You are on page 1of 66

ትምህርተ ሃይማኖት

በብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ወቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት
ትምህርት ክፍል ጥቅምት 2012 ዓ.ም ተዘጋጀ
ማውጫ

ገጽ 4
ርዕስ ገጽ
ምዕራፍ አንድ
1.1 ሃይማኖት ………………………………………………………………………………………5
የቃሉ ትርጉም
1.2 የሃይማኖት ጥቅም አስፈላጊነት…………………………………………………………………6
1.3 ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ……………………………………………………… ………. 7
1.4 የሃይማኖት መመሪያዎች……………………………………………………………………. 7
 ዶግማ (መሠረተ እምነት)…………………………………………………………… 8
 ቀኖና (መሠረተ ሥርዓት)
 ትውፊት (ቅብብል)
1.5 ሀልዎተ እግዚአብሔር………………………………………………………………………. 11
 የቃሉ ትርጉም
 ሀልዎተ እግዚአብሔር የሚታወቅባቸው ነገሮች
 ሕገ ልቡና (የኅሊና ምስክርነት)
 ሥነ ፍጥረት
 የሰው ልጆች የተፈጥሮ ዝንባሌ
 አምላካዊ መግቦት
 የቃለ እግዚአብሔርና የታሪክ ምስክርነት
1.6 አስማተ አምላክ …………………………………………………………………………… 12
 ስሞቹና ትርጓሜያቸው
1.7 የእግዚአብሔር የባሕርይ መገለጫዎች…………………………………………………… 13
 የእግዚአብሔርን የባሕርይ መገለጫ ማወቅ ጥቅም
ምዕራፍ 2
ሥነ ፍጥረት
 መግቢያ
 የቃሉ ትርጉም
2.1 የሥነ ፍጥረት ዓላማ ………………………………………………………………… 15
2.2 የሥነ ፍጥረት መገኛ ………………………………………………………………… 16
2.3 እግዚአብሔር ፍጥረታትን እንዴት ፈጠረ …………………………………………… 17
2.4 ሃያ ኹለቱ ሥነ ፍጥረት …………………………………………………………… 17
2.5 የስድስቱ ቀናት ፍጥረታት………………………………………………………… 18
2.5.1 የዕለተ እሑድ ፍጥረታትና ምሳሌ ………………………………………………. 18
2.5.2 የሰኞ ፍጥረትና ምሳሌ …………………………………………………………… 21
2.5.3 የማክሰኞ ፍጥረታትና ምሳሌ……………………………………………………… 22
2.5.4 የረቡዕ ፍጥረታትና ምሳሌ………………………………………………………… 22
2.5.5 የሐሙስ ፍጥረታትና ምሳሌ………………………………………………………. 23
2.5.6 የዓርብ ፍጥረታትና ምሳሌ…………………………………………………………. 23
2.5.7 ቀዳሚት ሰንበት …………………………………………………………………… 24
ምዕራፍ ሦስት
አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ……………………………………………………………………
 የቃሉ ትርጉምና ብዛታቸው
 ለምን አዕማድ ተባሉ?
 ለምን ምሥጢር ተባሉ
3.1 ምሥጢረ ሥላሴ ……………………………………………………………………………… 25
 መግቢያ
 የቃሉ ትርጉም
 የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር …………………………………………………
 የሥላሴ ሦስትነት …………………………………………………………………..
 የስም ሦስትነት
 የአካላት ሦስትነት
 የአካላት ግብር ሦስትነት
 የኩነት (ኹኔታ) ሦስትነት
 የኩነታት ሦስትነት በህልውና መገናዘብ
 የአንድነት ምሥጢር ……………………………………………………………………
 ምሥጢረ ሥላሴ በቅዱሳት መጸሕፍት
 መንፈስ ቅዱስ (ጰራቅሊጦስ)……………………………………………………………

ገጽ 4
 ማጠቃለያ
3.2 ምሥጢረ ሥጋዌ ………………………………………………………………………… 33
 መግቢያ
 የቃሉ ትርጉም
 የወልደ እግዚአብሔር ኹለት ልደታት ………………………………………………
 የወልደ እግዚአብሔር ልደታት በሊቃውንት መጻሕፍት
 አምላክ ለምን ሰው ሆነ ……………………………………………………………
 የሰው ተፈጥሮ
 የሰው ነጻ ፈቃድ
 እግዚአብሔር የሰጠው ትእዛዝ
 የሕግ ርግማን
 ለሰው ልጅ የተሰጠው ተስፋ
 ምሥጢረ ሥጋዌና ነገረ ድኅነት
 አምላክ እንዴት ሰው ሆነ ……………………………………………………………
 ምሥጢረ ተዋሕዶ
 አንድ አካል አንድ ባሕርይ
 የተዋሕዶ ምሳሌዎች
 ማጠቃለያ
3.3 ምሥጢረ ጥቅምት ……………………………………………………………………… 43
 መግቢያ
 የቃሉ ትርጉም
 ምሥጢረ ጥምቀት በነቢያት ትንቢትና ምሳሌ ……………………………………
 የጥምቀት ምሳሌዎች ………………………………………………………………
 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት …………………………………………………
 ጌታ ለምን ተጠመቀ?
 አንድነት ሦስትነትን ለመግለጥ
 ለትሕትና
 የዕዳ ደብዳቤ ለመደምሰስ
 ሕግንና ነቢያትን ለመፈጸም
 ጌታ ለምን በ፴ ዘመኑ ተጠመቀ?
 የብሉይ ኪዳንን ሕግና ሥርዐት ለመጠበቅ
 አዳም ያስወሰዳትን የእግዚአብሔር ልጅነት እንዳስመለለት ለማጠየቅ
 ክርስቶስ ለምን በዮርዳኖስ ተጠመቀ?
 ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ
 ምሳሌውን አማናዊ ለማድረግ
 ጌታችን ለምን በውኃ ተጠመቀ?
 መንፈስ ቅዱስ ለምን በርግብ አምሳል ወረደ?
 ጌታችን በማን ስም ተጠመቀ?
 የምሥጢረ ጥምቀት አመሠራረት ………………………………………………………
 የሰው ልጆች ጥምቀት …………………………………………………………………
 ሰዎች በማን ስም ሊጠመቁ ይገባቸዋል?
 የጥምቀት ዕድሜ
 የጥምቀት ጥቅም (አስፈላጊነት)
 የጥምቀት ዓይነት
 አንዲት ጥምቀት
 ማጠቃለያ
3.4 ምሥጢረ ቁርባን …………………………………………………………………………… 73
 መግቢያ
 የቃሉ ትርጉም
 ቅዱስ ቁርባን በብሉይ ኪዳን …………………………………………………………
 የቅዱስ ቁርባን ምሳሌዎች በብሉይ ኪዳን ……………………………………………
 የቅዱስ ቁርባን አመሠራረት በሐዲስ ኪዳን ………………………………………..
 ጌታ ሥጋ ወደሙን ለምን ተቀበለ?
 ምሥጢረ ቁርባን በመብልና በመጠጥ ለምን ሆነ?
 ለምን ስንዴና ወይን ተመረጡ?
 ከቅዱስ ቁርባን መቀበል የሚገባው ማነው?

ገጽ 4
 ከቅዱስ ቁርባን በፊትና በኋላ የሚደረግ ዝግጅትና ጥንቃቄ
 የቅዱስ ቁርባን አማናዊነት
 ለመታሰቢያ አድርጉት
 በምሥጢረ ቁርባን የሚገኝ ጸጋ
 ማጠቃለያ
3.5 ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ……………………………………………………………… 60
 መግቢያ
 የቃሉ ትርጓሜ
 ሞት ምንድን ነው?
 ትንሣኤ ሙታን በመጽሐፍ ቅዱስ …………………………………………………
 የጌታችን ትንሣኤና ዕርገት …………………………………………………………
 የሦስት ቀንና የሦስት ሌሊት አቆጣጠር
 የጌታችን ትንሣኤ አማናዊነት
 የጌታችን ዳግም ምጽአት
 የሰው ልጆች ትንሣኤ ………………………………………………………………
 የመለከት ድምፅ
 በትንሣኤ እንለወጣለን
 ከሞት በኋላ የሚገኘው ሕይወት
 የትንሣኤ ሙታን ምሳሌ
 በበግና በፍየል የተመሰሉት እነማን ናቸው?
 የቀኝና የግራ ምሳሌ
 ማጠቃለያ
ምዕራፍ አራት
ነገረ ማርያም …………………………………………………………………………………… 65
 የቅድስት ድንግል ማርያም የስሟ ትርጓሜ
 የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት
 የቅድስት ድንግል ማርያም ዘለዓለማዊ ድንግልና
 የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት
 የቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕናዋ ቅድስናዋ
 ማጠቃለያ
ምዕራፍ አምስት
ነገረ ቅዱሳን …………………………………………………………………………………… 69
 መግቢያ
 ክብረ ቅዱሳን
 የቅዱሳን ቃልኪዳንና አማላጅነት
 በምልጃ ወቅት የሚሳተፉ አካላት
 አማላጅነት ለምን አስፈለገ?
ዋቢ መጻሕፍት ………………………………………………………………………………… 73

ምዕራፍ አንድ
1.1 ሃይማኖት ማለት ምን ማለት ነው?

1. ማመን መታመን እምነት ጽኑ ተስፋ የአምልኮ ባሕል በልብ በረቂቅ ሐሳብ የሚሳል ማለት ነው፡፡ (ኪ.ወ.ክ ገጽ
369)
‹‹ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ
ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና›› ሮሜ. 10÷9
‹‹አንተም ድሀ ብትሆን በደስታው ጊዜ ከእርሱ ጋር ደስ ይልህ ዘንድ ከባልንጀራህ ጋር ታማኝነትን 1 ጠብቅ››
ሲራ 22÷23
ሃይማኖት ወይም እምነት 2 ማለት በባሕርዩ የማይታየውና የማይዳሰሰው አምላክ መኖሩን እርሱም የዓለም ፈጣሪ
ሠራኢ መጋቢ አዳኝ መሆኑን በኅሊና በልቡና ተገንዝቦ ያለመጠራጠር እውነት ነው ብሎ መቀበልን የሚያመለክት ቃል
ነው፡፡

ገጽ 4
ማመን
1. መቀበል መውደድ ማክበር አዎን እውነት ማለት ነው፡፡ (ደስታ ተክለ ወልድ መዝገበ ቃላት ገጽ 108)
‹‹በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ለአይሁድና ለግሪክ ሰዎች እየመሰከርሁ በጉባኤም በየቤታችሁም
አወራሁላችሁና አስተማርኋችሁ እንጂ ከሚጠቅማችሁ ነገር አንዳች እንኳ አላስቀረሁባችሁም›› ሐዋ.
20÷21
2. ‹‹ሃይማኖት በአንድ እግዚአብሔር ማመን በህላዌው በባሕርየ መለኮቱ በልዩ ሦስትነቱ በምልዓተ አካሉ ዓለምን
ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ በማስተዳደሩ ማመን ነው፡፡›› (ዕብ 11÷1፣ ዘፍ. 1÷1፣ ዘዳ 6÷1፣ ማቴ. 28÷19፣ መዝ
139÷7-10፣ ማቴ 5÷45፣ ዮሐ 5÷17፣ ዘጸ 3÷14፣ ራዕ 1÷8፣ ኢሳ 63÷9፣ ዮሐ 3÷16-17)
ማመን መቀበል 3 ነው
ማመን ማለት እግዚአብሔር በቅዱሳት መጻሕፍት እንዲሁም በሥጋዌው የገለጸውን የእውነት ትምህርት
ሳይቆነጻጽሉና ሳያጎድሉ መቀበል ነው፡፡ እግዚአብሔር አንድ መሆኑን በአንድነቱ ውስጥ ልዩና የማይመረመር ሦስትነት
ያለው መሆኑን ከሦስቱ አካላት አንዱ አካላዊ ቃል ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው መሆኑን መጠመቁን
ዞሮ ማስተማሩንና ያስተማረውን ቃልና ትእዛዝ ማመንን መከራ መቀበሉን በመጨረሻም በራሱ ፈቃድ ለእኛ ሲል
መሞቱን መቀበሩንና በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ በሥልጣኑ መነሣቱን እና በአርባኛው ቀን ወደ ቀደመ ክብሩ
ማረጉን መቀበል ነው፡፡
‹‹ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን
ሰጣቸው›› ዮሐ. 1÷12
መቀበል ለምን አስፈለገ?
1. እምነት ከስሜት በላይ ስለሆነ
ስሜት በሕዋሳት ልናረጋግጠው የምችለው ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ መንፈስ ነው፡፡ መንፈስን በስሜት ልንረዳ
ስለማንችል እንቀበላለን፡፡
‹‹እግዚአብሔር መንፈስ ነው የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል›› ዮሐ.
4÷23
2. ከአእምሮ (እውቀት) በላይ ስለሆነ

1. ሃይማኖት፡- (በ 1980 መጽሐፍ ቅዱስ)


2. እምነት ሃይማኖት ማመን መታመን አስተማመን እሙንነት ማለት ነው፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 226
3. አሚን ማመን መቀበል ተስፋ ማድረግ አለመጠራጠር መናዘዝ እውነት መናገር መመስከር ኪ.ወ.ክ ገጽ 226

ለአእምሮ ወሰን ሲኖረው ለእግዚአብሔር ግን ወሰን የለውም፡፡ ስለዚህ ሰው የማይችለውን ነገር ሊያደርግ ቢፈልግ
አይችልምና መቀበል ይኖርበታል፡፡

‹‹እንደ ባለአእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ ከመካከላችሁ ላለው
ለእያንዳንዱ እመክራለው›› ሮሜ. 12÷3

መታመን

መታመን እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋና የተናገረው ቃል ይሆናል ይደረጋል ብሎ በእምነት የተቀበሉትን እንዲሆን
እንዲደረግ ተግባራዊ ምላሽ መስጠት ነው፡፡ ይህም ሰው በጥምቀት ከሥላሴ ዳግም ልደት ይወለዳል ብለው ካመኑ በኋላ
መጠመቅ ነው፡፡

‹‹ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ በዚያም ቀን ሦስት ሺ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ›› ሐዋ. 2÷41

ሃይማኖት

 እግዚአብሔር ለሰው ልጆች በመገለጡ የተሰጠ አምላካዊ ስጦታ ነው፡፡

ገጽ 4
‹‹ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ
ሆነብኝ›› ይሁ. 1÷3
 ፈጣሪና ፍጡር የሚገናኙበት ረቂቅ መንገድ ነው፡፡
‹‹እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ›› ዮሐ. 14÷6
 ተስፋ የምናደርገውን ነገር የሚያስረግጥ የማናየውን ነገር የሚያስረዳ ነው፡፡
‹‹እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው›› ዕብ.11÷1
 ሃይማኖት መሠረት ነው፡፡ ምግባርና ትሩፋት ግን ጣራና ግርግዳ ናቸው፡፡ ዮሐ. አፈ .ድርሳን 9÷80
1.2 የሃይማኖት ጥቅም (አስፈላጊነት)

ሃይማኖት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ፈጥሮ የሕይወትን እስትንፋስ እፍ ሲልበት በመንፈሱ
አማካኝነት ሃይማኖትን ሰጥቶታል፡፡

‹‹እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ


አለበት፡፡ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ›› ዘፍ. 2÷7

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የክርስትና ሃይማኖት መሥራች ራስና ፈጻሚ ነው፡፡ እርሱ ክርስቶስ ተብሎ
በእርሱ ያመኑ ሁሉ ክርስቲያን ተባሉ፡፡

‹‹ደቀ መዛሙርቱም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ›› ሐዋ. 11÷26

ያለ ሃይማኖት እግዚአብሔርን ማየትና ማወቅ አይቻልም፡፡ እግዚአብሔርን በሃይማኖት እናየዋለን በጸሎት


እናነጋግረዋለን በዚህ ዓለም ሳለን ስለ እግዚአብሔር የሆነውን ሁሉ የምናስተውለው በሃይማኖት ብቻ ነው፡፡

ሃይማኖት

 ሰው ተፈጥሮውን ምንነቱን አቅሙን የሚያውቅበት የሚረዳበት ነው፡፡


‹‹እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ፡፡ ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ
የሚኖር እኔም በእርሱ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል›› ዮሐ. 15÷5
 ሰው የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን ሥልጣን የሚያገኝበት ነው፡፡ ዮሐ. 1÷12
 ሰው ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስ የዘላለም ሕይወት የሚያገኝበት ነው፡፡
‹‹ያመነ የተጠመቀም ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል›› ማር. 16÷16
1.3 ኦርቶዶክስ

ኦርቶዶክስ ቃሉ የኹለት የግሪክ ቃላት ጥምር ነው፡፡ ‹‹ኦርቶ›› ቀጥተኛ (ርትዕት) ማለት ሲሆን ‹‹ዶክስ›› ማለት ደግሞ
እምነት፣ አምልኮ ምስጋና ማለት ነው፡፡ ኦርቶዶክስ እንደ አንድ ስም ሆኖ ሲፈታ ቀጥተኛ ሃይማኖትና እውነተኛ አምልኮ
ማለት ነው፡፡ (ኪ.ወ.ክ ገጽ 243)
ኦርቶዶክስ የሚለው ስያሜ በቤተ ክርስቲያናችን የተጀመረው በ 325 ዓ.ም በኒቂያ በተደረገው ዓለም አቀፍ የቤተ
ክርስቲያን ጉባኤ ነው፡፡ 318 ቱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በኒቂያ ተሰብስበው አርዮስን ረትተው ሃይማኖትን አጽንተው
በጸሎተ ሃይማኖት ላይ ተስማምተው በአንድ ኀሳብ ሆነው ሃይማኖታቸውን ኦርቶዶክስ ብለዋታል፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ
ክርስቲያንም ሐዋርያዊት የሆነች ያልተበረዘች ከጌታችንና ከሐዋርያት ትምህርት ሌላ ያልተጨመረባት ያልተቀነሰላት
ርትዕት ቀጥተኛ ሃይማኖት ነች፡፡
ተዋሕዶ

ገጽ 4
ተዋሕዶ ማለት መዋሐድ አንድ መሆን ማለት ነው፡፡ (ኪ.ወ.ክ ገጽ 384)

ይህ ቃል ለምሥጢረ ሥላሴ እና ለምሥጢረ ሥጋዌ የሚያገለግል ነው፡፡ በብዛት የሚነገረው ለምሥጢረ ሥጋዌ ነው፡፡
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይህ ቃል በስፋት የተገለጸው ከጉባኤ ኤፌሶን (431) ዓ.ም በኋላ ነው፡፡

ክርስትና
የክርስትና ሃይማኖት የመገለጥ ሃይማኖት ነው፡፡ መገለጥ የሚባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት መታየቱን
ነው፡፡ ከሥጋዌ በፊት በቃልና በድርጊት የተፈጸመው መለኮታዊ መገለጥ ሁሉ በዚያን ጊዜ የነበሩትን ሰዎች በቀጥታ
የሚመለከት ታሪካዊ ይዘትና መልእክት ቢኖረውም ፍጻሜውም ለድኅነታችን ሲል ሊመጣ ላለው መሲህ ክርስቶስ
መገለጥ ነበር፡፡
‹‹ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፤ ሁሉን ወራሽ
ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ እርሱም የክብሩ
መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ ኹሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ፤ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ
በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ›› ዕብ. 1÷1-3

1.4 የሃይማኖት መመሪያዎች

ዶግማ ቀኖና እና ትውፊት ለቤተ ክርስቲያን እንደ አእማድ የሚታዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን
በእነዚህ ላይ ተመሥርታ የምትተዳደርና የምትመራ በመሆኑ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ገጽታ ለመረዳት
ዶግማ ቀኖናና ትውፊት የማዕዘን ድንጋዮች ናቸው፡፡
ዶግማ (መሠረተ እምነት)
ዶግማ የሚለው ቃል ዶኪዮ ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ዶኪዮ ማለት ማሰብ መላ መምታት መገመት የሚል
ፍቺ አለው፡፡ ይህም የማይሻር የማይለወጥ መርህን የያዘ እውነት ሆኖ የሚቀመጥ ነገር ማለት ነው፡፡ የእንግሊዝኛው
መዝገበ ቃላትም አስተምህሮ መርህ የፍልስፍና ትምህርት ተቀባይነት ያለው አስተሳሰብ በማለት እና በአንድ ቡድን
የተወሰነ ውሳኔ በቤተ ክርስቲያን የተደነገገ አዋጅ በማለት ይተረጉመዋል፡፡ ዶግማ ምእመናንን ወደ ድኅነት እና ወደ
እግዚአብሔር የሚያደርስ አዋጅ ነው፡፡ 4
ምሥጢረ ሥላሴ፣ ምሥጢረ ሥጋዌ፣ ምሥጢረ ጥምቀት፣ ምሥጢረ ቁርባን፣ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን፣ ነገረ
ማርያም እና ነገረ ቅዱሳን በዶግማነት የሚታዩ በመሆናቸው አይሻሻሉም አይለወጡም፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ዶግማ
መሠረቱ መለወጥ የሌለበት የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡
ቀኖና (መሠረተ ሥርዐት)
1. ቀኖና ቃሉ የግሪክ ሲሆን ሕግ ሥርዐት ደንብ ፍርድ ቅጣት ማለት ነው፡፡ (ኪ.ወ.ክ ገጽ 799 እና 800) ቅዱሳን
ሐዋርያት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሕግና ሥርዐት አድርገው ያኖሩት መመሪያን
የወሰኑት ቁጥርን ያመለክታል፡፡ ይኸውም የአጽዋማት ሥርዐት፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ቁጥርና ስያሜ ሥርዐተ
ጸሎት ወዘተ ናቸው፡፡ ይህ ሥርዐት እንደ ቤተ ክርስቲያን ጥቅም ታይቶ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሊሻሻል የሚችል
ውሳኔ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን የምናከናውነው ጫማ አውልቆ መቅደስ መግባት፣ ወደ ምሥራቅ ዞሮ መጸለይ፣
ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል በፊት ያሉ ዝግጅቶች፣ በቤተ ክርስቲያን በሥርዐተ ቅዳሴ የሚበሩ መብራቶች ሥርዐተ
ቀኖና ናቸው፡፡
ቀኖና በመጽሐፍ ቅዱስ
በዘመነ ሐዋርያት ከአይሁድ ወደ ክርስትና የመጡ ወገኖች ከአሕዛብ ወደ ክርስትና የገቡትን እንደ ሙሴ ሥርዐት
ካልተገረዛችሁ አትድኑም በማለት ቤተ ክርስቲያን በጥልና በክርክር እንድትሞላ አደረጉ፡፡ ሐዋርያትም ችግሩን ለመፍታት
በመጀመሪያ በኢየሩሳሌም ጉባኤ አደረጉ፡፡ በችግሩም ከመከሩ በኋላ ቀኖና ደነገጉ፡፡
‹‹ለጣዖት ከተሠዋ ከደምም ከታነቀም ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም
እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና›› ሐዋ. 15÷29

ገጽ 4
የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ምንጮች

መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ ዛሬ ላለው የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ልዩ ልዩ ምንጮች ቢኖሩም ተከታዮቹ አራቱ ግን በተለየ
ለቤተ ክርስቲያን ቀኖና ምንጭነት ይጠቀሳሉ፡፡
1. የሐዋርያት ሲኖዶስ
አብዛኞቹ ቀኖናት ቀኖናተ ሐዋርያት እየተባሉ በሚጠሩ ኹለት ቅዱሳት መጻሕፍት ተካተው ይገኛሉ፡፡ እነዚህም
ሲኖዶስና 5 ዲድስቅልያ ናቸው፡፡
2. ዓለም አቀፍ ጉባኤያት
በዓለም አቀፍ ጉባኤያት አበው ተከራክረው መናፍቃንን ከማውገዛቸው በተጨማሪ ሥርዐት (ቀኖናት) ሠርተዋል፡፡
እነዚህም ጉባኤያት ጉባኤ ኒቅያ፣ ጉባኤ ቁስጥንጥንያ እና ጉባኤ ኤፌሶን ናቸው፡፡

4. ቤተ ክርስቲያንና ዶግማ በግርማ አግዴ


5. ሲኖዶስ የተባለው መጽሐፍ ሥርዓተ ጽዮን፣ አብጥሊስ፣ ትእዛዝና ግጽው የተባሉ አራት ክፍሎች አሉት፡፡ በይዘቱም ስለቅዳሴ ማለትም
ወደ ምሥራቅ ዞሮ ስለመጸለይ በሰንበት፣ ረቡዕ፣ ዓርብና በበዓላት ወቅቶች ስለሚጸለዩ ጸሎቶች ይናገራል፡፡
2.1 ጉባኤ ኒቅያ (325 ዓ.ም)
በጉባኤ ኒቅያ ከተሠሩት ቀኖናት ውስጥ የትንሣኤ በዓል እሑድ ብቻ እንዲከበር መደንገጉ እና በአንድ ጳጳስ ሀገረ
ስብከት ክህነት መስጠት የሚችለው የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ በኒቅያ ጉባኤ 20 ቀኖናዎች ተደንግገዋል፡፡

2.2 ጉባኤ ቁስጥንጥንያ (381 ዓ.ም)


በጉባኤ ቁስጥንጥንያ ከተሠሩት ቀኖናት ውስጥ የጉባኤ የኒቅያ አባቶች ውሳኔ ማንም እንዳይቃወመው ብለው
የወሰኑበትና፤ ከክህደት ወደ ኦርቶዶክሳዊት እምነት የሚመለሱትን ቀጥተኛውን እምነት መቀበላቸውን ካረጋገጡ
እንቀበላቸዋለን የሚለው ይገኝበታል፡፡ በጉባኤ ቁስጥንጥንያ 7 ቀኖናዎች ተደንግገዋል፡፡

2.3 ጉባኤ ኤፌሶን (431 ዓ.ም)፡-


በጉባኤ ኤፌሶን የቆጵሮስ ቤተ ክርስቲያን ራሷን የቻለች እንድትሆን ተወስኗል፡፡ በዚህ ጉባኤ 8 ቀኖናዎች
ተደንግገዋል፡፡

3. ብሔራውያን ጉባኤያት፡-

ከዓለም አቀፍ ጉባኤያት በተጨማሪ በየአገሩ በየአካባቢው የተደረጉ ሲኖዶሶችም ቀኖናትን ወስነዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል
የዕንቆራ ጉባኤ፣ የቅርጣግና ጉባኤ፣ የጋንግራ ጉባኤ፣ የአንጾኪያ ጉባኤ፣ የሎዶቅያ ጉባኤ እና የሰርድቅያ ጉባኤ ተጠቃሽ
ናቸው፡፡

4. የአበው ውሳኔዎች
ከዓለም አቀፍም ሆነ ከብሔራውያን ጉባኤያት በተጨማሪ በአበው ልዩ ልዩ ቀኖናት ተወስነዋል፡፡ የሮሜው ሊቀጳጳስ
አቡሊደስ የደነገጋቸው ቀኖናት በምኅጻረ ቃል (በደስ)፣ ባስልዮስ የሠራቸው ቀኖናት (ባስ)፣ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የሠራቸው
ቀኖናት (ግር)፣ ዮሐንስ አፈወርቅ የሠራቸው ቀኖናት (ሐ) ተጠቃሾች ናቸው፡፡
የቀኖና ጠቀሜታ፡-

 መናፍቃንና ኑፋቄ ይለይበታል፣


 የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሥርዐት እንዲኖረው ያደርጋል፣
 የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ይጠብቃል፡፡ ሐዋ.
15÷1-29
 የቤተ ክርስቲያን የሆነውን የቤተ ክርስቲያን ካልሆነው መለያ በመሆን ያገለግላል፡፡

ትውፊት

ገጽ 4
ስጦታ፣ ልማድ፣ ትምርት፣ ወግ፣ ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ሥርዐት፣ ከጥንት ከአበው ሲያያዝ ሲወርድ ቃል በቃል ሲነገር የመጣ ማለት
ነው፡፡ ትውፊት 6 ሐዋርያት ከጌታችን የተቀበሉትንና ከመንፈስ ቅዱስ የተማሩትን ትምህርቶች፣ መሠረተ እምነት፣ ሥርዓተ ቤተ
ክርስቲያን እና መመሪያዎች ለአበው ያወረሱበት አበው ደግሞ በተራቸው ለተከታዮቻቸው ያስተላለፉበት መንገድ ነው፡፡
‹‹እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከኹሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ›› 1 ኛቆሮ 15÷3

6. ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ 397፡፡


ወፍይ (ወፈየ)፡- መስጠት፣ ማስያዝ፣ ማስጨበጥ፣ ዐደራ ማለት፣ ዐደራን ዕዳን መመለስ መክፈል፡፡ መጽሐፍ ግን በወፈየ ፈንታ አወፈየ ይላል አያሰኝም፡፡

ትውፊት በዘመነ ሐዋርያት


ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተማሩትን ትምህርተ ክርስትና ለተከታዮቻቸው ያስተማሩት
በትውፊት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ሐዋርያት ወንጌልን የሰበኩት በቃል፣ በተግባር በማሳየትና በሕይወታቸው ነው፡፡ የ ቤተ ክርስቲያን
ልጆች ከአበው ሐዋርያትና ከደቀ መዛሙርቶቻቸው ያዩትን የሰሙትንና የተማሩትን ትውፊት ተቀብለው እነርሱም በመኖር ለትውልድ
አወረሱት፡፡
ሐዋርያት በትምህርታቸው የአይሁድን የተቀደሰ ትውፊት ተጠቅመዋል፡፡ ለምሳሌ፡-
‹‹በነቢያት ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ ገብቶ ኖረ›› ማቴ. 2÷23
በ 46 ቱ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጌታ ‹‹ናዝራዊ ይባላል›› የሚል ትንቢት የለም፡፡ ይህ ትንቢት ግን በሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ
ተጠቅሷል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት ይህ ትንቢት በነቢያት ተነግሮ በምርኮ ጊዜ በጠፉት መጻሕፍት የነበረ ሲሆን መጻሕፍቱ
ቢጠፉም በቃል ለሐዋርያት ደርሷል፡፡
‹‹ሙሴም እጅግ እፈራለሁ እንቀጠቀጥማለሁ እስኪል ድረስ የሚታየው እጅግ የሚያስፈራ ነበር›› ዕብ. 12÷21
በኦሪት መጻሕፍት ውስጥ ሙሴ በደብረ ሲና ‹‹ፈራ ተንቀጠቀጠ›› የሚል አልተጻፈም፡፡ (ዘጸ. 19÷16-25) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
ግን ከአይሁድ ትውፊት ያገኘውን በመልእክቱ አስፍሮታል፡፡
‹‹ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደተቃወሙት እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም
የተጣሉ ሰዎች ሆነው እውነትን ይቃወማሉ፡፡›› 2 ኛጢሞ 3÷8
በኦሪት ዘጸአት ምዕ 7÷11 ላይ ሙሴን ለመቃወም የግብጽ ጠንቋዮች በፊቱ እንደተገዳደሩት ይነግረናል፡ ነገር ግን ‹‹የግብጽ
ጠንቋዮች›› ከማለት በቀር ሙሴ በኦሪት መጽሐፍ ስማቸውን አልገለጠውም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን በትውፊት ያገኘውን ተጠቅሞ
‹‹ኢያኔስና ኢያንበሬስ›› ብሎ ጠርቷቸዋል፡፡
‹‹ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ›› ሐዋ. 20÷35
ትውፊት በወንጌል ያልተጠቀሱ ነገር ግን በጌታ የተነገሩ ቃሎችን አስገኝቶልናል፡፡ ጌታ እንደዚህ ብሎ መናገሩ በወንጌል
አልተመዘገበም፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ በትውፊት ያገኘውን በመጽሐፍ አስፍሮልናል፡፡
‹‹የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲከራከር ጌታ ይገስፅህ አለው እንጂ
የስድብን ቃል ሊናገረው አልደፈረም›› ይሁ. 1÷9
የኦሪት ዘዳግም መጨረሻ ምዕራፍ ሙሴ በናባው ተራራ እንዳረፈና መቃብሩም እስከ ዛሬ እንደማይታወቅ ከመንገሩ በቀር ይህን
የቅዱስ ሚካኤልና የዲያብሎስ ክርክር አይገልጽልንም፡፡ ሐዋርያው ይሁዳ ይህን ታሪክ ያገኘው የሙሴን ታሪክ ከሚናገረው
ትውፊታዊው መጽሐፍ ነው፡፡ (The Assumption of moses)

ጥንታዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን በወንጌል ያልተመዘገቡ ከጌታ እና ከሐዋርያት በትውፊት የተላለፉ ትምህርቶችን፣ ምስክሮችን
እና ሥርዐቶችን ተቀብላለች፡፡
‹‹በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ›› 2 ኛተሰ 2÷15፣ (1 ኛቆሮ 11÷34፣ ቲቶ 1÷5፣ 2 ኛዮሐ
1÷12፣ 3 ኛዮሐ 13-14፣ ዮሐ 20÷30)
የክርስቲያናዊ ትውፊት ማረጋገጫዎች
ቤተ ክርስቲያን እንዲሁ ማንኛውንም ትውፊት ክርስቲያናዊ ነው በማለት አትቀበልም፡፡ አንድን ትውፊት እውነተኛ ክርስቲያናዊ
ትውፊት መሆኑን የምታረጋግጥባቸው መንገዶች አሉ፡፡ እነርሱም፡-
፩. ቃለ እግዚአብሔር
፪. ዲድስቅልያ
፫. የዓለም አቀፍ ጉባኤያት ውሳኔዎች
፬. ብሂላተ አበው ናቸው፡፡
1.5 ሀልዎተ እግዚአብሔር

ገጽ 4
ሀልዎት የግእዝ ቃል ሲሆን ሀለወ ከሚለው ግሥ የወጣ ነው፡፡ ትርጉሙም መኖር ወይም ህልውና ማለት ነው፡፡ ስለዚህ
ሀልዎተ እግዚአብሔር ስንል የእግዚአብሔር መኖር ማለት ነው፡፡ የክርስቲያን ህልውና መሠረተ ትምህርቱም መነሻው
የእግዚአብሔርን ህልውና ማወቅና በእርሱም ማመን ነው፡፡ የሃይማኖት መሠረት የሰው ልጅ ጥያቄዎች መልስ
የእግዚአብሔር መኖር ነው፡፡ እግዚአብሔር በባሕርዩ ህልው (ኗሪ) የሆነ ያለ የነበረ የሚኖር ለአኗኗሩ መጀመሪያና
መጨረሻ የሌለው ነው፡፡ ኹሉን የፈጠረ ለፍጥረታት ኹሉ የሕይወት መሠረት አስገኚ የሆነ ለእርሱ ግን ለአኗኗሩ
ምክንያት የሌለው ህልው አምላክ ነው፡፡ (ኪ.ወ.ክ ገጽ 370)

ሀልዎተ እግዚአብሔር የሚታወቅባቸው ነገሮች

ክርስቲያኖች አስገኚ የሌለውንና ዘመን የማይቆጠርለትን ከጥንት ከዘመን አስቀድሞ የነበረውን ፍጥረትን ኹሉ ፈጥሮ
የሚያስተዳድረውን ዘላለማዊ አምላክ እግዚአብሔርን ህልው (ኗሪ) መሆኑን እናምናለን፡፡ እግዚአብሔርም ሀልዎቱን
በተለያየ መልኩ ገልጦልናል፡፡ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሕገ ልቡና (የኅሊና ምስክርነት)


ሰው አዋቂ እንደመሆኑ መጠን በኅሊናው የተቀረጸለት ሕግ አለ፡፡ ሕገ ልቡና አንድ ሰው ሁልጊዜ ደጉን ተስማሚውን
ነገር እንዲሠራ መጥፎውን ክፉውን ግን እንዲተው የሚያነሣሣ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ፈቃድም የሚገልጥ ተቃራኒውን
ሁሉ እንዲሸሽ የሚያስታውስ ነው፡፡ ይህን ጥብቅ የሆነ የተፈጥሮ ሕግ በልቡናችን የሣለና የቀረጸ የዓለም ባለቤት የሆነ
ጥበበኛ ፈጣሪ እንዳለ ያስረዳል፡፡ በእግዚአብሔር መኖር እንድናምን ያደርገናል፡፡

“ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ
ለራሳቸው ሕግ ናቸውና፡፡ እነርሱም ኅሊናቸው ሲመሰክርላቸው ዐሳባቸውም ርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም
ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ፡፡” ሮሜ. 2÷14-15፣ ዮሐ 14÷1

ሥነ ፍጥረት
እግዚአብሔር በሚታየውና በማይታየው በሚዳሰስና በማይዳሰሰው ፍጥረቱ የዚህ ኹሉ ዓለም አስገኚና መጋቢ መሆኑ
ይታወቃል፡፡ ይህ ማለት የፈጠረው ፍጥረት ሀልዎቱን ይመሰክርለታል፡፡ የእግዚአብሔር የእጁና የቃሉ ፍጥረታት ኹሉ
የሰው ልጅ እርሱን ወደ ማመን ይስቡታል እምነቱንም ያረጋግጡለታል፡፡ ኹሉን የፈጠረ የኹሉ መሪ ያለ እርሱም
አንዳችም የሆነ ነገር የሌለ ልዑል እግዚአብሔር በፍጥረቱ ይታወቃል፡፡ (ዕብ. 3÷4፣ዮሐ 14÷17፣ዕብ. 3÷4፣ኢዮ 12÷7-
9፣መዝ 18÷1፣ሮሜ. 1÷20-21)
“እያንዳንዱ ቤት በአንድ ሰው ተዘጋጅቷልና ኹሉን ያዘጋጀ ግን እግዚአብሔር ነው፡፡” ዕብ. 3÷4

ቅዱስ አትናቴዎስ የፍጥረት ተስማምተውና ተቀናጅተው መኖራቸው እንዲሁም ወቅቶች መፈራረቃቸው ኅብረ ብዙ
መልክ መያዛቸውን በነፍስ ሥራ እና በመርከብ ጉዞ መስሎ በማስተማር የእግዚአብሔርን መኖር አስረድቷል፡፡ ፡
“ነፍስ በሰው ውስጥ እንደማትታይ ግን በሰውነት እንቅስቃሴ እንደምትታወቅ እግዚአብሔርም በሥጋዊ
ዐይን አይታይም፤ ግን በፈቃዱና በሥራው ይገለጣል፣ ይታወቃልም፡፡ በባሕር ተንሳፋ ወደፊት የምትጓዝ
መርከብን የሚመለከት ሰው በውስጧ ሊቀ ሐመር እንዳለ ማወቅ አለበት፡፡” (የዮሐንስ አፈወርቅ ትርጓሜ
ሮሜ. 1÷19-20)
የሰው ልጆች የተፈጥሮ ዝንባሌ
በተለያየ የዓለም ክፍሎች የሚገኝ ሰው ኹሉ እርዳታውና ጥበቃው የሚፈለግ፣ ፍጹምነትን የተሞላ፣ ደግ ኹሉን ቻይ
ሰውን የሚወድ ሊወደድና ሊሰገድለት የሚገባ አንድ አምላክ መኖሩን ያለ መሆኑን በማመን ይስማማሉ፡፡ የሰው ልጅ
በእግዚአብሔር መኖር የሚያምነው በጽሑፍ የቀረበለትን የሃይማኖት መጽሐፍ በማንበብ ወይም የሃይማኖት አስተማሪ
ስለሚሰብክለት ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ስሜቱ ፍላጎቱ ወይም ዝንባሌው ስለሚገፋፋው ጭምር ነው፡፡
“የአቴና ሰዎች ሆይ እናንተ በኹሉ ነገር አማልክትን እጅግ እንደምትፈሩ እመለከታለሁ፤ የምታመልኩትን
እየተመለከትኹ ሳልፍ ለማይታወቅ አምላክ የሚል ጽሕፈት ያለበትን መሠዊያ ደግሞ አግኝቼአለሁና”
ሐዋ. 17÷23-24
አምላካዊ መግቦት

ገጽ 4
ሥነ ፍጥረት መፈጠሩ ብቻውን የመኖር እድል ይሰጠዋል እንጂ በተሰጠው ዘመን በሕይወት መዝለቅ እንዲችል
አያበቃውም፡፡ ሥነ ፍጥረትን በሙሉ ከመፍጠሩ ባሻገር ለእያንዳንዱ ፍጥረት በሚስማማው መጠን የሚያስፈልገውን
እያዘጋጀ ያ ፍጥረት ሲፈጠር የተሰጠውን ሕይወት እንዲዘልቅና እንዲቀጥል የሚያደርገው መጋቢ ፍጥረታት
እግዚአብሔር ነው፡፡
“እርሱ በክፉዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና” ማቴ
5÷45 (ዮሐ. 5÷17፣ መዝ. 102(103)÷1-28፣ መዝ. 146(147)÷8-9)
የቃለ እግዚአብሔርና የታሪክ ምስክርነት
በመጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ልዩ ትንቢቶች ተነግረው እነዚያም የተነገሩት ትንቢቶች በጊዜአቸው የተፈጸሙ መሆናቸው
በታሪክም ጭምር የተረጋገጠ ነው፡፡ ወደፊት የሚደርሰውን ኹኔታ አስቀድመው የሚናገሩ በልዩ ልዩ መንገድ ለነቢያት
የገለጸላቸው እግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔርም የነበረ ያለና የሚኖር ነው፡፡
“ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል” መዝ. 14÷1
1.6 አስማተ አምላክ
ስም
በቁሙ ከባሕርይ ግብር የሚወጣ ቦታነትና አካልነት ህላዌና ሕይወት ያለው ማናቸውም ኹሉ በየክፍሉና በያካሉ በየራስ
ቅሉ በያይነቱ በየመልኩና በየነገዱ በየዘሩና በያባቱ በየዓይነቱ በየዘመዱ ተለይቶ የሚጠራበት የሚታወቅበት ማለት ነው፡፡
(ኪ.ወ.ክ ገጽ 869)
የአምላክን መኖር ላመነ ሰው የአምላኩን ስም ማወቅ ይጠበቅበታል፡፡ ሰው የአምላኩን ስም የሚያውቀው ጠርቶ
እንዲገናኝበት ብቻ ሳይሆን ስሙ ባሕርዩን የሚገልጥ ክቡር ነውና የሚገባውን ክብር እንዲሰጥ ነው፡፡ ቅድስት ሥላሴ
በባሕርይ የሚጠሩበት ስም አለ፣ በአካል የሚጠሩበት ስም አለ፣ በአካል ግብር የሚጠሩበት ስም አለ፡፡ በባሕርይ
የሚጠሩበትን ስም ለአካልና ለአካላት ግብር፣ በአካል የሚጠሩበትን ስም ለባሕርይና ለአካላት ግብር፣ በአካላት ግብር
የሚጠሩበትን ስም ለባሕርይና ለአካል ሰጥተው ሲናገሩ የአንድነታቸው የሦስትነታቸው ምሥጢር ይዛባል፡፡ ስለዚህ
ጠንቅቆ አስተውሎ መመልከት ይገባል፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የአካል ስም ነው፡፡ ወላዲ አሥራጺ፣ ተወላዲ፣ ሠራጺ
የአካላት ግብር ስም ነው፡፡እግዚአብሔር የባሕርይ ግብር ስም ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ስሞች ብንመለከት ባሕርይውንና
ከባሕርይው ተነሥቶ የሚሠራውን ግብር የሚያመለክቱ ናቸው፡፡
‹‹እኔ እግዚአብሔር ባልኩ ጊዜ ስለ አብ ስለ ወልድ ስለ መንፈስ ቅዱስ መናገሬ ነው›› ሃይ. አበ. ዘዲዮናስዮስ
ምዕ. 101 ክ 1 ቁ 1
ለምሳሌ
1. እግዚአብሔር በግእዝ ሁሉን የፈጠረ፣ ሁሉን ማድረግ የሚችል፣ በሁሉ ላይ ሥልጣን ያለው ማለት ነው፡፡
ሃይማኖተ አበው መግቢያ
2. አልሻዳይ፡- በዕብራይስጥ ሁሉን ቻይ ማለት ነው፡፡ ዘጸ. 6÷3
3. ያህዌ፡- በዕብራይስጥ ያለና የሚኖር ማለት ነው፡፡ ዘጸ. 3÷14
4. አዶናይ፡- በዕብራይስጥ ጌታ ማለት ነው፡፡
5. ኤል (ኤሎሄም) በዕብራይጥ አምላክ ማለት ነው፡፡
1.7 የእግዚአብሔር የባሕርይ መገለጫዎች
ባሕርይ ያልተፈጠረ የማይመረመር ኅቡዕ ረቂቅ ቅድስት ሥላሴን አንድ የሚያደርግ ማለት ነው፡፡ (ደስታ ተክለ ወልድ
ገጽ 162) እግዚአብሔር በቸርነቱ ራሱን በገለጠ ጊዜ ሀልዎቱን ብቻ በማወቅ ሳይወስነን ባሕርዩን ደግሞ በመጠኑ
እንድናውቅ ፈቅዶልናል፡፡ የማይታየውን ባሕርዩን በባሕርዩ የሰወረውን የእግዚአብሔር ማንነት የባሕርዩን ምንነት
በቀላሉ የምንማረው አይደለም፡፡ ምክንያቱም የነገረ ሃይማኖት ምሥጢር ከአእምሮ በላይ ረቂቁን ምሥጢር
ለማስተዋልና ለመገንዘብ ስለሚያዳግተን ነው፡፡ እግዚአብሔር በቸርነቱ ሰውን ለማዳን ራሱን ለሰው ልጆች ስለገለጸ ስለ
ባሕርዩ አንዳንድ ነገሮችን በመጠኑ ለማወቅ ረድቶናል፡፡
‹‹መሰወርያውን ጨለማ አደረገ›› መዝ. 17÷11
የእግዚአብሔርን የባሕርይ መገለጫ ማወቅ ጥቅም

