ›› የሚለው ታላቅ ቃል ነው (ማቴ 10፡16)፡፡ ጌታችን ይህንን ተልዕኮና
መመሪያ የሰጠው ለጊዜው ለደቀ መዛሙርቱ ሲሆን ኋላም በእነርሱ እግር ተተክተው በመንፈሳዊ
አገልግሎት ለሚሳተፉ ሁሉ ነው፡፡

በመንፈሳዊ አገልግሎት ተልእኮ ላኪው እግዚአብሔር ነው፡፡ ተልዕኮውን ለመፈጸም ፍላጎት፣ እውቀትና
ክህሎት ቢያስፈልግም ሰው ለመንፈሳዊ አገልግሎት የሚላከው በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ በእውቀቱ
ብዛት አይደለም፡፡ አገልጋይ በሰዎች ጋባዥነት ወደ አገልግሎት ቢቀርብም ሰዎች የተልዕኮው ምክንያት እንጂ
ላኪዎች አይደሉም፡፡ በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ የተልዕኮውን ባለቤት (ላኪውን) ማስተዋል እጅግ
መሰረታዊና የመጀመሪያው ነጥብ ነው፡፡ መልእክተኛ የላኪውን ፈቃድ እንደሚፈጽም ሁሉ መንፈሳዊ
አገልጋይም የጠራውንና የላከውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሊፈጽም እንጂ የራሱን ፈቃድ ወይም የሌሎች
ሰዎችን ፈቃድ ሊፈጽም አይገባም፡፡

1|Page
ደንብ አንድ፤ ስያሜ
ይህ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን _________________
ሕብረት የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ተብሎ ይጠራል።

ደንብ ሁለት፤ ትርጓሜ


2.1 ቤተክርስቲያን ማለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ነው።

2.2 ሕብረት እየተባለ የሚጠራው በኢትዮጽያ ኦ/ተ/ቤ/ክ/ያን ብ አዲስ


አበ__________________________ነው፡፡

2.3 አባል ማለት በሕብረቱ የአባላት ግንኙነት ክፍል ተመዝግቦ አስፈላጊውን መሥፈርት በማሟላት
መደበኛ/ቋሚ/ የሆነ ነው፡፡

2.4 ጠቅላላ ጉባዔ ማለት የሕብረጡ መደበኛ አባላት በሙሉ የሚሳተፉበትና ስለሕብረቱ አጠቃላይ ሁኔታ
የሚወስን አካል ነው፡፡

2.5 የሥራ አመራር ጉባዔ ማለት በጠቅላላ ጉዔው የሚሰየምና የሕብረቱን ሥራ ከበላይ በመሆን የሚመራ
አካል ነው፡፡

2.6 ክፍል ማለት የሕብረቱን መንፈሳዊ አገልግሎት ለማከናወን ይረዳ ዘንድ በሥራ አመራር ጉባዔ
የሚሰየም ክፍል ነው፡፡

2.7 ምድብ ማለት መርሃ ግብር በአመቺ ሁኔታ ለማካሄድ ይቻል ዘንድ ቋሚ የሆኑ አባላት ለአገልግሎት
የሚመደቡበት የአባላት ስብሰብ ነው፡፡

ደንብ ሶስት ፤ የሕብረቱ ዓላማና ተግባር


የሕብረቱ ዓላማና ተግባር ቀጥሎ የተመለከተው ነው፡፡

3.1 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሃይማኖትና ሥርዓት እንዳለ ጠብቆ እንግዳ በሆነ
ትምህርት ሳይለወጥ እና ሳይበረዝ በቀጥታ ለትውልድ ማስተላለፍ።

3.2 ወጥ የሆነ ሁሉን አቀፍ መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት (በዝማሬ፣ በኪነጥበብ፣በትምህርተ ወንጌል)

3.3 በመንፈሳዊ አገልግሎት ልዩ ልዩ ጸጋ ያላቸውን የቤተክርስቲያን ልጆች መሰብሰብ ማደራጀት እንዲሁም


ማገልገል እየቻሉና እየፈልጉ በተለያዩ ሁኔታዎች ለማገልገል ያልችሉ የቤተክርስቲያን ልጆችን ወደ ሰፌ
አገልግሎት እንዲመጡ መንገድ መስጥት።
3.4 ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት ጋር በመነጋገር እና በመቀናጀት ትምህርተ ወንጌልን
በመጽሔት፣ በጋዜጣ፣በበራሪ ጸሑፎች፣በካሴቶች፣በተልዕኮ ትምህርቶች፣ሴሚናሮች፣ዓውደ ጥናቶች እና
በመሳሰሉት እንዲስፋፋ ማድረግ።

3.5 የሕብረቱ አባላት ባላቸው የሙያ ዕውቀት፣ ገንዘብ እና ጉልበት ለቤተክርስቲያኒቱ አገልግሎት
እንዲያበረክቱ ማድረግ እና ማበራታት።

ደንብ አራት ፤ የሕብረቱመዋቅር


4.1 ሕብረቱ ተጠሪነቱ ለደብሩ ሰንበት ት/ቤት ይሆናል ይሆናል፡፡

4.2 ሕብረቱ የራሱ የሆነ ጠቅላላ ጉባዔ ይኖረዋል።

4.3 በጠቅላላ ጉባዔ ሥር ሕብረቱን ሥራ የሚመራ የሥራ አመራር ጉባዔ ይኖረዋል፡፡

4.4 በሥራ አመራር ጉባዔ የሚመራ ልዩ ልዩ ንዑሳን ክፍሎችና ምድቦች ይኖረዋል፡፡

ደንብ አምስት ፤ የአባልነት መመዘኛ


የሕብረቱ አባል ለመሆን የሚችሉት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ለአባልነት የሚያስፈልጉ
መመዘኛ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡

5.1 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የምታወጣውን ማንኛውም መመሪያ ሕግና ደንብ የሚያከብሩ።

5.2 የሕብረቱን የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ፈቃደኛ ሆነው የሚፈጽሙ።

5.3 ሕብረቱን ባላቸው ጊዜ፣ ጉልበት፣ ገንዘብና ዕውቀት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆኑ።

ደንብ ስድስት ፤ የአባላት መብትና ግዴታ

6.1 መብት
6.1.1 ማንኛውም የሕብረቱ አባል ከሕብረቱ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት ሲጠይቅ ለምሳሌ
በቅድስት ቤተክርስቲያን በሥርዓተ ጋብቻውን ሲፈጽም በመንፈስዊ አገልግሎት እንዲታጅብለት ሲጠይቅ፣
አስቀድሞ በጽሑፍ ማመልከቻ ከጠየቀ ይፈቀድለታል፡፡

6.1.2 ማንኛዉም የሕብረቱአባል ቋሚ አባል ከሆነበት ቀን ጀምሮ የመምረጥ መብት አለው፡፡፡

6.1.4 ማንኛውም የሕብረቱ አባል የሕብረቱን መደበኛ ጉባዔያት በማይጋጭ መልኩ ሌሎች
የቤተክርስቲያናችን የሆኑ መንፈሳዊ መርሃ ግብሮችን መካፈል ይችላል፡፡
6.1.5 ማንኛውም የሕብረቱ አባል ስለሕብረቱ የሚሰማውን ማለትም ሕብረቱየሚጠናከርበትንም ሆነ
ደካማ ጐን ለሚመለከተው ክፍል በግንባር ወይም በጽሑፍ በማንኛውም ጊዜ መግለጥ ይችላል፡፡

6.2 ግዴታ
6.2.1 ማንኛውም የሕብረቱ አባል የሕብረቱን የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡

6.2.2 አንድ የሕብረቱ አባል በመደበኛው መርሃ ግብር መቅረት አይፈቀድለትም፡፡ ነገር ግን መገኘት
የማይችልበት ሁኔታ ከአጋጠመው ለሚመለከተው ክፍል በማሳወቅ ይፈቀድለታል፡፡

6.2.3 ማንኛውም የሕብረቱ አባል ችግር ያለበት መሆኑን በማሳወቅ አስቀድሞ ካላስፈቀደ በስተቀር ጉባዔ
አቋርጦ መውጣት አይፈቀድለትም፡፡

6.2.4 አንድ የሕብረቱአባል በመደበኛ የጉባዔ ቀን ጉባዔውን የተካፈለ ለመሆኑ ማረጋገጫ በስም
መቆጣጠሪያው ላይ ምልክት ማስደረግ አለበት፡፡

6.2.5 ለረጅም ጊዜ በተለያየ ምክንያት ራቅ ብሎ የሚሄድ አባል ወይም የሕብረቱ አባል መደበኛ ጉባዔ
ወቅት በትምህርት፣ በሥራ ወይም በቤተሰብ ችግር ምክንያት ለረዥም ጊዜ መካፈል የማይችል ከሆነ
እስኪመጣ ድረስ ወይም ችግሩ እስኪቃለልለት ድረስ በአባልነት ለመቆየት እንዲፈቀድለት የሚመለከተውን
ክፍል መጠየቅና ፈቃድ ማግኘት አለበት፡፡

6.2.6 ማንኛውም አባል በሕብረቱየሚሰጡትን ሥልጠናዎች ልምምዶች ቋሚ ደብተር አዘጋጅቶ መጻፍና


በጥንቃቄ መያዝ አለበት፡፡

6.2.7 አንድ አባል ከሚመለከተው የሕብረቱክፍል ፈቃድ ከአላገኘ በስተቀር ሕብረቱን ወክሎ በማንኛውም
ቦታና ጊዜ ስብከት ማሰማት፣ መንፈሳዊ ዝግጅቶችን ማቅረብ፣ መዝሙር መዘመር አይችልም፡፡

6.2.8 በማንኛውም ወቅት ማንኛውም የሕብረቱአባል ከበሕብረቱ ቤቱ ካልተወከለ በቀር በሕብረቱ ስም


ከሌሎች ማሕበራትም ሆኑ ሕብረቶች ጋር እና ከሌሎች ግለሰቦች ጋር ግንኙነት ማድረግ ወይም ቋሚ እና
ተንቀሳቃሽ ንብረት መዋስም ሆነ ማዋስ አይችልም፡፡

6.2.9 ማንኛውም የሕብረቱ አባል በጠቅላላ ጉባዔ የሚወሰነውን ወርኃዊ መዋጮ ወቅቱን ጠብቆ መክፈል
አለበት፡፡

6.2.10 ማንኛውም የሕብረቱ አባል ንዑሳን ክፍሎችና ምድቦች በሚያቀርቡለት ጥሪ መሠረት መገኘትና
በሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት መሳተፍ አለበት፡፡

6.2.11 ማንኛውም የሕብረቱ አባል የሕብረቱን መርሃ ግብር ለማሰናከል ከውጭ መጥተው የማይገባ
ሥርዓት ከሚያሳዩ ግለሰቦች ጋር ምንም ዓይነት ጓደኝነት ወይም ዝምድና ቢኖር እንኳ በመጥፎ
ተግባራቸው መተባበር በሕብረቱ በኩል የተከለከለ ነው፡፡
6.2.12 የሕብረቱ የስራ አመራር አባላት በግልም ሆነ በጋራ በፖለቲካ መድረክ ላይ ሕብረቱን ወክለው
መሳተፍ አይችሉም።

