You are on page 1of 7

የክርስቶስ በጎነት መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን

/
የክርስቶስ በጎነት መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ ክርስቲያን

መተዳደሪያ ደንብ

2016 . ዓ ም

0
የክርስቶስ በጎነት መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን

ቁጥር

ቀን

ለኢትዮጵያ አማኞች አብያተ ክርስቲያን ካዉንስል ጽ/ቤት

አድስ አበባ ኢትዮጵያ

ጉዳዩ፡- በካውንስል ለመመዝገብ ስለማመልከት ይሆናል፡፡

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግስት በቅርብ በሀገርቱ


ውስጥ ያሉት ቤተክርስትያናት አንድ መልክ እንዲኖራቸው ባደረገው የመልካም ትግል ጥረት
አድሱ የቤ/ክ ፍቃድ አሰጣጥ ከመስከረም 1/2016 ዓ/ም ጀምሮ በካውንስሉ የሚፈጸም ስለሆነ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ በጌዴኦ ዞን በገደብ ወረዳ ሴሶሌ ቀበሌ ዉስጥ የሚገኝ የ ክርስቶስ በጎነት

መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን በካውንስሉ አባልነት እንድትመዘግቡና የቤተክርስቲያን የፍቃድ


ሕጋዊነት እንድታረጋግጡልን ስንል በታላቅ አክብሮት እናመለክታለን፡፡

ስለሚታደርጉልን ቀና ትብብር ከልብ እናመሰግናለን!!

ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር !!

ነብይ ገዛሀኝ አለሙ

ባለ ራዕይ

0935897732/0926281182
የክርስቶስ በጎነት መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን

ቁጥር………………………….

ቀን……………………………

ለኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጽ/ቤት

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የ የክርስቶስ በጎነት አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን መመስረቻ አጭር ጽሁፍ

እግዚአብሔር አምላክ በየዘመናቱ ለሰው ልጆች ለተለያየ አላማ ራዕይ የሚሰጥ አምላ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህም
ራዕይዎች አንዱ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ የመስበክና ሰዎችን በክርስቶስ የመጠቅለል ራዕይ ነዉ፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር አገልግሎቱ ደቀ-መዛሙርትን ካስተማረ በኋላ እንግዲህ ሂዱና
ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝሀኋችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ
እያስተማራችኋቸው ደቀ-መዛሙርቴ አድርጓቸው፡፡ ማቴ 28÷19-20 ብሎ ታላቁን ተልዕኮ ከሰጣቸው በኋላ ሐዋርያት
በፀሎት እየተጉ ሳለ መንፈስ ቅዱስ እንደወረደባቸው በመጽሐፍ ቅዱሳችን በሐዋሪያት 2÷1 ላይ ይናገራል፡፡ መንፈስ
ቅዱስም የወረደበት የበዓለ ሐምሳው ዕለት የቤ/ያን ውልደት ነበር ከዚያ በኋላ ሐዋርያት የክርስቶስ ተልዕኮ በመቀበል
ከኢየሩሳሌም ጀምሮ እስከ ምድር ዳርቻ ወንጌልን እየሰበኩ ዞረዋል፡፡

ዛሬም በምድር ያለን እኛ ከክርስቶስ የተቀበልነው ተልዕኮ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ የመስበክና ያመኑትንም ደቀ-
መዝሙር በማድረግ የክርስቶስ ማዕከል የሆነችው ቤ/ያን በምድር ማቋቋም በመሆኑ እግዚአብሔር አምላክ ለባለ ራዕዩ
ዓለማትን በክርስቶስ ለመድረስ የሰጠውን ተልዕኮ ተቀብለን ከግብ ለማድረስ በመስማማት ይህንን የ የክርስቶስ በጎነት
አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን ክርስቶስ ኢየሱስ ለጴጥሮስ አንተ አለት ነህ በዚህም አለት ላይ ቤ/ያንን እመሰርታለሁ
የገኃነም ደጆች አይችሏትም ባለው መሰረት ቤ/ያን የክርስቶስ ስለሆነች በምድር የሚደርስባትን ተጽዕኖ ሁሉ በመንፈስ
ቅዱስ ኃይል እየተቋቋመች በእግዚአብሔር ምሪት እስከ መጨረሻ ትቀጥላለች፡፡

ቀን …………………….

ቁጥር…………………..

የ የክርስቶስ በጎነት አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን የመስራቾች አባላት ስብሰባ ቃለ ጉባዔ

ስብሰባዉ የተካሄደበት ሰዓት ………………………


የክርስቶስ በጎነት መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን

በስብሰባዉ የተገኙ አባላት ብዛት ………………….

በስብሰባዉ ያልተገኙ አባላት ብዛት ………………..

በፍቃድ …………..

ያለፍቃድ …………

የስብሰባዉ አጀንዳዎች

1. ቤተክርስቲያን ስለማቋቋም “

የ የክርስቶስ በጎነት አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን በክርስቶስ የተዋጁ ምዕመናን ወይም ከዓለም ተጠርተዉ የወጡ ሰዎች
በአንድ ዓላማ የክርስቶስን ወንጌል ለዓለም ለማድረስ ለማገልገል እንዲሁም በምድር በጎ ተጽዕኖ ለማምጣት
የሚሰበሰብበትማዕከል ስንሆን እኛም በዚህ በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ሴሶሌ ቀበሌ እና አጎራባቾች ቀበሌያት የምንገኝ
የክርስቶስ በጎነት አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን አባላት በመስማማትና በመፈቃቀድ በአንድነት እግዚአብሔርን ለማገልገልና
ወንጌልን ለመስራት በገደብ ወረዳ የክርስቶስ በጎነት አለም አቀፍ ቤ /ክርስቲያን በ 1/1/2016 ዓ/ም ተስማምተን
የተከልን እና የመሰረትን መሆናችንን በእጅ ፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡

ቀን …………………….

