You are on page 1of 161

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ትምህርት


መግቢያ

መጽሐፍ ቅዱስ ምንድነው?

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 1


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ሐረግ መጽሐፍ እና ቅዱስ ከሚሉት ሁለት ጥምር ቃላት የተገኘ ሲሆን ‹‹መጽሐፍ››
የሚለው ቃል ተጠቃሎ በአንድ ጥራዝ ሥር የተሰበሰበ ጽሑፍን ሲገልጥ ‹‹ቅዱስ›› የሚለውን ቃል ደግሞ በዕብራይስጥ
‹‹ክዳሽ››፣ በጽርዕ ‹‹ሐጊዮስ››፣ በሱርስት ‹‹ካዲሽ››፣ በግእዝ እና በዐረብኛ ቅዱስ ይለዋል፤ ትርጉሙም የከበረ፣ የተለየ፣ የነጻ፣
የጸና ማለት ነው፡፡ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ ማለት የተቀደሰ፣ የተባረከ፣ የተለየ፣ የተከበረ ጥራዝ (ተጠቃሎ የተጻፈ) ማለት
ነው፡፡ ይህን በግእዝ እና በአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ እያልን የምንጠራውን በግሪክ /ቢብሎስ/ አጊያ ግራፊ ሲለው ይገኛል፡፡
ቢብሎስ የተባለው የግሪክ ቃል ///// ከተባለው ሀገር እንደመጣ ይነገራል፡፡ ይህም ከፊንቂያ ወደቦች ውስጥ አንደኛ የነበረና
ከቤይሩት 25 ማይል ያህል ርቆ የሚገኝ ቦታ ነው፡፡ ይህ ቦታ ለመጻፊያ ያገለግል ዘንድ ፓፒረስ /ደንገል/ የተባለውን ተክል
እንደ ወረቀት አድርገው ይሠሩበት የነበረ ቦታ ነው፡፡ ቢብሎስ የሚለውንም ስያሜ ያወጡለት ግሪካውያን እንደሆኑ
ይነገራል፡፡ ቢብሎስ በተባለው ቃል በመጀመሪያ ጊዜ ማንኛውም መጽሐፍ ይጠራበት ነበር፤ እየቆየ ግን ይህ ስያሜ
ለማንኛውም መጽሐፍ መሰጠቱ ቀርቶ ለቅዱስ መጽሐፍ ብቻ ተሰጠ፡፡
በላቲን ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስ ስክሪፕቸር /scripture/ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በእንግሊዘኛው ደግሞ ቀድሞ
ከተሰጠው የግሪክ አጠራር በመነሳት ባይብል /bible/ ተብሎ ይጠራል፡፡ በእኛ ቤተክርስቲያን ግን በፍትሐ ነገሥቱ
‹‹መጻሕፍት አምላካውያን›› ብሎ ሲጠራው እናገኘዋለን፡፡ እንዲሁም (በማቴ 22፡29፤ 22፡42፤ ሉቃ 24፡32፤ ሐዋ 18፡24)
ላይ ‹‹መጻሕፍት›› ተብሎ በብዙ ቊጥር ሲጠቀስ፤ በነጠላ ቊጥር ደግሞ ‹‹መጽሐፍ›› ተብሎ (በሐዋ 8፡32፤ ገላ 3፡22) ላይ
ተጠቅሷል፡፡ ‹‹ቅዱሳት መጻሕፍት›› እየተባለም ተነግሯል፡፡ (ሮሜ 1፡2፤ 2 ጢሞ 3፡15)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር
የልቡን አሳብ የገለጠበት የምስጢር መዝገብ(አሞ 3፡7)፤ የእግዚአብሔርን አሳብ የያዘ፣ ፍጽም እውነትነት ያለው ቅዱስ
ቃል፣ የማይሻር፣ የማይሻሻል፣ የማይገፋ ጽኑዕ ግንብ ነው (ኢሳ 40፡8፤ ማቴ 5፡17-24፣ዮሐ 10፡35)፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ለምን ቅዱስ ተባለ?

1. አስገኝው እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ፡- ከእግዚአብሔር የሆነው ሁሉ ቅዱስ ነው፡፡ እርሱ ለአገልግሎቱ
አክብሮ የለያቸው ሰዎች (ዘጸ 28፡40-41) እንዲሁም ለይቶ ያከበራት ዕለት ዕለተ ሰንበት (ራእ 1፡10) ቅድስት
ናት፡፡ እንደዚሁም ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ቅዱስ ነው፡፡ አስገኝው እግዚአብሔር
ስለመሆኑም ኢሳይያስ ‹‹በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም›› በማለት ነግሮናል፡፡ (ኢሳ 34፡16)
2. በመንፈሰ እግዚአብሔር የተነሣሱ ቅዱሳን ሰዎች የጻፉት በመሆኑ፡- ከመጻሕፍት ሁሉ የተለየውን መጽሐፍ
ከአማልክት ሁሉ ልዩ በሆነው አምላክ አማካኝነት ከሰዎች ሁሉ የተለዩ ሰዎች ሊጽፉት የተገባ ሆነ፡፡ ስለዚህም
እግዚአብሔር አምላክ አስቀድሞ ፊት ለፊት እየተገለጠ ያናግራቸው የነበሩትን ቅዱሳን እንዲሁም ነቢያት
ለሕዝቡ በቃል ሲያስተምሩ ዝንጉዓን ቢሆኑባቸው አምላካችን ለሰው ልጆች ካለው ፍቅር የተነሣ ቃሉን
በንግግር ብቻ ሳይሆን በጽሑፍ እንዲያሰቀምጡ አነሣሳቸው፡፡ ለዚህም ነው ‹‹እግዚአብሔርም ሙሴን
የአማሌቅን ዝክር ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለውና ይህን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፤ በኢያሱም
ጆሮ ተናገር አለው፡፡›› (ዘጸ 17፡14) ተብሎ የተጻፈው፡፡ (2 ኛ ጴጥ 1፡20-21፤ ራእ 1፡11)
3. ሰውን ወደ ቅድስና የሚያደርስ ስለሆነ ቅዱስ ተብሏል፡- መጻሕፍትን አምኖ መቀበል የእግዚአብሔርን
ድምፅ መስማት ነው፡፡ ‹‹የዚህን መጽሐፍ ቃል ትንቢት የሚጠብቅ ብጹዕ ነው፡፡›› (ራእ 22፡7) የመጽሐፍ
ቅዱስ ዋነኛ ዓላማ በእግዚአብሔር ወደሚኖር ፍጹም ሕይወት መጥራት ነው፡፡ (2 ኛጢሞ 3፡7)
4. ክብረ ቅዱሳንን የሚዘክር ስለሆነ ቅዱስ ተብሏል፡- መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም፣ ስለ ቅዱሳን መላእከት፣ ስለ ቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት፣ ስለ ቤተ መቅደስ፣ ስለ ንዋያተ ቅድሳት፣
ስለ ተቀደሱ ዕለታት ወዘተ . . . ስለሚናገር ቅዱስ ተብሏል፡፡
5. የሚያነቡትን፣ የሚሰሙትን፣ የሚያምኑበትንና የተሳለሙትን ሁሉ የሚቀድስ የሚባርክ ስለሆነ ቅዱስ
ተብሏል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 2


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

መጽሐፍ ቅዱስ ለምን መጻፍ አስፈለገው?

ይህንን ጥያቄ በ 4 ኛው መ/ክ/ዘ ከተነሡት ቅዱሳን ሊቃውንት አባቶች አንዱ የሆነው የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ በማለት ይመልስናል፡፡
‹‹በእርግጥም እኛ የተጻፉ ቃላት እርዳታ የሚያሻን ሁነን አልተፈጠርንም፤ ይልቁንም ለነፍሳችን በተጻፉት
መጻሕፍት
ምትክ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ፣ በብዕር ቀለም በወረቀት ላይ በሰፈሩት ቃላት ፈንታም በልባችን
ሰሌዳ ላይ መለኮታዊ /መንፈሳዊ/ ጽሑፍ ሊጻፍ በተገባ ነበር፤ ነገር ግን ይህንን ታላቅ ጸጋ ፈጽመን
ከእኛ ስላራቀነው ነው፤ ሁለተኛውንና በአንጻራዊነት የተሻለው አማራጭ እንድንይዝ ያስገደደን፡፡
የቀድሞው /በልባችን የነበረው ጽሑፍ/ የተሻለ እንደነበር እግዚአብሔር በቃልም በተግባርም
ገልጦልናል፡፡ እግዚአብሔር ኅሊናቸው ንጹሕ ሆኖ ስላገኘው ለኖኅ፣ ለአብርሃምና ለልጆቹ፣ ለኢዮብ
እንዲሁም ለሙሴ የተናገረው በተጻፈ ጽሑፍ ሳይሆን እርሱ ራሱ ፊት ለፊት ቀርቦ ነበር፤ ነገር ግን
ዕብራውያን በሙሉ በኃጢአት በወደቁ ጊዜና ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ሕግጋቱን በጽሑፍ፣
በጽላት በተግሣፅ መልክ ሰጠ፡፡ ይህ በብሉይ ኪዳን ብቻም ሳይሆን በሐዲስ ኪዳንም የተደረገ ነው፤
ምክንያቱም ጌታ የትኛውም ሐዋርያ የተጻፈ ነገር አልሰጠውም፤ ነገር ግን በተጻፉ ቃላት ፈንታ
የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ እንደሚሰጣቸው ቃል ገባላቸው፡፡ (ዮሐ 14፣ ኤር 31፣ 2 ኛ ቆሮ 3) ዳሩ ግን በጊዜ
ሒደት አንዳንዶች በሃይማኖት ሕጸጽ ሌሎች ደግሞ በምግባር ጉድለት ስላመጡ ቅዱሱን ቃል
ለማስታወስ ይቻል ዘንድ በተጻፈ ቃላት መቀመጡ ግድ ሆነ፡፡››
ዳግመኛም ግብጻዊው ካህን ታድሮስ ማላቲ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ መጻፍ ምክንያት ሲገልጡ
‹‹እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ካለው ፍቅርና ለሕይወታችንም ከሚሰጠው ዋጋ የተነሣ በዘመናት ሁሉ በእኛው
(ሰዋዊ ቋንቋና አቅም) ሲያናግረን ቆይቷል፡፡ ቅዱስ መንፈሱ ነቢያትን በልዩ ቃላት እየመራቸው እኛን ወደ
እውነቱ እንዲወስዱን፤ ከተሳሳተ መንገድ እንዲጠብቁን፣ የእርሱን ሕያው ቃል በሰው ልጆች ባሕል
ሊመዘግቡና እኛ እንረዳው ዘንድ ጽፈዋል፡፡›› ብለዋል፡፡
ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት ዓላማ፡-
የመጀመሪያውና ዋነኛው ዓላማ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር እንደሆነና በአካል፣ በአካል ስም እና በአካል
ግብር ሦስት፤ በአገዛዝ፣ በሥልጣን፣ በመሳሰሉት መለኮታዊ ተግባራት አንድ እንደሆነ ሊገልጥልን ነው፡፡
(ዘፍ 1፡26፣ ማቴ 28፡19፣ ዮሐ 1፡1-4)
እግዚአብሔር ብቻ አምላክ እንደሆነ አምነን እንድንቀበል እና በጠባብ ደረት፣ በአጭር ቁመት የተገለጠው
ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ
የተወለደው የዘላለምን ሕይወት እንድናገኝ መሆኑ እንድናውቅ ነው፡፡ (ዮሐ 20፡30፤ ዮሐ 5፡13) መጽሐፍ
ቅዱስ በዋነኛነት ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያስተዋውቀናል፡፡ ብሉይ ኪዳንም ሆነ
ሐዲስ ኪዳን በበደላችን ምክንያት ከመጣው የባሕርያችን መጎስቆል ያዳነን፣ በመስቀል ላይ በፈሰሰው
ደሙ ያነጻንና የቀደሰንን ኢየሱስ ክርስቶስን በሚገባ ይገልጻሉ፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ ሌላው ዋነኛ ዓላማ የእግዚአብሔርን የፍቅር ሥራ፣ አሳቡንና ፈቃዱን ለሰው
ማስታወቅ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የፍቅር መልእክት ስለሆነ ሰዎች ሁሉ ተፋቅረው፣ እግዚአብሔርንም በማፍቀር ለቃሉም
በመታዘዝ፣ የክብር ትንሣኤና ዘላለማዊ ሕይወትን በተስፋ እንዲጠባበቁ ለመግለጽ፣ ለማነቃቃት
እንዲሁም እግዚአብሔር እኛን እንደወደደን እንድንወደው ይፈልጋልና በውሰጣችን ያለውን የእርሱን
ክብር ተቀብለን እንድናየው፣ እንድንሰማው፣ እንድናናግረው፣ እንድንይዘውም በመጽሐፍ ቅዱስ ነግሮናል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 3


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

እግዚአብሔር የሚጠላው ኃጢአትን እንጂ ኃጢአተኞችን እንዳልሆነ እንድንረዳና መቼ እንደምንጠራ


ስለማናውቅ ተዘጋጅተን እንድንጠብቅ ለማድረግ (ማቴ 24፡25)
በእግዚአብሔር ቤት እንዴት መኖር እንዳለብን ሊያስተምረን (1 ኛጢሞ 6፡15)
እንድንማርበትና እንድንገሠጽበት መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል፡፡
“በአጠቃላይ የእግዚአብሔር ትልቁ ስጠታ የሆነው መጽሑፍ ቅዱስ ዓለም እንዴት እንደተፈጠረ፣
ኃጢአት እንዴት ወደ ዓለም እንደገባ እንዲሁም በብዙ ትውልዶች የተነሡ ነቢያት ሕዝቡን እንዴት ወደ
እግዚአብሔር ለመመለስ ጥረት ያደርጉ እንደነበር የምናይበት መዝገብ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እነዚህ ሁሉ
ጥረቶች እንዴት እንዳልተሳኩና በመጨረሻ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ልኮ ሰውን ከኃጢአት
እንዳዳነው እንመለከትበታለን፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ሰው ከዲያቢሎስ ከርኩስ መንፈስ ጋር
የሚያደርገውን ጦርነት፣ እግዚአብሔር ደግሞ ለሰው ልጅ ድኅነትን ለመስጠት ያለውን ፍላጎት የሚገለጽበት
መዝገብ ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች መጻሕፍት ልዩ የሚያደርጉት ምንድናቸው?

ሀ. በጸሐፊዎቹ፡- በእግዚአብሔር መንፈስ በተነሣሱ ቅዱሳን ሰዎች የተጻፈ በመሆኑ፤ ራእ 11


ለ. በዕድሜው፡- ከመጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ (በፊት) የተጻፈ መጽሐፍ ባለመኖሩ መጽሐፍ ቅዱስ
ከየትኛውም መጽሐፍ ይልቅ የዕድሜ ባለጸጋ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመጀመርያው መጽሐፍ
የተጻፈው ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ ትውልድ በሆነው በሄኖክ ሲሆን ይህም በ 1486 ዓ.ዓ ወይም 4014 ቅ.ል.ክ
የተጻፈ ነው፡፡
ሐ. ዘመን የማይሽረው በመሆኑ፡- በብዙና በተለያዩ ደራስያን የተጻፉ መጻሕፍት የአንድ ወቅት መወያያ ርእስ
እየሆኑ በዚያው እያረጁ ለታሪክ ወይም ለመረጃ ብቻ የተቀመጡና የሚቀመጡ ሲሆኑ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ግን
የማያረጅ፣ የዘመን ብዛት የማይገታው፣ ሥርዓተ ማኅበር የማያሻሽለው ዘላለማዊ ነው፡፡ ‹‹የአምላካችን ቃል
ግን ለዘለዓለም ጸንታ ትኖራለች፡፡›› ኢሳ 40፡8 (1 ኛ ጴጥ 1፡25፣ ዘዳ 31፡ 19፣ ገላ 26፡29፣ ማቴ 24፡35፣ 1 ኛጴጥ 12፡
5)
መ. የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት ስላለው ሁኔታ በርግጠኝነት የሚናገር በመሆኑ፡- መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጅ
ከተፈጠረ ከሺህ ዓመት በኋላ የተጻፈ ቢሆንም እንኳ የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት ስለተፈጸመው የሥነ
ፍጥረት ሥራ በእርግጠኝነት ይናገራል፡፡ ‹‹እግዚአብሔር መጀመሪያ ሰማና ምድርን ፈጠረ፡፡›› ዘፍ 1፡1
በተጨማሪም የሰው ልጅ ከተፈጠረ በኋላ ጸሐፊው ከነበረበት ዘመን በፊት ስላልው ሲናገርም እንዲሁ
በእርግጠኝነት ነው፡፡ የሚያስቀምጣቸውንም ነገሮች ልክ እንደ አንድ ሌላ የታሪክ ወይም የምርምር መጽሐፍ
በመላምት (በይሆናል፣ ሳይሆን አይቀርም) እያለ ሳይሆን በእርግጠኘነት ነው፡፡ ለምሳሌ ‹‹እግዚአብሔርም
አብርሃምን አለው፤ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ፡፡›› (ዘፍ
21፡1) አለ እንጂ ‹‹ እንዲወጣ ሳያደርገው አልቀረም›› አላለም፡፡
ሠ. ወደ ፊት ስለሚመጣው ነገር በእርግጠኝነት የሚናገር ስለሆነ፡- መጽሐፍ ቅዱስ ያለፈውን
እንደሚያስረግጥ ሁሉ የሚመጣውንም (መጻኢውንም) ካለ ምንም ጥርጥር በእርግጠኝነት የሚናገር በመሆኑ
ልዩ ነው፡፡ ሌሎች መጻሕፍት ወደ ፊት ስለሚመጣው ነገር የራሳቸውን መላምት በጥናትና ምርምር አልያም
በግምት ‹‹እንዲህ ሊሆን ይችላል›› ቢሉ እንጂ ‹‹እንዲህ ይደረጋል›› በማለት በእርግጠኛነት አይናገሩም፡፡
ለምሳሌ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፣ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ
ትጠራዋለች፡፡›› (ኢሳ 7፡14) አለ እንጂ ‹‹ ትፀንስ ይሆናል፣ ትወልድ ይሆናል›› እያለ አልተናገረም፡፡ ይህ ቃለ
ትንቢትም ነቢዩ ከተናገረ ከ 700 ዓመት በኋላ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጻሜን አግኝቷል፡፡ በዚህም ሁሉን

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 4


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ዐዋቂ በሆነው እግዚአብሔር መሪነት የሚጻፉት ቅዱሳን የትንቢታቸው ቃል ሳይፈጸም እንደማይቀር፣


በመፈፀሙም ደግሞ እውነተኛነታቸው እንደሚረጋገጥ እናሰተውላለን፡፡
ረ. የሚያነቡትንና የሚሰሙትን ስለሚባርክ፡- ሌሎች መጻሕፍት በማንበብ ዕውቀት ይገኛል፣ መጽሐፍ
ቅዱስን በማንበብ እና ቃሉን በመስማት ግን ቡራኬ ይገኛል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት መጻሕፍት
ትእዛዛት ብቻ አይደሉም፣ ነገር ግን ለእኛ ኃይልን የሚሰጡን መንፈሳዊ ቃልኪዳኖች ጭምር ናቸው እንጂ፡፡
በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ ለእኛ የተሰጠን እንድናጠናው ብቻ አይደለም ፤ ይልቁንም መንፈሳዊ ሕይወትን
እንድንለማመድበት፣ የሕይወታችን መመሪያ እንድናደርገው እና በቅድስና እንድመላለስበት ነው፡፡
ሰ. በይዘቱ፡- ሌላው መጽሐፍ ቅዱስን በዓይነቱ ልዩ የሚያደርገው በውስጡ ታሪክ፣ ግጥም፣ ጽሑፍ፣ ጥበብ፣
ትንቢትና መልእክቶችን መያዙ ነው፡፡ እነዚህም በተለያዩ ክፍለ ዘመናት በተነሡ ነቢያት፣ ፈላስፎች፣ ጠቢባን
ሰዎች፣ ነገሥታት፣ የበግ እረኞች እና የአሣ አጥማጆች የተጻፉ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሰዎች በተለያየ ጊዜና
ቦታ ቢጽፉትም ግን ሙሉ መጽሐፉ አሳቡ ወጥና እርስ በርሱ የማይጋጭ ነው፡፡
ሸ. መጽሐፍ ቅዱስ የሁሉ ምንጭ ወይም እናት ነው፡- በዓለም ላይ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉንም ነገር
ለሰው ልጅ የሚነግር፣ የሚያስረዳ ጠቃሚውንም ጎጂውንም ለይቶ የሚያስተምር፣ ለሌሎች መጻሕፍት
እናት ወይም ምንጭ የሆነ ለሁሉ አስተማሪ የሆነ መጽሐፍ የለም፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ ምንጭነት
1. የሃይማኖት መሠረት (ምንጭ) ነው፡- የነገረ መለኮትን ትምህርት፣ የአምልኮት ሥርዓት፣ ሰው በእምነት
ወደ እግዚአብሔር የሚደርስበትን መንገድ በሰው አእምሮ ሊዳሰስ፣ ሊለካ፣ ሊመረመር የማይችለውን
ሁሉ እንደ ሰው አቅም ተንትኖ የሚያስረዳ በመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ የሃይማኖት መሠረት ነው፡፡ (2 ኛ
ጢሞ 4፡7፣ይሁ 3፡20፣ 1 ኛ ቆሮ 16፡13)
2. የሥነ ምግባር መሠረት ነው፡- በሃይማኖት የሚኖር ሰው ሃይማኖቱን የሚጠብቅባቸው መሠረታዊያን ሥነ
ምግባራት ያሰፈልጉታል፡፡ ይህንንም መጽሐፍ ቅዱስ በአጽንዖት ሲፈልጽ ‹‹ሃይማኖት ያለ ምግባር በራሷ
የሞተች ናት፡፡›› (ያዕ 2፡17) ሲል ያስረዳል፡፡ ስለሆነም የሰው ልጅ ሊፈጽሙት የሚገባው ሥነ ምግባራት
በብሉይም በሐዲስም ተዘርዝረዋል፡፡ (ዘጸ 20፡7-17፤ ማቴ 5፡21)፡፡ የሰዎች ሥነ ምግባር ጥሩ መሆን ብቻ
ሳይሆን ከክፋት መራቅና ፈተናን ማለፍ የሚቻለው በመጽሑፍ ቅዱስ እንደተገለጠው እግዚአብሔርን
በማወቅና እርሱን በመፍራት ላይ ሲመሠረት ነው፡፡
3. የሕግ ምንጭ ነው፡- ብዙ ነገሮች ከመመኘት ጀምሮ እስከ መስረቅና መግደል ድረስ በሕግ የተከለከሉ
ሆነው እስከ ዘመናችን ዘልቀዋል፡፡ (ዘጸ 20፡12-17) ቀዳማዊ ሕግም ‹‹ከገነት ዛፍ ትበላለህ፣ ነገር ግን
መልካመንና ክፉውን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ›› የሚለው ሲሆን፤ የሕግ ሁሉ ፍጻሜ ግን ‹‹ጌታ
አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኃይልህ ውደድ፤ ታላቂቱና የመጀመሪያይቱ ሕግ
(ትእዛዝ) ይህች ናት ፡፡ የምትመስላት ሁለተኛይቱም ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ የምትለዋ ናት፡፡
ኦሪትና ነቢያትሁሉ በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ጸንተዋል ›› ማቴ 22፡34 የሚለው የፍቅር ሕግ ነው፡፡
ስለሆነም መጽሐፍ ቅዱስ የሕጎች ሁሉ ፈጻሜና መሠረት ነው፡፡ የሌሎች ዓለማውያን ሕጎችም መነሻ
ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡
4. የሥርዓት ምንጭ ነው፡- ሥርዓትን መጠበቅንና በሥርዓት የመኖር አስፈላጊነት መንፈሳዊ ግዴታም
እነዳለብን የሚነግረን መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ የነበረውን፣ የቀደመውን፣ የሚጠቅመውን ነገር፣ መለወጥም
መተላለፍም የሚያረክስ የሚጎዳ መሆኑን፣ ከሥርዓት መራቅ፣ ሥርዓትንም መጥላትና ድጋፍ አለማድረግ
ጉስቁልናን እነደሚያስከትል መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ (ኢሳ 24፡3፣ መዝ 118፡118፣ 1 ኛ ተሰ 5፡14፣ 2 ኛ ተሰ 3፡
6)
5. የገድላት፣ የድርሳናት፣ የተአምራትና የሌሎች መንፈሳዊያት መጻሕፍት ምንጭ ነው፡- መጽሐፍ ቅዱስ
በቅዱሳን ሰዎች መንፈሳዊ ሥራና ገድል የተሞላ መጽሐፍ ነው፡፡ (ዘፍ 4፡2-8፣ ማቴ 23፡35፣ ዕብ 11፡4፣ ሕዝ
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 5
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

14፡14-20፣ ዳን 3፡1፣ 2 ኛቆሮ 11፡22) በውስጡም የድርሳናትን የአጻጻፍ ስልት ይይዛል፡፡ (ሉቃ 3፡3፣ ሐዋ 1፡1)
በተአምር ደረጃም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሥፍር ቊጥር የሌላቸው በአምላክ ረቂቅ ጥበብ የተሰሩ
ተአምራት እንደሚገኙ እሙን ነው፡፡ (2 ኛ ነገ 6፡17፣ ዮሐ 2፡1-11፣ ሐዋ 14፡8-13፣ ሐዋ 5፡ 15-16)
6. የኪነ ጥበብ ምንጭ ነው፡- የምሕንድስና (ዘጸ 25፡21፣ ዘጸ 31፡1-11፣)፤የሥነ ጽሑፍ (ሐዋ 18፡24) የመሳሰሉትን
ጥበባት የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡
7. የሥራ አመራርና የፍትሕ ርትዕ፡- ለዓለም መንግሥታት መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን፣ በመንግሥትና
በሕዝብ መካከል ልዩነቶች እነዳይሰፉ፣ ሰላም እንዲሰፍን ጥላቻና መለያየት እንዲጠፋ፣ መልካም
አስተዳደር፣ ፍትሕ ርትዕ እነዳይጓደል ከነሙሴ ዘመን ጀምሮ ለሥራ አመራር ጥበብ (ሳይንስ) ታላቅ
መሠረት የጣለ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ (ዘጸ 18፡13-27)
8. የሥራ መሠረት ነው፡- ሥራን የጀመረው እግዚአብሔር ነው፡፡ (ዘፍ 1፡1፣ መዝ 111፣ ዘፍ 2፡15) መጽሐፍ
ቅዱስ ለሰው ልጆች ‹‹ገነትን ቆፍራት ተንከባከባት›› እንዲሁም ‹‹ ሊሠራ የማይወድ አይብላ›› (2 ኛ
ተሰ 3፡8-10) በማለት በሥራችን ሁሉ ቅንዓት፣ ታማኝነት፣ ታታሪነት፣ትጋት…ወዘተ እንዲኖረን
በአጽንዖት ያስገነዝበናል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ መቼ፣ በማን እና የት ተጻፈ?

መጽሐፍ ቅዱስ መቼ ተጻፈ?


የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፍት መጽሐፍ ቅዱስን የተጻፉበት ዘመን ይለያያል፡፡ እንደ ብሉያትና ሐዲሳት
መምህራን አስተምህሮ ሁለቱም ኪዳናት የተጻፉበት ጊዜና ወቅት የተረዳ ነው፡፡ ይህም ከ 1400 ዓ.ዓ (ዓለም
ከተፈጠረ ከ 1400 ዓመት በኋላ) እስከ 100 ዓ.ም ድረስ ያለውን ጊዜ ያጠቃልላል፡፡
መጀመሪያ የተጻፈው መጽሐፍ መጽሐፈ ሄኖክ ሲሆን እርሱም በ 1486 ዓ.ዓ ወይም በ 4014 ቅ.ል.ክ
ገደማ ተጽፏል፡፡ ከዚህም ቀጥሎ እስራኤል በግብጽ ሳሉ በፈርዖን ዘመን መጽሐፈ ኢዮብ ተጽፏል፡፡
በ 3843 ዓ.ዓ እስራኤል ከግብጽ ወጡ፤ በዚህም ጊዜ መጽሐፈ ኦሪት ተጻፈ፡፡ መዝሙረ ዳዊት ደግሞ
በ 4407 ዓ.ዓ ሳዖል ሞቶ ንጉሥ ዳዊት በነገሠ ጊዜ ተጽፏል፡፡ ከእነዚህም በተጨማሪ ከብሉይ ኪዳን፡
መጽሐፈ ኢያሱ- 1400 ቅ.ል.ክ
መዝሙረ ዳዊት- 100 ቅ.ል.ክ
መጻሕፈተ ሰሎሞን- ከ 1000 ቅ.ል.ክ-900 ቅ.ል.ክ
ትንቢተ ኢሳይያስ- 700 ቅ.ል.ክ
ትንቢተ ዳንኤል፣ ትንቢተ ኤርሚያስ፣ ትንቢተ ሕዝቅኤል- 500 ቅ.ል.ክ
ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት መጨረሻ የተጻፈው መጽሐፈ ሲራክ- 80 ቅ.ል.ክ
ከሐዲስ ኪዳን፡-
የመጀመሪያ የሆነው የቅዱስ ጳውሎስ የገላትያ ሰዎች መልእክት በ 45 ዓ.ም ተጽፏል፡፡
የመጨረሻ የሆነው የዮሐንስ ራእይ ደግሞ በ 98 ዓ.ም ተጽፏል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የት ተጻፈ?
 እንደጊዜው ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት ቦታም ይለያያል፡፡ አሁን ባለው መልክዓ ምድራዊ
አቀማመጥ አንጻር ሲታይ ሦስቱንም አኅጉራት ማለትም እስያን፣ አፍሪካንና አውሮፓን ያጠቃልላል፡፡
ለምሳሌ፡
 በእስያ ውስጥ ፡-
የሙሴ መጻሕፍት-በሲና ምድረ በዳ (ሳዑዲ ዐረብያ)

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 6


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

መጽሐፈ ኢያሱ- በኢየሩሳሌም


መጽሐፈ አስቴር-በፋርስ (ኢራን)
ትንቢተ ዳንኤል-ባቢሎን (ኢራቅ)
ራእየ ዮሐንስ- ፍጥሞ (ቱርክ)
 በአውሮፓ ውስጥ፡- የጳውሎስ መልእክታት-በሮምና ግሪክ
 በአፍሪካ ውስጥ፡- የማርቆስ ወንጌል- በግብጽ
የአሥራው ቅዱሳት መጻሕፍት አሠያየም
መጽሐፍ ቅዱስ የብዙ ቅዱሳን መጻሕፍት መድበል እንደመሆኑ መጠን በውስጡ ላካተታቸው ቅዱሳት
መጻሕፍት በተለያየ መልኩ ስያሜ ተሰጥቷል፡፡
1. በጸሐፊዎቻቸው ቅዱሳን ስም የተሰተሙ፡- ቅዱሳን መጻሕፍት የሚከተሉት ናቸው፡- መጽሐፈ ኢያሱ፣
መጽሐፈ ሄኖክ፣ መጽሐፈ ሳሙኤል፣ መጽሐፈ ዕዝራ፣ መጽሐፈ ነህምያ፣ ዐራቱ ወንጌላት፣ የቅዱስ
ጴጥሮስ፣ የቅዱስ ዮሐንስ፣ የቅዱስ ያዕቆብና የቅዱስ ይሁዳ መልእክታት ወዘተ ናቸው፡፡
2. ከይዘታቸው አንፃር የተሰየሙ፡- ይህም ማለቱ መጽሐፉ ከያዘው አሳብ፣ ከሚገልጸው ታሪክ በመነሳት
የተሰየትሙ ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል ጥቂቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ኦሪት ዘፍጥረት፡ የሥነ ፍጥረታትን ነገር ስለሚያስረዳ
ኦሪት ዘጸአት፡ ‹‹ዘጸአት›› ማለት መውጣት ማለት ሲሆን ይህም የእስራኤልን ከግብጽ መውጣት
ስለሚተርክ ነው፡፡
ኦሪት ዘሌዋውያን፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ለክህነት የተመረጡ የአሮን ልጆች ሌዋውያን ካህናት
አገልግሎትን እንዴት ትፈጸም እንደሚገባቸው ስለሚያስረዳ
ኦሪት ዘኁልቊ፡ ኁልቊ ማለት ቊጥር ማለት ነው፤ ይህም ስለ እስራኤላውያን መቆጠር የሚናገር
መጽሐፍ በመሆኑ ነው፡፡
መጽሐፈ መሳፍንት፡ በእስራኤል ስለ ነገሡት መሳፍንት ስለሚናገር
መጽሐፈ ነገሥት፡ ስለ ነገሥታት ታሪክና ሥራ ስለሚተርክ
መጽሐፈ ምሳሌ፡ በምሳሌያዊ ይዘት ስለተጻፈ
መጽሐፈ ዜና መዋዕል፡ ስለነገሥታት የዕለት ክንውን ስለሚያትት
መጽሐፈ ኩፋሌ፡ ከኦሪት የተከፈለ ስለሆነ
የሐዋርያት ሥራ፡ የሐዋርያትን ገድል ስለሚዘግብ
3. በባለታሪኩ ስም የተሰየሙ፡- በመጸሐፉ ውስጥ የሚገኘው ታሪክ ወይም ምስጢር ባለ ታሪክ ባለ ታሪክ
አንፃር የሚሰየም የአሰያየም ስልት ነው፡፡ እነዚህም፡ መጽሐፈ ሩት፣ መጽሐፈ አስቴር፣ መጽሐፈ ዮዲት…
ወዘተ
4. በጸሐፊውና በይዘታቸው (በሁለቱም) የሚጠሩ፡- መኃልየ መኃልየ ዘሰሎሞን፣ የትንቢት መጻሕፍት
(ትንቢተ ኢሳይያስ፣…) እና ወንጌላት (የማቴዎስ ወንጌል…) ጸሐፊያቸውንና ይዘታቸውን የሚገልጹ
መጻሕፍት ናቸው፡፡
5. በከተማ (አገር) ስሙ የሚጠሩ፡- ከዐሥራ ዐራቱ የጳውሎስ መልእከቶች ዘጠኙ መልእከታቱ በተላኩላቸው
አገሮች (ከተሞች) ስም የሚጠሩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡ ሮሜ፣ ቆሮንቶስ፣ገላትያ፣ ኤፌሶን፣ ተሰሎንቄ፣
ፊልጵስዮስ፣ ዕብራውያን፣ ቆላሲስ
6. በተላኩላቸው ሰዎች ስም የሚጠሩ፡- ጢሞቴዎስ፣ ፊልሞና፣ ቲቶ…ናቸው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በማን ተጻፈ?
አስቀድመን እነደገለጽነው የመጽሐፍ ቅዱስ አስገኝው እግዚአብሔር አምላክ ቢሆንም ወደ እኛ
የመድረሱ ምክንያቶች /መንገዶች/ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ያነሳሳቸው ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፡፡ እኒህ
ቅዱሳን እንዴት ጻፉት ከተባለ፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 7


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሀ. በእግዚአብሔር ፈቃድ ትእዛዝ (ዘጸ 17፡14፣ ራእ 1፡17-19፣ ዘጸ 34፡27፣ ኢሳ 8፡1፣ ኤር 36፡2)


ለ. በመንፈስ ቅዱስ መሪነት
ሐ. በእግዚአብሔር መገለጥ፡- ቸር የሆነው አምላካችን እግዚአብሔር ለቅዱሳት በራእይ፣ በሕልምና ፊት
ለፊት እየተገለጠ ያጽፋቸው ነበር፡፡ ዘኁ 12
መ.ከእውነተኞች ምስክሮች፡- በጥንቃቄና በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት በመሰብሰብ ጽፈውታል፡፡ ሉቃ 1፡
14
ሠ. ቅዱሳን በየራሳቸው የአጻጻፍ መንገድ ቋንቋና ባሕላቸውን ጠብቀው ጽፈውታል፡- ለምሳሌ፡- ቅዱስ
ማቴዎስ የዕብራውያንን ባህል ጠብቆ፣ ቅዱስ ሉቃስ ሥዕላዊ የሆነውን ወንጌሉን የግሪካውያንን ባሕል ጠብቆ
ጽፎታል፤እነዲሁም የመጽሐፈ አስቴር ጸሐፊ የሆነው መርዶክዮስ በአጻጻፉ የቤተ መንግሥት ዕውቀት
እነዳለው ይታወቃል፡፡
ረ. በብራናና በክርታስ ሰሌዳነት፣ በቀረክሃና በላባ ብዕርነት፣ ከእንስሳትና ከዕፅዋት ተቀምመው በተገኙ
ቀለማት ተጽፈዋል፡፡
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ሰዎች በእግዚአብሔር እየታዘዙ የጻፉት መሆኑን እንረዳለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ
በተለያየ ጊዜና ቦታ ከተለያዩ የሥራ መስክ በተጠሩ ሰዎች እንደተጻፈ ይታመናል፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ሰዎች ወደ
እዚህ ግብር ከመረጣቸው አስቀድሞ የተለያየ የሥራ ተግባር እንደነበራቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡
ለምሳሌ፡-
ከእረኝነት-ሙሴ (ዘጸ 3፡1)
ከካህን- ሕዝቅኤል (ሕዝ 1፡3)
ከዓሣ አጥማጅነት ጴጥሮስና ዮሐንስ (ማቴ 4፡ 18-22)
ከነገሥታት-ዳዊትና ሰሎሞን (ዜና 29፡ 28)
ከቀራጭ-ማቴዎስ (ቆላ 4፡4)
ከእነዚህ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች በእግዚአብሔር መንፈስ እየተገዙ ቢጽፉም በብሉይና
በሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች መካከል ልዩነት አለ፡፡ ይኸውም፡ የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች አምላክ ይወርዳል
ይወለዳል እያሉ ሲጽፉ (ኢሳ 7፡14) የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ግን አምላክ ተወለደ፣ ተጠመቀ፣ አስተማረ፣
ሞተ፣ ተቀበረ፣ ተነሣ፣ ዐረገ፣…ወዘተ እያሉ ጽፈዋል፡፡ (ሉቃ 2፡7፣ ማቴ 3፡15፣ ሉቃ 24፡ 51) የብሉይ ኪዳን
ጸሐፊዎች የጌታን ነገር ለማየት ቢመኙም በዘመናቸው አልሆነላቸውም፤ዐረፍተ ዘመን ገቷቸዋል፡፡ የሐዲስ
ኪዳን ጸሐፊዎች ግን ጻድቃን ሊያዩና ሊሰሙ ወደው ያልሆነላቸውን ሰምተዋል፣ አይተዋል (ማቴ 13፡16-17) ፡፡
ስለሆነም በዐይናቸው ያዩትን፣ በጆራቸው የሰሙትን፣ በእጃቸው የዳሰሱትን ተናግረዋል፤ ጽፈዋል፡፡ ያየነውን፣
የሰማነውን፣ ለእናንተ ደግሞ እንጽፍላችኋላን እያሉ አስረድተዋል፡፡ (1 ኛ ዮሐ 1፡3)

መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ የእግዚአብሔር መንፈስ ርዳታ ያስፈለገበት ለምን ምንድነው?

የሰው ልጅ አስቦ ሊደርስባቸው የማይችለውን እጅግ በጣም ጥልቅና ረቂቅ የሆኑ ነገሮችን የያዘ መጽሐፍ
በመሆኑ
ያለ ስህተት ያለ መጋጨት . . . ወዘተ እንዲጻፍ ለማድረግ
አንድ ዓይነት የሃይማኖት፣ የሥነ ምግባር ሥርዓት እንዲኖረን ለማድረግ
እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሚፈልጋቸውን ነገሮች እንዲጻፉና የማይፈልጋቸው ጉዳዮች ደግሞ
እንዳይጻፉ ለማድረግ ማለትም አንድን ጉዳይ የመምረጥና ሌላውን ጉዳይ የመተው ችሎታ
እንዲኖራቸው ነው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 8


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመጽሐፉ አከፋፈል በጸሐፊው ዕውቀት፣ ችሎታ፣ መጠን የተገደበ ሳይሆን የመጽሐፉ ባለቤት
እግዚአብሔር በሚገልጠው መጠን ይሆን ዘንድ ፤ እንዲሁም የሰው ዕውቀት በጊዜ የተወሰነና ከጊዜ
ውጭ መመልከት የማይቻለው ነው፤ ስለሆነም ዘለዓለማዊ ስለሆነው ስለ እግዚአብሔር ለመናገር ያለ
እግዚአብሔር መንፈስ አይቻልም፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ለጸሐፊዎቹ እጅግ አስፈልጓል፡፡ (1 ኛ ቆሮ 2፡11)

መጽሐፍ ቅዱስ በምን ቋንቋ ተጻፈ?


አብዛኞቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በዕብራይስጥ ቋንቋ የታጻፉ ሲሆን ትንቢተ ዳንኤል ግን የተጻፈው
በአረማይክ ቋንቋ ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት በዕብራይስጥ ከተጻፈው ከማቴዎስ ወንጌል በቀር የተጻፉት
በዘመኑ የአብዛኛው ሕዝብ መነጋገሪያ በነበረው በጽርዕ (በግሪክ) ቋንቋ ነው፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም

አብዛኞቹ ቅዱሳት መጻሐፍት የተጻፉት በዕብራይስጥና በግሪክ ቢሆንም መጻሐፍቱ ለሁሉም መዳረስ ስለሚገባቸው ወደ ሌላ ቋንቋ ይተረጎሙ
ዘንድ እግዚአብሔር መተርጉማንን አስነሣ፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ፈቃዱንና ትእዛዙን በአሕዛብ ምድር እንኳን እንዲታወቅ ዓይነተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡
ስለዚህም ብሉይ ኪዳን ከክርስቶስ ልደት በፊት ወደ ግእዝና ግሪከ የተተረጎመ ሲሆን የአዲስ ኪዳን መጻሐፍትም ወደ ሱርስት፣ ላቲን፣ ግእዝና ሌሎች
ቋንቋዎች ተተርጉመዋል፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በዓለም መድረክ

በዘመነ ብሉይ (ቅድመ ልደተ ክርስቶስ) የተሠሩ ትርጉሞች

መጻሕፍተ ብሉያት ለመጀመሪያ ጊዜ የተተረጎሙት ወደ ግእዝ ሲሆን ይህም በ 980 ቅ.ል.ክ ነው፡፡ ይህ ትርጉም ከሆነ ከ 480 ዓመት በኋላ
(5 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቅ.ል.ክ) ከባቢሎን ምርኮ የተመለሱት አይሁድ ዕብራይስጥ ጠፍቶባቸው ስለ ነበር በወቅቱ የነበሩት ሊቃውንት
የዕብራይስጡን ሀሳብ በአረማይክ አሳጥረው (Paraphrase) ተርጉመውታል፡፡ ይህም ትርጕም ‹‹ኤል ታርጉም›› (El Targum)1 የሚባለው ሲሆን፤
መጀመሪጀያ በቃል በኋላም በጽሑፍ የተረጐሙት ትርጕም ነው፡፡ ከዚህም በኋላ በ 284 ቅ.ል.ክ ሰብዓ ሊቃናት መጻሕፍቱን ወደ ግሪክ ቋንቋ ተርጉመውታል፡፡
ይህ ትርጉምም የዓለም ጥንታዊው ትርጉም ቢባልም የግእዙ ትርጉም እንደሚቀድመው ከዓመቱ መረዳት ይቻላል፤ መካከላቸው 696 ዓመት ልዩነት
ይታያልና፡፡

የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም የተደረገው በ 284 ቅ.ል.ክ በግብጽ ንጉሥ ዳግማዊ በጥሊሞስ ፊላደልፎስ(285-247 ቅ.ል.ክ) (Ptolemy II
Philadelphus)
ጠሪነት ከፍልስጥኤም በመጡ ግሪክ ተናጋሪ አይሁዳውያን ነው፡፡ ይህ ንጉሥ በእስክንድርያ ላቋቋመው አዲስ ቤተ መጻሕፍት ከተቻለ
የዓለምን ሁሉ መጻሐፍት ለመሰብሰብ ተመኝቶ እንደነበርና ብዙ መጻሐፍትን እንደሰበሰበ ይነገራል፡፡ በጣም ተፈላጊ የሆነውን የአይሁድ የሕግጋት
2
መጽሐፍ ቅጅ በቤተ መንግሥቱ ቤተ መጸሕፍት አለመኖሩን በመረዳቱ ደብዳቤ ጽፎ አርስቲያስ እና ሌሎች ያሉበትን የመልእክተኞች ቡድን
ኢየሩሳሌም ለሚገኘው ሊቀ ካህናት አልአዛር (Eleazar) ላከ፡፡ በዚህም መልእክቱ የአይሁድን ሕግ ቅጂና እሱን ወደ ግሪክኛ መተርጎም የሚችሉ
ምሁራንን ወደ እስክንድርያ እንዲልክለት ጠየቀ፡፡ መልእክቱም የተሳካ ውጤት አስገኘ፤ ሊቀ ካህኑ አልአዛር 72 ሊቃውንትን መርጦ ልኮለታል፡፡
3
በሊቃውንቱ ቁጥርም ትርጉሙ ሰብዓ ሊቃናት (ሰባው ሊቃውንት) (Septuagint) (LXX) የሚል ስያሜ ተሰጠው፡፡ እነዚህም ሊቃውንት
መጻሐፍቱን ወደ ግሪክ ድንቅ በሆነ ሁኔታ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ተርጉመውታል፡፡

ትርጉሙም የአይሁድ ካህናት፣ ሽማግሌዎችና ሕዝብ ተሰብስበው በተገኙበት ለብዙ ቀናት ተነበበ፡፡ ከምንጩ ከዕብራይስጡ ጋር
ፍጽም ተመሳሳይነት ያለው ሆኖ በመገኘቱ ሁሉም በአድናቆት ተቀብለውታል፡፡ ንጉሡም መጽሐፍቱን በቤተ መጻሐፍቱ አስቀምጧቸዋል፡፡
በእስክንድርያ ውስጥ የነበሩ አይሁዳውያንም በየምኩራባቸው እንዲጠቀሙበት የአዲሱ ትርጉም ቅጂዎችን እንዲሰጣቸው ንጉሡን
4
ጠይቀው ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነርሱም በትርጉሙ ላይ ምንም ለውጥ ሳያደርጉ ለምኩራባቸው ለመገልገያነት ተጠቅመውበታል፡፡

ቀስ በቀስ ይህ ትርጉም በመስፋፋት በግሪክ ተናጋሪ አይሁዳውያን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ በታሪክ እንደምንረዳው
በክርስቶስ ዘመን ብቻ በእስራኤል ከሚኖር አይሁዳውያን ከእስራኤል ውጪ የሚኖሩት አምስት ስድስት እጥፍ ይበዙ ነበር፡፡ እነዚህም
1
ይህ ትርጉም በውስጡ የቃል በቃል ትርጉም ብቻ ሳይሆን ማብራርያ ጭምር የያዘ ነው፡፡
2
ይህ ሰው ከመልእክተኛ ቡድኑ መካከል አንዱ ሲሆን ይህንን ታሪክንም ለወደንድሙ ለፊሎከራጥስ (Philocrates) በጻፈው ደብዳቤ ላይ ጽፎ ያቆየልን እርሱ ነው፡፡
3
በመጻሕፍት የሕዳግ ማስታውሻ ላይ LXX የሚለውን ጸሐፊያን አብዛኛውን ጊዜ የሚጠቀሙ ሲሆን፤ በላቲን ቁጥር 70 ማለት ነው፡፡
4
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በግእዝ ቋንቋ፣ ቀ/ዶ/ር ም/ሥላሴ ገ/አማኑኤል፣ ገጽ 21-24

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 9


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

አይሁዳውያን የዕብራይስጥን ቋንቋ ቀስ በቀስ ስለረሱ የሚናገሩት በግሪክ ነበር፡፡ ስለሆነም እነርሱም ይጠቀሙት የነበረው ይህን የሰብዓ
5
ሊቃናት ትርጉም ነበር፡፡ ሐዋርያትም የአዲስ ኪዳን መጻሐፍትን በግሪክ ሲጽፉ የተጠቀሙት ይህን ትርጉም ነበር፡፡ ከዚህ በተጫማሪም ይህ
ትርጉም እግዚአብሔርን በማያውቁ በጣዖት አምላኪያን ዘንድ እንኳን ስለ እግዚአብሔርና ስለመሲሑ መምጣት እንዲታወቅ ከፍተኛ የሆነ
አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ይህም ለክርስትና መስፋፋት የበኩሉን ድርሻ ተጫውቷል፡፡

በዘመነ ሐዲስ (ድኅረ ልደተ ክርስቶስ) የተሠሩ ትርጉሞች

የሱርስት ትርጉም
6
ሱርስት በሶርያ የሚነገር የአረማይክ ዲያሌክት ነው፡፡ ጥንታዊ የሱርስት ትርጉም የሚባለው በ 170 ዓ.ም በታቲአኖስ(Tatian) አራቱ
ወንጌላትን በመደባለቅ የተሠራው ዲአቴሳሮን (Diatessaron) የተባለው ትርጉም ነው፡፡ ይህ ለብዙ ዓመታት ለቤተ ክርስቲያን መገልገያነት ከዋለ በኋላ
ሁሉንም መጻሕፍት ባለመያዙ ምክንያት ሌላ ትርጉም አስፈለገ፡፡

ስለዚህም እስካሁን ድረስ የሚገኘው ፔሽታ የተባለው ትርጉም ከ 411-435 ዓ.ም ባለው ዘመን ውስጥ ተሠራ፡፡ ትርጉሙም በኤዴሳው ሊቀ ጳጳስ
በራቡላ እንደተሠራ ይታመናል፡፡ የዚህ ትርጉም ከ 350 በላይ ጥንታዊ መዛግብት (manuscripts) አሁን ሲገኙ አብዛኞቹም የተሠሩት በ 5 ተኛው እና
6 ተኛው መ.ክ.ዘነው፡፡ ይህ ትርጉም ከግሪኩ እጅ ጽሑፍ ጋር በጣም ተቀራራቢነት አለው፡፡ በአንዳንድ ሊቃውንትም የኢትዮጲያው የተሠዓቱ ቅዱሳን
የግእዝ መጽሐፍ ቅዱስ የተተረጎመው ከዚህ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ከዚህም በኋላ በምስራቅ ሶርያ ማቡግ በተባለች ቦታ ሊቀ ጳጳስ የነበረው ፊሎክሲነስ (Philoxenus of Mabbug) ፊሎክሲኒዎስ
(Philoxenian) በመባል የሚታቀውን ትርጉም ሠራ፡፡ ከዚህም መጽሐፍ ወንጌላትና የትንቢተ ኢሳይያስ አንዳንድ ክፍላት ብቻ አሁን ተርፈው ይገኛሉ፡፡
የግብጽ የቅብጥ ትርጉም

በግብጽ ከታላቁ እስክንድር ጀምሮ ግሪክ በሰፊው የሚነገርባት የሰብአ ሊቃናት የግሪክ ትርጉም የተሠራባት ሀገር ብትሆንም በገጠር በባላገሩ ብዙ
ዲያሌክቶች ስለ ነበር የግድ ወደ ተለያዩ የክፍለ ሀገራቱ ዲያሌክቶች መተርጎም አስፈለገው፡፡ በዚህም የመጀመሪያው ከሁሉም ጥንታዊ የሆነው ሳዲያክና
ቱባይክ እየተባለ የሚጠራው ትርጉም በ 2 ተኛ መቶ ክፍለ ዘመን ተሠራ፡፡ ይኸውም በላዕላይ ግብጽ ባሉ ሕዝቦች የሚነገር ሳሂዲያክ (Sahidic) በተባለው
ዲያሌክት ነው፡፡

ከዚያ በመቀጠል ከሁሉም የግብጽ ዲያሌክት ይልቅ በሀገሪቱ የተስፋፋና ሁሉንም ዲያሌክቶች መግለጥ ወደሚችል በታህታይ (በታችኛው) ግብጽ
አካባቢ በሚኖሩ ሕዝቦች ወደሚነገረው ቦሃይሪክ (Bohairic) ዲያሌክት ተተረጎመ፡፡ ትርጉሙም ሐይሪክ ወይም ማምፌቲክ በመባል ይታወቃል፡፡
ከዚህም በኋላ ወደ ተለያዩ ዲያሌክቶች ተተርጎሟል፡፡

የአርመን ትርጉም

መጽሐፍ ቅዱስ ወደ አርመን የተተረጎመው በ 5 ተኛው መ.ክ.ዘ ቅዱስ ሜስሮብ ማሽቶትስ በተባለ አባት እና በፓትርያርኩ በይስሐቅ ነው፡፡ ቅዱስ
ሜስሮብ ወንጌልን ለማስፋፋት በሚያደርገው ሐዋርያዊ አገልግሎት ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ወደ ሕዝቡ ቋንቋ አለመተርጎም፤ ሕዝቡን ለመምራትና
ለአገልግሎቱ እንቅፋት ሆነበት፡፡ ሕዝቡ ለመጻፊያ የሚጠቀመው የግሪክ፣ የፋርስ እና ሶርያ ፊደላት የቋንቋቸውን የተወሳሰቡ ድምጾች መግለጥ እንደማይችሉ
በተረዳ ጊዜ ለአረመን ቋንቋ የሚሆን አዲስ ፊደላትን ሠራ፡፡ ከዚህም በኋላ ፓትርያርኩ ይስሐቅ መጽሐፍ ቅዱስን ከሶርያ ቋንቋ በ 411 ዓ.ም ወደ አርመን
ተረጎመ፡፡ ነገር ግን ትርጉሙ ፍጹም ስላልነበር የቅዱስ ሜስሮብ ደቀመዛሙርት የሆኑት ዮሐንስና ዮሴፍ ወደ ሶርያው የትርጓሜ ቤት ኤዴሳ እንዲሁም እስከ
ቁስጥንጥንያ ድረስ በመሄድ ብዙ የግሪክ ትርጉሞች ከሰበሰቡ በኋላ የግሪኩን ሰብአ ሊቃናትና የአርጌንስን ሄክሳፔላ በመከተል 434 ዓ.ም የትርጉም ሥራው
ተሠርቷል፡፡ የአርመን ቤተ ክርስቲያንም እስካሁን ድረስ የምትጠቀመው ይህን ትርጉም ነው፡፡

የዐረብኛ ትርጉም

ይህ ትርጉም ዮሐንስ በተባለ ጳጳስ በ 8 ተኛው መቶ ዓመት ተተርጉሟል፡፡ ከዚያም እንደገና ይስሐቅ በተባለ ሰው በ 10 ኛው መ.ክ.ዘ እንደገና
ተተርጉሟል፡፡ አብዛኞቹ የዓረብኛ የጥንት ትርጉሞች አሁን የሚገኙት በሲና ተራራ በቅድስት ካትሪና ገዳም ነው፡፡

የእስላቦኒክ ትርጉም

5
ስለ ሰብአ ሊቃናት ትርጉም በሰፊውና በማስረጃ የተደገፈ በ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ ሁለት ሺህ ዓ.ም›› በተሰኘው
መጽሐፍ ላይ ከገጽ 160-166 የተጻፈውን መመልከት ይቻላል፡፡
6
ዲያሌክት ማለት አንድን ቋንቋ በተለየ ዘዬ(ድምጸ ንባብ)፣ በተለየ ፊደል እና ሰዋስው በሆነ አካባቢ ብቻ ሲነገር ነው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 10


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ይህም ቄርሎስና ማቶዲየስ በተባሉ ሁለት ግሪካዊ ወንድማማቾች በ 10 ኛው ምዕተ ዓመት የተሠራ ነው፡፡ እነዚህ አባቶች ወደ እስላቦኒያ ሄደው
ሀገሩን ወንጌል አስተምረው መጽሐፍ ቅዱስን ከግሪክ ተርጉመዋል፡፡ ለትርጉም ሥራቸውም ሲሉ ለአገሪቱ አዲስ ፊደልን ቀርጸዋል፤ በዚህም የሥልጣኔና የሥነ
ጽሑፍ በር ከፍተዋል፡፡

የላቲን እና እንግሊዘኛ ትርጉሞች


7
በሁለተኛው መቶ ዓመት መጨረሻ አካባቢ በምዕራቡ ዓለም የላቲን ቋንቋ በሰፊ መነገር ጀመር፡፡ ስለዚህም ጥሩ የሆነ የላቲን ትርጉም አስፈለገ፡፡
ከዚህ በፊት የነበሩት የላቲን ትርጉሞች ጥሩ አልነበሩም፡፡ ሊቁ አውግስጢኖስ እነዚህን ትርጉሞች ይነቅፋቸው እንደነበርና የቃላት አጠቃቀማቸውም ተራ
የሆኑ ትርጉሞች እንደሆኑ በመጽሐፉ ላይ ገልጧል፡፡

በዐራተኛው መቶ ክፍለ ዘምን መጨረሻ አካባቢ (በ 390 ዓ.ም) ላይ በቃላት አጠቃቀሙም በሰዋሰውም ጥሩ ሆነ የላቲን ትርጉም ተሠራ፡፡
የትርጉሙም ስም ቩልጌት(Vulgate) ይባላል፡፡ ትርጉሙም common (ለሁሉም የሚሆን) ማለት ነው፡፡ በሕዝቡ ቋንቋ ስለተተረጎመ ነው ይህ ስያሜ
የተሰጠው፡፡ ይህንን ትርጉም የሠራው አባት ቅዱስ ጄሮም (አባ ሄሮኒመስ) በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ አባት የተወለደው በስትሪዶን (Stridon) (የአሁኗ
ቦዝኒያ (Bosnia)) በተባለች ከተማ በ 347 ዓ.ም ነው፡፡ በዚያም ጥሩ የሚባል የምዕራቡ ዓለም ትምህርትን ተምሯል፡፡ በዚህም በጣም
ታላቅ ተናጋሪ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ነገር ግን ልክ እንደ ብዙ አባቶች ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የዓለሙን ትምህርትና ሥራውን ትቶ
የቤተክርስቲያንን ጥልቅ ትምህርት ለመማር ወደ ምስራቁ ዓለም ሄደ፡፡ አብዛኛው የቤተ ክርስቲያን ጥልቅ አስትምህሮዎች ይሰጡ የነበረው
በግሪክ ቋንቋ ስለነበር እና ቅዱስ ጄሮም ያውቀው የነበረው የግሪክ ቋንቋ ትምህርቱን ለመረዳት በቂ ስላልነበር ግሪክን በሰፊው ተማረ፡፡

በተለያዩ የምስራቁ ዓለም ለብዙ ዓመታት ቆየ፡፡ ወደ ግብጽ በመሄድ ከዲዲሞስ ዕውሩ ሥር ተማረ፡፡ ከአንጾኪያ ከተማ ውጪ
በሚገኝ በርሃ ውስጥ በአንድ ዋሻ ውስጥ ለብዙ ዓመታት በጸሎትና በተጋድሎ ቆየ፡፡ በእነዚህ ዓመታትም በአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ያገለግል
ነበር፡፡ በቁስጥንጥንያ ውስጥ ለብዙ ዓመታት ከቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት እና ከተለያዩ አባቶች ሲማር ከቆየ በኋላ ወደ ሮም በመሄድ
የሮም ሊቀ ጳጳስ ለነበረው ለድማሰስ(Pope Damasus) ጸሐፊ ሆነ፡፡ ይህም ጳጳስ ጥሩ የሆነ የላቲን ትርጉም እንደሌለ ያውቅ ስለነበር
አባ ጄሮምን ጥሩ የሆነ በቤተ ክርስቲያን መገልገያ ሊሆን የሚችል የዐራቱን ወንጌላት የላቲን ትርጉም እንዲሠራ ጠየቀው፡፡ በዚህ ሰዓት አባ
ጄሮም ላቲን፣ ግሪክ (በኋላም ዕብራይስጥን) በጥሩ ሁኔታ ይናገር ስለነበር የትርጉም ሥራውን ሠራ፡፡ ምንም እንኳን ጳጳሱ ዐራቱን
ወንጌላት እንዲተረጉም ቢያዘውም እርሱ ሌሎቹን መጻሐፍት መተርጎም ጀመረ፡፡ ትርጉሙ ወደ 20 ዓመት የፈጀ ሲሆን ከአባ ጄሮምም
ጋርም ሎሎች በትርጉም ሥራው ተሳትፈዋል፤ ቢሆንም ትርጉሙ በእርሱ ስም ይጠራል፡፡ ከዚህም በኋላ እስከ ዕለተ ዕረፍቱ ድረስ
ለመጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩ ትርጓሜያትን በማዘጋጀት ኖሯል፡፡

ቢድ(Bede) የተባለ የሮም ካቶሊክ ጳጳስ የመጽሐፍ ቅዱስን አንዳንድ ክፍሎች ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጥንቱ እንግሊዘኛ (Old English) ቋንቋ
የተረጎመው በ 9 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ ነበር፡፡ ነገር ግን ከተለያዩ የካቶሊክ ጳጳሳት ተቃውሞ ደረሰበት፡፡ ይህም የሆነው መጻሕፍቱን ተራው
ምእመን (ከተማሩት ውጪ ያሉት) በተሳሳተ መልኩ ሊተረጉሙት ስለሚችሉ ሊያነቡት አይገባም በማለት ነበር፡፡ ተቀባይነትም ስላልነበረው ትርጉምን አሁን
አናገኘውም፡፡

ጆን ወይክሊፍ በ 13 መቶ ክፍለ ዘመን ሁሉንም መጻሕፍት ወደ እንግሊዘኛ ተረጎመ፡፡ ይህም የመጀመሪያው ሙሉ የእንግሊዘኛ ትርጉም
ያደርገዋል፡፡ ትርጉሙንም የሠራው ከቩልጌቱ የላቲን ትርጉም ነበር፡፡ ይህም ቢሆን የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አመራሮች መጻሕፍቱን አወገዟቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ዊልያም ቴንድል ከዕብራይስጡና ከግሪኩ ባማነጻጸር መጽሐፍቱን ወደ እንግሊዘኛ ተረጎመ፡፡ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንና የእንግሊዝ
መንግሥት በሰዓቱ እጅግ የተያያዙ በመሆናቸው የተነሣ መጻሕፍትን ወደ ሌላ ቋንቋ መተርጎም ወንጀል ስለነበር፤ ሊገደል ሲል ከእንግሊዝ ለመሸሽ ቢሞክርም
ተይዞ በእሳት ተቃጥሎ እንዲሞት ተደርጓል፡፡ መጻሕፍቱም ተሰብስበው ተቃጥለዋል፡፡

በጥንት ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ይገለበጥ የነበረው በእጅ ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ መጽሐፍ ቅዱስ በጣም ውድ ነበር፡፡ ለምሳሌ በቅዱስ ዮሐንስ
አፈወርቅ ዘመን ሐዲስ ኪዳን የአንድ ሰው የዓመት ደሞዝ ነበር ዋጋው፡፡ ነገር ግን ጉትንበርግ (Gutenburg) 1455 ዓ.ም የማተሚያ መሳርያን ከፈለሰፈ
በኋላ ሁሉም ነገር ተቀይሯል፡፡ ስለዚህም መጻሐፍት በብዛት፣ በፍጥነት መታተም ጀመሩ ዋጋቸውም እንደ ድሮ ውድ አልነበረም፡፡ ይህም በሕዝቡ ዘንድ
እንዲስፋፋና ተፈላጊነቱ እንዲጨምር አድርጓል፡፡ በዚህ የተነሣ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ወደ እንግሊዘኛ እንዲተረጎሙ ፈለገች፡፡ ይህን
ሀሳብ የሚደግፍ ጄምስ የተባለ ንጉሥም ነገሠ፡፡ 1611 ዓ.ም የመጀመሪያው የተፈቀደ(ወንጀል ያልሆነ) የእንግሊዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲዘጋጅ ፈቀደ፡፡
በዚህም የተነሣ ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የንጉሥ ጄምስ መጽሐፍ (King James Version(KJV)) ወይም የተፈቀደው መጽሐፍ (Authorized
Version) በመባል ይታወቃል፡፡ ከሌሎች ትርጉሞች በተለየ ይህ ትርጉም በአንድ ሰው ሳይሆን በጣም ብዙ የእንግሊዝ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት
እንዲተረጉሙት አድርጓል፡፡ በኋላም የእንግሊዝኛ ቋንቋ እያደገ በመምጣቱና የተለያዩ የትርጉም ለውጦች በማምጣቱ በ 19 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አዲሱ

7
በጥንት ቤተክርስቲያን የምዕራቡ ዓለም የሚባሉት ሮም፣ ስፔን፣ ጋውል (Gaul)፣ እንግሊዝ እና ሰሜን አፍሪካ (ከግብጽ በቀር) ያሉት ሀገራት ናቸው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 11


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የንጉሥ ጄምስ ትርጉም(New King James Version(NKJV)) የተባለው ትርጉም ተሠራ፡፡ ካሉት የእንግሊዘኛ እጅግ ብዙ ትርጉሞች ይህ ትርጉም (
NKJV) የተሻለ ቢሆንም እርሱም የራሱ የሆነ አንዳንድ ችግሮች አሉበት፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቻይና ቋንቋ፣ በዐሥራ ዐራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፋርስ (Persia) ቋንቋ ተተርጉሟል፡፡
እንደነዚህ ያሉ ጥንታዊ ትርጉሞች ቢኖሩም የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጉም ሥራ በአያሌው የተስፋፋው ለአለፉት ሁለት መቶ ዓመታት ውስጥ ነው፡፡ ከ 19 ኛ
መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ሁለት ሺህ በሚጠጉ የተለያዩ ቋንቋዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ ተተርጉሟል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ መተርጎሚያ መንገዶች

1. ቀጥተኛ (Literal)፡- ከተጻፈበት (ከአቀባዩ) ቋንቋ ቃል በቃል በቀጥታ መተርጎምን ይከተላል፡፡ በተጫለው መጠን የዓረፍተ ነገሩን
አቀማመጥ እንኳን አይቀይርም፡፡ ይህም ለአቀባዩ ቋንቋ ያደላል፡፡
2. ገላጭ(Dynamic)፡- ከቃላት ይልቅ ድርጊትን ሐሳብን በመግለጥ ተነባቢነት ላይ ያተኩራል፡፡ የዓረፍተ ነገሩን ሀሳብ ለመግለጥ
የራሱን አገላለጥ ይጠቀማል፡፡ ይህም ከአቀባዩ ይልቅ ለተቀባዩ ቋንቋ ያደላል፡፡ ለምሳሌ፡- በመጽሐፍ ቅዱስ ኅብስት፣ ዳቦና ቂጣ
የሚሉትን ወደ አማርኛው ሲተረጎም እንጀራ ተብለው ተተርጉመዋል፡፡

ትርጉሞች ለምን ተለያዩ?

1. የተጠቀሙት የትርጉም መንገድ መለያየት፡- ከላይ ከተጠቀሱት የትርጉም ዓይነቶች አንዱን ወይም ሌላውን መጠቀም የገጸ ንባብ
ልዩነት ያመጣል፡፡ ይህም በምስጢራዊው ትርጓሜ የሚቃና ነው፡፡ ከላይ ያሉት ትርጉሞች ሁለቱም የራሳቸው የሆነ ድክመት
አላቸው፡፡
የቀጥተኛ አተረጓጎም ስልት ድክመት የመጽሐፉን ውበት የሚያሳጣው ሲሆን ከዚህ በተጫማሪ አንዳንድ ፊሊጣዊ
ወይም ምሳሌያዊ ንግግሮች በአቀባዩ ቋንቋ ትርጉም የሚሰጡ ለተቀባዩ ግን ምንም ትርጉም የማይሰጡ ሊሆኑ ስለሚችሉ
የትርጉም መዛባትን ያስከትላል፡፡ ለምሳሌ፡- ‹‹አንቺ ሴት ከእኔ ጋር ምን አለሽ›› የሚለው የዕብራውያን አገላለጥ በሌሎች ቋንቋ
የተዛባ ትርጉም ሊሰጠው ይችላል (የመጽሐፍ ቅዱስ ባህል የሚለውን ንዑስ ርዕስ ተመልከት)፡፡
ልክ እንደዚሁም የገላጭ አተረጓጎም ስልትም የራሱ ድክመት አለበት፡፡ ይህም ትርጉሙ የሚወሰነው በተርጓሚው
የአረዳድ መጠን ላይ ስለሆነ ወደ ፈለገው ሀሳብ አጣሞ መተርጎም ይችላል፡፡ በአብዛኛው የእንግሊዘኛ ትርጉሞች ላይ የሚታየው
ይህ ችግር ነው፡፡
2. የዶግማ ልዩነት፡- የዚህ ችግር ምንጭ ሁሉም የእምነት ተቋማት የየራሳቸውን ዶግማ(መሠረተ እምነት) መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ
ለመስጠት ሲሉ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በሚያስገቡት ሆነ በሚቀንሱት ንባብ ምክንያት የሚፈጠር ነው፡፡
ለምሳሌ፡- ለዚህም እንደ ዋና ተጠቃሽ የሚሆነው የይሖዋ ምስክሮች (Jehovah's Witnesses) የአዲሱ ዓለም
8
ትርጉም በመባል የሚታወቀው ትርጉም ነው፡፡ ይህም ትርጉም ለራሳቸው መሠረተ እምነት እንዲመች አድርገው
ከ 1000 በላይ ቃላትን በማስተካከል ያዘጋጁት ነው፡፡
3. የምንጩ እርግጠኝነት፡- የተጠቀሙት ምንጭ ጥንታዊ መሆንና አለመሆን የንባብና የሀሳብ ልዩነት ያመጣል፡፡ አብዛኞቹ ትርጉሞች
ያለተጠቀሙበትን የዕብራይስጥ ትርጉሞች የግሪኩን ጥንታዊ ትርጉሞች ተጠቅመናል ይላሉ፡፡
ለምሳሌ፡- ምንም እንኳን መጽሐፉ ቢታገድም፣ የአሜርካ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ባሳተመው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ
ኢትዮጵያ የሚሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በጠቅላላ ሱዳን በማለት ተክቶት ነበር፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያት አድርጎ
ያቀረበው በጥንታውያን ቅጂዎች ላይ አገኘሁት በማለት ነበር፡፡

ከትርጉም ስህተት ለመጠበቅ ምን እናድርግ?

1. ማመሳከር፡- የተለያዩ ትርጉሙችን ማየት የአንዱንም ከሌላው ማስተያየት ይገባል፡፡ በተለይ የመሠረተ እምነት (ዶግማ) አስተምህሮ
ከሆነ አንድ ትርጉም ላይ ብቻ መመሥረት ተገቢ አይደለም፡፡
2. ማነጻጸር፡- የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሉን ከአጠቃላይ የመጽሐፉ መልእክትና ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቦች ጋር ማነጻጸር፡፡ ከዚህ
በተጨማሪም አንድን ጥቅስ ከሙሉ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ለይቶ መመልከት አይገባም፡፡
3. ሙሉ ዓውዱን ማየት፡- ጥቅሱን ከአገባቡ አንጻር ማየት፤ አንድ ጥቅስን ብቻ ገንጥሎ ማየት አይገባም፡፡

8
THE HERESY OF JEHOVAH’S WITNESSES, BY H.H. POPE SHENOUDA III, pp14

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 12


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

4. የቤተ ክርስቲያንን ፈለግ መከተል፡- ቃለ እግዚአብሔርን ከሐዋርያት ጀምሮ በቃልና በጽሑፍ ያሰስተላለፈችልንን የቤተ ክርስቲያንን
ትምህርት በመያዝ ትርጉሙን ማቅናት፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና


ቀኖና የሚለው ቃል ካኖን ሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ፤ ካኖን ማለት ደግሞ በባሕር ዳር የሚበቅል እንደ ሣር ያለ ሸንበቆ ነው፡፡ ይህንንም
የጥንት ግሪካውያን ለመለኪያነት ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ከዚህ አገባብ አንጸር ቀኖና ማለት መለኪያ ማለት ነው፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ስንል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሊካተቱ የሚገባቸው የቅዱሳት መጻሐፍትን ዝርዝር ያመለክታል፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ
የቅዱሳት መጻሕፍት ዝርዝር በጠቀሰበት የፋሲካ መልእክቱ እነዚህን መጻሕፍት የተወሰኑና የተደነገጉ (Regulated and defined) ይላቸዋል፡፡
ስለዚህም“ቀኖናውያት ቅዱሳት መጻሕፍት” ሲባል የተደነገጉና ፍጹም ተቀባይነት ያላቸውን በእግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን
መጠበቂያና መመሪያ ይሆኑ ዘንድ የተጻፉና የተሠጡ የተለዩ የተመረጡ መጻሕፍትን ያመለክታል፡፡ እነዚህም መጻሕፍት
ቤተ-ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖትን ለማረጋገጥና ለማስተማር በጉባኤ የምታነባቸውና የምትተረጕማቸው፣ ለሃይማኖት
ጉዳይ መነሻና መድረሻ ለክርክርም የመጨረሻ ይግባኝ ሆነው የሚጠቀሱና የሚቀርቡ መጻሕፍት ናቸው፡፡

መጻሕፍትን በቀኖና መወሰን ለምን አስፈለገ?


 እውነተኞቹ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከመናፍቃን አስመሳይ መጻሕፍት
 በቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት መነበብ የሚገባቸውን መወሰን አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ፡፡
፡-በቅዳሴ፤ በሰዓታት፣ ሕማማት፣ ማኅሌት . . .
ቀኖና መጻሕፍት መመዘኛዎች
 ጸሐፊች ቅድስናቸው የተመሰከረ መሆን አለባቸው፡፡
ምሳሌ፡-
ሙሴ- ፊቱ የሚያበራ ነበር
ኢያሱ- ፀሐይ አቁሟል
ጴጥሮስ- በጥላው ይፈውሳል
ጳውሎስ- በልብሱ ይፈውሳል
ቀሌምንጦስ- የጴጥሮስ ደቀመዝሙር ነበር
 ይዘቱ ከቤተክርስቲያን መሠረት (ጌታችንና ሐዋርያት ካስተማሩት ትምህርት) ጋር መጋጨት /መውጣት/ የለበትም
 በቤተክርስቲያን የተመሰከረለት መሆን አለበት፡፡
የቀኖና መጻሕፍ ጥቅሞች
1. ጥበቃ፡- በቤተክርስቲያን የቅዱሳት መጻሕፍት ቊጥር ወስና ባትጠብቅ ኖሮ በየዘመናቱ እንደተነሡት መናፍቃን ብዛት
ልዩ ልዩ የኑፋቄ ትምርቶች በተሰገሰጉ ነበር፡፡ በቅዱሳን ስም ይጽፉት ስለነበር ከእውነተኞቹ ለመለየት ይከብድ ነበር፡፡
ፍት ነገ አንቀጽ 2፡19
2. ውርስ፡- ቤተክርስቲያንን ሊያጠፉ የተነሡ መናፍቃንና ዓላውያን ነገሥታት የሚመሪያ ዓላማቸው ቅዱሳት መጻሕፍትን
መቆንጸልና ማጥፋት ነበር፡፡ ነገር ግን ቤተክርስቲያናችን በዋሻ በፍርክታ በልጆቿ ልቡና አሳድራ በማቆየቷ ከትውልድ
ወደ ትውልድ ሊተላለፍ ችሏል፡፡
ለምሳሌ፡- የዮሐንስ ራእይ (የዮሐንስ አፈወርቅ)
3. ማረጋገጥ፡- በኑፋቄ ትምህርት የተሞሉ መጻሕፍት ከእውነተኛ መሠረተ እምነት ጋር በማስተያየት ሐሰትነታቸውን
ያረጋገጠች ቤተክርስቲያን ናት፡፡
ለምሳሌ፡- በኒቂያ ጉባኤ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 13


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

አስቀድመን እንደተነጋገርነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት መጻሐፍት በተለያየ ጊዜ የተጻፉና ራሳቸውን የቻሉ መጻሐፍት ነበሩ፡፡ ስለዚህ እነዚህ
መጻሐፍት በጊዜ ሂደት ተሰባስበው አሁን ያላቸውን ቅርጽ ያዙ እንጂ በአንድ ጊዜና ቦታ የተጻፉ ወይም እንዲህ ሆነው ከሰማይ የወረዱ መጻሕፍት
አይደሉም፡፡ በዚህም የተነሣ የተለያዩ ቤተ እምነቶች ሆነ ዓቢያተ ክርስቲያናት የተለያየ ቀኖና መጻሐፍት (የመጻሐፍት ዝርዝር) አላቸው፡፡ ይህንንም ከዚህ
በመቀጠል እናቀርበዋለን፡፡

የብሉይ ኪዳን ቀኖና


ከሐዲስ ኪዳን መጻሐፍት ቀኖና ይልቅ በብሉይ ኪዳን መጻሐፍት ቀኖና ላይ ያለው ልዩነት የሰፋ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን የሚተርከው
የእስራኤላውያንን ታሪክ እንዲሁም መጻሐፍቱ ጠብቀው ያኖረት እነርሱ ናቸውና ከአይሁዳውያን ቀኖና ብንጀምር የተሸለ ነው፡፡

አይሁዳውያን ብሉይ ኪዳንን “ብሉይ ኪዳን” ብለው አይጠሪትም፤ ምክንያቱም አዲሱን ኪዳን አይቀበሉምና፡፡ ነገር ግን “ትናክ (TaNaKh)”
በማለት ይጠሩታል፡፡ “ትናክ” የሚለው የዕብራይስጥ ቃል አሕጽሮተ ቃል (acronym) ነው፡፡ ይህም አይሁዳውያን መጻሕፍት (“ብሉይ ኪዳን”)
ከሚከፍሉባቸው ሦስት ክፍሎች የመጣ ነው፡፡ “ት” የሚለው የመጀመሪያው ቃል “ቶራ(Torah)” የተባለውን ክፍል ይክላል፣ “ና” ደግሞ
“ኔቪኢም(Nevi’im)” የተባለውን ክፍል ሲወክል፤ የመጨረሻው “ክ” ደግሞ “ኬቱቪም(Ketuvim)” የተባለውን ክፍል ይወክላል፡፡

1. ቶራ(Torah)፡- የሚለው ቃል በቀጥታ ሲፈታ አስተምህሮ ማለት ነው፡፡ አይሁዳውያን በዚህ ክፍል የመጀመሪያዎቹን አምስት የሕግ መጻሐፍትን
ማለትም ኦሪት ዘፍጥረት፣ ኦሪት ዘጸአት፣ . . . አካተው ይቆጥራሉ፡፡ ከመጻሐፍቱ ይዘትም አንጻር ቶራ የሚለው ቃል ሕግ የሚለውን ስያሜ እንዲይዝ
ሆኗል፡፡
2. ኔቪኢም(Nevi’im)፡- በዕብራይስጥ “ናቪ(Navi)” ማለት ነቢይ ማለት ሲሆን “ኔቪኢም” ማለት ደግሞ በብዙ ቊጥር ነቢያት ማለት ነው፡፡
ይህንንም ክፍል ከዘመን አንጻር በሁለት ንዑሳን ክፍላት ይከፍሏቸውል፡፡ እነዚህም
1. የቀደሙት ነቢያት(former Prophets)፡- በዚህ ክፍልም አራት መጻሐፍትን ሲያካትቱ እነርሱም መጽሐፈ ኢያሱ፣ መጽሐፈ መሳፍንት፣
መጽሐፈ ሳሙኤል(ሁለቱን እንደ አንድ)9 እና መጽሐፈ ነገሥት(ሁለቱን እንደ አንድ) ናቸው፡፡ እነዚህ መጻሐፍት በእኛ አቆጣጠር ከታሪክ
መጻሐፍት ሥር የምንቆጥራቸው ናቸው፡፡
2. ኋለኞቹ ነቢያት(later Prophets)፡- በዚህ ክፍል አራት መጻሐፍትን ብቻ ሲያካትቱ እነርሱም ትንቢተ ኢሳይያስ፣ ትንቢተ ኤርምያስ፣
ትንቢተ ሕዝቅኤልና የዐሥራ ሁለቱ መጻሐፍት በማለት 12 ቱን ደቂቅ ነቢያት እንደ አንድ መጽሐፍ10 አድርገው ይቆጥሯቸዋል፡፡
3. ኬቱቪም(Ketuvim)፡- ጽሑፋት ማለት ሲሆን በዚህም ክፍል ከሕግና ከነቢያት (ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ክፍሎች) ውጪ ያሉትን የመዝሙር
የጥበብና የታሪክ 11 መጻሐፍትን አካተው ይቆጥሩታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ትንቢተ ዳንኤልን ልክ እንደ ትንቢት መጽሐፍ ሳይሆን እንደ ታሪክ መጽሐፍ
ከዚህ ክፍል አካተው ነው የሚቆጥት፡፡
ፈሪሳውይን ከእነዚህ ክፍላት የመጀመሪያዎቹን ሁለቱን ብቻ ሲቀበሉ ሦስተኛውን ክፍል ግን መገልገያና ማስተማሪያ መጽሐፍ እንጂ እንደ አሥራው
መጻሐፍት አድርገው አይቆጥሯቸውም፡፡ ሰዱቃውያንና ሳምራውያን ደግሞ ቶራን ብቻ ይቀበላሉ፡፡ አሁን ያሉት አይሁድ ግን ሦስቱንም ከፍል በአጠቃላይ
22 መጻሐፍትን እንቀበላለን ይላሉ፤ ነገር ግን አቆጣጠራቸው ስሚለያይ ነው እንጂ እንደ እኛ አቆጣጠር ከሆነ 39 መጻሐፍትን ይቀበላሉ፡፡
11
ይህ የአይሁድ ቀኖና “ትናክ” በእንደዚህ መልክ የተዘጋጀው ከ 150-200 ዓ.ም አካባቢ በተበተኑት የአይሁድ ሊቃውንት(ረበናት) ነው፡፡ ለዚህም
ቀኖና መደንገግ ምክንያት የሆኑት ደግሞ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ አይሁዳውይን ከጥንት ጀምሮ በተለያዩ ሀገሮች ተበትነው ይኖሩ ነበር፡፡ በመጀመሪያው መቶ
ክፍለ ዘመን (ድ.ል.ክ) በአነስተኛ ቁጥም ቢሁን በሮማውያን ግዛት የአይሁድ ሕዝብ ያልነበረበት ከተማ አይገኝም ነበር፡፡ ክርስቶስ በተወለደበት ጊዜ በምድረ
እስራኤል ውስጥ ከነበሩት አይሁድ ከምድረ እስራኤል ውጭ የነበሩት አይሁድ አምስት ወይም ስድስት እጥፍ እንደነበር ይነገራል፡፡ ስለዚህም እነዚህ
አይሁዳውያን አብዘኞቹ በጊዜ በብዛት ይነገር የነበረውን የግሪክ ቋንቋን እንጂ ዕብራይስጥ አይናገሩም ነበር፡፡ ስለዚህም ይጠቀሙት የነበረው የሰብዓ
ሊቃናትን የግሪክ ትርጉም እንጂ የዕበራይስጡን አልነበረም፡፡ በዚህም የአይሁድ መሰራጨት የእውነተኛ አምላክ ዕውቀትና የመሲሕ መምጣት ተስፋ በሰብዓ
ሊቃናት ትርጉም አማካይነት በአሕዛብ ምድር በመጠኑም ቢሆን ይታወቅ ነበር፡፡ ይህም ለክርስትና መስፋፋት በእጅጉ ጠቅሟል፡፡

የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም ከመጀመሪያው አንስቶ የእስክንድርያ ግሪክ ተናጋሪ አይሁዶች ለምኩራባቸውና ማስተማሪያነት በፍልስጥኤም የሚገኙት ረበናት
መምህራን ሳይቀር ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ስለዚህም ይህ ትርጉም በአይሁዳውያን ዘንድ ትልቅ ቦታ ነበረው፡፡ ይህ የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም በአይሁድና
12
በአሕዛብ ዘንድ ተሰራጭቶ ስለነበር የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች እንደ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ አድርገው ተቀብለውታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስም በስብከቱ

9
የዕብራይስጥ ቋንቋ ለየት ባለ መልኩ የአናባቢ ፊደላት የሉትም፡፡ በዚህም የተነሣ ሁለቱም የሳሙኤል መጻሐፍት አንድ መጽሐፍ ነበሩ፡፡ በኋላ ግን ሰብአ ሊቃናት ወደ ግሪክ
ሲተረጉሙት መጠኑ እጅግ ስለበዛ በአንድ ጥቅልል መካተት ባለመቻሉ ለሁለት ከፍለውታል፡፡
10
በጥንት ዘመናት መጻሐፍት ተጠርዘው ሳይሆን የሚቀመት ተጠቅልለው ነበር፡፡ ስለዚህም አንድ ጥቅል ለመስራት ረዘም ያለ ክርታዝ ወይም ብራና ያስፈልግ ነበር፡፡
በመሆኑም እነዚህ 12 መጻሐፍት በመጠናቸው እጅግ አነስተኛ ስለነበሩ ብቻቸውን አንድ ጥቅልል መሆን አይችሉም፡፡ ስለዚህም ሁሉንም ጠቅልለው በአንድ መጻሐፍት
ስለሚያካትቷቸው ነው፡፡
11
አይሁዳውይን በ 70 ዓ.ም በሮም ላይ በማመጻቸው ምክንያት ሮማዊው ቄሳር መጥቶ ኢየሩሳሌምን አፈራርሶ ከሀገራቸው አፈናቅሏቸው ስለነበር እስከ 1945 ዓ.ም ድረስ
በዓለም ሁሉ ተበትነው እንጂ በእስራኤል ሀገር አይኖሩም ነበር፡፡
12
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ ሁለት ሺህ ዓ.ም፣ ገጽ 164

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 14


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሐዋርያትም በትምህርታቸውና ሐዲስ ኪዳንን በጻፉበት ወቅት ከብሉይ ኪዳን ሲጠቅሱ ዘወትር የሚጠቅሱት ከሰብዓ ሊቃናት ትርጉም ነበር፤ አብዛኞቹ
የሐዲስ ኪዳን መጻሕፈት በግሪክ ነውና የተጻፉት፡፡ ክርስትና ቀስ በቀስ ከተስፋፋ በኋላ ሰብዓ ሊቃናት በክርስቲያኖች ዘንድ በሰፊው ተሰራጨ፡፡ ይሁን እንጂ
አይሁዳውያን ሰብዓ ሊቃናት በክርክር ወቅት በእነርሱ ላይ እንደ መከራከሪያ ነጥብ እየሆነ በተግባር መዋሉን ባወቁ ጊዜ፣ ለሰብዓ ሊቃናት ይሰጡት የነበረው
አክብሮት ተቃራኒ ወደሆነ ስሜት ተለወጠ፡፡ ይባስ ብሎም ለሰብዓ ሊቃናት የነበረውን ዕውቅናና ሥልጣን ለማሳጣት የሚቻላቸውን ሁሉ አደረጉ፡፡ ሰብዓ
ሊቃናት ትክክለኛ ትርጉም አይደለም እያሉ ይካራከሩም ጀመር፡፡

ታዲያ እነዚህ የአይሁድ ሊቃውንት ከ 150-200 ዓ.ም መካከል ተሰባስበው “ትናክ” የተባለውን የአይሁድ ቀኖና ወሰኑ፡፡ ስለዚህ የመጻሐፍቱን ቁጥር
ሲወስኑ በሰብአ ሊቃናት የሚገኙ ነገር ግን በዕብራየይስጡ የጠፉ እንዲሁም ስለ ክርስቶስ ቀጥተኛ ትንቢትና ሱባኤ ያሉባቸውን መጻሐፍት
13
ከመጻሐፍቶቻቸው አውጥተው ቆጥረዋል፤ ትንቢተ ዳንኤልንም ከታሪክ መጽሐፍ ሥር ቆጠጥረውታል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መጻሐፍቱ በዕብራይስጥ ብቻ
መነበብ አለባቸው፣ ወደ ሌላ መተርጎም የለባቸውም ብለው ወሰኑ፡፡ የሰብዓ ሊቃናት ትርጉምንም ከምኩራባቸው አወጡት፡፡ ይህም ዕብራይስጥን
የማያውቁትን አይሁድ ያማከለ ስላልነበር ለእነሱ በግሪክ ፊደል የዕብራይስጥን ድምጸ ልሣን በተከተለ መልኩ አዲሱን ቀኖና (“ትናክ”ን) አዘጋጁላቸው፡፡
ቢሆንም የሚያነቡትን ስለማይረዱት በምኩራብ እየተረጎሙ የሚያስተምሯቸውን ሰዎች አዘጋጁላቸው፡፡

ከዚህም የተነሣ የሰብዓ ሊቀናት ትርጉም በ”ትናክ” የሌሉ እንደ መጽሐፈ ጦቢት፣ መጽሐፈ ዮዲት፣ መጻሕፍተ መቃብያን ... ያሉ ብዙ መጻሐፍትን
ይዟል፡፡ ነገር ግን እነዚህን መጻሐፍት አይሁድ አንቀበላቸውም ይበሉ እንጂ መጀመሪያ በዕብራይስጥ የነበሩ መጻሐፍት ናቸው፡፡ ይህንንም በ 1946 ዓ.ም
በሙት ባሕር አካባቢ በአርኪዮሎጂ ጥናት የተገኙት ጥንታዊያን መዛግብት (Dead Sea Scrolls) ያረጋግጡልናል፡፡ ስለዚህም ከዚህ ታሪክ
እንደምንረዳው የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም ከተጠናቀቀ ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ ነው የአይሁድ ቀኖና (ትናክ) የተሠራው፡፡ ይህም የሰብዓ ሊቃናት
ጥንታዊነት ያስረዳናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ እኛ ክርስቲያኖች አይሁዳውያን የሚቀበሉትን ሁሉንም መጻሐፍት ብንቀበልም አከፋፈላችን ሆነ አቆጣጠራችን ግን ከእነርሱ የተለየ
ነው፡፡ ይህም ብሉይ ኪዳንን በ 4 ክፍል ስንከፍለው እነርሱም 1. የሕግ መጻሐፍት 2. የታሪክ መጻሐፍት 3. የጥበብና የመዝሙር መጻሐፍት 4. የትንቢት
መጻሐፍት በማለት ነው፡፡

የፕሮቴስታንት ክፍልፋዮች የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ቀኖና ለምን ከኦርቶዶክሳውያን ቀኖና ተለየ ?

የፕሮቴስታንት እምነት የመጣው አንድ ማርቲን ሉተር የተባለ የጀርመን ሰው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለውጥ ያስፈልጋታል ትታደስ ብሎ በተነሣ
ጊዜ ነው፡፡ ከተቃወማቸው ነጥቦቸች መካከል ካቶሊካውያን ምእመኑን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያነቡ አያበረታቱም የሚል ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት
የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትጠቀም የነበረው ቩልጌት የተባለው የአባ ጄሮምን የላቲን ትርጉም ብቻ ስለነበር ነው፡፡ ከጊዜ ሂደት ሕዝቡ የላቲንን ቋንቋ መናገር
ትቶ በሌላ ቋንቋ ይናገር ስለነበር ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስን አያነብም ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ቤተክርስቲያኗ መጽሐፍ ቅዱስ ሊነበበብ የሚገባው
በካህናትና በመምህራን ብቻ ነው፤ እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ወደ ሌላ ቋንቋ መተርጎም የለበትም የሚል አቋም ስለነበራት ነው፡፡ ይህ ግን
በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ የነበረ ሀሳብ አልነበረም፤ አባቶቻችን ወንጌልን ለማስፋፋት ሲዘዋወሩ ሕዝቡን ካሳመኑ በኋላ የመጀመሪያው ግብራቸው አንዱ
መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ሕዝቡ ቋንቋ መተርጎም ነበር፤ ጽሕፈት ባይኖራቸው እንኳን አዲስ ፊደልን በመፍጠር ይተረጉሙ ነበር፡፡

ስለዚህም ማርቲን ሉተር ወደ ጀርመንኛ ተረጎመው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የተቃወመ እየመሰለው እንግዳ የሆኑ በጥንት
ክርስቲያኖች ዘንድ ያለነበሩ አዳዲስ ትምህርቶችን አስተማረ፡፡ ለምሳሌ፡ - Sola Scriptura (መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ) በማለት ለመጻሐፍት ትርጓሜ ሆነ
ትውፊት አያስፈልጋቸውም፤ ሁሉም ለራሱ ያንብብ እንደሚመቸውም ይተርጉም በማለት አዲስ አስተምህሮን ማስተማር ጀመረ፡፡

ማርቲን ሉተር መጽሐፍ ቅዱስን ሲተረጉም ለብሉይ ኪዳን መጻሐፍት የሰብዓ ሊቃናትን ትርጉም ከመጠቀም ይልቅ “ትናክ”ን ተጠቅሟል፡፡ ለዚህም
እንደምክንያት ያቀረበው ብሉይኪዳን የአይሁድ መጻሐፍት ከሆኑና እነርሱ ሰብዓ ሊቃናትን ከተቃወሙት እኛም ልንቀበላቸው አይገባም በማለት ነው፡፡ ነገር
ግን በዚያ ዘመን እነዚህ መጻሐፍት በሕዝቡ ዘንድ እጅግ ተቀባይነት ስለነበራቸው ለማውጣት አልደፈረም፤ ይልቁንም የማውጫ ዝርዝር ላይ ለብቻቸው
መጨረሻ ላይ አደጋቸው፣ ከብሉይ ኪዳን መጻሐፍትም በመስመር ለያቸው፡፡ በሁለተኛና በሦስተኛ እትሞቹ (Editions) ግን ጨርሶ አጠፋቸው፡፡

ይህንንም የማርቲን ሉተር ሀሳብ ሌሎች በሌላ ሀገር የሚገኙ የተለያዩ ተሀድሶዎች (የፕሮቴስታታዊነት አቀንቃኞች) እንደ ዚዊንግሊ (ስዊዘርላንድ)፣
ካልቪን(እንግሊዝ) ያሉት ደግፈውታል፡፡ ስለዚህ እነርሱም የእርሱን አካሄድ ተከትለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ፕሮቴስታንቶች ልክ እንደ አይሁድ 39
መጻሐፍትን ብቻ ይቀበላሉ፡፡ ይህም ከክርስትናው ዓለም ትንሹ የመጻሐፍት ቀኖና ነው፡፡ ከዚህም አልፎ እነዚህን “ተጨማሪ” ያሏቸውን መጻሕፍት አፖክሪፋ
በማለት ያልተገባ ስም ሰጧቸው፤ የሐሰት መጻሕፍት ማለት ነው፡፡

ይህንንም የሉተርን ሆነ የሌሎቹ ተሀድሶዎችን ሀሳብ ለመቃወም በ 1545 ዓ.ም በሰሜናዊ ጣልያን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጉባኤ አደረገች፡፡
ጉባኤውም ጉባኤ ትሬንት ይባላል፡፡ በዚህም የሰብአ ሊቃናትን ትክክለኝነት በወሰን 49 የብሉይ ኪዳን መጻሐፍትን ወስናለች14፡፡ ነገር ግን አነዚህ ተጨማሪ

13
ይህ የሆነበት ምክንያት በነቢዩ ዳንኤል በመጽሐፉ ስለክርስቶስ ልደትና ስቅለት ዘመኑን ቁልጭ አድርጎ ስለሚናገር ነው(ዳን 9፡21-27)፡፡ ትንቢተ ዳንኤል ከዘመነ ባቢሎን
እስከ ዓለም ፍጻሜ ፣ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣ ገጽ 10 ተመልከት፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 15


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

መጻሐፍት ከሌሎቹ የብሉይ ኪዳን ትርጉም እኩል ጠቀሜታ የላቸውም በማለት የሁለተኛ ቀኖና መጻሐፍት (Deutrocanonical) በማለት ጠራቻቸው፡፡
ነገር ግን ቅድስት ቤተክርስቲያን ይህን ሀሳብ ሆነ ስያሜ አትቀበለውም፡፡

በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት በቤተ ክርስቲያናችን ይህ ውዝግብ መጀመሪያውንም አልተነሣም፤ ጉባኤ ትሬንትንም አትቀበለውም፡፡ ስለዚህ መጻሐፍቱን
15
የሁለተኛ ቀኖና መጻሐፍት (Deutrocanonical) ብላ አትጠራቸውም ከሌሎቹ እኩል ጠቀሜታ እንዳላቸውም ታምናለች፡፡

የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የብሉይ ኪዳን 46 መጻሐፍትን ስትቀበል በሰብአ ሊቃናት የሌሉ ነገር ግን በግእዝ ብቻ የሚገኙ እንደ
መጽሐፈ ሄኖክ፣ መጽሐፈ ኩፋሌ፣ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን ያሉትን መጻሐፍትንም ጨምራ ትቆጥራቸዋለች፡፡

የሐዲስ ኪዳን ቀኖና


የሐዲስ ኪዳን ቀኖና ከመዘጋጀቱ በፊት ምንጫቸው ያልተረጋገጠ እና በመናፍቃን አማካኝነት በአዲስ ኪዳን
ጸሐፈያንና ሌሎች ቅዱሳን ስም የተጻፉ በብዛት የተሰራጩ መጻሕፍት ነበሩ፡፡ በዚህም ከ 50 በላይ ወንጌላት ብዙ
መልእክታትና ራእዮች ተጽፈው ነበር፡፡ እነዚህንም ቤተክርስቲያንችን አፖክሪፋ በማለት ትጠራቸዋለች፡፡ በቅዱሳን ስም
የተጻፉ የሐሰት መጻሕፍት ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
የቶማስ ወንጌል
የአስቆሮቱ ይሁዳ ወንጌል
የማርያም መግደላዊት ወንጌል
የጴጥሮስ ራእይ ይጠቀሳሉ፡፡
ይህን አደገኛ ጥፋት የተገነዘቡት አባቶች በጻፏቸው መጻሕፍትና መልእክታት የቅዱሳት መጻሕፍትን ስም ዝርዝር
አካተዋል፡፡ እነዚህም የአበውና የሲኖዶሳት ውሳኔዎች ቀኖና መጻሕፍት ይባላሉ፡፡ የሐዲስ ኪዳን መጻሐፍት ቀኖናም ከነዚህ
ከአበውና ከጉባኤ ስምምነቶች የተገኘ ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
1. አበው፡- ቅዱስ አትናቴዎስ ለፋሲካ በ 369 ዓ.ም በላከው ደብዳቤው፤ የቅዱስ ጎርጎሪዮስ ዘእንዚናዙ፣
የአምፊሊኪዩስ፣ ቀኖናት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
2. የሲኖዶሳት ውሳኔ፡- የሐዋርያት ሲኖዶስ 85 ኛው ቀኖና፣ የጉባኤ ኒቅያ ቀኖናት፣ የሎዶቅያው ጉባኤ 6 ተኛው ቀኖና
ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በአጠቃላይ 35 የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ትቀበላለች፡፡ ስለዚህም በአጠቃላይ 81
መጻሐፍትን በመቀበል ከዓለም አብያተ ክርስቲያናት ብዙ መጻሐፍትን በቀኖናዋ በማካተት የመጀመሪያዋ ናት፡፡
የሌሎች ዓቢያተ ክርስቲያናት አቆጣጠር
ሳምራውያን - 5 ቱን የሙሴ መጻሕፍትን ይቀበላሉ፡፡
አይሁዳውያን- 39 የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን ይቀበላሉ፡፡
ካቶሊክ- 46 ብሉይ ኪዳን እና 27 የሐዲስ ኪዳን በአጠቃላይ 73 መጻሕፍትን ይቀበላሉ፡፡
የግሪክ ኦርቶዶክስ 77 መጻሕፍት ይቀበላሉ፡፡ ይህም በ 1954 ዓም ባሳተሙት መጽሐፍ ቅዱስ
ይታወቃል፡፡
ፕሮቴስታንት እና የፕሮቴስታንት ክፍልፋዮች፡- 39 የብሉይ ኪዳንና 27 ሐዲስ ኪዳን በጥቅል 66 መጻሕፍትን
ይቀበላሉ፡፡

14
የሰብአ ሊቃናቱ 46 ሆኖ ሳለ 49 መጻሐፍት መወሰናቸው አቆጣጠራቸው ስለሚለያይ ነው፡፡ ለምሳሌ ሁለቱን የሳሙኤል መጻሐፍት እንደ አንድ መቁጠርና አለመቁጠር . .
. የመሳሰሉት በመጻሕፍት ቁጥር ላይ ልዩነት ያመጣል፡፡
15
Deutrocanonical የሚለው አጠራር በጣም የተለመደ ስለሆነ በአንዳንድ ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት ላይም ፕሮቴስታንቶች የማይቀበሉትን መጻሕፍት ለማመልከት
ሊቃውንቱ ይህን ስያሜ ሲጠቀሙበት ይታያል፡፡ ነገር ግን ስያሜውን ይጠቀሙበት እንጂ መጻሕፍቱ ከሌሎች መጻሕፍት ያንሳሉ በማለት አለመሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 16


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የጆሆቫ ምስክሮች፡- 66 መጻሕፍትን ብቻ ሲቀበሉ ነገር ግን አዲሲቱ ዓለም ትርጕም የሚለውን የራሳቸውን ትርጕም
ብቻ ይጠቀማሉ፡፡ ይህም ትርጕም ከ 1000 በላይ የሚሆን ቃላትን በመቀየር ለራሳቸው እንዲመች አድርገው
ያዘጋጁት ነው፡፡
በአቆጣጠር ላይ የሚነሡ ጥያቄዎች
1. ፕሮቴስታንቶች ተጨማሪ እያሉ የሚጠሯቸው መጻሕፍትን አይሁድ በቀኖናቸው አላካተቷቸውም፤ ሰብአ ሊቃናትም
አልተረጎሟቸውም ስለዚህ ልንቀበላቸው አይገባም?
አይሁድ በቀኖናቸው ያላካተቱበትን ምክንያት ከላይ በሰፊው ያስረዳን ሲሆን፤ ሰብአ ሊቃናት እነዚህን መጻሕፈት
አላተረጎሟቸውም የሚለው አባባል ግን መሠረት የሌለው ሐሰት ነው፡፡ ሰብአ ሊቃናት መጻሕፈትን በሰበሰቡ ወቅት እነርሱ
እስከነበሩበት ድረስ የተጻፉት ቅዱሳት መጻሕፍት ከጥቂት መጻሕፍት በቀር ሰብስበዋል፡፡ ከሰበሰቧቸውም መጻሕፍት
መካከል እነዚህ መጻሕፈት ይገኙበታል፡፡
ምንም እንኳን እዝራ በ 534 ዓመት ቅ.ል.ክ መጻሕፈትን ሲሰበስብ እነዚህን መጻሕፍት ባገኛቸውም መጻሕፍቱ ግን
ነበሩ፡፡ ኋላም እንደ እዝራ ያለ ተሰሚነት ያለው ነቢይ ባለመነሣቱና ቅድም በዘረዘርናቸው ምክንያት ከእርሱ በኋላ የተጻፉት
መጻሕፈት ሆነ እርሱ ያልሰበሰባቸው መጻሕፍት በአይሁድ ቀኖና ባይካተቱም በአይሁድ ምሁራን ዘንድ ግን ክብር
ነበራቸው፡፡ ለዚህም ዋነኛው ማሳያ የሚሆነው ሰብአ ሊቃናት ቅዱሳት መጻሕፍትን ሲሰበስቡ እነዚህንም አካተው
በመሰብሰባቸውና በመተርጐማቸው ነው፡፡ ይህንንም ለመረዳት ጥንታውያኑን የጽርእ ኮዴክሶች መመልከት ይቻላል፡፡
2. እነዚህ መጻሕፈት የሚታመንባቸው ቢሆን ኖሮ በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍ ከአባባላቸው ሆነ ከይዘታቸው በተጠቀሰ ነበር?
ሐዋርያት የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ሲጽፉ የተቀሙት ሰብዓ ሊቃናትን ስለሆነ ከእነዚህ መጸሕፍት ጠቅሰዋል፡፡
በመሠረቱ ግን አንድ መጻሕፍ ተቀባይነት እንዲገኝ በሐዲስ ኪዳን መጠቀስ የግድ የለበትም፡፡ ለምሳሌ፡- እነ መጽሐፈ
አስቴር፣ መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን፣ መጽሐፈ መክብብ፣ መጽሐፈ ሩት፣ መጽሐፈ መሳፍንትና 1 ኛ ዜና መዋዕል በሐዲስ
ኪዳን አልተጠቀሱም ነገር ግን ከቀኖና ገብተው ተቆጥረዋል፡፡ ይህም ቢሆን እንኳን መጻሕፍቱ ተጠቅሰዋል፡፡
ለምሳሌ፡-
 ይሁዳ 1፡14 ላይ ያለው ኃይለ ቃል በመጽሐፈ ሄኖክ 1፡9 ላይ ተጠቅሷል፡፡
 ጦቢት 7፡4-16 እና ማቴ 7፡12
 ተረፈ ኤርሚያስ 7፡13 እና ማቴ 27፡9
 ሲራክ 11፡18-19 እና ሉቃ 12፡19-20

መጽሐፍ ቅዱስ በኢትዮጵያ


የመጽሐፍ ቅዱስ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት
ኢትዮጲያ በዓለም ላይ ከሚገኙት ብዙ አገሮች ተለይታ በዘመነ ብሉይና ሐዲስ ሁለቱንም ኪዳናት
በመቀበል ብቸኛ አገር ናት፡፡ ምንም እንኳን በዘመነ ብሉይ የቃል ኪዳን ሕዝብ ተብለው የሚታወቁት
እስራኤላውያን ቢሆኑም ኢትዮጵያም በውቅቱ የዚህ ቃል ኪዳን ተካፋይ ለመሆን የበቃች አገር ናት፡፡
‹‹እናንተ እስራኤላውያን ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁንም?›› አሞ 9፡7
ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምራ በሕገ እግዚአብሔር ትመራ እንደነበር ልዩ ልዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎችን
እናገኛለን፡፡ በሦስቱም ሕግጋት (በሕገ ልቡና፣ በሕገ ኦሪት፣ በሕገ ወንጌል) ጸንታ መኖሯም ቅዱሳት
መጻሕፍትን ከእስራኤል ቀጥላ ለመቀበል የመጀመሪያዋ አገር አድርጓታል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 17


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ማክዳ /ንግሥተ ሳባ 1 ኛ ነገ 10፡1-13፣ ንግስተ አዜብ ማቴ 12፡42 ሉቃ 11፡31/ በአንድ
አምላክ የምታምን ንግሥት እንደ መሆኗ መጠን የጠቢቡ ሰለሞንን ጥበብ ለማድነቅ ወደ ኢየሩሳሌም
በተጓዘች ወቅት ‹‹በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ንጉሥ እንድትሆን በዙፋኑ ያስቀመጥህ ዘንድ የወደደህ
አምላክህ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን›› በማለት አመሰግናለች፡፡ የመጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ትርጓሜ
መግቢያ እንደሚያስረዳን የንግሥተ ሳባ ልጅ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከአባቱ ከሰሎሞን ዘንድ የሦስት ዓመት
ቆይታውን ፈጽሞ ሲመለስ ከሄኖክ ጀምሮ እስከ ሰሎሞን ያሉ መጻሕፍትን እንዲሁም 318 ሌዋውያን ይዞ
በመምጣቱ መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዕብራይስጥ ወደ ግእዝ ቋንቋ በ 982 ቅ.ል.ክ ሊተረጎም
ችሏል፡፡
ከዕብራይስጥ ወደ ግእዝ በተመለሱት መጻሕፍት ላይ አንዳንድ የዕብራይስጥ ቃላት በቁማቸው
መግባታቸው በተለይም በመጽሐፈ ነገሥት መደጋገማቸው ከዕብራይስጥ ወደ ግእዝ የተመለሱ ለመሆናቸው
ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡
አዶናይ- ጌታ ኤሎሄ-አምላክ ጸባዖት-አሸናፊ
ከሰሎሞን መጻሕፍት በኋላ ቀጥሎ ወደ ኢትዮጵያ የገባው መጽሐፈ ዳንኤል ነው፡፡ ይህም በ 4905 ዓ.ዓ
እስራኤላውያን በባቢሎን ተማርከው ፋርስ ባቢሎን ከወረዱ በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሥ አይሹር ለፋርስ ንጉሥ
ዳርዮስ ስለ እስራኤል አማላጅነት በላከው ሰው አማካይነት እስራኤላውያን ጽፈው የላኩት ነው፡፡ ይህንንም
የዳንኤል መጽሐፍ ተቀብለው በሰሎሞን ጊዜ ከመጡ መጻሕፍት ጋር ደርበውታል፡፡
ከምርኮም መልስ ዘሩባቤል በእስራኤል በነገሠ ጊዜ የኢትዮጵያን ንጉሥ ከእናንተ ያሉትን መጻሕፍት
ላኩልን እኛም እዚህ ያሉትን እንልክላችኋለን ብሎ ጠይቆ እነዚያ የቀሩትን የነቢያት መጻሕፍት እነዚህም
ከሄኖክ ጀምሮ እስከ ሰሎሞን የነበራቸውን መጻሕፍት ሁሉ ልከውላቸዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን ክርስትናን ከመቀበላቸው በፊት በቋንቋቸው ቅዱሳት መጻሕፍትን ተርጉመው
ይመሩባቸውና ይጠቀሙባቸው እንደነበር የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ታሪክ ያስረዳናል፡፡ (ሐዋ 8፡26-40) በዚያን
ዘመን የነበረችው ንግሥት (ሕንደኬ) ገርሳሞት አገልጋይ የነበረ ሲሆን በሠረገላው ውስጥ ተቀምጦ የትንቢተ
ኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብብ ነበር፤ በእርሱም አማካይነት በ 34 ዓ.ም ኢትዮጵያ ሕገ ወንጌልን ተቀብላለች፡፡
ሆኖም ግን የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ወደ ኢትዮጵያ የገቡት በ 4 ኛው መ.ክ.ዘ በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
አማካይነት ወደ ግእዝ ተተርጉመው ነው፡፡ በእርግጥ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትም በዚህ ዘመን ተተርጉመዋል፡፡
ምክንያቱም የጥንቱ የግእዝ ፊደላት ከአባ ሰላማ በፊት እንደ አሁን ስላልነበሩ ፊደሉ ሲስተካከል
መጻሕፍቱም እንደ ገና ተተርጉመዋል፡፡
ኋላም በ 5 ኛው መ.ክ.ዘ ወደ አገራችን የመጡት ተሰዓቱ ቅዱሳት (ዘጠኙ ቅዱሳን) የሐዲስ ኪዳን
መጻሕፍትን በሙሉ ወደ ግእዝ ቋንቋ ተርጉመዋል፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በኢትዮጵያ
የአማርኛ ትርጉም

መጽሐፍ ቅዱስ ከላይ እንደተጠቀሰው ወደ ግእዝ ተተርጉሞ ሲሠራበት ለረጅም ዓመታት ቆይቷል፡፡ በኋላም ግእዝ ሕዝባዊ ቋንቋ መሆኑ እየቀነሠ
ሲመጣና የሚያነቡት ሆነ የሚረዱት የቤተ ክርስቲያን ምሁራን ብቻ በመሆናቸው በ 17 ኛው ምዕተ ዓመት ጀምሮ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘሩ ግእዝ ቢሆንም
የአንድምታ ትርጓሜው ግን በአማርኛ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

ከዚህ በኋላ ግን መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ ወደ አማርኛ በአባ አብርሃም (አባ ሮሜ) በተባሉ መነኩሴ ተተርጉሟል፡፡ እኚህ አባት የ 28
ዓመት ወጣት እያሉ በግብጽ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ አደረጉ፡፡ በኢየሩሳሌም ቅዱሳት መካናትን ከተሳለሙ በኋላ ወደ ሶርያ፣ አርመን፣ ፋርስና ሕንድ ሄዱ፡፡
ከሕንድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱም 50 ዓመት ሞልቷቸው ነበር፡፡ በዚህ የተነሣ አባ አብርሃም የዐረብ፣ የፋርስ፣ የኢጣልያ፣ የግሪክና የሌላም ሀገር ቋንቋ
ተናጋሪ ነበሩ፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 18


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

እኚህ አባት ዳግም ገዳማተ ግብጽን ለመጎብኘት ወደ ግብጽ ሄዱ፡፡ በዚያም በግብጽ የፈረንሳይ ኤምባሲ ምክትል ቆንጽላ የነበረ አስሊን የተባለ
ፈረንሳዊ ወዳጅ ነበራቸው፡፡ ይህ ሰው የአባ አብርሀምን ሊቅነት ስለተረዳ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ አማርኛ እንዲተረጉሙ ምክር ለገሳቸው፡፡ አባ አብርሃምም
ምክሩን ተቀብለው በ 10 ዓመት ውስጥ የትርጉም ሥራውን በእጅ ጽሑፍ ሠርተው ጨርሰዋል፡፡ የተረጎሙት የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ የገጽ ብዛት 9539
ነበር፡፡ አባ አብርሃም ትርጉመን ከጨረሱ በኋላ በመጋቢት ወር መጀመሪያ በ 1811 ዓ.ም በኢየሩሳሌም ዐርፈዋል፡፡

የትረጉም ሥራው በቁም ጽሕፈት የተጻፈ እጅግ ውብ ነበር፡፡ ይህንንም ሥራ የእንግሊዝ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ከአስሊን እጅ ገዝቶ በተለያዩ
የቋንቋ ባለሙያዎች ካስመረመረ በኋላ በ 1816 ዐራቱን ወንጌላትን፣ በ 1821 ሙሉ ሐዲስ ኪዳንንና በ 1832 ደግሞ ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ
አሳትሟል፡፡16

ወደ ሌሎች ኢትዮጲያውያን ቋንቋ

የትግርኛ ትርጉም፡- የትግርኛ መጽሐፍ ቅዱስ በአለቃ ተወልደ መድኅን ገብሩ ከ 1861-1952 ዓ.ም ተተርጉሟል፡፡ አለቃ ተወልደ መድኅን በትግራይ ውስጥ
የማይ ማሻም ተወላጅ ነበሩ፡፡ በትርጉም ሥራም ሲውዲዊቷ ዊንክቪስት አማካሪያቸው ነበረች፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ ትግርኛ ትርጉም በ 1901 ዓ.ም ታትሟል፡፡
17
አለቃ ተወልደ መድኅን ትግርኛ፣ ትግረ፣ ግእዝ፣ አማርኛ፣ ዐረብኛ፣ ዕብራይስጥ፣ ጣልያንኛ እና ሲውድንኛ ያውቁ እንደነበር ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡

የኦሮምኛ ትርጉም፡- መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ኦሮምኛ የተረጎሙት የወለጋው ተወላጅ አናሲሞስ ነሲቡ ናቸው፡፡ የትርጉም ሥራውን ሲሠሩ አስቴር ገኖም
የቅርብ ረዳታቸው ነበሩ፡፡ የሐዲስ ኪዳን ኦሮምኛ መጽሐፍ ቅዱስ በ 1886 ዓ.ም ታትሟል፡፡ የብሉይ ኪዳኑ የትርጉም ሥራ በ 1890 ዓ.ም ተፈጽሞ
18
በ 1891 ዓ.ም ሙሉው የኦሮምኛ መጽሐፍ ቅዱስ ታትሟል፡፡

ከዚህ ውጪ መጽሐፍ ቅዱስ ወደ በጉራግኛ፣ በወላይትኛ፣ በሲዳምኛና በአኑዋክኛ ተተርጉሟል፡፡

1.6 መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ምን ያስፈልጋል?


1.6.1 መልክዐ ምድር
መላው መጽሐፍ ቅዱስ መልክዐ ምድራዊ ይዘት አለው፡፡ ይህን ያለመረዳትም አንዳንዴ የምንባቡ ዋና
ፍቺ እንዳንደርስበት ያደርገናል፡፡ መልክዐ ምድር ማለት የብስና ውኃማ አካሎች ማለት ነው፡፡ የብሰ ደረቅ
የመሬት ክፍል ሲሆን በውስጡም ተራራዎች፣ ሸለቆዎች…ወዘተ ያካተተ ሲሆን፤ ውኃማ አካል ስንል ደግሞ
ባሕር፣ ወንዞች፣ ሐይቆች…ወዘተ ማለታችን ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና መልክዐ ምድርን ልናጠና ግድ
ይለናል፡፡ መልክዐ ምድሩን ያለመረዳት የምንባቡን ትክክለኛ እና ዋና ፍቺ እንዳንደርስበት ያደርገናል፡፡
በአብዛኛው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያተኩረው የዓለም እምብርት በሆነችው በመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ
ከዚያም ደግሞ በእስራኤል ነው፡፡

ሀገረ እስራኤል ለምን ተመረጠች?


