Professional Documents
Culture Documents
“እውነተኛው የዓለም ብርሃን” - Copy (2)
“እውነተኛው የዓለም ብርሃን” - Copy (2)
ብርሃን÷ ብርሃን የጨለማ ተቃራኒ ነው፤ ለዚያም ነው ብርሃን የሌለበት ጨለማ ተብሎ የሚጠራው።
ጨለማ መኖሩ የሚታወቀው ብርሃን ሳይኖር ሲቀር ነው። ብርሃን በሁለት መልኩ ልንገልጸው
እንችላለን÷ ውጫዊ(ዓለማዊ) እና መንፈሳዊ(ውስጣዊ)፤ የመጀመርያው ከተፈጥሮአዊው(ፀሐይ) ወይም
ከሰው ሰራሽ የሚገኝ ሲሆን ያንን ብርሃን ወደ ዓይናችን ሲያንጸባርቅ ነገሮችን ማየት እንችላለን፤
ዓይናችን ያ ብርሃን ካላገኘ ግን ጨለማ ነው ምንም ማየት አይችልም። ሁለተኛው ግን ከመጀመርያው
በእጅጉ የተለየ የረቀቀ ብርሃን ነው÷ መንፈሳዊ ብርሃን፤ ውስጣዊ ብርሃን።
እንደ ቤተ- ክርስቲያናችን ሥርዓትና ቀኖና ከገና በፊት ያሉት ሦስት ሰናብት ማለትም ስብከት፣ ብርሃን፣
ኖላዊ አንድላይ ዘመነ ስብከት ተብለው ይጠራሉ፡፡ የዘመነ ስብከት ሁለተኛ እሁድ ብርሃን
ይባላል።ሌሊቱን ከቅዱስ ያሬድ መዝሙር «አቅዲሙ ነገረ በኦሪት» በኦሪት መናገርን አስቀደመ
ብለው በመጀመር በሊቃውንቱ ሲዘመር በዜማ አምላክን ሲወደስና ሲመሰገን ካደረ በኋላ ጧት ደግሞ
በሥርዓተ ቅዳሴ (ሮሜ.13፥11-ፍጻሜ)፣ (1 ዮሐ.1፥1-ፍጻሜ)፣ (የሐዋ.26፥12-19) በዲያቆናት እና
በካህናት ይነበባሉ። (መዝ.42፥3) በዲያቆኑ በዜማ ይቀርባል፡፡ (ዮሐ.1፥1-19) በካህኑ ይነበባል እንዲሁም
የሊቁ የአትናቴዎስ የምስጋና ጸሎት ይደርሳል ፡፡
ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በዘመነ ብሉይ÷ ደዌ-ሥጋ፣ ደዌ- ነፍስ የፀናበት፣ ለሰው ሁሉ አስጨናቂ ዘመን
የሆነበት፣ሁሉም ሰው ብርሃን ከሆነው አምላኩ ርቆ በጭንቅ፣ በመከራና በጨለማ ውስጥ በመኖሩ ተስፋ
ቢስ ሆኖ ስለነበር ዘመኑን « ዘመነ-ጨለማ» ብለው በመግለጥ ይህንን ጨለማ አስወግዶ ወደ ብርሃን
የሚቀይር በጨለማ የሚያበራ ብርሃን እንዲላክላቸውና ከብርሃን የተገኘ እውነተኛ ብርሃን፤አማናዊ
ብርሃን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመጣ ዘወትር ሲጸልዩ ነበር፡፡
መዝሙረኛውም ያን ብርሃን መሻቱን እንዲህ ሲል በመዝሙሩ ጸልዮአል÷<ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ
እማንቱ ይምርሐኒ ወይሰዳኒ ደብረ መቅደስከ ወውስተ አብያቲከ እግዚኦ> /መዝ. 42.3/ አቤቱ
ብርሃንህንና እውነትህን (ጽድቅህን) ላክ እነርሱ ይምሩኝ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደ ማደሪያህ
ይወሰዱኝ፣ብርሃን የሆነ፣ጽድቅ የሆነ፣ እውነት የሆነውን ቅዱስ ልጅህን (ወልድን) ክንድህን ልከህ ጨለማ
ሆኖ የጋረደንና ካንተ የለየን ኃጢአታችን አስወግዶ ከአንተ አስታርቆ ወደ አንተ ይውሰደን ሲል ነው።
የዚህ ሁሉ ትንቢትና ጸሎት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቱ ተልኮና በፈቃዱ ወደዚህ
ዓለም በመምጣት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በተዋህዶ ፍጹም አምላክና ሰው
ሆኖ በዓለም ሲያስተምር «እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ» /ዮሐ. 8.12/ በማለት ብርሃንነቱን አረጋግጧል፤
በመቀጠልም እርሱን የሚከተል ሁሉም ያንን ብርሃን እንደሚያገኝ እንዲህ በማለት ተናግሯል‹‹ እኔን
