You are on page 1of 89

ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን


ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል
የተዘጋጀ መጋቢት 2010 ዓ.ም
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ማውጫ
ምዕራፍ አንድ
ትምህርተ አበው
1.1. የትምህርተ አበው መግቢያ
1.2. የትምህርተ አበው ጥቅም
1.3. የትምህርተ አበው ዓላማ
1.4. የትምህርተ አብው ምንጮች እና መጸሕፍት
1.5. የትምህርተ አበው አከፋፍል
1.5.1. በቋንቋ
1.5.2. በዘመን
1.6. የቤተ ክርስቲን ባህርያት

ምዕራፍ - ኹለት
የተላውያን ሐዋርያነ አበው ሕይወት እና ትምሀርት (71-160 ዓ.ም)
2.1 መግቢያ
2.2 ቅዱስ አግናጢዮስ ሕይወቱ እና ትምህርቱ (Ignatius of Antioch)
2.3 ቅዱስ በርናባስ ሕይወቱ እና ትምህርቱ (st bernabase
2.4 ቅዱስ ቀሌሜንጦስ ሕይወቱ እና ትምህርቱ (clement of rome)
2.5 ቅዱ ስ ፖሊካርፐስ ሕይወቱ እና ትምህርቱ (Polycarp of Smyrna)

ምዕራፍ ሦስት
ዘመነ ሊቃውንት የቤተክርስቲያን ወርቃማ ዘመን (300-450 ዓ.ም)
3.1 መግቢያ
3.2 ሁለቱ መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች
3.3 ቅዱስ ባስልዮስ ሕይወቱ እና ትምህርቱ
3.4 ቅዱስ ጎርጎሪዮስ ዘእንዚናዙ ሕይወት እና ትምህርቱ
3.5 ቅዱስ ዩሐንስ አፍወርቅ ሕይወቱ እና ትምህርቱ
3.6 ቅዱስ አትናቲዎስ ሕይወቱ እና ትምህርቱ
3.7 ቅዱስ ቄርሎስ ሕይወቱ እና ትምህርቱ
3.8 ቅዱስ ኤፍሬም ሕይወቱ እና ትምህርቱ
3.9 ቅዱስ ህርያቆስ ሕይወቱ እና ትምሕርቱ
3.10 ቅዱስ ጎርጎረዮስ ዘኑሲስ ሕይወቱ እና ትምሕርቱ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 1
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ምዕራፍ - አራት
በዘመነ ሊቃውንት የተነሡ መናፍቃን እና የተሠጣቸው ምላሽ
4.1 ግኖስቲከውያን (gnostioism)
4.2 አርዮሳውያን (arionism)
4.3 ምንታናዊያን (montanism)
4.4 ሰባሊዮሳዊያን (sebollianism)
4.5 መቅዶኒዮሳዊያን (mocedonisnism)
4.6 ንስጥሮሳዊያን ( nestrianism )
4.7 አብሎኒያረሳውያን ( apollinarianism)
4.8 በዘመነ ሊቃውንት የተደረጉ ጉባኤያት
4.8.1 ጉባኤ ኒቂያ
4.8.2 ጉባኤ ቆስጠንጢኒያ
4.8.3 ጉባኤ ኤፌሶን

ምዕራፍ አምስት
የቤ ተክርስቲን አበው ጽሑፎች
5.1 ጸሎተ ሃይማኖት
5.2 ዲዲስቅሊያ
5.3 የበርናባስ መልዕክት
5.4 የቅዱስ ቀሊሜንጦስ መልዕክት
5.5 የቅዱስ አግናጥዮስ መልዕክት
5.6 የቅዱስ ኖላዊ ሄርማስ ያስተማርቸው ትዕዛዛት
5.7 የቅድስት ቤ/ክ የታሪክ አባት አውሳቢዮስ

ምዕራፍ ስድስት
ኢትዮጵያውያን አበው ሊቃውንት
6.1 የቅዱስ ያሬድ ሕይወቱ፣ ሥራዎቹ እና ትምህርቱ
6.2 አቡነ ኢየሱስ ሞዓ
6.3 የአባ ጊዮርጊስ ሕይወት እና ትምህርት
6.4 አቡነ ኢየሱስ ሞዓ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 2
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ምዘናና ግምገማ
ተማሪዎች ትምህርቱን እንደሚገባ መረዳታቸውን ለማወቅ
ትምህርቱም ሥርዓተ ትምህርቱም እንደሚፈለገው እየሄደ መሆኑን ለማወቅ
የመምህሩን የማስተማር ስልት እና ብቃት እና የተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል እና አረዳድ ለማወቅ
ትምህርቱ ዓላማውን ከግብ ማድረስ አለማድረሱን ለማረጋገጥ የሚከተሉት የምዘናእና ግምገማ ዘዴ ጥቅም ላይ ይውላሉ
1. የተማሩትን አባቶች ህይወት በመጠየቅ
2. የአበውን ዘመን የፈጸሙትንም ነገር በቃል እና በጽሁፍ በመጠየቅ
3. በየወቅቱ የቤት ስራ በመስጠት
4. ከተማሪዎች አንዱን ድንገት ስለ ቅዱስ ---- ግለጽ በማለት
5. በየወቅቱ ፈተና በመፈተን
6. የዕለቱን ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት ያለፈውን ትምህርት መጠየቅ
7. በየወቅቱ ስለተማሩት ትምህርት የክፍል ስራ በመስጠት መመዘን ይቻላል
የተማሪዎች ምዘና /በየወሰነ ትምህርቱ/
 አቴንዳንስ ------------------5
 ደብተር ማርክ -------------- 5
 የቡድን ሥራ(Assignment)--- 10
 ድንገቴ ፈተና ------------- 10
 አጋማሽ ፈተና ----------- 30
 ማጠቃለያ ፈተና------------ 40
 አጠቃላይ ------------------ 100

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 3
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

መስከረም 3ኛ ሳምንት
ምዕራፍ አንድ
ትምህርተ አበው /Patrology/
ትምህርተ አበው ምንድ ነው?
በቤተ ክርስቲያናችን ገድለ ቅዱሳንን የምናጠናበት የትምህርት መስክ “ዜና አበው” ወይም “ትምህርተ አበው”
ይባላል። የአበው ታሪክ፣ የአበው ትምህርት ማለት ነው። ግሪካውያን “PATROLOGY” ይሉታል። “ፓተር” አባት “ፓትሮን”
አበው ማለት ሲሆን “ፓትሮሎጂ” ማለት ነገረ አበው፣ ዜና አበው ማለት ነው። በመስኩ በርትዕት ሃይማኖት ጸንተው
ሕይወታቸውን በቅድስና የመሩ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያንን ዕውቅና የሰጠቻቸው አባቶች ዜና ሕይወት (Life) ሥራዎች
(Writings or Works) እና የእምነት አቋም (Doctrines) ሥርዓት በሆነ መንገድ ይጠናበታል። ትምህርተ አበው
“PATROLOGY” የነገረ መለኮት /THEOLOGY/ አንዱ ክፍል ነው።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አንስቶ በየፈርጁ አያሌ ቅዱሳን አበውን አፍርታለች።
በዚህም ክፍለ ትምህርታችን የሚያተኩረው ቤተ ክርስቲያናችን የምትቀበላቸውና ከኢትዮጲያ ውጪ በተነሱ ቅዱሳን አበው
ሊቃውንት ዜና ሕይወትና ሥራዎች ነው። እነዚህ ቅዱሳን አበውን ለምሣሌ ለመጥቀስ ያህል፦
 ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሥርያ
 ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ
 ቅዱስ ቀለሜንጦስ ዘሮም
 ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘቆስጠንጥኒያ
 ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
 ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ...... የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ።
የትምህርተ አበው ጥቅም
 ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አበው የጻፉትን መማር እና ማጥናት ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት
እንድናውቅ ይረዳናል።
 በመሠረቱ የነገረ ሃይማኖትን ትምህርት ለመማርና ለማጥናት ያለ ሊቃውንተ አበው ትምህርትና የሕይወት ልምድ አስቸጋሪ
ይሆናል። ስለዚህም የሊቃውንተ አበውን ትምህርት መማርና ማጥናት በቀላሉ የቤተ ክርስቲያንን ምስጢራትን በግልጽ መንገድ
እንድንረዳ ስለሚጠቅመን
 ስለዚህ አበው ሊቃውንት ያስተማሩን መንፈሳዊ ትምህርቶች መማር መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሠፈሩትን ትምህርቶች በተገቢው
ሁኔታ እንድንረዳ ይጠቅመናል። በተለይ በዚህ ዘመን ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ቀደምት ለነበሩት አበው የተለየ ክብር
አላቸው። ምክንያቱም ደግሞ የአብያተ ክርስቲያናት ሕብረትን ስለሚያጠነክር ነው። የቀደሙት አበው ትምህርታቸውና
ሕይወታቸው በበለጠ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ስላስተማረውና ስላደረገልን ድኅነት በሚገባ እንድንረዳ ያደርገናልና።

የትምህርተ አበው ዓላማ


 ዋና ዋና የቅዱሳን አበው ሊቃውንትን ሕይወትና ትምህርት አውቀን እነርሱ ያስተማሩትን በእኛ ሕይወት መግለጥ እንድንችል።
 ፈለገ ቅዱሳን አበው ሊቃውንትን በማወቅ አሠረ ፍኖታቸውን እንድንከተል።
 ውለታቸውን እንዳንዘነጋና በረከታቸውንም እንድንጠቀም።

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 4
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

 የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንተ አበው ትምህርትን ከአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ኑፋቄ ትምህርት ጠንቅቀን በመለየት እውነተኛውንና
ቀጥተኛውን ትምህርት መመስከር እንድንችል።

የትምህርተ አበው የጥናት አከፋፈል


ትምህርተ (ዜና) አበውን ግልጽ ባለ መንገድ ከፋፍሎ ለመማርና ለመመርመር አስቸጋሪ ቤሆንም ጠቅለል ባለ መንገድ
ግን ለመረዳት በዚህ መንገድ ከፋፍሎ መመልከት ይቻላል።
1. በቋንቋ
አበው ሊቃውንት ሕይወታቸውና ትምህርታቸው በተጻፈበት ቋንቋ
ምሣሌ፦ ፁር - ግሪክ
 ሱርስት - ሶርያ
 አርማይክ - አርመን
 ቅብጥ /ኮፕት/ - ግብፅ
 ግእዝ - ኢትዮጲያ
2. በቅድመ ዘመን
 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ መ/ክ/ዘ
 ወርቃማው የቤተ ክርስቲያን ዘመን (300 – 430 ዓ,ም)
 ከ430 ዓ.ም በኋላ ያለው ዘመን

መስከረም 4ኛ ሳምንት
የቤተ ክርስቲያን ባህርያት
ቤተ ክርስትያን የክርስቶስ አካሉ ናተና አንድ ባሕርይ ናት፡፡ ባሕሪዋ የሚገለጥበት ነጥቦችም
እንደሚከተሉት ናቸው፡፡
1 አንዲት ናት(Onese of the church)
ቅዱስ ጳወሎስ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሰራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ፡፡ አንድ
ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት አንንድ አካል አንድ መንፈስ እያለ የገለጣት ቤተ ክርስቲያንን ነው፡፡ምክንያቱም የቤተ
ክርስቲያን ራስ አንድ ነው እርሱም ክርስቶስ ነው ኤፌ 4÷ 4-5ጌታችን በዮሐንስ ወንጌል ላይ ራሱን በወይን ግንድ ምእመናንን
በቅርንጫፉ መስሎ እንዳስተማረን ሌላ እውነተኛ ወይን የለምና አሐቲ /አንዲት/ ከተባለች አማናዊት አቤተ ክርስቲያን
ሌላሁለተኛ ተደራቢ ቤተክርስቲያን ሊኖር አይችልም፡፡ ዮሐ 15÷ 1-7፤ ሰዎች በተለየ ሃሳብ የተለያየ መኞትና ፈቃድ ሊኖራቸው
ቢችልም ቤተ ክርስቲያን ግን የአንድ የክርስቲስ አካሉ ናትና አንዲት ናት፡፡አትከፈልም ከእምነ ከስርዓቱና ከትውፊቱ የወጣ
ቢኖር እርሱ ይለያል ወይም ከቡተ ክርስቲያን ወጪ ይሆናል፡፡አንድ ጊዜ ብቻ በክርስቶስ ደም የተመሰረተችና የጸናች
ቤተክርስቲያን አንዱ ዘመን አልፎ ሌላው ዘመን አነዱ ሰው አልፎ ሌላው ሰው ቢተካ በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ ሰዎች
ሥርዓን የጠበቁ የተለያዩ የሕንጻ አሠራር ሁኔታ ቢኖርም አነዲት ናት፡፡

2 ቅድስት ናት (Holiness of the church)


እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ ደግሞ እናንተም ደግሞ
በኑሮአችሁ ቅዱሳን ሁኑ 1ኛጴጥ 1÷15-16 በማለት የጌታ ደቀመዛሙርት ባስተማሩት መሰረት ቤተ ክርሰቲያን የተቀደሰ ሥራ
የሚሰራበት በውሰም የሚገቡትና የሚኖሩት ሁሉ በየጊዜው ራሳቸውን የሚቀድስባት ቤት ናት፡፡ቤተ ክርሰቲያን ቅዱስ
በሆነው በክርስቶስ ደም የተቀደሰች ስለሆነች ቅድስት ናት፡፡ሐዋ 20÷28 1ኛቆሮ 6÷19 በቤተ ክርስቲያን ኃጢያትና ርኩሰት

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 5
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

አይፈጸምባትም ፡፡ምእመናን በክርስቶሰ አ)ንድ አካል ናቸውና አንዱ ቢያጠፋም ሌላው በፍቅር ይመክረዋል፤የገስጸዋል እንጂ
እነዲሁ አያልፈውም፡፡ይህም የሚሆነው የአንዱ ጥፋትና በደል እንዲሁም በእርሱ ምክንያት የሚመጣው መቅሰፈት ሁሉንም
ያገኛቸዋልና ነው፡፡ለዚህም የካህኑ የመስፍኑ የኤሊም ልጆች ታሪክ ዓይነተኛ ማስረጃ ሊሆን ይችላል 1ኛሳሙ 2÷4 ፡፡ዔሊም
ሆነ ሌሎች ሰዎች አፍኒንና ፊንሐስን አሰቀድሞ በፍቅር ቀርበው ከክፉ ሥራቸው እንዲመለሱ ደጋግመው ቢገስጹአቸው ኖሮ
የእግዚአብሔር ቁጣ እነርሱንም ጭምር ባላጠፋቸው ነበር ፡፡ቤተ ክርስቲያን ቅድስት የሚያሰኘው ዋናው ነገር ግን በደመ
ክርስቶስ መመስረ በቻ ሳይሆን አካሉ ናትና ሁልጊዜ በእርሱ ቅድስና ትቀደሳለች፡፡ስለዚህም ቅድስት ናት፤፤ኤፌ 5÷26

3. ሐዋርያዊት ናት (Apostolicty of the church


ይህም ማለት በፈቃደኛ ሰዎች ስብሰባ ብቻ ዛሬም ተመስርታ ልትኖር የምትችል አይደለችም ፡፡መሰረ አንድ
ጊዜ በክርስቶስ ተጥሉአል ከዚያም ሐዋርያት ታንጹአል በዚህችም ቤተ ክርስቲያን ከመኖር ውጪ የክርስቶስን ስሙን
በመጥራትና ክርስቲያኖች ነን በማለት በቻ ቤተ ክርስቲያን ማድረግ አይቻልም፡፡ቀዱሰ ጳውሎስ ከተመሰረተው በቀር ማንም
ሌላ መሠረት ሊመሰርት አይችልምና እርሱም ኢየሱስ ክርሰቶስ ነው፡፡ማንም ግን በዚህ መሰረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም
በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያነጽ የእያነዳንዱን ስራ ይገለጣል በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና
የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳት ይፈትነዋል በማለት እደገለጸው በዚህ የሐዋርያት ትምህርት የታነጸች ነች
1ኛቆሮ3÷10-14 ስለዚህ ሐዋርያት ያስተማሩትን ትምህርት ታሰምራለች እንደ ሐዋርያት ምስጢራትን ትፈጽማለች፡፡ሐዋርያት
የተቀነበሉትንና የእነርሱ የሆነውን ቅዱስ ትውፊት ተቀብላ ታስተምራለች ትሰራበታለች እንጂ አዲስ ነገር ፈጥራ ራስዋን በግንዱ
የምትለይ ቀርንጫፍ አትሆንም ፡፡ቅዱሰ ጳውሎስ የህንኑ ሲያስረግጥ ’’በሐዋርያት በነቢያት መሰረት ላይ ታንጻችልና
’’የማዕዘኑም ዱደስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ ብመቅደስ እንዲሆን
ያድጋል በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን አብራችሁ ትሠራላችሁ’’ በሎአል ኤፌ2÷20-22 እንደ
ሐዋርያት የምታስተምር እንደ እነርሱም የተለየ (ቅዱስ) ስብስባ (ሲኖዶስ) ያላት በዚህም ሥርዓት የምትመራ በእርሱም
የሥርዓት መሰረት ላይ የታነጸች ስለሆነ ሐዋርያዊት ናት፡፡

4. ዓለማቀፋዊት ናት(Universality of the church


ቤተ ክርስቲያን አንዲት ብትሆንም መንፈሳዊት ናትና በሁሉም ያለች የሁሉም ናት ፡፡ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን
እግዚአብሔር ግእዛን ካላቸው ፍጥረታት ጋር የለው ግነኝነት ናትና በአንድ አካባቢ ብቻ ልትወሰን አትችልም ፡፡ቅዱስ ጳውሎስ
ይህንንም ሲገልጽ’’....ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይ ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው ፡፡ እርሱዋም
አካሉ ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላት ናት፡፡’’ ብሎአል ኤፌ 1÷23 ስለዚህ በሁሉ ያለች አምኖ ተጠምቆ በበb የሚገባውን
ሁሉ ተቀብላ አካልዋ የምታደርግ የሁሉም ናት እንጂ የተጀመረችባት የፍልስጥኤም ምድር የተስፋፋችበት የሮም ወይንም የሌላ
አካባቢና የትሰነ ነገድ ብቻ አይደለችም ፡፡ ክርስቶስ ለሚያምኑበት ሁሉ ጌታ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያን የሁሉ ናት ፡፡

ጥቅምት1ኛ ሳምንት
የቤተ ክርስቲያን አባት ለመባል የሚያስፈልጉ መሥፈርቶች
1. ሃይማኖት በመጠበቅና በማስጠበቅ ባበረከቱት አስተዋጽኦ
በኒቂያ፣ በቆስጠንጥኒያና በኤፌሶን ጉባኤያት መናፍቃንን አውግዘው የሃይማኖት መመሪያ የሆነውን ሃይማኖተ አበውን ያዘጋጁ
አባቶችን ቤተ ክርስቲያን የአባትነት ማዕረግ ከቅድስና ጋር ሰጥታቸዋለች
2. የቅድስና እና የንፅህና ሕይወት ያላቸውን
ማቴ 5፥19 “ከእነዚህ ከኹሉ ካነሱት ትዕዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር በመንግስተ ሰማያት ከኹሉ
ታናሽ ይባላል። የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግስተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።”
3. ቤተ ክርስቲያን “አባት” ብላ ተቀብላ የመሰከረችላቸው።
ቤተ ክርስቲያን እና የቅዱሳን አበው ሕይወት የተሰናሰለ ነው። አይለያዩም ደማቸውን አፍስሰው ቤተ ክርስቲያንን ለዚህ
ትውልድ ያስተላለፉትን ቅዱሳን አበውን ውለታ አትረሣም። ሥላደረጉትም ውለታ ትመሰክርላቸዋለች። ምሥክርነቷንም
በእነዚህ መንገዶች ትገልጣለች።

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 6
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ሀ. ህንፃ ቤተ ክርስቲያን በመሥራት


ለ. የመታሰቢያ መጽሐፍ በመጻፍ
ሐ. የተለያዩ ስማቸን ሊያስጠሩ የሚችሉ መታሰቢያዎችን በማድረግ
4. በቀደምት ዘመን የነበሩ አበውን በተለይ ከ6ኛው መ/ክ/ዘ በፊት የነበሩትን
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን መሥፈርት አሟልተው የተገኙ ቀደምት አበውን በእነዚህ ወገን ከፍሎ መመልከት
ይቻላል።
1. ሐዋርያውያን አበው /Apostolic Fathers/
በግእዝ ተላውያን ሐዋርያውያነ አበው የሚባሉት ከቅዱሳን ሐዋርያት በመቀጠል ወንጌልን ያስተማሩ
ምሣሌ፦ አግናጢዮስ ዘአንጾኪያ፣ ቀለሜንጦስ ዘሮም
2. የቤተ ክርስቲያን ጠበቆች /Apologists/
ጣዖት ማምለክን እምቢ ብለው እውነተኛውን አምላክ በማምለካቸው በአላውያን ነገሥታት ፊት ሰማዕትነትን የተቀበሉትን
ምሣሌ፦ ሰማዕቱ ዮስጣን፣ ሰማዕቱ ጀስቲን
3. ሊቃውንት መምህራን /Docters of the church/
ምሣሌ፦ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
4. ገዳማውያን አባቶች መነኮሳት
ማሣሌ፦ ርእሠ መነኮሳት ቅዱስ እንጦስ፣ ቅዱስ ጳውሊ፣ አባ መቃርዮስ /መቃርስ/
5. ሰማዕታት /ምሥክሮች/
ምሣሌ፦ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ ቅዱስ ሳዊሮስ

ጥቅምት 2ኛ ሳምንት
ምዕራፍ ኹለት
የተላውያን ሐዋርያነ አበው ሕይወትና ትምህርት
መግቢያ
ከ70-106 ዓ.ም ያለው ከዘመነ ሐዋርያት በኋላ ያለው የመሸጋገሪያ ዘመን ነው። በዚህም ጊዜ የነበሩት ቅዱሳን አበው
ሐዋርያነ አበው(ተላውያነ ሐዋርያት) ይባላሉ። እነረሱም ከቅዱሳን ሐዋርያት በቃልም በሥራም የተማሩ በመንፈስ ቅዱስ
የተሾሙ በሐዋርያት መንበር የተተኩ ደቀመዛሙርት ናቸው። በማንኛውም የሥራ መስክ መንፈሳዊ አደራቸውን ከቅዱሳን
ሐዋርያት ተቀብለው ቤተክርስቲያንን የመሩ ርቱአን ሃይማኖት “የሐዋርያት ሁለተኛ ዙር ሐዋርያት ናቸው።”
ከነዚህም አበው ብዙዎች መጽሐፍትን ጽፈዋል ተርጉመዋል በጽሑፎቻቸውም ክርስቲያኖች በደረሱባቸው ስደቶች
ተስፋ እንዳይቆርጡ አጽንተዋቸዋል እንዲሁም በየጊዜው በተነሱ መናፍቃን ትምህርት እንዳይታለሉ በማለት ሥጋዊና መንፈሳዊ
ሕይወታቸውን በሥርአት ለመምራት የሚያስችላቸውን ጽሑፎች በቅዱሳት መጽሐፍት ላይ ተመሥርተው ጽፈዋል። ከነዚህም
መካከል መጽሐፈ ዲዲስቅልያ፣ መልእክታተ በርናባስ፣ መልእክታተ፣ ቀለሜንጦስና ራእየ ሄርማ የሚጠቀሱ ናቸው። ስለሆነም
ቀደምት የክርስትና ጸሐፊዎች (early christian writers) ይባላሉ።
እነዚህ አበው ከቤተ አይሁድ ብቻ ሳይሆን ከቤተ አህዛብም የተገኙ ናቸው። በሐዋርያት ጊዜም እነሱን እየረዱ
ኖረዋል። ባስተማሯቸውም ትምህርት ጸንተው ማጽናታቸውንም በዓላውያን ነገሥታት ሰይፍ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።
ተላውያነ ሐዋርያት ከሚባሉት ውስጥ የሚከተሉት ዋነኞቹ ናቸው።
 ቀሌሜንጦስ ዘሮም
 አግናጥዮስ ዘአንጸኪያ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 7
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

 በርናባስ ዘቆጵሮስ
 ፖሊካርፐስ ዘሰርምኔስ

እነዚህ አባቶች ለቤተክርስቲያን ሰማዕትነትን እስከመቀበል ደርሰው ከሠሩትና ካስተማሩት ይልቅ ከሞቱ በኋላ ህያው
በሆነው ስማቸውና ትምህርታቸው እየሠሩ ያለው ሥራ ይበልጣል። ምክንያቱም እስከዛሬ ድረስ ትምህርታቸው መናፍቃንን
እያሳፈረ አጋንንትን እያስደነበረ ነውና ሊቃውንቱ እየተንቀሳቀሱ ያሉት በእነርሱ እስትንፋስ (ትምህርት) ነውና።
እነርሱን መሆን ባይቻልም ቤተክርስቲያንም የእነዚህን ቅዱሳን አበው ብሔረ ሙለጻቸውን፣ ጥንተ ነገዳቸውን የገድላቸውን
ጽንአትና የሥነ ጽሁፋቸውን ብስለት መዝግባ አስቀምጣለችና የጥቂቶቹን ሕይወት፣ ታሪክና ትምህርት እንመለከታለን።

ጥቅምት3ኛ ሳምንት
ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ
ዜና ሕይወቱ ለቅዱስ አግናጥዮስ
ቅዱስ አግናጥዮስ የተወለደው በ30 እስከ 35 ዓ/ም
በነበረው ጊዜ ውስጥ በዚያን ዘመን የሶርያ ዋና ከተማ
በነበረችውና ክርስቲያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስቲያን
በተባሉበት በአንጾኪያ ነው:: ቅዱስ አግናጥዮስ ከተላውያን
ሐዋርያት አንዱ ሲሆን የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደቀመዝሙር
የነበረ ነው:: የቤተክርስቲያን ትውፊት እንደሚነግረን ደግሞ
በህጻንነቱ ወቅት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ለድኅነተ ዓለም በሥጋ ተገልጦ ሲያስተምር ትህትናን
ያስተማረበት ህጻን ቅዱስ አግናጥዮስ ነው::
ማቴ 18፥2-5 “ በዚያችም ሰዓት የጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ደቀመዛሙርት በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ
ማነው? እያሉ ወደ እርሱ ቀረቡ:: ሕጻኑንም ጠርቶ
በመካከላቸው አቆመው እንዲህም አለ:- እውነት እላችኃለሁ
ካልተመለሳችሁ እንደዚህ ሕጻን ካልሆናችሁ ወደ መንግሥተ
ሰማያት ከቶ አትገቡም:: እንደዚህ ሕጻን ራሱን ዝቅ ያደረገ
በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ ይህ ነው:: እንደዚህም ያለውን
አንድ ህጻን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል::”
በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት በቀራንዮ የተመሰረተችው ቤተክርስቲያን በሐዋርያት ስብከት ወደ ዓለም መስፋፋት ጀመረች::
በዚህም የመጀመሪያ መሰበክ ወቅት የአንጾኪያ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በቅዱስ ጰጥሮስ ሲሆን እርሱም የአንጾኪያ
የመጀመሪያው ጳጳስና ፓትርያርክ ሆኗል:: በአንጾኪያ የነበሩ ክርስቲያኖች እጅግ በጣም ጠንካራና ጽኑዓን ስለነበሩ ቅዱስ
ጴጥሮስ ኤውድዮስን ጵጵስና ሹሞ በመንበሩ ካስቀመጠው በኃላ ወደ ሮም ሄዷል:: ኤውድዮስም ሁለተኛው የአንጾኪያ
ፓትርያርክ ሆኖ አገልግሎ ከዚህ ዓለም በሞት በሚለይበት ጊዜ ቅዱስ ጰጥሮስ በ70 ዓ/ም ቅዱስ አግናጥዮስን የአንጾኪያ
ሦስተኛ ፓትርያርክ አድርጎ ሾሞታል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰማዕቱ ቅዱስ አግናጥዮስን ጵጵስና ከሐዋርያት እጅ የመቀበሉን
ነገር እጅግ በጣም ያደንቃል፤ የተለየ ክብርም ይሰጠዋል:: ክርስቲያኖችም ቅዱስ አግናጥዮስን እውነተኛና ጥልቅ በሆነ ፍቅር
ይወዱት ነበር:: እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራና ፍጹም እምነት ያለው ትጉህና ታታሪ አባት ነበር:: ቅዱስ አግናጥዮስም
በጵጵስና መንበር ላይ 40 ዓመታት ያህል ቤተክርስቲያንን በፍጹም ትጋትና ለመንጋው እውነተኛ ምሳሌ የሚሆን አባት ሆኖ
አገልግሏል::

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 8
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ቅዱስ አግናጥዮስ ሌላ ተጨማሪ መጠሪያ ስምም ነበረው:: ይኸውም በግሪክ ቴኦፎሮስ(Theophoros)


እግዚአብሔርን የተሸከመ / ክርስቶፎሮስ/ (Christophoros) ክርስቶስን የተሸከመ እየተባለ ሲጠራ በቤተክርስቲያናችንም
ለባሴ እግዚአብሔር /The bearer of God/ የሚል ቅጽል ስም አለው:: ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ የክርስቶስን ስም ከአፉ
የማይለይ እና ”ክርስቶስን ልበሱት በውስጣችሁም ተሸከሙት“ እያለ ያስተምር ስለነበረ ነው:: እርሱም ራሱን በዚህ ስም
እየጠራ ይጠቀምበታል:: ለምሳሌ መልዕክታትን በሚልክበት ወቅት በመጀመሪያ ሰላምታው ላይ “ቴኦፎሮስ” ብሎ ነው
የጻፈው:: እንዲሁም በትራጃን ፊት በቆመበት ወቅት ትራጃን ቅዱስ አግናጥዮስን “ርጉም”ብሎ በሚሰድበው ጊዜ “ማንም
ቴኦፎሮስን ርጉም ብሎ የሜጠራው የለም” ብሎ መልሶለታል:: እንደገና ትራጃን ምን ማለት እንደሆነ ሲጠይቀው “ኢየሱስ
ክርስቶስን በውስጡያለው እርሱ ነው ቴኦፎሮስ”ብሎ መልሶለታል::
በእርግጥ ቅዱስ አግናጥዮስ ፍጹም መንፈውዊ ጸሎተኛ ስለ ክርስቶስ የሚያሣየው ውስጣዊ የተቃጠለ ፍቅር
ለክርስቲያኖች ምሳሌ የሚሆን አባት ነው፡፡በዚያ ወቅት እውነተኛው የበጎች እረኛ በመሆን የእግዚአበሄርን ፍቅር በአንጾኪያ
ህዝቦች መካከል በእውነት የተሸከመ ነበር ቅዱስ አገናጥዮሰ በክ በክርስቲያኖች ውስጥ ሁል ጊዜ እውነትኛ የሆነ የክርስትና
ህይወት እንዲኖር ከፍተኛ ጥረትና ጥንቃቄ ያደርግ ነበር ።ከሐዋርያት የተቀበለውን እውነተኛ የክርስቶስ ትምህርት በተለየ
ሁኔታ ለመጥብቅ እጅግ በጣም ይተጋ ነበር ።በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የነበሩት ክርስቲያኖች ከሐዋርያት የወጣ ትምህርት
እንዳይሰሙ እውነትኛው የክርስቶስ አስተምህሮ በሐሰተኞች መበርዝ የለበትም ይላችው ስለንበር እነርሱም ከአባታቸው
ከቅዱስ አግናጥዮስ ይርተቀበሉትን ቃል ይጠብቁ ነበር ።በመሆኑም በምካከላቸው እየተሽሎከልኩ የሚገቡትን መናፍቃን
በግልጽ ይቃወሟቸው ነበር።

ጥቅምት4ኛ ሳምንት
የቅዱስ አግናጥዮስ መልእክታት
የቅዱስ አግናጥዮስን ማንነት የሚገልጥልን አሁን በብቸኝነት እንደ ትልቅ መረጃ የምንጠቀምበት በሰማዕትነቱ
ወቅት የጻፋቸው ሰባቱ መልእክታት ናቸው። ስለዚህ በዚህ ክፍል የቀረበው ትምህርት ከመልእክቲቱ የተውጣጣ ነው።
በመልእክቱ ውስጥም የሚገኙት ትምህርቶች፦
1. ስለ ምስጢረ ሥላሴ
2. ስለ ነገረ ድኅነት (ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ)
3. ስለ ሥጋወ ደሙ
4. ስለ ጥምቀት
5. ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት
6. ስለ ቅድስና
7. ስለ ቤተ ክርስቲያን ዓለማቀፋዊነት
8. ስለ ክህነት ሥልጣን ተዋረድ አስፈላጊነት
9. ስለ ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና
10. ቤተ ክርስቲያንን ከመናፍቃንና ከመከራ መጠበቅ ሲሆን
በተለይ ስለ አምላክ ሰው መሆን አማናዊነት ለመግለጽ የተጠቀማቸው ቃላትና በዚህ ዙሪያ ያሉት አስተምህሮዎቹ
አጠቃላይ በወቅቱ የነበሩትን መናፍቃን ዶሴትስቶችንና አይሑድን እንዲሁም የመሰሎቻቸውን ስህተት የሚገልጥና ለእነርሱ
መልስ የሚሰጥ ነው።
ቅዱስ አግናጥዮስ ሰማዕትነትን ለመቀበል ከአንጾኪያ ወደ ሮም በሚሄድበት ጊዜ ሁለት ቦታዎች ላይ በማረፍ ለአብያተ
ክርስቲያናት ሰባት መልእክታትን ጽፏል። ይኸውም፦
1. በሰርምኔስ
2. በጢሮአዳ ባረፈበት ወቅት ነው።

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 9
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

1ኛ በሰርምኔስ
አራቱን መልእክታት የጻፈው በሰርምኔስ አርፎ በነበረበት ወቅት ነው።
1. ወደ ኤፌሶን
2. ወደ ማግኔዥያ
3. ወደ ትራሊያ
4. ወደ ሮም የጻፋቸው ናቸው።

2ኛ በጢሮኣዳ
ሦስቱን መልእክታት ደግሞ በጢሮአዳ ባረፈበት ወቅት ነው የጻፈው።
1. ለቅዱስ ፖሊካርፐስ
2. ወደ ሰርምኔስ
3. ፊላደልፊያ የተላኩ መልእክታት ናቸው።
ቅዱስ አግናጥዮስ መልእክታቱን በሚጽፍበት ጊዜ በእስር ላይ ሆኖ ወደ ሮም ለሰማዕትነት እየተወሰደ በመንገድ ላይ
እያለ የጻፋቸው ቢሆኑም ታላቅ የነገረ መለኮት ትምህርትን የያዙ ናቸው። በጉዞ ላይ እያለ ምንም ያህል ቢያሰቃዩትም እርሱ
ግን በቁርጥ ሕሊና እንደ ቸኮለ ያሳያል። የሚቀበለውንም መከራ ግልጽ ባለ መንገድ አስቀምጦታል።
መልእክታቱ በዚህ ታላቅ ጳጳስ እና ሰማዕት ውስጥ ያለውን እይታ የሚያሳዩን ከመሆናቸውም በላይ የሰውን ልቦና
የሚስብና በፍጹም የሚያነሳሳ ጥልቅ የሆነ ሃይማኖታዊ ቅናትን የሚያሳድሩ ናቸው። ቅዱስ ፓሊካርፐስም የቅዱስ አግናጥዮስን
መልእክት “ትምህርቶቹ በውስጣቸው እምነት ጽናትና የጌታችንን አምላክነት የሚገልጹ ስለሆኑ በጣም ጠቃሚ ሆነው
ታገኛችኋላችሁ” ይላል።
የቅዱስ አግናጥዮስ መልእክታት እኛን ከመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ጋር የሚያገናኙንና በኢየሱስ ክርስቶስ
ለሐዋርያት የተሰጣቸውን ትምህርት የሚያስተላልፉ ናቸው። በተጨማሪም የእግዚአብሔር ሰው የክርስቶስ አማናዊ ደብዳቤ
የሆነው ቅዱስ አግናጥዮስ ምን አይነት ሰው እንደ ነበር እውነተኛ ሕይወቱን ይገልጽልናል።
የቅዱስ አግናጥዮስ መልእክታት መጀመሪያ የተሰበሰቡት በሰሞርኔስ ጳጳስ በቅዱስ ፖሊካርፐስ ነው። ቅዱስ
አግናጥዮስ ከሰሞርኔስ ተነስቶ ወደ ሮም እየሄደ እያለ ነው ግልባጩን ለፊልጵስዮስ ቤተ ክርስቲያን የላከው። ምክንያቱም ለሮም
የጻፈውን መልእክቱ ለማግኘት እድሉ አልነበረውም። የሮም መልእክቱን ገና ጽፎ እንደላከው ስለነበር ሥርጭቱ ገና ስለነበር
ቅዱስ ፖሊካርፐስ የሁሉንም መልእክታት ግልባጭ ያገኘው ከኤፌሶኑ ዲያቆን ከበርሁስ እጅ ነበር። ቅዱስ አግናጥዮስ
በሰማዕትነት ጉዞ ወቅት የነበረውን ጊዜውን ሳይቀር ለአቢያተ ክርስቲያናት ሰባት መልእክታትን በመጻፍ በያረፈበት ሁሉ
ክርስቲያኖችን በማጽናናት በማበረታታት ፈጽሞ ተጠቅሞበታል።

ህዳር 1ኛ ሳምንት
መልእክታቱን የተጻፈበት ምክንያት
ቅዱስ አግናጥዮስ መልእክታቱን በሚጽፍበት ወቅት በብዙ ድካምና እንግልት በአሥር ወታደሮች እየተሰቃየ
ከአንጾኪያ እስከ ሮም ለሰማዕትነት በሚጓዝበት ጊዜ ቢሆንም ሁሉም መልእክታት የተጻፉበት ምክንያት አጠቃላይ ሃሳብ
በአጭሩ በአራት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነው።

1. ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት
ምዕመናን በካህናት ሥር በመሆንና ለእነርሱ በመታዘዝ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ብዙ ጊዜ ደጋግሞ በአጽንዖት
ጽፏል። እንዲህም ይላል። “መከፋፋት የተንኮል ሁሉ ምንጭ ነውና ከዚህ ሽሹ። ኢየሱስ ክርስቶስ አባቱን እንደታዘዘ ጳጳሳትን

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 10
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ተከተሉ። ካህናትንም እንደ ሐዋርያት ዲያቆናትን ደግሞ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ማክበር አላባችሁ። ማንም ሰው ከጳጳሳት
ውጪ በቤተ ክርስቲያን ምንም መስራት አይችልም። ሥጋወ ደሙን በተመለከተ የሚፈጸመው በጳጳስ ወይም ሥልጣነ ክህነት
ባለው ነው። ራሳቸውን ከክርስቲያኑ ማኅበረሰብ የሚለዩ በትክክል የእግዚአብሔር ፍቅር የሌላቸው ናቸው። ምንም ስህተት
እንዳታደርጉ በዚህ የተነሳ ማንኛውም በመቅደስ ውስጥ ያልሆነ የክርስቶስን ሥጋና ደም አያገኝም። በቤተ ክርስቲያን ሕብረት
አልሆነም የሚል በትዕቢት ራሱን ከቤተ ክርስቲያን እየለየ ነው።” እያለ ምዕመናንን ጭምር የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን
መጠበቅ እንዳለባቸው ይመክራል።

2. ቤተ ክርስቲያንን ወደ መከፋፈል ከሚመሩ መናፍቃን ከዶሴቲስቶች እና ከአይሁድ ትምህርት እንዲጠነቀቁ


ለማሳሰብ።
ቅዱስ አግናጥዮስ አብዛኛውን የጻፈው ዶሴቲስቶችን እና አይሁድን በተመለከተ ነው። ምክንያቱም እነዚህ ሁለቱም ለቤተ
ክርስቲያን ታላቅ እንደሆኑ በሚገባ ስለሚያውቅ ነው። “ቤተ ክርስቲያን ወደ መከፋፈል የሚያመሩትን የመናፍቃንን እንቅስቃሴ
አጋልጡ” ይላል።
ለቅዱስ ፖሊካርፐስ እንዲህ ይላል “አንተ እንደኔ ያለ ሐሳብ እንዳለህ አውቃለሁ። ይህንን ትዕዛዝ የምሰጥ ግን
አስቀድሜ የሰው መልክ ካለቸው የዱር አራዊቶች ላስጠነቀቅህ ነው። እነርሱን ላለመቀበል ብቻ መቃወም አይደለም። ነገር
ግን ከተቻለ ከእነርሱ ጋር መገናኘትን ማስወገድ ይገባሃል። ወደ ንስሐ እንዲመለሱ ስለ እነርሱ ጸልይ። ይህም ከባድ ነው፤ ነገር
ግን እውነተኛ ሕይወታችን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽን የማድረግ ኃይል አለው።” በማለት ለፖሊካርፐስ ምክር ለግሶታል።

3. በጸሎት ስለተራዱት ለማመስገን


“እኔ በእግዚአብሔር ሰላምታ ሰላም እላለሁ። ይኸውም በእኛ ዘንድ ተወዳጅ በሆናችሁ ትክክለኛ ቤተ
ክርስቲያናችሁ እና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ እምነት ነው። እናንተ በእርሱ ፍቅር ተይዛችኋልና። የበለጠ
ወደ ፍጹምነት የሚያደርስ ሥራ ትሠሩ ዘንድ ተስፋችንና የሁላችን መጠሪያ በሆነው ስማችን ምክንያት ብቻ እንደ እስረኛ ሆኜ
ከሶሪያ በመርከብ እያሄድኩ መሆኔን በሰማችሁ ጊዜ በታላቅ ቅናት መጥታችሁ እኔን ጎብኝታችሁኛልና በእናንተ ጸሎት በሮም
ከአናብስቱ ጋር የመታገል ዕድል ይኖረኛልና ብዬ በእውነት ተስፋ አደርጋለሁ። ስለዚህ ይህንን በማድረጌ እውነተኛ ደቀ
መዝሙር መሆን እችላለሁ። ስለዚህ በእግዚአብሔር ስም ከቃላት በላይ በሆነው በአናሲሞስ ፍቅር የእናንተን ብዙ ምዕመናን
አግኝቻቸዋለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ እንድትወዱት እና ሁላችሁም እሱን እንድትመስሉት ጸሎቴ ነው። እንደዚህ
ዓይነት ጳጳስ ስላላችሁ እግዚአብሔር የተመሰገነ የተባረከ ነው።” እንዲህ በማለት በሰማዕትነት ጉዞው የጎበኙትንና ያበረቱትን
በመልእክያቱ አመስግኗቸዋል።
4. ለሮም ክርስቲያኖች የሰማዕትነት አክሊል ይቀበል ዘንድ እንዳያደናቅፉበት በመማጸን የጻፈው ነው።
ለሮም ክርስቲያኖች የላከው መልእክት ላይ “ፈጣሪዬ ክርስቶስን በመከራው እመስለው ዘንድ ፍቀዱልኝ” ይላል።
ይኽ ሌሎችን ጠቅልሎ የሚገልጽ ቃል ነው። ቅዱስ አግናጥዮስ ሰማዕትነት “እውነተኛ ደቀ መዝሙር”፣ “ትክክለኛ ክርስቲያን”
የሚሆንበት መንገድ እና “እግዚአብሔርን የሚያገኝበት መንገድ እንደሆነ ይናገራል። እንዲሁም በሚያስገርም ሁኔታ በአናብስት
በመበላት ሰማዕትነትን ለመቀበል ምን ያህል እንደጓጓ ይገልጻል።

ቅዱስ አግናጥዮስ በመልእክቱ ላይ ያስተማራቸው ትምህርቶች


1. ስለ ቤተ ክርስቲያን
ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችው ለሚታየው ማኅበረሰብ በሰማያዊ ሥርዓት ነው። ይኽችውም የነፍስ ድኅነት የሚፈጸምባት
ናት። ራሳቸውን ከቤተ ክርስቲያን የሚለዩ ግን ከእግዚአብሔር ራሳቸውን ይለያያሉ። ቅዱስ አግናጥዮስ ከአንድ አገር ካለች ቤተ ክርስቲያን
ጋር በማነጻጸር “ካቶሊክ” ወይም ዓለም አቀፋዊት የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመግለጽ የተጠቀመ
አባት ነው። ጳጳሱ የትም ቦታ ቢሄዱ ምዕመናን ቢሰበስቡ ኢየሱስ ክርስቶስ በየትም ቦታ ስላለ በዚያም ዓለም አቀፋዊት የሆነች አንዲት
ቤተ ክርስቲያን አለች። ቤተ ክርስቲያንንም ሲጠራት “የመስዋዕት ቦታ” ይላታል። ሥጋ ወደሙን የዘውትር መስዋዕት በማድረግ
ታቀርባለች። እርሱም የደስታዋ ምንጭ ነው። ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት በክርስቶስ መሰዊያ ላይ ዙሪያውን ይሰበሰባሉ። ቤተ ክርስቲያን
መስዋዕትየሆነው የሰማያዊው ንጉስ ሙሽራ ናት። እኛ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን። ስለዚህ እግዚአብሔር በውስጣችን አለ። እርሱም
በከበረ ደሙ ገዝቶናል። ምንም ዓይነት መልካም ሥራ ብንሠራ እርሱ በእኛ አድሮ የሠራው ሥራ ነው። እኛ የእርሱ መቅደስ ስንሆን እርሱ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 11
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል
ደግሞ የእኛ አምላክ ይሆናል። ክርስቶስ በእኛ ላይ ያለ ብቻ አይደለም። እኛም ሁላችን በክርስቶስ አንድ ነን። ክርስቶስ ሁሉን ክርስቲያን
አንድ የሚያደርግ ነውና በክርስቶስ አንድ ሆነን እንገኝ በማለት ስለ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሰጥቷል።
2. ስለ ምዕመናን አንድነት
ቅዱስ አግናጥዮስ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል። የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ጌታችን መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ጋር ያለውን አንድነት እንዲሁም የክርስቶስ ፍፁም አምላክ እና ፍፁም ሰው መሆንን ማለትም መለኮት ከሥጋ
ጋር ካለው ተዋሕዶ ጋር በማነጻጸር ግሩም በሆነ ምስጢር እና አገላለጽ አስቀምጦታል። በዚህም አገላለጹ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን
ያደንቁታል። እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አንድነት መምህር ይሉታል። በመልእክቱ ውስጥ በመጀመሪያ የአንድ አገር ቤተ ክርስቲያን
/ምዕመናን/ የምትደዳደረው በአንድ ጳጳስ ነው። እርሱም በማኅበረ ካህናት እና በዲያቆናት አጋዥነት ደጋፊነት ነው ይላል። በየጊዜው
ያለማቋረጥ የሚናገረው ቤተ ክርስቲያን ከመከፋፈል እንድትድን ለቤተ ክርስቲያን አባቶች ታዘዙ ይላል።
ለቅዱስ ፖሊካርፐስ በላከው መለእክቱ እንዲህ ይላል። “ለአንድነት ትኩረት ስጥ ከዚህ የሚበልጥ ምንም ነገር የለምና።
እግዚአብሔር አንተን እንደያዘህ ሁሉንም በደንብ ያዛቸው፤ አንተን እንደደገፈህ ሁሉንም በፍቅር ደግፋቸው፤ በሕይወትህ እንደ ፍጹም
ሯጭ ሁን፤ ሥራውና ድካሙ ብዙ ነው፤ ነገር ግን የሚገኘው የበለጠ ነው።” በማለት ለምዕመናን አንድነት እንዲተጋ ጭምር መልእክት
አስተላልፎለታል።
3. ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ
ቅዱስ አግናጥዮስ እንደ ሐዋርያት ጌታችንን በዓይኑ ያየና በእጁ የዳሰሰ ቃሉንም የሰማ ስለነበር ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ
የሚያስተምረው ትምህርት ልብን በሚነካ እጅግ በሚደንቁና በሚጣፍጡ ቃላት ነበር። የአምላክን ሰው መሆን የሚክዱ በሰሞርኔስ
ተነስተው የነበሩ ዶሴቲስቶች ወንጌልን ከግሪክ ባህልና ፍልስፍና ጋር በመቀላቀል ስህተትን በቤተ ክርስቲያን ላይ ለመንዛት የሚሞክሩ
መናፍቃን በመሆናቸው። “ሥጋ መጥፎ ነው፤ ይህ ዓለም ክፉ በመሆኑ እግዚአብሔር ከሚዳሰስና ግዙፍ ቁስ አካላዊ ከሆነው ዓለም ጋር
ቀጥታ ግንኙነትና ውሕደት ማድረግ አይቻልም“ በማለት ምስጢረ ሥጋዌን ይቃወሙ ነበር። እንዲሁም ክርስቶስ ሰው የሆነ መስሎ ታየ
እንጂ እውነተኛ ሰው አይደለም፤ በእውነት ሰው አልሆነም ይላሉ።
በዚህ ጉደይ ላይ የቅዱስ አግናጥዮስ ትምህርት እጅግ ጥልቅና መሰረታዊ ነው። በእንደዚህ ዓይነት አስተያየት ላይ ማተኮር
የሚፈልገው ስለ ሁለት ነገር ነው። እነርሱም፦
1) የክርስቶስ አምላክነት
2) ክርስትና የተመሠረተው በክርስቶስ ፍጹም ሰው መሆን፣ በሕማሙ፣ በሞቱ፣ በትንሳኤው መሆኑን ነው።
እንዲሁም አምላክነቱን በመካድ ክርስቶስን የሰቀሉት አይድ ግዝረትና ቀዳሚት ሰንበትን መከበር አለበት እያሉ ይበጠብጡ ስለነበት
በክርስቶስ አምነው ክርስቲያን ለሆኑት መገረዝም አለመገረዝም እንደማይጠቅም ይገልጻል።
 የሰው ልጆች ድኅነት የተፈጸመው በአምላክ ፍጹም ሰው መሆን በመሰቀሉና በመነሣቱ የተፈጸመ ነው።
 እርሱ ጊዜ የሚባል ነገር ከመኖሩና በመጀመሪያ ከመፈጠሩ በፊት እምቅድመ ዓለም ከአባቱ የተቀለደ እግዚአብሔር ቃል ነው። ለዘላለም
ያለመለወጥ በቃልነቱ ጸንቶ ይኖራል።
 እግዚአብሔር ቃልም በእውነት የእኛን ባህርይ ገንዘቡ በማድረግ ከድንግል ማርያም ተወልዷል። ሰዎችን ሁሉ የሚቀርፀው እርሱ በማኅፀን
ውስጥ ተፀነሰ፤ ለራሱም ከድንግል ሰውነት ያለ ዘርዓ ብእሲ የሚዋሐደውን ሰውነት ፈጠረ።
 ስነዚህ ሦስት ታላላቅ ምስጢራት ከዚህ ዓለም ገዢ ተሰውረዋል።
1. የድንግል ማርያም ድንግልና
2. የአካላዊ ቃል ከእርሷ መወለድ
3. የጌታችን መወለድ
እነዚህ ነገሮች በእግዚአብሔር ዘንድ በዝምታ የተፈጸሙ ነገሮች ናቸው። ለእኛ ግን ተገለጡልን። እነዚህ በጣም ጥቂት በዚህ ትምህርት
የተገገለጹ ናቸው እንጂ ቅዱስ አግናጥዮስ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብዝቶ ሰብኳል። ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ
አግናጥዮስ ተመልከት።

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 12
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ህዳር 2ኛ ሳምንት
ቅዱስ በርናባስ ዘቆጵሮስ
የቅዱስ በርናባስ - ዜና ሕይወቱ
ቅዱስ በርናባስ የተወለደው በቆጵሮስ ደሴት
በሶለሚስ ከተማ ሲሆን የቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ አጎት እንደሆነ
በቤተ ክርስቲያን ትውፊት ይነገራል። በቆጵሮስ በ60 ዓ.ም
ከጌታችን ልደት በፊት ተማርከው የገቡ አይሁድ ነበሩ። የቅዱሱ
ትውልደ ነገዱ ከሌዋውያን ነው። ትምህርትም ይከታተል ዘንድ
ቤተሰቦቹ ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት። በዚያም የገማልያል ተማሪ
በመሆን ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር በአንድ የትምህርት ገበታ
ተምረዋል።
በኢየሩሳሌም እያለ ወደ እኅቱ ወደ ማርያም ወደ
ማርቆስ እናት ቤት ሲሔድ የጌታችንን ትምህርትና ተአምራት
የመስማትና የማየት ዕድል አግኝቷል። በይሁዳ ምትክ
የሐዋርያነትን ክብር ለማግኘት ከታጩት መካከል ዮሴፍ
የተባለው እርሱ መሆኑን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገልጧል።
ቁጥሩ ከ72ቱ አርድዕት ሲሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን
የሚጠጉ ድኾች ስለበዙ መሬቱን ሽጦ ዋጋውን ለሐዋርያት
አስረክቧል። ሐዋ 14፥9 ቅዱስ ጳውሎስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ
ሐዋርያት ሲመጣ ቀድሞ ያውቀው ስለነበር የመሰከረለት እርሱ
ነው። በቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት ምክንያት ክርስቲያኖች በየሀገሩ ሲበተኑ አስቀድሞ ፊልጶስ ወንጌላዊ ይሰብክበት ወደ ነበረ
የአንጾኪያ ከተማ ሔዷል። በዚያን ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ በቆጵሮስ ከተማ ያስተምር ነበር። በአንጾኪያ የነበረችው ቤተ ክርስቲያን
ክርስትናን ተቀብለው የሚመጡ አረማውያንና አይሁድ እየበዙ በመምጣታቸው በርናባስ ጳውሎስን ወደ አንጾኪያ አመጣው።
በቅዱስ ማርቆስ የተነሣ እስኪለያዩ ድረስ አብረው ነበሩ።
ከቅዱስ ጳውሎስ ተለይቶ ቅዱስ ማርቆስን በመያዝ ወደ ኢየሩሳሌም ከመጣ በኋላ አስቀድሞ ወደ ሮም በኋላም ወደ
እስክንድርያ ከዚያም ወደ ይሁዳ በመምጣት ተዘዋውሮ ወንጌል ከሰበከ በኋል በመጨራሻም ወደ ሀገሩ ገብቷል።
በቆጵሮስ በነበረችው ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጵጵስናን መሥርቶ የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ በመሆን አረማውያንን
እያጠመቀ ወንጌልን በማስተማር ላይ እያለ ከሶርያ የፈለሱ አይሁድ ወደ ቆጵሮስ መጡ። እነዚህ አይሁድ በምኩራባቸው
ሲያስተምር አይተው እጅግ ስለተበሳጩ ብዙ ካሰቃዩት በኋላ በ61 ዓ.ም አካባቢ በድንጋይ ወግረው ገደሉት።
የቅዱስ በርናባስ ትምህርት
ቅዱስ በርናባስ በሕይወተ ሥጋው ብዙ አገልግሏል አስተምሯልም። በጣም ከሚታወቀው መልእክቱ ‘The Epistele of
Barnabas’ የሚለው ሲሆን ይኽም በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ላይ ያተኮረ ነበር።
1. ክርስቲያኖች ከአይሁድ በዓላትና አጽዋማት እንዲታቀቡ።
2. የእግዚአብሔር እውነተኛ (ፍጻሜ) ቃል ኪዳን ለእስራኤል ዘሥጋ ሳይሆን ለእስራኤል ዘነፍስ (ክርስቲያኖች)
እንደሆነ ለማመልከት።
3. ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለሙ ጌታ እንደሆነ የነቢያት ትንቢት በእርሱ ላይ እንደተፈጸመ ለመግለጽ እና
4. እግዚአብሔር ከሰዎች የሚሻው ከኃጢያት የራቀ የተሰበረ ልብ መሆኑን ለመግለጽ ነው።

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 13
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

የመልእክቱ ይዘት
መልእክቱ በአጠቃላይ 21 ምዕራፎች ያሉትና በሁለት ክፍል የተከፈለ ነው።
1. የመጀመሪያው ክፍል፦ ከምዕራፍ 1 – 17 ሲሆን
 ትምህርቱ ሃይማኖታዊ ጠባይ ሲኖረው እውቀታችሁ በእምነታችሁ ፍጹም ሊሆን ይገባዋል በማለት ይህ እውቀት
የተለየ መንፈሳዊ እውቀት ነው እያለ ስለ ብሉይ ኪዳን ትንቢት ስለ አይሁድ የመሲሁን አለመቀበል፣ የግዝረትን
በጥምቀት መተካት እና አማናዊው በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመሆኑ ገልጿል።
2. ሁለተኛው ክፍል፦ ከምዕራፍ 18 – 21 ሲሆን
 ስለ ግብረ ገብና አድልዖ አግባብ እንዳልሆነ አስረግጦ ጽፏል።
 በአጠቃላይ የመልእክቱ (የጽሑፉ) አገላለጽ ልክ እንደ ዲድስቅልያ መጽሐፍ ሁለት መንገዶች አሉ። እነርሱም
የሕይወትና የሞት መንገድ በማለት
1. የሕይወት መንገድ - ብርሃን ነው።
2. የሞት መንገድ - ሞት ነው። እያለ ገልጿል።

ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ከብርሃን መንገድ ብሎ ከገለጻቸው


ማንኛውም ሰው ወደ ታሰበው የክርስትና ዓላማ የሚወስደውን መንገድ ለመከተል ከፈለገ በመልካም ሥራ ሁሉ
ጠንካራ ይሁን። በዚሁም የክርስትና መንገድ እንድንራመድበት የተሰጠን እውቀት የሚከተለው ነው።
 ፈጣሪህን አክብር፤ የፈጠረህን ፍራ፤ አንተን ከሞት ያዳነህን አመስግን
 ምስጋና ለራስህ አታድርግ፤ ነገር ግን በማንኛውም ነገር ቅን ሁን
 ቅዱስ (ንጹሐ) መንፈስ በሌለበት ሰውነትህ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ መነገር የለበትም
 የሰማኸውን የእግዚአብሔርን ቃል ፍራ
 የጌታችንን ስም አላስፈላጊ ቦታ አትጠቀም
 ከነፍስህ በላይ ወንድምህን ጎረቤትህን ውደድ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 14
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ህዳር 3ኛ ሳምንት
ቅዱስ ቀሌሜንጦስ ዘሮም
የቅዱስ ቀሌሜንጦስ ዘሮም - ዜና ሕይወቱ
በጥንታዊቱ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያትን አህለው
ሐዋርያትን መስለው ከተነሡና እጅግ ከሚታወቁት ሐዋርያነ
አበው መካከል፥ የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር
የነበረው ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም አንዱ ነው፡፡ ስለዚሁ ቅዱስ
ሰው ብዙ ዓይነት አመለካከት ያለ ሲኾን፥ አውሳብዮስ ዘቂሳርያ፣
አባ ጀሮም እና ሌሎች አርጌንስን ተከትለው የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ
መዝሙር እንደ ነበረ ያስተምራሉ /ፊልጵ.4፥3/፡፡ “የንጉሥ
ድምጥያኖስ የአጎት ልጅ ነው” የሚሉም ያሉ ሲኾን፣ ሌሎች ደግሞ
“እጅግ ጥበበኛና የተማረ ሰው የነበረና በኋላም ዕውቀትን ፍለጋ
ወደ ፍልስጥኤም ሲሔድ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ተገናኝቶ ክርስቲያን
ኾኗል” ይላሉ /አባ ቴዎድሮስ ያ.ማላቲ፣ ሐዋርያነ አበው፣ ገጽ
64/በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ሊቃውንት የሚታመነውና ሕዳር 29
የሚነበበው ስንክሳር እንደሚነግረን ደግሞ፥ ቀሌሜንጦስ
የተወለደው ሮም ውስጥ ነው። ያደገውም በሮምና አካባቢ ነው።
የቀሌሜንጦስ አባት ቀውስጦስ ከቀደምት ሮማውያን ነገሥታት
ወገን ነው። በውትድርና ተቀጥሮም ለሮም ንጉሥ ያገለግል ነበር።
በዚህ ሥራ ላይ እያለ ቀውስጦስ ከነቤተሰቡ በቅዱስ ጴጥሮስ
ትምህርት ከአረማዊነት ወደ ክርስትና ተመልሷል። ወደ
ክርስትናም በተመለሰም ጊዜ ሀብት ንብረቱን ለቤተ ክርስቲያን
በማስረከብ የጽድቅ ሐዋርያ ሆኗል።ቀሌሜንጦስ ከዚህ ደገኛ ሰው ነው የተገኘው። ቅድመ ክርስትና ከዮናናውያን
(ከግሪካውያን) የሥነፍጥረት የምርመራ ተቋም በመግባት የፍልስፍናን ትምህርት በመማሩ በሮማውያን ዘንድ የተከበረ ሰው
ነው። ይህን የፍልስፍና ትምህርቱን በከፍተኛ ደረጃ ለማራቀቅና ለማምጠቅ ወደ ጥንት ትምህርት ቤቱ ወደ አቴንስ በመርከብ
ሲጓዝ ማዕበል አቅጣጫውን አስለቅቆ ከእስክንድርያ ወደብ አደረሠው። በዚያም ሳለ ቅዱስ ጴጥሮስ በእግዚአብሔር ፈቃድ
ከሮም ወደ እስክንድርያ መጥቶ አስተማረው። ከፍልስፍናም ወደ አማናዊ ትምህርት ወደ ወንጌል መለሰው።ከዚህ ጊዜ ጀምሮ
ቅዱስ ቀሌሜንጦስ የአጋንንት ተጻራሪ የአረማውያን አስተማሪ የወንጌል አስከባሪ የቤተ ክርስቲያን ተጠሪ በመሆን በአምባገነኖች
መናኽሪያም በሮም ከሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ቀጥሎ ጵጵስና ተሹሟል።ቀሌሜንጦስ እንደ አባቶቹ ሐዋርያት የመዳን
ትምህርት ወንጌልን ለወገኖቹ ለአረማውያን በማስተማር ከሰይጣን ቁራኝነት አላቅቋቸዋል።ለአረማውያን ቤተ ክርስቲያንን
ሳያስደፍር ወንጌላዊ ሥራውን በማፋጠን ላይ እንዳለ ጠራብሎስ የተባለ መሪ ለጣዖት እንዲሰግድ ፈጣሪው ክርስቶስን
እንዲክድ ባስገደደው ጊዜ “ፈጣሪዬ ክርስቶስን አልክድም ለጣዖት አልሰግድም” ብሎታል። ጠራብሎስም ከቀሌሜንጦስ ይህን
መልስ በሰማ ጊዜ በሮም አደባባይ ቀሌሜንጦስን ለመግደል ወሰነ። ነገር ግን የምዕመናንን ተቃውሞ ስለፈራ በስውር ወደ ሌላ
ሀገር አስወስዶ በዚያ እንዲገደል አሰበ። ካለበትም ቦታ በስውር በወታደር አሳፍኖ በመርከብ ተጭኖ በባህር ላይ ወደ
የሚገደልበት ሲጓዝ ህዳር 29 ቀን ከተሳፈረበት መርከብ ወደ ባህር ጥለው ገድለውታል።ምዕመናንም የቀሌሜንጦስን አስክሬን
ሲፈልጉ ከውኃ ውስጥ በአውሬ ሳይበላ አግኝተውታል። በተአምር ውኃው ተከፍሎላቸው የቀሌሜንጦስን አስክሬን በሣጥን
አድርገው ከባህር ውስጥ እናወጣለን ቢሉ የማይወጣላቸው ሆኗል። በዚህ ምክንያት በዓመት በዓመት ባሕሩ እየተከፈለላቸው
ከባሕሩ ውስጥ በመግባት ያረፈበትን ዕለት የሚያከብሩ ሆነዋል።ምዕመናን ይህን የቀሌሜንጦስን እረፍት አክብረው ሲሔዱ
አንድ ልጅ በወላጆቹ ተረስቶ ከባሕሩ ውስጥ ቀረ። በዚያም በባህር አውሬ ሳይበላው በተአምር የሚበላውን የሚጠጣውን
ቀሌሜንጦስ እያቀረበለት ያን እየተመገበ ለብዙ ወራት ኖሯል። በዓመቱ ወላጆቹ በዓሉን ለማክበር ከምዕመናን ጋር በመጡ
ጊዜ በተአምር ባሕሩ ሲከፈት ከዚያ አግኝተውታል። ይኽም እግዚአብሔር በቅዱሳኑ አድሮ የሚሰራው ድንቅ ተአምር ነው።