እግዚአብሔር ሀገረ እስራኤል እና ሕዝቧን የመረጠበት በቂ የሆነ ምክንያት እነዳለው አንጠራጠርም፡፡
ምክንያቱ እግዚአብሔር በባህሪው ፈታሔ በጽድቅ/እውነተኛ ፈራጅ ሲሆን አድሎአዊነት የለበትም፤ ምንም
እንኳን እግዚአብሔር ቸር እና መሐሪ ቢሆንም ይህ ባህሪው ግን እውነተኛ ፈራጅነቱን አይከለክለውም፡፡
እግዚአብሔር ለምን ሀገረ እስራኤልን ለምን መረጣት የሚለውን ስንመለከት ግን፡
ሀገረ እስራኤል በአብዛኛው ቅድስት ሀገር በመባል ትታወቃለች፣ በተፈሯዊና ታሪካዊ ገፅታዋ
ከመካከለኛው ም-ሥራቅ ሀገሮች የተለየች ናት፡፡ በሰሜን ሊባኖስና ከፊል ሶሪያ፣ በደቡብ የሲና በረሃን
በምሥራቅ ሶሪያንና ዮርዳኖስን፣ በምዕራብ ታላቁ ባሕርን/ሜዲትራንያን/ እና በደቡብ በምዕራብ ደግሞ
ፍልስጤምን አዋሳኝ አድርጋ ያለች ሀገር ናት፡፡

16
የመጽሐፍ ቅዱስ መግቢያ ክፍል አንድ፤ በዲን ኅሩይ ባዬ ፤ገጽ 78
17
ዝኒ ከማሁ
18
ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ 79

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 19


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሀገሪቱ ከምድረ ግብጽ በዐረብ ምድረ በዳ /የሲና ምድረ በዳ ከታናሷ እስያ በታወርስ ሸንተረር
ትሄዳለች፡፡ የሀገሪቱ አቀማመጥ ከሰሜን ወደ ደቡብ ሲቃኙት እነደሚከተለው ነው፡፡ በስተምዕራብ በኩል
ከሜዲትራንያን /ታላቁ ባሕር/ ድረስ ተራሮች ይታያሉ፡፡ ከዚያም ቀጥሎ በዮርዳኖስ ሸለቆ የተከፈሉ ሁለት
ሸንተረሮች ይገኛሉ፡፡ የኢዝራኤል ሜዳ ደግሞ ምዕራባዊውን ሸንተረር ለሁለት በመክፈል የዮርዳኖስን ሸለቆ
ከባሕር ዳር ከሚነሳው ሜዳ ጋር ያገናኘዋል፡፡
ሄኖቭ እየተባለ የሚጠራው ደቡባዊ ክፍል በአብዛኛው ደረቃማ ሲሆን በቤርሳቤህና በኤውሳጥ ሰላጤ
መካከል ይገኛል፡፡ የሀገረ እስራኤል መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ መጣም ከሚያስደስቱ የዓለም ገፅታዎች
መካከል ይፈረጃል፡፡ ውብ ከሆነው አቀማመጧ በላይ ሃይማኖታዊ ጸጋ ሲታከልባት ልዩ ስፍራ እንዲሰጣት
ያደርጋታል፡፡
በዋናነት እስራኤል ስለሚከተሉት ምክንያቶች ተመረጠች
ሀ. ማዕከላዊ ምድር በመሆኗ
እስራኤል ከዓለም መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ አንፃር ስትታይ በመካከል ያለች ሀገር ናት፡፡
የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገሮች ተብለው ከሚጠሩት ሀገሮች መካከል አንዷ መሆኗ እውነታውን
ያጠናክረዋል፡፡ ይኸውም በኬክሮስ እና በኬንትሮስ መሥመሮች አኳያ ሳይሆን ለተለያዩ ሀገሮች ካላት
ማዕከላዊነት አንፃር ነው፡፡ ይኸው ማዕከላዊነቷ በመጽሐፍ ቅዱስ ተነግሮላታል፡፡ መዝ 73፡12 ‹‹ እግዚአብሔር
ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፣ በምድርም መካከል መድኃኒትነትን አደረገ›› ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ ይህም
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኃጢያት ለጎሰቆለው ለአዳምና ለልጆቹ በቀራንዮ የፈፀመውን
መድሀኒትነት ነው፡፡
ማቴ 12፡42 ‹‹የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና›› ብሏል ኢትዮጵያቷን ንግስት
ሳባ ሲያመሰግናት፣ ‹‹ከምድር ዳር መጥታለችና›› የሚለው ሐረግ የእስራኤልን ማዕከላዊነት ያመለክታል፡፡
በማዕከላዊነቷም በጥንት ጊዜ ለበርካታ ዓመታት የንግድ የሥልጣኔ መናኸሪያ ሆና ቆይታለች፡፡
አፍሪካን፣ እስያን፣ አውሮፓን የምታገናኝ በመሆኗ ታላላቅ አውራ ጎዳናዎች ይገኙባት ነበር፡፡ ዘፍ 37፡28
ለ. አጽመ አዳም ያለበት በመሆኗ
አዳም ከገነት እንደ ተሰደደ የመጣው ወደ መሬት ነው ዘፍ፡፡ 3፡23 በምድረ በዳ ላይ ለዘጠኝ መቶ ሠላሳ
ዓመታት ከኖረ በኋለ ሞተ፡፡ ከዚህ በኋላ ልጆቹ አጽሙን እንደ ታቦት አድርገው መሠዋዕት፣ ጸሎትን ያቀርቡ
ነበር፣ ይህ ሲያያዝ ከኖኅ ዘመን ደረሰ፡፡ ኖኅም ወደ መርከብ ሲገባ አጽመ አዳምን ይዞት ገባ፡፡ ከጥፋት ወኃ
በኋላ ኖኅ ሴምን ጠርቶ አጽመ አዳምን ወስደጅ እግዚአብሔር ካዘዘው ቦታ አኑረው አለው፤ ሴምም
መልከጼዴቅን ከእናቱና አባቱ አሰናብቶ አጽመ አዳምን አሲዞ አብረው ሄዱ፡፡ ከዚያም መላዕክት እየመሯቸው
ቀራንዮ ደረሱ፡፡ ከቀራንዮም በኋላ የክርስቶስ መስቀል ከሚተከልባት ቦታ ላይ ሲደርስ ምድር ተከፈተችለት፡፡
በዚያም አጽመ አዳምን አስገብቶ አኖረው፤ መልከፄዴቅንም ጠብቅ ብሎት ተመለሰ፡፡ መልከፄዴቅም አጽመ
አዳምን እንደ ታቦት አድርጎ መሥዕዋት እና ጸሎት ያቀርብ ነበር፡፡ የአዳምን ሞት ሊሞትለት የመጣውን ሰው
የሆነውን አምላክ አጽመ አዳም በተቀበረበት ሥፍራ ላይ ካሣ ከፈለለት፡፡ የአዳም መቃብር በሆነችው ስፍራ
ካሣ ሊከፍል ይገባው ነበርና ወልደ አምላክ ሀገረ እስራኤልን መረጠ፡፡
ሐ እግዚአብሔር ለቅዱሳን አባቶች ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ እና ለያዕቆብ ስለገባው ቃልኪዳን

1.6.2. የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት እና የቋንቋ ጠባያት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 20


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመጽሐፍ ቅዱስን የአፃፃፍ ይዘት እና ጠባይ ያልተረዳ ሰው በቀላሉ ትክክለኛውን ምስጢር ለመረዳት
ያስቸግረዋል፡፡ ያለ ስህተትና ያለ ጭንቀት ለማነበብና ለመረዳት የቋንቋውን ጠባይ በሚገባ ተንትኖ
ሁኔታውን ተገቢ ነው፡፡ ስለሆነም በአጠቃላይ መልኩ ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ የቋንቋ ጠባያትን
እንደሚከተለው እንመልከት፡፡
ሕዝባዊነት
መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ሁሉን ባቀፈና ባገናዘበ፣ ትውልድንም ሁሉ በሚታደግ መልኩ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ቀድሞም የነበሩትን አሁንም ያሉትን ወደ ፊትም የሚኖሩትን ሕዝቦች
ያጠቃልላል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ ለራሱ ምግብ የሚሆነውን ሃይማኖቱን
ለማጽናትም ሆነ ምግባሩን ለማስፋፋት ሕዝባዊ ሆኖ የተፃውን መጽሐፍ ቅዱስ በአግባቡ የመረዳትና
በአክብሮት የመቀበል መንፈሳዊ ኃላፊነት ግዴታ አለበት፡፡ ‹‹ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ
እንጂ በእንጀራ ብቻ አይደለም›› እንዲል ማቴ 4፡4፤ ነቢዩ ‹‹ የዚህ የሕግ መጽሐፍ ….ከአፍህ አይለይ፣ ነገር
ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አንብበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ
ይቃናልሀልና አስተዋይም ትሆናለህ፡፡››…………………..
ክስተታዊ ነው
መጽሐፍ ቅዱስን በማስተዋል ከተመለከትነው ቋንቋው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከሚገልጠው
ነገር ጋር ይዛመዳል፡፡ ማቴ 10፡42 ‹‹ ነብይን በነብይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፣ ማንም ከእነዚህ
ከታናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውኃ ብቻ በደቀመዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላች…ለው ዋጋው
አይጠፋበትም፡፡›› በማለት የገለፀውን በአጽንዖት መረዳት ካልተቻለ ለአንዲት ጽዋ ውኃ
…………………….. ልናቃልል ወይንም ቦታ ላንሰጥ እንችል ይሆናል፡፡ ዮሐ 2፡1-11 በቃና ዘገሊላ
የተፈፀመውን ተአምር መረዳት ያስፈልጋል፡፡
የምንባቡ ሥነ ጽሑፍ የአጻጻፍ ባሕርይ
የምንባቡ የሥነ ጽሑፍ አጻጻፍ ባሕርይ ምንድነው? ምን አይነት የአፃፃፍ ዘዴ የተከተለ ነው? ወዘተ
የሚለውን አጠቃላይ ሁኔታ መዳሰስ ይገባል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ ጽሑፋዊ አጻጻፍ ስልት በአራት ዋና ዋና
ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነዚህም፡
1. ትረካዊ አጻጻፍ፡- ታሪኮችን በዘገባ መልኩ ያቀርባል፡፡ ለምሳሌ፡ መጽሐፈ ሳሙኤል፣ የሉቃስ ወንጌል፣
የሐዋርያት ሥራ…ወዘተ
2. ሥነ-ግጥማዊ አጻጻፍ፡- መጽሐፈ ኢዮብ፣ መኃልየ መኃልየ ዘሰሎሞን፣ መ. ጥበብ፣ መ. ተግሳፅ፣መ.
ዳዊት፣ መ. ሲራክ፣ መ. ምሳሌ …ወዘተ
3. ትምህርታዊ አጻጻፍ፡- ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊትን በትንቢትና በትምህርት መልክ ያሳየናል፡፡ ለምሳሌ፡
ት. ኢሳይያስ፣ ት. ዘካርያስ፣ የጴጥሮስ፣ የዮሐንስና የጳውሎስ መልእክታት
4. ራዕያዊና ሕልማዊነትን የያዘ አጻጻፍ ስልት፡- ለምሳሌ፡ ት. ሕዝቅኤል፣ ት.ዳንኤል፣ ት. ኢዩኤል፣ ራዕየ
ዮሐንስ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በትንቢተ ሕዝቅኤል 44፡1-8 ‹‹ ወደ ምሥራቅም ወደ
ሚመለከተው በስተውጭም ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አወጣኝ፣ ተዘግቶ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ይህ
በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፤ ሰውም አይገባበትም የእስራኤል አምላከ እግዚአብሔር
ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል፡፡ አለቃው ግን እርሱ በእግዚአብሔር ፊት እንጀራ ይበላ ዘንድ
ይቀመጥበታል፤ በበሩ ደጅ ሰላም መንገድ ይገባል፤ በዚያም መንገድ ይወጣል፡፡ ›› የሚለው መልእክት
በቂ ማስረጃ ነው፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ ባህል

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 21


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

መጽሐፍ ቅዱስ የራሱ የሆነ ባህል አለው፡፡ ይኸውም ባህል መጽሐፉ የተጻፈላቸውን ሰዎች ወይም
የጽሐፊውን ሁኔታ የሚያመለክትበት ጊዜ አለው፡፡ በዓለም ላይ የተለያየ ባህል ያላቸው በርካታ ሕዝቦች አሉ፡፡
እነዚህ ሁሉ ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚያገ…ቸው ባህሎች ከእነርሱ ባህል ጋር ለማመሳሰል መሞከር
የለባቸውም፤ ምክንያቱም በተጻፈበት ጊዜ ከነበሩት ሁኔታዎች ጋር አብሮ የሚሄድ ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህም
የመጽሐፍ ቅዱስ ባህል ያልነው በወቅቱ የተጻፈላቸውን ሰዎች እና የጸሐፊዎቹን አካሄድ ነው፡፡ የአንዱ ሕዝብ
ባሕል ከሌላው ጋር ሊመሳሰልም ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡ ‹‹ወንድም›› የሚለው ቃል በመካከለኛው ምሥራቅ
እና በኢትዮጵያ ያለው ትርጉም አንድ አይነት ሲሆን በምዕራባውያን ዘንድ ያለው ትርጉም ደግሞ ሌላ ነው፡፡
ስለዚህም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‹‹ወንድም›› ሳይጨበጥ ይቀራል፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ
በአብዛኛው የሚያንፀባርቀው የመካከለኛው ምሥራቅን ባህል ነው፡፡
1. የዕብራዊያን ስም አወጣጥ
በዕብራውያን ዘንድ ስም ጠባይን ግብርንና ሁኔታን እንደሚገልጥ ሆኖ ይሰየማል፡፡ ከዚህም የተነሣ
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰው የምናገኛቸው አብዛኛዎቹ የእስራኤላውያን ስሞች ከመጠሪያነት
በተጨማሪ ሌሎች ብዙ ጉዳዮችን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ዕብራውያን ለልጆቻቸው ለቦታዎች ስም ሲያወጡ
በወቅቱ /ስሙ ሲወጣ/ በሀገራቸው በቤታቸው ወይም በግላቸው ተከስቶ ከነበረ ሁኔታ ጋር በማዛመድ ነው፤
ይህም ያንን ጊዜ እና ሁኔታ እንዳይረሱት ያደርጋቸዋል፡፡ ደስታን፣ ሀዘንን፣ ጦርነትን፣ ስደትን፣ ታሪካዊ
ክስተቶችን እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ወይም ሌላ ነገርን ሊያመለክት ይችላል፡፡ ለአብነት ያህል
የሚከተሉትን እንመልከት፡
1.1 ለሰዎች የሚሰጥ ስያሜ
 ያዕቆብ፡ ትርጉሙ ተረከዝ ይይዛል ማለት ነው፡፡ ይህም በተወለደ ጊዜ የመንትያው የዔሣውን ተረከዝ ይዞ
በመወለዱ የተሠጠው ስም ነው፡፡ ዘፍ 25፡26
 ሙሴ፡ ትርጉሙ ከባሕር የወጣ ማለት ነው፡፡ ‹‹እኔ ከውኃ አውጥቼ…ለውና ስትልም ስሙን ሙሴ ብላ
ጠራችው፡፡›› ዘጽ 2፡10፣ ዘጽ 1፡15-22
 ምናሴ፡ ትርጉሙ ማስረሻ ማለት ነው፡፡ ‹‹ ዮሴፍም የበኵር ልጁን ምናሴ ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል፤
እግዚአግሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት አስረሳኝ ›› ዘፍ 41፡51 ዮሴፍ ይህንን ስም ለልጁ ሲሰጠው
የራሱን ታሪክ በማስታወስ ነው፡፡
 ኤፍሬም፡ የዮሴፍ ሁለተኛ ልጅ ሲሆን ትርጉሙም ማፍራት ማለት ነው፤ ዮሴፍ ‹‹እግዚአብሔር
በመከራዬ አገር አፈራኝ›› ሲል ያወጣለት ስም ነው፡፡ ዘፍ 41፡52
 ፋሬስ፡ ትርጓሜው ጣሽ /የሚጥስ/ ማለት ነው፡፡ ለምን እንዲህ ተባለ ቢባል ሲወለድ የነበረውን ሁኔታ
ያመለከተናል፤ እናቱ ትዕማር በወለደቸው ጊዜ አንድ ለየት ያለ ሁኔታ ተከሰተ፤ ይኸውም እናትየው
መንታ ፀንሳ ነበርና በመውለጃዋ ሰዓት ከሁለቱ አንደኛው ዛራ ቀድሞ እጁን ሲያወጣ አዋላጇ የብኩርና
ምልክት የሆነውን ቀይ ፈትል በእጁ ላይ አሠረችለት፣ ነገር ግን ፋሬስ ዛራን ቀድሞ ተወለደ፡፡ በዚህም
ምክንያት እናቱ ‹‹ለምን ጥሰህ ወጣህ›› ስትል ስሙን ፋሬስ አለችው፡፡ ዘፍ 38፡29
 ኢካቦድ፡ የዔሊ ልጅ የፊንሐስ ሚስት ምጥ ደርሶባት ሳለ ፍልስጤማዊያን ታቦተ ጽዮንን እንደማረኩ
ሰማች፤ ልጁንም ከወለደች በኋላ ይህንን ታሪካዊ ክስተት ለማዘከር /ለማስታወስ/ ስትል ‹‹ ክብር
ከእስራኤል ለቀቀ ስትል የሕጻኑ ስም ኢካቦድ ብላ ጠራቸው፡፡›› 1 ኛ ሳሙ 4፡21
 ያቤጽ፡ ‹‹እናቱ በጣር ወልጄዋለሁና ብላ ስሙን ያቤጽ አለቸው›› ይህም ሲወለድ የደረሰባትን ሕማም
ያመለክታል፡፡ 1 ኛ ዜና 4፡9
1.2. ለቦታዎች የሚሰጥ ስያሜ
 ቤቴል፡ ከሁለት የዕብራይስጥ ቃላት የተገኘ ሲሆን እነርሱም ‹‹ቤት›› እና ‹‹ኤል›› ናቸው፤ ቤት ማለት
በአማርኛም ቤት ማለት ነው፣ ኤል ማለት ደግሞ አምላክ ወይም እግዚአብሔር ማለት ነው፤ በአንድነትም
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 22
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የእግዚአብሔር ቤት የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል፡፡ የጥንት ስሟ ሎዛ ነበር ነገር ግን ያዕቆብ በሕልሙ


እግዚአብሔርን ስላየባት ቤቴል ብሎ ሰይሟታል፡፡ እስከ ዛሬም በዚያው ስም ትጠራለች፡፡ ዘፍ 28፡14
ስያሜዋን ያገኘችውም በቦታው ከተፈፀመው ድርጊት አንፃር መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
 አቤንኤዘር፡ ነቢዩ ሳሙኤል የእስራኤል ልጆች ያመልኳቸው የነበሩትነን በኣሊምና አስታሮት የተባሉ
ጣኦታትን እንዲያርቁ ሲነግራቸውም ምክሩን ተቀብለው አስወግደዋል፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር
ይቅር እንዲላቸው እስራኤል በምልጃ ለጸሎት ሲሰበሰቡ ፍልስጤማውያን በጠላትነት ሊያጠቋቸው
መጡባቸው፤ ያን ጊዜ ነቢዩ ሳሙኤል ስለ ወገኖቹ ጸለየ እግዚአብሔርም ሰማው፣ እስራኤልም
ፍልስጤማውያንን አሳደው መቷቸው፣ ከበደሉ በኋላ ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ በም…..ና በሼን
መካከል አኖረው ስሙንም አቤንኤዘር አለው፤ ትርጉሙም እስካሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ማለት
ነው፡፡ 1 ኛ ሳሙ 7፡12
 ጎልጎታ፡ ቃሉ የዕብራይስጥ ሲሆን በግሪክ ደግሞ ቀራንዮ ማለት ነው፡፡ ትርጓሜውም የራስ ቅል ማለት
ነው፣ ዮሐ 19፡17 የራስ ቅል የተባለውም ቦታው የአዳም አጽም የተቀበረበት ስለሆነ ነው፡፡ ለዚህም ነው
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቦታ ሁሉ መርጦ የመሬት መካከለኛ በምትሆነው ስፍራ ስለ
አዳም ልጆች በደል በገዛ ደቃዱ ቅድስት ነፍሱን ከክቡር ሥጋው በዚህች ስፍራ ያኖረው፡፡
 ጌልጌላ፡ ጌልጌላ ማንከባለያ ማለት ነው፤ እስራኤል ከግብጽ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ የተወለዱት ወንዶች
አልተገዘሩም ነበር፤ እግዚአብሔርም ኢያሱን እነዚህ ሰዎች እንዲገዘሩ አዘዘው፤ ኢያሱም እንደታዘዘው
አደረገ፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚአብዘሔር ኢያሱን ‹‹ የግብጽን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለው አለው ››
በዚህ መነሻ የዚህ ስፍራ ስም ጌልጌላ ተባለ፡፡ መጽሐፈ ኢያሱ 5፡2-9
1.3 ለሰዎች የሚሰጥ ቅጽል
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተመሳሳይ ስም የሚጠሩ የተለያዩ ሰዎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ሰዎች አንዱን
ከሌላው ለመለየት ግብራቸውን ወይም የተወለዱበትን ቦታ ወይም ቤተሠባቸውን እንደመለያ በማድረግ
ቅጽል ይሰጣቸዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ተመሳሳይ ስም እንኳን ሳይኖር ቅጽል ሊሰጥ ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡ ዮሐንስ
እና ያዕቆብ ወልደነጎድ Õ ድ (ቦኤኔርጌስ) እንደተባሉ ነጎድ Õ ድ ደረቁ አየር እና እርጥቡ አየር ሲገናኝ
የሚፈጠር ከፍተኛ የሆነ ድምጽ ነው እንዲሁ ዮሐንስ እና ያዕቆብ በነገዳቸው በአባታቸው ከነገደ ይሁዳ
በእናታቸው ከነገደ ሌዊ ነበሩ እኚህ ሁለቱ ነገዶች ደግሞ ሀያላን እና እርስ በእርስ የማይግበቡ ስለነበሩ
ከእነርሱ የተኙ ለጆችም ቁጣን የሚያስተምሩ ናቸው ሲል ነው፡፡ በዋናነት የሚከተሉትን እነመልከት፡
1.3.1 በግብራቸው
ከጠባያቸው፣ ይሠሩት ከነበረው ሥራ ከቁመናቸው በመነሳት የተቀጸለላቸው ማለታችን ነው፡፡
ከእነዚህም መካከል፡-
 መጥምቀ ዮሐንስ፡ የጻድቁ ካህን ዘካርያስ እና የቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ ነው፤ በተወለደ በ 8 ኛው ቀን
እናቱና አባቱ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እነደነገራቸው ዮሐንስ አሉት፡፡ ነገር ግን ከሌሎች ዮሐንሶች
/በማቴ 3፡1፣ማቴ 14፡8፣ ማር 8፡25፣ ማቴ 17፡13 ካሉትየሚለየው ወለደ አምላከ ኢየሱስ ክርስቶስን
/ፈጣሪውን/ ያጠመቀ በመሆኑ ነው፤ በዚህም መጥምቀ ዮሐንስ ተብሏል፡፡
 ስምዖን ጴጥሮስ፡ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከል አንዱ ሲሆን ሊቀ ሐዋርያት እየተባለ ይጠራል፤
እናትና አባቱ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን ጴጥሮስ ያለው ጌታችን ነው ዮሐ 1፡43 ጴጥሮስ ቃሉ የግሪክ
ነው፣ በአርማይክ እና በሱርስት ደግሞ ኬፋ ማለት ሲሆን ትርጉሙም አለት ማለት ነው፤ ማቴ 16፡15-18፤
ቅዱስ ጴጥሮስ ስምዖን እንደሚባል በማቴ 4፡18፣ ማቴ 10፡2፣ ማቴ 16፡16፣ ሉቃ 5፡7፡፡
 ስምዖን አረጋዊ፡ ከሌሎች ስምዖኖች ለመለየት በዕድሜው አንጋፋነት ይጠቅሰዋል፡፡
 ማርያም እንተ እፍረት፡ የአልዓዛር እህት /እኅተ አለዓዛር/ በሚል ቅጽል ስም ትጠራለች፣ ማርያም እንተ
እፍረት ማለት ማርያም ባለ ሽቱ ማለት ነው፡፡ ባለ ሽቱ የተባለችበት ምክንያት ጌታ በቢታንያ
በፈሪሳዊው በስምዖን ቤት ሳለ ሽቱ ስለቀባችው ነው፡፡ ዮሐ 2፡1-8

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 23


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1.3.2. በትውልድ ቦታ
መጽሐፍ ቅዱስ በተመሳሳይ ስም የሚጠሩ የተለያዩ ሰዎች ስለሚኖሩት አንዱን ከሌላው ለመለየት
ከተጸውዖ /መጠሪያ/ ስማቸው በተጨማሪ የትውልድ ቦታቸውን እንደ ቅጽል ይጠቀማል፤ ለአብነት ያህልም፡
 መግደላዊት ማርያም፡ የትውልድ ቦታዋ ሜጌደል ስለሆነ በዚህም መግደላዊት እየተባለች ትጠራለች፤
ሜጌደል በጥብሪያዶስ ባሕር አጠገብ የምትገኝ መንደር ናት፡፡ ማቴ 15፡39፣ ማር 8፡110
 ቴስብያዊው ኤልያስ፡ በዚህ ስም የሚጠራው ታላቁ ነቢይ ኤልያስ ሲሆን በትውልድ ቦታው ‹‹ቴስቡ››
ቴስብያዊው በሚለው ቅጽል በ 1 ኛ ነገ 17፡1፣ 2 ኛ ነገ 1፡3-8 ተጠርቷል፡፡
 ሞዓባዊቷ ሩት፡ የትውልድ ሀገሯ ሞዓብ ስለሆነ ሞዓባዊቷ እየተባለች ትጠራለች፡፡ መ.ሩት 2፡21
1.3.3 በቤተሰብ መጠራት
ዕብራዊያን በሀገራቸው ለአንድ ሰው ስም ሲያወጡ ከቤተሰቦቻቸው መካከል የአንዱን ስም
በመውሰድ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ መጥምቁ ዮሐንስ በ 8 ኛው ቀን ዮሐንስ ከመባሉ በፊት ዘካርያስ ሊሉት አስበው
ነበር፡፡ ሉቃ 1፡ 59
 ኢያሱ ወልደ ነዌ፡ የሊቀ ነቢያት ሙሴ ደቀ መዝሙር የሆነው ኢያሱ፤ ወልደ ነዌ /የነዌ ልጅ/ በሚል
ተጠርቷል፡፡ ከሌሎች በስሙ ከሚጠሩት ሰዎች ይለያል፡፡ ኢያሱ 1፡1
 የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፡ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን በወንጌል የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ ተብሎ
ተጠርቷል፡፡ ማቴ 3፡17-18፣ ሉቃ 6፡14-16፣ የሐዋ. ሥራ 1፡13-14፤ በማር 5፡40 ላይ ታናሹ ያዕቆብም በሚል
ተጠርቷል፡፡
 የያዕቆብ እናት ማርያም፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማርያም በሚለው ስም ከሚጠሩት አንዷ ስትሆን
በልጆቿ ስም ቅጽልነት የያዕቆብ እናት ማርያም ተብላ ትጠራለች፡፡ ማር 12፡40፣ ማር 16፡1፣ ሉቃ 27፡10፤
ከዚህ በተጨማሪም በዮሐ 19፡25 የቀልዮጳ ሚስት ማርያም እየተባለች በባሏ ስም ቅጽልነትም
ትጠራለች፡፡
የአነጋገር ዘይቤ
በተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ እና በተለያየ ሀገር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የየራሳቸው የሆነ ይትባሀል አላቸው፡፡
ስለሆነም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በአብዛኛው የሀገረ እስራኤል ነዋሪዎችን የአነጋገር ዘይቤ እናገኛለን፡፡
አንድ ቃል በአንዱ ሀገር ሲነገር ካለው ትርጉም በሌላ ሀገር ሲነገር ካለው ትርጉም ጋር የማይመሳሰልበት ጊዜ
ይኖራል፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ለመረዳት የሕዝበ እስራኤልን የአነጋገር ዘይቤ ጠንቅቆ ማወቅን
ይጠይቃል፡፡ ዘይቤው ከታወቀ የንግግሩን ፍሬ አሳብ ወይም መዳረሻ በትክክል ያሳያል፡፡ ቀጥለን በመጽሐፍ
ቅዱስ ከሚንፀባረቁት የዕብራዊያን የአነጋገር ዘይቤዎች ጥቂቶቹን እንመልከት፡፡
ደጊሞተ ቃል
አንድን አሳብ በቁርጠኝነት ወይም በአፅንኦት መገለጥ ሲያስፈልግ ዕብራዊያን የሚጠቀሙበት
የአነጋገር ስልት ደጊሞተ ቃል ወይም ከሚናገሩት ዐረፍተ ነገር ውስጥ አንዱን ቃል ደግሞ በመናገር ነው፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ ያሉ አነጋገሮችን በብዛት እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ፡-
 ‹‹ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርሷ የተላኩትነም የምትወግር፣ ዶሮ
ጫጩቶቿን ከክንፎቿ በታች እንደምትሰበስብ ለጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ፣
አልወደዳችሁምም፡፡›› በማለት ጌታችን ሁለት ጊዜ ኢየሩሳሌም ብሎ መናገሩ የኢየሩሳሌም ልጆችን
አመጽ አፅንቶ መናገሩ ነው፡፡ ማቴ 23፡ 37
 ‹‹እውነት እውነት እልሃለው ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ያይ ዘንድ
አይችልም ›› ሲል ያለ ጥምቀት ጽድቅ እንደሌለ በአጽንኦት መናገሩን ያስረዳናል፡፡ ዮሐ 3፡ 3-5
 ‹‹ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ክፈትልን›› ማቴ 25፡11
 ‹‹አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ›› መዝ 21፡1

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 24


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

 ‹‹እውነት እውነት እላችኃለው ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚመጣ እርሱ ሌባ
ወንበዴ ነው፡፡›› ዮሐ 10፡1
‹‹ከ………………ጋር ምን አለኝ››
ዕብራዊያን የተጠየቁትን ነገር ለመፈፀም /ለማድረግ/ እንዳይችሉ የሚያግዳቸው ምንም ጠብ ወይም
ምንም ምክንያት እንደሌለ ለማስረዳት የሚጠቀሙበት የራሳቸው ስልት አለ፡፡ እርሱም ‹‹ ከአንተ ወይም
ከአንቺ ወይም ከእናንተ ጋር ምነ አለኝ›› የሚለው ጥያቄ አዘል አባባል ነው፡፡ በኢትዮጲያዊያን ዘንድ እንዲህ
ያለው አነጋገር/‹‹ ከአንተ ወይም ከአንቺ ወይም ከእናንተ ጋር ምነ አለኝ ››/ ምን ግንኙነት አለን የሚል
የተቃውሞ ትርጉም አለው፡፡ በዕብራዊያን ዘንድ ግን የፍቅር፣ የትህትና ወይም የታዛዥነት አነጋገረር ነው፡፡
ይህንንም ከሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ለመረዳት እንችላለን፡፡

የሰራፕታዋ መበለት፡- ነቢዩ ኤልያስ በምድር ላይ ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን በለጎመ ጊዜ እግዚአብሔር
ኤልያስን ወደ ሰራፕታ ሂድ በዚያም አንዲት ሴት ትመግብህ ዘንድ አዘጋጅቼልሃለው አለው፡፡ ኤልያስም ወደ
ሰራፕታዊቷ መበለት ቤት ገብቶ የነበረቻትን ጥቂት ዱቄትና ጭላጭ ዘይት ባርኮ ዝናብ እስከሚመጣ ድረስ
ለ 3 አመት ተኩል ያንኑ እየተመገቡ ቆዩ፡፡ ከዚያም ነቢዩ ኤልያስ ወደ ቄርሜሎስ ተራራ (ወደ ባዕቱ) ሄደ፡፡
ነገር ግን ለዚህች መበለት የነበራት ብቸኛ ልጅ በጠና ታመመና ሞተ፤በዚያን ጊዜም ነቢዩ ኤላያስን ካለበት
ድረስ ሄዳ እነዲህ አለችው፡ ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ›› ኃጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ
ልጄንስ ትገስፅ ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?›› አለችው፡፡ 1 ኛ 17፡18

መበለቷ በዚህ ንግግር ነቢዩ ኤልያስን ‹‹ከአንተ ጋር ምን አለኝ ›› ማለቷ ምን ጠብ አለኝ


ያጠፋሁትስ ነገር ምንድነው? ለማለት የተናገረችው ነው እንጂ የጠብ ወይም የጥላቻ ንግግር አይደለም፤ ነቢዩ
ኤልያስ በመበለቷ ቤት በነበረበት ሰዓት ኃጢአት ስትሰራ ያያት፣ ኋላም ለእግዚአብሔር ያመለከተባት ወይም
ያሳሰበባትና ላጠፋችው ጥፋት መቀጣጫ ልጅዋን ያስቀጸፈባት መስሏት፤ እንጨት ሰለቅም ከገኘሁህ ጀምሮ
አገለገልሁህ እንጂ ምን አጥፍቻለው ማለቷ ነው፡፡ በቋንቋውም ስለተግባቡ ነቢዩ ልጇን ከሞት
አሥነስቶላታል፡፡ ልጇን እንዲፈውስላት ልትለምነው ሄዳ የስድብ ቃል ልትናገር አትችልም፡፡

ቅዱስ ዳዊት፡- ንጉሥ ዳዊት በኦርዮና በሚስቱ ላይ ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔር ሊቀጣው ፈለገ፡፡ በዚህ
ምክንያት ካገኘው ቅጣት አንዱ የልጁ አቤሴሎም በእርሱ ላይ መሸፈት ነው፡፡ አቤሴሎም ራሱን አንግሦ
በነበረበት ወቅት ቅዱስ ዳዊት የዱሩያ ልጆችንና ሌሎችንም አስከትሎ ሸሸ፡፡ በሽሽት ላይ እያለም ከሳኦል
ቤት የሆነ ሳሚ የሚባል ሰው በዳዊትና በተከታዮቹ ላይ እየተሳደበ ድንጋይ ወረወረ፡፡ በዚህ ጊዜ ከንጉሥ ዳዊት
ተከታዮች አንዱ የሆነው የዱሩያ ልጅ የሆነው አቢሳ በንጉሡ መሰደብና መደፈር በጣም ተናደደና ‹‹ይህ
የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን ዳዊት ይረግማል? ልሂድና ራሱን ልቁረጠው›› አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሡ ቅዱስ
ዳዊት እናንተ የጽሩያ ልጆች እኔ ከእናንተ ጋር ምን አለኝ እግዚአብሔር ዳዊትን ስደበው ብሎ አዝዞታልና
ይርገምኝ ለምንስ እንዲህ ታደርጋለህ የሚለው ማነው? ›› አለ፡፡ እንደገናም ‹‹እነሆ ከወገቤ የወጣው ልጄ
ነፍሴን ይሻል፤ ይልቁንም ይህ የብንያም ልጅ እንዴት ነው? እግዚአብሔር አዝዞታልና ተዉት ይርገመኝ ፤
ምናልባት በዚህ ቀን መከራዬን አይቶ ስለ እርግማኔ መልካም ይመልስልኛል አላቸው፡፡›› 2 ኛ ሳሙ 16፡9-12
ኃይለ ቃሉን በረዥሙ ማስፈር ያስፈለገው ቅዱስ ዳዊት ለምን ‹‹ከእናነተ ጋር ምን አለኝ?›› ሊል እነደቻለ
በሚገባ እንድንረዳው ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ማለቱ የዱርያን ልጆች መሳደቡ አይደለም፣ የአብራኩ
ክፋይ የሆነው ልጁ ሲከዳው እነርሱ ግን ለእረሱ ወግነው ተከትለውታል ይልቁንም ሲሰድባቸው የማይወዱ
ናቸው፤ ታዲያ ቅዱስ ዳዊት ለምን እንደዚያ ተናገረ? ቅዱስ ዳዊት ለአቢሳ ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ከተናገራቸው
ውስጥ ‹‹እግዚአብሔር ዳዊትን ስደበው ብሎታልና ይርገመኝ ምናልባት በዚህ ቀን መከራዬን አይቶ ስለ
እርግማኔ መልካም ይመልስልኛል ›› ያለውን ማጤን ያስፈልጋል ፡፡ የቅዱስ ዳዊት እምነት ሳሚ የሚሰድበኝ
በራሱ ተነሣስቶ ሳይሆን እግዚአብሔር ፈቅዶለት ነው የሚል ነው፤ ይህ ደግሞ ለሠራሁት ኃጢአት የሚገባኝ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 25


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ቅጣቴ ነው፡፡ አንተ ሔደህ ብትገድለው እግዚአብሔር የወሰነብኝን ቅጣት ሳልቀበል እቀራለሁ፡፡ ለጊዜው
ያዋረደኝ ቢመስልም ግን በኋላ እከብርበታለሁ፤ ይህ ደግሞ ለእኔ ጥቅም ነው፡፡ ታዲያ ይህንን ጥቅም
እንዳላገኝ የሚያደርግ ‹‹ከእናንተ ጋር ምን ጠብ አለኝ? ›› ማለት ነው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡- በገሊላ ቃና በዶኪማስ ቤት ሰርግ ሆነ፤ በዚህም ሰርግ ላይ ጌታችን መድሀኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ደቀ መዛሙርቱ አብረው ነበሩ፡፡ ድንገት በሰርጉ
ቤት ውስጥ አስደንጋጭ ጉዳይ ተከሠተ፤ እድምተኛው ገና ሳይሸኝ የወይን ጠጁ አለቀ፡፡ በዚህ ጊዜ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማንም ሰው ሳይነግራት የወይን ጠጅ ማለቁን አወቀች፤ ስለሆነም
‹‹የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም›› ብላ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስን ጠየቀችው፡፡ እርሱም ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር
ምን አለኝ? ጊዜዬ አልደረሰምና›› አላት፡፡ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአገልጋዮቹ ‹‹የሚላችሁን
አድርጉ›› አለቻቸው፤ ዮሐ 2፡4

በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ‹‹ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ›› የሚለው የጌታ ንግግር አገባቡ ልክ በሌሎቹ
ክፍሎች እንዳየነው ተመሳሳይ ነው፡፡ ጌታችን በዕብራዊያን የአነጋገር ዘይቤ ነው የተናገረው፤ የሐረጉ ፍቺም
እናቴ የለመንሽኝን እንዳላደርግ የሚከለክል ምን ጠብ አለኝ? ማለት ነው፡፡ እንዲህማ ባይሆን ኖሮ
እመቤታችን ለአገልጋዮቹ ‹‹የሚላችሁን አድርጉ›› ባላለቻቸው ነበር፡፡ እናትና ልጅ በንግግሩ ስለተግባቡበት
የሚቀጥለው ውኃውን ሙላትና ወደ ወይን ጠጅ መለወጥ ስለሆነ አገልጋዮቹን ወዲያውኑ ያለምንም
የሚላችሁን በሚገባ ባለመረዳት ‹‹ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?››ስላላት እመቤታችን አታማልድም ይላሉ፡፡
ከደጋሾቹም ይሁን ከታዳሚዎቹ አንድም ሰው ስለደረሰው አስደንጋጭ ችግር ምንም ሳይተነፍሱ የልብን
አውቃ ከውርደት ከማውጣት በላይ ከቶ ምን ሊኖር ይችላል? ለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው
በዕብራዊያን ነው ስለሆነም የዕብራዊያንን ባህል ይከተላል፡፡ ይህም ከኢትዮጵያውያን ባህል ጋር ፈፅሞ
አይመሳሰልም፡፡ ከላይ እንደተረዳነው ከ……ጋር ምን አለኝ? የሚለው በዕብራዊያን ዘንድ ፍቅርን ሲገልጥ
በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ግን ጥላቻን ይገልጣል፡፡
ኃዘን
በመካከለኛው ምሥራቅ ይኖሩ የነበሩት ሰዎች ኃዘናቸውን በተለያየ መንገድ ይገልጡ ነበር፡፡ ከእነዚህም
መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡
ልብስ መቅደድ፡- ጥንት በመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ የመሪር ኃዘን ምልክት ነበር፡፡ ለምሳሌ፡ ታላቁ
የእግዚአብሔር ሰው ያዕቆብ ልጆቹ ዮሴፍን ሸጠው አውሬ በላው ባሉት ጊዜ የደረሰበትን ኃዘን ልብሱን
በመቅደድ ገልጧል፡፡ ‹‹ያዕቆብም ልብሱን ቀደደ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ፡፡››
እንደተባለ ዘፍ 37፡ 34
አካን የተባለው ሰው እርም የሆነ ነገር በምንካቱ እግዚአብሔር ተቆጣ፤ በሁኔታውም ኢያሱ እጅግ አዘነ፡፡
ይህንንም ‹‹ኢያሱም ልብሱን ቀደደ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ስር
…….ተደፋ፡፡›› መ.ኢያሱ 7፡6 ከዚህም እንደምንረዳው ልብስን መቅደድ ከኃዘን በተጨማሪ ቁጣንም
ያመለክታል፡፡
ታቦተ ጽዮንን ፍልስጤማውያን በማረኩ ጊዜ ‹‹አንድ የብንያም ሰው ከሰልፍ /ከጦር ሜዳ/ እየበረረ ልብሱን
ቀድዶ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ወደ ሴሎ መጣ፡፡›› ይላል 1 ኛ ሳሙ 4፡12 ብንያማዊው ሰው ልብሱን
የቀደደው ታቦተ ጽዮን በመማረኳ እጅግ በማዘኑ ነው፡፡
ነቢዩ ኤርሚያስ በእስራኤል ላይ ስለመጣው መከራ ሲያዝን ልብሱን ቀድዶ ነበር፡፡ ‹‹ያን ጊዜ ልብሱን ፤ቀደደ
በራሱም ላይ ትቢያ ነሰነሰ፡፡›› ተብሎ እንደ ተጻፈ ተረፈ ኤር 7፡19
እስራኤላዊያን ኃዘናቸውን ለመግለጥ ከልብስ መቅደድ በተጨማሪ ሌሎች ድርጊቶችንም ያከናውኑ ነበር፡፡
ለምሳሌ፡ ያዕቆብ ኃዘኑን ሲገልጥ ማቅ ታጥቆ ነበር፤ ዘፍ 37፡ 34

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 26


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ንጉሥ ሕዝቅያስም በራፋስቅያስ ድንፋታ ስለተበሳጨ እና ስላዘነ ልብሱን …..ማቅ ለብሷል፡፡ 2 ኛ ነገ 19፡1፤
ከእነዚህ በተጨማሪም ያዘኑ ሰዎች በራሳቸው ላይ ትቢያ መነሥነስ የተለመደ ነው፡፡ 1 ኛ ሳሙ 4፡12፣ 2 ኛ
ሳሙ 15፡32 ተረፈ ኤር 7፡19፣ መርዶክዮስ በመቶ ሃያ ሀገር ያሉ ወገኖች እንዲሞቱ በታወጀ ጊዜ ልብሱን ቀደደ
ማቅም ለበሰ አመድም ነሰነሰ፤ መ.አስቴር 1፡1 እንዲሁም ደረት መድቃት፣ የኃዘን መግለጫ ነው፡፡ በተለይም
በሴቶች ይፈፀማል፡፡ ሉቃ 18፡13

ራስን መላጨት፡- ራስን ሌላው የኃዘን መግለጫ ነው፡፡ መ.ኢያሱ 1፡20፤ ት. ኢሳ. 22፡12፣ 2 ኛ፣ የሐዋ ሥራ
4፡37፣ ማር 16፡1፣ ዮሐ 19፡40፣ ዮሐ 12፡3-7፣ ዮሐ 11፡44 ዘፍ 23፡4፣ ዮሐ 11፡38-41፣ ማቴ 27፡60፤ በኃዘን
ጊዜራስን መላጨት በእኛም ሀገር ያለ ባህል ነው፡፡

ሰው ሲሞት የኃዘን ጊዜ እስከ ሰባት ቀን ይቆያል፡፡ ኃዘንተኞች ሥራ መሥራት፣ መታጠብ፣መቀባት፣ ጫማ


መድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡ የኦሪትንና የነቢያትን መጻሕፍት ማንበብ ደስታን ይሰጣል ተብሎ ስለሚታመን
ኃዘንተኛ የሆነ ሰው እነዚህን መጻሕፍት አይመለከታቸውም፡፡ መጽሐፈ ኢዮብ፣ ትንቢተ ኤርሚያስ፣
ሰቆቃው ኤርሚያስን ግን ያነባሉ፡፡ ፀጉርን መከርከምም ጌጥ ማድረግ የተቀደደ ልብስ እንኳን ቢኖር እስከ
ሰላሳ ቀን ድረስ አይጠቀምም /አይሰፋም/ መንገድ መሄድ የሚባክን ሀብት እንኳን ቢኖር መሰብሰብ ሥጋ
መብላትና ወይን ጠጅ መጠጣት አይፈቀድም፡፡ ሲመገቡም መሬት ላይ ተቀምጠው ነው፡፡ከዚህም በቀር
እነቁላል በአመድና በጨው እያረመዱ እያጠቀሱ ወይም እየቀላቀሉ ይመገባሉ፡፡ አንዱ ኃዘንተኛ ሰላሳ ቀን
ሳይሞላው ከከተማ አይወጣም፡፡ ነገር ግን ባለቤቱ መካን ከነበረች ወይም ሕፃን ትታ ከሞተች ከሰባተኛው
ቀን በኋላ እነዲያገባ ይገቀድለታል፡፡ ከቤተሰብ መካከል አንዱ የቤተሰቦቹን ሃይማኖት ትቶ ሌላ ያገባ እነደሆነ
ልክ እንደ ሞተ ሰው ይለቀስለታል፡፡

