You are on page 1of 178

የፍጻሜ ዘመን ክስተቶች

ክርስቶስ ሊቀካህናችን
•የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ በአመዛኙ ስለ እስራኤል ታሪካዊ አነሳስ፣
እድገትና አወዳደቅ ይናገራል
•ይሁን እንጅ እግዚአብሔር ይህንን ህዝብ የመረጠው በእነርሱ
አማካኝነት የዓለምን ህዝብ ወደ መዳን ዕውቀት ለማምጣት እንጅ
እነርሱን ብቻ ለማዳን በማሰብ አልነበርም
•የእስራኤልን ህዝብ ታሪክ ስንመለከትደግሞ
ህይወታቸው ከቤተመቅደሱ ጋራ የተቆራኘ እንደነበር
እንረዳለን፡፡
•የቤተመቅደሱ መሰራት ዋና ዓላማው ምን ነበር?
•እግዚአብሔር የአይሁድን ቤተመቅደስ ማቋቋም ለምን
አስፈለገው?
•ለእስራኤል ህዝብ ወንጌልን ሊያስተምርበት
•ሙሴ የቤተመቅደሱን ዲዛይን ከየት አመጣው?
በዕብ 8፡1, 2 ላይ
“በሰማያት በግርማው
ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ
እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት
አለን፤እርሱም
የመቅደስና
የእውነተኛይቱ ድንኳን
አገልጋይ ነው፥ እርስዋም
በሰው ሳይሆን በጌታ
•ጳውሎስ በዕብ 8፡1, 2 በሰማይ ቤተመቅደስ እንዳለ ይናገራል
•ምድራዊ ቤተመቅደስም የሰማይ ቤተመቅደስ ግልባጭ ነበረች
•እግዚአብሔር ሙሴን በተራራ ላይ ባሳየው ምሳሌ እንዲሰራ
በመደጋገም አስጠንቅቆት እንነደነበር ሙሴ ራሱ ይናገራል (ዘጽ 25፡
40; 26፡ 30; 27፡ 8)
•እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ዘመን የድነትን እቅድ
ያስተማረበትና ወንጌል በብሉይ ኪዳን ዘመን የተሰበከበት
የቤተመቅደሱ አገልግሉት ነበር
•በመሆኑም የቤተመቅደሱን አገልግሎት ማጥናት ስለድነታችን
የበለጠ እንድናውቅ ይረዳናል
•በመዝመር 77፡ 13 ላይ “አቤቱ፥ መንገድህ በመቅደስ ውስጥ
ነው እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?” ይላል።
•ከዚህ የምንረዳው፡ የቤተመቅደሱ አገልግሎት ክርስቶስ
በድነት ዕቅድ ውስጥ የሚሰራው ሥራ ምሳሌ መሆኑን ነው
•የጥንቱን ቤተመቅደስ ስናጠና አራት
መሰረታዊ ነገሮችን በጥልቀት ማጥናት እጅግ
አስፈላጊ ነው፡፡ እነርሱም፡-
1ኛ) ስለ ቤተመቅደሱ አሰራር
የቤተመቅደሱን አሰራር ስንመለከት ሁለት
ክፍል ያለው ሆኖ ዙሪያውን በአጥር የተከበበ
አደባባይ ነበረው
•ወደ አደባባዩም ይሁን ወደ ቤተመቅደሱ መግቢያ በር
አንድ ብቻ ነበር፡፡
•ይህም ወደ እግዚአብሔር መንሥት መግቢያ መንገዱ
አንድ ብቻ እርሱም ክርስቶስ መሆኑን የሚያመለክት
ነው
ይህን በተመለከተ ክርስቶስ በዮሐ 10፡ 1, 7 ሲናገር “እውነት
እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ
መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው…ኢየሱስም
ደግሞ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች
በር ነኝ” ይላል
ቤተመቅደሱ ሁለት ክፍሎች ነበሩት
ቅዱስ ክፍል ቅዱስተ
ቅዱሳን
በቅዱስ ክፍል ውስጥ ካህናቶች በየዕለቱ
አገልግሎት የሚያካሂዱ ሲሆን በቅዱስተ ቅዱሳኑ
ግን በዓመት አንድ ጊዜ ሊቀ ካህኑ ብቻ አገልግሎት
ይሰጣል
2ኛ) ቤተመቅደሱ ውስጥ ያሉት ዕቃዎች
•ቤተመቅደሱ አደባባይ ላይ ሁለት እቃዎች አሉ
•i) መሰውያ ሲሆን በዚህ መሰውያ ላይ የሚቃጠል
መስዋዕት ዘወትር ጠዋትና ማታ ይቀርብበታል
ለሚቃጠል መስዋዕት የሚቀርበው እንስሳ
ከአካል ክፍሉ አንድም ሳይጎድል ሙሉ በሙሉ
በመሰውያው ላይ ይቃጠል ነበር
መስዋዕቱ የሚያመለክተው ክስቶስን ሲሆን ሙሉ በሙሉ
መቃጠሉ ደግሞ ክርስቶስ ስለኃጢያታችን ሁለንተናውን ሙሉ
በሙሉ እንደሰጠ፣ ከህይወቱ ያስቀረው ምንም ነገር እንደሌለ
ያመለክታል
በመሆኑም እኛም ለክርስቶስ ሁለንተናችንን ቀድሰን
መስጠት እንደሚያስፈልገንም የሚያመለክት ነው
•ችግሩ ግን ለክርስቶስ ያልሰጠናቸው በርካታ ነገሮች
አሉን፡፡
•አንዳንዶቻችን እጆቻችንን፣
•ሌሎቻችን አይኖቻችንን…
•ሌሎቻችን ምላሳችን
•ሌሎች እግሮቻችንን
•ሌሎቻችን ከናካቴው ልባችንን ቀድሰን ለክርስቶስ
አልሰጠንም
•ii) የመታጠቢያ ስሐን ነው (ዘጽ 30፡ 18)፡፡
•በስሃኑ ውስጥ ውኃ አለበት፡፡ ካህናቱ በየዕለቱ አገልግሎታቸውን
ከመጀመራቸው በፊት እጃቸውንና እግራቸውን ይታጠቡ ነበር
•ውኃው የኃጢያትን ቆሻሻ የሚያነጻው የክርስቶስ ደም ምሳሌ ነበር
ከአደባባዩ ወደ መቅደሱ ስንገባ
ቅድስ ክፍል ቅዱስተ
ቅዱሳን
መቅረዝ

የህብስት
ጠረጴዛ የዕጣን መሰውያ ታቦት
በቅዱሱ ክፍል ውስጥ ያሉ ሦስት ዕቃዎች
በቅዱስተ ቅዱሳን ውስጥ ደግሞ ታቦቱ ነበር
ከቤተመቅደስ ዕቃዎች የምንማራቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?
ራዕይ 8፡3 ሌላም
ሀ) የዕጣን መሰዊያ
መልአክ መጣና የወርቅ
ጥና ይዞ በመሰዊያው
አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም
ፊት ባለው በወርቅ
መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን
ሁሉ ጸሎት
እንዲጨምረው ብዙ
ዕጣን ተሰጠው።
ዮሐ 6፡ 35
ኢየሱስም እንዲህ
አላቸው፦ የሕይወት
እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ
እኔ የሚመጣ ከቶ
አይራብም በእኔ
የሚያምንም ሁልጊዜ ለ) የህብስት
ከቶ አይጠማም። ጠረጴዛ
ህዝ 3፡ 1-3 እርሱም፦ የሰው
ልጅ ሆይ፥ ያገኘኸውን ብላ
ይህን መጽሐፍ ብላ፥ ሄደህም
ለእስራኤል ቤት ተናገር አለኝ።
አፌንም ከፈትሁ መጽሐፉንም
አጐረሰኝ። እርሱም፦ የሰው ልጅ
ሆይ፥ አፍህ ይብላ፥ በምሰጥህም
በዚህ መጽሐፍ ሆድህን ሙላ
አለኝ። እኔም በላሁት፥ በአፌም
ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠ
ዮሐ 8፡ 12 ደግሞም
ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም
ሐ) መቅረዝ
ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ
የሕይወት ብርሃን
ይሆንለታል እንጂ በጨለማ
አይመላለስም ብሎ
ተናገራቸው።
•ማቴ 5፡ 14 እናንተ
የዓለም ብርሃን ናችሁ።
በተራራ ላይ ያለች ከተማ
ልትሰወር አይቻላትም።
ከላይ የጠቀስናቸው
ሦስቱ ማለትም ጸሎት፣
የጌታቃል ጥናትና
ምስክርነት ከክርስቶስ
ጋር ለሚኖረን
ግንኙነትና ለክርስትና
ህይወት እድገታችን፣
በአጠቃላይ ለድነታችን
ከፍተኛ አስተዋጽኦ
አላቸው
•እነዚህ ሦስቱ ዕቃዎችና
በእነሱ ላይ የሚካሄደው
አገልግሎት
የሚያመለክተው አንድ
ክርስቲያን እንዴት የቅድስና
ህይወት መኖር እንደሚችል
ነው
•አንድ ሰው የቅድስና
ህይወት ለመኖር በየዕለቱ
መጸለይ፣ የጌታን ቃል
ማጥናትና ዕውነትን
እነዚህ ሦስቱ
ማለትም ጸሎት፣
የጌታቃል ጥናትና
ምስክርነት ምን
ያክል አስፈላጊ
እንደሆኑ ከጌታ ቃል
አንጻር መመልከቱ
እጅግ አስፈላጊ ነው
•i) ጸሎት ማለት ምን
ማለት ነው ?
