You are on page 1of 72

• ኦርቶዶክሳዊ የስብከት ዘዴ

1. ስብከትና የስብከት ታሪክ


ሀ. የስብከት ትርጉም

ስብከት የሚለው ቃል ሰበከ አስተማረ፣ አዋጀ ነገረ


ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው፡፡

በግሪክ፣ ኬሪግማ /kerygma / በእንግሊዝኛ


/sermonl/ ይባላል፡፡ተዛማጅ /ተመሳሳይ/ የሆነ ትርጉም
አለው፡፡ማስተማር አዋጅ መንገር የሚለውን ይተረጉማሉ፡፡
የቤተክርስቲያን ዋናው ተልዕኮዋ
ሰዎችን ከአለማመን ወደ ማመን ማምጣት፣ያመኑትን ደግሞ
በእምነታቸው ማጽናት ያላመኑትን ማሳመን ነውና፡፡
ስብከት የቤተ ክርስቲያን ትልቁ የአገልግሎት ክፍል ነው፡፡
የእግዚአብሔር ፈቃድና አሰብ፣ በሰውም ላይ ያለው በጐ ዓላማ
ወደ ሰው ልብ የሚደርሰው ፣ ሃይማኖት የሚሰፋፋበትና
የሚተላለፍበት ከፍተኛው መሣሪያ ስብከትና ስብከት ብቻ
ነው፡፡‹በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር
በጐ ፈቃድ ሆኖአልና› /1ቆሮ 1፡21/ እንዲል፡፡
ስብከት
1. የአምልኮ ክፍል ነው
እግዚአብሔር የምናመልክው አምላካችን ነው፡፡ማምለክ፣ ማመንና መዳን
መሠረቱ መሰማቱ ነው፡፡ ስለምናመልከው አምላክ ምንነት መስማት፣ሰምቶም
እግዚአብሔርነቱን እንደሚገባ መረዳት የምንችለው በስብከት ነው፡፡ሮሜ. 10፡
10-17
2. ትእዛዘ እግዚአብሔር ነው
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን የጠራበትና የመረጠበት ዓላማና
የመጨረሻው ትእዛዝ ስብከት ነው፡፡ (ማር16፡15)ለሕዝብም እንድንሰብክና
በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንድሆነ
እንመሰክር ዘንድ አዘዘን(ሐዋ.10፡42)
3. ስለ እግዚአብሔር የምንመሰክርበት ነው

ምስክርነት ማለት ያዩትንና የሰሙትን እውነት ያላዩ


እንዲያዩ፣ ያልሰሙም እንዲሰሙና እውነት የሆነውን ነገር
እንዲያረጋግጡ በሆነው ሁሉ መናገርና መግለጽ ነው፡፡
መጥምቀመለኮትና ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ይህን እውነት
መስክራዋል፡፡ጌታም ስለ ምስክርነቱ አስተምሮአል
/ ዮሐ. 1፡6፣ 1ዮሐ 1፡1፣ ማቴ 10፡32/
4. የእግዚአብሔር መንግሥት የምትገለጥበት ነው

መንግሥተ ሰማያት እግዚአብሔርን ለሚወድና እንደ ፈቃዱ ለሚኖሩ


የተዘጋጀች ናት፡፡ መንግሥተ ሰማያትም የምትገለጠው /የምትሰበከው/
በስብከት ብቻ ነው፡፡ /ማር 1፡21/ ቅዱስ ጳውሎስ ‹ማንም ሳይከለክለው
የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበከ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርሰቶስም እጅግ
ገልጦ ያስተምር ነበር ተብሎ ተነግሮለታል፡፡› /ሐዋ 28፡41፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ደቀ መዛሙርቱን ‹በጨለማ የምንግራችሁን


በብርሃን ተናገሩ በጆርም የምትሰሙትን በሰገነት ስበኩ› በማለት
አዝዟቸዋል፡፡
በእነዚህ ነጥቦች መሠረት ፋለር የተባለው ሊቅ እንደተናረው ስብከት
በሦስት የተከፈለ ምሥጢራው ትርጉምን ይዞ ይገኛል፡-

1.ኬሪግማቲክ፡-የማያምኑ አረማውያን ወደ እግዚአብሔር


የምንመለስበት

2.ዲያክቴክ፡- አዳዲስ አማንያንን በእምነት የምናጸናበት

3.ፕራክሎቲክ፡- በእምነት በእውቀት የበሰሉትን ለቅድስና ሕይወት


የምናበቃበት ስብከት ነው፡

ለ. የስብከት ታሪክ፡ -
ስብከት የራሱ የሆነ ታሪካዊ ሂደትአለው ከቅዱስ መጽሐፍም ሆነ ከታሪክ መዛግብት
እንደምንረዳው የስብከት አጀማመርና ዕድገት አለው፡፡
1. ዓለመ መላእክት፡
- መላአክት በተፈጠሩበት በመጀመሪያው ቀን የመላእክት አለቃ የነበረው ሳጥናኤል
የተፈጠረበትን ዓላማ በመሳት ክህደትንና ሐሰተኛነትን ከራሱ አፍልቆ ‹እኔ ፈጠርኳችሁ›
ባለ ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ‹ንቁም በብህላዊነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ› በማለት መላአክትን
አጽናንቷል አረጋግቷል፡፡ስብከት ማለት ‹ማጽናናት ማረጋጋት› ማለት ነውና፡፡ ምሳ.1፡35፣
ኢሳ.40፡1፡፡

ቅዱስ ገብርኤል በተፈጥሮ የተሰጠውን እእምሮ ተጠቅሞ የማጽናናትና የማረጋጋት


አገልግሎት ከመፈጸሙ የተነሣ ‹ ወብእንተዝ ደለዎ ከመይጽር ዜናሃ ለማርያም› የሚለውን
ክብር አግኝቷል፡፡ ‹መጋቤ ሐዲስ› የሚለው ሰያሜም ከዚህ የሚጀምር ነው፡፡ሳጥናኤል
ክህደት አመንጭቶ ሲናገር ቅዱስ ገብርኤል አዲስ አሳብ አምጥቶ ሰብኳልና፡፡
2. ሕገ ልቡና ሕገ ልቡና የምንለው ከአዳም እስከ ሙሴ ያለው ዘመነ አበው ነው፡፡
በዚህ ጊዜ ሄኖክ ኃጢአተኞች ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ፣ ኖኅም ሊመጣ ካለው የጥፋት
ውሃ እንዲያመልጡ፣ አብርሃም የዑር ምድር ሰዎች ከጣዖት አምልኮ ወደ እግዚአብሔር
እንዲመለሱ ሰብከዋል፡፡(ይሁዳ 14፣ 2ጴጥ 2፡5፣ ኩፋሌ 11፡14)
3.ሕገ ኦሪት
ከሙሴ ጀምሮ እስከ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ያለው ዘመን በአጠቃላይ ዘመነ
ኦሪት ይባላል፡፡ በዚህ ዘመን የስብከት አገልግሎት ያደገበት፣መጽሐፋዊ የሆነት እንደሆነ
እንገነዘባለን፡፡ነቢያት‹እግዚአብሔር እንዲህ ይላል›እያሉ በቃልም በጽሑፍም ሰብከዋል፡፡
አገልግሎቱም በድንቅ ተአምራት የታገዘ ነበር፡፡ሕዝበ እስራኤል ከግብጽ ባርነት ነፃ የወጡት
በስብከት ነው፡፡በኢያሱ መሪነት ዮርዳኖስን የተሻገሩት፣ከነዓንን የወረሱት በስብከት ነው
በነህምያና በዕዝራ ዘመን በማንበብ፣ በመተርጎም አገልግሎቱ ተጠናክሮ ነበር፡፡ የባቢሎን
ምርኮኞች ወደ አገራቸው የተመለሱት በስብከት ነው ፡፡(ነህ 8፡1-8)
4. ዘመነ ወንጌል
ዘመነ ወንጌል የምንለው የአዲስ ኪዳንን ዘመን ነው፡፡
የዘመነ ወንጌል የመጀመሪያው በር ከፋችና መንገድ ጠራጊ
ሰባኪ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ነው፡፡

