Professional Documents
Culture Documents
በይትባረክ ሙላቱ
የዛሬው የትምሕርት ክፍለ ጊዜ የሚዳስሰው
❖ የቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት መከለስና ማጠቃለል
የክርስቲያኖች አንድነት
እያንዳንዱ ክርስቲያን
ቤተክርስቲያን ቅድስት ናት
ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊት ናት
የቤተክርስቲያን ዕድሜ
❖ ማኀበረ መላዕክት (ቤተክርስቲያን በዓለመ መላእክት)
2. የክርስቲያኖች አንድነት
3. እያንዳንዱ ክርስቲያን
ሕንፃ ቤተክርስቲያን
➢ የክርስቲያኖች መገናኛ መሰብሰቢያ በዓት
➢ ክርስቲያኖች በአንድነት የሚጸልዩበት፣ የሚሰግዱበት፣
ሥጋ ወደሙን የሚቀበሉበት፣ ከእግዚአብሔር ጋር
የሚገናኙበት ቦታና የጸሎት ቤት ማለት ነው፡፡(ኢሳ 56÷7፤
ኤር 7÷10-11፤ ማር 11÷17፤ ሉቃ 19÷46)
➢ ቤተ ክርስቲያንም በፊልጵስዩስ ለመጀመሪያ ጊዜ በጌታችን
ፈቃድ ከተሰራ
➢ ቤተክርስቲያን
የክርስቲያኖች አንድነት
የክርስቲያኖች አንድነት «ማኅበረ ምዕመናን» ማለት ነው
ይህም በአንድ ጌታ በአንድ እምነት እና በአንድ ጥምቀት
አምነው የተጠመቁ፣ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኙ፣
በዚህ ምድር በአንድ አሳብ እና ተስፋ የሚኖሩ፣
በመጪው ዓለምም በእግዚአብሔር መንግሥት
በዘለዓለማዊ አንድነት የሚኖሩ ክርስቲያኖችን
የሚያመለክት ነው፡፡ ማቴ 18÷20
ምሳሌ፡ - ቤተክርስቲያን ዘኢትዮጵያ
ከዓል፡ - በዓል ለማክበር ይሰባሰቡ የነበሩ
እስራኤላውያን ስያሜ (በዓል የዕብራውያን ቃል
ነው)
ቤተክርስቲያን ዘእስክንድርያ
እያንዳንዱ ክርስቲያን
❖ እያንዳንዱን ምዕመን ማለታችን ነው፡፡ ይህም
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የእግዚአብሔር ቤተ
መቅደስ መሆናችሁን አታውቁምን በማለት የገለፀው
ነው፡፡ (1ኛ ቆሮ 6÷19)፡፡
የቤተ ክርስቲያን ባሕሪያት /ቅፅል ስሞች/
ቤተክርስቲያን አንዲት ናት
ቤተክርስቲያን ቅድስት ናት
ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊት ናት
ቤተክርስቲያን አንዲት ናት
➢ቤተክርስቲያን በወርቅ፣ በአፈር፣ በከተማ፣ በገጠር
ብትሰራ ክብሯ አንድ ነው፡፡ ሮሜ 12÷5፡፡ «ብዙዎች
ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን» እንዲል፡፡
➢ምዕመናን አንድ ልብ አንድ ሃሳብ ሆነው በውስጥ
የሚደረገውን ክብር ስለሚካፈሉ ቤተክርስቲያን
አንዲት ናት፡፡ የሚሰራባት ሥርዓት የሚፈፀምባት
ጸሎት አንድ ስለሆነ ቤተክርስቲያን አንዲት ናት፡፡ ገላ
4÷5
ቤተክርስቲያን ቅድስት ናት
• ቅድስና የባሕሪው የሆነው ጌታችን በደሙ
የመሰረታት ስለሆነች ቤተክርስቲያን ቅድስት
ትባላለች፡፡ ሐዋ 20÷28
• በኃጢያትና በክህደት ረክሰው የነበሩ
በእምነት በንስሃ ወደ እርሷ ገብተው
ይቀደሳሉና ቤተክርስቲያን ቅድስት ናት፡፡ መዝ
45÷4
ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፋዊት (ኩላዊት) ናት
ቤተክርስቲያን አንዲት ብትሆንም መንፈሳዊ ናትና
በሁሉ ያለች የሁሉም ናት ምክንያቱም እግዚአብሔር
በአንድ አካባቢ ሊወሰን አይቸልም፡፡
ቤተክርስቲያን በዘር፣ በጎሳ በቋንቋ ተከፍላ የእገሌ
ናት የምትባል ሳትሆን የሁሉና በሁሉ ያለች ናት፡፡
ጌታችን በመስቀል ላይ የተሰቀለው ለሁሉም እንጂ
ለተወሰኑት ብቻ አይደለም፡፡ ማቴ 28÷19
ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊት ናት
❖ የሐዋርያትን ትውፊት፣ ቀኖና፣ ትምህርት ይዛ
ስለምትገኝ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊት ናት፡፡ ኤፌ
2÷20፡፡
ይቆየን!!!!