You are on page 1of 20

‹‹እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር

ስደተኞችን ይቀበላል፡፡››
መዝ.፻፵፭፥፱

ስምዐ ጽድቅ
ማውጫ

ስምዐ ጽድቅ
የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርተ ሃይማኖት፣
ሥርዓትና ትውፊት ጠብቆ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን በኅትመት
ሚዲያ መምሪያ እየተዘጋጀ በወር ሁለት ጊዜ
የሚወጣ መንፈሳዊ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ
ወርቅነሽ ቱፋ
ጳጉሜን ፭ ቀን ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ተጀመረ
ከፍተኛ ሪፖርተር
 011-1553555/ 011-1553442
ካሣሁን ለምለሙ
 80078
ሪፖርተር
አዲስ አበባ
ምኒልክ ብርሃኑ
የገጽ መልክ (Layout) ዲዛይነርና
ጸሐፊ
የዝግጅት ክፍሉ ኢሜይል
newspaper@eotcmk.org ገነት ታደሰ

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም


አጫጭ
ር ዜና
ዎች

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ጥልና አለመግባባትን በይቅርታና በዕርቅ


መፍታት እንደሚገባ ተገለጠ
ካሳሁን ለምለሙ
ጥልና አለመግባባትን በይቅርታና በዕርቅ መፍታት እንደሚገባ በዕርቅ ላይ የተመሠረተ የችግሮች መፍቻ መፍትሔ በፈጣሪም
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ሆነ በዓለማዊ ሕግ ፍጹም የሆነ ተቀባይነት ያለው መሆኑኑን
ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ አክለው አስረድተዋል፡፡
ተክለሃይማኖት ገለጡ፡፡
ሰዎች ጠብን በዕርቅ፣በደልን በይቅርታ፣ድኅነትን በልማት፣
ቅዱስነታቸው ይህንን የገለጡት የ!)05 ዓ.ም የመስቀል ደመራ ክህደትን በሃይማኖት እያረሙ መኖር እንደሚችሉ የጠቀሱት
በዓል አዲስ አበባ መስቀል ዐደባበይ በተከበረበት ወቅት ተገኝተው ቅዱስነታቸው ሰው ራሱን በራሱ ካላሸነፈ በስተቀር ይህንን
ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት ሲሆን በመልእክታቸውም መልካም ተግባር ለመፈጸም አቅምና ችሎታ እንደለሌውም
የሰው ልጆችን አለመግባባት በይቅርታና በዕርቅ ዘግቶ ሰላምና አስገንዝበዋል፡፡
አንድነትን አስፍኖ በመከባበርና በመተሳሳብ፣በመተዛዘንና
በመተጋገዝ፣ በመቻቻል እንዲሁም በፍቅር ከመኖር ውጭ ሰላም እጅጉን ከእኛ መራቋን የተናገሩት ቅዱስነታቸው ሰላም
የተሻለ ሌላ አማራጭ እንደሌለ አስገንዝበዋል፡፡ ወደ እኛ እንድትመጣ ሁላችንም በተለይ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበኩሏን ድርሻ ልትወጣ እንደሚገባ
ቅዱስነታቸው አክለውም የይቅርታና የዕርቅ ሄደቱ እውን አሳስበዋል፡፡
ሊሆን ሚችለው የራስ ወዳድነትን አስተሳሰብ በመተው እንደሆነ
አስረድተው ከእኔ ይልቅ ለሁላችን የሚለውን አስተሳሰብ አንግቦ በመጨረሻም እግዚአብሔር በሀገራችን አንዳንድ አካባቢዎች
ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ ያሉ ግጭቶችን አስወግዶ ሰላም፣ፍቅር፣አንድነትንና ስምምነቱን
እንዲያመጣ ሁሉም ሰው የዕርቅና የይቅርታ አካል እንዲሆን
ዕርቅና ሰላም ሊመጣ የሚችለው የጋራ መልካም አስተሳሰብ ቅዱስነታቸው ጠይቀው ለዚህ ዓላማም ሁሉም በያለበት በርትቶ
በሰዎች ልቡና የበላይነት ሲያገኝ መሆኑን የገለጡት ቅዱስነታቸው እንዲጸልይ አባታዊ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም 2


አጫጭ
ር ዜና
ዎች

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሬል

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሬል ከግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ


ክርስቲያን ተወካዮች ጋር ውይይት አደረጉ
ካሳሁን ለምለሙ
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ በአፍሪካ ለሚገኙ አብያተ ክስቲያናት የተለየ ከፍተኛ
ወቅዱስ አቡነ ኪሬል ከሌሎች ብፁዓን አባቶች ጋር በመሆን ትኩረት ሰጥታ እየሠራች መሆኑን ቅዱስነታቸው ተናግረው
ከግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ጋር የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና ሌሎች በአፍሪካ
የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ኦርቶዶክስ ኮግኔት ድረ የሚገኙ አብያተ ክስቲያናትን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ
ገጽ አስነበበ፡፡ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ራሱን የቻለ ማእከል
ውይይቱ የተካሄደው ሩሲያ ሞስኮ በሚገኘው መድኔዓለም ማቋቋሟን በውይይቱ ላይ አስረድተዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያን ሲሆን ውይይቱን የመሩትም በሩሲያ ቅዱስነታቸው አክለውም የበለጠ ግንኙነትና መግባባት
ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የአፍሪካ ጉዳዮች ተወካይ የሆኑት እንዲኖር በምሥራቅና በኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ
ሜትሮፖሊታን ልኦንድ መሆናቸውን ከዘገባው ለመረዳት ክርስቲያናት አስተምህሮ ላይ ውይይት እንዲደረግ በውይይቱ
ተችሏል፡፡
ጠይቀዋል፡፡ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስነታቸው በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት ከሆነ የሩሲያና ተወካይ የሆኑት ሜትሮፖሊታን ስራፒዮን በበኩላቸው
የግብፅ ሕዝቦች ለረጅም ጊዜ የዘለቀው ወዳጅነት በሁለቱ በውይይቱ ላይ መሳተፋቸው እንዳስደሰታቸው ገልጠው
አብያተ ክርስቲያናት መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንዲኖር
በዚህ ሰዓት የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ
ማድረጉን ተናግረው ለውይይቱ የተገኙ የግብፅ ኮፕቲክ
አገልግሎት በፈተና ውስጥ እያለፈ መሆኑ እንዳሳዘናቸው
ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮችን አመስግነዋል፡፡ ከዚህ
ከገለጡ በኋላ ለቤተ ክርስቲያኗ ሙሉ ድጋፍ እንዳላቸው
በኋላ በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የተለየና ጠንካራ
ተናግረዋል፡፡
ግንኙነት ለመፍጠር እንደሚሠሩም አክለው አስታውቀዋል፡፡
ተወካዩ አያይዘውም በዩክሬን ጉዳይ የተፈጠረው ችግር
ቅዱስነታቸው አክለውም “ምንም እንኳን በጦርነት፣በጥፋትና
በቅርቡ ሊፈታ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልጠው
በጭንቀት ውስጥ ብንሆንም በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናትና
ችግሩ በሰላማዊና በሰለጠነ መንግድ እንዲፈታም በጸሎት
በሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ
እንደሚያግዙ ገልጠዋል፡፡ በሩሲያና በዩክሬን መካከል
ይጠናከራል እንጅ አይቀዘቅዝም” ብለዋል፡፡
በተካሄደው ጦርነት የሞቱና የተጎዱ ዜጎችን በጸሎታቸው
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስቧቸውም አክለዋል፡፡

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፫


መልእ
ክ ት

‹‹አገልግሎት
‹‹ አንታክትም››
አገልግሎት ስላለብን አንታክትም››


ዛሬው የጸና መሠረት ላይ እንድንቆም የትላንት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአባቶቹ መንገድ የሚጓዝ፣
አባቶቻችን ሕይወታችውን ሙሉ ለቤተ ክርስቲያን የእነርሱን ፈለግ የሚከተል አገልጋይ ትውልድ ትሻለችና
አገልግሎት ደክመዋል፡፡ ከእግዚአብሔር ለዚያ ልንተጋ ይገባል፡፡
የተሰጣቸውን ሳይሰስቱ መልሰው በመስጠት ሥራን
ጥቂቶች የአባቶቻቸውን ፈለግ በመከተል ቤተ ክርስቲያን
በእምነት ገልጠዋል፡፡ እንደዛሬው ዘመናዊ መገናኛ
ከእነርሱ የምትጠብቀውን በትጋት ሲፈጽሙ ኖረዋል፤
ባልነበረበት በዚያ ዘመን ባሕር ተሻግረው ተራራ ዞረው
ዛሬም ያንን ትጋታቸውን አልተዉም፡፡ የሌሎችን በጎ
ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል፡፡ ገዳም ገድመው፣ ቤተ
አገልግሎትና ትጋት የራስ አድርጎ መውሰድ፤ በጥቂት
ክርስቲያንን አንጸው፣ ወንጌልን ሰብከው ብዙ የቤተ
ብርቱ አገልጋዮች ካባ ሥር ተጠልሎ የሌሎችን ብርቱ
ክርስቲያን ልጆችን አፍርተዋል፡፡ ቀለብ ሳይሰፈርላቸው
አገልግሎት እንደራስ አድርጎና ተዝናንቶ ለቀጣዩ ለዛሬው
ወንበር ዘርግተው ብዙዎችን ያፈሩ ሊቃውንቶቻችንን የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎት አይጠቅምምና
ሳይታክቱ በማገልገል ማን ይተካከላቸዋል? ከእንደዚህ ዓይነቱ ድንዛዜ በእውነት መውጣት ይገባል፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የብዙ ሺህ ዘመን ታሪክ ቅደስት ቤተ ክርስቲያን በጊዜ ቀመር የተለካ ከዓመት
ባለቤት ያደረጋት፣ በማይናወጽ ጽኑ መሠረት ላይ እስከ ዓመት የሚሠሩ ብዙ ሥራዎች አሏት፡፡ ትእዛዘ
እንድትቆም ያስቻላት የትላንቶቹ ጽኑዓን አባቶች፣ እግዚአብሔርን በተግባር በመግለጥ የመጀመሪያዋ
እናቶች ፣ወንድሞችና እኅቶች ተጋድሎ ሳይታክቱ ትምህርት ቤታችን ናትና ባሳየችን መንገድ መመላለስ
የመሥራታቸው ውጤት ነው፡፡ እኛ ዛሬ ያየነውንና ከእኛ ይጠበቃል፡፡ በቤተ ክርስቲያን፣ በቤታችን፣
የዳሰስነው እነርሱ ትላንት አሻግረው በእምነት አይተው በመሥሪያ ቤታችን ለአገልግሎቱ ታማኝ አድርጎ በሾመን
ሠርተው አልፈዋል፡፡ እነርሱ ዛሬ ላይ ባይኖሩም ቦታ ላይ ሁሉ ታምነን መገኘት ከእኛ ከክርስቲያኖች
ሥራዎቻቸው ሕያው ምስክሮች ናቸውና አፍ ይጠበቅብናል፡፡
አውጥተው ይመሰክራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ
የገጠማትን ልዩ ልዩ ፈተና በድል ልትወጣ የቻለችው ለሥራ ወይም ለአገልግሎት የተሰጠውን ጊዜ
ትላንት በነበሩ ሕይወትን በተግባር በተረጎሙ ልጆቿ እያባከኑ፤ የሥራ ወይም የአገልግሎት ጊዜ እየሸራረፉ፤
መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ ለእግዚአብሔር የሚገባውን ለራስ እያስቀሩ፤
የማይገባቸውን እየወሰዱ፤ ከእግዚአብሔር ጊዜ ላይ
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልእክቱ ሰርቆ ለራስ እያዋሉ፡ ታምነው በተሾሙበት ከእምነት
‹‹እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደደመና ጎድለው እየተገኙ ‹‹አገልግሎት ስላለብን አንታክትም››
በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም በሚል መንፈሳዊ ካባ ሥር ተጠልሎ መኖር፣ በሚተጉ
የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስ አገልጋዮች መሀከል አስመሳይ መሆን የቤተ ክርስቲያንን
ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን አገልግሎት አንድ ስንዝር ወደ ፊት አያራምድምና
ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ . . .›› (ዕብ.፲፪፥፩ እና ፪)ከእንደዚህ ዓይነቱ ራስን የማታለል አዙሪት መውጣት
እንዳለው አስተማሪዎቻችን፣ መንገድ መሪዎቻችን፣ ተገቢ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነው፡፡
ምሳሌዎቻችን ብዙዎች ናቸው፡፡ ሆኖም የአባቶችን
ወርቃማ አገልግሎት ከመተረክ፣ ጥቅስ ከመጥቀስ ባለፈ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የልጆቿን ብርቱና መንፈሳዊ
ስንቶቻችን በሚፈለግብን ልክ ለአገልግሎት ተግተናል? አገልግሎት በምትሻበት በዚህ ጊዜ እንደ ቃሉ