ገጽ 4
የእግዚአብሔርን ባሕርይ ማወቅ ለክርስቲያን ሁሉ ይጠቅማል፡፡ ባሕርዩን ካወቅን ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ
እንችላለን፡፡ ለማክበርና ለመፍራት፣ ለመውደድና ተስፋ ለማድረግ፣ እርሱንም በመንፈስና በእውነት ለማምለክ የበቃን
እንሆናለን፡፡
እግዚአብሔር በባሕርይው የማይመረመር ቢሆንም ባሕርይው የሚገለጥባቸው መገለጫዎች ብዙ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ
እኛ ስለባሕርይው የምንናገረው ከተገለጠልን ውስጥ ጥቂቱን ነው፡፡ ይህም የሚሆነው የእኛ ኅሊና መሸከም የማይችለው
ባሕርይ ስላለው ብቻ ሳይሆን ሰው መረዳት የቻለውን ያህል እንኳ የሚገልጽበት ቋንቋ ስለሌለው ጭምር ነው፡፡

1. እግዚአብሔር መንፈስ ነው
እግዚአብሔር በሁሉም ጊዜና በሁሉም ቦታ ይገኛል፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ነው ሲባል የሚታይ የሚዳሰስ ግዙፍ አካል
የለውም ለማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር መንፈሳዊ የሆነ ረቂቅ አካል አለው፡፡ መንፈስ ማለት ረቂቅ የማይታይ አጥንትና
ሥጋ ጅማትም የሌለው የማይዳሰስ አካል ማለት ነው፡፡
‹‹እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል›› ዮሐ.
4÷24

2. እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው
መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው በዘመናት ሁሉ የሚኖር የማያረጅ የማይሞት የማይለወጥ ሁሉን አሳልፎ የሚኖር
ማለት ነው፡፡ ጊዜ የማይወስነው ጊዜን የሚወስን ጊዜንም የፈጠረ መሆኑን መግለጽ ነው፡፡ ዘጸ. 3÷14፣ (ራዕ. 1÷8፣ መዝ.
101÷25-27፣ ራዕ. 4÷8)

‹‹ያለና የሚኖር እኔ ነኝ›› ዘጸ. 3÷14

3. እግዚአብሔር ሁሉን ዐዋቂ ነው


እግዚአብሔር ዓለምንና በውስጧ የሚገኙትን ሁሉ በጥበቡ ፈጠረ፡፡ ሁሉንም የፈጠረ ስለሆነ የሁሉንም ህላዌና አሠራር
ያውቃል፡፡ ከእርሱ የዕውቀት ዐይኖች የሚሰወር የለም፡፡

‹‹እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዐይኖች ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ በእርሱ ፊት የተሰወረ
ፍጥረት የለም፡፡ ዕብ. 4÷13

4. እግዚአብሔር ምሉዕ በኩለሄ (በሁሉም ቦታ የሚገኝ) ነው


እግዚአብሔር መንፈስ ነው:: ስለዚህ በሁሉም ቦታ ይገኛል፡፡ በዓለሙ ሙሉ በአንድ ጊዜ መገኘት የሚችል
እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ በዓለም ምሉዕ ነው ሲባል ደግሞ በሚታየውም በማይታየውም ፍጥረት በጠቅላላው በዓለም
ሁሉ ምሉዕ ነው፡፡ እርሱ የሌለበት የማይደርስበት ቦታ ከቶ የለም፡፡
‹‹ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለው? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ ወደ ሲዖልም
ብወርድ በዚያ አለህ እንደ ንሥር የንጋትን ክንፍ ብወስድ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር በዚያ እጅህ ትመራኛለች
ቀኝህም ትይዘኛለች›› መዝ. 139÷7-10፣ (ኤር. 23÷23-)
5. እግዚአብሔር ቅዱስ ነው
ቅድስና ማለት ከኃጢአት ከርኩሰት ስሜትና ከክፉ ሐሳብ ከአስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የራቀና የተለየ ፍጹም ንጹሕ የሆነ
እንከን ጉድለት ድክመት ነቅዕ የሌለበት ማለት ነው፡፡
‹‹እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ ቅዱሳንም ሁኑ እኔ ቅዱስ ነኝና›› ዘሌ. 11÷44

6. እግዚአብሔር እውነተኛ ፈራጅ ነው


ፍትሕ ርትዕ የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው፡፡ እግዚአብሔር ፍጹም ጻድቅና እውነተኛ ፈራጅ ነው፡፡ ፍጹም
ጻድቅና ሁሉን አዋቂ በመሆኑ የሚሰጠው ውሳኔ ሁሉ ፍትሕ ርትዕ የሞላበት ነው፡፡
‹‹ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ ፍርዶችህ እውነትና ጽድቅ ናቸው፡፡ ራዕ 16÷7

7. እግዚአብሔር ፍቅር ነው

ገጽ 4
የእግዚአብሔር ባሕርይ በፍጹም ፍቅር ይገለጻል፡፡ ፍጹም ፍቅር ስንል እግዚአብሔር የሰውን ዘር ሁሉ የወደደበት
መለኮታዊ ፍቅሩን ርኅራኄውን ኅዘኔታውን ቸርነቱንና በጎ ሥራውን ሁሉ የሚያመለክት ነው፡፡
‹‹ፍቅርም እንደዚህ ነው እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደወደደን ስለኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን
እንደላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደወደድነው አይደለም›› 1 ኛዮሐ 4÷8-10

8. እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው
እግዚአብሔር በባሕርይው የሚሳነው የሌለ የወደደውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ የሚችል አምላክ ነው፡፡ ዓለምን ካለመኖር
ወደ መኖር ያመጣ እርሱ ለመለኮታዊ ኃይሉ ፈጽሞ ወሰንና ገደብ የለውም፡፡ በዚህ ዓለም የሚኖሩትን ፍጥረታት
ሰዎችንም እንስሳትንም ዕፅዋትንም ሁሉን በሚችል ኃይሉ እንደ ባሕርያቸው ሕይወት የሰጣቸው ስለሆነ ሁሉንም በልዩ
ልዩ መንገድ ይመግባቸዋል፡፡
‹‹በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን›› ዘፍ. 18÷14፣ (ዘጸ. 14÷21-31፣ ዘፍ. 17÷1)

9. እግዚአብሔር መሐሪ ነው
እግዚአብሔር በባሕርይው መሐሪና አዛኝ ይቅር ባይም ነው፡፡ ቁጣው እንደ ሰው አይደለም ይታገሣል ከተመለሱለትም
ቂም የለውም ይቅር ይላል፡፡
‹‹አምላክህ እግዚአብሔር መሐሪ አምላክ ነው፤ አይተውህም አያጠፋህምም ለአባቶችህም የማለላቸውን
ቃልኪዳኑን አይረሳም›› ዘፍ. 4÷31

10. እግዚአብሔር አይለወጥም


አለመለወጥ አንዱ የእግዚአብሔር ባሕርይ መገለጫ ነው፡፡ መለወጥ ማሻሻልና ማረም የሰዎችን ጠባይና ሥራ
የሚገልጽ እንጂ በእግዚአብሔር ባሕርይ ውስጥ የሚገኝ አይደለም፡፡

‹‹እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም›› ሚል. 3÷6


ምዕራፍ ሁለት
ሥነ ፍጥረት
መግቢያ
የሥነ-ፍጥረት ታሪክ አበው ቅዱሳን፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ከአሥራው መጻሕፍት አውጣጥተው ጽፈው
ያቆዩልን ነው፡፡ በውስጡ ከዕለተ እሑድ እስከ ቀዳሚት ሰንበት ድረስ ልዑል እግዚአብሔር በከሃሊነቱ የፈጠራቸው የሃያ
ኹለቱ ሥነ-ፍጥረት ታሪክ ተጽፏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የፍጥረቱ ምሳሌነት ምን እንደሆነ ተገልጧል፡፡ ልዑል
እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን እንዲሁም በእነርሱ ውስጥ የሚገኙትን ፍጥረታት ሁሉ ካለመኖር ወደ መኖር የፈጠረበት
የአፈጣጠር ታሪክ በዝርዝር የሚያስረዳው ክፍል ሥነ-ፍጥረት ይባላል፡፡ በክርስትና አስተምህሮ ሥነ-ፍጥረት በራሳቸው
ያልተገኙ፣ በፈጣሪያቸው በእግዚአብሔር የተፈጠሩ በላይ በሰማይ በታች በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ረቂቅና
ግዙፋን ናቸው፡፡
ሥነ ፍጥረት ማለት ምን ማለት ነው?
ሥነ-ፍጥረት የሚለው ቃል ሠነየ 7፣ ተሰነዐወ 8 እና ፍጥረት 9 ከሚሉ ቃላት የተገኘ ነው፡፡ ትርጓሜውም፡-
1. የፍጥረት መበጀት፣ የበጀ፣ ያማረ፣ የተዋበ ፍጥረት ማለት ነው፡፡
‹‹እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ›› ዘፍ. 1÷31
2. የፍጥረት መስማማት፣ የተስማማ ፍጥረት ማለት ነው፡፡
ፍጥረታት የተፈጠሩባቸው አራቱ ባሕርያት (እሳት፣ ውኃ፣ መሬትና ነፋስ) በባሕርያቸው የማይስማሙ ሲሆኑ
በእግዚአብሔር ጥበብና ኃይል ተስማምተው ስለሚኖሩ ነው፡፡
‹‹ወአስተሰነዐዎሙ በበይናቲሆሙ እንዘ ዘዘዚአሁ ግዕዘ ጠባይዒሆሙ፤ የባሕርይ ጠባያቸው እየራሱ (የተለያዩ) ሲሆን
እርስ በርሳቸው አስማማቸው፡፡›› (ድርሳን ዘዮሐንስ አፈወርቅ)
እግዚአብሔር አምላክ ሁሉን ያስገኘ ለኹሉ ነገር መገኛ ጥንትና መሠረት ነው፡፡ ለእርሱ ግን ለህላዌው ምክንያት
የለውም፡፡ እግዚአብሔር ይህን የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም በውስጣቸው ያሉትን ሁሉ ከቸርነቱ ብዛት የተነሣ
ፈጠረ፡፡

ገጽ 4
‹‹ሁሉን በሚገዛ ሰማይን ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ
እናምናለን፡፡›› (ሃይ. አበ. ዘሠለስቱ ምዕት ምዕ 17 ክ 1 ቁ 3)
2.1 የሥነ-ፍጥረት ዓላማ
ፈጣሬ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር ይህን የሚታየውን ዓለምና የማይታየውን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ
የፈጠረበት እንዲገለጡም ያደረገበት ምክንያትና ዓላማ አለው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረታትን ያስገኘበትን
ምክንያት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያስተምራሉ፡፡
የእግዚአብሔር ህልውና መታወቂያ እንዲሆኑ
እግዚአብሔር ከሥነ ፍጥረቱ አስቀድሞ የነበረ ነውና መኖሩ ለፍጥረቱ ይገለጽ ዘንድ ፍጥረቱን ፈጠረ፡፡ እግዚአብሔር
ህልውናው ይታወቅ ዘንድ ፍጥረትን ፈጠረ ሲባል ፍጥረታቱ መኖሩን፣ አምላክነቱን፣ ፈጣሪነቱን፣ ሁሉን ቻይነቱን ገለጡ
ማለት ነው፡፡
‹‹ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደተዘጋጁ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት
እናስተውላለን›› ዕብ. 11÷3፣ (ሮሜ. 1÷20፣ ሐዋ. 14÷17)

7. ሠነየ፡- ማማር መዋብ ሐዲስ መልክ ማውጣት ጥሩ ውብ ደመ ግቡ መኾን በመልክና በጌጥ ደስ ማሰኘት ዳን. 1÷15፣ መሳ. 15÷2፣
ኪ.ወ.ክ ገጽ 671
8. ተሰነዐወ፡- ተስማማ፣ ተጋጠመ፣ ተባበረ አንድ ልብ አንድ ሐሳብ ኾነ፡፡ ኪ.ወ.ከ ገጽ 873
9. ፍጥረት፡- በቁሙ ከእሑድ እስከ ዐርብ የተሠራ ሥራ፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 721

ስሙን ለመቀደስ ክብሩን ለመውረስ


የፈጠራቸውን ፈጣሪ አውቀው ስሙን የሚቀድሱ የሚያመሰግኑ በኋላም ደግሞ ዘለዓማዊ የማትጠፋ ርስት
መንግሥተ ሰማይን እንዲወርሱ ለዚህ ታላቅ ክብር የተፈጠሩ ከኹሉም ፍጥረት በተለየ ቅዱሳን መላእክትና የሰው
ልጆች ናቸው፡፡
‹‹ጌታችን አምላካችን ሆይ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማል ክብር ውዳሴ
ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ›› ራዕ. 4÷9-11
ለምግበ ሥጋ ለምግበ ነፍስ
ፍጥረታት የተፈጠሩበት ሌላኛው ዓላማ ለሰው ልጆች መብል መጠጥ ይሆኑ ዘንድ ነው፡፡ ነገር ግን መብልና
መጠጥነታቸው ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን በዕለተ ኀሙስና ዓርብ ለተፈጠሩ አራዊት፣ እንስሳትና አዕዋፋት ጭምር
ነው፡፡ ፍጥረታት ለምግበ ሥጋ ይሆኑ ዘንድ ተፈጥረዋል ስንል የዕለተ ማክሰኞ ፍጥረት የሆኑ አዝርዕቱን አትክልቱን
ዕፅዋቱን እንዲሁም የኀሙስና የዓርብ ፍጥረታት የሆኑ የእንስሳት ውጤቶችን ነው፡፡
‹‹ልጆቹ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ የሚበሉትም አጥተው ሲቅበዘበዙ ለቁራ መብልን የሚሰጠው
ማነው?›› ኢዮ. 38÷41
ፍጥረታት ለምግበ ሥጋ ብቻ ሳይሆን ለምግበ ነፍስም ተፈጥረዋል፡፡ ነፍስ ረቂቅ ናትና ምግቧም ረቂቅ ነገር ነው፡፡
ከፍጥረታት መካከል ምግበ ነፍስ የሚሆኑ ከስንዴው ቅዱስ ሥጋው ይዘጋጅበታል፤ ከወይኑ ደግሞ ክቡር ደሙ
ይዘጋጅበታል፡፡
‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ›› ዮሐ. 6÷56፣ (ማቴ. 26÷26)
ለትምህርት ለተግሣጽ
እግዚአብሔር ሥነ-ፍጥረትን ለትምህርት ይሆኑ ዘንድ ፈጥሯል፡፡ በእነርሱም አድሮ መገሰጽ የሚገባውን ሰው
ይገስጻል፡፡ ይህንንም የሚያደርገው ቃል በቃል ሥነ- ፍጥረታት አንደበት አውጥተው የሰውን ልጅ ጉድለት እንዲናገሩ
እንደሚያደርገው ሁሉ ፍጥረትን በመመልከት በምሳሌ እየመሰለ ያስተምራል፡፡
‹‹አሁን ግን እንስሶችን ጠይቅ ያስተምሩህማል የሰማይንም ወፎች ጠይቅ ይነግሩህማል›› ኢዮ. 12÷6 (ኤፌ.
2÷10)
ለአንክሮ ለተዘክሮ ለተደምሞ
ከፍጥረታት በፊት የነበረ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ አምላክ ነውና ፍጥረቱን ዐይተን ከእኛ
ከደካማው ዕውቀት በላይ በሆነው አምላክ መገኘታቸውን ዘወትር በማሰብ፣ አፈጣጠራቸውንም በማድነቅ እንዲህ

ገጽ 4
ውብ አድርጎ የፈጠራቸውን አምላክ ዕፁብ ድንቅ ብለን እናመሰግነው ዘንድ ፍጥረታት ተፈጥረዋል፡፡ (መዝ. 18÷1፣
ኢዮ. 36÷33)
‹‹እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው፡፡›› መዝ. 65÷3
2.2 የሥነ-ፍጥረት መገኛ
እግዚአብሔር የሚታየውንና የማይታየውን፣ የሚዳሰሰውንና የማይዳሰሰውን ዓለም ፍጥረት ያስገኘው በኹለት
መንገድ ነው፡፡
1. እምኀበ አልቦ ኀበቦ 10
2. ግብር እም ግብር ናቸው፡፡ 11

10. እምኀበ አልቦ ኀበቦ ካለመኖር ወደ መኖር ደስታ ተክለ ወልድ ገጽ 106
11. ግብር እምግብር ከተፈጠረው የተፈጠረ ደስታ ተክለ ወልድ ገጽ ….
እምኀበ አልቦ ኀበቦ ማለት ካለመኖር ወደ መኖር ወይም ከኢምንት ወደ ምንት ማለት ሲሆን ግብር እምግብር
ማለት ደግሞ ከምንት ወደ ምንት ወይም አስቀድሞ ከተገኘ ነገር የተገኘ ማለት ነው፡፡
እምኀበ አልቦ ኀበቦ፤ ካለመኖር ወደ መኖር
እግዚአብሔር በባሕርይው ባለች ሥልጣኑ ብርሃንን፣ መሬትን፣ እሳትን፣ ውኃን፣ ነፋስን፣ መላእክትና ጨለማን ፈጠረ፡፡
እነዚህ ፍጥረታት በእግዚአብሔር ሥልጣን የተገኙ ናቸው እንጂ ሌላ መገኛ የሆናቸው ምክንያት የላቸውም፡፡
‹‹እርሱም፡- ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ እንደተጻፈ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ ‹‹የሌለውንም እንዳለ
አድርጎ በሚጠራ›› ባመነበት አምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው፡፡›› ሮሜ.4÷17
ግብር እምግብር‹ ከተፈጠረው የተፈጠረ
ኹለተኛው መንገድ ግብር እምግብር ነው፡፡ ይህም ማለት ከተፈጠሩት መልሶ ሌላ ፍጡር ማስገኘት ማለት ነው፡፡
እነዚህ ፍጥረታት አራቱ ባሕርያተ ሥጋ ከተባሉት ከመሬት፣ ከውኃ፣ ከነፋስና ከእሳት የተገኙ ናቸው፡፡ (ዘፍ. 2÷7፣11-
12፣14-21)
2.3 እግዚአብሔር ፍጥረታትን እንዴት ፈጠረ?
እግዚአብሔር እምኀበ አልቦ ያስገኛቸውንም ሆነ ከተፈጠሩት ላይ የፈጠራቸውን ፍጥረታት ያስገኘበት መንገድ
አለው፡፡ ይኸውም በሦስት ወገን ነው፡፡
በሐልዮ ሐልዮ ማለት ማሰብ፣ ሐሳብ ማለት ነው፡፡ ይኸውም ሊሠራው ሊፈጥረው የወደደውን ፍጥረት በአንደበቱ ቃል
ሳይናገር በኅሊናው ብቻ አስቦ በመፍቀድ በሥልጣኑ ያስገኛቸው ናቸው፡፡ እግዚአብሔር በሐልዮ ያስገኛቸው ፍጥረታት
ሰባት ናቸው፡፡ እነርሱም
 አራቱ ባሕርያተ ሥጋ
 ጨለማ
 ሰባቱ ሰማያት
 መላእክት ናቸው፡፡
በነቢብ እግዚአብሔር በመናገር፣ ቃል በማሰማት ወይም በአንደበት ቃል በማዘዝ ብቻ የፈጠራቸው ፍጥረታት አሉ፡፡
እነርሱም በቁጥር አሥራ አራት (ኪ.ወ.ክ ገጽ 618) (ዘፍ. 1÷3፣ 8፣ 11፣ 13-15፣ 20-22፣ 24) ናቸው፡፡
 ብርሃን  ፀሐይ
 ጠፈር  ጨረቃ
 አዝርዕት  ከዋክብት
 አትክልት  ውኀ አደር የሆኑ እንስሳት፣ አራዊት፣ አዕዋፍ
 ዕፅዋት  የብስ አደር የሆኑ እንስሳት፣ አራዊት፣ አዕዋፍ

በገቢር፡- እግዚአብሔር በሐልዮና በነቢብ ፍጥረታትን እንዳስገኘው በገቢርም ያስገኘው ፍጥረት አለ፡፡ ይኸውም ሰው
ነው፡፡ ልዑል እግዚአብሔር በሐልዮ፣ በነቢብና በገቢር ሥነ-ፍጥረትን በማስገኘቱ በኹሉም መንገድ የወደደውን ነገር
ማድረግ የሚቻለው መሆኑን እንረዳለን፡፡
2.4 ሃያ ኹለቱ ሥነ-ፍጥረት

ገጽ 4
እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ፍጥረት መቁጠርና ወስኖ መናገር አይቻልም፡፡ ይሁን እንጂ የሥነ-ፍጥረቱን ነገር
የሚናገረው አክሲማሮስ የተባለው መጽሐፍ እንደሚያስረዳንና 12 አባቶቻችንም እንዳስተማሩን ብዙውን አንድ እያሉ
ቢቆጥሯቸው 22 ናቸው፡፡

12. አክሲማሮስ ስድስት ቀን ማለት ነው፡፡ የመጽሐፍ ስም የ 6 ቱን ቀን ሥነ-ፍጥረት አምልቶ አስፍቶ የሚናገር ሃያ ኹለት ብሎ የሚቆጥር
የኤጲፋንዮስ መጽሐፍ፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 211

2.5 የስድስቱ ቀናት ፍጥረታት


እግዚአብሔር የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም ያስገኘው በስድስት ቀናት ውስጥ ነው፡፡ ይህም በአንድ ቀን
ለመፍጠር አቅም አጥቶ አይደለም፡፡ እርሱ ባወቀ ኹሉን በሥርዐትና በአግባቡ ለማድረግ ብሎ እንጂ፤ ደግሞም ፈቃዱና
ጊዜውም ስለሆነ ፍጥረታትን በስድስት ቀናት ውስጥ አከናወነ፡፡
2.5.1 የዕለተ እሑድ ፍጥረታት
13
እሑድ የሚለው የዕለት ስም አሐደ ካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አንደኛ፣ መጀመሪያ ማለት ነው፡፡
የዕለታት አንደኛ መጀመሪያ እሑድ ናት፡፡ እግዚአብሔር ክብሩ እንዲገለጽና እንዲመሰገን ፍጥረትን መፍጠር የጀመረበት
ዕለት ዕለተ እሑድ ትባላለች፡፡
እግዚአብሔርም በመጀመሪያ የፍጥረት ቀን እሑድ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ሰባት አንድም ስምንት ፍጥረታትን
ፈጠረ፡፡ መጽሐፈ ኩፋሌ በዚህ ቀን ሰባት ፍጥረታት ተፈጥረዋል ይላል፡፡ መጽሐፈ ኩፋሌ ሰባት ያለው ብርሃንን የተዳፈነን
እንደመግለጽ ነው ብሎ ጠቅሎ በመቁጠር ሲሆን ስምንት የሚሉ ሊቃውንት ብርሃንንም ጨምረው አንድ ብለው
ስለሚቆጥሩ ነው፡፡ የዕለተ እሑድ ፍጥረታት የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ፨ እሳት 5. ጨለማ
2. ነፋስ አራቱ ባሕርያተ ሥጋ 6. ሰባቱ ሰማያት
3. ውኃ 7. መላእክት
4. መሬት 8. ብርሃን ናቸው፡፡ (ኩፋሌ 2÷5-8፣ዘፍ.1÷1-5)

አራቱ ባሕርያተ ሥጋ
14
አራቱ ባሕርያተ ሥጋ የሚባሉት ነፋስ፣ እሳት፣ ውኃና መሬት ናቸው፡፡ አራቱ ባሕርያተ ሥጋ ሲፈጠሩ ሦስት ሦስት
ግብር (ጠባይ) እንዲኖራቸው አድርጎ ነው፡፡ ይኸውም በባሕርዬ አንድነት ሦስትነት እንዳለ እወቁ ማለት ነው፡፡
 የእሳት ግብሩ (ጠባዩ)፡- ማቃጠል፣ ብሩህነት፣ ደረቅነት ነው፡፡
 የነፋስ ግብሩ (ጠባዩ)፡- ርጥብነት፣ ሞቃትነት፣ ጨለማነት ነው፡፡
 የመሬት ግብሩ (ጠባዩ)፡- ደረቅነት፣ ጨለማነት፣ ቀዝቃዛነት ነው፡፡
 የውኃ ግብሩ (ጠባዩ)፡- ብሩህነት፣ ርጥብነት፣ ቀዝቃዛነት ነው፡፡

አራቱ ባሕርያትና የእግዚአብሔር ጠባያት


አራቱ ባሕርያተ ሥጋ አራት የሆኑበት ምክንያት እግዚአብሔር በባሕርዩ አራት ነገሮች እንዳሉት ለማመልከት ነው፡፡
እነርሱም ባለጠግነት፣ መንጽሒነት፣ ከሃሊነትና ፈታሒነት ናቸው፡፡
መሬት፡- የእግዚአብሔርን ባለጠግነት ያስረዳል፡፡ መሬት ለሰው ልጅ ሕይወት መሠረታዊ ፍላጎት የተባሉትን ምግብ፣
መጠለያና ልብስ ታስገኛለች፡፡ እግዚአብሔርም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚበቃ የማያልቅ ሀብት ያለው ምግበ ሥጋን ምግበ
ነፍስን የሚሰጥ አምላክ ነው፡፡
‹‹ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ ነው›› ሮሜ. 10÷12፣ (መዝ. 135÷25)
ውኃ፡- የእግዚአብሔር መንጽሒነት ምሳሌ ነው፡፡ ውኃ መንጽሒ (የሚያነጻ) ነው፡፡ እድፍን ከአካል አካልን ከእድፍ
ይለያል፡፡ እግዚአብሔርም ነፍስን ከኃጢአት ኃጢአትንም ከነፍስ ይለያል፡፡
‹‹እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ ከበደሌም ፈጽሞ እጠበኝ
ከኃጢአቴም አንጻኝ›› መዝ. 50÷1

13. እሑድ አንድ የሆነ አንደኛ መጀመሪያ የዕለት ስም፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 211

ገጽ 4
14. መሬት፣ ውኃ፣ ነፋስና እሳት የፍጥረት መገኛዎች በመሆናቸው አራቱ ባሕርያት ተብለው ይጠራሉ፡፡

ነፋስ፡- የእግዚአብሔር ፈታሒነት (ፈራጅነት) ምሳሌ ነው፡፡ ነፋስ ፈታሒ ነው፡፡ ገለባን ከፍሬ ፍሬን ከገለባ ይለያል፡፡
እግዚአብሔርም ጻድቃንን ከኃጥአን ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያል፡፡
‹‹መንሹም በእጁ ነው አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፡፡ ገለባውን ግን
በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል›› ማቴ. 3÷12
እሳት፡- የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት (ከሃሊነት) ምሳሌ ነው፡፡ እሳት ኃያል ነው፡፡ ውኃ ካልከለከለው ቆላውንም
ደጋውንም፣ ርጥቡንም ደረቁንም፣ ልብላ ቢል ይቻለዋል፡፡ እግዚአብሔርም ቸርነቱ ርኅራኄው ካልከለከለው ታላቁንም
ታናሹንም ክፉውንም መልካሙንም አንድ ጊዜ ላጥፋ ቢል ይቻለዋል፡፡
‹‹አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነው›› ዕብ. 12÷29፣ (ሉቃ. 1÷35)
5. ጨለማ፡- እግዚአብሔር አምላክ እሑድ በመጀመሪያው ሰዓተ ሌሊት ጨለማን ፈጠረ፡፡ ጨለማ አይዳሰስም፡፡ በጨለማ
ውስጥ ያለ አይታወቅም አይመረመርም፡፡ ይህም የእግዚአብሔር ባሕርየ መለኮቱ የማይመረመር የማይደረስበት መሆኑን
ያሳያል፡፡ (ዘፍ. 1÷2፣ መዝ. 17÷11)
6. ሰባቱ ሰማያት
ሰባቱ ሰማያት በሌላ አጠራር ብሩህ ሰማይ በመባል ይታወቃሉ፡፡ አጠራሩ ቀና ብለን ከምንመለከተው ሰማይ (ጠፈር)
የተለዩ ሰባት ሰማያትን ለማመልከት ነው፡፡
‹‹የሰማይ ምጥልቀቱ ሳይታይ ሰባቱ ሰማያት ሳይቆጠሩ›› ዕዝ.ሱ. 4÷4፣ (ነህ. 9÷6)
1. ጽርሐ አርያም፡- ከሁሉም በላይ ናት ለመንበረ መንግሥት እንደ ጠፈር ታገለግላለች፡፡
2. መንበረ መንግሥት፡- እግዚአብሔር በወደደው አምሳል ለፍጡራን የሚታይበት ነው፡፡ 15
3. ሰማይ ውዱድ፡- በኪሩቤል ላይ ተዘርግታ ለመንበረ መንግሥት እንደ አዳራሽ ወለል ሆና የምታገለግል ናት (ሕዝ. 1፥22 ፣ 66)
ይህ ሰማይ የእግዚአብሔር መረገጫ ዙፋን ነው፡፡
4. ኢየሩሳሌም ሰማያዊት፡- በፊት ሳጥናኤል የነበረባት በኋላም በዕለተ ምጽአት በጎ የሠሩ ሰዎች የሚወርሷት የክርስቲያኖች ርስት
ናት
5. ኢዮር
6. ራማ ዓለመ መላእክት ናቸው፡፡
16
7. ኤረር
7 መላእክት
መልአክ የሚለው የግእዝ ቃል ኹለት ዓይነት ትርጉም አለው፡፡ (ኪ.ወ.ክ ገጽ 554)
1. በቁሙ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ሰማያዊ ረቂቅ የእሑድ ፍጥረት ማለት ነው፡፡
‹‹ከሰማይ መጥቶ የሚያበረታው መልአክ ታየው›› ሉቃ. 22÷43
2. አለቃ ሹም አበጋዝ ተሹሞ ከንጉሥ የተላከ ማለት ነው፡፡
‹‹ኢየሱስም በገዢው ፊት ቆመ ገዢውም የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን ብሎ ጠየቀው ኢየሱስም አንተ አልህ
አለው›› ማቴ. 27÷11
የመላእክት ተፈጥሮ (ባሕርይ)
እግዚአብሔር አምላክ መላእክትን ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ፈጥሯቸዋል፡፡ መላእክት ረቂቃን መናፍስት ናቸው፡፡
ነገር ግን ርቀታቸው እንደፈጣሪያቸው አይደለም፡፡ እርሱ ፍጹም መንፈስ ነውና፡፡ መላእክት ፍጡራን እንደመሆናቸው
የማይዳሰሱ ይሁኑ እንጂ አካል አላቸው፡፡ መላእክት ረቂቃን መንፈሳዊያን እንደመሆናቸው ሥጋዊ ምግብ አይመገቡም፤
ምግባቸው መጠጣቸው ረቂቅ የሆነ የፈጣሪያቸው ፍቅርና ምስጋና ነው፡፡ መላእክት የወንድና የሴት ጾታ መለያ
የላቸውም፡፡ ይፈጠራሉ እንጂ አያገቡም፣ አይጋቡም፣ አይባዙም፡፡

15. መንበረ መንግሥት፡- መንበረ ብርሃን፣ መንበረ ስብሐት፣ መንበረ ጸባዖት የተባሉ ሌሎች ስሞች አሏት፡፡
16. ኢሳ. 6÷1፣ ራዕ፣ 4÷2፣ ሕዝ. 1÷22፣ መዝ. 17(18)÷10፣ ራዕ. 21÷10-15፣ ራዕ. 11÷9

‹‹በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም›› ማቴ. 22÷10-
30

ገጽ 4
የመላእክት ብዛታቸውና ማዕረጋቸው
መጽሐፍ ቅዱስ የመላእክት ቁጥር እጅግ ብዙ፣ የብዙ ብዙ፣ ሺ ጊዜ ሺ ናቸው ብሎ ከማስረዳት በቀር
ብዛታቸውን በአኀዝ ወስኖ ሲናገር አናገኝም፡፡
‹‹ስለዚህም በኋላ ፈጽመው የበዙ የብዙ ብዙ የሚሆኑ መላእክትን አየሁ በመላእክት ጌታ ጌትነት ፊት የሚቆሙ
መላእክትም ስፍር ቁጥር የላቸውም›› ሄኖ. 10÷1፣ (ራዕ. 5÷12፣ ዳን. 7÷10)
በመንፈሳዊው ዓለም ከፈጣሪ ዘንድ የሚሰጡት ማዕረጋት ወደ በለጠው ክብር የሚሸጋገሩባቸው እና በተጋድሎ
ሕይወትም አምላክን ወደ መምሰል የሚደርሱባቸው መወጣጫ መሰላላቸው ነው፡፡ በመላእክትም ዘንድ ያሉት መዓረጋት
ዓላማቸው መላእክትን የበለጠ ከእግዚአብሔር ጋር ማቆራኘትና ጽኑዕ የሆነ ውሕደትን መፍጠር ነው፡፡
‹‹ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም
ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊው ሁሉ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታት
ጉልበት ያታያል፡፡›› ኤፌ.1÷21 (ማቴ. 24÷31፣ 1 ኛተሰ. 4÷16፣ ሕዝ. 10÷1፣ ኢሳ. 6÷1-6)
የመላእክት ከተሞችና አሰፋፈራቸው
እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ሰማያት በቁጥር ብዛት ሰባት ናቸው፡፡ ከእነዚህም ሰባቱ
ሰማያት ሦስቱ ሰማያት ሀገረ መላእክት ናቸው፡፡ እግዚአብሔር በየመዓረጋቸው እና በየስመ ነገዳቸው ከፋፍሎ
መላእክትን በሦስቱ ሰማያት በኢዮር በራማና በኤረር በከተማ አሥር በነገድ መቶ አድርጎ አስፍሯቸዋል፡፡
የመላእክት ከተማ አለቃ ነገድ ስማቸው
ከተሞች
ኢዮር 1 ሳጥናኤል 10 አጋእዝት
2 ኪሩብ 10 ኪሩቤል
3 ሱራፊ 10 ሱራፌል
4 ቅ. ሚካኤል 10 ኃይላት
ራማ 5 ቅ. ገብርኤል 10 አርባብ
6 ቅ. ሩፋኤል 10 መናብርት
7 ቅ. ሱርያል 10 ሥልጣናት
ኤረር 8 ቅ. ሰዳክያል 10 መኳንንት
9 ቅ. ሰላትያል 10 ሊቃናት
10 ቅ. አናንያል 10 መላእክት

ኪሩቤል
ኪሩቤል 17 ቃሉ የአካድ/የጥንት ባቢሎን) ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን አማላጅ፣ ኀያል፣ ታላቅ ማለት ነው፡፡ ኪሩቤል
በአገልግሎታቸው ጸወርተ-መንበር (የሥላሴን መንበር የሚሸከሙ) ናቸው፡፡ ኪሩቤል የሥላሴን መንበር ተሸካሚዎች
ናቸው ማለት እግዚአብሔር በረድኤት በመንፈስ አድሮባቸው ይኖራል ማለት ነው፡፡
‹‹በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ›› መዝ. 79÷1፣ (መዝ. 18÷10)
ኪሩቤል ለነቢዩ ሕዝቅኤልና ለወንጌላዊ ዮሐንስ በገጸ ሰብእ፣ በገጸ አንበሳ፣ በገጸ ላህምና በገጸ ንስር ተገልጠዋል፡፡

17. ኪሩቤል መላእክት ኪሩቦች መንበር ተሸካሞች በእንስሳት አምሳል የሚታዩ ስመ ነገድ፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 544

‹‹ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል ሦስተኛውም እንስሳ እንደ
ሰው ፊት ነበረው አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል‹‹ ራእ. 4÷7-8፣ (ሕዝ. 1÷5-25)
ኪሩቤል የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ኪሩቤል የአምላክን መንበር ተሸክመው እንደሚታዩ እርሷም
ሰማይና ምድር የማይችሉትን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ ተሸክማዋለች፡፡

ሱራፌል
ሱራፌል 18 ማለት በዕብራይስጥ ‹‹እሳት›› ማለት ነው፡፡ ይህም ስያሜ ዙፋኑ የእሳት ነበልባል ከሆነው አምላክ ፊት
ቀርበው የሚያገለግሉ በመሆናቸው የተሰጣቸው ስያሜ ነው፡፡

ገጽ 4
‹‹ዙፋኖቹም እሰኪዘረጉ ድረስ አየሁ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ የራሱም ጠጉር
እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነው›› ዳን. 7÷9
ከአገልግሎታቸው የተነሣ ደግሞ ካህናተ ሰማይ ይባላሉ፡፡ ምክንያቱም የካህናትን ሥራ የሚሠሩ ስለሆነ ነው፡፡ በሌላ
አጠራር ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች ወይም ሽማግሌዎች
በሚል ስም ይጠራቸዋል፡፡
‹‹ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው በኹለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን
ነበር በኹለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር በኹለቱም ክንፍ ይበር ነበር›› ኢሳ. 6÷2፣ (ራእ. 4÷10)

8. ብርሃን
ብርሃን የዕለተ እሑድ የመጨረሻው ፍጥረትና በዕለቱ ብቸኛው በነቢብ የተፈጠረ ፍጥረት ነው፡፡ ብርሃን በነቢብ
የተፈጠረው ሰማዕያን መላእክት ስለነበሩ ነው፡፡
‹‹እግዚአብሔርም፡- ብርሃን ይሁን አለ፤ ብርሃንም ሆነ›› ዘፍ. 1÷3

2.5.2 የሰኞ ፍጥረት

ኹለተኛው ዕለት በግእዝ ሰኑይ (ሠኑይ) በአማርኛ ደግሞ ሰኞ ትባላለች፡፡ ሰኑይ 19 የሚለው ቃል ሰነየ ከሚለው ግስ
የወጣ ሲሆን መሰነይ ኹለት ማድረግን ኹለት መሆንን ያመለክታል፤ ሰኑይ ኹለተኛ ዕለት ማለት ነው፡፡

‹‹ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከኹለት ቀናትም በኋላ ከዚያ ወጥቶ ወደ ገሊላ ሄደ›› ዮሐ. 4÷43
በሌላ በኩል ደግሞ ሠኑይ ሠነየ ካለው ግስ ሲወጣ አማረ፣ ተዋበ፣ በመልክ በጌጥ ደስ አሰኝ የሚል ትርጉም ይይዛል፡፡ ዘፍ.
1÷31
እግዚአብሔርም ሰኞ ዕለት በመጀመሪያው ሰዓተ ሌሊት ጠፈርን ፈጠረ፡፡ ጠፈር ማለት ሰማይ የምድር ባጥ ማለት
ነው፡፡ ጠፈር ከመፈጠሩ በፊት ከምድር እስከ ኤረር ድረስ ውኃ ሞልቶ ነበር፡፡ እግዚአብሔር “በውኃና በውኃ መካከል
ይለይ ዘንድ ጠፈር ይሁን” ብሎ ቢያዝ በዓለም ሞልቶ የነበረው ውኃ ለሦስት ተከፈለ፡፡ እነዚህም
1. ሐኖስ
2. ጠፈር
3. ውቅያኖስ ናቸው፡፡

18. ሱራፌል ስመ ነገድ ልዑላን መላእክት ሊቃናት ዐጠንት ካህናት የሰማይ ቀሳውስት ቀዳሾች ኪ.ወ.ክ ገጽ 886
19. ሰኑይ የዕለት ስም ኹለተኛ ኹለት ሰኞ የእሑድ ማግስት፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 875

‹‹እግዚአብሔርም በውኆች መካከል ጠፈር ይሁን በውኃና በውኃ መካከልም ይክፈል አለ፡፡
እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኆች ለየ›› ዘፍ. 1÷6-7
ምሳሌነቱ
ከላይ የቀሩት ኹለቱ ማለትም ሐኖስና ጠፈር የተባሉት የውኃ ክፋዮች የአብና የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ናቸው፡፡ በዚህ
ዓለም የቀረው ውቅያኖስ የተባለው ውኃ የወልድ ምሳሌ ነው፡፡ ምክንያቱም አብ መንፈስ ቅዱስ ሰው አልሆኑም፤ ወልድ
ግን ሥጋን ተዋሕዶ በዚህ ዓለም ለመገለጡ ምሳሌ ነው፡፡
የጠፈር ጥቅም
1. ለፀሐይ ለከዋክብትና ለጨረቃ መመላለሻ ማኅደር ይሆን ዘንድ
2. የፀሐይን ሙቀት እንዲያቀዘቅዝ
2.5.3 የማክሰኞ ፍጥረታት
ሦስተኛይቱ ዕለት ሠሉስ 20 ትባላላች፡፡ ሠሉስ ማለትም ሦስተኛ ቀን ማለት ነው፡፡ ሦስተኛ መባሏም እግዚአብሔር
ፍጥረት መፍጠር ከጀመረበት ከዕለተ እሑድ ጀምሮ ስለሚቆጠር ነው፡፡ ይህች ዕለት በአማርኛ ማግሰኞ ትባላለች፡፡
እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን ማክሰኞ በቃሉ በማዘዝ ሦስት (አራት) ፍጥራትትን ፈጠረ፡፡
1. አዝርዕት
2. አትክልት

ገጽ 4
3. ዕፅዋት
‹‹እግዚአብሔርም፡- ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያንም በምድር ላይ እንደየወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን
የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ እንዲህም ሆነ፡፡ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደወገኑ ዘሩ ያለበትን
ፍሬን የሚያፈራ እንደ ወገኑ አበቀለች›› ዘፍ. 1÷11-12
መጽሐፈ ኩፋሌ የዕለተ ሠሉስ ፍጥረታት አራት ናቸው ይላል፡፡ በዕለተ ሠሉስ ሦስት ፍጥረታት ተፈጠሩ የሚሉ በዕለተ
እሑድ ስምንት ፍጥረታት ተፈጠሩ ይላሉ፡፡ መጽሐፈ ኩፋሌ በዕለተ እሑድ ሰባት ፍጥረታት ተፈጠሩ ይልና የዕለተ ሠሉስ
ፍጥረታት አራት በማለት ጠቅላላ 22 ናቸው ይላል፡፡ የዕለተ ሠሉስ ፍጥረታት አራት የሚኾኑት እንደሚከተለው ነው፡፡
1. አዝርዕት
2. አትክልት
3. ዕፅዋት
4. በገነት ያሉ አትክልት ናቸው፡፡ (መጽሐፈ አክሲማሮስ)
የማክሰኞ ዕለት ምድር ለእመቤታችን ትመሰላለች፡፡ የማክሰኞ ዕለት ምድር ያለዘር ምግብ የሚሆኑ አትክልት፣
አዝርዕት፣ ዕፅዋት እንዳስገኘች እመቤታችንም ለሰው ልጅ ሥጋውና ደሙን ምግበ ነፍስ አድርጎ የሰጠ ክርስቶስን
ያለወንድ ዘር በማኅፀኗ ይዛ ተገኝታለችና፡፡ ማቴ. 1÷18

2.5.4 የረቡዕ ፍጥረታት


21
ረቡዕ የሚለው ቃል ራብዕ ካለው የግእዝ ቃል የተገኘ ነው፡፡ ራብዕ ማለትም አራተኛ ማለት ነው፡፡ ረቡዕ ሲልም
አራተኛውን ዕለት ሲያመለክት ነው፡፡ አራተኛነቷም ለዕለተ እሑድ ነው፡፡ እግዚአብሔር በአራተኛው የፍጥረት ቀን ረቡዕ
ሦስት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡

20. ሠሉስ የዕለት ስምና ቅጽል ማግሰኞ ማግስተ ሰኞ የሰኞ ማግስት የእሑድ ሣልስት በሰኞና በረቡዕ መካከል ያለው ዕለት፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 670
21. ረቡዕ የዕለት ስም ቁጥር አራተኛ አራት፡፡ ኪ.ወ.ክ 820

1. ፀሐይ
2. ጨረቃ
3. ከዋክብት
‹‹እግዚአብሔርም ኹለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን ትንሹም ብርሃን
በሌሊት እንዲሠለጥን ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ›› ዘፍ. 1÷14-18
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በመጀመሪው ቀን ብርሃን ይሁን በተባለውና በአራተኛው ቀን ‹‹ብርሃናት ይሁኑ›› በተባለው
ቃል መካከል ያለውን ልዩነት ሲያስረዳ በመጀመሪያው ቀን ብርሃን ይሁን ሲባል ብርሃን ቅርጽ አልያዘም ነበር፤ በዕለተ
ረቡዕ ግን ብርሃናት ይሁኑ ሲባል በዕለተ እሑድ የተፈጠረው ብርሃን ቅርጽ ይዟል አለ፡፡
ምሳሌነት፡- ጻድቃን በፀሐይ ኃጥአን በጨረቃ ይመሰላሉ፡፡ ፀሐይ ሁልጊዜ ሙሉ ሆኖ እንደሚኖር ጻድቃንም በምግባር
በሃይማኖት ሙሉዓን ናቸውና፡፡ ጨረቃ አንድ ጊዜ ሙሉ ሌላ ጊዜ ጎዶሎ እንደምትሆን ኃጥአንም በምግባር አንድ ጊዜ
ሙሉ ሌላ ጊዜ ሲጎድሉ ይኖራሉ፡፡

2.5.5 የሐሙስ ፍጥረታት

ሐሙስ 22 ማለት አምስተኛ ማለት ነው፡፡ አምስተኛነቱም እግዚአብሔር ፍጥረታትን መፍጠር ለጀመረበት ለዕለተ
እሑድ ነው፡፡ እግዚአብሔር በአምስተኛው ቀን በዕለተ ሐሙስ ሦስት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ እነርሱም፡-
1. አራዊት
2. እንስሳት
3. አዕዋፋት
‹‹እግአብሔርም አለ፡- ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ
ጠፈር በታች ይብረሩ፡፡ እግዚአብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን ውኃይቱ እንደወገኑ ያስገኘቻቸውንም
ተንቃሳቃሾችም ሕያዋን ፍጥረት ሁሉ እንደወገኑ የሚበሩትን ወፎች ሁሉ ፈጠረ›› ዘፍ. 1÷20-21

ገጽ 4
የዕለተ ሐሙስ ፍጥረታት በደመ ነፍስ ሕይወት ህያዋን የሆኑ ሲሆኑ በደመ ነፍስ ሕያው ሆነው የሚኖሩ ናቸው፡፡
አፈጣጠራቸውም ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ነው፡፡
ምሳሌነታቸው
1. ሲፈጠሩ በርረው ከውኃ ወደ የብስ የወጡ የኢጥሙቃን
2. ከባሕር የቀሩ የጥሙቃን
3. በባሕርና በየብስ የሚመላለሱ ወደ ጽድቅና ኃጢአት የሚመላለሱ ሰዎች ምሳሌ ናቸው፡፡