•ጸሎት ከእግዚአብሔር
ጋር ቃል በቃል መነጋገር
ማለት ነው
•ጸሎት ለክርስትና
ህይወት ምን ያክል
አስፈላጊ ነው?
•ጸሎት የክርስትና ህይወት
እስትንፋስ ነው ማለት ይቻላል
•ጸሎት የልባችንን መሻት
ለእግዚአብሔር
የምንገልጽበት መንገድ ነው
(ዳን 9፡ 1-19)
•ጸሎት የመንፈስ ቅዱስን
ኃይል የምንቀበልበት ቻናል
ነው (የሐ/ሥ 2፡ 1-4)
•ጸሎት የሰማይን ግምጃ ቤት
•አንዳንድ የግል የጸሎት
ልምምድን እንመልከት
•ንጉስ ዳዊት በመዝ 55፡
17 ስለ ግል የጸሎት
ልምምዱ ሲናገር እንዲህ
ይላል “በማታና በጥዋት
በቀትርም እናገራለሁ
እጮኽማለሁ፥ ቃሌንም
ይሰማኛል”
ዳን 6፡ 10 “ዳንኤልም
ጽሕፈቱ እንደ ተጻፈ ባወቀ
ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ
የእልፍኙም መስኮቶች ወደ
ኢየሩሳሌም አንጻር
ተከፍተው ነበር ቀድሞም
ያደርግ እንደ ነበረ በየዕለቱ
ሦስት ጊዜ በጕልበቱ
ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት
ጸለየ አመሰገነም”
•ስለ ግል ጸሎት ሲነሳ ታላቁ
ምሳሌ ጌታችንና
መድኃኒታችን ክርስቶስ
የሱስ ነው
•ማር 1፡ 35 “ማለዳም
ተነሥቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ
ወደ ምድረ በዳም ሄዶ
በዚያ ጸለየ”
•ማቴ 4፡ 2 “አርባ ቀንና
አርባ ሌሊትም ከጦመ
በኋላ ተራበ”
ማቴ 26፡ 39 “ጥቂትም
ወደ ፊት እልፍ ብሎ
በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ።
አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች
ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር
ግን አንተ እንደምትወድ
ይሁን እንጂ እኔ
እንደምወድ አይሁን
አለ”
ማቴ 26፡ 40-41 “ወደ
ደቀ መዛሙርቱም መጣ፤
ተኝተውም አገኛቸውና
ጴጥሮስን። እንዲሁም
ከእኔ ጋር አንዲት ሰዓት
እንኳ ልትተጉ
አልቻላችሁምን? ወደ
ፈተና እንዳትገቡ ትጉና
ጸልዩ፤ መንፈስስ
ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን
ደካማ ነው አለው”
•ውጤቱ ምን ሆነ?
•ማቴ 26፡ 73, 74 “ጥቂትም
ቈይተው በዚያ ቆመው የነበሩ
ቀርበው ጴጥሮስን። አነጋገርህ
ይገልጥሃልና በእውነት አንተ
ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ
አሉት። በዚያን ጊዜ።
ሰውየውን አላውቀውም ብሎ
ሊራገምና ሊምል ጀመረ።
ወዲያውም ዶሮ ጮኸ”
ii) ለአንድ ክርስቲያን የጌታቃል ጥናት
ምን ያክል አስፈላጊ ነው?
ህዝ 3: 1-3 “እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥
ያገኘኸውን ብላ ይህን መጽሐፍ ብላ፥
ሄደህም ለእስራኤል ቤት ተናገር አለኝ።
አፌንም ከፈትሁ መጽሐፉንም አጐረሰኝ።
እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ አፍህ ይብላ፥
በምሰጥህም በዚህ መጽሐፍ ሆድህን ሙላ
አለኝ። እኔም በላሁት፥ በአፌም ውስጥ
እንደ ማር ጣፈጠ”
•የእግዚአብሔር ቃል የምግብ
ያክል አስፈላጊያችን ነው?
•ስጋዊ ህይወታችን በየዕለቱ ስጋዊ
ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁል
በመንፈሳዊ ህይወታችን ጠንካራ
እንድንሆን መንፈሳዊ ምግብ
ያስፈልገናል
ወንጌላዊ ዶ/ር ሉቃስ በየሐ/ሥ 17፡
10, 11 ላይ ስለ ቤርያ ሰዎች ሲናገር
እንዲህ ይላል “ወዲያውም
ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን
በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥
በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ
ምኵራብ ገቡ፤ እነዚህም
በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ
ሰፊዎች ነበሩና። ነገሩ እንደዚሁ
ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት ወንጌላዊ ዶ/ር ሉቃስ
መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን
በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ”
ስንጸልይ እኛ
እንናገራለን
እግዚአብሔር
ያዳምጣል የጌታን ቃል
ስናጠና ደግሞ
እግዚአብሔር ለእኛ
ይናገራል እኛ
እናዳምጣለን
•iii) ክርስትና
ህይወታችን እያደገ
የሚሔድበት ሌላው
መንገድ ምስክርነት
ነው
•ወንጌልን ዕውነት
ለሌሎች ስናካፍል
ዕውቀታችን የበለጠ
እያደገና እየጠነከረ
መ) ታቦቱ የእግዚአብሔር በህዝቡ
መካከል የመገኘቱ ምሳሌ ነው
ዘጽ 33፡ 15, 16 “እርሱም፦
አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥
ከዚህ አታውጣን።በምድርም
ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ እኔና
ሕዝብህ የተለየን እንሆን
ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር
ካልወጣህ፥ እኔና ሕዝብህ
በአንተ ዘንድ ሞገስ
ማግኘታችን በምን
ይታወቃል? አለው”
1ኛ ሳሙ 4፡ 19-21
ምራቱም (የዔ)የፊንሐስ
ሚስት…እርስዋም
የእግዚአብሔር ታቦት ስለ
ተማረከች ስለአማትዋና
ስለ ባልዋም። ክብር
ከእስራኤል ለቀቀ ስትል
የሕፃኑን ስም። ኢካቦድ
ብላ ጠራችው።
3ኛ)
የመስዋዕ
ቱ አይነትና
የሚሰጠው
አገልግሎት
•በምድራዊ
በተመቅደስ የተለያዩ
አገልግሎቶች ይካሄዱ
የነበረ ሲሆን
የመስዋዕት
አገልግሎት አንዱና
ዋናው ነበር
•እነዚህ መስዋዕቶች
ደግሞ ይቀርቡ
የነበረው በግልና
በግል የሚቀርቡ
መስዋዕቶች
በማንኛውም ቀን
የሚቀርቡ ሲሆን በየቀኑ
ሰዎች መስዋዕት ይዘው
ወደ ቤተመቅደስ
ይመጡ ነበር። በማህበር
የሚቀርቡት ግን
በሰንበትና በብዓላት ቀን
ነበር
በግል የሚቀርብ መስዋዕትን
ስንመለከት ኃጢያተኛው
የመስዋዕት በግ ይዞ
ይመጣል፡፡ ከዚያም
በቤተመቅደሱ አደባባይ
በተረኛው ካህን ፊት እጁን
በበጉ ላይ ጭኖ ኃጢያቱን ሁሉ
ይናዘዝበታል፡፡ በዚህ ጊዜ
የሰውየው ኃጢያት ከግለሰቡ
ወደ እንስሳው ይተላለፍና
እንስሳው የግለሰቡን ኃጢያት
ይሸከማል
• በጉ የማን ምሳሌ ነው? ዮሐ 1፡ 29
•በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ
እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦
እነሆ የዓለምን ኃጢአት
የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ
•በጉ ያልሰራውን ኃጢያት
እንደተሸከመ ሁሉ ክርስቶስም
እርሱ ያልሰራውን የዓለምን ሁሉ
ኃጢያት ተሸከመ
•ኢሳ 53፡4 “በእውነት ደዌያችንን
ተቀበለ ሕመማችንንም
ተሸክሞአል”
•ኃጢያተኛው ኃጢያቱን
በበጉ ላይ እጁን ጭኖ
ከተናዘዘበትና ኃጢያቱን ወደ
በጉ ካስተላለፈ በኋላ በጉን
ያውደዋል ፡፡ በጉ
በኃጢያተኛው ምትክ
ይሞታል፡፡ ይህም ክርስቶስ
ለሰብዓዊ ዘር ምትክ ሆኖ
በመስቀል ላይ በመሞት እኛን
ከኃጢያት እርግማን
እንደሚዋጀን የሚያመለክት
ነበር
ይህን በተመለከተ ነብዩ
ኢሳያስ ሲናገር እንዲህ
ብሏል “እርሱ ግን ስለ
መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ
በደላችንም ደቀቀ
የደኅንነታችንም ተግሣጽ
በእርሱ ላይ ነበረ፥
በእርሱም ቍስል እኛ
ተፈወስን” (ኢሳ 53፡ 5)
ለመስዋዕት የሚቀርብ እንስሳ ሁሉ እንከን
የሌለው መሆን አለበት፡፡ ይህም ክርስቶስ
አንድም ኃጢያት የሌለበት አዳኝ መሆኑን
ያመለክታል
ዕብ 4፡ 15
ከኃጢአት በቀር
በነገር ሁሉ እንደ
እኛ የተፈተነ ነው
እንጂ፥ በድካማችን
ሊራራልን የማይችል
ሊቀ ካህናት የለንም
ክርስቶስ ሊቀካህናችን