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 15
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ይኸውም በዐፅመ ኤልሳዕ እንዳደረገው ነው። 2ኛ ነገ 13፥40ቀሌሜንጦስ በሕይወተ ሥጋ ሳለ አንድ የሥነ ፍጥረት ታሪክ
መግለጫና የቤተ ክርስቲያን ቀኖናዊ መመሪያ መንፈሳዊ መጻሕፍት አዘጋጅቷል። ይኽንንም መጽሐፍ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን በክብር ተቀብላ ትጠቀምበታለች።ይኽ የእግዚአብሔር ሐዋርያ በግፍ ያረፈበትን ዕለት በሁሉም ዓለም
(በምድርም በሰማይም) ያለች እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያንም ምን ጊዜም ስታዘክር ትኖራለች።

የቅዱስ ቀሌሜንጦስ ትምህርት


ቅዱሱ ለቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በቃል አስተምሮ ከገለፃቸው በተጨማሪ በመጽሐፍ ጥሎልን ያለፈው
ትምህርትም ይገኛል። እነዚህ በግልፅ ከሚታወቁት መጻሕፍቶች መካከል
1. የሥነ ፍጥረት መግለጫ
2. ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን
3. ለወንዶችና ለሴቶች ደናግላን
4. የሥርዓት መጽሐፍ የሆነው መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዋንኞቹ ናቸው።
1. የሥነ ፍጥረት መግለጫ

እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት በቅድምና የነበረ ዘላለማዊ፣ ውሳጤ አፍኣ የሌለው፣ ዐይን ማየት በማይችለው
ብርሃን ውስጥ የሚኖር፣ ስብሐቲሁ ዘእምኀቤሁ - ምስጋናው ከባሕርዩ የኾነ፣ ፍጥረታትን በሙሉ የፈጠረ እንደ ኾነ
በመናገር ይጀምራል:: በዕለተ እሑድ ሰማይና ምድር፣ መላእክትም አሥር ወገን ኾነው እንደ ተፈጠሩ፤ ከኹሉም መላእክት
በማዕርግ የሚበልጠው የሳጥናኤል ወገን እንደ ነበረ፣ በዕለተ ሰኑይ እግዚአብሔር በምድር ባሉ ውኆችና በሰማይ ባሉ
ውኆች መካከል ልዩነትን (ጠፈርን) እንዳደረገ፣ በዕለተ ሠሉስ ከሰማይ በታች ያሉ ውኆች በአንድ ቦታ እንዲሰበሰቡ
እንዳዘዘ እና የብሱም እንደ ታየ፣ አዝዕርትንም ዛፎችንም እንደ ፈጠረ፣ በዕለተ ረቡዕ ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት እንደ
ተፈጠሩ፣ በዕለተ ሐሙስ ውኆች የዓሣዎችን ዓይነት ያወጡ ዘንድ እንደ ታዘዙ፣ በነፋስ የሚበሩትንም አስደናቂ ትላልቅ
አንበሪዎችንም እንደ ፈጠረ፣ በዕለተ ዓርብ ከምድር አራዊትን እንስሳትን እንደ ፈጠረ፣ በመጨረሻም ከአራቱ ባሕርያት
ትንሽ ትንሽ ወስዶ ሰውን በአርአያውና በምሳሌው እንደ ፈጠረ ሔዋንንም ከአዳም ከጎኑ ዐፅም እንዳስገኛት ይናገራል::
እግዚአብሔር አዳምን (ሰውን) በማይነገር ክብር እንደ ፈጠረው፤ የመለኮት ብርሃን በአዳም ፊት ያበራ እንደ ነበር፣ የፊቱ
ብርሃን ከፀሐይ የሚበልጥ ሰውነቱ እንደ ንጋት ኮከብ የሚያበራ እንደ ነበር፣ እግዚአብሔር ለአዳም የምስጋና አክሊል፣
ልብሰ መንግሥት፣ የግርማ ከፍተኛነት እንዳለበሰው፣ የመንግሥትን አክሊል እንዳቀዳጀው ንጉሥነትንና ነቢይነትን
እንደሰጠው፣ … መላእክት በታላቅ ግርማ እና ምስጋና ባዩት ጊዜ እንደ ፈሩት፤ አራዊት እንስሳት አዕዋፍ እግዚአብሔር
የፈጠራቸው ፍጥረታት ኹሉ ተሰብስበው ለአዳም እንደ ሰገዱለት … ሰይጣን የአዳምን ጸጋና ክብር አይቶ እንደ ቀና
የሚያስትበትንም ምክንያት ይፈልግ እንደ ነበር ይናገራል /ምዕ.1፥14-49/:

2 ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን
o ይህ መጽሐፍ በቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም እንደ ተጻፈ የሚታመንና በሌሎች አኀት አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም በካቶሊክ
ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነው፡፡ ከላይ ካየነውና የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ከምትቀበለው መጽሐፍም የተለየ ነው፡፡
መጽሐፉ 65 ምዕራፍ ያለው ሲኾን፡- ምእመናን መጽሐፍ ቅዱስን ኹልጊዜ ማንበብ እንደሚገባቸው፣ ኔሮን ቄሳር ስላደረሰው
ስደት፣ መሠረታዊ ስለሚባሉት የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች (ስለ ቅድስት ሥላሴ፣ ስለ እምነትና ምግባር፣…)፣ በጥንታዊቱ
ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቅዳሴ ምን ይመስል እንደ ነበር፣ ፌኖሽያ ከተባለች ወፍ ጋር በማያያዝ ስለ ትንሣኤ ሙታን መኖር
እንዲሁም ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያስተምራል፡፡
 በ96 ዓ.ም በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ባሉት ካህናትና ምዕመናን መካከል በተነሣው አለመግባባትና መከፋፈል - መለያየት
እንደሚጎዳቸው በተጫማሪም ስለ ማዕረገ ክህነት እና የመታዘዝ ሕይወት በሮም ቤተ ክርስቲያን ስም ጽፎላቸዋል።
 ለቆሮንቶስ የተላከው መልእክት በ65 ምዕራፍ የተከፈለ ሲሆን ይዘቱም፦
ሀ ከምዕራፍ 1 – 3 መቅድም
ለ ከምዕራፍ 4 – 36 የመልእክቱ ዋና ክፍል ሲሆን

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 16
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ሐ ከምዕራፍ 37 – 61 የመልእክቱ ዋና ክፍል ሲሆን


መ ከምዕራፍ 62 – 65 የመልእክቱ ዋና ማጠቃለያ ነው።
3 ለወንዶችና ለሴቶች ደናግል
ሀ መቅድሙ
 የቆሮንቶስ ምዕመናን ወደ ክፍፍል መንፈስ ከመግባታቸው በፊት የነበራቸው ፍቅር፣ ሰላማዊ ኑሮ፣ ለመልካም ነገር ያላቸውን
ትጋት፣ ብርታት .... ያትታል።
 ምዕራፍ ሦስት ላይ ሥጋዊ አስተሳሰብ በምዕመኑ ሕይወት እየገባ (ሲታይ) ቀስ በቀስ መንፈሳዊነትን እንደተው፣ የቀድሞ
ፍቅራቸውን እንደጣሉ፤ ምቀኝነት፣ ቅናትን እያጎለበቱ እንደመጡና ከብሉይ ኪዳን አንዳንድ ምሳሌዎችን በመግለፅ
እንዳስረዳቸው ይገልፃል።
 ከምዕራፍ 4 – 16 ቶሎ ብሎ የቆሮንቶስን ምዕመናን ንስሐ መግባት እንዳለባቸውና እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ያደረገውን መልካም
ነገር በስፋት ያሳያቸዋል። በእርስ በእርሳቸው መከፋፈልም እግዚአብሔር እንዳዘነ፤ የመታዘዝን ሕይወት ማሳየት እንዳለባቸው፤
መከፋፈል የቅናትና የምቀኝነት ውጤት እንደሆነ፤ ትህትናን ማዘውተር እንደሚገባቸው፤ ቆሮንቶስ ሳትውል ሳታድር ሰላምን
መከተልና አንድነትን ማጠንከር እንዳለባት ይናገራል።
 በተጨማሪም ስለ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ስለ ትምህርተ ሃይማኖት በስፋት ጽፎላቸዋል። በተለይም በዚሁ መልእክት ላይ
የጸለየው ሕያው ጸሎት ቤተ ክርስቲያን የምትረሳው አይደለም።

ለቆሮንቶስ በጻፈው መልእክት ውስጥ ያለ ሕያው ጸሎት


 የፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ የሆነ ስምህን ተስፋ እናደርጋለን። የልቦናችንን ዓይኖች ከፍተሃልና አንተ ብቻ የልዑላን
ልዑል የቅዱሳን ቅዱስ መሆንህን አውቀናል። አንተ የትዕቢተኞችን ኩራት ታዋርዳለህ፤ የመንግስታትንም እቅድ
በሕግህ ታደርጋለህ፤ የተዋረደውን ከፍ ትዕቢተኛውን ዝቅ ታደርጋለህ። ባለፀጋም ደሃም ታደርጋለህ፤ ትገድላለህ
ታድናለህም። የነፍሳት መጋቢና የሥራ ሁሉ ጌታ አንተ ነህ። እስከ ጥልቅ ታያለህ፤ ወደ ሰዎች ሥራም ትመለከታለህ።
በአደጋ ያሉትን ታድናለህ፤ ተስፋ ላጡት ተስፋ ትሆናለህ። የነፍሳት ሁሉ ፈጣሪና ጠባቂ አንተ ነህ። በምድር ላይ
ሕዝቡን ያበዛህ በተወደደው ልጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አንተን የሚወዱህን የመረጥህ አንተ ነህ። በልጅኽ
እኛን አስተማርኸን። ቅዱሳን አደረግኸን አከበርኸንም። ጌታ ሆይ አንተ የእኛ ረዳትና ጠባቂ ትሆን ዘንድ
እንለምንሃለን። ከእኛ ወገን በጭንቅ ያሉትን የወደቁትን አንሳ፤ ችግረኛውን እርዳ። የታመመውን ፈውስ፤ የጠፉትን
ወገኖችህን መልስ፤ የተራበውን መግብ፤ ምርኮኞቹን ፍታቸው፤ የደከመውን አበርታ፤ ልብ ያጡትን አስተዋይ አድርግ
አንተ ብቻ አምላክ እንደሆንክ ልጅህ ኢየሱስ ክርስቶስም የአንተ የባህርይ ልጅ እደሆነና እኛም የአንተ ሕዝብ
የመሰማሪያ ቦታህ በጎች እንደሆንን የሰው ዘር ሁሉ ይወቅ።አባት ሆይ በሠራኸው ሥራ ዓለማትን ለዘላለማዊ ፍቅርህ
አመጣህ ምድርን ፈጠርህ

ህዳር 4ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ወሰነ ትምህርት አጋማሽ ፈተና

ታህሳስ 1ኛ ሳምንት
4 መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ
ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም፥ ከመምህሩ ከቅዱስ ጴጥሮስ እየጠየቀ ብዙ ምሥጢራትን የተረዳ ሲኾን ይህንንም ጽፎ
አስቀምጦልናል - መጽሐፈ ቀሌምንጦስ የሚባል ይህ ነው:: በስሙ የተሰየመለት ይህ መጽሐፍ ይዘቱ ምን እንደሚመስል ከዚህ
ቀጥለን በአጭሩ እንመለከታለን::መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ቤተ ክርስቲያናችን ከምትቀበላቸው 81 (ሰማንያ አሐዱ) ቅዱሳት
መጻሕፍት ቍጥር ሲኾን ከስምንቱ የሥርዐት መጻሕፍት መደብ ነው:: 11 ምዕራፍም አለው፡፡ ቅዱስ ቀሌምንጦስ መጽሐፉን
ለመጻፍ ምክንያት የኾነው ነገር እንዲህ በማለት ያስቀምጣል፡- “የኦሪትና የነቢያት ዕውቀት ስላልነበረኝ አይሁድ ስለ አዳም
አፈጣጠር እና ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም በጠየቁኝ ጊዜ መልስ መስጠት አልቻልኩም፤ [የጌታችንን መምጣት ለማስታበል፣
ትንቢቱ አልተፈጸመም ለማለት እመቤታችንን ከይሁዳ ወገን አይደለችም እያሉ ይከራከሩት ነበር]:: በዚህ ጊዜ መምህሬ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 17
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ጴጥሮስን ኹሉንም ያስረዳኝ ዘንድ ጠየቅሁት፤ እርሱም አዘነ፤ በቅንአትም ኾኖ በቅድሚያ ስለ ዓለም አፈጣጠር ቀጥሎም ስለ
ቅድስት ድንግል ማርያም ከይሁዳ ወገን እንደ ኾነች እነግርሃለሁ አለኝ …” /ምዕራፍ 1፥11-13/፡፡ በዚህ ዓይነት ቀሌምንጦስ
እየጠየቀ ቅዱስ ጴጥሮስ እየመለሰ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ እስከ ዳግም ምጽአት ያለውን ምሥጢር ነግሮታል::

የመጽሐፉ አከፋፈል
 ምዕራፍ -1 አዳም መውደቅ
 ምዕራፍ -2 የአዳም የትእዛዝ መጽሐፍ
 ምዕራፍ -3 ዝርወት /መበተን
 ምዕራፍ -4 የአብርሃምና የልጅቱ ሂደት
 ምዕራፍ -5 ጴጥሮስ ለተማሪው ለቀለሌሜንጦስ ብዙ ምስጢራተ እግዚአብሔርን እንደገለፀለት።
 ምዕራፍ -6 የጴጥሮስ ስለ መላእክት ነገድ፣ ስለ ገነትና ስለ ሌሎችም ምስጢራት ከጌታችን መረዳት
 ምዕራፍ -7 ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ለጴጥሮስ፣ ከጴጥሮስ ለቀሌሜንጦስ የተነገረ መልእክተ ምስጢሮች
 ምዕራፍ -8 ከሊቀ ሐዋርያት ከጴጥሮስ የተሰጠ ትምህርት
 ምዕራፍ -9 ከጴጥሮስ ለውሉደ ክርስትና የተሰጠ ተግሳፅና ምክር
 ምዕራፍ -10 ስለ ጌታችን ሰው መሆን ስለ አዳም ምጽአት ስለ ሌሎችም የቤተ ክርስቲያናት ሥርዓቶች
 ምዕራፍ -11 ስለ ካህናት ክህነት

ጠቅለል ያለ የምዕራፎቹ ማብራሪያ


ሀ/የአዳም ውድቀት
በዚህ ክፍል ሰይጣን በአርዌ ምድር ተሰውሮ ሔዋንን ዕፀ በለስ ጣፋጭ እንደ ኾነች የአምላክነትንም ክብር
እንደምታሰጥ ዋሽቶ እንዳሳታት፣ አዳምም ሔዋንም አምላክ ሊኾኑ ዕፀ በለስን እንደ በሉ፤ ያደረባቸው ክብር እንደ ተገፈፈ
ከጸጋ እንደ ተራቆቱ ከገነት እንደ ወጡ … :: መፍቀሬ ሰብእ - ሰውን ወዳጅ የኾነው እግዚአብሔር ግን በውድቀታቸው ስንኳ
ፍቅሩን እንዳልቀነሰባቸው ይልቁንም እንደ ጎበኛቸው እንዳፅናናቸው ይተርካል:: ኪዳነ አዳም በመባል የሚታወቀው አባቶቻችን
በስብከት አብዝተው የሚጠቅሱት፣ የኪዳናት ኹሉ ቁንጮ: መጀመሪያ: መነሻ የኾነው ቃል ኪዳን የሚገኘው በዚሁ በመጽሐፈ
ቀሌምንጦስ ነው:: እግዚአብሔር ለአዳም እንዲህ ሲል ቃል የገባለት: “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ
አድንሃለሁ::” እግዚአብሔር ለአዳም ዐፅሙን ለልጅ ልጅ እንደሚያስጠብቅለት: ዐፅሙም በተቀመጠበት ቦታ መድኃኒትን
እንደሚያደርግለት /በዚያ እንደሚሰቀል/ እንደ ነገረው፤ አዳምና ሔዋን ከገነት ከወጡ በኋላ ከገነት በታች ባለ ተራራ በደብር
ቅዱስ መኖር እንደ ጀመሩ፤ አዳም ለሔዋን “በመካከላችን ምስክር ይኹን: አምኃነቱም ወልደ እግዚአብሔር ወደዚህ ዓለም
ሲመጣ ይኾናል” በማለት ወርቅ ዕጣን ከርቤ እንደ ሰጣትና ልጆችም እንደ ወለዱ፤ ቃየል የእናት አባቱን ምክር ባለመስማት
መልከ ጥፉይቱን የአቤልን መንትያ አላገባም እንዳለ፣ በቅንአት ተነሳስቶ አቤልን እንደገደለው ተቅበዝባዥም እንደ ኾነ
ይጠቅሳል:: አዳም የዕረፍቱ ጊዜ ሲደርስ ልጆቹን የልጅ ልጆቹን ሰብሰቦ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንዲጠብቁ፣ ከቃየል ልጆች
እንዲርቁ፣ ዐፅሙንና አምኃውን እንዲጠበቁ እንዳዘዛቸው፤ በተለይም ለልጁ ለሴት ብዙ ትእዛዛትን: ትንቢታትን እንደ ነገረው፤
ጌታ ከድንግል ማርያም እንደሚወለድ: እንደ ሰው እንደሚመላለስ: ሕሙማንን እንደሚፈውስ: እንደሚሰቀል: አዳምንና ዘሮቹን
እንደሚያድን፣ ስለ ቃየል ልጆች ኀጢአት ማየ አይህ - የጥፋት ውሃ እንደሚመጣ እንደ ነገረው፤ ከዚህ በኋላ ከቃየል ልጆች
በስተቀር ኹሉም በሴት መሪነት ትእዛዘ አዳምን በመጠበቅ በንጽህና በቅድስና በደብር ቅዱስ እንደ ኖሩ [ደቂቀ ሴት የሚባሉ፣
ከንጽህናቸውም የተነሣ የመላእክት ልጆች የሚባሉ እነዚህ ናቸው]፤ የቃየል ልጆች ግን ከደብር ቅዱስ በታች በኀጢአት እንደ
ኖሩ፤ ከአዳም በኋላ ሴትን ጨምሮ የተለያዩ አበው ደቂቀ ሴትን እየመሩ ሲሞቱም ሕዝቡን ትእዛዘ አዳምን እንዲጠብቁ፣
ከቃየል ልጆች እንዲርቁ በደመ አቤል እያስማሉ እንዳለፉ፤ ከአዳም ተቀብሎ ሴት: ከእርሱም በኋላ ሄኖስ: ቃይናን: መላልኤል:
ያሬድ በየተራ ሕዝቡን እንደ መሩ፤ በያሬድ ጊዜ ከደቂቀ ሴት የአባቶቻቸውን ትእዛዝ የማይጠብቁ ሰዎች ተነሥተው አንድ
አንድ እያሉ ከደብር ቅዱስ እየወረዱ ከቃየል ልጆች እንደ ተጨመሩ፤ በመብል በመጠጥ በዘፈን በዝሙት እንደ ረከሱ፤ ሄኖክ
ሲሰወር ከሦስቱ አበው (ማቱሳላ: ላሜህ: ኖኅ) በስተቀር ኹሉም ወደ ደቂቀ ቃየል እንደ ወረዱ ይናገራል::

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 18
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ከማቱሳላ እና ከላሜህ በኋላ ኖኅ የቀሩትን ደቂቀ ሴት እንደ መራቸው፤ እግዚአብሔርም ለኖኅ ማየ አይህ
እንደሚመጣ ገለጠለትና መርከብ እንዲሠራ እንዳዘዘው፤ መርከቡንም ከታች ደቂቀ ቃየል ካሉበት ወርዶ ኹሉም እያዩት: ስለ
መርከቡ ለሚጠይቁት ስለ ማየ አይህ መምጣት እየነገረ እንዲሠራ እንዳዘዘው፤ ከዚህ በኋላ ኖኅ እና ልጆቹ የደብር ቅዱስን
ድንጋዮቿን እንጨቶቿን በሐዘን እየሳሙ፣ ቀደምት አበውን እየተማጸኑ ዐፅመ አዳምንና አምኃውን ይዘው ከደብር ቅዱስ እንደ
ወረዱ፤ ኖኅም መርከቡን ሠርቶ ሲጨርስ ማየ አይህ ጀመረ፤ ደቂቀ ሴት ቢፀፀቱም የሚረዳቸው እንዳላገኙ፤ እግዚአብሔር
በነቢዩ ዳዊት ስለ ደቂቀ ሴት በተናገረበት ትንቢቱ:- “አንሰ እቤ አማልክት አንትሙ ወደቂቀ ልዑል ኩልክሙ አንትሙሰ ከመ
ሰብእ ትመውቱ ወከመ አሐዱ እመላእክት ትወድቁ - እኔ ግን አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁአልሁ፤እናንተ
ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ” እንዳላቸው ያስተምራል /መዝ.81(2):6-7/፡፡ ቅዱስ
ቀሌምንጦስ መርከብ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ እንደ ኾነች፣ ኖኅ ከመርከብ ወጥቶ ወይን ጠጥቶ ሰክሮ ተኝቶ ሳለ የሳቀበት ካምን
ተነሥቶ እንደረገመ - ክርስቶስ 3 ቀን 3 ሌሊት በንዋመ መቃብር ቆይቶ ከትንሣኤ በኋላ ሰይጣንንና ሰቃልያንን የመርገሙ
ምሳሌ መኾኑን ተርጉሞ አስቀምጧል:: ከኖኅ በኋላ ሴም በመልአከ እግዚአብሔር መሪነት ዐፅመ አዳምን ወደ ማእከለ ምድር
ጎልጎታ በስውር ወስዶ መልከ ጼዴቅን በዚያው ትቶ አስጠብቆታል::
ከዚህ በኋላ የኖኅ ልጆች ዝርዎት /መበተን/ እንደ ኾነ: አምልኮ ጣዖት: መተት ሟርት እንደ ተጀመረ ይገልጻል::
አብርሃም በ75 ዓመቱ ወደ ከነዓን ምድር እንደ ተጠራ: ይስሐቅን አዳም በተፈጠረበት ኋላም በተቀበረበት በደብረ ማኖስ
ሊሠዋው እንደ ወሰደው: ይኼውም ክርስቶስ የተሰቀለበት ቦታ እንደ ኾነ፣ በዚህም አብርሃም አምሳለ ስቅለትን እንዳየ፤ ጌታም
“አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ወደደ አየም ደስም አለው” ያለው (ዮሐ.8፥56) ይህንን እንደ ኾነ ይጠቅሳል:: ሌላም ስለ አብርሃም
እና ስለ ልጆቹ ሒደት ይተርካል፤ በተለይም እያንዳንዱን ታሪክ ለነገረ ሥጋዌ /ለክርስቶስ ሰው መኾን/ ትንቢት እንደ ኾነ
ይተረጉማል:: ለምሳሌ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያየው ምሥጢር አምሳለ ስቅለት እንደ ኾነ፣ ዐዘቅተ ያዕቆብ የቅድስት ጥምቀት
አምሳል እንደ ኾነ፣ ልያ እና ራሔል የቤተ እስራኤል እና የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ እንደ ኾኑ. . . እንዲሁም ስለ ያዕቆብ ልጆች:
ስለ ሙሴ: ስለ ኢያሱ: ስለ መሳፍንት: ስለ ዳዊት: ስለ ሰሎሞን: ስለ መንግሥት ለኹለት መከፈል ይተርካል

ለ/ ጴጥሮስ ለቀሌምንጦስ ሌሎች ብዙ ምሥጢራትን እንደ ገለጠለት


ጌታ ለጴጥሮስ የገለጠለትን እርሱም በተራው ለቀሌምንጦስ እንደ ገለጠለት፤ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ - ሥላሴ ከኹሉ
በላይ እንደ ኾኑና ፈጣሬ ፍጥረታት እንደ ኾኑ፤ ጌታ ለጴጥሮስ እንዲህ እንዳለው:- “ኹሉን ችዬ የምኖር ቦታ እኔ ነኝ: በምስጋና
መንበሬ ላይ ነበርኩ: በጸጋዬ ሀብት ነበርኩ፡ አብ በእኔ ዘንድ አለ: በእኔም ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አለ: በእኛ ዘንድ መቅደምና
ወደ ኋላ ማለት የለም: ከመካከላችንም ፊተኛና ኋለኛ ተብሎ የሚነገርለት የለም: መጀመሪያና መጨረሻም የለንም:: የእኛ ህላዌ
የእኛ መገኘት በኹሉ ዘንድ ነው: የኀይላችንም ታላቅነት በኹሉ ይገኛል: እኛ የፈጠርነው ኹሉ ከእኛ በታች ኾኖ ይኖራል:
ርዝመታችንና ስፋታችን በሰው አእምሮ አይገመትም: ኹሉን እንችላለን ኹሉ ግን ማንነታችንን ሊረዳ አይችልም: እኛ ከኹሉ
በላይ ነንና የኀይላችንም ታላቅነት ኹሉን ይዟልና:: ግራና ቀኝ የለንም: ውስጥና ውጭም በእኛ ዘንድ የለም: ውስጥ እኛ ነን
ውጭ እኛ ነን: ምስጋናችንና የጸጋችን ሀብት ከእኛ ዘንድ ነው: ከባዕድ የሚያስፈልገን ነገር ፈፅሞ የለም: አብ እውነተኛና
ትክክለኛ ነው እኔም ይቅርታና ምሕረት ነኝ መንፈስ ቅዱስ ኀይልና ጥበብ ነው:: እኛን መሸከም የሚቻለው ሰማይ የለም
ምድርም የለም: ከግብር ወደ ግብር መለዋወጥ በእኛ ዘንድ የለም: ከቦታ ወደ ቦታም አንመላለስም: የሰው ዐይን እኛን አያይም:
ሰውም በመራቀቅና በመመራመር እኛን ሊያውቅ አይችልም:: በእኛ ዘንድ ጭማሪም ኾነ ሕፀፅ የለም: አብ አእምሮ ነው እኔም
ሥምረት ነኝ መንፈስ ቅዱስም ኀይል ነው: እኛ ብዙዎች አይደለንም: አንለያይም: ልዩነት አያገኘንም: ጥፋትም አያገኘንም: አብ
በእኔ ኹሉን ፈጠረ በመንፈስ ቅዱስም ተፈፀመ:: አብ ነቢብ ነው እኔም ቃል ነኝ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ሕይወት ነው:
የሚመሳሰለን የለም እኛ ከመመሳሰል በላይ ነንና: እንደኛ የሚኾን የለም እኛ ከኹሉ በላይ ነንና: አባቴ እሳት ነው ብርሃኑም
እኔ ነኝ ሙቀቱም መንፈስ ቅዱስ ነው: አባቴ ውኃ ነው እኔም ጣዕሙ ነኝ መንፈስ ቅዱስም ሕይወት ነው: አባቴ ክብር ነው
እኔም ክብር ነኝ መንፈስ ቅዱስም ጸጋ ነው: ከእኛ ውጪ ፍጥረት የለም: ሰማያት ሳይፈጠሩ እኔ ከአብ ጋር ነበርኩ: አባቴ ግርማ
ነው እኔ ደግሞ ጸጋ ነኝ መንፈስ ቅዱስ ፍፃሜ ነው:: እኔ በአብ አለሁ: መንፈስ ቅዱስ በአብና በእኔ አለ: አባቴ ጥበብ ነው እኔም
ቃል ነኝ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የቃል ድምፅ ነው: በጥበባችን ኹሉን የፈጠርን እኛ ነን: ቀዳሚዎችም እኛ ነን: መጀመሪያና
መጨረሻም የለንም:: ዘመናችን በፍጡራን ዘንድ አይታወቅም: ከዘመንና ከአዝማን በፊት እኛ ነን: ከእኛ ዘንድ የሚቀርብ የለም:
የሰው ሕሊናና የመላእክት አእምሮ ሊደርስብን አይችልም: እኛ ከሕሊናት ኹሉ በላይ ነንና: ምስጋናችንም ከራሳችን ነው:: እኛ
መጀመሪያና መጨረሻ የለንም: ከፍቅራችን ብዛት የተነሳ ዓለምን እንፈጥር ዘንድ ወደድን …” /ምዕ.6፥13-18/፤ ሌሎችም ብዙ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 19
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ምሥጢራት እንደ ገለጠለት - ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ: ስለ ዳግም ምጽአት: ስለ ሐሳዊ መሲሕ: ስለ ነገደ መላእክት: ስለ ገነት:
ስለ ቤተ ክርስቲያን ምንነት …
ሐ/ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
ጳጳሳት ካህናትና ምእመናን እንዴት መመላለስ እንደሚገባቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ትእዛዝ፤ አዘውትሮ ወደ ቤተ ክርስቲያን መገስገስ እንዲገባ:
በትጋት ስለ መጸለይ: ስለ ንጽህና. . . በተለይ ጥንቆላንና ሟርትን: አምልኮ ጣዖትን: ስካርና ዝሙትን አጥብቆ ያወግዛል - እነዚህን
የሚያደርግ ተወግዞ ከቤተ ክርስቲያን መለየት እንዲገባው፣ ካህናትን ያቃለለ ኩነኔ እንዲገባው፣ ካህናት ሳያፍሩና ሳይፈሩ በድፍረት
ማስተማርና መገሠጽ እንዲገባቸው. . .

ታህሳስ 2ኛ ሳምንት

ቅዱስ ፖሊካርፐስ
ቅዱስ ፖሊካርፐስ - ዜና ሕይወቱ
ፖሊካርፐስ የተወለደው በ64 ዓ.ም አካባቢ
በሰርሜኔስ ከተማ ነው። ይህች ከተማ በታናሿ እስያ ይገኙ
ከነበሩትና ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ መልእክት ከላከላቸው ሰባቱ
ጥንታውያን ከተሞች አንዷ ስትሆን የታላቁ የግሪክ ባለ ቅኔ
የሆሜር የተውልድ ሥፍራ ናት።
ፖሊካርፐስን ያሳደገችው ካሊቶስ የተባለች ደግና
ሃይማኖተኛ ሴት ናት። አስቀድማ የክርስትና ትምህርት
ያስተማረችው እርሷ ስትሆን። በኋላም የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ
መዝሙር የነበረው የሰርሜኔሱ ሊቀ ጳጳስ ቡኩሎስ ነገረ
ሃይማኖትን ከልጅነቱ ጀምሮ በሚገባ አስተምሮታል። ዲቁናንም
የሾመው እርሱ ነው።
ቡኩሎስ ሲያርፍ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ
ፖሊካርፐስን በሰርሜኔስ መንበር ሊቀ ጳጳስ አድርጎ ሾመው።
በራእይ ዮሐንስ ምዕራፍ ሁለት “ለሰርሜኔሱ መልአክ” ተብሎ
የተጻፈው ፖሊካርፐስ መሆኑን የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት
ይተረጉማሉ። “መልአክ” ማለት አለቃ ማለት ይሆናል።
ሐዋርያው ፖሊካርፐስ በመንበሩ እንደተቀመጠ
የቅድሚያ ተግባሩ ያደረገው በበዓለ ትንሳኤ አከባበር ላይ በአካባቢው ክርስቲያኖች ዘንድ ለተነሳው ጥያቄ መልስ መስጠት
ነበር። በምዕራብና በምሥራቅ በሚኖሩ ክርስቲያኖች መካከል። “ትንሣኤ መቼ ይከበር?” በሚለው ጥያቄ ዙሪያ በዘመኑ ክርክር
ነበር። ቅዱስ ፖሊካርፐስም ወደ ሮም ሄዶ ከሮም ሊቀ ጳጳስ አነቅሊጦስና ከሌሎች አስር ሊቀ ጳጳሳት ጋር ጉባኤ በማድረግ
“የትንሣኤ (የፋሲካ) በዓል አይሑድ ፋሲካቸውን በሚያከብሩበት እለት መከበር የለበትም። የብሉይ ኪዳኑ የፋሲካ በዓል
ለሐዲስ ኪዳን ጥላ በመሆኑ ክርስቲያኖች ታላቁን የትንሣኤ በዓል ከአይሑድ ፋሲካ በኋላ በሚገኘው እሑድ እንዲያከብሩት
ወስነዋል። ይህ ውሳኔ በ325 ዓ.ም በጉባኤ ኒቂያ 318ቱ አበው ስለ ትንሣኤ በዓል ለደነገጉት ቀኖና መሠረት ነበር።
ቅዱስ ፖሊካርፐስ በሮም በነበረበት ጊዜ ግኖስቲኮች የክህደት ትምህርታቸውን እየነዙት ስለነበር በተዘዋወረበት ቦታ
ሁሉ ለኑፋኤ ትምህርታቸው መልስ ይሰጥ ነበር። እንዲያውም አንድ ቀን ከግኖስቲኮቹ ቀንደኛ መሪ ከመርቅያን ጋር መንገድ
ላይ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ፖሊካርፐስ መርቅያንን ትኩር ብሎ በመመልከት ሰላምታ እንኳን ሳይሰጠው ፊት ለፊት ይቃወመው

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 20
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ጀመር። መርቅያንም ኮራ ብሎ “ፖሊካርፐስ ታውቀኛለህን?” ሲል ጠየቀው። አባታችንም “አዎ አውቅሃለሁ አንተ የዲያቢሎስ
የበኩር ልጅ ነህ” ሲል እንደመለሰለት ይነገራል።
ፖሊካርፐስ አባቶቹ ካስተማሩት ትምህርት የወጣ የኑፋቄ ትምህርት ሲሰማ “ወደ እግዚአብሔር እንዴት ላለው ዘመን
አቆየኸኝ? እንዲህ ያለውንም አሳዛኝ ነገር ጆሮዎቼ ለመስማት በቁ!” እያለ ያለቅስ ነበር። የመንፈስ ቅዱስ ልጆቹንም “ልጆቼ
እባካችሁ ከስህተት ራቁ፤” እያለ ይመክር ነበር። አንድ ቀን በኤፌሶን ጎዳና ሲጓዝ ቀሪንጦስ የተባለው መናፍቅ ከፊት ለፊቱ
ስለመጣ ይከተሉት ለነበሩት ደቀ መዛሙርቱ “ልጆቼ እባካችሁ ከዚህ ቦታ እንራቅ የእውነት ጠላቷ ቀሪንጦስ ወደ እኛ የመጣ
ነውና” በማለት መንገዱን ትቶ በሌላ መንገድ ሄዷል።
አባታችን ፖሊካርፐስ በዘመኑ ከነበሩት መናፍቃን ከግኖስቲኮች ጋር ስለ እውነተኛዋ ሃይማኖት እየተጋደለ ባለበት
ጊዜ አንጦኒነስና ቬራስ የተባሉ የሮማ መንግስት ባለሥልጣናት በክርስቲያኖች ላይ የመከራ ዶፍ ማውረድ ጀመሩ። መከራውም
በሰርሞኔስ ከተማ እጅግ የባሰ ሆነ።
በዚህ ዘመን በሮማ ግዛት ረሃብ ተነሥቶ ስለነበር የሮማ የጣዖት ካህናት “ይህ መዓት የመጣው ክርስቲያኖች
አማልእክቶቻችንን ስላስቆጧቸው ነው በማለት አመካኙ። በዚህ የተነሣ ክርስቲያኖች ተሰደዱ፤ ለአናብስት ተሰጡ፤ ሰም
ተቀብተው በእሳት በየመንገዱ ነደዱ።
ሮማውያን “ከሃዲዎች ይጥፉ” የሚል መፈክር አንግበው በክርስቲያኖች ላይ ዘመቱ። አባታችን ፖሊካርፐስ ከሮም
የተመለሰው በዚህ የመከራ ጊዜ ነበር። በክርስቲያኖች ልጆች ጉትጎታ የሰርሜኔስን ከተማ ለቅቆ በአቅራቢያው ወደ ነበረው
መንደር በመሰደድ ቀንና ሌሊት በጾምና በጸሎት መትጋቱን ተያያዘው።
በሮማውያን ወታደሮች ከመያዙ ሦስት ቀናት አስቀድሞ በጸሎት ላይ እያለ በተመስጦ ትራሱ በእሳት ሲያያዝ
ተመለከተ። ከተመሰጠበት ሲመለስም በአጠገቡ ለነበሩት ደቀ መዛሙርት በእቶን እሳት ተጥለው እንደሚሞቱ ነገራቸው።
በማለዳም ወታደሮቹም መንደሯን ከበቧት። ፖሊካርፐስ አስቀድሞ በመንፈስ ተረድቶ ከተኛበት ሠገነት በመውረድ ወጣ።
በፍጹም ትህትና መንፈሳዊ ሰላምታ ከሰጣቸው በኋላ ቁርስ ይመገቡ ዘንድ ወደ ቤቱ ጋበዛቸው። የትሕትናው ሥራ
ያስገረማቸው ወታደሮቹም ወደ ቤት ገብተው የቀረበላቸውን ማዕድ መመገብ እንደጀመሩ “ለጥቂት ጊዜ ታገሱኝ” ብሎ ወደ
ሠገነቱ ወጣና ለሁለት ሰዓት ያህል ጸለየ። ጸሎቱን እንደፈጸመ ወታደሮቹ በአህያ ላይ አስቀምጠው ወደ ሰርሜኔስ ወሰዱት።
በመንገድ የከተማዋን የፀጥታ ኃላፊዎች ሄሮድስንና አባቱን ኒቄጦስን አገኟቸው። ሄሮድስ ፖሊካርፐስን ቢጠላውም ለማባበል
ያመቸው ዘንድ በሠረገላው አስቀምጦ “አሁን ቄሳርን ጌታዬ አምላኬ ነው ብትል ምን ችግር ያመጣብሃል?” እያለ ያባብለው
ጀመር። ፖሊካርፐስ ግን ምንም ነገር አልመለሰለትም። የሄሮድስ ንግግር ስለበዛበትም እንዲህ ያለውን ልመና በጭራሽ
ሊቀበለው እንደማይችል ቁርጥ አቋሙን ገለጠለት። በዚህ ጊዜም እየሰደቡና እየዘለፉ በዱላም እየቀጠቀጡ ከሰረገላው ላይ
አውርደው በጎዳና ላይ ጎተቱት። የሰርሞኔስ ጣዖት አምላኪው ሕዝብም በመያዙ ተደስቶ ዙሪያውን በጩኸት አደባለቀው።
በዚያን እለት በጨለማ እስር ቤት አደረ። በዚያ የጨለማ እስር ቤት ሌሊቱን በጨለማ አሳለፈው። ጠዋት የአካባቢው
ሕዝብ በአደባባይ ተሰበሰበ። ወታደሮቹም ፖሊካርፐስን ወደ ሕዝቡ አወጡት። ሮማዊው ሹምም “ፖሊካርፐስ ማለት አንተ
ነህ?” አለና ጠየቀው። ከዚያም “ተመልከት” አለው። “በዚህ ታላቅ እድሜ ከምናዋርድህ በእውነተኛው ቄሳር ማልና ለሰራኸው
ስሕተት ተጸጽተህ ይቅርታ ጠይቅ፤ ከእኛም ጋር እርኩሳን (ክርስቲያኖች) ይጥፉ ብለህ አውጅ” አለው። በአደባባይ የተሰበሰበው
ሕዝብ “ልክ ነው” እያለ ተንጫጫ። በዚህ ጊዜ ፖሊካርፐስ በእጁ ምልክት ስለሰጣቸው የሚንጫጩት ኹሉ ፀጥ አሉ።
አንገቱንም ወደ ሰማይ ቀጥ አድርጎ “አቤቱ በአንተ ላይ የተነሱትን እርኩሳኑን አጥፋ” ሲል ጸለየ። እነማንን እንደሚል ያልገባቸው
ሹማምንት ያሰቡት የተሳካ መስሏቸው ሊፈቱት ወደዱና “በል በዚያ በክርስቶስ ላይ ክፉ ነገር ተናገር” አሉት። “ጌታዬን ለሰማንያ
ስድስት ዓመታት አገልግየዋለሁ። እስካሁንም በሰላም ጠብቆኛል። ታዲያ በዚህች ሰዓት እንዴት አድርጌ ንጉሤንና መድኃኒቴን
ልስደበው” ሲል መለሰላቸው። ሹማምንቱ ተስፋ ሳይቆርጡ በቄሳርም እንዲያስተምር ጠየቁት። እርሱም “በቄሳር ስም
እንዳስተምር ምንም ያኽል ፍላጎት ቢኖራችሁ እኔ ግን አላደርገውም። እውነቱን ልንገራችሁ እኔስ ክርስቲያን ነኝ። ይልቅ
የክርስትናን እምነት ለመማር የተዘጋጀ ልብ ካላችሁ ጊዜ ስጡኝና ላስተምራችሁ” አላቸው።

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 21
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

የሰርሞኔሱ ሹም መከራከሩ እንዳላዋጣው ሲያውቅ “ለመመለስ ካልፈለግህ ለተራቡ አናብስት አሳልፌ እሰጥሃለሁ”
በማለት አስፈራራው። ፖሊካርፐስ ግን “እኛ የተሻለውን በክፉ አንለውጥም። ነገር ግን ክፉውን በመልካም እንለውጣለን
ስለዚህ ጥራቸው” አለው።
“ለአራዊት ምግብ መሆን ቀላል መስሎ ከታየህ በእሳት ማጋየትም እንደምችል አትርሳ” ሲል ሹሙ በንዴት ተቆጣ።
ፖሊካርፐስም “ወንድሜ ከአንድ ሰዓት በላይ መንደድ የማይችለው ምድራዊ እሳት ያስፈራኝ ይመስልሃልን? በሰማይ ለዘላለም
የማይጠፋ እሳት መኖሩን ምነው ባወቃችሁ። እኔ የምፈራው በመጨረሻው ቀን ተፈርዶብኝ ወደዚህ እሳት እንዳልገባ ብቻ
ነው” አለ
። በዚህ ጊዜ የተሰበሰበው ጣዖት አምላኪ ሕዝብ “መቃጠል አለበት፤ በሕይወቱ መንደድ አለበት!” እያሉ ከተማዋን
በጩኸት አናጋት። እርሱ ግን ወደ እግዚአብሔር እየጸለየ ነበር። ልክ ጸሎቱን እንደጨረሰ እንደ እቶን ይነድ ወደ ነበረው እሳት
ወረወሩት። በዚህ ጊዜ እድሜው 100 ዓመት ሆኖት ነበር።

ታህሳስ 3ኛ ሳምንት
ምዕራፍ ሦስት
ዘመነ ሊቃውንት
የቤተ ክርስቲያን ወርቃማ ዘመነ (300-450) የነበሩ ቅዱሳን አበው
ሕይወት እና ትምህርት
ሁለቱ የትርጓሜ ትምህርት ቤቶች
ቅዱሳት ሐዋርያት ከጌታ የተቀበሉት (የተማሩት) በሚገባ ለማስተላላፍ ከረዳቸው ነገር አንዱ ትምህርት ቤት
ማቋቋማቸው ነበር በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የሚታወቀው የመጀመሪያው ትምህርት ቤት በ80 ዓ.ም በቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ
የተመሰረተው የእስክንድርያ ትምህርት ቤት ነው የትምህርት ቤቱ ዓላማም አዳዲስ አማኞች በቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት
በማሰልጠንና ከዚያም ሲወጡ ወገኖቻቸውን ለማስተማር የሚያስችላቸውን እውቀት እንዲያውቁ ማድረግ ነው በ2ኛውና
በ3ኛው ክፍለ ዘመን ከመንፈሳዊ እውቀት ባሻገር ሁለገብ ዕውቀትና ፍልስፍናም ጭምር ይማሩ ነበር፡፡
ሁለተኛው ትምህርት ቤት በሶርያ ዋና ከተማ በነበረው በአንጸኪ ተመሠረተ፡፡ ይህን ትምህርት ቤት የመሠረተው ሉቂያኖስ
የተባለው ሰው ነው ትምህርት ቤቱም የተመሠረተው በ3ኛው ምዕተ ዓመት አጋማሽ ሲሆን በዚህ ትምህርት ቤት ብዙ ፈላስፎች
ገብተው ተምረዋል፡፡ በዚህ ጊዜ የፍልስፍናው አስተሳሰብ የክርስትናውን እምነትና ትምህርት በክሎታል፡፡ በዚህ ትምህርት
ቤት ፍልስፍና በጣም ነግሶ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
1. የእስክንድርያ የትርጓሜ ትምህርት ቤት

እስክንድርያ የተመሠረተችው በ311 ከጌታ ልደት በፊት በታላቁ እስክንድር ነው፡፡ እርሱ ከሞተ በኋላም ከ4ቱ
የእርሱ መኮንኖች አንዱ ግብጽን ሲገዛ እስክንድርያ ዋና ከተማው ነበረች፡፡ ከክርስቶስ መምጣት በኋላም ግብጽ በፋርሶች
ወይም በዓረቦች እስከወደቀችበት እስከ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ የታላቋ የሮም ግዛት ሁለተኛ ዋና ከተማ ሆና
ቆይታለች፡፡ በዚህ ከተማ ብዙ የግሪክ እና የግብጽ ፈላስፎችና የጥበብ ሰዎች ስለ ነበሩ ክርስቲያኖችም እምነታቸውን
ለማስተዋወቅና የጥበብ እና የፍልስፍና ሰዎችን ለመማረክ ሲሉ ትምህርት ቤቱን በእስክንድርያ በ60 ዓ.ም. በቅዱስ ማርቆስ
ተመሥርቷል፡፡
በእስክንድርያ የሚሠጠውም የትርጓሜ ትምህርትን ምሳሌን መተርጎምና መንፈሳዊ ትርጉም በመስጠት ‹‹ ንባብ
ይገድላል ትርጓሜ ግን ያድናል፡፡›› (2ኛ ቆሮ 3፡4) ላይ ባለው ቃለ እግዚአብሔር መሠረት ቅዱሳት መጻሕፍትን በአንድምታ
ትርጓሜ በመተርጎም ነው፡፡ ይህም ምስጢራቸውን እንጂ ንባባቸውን አይከተልም፡፡ ይህም ምስጢራዊ ትርጓሜ (Allegorical
interpretation) በመባል ይታወቃል፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 22
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

የትምህርት ቤቱ ዓላማ ከላይ እንደተገለጠው የፍልስፍናና የንባብ ሰዎችን ለመማረክ እና አዳዲስ አማኞችን
በቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት ለማሠልጠን እና ከዚያም ሲወጡ ወገኖቻቸውን ማስተማር የሚያስችል መንፈሳዊ እውቀት
እንዲገበዩበት ነው፡፡ በ2ኛው ና 3ኛው መቶ ክፍል ዘመን ይህ ትምህርት ቤት እየተስፋፋ ስለሔደ መንፈሳዊውን ብቻ ሳይሆን
ክርስቲያኖች ሁለገብ ሆነውን እውቀትና ፍልስፍና ጭምር ይማሩበት ነበር፡፡ ብዙ የፍልስፍና መምህራን ደቀ
መዛሙርቶቻቸውን እየያዙ ወደ እዚህ ትምህርት ቤት ገቡ የፍልስፍና አስተሳሰባቸውንም እየተው ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ በአንጻሩ
ደግሞ በፍልስፍናው ትምህርት ተጽዕኖ አንዳንድ ደቀመዛሙርት ኢ-ክርስቲያናዊ በሆነ ሥጋዊ አስተሳሰብ ተመርዘው
ጠፍተዋል፡፡

2. የአንጾኪያ የትርጓሜ ትምህርት ቤት

የአንጾኪያ ከተማ የተመሠረተችው በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከጌታ ልደት በፊት ገደማ ነው፡፡ ለሮማ መንገሥት
ሦስተኛው ዋና ከተማ ስትሆን በሶርያ ደግሞ የመናገሻ ከተማ ነበረች፡፡ በሐዲስ ኪዳን ታሪክ ውስጥ ከአህዛብነት ወደ ክርስትና
የተመለሱ የክርስቲያኖች ዝነኛ መናኸሪያ ስለ ነበረች ‹‹አርድዕት›› የሚለው ስያሜ ተለውጦ ለመጀመሪያ ጊዜ ‹‹ክርስቲያን››
የሚለውን ስያሜ ያገኙት በአንጾኪያ ከተማ ነው፡፡ (ሐዋ 11፡26)
አንጾኪያ ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ነዳያን ክርስቲኖች ምጽዋት የሚሰበሰቡበት ዋና መመላሻው
ነበረች፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስም በሰማዕትነት ሲያርፍ ክርስቲያኖች ወደ እዚች ከተማ ተሰደውባታል፡፡የአንጾኪያ ምእመናንም
ለመማር የብቁ የነቁ ፍላጎትም ያላቸው ስለነበሩ በዚህች ከተማ ይህ ትምህርት ቤት ሊመሠርት ችሏል፡፡
አንጾኪያ በግሪኮች በሮማውያን ስለተገዛች የነበራት የባሕልና ሥልጣኔ ሁለት መልክ ነበረው፡-
1ኛ አባሬዎች የሶሪያ ሴማዊ አስተሳሰብ
2ኛ የግሪካውያንና የሮማውያን ቅይጥ ወይም ውጥንቅጥ ባሕል ነበር፡፡
ከዚህም ጋር የሮማውያንና የግሪኮችን ፍልስፍና የሚያስተምሩ ጠበብተ ጽርዕ (የግሪክ ሊቃውንት) እና ጠበብተ
ሮም የሚኖሩባት ከተማ ስለ ነበረች በዚህ ምክንያት ክርስቲያኖች ቀስ በቀስ እያሉ ለአይሁድ መርገም ለአረማውያን ሞኝነት
ለእኛ ግን የእግዚአብሔር ኃይል የሆነውን የመስቀሉን ትርጕም የሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት በአንጾኪያ በ300 ዓ.ም.
ከፈቱ፡፡
የአንጾኪያ ትምህርት ቤት የሚሰጠው ትምህርት ቅዱሳት መጻሕፍትን በነጠላ ትርጓሜ (Literal interpretation)
ብቻ ያስተምር ነበር፡፡ ሆኖም ይህ አካሄድ አንዳንዶች ከመጠን በላይ ወደ ጽንፍ በመውሰዱ ወደ ስህተት መርቷቸዋል፡፡እነዚህ
ሁለት የቤተ ክርስቲያን የትርጓሜ ቤቶች በአተረጓጎም (መንፈሳዊ ትርጕም በመስጠት) ረገድ የተላያዩ ናቸው፡፡ ከዚህም የተነሣ
በሁለቱ ትርጓሜ ቤቶች የነበሩ ደቀ መዛሙርቶች እርስ በርሳቸው ይነቃቀፉ ነበር፡፡
እነዚህ ሁለት ትርጓሜ ቤቶች ለክርስትና መስፋፋት ትላቅ አስተዋጽዖ አበርክተዋል፡፡ ነገርግን አንዳንድ በእነዚህ የትርጓሜ
ትምህርት ቤቶች ያስተምሩ የነበሩ መምህራን ሆነ ተማሪዎቻቸው ከመንፈሳዊ አስተሳሰብ በመውጣት በሥጋዊ ፍልስፍናቸው
በመነዳታቸው ምክንያት ለተለያዩ ከባባድ የምንፍቅና ትምህርቶች ተዳርገዋል፡፡ ከሁለቱም ትምህርት ቤቶች የሚጠቀሱ
መናፍቃን ጥቂቶች
 ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ /Clement of Alexandria/
 አርጌንስ / Origen /
 ሰባልዮስ / Saballius /
 ጳውሎስ ሳምሳጢ / Paul of Samosata /
 ሉቂያኖስ //
 አርዮስ / Arius /
እነዚህ መናፍቃን ከሁለቱም የትርጓሜ ትምህርት ቤቶች በፍልስፍናው ዓለም ተመርተው ከቤተ ክርስቲያን መንጋ የጠፉ
መናፍቃን ናቸው፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 23
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ታህሳስ 3ኛ ሳምንት
ሉቂያኖስ እንደምን ያለ ሰው ነው?
ሉቂያኖስ በብዙ አባቶች እንደተነገረው የጳውሎስ ሳምሳጢ ደጋፊ ነው….. ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት
እለአስክንድሮስ የጳውሎስ ሳምሳጢ አልጋ ወራሽ ይለዋል፡፡ የቆጵሮሱ ሊቀጳጳስ ኤጲፋንዮስ ሉቅያኖስን ሲገልጣፀው ከአርዮስ
በፊት የነበረ አርዮስ ይለዋል፡፡ ሉቂያኖስ ግኖስቲክ ነው፡፡መዳን በዕውቀት ብቻ እንጂ በእምነት አይደለም የሚል ግኖስቲክ
ነበር፡፡ሉቂያኖስ በቅድምና የነበረው ቃል (ወልድ) የተካካለ፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት አንድ ሆነ፡፡ በሥልጣንም
የተካካለ መሆኑን አይቀበልም ነበር፡፡ ስለዚሕ እርሱ በመሰረተው የአንፆኪያ ትርጓሜ ወይም በዘመናችንን አነጋገር ስነ መለኮት
ትምሕርት ቤት /Theology College/ ገብተው ተምረው የሚወጡ ግለሰቦች በሙሉ:: በሉቂያኖስ መርዝ የተለከፉ እና
ትክክለኛውን የቤተክርስቲያን አስተምሕሮ ለመበረዝ ሆነ ተብለው ተፈልፍለው የሚወጡ በሀሰት ላይ የተመሰረቱ ነበሩ
በተቃራኒው ደግሞ የእስክንድርያው ትምሕርት ቤት፡፡ታላላቅ ሊቀጳጳሳትን ያፈራ፡፡ለቤተክርስቲያን የስነ መለኮት
ትምሕርት መሠረት የጣሉ ታላላቅ አባቶችን ያወጣ ወንበር ነው፡፡ታላላቅ መምሕራንን ያፈራ የትርጓሜ ቤት ነው

ታህሳስ 4ኛ ሳምንት

ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ


የቅዱስ ባስልዮስ ዜና ሕይወቱ

ቅዱስ ባስልዮስ በትንሹ ኢስያ ውስጥ በምትገኘው የአገረ


ቀጶዶቂያ ዋና ከተማ በሆነችው በቂሳሪያ በ329 ዓ.ም መገባደጃ ላይ
ከአባቱ ከኤስድሮስ እና ከእናቱ ከኤሚሊ(ያ) ተወለደ ፡፡ ይህ ቤተሰብ
በክርስትና ሕይወት የታነጸ በአገሩ ህዝብ ዘንድ በስነ ምግባሩ የተከበረ
ሲሆን በዓለማዊ ሀብቱ ረገድ ባለፀጋ ነበር ፡፡ቤተሰቡም በአስር ልጆች
በረከት የተጎበኘ ሲሆን አሰቀድሞ በሞት ከተለየው አንዱ በቀር
አምስቱ ሴቶች እና አራት ወንዶች ልጆች አድገው ለወግ ለማዕረግ
በቅተዋል፡፡ከእነዚህም መካከል የቤተሰቡ የበኩር ልጅ የሆነችው
ማክሪና ባስልዮስ (የቂሳሪያ ሊቀ ጳጳስ ) ጎርጎርዮስ (የኑሲስ ኤጲስ
ቆጶስ )እና ጴጥሮስ (የሰባቴ ኤጲስ ቆጶስ) እንደ ወላጆቻቸው እና ሴት
አያታቸው ቅድስት ማካሪና ሁሉ ለቅድስና ክብር ሲበቁ የተቀሩት
ልጆችም በተቀደስ ክርስቲያናዊ ጋብቻ በሕግ ሕይወት ተወስነው
ይኖሩ እንደነበር ወንድማቸው ጎርጎረርዮስ ዘኑሲስ መስክል፡፡
ታናሹ ጴጥሮስ ተወልዶ ብዙም ሳይቆይ ባስልዮስ
ሳይጎለምስ ወላጅ አባታቸው በ349 ዓ.ም ገደማ በማረፋቸው
ቤተሰቡ ቂሳሪያን በመልቀቅ ወ ደ ሴት ኤታቸው ቅድስት ማክሪና
ርስት ይገኝ ወደነበረት ወደ አገረ ፑንተስ ተዛወረ ፡፡ በዚያ ዘመን ይሰጥ
የነበረው ትምህርት የተሻለ ስለነበረ ባስልዮስ ከቤተሰቡ በመነጠል ከፑንተስ ወደ ቂሳሪያ እንዲመለስ ተደረገ ፡፡ባስልዮስም
አስቀድሞ በቂሳሪያ ቀጥሎም በቆስጠንጥንያ በዘመኑ ይሰጥ የነበረውን የሥነ ጽሑፍ እና የንግግር ዘዴ ትምህርትን በጥሩ
ውጤት ካጠናቀቀ በኃላ የበለጠ እውቀቱን እና ክህሎቱን ለማስፋፋት በመሻቱ በ352 ዓ.ም ወደ ግሪክ ተዘ ፡፡ አቴንስም
ሲደርስ አሰቀድሞ ያገኘው በቂሳሪያ የትምህርት ቤት ደኛው የነበረው ጎርጎርዮስን አገኘው፡፡ እንደ ባስልዮስ ሁሉ ጎርጎርዮስም
እውቀትን ለማስፋት በነበረው ታላቅ ጉጉት የተነሳ አቴንስ ጠደረሰው አስቀድሞ ነበር፡፡ ከዚያም አልፎ በዚያ ከተማ ይማሩ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 24
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