2.5.6 የዓርብ ፍጥረታት

ዓርብ 23 - ዓርበ ካለው ግሥ ሲወጣ ተካተተ ተከተተ የሚል ትርጉም ይኖረዋል፡፡ ዓርብ ማለትም መካተቻ ማለት ነው፡፡
ይኸውም ስድስተኛይቱ ዕለት የፍጥረት መካተቻ፣ መፈጸሚያ፣ ማብቂያ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ከዕለተ እሑድ እስከ
ሐሙስ ላሉት ዕለታት በተሰጠው የስያሜ አካሔድ ቢቀጥል ኖሮ ዓርብ ባለው ፈንታ ሰዱስ ስድስተኛ ቀን በተባለ ነበር፡፡

22. ሐሙስ ፭ኛ ቀን - ደስታ ተክለ ወልድ ገጽ 525


23. ዐርብ ስመ ዕለት ስድስተኛ ቀን በሐሙስና በቀዳም መካከል ያለ የፍጥረት የሥራ የመና ፍጻሜ መካተቻ፡፡
ኪ.ወ.ክ ገጽ 708

እግዚአብሔር በስድተኛው ቀን አራት ፍጥረታትን ፈጠረ፤ ከአዳም በስተቀር ሦስቱ ፍጥረታት እግዚአብሔር በቃል
ባዘዘ ጊዜ ከየብስ ተገኝተዋል፡፡ እግዚአብሔርን የብስን ባዘዛት ጊዜ የእንስሳት የአራዊት ዓይነት ሁሉ የአዕዋፍንም ቁጥር
የሌላቸው ታላላቅና ጥቃቅን ተባዕትና አንስትን አወጣች፡፡ እነርሱም፡-
1. አራዊት
2. እንስሳት
3. አዕዋፋት

‹‹እግዚአብሔርም አለ፡- ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደወገኑ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር


አራዊትንም እንደወገኑ ታውጣ እንዲሁም ሆነ›› ዘፍ. 1÷24

በዕለተ ሐሙስና በዕለተ ዓርብ የተፈጠሩት ፍጥረታት ‹‹እንስሳት›› በመባል አንድ ቢሆኑም በአኗኗራቸውና
በግብራቸው ይለያያሉ፡፡ የሐሙስ ፍጥረታት ከባሕር ተለይተው በምድር መኖር አይችሉም፡፡ የፀሐይ ሙቀት ሲነካቸው
ይሞታሉ፡፡ የዓርብ ፍጥረታትም ከምድር ተለይተው በባሕር ውስጥ መኖር አይችሉም፡፡ የባሕር ውርጭ ቅዝቃዜ
ይገድላቸዋል፡፡
ምሳሌነታቸው፡-
የዓርብ ፍጥረታት ምሳሌነታቸው ለምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ነው፡፡ በየብስ የሚኖሩ ሦስቱ ፍጥረታት መፈጠር የሦስት
ጊዜ የመለከት መነፋት ምሳሌ ነው፡፡

የሰው ልጅ አፈጣጠርና ክብሩ

በመጨረሻም ቅድስት ሥላሴ ለሰው አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ፈጥረው ካዘጋጁለት በኋላ ሰውን ‹‹በመልካችን
እንደምሳሌአችን እንፍጠር›› ብለው ዓርብ ዕለት በጠዋት አራቱን ባሕርያተ ሥጋ ሦስቱን ግብራተ ነፍስን አዋሕደው
አዳምን የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ አደርገው በማዕከለ ምድር ፈጠሩት፡፡

2.5.7 ቀዳሚት ሰንበት

ቀዳሚት ሰንበት 24 ዕለተ ሳብዕ ትባላለች፡፡ ሰባተኛው ዕለት ማለት ነው፡፡ ሰባተኛ ዕለት ቀዳሚት ሰንበት ናት፡፡ ሰንበት
ማለት ዕረፍት ማለት ነው፡፡በዚህ ዕለት ምንም ፍጥረት አልተፈጠረም፡፡

ገጽ 4
‹‹ሰማይና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ፡፡ እግዚአብሔር የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፡፡
በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ፡፡ እግዚአብሔርም ሰባተኛው ቀን ባረከው ቀደሰውም፤
እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ አርፏልና›› ዘፍ. 2÷1-3

24. ሰንበተ ቀዳሚት ሰንበተ አይሁድ ቅዳሜ የብሉይ ሰንበት የእሑድ ምሳሌ ዋዜማ ኪ.ወ.ክ ገጽ 874

ምዕራፍ ሦስት
አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነቷን(ዶግማ) የምትገልጥባቸውና
የምስታስተምርባቸው አምስት አዕማደ ምሥጢራት አሏት፡፡ እነዚህም በተለያዩ መጻሕፍት በቀደሙት አባቶቻችን
ተጽፈው ለዛሬው ትውልድ የተላለፉ ናቸው፡፡ አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት የቀደሙት አበው ሊቃውንት መጽሐፍ
ቅዱስን መሠረት አድርገው የጻፏቸውን መጻሕፍት በማናገናዘብ ምሥጢሩን ጠብቆ ትርጉሙ ሳይዛነፍ ለመረዳት
በሚያስችል መልኩ በየርእሳቸው ተዘርዝረው ቀርበዋል፡፡ የሃይማኖት መሠረት የሚባሉት አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት
የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ምሥጢረ ሥላሴ
2. ምሥጢረ ሥጋዌ
3. ምሥጢረ ጥምቀት
4. ምሥጢረ ቁርባን
5. ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አምስቱ አዕማደ ምሥጢራትን በተመለከተ “ከሁላችሁ ይልቅ በልሳኖች እናገራለሁና
እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ነገር ግን ሌሎችን አስተምር ዘንድ በማኅበር እልፍ ቃላት በልሳን ከመናገር ይልቅ ‹‹አምስት
ቃላትን‹‹ በአእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ” (1 ቆሮ 14፥18-19) አለ፡፡ ሐዋርያው አምስት ቃላት ያለው አምስቱ አእማደ
ምሥጢራትን እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያስረዳሉ፡፡
አዕማድ
ዐምድ ቃልነቱ የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ በአማርኛ ኹለት ዓይነት ትርጓሜ አለው፡፡
1. ለቤት ሲኾን ቃሉ ተለውጦ ምሰሶ 25 ይባላል፡፡ ዐምድ በምሰሶነቱ ቤትን እንደሚያጸና ይህም ስለሃይማኖት
በመጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈው ቃል የሰውን ልብ የሚያጸና ስለሆነ ነው፡፡
2. ለጽሕፈት ሲኾን በራሱ ሳይለወጥ ዐምድ 26 ተብሎ ይጠራል፡፡ ኹኔታውም የገጽ ስፋት መክፈያ መመጠኛ
ስለኾነ ምሰሶ ከማለት የራቀ ነገር የለውም፡፡
ዐምድ በገጽ ስፋት ላይ መክፈያ መመጠኛ በመኾኑ ለጽሕፈት ለንባብ ደንብ እንዲሰጥ ይህም ሰው ሰፊ ጥልቅ ረቂቅ
የኾነውን ባሕርየ ሥላሴ ሊመረምር ቢወድ በመጠኑ መርምሮ ኅሊናውን እንዲወስን ከዐቅሙ በላይ እንዳይመረምር
ሕግና ደንብ የሚሰጥ ስለሆነ ነው፡፡
“እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው እንደባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው
አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላቸው ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ” ሮሜ 12፣3
ምሥጢር
ምሥጢር ማለት፡- ረቂቅ ስውር ድብቅ ሽሽግ ነገር ለልብ ወዳጅ ካልሆነ በቀር የማይነገር ማለት ነው፡፡ ምሥጢር እንደ
አገባቡ በሁለት ትርጉም ይፈታል፡፡ (ደስታ ተክለ ወልድ ገጽ 813)
1. ለልብ ወዳጅ ካልሆነ በቀር ለማንም የማይነገር ድብቅ ሽሽግ ማለት ነው፡፡

ገጽ 4
2. ምሥጢሩ እየተነገረና እየተገለጠ ግን “የማይጨበጥ ረቂቅ ከሰው አእምሮ በላይ ምጡቅ በሥጋዊ ዐይን ሊያዩት
ሊመረምሩት የማይቻል ታላቅ ነገር” ማለት ነው፡፡
ለቤተ ክርስቲያን ትምህርት ምሥጢራት የሚወሰደው ትርጓሜ ሁለተኛው ነው፡፡ አንዳንዶች ምሥጢራት ሲባል
ትምህርቶቹ እውነት ስላልሆኑ ለማድበስበስ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ይመስላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ
ክርስቲያን የማይነገር ምሥጢር የላትም፡፡ የሚነገር ግን በሥጋዊ ዕውቀትና ሃሳብ ሊመረምሩት ሊናገሩትም ሆነ
ሊያስረዱት የማይችሉት ምሥጢር ባለቤት ናት፡፡ አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት የምሥጢር ትምህርቶች ናቸው፡፡
ምክንያቱም በሥጋዊ ጥበብ መመርመርና መረዳት የማይቻል ስለሆነ ነው፡፡ ምሥጢራቱን ለመረዳት ትሕትና፣ ጸሎትና
ትምህርት አስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡
“ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ” 1 ቆሮ 12፥12

25. ዐምድ ምሰሶ ደገፋ ኤር. 27÷19፡- ደስታ ተክለ ወልድ ገጽ 935
26. ዐምድ በጥፈትና በጥፈት መካከል ከአርእስት እስከ ኅዳግ ያለ የገጽ መክፈያ ባዶ ብራና፡- ደስታ ተክለ ወልድ ገጽ 935

መጽሐፍ ቅዱስ ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ውስጥ የተወሰኑትን ምሥጢር ብሎ ሲጠራቸው እናገኛለን፡፡
ለምሳሌ፡- ምሥጢረ ሥጋዌን በተመለከተ ‹‹ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን ተሰውሮም የነበረውን
የእግዚአብሔር ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን›› (1 ኛቆሮ.2÷7) (ሮሜ.16÷25፣ ቆላ.1÷16፣ ኤፌ.1÷9) ምሥጢረ ትንሣኤ
ሙታንን በተመለከተ ደግሞ ‹‹እነሆ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ ሁላችን አናንቀላፋም›› (1 ኛቆሮ. 15÷51)
3.1 ምሥጢረ ሥላሴ
መግቢያ
ከአዕማደ ምሥጢራት ቀዳሚው መጀመሪያው እግዚአብሔር በአካላት በኩነታት በአካላት ግብር ሦስት
በባሕርይ አንድ ብለን ማመንን የምንማርበት ክፍል ምሥጢረ ሥላሴ ይባላል፡፡ ምሥጢረ ሥላሴን የምንማርበት ዋናው
ምክንያት የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት አውቀንና ተረድተን እግዚአብሔርን በተገቢ ክብሩና ማዕረጉ ለማምለክ ነው፡፡
‹‹ከሁሉ አስቀድመን የሥላሴን አንድነት ሦስትነት እናስተምራን›› ቅዱስ ቄርሎስ
ሥላሴ ማለት ምን ማለት ነው?
ሥላሴ የሚለው ስም ሠለሰ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን መሠለስ ሥለሳ ሦስትነት ሦስት መሆን ማለት ነው፡፡
(ኪ.ወ.ክ ገጽ 669)
የቅድስት ሥላሴ ስም አጠራር
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥላሴ 27 ከሚለው ስም ጀምሮ ልዩ ልዩ በሆኑ መጠሪያዎች በመጠቀም ስለ ቅድስት ሥላሴ
ታስተምራለች፡፡ በዚህ ክፍል የተወሰኑትን የሥላሴ መጠሪያዎች እንመልከት፡፡
ቅድስት 28 ሥላሴ ትርጉሙ የተቀደሰች ሦስትነት ማለት ነው፡፡ (ደስታ ተክለ ወልድ ገጽ 1034)
ሥላሴ ዋሕድ በአንድ እግዚአብሔርነት ከሚገኝ ከሦስቱ አካላት በቀር መንትያ ወይም ተመሳሳይ የሌለውና ብቻውን
የሚኖር ‹‹ ሦስትነትን›› የሚያሳይ መጠሪያ ነው፡፡
ሥሉስ ቅዱስ 79 ሦስትነት ያለው አንድነትን የሚያመለክት መጠሪያ ነው፡፡ ሥሉስ ብሎ በብዙ ሦስትነትን ቅዱስ ብሎ
በነጠላ አንድነትን ያመለክታል፡፡
ልዩ ሦስትነት ለሦስትነትና ለአንድነት ምሳሌ የሚሆኑ ነገሮች የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት ጠንቅቀው የሚያስረዱ
ባለመሆናቸው ልዩ ሦስትነት ተብሏል፡፡
የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር
እግዚአብሔር በአካላት በኩነታት ሦስት በባሕርይ አንድ ብለን ማመንን የምንማርበት ክፍል ምሥጢረ ሥላሴ ይባላል፡፡
‹‹በአንድ አምላክ አምናለሁ አንድነት በሦስትነት ሦስትነት በአንድነት እንዳለ አውቃለሁ›› (ሃይ. አበ
ዘዮሐንስ ምዕ 90 ቁ 5)
ምሥጢረ ሥላሴ የሦስትነት ምሥጢር የማይመረመር መለኮት ዓለም ሳይፈጠር የነበሩ ዛሬም ያሉ ወደፊትም ዓለምን
አሳልፈው የሚኖሩ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የተባሉ አካላትን በማዋሐድ እንደ አለ ዐውቆ እግዚአብሔር በአካል በስም
በገጽ በግብር በኩነት (ኹኔታ) ሦስት በባሕርይ በሕልውና በመለኮት አንድ እንደሆነ ማመን ነው፡፡
‹‹ ከሥራው ሁሉ አስቀድሞ ሦስት አካላት ባሉት በአንድ መለኮት እንመን በባሕርይ አንድ በአካል ሦስት
የሚሆኑ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ሲሆኑ ሦስት ናቸው ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው›› (ሃይ. አበ ባስልዮስ
ምዕ 33 ቁ. 2)
በሥላሴ ዘንድ አንድነት ሳለ ሦስትነት ሦስትነት ሳለ አንድነት አላቸው፡፡ ሦስት መሆናቸው አንድነታቸውን አይከፍለውም
አንድ መሆናቸው ሦስትነታቸውን አይጠቀልለውም፡፡

ገጽ 4
“እንዲህ እናምናለን እንዲህም እንታመናለን አንድነትን ሳንለይ የተለየ እንዳይሆን የተቀላቀለ እንዳይሆን እንለይ እንደ
አብርሃምና እንደ ይስሐቅ እንደ ያዕቆብ ሦስት የምንል አይደለም፡፡ በገጽ ሦስት ሲሆን በባሕርይ አንድ ነው እንጂ፡፡ ከፍጥረት
ሁሉ እንደሚቀድም እንደ አዳም አንድ የምንል አይደለም፡፡ በባሕርይ አንድ ሲሆን ሦስት ነው እንላለን እንጂ” (ሰንበተ ቀዳሚት
ሰንበተ አይሁድ አባ ሕርያቆስ ቅዳሴ ማርያም ቁ. 68)

27. ሥላሴ የሚለውን ስም ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙበት ጠርጡለስና ቴዎፍሎስ ዘአንጾኪያ እንደሆኑ ይነገራል፡፡
28. ሥላሴን በሴት አንቀጽ ቅድስት ማለታችን እግዚአብሔር እንደ እናት ርኅሩኅ እንደሆነ ለመግለጽ ነው፡፡
29. ቅዱስ በቁሙ የተቀደሰ ክቡር ምስጉን ልዩ ምርጥ ንጹሕ ጽሩይ ማለት ነው፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 785

የሥላሴ ሦስትነት
ሥላሴ በአካላት ስም በአካላት ግብር በአካል ሦስት ናቸው ብንልም በባሕርይ፣ በመለኮት፣ በሕልውና በፈቃድ አንድ
አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አይባሉም፡፡ እግዚአብሔር በአካሉ በገጹ መጠቅለል መቀላቀል የሌለበት ልዩ ሦስት ነው፡፡
የስም ሦስትነት
ስም፡- የቦታና የአካል መጠሪያ ማንኛውም የሚታይና የማይታይ ነገር ኹሉ የሚጠራበትና የሚታወቅበት ስም ይባላል፡፡
(ደስታ ተክለ ወልድ ገጽ 1183) ሥላሴ የአካል ስም፣ የአካል ግብር ስም፣ አካላት በህልውና የሚገናዘቡበት የባሕርይ ከዊን ስም
አላቸው፡፡
የአካላት ስም
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የተባሉት ስሞች የሥላሴ አካላት መጠሪያ ስሞች ናቸው፡፡ መፋለስ ወይም መቀላቀል
የለቸባቸውም፡፡
‹‹እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ
እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው›› ማቴ 28÷19
የስም ተፋልሶ የአካላት ግብር ተፋልሶ ስለሚያመጣ አብ አብ ቢባል እንጂ ወልድ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባልም፤
ወልድም ወልድ ቢባል እንጂ አብ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባልም መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ቢባል እንጂ አብ
ወይም ወልድ አይባልም፡፡
‹‹ አብም አብ ነው እንጂ ወልድን መንፈስ ቅዱስን አይደለም ወልድም ወልድ ነው እንጂ አብን መንፈስ ቅዱስን
አይደለም መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ አብን ወልድን አይደለም፡፡›› (ሃይ. አበ ዘአግናጥዮስ ምዕ 11
ክፍል 1 ቁጥር 7)
ሦስቱ ስሞች ያለ መቀዳደምና ያለ መከታተል አካላተ ሥላሴ በነበሩበት ዘመን ሁሉ (ለዘላለም) የነበሩ ስሞች ናቸው፡፡
እነዚህ ስሞች ከጊዜ በኋላ የተሰየሙ ስሞች ሳይሆኑ አካላተ ሥላሴ በነበሩበት ዘመን ሁሉ የሚጠሩበት ስም ነው፡፡
‹‹የእግዚአብሔር አቃኒም ስሞች ናቸው ስሞችም አቃኒም ናቸው የአቃኒም ትርጓሜው በገጽ በመልክ
ፍጹማን የሚሆኑ ባለመለወጥ ጸንተው የሚኖሩ አካላት ማለት ነውና ባሕርይ አንድ ሲሆን ሦስቱ አካላት
ጸንተው በሚኖሩ በእሊህ ስሞች ይጠራሉ ሦስት አካላት አንድ መለኮት ናቸው፡፡›› (ሃይ. አበ ዘጎርጎርዮስ ምዕ 13
ክ 1 ቁ.6)
የአካላት ግብር ስም፡- ወላዲ አሥራጺ፣ ተወላዲ፣ ሠራጺ (መዝ 2፣7፣ ዮሐ 15፣26) የሥላሴ አካላት በግብር ሦስትነት
አላቸው፡፡ የግብር ስም የሚባሉት ወላዲነት አሥራጺነት፣ ተወላዲነት፣ ሠራጺነት ናቸው፡፡
የኩነት ስም፡- ልብነት ቃልነት እና እስትንፋስነት ነው፡፡ በኩነት (ከዊን) ስማቸው አብ ‹ልብ› ወልድ ‹ቃል› መንፈስ ቅዱስ
‹እስትንፋስ› ይባላሉ፡፡ መዝ 32(33)፥6-11
የአካላት ሦስትነት
አካል በቁሙ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ያለው ራሱን የቻለ ለራሱ የበቃ እኔ የሚል ህላዌ … የባሕርይ የግብር የስም
ባለቤት እገሌ የሚባል፡፡ (ኪ.ወ.ክ ገጽ 218)
ገጽ፡- በቁሙ ፊት፣ ግንባር፣ ዐይንና አፍንጫ አፍ ያሉበት ካንገት በላይ እስከ ራስ ጠጉር ወደ ታችም እስከ እግር ጥፍር
በስተፊት ያለው ክፍል ነው፡፡ (ሰንበተቀዳሚት ሰንበተአይሁድ ኪ.ወ.ክ ገጽ 329)
መልክእ፡- በአካላት ላይ ያለ የአካል ክፍሎች ለምሳሌ ዐይን እጅ እግር ወዘተ ነው፡፡
ሥላሴ በአካል ሦስት ናቸው፡፡ በአካል ሦስትነት ስማቸው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይባላሉ፡፡ ይኸውም ማለት አብ
በህልውና ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚገናዘብ የራሱ የኾነ የተለየ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክእ ፍጹም አካል አለው፤
ወልድም በህልውና ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚገናዘብ የራሱ የኾነ የተለየ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክእ ፍጹም አካል
አለው፤ መንፈስ ቅዱስም በህልውና ከአብና ከወልድ ጋር የሚገናዘብ የራሱ የኾነ የተለየ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክእ
ፍጹም አካል አለው፡፡ የአካላት ሦስትነት ስንልም መጠቅለል መቀላቀል ሳይኖርባቸው በተከፍሎ በተፈልጦ በፍጹም ገጽ
በፍጹም መልክእ በየራሳቸው የቆሙ ናቸው፡፡ አካላቸው ሦስት በመሆኑ መለኮታቸው ን አይከፍለውም መለኮታቸውም
አንድ በመኾኑ አካላቸውን አይጠቀልለውም በአካላቸው ሦስት በመለኮታቸው አንድ ሲባሉ ይኖራሉ፡፡

ገጽ 4
“በአካል ሦስት ሲኾኑ በመለኮት አንድ ናቸው” ሃይ አበው
የአካላት ግብር 30 ሦስትነት
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዳቸው ልዩ የአካል ግብር አላቸው፡፡ የአብ ግብሩ መውለድ ማሥረጽ የወልድ ግብሩ
መወለድ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረጽ ነው፡፡ ይኸውም አንድነት የማያገናኘው ግብር ነው፡፡ አብን ወላዲ አሥራጺ
ወልድን ተወላዲ መንፈስ ቅዱስን ሠራጺ ብሎ ማመን ነው፡፡ በሥላሴ የአካላት ግብር መፋለስ እና መቀዳደም
የለባቸውም፡፡
‹‹ አብ ወላዲ ነው እንጂ ተወላዲ አይደለም፡፡ ወልድ ግን ተቀዳሚ ተከታይ ሳይኖረው ቅድመ ዓለም
ከብቻው ከአብ ተወለደ፡፡ መንፈስ ቅዱስም ከአብ ሠረጸ በቀዳማዊነት በአገዛዝ በሥልጣን በከሃሊነት
ፍጥረትን ሁሉ በመፍጠር ከአብ ከወልድ ጋር አንድ ነው፡፡ በመለኮት አንድ የሚሆኑ ሦስት አካላት ከመወሰን
ከቁጥር ሕግ ሁሉ የራቁ ናቸው፡፡›› (ሃይ.አበ ዘካርያስ ዘእስክንድርያ ምዕ 108 ቁ.2)
‹‹ እኛ ግን በመለኮት ባሕርይ መቀዳደም አለ ብለን ይህን ልንናገር አይገባም ከአብ ጋር በዘመኑ ሁሉ
በቅድምና የነበረ እንደሆነ በወልድ ዋሕድ እናምናለን እንጂ›› (ሃይ. አበ ዘቴዎይጦስ ምዕ 53 ክፍል 1 ቁጥር 9)
አብ ወልድን ቢወልድ መንፈስ ቅዱስን ቢያሠርጽ እንጂ እንደ ወልድ አይወለድም እንደ መንፈስ ቅዱስ አይሠርጽም፡፡
ወልድም ከአብ ቢወለድ እንጂ እንደ አብ አይወልድም እንደ መንፈስ ቅዱስ አይሠርጽም፡፡ መንፈስ ቅዱስም ከአብ
ቢሠርጽ እንጂ እንደ አብ አይወልድም እንደ ወልድ አይወለድም፡፡
የአካላት ግብር ምሳሌ
ለፀሐይ ክበብ ብርሃን ሙቀት አለው፡፡ በክበቡ አብ በብርሃኑ ወልድ በሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ ክበብ ብርሃንን
ሙቀትን ያስገኛል እንጂ ብርሃን ሙቀትን ክበብን አያስገኝም፡፡ ሙቀትም ክበብን ብርሃንን አያስገኝም፡፡
እንደዚሁም በክበብ የተመሰለ አብ በብርሃን የተመሰለ ወልድን በሙቀት የተመሰለ መንፈስ ቅዱስን ያስገኛል እንጂ
በብርሃን በሙቀት የተመሰሉ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በክበብ የተመሰለ አብን አያስገኙትም፡፡ ብርሃን ሙቀትን ሙቀት
ብርሃንን ሊያስገኝ እንደማይችል መንፈስ ቅዱስ ወልድን ወልድም መንፈስ ቅዱስን ሊያስገኝ አይችልም፡፡
ክበብ ሲገኝ ብርሃን ሙቀት አብረው ይገኛሉ እንጂ ክበብ ቀድሞ ብርሃን ሙቀት ኋላ የሚገኙ አይደሉም፡፡ እንደዚሁም
ወልድ መንፈስ ቅዱስ እንደ አብ ቅድመ ዓለም ህልዋን ናቸው እንጂ አብ በዘመን ቀድሟቸው ኋላ የተገኙ አይደሉም፡፡
(መድሎተ አሚን ገጽ 209)
የአብ የአካል ግብር
አብ ማለት ጥንት መሠረት መገኛ ማለት ነው፡፡ ጥንት መሠረት መገኛ በመሆኑም ወላዲ 31 አሥራጺ ይባላል፡፡ አብ
ወልድን ወልዷል መንፈስ ቅዱስን አሥርጿል፡፡
‹‹የአካላት ስማቸው በሐሰት የተጠሩበት አይደለም አብን አብ ብንለው ወልድን የወለደ መንፈስ ቅዱስን
ያሠረጸ ስለሆነ ነው፡፡ ወልድንም ወልድ ብንለው ከአብ ስለተወለደ ነው መንፈስ ቅዱስንም መንፈስ ቅዱስ
ብንለው ከአብ ስለሠረጸ ነው ለአብ ለወልድም እስትንፋሳቸው ስለሆነ ነው፡፡›› (ሃይ. አበ. ዘመቃርስ ምዕ. 98 ክ 1
ቁጥር 4)
‹‹ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድሁህ›› መዝ 109(110)፥3
‹‹ እግዚአብሔርም አለኝ፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ›› መዝ 2፤7
‹‹እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ:- በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ›› ማቴ 3፤17
‹‹ ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል›› ሉቃ 1፤35
የወልድ የአካል ግብር
የወልድ የአካል ግብር ከአብ መወለድ 32 ነው፡፡ ወልድ ከአብ ተወለደ ሲባል አብን አህሎ አብን መስሎ ‹‹ባለመቀዳደም››
‹‹ባለመከፋፈል›› እና ‹‹ባለመለያየት›› ከባሕርይው ተወለደ ማለት ነው፡፡
ወልድ ከአብ ሲወለድ አካሉ በተከፍሎ ቢለይም ህላዌ መለኮት 33 በተከፍሎ መለየት የለበትም፡፡አወላለዱም ብርሃነ
ፀሐይ ተከፍሎ መለየት ሳይኖርበት ከክበብ እንዲገኝ በህላዌ መለኮት ከአብ ተከፍሎ መለየት ሳይኖርበት ነውና መቅደም
መቀዳደም መብለጥ መበለጥ የለበትም፡፡

30. ሰንበተ ቀዳሚት ሰንበተ አይሁድ ወላዲ = የሚወልድ ወላጅ አስገኝ አባት ኪ.ወ.ክ ገጽ 390
31. ሰንበተ ቀዳሚት ሰንበተ አይሁድ ወላዲ = የሚወልድ ወላጅ አስገኝ አባት ኪ.ወ.ክ ገጽ 390
32. ተወላዲ=የተወለደ ተወላጅ ልጅ ኪ.ወ.ክ ገጽ 390
33. ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከባሕርይ አምላክ የተገኘ የባሕርይ አምላክ የተወለደ እንጂ የተፈጠረ ያይደለ ባሕርዩ ከአባቱ ጋር በመለኮቱ አንድ
የሚሆን፡፡ ሃይ. አበ. ዘሠለስቱ ምዕት ምዕ. 17÷5

‹‹ሰው አባት ከሆነ አባት ከልጁ እንዲቀድም ነገሩ የታወቀ ነው፡፡ አባት መባልም ከልጁ አስቀድሞ መኖሩን ያስረዳል፡፡ እኛ
ግን በመለኮት ባሕርይ መቀዳደም አለ ብለን ይህን ልንናገር አይገባም ከአብ ጋር በዘመኑ ሁሉ በቅድምና የነበረ እንደሆነ
በወልድ ዋሕድ እናምናለን እንጂ፡፡ የአብ አንድ ልጅ ብርሃን ይባላል ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከብርሃን በኋላ የተገኘ ነው

ገጽ 4
አይባልምና ያ ብርሃን በተገኘ ጊዜ ከርሱ የተወለደው ብርሃን ተገኝቶ ከርሱ ጋር ህልው ሆኖ ዘወትር ይኖራል እንጂ
ብርሃንም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር በጊዜው ሁሉ ከአብ ጋር ህልው የሚሆን የወልድን ነገር ያስረዳል፡፡›› (ሃይ. አበ ዘቴዎዶጦስ
ምዕ. 13 ክ 1 ቁ 8-10)

‹‹ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፡- አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ›› ማቴ 16÷16 (ሐዋ. 8÷37፣ ዮሐ. 3÷16፣
1 ኛዮሐ. 5÷12፣ ምሳ. 8÷25፣ ሚክ. 5÷2፣ ዮሐ. 20÷27)

የመንፈስ ቅዱስ የአካል ግብር


የመንፈስ ቅዱስ የአካል ግብር መሥረጽ 34 (መውጣት) ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ ወጣ (ሠረጸ) ሲባል የባሕርይ
ጸአት ነው፡፡ ማለትም ‹‹ያለ መከፈል›› ‹‹ያለመለየት›› እንዲሁም ‹‹ያለመቀዳደምና›› ‹‹ያለመከተል›› ነው፡፡ መንፈስ
ቅዱስ ከአብ ሠረጸ ማለት አብን አህሎ አብን መስሎ ከአብ ተገኘ ማለት ነው፡፡ 35
‹‹ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ
እርሱ ስለእኔ ይመሰክራል›› ዮሐ 15፣26
የኩነት (ኹኔታ) ሦስትነት
ኩነት (ታት) መኾን አኳኾን ኹነታ አናዎር፡፡ (ኪ.ወ.ክ ገጽ 525)
የኩነታት ሦስትነት እንደ አካላት አይደለም፡፡ አካላት መጠቅለልና መቀላቀል ሳይኖርባቸው በተከፍሎ በተፈልጦ በፍጹም
ገጽ በፍጹም መልክ በየራሳቸው የሚቆሙ ናቸው፤ ኩነታት ግን ተከፍሎ ተፈልጦ (መለየት መከፈል) ሳይኖርባቸው
በተዋሕዶና በተጋብኦ በአንድነት አካላትን በህልውና (አኗኗር) እያገናዘቡ በአንድ መለኮት የነበሩ ያሉ የሚኖሩ ናቸው፡፡
እነርሱም ከዊነ ልብ ከዊነ ቃል ከዊነ እስትንፋስ ናቸው፡፡
‹‹ከዊነ ልብ›› በአብ መሠረትነት ለራሱ ለባዊ ሆኖ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ዕውቀት (ማወቂያ) መኾን ነው፡፡ ‹‹ከዊነ
ቃል›› በአብ መሠረትነት ለራሱ ነባቢ ኾኖ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ንባብ (ማናገሪያ) መኾን ነው፡፡ ‹‹ከዊነ እስትንፋስ››
በአብ መሠረትነት ለራሱ ሕያው ኾኖ ለአብና ለወልድ ሕይወት መኾን ነው፡፡
ስለዚህ በአብ ልብነት ወልድ መንፈስ ቅዱስ ህልዋን ናቸው፤ ያስቡበታል፡፡ በወልድ ቃልነት አብ መንፈስ ቅዱስ ህልዋን
ናቸው፤ ይናገሩበታል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት አብ ወልድ ህልዋን ናቸው፤ ሕያዋን ኾነው ይኖሩበታል፡፡
ከዊነ ልብ በአብ መሠረትነት ለራሱ ዐዋቂ ሆኖ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ዕውቀት መኾን ነው፡፡
‹‹የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘላለም ይኖራል የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው›› መዝ 32(33)፤11
‹‹ ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ›› መዝ፤ 15(16)፤8-9
ከዊነ ቃል በአብ መሠረትነት ለራሱ ነባቢ (ቃል) ኾኖ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ንባብ (ቃል) መኾን ነው፡፡
‹‹ በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ›› መዝ 32(33)፤6
‹‹በመጀመሪያው ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ››ዮሐ 1÷1
‹‹ ቃልም ሥጋ ሆነ›› ዮሐ 1፤14
‹‹ ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደተዘጋጁ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት
እናስተውላለን›› ዕብ 11፤3
‹‹ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል›› ራዕይ 19፤13
ከዊነ እስትንፋስ በአብ መሠረትነት ለራሱ ሕያው ኾኖ ለአብና ለወልድ ሕይወት መኾን ነው፡፡

34. ሠረጽ፡- መሥረጽ አሥራጺውን አህሎ በባሕርይ በመልክ መስሎ ተካክሎ ከአሥራጺው አካል መውጣት መገኘት ያው ግን ተድኅሮ
ተመትሮ የባሕርይ ተከፍሎ ሳይኖር፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 679
35. ከአብ አህሎ መስሎ በተገኘ የባሕርይ ገዥ የባሕርይ ሕይወት በሚሆን በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን ከአብ ከወልድ ጋር እንስገድለት እናመስግነው
በነቢያት አድሮ የተናገረ እርሱ ነው፡፡ ሃይ. አበ. ዘሠልስቱ ምዕት ምዕ. 17÷11

‹‹ሰማዮች በእግዚአብሔር ቃል ጸኑ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ›› መዝ 32(33)÷6


‹‹እርሱ ልቡን ወደ ራሱ ቢመልስ መንፈሱንና እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢሰበስብ ሥጋ ለባሽ
ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፡፡ ኢዮ 34÷14
የኩነታት ሦስትነት በህልውና መገናዘብ

መገናዘብ አንድነትን መዋሐድን ያመለክታል፡፡ ይኸውም በኩነታት መገናዘብ የሚፈጸም ምሥጢር ነው፡፡ አብ በወልድ
በመንፈስ ቅዱስ ወልድ በአብ በመንፈስ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ በአብ በወልድ ህልዋን ስለኾኑ በአብ ልብነት ወልድ መንፈስ
ቅዱስ ህልዋን ናቸው፤ ያውቃሉ፡፡ በወልድ ቃልነት አብ መንፈስ ቅዱስ ህልዋን ናቸው፤ ይናገራሉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ
እስትንፋስነት አብ ወልድ ህልዋን ናቸው፤ ይተነፍሳሉ፡፡

ገጽ 4
‹‹እኛም ከአካላት አንዱም አንዱ ከአንድ መለኮት አንድነትን እንዲገናዘቡ አካላትም በመለኮት አንድነት ያለ ፍጻሜ
እንዲገናዘቡ እናምናለን፡፡ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ህልው ነውና ወልድም በአብ በመንፈስ ቅዱስ ህልው ነውና
መንፈስ ቅዱስም በአብ በወልድ ህልው ነውና›› (ሰንበተ ቀዳሚት ሰንበተ አይሁድ ሃይ. አበ. ዘዮሐንስ ምዕ. 90 ቁ 11)
‹‹ወልድም ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስም ለአብ ለወልድ እስትንፋሳቸው
ነው፡፡ የሦስቱ አካላት መለኮት አንድ እንደኾነ በዚህ ዐውቀን ለእርሱ እንሰግዳለን›› (ሃይ. አበ. አቡሊዲስ ዘሮም
ምዕ 39 ክፍል 2 ቁጥር 8-9)
‹‹እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁ ቃል ከራሴ አልናገርም ነገር ግን በእኔ
የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ›› ዮሐ 14፤10-11
‹‹እርሱ ያከብረኛል ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው ስለዚህ ለእኔ ካለኝ ወስዶ
ይነግራችኋል አልሁ›› ዮሐ 16፤14
የኩነት (የኹኔታ) ምሳሌ
ምሥጢረ ሥላሴን ጠልቆ ጠንቅቆ ማወቅ አይቻልም፡፡ ነገር ግን የሚቻለውን ያህል በጥቂቱ ለመረዳት መጻሕፍት
የሰጡንን የነፍስን ምሳሌነት እንመልከት፡፡
ነፍስ፡- ነፍስ አካሏ ባሕርይዋ አንድ ነው፡፡ ነገር ግን ሦስት ኹኔታዎች ልብነት ቃልነት እስትንፋስነት አሏት፡፡ ልብነቷ
ከሥጋዊ ልብ ጋር በመዋሐድ ዕውቀቱን ይሰጣል ቃልን እስትንፋስን ያስገኛል፡፡ ቃልነቷ በልብነቷ መሠረትነት ሥጋዊውን
አንደበት (ምላስ) በመዋሐድ ይገለጣል፤ የልቡናንም ኀሳብ ይገልጣል፡፡ እስትንፋስነቷ በልብነቷ መሠረትነት ከሥጋዊ
እስትንፋስ ጋር ተዋሕዶ ለሰው ሕይወት ይሆናል፡፡
ልብ ቃል እስትንፋስ በመኾን እየተገናዘቡ በሚሠሩት ሥራ ልዩነት የለባቸውም፡፡ ነፍስ በአካሏ ለአንዲት ባሕርየ ሥላሴ
በሦስቱ ኹኔታዎች ለሦስቱ አካላት ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምሳሌነቷን ትሰጠናለች፡፡
የነፍስ አካሏ አንድነት የኹኔታዋን ሦስትነት እንዳይጠቀልለው እንዳያቀላቅለው የኹኔታዋ ሦስትነት አካሏን
እንዳይከፍለው እንዳይነጥለው ሥላሴም በልብነቷ አብ በቃልነቷ ወልድ በእስትንፋስነቷ መንፈስ ቅዱስ ሲመሰል የአንዲት
ባሕርያቸው ምሳሌ አንዲት አካለ ነፍስ ናትና የሥላሴ የባሕርያቸው አንድነት የአካላቸውን ሦስትነት አይጠቀልለውም
አይነጥለውም፡፡ ስለዚህ ነፍስ አንዲት ብትባል ሦስት እንዳትባል አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም አንድ አምላክ ይባላል እንጂ
ሦስት አምላክ አይባልም፡፡ 36
የአንድነት ምሥጢር
እግዚአብሔር በአካላት በኩነታት ሦስት በባሕርይ በህልውና በመለኮት በመፍጠር በመግዛት በሥልጣን በመንግሥት
አንድ ነው፡፡
‹‹እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ሦስት ሦስት ሲሆን አንድ እንደሆነ እንናገራለን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ
አንድ ባሕርይ አንድ መለኮት አንድ መንግሥት አንድ ኀይል አንድ አገዛዝ ናቸው ከእነርሱም አንዱም አንዱ
ፈጣሪ ገዢ እንደሆነ ይታወቃል፡፡›› (ሃይ. አበ ዘዲዮናስዮስ ምዕ 101 ክ 1 ቁ 2)

36. ሰንበተ ቀዳሚት ሰንበተ አይሁድ ሰው በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ በመፈጠሩ ለምሥጢረ ሥላሴ ምሳሌ
ሆኗል፡፡ ዘፍ. 1÷26-27
የባሕርይ አንድነት
ሥላሴ በባሕርይ አንድ ናቸው ሲባል ሁሉን ማወቅ ሁሉን መቻል ሁሉን መፈጸምና ማከናወን የባሕርይ ገንዘባቸው
ሲሆን ተለይቶ ዐዋቂ ዐሳዋቂ ቻይ አስቻይ ፈጻሚ አስፈጻሚ ሳይኖርባቸው እኩል ናቸው ማለት ነው፡፡ ዘጸ. 20÷2-4 ዘዳ
6÷4
የህልውና አንድነት
ህልውና ማለት አንዱ ባንዱ መኖር ነው፡፡ ይኸውም በኩነታት መገናዘብ የሚፈጸም ምሥጢር ነው፡፡ አካላትን አንድ
አምላክ የሚያሰኛቸው ህልውና ነው፡፡ ህልውናቸውም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐ. 10፣38 “እኔ በአብ እንደ
አለሁ አብም በእኔ እንደ አለ ታውቁ ትረዱ ዘንድ ስለ ሥራዬ በእኔ እመኑ” ብሎ ገልጾ ያስረዳው ነው፡፡ ዮሐ 14፣10-12

የመለኮት አንድነት
መለኮት ማለት አምላክነት ፈጣሪነት አምላክ መኾን ፈጣሪ መኾን የአምላክ ጠባዩ ኹኔታው ቅድስት ሥላሴን
የሚያዋሕድ የሚያስተባብር አንድ አምላክ የሚያሰኝ ፈጥሮ መግዛትና መፍጠር ማስገኘት የባሕርያቸው ስለሆነ
ባሕርያቸው በግብር ስሙ መለኮት ይባላል፡፡ (ኪ.ወ.ክ ገጽ 595)
የመለኮት ትርጓሜ ልዩ ልዩ ነው፡፡
1. ሕይወት፡- “መለኮት ሞተ ብትል አንተ የሥሉስ ቅዱስ ገዳያቸው እንድትሆን አታውቅም፡፡
የሥላሴ ባሕርይ ፩ ነው ይኸውም አንድ መለኮት ነው” (ሃይ. አበ አግናጥዮስ ዘአንዶኪያ
ምዕ. 11 ቁ 13-14)
2. አገዛዝ፡- ፍጥረቶቹ ሁሉ በግዛቱ ሥፍራ ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል (መዝ

ገጽ 4
102(103)፣22)
3. አምላክነት፡- “አብ አምላክ ነው ወልድ አምላክ ነው መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው ነገር ግን
አንድ አምላክ ይባላል እንጂ ሦስት አማልክት አይባልም” (ሃይ. አበ ዘአትናቴዎስ ምዕ.
25 ቁ 4)
“በአምላክነቱ ኃይል ወደ ጽድቅና ወደ ቅድስና ወደ ሕይወት የሚወስደውን በጎ ነገር ኹሉ የሰጠንን ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስን አምላካችንን በማወቅ ሰላምና ክብር ይብዛላችሁ” 2 ጴጥ 1፣2-3
4. ክብር፡- “ከዚህ ዓለም ርኩሰት ተለይታችሁ የክብሩ ወራሾች እንድትሆኑ በሰጠን ተስፋ በክብር ከፍ ብለን በምንኖር
ገንዘብ ወደ ሃይማኖት ወደ ልጅነት የጠራን እርሱ ነው” 2 ጴጥ 1፣4
5. ባሕርይ፡-“በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ
በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል” ቆላ 2፣8-9

ምሥጢረ ሥላሴ በቅዱሳት መጻሕፍት

የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት በልዑል እግዚአብሔር የተጀመረ መሠረታዊ ትምህርት ነው፡፡ ይህንንም የሚያረጋግጥልን
መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡
ብሉይ ኪዳን
ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አንዱ በሆነው ብሉይ ኪዳን የቅድስት ሥላሴን አንድነትና ሦስትነት በምሥጢርና በምሳሌ
ካልሆነ በቀር በገሃድ ተገልጦና ተብራርቶ አናገኘውም፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ኹኔታ እንኳን ቢሆን በሐዲስ ኪዳን
ለሚገለጠው ረቂቅና ጥልቅ ስለሆነው የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት ትምህርት መቅድም ሆኖ ያግዛል፡፡

‹‹ እግዚአብሔርም አለ፡- ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር›› ዘፍ 1፣26


‹‹ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ›› ዘፍ 3፣22
‹‹ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው›› ዘፍ 11፣7
‹‹ ዓይኑን አነሣና እነሆ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ
ተነሥቶ ሮጠ ወደ ምድርም ሰገደ እንዲህም አለ አቤቱ በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን
አትለፈኝ፡፡›› ዘፍ 18፣2-3
‹‹ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብርህ ተሞልታለች፡፡›› ኢሳ 6፣3
‹‹ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል›› ኢሳ 48፣16

ሐዲስ ኪዳን

የቅድስት ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በተሻለ በታወቀና በተረዳ መልኩ ተብራርቶ የተገለጠውና የተቀመጠው ከብሉይ
ኪዳን ይልቅ በሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ምክንያቱም ደግሞ የአምላክ ሰው መሆን ምሥጢር የተገለጠው በዚሁ በሐዲስ ኪዳን
በመኾኑ ነው፡፡
‹‹ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ
እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ፡- በእርሱ ደስ የሚለኝ
የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ›› ማቴ 3÷16-17
‹‹የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስም ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር
ይሁን፡፡ አሜን፡፡›› 2 ኛቆሮ 13፣13 ማቴ 28፣19 ማቴ 16፣12-15

መንፈስ ቅዱስ (ጰራቅሊጦስ)

መንፈስ፡- በቁሙ መንፈስ ቅዱስ ባሕርያዊ አካላዊ ሕይወት እንደ ነፍስ ፍጡር እንደ ነፋስ ዝርው ያይደለ የሥላሴ
ሦስተኛ አካል ከአብ የሚሠርጽ ነው፡፡ (ሰንበተ ኪ.ወ.ክ ገጽ 648)
ጰራቅሊጦስ (ጽርእ)፡- ናዛዚ፣ መንጽዒ፣ መስተፍሥሒ 37 መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
‹‹እግዚአብሔር መንፈስ ነው›› ዮሐ. 4÷24 (ኪ.ወ.ክ ገጽ 907)
በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጸው ቤተ ክርስቲያን ምሥጢራትን በመንፈስ ቅዱስ ትቀድሳለች በምሥጢራት አማካኝነት
የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ለምእመናን ትናኛለች፡፡ የክርስቲያኖችን እምነት በቤተ ክርስቲያን የሚጠብቅ (የሚያስፋፋ)
መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡
የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት

ገጽ 4
ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት አድርጋ መንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ሥላሴ
አካላት አንዱ የባሕርይ አምላክ አካላዊ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር ሁሉን የፈጠረ መሆኑን ታስተምራለች፡፡
(ሰንበተ 2 ኛቆሮ. 13÷14፣ 1 ኛቆሮ. 2÷10-12)
መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ነው
መንፈስ ቅዱስ የራሱ የሆነ የተለየ አካል አለው፡፡ የመንፈስ ቅዱስ አካል የማይታይና የማይዳሰስ ብቻ ሳይሆን ሕይወት
ያለው ባለአእምሮ ፈቃድና ኀይል ያለው ከአብና ከወልድ ጋር በተለየ ኹኔታ በተለየ መልክ የሚታወቅ ነው፡፡ የመንፈስ
ቅዱስ አካል እንደ አብና እንደ ወልድ መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ያስተምሩናል፡፡ ጌታችን በአብ በወልድ በመንፈስ
ቅዱስ ስም እንዲያጠምቁ ሐዋርያትን ሲያዛቸው መንፈስ ቅዱስ የተለየ ስም የተለየ አካል የተለየ ግብር እንዳለው
ያስረዳል፡፡ ማቴ. 28÷19፣ (ዮሐ.14÷16፣ ማቴ.3÷16፣ ሉቃ.3፥22፣ ዘፍ.18÷1፣ ኢሳ.48÷16)
መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ የሠረጸ ነው
መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ መሥረጹ በአንቀጸ ሃይማኖት ተገልጿል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሠረጸ ነው ስንል ከአብ
የወጣ የተገኘ ማለት ነው፡፡ ወልድ ከአብ እንደተገኘ መንፈስ ቅዱስም ከአብ ተገኝቷል፡፡ ከፀሐይ አካል ሙቀት እንደሚገኝ
መንፈስ ቅዱስም ከአብ ሠርጿል፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት በተጻፈው መሠረት መንፈስ ቅዱስ ከአብ መሥረጹን
(መውጣቱን) እናምናለን፡፡ የመንፈስ ቅዱስ መውጣት ወይም መገኘት ከአብ ብቻ ነው፡፡
‹‹ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ‹‹ከአብ የሚወጣ›› የእውነት መንፈስ በመጣ
ጊዜ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል›› ዮሐ. 15÷26
‹‹ከአብ በሠረጸ ከአብ ከወልድ ጋር በሚመሰገን በሚሰገድለት በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን›› (ሃይ. አበ.
ዘቆዝሞስ ምዕ. 97 ክ 1 ቁ 1)
መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ ነው
ቅድስት ሥላሴ በመፍጠር በመለኮት በአገዛዝ አንድ ስለሆኑ መንፈስ ቅዱስም ፈጣሪ ነው፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ፈጣሪነት
ከጥንት ፍጥረት ጀምሮ የተገለጸ ነው፡፡
‹‹የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወትን ሰጠኝ›› ኢዮ.
33÷14፣ (ዘፍ. 1÷1፣ ኢዮ. 26÷13፣ መዝ. 104÷30፣ መዝ. 33÷6)

37. በአማርኛ አረጋጊ አጽናኝ አስደሳች ማለት ነው፡፡

ማጠቃለያ
 እግዚአብሔር በአካል፣ በስም፣ በአካላት ግብር በኩነት ሦስት በባሕርይ በሕልውና በመለኮት አንድ ነው፡፡
 አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይባላል እንጂ ሦስት አማልክት አይባሉም፡፡
 አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዳቸው ልዩ የአካል ግብር አላቸው፡፡የአብ ግብሩ መውለድ ማሥረጽ
የወልድ ግብሩ መወለድ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረጽ ነው፡፡
 መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ ሠርጿል፡፡
 የአካላትና የኩነታት ሦስትነት አንድ አይደለም፡፡ አካላት መጠቅለልና መቀላቀል ሳይኖርባቸው በተከፍሎ
በተፈልጦ በፍጹም መልክ በየራሳቸው የቆሙ ሲሆኑ ኩነታት ተከፍሎ ተፈልጦ ሳይኖርባቸው በተዋሕዶ የነበሩ
ያሉ የሚኖሩ ናቸው፡፡
3.2 ምሥጢረ ሥጋዌ
መግቢያ
ምሥጢረ ሥጋዌ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ብለን ከምናምንባቸው ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል
እግዚአብሔር ወልድ ቃል ሥጋ ኾነ ብለን የአምላክን ሰው መኾን የሰውን አምላክ መኾን የምናምንበት ክፍል ነው፡፡
ሥጋዌ ማለት ምን ማለት ነው?
ሥጋዌ የሚለው ቃል መነሻው “ተሠገወ” የሚለው የግእዝ ቃል ነው፡፡ ተሠገወ ማለት ሥጋ ሆነ፣ሥጋ ለበሰ፣ ጎላ፣ ገዘፈ
ማለት ሲሆን ሥጋዌ ማለት ሥጋ መኾን ሰው መኾን ማለት ነው (ኪ.ወ.ክ ገጽ 661) ምሥጢረ ሥጋዌ አካላዊ ቃል ወልድ
ሰውን ለማዳን ሲል ሰው የሆነበት ሰውንም ያዳነበት መለኮትና ትስብእት በተዋሕዶ አንድ የሆኑበት ምሥጢር ነው፡፡
አካላዊ ቃል ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ በባሕርይ በህልውና፣ በአገዛዝ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ
ቅዱስ እኩል በመኾን በአንድነት ሲወደስ በሦስትነት ሲሠለስ ነበር፡፡
‹‹እኛን ስለማዳን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ሆነ››
(ሃይ አበ ዘሠልስቱ ምዕት ምዕ. 17 ቁ 7)

ገጽ 4
የወልደ እግዚአብሔር ኹለት ልደታት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኹለት ልደታት አሉት፡፡ እነዚህ ልደታትም ቀዳማዊ ልደት ከአብ በመለኮት
ደኃራዊ ልደት ከድንግል ማርያም በሥጋ የተወለዳቸው ናቸው፡፡ የጌታችን ልደት የባሕርይ ልደት ነው፡፡ የባሕርይ ልደት
የባሕርይ አባትን የባሕርይ እናትን መስሎ ተካክሎ መወለድ ነው፤ መብለጥና ማነስ የለበትም፡፡
ወልድ ከአብ ሲወለድ ያለ እናት ከወላዲተ አምላክ ከእመቤታችን ሲወለድ ያለ አባት በመወለዱ ልደቱ የባሕርይ ነው፡፡
በቀዳማዊ ልደቱ አብን አህሎ አብን መስሎ የተወለደ ሲኾን በደኃራዊ ልደቱ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ
ነሥቶ በመዋሐድ ተወልዷልና የባሕርይ ልደት እንለዋለን፡፡
“ኹለት ልደታትን እናምናለን” (ሃይ አበ ዘሳዊሮስ 84 ክ 1 ቁ 25፣ ሃይ አበ ባስልዩስ ዘቂሳርያ 34 ክ 5 ቁ 6)
ቀዳማዊ ልደት
ቀዳማዊ ልደት ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እግዚአብሔር ወልድ ከእግዚአብሔር አብ የሰው ኅሊና
በማይመረምረው ምሥጢር የተወለደው ልደት ነው፡፡ ልደቱም እንደ ሰው ልደት ሳይሆን ከአብ አካል ዘእም አካል
ባሕርይ ዘእም ባሕርይ ተወልዶ ከአባቱ ሳይከተል አባቱን አህሎ አባቱን መስሎ የተገኘበት ረቂቅ ጥበብ ነው፡፡
“አብ ጥንት ፍጻሜ የሌለው ቃልን ዓለምን ከመፍጠሩ አስቀድሞ ወለደው” (ሃይ.አበ ዘኤጲፋንዮስ ምዕ.54 ክ 1 ቁ 11)
“የወልድ ከአብ መወለድ የማይመረመር ሊናገሩትም የማይቻል ነው፡፡ የማይመረመር ረቂቅ ስለኾነ ግዙፉ ረቂቁን
መርምሮ ማወቅ የማይቻለው ነውና፡፡ የእርሱንም ነገር ይመረምር ዘንድ አይቻለውም፡፡ ከሰው ባሕርይ ጋር
አይመሳሰልምና ልደቱም እንደ ሰው ልደት አይደለም ረቂቅ ምሥጢር ነው አይመረመርም” (ሃይ. አበ ዘጎርጎርዮስ ምዕ
13 ክ 11 ቁ 12)
“ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድሁህ” መዝ 109፣3

ደኃራዊ ልደት
በደኃራዊ ልደት ቃለ እግዚአብሔር ወልድ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ
ነሥቶ ሰው ሆነ፡፡ ደኃራዊ ልደት ዓለም ከተፈጠረ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዓመት ከተፈጸመ በኋላ እግዚአብሔር
ወልድ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው ኹለተኛ ልደት ነው፡፡ ይህ ደኅራዊ ልደቱ እንደ ቀዳማዊ ልደቱ በረቂቅ
ሳይሆን የሰውን ግዙፍ ሥጋ ከእመቤታችን በመንሣት ነው፡፡ ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከአብ እንደ ተወለደ በኋላም
ከእመቤታችን ያለ አባት ተወለደ፡፡ ከእመቤታችን ያለ አባት መወለዱም ከአብ ያለ እናት መወለዱን ያስረዳል፡፡
“ልደት ቀዳማዊ ተአወቀ በደኅራዊ ልደት” (ሃይ. አበ. ሱኑትዩስ)
“ዛሬ ግን ከድንግል ብቻ ተወለደ፣ ድንግልናዋንም ባለመለወጥ አጸና ድንቅ የሚሆን መፅነስዋ የታመነ ይሆን
ዘንድ ቅድመ ዓለም ከአብ እንደ ተወለደም ለማመን መሪ ይሆን ዘንድ” (ሃይ. አበ ዘጎርጎርዮስ ምዕ. 6 ክ 1 ቁ 20)
“ነገር ግን ቀጠሮው በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከሴትም ተወለደ የኦሪቱንም ሕግ ፈጸመ” ገላ 4፣4
የወልደ እግዚአብሔር ልደታት በሊቃውንት መጻሕፍት
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማንያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኹለት ልደታት እንዳሉት
እናምናለን፡፡ ይኸውም ቀዳማዊ ልደትና ደኀራዊ ልደት ብለው አባቶቻችን ያስተማሩን ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት
ድኅረ ዓለም ከእመቤታችን ያለ አባት የተወለደው ልደት ነው፡፡
“ቅድመ ዓለም በመለኮቱ ከአብ ተወለደ በኋላ ዘመንም ዳግመኛ እኛን ለማዳን ከድንግል ማርያም አንድ አካል
አንድ ባሕርይ ሆኖ በሥጋ ተወለደ” (ሃይ. አበ ዘቄርሎስ 73 ክ 14 ቁ 24)
“ዳግመኛ ለወልደ እግዚአብሔር ኹለት ልደታት እንዳሉት እናምን ዘንድ ይገባናል እንጂ ከዘመን ኹሉ አስቀድሞ
ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው ልደት ነው፡፡ ኹለተኛውም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በኋላ
ዘመን የተወለደው ልደት ነው” (ሃይ. አበ ዘባስልዩስ ምዕ 34 ቁ 6)
“ኹለት ልደት እንዳለው በእግዚአብሔር ቃል እንዲሁ ልናምን ይገባናል አንዱ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት
የተወለደው የማይመረመር ልደት ነው፡፡ ኹለተኛውም በኋላ ዘመን ከንጽሕት ድንግል ማርያም ያለ አባት
የተወለደው የማይመረመር የማይነገር ልደት ነው” (ሃይ. አበ ዘሳዊሮስ ምዕ 84 ቁ 8)
“ወልደ አብ ወልደ ማርያም ኹለት ልደት በተዋሕዶ ከበረ” ሃይ. አበው

“ወልድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማይመረመር ተዋሕዶ ሰው የኾነ አምላክ ነውና ቀዳማዊ ሲሆን ከዘመናት
አስቀድሞ ከአብ የተወለደ ነው ዳግመኛም ከድንግል በሥጋ የተወለደ ነው ተብሎ ስለርሱ እንዲህ ይነገራል፡፡
(ሃይ. አበ ዘቄርሎስ 73 ክ 11 ቁ 4፣ ሃይ. አበ ዮሐንስ ምዕ. 62 ክ 5 ቁ 3 ሃይ. አበ ዘቄርሎስ 78 ክ 48 ቁ 9)

ገጽ 4
አምላክ ለምን ሰው ሆነ?

ሁሉን የፈጠረ ሁሉን ቻይ ሁሉን የያዘና ሁሉን የሚጠብቅ እግዚአብሔር አምላክ ምንም የሚሳነው ነገር የለም፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ከሃሊነት ገንዘቡ ነውና ሰው ሳይሆን ሰውን ማዳን ሲችል ለምን ሰው ሆነ?
እግዚአብሔር ወልድ ሰው የሆነው ከባሕርይው ከምትነሣ መልካምነት ከባሕርይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብና ከባሕርይ
ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፍጹም መልካምነት የተነሣ ነው፡፡ ስለሰው ልጆች ዘለዓለማዊ ድኅነት ሲባል
የተደረገ ነው፡፡
ሰብእ (ሰው) ማለት ምን ማለት ነው?
ሰብእ፡- ባሕርያዊ ስም በቁሙ ሰው፣ አዳም፣ የአዳም ዘር ሁሉ ነፍስና ሥጋ ያለው ከነፍስ ከሥጋ አንድ የሆነ፣ ሥጋ ብቻ
ወይም ነፍስ ብቻ ያይደለ ነው፡፡ (ኪ.ወ.ክ ገጽ 843)
የሰው ተፈጥሮ
እግዚአብሔር አምላክ ከእሑድ እስከ ዓርብ ድረስ የሚያስፈልጉትን ሁሉ ከፈጠረ በኋላ በስድስተኛው ቀን ሰውን
ፈጠረ፡፡ ግዙፍ አካል ሥጋን ከአራቱ ባሕርያት ከፍሎ አገናኝቶ በሥጋ አለስልሶ፣ በደም አርሶ፣ በጅማት አያይዞ፣ በአጥንት
አጽንቶ፣ ረቂቅ አካል ያላት ነፍስን እውቀት ቃል ሕይወት ሰጥቶ ሥጋንና ነፍስን አዋሕዶ 38 ፈጠረው፡፡ የሰው ልጅ
በአፈጣጠሩም ሆነ በተፈጠረበት ዓላማ ከሌሎች ፍጥረታት ይለያል፡፡ ሰው ከእንስሳት ጋር በባሕርያተ ሥጋ ከመላእክት
ጋር በግብራተ ነፍስ ይገናኛል፡፡ እግዚአብሔር ሌላውን ፍጥረት ሁሉ የፈጠረው በእጁ ሳይሆን በሃልዮና በነቢብ ነው፡፡
ሰውን ግን በሃልዮ በነቢብ በገቢር ሦስቱንም አጣምሮ ፈጠረው፡፡ ሰው ከሌሎች ፍጥረታት የሚለየው በእግዚአብሔር
መልክና ምሳሌ በመፈጠሩ ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚመስለው ሰው ብቻ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ክብር ያለው
መሆኑ የታወቀው በአምሳሉ ሲፈጠር ነው፡፡
‹‹እግዚአብሔርም አለ፡- ሰውን በመልካችን እንደምሳሌአችን እንፍጠር›› ዘፍ 1÷26
“እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት
ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ” ዘፍ 2÷7
የሰው ነጻ ፈቃድ
ነጻ ፈቃድ ማለት አንድ ሰው አንድን ድርጊት ለመፈጸም ወይም ላለመፈጸም ያለው ፍላጎትና ነጻነት ነው፡፡
እግዚአብሔር ሰውን በሕያዊት ነፍስ አክብሮ ነጻነት ያለው ክፉውንና በጎውን መለየትና መምረጥ የሚችል ዐዋቂና
አስተዋይ አድርጎ ፈጠረው፡፡ ሰው በነጻ ፈቃዱ ተጠቅሞ በኅሊው አስቦና አገናዝቦ ይበጀኛል የሚለውን ለመሥራትና
ለመምረጥ መብት የተሰጠው ከሞትና ሕይወት አንዱን ይመርጥ ዘንድ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ወደ ሕይወትና ሞት
የሚመሩት ኹለት መንገዶችን ያኖረለት በመሆኑ ሕይወትን ወይም ሞትን መምረጥ ለሰው የነጻ ፈቃድ ምርጫ የተሰጠ
ነው፡፡
“ተመልከት ዛሬ በፊትህ ሕይወትንና መልካምነትን ሞትንና ክፋትን አኑሬአለሁ” ዘዳ 30፣15፣
(ሲራክ 15÷15-17፣ ማቴ 23÷27)
እግዚአብሔር የሰጠው ትእዛዝ
አዳም በተፈጠረ በ፵ ቀኑ ሔዋንም በተፈጠረች በ፹ ቀኗ የልጅነት ጸጋ ከሥላሴ ተቀብለው ቅዱሳን መላእክት የብርሃን
ልብስ አጎናጽፈው፣ የብርሃን ዘውድ አቀዳጅተው፣ የብርሃን በትር አስይዘው፣ በብርሃን ሠረገላ አስቀምጠው
ከተፈጠሩባት ኤልዳ ወደ ገነት አስገቧቸው፡፡ 39
“በተፈጠረበት ምድር ለአዳም አርባ ቀን ከተፈጸመለት በኋላ ይገዛትም ይጠብቃትም ዘንድ ወደ ገነት አስገባነው፡፡
ሚስቱንም በሰማንያ ቀን አስገባናት” ኩፋ. 4÷9
እግዚአብሔር ለሰው መኖሪያነት ባዘጋጃት ገነት ዕፀ-ምግብ፣ ዕፀ-በለስ፣ ዕፀ-ሕይወት ነበሩ፡፡ አዳምና ሔዋን ዕፀ-በለስን
ሳይበሉ ጠብቀው አንድ ሺ ዘመን ከኖሩ በኋላ በዕፀ-ሕይወት እንዲታደሱ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፡፡ እግዚአብሔር
ለአምላክነቱ መታወቂያና ለቅዱስ ስሙ መታሰቢያ ከምትሆን ዕፀ-በለስ በቀር ለሰው ሁሉን ዕፀ-ገነት የፈቀደለት ሲኾን
ከዚህች ዛፍ እንዳይበላ አስጠንቅቆታል፡፡ ዕፀ-በለስን እንዲጠብቃት ከፍሬዋ እንዳይበላ ያዘዘው ለፈጣሪው ወድዶ
መታዘዙና መገዛቱ ይታወቅ ዘንድ ነው፡፡
‹‹ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ ነገር ግን መልካምንና ክፉውን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ
ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ›› ዘፍ. 2÷17
የሕግ ርግማን (ጥንተ አብሶ)
የሰው ልጅ የተሰጠውን ትእዛዝ በማፍረስ ስለበደለ የሞትና የርግማን 40 ፍርድ ተፈረደበት፡፡ የተከለከለውን ፍሬ በበላህ
ቀን ሞትን ትሞታለህ ተብሎ ስለተወሰነና ትእዛዙ ስላልተከበረ የሞት

ገጽ 4
38. ሥነ ፍጥረት ገጽ 61
39. መጽሐፈ አክሲማሮስ
40. ርጉም፡- በቁሙ የተረገመ ክፉ መጥፎ ውጉዝ ማቴ. 25÷41 ኪ.ወ.ክ ገጽ 822
ፍርድና የሕግ ርግማን በአዳምና በልጆቹ ሁሉ ላይ ደረሰ፡፡ አዳምና ሔዋን በበደላቸው ከክብራቸው ተዋረዱ ከጸጋቸው
ተራቆቱ፣ ከተድላ ገነት ወጡ፣ በሥራቸው በራሳቸው ላይ መከራን አመጡ ለአጋንንትም ተገዢዎች ሆኑ፡፡ በኃጢአት
ምክንያት ወደ ዓለም የገባው ሞት በሰው ላይ ሠለጠነ፡፡ ይህ ሁሉ መከራ የመጣባቸው ሕገ እግዚአብሔርን
በመተላለፋቸው መሆኑን አውቀው ተጸጸቱ ንስሐ ገብተው ፈጣሪያቸውን ለመኑት፡፡ እግዚአብሔርም በፈታሒነቱ
አንጻር መሐሪነቱ አለና የአዳምንና የሔዋንን ንስሐቸውን ተቀብሎ ሊያድናቸው ወድዶ ተስፋም ሰጣቸው፡፡
“አዳምንም አለው፡- የሚስትህን ቃል ሰምተኃልና ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም
በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን” ዘፍ 3፣17
‹‹ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ‹‹ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ›› እንኳ ከአዳም ጀምሮ
እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነው›፡ሮሜ.5÷14
ለሰው ልጅ የተሰጠው ተስፋ
እግዚአብሔር የአዳምን የንስሐ ዕንባ አይቶ ይቅር ባይና ሰውን ወዳጅ አምላክ በመሆኑ ከገነት ቢያባርረውም አዳም
የኖረው በገነት አቅራቢያ ነበር፡፡ ይኽም አዳም ተስፋ ቆርጦ እንዳይቀር ከኅሊናው ውስጥ የተስፋ ስንቅ እንዲሰንቅ
እግዚአብሔር የተጠቀመው ጥበብ ነው፡፡ አዳም በተወሰነበት የርግማንና የሞት ፍርድ ስላዘነና ስለጸለየ እግዚአብሔር
ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንዲያድነው ተስፋ ሰጠው፡፡
የተሰጠው ተስፋ የሚፈጸምበት ዘመን በደረሰ ጊዜ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲያገኝ ልዑል
እግዚአብሔር ተቀዳሚ ተከታይ የሌለውን አንድያ የባሕርይ ልጁን ወደ ዓለም ላከው፤ እግዚአብሔር ወልድም ከሰማየ
ሰማያት ወርዶ ንጽሕት ከምትሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ሆኖ ተወለደ፡፡
ከተወለደም በኋላ ከኀጢአት በቀር ሰው የሚሠራውን ሥራ ሁሉ እየሠራ አደገ፤ በዚህም ዓለም ሠላሳ ሦስት ዓመት
ከሦስት ወር ኑሮና አስተምሮ ስለእኛ የሞት ፍርድን ተቀበለ በመስቀል ተሰቅሎ ሞተ፣ በሞቱም ሞትን አጠፋ፣ ዓለምን
አዳነ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር አድሮ ተነሣ፡፡ በመላእክት ምስጋናና ክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
“በአንተና በሴቲቱ መካከል በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል አንተም
ሰኮናውን ትቀጠቅጣለህ” ዘፍ 3፣15፣ (ገላ 4÷4)
ምሥጢረ ሥጋዌና ነገረ ድኅነት
የሰው ልጅ የፈጣሪውን ቃል ትቶ የሰይጣንን ምክር ሰምቶ አምላኩን ካደ በሰው ልጆች ላይም ሞትና መርገም
ራቁትነትና ስደት ደረሰ፡፡ የሰው ልጅ ሁሉ በአዳምና በሔዋን በመጣው ፍዳና መርገም ምክንያት ከደረሰበት ነገር ሁሉ
ያድነው ዘንድ የሚችለው ደግሞ እግዚአብሔር ብቻ ነበር፡፡ ስለዚህም አካላዊ ቃል ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል
ማርያም ሰው ሆነ፡፡
‹‹ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ብዙ ጊዜ ራሱን ሊያቀርብ አልገባም
እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ
ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጧል›› ዕብ. 9÷25-26
ጌታችን በብሥራተ መልአክ በድንግል ማርያም ማኅፀን ከመፀነስ ጀምሮ ያደረገልን ሁሉ መወለዱ፣ በየጥቂቱ ማደጉ፣
መሰደዱ፣ መጠመቁ፣ ማስተማሩ፣ ተአምራት ማድረጉ፣ ሕግጋትን መቀበሉ፣ መሞቱ፣ መነሣቱ ማረጉ፣ ጸጋ መንፈስ
ቅዱስን መላኩ እያንዳንዳቸው ለመዳናችን ወሳኞችና አስፈላጊዎች ናቸው፡፡
መዳን እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠን ነጻ ስጦታ ነው፡፡ የሰዎች ድርሻ በዚህ የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ መጠቀም ነው፡፡
እኛን ለማዳን የሚያስፈልገውን ነገር እግዚአብሔር ፈጽሟል፤ የሚቀረው የእያንዳንዱ ድርሻ ነው፡፡
‹‹ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን በጸጋ
ድናችኋልና በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን
ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን፡፡
ጸጋው በእምነት አድኗችኋልና ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ማንም እንዳይመካ
ከሥራ አይደለም፡፡›› ኤፌ. 2÷5-10፣ (ገላ. 3÷13)
ለመዳን የሰው ልጅ ለዚህ የእግዚአብሔር ስጦታ በጎ ምላሽ መስጠትና ድኅነትን ያገኝበት ዘንድ በተነገረው መንገድ
መሄድና መዳንን ገንዘብ ማድረግ ነው፡፡ ከእነዚህም የመጀመሪያው ማመን ነው፤ ኹለተኛው ደግሞ መጠመቅና በሜሮን

ገጽ 4
መታተም እና ቅዱስ ቁርባንን መቀበል ናቸው፡፡ (ማር. 16÷16፣ ዮሐ. 3÷3፣ ዮሐ. 6÷53፣ ቲቶ. 3÷5፣ 1 ኛዮሐ. 2÷20፣ ኤፌ.
4÷4)
በምሥጢረ ጥምቀት የኀጢአት ሥርየት፣ የእግዚአብሔር ልጅነት በልጅነት ደግሞ መንግሥተ ሰማያትን መውረስ፣
ከክርስቶስ ጋር በሞቱና በትንሣኤው መሳተፍ ክርስቶስን መልበስ እንደሚገኝ፣ ያለ ጥምቀትም ከእነዚህ ጸጋዎች
አንዳቸውም እንደማይገኙ እናምናለን፡፡ በምሥጢረ ሜሮንም ሰውነታችን ለእግዚአብሔር እንደሚታተም እናምናለን፡፡
ምሥጢረ ቁርባን ደግሞ ኅብስቱ ተለውጦ የክርስቶስ አማናዊ ሥጋ ወይኑም ተለውጦ አማናዊ የክርስቶስ ደም
እንደሚሆንና በዚህ ምሥጢርም የዘላለም ሕይወትና ከክርስቶስ ጋር መዋሐድ እንደሚገኝ እናምናለን፡፡ እነዚህን ምሥ
ጢራት ከመሳተፍ በተጨማሪ ሰው ለመዳን የተቀበለውን የመዳን ጸጋ አጽንቶ ለመያዝ መንፈሳዊ ተጋድሎ እና
ክርስቲያናዊ መልካም ሥራን መሥራት ያስፈልጉታል፡፡ (ፊል. 2÷12፣ ራዕ. 22÷12-13)
‹‹ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ፡፡ እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ
በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን? ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደሆነ እንደዚሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ
እምነት የሞተ ነው›› ያዕ. 2÷24-26
አምላክ እንዴት ሰው ሆነ?
የቃል ሥጋ ኮነን ምሥጢር ባለመረዳት ብዙዎች በኑፋቄ ትምህርት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተለይተዋል፡፡ ውላጤ፣
ሚጠት፣ ቱሳሔ፣ ኅድረት፣ ትድምርት፣ ቡዐዴ፣ ተጋውሮ፣ ፍልጠት በየጊዜው የተነሡ መናፍቃን ያመነጯቸው የስህትት
ትምህርቶች ናቸው፡፡ ስህተቶቻቸውም የሚከተሉት ናቸው፡፡
ውላጤ፡- የቃሉ ትርጓሜ መለወጥ ማለት ነው፡፡ 41 አንድ አካል የቀድሞ ቁመናውን ወይም ማንነቱን ለቅቆ አዲስ ማንነት
ሲይዝ ውላጤ (መለወጥ) ይባላል፡፡ ለምሳሌ ብእሲተ ሎጥ ከሰውነት ወደ ጨው ሐውልትነት መለወጥ፣ ጌታችን በቃና
ዘገሊላ ውኃውን ወደ ወይን መለወጡ አስረጂዎች ናቸው፡፡ ብእሲተ ሎጥ የጨው ሐውልት ‹‹ኾነች›› ሲባል ‹‹ሰውነቷን
ለቃ›› ነው፤ ማየ ቃና ወይን ‹‹ኾነ›› ሲባል ‹‹ውኀነቱን ለቆ›› ነው፡፡ ቅድመ ውላጤ የነበረው ባሕርይ ድኅረ ውላጤ ሙሉ
በሙሉ ተቀይሯል፡፡
“የሎጥ ሚስት ወደ ኋላዋ ተመለከተች የጨው ሐውልትም ኾነች” ዘፍ 19፣26
“አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የኾነውን ውኀ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደመጣ አላወቀም፤ ውኀውን የቀዱት
አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር” ዮሐ. 2÷9
ወንጌላዊው ‹‹ቃል ሥጋ ኮነ ወኀደረ ላዕሌነ›› ብሎ ቢጽፍ ኀደረ ላዕሌነን ያልተመለከቱ ሰዎች ሥጋ ኮነን ብቻ
ተመልክተው ብእሲተ ሎጥ ተለውጣ ሐውልተ ፄው እንደሆነች፣ ማየ ቃና ተለውጦ ወይን እንደሆነ ቃልም ተለውጦ ሰው
ሆነ ብለዋል፡፡ አምላክ ሰው ኾነ ሲባል ግን በአንድ ‹‹ኾነ›› የተነገሩ ቃላት በመሆናቸው ንባቡ ቢመሳሰልም ምሥጢሩ
አይገናኝም፡፡ ምክንያቱም አምላክ ሰው የኾነው ጥንተ ባሕርዩንና አካሉን ሳይለቅ ነው፡፡
“ቃል ሥጋ ኾነ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ” ዮሐ 1፣14
ሚጠት፡- የቃሉ ትርጓሜ መመለስ 136 ማለት ነው፡፡ ውኀ ሲቀዘቅዝ በረዶ ይሆናል ሲሞቅ ተመልሶ ፈሳሽ ይሆናል፣ ውኀ በእሳት
ሲፈላ ይተናል ትነቱ ደግሞ ቀዝቅዞ ተመልሶ ፈሳሽ ይኾና ል፡፡በትረ ሙሴ መሬት ላይ ሲጥላት እባብ እንደ ኾነች በእጁ ሲይዛት ደግሞ
ተመልሳ በትር እንደ ኾነች፣ ናቡከደነጾር ከሰውነት ወደ አውሬነት ከአውሬነትም ወደ ሰውነት እንደተመለሰው መኾን ማለት ነው፡፡

41. ውላጤ፡- መለወጥ አለዋወጥ ልወጣ ልውጥነት ኪ.ወ.ክ ገጽ 393 በትር እንደኾነች፣ ናቡከደነጾር ከሰውነት ወደ
አውሬነት ከአውሬነትም ወደ ሰውነት እንደተመለሰው መኾን ማለት ነው፡፡
42. ሚጠት መመለስ መዘር ኪ.ወ.ክ ገጽ 588
‹‹በዚያም ሰዓት ነገሩ ናቡከደነፆር ላይ ደረሰ ጠጉሩም እንደ ንሥር ጥፍሩም እንደ ወፎች እንኪረዝም ድረስ
ከሰዎች ተለይቶ ተሰደደ እንደ በሬም ሣር በላ አካሉም በሰማይ ጠል ረሰረሰ›› ዳ.ን 4፣28-33 (ዘጸ 4፣2-5)
መናፍቃን ክርስቶስ ወደ ዓለም ሲመጣ ሰው ወደ መሆን ተለውጧል ሲያርግ ደግሞ በሥጋ ሳይሆን በባሕርየ መለኮቱ
ዐርጓል ሥጋውን ልብስን አውልቀው እንደሚጥሉት ጥሎት ሄዷል ብለው ያስተምራሉ፡፡ አምላክ እንደ ሙሴ በትር፣ እንደ
ናቡከደነፆር፣ መመለስ ባለበት መለወጥ አምላክ ሰው ኾነ ካልን ሰው በፍጡር ሊድን አይችልምና አልዳነም ወደ ማለት
ያደርሰናል፡፡ የቃልና የሥጋ ተዋሕዶ ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ ቃል ሥጋ ኾነ ሲባል እንበለ ሚጠት በተዋሕዶ አካላዊ ቃል
ሰው ኾነ ማለት ነው፡፡
ቱሳሔ፡- የቃሉ ትርጓሜ መቀላቀል መደባለቅ 43 ማለት ነው፡፡ ልዩ ልዩ ኅብረ መልክእ፣ ልዩ ልዩ ጣዕም ያላቸው ኹለት
ነገሮች ቢደባለቁ ከኹለቱም ወገን የተወጣጣ ልዩ ኅብረ መልክእ ያሳያሉ፤ ልዩ ጣዕም ይሰጣሉ፡፡ ለምሳሌ ወተትና ቡና
ቢቀላቅሏቸው ወተት ነጭነቱን ለቅቆ ወደ ጥቁረት ይሳባል ቡናም ጥቁረቱን ለቅቆ ወደ ነጭነት ይሳባል፡፡ ከኹለቱም

ገጽ 4
የተወጣጣ ልዩ መልክእ ይታያል፤ ልዩ ጣዕም ይገኛል፡፡ ኹለቱም ነገሮች የየድርሻቸውን አበርክተው የሚያስገኙት እንግዳ
ውጤትን ያሳያል፡፡
በቱሳሔ ኹነትነት ቢጠፋ አንድነት ቢመጣም አዲስ ባሕርይ አዲስ መልክእ አዲስ ጣዕም አዲስ አካል ይገኛልና ለቃልና
ለሥጋ ተዋሕዶ አይቀጸልም፡፡ ምክንያቱም “መለኮት መለኮትነቱን ለቅቆ ትስብእትም ትስብእትነቱን ለቅቆ
በመካከላቸው ሌላ ሕማም ሞት የማይስማማው ረቂቅ ሥጋ ኾነ” ወደሚል የአውጣኪ ስህተት ያደርሳል፡፡ በተዋሕዶ ግን
እንደዚህ አይደለም፡፡ መለኮት ምልዐቱን ስፍሐቱን ርቀቱን ሳይለቅ ትስብእትም ውሱንነቱን ግዙፍነቱን ሳይለቅ ፍጹም
አንድ መኾንን ያስከተለ ነው፡፡ በቱሳሔ መጠፋፋት ሲኖር በተዋሕዶ ግን ተዐቅቦ አለ፡፡
ኅድረት፡- የቃሉ ትርጓሜ ማደር 44 ማለት ነው፡፡ በወንጌል ‹‹ኀደረ ላዕሌነ›› የሚለውን በመመልከት አንዱ አካል በሌላው
አካል አደረበት ይላሉ፡፡ ለምሳሌ እንደ ዳዊትና ማኅደር እንደ ሠይፍና ሰገባ ማለት ነው፡፡ ዳዊት በማኅደር ሠይፍ በሰገባ
ገብተው ኹለቱ አካላት አንድ ይኾናሉ፡፡ ዳዊት በማኅደር ሠይፍ በሰገባ ገብተው ኹለቱ አካላት ለጊዜው አንድ የኾኑ
ይመስላሉ፡፡ አንድነታቸው ግን ለጊዜው ነው ዳዊት ከማኅደር ወጥቶ ወደ ኹለትነት ይከፈላሉ፡፡ ሠይፍ ከሰገባው ወጥቶ
እንዲሁ ወደ ኹለትነት ይከፈላሉ፡፡
ንስጥሮስ በምሥጢረ ሥጋዌ ክርስቶስን ከኹለት ከፍሎ አንዱን ወልደ ዳዊት ሌላውን ወልደ እግዚአብሔር ነው
ብሎ ያምን ነበር፡፡ በእርሱ አባባል ከማርያም የተወለደው ወልደ ዳዊት ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው ወልደ
እግዚአብሔር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው ቃል ከማርያም በተወለደው ወልደ ዳዊት አደረበት፡፡ ስለዚህ
የዳዊት ልጅ ለእግዚአብሔር ልጅ መቅደስ ማኅደር ነው፡፡
የቃል ከሥጋ ጋር መዋሐድ ግን እንዲህ ያለ አይደለም፡፡ ስለዚህም ቃል ሥጋ ኾነ ሲባል እንበለ ኅድረት በፍጹም
ተዋሕዶ አካላዊ ቃል ሰው ኾነ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ የኤፌሶኑን ጉባኤ ሲመራ ለንስጥሮስ ኹለት
ጥያቄዎችን አንሥቶለታል፡፡
1. አብ በደመና ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› ብሎታል፡፡ ኅድረት ቢሆን ኖሮ ‹‹በዚህ ላይ ያደረው›› ይለው
አልነበረምን?፡፡ ማቴ. 3÷17
2. አማኑኤል ‹‹እግዚአብሔር ከእኛ ሆነ›› ማለት ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው
ሆነ ማለት ነው፡፡ ቃል ሥጋ የሆነው በኅድረት ከሆነ ወንጌላዊው ይህን እንዴት ጻፈ? ወንጌላዊው ዋሸ ማለት ነውን?
ማቴ.1÷23፣ (ማቴ. 3÷17፣ ማቴ. 1÷23፣ ሉቃ. 1÷35፣ መዝ. 109÷1)
‹‹እርሱ በአብ ዕሪና ሳለ በድንግል ማኅፀን ተወሰነ ከእርሷም ተወለደ በእናቱ ክንድ ላይ ሳለ በነፋስ ክንፍ
ይመላለስ ነበር መላእክትም ይሰግዱለት ነበር›› (ሃይ. አበ. ዘኤራቅሊስ ምዕ. 48 ክ 1 ቁ 2)

43. ቱሳሔ መቀላቀል፣ አቀላቀል፣ ቅልቅልነት፣ ቅልቅል መኾን ኪ.ወ.ክ ገጽ 894


44. ኅድረት ማደር መኖር አስተዳደር፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 473
ትድምርት፡- የቃሉ ትርጓሜ መጨመር 45 ማለት ነው፡፡ ትድምርት አፍዐዊ ዋሕድና ላላቸው ነገሮች የሚነገር ቃል ነው፡፡
ይህም እንደ ልብስ እንደ አነባብሮ ነው፡፡ ልብስ ቢደርቡት ይደረባል
ቢነጥሉት ይነጠላል፤ እንጀራም ቢደርቡት ይደረባል ቢነጥሉት ይነጠላል፡፡ የቃልና የሥጋ ተዋሕዶ ግን እንደዚህ አይደለም፡፡
ትድምርት ቢሆን ኖሮ ፍልጠትን ቡዐዴን ያስከትል ነበር፡፡ አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ
ነፍስን ነሥቶ በሥጋ ርስት ወልደ ዳዊት ወልደ አብርሃም ተባለ፡፡
‹‹እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር
ይኸውም ዲያብሎስ ነው፡፡ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ
እንዲያወጣ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ፡፡ የአብርሃምን ዘር ይዟል እንጂ የያዘው የመላእክትን
አይደለም›› ዕብ. 2÷14
ሥጋ ደግሞ ከአካላዊ ቃል ጋር አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆኑ ከሦስቱ አካላት እንደ አንዱ ሆነ፡፡
‹‹እግዚአብሔርም አለ፡- እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ›› ዘፍ. 3÷22
ቡዐዴ፡- የቃሉ ትርጓሜ 45 ባዕድነት ተላጽቆ ተቃርቦ ማለት ነው፡፡ የእንጨት እና የብረት ሠራተኛ እንጨቱን ጠርቦ
አለዝቦ፣ ብረቱን ሞርዶ አስማምቶ በማሠሪያ ወይም በቡሎን በምስማር አንድ ቢያደርጋቸው አንድ ይኾናሉ፡፡
ማሠሪያውን ወይም ቡሎኑን ቢፈታው ይለያያሉ፡፡ ቡዐዴ ተላጽቆ ተቃርቦ ማለት እንዲህ የተለያየ ነገር ስለሆነ የክርስቶስ
ተዋሕዶም እንደዚህ ነው ማለት ታላቅ ስሕተት ነው፡፡
ተጋውሮ የቃሉ ትርጓሜ መጎራበት ማለት ነው፡፡ ቤትን ከቤት ጋራ አጠጋግተው ቢሰሩት አንድ መንደር እንጂ አንድ ቤት
አይባልም፡፡ ምክንያቱም አካሉ የየራሱ ነውና፡፡ ተዋሕዶ ግን እንደዚህ አይደለም፤ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው፡፡
ሙሽሪት ሙሽራ አንድ እንደሚባሉት ያለ አንድነት አይደለም፤ ሙሽሮች አንድ ሆኑ የሚባለው ኹለቱ ተገናኝተው አንድ

ገጽ 4
አካል የሚያስገኙ ስለሆነ ነው፡፡ ቤት ከቤት ጋር እንዲጎራበት፣ ባልም ከሚስቱ ጋር እንዲጣበቅ አይደለም፤ አንድ አካል
አንድ ባሕርይ አንድ ግብር ነው፡፡ 46
ፍልጠት፡- ማለት ከተዋሕዶ በኋላ የሚመጣ መለየት 48 ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ነፍስና ሥጋ ተዋሕደዋል ነገር ግን ተፈልጦ
አለባቸው፡፡ የመለኮትና የትስብእት ተዋሕዶ ግን ምንም በነፍስና ሥጋ ተዋሕዶ ቢመሰል እንደ ነፍስና ሥጋ ተፈልጦ
የለበትም፡፡ ጌታችን በመልዕልተ መስቀል ክብርት ነፍሱን ከክቡር ሥጋው በገዛ ሥልጣኑ በለየ ጊዜ መለኮት ከነፍስም
ከሥጋም ተፈልጦ ሳይኖርበት በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወርዶ ሙስና መቃብርን አጥፍቶልናል፡፡ በአካለ ነፍስም መለኮት
ወደ ሲዖል ወርዶ ነጻነትን ለነፍሳት ሰብኮ ከባርነት አስለቅቆናል፡፡

ምሥጢረ ተዋሕዶ
ተዋሕዶ ማለት አንድ መሆን መዋሐድ አለመለያየት 49 ማለት ነው፡፡ ተዋሕዶ የማይዳሰሰው አካላዊ ቃል እግዚአብሔር
ወልድ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በማኅፀነ ድንግል ማርያም አድሮ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ መወለዱን
ያሳየናል፡፡ ተዋሕዶ ከኹለት አካል አንድ አካል ከኹለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የመሆን ምሥጢር ነው፡፡ የቃልና የሥጋ
ተዋሕዶ ፍጹም ተዋሕዶ ነው፡፡ ፍጹም የሚባለውም መከፈል፣ መለወጥ፣ መለየት፣ መነጠል፣ መቀላቀል፣ መደባለቅ፣
ማደር፣ መጨመር የሌለበት ስለኾነ ነው፡፡
“ጥንት የሌለው ዘለዓለም የሚኖር እርሱ ከመዓርጋት ኹሉ በላይ በሚሆን ተዋሕዶ የኛን ባሕርይ ነሥቶ
ዘመን ተቆጠረለት ያለመለወጥ ያለመቀላቀል በእውነት ሰው ኾነ በባሕርየ መለኮቱም ሕፀፅ የለበትም
በሦስትነቱ ያመንበትን እኛን በአምላክነቱ በሠራው ሥራ እንድናደንቀው አደረገን” (ሃይ. አበ. ዲዮናስዮስ ምዕ.
10÷16)

45. ደመረ መደመር፣ መጨመር፣ ማግባት፣ መግጠም፣ ማገናኘት … ኪ.ወ.ክ ገጽ 352


46. ቡዐዴ መለየት፣ አለያየት፣ ልዪነት ኪ.ወ.ክ ገጽ 723
47. ቃለ ጽድቁ ለአብ ገጽ 112
48. ፍልጠት መለየት አለያየት ልዩነት፡፡ ኪ.ወ፣ክ ገጽ 723
49. ተዋሕዶ መዋሐድ አንድ መኾን ኪ.ወ.ክ ገጽ 384

አንድ አካል አንድ ባሕርይ


ተዋሕዶ ከኹለት አካላት አንድ አካል ከኹለት ባሕርያት አንድ ባሕርይ ከኹለት ፈቃዳት አንድ ፈቃድ የኾነበት
ምሥጢር ነው፡፡ በተዋሕዶ አምላክ ሰው ኾኗል ሰውም አምላክ ኾኗልና ለቃል የሚነገረው ለሥጋ፣ ለሥጋ የሚነገረውም
ለቃል ይኾናል፡፡ ከተዋሕዶ በኋላ ቃል እና ሥጋ አይለያዩም አይከፋፈሉም አይነጣጠሉም ኹለትነት አይከተላቸውም፡፡
አካል ምንድ ነው
አካል ማለት ከራስ ጠጉር እስከ እግር ጥፍር በአጥንት፣ በጅማት፣ በሥጋ፣ በቁርበት የተያያዘ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክእ
ያለው ነፍስ የተዋሐደችው የባሕርይ፣ የስም፣ የግብር ባለቤት ነው፡፡ ይህም አካል መባል ለሰውም ለአምላክም ይነገራል፡፡
ባሕርይ ምንድ ነው
ባሕርይ ማለት የአካል መገኛ ሥር፣ አካል ሥራውን የሚሠራበት መሣርያ ነው፡፡ ስለዚህ አካል ያለ ባሕርይ ብቻውን
አይቆምም ባሕርይም ያለ አካል አይፈጸምም፡፡ አካልና ባሕርይ እንደ ሥርና እንደ ዐፅቅ፣ እንደ ቅንጣትና እንደ አገዳ
የተያያዙ የማይለያዩ ናቸው፡፡
ባሕርይ አካል ሥራውን የሚሠራበት የአካል መሣሪያ ነው፡፡ ለምሳሌ ለውኃ አካልም ባሕርይም አለው፤ አካሉ በጽዋዕ
በማድጋ የሚቀዳው ባሕርዩ ርጥበት ነው፡፡ ሥራውም የደረቀውን ማራስ የራሰውን ማበስበስ ነው፡፡ ውኃ ማናቸውንም
የደረቀ ነገር ሲነክሩበት ማራሱ ርጥበት ባሕርዩ ስለሆነ ነው፤ ርጥበት ባይኖረው ሊያርስ አይችልም ነበር፡፡
ባሕርይ የአካል መገኛ ነው ባልን ጊዜም ውኃን መሬትን ነፋስን እሳትን ባሕርያት ብለን የአዳም ሙሉ አካሉ ከእነዚህ
ከውኃ ከመሬት ከነፋስ ከእሳት መገኘቱን መናገራችን ነው፡፡ (መዲሎተ አሚን ገጽ 247)
ቅድመ ተዋሕዶ
ቅድመ ተዋሕዶ መለኮታዊ ባሕርይ ያለው አካለ መለኮት በቃልነት ከዊን ለብቻ ሰብአዊ ባሕርይ ያለው አካለ ትስብእት
በአዳምነት ለብቻ ነበር፡፡
መለኮት
የመለኮት አካሉ ምሉዕ ስፉሕ ረቂቅ ነው፤ ባሕርየ መለኮት ይህ ነው ተብሎ የማይመረመር ነው፡፡
ትስብእት