የዮሐንስ አገልግሎት ሰማዕትነት ከአዲስ ኪዳን


እንደሚቆጠር የመሰከረለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው/
ማቴ 23፡ 35/ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ
እያለ ክርስቶስንና ክርስትናን ያስተዋወቀ ዮሐንስ ነውና፡፡
ማቴ 3፡2/
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከተማ በገጠር በተራራ በባሕር ዳርቻ በሠርግና
በለቅሶ ቤት በየመንገዱ ሁሉ ከሥፍራ ሥፍራ እየተንቀሳቀሰ ‹የእግዚአብሔር
መንግሥት ወንጌል እየሰበከና ዘመኑ ተፈጸመ ፤የእግዚአብሔርም መንግሥት
ቀርባለችና ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ፤ኢየሱስም
በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ…
በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር› ተብሎ እንደተነገረው በአንድ
ማዕከል በምኩራብ ብቻ ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት ወደ ተለያዩ ማዕከላት
በላቀ ደረጃ አስፋፍቶታል፡፡ ከእርሱ ዕርገት በኃላም ቅዱሳን ሐዋርያት
በተለይም የተስፋውን ቃል ከተቀበሉ በኋላ፡-
በአይሁድ ምኩራብ
በጣኦታት ቤቶች
በፍልስፍና ዐደባባይ
በለቅሶ ቤት ከተጋድሎ ጋር ሰብከዋል
ከሐዋርያትም በኋላም የእነርሱ ተከታዮች ሐዋርያውያን
አበው፣በዘመነ ሰማዕታት፣ በዘመነ ሊቃውንትም ስብከተ
ወንጌል፡-
በቃል
በጽሑፍ
በትርጉም ሥራ
በድንቃድነቅ ተአምራት
በክርስቲያኖች የአንድነትና የፍቅር ኑሮ
በተለያዩ ተጋድሎዎች ሊስፋፋ ችሏል፡፡
ሐ. ስብከተ ወንጌል በኢትዮጵያ፡-
ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው በጀንደረባው አማካይነት እንደሆነ የታወቀ እውነት ነው፡፡
ጃንድረባው አምኖና ተጠምቆ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ የክርስትናን ዜና
ለኢትዮጵያውያን አብሥሯል፡፡
ይህ ማለት ግን ቅድመ ክርስትና የብሉይ ኪዳን ሥርዓተ አምልኮ ወደ ኢትዮጵያ እንደገባና
የኦሪት ሥርዓተ አምልኮ መስፋፋቱን ሳንዘነጋ ነው፡፡ ዛሬም ድረስ መገለጫ የሆኑ መንፈሳዊ
ማስረጃዎች መኖራቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ባሻገር የተረዳ እውነት ነው፡፡
ጃንደረባው ባኮስ በ35 ዓ.ም ያሰገባውን የምሥራች ወንጌል ስብከት ያቀጣጠለውና
ወደ ብሔራዊነት ደረጃ ከፍ ያደረገው የሥነ ጽሑፍ ይዘት የፊደል ቅርጽና ሆሄ አሁን ባለበት
ደረጃ አገልግሎት እንዲሰጥ ያደረገው ቅዱስ ፍሬምናጦስ ከነገሥታቱ ጋር በመሆን ነው፡፡
እስከ ዮዲት መነሣት ድረስ ነገሥታቱ፣ ዘጠኙ ቅዱሳን ቅዱስ ያሬድ መጻሕፍትን በመተርጉም
ስብከተ ወንጌልና የምንኩስና ሕይወት እንዲሰፋ አድርገዋል፡
ከዮዲት መነሣት በኃላ ደብዝዞ የነበረው የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ ትንሣኤ
ያገኘው ወርቃማው ከሚባለው ከ11ኛው እስከ 14ኛው በነበረው ክፍለ ዘመን
ውስጥ ነው፡፡
በዚህ ዘመን፡-
• በዮዲት ምክንያት ወደ አረማዊነት ሂዶ የነበረው ወደ ክርስትና
ተመልሷል፡፡
• በርካታ መጻሕፍት ተጽፈዋል
• ብዙ ገዳማት ተገድመዋል
• ሥርዓተ ምንኩስና ተስፋፍቷል
• ብዙ የአብነት ትምህርት ቤቶች ተከፍተው የስብከተ ወንጌል ማዕከል
በመሆን አገልግለዋል፡፡
• ብዙ ቅዱሳንና አያሌ ሊቃውንት የተገኙበት ዘመን ነው
 የመጻሕፍት ትርጉም ሥራ ተከናውኖበታል
• ድንቅ የሆነው የቅዱስ ላሊበላ ሥራዎች የዚህ ዘመን ውጤቶች ናቸው፡፡
የግራኝ መሐመድ መነሣት ለስብከተ ወንጌል፣ለክርስትና መዳከም ዋና ምክንያት ነው፡፡ በዚህ
ዘመን ከዮዲት በኋላም ከድርቡሾች፣ከእንግሊዞችና ከጣሊያኖች ወረራ ጋር ሊነጻጸር
የማይችል ጥፋት በቤተክርስቲያን እና በሀገሪቱ ደርሷል፡፡አሻራዎቹም 500 ዘመናት
ተሻግረው ዛሬም ድረስ ተጽእኖ እንደፈጠሩ ነው፡፡
ለምሳሌ፡-

ሙስሊምና ክርስቲያን መጋባት


የቤተ ክህነት የሙያ ደረጃ ዝቅ ማለት
የአረማዊነት ባሕል መቀላቀል
ያለ ንስሐ አባት መኖር
ያለ ምክረ ካህን ፣ ያለ ሥርዓተ ተክሊል መጋባት
ብዙ ሚስቶች ማግባት፣ ዕቁባት ማስቀመጥ

ከዚህ ዘመን በኋላም ይህንን


2. ለሰባኪው የሚያስፈልገው ምንድን ነው)
ነቢያት ወደ ሕዝቡ ከመላካቸው በፊት ስለሚሄዱበት ጉዳይ በራዕይ በተለያዩ
መንገዶች ተገልጦ እግዚአብሔር ያነጋግራቸውና ተልዕኳቸውን ይፈጽሙ
ነበር፡፡ሐዋርያትም ወደ ዓለም የምሥራቹን ወንጌል ይዘው ከመሄዳቸው በፊት
ሦስት ዓመት ተምረዋል፡፡ ያልገባቸውን በመጠየቅ፣ የረሱትንም
እያስታወሳቸው በትምህርትና በተአምራት መረጃዎችን
አግኝተዋል፤ስለሚያጋጥማቸው መከራም አስቀድሞ መረጃውን ነግሮ
ልኳቸዋል፡፡/ማቴ 1ዐ፡16፣ዮሐ.16፡1 /አንድ ሰባኪም የስብከትን አገልግሎት
ከመጀመሩ በፊት ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡
ሀ.ትምህርት
ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ ‹እንጸልይ ዘንድ አስተምረን› ብለው
ለጠየቁት ሉቃ.11፡1 የተሰጣቸው መልስ አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር
የሚለው የዘውትር ጸሎት ነው፡፡ይህም ማለት ሰባኪው በየትኛውም ደረጃና
ሁኔታ ውስጥ ቢሆን በሁሉም መንገድ ቃለ እግዚአብሔር የተማረ፣ ለመማር
የተዘጋጀ፣ ሊሆን ይገባል፡፡‹ብርጭቆ ካልሞላ አይፈስም› እንደሚባለው ሰባኪ
ሙሉ የሆነ ነገር ከሌለው የምእመናን ልብ ማርካት አይችልም፡፡ እርሱም
የሚናገረው ይጠፋዋል፡፡ስለዚህ ከሌሎች መምህራን፣ ከቅዱሳት መጻሕፍት፣
ከምቹ አጋጣሚዎች ወዘተ መማር አለበት፡፡
የቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስረዳን አባጀሮም መምህራን ባልነበሩበት
ዘመን የነበረ ቢሆንም በማንበብ ግን የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ሊሆን ችሏል፡፡
በዘመናችንም በማንበብና በመጠየቅ ብቻ ‹አንቱ› የተባሉ ሰባክያን አሉ፡፡
ለ. ክርስቲያናዊ ሕይወት
የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚያገለግል ፣ክርስቶስ የሰበከውን ቅዱስ ወንጌል የሚናገር
አባቶች በቆሙበት የሰብከት ሰገነት የሚቆምና ምእመናንን ወደ እግዚአብሔር የሚጠራ
ሰባኪ ሃይማኖቱ የቀና፣ ስነ ምግባሩ የተስተካከለ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተናገረው ሰባኪው፡-
የሚጣፍጥ ጨው
የሚያበራ መብራት
መልካም መዓዛ ያለው መሆን አለበት፡፡
ከእውቀት ይልቅ ተግባር ይስብካልና፡
፡በመድረክ የሚያሰገርምና የሚያስደነቅ ስብከት እየሰበኩ ከመድረክ ጀርባ ምእመን
የማይደፈረውን የደፍረት ኃጢአት የሚያደርግና በወረደ የክርስትና ሕይወት የሚኖር
ከሆነ እርሱም ትምህርቱም ይናቃል፡፡ሰባኪው በክርስትና ሕይወት እየኖረ ሌላውን ኑሩና
እንደ እኔ ሁኑ የሚል ስለሆነ /1ቆሮ 11፡1/ በሁሉም ነገር አርአያ መሆን አለበት፡