የነበሩት ተማሪዎች በእንግዳ ተማሪዎች ላይ ያሳዩት የነበረውን ማን ጠጥ እና አጉል ድርጊቶች ባስልዮስን እንዳይረብሹት
በዘህም ተነሳስቶ የጥላቻ ስሜት ልቦናው እንዳያድር በማድረግ በኩል ትልቅ ወንድማዊ ኃላፊነትን ተtውተጥል :::
የቅዱስ ባስልዮስ እና የቅዱስ ጎርጎርዮስ የአቴንሰ ሕይወት አጅግ አስደሳች ነበር ፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያቸው
ከምቀኝነት እና ከቅናት የራቀ አድናቆት እና መከባበር መንፈሰዊነት ታላቅ ስብዕና እራስ ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠት
የሚገኘውን ዠላለማዊ ሕይወት የሚሻእና የማያወላውል ጽኑ መሰረት ያለው ፍቅር ነበር ፡፡ወዳጅነታቸው ዘወትር
ሕይወታቸውን በጭምተኝነት በአስተውሎት በሎም እራስን በመግዛት ተግቶ በመጸለይ እንዲተጉ ያደረጋቸው ሲሆን በbዚህም
የመንፈስ ቅዱስ ጠላት የሆነውን ድል እንዳያደርጋቸው ጠብsቸወል ፡፡በዕለት ተዕለት ሕይወታቸውም አንዳቸው ላንዳቸው
የሚያደርጉት መረዳዳት ማጽጽናናት እና ማበረታታት ደስታን ይሰጣቸው የነበር ሲሆን የህም በእግዚአብሐሔር ለሆነ
የተቀደሰ የወዳጅነት መንፈስ እና ለሃይማኖጣቸው ጽናት በጣሙን ያገዛቸው ሲሆን ይኖሩ የነበሩባት በነበረባት ክፍል ውስጥ
የሚገኙት ቁሳቁሶች ሳይቀር ካለ እንከን በአነድነት ይገለገሉባቸው ነበር፡፡ ይህ በእውነተኛ ጽነዕ መሰረት ላይ የተገነባው
የመተሳሰብ ፍቅር በትንሹም በትልቁም አሊያም በጊዜያዊ ጥቅም እና ጉርምስ እና ስሜት ሳይተበተብ ሌላም ተጨማሪ አጉል
ባልደባረ በመሀል ሳይገባ እና ሳይለያያቸው እስከ እለተ ሞታቸው ዘልsል፡፡ን
ቅዱስ ባስልዮስ ከቂሳሪያ እስከ አቴንስ የነበረውን የዘመኑን ትምህርት ዓለማዊ ትምህርት በሰፊው ከቀሰመነ
ካጠናቀቀ በላ ይህውን ያካበተውን ጥልቅ እውቀትን ያካፈላቸው እና አብሮአቸውም ከእነርሱ ጋር በመሆን የጥበብ እና
የፍልስፍና ን ጉዳይ ይሠራ ዘንድ የሚፈልጉ በርካታ ተማሪዎች እና ሊቃውንት ነበሩ ፡፡ ስለዚህ በአቴንስ ከእነርሱ ዘንድ
እንዲቆይ ተማጸኑት ፡፡ነገር ግን ባስልዮስ በአቴንስ ከመቆየት ይልቅ ወደ ትውልድ አገሩ በመመለስ በአገሩ የሚገኙትን
ተማሪዎች ማስተማር ወገኑንም ማገልገል የውዴታ ግዴታው መሆኑን በማመኑ ጥያቄያቸውን አልተቀበለም ፡፡በውሰሳኔው
በመጽናት ወዳጁን ጎርጎርዮስን ተሰናብቶ በ355 ዓ.ም ከአቴንስ ወደ ቀሳሪያ ተመለሰ ፡፡በቂሳሪያም በወገኖቹ መካከል የሕግ እና
የንግግር ከህሎት ማጎልበቻ ትምህርት ቤት በግሉ በማssም የማስተማር ስራውን ጀመረ ሆኖም ዕለት ተዕለት በውስጡ
እያደገ የመጣው የውስጥ እርካታ ማጣት ግን በማስተማር ስራው እንገዲገፋበት አላደረገውም፡፡
አስቀድሞ እንደተጠቀሰው ሁሉ ቅዱስ ባስልዮስ ለቂሳሪያ እንግዳ አልነበረም ፡፡ይኽውም ቀድሞ ቤተሰቡ
በቂሳሪያ ይኖር በነበረበት ወቅት የነበረውን የቤተሰቡ ክብር አለመረሳቱ ባስልዮስም ቢሆን አገር አቋርጦ ወርዶ ወጥቶ ሄዶ
የቀሰመውን ትምህርት ለወገኖቹ ማሳወቅ ማካፈል አለብኝ ብሎ የመጣ ሊቅ በመሆኑ የሃገሮ ሰዎች በአክብሮት እና በአድናቆት
ከመቀበል አንስቶ በሌሎቹም ጉዳዮች ከጎኑ አልተለዩትም ነበር ፡፡ ሆኖም ዕለት ተእለት በሕሊናው ውስጥ ውስጡን እያደገ
የመጣውን የከንቱነት ስሜት ይህ መልካም ቀረቤታ እና ወዳጅነት ሊያሸንፈው አልቻለም ፡፡ስለዚህም ነፍሱ እየታወከችበት
ሄደች፡፡የዚህን ጊዜ ቆም ብሎ ሕይወቱን እና ልቡን መረመረ ፡፡ነፍሱ ዓለምን እና ጉዛንጉዟን ፈራችበት ፡፡ይህን ጊዜ ነው
የእውነተኛዋ ለእግዚአብሔር ነፍሷን የሰጠችው ቅን እኅቱ ማክሪና እና ወዳጇ ናዚአንዝን ከጎን በመገኘት ከገጠመው የመንፈስ
መረበሽ ይወጣ ዘንድ መፍትሔው ነፍሱን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚእብሔር በመስጠት እና በማስገዛት ብቻ እንዲሆን መከሩት ፡
፡ ምክርቸውንም ቸል ያላለው ባስልዮስ ትክክለኛውን የሕይወት ፍልስፍና የከተል ዘንድ ዓለምን መተው እንዳለበት አመነ
ለዚህም ቁርጥ ውሳኔ ወሰነ፡፡እንደ እኅቱ ወዳጁ ምክርም የሀብቱን አብላጫውን ክፍል ለድሆች ሽጦ ሰጠ ፡፡ልውጣ ልቅር
ሲል ከነበረበት የዓለም አዙሪት በመውጣት እውነተኛ የሆነው የመንግስተ ሰማያት የጥበብ ብርሃን ሊፈልግ ተነሳ ፡፡በዚህችም
ዓለም ያለውን የሰው ልጆች ጥበብ ባዶ እና ከንቱ መሆኑን በግልጽ ተረዳ ዓለምን ንቀው ንስሐ ገብተው የዘውትር ትጋት እና
ተጋድሎ በሚጠይቀው የምንኩስና ሕይወት ውስጥ የሚኖሩትን አባቶች እና እናቶች ከዋሉበት ውሎ ካደሩበት አድሮ
ሕይወታቸውን ይቀምሰው ያጣጥመው ዘንድ ናፈቀ፡፡ ለዚህም መንፈሳዊ ረሀቡ ማስታገሻ ይሆን ዘንድ እርሱ ከሚገኝባትሪ
ቂሳረያ በቅርብ እርቀት ላይ ከሚገኘው በግርማ ሞገሱ እና በምናኔ ሕይወቱ በዚያን ዘመን ይጠቀስ ከነበረው ከኤዎስጣጤዎስ
ዘሰባስቴ ዘንድ በአካል በመገኘት የምናኔ ሕይወት ለመጎብኘት ተነሳ፡፡
በዚያን ዘመን ኤዎስጣጤዎስ በሮማውያን አገዛዝ ሥር በነበሩት በአርሜንያ በፑንተስ እና በፓፍላጎኒያ ማኅበረ
መነኮሳት አsቁሞ ያስተዳድር ነበር፡፡መልካም የሆነውን ትምህርት ከኤዎስጣጢዮስ ከቀሰመ በኋላ ስለቀደመ ሕይወቱ የንስሐ
ጥምቀትን በመጠመቅ በሌሎች አገራት የሚገኙትን ክርስቲኖች በመጎብኘት ያላቸውን ምናኔ እና ገዳማዊ ሕይወት በጥልቀት
እና በተመስጦ ለማጥናት ስለወደደ በ357 ዓ.ም ወደ ፍልስጤም ግብጽ ሶርያ እና ሜሶፖታምያ ረዥም ጉዞን አደረገ፡፡በዚህም
ጉዞው በተለይ በምስራቃዊው እና በምዕራባዊው የግበጽ በረሃማ አካባቢዎች የሚገኙትን ብዛት ያላቸውነ ገዳማት እና
መናንያኑን ጎበኘ፡፡በጉብኝቱም የግብጻውያኑን መነኮሳት አኑኑር ለእግዚአብሔር ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር አክብሮት ታማኝነት
ስለ እምነታቸው ሰማዕት ለመሀን ያላቸውን ዝግጁነት እና ጠንካራ እመነት በተመለከተበት ወቅት በልቡ ውስጥ ጥልቅ የሆነ
የመንፈሳዊ ሕይወት በጣሙን ማረከው ፡፡ይኽንን ጉብኝቱን አጠናቆ ወደ አገሩ እንደተመለስ ሀብት ንብረቱን ለድሆች

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 25
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

አከፋፍሎ በመስጠት ለአጭር ግዜም ቢሆን በኒዖቂሳሪያ ፑንተስ በኢሪስ ወንዝ አቅራቢያ ከሚገኙት ቦታ ለብቻው በኣት ዘግቶ
ተቀመጠ ፡፡ላ ላይ እርሱን አርአያ ምሳሌ በማድረግ በዙሪያው የተሰበሰቡትን ብዛት የላቸው ምዕመናን አለበት ስፍራ ድረስ
እስከመጡት ጊዠተ ድረስ በፍጹም መነረፈሳዊ ተመስጥኦ በጸሎት እየተጋ በበኣቱ ውስጥ ቆየ ፡፡በ358 ዓ.ም ከቆየበት የብቸኝነት
ምናኔ ከወጣ በላ ወንድሙን ጴጥሮስ ጨምሮ ብዛት ያላቸውን ምዕመናን በመያዝ የቤተሰቡ ርስት ከሚገኝበት ከአርነስ
ፑንተስ ገዳም ገደመ ፡፡ለዚህም ተግበሩ ዋና አርአያው ግብጻዊው መነኩሴ አባ ጳኩሚስ ዘባድ ናቸው፡፡
የቅዱስ ባስልዮስ የጵጵስና ሕይወት
ቅዱስ ባስልዮስ ዓለመን ትቶ ሙሉ ልቡን ለእግዚአብሔር ከሰጠ በላ በ362 ዓ.ም ድቁናን ከአንጾኪያው ሊቀ
ጳጳስ ከሜሊተስ ቅስናን የቂሳሪያ ሊቀ ጳጳስ ከነበረው ከአውሳብዮስ ተቀበለ፡፡አንዳንዶች ስለ ቅዱስ ባስልዮስ ለስልጣነ ክህነት
መታጨት እና መቀሰስ ዋናው ምክንያት ባስልዮስ የነበረው ሃይማኖታዊ እውቀት እና የንግግር ክህሎቱን በመጠቀም በወቅቱ
በቆስጠንጥንያ ንጉሠ ነገሥት በዋለንስ አይዟቸሁ ባይነት የፈሉትን አርዮሳውያን ስለ ሐሰት ትምህርታቸው መልስ ይሰጣቸው
እና ይመክታቸው ዘንድ ስለታመነበት ነበር የመሉ አሉ፡፡ ይህም ተባለ ያ ይህ አባት ከወዳጁ ጎርጎርዮስ ዘእንዝናዙ ጋር በአንድነት
በንጉሡ ዋለን እንደራሴ ፊት በተደረጉ ተከታታይ የአደባባይ (የህዝብ ፊት) ክርክሮች አርዮሳውያኑን አፍ ከማስያዛቸው ባሻገር
መናፈቃኑ ከኑፋቄያቸው ጋር በተያዘ በቀጰዶቂያ ግዛት አንድነተ ላይ የጋረጡትን የመለያት ሥጋት ደመና ለመግፈፍ
በመቻላቸው ተውንከው

ጥር 1ኛ ሳምንት

ቅዱሰ ባስልዮስ ያደረጋቸው ተአምራት


1. ወንድሙ የስብስጥያ ኤጲስቆጶስ ከሚስቱ ጋር በድንግልና ሲኖር ሕዝቡ ግን ያሙት ነበርና ቅዱስ ባስልዮስ መላእክት
ሲጠብቋቸው እንደተመለከተ ለሕዝቡ ገልጦላቸው ሕዝቡ ከሐሜት ርቀው ንስሓ እንዲገቡ አድርጓቸዋል፡፡
2. ቅዱስ ኤፍሬምም ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ በተመለከተ ጊዜ ‹‹ይህ የቂሳርያው የባስልዮስ ነው›› የሚል
ቃልን ሰምቷል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ወደ ቂሳርያ ሄዶ ከቅዱስ ባስልዮስ ዘንድ ዲቁናና ቅስና ተቀብሏል፡፡ ቅዱስ ባልዩስም
በቅዱስ ኤፍሬም በላዩ ጸልዮለት የማያውቀውን አዲስ የዮናኒን ቋንቋን እንዲናገር አድርጎታል፡፡
3. ቅዱስ ባስልዮስ ሰው ሁሉ የሚያምንበትና በአቆጣጠሩም የሚታወቀውን ጠንቋይም በተአምሩ አሳምኖታል፡፡ ይኸውም ቅዱስ
ባስልዮስ በታመመ ጊዜ የሚሞትበትን ጊዜ ዐውቆ ይህን ጠንቋይ ጠርቶ ‹‹ንገረኝ እስቲ መቼ እሞታለሁ?›› አለው፡፡ ጠንቋዩም
‹‹ማታ ነፍስህ ከሥጋህ ትለያለች›› አለው፡፡ እርሱም ‹‹እስከ ጠዋት ካልሞትኩ ክርስቲያን ትሆናለህ?›› በማለት ቃል አስገባው፡
፡ ቅዱስ ባስልዮስም ወደ ጌታችን በመጸለይ በዕድሜው ላይ ሦስት ቀናት አስጨመረ፡፡ ያም ጠንቋይ ሥራው ከንቱ እንደሆነ
ታወቀበትና እርሱም አምኖ ከነቤተሰቦቹ ተጠምቆ ክርስቲያን ሆነ፡፡
4. ሌላው ተአምር ለቅዱስ ባስልዮስ እመቤታችን ስለ ሥዕሏ የነገረችው ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ባስልዮስ የእመቤታችንን ቤተ
ክርስቲያን ከሠራ በኋላ በውስጧ የሚያኖረውን የእመቤታችንን ሥዕል ሊያሠራ መሳያ ሠሌዳ ፈለገ፡፡ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ
ቤት ጥሩ ሠሌዳ እንዳለ ነገሩትና ሄዶ ባለጸጋውን ሠሌዳውን እንዲሰጠው ለመነው፡፡ ባለጸጋውም የልጆቼ ነው አልሰጥም
አለው፡፡ በትዕቢትም ሆኖ በታነጸቸው ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብን ነገር ተናገረ፡፡ ወዲያውም ወድቆ ክፉ አሟሟት ሞተና
ልጆቹ ፈርተው ሠሌዳውን አምጥተው ለባስልዮስ ሰጡት፡፡ እርሱም ያንን ሠሌዳ የእመቤታችንን ሥዕል አሳምሮ ይስልበት
ዘንድ ለሰዓሊ ወስዶ ሰጠው፡፡ በዚህም ጊዜ እመቤታችን በራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጠችለትና ከአመፀኛ ሰው የተገኘ ነውና
በዚያ ሰው ሠሌዳ ሥዕሏን እንዳያስል ከለከለችው፡፡ ሥዕሏ የተሳለበትን ሠሌዳም የት እንደሚገኝ ነገረችውና ሄዶ በታላቅ
ክብር አምጥቶ በቤተ ክርስቲያኑ አስቀመጠው፡፡ ከሥዕሉም ሥር ድውያንን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት መፍሰስ ጀመረ፡፡
በዚህም ብዙዎች ድንቅ የሆነ ፈውስን አገኙ፡፡ ይህም የተፈጸመው ሰኔ 21 ቀን ነው፡፡
5. ላም እንዲሁ ቅዱስ ባስልዮስ ያደረገው ተአምር የሰይጣንን የጽሕፈት ደብዳቤ በጸሎቱ የደመሰሰ መሆኑ ነው፡፡ አንድ ጎልማሳ
አገልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት ወደ አንድ ሥራይኛ ዘንድ ሄደ፡፡ ሥራይኛውም የክህደት ደብዳቤ ጽፎ ሰጠውና ወደ
አረሚ መቃብር ሄዶ በመንፈቀ ሌሊት ደብዳቤዋን ይዞ በመቃብሩ እንዲቆ ላይ አዘዘው፡፡ ወጣቱም እንደታዘዘው አደረገ፡፡
ከሰይጣናትም አንዱ መጥቶ ወደ ወደ አለቃቸው አደረሰው፡፡ ያችንም የክህደት ደብዳቤ ከእጁ ወሰዳት፡፡ ሰይጣንም
‹‹የፈለከውን አደርግልሃለሁ ነገር ግን አምላክህን ክርስቶስን ትክደዋለህ ፈቃድህን ከፈጸምኩልህ በኋላም ወደ እርሱ
አትምለስም›› ሲለው ወጣቱም በልጅቷ ፍቅር አብዶ ነበርና ‹‹አዎን ጌታዬ ያዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ›› አለው፡፡ ሰይጣኑም

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 26
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

‹‹ይህን ልታደርግ በእጅህ ጻፍልኝ›› አለውና አጻፈው፡፡ ከዚህም በኋላ ሰይጣን በጌታው ሴት ልጅ ልብ ውስጥ አደረና ያንን
ወጣት እጅግ ወደደችው፡፡ የፍትወት እሳትንም በልቧ ላይ ስላነደደባት መታገስ አልቻለችምና ወደ አባቷ ቀርባ ልጁን አጋባኝ
አለችው፡፡ የልጁም ፍቅር በየዕለቱ ይጨምርባት ነበርና ራሷን እንዳታጠፋ ቤተሰቦቿ አጋቧት፡፡ ከእርሱ ጋር መኖር ከጀመረች
በኋላ ሲያማትብ እንኳን አይታው አታውቅም ነበርና ስትመረምረው ክርስቲያን አለመሆኑንና ያደረገውንም ሁሉ ነገራት፡፡
ይህንንም ስትሰማ እጅግ ደንግጣ ወደ አገሯ ሊቀ ጳጳስ ወደ ባስልዮስ ዘንድ ሄዳ ከእግሩ ሥር በመውደቅ የደረሰባትን በመንገር
ከሰይጣን እጅ እንዲያድናት ለመነችው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም በሏ የሆነውን የአባቷን ባርያ አስመጣውና በንስሓ ተመልሶ
ክርስቲያን መሆን እንደሚፈልግ ጠየቀው፡፡ ወጣቱም ፈቃደኝነቱን ሲገልጥለት በአንድ ቦታ ውስጥ አስገብቶ ዘጋበትና ከላይ
በመስቀል ምልክት አተመበት፡፡ እንዲጸልይም አዘዘው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ስለ ወጣቱ ብዙ ጸለየ፡፡ ከሦስት ቀንም በኋላ
ጎበኘውና በ3ቱ ቀን የደሰበትን ጠየቀው፡፡ ወጣቱም በላዩ በመጮህ ሰይጣናት ሲያስፈራሩት ያንንም ደብዳቤ ሲያሳዩትና በእርሱ
ላይ ሲቆጡ በመከራ ውስጥ እንደኖረ ነገረው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ‹‹ከሰይጣናቱ ቁጣ የተነሣ አትፍራ አይዞህ እግዚአብሔር
ይረዳናል›› ብሎ ጥቂት ከመገበው በኋላ መልሶ ዘጋበትና ሄዶ ይጸልይለት ጀመር፡፡ ዳግመኛም ከ3 ቀን በኋላ መጥቶ ጠየቀው፡
፡ ወጣቱም ‹‹የአጋንንቱን ጩኸታቸውን እሰማዋለሁ ነገር ግን አላያቸውም›› አለው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ አሁንም ጥቂት ከመገበው
በኋላ መልሶ ዘጋበትና እስከ 40 ቀን ድረስ እንዲሁ አደረገ፡፡ ከ40 ቀንም በኋላ መልሶ ሲጠይቀው ወጣቱ ‹‹ቅዱስ አባቴ ሆይ
ስለ እኔ ሰይጣንን ስትጣላውና ድል አድርገህ ጥለህ ስትረግጠው በዛሬዋ ሌሊት አየሁ›› አለው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ይህን
ሲሰማ እጅግ ደስ አለው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችንም ጠርቶ እግዚኦታ አደረሱና ከእግዚኦታው በኋላ ያ ወጣት ጽፎ
ለሰይጣን የሰጠው የክህደት ደብዳቤ ከሰይጣን እጅ ተወስዶ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ወደቀ፡፡ ሁሉም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን
አመሰገኑት፡፡ ይኸውም የተደረገው መስከረም 13 ቀን ነው፡፡
6. አንዲት ሴት ኃጢአቷን ሁሉ በዝርዝር ጽፋ በክርስታስ አሽጋ እንዲጸልይላት ቅዱስ ባስልዮስን ለመነችው፡፡ እርሱም ከአንዲት
ኃጢአቷ በቀር ሁሉንም በጸሎቱ ደመሰሰላት፡፡ ስለ አንዲቱም ኃጢአቷ ወደ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲትሄድ አዘዛት፡፡ ቅዱስ
ኤፍሬምም ‹‹ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ሳይሞት ፈጥነሽ ተመለሽ የካህናት ሁሉ አለቃ ስለሆነ የቀረች ኃጢአትሽን የሚደመስስልሽ
እርሱ ነው›› ብሎ መለሳት፡፡ በተመለሰችም ጊዜ ቅዱስ ባስልዮስ ዐርፎ ሊቀብሩት ሲወስዱት አገኘችው፡፡ እርሷም መሪር ልቅሶን
ካለቀሰች በኋላ በእምነት ሆና ያንን ክርስታስ ከአስክሬኑ ላይ ጣለችው፡፡ ስለ እምነቷም ጽናት ያች የቀረች በደሏ

የቅዱስ ባስልዮስ ስራዎች እና ትምህርት


የቅዱስ ባስልዮስ ስራዎች
1. ዶግማ ሁሉም የዶግማ ስራዎቹ ያተኮሩት በዘመኑ ተነስተው ለነበረት መናፍቃን (አረዮሳውያን መቅዶኖሳውያን
አቡለኖሮሳውያን) መልስ ለመስጠት ነው፡፡
2. ትርጉሜ ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍላት መካከል የተረጎማቸው መጽሐፍት
 ኦሪት ዘፍጥረት
 መዝሙረ ዳዊት
 መኃለየ መኃልይ ዘሰለሞን
 ትንቢተ ኢሳይያስ
3. ስለ ምነና ስለ መናንያን ሕይወት በተመለከተ የጻፈው መመረያዎች
1 ማሕበረ መናንያን በተመለከተ
1 የምንኩስ ሕይወት የክርስቶስ ጃንደረበ መሆን ነው
 ስለ አስደሳች ገዳማዊ ሕይወት
 አስደሳቸ ስለመሆኑ
 የምንኩስና ጥቅም
የምንኩሰና ሕይወት የሥነ ምግበር መመሪያ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 27
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

2 የመነኮሳተ ሰማንያ መመሪያዎች


3 ሁለት ልዩ የሆነ የገዳም መመረያ
 55 ረጅም መመሪያዎች
 313 አጭር መመሪያዎች
ሁለቱም መመሪያዎች የተዘጋጁት በጥያቄ እና መልስ መልክ ነው፡፡

4. ድርሳናት መልእክታት አደና ቅዳሴ


ቅዱስ ባስልዮስ ከቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት አነዱ እና ዋነኛው አባት ሰልነበር በርካታ ድርሳናትን
ትቶልን አልፉዐል እነዚሀም 24 ድርሳናት በርካታታ መልእክታት እና አነድ በስሙየሚጠራ ቅዳሴ ደርሱአል

ጥር 2ኛ ሳምንት
ትምህርተ ቅዱሰ ባስልዮስ
ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን ይመስላል፡፡ /ፊል------/ ያለውን ሲተረጉም
ያለምንም መቀዳደም ቃል ከልብ እንዲገኝ ቀዳማዊ ቃል እግዚአብሔር /ዩሐ-----/ ከቀዳማዊ እግዚአብሔር አብ
ባሕርየ መለኮት እንደተገኘ በማንኛውም መለኮታዊ ስራ ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደ መሆኑ የባሕርይ አባቱ እግዚአብሔር
አብን ይመስላል ወይም ያህላል፡፡ ባሕርየ መለኮት እግዚአብሐየር አብ የብቻው አይደለም የሦስትነትም አካል ማለት የአብ
ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያንድነታቸው ያለመቀዳደማቸው የእኩልነታቸው መነጋገርያ ቋንቋ ነው፡፡ ስለሆነም ይወልደዋልወይም
ተወለደ ብሎ ይናገራል፡፡ ነገር ግን አይቀድመውም የሚለው በባህሪይ አንድ ስለሆነ ነው፡፡ እግዚአብሐየር ወልድ ከአብ ብቻ
ተወለደ ወይም ተገኘ፡፡ እግዚአብሐየር መንፈስ ቅዱስም ከአብ ብቻ ወጣ የሚል ቋንቋ ከፍጡራን የባህሪይ ግኝት ቋንቋ የተለየ
ነው ፍጡራን ከወለደው ወይም ከሰራ ወላጁ ከተወላጅ ሰሪው ከሥራው ይቀድማል በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ዘንድ
ግን እንዲህ አይደለም፡፡ ወልድ ከአብ ተወለደ ወይም ተገኝ ቢልም በከዊነ ቃልነት በአብና በመንፈስ ቅዱስ አካል ውስጥ ምን
ጊዜም ያለና የሚኖር የሦስትነት አካል አንድ ቃል ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስም የሦስትነት አካል፤ አንድ እስትንፋስ ነው፡፡ አብም
የሦስት አካል አንድ ልብ ነው፡፡ ለሦስት አካል እንደ ፍጡር ከአካል በቀር የተለየ ልብ ቃልና እትንፋስ ስለሌላቸው አንድም
ሦስትም ይባላሉ፡፡ ከፍጡራንም ሦስትነት ኖሯቸው ሦስትነታቸው የማይቀዳደም ጥቂት ፍጡራን ይገኛሉ፡፡ የፀሐይ አካል ያለ
ብርሃንና ያለ ሙቀት ፣ የእሳትም አካል ያለ ብርሃን እና ያለ ሙቀት ለብቻው መኖር ወይም ማኖር ለፍጡራን ችሎታ የላቸውም፡
፡ እነዚህ እንኳ ፍጡራን ናቸው፡፡ ለደካማው አእምሯችን በፈጣሪያችን ዘንድ የመለኮት አንድነትና የአካል ሦስትነት እንዴት
እንደሆነ ለመረጃነት ቀደምት ሊቃውንት መዝግበዋል፡፡ እግዚአብሔር ወልድ የእግዚአብሔር አብ ቃሉ ስለሆነ የፈጣሪያችንን
የእግዚአብሔር አብን ቃል ፍጡር ወይም አማላጅ ብሎ መናገር በፈጣሪ ላይ የፍጡርን ባሕርይ መቀላቀል ስለሆነ ይህን
የሚል ክፍል ፈጣሪውል ለይቶ ሊያውቅ ያስፈላጋል፡፡ ብሏል፡፡

የባርያ መልክ ይዞ በሰው ምሳሌ ሆኖ ለሰው ሲል ራሱን አዋረደ /ፊሊ------/ ያለውን ቃል ሲተረጉም
ቀዳማዊ እግዚአብሔር ወልድ የድኀራዊ ፍጥረቱ የሰውን ባሕርይ ተዋሐደ በዚህም የፈጠረውን ሥጋ ለብሶ ቀዳማዊ
እግዚአብሔር አደረገው፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ከእመቤታችን ለነሳው ሥጋ ፈጣሪውና አምላኩን ነው፡፡ ያለ እግዚአብሔር
ወልድ እግዚአብሔር አብ ምንም የፈጠረው የለም መፍጠርም አይችልም፡፡ ዘፍ/--------/ም-----./ዪሐ------፡፡
በአንዳንድ ዐርፍተ ነገር ቅዱስ መፅሐፍት እግዚአብሔር ወልድ ወይም ክርስቶስ አምላኬ እንዳለ ወይም የኢየሱስ
ክርስቶስ አምላክ የሚል መዝግቦ ይገኛል፡፡ መዝ----ማቴ----ጴጥ-------ራዕ---- እነዚህንና የመሰሏቸውን ጥቅሶችን ማስተዋል
ያስፈልጋል፡፡
እግዚአብሔር ወልድ ሥጋ ከመልበሱ ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ እግዚአብሔር ወይም አምላኬ የሚለውን ቋንቋ
የጠራበት አንቀፅ አልተመዝገበም፡፡ “ወደፊት ሰዉ እንደሚሆን ሰዉ ሆኖ አምላኬ እንደሚል ግን በትንቢት አኗግሯል፡፡መዝ--

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 28
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

----ስለ ሆነም ክርስቶስ አምላክ ሲሆን ሰው በሆነበት ወራትም በሥጋ ርስት በሰው አንደበት አማላኬ ብሎ ሲናገር
እግዚአብሔርን አብን ብቻ አምልኬ ብሎ የጠራ እንዳይመስልህ አስተውል፡፡ ራሱን ከባህርይ አባቱ ከአብ ጋር አንድ አድርጐ
ነው፡፡ ክርስቶስ ለለበሰው ሥጋ አምላኩ ነውና፡፡ ሥጋ በሦስት አካል በአንድ አምላክነት የተፈጠረ መሆኑን አይዘንጉ፤
በትምህርተ መለኮት ትርጓሜ ክርስቶስ መምህር እንደ መሆኑ ሰውን ለማዳን አምላካዊ ስራውን ሲሰራ ወደፊት ተከታዮች
ምዕመናን እና ሐዋርያት ማንኛውም ምድራዊ መከራ በገጠማቸው ጊዜ ማንን መለመን ወደ ማና መጮኽ እንደሚገባቸው
ሲያስተምር አምላክ ሲሆን አምላኬ ብሎ ተኗግሯል፡፡ ይህም አስተማሪ ለተማሪው እናት ለልጆ እንደምታደርገው ምሳሌያዊ
ስራ ነው ብሏል፡፡
አፈወርቅ ዩሐንስ እግዚአብሔርን አብ ያለው እግዚአብሔር ወልድንና መንፈስ ቅድስን ለብቻው እግዚአብሔር
ወልድንና መንፈስ ቅዱስም ለየብቻቸው አምላኩ ወይም አምለክ ተብለው ቢጠሩም ለሦስቱም አካል ሦስት አምላክነት
ኖሯቸው አይደለም ሦስቱም አካል በአንድ እግዚአብሔርነት በአንድ ፈጣሪነት በአንድ አምላክነት አምላኬ ፈጣዬ ይባላሉ
እንጂ ለየብቻ የአማላክት ፈጣሪዎች አያባሉም፡፡ በአምላካነት ሦስት አካላት አንድ ናቸውና አንድ አምላክ ይባላሉ፡፡፡
አምላካችን አንድ ነው፡፡ ብሎናል፡፡ ዘፀ----- ዘዳ--------- ማቴ-------፡፡ እንዲህ ስለሆነ አንዱ አካ እንዲህ አድርግልኝ ወይም
ስጠኝ ብሎ አያመለክትም፡፡ አንዱ ምን ጊዜም አንድ ነውና፡፡ የቅዱስ ባስልዮስ ትምህርተ መለኮት ስልት እንዲህ ነው፡፡
ባስልዮስ መንፈሳዊ ትምህርቱን በመቀጠል እግዚአብሔር ወልድ እግዚአብሔር አብን በመልክ የሚመስለው በባህርይ
የሚተካከለው ስለሆነ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ በመለኮት በባህርይ አንድ በሆኑን ማመን ነው፡፡ ብሎ እንደ አንድ ለማስረዳት
ማንኛውም ፍጡር በሰማይ ሆነ በምድር የማወቂያ መሳሪያው አልተፈጠረለትም፡፡
ስለዚህ ወልድንና መንፈስ ቅዱስን የሚያውቃቸው ያልተፈጠረ የሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር አብ ነው አብና መንፈስ
ቅዱስን የሚያውቃቸው ያልተፈጠረ ከሃሊ ፈጣሪ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የባህሪ አንድነት ያለው እግዚአብሔር ወልድ
ነው፡፡ የመስፈስ ቅዱስንም እንደዚሁ ያስተረጉማል የሦስት አካላት አምላካዊ እውቀት አንድ ነው ብሏል፡፡ ዘፀ--------- ማቴ-
-------ዩሐ-------1ዩሐ------ቆሮ----------፡፡
ቀድሞ ሦስት አካላት በአንድ መለኮት በአርያቸው በአሳላቸው እበርሱ ባወቁ እንደ ፈጠሩን /ዘፍ-------/ ኃላም
በሦስት አካላት ስም ተጠምቀን በሦስቱም እንደ ተወለድን ሲያስረዳ በከበርንባቸው እነዚህ ስሞች በአብ በወልድ በመንፈስ
ቅዱስ እንመን፡፡ ሰው የሆነ ቀዳማዊ ቃል መድኃኒታችን ክርስቶስ እንዳዘዘን፡፡ ማቴ/-------/ ዩሐ---------/በሦስቱም ተፈጥረን
በሦስቱም ስለ ተወለድን ሦስቱንም አባታችን ሆይ እያልን እንጠራለን፤ ብሏል፡፡

ጠቢቡ ሰሎሞን እግዚአብሔር የመንገዱን መጀመሪያ አደረገኝ ምሳ/-------/ ያለውን ሲገልጥ


ቀዳማዊ እግዚአብሔር ቃል ሰው ስለመሆኑ ሊገልጥ ይገባል የለበሰው ሥጋ ፍጡር ስለሆነ ስለ ቀዳማዊ መለኮት
ግን ሰለሞንም በሠጋ ትገለጥ ዘንድ ስለ አላት የእግዚአብሔር ጥበብ ይህን ተናገረ ብሏላ፡፡ ይህ የሰሎሞንን ማሳሌያዊ ቃል
ሐዋርያው ጠቅሶ ሲናገር ሰው በማያውቀው በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበቧ ስለ አላወቀች
በነገር ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኗልና ብሏል፡፡ ቆሮ-----፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ ስለ ምሳሌ
ሲናገር አማና አይደልም ንግግር ነው ብሏል፡፡ ይኽውም በምሳሌ ሰሎሞን እርሱ እግዚአብሔር ወልድ እግዚአብሔር ፈጠረን
ካለ አምልክ እግዚአብሔር ለምን ይላል ?? ብሏል፡፡ ስለ ወልድ እግዚአብሔር እግዚአብሔርነት የሚከተሉትን እንመልከት፡፡
ዩሐ--------ዩሐ------ዘዳ------ሮሜ-------ቆላ-----ቲቶ-----2ጴጥ-- ዩሐ---- ራእ- እንዲህም ስለሆነ ወለደኝ ብሎ የተመዘገብዉ
እግዚአብሔር አብ የባህሪ ልጅ ስለመሆኑ ይተረጉማል፡፡ ፈጠረኝ የተባለዉም በኋላ ዘመን ሰዉ ስለመሆኑ ለማዎቅ አያዳግትም፡
፡ እነ አርዮስ እና መሰሎቹ ምሥጢሩን ባለመረዳት በክህደት ጭቃ ላይ ቢንከባለሉም ወለደኝ የሚለዉንና ፍጠረኝ የሚለዉን
ቋንቋ የሰማይና የምድር ያህል የተራራቀ ነወ፡፡ስለዚህ ከፈጠረዉ አይወልደውም ከወለደዉም አይፈጠረዉም ፡፡ ሰዉ
ከእግዚአብሔር ተወለደ ትብሎ የንደትፃፈ ሰዉ እንደመሆኑ በስጋ በተወለደዉ ልደት ወንጌላዊ ይህን ተናገረ ብሏል፡፡
ሉቃ------መዝ--------የፍጡራንን ደካማነት ባስረዳበትም አንቀፅ የምናያቸዉን ፍጡራንና ፍቱራንን ባህሪይ ከምንና
እነዴት እንደሆኑ ምክንያታቸዉን ድረስ መንስኤያቸዉን መርምሮ ማወቅ ያቃተን የማናዉቀውንና የማናየዉን ለመመርመር
እንዴት እንደፍራለን/.. ብሎ ካደነቀ በኋላ እደአቅሙ ማወቅ የሚገባዉን እንደመሆኑ ፈጣሪዉ እግዚአብሔርን ወደማወቅ
እንደ ደረሰ አድርጎ ራሱን ከሚያስት ይልቅ ማን ደካማ ፍጥረት የለም ብሏል፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 29
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ባስልዮስ ስለደጋጉች አበው ትህትና ሲናገር


 ደገኛው አብርሃም ፈጣሪውን ሰው ሊያየው በማይችል አምሳል አይቶ ራሱን በመንቀፍ ‹‹ እኔ ትቢያ አመድ ነኝ ›› አለ፡፡ ዘፍ-
----
 የዋው ሙሴ ማንነቱን ተረድቶ ‹‹ እኔ ዱዳ ነኝ መናገር አልችልም›› አለ፡፡ ዘፀ--------
 ኤርምያስም ደካማነቱን ተረዶቶ ‹‹ ብላቴና ነኝ ለመናገር አልችልም›› አለ፡፡ ኤር--------
 የዋው ዮናስም ማንነቱን በማመዛዘን የሚያመልጥ መስሎት ለመሸሽ ሞከረ፡፡ ዩና----
 ልበ አምላክ የተባለው ዳዊትም ማንነቱን ተረደረቶ ‹‹ እኔ ትል ነኝ እንጂ ሰው አደለሁም ››አለ፡፡
 እዮብም ስለ ‹‹ እኔ እንደሚጠፋ በስባሳ ነገር ብልም እንደሚበላው ልብስ ነኝ ›› አለ፡፡ ኢዮብ-------
 ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ ከሁሉም በኃላ እንደ ጭንጋፍ ለመሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ›› ብሏል፡፡ቆሮ------፡፡
ባስልዮስ ብሉይን ከሐዲስ በማጣቀስ በማንኝውም መለኮታዊ ሥራ ስለ አብ የተነገረው ሁሉ ወይም የሚነገረው ሁሉ ለወልድ
የባህርይ ገንዘቡ ነው፡፡ ዩሐ----ም---- ይህ ቋንቋ ግን ለሜዳ ፃድቃን ለተረፈ ፈሪሳውያን አይረዳቸውም፡፡ ስለ እግዚአብሔር
መንፈስ ቅዱስ ሲናገር ቀራጭ ማቲዎስን ቢያምንበት ማቴ-----ሰማያዊ ህግ ወንጌልን እንዲፅፍ ዓሳ አጥማጅ ዮሐንስም
ቢያምንበትም ከአዋቂዎች የበለጠ አዋቂ አደረገው፡፡ዩሐ---------ም-----ራዕ-------፡፡ ፈሪሳው ጳውሎስን ሰው አድርጎ የወንጌል
ሰባኪ አደረገው፡፡ የሐዋ----ገላ------1ጢሞ----ጴጥሮስና ዩሐንስ ሰማያዊ ሀብትን ሰጣቸው ብሏል፡፡ የሐዋ---ም---ም------፡፡

ጥር 3ኛ ሳምንት
ቅዱስ ጎርጎሪዮስ ዘእንዚናዙ
የቅዱሪ ጎርጎረዮስ ዜና ዘእንዚናዙ ሕይወቱ
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ በ326 ዓ.ም
በኒዬቄሳርያ ተወለደ፡፡ ከቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ ጋር በአቴንስ
ዩኒቨርስቲ አብረው ተምረዋል፡፡ የቅዱስ ጎርጎርዮስ ምስጢረ ሥላሴና
ምስጢረ ሥጋዌ ትምህርት ከጥርጣሬ የሚፈውስ ታማኝ
ትምህርትነው፡፡ ይኸው ቅዱስ አባት በ381 ዓ.ም በተደረገው
የቁስጠንጥንያ ጉባዔ ላይ 150ኛው ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ የመንፈስ ቅዱስን
የባሕርይ አምላክነት አብራርቶ በማስረዳትና መቅደንዮስን በማውገዝ
ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሕይወት የሆነ ትምህርቱን አጽንቶ
አልፏል፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ጓደኛው ባስልዮስ ዘቂሳርያ
ካረፈ በኋላ ለ10 ዓመታት ያህል ከአርዮሳውያን ጋር ሲታገል ኖሮ
በ389 ዓ.ም አርፏል

ቅዱስ ጎርጎሪዮስ ዘእንዝናዙ ስረዎች እና ትምህርቱ

የጎርጎርዮስ መጻሕፍትና የቅድስና ተምሳሌት ያለው ሕይወቱ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እስከ ዘለዓለም
ሲነገር ይኖራል፡፡
ስለ ክርቶስ የባሕርይ አምላክነት ካስተማረበት አንቀጽ የተወሰደውን ድንቅ ትምህርት -
“የክርስትና ኃይማኖት በክርስቶስ ማመን ነው፡፡ /ሐዋ.ሥራ 2÷35/ መወለዱን፣ መጠመቁን፣ መገረፉን መከራ
መቀበሉን፣ ሞቱን፣ ትንሳኤውን፣ ዳግም ትንሣኤውን፣ ዳግም ምጽአቱንና እግዚአብሔር ሥጋ መልበሱን ደግሞም ዓለምን
ሊያሳልፍ መምጣቱን፡፡ ሥጋ የለበሰው እግዚአብሔር ሞትን በሥልጣን፣ በኃይል አሸንፎ ከሙታን ተለይቶ ተነሳ፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 30
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

እግዚአብሔር ከመጀመሪያው የክብር ጠርዝ ወደ መጨረሻው የውርደት ጠርዝ፣ ከጽርሐ አርያም ወደ ከብቶች ግርግም
በመውረድ ተዋርዶ የነበረውን የሰው ልጅ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው፡፡
ባሕርይውን አዋርዶ ዝቅ ብሎ የታየው ከሁላችንም በላይ ከዘመናት ሁሉ አስቀድሞ የነበረ ነው፡፡ ይህ ሰው
የሆነው ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ የሚኖረው ነው የሆነው ሁሉ በርሱ የተደረገ ነበር /ዬሐ 1÷3/ የሆነው
ሁሉ የተደረገው በምክንያት ነው ያለምክንያት የተደረገ አንዳችም ነገር የለም፡፡ እርሱም ለሰው ልጆች ዘለዓለማዊ ዋስትና ሲባል
የተደረገ ነው እርሱ ከመጀመሪያው ያለምክንያት ነበር /ዬሐ 1÷13/ ለእግዚአብሔር ሐልዎት ምን ምክንያት ይኖረዋል? ነገር ግን
በምክንያት እርሱም የሰው ልጅን ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ሥጋ ለብሶ ሰው ሆነ፡፡ የተፈጸመውም የእኛ ድህነት ነው
ያዋረድነውን እግዚአብሔነቱን፣ የናቅነውን መንግሥቱን፣ ያቃለልነውን ወገኖቹ ሊያደርገን ስለዚህ ምክንያት የኛን ባሕርይ ነሳ፡
፡ ሥጋ ዝቅ ያለ ሲሆን እግዚአብሔርን ሆነ፡፡
እግዚአብሔርም የሰውን ልጅ ሆነ፡፡ በሥጋ ከድንግል ማርያም ተወለደ፡፡ አስቀድሞ ግን ከባሕሪይ አባቱ
ለዘለዓለም የተወለደ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ነበር፡፡ ከሴት ተወለደ ነገር ግን ድንግል ነበረች ልዩም ነበረች፡፡
የመጀመሪያው ሰው ሁለተኛው ደግሞ መለኮት ነው፡፡ ሁለት ባሕርይ ያሉት አይደለም በፍጹም ተዋህዶ ፍጹም ሰው ፍጹም
አምላክ ሆነ እንጂ፡፡ ሰው እንደ መሆኑ አባት የለውም፣ አምላክ እንደመሆኑ እናት የለውም፣ በማህጸነ ድንግል ተወሰነ በነቢያቱ
አፍ አምላክነቱ ተመሰከረለት፣ ነቢያቱ ብቻ የመሰከሩ አይደለም አብም የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ /ማቴ 17÷4/ እርሱም
አባቴ ነው አለ /ዬሐ 14÷3/ /ዬሐ 14÷9/ ሰው እንደመሆኑ በጨርቅ ተጠቀለለ፣ አምላክ እንደመሆኑ ደግሞ የተገነዘበትን መግነዝ
(ጨርቅ) ጥሎት ተነሳ /ዬሐ 20÷7/ በበረት ላይ ተኛ፣ መላዕክት ገን አመሰገኑት፡፡
ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡ በዚያም የነበሩ የግብጽ የሐሰት አማልክት (ጣዖታት) እንዲሰደዱ አደረገ በአይሁድ አለቆች
ዘንድ መልክም ደምግባትም አልነበረውም፣ በዳዊት ዘንድ ግን ውበቱ ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ እጅግ ያማረ ነው /መዝ 45÷2/፡
፡ ስለ እኛ ያለውን ዘለዓለማዊ እቅድ በቅዱሱ ተራራ ላይ ሲገልጥልን ውበቱ እንደ ብርሃን ብሩህ ከፀሐይ ብርሃን ይልቅ እጅግ
የሚያበራ ከበረዶም ይልቅ ነጭ ነበረ /ማቴ 17÷2/፡፡
እንደሰው ተጠመቀ እንደ እግዚአብሔርነቱ ኃጢአትን ይቅር የሚል ግን እርሱ ነው፡፡ በራሱ መንጻት
ስለሚያስፈልገውም አልነበረም፤ በባሪያው እጅ መጠመቁ እኛን ለመቀደስ ነው፡፡ ተራበ፤ ፍጥረትን የሚመግብና የሚያጠግብ
ግን እርሱ ነው፡፡ ላመኑበት የሕይወት እንጀራ ሆኖ ከሰማይ የተሰጠም እርሱ ነው፡፡ የተጠማ ማንም ቢኖር ወደ እኔ ይምጣ
ያለ አምላክ ተጠማሁ አለ፤ መጽሐፍ ግን የሕይወት ምንጭ ውኃ ከሆዱ ይፈልቃል አለ /ዬሐ 6÷5/፡፡ ዓለምን ያሸነፈልን እርሱ
ነው፡፡ ደከመ፤ ደካሞችን፣ ሸክማቸው የከበደባቸውን የሚያሳርፍ ግን እርሱ ነው /ማቴ 11÷29/፡፡ እስራኤልን የሚጠብቅ፣
የማያንቀላፋ፣ የማይተኛ አምላክ /መዝ 121÷4/ ደክሞት አንቀላፋ፤ በውሃ ላይ ተራመደ፣ ነፍሳትን ገሠጸ፣ ጴጥሮስን በውሃ ላይ
ሲራመድ ከመስጠም አዳነው /ማቴ 18÷25/፡፡
በሰውነቱ ለምድራውያን ነገሥታት ግብርን ገበረ፤ በአምላክነቱ ወርቅ፣ ከርቤና ዕጣን እጅ መንሻን ተቀበለ፡
፡ ጸለየ ፤ ጸሎትን የሚቀበል ምልጃንም የሚሰማ ግን እርሱ ነው፡፡ የሰዎችን እንባ የሚያብስ አምላክ ሲያለቅስ ታየ፡፡
እንደሰውነቱ የአልዓዛርን ሥጋ ወዴት አኖራችሁት አለ፤ እንደአምላክነቱ ከሞት አስነሳው፡፡ ተሸጠ፤ እጅግ ርካሽ በሆነ በ30
ዲናር፡፡ ዓለምን ግን እጅግ በከበረና በተወደደ ዋጋ አዳነው፤ እርሱም በደሙ በኩል በተደረገ ቤዛነት ነው፡፡ እንደበግ ለመታረድ
ተነዳ፤ እርሱ ግን የእስራኤል ጠባቂ እውነተኛ የበጐች እረኛ ነበር፤ አሁን የዓለም ሁሉ አዳኝ መሆኑ በትንሣዔው ብርሃን
በታወቀ፣ በተረዳ ነገር ተገለጠ፡፡ ተጨነቀ፤ ተሰቃም፤ አፉንም አልከፈተም፣ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፤ በሸላቾቹም ፊት
ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም /ኢሳ 53÷7/ ፤ እንደሚታረድ ጠቦት ዝም አለ፤ ሰማይና ምድርን ግን በቃሉ
የፈጠረ እርሱ ነው፡፡
በሕዝቡ ሁሉ ላይ የነበረውን ደዌ ፈወሰ /ማቴ 9÷36/ ነገር ግን እርሱ በጅራፍ ተገረፈ፤ በበትርም
ተደብድቦ ቆሰለ፤ በመስቀል ላይ ተቸነከረ ከምድርም ከፍ ከፍ አለ፤ እኛንም ወደ ቀደመ ክብራችን መለሰን በሕይወት ዛፍም
አዳነን /ራዕይ 22÷23/ አብሮት የተሰቀለውን ወንበዴ የገነትን መክፈቻ ቁልፍ አስቀድሞ ሰጠው፡፡ አባት ሆይ ነፍሴን በእጆችህ
አደራ እስጣለሁ አለ፤ እንደተናገረ ግን ሕይወቱን ሊያሥነሳትም ሆነ ሊጥላት ሥልጣን ያለው እርሱ ነው /ዬሐ 10÷18/ ፡፡
በትንሳዔው ብርሃን ነፍሳት ከሲኦል የሚወጡበት ደውሉ ተደወለ፤ የገነት የሚስጢር በሮች ተከፈቱ፤ አለቱ ተሰነጠቀ፤ ሙታን
ከመቃብር ተነሱ፡፡ ሞተ ነገር ግን ሕይወትን ሰጠ፤ በሞቱም ሞትን ደመሰሰ፡፡ በሐዲስ መቃብር ቀበሩት፤ ነገር ግን ሞትን
አሸንፎ ሙስና መቃብርንም አጥፍቶ ተነሳ፤ ወደ ሲኦል በአካለ ነፍስ ወረደ፡፡ ነፍሳትን ከመከራ ወደ ደስታ፣ ከሲኦል ወደ ገነት
መለሰ /1ዬሐ 3÷19/ ፡፡ ወደ ሰማይም ዐረገ፤ በእግዚአብሔርነቱም ስፍራ በቀኝ ተቀመጠ፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን
ለመፍረድ በታላቅ ኃይልና ስልጣን በልዩም ክብር በመላዕክት በምስጋና ይመጣል፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 31
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ጥር 4ኛ ሳምንት
ቅዱስ ጎርጎሪዮስ ዘኑሲስ
የቅዱሪ ጎርጎረዮስ ዘኑሲስ ዜና ሕይወቱ
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘ ኑሲስ የቀጰዶቅያ አበው በመባል
የሚጠሩት ሊቃውንት መካከል ነው፡፡ የተወለደው በቂሳርያ ከተማ
በ335/36 ዓ.ም አካባቢ ሲሆን አባቱ ባስሊዮስ እናቱ ደግሞ ኤሜልያ
ትባላለች፡፡ አባቱ ባስሊዮስ ንግግር አዋቂ ነበር፡፡ የጥር ስድስት ቀን
ስንክሳር አባቱ ኤስድሮስ እንደ ሚባል ይናገራል፡፡አያይዞም ‹‹እርሱም
ከአጾኪያ ሀገር ሰዎች ንፁህና ቅዱስና የሆነ ቄስ ነው ›› ይለዋል፡፡
በሀብቱ የተሟላላት፣ በክርስትና ሕይወቱም ጠንካራ ነበር፡፡የጎርጎርዮስ
የእናቱ አባት በዘመን ዲዮቅልጢያኖስ በመሰደዱ ምክንያት ሀብቱም
ሕይወቱንም አጣ፡፡የዲዮቅልጥያኖስ ዘመን አልፎ ሰላም ሲሰፍን መላ
ቤተሰቡ ወደ ቂሳርያ መጥቶ በዚያ ኑሮ ጀመረ፡፡
በቤተሰቡ ውስጥ በጠቅላላ ዐሥር ልጆች ሲኖሩ አምስቱ ወንዶች
አምስቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡ አባቱ ባስልዮስ ገና በልጅነታቸው
በመሞቱ ልጆቹን ያሳደጉአቸው ሴት አያታቸው ማቅሪና እና
እናታቸው ኤሜሊያ ነበሩ፡፡እነዚህ ሁለቱ እናቶች በቅንነታቸውና
በጠንካራ ክርስቲያናዊ ሕይወታቸው የታወቁ ናቸው፡፡ ሁለቱም ልጆች
ለከፍተኛ መዓረግ የደረሱ መሆናቸው ቢገለጥም በዝርዝር ታሪካቸው የታወቀው ግን የዐራቱ ወንዶችና የአንዲት ሴት
እህታቸው ብቻ ነው፡፡

ከሴት አያቷ ስሟን የወረሰችው ማቅሪና የቤተሰቡ ዋና አገልጋይ ነበረች፡፡ የሕፃናቱን ትምህርትና አስተዳደግ
በተመለከተ ከእናቷ ከአያትዋ ጋር ሱታፌ ነበራት፡፡ በዐራቱም ወንዶች መንፈሳዊ ህይወት ውስጥ የርስዋ አስተዋፅዎ እንዳለበት
ድርሳናት ይመሰክራሉ፡፡ በልጅነቷ አጭቷት የነበረው እጮኛዋ በሞት ቢለያት እንካን ከእርሱ በኃላ ሌላ ሳታጭ በቃል ኪዳንዋ
ፀንታለች፡፡ሕይወትዋን በሙሉ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመሰዋት ለእናትዋና ከአያትዋ ጋር በቤተሰብዋ ርስት ላይ የሴቶች
ገዳም መሰረተች፡፡ ይህ ገዳም በኤሬስ ወንዝ ቆሬ ውስጥ ፣ አነሲ በተባለ ቦታ የሚገኝ ነበር፡፡

ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ለቤተሰቡ ሦስተኛ ልጅ ነው፡፡ ከርሱ በላይ ኔክታርዮስ የተባለ በአባቱ ሙያ የተተካ ወንድም
አለው፡፡ የርሱ ታናሽ ጴጥሮስም በኃላ የስብስጥያ ጳጳስ ሆኖ ነበር፡፡

ጎርጎርዮስ የመጀመሪያውን ትምህርት ያገኛው ከቤተሰብ መሆኑ ይታመናል፡፡ በተለይም የቤተሰብ የመጀመሪያው
ልጅ ከሆነው ከባስልዮስ ዘቂሳርያ ዘንድ ከአቴናውያን ትምህርት እስከ ሕክምና ያለውን መማሩ ይታመናል፡፡ ጎርጎርዮስ
በፁሁፎቹ ላይ ወንድሙን ‘የኔታ’ እያለ ነበር የሚጠራው፡፡ ሴት አያቱን ፣ እናትና እህቱን በትምህርተ ሃይማኖት ቀርፀው
ያሳደጉት በመኾኑ በየድርሳኑ ደጋግሞ አመስግኗቸዋል፡፡

ጎርጎርዮስ ዐይን አፋር በመሆኑ ከቤተሰብ ርቆ አልሄደም፡፡አንድ ጊዜ እናቱ ኤሜሊያ ቀደ አኒስ ከመነነች ጥቂት ጊዜ በኃላ
የዐርባ ሐራን በዓል ለማክበር ጎርጎርዮስን ጠራችው፡፡ ጎርጎርዮስ ያኔ ሕፃን ስለ ነበር በመንገዱና በአገልግሎቱ ተሰላችቶ
በእኩለ ለሊት በአትክልቱ ስፍራ ጋደም አለ፡፡ በሕልሙ ሰማዕታቱ ተገልጠው፡፡ በመሰላቸቱ ገስፀው በበትር መቱት፡፡ ሲነቃ
በፀፀት ተሞልቶ ነበር፡፡ ከዚህ በኃላ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንባቢ ሆኖ ማገልገል ጀመረ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ግን የንግግርን
ጥበብ በመውደዱ አንባቢነቱን ተወው፡፡ ወደ ሲቪል አንባቢነቱን ተመለሰ፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 32
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

እህቱ ማቅሪና ባደረገችው የተጋ ውትወታና ምክር የሲቪል አገልግሎቱን ትቶ ወደ ገዳማዊ ኑኖ ተመለሰ፡፡ ወንድሙ ባስልዮስ
መስርቶት ወደ ነበረው በጳንጦስ ወደ ነበረው ገዳም ገባ፡፡ በጳንጦስ ገዳም ለብዙ አመታት ተቀምጦ ቅዱሳት መፃሕፍትን
በሚገባ ተማረ፡፡

በ365ዓ.ም ባስልዮስ ከገዳም ተጠርቶ ለአውሳብዮስ ዘቂሳርያ ረዳት ጳጳስ ይሆን ዘንድ ተሸመ፡፡ በዚያን ጊዜ
አርዮሳውያን በንጉስ ቫሌንስ እየተደገፉ በቀጳዶቅያ ያስቸግሩ ስለነበር የባስሎዮስ አስፈላጊነት የጎላ ነበር፡፡ባስልዮስ እስኪ ሞተ
ድረስ መከራውን ተቋቁሞ ለርዕቱ ሃይማኖት ባደረገው ተጋድሎ የቂሳርያው አውሳብዮስ ሲያርፍ በ270 ዓ.ም የቂሳርያው ጳጳስ
ሆኖ ተሸመ፡፡ ባስልዮስ መንበሩን እንደ ያዘ የኦርቶዳክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ሊያቀኑ ከአርዮሳውያንም ሊጠብቁ የሚችሉ
ሊቃውንትን ማሰባሰብ ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ ወንድሙ ጎርጎርዮስን የኑሲስ ጳጳስ አድርጐ ሾመው፡፡ ጎርጎርዮስ ሹመቱን እንቢ
ቢልም ሊያመልጥ ግን አልቻለም፡፡ መፅሐፈ ስንክሳርም ኑሲስ በሚባል ሀገር ላይ ሳየረወድ በግድ መርጠው ኤጲስ ቆጶስነት
ሾሙት ይላል፡፡ ጎርጎርዮን ያህል ሰው እዚህ ግባ በማትባል ከተማ እንዴት ትሾመዋለህ ? በሚል የቀረበለትን ጥያቄ ባስልዮስ
ሲመልስ ፡- ወንድሜን በኑሲስ የሾምኩት ከመንበሩ መዓረግና ክብር እንዲያገኝ ሳይሆን ፣ ለመንበሩ መዓረግና ክብር
እንዲያመጣለት ነው ብሎ ነበር የመለሰው፡፡

ጎርጎርዮስ ስለ ምሥጢረ ሥላሴና ስለ ምስጢረ ሥጋዌ በሚገባ እየተነተነ ከአርዮሳውያን ጋር የተጋደለው በኑሲስ
ከተማ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ በንጉስ ይደገፋ የነበሩ አርዮሳውያን ልዩ ልዩ ክስ እየመሰረቱ ያንገላቱት ነበር፡፡ በየከተማው ደጋፊ
ጳጳሳትን እየሰበሰቡ ሊያወግዙት ያስጠሩት ነበር፡፡ ጎርጎርዮስ ግን በዚህ መሰሉ ጉባኤ መገኘትን አልፈለገም፡፡ በተለይም በ376
ዓ.ም በኑሲስ የተሰባሰቡ የንጉስ ደጋፊዎች ጎርጎርዮስ ከመንበሩ እንዲነሳ አደረጉ፡፡ ንጉሱም አፀደቀላቸው፡፡ ጎርጎርዮስ ወደ
ምናኔ ገባ፡፡

በ378 አርዮሳዊው ንጉስ ቫሌንስ ተገድሎ ግራቲያን ሲነግሥ አርዮሳውያን ኃይላቸው ተዳከመ፡፡ ተሰድደው የነበሩ
ኦርቶዶክሳውያን አበውም ወደ መንበራቸው ተመለሱ፡፡ ጎርጎርዮስም ወደ ኑሲስ መጣ፡፡ ሕዝቡም በዕልልታ በሆታ ተቀብለው፡
፡ ከጥቂት ጊዜ በኃላ ታላቅ ወንድሙ ባስልዮስ በስደት በደረሰበት እንግልት ብዛት በ50 ዓመቱ ዐረፈ፡፡ በቀጣዩ ዓመትም እህቱ
ማቅሪና ዐረፈች፡፡ ከዚህ በኃላ በምድረ ቀጰዶቅያ ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጥብቅና በመቆምና መናፍቃንን በማሳፈር ጎርጎርዮስን
የሚተካከለው አልነበረም፡፡ በ379ዓ.ም በአንፆኪያ በተደረገው ጉባኤ ከተካፈለ በኃላ ጉባኤው በዓረቢያ በሚገኙ አብያተ
ቤተክርስቲያናትን እንዲጐበኝ ላከው፡፡ እግረ መንገዱን ኢየሩሳሌምን ጐበኘ፡፡

በ381 ዓ.ም በጉባዬ ቁስጥንጥንያ ከተሰበሰቡት 150 አበው ጳጳሳት አንዱ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ነበር፡፡ በጉባዩው ላይ
የአውኖሚያውያንን ኑፋቄ የሚቃወም ፁሁፍ አቅርቧል፡፡ መፅሐፈ ስንክሳር ስለ ከሃዲው መቅዶንዮስ በንጉሥ ቴዎዶስዮስ
ዘመን በቁስጥንጥንያ ከተማ የመቶ አምሳ ኤጲስ ቆጶሳት የአንድነት ስብሰባ በሆነ ጊዜ ይህ ጎርጎርዮስ ከአባቶች ኤጲስ ቆጶሳት
ጋር ሆኖ የባስልዮስን ወገኖች መቅዶንዮስንና አቡሊናርዮስን ተከራከራቸው፡፡ መልስ አሳጥቶም አሳፈራቸው ይላል፡፡ ከዚህ
በኃላ በቤተ-መንግስቱ ታቀባይነትን በማግኘቱ ሃይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ወሳኝ ሚና ነበረው፡፡ የወንድሙ የባስልዮስ
ትንቢት እውነት ሆኖ ኑሲስ በጎርጎርዮስ የተነሳ ታዋቂ ሆነች፡፡ከከተማ ውጭ በመላው ታናሽ እስያ እየተዘዋወረ ያስተምር ነበር፡
፡ ከብቃቱ የተነሳ ቅዳሴ ሲቀድስ ኪሩቤልን ያይ ነበር፡፡ የጥር 21 ቀን ስንክሳር ፡- እርሱ መሥዋዕቱን ለማክበር በሚቀድስ ጊዜ
በመሰዊያው ላይ ሲወርድ መንፈስ ቅዱስን የሚያየው ሆነ፡፡ ከዚህም በኃላ ኪሩብን አየው፡፡ በደረቱም ውስጥ አቀፈው፡፡
በመሰዊያው ላይ ሳለ ወደ ዝምትና ተደሞ አደረሰው፡፡ ሰዎች ሁሉ ሥጋዊ እንቅልፍ የሚያንቀላፉ ይመስላቸው ነበር ይላል፡፡

መፅሐፈ ስንክሳር በነፍስ በሥጋ በበጐ ስራ ሁሉ ከወላጆቹ ጋር ፍፁም ነው፡፡ እርሱ እግዚአብሔርን መፍራትንና ትምህርቶችን
ተምሮ አውቋልና፡፡ የቋንቋ ትምህርት እጅግ የሚያውቅ የዮናናውያንን ቋንቋ የሚያነብና የሚተረጉም ለቀና ሃይማኖትም
የሚቀና ሆነ ይለዋል፡፡

ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ በ395ዓ.ም በተወለደ በ60 ዓመቱ አካባቢ በኤጲስ ቆጶስነት ማገልገል በጀመረ በ33 ዓመቱ
ወንድሙ ባስልዮስ ሊጠይቀው መጣ፡፡ በዚያን ጊዜ እጅግ ታሞ ነበር፡፡ ቅዳሴ ይድስ ዘንድ ባስልዮስ አጥብቆ ስለለመነው
ፈቃድን ሊፈፅም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ በዚያም እመቤታችንን አያት፡፡ እርሷም ዛሬ ወደ እኛ ትመጣለህ አለችው፡፡
እንዳለችውም በዚያው ጥር 21 ቀን ዐረፈና ወንድሙ ቀበረው፡፡ ግሪኮች ጃንዋሪ 10 ሮማውያን ማርች 9 ይላሉ፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 33
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ሥራዎቹ እና ትምህርቱ


የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ሥራዎቹ
ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ድንግልና ሕይወትን ምሥጢረ ሥላሴ፣ምሥጢረ ሥጋዌን፣የተመለከቱ ድርሳናት ጿፏል፡፡
የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ትርጓሜ ተንትኗል፡፡

1 ትርጓሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍላት


 አንደኛ እና ሁለተኛ ነገሥት
 መዝሙረ ዳዊት
 መኃለይ መኃልይ ዘሰሎሞን

2 ትምህርቶች
 ስለቅዱሳን
 ስለ ሰማዕትነት
 ስለ ሥነ ምግባር

3 ዶግማ ምሥጢረ ሥላሴ፣ምሥጢረ ሥጋዌን የተመለከተ ሆኖ ለመናፍቃን አይሁድ የጻፋው ትምህርት ነው


4 ሰለ ምንና
5 መልእክታት 29 መልእክታት

የካቲት 1ኛ ሳምንት

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 34
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ


የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዜና ሕይወቱ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በ347ዓ/ም የሶርያ
ዋና ከተማ በነበረችው ከአሕዛብ ወደ ክርስትና የሚገቡ ክርስቲያኖች
መነኃርያ ማዕከል በነበረችውና ክርስቲያኖች መጀመሪያ ‹‹ክርስቲያን››
ተብለው በተጠሩባት በአንጾኪያ ከተማ ተወለደ፡፡አንጾኪያ የምስራቁ ሮም
ግዛት ሁለተኛ ከተማ (ቁስጥንጥንያ ቀጥላ) ነበረች፡፡አራተኛው መቶ
ዓመት የተለያዩ መናፍቃን (መነናውያን፤ግኖስቲኮች፤አርዮሳውያን
አቡሊናርዮሳውን ወዘተ) እንዲሁም አይሁዶችና መምለክያነ ጣዖታት
የሆኑት ሁሉ በአንጾያ ከተማ ሁሉም የየራሳቸውን እምነት ለማስፋፋት
ይሯሯጡ የነበረበት ዘመን ነው፡፡ ኦርቶዶክሳውያኑ ደግሞ በጳጳስ
መላጥዮስና በጳጳስ ጳውሊኖስ መካከል በነበረው ልዩነትና ክፍፍል
ምክንያት ለሁለት ተከፍለው ነበር፡፡ስለዚህ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የወጣትነት ዘመን ቤተ ክርስቲያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ በነበረችበት ጊዜ
ላይ ነበር፡፡
ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ አባቱ አስፋኒዶስ የታወቀ
የጦር መኮንን የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ ገና ሕጻን
እያለ ነበር የሞተው ፡፡እናቱ አትናስያ ትባላለች ፤በሃይማኖትና በምግባር
እጅግ በጣም የተደነቀችና የተመሰገነች ክርስቲያናዊት ሴት ነበረች፡፡ገና በሃያ ዓመቷ ባለቤቷ በሞት ቢለያትም ማንኛውንም
ሁለተኛ ጋብቻ ጥያቄ ሁሉ ባለመቀበል አባታቸው ጥሏቸው የሞቱትን ሁለቱን ልጆቿን ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅንና ታላቅ እኅቱን
በማስተማር ላይ አተኮረች፡
አንቱዛ ልጇ ዮሐንስ አፈወርቅ ፍልስፍናንና ሕግን እንዲሁም የንግግርን ጥበብ በዘመኑ ከነበሩት ታላላቅ መምህራን እንዲማር
አደረገች፡፡እንዲሁም በልጇ አዕምሮ ውስጥ ከልጅነቱ ጀምሮ የእምነትን ዘር ጥሩ አድርጋ ዘራችበት፡፡ይህ የእምነት ዘርም
ለራሱና ለቤተ ክርስቲያን እጅግ ጠቃሚ የሆነ ብዙ ፍሬ አፍርቷል፡፡በእናቱ ተግሳጽና በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ በዘመኑ
ተንሰራፍቶ ከነበረው አሕዛባዊ ነገረ ዘርቅና ከንቱ አስተሳሰብ ተጠበቀ፡፡ሆኖም ግን እስኪያድግ ድረስ አልተጠመቀም ነበር፡፡
ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ ከአህዛብነት ወደ ክርስትና በሽግግር ላይ በነበረበት በዚያን ዘመን የንዑሰ ክርስቲያን ተጠማቂዎች ብዛት
ብዙ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት (እነ ቅዱስ ቄርሎስ ጳጳስ ዘኢየሩሳሌም ፤ራሱ ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ እና ሌሎቹም) ለንዑሰ
ክርስቲያኖች ከመጠመቃቸውና ወደ ቅዱስ ቁርባን ከመቅረባቸው በፊት የሚማሯቸው ወጥና መሠረታዊ ትምህርቶችን
አዘጋጅተዋል፡፡አንዳንድ ክርስቲያን ቤተ ሰብች ሳይቀሩ የልጆቻቸውን ጥምቀት ካላቸው ከፍተኛ ከበሬታ የተነሳና ቶሎ
መጠመቅ የጥምቀትን ጸጋ መልሶ የማጣት ሥጋት አለው ከሚል በዘመኑ ከነበረ የፍርሃት አስተሳሰብ የተነሳ ነበር፡፡ይህም ዛሬ
ብዙች ንስሃ መግባትንና መቁረብን ሊሞቱ እስኪጣጣሩ ድረስ እንደሚያዘገዩት ዓይነት ያ አስተሳሰብ ነው፡፡ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ
በኋላ ላይ ይህ ልማድ ትክክል አለመሆኑን በመግለጥ አጥብቆ ይኮንናል፡፡
ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ በዘመኑ የነበረውን የንግግር ጥበብ ትምህርት ከሊባንዮስ ከተባለው መምህር ተምሯል፡፡
ፍልስፍናንም በዘመኑ አሉ ከተባሉ መምህራን ተምሯል፡፡በአጠቃላይ ዕውቀቱና ማስተዋሉ አብረውት ከሚማሩት ሁሉ በላይ
የነበረ ትጉህ ተማሪ ነበር፡፡እንዲያውም መምህሩ ሊባንዮስ ሊሞት ሲል ‹‹ማን ቢተካህ ትወዳለህ ;›› ብለው ቢጠይቂት
‹‹ክርስቲያኖች ከእኛ ሰርቀው ባይወስዱት ኖሮ የሚተካኝ ዮሐንስ ነበር›› ማለቱ ይነገራል፡፡ቅ/ዮህንስም ትምህርቱን እንደጨረሰ
ለትንሽ ጊዜ ጠበቃ ሆነ፡፡ይህም ሥራ ለመንግሥት ሹመትና ሥልጣን ዋና በር ከፋች ነበር፡፡ቤቶች ውስጥ የንግግር ክህሎትንና
ልዩ ተሰጥዖን ማሳየት ለታላላቅ ሹመቶች ከሚኒስትርነት እስከ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ድረስ ሊደርስ የሚችል ዋና ጥርጊያ ጎዳና
ነበር፡፡በፍርድ ቤት የሚያደርጋቸው ንግግሮቹ በሰማያኑና በመምህሩ በሊባንዮስ ሳይቀር ከፍተኛ አድናቆትን አስገኝቶ ነበር፡፡
ሆኖም ግን እርሱ በነዚህ ነገሮች ሆሉ ደስተኛ አልነበረም የልቡ ምኞትና ሐሳብ ቤተ ክርስቲያን ነበር፡፡ለክርስትናው ትልቅ
ፍቅር ነበረው፡፡ ከዚያም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ መማር ጀመረ፤ቅዱሳት መጻሕፍትን ተማረ ፤በተለይም ከጳጳሱ መላጥዮስ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 35
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ጋር ተዋወቀ በጊዜውም ካደጉ በኋላ ከሚጠመቁበት የ3ት ዓመት ትምህርት ተምሮ በ23 ዓመቱ በ370ዓ/ም በጳጳሱ መላጥዮስ
እጅ ተጠመቀ፡፡
ቅ/ዮሐንስም ከጊዜ ወደ ጊዜ ሃይማኖቱና ምግባሩ ተወዳጅነትን አገኘ በተለይም ለጳጳሱ መላጥዮስ ይህንንም
አይቶ የአናገጉንስጢስነት(የአንባቢነት ማዕረግ) ሾመው፡፡እርሱ ግን ፍላጎቱ የነበረው በገዳም ገብቶ በምንኩስና ሕይወት መኖር
ነበር፡፡ትንሽ ትንሽ እያለም የጾምና የጸሎት ሕይወትን አጠንክሮ ያዘ፡፡ለስጋው ምቾትና ድሎትን ነፈገውም የገዳማዊ ሕይወትን
መኖር ጀመረ፡፡በቤተ ክርስቲያንም የሚያገለግሉ ካህናትና ሕዝብ እርሱንና ጓደኛው የነበረውን ባስልዮስን ጵጵስና ሊሾሟቸው
ፈለጉ፡፡እርሱ ግን እኔ ለዚህ ከባድ የቤ/ክ ኃላፊነት የሚያበቃውና የሚጠቅመው ወንድሜ ባስልዮስ ነው፡፡በማለት ባስልዮስ
እንዲሾ ለማድረግ እርሱ ተደበቀ፡፡ባስልዮስ ይህንን ሹመት የተቀበለው ጓደኛው ቅ/ዮሐንስም አብሮ የሚሾም መስሎት ነበር፤
ባስልዮስም ጳጳስ ተደርጎ ተሾመ ፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የጵጵስና ሹመት

ቅ/ዮሐንስ ምንም ከባስልዮስ ጋር ለጊዜው ባይሾም በኋላ ግን ለመቀበል ችሏል፡፡በ347 ዓ/ም የቁስጥንጥንያ
ፓትርያርክ የነበረው ኔክታርርዮስ ዐረፈ፡፡በዚያን ጊዜ ክፍት በሆነው በሮም ምስራቃዊ ግዛት ወዋና ከተማ በቁስጥንጥንያ
መንበር ላይ ለመሾም በገሃድም ሆነ በስውር አጠቃላይ የሆነ ሽኩቻ ነበር፡፡ሆኖም ከትንሽ ወራት በኋላ በመንበሩ ላይ ለመተካት
ሲናፍቁ ሆኖም ከትንሽ ወራት በኋላ በመንበሩ ላይ ለመተካት ሲናፍቁ የነበሩትን ጳጳሳት የሚያስደነግጥ ነገረ ተሰማ የአንጾኪያ
ምዕመናን አባታችንን አንሰድም ብለው ረብሻ እንዳያስነሱና ሁከት እንዳይፈጠር ከእርሱ በከራሱም ሆነ ሌላ የሚመጣውን
ተቃውሞ ዋጋ ቢስ ለማድረግ በዘዴ ከከተማው እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ ከቤተ መንግስት በተላከ አጃቢ በአስቸኳይ ወደ
ቁስጥንጥንያ ተወሰደ፡፡የአንጾኪያው ገዢ የነበረው ሰው የንጉሡ ትእዛዝ እንደደረሰው ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅን ከከተማ ውጪ
ወደሚገኝ አንድ ቤተ ክርስቲያን አብሮት እንዲሄድ ጠየቀው፡፡በእርሱ ሠረገላ ላይ እንደ ተቀመጠለትም ወዲያውኑ በፍጥነት
ወደ ቁስጥንጥንያ ሊወስዱት ተዘጋጅተው የሚጠብቁ መኳንንትንና ወታደሮች ወደ ነበሩበት ወደ ቁስጥንጥንያ ወደሚወስደው
ጎዳና ይዞት ሄደ፡፡በቤተ ክርስቲያን ታሪክና በቅዱሳን መዝገብ የጎላና ደማቅ ስምና ክብር ሊያሰጡት ወዳሉት የፈተናዎችና
የተጋድሎዎች መድረክ በዚህ ዓይነት ድንገተኛ ሁኔታ ተወሰደ፡፡ወዴትና ለምን እንደሚወስዱት ያወቀው ቁስጥንጥንያ ከደረሰ
በኋላ ነበር፡፡እንዲያ ባለ ሁኔታ ያለ ፈቃድና ያለ ውዴታው ፈቃደኝነቱን እንኳን ሳይጠየቅ በድንገት የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳ
እንዲሆን ተደረገ፡፡የካቲት 26 ቀን 398ዓ/ም ብዙ ጳጳሳት ባሉበት በታላቅ ሥነ ሥርዓት በቁስጥንጥንያ መንበር ላይ 23ኛው
የእስክንድርያ ፓትርያሊክ በነበረው በቴዎፍሎስ እጅ ፓትርያርክ ተደርጎ ተሸመ፡፡ፓትርያርክ ቴዎፍሎስም ያለውዴታው
በንጉሡ በአርቃዴዎስ ትእዛዝ ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ ወርቅ ለመሾም ተገደደ፡፡ቴዎፍሎስም በቁስጥንጥንያ መንበር ላይ ለመሾም
የራሱ ዕጩ አዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም ይህን ማድረግ እንደማይችል በመረዳቱ የንጉሡን ትእዛዝ ፈጸመ፡፡ ዮሐንስ አፈወርቅም
ገና እንደተሸመ ያደረገው ነገር ለብዙ ጊዜ ዘልቆ የነበረውን የአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ችግር መፍታት ነበር፡፡
ዮሐንስ ‹‹አፈወርቅ›› ስለመባሉ
ዮሐንስ ‹‹አፈወርቅ›› ብላ ስም ያወጣችለት ቤተ መቅደስ የነበረች ስዕለማርያም ናት ፡፡በቁስጥንጥንያ እያለ
በዚያ የሁለት ባህርይ ምንፍቅና ትምህርትን በልቡ የቋጠረ ንስጥሮስ ነበር፡፡ንስጥሮስ ምንፍቅናውን ሊቀ ጳጳስ ሆኖ
እስኪሾምበት ጊዜ ድረስ አልገለጣትም፡፡ከጊዜያትም በአንዱ በዓል ዕለት ምዕመናኑ ቅርባን ሲቀበሉ አንዲት በወር ግዳጅ(የወር
አበባ) ላይ ያለች ሴት ሳትነጻ ልትቀበል ቀረበች፡፡ሕዝቡም የመንፈስ ቅዱስ ጥላ ከእርሷ ሲርቅ አዩ፡፡የጸሐይ ጮራም በራሷ
ላይ አላረፈም፡፡ሕዝቡም ፓትርያርክ ወደሆነው ንስጥሮስ ፊት አቆሟት ፡፡አንቺ ሴት ንገሪኝ የመንፈስ ቅዱስ ጥላ ካንቺ
እስኪጠፋ ድረስ ኃጢአትሽ ምንድር ነው፡፡ንስጥሮስም ተቆጥቶ የሥጋዋ ዕርቃን እንደተገለጠ ቁልቁል ይሰቅሉት ዘንድ አዘዘ፡፡
እግዚአብሔር በዚህ ስጋ ከማርያም ከተወለደ መንፈስ ቅዱስ ይህችን ሴትእንደምን ናቃት፡፡እግዚአብሔር ከሴት ከተወለደ
በማርያም ምክንያት ሴቶች ሁሉ ርኩሰታቸው በተቀደሰ ነበር አለ፡፡ሕዝቡም ሁሉ ወደርሷ ቀርበው እግዚአብሔር በዚህ ሥጋ
ከሴት እንደተወለደ የሚያምን የተለየ ይሁን እግዚአብሔር በመወለጃ ማኅጸን እደተወሰነ የጡት ወተት በመመገብ በሴቶች
የመወለድ ሥርዓት ነው ሁሉ ሕጻናትን እንደመሰላቸው የሚያምን የተረገመ ነው እያሉ በአፍረተ ሥጋዋ ላይ ምራቅ እንዲተፉ
አዘዘ፡፡ ያንጊዜ ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ጠርዜቤጤር(ቀሲስ) በዚያ ነበር፡፡እንዲህ አለ‹‹እኔ እግዚአብሔር በድንግልና ወተት
እንዳደገ በሕጻናትም ሥርዓት ሕጻናትን እንደመሰላቸው ከብቻዋ ከኃጢአትም በቀር የሰውን ሕግ ሁሉ እንደፈጸመ አምናለሁ››
ብሎ ኃፍረተ ስጋዋን በአፉ ሳመ፡፡በቤተ መቅደስም የነበረ የእመቤታችን ስዕል ‹‹አፈወርቅ›› ብላ ጠራችው፡፡ከዚያን ጊዜም
በኋላ ‹‹ዮሐንስ አፈወርቅ›› እየተባለ የተጠራው፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 36
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ታላቁ ሊቅ ኢትዮጵያዊው ዮሐንስ አፈወርቅ የተሰኘ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስለርሱ ሲያደንቁ ‹‹እኔም ስለርሱ እላለሁ
በእውነት አፈወርቅ ፤አፈ ዕንቁ፤አፈ ጳዝዮን በድርሰቱ ቤተ ክርስቲያንን የሚያጌጣት አፈ ባህርይ በእውነት አፈ መዓር በቃ
ጣፋጭነት ምዕመናንን የሚያለመልማቸው አፈ ሦከር በእውነት በትምህርቱ መዓዛ የምስጢር በጎችን ደስ የሚያሰኛቸው አፈ
ሽቱ አፈ ርኄ ነው፡፡በእውነት በውግዘቱ ሥልጣን ከሃዲዮችን የሚቆርጥ አፈ ሰይፍ ፤አፈ መጥባህት ነው፡፡በእውነት
የማይነዋወጥ ዓምድ የማይፈርስ መሠረት በእውነት ከሞገዶች መነሳት የሚዋኝ ዋናተኛ ነው በእውነት የማይፈርስ ግንብ
በጠላት ፊት የሚጸና አዳራሽ ነው›› መጽሐፈ ምስጢር ገጽ 37 ተአምኖ ቅዱሳን በተባለው መጽሐፉት ‹‹ሰላም ለዮሐንስ አፉሁ
ዘወርቅ ለጳጳሳት ሊቅ እለይነባ ከናፍሪሁ ምድራሳተ ጽድቅ -ከናፍሮቹ የእውነት ድርሳናትን የሚናገሩ የጳጳሳት አለቃቸው አፉ
የወርቅ የተባለ(ለሆነ) ለዮሐንስ ሰላምታ ይገባል››

የካቲት 2ኛ ስምንት
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት እና ሥራዎች
ከትርጓሜ ሥራው ጥቂቱን ብንመለከት የብሉይና የሐዲሰ ኪዳን ትርጓሜ ሲገኙ፡-
1. ስሳ ሰባት የትርጓሜ ድርሳናት በኦሪት ዘፍጥረት
2. ዐምሳ ዘጠኝ የትርጓሜ ድርሳናት በመዝሙረ ዳዊት
3. የኢሳይያስ ትንቢት ምዕ አንድ ሐተታ
4. የመጽሐፈ ኢዮብ የተወሰኑ ክፍሎች
5. የመጽሐፈ ምሳሌ የተወሰኑ ክፍሎች
6. የትንቢተ ኤርምያስና ዳንኤል የትርጓሜ ድርሳናት እና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡
7. ዘጠና የትርጓሜ ድርሳናት በማቴዎስ ወንጌል ላይ
8 .ሰማንያ ስምንት የትርጓሜ ድርሳናት በዮሐንስ ወንጌል ላይ
9. ዐምሳ ዐምስት የትርጓሜ ድርሳናት በግብረ ሐዋርያት ላይ
10 .ሠላሳ ኹለት የትርጓሜ ድርሳናት ወደ ሮሜ ሰዎች
11. አርባ አራት የትርጓሜ ድርሳናት በ፩ኛ ቆሮንቶስ ላይ
12. ሠላሳ የትርጓሜ ድርሳናት በ፪ኛ ቆሮንቶስ ላይ
13.ኻያ አራት የትርጓሜ ድርሳናት ወደ ኤፌሶን ሰዎች
14. ዐሥራ ዐምስት የትርጓሜ ድርሳናት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች
15. ዐሥራ ኹለት የትርጓሜ ድርሳናት ወደ ቆላስይስ ሰዎች
16. ዐሥራ አንድ የስብከት ድርሳናት በ፩ኛ ተሰሎንቄ
17. ዐምስት የትርጓሜ ድርሳናት በ፪ኛ ተሰሎንቄ
18. ዐሥራ ስምንት የትርጓሜ ድርሳናት በ፩ኛ ጢሞቴዎስ
19. ዐሥር የትርጓሜ ድርሳናት በ፪ኛ ጢሞቴዎስ ላይ
20. ስድስት የትርጓሜ ድርሳናት ለቲቶ
21. ሦስት የትርጓሜ ድርሳናት ለፊልሞና
22. ሠላሳ አራት የትርጓሜ ድርሳናት ለዕብራውያን ሰዎች
ሌሎች ሠላሳ ስድስት የትርጓሜ ድርሳናት አሉት፡፡

በጥበብና በዕውቀት የተመሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም ቅድሳት መጻሕፍትን
በጥልቀት በመመርመራቸው ምክንያት በብዙ ሺሕ የሚቈጠሩ ጥበብ መንፈሳዊና ጥበብ ሥጋዊን የያዙትን መጻሕፍት ብራና
ዳምጠው፣ ቀለም በጥብጠው፣ ብርዕ ቀርጠው በብዙ ድካም ጽፈውና ተርጉመው ዐልፈዋል፡፡ በዚኽም ከ30 በላይ የሚኾኑ
የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን መጻሕፍት ወደ ግእዝ ቋንቋ ተርጒመው የጻፉልን ሲኾን፤ በአኹን ጊዜ ግን ብዙዎቹ በስርቆት
ጠፍተዋል፤ በውጪ ሀገራት ቤተ መጻሕፍት ተቀምጠዋል፤ እኩሌቶቹም መርማሪ በማጣት እንደተቀመጡ አሉ፡፡

በግእዝ በቀደሙት አባቶቻችን ተተርጒመው ከነበሩት ውስጥ፡-

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 37
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

1) ድርሳን ዘልደት ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ፡-“ዮም ተወልደ ቀዳማዊ ወኮነ በዘዚኣሁ ውእቱ አምላክ ቀዳማዊ…” (ቀዳማዊ አምላክ ዛሬ
ተወለደ፤ ጥንቱን ገንዘቡ ባይደለ ባሕርይ ተገኘ፤ ርሱ ቀዳማዊ አምላክ ነው፤ ሰው በመኾኑም ባሕርዩ አልተለወጠም…) ይላል
2) ድርሳን በእንተ እስጢፋኖስ ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ (ስለ እስጢፋኖስ)
3) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ ኤጲፋንያ (ስለ መገለጥ)
4) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ ዘሳኒታ ጥምቀት (ስለ ጥምቀት ማግስት)
5) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ ዘሣልስ ጥምቀት በእንተ ቃና ዘገሊላ (ስለ ቃና ዘገሊላ)
6) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ ሕፃናት ዘቀተሎሙ ሄሮድስ (ሄሮድስ ስለገደላቸው ሕፃናት)
7) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ ብእሲት ዘቀብዐቶ ዕፍረተ (ሽቱ ስለቀባችው ሴት)
8) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ ስምዖን (ስለ ስምዖን)
9) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ ሰንበተ ሆሣዕና (ስለ ሆሣዕና ሰንበት)
10) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ ትንሣኤሁ (ስለ ጌታ ትንሣኤ)
11) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ ዘበዓለ ትንሣኤ (ስለ ትንሣኤ በዓል)
12) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ አንስት (ስለ ቅዱሳት ሴቶች)
13) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ ፋሲካ (ስለ ፋሲካ)
14) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ ካልዕ በእንተ ፋሲካ (ስለ ፋሲካ ሌላ)
15) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ አልዓዛር (ስለ አልዓዛር)
16) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ ሳምራዊት (ስለ ሳምራዊቷ ሴት)
17) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ ቶማስ (ስለ ቶማስ)
18) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ ዘርክበ ካህናት (ስለ ርክበ ካህናት)
19) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ ዘበዓለ 50(ስለ በዓለ 50)
20) ድርሳነ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ካልዕ በእንተ ቁርባን (ስለ ቁርባን)
21) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ ዘገብርኤል ወዘዘካርያስ በገሊላ
22) ድርሳን ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ ዕርገት (ስለ ዕርገት)
23) ድርሳነ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ሣልስ ዘበዓለ 50 (የዕለተ ፍዳን ነገር የሚናገር፤ ነፍስ ከሥጋ ስትለይ ያልታዘዘችውን ጽፈው
ያሳይዋታል የሚል) በተንቤን ደብረ ዓሣ በክብራን ገብርኤል የሚገኝ
24) ድርሳን ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ (የታተመ)
25) ተግሣፅ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ (የታተመ)
26) ግእዝ በግእዝ ትርጓሜ ላይ በዘፍጥረት እና በሐዲሳት ላይ “ከመዝ ይቤ ዮሐንስ አፈ ወርቅ” እያለ ተጠቅሷል፡፡ ይኽም
የትርጓሜ መጻሕፍቱ እንዳለ አመላካች ነው፡፡
27) በሃይማኖተ አበው ላይ የሚገኝ 10 ምዕራፍ ያለው ከተለያዩ ትርጓሜዎቹ ከዮሐንስ ወንጌል ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት
ትርጓሜያቱ የተውጣጡ
28) የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ፍሬ ቅዳሴው
29) በእንተ ዕፀ በለስ ዘረገማ እግዚእ በቢታንያ (በ122ቁጥር የተከፈለ) (ጌታ በቢታንያ መንገድ ስለረማት በለስ)
30) “እንዘ ሀሎ ዕራቆ በውስተ ገነት በአይኑ ቆጽል ሰፍዮ ዘተከድነ ወለብሰ እምኔሃ ዐጽፈ…” (አዳም በገነት ዕርቃኑን ኹኖ በየትኛው
ቅጠል ነበር መሸፈኛ ሠፍቶ ዕርቃኑን የሸፈነ?ይኽቺ ቅጠል እንዴት እንደደረቀች አየኽን? አዳም የለበሳት ዕርቃኑን የሸፈነባት
አይደለችምን? ጌታ ኢየሱስ ወደ ለመለመችው የበለስ ዛፍ መጥቶ አዳም ዕርቃኑን የሸፈባትን ቅጠል በቃሉ አደረቃት፤ አዳምን
ድኻ ኹኖ ስለ አገኘው ንጹሕ የኾነ የብርሃንን ልብስ ሰጠው፤ ይኸውም ብርሃን ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ የተሠራ ነው፤ የበለስን
ቅጠል አድርቆ የነፍሱን ድኅነትን ሰጠው…) (ቍ 50-53) እያለ ይቀጥላል፡፡
31) ድርሳን ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ ዐሥሩ ደናግል” (83 ቁጥር ያለው) (ስለ ዐሥሩ ደናግል) “አይ ውእቱ ግምዔ ዘወደያ
ውስቴቱ ቅብዐ ዘእንበለ ዳዕሙ ከርሦሙ ለርኁባን ነዳያን እለ ግዱፋን በኀዋኅወ አብያተ ክርስቲያን…” (በውስጡ ዘይት
የጨመሩበት ማሰሮ የቱ ነው? በየአብያተ ክርስቲያኑ ደጅ በየዐደባባዩ በየገበያው የወደቁ የተራቡ ድኆች ኾዳቸው ነው እንጂ፤
ለጦም አዳሪዎች ምጽዋትን ባደረጉ ጊዜ በርኅራኄያቸው ዘይትነት መብራታቸውን አበሩ…) እያለ የሚቀጥል እጅግ ድንቅ
ትርጓሜ አለው፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 38
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

32) ትርጓሜ ወንጌላት ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ (የአራቱ ወንጌላት ትርጓሜ) በስመ አብ ..... ንዌጥን በረድኤተ እግዚአብሔር
ብለው የሚጀምሩ በግእዝ የተተረጎሙ መጻሕፍት አሉን፨
በጊዜያችን በቀሪው እና በምድራዊ ባዶ ሥራ በመወጠራችን እንደ ቀደምት አበው የቅዱሳት መጻሕፍት የንባብ፣
የመመርመር፤ የመራቀቅ ፍቅር ከልባችን ስለቀዘቀዘ የግእዝ መጻሕፍቱን እንኳን መተርጎም ያሉበትንም የሚያውቁ ጥቂቶች
በመኾናቸው ዘመነ ሊቃውንትን ይመልስልን እንላለን፨ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምኆ ቅዱሳን አስደናቂ መጽሐፉ
ላይ ታላቁን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን፡-

የካቲት 3ኛ ሳምንት
ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ
የቅዱስ አትናቴዎስ ዜና ሕይወቱ
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሐዋርያት ቀጥሎ
የቅዱስ አትናቴዎስን ያህል ስለ ሃይማኖት የተዋጋ ቅዱስ ፈልጐ
ማግኘት አይቻልም፡፡ቅዱስ አትናቴዎስ በቤተ ክርስቲያን
ትውፊት መሠረት በዘመነ ሰማዕታት መጠናቀቂያ በ296/300
ዓ.ም አከባቢ እስክንድርያ ግብፅ ውስጥ ነው የተወለደው::
ወላጆቹ አረማውያን በመሆናቸው ክርስትናን አልተማረም
ነበር:: አሞጽን ከእረኝነት ሐዋርያትን ከአሳ አጥማጅነት የጠራ
እግዚአብሔር አምላክ አትናቴዎስን ከጨዋታ ሜዳ ጠርቶ
የቤተክርስቲያን ወርቃማ ልጅ አድርጎታል፡፡ ሕጻን እያለ
ለጫዋታ ከቤቱ ሲወጣ የክርስቲያን ልጆች ሃይማኖታዊ
ጨዋታ ሲጫወቱ ተመለከተ:: ሊቀላቀላቸው ቢፈልግም
ክርስቲያን ባለመሆኑ ከለከሉት:: አትናቴዎስም ክርስቲያን
ልሁንና አጫውቱኝ ቢላቸው እሺ ስላሉት ሕጻናቱ ዕጣ
ተጣጣሉ:: ላንዱ ቄስ: ላንዱም ዲያቆን መሆን ሲደርሳቸው
ለአትናቴዎስ ፓትርያሪክ መሆን ስለ ደረሰው ሌሎቹ ሕጻናት
ይሰግዱለት ጀመር:: በአጋጣሚ ሕጻናቱ ይሕንን ሁሉ
ሲያደርጉ የወቅቱ ፓትርያሪክ ቅዱስ እለ እስክንድሮስ
በመገረም ያያቸው ነበርና ለሕጻኑ አትናቴዎስ ትንቢት
ተናገረለት::
ከዚያም የአትናቴዎስ አባቱ ሲሞት ሊቀ
ዻዻሱ ከእናቱ ወስዶ አጥምቆ የሚገባውን መንፈሳዊ
ትምሕርት ሁሉ በልቡናው ላይ ቀረጸበት:: ከዚህ በኋላ ዲቁናን ሹሞ አስተምር አለው:: ምንም ሕጻን ቢሆንም ከሊቅነቱ:
ከአመላለሱና ከአንደበቱ ጣፋጭነት የተነሳ የሰማው ሁሉ ይደነቅ ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ አድራለችና::ቅዱስ
አትናቴዎስ ሊቀ ዲቁና በተሾመ ወራት አርዮስ ቤተ ክርስቲያንን በመረበሹ ኒቅያ ላይ 318ቱ ሊቃውንት ሲሰበሰቡ ጸሐፊ
አድርገው ሾሙት:: በጊዜውም በዕድሜ የስንት ጊዜ ትልቁ የሚሆነውን አርዮስን ተከራክሮ ምላሽ አሳጣው:: ቅዱስ አትናቴዎስ
ከሊቃውንቱ ጋር ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: እግዚአብሔር መሆኑን በአደባባይ መሠከረ:: ጸሎተ
ሃይማኖትንም ያረቀቀው እርሱ ነው::
ፓትሪያሪክ አለ እስክንድሮስ ባረፈ ጊዜ በመንበሩ አትናትዮስን ይሾሙት ዘንድ አሳስቧቸዉ ነበር ህዝቡም ጸጋ
እግዚአብሔር የበዛለት እንደሆነ ስለ ተረዱ ሊሾሙት ወሰኑ ቅዱሱ ግን እኔ ምናምንቴ ነኝ ለዚህ ክብር የምገባ አይደለሁም
ሲል እራሱን በተራራዎች ስር ደበቀ፤ ህዝቡ ግን ፈልገዉ አመጡት፤ ከዚህ በኃላ በ33 ዓመቱ በ328 ዓ/ም የእስክንድርያ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 39
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

(የግብፅ) 20ኛ ፓትርያሪክ ሆኖ ተሾመ:: ከቅዱስ እንጦንስ ምንኩስናን የተቀበለ የመጀመሪዉ ፓትርያሪክ ነዉ፡፡ የምንኩስና
ልብሱንም የጳጳሳት ዩኒፎርም እንዲሆን አድርጓል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን በመልካም እረኝነት ለ48 ዓመታት ሲመግብ ብዙ
መከራዎችን ተቀብሏል::

ቅዱስ አትናቴዎስ ለኢትዮጵያ


በ328 ዓ.ም. ቅዱስ ፍሬምናጦስ በእስክንድርያ ቤተክርስቲያን ፓትርያሪክን ለኢትዮጵያ ለማሾም በመጠባበቅ ላይ
እያለ 19ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ አለ እስክንድሮስ አርፎ በምትኩ በእስክንድርያ መንበር ቅዱስ አትናቴዎስ ተተካ፡፡በዚህ
ጊዜ ፍሬምናጦስ የተላከበትን ጉዳይ ለቅዱስ አትናቴዎስ አቀረበ ፓትርያሪክ አትናቴዎስም በጉዳዩ ተደስቶ ለኢትዮጵያ
ክርስቲያኖች ቋንቋቸውንና ባህላቸውን የሚያውቅ ሌላ ባለመገኘቱ ራሱን ቅዱስ ፍሬምናጦስን ‹‹ጳጳስ ዘአክሱም ወዘኩሉ
ኢትዮጵያ›› ብሎ የመጀመሪያዉን ጳጳሳችንን በቅብአትና በአንብሮተ እድ ሹሞ ላከው፡፡

መከራዉና ስደቱ
የቅዱስ አትናቴዎስን መከራዉንና የስደት ሕይወቱን ማወቅና መረዳት በተለይ የአራተኛውን መቶ ዓመት፣
በአጠቃላይ ደግሞ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የተመሠረተችውን የቤተ ክርስቲያንን የዚህ ዓለም የመስቀል ጉዞ መረዳት ነው፡
፡ ይህ አራተኛው መቶ ዓመት ደግሞ ምንም እንኳን ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር እጅ ቢሆንም እንደ ሰው ስንመለከተው ግን
የቤተ ክርስቲያንን መሠረታዊ አቅጣጫ ሊያስለውጡ የደረሱ ከባድ ኑፋቄያዊ ፈተናዎች የተነሡበት ዘመን ነበር፡፡
ቤተ ክርስቲያን ከግማሽ ምዕተ ዓመት ለሚበልጥ ዘመን ከአርዮሳውያን ጋር ላደረገችው እልህ አስጨራሽ ትግል መለያ ግርማና
ወካይ መገለጫው ቅዱስ አትናቴዎስ ነው፡፡ ዘመን ገጠሙ የነበረው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ የቅዱስ
አትናቴዎስን ተጋድሎ በተመለከተ ሲናገር‹‹ አትናቴዎስን ሳመሰግን የማመሰግነው የመልካም ተጋድሎ ሕይወትን ነው፤ ስለ
እርሱ መናገርና ስለ መልካም ተጋድሎ ሕይወት መናገር አንድ ናቸውና፣ ምክንያቱም እርሱ የመልካም ተጋድሎ ሕይወትን
በምልዓት ገንዘብ አድርጓልና ›› ያለው ለዚህ ነበር፡፡
ቅዱስ አትናቴዎስ በዘመኑ ለ5 ጊዜ ከመንበሩ አፈናቅለው ወደ በርሃ እንዲጋዝ አድርገዉታል፡፡ (በስደት ከ15/16 ዓመታት በላይ
አሳልፏል)፡፡ ቅዱሱ በተሰደደባቸው ቦታዎች መከራን እየተቀበለ ያላመኑትን አሳምኗል:: በጎቹ እንዳይባዝኑበት ደግሞ በጦማር
(በደብዳቤ) ይጠብቃቸው ነበር:: ዛሬ በሃይማኖተ አበው የምናገኘው ቃለ ሃይማኖት በዚህ ዘመን የተጻፈ ነው::
· የቅዱሱ የመጀመሪያ ስደቱ መንስኤ የአርዮሳዊያን መናፍቃን የሐሰት ክሶች ነበሩ አትናቴዎስም በጉባኤ መዓል
ሐሰተኝነታቸዉን አጋልጦ ንጽሕናዉን አስመስክሩዋል፡፡ በዘመኑ የነበረዉ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ንጽህናዉን ቢረዳም እነዚህ
መናፍቃን እርሱን ለማጥፋት ቆርጠዉ እንደተነሱ ስለተረዳ ከነሱ ሊሰዉረዉ ሲል ወደ ትሬቬሬ እንዲጋዝ አደረገዉ::
· ሁለተኛ እና ሶስተኛ ስደቱ ደግሞ (ትንሹ ቆስጠንጢኖስ) የአባቱን (ታላቁ ቆስጠንጢኖስን) ዕረፍት ተከትሎ ነገሠ::
ወዲያውም አርዮሳዊ መናፍቅ ሆነ:: ሃይማኖታቸው የቀና አባቶችንም ያሳድድ ገባ:: ከአበው ቅዱሳን መካከል ግን የዚህ መከራ
ቀዳሚው ገፈት ቀማሽ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ አትናቴዎስ ነበር:: ከ መንበሩም ሁለት ጊዜ አፈናቅሎታል፡፡ በተለይ አንድ ጊዜ ቅዱሱን
ወደ በርሃ አግዞ: መናፍቅ ዻዻስ በግብጽ ሹሞ: ብዙ ክርስቲያኖችን በግፍ ሲያስገድል: ቅዱሱን ለ6 ዓመታት አሰቃየው:: የወገኖቹ
(የልጆቹን) ስቃይ የሰማው ቅዱስ አትናቴዎስ ግን በድፍረት ወደ ቤተ መንግስት ገብቶ ተናገረው:: ሁለት አማራጭን አቅርቦ
"ወይ ግደለኝና እንደ አባቶቼ ሰማዕት ልሁን: ካልሆነ ግን ወደ መንጐቼ (ምዕመናን) መልሰኝ" አለው:: መናፍቁ ንጉሥም
ቢገድለው ብጥብጥ እንደሚነሳ ስለሚያውቅ በስልት ሊያጠፋው ወሰነ:: ቀዛፊ መቅዘፊያ ምግብና ውሃ በሌላት ጀልባ ውስጥ
ከቶም ሜዲትራኒያን ባሕር ውስጥ ጣለው:: ድንገት ግን ከሰማይ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ ወረደ:: ሚካኤልና ገብርኤል
ባሕሩን እየቀዘፍ: ሌሎች መላእክት እየመገቡት እስክንድርያ (ግብጽ) አድርሰውት ተሠውረዋል:: ሕዝቡም በታላቅ ሐሴት
እየዘመሩ አባታቸውን ተቀብለውታል:: ቀጥሎም ንጉሡ አረማዊዉ ዮልዮስ ሲነግስ ቅዱሱ ጣኦት አምላኪዎችን እያሳመነ
ያጠምቅ ነበርና በዚህ ስራዉ ተናዶ ሊያሲዘዉ ትእዛዝ አዘዘ በዚህም ንጉሱ እስኪሞት ድረስ በስደት ቆየ፡፡በመጨረሻም ንጉስ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 40
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ጁቪያን ሲነግስ አሪዮስያዊ ነበርና 30 ጳጳሳትን አስገደለ አትናትዮስም በመቃብር ቤት ተሸሸገ ነገር ግን ንጉሱ የሕዝቡንና
የጳጳሱን ጽናት ሲመለከት አትናትዮስን ወደ መንበሩ መለሰዉ፡፡ አትናትዮስ በዚህ ጊዜ 72 ዓመት ሞልቶት ነበር በብዙ
እንግልትም ደክሞ ነበር ቢሆንም ግን ለሕግ የቆመ ጠንካራ የቤ/ክ ታላቅ ጠበቃ ነበር፡፡ ቅዱሱ ብቻዉን የሮማዉያን ቄሳሮችን
ዛቻና ኃይል ያለ ምንም ፍርሃት የተጋፈጠ ልዩ ጀግና ነዉ፡፡ በዚያ ዘመን የነበረዉ በቅዱስ አትናትዮስና በ አሪዮስያዊያን መካከል
የተካሄደዉ ተጋድሎ ‹‹አትናቴዎስ ከዓለሙ ጋር፤ ዓለሙም በአትናቴዎስ ላይ›› "Athanasius against the world." ብለዉ
ገልጸዉታል፡፡
አትናቴዎስ በዘመኑ ሁሉ በቤተ ክርስቲያን የተቃጣዉን ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ዘመቻ ሲዋጋ የኖረ ታላቅ የቤተ
ክርስቲያን አርበኛ ነዉ፡፡ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ አትናቴዎስን ‹‹ የቤተክርስቲያን ምሶሶ›› ይለዉ ነበር፡፡ አትናትዮስ ሃይማኖተኛ፤
ጀግና፤ ዘዴኛ፤ ታላቅ የትህትና አባት እና የሚያስደሰት ጥበብን አሙዋልቶ የያዘ ነበር፡፡ ቅድሱ በሕይወት ዘመኑ ብዙ
ሃይማኖታዊ ሥራዎችን ሠርቶ አልፏል፡፡ ሐዋርያዊው ቅዱስ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋግቶ: ብዙ ስቃይንም ተቀብሎ በ 75 ዓመቱ
ግንቦት 7 ቀን በ373 ዓ/ም አካባቢ አርፏል:: ቤተ ክስርቲያን "ሊቀ ሊቃውንት፤ ርዕሰ ሊቃውንት፤ የቤተ ክርስቲያን (የምዕመናን)
ሐኪም (Doctor of the Church)፤ ሐዋርያዊ፤ የሕይወት ምንጭ" ብላ ትጠራዋለች::

የቅዱስ አትናቴዎስ ሥራዎቹ


ከሊቅነቱ የተነሣ ቅዱስ አትናቴዎስ በርካቶች የነገረ መለኮትን መጻሕፍትን የጻፈ ሲኾን ከእነዚህ መኻከል፦
 የኦሪት ዘፍጥረት ትርጓሜ
 የመዝሙረ ዳዊት ትርጓሜ
 የመኃልየ መኃልይ ትርጓሜ
 ገድለ አባ እንጦንስ
 የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት
 ለአርዮስ ክሕደት መልስ
 የአካላዊ ቃል ሥጋዌ
 የጉባኤ ኒቅያ ውሳኔና የሃይማኖት መግለጫ
 የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ቀኖና እና ሌሎችም መጻሕፍት ጽፏል፨
ስለ ቀናችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ በአርዮሳውያን መሪዎች ለ5 ጊዜ ተግዟል፨
የቅዱስ አትናቴዎስ ትምህርት
ስለ እግዚአብሔር መግቦት
ህዝቡን ስለጎበኘና የቅርታ ስላደረገለት የእስራኤል አምለክ ይመስገን ብሎ ትምህርቱን በእግዚዘብሔር መግቦት
ላይ በመጀመር ከእርሱ በፊት የነበረውን የፕላቶናውያን የፍልስፍነ አስተሳሰብ ሽሯል ፡፡ እግዚአብሔር ልዑል ምጡቅ ይሁን
በመግቦቱ በረድኤት ከፍጥረቱ የተለየ አይደለም፡፡ቅዱስና ሰው ወዳጅ አምላክ ነው፡፡በአምሳሉ በአርአያው የፈጠረው ሰው
ለእርሱ ፍጹም የሆነ ግኑኝነት እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ሕይወቱ ከእርሱ ፈቃድ ጋር እንዲስማማ ይፈቅዳል እና በሰው ልጀ
የታሪክ ጉዞ ውስጥ እየተገኘ ይመራዋል ይደግፈዋል፡፡
እግዚአብሔር አንድ ነው የሚባልበትም አንዱ ምክንያት ዓለምን የፈጠረ ያስገኘ ስለሆነ ነው፡፡ ብዙ ስለሆነ ነው፡፡
ብዙ አማልክት ቢኖሩ ኖሮብዙ ዓለማትን በፈጠሩ ነበር፡፡ ተስማምቶ መግዛቱስ ወዴት ተገኝቶ ፡፡ዳግመኛም በዓለም ያሉ ሥነ
ፍጥረታት ተስማምቶና ተቀናጅቶ መኖሩ እግዚአብሔርን አንድ ያሰኘዋል ፡፡ውኃው እሳቱን ሳይደመስሰው እሳቱ ዓለምን
ሳያቃጥል ከዋክብት ከጨረቃ ጨረቃ ከፀሐይ ሳይጋጩ በተለዩ መሰመሮች በተለያዩ አቅጣጫዎች መጓዛቸው የዘመናት ልዩነት
የዘሩ ከአበባው የእሸቱ ከመከሩ ሳይለወት እና ሳይገለባበጥ ሰዓቱን እና ወራቱን ጠብቆ መምጣቱ ይህ ሁሉ አንድ አመላክ
አንድ መሪ አንድ መጋቢ መኖሩን ያስረዳል፡፡ ብዙ አማልክት ቢኖሩ ግን ምንዝርዝሩ በወጣ ነበር ፡፡ ዳግመኛም በአንድ አካል

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 41
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

እንደሚገኙ አባላት ዐይን አፍነጫ እጅ እግር ሌሎችም እርስ በርሳቸው ሳይጣሉ ተስማምተው ተቀናጅተው መኖር አንድ
አምለክ አንድ መጋቢ መኖሩን ይመሰክራል በማለት አስትምሯል::

የካቲት 4ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና

መጋቢት 1ኛ ሳምንት
ቅዱስ_ቄርሎስ
የቅዱስ ቄርሎስ ዜና ሕይወት

ቅዱስ ቄርሎስ ቄርሎስ ማለት ማኅቶት ማለት ነው፡፡

ቅዱስ ቄርሎስን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን "ዓምደ ሃይማኖት-


የሃይማኖት ምሰሶ" ይሉታል::
ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ሊቁ የተወለደው በእስክንድርያ (ግብጽ) 376 ዓ ም ነው: እናቱ
የወቅቱ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስ እህቱ ነበረችና አጎቱ ቅዱስ ቴዎፍሎስ
ወስዶ አሳድጐታል:: ገና በልጅነቱ ወደ አባ ሰራብዮን ገዳም ገብቶ ቅዱሳት
መጻሕፍትንና ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል:: በ5 ዓመት ብሉይንና ሐዲስን
አጥንቷል፡፡ በጾም: በጸሎትና በትሕትና የታሸ ነውና ሲማር አንድ ጊዜ
ካነበበው በሕሊናው ተስሎ ይቀር ነበር::
ቅዱስ ቴዎፍሎስ "ምዕመናንን አስተምርልኝ" ብሎ ወደ ከተማ
አመጣው:: መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና ሲያስተምር ወይ ደግሞ
መጻሕፍትን ሲያነብ ከምዕመናን ወገን ስንኩዋን የሚያወራና የሚንቀሳቀስ
ቀርቶ የሚቀመጥም አልነበረም:: ጣዕመ ስብከቱም ብዙዎችን
ለወጠ::ከዚያም በ412 ዓ/ም አጎቱ የነበረው ፓትርያርክ አባ ቴዎፍሎስ
ሲያርፍ ዻዻሳትና ሊቃውንት በአንድነት ቅዱስ ቄርሎስን መረጡ:: የእስክንድርያም 24ኛ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ
ቤተ ክርስቲያን አበራች:: በቅድስናው: በሊቅነቱ: በስብከቱ: በድርሰቶቹና በትጋቱ በፍጹም አገለገላት::በወቅቱ ስመ ክፉ መናፍቅ
ንስጥሮስ ተነስቶ የእስያ አብያተ ክርስቲያናትን አወካቸው:: ትምሕርቱ ክርስቶስን 2 አካል: ባሕርይ ነው (ሎቱ ስብሐት!) የሚል
ነበር:: በእውነት እንየው ከተባለ ግን ጠቡና ጥላቻው ከድንግል ማርያም ጋር ነበር:: ምክንያቱም ጌታችንን ወደ 2 የከፈለው
እመቤታችንን የአምላክ እናት አይደለሽም ለማለት ነው:: (ላቲ ስብሐት)
ነገሩን ቅዱስ ቄርሎስ በሰማ ጊዜ ወዳለበት ሒዶ ቢመክረውም ንስጥሮስ ሊሰማ አልፈለገም:: በዚህ
ምክንያት በትንሹ ቴዎዶስዮስ (የቁስጥንጥንያ ንጉሥ) ትዕዛዝ በኤፌሶን ታላቅ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሆነ:: ይህ ጉባዔ በቤተ
ክርስቲያናችን የመጨረሻው የተቀደሰ ጉባዔ ነው:: በ431 ዓ/ም በኤፌሶን ከተማ የመናፍቃኑን ጥርቅም ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው
የቀና 200 ቅዱሳን ሊቃውንት ተገኙ::የሚገባው ጸሎትና ሱባዔ ከተፈጸመ በሁዋላ ጉባዔው ተጀመረ:: አፈ ጉባዔው ሊቀ
ማሕበር ማር (ቅዱስ) ቄርሎስ ነበርና በጉባዔ ፊት ንስጥሮስን ተከራክሮ ረታው:: ምላሽም አሳጣው:: ከቅዱሳት መጻሕፍት
ክርስቶስ አንድ ባሕርይ መሆኑን: ድንግል ማርያምም ወላዲተ አምላክ መሆኗን እየጠቀሰ: በምሳሌም እያሳየ አስረዳ::የሰይጣን
ማደሪያ ንስጥሮስ ግን እንቢ: አላምንም በማለቱ ተወግዞ ተለየ:: ቅዱሳን ሊቃውንቱም በቅዱስ ቄርሎስ አርቃቂነት 12 አንቀጾችን
አዘጋጅተው ወደ ዓለም ሁሉ ላኩ:: እሊህ አንቀጾች ዛሬም በሊቃውንቱ እጅ አሉ:: ይነበባሉ: ይተረጎማሉ::ከእነዚህም አንዱ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 42
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ድንግል ማርያም "ታኦዶኮስ (የእግዚአብሔር እናቱ) ናት" የሚል ነው:: እመቤታችንን የአምላክ እናት: ዘላለማዊት ድንግል:
ፍጽምት: ንጽሕትና አማላጅ ብሎ ማመን ለሰማያዊ ርስት የሚያበቃ በጐ ሃይማኖት ነውና::
ጉባዔው ከተጠናቀቀ በሁዋላ ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን ጠርቶ "በድንግል ማርያም እመን:: እርሷ ከልጇ
ታስታርቅሃለች" ቢለው በድጋሚ "እንቢ" አለው:: ያን ጊዜ ሊቁ "ለአምላክ እናት ያልታዘዘ ምላስህ ላንተም አይታዘዝህ" ብሎ
ረገመው:: ወዲያው ምላሱ ተጐልጉሎ ወጥቶ ደረቱ ላይ ወደቀ::እንደ ውሻ እየተዝረከረከ ሃዶ ከወዳጆቹ ጋር ቁሞ ሳለ መሬት
ተከፍታ ውጣዋለች::ቅዱስ ቄርሎስ ግን ለ32 ዘመናት በመንበሩ ላይ አገልግሎ: ፍሬ ትሩፋት አፍርቶ: ብዙ ድርሰቶችንም ደርሶ
በ444 ዓ/ም ሐመሌ 3 ቀን ዐርፏል::

የቅዱስ ቄርሎስ ትምህርት እናሥራዎች


1 የመጽሐፍ ቅዱስን አንድምታ ትርጓሜ (ኮመንተሪ) ሠርቷል፡፡ አንድምታዎቹ
 የሙሴ መጻሕፍት
 ትንቢተ ኢሳይያስ
 የዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት የትንቢት መጻሕፍት
 መዝሙረ ዳዊት
 መጽሐፈ ምሳሌ
 መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን
 ትንቢተ ዳንኤል
 ትንቢተ ሕዝቅኤል
 ትንቢተ ኤርምያስ
 የዮሐንስ ወንጌል
 የሮሜ መልእክት፣
 የዕብራውያንመልእክትና
 ሁለተኛ የቆሮንቶስ መልእክት ናቸው፡፡
2 የበዓል መልእክታትን ጽፏል፡፡
 ከ414-442 ዓ.ም ሃያ ዘጠኝ የበዓል መልእክታት ለአማኞች ጽፏል፡፡

3 በጽሑፍ ስብከቶችን አዘጋጅቶ ለምእመናን ልኳል፡፡


 ሃያ ሁለት ጥልቅ የሆኑ ሃይማኖታዊ ስብከቶቹ በመጽሐፍ ታትመው ይገኛሉ፡፡
4. ስለ ነገረ መለኮት ነገረ ክርስቶስ ነገረ ማርያምና ክርስቲያናዊ ኑሮን በሚመለከት ብዙ መጻሕፍትን ጸፏል፡
5. በቤተክርስቲያናችን አገልግሎት ከሚሰጡት የቅዳሴ መጻሕፍት መካከል የቅዱስ ቄርሎስ የቅዳሴ
መጽሐፍ አንዱ ነው፡፡

በአጠቃላይ ቅዱስ ቄርሎስ የቤተክርስቲያንን ትምህርት በመናፍቃን ክፉ ዘር እንዳይበከል የጠበቀ በሃይማኖታዊ


ትምህርቱ የተመሰከረለት ታላቅ አባት ነው፡፡ የሃይማኖት ቅንዓትን በዓላማ መጽናትን ለእውነት መቆምንና በቅድስና መትጋትን
ከቅዱስ ቄርሎስ ሕይወት እንማራለን፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 43
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

መጋቢት 2ኛ ሳምንት
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
የቅዱስ ኤፍሬም ዜና ሕይወቱ

ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም የተወለደው በ306


ዓ.ም. ገደማ በሜሶፖታሚያ ውስጥ በምትገኝ “ንጽቢን” በተባለ
አከባቢ እንደኾነ ይታመናል፡፡ ንጽቢን በአሁኑ ሰዓት በደቡባዊ
ቱርክ እና በምዕራባዊ ሶርያ መካከል የምትገኝ ቦታ ናት፡፡ ምንም
እንኳን አንዳንድ መዛግብት ከቅዱስ ኤፍሬም ሕይወት በመነሣት
የቅዱስ ኤፍሬም ወላጆቹ ክርስቲያኖች እንደነበሩ ቢያወሱም
ሐምሌ 15የሚነበበው ስንክሳር እንደሚነግረን ግን አባቱ ካህነ
ጣዖት ከመኾኑም በላይ ክርስትናን የሚጠላ እንደነበር
ይነግረናል፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም ከወላጆቹ ጋር የቆየው እስከ 15
ዓመቱ ብቻ ሲኾን ትምህርተ ክርስትናንም ተምሮ የተጠመቀው
በጊዜው የንጽቢን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ከሠለስቱ ምዕት
አንዱ ከሚኾን ከያዕቆብ ዘንጽቢን ዘንድ ነበር፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ
ቅዱስ ኤፍሬምን አስተምሮ ካጠመቀው በኋላ ዓቅሙ ሲደረጅ
ንጽቢን በሚገኘው መንፈሳዊ ትምህርት ቤት በኃላፊነት ሾሞት
ነበር፡፡
በሮማውያን ግዛት ክርስትና እንዲስፋፋ ዋና
አስተዋጽኦ ያደረገው ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ በ337 ዓ.ም. ሲሞት
ፋርሳውያን በሮማውያን ላይ ስለዘመቱ ንጽቢን በ338፣ በ346ና በ350 ዓ.ም. በተደጋጋሚ ወረራ ተካሂዶባት ነበር፡፡ በ363
ዓ.ም. ግን በንጽቢን ዙርያ የነበሩ ከተሞች በፋርሳውያን ተደመሰሱ፤ ዜጐቻቸውም ግማሾቹ ተገደሉ፤ ግማሾቹ ደግሞ
ሀገራቸውን ትተው ተሰደዱ፡፡ በመኾኑም ቅዱስ ኤፍሬም ከተሰደዱት ክርስቲያኖች ጋር በመኾን የሮም ግዛት ወደ ነበረችው
ኤዴሳ (ታናሽ እስያ፣ዑር) አብሮ ተሰደደ፡፡ ይህች ቦታ (ኤዴሳ - በአሁኑ ሰዓት ሳን ሊ ኡርፍ ተብላ የምትታወቅ) ቅዱስ ኤፍሬም
ከመናፍቃን ጋር የተጋደለባት፣ በቤተክርስቲያን ትምህርት ላይ ያላቸውን አብዛኞቹን የክሕደት ትምህርቶች የሞገተባትና
አብዛኞቹን መጻሕፍቱን ያዘጋጀባት ናት፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም ከመምህሩ ከቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢ ጋር በመኾን በአርዮስ ምክንያት በ325ዓ.ም. በተካሄደው
ጉባኤ ኒቅያ ላይ ተገኝቶ ስለነበር የአርዮስን ክሕደትና ምክንያተ ውግዘት በሚገባ ያውቃል፡፡ ከኒቅያ ጉባኤ መልስ መንፈሰ
እግዚአብሔር በራዕይ በገለፀለት መሠረት ቅዱስ ኤፍሬም ቁጥሩ ከሠለስቱ ምዕት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ከሚኾን ከቅዱስ
ባስልዮስ ዘቂሳርያ ዘንድ ለመገናኘት ወደ ቂሣርያ ሄዷል፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም የዲቁና ክህነት ሠጥቶ ከሀገረ ስብከቱ ከፍሎ
እንዲያስተምር ወስኖ በእርሱ ዘንድ አኑሮታል፡፡ በዚያም ቦታ ብዙ ተአምራትን አድርጓል፤ መጻሕፍትንም ጽፏል፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም በትውፊት እንደሚታወቀው ምንኩስናን በገቢር ገለጣት እንጂ ሥርዓተ ምንኩስናን መፈጸሙን
በግልጽ የሚያመለክት ማስረጃ አልተገኘም፡፡ እንዲያውም በሶርያውያን ክርስቲያኖች የሚዘወተረውን ራስን በአንድ ስፍራ
ወስኖ በብሕትውናና በመምህርነት ቤተክርስቲያንን የማገልገል (Proto-monasticism) ሕይወት ይኖር እንደነበር ይታመናል፡
፡ በትውፊት ቅዱስ ኤፍሬም ቅዱስ ባስልዮስን ለመጎብኘት ወደ ቀጰዶቅያ እንዲሁም አባ ቢሾይን ለመጎብኘት ወደ ግብጽ
እንደተጓዘ የሚነገረውም ከዚህ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ፍጹም በኾነ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቱ፣ ምሳሌ በሚኾነው የምናንኔ ሕይወቱ
የሚታወቀው ቅዱስ ኤፍሬም ሐምሌ 15 ቀን በ370ዓ.ም ዐርፏል፡፡ በዚህ ኹሉ ትጋቱም ሶርያውያን ክርስቲያኖች “ጥዑመ
ልሳን”፣ “መምህረ ዓለም”፣ “ዓምደ ቤተ ክርስቲያን” ፤ ከሚያስተምረው የትምህርቱ ጣዕም የተነሣም “የመንፈስ ቅዱስ በገና”
በማለት ይጠሩታል፤ ያመሰግኑታልም፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 44
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

የቅዱስ ኤፍሬም ሥራዎች


ቅዱስ ኤፍሬም እንደ ሌሎቹ የ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እጅግ በጣም በርካታ መጻሕፍትን
ጽፏል፡፡ ሐምሌ 15የሚነበበው ስንክሳርም፡- “እጅግም ብዙ የኾኑ 14 ሺሕ ድርሳናትንና ተግሳጻትን ደረሰ፤ ከእርሳቸውም ውስጥ
አምላክን የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ውዳሴዋን ነው፡፡ ‘አቤቱ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ’ እስከሚል
ድረስ ድርሳናትን ደርሶአል” በማለት ይገልጧል፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም የደረሳቸው የዜማ ድርሰቶች ከ400 ሚልዮን ቅኔያዊ ግጥሞችን ያዘሉ ሲኾኑ፣ “ሶዞሜን” የተባለ የታሪክ ጸሐፊም
በውስጣቸው ከ3 ሚልዮን በላይ ስንኞችን እንዳካተቱ ተናግሯል፡፡ በአጠቃላይ የቅዱስ ኤፍሬም ጽሑፎች በ4 ከፍሎ ማየት
ይቻላል፡-
ይኸውም መጻሕፍቱ በዝርዝር ሲታዩ፡-

1) በመዝሙራት መልክ የተዘጋጁ


 ስለ እምነት (ባለ (87) ክፍል መዝሙራት)፤
 መናፍቃንን በመቃወም (ባለ(56) ክፍል መዝሙራት)፤
 ስለ ገነት ((15) ክፍል መዝሙራት)፤
 ጁሊያንን በመቃወም (5 ክፍል መዝሙራት)፤
 ስለ ክርስቶስ ልደት ( (59) ክፍል መዝሙራት)፤
 ስለ ቤተ ክርስቲያን (52) ክፍል መዝሙራት)፤
 ስለ ንጽቢን (77) ክፍል መዝሙራት)፤
 ስለ ድንግልና (52) ክፍል መዝሙራት)፤
 ስለ ጾም (67) ክፍል መዝሙራት)፤
 ስለ ኅብስት፤ ስለ ጥምቀት፤ ስለ ስቅለት፤
 ስለ ትንሣኤ (35) ክፍል ያላቸው መዝሙራት) ወዘተርፈ ጽፏል፡፡

2) በድርሳናት መልክ የተዘጋጁ


 ስድስት የሃይማኖት ድርሳናት፤
 በ 358) ዓ.ም በመሬት ንውጽውጽውታ ስለ ኒኮሜድያ ጥፋት ድርሳን፤
 ስለ ሰሙነ ሕማማት፤ ሌሎች በርካቶች ድርሳናት ወዘተርፈ. ጽፏል፡፡

3) ጥበባዊ፤ ግጥማዊም፤ ስድ ንባባዊም ይዘት ከኾኑት፡-


 ስለ ጌታችን ንግግር(ትምህርት)፤
 ስለ ዕለተ ምጽአት የሚናገር ወዘተርፈ
4) ሙሉ በሙሉ ስድ ንባብ የኾኑ (ቀጥተናኛ ትርሜ)
ይህ ክፍል ከመጽሐፍ ቅዱስ አንዱን መጽሐፍ በመውሰድ የተጻፉ ትርጓሜያትን የሚያጠቃልል ነው፡፡
 የኦሪት ዘፍጥረትና ዘጸአት ትርጓሜ፤
 የአራቱ ወንጌላት ትርጓሜ፤
 የግብረ ሐዋርያት ትርጓሜ፤
 የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት ትርጓሜ፤
 ለባርዳይሰን፤ ለማኒ፤ ለመርቅያን ክሕደቶች መልስ ወዘተርፈ ጽፏል፡፡
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ይኽነን ሊቅ ሲያወድሰው፡-
“ሰላም ለኤፍሬም ደራሲ ዘጽሩይ ልሳኑ፤
አብያተ ክርስቲያናት ይሠረጉ በድርሳኑ”፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 45
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

(በድርሳኑ አብያተ ክርስቲያናት የሚሸለሙ (የሚያጌጡ) አንደበቱ የጠራ ለደራሲው ለኤፍሬም ሰላምታ ይገባል)
ብሎታል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም እነዚኽን ድርሰቶቹን በሶርያ ቋንቋ የጻፋቸው ሲኾኑ ወደ በርካቶች ቋንቋዎች የተወሰኑ ሥራዎቹ
ሲተረጐሙ ከዚኽ ውስጥ በአርማንያ፤ በኮፕቲክ፤ በግእዝ፤ በሕንድ፤ በአረብኛ፤ በጆርጂያ፤ በግሪክና በሌሎች ተተርጒመዋል፡
፡ በእጅጉ የሚገርመው በእኛ ቋንቋ በግእዝ ከተተረጐሙት ውዳሴ ማርያምን ጨምሮ በጥንታዊ ብራና መጻሕፍቶቻችን ውስጥ
ዐሥራ ሰባት የቅዱስ ኤፍሬም መጻሕፍቶች ሲገኙ እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ብቻ በሃይማኖተ አበው ላይና በግብረ ሕማማት ላይ
ብቻ ለሕትመት ሲበቁ ሌሎቹ ግን በዘረፋ ብራናዎቹ ከሀገር በመውጣታቸው ምክንያት ሊገኙልን አልቻሉም፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴ ማርያም እንዴት ሊጽፈው ቻለ?