ገጽ 4
የትስብእት አካሉ ግዙፍ የሚታይ የሚጨበጥ የሚዳሰስ ነው፡፡ ባሕርዩም ለተፈጥሮው ምክንያት የሆኑ
የውኃ የመሬት የነፋስ የእሳት የነፍስ ባሕርያት ናቸው፡፡
ድኅረ ተዋሕዶ
የማይወሰነው የማይዳሰሰው አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በማኅፀነ ድንግል አድሮ
ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ተወለደ፡፡ በማይመረመር የተዋሕዶ ምሥጢር የቃል ገንዘብ ለሥጋ የሥጋ ገንዘብ ለቃል
ሆነ፡፡
‹‹ወልድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማይመረመር ተዋሕዶ ሰው የኾነ አምላክ ነውና ቀዳማዊ ሲሆን ከዘመናት
አስቀድሞ ከአብ የተወለደ ነው፤ ዳግመኛም ከድንግል በሥጋ የተወለደ ነው ተብሎ ስለእርሱ እንዲህ ይነገራል፡፡››
(ሃይ. አበ. ዘቄርሎስ ምዕ. 73 ክ 11 ቁ. 4)
አካላዊ ተዋሕዶ
አካሉ ምሉእ ስፉሕ ረቂቅ ባሕርዩ ክሂል የሆነ መለኮት ይህን አካሉ ግዙፍ ውሱን ባሕርዩ የውኃ የመሬት የነፋስ የእሳት
የነፍስ ባሕርይ የሆነ ትስብእትን ሲዋሐድ መለኮት ምልአቱን ርቀቱን ስፍሐቱን ለቅቆ ሳይገዝፍ ሳይለወጥ ትስብእትም
ውሱንነቱን ግዙፍነቱን ለቅቆ ሳይረቅ ሳይለወጥ በተዐቅቦ ነው፡፡
ተዐቅቦውም እንደ ነፍስና እንደ ሥጋ ተዐቅቦ ነው፡፡ ሥጋ አካሉ ግዙፍ፣ ባሕርዩ በውኃ፣ በመሬት፣ በነፋስ፣ በእሳት ያሉ
ባሕርያት ርጥበት፣ ይብስት፣ ውእየት፣ ቁረት ነው፡፡ የነፍስ አካሏ ረቂቅ ባሕርይዋ ለባዊነት፣ ነባቢነት፣ ሕያዊትነት ነው፡፡
እኒህ ሁለቱ ነፍስና ሥጋ ሲዋሐዱ ሥጋ ግዘፉን ለቅቆ ሳይረቅ ሳይለወጥ፣ ነፍስ ርቀቷን ለቅቃ ሳትገዝፍ ሳትለወጥ ነው፡፡
አካላቸው ሲዋሐድ ባሕርያቸውም ተዋሕዷል፡፡ (መድሎተ አሚን ገጽ 107-108)
“ቃል ሥጋ ኾነ፤ እንደተጻፈ የማይመረመር፤ የተዋሕዶ ሥርዐት እንደመሆኑ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ኾነ
መለኮትና ትስብእት እርስ በእርሳቸው ሳይቀላቀሉ መለየት በሌለበት ተዋሕዶ እንዲህ ፈጽመው አንድ
ኾኑ” (ሃይ. አበ. ዘቄርሎስ ምዕ. 73 ክ 16 ቁ.30)
“ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት አይሁድን ስለ ፈሩ
ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ በመካከላቸውም ቆሞ፡- ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው፡፡ ይህንም
ብሎ እጆቹንም ጎኑንም አሳያቸው፡፡” ዮሐ 20÷19፣ ማቴ 28÷2
ባሕርያዊ ተዋሕዶ
ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የምትሆን በከዊን የምትለይ ባሕርይ ያለችው አካለ ቃል ሰብአዊ ባሕርይ ያለው
ሰብአዊ አካልን እንበለ ዘርእ በሕፃናት መጠን ነሥቶ ተዋሐደ፡፡ በተዋሕዶ ምንታዌ ጠፋ፡፡ የቃል ገንዘብ ለሥጋ የሥጋ
ገንዘብ ለቃል ሆነ፡፡
‹‹ከተዋሕዶ በኋላ ወደ ኹለት ባሕርይ አይከፈልም ተዋሕዶ መንታነትን አጥፍቷልና›› (ሃይ አበ. ዘባስልዮስ ምዕ. 96 ክ 1
ቁ 17)
የቃል ገንዘብ፡- ሁሉን ቻይነት፣ ቀዳማዊነት፣ ዘላለማዊነት፣ ረቂቅነት፣ ፊተኝነት፣ ኋለኛነት፣ ፈጣሪነት ወዘተ
ነው፡፡
የሥጋ ገንዘብ፡- መራብ፣ መጠማት፣ መድከም፣ መሞት፣ ግዙፍነት ውሱንነት ወ.ዘ.ተ ነው፡፡
አካላዊ ቃል ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ሥጋ ማርያምን
ተዋሐደ፡፡ በዚህ ጊዜ የሥጋ ገንዘብ ለቃል፤ የቃልም ገንዘብ ለሥጋ ኾነ፡፡ ቀዳማዊነት ያልነበረው ሥጋ ቃልን ተዋሕዶ
ቀዳማዊ አምላክ ተባለ፡፡ ዘመን የማይቆጠርለት ቃል ደግሞ ሥጋን ተዋሕዶ ዘመን ተቆጠረለት፡፡ የማይመረመር
የማይለወጥ ቃል የሚለወጥ ሥጋን ተዋሕዶ መለወጥ ይስማማው የነበረ ሥጋን የማይለወጥ አደረገው፡፡ ስለዚህ
በተዋሐደው በመዋቲ አዳም ሥጋ ተገለጠ፤ የማይለወጥ ባሕርይ ያለው ቃል የሚለወጥ ባሕርይ ባለው ሥጋ ሞቶ በፍዳ
የተያዙትን በወንጌሉ አዳናቸው፡፡ (ዮሐ.1÷14፣ 1 ኛጢሞ.3÷16፣ ፊል.2÷6-8፣ 1 ኛጴጥ. 3÷2)
‹‹በመጀመሪያው ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበር …ቃልም ሥጋ ሆነ
ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ›› ዮሐ. 1÷1-14
“አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሴት አደረገ አየም ደስም አለው፡፡ አይሁድም፡- ገና ሃምሳ ዓመት ያልሆነህ
አብርሃምን አይተሃልን አሉት፡፡ ኢየሱስም እውነት እውነት እላችኋለሁ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው”
ዮሐ 8፣56
“እንዲህም አለኝ፡- አትፍራ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ እነሆም ከዘላለም እስከ
ዘለዓለም ድረስ ሕያው ነኝ የሞትና የሲዖልም መክፈቻ አለኝ፡፡” ራዕ 1፣17

ገጽ 4
ተዋሕዶ በተዐቅቦ ነው
ተዐቅቦ 155 መጠባበቅ ማለት ሲኾን የኹለቱን አካላት ያለመጠፋፋት ያመለክታል፡፡ ተዐቅቦ ትስብእትና መለኮት
ከውላጤና ከቱሳሔ የሚጠብቅ ምሥጢር ነው፡፡ ሥጋ ከመለኮት መለኮት ከሥጋ ጋር ሲዋሐዱ አንዱ አንዱን ሳያጠፋው
አንዱ አንዱን ሳይለውጠው ከኹለት አካላት አንድ አካል ከኹለት ባሕርያት አንድ ባሕርይ ኾኖ መኖር ነው፡፡ (ተዓቀበ፡-
ተጠባበቀ፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 705)
የተዋሕዶ ምሳሌዎች
እግዚአብሔርን በምሳሌ ገልጠን አንደርስበትም፡፡ ነገር ግን የተወሰነ ጥቂት ግንዛቤን ይፈጥርልን ዘንድ ምሳሌዎችን
መመልከት የተለመደ ነው፡፡ በሚገባን መልኩ በቀላሉ ለመረዳት ነው እንጂ የቃልን እና የሥጋን ተዋሕዶ ምሳሌ
አይገልጠውም፡፡
የሰው ነፍስና ሥጋ
ከእናቱ ደም ከአባቱ ዘርዕ ተከፍሎ ነፍስና ሥጋን ነሥቶ የተፀነሰ ፅንስ ከ፵ ቀኑ ጀምሮ ነፍስና ሥጋውን መለያየት
አይቻልም፡፡ ረቂቅ ነፍስ ከግዙፉ ሥጋ ተዋሐዶ ያለመለየት ያለመለወጥ በሰውነቱ ይኖራል፡፡ ነፍስ ረቂቅ በመኾኗ የሥጋን
ግዙፍነት እንደማትለውጠው የሥጋ ግዙፍነት የነፍስን ረቂቅነት እንደማይለውጣት ኹሉ የቃልና የሥጋ ተዋሕዶም
እንደዚህ ነው፡፡ ምሳሌ ዘየሐፅፅ እንዲሉ ነፍስና ሥጋ ዘለዓለማዊ ተዋሕዶ የላቸውም በሞት ተፈልጦ ተከፍሎ
ይደርስባቸዋል፡፡
‹‹ነባቢት ነፍስ ረቂቅ ስትሆን ከሥጋ ጋር ትዋሐድ ዘንድ ኃይል እንዳላት ሥጋ ያይደለች የባሕርይ ረቂቅነቷንም ከርሱ
እንዳትለቅ ኹለቱም በየገንዘባቸው የጸኑ ሲሆኑ በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ አንድ ፍጹም ሰው እንደሆኑ ከዘመን
በኋላ ከተገኘ ከሥጋ ጋር ያለመለወጥ አንድ አካል በመሆን የተዋሐደ ቀዳማዊ የእግዚአብሔር ልጅም እንዲሁ ነው፡፡›› (ሃይ.
አበ. ባስልዮስ)
የጋለ ብረት
ብረትና እሳት ሲዋሐዱ ብረቱ ከእሳት በገባ ጊዜ እሳቱ የብረቱን ገንዘብ (ባሕርይ) ገንዘብ ያደርጋል ብረቱም
የእሳቱን ገንዘብ ገንዘብ ያደርጋል፡፡
“በእግዚአብሔር ቃል በረቂቅ ባሕርይ የሆነውን አንካድ ብረት ከእሳት በተዋሐደ ጊዜ ከእሳትም በመዋሐዱ
የእሳትን ባሕርይ ገንዘብ እንዲያደርግ ብረት በመዶሻ በተመታ ጊዜ ከእሳት ጋር በአንድነት እንደሚመታ ግን
ከመዶሻው የተነሳ የእሳት ባሕርይ በምንም በምን እንዳይጎዳ ሰው የሆነ አምላክ ቃል በመለኮቱ ሕማም
ሳይኖርበት በሥጋ እንደታመመ እንዲህ እናስተውል” (ሃይ.አበ ዘቄርሎስ 73 ክፍል 12 ቁ 12)
ሙሴ ያየው ሐመልማል ወነበልባል
“የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾህ ቁጥቋጦ መካከል ታየው፣ እነሆም ቁጥቋጦው በእሳት ሲነድ
ቁጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ፡፡ ሙሴም ልሒድና ቁጥቋጦው ስለምን አልተቃጠለም ይህን ታላቅ ምሥጢር ልይ
አለ” ዘጸ 3፣2
ነበልባሉ ከቁጥቋጦው ተዋሕዶት ነበልባሉ ቁጥቋጦውን ሳያቃጥለው ቁጥቋጦውም ነበልባሉን ሳያጠፋው መገለጹ
አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ከድንግል ማርያም ማኅፀን ባደረ ጊዜ ድንግል ማርያምን እሳተ መለኮት ሳያቃጥላት
ከእርሷ የነሣውን ሥጋ እና ነፍስ ሳይለውጠው ፍጹም የመዋሐዱ ምሳሌ ነው፡፡ ሐመልማሉም እሳቱን አለማጥፋቱ
የድንግል ማርያም ሥጋ እሳተ መለኮቱን ሳይሽረው ሳይለውጠው በፍጹም ተዋሕዶ ሰው የመኾኑ ምሳሌ ነው፡፡
ኢሳይያስ ከለምጽ የተፈወሰበት ፍሕም
“ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ በእጁም ከመሰዊያው በጉጠት የወሰደው ፍም ነበር፡፡ አፌንም
ዳሰሰበትና፡- እነሆ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል በደልህም ከአንተ ተወገደ ኃጢአትህም ተሠረየልህ አለኝ፡፡” ኢሳ
6፣6-7
ፍሕም የእሳትና የከሰል ተዋሕዶ ነው፡፡ እሳት በባሕርይው የማይዳሰስ የሚታይ የሚያቃጥል ሲሆን የከሰል ደግሞ
የሚታይ የሚያዝ የሚጨበጥ ነው፡፡ ነገር ግን ሁለቱ ከተዋሐዱ በኋላ በጋራ ስም ፍሕም ሲባል የማይያዘው እሳት በከሰሉ
ይያዛል፡፡ የማያቃጥለው ከሰል በእሳቱ ያቃጥላል፡፡ ኢሳይያስ በጉጠት በተያዘ ፍሕም እንደተፈወሰ ሁሉ የሰው ልጆችም
በፍጹም ተዋሕዶ ሰው በሆነ አምላክ መዳናችንን ያሳያል፡፡
ማጠቃለያ
- ክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው፡፡ በመለኮቱ የእግዚአብሔር አብ ልጅ በሥጋ የማርያም ልጅ እንደሆነ
እናምናለን፡፡

ገጽ 4
- ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋሕዶ ከበረ
- ሁለት ልደታትን እናምናለን፡፡ ሃይ.አበ ባስልዮስ ዘቄሳርያ 34 ክፍል 5-6
- ክርስቶስ የሰው ልጆችን ከሕግ ርግማንና ከምልዐተ ኃጢአት ለማዳን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን
ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ተወለደ፡፡
- የቃልና የሥጋ ተዋሕዶ ፍጹም ተዋሕዶ ነው፡፡ ፍጹም የሚባለውም መከፈል፣ መለወጥ፣ መለየት፣ መነጠል፣
መቀላቀል፣ መደባለቅ፣ ማደር፣ መጨመር የሌለበት ስለሆነ ነው፡፡
- መለኮትና ትስብእት በተዐቅቦ ተዋሐዱ፡፡
3.3 ምሥጢረ ጥምቀት
መግቢያ

ምሥጢረ ጥምቀት ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት አንዱ ነው፡፡ ጥምቀት ለድኅነት አስፈላጊ በመሆኑ ቅድስት ቤተ
ክርስቲያን ወንዶችን በ፵ ቀን ሴቶችን በ፹ ቀናቸው እንዲጠመቁ ሕግ ሠርታለች፡፡ በዚህ ምዕራፍ የጌታችን
የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት፣ የሰው ልጆች ጥምቀት መቼ ለምንና እንዴት እንደተመሠረተ በብሉይ
ኪዳን ስለነበሩ የጥምቀት ምሳሌዎችን እናያለን፡፡

ጥምቀት ማለት ምን ማለት ነው?


ጥምቀት 50 “አጥመቀ” ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም በገቢር መንከር፣ መድፈቅ፣ መዝፈቅ በተገብሮ
መነከር፣ መደፈቅ፣ መዘፈቅ መላ አካልን በውኀ ውስጥ በስመ ሥላሴ መዝፈቅ ማለት ነው፡፡ ጥምቀት በልዩ ልዩ
መጠሪያዎች ተጠርቶ ይገኛል፡፡ በግሪክ ‹‹ኤጲፋንያ››51 በግእዝ ‹‹አስተርእዮ›› በአማርኛ መገለጥ ይባላል፡፡
መገለጥ ሲል ክርስቶስ በተጠመቀበት ወቅት አብ በደመና ሆኖ የምወደው ልጄ ይህ ነው ሲል፣ ወልድ በተለየ አካሉ
በዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ፣ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ሆኖ የታየ ወይም የተገለጠ ስለሆነ ነው፡፡
ጥምቀት በምሥጢረ ሥላሴና በምሥጢረ ሥጋዌ ለሚያምን ሰው ሁሉ የሚሰጥ የኃጢአት መደምሰሻ ከእግዚአብሔር
የልጅነትን ጸጋ መቀበያ፣ የመንግሥተ ሰማያትም መውረሻ ነው፡፡ ምሥጢር መባሉም ካህኑ ለጥምቀት የተመደበውን
ጸሎት አድርሶ ሲባርከው ወኃው ተለውጦ ማየ ገቦ ስለሚሆንና ከእግዚአብሔር ዘንድ የጸጋ ልጅነትን ስለሚያሰጥ ነው፡፡

ምሥጢረ ጥምቀት በነቢያት ትንቢትና ምሳሌ

ጥምቀት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ ሆኖ በድንገት የተገኘ ወይም የተከሰተ
ምሥጢር አይደለም፡፡ አስቀድሞ የእግዚአብሔር ነቢያት በሀብተ ትንቢታቸው የተናገሩት
አበውም በምሳሌዎቻቸው የመሰሉት እና ለትውልድም ጠብቀው ያስተላለፉት ዐቢይ ቁም
ነገር ነው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የነቢያትን ትንቢት እንመለከታለን፡፡
‹‹ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ ከርኩሰታችሁም ሁሉ
ከጣዖቶቻችሁ ም ሁሉ አጠራችኋለሁ፡፡ አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ
በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋይንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ
እሰጣችኋለሁ›› ሕዝ. 36÷25-26
‹‹ተመልሶ ይምረናል ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ

ይጥለዋል፡፡ ሚክ. 7÷19


“በዚህ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ርኩሰት የሚያጻ ምንጭ
ይከፈታል” ዘካ. 13÷1
የጥምቀት ምሳሌዎች
የሰው ልጅ ድኅነት የሚያገኘው ከሥላሴም የሚወለደው በጥምቀት ስለሆነ ጥምቀት ከፍተኛ
ምሥጢር ነው ስለዚህ አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን ዘመን በምሳሌ ሲሠራ ሲፈጽም ቆይቷል፡፡

ገጽ 4
ምሳሌ ሊመጣ ላለው ነገር ጥላ ሆኖ የሚታይና አካሉ ሲገለጽ በአማናዊና በፍጹም እንደሚተካ
ይታወቃል፡፡ ብሉይ ኪዳን ለሐዲስ ኪዳን ጥላው መርገፉ እንደመሆኑ ለጥምቀትም እንዲሁ
የተነገሩ በርካታ ምሳሌዎች አሉ፡፡ ለአብነት ያህልም ዐበይት የሆኑት የሚከተሉት ናቸው፡፡

50. ጥምቀት፡- በቁሙ ማጥመቅ ፣ መጠመቅ፣ አጠማመቅ፣ ጠመቃ፣ የማጥመቅና የመጠመቅ ሥራ ኅፅበት በጥሩ
ውኃ የሚፈጸም፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 503
51. ኤጲፋንያ፡- አስተርእዮ፣ መታየት፣ መገለጽ ዕለተ ጥምቀት፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 250

ማየ አይኀ (የጥፋት ውኃ) ዘፍ. 6÷7


ለምሥጢረ ጥምቀት ምሳሌ ሆነው የሚነገሩ በብሉይ ኪዳን የሚገኙ ታሪኮች አሉ፡፡
ከእነዚህም አንዱ የኖኅ መርከብ እንደሆነ ቅዱስ ጴጥሮስ ያስተምራል፡፡ ሊቀ ነቢያት
ሙሴ የጥንት ዘመን ሰዎች በምድር ላይ መብዛት በጀመሩ ጊዜ ክፋታቸውም መብዛቱን
ይነግረናል፡፡ (ዘፍ. 6÷1-3) በዚህም የተነሣ ኖኅን ሰባኪ አድርጎ ቢያስነሣላቸው እንኳን ንስሐ
መግባትና መመለስ ባለመቻላቸው ኖኅንና ቤተሰቡን በድምሩ ፰ ነፍሳትን በመርከብ
አስገብቶ ሲያድን የተቀረውን ሁሉ ከላይ በሚዘንብና ከታች በሚፈልቅ ንፍር ውኃ
አጥፍቷቸዋል፡፡ በመርከቧ የገቡት ግን ድነዋል፡፡ ሊቃውንት አባቶቻችን
እንደሚተረጉሙልን ኖኅና ቤተሰቡ የምእመናን ምሳሌ መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን
ውኃው የጥምቀት ምሳሌ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ግዝረት ዘፍ. 17÷9
ጥምቀት በግዝረት ምትክ የተሠራ ሕግ ነው፡፡ ግዝረት በብሉይ ኪዳን ዘመን
ለእስራኤል መለያ ምልክት ነበር፡፡ ያልተገረዘ ሁሉ የአብርሃም ወገን የእግዚአብሔር
ሕዝብ አይባልም ነበር፡፡ አብርሃም በእግዚአብሔር ሲጠራ ዕድሜው ሽማግሌ ነበር፡፡ ነገር
ግን የእግዚአብሔር ወገን ለመሆኑ መለያ እንዲሆነውና ለማመኑ ምልክት እንዲሆን
ተገዝሯል፡፡ ከዚያም በኋላ ዘሮቹ ሁሉ የእግዚአብሔር ሕዝቦች መሆናቸው እንዲታወቅ
አባታቸው አብርሃምን አብነት አድርገው ወንዶች በተወለዱ በስምንተኛ ቀናቸው ሲገዘሩ
ኖረዋል፡፡ በወቅቱ ይህ ግዝረት የቃል ኪዳን ምልክት ተደርጎ በእግዚአብሔር ለአብርሃም
የተሰጠ ስለሆነ አለመገረዝ ፍርድ ነበረበት፡፡
ስለዚህ ግዝረት ለሕዝበ እስራኤል ግዴታ እንደነበር ሁሉ ዛሬም ጥምቀት እስራኤል
ዘነፍስ ለተባልን ክርስቲያኖች ሁሉ ልንፈጽመውና ልንጠብቀው የሚገባ ሃይማኖታዊ
ግዴታችን ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳን ጥምቀት ክርስቲያን የምንሆንበት ምልክት የሥላሴን
የጸጋ ልጅነት የምናገኝበት ለዘላለም ሕይወት ዋስትና ነው፡፡ (ቆላ. 2÷11-12)
‹‹የቊልፈቱን ሥጋ ያልተገረዘ ቈላፍ ሰው ሁሉ ያች ነፍስ ከወገንዋ ተለይታ ትጥፋ
ቃልኪዳኔን አፍርሳለችና›› ዘፍ. 17÷14
አበ ብዙኀን አብርሃም የዮርዳኖስን ወንዝ መሻገሩ ዘፍ. 14÷17-23

ገጽ 4
አብርሃም ወንድሙ ሎጥ ስለተማረከ ያስለቅቀው ዘንድ ከቤተሰቡ ጋር ሆኖ ሄደ፡፡
ኮሎዶጎሞርንና አብረውት የነበሩ ሎጥን የማረኩትን ነገሥታትን ወግቶ ድል አደረጋቸው፡፡
ወግቶም ሲመለስ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ማቅረብ ስለፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግሮ
ሲሔድ በመንገድ ላይ መልከ ጼዴቅ የተባለውን ካህን ኅብስተ አኮቴት ጽዋዕ በረከት ይዞ
አብርሃምን ተቀበለው፡፡ አብርሃምም ከያዘው ሁሉ አሥራትን ሰጠው፡፡ ይህ ታሪክ
ምሳሌነት አለው፡፡ ምሳሌነቱ አብርሃም የምእመናን፣ ዮርዳኖስን መሻገሩ የጥምቀት፣
መልከ ጼዴቅ የክርስቶስ፣ ኅብስትና ወይን የሥጋ ወደሙ ምሳሌ ነው፡፡
‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሴት አደረገ አየም ደስም አለው›› ዮሐ. 8÷56
የእስራኤላውያን በኤርትራ ባሕር መካከል ማለፍ ዘጸ. 14÷22
እስራኤል ዘሥጋ ከ 430 ዓመታት የባርነት ሕይወት የተላቀቁትና ወደ ነጻነት ሕይወት
የተሸጋገሩት ከኃይለኛውና ከግፈኛው ከጨካኙ የግብጽ ንጉሥ ከፈርዖን አገዛዝ
ያመለጡት በግብር አምላካዊ የኤርትራን ባሕር ተሻግረው ነው፡፡ ይህ ባሕር ፈርዖንና
ሠራዊቱን አስጥሞ ሲያስቀራቸው ለእስራኤል ዘሥጋ ግን ሕይወት ደስታና ነጻነት
ሆኗቸዋል፡፡
ይህም ለሐዲስ ኪዳኑ ጥምቀት ምሳሌ ነው፡፡ ፈርዖን የሳጥናኤል፣ ሠራዊቱ የሠራዊተ
ሳጥናኤል፣ ግብጽ የሲዖል፣ ሙሴ የክርስቶስ፣ እስራኤል ዘሥጋ የምእመናን፣ ባሕረ
ኤርትራ የጥምቀት ምሳሌዎች ናቸው፡፡እኛም ለርኩሳን አጋንንት ከመገዛት፣ ከፍዳና
ከባርነት ነጻ የምንሆ ነው በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነን
ስንጠመቅ ነው፡፡
‹‹ወንድሞች ሆይ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች
ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና
በባሕር ተጠመቁ›› 1 ኛቆሮ.10÷1-2
ነቢዩ ኤልያስ ባሕረ ዮርዳኖስን መሻገሩ 2 ኛነገ.5÷14
ነቢዩ ኤልያስ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ብሔረ ሕያዋን ማረጉ የጥምቀት ምሳሌ ነው፡፡
ይህም ምእመናን አምነው ተጠምቀው ገነት መንግሥተ ሰማያት የመግባታቸው ምሳሌ
ነው፡፡
‹‹ኤልያስም መጎናጸፊያውን ወስዶ ጠቀለለው ውኃውንም መታ ወዲህና
ወዲያ ተከፈለ ኹለቱም በደረቅ ተሻገሩ›› 2 ኛነገ.2÷8
የንዕማን በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅ 2 ኛነገ.5÷14
የሶርያው ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማን በዮርዳኖስ ውኃ ተጠምቆ ከደዌ ሥጋው
መፈወሱና ከለምጹ መንጻቱ የጥምቀት ምሳሌ ነበር፡፡ ምእመናንም በጥምቀት ከደዌ
ነፍስ ይፈወሳሉ፡፡ ምሳሌነቱም ንዕማን የአዳምና የልጆቹ ምሳሌ፣ ዮርዳኖስ የጥምቀት
ምሳሌ ነው፡፡
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት

ገጽ 4
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነቢያት የተነገረው ትንቢት የተመሰለው
ምሳሌ ይፈጸም ዘንድ በተወለደ በሠላሳ ዘመኑ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ
ተጠመቀ፡፡ መድኃኒታችን ኀጢአት ኖሮበት ንስሐ ሊገባ አልተጠመቀም፡፡ የሰው ሁሉ
ጽድቅ እንደ መርገም ጨርቅ ኾኖ ነበርና፡፡ አይሁድ እንደሚያደርጉት የመንጻት ልማድ
ወይም ኃጥአን ከዮሐንስ እንደተጠመቁት ጥምቀት አልነበረም፡፡
ጌታ ለምን ተጠመቀ?
ጌታችን የተጠመቀው እስራኤላውያን ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ እንደሚጠመቁት ያለ
ጥምቀት ወይም እኛ የልጅነት ጸጋን ለማግኘት እንደምንጠመቀው ጥምቀት አይደለም፡፡
መጠመቁም ለእኛ እንጂ ለእርሱ የሚጨምርለት ክብር፣ የሚያስገኝለት በረከት ኖሮ
አይደለም፡፡ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ ጥምቀታችንን
ሊመሠርትልን፣ ሊባርክልንና ሊቀድስልን፣ ጥምቀቱ ለጥምቀታችን ኃይል እንዲሆነን፣
የእግዚአብሔር ልጅ የምንሆንበትን ጸጋ ሊያድለን ተጠመቀ፡፡ ክርስቶስ የተጠመቀበት ብዙ
ምክንያት አለ፡፡ ከብዙ በጥቂቱ የተወሰኑትን እንመልከት፡፡
አንድነት ሦስትነትን ለመግለጥ
የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በግልጽ የታወቀው ጌታችን በዮርዳኖስ ወንዝ ሲጠመቅ
ነው፡፡ ሰማያት ተከፈቱ የሚለው ንባብም አዲስ ምሥጢር መገለጡን ለመንገር እንጂ
ለሰማይ በር ኖሮት አይደለም፡፡ ጌታችን ተጠምቆ ከወጣ በኋላ አብ በደመና ሆኖ
‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው›› አለ፡፡ መንፈስ ቅዱስም በርግብ
አምሳል በራሱ አርፎ ታየ፡፡ የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በገሀድ ታወቀ፡፡ ስለዚህ
ጥምቀት አስተርእዮ ይባላል፡፡ ትርጉሙም መገለጥ ማለት ነው፡፡
‹‹ሕዝቡም ሁሉ ከተጠመቀ በኋላ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ፡፡ ሲጸልይም ሰማይ
ተከፈተ መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ
ልጄ አንተ ነህ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምጽም ከሰማይ ወጣ›› ሉቃ. 3÷21-22
ለትሕትና
ጌታችን የተጠመቀው በአገልጋዩ በዮሐንስ እጅ ነው፡፡ ዮሐንስ መጥምቅ ለጌታ መንገድ
ጠራጊ በመባል ይታወቃል፡፡ ጌታችን ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ዮሐንስን የሚበልጥ
የለም ብሎ መስክሮለታል፡፡ ዮሐንስ ደግሞ እርሱ ፍጡር ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጣሪ
መሆኑን ያውቃልና ‹‹የእግሩን ጫማ ልፈታ፣ ልሸከም የማይገባኝ›› እያለ ለንስሐ
ጥምቀት ለተሰበሰቡት አይሁድ ይነግራቸው ነበር፡፡ ጌታችን ሲጠመቅ መጥምቀ መለኮት
ቅዱስ ዮሐንስ ወዳለበት ወደ ዮርዳኖስ ሔዶ ተጠመቀ እንጂ መጥምቁ ዮሐንስን
መጥተህ አጥምቀኝ አላለውም፡፡ ይኸውም ጌታችን መምህረ ትኅትና ስለሆነ በዚያውም
ነገሥታት፣ ሹማምንት፣ ንግሥታት፣ ወይዛዝርት ሊጠመቁ ቢወዱ ወደ ካህናት ሔደው
መጠመቅ እንጂ ካህናትን መጥታችሁ አጥምቁን ማለት እንደሌለባቸው ሥርዐት ሲሠራ
ነው፡፡

ገጽ 4
‹‹ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ዮሐንስ ግን
እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን ? ብሎ ይከለክለው
ነበር፡፡ ኢየሱስም መልሶ፤ አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም
ይገባናልና አለው፡፡›› ማቴ. 3÷13
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ‹‹እንግዲህ ጽድቅን ሁሉ ማድረግ ይገባናል›› የሚለውን
ቃል ሲተረጉሙ ‹‹አንተ አምላኩን ያጠመቀ መጥምቀ መለኮት እየተባልህ ልዕልናህ
ሲነገር ይኖራል፡፡ እኔም የመጣሁበትን ፈቃዴን እፈጽማለሁ፤ በባርያው እጅ ተጠመቀ
ተብዬ ትኅትናዬ ሲነገር ይኖራል›› አለው ብለዋል፡፡ ይህንንም ማለቱ ጌታ መምጣቱ
ለትኅትና እንጂ ለልዕልና እንዳይደለ ለማጠየቅ ነው፡፡ (ትርጓሜ ወንጌል ዘማቴዎስ ገጽ 97)
የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ
በመጽሐፈ ቀሌምንጦስ እንደተጻፈ አዳምና ሔዋን ከገነት ተሰደው በደብረ -ቅዱስ ሳሉ
ዲያብሎስ መከራ አጸናባቸው፡፡ አዳምና ሔዋንም መከራው ጸናብን አቅልልን አሉት፡፡
የባርነታችሁን ስም ጽፋችሁ ስጡኝ እና መከራችሁን ላቅልላችሁ አላቸው፡፡እነርሱም
መከራ የሚቀልላቸው መስሏቸው ‹‹አዳም የዲብሎስ ወንድ አገልጋይ ሔዋን
የዲያቢሎስ ሴት አገልጋይ›› ብለው በኹለት ዕብነ ሩካብ ጽፈው ሰጥተውታል፡፡
ዲያብሎስም አንዱን በዮርዳኖስ አንዱን በሲዖል አስቀምጦት ነበር፡፡ ጌታም በተጠመቀ
ጊዜ ዮርዳኖስ ያለውን የዕዳ ደብዳቤ በእግሩ ተረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ
አጥፍቶታል፡፡ በሲዖል የተጣለውን በዕለተ ዓርብ በአካለ ነፍስ ወርዶ ነፍሳትን ሲያወጣ
አጥፍቶታል፡፡
‹‹በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት
ደመሰሰው እርሱም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል›› ቆላ. 2÷14
ሕግንና ነቢያትን ለመፈጸም
ጌታችን ለጸሐፍት ፈሪሳውያን ‹‹ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽማቸው
መጣሁ እንጂ›› እንዳለ ከኃጢአት በስተቀር ሰው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕግ
ጠባያዊን ሕግ መጽሐፋዊን እየፈጸመ በጥቂት በጥቂት ማደጉን መተርጉማነ መጻሕፍት
ይናገራሉ፡፡ ስለዚህ ጌታችን የዕብራውያንን ሕግና ሥርዐት ለመፈጸም ተጠምቋል፡፡
የዕብራውያንን ሕግና ሥርዐት መፈጸም ማለት አንዱ በዮሐንስ እጅ መጠመቅ ነው፡፡
ዓለማትን የፈጠረ ጌታ ሊቀ ካህናት ሆኖ ሳለ በራሱ እጅ ሳይሆን በባርያው በዮሐንስ
እጅ መጠመቁ አይሁድ ካህናተ ኦሪትን አቃሏል፤ አንድም ኦሪትና ነቢያትን ሊሽር
መጥቷል ብለው ወንጌልን ከመቀበል እንዳይከለከሉ ምክንያት ሲያሳጣቸው ነው፡፡
ጌታችን በ፴ ዘመኑ ለምን ተጠመቀ?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በዘመነ ሉቃስ በወርኀ ጥር
በ 11 ኛው ቀን በዕለተ ማክሰኞ ከሌሊቱ ፲ ሰዓት በ፴ ዓመቱ ነው፡፡ ክርስቶስ ጥምቀቱን

ገጽ 4
ከፍ ብሎ በ፵ ዝቅ ብሎ በ፳ ዓመቱ ያላደረገበት ምክንያት የሕግጋት ባለቤት ልዑል
እግዚአብሔር ሁሉን በሥርዐት ምሥጢራቱን በመጠበቅ መፈጸም ስለነበረበት ነው፡፡
ጌታችን በ፴ ዓመቱ የተጠመቀው እናንተም በ፴ ዘመናችሁ ተጠመቁ ለማለት
አይደለም፡፡ ክርስቶስ በ፴ ዘመኑ የተጠመቀበት ምክንያት፡-
የብሉይ ኪዳንን ሕግና ሥርዐት ለመጠበቅ
በአይሁድ ሥርዐት ለቤተ እግዚአብሔር ተልዕኮና መንፈሳዊ አገልግሎት መመረጥ
የሚገባው ሠላሳ ዓመት ሲሞላው ነው፡፡ በመሆኑም በኦሪት ሕግ መሠረት ለአገልግሎት
የሚሾሙበት ዕድሜ ፴ ዓመት እንደሆነ የሐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናትና የቤተ ክርስቲያን
ራስ የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የብሉይ ኪዳንን ሥርዐት ጠብቆ
ድውያነ ሥጋን በተአምራቱ ድውያነ ነፍስን በትምህርቱ የመፈወስ፣ ለድሆች
የምሥራችን መስበክ፣ አገልግሎት የጀመረው በ፴ ዘመኑ በፈለገ ዮርዳኖስ በዮሐንስ እጅ
ከተጠመቀ በኋላ ነው፡፡
‹‹የቀዓትን ልጆች ድምር ውሰድ ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ሃምሳ ዓመት ድረስ
በመገናኛው ድንኳን ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡበትን ሁሉ ትደምራለህ››
ዘኊ. 4÷3
አዳም ያስወሰዳትን የእግዚአብሔር ልጅነት እንዳስመለሰ ለማጠየቅ
እግዚአብሔር አዳምን የ፴ ዓመት ጎልማሳ አድርጎ ከፈጠረው በኋላ በ፵ኛው ቀን
ሔዋንንም የ፲፭ ዓመት ቆንጆ አድርጎ ፈጥሮ በ፹ ቀኗ ወደ ገነት አስገባቸው፡፡ አዳምና
ሔዋን በዐርባና በሠማንያ ቀን ያገኙትን ልጅነት በገነት ውስጥ ለ፯ ዓመታት ጸንተውና
ጠብቀው ከቆዩ በኋላ አስወስደዋታል፡፡ ይኽንንም የእግዚአብሔር ልጅነት ለአዳምና ለዘሩ
ሁሉ ለማስመለስ ከሰማየ ሰማያት የወረደውና ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም
ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ አዳም በ፴ ዘመን
አግኝቶት የነበረውን ኋላም ያጣውን ልጅነት እንደመለሰለት ለማጠየቅ በ፴ ዘመኑ
ተጠመቀ፡፡
ክርስቶስ ለምን በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅ የአጋጣሚ ጉዳይ
አይደለም በወቅቱ ብዙ ወንዞች እያሉ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በዮርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀበት ምክንያት ትንቢቱ ምሳሌውና ምሥጢሩ ይፈጸም
ይታወቅ እና ይገለጥ ዘንድ ነው፡፡
ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ
ጌታ በዮርዳኖስ ወንዝ እንደሚጠመቅ ድርጊቱ ከመፈጸሙ ከሺህ ዘመን ቀደም ብሎ
በቅዱስ ዳዊት አማካኝነት ትንቢት ተነግሮ ነበር፡፡
‹‹ባሕር አየች ሸሸችም ዮርዳኖስም ወደ ኋላ ተለመሰ›› መዝ. 113÷3
ምሳሌውን አማናዊ ለማድረግ

ገጽ 4
አብርሃም፡-ከገንዘቡ አሥራት አውጥቶ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ መልከጼዴቅ መሄዱ
ዘፍ.14÷17-24
ነቢዩ ኤልያስ፡- ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ብሔረ ሕያዋን ማረጉ 2 ኛነገ.2÷7-11
የሶርያው ንዕማን፡-በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ከሥጋ ደዌ መፈወሱና ከለምጹ መንጻቱ 2 ኛነገ.5÷14
ጻድቁ ኢዮብ፡-በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ከሥጋ ደዌ መፈወሱ፣ እነዚህ ሁሉ የጥምቀት ምሳሌዎቹ
ይፈጸሙ ዘንድ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ፡፡
ዮርዳኖስ ከላይ ነቁ (መነሻው) አንድ ነው፡፡ ዝቅ ብሎ በደሴት ይከፈልና ከታች ወርዶ ይገናኛል፡፡ ዮርዳኖስ ከላይ
ነቁ ምንጩ አንድ እንደሆነ ሁሉ የሰው ልጅ መነሻው አንድ አዳም ነው፡፡ ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ በደሴት
እንደተከፈለ እስራኤል በግዝረት አሕዛብ በቁልፈት (ባለመገረዝ) ተለያይተው ኖረዋል፡፡ ዮርዳኖስ ከታች ወርዶ
በወደብ እንዲገናኝ ሕዝብና አሕዛብ ተብሎ ለኹለት የተከፈለው የሰው ልጅ በክርስቶስ ጥምቀት አንድ ሆኗል፡፡
(ትርጓሜ ወንጌል ዘማቴዎስ ገጽ 97-98)
ጌታችን ለምን በውኀ ተጠመቀ?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በውኃ ነው፡፡ጌታችን የዓለም ፈጣሪ ሆኖ ሳለ ጥምቀቱን
ውድ በሆኑ ሌሎች ነገሮች ያላደረገው ይልቁንም በውኃ ያደረገው ለምንድነው?
የውኀ ጥምቀት መሠረቱ ሕገ ወንጌል ነው፡፡ ጌታችን ኒቆዲሞስን ስለነገረ ጥምቀት ሲያስተምረው ‹‹ሰው
ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም›› ያለው ለዚህ
አብነት ነው፡፡ ጥምቀት በውኃ የመሠራቱ ምሥጢር፡-
 በኖኅ ዘመን ፍጥረት ሁሉ በውኃ ጠፍቶ ነበር፡፡ ከዚህ የተነሣ ውኃ ለመዓት እንደተፈጠረ ይታሰብ
ነበር፡፡ ዳሩ ግን ውኃ ለምሕረትና ለድኅነት የተፈጠረ መሆኑን ለማሳየት ጌታም ጥምቀቱን በውኃ
አድርጓል፡፡ እኛም በውኃ ተጠምቀን ድኅነት እንደምናገኝ አስገንዝቦናል፡፡
 ውኃ በአትክልት ላይ ቢያፈሱት ያለምልማል እናንተም በውኀ ብትጠመቁ ልምላሜ ሥጋና ነፍስን
ታገኛላችሁ ሲል ነው፡፡
 ውኀ በኹሉም ቦታ ላይ ለሁሉ ሰው ይገኛል፤ጥምቀትም ለመላው የሰው ዘር የተሰጠ ነው፡፡ (ትርጓሜ
ወንጌል ዘማቴዎስ ገጽ 100)
መንፈስ ቅዱስ ለምን በርግብ አምሳል ወረደ?
 በኖኅ ዘመን ርግብ ‹‹የጥፋት ውኀ ጎደለ›› ስትል የወይራ ቅጠል ይዛ መጥታለች፡፡ አሁን ደግሞ
መንፈስ ቅዱስ ‹‹የኃጢአት ባሕር ጎደለ›› ሲል በርግብ አምሳል ታየ፡፡
 ርግብ ቢመቷት እንቁላሏን ቢያፈርጡባት ቤቷን ካላፈረሱባት በስተቀር ቦታዋን አትለቅም መንፈስ
ቅዱስም ኃጢአት ቢሠሩ ጨርሰው ካልካዱት ማለትም ሰው ሕንፃ እግዚአብሔር መሆኑን ዘንግቶ
በራሴ ሐሳብና ምኞት የምንቀሳቀስ ፈጣሪ የሌለኝ ነኝ ብሎ ካልካደ በስተቀር ከፍጥረቱ አይለይም፡፡
 ርግብ የዋህ ናት ቂም በቀል አትይዝም መንፈስ ቅዱስም በደልን ይቅር ባይ የዋህ በኃጢአት በደል
ቂም የማይዝ ተጸጽተን ይቅር በለን ካልነው ይቅር የሚል ነው፡፡
ጌታችን በማን ስም ተጠመቀ?
ጌታችን ዮሐንስን አጥምቀኝ ባለው ጊዜ ሌላውን ያጠምቅ ነበርና ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለሁ አንተን ግን በማን ስም
ላጥምቅህ? በአብ ስም እንዳላጠምቅህ አብ አባትህ በአንተም ህልው ነው በወልድ ስም እንዳላጠምቅህ ወልድ አንተ ነህ
በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳላጠምቅህ መንፈስ ቅዱስ ሕይወትህ በአንተም ውስጥ ህልው ነው፡፡ ታዲያ በማን ስም
ላጥምቅህ ብሎ በጠየቀው ጊዜ ‹‹እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዐት አንተ የዘላለም ካህን ነህ ብርሃንን የምትገልጥ የብሩክ የአብ የባሕርይ
ልጅ ሆይ ይቅር በለኝ›› 52 ብለህ አጥምቀኝ አለው፡፡
ዮሐንስ ጌታን ሲያጠምቀው እጁን ለምን አልጫነበትም?
 እጁን ቢጭንበት ኖሮ ዮሐንስ ጌታን አከበረው ብለው በኋላ ዘመን የሚነሡ ሐሰተኞች በተናገሩ ነበር፡፡
 የመለኮትን አካል መንካት ስለማይችል ነው፡፡
የምሥጢረ ጥምቀት አመሠራረት

ገጽ 4
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአዳምን ዘር ሁሉ ለማዳን ሰው ሆኖ በመዋዕለ ሥጋዌው በትእዛዝና
በተግባር ጥምቀተ ክርስትና ከመመሥረቱ በፊት በኦሪትና በአይሁድ ልማድ የተለመዱ የጥምቀት ዓይነቶች ነበሩ፡፡
እነርሱም፡-
የአይሁድ ጥምቀት
በአይሁድ ሕግ መጽሐፈ ኦሪትን መሠረት አድርገው ይፈጽሙት የነበረ መታጠብ ሲሆን በእነርሱ እምነት አንድ
ሰው በኦሪት ከተጻፉት የረከሱ የሚባሉትን የነካ፣ ወደ እርሱ ማደሪያ የገባ ሁሉ ከርኩሰት ለመንጻት ይፈጽሙት
የነበረ የመታጠብ ልማድ ነበር፡፡ በመሆኑም የአይሁድ ጥምቀት አፍአዊ ወይም ሥጋዊ እንጂ መንፈሳዊ ንጽሕና
ድኅነት አያስገኝም ነበር፡፡ (ዘሌ.6÷27፣ ዘኊ.19÷18-20፣ መዝ.50÷51)
የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ጥምቀት
የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጥምቀት የንስሐ ወይም የዝግጅት ጥምቀት ነው፡፡ ለሰው ልጆች ድኅነት
የሆነው መድኃኔዓለም መምጣቱን እየተናገረ ሰዎች ኹሉ የመሲሁን መምጣት ተዘጋጅተው እንዲጠብቁ የንስሐ
ጥምቀት ያጠምቅ ነበር፡፡ (ማቴ.3÷11፣ ማር 1÷4-6)
በዘመነ ክርስትና
በሐዲስ ኪዳን ምሥጢረ ጥምቀት የሚፈጸመው በኦሪት እንደነበረው ልማድ ለመንጻት ሥጋዊ ሥርዐት ሳይሆን
አማናዊ ምሥጢር ነው፡፡ የምሥጢረ ጥምቀት መሥራች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ጌታችን
ምሥጢረ ጥምቀትን የመሠረተው በተግባር በማሳየት፣ በቃል (በትምህ ርት)፣ በማዘዝ ነው፡፡ (ማቴ.3÷3-16፣
ማቴ.28÷19፣ ዮሐ.3÷5፣ ማር.6÷16)
የሰው ልጆች ጥምቀት
ጥምቀትን የመሠረተልን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የጥምቀትን ዕድሜ በተመለከተ ግን
ጌታችን በ፴ ዓመቱ ስለተጠመቀ እኛም ይህንኑ ዕድሜ እንጠብቃለን ማለት አይደለም፡፡ ሥርዐተ ጥምቀትን
ስንመለከት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለጥምቀት ቀዳሚውን ሥፍራ መስጠቷን
እንመለከታለን፡፡ በመሆኑም በማን ስም እንጠመቅ? መቼ እንጠመቅ? የሚሉትን ጥያቄዎች ሁሉ መልስ በመስጠት
ታስተምራለች፡፡
ሰዎች በማን ስም ሊጠመቁ ይገባቸዋል?