6.2.13 የሕብረቱ አባላት የፖለቲካ አቋማቸውን (አስተሳሰባቸውን) በሰንበት ት/ቤትም ሆነ በቤተክርስቲያን


አገልግሎት ውስጥ ማንፀባረቅ አይችሉም።

6.2.14 የሕብረቱ አባላት ለደብሩ ሰንበት ት/ቤትየአገልግሎት ጥያቄ የመተባበር ግዴታ አለባቸው፡፡

6.2.15 እያንዳንዱ የ ሕብረቱ ዓባል በአባላት መካከል የመግባባት እና የመተባበር ስሜት እንዲዳብር
ማድረግ።

ደንብ ሰባት ፤ የጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣንና ተግባር


ሕብረቱ የአባልነት መመዘኛ አሟልተው በተመዘገቡት አባላት የተመሠረተው ጠቅላላ ጉባኤ የሚከተለው
ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል፡፡

7.1 ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ወይም እንደአስፈላጊነቱ በየ6 ወሩ የደብሩ ሰንበት ት/ቤትተወካይ
በተገኙበት አጠቃላይ ስብሰባ ያደርጋል፡፡

7.2 የሕብረቱን የሥራ ሂደት ከሥራ አመራር በሚቀርበው ሪፖርት መሠረት ይገመግማል፡፡

7.3 የሕብረቱን የሥራ ዕቅድ ያጸድቃል፡፡

7.4 የሕብረቱን አጠ ቃላይ ጉዳዮች ይወስናል፡፡

7.5 የሥራ አመራር ጉባዔ አባላትን በሕብረቱ የምርጫ ሥነ ሥርዓት ደንብ መሠረት ይመርጣል፡፡

7.6 በደብሩ ሰንበት ት/ቤትበኩል ሲጠየቅ የሕብረቱ ተወካይ የሥራ አመራር ጉባዔ በሚያቀርብለት ዕጩ
መሠረት ይመርጣል፡፡ አሳማኝ ሆኖ ሲያገኝ ሥራ አመራሩ ለጠቅላላ ጉባኤው አቅርቦ እንዲሻሻል ያደርጋል።

7.7 ሕብረቱ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው እንዲሻሻል ጥያቄ ያቀርባል።

7.8 ከጠቅላላው ጉባኤ 2/3 አባላት የተገኙበት ጠቅላላ ስብሰባ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል ውሳኔዎችንም
ማሳለፍ ይችላል።

ደንብ ስምንት ፤ የሥራ አመራር ጉባዔ ሥልጣንና ተግባር


በጠቅላላ ጉባዔ የተመረጠው የሥራ አመራር ጉባዔ የሚከተለው ሥልጣንና ተግባር ወይም አገልግሎት
ይኖረዋል፡፡

8.1 ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤው ይሆናል


8.2 አጠቃላይ የሕብረቱ ሥራ ወይም አገልግሎት ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፣ ይመራል፡፡

8.3 በሥሩ ያሉትን ክፍሎችና ምድቦች ተግባራቸውን በበቂ ሁኔታ ማከናወናቸውን ይገመግማል፣ አስፈላጊ
ሆኖ ሲገኝ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመተባበር የክፍል የምድብ አባላትን ይመርጣል፣ ይመድባል፡፡

8.4 በሥራ ወይም በአገልግሎት ሂደት ለሚከሰቱ ችግሮች እንደአስፈላጊነቱ ሰንበት ት/ቤትና ከሚመለከትው
ክፍል ጋር በመነጋገር መፍትሔ ይፈልጋል፡፡

8.5 አስፈላጊ ሆኖ ባገኘው ጊዜ የጠቅላላ ጉባዔውን ስብስባ ይጠራል፣ የመወያያ አጀንዳ ያዘጋጃል፡፡

8.6 የጠቅላላ ጉባዔውን ውሳኔዎች ተግባራዊ ያደርጋል፣ ያስደርጋል(ያስፈጽማል)፡፡

8.7 ስለ ሕብረቱ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ በዓመት ውስጥ ሁለት ጊዜ በስብሰባ ለጠቅላላ ጉባዔው ገለጻ
ያደርጋል፡፡

8.8 የክፍሎችንና ምድቦችን የሥራ መመሪያ ያወጣል፣ መሻሻል በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ከሚመለከታቸው


ክፍሎች ጋር በመወያየት ያሻሽላል፡፡

8.9 ሕብረቱ ገንዘብ ወጪና ገቢ ይወስናል፣ በሥራ ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል።

8.10 ተጠሪነታቸው ለሕብረቱ የሥራ አመራር ጉባዔ የሆኑ ልዩ ልዩ ጊዜዊም ሆነ ቋሚ ኮሚቴዎችን


እንደአስፈላጊነቱ ያዋቅራል፡፡

ደንብ ዘጠኝ ፤ የሥራ አመራር ጉባዔ ዓይነትና ብዛት

9.1 የሕብረቱ የሥራ አመራር ጉባዔ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡፡

9.1.1 ሰብሳቢ

9.1.2 ምክትል ሰብሳቢ

9.1.3 ጸሐፊ

9.1.4 ስልጠና ክፍል

9.1.5 የአባላት ግንኙነት

9.1.6 መዝሙር እና ሥነ ጥበባት

9.1.7 ሒሳብ ክፍል ኋላፊ/ ንብረት ተቆጣጣሪ


9.1.8. የመድረክ ዝግጅትና የመርሀ ግብር ቅንብር

እነዚህን አባላት የሚመርጠው ጠቅላላ ጉባዔው ሲሆን ከላይ የተዘረዘረውን የሥራ ክፍፍል የሚያደርጉት
ውስጥ እርስ በእርሳቸው ናቸው፡፡

9.2 የሥራ አመራር ጉባዔ ምርጫ የሚከናወነው በሕብረቱ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ነው።

9.4 የሥራ አመራር ጉባዔ የአገልግሎት ዘመን ሁለት /2/ ዓመት ብቻ ነወ፡፡ አንድ አባል በጠቅላላ ጉባዔው
ከታመነበት ሌላ የምርጫ ዘመን በድጋሚ ሊመረጥ ይችላል፡፡