-
በጾምና በጸሎት የሚታወቅ
የሚወልበትና የሚያድርበት የተወሰነና የሚታወቅ
የሚገናኛቸው የዘወትር ጓደኞች ማንነት የታወቀ
አንደበቱ የታረመ እጁ ንጹሕ የሆነ
በቅድስና ሕይወቱ የተመሰከረለት
በፍቅርና በትሕትናው የሚታወቅ
ትእግስትን የተላበሰ ጨዋ፣ ቁጥብና አስተዋይ የሚባል
(የምሥጢራት ተሳታፊ የሆነ( ምስጢረ ንስሓ፤ምስጠረ ቅዱስ ቁርባን፤ምስጢረ
ተክሊል………………
ክፋውን ነገር ሁሉ የተጸየፈ
ከቡድነኝነትና ከአድማ ሕይወት የተለየ
ከዘረኝነትና ከጐጠኝነት ስሜት በእጅጉ የራቀ…
በተቃራኒው ከተሰለፈ ደግሞ ‹በእናንተ ሰበብ የእግዚአብሔር ስም
ይሰደባል›ተብሎ የስድብና የእርግማን ምልክት ይሆናል፡፡ /ሮሜ 2፡21-24
ሐ. አርአያ ክህነት ያለውን ቢሆን
‹ኢኃደጋ ለምድር እምቅድመ ዓለም ወእስከ ለዓለም እንበለ ካህናት ወዲያቆናት› እንዳለ
ቅዱስ ያሬድ በተገኘንበት ምድር የተጠራነውን /1ቆሮ15፡45/ ሕዝቦችን እግዚአብሔር
አልተወንም፡፡ክህነት ከእግዚአብሔር የተሰጠ የአገልግሎት ፀጋ ነው፡፡በሕገ ልቡና የነበሩ አበው
በእግዚአብሔር ቸርነት ከህነትን እየተቀበሉ መሥዋዕት ይሰዉ ፣ዐሥራት ይቀበሉ ነበር/ ዘፍ
14፡17/፡፡

ሕገ ኦሪት ስትመሰረትም ከሌዊ ነገድ የሆነው አሮን ካህን ሆኖ ተሹሟል፡፡እርሱና ልጆቹ


የቤተክርስቲያን ምሳሌ በነበራቸው ደብተራ ኦሪት አገልግሎታቸውን አከናውነዋል፡፡/ዘዳ 28፡
1-30፣ ዕብ 9፡1/ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ የሆነውመልከጼዴቅም
በዘመነ ሐዲስ ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ለመሠረተው አማናዊ ክህነት ታሪካዊ ነው፡፡/ዕብ 7፡
20/ ቤተክርስቲያን በምሥረታ ዋዜማ ላይ በነበረችበት ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
አስቀድሞ የሠራው ለደቀ መዛሙርቱ ሥልጣነ ክህነት መስጠት ነበር፡ዮሐ 20፡23/
ሐዋርያትም ወደ አገልግሎት በተሰማሩ ጊዜ በየሥፍራው ካህናትን ዲያቆናትን
እየሹሙ አገልግሎቱን ወደ ላቀ ደረጃ አድርሰውታል፡፡ ሐዋ 6፡1-6፣ሐዋ 20፡
28፡፡ ሥልጣነ ክህነት ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት ትልቅና ሰፊ ድረሻ አለው፡፡
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ታሪክ በጃንደረባው ቢጀመርም
የተሟላ ሆኖ የተፈጸመውና በተግባራዊነት ዕድገት ያሳየው ከፍሬምናጦስ
የክህነት አገልግሎት በኃላ ነው፡፡

የካህናት ትልቁ ሥራ /አገልግሎት/፡-


መስበክ /ማስተማር/
ማሳመንና ማጥመቅ
መመገብ /ምሥጢራትን/
ምሥጢራትን መፈጸም
መጠበቅና መከታተል ነው፡፡
በስብከተ ወንጌል የተሰማራ ሰው የክህነት አገልግሎት ሊኖረው
ይገባል፡፡ያሰተማረውን እንዲያጠምቅ፣ ያጠመቀውን ቀድሶ
እንዲያቆርብ በንስሐ አባትነት እንዲያገለግላቸው፡፡

በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን ትልቁን የስብከት አገልግሎት


ሲያከናወኑ የነበሩት ካህናት ናቸው፡፡ ነገሥታቱም ሁሉ ካህናት ነበሩ
በምድራችን በኢትዮጵያም ነገሥታቱ ካህናቱ ነበሩ ፤ ቅዱሳን
ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሐዋርያውያን አበው ሊቃውንትም ሁሉ
ካህናት ነበሩ፡፡ ክህነት ለቤተ ክርስቲያን ሁለነታናዊ አገልግሎት
ማኅተምና ፊርማ ነው፡፡ ምድራዊና ሰማያዊው ከፍ ያለና ልዩ ነው፡፡
መ. ራስን አለመስበክ
ምንም እንኳን በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በሕልውና፣ በባሕርይ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር
አንድ /ትክክል/ ቢሆንም በተዋሐደው ሥጋ ምክንያት ወልድ ከአብ ዘንድ የተላከና ለአብ
የታዘዘ ነው፡፡ ‹ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን ላደርግ አልሻምና›በማለት እንደተናገርው፡፡
/ዮሐ 5፡30/
መጥምቀ መለኮት ዮሐንስም ‹ስለ ራስህ ምን ትላለህ› ብለው ለጠየቁት የሰጠው መልስ ‹
የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምጽ እኔ ነኝ› ብቻ ነበር
ያለው፡/ዮሐ 1፡23/ ዮሐንስ የክርስቶስን ፈቃድ እንጂ የራሱን የሚያውቀውን እውነተኛ
ታሪኩን እንኳን መናገር አልፈለገም፡፡

ሐዋርያው ዮሐንስም በፍጥሞ ደሴት ታስሯል፡፡የታሰረበት ቦታና ምክንያትም እንደ ሮማ


ምክር ቤት ከባድ ነበር፡፡ ነገር ግን ‹ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ክርሰቶሰ ምስክር
ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርኩ› በማለት ብቻ ነበር ራዕዮን የጻፈውራዕ 1፡19/
ሐዋርያት የሰበኩትን የተጋደሉለትን
የእግዚአብሔርን መንግስት ወንጌል የሚሰብክ
ሊቃውንት የተረጐሙትንና ያመሰጠሩትን
ሰማዕታት የተለያዩ ጸዋተው መከራዎችን የተቀበሉበትን ክርስቶስን የሚሰብክ
ሰባኪ የራሱን ነገር መናገር የለበትም፡፡

