You are on page 1of 110

ነገረ አበው

አጠቃላይ መግቢያ
• የቀደም አበው ታሪክ በቀጥታም ኾነ በተዘዋዋሪ
የቤተክርስቲያን ታሪክ ነው፡፡
• ቀደም አበው የነበራቸው የአምልኮ ሥርዓት፣ መንፈሳዊነት፣
እረኝነት፣ ትምህርት፣ ወዘተ ኹሉ ቤተክርስቲያን በእነዚህ
ነገሮች የነበራት አካሔድ እንዴት እንደ ነበረ የሚያስረዳ ነው፡፡
• የአበው መጻሕፍት ሲተረጎሙ በምዕራቡ ዓለምና በምሥራቁ
ዓለም ኹለት ተቃራኒ የኾነ ዓላማ ያለው ነው፡፡
– በምዕራቡ ዓለም መጻሕፍቱ የሚተረጎሙት ለመተቸት፣ ቋንቋውን
ለመመርመር፣ ትምህርቱን እንዲሁ እንደ ሳይንስ ለማጥናት ነው፡፡
– በምሥራቁ ዓለም ግን መጻሕፍቱ የሚተረጎሙት የአበውን ልብ
ብሎም የክርስቶስን ልብ አግኝቶ በዚያ መሠረት ወደ መሬት
አውርዶና ተግብሮ ለመዳን ነው፡፡
• ነገረ አበው (ፓተር - አባት፣ ፓትሮሎጂ - ነገረ አበው) የአበው ሕይወት፣
ተጋድሎ፣ ጽሑፍ (ትምህርት)፣ አባባሎች፣ እምነት ኹሉ የሚያጠና ነው፡፡
• ሕይወታቸው የሚጠናው ጽሑፋቸውንና አባባላቸውን በቀላሉ ለመረዳት
ይጠቅማል፡፡ በዙሪያቸው የነበረው ማኅበረሰብም ይህን ለመረዳት
አስፈላጊ ነው፡፡
• ያደረጉአቸው ተጋድሎዎችም ከሕይወታቸው የተለየ አይደለም፡፡
• በተለይም በእግዚአብሔር፣ በሰው፣ በቤ/ክ.፣ በነገረ ድኅነት፣ በሥነ
ፍጥረት፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያላቸው ትምህርት እጅግ
ወሳኙ ነው፡፡
• ስለዚህ ነገረ አበው ነገረ ቤተክርስቲያንን ለመረዳትና ወደ ቤ/ክ. ውስጥ
ገብተን አሳብዋን ለመረዳት በር (ደጅ) ነው፡፡
• አበው ብለው መጥራት የተጀመረው ከእነ አብርሃም፣ ይስሐቅ ያዕቆብ
አንሥቶ ነው፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ አይሁድና አረማውያን ቅዱስ
ፖሊካርፐስን “የክርስቲያኖች አባት ይኼ ነው” ይሉት ነበር፡፡ ቅዱስ
አትናቴዎስም ቅዱስ ዲዮናስዮስን “አባት” ብሎ ጠርቶታል፡፡
• “አንድ ሰው ከሌላ ሰው አንደበት ሲማር ይህ ሰው የዚያ
አስተማሪው ሰው ልጅ ነው ይባላል፤ ኹለተኛው ደግሞ አባት
ይባላል” (ቅዱስ ሄሬኔዎስ፣ በእንተ መና.4፡41፣2)፡፡
• በነገረ አበው ትምህርት አንድ ሰው አባት ለመባል
– ጽሑፍ በመጻፍ ሱታፌ ያለው፣
– ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ያለው፡፡ በምዕራቡ ዓለም እነ
ጠርጡለስ፣ አርጌንስ፣ ታቲያን፣ ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ፣
አውሳብዮስ ዘቂሳርያን ያካትታሉ፡፡
– የቅድስና ሕይወት
– ጥንታዊነት፡፡ ብዙውን ጊዜ እስከ 6ኛው መ.ክ.ዘ.፣ አንዳንዶች
እስከ 8ኛ መ.ክ.ዘ.፣ ሌሎች ደግሞ በየትኛውም ጊዜ ያሉ ናቸው
ይላሉ፡፡
የነገረ አበው ታሪክ

• ነገረ አበው የተጠበቀው በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ በቅዱሳን


ሕይወት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ በሙዝየም ወይም በቤተ መጻሕፍት
ውስጥ አይደለም የሚጠበቀው፡፡ በቤ/ክ. ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ነው
የሚጠብቀው፡፡

• ስለዚህ ነገረ አበውን ስናጠና እንደው ታሪክን አይደለም የምናጠናው፤


የቤተ ክርስቲያንን ሕይወት ነው የምንመለከተው፡፡

• በመኾኑም የነገረ ሃይማኖት አንድ አካል ኾኖ ነው የሚጠናው፡፡

• የሚጠበቀውም የዚሁ ደቀ መዝሙር በመኾን ነው፡፡ ያ አባት ሲያርፍ


ደቀመዝሙሩ ይጽፈዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜም በአጭር በአጭር እየተጻፉ
ትንሽ ቆይቶ ወደ ሙሉ ጽሑፍ ሊቀየር ይችላል፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ
• አንዳንድ ጊዜም የጎበኙዋቸው ሰዎች ታሪካቸውን ሊጽፉላቸው ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ
ከ365-425 ዓ.ም. የነበረው ጰላድዮስ ወደ ግብፅ ተጉዞ “መጽሐፈ ገነት”ን ጽፎልናል፡፡

• የነገረ አበው አባት ተብሎ የሚጠራው አውሳብዮስ ዘቂሳርያ ነው፡፡ እርሱ በ326 ዓ.ም.
የአበውን አባባሎችና ጽሑፎች ተርጉሞ ጽፎአልና፡፡

• ከእነ ብዙ እንከኖቹና ብዙ የጠፋ ክፍል ያለው ቢኾን የአውሳብዮስ ዘቂሳርያ መጽሐፍ


የነገረ አበው ዋቢ ተደርጎ በብዙዎች ዘንድ የሚጠቀስ መጽሐፍ ነው፡፡

• አባ ሄሮኒመስም እስከ 371 ዓ.ም. ድረስ የነበሩትን “Illustrious Fathers - የገነኑ


አበው” ብሎ ዋና ዋናዎቹን ጽሑፋቸውንና ታሪካቸውን ጽፎአል፡፡ ነገር ግን በየመካከሉ
አንዳንድ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ የኾኑትን (ለምሳሌ ታቲያን፣ አውኖሚዮስ) እንደ
ቤ/ክ. አባቶች አድርጎ መጻፉ አስተችቶታል፡፡

• በውጪው ዓለም የነገረ አበው መጻሕፍት እንደ ገና መጠናት የጀመሩት ከ16ኛው


አንሥቶ እስከ 19ኛው መ.ክ.ዘ. ባለው ጊዜ ላይ ነው፡፡ ይህም የኾነው ብዙ የትምህርት
የነገረ አበው ትምህርት ጥቅም
• የነገረ አበው ትምህርት ራሱን የቻለ የነገረ መለኮት የትምህርት ዘርፍ ሳይኾን
ለኹሉም የትምህርት ዘርፎች ምንጭ ነው፡፡ ምክንያቱም በዚያ ውስጥ
የሚገኘው የአበው ሕይወትና ጽሑፋቸው በጠቅላላ ነው፡፡
1. ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር፡- በነገረ አበው ትምህርት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ
ቀዳሚውን ሥፍራ የሚይዝና ኦርቶዶክሳዊነትን ለመከላከል የተጠቀሙበት
ተቀዳሚ መጽሐፍ ነው፡፡
2. ከትምህርተ ሃይማኖት አንጻር፡- የነገረ አበው መጻሕፍት በተለይም
በቅድስት ሥላሴ ያለንን እምነት ይበልጥ አጎልምሰን የቤተ ክርስቲያንን
ዶግማ እንድንረዳ የሚያደርግ ነው፡፡
3. ከንጽጽራዊ ትምህርት አንጻር፡- የነገረ አበው ትምህርት አበው ከቤ/ክ.
ጠላቶች ጋር ስላደረጉት ክርክር፣ ስለ ተከራከሩበት ዘዴ፣ በዚያ ውስጥ
ስላብራሩት ትምህርት ይዘት፣ በአጠቃላይ የቤ/ክ. ልብ ወይም አሳብ
እንድናገኝ ይነግረናል (ይረዱናል)፡፡
4. ከነገረ ቤተ ክርስቲያን አንጻር፡- ነገረ አበው የሕያዊት ቤ/ክ. ምንነት፣ በቅድስት ሥላሴ ስላላት
እምነት፣ ስለ ክርስቶስ ሥራና ትምህርት፣ ስለ ክርስቲያን ሥነ ምግባርና ሥርዓተ አምልኮ
በጥልቀት የሚነግረን ነው፡፡
5. ከምሥጢራተ ቤ/ክ. አንጻር፡- የአበው ቅዳሴያትን በማኖር በምሥጢራት በኩል ያለው
ትምህርት ምን እንደ ኾነ ይነግረናል፡፡
6. ከቤ/ክ. ታሪክ አንጻር፡- የነገረ አበው ት/ት በቤ/ክ. ታሪክ ስለ ተከናወኑ ክንውኖች በደንብ
ይነግረናል፡፡
7. ከነገረ ማርያም አንጻር፡- ከነገረ ክርስቶስ ጋር ተቀናጅቶ ይቀርብ ስለ ነበረ ራሱን ችሎ ጎልቶ
አልወጣም ነበር፡፡ በመኾኑም በጥንት አበው ትምህርት ውስጥ ነገረ ማርያምን የምናገኘው
በዋናነት በ2 መንገድ ይኸውም አንደኛው በዶግማ ውስጥ (ለምሳሌ ወላዲተ አምላክነትዋ)
ኹለተኛው ደግሞ በዕቅበተ እምነት ውስጥ (ለምሳሌ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ) ውስጥ ነው፡፡
8. ከገዳማዊ ሕይወት አንጻር፡- ቅዱስ አትናቴዎስ ስለ ቅዱስ እንጦንስ የጻፈው፣ ጰላድዮስ ስለ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅና በገዳማተ ግብጽ ስለ ተመለከተው የጻፉት ተጠቃሽ ነው፡፡
9. ከመንፈሳዊ ሕይወት አንጻር፡- አበው ከጻፉአቸው ዶግማዊና ዕቅበተ እምነታዊ መጻሕፍት
በተጨማሪ የመንፈሳዊ ሕይወት ትርጉሙ ምን እንደ ኾነም አኑረዉልናል፡፡
10. ከኖላዊነት አንጻር፡- በዚህ ረገድም እጅግ የበለጸገ ትምህርታቸውንና ሕይወታቸውን
እንመለከታለን፡፡
ነገረ አበውና የእኛ ዘመን፡-
• ብዙ ሰዎች ቤተ ክርስቲያንን ሲነቅፉ የድሮ ነገር ናፋቂ
አድርገው ያስብዋታል፡፡ ወደ ፊት ሳትጓዝ የድሮውን ብቻ
የምትናፍቅና ኋላ ቀር ነች እንደኾነች አድርገው
ይሥልዋታል፡፡
• ዳሩ ግን የነገረ አበው ትምህርት ዘመናችንን እንደ
አባቶቻችን እንድንኖር የሚያደርግ፣ ከጥንቱ መንገድ
እንዳንወጣ የሚጠብቅ ስለ ኾነ አስፈላጊነቱ አጠያያቂ
አይደለም፡፡
የነገረ አበው መጻሕፍት አከፋፈል
1. ከጊዜ አንጻር፡- የነገረ አበው መጻሕፍት በተለይ እስከ አምስተኛው
መ.ክ.ዘ. የነበሩትን በኹለት ይከፈላሉ፡- ቅድመ ኒቅያ እና ድኅረ
ኒቅያ በመባል !
2. ከቋንቋ አንጻር፡- የምሥራቃውያን አበው መጻሕፍት አብዛኞቹ
በጽርዕ የተጻፉ ሲኾኑ የምዕራባውያን ደግሞ የተጻፉት በላቲን ነው፡፡
3. ከቦታ አንጻር፡- የእስክንድርያ፣ የአንጾክያ፣ የቀጰዶቅያ እና የላቲን
ብሎ በ4 መክፈል ይቻላል፡፡
4. ከይዘታቸው አንጻር፡- ዕቅበተ እምነት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ
ትርጓሜያት፣ ድርሳናትና ስብከቶች፣ መልእክታት፣ ቅዳሴያት፣
ግጥሞችና ቅኔዎች፣ ክርክሮች፣ የገዳማዊ ሕይወት ጽሑፎች፣ የቤ/ክ.
ቀኖናዎችና የቤ/ክ. ታሪክ ብሎ መክፈል ይቻላል፡፡
ትውፊትና ቤተክርስቲያን
1.የምዕራባውያን ትውፊት
 በ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሮማ ቤተክርስቲያን መሪዎች የስልጣን ጥማት የተነሳ ስትከፈል ከግሪክ ጀምሮ
ወደ ምዕራብ ምዕራብውያን ተባሉ፡፡
 ትውፊታቸው የምዕራብያኑ ትውፊት(western tradition) በመባል ይጠራሉ፡፡
2. የምስራቅ ኦርቶዶክስ ትውፊት
የምስራቅ አበው አብዛኞቹ የሐዋርያት ደቀመዝሙርት ከነበሩት አበው የተማሩ ናቸው፡፡
1. ከ12ቱ ሐዋርያት አብዛኞቹ ያስተማሩት፤ሰማዕትነትም ያረፉት በዚህ ስፍራ ነው
2.ለዕብራውያን ትውፊት የቀረቡ በመሆናቸው(ቤተ-ክርስቲያን ከዕብራውያን የወረሰቻቸው ብዙ በጎ ትውፊት
አላት)፡፡
3. ቤተ- ክርስትያን የተመሠረተቸውና የመጀመሪያዎቹ ጥንታዊያን የክርስትና ትምህርት ቤቶች የተssሙት
በዚህ ቦታ በመሆኑ የሐዋርያት ትምህርት፤ሥርዐትና ትውፊት በሚገባ ተጠብቆ ደርfM::
3. የቢዛንታይን ኦርቶዶክስ ትውፊት
 በዚህ ስም የሚታወቁት የኬልቄዶን ጉባዬ ውሳኔ የተቀበሉ ማለትም የሁለት ባህርይ እምነት የሚያራምዱ
አብያተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡

 ለምሳሌ፡- ሩሲያ፡ዩክሬን፡ሰርቪያ፡ቦሲኒያ፡ግሪክ
ሐዋርያነ አበው (ተላውያነ
ሐዋርያት)
• በዚህ ውስጥ የሚካተቱት በዋናነት፡-
– ቅዱስ አግናጥዮስ፡- 7 መልእክታት አሉት፡፡

– ፖሊካርፐስ፡- 1 መልእክት አለው፡፡

– ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም፡- 2 መልእክታት አሉት፡፡

– ሄርማስ፡- 1 መልእክት አለው፡፡


• ሐዋርያነ አበው የምንላቸው ከሐዋርያት ቀጥለው በቤ/ክ.
የነበሩት ክርስቲያን መምህራን ጸሐፊዎች ናቸው፡፡

• ሐዋርያነ አበው የሚል ስም የተሰጣቸውም በ17ኛው


መ.ክ.ዘ. (1664 ዓ.ም.) ነው እንጂ ድሮ እንዲህ የሚል
መጠሪያ አይታወቅም፡፡

• አብዛኞቹ ጽሑፎቻቸው “መልእክታት” በሚል ምድብ


የሚመደቡ ናቸው፡፡
ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ
• የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ የነበረ ነው፡፡
• ለባሴ እግዚአብሔር በመባልም ይታወቃል፡፡
• በ30 ዓ.ም. የተወለደ ሲኾን በማቴ.18፡2-4 ላይ እንደ
ተገለጠው ጌታችን ያቀፈው ሕፃን እንደ ኾነ ይነገራል፡፡ ቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ ግን አግናጥዮስ ጌታችንን እንዳላየው
ይናገራል፡፡
• አውሳብዮስ እንደሚነግረን ከቅዱስ ጴጥሮስ ቀጥሎ ሦስተኛ ኾኖ
በአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ነበር፡፡
• ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔርን “ቅዱስ እግዚአብሔር፣ ቅዱስ
ኀያል፣ ቅዱስ ሕያው የማይሞት ማረን ይቅር በለን” ብለው
ሲያመሰግኑት በራእይ በማየቱ ይህን በአንጾኪያ ቤ/ክ. በቅዳሴ
ውስጥ አካትቶታል፡፡ ይህ ተሰጥኦን የመመለስ ሥርዓትም ሌሎች
አብያተ ክርስቲያናትም ሔዶአል፡፡
• ከንጉሥ (ከትራጃን) ጋር ስለ መገናኘቱ!