52. ትርጓሜ ወንጌል ዘማቴዎስ ገጽ 100


ጥምቀት የሚፈጸመው በቅድስት ሥላሴ ስም ነው፡፡ ‹‹ሂዱና አሕዛብን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
አጥምቁ›› የሚለውን አምላካዊ ትእዛዝ መሠረት በማድረግ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በቅድስት ሥላሴ
ስም ታጠምቃለች፡፡ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምታመልከው የሥርዐት አምላክ የሆነውን ልዑል እግዚአብሔርን
ነው፡፡ በመሆኑም በደነገገላት ሥርዐት እየተመራች አምልኮቷን ትፈጽማለች፡፡
የጥምቀት ዕድሜ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት እና ሥርዐት መሠረት ለጥምቀት የተወሰነ የተገደበ
የዕድሜ ወሰን የለውም፡፡ አምኖ የእግዚአብሔርን ልጅነት ፈልጎ የመጣውን ሁሉ አስተምራ አዘጋጅታ
ታጠምቃለች፡፡ ይህም ቢሆን ግን የሕፃናት ወላጆቻቸው ክርስቲያኖች ከሆኑ የቤተሰቦቻቸውን እምነትና
መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ በ፵ና በ፹ ቀናቸው ታጠምቃቸዋለች፡፡ ሕፃኑ ለሞት የሚያሰጋ ሆኖ ከተገኘ
በሞግዚት አማካኝነት ከዚያ ቀን በፊት ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሄዶ መጠመቅ ይችላል፡፡
የሕፃናት ጥምቀት
ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ወንዶች በተወለዱ በ፵ቀናቸው ሴቶች ደግሞ በተወለዱ በ፹ቀናቸው
ታጠምቃለች፡፡ ለዚህም ኹለት ምክንያቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው አዳም በተፈጠረ በ፵ ቀኑ ከመንፈስ ቅዱስ
ተወልዶ ወደ ገነት ገብቷል፡፡ ሔዋንም በተፈጠረች በ፹ ቀኗ ከመንፈስ ቅዱስ ተወልዳ ወደ ገነት ገብታለች፡፡
ኩፋ. 4÷12-15

ገጽ 4
ኹለተኛው ምክንያት በኦሪት ወንድ ሲወለድ በ፵ ሴት ስትወለድ በ፹ ቀኗ መዋዕለ ንጽሕ ስለሚፈጸም ከዚያ
በኋላ ሕፃናቱን ወደ መቅደስ በማምጣት መሥዋዕት ያቀርቡላቸው ነበር፡፡ ዘሌ. 12÷1-8 (ሐዋ.16÷34፣ 16÷15፣
1 ኛቆሮ.1÷10፣ ማር.10÷14)
የንዑሰ ክርስቲያን ጥምቀት
ንዑሰ ክርስቲያን የሚባሉት ካደጉ በኋላ የክርስትና እምነት ተቀብለው እስኪጠመቁ ድረስ በትምህርት የሚቆዩ
ሲሆኑ በቤተ ክርስቲያን እየተማሩ ከምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በስተቀር በሌሎች አገልግሎት እየተሳተፉ
ለሦስት ዓመታት እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡ የሦስት ዓመቱን ትምህርት ከጨረሱና እምነታቸውን ካረጋገጡ በኋላ
ይጠመቃሉ፡፡ (ሲኖዶስ 8÷32፣ ቀኖና ኒቂያ አንቄጽ 14)
የጥምቀት ጥቅም (አስፈላጊነት)
ጥምቀት ከምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን መካከል የመጀመሪያ የሆነ ምሥጢር ነው፡፡ ያለ ጥምቀት ከሌሎች
ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ተሳታፊ መሆን አይቻልም፡፡ በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጅ እንባላለን፡፡ ከሥላሴ
በጥምቀት መወለድም የእግዚአብሔርን ርስት መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ ነው፡፡ መንግሥተ ሰማያትን
በጥምቀት እንጂ ያለ ጥምቀት ልንገባበት እንደማንችል ጌታችን አስተምሮናል፡፡ ከጥምቀት ውጭ ድኅነት
የለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደተነገረው ጥምቀት የሚከተሉት ዋና ዋና ጠቀሜታዎች አሉት፡፡
የእግዚአብሔርን ልጅነት ማግኘት
ሰው ከአባቱና ከእናቱ ሥጋዊ ልደትን እንደሚወለድ ሁሉ ከመንፈስ ቅዱስ ደግሞ በጥምቀት አማካኝነት
መንፈሳዊ ልደትን ይወለዳል፡፡ በዚህ መንፈሳዊ ልደትም የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል፡፡ በልጅነት ጸጋውም
የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ ባለ ተስፋ ይሆናል፤ በጊዜውም የተዘጋጀለትን የአባቱን መንግሥት
ይወርሳል፡፡ ጌታችን በጥምቀቱ ማያትን ስለቀደሳቸው በጸሎት አማካኝነት ማየ ጥምቀቱ ሲቀደስ ተጠማቂዎች
በሚታየው በውኃው የማይታየውን ረቂቅ ልደት የሚወለዱበት ማኅፀን ይሆናል፡፡ ይህ በጥምቀቱ የሚገኘው
ዳግመኛ ልደት የማይጠፋና የማያዳግም ዘለዓለማዊ የልጅነት ማኅተም ነው፡፡ (ዮሐ.3÷5፣ 1 ኛጴጥ.1÷23፣ ገላ.4÷6-7፣
ዮሐ.1÷12)
‹‹በዮርዳኖስ ውኀ በተጠመቀ ጊዜ ክርስቶስ ይህ ምሥጢር ዳግመኛ ተገለጠ ጥምቀትንም ሽቶ
አልተጠመቀም አምላክ በሥጋ ተገልጦ ጥንተ ልደትን ዳግመኛ ይሰጠን ዘንድ ነው እንጂ›› (ሃይ. አበ.
ዘሳዊሮስ ምዕ 87 ቁ.15)
መንግሥተ ሰማያትን መውረስ
በጥምቀት የምናገኘው የእግዚአብሔር የልጅነት ጸጋ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ የምንችል ባለ
ተስፋዎች እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ልጅ ያልሆነ ርስት የመውረስ መብት እንደሌለው ሁሉ በጥምቀት ዳግመኛ
ያልተወለደና የእግዚአብሔርን የልጅነት ጸጋ ያላገኘ ሰውም በራሱ ምግባርና ትሩፋት ብቻ የእግዚአብሔርን
መንግሥት መውረስ አይችልም፡፡ (ዮሐ.3÷5፣ 2 ኛቆሮ.5÷5፣ ገላ.4÷7)
‹‹ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን አብረንም ደግሞ
እንድንከብር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን››ሮሜ. 8÷15-17
ሥርየተ ኃጢአት
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን ከፅንሠቱ ጀምሮ እስከ ዕርገቱ ድረስ ያደረገው
ነገርና የሰጠው ጸጋ፣ እንዲሁም በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ የቆረሰው ሥጋውና ያፈሰሰው ደሙ ሞትን ድል
አድርጎ መነሣቱ ሁሉ ለእያንዳንዳችን የሚደርሰን በጥምቀት አማካኝነት ነው፡፡ ጌታችን በዕለተ ዓርብ በመስቀል
ላይ ሳለ ሌንጊኖስ ጎኑን በጦር በወጋው ጊዜ ከቅዱስ ጎኑ ውኃ እና ደም እንዲወጣ የፈቀደው ለዚህ ነበር፤ ከጎኑ
በተገኘው በውኃውና በደሙ ልጅነትንና ሥርየተ ኃጢአትን እንድናገኝ ነው፡፡ በማየ ገቦው እንጠመቃለን ደሙን
ደግሞ በምሥጢረ ቁርባን እንቀበለዋለን፡፡ በተለያየ ኃጢአት የነበሩ ሰዎች (ንዑሰ ክርስቲያን) በአሕዛብነት
በነበሩበት ጊዜ የፈጸሟቸው የርኩሰት ሥራዎች በጥምቀት ሥርየት ያገኛሉ፡፡ 53
‹‹ንስሐ ግቡ ኃጢአታችሁ ይሠርይላችሁ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ›› ሐዋ. 2÷37
‹‹ኃጢአት የሚሠረይባት ጥምቀት አንዲት እንደሆነች እናምናለን››(ሃይ. አበ. ዘሠልስቱ ምዕት ምዕ.17 ክ 1 ቁ 12)
የድኅነት ዋስትና ነው

ገጽ 4
ድኅነት በሐዲስ ኪዳን ያለ ምሥጢረ ጥምቀት ሊፈጸምና ሊከናወን አይችልም፡፡ አንድ ሰው ሳይጠመቅ
የዘለዓለም ሕይወት መውረስ አይችልም፡፡ስለዚህ ምሥጢረ ጥምቀት ዘላለማዊ ሕይወት ድኅነትን ገንዘብ
የምናደርግበት ነው፡፡
‹‹ያመነ የተጠመቀም ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል›› ማር. 16÷16
ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ጋር መተባበር
ጥምቀት የጌታችንን ሞትንና ትንሣኤውን ማመናችንን በተግባር የምንመሰክርበትና ከሞቱና ከትንሣኤው
የምንሣተፍበት ምሥጢር ነው፡፡ ጌታችን ስለ እኛ ሲል ሞትን በፈቃዱ ተቀብሎ ከዚያም ወደ መቃብር
ወርዶ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደቆየ እኛም ያን ማመናችንን በተግባር ለመመስከር እንዲሁም ከሞቱ ጋር
ለመተባበርና ሞቱን እንደ እርሱ ነፍሳችንና ሥጋችን ተለያይተው በተግባር በመሞት ባይሆንም እንኳ በምሳሌ
ለመሳተፍ እንጠመቃለን፡፡ ስንጠመቅም ወደ ውኃው ሦስት ጊዜ እየገባን እንወጣለን፡፡ ክርስቶስ ወደ መቃብር
ወርዶ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ቆየ እኛም የፈለገ ዮርዳኖስ አምሳል በሆነው ማየ ጥምቀት ውስጥ
ሦስት ጊዜ በመግባት ከሞቱ ጋር እንተባበራለን፤ ጌታችን ሞትንና የመቃብርን ይዞ የማስቀረት ኃይል ሰውነትን
የማፍረስና የመለወጥ ኃይሉን ድል አድርጎ ዳግመኛ ሳይሞት እንደተነሣ እኛም ከውኃው እንወጣለን፡፡
‹‹ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን
ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደተነሣ እንዲሁ
እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር
ተቀበርን፡፡ ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ
ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን›› ሮሜ. 6÷3-5

53. ጥምቀት የኃጢአት ሥርየት የሚያስገኘው ለንዑሰ ክርስቲያን ነው፡፡

የክርስቶስ አካል የቤተ ክርስቲያን አባል እንሆናለን


በዘመነ ኦሪት ለአብርሃም ዘሮች የእግዚአብሔር ሕዝብ መሆናቸው ለማረጋገጥ መገረዝ ሃይማኖታዊ
ግዴታቸው ነበር፡፡ ለክርስቶስ ዜጎችም መጠመቅ የክርስቶስ ቤተሰቦች የቤተ ክርስቲያን አባልነታቸው
የሚረጋገጥበት ማኅተም ነው፡፡
‹‹ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና›› ገላ. 3÷27
የጥምቀት ዓይነት
ጥምቀት በመሠረቱ የሚፈጸመው በውኃ ነው፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜ ለሰው ልጅ ይህ ሁሉ ተሟልቶ ባይገኝ ሰው
ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከመግባት እንዳይከለከል ጥምቀት የሚፈጸምባቸው መንገዶች አሉ፡፡ ይህ ማለት
ግን የተለያየ ጥምቀት አለ አያሰኝም፡፡ የጥምቀት ባሕርይዋ ዓላማዋ አንድ ሲሆን በተለያየ ሁኔታ ይፈጸማል፡፡
የውኃ ጥምቀት
የውኃ ጥምቀት መሠረቱ ሕገ ወንጌል ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ወንዶች በተወለዱ በ፵ ቀናቸው
ሴቶች በተወለዱ በ፹ ቀናቸው ይፈጸምላቸዋል፡፡ ይህም የአዳምና የሔዋንን ልደት መሠረት በማድረግ ነው፡፡
አዳም በተፈጠረ በ፵ኛ ቀኑ ሔዋን በተፈጠረች በ፹ ቀኗ አግኝተውት የነበረውን የልጅነት ጸጋ አስወስደው
ስለነበር የልጅነት ጸጋ ባገኙበት ቀን እንድንጠመቅ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ሠራች፡፡ (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 3)
‹‹ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት አይገባም›› ዮሐ. 3÷3
የደም ጥምቀት
አስቀድመው ኢአማኒ የነበሩ በኋላ ግን ለመጠመቅና የክርስቶስ ቤተሰቦች ለመሆን ወስነው ለዚህም ለመብቃት
በመማር ላይ እንዳሉ ከመጠመቃቸው በፊት ስለ እግዚአብሔር ብለው በአላውያን ነገሥታት እጅ በሰማዕትነት
ቢያልፉ ያፈሰሱት ደም ጥምቀት ይሆንላቸዋል፡፡
‹‹ጥምቀትን ያልተቀበለ ማንም ቢሆን ድኅነትን አያገኝም፡፡ በደመ ጥምቀት በሰማዕትነት ያለፉ ሰማዕታት ግን
በውኃ ባይጠመቁ እንኳን ድኅነትን ያገኛሉ፡፡›› (ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፣ ማቴ.10÷32-39)

ገጽ 4
አንዲት ጥምቀት
ጥምቀት አንዲት ናት፡፡ ኦርቶዶክሳውያን አባቶቻችን ‹‹ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት›› ሲሉ
ጥምቀት አንድ ጊዜ ብቻ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የልጅነት ጥምቀት አንዲት እንደሆነች ሲያስረዳ
‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት›› ሲል ይገልጽልናል፡፡ (ኤፌ. 4÷6) የልጅነት ጥምቀት የማይደገም
አንድ ብቻ የሆነበት ምክንያት አለው፡፡ ይኸውም፡-
 ከሥጋዊ ወላጆቻችን በሥጋ የምንወለደው አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ ሁሉ ከመንፈሳዊ አባታችን
የምንወለደው መንፈሳዊ ልደታችንም አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ዮሐ. 3÷6-8
 የጥምቀት ምሳሌ የሆነው ግዝረት አንድ ጊዜ ብቻ እንደሚፈጸም ጥምቀትም አንድ ጊዜ ብቻ
ይፈጸማል፡፡ ቆላ. 2÷11-13
 ጥምቀት ከጌታ ሞትና ትንሣኤ ተሳታፊ የምንሆንበት ምሥጢር በመሆኑ ጌታም የሞተውም
የተነሣውም አንድ ጊዜ ነውና፡፡ ሮሜ. 6÷8
ማጠቃለያ
 ጥምቀት የሚፈጸመው በሥላሴ ስም ነው፡፡ ማቴ. 28÷19
 ጥምቀት አትደገምም፡፡ ሮሜ. 6÷3፣ ኤፌ. 4÷5
 ከክርስቲያን ቤተሰብ የሚወለዱ ሕፃናት ወንዶች በ፵ ቀን ሴቶች በ፹ ቀን ይጠመቃሉ፡፡
 ጥምቀት ወደ እግዚአብሔር መንገሥት ያገባል፡፡ ያልተጠመቀ የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ
አይችልም፡፡ ዮሐ. 3÷5
 ጥምቀት የኃጢአት ሥርየት የሚያስገኘው ለንዑሰ ክርስቲያን ነው፡፡
3.4 ምሥጢረ ቁርባን
መግቢያ
ምሥጢረ ቁርባን ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት አንዱ ነው፡፡ ቁርባን መዳናችን የተፈጸመበትና የታተመበት
የምሥጢራት ሁሉ ዘውድ እና ማኅተም ነው፡፡ ምሥጢረ ቁርባን ክርስቶስ ስለእኛ ኃጢአት በመስቀል ላይ
መሥዋዕት ሆኖ በሥጋው በመሞቱ የዓለምን ኃጢአት ያስወገደበት የዘለዓለም ሕይወት ያስገኘበት የመዳናችን
መሠረት የጸጋችን ሁሉ ምንጭ የሆነውን የቅዱስ ሥጋውንና የክቡር ደሙን የማዳን ጸጋ የሚያመለክት ታላቅ
የክርስትና ሃይማኖት ምሥጢር ነው፡፡
ቁርባን ማለት ምን ማለት ነው?
ቁርባን የሚለው ቃል የሱርስት ሲሆን ትርጉሙ በቁሙ መንፈሳዊ አምኃ፣ መሥዋዕት፣ መባዕ፣ ለአምላክ የሚቀርብ
የሚሰጥ ገንዘብ 180 ማለት ነው፡፡ (ኪ.ወ.ክ ገጽ 807) ቁርባን በብሉይ ኪዳን በኹለት መንገዶች ይቀርብ ነበር፡፡ ከሥጋና ከደም ወገን
የሆነው ‹‹መሥዋዕት›› ሲባል ከእኅል ወገን የሆነው ደግሞ ቁርባን ይባላል፡፡
ምሥጢረ ቁርባን ካህኑ ኅብስቱን በጻሕል ወይኑን በጽዋዕ አድርጎ በጸሎተ ቅዳሴው በባረከው ጊዜ ኅብስቱ ወደ ሥጋ መለኮት ወይኑ
ወደ ደመ መለኮት የሚለወጥበትና እኛም የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት ይኽንን የክርስቶስ ሥጋና ደም የምንቀበልበት ዐቢይ
ምሥጢር ነው፡፡
ቅዱስ ቁርባን በብሉይ ኪዳን
ቁርባን ወይም መሥዋዕት ለአምላክ ስለ ኃጢአት ይቅርታ የሚቀርብ መባዕ ወይም ስጦታ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን
የሚቀርበው መሥዋዕት እንደ ዓላማው ዓይነት የድኅነት፣ የበዓል፣ የኃጢአት፣ የሚቃጠል ነበር፡፡ እነዚህ የመሥዋዕት
ዓይነቶች ከርግብና ከዋኖስ ጀምሮ እስከ ወይፈኖችና ጊደሮች ድረስ ለኃጢአት ማስተሥሪያ ይታረዱ፣ ይቃጠሉ፣ ይበሉ
የነበሩ ናቸው፡፡ የብሉይ ኪዳን ቁርባን ዓይነቶችና አፈጻጸማቸው ለሰው ልጅ ፍጹም የሆነውን የነፍስ ድኅነት ባያሰጡትም
በጊዜው ድኅነተ ሥጋና ጊዜያዊ እርቅን ከማሰጠት አልፈው ተስፋ አሰጥተዋል፡፡ (ገላ.4÷3-7፣ ዘፍ.8÷20-22፣ ዘፍ.9÷8-17፣
መዝ.101÷3) ሰው ከበደለ በኋላ ከኃጢአቱ ነጻ የሚሆነው ንስሐ በመግባቱ ብቻ አይደለም፡፡ ከንስሐው በኋላ መሥዋዕት
ማቅረብ ደም ማፍሰስ ይጠበቅበታል፡፡ የኃጢአተኛውን በደል የሚሸከም ወይም ፍርዱን የሚቀበል ሌላ ያልበደለ ነጻ አካል
ለመሥዋዕትነት ሊቀርብ ያስፈልጋል፡፡ በብሉይ ኪዳን ብዙ ጥጆችና ጊደሮች በጎችና ፍየሎች ለመሥዋዕትነት ቀርበዋል፡፡
ሆኖም የሰውን ኃጢአት በሙሉ ሊያነጹ አልቻሉም፡፡
‹‹ደምም ሳይፈስ ሥርየት የለም›› ዕብ. 9÷22

ገጽ 4
‹‹የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና›› ዕብ. 10÷4
የቅዱስ ቁርባን ምሳሌዎች በብሉይ ኪዳን
ብሉይ ኪዳን ለሐዲስ ኪዳን ባለው ቀዳማዊነትና ጥላነት አካሉን ሐዲስ ኪዳንን የሚያሳይበት በርካታ ምሳሌዎችንና
ትንቢቶችን ይዟል፡፡ በዚሁ መሠረት እንደሌሎቹ ምሥጢራት ሁሉ ምሥጢረ ቁርባንም ምሳሌ የሚሆኑለት ድርጊቶች
በብሉይ ኪዳን ተከናውነዋል፡፡ አማናዊው ምሥጢረ ቁርባን በሐዲስ ኪዳን ከመመሥረቱ በፊት በሕገ-ልቡናና በሕገ-ኦሪት
በተለያዩ ምሳሌዎች ሲቀርብ ነበር፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ለአብነት የሚሆኑትን እንጠቅሳለን፡፡
የአብርሃም መሥዋዕት ዘፍ 22÷13
እግዚአብሔር አብርሃምን የሚወደውን አንድ ልጁን መሥዋዕት አድርጉ በሞሪያ ተራራ ላይ እንዲሠዋለት በጠየቀው
ጊዜ አብርሃም ልጁን ይስሐቅንና ሌሎች አገልጋዮችን አስከትሎ የመሠዊያውን እንጨት፣ ቢላዋና እሳት ይዞ ሄደ፡፡ ወደ
ቦታውም ከመድረሱ በፊት ኹለቱን አገልጋዮቹን በሩቁ እንዲጠብቁት አድርጎ እንጨቱን ለልጁ አሸክሞ ሲሔድ ይስሐቅ
“የመሥዋዕቱ በግ የት አለ”? ብሎ ሲጠይቀው አብርሃምም የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል ብሎታል፤
ሊሠዋውም በተዘጋጀበት ወቅት መልአከ እግዚአብሔር ተገልጾ ከልክሎታል፡፡ በይስሐቅም ፈንታ እግዚአብሔር
ያዘጋጀውንና በዕፀ ሳቤቅ ታስሮ የወረደውን በግ ሠውቷል፡፡
‹‹አብርሃምም ዐይኑን አነሣ በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ
አብርሃምም ሄደ በጉንም ወሰደው በልጁም ፋንታ መሥዋዕት አድርጎ ሠዋው›› ዘፍ 22÷13
አብርሃም በልጁ በይስሐቅ ፈንታ የሠዋው ይህ በግ ለአማናዊው የእግዚአብሔር በግ ለጌታችን ለመድኃኒታችን
ለኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ አብርሃም በጉን በይስሐቅ ፋንታ እንደሠዋው ኹሉ ክርስቶስም ለአዳምና ለልጆቹ ኹሉ
መሥዋዕት ሆኖ ተሠውቷል፡፡

የመልከ ጼዴቅ መሥዋዕት ዘፍ. 14÷18-20


መልከ ጼዴቅ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ በብሉይ ኪዳን ይኖር የነበረ ሰው ነው፡፡ መልከ
ጼዴቅ በዘመነ ኦሪት ከቀደምት አበው ሁሉ ለየት ባለ መልኩ በቀራንዮ ኮረብታ ላይ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱም በኋላ
እንደሚያቀርቡት የደም መሥዋዕት ሳይሆን በኅብስትና ወይን ይሠዋ ነበር፡፡ አብርሃም አምስቱ ነገሥተ ኮሎዶጎሞርን
ወግቶ ሲመለስ መልከ ጼጼቅ ኅብስትና ወይን ይዞ ተቀብሎታል፡፡
‹‹የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ፤ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን
ነበር፡፡›› ዘፍ. 14÷18
መልከ ጼዴቅ የጌታ አንድም የቀሳውስት ምሳሌ፣ ኅብስተ አኮቴት ጽዋዕ በረከት የጌታ ሥጋና ደም ምሳሌ ነው፣
አብርሃም የምእመናን፣ አብርሃም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ኅብስቱንና ጽዋዕ እንደተመገበ ክርስቲያኖችም ተጠምቀው የጌታን
ሥጋና ደም የመቀበላቸው ምሳሌ ነው፡፡

የደብተራ ኦሪት ቁርባንና መሥዋዕት ዘሌ 16፣2-23


በብሉይ ኪዳን በደብተራ ኦሪት በመቅደሱ ውስጥና በዙሪያዋ ልዩ ልዩ የመሥዋዕት ቁርባንና መባዕ ይከናወኑ ነበር፡፡
የደብተራ ኦሪት ቁርባንና መሥዋዕት ለሐዲስ ኪዳን ቁርባን ምሳሌ ነው፡፡ (ዘሌ 23÷1-5፣ ዘሌ 12÷6)
‹‹መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት
እንዲሠምር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል፡፡›. ዘሌ. 1÷3

እስራኤል ከሞተ በኩር የዳኑበት በግ ዘጸ 12÷1-12


በግብጽ ባርነት ለ፬፻፴ ዘመን የኖሩት እስራኤላውያን በሙሴ መሪነት በእግዚአብሔር ኃይል ከፈርዖን መዳፍ ነፃ
የወጡት በግብጻውያን ላይ በታዘዘው ሞተ በኩር ምክንያት ነው፡፡ እግዚአብሔር በግብጻውያን ላይ የበኩር ልጅ ሞትን
እንደሚያመጣ ለሙሴ ሲናገር ሞተ በኩር እስራኤልን እንዳያገኛቸው ሊያደርጉት የሚገባውን በማስገንዘብ ነበር፡፡
እስራኤላውያን ከግብጽ ከመውጣታቸው በፊት እግዚአብሔር የግብጻውያንን በኩር ከሰውም ከእንስሳትም ሲያጠፋ
እስራኤል ከዚህ ጥፋት ይድኑ ዘንድ መልአከ ሞት እንዳይቀርባቸው የተሰጣቸው የበግ ደም ምልክት ነበር፡፡ እነርሱም
በታዘዙት መሠረት ሁሉን አድርገው ከሞተ በኩር ድነዋል፡፡ ይህም ሊመጣ ላለው ምሳሌ ነበር፡፡

የፋሲካ 54 በግ ዘጸ 12፣3-5

ገጽ 4
ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ጠቦት ምክንያተ ኃጢአት የሌለበት የንጹሐ ባሕርይ አምላክ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ
ነው፡፡ የበጉ ደም በተቀባበት ቤት ሞተ በኩር እንዳልደረሰ እንዲሁም ዛሬም በመስቀል ላይ ደሙን ባፈሰሰው ጌታ አምኖ
ሥጋውንና ደሙን የተቀበለ ሁሉ የዘላለም ሞት አያገኘውም፡፡ (1 ኛቆሮ 5÷7፣ራዕ 19÷9፣ 1 ኛጴጥ 1÷19)
‹‹የእናንተ ጠቦት ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ይሁን›› ዘጸ. 12÷5

54. ኦሪት ዘጸአት ትርጓሜ ገጽ 70 ላይ የፋሲካው በግ ማብራሪያ ይገኛል፡፡


መቃኑንና ጉበኑን ደም መቀባት ዘጸ 12÷7
እስራኤል የበጉን ደም በቤታቸው መቃንና ጉበን ላይ እንዲቀቡ ታዝዘው ነበር፡፡ ጠቀሜታው ከቀሳፊ መልአክ ይድኑ
ዘንድ ለምልክትነት ነበር፡፡ መልአኩ ደም የተቀባውን ቤት ሲያይ አልፎ ይሄድ ነበር፡፡ ለጊዜው ይህ ጠቀሜታ የነበረው
ሲሆን ፍጻሜው ግን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የተቀበሉ ሰዎች ከሞተ ነፍስ እንደሚድኑ ያመለክታል፡፡ (ዮሐ 6÷54)
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መቃኑና ጉበኑ የምእመናን ከንፈር ምሳሌ ነው በማለት ተርጉሞታል፡፡
‹‹ከደሙም ወስደው በሚበሉበት ቤት ኹለቱን መቃንና ጉበን ይቅቡት›› ዘጸ 12÷7
በእሳት የተጠበሰውን ብሉ ዘጸ 12÷8
በእሳት የተጠበሰውን ብሉ መባሉ በበግ የተመሰለው የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ
መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው መሆኑን አምናችሁ ተቀበሉ ማለት ነው፡፡
‹‹በእሳት የተጠበሰውን ሥጋውንና ቂጣውን እንጀራ በዚያች ሌሊት ይብሉ›› ዘጸ 12÷8
ከመራራ ቅጠል ጋር ብሉት ዘጸ 12÷8
እስራኤላውያን የፋሲካውን በግ በበሉ ጊዜ ከመራራ ቅጠል ጋር ብሉት የተባሉበት ምክንያት ለጊዜው የበሉት
እንዲዋሐዳቸው በኋላ ደግሞ የፋሲካውን በዓል ባከበሩ ቁጥር ያን መራራ የግብጽ ባርነት ዘመን እንዲያስቡት እና
እግዚአብሔርም ከዚያ ባርነት እንዳዳናቸው እንዲያስተውሉ ነው፡፡
ፍጻሜው ግን በፋሲካው በግ የተመሰለው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መራራ ሐሞትን እንደተቀበለ
ሥጋውና ደሙን በተቀበልን ቁጥር እንድናስታውስ ነው፡፡ (ዮሐ. 19÷28) ዛሬም ከመቁረብ በፊት አፋችን ምሬት
እስኪሰማው ድረስ አሥራ ስምንት ሰዓት መጾምና አሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል ማሰብ እንደሚገባን ሲያስተምረን
ነው፡፡
‹‹ከመራራ ቅጠል ጋር ይበሉታል›› ዘጸ. 12÷9
ጥሬውን አትብሉ ዘጸ. 12÷9
ጥሬውን አትብሉ የተባለበት ምክንያት ጥሬ ሥጋ በውስጡ ደም አለው፤ በደም ውስጥ ደግሞ ነፍስ ትኖራለችና ሥጋውን ከደም ጋር
አትብሉ ሲል ነው፡፡ (ሄኖ. 37÷26፣ኩፋ.7÷9) ምሥጢሩ ደግሞ ጥሬውን አትብሉ ሲል ነፍስ ያልተለየውን መለኮት ያልተዋሐደውን
የክርስቶስን ሥጋ እንደምትቀበሉ አድርጋችሁ አትውሰዱ ሲል ነው፡፡
‹‹ጥሬውን በውኃም የበሰበሰውን አትብሉ›› ዘጸ. 12÷9
ቅቅሉን አትብሉ ዘጸ. 12÷9
የተቀቀለ ሥጋ ብዙ እሳት ስለሚነካው ወደ መበስበስና መፈራረስ ይደርሳል፡፡ በውኃ ተቀቅሎ የፈረሰውን ሥጋ አትብሉ መባሉ ደግሞ
በበግ የተመሰለ የጌታችን ሥጋ በመቃብር ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ቢያድርም ሙስና መቃብር አገኘው አትብሉ ሲል ነው፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙስና መቃብር ሳያገኘው ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቷል፡፡
‹‹ነፍሴን በሲዖል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም›› መዝ. 15÷50
ራሱን መሐሉን እግሩን ብሉ ዘጸ. 12÷9
የጌታን ሥጋና ደም ስትቀበሉ ምንም ጌታችን ሥጋ ቢለብስ ራሱን (ቀዳማዊነቱን) መሐሉን (ማዕከላዊነቱን) እግሩን (ደኀራዊነቱን)
አምናችሁ ያለና የሚኖር አልፋና ኦሜጋ እርሱ እንደሆነ አምናችሁ ተቀበሉ ማለት ነው፡፡ (ራዕ. 1÷8)
‹‹ነገር ግን ከራሱ ከጭኑ ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት የተጠበሰውን ብሉት›› ዘጸ. 12÷9

የቀረውን በእሳት አቃጥሉት ዘጸ. 12÷10


እስራኤላውያን የተረፋችሁን ከእሳት ጨምሩት በተባሉበት መሠረት የተረፋቸውን የበጉን ሥጋ በእሳት ውስጥ
ጨምረውታል፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ይህን መሠረት በማድረግ መሥዋዕት አያድርም በማለት ሥርዐትን ደንግጋለች፡፡
ወገባችሁን ታጥቃችሁ ጫማ አድርጋችሁ በትር ይዛችሁ ፈጥናችሁ ትበሉታላችሁ ዘጸ. 12÷11

ገጽ 4
እስራኤላውያን የበጉን ጥብስ ሥጋ ሲበሉ ጫማቸውን ተጫምተው ወገባቸውን ታጥቀው ኩፌታቸውን ደፍተው በትራቸውን ይዘው እየተቻኮሉ
እንዲበሉ ታዘው ነበር፡፡ ለጊዜው እስራኤል መንገደኞች ነበሩና ለጉዞ የተዘጋጁ እንዲሆኑ ነበር፡፡ ፍጻሜው ዛሬ ላለነው ክርስቲያኖች ምሳሌ ሆኖን
የአማናዊውን በግ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋውን ደሙን ስንቀበል ምግባረ ወንጌል ሠርተን (ወንጌልን ተጫምተን) የንጽሕናን
ዝናር በወገባችን ታጥቀን አክሊለ ሦክን ነገረ መስቀሉን እያዘከርን (መስቀሉን ተመርኩዘን) ሞት እንዳለብን በማሰብ ፈጥነን ንስሐ በመግባት መሆን
እንዳለበት ያስረዳናል፡፡(ሉቃ. 12÷35፣1 ኛጴጥ.1÷13፣2 ኛቆሮ.6÷2፣ ማቴ.6÷36)
‹‹ወገባችሁን ታጥቃችሁ ጫማችሁን በእግራችሁ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ እንዲህ ብሉት ፈጥናችሁም
ትበሉታላችሁ›› ዘጸ. 12÷11
አጥንቱን አትስበሩ ዘጸ. 12÷46
እስራኤላውያን የመሥዋዕቱን በግ አጥንት እንዲሰብሩ አልተፈቀደም ነበር፡፡ ለጊዜው በአጥንት የተመሰሉት እስራኤላውያን አትሰበሩም መከራ
አያገኛችሁም ለማለት ሲሆን ፍጻሜው ግን እንደ አርዮስ አጥንት የሚሰብር ንግግር አትናገሩ ሲል ነው፡፡ አርዮስ ‹‹ወልድ ፍጡር በመለኮቱ››
ብሏልና፡፡ የፋሲካው መሥዋዕት አጥንት እንዳልተሰበረ ሁሉ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ በዕለተ ዓርብ በቀራንዮ
በሚሰቀልበት ጊዜ አጥንቱ እንደማይሰበር ለማጠየቅ ነው፡፡ (ዮሐ 19÷34)
‹‹በአንድ ቤትም ይበላ ከሥጋውም አንዳች ከቤት ወደ ሜዳ አታውጡ አጥንትም አትስበሩበት›› ዘጸ. 12÷46
ለእስራኤል የወረደው መና ዘጸ. 16÷13-20
የእስራኤል ልጆች ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት በሚጓዙበት ጊዜ መና ወርዶላቸው ያን ተመግበው ከረሃብ ድነዋል፡፡
ለእስራኤል ልጆች ከምድረ በዳ ከደመና የወረደላቸው መና ጌታ በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ ለሰው ልጆች ሲል የቆረሰው
ሥጋ ያፈሰሰው ደም ምሳሌ ነው፡፡ መናው የተገኘው ከደመና እንደሆነ ሁሉ ጌታም ሥጋና ነፍስን የነሣው ከቅድስት
ድንግል ማርያም ነው፡፡ ስለዚህ ደመናው ጌታ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነሥቶ ሰው የሆነባት የቅድስት ድንግል
ማርያም ምሳሌ ነው፡፡
‹‹አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ ሞቱም ሰው ከእርሱ በልቶ እንዳይሞት አሁን የወረደ እንጀራ ይህ
ነው፡፡ ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፡፡›› ዮሐ. 6÷49
ኢሳይያስ ከለምጽ የተፈወሰበት ፍሕም (ኢሳ 6÷6-8)
‹‹ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ በእጁም በመሠዊያው በጉጠት የወሰደው ፍሕም ነበር፡፡ አፌንም ዳሰሰበትና፡ - እነሆ ይህ
ከንፈሮችህን ነክቷል በደልህም ከአንተ ተወገደ ኃጢአትህም ተሠረየልህ አለኝ፡፡ ኢሳ. 6÷6-8
ለእግዚአብሔር ባለመታዘዙ ምክንያት የተነሣ በኢሳይያስ ከንፈር ላይ ለምጽ ወጥቶበት ነበር፡፡ ከለምጹ የተፈወሰው በፍሕም ነው፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ ከለምጽ የተፈወሰበት ፍሕም የቅዱስ ቁርባን ምሳሌ ነው፡፡ መልአኩ የቀሳውስት አንድም የዲያቆናት፣ ጉጠቱ የዕርፈ
መስቀል፣ ፍሕም የሥጋ ወደሙ፣ ኢሳይያስ የምእመናን፣ ለምጹ የፍዳ የመርገም ምሳሌ ነው፡፡ ኢሳይያስ ከለምጹ በፍሕሙ እንደዳነ
ምእመናንም ሥጋ ወደሙን ተቀብለው የኃጢአት ሥርየት የማግኘታቸው ምሳሌ መልአኩ ፍሕሙን በእጁ ሳይሆን በጉጠቱ መያዙ
ዲያቆናትም ሥጋ ወደሙን በእጃቸው መንካት እንደማይችሉ ያስረዳል፡፡፡
የቅዱስ ቁርባን አመሠራረት በሐዲስ ኪዳን
መሥዋዕተ ኦሪት ነፍስንና ሥጋን የማንጻት ኃይል ስላልነበረው ለሰው ልጆች ፍጹም ድኅነት ሊሰጥ አልቻለም ነበር፡፡
ነገር ግን ከአምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን በኋላ ለሚሠራው ለሐዲስ ኪዳን ሥርዐት ምሳሌ በመሆን አገልግሏል፡፡
በሐዲስ ኪዳን ምሥጢረ ቁርባን የተመሠረተው በጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የብሉይ
ኪዳን መሥዋዕት የሰው ልጅን ከሞተ ነፍስ እንዳላዳነ እግዚአብሔር አይቶ የጠፋውን አዳም ሊያድን ራሱ መሥዋዕት
አቅራቢ ካህን፣ ይቅር ባይ ዋጋ ከፋይ ሆኖ መሥዋዕተ ኦሪትን ሽሮ መሥዋዕተ ሐዲስን(ምሥጢረ ቁርባንን) በትምህርትና
በተግባር መሥርቶታል፡፡ (ኤር.31÷33-34፣ ዮሐ.6÷54፣ ማቴ.26÷26፣ 1 ኛቆሮ.11÷23-26)
መሥዋዕተ ኦሪት አልፎ መሥዋዕተ ሐዲስ የተጀመረው በምሴተ ሐሙስ በአልዓዛር ቤት ነው፡፡ በኦሪቱ ለኃጢአት
ማስተሥሪያ ይቀርብ የነበረው የበግ የፍየል ደም መሥዋዕት ሊመጣ ላለው ለሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት ለአማናዊው በግ
ለኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ በመሆኑ ጌታም በሐሙስ ምሽት በአልዓዛር ቤት የቀደመውን ምሳሌያዊ የነበረውን መሥዋዕት
ሽሮ አዲሱንና ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚገኝበትን መሥዋዕት ተክቷል፡፡ ስለዚህ ይህ ምሽት ምሥጢረ ቁርባን
የተመሠረተበት ዕለት ነው፡፡

ጌታ ሥጋ ወደሙን ለምን ተቀበለ?


ጌታ ሥጋ ወደሙን የተቀበለው ዛሬ እኛ ተቀብለን የምናገኘውን ክብር ጸጋ ሊያገኝ አይደለም፡፡ ሥጋዬ እውነተኛ መብል
ነው ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነው ብሎ ባስተማረ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ተጨንቀው ነበርና እነርሱን ለማደፋፈር አብነት
ለመሆን ነው፡፡ አንድም ሥርዐትን ለሐዋርያት ለማሳየት ነው፡፡ በኋላ ዘመን የሚነሡ ካህናት ምንም ቢቀድሱ ቢያቆርቡ
ራሳቸው ቆርበው ሌላውን ማቁረብ እንደሚገባቸው ሥርዐት ሲሠራ ነው፡፡

ምሥጢረ ቁርባን በመብልና በመጠጥ ለምን ሆነ?

ገጽ 4
ቅዱስ ቁርባን የሚዘጋጀው ከምግብና ከመጠጥ (ኅብስትና ወይን) ነው፡፡ ስንዴው ወፍ ካልጠረጠረው፣ ዋግ ካልመታውና
ነቀዝ ካልበላው ሲዘጋጅ ወይኑ ደግሞ ወፍ ካልመጠጠው እንዲሁም ዓመት ካላለፈው ንጹሕ ወይን ይዘጋጃል፡፡ ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ቁርባንን በመብልና በመጠጥ ያደረገበት ምክንያት አለው፡፡ ይኸውም፡-
 አስቀድሞ ኃጢአት ወይም ሞት ወደ ዓለም የገባው በመብል ነበርና በመብል ምክንያት የመጣውን ኃጢአት
በመብል በመጠጥ ለማጥፋት ሲል ነው፡፡ (ዘፍ. 3÷6)
 መብል መጠጥ ከሰውነት ይዋሐዳል፤ ስለዚህ ሥጋ ወደሙ በሚበላ በሚጠጣ መልክ መሆኑም ከሥጋችን
ከነፍሳችን ተዋሕዶ ሕይወት ልምላሜ የመሆኑ ምሳሌ ነው፡፡

ለምን ስንዴና ወይን ተመረጡ?


ቤተ ክርስቲያን የጌታን ቅዱስ ሥጋ ክቡር ደም ከወይንና ከስንዴ ታዘጋጃለች፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት የመጀመሪያው
ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ ሥጋውና ደሙን በስንዴና በወይን ስለሰጠ ነው፡፡ ከአዝርእት ሁሉ ለጌታ ሥጋ ይሆን ዘንድ ስንዴ
ከፍራፍሬ ደግሞ ለደሙ ወይን መሆኑ ምሳሌና ምሥጢር አለው፡፡
ምሳሌ፡- ክህነቱ ለወልደ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ ክህነት ምሳሌ ሆኖ የተጠቀሰው መልከ ጼዴቅ በወይን በስንዴ
ይሠዋ ነበር፡፡ ይህም ምሳሌነቱ ለጌታ ሥጋና ደም ነው፡፡ ዘፍ 14÷18
ትንቢት፡- ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት “በልቤ ደስታ ጨመርኩ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ” በማለት ትንቢት
ተናግሯል መዝ 4÷7
ምሥጢሩ፡- ስንዴ ስብ ሥጋን ይመስላል ወይን ደግሞ ትኩስ ደምን ይመስላል፡፡ በመሰለ ነገር ለመስጠት በታወቀ በተረዳ
ነገር ለማረጋገጥ በስንዴ በወይን አደረገው፡፡

ከቅዱስ ቁርባን መቀበል የሚገባው ማነው ነው?