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፬


መልእ
ክ ት

ታምኖ አለመገኘት፤ እንደ አንድ ክርስቲያን የድርሻን አገልግሎት በመንፈሳዊ ትጋት መካስ ይጠበቅብናል፡፡
አለመወጣት ለራስ ውድቀት ለቤተ ክርስቲያንም ትልቅ
‹‹አገልግሎት ስላለብን አንታክትም›› የሚለው ጥቅስ
ጉዳት ነውና በቤቱ ሳለን እንደሚገባን ያልሆንን ሁሉ
ሕይወት የሚኖረው በትሑት ሰብእና፤ በብርቱ
የቤተ ክርስቲያን ዕዳ እንዳለብን ልንዘነጋው አይገባም፡፡
አገልግሎት ውስጥ ነውና ከተለምዶ አሠራር መውጣት
የትላንትናው በትጋት የተሞላ የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ
አለብን፡፡ ይልቁንም ለሌሎች አርአያ ለመሆን
ጉዞ ዛሬን እንድንኖር አድርጎናል፡፡ ትላንት የተሻለ
በመንፈሳዊ አገልግሎታችን ልንበረታ ይገባል፡፡ ቅድስት
መንፈሳዊ አገልግሎት ባይኖር ዛሬ እኛ አሁን ባለንበት
ቤተ ክርስቲያን አምና ባስቀመጠችን ሥፍራ ታምኖ
ቦታ ላይ አንገኝም ነበር፡፡ በመሆኑም በተቀበልነው
በመገኘት፣ ሳይታክቱ እግዚአብሔር እንደሚያየን
ልክ እንድንሰጥ፤ በተገለገልነው ልክ እንድናገለግል፤
አድርጎ በመሥራት ክርስቲያናዊ ግዴታችንን መወጣት
በተላለፈልን ልክ ለሌሎች እንድናስተላልፍ፤ ዛሬያችንን
አለብን፡፡
የተሻለ አድርገው ባቆዩልን ልክ ነገን የተሻለ አድርጎ
ለሌሎች ለማስረከብ ከጥቅስ ያለፈ በተግባር የተገለጠ ይልቁንም ዛሬ ቤተ ክርስቲያን በስደት፣ በመከራና
አገልግሎት ከእኛ ይጠበቃል፡፡ በመገፋት ውስጥ ባለችበት ጊዜ ተግባራዊ ክርስትና
ከሁሉም የቤተ ክርስቲያን ልጅ ይጠበቃል፡፡ በአገልጋይ
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በብዙ አገልግሎቶቿ ውስጥ
ስም ተጠርቶ ሳያገለግሉ ከመኖር፤ በቤቱ ውስጥ እያሉ
ልጆቿን ትፈልጋለች፡፡ በፈረሰው በኩል የሚቆሙ
እንደሌሉ ከመሆን ተጠብቀን፤ የቤተ ክርስቲያንን
የቁርጥ ቀን ልጆችን ትሻለች፡፡ ብዙ ሰጥታናለችና ብዙ
መንፈሳዊ አገልግሎት ማስመሰል በሌለበት ትጋት
ከእኛ ትጠብቃለች፡፡ አምና በሾመችን ቦታ ሁሉ ዛሬ
ታምኖ መገኘት ክርስቲያናዊ ግዴታ መሆኑን ሁሉም መፈጸም ተገቢ ነው፡፡ የነገዋን ቤተ ክርስቲያን እና
ልብ ሊለው ይገባል፡፡ ይልቁንም በጀመርነው በዚህ አዲስ መንፈሳዊ አገልግሎት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ
ዓመት የትላንት ዳተኝነታችንን በመተው፤ በቸልተኝነት፣ ዛሬ ላይ በእውነት ተግቶ ማገልገል ከእኛ በቤቱ ውስጥ
በማናለብኝነት፣ የጎዳነውን የእግዚአብሔር ቤት ካለነው ሁሉ ይጠበቃል እንላለን፡፡

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፭


ሪፖርታ

ማኅበረ ቅዱሳን የተቋማዊ ለውጥ ጥናት


ፕሮጀክትን አጸደቀ
እንዳለ ደምስስ

ማኅበረ ቅዱሳን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ችግር ከጊዜ ርዕስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ እና አፋር
ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር እና እየተወሳሰበ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ትምህርት የሰጡ ሲሆን
መምጣት እንዲሁም የአገልግሎት ከባቢ ሁኔታዎች በሃይማኖት መቆም ማለት ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ
መቀያየርን ተከትሎ የተቋማዊ ለውጥ ጥናት ፕሮጀክትን እስከምናልፍ ድረስ እንጂ ጊዜያዊ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡
በማዘጋጀት አጸደቀ፡፡ ለዚህም ፍቅር፣ ጥንካሬና ብርታት እንደሚያስፈለግና
አገልግሎቱም ሰማያዊ ክብር የሚገኝበት ከመሆኑ
የተቋማዊ ለውጥ ጥናት ፕሮጀክቱንም ማኅበረ ቅዱሳን አንጻር ከሁሉም ጋር ተግባብቶ ማከናወን ያስፈልጋል
የተመሠረተበትን ፴ኛ ዓመት ፲፭ኛ መደበኛ ጠቅላላ ሲሉ አባታዊ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡
ጉባኤውን ከነሐሴ ፳፪-፳፬ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም “አገልግሎት
ስላለን አንታክትም” በሚል መሪ ቃል በቅድስት ሥላሴ ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ከተመሠረተበት
መንፈሳዊ ኮሌጅ አዳራሽ ሲያከናውን ብፁዓን አበው ከ፲፱፻፹፬ ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ፴ ዓመታት
ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ልዩ ልዩ የመምሪያ
የሚያጋጥሙትን ፈተናዎች በጽናት በማለፍ አገልግሎቱን
ኃላፊዎችና ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና
አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት
የማእከላት ተወካዮች በተገኙበት ተወያይቶ ለማጽደቅ
ወደፊት ማከናወን እንዲችል የተቋማዊ ለውጥ ጥናት
ችሏል፡፡
ማስፈለጉ በጉባኤው ላይ ተገልጿል፡፡
በዚህ ጠቅላላ ጉባኤም የተቋማዊ ለውጥ ጥናት
ማኅበሩ በሁለንተናዊ አገልግሎቱ የሚፈጠሩ ችግሮችን
ፕሮጀክቱን ተወያይቶ ከማጽደቅ በተጨማሪ የሁለት
በዘላቂነት ለመፍታት፣ ከማኅበሩ ዕድገት ጋር የሚስማማና
ዓመት የሒሳብ ሪፖርት እና የማስተባበሪያዎች ሪፖርት
ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ለውጥ የሚጠበቅበትን
ቀርቦ ውይይት ተካሂዶባታል፡፡
ሚና መወጣት እንዲያስችለው የተቋማዊ ለውጥ
በጉባኤው መክፈቻም ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ጥናት ፕሮጀክት እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡ የተቋማዊ
ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕር ዳርና አካባቢው ለውጡ ጥናት ፕሮጀክትም ዐራት መሠረታዊ ዝርዝር
ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ “ሃይማኖት እና ፍጹም ተጋድሎ” ዓላማዎችን ይዞ መዘጋጀቱን ጥናቱ ለጉባኤው በቀረበበት
በሚል ርእስ የወንጌል ትምህርት የሰጡ ሲሆን ማኅበሩ ጊዜ ተገልጿል፡፡
በሚሠራው ሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት
የሚያጋጥሙትን ፈተናዎች በጽናት በመቋቋም አልፎ እነዚህም፡- የመጀመሪያው ማኅበሩ ተቋማዊ እሳቤውን፣
እዚህ እንደደረሰ ሁሉ ወደፊትም ለቅድስት ቤተ ቅርጹንና የአገልግሎት ይዘት ለውጥ በማድረግ
ክርስቲያን የሚጠቅሙ ተግባራትን በፍጹም ተጋድሎ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በመፈተሸ፣ የአገልግሎት
በአንድነት ሊያከናውን ይገባል” ብለዋል፡፡ መስጫ መንገዶችን በመመርመር እና የፋይናስ
ሁኔታዎችን በጥልቀት ፈትሾ የተቋቋመለትን ዓላማ
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በማኅበሩ የቀረበውንም የሁለት እንዲያሳካ የለውጥ ሂደቱን መትለምና መተግበር፤
ዓመታት ሪፖርት ካደመጡ በኋላም ለሚቀጥለው
ዓመት ደግሞ የተሻለ ሥራ ለመሥራት የሚታቀድበትና ሁለተኛው ደግሞ ማኅበሩ የአገልግሎት አፈጻጸም
ውጤታማ አገልግሎት ሊፈጸም እንደሚችል ተስፋ ለውጥ ለማድረግ የአመራር ዘይቤውን፣ አደረጃጀቱን፣
ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ የሰው ኃይሉን፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀሙን እና
የአገልግሎት አፈጻጸም ሂደቱን በጥልቀት በመፈተሸ
በተጨማሪም “ንቁ በሃይማኖት ጸንታችሁ ኑሩ” በሚል የአደጋ ተጋላጭነትን በማጥናት ሁለንተናዊ ለውጥ

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፮


ሪፖርታ

የሚመጣበትን አቅጣጫ ማሳየትና ለውጡን መተግበር፤ ዘመኑን የዋጀ ጠንካራ አገልግሎት ማብቃት፤

ሦስተኛው የቤተ ክተርስቲያንን ሁለንተናዊ አገልግሎት በተደራጀና ተደራሽነትን ማእከል ባደረገ መንገድ

ለማሳደግ የሚያስችል የአጋር አካላትና የተጽእኖ ፈጣሪ ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮን ዘርፈ ብዙ
አካላት ጥምረት በመፍጠር ለቤተ ክህነት ተቋማዊ በሆኑ መንገዶች በመላው ዓለም ማስፋፋት፤
ለውጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ፤
 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ሙሉ
ማኅበሩ እስከ አሁን የሠራቸውን ሥራዎች ገምግሞ ሰብእናን በሚገነባ ሥርዓተ ትምህር በማስተማር
የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን በመለየት ተጠያቂነት ዘመኑን የዋጁ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ በቤተ
ያለው የአመራር ሥርዓት በመዘርጋት አሠራሩንና ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር የሚያገለግሉ
አደረጃጀቱን ማዘመን የሚሉ ናቸው፡፡ እንዲሁም በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በፖለቲካዊ
እና በሀገር አስተዳር ጉዳዮች መሪ/ንቁ ተሳታፊ
እነዚህን የጥናት ዓላማዎች መሠረት በማድረግ አዲስና አገልጋዮችን ማፍራት እና ማሰማራት፤
ጥርት ያለ ተቋማዊ ርእይ፣ ተልእኮ እና ዓላማ ለመቅረጽ
ተቋማዊ ወሰን፣ ተቋማዊ ጠባይ፣ የተቋማዊ ዓላማ  በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚነዙትን የርእዮተ ዓለም፣
ትኩረት እና ተቋማዊ ቅርጽ አመላካች ርእሰ ጉዳዮችን የሐሰት ትርክቶች እና የአጽራረ ቤተ ክርስቲያንን
በዝርዝር በመመልከት ለውሳኔ በሚመች መልኩ እንቅስቃሴን በጥናት እና ምርምር ላይ ተመርኩዞ
አጠቃልሎ በማቅረብ የቀጣዮችን ዘመናት የማኅበሩ መሞገት እና የተሳሳቱትን በማረም በጠንካራ
ርእይ፣ ተልእኮና ዓላማዎች መወሰናቸውን በዝርዝር የዕቅበተ እምነት አገልግሎት የቤተ ክርስቲያንን
የተቋማዊ ጥናት ፕሮጀክቱ ሲቀርብ ተገልጿል፡፡ ህልውና ማስጠበቅ፤

ማኅበረ ቅዱሳን ይህንን ተቋማዊ ለውጥ ለመተግበር  የተተኪውን ትውልድ መሠረት ለማጎልበት የሰንበት
ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራቸውን የአገልግሎት ዘርፎች ትምህርት ቤቶችን አቅም በማጠናከር የሕፃናት እና
ለመምረጥ የተቀመጡ መሥፈርቶችን ስንቃኝ የወጣቶች የተተኪነት ሚና ማሳደግ፤
ደግሞ፡- የቤተ ክርስቲያንን አቅም የሚገነቡ፣ ዘላቂ፣
ተግባራዊ ኦርቶዶክሳዊነትን የሚያጸኑ፣ አስተማማኝ  ማኅበሩ ዘመኑን የዋጀ ተቋማዊ የአሥራር ሥርዓት
የቤተ ክርስቲያን ሕልውና እና ተልእኮ ማስፈጸም በመዘርጋት ተልእኮውን ማሳካት የሚችልበት
የሚያስችሉ፣ የዕድገት ጥራት ኖሯቸው ለማስፋትና አቅም መፍጠር (በአመራር፣ በሰው ኃይል፣
ለማጠናከር የሚያግዙ፣ አሳታፊ አገልግሎት፣ ልማትን በመንፈሳዊነት፣ በግንኙነት፣ በዕውቀት፣ በልማት፣
የሚያፋጥኑ፣ እንዲሁም አጭር እና ረጅም ጊዜያትን በፋይናንስ፣ በቴኖሎጂ)
ያማከሉ ትውልድ ተሻጋሪ ለውጦች ናቸው፡፡
 ዓለም አቀፍ ግንኙነትንና የትብብር አገልግሎትን
በዚህም መሠረት የማኅበረ ቅዱሳን ርእይ፣ ተልእኮና መርህ ያደረገ የኦርቶዶክሳውያንን ኢኮኖሚያዊ፣
ዓላማዎች የሚከተሉት ሆነው ተቀርጸዋል፡- ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ማሳደግ፡፡

 ርእይ፡- ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ የመሪነት እነዚህንና ሌሎችን ዓላማዎች መሠረት በማድረግ


ሚናዋን ስትወጣ ማየት፤ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋትና በማጠናከር መፈጸም
እንዲችል ይህ የተቋማዊ ለውጥ ጥናት ፕሮጀክት ይፋ
 ተልእኮ፡- ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካት መደረጉ ለጉባኤው ተገልጿል፡፡
እና ለህልውናዋ የሚተጋ፣ የተደራጀች፤ ምሉዕ
ጉባኤውም በቀረበው የተቋማዊ ለውጥ ጥናት ፕሮጀክት
ኦርቶዶክሳዊት፣ ርቱዕ ዘመናዊ፣ ሁለገብ መሪ
ላይ ለአንድ ቀን ሙሉ ትኩረት ሰጥቶ ሲወያይ ከቆየ
ትውልድ ማፍራት እና ማሰማራት፤
በኋላ እንዲጸድቅ ተደርጓል፡፡
 የማኅበሩ ዝርዝር ዓላማዎች፡- የቤተ ክርስቲያንን
ከተቋማዊ ለውጡ ጥናት ፕሮጀክት በተጨማሪ ማኅበረ
ተቋማዊ አስተዳር፣ የአሠራር ሥርዓትና አስተሳሰብ
ቅዱሳን ባለው መዋቅር መሠረት እያንዳንዱ የአገልግሎት
በቴክኖሎጂ እና በልዩ ልዩ መንገዶች በመደገፍ ማስተባበሪያ ተሰፍሮና ተለክቶ የተሰጠውን አገልግሎት