– ንጉሥ ክርስትናን ለማስፋፋት የነበረውን የቅዱስ አግናጥዮስን ትጋት በሰማ ጊዜ


አስጠራው፡፡ “ስለ ተሰቀለው ክርስቶስ” መነጋገርም ጀመሩ፡፡

– ትራጃን፡- “አንተ ማን ነህ አንተ ርኩስ ርጉም፤ የእኛን ትእዛዝ የምትጥስና ሌሎቹም


እንዲሁ እንዲያደርጉ የምታሳምን የምታሳምፅና በአሰቃቂ ሞት እንዲሞቱ የምታደርግ?”

– ቅዱስ አግናጥዮስ፡- “ማንም ቲኦፎሮስን ርጉም ብሎ የሚጠራው የለም፡፡ ኹሉም ርኩስ


መንፈሶች ከእግዚአብሔር አገልጋዮች ተለይተዋል፡፡ ምክንያቱም እኔ የእነዚህ መንፈሶች
ጠላት ነኝ፡፡ ነገር ግን አንተ እነርሱን በማክበር እኔን ርኩስ አልከኝ፡፡ ይኹን እንጂ ሰማያዊ
ንጉሥ የሚኾን ክርስቶስ በእኔ ላይ አለ፡፡ በእርሱም እነዚህን የርኩስ መንፈስ መሣሪያዎች
በሙሉ እጠየፋቸዋለሁ፡፡”

– ትራጃን፡- ቲኦፎሮስ ማን ነው?

– ቅዱስ አግናጥዮስ፡- “ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረበት እርሱ ቲኦፎሮስ ነው፡፡”


– ትራጃን፡- “በእኛ አእምሮ ያለው አምላክ ለአንተ አምልክ አይመስልህም ማለት ነው?
በጦርነት ጊዜ በጠላቶቻችን ላይ ድል እንድናደርግና እንድንደሰት የሚረዱን እነርሱ
አማልክት አይደሉም ማለት ነው?”
– አግናጥዮስ፡- “የሀገሩን ኹሉ አጋንንት እየጠራህ አምላክት የምትል አንተ ያለኸው
በስሕተት ውስጥ ነው፡፡ ነገር ግን ሰማይንና ምድርን ባሕርንና በውስጥዋ ያሉትንም ኹሉ
የፈጠረ አንድ እግዚአብሔር አለ፡፡ እርሱም እኔ በመንግሥቱ የምደሰትበት
የእግዚአብሔር አንድያ ልጁ የኾነ አንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡”
– ትራጃን፡- አንተ የምትለው በጴንጠናዊው በጲላጦስ ዘመን የተሰቀለውን ነው?
– አግናጥዮስ፡- “ስለ እኔ ኀጢአት ሲል የተሰቀለው የፍጥረታት ኹሉ ፈጣሪ አታላይና
ተንኮለኛ የኾነውን ዲያብሎስንም የፈጠረና በጥፋቱም እመቀ እመቃት እንዲወርድ
የፈረደበትን፣ እርሱን በመከተል በልባቸው የተሸከሙትንም ኹሉ እንዲሁ እመቀ
እመቃት እንዲወርዱ የሚፈርድባቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ማለቴ ነው፡፡”
– ትራጃን፡- “ስለዚህ እርሱ የተሰቀለው በአንተ አለ ማለት ነው?”
– አግናጥዮስ፡- “በርግጥ በእውነት ደግሞም ተጽፎአል፡፡ እንዲህ ተብሎ፡- “በእነርሱም
እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እኾናለሁ፤ እነርሱም
ሕዝቤ ይኾናሉ” (1ኛ ቆሮ.6፡16)፡፡ እኔ የጌታዬ የመድኀኒቴ የኢየሱስ ክርስቶስ ካህን
ነኝ፡፡ ለእርሱ የዘወትር መሥዋዕትን አቀርባለሁ፡፡ እርሱ ስለ እኔ ፍቅር ሲል ራሱን
መሥዋዕት አድርጎ እንዳቀረበ እኔም ሕይወቴን ለእርሱ መሥዋዕት አድርጌ ለማቅረብ
እመኛለሁ፡፡”
– ከዚህ ተከትሎም ንጉሡ እጅግ ተቆጣ፡፡ ቅዱስ አግናጥዮስ አሳቡን እንደማይቀይር ተመልክቶአልና፡፡
በመኾኑም በአንጾኪያ ቢቀጣው ሕዝቡ ረብሻና ሁከት ሊያነሣ ይችላል ብሎ በማሰብ እንዲህ አለ፡-
“አግናጥዮስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንደ ተሸከመና በውስጡ እንዳለ አረጋግጦአል፡፡ ስለዚህ
ለሕዝቡ መቀጣጫ እንዲኾን በወታደሮች ታስሮ ወደ ታላቅዋ ከተማ ወደ ሮም ሔዶ ለተራቡ
አንበሶች ይሰጥ፡፡ ሕዝቡን ለማስደሰትና ለማርካት ሲባል ይህ እንዲኾን አዘናል፡፡”

– ሊቀ ጳጳሱም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ተሰኘ፡፡ ተንበርክኮም እንዲህ አለ፡- “አምላክ ሆይ !


የፍቅርህን ብዛት ለግሰኸኛልና ስለሰጠኸኝ ክብር አመሰግንሃለሁ፡፡ ሐዋርያህ እንደ ኾነው እንደ
ቅዱስ ጳውሎስ በብረት ሰንሰለት እንድታሰር ፈቅደህልኛልና አመሰግንሃለሁ፡፡” እንዲህ በደስታ
እየተናገረ እያለም የብረት ሰንሰለትን አመጡ፡፡ እርሱም ሰንሰለቶቹን ሳማቸው፡፡ ለ40 ዓመታት
ኖላዊ የኾነላትን ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅ ዘንድም እግዚአብሔርን ማለደው፡፡

– በጉዞው ላይ ብዙ እንግልት ደርሶበታል፡፡ የሔደው በ10 ወታደሮች ታጅቦ ነውና፡፡

– ሰርምኔስ በደረሰ ጊዜም ቅዱስ ፖሊካርፐስ መጥቶ ተጎንብሶ ሰንሰለቶቹን ስሞታል፡፡ ቅዱስ
አግናጥዮስም፡- “ቤተ ክርስቲያንን አደራ” ብሎታል፡፡

– አራቱን መልእክታት ማለትም ወደ ኤፌሶን፣ ወደ ማግኔዥያ፣ ወደ ሮምና ወደ ትራልያ የጻፋቸው


መልእክታትም በዚህ (በስምርናስ ባረፈ) ጊዜ በረከት ሊቀበሉ ለመጡት ክርስቲያኖች የጻፋቸው
ናቸው፡፡ በተለይ የሮም መልእክቱ ስለ ሰማዕትነቱ የጻፈው ነው፡፡
– በዚህ ጊዜ ምእመናን ቅዱሱ ሰማዕት እንዳይኾን ማልደዉትና ከልክለዉት ነበር፡፡ እርሱ ግን፡-
“እግዚአብሔርን ለማግኘት ከዚህ የበለጠ ሌላ ዕድልን አላገኝም፡፡ ስለዚህ ይህን ውለታ ብቻ
ትውሉልኝ ዘንድ እለምላችኋለሁ፡፡ የተዘጋጀ መሠዊያ በፊቴ ሳለልኝ ለእግዚአብሔር መባ ኾኜ
እቀርብ ዘንድ ፍቀዱልኝ” ብሎአቸዋል፡፡

– “እርሱን እፈልገዋለሁ፡፡ ስለ እግዚአብሔር በደስታ እንደምሞት ይታወቅ ዘንድ ለኹሉም


አብያተ ክርስቲያናት እጽፋለሁ፡፡ ስለዚህ የሰማዕትነት ጉዞዬን አታሰናክሉብኝ፡፡ ጊዜው ያልኾነ
ፍቅር አታሳዩኝ፤ አይጠቅመኝምና፡፡ ክርስቶስን በመከራው እመስለው ዘንድ እንድትፈቅዱልኝ
እለምናችኋለሁ፡፡ እኔ ንጹህ መገበሪያ ስንዴ ነኝ፡፡ በአናብስት ጥርሶች እፈጫለሁ፡፡ እነርሱም
የእኔ ወደ እግዚአብሔር መድረሻ መንገዶቼ ናቸውና፡፡ አናብስቱ ወደ ክርስቶስ መሔጃ
ምክንያት ይኾኑኝ ዘንድ ጸልዩልኝ፡፡ በዚያም ንጹህ የክርስቶስ ኅብስት እኾናለሁ፡፡”

– “አናብስቱን እጎበኛቸዋለሁ፡፡ ወዲያውኑ ጓጉተው ፈጥነው እንዲበሉኝ እጸልያለሁ፡፡


አባብላቸዋለሁ፡፡ ከእኔ ጋር ጥቂት እንዲቆዩ አልፈቅድላቸውም፡፡ ያለ ምንም ፍርሐት
እንዲነኩኝና እንዲቀርቡኝ አደርጋለሁ፡፡ ነገር ግን ሌሎችን (ለምሳሌ እነ ዳንኤልን) እንደ
ተዉአቸው እነርሱ እኔን ለመብላት እንቢ ብለው ፈቃደኞች ባይኾኑ እንዲበሉኝ
አስገድዳቸዋለሁ፡፡ ይህን በማለቴ ይቅርታ አድርጉልኝ፡፡ ለመሞት የጓጓሁት ምን እንደማገኝና
ምን እንደምጠቀም ስለማውቅና ስለሚታየኝ ነውና፡፡ አሁን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር
እየጀመርኩ ነውና፡፡”
– “እኔ ክርስቲያን ተብዬ የምጠራው እንዲሁ ዝም ብዬ አይደለም፡፡ ነገር
ግን በእውነት ኾኜ መገኘት አለብኝ፡፡ ስለዚህ እውነተኛ ክርስቲያን ኾኜ
መገኘት እፈልጋለሁ፡፡ እንደዚያ ከኾነ እንደ አንዱ ክርስቲያን ኾኜ
መጠራት እጀምራለሁና፡፡ ከዚያ በኋላ እውነተኛ ምእመን እኾናለሁና፡፡”

– “እኔ መከራ ከተቀበልሁ በእውነት ትወዱኛላችሁ፤ ሳልቀበል ብቀር ግን


ትጠሉኛላችሁ ማለት ነው፡፡”

• ይህን ኹሉ የተማጽኖ መልእክት የጻፈው በተለይ የሮም ክርስቲያኖች


ከሰማዕትነት እንዳያስቀሩት ነው፡፡

• ከሰርምኔስ በተነሣ ጊዜም ቀጥሎ ያረፈው ጢሮአዳ በተባለ ቦታ ነው፡፡

• በጢሮአዳም የቀሩትን ሦስቱን መልእክታት ማለትም ወደ ፊላደልፍያ፣ ወደ


• ቀጥሎም ብዙ ቦታዎችን አቆራርጦና ከብዙ እንግለት በኋላ ሮም ደረሰ፡፡ ወደ ብዙ
ቦታዎች የወሰዱት ግን ሥቃዩ ሲበዛበት ይሞታል የሚል ተስፋ ስለ ነበራቸው ነው፡፡

• የቅዱስ አግናጥዮስ ለአናብስት ተሰጥቶ መሞት ውሳኔ በብዙዎች ዘንድ ተሰምቶ ስለ


ነበር ወደ ሮም በደረሰ ጊዜ እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ ተሰብስቦ ነበር፡፡ ሰማዕት
እንዳይኾን ሊከለክሉት ቢፈልጉም እጅግ ተማጸናቸው፡፡ አረጋጋቸው፡፡ “ጌታዬ ፈጣሪዬ
አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ በእኔ ልብ ፈጽሞ በጥልቅ ተጽፎአል፡፡ ልቤ የሚያምነው
በፍጹም እምነትና ብርታት ነው፡፡ በአናብስት ተከታትፎ ቢቆራረጥ የጌታዬ የመድኀኒቴ
የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእያንዳንዱ የልቡ ቁርጥራጭ ተጽፎ ታገኙታላችሁ” አላቸው፡፡

• ገሚሱ ያለቅሳል፡፡ ገሚሱ በቅዱሱ ጥብዓት በቅንአት ደስ ይሰኛል፡፡ ከፊሉ አዝኖ ተክዞ
ይመለከታል፡፡

• በሌላ መልኩ ደግሞ የንጉሡ ፍርድ አስፈጻሚዎች ቅዱሱን ያጣድፉታል፡፡ ክርስቶስን


እንዲሰድብ ያግባቡታል፡፡ እርሱ ግን “እንድታውቁ የምፈልገው የክርስቶስ ስም
በአንደበቴ ብቻ ያይደለ በልቤ ሰሌዳ ላይም የተጻፈ የታተመ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ስም
• ቀጥሎም በስታድዮሙ ውስጥ በሚገኝ አንድ ጉረኖ ውስጥ ከተቱት፡፡
የአናብስቱን ግሳት ሰምቶ እንዲደነግጥ ብለው አስበው ነበር ይህን ያደረጉት፡፡

• ቅዱሱ ግን እንዲህ አላቸው፡- “እናንት ሮማውያን ሆይ ! ኹላችሁ ከዚህ


የመጣችሁት ይህን ተጋድሎ በዓይናችሁ ለማየት ነውን? እንድታውቁት
የምፈልገው ይህ የሞት ቅጣት በእኔ ላይ የተፈረደው ምንም ወንጀልና ክፉ
ሥራ ሠርቼ አይደለም፡፡ ይህ ነገር ወደ እግዚአብሔር ስለሚያደርሰኝ ነው
እንጂ፡፡ በዚህ ለጌታዬ ያለኝን ፍቅር የምረካበትና ምኞቴ የሚፈጸምበት ስለ
ኾነ ነው እንጂ፡፡ እኔ ንጹህ መገበሪያ ስንዴ ነኝ፡፡ በአናብስቱ ጥርስ
በመፈጨት የክርስቶስ ንጹህ ኅብስት እኾናለሁ፡፡ እርሱ ለእኔ ኅብስተ
ሕይወት ኾኖአልና፡፡”

• ይህን ተናግሮ ሲጨርስም ኹለት የተራቡ አናብስት መጥተው እላዩ ላይ


በመውጣት ቅዱሱን ሰማዕት ቆራርጠው ጥቂት አጥንቱ ብቻ ሲቀር ከሥጋው
ምንም ሳያስቀሩ በሉት፡፡
• ይኸውም በ111 ዓ.ም. ማለት ነው፡፡

• የአ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. የዚህን ታላቅ ሰማዕት የዕረፍት ቀን ታኅሳስ 24 ቀን ታከብረዋለች፡፡ በሐምሌ ሰባት ስንክሳር
ላይ ታነሣዋለች፡፡
የቅዱስ አግናጥዮስ
ትምህርቶች
ሰባት መልእክታትን ጽፎአል