9.5 ሁለት የምርጫ ዘመን በተከታታይ ያገለገለ የሕብረቱ አባል አንድ የምርጫ ዘመን አርፎ እንደገና
መመረጥ ይችላል።

9.6 በልዩ ልዩ ምክንያት ማገልገለ ባልቻሉ የሥራ አመራር ጉባዔ አባላት ከተጠባባቂዎች ይተካል፡፡
የአገልግሎት ዘመኑ ሳያልቅ ተጠባባቂዎች በሙሉ ከገቡ የጐደሉትን የሥራ አመራር አባላት ጠቅላላ ጉባዔው
ያስመርጣል።

ደንብ አሥር ፤ በሥራ አመራር ጉባዔ የሰብሳቢ የሥራ ድርሻ


10.1 የሥራ አመራር ጉባዔንና ጠቅላላ ጉባዔን በሰብሳቢነት ይመራል፡፡

10.2 የጠቅላላ ጉባዔውንና የሥራ አመራር ጉባዔውን ውሳኔዎች ለሚመለከታቸው ሁሉ ያስተላልፋል፣


ተግባራዊ ለመሆኑም ክትትል ያደርጋል፡፡

10.3 አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በአስቸኳይ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ከመደበኛ ስብሰባ ውጭ የሥራ አመራር ጉባዔ
አባላትን በመጥራት ስብሰባ እንዲካሄድ ያደርጋል፡፡

10.4 የሥራ አመራር ጉባዔው አባላት የተሰጣቸውን የሥራ ድርሻና ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት
አለመወጣታቸውንና ጠቅላላ የሕብረቱን አስተዳደራዊ ሥራ ይቆጣጠራል፡፡

10.5 በልዩ ልዩ ጉባዔዎች ላይ እንደአስፈላጊነቱ ሕብረቱን ወክሎ ይገኛል፡፡

10.6 የሥራ አመራር ጉባዔው በውሳኔ ያጸደቃቸውን በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፡፡

10.7 በማንኛውም ስብሰባ ወቅት በውሳኔ አሰጣጥ በኩል እኩል ድምጽ በሚሆንበት ጊዜ ሊቀመንበሩ
የደገፈው ሐሳብ ይወስናል፡፡
ደንብ አሥራ አንድ ፤ በሥራ አመራር ጉባዔ የምክትል ሰብሳቢ የሥራ
ድርሻ
11.1 ተጠሪነቱ ለሰብሳቢው ነው።

11.2 የሰብሳቢው የቅርብ ረዳት ወይም አማካሪ በመሆን ይሠራል፡፡

11.3 ሰብሳቢው በማይኖርበት ጊዜ ተክቶ ይሰራል፡፡

11.4 የክፍሎችን ስራ ይቆጣጠራል፡፡

ደንብ አሥራ ሁለት ፤ በሥራ አመራር ጉባዔ የጸሐፊው የሥራ ድርሻ


12.1 ተጠሪነቱ ለሰብሳቢው ነው።

12.2 ሰብሳቢው እና ምክትል ሰብሳቢው በማይኖሩበት ጊዜ ተክቶ ይሠራል።

12.3 በጠቅላላ ጉባዔውም በሆነ በሥራ አመራር ጉባዔ ላይ ቃለ ጉባዔ ይይዛል፣ በውሳኔውም ላይ
የጉባዔውን አባላት ያስፈርማል፡፡

12.4 ከሥራ አመራር ጉባዔና ከጠቅላላ ጉባዔ አባላት የሚቀርቡ ጠቃሚ ሐሳቦችን በአጀንዳዎች ያዘጋጃል፡፡

12.5 የሥራ አመራር ጉባዔውን ውሳኔ ለሚመለከተው ክፍል በሰብሳቢው ፊርማ በጽሑፍም ሆነ በቃል
ያሳውቃል።

12.6 የጽ/ቤቱ ንብረቶችን፣ መሣሪያዎችን፣ መዛግብትንና ሰነዶችን እንዲሁም ልዩ ልዩ የማኅደር ጉዳዮችን


በጥንቃቄ ይይዛል፣ በአግባቡ ይጠቀማል፡፡

12.7 ለሕብረቱ የሚመጡትን ደብዳቤዎች ተቀብሎ እንደ አስፈላጊነቱ በሥራ አመራር ጉባዔ ላይ ያቀርባል፡፡

12.8 በመደበኛ የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ወቅትና በሕብረቱ ዓመታዊ በዓል እንዲሁም አስፈላጊ በሆነ ልዩ ልዩ
በዓላት ሁሉ የሕብረቱን የሥራ ሂደት በሪፖርት መልክ አርቅቆ በሥራ አመራር አጽድቆ ያቀርባል፡፡

12.9 የሥራ አመራር ጉባዔውን የስብሰባ ወቅት ላለመሻማት ሲባል ቀላል በሆኑ የተለመዶ ሥራዎች ላይ
ውሳኔ ይሰጣል፡፡

12.10 የሥራ አመራር ጉባዔውን የረጅምና የአጭር ጊዜ ዕቅድ በየወቅቱ በማስታወስ ተፈጻሚ እንዲሆን
ያደርጋል።
ደንብ አሥራ ሦስት ፤ በሥራ አመራር ጉባዔው የሒሳብ ክፍል እና ንብረት
ተቆጣጣሪ ድርሻ
13.1 ተጠሪነቱ ለጽ/ቤት ነው።

13.2 የክፈሉን ዕቅድ እና ሪፖርት ያዘጋጃል።

13.3 የሒሳብ ክፍል

13.3.1 በሕብረቱ የተፈቀደለትን እና በጠቅላላ ጉባኤ የፀደቀውን በጀት ስራ ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል።