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፯


ሪፖርታ

ለማከናወን የተደረጉ ጥረቶች፣ በአገልግሎት ላይ የነበሩ ግራ ቀኛቸውን መለየት የተሳናቸው ምእመናን ቊጥር
መልካም ዕድሎች፣ እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችና ከፍተኛ መሆን አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ በየዓመቱ በሰበካ
ስጋቶችን ያካተተ ሪፖርት በየማስተባበሪያ ኃላፊዎች መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የሚቀርቡ ሪፖርቶች የሚያሳዩት
ቀርቦ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ ይህንን ነው፡፡ ስለዚህ ነባራዊውን ሁኔታ በመረዳት
እና ልዩ ልዩ ስልቶችን በመቀየስ ነፍሳትን የማዳንና
የተቋማዊ ለውጥ ጥናት ፕሮጀክቱ መጽደቁ እንደ የማጽናት ሥራ ላይ ብዙ መሥራት ያስፈልጋል፡፡
መልካም አጋጣሚ መመልከት ይቻላል፡፡ ይህም
ማኅበሩ አገልግሎቱን እንዲፈትሽ ያደርገዋልና፡፡ ነገር ሌላው ማኅበረ ቅዱሳን ትኩረት አድርጎ መፈተሽ
ግን ከመተግበሩ በፊት ማኅበረ ቅዱሳን ባሳለፈው ያለበት የተቋማዊ ለውጥ ጥናቱን በታቀደለት መሠረት
የአገልግሎት ጉዞ ሲያጋጥሙት የነበሩ ችግሮችን መለየት ውጤታማ አገልግሎት ለማበርከት የሚያስችለው
እና ለችግሮቹ መፍትሔ መሻት ያስፈልጋል፡፡ በተለይም መሆኑን በመገምገም ቅደም ተከተሎችን በማውጣት
ለአገልግሎት እንቅፋት ሆነው የቆዩትን ከተለያዩ አካላት ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን
ያጋጥሙ የነበሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ትኩረት መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ በወረቀት ላይ የሰፈረውን
መስጠት ይገባል፡፡ አገልግሎት በመግባባትና በፍቅር ወደ ተግባር ለመለወጥ ስልታዊ ዕቅዶችን በመንደፍ
የሚከናወን ነውና፡፡ አገልጋዮችን ማሠማራት፣ ሥራን ሰፍሮና ለክቶ
መስጠትና መከታታልን፣ በዚያው መጠን ደግም
አንዳንድ አካላት በተለይም መንግሥት በተለወጠ የሚያጋጥሙ ችግሮችን መፍታት ይገባል፡፡
ቊጥር ከሚከተለው ርእዮተ ዓለም አንጻር ከቅድስት
ቤተ ክርስቲያን ጋር ተቀራርቦ ከመሥራት ይልቅ በቤተ በዚህም መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን በአገልግሎት
ክርስቲያንና በምእመናን ላይ ያነጣጠረ የመግፋት ብሎም ባለፈባቸው ፴ ዘመናት ያጋጠሙትን ችግሮች፣
የማጥቃት ሴራ ሲሠራባት ቆይቷል፡፡ በዚህም መሠረት ችግሮቹንም ለመፍታት ያደረጋቸውን ጥረቶችና የተገኙት
ለቤተ ክርስቲያን ጠበቃነቱን የሚገልጸውንና ለዚህም ውጤቶችን በመገንዘብ፣ በመመርመርና በመተንነተን
ዓላማ በቆራጥነት የሚያገለግለውን ማኅበረ ቅዱሳንን ጊዜውን የዋጀ አገልግሎት ለመፈጸም የተቋማዊ ለውጥ
በተለያዩ መንገዶች ለማዳከም የሚሠራው ክፋት አዘል ጥናቱ ጊዜውን የጠበቀ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ቅድስት
ሴራ አገልግሎቱን በተፈለገው መጠን ለማከናወን ቤተ ክርስቲያንና ሀገራችን እንዲሁም ዓለም ያሉበትን
እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትም ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ እንደመዘጋጀቱ ከበፊት
“ፖለቲካን በሩቁ” በሚል አካሄድ መሸሻቸው መንግሥትና ይልቅ መትጋትን፣ ከሌሎች አጋር አካላት ጋር ተቀራርቦ
በመንግሥት አስተዳደር ውስጥ ተሰግስገው ያሉ አካላት መሥራትና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ህልውና
በቤተ ክርስቲያን ላይ አሉታዊ ረጅም እጃቸውን ማስጠበቅ ስለሚገባ ሁሉም ሊረባረብ ይገባል፡፡ ተቋማዊ
እንዲያሳርፉ ዕድል ሰጥቶቷቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያንና ለውጥ ማደረግ ብቻ ሳይሆን ለአገልግሎቱ ምቹ ከባቢያዊ
ማኅበረ ቅዱሳንን ለመለያየትም ብዙ ደክመዋል፡፡ ሁኔታዎችንም ማመቻቸት ያስፈልጋል፡፡

ለዚህ ችግር ቤተ ክህነትም ሆነ ማኅበሩ መቋቋም ማኅበረ ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ
የሚችሉበትን አቅም መፍጠር፣ እርስ በእርስ ከመገፋፋት ሕጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶት ከተመሠረተበት ከ፲፱፻፹፬
ይልቅ በጋራ ለመሥራት፣ ብሎም በመንግሥት አስተዳደር
ዓ.ም ጀምሮ መዋቅሩን በሀገር ውስጥ እና በመላው
ውስጥ ለቤተ ክርስቲያን የሚቆም ትውልድ መፍጠር
ዓለም በመዘርጋት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በዚህም
ይገባል፡፡ በዚህ ሂደት የማኅበረ ቅዱሳን ተቋማዊ ለውጥ
አገልግሎቱ በሀገር ውስጥ፡- ፶ ማእከላት፣ ፬፻፵፬ ወረዳ
ችግር ፈቺ ሆኖ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ማእከላት፣ ፪፻፲፬ የግንኙነት ጣቢያዎች እና ፬፻፳፯ ግቢ
ሌላው የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴን ለመግታት ጉባኤያት አሉት፡፡ እንዲሁም በውጪ ሀገራት ስድስት
እንዲሁም ምእመናንን ከሐሰተኛ መምህራንና ማእከላት፣ ፳፬ ንዑሳን ማእከላት፣ ፳፮ ግንኙነት
አስተምህሮአቸው ለመጠበቅ ከዚህ ቀደም ብዙ ጣቢያዎች እና ፲፰ ግቢ ጉባኤያት አሉት፡፡ ከ፶ ሺህ
ተደክሟል፡፡ በዚህም መልካም ውጤት ማምጣት በላይ አባላት፣ ከ፲፭፻፶፪ በላይ መደበኛ አገልጋዮች እና
ቢቻልም የሚፈለገውን ያህል ማኅበሩም ሆነ ቤተ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደጋፊ ምእመናን በመያዝ ላለፉት
ክህነት ተጉዘዋል ለማለት አያስደፍርም፡፡ ለዚህም ማሳያ ፴ ዓመታት መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን
የሚሆነው በየጊዜው በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን የሚነጠቁ አከናውኗል፡፡

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፰


ቤተ አ
ብ ርሃም

ልዩ በሆነው የሥነ ጹሑፍ ችሎታቸው ስብከተ


ወንጌልን ሲያስተምሩ የነበሩ አባት
ካሳሁን ለምለሙ ክፍል አንድ
መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ የቤተ ክርስቲያንን ሀ. ልደትና የትምህርት ሕይወት
ትምህርት በሚገባ ጠንቅቀው የተማሩና በተማሩት
ትምህርትም ቤተ ክርስቲያንንና ምእመናንን በተለያዩ ክቡር መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በድሮው
የአገልግሎት ዘርፎች ውስጥ ተሠማርተው ሲያገለግሉ አጠራር በወሎ ጠቅላይ ግዛት በየጁ አውራጃ ኀብሩ
የነበሩ አባት ነበሩ፡፡ እንዲሁም መንፈሳዊ ዕወቀታቸውንና ወረዳ ልዩ ስሙ ዳኅና ማርያም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
የሥነ ጹሑፍ ችሎታቸውን ተጠቅመው በጋዜጣና በቃል ታዋቂ ከሆኑት ሊቅ አባታቸው ከአለቃ ፈታሒ
ስብከተ ወንጌልን በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውረው ወልደ ማርያምና ከእናታቸው ከወይዘሮ አበበች ያዘው
በትጋት አገልግለዋል፡፡ በተለይ በኅትመት ሚዲያው ሐምሌ ፳፬ ቀን 0፱)!8 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ በተወለዱ
ዘርፍ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛና የቤተ ክርስቲያን በ# ቀናቸው ጳጉሜን ፫ ቀን ሀብተ ወልድና ስመ
የኅትመት ሚዲያ ደረጃን ከፍ ያደረገ ነው፡፡ በመሆኑም ክርስትና ሲፈጸምላቸው ወልደ ሩፋኤል የሚል ስም
መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒን የዚህ ወር ተሰይሞላቸዋል፡፡ ከዚያም ዕድሜያቸው ለትምህርት
ዕትማችን የቤተ አብርሃም እንግዳ አድርገናቸዋል፡፡ በዚህ ሲደርስ ንባብንና ጽሕፈትን ተምረው ዳዊት ከወላጅ
ጽሑፍም ልደታቸውን፣ የትምህርትና የአገልግሎት አባታቸው (ከአለቃ ፈታሒ ወልደማርያም) በመማር
ጊዜያቸውን ቃኝተናል፤መልካም ንባብ፡፡ የቃል ትምህርትን ካጠናቀቁ በኋላ የባሕረ ሐሳብ ወይም
የዘመናት ማውጫ (መቁጠሪያ) ትምህርትን ከወላጅ
አባታቸው አለቃ ፈታሒ ወልደ ማርያም ዘንድ ተምረው
አጠናቀዋል፡፡

ትምህርታቸውን ለመቀጠል የነበራቸው ፍላጎት ከፍተኛ


በመሆኑ መምህራቸውና ወላጅ አባታቸው ከሆኑት
አለቃ ፈታሒ ወልደ ማርያምና በወቅቱ ከነበሩት
ሌላ መምህር ዘንድ ፈቃድ ጠይቀው በርካታ የአብነት
መምህራን ወደሚገኙበትና መንፈሳዊ ትምህርት
በስፋት ወደሚሰጥበት ሰሜን ወሎ ወደ ሚገኘው ታላቁ
የመርጦ ኢየሱስ ደብር በማቅናት ከታወቁት የድጓ ሊቅ
ከሆኑት ከየኔታ ሐዋዝ ዘንድ የቃል ትምህርታቸውን
አጠናክረው ተምረዋል፡፡

ከዚያ በኋላም ለምርምርና ለፍልስፍና የሚያበቃቸውን


ከፍተኛውን የቅኔ ትምህርት ለመማር በነበራቸው ከፍተኛ
ፍላጎት የወሎ ክፍለ ሀገር ርእሰ ከተማ በሆነችው ደሴ
ርእሰ አድባራት ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ደብር
የቅኔ ጉባኤ ቤት ወንበር ዘርግተው ያስተምሩ ከነበሩት
ከየኔታ ኃይለ ማርያም ጉባኤ ቤት በመግባት ለተወሰነ
ጊዜ ከተማሩ በኋላ እንደገና ወደ ታወቀችውና ግማደ
መስቀሉ በእንግድነት ወደአረፈባት የጁ አውራጃ ውስጥ
መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ወደ ምትገኘው ገነተ ልዑል ማርያም ቤተ ክርስቲያን
በማምራት ጉባኤ ዘርግተው ያስተምሩ ከነበሩት የኔታ