• ወደ ሮም ለሰማዕትነት እየሔደ ሳለ የጻፋቸው አጫጭር መልእክታት ናቸው፡፡


– ወደ ኤፌሶን
– ወደ ማግኔዥያ
– ወደ ትራሊያ
– ወደ ሮሜ
– ወደ ፖሊካርፐስ
– ወደ ሰምርኔስ
– ወደ ፊላደልፊያ

• የተወሳሰቡ አይደሉም፡፡

• መላ ዘመኑን ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ሲናገር ኖሮአል፡፡ “እኔስ [ለቤተ


ክርስቲያን] አንድነት ምክንያት ለመኾን የድርሻዬን ተወጥቻለሁ”
(ፊላደ.8፡1)፡፡
ትምህርቶቹ
ሀ) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መኾኑን
ገልጦአል!
– “አንድ ባለ መድኀኒት ብቻ አለ፡፡ እርሱም በተዋሕዶ ፍጹም
ሰው ፍጹም አምላክ፣ [ከእመቤታችን በነሣው ሥጋ]
የተፈጠረም ያልተፈጠረም፣ በሥጋ የተገለጠ እግዚአብሔር፣
በሞቱ እውነተኛ ሕይወትን የሰጠ፣ ወልደ አብ ወልደ
ማርያም፣ [በለበሰው ሥጋ] መከራ የሚቀበልም [እንደ መለኮቱ
ግን መከራ] የማይቀበልም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው”
(ኤፌ.7፡2)፡፡

– “እንደ ሰውነቱ በእውነት የዳዊት ዘር ነው (ሮሜ.1፡3)፤ እንደ


እግዚአብሔር ፈቃድና ኀይል ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ
ነው፡፡ በእውነት ከድንግል ተወለደ፤ ጽድቅን ኹሉ ይፈጽም
ዘንድም በእደ ዮሐንስ ተጠመቀ (ማቴ.3፡15)” (ስምር.1)፡፡
• ጌታችን መድኀኒዓለም እንደ ኾነ የመልእክታቱ ኹሉ ዋና ማዕከል
ነው፡፡ መምህራችን እርሱ መኾኑን እንዲህ ብሎ ገልጦታል፡-

“ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛው ጌታችን ነው፡፡ እንደዚህ ከኾነ


ታዲያ እንደ ምን ከእርሱ ርቀን መኖር ይቻለናል?
ነቢያት እንኳን ቀድመው በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት
ተመልክተዉት ደቀ መዛሙርቱ ኾነው መምህራችን
ብለው ብለው ተስፋ አድርገው ጠብቀዉታልና፡፡ ስለዚሁ
ምክንያትም በትክክል ለጠበቁት ተስፋ ላደረጉት ሥጋ
ለብሶ በመጣ ጊዜ ከሞት አስነሥቷቸዋል” (ማግን.9)፡፡
ለ) ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ
• ቅዱስ አግናጥዮስ ከቤተ ክርስቲያን መታወቂያዎች አንዱ የኾነውንና “እንተ ላዕለ ኩሉ -
ካቶሊክ - ዓለም አቀፋዊት” የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመ አባት ነው (ስምር.8፡
2)፡፡

• በሌላ መልኩ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን ሲጠራት “የመሥዋዕት ቦታ” ይላታል (ኤፌ.5፡2)፡፡


ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ዘወትር መሥዋዕት በማድረግ ታቀርባለችና፡፡

• ቅዱስ አግናጥዮስ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ከፍተኛ የኾነ ትኩረት ሰጥቶ ያስተማረ ሲኾን
ቀጥሎ ያለውም ከትምህርቶቹ ውስጥ ተጠቃሽ ነው፡-
– “መከፋፈልና ቁጣ ባለበት በዚያ እግዚአብሔር አያድርም፡፡ በንስሐ ለሚመለሱት ግን በእውነት ወደ
እግዚአብሔር አንድነትና ወደ ቤተ ክርስቲያን ኅብረት ቢመለሱ ጌታ ይቅር ይላቸዋል፡፡ ምንም ዓይነት
ነገር በሁከትና በጠብ እንዳታደርጉ እመክራችኋለሁ፡፡ ለእርሱ አስተምህሮ እንደሚገባ ኢየሱስ
ክርስቶስ ባስተማረን መሠረት በፍቅርና በሰላም እንጂ” (ኤፌ.5)፡፡

– “የሰዎችን ቤተ ሰቦች የሚያፈርሱ ሞት የሚፈረድባቸው ከኾነ የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ መስቀልን


እስኪሸከም ድረስ የወደዳትንና የሞተላትን የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን በመለያየት የሚያፈርሱማ ምን
ሐ) ቅዱስ ቁርባንን በተመለከተ

• በጊዜው የነበሩት መናፍቃን ዶሴይስት ይባላሉ፡፡ እነርሱም የጌታችን ሥጋና ደም


አማናዊነትን ይክዱ ስለ ነበሩ ከጸሎትና ከቁርባን ራሳቸውን ያርቁ ነበር (ስምር.6፡2)፡፡
ይህን የሚሉበት መነሻቸውም ሥጋ የክፉው አምላክ ሥራ ውጤት ነው ይሉ ስለ ነበርና
አምላክ በርግጥ ሰው አልኾነም ብለው ያስቡ ስለ ነበረ ነው፡፡

• ስለዚህም ቅዱስ አግናጥዮስ እንዲህ አለ፡- “ከምሥጢረ ቁርባንና ከጸሎት የማይሳተፉና


ራሳቸውን የሚያርቁ መሥዋዕቱ ስለ እኛ ኀጢአት መከራን የተቀበለውንና ሞትን ድል
አድርጎ የተነሣው የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አማናዊ ሥጋ እንደ ኾነ
የማያምኑ ናቸው፡፡ በዚህ የእግዚአብሔር ጸጋ ላይ የማይገባ ነገር የሚናገሩ
በክርክራቸው መካከል ሞታቸውን ይቀበላሉ፡፡ ነገር ግን የክብር ትንሣኤን ይነሡ ዘንድ
ቢያከብሩት ይሻላቸው ነበር” (ስምር.7)፡፡

• እንዲያውም ከሰማዕትነቱ ጋር ሲያነጻጽረው እንዲህ አለ፡-


• “እኔ የእግዚአብሔር ንጹህ መገበሪያ ስንዴ ነኝ፤ እናም በአናብስቱ ጥርስ እፈጫለሁ፤
መ) ክህነትን በተመለከተ

• እንደ ቅዱስ አግናጥዮስ አስተምህሮ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን በፍቅር፣


በአንድነትና በክርስቶስ እርስ በእርስ በመታዘዝ የሚሰባሰቡባት ናት፡፡ ስለዚህም፡-
“ለካህናት መታዘዝ የአንድ ሰው የደካማነት ምልክት አይደለም፤ ነገር ግን ክርስቶስ
በሥጋው ወራት ለአባቱ እንደ ታዘዘ ከእርሱ ጋር ኅብረት ይኖረዋል፡፡ እንዲሁም ሐዋርያት
ለክርስቶስና ለአባቱ እንደ ታዘዙ ለጳጳሳት ታዘዙ፤ እንዲሁም እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ”
አለ (ማግ.13)፡፡

• ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ተናገረ ጳጳሳት፣ ካህናት ለእኛ እንደሚተጉ (ዕብ.13፡17) ምንም ነገር
ብናደርግ ያለ ጳጳሳት ልናደርግ እንደማይገባን፣ የምድራዊ መብልና መጠጥ ሳይኾን
የሰማያዊ ምሥጢር አገልጋዮች ስለ ኾኑ እነርሱን ደስ ማሰኘት እንደሚገባን፣ ከእነርሱ
ውጪም ቤተ ክርስቲያን የሌለን እንደ ኾንን አስተምሮአል (ትራ.2)፡፡

• “ጳጳሳትን የሚያከብር እግዚአብሔር ደግሞ ያከብረዋል፡፡ ነገር ግን ጳጳሱን የማያከብርና


ከእርሱ ውጭ የሚሔድ ዲያብሎስን እያገለገለ ነው፡፡ ጳጳስን የሚያቃልልና የማያከብር
በእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚቀጣ ኹሉ የሚያከብረውን ደግሞ እግዚአብሔር
ሠ) ቤተሰብን በተመለከተ

• “ጌታን እንዲወዱና ኹሉም በሥጋም በነፍስም ከባላቸው ጋር


ተደስተው እንዲኖሩ ለእኅቶቼ ንገራቸው፡፡ እንደዚሁም ለወንድሞቼ
ምከራቸው፡፡ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደደ በጌታ ስም
ሚስቶቻቸውን እንዲወድዱ ንገራቸው፡፡ ማንኛውም ስለ ጌታ ሥጋ
ክብር ብሎ በድንግልና ለመኖር ቢፈቅድ ያለ ትምክሕት ይኹን፡፡
ነገር ግን እንዲህ ስለ ማድረጉ የትዕቢት ነገር የሚያሳይ ከኾነ
ምንም አልሠራም፡፡… ወንድና ሴት ጋብቻ ለመፈጸም ቢፈልጉ
አንድነታቸው በጳጳሱ ይረጋገጣል፡፡ በዚህም ጋብቻው በሥጋቸው
ፈቃድ ሳይኾን በእግዚአብሔር ፈቃድ የተመሠረተ ይኾናል”
(ኤፌ.5፡25)፡፡
ረ) መናፍቃንን በተመለከተ

• ቀደም ብሎ ለመግለፅ እንደ ተሞከረው በጊዜው የነበሩት መናፍቃን ዶሰይስቶች


ናቸው፡፡ እነርሱም ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ፡- “ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና
እነርሱን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው” ብሎ የገለፃቸው
ናቸው (2ኛ ዮሐ.1፡7)፡፡

• “የሞትን ፍሬ ከሚያመርቱ ከእነዚህ ክፉ የሰይጣን ልጆች ሽሹ፡፡ ማንም ከእነርሱ
የቀመሰ ወዲያው በፍጥነት ይሞታልና፡፡ እነዚህ አብ ያልተከላቸው ናቸው፡፡
ስለዚህ እኔ እማጸናችኋለሁ፤ በርግጥ እኔ ሳልኾን የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ነው፡፡
ይህም ለክርስቲያን የሚገባ ምግብን ብቻ ትመገቡ ዘንድና ራሳችሁን የተለየ ከኾነ
ውዳቂ ነገር ትጠብቁ ዘንድ ነው፡፡ ይህም ከኑፋቄ ማለቴ ነው፡፡ እንደዚህ ላለ ነገር
የተሰጡ ሰዎች ገዳይ የኾነን መርዝ በጣፋጭ ወይን አድርገው እንደሚሰጡ
ሰዎች ተገቢ ያልኾኑ ነገሮችን በመናገር ኢየሱስ ክርስቶስን ከመርዛቸው ጋር
ይቀላቅሉታልና፡፡ እንዲህ ያለ መርዝም ያላወቁ ሰዎች በጉጉት ይጠጡታል፡፡
መርዙም በሰውነታቸው ተሰራጭቶ ሞታቸውን ያመጣባቸዋል” (ትራ.11)፡፡
ቅዱስ ፖሊካርፐስ
ልጅነት

• ቅዱስ ፖሊካርፐስ የተወለደው ከክርስቲያን ቤተሰቦች በ70 ዓ.ም. በጥንታዊቷ ሰምርኔስ ከተማ
(ቱርክ ውስጥ የአሁኗ እዝሚር) ነው፡፡

• ቤተሰቦቹን በልጅነቱ ስላጣ ካሊቶስ/ካሊስታ የተባለች ደግ ክርስቲያን አሳድጋዋለች፡፡

• ይህች ካሊስቶ መጀመሪያ እንደ ባሪያ አድርጋ ገዝታዋለች፡፡ ባደገ ጊዜም የቤትዋን ንብረት አለቃ ኾነ፡፡

• አንድ ቀንም ንብረትዋን ኹሉ ለእርሱ አደራ ሰጥታ ወደ ሌላ ቦታ ኼደች፡፡ እርሱም ንብረትዋን


ለድኾች ለድኻ አደጎችና ለመበለቶች ሰጠው፡፡

• ካሊስቶ በተመለሰች ጊዜም አንድ ሌላ ባሪያ ንብረትዋን ኹሉ ለሰዎች እንደ ሰጠባት ነገራት፡፡ ወደ
መጋዘኑ ስትመጣ ግን አንድም ሳይየጎድል ሙሉ ኾኖ አገኘችው፡፡

• በመኾኑም ያን የነገራትን ባሪያ ለምን ዋሸህ ብላ ልትቀጣው አሰበች፡፡ ቅዱስ ፖሊካርፐስ ግን


እውነቱን ነግሮ እንዳትቀጣው አደረገ፡፡ እርስዋም ደስ ተሰኝታ ንብረትዋን ኹሉ እንዲወርስ
አደረገችው፡፡ ቅዱሱ ግን ለገንዘብ ደንታ አልነበረውም፡፡
• ከእርሷም በኋላ የሰምርኔስ ከተማ ጳጳስ ቡኩሎስ
ወስዶ ትምህርተ ሃይማኖትን በሚገባ እያስተማረ
አሳድጎታል፡፡

• ይህ ቅዱስ ቡኩሎስ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ


መዝሙር ስለ ነበር ቅዱስ ፖሊካርፐስ ዮሐንስ
ወንጌላዊን እና ሌሎችንም ሐዋርያት የማግኘት
ዕድል ነበረው፡፡
• ቅዱስ ቡኩሎስ ቅንዓቱንና ትጋቱን አይቶ ዲቁና ሾመው፤
ቀጥሎም ቅስናን ሾመውና የቅርብ ረዳቱ አደረገው::

• ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ሐዋርያዊ ጉዞ በሚያደርግበት


ወቅት አስከትሎት ይኼድ ነበር፡፡

• ከሌሎች ሐዋርያት ረዘም ላለ ጊዜ በምድር ላይ ስለነበር


ለብዙ ዓመታት የእርሱ ደቀ መዝሙር ኾነ::

• ቅዱስ ቡኩሎስ ካረፈ በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ የሰምርኔስ


ከተማ ጳጳስ አድርጎ ሹሞታል::
• ቅዱስ ፖሊካርፐስ ወንጌልን ከሐዋርያት በተለይም ከዮሐንስ በቀጥታ እየሰማ
ያደገ፣ የሐዋርያትን ትውፊት በሚገባ የወረሰ፣ በሥራዎቹ በሙሉ እነርሱን መስሎ
እነርሱን አክሎ የተነሣ አባት ነው፡፡ እንዲያውም ቅዱስ ሄሬኔዎስ ፖሊካርፐስ
የነገረውን እንዲህ ሲል ጽፎልናል፡- “ከዮሐንስ ወንጌላዊና ጌታችንን በዓይን ካዩት
ከሌሎች ጋር የነገረው ግንኙነት ሲናገር፣ እነርሱ የተናገሩትን ጠቅሶ ሲያስተምር፣
ከእነርሱም ስለ ጌታችንና ስላደረጋቸው ተአምራት እንደዚሁም ስላስተማረው
ትምህርት እጅግ መማሩን ሲናገር ሰምቼዋለሁ፡፡”

• የሰምርኔስን ቤተ ክርስቲያን በሚገባ የጠበቀ እና በካህናትና ምእመናን ዘንድም


እጅግ ተወዳጅ የነበረ አባት ነው፡፡

• ብዙ ደቀ መዛሙርትን ያፈራ ሲኾን ከእነዚህም ታላላቆቹ ቅዱስ ሄሬኔዎስ እና


ቅዱስ ፓፒያስ ይገኙበታል፡፡

• የአንጾኪያው ጳጳስ ቅዱስ አግናጥዮስ ቅዱስ ፖሊካርፐስን እጅግ ይወደውና


• ኹለቱ ቅዱሳን ሰፊ የኾነ የዕድሜ ልዩነት የነበራቸው ቢኾንም በሐዋርያት
መካከል ዐዋቂውም ሕፃኑም ቃላቸውን ለመስማት ይሰበሰብ ስለ ነበር በዚያ
ተዋወቁ:: ስለዚህም ኹለቱም የዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዛሙርት ናቸው፡፡