የውዳሴ ማርያም መተርጕማን እንደሚያስተምሩት ቅዱስ ኤፍሬም ቢረሌ፣ መርጠብ፣ ብርጭቆ፣ ኩዝ፣ ካቦ
እየሠራ የዓመት ልብሱን የዕለት ምግቡን እያስቀረ ይመፀውት ነበር፡፡ ሲመፀውትም በሥላሴ፣ በመላእክት፣ በጻድቃን ወይም
በሰማዕታት ስም አይመፀውትም፤ በእመቤታችን ስም ይመጸውት ነበር እንጂ፡፡ ከእናንተ መካከል “ንቋቸው አጥቅቷቸውን
ነውን?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ በፍጹም! ንቋቸው፤ አጥቅቷቸውም አይደለም፡፡ የእመቤታችን ፍቅር ባያደርሰው
ነው እንጂ፡፡ በመኾኑም እመቤታችንን እጅግ ከመውደዱ የተነሣ ኹል ጊዜ “ምነው የእመቤቴ ምስጋናዋ እንደ ሰማይ ኮከብ፤
እንደ ባሕር አሸዋ በዝቶልኝ፤ እንደ ልብስ ለብሼው፤ እንደ ምግብ ተመግቤው ጠግቤው በበዛልኝ” እያለ ይመኝ ነበር፡፡ ያሹትን
መግለጽ ለእግዚአብሔር ልማዱ ነውና ገልጾለት አስቀድመን እንደተናገርነው “አኃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ- አቤቱ የጸጋህን
ሞገድ ግታልኝ” እስኪል ድረስ 14 ሺሕ ድርሳናትንና ተግሳጻትን ደርሷል፡፡ የሚጸልየውም ጸሎት ከሉቃስ ወንጌል “በ6ኛው
ወር ገብርኤል መልአክ” ከሚል አንሥቶ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን አውጥቶ 64 64 ጊዜ ይጸልይ ነበር /ሉቃ.12÷6/፡፡
ከዕለታት በአንድ ቀን ግን (ዕለቱ ሰኑይ ጊዜው ነግህ ነው) የነግህ ተግባሩን አድርሶ ከመካነ ግብሩ ተቀምጦ ሳለ እመቤታችን
መጣች፡፡ የብርሃን ምንጣፍ ተነጥፏል፡፡ የብርሃን ተዘርግቷል፡፡ ከዚያ ላይ ኹናም “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም” አለችው፡፡
እሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ቆመ፡፡ “ወድሰኒ” አለችው፡፡ እዚህ ጋር አንዳንድ ልበ ስሑታን የሚያነሡት ጥያቄ ስላለ መልስ
ሰጥተንበት እንለፍ፡፡ እመቤታችን ቅዱስ ኤፍሬምን “አመስግነኝ” ስላለችው ክብር፣ ውዳሴ፣ ልዕልናን የፈለገች መስሏቸው
“ማርያም በፍጹም እንዲህ አታደርግም፤ በመጽሐፍ ቅዱስ የምናውቃት ማርያም ትሑት ናት” የሚሉ አሉ፡፡ ነገር ግን ይህ
ስሕተት ነው፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ ኤፍሬም “ምነው የእመቤቴ ምስጋናዋ እንደ ሰማይ ኮከብ፤ እንደ ባሕር አሸዋ በዝቶልኝ፤
እንደ ልብስ ለብሼው፤ እንደ ምግብ ተመግቤው ጠግቤው በበዛልኝ” እያለ ይመኝ ስለ ነበር እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰምቶለት
እንጂ እመቤታችን ልዕልናን ፈልጋ አመስግነኝ ያለችው አይደለም፡፡ እመቤታችንን የሚቀድስ ማንኛውም ሰው በእመቤታችን
ላይ የሚጨምረው አንዳች ነገር የለም፡፡ እርሱ ይከብራል፤ የሰሙትም ኹሉ ይከብራሉ እንጂ /ቅዳ.ማር. ቁ.172፡ እመቤታችን
“ወድሰኒ” ካለችው በኋላ ሊቁም መልሶ “እፎ እክል ወድሶተኪ ዘኢይክሉ ሰማያውያን ወምድራውያን- ምድራውያን ጻድቃን
ሰማእታት፣ ሰማያውያን መላእክት አንቺን ለማመስገን የማይቻላቸው ለእኔ እንደምን ይቻለኛል?” አላት፡፡ በተረቱበት መርታት
ልማድ ነውና /ሉቃ.1፡37 “በከመ አለበወከ መንፈስ ቅዱስ ተናገር” አለችው፡፡ ከዚህ በኋላ “ባርክኒ” ብሏት እርሷም “በረከተ
ወልድየ ወአብሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኀድር በላእሌከ” ብላ ባርካው ምስጋናዋን ጀምሯል፡፡ ሲያመሰግናትም ደቀ መዝሙር ቅኔ
ቆጥሮ እንደሚቀኝ፣ ድርሰትም አስቦ እንደሚጽፍ አይደለም፡፡ ብልህ ደቀ መዝሙር ያጠናውን ቀለም ከመምህሩ ፊት ሰተት
አድርጎ እንዲያደርስ እንደዚያ ነው እንጂ፡፡ ስታስደርሰውም ከሰባት ከፍላ አስደርሳዋለች፡፡ “ለምን?” ቢሉ በሰባቱ ዕለታት
መመስገን ፈቃድዋ ስለኾነ /ሉቃ.1፡48/፤ አንድም ሰባቱ ዕለታት ምሳሌዋ ናቸውና፡፡ ይኸውም፡-

በዕለተ እሑድ አሥራወ ፍጥረታት አራቱ በሕርያት (እሳት፣ ውሃ፣ ነፋስና መሬት) ተገኝተዋል /ዘፍ.፩፡፩፣ ኩፋ.፪፡፰/፡፡ ከሷም
ለዘኮነ ምክንያተ ፍጥረት በህላዌሁ የሚባለው፣ ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደመኖር ያመጣ፣ ያለ እርሱ ቃልነት ያለ እርሱ
ሕልውና ምንም ምን የተፈጠረ የሌለ፣ አምጻኤ ዓለማት ፈጣሬ ዓለማት ፤ በአጭር ቃል አሥራወ ፍጥረት ጌታችን በግብረ
መንፈስ ቅዱስ ተገኝቷል/ዮሐ.፩፡፫/፡፡
በሰኞ ዕለት የብርሃን ማኅደር የኾነው ጠፈር ተገኝቷል /ዘፍ.፩፡፮-፯/፡፡ ከእርሷም ብርሃን ክርስቶስ ተገኝቷል /ዮሐ.፩፡፭-፱/፡፡
በዕለተ ሠሉስ ምድር ገበሬ ሳይጥርባት፣ ሳይደክምባት፣ ዘር ሳይወድቅባት በቃሉ ብቻ በእጅ የሚለቀሙ አትክልት፣ በማጭድ
የሚታጨዱ አዝርእት፣ በምሳር የሚቆረጡ ዕፅዋት ለሥጋውያን ምግብ የሚኾኑ ተገኝተዋል፡፡ ከእሷም የወንድ ዘር
ሳይወድቅባት ዕፀ ሕይወት፣ ፍሬ ሕይወት (የመንፈሳዊያን ምግብ) የሚኾን ጌታ ተገኝቷል፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 46
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

በዕለተ ረቡዕ “ለይቁሙ ብርሃናት በገጸ ሰማይ” ባለ ጊዜ የተሠወረውን የሚገልጡ፣ የጨለመውን የሚያስለቅቁ ፀሐይ፣ ጨረቃና
ከዋክብት ተገኝተዋል /ዘፍ.፩፡፲፬-፲፱/፡፡ ከእሷም በብርሃኑ ኅልፈት ውላጤ የሌለበት፣ ጠፈር ደፈር የማይከለክለው፣ መዓልትና
ሌሊት የማይፈራረቀው፣ የጽድቅ ፀሐይ (ለመንፈሳዊያን ምግብ) የሚኾን ጌታ ተገኝቷል፡፡
በዕለተ ሐሙስ “ለታወጽእ ባሕር ዘቦ መንፈሰ ሕይወት” ባለ ጊዜ በልባቸው የሚሳቡ፣ በእግቸው የሚሽከረከሩ፣ በክንፋቸው
የሚበሩ፣ በደመ ነፍስ ሕይወት ሕያዋን ኹነው የሚኖሩ ደመ ነፍስ ከሌለባት ከባሕር ተገኝተዋል፡፡ ዘርዐ ብእሲ፣ ሩካቤ ብእሲ
ከሌለባት ከእመቤታችንም ለምእመናን ምክንያተ ሕይወት የሚኾን ያውም ከጐኑ በፈሰሰ ውሃ ተጠምቀው ምእመናን ሕያዋን
የኾኑለት ኢየሱስ ክርስቶስ ተገኝቷል፡
በዕለተ ዐርብ በኩረ ፍጥረት አዳም ከድንግል መሬት ተገኝቷል፡፡ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያምም ዳግማዊ አዳም
ኢየሱስ ክርስቶስ ተገኝቷልና፡፡
በዕለተ ቀዳሚት ሥጋዊ ዕረፍት ተገኝቷል፡፡ ከእርሷም የመንፈሳውያን ዕረፍት ጌታ ተገኝቷልና ነው /ማቴ.፲፩፡፳፰-፴/፡፡

መጋቢት 3ኛ ሳምንት
ሊቁ አባ ህርያቆስ
የአባ ህርያቆስ ዜና ሕይወቱ
ክርስቲያን ሆኖ እመቤታችንን የሚወድ ሰው ሁሉ
ይህንን አባት ያውቀዋል::ሕርያቆስ ማለት ህሩይ ማለት ነው : ለሹመት
መርጠውታልና: አንድም ረቂቅ ማለት ነው ምሥጢረ ሥላሴን
ይናገራልና : ከሊቃውንትስ ምሥጢረ ሥላሴን የማይናገር የለም ብሎ
ከሁሉ ይልቅ እሱ አምልቶ አስፍቶ አጉልቶ ይናገራልና አንድም ፀሐይ
ማለት ነው: አብ ፀሐይ ወልድ ፀሐይ መንፈስቅዱስ ፀሐይ ብሎ
ጽፏልና : አንድም ብርሃን ማለት ነው: የምዕመናንን ልቦና በትምህርቱ
ብሩህ ያደርጋልና : ዘአብርሃ መንበረ ማርቆስ በብርሃን እንዲል
:አንድም ንብ ማለት ነው: ንብ የማይቀምሰው አበባ የለመ እሱም
የማይጠቅሰው ሊቅ የለም: አባ ሕርያቆስ ተወልዶ ያደገው በምድረ
ግብጽ ሲሆን አካባቢው ብህንሳ (ንሒሳ) ይባላል:: ይህቺ ቦታ አቡነ
ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳንን ያፈራች ናት::አባ
ሕርያቆስን በዚህ ዘመን ነበረ ብየ ትክክለኛውን ዓ/ም ለመናገር
ይከብደኛል:: ከቤተ ክርስቲያን ትውፊት መረዳት እንደሚቻለው ግን
የነበረበት ዘመን 4ኛው: ወይ 5ኛው መቶ ክ/ዘመን እንደ ሆነ መገመት
ይቻላል::ቅዱሱ በዘመኑ የተለየ ማንነት የነበረው ሰው ነው:: ገና
ከልጅነቱ እመ ብርሃንን የሚወዳት በመሆኑ ቅን: የዋህና ገራገር ነበረ::
መቼም እመቤታችን ይወዳል ሲባል እንደ ዘመኑ በአፍ ብቻ እንዳይመስለን:: ቀንና ሌሊት ለፍቅሯ የሚተጋ: ማዕበለ ፍቅሯ
የሚያማታው ሰው ነበር እንጂ::የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ስም ሲጠራ ምስጥ ብሎ ልቡናው ይሰወርበት ነበር:: ዘወትር
የእርሷን ፍቅር ከማሰብ በቀር ሌላ ሥራ አልነበረውም:: የልጅነት ጊዜው ሲያልፍም ድንግልንና ቸር ልጇን ያገለግል ዘንድ
መነነ::ዘመኑ ዘመነ ሊቃውንት እንደ መሆኑ ሁሉም ለትምሕርት ሲተጉ እርሱ ግን ለጸሎትና ለደግነት ብቻ ነበር የሚተጋው::
ከትምሕርት ወገንም የሰሞን ጉዋዞችን: አንዳንድ ቅዳሴያትንና የዳዊትን መዝሙር ተምሮ ነበር::በተለይ ግን የዳዊትን መዝሙር
እየጣፈጠው መላልሶ: መላልሶ ያመሰግንበት ነበር:: ከዳዊት መካከል ደግሞ መዝ. 44ን ፈጽሞ ይወዳት ነበር:: ይህቺ ጥቅስ
የምትጀምረው "ጐስዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" ብላ ነው::የውስጧ ምሥጢርም ስለ ድንግል ማርያምና ስለ ክርስቶስ ነው::
አባ ሕርያቆስ ይህቺን መዝሙር በቃሉ አጥንቶ: ቁሞም ተቀምጦም: ተኝቶም ተነስቶም ያለ ማቁዋረጥ ይላት
ነበር:: እየጣፈጠችው "ልቡናየ በጐ ነገርን አወጣ" እያለ ይዘምር ነበር:: በወቅቱ ታዲያ የብህንሳ ኤዺስ ቆዾስ በማረፉ ምትክ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 47
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ሲያፈላልጉ መንፈስ ቅዱስ አባ ሕርያቆስን መረጠ::ምንም አለመማሩ ቢያሰጋችቸውም "በጸሎቱ: በደግነቱ ሃገር ይጠብቃል"
ብለው ሾሙት:: ነገር ግን ምንም በሥልጣን የበላያቸው ቢሆን ተማርን የሚሉ ሰዎች ይጠሉት: ይንቁትም ነበር:: እርሱ ግን
እንደ ጠሉኝ ልጥላቸው: እንደ ናቁኝ ልናቃቸው ሳይል በፍቅር ያገለግል ነበር::አንድ ቀን ታዲያ መንገድ ይወጣል:: በበርሃ
ብቻውን እየተራመደ: "ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" እያለ እየዘመረ: ተመሥጦ ቢመጣበት መንገድ ሳተ:: እርሱ በምስጋናው ሲደሰት
እግሩ ግን ከገደል ጫፍ ደርሶ ነበር:: ገደሉን ልብ አላለውም ነበርና ሳይታወቀው ወደ ገደሉ ውስጥ ተወረወረ::በዚህ ጊዜ ደንግጦ
ቢመለከት እጅግ ጥልቅ በሆነ ገደል ውስጥ ራሱን አገኘው:: ነገር ግን አንድም አካሉ አልተነካም:: ልብሱም አልቆሸሸም:: ለራሱ
ተገርሞ ዙሪያ ገባውን ሲመለከት እርሱ ቁጭ ያለበት ብርሃንን የተሞላ የልብስ ዘርፍ ነበር::"እመ ብርሃን!" ብሎ ሲጮህ የሰማይና
የምድር ንግሥት የሆነች እመቤታችን ከፊቱ ቁማ ታየችው:: እመ አምላክን በገሃድ ቢያያት እንደ እንቦሳ ዘለለ::የሚገርመው
ደግሞ የተቀመጠበት የድንግል ማርያም የቀሚሷ ዘርፍ ነበር:: እመቤታችን አነጋገረችው: ባረከችው:: ፍቅሯ ቢመስጠው ከሰው
ሳይገናኝ: ምግብም ሳይበላ: እዚያው ገደሉ ውስጥ ለ1 ዓመት ያህል በተመስጦ ቆይቷል::በላ እመ ብርሃን መጥታ ከገደሉ
አውጥታ ወደ ሐገሩ መለሰችው::ከጥቂት ጊዜ በላም አንድ ፈተና ገጠመው:: አንድ ቀን እመቤታችን በተወለደችበት ግንቦት
1 ቀን ቅዳሴ "ማን ይቀድስ" ሲባል ሰዎቹ "አባ ሕርያቆስ ይሁን" አሉ::እርሱ ግን "እኔ አይቻለኝም: እናንተ ሊቃውንት ቀድሱ"
አላቸው:: "አይሆንም" ብለው እርሱኑ አስገቡት:: ይህንን ያደረጉት ለተንኮል ነበር:: ልክ ወንጌል ተነቦ ፍሬ ቅዳሴ ሲመረጥ
እርሱ "እግዚእን (የጌታ ቅዳሴን) ልቀድስ" ቢል እነርሱ "የሚቀደሰው የሊቅ ቅዳሴ ነው" አሉት::ይህንን ያሉት እርሱ
የሊቃውንቱን ቅዳሴ አያውቅምና በሰው ፊት እንዲዋረድ ነው:: እንዲህም ብለው ባለመማሩ ተሳለቁበት:: አባ ሕርያቆስ ግን
እያዘነ ወደ መንበሩ ዞረ:: ድንግልንም "እመቤቴ መናቄን: መገፋቴን ተመልከች" አላት::ወዲያው ግን ድንግል ማርያም ወርዳ
ቀጸበችው (ጠራችው):: በዘርፋፋው ቀሚሷ ላይም ረቂቅ የሆነ ቅዳሴን አሳየችው:: ደጉ ሰው ደስ ብሎት "ጐሥዐ ልብየ" ሲል
2ቱ እግሮቹ ከመሬት ከፍ አሉ:: እርሱም "ወአነ አየድእ ቅዳሴሃ ለማርያም" ብሎ እስከ ኃዳፌ ነፍሱ ድረስ አደረሰው::ሕዝቡና
ካህናቱ በሆነው ነገር ሲደነቁ: አንዳንዶቹ "ዝም ብሎ ነው የቀባጠረ" አሉ:: ቅዱሱ ግን ቅዳሴ ማርያምን በብራና ጠርዞ በሕዝቡ
መካከል ድውይ ፈወሰበት:: እሳት ሳያቃጥለው: ውሃ ሳይደመስሰው ቀረ::+መጽሐፈ ቅዳሴው ሙትንም አስነስቷል:: ከዚህች
ሰዓት ጀምሮ በዘመኑ ቁጥር 1 ሊቅ ሆነ:: ብዙ መጻሕፍትን ሲተረጉም አጠቃላይ ድርሰቶቹም እልፍ (10,000) ናቸው::

የቅዱስ አባ ህርያቆስ በቅዳሴው ውስጥ ያየገለጣቸው ትምህርቶች

1) ስለ ምስጢረ ሥላሴ
2) ስለ ነገረ ድኅነት
3) ስለ ድንግል ማርያም
4) ስለ ምሥጢረ ቁርባን

መጋቢት 4ኛ ሳምንት

ምዕራፍ አራት
በዘመነ ለቃውንት የተነሱ መናፍቃን
መግቢያ
በመጀመሪያው አራት መቶ ዓመታት ውስጥ ቤተ ክርስቲያን በብዙ አቅጣጫ የተለያዩ ችግሮች ደርሰውባት እጅግ
ስትሠቃይ ቆይታለች፡፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሱት ችግሮችም ከሁለት አቅጣጫዎች የመጡ ነበሩ፤ አንደኛው ከቤተ
ክርስቲያን ውጭ ሲሆን ሁለተኛው ከዚያው ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተነሡ ችግሮች ነበሩ፡፡ በመጀመሪያው አብዛኛውን ጊዜ
ችግር የተነሣው ከአሕዛብ ነገሥታት ሲሆን፣

1) የሮም መንግሥት ገዢዎችና በክፍላተ ሀገሩ የነበሩት የእነርሱ ወኪሎች እነሱ ያመልኩአቸው የነበሩትን ጣዖታት ክርስቲያኖች
ስለማይቀበሉና ጨርሰውም ስለሚያወግዙ፤

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 48
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

2) አሕዛብ ያደርጉት እንደነበረው ክርስቲያኖች ለሮም ነገሥታት የአምልኮ ክብር ስለማይሰጡ፣ በቤተ ክርስቲያን ላይና
በክርስቲያኖች ላይ በየጊዜው ስደት ታውጆ ክርስቲያኖች ሲሠቃዩ ኖረዋል፡፡
3) የጣዖታት ካህናትና የጣዖታት ምስል ሠራተኞች በክርስትና ሃይማኖት መስፋፋት ምክንያት የጣዖት አምልኮ እጅግ ስለቀነሰና
በአንዳንድ ቦታዎችም አምልኮ ጣዖት ጨርሶ ስለቀረ ኑሮአቸው በመቃወሱ፣ ከአሕዛብ ነገሥታት ጋር በመወገን በክርስቲያኖች
ላይ ልዩ ልዩ ችግሮች ይፈጥሩ ነበር፡፡

በቤተ ክርስቲያን ላይ ከውስጥ የተነሡ ችግሮችም እጅግ የበዙና የከፉም ነበሩ፡፡ ከመጀመሪያ ጀምሮ በቤተ
ክርስቲያን ውስጥ ብዙ መለያየትና መከፋፈል ስለታየ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ክፍሎች ትከፋፈል ይሆናል ተብሎ ተፈርቶ
ነበር፡፡ በግብረ ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ከአይሁድ ወገን ወደ ክርስትና በገቡትና ከአሕዛብ ወገን ወደ ክርስትና በገቡት
ክርስቲያኖች መካከል የታዩት ብዙ ልዩነ ቶች ነበሩ፡፡ ይህ ችግር በ51 ዓ.ም በተደረገው በሐዋርያት ጉባኤ በተሰጠው ውሳኔ
መፍትሔ አግኝቶ በመጠኑም ቢሆን ችግሩ ተወግዶ ነበር፡፡ በኋላ ደግሞ በሁለተኛውና በሦስተኛው መቶ ዓመት ላይ ተነሥተው
የነበሩት ዶኬቲኮች፣ ግኖስቲኮችና የሰባልዮስና የጳውሎስ ሳምሳጢ ተከታዮች የነበሩ መናፍቃን ተነሥተው በቤተ ክርስቲያን
ውስጥ ብዙ የከፋ ብጥብጥ ተነሥቶ ነበር፡፡

ይህም ችግር በየክፍላተ ሀገሩ በተጠሩ ሲኖዶሶች (ጉባኤዎች) የቤተ በክርስቲያን አንድነት ተጠብቆ
ቆይቷል፡፡ እንደዚሁም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለምሥጢረ ሥላሴ ዶግማ (ትምህርት) በቤተ ክርስቲያን መምህራን መካከል
ብዙ ልዩነቶች ተፈጥረው ነበር፡፡ የእነጳውሎስ ሳምሳጢና የእነሰባልዮስ የኑፋቄ ትምህርቶች በቤተ ክርስቲያን አህጉራዊ
ጉባኤያት (ሲኖዶሶች) ተወግዘው በዚህ ምክንያት የተነሣው ውዝግብ ጥቂት ረገብ ብሎ ነበር፡፡ ነገር ግን ከግማሽ ምእት ዓመት
በኋላ በአርዮስ የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት ምክንያት ማለት አርዮስ ‹‹ወልድ ፍጡር ነው›› (ሎቱ ስብሐት) ብሎ በመነሣቱ
ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ዓመታት ስትታወክና ስትበጠበጥ ቆይታለች፡፡
መናፍቅ “ናፈቀ” ካለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲኾን የቋንቋው ሊቅ ትርጒሙን ሲፈቱት የሚጠራጠር፣
የሚያጠራጥር፣ አጠራጣሪ፣ ሃይማኖቱ ግማሽ የኾነ፤ ምሉእና ፍጹም ትክክል ያይደለ፤ መንፈቁን አምኖ መንፈቁን የሚክድ
ማለት ነው፡፡ በጽርዕ ቋንቋ ኤሬቲክ፤ በእንግሊዘኛ ሄሬቲክ፤ በግእዝ ደግሞ “ሐራ ጥቃ” ይባላል፤ ትርጒሙን በቋንቋው
የተራቀቁት ሊቅ በመዝገበ ቃላታቸው ሲገልጡት መናፍቅ፣ ጠዋየ ሃይማኖት፣ ባህሉና ትርጓሜው ከመጽሐፍ ከንባብ
የማይገጥም፤ መጻሕፍት ነው ያሉትን፤ አይደለም፤ አይደለም ያሉትን ነው የሚል የርሱን ሐሳብ ብቻ የሚከተል፤ ነገሩ
ካልተማሩት የሚስማማ ከሊቃውንት ግን የማይስማማ ብለውታል፡፡
ጌታችን በዮሐንስ ወንጌል ምዕ 8፡44 ላይ ዲያብሎስን “ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና” እንዳለ፤ የመጀመሪያው መናፍቅ
ዲያብሎስ ሲኾን በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ኅልውና በመጠራጠር፤ የርሱን ነገድ ለማጠራጠር ሞክሮ፤ በጥቂቶቹ
ተሳክቶለታል፤ ዛሬም እንክርዳዱን የዘራበት የርሱ መንፈስ ያደረበት ሰው አስቀድሞ ነገረ እግዚአብሔርን አጠራጥሮ ካስካደው
በኋላ፤ ሌሎችን ለማስካድ መሣሪያ ያደርገዋል፤ አዳምንና ሔዋንን ከገነት ለማስወጣት በእባብ ሰውነት እንዳደረና
እንደተሳካለት፡፡
በመጨረሻም ዘንዶ የተባለው ዲያብሎስ በሰማይ እያለ ከክሕደቱ በመቀጠል ልዑል እግዚአብሔርንና ነገደ
መላእክትን ለመስደብ ጀመረ፤ ዛሬም ትክክለኛውን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ላስካዳቸው መናፍቃን አስቀድሞ የስድብ
መንፈስን በውስጣቸው አሳድሮ ሥልጣን የተሰጣቸው ቅዱሳንን እንዲንቁ እንዲሰድቡ አድርጎ ለሥራው ያመቻቻቸዋል (ራእ
13፡4-7)።
ሆኖም ግን ይህ ጠላት ዲያብሎስ ሲሳደብ ቅዱሳን መላእክት ዝም ብለው አላዩትም ይልቁኑ ከቅዱስ ሚካኤል
ጋር በመኾን ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው አሳቹን ዘንዶ ተፋልመው፣ ተዋግተው ወደ ጥልቁ እንዲወረወር አደረጉት እንጂ (ራእ
13፡7-9) ይህ ለእኛ አብነት ነው፤ ዛሬም ከእውነተኛው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትምህርት ፈቀቅ ያለውን፤ ብንችል ደጋግመን
መምከር፣ መገሠጽ ሲገባ እንቢ ካለ ግን ሌላውን አካል በክሕደቱ መርዞ እንዳይጥል በጉባኤ በውግዘት ቈርጦ መጣል ይገባል፤
እንጂ ዝምታ የክፋት ተባባሪ መኾን ነው።
ጌታችን እንኳ ዲያብሎስ ሁለቴ ፈትኖት መልስ ከመለሰለት በህዋላ በሦስተኛው ገንዘብ ወርቅ እሰጥኻለኊ
ብሎ ስገድልኝ ቢለው “ኺድ አንተ ሰይጣን” በማለት የመጨረሻ ቃል ተናግሮታል! (ማቴ 4፡10)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በገላ 1፡
7 ላይ “ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን” በማለት በአጽንዖት ተናግሯል፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 49
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

በዘመነ ሊቃውንት የነበረው የጥንቱ መናፍቅነት እና ያሁኑን ስናስተያየው የሰማይና የምድር ያህል ሰፊ ርቀት አለው፤ አበው
በብኂላቸው “ቀን አይጥለው፣ ጠጅ አያሰክረው፣ የቀለም ሠረገላ አያሰነካክለው የለም” እንዲሉ የጥንቶቹ መናፍቃን ከስመ ጥር
መምህራን የተማሩ፣ ብዙ መጻሕፍት የጻፉ እጅግ ከመማራቸው የተነሣ ከመጠን ከተጻፈው አልፈው በመመራመር
ተጠራጥረው የካዱ ነበሩ።

የዘመናችን ግን ከቤተ ክርስቲያን የጉባኤ ቤት በፍጹም ያልዋሉ፣ ምስጢር ያላደላደሉ፤ አንብበው


የማይተረጒሙ፤ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ!!! እንዲሉ አበው የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ለማንቋሸሽ የማያውቁትን ግእዝ
ሲጠቅሱ እንኳ የማያፍሩ፤ በጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ብቻ የሚመላለሱ፣ የቤተ ክርስቲያን የሴቶችና የወንዶችን መግቢያ እንኳ
ያለዩ መሆናቸውን ስናይ እንኳን መናፍቅ ሊባሉ ቀርቶ እንደው ለአቅመ መናፍቅነት (ለመጠራጠር ደረጃ) ራሱ ደርሰዋል ወይ
ሲባል፤ በፍጹም አልደረሱም ቢያንስ ለመጠራጠር እኮ መማር፣ ማንበብ፣ መመራመር፣ መፈላሰፍ ያስፈልጋል፤ አኮ!!!
ጌታችን በወንጌል “በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥
የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና” በማለት እንዳስተማረ፤ በዘመነ ሊቃውንት የነበሩ ምእመናንም እረኞቻቸውን ስለሚያውቁ
በድፍረት ሳይማር ላስተምራችሁ የሚላቸው አንድም አልነበረምና በእኛ ዘመን ካሉት ጋር ሊነጻጸሩ አይችሉም፤ ምክንያቱም
እረኞቻቸውንና የቀናውን ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮን ጠንቅቀው ያውቁ ነበርና በስሜት ዝም ብለው የሚነዱ አልነበሩም።
ጌታችን እኮ ሐዋርያትን ለስብከተ ወንጌል ከመስደዱ በፊት 3 ዓመት ከ3 ወር በቃልም በተግባርም
ካስተማራቸው በኋላ ነበር “ሑሩ ወመሐሩ” (ሒዱ አስተምሩ) ያላቸው፤ እንኳን በመንፈሳዊው ዓለም ቀርቶ በዓለማዊው
ጥበብ እንኳ ሰው በድፍረት ስለማያቀው ነገር መለፍለፍ አይችልም፤ በሠለጠነው ዓለም አንድ ሰው ሌክቸር ከማድረጉ በፊት
የተማረበት ተቋም፤ የትምህርት ደረጃው ከቀረበ በኋላ ነው መልእክቱን (ጥናቱን) በሰዎች ፊት የሚያቀርበው፤ በእኛ ጊዜ ግን
ጸጋ በሚል ሽፋን ሰው ስለማያውቀው በድፍረት ሲናገር ብዙዎች ዐውቀው ሳይሆን በስሜት ብቻ ሲያዳምጡ ሲታይ፤ በዘመነ
ሊቃውንት የነበሩ በዐፀደ ነፍስ ሕያው የሆኑት አበው እና ክቡራን ምእመናን ለጥቂት ቀናት ከሞት ተነሥተው ዐብረውን ሆነው
ቢያዩን ምን ይሉን ይሆን!!! ፡፡
ወደ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ስንመጣ ቤተ ክርስቲያን ቀድም ሲል ከተጠቀሱት ከሮማውያን ነገሥታት
የደረሰባትን ስቃይና መከራ በመቀበል እንዳትጠፋ ደግሞ በመጋደል ላይ ሳለች ከውስጧ አማኝ መስለው አደገኞች ዋቂዎች
ናቸው፡፡እነዚህም መናፍቃን ቤተ ክርስቲያን የምታምነውን የምታስተምረውን ቀጥተኛ እምነት ተቀበለው በማመንና
በማስተማር ፈንታ ተቃዋሚ የሆኑ የከህደት ትምህርቶችን የተሚያስተምሩ ናቸው’፡፡ ለብዝዎቹም መነሻቸው የጥንት ግሪኮች
የፍልስፍና አሰተምህሮት በመሆኑ የህንን በዝርዝር እንመለከታለን፡፡

ሚያዚያ 1ኛ ሳምንት

ግኖስቲኮች
ግኖስቲኮች ማለት አዋቂዎች/የዕውቀት ሰዎች/ማለት ነው፡፡የቃሉን ስያሜ የወሰዱት’’ግኖሲስ ’’ዕውቀት ከሚለው
የጽርዕ ቋንቋት ነው፡፡ትምህርታቸው ግኖስቲዝም(gnostisism) ይባላል ፡፡ዕውቀታዊ እንደማለት ሲሆን መዳን በዕውቀት ብቻ
እንጂ በእምነት አይደለም የሚሉ ናቸው፡፡
ግኖስቲኮች ክርስትናን ከተቀበሉ በላ ዐወቅን ብለው በዘመናቸው የነበረውን የፍልስፍና የጥንቆላና የምትሐት
እንዲሁም ልማዳዊ አስተሳሰባቸውን ከክርስትና ትምህርት ጋር የቀላቅሉ የነበሩ ናቸው፡፤ግኖስቲኮች በአጠቃላይ ክርስትናን
ከእምነት ይልቅ በፍልስፍና ላይ ለመመስረት የጠሩ የነበሩ ሁሉም ፍልስፍና በራሱ ጎጂ አይደለም የሚሉ ናቸው፡፡
አስተሳሰባቸው የመነጨው ከቤተ አህዛብ ከተመለሱ ክርስቲያኖች ነው፡፡ የህ የሐሰት ትምህርት የቅልቅል ሕይወት የተጀመረው
በምለመሪያ ክርስቲያኖች በብዛት በሚገኙባቸው ከተሞች በሶርያ/አንጾኪያ/ በግብጽ/እስክንድርያ/ በታናሽ እስያ ነበር፡፡ ሁሉም
መናርያ ከተሞቻቸው የሚገኙት በሮም ግዛት ምስጥ ነበር፡፡ ግኖስቲኮች የአይሁድን ባሕል ከግሪኮች ፍልስፍና ጋር
የተቀላቀለውን በሁለት አማልክት ማምለክ መመሪያ አድርገው ይጠቀሙባቸው ነበር፡፡በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እምነትና
ዕውቀት የተለያዩ መሆናቸውን ተገልጿል፡፡ማቴ 13÷11 1ኛቆሮ 1÷10 1ኛቆሮ 12÷8

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 50
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ዋና ዋና የኖስቲኮች ትምህርተ
ስለ አምላክ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ መነሻ ሳይኖራቸው ፈጣሪ ከፍጡሩ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም እንዲሁም ክፍና ደግ
አምላክ የተባሉ ሁለት አማልክት እንዳሉ ያስተምራሉ፡፡ ብርሃንን፣ ፀሐይን ሐዲስ ኪዳንን የፈጠረ ደጉ አምላክ ሲሆን፤ ጨለማን
ብሉይ ኪዳንን የፈጠረ ደግሞ ክፉ አምላክ ነው ብለው ያስተምራሉ፡፡

ስለ ሥነ ፍጥረት
ይህ ዓለም በክፉ አምላክ የተፈጠረ ስለሆነ የኃጢአት ምንጭ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ስለ ዓለም አፈጣጠርም ሲናገሩ
በባህርይ መለኮቱ እደ እሳት ነበልባል ክፋይ ከሚወጡ ነገሮች ሲሆን እነዚህ ነገሮች እየራቁ በሄዱ መጠን ፍፁምነታቸው
እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ ከእነዚህ ነገሮች አንዱ ተሳስቶ ከመስመር ወጣ ስለዚህ ወደዚህ ዓለም ተጣለ፡፡ ይህ የተሳሳተና የተጣለው
ሰውንና ቁሳዊ ዓለም ፈጠረ ይላሉ፡፡ የክርስቶስም አመጣጥ እንደዚሁ ነው ብለው ያምናሉ፡፡

ስለ ሰው ተፈጥሮ
ግኖስቲኮች ሰው በመባል የሚታወቀውና ሰብዓዊ ክብርም ያለው ነፍስ እንጂ ስጋ አይደለም፡፡ ይህች የሰው ነፍስም
እንደ እሳት ነበልባል ክፋይ ከመለኮት ባህርይ እየተከፈለች የምትወጣ ናት፡፡ የመዳን ተስፋ ያላት ነፍስ ብቻ ናት፡፡ ሥጋ
በባህርይው ለጥፋት የተፈጠረ ስለሆነ ፈርሶ በስብሶ ይቀራል፡፡ ነፍስ በመዋቲ ስጋ ውስጥ በእድል ሰንሰለት ተጠፍራ (ታስራ)
ትኖራለች፡፡ ከዚህ እስራት ሊፈታት የሚችለው እውቀት ብቻ ነው ብለው ያምናሉ፡፡

ግኖስቲኮች ሰውን በሦስት ደረጃዎች ይከፍሉታል


1) መንፈሳዊ
2) ነፍሳዊና
3) ሥጋዊ ናቸው
 መንፈሳዊ፡ የሚሉት እራሳቸውን ነው፡፡ ደረጃውም የፍፁምነት ነው፡፡ በእውቀታችን አስቀድመን ድነናል ባዮች ናቸው፡፡
 ነፍሳዊ፡- የሚሉት ክርስቲያኖችን ነው፡፡ ደረጃው የማዕላዊነትና የወጣኒነት ነው፡፡ እነዚህ በመዳንና በመጥፋት መካከል ያሉ
ናቸው፡፡ ቢያውቁ ይድናሉ ያለዚያ ግን ተስፋ የላቸውም ይላሉ፡፡
 ሥጋዊ፡- የሚሉት አህዛብንና አይሁድን ነው፡፡ እነዚህ ለጥፋት የተፈጠሩና ተስፋ የሌላቸው ናቸው ብለው ያምናሉ፡
በግኖስቲኮች እምነት ነፍስ ከሥጋ በምትለይበት ጊዜ ሥጋ በስብሶ ሲቀር ነፍስ ወደ ቀደመ ባህሪዋ ትመለሳለች ብለው ያምናሉ፡

ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ ያላቸው አመለካከት
ግኖስቲኮች በምሥጢረ ሥጋዌ(ተዋህዶ) ትምህርታቸው ሥጋ የኃጢአት ምንጭ ስለሆነ ከመለኮት ጋር
አልተዋሀደም ብለው ያምናሉ፡፡ ስለዚህ መለኮታዊ ቃል ሥጋ የለበሰ መስሎ ታየ ብለው ያስተምራሉ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ
የዮሴፍ ልጅ እንጂ በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና አልተወለደም ይላሉ፡፡ በዮርዳኖስ ወንዝ ሲጠመቅ ጀምሮ እስከ ስቅለት
ድረስ ተዋህደው ድህነትም የሚገኘው ክርስቶስ ባደረገው ሥራ ሳይሆን በእርሱ በተገለጠው እውቀት ነው ይላሉ፡፡ የማስተማር
ስራውን ጨርሶ ወደ መስቀል በሚወጣበት ጊዜ ከእርሱ ተለይቶ ሄደ ኢየሱስ ብቻውን መከራ ተቀበለ ብለው ያስተምራሉ፡፡
በዚህም ትምህርታቸው እስከ 3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቤተክርስቲያንን ሲያውኳት ኖረዋል፡፡
የግኖስቲኮችን ስምና የተዘበራረቀ ትምህርታቸውን በሙሉ ለመጥቀስ አስፈላጊ ባይሆንም ዋና ዋናዎቹን ስምና
ከትምህርታቸውም በመጠኑ እንመለከታለን፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 51
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ሚያዚያ 2ኛ ሳምንት
አርዮሳውያን
አርዮስ ከሦስተኛው ምእት ዓመት አጋማሽ በኋላ በ257 ዓ.ም አካባቢ በሰሜን አፍሪካ በሊብያ ነው የተወለደው፡፡
ስሙ እንደሚያመለክተው የትውልድ ዘሩ (የዘር ሐረጉ) የሚመዘዘው ከግሪክ ሲሆን፣ የተገኘውም ከክርስቲያን ቤተሰብ ነበር፡
፡ በትውልድ ሀገሩ መሠረታዊ ትምህርቱን ከአጠናቀቀ በኋላ እስክንድርያ በሚገኘው ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ገብቶ
ከፍተኛ ትምህርት ተምሯል፡፡ አርዮስ በእስክንድርያ ከፍተኛ ትምህርት ቤት ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ወደመካከለኛው
ምሥራቅ ሔዶ በአንጾኪያ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ገብቶ ከፍተኛ የትርጓሜ መጻሕፍት ትምህርትና የነገረ መለኮት
ትምህርት ተምሯል፡፡ መምህሩም የታወቀው ሉቅያኖስ ነበር፡፡ ከእስክንድርያ ትምህርት ቤት ይልቅ የአንጾኪያ ትምህርት ቤት
ለአርዮስ የክህደት ትምህርት ቅርበት እንደነበረው ብዙ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡

አርዮስ አብዛኛውን የኑፋቄ ትምህርቱን ያገኘው ከሉቅያኖስና ከአንጾኪያ ትምህርት ቤት ነው፡፡ በአንጾኪያ
የሚፈልገውን ትምህርት ከጨረሰ በኋላ ወደ እስክንድርያ ተመልሶ ኑሮውን በዚያው አደረገ፡፡ አርዮስ እጅግ ብልህና ዐዋቂ
ሰው በመሆኑ ብዙ ሰዎች ያደንቁት ነበር፡፡ አንደበተ ርቱዕም ስለነበረ ተናግሮ ሕዝብን በቀላሉ ማሳመን እንደሚችል
ይነገርለታል፡፡ በዚያ በነበረው ዕውቀትና ታላቅ የንግግር ችሎታ የእስክንድርያ ፓትርያርክ የነበረው ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ
ጴጥሮስ ዲቁና ሾመው፡፡ የእስክንድርያ ከፍተኛ ትምህርት ቤት ከከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ሌላ የግሪክ ፍልስፍናን በተለይም
የፕላቶንን ፍልስፍና ያስተምሩ ስለነበር፣ አርዮስም ፍልስፍናን በተለይም ሐዲስ ፕላቶኒዝም (Neo-Platonism) የተባለውን
ፍልስፍና በሚገባ ተምሯል፡፡

በዚህም የእስክንድርያውን ከፍተኛ ትምህርት ቤት ታላቅ መምህር የነበረውን የአርጌንስን (Origen) የተዘበራረቀ
የምሥጢረ ሥላሴን ትምህርት ተከትሎ መጓዝ ጀመረ፡፡ አርጌንስ በምሥጢረ ሥላሴ ትምህርቱ አብን ከወልድ፣ ወልድን ደግሞ
ከመንፈስ ቅዱስ በማዕረግና በዕድሜ ያበላልጥ ነበር፡፡ አርጌኒስ አብን፣ ወልድንና መንፈስ ቅዱስን በማበላለጥ አብ ከወልድ
እንደሚበልጥ፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ከወልድ እንደሚያንስ ያስተምር ነበር፡፡ ስለዚህ የአርዮስ የክህደት ትምህርቱ ዋናው
መሠረት አርጌኒስ እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ ምንም እንኳን አርጌኒስ ስለቅድስት ሥላሴ ቢያስተምርም፣ አርዮስ አጥብቆ
የተናገረውና የኑፋቄ ትምህርቱን ያስተማረው ስለአብ እና ስለወልድ ነበር፡፡
በአጠቃላይ የአርዮስ የክሕደት ትምህርት የሚከተለው ነው፤

1) አብ ብቻ ዘለዓለማዊ (ዘአልቦ ጥንት ወኢተፍጻሜት) ነው፡፡ ወልድ ግን ዘለዓለማዊ አይደለም፡፡ ነገር ግን እርሱ ያልነበረበት
ጊዜ ነበር ለማለት ‹‹ሀሎ አመ ኢሀሎ›› (እርሱ ያልነበረበት ጊዜ ነበር) እያለ ያስተምር ጀመር፡፡ ስለዚህ አብ አባት ተብሎ
የተጠራውና እንደ አባት የታወቀው ከዘመናት በኋላ እንጂ ከዘመናት በፊት አብ ተብሎ አይጠራም አለ፡፡ ይህንን ያለው ‹‹ወልድ
ፍጡር ነው›› (ሎቱ ስብሐት) ብሎ ያልነበረበት ጊዜ ነበረ ለማለት ነበር፡፡

2) የአርዮስ ዋናው የክሕደት ትምህርቱ ‹‹ወልድ ፍጡር ነው›› (ሎቱ ስብሐት) ማለትም ‹‹ወልድ ከመፈጠሩ በፊት አልነበረም፤››
የሚል ነው፡፡ ‹‹አብ፣ ወልድን ከምንም ፈጠረና የእግዚአብሔር ልጅ እንዲሆን አደረገው … ለወልድ ጥበብ፣ ቃል የሚባሉ
የኃይላት ስሞች አሉት›› እያለ ያስተምር ነበር፡፡ ለክሕደቱ መሠረት የሆነውና ሁልጊዜ ይጠቅሰው የነበረውም፡- ‹‹ትቤ ጥበብ
ፈጠረኒ መቅድመ ኵሉ ተግባሩ፤ ጥበብ ከፍጥረቱ ሁሉ አስቀድሞ እኔን ፈጠረኝ አለች፤›› ተብሎ በመጽሐፈ ምሳሌ ፰፥፳፪ ላይ
የተጠቀሰው ኃይለ ቃል ነበር፡፡ በአርዮስ አስተሳሰብ ጥበብ የተባለ ወልድ ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አብ መጀመሪያ ወልድን
ፈጠረ፡፡ ከዚያ በኋላ ወልድ ዓለምንና በውስጡ ያሉትን ሁሉ ፈጠረ ብሎ ያምን ነበር፡፡ ያለ ወልድ ምንም የተፈጠረ ፍጥረት
የለም ብሎ ያስተምርም ነበር፡፡

3) ከዚህም ሌላ አርዮስ ወልድን ከአብ ሲያሳንስ ‹‹ወልድ በባሕርዩ ከአብ ጋር አንድ አይደለም›› ይል ነበር፡፡ በሌላ በኩል ግን
ወልድን ከሌሎች ከፍጡራን እጅግ ያስበልጠዋል፡፡ ወልድም በጸጋ የአብ ልጅ እንደሆነ ይናገራል፡፡ እንደዚሁም ወልድ በምድር

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 52
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ሕይወቱ ታላቅ ትሕትናንና ተጋድሎን በማሳየቱ በባሕርይ ሳይሆን በጸጋ የአምላክነትን ክብር እንዳገኘ አርዮስ በአጽንዖት ይናገር
ነበር፡፡

4) በአርዮስ አመለካከት ወልድ በባሕርዩ ፍጹም ስላልሆነ የአብን መለኮታዊ ባሕርይ ለማየትም ለማወቅም አይችልም ይል ነበር፡

5) አርዮስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር ‹‹ወልድ ለአብ የመጀመሪያ ፍጥረቱ እንደሆነ፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ለወልድ የመጀመሪያ
ፍጥረቱ ነው›› ይል ነበር፡፡

ይህን የአርዮስን ክሕደት የሰማው የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ (ፓትርያርክ) ተፍጻሜተ ሰማዕት
ቅዱስ ጴጥሮስ አርዮስን አስጠርቶ የሚያስተምረው ትምህርት ሁሉ የተሳሳተ መሆኑን ገልጾለት ከስሕተቱ ተመልሶና ተጸጽቶ
ከቅዱሳን አበው ሲተላለፍ በመጣው በኦርቶዶክስ እምነት እንዲጸና መከረው፡፡ አርዮስ ግን ከአባቱ ከተፍጻሜተ ሰማዕት
ጴጥሮስ የተሰጠውን ምክር ወደ ጎን በመተው የክሕደት ትምህርቱን በሰፊው ማስተማር ቀጠለ፡፡ ይህንን የተመለከተ ያ ደግ
አባት አርዮስን አውግዞ ከዲቁና ማዕረጉ ሻረው፡፡ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት እንደሚለው፣ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ
ጴጥሮስ አርዮስን ያወገዘው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በራእይ ተገልጦለት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነው፡፡

በአንድ ሌሊት በራእይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድ ወጣት አምሳል እንደ ፀሓይ የሚያበራ ረጅም ነጭ
ልብስ (ቀሚስ) ለብሶ ለቅዱስ ጴጥሮስ ይታየዋል፡፡ ልብሱ ለሁለት የተቀደደ ሆኖ ቢያየው ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ደንግጦ ጌታን
‹‹መኑ ሰጠጣ ለልብስከ፤ ልብስህን ማን ቀደደብህ?›› ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ጌታም ‹‹አርዮስ ልብሴን ቀደደብኝ›› ብሎ መለሰለት፡
፡ ይኸውም በአባቶች ትርጕም ‹‹አርዮስ ከባሕርይ አባቴ ከአብ ለየኝ (አሳነሰኝ)›› ማለት ነው፡፡ ጌታም አርዮስን ከእንግዲህ
ወዲያ ወደ ቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዳይቀበለው አዝዞት ተሰወረ፡፡ ተፍጻሜተ ሰማዕት ጴጥሮስ ራእዩን ያየው
በዲዮቅልጥያኖስ ስደት ጊዜ ተይዞ ለመገደል በእስር ቤት በነበረበት ወቅት ነበር፡፡ አርዮስም ቅዱስ ጴጥሮስ እንደሚገደል
አውቆ ከውግዘቱ ሳይፈታው እንዳይሞት ከውግዘቱ እንዲፈታው አማላጆች ይልክበታል፡፡ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ
ግን አርዮስን ‹‹በሰማይና በምድር የተወገዘ ይሁን!›› በማለት ውግዘቱን አጸናበት፡፡ በዚያኑ ቀን ተማሪዎቹን አርኬላዎስን እና
እለእስክንድሮስን አስጠርቶ ያየውን ራእይ በመግለጥ አርዮስን እንዳይቀበሉትና ከእርሱም ጋር ኅብረት እንዳይኖራቸው
አዘዛቸው፡፡

መርቅያኒዝም
በ144 ዓ.ም መርቅያን የሚባል ቤተ ክረስቲያኒቱን በእጅጉ ከፈተኑት መናፍቃን መካከል የሚመደብ ሰው
ተነስቶ ነበር፡፡ መርቅያን በክህደቱ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከምናውቃቸው፣ በዘመናችንም ከምንሰማቸው ተጠራጣሪዎች
የተለየ ሀሳብ ይዞ ነው የተነሳው፡፡ የመርቅያን ክህደት በዋናነት በእግዚአብሔር አምላክነት፣ በክርስቶስ የባህሪይ አምላነት
ወይም ፈራጅነት አሊያም በጻድቃን መላእክት አማላጅት ላይ ያነጣጠረ አልነበረም፡፡ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን ሊቃዉንት
ምሁራን መርቅያንን ቤተ ክርስቲያኒቱን ከእንቅልፏ የቀሰቀሰበትን ሀሳብ ያነሳ መናፍቅ ነው ይልቱል፡፡ መርቅያን የተነሳው
ከወንጌላቱ መካከል ከፋፍሎ ይህንን እቀበላሁ ይህንን አልቀበልም በማለት ነው፡፡ ከአራቱ ወንጌላት የማርቆስን፣ ከጳውሎስ
መልእክታት ደግሞ አስሩን ብቻ ነው የምቀበለው ከዚህ ውጪ ያሉትን ከጳውሎስ መልእክታት አራቱን እንዲሁም የይሑዳን፣
የጴጥሮስን፣ የዮሐንስን መልእክትና ራዕይን አልቀበልም ብሎ ክህደቱን አወጀ፡፡ ብዙ ሊቃዉንት መርቅያን ይህንን ያለበትን
ምክንያት በብዙ መንገድ ለማየት የሞከሩ ሲሆን ብዙዎች ግን መርቅያን በትንሹም ቢሆን የዘረኝነት መንፈስ አለበት ብለው
ያምናሉ የይሁዲነት መንፈስ ይታይበታል የመረጣቸው መጻህፍት ከይሁዲነት ጋር ዝምድና ያላቸውን መጻህፍት ብቻ ነው
መርጦ እቀበላሁ ያለው ብለው ያምናሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ ቤተ ክርስቲያን የመርቅያንን ሀሳብ ለመቃወምና ክህደቱን ለመቀልበስ
ብዙ እርቀት እንድትጓዝ ተገዳለች፡፡
ቤተ ክርስያኒቱ የመርቅያንን ክህደት ለመጣል እና ወንጌሎቿ፣የቀሩት የጳውሎስ መልእክታት እና
እንዲሁም የዮሐንስ ራዕይም ሆነ የሀዋርያቱ መልእክታት በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት፣ ያለፈውን ዘመን እንዲያስታዉሱ፣
የነበሩበትን ዘመን እነዲያስተዉሉ፣ የሚመጣውንም ጊዜ እንዲያመለከቱ በማድረግ የተጻፉ እውነተኛ መጻህፍት መሆናቸውን
ለማሳመን በተነሳች ግዜ ያላሰበችው ፈተና ገጥሟታል፡፡ ፈተና የሆነውም የማቴዎስ ወንጌል፣ የማርቆስ ወንጌል ፣የሉቃስ ወንጌል
የዮሐንስ ወንጌል እና መልእክታም እንደዚሁ በስማቸው የተሰየሙ መጻህፍት በተመሳሳይ ስም ነገር ግን በሀሳብ እጅጉኑ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 53
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ተራርቀው ብዙዎችም በምንፍቅና ሀሳብ ተበርዘው በቁጥር በዝተው መገኘታቸው ነው፡፡ ይህም ማለት ማንም እየተነሳ
የሚፈልገውን ጽፎ የማቴዎስ ወንጌል፣ የሉቃስ ወንጌል፣ የማርቆስ ወንጌል እያለ እየሰየመ ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያስገባ ነበር፡፡
በዘመኑ መጻህፍቱ ሳይመረመሩ ፣ሳይጠኑ፣ ማን እንደጻፋቸው ሳይረጋገጥ ፣መንፈሳቸው ይዘታቸው ሳይታይ እና ሳይመዘን
የማቴዎስ፣ የማርቆስ፣ የሉቃስ ወይም የዮሐንስ ወንጌል ስለሚል ብቻ ቦታ እየተሰጣቸው የተሰበሰቡ ሲሆን፤ መርቅያን ያነሳውን
ሀሳብ እና ክህደት ለማረም በተደረገ ጥረት ትክክለኛ የሆኑትን ወንጌላት ልክ ካልሆኑት ለመለየት ቤተ ክርስቲያን ከሶስት መቶ
ሀምሳ እስከ አራት መቶ ዓመታት እንደፈጀባት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይነግረናል፡፡
ይህም የሆነው በቀላሉ በማቴዎስ ወንጌል ስም ብቻ ይዘታቸው የተለያየ በምንፍቅና ሀሳብ የተሞሉ እስከ
አንድ መቶ ሀያ የሚጠጉ መጻህፍት መገኘታቸው ነው፡፡ ይህንን ትክክለኛ የሆነውን መጽሐፍ ለመለየት ምን ያክል ከባድ
እንደሆነ ማንም ሊረዳው ይችላል፡፡ ከዚህ በኋላም ነው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ቅዱስ ሲኖዶስ በየሶስት ወሩ እየተሰበሰበ
በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የሚወጡ መጻህፍትን እንዲመረምርና እንዲለይ በቀኖና የደነገጉት፡፡ ይሁን እና የሚመለከታቸው
የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት የሊቃዉንት ጉባኤ ቅዱስ ሲኖዶሱንም ጨምሮ በንቃት ሊከታሉት ባለመቻላቸው መጻሕፍት፣
ዝማሬያትን እና የስብከት ይዘቶችን ለይተው መያዝ ባለመቻላቸው በዘመናችን ባህታዊ የሚመስሉ ሽፍቶች፣ ካህናት የሚመስሉ
ተርታ ሰዎች፣ ሰባኪያን የሚመስሉ አጉራ ዘለሎች፣ መንፈሳዊ መጻህፍት የሚመስሉ ልብ ወለዶች፣ መዝሙር የሚመስሉ
ዘፈኖች እና ክርስቲያን የሚመስሉ አህዛቦች በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ተከብረውና ቦታ አግኝተው ተሰግስገው የሚገኙት፡፡
በእርግጥም መርቅያን በዛን ዘመን አንቀላፍታ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ከእንቅልፏ እንድትነቃ ቀስቅሷላታል ማለት ይቻላል፡
፡ ምናልባት ዛሬም ቤተ ክርስቲያኒቱ በየትኛውም ሁኔታ ላይ በመልካም አስተዳደር፣ በፋይናስ ስርዓት፣ በእስታቲክስ፣ በሰው
ሀይል አስተዳደር፣ በህትመትና ስርጭት ብቻ በሁሉም ዘንድ ከተኛችበት ልትነቃ የሚገባበት ዘመን ይመስለኛል፡፡ በዚህ ወቅት
በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ የቤተ ክርስቲያኒቱ እውነተኛ መምህራንን፣ ሊቃውንትን፣ ካህናትን፣ ሰባክያነ ወንጌልን፣
መዘምራንን፣ አስተዳደርን ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪና ድብልቅልቅ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
ለጊዜው ግን ጎልቶ የወጣውና ምእመናኑንም ሆነ የሚመለከታቸውን የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት ፈተና
ውስጥ የጨመረው የተሀድሶ ነን ባዮች ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ውጥንቅጡ በበዛበት ዘመን ማንን ከማን መለየት እስኪያቅት ድረስ
አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ በዚህ ግርግር ወቅት ራሳቸውን ለመግለጥም ሆነ ለማኖር የተመቸ ግዜ ያገኙ አካትም ቀላል የሚባሉ
አይደሉም፡፡ አንዳንዶቹ በዚያኛው ወገን ያለውን ሁኔታ ሲያመቻቹ፣ ሲያደራጁ እና ሲመሩ ቆይተው በየትኛው ቀኖና ቤተ
ክርስቲያን እንደተመለሱ ሳይታወቅ አሁን ደሞ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ተቆርቋሪ አካላት መካከል በመገኘት ሲተቹ፣ ሳሳደቡ፣ ሲዝቱ
ሲያሳድሙ እና ሊያስወግዙ ሲሯሯጡ እንመለከታቸዋለን፡፡ አንዳንዶችም በወዲያኛው ወገን አሉ ከሚባሉት በአቋም ከመለየት
ወዲህ ማዶ ካሉት ጋር በጥቅም ሲጣሉ ሀይማታዊ ጉዳይ በማልበስ እሰራልሃለሁ ያሉትን ሀሳብ ይዘው መጥተው አላማቸውን
ለማሳካት ሲታገሉ ይታያሉ፡፡ የሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላትም ጉዳዩን መንፈሳዊ በሆነ ምልኩ ከመመርመር
ይልቅ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል ስንኩል ተረት አብረው ሲዘምቱ ማየት እንግዳ መሆኑ ቀርቷል፡፡
መምህራነ ወንጌልም እንዲህ ያለውን ሀይማታዊ ልዩነት መሰረታዊ በሆነ ትምህርት እየለዩ ከማስተማር ይልቅ መድረክ
በደመቀበት እና ሞንታርቦ በጮኸበት እና ነጣ ነጣ ያለ ልብስ የለበሱ ምዕመናን ባሉበት ብቻ በመገኘት ለየት ያሉና
የሚያስደምሙ ጥቅሶችን በመምረጥ ምዕመኑን በማስደመም ብቻ ይበትኑታል፡፡ ስለዚህ ከእንደዚህ ካሉ ቦታዎች እና መድረኮች
ምንም ሳይወለድ ይቀራል፡፡ ከስብከት የሚወለድ መናኝ የለም ካለም ክዶ ይሞታል፡፡ ከስብከት የሚወለድ አገልጋይ የለም
ካለም ራሱን የሚያገለግል ነው፡፡ ከስብከት የሚወለድ ካህን የለም ካለም የአገልግሎት ሳይሆን የክብር ክህነት ያለው ቀረርቶን
ከዜማ የማይለይ ነው፡፡ ከስብከት የሚወለድ ዘማሪ አይኖርም ቢኖርም በዘፈን ይደመድመዋል ፡፡
በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የተጨበጠ ለውጥ ማምጣት ካስፈለገ ደጉን ከክፉው፣ መልካሙን ከመጥፎው፣
ሰባኪውን ከፎካሪው፣ ዘማሪውን ከዘፋኙ እና ቀዳሹን ከአንጎራጓሪው በአጠቃላይ ተኩላውን ከበጉ ስንዴውን ከእንክርዳዱ
መለየት ካስፈለገ አሁን በየአውደ ምህረቱ ያለው የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ እንዳለ ሆኖ መሰረታዊ ወደ ሆነ ስር የሰደደ
ተካታታይ በቤተክርስቲያኗ ዶግማ እና ቀኖና ላይ እንዲሁም ስርዓተ ቤተክርስቲያን ላይ ወዳተኮረ ትምህርት መመለስ
ያስፈልጋል፡፡መምህራኖቻችንንም አፍ ከሚያስከፍተው የአውደ ምህረታችን ስብከት ባሻገር በየ ሰንበት ትምህርት ቤቱ በተለዩና
ቤተ ክርስቲያኒቱ በምታዘጋጃቸው ልዩ እና ተከታታይነት ባላቸው ጉባኤያት ላይ ልናያቸው ግድ ይላል፡፡
ያልተጨበጠ ዶግማ፣ የማይታይ እውነት እና የማይደረስበት ተስፋ የያዙ ቡድኖች እና ግለሰቦች እንኳን ተከታታይነት ባለው
መሰረታዊ አስተምህሮታቸው አድናቂዎቻቸውን እና ተከታዮቻቸው እምነት አስታጥቀው የእውነት ጠብታ ለማይገኝበት ነገር
ግን ላመኑበት አላማ ነብሳቸውን እንኳን እስከመስጠት ቆራጥ ሲሆኑ እናያለን፡፡ እነዚህ አላማን መሰረት ባደረገ እና
ተከታታይነት ካለው መሰረታዊ አስተምህሮቶች የሚወለዱ እና የሚገኙ ፍሬዎች ናቸው፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 54
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