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፱


ቤተ አ
ብርሃም

ቂርቆስ የቅኔ ጉባኤ ቤት ገብተው ቅኔ ተቀኝተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ተምረው ለቁም ነገር ወደበቁበት ወደ
ምንም እንኳን የወላጅ አባታቸውን ያህል የተሟላ ሙያ ዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በዓታ
ባይኖራቸውም ትምህርታቸውን ለማሳደግና በመንፈሳዊ ለማርያም ገዳም የካህናት ማሠልጠኛ አምርተዋል፡፡
ዕውቀት የተሟላ ሰው ለመሆን ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ከዚህ በፊትም በደብረ ወገግ አሰቦት ቅድስት ሥላሴ
ቆይተዋል፡፡ በመቀጠልም የቅኔ ትምህርታቸውን ገዳም ቅኔ በሚማሩበት ወቅት ማታ ማታ ቅኔ እየተማሩ
ለማጠናከር በነበራቸው ዕቅድ በድሮ አጠራሩ በየጁ ቀን ቀን ደግሞ የገዳሙ መጻሕፍተ ብሉያት ትርጓሜ
አውራጃ ደቦት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ወንበር መምህር ከነበሩት ከመምህር መልአኩ ዘንድ የመጽሐፈ
ዘርግተው ጉባኤ አስፍተው የቅኔ ትምህርት ያስተምሩ ነገሥትን ትርጓሜ ተምረዋል፡፡ ከዚያ በመቀጠል
ከነበሩት ከመምህር የኔታ ገበየሁ ዘንድ ትምህርታቸውን በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ አዳሪ ትምህርት ቤት
በሚገባ ተከታትለው ተመርቀዋል። ገብተው ከታዋቂው የመጻሕፍተ ሐዲሳት ትርጓሜ
መምህር ከሆኑት ከመምህር ገብረ ማርያም ዓለሙ
ከዚያም ወደላስታ አውራጃ ተጉዘው በኩልመስክ ደብረ
ዘንድ ከዘመናዊ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የመጻሕፍተ
ፀሐይ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የቅኔ ትምህርት
ሐዲሳትን ትርጓሜ ጠንቅቀው ተምረዋል፡፡ ከነበራቸው
ያስተምሩ ከነበሩትና በተለይ በአማርኛ ቅኔያቸው
ከፍተኛ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በተጨማሪ ሁለገብ
ይታወቁ ከነበሩት መምህር ወልደ ትንሣኤ አካሌ ዘንድ
ሰው ለመሆን በማሰብ በአማኑኤል ባብቲስት ቤተ
የቅኔ አገባብ ቀጽለዋል፡፡ በዚሁ የቅኔ ጉባኤ ቤት የቅኔ
ክርስቲያን ዘመናዊ ትምህርት ቤት ገብተው የማታ
ትምህርታቸውን አገባባቸውን በሚገባ አጠናክረው
ትምህርት በመማር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን
በመማር ለሦስጠኛ ጊዜ እስከ ዘረፋና ማስነገር በመድረስ
በሚገባ ተከታትለው አጠናቀዋል::
ለመምህርነት በሚያበቃ ሁኔታ ተመርቀዋል፡፡ ይህንኑ
የቅኔ ትምህርት የበለጠ ለማጠናከር በነበራቸው ከፍተኛ በሥነ ጽሑፍና ድርሰት ችሎታቸው ለሁለተኛ ጊዜ የዜና
ፍላጎትም በምዕራብ ሐረርጌ ክፍለ ሀገር ወደ ታላቁ ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆነው አገልግሎት
ደብረ ወገግ አሰቦት የአንድነት ገዳም አምርተው የኔታ በመስጠት ላይ እያሉ ቤተ ክርስቲያኗ የረጅም ጊዜ
ቃለ ማዕነቅ ዘንድ ተምረዋል፡፡ በዚሁ ገዳም የቅኔ አገባብ አገልግሎታቸውን እና የሙያ ብቃታቸውን ከግምት
ከመቀጸላቸው በተጨማሪ የተማሪዎች አስነጋሪና ዘራፊ ውስጥ በማስገባት በ0፱)%7 ዓ.ም ከሌሎች የቤተ
ሆነው ለትንሽ ጊዜ ሲያስነግሩ ከቆዩ በኋላ ለሦስተኛ ክርስቲያን ደቀ መዛሙርት ጋር በመሆን ለከፍተኛ
በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡ በጉባኤ ቤቱ በቆዩበትም ትምህርት ወደ ራሽያ ተልከው በራሽያ ኦርቶዶክስ ቤተ
ወቅት በሰፊው የቀጸሉትን የሊቀ ኅሩያን ዘገየን አምስት ክርስቲያን በሌኒንግራድ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከፍተኛውን
መቶ የቅኔ ዓይነት መንገድ አስፈቅደው ጽፈዋል፡፡ የነገረ መለኮት ትምህርት በሚገባ በመከታተል
ተምረዋል፡፡ በዚያም ወቅት ኮሌጁ የሥነ ጽሑፍና
ከዚያ በኋላም ስለ ቅኔ ትምህርት ስፋትና ጥልቀት
የድርሰት ችሎታቸውን ተመልክቶ በራሻያ ቋንቋ የሥነ
ከታወቁ መምህራን ጋር ከፍተኛ የሆነ ጥናትና
ጽሑፍና የድርሰት ትምህርትን እንዲከታተሉ በመፍቀድ
ምርምር አድርገዋል፡፡ ከታዋቂ የቅኔ መምህራን
ትመህርታቸውን ተከታትለው ተመርቀዋል፡፡
መካከል አንዱ ከሆኑትና የቅኔን ይትበሃልና ሙያ
ጠንቅቀው ከሚያውቁት የደሴ ገነተ ጊዮርጊስ ቤተ ለ. የአገልግሎት ሕይወት፡-
ክርስቲያን አገልጋይና በግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ
በዚያ መልኩ መንፈሳዊና ዘመናዊ የሁለተኛ ደረጃ
ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የግእዝ መምህር ከነበሩት ከአለቃ
ትምህርታቸውን አጠናቀው ከጨረሱ በኋላ ያላቸውን
ይኩኖ አምላክ ዘንድም የየኔታ ቡሩኬን የቅኔ መንገድ፣
መንፈሳዊና ዘመናዊ ዕውቀት ተጠቅመው አገልግሎት
የጥንቱን የቅኔ ይትበሃልና መንገድ በስፋትና በጥልቀት
ለመጀመር የሚያበቃቸውን በጠቅላይ ቤተ ክህነት
ተምረዋል፡፡
ትምህርትና ሥልጠና መምሪያ በኩል የተሰጠውን
በተጨማሪም በአጭሩ የማይገታ ከፍተኛ የሆነ ፈተና አልፈው ጥር ፳፭ ቀን 0፱)$6 ዓ.ም በተጻፈ
የትምህርት ፍላጎት ስለነበራቸው የትርጓሜ መጻሕፍት የሥራ ምደባ ደብዳቤ በመጀመሪያ በኢሉባቡር ሀገረ
ትምህርት ለመማር በርካታ ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንተ ስብከት በሰባኬ ወንጌልነት ተመድበው ለሁለት ዓመታት

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፲


ቤተ አ
ብ ርሃም

አገልግለዋል፡፡ ከዚያም ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የአፄ ፋሲለደስ ግንብ ምስል
ተመልሰው ባላቸው ልዩ የሆነ የቅኔና የሥነ ጽሑፍ ያለበት ከብር ቅብ የተሠራ ሽልማት በጓድ መልአኩ
ችሎታ ጥር ፱ ቀን 0፱)$8 ዓ.ም በተጻፈ የሥራ ተፈራ ወኪል በአቶ ዘመነ ካሣ እጅ ሽልማት በክብር
ምደባ ደብዳቤ ያን ጊዜ በቤተ ክርስቲያን እየተዘጋጀ ተበርክቶላቸዋል፡፡
‹‹በማስታወቂያና መርሐ ብሔር ሚኒስትር›› በሬዲዮ
ከዚህ በተጨማሪ ከያዙት ሥራ ላይ ደርበው በስብከተ
ይሰጥ ለነበረው መንፈሳዊ ትምህርት አዘጋጅና የዜና
ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ የማስታወቂያ ዋና
ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ሪፖርተር በመሆን ሲያገለግሉ
ክፍል ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡ እንዲሁም ከመጋቢት
ቆይተዋል፡፡ ከዚያ በኋላም ታኅሣሥ ፪ ቀን 0፱)%3
፲፰ ቀን 0፱)'4 ዓ.ም ጀምሮ በልማትና ክርስቲያናዊ
ዓ.ም በተጻፈ የሥራ ምደባ ደብዳቤ በዚያው በጠቅላይ
ተራድኦ ኮሚሽን መምሪያ ረዳት አስተባባሪና የሕዝብ
ቤተክህነት የሥነ ጽሑፍ ክፍል ኃላፊና በየሳምንቱ
ግንኙነት መኮንን በመሆንም አገልግለዋል፡: በተጨማሪ
ለሚታተመው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ አዘጋጅ
የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታና መድኃኔዓለም ቤተ
ሆነው እንዲያገለግሉ ተመድበዋል፡፡
ክርስቲያን በስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንዲሳተፉ
በድጋሚ ታኅሣሥ ፬ ቀን 0፱)%7 ዓ.ም የዜና ቤተ በቅዱስ ፓትርያርኩ ዘንድ ስለተፈቀደላቸው የወንጌል
ክርስቲያን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ፍጹም በሆነ አገልግሎት በመስጠት አገልግለዋል፡፡ እንዲሁም በያዙት
ታታሪነትና መንፈሳዊነት አገልግለዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያን የሥራ መደብ ላይ በተጨማሪ የሥነ ጽሕፈት የበላይ
የአገልግሎት ዘመናቸው ውስጥ ከገጠሟቸውና ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡
በትዕግሥት ካሳለፏቸው ፈተናዎች መካከል በየዓመቱ
መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በረጅም ጊዜ
ጥር ወር የሚከበረውን በዓለ ጥምቀት ምክንያት
የቤተ ክርስቲያን አገልግሎታቸው በአሜሪካ፣ በራሽያ፣
በማድረግ ጥር ፲፩ ቀን 0፱)%7 ዓ.ም በጅማ
በደቡብ አፍሪካ፣ በናይሮቢ፣ በግብጽ፣ በሶርያ፣ በሊባኖስ
ከተማ በሶጦ ሜዳ በተከበረው የጥምቀት በዓል ላይ
በአረብ ኢምሬቶችና በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ አህጉረ
ተገኝተው ወንጌል በሰበኩበት ወቅት “ሶሻሊዝምን
ስብከት በአካል በመገኘት ሰፊ የሆነ የስብከተ ወንጌል
ነቅፈህ አስተምረሃል” ተብለው በመከሰሳቸው ያለምንም
አገልግሎት የሰጡ ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ
ጥፋታቸው ለአምስት ወራት ያህል ታስረው ከቆዩ በኋላ
ነበሩ፡፡ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ
ዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ በማድረጉ በነጻ
ያላቸውን ከፍተኛ የሥነ ጽሑፍ ችሎታ ተጠቅመው
ተፈትተው ወደ አገልግሎታቸው ተመልሰዋል።
በኃላፊነት በሚያዘጋጁት ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ
ከራሽያ መልስም ታኅሣሥ ፱ ቀን 0፱)&1 ዓ.ም አማካኝነት ቃለ እግዚአብሔርን ለበርካታ ዓመታት
የስብከትና ማስታወቂያ መምሪያ ኃላፊ በመሆን አስተምረዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን መልእክት
ተመድበው እስከ ግንቦት ፲፩ ቀን 0፱)&5 ዓ.ም በጽሑፋቸው አስተላልፈዋል፤ ጠንካራ፣ ገላጭና ተቋም
ድረስ አገልግለዋል፡፡ ከዚህ ሥራ በተጨማሪም በቅዱስ ተኮር ምክረ ሐሳብ በማቅረብም ለቤተ ክርስቲያናቸው
ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በልማትና ክርስቲያናዊ በሙያቸው ጥብቅና የቆሙ ሊቅ ነበሩ፡፡ ከልጅነት እስከ
ተራድኦ ኮሚሽን የካህናት ማሠልጠኛዎች፣ የሰበካ ዕውቀት ቤተ ክርስቲያን ባስተማረቻቸው ትምህርት
ጉባኤና የሰንበት ትምህርትቤቶች ማስተባበርያ ኃላፊ ሲያገለግሉ ከኖሩ በኋላ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና
በመሆንም አገልግለዋል፡፡ በዚሁ አገልግሎት ላይ እያሉ ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል፡፡ ብፁዕዓን
የጎንደር ክፍለ ሀገር ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ለሀገረ አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣
ስብከቱ ላበረከቱት መንፈሳዊ አገልግሎት፣ ለቤተ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም የሥራ
ክርስቲያን ለውጥና በምእመናን ማኅበራዊ አገልግሎት ባልደረቦቻቸው በተገኙበት ጳጉሜን ፫ ቀን !)04 ዓ.ም
ላይ አዘውትረው በመሥራታቸው እና ያላቸውን የሥነ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሥርዓተ
ጽሑፍ ተሰጥዎና ዕውቀት ተጠቅመው ላበረከቱት ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፲፩


ቃለ መ
ጠ ይቅ

ማእከላት ለቤተ ክርስቲያን አሳቢያን ተቆርቋሪ የሆኑ


ወጣቶችን አፍርተዋል
ክፍል ሁለት
ካሣሁን ለምለሙ

ከላይ ከተጠቀሱት ለማእከላት አገልግሎት ፈተና እንዲያገኙና የቤተ ክርስቲያናችን አባላት


ከሆኑ ምክንያቶች በተለየ ሁኔታ የማኅበረ እንዲሆኑ ማእከላት አድረገዋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ
ቅዱሳንን አገልግሎትና ዓላማ ያልተረዱ አንዳንድ ደግሞ አብነት ትምህርት ቤቶች በከፍተኛ ሁኔታ
የቤተ ክርስቲያን አካላት የሚፈጥሩት ችግር እንዲጠናከሩ አድርገዋል፡፡ አብነት ትምህርት ቤቶች
ለማእከላት አገልግሎት መጠናከር ተግዳሮት ሲሆኑ በመጠናከራቸው ደግሞ የነገዋን ቤተ ክርስቲያን
ይስተዋላል፡፡ ይህ በመሆኑም ማኅበረ ቅዱሳን የሚረከቡ በርካታ ሊቃውንትን ማፍራት
በማእከላት በኩል የሚያስፈጽማቸው አገልግሎቶች ተችሏል፡፡ ጉባኤ ቤቶቻችን ከመጠናከራቸው
በተፈለገው መንገድ ሊሄዱ አልቻሉም፡፡ በማእከላት በተጨማሪ የተለየ ትኩረት እንዲያገኙ
አገልግሎት ላይ እንቅፋት ለሚሆኑ አንዳንድ አግዘዋል፡፡ ማኅበሩ በፈጠረው ግንዛቤ የጉባኤ ቤቶች
የቤተ ክርስቲያን አካላት የማኅበረ ቅዱሳንን ጥቅም በደንብ እንዲታወቅ ሆኗል፡፡
የአገልግሎት ዓላማ በተደጋጋሚ በማስረዳት ግንዛቤ
እንደሚታወቀው ማኅበረ ቅዱሳን የተለያዩ መገናኛ
ለማስጨበት ቢሞከርም እንዚህ አካላት የራሳቸው
ዓላማ ያላቸው በመሆኑ ከክፉ ድርጊታቸው
ሊታቀቡ አልቻሉም፡፡ በራሳቸው ዓላማ የሚሠሩ
በመሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በሙሉ
ለውጥ አላመጡም፡፡ ጥቂቶች የማኅበሩን ዓለማ
ተረድተው ከጥፋት ድርጊታቸው የተመለሱ ሲሆኑ
ሌሎች ግን በጥፋታቸው እንደቀጠሉ ናቸው፡፡

ስምዐ ጽድቅ፡- ማእከላት ከሚሰጡት አገልግሎት


አንጻር ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ምን ተጠቀሙ
ዲያቆን አስቻለሁ ጥላሁን
ማለት እንችላለን?