ከቅዱስ ቁርባን መቀበል የሚገባው በ፵ና በ፹ ቀን ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ተጠምቆ ሀብተ ወልድና ስመ
ክርስትና የተሰጠው ሁሉ ነው፡፡ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ መወለድ እንዳለበት ሁሉ
የዘላለም ሕይወት ለመውረስ ቅዱስ ቁርባን መቀበል መንፈሳዊ ግዴታው ነው፡፡ ለተጠመቁ ሕፃናት በዕድሜ ለገፉ አረጋውያን፣ በቤተ
ክርስቲያን አገልግሎት ለሚሳተፉ ካህናት ብቻ ሳይሆን ለምእመናን በሙሉ መፈጸም ያለበት ምሥጢር ነው፡፡

‹‹እንዲህም አለ፡- ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው፡፡››
ማቴ. 26÷27
ከቅዱስ ቁርባን በፊትና በኋላ የሚደረግ ዝግጅትና ጥንቃቄ
ማንኛውም ክርስቲያን የጌታን ሥጋና ደም መቀበል ሃይማኖታዊ ግዴታው ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ሥጋ ወደሙ ከመቅረቡ በፊት
የሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት እና ቅዱስ ቁርባን ከተቀበለ በኋላ ማድረግ ያለበት ጥንቃቄ አለ፡፡
‹‹ስለዚህ ሳይገባው ይህን እንጀራ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት፡፡ ሰው ግን ራሱን
ይፈትን እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስሰማይለይ
ለራሱ ፍርድ ይበላልና ይጠጣልምና›› 1 ኛቆሮ.11÷27

ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የሚደረጉ ዝግጅቶች


 ሥጋ ወደሙን የሚቀበል ሰው አስቀድሞ ራሱን በካህን ማስመርመር ይገባዋል፡፡ የንስሐ ቀኖናውን ሳይጨርስ አይቆርብም፡፡
 ቅዱስ ቁርባን አማናዊ የጌታ ሥጋና ደም መሆኑን አምኖ መቁረብ አለበት፡፡
 አካልን መታጠብና አቅም የፈቀደውን ንጹሕ ልብስ መልበስ (ቢቻል ሙሉ ነጭ ቢሆን ይመረጣል) ይኖርበታል፡፡
‹‹ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው›› ራዕ. 6÷11
 ሥጋ ወደሙን ለመቀበል ለ 18 ሰዓት ያህል ከምግበ ሥጋ መከልከል ይገባል፡፡
 ቆራቢዎቹ የሚኖሩት በቅዱስ ጋብቻ ተወስነው ከሆነ ከቁርባን በፊት ለ 3 ቀናት ከቁርባን በኋላ ለ 2 ቀናት ከሩካቤ
መከልከል አለባቸው፡፡
 ለወንዶች ህልመ ሌሊት ሴቶች ደግሞ ልማደ አንስት (የወር አበባ) ቢያገኛቸው ወይም በልዩ ልዩ ምክንያት የሚደማ፣
የሚፈስ ቁስል ያገኛቸው ሁሉ ስለ ቅዱስ ቁርባን ክብር ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው ከምሥጢራት አይካፈሉም፡፡
 ሴቶች ወንድ ልጅ ከወለዱ እስከ ፵ ሴት ልጅ ቢወልዱ ከ፹ ቀናቸው በፊት ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው ቅዱስ ቁርባን
አይቀበሉም፡፡
 በአፉ ተዋሕሲያን የገቡ እንደሆነ በዚያን ቀን ሊቆርብ አይገባውም፡፡

ቅዱስ ቁርባን ከተቀበሉ በኋላ የሚደረግ ጥንቃቄ

ገጽ 4
 ከቆረቡ በኋላ በዚያው ዕለት ወደ ፍርድ ቤት መሔድና መሟገት ክልክል ነው፡፡
 ሥጋ ወደሙን ከተቀበልን በኋላ መስገድ የተከለከለ ነው፡፡
 በዚሁ ዕለት ለባለትዳሮች ሩካቤ፣ አብዝቶ መብላትና መጠጣት ጥፍር መቁረጥ፣ ጸጉር መላጨት በውኃ መታጠብና
ከልብስ መራቆት ክልክል ነው፡፡
 ሩቅ መንገድ መጓዝ፣ ሥራ መሥራት፣ ተላምጦ የሚተፉ ምግቦችን መብላት አይፈቀድም፡፡
 ምራቅ መትፋት አይፈቀድም፡፡
የቅዱስ ቁርባን አማናዊነት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት መሠረት የምንቀበለው ቁርባን አማናዊ (እውነተኛ) ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነት በቀራንዮ አደባባይ በመስቀል ላይ የቆረሰው እና ያፈሰሰው ቅዱስ
ሥጋውንና ክቡር ደሙን ነው፡፡ ለዚህ አብነት የምናደርገው የጌታን ትምህርት፣ የሐዋርያትን ስብከት እና የቅዱሳን አበው
የእምነት ውሳኔዎች ነው፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥርዐተ ቁርባንን ካቋቋመበት ከስቅለተ ዓርብ ዋዜማ ከምሴተ ሐሙስ በፊት
ኹለት ዓመት ያህል ቀደም ብሎ ከሰማይ ስለወረደው የሕይወት እንጀራ ማለት ስለ ሥጋውና ደሙ ምሥጢር ጌታ
ለሕዝቡ አስተምሯል፡፡ ጌታችን ስለ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ሲያስተምር እርሱ የሕይወት ኅብስት ከሰማይ የወረደ
የዘለዓለም ሕይወት ሰጪ መሆኑን አስተምሯል፡፡ ይህ ኅብስት ሥጋዬ ነው፤ ይህ ወይን ደሜ ነው እያለ ኅብስቱ ተለውጦ
ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት እንደሚሆን አስተምሯል፡፡

‹‹ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና›› ዮሐ. 6÷55

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ቁርባንን በመሠረተበት በሐሙስ ማታ ኅብስቱን አንሥቶ የሥጋው
ምሳሌ ወይም መታሰቢያ እንዳልሆነ አማናዊ ሥጋው እንደሆነ ገልጿል፡፡ በጽዋ ያለውንም ወይን ይህ ደሜ ነው አለ እንጂ
የደሜ ምሳሌ ወይም መታሰቢያ ነው አላለም፡፡

‹‹ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቆረሰም ለቀደ መዛሙርቱ ሰጠና፡- እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ
ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፡- ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች
ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው፡፡›› ማቴ. 26÷26-28

ለመታሰቢያ አድርጉት ሉቃ 22÷19-20

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የቅዱስ ቁርባንን ሥርዐቱን ከፈጸመላቸው በኋላ ‹‹ይህን
ለመታሰቢያዬ አድርጉት›› ብሏቸዋል፡፡ ይህንንም ያለበት ምክንያት ሥጋውን በበላን ደሙን በጠጣን ጊዜ ስለእኛ ሲል
መከራ የተቀበለውን እርሱን እናስባለን ከቤተልሔም ዋሻ እስከ ቀራንዮ ኮረብታ ለሰው ልጆች ድኅነት የፈጸመውን
የማዳን ሥራ እንድናዘክር የሚያስገነዝብ አነጋገር እንጂ የሥጋ ወደሙን አማናዊነት የሚያስተባብል አይደለም፡፡
‹‹ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ይህንንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን
ትናገራላችሁና፡፡›› 1 ኛቆሮ.11÷24-26

በምሥጢረ ቁርባን የሚገኝ ጸጋ

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም በብሉይ ኪዳን ዘመን ለመሥዋዕት ከሚታረዱ የበጎች ደም
የላቀና የከበረ ነው፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የከበረ ደም በመሆኑ ከፊተኛው ይልቅ የሚቀድስና የሚያነጻ ብዙ መንፈሳዊ
በረከትንና ጸጋን የሚሰጥ ነው፡፡
የብሉይ ኪዳኑ መሥዋዕት ሥጋን ለጊዜው ብቻ ከኃጢአት በማንጻት ሲያገለግል የሐዲስ ኪዳኑ ግን ነፍስና ሥጋን
የሚቀድስ ታላቅ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሚያድል ነው፡፡ የክርስቶስን ሥጋ ከደሙም የሚጠጣ በምሥጢራዊ መንገድ
ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ይኖረዋል፤ መንፈሳዊ ሀብትንና ጸጋን ያገኛል ርስት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳል፡፡ ቅዱስ ቁርባን
በመቀበላችን ፍጹም የሆኑ ሰማያዊያን እና መንፈሳዊያን በረከቶችን እናገኛለን፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡-

ዘላለማዊ ሕይወት ይሰጣል

ገጽ 4
የምንቀበለው ሥጋና ደም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አማናዊ ሥጋና ደሙ ነው፡፡ ስለዚህም
እግዚአብሔር ሕያው እንደሆነ ይህንን ሥጋ በበላን ጊዜ ሕያዋን እንሆናለን፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞት እንደሌለ ጌታችን
አምላካችን እርሱ ሞትን ድል እንዳደረገው ሁሉ ከዚህ ምሥጢር ተካፋዮች በሆንን ጊዜ ሞትን ድል የመንሣት እና
በፍጹም ዘለዓለማዊ መንግሥቱ የመኖር ክብርና ጸጋን እናገኛለን፡፡

‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው፡፡ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ›› ዮሐ.
6÷53
የኃጢአት ስርየት ያስገኛል

በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረው በመሥዋዕትነት የሚፈሰው የእንስሳት ደም የሰውን ልጅ መልሶ መቀደስ ማዳንና
ለኃጢአታቸውም ይቅርታ ሊሰጥ ስላልቻለ እግዚአብሔር ፍጹም ሰው ሆኖ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ
በደሙ መፍሰስ አዲስ የሥርየት ቃል ኪዳን ይኸውም ምሥጢረ ቁርባንን መሠረተልን፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የሰጠን የቀድሞ
ኃጢአታችንን ለማስተሥረይና እርሱን ተከትሎ የደረሰብንን መርገም ለማስወገድ ነው፡፡ ይህ የመጀመሪያው ሥርየትና
ኃጢአት ሲሆን ኹለተኛው ደግሞ የሰው ልጅ አምኖና ተጠምቆ ክርስትና ተቀብሎ እየኖረ በሃልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር
በሚሠራው ኃጢአት ተጸጽቶ ወደ ካህን ቀርቦ የሠራውን ኃጢአት ተናዞ ተገቢውን ምክር አግኝቶ ቅዱስ ሥጋውንና
ክቡር ደሙን ይቀበላል፤ ቅዱስ ቁርባኑም መድኃኒተ ሥጋ መድኃኒተ ነፍስ ይሆነዋል፡፡
‹‹ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደተመደበባቸው እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ
የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሠዋ በኋላ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ኹለተኛ ጊዜ ያለ
ኃጢአት ይታይላቸዋል፡፡›› ዕብ. 9÷28

ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ይሰጣል

በቅዱስ ቁርባን ከምናገኛቸው ጸጋዎች መካከል ከእግዚአብሔር ጋር በኅብረት መኖር ነው፡፡ ጌታችን ከእርሱ ጋር ኅብረት
የምናገኝበት ቅዱስ ቁርባንን ከመመሥረቱ በፊት አስቀድሞ በመዋዕለ ትምህርቱ ቁርባን በመቀበል ከፈጣሪያችን
የተለያየንበት ዘመን እንደተፈጸመና አሁን ግን ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የምንመሠርትበት ጊዜ እንደቀረበ አስተማረ፡፡
“ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ” ዮሐ 6፣57

የጋብቻ አንድነት ያረጋግጣል

ቅዱስ ቁርባን የምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ሁሉ ዘውድ እንዲሁም መደምደምያ ስለሆነ በሥርዓተ ተክሊል
የሚጋቡትን ተጋቢዎች አንድ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር ኹለቱን ተጋቢዎች አንድ እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው
የሚያጣምራቸው በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ ነው፡፡
ባልና ሚስት በገንዘብ፣ በዕውቀት፣ በዘር፣ በውበት ፍጹም አንድነትን ኅብረት ስምምነትን ሊያገኙ አይችሉም፡፡ ለባልና
ለሚስት አንድነት መሠረቱ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው፡፡
“ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው ወደ ፊት ሁለት አይደሉም፡፡ እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው”
ማቴ 19÷4

ማጠቃለያ

- ቅዱስ ቁርባን መታሰቢያ ወይም ምሳሌ ሳይሆን እውነተኛ የጌታ ሥጋና ደም ነው፡፡
- መሥዋዕት ከዕለት አያልፍም አይውልም አያድርም
- ቅዱስ ቁርባን የሚቆረበው ሳይበላ ሳይጠጣ ለ 18 ሰዓት በመጾም ነው፡፡
- ቅዱስ ቁርባን በተደጋጋሚ የምንቀበለው ምሥጢር ነው፡፡
- ቅዳሴ ሲጀምር ያልነበረ ሰው አይቆርብም

ገጽ 4
- በንስሐ ያለ ሰው የንስሐ ጊዜውን ሳይፈጽም ለሞት የሚያበቃ ደዌ ቢታመም ሥጋ ወደሙን ከመቀበል
አይከለከልም፡፡
3.5 ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን
መግቢያ
ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ማለት ሙታን በዓለም መጨረሻ የፈጣሪያቸውን የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰምተው ነፍስና
ሥጋቸው ተዋሕዶ በመቃብር የሚነሡና የዘለዓለም ሕይወትን የሚያገኙ መሆናቸውን የምንማርበት ምሥጢር ነው፡፡
ምሥጢር የተባለበትም ምክንያት ድርጊቱ የሚፈጸመው በመለኮታዊ ኃይልና ሥልጣን ስለሆነ በተፈጥሮ አእምሮአችን
ሁኔታውን በቀላሉ ለመረዳት ስለሚያዳግተን ነው፡፡ ትንሣኤ ሙታን ከአዳም እስከ ምጽአተ ክርስቶስ ከዚህ ዓለም በሞት
የተለዩና የሚለዩ የሰው ልጆች ሁሉ በነፍስና በሥጋ አዲስ ሕይወት ለብሰው የሚነሡበት ምሥጢር ነው፡፡
ትንሣኤ ማለት ምን ማለት ነው?
ትንሣኤ 55 ለሚለው ቃል መነሻ ግሡ ‹‹ተንሥአ›› 56 የሚለው የግእዝ ቃል ነው፡፡ ተንሥአ ማለት ‹‹ተነሣ›› ማለት
ሲሆን መነሣት፣ አነሣስ፣ አዲስ ሕይወት ማለት ነው፡፡ ሰው ጊዜው ሲደርስ ይሞታል፤ ነፍስና ሥጋው ይለያያል፡፡ ሰው ሁሉ
በሚሞትበት ጊዜ የጻድቅም ሆነ የኃጥእ ሥጋው በመቃብር ይቆያል፡፡ የጻድቃን ነፍስ በገነት የኃጥአን ነፍስ በሲዖል
ትቆያለች፡፡ ነገር ግን የተለያዩት ሥጋና ነፍስ በመጨረሻው ዘመን እንደገና እንደሚዋሐዱና በማይፈርስና በማይበስብስ
ሥጋ እንደሚነሡ እናምናለን፡፡ (ሃይ. አበ. ዘሠለስቱ ምዕት ምዕ. 17 ክ፣ 1 ቁ.13)
ሞት ምንድነው?
መሞት መለየት በነፍስ ከሥጋ በሥጋ ከነፍስ መራቅ እየብቻ መሆን መድረቅ መፍረስ መበስበስ መነ ቀል መፍለስ
መጥፋት መታጣት ነው፡፡ (ኪ.ወ.ክ ገጽ 581) የዚህ ዓለም ኑሮ መግቻ፣ የነፍስ ከሥጋ መለየት ወይም ሞት በቅድስት ቤተ
ክርስቲያን አስተምህሮ እረፍት፣ እንቅልፍ ይባላል፡፡ ይህ ሞት የሥጋ ስለሆነ የነፍስን ኑሮ አይገታውም፡፡ የሥጋ ሞት
ማለት የነፍስን ከሥጋ መለየት፣ እረፍት፣ እን ቅልፍ ከዚህኛው ከሚያፍፈው ዓለም ወደዚያኛው የማያልፈው ዓለም
መሔጃ፣ መሸጋገሪያ መንገድ ማለት ነው
ትንሣኤ ሙታን በመጽሐፍ ቅዱስ
ሙታን በመቃብር ውስጥ ፈርሰው በስብሰው እንደማይቀሩ ትንሣኤ እንዳላቸው በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ሥፍራ
ተጽፎ ይገኛል፡፡ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን የተጻፉትን የትንሣኤ ሙታን ማስረጃዎች እንደሚከተለው
ቀርቧል፡፡
ትንሣኤ ሙታን በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት
መላው የሰው ዘር በእግረ አጋንንት ይቀጠቀጥ በነበረበት ዘመን ስለሙታን መነሣት በብዙዎች ዘንድ የማይታመንና
የማይታሰብ ቢሆንም ቀደምት አበው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገልጦላቸው በኋላ ዘመን የሚሆነውንና
የሚደረገውን ትንሣኤ ሙታን የራቀውን እያቀረቡ ተናግረዋል፡፡ ለአብነት ያህል ብንጠቅስ፡-
“ሙታንም ሕያዋን ይሆናሉ ሬሳዎችም ይነሣሉ፡፡ምድር ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩ”ኢሳ 26÷19
“በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ይነቃሉ እኩሌቶቹ ወደ ዘለዓለም ሕይወት እኩሌቶቹ ደግሞ ወደ ዕረፍትና ወደ
ዘለዓለም ጉስቁልና” ዳን. 12÷2፣ (መዝ.16÷9፣ ሕዝ.37÷5፣ ዮናስ 2÷1)
ትንሣኤ ሙታን በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት
በሐዲስ ኪዳን ለምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ማስረጃ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ነው፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሙታንን ትንሣኤ አስመልክቶ ሲናገር ‹‹በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን
የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ
አታድንቁ›› (ማቴ. 5÷28-29) ብሏል፡፡ ክብር ምስጋና ይግባውና እርሱ ራሱ በገዛ ፈቃዱ በመስቀል ተሰቅሎ ቅድስት ነፍሱን
ከቅዱስ ሥጋው ለይቶ መለኮት ባልተለየው አካለ ነፍስ ወደ ሲዖል ወርዶ መለኮት ባልተለየው ሥጋው ወደ መቃብር ወርዶ
ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በምድር ልብ ቆይቶ መግነዙን ፍቱልኝ መቃብሩን ክፈቱልኝ ሳይል በታላቅ ኃይልና ግርማ
ተነሥቶ ትንሣኤያችንን አረጋግጦልናል፡፡
‹‹ኢየሱስ እንደሞተና እንደተነሣ ካመንን እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣችኋልና››
1 ኛተሰ 4÷14፡፡

55. ትንሣኤ በቁሙ መነሣት፣ አነሣስ፣ መውጣት፣ ብቅ ማለት መታደስ መብቀል ሐዲስ ሕይወት፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 642
56. ተንሥአ ተነሣ ነቃ፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 642
የጌታችን ትንሣኤና ዕርገት
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የከበረና የደስታ ሁሉ ምንጭ ነው፡፡ በትንሣኤው የዲያብሎስ ኃይል የተሻረበት
መቃብር የተዋጠበትና ሞት ራሱ የሞተበት ስለሆነ በክርስቲያኖች ዘንድ የጌታ ትንሣኤ በታላቅ ክብርና ደስታ የሚታሰብ
ነው፡፡ ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው እንደሚሞትና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ደጋግሞ ተናግሮ ነበር፡፡ በኋላም

ገጽ 4
የተናገረውን ቃል በተግባር በመፈጸም ሞትን ድል አድርጎ በመነሣት ትንሣኤውን አማናዊ አድርጓል፡፡ (ማቴ.20÷19፣
ሉቃ.18÷31-33፣ ማቴ.27÷62)
ጌታችን ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ቅድስት ነፍሱን ከክቡር ሥጋው በገዛ ሥልጣኑ ለየ፤ አሥራ አንድ ሰዓት ሲሆን ዮሴፍና
ኒቆዲሞስ ሥጋውን ከመቃብር አውርደው በአይሁድ የአገናነዝ ልማድ ሽቱ ቀብተው በተልባ እግር ልብስ ከፍነው ማንም
ባልተቀበረበት የአርማትያሱ ዮሴፍ ለራሱ ባዘጋጀው አዲስ መቃብር ቀበሩት፡፡ የመቃብሩም ደጃፍ በታላቅ ድንጋይ ተዘጋ
በማኅተም አተሙት፡፡ (ዮሐ.19÷30፣ ማቴ.26÷57-61፣ ማር.16÷16፣ ሉቃ.24÷3)
ጌታችን ቅድስት ነፍሱን ከክቡር ሥጋው በለየ ጊዜ በሥጋው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በመቃብር አደረ፡፡ በነፍሱ
ደግሞ ወደ ሲዖል ወርዶ በዚያ ለነበሩ ነፍሳት ነጻነትን ሰበከላቸው፡፡ ጌታችን እንደተናገረ በሦስተኛው ቀን መግነዝ ፍቱልኝ
መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ሙስና መቃብርን አጥፍቶ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሞት ተነሣ፡፡ በዚህም የነቢያት ትንቢት
ተፈጸመ፡፡ (1 ኛጰጥ.3÷13-19፣ መዝ.85፣ 11÷5፣ 3÷5፣ 106÷16)
ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ እስከ ዐርባኛው ቀን በተለያየ ቦታ ለሐዋርያት ተገለጠላቸው፡፡ በዐርባኛው ቀን
ወደ ቢታንያ አወጣቸው፡፡ እጁንም በመጫን ባረካቸው፤ ሥልጣነ ክህነት ሾማቸው፡፡ ድንገት የብርሃን ደመና ከበበው
ሁሉም እያዩት በርቀት ሳይሆን በመራቅ ከዐይናቸው ተሰወረ፡፡ በዐረገ በአሥረኛው ቀን ደግሞ ለሐዋርያት መንፈስ
ቅዱስን ላከላቸው፡፡ (ሉቃ. 24÷36-43)
‹‹የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ሆነ በጳንጦስ ሰው በጲላጦስ ዘመን ስለእኛ ተሰቀለ፤ ስለእኛ ታመመ ሞተ ተቀበረ፡፡
በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ በምስጋና በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱ
ዕሪና ተቀመጠ፡፡›› (ሃይ. አበ. ዘሠልስቱ ምዕት ምዕ. 17 ክ 1 ቁ 8-9)
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ የተነሣው በባሕርይ አባቱ በአብ ሥልጣን
በራሱ ሥልጣን እንዲሁም በባሕርይ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን ነው፡፡ (ሐዋ. 2÷32፣ 1 ኛቆሮ 15÷15፣ ሮሜ 6÷4፣ ዮሐ 2÷19)
የሦስት ቀንና የሦስት ሌሊት አቆጣጠር
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓርብ በሰርክ 11 ሰዓት ተቀብሮ እሑድ በመንፈቀ ሌሊት ከተነሣ እንዴት
ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር አደረ ሊባል ይችላል? ይህን ጥያቄ ብዙ ሰዎች ሲያነሡት ይደመጣል፡፡ ይህ ግን
የዕብራውያንን አቆጣጠር ካለመረዳት የመጣ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት
በከርሰ መቃብር እንደሚቆይ የተነገረ ትንቢትና ምሳሌ ነበር፡፡ (ማቴ. 12÷40፣ ዮሐ 2÷19)
አንድ ሰው ጌታ ዓርብ ተቀብሮ ቅዳሜ ሌሊት ለእሑድ አጥቢያ ከተነሣ እንዴት ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት በመቃብር
አደረ ሊባል ይችላል ቢል እንደ ዕብራውያን አቆጣጠር ሌሊት የሚቆጠረው በዋዜማው ካለው ዐሥራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ
ነው፡፡ ከዐሥራ ሁለት ሰዓት በፊት ያሉት ሰዓቶች ግን አንድ ሰዓትም ቢሆን እንደ አንድ መዓልትና ሌሊት ይቆጠራል፡፡ ጌታ
የተቀበረው ዓርብ ከአሥራ ሁለት ሰዓት በፊት ነው፡፡ ይህንንም የሚያረጋግጥልን ‹‹የመዘጋጀት ቀን ነበር ሰንበትም
ሊጀምር ነበር›› (ሉቃ. 23÷54-55) የሚለው አነጋገር ነው፡፡ ሰንበተ አይሁድ ቅዳሜ የሚገባው ከዓርብ አሥራ ሁለት ሰዓት
ጀምሮ ነው፡፡ ጌታ ወደ መቃብር የወረደው ዓርብ ዕለት አሥራ ሁለት ሰዓት ከመግባቱ በፊት ስለሆነ የተቀበረበት ሰዓት
የዓርብን መዓልትና ሌሊት ጠቅልሎ ይይዛል፡፡
ዓርብ ከሠርክ አሥራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ አሥራ ሁለት ሰዓት ከሰዓት በኋላ ድረስ ያለው የቅዳሜ መዓልትና
ሌሊት፤ ቅዳሜ ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ ጌታ እስከተነሣበት ሌሊት ያለችው እንደ አንድ ሙሉ ቀን
ይቆጠራል፡፡ በአጭር አገላለጽ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ዓርብ፡- ከዐሥራ ሁለት ሰዓት በፊት ያለችው ጌታ የተቀበረባት ሰዓት ከፊትዋ ያለውን ቀንና ሌሊት ስባ እንደ አንድ ሙሉ ቀን
ትቆጠራለች፡፡ (አንድ መዓልት አንድ ሌሊት)
ቅዳሜ፡- ዓርብ ከሠርክ ዐሥራ ሁለት ሰዓት እስከ ቅዳሜ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ያለው አንድ መዓልት አንድ ሌሊት
እሑድ፡- ከቅዳሜ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ጌታ እስከተነሣባት የእሑድ አጥቢያ ሌሊት እንደ አንድ መዓልት
አንድ ሌሊት ይቆጠራል፡፡ መዓልቱንም ይስባልና፡፡ 57
የጌታችን ትንሣኤ አማናዊነት
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ በሦስተኛው ቀን በመቃብር አለመገኘቱ ለአይሁድና ለተረፈ አይሁድ
እስከ ዛሬ ምሥጢር ቢሆንባቸውም ትንሣኤውን ለምናምን ክርስቲያኖች ግን የሕይወ ታችን ብርሃን ነው፡፡ የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሣት ለክርስትና ሃይማኖት የማዕዘን ደንጊያ ነው፡፡ጌታ ከሞት ባይነሣ ኖሮ ክርስትና
አይኖርም ነበር፡፡በመሆኑም የጌታ ትንሣኤ የክርስትና ሃይማኖት መሠረት ነው፡፡የጌታ ትንሣኤ ፍጹም ድኅነታችንን
ያሳያል፡፡ ምክንያቱም አስቀድሞ እንደሚነሣ ተናግሮ ስለነበር የተናገረው ሁሉ እውነት መሆኑን አረጋገጥን፡፡
በትንሣኤው እውነተኝነት ማመን በእምነት ውስጥ ወሳኝ ነገር ነው፡፡ በጥንት ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ሲገናኙ
‹‹ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ…. በእውነት ተነሣ›› በማለት ሰላምታ ይለዋወጡ ነበር፡፡ እነዚህ የክርስቶስን ትንሣኤ
አማናዊነት የሚያመለክቱ ሰላምታዎች ክርስቲያኖች በክርስቶስ ትንሣኤ ላይ ያላቸውን ጽኑ እምነት የሚያሳዩ ናቸው፡፡
የክርስቶስ ትንሣኤ አማናዊ ባይሆን ኖሮ ክርስትና ከንቱ ይሆን እንደነበር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ገልጿል፡፡

ገጽ 4
“ክርስቶስ ከሙታን እንደተነሣ የሚሰበክ ከሆነ ግን ከእናንተ አንዳንዶቹ ትንሣኤ ሙታን እንዴት የለም ይላሉ ? ትንሣኤ
ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሣማ ክርስቶስ ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው፤ እምነታችሁም ደግሞ
ከንቱ ናት … በዚህች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ ከሰው ይልቅ ምስኪኖች ነን” 1 ቆሮ 15÷12-
19
የጌታችን ዳግም ምጽአት
58
ዳግም ምጽአት ማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ ማለትም ለኃጥአን ሊፈርድባቸው ለጻድቃን
ሊፈርድላቸው የሚመጣበት ማለት ነው፡፡ ዳግም ወይም ኹለተኛ መባሉም ከዚህ በፊት እኛን ለማዳን በመምጣቱ ነው፡፡
ይህ አመጣጡ የሚጠበቅ ብቻ ሳይሆን የሚያስፈራና የሚያስደነግጥም ነው፡፡ ምክንያቱም ዳግም የሚመጣው እንደ
ፊተኛው በጥፊ ሊመታ፣ ምራቅ ሊተፋበት፣በገመድ ሊጎተት፣ በጅራፍ ሊገፈፍና በመስቀል ሊሰቀል አይደለም፡፡ ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አዕላፋት ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በጌትነት ይገለጻል፡፡ አመጣጡም በሥጋ
ማርያም በክበበ ትስብእት መሆኑን ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ገልጿል፡፡ (መዝ. 49÷2) ትክክለኛውን የሚመጣበትን ቀን
ማንም ፍጡር አያውቅም፡፡ (ማቴ. 24÷36) ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ በስተቀር የሰማይ መላእክትም ሆኑ የሰው
ልጆች አያውቁአትም፡፡ ስለዚህ የእኛ ድርሻ የመምጫውን ቀን ማስላት ሳይሆን እንደሚመጣ ማመንና ሲመጣ ከግራ
ቁመት ለመዳን መልካም ሥራ እየሠራን በኃጢአት በወደቅን ጊዜ ደግሞ ንስሐ እየገባን ተዘጋጅተን መኖር ብቻ ነው፡፡
የሰው ልጆች ትንሣኤ
በመጨረሻ ዘመን የሞቱ ሰዎች ይነሣሉ፡፡ ይህ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን አጠራር ‹‹ትንሣኤ ዘጉባኤ›› 59 ይባላል፡፡ የማኅበር
ትንሣኤ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በዚህ ወቅት የሞቱ ሁሉ በሥልጣነ እግዚአብሔር ተነሥተው ለፍርድ ቀርበው ጻድቃን
ወደ ዘለዓለም ክብር ኃጥአን ወደ ዘለዓለም መከራ የሚሔዱበት ቀን ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ በመነሣት አንድ ሲሆኑ
አነሣሣቸው ግን ለክብርና ለውርደት በመሆኑ ‹‹ትንሣኤ ዘለክብር›› እና ‹‹ትንሣኤ ዘለኀሳር›› ይባላል፡፡
ትንሣኤ ዘለክብር
ትንሣኤ ለመላው የሰው ዘር ሁሉ ነው፡፡ የኃጥኡም የጻድቁም ሥጋ ከፈረሰበት ትቢያውን አራግፎ ይነሣል፡፡ ትንሣኤ
ከሌላቸው እንስሳት በስተቀር የሰው ልጅ ሁሉ ይሞታል፣ ይፈርሳል አፈር ትቢያ ይሆናል፡፡ በአዲስ አካል ደግሞ በትንሣኤ
ዘጉባኤ ይነሣል፡፡

57. አዕማደ ምሥጢር፣ ማኅበረ ቅዱሳን ገጽ


58. ድጋሚ፡- ዳግሞሽ፣ዳግመኛ፣ኹለተኛ፡፡ኪ.ወ.ክ ገጽ 339
59. ጉባኤ፡- መሰብሰብ፣ አሰባሰብ፣ ስብሰባ፣ አንድነት፡፡

በዚህች ምድር ላይ ሳሉ በተቀደሰቸው ሃይማኖት ጸንተው መልካም ምግባር የሠሩ ሁሉ የክብር ትንሣኤ ይነሣሉ፡፡
ወንዶች የ፴ ዓመት ጎልማሳ ሴቶች ፲፭ ዓመት ቆንጆ ሆነው ፈጣሪያቸው ኢየሱስ ክርስቶስን መስለው በክብር ይነሣሉ፡፡
በመንግሥተ ሰማይ እንደ ክዋክብት ደምቀው በዘላለማዊ ደስታ ይኖራሉ፡፡ይህ የጻድቃን ትንሣኤ የክብር ትንሣኤ
‹‹ትንሣኤ ዘለክብር›› 60 ተብሎ ይጠራል፡፡
“ንጉሡም በቀኙ ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፡- እናንተ የአባቴ ቡሩካን ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ
የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ፡፡›› ማቴ 25÷34
ትንሣኤ ዘለኀሳር
ኃጥአን አፈር ትቢያ የነበረ ሥጋቸው ከነፍሳቸው ጋር ተዋሕዶ ይነሣል፡፡ ነገር ግን ትንሣኤያቸው የክብር አይደለም፡፡
አበጋዛቸው ዲያብሎስን መስለው ተስፋቸው ጨልሞ በገሃነመ እሳት ለዘለዓለም ይሰቃዩ ዘንድ ነው፡፡ ይህ የኃጥአን
ትንሣኤ ወደ መከራ ወደ ሥቃይ የሚሄዱበት በመሆኑ ‹‹ትንሣኤ ዘለኀሳር››61 ይባላል፡፡ “በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን
ደግሞ ይላቸዋል፡- እናንተ ርጉማን ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደተዘጋጀ ወደ ዘለዓለም እሳት ከእኔ ሂዱ” ማቴ 25÷41
የመለከት ድምፅ
የሰው ልጆች ትንሣኤ ሲፈጸም የራሱ የሆነ ሂደት አለው፡፡ ጌታ ዳግም በሚመጣበት ወቅት መላእክት የመለከትን ድምፅ
ያሰማሉ፡፡ የመለከት ድምፅ የተባለው የጌታ ትእዛዝ ምሳሌ ነው፡፡ በጌታ ትእዛዝ ሙታን ከያሉበት የሚሰበሰቡ ስለሆነ
በመለከት ድምፅ ተመስሏል፡፡ የመለከቱም ድምፅ ሦስት ጊዜ ይሰማል፡፡
1. በመጀመሪያው የመለከት ድምፅ በዓለም ዳርቻ ሁሉ የተበተነ የሥጋ ትቢያ ይሰበሰባል፡፡ በልዩ ልዩ ሞት
የተወሰደው፣ ፈጽሞ ያረጀና የጠፋው፣ ሁሉ ወደ ቀደመ መገናኛው ይሰበሰባል፡፡
2. በሁለተኛው የመለከት ድምፅ አጥንቶች ከሥጋና ከደም ጋር ይያያዛሉ፣ ያለ መንቀሳቀስ ያለመናወጥም እስከ
ጊዜው ድረስ ፍጹም በድን ይሆናል፡፡

ገጽ 4
3. በሦስተኛው የመለከት ድምፅ ሙታን እንደ ዐይን ጥቅሻ ይነሣሉ፡፡ ጻድቃንና ኃጥአን ክፉም ቢሆን በጎም ቢሆን
በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ የሠሩትን ከምድር የተከተላቸውን ሥራቸውም ተሸክመው ይነሣሉ፡፡
‹‹መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት
ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ፡፡ ማቴ. 24÷31፣ (1 ኛቆሮ.15÷52፣ 1 ኛተሰ 4÷16)
በትንሣኤ እንለወጣለን
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ከትንሣኤ በኋላ የሚኖረን አካል ከመሞታችን በፊት ከነበረን አካል ጋር አንድ እንደሆነ
አስተምረዋል፡፡ ልዩነቱ የማይሞትና የማይበሰብስ ወደ መሆን መለወጡ ብቻ ነው፡፡ ይህ መለወጥ የማይሆን ከሆነ ትንሣኤ
ረብ የሌለው ይሆናል፡፡ ጌታችን በከበረ ሥጋ እንደተነሣ የሰው ልጆችም በማይደክም፣ በማይራብ፣ በማይታመምና
በማይሞት ሥጋ ይነሣሉ፡፡
‹‹የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው፡፡ በመበስበስ ይዘራል ባለመበስበስ ይነሣል፤ በውርደት ይዘራል
በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል በኃይል ይነሣል፡፡››1 ኛቆሮ 15÷42-44
ከሞት በኋላ የሚገኘው ሕይወት
ሞት የሰው ልጆች የሕይወት ፍጻሜ አይደለም፡፡ ይልቁንም ለጻድቃን ከዚህች ምድር ወደ ተሻለችውና ዘለዓለማዊ
ደስታ ወዳለበት ቦታ መሸጋገሪያ ድልድይ ነው፡፡ የአንድ ሰው ነፍስ ከሥጋው በምትለይበት ጊዜ ወደ ዐፀደ ነፍስ ትጓዛለች፡፡
ዐፀደ ነፍስ የሚባሉት ገነትና ሲዖል ሲሆኑ ገነት የጻድቃን ጊዜያዊ ማረፊያ ስትሆን ሲዖል ደግሞ የኃጥአን ጊዜያዊ ማቆያ
ነው፡፡ ከምጽአተ ክርስቶስ በኋላ በገነት ያሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ በሲዖል ያሉ ወደ ገሃነመ እሳት ይዘዋወራሉ፡፡ የጻድቃን
ነፍስ በገነት ውስጥ ተድላ ደስታ ብታደርግም ፍጹም ተድላና ደስታ የሚገኝባትን መንግሥተ ሰማያትን ወርሰው በፍጹም
ክብር የሚኖሩባት ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላ ነው፡፡
‹‹ጌታ ኢየሱስም እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ አለው›› ሉቃ. 23÷43

60. ክብር፡- በቁሙ ልዕልና፣ ላቂያ፣ ብልጫ፣ ሹመት፣ ሸልማት፣ ታላቅነት፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 519
61. ኀሳር፡- ሕጸጽ፣ ውርደት፣ መከራ፣ ዕጦት፣ ጉዳት፣ ጉስቁልና፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 487
የትንሣኤ ሙታን ምሳሌ በመጽሐፍ ቅዱስ
በሰው ልጆች ትንሣኤ እንደተነገረ ሁሉ ሙታን ለመነሣታቸው ምሳሌዎች አሉ፡፡ (ዘፍ. 21÷2፣ ዮሐ 11÷44፣ ማቴ 9÷25፣ ሉቃ
7÷15፣ ሐዋ 9÷36)
 በአቤል ሞት ሞታችን ከሞተ በኋላ በደሙ መናገሩ ትንሣኤያችን ታውቋል፡፡
‹‹ሞቶም ሳላ በመሥዋዕቱ እስከአሁን ይናገራል›› ዕብ. 11÷4
 በኄኖክና በኤልያስ ዕርገት ትንሣኤ እንዳለ ታውቋል፡፡
‹‹ኄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ እግዚአብሔርም ስለወሰደው አልተገኘም›› ዕብ. 11÷5
 ይስሐቅ አባቱ በኅሊናው ከሠዋው በኋላ ከሞት መዳኑ የትንሣኤ ምሳሌ ነው፡፡
‹‹እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንዲቻለው አስቦአል›› ዕብ. 11÷19
የትንሣኤ ሙታን ምሳሌ በሥነ ፍጥረት
ፀሐይ፡- ከምሥራቅ መውጣቷ ለመወለዳችን ወደ ምዕራብ መሔዷ በዚህ ዓለም ለመኖራችን በምዕራብ መግባቷ
ለመሞታችን ዞራ በምሥራቅ መውጣቷ የትንሣኤያችን ምሳሌ ነው፡፡
እኅል፡- ስንዴ መዘራቱ ለመቀበራችን መብቀሉ ለመነሣታችን ምሳሌ ነው፡፡
‹‹አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም›› 1 ኛቆሮ 15÷36
እንቅልፍ፡- መተኛታችን የመሞታችን ከእንቅልፍ መንቃታችን የመነሣታችን ምሳሌ ነው፡፡
‹‹ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን ኀሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ
መበስበስን አየ›› ሐዋ. 13÷36
በበግና በፍየል የተመሰሉት እነማን ናቸው?
ጻድቃን በበግ ኀጥአን በፍየል ተመስለዋል፡፡ ይህም የበጎች ተፈጥሮአዊ ባሕርይ ለጻድቃን፣ ወይም የፍየሎች ተፈጥሯዊ
ባሕርይ ለኃጥአን ተመስሎ ነው፡፡ ምክንያቱም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
በጎች ደጋ እንጂ ቆላ አይስማማቸውም፣ ጻድቃንም በመከራ ሥጋ እንጂ በተድላ በደስታ ለመኖር ሲሉ ሃይማኖታቸውን ክደው
ስብእናቸውን አጉድፈው በምግባር ብልሹነት አይገኙም፡፡ ፍየሎች በቆላ እንጂ በደጋ አይኖሩም ኃጥአንም በተድላ በደስታ
ለመኖር ሲሉ ሃይማኖታቸውንም ለኃላፊ ነገር ይለውጣሉ፡
በጎች እረኛቸው ባሰማራቸው ሥፍራ ጸንተው ይኖራሉ፡፡ ጻድቃንም እረኛቸው ክርስቶስ ባሰማራቸው በአንዲት
ሃይማኖት ጸንተው ይኖራሉ፡፡ ፍየሎች እረኛቸው ባሰማራቸው ሥፍራ ጸንተው አይቆዩም እንዲሁ ሲባዝኑ

ገጽ 4
እረኛቸውንም ያደክማሉ፡፡ ወይም የአውሬ ቀለብ ይሆናሉ፡፡ ኃጥአንም በሃይማኖታቸው አይጸኑም፤ እምነት መሰል
በሆነው ሁሉ ዘመናቸውን ያባክናሉ፣በአንድ አይረጉም፡፡
በጎች ላታቸው የወደቀ ኀፍረተ ሥጋቸው የተሸፈነ ነው፡፡ የጻድቃንም ኃጢአታቸው በሰው ዘንድ የተገለጠ
አይደለም፤ በኃጢአት ተሰናክለው ቢወድቁ ሌላ ሰው ሳይሰናከልባቸ ው የንስሐን ምርኩዝ ተመርኩዘው በፍጥነት
ይነሣሉ፡፡ የፍየሎች ላታቸው የተሰቀለ ኀፍረታቸው የተገለጠ ነው፡፡ ኀጥአንም እንዲሁ ናቸው፡፡ ነውራቸው አደባባይ
የወጣ ኃጢአታቸው ለሰው የተገለጠ እነርሱም በዚህ የማያፍሩ ናቸው፡፡
ከበጎች መካከል አንዲቱ በአውሬ ከተነጠቀች የቀሩት ሁሉ በርግገው ከበረታቸው ወጥተው ይሔዳሉ፡፡ በዚያውም
እንደወጡ ይቀራሉ፡፡ ፊታቸውን ወደዚያ ሥፍራ አይመልሱም፡፡ ጻድቃንም ሞት ከእነርሱ መካከል አንዱን ድንገት
ነጥቆ በወሰደው ጊዜ ነገም የእነርሱ ተራ እንደሚሆን ተረድተው ከኃጢአት በረት በንስሐ ይወጣሉ፡፡ ዳግመኛም ወደ
ቀደመ ግብራቸው አይመለሱም፡፡
ፍየሎች ግን ከመካከላቸው አውሬ አንዷን ሲወስድ ለጊዜው ደንብረው ከበረታቸው ውስጥ ይወጣሉ፡፡ የኋላ ኋላ
ግን እዚያው ተመልሰው ይገኛሉ፡፡ ኃጥአንም ከመካከላቸው አንዱ ባልጀራቸው ድንገት ሲሞት ለጊዜው ይደነግጣሉ፡፡
በኀሳባቸውም ከኃጢአት በረት ለመውጣት ይወስናሉ፡፡ ዳሩ ግን ጥቂት ቆይተው ይዘነጉታል፤ ወደ ቀደመ ግብራቸው
ይመለሳሉ፡፡
‹‹አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ እረኛም በጎችን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው
ይለያቸዋል፡፡›› ማቴ. 25÷32
የቀኝና የግራ ምሳሌ
ቀኝና ግራ የተባለው ቦታውን ለማመላከት ሳይሆን የጻድቃንና የኃጥአን ዕድል ፈንታ ለመግለጥ ነው፡፡
ቀኝ፡- ኃይለኛ፣ ቅን፣ ቀልጣፋ ነው፡፡ ጻድቃንም ለምግባር ለትሩፋት ኃይለኞች፣ ቅኖችና ቀልጣፎች
ናቸው፡፡ በክርስትናቸው ምክንያት በሚገጥማቸው መከራና ፈተና ሳይረበሹ ክርስትናው የሚፈቅደውን ሕግና
ሥርዐት ሲጠብቁ ሃይማኖታቸውን ከምግባራቸው ጋር ሲያስተባብሩ አያማርሩም፣ ተስፋ አይቆርጡም፡፡
ግራ፡- ደካማ፣ ጠማማ፣ ዳተኛ ነው፤ ኃጥአንም ለምግባር ለትሩፋት ደካማ፣ ጠማማ፣ ዳተኞች
ናቸው፡፡ በክርስትናቸው ምክንያት በሚገጥማቸው መከራና ፈተና ይረበሻሉ፡፡ ክርስትናው የሚፈቅደውን ሕግና
ሥርዐት አይጠብቁም፡፡ሃይማኖት ከምግባር አያስተባብሩም፡፡
‹‹በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል፡፡›› ማቴ. 25÷33
ማጠቃለያ
- ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣው በራሱ ሥልጣን ነው፡፡
- በትንሣኤ ሙታን እናምናለን፣ የሚመጣውንም ሕይወት ተስፋ እናደርጋለን….. ሠለስቱ ምዕት
- የሰው ልጆች ከሞት ከተነሡ በኋላ ጻድቃን ወደ ዘለዓለም ዕረፍትና ሕይወት ኃጥአን ደግሞ ወደ ዘለዓለም
ዕረፍትና ጉስቁልና ይሄዳሉ፡፡

ምዕራፍ አራት
ነገረ ማርያም
ነገረ ማርያም ከኹለት ተባባቢ ቃላት የተገኘ ነው፡፡ ነገር የሚለው ቃል በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የአንድን
ትምህርት መግለጫ አጉልቶ የሚያሳይ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ማርያም ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም የተሰጠ ክቡር ስም
ነው፡፡
ነገረ ማርያም በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም በኩል ለሰው ልጅ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተገለጠውን ሁሉ
የምንማርበት ነው፡፡ በዚህ ትምህርት በሰው ልጆች የመዳን ምሥጢር ውስጥ የእመቤታችን የድንግል ማርያም
አስተዋጽኦ እንመለከታለን፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም የተሰጣት ጸጋ፣ ክብርና ቅድስና እኛ ልናቀርብላት የሚገባን ክብር፣
ስግደት፣ ምስጋና ወዘተ ምን እንደሆነ ተገቢ ዕውቀት እናገኛለን፡፡ የሚጀምረውም ከስሟ ትርጓሜ ነው፡፡
የቅድስት ድንግል ማርያም የስሟ ትርጓሜ
ማርያም 62 የሚለው ስም በተለያዩ ቋንቋዎች ልዩ ልዩ ትርጉም ተሰጥቶት ይገኛል፡፡ ከዚህ መካከል በዕብራይስጥ
ማርያም ማለት እመ ብዙኃን (የብዙዎች እናት) ማለት ነው፡፡ በግብጻውያን ቋንቋ ደግሞ ማርያም የኹለት ቃላት ጥምር
ሲሆን ‹‹ማር›› ማለት ‹‹ተወዳጅ›› ማለት ነው፡፡ በግብጻውያን ‹‹ያም›› በዕብራይስጥ ስመ አምላክ የሆነው ‹‹ያህዌ››
ማለት ነው፡፡ ስለሆነም ማርያም ‹‹በእግዚአብሔር የተወደደች›› ማለት ነው፡፡
የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት

ገጽ 4
ወላዲተ አምላክ የሚለው ቃል ምንጩ ቴኦቶኮስ የሚለው የግሪክ ቃል ነው፡፡ ቴኦቶኮስ ከኹለት ተናባቢ ቃላት የተገኘ
ነው፡፡ ይኸውም ቴኦስ ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲሆን ቶኮስ ማለት ደግሞ እናት ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል ወደ አማርኛ
ሲተረጎም ‹‹የእግዚአብሔር እናት›› ፣ ‹‹የአምላክ እናት›› ‹‹አምላክን የወለደች›› ማለት ነው፡፡ የእመቤታችን ወላዲተ
አምላክነት ከአካላዊ ቃል ሰው መሆን ጋር ይያያዛል፤ የእመቤታችን ወላዲተ አምላክነት ከነገረ ድኅነት ጋር ቁርኝት
አለው፡፡ የእመቤታችን ወላዲተ አምላክነት ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት፣ ፈጣሪነት፣
አዳኝነት እና እግዚአብሔርነት ጋር ተያያዥነት አለው፡፡