የሟችን አስከሬን በ 3 ኛው ቀን ወደ መቃብር ሄዶ ሽቱ መቀባት ሌላው ባህል ነው፤ ማር 16፡1-3፣ በዚያም


ሆነው ያለቅሳሉ፤ ዮሐ 11፡36፡፡ በእኛም ሀገር ሠልስት ይባላል፡፡
አመጋገብ
የእስራኤላዊያን ዋና ምግብ ቂጣ ወይም ዳቦ ነበር፡፡ ስንዴው አስቀድሞ ገለባውና እንክርዳዱ
እንደዚሁም አፈሩ ተለቅሞ ይበጠርና ታጥቦ ከቤት ጣሪያ ላይ ይቀመጣል፡፡ ከደረቀ በኋላ በእህል ጎተራ ውስጥ
ይደረጋል፡፡ እህል የሚፈጨው በቤት ወፍጮ ሲሆን የወፍጮ መጅ ለሁለት ሴቶች እንዲያመች ተደርጎ
የተሠራ እጀታ አለው፡፡ እህሉ የሚፈጨው ሁለት ሴቶች በአንድነት የመጁን እጀታ ጨብጠው መጁን ወደ
ፊትና ወደ ኋላ በማመላለስ ነው፡፡ በአንድ ወፍጮ ላይ ሁለት ሴቶች በአንድ ጊዜ ስለሚፈጩ ጌታችን ሰለ
ዳግም ምፅዓት ሲናገር ‹‹ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ አንዲቱ ትወስዳለች አንዲቱም ትቀራለች፡፡››
አለ፡፡ ማቴ 24፡41 በእኛ ሀገር ግን በአንድ ወፍጮ ላይ አንዲት ሴት ብቻ ትፈጫለች፤ ይህም የሀገሩን ባህል
ካለማወቅ ያደናግራል፡፡

ዳቦ ወይም ቂጣ የሚጋገረው ከስንዴ ከገብስና ከበቆሎ ነው፡፡ እንጀራ ወይም ቂጣን በእጅ ቆርሶ
መብላት የተለመደ አመጋገብ ነው፡፡ እንደዚሁም እንጀራና ቂጣ በእጅ እየቆረሱ መስጠት ወይም መቀበል
በእንግዳ ተቀባይና በእንግዳው መካከል ሰላምና ፍቅር መኖሩን ያሳያል፤ እንደ እኛ ሀገር መጎራረስ ያለ ነው፡፡
የአስቆሮጡ ይሁዳ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ እጅ እንጀራ ተቀብሎ ከበላ በኋላ ጌታውን አሳልፎ
በመስጠቱ ይህን የአይሁድ ሥርዓት ጥሷታል፡፡
የከብት ሥጋ በእስራኤል ዘንድ የተለመደ ምግብ ነው፡፡ ከጎመን፣ ከአትክልት ጋር ከበሰለ በኋላ በቂጣ እያጠበቁ
መመገብ የተለመደ ነው፡፡ ለማዕድ ከተሰበሰቡ በኋላ ቂጣ ቆርሶ መስጠት የፍቅር መግለጫ ነው፡፡ ጌታ ለይሁዳ
ቁራሽ አጥቅሶ ሰጥቶታል፡፡ ዮሐ 13፡26 ይህም ምንም እንኳን ይሁዳ አሳልፎ እንዲሰጠው ጌታችን ቢያውቅም
እርሱ ግን በፍፁም ፍቅር እንደሚወደው ያሳየናል፡፡ ሌላም ተወዳጅ ምግባቸው ዓሣ ነው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 27


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ከፍራፍሬ ውስጥ በእስራኤል በብዛት የሚበቅሉት በለስና ወይን ናቸው፤ እነዚህም በጣም የሚወደዱ
ሲሆን ከቂጣና ከዳቦ ጋር ይመገቧቸዋል፡፡ በምግብ ሰዓት ብዙ ውኃ መጠጣት የተለመደ ነው፡፡ ውኃ ሲጠጡ
የመጠጫውን ዕቃ በከንፈራቸው ሳይነኩ ወደ አፋቸው እንዲንቆረቆር ያደርጋሉ፡፡ የወይን ጠጅ በመጠጣትም
የሚታወቁ ሲሆን ብዙ ግን አይጠጡም፡፡
በቀን ሁለት ጊዜ ምግብ የመመገብ ልማድ አላቸው፡፡ አንደኛው ከገበያ ተመልሰው በሚያርፉበት ሰዓት
በቀትር ሲሆን በዚህም ሰዓት ቀላል ምግብ ፡ ቂጣ በወይን ጠጅ ወይም ዓሣ ሊሆን ይችላል፡፡ በሁለተኛው ጊዜ
ዋናው ምግብ የሚበላው ጀምበር መጥለቂያ ላይ ነው፡፡ ይህም ተሠርቶ ድንክ ጠረጴዛ ላይ ያደርጋል፡፡
ቤተሰቡም በማዕዱ ዙሪያ ይሰበሰቡና ይመገባሉ፡፡ ሰዎች ለማዕዱ ሲቀርቡ እንደ ክብራቸው እንደ
ዕድሜያቸው በቅደም ተከል ነው፡፡ የሕገ ኦሪት መምህራን ምንም እንኳን ድሃ ቢሆኑም ከሀብታሞች ይልቅ
ከፍተኛውን ወንበር እንዲይዙ ይደረጋል፡፡ ይህም የአቀማመጥ ሥርዓት በሀገራችን ይደረጋል፡፡
የሰዓት አቆጣጠር
በእስራኤል አንድ ቀን የሚባለው ፀሀይ ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ ያለውን ጊዜ ነው፡፡ ስለዚህም
የመጪው ቀን ዋዜማ በቀዳሚው ቀን ማታ ይጀምራል፡፡ ይህም ማለት አንድ ቀን የሚባለው 24 ሰዓት ያለው
ሲሆን ዕለቱ የሚጀምረው ከምሽት ነው፡፡ ለምሳሌ፡ የቅዳሜ ሰንበት ዕለቱ (ቀኑ) ከዓርብ ምሽት ይጀምራል፡፡
ለዚህም ነው ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ ዓርብ እየመሸ ሲሄድ ‹‹ሰንበትም ሲጀምር ነበር›› የተባለው ማር 15፡54
፡፡ ለሥራም የሚሠማሩት ፀሀይዋ ስትወጣ ነው፡፡ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሲሆን እኩለ ቀን ይባላል፡፡ አሥራ አንድ
ሰዓት የሚባለው ፀሀይ ልትጠልቅ አንድ ሰዓት ሲቀራት ነው፡፡ ይህም ማለት ፀሀይ የምትጠልቀው አሥራ
ሁለት ሰዓት ላይ ነው፡፡
ሰርግ
የሀገረ እስራኤል ሰርግ ከፍተኛ ከበሬታ ነበረው፡፡ የመተጫጨት ውልም የሚፈፀመው በአብዛኛው
በወላጆች አማካኝነት ነው፡፡ የጋብቻው ሥነ ሥርዓት የሚፈፀመው በወንድየው ቤት ውስጥ ነው፡፡ ሙሽራው
የጋብቻው ዕለት ከቤቱ ወጥቶ ወደ ዘመድ ቤት ሄዶ ይቀመጣል፡፡ በዚህ ጊዜ መሽራይቱ ወደ እጮኛዋ ቤት ሄዳ
የሰርግ ልብስዋ….ን ለብሳ የሙሽራውን መምጣት ትጠባበቃለች፡፡ ዘመድ አዝማድ በዕለቱ በመሰብሰብ
አመሻሽ ላይ በሙሽራው ቤት ይገኛሉ፡፡ ሚዜዎቹና እድምተኞች ሙሽራው ቤት ተሰብሰበው የሙሽሮቹን
ቤተሰቦች በማሞገስ ሲጫወቱ ያመሻሉ፡፡ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ ሙሽራው ወደ ቤቱ ለመመለስ ፈቃድ
ይጠይቅና ሲፈቀድለት ለመሄድ ይነሳል፡፡ የሙሽራው አጃቢዎች መውጣት ሲጀምሩ አንዳንድ የሻማ ወይም
የኩራዝ መብራት ይሠጣቸውና እያያዙ ጉዞውን በዝግታ ይቀጥላል ሸኚዎቹ ችቦ እያበሩ ይከተላሉ፡፡

ሙሽራው በሚያልፍበት መንገድ ሁሉ ግራና ቀኝ የሚኖሩት ሰፈርተኞች ሙሽራው ሲያልፍ እልል


እያሉ ደስታቸውን በመግልፅ ያሳልፋታል፡፡ በዚህ ሁኔታ እልልታው እያስተጋባ እኩል ሌሊት ሲሆን ሙሽራይቱ
ካለችበት ጊዜ ሲደርሱ ከሙሽራቱ ጋር የሙሽራውን መምጣት ይጠባበቁት የነበሩት የመሽራይቱ ሚዜዎች
የችቦ መብራትን ሻማ ወይም ኩራዝ አብርተው ሙሽራውን ከበር ውጪ ድረስ ወጥተው ይቀበሉታል፡፡
ጌታችን በወንጌል መንግሥተ ሰማያትን በዓሥር ቆነጃጅት መስሎ ሲያስተምር ‹‹እኩለ ሌሊትም ሲሆን
እነሆ ሙሽራው ይመጣል ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ፡፡›› ያለው በሀገራቸው ሙሽራ ወደ ቤቱ
የሚመጣው በእኩለ ሌሊት መሆኑን ያጠይቀል፡፡ ማቴ 25፡6 በእኛ ሀገር ባህልም ሙሽራው ወደ ቤቱ
የሚገባው ሙሽሪቱን ካለችበት ከወላጆቿ ቤት አምጥቶ በምሽት ነው፤ አሁን ግን የከተማ ሰርጎች በቀን
እየሆኑ ነው፡፡

በሙሽራው ከአጃቢዎች እና ከእድምተኞች ጋር ወደ አዳራሹ ከገባ በኋላ ቤቱ ይዘጋል፡፡ ከዚህ በኋላ


ትምህረተ ሙሽራው ከገባ በ…ላ የመጡት አምስቱ ሰነፎች ‹‹ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ክፈትልን እያሉ ቢጮኹም
እውነት እውነት እላችኋለው አላውቃችሁም›› የተባሉት በሀገራቸው ሰርግ ተጠርቶ መቅረት ያሳፍራል፤
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 28
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

እድምተኞችም ወደ ሰርጉ ቤት ሲሄዱ የሰርግ ልብሳቸውነ ይለብሳሉ፡፡ ይህንን ካላደረጉ ደጋሹን ንቀዋል
ተብሎ እንዲወጡ ይደረጋል፡፡ ማቴ 22፡3-13
እግር ማጠብ
እስራኤላዊያን እንግዳ ወደ ቤታቸው ሲመጣ እግሩን የማጠብ ባህል ነበራቸው፡፡ እንግዳን በሚገባ
መቀበልና ማስተናገድ በዘመነ ብሉይም ሆነ በዘመነ ሐዲስ ታዝዟል፡፡ ኦ. ዘሌ 19፡34፣ ሮሜ 12፡13፣ 1 ኛ ጴጥ 4፡9
በዚህም መሠረት ለእንግዳ አቀባበል ከሚከናወኑ ሥርዓቶች አንዱ እግር ማጠብ ነው፡፡ አብርሃም የሥላሴን
እግር ያጠበው በዚሁ መሠረት ነው፡፡ ዘፍ 18፡4፣ ዘፍ 24፡32 ጌታችን ዝቅ ብሎ የደቀመዛሙርቱን እግር
ያጠበውም ማንም እንግዳ ወደ ቤታችን ሲመጣ ዝቅ ብለን እንድናገለግለው ለማሳየት ነው፡፡ ዮሐ 13፡1-10

ጌታችንን በቤቱ ያስተናገደው ፈሪሳዊው ሰምዖን እንደ እንግዳ አቀባበል ሥርዓት የጌታችንን እግር
ባለማጠቡ ተወቅሷል፡፡ ማርያም እንተእፍረት የጌታችንን እግር በአልባስፕሮስ ሽቱ እየቀባች ሳለች ስምዖን
ተቃወመ፤ ያን ጊዜ ጌታችን ‹‹እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ ውኃ ስንኳ ለእግሬ አላቀረብክልኝም እርሷ ግን በእንባዋ
እግሬን አራሰች በፀጉሯም አበሰች፡፡›› ሲል ገልፆታል፡፡ ሉቃ 7፡44 እግርን ከማጠብ በተጨማሪ እንግዳን ስሞ
መቀበልና ራሱን ዘይት መቀባት የተለመደ ነበር፡፡ ሉቃ 7፡45-46
የበግ እረኛ
መጽሐፍ ቅዱስ በአብዛኛው በእስራኤላዊያን ባህል የተጻፈ እንደመሆኑ የበግ እረኛንም ሁኔታ
ስንመለከት ከእኛ ሀገር የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በሀገራቸው እረኛ ከበጎች ሆኖ መንጋውን እየነዳ ነው
የሚጠብቀው፡፡ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ‹‹የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል በጎቹም
ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፡፡›› የተባለውም ለዚህ ነው ዮሐ 10፡3 በጎች እረኛውን በድምፁ በጠሩኑና
በበትሩ ያውቁታል፡፡

እረኛው በጎቹን እየመራ በመሄድ ለምለም ሳር ላይ ሲደርስ በትሩን ይተክላል፡፡ ያንጊዜ


ወደሚሄድበትም ይከተሉታል፡፡ ውኃ ሲጠጡም እንደዚሁ ነው፡፡ ዘፍ 30፡37-93

‹‹በሬ የገዥውን አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ፡፡›› በኢሳ 1፡3 ላይ የተባለው የቃሉ ፍፃሜ ጌታ ሲወለድ
እንስሳቱ ትንፋሻቸውን ገበሩ የሚለው ቢሆንም ከብቶች የጌታቸውን ቤት ማወቅ ግን የተለመደ እንደ ሆነ
ያሳየናል፡፡
ጫማ ማውለቅ
በመካከለኛው ምሥራቅ ጫማ ማድረግ የተለመደ ነው፤ ጫማ በምድር ላይ ያለውን ማንኛውንም
ነገር የሚነካ ስለሆነ በእስራኤላዊያን ዘንድ የተናቀ ነው፡፡ መጥምቀ ዮሐንስ ስለ ጌታችን ክብር ሲናገር
‹‹የጫማውን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ›› ብሏል፡፡ ዮሐ 1፡27፣ ሉቃ 3፡16 ዮሐንስ የተናቀውን ነገር እንኳን
መንካት አይገባኝም በማለት የክርስቶስን ክብር መስከሯል፡፡
እግዚአብሔር ሙሴን፣ ቅዱስ ሚካኤልም ኢያሱን ‹‹የቆምክባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን
ከእግርህ አውጣ፡፡›› ያላቸው ጫማ የተናቀ ነገር በመሆኑ ለስፍራው ክብር ሲባል ማውለቅ እንዲገባ
ያስረዳል፡፡ ዘዳ 3፡5፣ መ.ኢያሱ 5፡15

ዛሬም የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡ ጫማቸውን


ከእግራቸው ያወልቃሉ፤ ይህም የተቀደሰውን ስፍራ በቆሻሻና በተናቀ ጫማችን እንረግጥ ዘንድ አይገባንም
ሲሉ ነው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 29


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ከዚህም በተረፈ በጥንት ጊዜ አንድ ሰው የራሱ የሆነውን ነገር ቢሸጥ ወይም ቢለውጥ ነገሩን ለማጽናት
ወይም እርግጠኛ መሆኑን ለማሳየት የእግሩን ጫማ ያወልቅ ነበር፤ ጫማውነ ካወለቀ በኋላ ለባልንጀራው
መስጠት የተለመደ ነው፡፡ መ.ሩት 4፡7
በኵር
በኵር የግእዝ ቃል ሲሆን በዕብራይስጥ ደግሞ ቤኩራቲ ይባላል፡፡ ትርጉሙም የመጀመሪያ ልጅ ማለት
ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ በኵር የሚለው ቃል ማህፀን ከፋች ማለት እንደ ሆነ ያስረዳል፡፡ ዘኁ 18፡15-16 ከአንድ
እናትና አባት የተወለዱ ሁለትና ከዚያም በላይ ልጆች ቢኖሩ ከእነዚህ መካከል የመጀመሪያ የሆነው የበኵር
ልጅ ይባላል፡፡ ይሁን እንጁ የበኵር ለመባል የግድ ተከታይ ሊኖረው አይገባም፤ ብቸኛ ልጅ ከሆነም በኵር
ይባላል፡፡ አባ ጄሮም ‹‹ብቸኛ ልጅ የበኵር ልጅ ነው፣ የበኵር ልጅ ሁሉ ግን ብቸኛ አይደለም›› ብሏል፡፡

‹‹ማህፀንን የሚከፍት ሁሉ ለእግዚአብሔር ለይ›› ዘጸ 13፡12 ሲል ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ ወይም


ከዚያ በላይ ቢወለድ ባይወለድ መጀመሪያ የተወለደውን /በኵር የሆነውን/ ለእግዚአብሔር ለይ ማለት ነው፡፡
ለእግዚአብሔር የተለየ ከሰውም የተመረጠ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ የበኵር ልጅ አባቱ ሲሞት፣ ወደ ሌላ ስፍራ በሄደ
ጊዜ ቤተሰቡን ያስተዳድራል፤ በቤተመንግሥት ደግሞ አልጋ ወራሽ ነው፡፡ ዘፍ 29፡26 ‹‹ዔሳው ብኩርናውን
አቃለላት›› ሲል ለመጀመሪያ ልጆች ከእግዚአብሔርም ከሰውም የሚሰጠውን ክብር መናቁን ያመለክታል፡፡
ዘፍ 25፡34፣

ቃየን የአዳም (ዘፍ 4፡1)፣ ሴም የኖኅ (ዘፍ 4፡32)፣ ኩሽ የካም (ዘፍ 10፡6)፣ አብርሃም የታራ (ዘፍ 11፡27)፣
ኤሳው የይስሐቅ (ዘፍ 25፡25)፣ ሮቤል የያዕቆብ (ዘፍ 49፡2) የበኵር ልጆች ናቸው፡፡ ዕብ 1፡ 6 እግዚአብሔር
ወልድ የበኵር ልጅ እንደተባለ እንመለከታለን፡፡ ዮሐ 3፡16 ‹‹አንድያ ልጁ ነውና›› ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው
የአብ ብቸኛ የባሕርይ ልጁ ቢሆንም ግን በኵር ተብሏል፡፡ ስለዚህ በኵር ለመባል ግድ ተከታይ መኖር
የለበትም፡፡ ዘጸ 12፡29

በኵር የሚለው ቃል ቅድምናን ብቻ የሚያሳይበት/የሚያመለክትበት/ ጊዜ አለ፡፡ ለዚህም


የሚከተለውን የመጽሐፍ ክፍል እንመልከት፡ ቆላ 1፡15 ‹‹ከፍጥረት ሁሉ በኵር ነው፡፡›› ከክርስቶስ በፊት
ማንም እንዳልነበረ እርሱ አልፋ የመጀመሪያ መሆኑን ያለ እርሱ ፈጣሪነት ምንም ምን የተገኘ እንደሌለ
ለማስረዳ ነው፡፡ በሌላ ቦታም ‹‹ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፡፡››ይላል ቆላ 15፡23 ሐዋርያው ቅ. አትናቴዎስ
ይህን አንቀፅ ሲተረጉም ‹‹በኵር የተባለው ከእኛ አስቀድሞ ስለ ሞተ አይደለም፤ ነገር ግን ሰለ እኛ ሞቶ
ሞትን ድል በመንሳቱ ነው፡፡ ትንሣኤን በእርሱ ከእርሱ በኋላ ስለምናገኘው ነው፡፡›› ብሏል በሃይማኖተ
አበው፡፡
ወንድም
በእስራኤላዊያን ዘንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‹‹ወንድም›› የሚለውን መጠሪያ ለማግኘት የግድ
የእናትና የአባት ወይም የአንዱ ብቻ ልጅ መሆን አያስፈልግም፡፡ በተለያዩ ሁኔታ የሚቀራረቡ ሰዎችም
ወንድማማቿች ይባላሉ፡፡ ለዚህም የሚከተሉትን እንመልከት፡፡
 በሀገር ልጅ፡- በአንድ ሀገር የተወለዱ ወይም የአንድ ሀገር ሰዎች ወንድማቿች ይባላሉ፡፡ ‹‹ሙሴ ጎበዝ
በሆነ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ መጣ፡፡››ዘዳ 2፡17
 በአንድ ነገድ፡- ንጉሥ ዳዊት ለካህናቱ ለሳዶቅና አቢያታ መልእከት ሲልክ በ 2 ኛ ሳሙ 19፡11 በዚህ
ንግግሩ ቅዱስ ዳቲት የይሁዳን ሽማግሌዎች ‹‹ወንድሞቼ›› ብሎ ተጣርቷል፡፡ ዕዝ 3፡2
 በዝምድና፡- ዘኁ 20፡14 ‹‹ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል…›› ኤዶም ሌላው የዔሳው ስም ነው፡፡
ዘፍ 36፡1 የዔሳው ወንድም የያዕቆብ ልጆች ናቸው ከግብጽ የወጡት ለዚህም የዔሳው /የዔዶም/
ዘመዶች ናቸው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 30


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

 በባልንጀራነት፡- የቅርብ ወዳጅ ወይም ጓደኛ ማለትም ባልንጀራ ወንድም ይባላል፡፡ ምሳሌ፡ ቅ. ዳዊትና
የሳኦል ልጅ ዮናታን 2 ኛ ሳሙ 1፡26
 በቤተሰብ አባልነት፡- አብርሃም ሎጥን ‹‹እኛ ወንድማማቿች ነንና በእኔና በእናንተ በእረኛህና በእረኛዬ
መካከል ጠብ እንዳይኖር እለምንሃለው፡፡›› ዘፍ 13፡8 አብርሃም የሎጥ አጎት ሲሆን የሎጥ አባት ሐራን
የአብርሃም ወንድም ነው፡፡ ዘፍ 11፡27
 በሃይማኖት፡ ሮሜ 1፡13 ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች ‹‹ወንድሞቼ ሆይ በሌሎች አሕዛብ ደግሞ
ልማድ እንደ ሆነ በእናንተም ፍሬ አግኝ ዘንድ ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳሰብኩ እስካሁን ግን
እንዳልተሳካልኝ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡›› ፊል 1፡12፣ ፊል 3፡1፣ የሐዋ ሥራ 12፡17

አዋልድ መጻሕፍት
አዋልድ ቃሉ የግእዝ ሲሆን ትርጉሙም “ልጆች” (በአነስታይ ፆታ) ማለት ነው፡፡ አዋልድ መጻሕፍት ሲልም ልጆች
የሆኑ መጻሕፍት ማለት ነው፡፡ ልጅነታቸውም ለመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ልጅ ከአባቱ አብራክ፣ ከእናቱ ማኅጸን ተከፍሎ
ወላጆቹን መስሎ እንደሚወጣ እነዚህም መጻሕፍትም በቅርጽ፣ በይዘት፣ በመንፈስ፣ በምስጢር እና በመሠረተ አሳብ
አሥራው መጻሕፍትን መስለው የተገኙ ናቸው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ አሳብ ና እውነታ ሳይወጡ በእርሱ ላይ ተመሥርተው
የመጽሐፍ ቅዱስን ኃይለ ቃልና ውስጠ ምስጢር ለመተርጎም፣ ለማብራራት፣ ለማተትና ለመተንተን፣ ለልዩ ልዩ የቤተ
ክርስቲያን አገልግሎት የሚውሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች በአንድ ላይ ለማሰባሰብ(እንደ መጽሐፈ ግጻዌ ያሉት)፣
በመጽሐፍ ቅዱስ በተገለጸው መሠረት ተዛማጅና አስረጅ የሆኑ ነገሮችን ለማዘጋጀት፣በነቢብ የተገለጠውን በገቢር፣
በትምህርት የተሠጠውን በሕይወት ለማሳየት የሚጻፉ መጻሕፍት በአጠቃላይ አዋልድ መጻሕፍት ይባላሉ፡፡
መሠረታቸውና ቊጥራቸው
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ መጻሕፍት አሥራው መጻሕፍት ይባላሉ፡፡ አሥራው ማለትም ሥሮች ማለት ሲሆን
አሥራው መጻሕፍት ማለት ደግሞ ለሌሎች መጻሕፍት ሥሮች ወይም መገኛዎች (መሠረቶች) የሚሆኑ መጻሕፍት ማለት
ነው፡፡ ስለዚህም አዋልድ መጻሕፍት በአሥራው መጻሕፍት ሥርነት የሚበቅሉ እና የሚያድጉ ቅርንጫፎች ናቸው፡፡
ስለዚህም የአዋልድ መጻሕፍት ነቅዕ እና መሠረት አስቀድመን እንደተናገርነው መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡
አዋልድ መጻሕፍት ከመጽሐፍ ቅዱስ መሠረተ አሳብ ፈጽመው መውጣት የለባቸው፡፡ ከወጡ ግን ልጅ መባላቸው
ቀርቶ ዲቃላ መጻሕፍት ይባላሉ፡፡ ዲቃላ መጻሕፍት የሚባሉት በአንዳንድ ይዘታቸው መጽሐፍ ቅዱስን የሚመስሉ ነገር ግን
ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ፣ በጌታችን ከተገለጠውና ከሐዋርያት ጀምሮ ሲያያዝ ከመጣው የቤተ ክርስቲያን እምነትና
ትምህርት ጋር ተቃርኖ ያላቸው መጻሕፍት ናቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ከመሠረታዊ አስተምሮዋና እምነቷ
እንዲሁም ከአሥራው መጻሕፍት ጋር የሚቃረኑትን መጻሕፍት አትቀበላቸውም ይልቁንም ታወግዛቸዋለች፡፡ ሐዋርያው
ቅዱስ ጳውሎስ “ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ከሰበከላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ
የተረገመ ይሁን፡፡”(ገላ 1÷8) ብሏልና ከአሥራው መጻሕፍት ውጪ የምያስተምሩ ከሆነ ተቀባይነት አያገኙም፡፡
ስለዚህ ከእነዚህ ዲቃላ መጻሕፍት አዋልድ መጻሕፍትን መለየት እንድንችል የነገረ መለኰት ሊቁ የሆኑት ሕንዳዊው
ጢሞቴዎስ እነዚህን ነጥቦች ሰጥተውናል፡፡
 ዓላማቸው መንግሥተ እግዚአብሔር የሆነ፣
 በአሳብ ፣ በመንፈስ፣ በምስጢር፣ በነገረ መለኰት ከአሥራው መጻሕፍት እና ከቅዱሳት የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ጋር
የማይጋጩ፣
 ለክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር፣ ሞራል፣ ሕይወት፣ እና አነዋወር ተስማሚ የሆኑ፣
 በቤተክርስቲያን አበው፣ ትውፊት ወይም ጉዞ ምስክር ያላቸው፣

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 31


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

 ውስጣዊ ተቃርኖ የሌለባቸው፡፡ በማለት አስረድተዋል፡፡


ስለዚህም በእነዚህ ነጥቦች መሠረትነት ዲቃላ መጻሕፍትን ከአዋልድ እንለያቸዋለን፡፡
ወደ አዋልድ መጻሕፍት ቊጥር ስንመጣ ደግሞ አዋልድ መጻሕፍት የተለያዩና ብዙ ከመሆናቸውም በተጨማሪ
በየዘመኑ እየተጻፉና እየተጨመሩ የሚሄዱ ስለሆነ ቊጥራቸው እንደ አሥራው መጻሕፍት ተለክቶ እና ተሰፍሮ የሚወሰን
አይደለም፡፡ ምክንያቱም የአንድን ነገር ቊጥር ለማወቅ ማቆምን ይጠይቃልና ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም በመኃ 6÷8 ላይ
“አዋልድ እለ አልቦን ኁልቊ- ቊጥር የሌላቸው (ብዙ የሆኑ) ልጆች” በማለት ስለ ብዛታቸው ተናግሯል፡፡
እግዚአብሔር ከሚሠጣቸው የጸጋ ብዛት የተነሣ አንዱ አባት ብቻ ብዙ መጻሕፍትን ሊደርስ ይችላል፡፡ ለምሳሌ
ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም “ አቤቱ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ” እስከሚል ድረስ 14000 ድርሳናትና ተግሳጻትን የሚጽፍበት
ጸጋና ኃይል ተሰጥቶት ብዙ መጻሕፍትን ጽፏል፡፡(ስንክሳር ዘሐምሌ 15 ተመልከት)፡፡ ሊቁ ኦሪገንም(አርጌንስ)19
በዚያ ለጽሑፍ ተስማሚ የሆነ ሁኔታ ባልነበረበት ዘመን 6000 መጻሕፍትን ደርሷል፡፡ ይህም አንድ ጥሩ አንባቢ በሕይወት
ዘመኑ ሙሉ ቢያነባቸው ተነበው የማያልቁ ብዙ መጻሕፍት ናቸው፡፡ ከዚህም የተነሣ አዋልድ መጻሕፍትን እንደ አሥራው
መጻሕፍት እገሌ መጽሐፍ አንድ ፣ እገሌ መጽሐፍ ሁለት ተብለው ተለይተው ተወሥነው ለመቊጠር አዳጋች ነው፡፡
ምክንያቱም በተለያዩ ዘመናት በተለያዩ ቦታዎችና ጸሐፍያን የተጻፉ ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህም የሚያገኛቸው ሰው ዐይቶና
ተመልክቶ ከመሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮና የቤተ ክርስቲያን ትውፊት የሚስማሙ ከሆነ ይጠቀምባቸዋል እንጂ
እያንዳንዱ መጽሐፍ በተጻፈ ቊጥር እየታየ በቀኖና ተወስኖ የሚዘለቅ አይደለም፡፡
በተጨማሪ አዋልድ መጻሕፍት ብዙ ከመሆናቸው የተነሣ በሁሉም ዘንድ ላይታወቁ ይችላሉ፡፡ ይህም መጻሕፍቱን
ከመቀበል አያግደንም፡፡ የነገረ መለኰት ሊቁ የሆኑት ሕንዳዊው ጢሞቴዎስም ይህን ሲያስረዱ “የሰው ሀሉ ዘር እናትና አባት
አዳም እና ሔዋን ናቸው፡፡ ልጆቻቸው ግን በዝተዋል ሞልተዋል፤ ይበዛሉ ይሞላሉም፡፡ አዋልድ መጻሕፍትም አባት
እናታቸው አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ቢሆንም ልጆቹ ግን በዝተዋል ሞልተዋል፤ ይበዛሉ ይሞላሉም፡፡ የሰው ዘር እናት እና
አባት አዳምና ሔዋን በየሀገሩ በየዘመኑ ያለ ትውልድ ሁሉ ያውቃቸዋል፡፡ ልጆቻቸው ግን በልዩ ልዩ ሀገር በልዩ ልዩ ዘመን
ስለተወለዱ ላይታወቁ ይችላሉ፡፡ አዋልድ መጻሕፍትም በየሀገሩ በየትውልዱ በተነሡ ቅዱሳን ስለተጻፉ፤ ሰው ሁሉ
ላየውቃቸው ይችላል፡፡ ከላይ ያሉትን መመዘኛዎች እስካሟሉ ድረስ ግን ሁሉም ይቀበላቸዋል፡፡” ብሏል፡፡
የአዋልድ መጻሕፍት ጥቅም
አዋልድ መጻሕፍት ለሰው ልጀች የዕለት ተዕለት ኑሮና ሥነ ምግባር እንዲሁም መሠረታዊ የሆነውን የቤተ
ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዶግማ ለመረዳት ወሳኝና እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብና ማወቅ
እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ሆነ ማወቅ በመንፈሳዊ ሕይወት ላይ ያለውን
ፋይዳ ሲያስረዳ “ቅዱሳት መጻሕፍትን ማወቅ (መረዳት) መንፈስን ያጠነክራል፣ ሕሊናን ያነጻል፣ ጽኑ የሆኑ ሥጋዊ
ፍትወታትን ነቅሎ ይጥላል፣ መልካምነትንም ያጎለብታል፣ አስተሳሰብንም ያሳድጋል፣ ያልጠበቅናቸው ጉዳዮች ሲያጋጥሙን
መቋቋም እድንችል ያደርገናል፣ ከሰይጣን ፍላጻ ይታደገናል፣ ሰውንም ከሥጋው ነጥሎ ለነፍሱ ወደ ሰማይ የምትነጠቅበትን
መንፈሳዊ ክንፎች ያድላታል፡፡” 20 በማለት ጥቅማቸውን በዝርዝር አጉልቶ አሳይቷል፡፡
በቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት አተናተን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ንባብ፤ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ምስጢር
ሲባሉ፤ አዋልድ መጻሕፍት ደግሞ የእነዚህ መጻሕፍት ትርጓሜ ይባላሉ፡፡ ስለዚህም የአሥራው መጻሕፍት ምስጢር
19
ይህ ሊቅ ምንም ሕይወቱን በተጋድሎ ይመራ የነበረ፤ በሊቅነቱም የተመሰከረለት በ 12 ዓመቱ መጻሕፍትን አጠናቆ የጨረሰ ቢሆንም በዕድሜው መጨረሻ አካባቢ
የክርስትና ሃይማኖትን ከተማረው የግሪክ ፍልስፍና ጋር በመቀላቀሉ ምክንያት በምስጢረ ሥላሴና በምስጢረ ሥጋዌ በተጨማሪም በትንሣኤ ሙታን ላይ የከፋ የምንፍቅና
ትምህርት በማስተማሩና በመጻፉ ምክንያት የተወገዘና ከቤተ ክርስቲያን የተለየ ሰው ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያናችን ከጻፋቸው መጻሕፍት መካከል ምንፍቅና
የሌለባቸውን ብቻ(መጀመሪያ አካባቢ የጻፋቸውን) ትቀበላለች፡፡ በተጨማሪም በምንፍቅናው ምክንያት ሊቅ [scholar] እንጂ ቅዱስ ብላ አትጠራውም፡፡
20
66De Stud paes, PG 63: 485, A PATRISTIC COMMENTARY THE SECOND EPISTEL OF PAUL THE APOSTEL TO
TIMOTHY BY Fr. Tadros Y. Malaty

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 32


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሚገለጠው በአዋልድ መጻሕፍት ነው፡፡ በገመድ ውስጥ ያለ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚታየው በአምፖል ሲበራ እንደሆነ ሁሉ
በአሥራው መጻሕፍት (በመጽሐፍ ቅዱስ) የሚገኝ ጥበብ ትምህርትና ምስጢርም የሚረዳው የሚገለጠው በአዋልድ
መጻሕፍት ተብራርቶ ሲታይ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ኃይለ ቃል ባለመረዳት (በራሳቸው በመተርጎም)
ወደ ምንፍቅና የሚሄዱት እነዚህን በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ የአባቶችን የትርጓሜ መጻሕፍት ባለ ማንበባቸው ምክንያት
ነው፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ኤጲፋንዮስ “ቅዱሳት መጻሕፍትን አለማወቅ በአዘቅትና በጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ መኖር ነው፡፡”
ያለው፤ ስለዚህም አዋልድ መጻሕፍት በጨለማ ውስጥ ከመኖር የምንድንባቸው መብራቶች ናቸውና ለእኛ እጅግ አስፈላጊ
ናቸው፡፡ ስለዚህ በአጠቃላይ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረተ አሳብ ለመረዳት ሆነ ለመንፈሳዊ ሕይወት እጅግ ወሳኝ ናቸው፡፡
የአዋልድ መጻሕፍት ዓይነቶች
አባቶች ቅዱሳን በመንፈሰ እግዚአብሔር እየተቃኙ የደርሷቸው እጅግ ብዙ ቅዱሳት መጻሕፍት አሉ፡፡
እነዚህ ቊጥር የለሽ መጻሕፍት አንድ በአንድ ለማየት እጅግ አስቸጋሪ ስለሆነ ከይዘታቸው አንጻር እንደሚከተለው
እንከፍላቸዋለን፡፡
1. የትርጓሜ መጻሕፍት- እነዚህ መጻሕፍት የመጽሐፍ ቅዱስን ውስጣዊ ምስጢር ለማተትና ለማብራራት መሠረታዊ
ሐሳቡንና ይዘቱን ለማትትና ለመተንተን የሚጻፉ መጻሕፍት ናቸው፡፡ የእነዘህ መጻሕፍት ይዘትም እያንዳንዱን
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ምዕራፍና ቊጥር አንድ በአንድ የያዙትን መንፈሳዊ መልእክት የሚያስረዱ ናቸው፡፡
በተጨማሪም በተለያዩ ቅዱሳን አባቶች የተደረሱትን የጸሎትና ነገረ ሃይማኖታዊ መጻሕፍትን ለመተርጎም የሚጻፉትን
መጻሕፍትንም ያጠቃልላል፡፡ አብዛኛዎቹ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፉት የትርጓሜ መጻሕፍት በስፋት የተደረሱት
በሐዲስ ኪዳን (ከክርስቶስ ልደት በኋላ) ይልቁንም ደግሞ ዘመነ ሊቃውንት ተብሎ በሚጠራው ዘመን ነው፡፡
ምክንያቱም በዚያ ዘመን የተነሡት መናፍቃን (በተለይ ግኖስቲኮች) መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳቸው ትምህርት ይመች ዘንድ
እያጣመሙ በመተርጎማቸውና የምንፍቅና ትምህርታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ለማመሳከር በመሞከራቸው ነው፡፡
ስለዚህም አበው ሊቃውንት ምእመኑን ከዚህ የሐሰት ትምህርት ለመጠበቅ በእግዚአብሔር አጋዥነትና መሪነት
አሥራው መጻሕፈትን ተርጉመዋል፡፡ ከነዚህም ሊቃውንት መካከል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ውብ በሆነ አገላለጽ እጅግ
የሚደንቁና ጠቃሚ የሆኑ መጻሕፍትን ሲጽፍ በትርጓሜ ሥራዎቻቸውና በሊቅነታቸው የሚታወቁት እነ ቅዱስ አትናቴዎስ፣
እነ ቅዱስ ቄርሎስ፣ ሦስቱ የቀጰዶቅያ አባቶች (ቅዱስ ባስልዮስ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ)፣ እነ
ቅዱስ ኤጲፋንዮስ፣ እነ ሰማዕቱ ዮስጢኖስ(Justin Martyr)፣ እነ ቅዱስ ጀሮም(አባ ሄሮኒመስ) . . . እንዲሁም ሌሎች
አባቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ወደ ሀገራችን አትዮጵያ ስንመጣ ደግሞ በዜማ ሊቅነቱ የሚታወቀው ቅዱስ ያሬድ፣ በግሩም በሆነ የነገረ መለኮት
እውቀታቸውና ትርጓሜያቸው የሚታወቁት ሊቁ ቅዱስ አባ ጊየርጊስ ዘጋስጫ፣ በትርጓሜ መምህርነታቸው የሚታወቁት
መምህር ኤስድሮስ . . . እንዲሁም በተለያየ ዘመን የተነሡ ቅዱሳንና ሊቃውንት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ለእነዚህ መጻሕፍት እንደ ምሳሌነት የሚጠቀሱት ወንጌል ትርጓሜ፣ ሠለስቱ ሐዲሳት፣ መጽሐፈ ቅዳሴ ትርጓሜ፣
ፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ . . . ናቸው፡፡
2. በመናፍቃን መልስ ላይ የሚጻፉ መጻሕፍት- ቅዱሳን አባቶች መጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ የምንፍቅና ትምህርት
እንዳይበረዙ ከመጠበቃቸው በተጨማሪ ለግሪክ ፈላስፎች ሆነ ለዐላውያን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለሚያነሡት ጥያቄ
መልስ የሚሆን እንዲሁም ምንፍቅናቸውን መጽሐፍ ቅዱስን በመጥቀስ ለሚያስተምሩ አወናባጅ መናፍቃን መልስ ይሆን
ዘንድ የጻፏቸው መጻሕፍት ናቸው፡፡ እነዚህም መጻሕፍት ምዕመናን በመናፍቃን የማተለያ ቃል ተስበው ቅድስት
ከሆነቸው እምነታቸው እንዳይወጡ የሚረዱ ናቸው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 33