በዚህ ዘመን ሃይማኖት፣እወቁት፣ሕይወትና የስብከት ዓላማው የሌላቸው ሰዎች


በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ዐውድ ምሕረት ቆመው የምሥራቹን ወንጌል፣
የቅዱሳኑን የተጋድሎ ሕይወት ለመስማት፣ የራሱንም ኃጢአት ለማስተሰረይና
ከአምላኩ ጋር ለመገናኘት የመጣውን ሕዝብ የራሳቸውን የማይረባ ጩኸት
ሲጮሁበት መስማታችን እየተለመደ መጥቷል፡፡ በዚህም ምናምንቴ ጮኸት
እተየማረ ሁልጊዜ እውነትን የማያውቅ የዋሁ ምእመን በስስ ስሜቱ
ይከተላቸዋል፡፡
የሚያደንቁት ሰባኪና ምን ልሥራ ብለው የሚጠይቁት ሰባኪ
በእጅጉ ይለያልና ሰባኪ ራስን ከመስበክ ነጻ መሆን
ይጠበቅበታል፡፡
‹ብዙ ሰዎች ቸርነታቸውን ያወራሉ የታመነውን ሰው ግን
ማን ያገኘዋል› ምሳ 20፡6
‹እግዚአብሔር የላክው የእግዚአብሔር ቃለ ይናገራል›
ዮሐ. 3፡34
‹ ልቡናዬ መልካም ነገርን አፈለቀ /አወጣ/ ዳዊት
፣ሕርያቆስ›
‹እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን› 1ቆሮ 1፡
23 እንዲል እንደተባለ፡፡
ሠ. የተሰባክያንን ሥነልቡና መረዳት
በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ የተሰባክያንን ስነ ልቡና ማወቅ ለስበከተ
ወንጌል መስፋፋትና ውጤታማነት የላቀ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ጌታችን በዚህ
ምድር በነበረበት ጊዜ ውስጥ የተጠቀመበት ዘዴ የአድማጮችን የልብ ፍላጐት
በጥልቀት መረዳት ነበር፡፡
ሊጠይቁት እንደፈለጉ ማውቀና መረዳት
መዳን እንደሚወዱ ማወቅ፣ ጠይቆ መረዳት
እንደራባቸውና ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው መገንዘብ
ሊፈትኑት እንደሚጠየቁት ማወቅ ወዘተ… ለእያንዳንድም እንደ መሻቱ
አድርጐለታል፡፡
የሕዝቡን ማንነት ማወቅ ስንል ማኅበራዊና ባሕላዊ ኑሮአቸውን፣ ሥነ
ልቡናቸውን የግለሰቡን ማንነት መረዳት ማለት ነው፡፡
ተሰባኪን ወይም አድማጭን የማወቅ ጠቀሜታው፡-
1. የትምህርቱን ዓይነት ለመምረጥ
2. የትምህርቱን ይዘት ለመወሰን
3. የትምህርቱን መጠን ለመወሰን
4. የትምህርቱን ጊዜ ለመወሰን
5. የትምህርቱን አቀራረብ ለመወሰን
6. የምናስተምረበትን ዘዴ ለመምረጥ
7.ከመወቀስና ከማወደስ ለመቆጠብ
8.የተፈለገው ለውጥ እንዲመጣ ለማድረግ
9. ከማጽድቅና ከመኮነን ለመጠበቅ
10. ከመፍረድ ለመዳን
11. በአድማጩ ከመተችት ለመዳን
ረ. የስብከት ሰዓትን መጠበቅ
ሰባኪው ሰብከቱን ወጤታማ ለማድረግ በጊዜ መወሰን ግድ
ይልዋል፡፡ የሚጠቀምባቸውን ጊዜያት ወስኖ ማክበርና በአገባቡ
ሥራ ላይ ማዋል፡፡ሰዓት ከረዘመ ስብከቱ ሊንዛዛና አስልቺ ሊሆን
ይችላል፡፡ምእመናኑ የመደንዘዝ፣ የመሰላቸት የወሬ የእንቅልፍ
ስሜትና አቋርጦ መሄድ ይፈልጋል፡፡የስብከቱ ሰዓት ካጠረም
የሚፈለገው መልእክት አይተላለፍም ሰማዕያኑ ይታወካሉ
ጥያቄም ይፈጠርባቸዋል፡፡መምህሩ እወቀት /ፍላጐት/
እንደሌለው ሊገመቱ ይችላሉ የስብከት ሰዓት እንደየሁኔታው
ለመወሰን፡-
ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ፡- ቀዝቃዛ ፣ሞቃታማ፣ ዝናብ
የሚበዛበት፣ ዝናብ ያልወቅቱ የሚዘንብበት
ትምህርቱ የሚሰጠው ሜዳ ላይ ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ አዳራሽ
ትምህርቱ የሚሰጠወ ጧት፣ ከሰዓት፣ ማታ
በአካባቢው የተለመደው ምቹ ሰዓት የትኛው ነው
ለምን ያህል ሰዓት ሕዝቡ መቆየት ይችላል
በአካባቢው ያሉ ሌሎች ተጽእኖዎች
የአሕዛብ
የመናፍቃን
የፖለቲከኞች
የኅብረተሰቡ አመለካከት እነዚህ ሁሉ ታሳቢ ሊደረጉ ይገባቸዋል፡፡

ሰዓት መጠበቅ እንዴት ይችላል?


ሰዓት መጠበቅ እንዴት ይችላል?

 ሰዓት ወስኖ ከሚመለከታቸው ጋር ተነጋግሮ መጀመር


 ሰዓቱን በተወሰነ ጊዜ መመልክት
 ሰዓቱን በመመልከት እያጠቃለለ መሄድ
 ድንገት የሚፈጥር ካለ ማቋረጥ
ሰ. የስብከት ርዕስ መጠብቅ
ስብከት ርዕሱ ካልተጠበቀ ውጤታማ ሊሆን አይችልም፤ ምእመናኑ
የሚጨብጡት ነገር አይኖራቸውም ሰባኪውም ትዝብት ውስጥ ይወድቃል፡፡
ርዕስ መጠበቅ የሚሰጠው ትምህርት ወጥና ያልተደባለቀ ያደርገዋል

ለምሳሌ፡- ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ጀምሮ ስለ ጾም


ስለ ቅዱስ ቁርባን ጀምሮ ስለ ሥዕል
ስለ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ጀምሮ ስለ ታቦት… የሚል ከሆነ ‹ አርባ
ስድስት ጥዳ አንዱንም… አረረባት› እንደተባለው ይሆናል፡፡ ሰዓትና ርዕስ
መጠበቅ የአንድ ሰባኪ መታወቂያዎች ናቸው፡፡
ውይይት
1. ከላይ የተገለጹት ለሰባኪ የሚያስፈልጉ ጉዳዮች በሁለት ሊከፈሉ ይችላሉ

ሁልጊዜ የሚደረጉ / የሚያስፈልጉ በስብከት ሰዓት የሚደረጉ


ትምህርት ራስን አለመስበክ
ክርስቲያናዊ ሕይወት የተሰባክያን ስነልቦና መረዳት

አርአያ ክህነት ሰዓት መጠበቅ


ርዕስ መጠበቅ

1. ከላY ktzrzሩT DKmቶC WS_ xND _ሩ SBkTN bጣM l!ÃbላሸW y¸ClW yTኛW CGR
nW)

2. \LጣኞC Xnz!H klY ytzrzሩT ngሮC yጎdl#T sባk! Mglጫãc$ MN XNdሆn# XNÄ!
zrZር mFT/@ãc$ lY XNÄ!wÃይ ÃDRg#ÝÝ lMúl@ xND sባk! SዓT m-bQ y¸ÃQtW
MN s!ሆN nW) R:S m-bQ yሚÃQtW MN s!ሆN nW) Xnz!HN lmFታTS MN ማDrG
YgባL)
3 . የስብከት ዓይነቶች፡
3.1 ይዘትን መሠረት ያደረገ አከፋፈል፡፡
የስብከት ዓይነት በይዘታቸው በሦስት ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም
ትምህርት ፡-
በእውቀት ላይ የተመሠረተ
ተከታታይነት ያለው
በማስረጃ የተደገፈ
ማብራራትን መተርጉምን፣ ማመሥጢርን የሚጠይቅ
ትምህርታዊ ስብከት፡-
በጥምረት የሚስጥ
መነሻው ትምህርት መድርሻው ስብከት የሆነ
ማስረጃ በመስጠት ሰውን ወደ ፈጣሪው የሚያቀርብ
እውቀትና ሕይወት በአንድ ጊዜ የሚያስጨብጥ
ስብከት ፡-
ቀለል ባለ አገላለጽ የሚቀርብ
ማስረዳትና ማሳየት ላይ የሚያተኮር
የሰውን ልቡናና አእምሮ መማረክ እና መግዛት የሚችል
ሁለንተናዊ ስሜቱን የሚቆጣጠር
ምእመናን በሰሩት ኅጢአት ተጸጽተው ንስሐ እንዲገቡ የሚያደርግ
የእግዚአብሔርን ቁጣውን፣ ቸርነቱንና ፍቅሩን በአንድ ጊዜ የሚያሳይ
ጥያቄ

ከላይ ከተዘረዘሩት ሦስት የስብከት ዓይነቶች


ለማዘጋጀትና ለማቅረብ የሚከብደው የትኛው
ይመስላችሁዋል ለምን
3.2 በትምህርት አቀራረብ
በአቀራረብ ሲታይ ስብከት በሚከተሉት ዘርፎች ይከፈላል
3.2.1 ታሪካዊ /Historical/
ይህ ዘዴ አብዛኛውን ጊዜ በበዓላት ቀን የምናስተምርበት መንገድ ነው፡፡ በየበዓላቱ የዕለቱ
ስንክሳር፣ ገድል፣ ድርሳን ይነበባል፣ ይተረካል፡፡ ሰባኪውና የስብከቱ ቦታ የኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን እንደመሆኑ እነዚህን አስቀድሞ አንብቦና አጥንቶ ለምእመናን ማስተማር
ይጠቅበታል፡፡
ሰባኪው ሕዝቡን በሚመጥንና በማያስለች መልኩ ቀላልና ግልጽ በሆነ አቀራረብ ሰዓት
መጥኖ ርዕስ መርጦ ምእመናን ከታሪኩ ተነስተው በሕይወታቸው ላይ ትርጉም
እንዲኖራቸው ወደ ሕይወት በመቀየር ማጠቃለያውን ስብከት አድርጎ መጨረስ ማለት
ነው፡፡

ውይይት፡
ሠልጣኞች ለታሪካዊ ስብከት መነሻ የሚሆን አንድ ታሪክ እንዲመርጡና ርዕስ እንሲሰጡት
ያድርጉ፡፡ ወይንም አንድ የስብከት አውድ ምሳሌ አድርገው ይስጡዋቸውና ለዚያ
የሚስማማ ታሪካዊ ስብከት ለማዘጋጀት ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ አውጥተው ርዕስ
እንዲመርጡ ያድርጉዋቸው፡፡
3.2.2 ነገረ ሃይማኖት /Dogmatic/
ከስብከቶች ሁሉ ጠጣርና ከባድ የሚባለው የስብከት ዓይነት ነው፡፡ ይህን ትምህርት
ለማስተማር ሰባኪው የሚከተሉትን ነጠቦች ማስታዋል ይጠበቅበታል፡፡
ሀ. አንድ ነጥብ ላይ ብቻ ማተኮር
ለምሳሌ፡- ሀልዎተ እግዚአብሔር ፣ ምሥጢረ ሥላሴ…
ለ. በሚገባ ማብራራት፡- ሊያስተምር የፈለገውን ነጥብ በሚገባ ማብራራት
ይኖርበታል፡፡ የሚያበራራባቸው ዘዴዎችም፡-
ምሳሌዎችን በማንሳት፡- ምሥጢረ ሥላሴን ማስተማር ቢፈልግ
በፀሐይ፣ በእሳት፣ በሰው መስሎ ማስተማር
ስለ እመቤታችን አማላጅነት፡- የበላኤሰብን ታሪክ በማስታወስ መተረክ
ለትምህርት አስረጂ ጥቅሶችን በማንሳት
የሊቃውንትን ብሒል በመጠቀም