62. ማርያም፤- ከቅድስት ሥላሴ ኹለተኛውን አካል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች (ወላዲተ አምላክ በሥጋ) እመቤታችን፡፡ ደስታ
ተክለ ወልድ ገጽ 808
የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት ከአካላዊ ቃል ሰው መሆን ጋር ይያያዛል፡፡ አምላክ ሰው ሲሆን የሰዎችን
ባሕርይ ባሕርዩ ሲያደርግ አምላክን በመውለዷ ወላዲተ አምላክ የሚል ስያሜ አግኝታለች፡፡
‹‹የእውነት ብርሃን እናቱ ድንግል ሆይ እናከብርሻለን የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ሆይ ከፍ ከፍ
እናደርግሻለን ምክንያቱም ነፍሳችንን ይታደጋት ዘንድ የመጣውን የዓለም መድኃኒት የሆነውን ወልደሽ
ሰጥተሽናልና፡፡›› (በኤፌሶን ጉባኤ ላይ የረቀቀ)
ቅድስት ድንግል ማርያም የወለደችው መለኮትን ነውን?
አካላዊ ቃል በባሕርየ መለኮቱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሦስትነት
ሲመሰገን የነበረ ዘመን የማይቆጠርለት አስገኚ የሌለው፣ ለዘመኑ ጥንት ያልነበረው፣ ያለና የሚኖር ነው፡፡ ቅድመ ዓለም
አካል ዘእም አካል ባሕርይ ዘእም ባሕርይ ከአብ የተወለደ ነው፡፡ ከብርሃናዊው አብ የተገኘ እርሱ ብርሃን ነው፡፡
ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ተብላ የምትጠራው አካላዊ ቃልን በመለኮቱ ስለወለደችው አይደለም፡፡
ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረው ከባሕርይ አባቱ ከአብ በመወለዱ ‹‹ወልደ አብ በመለኮቱ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ይኽውም
‹‹በመለኮቱ የአብ ልጅ›› ማለት ነው፡፡
‹‹የመለኮቱ መገኘትም ከእመቤታችን ከተወለደ ወዲህ አይደለም፣ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዓለም
ሳይፈጠር የነበረ ጥበብ ነው እንጂ የማይታመም እርሱ ከባሕርየ መለኮቱ ሳይለወጥ ሕማም የሚስማማውን
ሥጋን ተዋሐደ›› (ሃይ. አበ ዘዮሐንስ አፈወርቅ ምዕ. 96 ክ 3 ቁ 3)
ቅድስት ድንግል ማርያም የወለደችው ሥጋን (ሰውን) ብቻ ነውን?
ቅድስት ድንግል ማርያም የወለደችው ሥጋን ወይም ሰው ብቻን ሳይሆን አማኑኤልን፣ የእግዚአብሔርን ልጅ እና ኃያል
አምላክ ተብሎ የሚጠራውን ሥግው ቃልን ነው፡፡ እመቤታችን የወለደችው ሥጋን ብቻ ቢሆን ኖሮ ሰብአ ሰገል
ለአምላክነቱ የሚገባውን እጅ መንሻና የአምልኮት ስግደት አያቀርቡለትም ነበር፡፡ እመቤታችን ሥጋን ብቻ የወለደች
ቢሆን ኖሮ መልአኩ ‹‹ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል›› በማለት አይናገርም
ነበር፡፡ ምክንያቱም በዳዊት ከተማ የተወለደው ያ ሕፃን ‹‹መድኃኒት›› እንደሆነ መገለጹ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ከእኔ በቀር
መድኃኒት የለም›› ከሚለው የእግዚብሔርን አዳኝነት ከሚገልጸው ቃል ጋር አንድ ነው፡፡ የተወለደው ሕፃን መድኃኒት
እንደሆነ መገለጹ ዕሩቅ ብእሲ ፍጡር ሰው ብቻ እንዳልሆነ ስለሚያሳይ ነው፡፡ ሰው ብቻ ካልሆነ እናቱም ወላዲተ ሰብእ
እንደማትባል መረዳት ይገባል፡፡ (ማቴ. 1÷23፣ 2÷11፣ ሆሴ. 13÷14፣ ኢሳ. 43÷11)
‹‹ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ
የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል›› ኢሳ. 9÷6፣ (ማቴ. 1÷23፣2÷11 ሉቃ. 1÷35)
ቅድስት ድንግል ማርያም የወለደችው ሥግው ቃልን ነውን?
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ ብላ በምታስተምርበት ጊዜ ሥግው ቃልን
እንደወለደች ለማጠየቅ ነው እንጂ የመለኮታዊ ባሕርይ ምንጭ እመቤታችን ናት እያለች አይደለም፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ
ስለእመቤታችን ወላዲተ አምላከነት ምስክርነት ሲሰጥና ስለምን ወላዲተ አምላክ እንደምትባል ሲያብራራ ‹‹ድንግል
ማርያምን ወላዲተ አምላክ የምንላት ቃል ከዊነ ቃልነቱን ከእርሷ ያገኘው ነው፤ ወይም የወልድ አካል የተገኘው ከእርሷ
ነው ብለን አይደለም፡፡ በመግቦት ምሥጢሩ ሰውን ለማዳን ከእርሷ በሥጋ ስለተወለደ ነው እንጂ›› በማለት ይናገራል፡፡
ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ ናት ብሎ የማይቀበል ማርያም የወለደችው ዕሩቅ ብእሲ ነው የሚል ምሥጢረ
ሥጋዌ ያልገባው ነው፡፡ የተዋሕዶን ምሥጢር፣ የምሥጢረ ሥጋዌን ትምህርት በሚገባ ሳይረዱና ሳይገነዘቡ
የእመቤታችን ወላዲተ አምላክነትና የሥግው ቃልን የባሕርይ አምላክነት መረዳት አይቻልም፡፡
‹‹መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፡- መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል፤ ስለዚህ
ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፡፡ ሉቃ.1÷35

ገጽ 4
የቅድስት ድንግል ማርያም ዘለዓለማዊ ድንግልና

ድንግልና የሚለው ቃል ‹‹ተደንገለ›› ተጠበቀ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ‹‹መጠበቅ›› ማለት ነው፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተለዩ የተለየች ከከበሩ የከበረች የሚያደርጋት ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ
አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለዷ ነው፡፡እመቤታችን ጌታን ከመፅነሷ በፊት፣ በፀነሰች ጊዜ፣ ከፀነሰች በኋላ፣
ከመውለዷ በፊት፣ በወለደች ጊዜ፣ ከወለደች በኋላ ድንግል ናት፡፡
እመቤታችን ከሌሎች ሴቶች ሁሉ ተለይታ እግዚአብሔር ከፈጠራት ጀምሮ በሃሳብ፣ በመናገር፣ በመሥራት
ንጽሐ ጠባይዕ ያላደፈባት ንጽሕት ድንግል ናት፡፡ በዓለም ከነበሩና ከሚኖሩ ሴቶች እንደ እመቤታችን ድንግልናን
ከእናትነት እናትነትን ከድንግልና አስተባብራ የተገኘች ሴት የለችም፡፡ እመቤታችን ዘለዓለም ድንግል ናት፡፡
‹‹በሚያስደንቅ ግብርም ከባሕርዩ ተወለደ እርሱ እግዚአብሔር ቃል ሲሆን በሚያስደንቅ ምሥጢር
ከሰው መወለድን እንደ እኔ ገንዘብ አደረገ፤ በድንግልና ሳለች ከእርሷ ተወልዶ ድንግል ማርያምን እናቴ
አላት፤ ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን ከድንግልናዋ አልተለወጠችምና›› (ሃይ. አበ ቴዎዶጦስ ዘእንቆራ ምዕ 53
ክ 1 ቁ 22)
‹‹ቅዱስ ገብርኤል ወደ አንዲት ድንግል ተላከ የዚያችም ድንግል ስም ማርያም ነው፡፡›› ሉቃ. 1÷27
(ሕዝ. 44÷3 መኃ. 4÷15)
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለዷ ታላቅ ትምህርታዊ ምሥጢር
ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘር በሩካቤ ቢወለድ ኖሮ ዕሩቅ ብእሲ ነው ባሉት
ነበርና ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ትንቢቱና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ ትንቢቱ ‹‹ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም
ትወልዳለች›› ተብሎ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ኢሳ. 7÷14
ምሳሌው ደግሞ ቀዳማዊ አዳም ከኅቱም ምድር ተገኝቷል፡፡ ይህም የክርስቶስ ምሳሌ ነው፤ ምክንያቱም
ከኅቱም ማኅፀነ ድንግል ተገኝቷልና ነው፡፡
ስለ ወላዲተ አምላክ ዘላለማዊ ድንግልና ሲነሣ ለማመን የሚቸገሩ አንዳንድ ሰዎች የሚያሱት ጥያቄ አለ፡፡
በሉቃስ ወንጌል 2÷7 ላይ የበኩር ልጇን ወለደች መባሏ ሌሎች ልጆች ያሏት መሆኑን ያመለክታል ይላሉ፡፡
በማቴዎስ ወንጌል 1÷25 ላይ የበኩር ልጇን እስከምትወልድ አላወቃትም መባሉ ከወለደች በኋላ አወቃት
ለማለት ነው የሚሉ አሉ፡፡ ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍት ለዚህ አባባል መልስ አላቸው፡፡
በኩር፡- የጌታችን ልደቱ፣ ሞቱ፣ ትንሣኤው ‹‹በኩር›› በሚሉ ቃላት የሚገለጡት የእርሱን በመሰለ ልደት
የተወለደ፣ የእርሱን ሞት የመሰለ (በራስ ሥልጣን መሞት) ሞት የሞተ፣ የእርሱንም ትንሣኤ በምትመስል
ትንሣኤ የተነሣ ስለሌለ ስለማይኖርም ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ በኩረ አብ፣ በኩረ ሙታን፣ በኩረ ትንሣኤ ስንለው
ተመሳሳይ አለው ላለማለት እንደሆነ ሁሉ በኩረ ማርያም ስንል ተቀዳሚ ተከታይ ተመሳሳይ የሌለው ልዩ
ማለታችን ነው፡፡ ጌታችን ለእመቤታችን የበኩር ልጅ መባሉ መጀመሪያ በመወለዱ በታላቅነቱና በኃይልነቱ
እንጂ ተከታይ አለው ለማለት አይደለም፡፡
እስከ፡- የሚለው ደግሞ ኹለት ዓይነት አግባብ አለው ፍጻሜ ያለው እስከ እና ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው፡፡
ፍጻሜ የሌለው እስከ 2 ኛሳሙ 6÷23 ‹‹የሳኦል ልጅ ሜልኮል እስከሞተችበት ድረስ ልጅ አልወለደችም›› ሲል
እስከ መቼም ድረስ አለመውለዷን እንጂ ከሞተች በኋላ ወለደች ለማለት አይደለም፡፡ በማቴ 28÷20 ላይ
‹‹እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ›› ያለው ከዓለም ፍጻሜ በኋላ ከእነርሱ ይለያል
ለማለት አይደለም፡፡ በተመሳሳይ ለድንግል ማርያም እስከ ተብሎ መነገሩ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋን
አያስቀረውም፡፡
አላወቃትም፡- ዮሴፍ አላወቃትም መባሉ በኹለት መንገድ ይተረጎማል፡፡ ቅዱስ ኤራቅሊስ የተባለ አባት
እንደተናገረው ዮሴፍ ነቢያት በትንቢታቸው የተናገሩለትን ጌታ እንደፀነሰች አላወቀም አልተረዳም ብሏል፤
ሌላው በሩካቤ አላወቃትም ሲል ነው፡፡
የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት

ገጽ 4
ምልጃ ማለት ‹‹ተንበለ››63 ለመነ አማለደ ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን የሚለምን፣ የሚጸልይ፣ ማላጅ አማላጅ
የሚል የተግባር ስም ይወጣዋል፡፡ የምልጃ ትርጉም በደለኛ ልጅን ከአባቱ፣ በደለኛ ፍጥረትን ከፈጣሪው ጋር
ማስታረቅ ነው፡፡ ምልጃ የታዘዘውና የተፈቀደው (ያስፈልገው) እግዚአብሔር ከኃጥአን ይልቅ የጻድቃንን ጸሎት
የበለጠ ስለሚሰማ ነው፡፡
‹‹የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና፡፡ መዝ. 33÷15
እመቤታችን የእናትነት ክብርና የአማላጅነት ቃል ኪዳን ከልጅዋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ተቀብላለች፡፡ በቃና
ዘገሊና ሰርግ ቤት ልጅዋ መድኅነ ዓለም ክርስቶስ ውኃውን ወደ ወይን ለውጦ የመጀመሪያውን ተአምር ያደረገው
በእመቤታችን አማላጅነት መሆኑ የታመነ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን እምነትና ትምህርት ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ
በታች ከስመ ሥላሴ ቀጥሎ ስሟ የሚጠራ ስለሆነ ታማልዳለች ብለን ማመናችን ቢያንስ እንጂ ሊበዛ አይችልም፡፡

‹‹ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና አትፍሪ›› ሉቃ. 1÷30

የቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕናዋና ቅድስናዋ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኃጢአት (ጥንተ አብሶ) ያላገኛት መርገመ ሥጋ መርገመ
ነፍስ የሌለባት ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር የነበረች በሰው ልማድና ጠባይ ከሚደርሰው ሥጋዊ
ኀሳብና ፈቃድ ሁሉ የተጠበቀች ከተለዩ የተለየች፣ ንጽሕት ቅድስተ ቅዱሳን ናት፡፡ እመቤታችን በውስጥ በአፍአ በነፍስ
በሥጋ ቅድስት ስለሆነች እግዚአብሔር ለልጁ ማደሪያ መርጧታል፡፡ ማኅደረ መለኮት እንድትባል አድርጓታል፡፡ አምላክን
ለመውለድ ያስመረጣትና ያበቃት ድንግልናዋ ንጽሕናዋ ነው፡፡ ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና ለእመቤታችን
ገንዘቦቿ ናቸው፡፡

‹‹እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር›› ኢሳ. 1÷9

ማጠቃለያ

 ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ነች፡፡


 ቅድስት ድንግል ማርያም ዘለዓለማዊ ድንግል ነች፡፡
 ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅ ነች፡፡
 ቅድስት ድንግል ማርያም መርገመ ነፍስ መርገመ ሥጋ የሌለባት በረከተ ነፍስ በረከተ ሥጋ የምታሰጥ ናት፡፡

63. 224 ተንበለ መለመን፣ መጸለይ፣ ማማለድ፣ ማላጅ፣ አማላጅ መኾን፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 900

ምዕራፍ አምስት
ነገረ ቅዱሳን
መግቢያ
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእምነቷ መሠረት አንድ አምላክ በሆነ በአንድነት ውስጥ ልዩ ሦስትነት ባለው
በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ማመን ነው፡፡ ከዚህም ጋር እኛን ለማዳን ሲል በራሱ ፈቃድ፣ በአባቱ ፈቃድ፣ በመንፈስ
ቅዱስ ፈቃድ በተለየ አካሉ ሰው በሆነው አካላዊ ቃል ሰው መሆን ታምናለች፡፡የእምነቷ መሠረትና ጉልላት በመጽሐፍ
ቅዱስ የተገለጠው እውነትና ትምህርት ነው፡፡ በዚህም መሠረት ቤተ ክርስቲያናችን ስለ ቅዱሳን የምታስተምረው በራሷ
ፈቃድ ወይም ፍላጎት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ በመሆኑና ከሐዋርያት ጀምሮ የተነሡ ቅዱሳን አባቶቻችን ፈለጋቸውን
የምትከተል ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን በመሆኗ ነው፡፡

ገጽ 4
ክብረ ቅዱሳን
ቅዱስ የሚለው ቃል በግእዝ ንጹሕ ክቡር ልዩ መሆንን የሚያመለክት ነው፡፡ቅዱስ የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር ሲነገር
‹‹ቅዱሳን›› ይሆናል፡፡ ቅድስና የባሕርይና ጸጋ ተብሎ በኹለት ይከፈላል፡፡
የባሕርይ ቅድስና፡-
ቅድስና የባሕርይ ገንዘብነቱ ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት ቅድስናው ከእርሱ የማይለይ፣ ቅድስናውን
ከማንም ያልተዋሰው ወይም ያልተቀበለው፣ ማንም ሊወስድበት የማይችል የራሱ ገንዘብ የሆነ ማለት ነው፡፡
እግዚአብሔር በባሕርይ ቅዱስ ስለሆነ ቅድስና ከእርሱ እርሱም ከቅድስና ተለይተው የማይታሰቡ ናቸው፡፡ በእርሱ ዘንድ
ከቅድስና በስተቀር ሌላ ነገር የማይታሰብበት በቅድስናው ርኩሰት በጻድቅነቱ ሐሰት በብልጽግናው ንዴት የሌለበት ነው፡፡
‹‹እኔ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝ›› ዘሌ. 19÷2›
የጸጋ ቅድስና
የጸጋ ቅድስና ማለት ከእግዚአብሔር በጸጋ የተሰጠ ወይም የተገኘ ማለት ነው፡፡ በባሕርይው ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር
ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ የፍጡራን የቅድስና ምንጭ እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር በባሕርይው ቅዱስ እንደሆነ ሁሉ
ሰዎችም የእርሱን አርአያ ተከትተለው ቅዱስ ይሆኑ ዘንድ ጥሪ አቅርቧል፡፡
‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ
ቅዱሳን ሁኑ›› 1 ኛጴጥ 1÷13-15
ቅዱሳን የሚለው ቃል በባሕርዩ ቅዱስ የሆነውን አምላክ ለሚያገለግሉ መላእክትና ደጋግ ሰዎች የሚሰጥ ነው፡፡
መላእክትን ቅዱሳን እንላቸዋለን፡፡ ከማንኛውም ክፉ ነገር የራቁ እግዚአብሔርን ያወቁ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑ
ስለሆኑ ቅዱሳን ይባላሉ፡፡ ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት ሁሉ ለቅዱስ እግዚአብሔር ሲሉ ሕይወታቸውን
መሥዋዕት አድርገው ስለሰጡ ለስሙ ስለመሰከሩ በተጋድሎአቸውና በትሩፋታቸው ስላገለገሉ የቅድስናና የብፅዕና
ማዕረግ ተሰጥቶአቸዋል፡፡ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የቅዱሳን አክሊል የሆነች ቅድስት ናት፡፡ ስለዚህም ቅድስተ
ቅዱሳን ትባላለች፡፡
የቅዱሳን ቃል ኪዳንና አማላጅነት
ቅዱሳን በዚህ ዓለም ሳሉ ባደረጉት ተጋድሎ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነት ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህ ዓለም ሳሉ
ሙታንን በማንሣት፣ ድውያንን በመፈወስ፣ አጋንንትን በማውጣት ብዙ የተአምር ሥራ እንዲሠሩ መንፈሳዊ ኃይልና
ሥልጣን እንደተሰጣቸው ሁሉ ከዚህ ዓለም በሞት በሚለዩበት ጊዜም ስማቸውን የሚጠራ መታሰቢያቸውን የሚያደርግ
በአማላጅነታቸው የሚያምን ሁሉ ዋጋ እንደሚያገኝ ከልዑል እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ተሰጥቷቸዋል፡፡
ጻድቅን በጻድቅ ነቢዩን በነቢይ ስም የተቀበለ በክርስቶስ ተከታዮችና አገልጋዮች ስም ቀዝቃዛ ውኃ እንኳ የሰጠ ዋጋው
እንደማይጠፋበት ጌታችን በወንጌል አረጋግጧል፡፡ ቅዱሳን በዐፀደ ሥጋ ብቻ ሳይሆን በዐፀደ ነፍስም ያማልዳሉ፡፡ ለዚህም
ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ፡፡ (ማቴ 10÷41-42፣ ዘጸ 32÷2-15፣ ሄኖ 12÷33-40፣ ሉቃ. 20÷37-40)
የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነው፡፡ በሕያዋንም ላይ ሲሠራ ይኖራል ቃል ኪዳኑም አይለወጥም፤ ቅዱሳንም ሕያዋን
እንደሆኑ ራሱ ተናግሯል፡፡ በዚህ እምነትና ትምህርት መሠረት ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን ሐዋርያትን የሰማዕታትንና
የጻድቃንን ቃል ኪዳንና ክብር ትቀበላላች፡፡

በምልጃ ወቅት የሚሳተፉ አካላት-


ምልጃ አንዱ ስለሌላው የሚያቀርበው ልመና ነውና የሚለምን፣ የሚለመንለት፣ የሚለመን ሦስት አካላት ይሳተፉበታል፡፡
ሀ. የሚለመነው /የሚማለደው/፡-
ይህ አካል የመፍረድ ሥልጣን ያለው የፈቀደውን ያደርግ ዘንድ የሚቻለው አካል ነው፡፡ በነገረ ድኅነት ለሚፈጸመው ምልጃ ይህ አካል /ተለማኙ/
የቅዱሳንን ልመና ተቀብሎ ኃጢአተኛውንና በደለኛውን ይቅር የሚለው በባሕርዩ መሐሪ የሆነው መፍቀሬ ሰብእ የሆነው እግዚአብሔር አምላክ
ነው፡፡ (መዝ፣ 64፥1) ለሰውም ሁሉ እንደ ሥራው መክፈል የሚቻለው፣ የሁሉም ዋጋ በእርሱ ዘንድ ያለ፣ የሚተካከለው የሌለ፣ ባዕለ ጸጋ ዳኛ፣
እውነተኛ ፈራጅ አምላክ ነውና፡፡ (ራዕ. 22፥12፣ ኢሳ. 40፥10፣ መዝ. 49፥2) በአጭሩ ተማላጅ ስንል ምልጃ ተቀባይ ተለማኝ ነው፡፡ ተማላጁ
እግዚአብሔር እንደ አማላጆቹ ብዙ አይደለም አንድ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሲባል አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለት እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ለ. የሚለምነው /የሚማልደው/፡-
ይህ ደግሞ ከተለማኙ ጋር በቅርብ የሚተዋወቅ፣ እውነቱን ለማስረዳት የበቃ ይቅርታ ሊያሰጥ የታመነ፣ ይልቁንም ከተማላጁ ባለሟልነትን ያገኘ
ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ በሁሉቱም ወገኖች ማለትም በተማላጅና በሚማለድለት ወይም በተለማኝና በሚለመንለት ወገን /አካል/ የሚወደድ ታማኝ
አስታራቂ መሆን አለበት፡፡ ይህንን ሊያሟሉ የሚችሉት ማማለድ ለፍጡራን ባሕርይ የሚስማማ የትኅትና ሥራ እንደመሆኑ በባሕርይው ቅዱስ
ከሆነው ከእግዚአብሔር ተመርጠው በጸጋ የከበሩ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ምክንያቱም ቅዱሳን በሃይማኖት በምግባር እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙና
በፊቱም እውነትን የሚናገሩ በእግዚአብሔር ፊትም የከበሩ ስለሆኑ የበደሉትን ይቅር እንዲል በለመኑት ጊዜ ከሰጣቸው ባለሟልነት የተነሣ
ጸሎታቸውን ሰምቶ፣ ልመናቸውን ተቀብሎ ፈጥኖ ይቅር ይልላቸዋልና፡፡ (ዘፍ 18፥3፣ 2 ኛ ሳሙ. 2፥6፣ 3፥1-21)፤ የሚማልዱትም
ሕይወታቸውን እስከመስጠት ድረስ ነው፡፡ (ዘጸ. 32፥9-14፣ መዝ. 105፥23፡፡) እነዚህም ቅዱሳን፡-

ገጽ 4
1. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ጸጋ ከዓለም ርቆ /ጠፍቶ/ በነበረበት ዘመን ስንኳ ሳይቀር ምልዕተ ጸጋ ሆና ከአንስተ ዓለም
ተለይታ የተባረከች፣ መንፈስ ቅዱስ የጸለላት፣ የልዑል ኃይልም አጽንቶ የጠበቃት፣ ጸጋ ምድራዊ ጸጋ ሰማያዊ ገንዘቧ የሆነላት ከሁሉም በላይ ደግሞ
ፈጣሪዋን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ወልዳ ከወለደችም በኋላ ያለተፈትሖ በፍጹም ድንግልና ጸንታ የኖረች እናት ናት፡፡ /ሕዝ. 44፥1-3፣
ኢሳ.7፥14፣ ሉቃ.1፥28-38፣ መኃ.4፥12/ ድንግል ማርያም ለ 5500 ዘመናት ተጣልተው የነበሩት ሰዎችና እግዚአብሔር የታረቁባት፣ ሰዎችና
መላእክት በምስጋና አንድ የሆኑባት የእርቅ አደባባይ ናት፡፡ /ሉቃ 2፥8-14/ ድንግል ማርያም ከአማላጆች ሁሉ የበለጠች አማላጅ ናት፡፡
2. ቅዱሳን መላእክት፡-
ቅዱሳን መላእክት በኃጢአታቸው ምክንያት ከእግዚአብሔር ሕይወት ስለራቁት ሁሉ የሚለምኑና በሰይጣን ምክር ተሳስተው
በዓለም ምኞት ተታለው ጽድቃቸውን በኃጢአት ለውጠው የተሰናከሉ ሰዎች በንስሐ ወደ ፈጣሪያቸው ሲመለሱ ታላቅ ደስታ
ተሰምቷቸው ፈጣሪቸውን እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑ እንዲሁም ከሥጋ ጠላቶቻችን ከከኃዲያን ከነፍስ ጠላቶቻችን ከአጋንንት
የሚጠብቁንና ወደ እግዚአብሔር ምልጃን (ልመናን) በማቅረብ የሚያስምሩን ናቸው፡፡ (ዘጸ. 23፥20፣ 2 ኛነገ. 6፥16-18፣ ዘካ.
1፥12-15)
3. ቅዱሳን ሰዎች፡- ዘሌ. 19፥2፣
ቅዱሳን “ልዩ ልዩ ፍትወታትና እኩያትን ያሸነፉ” (ኤፌ. 6፥12)፣ ብዙዎቻችንን ያንበረከኩትን ዓለምና ሰይጣንን ድል ነሥተው የሚኖሩ በዚህ
መልካም ምግባራቸው የሕይወት አክሊል ለመቀዳጀት የበቁ ናቸው፡፡ /2 ኛጢሞ. 4፥7-8፣ ራዕ 2፥9-12/

ሐ. የሚለመንለት /ምልጃ የሚቀርብለት/፡- ይህ ሦስተኛው አካል ሲሆን፣ መበደሉንና ኃጢአት ማድረጉን ዐውቆ
በእግዚአብሔር ፊት በትኁት ሰብእና ልመናውን በማቅረብ ምልጃን የሚጠይቅ ምእመን ነው፡፡ አማላጆች በአንድነትና
በሦስትነት ወደሚመሰገን እግዚአብሔር ምልጃ የሚያቀርቡት ስለኃጥአን ሰዎች ነውና፡፡ በኃጢአት የተገኘው
ማንኛውም አካል የኃጢአት ሥራ በመሥራቱ ፈጣሪውን እንዳሳዘነ ተረድቶ ለኃጢአቱ ሥርየትን፣ለበደሉ ይቅርታን
እንዲያገኝ ከፈለገ በቅዱሳን አማላጅነት ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ አለበት፡፡ (ሉቃ. 7፥2-10) ቅዱሳን ይቅርታ
በማድረግም አምላካቸውን ይመስላሉ፡፡ (ሐዋ. 7፥60)
የአማላጅነት ተጠቃሚ ለመሆን ምን ያስፈልጋል?
አንድ ዜጋ ዜግነታዊ መብቱ የሚጠበቅበት በመጀመሪያ ዜግነታዊ ግዴታውን መወጣት ሲችል ብቻ እንደሆነ ሁሉ
እንዲሁ አንድ ሰው በቅዱሳን አማላጅነት ተጠቃሚ ሊሆን የሚችለው፡-
ሀ. የቅዱሳን አማላጅነት አስፈላጊ እንደሆነ የሚረዳ፣
ለ. ከእኔ ጸሎት ይልቅ እግዚአብሔር የቅዱሳንን ጸሎት ተቀብሎ ይቅር ይለኛል የሚል፣
ሐ. በአማላጁ ጸሎትና በተማላጁ ቸርነት አምኖ ንስሐ በመግባት ከሚሠራው ኃጢአት ተመልሶ ፊቱን ወደ
እግዚአብሔርና ወደ ቅዱሳኑ ማቅናት እንዳለበት የሚያምን፣ በቅዱሳን ምልጃ በመታመን የእግዚአብሐርን ምሕረትና
ቸርነት የሚናፍቅ ሲሆን ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት በእርሱ ይገለጣልና፡፡ (ኢሳ. 59፥1-2፣ ማቴ.15፥25፣ 1 ኛ ጢሞ
1፥12-17)
ነገር ግን ኃጢአተኛው /የሚለመንለት ሰው/ ከላይ የተጠቀሱትን የማያምን ከሆነና ከኃጢአቱ ካልተመለሰ ቅዱሳን
የኃጢአተኞች ዋሻ /መደበቂያ/ አይደሉምና ለእንደዚህ ዓይነት ሰው ጸሎትን /ምልጃን/ አያቀርቡም፡፡ ይልቁንም ከባድ
ቅጣት ያወርዱበታል፤ እነርሱ አማላክት ዘበጸጋ ናቸውና፡፡(ሐዋ. 5፥1-11፣8፥17-21፣13፥6-12፣ ዘጸ 7፥6) እግዚአብሔር
እስራኤላውያን ሲያጠፉ ከመቅጣት አልፎ ቅዱሳን እንዳይማልዱ ይከለክላል፡፡(1 ኛሳሙ.16፥1፣ ኤር. 7፥16-20)፡፡ ከዚህ
ሁሉ የምንረዳው የቅዱሳን አማላጅነት ሊረዳን የሚችለው፡-ለቅዱሳን የማማለድ ጸጋ ስለተሰጣቸውና እግዚአብሔር
የእነርሱን ልመና ስለሚቀበል ብቻ ሳይሆን፡- የሚከተሉትን ነጥቦች ማሟላት ሲችል ነው፡፡
1. በሃይማኖት ጥርጥር የሌለው አማኒ መሆንና ሃይማኖቱን የጠበቀ ሲሆን ለማያምንና ለተጠራጣሪ ምልጃ ዋጋ
የለውምና፡- (1 ኛዮሐ. 5፥16፣ ማቴ. 12፥31-32፣ 2 ኛ ጴጥ. 2፥20-22፣ 1 ኛሳሙ.16፥1)
2. አንደበቱን ከዘለፋ አንጽቶ፣በንስሐ የተመለሰ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡/ኤር.11፥12-41፣ሕዝ.14፥12-20
አማላጅነት /ምልጃ/ ለምን አስፈለገ?
፩. ምልጃ የእግዚአብሔር ትእዛዝና ፈቃድ ስለሆነ ነው፡፡ /ዘፍ 20፥1-7፣ ኢዮ.42፥7-9፣ 2 ኛቆሮ.5፥19-20፣ ፊሊ 4፥6፡፡
አማላጅነት የእግዚአብሔር የቸርነቱ ጸጋ /ስጦታ/ ነው፡፡ ምክንያቱም ምግባራቸው የደከመና ጸሎታቸው እንደ እርሱ
ፈቃድ ያልሆነ ተነሣሕያን ኃጥአን ፈቃዱን በሚያውቁና በሚፈጽሙ ጻድቃን እንዲደገፉ ማድረጉ የቸርነቱ መገለጫ
ነው፡፡ (ሮሜ. 14፥1፣ ገላ. 6፥2፣ ኢሳ. 35፥3፣ ማቴ. 9፥13)
፪. ድኅነት ሥርዓት ስላለው፡- ምልጃ አንዱ የድኅነት መንገድ ነው፡፡ 1 ኛቆሮ 15፥28፣ ዮሐ.3፥1-12፣ ማቴ 6፥1-34፣
ዮሐ.2፥1-11 ኢዮ 42፥7-8

ገጽ 4
፫. የእግዚአብሔርን የምሕረት ብዛት እንድናውቅ፡-ዘጸ. 32፥13-14፣ ሉቃ. 1፥55፣
፬. የእግዚአብሔርን ባለሟሎች እንድናውቅ በቃል ኪዳናቸው እንድንጠቀም፡-(መዝ. 88፥3፣ኢዮ. 42፥7-8፣ ዘኁ. 12፥1-
15፣ ሉቃ. 1፥19፣ 1 ኛ ነገ. 11፥13)
፭. ስለ ትኅትና፡- 1 ኛ ቆሮ 5፥5፣ ሮማዊው መቶ አለቃ በትኅትናው እንደተመሰገነ

አማላጅ ለምን ይማልዳል?

1. ከእነርሱ የማይገኘውን ለማሰጠት፡-


 ቅዱሳን ከእግዚአብሔር ባገኙት ሀብት ከተሰጣቸው ጸጋ ለሰው ይሰጣሉ፡፡2 ኛነገ.2፥9-10፣4፥8-17
 ቅዱሳን የበደለውንም ሊገስጹት ይቻላቸዋል፡፡ ሐዋ.5፥1-11፣ ዘጸ. 23፥20-11፣ ሐዋ. 12፥23
2. ምሕረትና ልመና ግብራቸው ስለሆነ፡- ሔኖ. 9፥21-23፣ ለማያምኑትም ይጸልያሉ፡- ሐዋ. 7፥60
3. ባለሟልነት ስላላቸው፡- ዘሌ. 26፥12-45፣ሉቃ.1፥19፣ማቴ.18፥10፣ራዕ 6፥9-11፣7፥14-17፣ 8፥3-4
የቅዱሳን አማላጅነት በሕይወተ ሥጋ
ቅዱሳን በሕይወተ ሥጋ ሳሉ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ሲል ምሕረትንና ይቅርታን እንደሚደርግ መጽሐፍ ይናገራል፡፡
‹‹እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ወይን በዘለላው በተገኘ ጊዜ፡- በረከት በእርሷ ላይ አለና አታጥፏት እንደሚባለው ሁሉን እንዳላጠፋ
ስለ ባርያዎቼ እንዲሁ አደርጋለሁ›› (ኢሳ. 65፥8) ስለወዳጆቹ ሲል እንደሚምር ራሱ እግዚአብሔር ምሳሌውን ከነትርጉሙ
አስረድቶናል፡፡ ከወይን ዛፍ ዘለላ ፍሬ በተገኘ ጊዜ ሊቆረጥ የነበረው ዛፍ ስለፍሬው ሲባል ይቆይ ተብሎ ከጥፋት እንደሚድን፤ ቅዱሳን
ያሉበትን ሕዝብና ሀገርም እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ሲል ከማጥፋት ይታገሳል፡፡ ለምሳሌ
 በሰዶምና ገሞራ ዐሥር ጻድቃን ቢኖሩ ኖሮ በአብርሃም ምልጃ ከተማዋ ባልጠፋች ነበር፡፡ ዘፍ 18፥22-
 እስራኤላውያን በሙሴ ምልጃ ከመጥፋት እንደዳኑ፡-ዘጸ.32፥10-14፣ዘዳ. 9፥18-19፣መዝ.105፥23፣ በተጨማሪም ዘኁ.
11፥1-3፣ 16፥41-50፣ 12፥1-15 የሙሴን አማላጅነት ያመለክታሉ፡፡
 አብርሃም ስለ አቤሜሌክ ንጉሠ ጌራራ፡- ዘፍ. 20፥7
 ኢዮርብዓም የእግዚአብሔርን ነቢይ ስለ እኔ ጸልይ ማለቱ፡- 1 ኛነገ. 13፥1-10
 እስራኤላውያን በመከራቸው ሰዓት የነቢዩ ኤርምያስን ልመና እንደሻቱ፡- ኤር. 42፥2-3፣9-11
 በተጨማሪም ማቴ. 18፥18፣ ማቴ. 15፥21-28፣ ሐዋ. 7፥57-60፣ 1 ኛቆሮ. 1፥13፣ 2 ኛቆሮ. 3፥9፣ 5፥18-20፣ፊሊ. 4፥6፣
1 ኛጢሞ 2፥1-2፡- የቅዱሳንን ምልጃና የምልጃን አስፈላጊነት ያመለክታሉ፡፡
የቅዱሳን አማላጅነት በዐጸደ ነፍስ
ቅዱሳን በተሰጣቸው ጸጋ
፩. በዐጸደ ነፍስ ሆነው
ሀ. በምድር የሚደረገውን ያውቃሉ፡፡ 1 ኛቆሮ 13፥12፡-2 ኛነገ.2፥112 ኛዜና.21፥1-15 (የኤልያስ መልእክት)
፣ዘፍ.25፥8ሉቃ 16፥19-31(የአብርሃም ንግግር)፣ ራዕ. 6፥10-11፡፡ ቅዱሳን በዚህ ምድር /ዓለም/ እያሉ የተሰወረውንና የራቀውን
የማየት ብቃት እንዳላቸው ሁሉ በዐጸደ ነፍስም ሆነው የሚሠራውን ሁሉ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ /2 ኛነገ.5፥15-25፣ 6፥8-16፣
ሐዋ.5፥1-11፣ ማቴ 5፥8/
ለ. ከምድራውያን ጋር እኩል ይታያሉ፡- ማቴ. 17፥1-8
፪. ከማማለድ በላይ የሚያስገርም ተአምራት ያደርጋሉ፡፡ መዝ. 67፥35፣ ማር.16፥17-18፣ ዮሐ 14፥12
፪.፩- በትረ - ነቢይ ሙሴ፡- ሙሴ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ እስራኤላውያንን አሻግሯል፡፡ በዐጸደ ነፍስም ያለችው የቅዱሳን ነፍስም
ባሕረ እሳትን በአማላጅነት ታሻግራለች፡፡ ዘጸ.14፥12-20፣መዝ 96፥10
፪.፪፡- አጽፈ - ኤልያስ ነቢይ፡- 2 ኛነገ 2፥14 (ነፍሱ ከጨርቅ እጅግ አድርጋ ትበልጣለች)
፪.፫፡- አጽመ - ኤልሳዕ ነቢይ፡- በምድር የሠራው ሥራ ተከትሎትና በአጥንቱ ሙት አሥነስቷል፡፡
(2 ኛ ነገ. 4፥34-37፣ 2 ኛ ነገ. 13፥20-21፣ መዝ. 33፥20) (በገነት ያለችው የቅዱሳን ነፍስ
በመቃብር ካለው አጥንት ይበልጣል፡፡)
፪.፬፡- ጽላሎተ - ጴጥሮስ ሐዋርያ፡- ሐዋ. 5፥12-16
፪.፭፡- ልብሰ - ጳውሎስ ሐዋርያ፡- ሐዋ. 19፥12-14
ቅዱሳን ከእግዚአብሔር ሕያውና ዘላለማዊ የሆነ ቃል ኪዳን ተሰጥቷቸዋል፡፡
ቃል ማለት በቁሙ /እንዳለ/ ቃል ሲሆን ኪዳን ማለትም በሁለት ወገኖች መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ፣ ኑዛዜ፣ ቁርጥ
ቃል ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት እግዚአብሔር ከፍቅሩ ብዛት የተነሣ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ካገለገሉት ቅዱሳን ጋር የማይሻር፣
የማይለወጥ፣ የማይረሳ፣ የማያረጅ፣ ሕያውና ዘላለማዊ ቃል ኪዳን ገብቷል፡፡ /መዝ. 88፥3/፣ መዝ.110፥5፣ እግዚአብሔር
አይለወጥም ቃል ኪዳኑም አይለወጥም፡፡ /ሚል.3፥6፣ ዕብ.13፥8/ በተጨማሪም ዘጸ.19፥9፣ መዝ.111 ፥ 6፣ 110፥6፣ ኢሳ.59፥21፣
ማቴ. 28፥20 ለቅዱሳን የተሰጠው ቃል ኪዳን ሞት የማይለውጠው፣ የዘመናት ርዝማኔም የማይሽረው ዘላለማዊ መሆኑን
ያመለክታሉ፡፡
 ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ በገባላቸው ቃልኪዳን መሠረት እስራኤልን ይቅር ብሏል፡፡ ዘጸ. 32፥13-14
 (ዘፍ. 15፥13-16፣ ዘዳ. 7፥7-8)፣ ሉቃ. 1፥17፣ 1፥55፣ ማቴ.22፥31-32፣ ዕብ. 11፥4
 ለዳዊት በገባው ቃል ኪዳን መሠረት እግዚአብሔር የቸርነቱን ሥራ እንደሠራ መዝ. 131፥9-14፣ 1 ኛ ነገ.11፥12፣
11፥34-38፡፡

ገጽ 4
ማጠቃለያ
 ቅዱሳን አማልክት ዘበጸጋ ናቸው፡፡
 ቅዱሳን ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ቃል ኪዳን በዐፀደ ሥጋና በዐፀደ ነፍስ ያማልዳሉ፡፡
 ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳንን በስማቸው ቤተ ክርስቲያን በማነጽ፣ ጽላት በመቅረፅ፣ በዓላቸውን
በማክበር በተገባላቸው ቃል ኪዳን ትጠቀማለች፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዋቢ መጻሕፍት
1. መጽሐፍ ቅዱስ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት አ.አ 1947 ዓ.ም
2. ሃይማኖተ አበው ተስፋ ገ/ሥላሴ ማተሚያ ቤት፣ አ.አ 1982 ዓ.ም.
3. መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ፣ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፣ አ.አ
1948 ዓ.ም
4. ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት፣ ደስታ ተክለ ወልድ፣ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፣ አ.አ 1962 ዓ.ም
5. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ሥርዐተ አምሎኮትና የውጭ ግንኙነት፣ ትንሣኤ
ማተሚያ ድርጅት፣ አ.አ 2009 ዓ.ም
6. መጻሕፍት ብሉያት ፪ቱ አንድምታ ትርጓሜ፣ ትንሣኤ ማተሚያ ድርጅት፣ አ.አ 1999 ዓ.ም
7. ወንጌል ቅዱስ አንድምታ ትርጓሜ፣ ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ ቤት አ.አ 1988 ዓ.ም
8. የኢትዮጵያ እምነት በሦስቱ ሕግጋት፣ አለቃ አያሌው ታምሩ፣ ኢትዮ ጥቁር ዓባይ ማተሚያ ቤት አ.አ
2003 ዓ.ም
9. ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት፣ ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ፣ ማኅበረ ቅዱሳን አ.አ 2008
ዓ.ም
10. ነገረ ሃይማኖት፣ ሳሙኤል ፍቃዱ፣ ፋር ኢስት ትሬዲንግ፣ አ.አ 2005 ዓ.ም
11. ነገረ ሃይማኖት፣ ዲ/ን ምትኩ አበራ፣ ማኅበረ ቅዱሳን፣ አ.አ 2010 ዓ.ም
12. በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤት ለቀዳማይ ክፍል የተዘጋጀ መጽሐፍ
ሚሊኒየም ማተሚያ ቤት 2008 ዓ.ም
13. በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤት ለካልዓይ ክፍል የተዘጋጀ መጽሐፍ
ሚሊኒየም ማተሚያ ቤት 2007 ዓ.ም
14. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ትምህርት፣ አባ መልከጼዴቅ (ሊቀ ጳጳስ)
ካሊፎርኒያ አሜሪካ 1994 ዓ.ም
15. ትምህርተ መለኮት፣ ዓሥራት ገ/ማርያም፣ አ.አ 1994 ዓ.ም
16. የትምህርተ ሃይማኖት መግቢያ፣ ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ፣ ማኅበረ ቅዱሳን አ.አ 1998 ዓ.ም
17. መጽሐፈ አክሲማሮስ፣ አባ ሠናይ ምስክር፣ጉተንበርግ ማተሚያ ቤት ባሕር ዳር 2006 ዓ.ም
18. ሥነ ፍጥረት፣ ቀሲስ ስንታየሁ አባተ፣ ማኅበረ ቅዱሳን፣ አ.አ 1996 ዓ.ም
19. ሰማዕት ወመምህር፣ ዲ/ን ሚኪያስ ግዛቸው፣ 2010 ዓ.ም
20. መላእክት፣ ዲ/ን አቤል ካሳሁን፣ አርሞንኤም ማተሚያ ቤት 2010 ዓ.ም
21. አዕማደ ምሥጢር፣ መ/ር ብርሃኑ ጎበና፣ ማኅበረ ቅዱሳን፣ አ.አ 1947 ዓ.ም
22. አዕማደ ቤተ ክርስቲያን፣ አብርሃም ገ/ዮሐንስ፣ አ.አ 1999 ዓ.ም
23. ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን፣ አባ በትረ ሃይማኖት፣ማኅበረ ቅዱሳን አ.አ 1998 ዓ.ም
24. ፍኖተ እግዚአብሔር፣ አለቃ ኅሩይ፣ አሳታሚ ቅዱስ ያሬድ የጥናትና ተራድኦ ማዕከል 2001 ዓ.ም
25. መድሎተ ጽድቅ፣ ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ፣ ጃጃው አሳታሚዎች 2008 ዓ.ም
26. መድሎተ አሚን፣ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ፣ ጃጃው አሳታሚዎች 2010 ዓ.ም
27. ጌራ መድኃኒት፣ ዲ/ን ዓባይነህ ካሤ፣ ሜጋ ፕሪንቲንግ አ.አ 1996 ዓ.ም
28. ዓምደ ሃይማኖት፣ ብርሃኑ ጎበና፣ ኢትዮ ጥቁር ዓባይ አታሚዎች 2000 ዓ.ም
29. ኆኀተ ሃይማኖት፣ ብርሃኑ ጎበና፣ አ.አ 1986 ዓ.ም
30. ደብረ አሚን፣ ዲ/ን መልካሙ በየነ፣ ፋር ኢስት ትሬዲንግ፣ ደብረ ማርቆስ 2011 ዓ.ም
31. ቃለ ጽድቁ ለአብ፤ ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ፣ ይኩን ለነ ማተሚያ ቤት 2008 ዓ.ም
32. ነገረ ማርያም፣ ሊቀ ጠበብት ሐረገ ወይን አገዘ፣ ማኅበረ ቅዱሳን 2006 ዓ.ም
33. ቅድስት ድንግል ማርያም በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት፣ በመ/ር ጌታቸው ዲቢቶ፣ ፈለገ ሕይወት
ሰ/ት/ቤት 2008 ዓ.ም
34. ፍኖተ ቅዱሳን፣ ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ፣ አ.አ 2002 ዓ.ም

ገጽ 4

You might also like