ዲያቆን አስቻለሁ ጥላሁን፡- የማእከላት አስተዋጽኦ ብዙኃንን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ስብከተ
ሲታሰብ ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ወንጌልን ለምእመናን ያደረሰና እያስፋፋ
ላይ እያደረገ ያለውን ተጋድሎ ይታሰባል፡፡ በዚህ ቆይቷል፡፡ ይህ በመሆኑም ምእመናንም ሆኑ
ኢ-አማንያን ቤተ ክርስቲያንና ሥርዓቷን በሚገባ
ሁኔታ ማእከላት ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን
እንዲያውቁ አድርጓል፡፡ በተሠራው ሥራ የቤተ
እያበረከቱ ያለው አስተዋጽኦ ተዘርዝሮ የሚልቅ ክርስቲያን አገልግሎትና ነገር ያገባኛል የሚሉ
አይደለም፡፡ የመጀመሪያውና ዋናው ነገር ወጣት ኦርቶዶክሰውያን እንዲፈጠሩ ማእከላት
ከዚህ ቀደም የቅደስት ቤተ ክርስቲያን አባል ከፍተኛ ድርሻ አላቸው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን
ያልሆኑ ኢ-አማንያን እንዲሁም አሕዛብ ወገኖች ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ የቤተ ክርስቲያንን
አምነው፣ተምረውና ተጠምቀው የሥላሴ ልጅነትን አገልግሎት ሊደግፉ የሚችሉ በሁለት ጎን የተሳሉ

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፲2


ቃለ መ
ጠ ይቅ

እንቁና ብቁ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን በውጭ ሀገራት የሚገኙ ማአእከላት የኢትዮጵያ


ማስመረቅ ችሏል፡፡ የተመረቁትም በተለያዩ የቤተ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ
ክርስቲያን የአገልግሎት ዘርፎች ተሳታፊ እየሆኑ በመላው ዓለም እንዲሰፋፋ የተሻለ አፈጻጸም
ይገኛሉ፡፡ ወጣቱ ትውልድ ሃይማኖቱን ጠንቅቆ ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በማወቅ ከሱስ፣ ከኃጢያት፣ ከስርቆት፣ጊዜን
ስምዐ ጽድቅ፡- እንደ አጠቃላይ ማእከላት መሥራት
በአለባሌ ቦታ ከማሳለፍና ከመሳሰሉት ጎጄ
የሚጠበቅባቸውን ያህል ሠርተዋል ማለት
ድርጊቶች እንዲቆጠብ ሆኗል፡፡ ወጣቶች
ይቻላል? አገልግሎታቸውስ ዘመኑን የዋጀ ነው
ለሥጋና ለነብሳቸው የሚጠቅማቸውን ለይተው
ማለት ያስችላል?
መረዳታቸው በመልካም ሥራ እግዚአብሔርን
ከማስደሰት ባሻገር ለቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ዲያቆን አስቻለሁ ጥላሁን፡- በተወሰነ ደረጃ ማእከላት
የአዕምሮ ረፍትን ሰጥተል፡፡ የሚጠበቅባቸውን ያህል ቤተ ክርስቲያንን እገለገሉ
እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ጉድለት ወይም የሚቀራቸው
በተጨማሪም በተቻለ መጠን አጽራረ ቤተ
ነገር የለም ብሎ ለመናገር ግን አያስደፍርም፡፡
ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያንን እንዳይደፍሩና
ጉድለቶች ክፍተቶች ይኖራሉ ነገር ግን ሁሉም
እንዳያፈርሱ በማእከላት ሥር ያሉ አባላት ከፍተኛ
ማእከላት የአሠራር ክፍተቶች በተቻለ መጠን
ድርሻ አላቸው፡፡ የማእከላት ልጆች ከሌሎች
በመሸፈን ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመፈጸም
የቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር በጋራ በመሆን
ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ አሠራር፣አካሄድና
ቤተ ክርስቲያንን ሊያፈርሱ ከሚመጡ ተሕድሶ
ትኩረት ማድረግ ካለባቸው ጉዳዮች አንጻር ደግሞ
መናፍቃን፣ አክራሪ እስላሞችና ሌሎች ኃይሎች ማእከላት ገና ብዙ መንገድ መጓዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ጋር ተፋልመው ነው የቤተ ክርስቲያንን ክብርና አገልግሎታቸውን ዘመኑን የዋጀ ለማድረግ ጥረት
መብት የሚያስጠብቁት፡፡ ስለሆነም ማእከላት የሚደረጉ ሲሆን በማእከላት የአገልግሎት አፈጻጸም
የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት እንዲጠበቅ ዙሪያ አንዱ ከሌላው በአፈጻጸም ውጤት ሊለያይ
ከፍተኛ የሆነ ሃይማኖታዊ ተጋድሎ እያደረጉ ይችላል፡፡ አጠቃላይ በአገልግሎት ላይ ያለው ጅምር
ያሉ ናቸው፡፡ ከዚህ ባሻገር ቤተ ክርስቲያን
መልካም ቢሆንም ጅምሩን ለማስቀጠልና የተሻለ
ከሀገር ውስጥ እሰከ ውጭ ሃገር ዘመኑን የዋጀ
አገልግሎት አፈጻጸም እንዲኖር ከመሥራት አንጻር
አገልግሎት እንድትሰጥና ምእመናንም የተሻለ
በሁሉም መዋቅር ላይ ያሉ ሁሉ ድርሻቸውን
መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ከማድረግ አኳያ ሊወጡ ይገባል፡፡
የማእከላት ድርሻ የማይተካ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን
አገልግሎት እስከ ውጭ ሀገራት ድረስ ተደራሽ ስምዐ ጽድቅ፡- የማእከላት አቅም ግንባታና አባላት
በማድጋቸውም የውጭ ሀገር ዜጎች የተጠምቀው አገልግሎት ማስተባበሪያ ክፍል እያከናወነ ያለው
የሥላሴ ልጅነትን ከማግኘታቸው በተጨማሪ ተግባራት ምንድን ናቸው?
በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች መንፋሳዊ ትምህርት
ዲያቆን አስቻለሁ
አስቻለሁ ጥላሁን፡- የእኛ ከፍል እየሠራ
ተምረው ዲያቆናት፣ካህናትና መምህራን ሆነው
ያለው በዋናነት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት
ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ ያደረጉት በውጭ
ማእከላትን መዋቅር መምራት ነው፡፡ ይህ ሲባል
ሀገራት የሚገኙ ማእከላት ናቸው፡፡
ማእከላትን የሚመሩ ሥራ አስፈጻሚዎችን
ይህ ሥራ በቂ ነው ማለት ባይቻለም በተለይ አቅም የማሳደግ ሥራ እንሠራለን፡፡ የገንዘብ፣

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፲፫


ቃለ መ
ጠ ይቅ

የ ቁ ሳ ቁስና የሐሳብ ድጋፍ ሲያስፈልግ ድጋፍ በሚፈልጉ አካባቢዎች ለሚገኙ ማእከላት


ማ እ ከ ላ ት ን እ ን ደ ግ ፋ ለ ን ፡ ፡ ከፍተኛ ሁለንተናዊ አቅጣጫ የመሥጠት፣የመከታተል ሥራ፣
ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ማእከላትን በከፍተኛ በሚያጋጥማቸው ችግር ላይ መውሰድ ስላለባቸው
ደረጃ እየደገፍን ነው፡፡ አባላት ወደ አገልግሎት ርምጃ የማሳወቅ ሥራዎችን እንሠራለን፡፡
እንዲቀርቡና በአገልግሎታቸው እንዲተጉ የመድረግ
ሥራ እንሠራለን፡፡ የአባላትን መረጃ ከመያዝ ስምዐ ጽድቅ፡- በመጨረሻ በማእከላት ላይ በቀጣይ
ጀምሮ በአገልግሎት ላይ የማሰማራት ሥራዎችን ምን የተለየ ነገር ለመሥራት ታስቧል?
እንሠራለን፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን የተለያዩ የአሠራር
ዲያቆን አስቻለሁ ጥላሁን፡- በቀጣይ የአባላትን
መመሪያዎች ተግባሪዊ እንዲሆኑ እንደግፋለን፤
ቁጥር መጨመርና የአገልግሎት አቅማቸውን
አቅጣጫ እናሳያለን፡፡ በተጨማሪም ዕቅድ አቅደን
ማሳድግ ላይ ትኩረት አድርገን የምንሠራ
ማእከላት እርስ በርሳቸው እንዲደጋገፉ እንሠራለን፡፡
ይሆናል፡፡ የአባላትን መረጃ በተገቢ መንገድ ከመያዝ
እንዲሁም ማእከላት የአገልግሎት ልምድ እንዲጋሩ አንስቶ አባላት በስፋትና በጥረት በአገልግሎት
እናደርጋለን፡፡ የአቅም ማሳደጊያ ሥልጠናዎች፣ ላይ እንዲሳተፉ የማድረግ ሥራ እንሠራለን፡፡
ውይይቶችና የማእከላት ቅኝቶች ይደረጋሉ፡፡ ሌላው ማእከላትን የማስፈጸም አቅም መገንባት
ትልቅ የትኩረት አቅታጫችን ነው፡፡ ማእከላት
ስምዐ ጽድቅ፡- ማእከላት ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት
አመራሮች የመምራት አቅማቸው እንዲያድግ
እንዲፈጽሙ ተለዋዋጭ የሆነውን የሀገሪቱን
እናደርጋለን፡፡ ምቹና የተሟላ የአገልግሎት ቦታ
ሁኔታ ለማእከላት የምታስረዱበት መንገድ ምንድ እንዲኖራቸው ከማድረግ አኳያም ሰፊ ሥራ
ነው? የሚሠራ ይሆናል፡፡ በግዢ፣ በክራይም ሆነ
በሥጦታ የሚገኝን የአገልግሎት ቦታ የተሻለ
ዲያቆን አስቻለሁ ጥላሁን፡- የሀገሪቱን ነባራዊ
እንዲሆን ጥረት እናደርጋለን፡፡ የማእከላትን
ሁኔታ ለማእከላት ከምናሰረዳበት መንገድ አንዱ
አሁናዊ ችግሮች መፍታት ሌላው የወደፊት
ተከታታይ ሥልጠና ሲሆኑ ከሥልጠናው
ትኩረት አቅጣጫችን ነው፡፡ ማእከላት ችግሮች
በተጨማሪም በቀጥታ የበይነ መረብ ውይይቶች
ከቦታ ቦታ ይለያያልና ያጋጠሟቸውን ችግሮች
በማድረግ፣የአካል ቅኝት በማድረግና በተለያዩ ጊዜያት
እየለየን እንደ ማእከላቱ ነባራዊ ሁኔታ የምንፈታ
በሚኖሩ የጋራ መድረኮችን እንጠቀማለን፡፡
የተለየና ድንገተኛ ነገር ከተከሰተ በጉዳዩ ዙሪያ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም በስጋት ቀጠና ላይ ላሉ
ፈጣን የሆነ አቅጣጫ ለማእከላት ይሰጣል፡፡ ማእከላት የምናደርገውን በጥናት የተደገፈ ልዩ
ጉዳዩን በትክክል እንዲረዱና አገልግሎታቸውም ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
ጉዳዩን ያገናዘበ እንዲሆን መመሪያ እንሰጣለን፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- ለነበረን ቆይታ እግዚአብሔር
ለማእከላት የምንሰጠው አቅጣጫ እንደ ሁኔታውና
ይስጥልን፡፡
እንደአካባቢው ይለያያል፡፡ ለቤተ ክርስቲያንና
ለምእመናን ሁልጊዜ የስጋት ቀጠና ለሆኑ ዲያቆን አስቻለሁ ጥላሁን፡- እኔም ስለ
አካባቢዎች ቅድሚያ በመስጠት ተከታታይና ልዩ ማእከላት የማውቀውን እንድናገር ስለጋበዛችሁኝ
ድጋፍና ክትትል እናደርግላቸዋልን፡፡ እነዚህ ልዩ በእግዚአብሔር ስም አመሰግናለሁ፡፡