13.3.2 የሕብረቱ ሒሳብ ነክ እንቅስቃሴ /ገቢና ወጪ/ ይቆጣጠራል፣ የሕብረቱቤቱን ተንቀሳቃሽ፣ ቋሚና
አላቂ ንብረት በንብረት መዝገብ መዝግቦ በኃላፊነት ይቆጣጣራል ፡፡ ይህ ክፍል በሥሩ ሁለት ንዑሳን
ክፍሎች በሥራ አመራሩ በኩል ይመደብለታል።

13.3.3 ከአባላት የወራኋዊ መዋጮ ይሰበስባል።

13.3.4 ከልዩ ልዩ ዝግጅቶችና ከተለያዩ ንዑሳን ክፍል የሚገኘውን ለሕብረቱ ሒሳብ ክፍል በወቅቱ በደረሰኝ
ገቢ መሆናቸውን ይቆጣጠራል።

13.3.5 የሥራ አመራር ጉባዔው የፈቀደውን ወጪ በወጪ ማዘዣ ላይ ይሞላል። በገንዘብ ያዥ በኩል
እንዲከፍል ያዛል፡፡

13.3.6 ሕብረቱ በግዥም ሆነ በእርዳታ በሚያገኛቸው ንብረቶች በንዑሳን ክፍሎችና በኩል በአግባቡ
መቀመጣቸውን ይቆጣጠራል፡፡

13.3.7 ገንዘብ ወጪ የተደረገለት ክፍል/አካል/ የሚያቀርበውን የገንዘብ ማወራረጃ ቅጽ በመመርመር


የተፈቀደውን ገንዘብ በአግባቡ በሥራ ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል፡፡

13.3.8 የሒሳብ ደረሰኞችን ማወራረጃዎችንና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን በጥንቃቄ ያስቀምጣል።

13.3.9 የሕብረቱን ሒሳብ አያያዝና የገንዘብ መጠን የሚገልጽ ሪፖርት በማዘጋጀት በየሦስት ወሩ ለሥራ
አመራር ጉባዔው ያሳውቃል፡፡

13.4 ንብረት ተቆጣጣሪ

13.4.1 በዓመት አንድ ጊዜ የንብረት ቆጠራ አድርጐ የሕብረቱን ንብረት ዓይነት ብዛት የሚገልጽ ሪፖርት
በማዘጋጀት ለሥራ አመራር ጉባዔው ሪፖርት ያደርጋል፡፡
13.4.2 እንደአስፈላጊነቱ በሕብረቱ የሥራ አመራር ጉባዔ ለሚወክል ኦዲተር /መርማሪ/ ስለሂሳብ አሠራሩ
ገለጻ ያደርጋል፣ ሒሳቡን ያስመረምራል፡፡

13.4.3 በሥራ አመራር ጉባዔው ሲታዘዝ ከተለያዩ የሕብረቱቤቶችና ሌሎች አካላት ለሚቀርቡ ሒሳቡ ነክ
ጥያቄዎች አስፈላጊውን መልስና ሙያዊ መብራሪያ ይሰጣል፡፡

13.4.4 ንዑሳን ክፍሎችም በእጃቸው ካለው ገንዘብ ምንም ዓይነት ወጪ እንዳያደርጉ ይቆጣጠራል፡

13.4.5 አገልግሎት በመስጠት የተበላሹ ከጥቅም ውጭ የሆኑ ንብረቶች ሲኖሩ ለሥራ አመራር ጉባዔው በቂ
መረጃ በመስጠት እንዲጠገኑ ወይም በምትካቸው ሌላ እንዲገዛ ያደርጋል፡፡ ያለአግባብ የባከኑ፣ የጠፉ
ወይም የተሰበሩ ንብረቶች ካሉም ለሥራ አመራር ጉባዔው ሪፖርት በማድረግ ውሳኔ እንዲሰጣቸው
ያደርጋል፡፡

ደንብ አሥራ አራት ፤ በሥራ አመራር ጉባዔ የልማት፣የንድረክ ዝግጅትና


የመርሐ ግብር ክፍል የሥራ ድርሻ
14.1 ተጠሪነቱ ለጽ/ቤት ነው።

14.2 የክፈሉን ዕቅድ እና ሪፖርት ያዘጋጃል።

14.3 የሕብረቱን ሙያ ነክ ሥራዎች ይሠራል፣ ያሠራል፡፡

14.4 በሕብረቱ ወይም በሕብረቱአማካይነት በሚደረጉ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ይሳተፋል፡፡ ከዚህም
ጋር በማያያዝ በሕብረቱ ኃላፊነት መንፈሳዊ ጉዞ መርሃ ግብሮችን ይነድፋል፣ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል
ያስፈጽማል፡፡

14.5 ሕብረቱ ገቢ የሚያገኝበትን መንገድን ያመቻቻል፣ ለተግባራዊነቱም ጥረት ያደርጋል።

14.7 ሕብረቱ ለሽያጭ የሚያዘጋጀውን ንዋያተ ቅዱሳትም ሆነ ሌሎች መንፈሳዊ ቁሳቁሶች ተረክቦ ይሸጣል።

14.8 ለክፍሉ የሚያስፈልጉትን መገልገያ ቁሳቁሶችን ያሟላል።

14.10 በየሦስት ወሩ ለጽ/ቤት የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ያቀርባል።

14.11 በክፍሉ የሚገኙትን ማንኛውንም ንብረቶች በጥንቃቄና በሥርዓት ይይዛል።

ደንብ አሥራ አምስት ፤ በሥራ አመራር ጉባዔ የስልጠና ክፍል የሥራ ድርሻ
15.1 ተጠሪነቱ ለጽ/ቤት ነው።

15.2 የክፈሉን ዕቅድ እና ሪፖርት ያዘጋጃል።


15.3 አገልግሎትን በሚመለከት እንዲሁም ጠቃሚ ስልጠናዎችን ለአባላት እንዲዳረስ ያደርጋል።

15.4 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን እምነት ሥር የሚገኙ መምህራንን በሕብረትቱ ጉባኤ ላይ ከደብሩ ሰንበት