ቁጥር…………………..

የ የክርስቶስ በጎነት አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን የአባላት ስብሰባ ቃለ ጉባዔ

ስብሰባዉ የተካሄደበት ሰዓት ………………………

በስብሰባዉ የተገኙ አባላት ብዛት ………………….

በስብሰባዉ ያልተገኙ አባላት ብዛት ………………..

በፍቃድ …………..

ያለፍቃድ …………
የክርስቶስ በጎነት መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን

የሥብሰባ አጀንዳዎች

1. የቤተክርስቲያኑን መተዳደሪያ ደንብ ስለማጽደቅ


2. የቤተክርስቲያኑን የእምነት አቋም ስለማጽደቅ

ዉሳኔዎች
1. የ የክርስቶስ በጎነት አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን መተዳደርያ ደንብ ስለማጽደቅ
አንድ ህጋዊ ህልዉና ያለዉ ቤ/ክቱን መጽሐፍ ቅዱስን በማይጋጭ መልኩ የምትመራበት የዉስጥ መተዳደርያ ደንብ
ሊኖራት የታመነ በመሆኑ የ የክርስቶስ በጎነት አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን 19 አንቀጾች ያሉትን መተዳደሪያ ደንብ
ደንባችን እንዲሆን ተነቦ ፈቅደንና አምነን ተስማምተን ያፀደቅን መሆናችንን በእጅ ፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡
2. የ የክርስቶስ በጎነት አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን የእምነት አቋም ስለማጽደቅ
ቤተክርስቲያናችን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረተ የምታምንባቸዉ የጋራ የእምነት አቋም እንዲኖራት
ስለሚያስፈልግ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ በሆነዉ በ 26 ነጥቦች የጋራ አቋም በመያዝ በሙሉ ድምፅ የእምነት
አቋማችንን ተቀብለን ያጸደቅን መሆኑን በእጅ ፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡

ቀን …………………….

ቁጥር…………………..

በየክርስቶስ በጎነት አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን መደበኛ የአባላት ስብሰባ ቃለ ጉባዔ

ስብሰባዉ የተካሄደበት ሰዓት ………………………

በስብሰባዉ የተገኙ አባላት ብዛት ………………….

በስብሰባዉ ያልተገኙ አባላት ብዛት ………………..

በፍቃድ …………..

ያለፍቃድ …………

የሥብሰባ አጀንዳዎች

1. የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ምርጫ


2. የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች የአገልግሎት ዘመን ዉሳኔዎች
ዉሳኔዎች
1. የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ምርጫን በተመለከተ
ምንስትሪያችን ከባለ ራዕዩ ጎን በመቆም በበላይነት ሥራን የሚያስኬዱ መሪዎች ስለሚያስፈልጓት እንደ
ቤተክርስቲያናችን አባላትና ስፋት መጠን
1/ ገዛሀኝ አለሙ (ሰብሳቢ)
የክርስቶስ በጎነት መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን

2/ አንድነት ጀጎ (ፀሐፊ)
3/ ክጴ ሆርዶፋ (ገ/ያዥ)
4/ ታሪኩ ሀይሌ(ሒሳብ ሹም)
5/ አለሙ ጅግሶ( ንብረት ክፍል) እንድሆን ተስማምተን የመረጥን መሆናችንን በእጅ ፍርማችን እናረጋግጣለን ፡፡

2. የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች የአገልግሎት ዘመን ውሳኔዎች


ይህንን በተመለከተ የቤተክርስቲያናችን መተዳደርያ ደንብ ላይ እንደተጠቀሰዉ መሰረት የኮሚቴዎች የስራ ዘመን
ሶስት ዓመት ይሆናል፡፡
ይህንንም ተስማምተን የተቀበልን መሆኑን በእጅ ፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡

ቀን …………………….

ቁጥር……………………

አባላት ስብሰባ ቃለ ጉባዔ

ስብሰባዉ የተካሄደበት ሰዓት ………………………

በስብሰባዉ የተገኙ አባላት ብዛት ………………….

በስብሰባዉ ያልተገኙ አባላት ብዛት ………………..

በፍቃድ …………..

ያለፍቃድ …………

አጀንዳዎች

1. የቤተክርስቲያኒቱን አርማ ስለማጽደቅ


2. የቤተክርስቲያኒቱን ስያሜ ስለማጽደቅ

ዉሳኔዎች
1. የ ክርስቶስ በጎነት መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን አርማ ስለማጽደቅ
የክርስቶስ በጎነት መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን

የ ክርስቶስ በጎነት መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን የሚኖራት አርማ በተገለጠ መጽሀፍ ቅዱስ፣ላይ የአለም
ካርታና እርግብ ከላይ እና ያለበት ሲሆን በአማርኛ የ ክርስቶስ በጎነት መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ /ክርስቲያን የሚልና ከታ
በእንግሊዝኛ YEKIRSTOS BEGONET MESKARIWOCH INTERNATIONAL CHURCH
እንዲሆን ተስማምተን ማጽደቃችንን በእጅ ፊርማችን እናረጋግጣል፡፡

2. የ ክርስቶስ በጎነት መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን ስያሜ በተመለከተ ቤተክርስቲያናችን ከተልዕኮ
አንጻርክርስቶስ በጎነት መስካሪዎች አለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን ተብሎ እንድትጠራ ተስማምተን ያፀደቅን
መሆናችንን በእጅ ፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡

You might also like