•የጥንቱ የአይሁድ ቤተመቅደስ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን
ዘመን ስለ ወንጌል ያስተማረበት ምሳሌያዊ ስርዓት ነበር
•ስለቤተመቅደስ ስናጠና በዋናነት አራት ዋና ነገሮችን
በጥልቀት ማጥናት እንደሚያስፈልግ ተነጋግረናል
•1ኛ) የቤተመቅደሱ አሰራር
•2ኛ) የቤተመቅደሱ ዕቃዎች
•3ኛ) መስዋዕቶቹ
•4ኛ) የካህናቱ አገልግሎት
ቀጥለን ስለ ካህናት አገልግሎት
እናጠናለን
4ኛ)
ካህናቱና
አገልግሎ
ታቸው
አንድ ሰው ለሰራው ኃጢያት ይቅርታ ለማግኘት የእርሱ
መስዋዕት ማምጣት ብቻውን በቂ አይደለም፣ የካህናት
አገልግሎትም ያስፈልገዋል
አንድ ኃጢያተኛ የመስዋዕት በግ አምጥቶ እጁን በመጫን ኃጢያቱን
ሲናዘዝበት የእርሱ ኃጢያት ወደ እንስሳው ይተላለፋል፡፡ ንጹሁ
እንሰሳም እርሱ ያልሰራውን ኃጢያት ይሸከምና ይታረዳል
ካህኑ የእንሰሳውን ደም ይዞ ወደ ቅዱሱ ክፍል በመግባት በቤተመቅደሱ መጋረጃ
ላይ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፡፡ ካህኑ በሚያካሂደው አገልግሎትም የኃጢያተኛው
ኃጢያት ከእንስሳው ወደ ቤተመቅደሱ መጋረጃ ይተላለፋል (ዘሌ 4)
•ኃጢያትን የሚሸከመው መጋረጃ የምን ምሳሌ ነው፡፡
•ዕብ 10፡ 19, 20 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና
በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት
በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን
•በዚህ አይነት ሁኔታ ካህኑ በሚያካሂደው የማስታረቅ (የምልጃ)
አገልግሎት የኃጢያተኛው ኃጢያት ወደ ቤተመቅደሱ መጋረጃ
ይተላለፋል፡፡
•በዚህ ጊዜ ኃጢያተኛው የኃጢያት ይቅርታ ያገኛል
የምድራዊ ቤተመቅደስ አገልግሎት (በአደባባዩ፣ በቅዱሱና
በቅዱስተ ቅዱሳን የሚፈጸሙት ሥነ-ስርአቶች) በድነት ዕቅድ
ውስጥ የክርስቶስን ሦስት አገልግሎት ክፍፈሎች (Phases)
የሚያመለክት ነበር፡፡ እነርሱም፡-
(1ኛ) የክርስቶስን
ምትክ መስዋዕትነት
(Substitutionary
Sacrifice)
(2ኛ) የክርስቶስን
የካህንነት--የማማለድ
ሥራ (Priestly
Meditation) እና
(3ኛ) የክርስቶስን የፍርድ ሥራ (The Final Judgment)
•ምትክ መስዋዕትነት
(Substitutionary
Sacrifice) ሁለት ዋና
ነገሮችን ያስተምረናል
•(1ኛ)ለኃጢያት ይቅርታ
የየሱስ መሞት አስፈላጊ
መሆኑን
•(2ኛ) ደም ሳይፈስ
ስረየት አለመኖሩን ያሳያል
•የካህንነት የማማለድ
ሥራ (Priestly
Meditation)ደግሞ
ሁለት ዋና ነገሮችን
ያስተምረናል
•1ኛ) በኃጢያተኛው
ሰብዓዊ ፍጥረትና በቅዱሱ
አምላክ መካከል
የማስታረቅ ሚና አስፈላጊ
•2ኛ) የኃጢያት ጉዳይ ምን
ያክል ጥብቅ እንደሆነና
ቅዱሱን አምላክና
ኃጢያተኛውን ስብአዊ
ፍጥረት ምን ያክል
እንዳለያያቸው
ያመለክታል።
•የማማለድ (የማስታረቅ)
ስራ የሚፈጸመው በደም
ነበር
•ካህኑ በቅዱሱ ክፍል
የሚፈጽመው ተግባር
አራት ነገሮችን ያካትታል
•(1ኛ) ማማለድ
(Intercession)
•(2ኛ) ይቅርታ
(Forgiveness)
•(3ኛ) ማስታረቅ
(Reconcilation)
•(4ኛ) ወደ ነበረበት
መመለስ
(Restoration)
ናቸው።
•የካህኑ አገልግሎት
ኃጢያተኛው
በማንኛውም ጊዜ ወደ
እግዚአብሄር ለመቅረብ
የማያቋርጥ ዕድል
(Access) እንዲያገኝ
•ታዲያ በአዲስ ኪዳን ዘመን ምድራዊ ቤተመቅደስ፣ የእንስሳት
መስዋዕትና ሰብዓዊ ካህን ያስፈልገናል ወይ?
•በዕብ 7፡ 11-28 ላይ በአዲስ ኪዳን ዘመን ምድራዊ ቤተመቅደስ፣
የእንስሳ መስዋዕትና ሰብዓዊ ካህን እንደማያስፈልጉን በግልጽ
ይናገራል
ማቴ 27፡ 50, 51
ኢየሱስም ሁለተኛ
በታላቅ ድምፅ ጮኾ
ነፍሱን ተወ። እነሆም፥
የቤተ መቅደስ መጋረጃ
ከላይ እስከ ታች ከሁለት
ተቀደደ፥ ምድርም
ተናወጠች፥ ዓለቶችም
ተሰነጠቁ
ክርስቶስ በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ የቤተመቅደሱ መጋረጃ
መቀደዱ የምድራዊ ቤተመቅደስ አገልግሎት ማብቃቱንና ወደ
አዲስና የበለጠ ሥነ-ስርዓት መሸጋገርችንን ያመለክታል
ዕብ 7፡ 11-19 “ህዝቡ በሌዊ ክህነት የተመሠረተን ሕግ
ተቀብለዋልና፣ በዚያ ክህነት ፍጹምነት የተገኘ ቢሆን፥ እንደ
አሮን ሹመት የማይቈጠር፥ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ግን
የሆነ ሌላ ካህን ሊነሳ ወደፊት ስለ ምን ያስፈልጋል?
ክህነቱ ሲለወጥ፥ ሕጉ ደግሞ ሊለወጥ የግድ ነውና። ይህ ነገር
የተነገረለት እርሱ በሌላ ወገን ተካፍሎአልና፥ ከዚያም መሠዊያውን
ያገለገለ ማንም የለም፤ ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የተገለጠ
ነውና፥ ስለዚህም ነገድ ሙሴ ምንም እንኳ ስለ ክህነት አልተናገረም
በማያልፍም ሕይወት ኃይል እንጂ በሥጋ ትእዛዝ ሕግ ሳይሆን ሌላ
ካህን በመልከ ጼዴቅ ምሳሌ ቢነሳ፥ ይህ እጅግ አብልጦ የሚገለጥ ነው።
አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ
ይመሰክራልና። ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፥ ስለዚህም
የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች፥
ወደ እግዚአብሔርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ገብቶአል
መስዋዕቱን በተመለከተ በ1ኛ ጴጥ 1፡ 18, 19 ከአባቶቻችሁ
ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ
ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ
ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ
ክህነቱን በተመለከተ በዕብ 7፡ 22-25 “እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ
ሆኖአል። እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ
ናቸው፤ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ስለ
እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ
እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል
1ኛ ጢሞ 2፡ 5 “አንድ
እግዚአብሔር አለና፥
በእግዚአብሔርና
በሰውም መካከል
ያለው መካከለኛው
ደግሞ አንድ አለ፥
እርሱም ሰው የሆነ
ክርስቶስ ኢየሱስ ነው”
መካከለኛው ክርስቶስ
1ኛ ዮሐ 2፡ 1 ልጆቼ
ሆይ፥ ኃጢአትን
እንዳታደርጉ ይህን
እጽፍላችኋለሁ።
ማንም ኃጢአትን
ቢያደርግ ከአብ ዘንድ
ጠበቃ (አማላጅ) አለን
እርሱም ጻድቅ የሆነ
ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
ስለዚህ ሊቀካህናችን (አማላጃችን) ክርስቶስ ብቻ ነው
•ክርስቶስ በሰማያዊ
ቤተመቅደስ የማማለድን
ሥራ የጀመረው ወደ
ሰማይ ካረገ በኋላ
በጴንጤቆስጤ ቀን ነበር።
•በዳንኤል 8፡ 14 ትንቢት
መሰረት ይህ አገልግሎት
እስከ 1844 ድረስ
ተካሂዷል
•በምድራዊ ቤተመቅደስ ኃጢያትን በተመለከተ በዋናነት ሁለት አይነት
አገልግሎቶች ይካሄዱ ነበር (1ኛ) የዕለትና (2ኛ) የዓመት
•በየዕለቱ የሚካሄደው አገልግሎት የሚከናወነው በቅዱሱ ክፍል ሲሆን
በየአመቱ የሚካሄደው ደግሞ በቅዱስተ ቅዱሳን ውስጥ ነበር
•የየእለቱ አገልግሎት የኃጢያት ይቅርታን የሚያስገኝ
ሲሆን የዓመቱ አገልግሎት ደግሞ ኃጢያትን ስረየት
ሥራ (ኃጢያትን የማስወገድ ሥራ) ነበር።
•ኃጢያት የሚወገደው በፍርድ ነው
•ኃጢያትን የማስወገድና የማንጻት ስራ እንዴት ነበር
የሚከናወነው?