በተለያየ መልክ የተደራጁ የማህበራት አባላት እንኳን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጥቅምና ክብር ይልቅ
ለማህበራቸው ጥቅምና ክብር በጽናት ሲቆሙ የምናያቸው ተከታታይነት ካለው አስተምህሮት ስለሚወለዱ ነው፡፡
በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ግን እንደዚህ ያለውን እውነት ማየት እየጠፋ ያለ ቅርስ እየሆነ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ
ሆዳቸው አምላካቸው የሆኑ ቅጥረኞች እንጂ ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች እየበዙ ያሉት እንዲህ ያለ መሰረታዊና አግባብነት ያለው
የትምህርት ወንፊት በመጥፋቱ ነው፡፡
ዛሬ ዛሬ ስማቸውን የገነቡ ሰባክያነ ወንጌል ለአገልግሎት በሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ ውስጥ እንዲሁም
የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትም በሰርክ ጉባኤ የማይገኙበት ግዜ ነው፡፡ መምህራን በአውደ ምህረት ትምህርተ ወንጌል
ሲሰጡ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በአዳራሻቸው ጸሎት ያደርሳሉ ወይም መዝሙር ያጠናሉ፡፡ አንዳንድ ማህበራትም
አባሎቻቸውን በራሳቸው መምህራን ካልሆነ በስተቀር ቤተ ክርስቲያን አምናበት ባሰማራቻቸው መምህራን ያለማሰበክ ጥብቅ
ጥበቃ የሚደርጉበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ምዕመናን መንፈሳዊ አባቶቻቸውን በግልጥ የማያምኑበት የሚያሙበት የቤተ
ክርስቲያኒቱ ታላላቅ ምንፈሳዊ አባቶችም በልጆቻቸው የሚጨክኑበት ዘመን ሆኗል፡፡
ማህሌታዉያኑ ከቀዳስያኑ፣ ቀዳስያኑ ከመምራኑ፣ መምህራኑ ከሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ጋር የሰንበት
ትምህርት ቤት አባላቱ በተለያየ መልክ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሊረዱ ምን እናድርግ ብለው ከተደራጁ ማህበራት ጋር በአንድነት
ለአንድ አላማ በፍቅር መስማማት እስካልቻልን ድረስ “የመቀናጆ በሬ ወደየ ሀገሩ ይስባል” እንደሚባለው ቤተ ክርስቲያኒቱን
ወደየ ፍላጎታችን በተለያየ አቅጣጫ እንደብራና ወጥረን እንደምናስጨንቃት ምንም ጥርጥር የለውም

ጌታ በደሙ የመሰረታት ቤተ ክርስቲያን አለች በስሙ፣ የተጠመቁ እና የተመዘገቡ ምዕመናንም አሉ ክርስትናው


ግን የታለ ያስብላል፡፡ቤተ ክርስቲያኒቱ በቁጥር ከሚያታክቱ የውጭ አካላት የሚዘንብባት የመከራ ቀስት አልበቃ ብሎ
ለአገልግሎት የተጠሩበትን መንፈሳዊ ስራቸውን ትተው የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት እርስ በስርስ የሚፋለሙበት፣ የሚቋሰሉበት
እና የሚጨካከኑባት መድረክ ሆናለች፡፡በቤተ ክርስቲያኒቱ የተበላሸ የውስጥ አስተዳደርን ለማቃናት ደፋ ቀና የሚሉትን መጥፎ
ስም በመለጠፍ ማሸማቀቅ፣ ሊስተካከል ሊፈተሸ የሚገባውን ጠማማ መንገድ ለማስተካከል ከመጣር ይልቅ ልዩነቱን
ሀይማኖታዊ በማስመሰል ድጋፍ ለማግኘት መጣር የጊዜአችን አሳዛኝ ክስተት ነው፡፡ምናልባትም በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ
ሊስተካከል የሚገባው የተበላሸ አስተዳደር፣ ጽንፈኝነት እና ጉቦኝነት እንዳይታረምና እንዳይስተካከል ይህ አስተሳሰብ የተሀድሶ
መንፈስ ነው የሚለው ጥቁር መጋረጃ ጋርዶ የያዘው ይመስለኛል፡፡ የተሀድሶ መንፈስን እና መልካም አስተዳደርን ለይቶ የሚያይ
አይን መፍጠር ያስፈልጋል፡፡ ከመናፍቃን ክህደት እና ከተሃድሶ መንፈስ ይልቅ ቤተ ክርሰቲያኒቱን የዘረኝነት መንፈስ የመልካም
አስተዳደር እጦት ጉቦኝነት አብልጦ ይጎዳት እንደሆነ ማን ያውቃል?
ይህ ዘመን ለመልካም አስተዳደር ለተኛችው በጥቅም ፈላጊዎች፣ በጉበኞች፣ በዘረኞች፣ በአማኞች ሳይሆን
በቅጥረኞች ለተሞላችው የዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን እንደ መርቅያን ዘመን ከእንቅልፏ የምትነቃበት ጊዜ አሁን ይመስለኛል፡፡
ጠላትን ለይቶ ማሳየት ተገቢ ነው፡፡ ዘመቻውም ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን በዘመቻው የሚሳተፉ ሰዎችን መለየት ያስፈልጋል፡፡
ጠላትን ለይቶ ማወቁ ብቻውንም በቂ አይደለም፡፡መለየት ያስፈልጋል መለየት ሲባል ሊለይበት በሚገባው መንፈሳዊ
አስተዳደር ወይም ሊለይ በሚችለው የቤተ ክርስቲያኒቱ አካል በአዋጅ መለየት ያስፈልጋል፡፡ቤተ ክርስቲያኒቱ ከጥቂት ሰዎች
ይሁንታዊ አስተዳደር ወጥታ በተጨበጠ እና መሬት ላይ ባረፈ ህግ መገዛት አለባት ወይም በመተዳደሪያ ደንቧ ላይ የሰፈረውን
ህግ ልትተገብረውና ህጋዊ መሰረት ልታስይዘው የመምትችልበት ማንነት ያስፈልጋታል፡፡

በዘመነ መርቅያን ቤተ ክርስቲያኒቱ ደገኛውን እና ክህደት የተሞባቸውን በጻህፍት በመለየት መጻህፍቶቼ እንዚህ
ናቸው እንዚህ በስም እንጂ የእኔ አይደሉም ብላ እንደለየች የዛሬይቱም ቤተ ክርስቲያን ልጆቼ፣ ካህናቱ፣ ሊቃዉንቱ፣
መዘምራኑ፣ ሰባኪያነ ወንጌል፣ ባህታዉያኑ፣ ማህበራቱ፣ምዕመናኑ እንዚህ ናቸው፡፡እነዚህ ግን በስም እንጂ በግብር ልጆቼ
አይደሉም ብላ መለየት እና ማሳወቅ ያለባት ዘመን አሁን ነውና ቤተ ክርስቲያኒቱ ልትነቃ ያስፈልጋል፡አለበለዚያ ግን ያልተለየ
ጠላት መብት ያለው በጥባጭ ነውና በአንዳንድ ቦታዎች እንደምነሰማውና እንደምናየው ሁለት መልክ ባላቸው ምዕመናን
ቅዳሴያችን በነውጥ እና ድብድብ ከመቋረጡ በፊት ልንነቃ ያስፈልጋል፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 55
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ሚያዚያ 3ኛ ሳምንት
ሞንታኒዝም
ሞኖፊሲትስ ማለት በውላጤ የተገኘ አንድ ባሕርይ ይህ ስም ተዋሕዶን የሚገልጥ አይደለም፡፡
ምክንያቱም ተዋሕዶ ስንል ያለ መጠፋፋት ተዋሐዱ አንዱ የአንዱ ባሕርይን ያለመለወጥ ያለፍልጠት ያለኅድረት ያለሚጠት
ተዋሐደ ብለን እናስተምራለንና ነው፡፡ ይህ ትምህርት ግን የአውጣኪን ክህደት በትክክል የሚገልጥ ቃል ነው፡፡ ዳዩፊሲስትስ
ይህ በትክክል የንስጥሮስን ክህደትና የልዮንን የፍልስፍና ትምህርት የሚገልጥ ነው ፡፡ የንስጥሮስ ሁለት ባሕርይ ሁለት አካል
ሁለት ሕላዌ አለው ስለሚል ዳዩፊሲስትስ ነው የልዮንም ሁለት ባሕርይ ስለሚል ዳዩፊሲስትስ ብለን መጥራት እንችላለን፡፡
ይህን ጉባኤ ማድረግ የተፈለገበት ምክንያት የተዋሕዶ አርበኞች ተዋሕዶን በማስተማር ስለበረቱና በክርስትናው ዓለም ተዋሕዶ
እየታወቀ እየተረዳ ስለመጣ በዚህ ምክንያት ካቶሊካዊያኑ የኬልቄዶን ጉባኤን አንደ ሕጋዊ ጉባኤ በመቁጠር የጉባኤውን ሐሳብ
ለማጽናት ነው፡፡

ተዋሕዶ ከአውጣኪ ትምህርት ጋር ያለው ልዩነት


ጥንታዊያን ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት አውጣኪን ቁጥሩ ከመናፍቃን እንጂ ከቅዱሳኑ ተርታ አላኖሩትም፡፡
ትምህርቱም በቅዱስ አባታችን ዲዮስቆሮስ አማካኝነት የተወገዘ ነው፡፡
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስትል
1. እንበለ ዉላጤ(ያለ መለወጥ)ዉላጤ ስንል ሥጋ ወደ መለኮት መለኮት ወደ ሥጋነት መለወጥ ማለታችን ነው፡፡ በመጽሐፍ
ቅዱስ ከምናገኛቸው ታሪኮች የመለወጥን ትርጉም ለመረዳት ምሳሌ እንጥቀስ የሎጥ ሚስት ወደ ጨው አምድነት (ዘፍ 19፥
26) መለወጥ የቃና ዘገሊላ ውኃ ወደ ወይን ጠጅነት (ዮሐ 2፥1-3) መለወጥም ፍጹም ባሕርውን ለቆ አዲስ ወደ ሆነ ባሕርይ
መለወጡን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ለተዋሕዶ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ መለኮት ወደ ሥጋነት ተለወጠ ካልን መለኮት ፍጹም
ሰው ሆነ ማለት ነው፡፡ ይህም ነገረ ድኅነቱን ከንቱ ያደርገዋል ምክንያቱም የሰው ልጅ በፍጡር ደም አይድንምና በፍጡር ደም
ቢድን ኖሮ ቀድሞ በዳነ ነበር፡፡ ሥጋ ወደ መለኮትነትም ተለወጠ ብንል ዓለም አልዳነም ወደሚል ሐሳብ የሚመራ ነው፡፡
መለኮት በባሕሪው ሊዳሰስ ሕማም ሊቀበል ወደ መቃብር ሊወርድ አይችልምና፡፡በተዐቅቦ(በመጠባበቅ) አንድ ሆኑ እንጂ
መለኮት የሥጋን ባሕርይ ገንዘብ አደረገ ሥጋም የመለኮትን ባሕርይ ገንዘብ አደረገ
2. እንበለ ሚጠት(ያለመመለስ)ይህም ዉላጤ ባሕርይው ከነበረበት ሁኔታ ከተቀየረ በኃላ መልሶ ወደ ቀድመ ግብሩ(ባሕርይው)
ሲመለስ ሚጠት ይባላል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ የሙሴን በትር እንደምሳሌ ብናነሳ ወደ እባብነት ተለወጠ በኃላ መልሶ በትር
እንደሆነው ሁሉ ለመለኮትና ለሥጋ እንዲሁ ነው ብሎ ማስተማር ሚጠት ይባላል፡፡
3. እንበለ ኅድረት ይህ ትምህርት የተወገዘው የንስጥሮስ ትምህርት ነው፡፡ ዳዊት ከማኅደር ሰይፍ ከሰገባው እንደሚያድር
በማርያም ልጅ በኢየሱስ ላይ አምላክ አደረበት በማለት የስህተት ትምህርት አስተምሮል ይህ ኅድረት ይባላል፡፡ ቅድስት ቤተ
ክርስቲያናችን ተዋሕዶ ስትል ከዚህ የሚለይ ነው፡፡ ይህ ባሕርይን ለሁለትለመክፈል የተመቸ ነው ይኸውም ዳዊት ከማህደሩ
ቢቀመጥ ማኅደር እነደማይባል ሁሉ ኢየሱስም የሰው ልጅ እንጂ አምላክ አይባልም እንደማለት ነው፡፡ ስለዚህም አምላክ
ወሰብእ (ፍጹም ሰው ፍጹም)ማለት አይቻልም ማለት ነው፡፡ ይህን የስሕተት ትምህርት በጉባኤ ኤፌሶን የተወገዘ ትምህርት
ነው፡፡
4. እንበለ ቱሳሔ(ያለመቀላቀል) ቱሳሔ የአውጣኪ ትምህርት ነው ይህ ሰው በአካልም በባሕርይም አንድ ነው ብሎ ቢያስተምርም
ነገር ግን በመቀላቀል በመደባለቅ ነው የሚል ነው፡፡ መለኮት ግን ምንም ቱሳሔ ሳይኖርበት ከእመቤታችን የነሣው ሥጋ ባለው
አጽንቶ የፍጡር ልቡና መርምሮበማይደርስበት ግብረ አምላካዊ ጥልቅ በኾነ ምሥጢር(በመሆን) ተዋሕደው እንጂ በመቀላቀል
እንደወተትና ቡና ተቀላቅለው በመካከላቸው ሌላ ነገርን ያስገኙ ወይም የተጠፋፉ አይደሉም ወይም እንደ ትድምርት
ያለ(በመደራረብ) እንደ ልብስ እንደእንጀራ ዓይነት ባለሆነ ወይም እንደቡዐዴ(ማዋሐድ ማያያዝ ተቃርቦ ተላስቆ)
እንደእንጨትና ብረት ባልሆነ እንደነፍስናሥጋ በኃላ መለያየት ያለው ያለ ፍልጠት በተዋሕዶ ከበረ እንላለን፡፡ የጥንታዊያን
ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እምነታቸው ይህ ነው፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 56
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

አውጣኪ
የአውጣቂ ማንነት ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ አንጻር
አውጣኪ እ.አ.ዘ ከ380-456 ዓመተ ምህረት በቁስጥንጥንያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የአንድ ገዳም አበ-
ምኔት የነበረ፣ ለኦርቶዶክሳዊት ዕምነት በእጅጉ የሚቀና ነገር ግን ብዙ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የሌለው ሽማግሌ ቄስ ነበር።
"መሰናክል ግድ ሳይመጣ አይቀርም፥ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት (ሉቃ 17፡1) ሲል ጌታ እንደተናገው የአጋጣሚ
ሆነና አውጣኪ በክህደት ትምህርቱና ነገር በማወሳሰቡ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ለኬልቄዶን ጉባኤ መካሄድና ለቤተ
ክርስቲያን ከሁለት መከፈል ምክንያት የሆነ ሰው ነው።
በዘመኑ የነበረው መናፍቅ ፓትርያርክ ንስጥሮስ ለክርስቶስ ሁለት አካላት ሁለት ባህርያት አሉት በማለት
ሰው የሆነውን አምላክ ከሁለት በመክፈሉና ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ ሰብዕ እንጅ ወላዲተ አምላክ ልትባል አይገባም
በማለቱ "የተዋሕዶ ማኅተም" እየተባለ በሚጠራው በቅዱስ ቄርሎስ መሪነት በ431 ዓ.ም በኤፌሶን ጉባኤ ተደርጎ ተወግዞ
ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ተልይቷል። በዚህ ጊዜ አውጣኪ የቄርሎስ ትምህርት ደጋፊና ዋና የተዋሕዶ እምነት አርበኛ መስሎ
ሲራመድ ነበር። ይሁን እንጅ የቅዱስ ቄርሎስትን ትምህርት በአግባቡ ለመረዳትና ለማስረዳት የጠለቀ የሥነ-መለኮት ትምህርት
የሌለው ተራ ካህን በመሆኑ ከንስጥሮስ ሞት በኋላ በንስጥሮስ ደጋፊዎችና በተዋሕዶ እምነት ተቀባዮች መካከል ያለው ክርክር
እየጦፈ ሲመጣ አውጣኪ በቄርሎስ ትምህርት ላይ የሚሰጠው ማብራሪያ መስማሩን እየሳተ መጣ። የንስጥሮስ ትምህርት ዋና
ችግሩ "በተዋሕዶ አምላክ ሰው ሰውም አማልክ ሆነ" የሚለውን ትምህርት አምኖ አለመቀበል ስለነበር የአውጣኪ ትኩረት
ደግሞ ለክርስቶስ መለኮታዊነት ትኩረት መስጠትና የቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አማላክነት ማረጋገጥ ነበር። ይሁን
እንጅ አውጣኪ "አንድ አካል አንድ ባሕርይ" የሚለውን የቅዱስ ቄርሎስ ትምህርት የተረዳው በሌላ መንገድ ነበር። እናም
ፍጹም መስመር አልፎ በመሄድ ክርስቶስ ሰው በሆነ ጊዜ መለኮት የሥጋን ባሕርይ ውጦ አጥፍቶታል ብሎ በማስተማር
የክርስቶስን ትስብዕቱን (ፍጹም ሰው መሆኑን) ካደ። ይህም በቤተ ክርስቲያናችን አስተምሕሮ "የአንድ ገጽ" ትምህርት
(Monophysitism) ይባላል። የቅዱስ ቄርሎስ ትምህርት Miaphysitism እንጂ Monophysitism አይባልም።
Miaphysitism "ለክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባሕርይ አለው" ማለት ሲሆን ይህም መለኮትና ትስብዕት በልዩ የረቀቀ ተዋሕዶ
ከሁለት አካላት አንድ አካል ከሁለት ባሕርያት አንድ ባሕርይ መሆናቸውን የሚያመለክት ነው። የአውጣኪ የክህደት ትምህርት
ግን Monophysitism ይባላል። ምክንያቱም Monophysitism ማለት የሥጋ ባይህርይ በመለኮታዊ ባሕርይ ተተክቶ አንድ
አካል አንድ ባሕርይ ማለት ነውና።
አውጣኪ ከዕውቀት ማነስ የተነሳ የፈጠረው ክህደት የቤተ ክርስቲያንን ቀጥተኛ አስተምህሮ ከማዛባት አልፎ
አባቶችንም ማወናበዱ አልቀረም። ይህ አዲስ ትምህርት በቁስጥንጥንያ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ሲሰማ የቁስጥንጥንያው ሊቀ
ጳጳስ ፍላቪያን በአካባቢው ያሉ ጳጳሳትን ሰብስቦ በ448 ዓ.ም. በውግዘት ከ30 ዓመታት በላይ በአበ-ምኔትነት ካገለገላት ቤተ
ክርስቲያን እንዲለይ አደረገው። በዚህ ጊዜ አውጣኪ የልቡን ከልቡ አድርጎ የቅዱስ ቄርሎስትን ትምህርት ስላስተማርኩ
በውግዘት ከቤተ ክርስቲያን ተለይቻለሁና እንደተለመደው በእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን መሪነት ዓለም-አቀፍ ጉባኤ ተጠርቶ
ይታይልኝ እያለ መወትወት ጀመረ።
እዚህ ላይ ከቅዱስ ቄርሎስ ሞት በኋላ የእስክንድርያን ቤተ ክርስቲያን በፓትርያርክነት ይመራ የነበረው ቅዱስ
ዲዮስቆሮስ በጣም ተሸውዷል የሚሉ ሊቃውንት ብዙ ናቸው። ምክንያቱም የአውጣኪን ተለዋዋጭ ባሕርይ ሳያውቅ በ449
ዓ.ም. ጉባኤ አድርጎ አውጣኪን ከውግዘቱ እንዲፈታና ወደ ቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲመለስ ማደረጉ ነው። በዚህ ጉባኤ
የቁስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ ፍላቪያን አልተገኘም፤ ምክንያቱም እርሱ ያወገዘው ማናፍቅ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሊመለስ ይችላል
የሚል ጥርጣሬ ስለነበረው ነው። የሮሙ ሊቀ ጳጳስ ሊዮንም አልተገኘም። ነገር ግን "ለክርስቶስ አንድ አካል ሁለት ባሕርያት
አሉት" የሚል ጽሑፍ አስይዞ መልእክተኞችን ልኳል። "የልዮን ጦማር" ካቶሊኮችና የምሥራቅ ኦሮቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት
እስከ አሁን ድረስ የሚመኩበት የእምነታቸው መሠረት የሆነ መልእክት ነው። ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ይህን ጽሑፍ "ጦማረ-ልዮን"
በጉባኤ እንዲነበብ አላደረገም። ከንስጥሮስ ትምህርት ብዙም ያልራቀ ሆኖ አግቶታልና። በዚህም ምክንያት ምዕራባውያን
ቅዱስ ዲዮስቆሮስንና የእስክንድርያን ቤተ ክርስቲያን "Monophysite" የአንድ ገጽ እምነት አራማጅ ብለው አውግዘዋል። ቅዱስ
ዲያስቆሮስና ተከታዮቹም ሊዮንና ተከታዮቹን በዚች ጽሑፍ ምክንያት "ንስጥሮሳዊያን" ብለው አውግዘዋቸዋል።
ቅዱስ ዲዮስቆሮስ አውጣኪ መናፍቅ መሆኑን ተገንዝቦ በኋላ እንደገና ያወገዘው ቢሆንም በሁለተኛው
የኤፌሶን ጉባኤ በ448 ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመለስ ማድረጉና ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል
የተፈጸመው ወደ ልዩነት የሚያመራ መወጋገዝ የእስክንድርያን ቤተ ክርስቲያን ከዓለም-አቀፍ የቤተ ክርስቲያን መሪነት
ለማውረድ ሲጥሩ ለነበሩ ምዕራባውያን ምቹ ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል። ከዚህ በኋላ ከፖለቲካው ጋራ ተጣብቀው በእስክንድርያ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 57
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ላይ በማሴር ያለ አንዳች ምክንያት የኬልቄዶንን ጉባኤ እንዲጠራ አድርገዋል። በኬልቄዶን ጉባኤ
ቅዱስ ዲዮስቆሮስን መናፍቅ ለማለት ሞክረው ነበር። ነገር ግን ከመምህሩ ከቅዱስ ቄርሎስ ያገኘውን ዕውቀት መሠረት አድርጎ
የሚሰጣቸውን ምላሽ መቋቋም አልቻሉም። እናም በአልታዘዝ ባይነትና በሌላም ፖለቲካዊ መስመር ወንጅለው ከዓለም-አቀፍ
የጉባኤ መሪነት ቦታውን ለቆ እንዲወርድና ጥርሱ እስከሚረግፉ ድረስ በጭካኔ እንዲደበደብ አድርገዋል። ሕይወቱም ያለፈው
በግዞት

ሚያዚያ 4ኛ ሳምንት
ሰባሊዮሳውያን
ሰባልዮስ በሦስተኛው ሞቶ ክፍለ ዘመን የነበረ የሊቢያ ሰው ነው፡፡በትምህርት ምክንያት ወደ ሮም ሔደ ያን ጊዜም
ሮም ዓለም አቀፍና የንጉሠ ነገሥት መዲና ስለነበረች የፍልስፍናና የሃይማኖት ሰዎች መሰብሰበያም ነበረች፡፡ በዚህም ምክንያት
ብዙ ክህደት እና መፈላሰፍ የፈልቀባት ነበር፡፡ሰባልዮስም በሮም እግዚአብሔር አንድ አካል አንድ ገጽ ነው የሚለውን
ትምህርት ተማረ፡፡ ይህን የተማረው አብ መከራ ተቀብለ ከሚሉ መናፍቃን ፡፡እነዚህ መናፍቃን በሮም ያስተምሩት የነበረው
ትምህርት ሞዳሊሰቲክ ሞናርኪያኒዝም ይባላል አንድ ገጽ በተለያ ዘመናት ቅርጹን ለዋውጦ ታየ ማለት ነው፡፡ሰባልዮስ ይህን
ኹሉ አግበስብሶ ወደ አገሩ በመመለስ ይህንኑ ማስተማር ጀመረ ፡፡ሰባልዮስ እንደሚለው አንዱ አካል ሰው ሆኖ ሥጋ ለብሶ
ስለታየና ሐዲስ ኪዳንንም ስለሰጠን ወልድ ተባለ በኃላምበበዓለ ሃምሳ ጰንጠቆስጤ በአምሳለ እሳት ወርዶ ለሐዋርያት
ምሥጢር በመግለጡ በማናገሩ መንፈስቅዱስ ተባለ እንጂ አንድ አንድ ገጽ ነው ብሏል ::ይህ የሰባልዮስ ትምህርት በማቴዎስ
ወንጌል 28÷19 ወእንዘ ታጠምቅዎሙ በሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ የሚለውን አምላካዊ ትምህርት ምሥጢረ
ሥላሴን ያፋልሳል ፡፡ የሰባልዮስንም ትምህርት የተቀበሉ ሰባልዮሳውያን ተበለው ይጠራሉ፡፡
ሰባልዮስ በአባ ጊዮርጊስ አጠራር “ሰብልያኖስ” ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ስለ ሰባልዮስ ከብሉይ ከሐዲስ
እየጠቀሰ መልስ ሰጥቷል፡፡ ሊቁ “እኛ ግን ሦስት ገጽ አንድ ባሕርይ፣ ሦስት አካል አንድ አምላክ፣ ሦስት ስሞች አንድ
እግዚአብሔር እንላለን” በማለት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ይመሰክራል፡፡ ሰባልዮስንም “ተጠራጣሪ ሆይ እንግዲህ ባንተ
ያለውን ክሕደት ትተህ በሥላሴ እመን፤ ለሥላሴ ገጻትም ምስጋናን አቅርብ” በማለት ይመክረዋል፡፡
መቅዶኒዮወሳውያን
ከአርዮስ ቀጥሎ የምፍቅና ትምህርቱን ያሰማው መቅዶንዮስ የተባለው መናፍቅ ነው። ይህ መናፍቅ ከቅድስት ሥላሴ
አንዱን መንፈስ ቅዱስን አካል የለውም በማለት የምንፍቅና ትምህርቱን በቆስጠንጥንያና በአካባቢው አሰማ። በዚህ ጊዜ
ቤተክርስቲያን የተቃውሞ ደውሏን አሰማች። በ381 ዓመተ ምህረት በቆስጠንጥንያ 150 ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በተገኙበት
መቅዶንዮስ የክህደት ትምህርቱን አቀረበ። ጉባኤውም የመንፈስ ቅዱስ የባህሪ አምላክነት ከአብ ከወልድ ጋር በአንድነት
የሚሰለስ የሚቀደስ መሆኑን መፅሐፍ ቅዱስን በመጥቀስ አስረዳ። መቅዶንዮስም ከዚህ ሰይጣናዊ ትምህርቱ እንዲታቀብ
ተጠየቀ። እሱ ግን እንቢ በማለቱ ተወግዞ ከቤተክርስቲያን አንድነት ተለይቷል።
መቅዶንዮስ ቁጥሩ ከመንፈቀ አርዮሳውያን ነው፡፡ አርዮሳውያን ገነው ቁስጥንጥንያን ባጥለቀለቁበት ሰዓት
እየተመላለሰ የቁስጥንጥንያ መንበር ይዟል ፡፡ የሞተው በ369 ዓ.ም ነው፡፡ ይኧው መናፍቅ ከቅድስት ሥላሴ ሦስተኛው አካል
መንፈስ ቅዱስ ሕጹጽ ነው፤ ፍጡር ነው፤ ብሎ በቁስጥንጥንያና በአካባቢዋ መርዙን ባገሳ ጊዜ በግሳቱ የተመረዙ አጽራረ
መንፈስ ቅዱስ የሚባሉ መናፍቃን ቤተ ክርስቲያንን ሲያውኳት ኖረዋል፡፡
ይህ የመቅዶንዮስ ክህደት በተሰማ ጊዜ እንደተለመደው ቤተ ክርስቲያን የተቃውሞ ድምጧ አሰማች ፡፡ ያን
ጊዜም የቁስጥንጥንያ ንጉሥ የነበረው ቴዎዶስዮስ ቀዳማዊ ይህን የቤተ ክርስቲያን ችግር የሚፈታ ጉባኤ በቁስጥንጥንያ
እንዲደረግ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች መልእክት አስተላለፈ ፡፡ በዚህ ምክንያት 150 ሊቃውንት በቁስጥንጥንያ ተሰበሰቡ የዚህ
ጉባኤ ሊቃነ መናብርት ብዙ ጊዜ ተለዋውጠዋል ፡፡ በመጀመሪያ የተሰየመው ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ነበር ፤እሱ ወዲያው
ሊቀመንበርነቱን ሲተው ኔታሪዎስ የተባለ መጥሮጰሊስ ተሠየመ ፡፡ ኔክታሪዮስም እንዲሁ ሊቀ መንበርነቱን ተወ በዚህ ጊዜ
ጢሞቴዎስ የተባለው የእስክንድርያ ሊቀጳጳስ ተሠየመ፡፡ በግንቦት ወር 381 ዓ.ም የመቅዶንዮስ ጉዳይ ለጉባኤው ቀረበ፤
መንፈስ ቅዱስ ሕጹጽ ነው፤ ለማለቱ ግን ያቀረበው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምንጭ አልነበረውም፡፡ ጉባኤው በጥሞና ሁኖ ስለ
መንፈስ ቅዱስ አምላክነት በቅድሳት መጻሕፍት የተጻፉትን ምስክሮች በኢሳያስ ምዕራፍ 6 ‹‹ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ጸባኦት ›› እያሉ ሲያመሰግኑ የሰማቸው መላእክት ‹‹ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን ›› አንድ አምላክነት የአካልን ዕሪና

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 58
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

የባሕርይን አንድነት መመስከራቸው መሆኑን ገልጧል፡፡ ከዚህም ጋር ራሱ ጌታ በመጨረሻ ለሐዋርያት በሰጠው ትእዛዝ ‹‹
በአብ ፤ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቁ ›› ሲላቸው ‹‹ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ›› አንድ አምላክ ናቸው እንጂ
የሚበላለጡ አለመሆናቸውን ገልጦ ተናግሯል፡፡ ነገር ግን መቅዶንዮስ በአርዮስ ፈር የሚጓዝ ተረፈ አርዮሳዊ ስለሆነ ከአርዮሳዊ
አስተሳሰቡ ፍንክች አላለም ፡፡ ከዚህ በኋላ 150ው ሊቃውንት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሁነው መንፈስ
ቅዱስን ሕጹጽ/ፍጡር/ የሚል የመቅዶንዮስን ትምህርት አውግዘው የሠለስቱ ምእትን ትምህርተ ሃይማኖት አጽድቀዋል ፡፡

ንስጥሮሳውያን
መቅዶንዮስ ቀጥሎ የተነሳው መናፍቅ ደግሞ የቆስጠንጥንያው ሊቀ ጳጳስ ንስጥሮስ ሲሆን የኑፋቄ ትምህርቱም
ኢየሱስ_ክርስቶስ_ሁለት_አካል_ሁለት_ባህሪ_ነው።" ከማርያም የተወለደው ዕሩቅ ብእሲ ነው፤ ቃል በጥምቀት በዮርዳኖስ
እስኪያድርበት ድረስ ወልደ ማርያም የቃል ማደሪያ ለመሆን ተወለደ። ስለዚህ ማርያም ወላዲተ ሰብእ ናት እንጅ ወላዲተ
አምላክ አይደለችም በሚል አይን ያወጣ የኑፋቄ ትምህርት አቀረበ።
መስከረም 12 ኹለት መቶው ሊቃውንት በ431 ዓ.ም በኤፌሶን ተሰባሰቡ፤ ጉባኤው የተደረገው ታናሹ
ቴዎዶስዮስ በነገሠ በ20 ዓመት ነው፤ እነርሱም ቅዱስ ቄርሎስን መርጠው አፈ ጉባኤ አደረጉት፤እርሱም የክርስቶስን አንድ
አካል አንድ ባሕርይ መኾኑን፤ የቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክነት ከቅዱሳት መጻሕፍት በመተንተን መናፍቁ
ንስጥሮስን ተከራክሮ ረታውና ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት አውግዘው ለይተውታል፡፡
ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስም በተራቀቀ የቅዱሳት መጻሕፍት ዕውቀቱ መልስ ሲሰጠው፡-
“ቃል በማይመረመር መግቦቱ ሰው ኾኖ ሥጋ ለብሶ ከኀጢአት በቀር ሰው የሚሠራውን ኹሉ ሠራ፤ ሰው ስለኾነ
ሥጋ ስለለበሰ የሠራውን ኹሉ ለይቶ ከፋፍሎ ግማሹን ለመለኮት ግማሹን ለትስብእት ሰጥቶ መናገር ጠቅላላውን የምስጢረ
ሥጋዌ ጠባይ ይለውጠዋል፤ ሰው ኾነ ካልን የሰብእናን ሕግ መፈጸሙን ማወቅ አለብን፤ ቃል ከሥጋዌ በፊት በሥጋዌ ጊዜ
ከሥጋዌም በኋላ የማይለወጥ ነው፤ ሰው ኾነ ሥጋ ለበሰ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ኾነ፤ ፍጹም ሰው መኾኑንም የምናውቀው
ሰብአዊውን ኹሉ የራሱ በማድረጉ ነው፤ ተዋሕዶውም ባሕርያዊ ነው፤ በከዊን የተደረገውን ባሕርያዊ ተዋሕዶ ካልተቀበልን፤
ኹለት ልጆች ከማለት አዘቅት ውስጥ እንገባለን፤ ቃል የሥጋን ገንዘብ የሥጋን ሀብት የራሱ ካደረገው እንደገና የሌላ ሊኾን
አይችልም” በማለት እውነተኛውን ኦርቶዶክሳዊዉን ትምህርት ባስተማረ ጊዜ ቃልና ሥጋን ጐን ለጐን አድርገው ምንታዌን
የሚያስተምሩ መናፍቃን ኹሉ ደንግጠዋል፡፡
“ቅድስት ድንግል የፈጣሪ እናት ተብላ መጠራት እንደምትችል ለማመን አንዳንዶች ጥልቅ ወደ ኾነ ጥርጣሬ
ውስጥ በመግባታቸው ተደንቄያለኊ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጣሪ ከኾነ የወለደችው ቅድስት ድንግል እንደምን የፈጣሪ
እናት አትኾንም?” (ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ 412-444 ዓ.ም)
“ያም ኾኖ “ቃል ሥጋ ኾነ” (ዮሐ 1፡14) የሚለው አገላለጽ የባሕርይ አምላክነቱን ወይም ከእግዚአብሔር አብ
መገኘቱን ሳይሽር እንደ እኛ ሥጋን ደምን ነሣ የኛን አካል የራሱ አደረገ ከድንግል የተገኘ ሰው ኾነ ለማለት ካልኾነ በስተቀር
ሌላ ትርጉም የለውም፤ ሥጋን ተውሕዶ የነበረ ቢኾንም እንኳን ርሱ ራሱ እንደነበር ነበር፤ ይኽ የትክክለኛው እምነት ዐዋጅ
በኹሉም ቦታ ይነገራል፤ ይኽ የቅዱሳን አባቶች ስሜት ነበር ስለዚኽ ቅድስት ድንግልን የአምላክ እናት ብለው ጠሯት፤ አንዲኽ
ብለው የጠሯትም የአካላዊ ቃል ባሕርይ ወይም መለኮታዊነቱ የተዠመረው ከቅድስት ደንግል ነው ለማለት ሳይኾን በርሷ
ምክንያት አካላዊ ቃል ነባቢት ነፍስ ያለችውን ቅዱስ ሥጋ ተውሕዶ አንድ አድርጎ በሥጋ በመወለዱ ነው” (ቅዱስ ቄርሎስ
በ430 ዓ.ም ለንስጥሮስ ከላከው የመዠመሪያ ደብዳቤ የተወሰደ)

“ማንም ዐማኑኤልን ፈጽሞ የባሕርይ አምላክ እንደኾነ ሥጋንም የተዋሐደ አካላዊ ቃልን በሥጋ የወለደች ርሷ
የአምላክ እናት እንደኾነች የማይመሰክር ርሱ የተወገዘ ይኹን” (ቅዱስ ቄርሎስ በ430 ዓ.ም ለንስጥሮስ ከላከው ሦስተኛ
ደብዳቤ የተወሰደ)
“እናም ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ ልጅ የኾነው፣ ፍጹም አምላክም
ነባቢት ነፍስን ሥጋን ነሥቶ ፍጹም ሰውም የኾነው፤ በመለኮቱ ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው በዘመኑ ፍጻሜ
ለእኛና ለድኅነታችን በሥጋ ከድንግል ማርያም የተወለደው፣ በአምላክነቱ ከአብ ጋር የተካከለ በትስብእቱም ከእኛ ጋር የተካከለ
ከኹለት አካል አንድ አካል ከኹለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ስለኾነው ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንመሰክራለን፤ ስለዚኽ
አንድ ክርስቶስ፣ አንድ ወልድ እና አንድ ጌታ ብለን እንመሰክራል፤ በዚኽ መቀላቀል በሌለበት ተዋሕዶ መሠረት አካላዊ ቃል
እግዚአብሔር ወልድ በፅንስ ከርሷ ሥጋን ነሥቶ ሰው በመኾኑ ቅድስት ድንግል የአምላክ እናት ናት ብለን እንመሰክራልን”

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 59
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

(የጉባኤ ኤፌሶን ውሳኔ)መናፍቁ ንስጥሮስ ግን ይኽነን ተዋሕዶ በመካድ የምንታዌ ትምህርትን በመዝራት የሥጋን የባሕርይ
አምላክነት ሽምጥጥ አድርጎ ቢክድም እነ ቅዱስ ቄርሎስ ከቅዱሳት መጻሕፍት ጠቅሰው በመስከረም 12 ቀን, 200 ቅዱሳን
ሊቃውንት በኤፌሶን ጉባኤ ሲከራከሩት መልስ አልነበረውም፡
አቡሉናርሳውያን
አቡሊናርዮስ በታናሽ እስያ በሎዶቅያ ተወልዶ ያደገ ሰው ነው ፡፡የትርጓሜው ስልት የእስክንድርያን
ትምህርት ቤት ስልት ይከተል ስለነበር የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ የሚያውቁ ሰዎች ከእስክንድርያ መናፍቃን ይቆጥሩታል ፡፡
አቡሊናርዮስ የፕላቶንን ፍልስፍና ወስዶ ሰውን ለማወቅ ለማሰብ የምታስችለው ነባቢት ፤ ለባዊትና ሕያዊት ነፍስ ከመለኮት
ተከፍላ የመጣች ናት ብሎ ያምን ነበር ፡፡ ስለዚህም በምስጢረ ሥጋዌ አምላክ ሰው በሆነ ጊዜ የተዋሐደው ሥጋን እንጂ
ነፍስን አይደለም ስለ ነፍስ በነፍስ ፈንታ መለኮት ለሥጋ ነፍስ ሆነው ሁለቱ ማለት ነፍስ መለኮት ለመዋሐድ አይችሉምና
ብሏል ፡፡‹‹ ህየንተ ነፍስ ወልቡና ኮኖ መለኮቱ ›› አቡሊናርዮስ ለዚህ አስተሳሰብ አስረጂ እንዲሆነው ያቀረበው በዮሐንስ
ወንጌል 1፡4 ‹‹ቃል ሥጋ ኮነ ›› ቃል ሥጋ ሆነ የሚለውን ንባብ ነበር ፡፡ በሱ አስተሳሰብ ዮሐንስም መለኮት ሥጋን እንጂ ነፍስን
አልተዋሐደም ያለ መስሎት ነበር ፡፡ ነገር ግን ዮሐንስ በተከታታይ ጽሑፍ እንደሚያስረዳው ቃል ሥጋ ሆነ ማለቱ
የእግዚአብሔር ቃል ነፍስንም ሥጋንም ተዋሐደ ማለቱ እንጂ ከፍሎ ተዋሐደ ከፍሎ ተወ ማለቱ አይደለም ፡፡ መጽሐፍ
ቅዱስ ብዙ ጊዜ ሰው ለማለት ሥጋ ይላል ፡፡ ነብዩ ኢዩኤልም እንደ ዮሐንስ አባባል ሰው ለማለት ‹‹ሥጋ›› ብሏል ፡፡ ለምሳሌ
ኢዩኤል ‹‹እፌኑ መንፈስየ ዲበ ኩሉ ዘሥጋ›› በሥጋ ሁሉ ላይ መንፈሴን እልካለሁ አለ እግዚአብሔር ፤ማለቱ ‹‹ በሰው ››
ሁሉ ላይ ማለቱ እንጂ ነፍስ በሌለው ሥጋ ላይ ወይም በበድን ላይ ማለቱ አይደለም ፡፡ ‹‹ ነፍስ ሥጋ ›› ብሎ ሰው ማለት
በመጽሐፍ ቅዱስ የተለመደ ነው፡፡
የአቡሊናርዮስን አስተሳሰብ በዘመኑ የነበሩ ሊቃውንት ይልቁልም ጎርጎርዮስ ዘእንዚናሁ ሥጋ የሚባለው ነፍስና
ሥጋ ነው ፡፡ መለኮት ሥጋ ሁኖ ሰውን አዳነ ማለትም ነፍስንም ሥጋንም ተዋሐዶ ነፍስንም ሥጋንም አዳነ ማለት ነው፡፡ ሥጋ
እንጂ ነፍስ አልነሳም ፤ አልተዋሐደም ከተባለማ ‹‹ ዘኢተነሥአ ኢድኀነ ወይም ኢያድኀኖ ለዘኢነሥአ›› ቃለ እግዚአብሔር
ወልድ ያልተዋሐደውን አላዳነውም ፡፡ የሰው ሥጋው እንጂ ነፍሱ አልዳነም ማለት ይሆናል ፤ ብሎ መልሷል ፡፡ ምንጊዜም
የኦርቶዶክሳዊ ሊቃውንት የአምላክን ሰው መሆን የሚተረጉሙት ከሰው መዳን ጋር አዛምደው ነው ፡፡ ከተዛነፈ ግን ሁሉም
ቀረ ነው ፡፡ ይኧው ኦርቶዶክሳዊ ሊቅ ጎርጎርዮስ እንደጻፈው ሥጋ በቅድምና ነበር ፡፡ ባሕርዩን አግዝፎ ታየ ብሎ ያስተማረም
ይኧው አቡሊናርዮስ ነው፡፡ ይህ ከግኖስቲኮች የተወረሰ የአቡሊናርዮስ አስተሳሰብ መጀመሪያ በ362ዓ.ም . በእስክንድርያ
ሲኖዶስ ተወግዟል ፡፡ ሁለተኛም በአንጾኪያ ሲኖዶስ በ379ዓ.ም. ተወግዟል፡፡ በመጨረሻም በዚህ ጉባኤ ቁስጥንጥንያ
ተወግዟል፡፡ ከዚህ በኋላ ግን እየጠፋ ሄዷል፡፡ መለካውያን ግን ወደፊት እንደምናየው የአትናቴዎስንና የቄርሎስን የአንድ
ባሕርይ ትምህርት ከአቡሊናርዮስ የተወረሰ አድርገው ፈራ ተባ እያሉ ይናገራሉ፡፡ ነገሩ ግን ጩኧቴን ቀማችኝ›› እንደተባለው
ነው እንጂ የአቡሊናርዮስን ትምህርት የሚመስል የራሳቸው ትምህርት ነው፡፡ ይህንም ኋላ በቦታው እናመጣዋለን ፡፡
ይህ ጉባኤ የሠለስቱ ምእትን ትምህርተ ሃይማኖት አጽድቆ ፤ መናፍቃንን አውግዞ፤ ከመለያየቱ በፊት በጉባኤ
ኒቂያ አንቀጸ ሃይማኖት ውስጥ ተጨማሪ (ሥርዋጽ) ቃላትንና አምስት አንቀጾች ያሉት ተጨማሪ ጸሎተ ሃይማኖት አርቋል፡፡
እንዲሁም ሰባት ቀኖናዎችን ሠርቷል፡፡ ተጨማሪ ሆነው(ሥርዋጽ) የገቡት ቃላት የሚከተሉት ናቸው፡፡ ‹‹እመንፈስ ቅዱስ
ወእማርያም ድንግል›› ‹‹ወተሰቅለ በእንቲአነ በመዋዕለ ጲላጦስ ጰንጤናዊ›› ‹‹ሐመ ወተቀብረ›› ‹‹በከመ ጽሑፍ ውስተ መጻሕፍት
ቅዱሳን›› ‹‹ወነበረ በየማነ አብ›› ‹‹በስብሐት›› ‹‹ወአልቦ ኀለቅት ለመንግስቱ ›› እነዚህ ምንባባት በጉባኤ ኒቅያው አንቀጸ ሃይማኖት
እንደማሟያ እየሆኑ የገቡ ናቸው፡፡ እንዴት እንደገቡ ለማወቅ ባለፈው ምዕራፍ የተጻፈውን አንቀጸ ሃይማኖትና አዲስ የገቡትን
እነዚህን ይመለከታል ፡፡ ሌሎቹ ባለአምስት ተራ ቁጥር ምንባባት ደግሞ ‹‹ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ›› ብለው ሠለስቱ ምእት
የጀመሩትን እነዚህኞቹ የተሰበሰቡበት ዋናው ምክንያት የመንፈስ ቅዱስ ነውና የሱን ማንነት በይበልጥ አብራርተውታል፡፡

ግንቦት 1ኛ ሳምንት

በዘመነ ሊቃውንት የተደረጉ ዓለም አቀፍ የቤተክርስቲያን ጉባኤያት


በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተቀዳሚና ተቀባይነት ያላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም
የምትቀበላቸው አበይት ጉባኤያት 3 ናቸው፡፡ እነርሱም

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 60
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

1. ጉባኤ ኒቅያ
2. ጉባኤ ቁስጥንጥንያ
3. ጉባኤ ኤፌሶን
1.ጉባኤ ኒቅያ
ኒቅያ በጥቁር ባህር ወደብ አካባቢ የምትገኝ ስትሆን የተመሠረተችውም በዲዮናሲዮስ ነው፡፡ አርዮስ የተባለው
መናፍቅ በተፍፃሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ተወግዞ የተለየ ሲሆን በአኪላስ ከውግዘቱ የተፈታ ሲሆን በኋላም
በእለእስክንድሮስ ቢመከር አሻፈረኝ በማለቱ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ የሊቢያና የእስክንድሪያን ኤጲስ ቆጶሳት ሰብስቦ
በ320ዓ.ም ምንፍቅና በጀመረ በ2ት አመቱ አውግዞ ለይተውታል አርዮስ ሲወገዝ የቀድሞ ጓደኛው የነበረው የኒቆሜድያ
ኤጲስ ቆጶስ አውሳቢዮስ ሰብስቦ አርዮስ ከእስክንድርያ የተባረረው በግፍ ነውና ከውግዘቱ ፈተነዋል ብለው ተናገሩ፡፡ ይህንን
ጉባኤ የመራው እራሱ አውሳብዮስ ነበረ፡፡ በ322 ዓ.ም አርዮስ ወደ እስክንድርያ በመመለስ እለእስከንድሮስ ቢያወግዘኝ ተፈትቼ
መጣሁ በማለት በማን አለብኝነት የክህደት ትምህርቱን ማስተማር ቀጠለ ብዙ ተከታዮችንም አፈራ፡፡ ይህን አለመግባባት
ሥር በመስደዱ ቆስጠንጢኖስ የእስፓኝ ጳጳስ ሆስዮስ ወደ እስክንድርያ ልኮ ነገሩን እንዲያጣራ ካደረገ በኋላ ጠቡ የሃይማኖት
እንጂ የስልጣን አለመሆኑን በተረዳ ጊዜ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ እንዲደረግ አዋጅ አስነገረ፡፡ ጉባኤው በመጀመሪያ
በእንቆራ ነበር ሊካሄድ የታሰበው ባልታወቀ ምክንያት ወደ ኒቂያ ተዘዋውሯል፡፡ በአዋጁ መሠረትም ብዙ ኤጲስ ቆጶሳትንና
ሊቃውንት በኒቂያ ተሰብስበዋል፡፡ በጉባኤው ላይ ወልድ ዋህድ በማለት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ
ሆነው የተገኙት 318ቱ ሊቃውንት ብቻ ነበሩ ቤተክርስቲያንም ይህንን ቁጥር ትቀበለዋለች፡፡ ለፍትሐዊነት በጉባኤው የአርዮስ
ደጋፊዎችም ተገኝተው ነበር፡፡ ጉባኤውን የመሩት ሊቀጳጳሳቱ እለእስክንድሮስ፣ ኤዎስጣቴዎስ እንዲሁም ኤጲ ቆጶሱ ሆሲዮስ
ነበሩ፡፡ ለምዕመኑ አንድነት የመሰላቸውን እንዲያደርጉ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ሙሉ ስልጣን ሰቷቸዋል፡፡

ጉባኤው መጀመሪያ የተነጋገረባቸው አንቀጾች

1) አርዮስ ያቀረባቸው ሁሉንም ጥቅሶች መመርምር


2) ጥበብ የሚለውን ቃል እንዴት እንደተረጎመው ማየት
3) ወልድ በባሕርይው ፍጡር ከሆነ በመዳን ምሥጢር ላይ ስለሚደርሰው አደጋ መወያየት
4) የእግዚአብሔር ቃል ለሰው ልጆች ሲል ወዶ ያደረገውን ተዋሕዶ አርዮስ የባሕርይ ተወራጅነት ቢኖርበት ነው ስለማለቱ
5) ወልዱ በባሕርይ ፍጡር ሳለ እንደሌሎች ፍጡራን በገድል በትሩፋት የአምላክነት ክብር አገኘ ስለማለቱ፡
አርዮስ ከፍልስፍና ጋር በማዛመድ የሚመቸውን ጥቅስ በመጥቀስ ጥያቄ በመጠየቅ ሰጣ ገባ ውስጥ ሲገባ እነ
ቅዱስ አትናቴዎስ ግን ጌታ አዳኝ መሆኑን መድኃኒትነቱም የባህርይ አምላክነትን የሚያስረዳ ነው፡፡ የሚያድንም እግዚአብሔር
ብቻ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ መልኩ አስረዱ፡፡ ክርስቶስ አምላክ ካልሆነ አሁንም አልዳንም ማለት ነው፡፡ በእርሱ
መዳናችንን ካመንን ግን ያዳነን እርሱ አምላክ መሆኑን ማወቅና ማመን አለብን፡፡ ፍጡር ፍጡርን አያድነውምና በማለት ምላሽ
ሰጥተዋል፡
ጌታ በገድል በትሩፋት አምላክ ስለሆነ ሊሰገድለት ይገባል ላለው ቅዱስ አትናቴዎስ ሲመልስ ፍጡር ከሆነና
ለእርሱ የአምልኮ ስግደት የምንሰግድ ከሆነ አምልኮ በዓድ ነው ሲል ሀሳቡን ተቃውሞታል፡፡ ከዚህ ሁሉ ክርክርና መልስ በኋላ
በጉባኤው የነበሩ አባቶች አትናቴዎስ እንዳቀረበው ከአብ ጋር አንድ ባሕርይ ነው በማለት የመለኮትን አንድነትና የአካል
ሦስትነት የወልድን የባሕርይ አምላክነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ አንቀጸ ሃይማኖታቸው አጽድቀዋል፡፡ አርዮስንም አውግዘው
ለይተውታል፡፡አሁንም በቤተክርስቲያን የሚሠራበት የሃይማኖት ቀኖና ይህ ነው፡፡ ይህም 12 አንቀጾች ያሉት ሲሆኑ 7ቱ በዚህ
ጉባኤ የተረቀቁ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ይህ የኒቅያ ጉባኤ የተካሄደው በ325 ዓ.ም በ318 ተሰብሳቢዎች በተገኙበት
በእለስክንድሮስ ሊቀመንበርነት የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት በቅዱሳት መጻሕፍት ቃል በማረጋገጥ "ወልድ ፍጡር" ሲል
የሳተውን ቀንደኛ መናፍቅ አርዮስን አውግዘው ለይተዋል፡፡

7ቱ አንቀጸ ሃይማኖት
1) በአንድ አምላክ እናምናለን ሁሉን የያዘ አባት፣ ሁሉን የፈጠረ የሚታየውንና የማይታየውንም
2) በእግዚአብሔር ልጅ በአንድ ክርስቶስም እናምናለን

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 61
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

3) ብቻውን ከአብ የተወለደ ይኸውም ከአባቱ ባሕርይ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተወለደ
እውነተኛ አምላክ፣ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ የሚሆን ሁሉ በእርሱ የሆነ
4) ታመመ፣ ሞተ ተቀበረ
5) በሦስተኛው ቀን የተነሳ
6) ወደ ሰማይ አረገ
7) ህያዋንና ሙታንን ይገዛ ዘንድ ዳግመኛ የሚመጣ የሚሉት ናቸው፡፡

2.ጉባኤ ቁስጥንጥንያ
ጉባኤው የተካሄደው በ381 ዓ.ም በታናሽ እስያ ክፍል በሆነችው በቁስጥንጥንያ ነው፡፡ ምክንያት የሆነ መቅዶኒዮስ
መንፈስ ቅዱስ ሕጹጽ ነው በማለት ባስተማረው ትምህርት ነው፡፡ ይህ ክህደት ሲነሳ የቁስጥንጥንያ ንጉስ የነበረው ቴዎዶስዮስ
ቀዳማዊ ይህ የቤተክርስቲያን ችግር በጉባኤ እንዲፈታ ባስተላለፈው መልእክት መሠረት 150 ሊቃውንት ተሰብስበዋል፡፡
ጉባኤውን በየጊዜው የተለያዩ ሰዎች መርተውታል ፡፡በመጀመሪያም ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ቀጥሎ ኔክታሪዎስ በመጨረሻም
የእስክንድርያው ጢሞቲዎስ ጉባኤውን በሊቀመንበርነት መርተውታል፡፡
በዚህ ጉባኤ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የተወያዩባቸው መሠረታዊ ጉዳዮችም የሚከተሉት ናቸው፡፡
1) የመቅዶንዮስነ ትምህርት (በምስጢረ ሥላሴ መንፈስ ቅዱስ ህጹጽ ነው የሚለውን ክህደቱነ)ለማውገዘ
2) አቡሊናርዮስንና ትምህርቱን (በምሥጢረ ሥጋዌ ቃል እግዚአብሔር ሰው በሆነ ጊዜ ሥጋን እንጂ ነፍስን አልተዋሃደም
የሚለውን ክህደት) ለማውገዝ
3) ወልድ የተዋሃደው የአዳምን ሥጋ አይደለም ሌላ በቅድምና የነበረ ሥጋ ነው እንጂ የሚሉ መናፍቃንን ለማውገዝ፡፡
4) በኒቅያ ጉባኤ ላይ በተረቀቀው ጸሎተ ሃይማኖት ላይ የተጨመሩ 5ቱን አንቀጽ ያለው የሃይማኖት ቀኖና ማርቀቅ ሲሆን
የኒቂያው ረቂቁ ንባቡን ለማስተካከል የገቡ አንዳንደ ቃላት ጭምር ተመልክል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ መቅዶንዮስ መንፈስ ቅዱስ ሕፁጽ፣ ፍጡር ነው ያለበትን ምክንያት ሲጠየቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ማስረጃ አላቀረበም፡፡ ከዚህም በኋላ ጉባኤው በኢሳይያስ 6-3፣ በማቴዎስ 28-19 በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አንድነትንና
ሦስትነን በማስረዳት ቢነገረው ከኑፋቄው አልመለስም በማለቱ 150ው ሊቃውንት የክህደት ትምህርቱንና እርሱን አውግዘው
ለይተውታል፡፡
ሌላው ጉባኤው የአቡሊናርዮስን በምሥጢረ ሥጋዌ ቃል እግዚአብሔር ሰው በሆነ ጊዜ ሥጋን እንጂ ነፍስን
አልተዋሃደም የሚለውን የክህደት ትምህርት አውግዘዋል፡፡ ለዚህም በዮሐንስ 1-14 ላይ "ቃል ሥጋ ሆነ" የሚለውን በመጥቀስ
በትክክል የቃልና የሥጋን ውህደትና መጽሐፍ ቅዱሳዊነት ሊቃውንት አስረድተዋል፡፡
ቅዱስ ጎርጎሪየስ ዘእንዝናዙም ሰው ማለት ነፍስና ሥጋ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን እንጂ ነፍስ አልነሳም
ከተባለ ያዳነው ሥጋን እንጂ ነፋስን አይደለም ብሎ በመመለስ የአቡሊናርዮስን ክህደት ተናግሯል፡፡ ከዚህም በማያያዝ ጉባኤው
በኒቅያ ጉባኤ አንቀጸ ሃይማኖት ከተጠቀሱት ተጨማሪ 5 አንቀጾችን አስቀምጧል፡፡ እነርሱም
1. በጌታ በአዳኝ ከአብ በሠረፀ ከአብና ከወልድ ጋር በነቢያት በተናገረ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን፣
እንስገድለት እናመስግነው
2. በሁሉ ባለች በሐዋርያት ጉባኤ በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፡፡
3. ለኃጥያት ማስተሰርያ በምትሆን በአንዲት ጥምቀት እናምናለን
4. የሙታንን ትንሳኤ ተስፋ እናደርጋለን
5. የሚመጣውንም ሕይወት እንጠባበቃን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ግንቦት 2ኛ ሳምንት
3.ጉባኤ ኤፌሶን
ይህ ጉባኤ ሦስተኛው ዓለማቀፍ ጉባኤ ሲሆን ለጉባኤው መሰባሰብ ምክንያት የሆነው የንስጥሮስ የክህደት ትምህርት
ነው፡፡ በምሥጢረ ሥጋዌ ክርስቶስን በሁለት ከፍሎ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 62
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

1) አንዱን የዳዊት ልጅ
2) ሁለተኛውን የእግዚብሔር ልጅ ነው ብሎ ያምንና ያስተምር ነበር፡፡
ስለዚህ እመቤታችን የወለደችው የዳዊትን ልጅ እንጂ የእግዚብሔርን ልጅ አይደለም በማለት ያስተምር ነበር፡፡
ንስጥሮስ ለክህደት ትምህርቱ የተጠቀመበት ዮሐ 1-14 "ቃል ሥጋ ሆነ" የሚለውን መለወጥን ያስከትላል ያለውን ቃል በሥጋ
አደረ ብሎ እንዲመቸው አድርጎ በመተርጎም መሪ ጥቅሱ ነበረ፡፡ ለንሥጥሮስ ለክህደት ትምህርቱ በሚገባ ምላሽ የሰጠው
የእስክንድርያው ሊቀጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ ነው፡፡ ታላቁ አባት ቅዱስ ቄርሎስ የቃልና የሥጋን ተዋህዶ በማስረዳት የውላጤንና
የኅድረትን ትምህርት ክህደቱን አጋልጧል፡፡ የንስጥሮስን ትምህርት በመጀመሪያ የተቃወመችው የእስክንድርያ ቤተክርስቲያን
ነች የሚባለው በቅዱስ ቄርሎስ አማካኝነት ነው፡፡

ጉባኤ ኤፌሶንየመቅዶንዮስን እና የሌሎችንም የእርሱን መሰል ምንፍቅና አራማጆች በጉባኤ ቁስጥንጥንያ ከተወገዙ እና ከተለዩ
ከ50 ዓመታት በኋላ ከወደ ግሪክ ሌላ ክህደት የያዘ ሰው ስለተገኘ ሌላ ጉባኤ ተጠርቷል፡፡ ይህ ጉባኤ የተጠራው በ431 ዓ.ም
ሲሆን በዚህ ጉባኤ ተሳታፊ የሆኑ ሊቃውንት ቁጥርም 200 ነበር፡፡ ለዚህ ጉባኤ መጠራት ምክንያት የሆነው በግሪክ ባለ አንድ
ገዳም ውስጥ ይኖር የነበረው የንስጥሮስ ክህደት ነው፡፡ ይህ ንስጥሮስ ሁለት መሠረታዊ ክህደቶች አሉበት፡፡ እነዚህም፡-
 ከተዋሕዶ በኋላ መለያየት እንዳለ ያምን የነበረውን ዲያድርስ የሚባለውን መናፍቅ አስተምህሮ ያምን ነበር፡፡ የዚህ
መሠረታዊው ክህደት ሁለት ባሕርይ የሚል ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከተዋሕዶ በኋላ አንዱን ወልደ ዳዊት አንዱን ደግሞ
ወልደ እግዚአብሔር ነው በማለት ያምን ነበር፡፡
 ሁለት ባሕርይ የሚል እምነት ስለነበረው ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው ወልደ እግዚአብሔር ከድንግል ማርያም የተወለደው
ደግሞ ወልደ ዳዊት ነው ብሎ ያምን ስለነበር እመቤታችን የወለደችልን እሩቅ ብእሲ ሰውን ነው እንጅ አምላክን አይደለም
ይል ነበር፡፡ በዚህም ድንግል ማርያምን “ወላዲተ ሰብእ” በማለት ክህደቱን ጀምሯል፡፡
እነዚህን ክህደቶቹን በአደባባይ በማስተማር እርሱን መሰሎችን መሰብሰብ ጀመረ፡፡ ለዚህ ክህደቱም ይደግፋል
ብሎ ይጠቅስ የነበረው “ቃል ሥጋ ሆነ” ዮሐ1÷14 የሚለውን ቃል ነበር፡፡ ይህንን ቃል ለራሱ እንዲመች አድርጎ መለወጥ
አለበት በማለት ኑፋቄውን ቀጥሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፊል 2÷5-6 ላይ “በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ ዐሳብ በእናንተ
ዘንድ ደግሞ ይኹን እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር
አልቆጠረውም” የሚለውን ቃል ይዞ በራሱ ለራሱ እንዲመች አድርጎ በመተርጎም ቃል በሥጋ አደረ ብሎ ኅድረትን ደግፎ
ያስተምር ነበር፡፡ ስለዚህ ይህ ንስጥሮስ በውስጡ ብዙ ምንፍቅናዎችን የያዘ ትምህርት በዐደባባይ ያስተምር ነበር፡፡ ይህንን
የክህደት ትምህርቱን የሰሙ ሊቃውንት በተለያዩ ጊዜያት ተገቢውን መልስ እየሰጡ ይመክሩት ነበር፡፡ ለዚህ ለንስጥሮስ ክህደት
ተገቢውን ምላሽ ከሰጡት አባቶች መካከል በእስክንድርያ 24ኛ ፓትርያርክ የተሾመው ቅዱስ ቄርሎስ ግንባር ቀደሙ ነው፡፡
ይህ ታላቅ አባት የቃልና የሥጋን ተዋሕዶ በሚገባ ከምሳሌ ጋር በማስረዳት ውላጤ እና ኅድረት የሚሉትን የንስጥሮስ ክህደቶች
በሚገባ አጋልጧል፡፡