አባቶቻችን በእያንዳንዱ ርዕስ ጉዳይ ላይ ያስተማሩበት መንገድ፣ የገለጡበት አባባል፣


የሰጡት ምሳሌ አለ፡፡ እነዚህን በሚገባ ማብራራት፡፡
ሐ. የአባቶችን ቃላት መጠቀም፡- ሰባኪው በሚያስተምርበት ሰዓት የማይገቡ ቃላት ተጠቅሞ ምሥጢራትን
እንዳያፋልስ የአባቶችን አባባል በሚገባ መጠቀም፡፡
ለምሳሌ፡- ዮሐንስ /ወንጌላዊው/ በተለያዩ ሰሞች ይጠራል
ነባቤ መለኮት
ታዖሎጐስ
ወልደ ነጎድጓድ
አቡቀለምሲስ
ፍቁረ እግዚእ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፡-
እመ ብርሃን
እመ አምላክ
እመ አዶናይ
እመ ብርሃን
እመ ብዙኃን
ማኅደረ መለኮት
እግዝዕተ ብዙኃን
ወላዲተ አምላክ እያሉ ጠርተዋቸዋል፡፡
የነገረ ሃይማኖት ትምህርት በጣም መርዘም የለበትም፡፡ ከረዘመ የሰማዕያኑ አእምሮ ይከብደውና
የሚይዘው አይኖረውም፡፣ በትምህርቱ መካከልም ‹መናፈቃን እንዲህ ይላሉ› ከማለት ይልቅ
የቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት በማደረግ የትምህርቱን ጭብጥ ተረድቶ ለጥያቄዎች መልስ
የሚሰጥ ትምህርት አዘጋጅቶ ቢያቀርብ መልካም ነው፡፡
ባለ አንድ ሐረግ ስብከት
ባለ አንድ ሐረግ ስብከት የሚባለው ሰባኪው ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሐረግ
መዝዞ ያንን ተመርኩዞ የሚሰጥ ትምህርት ነው፡፡
ለምሳሌ ‹በፈተና የሚጸና የተባረከ ነው› / ያዕ 1፡12/ ብሎ ከተነሣ፡-
 የፈተናን ምንነት
 የፈተናን ዓይነት
 ፈተና የሚመጣባቸውን መንገዶች
 ፈተናን እንዴት ማለፍ ይቻላል)
 በፈተናው ጸንተው ያለፉ ቅዱሳን ሰወችን ታሪክ እያነሣ ከዘመኑና ከሰው
ሕይወት ጋር በማዋሃድ በሰፊው ማስተማር ነው፡፡ ‹አንደ ሐረግ ሲሰቡ ድር
ይሰበስቡ› እንዲሉ፡፡

ባለ አንድ ሃረግ› የሚለው መነሻ ይሁን እንጂ ብዙ ዓይነት የስብከት
ስልቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል፡-
ባለብዙ ሐረግ ፡- ያለ ርዕስ የሚሰበከ /በቅዳሴ ሰዓት፣ በከብረ በዓል/
ሰምና ወርቅ፡- ማቴ 7፡1-5፣ 2ዜና 25፡17 አሜስያስና ኢዮአስ
ያደረጉት ውይይት
አንጻራዊ ፡- ማቴ 7፡24፣ ማቴ 24፡37

ውይይት፡
ባለ አንድ ሐረግ ስብከት ለማዘጋጀት የሚሆን የቅዱስ መጽሐፍ
ጥቅስ ወይም ሐረግ እንዲመርጡና ለምን እንደመረጡት ምን
መልዕከት ሊያስተላልፉ እንደፈለጉ በመጠየቅ ያወያይዋቸው፡፡
2.4 ቅዳሴያዊ ስብከት
ይህ ዓይነት ስብከት ፣በጾም ወቅት በኪዳን የጸሎት ሰዓት፣ በንግስ ጊዜ፣
በሥርዓተ ቅዳሴ መካከል የሚሰጥ ትምህርት ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን
ዋነኛው የስብከት ዘዴ ነው፡፡
ይህ የስብከት ዘዴ ብዙ ጥቅሞች አሉት፡-

 በአንድ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ይገኝበታል


 ሕዋሳት በሙሉ ተሳትፎ ያደርጋሉ
 በሁሉም ንዋያተ ቅድሳት ማስተማር ይቻላል
 ከሕፃን እስከ አዋቂ ይታደሙበታል
 በየጊዜው ስለሚሰጥ ትምህርቱ አይረሴ ይሆናል
 ብዙ ታሪኮችንና ትምህርቶችን በአንድ ጊዜ ያቀርባል
ለምሳሌ፡- የቅዳሴው ምንባብ፣ ዜማው /የ3ቱም የዜማ ስልት/
የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ፣ /ወንጌል፣ ግብረ
ሐዋርያት፣ መልእክት፣ መዝሙረ ዳዊት/
ምስባክ/ የዕለቱ ዜና /የቅዱሳን ሕይወት/
ስንክሳር እነዚህ ሁሉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን ሕዝበ ክርስቲያንን በሙሉ
ማንነቱን የሚያሳውቁ ስለሆነ ተዋሕዶት
ይኖራል፡፡
ውይይት፡
በሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ ትምህርት ለማስተማር ቢመደቡ የትኛዋን
ዓይነት ትምህርት በምን ዓይነት አቀራረብ እንደሚመርጡ ይጠይቁዋቸው፡፡
ሰልጣኞችን ምርጫቸውን ያብራሩ

ሀ) የኅዳር 21 የእመቤታችንን በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀ መርሐ ግብር ላይ

ለ) የአዳዲስ ተማሪዎች አቀባበል መርሐ ግብር ላይ

ሐ) ሰርክ ጉባኤ ላይ ሆኖ ዕለቱ ዘመነ ጽጌ ቢሆን


4. ስብከትን በሚዘጋጅ ወቅት ታሳቢ የሚደረጉ
ጉዳዮች
4.1. ሕዝብን ማወቅ፡-
ስብከተ ወንጌልን ለአንድ ሕዝብ ለማስተማር የሕዝቡን ማንነት ማወቅ
የስብከት ወንጌል መመሪያ ነው፡፡ አንድ ሰባኪ የሕዝቡን ማንነት ሳያውቅ
የሚሰጠው የመግባርም ሆነ የቃል ትመህርት ከተሰባኪው ሕይወት ጋር መዋሐድ
አይችልም፡፡