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ለምሳሌ፡- ቅዱስ አትናቴዎስ በአርዮስ21 ላይ፣ ቅዱስ ጄሮም በሄሊቪዲየስ22 ላይ ፣ ቅዱስ ቄርሎስ በንስጥሮስ23 ላይ፣
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በአርዮሳውያን ላይ እና የእግዚአብሔርን ሀልዎትና ጥበቃ በሚጠራጠሩ ሰዎች ላይ፣ ቅዱስ
ኤጲፋንዮስ በተለያዩ መናፍቃን ላይ፣ አባ ጊዮርጊስ በቢቱ24 እና በተለያዩ መናፍቃን ላይ የጻፉት መጽሐፍ . . . እንዲሁም
በተለያዩ ቅዱሳን አባቶች የተደረሱ ድርሰቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
3. የነገረ ሃይማኖት መጻሐፍት- እነዚህ መጻሕፍት የቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት ማለትም አምስቱ አዕማደ ምስጢር፣
ሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን፣ ነገረ ማርያም፣ ነገረ ቅዱሳን . . . በአጠቃላይ ትምህርተ ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸውን
መጻሕፍት የሚያካትት ነው፡፡ ለምሳሌ ፡- ሃይማኖተ አበው፣ መጽሐፈ ቄርሎስ፣ ተረፈ ቄርሎስ፣ መጽሐፈ አክሲማሮስ፣
መጽሐፈ ምስጢር፣ መጽሐፈ ባሕርይ፣ እንዚራ ስብሐት፣ ተአምኆ ቅዱሳን፣ … ተጠቃሽ ናቸው፡፡
4. ገድላት፡- ገድል ለሚለው የግእዝ ቃል ብዙ ቊጥር ሲሆን ገድል የሚለው ቃል በቁሙ ሲፈታ ደግሞ ትግል፣ ፈተና፣
ውጊያ፣ ሰልፍ፣ ድልና አክሊል እስኪገኝ ድረስ የሚደክሙት ድካም፣ የሚሠሩት ሥራ የሚቀበሉት መከራ ማለት ነው፡፡
ከዚህ ጽሑፍ ዐውድ አኳያ ግን መንፈሳዊ ዜና፣ ወግ፣ ታሪክ፣ የቅዱሳንን መከራ ጸጋን ተጋድሎ የሚናገር መጽሐፍ
የሚለውን ትርጓሜ ይይዛል፡፡25 ገድል በተለያዩ ቋንቋዎች የተለያየ መጠሪያ ሲኖረው በግሪክ ሃጊዮስ {HAGIOS} ሲባል
ትርጉሙም የቤተ ክርስቲያን አባቶች ታሪክ የሚይዝ ጽሑፍ ማለት ነው፡፡ በላቲን ደግሞ አክታ {ACTA} ሲባል
ትርጉሙም ግብረ ቅዱሳን ማለት ነው፡፡26
ስለዚህ በጥቅሉ ዲን ኤፍሬም እሸቴ በ 1992 የገድላት ዘመናዊ አከፋፈልና ሥነ ጽሑፋዊ ፋይዳ በሚል ርእስ ባዘጋጀው
ጥናታዊ ጽሕፍ ላይ እንደ ገለጸው “ገድል ማለት ገድሉ የተጻፈለትን ቅዱስ የተመለከቱ ወጎችን፣ ታሪኮችን፣ ጸዋትወ
መከራዎችን የያዙ፣ የተቀበለውን ጸጋና በእርሱ ቃልኪዳን ምእመናን ሊያገኙ የሚችሉትን በረከት የሚያትት መጽሐፍ
ነው፡፡” ብሏል፡፡ ገድል በተናጥል የአንድ ቅዱስ ሆነ የብዙ ቅዱሳንን ተጋድሎ ሊይዝ ይችላል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን የተለያዩ
የቅዱሳንን በክርስትና ሕይወት ሳሉ ከሚመጡባቸው እና ከሚያጋጥማቸው ፈተና ጋር የሚደረግ መንፈሳዊ ተጋድሎን
የሚገልጹ “ገድለ እገሌ” እየተባሉ የሚጠሩ ብዙ ገድላት አሉ፡፡
ለምሳሌ፡- ገድለ አዳም፣ ገድለ ጊዮርጊስ፣ ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ፣ ገድለ አርሴማ፣
ገድለ ሐዋርያት፣ ገድለ ሰማዕታት፣ . . . ተጠቃሽ ናቸው፡፡
5. ድርሳን፡- ይህን ቃል አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላታቸው ላይ እንዲህ ብለው ፈተውታል “የተደረሰ፣ የተጻፈ፣
ቃል፣ ነገር፣ ሰፊ ንባብ፣ ረዥም ስብከት፣ ትርጓሜ፣ አፈታት፣ ከልብ የሚወጣ መዝሙር፣ ምስጢሩ የሚያጠግብ፣ ቃሉ
የሚያረካ፣ አነጋገሩ የተሳካ፣ ጣዕመ ቃሉና ኃይለ ቃሉ ደስ የሚያሰኝ፣ ልብ የሚነካ” ማለት ነው ብለዋል፡፡ ስለዘህ
ድርሳን ማለት ስለ አንድ ነገር የሚናገር የሚተነትን መጽሐፍ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ለመላእክት ተሰጥቶ ይነገራል፡፡
ነገር ግን ከቃሉ ትርጉም አኳያ ለጌታ፣ ለድንግል ማርያም፣ ለሰንበት፣ . . . ሊደረስ ይችላል፡፡ በዚህም ጊዜ “ነገር”
በሚለው ፍቺው ይተረጎማል፡፡
ስለዚህም ድርሳነ ማርያም ሲል ነገረ ማርያም እንደማለት ነው፡፡ ድርሳን ከሚባሉት መጻሕፍት መካከል ለምሳሌ፡-
ድርሳነ ማኅየዊ (ስለ ጌታ ሕማም የሚናገር) ፤ ድርሳነ ሰንበት (ስለ ሰንበት ክብር ቅድስና ቃልኪዳን የሚናገር) ፤ ድርሳነ
ማርያም (ስለ እመቤታችን ልደት፣ ዕድገት፣ ጌታን ስለመውለዷ፣ ስለ ተቀበለችው መከራ፣ ስለዕረፍቷና ስለ ትንሣኤዋ፣
ስላደረገቸው ተአምራት የሚናገር)፣ ድርሳነ ሚካኤል፣ ድርሳነ ገብርኤል፣ . . . ተጠቃሽ ናቸው፡፡
6. የሥርዓት መጻሕፍት፡- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ሥርዓቶች አሉ፡፡ እነዚህን ሥርዓቶች ሥርዓቱ ከሚሠራላቸው
ሰዎች (ማኅበረሰብ) ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማዛመድ ዘረዘር ያሉ የአሠራር ፣ የአኗኗር፣ . . . ሥርዓቶችን የሚገልጹ
መጻሕፍት ናቸው፡፡ እነዚህም መጻሕፍት አብዛኛውን ጊዜ በማኅበር ለሚኖሩ መነኮሳት እና ለባሕታውያን ይጻፋሉ፡፡

21
በክርስቶስ አምላክነት ላይ ላነሣው የምንፍቅና ትምህርት የተሰጠ ምላሽ
22
የእመቤታችንን ዘላለማዊ ድንግልና አስመልክቶ ለጻፈው አጸያፊ ትምህርት የተሰጠ ምላሽ
23
በምስጢረ ሥጋዌ ላይ ላነሣው የተሳሳተ የምንፍቅና ትምህርት የተሰጠ ምላሽ
24
ቢቱ አትዮጵያዊ ሲሆን በጌታ ዳግም ምጽአት ላይ ላነሣው የምንፍቅና ትምህርት በዘመኑ የነበሩት ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ ምስጢር ላይ መልስ ሰጥተውታል፡፡
25
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ 301
26
The complete book orthodox pp 161
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 34
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ለምሳሌ ቅዱስ ጳኩሚስ (290-346 ዓ.ም) ማኅበረ መነኮሳት የሚመሩበትን በነሐስ ሰሌዳ ላይ የተጻፈ ሥርዓተ ማኅበረ
ገዳም ከመልአክ እጅ ተቀብሎ ሥርዓት ሠርቷል፡፡
በተጨማሪ እነዚህ መጻሕፍት ምእመናን፣ ዲያቆናት፣ ካህናትና ጳጳሳት ለሚፈጽሟቸው ለእያንዳንዱ መንፈሳዊ ተግባራት
መመሪያ ይሆኑ ዘንድ የተጻፉ ናቸው፡፡ ለዚህም የሚጠቀሰው በ 318 ቱ ሊቃውንትና በሌሎች ቅዱሳን የተጻፈው ፍትሐ
ነገሥት ፍትሕ መንፈሳዊ ወሥጋዊ ነው፡፡ በአጠቃላይ የሥርዓት መጻሕፍት ከሚባሉት ውስጥ
ለምሳሌ፡- ሥርዓተ ቤተክርስቲያን በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተደረሰ፣ ፍትሐ ነገሥት ፣ በቅዱስ ባስልዮስ ፣ በአባ
መቃርዮስ፣ በአባ ሲኖዳ እና በሌሎች የተደረሱ ሥርዓተ ገዳማት . . . ተጠቃሽ ናቸው፡፡

7. ተአምራት፡- ተአምር ማለት በእግዚአብሔር አማካኝነት ክብሩ ይገለጥ ዘንድ በወዳጆቹ በቅዱሳን እያደረ የሠራቸውና የሚያሠራቸውን ድንቅ ሥራ
ማለት ነው፡፡ ተአምራት የተባሉበትም ምክንያት ከተለመደው ነገር ወጣ ያሉ፣ ከዚያም አልፎ ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ የሚፈጸሙ ስለሆነ ነው፡፡
በተጨማሪም የሚከተሉትን ነጥቦች የያዘ መሆን አለበት፡፡
1. በእግዚአብሔር ቸርነት የሚፈጸም
2. ሃይማኖታዊ ዋጋ ያለው
3. ትርጉም ያለው ተግባር
4. የተፈጥሮ ሕግጋትን ሊተው ወይም ሊጥስ የሚችል

ስለዚህ ቅዱስ ዳዊት እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው፡፡ (መዝ 67፥35) እንዳለ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሚገለጥባቸውን ስሙ
የሚመሰገንባቸውን እነዚህን ተአምራት ያካተተ መጽሕፍ “ተአምር” ይባላል፡፡ በእነዚህ የተአምር መጻሕፍት ውስጥ የሚመደቡ መጻሕፍት በመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ተአምራት በማብራራትና በመተንተን እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ መጻፍ ካቆመ በኋላ የተፈጸሙትን የተለያዩ ተአምራትን የተጸፉባቸው
መጻሕፍት ናቸው፡፡

ለምሳሌ ተአምረ ኢየሱስ፣ ተአምረ ማርያም . . . ተጠቃሽ ናቸው፡፡

8. የጸሎት መጻሕፍት፡- በግልና በማኅበር (የቤተ ከርስቲያን) ጸሎት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት ሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያንን
ለመፈጸም ወሳኝና እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ በተጨማሪ ምእመናን ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙባቸው፣ ዘመናዊ ሐኪም ባልነበረበት ወቅት በሽተኞችን
በመፈወስ፣ የተጨነቁትን በማጽናናት፣ እንዲሁም አጋንንት ያደረባቸውን ክፉ መንፈሱን ከእነርሱ በማስወገድ ለምእመናኑ ታላቅ አስተዋጽኦ
አበርክተዋል፡፡ የጸሎት መጻሕፍት ከሚባሉት መካከል

ለምሳሌ በግል ጸሎት - ውዳሴ አምላክ፣ የኅሊና ጸሎት . . . ሲጠቀሱ


በማኅበር ጸሎት- መጽሐፈ ቅዳሴ፣ መጽሐፈ ተክሊል፣ መጽሐፈ ክርስትና፣ ጸሎተ ሙታን፣ መልካ መልከች፣ ውዳሴ ማርያም፣ ወዘተ ተጠቃሽ
ናቸው፡፡

9. የጥበብ መጻሕፍት፡- እነዚህ መጻሕፍት ቅዱሳን አበው እግዚአብሔር እንደገለጠላቸው መጠን ስለ ከዋክብት፣ ስለ ካልዕ ፍጥረታት (እንስሳት፣
አራዊት፣ አዕዋፋት) ፣ ስለ አኃዝ፣ ስለ ማኅበራዊ ኑሮ፣ ስለ መድኃኒት፣ እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነት ጋር ፍጹም የማይገጩ ዓለማዊ
ፍልስፍናዎችን የዘገቡባቸው መጻሕፍት ናቸው፡፡ እነዚህም መጻሕፍት ጥበብ መንፈሳዊና ሥጋዊ ተብለው ይከፈላሉ፡፡

ለምሳሌ ፡- መጽሐፈ ማትያስ (ስለ ዓለማት፣ስለ ዓለም ክብነት ... የሚናገር)፣ መጽሐፈ ፊሳሊጎስ (ሥነ ፍጥረትን ከትምህርተ ሃይማኖት ጋር
27
እያያዘ የሚያስተምር)፣ መጽሐፈ ሐዊ (ስለ ማኅበራዊ ኖሮ)፣ መጽሐፈ አቡሻኸር (ስለ ዘመን አቆጣጠርና ስለ ከዋክብት ዑደት) . . . መጻሕፍት ተጠቃሽ
ናቸው፡፡

10. የታሪክ መጻሕፍት ፡- የቤተ ክርስቲያንን ጉዞ፣ የደረሰባትን ፈተናዎች፣ የመካናትን ታሪክ በየዘመናቱ ከታሪክ አንጻር የሚተርኩ መጻሕፍት
ናቸው፡፡

27
ይህ መጽሐፍ ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ በኩል በሆነችው ደብረ ሲቅ በምትባል ቦታ በታላቁ አባትና ሊቅ በአንትያኩስ የተደረሰ ሲሆን ለሕፃናት
ማስተማሪያነት ብሎ የጻፈው መጽሐፍ ነው፡፡ በውስጡም የቅዱስ ጎርጎርዮስ፣ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እና የሌሎች አባቶች አባባሎቸች በሰፊው
ይገኙበታል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 35


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ለምሳሌ፡- ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ፣ መጽሐፈ ጤፉት፣ ክብረ ነገሥት፣ የአውሳቢዮስ የኤጲፋንዮስ እና የዮሐንስ አፈ ወርቅ የታሪክ መጻሕፍት ..
. ተጠቃሽ ናቸው፡፡

አዋልድ መጻሕፍት በመጽሐፍ ቅዱስ


ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት፣ በጽድቅም ላለው ምክር
ደግሞ ይጠቅማል፡፡” (1 ጢሞ 3፥17) በማለት ለደቀመዝሙሩ ለጢሞቴዎስ እንደነገረው የእግዚአብሔር መንፈስ ያልተለያቸው ቅዱሳን የጻፏቸው
ለትምህርትና ለተግሳጽ የሚያገለግሉ አዋልድ መጻሕፍት አሉ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊያንም መጻሕፍቶቻቸውን ሲጽፉ ከእነዚህ መጻሕፍት በመጥቀስ
የመጻሕፍቱን አስፈላጊነት በጉልህ ሁኔታ አስረድተዋል፡፡

28
በብሉይ ኪዳን ጸሐፊያን ከተጠቀሱ መጻሕፍት ውስጥ የያሻር መጽሐፍ (2 ሳሙ 1፥18፣ ኢያ 10፥13) ፣ የእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ29
(1 ነገ 11፥43) ፣ የእስራኤል የነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ30 (1 ነገ 15፥23፣ 15፥32፣ 16፥14፣ 16፥20፣ 16፥27) እና የይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ31
(2 ነገ 8፥23፣ 2፥20፣ 15፥6) ተጠቃሽ ናቸው32፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፍያን ያልተጠቀሱ የአይሁድ ሊቃውንት በየዘመኑ
ያሰባሰቧቸው የሐተታ፣ የትርጓሜ እና የትምህርት መጻሕፍት ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ በረበናተ አይሁድ የተደረሰ ሚሽናህ የተባለ መጽሐፍ እና ገማራ የተባለ
የሚሽናህ ትርጓሜ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በሐዲስ ኪዳንም ሐዋርያት በብሉይ ዘመን የነበሩትን አዋልድ መጻሕፍት በመጥቀስ የአዋልድ መጻሕፍትን አስፈላጊነት አጽንተውታል፡፡ ለምሳሌ
ሐዋርያው ይሁዳ በኦሪት መጻሕፍት ላይ ተጽፎ የማይገኘውን ቅዱስ ሚካኤል ስለ ሙሴ ሥጋ (መቃብር) ከዲያቢሎስ ጋር ያደረገውን ክርክር
ሲናገር የጠቀሰው “ዜናሁ ለሙሴ” (The Assumption of Moses) የተባለውን የሙሴን ገድል ነው፡፡ በተጨማሪም ቅዱስ ጳውሎስ በ 2 ጢሞ 3፥8
ላይ “ኢያኔስ እና ኢያንበሬስ” ብሎ የጠራቸው የፈርዖን ጠንቋዮች ስማቸው በሙሴ የኦሪት መጻሕፍት በአንዱም አልተጠቀሰም ፤ ነገር ግን ከአይሁድ ትውፊት
መጻሕፍት ወስዶ የጻፈው ነው፡፡ ወንጌላዊው ማቴዎስም በምዕራፍ 2 ቊጥር 23 ላይ “በነቢያት ናዝራዊ ይባላል” በማለት በዓበይትም ሆነ በደቂቅ ነቢያት
ያልተጻፈ ነገር ግን በትውፊት የተገኘ ትንቢትን አስቀምጧል፡፡ ይህም አዋልድ መጻሕፍት በሐዲስ ኪዳንም ተቀባይነት እንዳላቸው በግልጥ ያስረዳል፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ስለ አዋልድ መጻሕፍት አስፈላጊነት በምሳሌ አስተምሯል፡፡ ይህም በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ላይ ተጽፎ
በሚገኘው በደጉ ሳምራዊ ታሪክ ነው፡፡ በዚህ ታሪክ ላይም አንድ መንገደኛ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ ወንበዴዎች ደብድበው በሞትና በሕይወት
መካከል ጥለውት ይሔዳሉ፡፡ ሌሎች እያዩት ትተውት ሲሔዱ አንድ ርኅሩኁ ሳምራዊ ግን አይቶት አዝኖለት ወደ እንግዶች ማረፊያ በመውሰድ ከጠበቀው
በኋላ በነጋታው ለእንግዶች ማደሪ ጠባቂው ሁለት ዲናር በመስጠት “ጠብቀው፣ ከዚህ በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለው” አለው፡፡ ይህም
ምሳሌ ነው፡፡ በወንበበዴዎቹ የተመሰሉት አጋንንት ሲሆኑ ፣ መንገደኛው ደግሞ አዳም ነው፡፡ ደጉ ሳምራዊ የተባለው ደግሞ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሲሆን
የእንግዶች ማረፊያ የተባለቸው ደግሞ ቤተክርስትያን ናት፤ ቅዱስ ዳዊት “እኔ በምድር መጻተኛ ነኝና፤ እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝ፡፡” (መዝ 38፥12) እንዳለ
እንግዶች የተባሉትም ምዕመናን ናቸው፡፡ ቅዱስ ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ ላይ “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ
ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመበት ለመንጋው ተጠንቀቁ፡፡” (ሐዋ 20፥28) እንዳለ የእንግዶች ማረፊያ ጠባቂ የተባሉት ደግሞ መምህራን ካህናት
ጳጳሳትና ሊቃውንት ናቸው፡፡ ደጉ ሳምራዊ የተባለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእንግዶች ቤት ማደሪያ ጠባቂ (ለቤተ ክርስቲያን መምህራን) የሰጠውን ሁለቱ
ዲናሮች ደግሞ የብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳንን ምሳሌ እንደሆነ እንደ ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ፣ ቅዱስ አምብሮስ እና ሊቁ ኦሪገን ያሉ ታላላቅ
የቤተክርስቲያን ሊቃውንት አስተምረዋል፡፡ ሁለቱን ዲናር ከሰጠው በኋላ በዚያ ብቻ ሳይወሰን “ከዚህም በላይ የምትከስረው ሁሉ እኔ ስመለስ
እከፍልሃለሁ፡፡” ብሎታል፡፡(ሉቃ 10፥29-35) ይህም የሚያመለክተው መምህራነ ቤተክርስቲያን (ሊቃውንት) በሁለቱ ዲናሮች ማለትም በብሉይና
በሐዲስ ኪዳን መጻሕፈት ተመሥርተው የረቀቀውን አጉልተው የተሰወረውን ምስጢር ገልጠው ምእመናንን የሚያስረዱ የተለያዩ የትርጓሜ፣ የምክር፣
የተግሣጽ፣ የታሪክ፣ . . . በአጠቃላይ አዋልድ መጻሕፍትን በመጻፍ እንዲያስተምሩና የዚህም ተጨማሪ መጻሕፍትን የመጻፋቸውን የድካማቸውን ዋጋ
እንደማያጡ ይልቁንም “እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ” በማለት በዳግም ምጽአቱ ዋጋቸውን እንደሚከፍላቸው አስረድቷል፡፡

ገድላትና ተአምራት በመጽሐፍ ቅዱስ


አዋልድ መጻሕፍት አስቀድመን እንደተናገርነው በቅርጽ፣ በይዘት፣ በመንፈስ፣ በምስጢር እና በመሠረተ ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱስን ይመስሉታል፡፡
ስለዚህም በመጽሐፍ ቅዱስ ይዘታቸው ከአዋልድ መጻሕፍት ጋር አንድ ዓይነት የሆኑ መጻሕፍትን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ በመጽሐፍ ቅዱስ የታሪክ (እንደ
28
መዝሙራት የተሰባሰቡበት መጽሐፍ ሲሆን በሰብአ ሊቃናት ትርጉም “መጽሐፈ ልዑላን” ሲባል በቩልጌት ትርጉም ደግሞ “የምርጦች መጽሐፍ”
ይባላል፡፡
29
የሰሎሞንን ታሪክ እና በእርሱ ዘመን የተፈጸመውን የሚተርክ መጽሐፍ
30
የእስራኤል ነገሥታት የሠሩትትን ሥራ እና በዘመናቸው የረተፈጸመውን ታሪክ የያዘ መጽሐፍ
31
እስራአል ለሁለት ከተከፈለች በኋላ በኢየሩሳሌም የነገሡት ነገሥታት ታሪክን የያዘ መጽሐፍ
32
አንዳንድ ሰዎች እነዚህን መጻሕፍት ባያስፈልጉ ነው እንጂ ለምን ከቀኖና ገብተው ከአሥራው መጻሕፍት ጋር አልተቆጠሩም ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ነገር
ግን እነዚህ መጻሕፍት ከይዘታቸው ስፋትና በየዘመኑ የሚጻፉ ስለሆነ፤ በተጨማሪም የያዙት ታሪክ በአጭሩ በዜና መዋዕልና በነገሥት መጻሕፈት ላይ
ስለቀረበ ነው እንጂ ሳያስፈልጉ ቀርተው አይደለም፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 36


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

መጽሐፈ ነገሥት ያሉ)፣ ስለ አንድ ቅዱስ (ቅድስት) የሚናገሩ መጻሕፍት (እንደ መጽሐፈ ኢዮብ፣ መጽሐፈ ሩት ያሉት )፣ የሕግ መጻሕፍት እና ሥርዓት
(እንደ ኦሪት ዘጸአት የመሰሉ)፣ የትንቢትና የራእይ መጻሕፍት (እንደ ትንቢተ ኢሳይያስ፣ ራዕየ ዮሐንስ ያሉ)፣ የጥበብ የምስጋና እና የቅኔ መጻሕፍት (እንደ
መጽሐፈ ምሳሌ፣ መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ያሉት)፣ የጸሎት (እንደ መዝሙረ ዳዊት ያሉት) . . . ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህም አስቀድመን ካየነው
ከአዋልድ መጻሕፍት ዓይነት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ስለዚህም ስለ ገድላት እና ስለ ተአምራት ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር እንመለከታለን፡፡

1 ገድል ፡- ገድላትና መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ዓይነት የአጻጻፍ ስልት አላቸው ይኸውም የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ የቅዱሳኑ ታሪክ
ዋና የታሪኩ ማዕከል በማድረግ መጻፍ ሲሆን በዚህም የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የያዕቆብ፣ የመልከጼዴቅ፣ የሙሴ፣ የዳዊት፣ የሰሎሞን፣ . . . ወዘተ ታሪክ
ተጽፏል፡፡ ሁለኛተው መንገድ ደግሞ በቅዱሳኑ ስም ለብቻ መጻሕፍትን መጻፍ ነው፡፡ በዚህም መጽሐፈ አስቴር፣ መጽሐፈ ሩት፣ መጽሐፈ አዮብ፣ መጽሐፈ
ዮዲት፣ መጽሐፈ ሶስናና ግብረ ሐዋርያት የመሳሰሉ መጻሕፍት ተጽፈዋል፡፡ በአዋልድ መጻሕፍትም በመጀመሪያው መንገድ የተጻፉ እንደ መጽሐፈ ገነት፣ እንደ
መጽሐፈ ስንክሳር ያሉ ስለ ብዙ ቅዱሳን የሚናገሩ መጻሕፍት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በሁለተኛው መንገድ ማለትም በቅዱሳኑ ስም ለብቻቸው ከተጻፉላቸው
መጻሕፍት መካከል ደግሞ ገድለ ጊዮርጊስ፣ ገድለ ፋሲለደስ፣ ገድለ አዳም. . . ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት መካከል ከገድላት ጋር አንድ አይነት አጻጻፍ ያለው ደግሞ ግብረ ሐዋርያት ( የሐዋርያት ሥራ) ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ
ሐዋርያት ኃይለ መንፈስ ቅዱስን በማግኘት ከዲያቢሎስ፣ ከሐሳውያን መምህራን፣ ለባለሥልጣናት፣ ከጠንቋዮች፣ እና በክርስትና መስፋፋት ጥቅማቸው
ከተነካባቸው ሰዎች ጋር ያደረጉትን ተጋድሎ ማለትም ሲታሠሩ፣ ሲገረፉ፣ ሲከሰሱ፣ መርከባቸው ሲሰበር፣ በባዕድ ሀገር ሲንገላቱ በአጠቃላይ የደረሰባቸውን
መከራ የሚናገር መጽሐፍ ነው፡፡ ይህም አጻጻፍ ከገድላት ጋር ከፍተኛ የሆነ መመሳሰል ይታይበታል፡፡

2 ተአምር፡- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በእግዚአብሔር እንዲሁም እርሱ በፈቀደላቸው ቅዱሳን የተፈጸሙ ብዙ ተአምራት ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ
ሊቀ ነቢያት ሙሴ በግብጻውያን ላይ መቅሰፍት ማምጣቱና ሕዝቡን የኤርትራ ባሕርን ከፍሎ በደረቅ ማሻገሩ (ዘጸ 8፥12፣ 14፥21-31)፣ ኢያሱ ፀሐይን
በገባዖን ማቆሙ(ኢያ 10፥12-13)፣ ካህናተ ኦሪት ታቦተ ሕጉን ተሸክመው ዮርዳኖስን መክፈላቸውና በደረቅ መሻገራቸው (ኢያ 3፥1-15)፣ ሦስቱ ሕጻናት
በእቶን እሳት ውስጥ ተጥለው አለመቃጠላቸው (ዳን 3)፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሕቱም ድንግልና እንበለ ዘር ተጸንሶ መወለዱ፣ ውኃን ወደ ወይን
መቀየሩ፣ አላዛርንና ወለተ ኢያኢሮስን ከሞት ማስነሣቱ፣ . . . እና ሌሎች ድንቅ ተአምራቶች ተጽፈው ይገኙበታል፡፡ በአጠቃላይ ተአምርና መጽሐፍ ቅዱ
ተለያይተው አያውቁም፡፡ የተለያዩበት ጊዜም የለም፣ ሊኖርም አይችልም፡፡ ምክንያቱም ጻድቁ ኢዮብ “የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና
የማይቈጠረውን ተአምራት ያደርጋል።” (ኢዮ 5፡9) እንዳለ እግዚአብሔር ተአምራትን አድራጊ ነውና ነው፡፡ ታዲያ በዘመነ ብሉይና ሐዲስ
እኒህን ተአምራት ያደረገ እግዚአብሔር ለሐዋርያት ቃል እንደገባው እስከ ምጽአት ከቅዱሳን ጋር ነውና ቅዱሳን አባቶቻችን በእርሱ እርዳታ ታላላቅ
ተአምራትን ያደርጋሉ፡፡ ቅዱስ ዳዊት “ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።” (መዝ 105፥2) እንዳለ አሥራው መጻሕፍት መጻፍ ካቆሙ
በኋላ አምላካችን እግዚአብሔር በቅዱሳን ላይ አድሮ ያደረገውን ተአምር አዋልድ መጻሕፍት ልክ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራሉ፡፡

አዋልድ መጻሕፍትን ስናነብ ልናስተውላቸው የሚገቡ ነጥቦች


1. የእግዚአብሔርን ከሃሊነትና ቸርነት ያለ ምንም ጥርጥር ፍጹም መቀበል፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ እንደመሆኑ መጠን ከእምነት፣
ከዕውቀትና ከኅሊና በላይ የሆኑ ሥራዎች መሥራት እንደሚቻለው ማመን
2. በብሉይና በሐዲስ ኪዳን የተገለጡትን መሠረታዊ የሃይማኖትና የሥነ ምግባር ትምህርቶች ጠንቅቆ ማወቅ፡፡ ይህም ይህም በአዋልድ
መጻሕፍት የሚጻፈው ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ ወጭ የሆነ እንግዳ ነገር እንዳልሆነ እድንናውቅ ይረዳናል፡፡
3. ለቅዱሳን የተሠጠውን ክብርና ሥልጣን መረዳት፡፡ይህም ማለት ቅዱሳን ተአምር ቢሠሩ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ክበርና ሥልጣን
እንጂ በራሳቸው እንዳልሆነ ወይም ሥልጣናቸው የባሕርይ ሳይሆን የጸጋ መሆኑን መረዳትና የሚሠሩትም እግዚአብሔር ይመሰገንበት ዘንድ
እንጂ ለራሳቸው ክብር እንዳልሆነ መረዳት ነው፡፡
4. ከሥጋዊ ፍልስፍና ጋር ቀላቅሎ ለመረዳት አለመሞከር፡፡ በተለይ ተአምራት ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ የሆኑ ለማንኛውም ሰው
የማይቻሉ ነገር ግን ለቅዱሳን ግን የሚቻሉ ስለሆነ ከምናውቀው የዓለም ፍልስፍና ራሳችንን ነጻ ካላደረግን ልንረዳው
አንችልም፡፡
5. መጽሐፉ የተጻፈበት ዘመን የነበሩበትን ሁኔታዎች ማገናዘብ፡፡ ይህ ደግሞ መጽሐፉ ሲጻፍ የነበረው የኅብረተሰቡ ባሕልና የአኗኗር
ዘይቤ አሁን ጋር ሰፊ ልዩነት ሊኖረው ስለሚችል ይህንን ታሳቢ በማድረግ የዘመኑን ባሕልና ወግ እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤ
ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡

ምዕራፍ ሁለት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 37


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት


የቃሉ ትርጉም
ብሉይ ማለት ያረጀ፣ የቆየ፣ ጥንታዊ፣ ቀዳማዊ ማለት ሲሆን ኪዳን ማለት ደግሞ በተለያዩ ወገኖች
መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ፤ ቢያፈርሱት ጉዳትና ጠብ የሚያመጣ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ
ብሉይ ኪዳን ስንል የቆየ ጥንታዊ ቃል ኪዳን ማለታችን ነው፡፡ ነገረ ግን ብሉይ ሲባል ሕጉ ሁሉ ወይም
ቃልኪዳኑ ሁሉ ያረጀ (ያለፈበት) ነው ማለታችን አይደለም፤ ነገር ግን ዘመኑ አርጅቷል፣ ብዙ ጊዜም
አልፎታል ማለት ነው፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር አስቀድሞ ከእስራኤል ዘሥጋ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ነው፡፡
ኪዳኑ ብሉይ መባሉ በኋላ በጌታችን በአምላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተመሠረተ ሌላ
ሐዲስ (አዲስ) ኪዳን ለእስራኤል ዘነፍስ ስለተሰጠ ነው፡፡ ስለዚህም አዲሱ ኪዳን የመጀመሪያውን ብሉይ
አሰኝቶታል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ከፈጠረበት ጊዜ አንሥቶ የሰውን ልጅ ያለ ቃልኪዳን ትቶት


አያውቅም፡፡‹‹የባሕር ዓሣዎችን፣ የሰማይ ወፎችን፣ እንስሳትና ምድርን ሁሉ፤ በምድር ላይ
የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ፡፡›› ሲል ከመፍጠሩ በፊት ቃል ኪዳን ገብቶለታል፡፡ ከፈጠረውም በኋላም
ሕግጋትን እየሰጠው እነርሱን ሲጠብቅ በጸጋ እና በበረከት እየጎበኘው ሲያፈርስ ደግሞ ፈታሔ በጽድቅ እንደ
መሆኑ ተገቢውን ፍርድ በመስጠት ቃል ኪዳኑን ከሰው ልጆች አላራቀም፡፡

ብሉይ ኪዳን ከመጀመርያ ፍጥረት መፈጠር ጀምሮ እስከ ክርስቶስ መወለድ ድረስ የነበውን የሰዎችንና
የእግዚአብሔርን ግንኙነት የሚናገር መጽሐፍ ነው፡፡ የተጻፈው ከ 1400-400 ቅ.ል.ክ ሲሆን ሠላሳ ሁለት ያህል
ጸሐፍት ጽፈውታል፣ የተጻፈበት ቋንቋ በአብዛኛው በዕብራይስጥ ሲሆን፣ በአርማይክ ቋንቋም የተጻፉ
መጻሕፍትን አካትቶ ይይዛል፡፡ ለምሳሌ፡ ትንቢተ ኤርምያስ፣ መጽሐፈ ዕዝራ፣ ትንቢተ ዳንኤል እና
የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡

ከክርስትና በፊት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያለው የአምልኮ ሥርዓትና የመሥዋዕት አቀራረብ፣ የሰንበት
አከባበርና የመሰለው ሁሉ በሀገራችን ተሠርቶበታል፣ ከክርስትናውም በኋላ መጻሕፍተ ብሉያት ለሐዲስ
ኪዳን ትንቢትና ታሪክ፣ አምሳልና መርገፍ እንደመሆናቸው መጠን ከመሥዋዕዋቱና ከሥርዓተ አምልኮቱ በቀር
ሃይማኖታዊና ሥነምግባራዊ ሕጋቸውና ትእዛዛቸው፣ እንደዚሁም ትምህርታቸው ዛሬም እንደተጠበቀ ነው፡፡
በመሆኑም እነዚህ ኪዳናት የማይነጣጠሉ መሆናቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከተጻፉበት ጊዜ፣ ከይዘታቸው አንጻርና ከአጻጻፋቸው ሁናቴ የተነሣ
1. የሕግ፣
2. የታሪክ፣
3. የመዝሙር የቅኔና የጥበብና
4. የትንቢት ክፍል በመባል በአራት ዐበይት ክፍል ይከፈላሉ፡፡

1. የሕግ መጻሕፍት

የሕግ በመባል የሚታወቁት መጻሕፍት ሊቀ ነቢያት ሙሴ በሲና ምድረ በዳ የጻፋቸው አምስቱ ብሔረ
ኦሪት ናቸው፡፡ ጥንተ ነገሩስ እንደምን ነው ቢሉ፤ ጌታ እስራኤልን ከግብጽ ካወጣቸው በኋላ ሙሴን ጠርቶ
ሕግ እሠራላችኋለሁና ወደ ደብረ ሲና ውጣ አለው፣ እሱም ሕዝቡን ለአሮንና ለሖር አስጠብቆ ግርግር
አትበሉ፤ ‹‹ነገርም ያለበት ሰው ቢኖር እነዚህ ይስሟቸው፤ ካስተማርኋችሁ ትምህርት፣ ከሠራሁላችሁ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 38


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሥርዓት አትውጡ›› ብሎ ኢያሱን አስከትሎ ወደ ደብረ ሲና ወጣ፤ ኢያሱን ከእግረ ደብረ ትቶ እርሱ ከርእሰ
ደብር ወጣ፤ ሰባት የብርሃን መጋረጃ ተጋርዶ ነበር፣ ስድስቱን ገብቶ ከሰባተኛው ሲደርስ ቆመ፣ ስድስቱን ቀን
በስድስቱ ዕለታት የተፈጠሩ ሀያ ሁለቱን ሥነ-ፍጥረት በልቡናው ሲሥልበት ሰንብቷል፡፡ ይህንንም በደብረ ሲና
የነገረውን ጻፍ ብሎት አምስት ክፍል አድርጎ ጽፎታል፡፡ 33

ኦሪት ቃሉ የሱርስት ሲሆን ትርጉሙም ብርሃን ማለት ነው፡፡ ‹‹ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴ
ብርሃን ነው›› መዝ 118፡105 እንዲል፡፡ በዕብራይስጥ ቶራ፣ በግሪክ /ዕርእ/ ኖሞስ ይባላል፤ ትርጉሙም ሕግ
ማለት ነው፡፡ እነዚህም መጻሕፍት በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹የሙሴ መጻሕፍት››(1 ዕዝ 6፡18) ‹‹የሕግ
መጻሕፍት››(ገላ 3፡10) ‹‹የሙሴ ሕግ››(ሉቃ 2፡22፤ ዮሐ 1፡16) ‹‹የጌታ ሕግ››(ሉቃ 2፡23፤ 10፡16፤ ማቴ 5፣17)፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ከሚለው ቃል ጋር ተያይዘው ከሚጠሩ አምስት መጻሕፍት ሌላ ‹‹ስምንቱ


ብሔረ ኦሪት›› የሚል ሥያሜ በቤተክርቲያናችን አለ፤ ስያሜውም የተወረሰው ከሰብዓ ሊቃናት ነው፤
ይኸውም የኢያሱ፣ የመሳፍንትና የሩት መጻሕፍት በአምስቱ መጽሐፈ ሙሴ ላይ ተደምረው ነው፡፡ ከዚህም
የተነሣ በቤተክርስቲያን ትውፊት ሦስቱ መጻሕፍት ማለትም ኦሪት ዘኢያሱ፣ ኦሪት ዘመሳፍንት፣ ኦሪት ዘሩት
ተብለው ይጠራሉ፤ ነገር ግን ሦስቱ መጻሕፍት የታሪክ እንጂ የሕግ አይደሉም፤ በዚህ ይዘት ኦሪት ዘኢያሱ
ሲባል መጽሐፍ ዘኢያሱ ወይም መጽሐፈ ኢያሱ ለማለት መሆኑን መገንዘብ ያሻል፡፡ ሦስቱ ከአምስቱ ጋር
ተደምረው ስምንቱ ብሔረ ኦሪት መባላቸው ግን አይሁድ ከአምስቱ መጻሕፍተ ሙሴ ቀጥሎ እነዚህን
ሦስቱን መጻሕፍ ተቀብለው ስለያዟቸው እና የታሪክ ይዘታቸውም ከአምስቱ የሙሴ መጻሕፍት ታሪክ ጋር
ተከታታይነት ስላላቸው ነው፤ እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሩ የሰጣቸው ተስፋ ከግብጽ ወጥተው ወደ
ከነዓን መግባታቸውን ነበር፡፡ /ዘፍ 12፡2-3፣ 15፣ 18-21/ ከግብጽ ባርነት ነጻ መውጣትም ምድረ ርስትን ከመውረስ
ተነጥሎ አይታይም፤ በመሆኑም መጽሐፈ ኢያሱ ምድረ ርስት ለነገደ እስራኤል እንዴት እንደ ተከፈለች
ስለሚብራራ፣ የርስቱንም አከፋፈልና አመዳደብ ሥርዓት ስለሚናገር ከመጻሕፍተ ሙሴ ጋር ተያይዞ
በመክብቡ ስምንቱ ብሔረ ኦሪት ተብሏል፡፡

የመጽሐፈ መሳፍንትና፣ የመጽሐፈ ሩት ታሪክም ከአምስቱ መጻሕፍተ ሙሴ እንደ ተጻፉበት ዘመን


የእስራኤል ልጆች ንጉሥ ሳያነግሡ እግዚአብሔር አምላካቸውን ንጉሣቸው አድርገው ይኖሩ በነበረበት ዘመን
/መሳ 18፡1፣ ሩት 1፡1/ ስለተፈጸመ እንደ መጽሐፈ ኢያሱ ከአምስቱ መጻሕፍተ ኦሪት ተደምረው ስምንቱ
ብሔረ ኦሪት ተብለዋል፡፡ ይህም ተጽፎ ሲነበብ፣ ሲተረጎም ከነቢያት እስከ ሐዋርያት ደረሰና ሐዋርያትም
ለቀለሜንጦስ ሰማንያ አንዱን መጻሕፍት ቆጥረው ሲሰጡት ከብሉያት ስምንት በሐውርተ ኦሪት ብለው
ሰጥተውታል፡፡