የጉባኤ ኤፌሶን መጀመር


ይህ ጉባኤ በዋናነት የንስጥሮስን ክህደት በሚገባ መርምሯል፡፡ ጉባኤው በኤፌሶን እንዲደረግ ዐዋጅ
ያወጀው ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘይንዕስ ነው፡፡ በዚህም የጌታን አምላክነት የድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክነት ነቅፎ ያስተምር
የነበረው ንስጥሮስ በቅዱስ ቄርሎስ አፈጉባኤነት በተመራው ጉባኤበ200 ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ተወግዞ ተለይቷል፡፡ በዚህ
ጉባኤ ላይ ታላቁ አባት ቅዱስ ቄርሎስ ምሥጢረ ተዋሕዶን በጋለ ብረት መስሎ በሚገባ አስረድቷል፡፡ ብረት የሚስማማው
ባህርይ እሳት ከሚስማማው ባህርይ ጋር ፈጽሞ የተለያየ ነው፡፡ ብረት እና እሳት ሁለት የተለያዩ አካላት የተለያዩ ባሕርያት
ናቸው፡፡ እሳት አንድ አካል ነው አንድ ባሕርይ ነው ብረትም እንዲሁ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው፡፡ እሳትና ብረት የራሳቸው
የሆነ አካልና ባሕርይ አላቸው፡፡ በጊዜ ግለት ግን እሳት የብረትን ብረትም የእሳትን ባሕርይ ገንዘባቸው ያደርጋሉ፡፡ በጊዜ ግለት
ጥቁር የነበረው ብረት የእሳትን ቀይነት፣ሙቀት፣ መልክእ ገንዘቡ አድርጎ ቀይ፣ሞቃት እንደሚሆን ሁሉ ጎንና ዳር የሌለው
የማይጨበጠው ረቂቅ እሳትም ግዙፍ የሆነውን የብረት ቅርጽና ግዘፍነት ገንዘቡ አድርጎ የብረቱን ቅርጽ የብረቱን ግዘፍነት ይዞ
ይገኛል፡፡ በዚህም አንድ አካል አንድ ባሕርይ ይሆናል፡፡ የመለኮትና የሥጋ ተዋሕዶም እንደዚሁ ያለ ነው፡፡ መለኮት ከሥጋ
ጋር በተዋሐደ ጊዜ መለኮት የሥጋን፣ ሥጋም የመለኮትን ገንዘብ ገንዘቡ በማድረግ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆነ በማለት
ለንስጥሮስ በዚህ ምሳሌ አስረድቷል፡፡ የንስጥሮስንም ምንፍቅና ለሁሉ አጋልጧል፡፡ በዚህም መሠረት የንስጥሮስ ክህደት
ተወግዞ ተለይቷል፡፡በዚህ ጉባኤም አባቶቻችን የጨመሩልን አንቀጸ ሃይማኖት “በአማን ወላዲተ አምላክ፤ በእውነት አምላክን

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 63
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

የወለደች” የሚል ነው፡፡ ንስጥሮስ “ሕስወኬ ትሰመይ ቅድስት ድንግል ወላዲተ አምላክ ወአማነ ትሰመይ ወላዲተ ሰብእ”
በማለት ክዶ ነበርና ሊቃውንቱ እርሱን አውግዘው “በአማን ወላዲተ አምላክ፤ በእውነት አምላክን የወለደች” ናት በማለት
ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ ብለው አንቀጸ ሃይማኖት ጽፈውልናል፡፡

ንስጥሮስ ከጉባኤ ኤፌሶን በኋላ


ንስጥሮስ በክህደቱ ተወግዞ ከተለየ በኋላ ላዕላይ ግብጽ ይኖር ነበር፡፡ በዚህ ኑፋቄውም ጸንቶ ስለነበር ቅዱስ
ቄርሎስ ዝም ብሎ አልተወውም ነበር፡፡ ንስጥሮስ ካለበት ዘንድ ሄዶ ወንደሜ ጌታን አምላክ ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ
ብለህ እመን አለው፡፡ ንስጥሮስ ግን እኔስ አንተ እንደምትለው አልልም ጌታን እሩቅ ብእሲ ድንግል ማርያምን ወላዲተ ሰብእ
እላለሁ እንጅ በማለት አሻፈረኝ አለ፡፡ ቅዱስ ቄርሎስም እመቤቴን ላዋርድ ብለህ እንዲህ እንዳልክና እኔንም አልታዘዝም
እንዳልክ ላንተም አንደበትህ አይታዘዝልህ ብሎ ረገመው፡፡ በዚህም የተነሣምላሱ ተጎልጉሎ ከደረቱ ተንጠልጥሎ ደምና መግል
እየተፋ በከፋ አሟሟት ሞቷል፡፡
በአጠቃለይ እነዚህ ሦስቱ ዓለም አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤዎች በየዘመናቱ ለተነሡት መናፍቃን እና የኑፋቄ
ትምህርቶቻቸው ተገቢውን ውሳኔ በመስጠት እና ቀኖና ቤተክርስቲያንን በመደንገግ ከዚህ አይለፍ ከዚህም አይትረፍ እያሉ
በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደአንድቃል ተናጋሪ በመሆን የተሰበሰቡ ሊቃውንትየአባትነት ምስክራቸውን
ያሳዩባቸው ጉባኤዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ጉባኤዎች በኋላ ሁሉም ሊቃውንት ለጉባኤው ምክንያት ለሆኑት ምንፍቅናዎች
በየራሳቸው ድርሳናትንና ተግሳጽን ጽፈዋል፡፡ እነዚህ ጉባኤዎች ቤተክርስቲያናችን ሉዓላዊት እንደሆነች ያሳየችባቸውም ጭምር
ነበሩ፡፡ በእነዚህ ጉባኤዎች ትምህርተ ሃይማኖትን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እና ትውፊትን በአግባቡ እንድንረዳባቸው
አባቶቻችን ብዙ አስተምረውናል፡፡ እውነተኛ አባቶቻችን እነማን እንደነበሩ፣ የክህደት ትምህርት አራማጆችና ጋፊዎችም እነማን
እንደነበሩ አውቀንባቸዋል፡፡ በዚህም የአባቶቻችን የቀናች የተረዳች ሃይማታችን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እንደሆነችና ከዚህች
ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አንድነትም ያፈነገጡትን መናፍቃን ለይተን እንድናውቅ ረድቶናል፡፡
የጉባኤያቱ ማጠቃለያ

ጉባኤ ኒቂያ ጉባኤ ቆስጥንጥንያ ጉባኤ ኤፌሶን


ጉባኤው ተከናወነበት ዓ ም 325 381 430
የዘመኑ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ቴዎዶስዮስ ዳግማዊ ቴዎዶስዮስ
የተስብሳቢዎች ብዛት 318 150 200
የጉበባኤው ሊቀ መንበር እለእስክንድሮስ ጢሞቴዎስ ዘእስክንድርያ ቅዱስ ቄርሎስ
ጎርጎርዮስ ዘእንዚነናዙ
ኔክትርዮ ዘቆስጠንጥኒያ
በጉባኤው መካሄድ ምክንያት የሆነው ወልድ ፍጡር ነው መንፈስ ቅዱስ ህጹጽ ነው ደንግል ምርያም ወላዲተ
ኑፋቄ አምላክ አትባልም
የጉባኤው ውሳኔ የክርስቶስ አምላክነት የሥላሴን መዓረግ የእመቤታችንን ወላዲተ
በመካድና ወልድ ፍጡር መንግስት በማበላለጥና አምላክነት ክዶ ለማስካድ
በማለት አልመለስ ያለውን መንፍስ ቅዱስን ሕጹጽ የተነሳውን ንስጥሮስን
ቀንደኛ መናፍቅ አርዮስን በማለት የካደውን አውግዞ መለየት
በማውገዘ መለየት መቅዶንዮሰን አውግዞ
መለየት
የጉባኤው አንቀጽ ነአምን በአሐዱ አምላክ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ በአማን ወላዲተ አምላክ
ከሚለው ጀምሮ ወነአምን ከሚለው ጀምሮ እስከ
በመንፈስ ቅደስ ወሕይወት ዘይጽእ ለዓለም
እስከሚለው ድረስ ያለው ዓለም ድረሰ
ክፍል

ግንቦት 3ኛ ሳምንት
በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 64
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ምዕራፍ አምስት
የቤተ ክርስቲያን አበው ጽሐፎች
ጸሎተ ሃይማኖት
ጸሎተ ሃይማኖትን ከነትርጉሙ ጠንቅቆ ማወቅ ሃይማኖትን በተገቢው መንገድ መረዳት መቻል ማለት ነው።
ስለዚህም እያንዳንዳችን ስለ ሃይማኖታችን ብንጠየቅ የጸሎተ ሃይማኖትን ትርጉም ጠንቅቀን ካወቅን ማንነታችንን በሚገባ
መግለጽ እንችላለን። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ እንደ አባታችን ሆይ እና እንደ
እመቤታችን ጸሎት በቃሉ ጸሎተ ሃይማኖትን ማወቅ ይኖርበታል።
የጸሎተ ሃይማኖት አንቀጾች
1. ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።
2. ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን።
3. ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፤ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ፤ በመለኮቱ ከአብ ጋር
የሚተካከል።
4. ሁሉ በእርሱ ሆነ ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የለም፤በሰማይም ያለ በምድርም ያለ።
5. ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ። በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ።
6. ሰው ሆኖ በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለእኛ ተሰቀለ፤ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ
ተነሣ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ።
7. በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ።ዳግመኛም ሕያዋንንና ሙታንንም ይገዛ ዘንድ በጌትነት ይመጣል።
ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።
8. ጌታ ማኅየዊ በሚሆን ከአብ በሰረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን፤ እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋር
በነቢያት የተናገረ።
9. ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን።
10. ኃጢአትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን።
11. የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን።
12. የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን።

የጸሎተ ሃይማኖት አንቀጾች ትርጉም

1- ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።

 እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን


ዐርፎአልና።ዘጸ.፳፡፲፩
 አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤ ዘዳ.፮፡፬
 ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ
እርሱ ነው-………… ..በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም። ኢሳ.፵፤፳፮
 እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም። ኢሳ.፵፬፡፲፩
 እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔም በቀር አምላክ የለም፤ በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ
ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥
ከእኔም ሌላ ማንም የለም። እሳ.፵፭፡፭-፮

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 65
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

 እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔም በቀር አምላክ የለም፤ በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ
ከእኔ በቀር ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ ግን አላወቅኸኝም፤ ኢሳ.፵፭፡፲፰
 ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ፩ ቆሮ.፰፡፮
 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ። ኤፌ.፬፡፮

2 ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን።
 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ
ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሐ.፫፡፲፮
 በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት። ሐዋ.፲፮፡፴፩
 እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን። ፩ ቆሮ.፰፡፮
 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ መላስም ሁሉ
በእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። ፊል.፪፡፲-፲፩
 አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፥ ደግሞም። እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል። ዕብ.፩፡፭
 ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ... ይህ ተጽፎአል። ዮሐ.፳፡፴፩
 አባት ሆይ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ። ዮሐ.፲፯፤፭

3 ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፤ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ፤ በመለኮቱ ከአብ ጋር
የሚተካከል።

 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ዮሐ.፩፡፩
 እኔና አብ አንድ ነን። ዮሐ.፲፡፴፤
 እኔን ያየ አብን አይቶአል። ዮሐ.፲፬፡፱
 ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው። ዮሐ.፲፮፡፲፭
 ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ። ዮሐ.፲፮፡፳፰
 ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ
ነው። ዮሐ.፫፡፲፱

4-ሁሉ በእርሱ ሆነ ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የለም፤ በሰማይም ያለ በምድርም ያለ።


 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። ዮሐ.፩፡፫
 እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው።
 የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት
ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው።
 ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። ቆላ.፩፡፲፮

5- ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ። በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ።
 እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።ኢሳ.፯፡፲፬
 እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። ማቴ.፩፡፲፰
 የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ ገላ.፬፡፬

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 66
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

6- ሰው ሆኖ በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለእኛ ተሰቀለ፤ ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ
ተነሣ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ።
 ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውኃ አንሥቶ። እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም
ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ። ማቴ.፳፯፡፳፬
 በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ። ማቴ.፳፯፡፳፮
 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
 ጲላጦስም እንዲሰጡት አዘዘ። ዮሴፍም ሥጋውን ይዞ በንጹሕ በፍታ ከፈነው፥ ከዓለት በወቀረው በአዲሱ
መቃብርም አኖረው፥ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ። ማቴ.፳፯፡፶፱
 እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ። ማቴ.፳፰፡፮
 ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም። ሉቃ.፳፬፡፭
 አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ
ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ፩ቆሮ.፲፭፡፳-፳፩

7- በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ። ዳግመኛም ሕያዋንንና ሙታንን ይገዛ ዘንድ በጌትነት ይመጣል። ለመንግሥቱም
ፍጻሜ የለውም።

 ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። ሉቃ.፳፬፡፶፩


 በያዕቆብ ቤትም ለዘለዓለም ይነግሳል ለመንግስቱም መጨረሻ የለውም፡፡ሉቃ 1÷ 33
 ከሰማይ ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው፡፡ ዮሐ 3÷ 13
 ይህመ ከተናገረ በኃላ እያዩተ ከፍ ከፍ አለ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበላቸው፡፡ሐዋ 1÷ 9
 ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለው አለ ሐዋ 7÷56
 የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣል ለሁሉ እንደየስራው ያስረክበዋል ማቴ 16÷27
 ጌታ እራሱ በመላእክትም አለቃ ድምጽ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወረዳልና በክርስቶስም የሞቱ
አስቀድመው ይነሳሉ 1ኛ ተሶ 4÷16

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 67
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

8 ጌታ ማኅየዊ በሚሆን ከአብ በሰረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን፤ እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና
ከወልድ ጋር በነቢያት የተናገረ።
 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም
ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ
ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴ.፳፰፡፲፱-፳
 እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ
ይመሰክራል። ዮሐ.፲፭፡፳፮
 ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ
ተነድተው ተናገሩ። ፪ጴጥ.፩፡፳፩
 መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው። የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት
ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ። ፩ዮሐ.፭፡፰

9 ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን።

 አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። ማቴ.፲፮፡
፲፰
 ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ። ኤፌ.፭፡፳፭
 ...እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ
ቀራጭ ይሁንልህ። ማቴ.፲፰፡፲፯

10 ኃጢአትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን።

 ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ማር.፲፮፡፲፮


 ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ
ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። ዮሐ.፫፡፭
 ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ
ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ። ሐዋ.፪፡፴፰
 አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ኤፌ.፬፡፭

11- የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን።

 በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ፤ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ
እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና። ዳን.፲፪፡፪
 በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉም
ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና። ዮሐ.፭፡፳፱

12- የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን።

 እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት
ናት። ዮሐ.፲፯፡፫

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 68
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ግንቦት 4ኛ ሳምንት የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት አጋማሽ ፈተና

ሰኔ 1ኛ ሳምንት
ዲድስቅልያ
ዲድስቅልያ የመጽሐፉ ስም ሲሆን ትርጒሙም ትምህርት ማለት ነው። ይህም የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 35 የሐዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጽሐፍት ዝርዝር ውስጥ አንዱና ጥንታዊው ነው። ዲድስቅልያ ዘቅዱሳን
ሐዋርያት /Apostolical constitution/ ይባላል። መጽሐፉ ቀደም ሲል ወደ ግእዝ ቋንቋ ተተርጒሞና ተጠብቆ ኖሯል።
እንዲያውም ከፍተኛ ዋጋው ቀደም ብሎ ስለታወቀ ከእንጊለዘኛ ትርጓሜው ጋር በአውሮፓ ታትሟል። ይህ መጽሐፍ የቅዱሳን
ሐዋርያት አስተምሮ የሥርዓት ክፍል ሲሆን 43 አንቀጾችን የያዘ መድብል ትምህርት ወተግሣጽ ነው። እነዚህም ስለ ሰው ልጅ
ሕይወትና ሞት ስለ ፍቅረ ስብእና እና ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር፣ ስለ ምስጢረ ጥምቀት፣ ስለ ጾምና ጸሎት፣ ስለ ጾምና ጸሎት፣
ስለ ምስጢረ ቁርባን፣ ስለ ካህናት ክብርና አገልግሎት፣ ስለ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለሚፈጸሙ የተለያዩ ምሥጢራት
ይናገራል።

ታሪክ
ሐዋርያት የሰማርያን ሰዎች ባስተማሩ ጊዜ ሲሞን መሠርይ እጃቸውን በጫኑበት ላይ፣ መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ፣
ተአምራት ሲደረግ፣ ድውያን ሲፈወሱ አይቶ ይህ ተአምራቸው የሥራይ መስሎት እኔም እጄን በጫንኩበት መንፈስ ቅዱስ
እንዲያድር፣ ተአምራት እንዲደረግልኝ አድርጉኝ ብሎ በሥራይ የሰበሰበውን ብዙ ወርቅ ብር አምጥቶ ለሐዋርያት ሰጣቸው፤
ጴጥሮስ ወርቅከ ወብሩርከ ይኩንከ ለከ ለሕርትምና፤ ወርቅህ ብርህ ላንተ ለጥፋትህ ይሁንኽ፣ ይመስለከኑ ዘበወርቅ ትሣየጦ
ለጸጋ እግዚአብሔር፣ አንዱን አካል ወልድን ይሁዳን ሸጠው፤ እኛ ደግሞ አንዱን አካል መንፈስ ቅዱስን የምንሸጥልህ በወርቅ
የምትገዛው ይመስልሃልን፣ አልብከ ክፍል ውስትዘ ነገር፣ መንፈስ ቅዱስን ማሳደር፣ አንድም ከኛ ጋር እድል ፈንታ ጽዋ ተርታ
የለህም፣ በጽኑ ክህደት ተይዘህ አይሃለውና አለው፤ እሱም ይህ ሁሉ እንዳይደረግብኝ ጸልዩልኝ አለ።
ከዚህ የማይሆንለት ቢሆን አንጾኪያ ወርዶ ያስት ከመር፣ ለጴጥሮስ ደቀ መዛሙርትህን አሳተ ብለው ነገሩት፣
ዮሐንስን አስከትሎ አንጾኪያ ወረደ፣ ሲሞን መከራከር የማይቻለው ቢሆን ሮም ወረደ፣ ከዚያም ሄዶ አልተወም፣ ያስታል
ብለው ነገሩት፣ ጴጥሮስ ዮሐንስን አስከትሎ ወርዶ ቅብውን በአንቀጸ ሮም አግኝተው ፈውሰውት ገብተዋል። ተአምራትስ
ይሕታ (ይህ ነው) ብለው ሕዝቡ ወደ እነሱ ተሳቡ፣ ለመስዋዕት የቀረበ ላም ነበር። ሹክ ሹክ ቢለው ከሁለት ተከፈለ፣ ከሚዛን
ቢያገቡት ትክክል ሆኗል፣ ሚዛኑ የዓይን ነው።
ተአምራትስ ይሕታ (ይህ ነው) ብለው ወደ ሲሞን ተሳቡ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ቢባርከው ተነሳ፣ በሬ አስነሥቶ
ማስቀባጠር ቁም ነገር ነውን ብሎ አጋንንትን በምስሐቦ ስቦ ያንተ ሀብት ይህ ነው፣ አንተን ቅስና፣ አንተን ዲቁና ሹሜሃለሁ
ብሎ ዐረግሁ አለ፣ ዮሐንስ ቅዱስ ጴጥሮስን አበ ዓለም ዝም ትላለህን አለው፣ ተወው በእምር ከፍ ይበል አለው፣ በእምር ከፍ
ሲል ቢያማትብበት አጋንንት ጥለውት ሸሹ፣ ወድቆ ተንቆጫቁጮ ሙቷል። ከዚያ የነበሩት የእርሱ ደቀ መዛሙርትም ብዙ
ክህደትና ኑፋቄ አፍልቀዋል።
በዚህም ምክንያት አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት፣ ሰባ ሁለቱ አርድዕት፣ ንዋየ ኅሩይ ጳውሎስ፣ ያዕቆብ እኁሁ
ጳውሎስ፣ ያዕቆብ እኁሁ ለእግዚእነ ሁነው በኢየሩሳሌም ተሰብስበው አርባ ሦስት አንቀጽ፣ ዲድስቅልያ ተናግረዋል። ይህንኑም
ጌታ ባረገ በሃያ ሁለት ዓመት በፊልጵስዮስ ሕንጸተ ቤተ ክርስቲያንን ካሳያቸው፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ካሳያቸው፣ ሥርዓተ
ቤተ ክርስቲያንን ካስተማሯቸው በኋላ፣ እንደ አንደ ቃል ተናጋሪ፣ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሁነው ወስነው ጽፈው ለቀለሜንጦስ
ሰጥተውታል፣ ከዚያ አንሥቶ በመምህራን ቃል ሲነገር ከዚህ ደርሷል። ይኸውም ለኛ ምክር እዝናት ሊሆን ተጽፎልናል።
መጽሐፉ ባዘዘው ሥርዓት ብንጸና ተስፋችንን ካለኝታችን ፍጻሜ ከኢየሱስ ክርስቶስ እናገኝ ዘንድ፣ ወኲሉ ዘተጽሕፈ ለተግሣጸ
ዚአነ ተጽሕፈ፣ ከመ በትዕግሥትነ ወበተወክሎተ መጻሕፍት ንርክብ ተስፋነ እንዲል።
መጽሐፈ ዲድስቅልያ ዐበይትና ንዑሳን አንቀጾች አሉት። በእያንዳንዱ አብይ አንቀጽ ብዙ የተለያዩ ንዑሳን ክፍሎች ይገኛሉ።

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 69
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

የመጽሐፈ ዲድስቅልያ ዐበይት አንቀጾች ዝርዝር


አንቀጽ 1 ፦ የቅዱሳን አበው ሐዋርያት (ትምህርት) ዲድስቅልያ፣
አንቀጽ 2 ፦ ባለጸጎች በመንፈስ ቅዱስ የሚገኘውን ጥቅም ከመጽሐፍት ይፈልጉ ዘንድ እንዲገባ፣
አንቀጽ 3 ፦ ሴቶች ለባሎቻቸው መታዘዝ እንደሚገባቸው፣
አንቀጽ 4 ፦ ስለ ኤጲስ ቆጶስ ስለ ቄስና ስለ ዲያቆናት አገልግሎት፣
አንቀጽ 5 ፦ ኤጲስ ቆጶስ የነገረ ሥራን መቀበል እንደማይገባው፣
አንቀጽ 6 ፦ ካህናት በፍቅር በየወሃት ሆነው ከኃጢያት ወደ ጽድቅ የሚመለሱትን ሰዎች ንስሐቸውን መቀበል
እንደሚገባቸው፣
አንቀጽ 7 ፦ አንድ ሰው መበደሉን ሳያረጋግጡ መቅጣት እንደማይገባ፣
አንቀጽ 8 ፦ ምዕመናን ለቤተ ክርስቲያን መብዓ ማቅረብ እንዲገባቸው፣
አንቀጽ 9 ፦ ዲያቆናት ለካህናትና ለኤጲስ ቆጶሳት መታዘዝ እንዲገባቸው፣
አንቀጽ 10 ፦ ኤጲስ ቆጶሳት መንፈሳዊ እውቀትና ጥበብ ሊኖራቸው እንዲገባ፣
አንቀጽ 11 ፦ ክርስቲያኖች ዘወትር የወንድሞቻቸውን በደል ይቅር ይሉ ዘንድ እንዲገባ፣
አንቀጽ 12 ፦ ክርስቲያኖች በሃይማኖት ወደማይመስሏቸው ቤት ጨዋታ ለማየት፣ ዘፈን ለመስማት መሔድ እንዳይገባቸው፣
አንቀጽ 13 ፦ ባል የሌላቸው ባልቴቶች ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማበርከት እንዲገባቸው፣
አንቀጽ 14 ፦ ሴቶች ማጥመቅ እንደማይገባቸው፣
አንቀጽ 15 ፦ ሥልጣነ ክህነት የሌለው የክህነትን ሥራ እንደማይሠራ፣
አንቀጽ 16 ፦ ስለፈት ሴቶች (መበለታት) የሚናገር፣
አንቀጽ 17 ፦ አባትና እናት ስለሞቱባቸው ልጆች፣
አንቀጽ 18 ፦ ኤጲስ ቆጶሳት አባትና እናት ስለ ሞቱባቸው ልጆችና ባልቴቶች ማዘንና መርዳት እንዲገባቸው፣
አንቀጽ 19 ፦ ባሎቻቸው የሞቱባቸውና ባልቴቶች የሚሰጣቸውን ዕርዳታ በምስጋና መቀበል እንዳለባቸው፣
አንቀጽ 20 ፦ ኤጲስ ቆጶስ መብዓ የሚቀበላቸውን ሰዎች ሥነ ምግባር ማወቅ እንዳለበት፣
አንቀጽ 21 ፦ ወላጆች ልጆቻቸውን መምከርና መገሠጽ እንዲገባቸው፣
አንቀጽ 22 ፦ አገልጋዮች ለአሳዳሪዎቻቸው በግብረገብነት መታዘዝ እንዳለባቸው፣
አንቀጽ 23 ፦ ደናግል ከልባቸው አስበው ሳይመክሩ በድንግልና ለመኖር እንዳይሳሉ፣
አንቀጽ 24 ፦ ስለ ፋሲካ በዓል አከባበርና ስለ ዓበይት በዓላት ክብር እንዲገባ፣
አንቀጽ 25 ፦ ስለሙታን መነሣት፣
አንቀጽ 26 ፦ ስለ ሰማዕታት የሚናገር፣
አንቀጽ 27 ፦ ክርስቲያኖች ወደ ዘፈን ወደ ጨዋታ ቤት መሔድ እንደማይገባቸው፣

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 70
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

አንቀጽ 28 ፦ ክርስቲያኖች በጣዖትና በአጋንንት ስማቸውን ይጠሩና ይምሉ ዘንድ እንዳይገባ፣


አንቀጽ 29 ፦ የበዓላትን ቀን በመንፈሳዊ ደስታ ማክበርና መጠበቅ እንደሚገባ፣
አንቀጽ 30 ፦ ሰሙነ ሕማማትንና የፋሲካ በዓላትን ማክበር እንደሚገባ፣
አንቀጽ 31 ፦ ከዳተኞችና መናፍቃንን ካልተመለሱ መለየት እንዲገባ፣
አንቀጽ 32 ፦ ጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ በቤተ ክርስቲያን ክርክርና መለያየትን እንደሚፈጥር፣
አንቀጽ 33 ፦ ስለ ቀናች ሃይማኖትና ስለ ቅድስት ሥላሴ፣
አንቀጽ 34 ፦ ለሞቱ ሰዎች መጸለይና መዘመር እንዲገባ፣
አንቀጽ 35 ፦ ስለ መንፈሳዊ ምስጋናና ስለ ድካም፣
አንቀጽ 36 ፦ ስለ ሜሮን አስፈላጊነት፣
አንቀጽ 37 ፦ ስለ ቤተ ክርስቲያንና ስለ ሠራዊተ መላእክት አገልግሎት፣
አንቀጽ 38 ፦ በሰንበት ማረፍ እንዲገባ፣
አንቀጽ 39 ፦ ይጠመቁ ዘንድ ስለሚወለዱ ንዑስ ክርስቲያን፣
አንቀጽ 40 ፦ በክርስትና ጊዜ በመጠመቂያ ውሀ ላይ የሚጸለይ ጸሎት፣
አንቀጽ 41 ፦ በሜሮን ላይ ስለሚጸለይ ጸሎት፣
አንቀጽ 42 ፦ አዲስ አማንያን ሲጠመቁ ስለሚጸልዩት ጸሎት፣
አንቀጽ 43 ፦ በሐዋርያት ስለተሾሙ ኤጲስ ቆጶሳት የሚናገር፣

የበርናባስ መልዕክት
የቅዱስ በርናባስ ሕይወት እና ትምህት ተመልከት

የቅዱስ ቀለሜንጦስ መልዕክት


የቅዱስ ቀለሜንጦስ ሕይወት እና ትምህርት ተመልከት

የቅዱስ አግናጥዮስ መልዕክት


የቅዱስ አግናጥዮስን ሕይወት እና ትምህርት ተመልከት

ሰኔ 2ኛ ሳምንት
የቅዱስ ኖላዊ ሄርማስ ያስተማርቸው ትዕዛዛት
ሄርማስ ኖላዊ
ኖላዊ ሄርማ በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረ ሥራ (ጽሑፍ) ነው። ፀሐፊውም ምንም እንኳን አከራካሪ ሀሳቦች
ቢኖሩትም ሄርማስ የተባለ ሰው እንደሆነ ብዙዎችን ያስማማል። ስለዚህ ሰው የምናውቀው ከዚህ መጽሐፍ ላይ የተጻፈውን
ብቻ ነው። ይኽም ሰው በመጀመሪያ ለአንዲት ሮማዊት ሴት ባሪያ ሆኖ የተሸጠ የነበረ ሲሆን ኋላ ላይ ግን ነጻ ለመሆን ችሏል።

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 71
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ነፃ በሆነ ጊዜ የራሱን ህይወት መምራት በመጀመር አግብቶ ልጆችን ወልዷል። በባርነት በነበረበት ጊዜ ሃይማኖቱን የካደ ሰው
ነበር። ኋላ ላይ ግን ወደ እምነት (ሃይማኖቱ) ተመልሷል። ምንም እንኳን ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠ ባይሆንም አይሁዳዊ
መሠረት እንደነበረው ይታመናል። የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያውያን አበው ተብለው ከሚጠሩት ውስጥ የሚመደብ አባት ነው።
ሄርማስ የታዋቂ (ዝነኛ) ሰው ልጅ አልያም ምሁር ያልነበረ ከተራው ማህበረሰብ ዘንድ የሆነ ሰው ነበር።
ከሐዋርያት በኋላ ከተነሡ ሐዋርያውያን አባቶች ከጻፏቸው መጻሐፍት ሁሉ እንደ ሄርማስ ኖላዊ በጥንት
ክርስቲያኖች ዘንድ እጅግ ታዋቂና የተወደደ ማንም የለም። ሆኖም ይህን መጽሐፍ ለማብራራትና ለመተርጎም እጅግ አስቸጋሪ
መሆኑን ብዙ ሊቃውንት ይናገራሉ። የመጽሐፉ ስም በእያንዳንዱ ዘንድ “ሄርማስ ኖላዊ” (ሄርማስ እረኛ/ጠባቂ) ሲሆን በሌሎች
ዘንድ ደግሞ “ኖላዊ ሄርማስ” (ሄርማስ እረኛ/ጠባቂ) ይባላል። በኢትዮጲያ ግእዝ ቋንቋ ግን የመጽሐፉ ርዕስ “ሔርማስ ኖላዊ”
ነው። ሔርማስ ኖላዊ በሁለተኛው ምዕተ አመት ላይ በጥንት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም። በመካከለኛው
ምስራቅ ደግሞ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ተቀባይነቱ በከፍተኛ ደረጃ ቀጥሏል፤ ከአራተኛው ምእት ዓመት ጀምሮ ግን
መጽሐፉ ከመላው የክርስቲያን ዓለም ጠፋ። ሆኖም በአራተኛው ምእት ዓመት ላይ የተጻፈው ጠፍቶ ግን በ19ኛው ምእት
ዓመት ላይ በሲና ተራራ ገዳም ላይ በተገኘው የሲና የመጽሐፍ ቅዱስ መድብል ኮዲክስ (Sinaiticus Codex) (የጥንት የብራና
ጽሑፍ) ከፊሉ ተጽፎ ተገኘ። በ1862 በግሪክ አገር በደብረ አቶስ (Mount Athos) በመጀመሪያ በተጻፈበት በግሪክኛ ቋንቋ
ተገኝቷል።

ሄርማስ ለምን ኖላዊ ሄርማስን ጻፈ?


መጽሐፉ ስለ ዳግም ምጽአት የሚያወራ መጽሐፍ ነው። አማኞችን የመጨረሻውን ቅጣት ወይም ስቃይ
ከማግኘታቸው በፊት ወደ ጸጸት የሚያመጣ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ በቀጥታ ስለዳግም ምጽአት አያወራም (በራእይ ዮሐንስ፣
በትንቢተ ዳንኤል፣ በማር 13 ፣ በማቴ 24 ፣ ላይ በትንሹ እንደተገለጸው)። ነገር ግን ምዕመናን ይህ ቀን ከመድረሱ በፊት
እንዲጸጸቱ ይመክራል።

የሄርማስ ሚና (አስተዋጽዖ)
ሄርማስ ለሰው ልጆች ከሰማይ የመጣውን የመጨረሻ የንስሐ ጥሪ የተቀበለ ሰው ነው። የተቀበለውን መጽሐፍ
በብዛት ኮፒ እንዲሆን አድርጓል። ለዚህም እንዲረዳው አንዱን ኮፒ ለቀሌሜንጦስ ወደ ሌሎች አገሮች እንዲያዳርስ ሰጥቶታል።
ሌላኛውን ደግሞ ሴቶችና ወላጅ አልባ ህጻናትን ለሚያስተምሩ ሰጥቷል። በሮም ሄርማስና የአካባቢው ቀሳውስቶች መጽሐፉን
ለሕዝቡ ያነቡላቸው ነበር። ሄርማስም ይህንን ትምህርት ለእያንዳንዱ ሰው ያደርስ ነበር። ትምህርቱን የሚቀበሉትም ደስተኛ
ሆነው ይኖራሉ። የማይቀበሉት ግን በዚህ ህይወት ደስተኛ ሳይሆኑ ይኖራሉ።
ሄርማስ ራሱን ስለንስሐ ለመስበክ (ለማስተማር) በመጨረሻዎቹ ቀናት የተላከ ነቢይ አድርጎ በመቁጠር የነቢይነት
ሚና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲታወቅ ለማድረግ ሞክሯል። አትናቴዎስ፣ አውሳብዮስ እና ጄሮም ኖላዊው ጠቃሚ ምንባብ
እንደሆነ ተቀብለውታል። በ4ኛው መ/ክ/ዘ የነበረው እውሩ ዲዲሞስም ይህንን መጽሐፍ ጠቅሶታል። ጄሮም ኖላዊው
በአንዳንድ የግሪክ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ እንደሚነበብ ጠቅሷል። ኖላዊው በግብጽም እስከ 6ኛው መ/ክ/ዘ እየተነበበ
ቆይቷል። በፍልስጤምም ማር ሳባ በተደጋጋሚ ተጠቅሞታል። በምዕራብ ክርስቲያኖች ዘንድ ከ 6ኛው መ/ክ/ዘ በኋላ ሙሉ
በሙሉ ባይሆንም ተቀባይነት እያጣ መጥቷል። ኖላዊው ይዘቱ አወቃቀሩ (አጻጻፉ) የተበታተነ ቢሆንም በውስጡ ግን ብዙ
ነገር ይዟል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጥናት የማይቻል መጽሐፍ ነው።
የመጽሐፉ ይዘት
ሄርማስ ኖላዊ ጥልቅ የሆነ የትምህርት ሃይማኖት መጽሐፍ ሳይሆን በቀላልና ጥልቅ በሆነ ስእላዊ አገላለጥ የተጻፈ
ክርስቲያናዊ የስነ ምግባር መጽሐፍ ነው። ለዚህ ነበር በሁሉም ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው። መጽሐፉ የራእይ መጽሐፍ ነው
የሚመስለው። መጽሐፉ በሦስት ክፍሎች ይከፈላል። ይኸውም
1. ራእዮች ናቸው፦ በዚሁ ክፍል ለጸሐፊው የተገለጡ 5 ራእዮች ይገኛሉ፤ ራእዮቹ ለጸሐፊው ለሔርማ በሱም
አማካይነት ለመላ የቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ንስሐ እንዲገቡ የተሰጠ ጥሪ ነው።
2. ትእዛዛት ናቸው፦ ይህ በጣም ረጅሙ ክፍል ነው። በዚህ ክፍል ውስጥ 10 ትእዛዛት ይገኛሉ፤ ትእዛዛቱም
የተሰጡት በጠባቂ መልአክ ሔርማ ሆኖ በእርሱም አማካይነት ንስሐ እንዲገቡ ለምእመናን የተሰጡ ናቸው።
3. ምሳሌዎች ናቸው፦ ይኽም ክፍል 10 የተለያዩ ምሳሌዎችን የያዘ ነው። መልእክቱም ያው የንስሐ ጥሪ ነው።

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 72
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ይህ መጽሐፍ በማንና መቼ ነው የተጻፈው?


መጽሐፉን ማን እንደተጻፈው አይታወቅም። ስለዚህ ችግር የሚከተሉት 5 ግላዊ አመለካከቶች ይገኛሉ፦
1. አንዳንድ ሰዎች የዚህ መጽሐፍ ደራሲ የሐዋርያው የጳውሎስ ጓደኛ የነበረና ጳውሎስም በሮሜ መልእክቱ 16፥14
ሰላምታ የላከለት ሄርማን ነው ይላሉ። ከእነዚህም አርጌንስ (Origen) እና ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስ
(Eusebius) ይገኙበታል።
2. በሮሙ ኤጲስ ቆጶስ በቀለሜንጦስ (92-101) ጊዜ የነበረው ነው ይላሉ፤ ይኽም የተባለበት ምክንያት የቀሌሜንጦስ
ስም በመጽሐፉ ውስጥ በመጠቀሱ ነው።
3. ጸሐፊው የሮሙ ኤጲስ ቆጶስ የፓያስ (Pius of Rome) (140-154) ወንድም ሄርማስ ነው ይላሉ።
4. አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ሄርማስ የእውነት ስም ሳይሆን የፈጠራ ስም ነው ይላሉ።
5. የኢትዮጲያው ሄርማስ ኖላዊ እንደሚለው ደራሲው ሐዋርያው ጳውሎስ ሲሆን የልስጥራ ሰዎች በሰጡት ሄርማስ
በሚለው ስም ነው የሚሉ አሉ።
ብዙ ሊቃውንት ከአንደኛው ጋር ትስስር ሊኖረው የሚችለውን 2ኛውን ሀሳብ ይቀበላሉ። መጽሐፉም የተጻፈበት ጊዜ
የመጀመሪያው ምእት ዓመት መጀመሪያ ላይ እንደሆነ ይታመናል።

የቅድስት ቤ/ክ የታሪክ አባት አውሳቢዮስ


አውሳብዮስ
 የተወለደው ከከርስቲየን ቤተሰብ በ265 ዓ.ም በቂሳሪያ ከተማ ነው፡፡
 ትምህርቱንም የተከታተለው ፓምፊለስ ከተባለ ካህን ዘንድ ነው፡፡
 ፓምፊለስ ከዐረፈ በኋላ በ 313 ዓ.ም የቂሳሪያ ጳጳስ ሆኖ ተሾመ፡፡
 አበዛኛው የሰራቸው ስራዎች የቤተ ክርስቲያን ታረክ የተመለከቱ ናቸው
 ከንጉሱ ቆስጠንጢኖስ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ስለመነበረው መልካም ተግባራት ሲያከናውን ቆይቱል
 በኋላም 340 ዓ.ም ዐረፈ
 የቤተ ክርስቲያን የታሪክ አባት በመባል ይታወቃል

የቅዱስ አውሳብዮስ ሥራዎች


1 ታሪካዊ ሥራዎች
የተለያዩ የዓለም ታሪክ ጽሁፎች (በቅደመ ዘመን) እና በዘመኑ የተከናወኑ ተግባራት ከዘመኑ ጋረ በማጣመር
በከፍተኛ ሁኔታ የታሪክ ድርሳናትን ጽፉል

2 የቤተ ክርስቲያን ታሪክ


የቀደመት ቤተ ክርስቲንያን ታሪክ በመመዝገብ ዜና መዋዕሎችን በማዘጋጀት በርካታ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ
መጻሕፍት ጽ ፏል እስከ ንጉስ ቆስጠንተጢኖስ ዘመን ድረስ የቤተ ክርስቲያን ጣሪክን በሚመለከት 19 መጽሐፍትን
አዘጋጅቷል
2 የቅዱሳት መጻህፍት የትርጉም ሥራዎች
በርካታ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍን ተርጉሟል
3 የዕቅበተ እምነት ሥራዎች

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 73
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

4 ሃይማኖታዊ ሥራዎች (ትምህርቶች)


 ሁለት የተለያዩ መጻህፍትን ለተረፍ ሰባልዮሳውያን መልስ በመስጠት አዘጋጀቷል ::
 ሶስት የቤተ ክርስቲያን የነገረ ሃይማኖት ትምህርትን መስፋፋት የተመለከቱ መጻሕፍትን አዘጋጀቷል

ሰኔ 3ኛ ሳምንት
ምዕራፍ ስድስት
ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን አበው
የኢትዮጵያዊ ቅዱስ ያሬድ ዜና ሕይወቱ
የቅዳስ_ያሬድ_ አባቱ አብድዩ ይስሐቅ እናቱ ክርስቲና /ታውክልያ/ ይባላሉ /በሌላም በኩል አባቱ እንበረም
እናቱ ትውልያ ይባላሉ የሚል ታሪክም አለ፡፡/ የትውልድ ሥፍራው አከሱም ነው፡፡ የተወለደው በ505 ዓ.ም/ ሚያዝያ 5 ቀን
የሚል አለ/ ሲሆን በተወለደ በ7 ዓመቱ ወላጅ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ጽዮን መምህር ለነበረው ለአጎቱ ለጌዴዎን
እያስተማረ እንዲያሳድገው ሰጠችው፡፡ ከአባ ጌዴዎንም ዘንድ እየተማረ ለ25 ዓመት ተቀመጠ፡፡ ሆኖም ቃለ እግዚአብሔር
የመቀበል ችሎታው ደካማ ስለሆነ በጣም ያዝን ነበር፡፡ ከዕለታት
አንድ ቀን ከትምህርት ድክመቱ የተነሣ አጎቱ በጨንገር ቢገርፈው
በዚህ ተበሳጭቶ ትምህርቱን ትቶ ሄደ፡፡ በመንገድም ሲጓዝ ውሎ
በቀትር ደክሞት ከዛፍ ሥር ዐረፈ፡፡ በዚያ ጊዜ አንድ ትል ከዛፉ ላይ
ያለውን ፍሬ ለመብላት ስድስት ጊዜ በመውደቅና በመነሣት ዛፉ ላይ
ለመውጣት ሞክሮ በሰባተኛው ሰተት ብሎ ወጥቶ ሲበላ ተመለከተ፡
፡ እርሱም በፈጸመው የብስጭት ተግባር በመጸጸት ተመልሶና አጎቱን
ይቅርታ ጠይቆ ትምህርቱን ቀጠለ፡፡ አጎቱም ተደስቶ ዓይነ
ልቡናውን ያበራለት ዘንድ እያለቀሰ ፈጣሪውን ለመነለት፡፡
እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ለቅዱስ ያሬድ ዕውቀትን ገልጾለት
መጻሕፍተ ብሉያትንና ሐዲሳትን ዐወቀ፡
ከዚያም በኋላ ወደ መምህሩ ተመልሶ
ትምህርቱን ቀጠለና ቅዱሳት መጻሕፍትን በሚገባ አጠና፡፡ ሢመተ
ዲቁናን ቀጥሎም ሢመተ ቅስናን ተቀበለ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ግእዝ፣
እዝልና አራራይን ከሦስት ወፎች/መላእክት በወፎች ተመስለው/
መማሩን ሊቃውንት ይገልጣሉ፡፡ እነዚህ በወፍ የተመሰሉ መላእክት
እየመሩት ወደ አርአያም አርጎ የ24ቱን ካህናተ ሰማይ ዜማ ከተማረ
በኋላ ጠዋት በ3 ሰዓት በአክሱም ቤተ ክርስቲያን «ሃሌ ሉያ ለአብ
ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሣረረ ወበዳግመ አረአዮ ለሙሴ ዘከመ ይግበር ግብራ ለደብተራ»
ብሎ አዜመ፡፡ ይህን ዜማ የደረሰበት ወሩ ታኅሳስ ቀኑም ዕለተ ሰኞ ነው ይባላል፡፡ የቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያ ዜማው «አርያም»
በመባል ይታወቃል፡፡ ይህም ከመላእክት ወይም ከሰማይ የተገኘ መሆኑን ለማጠየቅ የተሰጠው ስም ነው፡፡
ቅዱስ ያሬድ ይህንን ዜማ በተመስጦ ሲያዜም ንጉሡ፣ንግሥቲቱ፣ ጳጳሱ መኳንንቱና ካህናቱ ወደ አኩስም ቤተ
ክርስቲያን ተሰባስበው መጥተው በአድናቆት ያዳምጡት ነበር፡፡ ምክንያቱም ገደለ ቅዱስ ያሬድ እንደሚገልጥልን ከዚያ በፊት
በውርድ ንባብ ከሚደረግ ጸሎትና መንፈሳዊ አገልገሎት በቀር ይህን የመሰለ ዜማ አልነበረምና፡፡
የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ብሉይን ከሐዲስ ያስማማ፣የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በሚገባ የያዘ፣
እንዲሁም ለልዑል እግዚአብሔር፣ለእመቤታችን፣ለቅዱሳን መላእክት፣ ለጻድቃንና ለሰማዕታት ተገቢ የሆነውን ምስጋና የያዘ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 74
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ነው፡፡ ከዚህም በላይ ለአራቱ የዓመቱ ወቅቶች እንዲስማማ አድርጎ ለበጋ፣ ለክረምት፣ ለመጸውና ለጸደይ እንደሚሆን አድርጎ
ከፋፍሏቸዋል፡፡ ለየበዓላቱም ተስማሚ ድርሰት መድቦላቸዋል፡፡ ይህንን ድርሰቱን በግእዝ፣ በእዝልና በአራራይ ዜማ ያዘጋጀው
ሲሆን ለነዚህም ስምንት የዜማ ምልክቶች ሠርቶላቸዋል፡፡
የቅዱስ ያሬድ ዜማ አንዴት ሁሉንም ይመስጥና ወደ አርያም በመንፈስ ይወስድ እንደ ነበር
ለማስረዳት በገድሉም በሌሎችም መጻሕፍት የተመዘገቡ ታሪኮች አሉ፡፡ አንድ ቀን ንጉሥ ገብረ መስቀል፣ንግሥቲቱ፣ ጳጳሱ፣
ካህናቱና ምእመናኑ በተሰባሰቡበት ቅዱስ ያሬድ ዜማውን ሲያዜም ንጉሡ በመመሰጡ የተነሣ በመሰቀል ተሰላጢኑ ጫፍ
የቅዱስ ያሬድን እግር ወጋው፡፡ ነገር ግን ማንም አላወቀም ነበር፡፡ ቅዱስ ያሬድ መዝሙሩን ሲፈጽም ንጉሡ መስቀል ተሰላጢኑን
ቢያነሳው የቅዱስ ያሬድ ደሙ ፈሰሰ፡፡ ንጉሡ በዚህ ደንግጦ ለዚህ ካሣ ይሆን ዘንድ የፈለግከውን ጠይቀኝ እሰጥሃለሁ ብሎ
ቃል ገባለት፡፡
ቅዱስ ያሬድ ዜማውን ያዘጋጀበት ዘመን ከ540-560 ዓ.ም. ባለው ጊዜ መሆኑ ይነገራል። ዜማውን
ካዘጋጀ በኋላ 11 ዓመት አስተምሯል፡፡ በእርሱ ዘመን ተሰዓቱ ቅዱሳን በሃይማኖት ችግር ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው
መጥተው ስለ ነበር ቅዱስ ያሬድ ከአንዱ ከአባ ጰንጠሌዎን የውጭውን ሀገር ቤተ ክርስቲያን ባሕልና ሥርዓት ይጠይቅ ነበር፡
፡ ቅዱስ ያሬድ ማትያስና ዮሴፍ በተባሉ የአቡነ አረጋዊ ደቀ መዛሙርት መሪነት ወደ ደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ወጥቶ ከጻድቁ
ጋር በመገናኘትና የቤተ ክርስቲያኑን ሥራ እያደነቀ ዙሪያውን ከዞረ በኋላ «ዖድክዋ ወርኢኩ ሥነ ሕንፃሃ ለቅድስት ቤተ
ክርስቲያን» ሲል ዘመረ፡፡ በዚያም ለአንድ ሳምንት ሰንብቶ ሄዷል፡፡
ቅዱስ ያሬድ ከአቡነ አረጋዊ እና ከዐፄ ገብረ መስቀል ጋር በመሆን በወሎ፣ በጎንደር፣ በሸዋ እና እስከ ጋሞጎፋ
ብርብር ማርያም ድረስ በመሄድ አስተምሯል፡፡ አንዳንድ መረጃዎች የዐርባ ምንጭን ታሪክ ከቅዱስ ያሬድ፣ ከአቡነ አረጋዊ እና
ከዐፄ ገብረ መስቀል ታሪክ ጋር ያያይዙታል፡፡ ሦስቱም ብርብር ማርያምን ለማየት ሄደው በነበረ ጊዜ በዛሬው ዐርባ ምንሥ
አካባቢ ሠፍረው ነበር፡፡ በዚያ ቦታ ለወታደሩ የሚበቃ የሚጠጣ ውኃ በመጥፋቱ አቡነ አረጋዊ ጸልየው መሬቱን በመስቀል
ቢመቱት ዐርባ ውሃዎች ፈለቁ ይባላል፡፡ዐፄ ገብረ መስቀል የጣና ቂርቆስን ቤተ ክርስቲያንን በሚያሠራ ጊዜ በዚያ ቦታ ለሁለት
ዓመት ተቀምጦ ድጓውን በማስተማሩ ምልክት የሌለው ድጓው እስከ ዛሬ በገዳሙ ይገኛል፡፡ ቀጥሎም የዙር አባን ቤተ
ክርስቲያን ለማሠራት ወደ ጋይንት በተጓዙ ጊዜም በዚያ ሁለት ዓመት ዝማሬ መዋሥዕት የተባለ ድርሰቱን አስተምሯል፡፡ ይህ
ቦታ እስከ ዛሬ የዚህ ትምህርት ማስመስከሪያ ነው፡፡
ቅዱስ ያሬድ ከዚያ በኋላ ወደ አከሱም ተመልሶ በመደባይ ታብር በተባለ ቦታ ቅዳሴያትን በዜማ
አዘጋጅቷል፡፡ ይህ ቦታ ከአከሱም 15 ኪ.ሜትር ርቆ ይገኛል፡፡ ከዚህ በኋላ ለመጨረሻ ጊዜ አኩስምን ተሰናብቶ ለመሄድ ወደ
ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ገባና «ቅድስት ወብጽዕት ስብሕት ወቡርክት ክብርት ወልዕልት አንቀጸ ብርሃን ማዕርገ ሕይወት» እያለ
አንቀጸ ብርሃን የተባለውን ድርሰቱን ሰተት አድርጎ አዘጋጀው፡፡ ይህንን ድርሰት ሲያዜም አንድ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ብሎ
ይታይ ነበር ይባላል፡፡
ቅዱስ ያሬድ በሰሜንና ወገራ፣ አገውና በጌምድር እየተዘዋወረ አስተምሮ ከሰሜን ተራራዎች ውስጥ እየጾመና
እየ[ለየ በብሕትውና ለብዙ ዘመን ከኖረ በኋላ በሰሜናዊ ምሥራቅ በኩል ባለው በጸለምት ዋሻ ውስጥ በ571 ዓ.ም ግንቦት 11
ቀን ተሠውሯል፡፡ ይህ ቦታ በተለምዶ የሰሜን ተራሮች በሚባለው ወስጥ የሚገኝ ከፍተኛና ብርዳማ ቦታ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ
ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሰማያዊ ዜማን ከማበርከቱም ሌላ በትምህርት ሂደትም አስተዋጽዖ አድርጓል፡፡

የቅዱስ ያሬድ ዜማ እና ዓይነቶቹ


የቅዱስ ያሬድ ዜማ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተገለጸለት ለመሆኑ መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ቅዱስ ያሬድ ዜማዉን
ያዘጋጀዉ በሦስት ዓይነት ድምፅ ማለትም በግእዝ፣በዕዝል፣እና በዓራራይ ዜማ ነዉ፡፡እነዚህ የዜማ አይነቶች የአንዱ ድምፅ
ከሌላኛዉ ድምፅ ያልተደበላለቀ ወጥ የሆነ ድምፅ አላቸዉ፡፡ዜማዎቹንም በስምንት ምልክቶች ቀምሮታል፡፡የምልክቶች
አገልግሎትም በትምህርት ሂደት ጊዜ የጠቋሚነት ሚና በመጫወት ለዜማዉ መጠበቅ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ናቸዉ፡፡
↪�ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀል ቅዱስ ያሬድ የተነሳዉ ዘጠኙ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ በገቡበት ዘመን ነዉ፡፡በዘጠኙ
ቅዱሳን የተተረጎሙት ቅዱሳን መጻሕፍት በቅዱስ ያሬድ የድርሰት ስራ ዉስጥ ጉልህ ድርሻ ነበራቸዉ፡፡ቅዱስ ያሬድ ከመጻሕፍቱ
ያገኛቸዉን ምስጢራት ቃል በቃል እየጠቀሰ እንዲሁም ሐሳባቸዉን ጨምቆ በመዉሰድ በራሱ ቋንቋ እያራቀቀ ለድርሰቱ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 75
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ተጠቅሞባቸዋል፡፡ቅዱስ ያሬድ ሙራደ ቃልበተባለ ቦታ ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሲያዜም ንጉሱ አፄ ገብረ መስቀል
ከነሰራዊቶቻቸዉ ንግስቲቱ ከነደንገ ጡሮቿ ፣መሳፍንቱ፣ መኳንንቱ፣ሊቃዉንቱና ካህናቱ አየመጡ ያዳምጡ ነበር ይላሉ ርእሰ
ደብር ጥዑመ ልሳን ካሣ በመጽሐፋቸዉ፡፡ቅዱስ ያሬድ በግእዝ፣በዕዝል በዓራራይ ዜማ ዝማሜ እየደረሰ እያለ ንጉሱ አፄ ገብረ
መስቀል ተገኝተዉ ነበር፡፡
በዜማዉ ተመስጠዉ አይን አይኑን እያዩ እንደ እርሱ እዘምማለሁ ብለዉ በያዙት የብረት ዘንግ ሳያዉቁት ቅዱስ
ያሬድ እግር ላይ ቸከሉት፡፡ ሁለቱም በተመስጦ ስለነበሩ የሆነዉን ነገር አላስተዋሉትም ነበር፡ዜማዉ አብቅቶ ሁለቱም
ከተመስጧቸዉ ሲነቁ የቅዱስ ያሬድ እግር ዘንጋቸዉ ተሰክቶ ብዙ ደም ፈሶት ነበር፡፡ንጉሡም ደንግጠዉ እጅግም
አዝነዉ‹‹ደምህን አፍስሻለሁና የምትፈልገዉን ማንኛዉንም ነገር ጠይቀኝ እሰጠሃለሁ››ሲሉ ቃል ገቡለት፡፡ቅዱስ
ያሬድም‹‹ይምለምነዉ አንድ ነገር አለ እርሱን ፈጽምልኝ››አላቸዉ፡፡‹‹የፈለከዉን ጠይቅ ፈቅጄልሃለሁ››አሉት፡፡
እርሱም‹‹እስካሁን እግዚአብሔር በፈቀደልኝ መሰረት በዚህ ከተማ ከእርሰዎ ጋር ቆይቻለሁ፡፡ብዙ ደቀ መዛሙርትም
ተክቼያለሁ፡፡ከእንግዲህ በኋላ የቀረኝን ዘመን በጸሎትና በብሕትዉና መኖር እንድችል ከከተማዉ ራቅ ወዳለ ቦታ ሔጄ ማ
ድበገቡለት ቃል መሰረት ፈቀዱለት፡፡ከዚያም ጉዞዉን ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወደ ሰሜን ተራሮች አደረገ፡፡በዚያም አሁን በስሙ
የታነጸዉ ቤተ ክርስቲያን ባለበት ቦታ ላይ በምናኔ ተወስኖ ፈጣሪዉን በብሕትዉና እያገለገለ ኖረ፡፡ምናኔ ደብረ ሐዊ ከተባለዉ
ተራራ ላይ ብዙ ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ በጸለምት ዋሻ በአንዱ ግንቦት 11 ቀን በ571 ዓ/ም ተሰወረ፡፡

ሰኔ 4ኛ ሳምንት
የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች
ቅዱስ ያሬድን ብቸኛ የግእዝ ሥነ ጽሑፍ መስራች አድርጎ ለማየት በቂ ምክንያት አለን፡፡እንዲያዉም የግእዝ ስነ
ጽሑፍ መስራች ከማለት ይልቅ የኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ መሥራች ልንለዉ ይገባል፡፡《ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ኃይሌ የቅዱስ ያሬድ
ታሪክና የግእዝ ስነ ጽሑፍ፤1999፤ገጽ3》ፕሮፌሰሩ በዚሁ ጥናታቸዉ እንዳብራሩት የግእዝ ስነ ጽሑፍን ለሁለት ልንከፍለዉ
እንችላለን ይላሉ፡፡ምክንያቱን ሲያብራሩ፡-አንዱ ክፍል ከባህር ማዶ ተጽፈዉ ወደ ግእዝ የተተረጎሙትን መጻሕፍት ይይዛል፡፡
ሁለተኛዉ ክፍል በቀጥታ በግእዝ የተደረሱትን ድርሰቶች ያጠቃልላል፡፡�እነዚህም፡-የቅዱስ ያሬድ፣የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
የርቱዐ ሃይማኖት፣የ አፄ ዘርአ ያዕቆብ፣የ ዐርከ ሥሉስ፣የ አባ ባሕርይ ድርሰቶች የሚቀድም በ ግእዝ ቋንቋ የተደረሰ ድርሰት
እስከ አሁን አለመገኝቱን ጥናቱ ያሳያል፡፡《1999፡3》
ቅዱስ ያሬድ ድርሰቶችን ሲያዘጋጅ ከቅዱሳን መጻሕፍት የወሰዳቸዉን ርእሰ ጉዳዮች በፈርጅ በፈርጁ
እየለየ በድርሰት ሥራዎቹ እንደ ፈርጥ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ብሉያትን ከሐዲሳት፣ከሊቃዉንት እያጣቀሰ ያለምንም ችግር የድርሰት
ሥራዉን ሊያከናዉን ችሏል፡፡የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች መንፈሳዊ ይዘት ያላቸዉ ናቸዉ፡፡በድርሰቶቹ የሚታዩት የቃላት
አመራረጥ፣የ ዐረፍተ ነገር አወቃቀር፣የሚስጥር፣የዘይቤ አገላለጥ ቅዱስ ያሬድ ከፍተኛ የስነ-ጽሑፍ ተሰጥኦ እንደነበረዉ
ለመረዳት ይቻላል፡
በቅዱስ ያሬድ የተደረሱት የዜማ መጻሕፍት አምስት ናቸዉ፡
1) ድጓ፣
2) ጾመ ድጓ፣
3) ዝማሬ፣
4) ምዋስዕትና
5) ምዕራፍ ናቸዉ፡፡

1 ድጓ
ድጓ ማለት ስብስብ ማለት ነዉ፡ምክንቱም በዉስጡ የዓመቱን በዓላትና የሳምንታት መዝሙራት ተሰብስቦ ስለሚገኝ
ነዉ፡፡ይህ መጽሐፍ በዐበይት በዓላት በዜማ የሚቀርበዉን ምስጋና ሰብስቦ የያዘ የዜማ መድብል ነዉ፡፡ -የቅዱስ ያሬድ ትልቁ
የዜማ መጻሕፍ ነዉ፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 76
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ድጓ በአራት ትልልቅ ክፍሎች ይከፈላል፡


1. የዮሐንስ ድጓ፣
2. አስተምህሮ ድጓ
3. ጾመ ድጓ፣
4. የፋሲካ ድጓ ተብሎ ይታወቃል፡፡

2 ጾመ ድጓ፡
የዜማ መጽሐፍ ሲሆን የሚጠናና ለመምህርነት የሚያበቃ ነዉ፡፡ድጓ ቁጥሩ ከአስተምህሮ ሲሆን በዐቢይ ጾም
የሚደርስ ራሱን የቻለ መጽሐፍ ነዉ፡፡

3 ዝማሬ፡-
ዝማሬ የዜማ መጽሐፍ ነዉ፡፡ዝማሬ ምስጋና ማለት ነዉ፡፡ዝማሬ በጸሎተ ቅዳሴ ከድርገት በኋላ በቅዳሴ ማብቂያ
አካባቢ የሚዜም የሚዘመር የጸሎተ ቅዳሴዉን ዓላማ ተከትሎ የሚሔድ ማለት ነዉ፡፡ መጽሐፈ ዝማሬ በይዘቱ አምስት ነገሮች
አሉት፡
፡እነርሱም
ኅብስት፣ ጽዋ፣ መንፈስ አኮቴት እና ምስጢር ናቸዉ፡፡

4 መዋሥዕት፡
መዋሥዕት የዜማ መጽሐፍ ነዉ፡፡መዋሥዕት የቃሉ ትርጓሜ ሁለት ዓይነት ነዉ፡፡
1. ምልልስ ማለት ነዉ፡፡በግራና በቀኝ እየተመላለሰ ወይም እየተቀባበለ የሚባል ስለሆነ ነዉ፡፡
2. የነፍስ መመላለስ《መሸጋገሪያ》ማለት ነዉ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀትን፣ሞቱን፣ትንሣኤዉን፣ዕርገቱን
የሚያስረዳ ነዉ፡፡የመሥዋዕት አገልግሎት ለሙታን ጸሎተ ፍትሐት ለማድረስ በበዓላትና በአጽዋማት ደግሞ ስብሐተ
ነግሕ ለማድረስ ነዉ፡፡

5 ምዕራፍ፡
የቅዱስ ያሬድ አምስተኛዉና የመጨረሻዉ የዜማ መጽሐፍ ምዕራፍ ነዉ፡፡የምዕራፍ ቀጥተኛ ትርጉሙ ማረፊያ
ወይም ማሳረፊያ ማለት ነዉ፡፡ምዕራፍ ከመዝሙረ ዳዊት የተዉጣጣ ድርሰት ሲሆን የዳዊት መዝሙራትን በመስመር《
ምዕራፍ》እየከፋፈለ የዜማዉን አይነትና ማሳረፊያ ይገልጻል፡፡

አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ዘሐይቅ


የአቡነ ኢየሱስ ዜና ሕይወት
እግዚአብሔር በ13ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ
ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና
ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው::እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን
ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል::
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር: የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው
ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም
ያደርጉታል::+ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር::