ሰለዚህ ሰባኪ በተቻለ መጠን የሚያስተምራቸውን/ የሚሰብካቸውን ሰዎች


ባሕልን ማወቅና ማጥናት ቋንቋን፤ የሃይማኖታዊ ዳራ፤ የተሰባክያኑ የእውቀት
ደረጃ፤ የኑሮ መጠናቸውን፤ በአካባቢው ያሉ አስተሳሰቦች ወዘተ በተቻለው
መጠን ማወቅና መረዳት ይኖርበታል፡፡
4.2 የስብከት ቦታዎችን ማወቅ ፡-
መቼም ቢሆን የስብከት ማእከላዊ ቦታ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ በዚህ በተጨማሪ
የምሥራቹነ ወንጌል ወደ ሕዝበብ ጆሮ ለማድረስ ምቹ ቦታዎች አጎጣሚዎችን መጠቀም
አለበት፡፡
የዚህ ሃሳብ መነሻም አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ "በእኔ ተመሩ ብሏልና እርሱን
አብነት አድርገን በሚከተሉት ቦታዎች አጎጣሚዎች መስበክ"
ሀ. ቤተ ክርስቲያን፡-
 በዘወትር የሰረክ መርሃ ግብር
 በኪዳን የጸሎት ሰአት
 በሳምንታዊ መርሃ ግብር
 በወርሃዊና አመታዊ በዓላት
 ልዩ ልዩ መርሃ ግብር በማዘጋጀት
 በቀብር ሰአት
በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ስበከተት ተግባራዊ ነው ማለት እንችላለን፡፡
ለ. በሃዘን ቤት፡-
በለቅሶ ቤት የማገኙ ወኖች ሃዘን ልናቸውነ የሰበረባቸው፣መጽናትን የሚፈልጉ ናቸው፡፡
ሃዘንተኞች ምትንና ሕየወትን፣ጽድቅንና ኩነኔን፣ የማያስቡበት ምቹ አጋጣሚ ነው፡፡ በዚህ ቦታ
ሰባኪው፡-
ሃዘንተኞችን ማጽናናት፡-
ተስፋ ተንሣኤን ማሳየት ዮሐ. 11÷25
የሁለተኛውን ዓለም ኑሮ ማሳየት 2ቆሮ. 5÷1
ሞት የሥጋ ባሕርይ መሆኑን መንገር መዝ 88÷48
አስተዛዛኙን ስለ ንስሐ መንገር፡-
አስተዛዛኙ ሕዝብ የተለያየ እምነት፣ አመለካከት፣ጠባይ ያለው ነው፡፡ በሞተ ሰው፣በሌላም
ጉዳይ የለያዩ ወሬዎችን ያወራል፡፡
ስለሞት አስቦ ባያውቅም አሁን ግን እያሰበ ነውና ልቡናውን ሊሰብሩ ማንነቱነ ሊያሳያ
የሚችሉ ጥቀሶችን በመጥቀስ ማስተማር
ጌታችን ሃዘንተኞችን አጽናኗቷል፣በለቅሶ ቤት አሰተምሯል
ስለወሬ አንድ ነገር ትዝ አለኝ ሰወች ሃሜት የለመደባዠውና ናቸውና ሁለጊዜ ይሄዳሉ፡፡
እስከሬኑ ይዘገያል፡፡ እናም ሰወቹ "ይህ ሰውኮ በሕየወት እያለም ቀጠሮ አያከብርም ነበር"
እያሉ ሲያወሩ ወዲየውኑ "ሬሳው ደረሰ" ሃሜት የለመደባቸው ሰዎተ "ይህ ሰው እድሜው
ረጅም ነው" ስናነሳው መጣ አሉ ይባላል
ሐ. በሠርግ ቤት
በሠግ ቤት የሚገኘው ሰው ሁሉ ከርሰቲያን አይለም፡፡ የተሰበሰበውም ቃለ እግዚአብሔር
እማራለሁ ብሎ አይደለም፡፡ በዚህ ሰአት ሰባኪው፡-
አዲስ ተጋቢዎች (የዐለቱን ሙሽሮች)
ያላገቡትን
በትዳር ውስጥ ያሉትንም አንድ የሚያደርግ ስብከት መሰበክ ይጠበቅበታል፡፡
ሙሽሮች የዛሬ ደስታቸውን ብቻ ሳይሆን የነገውነ እንዲመለከቱ፤ ትዳር በፈተና የተከበበ
ሕይወት መሆኑን በማሳየት እንዲጸልዩ፣በእምነት ጸንተው በመውያት፣ በመግባባት፣
በመተሳሰብና በመረዳዳት እንዲኖሩ፣ በመካከላቸው ማንም ጣልቃ እንዳይገባ መምከር
ያላገቡ እስኪያገቡ ድረሰ ራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸውና ጋብቻቸውን በቤተ ክርስቲያን
በስርአተ ተክሊል እንዲፈጽሙ መቀስቀስና ክብሩን ማሳየት፡፡ ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ጾታዉ
ግንኙነት ኃጢአት፣ ለነገ ትዳርም ጠንቅ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥቶ ማስተማር፡፡
በትዳር ውስጥ ያሉትን ጋበቻቸውን በስርአተ ተክሊል የፈጸሙትን የበለጠ እንዲበረቱ፣
በስርአተ ተክሊሉ ያልፈጸሙትም ወደ ቅዱስ ቁርባን እንዲመጡና የሚያገኙትን ክብር
በማሳየት መስበክ፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሠርግ ቤት ማስተማሩና የተገኘው ጥቅም መነገር አለት ዮሐ.
2÷1-11፡፡
መ. በማረማያ /ውህኒ/ ቤት፡-
በወህኒ ቤት የታሰሩ ሁሉ ወንጀለኞች አይደሉም
ወንጀል ሰርተው፣ኃጢአት መሆኑን አውቀው የሚጸጸቱ አሉ
ከታሰሩበት ቦታ ሌላ ወንጀል የሚሰሩም አሉ
ሠስርቆት ተግባር የሚፈጽሙ
እርስ በእርስ ሚደባደቡ
ግቢ ሰዶም የሚፈጽሙ አሉ
እነዚህ ሁሉ የታሰሩበት ቦታ አነድ ነው በጥበብ ማስተማር የሰባኪው ብልህነት ነው፡፡ ወደ
እግዚአብሔር መቀረብና ወደላይ እንዳለባቸው፣ የወንጀለነ አስፈፊነት
ለራስ ሕሊና እና መልካም ስም
ለቤተሰብ፣ለሀገር፣ለወገን
ለቤተ ክርስቱያን የማየደርሰውን ጉዳት
በአደር፡- የሰው ልጅ ክቡና ቅዱስ መሆኑን
በሰውና በጢት መጠበቅ እንደለለበት
ጠባቂወቹ ቀዱሳን መለአክት
የእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል እንደሆነ መለየት
4.3 የኦርቶዶክሳዊ ስብከት ጠባያትን መከተል
የኦርቶዶክሳዊ ስብከት መለያ ጠባያት ባሕርያት የሚባሉት
መጽሐፋዊ፡- ሶሰት ነጠቦችን ያካትታል

ሀ. መጽሐፍ ቅዱስ፡-
የስብከት መሰረት መጽሐፍ ቅድስ ነው
በቤተ ክርሰቲያን የሚከናወኑ ተግባራት በሙሉ መጽሐፍ ቅድስ ናዠው

ለ. አዋልድ፡- መጽሐፍ ቅዱስን የሚተረጐሙ፣ የሚያብራሩ፣ በተግባርም


ለሚያሳዩ ናቸው አዋልድ መጽሐፍትን መጠቀም

ሐ. ታሪካዉ መጽሐፍት፡- የቤተ ክርስቲያን የታሪክ መጽሐፍትን መመሠረት


አድርጐ አሌሎች መጽሐፍት ጋር አወሐዶ ማቅረብ
ነገረ መለኮት፡-
አራት ነጥቦችን በውስጡ ያካትታል፡-

ሀ. ምሥጠራተ ቤት ክርስቲያን
ለ. መሠረተ እምነት /ይግማ/
ሐ. ስርአተ ቤተ ክርስቲያ
መ. የቤተ ክርስቲያን ትውፊት
ስርአተ ቤተ ክርስለቲያን፡-
ሀ. የፆም፣የፆሎት ስርአትን መሠረት ያደረገ
ለ. የበአላት አከባበር ስርአትን በተመለከተ
ሐ. ስርአተ ቅዳሴን መሠረት ያደረገ
መ. የቤተ ክርስቲያን መዝሙራትን ያካተተ
ሠ. የስግደትና የአገለግሎት ስርአት
ማኅበራዊ ኑሮን በተመከተ፡-
በማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ክርሰቲያኖች ሊኖራቸው ስለሚገባ ግንኙት
ሰለ ክርስቱያን ቤተሰብ አኗኗር በግልጸ ማሳወቅ
ከሌለው /በእመነት ከሚስቷቸው/ ጋር ስለሚኖራቸው አንድነትና ልዩነት ማሳወቅና መወሰን
ቢቻላችሁስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ ተብሏልና፡፡
እለታዉና ወቅታዊ ጉደዮችን በመዳሰስ
ጥምረት ያለው፡-
ነገረ ሃይማኖትንና ስርአትን
ሃይማኖትንና ስነ መግባርን
ሃየማኖትንሃ ማኅበራዊ ኑሮን በማጣመር ማስተማር ይቻላል፡፡