ሊቀነቢያት ሙሴ ኦሪትን አምስት አድርጎ መጻፉ ስለምንድነው? ቢሉ፡-


ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከአምስተኛ ባሕርየ ነፍስ የተፈጠረ ሰው እንዲያመሰግንበት፤ እንዲጠብቅበት
አንድም አምስቱ ሕዋሳተ አፍአ (ውጫዊ ሕዋሳት) እንዲያመሰግኑበት እንዲጠብቁበት
አንድም ኋላ ጌታ ሰው ሆኖ አምስቱን አዕማደ ምስጢር የሚያስተምር ነውና የዚያ ምሳሌ ነው፡፡
ኦሪት ዘዳግምስ ለአበው (ለአባቶቻቸው) የነገረውን ለውሉድ (ለልጆቻቸው) መልሶ ለመንገር መልሶ
አንብቦታል እንጂ አንድ ነው ብሎ አራት ክፍል አድርጎ ጽፎታል ስለ ምን? ቢሉ፡-
በአራቱ ማዕዘን ያለ ሰው በአራቱ ማዕዘን ምሉዕ የሆነ ጌታን እንዲያመሰግንበት
አንድም ሐዋርያት ከነቢያት ያላገኙትን አምሳል መርገፍ አያደርጉም፤ ወንጌል አራት ክፍል ሁና
የምትጻፍ ናትና፣ ለወንጌል አምሳል መርገፍ ልትሆን34

33
ኦሪት ዘፍጥረት መቅድም
34
ኦሪት ዘፍጥረት መቅድም

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 39


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ይህስ አይደለም ሐዋርያት በሲኖዶስ፣ ሠለስቱ ምዕት በፍትሐ ነገሥት አምስቱ መጻሕፍተ ሙሴ ብለው
ቆጥረውታል፡፡ እኛም ይህን ተከትለን አምስቱን የኦሪት መጻሕፍትን ብቻ በሕግ መጻሕፍት ሥር አካተን
እንቆጥራለን፡፡

እነዚህም መጻሕፍት እያንዳንዳቸው በዕብራይስጥ ያለው ስያሜ ከግእዙ ጋር ይለያያል፡፡ ይህም የሆነበት
ምክንያት ግእዙ የሰብዓ ሊቃናትን የመጽሐፍት አሠያየም ሲከተል ዕብራይስጡ ግን የየመጻሕፍቱን
የመጀመርያ ቃል እንደ መጽሐፉ ርዕስ አድርጎ ይወስደዋል፡፡

ከዚህ በመቀጠል የመጻሕፍቱን ስያሜና ትርጉም፣ የተጻፉበትን ዓላማ እንዲሁም አጠቃላይ ይዘታቸውን
እንመለከታለን፡፡
1. ኦሪት ዘፍጥረት /ዘልደት/
ኦሪት ዘልደት ማለት ዜና ፍጥረት (የፍጥረት ዜና) ማለት ነው፡፡ የዚህ መጽሐፍ ስያሜ የተወሰደው
ከመጽሐፉ አንደኛ ምዕራፍ መጀመሪያ ቊጥር ላይ ባለው ‹‹በመጀመርያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን
ፈጠረ›› በሚለው መነሻ ቃል ነው፡፡ መጽሐፉ ዘልደት መባሉ ሃያ ሁለቱን ሥነ ፍጥረት ቆጥሮ ስለሚናገር
ነው፤ ከአዳም ጀምር እስከ ዳዊት ያለውን ትውልድ እገሌ እገሌን ወለደ እያለ ልደተ አበውን ይናገራልና ነው፡፡

ይህ መጽሐፍ በዕብራይስጥ ‹‹በረሺት›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ትርጉሙም በመጀመርያ ማለት ነው፡፡


ይህም በዕብራይስጡ ኦሪት ዘፍጥረት የመጀመርያው ቃል ስለሆነ ነው፡፡ ዘፍጥረት የሚለውን ስያሜ ያገኘው
ከሰብዓ ሊቃናት ትርጉም በኋላ ነው፡፡

በትርጓሜ ኦሪት ዘፍጥረትን በተራራ መስለውታል ምክንያቱም ከተራራ ላይ የወጣ ሰው አቆልቁሎ


በተመለከተ ጊዜ የወጣ የወረደውን፣ ያለፈውን ያገደመውን ያያል፤ ዘፍጥረትንም የተማረ ሰው ዓለም
ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ ምጽአት የሚሆነውን ነገር በውስጡ ይመለከታልና ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
ስለ ሥነ ፍጥረት አጀማመርና አመጣጥ እንዲሁም እግዚአብሔር ከአባቶች ጋር የነበረውን ግንኙነትና
ቃልኪዳን ማስረዳት ነው፡፡
ቅዱስ ዲዲሞስ ዓይነ ሥውሩ የአሪት ዘፍጥረት የመጻፉ ዓላማ እስራኤል በግብጽ ሳሉ ስለ ፍጥረታት
መፈጠር ከግብጽ ጣዖት አምላኪያን ይሰሙ የነበሩትን የሐሰት ትምህርቶች ትተው ትክክለኛውን
አስተምህሮ ያውቁት፣ ይረዱት ዘንድ ነው፡፡
እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ፍቅርን አብልጦ ቢሰጥም የሰው ልጅ ግን አሻፈረኝ ብሎ የራሱን መንገድ
በመምረጡ ከእግዚአብሔር መራቁን ማስረዳት ነው
የመጽሐፉ አከፋፈል
ኦሪት ዘፍጥረት 50 ምዕራፎች ያሉት መጽሐፍ ሲሆን የመጽሐፉንም ይዘት እንደሚከተለው በአራት ዋና
ዋና ክፍሎች በመክፈል መላ ታሪኩንና ትምህርቱን ማጥናት ይቻላል፡፡ እነዚህም፡-
ዘፍ 1-5፡- የሥነ ፍጥረት አፈጣጠር፣ የሰው ልጅ ውድቀትና የመጀመርያዎቹ አባቶች ዕድሜ በዝርዝር
ቀርቧል፡፡ በዚህ ክፍል ለሰው ልጅ የተሰጠው ፈቃድና የፍላጎት ነጻነትም ተጽፏል፡፡
ዘፍ 6-11፡- የሰው ልጅ በኃጢአት መጥፋቱና ከኖኅና ከቤተሰቦቹ በቀር በንፍር ውኃ መቀጣታቸውን፣ ስለ
ባቢሎን ግንብ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 40


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ዘፍ 12-26፡- ስለ አበው የእምነት ተጋድሎ፣ ስለ አብርሃም መጠራትና የእምነት ጉዞና ጽናት፣ አብርሃም
ኮሎዶጎሞርንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ስለማሸነፉ፣ ስለ ካህኑ መልከጼዴቅና ስለ መሥዋዕት፣
ስለ ሎጥና ቤተሰቦቹ፣ የሰዶምና የጎሞራ ጥፋት፣ ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት በእንግድነት ስለ
መገኘታቸው፣ ስለ አብርሃምና ስለ አቤሜሌክ፣ ስለ ተስፋው ልጅ ይስሐቅ ውልደትና ለመሥዋዕት
ስለመቅረቡ እንዲሁም ስለ አብርሃም እረፍት በሰፊው ያትታል፡፡
ዘፍ 27-50፡- የያዕቆብና የዔሳው ታሪከ፣ የዮሴፍ ታሪክ፣ የእስራኤልን ወደ ግብጽ መውረድ እናገኛለን፡፡

2. ኦሪት ዘጸአት
‹‹ዘጸአት›› የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም መውጣት ማለት ነው፡፡ የዚህ መጽሐፍ ስያሜ የተወሰደው
‹‹ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የገቡት የእስራኤል ልጆች›› ከሚለው ከመጽሐፉ መጀመሪያ ምዕራፍ ከቊጥር
አንድ ላይ ነው፡፡ ኦሪት ዘጸአት ማለት የአወጣጥ ወይም የመውጣት መጽሐፍ ማለት ነው፡፡ የእስራኤልን
ከ 430 ዓመት በኋላ ከግብጽ መውጣት ስለሚያወሳ ይህ ስም ተሰጥቶታል፡፡
ይህ መጽሐፍ በዕብራይስጥ የኦሪት ዘጸአት የመጀመርያው ቃል በሆነው ‹‹ኤልሼሞት›› ተሰይሟል፡፡
ትርጉሙም ‹‹ስሞች እነዚህ ናቸው›› ማለት ነው፡፡ ይህም የያዕቆብን ትውልድ ስም በመዘርዘር ይጀምራልና
ነው፡፡ ዘጸአት የሚለውን ስያሜ ያገኘው ከሰብዓ ሊቃናት ትርጉም በኋላ ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
የዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማዎች ሁለት ናቸው፡፡ እነርሱም፡-
በገፋዕያን ላይ የተደረገው ፍትሐ እግዚአብሔር፣ ለግፉዓን የተሰጠውን ነጻነት ይናገራል፡፡
እግዚአብሔር የሰው ልጆች ምንም እንኳን በኃጢኣት ቢወድቁም የሚቀደሱበትን መንገድ
እንዳዘጋጀላቸው ይገልጻል
የሃይማኖትና የአስተዳደር ሕግ ስለተሰጠው ስለ አዲሱ ሕዝበ እግዚአብሔር ያስረዳል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
መጽሐፉ 40 ምዕራፎች ሲኖሩት፤ ለማጥናት ያመች ዘንድ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡-
ዘጸ 1-4፡- ግብጻውያን በእስራኤል ላይ ያደረሱት ግፍና መከራ፣ ሙሴ ከልደቱ እስራኤልን ነጻ ለማውጣት
በእግዚአብሔር እስከመጠራቱ ጊዜ ያለውን ታሪክ ይተርካል፡፡
ዘጸ 5-11፡- ሙሴ፣ አሮንና እስራኤላዊያን በፈርዖን ፊት ቆመው ነጻ እንዲወጡ ስለመጠየቃቸው፣
በእስራኤላውያን ላይ የባርነት ቀንበር ስለመጥበቁ፣ በግብጻውያን ላይ ስለወረዱት 10 መቅሰፍቶች
ዘጸ 12-15፡- እስራኤላውያን ከግብጽ ወጥተው የኤርትራን ባሕር በእግዚአብሔር ኃይል ስለ መሻገራቸው፣
ግብጻውያንም በባሕር ውስጥ ሰጥመው መቅረታቸውን፣ ሙሴና የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ፊት
የምሥጋና መዝሙር ስለማቅረባቸው ይናገራል፡፡
ዘጸ 16-40፡- ሙሴ በሲና ሕግ መቀበሉን፣ ስለ ደብተራ ኦሪት አሠራር የተሰጠ መመርያ፣ ስለ አሮን ሥልጣነ
ክህነት፣ ስለ ልብሰ ተክህኖና ሥርዓተ አምልኮ፣ የእስራኤል በጣዖት ማምለክና መቀጣት፣ መና ከሰማይ
እንደወረደላቸው እናገኛለን፡፡
3. ኦሪት ዘሌዋውያን
ሌዋውያን ከ 12 ቱ የእስራኤል ነገድ የአንዱ የሌዊ ዘር ናቸው፡፡ የብሉይ ኪዳን ካህናትና ዲያቆናት
ሌዋውያን ስለነበሩ፣ ስለ ኦሪት ካህናት፣ ስለ ክህነትም ሥርዓትና አገልግሎት በሰፊው የሚገልጸው ይህ 3 ኛው
የሙሴ መጽሐፍ ዘሌዋውያን ሊባል ችሏል፤ ነገር ግን መጽሐፉ ዘሌዋውያን ተብሎ ይሰየም እንጂ ስለ
ሌዋውያን ብቻ አይናገርም፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 41


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሕዝበ እግዚአብሔር እስራኤላውያን በሃይማኖታዊና በማኅበራዊ ሕይወት የሚመሩባቸውን ሕጎች


ይዟል፡፡ ሕዝቡ ወደ ተስፋው ሀገር ጉዟቸውን ከመቀጠላቸው በፊት በማደርያው ውስጥ እግዚአብሔርን
ለማምለክ መመርያ የሚሆኗቸውን ሕጎች ማወቅ ለእነርሱ አስፈላጊ ነበር፤ ሕጎቹም በዚህ መጽሐፍ
ይገኛሉ፡፡ ሕዝበ እስራኤል ርኩስ ከሆነው ነገር ሁሉ እንዲርቁ ያስጠነቅቃል፤ ተቋርጦ የነበረው የሰውና
የእግዚአብሔር ግንኙነት እንደገና እንደቀጠለ ያስረዳል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
ዘሌዋውያን 27 ምዕራፎች ሲኖሩት ለጥናት ያመች ዘንድ በ 8 ዋና ዋና ክፍሎች ከፍለን እናያቸዋለን፡፡
እነርሱም፡
ዘሌ 1-7፡ ስለ መሥዋዕት አቀራረብና ሥርዓቱ
ዘሌ፡ 8-10፡ ስለ ሥርዓተ ክህነት፣ ናዳብና አብዮድ ሥርዓት በማፍረሳቸው የደረሰባቸው ቅጣት
ዘሌ 11-14፡ ስለሚበሉና ስለማይበሉ እንስሳ፣ ሴቶች ከወለዱ በኋላ መንጻት እንደሚገባቸው፣ ስለ ለምጽ
አይነቶች
ዘሌ 15-16፡ ስለ መንጻት ሥርዓት (ከወንድም ሆነ ከሴት ሰውነት በሚፈስ ፈሳሽ ምክንያት ከሚመጣው
ርኩሰት)፣ ስለ ኃጢያት ማስተሥረያ ቀን
ዘሌ 17-19፡ ደም መብላትና ደሙ ሳይፈስ የሞተ እንስሳ መብላት ስለመከልከሉ፣ ስለተከለከሉ ጋብቻዎችና
ፍትወታዊ ግንኙነቶች
ዘሌ 20-22፡ ካህናት የተቀደሱ መሆን እንደሚገባቸው፣ ወደ ጠንቋዮች የሚሄዱ ሰዎችና አረማውያን
የሚደርስባቸው ቅጣት፣ ለእግዚአብሔር ስለሚቀርቡና ስለማይቀርቡ መሥዋዕት
ዘሌ 23-25፡ ስለ ሕግጋትና በዓላት አከባበር፣ የድፍረት ኃጢአት በሚያደርጉ ሰዎች ላይ ስለሚደርሰው ከፍ
ያለ ቅጣት፣ ስለ ዕረፍት (ሰንበት)
ዘሌ 26-27፡ ስለ ስእለት፣ ስለ በረከትና መርገም
4. ኦሪት ዘኁልቊ
አራተኛው የሙሴ መጽሐፍ ዘኁልቊ በመባል ይታወቃል፤ ይህ ቃል ከግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን
ትርጉሙም የቊጥር ማለት ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ በዕብራውያን “በሚድባር” (bemidbar) ትርጉሙም
በበርሃው ውስጥ ማለት ነው፡፡ ዘኁልቁ ተባለውን ስያሜ ያገኘው ከሰብኣ ሊቃናት ትርጉም በኋላ ነው፡፡
መጽሐፉ ዘኁልቊ የተባለበት ምክንያት እስራኤላውያን ከግብጽ ወጥተው በምድረበዳ ሳሉ ሁለት ጊዜ
መቆጠራቸውን ስለሚተርክ ነው፡፡ ቆጠራው የተካሄደው በሲናና በሞዓብ ሜዳ ነበር፡፡ ዘጸአት የአበውን
(የአባቶችን) ነገር ይናገራል፤ ዘኁልቊ ደግሞ የውሉድን (የልጆችን) ነገር ይተርካል፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
ኦሪት ዘኁልቊ እስራኤላውያን ከሲና ተነሥተው እስከ ከነዓን ድንበር ያደረጉትን ጉዞ ይገልጣል፤
በምድረ በዳ ስለገጠማቸው ችግርም ይዘረዝራል፡፡ በተጨማሪም የሽማግሌዎችን ወደ ተስፋ ሀገር
አለመግባትና ለ 38 ዓመታት በምድረበዳ እንዲንከራተቱ የተፈረደባቸውን ፍርድ ይናገራል፤ እንደዚሁም
የተለያዩ ሕጎች ይገኙበታል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
መጽሐፉ 36 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 4 ዐበይት ክፍላት ከፍለን እናያቸዋለን፡፡ እነርሱም፡-
ዘኁ 1-10፡- በሲና ተራራ ሕዝበ እስራኤል መቆጠራቸውን፣ ከዚያ ለመውጣት ማሰባቸውንና ወደ
ዮርዳኖስ መሄዳቸውን ይነግረናል፡፡
ዘኁ 11-12፡- ከሲና ወደ ቃዴስ በረሃ ያደረጉትን ጉዞ ይተርካል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 42


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ዘኁ 13-25፡- 12 ሰላዮች ወደ ከነዓን መላካቸውንና ከእነርሱ ግን እስራኤልን ለማገልገል ከእግዚአብሔር


የተላኩት 2 ቱ መሆናቸውን (ኢያሱና ካሌብ)፣ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ላይ በማመንዘራቸው
(ጣዖት በማምለካቸው) የደረሰባቸውን 10 ቅጣት፣ ባላቅ በበለዓም አማካኝነት እስራኤልን ለማስረገም
ቢሞክርም እግዚአብሔር ግን እንደ ባረካቸው ተገልጧል፡፡
ዘኁ 26-36፡- እስራኤላውያን ምድረ ርስት ከነዓንን መውረሳቸውና እዚያም መሬት(ርስት)
መከፋፈላቸውን ይተርካል፡፡
5. ኦሪት ዘዳግም
ኦሪት ዘዳግም ከግብጽ የወጡት ከ 45 ዓመት በላይ የነበሩት አበው በምድረበዳ ከሞቱ በኋላ ወደ ከነዓን
እንዲገቡ ለተፈቀደላቸው ውሉድ ሙሴ በሦስቱ መጻሕፍት (ዘጸአት፣ ዘሌዋውያንና ዘኁልቊ) የተመዘገበውን
ታሪክ፣ ሕግና፣ ትእዛዝ ከማስጠንቀቂ ጋር በድጋሚ መናገሩን የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
ሙሴ የሕዝበ እስራኤል መሪ ሆኖ ለብዙ ዓመታት ካገለገለ በኋላ የአገልግሎቱ ዘመን ፍጻሜ ሲቃረብ
በምድረበዳ ውስጥ ተወልዶ ላደገው አዲስ ትውልድ ቀድሞ በደብረ ሲና የተሰጠውን ሕግ በልዩ ልዩ ንግግር ፣
ምክርና ፣ ማሳሰቢያ እየከለሰ በሞዓብ ሜዳ የተናገረውን ያስረዳል፡፡ የሙሴን እረፍትና ከሙሴ በኋላ
የአመራሩን ኃላፊነት ኢያሱ መረከቡንም ይገልጣል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
ኦሪት ዘዳግም 34 ምዕራፎች ሲኖሩት በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡
ዘዳ 1-3፡- እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ያደረገላቸውን ድንቅ ሥራ ይነግረናል፡፡
ዘዳ 4-26፡- እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጣቸውን ሕጎችና ደንቦች በድጋሚ ይተረጉማል፡፡
ዘዳ 27-30፡- ግብረገባዊ ሕጎችን ያረጋገጠበትና ሕግን ማንና እንዴት መፈጸም እንዳለበት ያስረዳናል፡፡
ዘዳ 31-34፡- ሊቀ ነቢያት ሙሴ ስለ ጌታችን የተነበየውን ትንቢት፣ ኢያሱን ሾሞና ሕዝቡን ባርኮ
ተልይቷቸው እንዳረፈ ይተርካል፡፡
2. የታሪክ መጻሕፍት

የታሪክ መጻሕፍት ተብለው የሚጠሩት ከኢያሱ ወልደ ነዌ እስከ መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን ያሉት ሲሆኑ የመጻሕፍቱ ብዛት 17 ነው፡፡
35
በዕብራይስጡ ጽሑፋት ድርሳናት (a-kethubim) በተባለው ክፍል ውስጥ ይካተታሉ፡፡ በመጻሕፍቱ ውስጥ የምናገኘው ጠቅላላ ሐሳብ
በተለይ እስራኤላውያን የአምላካቸውን ሕግ ሲያከብሩ ሰላምና ብልጽግና ያገኙ እንደነበር፤ ከአምላካቸው ፈቃድ ሲወጡ ደግሞ ጦርነት እና
መዓት ይገጥማቸው እንደነበር ነው፡፡

1. መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ


የመጽሐፉ ጸሐፊ ከኤፍሬም ነገድ የሆነው የነዌ ልጅ ኢያሱ ሲሆን የስሙም ትርጓሜም አዳኝ፣ መድኃኒት፣ እግዚአብሔር አዳኝ
(መድኃኒት) ነው ማለት ነው፡፡ ከሌሎች ኢያሱ በሚል ስም ከሚጠሩ ሰዎች ለመለየት ኢያሱ ወልደ ነዌ (የነዌ ልጅ) ይሏል፡ የመጀመሪያ
ስሙ አውሴ ሲባል ኢያሱ ብሎ ያወጣለትም ሊቀ ነቢያት ሙሴ ነው፡፡ ዘኁ 13፡8-16

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስምና የኢያሱ ስም በዕብራይስጥ አንድ ዓይነት ትርጓሜ አላቸው፡፡ ይኽውም መድኃኒት፣ አዳኝ
ማለት ነው፡፡ ኢያሱ አዳኝ፣ መድኃኒት መባሉ የእስራኤልን ሕዝብ ከሥጋ ጠላቶቻቸው ከአማሌቃውያን በማዳኑ ምክንያት ነው፡፡
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ቅዱስ ሥጋውን ቆርሶ ክቡር ደሙን አፍስሶ ከነፍሳችን ጠላትና ከዘለዓለም ሞት አድኖናልና
እርሱ እውነተኛ መድኃኒት ተብሏል፡፡ ሉቃ 2፡10፣ የሐ 4፡42

35
ይህ ክፍል ከነዚህ ውጪ ሌሎች መጻሕፍትን ያካተተ ክፍል ነው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 43


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ኢያሱ የተወለደው በግብፅ ነው፡፡ እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ በኋላም በዘጸ 17፣9 ከአማሌቃውያን ጋር ሲዋጉ 44 ዓመቱ ነበር፡፡ ኢያሱ
ሙሴን ሲያገለግል የኖረ ሲሆን ከሙሴ ሞትም በኋላ እስራኤልን አገልግሏል፡፡ ከነዓንን ሊሰልሉ ከተላኩት ከዐሥራ ሁለቱ ሰላዮች መካከል
አንዱ ነበር፡፡ ዘጸ 24፡13፣ ዘኁ 13፡2

አብዘኞቹ የአይሁድ ምሁራን እንደሚስማሙት ከመጨረሻዎቹ አምስት ሐረጎች (ቊጥሮች) በስተቀር የመጽሐፉ ጸሐፊ ኢያሱ ነው፡፡
እነዚህን አምስት ሐረጎች (ኢያ 24፣29-33) ግን ከነቢዩ አያሱ እረፍት በኋላ አልአዛር ልጅ ፊንሐስ ጨምሯቸዋል ይባላል፡፡

36
መጽሐፉ በአጠቃላይ 31 ዓመታትን ማለትም በሙሴ ዕረፍት እና የአሮን ልጅ አልአዛር ዕረፍት መካከል ያለውን ታሪክ የያዘ
ነው፡፡ የመጽሐፉም ዋና ሐሳብ የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ኃይል እና በኢያሱ መሪነት የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው፣ የኢያሪኮን
ከተማ ወርረው፣ የከነዓንን ነገሥታት አሸንፈው ምድረ ርስት ከነዓንን እንደወረሱና ምድሪቷም በነገድ ኢያሱ እንዳከፋፈላቸው ይተርካል፡፡
ታሪኩ የተፈፀመው በቤተ ክርስቲያን ትውፊት 1450 ቅ.ል.ክ ባለው ዘመን ውስጥ ነው፡፡ ኢያሱ በ 110 ዓመቱ አርፎ በኤፍሬም ሀገር
ተቀብሯል፡፡ ኢያ 24፡29-31

የመጽሐፉ ዓላማ
የመጽሐፉ ዋና አሳብ የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ኃይል እና በኢያሱ መሪነት የዮርዳኖስን ወንዝ
ተሻግረው የኢያሪኮን ከተማ ወርረው የከነዓንን ነገሥታት ማሸነፉን ይተርካል፡፡ ታሪኩ የተፈጸመው ከ 1400-
1300 ዓ.ዓ ባለው ዘመን ውስጥ ነው፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
መጽሐፉ 24 ምዕራፎች አሉት፤ በ 3 ዓበይት ክፍሎች ከፍለን እናየዋለን፡፡
ኢያ 1-7፡ የሕዝበ እስራኤል ዝግጅት፣ የዮርዳኖስ ወንዝን ስለመሻገራቸው፣ የኢያሪኮ ግንብ መፍረስ፣ ረዓብ
ሁለቱን ሰላዮች በማዳኗ ከኢያሪኮ ሕዝብ መካከል ከቤተሰቦቿ ጋር መዳኗ፣ የኢያሪኮ መያዝና
እስራኤላውያን ወደ ኢያሪኮ ሲገቡ እርም የሆነውን እንዳትነኩ የሚለውን ትእዛዝ ያፈረሰው የአካን
መቀጣትን ያነሣል፡፡
ኢያ 8-12፡ የሕዝብ እስራኤል ወደ ከነዓን መዝመት፣ ኢያሱ የከነዓንን፣ የአሞራውያንንና የአሦርን
ነገሥታት አሸንፎ ግዛቶቹን እንደያዘና ያሸነፋቸውን ነገሥታት ስም ዝርዝር ይገኝበታል፡፡
ኢያ 13-24፡ የኢያሱ የመጨረሻ ምክር ፣ ስንብትና ዕረፍት በስፋት ተገልጽዋል፡

2. የመጽሐፈ መሳፍንት
መሳፍንት ማለት አስተዳዳሪዎች፣ ፈራጆች ማለት ነው፤ መጽሐፉ ከኢያሱ በኋላ የተነሡትን የ 13 ቱን መሳፍንት የአገዛዝ ታሪክ
ስለሚተርክ መጽሐፈ መሳፍንት ተብሏል፡፡ ጸሐፊው ነቢዩ ሳሙኤል ሲሆን ከመሳፍንት ዘመን በኋላ የተነሣ ነቢይ ቢሆንም እግዚአብሔር
ያለፈውን ነገር ገልጾለት ጽፏል፡፡

ከነዓናውያን የሚያመልኳቸው የነበሩት በአል እና አስተሮት የተባሉት አማልክት በሕዝበ እስራኤላውያን ዘንድ ገብተው ይመለኩ
እና ሕዝቡን ይመርዙ ነበር፤ እስራኤላውያንም በእስራኤል ዘንደ ቋሚ አስተዳደር አልነበረም፡፡ በዘመኑ ራሱ እግዚአብሔር የሕዝቡ መሪና
አስተዳዳሪ ነበር እንጂ፤ ሆኖም ኃጢአታቸው ሲበዛ ጠላት እያስነሳ ሲቀጣቸው ምሕረት፣ ይቅርታን ሲጠይቁት ከሕዝቡ መካካል
መሳፍንትን እያስነሳ ነጻ ያወጣቸው ነበር፡፡ መጽሐፉ ከ 1380-1050 ቅ.ል.ክ. ክርስቶስ እንደተጻፈ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይናገራሉ፡፡

በመጽሐፍ መሳፍንት ላይ ተመሳሳይ ታሪክ ይደጋገማል፡፡ ይኸውም ወረተኛ የሆኑት የእስራኤል ሕዝቦች ለጥቂት ጊዜ ያህል
እግዚአብሔርን ያመልኩና ሲደላቸው አምላካቸውን በመርሳት ወደ ጣዖታት ማምለክ ይጀምራሉ፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔርም ከእነርሱ
ይርቃል፡፡ በዚህም በዙሪያቸው ያሉት ፍልጤማውያንና ሌሎች ሕዝቦች መጥተው ይወሯቸዋል፣ በባርነትም ይገዟቸዋል፡፡ በዚህ የመከራ
ወቅትም አምላካቸውን እግዚአብሔርን ያስታውሳሉ፤ ንስሓ በመግባትም እንዲያድናቸው ወርሱ ይጮሀሉ፡፡ ጌታችንም መሐሪ ነውና
የሚያድናቸውን መስፍን ያስነሳና ያድናቸዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ ታሪክ በዚህ በመጽሐፍ ላይ ከ 10 ጊዜ በላይ ተጽፏል፡፡ አባ ዳውድም ከዚህ ታሪክ
በመነሣት “መጽሐፈ መሳፍንት የሚያስተምረው ስንፍና ወደ ኃጢአት (ከእግዚአብሔር መለየት)- ኃጢአትም ወደ ቅጣት (ባርነት)-

36
ኢያሱ ካረፈ ከ 6 ዓመት በኋላ ዐርፏል
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 44
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ባርነትም (በስቃይ ምክንያት የሚመጣው ጸጸት) ወደ ንስሓና ድኅነት እንደሚመራ ነው” ብለዋል፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን መሐሪነት
የሚያስረዳ ነው፡፡

የመጽሐፉ ዓላማ

 ነገደ እስራኤል ዋና ንጉሥ እንዳልነበራቸው በእግዚአብሔር ተመርጠው ከጠላቶቻቸው ባዳኗቸው


መሳፍንት መገዛታቸውን ይተርካል።
የመጽሐፉ አከፋፈል
መሳ 1-3 እስራኤላውያን የከነዓንን ሰዎች ጨርሰው እንዳላጠፉ የተሰጣቸውንም ትእዛዝ ሳይፈጽሙ
መቅረታቸው፣በዚህም መጨነቃቸውን
መሳ 3-16 ብዙ መከራዎች እንዳጋጠሟቸው እና የተለያዩ መሳፍንት በየጊዜው ከእነዚህ መከራዎች
እንዳዳኗቸው
መሳ 17-18 የሰዎች በእግዚአብሔር አለመታመን ምሳሌ
መሳ 19-21 የሰዎች የግብረ ገብነት ምሳሌ እስራኤልን ለ 400 ዓመታት ያህል 13 መሳፍንት በየተራ
መርተዋታል፡፡ የዐሥራ ሦስቱም መሳፍንት ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 45


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

 ጎቶንያል መሳ 3፡7-11
 ናዖድ መሳ 3፡12-30
 ስሜገር መሳ 3፡31
 ባርቅ መሳ 4፡1-5፣31
 ጌዴዎን መሳ 6፡11
 አቤሜሌክ መሳ 9፡22
 ቶላ መሳ 10፡1-2
 ኢያዕር መሳ 10፡3-5
 ዮፍታሔ መሳ 11፡1
 ኢብጻን መሳ 12፡11
 ኤሎም መሳ 12፡8
 ዓብዶን መሳ 12፡13
 ሶምሶን መሳ 13፡1-16

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 46


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

3. መጽሐፈ ሩት
37
በዕብራውያን ታልሙድ መሠረት የመጽሐፉ ጸሐፊ ነቢዩ ሳሙኤል ነው፡፡ መጽሐፉ በቅዱሳት አንስት ስም ከተጠሩ መጻሕፍት
መካከል አንዱ ነው፡፡ የተጻፈበት ዘመንም በ 1100 ቅ.ል.ክ ነው፡፡

ሩት ማለት መልከ መልካም፣ ቅንጆ፣ ወዳጅ፣ ጓደኛ ማለት ነው፡፡ መሳፍንት እስራኤልን ይገዙ በነበረበት ዘመን የነበረች ከሞዓብ
ወገን የሆነች አሕዛባዊት ሴት ናት፡፡ ሞዓባውያን ከጨው ባሕር በስተ ምሥራቅ የሚኖሩ፣ ጣዖት ያመልኩ የነበሩ ሕዝቦች ናቸው፡፡
38
አቤሜሌክ የተባለው እስራኤላዊ በሀገሩ ረሀብ ተነሥቶ ኑኃሚን ከተባለች ሚስቱና ከሁለት ልጆቹ ጋር ወደ ሞዓብ ሀገር ሄደዋል፤
በሞዓብ ሳሉም የአቤሜሌክ ልጅ ሩትን አግብቷት ነበር፤ ልጅ ሳይወልድም ሞቷል፡፡ በሞዓብም አቤሜሌክና ልጆቹ በመሞታቸው ኑኃሚን
በሰው ሀገር ብቸኝነቱን ጠልታ ወደ ሀገሯ ከነዓን ስትመለስ ሩትም ‹‹ሕዝብሽ ሕዝቤ፣ አምላክሽ አምላኬ ነው ፡፡›› በሚል የእምነት ቃል
ከእርሷ መለየት አለመፈለጓን ገልጻ ከኑኃሚን ጋር ከነዓን ገብታለች፤ ከዚያም ከይሁዳ ወገን የሆነውን ቦኤዝን አግብታ ኢዮቤድ የተባለውን
የዳዊትን አያት ወልዳለች፤ ይህ ጽኑ እምነቷና ጥንካሬዋ ከአሕዛብ ወገን ሆና የክርስቶስ የዘር ሐረግ ውስጥ እንድትካተት አድርጓቷል፡፡ ግብሯ
ልክ እንደ ስሟ ያመረ እናት ነበረችና፡፡/ሩት 1፡16-17፣ ማቴ 1፡5/

የመጽሐፉ አከፋፈል
ይህ መጽሐፍ 4 ምዕራፎች ሲኖሩት፤ በ 4 ከፍለን እንመለከተዋለን
ሩት 1፡ የአቤሜሌክ ቤተሰብ በሞዓብ ሀገር፣ ሩት ከኑኃ፣ም ጋር ወደ በቤተልሔም እንደሄደች
ሩት 2፡ ሩት ከኑኃሚን ጋር ወደ ከነዓን መጓዟና በቦኤዝ አውድማ ውስጥ እንደቃረመች
ሩት 3፡ ሩት ቦኤዝ እንዲያገባት ያደረገችው ጥረትና ጥበብ
ሩት 4፡ ሩት የቦዔዝ ሚስት ሆና የዳዊትን አያት ኢዮቤድን እንደወለደችው ይተርካል፡፡

4. መጻሕፍተ ሳሙኤል
በውስጡ ሁለት መጻሕፈትን ይይዛል፡፡ እነዚህ መጻሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊና ካልዕ ናቸው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በዕብራይስጡ እንደ አንድ
መጽሐፍ ይቆጠራሉ፡፡ በኋላም ሰብአ ሊቃናት መጻሕፈትን ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ ሲተረጕሙ ለሁለት ከፍለዋቸዋል፡፡ ይህም የሆነበት
ምክንያት የዕብራይስጥ ቋንቋ አናባቢ የሌለው በመሆኑ በአንድ ጥቅልል መጠቅለል ሲችል ወደ ግሪክ በተረጎሙት ጊዜ ግን እጅግ ስለበዛ ወደ
ሁለት መጻሐፍት ከፍለውታል፡፡

የመጻሐፉ ስምም በዕብራይስጡ ልክ እንደ አማርኛው “ሳሙኤል” ይባላል፡፡ ይህን ስያሜ ያገኘውም መጽሐፉ ስለ ነቢየ እግዚአብሔር
ሳሙአል እና እርሱ ቀብቶ ስላነገሣቸው ነገሥታት የሚተርክ ስለሆነ ነው፡፡ ሳሙኤል ማለትም እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ሰብአ
ሊቃናት መጽሐፉን ሲተረጕሙረት “የመንግሥት መጻሕፍት” (kingdom books) ብለውታል፡፡ ቅዱስ አባ ሄሮኒመስ (ጄሮም) መጻሕፍትን
ወደ ላቲን ቋንቋ በተረጎመበት ቩልጌት ትርጉሙ የሰብአ ሊቃናትን አከፈፈል ተከትሏል፡፡ ነገር ግን መጻሕፈቱን “የነገሥት መጻሕፍት” (Regum
books; namely The Royal Books) ብሏቸዋል፡፡
በ 14 ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የዕብራጥስጡም ትርጉም ይህን የግሪክ አከፈፈል በመከተል መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊና ካልዕ ተብሏል፡፡
አማርኛው ይህን ይከተላል፡፡ በግእዙ ግን ነገሥት ቀዳማዊና ካልዕ ነው የሚባለው፡፡ ግእዙ ለያይቶ ቢጠራቸውም ሲቆጥራቸው ግን እንደ አንድ
መጽሐፍ ነው፡፡ “መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ወካልእ አሐዱ መጽሐፍ ” እንዲል ፍትሕ መንፈሳዊ፡፡

የመጽሐፉ ጸሐፊ በተመለከተ በአይሁዳውያን ትውፊት መሠረት እስከ ምዕራፍ 25 ማለትም ነቢዩ ሳሙኤል እስከሚያርፍበት ድረስ
ያለውን የጻፈው ራሱ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ሳሙኤል ሲሆን ከዚያ በኋላ እስከ መጨረሻ ድረስ ያለውን ግን ነቢዩ ናታንና ጋድ እንደጨረሱት
ይነገራል፡፡ (ሳሙ 10፡25)

4.1 መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ /መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ/


በግእዙና በቩልጌት ትርጉም ነገሥት ቀዳማዊ ይባላል፡፡ የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ ሳሙኤል ሲሆን ነገር ግን መጽሐፉን ጽፎ
አልጨረሰውም ከምዕራፍ 25 በኋላ ያሉትን ክፍሎች የጻፏቸው እንደ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ናታን እና ጋድ ናቸው። ሳሙኤል ማለት
37
በሺዎች የሚቆጠሩ የአይሁድ ረበናት ትምህርት የተመዘገበበት ሚሽናህና ገማራ የተባሉትን መጻሕፍት የያዘ ጥንታዊ መጽሐፍ ነው፡፡
38
በጌዴዎን ዘመን የተነሣው ረሀብ ነው መሳ 6 ፡1-11

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 47


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የእግዚአብሔር ስም ወይም አምላካዊ ስም፣ እግዚአብሔር ጸሎቴን ሰማኝ ማለት ነው፡፡ ሳሙኤል ከዘመነ መሳፍንት
መጨረሻ የነበረ ነቢየ እግዚአብሔር ነው፡፡

ይህ መጽሐፍ ከሰባው ሊቃውንት ትርጓሜ በፊት ከሁለተኛው መጽሐፈ ሳሙኤል ጋር አንድ መጽሐፍ ነበር፡፡ ሰባው
ሊቃውንት ግን ለሁለት ከፍለውታል፡፡

የመጽሐፉ ዓላማ

 የዘመነ መሳፍንት መፈጸምና የዘመነ ነገሥት መጀመርን ማስረዳት


የመጽሐፉ አከፋፈለል
መጽሐፉ 31 ምዕራፎች ሲኖሩት በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል
1 ሳሙ 1-7 ስለ ዔሊና ሳሙኤል
1 ሳሙ 8-15 ስለ ሳሙኤልና ሳዖል
1 ሳሙ 16-31 ስለ ሳዖልና ዳዊት

4.2 መጽሐፈ ሳሙኤል ካልእ /መጽሐፈ ነገሥት ካልእ/


በግእዙና በቩልጌቱ ትርጉም ነገሥት ካልዕ ይለዋል፡፡ ይህ ሁለተኛው የሳሙኤል መጽሐፍ የሚገልጸው ታሪክ ሳሙኤል ከሞተ
በኋላ ያለውን ነው፡፡ መጽሐፉም በሳሙኤል ስም መሰየሙ እርሱ ቀብቶ ያነገሣቸው ነገሥታትን ታሪክ ስለያዘ ነው፡፡

የመጽሐፉ ዓላማ

 ስለ ዳዊት አገዛዝ በሰፊው ይተረካል። ይህ ታሪክ በድጋሜ በ 1 ኛ ዜና መዋ. 11-19 ይገኛል።


የመጽሐፉ አከፋፈል
2 ሳሙ 5-10 የዳዊት ድል መንሣት
2 ሳሙ 11-19 የንጉስ ዳዊት ችግሮች
2 ሳሙ 20-24 በዳዊት መጨረሻ ዘመኖች የሆኑ ልዩ ልዩ መከራዎች

5. መጽሐፈ ነገሥት
6. ሀ. መጽሐፈ ነገሥት አንደኛ
7. ለ. መጽሐፈ ነገሥት ሁለተኛ
እነዚህ ሁለት መጻሕፍት በዕብራይስጡ አንድ እንደነበሩና በኋላ ዘመን በ 150 ቅ.ል.ክ 70 ሊቃናት ብሉያትን ወደ ግሪክ ቋንቋ
በተረጎሙት ጊዜ በሊቃውንት ውሳኔ ሁለት እንደሆኑ የብሉይ ኪዳን ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ በዕብራይስጥ ሁለቱም
መጻሕፍት አንድ ላይ መለኪያ ይባላሉ፡፡ የመጽሐፉ ጸሐፊ በታልሙድ 17 (15) ላይ እንደተጠቀሰው ነቢዩ
ኤርምያስ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ይህም ነቢዩ ኤርምያስ በነገሥት 24 እና 25 ላይ መጠቀሱ በዘመኑ እንደ
ነበርና መጽሐፉን ለመጻፉ ማስረጃ ነው፡፡ የተጻፈበትም ዘመን በ 567 ቅ.ል.ክ ነው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 48