•ለዚህ ተግባር ሁለት ፍየሎች ያስልጉ ነበር፣ አንደኛው
ለእግዚአብሔር፣ ሌላኛው የሚለቀቅ (አዛዜል)
ሊቀ ካህኑ የመስዋዕቱን
የእግዚአብሄርን ፍየል
ደም ይዞ ወደ ቅዱስተ
ቅዱሳን በመግባት
የእግዚአብሄርን ህግ
በያዘው በታቦቱ ላይ
ባለው የስረየቱ መክደኛ
ላይ ደሙን ሰባት ጊዜ
ይለጫል
•ሊቀ ካህኑ በዚህ ድርጊቱ
የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ
ህግ ጥያቄ ያሟላል።
•የህጉ ጥያቄ ምንድን
ነው?
•“ኃጢያት የምትሰራ ነፍስ
እርሷ ትሞታለች” (ህዝ
18፡ 4)፤ “የኃጢያት
ዋጋው ሞት ነው” (ሮሜ 6፡
ወደ ቅዱሱ ክፍል ይመለስና
የዕጣን መሰውያውን፣
መቅረዙንና የህብስት
ጠረጴዛውን በያዘው
የእግዚአብሔር ፍየል ደም
ይቀድሳቸዋል፡፡ ወደ
አደባባዩም በመውጣት
የሚቃጠል መስዋዕት
የሚቀርብበትን መሰወያ
ይቀድሳል (ዘሌ 16፡20ን
ከ16፡ 16-18 አነጻጽር)
ሊቀ ካህኑ ከቅድስተ ቅዱሳኑ
ሲወጣ በዓመቱ ጊዜ ውስጥ
ለኃጢያታቸው መስዋዕት
አቅርበው በካህኑ የማማለድ
ሥራ በመስዋዕቱ በግ ደም
አማካኝነት ኃጢያታቸው
ወደ ቤተመቅደሱ
የተላለፈላቸውን ሰዎች
ኃጢያት ይዞ ይወጣና
አዛዜል በሚባለው ፍየል ላይ
ይጭንበታል
በዚህ ጊዜ እነዚያ
አስቀድመው በዓመቱ
ውስጥ ለኃጢያታቸው
መስዋዕት አቅርበው በካህኑ
የማማለድ ሥራ በመስዋዕቱ
በግ ደም አማካኝነት
ኃጢያታቸው ወደ
ቤተመቅደሱ
የተላለፈላቸው
ኃጢያታቸው በሊቀ ካህኑ
አማካኝነት ከቤተመቅደሱ
የሰይጣን ምሳሌ ወደ ሆነው
ወደ አዛዜል ይተላለፍላቸውና
የኃጢያት ስረየትን
(መደምሰስን) ሲያገኙ፣
ኃጢያታቸውን ያልተናዘዙትና
ለኃጢያታቸው ምትክ የሚሆን
የዕንስሳ መስዋዕት ያላቀረቡት
ግን ከህዝቡ ተለይተው
ይጠፋሉ
የታረደውና በደሙ
ቤተመቅደሱ፣ የቤተመቅደሱ
ዕቃዎችና ህዝቡ
የተቀደሱበት ፍየል
የክርስቶስ ምሳሌ ሲሆን
ያልታረደውና ከቤተመቅደሱ
የወጣውን የሰዎች ኃጢያት
የተሸከመው አዛዜል
የተባለው ፍየል የሰይጣን
ምሳሌ ነው
ሰዎች ለተናዘዙባቸው
ኃጢያቶች ሁሉ
ሰይጣን ተጠያቂ
ይሆናል፣ ለነዚያ
ኃጢያቶች ሁሉ
ሰይጣን ይቀጣል
አሁን ታላቁ ሊቀ
ካህናችን ክርስቶስ በድነት
እቅድ የመጨረሻ
የሆነውን የፍርድ
ምርመራን ስራ በማከናወን
ላይ ይገኛል በቅርቡም
እርኩሱም ይርከስ
ጻዲቁም ለዘላለም ይጽደቅ
ብሎ ነገሮችን ወደፍጻሜ
ለማምጣት በዝግጅት ላይ
• ብዙ ክርስቲያኖች አዛዜል የክርስቶስ ምሳሌ ነው ይላሉ።
ይህ ሃሳብ ስህተት ነው። አዛዜል የሰይጣን ምሳሌ
መሆኑን የምናውቅባቸው ሦስት ምክኒያቶች አሉ (1)
አዛዜል ባለመታረዱ የሃጢያት ይቅርታን ሊያመጣ
አይችልም “ደም ሳይፈስ ስረየት የለም” (ዕብ 9፡ 22)
(2) መቅደሱ ሙሉ በሙሉ የነጻው በእግዚአብሄር ፍየል
ነው (3) ዘሌ 16፡ 8 ላይ “ አንድ ለእግዚአብሄር
ሌላኛው ለሚለቀቅ” በማለት የሚለቀቀው ፍየል
የእግዚአብሄር አለመሆኑንና እንዲያውም የእግዚአብሄር
ፍየል ተቃራኒ መሆኑን ያመለክታል
• በስረየት ቀን በአዛዜል ፍየል ላይ
የሚደረገው ሥነ-ስርዓት ከቀራንዮ ያለፈና
የኃጢያትን ችግር ወደ ፍጻሜ ለማምጣት
የሚደረገውን ሥነ-ስእዓት ማለትም
የሰይጣንንና የኃጢያትን ለዘላለም
መጥፋት የሚያመለክት ነው። የኃጢያት
ተጠያቂነት ጀማሪና አስፋፊ በሆነው
• በስረየት ቀን ኃጢያታቸውን አስቀድመው
ያልተናዘዙና መስዋዕት ያላቀረቡ ኃጥያተኞች
ኃጢያታቸው በእነርሱ ላይ ይሆንና በኃጢያተቸው
ምክኒያት ይጠፋሉ። ይህም የፍርድ ነው። ይህ
የሚያስረዳን በቅዱስተ ቅዱሳን ውስጥ የሚካሄደር
የማስተስረይና የፍርድ ሥራ መሆኑን ነው።
ኃጥያታቸውን የተናዘዙ ኃጢያታቸው ይሰረዝላቸዋል
ኃጢያታቸውን ያልተናዘዙ የኃጢያትን ዋጋ ይቀበላሉ።
• የፍርድ ሥራ በድኅነት እቅድ ውስጥ የመጨረሻው
ሥራ ነው
• ክርስቶስ ፍርድ የሚሰጠው መቼ ነው?