ለምሣሌ፡- በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ ማቴ. 10÷5

በአሕዛብ ሃይማኖት
በአሐዛብ ስርአተ
በአሐዛብ ማኅበራዊ ኑሮ
5. የስብከት ዝግጅት
xND ሰባኪ SBkT l!ÃzUJ SBkt$ ለማን XNd¸¸s_Ý yT እንደሚሰ_
ካወቀq በç® ኦርቶዶክሳêE ySBkT -ባÃTN bmktL SBkt$N ያዘጋጃል፡፡
SBkT bማዘጋጀት ሂdT WS_ ymjm¶ÃW የቃሉ ባlb@T የሆነውን L;#L
XGz!xB/@RN በፀሎት m-yQ nWÝÝ
የቃሉን ደጅ ይከፍትልኝ ዘንድ ጸልዩልኝ እንዳለው፡፡ ሰባኪው ሁልጊዜ የሚያነብና
የሚማር ከሆነ የስብከት ዝግጅትን ቀላል ያደርገዋል፡፡ ሆነም ግን ሰባኪው ማንበብ
ትዝ የሚለው ስብከት ለመዘጋጀት ሲል ብቻ ከሆነ የስብከት ዝግጅቱ ጠባብ
ይሆናል፡፡ በስብከት ዝግጅት ውስጥ ሌላው ወሳኝ ጉዳይ ማስተወሻ መያዝ ነው፡፡
ሰባኪ የሚያስተምረውን ስብከት/ትምሕርት/ በማስታወሻ ደብተሩ ላይ በጥሩ
ዝግጅት ላይ ካሰፈረ ለማስተማር ቀላል ይሆንለታል፡፡ በተለይ በማስታወሻ ላይ
ለማስፈር እንዲመች የሚከተሉትን የስብከት ክፍሎች ማወቅና መከተል ጠቃሚ
ነው፡፡
አንድ ስብከት ስድስት ንዑሳን ዘርፎች
/ክፍሎች/ አሉት፡፡ እነዚህም
1.ርእስ 4. ዋና ክፍል
/ሐተታ/
2.አላማ 5. ምክር
3.መግቢያ
6.መደምደሚያ
ሰባኪ ተከታታይ ትምህርት፣ ረጅመ ሰብከት፣ አጭር ሰብከት ለማዘጋጀት እነዚህን ቅደመ
ተከተሎተ ማወቅ ይጠብቅበታል
5.1 ርዕስ መምረጥ
ርእስ በሚመረጥበት ጊዜ የሰዎችን ትኩረት የሚስብ
የተማሪዎችን የመማር ፍላጐት የመቀስቀስ ኃይል ያለው
አላማውን በትክክል መግለጽ የሚችል
አጠር ያለና ግልጽ የሆነ፡፡ ርእስ የስብከት ማስታወቂያ ነው፡፡
የርዕስ አመራረጥ መርሆዎች፡-
በሰማእያኑ ዘንድ አይረስነት ያላቸው፣ በቀላሉ ሊረዱት የሚችሉ ቃላት
ሊተላለፍ የሚገባውን መልእክተ ጠቅለል አድርገው የያዙ ቃላት
ሰባኪው አብራርቶ ለማስተማር አመቺነት ያላቸው
ምሥጢራትን ያዘለ ቃላተ /ሐረጐች/
ርዕስ ከመምረጥ በፊት ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮች፡-
ተሰባኪዎች ባሉት አካባቢ እድሜ፣ እውቀት፣ ፆታ የሚዘወትረ አጉል ልምዶች ጠባዮች
እምቶችን ለይቶ ማወቅ፡፡
የአካባቢው ማኅበረሰብ ኢኮኖሚያዉ፣ባሕላዊ፣ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን ለይቶ
ማወቅ
እለታዊሃ ወቅታዊ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ክስተቶችን ግመት ውስጥ ማሰገባት
ልምምድ፡

ለሠልጣኞች አንድ የስብከት ጉባኤ ወይም ሁኔታ


ወይንም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመስጠት ለዚያ
የሚሆን ስብከት የስብከት ርዕስ እንዲመርጡ ያድርጉ፡፡
5.2 የስብከቱን ዓላማ መለየት
አጠቃላይ የስብከት ዓላማ ምዕመናን ስለእግዚአብሔር ፍቅርና ሀልዎት ስላደረገልንም
የማዳን ሥራ ተረድተውና ተገንዝበው እግዚአብሔርን በመውደድ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ
ከክፋት ወደ ደግነት እንዲመለሱ ማድረግ ቢሆንም በእያንዳንዱ ስብከት ከዚህ አጠቃላይ
ዓላማ በመነሳት ትኩረት የሚደረግበት ዝርዝር ዓላማ ሊኖር ይገባል፡፡

ዓላማ የስብከት አንጐል ነው ይባላል ይህም ማለት ስብከቱ ምን መምሰል እንዳለበት፤


በምን መልክ መቅረብ እንዳለበት፤ ምን ምሳሌዎች መነሳት እንዳለባቸው የሚያመለክተው
ዓላማው ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ሰባኪው ስብከቱን በሚያዘጋጅበት ጊዜ በዚህ ትምህርት
ምዕመናኑ ምን እንዲሆኑ ነው የምፈልገው ምን እንዲረዱ ነው የምፈልገው ብሎ በማሰብ
ከዚህ አንጻር የትምህርቱን መዋቅር ማስኬድ ይኖርበታል፡፡
የትምህርቱን ዓላማ በትክከል ማስቀመጥ
ዓላማ የሚሰጠው ጥቅም
ሀ. የተምህርቱን ዝግጅትና መደምደሚያ መልእክት ይቆጣጠራል
ለ. በትመህርቱውስጥ ሊካተቱ የማገባዠውን ሊካተቱ
የማይገባቸውን የወስናል
ሐ. የሚዛመዱ አሳቦችነ ለመወሰን ይረዳል
መ. የትምህርቱን አላማ ለመፈጸም የሚረድ ምሣሌወችን
ለመምረጥ
ሠ. ትምህርቱ ግቡን መምታቱን ለመለካት
መ. መደምደሚያ ለመስጠት
የዓላማ አጠቃላይ ግብ ምድን ነው?

እውቀት ለማስተላለፍ፡-
የአንድምታ ትምህርት፣ነገር ሃይማኖተ፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ነገር ቅድስን
መንፈሳዊ ሕይወት ለማስተማር፡-
ጸሎጽ፣ፆም፣ንስሐ ሕይወት፣ ቅዱስ ቁርባን
የጠባይ ለውይ ለማምጣት፡-
ሰው ከመጥሮ ሥራ እንዲመለስ
እኩይ ተግርን እንዲተው
ከኃጢአት ከወንጀል እንዲጠበቅ
የአመለካከት ለውጥ ለመምጣት፡-
ሰው በአስተሳሰቡ፣ በአመለካከተ አውንታዉ ለውጥ እንደየመጣና አቋም
እንዲኖረው
1. መግቢያ፡-

የአንድ ትምህርት መግቢያ የመርነር ይቀሰቅሳል


ርዕሰ ጉዳዩን የበለጠ ያስተዋውቃል
አላማውን በትክክል ይገልጣል
የሰማዕያኑን ትኩረተ የሚሰብር የሚገዛ ይሆናል፡፡
ይህ ክፍል ሰባኪው ራሱን ከምዕመናኑ ጋር የሚያለማምድበት፡ የምዕመናኑን
ዝግጅት የሚቃኝበት፤ ርዕሱን እና ዓላማውን የሚያስተዋውቅበት ጊዜ ነው፡፡
ስለዚህ ሰባኪው ተገቢውን ክርስቲያናዊ ሠላምታ ካቀረበ በኋላ ርዕሱን
ያስታውቃል፡፡ በዚህ ወቅት ረጋ ማለትና በጣምም ሳይቆጡ በጣምም ሳቅ
ሳያበዙ በተረጋጋ ሁኔታ ርዕሱን ካስተዋወቁ በኋላ ርዕሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ
ከተወሰደ ለርዕሱ መነሻ የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ማንበብ፡፡
2. የትምህርቱ ዋና ክፍል
በተከታታይ ትምህርት ጊዜ ተማሪወች በመግቢያ ከተሰጠው ገለጸና
ከተመረጠው ርእስ አኳያ ከትምህርቱ በእውቀትም በሕይወትም ምን
እንደሚጠብቁ መጠየቅና መረጃዎችን ማሰባሰብ፡፡
ትምህርቱን መረዳት በሚችሉበት ሁለንተናዊ የማስተማሪያ ዘዴ በግልጽ ቋንቋ
ማስተማር፡፡
ተማሪዎችን አሳታፊ እንዱየደርግ በጥያቄና መልስ ማስተማር
በውይይት በቡድን ከፋፍሎ ማስተማር
ከትምህርቱ ጋር የሚሄዱ ምሳሌዎችን መጠቀም
አጠር ያለ የቤተ ሥራ መስጠት
ለቀጣዩ አስተየየት መቀበል
የዕለቱን ማጠቃለያ መስጠት
3. የትምህርት ምክር አስፈላጊነት፡-
ትምህርቱን ከተማሪዎች እለታዊ ኑሮ ጋር አገናዝበን ከላስተማረን ያዘጋጀነው ትምህርተ
ውጠት አይኖረውም፡፡

የቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ከሕይወት ጋር ካልተዛመደ መንፈሳዊ ድርቀት የስከትልላል


ትምህርቱ በይዝቱና በአቅራረቡ እንከን የሌለው ቢሆነ እንኳን የተማሪዎችን ሕይወት
ካልለወጡ ትርጉም አይኖረውም
የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርተ ተግባራዊ እንዲሆን
ከእለት ተእለት ሕይወታቸው ጋር ወቅታዊ ማድረግ
መሆን ያለባቸውን እንዲሆኑ ትእዛዝ መስጠት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ምን እደሚፈልግ
በግለጽ በመንገር ትምህርቱን ከሕይወታቸው ጋር ተጨባጭ ማድረግ
እንዲህ ብታደርጉ መልካም ነው ባታደርጉ ግን ብሎ ምክር መስጠት
ምን እናድርግ ?ብለው ራሳቸውን እንዲጠይቁ ማድረግ
4. ለትምህርቱ መደምደሚያ መስጠት፡-