ት/ቤት ጋር በመነጋገር ትምህርት እንዲሰጡ ያደርጋል።

15.5 በተለያዩ ርዕሶች ላይ ትምህርታዊ ሴሚናሮች፣ ስልጠናዎችን ያዘጋጃል

15.6 ትምህርታዊ ጽሑፎችን በተለያዩ የቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት እንዲዘጋጅና እንዲታተም ያደርጋል።

15.7 የሕብረቱ መርኃ ግብር ላይ መርሐ ግብር መሪ ያዘጋጃል።

15.8 የአባላቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀትና የቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ትምህርት ይበልጥ ለማጠናከር
መንፈሳዊ ስልጥናዎችን እንዲሰጡ ያደርጋል።

15.10 የክፍሉን እንቅስቃሴ በየሦስት ወሩ ለጽ/ቤት በጽሑፍ ሪፖርት ያደርጋል።

15.11 በክፍሉ የሚገኙትን ንብረቶችን በጥንቃቄ እና በሥርዓት ይይዛል።

15.12 ለ ሕብረቱ አባላት በሀዘንም ሆነ በደስታ ጊዜ በመገኘት ትምህርት እንዲሰጥ ያደርጋል።

15.14 የማሕበሩን ድረ ገጽ እና ሌሎች የመገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም መንፈሳዊ አገልጎት እንዲሰጥ


ያደርጋል።

ደንብ አሥራ ስድስት ፤ በሥራ አመራር ጉባዔ የመዝሙርና የሥነ-ጥበብ


ክፍልየሥራ ድርሻ
16.1 ተጠሪነቱ ለጽ/ቤት ነው።

16.2 የክፈሉን ዕቅድ እና ሪፖርት ያዘጋጃል።

16.3 የመዝሙር ክፍል


16.3.1 በሕብረቱ ውስጥ የሚዘመሩት መዝሙራት የቤተክርስቲያናችን የዜማ ደራሲ ቅዱስ ያሬድ
ያወጣውን የዜማ ስልት የተከተሉ ብቻ ሲሆኑ ሕብረቱ የሚጠቀምባቸው የዜማ መሣሪያዎችም በቅዱስ
ሲኖዶስ የተወሰኑት ትውፊታዊ የዜማ መሣሪያዎች ብቻ ይሆናሉ፡፡ መዝሙር ክፍሉም ተፈጻሚነቱንም
ለማረጋገጥ በኃላፊነት ይቆጣጠራል፣ ይመራል፡፡

16.3.2 ከስልጠና ክፍል ጋር በመተባበር መዝሙር እና ምሥጢራዊ ሥርዓቱን ለአባላቱ እንዲሰጥ ማድረግ።
16.3.4 በሕብረቱ ልዩ መርሀ ግብር፣ በአዳራሽ ወይም በቤተክርስቲያኑ ዓውደ ምህረት ላይ የሚቀርቡ
መዝሙራት ከመቅረባቸው በፊት በሙያው በቂ እውቀት ያላቸውን ሊቃውንት በማሳየት እንዲቀርቡ
ማድረግ።

16.3.6 የመዘምራንን መዝሙራትን በካሴት ቀርጾ ያስቀምጣል።

16.3.8 ማንኛውም ዘማሪ መዝሙር ለማቅረብ ወደ ዓውደ ምህረት ላይ በሚወጣበት/ በምትወጣበት ጊዜ


መላ ሰውነቱ/ሰውነቷ ኦርቶዶክሳዊ መልክ እንዲኖረው በተጨማሪም ለቦታው የማይገባ አለባበስ እና
ጌጣጌጥ እንዳይታይ ይቆጣጠራል።

16.3.9 የቤተክርስቲያኑን ድረ ገጽ እና ሌሎች የመገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም ከደብሩ ሊቃውንት ጋር


እንዲሁም ከሥራ አመራር ጋር በመተባበር ለምዕመናን መዝሙራት እንዲዳረሱ ያደርጋል።

16.3.10 የክፍሉን እንቅስቃሴ በየሦስት ወሩ ለጽ/ቤት በጽሑፍ ሪፖርት ያደርጋል።

16.4 የሥነ-ጥበብ ክፍል


16.4.1 በሕብረቱ ውስጥ የሚቀርቡትን የሥነ-ጽሑፍ ሥራዎች እንዲሁም ተውኔቶች በጥንቃቄ መዝገብ
ላይ ያስቀምጣል፡፡

16.4.2 ሥነጽሑፍና ተውኔት ያዘጋጃል።

16.4.3 በሕሕብረቱ ትዕዛዝ ሥነ ጽሑፎችንና ተውኔቶችን የተለያዩ ሰ/ት/ቤቶች በሚጠይቁበት ጊዜ አባዝቶ


ይስጣል።

16.4.4 በመደበኛ ጉባኤ ላይ ሥነ ጽሑፍ ያቀርባል።

16.4.5 ተውኔቶችን በማሳየት፣ ሲዲ እንዲሁም የመዝሙር መድብል በማዘጋጀት ለሕብረቱ ገቢ ያደርጋል።

16.4.6 የተውኔት መስሪያ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን በተለያዩ መንገድ እንዲሟሉ ማድረግ።

16.4.7 የአባላቱን የመጻፍም ሆነ ተውኔት የመስራት ሁኔታ ያበረታታል።

16.4.8 በኢትዮጵያ ከሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች ጋር በመቀራረብ የተውኔት ጽሑፎችን ያሰባስባል።