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 77
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን (ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው)
ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ::+አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት:
የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ::
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ: ሲፈጩ: ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት
እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ::በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን
ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል
ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ: ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው:፤በአንዴም ከዳሞ (ትግራይ) ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ
(ወሎ) አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ: በስብከተ ወንጌል: በማዕጠንትና
ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ::ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው
እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:-ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት
ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ::ባዕድ አምልኮም ነገሠ::
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ
ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ::በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና
በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው::ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን
አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም
ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ::ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ
አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ
የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል::እንዲህ ለቤተ
ክርስቲያን ሲተጉ: በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም
ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም:
"እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ::
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል::
+ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ
በ82 ዓመታቸው (በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ) በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: <<ጻድቁ ስም
አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው!!>

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 78
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ሐምሌ 1ኛ ሳምንት

አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዜና ሕይወቱ
ኢትዮጵያዊው ሊቅና ጻድቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ
ከቅዱስ ያሬድ ቀጥሎ ታላቅ ቦታ የያዘ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ነው፡፡
አባ ጊዮርጊስ የተወለደው በ1357 ዓ.ም በወሎ ክፍለ ሀገር
በቦረና ወረዳ ሰግላ በተሰኘች ቦታ ነው፡፡ ወላጆቹ ልጅ
ስለሌላቸው ዘወትር እያዘኑ ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር፡፡
አባ ጊዮርጊስ የተወለደው በቅዱስ ዑራኤል አብሳሪነት መሆኑን
ድርሳነ ዑራኤል ይተርክልናል፡፡ አባቱ ሕዝበ ጽዮን እናቱ አምኃ
ጽዮን ይባላሉ፡፡ አባቱ ጠቢብና የመጻሕፍት ዐዋቂ፤
የእግዚአብሔር ወዳጅና በቤተ መንግሥት በነበረችው ድንኳን
“ሥዕል ቤት” ከሚያገለግሉ ካህናት ወገን ሲሆን የሰግላ ሀገረ
ገዥም ነበር፡፡ የአባ ጊዮርጊስን እናት እምነ ጽዮን ከወለቃ
/የዛሬው ደቡብ ወሎ፣ ቦረና/ ከሹማምንት ወገን የሆነች ደግ
ሰው ነበረች፡፡
አባ ጊዮርጊስ በመጀመርያ እናቱ ፈሪሐ
እግዚአብሔርን እያስተማረች በጥበብና በዕውቀት አሳደገችው፡
፡ አባ ጊዮርጊስ የመጀመርያውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት
የተማረው ከአባቱ ነበር፡፡ ምክንያቱም አባቱ የመጻሕፍት ሊቅ
መሆኑን ስንመለከትና ገድሉም አባ ጊዮርጊስን በተመለከተ
“ወሶበ ልሕቀ ሕቀ ወሰዶ ኀበ ጳጳስ ወሴሞ ዲያቆን” የሚለውን ስናጤነው አባቱ የመጀመርያውን ደረጃ ትምህርት ካስተማረው
በኋላ በ1341 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ከመጡትና እስከ ዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ጳጳስ የነበሩት ከአቡነ ሰላማ መተርጕም ዘንድ
ወስዶ ዲቁና አሹሞታል ማለት ነው፡፡ዲቁና ከተቀበለ በኋላ ለትምህርት ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ተላከ፡፡ ወደ ሐይቅ የገባው
በዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት መሆኑን ገድሉ ይገልጣል፡፡ ሐይቅ እስጢፋኖስ የተለያዩ ሊቃውንት የሚገኙባት፣ በብዙ
መጻሕፍት የተሞላችና ዙሪያዋን በሐይቅ በመከበቧ የተማሪን ሐሳብ ለማሰባሰብ አመቺ የሆነች ቦታ ናት፡፡ አባ ጊዮርጊስ
በሐይቅ እስጢፋኖስ ትምህርት አልገባው ብሎ ለሰባት ዓመታት ተቀምጦ ነበር፡፡ አብረውት የሚማሩት ተማሪዎች “ይህ
ትምህርት የማይገባው ስለ ምንድን ነው? በእርሱ ኃጢአት ነው ወይስ በወላጆቹ ?” ይሉት ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ የሐይቁ መምህር
የነበረው ዐቃቤ ሰዓት ሠረቀ ብርሃን ለአባቱ “ልጅህ ትምህርት አይገባውምና የቤተ መንግሥት ነገር አስተምረው” ብሎ
መለሰው፡፡ አባቱ ሕዝበ ጽዮን ግን “አንድ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፤ እዚያው ገዳሙን ያገልግል” ብሎ እንደ ገና ላከው፡

አባ ጊየርጊስ በቀለም ትምህርት እንዲሰንፍ ምክንያት የሆነው ከመማር ይልቅ በሥራ እየደከመ የገዳሙን
አባቶች መርዳትና ብሕትውናን ይማርከው ስለ ነበር ነው፡፡ በገዳሙ እህል በመፍጨት ያገለግል ነበር ፡፡ አባ ጊዮርጊስ እህል
ይፈጭበት የነበረውን የድንጋይ ወፍጮ እስከ አሁን በገዳሙ አለ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዕውቀት ስለ ተሠወረውና ጓደኞቹ በትምህርት
ሲቀድሙት ባየ ጊዜ እጅግ አዘነ፡፡ ስለዚህም በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መጮኽ ጀመረ፡፡ ሁልጊዜም በሥዕለ ማርያም
ሥር እየተንበረከከ “የአባቶቻችን አምላክ፣ የምህረት ጌታ፣ ሁሉን በቃልህ የፈጠርክ፣ ሰውንም በረቂቅ ጥበብ የፈጠርክ አቤቱ
አንተ ከልዑል ጌትነትህ ጥበብን ስጠኝ በእውነትም አትናቀኝ አኔ ባርያህ ነኝና የባርህም ልጅ ነኝና” እያለ በጠለቀ ተመስጦ
ልቦና እንባን በማፍሰስ ይጸልይ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ በነሐሴ 21ኛው ቀን እመቤታችን ተገለጠችለትና «አይዞህ ዕውቀት

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 79
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

የተሠወረብህ ትምህርት ስለማይገባህ ሳይሆን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ እንዲገለጥ ነውና ታገሥ» አለችው፡፡ ጽዋዕ ልቦናም
አጠጣችው፡፡ከዚህ በኋላ በሐይቅ እስጢፋኖስ የዜማ የቅኔና የመጻሕፍትን ትርጓሜ ትምህርቱን በሚገባ ተምሮ አጠናቀቀ፡፡
በዕውቀቱም ቀድሞ የሚያውቁት ሁሉ ይደነቁበት ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ የያሬድን ዜማ ከአቡነ ሳሙኤል ዘጋርማ እንደተማረው
ገድሉ ይነግረናል፡፡ በዚያ ዘመን በዐፄ ዳዊት አማካይነት በሰሜን ኢትዮጵያ የያሬድ ድጓ ዋና ማዕከል በሆነው በደብረ ነጎድጓድ
ተሾሞ ያስተምር ነበር፡፡የማስተማር ሥራውን የጀመረው በዚያው በሐይቅ እስጢፋኖስ መሆኑን ገድሉ በሚከተለው መልኩ
ይገልጠዋል “ወአብርሃ ለቤተ ክርስቲያን እንተ ተሐንጸት በሐይቅ ባሕር፣ ወእም አሜሃ አሐዙ ይስአሉ እም ኀቤሁ ኩሎሙ
ሰብአ ሀገር ቃለ መጻሕፍት ወትርጓሜሆሙ፣ ወኩሉ ቃለ ማኅሌት፡፡”ከሐይቅ በኋላ በዚያ ዘመን ሸግላ በመባል ትጠራ ወደ
ነበረችው ወደ ትውልድ ሀገሩ ወደ ጋሥጫ ተጓዘ፡፡
አባ ጊዮርጊስ ወደ ሸግላ ሲመጣ አባቱ በጣም አርጅቶና መንኩሶ ነበር፡፡ ስለዚህም በአባቱ እግር ተተክቶ
በቤተ መንግሥቱ ያለችውን ሥዕል ቤት እንዲያገለግል ወደዚያው አስገቡት፡፡ በቤተ መንግሥቱም የንጉሡን ልጆች
ከማስተማሩም በላይ በቤተ መንግሥቱ ዙርያ ከነበሩት ሊቃውንት መካከል አባ ጊዮርጊስ አንዱ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ግብፃዊው
ጳጳስ አቡነ በርተሎሜዎስ “ሥላሴን አንድ ገጽ” ብለው ያምናሉ ተብለው በተከሰሱ ጊዜ ነገሩን እንዲያጣሩ ከተመረጡት ከቄስ
ሐፄ ተከሥተ ብርሃንና ከሐይቁ መምህር ከዐቃቤ ሰዓት ዮሴፍ ጋር አብሮ ተልኮ ነበር፡፡ እነዚህ ሦስት አበው ጳጳሱን ካነጋገሩ
በኋላ ክሱ ውሸት መሆኑን በማረጋገጥ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የሚገልጠውን የጳጳሱን እምነት በጽሑፍ ይዘው መጡ፡፡በቤተ
መንግሥቱ በነበረ ጊዜ የንጉሡን ልጆች ይስሐቅን፣ ቴዎድሮስን፣ እንድርያስን፣ ሀብተ ኢየሱስን፣ ሕዝቅያስን፣ ኢዮስያስን፣ ዘርዐ
ያዕቆብንና ሴት ልጁን እሌኒን በምግባርና በሃይማኖት ቀርጿቸዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ዘርዐ ያዕቆብ በድርሰቱ ሲመስለው
ቴዎድሮስ ደግሞ በሕይወት መስሎታል፡፡ ዐፄ ዳዊት የአባ ጊዮርጊስን ሊቅነትና መልካም ሥነ ምግባር በሚገባ ስላወቀ በጋብቻ
ሊዛመደው ወዶ ስለነበር ልጁን እንዲያገባ ዘወትር ይጠይቀው ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በድንግልና ጸንቶ ለመኖር እንደሚፈልግ
ከመግለጽ አልተቆጠበም፡፡ የዐፄ ዳዊት ጥያቄ ስለበዛበት ወደ አቡነ በርተሎሜዎስ ሄዶ ቅስናን ከተቀበለ በኋላ ወዲያው መነኮሰ፡
፡ከመነኮሰ በኋላ ወደ ሸግላ በመምጣት ለነገሥታትና በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ካህናት እንዲሁም በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ
ታላላቆች፣ ለንቡራነ እድና ለመኳንንት፣ ለመሳፍንትና በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ባለሟሎች ሁሉ መምህር ሆነ፡፡

አባ ጊዮርጊስ በሸግላ በነበረ ጊዜ በወባ በሽታ ታምሞ ሊሞት ደርሶ እንደ ነበር ገድሉ ይናገራል፡፡ ታምሞ
በነበረ ጊዜ አንድ ሌሊት ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ተገልጠውለት “ከእኛ ጋር ትኖር ዘንድ ልንወስድህ” መጣን አሉት፡፡
እርሱም “የድርሰት ሥራዬን ሳልሠራና እግዚአብሔርንም አብዝቼ ሳላመሰግነው አሁን አትውሰዱኝ” ሲል ለመነ፡፡ እነርሱም
ልመናውን ተቀብለውት ከሕመሙ ፈውሰውት ሄዱ፡፡ ለዚህም ይመስላል ከበሽታው እንደ ተፈወሰ ወድያው የድርሰት ሥራውን
የጀመረው፡፡
የመጀመርያ መጽሐፉን ጽፎ እንደ ጨረሰ ጠፍቶበት እንደ ነበር ገድሉ ይተርካል፡፡ በቤቱ ውስጥ
የነበሩትን መጻሕፍት ሁሉ እያገላበጠ ቢፈልገውም ሊያገኘው አልቻለም፡፡ አንድ ቀን በቤተ ክርስቲያን ሌሊት በአገልግሎት
ላይ እያለ እመቤታችን ተገልጣ “ለምን አስቀድመህ ሳትነግረኝ ጻፍክ?” ስትል ጠየቀችው፡፡ እርሱም «አንቺን ደስ ያሰኘሁ
መሰሎኝ ነውና ይቅር በይኝ» ሲል መለሰላት፡፡ ከዚህ በኋላ የድርሰት ሥራውን ፈቅዳለት ተሠወረችው፡፡ “ወሶቤሃ በርሃ ልቡ
ከመ ፀሐይ ወሐተወ ውስተ ኅሊናሁ ባሕረየ መለኮት፤ ወነጸረ ኩሎ ኅቡአት - ከዚህ በኋላ ልቡ በራለት፣ ኅሊናውም ነገረ
መለኮትን ዐወቀ፡፡ የተሠወረውንም ሁሉ ተመለከተ” ይላል ገደሉ፡፡
የመጀመርያው ድርሰቱ አርጋኖን የተሰኘውና በቅኔ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
የሚያመሰግነው መጽሐፉ ነው፡፡ ስለ አርጋኖን ድርሰቱ ገድሉ በሚከተለው መንገድ ይገልጠዋል “ወሰመዮ በሠለስቱ አስማት
ዘውእቶሙ አርጋኖነ ውዳሴ፣ ወመሰንቆ መዝሙር ወእንዚራ ስብሐት - በሦስት ስሞችም ሰየማቸው እነርሱም አርጋኖነ ውዳሴ፣
መሰንቆ መዝሙርና እንዚራ ስብሐት ይባላሉ፡፡”
እመቤታችን አርጋኖንን ስለ ወደደችለት ዚማት በሚባለው ሀገር በነበረ ጊዜ “ከድርሰቶችህ ሁሉ እንደ
አርጋኖን የምወደው የለም” ብላዋለች፡፡ ዐፄ ዳዊትም ድርሰቱን በጣም ከመውደዱ የተነሣ በወርቅ ቀለም እንዳጻፈው ገድሉ
ይገልጣል፡፡ከዚህ በኋላ የደረሰው ደርሰት ውዳሴ መስቀል ይባላል፡፡ ቀጥሎም መጽሐፈ ስብሐት ዘመዓልት ወዘሌሊት
የተባለውን /ወይም እርሱ ራሱ መጽሐፈ ብርሃን ብሎ የሰየመውን/መጽሐፍ አዘጋጅቷል፡፡ ይህን መጽሐፍ «መጽሐፈ ብርሃን»

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 80
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ብሎ የሰየመበትን ምክንያት ገድሉ ሲያበራራ “አስመ ውእቱ ያበርህ ወያስተርኢ ፍናወ ስብሐቲሁ ለእግዚአብሔር ወፍናወ
ስብሐቲሆሙ ለትጉኃን ወለኩሎሙ ማኅበረ ቅዱሳን ልዑላነ ብርሃን ወዓዲ ይነግር እንዘ ያስተሐውዝ ውዳሴሃ ለድንግል
ንጽሕት— የእግዚአብሔርን የምስጋናውን መንገድ ያበራል /አብርቶ ያመለክታልና፣ ልዑላነ ብርሃን የሆኑትን የማኅበረ
ቅዱሳንንና የትጉኃንን የምስጋናቸውን መንገድ ያመለክታልና፣ የእመቤታችንንም የምስጋናዋን ጣዕም ይገልጣልና/ ይላል፡፡”
በዚያ ጊዜ በነበረው ልማድ ካህናቱ ቁርባን በሚያቀብሉ ጊዜ ሕዝቡ ወደ ካህናቱ መጥተው ሲቀበሉ ንግሥቲቱ ግን ካለችበት
ካህናቱ ሄደው ነበር የሚያቆርቧት፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን “ይህ ቁርባን ንጉሠ ነገሥት ነውና ንግሥቲቱ ወደዚህ መጥታ ልትቀበል
ይገባታል እንጂ እኛ መሄድ የለብንም” ሲል ተቃወመ፡፡ ይህ ነገር ንግሥቲቱንና አባ ጊዮርጊስን ስላጋጫቸው ዐፄ ዳዊት ችግሩን
ለመፍታት አባ ጊዮርጊስን ወደ ሀገረ ዳሞት ንቡረ እድነት ሾሞ ላከው፡፡
አባ ጊዮርጊስና አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ የተገናኙት አባ ጊዮርጊስ ወደ ዳሞት በሚጓዝ ጊዜ ነበር፡፡ አባ
ጊዮርጊስ አለባበሱ እንደ ተርታ ሰው በመሆኑ አቡነ ሳሙኤል በመጀመርያ አላወቁትም ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ አባ ጊዮርጊስ
ቅር ብሎት ወደ ዳሞት ተመለሰ፡፡ እንደ ሥርግው ሐብለ ሥላሴ ግምት ሁለቱን ያላግባባው ሥርዓተ ጸሎት ሳይሆን አይቀርም፡
፡ በዚያ ጊዜ በዋልድባ ሥርዓተ ጸሎቱ ሰባት ጊዜ በቀን መጸለይን የሚያዝ ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በቀን ሰባት ጊዜ ብቻ
መጸለዩ ለእግዚአብሔር ያንሰዋል ብሎ ያምን ነበር፡፡ ምናልባትም በዚያን ጊዜ 22 ሰዓት የሚፈጀውን ሰዓታት ሳያዘጋጅ
አልቀረም፡፡ከዚህ በኋላ የአባ ጊዮርጊስ ዋናው ትኩረቱ በድርሰቱ ላይ ሆነ፡፡ ወደ ጳጳሱ ወደ አቡነ በርተሎሜዎስ ዘንድ በመሄድ
የቅዳሴ ድርሰት ለመድረስ እንዲፈቀድለት ከጠየቀ በኋላ የቅዳሴ ድርሰት ማዘጋጀቱን ገድሉ ይገልጣል፡፡ ይህም የኢትዮጵያ
ቅዳሴያት ደራሲያቸው ማን ነው? ለሚለው ጥያቄ መልስ ፍንጭ የሚሰጠን ይሆናል፡፡ ገድሉ እንደሚተርከው አንዳንድ ካህናት
የአባ ጊዮርጊስን ቅዳሴ ተቃውመው ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር አርዮስን በቀጣበት መንገድ ቀጥቷቸዋል፡፡
አባ ጊዮርጊስ ነገረ ሃይማኖትን ጠንቅቆ የተረዳና የሚያስረዳ ስለነበር በዘመኑ የተነሡ የሃይማኖት ክርክሮች
ሁሉ እርሱ ከሌለ አይሳኩም ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ በሸዋ በይፋት ራሳቸውን ቤተ እስራኤል እያሉ የሚጠሩ አይሁድ ነበሩ፡፡ ከአቡነ
ዜና ማርቆስ ጀምሮ ብዙ መምህራን ወደነዚህ ሕዝቦች እየተሠማሩ ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ክርስትና
ለተመለሱት ቤተ እስራኤላውያን በእመቤታችን፣ በቅዱስ ሚካኤል፣ በአባ ኖብና በሰማዕቱ በጊጋር ስም አራት አብያተ
ክርስቲያናትን አሠርተው ነበር፡፡ ሁለቱ የመጀመሪያዎቹ አሁንም አሉ፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ቤተ እስራኤላውያኑ ሙሉ በሙሉ
ወደ ክርስትና አልተመለሱም ነበር፡፡ከእነዚህ አይሁድ መካከል አንዱ ከክርስቲያኖች ጋር በነገረ ሃይማኖት ለመከራከር ጥሪ
አቀረበ፡፡ “ክርስቲያኖች ከረቱኝ ወደነርሱ ሃይማኖት እገባለሁ እኔ ከረታኋቸውም ወደኔ ሃይማኖት ይገባሉ” ሲል ነገሩን ጥብቅ
አደረገው፡፡ ዐፄ ዳዊት ይህን ጉዳይ ሲሰማ በጣም ስለ ተናደደ ሊቃነ ካህናቱን፣ ንቡራነ እዱንና የመጻሕፍት ዐዋቂዎችን ሁሉ
ከየሀገሩ እንዲሰባሰቡ አዘዘ፡፡ አይሁዳዊው በአንድ ወገን መምህራኑ በአንድ ወገን ሆነው ክርክሩን ጀመሩ፡፡ የመጀ መርያው
እድል የተሰጠው ለአይሁዳዊው በመሆኑ ቀጥሎ ያለውን ጥያቄ አቀረበ፡- “እናንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የምትሉት ይሄ
ክርስቶስ እውነት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፣ ወደ ቢታንያ በመጣ ጊዜ አልዓዛር የተቀበረበትን ቦታ ሳያውቅ ቀርቶ 'አልዓዛርን
የት ቀበራችሁት?” ብሎ እንደ ጠየቀ በወንጌላችሁ ተጽፏል፡፡ ለዚህ መልስ ስጡኝ፣እኔንም ከመጽሐፈ ኦሪቴ ጠቅሳችሁ
ጠይቁኝ?” ሲል የመከራከርያ ነጥቡን አቀረበ፡፡በዚህ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ ታሞ አልጋ ላይ ነበር፡፡ ሊቃውንቱም “እንዲህ ያለው
ነገር ያለ እርሱ አይሆንምና አባ ጊዮርጊስ ይምጣ” ሲሉ ለዐፄ ዳዊት ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አባ ጊዮርጊስም በአልጋ ላይ እያለ
እንዲመጣ ተደረገ፡፡ በአልጋ ላይ ሆኖም በጉባኤው ላይ ተገኘ፡፡ ጉባኤተኞቹ የቀረበውን ጥያቄ ነገሩት፡፡ አባ ጊዮርጊስ የሰጠውን
መልስ ገድሉ በሚከተለው መንገድ ይገልጥልናል “እኔ ግን በወንጌል ሳይሆን በኦሪት እከራከርሃለሁ፡፡ የምኩራብ መጻሕፍት
ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን የታወቁ ናቸውና፡፡ ምኩራብ ዘራች ቤተ ክርስቲያንም አጨደችው፤ ምኩራብ ፈተለችው ቤተ ክርስቲያን
ለበሰችው፤ አዳምን በገነት ሳለ አዳም ሆይ ወዴት ነህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? አብርሃምንስ ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? ብሎ
የጠየቀው ማነው? እስቲ መልስልኝ? ሰይጣንንስ ከወዴት መጣህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? እግዚአብሔር አብ አይደለምን?”
በዚህ ጊዜ አይሁዳዊው መልስ አጥቶ ዝም አለ፡፡ ንጉሡ፣ ሊቃውንቱና መኳንንቱም እጅግ ተደሰቱ፡፡

አባ ጊዮርጊስ ሌላው ያጋጠመው ክርክር ቢቱ ከተባለው ሰው ጋር ያደረገው ክርክር ነበር፡፡ ቢቱ


“በምጽአት ጊዜ የሚመጣው ወልድ ብቻውን እንጂ አብና መንፈስ ቅዱስ አይመጡም” የሚል ኑፋቄ ማስተማር ጀምሮ ነበር፡፡
ቢቱ ከዚህ ኑፋቄው በተጨማሪ የጥንቆላ ሥራም ይሠራ ነበር፡፡ ቢቱ በጥንቆላ ሥራው የተነሣ በቤተ መንግሥቱ ተቀባይነት

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 81
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

የነበረው ሰው እንደ ነበረ ገድሉ ይናገራል፡፡ ይህን መሰሉን ተግባር አጥብቆ የተዋጋው ዘርዐ ያዕቆብ እስኪመጣ ድረስ ነገሥታቱ
ምንም ክርስቲያኖች ቢሆኑ በዚህ መሰሉ ስንኩል ሕፀፅ ይዋጡ ነበር፡፡ቢቱና አባ ጊዮርጊስ ወደ ንጉሥ ዳዊት ቀርበው በጉዳዩ
ላይ መነጋገር እንደሚፈልጉ ገለጡ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ጳጳሱና ሊቃውንቱ ባሉበት እንዲነጋገሩ ስለ ወሰነ ጳጳሱ እንዲመጡ አዘዘ፡፡
በዚህ ጊዜ ተንኮለኛው ቢቱ ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ከተከራከረ እንደሚረታ ስላወቀ “ንጉሡ የአባቶቻችንን ሃይማኖት ክዷልና
አትምጣ” የሚል ደብዳቤ በአባ ጊዮርጊስ ስም ጽፎ ጳጳሱን ሊጠሩ በሄዱት መልእክተኞች እጅ ላከ፡፡ ወድያውም ለዐፄ ዳዊት
ይህንን ነገር አሳበቀ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ፈጣን መልእክተኞች ልኮ የፊተኞቹ መልእክተኞች እንዲመለሱ አደረገና ደብዳቤው ተነበበ፡
፡ የቢቱ ተንኮል ያልገባው ንጉሥ ዳዊት ይህን ደብዳቤ ሲመለከት አባ ጊዮርጊስን በደም አበላ እስኪነከር ድረስ እንዲደበደብ
አድርጎ ወደ እስር ቤት አስገባው፡፡ ዐፄ ዳዊት እስኪሞትና ልጁ ቴዎድሮስ እስኪነግሥ ድረስም በዚያ ቆየ፡፡ ቢቱ ግን በመልአክ
ተቀስፎ ሞተ፡፡
አባ ጊዮርጊስ በወኅኒ ቤት እያለ ጴጥሮስና ጳውሎስ እየመጡ ያጽናኑት ነበር፡፡ ውዳሴ ሐዋርያት የተሰኘውንና
ከሐምሌ 5 ጀምሮ በ12ቱም ወራት የሚመሰገኑበት የሐዋርያትን ምስጋና የያዘውን መጽሐፍ ያዘጋጀው በወኅኒ በነበረ ጊዜ ነው፡
፡ዐፄ ቴዎድሮስ አባ ጊዮርጊስን ከወኅኒ ቤት አውጥቶት በጥንቱ ቦታ አስቀመጠው፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን የቤተ መንግሥትን ነገር
ለመሸሽ ስለ ፈለገ በጋሥጫ ከመቀመጥ ይልቅ ርቆ ጥንት ወደ ነበረበት ወደ ዳሞት በመሄድ ማስተማር ጀመረ፡፡ ወደ ዳሞት
ሲሄድ እግረ መንገዱን ወደ ደብረ ሊባኖስ ገብቶ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን መቃብር ተሳልሟል፡፡ በዚያ ጊዜ የደብረ ሊባኖሱ
አበ ምኔት እጨጌ ዮሐንስ ከማ /ሰባተኛው የደብረ ሊባኖስ እጨጌ/ እንደ ነበሩ ገድሉ ይናገራል፡፡ነገር ግን በዕውቀቱ
የሚቀኑበት፣ በችሎታው የሚመቀኙት ሰዎች ነገር ሠርተው ከንጉሥ ቴዎድሮስ ጋር ስላጣሉት እልም ካለ በረሃ እንዲጋዝ
ተደረገ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ከግዞት የወጣው ዐፄ ቴዎድሮስ ሲሞት ነበር፡፡
የአባ ጊዮርጊስ ሌላው ተማሪ የነበረው ዐፄ ይስሐቅ በ1399 ዓ.ም መንግሥቱን ሲይዝ አባ ጊዮርጊስን
ከግዞት አውጥቶ ወደ ጋሥጫ መለሰው፡፡ በዚያ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ እድሜው 42 ዓመት ሲሆን በስደትና በጤንነት መታወክ
የተነሣ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜውን በጾም፣ በጸሎትና በድርሰት ያውለው ነበር፡፡“አንድ ቀን
ቴዎድሮስ የተባለ መስፍን፣ ዳግመኛም የጦሩ አዛዥ የሚሆን፣ አባ ጊዮርጊስን ስለ ርትዕት ሃይማኖት ጠየቀው፡፡ አባ ጊዮርጊስም
ፍካሬ ሃይማኖት የተባለውን መጽሐፍ ደርሶ ሰጠው፡፡ ንጉሡና የምሥጢር ሊቃውንት የሆኑ ካህናት ይህንን በተመለከቱና
ባነበቡ ጊዜ በእውነት ዮሐንስ አፈወርቅና አፈ በረከት የሆነው ቄርሎስ በዘመናችን ተነሥተዋል፡፡ ኢትዮጵያም ቁስጥንጥንያን
መስላለች፣ ከእስክንድርያም በላይ ከፍ ከፍ ብላለች ብለው አደነቁ” ይላል ገድሉ አባ ጊዮርጊስ ፍካሬ ሃይማኖት የተሰኘውንና
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የምታምነውንና የምታወግዘውን በግልጥና በዝርዝር የጻፈበትን መጽሐፍ እንዴት እንደ ደረሰው
ሲገልጥ፡፡ ፍካሬ ሃይማኖት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን እምነት በግልጥና በዝርዝር በማስቀመጥ ረገድ በኢትዮጵያ ቤተ
ክርስቲያን ታሪክ የመጀመርያው ሥራ ይመስላል፡፡ የዘረዘራቸው የመናፍቃን ስሞችን እና ክህደታቸውን ስናይ በዘመኑ የነበሩ
ሊቃውንት ስለ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያላቸውን ዕውቀት ያሳየናል፡፡
አባ ጊዮርጊስ መከራ ያልተለየው አባት ነበር፡፡ ገድሉ እንደሚተርከው በቤተ መንግሥቱ የነበሩ ሰዎች
የርሱን መከበርና መወደድ አይፈልጉትም ነበር፡፡ በተለይም ፍካሬ ሃይማኖት የተሰኘውን መጽሐፍ በመጻፉ የተነሣ መከበሩ
አልተዋጠላቸውም፡፡ ስለዚህም ነገር ሠርተው ከዐፄ ይስሐቅ ጋር አሁንም አጣሉት፡፡ዐፄ ይስሐቅ አባ ጊዮርጊስን አሳስሮ ውኃ
ወደማይገኝበት ዐለታማ ቦታ አጋዘው፡፡ በዚያም በመከራ ለብዙ ጊዜ ኖረ፡፡ በዚያ እያለ ዘወትር በጸሎት አብዝቶ ይተጋ ነበር፡
፡ እግዚአብሔርም ዐፄ ይስሐቅ ወደ ልቡናው እንዲመለስ አደረገ፡፡ ንጉሡ በአባ ጊዮርጊስ ላይ የፈጸመው ነገር ሁሉ ፀፀተው፡
፡ አገልጋዮቹንም ጠርቶ አባ ጊዮርጊስን እንዲያመጡት አዘዘ፡፡ ነገር ግን እነዚያ ተንኮል ሠሪዎች የአባ ጊዮርጊስ መምጣት
ተንኮላቸውን ስለሚያጋልጠው “አባ ጊዮርጊስ ሞቷል” ብለው አስወሩ፡፡ ይህንን ሲሰማ ዐፄ ይስሐቅ ፈጽሞ አዘነ፡፡አባ ጊዮርጊስ
ሞቷል እየተባለ መወራቱን ከደቀ መዝሙሩ ስለ ሰማ በሕይወት የመኖሩን ዜና ጽፎ ለዐፄ ይስሐቅ እንዲያደርስለት አውሎ
ንፋስን ላከው፡፡ አውሎ ንፋሱ ደብዳቤውን ተሸክሞ በመሄድ ዐፄ ይስሐቅ በድንኳን ተቀምጦ በነበረ ጊዜ ጉልበቱ ላይ
አስቀመጠው፡፡ ንጉሡ ምትሐት የተሠራበት ስለ መሰለው ደነገጠና መኳንንቱንና ሕዝቡን ሰብስቦ ጉዳዩን ገለጠ፡፡ ወዲያውም
እሳት አስነድዶ ቢጥለው ሊቃጠል አልቻለም፡፡ ወደ ውኃም ቢጨምረው አልጠፋም፡፡ በዚህ ተደንቆ ወረቀቱን ከፍቶ
አነበበው፡፡ ደብዳቤው ከአባ ጊዮርጊስ የተላከ መሆኑን ሲያውቅ ዐፄ ይስሐቅ ደነገጠ፡፡ እነዚያን መልእክተኞች ይዞ ወደ ወኅኒ
ጨመራቸው፡፡ አባ ጊዮርጊስንም ከግዞት ያወጡት ዘንድ ላከ፡፡አባ ጊዮርጊስ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሲመጣ ንጉሡ በደስታ
ተቀበለው፡፡ ደብዳቤውን በማን እጅ እንደ ላከውም ጠየቀው፡፡ አባ ጊዮርጊስም ደብዳቤውን በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር
ፈቃድ በነፋስ እንደ ላከው አስረዳ፡፡ከግዞት ከተመለሰ በኋላ እመቤታችን ተገልጣለት መከራው ሁሉ እንደ ሐዋርያት መሆኑን

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 82
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ገለጠችለት፡፡ አእምሮውን ብሩህ፣ ልቡናውን ትጉኅ የሚያደርግ እጅግ ብዙ ምሥጢር ነገረችው፡፡ ተሰናብታው ከሄደች በኋላ
“እጅግ ብዙ መብራት አቅርቡ አምስት ፈጣን ጸሐፊዎችንም አምጡ” ብሎ አዘዘ፡፡ እርሱ እየነገራቸው እነርሱ እየጻፉ እረፍት
ሳያደርጉ ሦስት ቀን ሙሉ አስጽፎ መጽሐፈ ምሥጢር የተሰኘውን መጽሐፍ ፈጸመ፡፡ አምስቱ ጸሐፍትም የየድርሻቸውን
አጠናቅቀው በአንድ አደረጉት፡፡ አባ ጊዮርጊስም ይህን ተመልክቶ በእጅጉ አደነቀ፡፡ “እኔ የዚህን መጽሐፍ ቃል አልተናገርኩም፤
መንፈስ ቅዱስ በእኔ አፍ ተናገረ እንጂ” ሲል በወቅቱ መመስከሩን ገድሉ ይናገራል፡፡ ይህንም መጽሐፍ መጽሐፈ ምሥጢር
ሲል ሰየመው፡፡ የጻፈው በ1409 ዓ.ም እድሜው 52 በደረሰ ጊዜ ሲሆን የዚህ መጽሐፍ ቅጅ በነጋድያን እጅ እስከ ኢየሩሳሌም
ድረስ በወቅቱ ሄዶ እንደ ነበር ገድሉ ያስረዳል፡፡ዐፄ ይስሐቅ ለአባ ጊዮርጊስ ምድረ ሰዎን የተባለውን የጳጳሳት መቀመጫ
የነበረውን ሀገር በርስትነት ሰጥቶት ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ በምድረ ሰዎን ንጉሥ ይስሐቅ ክረምቱን ያሳልፍበት በነበረው ቦታ
ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠራ፡፡ በዚያም በማስተማርና በጾም በጸሎት ይተጋ ነበር፡፡ በጋሥጫ እያለ ዐፄ ይስሐቅ አስጠራው፡፡
በዚያ ጊዜ ንጉሡ የመናገሻ ማርያምን ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ ስለ ነበር እንዲባርክለት ፈልጎ ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ምንም እንኳን
በዚያ ጊዜ ታምሞ የተኛም ቢሆን ወደ ንጉሡ ተጓዘ፡፡ እዚያ ሲደርስ በጣም ተዳክሞ ነበር፡፡ ሥርዓቱን ለመፈጸምም ዐቅም
አልነበረውም፡፡ ስለዚህም ንጉሥ ይስሐቅ በአልጋ ተሸክመውት እንዲዞሩና ቤተ ክርስቲያኗን እንዲባርካት አደረገ፡፡ቡራኬውን
ከፈጸመ በኋላ ደቀ መዝሙሮቹን ሰብስቦ “ከሞትኩ አባቴ በጸሎተ ሚካኤል መከራ ወደ ተቀበለባትና እኔም ቤተ ክርስቲያን
ወዳነፅኩባት ቦታ ወስዳችሁ ቅበሩኝ” ሲል አዘዛቸው፡፡ ለደቀ መዛሙርቱ የመጨረሻ የስንብት ትምህርቱን እያስተማራቸው
እነርሱም በአልጋ ተሸክመውት ወደ ጋሥጫ እያመሩ ሳለ በመንገድ ላይ ሐምሌ ሰባት ቀን 1417 ዓ.ም በ60 ዓመቱ ዐረፈ፡፡

የአባ ጊዮርጊስ ሥራዎች


እስካሁን ድረስ ያሉን ምንጮች የአባ ጊዮርጊስ ድርሰቶች ቁጥራቸው ከዐርባ በላይ እንደሆኑ ይገልጣሉ፡፡ በስም የምናውቃቸው
ግን የሚከተሉትን ብቻ ነው፡፡ ምናልባት ብዙ ጥናት ማድረግ ሳያስፈልገን አይቀርም፡፡
1) ሰዓታት ዘመዓልት ወዘሌሊት
2) ኖኅተ ብርሃን /ከመጽሐፈ አርጋኖን ጋር አብሮ ታትሟል/
3) ውዳሴ መስቀል
4) ቅዳሴ
5) ውዳሴ ሐዋርያት
6) አርጋኖነ ውዳሴ
7) ፍካሬ ሃይማኖት
8) መጽሐፈ ምሥጢር
9) ውዳሴ ስብሐት
10) እንዚራ ስብሐት
11) ሕይወተ ማርያም
12) ተአምኖ ቅዱሳን
13) መጽሐፈ ብርሃን
14) ጸሎት ዘቤት ቤት

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 83
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ሐምሌ 2ኛ ሳምንት
አቡነ ተክለ ሃይማኖት
የአቡነ ተ/ሃይማኖት ዜና ሕይወት
በቡልጋ ደብረፅ-ላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል
ቤተክርስቲያን አካባቢ ካህኑ ጸጋዘአብና ባለቤታቸው
እግዚእሐሪያ የሚባሉ የእግዚአብሔር ባለሟሎች ይገኙ ነበር፡
፡ ታዲያ እነዚህ በእምነታቸው የፀኑ ባልና ሚስቶች ለብዙ
አመታት ያለ ልጅ ቢኖሩም በትዕግስትና በጽናት
እንደኤልሳቤጥ እና ዘካሪያስ እግዚአብሔርን በመማፀንና
በመለመን ፀንተው እየኖሩ የዳሞት ገዢ ሞተላሚን ሠይጣን
አነሣስቶት የሸዋን አውራጃዎች እስከጅማ ድረስ በጦርነት
በሐይል ገዛ፡፡ ይህ ንጉስም ፈሪሐ እግዚአብሐሔር በውስጡ
አልነበረውምና የአይሁድ መኳንንቶች በየተራቸው
ሚስቶቻቸውን እንዲሰጡት አድርጎ ነበር፡፡ በሚገዛቸው
ግዛቶችም መልከ መልካም ያገኝ እንደነ እቁባቱ ከማድረግ
አይመለስም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ታዲያ ወደ ጽላልሽ ደርሶ
ኖሮ ብዙ ክርስቴያኖችን ገደለ፡፡ ከመካከላቸው የሚበዙትን
ማረከ ጸጋዘአብም ከግድያ ፍርሐት የተነሣ ሲሸሽ አንድ
ወታደር አይቶ ቢከተለውም ባሕር ውስጥ ተወርውሮ ገብቶ
በእግዚአብሔርም ፈቃድ በባህሩ ውስጥ ተሸሸገ፡፡ ሚስቱ
እግዚእሐርያ ግን በወታደሮቹ እጅ ወድቃ ነበርና ይዘዋት ወደ ሞተለሚን አደረሷት፡፡ ሞተላሚንም ባያት ጊዜ ውበትዋን አደነቀ
ስለውበትዋም ደስ ስላለው ብዙ ሽልማትን አበረከተላት ሊያገባት መወሰኑን እግዚእሐሪያ በሠማች ጊዜ ከአረማዊ ጋር አንዷ
ከመሆን ያድናት ዘንድ በብዙ ለቅሶ ወደ እግዚአብሔር ጸሎትን አደረች፡፡ እግዚአብሔርም መላእኩን ቅዱስ ሚካኤል ልኮ
በብርሃናት ክንፎቹ ተሸክሞ ወደምድረ ዞረሬ አድርሶ ወዲያውኑ በቤተመቅደስ ውስጥ በሴቶች መቆሚያ አቆማት፡፡ ባሏ
ፀጋዘአብም ከማዕጠንት ጋራ በወጣ ጊዜ እንደተሸለመች ቆማ አያት በልቡ አደንቆ ይህች ሴት ምንድነች; ወደዚህም ማን
አመጣት; እያለ ካሠበ በኋላ ማጠንቱን ሲጨርስ ከየት እንደመጣች በመረመራት ጊዜ እርሷ ሚስቱ እግዚእሐሪያ እንደሆነች
አገኛት፡፡ እርሷም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እግዚአብሔር ያደረገላትን ነገረችው፡፡

ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መላእክ በአንድ ሌሊት መጋቢት 24 ቀን ለፀጋዘአብና ለእግዚእሐሪያ


ተገልጦላቸው የዜናው መሠማት በዓለሙ ሁሉ የሚደርስ የተባረከ ልጅ እግዚአብሔር እንደሚሰጣቸው የሠሙትም ብስራት
በታህሳስ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተፈፀመ፡፡ ታላቅ ሕፃንም ወለዱ፡፡ ይህ ታላቅ ሕፃን በተወለደ በሦስተኛው ቀን በታህሳስ 27 ቀን
በዕለተ እሁድ ከጠዋቱ በ3 ሰዓት ከእናታቸው እቅፍ ወርደው በዛ በሚጣፍጠውና በሚያለመልመው አንደበታቸው “አሀዱ
አብ ቅዱስ አሀዱ ወልድ ቅዱስ አሀዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ትርጓሜውም “አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው
አንዱ መንፈስ ቅዱስም ቅዱስ ነው” ብለው ፈጣሪያቸውን አመሰግነዋል፡፡
ዳዊት በመዝሙሩ 2.2 ላይ “ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለጠላትም ጠላትንና ቂመኛን
ለማጥፋት” ብሎ አስቀድሞ እንደተናገረ ይህ ታላቅ ሕፃን በክርስትና ማጥመቂያ ቤት ባስገቡት ጊዜ “ፍስሐ ጽዮን” ብለው
ሰየሙት፡፡ ትርጓሜውም ጽዮን ደስታዋ ነው ማለት ሲሆን አንድም ---------- በተወደደ ትምህርቱ ቤተክርስቲያን /ምዕመናንን/
ደስ ያሰኛት ዘንድ ነው፡፡
ፍስሐ ጽዮን አንድ ዓመት ከሶስት ወር ከሆነው በኋላ በሸዋ አውራጃ ሁሉ ረሀብ ሆኖ እግዚእሐሪያ ጸጋዘአብን እነሆ
የቅዱስ ሚካኤል በዓል ደረሰ በእጃችን ምንም ስለሌለን ምን እናድርጋለን አለችው፡፡ ወይስ ከዚህ ዓለም በሞት ሣንለይ በዓሉን
እንተዋለን አሁንም ወደ ቤተ መቅደስ ሄደህ ወደ እግዚአብሔር አመልክት እግዚአብሔር ቸር ነውና የምናደርገውን ነገር

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 84
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ያመለክተናል፡፡ ይህንንም ስትናገር እንባዋን እያፈሠሠች ነበር፡፡ ጸጋዘአብም ሚስቱ በቅዱስ ሚካኤል በዓል ታጎለብኝ ብላ
ስታለቅስ ባየ ጊዜ ልቡ ስብርብር ብሎ አዘነ፡፡ እንደተናገራቸውም ወደ ቤተመቅደስ ሄደ ከመቅደስ ገብቶ ከመንበሩ ላይ ተደፍቶ
“አቤቱ በእጄ ምንም የለኝም የሚካኤል በዓል ታጎለብኝ ምን ላድርግ እያለ አለቀሠ አቤቱ ቅዱስ አምላክ ሆይ ልቦናዬን
መርምረው ፈጣሪዬ አንተ ነህና ወደ አንተ አንጋጥጣለሁ፡፡ የልቦናዬን ሐሣብም ለአንተ አቀረባለሁ፡፡ ችግሬን የልቦናዬን
ሐሣብም ለአንተ እነግራለሁ፡፡ በባለሟልህ በሚካኤል እጅ እሥራኤልን መና የመገብካቸው አንተ ነህ ከሲና ዱር ጀምረህ እስከ
ቃዴስ በረሀ ድረስ ዛሬም አንተ ነህና፡፡ ምን ማድረግ እንደምችል አንተው አመልክተኝ” እያለ በቤተመቅደሱ ውስጥ እንዲህ
እያለ ሲለምን ሚስቱም ልጅዋን ፍስሐ ጽዮንን ታቅፋ በቤቷ ደጃፍ ተቀምጣ ተለቅስ ነበር፡፡

የተመረጠ ልጀዋ ስታለቅስ አይቶ እንባዋን በጣቱ ጠረገላት ወደ ቤት ይገቡ ዘንድም በጣቱ አመለከታት እርሷም ይህ
ልጅ ምን ይለኛል ብላ ጡት የሚለምን መስሏት ይጠባ ዘንድ ጡቷን አጎረሰችው፡ ፍስሐ ጽዮንም መጥባቱን ትቶ ወደ ቤት
ውሰጥ አግቢኝ እንደሚል ጠቅሶ አሣያት እርሷ ግን አላወቀችም ነበር፡፡ ህፃኑ ግን ወደ ቤቱ ለመግባት እያመለከተ ጮኾ
አለቀሠ፡፡ እናቱም ወደ ቤት አግቢኝ ማለቱን ባወቀች ጊዜ ልጅዋን ይዛ ገባች፡፡ በቤቱ ውስጥ ጥቂት የሥንዴ ዱቄት በእንቅብ
ውስጥ አንድ ድርጎ የሚሆን ነበር፡፡ ህፃኑም እንቅብ ስጭኝ እንደሚል ጠቅሶ አሣያት፡፡ እርሱም ብከለክለው ያለቅስብኛል ብላ
አምጥታ ሠጠችው እጁን በዱቄት ላይ በአደረገው ጊዜ እንቅቡ ወዲያኑ ሞልቶ ፈሰሰ፡፡ እናቱም ይህንን ሥራ አይታ አደነቀች፡
፡ ዳግመኛ ልጅዋ ፍስሐ ጽዮን ሁለተኛውን እንቅብ ታመጣ ዘንድ ጠቀሣት ባቀረበችለብም ጊዜ እንደሚጫወት ሕፃን
ከመጀመያው እንቅብ መልቶ ከፈሠሠው ላይ በእጁ ዘግኖ በባዶው እንቅብ ላይ ቢያደርገው ከዚያም መላ ሦስተኛም እንቅብ
አመጣችለት እንደቀድሞው ሞላ እግዚእኃሪያም እንቅብ ማቅረብ ቢደክማት ትረዳት ዘንድ ገረዷን ጠራቻት እርሷም ዘጠኝ
እንቅብ ለሕፃኑ ለፍስሐ ጽዮን አቀረበች፡፡ በእነሱ ሁሉ መላ አሥራ ሁለት እንቅብ ሆነ በዚያች ቀን በጸጋዘአብ ቤት
እግዚአብሔር በረከት ሞላ፡፡

ይህ ታላቅ ሕፃን ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ እውቀትንና ኃይልንም መንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተሞልቶ አደገ፡፡ ከወላጅ
አባቱም ከካህኑ ጸጋአዘአብ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ሲያጠና ቆይቶ በአሥራ አምስት አመታቸው በ1212 ዓ.ም ድቁናን ከግብጽ
ሊቀጳጳስ ከሆኑት አቡነ ቄርሎስ ተቀብለዋል፡፡ ተቀብለውም ወደ ትውልድ ሀገራቸው በመመለስ እግዚአብሔርን ሲያገለግሎ
ቆዩ፡፡ በአንድ ወቅት ፍስሐ ጽዮን ከጓደኞቹ ጋር ወደ አደን ወጥቶ በዚያ በዱር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልኩ
በሚያምር አምሣል በቅዱስ ሚካኤል…………………………………….ትሆናለህ እንጂ አራዊትን የምታድን አትሆንም ስምህም
ተክለሐይማኖት ይሆናል” ትርጓሜውም /ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው/ አላቸው፡፡ እኔም እንደ
ኤርምያስና እንደ አጥማቂው ዮሐንስ ከእናትህ ማህንፀ መርጨ አክብሬሃለሁና እነሆ በሽተኞችን ትፈውስ ዘንድ ሙታንንም
ታስነሣ ዘንድ ስልጣንን ሰጠሁህ እርኩሣን አጋንንትንም ከሁሉ ቦታ ታስወግዳቸዋለህ ብሎ ከተግናገራቸው በኋላ ተሰወረ”፡፡
አስቀድሞ በደማስቆ ቅዱስ ጳውሎስን ለሐዋርያነት እንደመረጠው አባታችን ተክለሐይማኖትንም ለኢትዮጵያውያን
ክርስቲያኖች ሐዋርያት እንዲሆኑ መርጦ ከአውሬ አዳኘነተ ወደ ሠው አዳኝነት በትምህርተ ወንጌል እያደኑ ለመንግስተ ሰማያት
እንዲያበቁ ጠራቸው የሐዋርያ ስማቸውንም የሃይማኖት ተክል በማለት ሰየማቸው፡፡ ከዚያም ዕለት ጀምሮ አባታችን
ተክለሃይማኖት ተብለው መጠራት
ቅስናን ከተቀበሉ በኋላ በሸዋ ሐገር ሁሉ ወንጌልን መስበክ ጀመሩ ……………. ነፍስን አጠመቁ አጥምቀዋቸውም
ለጣኦት የሚሰውባቸውን ነገሮች እቃዎች ሻሩ በውስጡ የሚኖሩ አጋንንትንም እስኪሸሹ ድረስ አጸዶቻቸውን ሁሉ ቆረጠ፡፡
ከ1219 ዓ.ም እስከ 1222 ዓ.ም በተከታታይ ለሦስት ዓመታት ወንጌልን አስተማሩ፡፡ ከዚያም ቀጥለው ለዘጠኝ ወር
በዊፋት አገልግሎታቸውን ፈጽመዋል፡፡
በቡልጋ ደብረፅ-ላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ካህኑ ጸጋዘአብና ባለቤታቸው
እግዚእሐሪያ የሚባሉ የእግዚአብሔር ባለሟሎች ይገኙ ነበር፡፡ ታዲያ እነዚህ በእምነታቸው የፀኑ ባልና ሚስቶች ለብዙ
አመታት ያለ ልጅ ቢኖሩም በትዕግስትና በጽናት እንደኤልሳቤጥ እና ዘካሪያስ እግዚአብሔርን በመማፀንና በመለመን ፀንተው
እየኖሩ የዳሞት ገዢ ሞተላሚን ሠይጣን አነሣስቶት የሸዋን አውራጃዎች እስከጅማ ድረስ በጦርነት በሐይል ገዛ፡፡ ይህ ንጉስም
ፈሪሐ እግዚአብሐሔር በውስጡ አልነበረውምና የአይሁድ መኳንንቶች በየተራቸው ሚስቶቻቸውን እንዲሰጡት አድርጎ ነበር፡
፡ በሚገዛቸው ግዛቶችም መልከ መልካም ያገኝ እንደነ እቁባቱ ከማድረግ አይመለስም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ታዲያ ወደ
ጽላልሽ ደርሶ ኖሮ ብዙ ክርስቴያኖችን ገደለ፡፡ ከመካከላቸው የሚበዙትን ማረከ ጸጋዘአብም ከግድያ ፍርሐት የተነሣ ሲሸሽ
አንድ ወታደር አይቶ ቢከተለውም ባሕር ውስጥ ተወርውሮ ገብቶ በእግዚአብሔርም ፈቃድ በባህሩ ውስጥ ተሸሸገ፡፡ ሚስቱ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 85
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

እግዚእሐርያ ግን በወታደሮቹ እጅ ወድቃ ነበርና ይዘዋት ወደ ሞተለሚን አደረሷት፡፡ ሞተላሚንም ባያት ጊዜ ውበትዋን አደነቀ
ስለውበትዋም ደስ ስላለው ብዙ ሽልማትን አበረከተላት ሊያገባት መወሰኑን እግዚእሐሪያ በሠማች ጊዜ ከአረማዊ ጋር አንዷ
ከመሆን ያድናት ዘንድ በብዙ ለቅሶ ወደ እግዚአብሔር ጸሎትን አደረች፡፡ እግዚአብሔርም መላእኩን ቅዱስ ሚካኤል ልኮ
በብርሃናት ክንፎቹ ተሸክሞ ወደምድረ ዞረሬ አድርሶ ወዲያውኑ በቤተመቅደስ ውስጥ በሴቶች መቆሚያ አቆማት፡፡ ባሏ
ፀጋዘአብም ከማዕጠንት ጋራ በወጣ ጊዜ እንደተሸለመች ቆማ አያት በልቡ አደንቆ ይህች ሴት ምንድነች; ወደዚህም ማን
አመጣት; እያለ ካሠበ በኋላ ማጠንቱን ሲጨርስ ከየት እንደመጣች በመረመራት ጊዜ እርሷ ሚስቱ እግዚእሐሪያ እንደሆነች
አገኛት፡፡ እርሷም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እግዚአብሔር ያደረገላትን ነገረችው፡፡

ያከናውኑት መንፈሳዊ ተግባራት እና ያደረጉት ገቢረ ተአምር


 ቅስናን ከተቀበሉ በኋላ በሸዋ ሐገር ሁሉ ወንጌልን መስበክ ጀመሩ ……………. ነፍስን አጠመቁ አጥምቀዋቸውም ለጣኦት
የሚሰውባቸውን ነገሮች እቃዎች ሻሩ በውስጡ የሚኖሩ አጋንንትንም እስኪሸሹ ድረስ አጸዶቻቸውን ሁሉ ቆረጠ፡፡
 ከ1219 ዓ.ም እስከ 1222 ዓ.ም በተከታታይ ለሦስት ዓመታት ወንጌልን አስተማሩ፡፡
 ከዚያም ቀጥለው ለዘጠኝ ወር በኢፋት አገልግሎታቸውን ፈጽመዋል፡፡
 ዳሞት በተባለው ስፍራ ወይም ወላይታ ሀገር በአሥራ ሁለት አመታት ሕዝቡን ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ
እግዚአብሔር፣ ከገቢረ ኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ ትምህርትን በመስጠት …………..ሕዝቡን መልሰዋል፡፡
 ቤተክርስቲያንንም አንፀዋል፡፡
 በዚህም ሀገር ዲያቢሎስ በዛፍ ላይ አድሮ አምላክ ነኝ እያለ ለረጅም ዘመናት ሕዝቡን በማሣት የሚጠቀምበትን ዛፍ
በተአምራት ከሥሩ ነቅለው በሃይማኖት ያፈለሱት፡፡
 በእግዚአብሔር ትዕዛዝና ፈቀድ ወደ አማራ ሳይንት ወሎ በመሄድ ስርዓተ ምንኩስናን ከአባ በጸሎጸሚካኤል ገደም
ገብተው ለ10 ዓመታት የእርድናን ስራ በመሥራትና ገቢረ ተአምራትን በማሣየት ጌታ በቅዱስ ወንጌል “ማንም በእናንተ
ታላቅ ሊሆን የሚወድ ለእናንተ አገልጋይ ይሁን ከእናንተ ማንም ፈተኛ ሊሆን የሚወድ የእናንተ ባሪያ ይሁን እንዲሁም
የሠው ልጅ ያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሎት …
 አባ ኢየሱስ ሞአ ወደሚገኙበት ገዳም ሐይቅ እስጢፋኖስ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ሐይቁን /ባህሩን/ በእግራቸው እንደ
ደረቅ መሬት በመርገጥ ወደ ደሴቲቱ በመግባት የምንኩስናን ቀሚስ የንፅሕናን ምልክት ተቀብለዋል፡፡
 ለዐሥራ ሁለት ዓመታት አቡነ አረጋዊ ወደ አቀኑበት ገዳም በትግራይ ሐገረ ስብከት ወደሚገኘው ደብረ ዳሞ ገዳም
በመግባት በጊዜው ከነበሩት አበምኔት ከአባ ዮሐኒ ቆብና አሥኬማ ተቀብለው በገድል በትሩፋት መንፈሳዊ
ተጋድሎዋቸውን ቀጠሉ፡፡ ከደብረ ዳሞ ገዳም ወደ ሌላ ለመሄድ ሲነሱ ክቡር አባታችን ተክለ ሃይማኖት አበምኔቱና
መነኮሳቱ ሲሸኙዋቸው ሳለ አርባ ክንድ ርዝመት ባለ ገመድ ገደሉን ለመውረድ እንደጀመሩ ገመዱ ከካስማው ስር
በመቆረጡ እንዳይወድቁ በተሰጣቸው ስድስት የብርሃን ክንፎች እየበረሩ ክንፎቻቸውን እያማቱ ሦስት ምዕራፍ ያህል
በረዋል፡፡ በዚያም ወደ ገዳመ ዋሊ ገብተዋል፡፡ አንድ ዓመት ሙሉ የትግራይ ገዳማትን በመጎብኘት ኢየሩሳሌምንና ግብጽ
ያሉትን ገዳማትና ቅዱሳን መካናትን ሲጎበኙ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ አንድ ወር ሙሉ ዳዳ በተባለ ስፍራ ቆይተው
ይመለክ የነበረውን ቁመቱ 75 ክንድ በጸሎት ኃይል በተአምራት ገድለውታል፡፡ በአርባዕቱ እንስሣት /በኪሩቤልና
በሱራፌል/ ስም ቤተክርስቲያን አሣንፀው ታቦተ ሕግ ጽላተ ሕግ አስገብተዋል፡፡ ከሴቶችና ከልጆች ሌላ ሦስት ሺህ
ወንዶችን በጣኦት የሚያመልኩትን ወደ ክርስትና መልሰው አጥምቀው አቁርበዋል፡፡ በዚህም ተግባራቸው መድኃኒታችን
ያለውን ፈጽመዋል፡፡
 በደብረ ሊባኖስ ካለችው ገዳም አስቦ ዋሻ በመግባት ስምንት ጦሮችን ሁለቱን ከፊት፣ ሁለቱን ከኋላ፣ ሁለቱን ከቀኝና
ሁለቱን ከግራ አስተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል አምሣል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት ነገረ
መስቀሉን በማሰብ በተመስጦ ሌትና ቀን ያለማቋረጥ በፀጋ በጸሎት በአርምሞ ተወስነው ሲጋደሉ ከቁመት ብዛት የተነሣ
ጥር 4 ቀን 1282ዓ.ም የእግራቸው አገዳ ተሠብራለች፡፡ ደቀመዛሙርቱም የመንፈሳዊ አባታቸውን ሰባራ አጽም አክብረው
በስርዓት አኖረውታል፡፡ እግራቸውም እስኪሰበር የቆየባቸው አመታት በቁጥር 22 ዓመታት ናቸው፡፡ ሐዋርያው “በስጋ
መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአል” እንዳለ 1ኛ ጴጥ 4.12 አባታችን ኃጢአትን ርቀው መስቀል ተሸክመው ራስን በመካድ
በመስዋዕትነት ህይወት ፈጣሪያቸውን አገልግለዋል፡፡ ማቴ 16.24-27 እግራቸው በትጋትና በተጋድሎ ብዛት ተገንጥላ
ስትወድቅ አባታችን የዘጠና ሁለት አመት እድሜ ባለቤት ነበሩ፡፡

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 86
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

የሕይወት አክሊልን ስለመቀበላቸው


ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ብቻ በመቆም ያለምግብ በትእግስት ሌትም ቀንም እንቅልፍ በአይናቸው ሣይዞር
እንደምሰሶ ፀንተው በተመስጦ በትጋት ለሠው ዘር ሁሉ ድኅነትን ሲለምኑ ኖረዋል፡፡ ከሠባቱ ዓመታት ውስጥ ጥቂት ውሃ
የቀመሱት በአራተኛው ዓመታት ብቻ ነበር፡፡ ማቲ 4.4፣ ሐዋ 14.22፣ 2ቆሮ 11.26 በዚህም ጊዜ ጌታችን ተገልጦ ሰባት የሕይወት
አክሊላትን ሠጥቶአቸዋል፡፡ ዝክራቸውን በማዘከር መታሰቢያቸውን የሚያደርጉ ሁሉ በዚህ አለምም ሆነ በወዲያኛው ዓለም
ፍጹም ዋጋ ፍፁም ክብር እንደሚሠጣቸው ጌታ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡
በመጨረሻም ከነሐሴ 14 እስከ ነሐሴ 24 ቀን 1296 ዓ.ም ለዐሥር ቀናት በሕማም ቆይተው ፊጣሪያቸው የገባላቸውን
ቃልኪዳን ለመነኮሳት መንፈሳዊያን ልጆቻቸውና ለደቀመዝሙሮቻቸው ከነገሩ በኋላ በክብር አርፈዋል፡፡

አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮ ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 87
ትምህርተ አበው ለዘጠነኛ (ሣልሳይ) ክፍል

ዋቢ መጻሕፍት
1) ሃይማኖተ አበው፣ አዲስ አበባ፣ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፣ 1986 ዓ.ም.
2) አባ ጎርጎርዮስ (ሊቀ ጳጳስ)፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ፣ አዲስ አበባ፣ ብርሃንና ሰላም
ማተሚያ ቤት፣1974 ዓ.ም፡፡
3) ሉሌ መልአኩ (መምህር)፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ፣ አዲስ አበባ፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣1997 ዓ.ም፡፡
4) መጽሐፈ ስንክሳር፣ አዲስ አበባ፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ 1983 ዓ.ም
5) መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው፣ አዲስ አበባ፣ ንግድ ማተሚያ ድርጅት፣ 1988 ዓ.ም፡፡
6) መጽሐፈ ስንክሳር፣ አዲስ አበባ፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ 1983 ዓ.ም
7) መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው፣ አዲስ አበባ፣ ንግድ ማተሚያ ድርጅት፣ 1988 ዓ.ም
8) መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲስ አበባ፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ 1980 ዓ.ም
9) ምክረ ሥላሴ ገብረ አማኑኤል (ዶ/ር)፣ ጠቅላላ የቤተክርስቲያን ታሪክ፣ አዲስ አበባ፣ 2000 ዓ.ም.
10) የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፣ 1996 ዓ.ም፡፡
11) ጎርጎርዮስ(ብፁዕ አቡነ)፡፡ 1996 ዓ.ም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ፡፡አዲስ አበባ፡፡ ትንሣኤ ዘጉባኤ
ማተሚያ ቤት፡፡
12) ሰሎሞን መላኩ(ዲያቆን)፡፡ 2001 ዓ.ም፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ወርቃማ ዘመናት፡አዲስ አበባ፡፡ ባናዊ
ማተሚያ፡፡
13) ዜና ሐዋርያት
14) ያረጋል አበጋዝ (ዲ/ን)፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ Aፈወርቅ ሕይወቱና ትምህርቱ ፤ አዲስ Aበባ
15) ያረጋል አበጋዝ (ዲ/ን)፡፡ ነገረ ቅዱሳን ቁጥር 3
16) Holy Trinity College.(2004) Patrology፡ Holy Trinity College module/ unpublished./
17) Malaty T.Y( Father)Patrology ;
18) Malaty T.Y( Father) Apostolic fathers

መካነ ድር (ማህበራዊ ሚዲያ)


1) መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደስ ገጽ
2) ማኅበረ ቅዱሳን ገጽ
3) ገብረ እግዚአብሔር ኪዱ ገጽ

በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ገጽ 88

You might also like