• “በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም
ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም
ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል
ሲበር አየሁ፤ በታላቅ ድምፅም። የፍርዱ ሰዓት
ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤
ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም
ምንጮች ለሠራው ስገዱለት አለ” (ራዕይ 14፡ 6,
7)።
• “ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን
አየሁ፥ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ ስፍራም
አልተገኘላቸውም። ሙታንንም ታናናሾችንና
ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፥ መጻሕፍትም
ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት
መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ
ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ። ባሕርም በእርሱ
ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፥ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ
ዘንድ ያሉትን ሙታን ሰጡ፥ እያንዳንዱም እንደ
ሥራው መጠን ተከፈለ” (ራዕይ 20፡ 11-13)።
• የጌታ ቃል ክርስቶስ የመጨረሻውን ፍርድ
ለመስጠት መዛግብት በፊቱ እንደቀረቡለት
ይነግረናል። የቤተመቅደሱ የስረየት ቀን አገልግሎት
የመጨረሻው ፍርድ (Final Judgment) ሦስት
ክፍል እንዳለው ይነግረናል (1) ከሺው ዓመት
መጀመር በፊት የሚሰጠው ፍርድ--Premillenial
Judgment ወይም የፍርድ ምርመራ--
Investigative Judgment ከዳግም ምጻት በፊት
የሚካሄድ ፍርድ--Pre-Advent Judgment
• (2) የሺው ዓመት ፍርድ--Millenial Judgment
(3) የመጨረሻው ፍርድ--Excutive Judgment
• የኃጢያት ከቤተመቅደስ መወገድ የፍርድ ምርመራን
ያመለክታል። የስረየት ቀን ሥነ-ስርዓት ኑዛዜ
የተደረገባቸውን ኃጢያቶች ብቻ ከቤተመቅደስ
እንደሚያነጻ ሁሉ የፍርድ ምርመራ የሚያተኩረው
ስማቸው በህይወት መጽሃፍ የተጻፉትን ብቻ ነው።
ሃሰተኛ ክርስቲያኖች በምርመራው ተበጥረው
ይወጣሉ፡ የእውነተኛ ክርስቲያኖች ኃጢያት ደግሞ
ከመዝገብ ይፋቃል
• የአዛዜል ወደ ምድረበዳ መለቀቅ የሰይጣንን ለሺ
ዓመት በዚች በክርስቶስ ዳግም ምጻት ጊዜ
በምትፈራርሰው ዓለም መታሰርና (ራዕይ 20፡4; 1ኛ
ቆሮ 6፡ 1-3) ቅዱሳን በሰማይ የኃጢያተኞችን ፍርድ
መመርመር የሚያመለክት ነው። ይህም የሺው ዓመት
ፍርድ--Millenial Judgment ይባላል። የሺው
ዓመት ፍርድ ቅዱሳን እግዚአብሄር በኃጢያትና
በጠፉት ኃጢያተኞ ላይ የሰጠውን ብይን የበለጠ
እንዲያስተውሉትና ስለጠፉት ወገኖቻቸው
የሚያነሱትን ማንኛውም ጥያቄ ለመመለስ ይረዳቸዋል
• የህዝቡና የካምፑ ከኃጢያት መንጻት ሦስተኛውንና
የመጨረሻው ፍርድ--Excutive Judgment
የሚያመለክት ነው። ከሰማይ የሚወርደው እሳት
ኃጢያተኞችን ካጠፋ በኋላ ምድርን ያነጻታል (ራዕይ
20፡ 11-15; ማቴ 25፡31-46; 2ኛ ጴጥ 3፡7-13)
• የምድራዊ ቤተመቅደስ መንጻት እንዳስፈለገው ሁሉ
የሰማይ ቤተመቅደስም መንጻት ያስፈልገዋል
ምክኒያቱም የኃጢያት ሬኮርድ በዚያ አለ። ያ
የሃጢያት ሬኮርድ ለዘላለም የሚወገደው ደግሞ
ክርስቶስ በሚያካሂደው የፍርድ ምርመራ ነው።
• ዳንኤል 8፡ 14 እንደሚነግረን የሰማይ ቤተመቅደስ
የሚነጻው በ2300 ዓመት ትንቢት ፍጻሜ ላይ ነው።
ይህ ትንቢት የሚጀምረው እየሩሳሌምን ለመጠገን
ዓዋጅ ከሚወጣበት ጊዜ ጀምሮ ነው (ዳን 9፡ 25)
• እየሩሳሌምን ለመጠገን አዋጁ የወጣው በ457
ከክ/በፊት ነበር። በዚህ መሰረት የ2300ዓመት
ትንቢት የተፈጸመው በ1844 ነው። ከ1844 ጀምሮ
ክርስቶስ የፍርድ ምርመራ ሥራ በመስራትላይ ነው
• ክርስቶስ ከ1844 ጀምሮ በሰማያዊ ቤተመቅደስ
የድህንነት የመጨረሻ ሥራ የሆነውን የፍርድ
ምርመራ ሥራ በመስራት ላይ ነው። በቅርብ ቀን
“ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኵሱም ወደ ፊት
ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥
ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ” በማለት ሥራውን
ያጠናቅቃል። በዚህ ጊዜ እግዚአብሄር ለሰብዓዊ
ፍጥረት የሰጠው ረዥም የምህረት ጊዜ ያበቃና
ክርስቶስ ዳግም ይመጣል።
የዘመናት ምኞት
የዘመናት ምኞት
• የሱስን ፊት ለፊ ማየት! ከምናስበውና ከምንገምተው
በላይ ከሚወደን ወዳጃችን ጋር ለዘላለም አንድ መሆን!
ይህ ሁሉ የምናየው የምንሰማውና በራሳችንም ላይ
እየደረሰ የሚያሰቃየን የምድር መከራ መፈጸም! ዛሬ
በእንቅልፍ ከተለዩን በጣም ከምንወዳቸው ወዳጆቻችን
ጋራ ለዘላለም መደሰት! ክርስቶስ ካረገበት ጊዜ ጀምሮ
ቅዱሳን ሲናፍቁት የነበረ ያለና ወደፊትም የሚኖር ነገር
ግን አንድ ቀን ክርስቶስ “ተፈጽሞአል”(ራዕይ 16፡
17)የሚል ድምጽ በሚያሰማበት ጊዜ መላውን ዩኒቨርስ
በታላቅ ደስታ የሚያጥለቀልቅ አስደናቂ ክስተት ይሆናል
• ክርስቶስ ወደ ሰማይ ካረገ ሁለት ሺ ዘመናት
ከመቆጠራቸው አንጻር፤ መከራ ስቃይና ውጥረት
የሰብአዊ ፍጥረትን ነፍስ ከማስጨነቃቸው አንጻር፤
ክርስቶስ ይህን ሁሉ የሰው ልጆች ስቃይ
እየተመለከተ ሁለት ሺ ዘመናትን በዝምታ
ከመመልከቱ አንጻር ሰዎች ስለክርስቶስ ዳግም
መምጣት እንዴት እርግጠኛ መሆን ይችላሉ?
• እርግጠኛ መሆን የምንችልባቸው በርካታ ነገሮች
ቢኖሩም ዋና ዋናዎቹ ግን ሦስት ናቸው
1ኛ) የመጀመሪያው
ምጻትና

በመስቀል ላይ መሞት
• የክርስቶስ የመጀመሪያው ምጻትና ዳግም ምጻቱ
የተሳሰሩ ናቸው። ከርስቶስ ከሁለት ሺ ዓመታት
በፊት ወደዚች ምድር መጥቶ በኃጢያትና
በሰይጣን ላይ ወሳኝ ድል ባይቀዳጅ ኑሮ(ቆላ 2፡
15) በፍጻሜ ዘመን የሰይጣንን የዚች ዓለም
ገዥነት ሥልጣን አጥፍቶ ከመጀመሪያ
የነበረውን ፍጽምና ለመመለስ ዳግም ይመጣል
ብለን ለማመን ምንም ምክኒያት አይኖረንም
• ነገር ግን ክርስቶስ “በዓለም ፍጻሜ ራሱን
በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ”
ለመገለጡ ከበቂ በላይ መረጃ ስላለን
“ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ
ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል” (ዕብ
9፡ 26, 28) ብለን በዚህ ዘመን ለማመን
በቂ ምክኒያት አለን።
2ኛ) በእግዚአብሄር ቃል የሰጠው ማረጋገጫ

2) በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ
የተሰጠ ማረጋገጫ
• ዕብ 10: 37
• ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው፥ ሊመጣ ያለውም
ይመጣል አይዘገይምም
• ራዕይ 22፡ 12-13
• እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም
እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ
ጋር አለ። አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥
መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
• ዮሐ 14፡ 1-3
• ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥
በእኔም ደግሞ እመኑ። በአባቴ ቤት ብዙ
መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ
ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤
ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት
እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ
ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።
• ዕብ 9: 26-28
እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ
መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን
በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር
አንድ ጊዜ ተገልጦአል። ለሰዎችም አንድ ጊዜ
መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ
ተመደበባቸው፥ እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥
የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ
በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት
• 1ኛ ቆሮ 15፡ 51-55
• እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን
አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን
በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና
ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም
እንለወጣለን። ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን
ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ
ይገባዋልና። ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን
ሲለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥
በዚያን ጊዜ። ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው
• 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡ 15-17
• ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ
ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ
ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው
ይነሣሉ፤ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን
የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ
ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ
ከጌታ ጋር እንሆናለን።
ሐ) ክርስቶስ በሰማያዊ ቤተመቅደስ የሚሰጠው
አገልግሎት
• በሰማይ ያለው ቤተመቀደስ በድነት ዕቅድ
ማዕከል መሆኑን የራዕይ መጽሐፍ በሰፊው
ያብራራል (ራዕይ 1፡ 12, 13; 3: 12; 4: 1-5;
5: 8; 7: 15; 8: 3; 11: 1, 19; 14: 15, 17;
15: 5, 6, 8; 16; 1, 17)
• የራዕይ ትንቢቶች ክርስቶስ በድነት ሥራ ውስጥ
የመጨረሻውን ክፍል በመስራት ላይ መሆኑን
ያረጋግጣሉ። ይህም የክርስቶስን ዳግም ምጻት
ለሚጠባበቁ ሁሉ ታላቅ ዋስትና ነው
• ክርስቶስ የሚመጣበትን ቀን ማወቅ ይቻላል ወይ?