የሚከተል ሁሉ የሕይወት ብርሃን ያገኛል በጨለማም አይመላለስም››(ዮሐ 8:12)። ኢየሱስ ክርስቶስ
የሰው ሁሉ ሕይወት የሆነች ብርሃን ገልጧል፤ ብርሃን መሆኑን ደቀመዛሙርቱም ስለ ብርሃንነቱ እንዲህ
በማለት መስከሯል «ሕይወት በእርሱ ነበረ፣ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረ፤ ብርሃንም በጨለማ
ያበራል፤ ጨለማም አላሸነፈውም» /ዮሐ. 1.4-5/።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጨለማ ያላሸነፈው ዘወትር የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ነው።
ሊቃውንትም ‹ዘዘልፈ ያበርህ፣ብርሃን ዘበአማን› ሁሉ ጊዜ የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ‹ዘእንተ ውስጥ
አይነነ አብራህከ ወጽልመተ ሐሊናነ፣ብርሃነ_ፍጹማን ወልደ አምላክ ሕያው› የሕሊናችንን ጽልመት
ያበራ፣ ዓይነ ልቡናችንን የገለጠው፣ የሕያው አምላክ ልጅ የፍጹማን ብርሃን ብለውታል። ዮሐንስም
ስለዚህ ብርሃን ሲመሰክር ለሰው ሁሉ የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ ሲል፣ ቅዱስ
ጴጥሮስም ይህ ብርሃን በልቡናችን ውስጥ የሚያበራ ብርሃን ነው ብሎታል(1 ኛጴጥ 1:19)።
ቅዱስ ጳውሎስም መጀመርያ በብርሃን የነበረ እንኳ ቢመስለውም ያ ብርሃን ሳይበራለት በጨለማ ሆኖ
ይህንን ብርሃን ለማጥፋት የብርሃን ልጆቸና ብርሃን እያሳደደ ሳለ ጌታችንም ትጋቱንና ቅንነቱን
በመመልከት ጌታችን በሚያንፀባርቅ ብርሃን አምሳል እንደተገለጠበት ተናግሯል፡፡ « በመንገድ ሳለሁ እኩለ
ቀን ሲሆን በዙሪያዬና ከኔ ጋር በሄዱት ዙሪያ ከፀሐይ ብሩህነት የበለጠ ብርሃን ከሰማይ ሲበራ አየሁ …
አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ ” አለኝ(የሐዋ 26:13_15) ቅዱስ ጳውሎስ ያ ብርሃን
ከበራለት በኋላ ጨለማ ከእርሱ ውስጥ ስፍራ ስላላገኘ ብርሃንነቱን ለማወጅ ተሯሩጧል፤ ሌሎችም
ሲያሰተምር እርሱንም ራሱ ጨምሮ እንደህ ሲል ተናግሯል ‹‹ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን
በጌታ ብርሃን ናችሁ፤ የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን
እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥
ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን
ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና።
ስለዚህ አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል ይላል›› (ኤፌ 5:8-14)። ክርስቶስ
በአህዛብም ብርሃን እንደሆነ ቀድሞዉኑ ተወስኖ ነበር፤ (ኢሳ 49:6)‹…እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኃኒት
ትሆን ዘንድ ለአህዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ› ይላል። በጨለማ የተጓዘ እንቀፋት ሳይመታው
አይቀርም፣ ክርስቶስ ግን ይህንን ጨለማ በማስወገድ ብርሃን በመሆን ከእንቅፋትም ከመሰናክልም
ሊያድን መጥቷል፤ እንቅፋቱንም ያሳያል። ስለዚህ ከእንቅፋትም ከውድቀትም ለመዳን በዚህ ብርሃን
መራመድ ይገባል። እመኑ በብርሃኑ ወአንሰውስዉ እንዘ ብክሙ ብርሃን እንዳለው ሊቁ፤ በብርሃኑ አምነን