መደምደሚየ መስጠት ትምህርቱን መሉና


የተጨበጠ ያደርገዋል
የተለያዩ ክፍሎችን ያዋህዳል
የትምህርቱን ማእከላዊ አሳብ ያካልላል
የትምህርቱን አላማ ያስታውሳል
ትምህርቱን ያስተሳስራል
• ተጨማሪ የሰባክያን አገልግሎት ምንድን ነው?
• ሀ. የመክር አገልግሎት መስጠት

• ምክር ማለት የሰው ልጅ በእለት ተእለት ሕይወተ ከሚገጥመው የግልና


የማኅበረሰብ ችግር ለመወጣተ የሚያደርገውን ትግል መስመር በማስያዝ የራሱን
አቅምና ችሎታ እንደጠቀምና በእግዚአብሔር ቸርነትና እርዳታ ሕይወቱ
የተስተካከለ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡

• የምክር አገልግሎት አሰጣጥ ዘዴ


• በግል፡- መካሪውና /ሰባኪው/ ተመካሪው ብቻቸውነ በመሆን ምሥጢራዉ በሆነ
መንገድ የሚያከናውኑት ስጋዊ መንፈሳዉ የሕይወት አገልግሎት ነው፡፡
• በቡድን፡- ተመሳሳይ ችግር ያለባቸውን አንድ ላይ በማድረግ አገልግሎት መስጠት
ነው

• የምክር አይነቶች
• የጋብቻ የምክር አገልግሎት
• የሀዘን “ “
• የቤተሰብ “ “
• የትምህርት “ “
• የንስሐ ሕይወት የምክር አገልግሎት
• የሕመምተኛ “ “
• የሥራ “ “
• የመንፈሳዊ ሕይወት የምክር አገልግሎት
• የምስጢራት ተሳትፎ “ “
• የተቃራኒ ፆታ ችግር “
• የምክር ግብ ምንድን ነው?

• የችግሩ ባለቤት የአመለካከትና የጠባይ ለውጥ እንደየመጣ


ሁኔታዎችን ማመቻቸት
• የችግሩ ባለቤት አስፈላጊው ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ማገዝ
• የችግሩ ባለቤት ጠንካራና ደካማ ጐኑን እንዲለይና የተሻለውን
እንዲያደርግ
• የችግሩ ባለቤት በእግዚአብሔር እንዲነየምንና የእምነትን ጥቅም
መንገር
• የችግሩ ባለቤት በእምነት የተጠቀሙ ሰዎችን በአረአያነት ማሳየት
• የምክር አገለግሎት ዓላማ፡-

• በማኅበራዊ፣በኢኮኖሚ፣በስነ ልቦና፣ በመንፈሳዉ ሕይወት፣በጤንነት


ለሚያጋጥሙ ችግረኛ ትክክለኛ ግንዛቤ ለመስጠት
• ሰዎች በግንዛቤ ማነስ ራሳቸውንና ሌላውን ወደሚጐዳ ውሳኔ
እንዲደርሱ ለማድረግ
• በሃይማኖት ለሚኖር መፍትሄ የሌለው ችግር እንደሌለ ለማሳየት
• ለአንዱ የሚታየው ለሌላው አይታይውምና ለመረዳዳት
• ሰዎች በችግራቸው ጊዜ ሚዛናዊ አስተሳሰባቸው ስለሚዛባ
የምክር አገልግሎት አሰጣጥ ዘዴ

• አመቺ በሆነ ቦታና ጊዜ


• መልእክተን ማስተላለፍ በሚችልበት ዘዴ /በስልክ፣ፊት
ለፊት፣በደብዳቤ/
• እንደ አስፈላጊነቱ ተከታታይ ወይም በአንድ ጊዜ
• በስነ ልቡና ባለሙያ
• በሰባኪው ወይም በንስሐ አባት
• የምክር መርሆዎች፡-
• የሰዎችን ልዩነት ማክበር
• መግባባት መቻል
• ምስጢር መጠበቅ
• መንፈሳዊ ግዴታ መሆኑን መረዳት
• የግል ውሳኔን ማክበር /ከወንጀልና ኃጢአት በስትቀር/
• ስብእና ላይ ማተኮር
• የውጤታማ አማካሪ በሕርያት /ጠባያት/
• የተረጋጋ አዕምሮ /ስሜት ያለው
• ሰፊ የአስተሳሰብ አድማስ ያለው
• አካባቡያዊና ነባራዉ ሁኔታዎች መገንዘብ የቻለ
• የአእምሮ ጥቃት ያለው
• ሚዛናዉና ሐቀኛ የሆነ
• ብዙ ማዳመጥ የሚችል
• ግልጽነት ያለው
• የሰዎችን ባሕል የሚጠበቅ
• ኃላፊነት የሚሰማው
• ትዕግስተኛ የሆነ
• በሰዎች እኩልነት የሚያምን
• የሰዎችን ሐሳብ ቀድመ የደረዳ
• ሰዎችን ለመርዳት ፍላጐት ያለው
• የመፍትሄ ሐሳቦችን ማመንጨት የማተት
• በሕይወቱ ጥንቁቅ የሆነ
• በውይይት ሰዓት ለጉዳዩ ትኩረተ የሚሰጥ
• ውሳኔ ከመስጠት ይልቅ አማራጮተን የሚያቀርብ
• ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ያለው
• በሁሉም ነገር ታማኝ የሆነ
• መጽሐፍ ለመጻፍ፡- ከዕለተ የስብከት ዝግጅት መጀመር
• የመናስተምረውነ /ያስተማርነውን/ በጽሑፍ መከለስ
• በመናነብበት ጊዜ ማስታወሻ መያዝ
• በበራሪ ወረቀቶች፣በጋዜጣና መጽሔተ መጀመር
• የስለጠና ማንወሎችን ማዘጋጀት
• ከዚህ ማመነሳት አንድ ቀን ትልቅ መጽሐፍ መጻፈ እንችላለን፡፡
• ሐ. ማሰለጠን፡- በነቢያት ዘመን
• ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
• ቅዱሳን ሐዋርያት
• በአገራችንም፡- አባ ፍሬ ምንጦስ
• ቅዱስ ያሬድ
• ዘጠኙ ቅዱሳን
• እነ አባ ኢየሱስ ሞአ ደቀ መዛሙርትን እያሰለጠኑ ለአገልግሎት ብቁ እያደረጉ ስበከተ ወንጌልን
በጽሑፍ፣ በቃል በመላው ኢትዮጵያ እንዲዳረስ አድርገዋል፡፡
• አባ ጎርጎርዮስ በዝዋይ የለኮሱት መልካም ችቦ በተቀጣጥሎ ዛሬ ላይ ከደረሰበት ደረጃ ደርሷል፡፡
• ሰባኪ በተቻለ መጠን፡- መሰልጠን፣ካህናትን፣ምዕመናነ
• መተካት/ተተኪ ማፍራት/ ይጠቅበታል፡፡
• ማስተባበር፡-

• ስብከተ ወንጌል በአንድ ሰው ብቻ የትም ሉደርሰ አየችልም፡፡ በአንድ በሬ አይታረስም፣አንድ እጅ አያጨበጭብም እንደማባለው፡፡
አገለግሎቱ የተፈጠነና ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ተባባሪ ባለ ድረሻ አካላት በየደረጀውና በየአይነቱ ያስፈለጉታል፡፡
• በኤልያስ ዘመን የስራፕታዋ ሴት
• በኤለሳዕ ዘመነ የሱናማዊቷ ሴት የአገልግሎት ተባባሪዎች ነበሩ፡፡
• በጌችን በኢየሱስ ክረስቶስ የአገለግሎት ጊዜሙ እነ ማርታ፣የማርቆስ ቤተሰቦች
• በሐዋርያት ዘመን እንደ ልድያ የመሳሰሉት ተባባሪ አካላት ነበሩ፡፡
• ስብከተ ወንጌል እንዲስፋፋና እንዲጠናከር፡-
• በእውቀታቸው
• በገንዘባቸው
• በቁሳቁስ
• በጉልበት
• በበጐ አሳብር ምክር እንዲያገለግሉ ማስተባበር፡፡
• የሚያስገኘው ጥቅም፡-
• የጊዜ ብክነት
• የሰው ኃይል እጥረት
• የገንዘብ እጥረት
• ሰዎችን አሳታፊ ያደርጋል
• የባለቤትነት ስሜት እንዲያድርባቸው ያደርጋል
• አገልግሎቱን የተፋጠነ ያደረገዋል
• አንድነትን፣ ፍቅርን ያሳድጋል
• ሰዎች በረከት እንዲያገኙ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

You might also like