• ቅዱስ አግናጥዮስ ለሰማዕትነት ወደ ሮም ሲጓዝ ለመጨረሻ ጊዜ


ተገናኝተው እንዲህ ብሎታል:- “የአንጾኪያን ቤተ ክርስቲያን አደራ፤ እኔ
መልእክት ላልጻፍሁላቸው አብያተ ክርስቲያናት አንተ ጻፍላቸው::”

• በዚህም ምክንያት ለፊልጵስዩስ ክርስቲያኖች ደብዳቤ ጽፎ ለሌሎች


አብያተ ክርስቲያናት የተጻፉ የአግናጥዮስ መልእክታትንም ጨምሮ
ልኮላቸዋል::

• በመጨረሻም ቅዱስ አግናጥዮስ ለግሉ በስሙ ደብዳቤ ጽፎለታል፤ ይህም


ለግለሰብ የጻፈው ብቸኛው መልእክት ነው::
የእምነት ጠበቃ

• ቅዱስ ፖሊካርፐስ ጠንካራ የኦርቶዶክስ እምነት ጠበቃ ነበር::

• ዘመኑ መናፍቃን (መርቅያንና ቫለንቲነስ) ከቀናችው የሐዋርያት


ትምህርት የወጣ ልዩ ልዩ ትምህርቶችን ያፈሉበትና ምእመናንን
የሚያደናግሩበት ወቅት ስለነበር እነርሱን በመርታት ትክክለኛውን
የሐዋርያት ወንጌል ያስተምር ነበር::

• በምንፍቅና ትምህርት የተወሰዱ ብዙዎችንም ወደ ቀናችው ትምህርት


መልሷል:: ከዚህ የተነሣም፡- “የእስያ መምህር፣ የክርስቲያኖች አባት፣
ጣዖታትን ያጠፋ” እየተባለ ይጠራል፡፡

• ደቀ መዛሙርቱንም “ልጆቼ እባካችሁ ከስሕተት ራቁ” እያለ በተደጋጋሚ


• በአስተምህሮውም ኹሉ መምህሩን ወንጌላዊ ዮሐንስን ይመስል ነበር::
ለምሳሌ ወደ ፊልጵስዩስ ከጻፈው መልእክቱ ብንመለከት:- “ማንም ኢየሱስ
በሥጋ እንደመጣ የማያምን ፀረ-ክርስቶስ ነው:: በመስቀል ላይ መከራ
መቀበሉን የማያምንም ዲያብሎስ ነው:: ማንም የክርስቶስን ትምህርት ለራሱ
እንደሚመቸው የሚያጣምም፤ ትንሣኤና የመጨረሻ ፍርድ የለም የሚል
ይህም የሰይጣን የበኩር ልጅ ነው. . .”

• ይህም ነገረ ሥጋዌን የካዱትን በሚመለከት የጻፈው ሲሆን ከሐዋርያው ቃል


ጋር በእጅጉ ይመሳሰላል:- “የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ
ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ
ከእግዚአብሔር ነው፥ ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን
መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው
መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥” (1ዮሐ. 4፥2-3)::

• በእስያ ብቻ ሳይሆን ሮም ድረስ ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ በዚያ በነበሩ


• ቅዱስ ፖሊካርፐስ ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ አስተምህሮ ሲሰማ
ያለቅስ ነበር፤ እጅግም ስለሚዘገንነው ሥፍራውን ለቆ ይወጣ ነበር::

• ይህንንም ከሐዋርያው ዮሐንስ እንደ ተማረው ያደርግ ነበር፤ በነገር


ኹሉ እርሱን ይመስለው ነበርና::

• ቅዱስ ሄሬኔዎስ ቅዱስ ፖሊካርፐስ እንዲህ ሲል ተሰማ በማለት


ጽፏል: “ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በኤፌሶን ወደ አንድ መታጠቢያ
ክፍል ሲገባ መናፍቁ ቀሪንጦስን አየውና ‘ከዚህ እንሽሽ የእውነት
ጠላቷ ቀሪንጦስ በዚህ አለና’ እያለ ወዲያውኑ ክፍሉን ለቆ ወጣ::”

• እርሱም ቀንደኛ የኾኑ መናፍቃንን መንገድ ላይ በሚያገኝበት ጊዜ


እንዲሁ ያደርግ ነበር::
• ወደ ሮም በተጓዘበት ወቅት መርቅያን የተባለውን መናፍቅ አየውና
ትኩር ብሎ በመመልከት ሲቃወመው መርቅያን “ታውቀኛለህን” አለው::

• ፖሊካርፐስም “አዎን አውቅሃለሁ፤ አንተ የዲያብሎስ የበኩር ልጁ ነህ”


ብሎ መልሶለታል::

• ቅዱስ ሄሬኔዎስም ለመናፍቃን ምላሽ በጻፈው መጽሐፉ ውስጥ ፍሎሪነስ


ለተባለው መናፍቅ መልስ በሰጠበት ክፍል ስለ ፖሊካርፐስ እንዲህ ሲል
ዘግቧል:- “. . . ነግር ግን ይህ ቅዱስ [ፖሊካርፐስን ነው] እንዳንተ
ትምህርት ያለ የተሳሳተ ትምህርት ሲሰማ እንደልማዱ ፈጥኖ ጆሮውን
በመያዝ እንዲህ በማለት ይጮሃል ‘አቤቱ ቸር ፈጣሪዬ ሆይ እስከዚህ
ዘመን ድረስ ያቆየኸኝ ይህን ነገር ልታሰማኝ ነውን?’ . . .ወዲያውም
ይህን ዓይነት የክሕደት ትምህርት የሰማበትን ሥፍራ ለቆ እያለቀሰ
በፍጥነት ይወጣል::”
ሰማዕትነት

• ከሐዋርያነ አበው የመጨረሻ የኾነው የዚህ የቅዱስ ፖሊካርፐስ


የሰማዕትነቱ ዜና የተገኘው የራሱ የኾነችው የሰምርኔስ ቤተ
ክርስቲያን ሰማዕትነቱን በአካል በተከታተሉ ወንድሞች አማካኝነት
ጽፋ ለሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ከበተነችው መልእክት ነው::

• በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት የሰማዕትነታቸው ኹኔታ፣


ሳይፈሩ ሰውነታቸውን ለሰይፍ ለስለት እንዴት እንደ ሰጡ፣ ስለ
ክርስቶስ ለመመስከር እንዴት ይጨክኑ እንደ ነበር በሙሉ ዜና
ገድላቸው እየተጻፈ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ይሰራጭ ነበር::

• እንደ አግናጥዮስ ኹሉ (በሮም እንደ ነበረ) ፖሊካርፐስ ሰማዕት


• እንደልማዳቸው በዓሉ በሚከበርበት በስታድየማቸው
የአራዊት ትርኢት ነበር::

• አሬኒከስ የተባለ አንድ ክርስቲያንም የአሕዛብ


ጣዖታትን ካላመለክህ ለአራዊት እንሰጥሃለን ብለውት
አሻፈረኝ ብሎ በመፅናቱ በዚያ በአራዊት ተበልቶ
ሰማዕት ኾነ::

• በዚህ ጊዜም ሕዝቡ፡- “ክርስቲያኖች እንዲህ እንዲጸኑ


የሚያስተምራቸው ዋነኛው የክርስቲያኖች አባት
• ቅዱስ ፖሊካርፐስ የሞት ፍርድ ሲፈረድበት ጸንቶ በከተማዋ ቢቆይም
ምእመናን እንዲሸሽ እያለቀሱ ስለ ለመኑት ባጠገብ ወዳለች መንደር
ሸሸ::

• በዚያ ቀን ከሌሊት ስለ አብያተ ክርስቲያናት እየጸለየ ሳለ ሰማዕት


እንደሚኾን በራእይ ተረድቶ እንደሚሞት ለወንድሞችና እኅቶች
ነገራቸው፡፡ ያየው ራእይም ትራሱ በእሳት ሲቃጠል ነበር፡፡

• ወዲያው በጥቆማ ተይዞ ወደ ሰምርኔስ ከተማ እያንገላቱ ወስደው


ሕዝብ በተሰበሰበበት በበዓሉ አደባባይ አቆሙት::

• እርሱም ክርስቶስ በሕዝብ አደባባይ ቆሞ የተቀበለውን መከራ እያሰበ


የመከራው ተካፋይ ስላደረገው በፍጹም ደስታ መከራውን ይቀበል
• በሕዝቡ ፊት አቁሞ የሚያናዝዘው ሹም ክርስቶስን እንዲክድ
ሦስት ዕድል እሰጥሃለሁ አለው፡-
• ንጉሡ ወደ ክርስቲያኖች እየጠቆመ፡- “ከከሐዲዎች ራስህን ለይ”
አለው፡፡
• ቅዱስ ፖሊካርፐስም ጣቱን ወደ ጣዖት አምላኪዎችና ወደ
ወታደሮች እያመለከተ፡- “ንጉሥ ሆይ አንተ ራስህ ከከሐዲዎች
ራስህን ለይ” አለው፡፡
• ንጉሡ ለ2ኛ ጊዜ “ኢየሱስ ክርስቶስን ስደበው” አለው፡፡
• ቅዱስ ፖሊካርፐስ ግን እንዲህ አለ፡- ለ86 ዓመታት ያህል እኔ የእርሱ ባሪያ
ነበርኩኝ፡፡ አንድ ቀንም በድሎኝ አያውቅም፡፡ ታዲያ ያዳነኝን ንጉሤን እንዴት
እሰድበዋለሁ?
• ንጉሡ ለመጨረሻ ጊዜ እንዲህ አለ፡- “ክርስቶስ የሚለውን ስም ትተህ በቄሣር ስም
ማል” አለው፡፡ በዚህ ጊዜም ቅዱስ ፖሊካርፐስ እንዲህ አለ፡- “እኔ የክርስቶስ ነኝ፡፡
• በዚህ ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተቆጥቶ በእሳት እንዲቃጠል
ፈረደበት፡፡

• ሕዝቡም፡- “ይህ ሰው የክርስቲያኖች አባት፣


የአማልክቶቻችን ጠላት፣ ጣዖቶቻችንን እንዳናመልክና
እንዳንሰግድላቸው የተቃወመን ክፉ ሰው ነው፡፡ ስለዚህም
ይገደል” ይሉ ነበር፡፡

• ወታደሮቹ እሳቱ ውስጥ ከገባ በኋላ የሚያመልጠን


መስሏቸው ለማጠር ሲዘጋጁ አይቶ “ወደ እሳቱ እንድገባ
ያበረታኝ ጌታዬ በእሳቱ ውስጥም ፀንቼ እንድቆይ
• ወታደሮቹ እጅና እግሩን አስረው ወደ እሳቱ ሲያቀርቡት አይኑን ወደ ሰማይ
አቅንቶ እንዲህ በማለት የመጨረሻ ጸሎት አደረገ:-

• “አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር የተወደደው ልጅህ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት


ሆይ በልጅህ አንተን እንድናውቅ ሆነናል:: የመላእክትና የኀይላት እንዲሁም
የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ አንተ ነህ፤ ፍጥረታትም ሁሉ የሚኖሩት ባንተ ነው::
በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ለዘላለማዊ ሕይወት ትንሣኤ ያለፍርሃት
ከክርስቶስ መከራ ተካፋይ ከሆኑት ከሰማዕታት ወገን እንድቆጠር ስላደረግኸኝ
እና በዚህች ቀንና ሰዓት በሚገባ ስላስተማርኸኝ አመሰግንሃለሁ:: እንደ
እነርሱ ዛሬ በፊትህ ተቀብያለሁና እንደ መልካምና የተወደደ መሥዋዕት
አድርገህ ተቀበልልኝ:: አንተ አስቀድመህ እንዳሳየኸኝ እና እንዳዘጋጀኸኝ :
አንተ እውነተኛና ታማኝ አምላክ ነህና ስለሁሉ ነገር አመሰግንሃለሁ፣
አከብርሃለሁ፣ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ:: ከሰማያዊው ዘላለማዊ ሊቀ ካህናት
ከተወደደው ልጅህ ኢየሱስ ክርስቶስ: ከእርሱ ጋር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር
ክብርና ምስጋና ለአንተ ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን!”
• የጸሎቱ ይዘት ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን ከምታስተምረው ምሥጢረ
ሥላሴ ጋር አንድ ዓይነት ሲኾን ይህንኑም የመሰለ ጸሎት አላት::

• በዚህም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጥንታዊና ከምንጮቹ


ከሐዋርያት የተረከበችው ለመሆኑ ታላቅ ማስረጃ ነው::

• ቅዱሱ ጸሎቱን ሲጨርስ በእሳቱ ውስጥ ወረወሩት::

• በቅዱሳኑ ላይ አድሮ ተአምር የሚሠራ እግዚአብሔር ለምእመናን


መጽናኛ የሚኾን ድንቅ ተአምርን አደረገ::

• እሳቱ የቅዱሱን ሰውነት ዙሪያውን እንደግድግዳ ከቦ የማያቃጥለው


ኾነ::
• ሕዝቡም እሳቱ እንዳላቃጠለው ባዩ ጊዜ በጦር ተወግቶ ይሙት
እያሉ ጮሁ፤ ወታደሮቹም በጦር ወጉተው አንገቱን ቆርጠው በዚህ
ሰማዕትነቱን በ156 ዓ.ም. ፈጸመ፡፡

• ክርስቲያኖች እንዳያመልኩት በሚል የከበረ ሥጋውን አቃጠሉ፤


በዚህ ጊዜ ደስ የሚያሰኝ የእጣንና የሽቶ መዓዛ ሸተተ፡፡

• ክርስቲያኖችም ተረፈ ዓፅሙን በክብር ወሰደው ቀበሩት፡፡


በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. የካቲት 29 ስንክሳር ይታሰባል፡፡

• ቤተ ክርስቲያንም በስሙ ሠሩለት፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን


እኛንም በዚህ ቅዱስ ጸሎት ይማረን አሜን!
የቅዱስ ፖሊካርስ ትምህርት
• እስከ አሁን ባለው መረጃ ቅዱስ ፖሊካርፐስ የጻፈው አንድ መልእክት ነው -
ወደ ፊልጵስዮስ የሚል!