16.4.9 የክፍሉን እንቅስቃሴ በየሦስት ወሩ ለጽ/ቤት በጽሑፍ ሪፖርት ያደርጋል።


ደንብ አሥራ ሰባት ፤ በሥራ አመራር ጉባዔው የግንኙነት ክፍል የሥራ
ድርሻ
18.1 ተጠሪነቱ ለጽ/ቤት ነው።

18.2 የክፈሉን ዕቅድ እና ሪፖርት ያዘጋጃል።

18.3 ወደ ሕብረቱ የሚመጡትን አባላት ተቀብሎ በመመዝገብ ትምህርት እንዲከታተሉ በማድረግና


የሰ/ትቤቱን ህግ በማሳወቅ ቋሚ አባል ያደርጋል።

18.4 ከአባላት ጋር የቅርብ ግንኙነት እያደረገ ችግራቸውን ለመፍታት ጥረት ያደርጋል፣የመፍትሄ ሀሳብም
ይሰበስባል።

18.5 ከሕብረቱ የራቁ አባላትን ከሕብረቱ ሊያርቃቸው የቻለውን ዋና ዋና ምክንያት በማጥናት


የሚመለሱበትን መንገድ ያመቻቻል።

18.6 ከስራ አመራሩ ጋር በመነጋገር ማንኛውንም የሕብረቱን ጉዞ በመቀናጀት ይመራል።

18.7 ሕብረቱ ከተለያዩ ሰ/ት/ቤቶችና ማኅበራት ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖረው ሁነታዎችን ያመቻቻል።

18.8 በክፍሉ የሚገኙትን ንብረቶች በጥንቃቄና በሥርዓት ይይዛል።

18.9 የሕብረቱ አባል አደጋ ወይም ኃዘን ቢደርስበት አባላቱን በማስተባበር እንዲገኙ ያደርጋል።

18.10 በበዓላት እና ሕብረቱ ጋብዟቸው ከሌላ ቦታ የሚመጡትን እንግዶች ይቀበላል፣ የምግብ መስተንግዶ
ያደርጋል።

18.11 በሕብረቱ ለሚዘጋጅ ልዩ ዝግጅት ከጽ/ቤት ሲታዘዝ የጸበል ጸዲቅ ዝግጅት ያደርጋል።

18.12 የአባላት የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲጠናከር ልዩ ልዩ መርሀ ግብሮችን ያዘጋጃል።

18.13 የክፍሉን እንቅስቃሴ በየሦስት ወሩ ለጽ/ቤት በጽሑፍ ሪፖርት ያደርጋል።

ደንብ አሥራ ዘጠኝ ፤ በኃላፊነት ሊመረጡ የሚችሉ አባላት መመዘኛ


ነጥቦች
19.1 የሥራ አመራር ጉባዔ አባላት ሊሆኑ የሚችሉ ፤

19.3.1 በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሐይማኖቱ/ቷ/ ጽኑዕ የሆነ/ች/፣ በግብረ ገብነቱ/ቷ/ የተመሰከረለት/ላት/ ፤

19.3.2 የሕብረቱን መተዳደሪያ ደንብ ጠብቆ/ቃ ማስጠበቅ የሚችል /የምትችል/ ፤


19.3.3 እድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች/ ፤

19.3.4 ከሶስት ዓመት በላይ በሕብረቱቤቱ አባልነት የቆየ/ች/ ፤

19.3.5 አዲስ አማኝ ከሆነ/ች/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሐይማኖትን ከተቀበለ/ች/ አምስት ዓመትና
ከዚያም በላይ የሆነው /የሆናት/ ፤

19.3.6 ለአገልግሎት በቂ ጊዜ ያለው/ያላት/ ፤

19.2 የንዑሳን ክፍሎች አባላት ሊሆኑ የሚችሉት ፤

19.2.1 በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሐይማኖቱ/ቷ/ ጽኑዕ የሆነ/ች/፣ እንዲሁም በግብረ ገብነቱ/ቷ/


የተመሰከረለት/ላት/ ፤

19.3 የአስመራጭ ክፍል አባላት ሊሆኑ የሚችሉ ፤

19.5.1 በሕብረቱቤቱ አባልነት ከሁለት ዓመት በላይ ያገለገለ/ች/ እና ለታማኝነቱ/ቷ/ የተመሰከረለት/ላት/ ፤

19.5.2 ለሥራ አመራር ጉባዔ በእጩነት የማይቀርብ /የማትቀርብ/ ፤

19.5.3 የተሰጠውን/የተሰጣትን/ ኃላፊነት በብቃት በጥራት መወጣት የሚችል/የምትችል/ ፤

19.5.4 የአባላቱን መንፈሳዊ ጥንካሬና ብስለት የሚያውቅ/የምታውቅ ፤

19.5.5 ከዚህ ቀደም በአስመራጭ ኮሚቴ ወይም በሌላ ተመሳሳይ የኮሚቴ አገልግሎት ላይ ተሳትፎ/ተሳትፋ
የነበረ ፤

19.5.6 የሕብረቱን የውስጥ መተዳደሪያ ደንብን በሚገባ የተረዳች/የተረዳ ፤

ደንብ ሃያ ፤ የቅጣት ደረጃዎች


ማንኛውም የሕብረቱ አባል በቃለ ዓዋዲውና በዚህ ውስጠ ደንብ ላይ የተደነገገውን ተላልፎ ቢገኝ ፤

20.1 ለመጀመሪያ ጊዜ በአባላት እና ግንኙነት ክፍል ምክር ይሰጠዋል፡፡

20.2 ለሁለተኛ ጊዜ ጥፋት ከፈጸመ በሥራ አመራር ጉባዔው በኩል ምክርና ግሳጻ ይሰጠዋል፡፡

20.3 አሁንም በተሰጠው ምክርና ተግሳጽ የማይታረም ሆኖ ከተገኘና ለሦስተኛ ጊዜ ጥፋት ከፈጸመ በምክረ
አበው ክፈል የመጨረሻ ምክርና ተግሳጽ እንዲሁም ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡
20.4 ከላይ ደረጃ በደረጃ የተሰጡት ምክርና ማስጠንቀቂያዎች በጽሑፍ በዝርዝር ተይዘው በአባሉ የግል
ማኅደር እንዲቀመጡ ይደረጋል፡፡