• ማቴ 24፡ 36
• ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር
የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ
የለም።
• እግዚአብሄር ክርስቶስ የሚመጣበትን ቀን ባይነግረንም
ክርስቶስ ከመምጣቱ በሚት የሚፈጸሙትን ምልክቶች
በዝርዝር ነግሮናል። ስለዚህ እንደክርስቲያን እነዚህን
ምልክቶች በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል
• የክርስቶስ ዳግም ምጻት ምልክቶች በሦስት
ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈሉ ናቸው (1)
በተፈጥሮው ዓለም--Natural World
የሚፈጸሙ ምልክቶች (2) በፖለቲው
ዓለም--Political World የሚፈጸሙ
ምልክቶች (3) በሐይማኖቱ ዓለም--
Religious World የሚፈጸሙ ምልክቶች
ናቸው
• በተፈጥሮው ዓለም--Natural World
የሚፈጸሙት ምልክቶች ምንድን ናቸው?
• (1) የምድር መናወጥ (ማቴ 24፡ 7)
• እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ህዳር 1 ቀን
1755 ዓ. ም በፖርቹጋል ዋና ከተማ ሊዝቦን ላይ
የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ በአውሮፓ
በአፍሪካና በአሜሪካ ክፍለ አህጉራት ላይ ጉዳት
ያደረሰ የመጀመሪያው የምድር ነውጥ ነበር
• የምድር መናወጥ አሁን ባለንበት ዘመን የየዕለት ክስተት
እየሆነ መጥቷል። ለአብነት ያክል ከ273,000 በላይ
ህዝብ የፈጀው ሱናሚንና በቅርቡ ከ350,000 በላይ
ህዝብ ፈጅቷል የሚባለውን የሄይቲን የመሬት መንቀጥቀጥ
መጥቀሱ ብቻ ይበቃል። ከመስከረም 17 እስከ
መስከረም 23, 2002 ዓ.ም ባሉት ሰባት ቀናት ብቻ 196
የ መሬት መንቀጥቃጦች በዓለም ተመዝግቧል። ከነዚህ
መካከል አፍሪካ 2፡ ኤዥያ 24፡ አውስትራሊያ 17፡
አውሮፓ 1፡ ሰሜን አሜሪካ 121፡ ደቡብ አሜሪካ 35፡
እና ደቡብ ፓስፊክ 20 የመሬት መንቀጥቀጦችን
• (2) የጸሐይ መጨለምና የጨረቃ ወደ ደምመለወጥ
(ማቴዎስ 24:29; ኢዩ 2:31)
• ግንቦት 19, 1780 የሰሜናዊ አሜሪካ ሰሜናዊ ክፍል
ከዚያ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ
ተውጦ ነበር
• (3) የክዋክብት መውደቅ (ራዕይ 6፡ 13 ማቴ 24፡
29) በህዳር 13 ቀን 1833 ዓ. ም በታሪክ እጅግ ብዙ
ክዋክብት የወደቁበት ቀን ነበር። በዕለቱ ከ60,00
በላይ ክዋክብት እንደበረዶ እንደዘነቡ የታሪክ
መዛግብት ያመለክታሉ
• በፖለቲው ዓለም--Political World
የሚፈጸሙ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
• (1) ጦርነት (ማቴ 24፡ 6)
• (ሀ) መንግስት በመንግስት ላይ ይነሳሉ፦ ይህ
በተለያዩ በሁለት መንግስታት መካከል በፖለቲካ
ወይም በኢኮኖሚ ጥቅም ምክኒያት የሚነሳ
ግጭት ነው። ዛሬ በዓለማችን በብዙ ቦታ ጦርነት
ይካሄዳል፤ ለምሳሌ፡ በአሜሪካንና በኢራቅ፡
በህንድና ፓኪስታን....
• (ለ) ህዝብ በህዝብ ላይ፦ ይህ በአንድ አገር ውስጥ
በፖለቲካ ወይም በጎሳ ምክኒያት የሚነሱ
እልቂቶች ናቸው።
• ከእርስ በርስ ጦርነቶች መካከል 1994/1986
በሩዋንዳ የተካሄደው እልቂት የማይረሳ ነው።
ሁለቱ ጎሳዎች (ሁቱና ቱትሲ)ባካሄዱት ጦርነት
ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች አልቀዋል
• ዛሬ በብዙ አገሮች የእርስ በርስ ጦርነት እየተካሄደ
ይገኛል
• በሐይማኖቱ ዓለም--Religious World የሚፈጸሙ
ምልክቶች ምንድን ናቸው?
• (1) የወንጌል ለዓለም መዳረስ
• ማቴ 24፡ 14
• ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል
በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።
• በአሁኑ ጊዜ ወንጌል በሳተላይትና በሬድዮ በመላው ዓለም
በመሰራጨት ከመሆኑም በላይ መጽሐፍ ቅዱስ በትናንሽ
ቋንቋዎች እንኳን ሳይቀር እየተተረጎመ በመሰራጨት ላይ
ይገኛል።
• (2) በመካከለኛው ክ/ዘ ለ1260 ዓመታት
የሐይማኖትና የፖለቲካ ሥልጣንን ደርቦ ይዞ
የነበረውና (ዳን 7፡ 24, 12; ራዕይ 12፡ 6, 14)
ለተወሰነ ጊዜ ሥልጣኑን አጥቶ የነበረው የጳጳሳዊ
አስተዳደር እንደገና ማንሰራራት(ራዕይ 13፡ 3)
• የሮም ካቶሊካዊት ቤ/ክ ዛሬ የዓለማችንን የፖለቲካ
አቅጣጫ ከመጋረጃ በስተጀርባ በማሽከርከር ላይ
ትገኛለች። ፕሮቴስታንት አሜሪካ እንኳን ሳትቀር
እጇን ለካቶሊክ መስጠቷ የአደባባይ ምስጢር ከሆነ
ቆይቷል
• (3) የሐይማኖት ህብረት(ራዕይ 16፡ 12-16)
• የሐይማኖት ህብረት(ኤክዩሜኒዝም)፦ ዛሬ በዓለማችን
እየተስተጋባ ያለ አንድ ነገር አለ እሱም “The New
World Order--አዲሱ የዓለም ስርአት ” መመባል
ይታወቃል። የዚህ ስርዓት ዋና ሰላምን በዓለም ላይ
በማስፈን ዓለማችንን ለሰው ልጆች ምቹ የመኖሪያ
ቦታ እንድት ሆን ማድረግ ነው ይባላል። ይህ ሊሆን
የሚችለው ደግሞ ዓለም አንድ ወጥ የፖለቲካ
የኢኮኖሚና የሃይማኖት ስርአት ሲኖራት ነው ተብሎ
ይታመናል
• ታዲያ እነዚህ የአዲሱ የዓለም ስርዓት አራማጆች
ለሃይማኖት አንድነት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተዋል ለምን
ቢባል በታሪክ ከዚህ በፊት በሃይማኖት ምክኒያት
የተነሱ ጦርነቶች በፖለቲካም ይሁን በኢኮኖሚ ጥቅም
ምክኒያት ከተነሱት ጦርነቶች የበለጠ ረዥም ጊዜ
ወስደዋል የበለጠ ጉዳትም አድርሰዋል። እንደምሳሌም
የመስቀል ጦርነትን መውሰድ ይቻላል። ይህ
በክርስቲያኖችና በሙስሊሞች መካከል የተካሄደው
ጦርነት ለ196 ዓመታት (1095-1291) ተካሂዷል።
• የአንድነቱ ዋና አላማ ወይም ግብ በአለም ላይ አንድ
እምነት ብቻ ለመመስረት ነው። መነሻ
ምክኒያታቸውም የክርስቶስ ጸሎት (ዮሐ 17፡20-22)
እና የጳውሎስ ማሳሰቢያ (ኤፌ 4፡1-4) ናቸው።
• የሃዋ/ሥ 15 እንደሚነግረን በየሩሳሌም የሃዋርያት
ጉባኤ የሚባል ነበር። ይህ ጉባኤ የተቋቋመው አዲሷን
የሃዋርያት ቤተ/ክ ለመምራት ሲሆን የዶክትሪን
አንድነቷንም የመጠበቅ ሃላፊነት ነበረው።
• በመሆኑም በ1910 በኤደንብራ ዓለም አቀፍ የወንጌል
ተልዕኮ ኮንፍራንስ--World Missionary
Conferance--ተዘጋጀ።
• በ1948 ደግሞ ከ147 አለም አቀፍ የፕሮቴስታንት
አብያተክርስቲያናት የተውጣጡ 351 ተወካዮች በሆላንዷ
መዲና በአምስተርዳም ተሰብስበው “የዓለም
አብያተክርስቲያናት ህብረትን” መሰረቱ።
• የህብረቱ ዓላማ በኃይማኖቶች መካከል መቻቻልና
መከባበር እንዲኖር ለማድረግ ነው ቢባልም ዋና ተልዕኮው
ግን ዓለምን ወደ ካቶሊክ መዳፍ መውሰድና ጳጳሳዊ
አስተዳደርን እንደገና ለመመለስ ነው
• ክርስቶስ የሚመጣው በምን አይነት ሁኔታ ነው?