በብርሃን እንመላለስ።
ዮሐንስም እኛም በዓይናችን አይተናል እንመሰክርማለን ብሏል። ውድ አንባብያን ሆይ! እኛም ሁላችን
በዚህ ብርሃን አምነን በብርሃኑ ከተመላለስን ለእኛ ብሎ ነው የመጣና የዚህ ክብርና ብርሃን ባለቤቶች
ነን። በዚህ ዓለም የምናገኘው የፀሐይ ብርሃን ከሁሉም ዓለም በጋራ ነው የምንጠቀመው ውስጣዊ
ማንነታችንም አይደለም አይገልጽምም፤ የሚያስደንቀው ግን የእግዚአብሔር ቸርንት ነው፤ ምክንያቱም
ያ ብርሃን ለሚያምኑት ሆነ ለማያምኑት፤ ለጠላቶቹም ሆነ ለወዳጆቹም በእኩል መስጠቱ ነው፤ ሙሉ
በሙሉ ባይሆንም ቀኑን በማፈራረቅ ለዓለም ስታበራ የቆየች ፀሐይ እንደ ሌሎቹ ፍጡራን አንድ ቀን
ማለፍዋ ስለማይቀር የምትሰጠው ብርሃን የተፈራረቀና ውጫዊ ብርሃን ቢሆንም እንኳ እሱም
ቀጣይነት እንደሌለው የተረጋገጠ ነው፡፡
ስለዚህ ብርሃን ከሚጠሉና ጨለማን ከመረጡ ሰዎች መለየት አለብን፤ ከጨለማው ዓለምና አስተሳሰብ
ወጥተን በፈጠራት ፀሐይ ዓለምን ያበራ እርሱ ራሱ ብርሃን በመሆን ደግሞ ውጫዊውንና ውሰጣዊውን
የሚያበራ የሥጋና የነፍስ ብርሃን የሆነ የሕይወት ብርሃን እንያዝ እንከተል <የመዳን ቀን አሁን ነው>
እንዳለው ሐዋርያው ከዓለማዊ አስተሳሰብ ወጥተን ወደመንፈሳዊና ዘላለማዊ ሕይወት ግዜው ሳይመሽ
አሁን ተሎ ብለን እንግባ፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በእውነት ይህንን ክብርና ብርሃን ሊያመልጠን አይገባም፤ በዚህ ብርሃን
ከብርሃን አባትና ብርሃን ከሆነው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑምጋር ለዘላለም
ለመኖር በብርሃኑ አምነን ከብርሃንና ከብርሃን ልጆች ቅዱሳን ጋር አሁን በትንሳኤ ልቡና በአብ ቀኝ
እንቀመጥ (ቈላ 3:1-3፤ ኤፌ 2:6-7)። በብርሃኑ ልቡናችንና ሁለንተናችንን ያብራ !!!
በመምህር ኪዱ ዜናዊ
ክርስቲያናዊ ህይወት
ክርስቲያኖች ክርስቲያን ከመባላቸው አስቀድሞ ምዕመናን (መዝ 100፡7) ፤ ደቀመዛሙርት (ኢሳ 8፡16) ፤
ወንድሞች (ማቴ 8፡10) የመሳሰሉት በመባል ይጠሩ ነበር፤ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ ክርስቲያን ተብለው
ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰየሙት በአንጾኪያ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት እንደነበር ቅዱስ መጽሀፍ
ይነግረናል፡፡ (የሐዋ 11፡26)
1. እግዚያብሔርን ማወቅ
እግዚአብሄርን ማወቅ፡-
በምድራችን ትርጉም ያለው ሕይወት ማለት ምን አልባት የሚመስለን ሀብት፤ ንብረት፤ ስልጣን ፤ ጥሩ
መልበስ፤ ጥሩ መመገብ ፤ ጥሩ ቤት መኖር ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን ትርጉም ያው ህይወት መኖር
የሚቻለው እግዚአብሄርን ሲያውቅ ነው፡፡ በዚህ ዘኪዎስ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል፡፡ ዘኪዎስ ጌታውን ሳያውቅ
የኖረበት ዘመን ትርጉም አልባ ህይወት ነበር አምላኩን ሲያውቅ ግን “ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን
ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሃሰት ከስሼ እንደሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው” (ሉቃ 19 ፤9)
በማለት አዲሱ ክርስቲያናዊ ህይወት ምን እንደሚመስል ነግሮናል፡፡