• ይህም ቀደም ብለን እንደ ተመለከትነው ቅዱስ አግናጥዮስ ራሱ ላልጻፈላቸው


እርሱ (ፓፖሊካርፐስ) እንዲጽፍላቸው አሳስቦት ስለ ነበረ ነው፡፡

• ቅዱስ ሄሬኔዎስም ስለዚህ መልእክት ሲናገር፡- “ከፖሊካርፐስ ወደ


ፊልጵስዮስ ሰዎች የተጻፈ እጅግ ድንቅ መልእክት” ብሎታል፡፡

• መልእክቱ ቅዱስ ቀለሜንጦስ ዘሮም ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ከጻፈው ጋር


በእጅጉ የሚመሳሰል ሲኾን በታናሽ እስያ አብያተ ክርስቲያናት እስከ
አራተኛው መ.ክ.ዘ. መገባደጃ ድረስ በቅዳሴ ጊዜ ይነበብ ነበር፡፡

• በዋናነትም በፊልጵስዮስና በሜቄዶንያ ይኖሩ የነበሩት ክርስቲያኖች በምግባር


በሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ የሚመክር ነው፡፡
• የባለ ትዳሮች፣ የመበለቶች፣ የዲያቆናት፣ የወጣቶች፣ የደናግልና የካህናት ሥርዓትና ኀላፊነት
እንዲሁም ተግባራት የሚናገር መጽሐፍ ነው፡፡

• መጽሐፉ በአጠቃላይ የኖላዊነት ጠባይ ያለው መጽሐፍ ነው፡፡

• ትምህርቶቹን በዘርፍ በዘርፍ ለማየት ያህል፡-

• ሀ) ነገረ ክርስቶስን የተመለከተ

• “ማንም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምን ፀረ ክርስቶስ ነው፡፡ በመስቀል ላይ


መከራ መቀበሉን የማያምንም ዲያብሎስ ነው፡፡ ማንም የክርስቶስን ትምህርት ለራሱ
እንደሚመቸው የሚያጣምም፣ ትንሣኤና የመጨረሻ ፍርድ የለም የሚል ይህን የሰይጣን
የበኩር ልጅ ነው፡፡”

• “ስለዚህ ዘወትር በተስፋችንና በጽድቃችን - ይኸውም በመስቀል ላይ በደላችንን በገዛ ሥጋው


ላይ በተሸከመው፣ ነውር ነቀፋ በሌለበት፣ በአንደበቱም ሐሰት ባልተገኘበት፣ ለእኛ ሲል
ማለትም እኛ በእርሱ እንኖር ዘንድ ግን ኹሉንም ነገር በታገሠው በተቀበለው በኢየሱስ
• ለ) በተግባር ሊገለጥ ስለሚገባው እምነት

• “ስለዚህ ወገባችሁን ታጠቁ፡፡ ከንቱውንና ነገረ ዘርቅን


የብዙዎችንም የስሕተት አካሔድን ትታችሁም እግዚአብሔርን
በፍርሐትና በረዓድ አገልግሉ፡፡ ይህን ማድረግ ይቻላችሁ ዘንድ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን ለይቶ ባስነሣውና ክብርን
[የባሕርይ አምላክነትን] እና በቀኙ መቀመጥን በሰጠው፣ በላይ
በሰማይ በታች በምድር ያሉትም ኹሉ ከእግሩ በታች ባስገዛለት
በእግዚአብሔር አምናችኋልና፡፡”

• “ስለዚህ በትዕግሥት ጸንተን እርሱን እንምሰል፡፡ ስለ ስሙ ብለን


መከራን ብንቀበል እርሱን እናመስግነው፡፡ በገዛ ራሱ ሰውነት
ለዚህ አብነት ኾኖናልና፤ አምነንበታልምና፡፡”
• ሐ) ስለ ዲያቆናትና ካህናት
• “በተመሳሳይ ዲያቆናትም የእግዚአብሔርና የክርስቶስ እንጂ የሰዎች
ዲያቆናት ስላይደሉ በጽድቁ ፊት ነውር የሌለባቸው፣ የማይሳደቡ፣ ኹለት
ቃል የማይናገሩ፣ ገንዘብን የማይወድዱ፣ በኹሉም ነገር ልከኞች የኾኑ፣
ርኅሩኀን፣ መስተጋድላን፣ ጌታ ሲኾን የኹሉም አገልጋይ (ዲያቆን) የኾነውን
የእርሱን የእውነት አሰረ ፍኖት ተከትለው የሚኼዱ ሊኾኑ ይገባቸዋል፡፡”

• “ካህናትም እንደዚሁ ሩኅሩኀን፣ ለሰዎች ኹሉ ምሕረት የሚያደርጉ፣


የኮበለሉትን በጎች የሚመልሱ፣ የደከሙትን ኹሉ የሚጎበኙ፣ መበለቶችን
ወይም ድኻ አደጎችን ወይም ድኻ ሰዎችን ችላ የማይሉ፣ ይልቁንስ
በእግዚአብሔርና በሰዎች ፊት ክብር የሚያጎናጽፈውን ሥራ የሚሠሩ፣
የማይቆጡ፣ ኹሉንም ሰው የሚያከብሩ፣ የማያዳሉ፣ ገንዘብን ከመውደድ
የራቁ፣ እኛ ኹላችንም የኀጢአት ባለ ዕዳዎች መኾናችንን ዐውቀው
በማንኛውም ሰው ላይ የሚነገረውን ነቀፋ ለማመን የማይቸኩሉ፣ በሰው ላይ
ለመፍረድ የማይፈጥኑ ሊኾኑ ይገባቸዋል፡፡”
• መ) ምጽዋትን በተመለከተ

• “መልካም ሥራን መሥራት እየተቻላችሁ እርሱን ከመሥራት ቸል


አትበሉ፡፡ ምጽዋት ከሞት ታድናለችና፡፡ ኹላችሁም አንዳችሁ
ለአንዳችሁ ተገዙ (ታዘዙ)፡፡ በበጎ ሥራችሁ ምስጋናን ትቀበሉና በእናንተ
ምክንያት እግዚአብሔር እንዳይሰደብ በመካከላችሁ ነውር ነቀፋ
አይኑር፡፡”

• ሠ) አገርን በተመለከተ

• “[የእምነት] ፍሬያችሁ በሰዎች ኹሉ ፊት ይገለጥ ዘንድ፣ በእርሱ


(በእግዚአብሔር) ዘንድም ፍጹማን ትኾኑ ዘንድ ስለ ነገሥታት፣ ስለ
ሹመኞችና ስለ መኳንንት፣ ስለሚያሳድድዋችሁና ስለሚጠልዋችሁ፣ ስለ
መስቀል ጠላቶችም ጭምር ጸልዩ፡፡”
ቀሌምንጦስ ዘሮም
• በጥንታዊቱ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያትን አህለው ሐዋርያትን
መስለው ከተነሡና እጅግ ከሚታወቁት ሐዋርያነ አበው መካከል፥
የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር የነበረው ቅዱስ
ቀሌምንጦስ ዘሮም አንዱ ነው፡፡

• ስለዚሁ ቅዱስ ሰው ብዙ ዓይነት አመለካከት ያለ ሲኾን፥ አውሳብዮስ


ዘቂሳርያ፣ አባ ጀሮም እና ሌሎች አርጌንስን ተከትለው የቅዱስ
ጳውሎስ ደቀ መዝሙር እንደ ነበረ ያስተምራሉ /ፊልጵ.4፥3/፡፡

• “የንጉሥ ድምጥያኖስ የአጎት ልጅ ነው” የሚሉም ያሉ ሲኾን፣


ሌሎች ደግሞ “እጅግ ጥበበኛና የተማረ ሰው የነበረና በኋላም
ዕውቀትን ፍለጋ ወደ ፍልስጥኤም ሲሔድ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር
ተገናኝቶ ክርስቲያን ኾኗል” ይላሉ /አባ ቴዎድሮስ ያ.ማላቲ፣
ሐዋርያነ አበው፣ ገጽ 64/፡፡
• በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ሊቃውንት የሚታመነውና ሕዳር 29 የሚነበበው
ስንክሳር እንደሚነግረን ደግሞ፥ ቀሌምንጦስ ዘሮም ትውልዱ
ከንጉሣውያን ቤተ ሰቦች ነው፡፡

• አባቱ “ቀውስጦስ” የሮማው ንጉሥ የጦር አለቃ የነበረ ሲኾን፥ በቅዱስ


ጴጥሮስ ስብከት አምኗል::

• በአንድ ወቅት “ቀውስጦስ” ወደ ሮማው ንጉሥ ሔዶ ለብዙ ቀናት


ቢዘገይ ወንድሙ ሚስቱን ለማግባት ፈለገ::

• የቀሌምንጦስ እናት ይህንን ስትሰማ ቀሌምንጦስንና ታናሽ ወንድሙን


ይዛ አባታቸው እስኪመለስ ድረስ ፍልስፍና ይማሩ ብላ ወደ አቴንስ
ከተማ ለመሔድ ተነሣች::
• በመርከብ ተሳፍረው ሲሔዱ ሳሉ ግን ኃይለኛ ማዕበል ተነሥቶ
መርከቧን ሰባበራት፤ ሰዎቹንም በታተናቸው::

• ቀሌምንጦስንም ከቤተ ሰቦቹ ለይቶ እስክንድርያ አደረሰው::

• ቅዱስ ጴጥሮስ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ እስክንድርያ


ከተማ ገብቶ ሲያስተምር ከቀሌምንጦስ በቀር አማኝ አላገኘም::

• ቀሌምንጦስ የቅዱስ ጴጥሮስን ስብከት ሲሰማ በጌታችን አምኖ


የክርስትና ጥምቀት ተጠመቀ፤ ከዚችም ሰዓት ጀምሮ የቅዱስ
ጴጥሮስ ደቀ መዝሙር ኾነ፡፡
• ቅዱስ ሄሮኔዎስ እንደሚነግረን፥ በኋላ ላይ የሮማ ከተማ አራተኛው ሊቀ
ጳጳስ ኾኗል /በእንተ መናፍቃን፣ ሣልሳይ መጽሐፍ 3:3/፡፡

• አውሳብዮስ ዘቂሳርያም ከዚህ ተነሥቶ “ጊዜው ከ92 እስከ 101 ዓ.ም. ነው” ይላል፡፡

• ቅዱስ ጴጥሮስ ከጌታችን ያገኘውን ጥልቅ ምሥጢር በሙሉ ለተማሪው ለቀሌምንጦስ


ነግሮታል::

• የቤተ ክርስቲያንን አደራ ከብዙዎች ሐዋርያት በተለይም ከቅዱስ ጴጥሮስ


ተቀብሏል::

• ቅዱሳን ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን የምትመራበትን ቀኖናና ሥርዐት (ዲድስቅልያን፣


አራቱ ከፍል ሲኖዶስን) አስረክበውታል::

• ቀሌምንጦስ ዘሮም ገድለ ሐዋርያትንና በዓላውያን ነገሥታት ፊት በእምነት


መመስከራቸውን ጽፏል::
ዕረፍቱ

• አባታችን ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም በብዙ ከተሞች ወንጌልን ሰብኳል፤


ብዙዎችንም እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መርቶ አሳምኗል::

• ይህንን የሰማው የወቅቱ የሮማ ንጉሥ ጠራብሎስ ወታደሮቹን ልኮ


አስመጣው፤ ክርስቶስን ክዶ ጣዖታትን እንዲያመልክ አዘዘው::

• ትእዛዙንም እንዳልሰማ ባየ ጊዜ ሕዝቡን ፈርቶ በዚያ ማሰቃየትን


ስላልወደደ ወደ ሌላ ከተማ ሰደደው::

• የከተማይቱንም ገዥ በብዙ ማሰቃያ እንዲያሰቃየው አዘዘ፤ ያም ገዥ


ከባድ ብረት በአንገቱ አስሮ ወደ ባሕር ወረወረው::
• ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ አደራ ሰጠ፤ እንዳስተማሩት ሐዋርያትም
የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጀ::

• በዓመቱም የቀሌምንጦስ ሥጋው በባሕሩ ላይ ታየ በጥልቁም እንደ ሕያው


ያስተምር ነበር::

• ምእመናን ሥጋውን አውጥተው ለመውሰድ ፈልገው አልንቀሳቀስ ስላላቸው


ፈቃዱ እንዳልኾነ ዐውቀው ትተውት ሔዱ::

• በየዓመቱም ሥጋው ይገለጥላቸው ነበር፤ እነርሱም እየመጡ ይባረኩ ነበር፤


ከሥጋውም ብዙ ልዩ ልዩ ተአምራት ይደረጉ ነበር /ሕዳር 29 የሚነበብ
ስንክሳር/::

• ለእግዚአብሔር ምስጋና ይኹን፤ እኛንም በሐዋርያ ቀሌምንጦስ ጸሎት


ይማረን፤ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር፤ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
የቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም
ትምህርት
መጽሐፈ ቀሌምንጦስ

• ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም፥ ከመምህሩ ከቅዱስ ጴጥሮስ እየጠየቀ ብዙ


ምሥጢራትን የተረዳ ሲኾን ይህንንም ጽፎ አስቀምጦልናል - መጽሐፈ
ቀሌምንጦስ የሚባል ይህ ነው፡፡

• በስሙ የተሰየመለት ይህ መጽሐፍ ይዘቱ ምን እንደሚመስል ከዚህ


ቀጥለን በአጭሩ እንመለከታለን፡፡

• መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ቤተ ክርስቲያናችን ከምትቀበላቸው 81 (ሰማንያ


አሐዱ) ቅዱሳት መጻሕፍት ቍጥር ሲኾን ከስምንቱ የሥርዐት መጻሕፍት
መደብ ነው::

• 11 ምዕራፍም አለው፡፡
• ቅዱስ ቀሌምንጦስ መጽሐፉን ለመጻፍ ምክንያት የኾነው ነገር እንዲህ
በማለት ያስቀምጣል፡-

• “የኦሪትና የነቢያት ዕውቀት ስላልነበረኝ አይሁድ ስለ አዳም አፈጣጠር


እና ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም በጠየቁኝ ጊዜ መልስ መስጠት
አልቻልኩም፤ [የጌታችንን መምጣት ለማስታበል፣ ትንቢቱ
አልተፈጸመም ለማለት እመቤታችንን ከይሁዳ ወገን አይደለችም እያሉ
ይከራከሩት ነበር]:: በዚህ ጊዜ መምህሬ ጴጥሮስን ኹሉንም ያስረዳኝ
ዘንድ ጠየቅሁት፤ እርሱም አዘነ፤ በቅንአትም ኾኖ በቅድሚያ ስለ ዓለም
አፈጣጠር ቀጥሎም ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ከይሁዳ ወገን
እንደ ኾነች እነግርሃለሁ አለኝ …” /ምዕራፍ 1፥11-13/፡፡

• በዚህ ዓይነት ቀሌምንጦስ እየጠየቀ ቅዱስ ጴጥሮስ እየመለሰ ከዓለም


ፍጥረት ጀምሮ እስከ ዳግም ምጽአት ያለውን ምሥጢር ነግሮታል::
ሀ) ሥነ ፍጥረት

• እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት በቅድምና የነበረ ዘላለማዊ፣ ውሳጤ አፍኣ የሌለው፣


ዐይን ማየት በማይችለው ብርሃን ውስጥ የሚኖር፣ ስብሐቲሁ ዘእምኀቤሁ -
ምስጋናው ከባሕርዩ የኾነ፣ ፍጥረታትን በሙሉ የፈጠረ እንደ ኾነ በመናገር
ይጀምራል::

• በዕለተ እሑድ ሰማይና ምድር፣ መላእክትም አሥር ወገን ኾነው እንደ ተፈጠሩ፤
ከኹሉም መላእክት በማዕርግ የሚበልጠው የሳጥናኤል ወገን እንደ ነበረ፣ በዕለተ
ሰኑይ እግዚአብሔር በምድር ባሉ ውኆችና በሰማይ ባሉ ውኆች መካከል ልዩነትን
(ጠፈርን) እንዳደረገ፣ በዕለተ ሠሉስ ከሰማይ በታች ያሉ ውኆች በአንድ ቦታ
እንዲሰበሰቡ እንዳዘዘ እና የብሱም እንደ ታየ፣ አዝዕርትንም ዛፎችንም እንደ ፈጠረ፣
በዕለተ ረቡዕ ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት እንደ ተፈጠሩ፣ በዕለተ ሐሙስ ውኆች
የዓሣዎችን ዓይነት ያወጡ ዘንድ እንደ ታዘዙ፣ በነፋስ የሚበሩትንም አስደናቂ
ትላልቅ አንበሪዎችንም እንደ ፈጠረ፣ በዕለተ ዓርብ ከምድር አራዊትን እንስሳትን
እንደ ፈጠረ፣ በመጨረሻም ከአራቱ ባሕርያት ትንሽ ትንሽ ወስዶ ሰውን በአርአያውና
በምሳሌው እንደ ፈጠረ ሔዋንንም ከአዳም ከጎኑ ዐፅም እንዳስገኛት ይናገራል::
• እግዚአብሔር አዳምን (ሰውን) በማይነገር ክብር
እንደ ፈጠረው፤ የመለኮት ብርሃን በአዳም ፊት ያበራ
እንደ ነበር፣ የፊቱ ብርሃን ከፀሐይ የሚበልጥ ሰውነቱ እንደ ንጋት
ኮከብ የሚያበራ እንደ ነበር፣ እግዚአብሔር ለአዳም የምስጋና
አክሊል፣ ልብሰ መንግሥት፣ የግርማ ከፍተኛነት እንዳለበሰው፣
የመንግሥትን አክሊል እንዳቀዳጀው ንጉሥነትንና ነቢይነትን
እንደሰጠው፣ … መላእክት በታላቅ ግርማ እና ምስጋና ባዩት ጊዜ
እንደ ፈሩት፤ አራዊት እንስሳት አዕዋፍ እግዚአብሔር
የፈጠራቸው ፍጥረታት ኹሉ ተሰብስበው ለአዳም
እንደ ሰገዱለት … ሰይጣን የአዳምን ጸጋና ክብር አይቶ
እንደ ቀና የሚያስትበትንም ምክንያት ይፈልግ
እንደ ነበር ይናገራል /ምዕ.1፥14-49/፡፡
ለ) የአዳም ውድቀት