• ይህን በተመለከተ ሁለት አይነት አመለካከቶች አሉ (1)
የማይታይ/ ድብቅ (Invisible)---የድብቅ ንጥቀት
(Secret Rapture) በመባል ይታወቃል (2) የሚታይ
(Visible)
• ድብቅ ንጥቀትን የሚያምኑ ክርስቲያኖች የክርስቶስ ምጻት
የሚፈጸመው በሁለት የተለያዩ ስቴጆች ነው።
የመጀመሪያው የሰባቱ ዓመት የመከራ ጊዜ ከመጀመሩ
በፊት የሚፈጸመው የድብቅ ንጥቀት ሲሆን ሁለተኛው
ደግሞ ክርስቶስ ከሰባቱ ዓመት የመከራው ዘመን ፍጻሜ
በቤተክርስቲያን ታጅቦ በሚመጣበት ጊዜ ነው
• እነዚህ የእምነት ተቋማት ለዚህ ትምህርታቸው
በዋቢነት የሚጠቅሷቸው ጥቅሶች ማቴ
24:43-44; 1ኛ ተሰ 5:2; ራዕይ 3፡ 3; 2ኛ
ጴጥ 2፡ 10 ናቸው። እነዚህ ሁሉ ጥቅሶች
“እንደሌባ” የሚል ቃል በጋራ ይዘዋል። በዚህ
ምክኒያት ነው ክርስቶስ በድብቅ ይመጣል
የሚባለው። ይህ የድብቅ ንጥቀት አስተምሮ
በአብዛኛው የፕሮቴስታንት
• ስለክርስቶስ አመጣጥ ሁለተኛው
አስተምሮ የሚታይ (Visible) ነው።
በዚህ አስተምሮ መሰረት ክርስቶስ
የሚመጣው በታላቅ ክብር በብዙ እልፍ
አዕላፋት መላዕክት ተከቦ ሁሉም ሊያየው
በሚችለው መልኩ ነው። ለዚህም በርካታ
የመጽሐፍ ቅዱስ መረጃዎችን በዋቢነት
• በማቴ 24፡ 27
• መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ
እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ
ይሆናልና
• ማቴ 24፡ 30
• የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው
ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም
የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም
በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል
• ማቴ 24፡ 31
• መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር
ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ
ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ
የተመረጡትን ይሰበስባሉ
• 1ኛ ቆሮ 15፡ 52
• መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ
ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን
• ራዕይ 1፡ 7
• እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥
የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ።
• ራዕይ 6፡14-17
• ሰማይም እንደ መጽሐፍ ተጠቅልሎ አለፈ፥ ተራራዎችና ደሴቶችም
ሁሉ ከስፍራቸው ተወሰዱ። የምድርም ነገሥታትና መኳንንት
ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም
ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ፥ ተራራዎችንና
ዓለቶችንም። በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም
ቍጣ ሰውሩን፤ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፥ ማንስ ሊቆም
ይችላል? አሉአቸው።
• የድብቅ ንጥቀትን የሚያምኑ የዕምነት ተቋማት
በሚያነሷቸው ጥቅሶች ማቴ 24:43-44; 1ኛ
ተሰ 5:2; ራዕይ 3፡ 3; 2ኛ ጴጥ 2፡ 10 )
“እንደሌባ” የሚለው ቃል የሚገልጸው
የጊዜውን ሁኔታ እንጅ የአመጣጡን ሁኔታ
አይደለም። ክርስቶስ የሚመጣበትን ቀን ማንም
የሚያውቅ የለም ልክ እንደሌባ ነው
በሚመጣበት ጊዜ ግን አይን ሁሉ ያያዋል እንጅ
ሞትና ትንሳኤ
ሞትና ትንሳኤ
• መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው እግዚአብሄር
ዘላለማዊ አምላክ ነው (1ኛ ጢሞ 1፡ 17)። እርሱ
ብቻ ነው የማይሞት (1ኛ ጢሞ 6፡ 16)። እርሱ
ያልተፈጠረ፡ በራሱ ህያው የሆነ፡ መጀመሪያና
መጨረሻ የሌለው አምላክ ነው።
• ሰው ህይወትን ያገኘው ከእግዚአብሄር ነው
“እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር
አበጀው በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ
አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ” (ዘፍ 2፡ 7)
• ዘላለማዊ አምላክ ሰውን በፈጠረበት ጊዜ እርሱም ለዘላለም
ይኖር ዘንድ ነበር የፈጠረው። ለዚህ ነበር በኤደን ገነት
የህይወትን ዛፍ ያበቀለው “እግዚአብሔር
አምላክም...በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥
መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ” (ዘፍ
2፡ 9)እግዚአብሄር ለአዳምና ለሄዋን የምርጫ ነጻነት--
የመወሰን ኃይል ሰጥቷቸው ነበር። የመታዘዝም ሆነ
ያለመታዘዝ ሙሉ ነጻነት ነበራቸው።
• የእነርሱ ለዘላለም የመኖር ሁኔታ የተመሰረተው
በእግዚአብሄር ኃይል ለእግዚአብሄር ፈቃድ እስከ
መጨረሻው በመታዘዛቸው ላይ ነው
• ይህንንም ከህይወት ዛፍ እንዲበሉ ክፉና በጎን
ከምታስታውቀው ዛፍ ግን እንዳይበሉ በማዘዝ
ገለጸላቸው።
• ከአጠቃላይ ሁኔታው የምንረዳው አንድ ነገር ቢኖር የሰው
ዘላለማዊነት በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ
ዘላለማዊነት--Conditional Immortality መሆኑን
ነው
• ሰይጣን ግን አዳምና ሄዋንን “ሞትን አትሞቱም” በማለት
አታለላቸውና የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ በምርጫቸው
ተላለፉ። በዚህም የኃጥያት ዋጋ የሁነውን ሞትን (ሮሜ 6፡
• ሞት ማለት የህይወት መቋረጥ ማለት እንጅ ሰው
ከአንድ ሁኔታ ወደ ሌላ ሁኔታ የሚለወጥበት
ክስተት ማለት አይደለም። ሞት የህይወት ተቃራኒ
ነው።
• እግዚአብሄርም አዳምና ሄዋን የህይወትን ዛፍ
ደግመው እንዳይበሉ ከኤደን ገነት አስወጣቸው
(ዘፍ 3፡ 22)። ይህም እግዚአብሄር ቃል የገባላቸው
በመታዘዝ ላይ የተመሰረተው ዘላለማዊነት
በኃጢያት ምክኒያት መታጣቱን ያመለክታል
• መልካሙ የምስራች ምንድንነው የሰው ልጅ
ባለመታዘዝ ምክኒያት በፍጥረት እግዚአብሄር የሰጠውን
ዘላለማዊነት ቢያጣም የዘላለማዊነት ምንጭ ክርስቶስ
ዘላለማዊነትን በስጦታ መልክ ሊሰጠው መወሰኑ ነው
“የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ
በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው” (ሮሜ 6፡ 23)
• አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ
ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና...በወንጌል
ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል
(2ኛ ጢሞ 1፡ 10, 11)።
• ይህ የሆነው እንዴት ነው?
• “ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ
ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና” (1ኛ ቆሮ 15፡ 22)።
• እዚህ ላይ ሁለት ከባድ ሚና የተጫወቱ ሰዎችን
እናገኛለን--አዳምና ክርስቶስ። አዳም ሰብአዊ ፍጥረትን
ሁሉ ይዞት ሞተ ክርስቶስ ደግሞ ሞትን ድል አድርጎ
በተነሳበት ጊዜ ሰብአዊ ፍጥረትን ሁሉ ይዞ ተነሳ
• በአዳም የመጣው ሞት በሰብአዊ ፍጥረት ሁሉ ላይ
የነገሰው ያለምርጫ ሲሆን በክርስቶስ የመጣው
የዘላለም ህይወት ግን የሚገኘው በምርጫ ነው
• ስለሞት ስናነሳ ሁለት አይነት ሞት እንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ
ይናገራል። የመጀመሪያው (ኢዮብ 14፡ 1, 2) እና ሁለተኛው
ሞት(ራዕይ 20፡ 14)በመባል ይታወቃሉ።
• የመጀመሪያውን ሞት ማንኛውም ሰው ጻዲቅም ይሁን
ኃጢያተኛ ይሞታል።
• መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ሞት እንቅልፍ (1ኛ ተሰ 4፡ 13; ዮሐ
11፡ 11) በማለት ይጠራዋል። እንቅልፍ ያለበትም ምክኒያት
በክርስቶስ ለሚያምኑ አንድ ቀን መነሳታችን እርግጥ በመሆኑ ነው
• ሰው ሲሞት ለተወሰነ ጊዜ ህይወት ይቋረጣል።
• ሰው ከሞተ በኋላ በሌላ አይነት ፎርም በህይወት ይኖራል
የሚለው ዕምነት ክርስቲያኑን ዓለም ወደ መናፍስት ጠሪነት--
• ሁለተኛው ሞት ግን የእግዚአብሄር የጸጋ ስጦታ
የሆነውን የዘላለምን ይህወት አንቀበልም ላሉ
ኃጢያተኞች የሚሰጥ የምርጫቸው ውጤት ነው
(ራዕይ 20፡ 14)።
• ከዚህ ሞት በኋላ እንደገና ወደ ህይወት የመመለስ
ዕድል የለም። በብዙ የፕሮቴስታንት አብያተክርስቲያን
ዘንድ ተቀባይነት ያለው ወንጌል በ144,00 አማካኝነት
ለሁለተኛ ጊዜ ለዓለም ሁሉ ይሰበካል የሚለው
አስተምሮ የመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት የለውም
• ትንሳኤም እንዲሁ ሁለት ነው የመጀመሪያው ትንሳኤ (ራዕይ
20፡ 4-6) እና ሁለተኛው ትንሳኤ (ራዕይ 20፡ 7, 8)
• ሁለቱ ትንሳኤዎችና ሁለቱ ሞቶች አፈጻጸማቸው እንዴት
ነው?