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፲፬


የሕፃና
ት ዓምድ

የቤተ ክርስቲያን ሐኪም ቅዱስ አትናቴዎስ


እህተ ሚካኤል

ልጆች! እንዴት ከረማችሁ! እግዚአብሔር እንዴት ነው? በመንፈሳዊ ሕይወታችሁ በርቱ


ይመስገን! ለወጆች! አዲሱን ዓመት እንዴት እሺ ልጆች! ጎበዞች!
ተቀበላችሁት? መልካም ሰብዕና እንዲኖራችሁ፣
ለወላጆቻችሁ ብሎም ለታላላቆቻችሁ ታዛዥ ልጆች! ዛሬ መስከረም ፴ የስደቱ መታሰቢያ
ተወዳጅ ልጆች ለመሆን በአጠቃላይ ከአምናው ስለሆነው በተለይም ‹‹የቤተ ክርስቲያን ሐኪም››
የተሻሉ ልጆች ለመሆን አቅዳችኋል? ይህን ተብሎ ስለሚጠራው ስለታላቁ ሐዋርያ ስለ
እየተገበራችሁ ካላችሁ በጣም ጥሩ ነው፡ ቅዱስ አትናቴዎስ እንነግራችኋለንና በጥሞና
፡ ትምህርታችሁንስ እየተከታተላችሁ ነው? ተከታተሉን፡፡
አዎን ገና ከአሁኑ ከሥር ከሥር እያጠናችሁ ልጆች! ቅዱስ አትናቴዎስ በ3) ዓ.ም አካባቢ
ጥሩ ውጤት ማምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡ በቤተ እስክንድርያ ግብፅ ውስጥ ነው የተወለደው፡፡
ክርስቲያን፣ በሰንበት ት/ቤት ያላችሁ ተሳትፎ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የማያውቁ አረማውያን
ስለነበሩ ስለ ክርስትና ምንም አያውቅም ነበር፡፡
ከእለታት አንድ ቀን ሕፃኑ አትናቴዎስ ሊጫወት
ከቤቱ ሲወጣ ጎረቤቶቹ የሆኑ የክርስቲያን ልጆች
ሃይማኖታዊ ጨዋታ ሲጫወቱ ተመለከተና
‹‹ክርስቲያን ልሁንና አጫውቱኝ›› አላቸው፡፡
ልጆቹም እሺ አሉትና ዕጣ ተጣጣሉ፡፡ ለአንዱ
ቄስ፣ ለአንዱ ዲያቆን ዕጣ ደረሳቸው፡፡ ለሕፃኑ
አትናቴዎስም ፓትርያርክ የመሆን ዕጣ
ደረሰው፡፡ በዚህን ጊዜ ሌሎቹ ሕፃናት
ለአትናቴዎስ ይሰግዱለት ጀመር፡፡
ይህን የሕፃናቱን መንፈሳዊ ጨዋታ የእስክንድርያው
ፓትርያርክ ቅዱስ እለ እስክንድሮስ ሰገነቱ ላይ
ሆኖ ይመለከት ነበርና ሕፃኑ አትናቴዎስ ወደፊት
ትልቅ የቤተ ክርስቲያን አባት እንደሚሆን
ትንቢት ተናገረለት፡፡ የአትናቴዎስ አባቱ
ሲሞትም እለ እስክንድሮስ ሕፃኑን ከእናቱ ተቀብሎ
አጥምቆትና መንፈሳዊ ትምህርት አስተምሮት
የዲቁና መዓረግን ሾመው፡፡ ወዲያውም የክርስትና
ትምህርትን እንዲያስተምር አዘዘው፡፡ ሕፃኑ
አትናቴዎስ ሲያስተምር ብዙ ሰዎች በአንደበቱ
ጣፋጭነት፣ በትምህርቱ ይደነቁ ነበር፡፡ እለ
እስክምድሮስም ፀጋ እግዚአብሔር በሕፃኑ ላይ
ስላደረ ሊቀ ዲያቆን አድርጎ ሾመው፡፡
ልጆች! ቅዱስ አትናቴዎስ ሊቀ ዲያቆናት ሆኖ
በተሾመበት ጊዜ መናፍቁ አርዮስ ‹‹ ወልድ ፍጡር
ቅዱስ አትናቴዎስ ነው›› የሚል የምንፍቅና ትምህርትን በማስተማሩ

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፲፭


የሕፃና
ት ዓምድ

በቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ተደርጎ አርዮስን ተቀብሏል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ለ5 ጊዜ


ለማውገዝ 3)08 ሊቃውንት ተሰብስበው ነበርና ከመንበሩ በማፈናቀል ወደ በረሃ እንዲሰደድ
የጉባኤው ጸሐፊ አድርገው ቅዱስ አትናቴዎስን አድርገውታል፡፡ ለ05 ዓመታት ያህልም በስደት
ሾሙት፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስም በጉባኤው ላይ አሳልፏል፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ ግን በተሰደደባቸው
መናፈቁ አርዮስን ተከራክሮ አሸነፈው፡፡ ከሌሎች ቦታዎች ሁሉ መከራን እየተቀበለ ያላመኑትን
ሊቃውንት አባቶች ጋር በመሆንም የኢየሱስ ስለክርስቶስ በማስተማር ክርስቲያን ሲያደርግ
ክርስቶስን አምላክነት በዐደባባይ በመመስከር ኖሯል፡፡ ከሩቅ ላሉት ደግሞ የማጽናኛ መልእክቶችን
አርዮስን አሸነፈው፡፡ አርዮስን ተከራክሮ በመጻፍ ክርስቲያኖች በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ፣
ከመርታቱም በላይ ጸሎተ ሃይማኖትን ያረቀቀው ሃይማኖታቸውን እንዲጠብቁ ሲመክር ዘመኑን
ቅዱስ አትናቴዎስ ነው፡፡ አሳልፏል፡፡ በቤተ ክርስቲያን የሚነበበው
ሃይማኖተ አበው የተጻፈው በቅዱስ አትናቴዎስ
ልጆች! የእስክንድርያው 0፱ኛ ፓትርያርክ እለ ዘመን ነው፡፡
እስክንድሮስ በሕይወት በነበረበት ጊዜ ቅዱስ
አትናቴዎስ ከእርሱ በኋላ በእስክንድርያ መንበር ልጆች! ቅዱስ አትናቴዎስ በኖረበት ዘመን ሁሉ
እርሱን ተክቶ ፓትርያርክ እንዲሆን ለሕዝቡ ነግሮ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት የሚነሱ አረጋውያንን
ነበርና ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ ባረፈ ጊዜ ሲታገል የኖረ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን አርበኛና
ሕዝቡ ቅዱስ አትናቴዎስን ሊሾሙት ወሰኑ እርሱ ጠበቃ ነው፡፡ ይህ ቅዱስ አባት በሕይወት ዘመኑ
ግን ‹‹አኔ ለዚህ ክብር የምበቃ አይደለሁም›› ብሎ ብዙ መንፈሳዊ ሥራዎችን በመስራት፣ ታላላቅ
በተራራ ሥር ተደበቀ፡፡ ሕዝቡም ከተደበቀበት ተጋድሎዎችን በመጋደል ቤተ ክርስቲያንን ከብዙ
ፈልገው አምጥተው በ፴3 ዓመቱ በ3)!8 ዓ.ም ጥቃት ተከላክሏል፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ እጅግ ሲበዛ
የእስክንድርያ !ኛ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ፡ ሃይማኖተኛ እና ለእምነቱ ቀናኢ ነበር፡፡ ጀግና፣
፡ ልጆች! ቅዱስ አትናቴዎስ ከቅዱስ እንጦንስ ዘዴኛ፣ ትሁት አባትና ጥበብን የተሞላ ጻድቅ
ምንኩስናን የተቀበለ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ነበር፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ በሕይወት ዘመኑ ብዙና
ነው፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ ለ፵፰ ዓመታት ቤተ
ታላላቅ ሃይማኖታዊ ሥራዎችን ሠርቶ፣ በ፸፭
ክርስቲያንን ያገለገለ ታላቅ አባት ነው፡፡
ዓመቱ አርፏል፡፡ ቅደስት ቤተ ክርስቲያን ይህን
ልጆች! ቅዱስ ፍሬምናጦስ በ3)!8 ዓ.ም አባት ‹‹ሊቀ ሊቃውንት››፣ ‹‹ርዕሰ ሊቃውንት››፣
ለኢትዮጵያ ፓትርያርክ ይሾምላት ዘንድ ‹‹የቤተ ክርስቲያን ሐኪም››፣ የሕይወት ምንጭ››
ለመጠየቅ ከኢትዮጵያ ወደ እስክንድርያ ተልኮ በማለት ትጠራዋለች፡፡
ሄዶ ነበር፡፡ ቅዱስ ፍሬምናጦስ እዚያ ሲደርስ
፲፱ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ ልጆች! መስከረም ፴ ሐዋርያው ቅዱስ አትናቴዎስን
አርፎ በምትኩ ቅዱስ አትናቴዎስ ተተክቶ ስለነበር የስደቱ መታሰቢያ፤ ከስደቱ የተመለሰባት ቀን
የመጣበትን ጉዳይ ለፓትርያርኩ አቀረበ፡፡ ቅዱስ ናትና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህችን ዕለት
አትናቴዎስም ቅዱስ ፍሬምናጦስ በጠየቀው ታከብራለች፡፡
ነገር እጅግ በመደሰት ‹‹ለኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ልጆች! በሚቀጥለው ጊዜ በሌላ ታሪክ እስክንገናኝ
ቋንቋቸውንና ባህላቸውን የሚያውቅ ከአንተ በላይ ቸር ቆዩ!
ማንም የለም›› በማለት ቅዱስ ፍሬምናጦስ ራሱን
የኢትዮጵያ ጳጳስ አድርጎ በመሾም ወደ ኢትዮጵያ የቅዱስ አትናቴዎስ በረከቱ ይደርብን አሜን!
መልሶታል፡፡
ምንጭ
ልጆች! ቅዱስ አትናቴዎስ በሕይወት ዘመኑ ቅዱስ አትናቴዎስ ሕይወቱ እና ትምህርቱ
ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብዙ መከራዎችን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፲፮


ትዝብ

ከመባቻ እስከ መካተቻ


ኪኑኪሩ ከአዲስ አበባ
እግዚአብሔር በሠራው ፍጥረት መታደስን፣ተስፋና መስከረም ወር ላይ ቃለ እግዚአብሔርን ለመስማት
ብርሃንን እናያለን፡፡ የዚህ ምስክሩ የአዲስ ዓመት መባቻ በየጉባኤው የሚታደሙ በየዓውደ ምሕረቱ የሚያዘወትሩ
ተፈጥሮ የምታሳየን የመታደስ ገጽታ ነው፡፡ የተፈጥሮ ሰዎች ወራት ሲቆጠሩ ከዕለት ዕለት እየረሷቸው ጭራሹኑ
መታደስ ሀበትን፣ ውበትን፣ ርካታን፣ ዕድልን ለመጨመር እስከ መተው ሲደርሱ ቢታዩም እንዲሁ ነው፡፡ ከራሳቸው
ነው፡፡ ለሚሠራበት በትናንቱ ላይ የሚጨምርበት፣ ጀምሮ ያያቸው ሁሉ ይታዘባቸዋል፡፡ ከመታዘብ አልፎ ግን
ከትናንት በተሻለ ከፍ ከፍ የሚልበት ጸጋ ማግኘት ነው፡፡ የሚሰናከልባቸውም ይኖራል፡፡

ሰዎች የተሰጣቸውን የተፈጥሮ ጸጋ በውል መጠቀም ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብ፣ ገዳማትን ለመሳለም፣
ይገባቸዋል፡፡ የተፈጥሮ አዲስነት በራሱ ለሰዎች አዲስና አብያተ ክርስቲያናትን ለማገልግል በመጀመሪያዎቹ
ብሩህ ነገር እንዲያስቡ ገፊ ምክንያት ይሆናቸዋል፡፡ ራሳቸውን ወራት የተነሣሡ ሰዎች ሲቆዩ ከራሳቸው ጋር የገቡትን
ይጠይቃሉ፡፡ ለምን እኔስ አልታደስም፣ አላንሠራራም፣ ቃል ሲያፈርሱ ሊስተዋል ይችላል፡፡ ይህ በብዙዎቻችን
አልሻሻልም ይላሉ፡፡ ከተፈጥሮ አዲስነት ጋር ራሳቸውን ሕይወት ውስጥ ሊንጸባረቅ ይችላል፡፡ አለመጽናታችን
አብረው ለማራመድ ይጥራሉ፡፡ ስለዚህም ብሩህ ሐሳብ ግን በራሳችን በሰውም በእግዚአብሔርም ፊት ግን ደስ
ስለሚይዙ በዓመቱ መባቻ ላይ በተነሣሽነት መንፈስ የማያሰኝ ይሆንብናል፡፡
ይራመዳሉ፡፡
ለሰዎች መልካም ለማድረግ፣ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን
ይህ በክርስቲያኖችም ሕይወት ዓመቱን ለንስሓ፣ ለመሥራት በመስከረም የተነሣሡ ሰዎች ከወራት በኋላ
ለመንፈሳዊ ፍሬ ማፍሪያ፣ ለበጎነት መንደርደሪያ ሰው የሚጠሉ ቁጡና ተሳዳቢ ሆነው ቢገኙ ትዝብት
ያደርጉታል፡፡ ለብርቱዎች በትናንት ላይ ለመጨመር፣ ላይ ይወድቃሉ፡፡ ‹‹የቀደመ ፍቅርህን አትተው›› እንዲል
ከትሩፋት ወደ ትሩፋት ለማደግ ያልሙበታል፡፡ ለደካሞች መጽሐፍ ለሰውም ሆነ ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር
ከትናንት ራስን አጠንክሮ ለመራመድ ያቅዱበታል፡፡ ማጽናት ከክርስቲያን በብርቱ ይፈለጋል፡፡ ጀምረን ሳለን
መሐል ላይ ማነከስ ያሳዝናል፡፡
ይሁን እንጂ ትልቁ ጭንቅ በዓመቱ መጀመሪያ ሳይሆን
ቀናት ቀናትን እየወለዱ፣ ወራትም ወራትን እያስከተሉ ጅማሬያችን ከልብ ሲሆን ፍጻሜያችንም እንዲሁ
ሲነጉዱ በመንፈቀ ዓመት ማነከስና መሰልቸት፣ ይሆናል፡፡ መነሣሣታችን ከስሜት የጸዳ መሆን
አለመጽናትና መንገዳገድ የሚከበን ሰዎች ራሳችንን አለበት፡፡ ‹‹በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን
እንታዘባለን፣ ሌሎችም ይታዘቡናል፡፡ ዓለም አትምሰሉ።›› (ሮሜ. ፪፥፪) ያለው የመጽሐፍ ቃል
መደገፊያ ሊሆነን ይገባል፡፡ ስሜታዊ ሆነን ሰንጀምር
በመባቻ የያዝነውን መነቃቃት በመካተቻ እንጥለዋለን፡፡ የቆምን ሊመስለን ይችላል፤ መዛልና መብረክረኩ መፈተኑ
የጀመርነውን አንጨርስም፡፡ በዚህ ጊዜ መዛልና መውደቅ የሚመጣው ውለን ስናድር ነው፡፡ የጽናት ጉዳይ የሚመጣው
ይከተላል፡፡ በመጨረሻዎቹ ወራት ነው፡፡