• በዚህ ክፍል ሰይጣን በአርዌ ምድር ተሰውሮ ሔዋንን ዕፀ በለስ


ጣፋጭ እንደ ኾነች የአምላክነትንም ክብር እንደምታሰጥ ዋሽቶ
እንዳሳታት፣ አዳምም ሔዋንም አምላክ ሊኾኑ ዕፀ በለስን
እንደ በሉ፤ ያደረባቸው ክብር እንደ ተገፈፈ ከጸጋ እንደ ተራቆቱ
ከገነት እንደ ወጡ … ::

• መፍቀሬ ሰብእ - ሰውን ወዳጅ የኾነው እግዚአብሔር ግን


በውድቀታቸው ስንኳ ፍቅሩን እንዳልቀነሰባቸው ይልቁንም
እንደ ጎበኛቸው እንዳፅናናቸው ይተርካል:: ኪዳነ አዳም በመባል
የሚታወቀው አባቶቻችን በስብከት አብዝተው የሚጠቅሱት፣
የኪዳናት ኹሉ ቁንጮ: መጀመሪያ: መነሻ የኾነው ቃል ኪዳን
የሚገኘው በዚሁ በመጽሐፈ ቀሌምንጦስ ነው::
• እግዚአብሔር ለአዳም እንዲህ ሲል ቃል የገባለት: “ከአምስት ቀን
ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ::”

• እግዚአብሔር ለአዳም ዐፅሙን ለልጅ ልጅ እንደሚያስጠብቅለት:


ዐፅሙም በተቀመጠበት ቦታ መድኃኒትን እንደሚያደርግለት /በዚያ
እንደሚሰቀል/ እንደ ነገረው፤ አዳምና ሔዋን ከገነት ከወጡ በኋላ
ከገነት በታች ባለ ተራራ በደብር ቅዱስ መኖር እንደ ጀመሩ፤ አዳም
ለሔዋን “በመካከላችን ምስክር ይኹን: አምኃነቱም ወልደ
እግዚአብሔር ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ይኾናል” በማለት ወርቅ ዕጣን
ከርቤ እንደ ሰጣትና ልጆችም እንደ ወለዱ፤ ቃየል የእናት አባቱን ምክር
ባለመስማት መልከ ጥፉይቱን የአቤልን መንትያ አላገባም እንዳለ፣
በቅንአት ተነሳስቶ አቤልን እንደገደለው ተቅበዝባዥም እንደ ኾነ
ይጠቅሳል::
• አዳም የዕረፍቱ ጊዜ ሲደርስ ልጆቹን የልጅ ልጆቹን ሰብሰቦ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ
እንዲጠብቁ፣ ከቃየል ልጆች እንዲርቁ፣ ዐፅሙንና አምኃውን
እንዲጠበቁ እንዳዘዛቸው፤ በተለይም ለልጁ ለሴት ብዙ ትእዛዛትን:
ትንቢታትን እንደ ነገረው፤ ጌታ ከድንግል ማርያም እንደሚወለድ: እንደ ሰው
እንደሚመላለስ: ሕሙማንን እንደሚፈውስ: እንደሚሰቀል: አዳምንና ዘሮቹን
እንደሚያድን፣ ስለ ቃየል ልጆች ኀጢአት ማየ አይህ - የጥፋት ውሃ
እንደሚመጣ እንደ ነገረው፤ ከዚህ በኋላ ከቃየል ልጆች በስተቀር ኹሉም በሴት
መሪነት ትእዛዘ አዳምን በመጠበቅ በንጽህና በቅድስና በደብር
ቅዱስ እንደ ኖሩ [ደቂቀ ሴት የሚባሉ፣ ከንጽህናቸውም የተነሣ የመላእክት ልጆች
የሚባሉ እነዚህ ናቸው]፤ የቃየል ልጆች ግን ከደብር ቅዱስ በታች
በኀጢአት እንደ ኖሩ፤ ከአዳም በኋላ ሴትን ጨምሮ የተለያዩ አበው ደቂቀ ሴትን
እየመሩ ሲሞቱም ሕዝቡን ትእዛዘ አዳምን እንዲጠብቁ፣ ከቃየል ልጆች እንዲርቁ
በደመ አቤል እያስማሉ እንዳለፉ፤ ከአዳም ተቀብሎ ሴት: ከእርሱም በኋላ ሄኖስ:
ቃይናን: መላልኤል: ያሬድ በየተራ ሕዝቡን እንደ መሩ፤ በያሬድ ጊዜ ከደቂቀ
ሴት የአባቶቻቸውን ትእዛዝ የማይጠብቁ ሰዎች ተነሥተው አንድ አንድ እያሉ
ከደብር ቅዱስ እየወረዱ ከቃየል ልጆች እንደ ተጨመሩ፤ በመብል በመጠጥ በዘፈን
በዝሙት እንደ ረከሱ፤ ሄኖክ ሲሰወር ከሦስቱ አበው (ማቱሳላ: ላሜህ: ኖኅ)
• ከማቱሳላ እና ከላሜህ በኋላ ኖኅ የቀሩትን ደቂቀ
ሴት እንደ መራቸው፤ እግዚአብሔርም ለኖኅ ማየ አይህ እንደሚመጣ
ገለጠለትና መርከብ እንዲሠራ እንዳዘዘው፤ መርከቡንም ከታች ደቂቀ
ቃየል ካሉበት ወርዶ ኹሉም እያዩት: ስለ መርከቡ ለሚጠይቁት
ስለ ማየ አይህ መምጣት እየነገረ እንዲሠራ እንዳዘዘው፤ ከዚህ በኋላ
ኖኅ እና ልጆቹ የደብር ቅዱስን ድንጋዮቿን እንጨቶቿን በሐዘን
እየሳሙ፣ ቀደምት አበውን እየተማጸኑ ዐፅመ አዳምንና አምኃውን
ይዘው ከደብር ቅዱስ እንደ ወረዱ፤ ኖኅም መርከቡን ሠርቶ ሲጨርስ
ማየ አይህ ጀመረ፤ ደቂቀ ሴት ቢፀፀቱም
የሚረዳቸው እንዳላገኙ፤ እግዚአብሔር በነቢዩ ዳዊት ስለ ደቂቀ ሴት
በተናገረበት ትንቢቱ:- “አንሰ እቤ አማልክት አንትሙ ወደቂቀ ልዑል
ኩልክሙ አንትሙሰ ከመ ሰብእ ትመውቱ ወከመ አሐዱ እመላእክት
ትወድቁ - እኔ ግን አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች
ናችሁአልሁ፤እናንተ ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ
አንዱ ትወድቃላችሁ” እንዳላቸው ያስተምራል /መዝ.81(2):6-7/፡፡
• ቅዱስ ቀሌምንጦስ መርከብ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ
እንደ ኾነች፣ ኖኅ ከመርከብ ወጥቶ ወይን ጠጥቶ ሰክሮ ተኝቶ
ሳለ የሳቀበት ካምን ተነሥቶ እንደረገመ -
ክርስቶስ 3 ቀን 3 ሌሊት በንዋመ መቃብር ቆይቶ ከትንሣኤ
በኋላ ሰይጣንንና ሰቃልያንን የመርገሙ ምሳሌ መኾኑን ተርጉሞ
አስቀምጧል::

• ከኖኅ በኋላ ሴም በመልአከ እግዚአብሔር መሪነት ዐፅመ


አዳምን ወደ ማእከለ ምድር ጎልጎታ በስውር ወስዶ መልከ
ጼዴቅን በዚያው ትቶ አስጠብቆታል፡፡
• ከዚህ በኋላ የኖኅ ልጆች ዝርዎት /መበተን/ እንደ ኾነ: አምልኮ ጣዖት: መተት
ሟርት እንደ ተጀመረ ይገልጻል:: አብርሃም በ75 ዓመቱ ወደ ከነዓን ምድር
እንደ ተጠራ: ይስሐቅን አዳም በተፈጠረበት ኋላም በተቀበረበት በደብረ ማኖስ
ሊሠዋው እንደ ወሰደው: ይኼውም ክርስቶስ የተሰቀለበት ቦታ እንደ ኾነ፣
በዚህም አብርሃም አምሳለ ስቅለትን እንዳየ፤ ጌታም “አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ
ወደደ አየም ደስም አለው” ያለው (ዮሐ.8፥56) ይህንን እንደ ኾነ ይጠቅሳል::

• ሌላም ስለ አብርሃም እና ስለ ልጆቹ ሒደት ይተርካል፤ በተለይም እያንዳንዱን


ታሪክ ለነገረ ሥጋዌ /ለክርስቶስ ሰው መኾን/ ትንቢት እንደ ኾነ ይተረጉማል::

• ለምሳሌ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያየው ምሥጢር አምሳለ ስቅለት


እንደ ኾነ፣ ዐዘቅተ ያዕቆብ የቅድስት ጥምቀት አምሳል እንደ ኾነ፣ ልያ እና
ራሔል የቤተ እስራኤል እና የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ እንደ ኾኑ. . . እንዲሁም
ስለ ያዕቆብ ልጆች: ስለ ሙሴ: ስለ ኢያሱ: ስለ መሳፍንት: ስለ ዳዊት:
ስለ ሰሎሞን: ስለ መንግሥት ለኹለት መከፈል ይተርካል . . .
ሐ) ጴጥሮስ ለቀሌምንጦስ ሌሎች ብዙ ምሥጢራትን እንደ ገለጠለት

• ጌታ ለጴጥሮስ የገለጠለትን እርሱም በተራው ለቀሌምንጦስ


እንደ ገለጠለት፤ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ - ሥላሴ ከኹሉ በላይ እንደ ኾኑና ፈጣሬ
ፍጥረታት እንደ ኾኑ፤ ጌታ ለጴጥሮስ እንዲህ እንዳለው:-

• “ኹሉን ችዬ የምኖር ቦታ እኔ ነኝ: በምስጋና መንበሬ ላይ ነበርኩ: በጸጋዬ ሀብት


ነበርኩ፡ አብ በእኔ ዘንድ አለ: በእኔም ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አለ: በእኛ ዘንድ መቅደምና
ወደ ኋላ ማለት የለም: ከመካከላችንም ፊተኛና ኋለኛ ተብሎ የሚነገርለት የለም:
መጀመሪያና መጨረሻም የለንም:: የእኛ ህላዌ የእኛ መገኘት በኹሉ ዘንድ ነው:
የኀይላችንም ታላቅነት በኹሉ ይገኛል: እኛ የፈጠርነው ኹሉ ከእኛ በታች ኾኖ ይኖራል:
ርዝመታችንና ስፋታችን በሰው አእምሮ አይገመትም: ኹሉን እንችላለን ኹሉ ግን
ማንነታችንን ሊረዳ አይችልም: እኛ ከኹሉ በላይ ነንና የኀይላችንም ታላቅነት ኹሉን
ይዟልና:: ግራና ቀኝ የለንም: ውስጥና ውጭም በእኛ ዘንድ የለም: ውስጥ እኛ ነን ውጭ
እኛ ነን: ምስጋናችንና የጸጋችን ሀብት ከእኛ ዘንድ ነው: ከባዕድ የሚያስፈልገን ነገር
ፈፅሞ የለም: አብ እውነተኛና ትክክለኛ ነው እኔም ይቅርታና ምሕረት ነኝ መንፈስ
ቅዱስ ኀይልና ጥበብ ነው:: …
• “እኛን መሸከም የሚቻለው ሰማይ የለም ምድርም የለም: ከግብር ወደ ግብር
መለዋወጥ በእኛ ዘንድ የለም: ከቦታ ወደ ቦታም አንመላለስም: የሰው ዐይን
እኛን አያይም: ሰውም በመራቀቅና በመመራመር እኛን ሊያውቅ አይችልም::
በእኛ ዘንድ ጭማሪም ኾነ ሕፀፅ የለም: አብ አእምሮ ነው እኔም ሥምረት ነኝ
መንፈስ ቅዱስም ኀይል ነው: እኛ ብዙዎች አይደለንም: አንለያይም: ልዩነት
አያገኘንም: ጥፋትም አያገኘንም: አብ በእኔ ኹሉን ፈጠረ በመንፈስ ቅዱስም
ተፈፀመ:: አብ ነቢብ ነው እኔም ቃል ነኝ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ሕይወት ነው:
የሚመሳሰለን የለም እኛ ከመመሳሰል በላይ ነንና: እንደኛ የሚኾን የለም እኛ
ከኹሉ በላይ ነንና: አባቴ እሳት ነው ብርሃኑም እኔ ነኝ ሙቀቱም መንፈስ
ቅዱስ ነው: አባቴ ውኃ ነው እኔም ጣዕሙ ነኝ መንፈስ ቅዱስም ሕይወት ነው:
አባቴ ክብር ነው እኔም ክብር ነኝ መንፈስ ቅዱስም ጸጋ ነው: ከእኛ ውጪ
ፍጥረት የለም: ሰማያት ሳይፈጠሩ እኔ ከአብ ጋር ነበርኩ: አባቴ ግርማ ነው
እኔ ደግሞ ጸጋ ነኝ መንፈስ ቅዱስ ፍፃሜ ነው:: …
• እኔ በአብ አለሁ: መንፈስ ቅዱስ በአብና በእኔ አለ: አባቴ ጥበብ
ነው እኔም ቃል ነኝ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የቃል ድምፅ ነው:
በጥበባችን ኹሉን የፈጠርን እኛ ነን: ቀዳሚዎችም እኛ ነን:
መጀመሪያና መጨረሻም የለንም:: ዘመናችን በፍጡራን ዘንድ
አይታወቅም: ከዘመንና ከአዝማን በፊት እኛ ነን: ከእኛ ዘንድ
የሚቀርብ የለም: የሰው ሕሊናና የመላእክት አእምሮ ሊደርስብን
አይችልም: እኛ ከሕሊናት ኹሉ በላይ ነንና: ምስጋናችንም ከራሳችን
ነው:: እኛ መጀመሪያና መጨረሻ የለንም: ከፍቅራችን ብዛት የተነሳ
ዓለምን እንፈጥር ዘንድ ወደድን …” /ምዕ.6፥13-18/፤

• ሌሎችም ብዙ ምሥጢራት እንደ ገለጠለት - ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ:


ስለ ዳግም ምጽአት: ስለ ሐሳዊ መሲሕ: ስለ ነገደ መላእክት:
ስለ ገነት: ስለ ቤተ ክርስቲያን ምንነት …
መ) ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን

• ጳጳሳት ካህናትና ምእመናን እንዴት መመላለስ እንደሚገባቸው


የቅዱስ ጴጥሮስ ትእዛዝ፤ አዘውትሮ ወደ ቤተ ክርስቲያን መገስገስ
እንዲገባ: በትጋት ስለ መጸለይ: ስለ ንጽህና. . . በተለይ ጥንቆላንና
ሟርትን: አምልኮ ጣዖትን: ስካርና ዝሙትን አጥብቆ ያወግዛል -
እነዚህን የሚያደርግ ተወግዞ ከቤተ ክርስቲያን መለየት
እንዲገባው፣ ካህናትን ያቃለለ ኩነኔ እንዲገባው፣ ካህናት ሳያፍሩና
ሳይፈሩ በድፍረት ማስተማርና መገሠጽ እንዲገባቸው. . .
• ከብዙ በጥቂቱ ስለ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ይህን ያህል ካልን ሙሉውን
መጽሐፉን አንብባችሁ እንድትረዱ በትሕትና እንጋብዛለን:: ከዚህም
መጽሐፍ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዋ: ዶግማዋና ቀኖናዋ፣
የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ስልቷ ወ.ዘ.ተ. ከሐዋርያት ሲያያዝ የመጣ
እንደ ኾነ፣ በቅዱስ ጴጥሮስ እና በሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት
የእምነት መሠረት ላይ የታነጸች መኾኗን ልብ ይሏል::
ወደ ቆሮንቶስ የተላከ መልእክት

• ይህ መጽሐፍ በቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም እንደ ተጻፈ የሚታመንና በሌሎች


አኀት አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ
ተቀባይነት ያለው ነው፡፡

• ከላይ ካየነውና የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ከምትቀበለው መጽሐፍም የተለየ ነው፡፡

• መጽሐፉ 59 ምዕራፍ ያለው ሲኾን፡- ምእመናን መጽሐፍ ቅዱስን ኹልጊዜ


ማንበብ እንደሚገባቸው፣ ኔሮን ቄሳር ስላደረሰው ስደት፣ መሠረታዊ
ስለሚባሉት የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች (ስለ ቅድስት ሥላሴ፣ ስለ
እምነትና ምግባር፣…)፣ በጥንታዊቱ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቅዳሴ ምን
ይመስል እንደ ነበር፣ ፌኖሽያ ከተባለች ወፍ ጋር በማያያዝ ስለ ትንሣኤ
ሙታን መኖር እንዲሁም ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያስተምራል፡፡
ሔርማስ ባለ ራእዩ
ማንነቱ
• ጥንተ ህይወቱ በዙም አይታውቅም::
• እንደ ራሱ ገለጻ_ በሮም የነበረ አገልጋይ
ሲሆን ነጻነት ሲያገኝ ክርስትናን ተቀበለ::
• በዘመነ ስማእታት ከሚስቱጋ በእምነቱሲጸና
ልጆቹ ግን ክደዋል::
• የጠፉትን ወደ ንስሃ ለመጥራት ራእዩን
ይጽፋል::
ራእየ ሔርማስ
• የሔርማስ ራእይ ሰዎችን ወደ ንስሃ ለመጥራትና የመጨረሻ ዘመን
መድረሱን
• ለማሳሳብ የተዘጋጀ ነው
• ራእዩም በአሮጊት ሴት በተመሰለች ቤተ ክርስቲያንና በእረኛ
በተመሰለ የንስሃ
• መልአክ አማካይነት ለሔርማስ የተገለጠ ነው
• ይዘቱም 5 ራእያት፣ 12 ትእዛዛትና 10 ምሳሌያት ያካተተ ነው
• መጽሐፋ በሁለት ክፍል የተዘጋጀ ነው፡
– ክፍል 1፡ የመጀመርያዎቹ 4 ራእያት
– ክፍል 2፡ 5ኛው ራእይና ሌሎቹ መልእክታት
5ቱ ራእያት
• 1. በቤተ ክርስቲያን የተመሰለችው ሴት ወንበር ላይ ተቀምጣ ስለ ራሱና
ቤተሰቡ
• ኃጢአት ንስሃ እንዲገባ ትገስጸዋለቸ
• 2. ቤተ ክርስቲያን/በሴት አምሳል/ ጥንካሬዋ ተመልሶላት ትታየዋለች
• 3. ቤተ ክርስቲያን በቆንጆ ወጣት አምሳል ተገልጻ የቅዱሳን ሕብረት እየተሰራ
ባለ ህንጻ
• ምሳሌ አሳይታዋልች
• 4. አስፈሪ ዘንዶና በሙሽሪት የተመሰልች ቤተ ክርስቲያን ያየሲሆን
የምእምናን ፈተናና
• ከድል በኋላ ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ይወክላሉ
• 5. የንስሃ መልአክ በእረኛ መልክ ይተገለጠለት ሲሆን የንስሃን መንገድ
የሚያቃናና

12ቱ ትእዛዛት
• 1. በአንድ አምላክ ማመን
• 2. ትሕትና
• 3. ታማኝነት
• 4. ንጹህ ጋብቻ
• 5. ትዕግስት
• 6. በእውነተኛ መንገድ መጓዝ
• 7. እግዚአብሔርን እንጂ ሰይጣንን አለመፍራት
• 8. መልካም ማድረግ፣ ክፋትን መተው
• 9. ጥርጥርን ማራቅ
• 10. አለመጨንቅ
• 11. ሀሰተኛ ነቢያትን መለየት
• 12. መጥፎ ፍላጎቶችን መተው
10ሩ ምሳሌያት
• 1. የእንግድነት ሕይወት
• 2. ሐረግና ዛፍ፡ ድሀን መውደድ
• 3. ቅጠል አልባ ዛፍ በበጋ ወቅት_የሰው ልጅ ሕይወት በዚህ ዓለም
• 4. የዕጸዋት መለያየት በክረምት ወቅት _የሰው ልጅ ሕይወት
በወድያኛውዓለም
• 5. ትክክለኛ የጾም አስተምህሮ_የትሩፋት ተግባርና ዕሴቱ
• 6. ቃለ ምልልስ በቅጣት መልአክና በፍትወትና ማታለል መልአክ
መካከል
• 7. የሔርማስ ስቃይ ስለ ቤተሰቡ ኃጢአት
• 8. ባለ ጥላው ዛፍና የጸጋ ተግባር
• 9. ቤተክርስቲያን እንደ አስደናቂ ህንጻ

የራእዩ አስተምህሮዎቹ
• ንስሃ፡ ከጥምቀት በኋላ በኃጢአት እንዳንጠፋ የተሰጠ ዕድል ነው
• ምስጢረ ሥላሴ፡ ክርስቶስን ወልደ እግዚአብሔር ወይም ጌታ እያለ
ይጠራዋል
• ነገረ ቤተ ክርስቲያን፡ አንድ ሕብረት እንድሆነችና ከክርስቶስ ጋር
ያላትን ግንኙነት
• ያብራራል
• ጥምቀት፡ የቤተ ክርስቲያን አባል የምንሆንበትና የድኅነት ምልክት
ነው
• ስነ ምግባር፡ ትሩፋት መስራት የበለጠ ዋጋ ያሰጣል /ጾም፣ ንጽህናና
ሰማዕትነት/
• ጋብቻ፡ ሁለተኛ ጋብቻ በሞት ምክንያት ብቻ የሚፈቀድ ሲሆን
ቅዱስ ሄሬኔዎስ
ሕይወቱና ትምህርቱ
ሕይወቱ
• በኹለተኛው መቶ ክፍል ዘመን አጋማሽ ከ125 ዓ.ም. መካከል በሰርምኔስ (ኤዶም) -
በዛሬዋ ኢዝሚር ቱርክ - ተወለደ፡፡

• በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ ያደገ ነው፡፡

• የቅዱስ ፖሊካርፐስ ደቀ መዝሙር ሲኾን ፍጹም ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ


የሚወድድ ነው፡፡

• ከ161-180 ዓ.ም. ባለ ጊዜ ውስጥ ካህን ነበር፡፡

• በኋላም የሊይኦን ጳጳስ ኾኖአል፡፡

• በዋናነት ኹለት ተግባራትን ያከናውን ነበር፡-


– የኖላዊነት ግርብርና
• ጽሑፎቹ በዋናነት የሚያተኩሩት በግኖስቲኮች ላይ ናቸው፡፡

• በተለይ የሚታወቅለት መጽሐፉ ደግሞ በአንድ ወዳጁ ጥያቄ መሠረት


የጻፈውናነ “መድፍነ መናፍቃን” የተባለው ነው፡፡

• ቅዱስ ሄሬኔዎስ መጀመሪያ የግኖስቲኮችን፣ የግሪክ ፈላስፎችን የምንፍቅና


ትምህርት በአግባቡ ይመረምር ነበር፡፡ በመኾኑም ዕውቀቱ ጥልቅ ነበር፡፡

• መልስ ይሰጥባቸው የነበረው ከዚያ በኋላ ነበር፡፡

• ዕለተ ዕረፍቱን በተመለከተም የተገኘ መረጃ የለም፡፡

• በኹለተኛው መ.ክ.ዘ. ማገባደጃ ወይም በሦስተኛው መ.ክ.ዘ. መጀመሪያ


የቅዱስ ሄሬኔዎስ ሥራዎች
• መድፍነ መናፍቃን

• እግዚአብሔር ክፋትን እንዳልፈጠረ የሚናገር መጽሐፍ

• ስለ ዕውቀት

• ለተለያዩ ሰዎች የተላኩ መልእክታት

• በጣም የታወቀውና ከሌሎች አንጻር ሙሉ ኾኖ ወደ እኛ የደረሰው


ሥራው ግን ከላይ መጀመሪያ ላይ የጠቀስነው መድፍነ መናፍቃን
የተባለው መጽሐፉ ነው፡፡
• ቅዱስ ሄሬኔዎስ መጀመሪያ ላይ መድፍነ መናፍቃንን መጻፍ ሲጀምረው
ለቫለንቲነሳውያን ምንፍቅና መልስ እንዲኾን ተደርጎ የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው፡፡
ያውም ለአንድ ባልንጀራው ጻፍልኝ ባለው መሠረት የጻፈው ነው፡፡

• ቀስ በቀስ ግን ወፈር ያለ መጽሐፍ ወደ መኾን አደገ፡፡ ለቫለንቲነሳውያን የሚኾን


መልስ ካዘጋጀ በኋላ የ(ግ)ኖስቲካውያን መነሻ ኑፋቄ ምን እንደ ኾነ ከሲሞን መሰሪ
አንሥቶ በየጊዜው የተነሡትን ወደ መመርመር ነበር ያመራው፡፡ ይህ የመጽሐፉ
የመጀመሪያው ክፍል ነው፡፡

• የመጽሐፉ ኹለተኛው ክፍል ደግሞ ለእነዚህ ኑፋቄዎች የተሰጠ ድንቅ ምላሽ ነው፡፡
አመክንዮአዊ በኾነ ምላሹም የ(ግ)ኖስቲካውያን ትምህርት በኹለት ጎራ ማለትም
በኹለት አማልክትና በብዙ አማልክት ኑፋቄነት እንደሚከፈል አሳይቶአል፡፡

• ይህን በማድረግ ማለትም ኑፋቄአቸውን በመግለጥ ላይም አላበቃም፡፡


ኦርቶዶክሳዊውን ትምህርትም ክሽን አድርጎ አብራራው እንጂ፡፡ የሦስተኛው፣
የአራተኛውና የአምስተኛው መጽሐፍ በዋናነት ይህን የሚያስረዳ ነው፡፡
• ከዚህ የተነሣም ብዙ ሊቃውንት “የኩላዊት ቤተ ክርስቲያን የሥነ
መለኮት ትምህርት አባት” ብለው ይጠሩታል፡፡

• በመጽሐፉ ውስጥ ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ጌታችን ክርስቶስ፣ ስለ


ፍቅርና ስለ ብርሃን አብዝቶ ማስተማሩ (በቅዱስ ፖሊካርፐስ በኩል)
የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙር መኾኑን በደንብ ያሳያል፡፡
የቅዱስ ሄሬኔዎስ ትምህርት
• ሀ) ጸሎተ ሃይማኖትን በተመለከተ

– “ሕግም ነቢያትም የመሰከሩለት ሰማይንና ምድርን የፈጠረ አንድ እግዚአብሔርና


አንድ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ አለ” (መድ.መናፍ.3፡1፡2)፡፡

– ይህንንም ከሐዋርያት የተማረው እንደ ኾነ ይናገራል፡፡ ስለዚህ ጸሎተ ሃይማኖት


ከሐዋርያት የተማርነው ነው፡፡

• ለ) ምሥጢረ ሥላሴን በተመለከተ

– “[ወልድ] የአብ ሕሊናው የሚኾን ፍጹም የአብ አካላዊ ቃል ነው፡፡ የአጥቢያ


ኮከብ ሳይፈጠር ከአብ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ የተወለደ ነው፡፡
ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ኹሉን የፈጠረ ነው” (ሃይ.አበ.7፡4-5)፡፡
• ሐ) ምሥጢረ ሥጋዌን - ነገረ ክርስቶስን በተመለከተ

– “ከድንግል ሰው የኾነ እርሱ ነው፡፡ በቤተ ልሔም የተወለደ፣ በጨርቅ


የተጠቀለለ፣ በጎል በበረት የተጣለ፣ በጎል ተጥሎ በጨርቅ ተጠቅልሎ ኖሎት
ያዩት፣ መላእክት ስብሐት ለእግዚአብሔር ብለው ያመሰገኑት፣ ሰብአ ሰገል
የሰገዱለት፣ ዮሐንስ ነዋ በግዑ ብሎ አምላክነቱን የመሰከረለት
በዮርዳኖስም ያጠመቀው፣ ካህናትን በመሾም ጊዜ ካህናትን የሚሾም ሊቀ
ካህን፣ በገዳም በሦስት አርእስተ ኀጣውእ የተፈተነ፣ ሐዋርያትን መርጦ
የሾመ፣ ወንጌልን ያስተማረ፣ አንካሳንን እንዲኼዱ ያደረገ፣ ልሙጻን
እንዲነጹ ያደረገ፣ ምዉታነ ሥጋን በተአምራት ምዉታነ ነፍስን በትምህርት
ያስነሣ እርሱ ነው፡፡ … በሥጋ ተሰቀለ፣ በመስቀል ላይ መከራን ተቀበለ፣
ሞተ፣ ተገነዘ፣ በመቃብር ተወሰነ፣ ከሙታን ተለይቶም ተነሣ፡፡ የሞቱትን
የሚያስነሣቸው እርሱ ነው፡፡ በፍዳ የተጎዱትን የሚያድናቸው እርሱ ነው፡፡
… የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ እርሱ ነው፡፡ … ከባሕርይ አምላክ የተገኘ
የባሕርይ አምላክ፣ የአብ የባሕርይ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት
– “እንደ ሰውነቱ ደከመ፤ እንደ አምላክነቱ በኀጢአት የደከሙትን ዕረፍተ
ነፍስን ሰጥቶ እንዳሳረፈ እናውቃለን፡፡ እንደ ሰውነቱ የዳዊት ልጅ ነው፤
እንደ አምላክነቱ የዳዊት ፈጣሪ ነው፡፡ … እንደ ሰውነቱ ከፊቱ ላይ ምራቅ
ትፍ እንዳሉበት በጥፊም እንደ መቱት እንደ አምላክነቱ በደቀ
መዛሙርቱ በሐዋርያት ፊት መንፈስ ቅዱስን በንፍሐት አሳደረ፡፡ እንደ
ሰውነቱ እንደ ተያዘ እንደ ተዳሰሰ እንደ አምላክነቱ በደንጊያ ወግረው
ሊገድሉት ከወደዱ ሰዎች በመካከላቸው ተሰውሮ አልፎ እንደ ኼደ
እናውቃለን፡፡ …” (ሃይ.አበ.7፡23-26)፡፡