• ዛሬ ሰዎች በሚወለዱበት ጊዜ ከወላጆቻቸው የሚወርሱት
በኃጢያት የወደቀ ስጋን ነው። በመሆኑም የተወሰኑ
ዓመታትን ከኖሩ በኋላ ጻድቃንም ይሁኑ ኃጢያተኞች በልዩ
ልዩ ምክኒያቶች ይሞታሉ። ይህ እንቅልፍ የሚባለው
የመጀመሪያው ሞት ነው
• ክርስቶስ የነገሥታት ንጉስ የጌቶች ጌታ ሆኖ ዳግም
በእልፍ አዕላፋት መላዕክትታጅቦ በታላቅ ክብር
በሚገለጥበት ጊዜ ከነዚህ ከአዳም ጀምሮ
ከሞቱት ሰዎች ክርስቶስን የግል አዳኛቸው
አድርገው የተቀበሉ ሁሉ የማይበሰብስ አዲስ ሥጋ
ለብሰው በክብር ይነሳሉ። በህይወት ያሉ ጻድቃን
ደግሞ በቅጽበተ አይን ይለወጣሉ። ከዚያም
ክርስቶስን በአየር ለመቀበል ይነጠቃሉ (1ኛ ቆሮ
15፡ 51-55; 1ኛ ተሰ 4፡ 13-18)።
• ከዚያስ ምን ይሆናል?
• ዙፋኖችንም አየሁ፥ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት
ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ
እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን
ሰዎች ነፍሳት፥ ለአውሬውና ለምስሉም
ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው
በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤
ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ (ራዕይ
20፡ 4)።
• ክርስቶስ የሞቱ ቅዱሳንን ከሞት በማስነሳት በህይወት ያሉ
ቅዱሳንን ደግሞ በቅጽበተ አይን በመለወጥ ወደ ሰማይ
ሲወስድ በህይወት የነበሩ ኃጥአንና በመቃብር ያሉ ኃጥአን
ጉዳይ ምን ይሆናል?
• ራዕይ 6፡ 12-17
• ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ታላቅም
የምድር መናወጥ ሆነ፥ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር
ሆነ፥ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፥ በለስም በብርቱ
ነፋስ ተናውጣ ቃርያዋን ፍሬ እንደምትጥል የሰማይ
ከዋክብት ወደ ምድር ወደቁ፥ ሰማይም እንደ መጽሐፍ
• ተራራዎችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው
ተወሰዱ። የምድርም ነገሥታትና መኳንንት
ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም
ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና
በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ፥ ተራራዎችንና
ዓለቶችንም። በላያችን ውደቁ በዙፋንም
ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤
ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፥ ማንስ ሊቆም
• ለመሆኑ የማምለጥ ጥረቱ ይሳካ ይሆን?
• ኤር 4፡ 23-27
• ምድሪቱን አየሁ፥ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም
አልነበረባትም ሰማያትንም አየሁ፥ ብርሃንም
አልነበረባቸውም።ተራሮችን አየሁ፥ እነሆም፥ ተንቀጠቀጡ፥
ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ።አየሁ፥ እነሆም፥ ሰው
አልነበረም፥ የሰማይም ወፎች ሁሉ ሸሽተው ነበር። አየሁ፥
እነሆም፥ ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፥ ከተሞችም ሁሉ
ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ ቍጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር።
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። ምድር ሁሉ ባድማ
ትሆናለች፥ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም።
• በዚህ አንድ ሺ ዓመት ሰይጣን ምን ይሆናል? ሥራፈት
• ራዕይ 20፡ 1-3
• የጥልቁንም መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት በእጁ የያዘ
መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። የቀደመውንም እባብ
ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን
ያዘው፥ ሺህ ዓመትም አሰረው፥ ወደ ጥልቅም ጣለው
አሕዛብንም ወደ ፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት
እስኪፈጸም ድረስ በእርሱ ላይ ዘግቶ ማኅተም
አደረገበት፤ ከዚያም በኋላ ለጥቂት ጊዜ ይፈታ ዘንድ
ይገባዋል።
• በዚህ ሺ ዓመት ጊዜ ውስጥ ቅዱሳን በሰማይ ምን ያደርጋሉ?
• 1ኛ ቆሮ 6፡ 2
• ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? በዓለምስ
ላይ ብትፈርዱ ከሁሉ ይልቅ ትንሽ ስለሚሆን ነገር ልትፈርዱ
አትበቁምን? ይህ የሺው አመት ፍርድ--Millenial
Judgment የሚባለው ነው
• በዚህ ወቅት ቅዱሳን ክርስቶስ የሰጠውን ፍርድ
በመመርመር ቅንና እውነተኛ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ከዚያ
በኋላ ስለማንም መጥፋትም ሆነ መጽደቅ የሚነሳ ጥያቄ
አይኖርም
• ሺው ዓመት ሲፈጻም ምን ይሆናል?
• ራዕይ 20፡ 3
• ሺህ ዓመትም አሰረው፥ ወደ ጥልቅም ጣለው
አሕዛብንም ወደ ፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት
እስኪፈጸም ድረስ በእርሱ ላይ ዘግቶ ማኅተም
አደረገበት፤ ከዚያም በኋላ ለጥቂት ጊዜ ይፈታ
ዘንድ ይገባዋል
• ይፈታ ዘንድ ይገባዋል ማለት ማን ማለት ነው?
• ራዕይ 20፡ 7, 8
• ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፥
በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና
ማጎግን፥ እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው
ይወጣል፤ ቍጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል
ነው።
• ሺው አመት ሲፈጸም ከአዳም ዘመን ጀምሮ እስከ
ክርስቶስ ዳግም ምጻት ድረስ የሞቱ ኃጥአን የመጨረሻ
ዋጋቸውን ለመቀበል ይነሳሉ። በዚህ ጊዜ ሰይጣን
እንደገና ለመጨረሻ ጊዜ የማታለል ሥራውን ይጀምራል
• ሰይጣን እንዴት ነው የሚያታለው?
• ራዕይ 21፡ 1, 2
• አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው
ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ
ፊት የለም። ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥
ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ
ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ
• ከሽው አመት ፍጻሜ በኋላ ክርስቶስና ቅዱሳን
ቅድስቲቷን እየሩሳሌምን ይዘው ከሰማይ ይወርዳሉ።
• ድራማው ታዲያ እንዴት ይጠናቀቃል?
• ራዕይ 20፡ 9, 10
• ወደ ምድርም ስፋት ወጡ የቅዱሳንንም ሰፈርና
የተወደደችውን ከተማ ከበቡ፤ እሳትም ከሰማይ
ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ
በላቻቸው።ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና
ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ
ባሕር ተጣለ፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና
ሌሊት ይሣቀያሉ።
• በእርግጥ ለዘላለም በእሳት ባህር ውስጥ ሌትና
ቀን ይሰቃያሉ?
• ሚክ 4፡ 1
• እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን
ይመጣል ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ
ገለባ ይሆናሉ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥
ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር
• ህዝ 28፡ 18
• በበደልህ ብዛት በንግድህም ኃጢአት መቅደስህን
አረከስህ ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አውጥቻለሁ
እርስዋም በልታሃለች፥ በሚያዩህም ሁሉ ፊት በምድር
ላይ አመድ አድርጌሃለሁ።
• ይሁዳ 1፡ 7
• እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ
የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ
ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል
• ዘላለም የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ በተለያየ መንገድ አገልግሎት ላይ
ስለዋለ ቃሉ አገልግሎት በዋለለበት ጉጋይ
ምን ትረጉም እንዳለው በጥንቃቄ
መመርመር ያስፈልጋል። ዮሐንስ ለዘላለም
ይሰቃያሉ ሲል እሳቱ እስኪያጠፋቸው
ድረስ መሆኑን ከሌሎቹ ጥቅሶች መረዳት
• የነገሩ ሁሉ ፍጻሜው ምንድን ነው?
• ራዕይ 21፡ 1-4
• አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥
ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር
አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም...
እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ
አምላካቸው ይሆናል
• በዚህ አይነት ሁኔታ ዘላለማዊነት ይጀመራል

You might also like