ሕይወቱን በንስሓ የጀመረ


የጀመረ ሰው መልሶ ወደ ኃጢአት ጎዳና ለአንዳንዶች ግን ራሳቸውን እስኪታዘቡ የሚያደርሳቸው
ካዘነበለ፣ የተጸጸተበትን ነገር መልሶ ካደረገ፣ ሲጀመር በመስከረም የቆሙ መስሏቸው ሳለ ከወራት በኋላ ወድቀው
የታጠበ ሰው መልሶ ከጨቀየ ‹‹ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ መገኘታቸው ነው፡፡ የትዕግሥታችን ፍሬ ጣፋጭ ሊሆን
ደግሞ፦ የታጠበች እሪያ
እሪያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች የሚችለው መጨረሻ ላይ ነው፡፡ ከወራት ወራት የምንራመደው
እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ይሆንባቸዋል።›› በትዕግሥት መሆን አለበት፡፡ ቆመን መጽናታችንን
እንዳለው ይሆናል፡፡ (፪ኛ ጴጥ ፪፥፳፪) የምናወድሰው እግዚአብሔርንም የምናመሰግንበት አዲስ
ብለን ጀምረን የያዝነውን ነገር ጳጉሜን ድረስ ይዘን ተጉዘን
ሕይወታቸውን በጾም በጸሎት ለመምራት ወስነው ለተጨማሪ ጸጋና ትሩፋት አዲስ ብለን መጀመራችንን
መስከረም ላይ የጀመሩ ሰዎች ጥቅምትና ኅዳር ሲታክቱ ስናረጋግጥ ነው፡፡ እንዲህ ሲሆን በአዲስ ዓመት ከፍ ላለ
ቢገኙ መጀመሪያ በራሳቸው ፊት ትዝብት ላይ ሲወድቁ ተጋድሎና በተጋድሎም ለሚገኝ ከፍ ላለ ጸጋ ተነሣሥተናልና
ይታያሉ፡፡ ከዚያ ሌሎች መጀመራቸውን ያስተዋሉ ሰዎች አዲስ ሕይወት እንጀምራለን፡፡ የያዝነው ነገር ሲዘልቅልን፣
መታዘብ ይቀጥላሉ፡፡ አዲስ እንደሆነ ሲቀጥል በእጅጉ ያስደስታል፤ መጽሐፍ

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፲፯


ትዝብ

እንዲህ እንዳለ ‹‹በእነዚህ አርባ ዓመታት የለበስኸው ልብስ ሌላው የጀመርነውን መፈጸም በሂደት አለመጽናት
አላረጀም፥ እግርህም አላበጠም።›› (ዘዳ ፰፥፬) የሚወለደው በትዕግሥት ለመመላለስ ካለመፍቀድና
ካለመዘጋጀት ነው፡፡ ሥጋ ለባሾች ስለሆነን በጎውንም
አዲስ መሆንን ማስቀጠል የምንችለው በጽናት ነው፡፡ ነገር ለመሰልቸት ልንጋለጥ እንችላለን፡፡ ሥጋ ምንም
ዓመት ብዙ ዕለታት አሉት፡፡ በእነዚያ ዕለታት ብዙ ያህል ቢመረው ነፍሳችን ልታጣጥመው ለተዘጋጀችበት
ነገሮች ይፈራረቃሉ፡፡ በእነዚህ ለውጦች ውስጥ ደግሞ ጣፋጭ ፍሬ ራሳችንን ወደፊት ማራመድ ያስፈልጋል፡፡
መፈተን ይኖራል፡፡ በእነዚህ ፈተናዎች ፊት መጽናት ‹‹በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤›› (ዕብ
ደግሞ በአዲስ ዓመት መባቻ ለማድረግ የጀመርነውን ፲፪÷፩) እንደተባለው ነው፡፡
እስከ መካተቻ ይዘን እንድንቀጥል ያስችላል፡፡ በጎን ነገር
አጽንተን መቀጠል የምንችለው ደግሞ በእግዚአብሔር ሌላው ፈታኝ ሁኔታችን ግን አሁንም ቀን አለኝ ብሎ
ረድኤት ነው፡፡ በ እ ር ሱ ተ መ ክ ተ ን መ ጀ መ ር ለ ፍ ጻ ሜ ከመዘናጋት የሚመጣ ስንፍና ነው፡፡ መስከረም የጀመረ
ያ በ ቃ ል ፡ ፡ ቅ ዱ ስ ጳውሎስም ‹‹በበጎ ሥራ በመጽናት ሰው ጥቅምት ላይ ሰንፎ ሌላ መስከረም ስላለኝ ያን
ምስጋናንና ክብርን የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ ጊዜ አደርገዋለሁ ብሎ ማሰብ ትዘብት ላይ የሚጥል
የዘለዓለም ሕይወት ይሰጣቸዋል፤›› (ሮሜ ፪፥፯) ያለውን ነው፡፡ በዚህ ግን ብዙዎች ራሳቸውን ያታልላሉ፡፡ ነገር
ቃል ማሰብ ይገባናል፡፡ ለደቀ መዝሙሩም ‹‹በጊዜውም ግን ሁሉም ዓመት ለሰዎች ምቹ አይሆኑም፤ ‹‹ነገ›› ብሎ
አለጊዜውም ጽና፥›› (፪ኛ ጢሞ ፬፥፪) ማለቱ በጊዜያት ውስጥ መቅጠር የሚገባ አይሆንም ፤ የተሰጠንን ዘመን መጠቀም
በሚመጡ ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ውስጥ ከእኛ የሚፈለግ
እንጂ፡፡ ‹‹ነገ›› ምን አልባትም ያቀድነውን ሁሉ ልንፈጽም
በደረጃ ላቅ ያለ ጽናት አለ ማለት ነው፡፡
የማንችልበት የከፋ ዘመን ሊሆን ሊሆን ይችላል፡፡ ጠቢቡ
ሰዎች ለራሳችን ባልታመንን ቁጥር ራሳችንን ሰሎሞን ‹‹የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት
እንጠላለን፡፡ ራሳችንን ደጋግመን በትዝብት ዓይን ካየነው ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት
ውስጣችን ይቃወሳል፡፡ ሰው ራሱን የመምራት ችግር ሳይደርሱ፤›› (መክ ፲፪፥፩ ) ያለው ይህንን ዓይነት ስንፍና
እንዳጋጠመው ካሰበ ራሱን የሌላ አድርጎ ስለሚቆጥር ለመዋጋት ነው፡፡
ተስፋም ሊቆርጥ ይችላል፡፡ የዚህ መፈተኛው ደግሞ
ይህ አስተሳሳብ ግን በእጅጉ የሚነቀፈው በሌለን ሥልጣን
በጊዜያት ውስጥ እናደርገዋለን ያልነውን ነገር ባሰብነው
ነገን እንደምንኖርበት ማሳባችንም ነው፡፡ የተሰጠንን
ጊዜ መፈጸም አለመቻል አንዱ ነው፡፡ ይህ ራስን ከመግዛት
ሳንጠቀም ሌላ አዲስ ዓመትና መስከረም እንደሚመጣ
ጋርም ይገናኛል፡፡ ‹‹በበጎነትም ዕውቀትን ፥ በዕውቀትም
አስበን መዘናጋት፣ የጀመርነውን ማቋረጥ አስተዛዛቢ
ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም
ነው፡፡ ሐዋርያው ‹‹ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ
እግዚአብሔርን መምሰል፥›› የሚለው የሐዋርያው ቃል
እንሄዳለን፤ በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን
(፪ኛ ጴጥ ፩፥፮) ይህንን ያሳስባል፡፡
እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ
የጀመርነውን መፈጸም በሂደት አለመጽናት የሚወለደው የሚሆነውን አታውቁምና። ሕይወታችሁ ምንድር ነው?
ስሜታዊ ሆኖ ከመመላለስ ነው፡፡ ያለንበትን ጊዜያዊ ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ
ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋሎት ናችሁና።
ሁኔታ ሳይሆን ዘላቂውን በብዙ ለውጦች ውስጥ በዚህ ፈንታ ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን
የማለፋችንን ነገር ካለማሰብ ነው፡፡ ክርስቲያኖች ከትናንት እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።››
ይገባችኋል።›› ያለው ይህን መሰል
መማር ይገባል፤ ከታላላቆቻችን መማር ይገባል፡፡ ከላይ ስሜት ያላቸውን ሰዎች ሲመክር ነው፡፡ (ያዕቆ ፬፥ ፲፫)
በዕውቀት ራስን መግዛት ያለው የሐዋርያው ቃል ሊጠበቅ
የሚችለው ከትናንት ልምዶቻችን፣ ከታላላቆቻችን፣ ስለዚህ ክርስቲያኖች ሆነን ሳለን በዕውቀት ሳይሆን
ከመጻሕፍትም ስንማር ነው፡፡ ይህ ከስሜት ያድነናል፡፡ በስሜት፣ በትሕትና ሳይሆን በትዕቢት፣ በትዕግሥት
መጽሐፍ ‹‹የዱሮውን ዘመን አስብ፥ የብዙ ትውልድንም ሳይሆን በመታከት፣ ራስን በመግዛት ሳይሆን በመደዴነት
ዓመታት አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ ከተጓዝን አዲስ ዓመት ያሰብነውን ያህል አዲስ
ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል።›› (ዘዳ ፴፪፥፯) አይሆንልንም፡፡ በአዲስ ዓመት መባቻ በብሩህ መንፈስ
ያለውን እንደትጥቅ መያዝ ይገባል፡፡ በእርግጥም ዕውቀት የጀመርነው ሁሉ አይቀጥልም፡፡ ይህንን ካላደረግን ደግሞ
ከስሜት ያወጣል፡፡ ስለዚህ አቅማችንን፣ የሕይወት ራስን ከመታዘብ ጀምሮ በሰውና በእግዚአብሔር ሚዛን
ዓላማችንን፣ ያለንን ጸጋና ሀብት ከግምት አስገብተን ፊት መቅለል ያስከትልብናል፡፡
በመስከረም እናቅዳለን፤ ይህ ሲሆን እስከ ጳጉሜን ድረስ
በጽናት ያቀድነውን እየፈጸምን እንጓዛለን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፲፰