ታሪክን ይቀይራል
ሰዎች እግዚአብሄሔርን ሲያውቁ ዘማዊ የነበረው ድንግል፤ ዘረኛና ወገንተኛ የነበረው ሁሉን በክርስቶስ
አንድ አድርጎ የሚያይ ፍትሃዊ፤ አሳዳጅ የነበረው ስለ ክርስቶስ ተሳደጅ፤ ክፉ የነበረው ደግ፤ ዘፋኝ
የነበረው ዘማሪ፤ ነፍሰ ገዳይ የነበረው የሰውን ህይወት የሚያድን ወዘተ ይሆናል፡፡ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ
ጥሩ አስረጅ ይሆናል፡፡
2. በዕምነት ማደግ
ብዙዎች ክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ ጥቂቶች ብቻ በእምነት ውስጥ በጥበብ ይኖራሉ፡፡ “ዕምነት
ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነውና” (ዕብ 11፡1) የሰው ልጅ
በሃይማኖት ካልኖረ ለምኞቱ ገደብ የለውም፡፡ ያለኝ ይበቃኛል አይልም፡፡ አመንዝራ ሲያይ በፍትወት
ስሜት ይቃጠላል፣ የወይን ጠጅ በብርሌ ባማረ መልኩ ባየ ጊዜ መጠጥ ያምረዋል ለዚህ እኮ ጥበበኛው
ጠቢቡ ሰለሞን “ከተማን ከመግዛት ራስን መግዛት ይበልጣል ያለው”
4. እግዚአብሔርን መምሰል
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዓለም ሶስት ዓመት ከሶስት ወራት
በአገልግሎት ሲቆይ በርካታ ትምህርቶችን ከማስተማሩም በላይ በሕይወቱ አብነት ለመሆን መልካም
ሥራ ካደረገ በኋላ ከመዝ ግበሩ እናንተም እንዲሁ አድርጉ(ዮሐ 13፡14)(ምንም እንኳን መልካምነት
የባህርይው ቢሆንም) በማለት ክርስቲያኖች በሕይወት ዘመናቸው ክርስቶስን መምሰል እንዳለባቸው
መጽሀፍ ይስተምረናል፡፡ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስም ይህንን ቃል ”እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን
ምሰሉ”(1 ኛቆሮ 11፡1) በማለት ያረጋግጥልናል፡፡በመሆኑም የመንፈስን ፍሬ በማድረግ የስጋን ሥራ
በመተው አምላካችንን መምሰል ይገባናል ማለት ነው፡፡(ገላ 5፡18)ይህንን በማድረግ ቅዱሳን ቅድስናን
ገንዘብ አድርገዋል፡፡“እግዚአብሔር መምሰል ግን ለአሁኑ እና ለሚመጣው ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉ
ይጠቅማል”(2 ጢሞ 4፡8)
5. ፍቅር ሊኖረን ይገባል
6. ከመስቀሉ መካፈል
1. ጥምቀት
2. ሜሮን
3. ቁርባን
4. ክህነት
5. ንስሀ
6. ቀንዲል
7. ተክሊል ናቸው፡፡
1. ሚስጢረ ጥምቀት
2. ምስጢረ ሜሮን
3. ምሥጢረ ቁረባን
ይህ ቃል የሱርስት ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም አምኃ ስጦታ ማለት ነው፡፡ ሥጋውና ደሙ የተሰጠን በነፃ ያለ
ዋጋ ሳይገባን በችሮታ ነውና፡፡ በቤተክርስቲያን ምሥጢራት ሁሉ መደምደሚ ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡
መስዋዕት ማቅረብ የተጀመረው በአዳም ጊዜ ሲሆን ከአዳም እስከ ሙሴ የተነሱ አበው ሁሉ በህገ ልቦና
ለእግዚአብሔር መስዋት ይሰው ቁርባን ያቀርቡ ነበር፡፡ መስዋዕታቸው ከእንሰሳ ቁርባናቸው ከእህልና
ከአትክልት ማለት ከስንዴ እህል፣ ከወይን ፍሬ የሚቀርብ ነው፡፡ ዘመነ ኦሪት በብሉይ ኪዳን በሙክራብ
የተሰዋ እንሰሳት ሁሉ በአዲስ ኪዳን በቤተክርስቲያን ለሚሰዋው ሁሉ የክርስቶስ ሥጋና ደም ምሳሌ
ነበር፡፡ መልከ ጼዴቅ ያበረከተው ኅብስተ አኮቴት ጽዋዐ በረከት ለአምላክ የሥጋውና የደሙ ምሳ ሆነው
አልፈዋል፡፡ ከምሥጢራት አንዱ መሆኑ ሕብስቱ ተለውጦ የክርስቶስ ሥጋ ጽዋው ተለውጦ የክርስቶስ