20.5 በእነኝህ የቅጣት ደረጃዎች በጥፋቱ የማይመለስ ከሆነ እና አራተኛ ጊዜ ሲያጠፋ ከተገኘ ከሕብረቱ
ይሰናበታል፡፡ ውሳኔውንም የሕብረቱ አጠቃላይ ጉባዔ፣ የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ጽ/ቤት እንዲያውቁት
ይደረጋል፡፡

ደንብ ሃያ አንድ ፤ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎት

21.1 ሥርዓተ-ትምህርት
ሕብረቱ አባላቱን በዕድሜና በዕውቀታቸው መጠን ከፋፍሎ በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች የሚያስተምር ሲሆን
ለሕፃናት ፣ ለእንግዶችና ለወጣቶች የሚመጥን ሥልጠና በሕብረቱ ትምህርት ክፍል ይቀረጻል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ እንደአስፈላጊነቱ ልዩ ልዩ ወቅታዊ ሴሚኖሮች በስልጠና ክፍሉ ተዘጋጀተው በሥራ መራር
ጉባዔው ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡

21.2 መምህራን
በሕብረቱ የሚያስተምሩ መምህራን ፤

21.2.1 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዋ ተልዕኮ መምሪያ
ወይም በሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል መምሪያ በኩል እንዲያስተምሩ የተፈቀደላቸውን ሰባኪያን ፤

21.2.2 የደብሩ የስብከተ ወንጌል ኃላፊና የአብነት መምህራን ፤

21.2.3 በሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤት ማደረጃ መምሪያ ለሕብረቱ የተመደበው መምህር ፤

21.2.5 የሕብረቱ የትምህርት ክፍል አምኖባቸው የሚጋብዛቸው ታዋቂ መምህራን ፤

21.2.6 ከቤተክርስቲያኒቱ ኮሌጆችና ከፍተኛ ትምህርት ቤቶች የተመረቁና በትምህርት ክፍሉ የታመነባቸው
ናቸው፡፡

21.3 መዝሙርና የመዝሙር መሣሪያዎች


ሕብረቱ የሚጠቀምባቸው የመዝሙር መሣሪያዎች በቅዱሳት መጻሕፍት የተረቀቁና እስካሁንም
ቤተክርስቲያናችን ስትገለገልባቸው የቆዩት (የኖሩት) የመዝሙር መሣሪያዎች ከበሮ፣ጸናጽል፣ መቋሚያ
ሲሆኑ በተጨማሪም በገና፣መሰንቆ፣ዋሽንት፣መለከት እና እንዚራ ናቸው። እነዚህ መሣሪዎች እንዳሉ
መጠበቅ እና መንከባከብ።
21.4 የንብረት አያያዝ
ሕብረቱ በግዥም ሆነ በእርዳታ የሚያገኛቸውን ተንቀሳቃሽ፣ ቋሚና ያላቂ ንብረቶች የንብረት ክፍል
ኃላፊው በንብረት መመዝገቢያ መዝግቦ ያስቀምጣል፡፡ ንብረቶቹ እንደአስፈላጊነቱ በልዩ ልዩ ክፍሎችም ሆነ
የምድብ ተጠሪዎች እጅ ሊቀመጡ ቢችሉም ለሕብረቱ ንብረት በኃላፊነት ሊጠየቅ የሚችለው የንብረት
ክፍል ኃላፊው ነው፡፡

21.5 የሒሳብ ክፍል


የሕብረቱ የሥራ ማስኬጃ ገንዘብ በገቢም ሆነ በወጪ ጊዜ የሥራ አመራር ጉባዔው ውሳኔ የግድ አስፈላጊ
ይሆናል፡፡ ገንዘቡ በጽ/ቤቱ የሚቀመጥ ሲሆን በኃላፊነት ሊጠየቅ የሚችለው ገንዘብ ያዥ ነው፡፡

21.6 የስብሰባ ጊዜ
የሕብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራ ለማከናወን በኃላፊነት የሚያገለግሉት አባላት ስብሰባ ማድረግ አስፈላጊ
በመሆኑ የሥራ አመራር ጉባዔው በ 2 ሳምንት አንድ ጊዜ ስብሰባ ሲያደርግ እያንዳንዱ ንዑስ ክፍል
በሳምንት ቢያንስ አንድ ጊዜ መሰብሰብ ይኖርበታል፡፡

ደንብ ሃያ ሁለት ፤ ደንቡ የሚጸናበት


ይህ ደንብ ለሕብረቱብጠቅላላ ጉባዔ ቀርቦ ከታየ በኋላ ጸድቆ ካለፈበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

ደንብ ሃያ ሦስት ፤ ስለደንቡ መሻሻል


ይህ ደንብ እንዲሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና የጠቅላላ ጉባዔው አባላት ከግማሽ በላይ ሲስማሙበት በሥራ
አመራር ጉባዔው አዲስ ደንብ ተረቅቆ ለጠቅላላ ጉባዔው ከቀረበ በኋላ ሲጸድቅ የቀድሞ መመሪያ ሊሻሻል
ወይም ሊለወጥ ይችላል፡፡

ደንብ ሃያ አራት ፤ የደንቡ የበላይነት


ይህ ደንብ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች መመሪያ ይሆን ዘንድ በቅዱስ ሲኖዶስ ከወጣው ውሰጠ ደንብ
በመቀጠል በሕብረቱ ከሚገኙ ሌሎች የውስጥ ደንቦችና መመሪያዎች ሁሉ የበላይ ነው፡፡

You might also like