ምሥጢ
ሬን ላካፍ
ላች ሁ

በሥራ ቦታዬ ካሉ ሰዎች ጋር መስማማት አልቻልኩም


ውድ የስምዐ ጽድቅ አዘጋጆች እንዴት አላችሁ? እኔ እግዚአብሔር አስቸጋሪ ሰዎች ስለሆኑ አንድናስቆጣቸው፣ እንድናወግዛቸው፣
ይመስገን ደኅና ነኝ፡፡ ስሜ ወለተ ጊዮርጊስ ይባላል፡፡ በአንድ እንድናገላቸው የተፈረደባቸው ናቸው ማለት ሳይሆን
ትልቅ የመንግስት መሥሪያ ቤት ውስጥ ሠራተኛ ነኝ፡፡ በዚህ ልናገለግላቸውም ኃላፊነት ይዘን አብረውን እንዲኖሩ እንፈቅዳለን
መሥሪያ ቤት ውስጥ በዙሪያዬ ባሉ ሰዎች ብዙም ደስተኛ ማለትም ነው፡፡
አይደለሁም፡፡ በብዙ መልኩ ከተገልጋይ ጋር የሚያገናኝ
መሥሪያ ቤት እንደመሆኑ መጠን ብዙ ወንጀልና ግፍ በተገልጋይ ‹‹ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ
ላይ ሢሰራ ሳይ አዝናለሁ፡፡ ከበታቼም ሆነ ከበላዬ ያሉና በአጠገቤ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ። ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል
ያሉ የሥራ ባልደረቦቼ የሚሠሩትም ሆነ የሚናገሩት ነገር ከሥነ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።›› (ሮሜ ፲፪፥ ፲፯) የሚለው
ምግባር የወጣ ነው፡፡ በተለይም ከእኔ ክርስቲያናዊ ሕይወትና የሐዋርያውን የምክር ቃል ገንዘብ ማድረግ ነው፡፡ ከሰዎች ጋር
ተገቢ ነው ብዬ ካመንኩበት አኗኗር በተለይ ደግሞ መሥሪያ መኖር ማለት ደግሞ ከክርስቲያን ማኅበረሰብ ጋር፣ ቤተሰባችን
ቤቱ ካለው መመሪያ አንፃር በብዙ ነገር ግራ እጋባለሁ፡፡ ብዙ ጋር፣ ከጎረቤቶቻችን ጋር፣ ከሥራ ባልደረቦቻችን ጋር፣ እንደ
ጥፋት ሢሠራ ባይም ዝም እላለሁ እንጂ መጋጨቱን ብዙ ሀገር ከሀገራችን ዜጎች ሁሉ ጋር፣ ከዓለሙም ሁሉ ሕዝብ ጋር
አልፈልግም፤ ብዙ ጊዜም መታገሥ እመርጣለሁ፡፡ ከተቻለ ማለታችን ነው፡፡
መሥሪያ ቤቱን ለቅቄ በመሔድ መለየት አስባለሁ፤ ነገር ግን
ከቤተሰባችን ጋር ጋብቻ፣ የመዋለድ፣ የዝምድና ሕግን ጠብቀን
የተሻለ ደሞዝ የሚከፍለኝና ለሙያዬ በእጀጉ የቀረበ መሥሪያ
መኖር ማለት ነው፡፡ ከጎረቤቶቻችን ጋር የመንደሮቻችንን
ቤት በመሆኑ ብለቅ በእኔም ሆነ በቤተሰቤ የኑሮ ሁኔታ ላይ
የጋራ ማኅበራዊ፣ ባህላዊ፣ አስተዳደራዊ ወዘተ ሕግ ጠብቀን
ጫና ይፈጥራል፡፡ ስለዚህ አንዳንዴ ሲመረኝ ክፉ ደግ ለመነጋገር
ማለታችን ነው፡፡ በሥራ ቦታችን አሠሪና ሠራተኞች፣ ሥራና
እገደዳለሁ፤ የሚሠሩት ሥራ ተገቢ አለመሆኑን ጭምር ፊት
ሠራተኛን፣ ሠራተኛና ተገልጋይን፣ሠራተኛና ሠራተኛን ወዘተ
ለፊት በመናገር ለማሳመን ብሞክርም አልተሳካልኝም፡፡ በዚህ
በሚያስተሳስሩ ሕግና መመሪያዎች እየተገዛን ማለት ነው፡፡
ዓይነት ሁኔታ ከእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ጋር እንዴት ሆኜ
በሀገር ደረጃም የሀገርን ሕግ፣ በዓለም ውስጥም ሰብአዊና ዓለም
መቀጠል እችላለሁ ብዬ እጨነቃለሁ፡፡ ሕይወቴን በእንደነዚህ
አቀፍ ሕግጋትን ጠብቆ መኖር ማለታችን ነው፡፡ በዚህ ሁሉ
ዓይነት ሰዎች መካከል እንዲት መምራት እችላለሁ? ምንስ
ውስጥ ግን የማይገሰሰው ክርስቲያናዊ ሕግጋት ሳይሸራረፉብን
ማድረግ አለብኝ? የዕናንተን ምክር እሻለሁ፡፡
እንዲሆን ተጋድሎ እናደርጋለን፡፡
ውድ ጠያቂያችን! በመጀመሪያ አክብረው ለዓምዳችን በላኩት
ውድ ጠያቂያችን! ያጋጠመዎትን በሥራ ቦታ የሚያጋጥም
ጥያቄ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ እንደሚረዱት ሰዎች ከሚኖሩት የግንኙነት ችግር መፍትሔ ለመስጠት ወይም አቋም ለመያዝ
የእምነት ሕይወት፣ ካደጉበት አካባቢ ባህልና ሥነ ልቡና ፣ ተቋማዊ ሕግጋትንና ክርስቲያናዊ ሕይወትን መነሻ አድርጎ
በየጊዜው ባሉ ሁኔታዎች ውስጥ በግል ወይም በጋራ ካሉብን በየቅጽበቱ መራመድን ይሻል፡፡
ልዩ ልዩ ዝንባሌና ፍላጎቶች ምክንያት አንዱ ከአንዱ ጋር
የሚስማማባቸው ወይም የሚቃረንባቸው ሁኔታዎች ከምንም በላይ ግን ግንኙነትን የሠመረና ተገቢ ለማድረግ
ይፈጠራሉ፡፡ ራስን ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ራስን በመጀመሪያ መመርመር
ግድ ነው፡፡ በራስ ማንነት፣ሐሳብና ተግባር ላይ ዕውቀት ሊኖረን
ክርስቲያኖች በዚህ በፍላጎትና በዝንባሌ በእምነት የተለያየ ይገባል፡፡ ሰዎች አልተመቹኝም ከማለት በፊት እኔ ምን ያህል
ማኅበረሰብ በሚኖርበት ዓለም ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ ትክክለኛ፣ ቅን፣ ታማኝና የፍቅር ሰው ነኝ ወይ ብሎ ራስን
ከእነዚህ ሁሉ ጋር እንዴት እንደሚኖሩ ክርስቲያኖች እንዲጠበቡ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ሌላው ሰው ላይ ያለን ችግር ለማየት
ያስፈልጋል፡፡ ይህ ዓለም ክፋትና መከራ ያለበት ዓለም ነው፡፡ አስቀድሞ ራስን በጠራ ዓይን ማየት ይገባል፡፡ ‹‹አስቀድመህ
‹‹እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን
ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።››ብሎ ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።›› በማለት ተጽፏልና
ጌታችን ሲናገር የክርስቲያኖች መንገድ አስጨናቂ መሆኑን (ማቴ ፳፫፥፳፮)
እናስተውላለን፡፡(ማቴ፲፥፲፮)
ውድ ጠያቂያችን! አስቀድመው የሥራ ባልደረቦችዎ በእርስዎ
በዓለም ውስጥ ሁሉም ሰው ክርስቲያናዊ የእምነት ሕይወት፣ ላይ ያላቸውን የቅሬታና የቍጣ ምንጮችን በውል ይለዩ፤
አመለካከትና አኗኗር ሊኖረው አይችልም፡፡ ስለዚህ ሕይወትን በትጋትና በታማኝነት ሥራዎን አይሠሩ ከሆነ፣ ሥራዎን
የምንኖረው ከአስቸጋሪ ሰዎችም ጋር ነው፡፡ ይህ ማለት ግን በብቃት ለመፈጸም የአቅም ውስንነት አጋጥሞዎት ከሆነ፣

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፲፱


ምሥጢ
ሬን ላካፍ
ላች ሁ

ለመምከርና ለማገዝ ሳይሆን ለቍጣ፣ ለነቀፌታና ለክስ ከማድረጉም በላይ የሰዎችን አስቸጋሪ ባሕሪ መቀየር ይቻላል፡፡
የሚቻኮሉ ከሆነ፣ አለአግባብ ጥቅምን የሚያገኙ ከሆነ፣ ሰዎችን
በአድልዎ የሚያዩ ከሆነ፣ የተቋሙንና የተቋሙን ማኅበረሰብ ከዚህ አልፎም የሚያስቆጣ የሚያሳዝን ነገርም እያደረጉብን
ሕግና ደንቦች የማያከብሩ ከሆነ ወዘተ ባልደረቦችዎ ለእርስዎ ስለፍቅር ብለን ክፉውን በበጎ እየመለስን ልባቸውን ወደ ቀናው
ባላቸው አመለካካትና ግንኙነት ላይ እንቅፋት ይፈጠራል፡፡ መንገድ ለመመለስ መትጋት አለብን፡፡ ይህ በወንጌል ጌታችን
‹‹በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን
ውድ ጠያቂያችን! እርስዎን ከሚያስነቅፉ ነገሮች ነጻ ሆነው፣ ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም
እንደገለጹልንም ክርስቲያናዊ መንፈሰን ይዘው የሚመላለሱ መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤››(ማቴ ፭፥ ፵፬)
ከሆነ ከእርስዎ የሚጠበቀው በባልደረቦችዎ በኩል ለእርስዎ በማለት በሰጠን ቃሉ መሠረት የምንጠልፍበት ተጋድሎ ነው፡፡
ፈተና የሆኑ ጠባያትን ምንነትና ደረጃ በውል መለየት ነው፡፡
እነዚህ ጠባያት በሥራ አካባቢ እንዲዳብሩ ምክንያት የሆነባቸውን ውድ ጠያቂያችን! ይህ ማለት ግን ከአቅማችን በላይ የሆነ
መሠረታዊ ነገሮች ማጥናት ነው፡፡ ይህንን ሲያደርጉ ግን ነገር አያጋጥመንም ማለት አይደለም፡፡ ክፋትን አጽንተው
እነርሱን የሚያዩበትን ዓይን ጤናማ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ እስከ መጨረሻው ፈተና የሚሆኑብን ሰዎች በሥራ ገበታችን
አካባቢ ላይጠፉ ይችላሉ፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ በራስ ጥረት፣
ባልንጀሮቻችንን የምናይብት ዓይን ጤናማ የሚሆነው ፍቅር በጓደኞች ጥረትና በተቋማዊ አሠራር ተደግፎ ፈተናውን
ያልተለየው ሲሆን ነው፡፡ ባሳለፏቸው የሥራ ጊዜያት አዋኪ ለማራቅ መትጋት ደግሞ ያስፈልጋል፡፡ ይህም ጌታችን በሰጠው
ሆነዋል ብለው ያሰቧቸውን ባልደረቦች በቍጣ፣ በክስ፣ በወቀሳ፣ በሚከተለው ቃሉ መሠረት ቢሆን የተመረጠ ነው፡፡ ‹‹ከእነዚህ
በምሬት፣ በጠላትነት ወዘተ ከማየትዎት በፊት በርኅራኄ
ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ በሰማያት ያለው አባታችሁ
መንፈስ፣ በትዕግሥት መንፈስ፣ በማገልግል መንፈስ ያዩባቸውን
ፈቃድ አይደለም። ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ
ቅጽበቶች ምን ያህል እንደሆነ ገምግሙ፡፡ በዚህ መንፈስ
ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ
አዋኪ ባልደረቦችዎን ባዩባቸው ቅጽበቶች ምን አደረጉ? በጸሎት
አደረግኸው፤ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር
አስበዋቸው እንደሆነ፣ በምክር ጎብኝተዋቸው እንደሆነ በቃል
ወይም በመጽሐፍ ቃለ እግዚአብሔር አገልግለዋቸው እንደሆነ አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ
ወዘተ ያስቡ፡፡ ጋር ውሰድ፤ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤
ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ
ሰዎች ትክክለኛና የለዘቡ ሆነው እንዲቀርቡን ብቻ መጠበቅ ቀራጭ ይሁንልህ።›› ብሏል፡፡ (ማቴ ፲፰፥፲፬)
የለብንም፡፡ ሰዎች ትክክለኛና የለዘቡ እንዲሆኑ ልናገለግላቸውም
ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ መጠበብ ያስፈልጋል፡፡ ሐዋርያው በመሥሪያ ቤት የሚኖሩ ባልደረቦች ክርስቲያኖች ሆኑ ሌሎች
‹‹እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ በተቻለ መጠን ከላይ በተጠቀሰው መንገድ በበጎ መንፈስ
ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤›› (ኤፌ ፬፥፲፭) እንዳለ እንዲራመዱና ለመንፈሳዊ ሕይወታችን የተስማማ ስብእና
እውነትን ለማጽናት ብለን የምንጣላቸው፣ ጦር የምንሰብቅባቸው እንዲኖራቸው መትጋት ያስፈልጋል፡፡ ከአቅም በላይ ሲሆን
ባልንጀሮች እንዳይኖሩን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ግን በተቻለ መጠን መምከርና መገሠጽ ተገቢ ነው፡፡ ግላዊ
ምክርና ተግሣጻችንን የማይቀበል(ሉ) ከሆነ ያግባባናል
በዚህ ረገድ ተግባራችን፣ ቃላችን፣ ገጽታችን ሁሉ በጎ ተጽእኖ ብለን ከምናምንባቸው የሥራ ኃላፊዎች ጋር ሆኖ መምከር
ሊፈጠር ይገባል፡፡ የሰዎች አልጫ መሆን ሊያበሳጨን አይገባም፡፡ ያስፈልጋል፡፡
ጨው ሆነን ልናጣፍጣቸውም ኃላፊነት አለብን፡፡ ልባም መሆን
ለክርስቲያን ግዴታው ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ክፉውን መንፈስ ሁሉ ከዚህ ከተሻገረ ደግሞ ወደ አደባባይ ማምጣት ይገባል፡፡ አደባባይ
በበጎ እንለውጠዋለን፡፡ መጽሐፍም እንዲህ እያለ ይመክረናል፡፡ የምንለው አስተዳደራዊ ሕግጋት ጉዳዮች የሚታዩበት አሠራር
ነው፡፡ በዚህም መሠረት የአስተዳደር ሕግጋትን መነሻ አድርገን
‹‹የለዘበች መልስ ቍጣን ትመልሳለች፤ ሸካራ ቃል ግን ቍጣን
በሚመለከተው አካል በኩል ጉዳዩን ማቅረብና ፍትሕ መሻት
ታስነሣለች።›› (ምሳ. ፲፭፥፩)፤
ተገቢ ይሆናል ማለት ነው፡፡
‹‹በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ። ለእያንዳንዱ እንዴት
ውድ ጠያቂያችን! እርስዎ ክርስቲያናዊነትን ጠብቀው
እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ
መራመድዎን ካረጋገጡ በኋላ አንድ ክርስቲያን ለማገልገል
ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።›› ቆላ. ፬፥፭)
የሚሄዱበትን ምዕራፍን አይርሱ፡፡ በግልና በጋራ መምከርንና
ተብሎ እንደተጻፈ ክርስቲያን የሆነ ሰው ከሌሎች ተሽሎ
በመጨረሻም ፈተና ለማቅለል የሥራ ባልደረቦችን ፈተና
መግኘት እንዳለብን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ሰዎች የኛን አርአያ
በአስተዳደራዊ እና በሥነ ምግባር ሕግጋት ለማቅልል እንዲተጉ
ይከተሉ ዘንድ አሊያም የምንለውን የሰሙ ዘንድ እኛ በነገር ሁሉ
ለመምከር እንወዳለን፡፡
ከእነርሱ የተሻልን ሆነን መገኘት ሁሉን በትዕግሥት ማሳለፍና
ድካማቸውን ቀስ ብሎ ማስረዳት መልካም ግኙንነት እንዲኖረን ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ስምዐ ጽድቅ መስከረም ፩-፴/፳፻፲፭ ዓ.ም ፳

You might also like