– ከዚሁ ጋር ተያይዞ ድኅነትን በተመለከተ ሲናገርም ድኅነት ፍጻሜን


የሚያገኘው በወዲያኛው ዓለም ነው፤ የሚጀመረው ግን በዚህ ዓለም
ነው፡፡ ከጥምቀት ጀምሮ (ሕፃናትም ይጠመቃሉ ብሎአል)፣ ሕይወት ባለ
እምነት ጸንቶ በተለይ በተለይ በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ ሲታተም
ድኅነት ፍጹም ይኾናል (መድ.መና.4፡17፡5)፡፡
• መ) ነገረ ማርያምን በተመለከተ

– “ድንግል ማርያም በሔዋን በደል የተቋጠረውን ማሰሪያ በጠሰች፡፡ አንድዋ


የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ተቃወመች፤ ሌላዋ ደግሞ ታዘዘች፡፡ ሔዋን
የዲያብሎስን ቃል አደመጠች፤ ድንግል ማርያም ግን የመልአኩን
(የገብረኤልን) ቃል አደመጠች፡፡ ሰው በድንግል ምክንያት ሞተ፤ በሌላ
ድንግልም ዳነ” (መድ.መና.3፡22፡3)፡፡

– “በድንግል ማርያም መታዘዝ የሔዋንና የሰው ልጅ በጠቅላላ ድኅነት ተደረገ፡፡”

– ቅድስት ድንግል ማርያም በመታዘዝዋ “የሔዋን ረዳትዋ ኾነች” (መድ.መና.5፡


19፡1)፡፡

– ቅድስት ድንግል ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል መኾንዋንም አስረግጦ


አስተምሮአል (ዝኒ ከማሁ፣ 4፡23፡2)፡፡
• ሠ) ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትን በተመለከተ

– መንፈሳዊነት የግኖስቲካውያን ዓይነት ሐሰተኛ መንፈሳዊነት እንዳይኾን መጠንቀቅ ይገባል፡፡

– የኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት ምንጩ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነውና፡፡

– መንፈሳዊነትና መንፈስ ቅዱስ የማይለያዩ ናቸው፡፡

– አዳም የበለጠ መንፈሳዊ ልኹን ብሎ የወደቀውም ያለ መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ልኹን በማለቱ
ነው፡፡

– ሰው ነጻ ፈቃድ አለው፡፡ ግን ለሚያዝዘው ቅዱስ መንፈስ መታዘዝ አለበት፡፡

– እንዲህ ሲያደርግ መንፈሳዊነቱ በዚህ ዓለም ጀምሮ ፍጹም የሚኾነው በመንግሥተ ሰማያት
ነው፡፡

– በዚህ ዓለም ውስጥ ኾኖም ግን ክፉውንና ደጉን ለይቶ ማወቅ ይቻለዋል፡፡ የአሕዛብንና
የመናፍቃንን ስንፍና መለየት ይቻለዋል፡፡ ይህን ተጸይፎም ለእግዚአብሔር፣ ለክርስቶስና ለቤተ
ቅዱስ አቡሉዲስ ዘሮም
ሕይወቱና ትምህርቱ
• የቅዱሱ ታሪክ የተከናወነው ሮም ውስጥ ቢኾንም ሮማዊ ሳይኾን ግሪካዊ
ነው፡፡

• ይህ በ170 ዓ.ም. የተወለደው ቅዱስ አባት የቅዱስ ሄሬኔዮስ ደቀ


መዝሙር ነው፡፡

• ትጋቱ፣ የሕይወት ምልልሱና ዕውቀቱ፣ የእረኝነቱ አካኼድ ቅዱስ


ሄሬሬዮስ እንደ ገና የተነሣ ያስመስላል ይሉታል፡፡

• በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የሮም ጳጳስ (ፖፕ) ሊሳሳት ይችላል ብሎ


ያስተማረ የመጀመሪያው አባት ነው፡፡

• በ212 ዓ.ም. ካህን ኾኖ በሮም ያገለግል ነበር፡፡ በአገልግሎቱም


• ሕዝቡን ከአረማውያን ጠባይ የሚጠብቃቸው የሚያስተምራቸውና በክብር ባለቤት በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት የሚያጸናቸው ኾነ፡፡

• በጊዜው የነበረው ከሐዲ ንጉሥ ከላድያኖስ ይባላል፡፡ ማክሲመስም ይለዋል፡፡

• ንጉሡ ስለ ዓለሙ ኹሉ መምህር ስለ ቅዱስ አቡሊዲስ በሰማ ጊዜ ይዞ በብዙ ግርፋትና ድብደባ


አሠቃየው፡፡

• ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ በእግሮቹ ውስጥ ታላቅ ደንጊያ አስሮ ከጥልቅ ባሕር የካቲት
አምስት ቀን 236 ዓ.ም. አሰጠመው፡፡

• በማግስቱ የካቲት ስድስት ሲኾንም የዚህ አባት ሥጋው በውሃ ላይ ተንሳፍፎ ተገኘ፡፡
ደንጊያውም በእግሮቹ እንደ ታሰረ ነበር፡፡

• አንድ ምእመንም ወስዶ በእርሱ ዘንድ አኖረው፡፡ በከበሩ ልብሶችም ገንዞ ሰወረው፡፡

• ወሬው በሮሜ አገሮች ኹሉ ተሰምቶ ስለ ነበር ንጉሡ ሊያቃጥለው ፈልጎት የነበረ ቢኾንም ያ
የቅዱስ አቡሉዲስ ሥራዎችና ትምህርቶች
• ቅዱስ አቡሉዲስ ብዙ ድርሳናትን ደርሶአል፡፡ ለምሳሌ ስለ እውነተኛዋ እምነት፣ ስለ ወልደ
እግዚአብሔር ሰው መኾን፣ እግዚአብሔርን ደስ ስለ ማሰኘት የተሰጠ ምክር ሠናይት
ይገኙበታል፡፡ እነዚህን በተመለከተም እ.ኤ.አ. በ1551 ዓ.ም. በሐውልት ውቅር ሥራዎቹ
ተዘርዝረው ተገኝተዋል፡፡

• ብዙ የትርጓሜ መጻሕፍትም ጽፎአል፡፡ ከእነርሱ ውስጥ ተጠቃሾቹም በትንቢተ ዳንኤል ላይ


የሠራው ትርጉም፣ ፀረ ክርስቶስን በተመለከተ የጻፈው ተጠቃሽ ናቸው፡፡

• አተረጓጎሙም የእስክንድርያ ዓይነትና ምሳሌያዊ ማለትም ወደ ምሥጢራዊ አተረጓጎሙም


የሚያዘነብል ነው፡፡

• ቀደም ብለን እንደ ገለፅነውም የቅዱስ ሄሬንዮስ ደቀ መዝሙር እንደ መኾኑ ለ32 መናፍቃን
መልስ ጽፎአል፡፡

• በ234 ዓ.ም. ላይም ከፍጥረተ ዓለም አንሥቶ እስከ እርሱ ዘመን የነበረውን ታሪክ ጽፎአል፡፡
• “ትውፊተ ሐዋርያት” የተሰኘና ዲድስቅልያን የመሰለ መጽሐፍም
ጽፎአል፡፡ ይህ ሥራ በተለይም በብዙዎች በኢትዮጵያ ያለው ቅጂ
እንደ ኾነ ያምናሉ፡፡

• እግዚአብሔር አንድ ስለ መኾኑ፡-


– “አንዱ፣ ቀዳማዊው፣ ብቸኛውን የፍጥረታት ኹሉ ፈጣሪና ጌታ የኾነው
እግዚአብሔር ሌላ እርሱን የሚመስል ተካካይ አምላክ የለውም”
(መድፍነ ኩሉ መናፍቃን፣ …)፡፡
• ምሥጢረ ሥላሴን በተመለከተ፡-
– “ባሕርያቸው በእውነት አንድ ሲኾን በመልክ በአካል ፍጹማን የሚኾኑ
ሦስት ገጻት እንደ ኾኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን”
(ሃይ.አበ.40፡3)፡፡
• ምሥጢረ ሥጋዌን በተመለከተ፡-
– “ወልድ በመለኮቱ ከአብ እንደ ተገኘ እንናገራለን፡፡ በሰውነቱም ከድንግል
እንደ ተገኘ እንናገራለን፡፡ የአንዱን አካል መለየት አናውቅም፤ ማለት
ኹለት አካል ኹለት ባሕርይ አንለውም” (ሃይ.አበ.39፡19)፡፡

• ውርጃንና የወሊድ መቆጣጠሪያን በተመለከተ፡-


– “ምእመናን ናቸው ተብለው የሚታወቁ ሴቶች ሳይቀሩ ራሳቸውን መካን
ለማድረግ፣ የተጸነሰውን ለማስወረድ ብለው አስበው፣ ከዘመድ የተጸነሰ
ነው ብለው አስበው፣ የምናሳድግበት ሀብት ንብረት የለንም ብለው፣
ከባሪያ ወይም እዚህ ግባ ከማይባል ከሌላ ሰው የተጸነሰ ነው ብለው
መድኀኒትን መውሰድ ጀመሩ፡፡ እንግዲህ በአንድ ጊዜ ዝሙትንና
መግደልን በማስተማር ወደ ምን ዓይነት ዓመፃ እንደ ከተታቸው
ተመልከቱ” (መድፍነ ኩሉ መናፍቃን፣ …)፡፡
• የሕፃናት ጥምቀትን በተመለከተ፡-
– “መጀመሪያ ሕፃናትን አጥምቁ፡፡ እነርሱ ራሳቸው መናገር (መመስከር)
የሚችሉ ከኾነ ይመስክሩ፡፡ ካልኾነ ግን ወላጆቻቸው ወይም ሌላ ዘመድ
[በአሁኑ ሰዓት ክርስትና አባት የምንለው] ይመስክርላቸው” (ትውፊተ
ሐዋርያት፣ 21፡16)፡፡
የቤተክርስቲያን አበው ፅሁፎች
1.ዲድስቅልያ(የአሥራሁለቱ ሐዋርያት ትምህርት)
 በሌላ አጠራር ጌታ ለደቀመዛሙርቱ ያስተማረው በእነርሱም በኩል ለህዝብና አሕዛብ የተላለፈ ትምህርት
ነው፡፡
 ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ ከመፅሀፍ ቅዱስ አንዱ ክፍል እንደ ሆነ ተናግbል፡፡አውሳብዮስ ቤተክርስቲያን የሚጠቅማት
መፅሀፍ ይህ ነው ብላል፡፡ቅዱስ አትናቴዎስ፡- በተለይ መሰረታዊ የሆነውን የክርስትናን ትምህርት ማወቅለሚፈልጉ ሁሉ
ተቃሚ መጽሐፍ ነው፡፡
 መጽሐፉ አስራ ስድስት ምዕራፍ ሲኖረው በአጠቃላይ በሦስት ዐባይት ክፍሎች የተከፈለ ነው፡፡
 የመጀመሪያው ክፍል የሕይወትና የሞት ስለሚባሉ ሁለት መንገዶች ያወራል፡፡
 ሁለተኛው ክፍል ደግም የአምልኮ አፈጻጸም ሥርዐትን የሚመለከት ትምህርት የሚሰጥ ነው፡፡ ለምሳሌ ፡- ሰባተኛው
ምዕራፍ የምስጠረ ጥምቀትን አፈጻጸም በስመ ሥላሴ ሥስት ጊዜ መበጥለቅ ወይም በመረጨት መሆን እንደሚገባው
8ተኛው ምዕራፍ፡- ክርስናዊ ጾም ናጸሎት ምን መምሰል እንዳለባቸው፡፡ ረቡና አርብ የጾም ቀናት እንደሆኑ፤ የጌታ
ጸሎት(አባታችን ሆይ) በቀን ቢያንስ ሥስት ጊዜ መጸለይ እንዳለበት፡፡
 ሦስተኛው ክፍል፡- ስለ ቤተክርስቲያን የውስጥ መዋቅሮችና ስለ ሕይወታ በዝርዝር ያስረዳል፡፡
2. የሐዋርያት የእምነት መግለጫ
በትውፊት የተላለፈልን የአባቶቻችን መረጃ መግለጫው በ50ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ በወረደ ጊዜ
በኃይሉና በጥበቡ ተቃኝተው ከእያንዳንዳቸው ተዋጣጥቶ የተዘጋጀ ነው፡፡
 በዚህ መልክ ዛሬ ሃይማኖተ ጸሎት ብለን የምንቀምበት የእምነት መመስከሪያ ከሐዋርያት ሲሆን ከሐዋርያት
በኃላ የተነሱ ሐዋርያን አበው በየዘመናቱ የመናፍቃን አሳቦችን ለማጥፋት ሲሉ ተጨማሪ ግላጭ ሐረግና
ዐረፍተ ነገር በመጨመር አዳብረውታል፡፡
 በመጀመሪያው ቅጂ ላይ የማይገኙ ትምህርተ ሥጋዌ፣ምሥጢረ ሥላሴን፣የክረስቶስና ነመንፈስ
ቅዱስን የባህሪ አምልክነት የተመለከቱ ጉዳዮች በኃለኛ ዘመን ተጨምረውበታል፡፡
ለምሳሌ ፡-የጥንቱ መግለጫ “በእግዚአብሔር አብ እናምናለን”….. የሚለውን ኃላ እየዳበረው የመጣው
ቅጂ ላይ “ሁሉን በያዘ፣ሰማይንና ምድርን፣የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ
በእግዚአብሔር እናምናለን፡፡”በሚል አስፋፍተው ደንግገዋል
 ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምራ ቤተ-ክርስቲያን በጥምቀት ወደ ክርስትና የሚቀላቀሉ ሁሉ
በዚህ የእምነት መግለጫ መሰረት ሃይማኖታቸውን መስክረው የሚቀላቀሉበት ስርዐት ነበራት፡፡
በሌላ አነጋገር ይህ የእምነት መግለጫ ክርስቲያን ለመሆን ተቀዳሚውና ዋና ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡
የምዕራፍ ማጠቃለያ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ/ሽ
1. ሐዋርያን አበው ብለን ስለምንላቸው ኣበቶች በዝርዝር
አስረዱ?
2. ትምህረት አበው ማለት ምን ማለት ነው?
3. የቤተክርስትያን የአባትነት መለኪያዎች አብራሩ?
4.ይህ ክፍለ ትምህርት ለዛሬው ክርስትናዊ ሕይወታችን ያለውን
ጠቀሜታ ምንድ ?
5. የሔርማስ አስሩን ትእዛዛት ዘርዝሩ?
Assigment( 35%)

የአሳይመንቱ ይዘት
አበው 1. ታሪካቸው(የት እንደ ተወለዱ፣እናት እና አባታቸው፣
እድገታቸው……)(2%)
2. የሰሩዋቸውን ስራቸውን እና ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቻውን
ግኑኝነት(10%)
3. የጻፎችው መጽሃፍት እና በዘመናቸው የነበረውን የተከናወኑ
1.ሰማዕቱ ጀስቲን እና ዐባይት ክስተቶች ያስተማረቸውን ዋናዋና ቁምነገሮችን
የቤተክርስቲያን ጠበቆች ማብራረት(10%)
2. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ 4. በነበሩበት ዘመን የነበረው የቤተክርስቲያን ሁኔታና ለዛሬው
ያለው ፋይዳ(5%)
3. የምንኩስና መስራቾች 5. ያረፉበት ቀን፤ የተደረገላቸው ቃል ኪዳን ፤ የታነፀላቸው
ቤተክርስቲያን እና ቤተክረስቲያን በዐላቸውን የምታስብበት
4. ቅዱስ ያሬድ ቀን (3%)
5.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ማሳሰቢያ፡-1. በጽሁፍ ይገባል

2.የተዘጋጀውጽሑፍታቀርባላችሁ (5%)
3. ቢያንስ ከ ሦስት በላይ መርጃ መጽሐፍት
መጠቀም እና መጻፍ አለበት

You might also like