ደም ሲሆን አይታይም፡፡ ነገር ግን እምነት ያለው ሁሉ በእምነት መነጽር ይመለከተዋል፡፡ ይህ ሳይሆን
ሳይታይ የሚወደድን ሕይወት ለማግኘት ከቁርባን በፊት ንስሐ መግባት ለአስራ ስምንት ሰዓት መጾም
አለበት፡፡ ንጽሕናውን በጠበቅ አለበት፡፡ መምክረ ካህን ጸንቶ መገኘት ያስፈልጋል፡፡
4. ምሥጢረ ክህነት
ይህ ቋንቋ የግዕዝ ቋንቋ ነው፡፡ ተክህነ አገልገለ ከሚለው ግስ የወጣ ነው፡፡ ክህነት የተጀመረው በአባታች
አዳም ነው፡፡ ክህነት የአገልግሎት ስም ሆኖ የቤተክርስቲያን ከፍተኛ መንፈሳዊ ማዕረግ ነው፡፡
እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ በልጅነት አክብሮ ነብይና ካህን አድርጎ ሾሞ በኦሪት በወንጌል ሥርዓት
እስኪወሰን ድረስ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ የነበሩ አበው በበረከት አበው ከእግዚአብሔር እየተሾሙ
ትንቢትን ክህነት ከቅዱሱ መንፈስ እየተቀበሉ (እየተሾሙ) በነብይነታቸው ያለውን የሚመጣውን
ሲገልጽ ሲያስተምሩ በሀብተ ክህነታቸው መስዋዕት ሲቀርቡ ነበር፡፡ ክህነት በዘመነ ኦሪት ለሌዊ ነገድ
ከተሰጠ በኋላ ሲወርድ ሲወራረድ እስከ ክርስቶስ ደርሷል፡፡ ታላቁ ሊቀ ካህናት እየሱስ ክርስቶስ እንደ
ብሉይ ኪዳን መስዋዕት እንሰሳ ሳሆን እራሱን መስዋዕት፣ እርሱ ሰዋዒ ሆኖ ወደ መቅደስ ገብቷል፡፡ ዮሐ
20፡22 ማሬ 18፡18 1 ኘና ቆሮ 4፡1 ማሬ 28፡20
5. ምሥጢረ ንስሐ
6. ምሥጢረ ቀንዲል
ይህ ቃል የላቲን ቋንቋ ነው ትርጉሙም ፍፁም መብራት ማለት ነው፡፡ ከሰባቱ ሚስራት አንዱ ቀንዲል
ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘይት የፈውስ ምልክት ነው፡፡ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው የሚሰቃዩ
ህሙማን ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ቁስለኞች እየተቀቡ ይፈወሱ ነበር፡፡
ኢሳ 1፡6 ሉቃ 10፡34 ራዕ 3፡18 ማር 6፡13 ይህ ቅብዓተ በሐዲስ ኪዳን ለሚጠመቁ ከሚደረግ ቅብዐ
ሜሮን ጋር ግንኙነት የለውም ራሱን የቻለ ሕሙማነ ሥጋ ብቻ ሳይሆን ሕሙማነ ነፍስ ኃጥአን
የሚቀቡት ፈውስ የሚያገኙበት ነው፡፡ ማር 6፡13 ያዕ 5፡13-15 ራዕ 1፡17፡፡
7. ምሥጢረ ተክሊል
ይህ ማለት “ተከለለ” ተቀናጀ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ በሥርዓተ ጋብቻ ቅደም ተከተል
መሰረት በመተጫጨት እና በቃል ኪዳን የተመሰረተ ጋብቻ በተክሊል ይፈጸማል፡፡ ቤተክርስቲያን
ምስክርነት የሚፈጸመው ጸጋ መንፈስ ቅዱስን የሚያሰጥ ስለሆነ ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ
ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በተክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም
የሚታወቀው በትክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ዘፍ 1፡27-28 ፣ 2-18 ማቴ 19-4 እነዚህን
ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አውቀን ተረድተን የእምነታችን ፍጻሜ የሆነውን አምላካችንን
ለተፈጠርንለት ዓላማ በመገዛት የነፍሳችንን መዳን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