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

5.1 መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ /መጽሐፈ ነገሥት ሣልስ/


በግእዙና በቩልጌት ትርጉም ነገሥት ሦስተኛ በመባል ይጠራል፡፡ መጽሐፉ ስለ ንጉሥ ሰሎሞን ቤተ
መቅደስ ማነጽና ስለ እስራኤል ለሁለት መክፈል በሰፊው ያትታል፡፡
መጽሐፈ ነገሥት አንደኛ 22 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን በ 3 ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡
1 ነገ 1-10፡ ሰሎሞን የሰባቱን ዙፋን መውረሱ
፡ ሰሎሞን ከአባቱ ጠላቶች ላይ የወሰደው የበቀል ርምጃ
፡ በሁለቱ እናቶች የፍርድ ችሎት የሰሎሞን ጥበበኝነት መገለጥ
፡ ሰሎሞን ስለ ሠራው ቤተመቅደስ
፡ ንግሥት ሳባ የሰሎሞንን ጥበብ ለማየት ወደ እስራኤል መሄዷ
1 ነገ 11፡ በዚህ ክፍል በፍቅረ አንስት የወደቀበት፣ በአምልኮ ጣዖት የተጠመደበት፣ እግዚአብሔርን
ያሳዘነበትን ታሪክ እናገኛለን፡፡ በሰሎሞን ላይ ዐመጸኞች ስለ መነሳታቸው፣ እግዚአብሔርም ከኤፍሬም
ነገድ ኢዮርብዓምን በሰሎሞን ላይ እንዳሥነሳበት ተጽፎ ይገኛል፡፡
1 ነገ 12-22 ፡ የሰሎሞን ልጅ ሮብአም መንገሥና በክፋት መንገድ መቆሙ
፡ የእስራኤል መንግሥት ለሁለት መከፈል
፡ ስለ አራቱ የይሁዳ ነገሥታት ማለትም ሮብአም፣ አብያ፣ አሳ፣ ኢዮሳፍጥ፤

ተ. ንጉሥ የነገሠበት መግለጫ


ቁ ጊዜ
1 ሮብዓም 17 ዓመት የሰሎሞን የመጀመርው ልጅ ጣዖትን በማምለኩ እግዚአብሔር የቀጣው
2 አብያ በምግባር አባቱን ሮብዓምን የመሰለ
3 አሳ 41 ዓመት ደግና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጻሚ
4 ኢዮሳፍ 25 ዓመት የአባቱን የአሳን አርአያ የተከተለ ደግ ንጉሥ

፡ ስምንቱ የእስራኤል ነገሥታት፡ ኢዮርብአም፣ ናዳብ፣ ባኦስ፣ ኤላ፣ ዘምሪ፣ አክዓብ፣ አካዝያስ
ይናገራል፡፡
ተ.ቁ ንጉሥ የነገሠበት መግለጫ
ጊዜ
1 ኢዮርብአ 21 ዓመት የናባጥ ልጅና ቴቴልን መናገሻ ከተማ ያደረገ

2 ናዳብ 2 ዓመት የኢዮርብዓም ልጅ
3 ባኦስ 23 ዓመት ናደብንና ቤተሰቡን ሁሉ ገድሎ የነገሠ
4 ኤላ 2 ዓመት የባኦስ ልጅ
5 ዘምሪ 7 ቀን የባኦስን ቤተሰብ ከገደለ በኋላ ራሱን የገደለ
6 ዖምሪ 12 ዓመት ሰማርያን ዋና ከተማ ያደረገ
7 አክዓብ 21 ዓመት የዖምሪ ልጅን የጣዖት አምልኮን ከሚስቱ ከኤልዛቤል ጋር ያስፋፋና በነቢዩ
ኤልያስ የተገሠጸ
8 አካዝያስ 2 ዓመት የአክዓብ ልጅና የቤተሰቡን መጥፎ አርአያ የተከተለ

5.2 መጽሐፈ ነገሥት ካልእ /መጽሐፈ ነገሥት ራብዕ/

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 49


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

በግእዙና በቩልጌት ትርጉም ነገሥት አራተኛ በመባል ይጠራል፡፡ መጽሐፉ በአጠቃላይ የሁለቱን
መንግሥታት ታሪክ ከመጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ተቀብሎ በመቀጠል ሁለቱ መንግሥታት በጠላት ተከበው
እስከተያዙበትና ሕዝቦቻቸውም በምርኮ እስከተወሰዱበት ድረስ ያለውን ታሪክ ይተርካል፡፡
ይህ መጽሐፍ 25 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 2 ዋና ዋና ክፍሎች ከፍለን እናየዋለን፡፡
2 ኛ ነገ 1-17፡ ይህ ክፍል እስራኤላውያን በአሦራውያን እስከተማረኩበት ባለው ጊዜ ስለ ይሁዳና ስለ
እስራኤል መንግሥታት የሚናገር ነው፡፡
2 ኛ ነገ 18-25፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ናቡከደነፆር ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አስፋፍቶ ሕዝቡን ወደ
ባቢሎን እስከ ወደሰበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሁኔታ የሚገልጥ ነው፡፡ እንዲሁም በወቅቱ ስለበነሩት 16
የይሁዳ ነገሥታትና 11 የእስራኤል ነገሥታት ታሪክ በሰፊው ይገልጻል፡፡
ዐሥራ ስድስቱ የይሁዳ ነገሥታት
ኢዮራም፣ አካዝያስ፣ አታልያ፣ ኢዮአስ፣ አሜስያስ፣ ዖዝያን፣ ኢዮአታም፣ አካዝ፣ ሕዝቅያስ፣ ምናሴ፣
አሞን፣ ኢዮስያስ፣ ኢዮአክስ፣ ኢዮአቄም፣ ዮአኪን፣ ሴዴቅያስ
ተ. ንጉሥ የግዛት መግለጫ
ቁ ዘመን
1 ኢዮራም 7 ዓመት የኢዮሳፍጥ ልጅና የአካዓብን ልጅ በማግባትና ወንድሞቹን ሁሉ በመግደል
በክፋት የቆመ ነበር
2 አካዝያስ 1 ዓመት የኢዮራም ልጅና በኃጢያት እግዚአብሔርን ያሳዘነ
3 አታልያ 6 ዓመት የአካዝያስ እናት የነገስታት ዘሮችን ሁሉ ክኢዮአስ በስተቀር የገደለች
4 ኢዮአስ 40 ዓመት ጣዖት አምላኪ የሆነና በክፉ ስራው በአገልጋዮቹ የተገደለ
5 አሜስያ 29 ዓመት እግዚአብሔርን በማምለክ ጀምሮ ጣዖት በማምለክ የጨረሰ

6 ዖዝያን 52 ዓመት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጻሚ የነበረ
7 ኢዮአታ 16 ዓመት ጻድቅ እና ደግ ሰው የነበረ

8 አካዝ 16 ዓመት አምልኮ ጣዖትን ያስፋፋ ክፉ ሰው
9 ሕዝቅያ 29 ዓመት በጣም ጻድቅ የይሁዳ ንጉሥና በንስሐው 15 ዓመት ከእድሜው ላይ
ስ የተጨመረለት
10 ምናሴ 45 ዓመት መምላኬ ጣዖት የነበረ
11 አሞን 2 ዓመት ክፉ የነበረና በአገልጋዮቹ የተገደለ
12 ኢዮስያስ 31 ዓመት ባዕዳን አማልክትን ሁሉ ከአገሩ ያጠፋ እግዚአብሔርን የሚወድ ጻድቅ
ንጉሥ
13 ኢዮአክስ 3 ዓመት በክፉ መንገድ ቆሞ የነበረና በግብፃውያን ተማርኮ እዚያው የሞተ
14 ኢዮአቄ 11 ዓመት ኃጢአት በመስራት እግዚአብሔርን ያሳዘነ

15 ዮአኪን 3 ወር ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ የነበረና ተማርኮ ወደ ባቢሎን የወረደ
16 ሴዴቅያስ 11 ዓመት በክፉ ስራው እግዚአብሔርን ያሳዘነ
ዐሥራ አንዱ የእስራኤል ነገሥታት
ኢዮራም፣ ኢዩ፣ ኢዮአክዝ፣ ዮአስ፣ ዳግማዊ ኢዮርብአም፣ ዘካርያ፣ ሰሎሞን፣ ምናሔም፣ ፍቂስያስ፣
ፍቁሔ፣ ሆሴዕ
ተ. ቁ ንጉሥ የነገሠበት መግለጫ
ዘመን

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 50


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1 ኢዮራም 7 ዓመት በክፉ ስራው እግዚአብሔርን ያሳዘነ


2 ኢዩ 28 ዓመት የበዓልን ካህናት በዘዴ የፈጀ ቢሆንም ኢዮርብዓም ላቆማቸው ጣዖታት
የሰገደ
3 ኢዮአክዝ 17 ዓመት ኃጢአት በመስራት እግዚአብሔርን ያሳዘነ
4 ዮአስ 16 ዓመት እግዚአብሔርን በማሳዘን ጀምሮ በንስሐ የጨረሰ
5 ዳግማዊ 41 ዓመት በእግዚአብሔር ፊት ክፋት ያደረገና በሶርያ ነገስታት የተማረከውን አገር
ኢዮርብአ ያስመለሰ

6 ዘካርያ 6 ወር በክፉ መንገድ የተዘ
7 ሰሎሞን 1 ወር ዘካርያን ገድሎ በሰማርያ የነገሠ
8 ምናሔም 10 ዓመት ክፉም አደረገ እስራኤልንም ለአሶር ንጉሥ ግብር እንዲከፍሉ አደረገ
9 ፋቂስያስ 2 ዓመት ክፉም ሥራ ሠራ ፋቁሔም ገደለው
10 ፋቁሔ 8 ዓመት የአሦር ንጉሥ ሕዝቡን ማርኮ የወሰደበት ሥርአተ ንግሥና
11 ሆሴዕ 2 ዓመት በዘመኑ ሰማርያ ወደቀች

6. መጽሐፈ ዜና መዋዕል
ዜና መዋዕል ሁለት ክፍሎች አሉት፡

1. መጽሐፈ ዜና መዋዕል አንደኛ


2. መጽሐፈ ዜና መዋዕል ሁለተኛ
ዜና መዋዕል ማለት የዕለት ዜና ማለት ነው፤ በዕብራይስጥ ጀባር ሐዩሚም ሲባል አባ ጄሮም በቩልጌት ትርጕማቸው ላይ
ሸርባ ዲያሪዩም ይሉታል፤ ትርጕሙም ዜና መዋዕል ማለት ነው፡፡ ሰብአ ሊቃናት ፓራሊፓሜና ሲሉት ግእዙ ደግሞ መጽሐፈ
ሕጸጻን ይለዋል፤ ትርጕሙም የተተወ የቀረ ማለት ነው፡፡ ይኸውም ከመጻሕፍተ ሳሙአልና ነገሥት የቀረውን ስለያዘ ነው፡፡
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ መጽሐፈ ነገሥት ላይ ያሉ ታሪኮች በይበልጥ ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡ ልዩነቱ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ስለ
ሀይማኖታዊና ስለ መንፈሳዊ ነገሮች አብዝቶ ሲያወሳ፤ መጽሐፈ ነገሥት ግን ስለ መንግሥቱ አስተዳደር በይበልጥ ያስረዳል፡፡

የሁለቱም መጻሕፍት ጸሐፊ ካህኑ ዕዝራ ነው፡፡ መጻሕፍቱንም ከምርኮ ሲመለሱ በኢየሳሌም ጽፏቸዋል፡፡ ዘመኑም ከ 450
እስከ 300 ቅ.ል.ክ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡

6.1 ዜና መዋዕል ቀዳማዊ


ዜና መዋዕል አንደኛ 29 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 2 ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡
1 ኛ መዋ 1-9፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የቀደሙ የእስራኤል አባቶች የትውልድ ሐረግ ከአዳም እስከ
አብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ እስከ ዳዊት፣ ከዳዊት እስከ ዘሩባቤል ተዘርዝሯል፡፡
1 ኛ መዋ 10-29፡ የሳኦል መንግስት ወድቆ የዳዊት መንግሥት መተካት
፡ ዳዊት ብዙ ጦርነቶችን ማሸነፉ
፡ በዳዊት ኃያልነት በአካባቢው ያሉ ነገሥታት መጨነቃቸውን
፡ ለቃልኪዳኑ ታቦት ማረፊያ ዳዊት ቤት ማዘጋጀቱ
፡ ዳዊት መንግሥቱን ለልጁ ለሰሎሞን ማስረከቡ

6.2 መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእና ጸሎተ ምናሴ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 51


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ይህ መጽሐፍ ሠላሳ ስድስት ምዕራፎች ያሉት ሲሆን ከዜና መዋዕል አንደኛ የሚቀጥል መጽሐፍ ነው፡፡
መጽሐፉም በ 4 ዋና ዋና ክፍሎች ተከፍሏል፡፡
2 ኛ ዜና 1-9 ፡ የሰሎሞን ሀብታምነት
፡ የቤተ መቅደሱ መታነጽና የፈጀው ገንዘብ
፡ ስለ ሰሎሞን ገናናነትና ክብር
፡ ጥበቡን ለማየት ስለመጣችው ስለ ንግሥት ሳባ
2 ኛ ዜና 10-16፡ ከሰሎሞን ሞት በኋላ የልጁ የሮብአም መንገሥ
፡ በሮብአም ዘመን የመንግሥቱ ለሁለት መከፈል
፡ የይሁዳ ንጉሥ አብያ የእስራኤልን ንጉሥ ኢዮርብአምን ማሸነፉ
፡ የይሁዳ ንጉሥ አሳ ኢትዮጵያውያንን ድል ማድረጉና ሌሎችን በሰፊው ያትታል፡፡
2 ኛ ዜና 17-21፡ ኢዮሳፍጥ የአባቱን ዙፋን መውረሱ
፡ መምነኬው የእስራኤል ንጉሥ አክዓብን ለመርዳት መውጣቱ፣ ኢዮሳፍጥ የእግዚአብሔርን
መንገድ መከተሉ
፡ የአሞንና የሞአብ ሰዎች በኢዮሳፍጥ መንግሥት ላይ በተነሡ ጊዜ በእግዚአብሔር ኃይል
መደምሰሳቸው
፡ ኢዮሳፍጥ ከሞተ በኋላ ልጁ ኢዩራም ዙፋኑን መውረሱ
፡ ኢዮራም በአባቱ መንገድ ባለመሄዱ በኤልያስ መገሰፁ ይገኛል፡፡
2 ኛ ዜና 22-36፡ በዳዊት ስርው መንግሥት ስር ስለተነሱት ነገስታት ታሪክ
፡ ናቡከደነፆር ዋና ከተማዋን ኢየሩሳሌምን አፍርሶ አብዛኛዎቹን የይሁዳ ሕዝብ ማርኮ
መውሰዱ ተዘርዝሮ ይገኛል፡፡
ጸሎተ ምናሴ
የንጉሡ ምናሴ የጸሎት መጽሐፍ ባለ አንድ ምዕራፍ ሲሆን ይኸውም 13 ቁጥሮችን የያዘ ነው፡፡ በ 2 ኛ
ዜና 33፡18 ላይ የሕዝቅያስ ልጅ ንጉሡ ምናሴ የጸለየው ጸሎት እንደሆነ ስለሚናገርና ሙሉ በሙሉ
ተያያዠወነት ስላለው ጸሎተ ምናሴ የተሰኘው የጸሎት መጽሐፍ በሰማንያ አሐዱ የቀኖና ቅዱሳት
መጻሕፍት አቆጣጠር ከሁለተኛ ዜና መዋዕል ጋር በአንድነት ይቆጠራል፡፡
የመጽሐፉ ይዘትም የንስሐ ጸሎት ሲሆን በውስጡም ምናሴ ከኃጢአቱ መመለሱንና ምህረትን
ከእግዚአብሔር መለመኑን ያስረዳል፡፡
7. መጽሐፈ ኩፋሌ
ኩፋሌ ማለት ዘተከፍለ እምኦሪት (ከኦሪት የተከፈለ) ማለት ነው፡፡ አንዳንዴም ትንሹ ኦሪት በመባል ይታወቃል፡፡ መጽሐፉ በኦሪት ዘፍጥረትና
በኦሪት ዘጸአት በከፊል የተጻፈውን አብራርቶና አስፍቶ የሚተርክ መጽሐፍ ሲሆን ጸሐፊው ነቢየ እግዚአብሔር ሙሴ ነው፡፡ መጽሐፉ ሠላሳ ዐራት
ምዕራፎች ሲኖሩት ከዘፍጥረት 1፤1 እስከ ዘፀ 14፤31 ያለውን ታሪክ ከአይሁድ ትርጓሜ መጻሕፍት ጋር በመቀላቀል የተጻፈ ነው፡፡

አንዳንድ በመጽሐፉ ላይ ጥናት አድርገናል የሚሉ ሰዎች ጸሐፊው ሙሴ ሳይሆን እጅግ በጣም ጥብቅ የሆነ አቋም ያለውና ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ
ሰው እንደጻፈው ይናገራሉ፡፡ የተጻፈበትንም ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት በነበሩት አንድ መቶና ሁለት መቶ ዓመታት እንደነበር ያስቀምጣሉ፡፡ በኢትዮጵያ
ቤተክርስቲያን ትውፊት መሠረት የመጽሐፈ ኩፋሌ ጸሐፊ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ነው፡፡ ይህንንም መጽሐፉ ራሱ ሲጻፍ ሙሴ እግዚአብሔር ራሱን እያነገረው
እንደሆነ አድርጎ ጽፎታል፡፡ ከዚህም ሌላ የታሪኩ ሂደት የሚቋጨው ራሱ ሙሴ እስከነበረበት ጊዜ ነው፤ ይህም ጸሐፊው ራሱ ሙሴ እንደሆነ ያስረዳናል፡፡

የመጽሐፉ ተቀባይነት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከቀኖና መጻሕፍት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እነ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ፣ እነ ቅዱስ ዮስጢኖስ ሰማዕት፣ እነ
ሊቁ ኦሪገን፣ እነ ቅዱስ የጠርሴሱ ዲዮዶሮስ፣ እነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኑንክሉስ፣ እነ ቅዱስ አባ ጄሮም፣ እነ ዲዲሞስ ዘእስክንድርያ ስለመጽሐፉ እውነተኛነት
በጽሑፎቻቸው ገልጠዋል፡፡ መጽሐፉ በእንግሊዝኛ 'The book Jubilees' (መጽሐፈ ኢዮቤልዩ) ይሰኛል፡፡ ይኸውም መጽሐፉ ዓመታቱን በኢዮቤልዩ
እየከፋፈለ ስለሚናገር ነው፡፡ ኢዮቤልዩ በሰባት ብዜት ላይ የተመሠረተ ሲሆን አንዱ ኢዮቤልዩ (ሰባት የዓመት ሳምንታትን 'year-weeks' ) ዐርባ ዘጠኝ
ዓመታትን ይይዛል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 52


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ወደ 12 የሚሆኑ በሙት ባሕር ጥቅሎች እስኪገኙ ድረስ በወቅቱ የመጽሐፈ ኩፋሌ ብቸኛ ማስረጃ ሆነው ያገለገሉት በኢትዮጵያ የሚገኙት አራት
የተሟሉ የግእዝ ጽሑፎችና ከላይ የጠቀስናቸው አባቶች የጻፏቸው ጽሑፎች ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ. በ 1947 እና በ 1956 ዓ.ም መካከል በአምስት የቁምራን
ዋሻዎች ውስጥ በእብራይስጥ ቋንቋ የተጻፉ አሥራ አምስት የመጽሐፈ ኩፋሌ ጥቅሎች ተገኝተዋል፡፡ በዚያ የተገኙት ብዛት ያላቸው ጽሑፎች የሚያመለክቱት
ከሌሎች መጻሐፍት በሚበልጥ መልኩ (ከመዝሙረ ዳዊት፣ ከኦሪት ዘዳግም፣ ከትንቢተ ኢሳይያስ፣ ከኦሪት ዘጸአት እና ከኦሪት ዘፍጥረት በስተቀር ) መጽሐፈ
ኩፋሌ በቁምራን ደሴቶች በስፋት ያገለግሉ እንደነበር ነው፡፡ ጄምስ ቫንደርካም (James VanderKam) በተባለው ሰው በደረገው የማነጻጸር ሥራም
ኢትዮጵያዊው ቅጂ በቁምራን ከተገኘው ጋር ፍጹም ተመሳሳይና በቀጥታ ቃል በቃል የተተረጎመ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡

በመጀመርያ መጽሐፉ ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ ቋንቋ የተተረጎመ ሲሆን ኋላ ወደ ላቲንና ወደ ግእዝ ቋንቋዎች ተተርጉሟል፡፡ እንዲሁም ከጠቅላላ
መጽሐፉ አንድ አራተኛውን የሚይዘው ከግሪክ ወደ ላቲን የተተረጎመው መጽሐፍም አንዱ ማስረጃ ነው፡፡ የግእዙ ትርጉም ለመጀመርያ ጊዜ በኦገስት ዲልማን
አማካኝነት በ 1859 ዓ.ም እ.ኤ.አ ታትሟል፤ ይህ ሰው መጽሐፉን ወደ ጀርመንኛ ቋንቋ ተርጉሞታል፡፡ ሮበርት ሄነሪ ቻርልስ የተባለው ሰው ደግሞ የግእዙን
መጽሐፍ ለሁለተኛ ጊዜ ተሻሽሎ እንዲታተም ያደረገው ሲሆን ከዚህ እትም ወደ እንግሊዘኛ ተርጉሞታል፡፡

በሱርስት ቋንቋ የተጻፈውና “የካህናት ሚስቶች ስም ኢዮቤልዩ በሚለው የአይሁድ መጽሐፍ ላይ እንደተጻፈው” (“Names of the wives of
the patriarchs according to the Hebrew books called Jubilees”) የተሰኘው መጽሐፍ የተወሰኑ ክፍሎቹ በብሪታንያ ሙዚየም
ውስጥ መገኘታቸው በአንድ ወቅት በሶርያኛ ቋንቋ የተተረጎመ ቅጂ እንደነበረው ያመለክታል፤ እንዲሁም ብዙ ተጨማሪ የመጽሐፉ ክፍሎች መኖራቸውንም
ያሣያል፡፡

በፈሪሳዊና በረበናዊ (Pharasidic and Rabbinic) ቋንቋዎች (አይሁድ ከ 6 ኛው-15 ኛው መክዘ የነበረ የዕብራውያን ቋንቋ) የተጻፈ
አልተገኘም፤ ይህም ሳንኸርዲን (የአይሁድ ሸንጎ) ከሚቀበሏቸው ቀኖና መጻሕፍት ውጪ መሆኑን ያመለክታል፡፡

መጽሐፈ ኩፋሌ ከኦሪት ዘፍጥረት ጋር በአብዛኛው የሚመሳሰል ይዘት ቢኖረውም ታሪኩን የበለጠ በዝርዝር አስፋፍቶ ይጽፋል፡፡ ሙሴ በአጠቃላይ
የፍጥረትን እንዲሁም የእስራኤልን ታሪክ በኢዮቤልዩ (በዐርባ ዘጠኝ ዓመት) እየተከፋፈለ የተነገረውን የጻፈበት ነው፡፡ ከፍጥረተ ዓለም ሙሴ በስደት ወቅት
በሲና ተራራ ጽላቶቹን እስከተቀበለበት ድረስ ያለው ጊዜ አምሳ ኢዮቤልዩ ሲቀነስ ከነዓን ከመግባታቸው በፊት በበረሃ የተንከራተቱበት ዐርባ ዓመት ነው፤
ይህም 2,410 ዓመታትን ይሰጠናል፡፡

የመጽሐፈ ኩፋሌ ጸሐፊ የሆነው ሙሴ የመጀመርያዎቹን ሰዎች፣ የአበውን እና የእስራኤልን ወደ ግብፅ ስደት ታሪክ በድጋሜ
ጽፎታል፤

የመጽሐፉ አከፋፈል
ይህ መጽሐፍ 34 ምዕራፎች አሉት፣ በ 4 ክፍሎች ከፍለን እናየዋለን፡
ኩፋ 1- ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘቱን
ኩፋ 2-7- ከአዳም እስከ አብርሃም እና ኖኅ ድረስ ያለውን ታሪክ ይዟል፡፡
ኩፋ 8-32- የያዕቆብንና የልጆቹን ታሪክ
ኩፋ 33-34- የሙሴ ከግብጽ አርነት ነፃ በመውጣት ያገኘውን ድል እናገኛለን፡፡

8. መጽሐፈ ሄኖክ
ሄኖክ የአዳም 7 ኛ ትውልድ ሲሆን የያሬድ ልጅ የማቱሳላ አባት ነው፡፡ ሄኖክ ማለት አዲስ ወይም
ተሐድሶ ማለት ነው፡፡ የሄኖክ እናት ስም ባረካ ይባላል፤ ሄኖክ በ 12 ኛው ኢዮቤል ሚስት አገባ ስሟ አድኒ
ይባላል፡፡ በ 6 ኛው ዓመት ልጅ ወለደችለት ልጁንም ማቱሳላ ብሎ ጠራው፤ ሄኖክም 365 ዓመት ከኖረ በኋላ
ተነጠቀ ሄኖክም እስከ አሁን ድረስ ሞትን ሳይቀምስ በሕይወት ይገኛል፡፡ ሞትን ባይቀምስም፤ ነገር ግን ሰው
ሟች ነውና ለእለተ ምጽአት ዋዜማ ሞትን ይቀምሳል፡፡ የመጽሐፈ ሄኖክ ጸሐፊው ራሱ ቅዱስ ሄኖክ ነው፡፡
ይህ መጽሐፍ የተጻፈው በ 4014 ዓ.ዓ ነው ወይም አዳም ከተፈጠረ ከ 1486 ዓመት በኋላ ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 53


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ስለ እግዚአብሔር ሕልውና ስለ ቅዱሳን መላእክት ስለ ፀሐይ እና ጨረቃ ዑደት ስለ ከዋክብት


አፈጣጠር ስለ ዕፅዋት ስለ ጻድቃንና ኃጥአን እንዲሁም በዘመነ ኖኅ ስለተፈጸመው ኃጢአትና ቅጣት ወዘተ
በሰፊው ይገልጻል።
የመጽሐፉ አከፋፈል
ሄኖ 1-20፡ ስለ ቅዱሳን መላእክት ሥራ፣ ስለ ደቂቀ ሴትና አጋንንት ሥራ፣ ስለ ጌታችን
ሄኖ 21-26፡ ስለ ፀሐይና ጨረቃ ስለ ከዋክብት ውሕደትና ወቅታት ይነግረናል
ሄኖ 27-35፡ ስለ እስራኤላውያን ከግብፅ መውጣትና ካህናት፣ ነቢያት፣ መሳፍንትና ነገሥታት ይናገራል
ሄኖ 36-42፡ ስለ ጻድቃንና ኃጥኣን ዋጋና ቦታ ይገልጽልናል

9. መጽሐፈ ዕዝራ
ዕዝራ ማለት ረድኤት ማለት ነው፡፡ ዕዛራ ካህን፣ ነቢይ፣ ጸሐፊም ነበር፡፡ አባቱ አዛርያስ ይባላል፡፡ ነገዱ
ከነገደ ሌዊ ሲሆን በባቢሎን ምርኮ በሰባው ዘመን የተወለደ ሰው ነው፡፡ ጸሐፊው ራሱ ዕዝራ ነው፡፡ የጻፈውም
ከምርኮ መልስ በኢየሩሳሌም ነው፡፡

ብዙዎች የብሉይ ኪዳን ሊቃውንት መጽሐፈ ዕዝራን እና መጽሐፈ ነህምያን በአንድነት


ያስተምሯቸዋል፤ ይህንንም ለማድረጋቸው ሁለት ምክንያት ያቀርባሉ፡
1. ሁለቱ አንድ መጽሐፍ የነበሩ ሲሆን፣ የተከፈሉት በኋላ እንደሆነ ይናገራሉ
2. ሁለቱም የሚተርኩት እስራኤል ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ በኋላ ስለሆነው ስለ ይሁዳ መንግሥት ነው፡፡

መጽሐፈ ዕዝራ በዋነኝነት የእስራኤል ሕዝብ ከ 70 ዓመት የባቢሎን ምርኮ በኋላ ወደ ሀገራቸው
መመለሳቸውንና ቤተመቅደስንም እንደገና መሥራታቸውን ይገልጻል፡፡ በሰማንያ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ
አቆጣጠር መጽሐፈ ዕዝራ የሚቆጠረው ከመጽሐፈ ነህምያ ጋር በመጣመር ነው፤ ለዚህም ምክንያቱ፡-
 ሁለቱም መጻሕፍት የተጻፉት በአንድ ሰው ሲሆን ጸሐፊያቸውም ካህኑ ዕዝራ ነው፤ ለዚህም
የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን የሚያቀርቡት መረጃ ሁለቱም መጻሕፍት በይዘት ተመሳሳይ መሆናቸውን
ነው፡፡
 ሁለቱም መጻሕፍት በይዘት ተመሳሳይ መሆናቸውን በመጽሐፈ ዕዝራ ላይ የመጀመሪያዎቹ ከስደት
ተመላሾች መሪዎች ነበሩ ተብለው ስሞቻቸው ከተጠቀሱት ሰዎች መካከል ነህምያ ይገኝበታል፤
በመጽሐፈ ነህምያ ደግሞ በምዕራፍ 8 እና 9 ላይ ካህኑ ዕዝራ የእግዚአብሔርን ሕግ አንብቦ ኃጢአቱን
እንደተናዘዘ ስለተገለጠ ነው፡፡
ጸሐፊው ራሱ ካህኑ ዕዝራ ነው፡፡ ዕዝራ 8፡1፣ ዕዝ 10፡ 1፡፡ የተጻፈበት ዘመን በ 467 ቅ.ል.ክ ሲሆን ቦታው
ከባቢሎን መልስ በኢየሩሳሌም ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ፡-
ስለሚጠት፡- ከባቢሎን ምርኮ ስለመመለሳቸው፣ ስለ ቤተ መቅደስ መታነጽ፣ እስራኤላውያን ከአሕዛብ ጋር
በጋብቻ ስለመቀላቀላቸውና እግዚአብሔር ለሕዝቡ ስላለው ፍቅር፣ እስራኤላውያን ወደ እውነተኛ አምልኮ
መመለሳቸውን ይገልጻል፡፡

የመጽሐፉ አከፋፈል
መጽሐፈ ዕዝራ 10 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን፤ ለጥናትም ያመች ዘንድ በ 2 ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡
ዕዝ 1-6፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የፋርሱ ንጉሥ ቂሮስ የእስራኤል ልጆች ወደ ሀገራቸው ወደ ኢየሩሳሌም
እንዲመለሱ ሲል የደነገገው አዋጅ ይገኝበታል፡፡ ከተመላሾቹም አብዛኛዎቹ ከይሁዳ፣ ከብንያምና

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 54


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ከሌዊ ነገዶች እንደነበሩና ንጉሥ ቂሮስም ለቤተመቅደሱ ሥራ የሚያገለግል ቁሳቁስ እንደሰጣቸው


ተገልጽዋል፡፡
ዕዝ 7-10፡ በዚህ ክፍል የተቀሩት የእስራኤል ነገዶች በዕዝራ መሪነት ወደ ኢየሩሳሌም መመለሳቸውን፣
በዕዝራ ልመናና ልቅሶ ከስደት የተመለሱ ወገኖች ከአረማውያን ሚስቶቻቸው ቃል መግባታቸው፣
በ 460 ቅ.ል.ክ ገደማ በንጉሡ በአርጤክስ ፈቃድ በዕዝራ መሪነት ሁለተኛ የምርኮ ጓድ ወደ ከነዓን
መመለስና የቤተመቅደሱ መጨረስ መታደስ ተዝርዝሯል፡፡

10. መጽሐፈ ነህምያ

ነህምያ እግዚአብሔር አጽናኝ /አዳኝ/ ነው ማለት ነው፡፡ በሰብዓ ሊቃናት ኒምያ ይባላል፡፡ ነህምያ
የፋርስ ንጉሥ የነበረው አርጤክስ ጠጅ አሳላፊ የነበረ አይሁዳው ነው፡፡ ነህ 1፡ 1-2፤ ነህምያ የኢየሩሳሌምን
ፍርስራሽ ከተመለከተ በኋላ ከአርጤክስ ፈቃድ ተቀብሎ የከተማይቱን ሹማምንት ለሥራ በማነሣሣት
የጠላቶቹን ተቃውሞ ሳይፈራ በ 52 ቀናት የኢየሩሳሌምን ቅጥርዋን ለማሠራት የቻለ የእምነት ሰው ነበር፡፡
ጸሐፊው ራሱ ነህምያ ነው፡፡ /ነህ 1፡ 1-4/
የተጻፈበት ዘመን በ 446 ቅ.ል.ክ ሲሆን ቦታው በኢየሩሳሌም ነው፡፡

የመጽሐፉ ዓላማ ፡-
ስለ ኢየሩሳሌም ቅጽር ድጋሚ መታነጽ፣ የጸሎትን ኃይልና ነህምያ በማስተዳደር ዕዝራ በካህንነት ሕዝቡን
በማኅበራዊ ኑሮና በሃይማኖት ማገልገላቸውን ይገልጻል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
መጽሐፈ ነህምያ 13 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 3 ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡
ነህ 1-2፡ በዚህ ክፍል ነህምያ ወደ ኢየሩሳሌም የሚመለስበት ምክንያት የኢየሩሳሌም ቅጽሮች
በመፍረሳቸውና፡፡ በሮቹም በእሳት በመቃጠላቸው እነርሱን ለማሠራት እንደሆነ ተገልጽዋል፡፡
ነህ 3-6፡ በዚህ ክፍል የአይሁድ ጠላቶች በነህምያ ላይ ተቃውሞና ትችት ቢሰነዘሩም ነህምያ በነበረው
ድፍረትና እምነት የኢየሩሳሌም ቅጽሮችና በሮች መሥራት መቻሉ ተገልጽዋል፡፡
ነህ 7-13፡ በዚህ ክፍል ውስጥ፡ የሕጉ መጽሐፍ መነበቡ፣ የተደረገው የንስሐ ጸሎት፣ ነህምያ
የእግዚአብሔርን ቤት ማስተዳደሩና፣ ነህምያ ሕግ ተላላፊዎችን መገሰጹ ተገልጽዋል፡፡

11. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል


ሱቱኤል ማለት ዘሰትዓ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን የጠጣ ማለት ነው፡፡ ሱቱኤል (ሰላትያል) የካህኑ ዕዝራ
ድርብ (ቅጥያ) ስም ነው፡፡ የመጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ጸሐፊ ካህኑ ዕዝራ ነው፡፡ /ዕዝ ሱቱ 1፡1/ የተጻፈበት ዘመን በ 457 ዓ.ዓ
ቅ.ል.ክ ሲሆን ቦታው በኢየሩሳሌም ነው፡፡

የመጽሐፉ ዓላማ
ካህኑ ዕዝራ በተማረከበት በባቢሎን ሀገር በነበረበት ጊዜ ስላያቸው ሰባት ራዕዮች፣ ዕዝራ ለጠየቃቸው ጥያቄዎች
በምሳሌ የተሰጠውን መልስና በመጨረሻ ዕዝራ እግዚአብሔርን በጸሎት ጠይቆ መንፈሳዊ ጸጋና ዕውቀት ተሰጥቶት 40 ቀን
ጾሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደጻፈ ይገልጻል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል፡-
በመጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል 13 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 3 ዓበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡
ዕዝ.ሱቱ 1-3፡ ዕዝራ ከእግዚአብሔርና ከሊቀ መልአኩ ኡራኤል ጋር መነጋገሩ
ዕዝ.ሱቱ 4-7፡ ስለ አዕማደ ምስጢራት፣ ስለ ጻድቃንና ስለኃጥአን ያየው ራእይ
ዕዝ.ሱቱ 8-13፡ ስለ ዕዝራ ጾምና ስለተገለጸለት ምስጢር ይገልጻል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 55


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

12. መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ


የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊው፣ የተጻፈበት ቦታ እንደ መጽሐፈ ዕዝራ ቀዳማዊ ነው፡፡ /2 ኛ ዕዝ 8፡3/ ጸሐፊው ራሱ ካህኑ
ዕዝራ ነው፡፡ /ካ ዕዝራ 8፡1፣ 10፡1/፡፡ የተጻፈበት ዘመን በ 467 ቅ.ል.ክ ሲሆን ቦታው ከባቢሎን መልስ በኢየሩሳሌም ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
በመጽሐፈ በ 2 ኛ ዜና መዋዕል ከምዕራፍ 35-36፣ በመጽሐፈ ዕዝራ ከምዕራፍ 2-9 እና በመጽሐፈ ነህምያ
ከምዕራፍ 7-8 የተገለጸውን ታሪክ በድጋሚ በስፋት የሚገልጽ መጽሐፈ ነው፡፡ ይህም በመጽሐፈ ነገሥት የተነገረው ታሪክ
በድጋሚ በዜና መዋዕል እንደተገለጸው ዓይነት ነው፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል፡- 2 ኛ ዕዝራ 9 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 4 ዓበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡
ዕዝ.ካል 1-2፡ እስራኤላውያን ከምርኮ መመላለሳቸውን እና ቤተ መቅደስ ማነጻቸውን
ዕዝ.ካል 3-4፡ በዳርዮስ ፊት ሦስት ሰዎች በወይን፣ በንጉሥ፣ በሴትና፣ በእውነት መከራከራቸውንና ሴትና እውነት
ያሸንፋል ያለው ነህምያ መሸለሙ
ዕዝ.ካል 5-7፡ በዳርዮስ ፈቃድ ቤተ መቅደስ መሠራት
ዕዝ.ካል 8-9፡ ዕዝራ ሕጉን ማንበቡና የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን መውረሩን፡፡
13. መጽሐፈ ጦቢት
ጦቢት ዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጕሙም እግዚአብሔር ድግ ነው ማለት ነው፡፡ በግእዙ ጦቢያ ማለት ሠናይ፣ ልኁይ፣ ጻድቅ፣ ኄር ማለት ነው፡፡
ወርእየ እግዚአብሔር ከመ ሠናይ የሚለውን ከመጦብ ይለዋል፡፡ አንድም ጠቢብ ማለት ነው፤ ትውልዱ ከነገደ ንፍታሌም ነው፡፡ ጦቢትና ልጁ ጦቢያ በአሦር
ንጉሥ በስልምናሶር ዘመን በ 722 ቅ.ል.ክ ሁለተኛው የዐሥሩ ነገድ ምርኮ በተደረገ ጊዜ የነበሩ ናቸው፡፡ (2 ኛ ነገ 17፡1-6)

የመጽሐፉ ጸሐፍያን ጦቢትና ልጁ ጦቢያ እንደሆኑ ተለያዩ ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ለዚሀም እንደመነሻ ያደረጉት በመጽሐፉ ላይ ያሉትን ኃይለ
ቃላት ነው፡፡ ለምሳሌ “ሩፋኤልም የዚያን ጊዜ ሁለቱን ሁሉ ጦቢያና ጦቢትን ጠርቶ ቆይታ አድርጎ ፡ እግዚአብሔርን አመስግኑ አላቸው፡፡ . . .
እግዚአብሔርን አመሰገኑት ስሙንም አመሰገኑ የእግዚአብሔርን ክብር ሥራ በክብር ተናገሩ፡፡” ጦቢ 12፡6 የሚለውን በግሪኩ ትርጉም “የሆነውን ሁሉ
በመጽሐፍ ጻፍ፡፡” ይላል፡፡ በተጨማሪም “አሁንም በእግዚአብሕር እመኑ፤ ይህን ሁሉ በመጽሐፍ እጽፍ ዘንድ መጣሁ አለ፡፡” ጦቢ 12፡20 የሚሉት
ኃይለ ቃላት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

መጽሐፉ በነነዌ በሰባተኛው መቶ ዘመን ቅ.ል.ክ በአረማይክ ቋንቋ የተጻፈ ሲሆን በምርኮኞች ተጠብቆ የቆየ ነው፡፡ በወቅቱ በኢየሩሳሌም
ባለመኖሩም ዕዝራ መጻሕፍትን ሲበስብ ይህን መጽሐፍ አላገኘውም፡፡ ሰብአ ሊቃናት ግን ወደ ግሪክ ቋንቋ ተርጕመውታል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም
ከ 46 መጻሕፍተ ብሉይ መካከል ትቆጥረዋለች፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ያሬድ በድጓው “ይኄይስ ምጽዋት እምዘጊቦቱ ለወርቅ . . . ይበሉ
በኵሉ ፍናዊሃ ሃሌ ሉያ ይትባረክ እግዚአብሔር” እያለ ከርሱ ጠቅሶ ይዘምራል፡፡

የመጽሐፉ አጠቃለይ ይዘት ጦቢት ስለተባለው ቅዱስ በንጉሥ ስልምናሶር ዘመን ወደ አሦር ከተማረከ በኋላ እርሱና ልጁ ጦቢያ ተቸግረው ሳለ
እግዚአብሔር በመልአኩ ሩፋኤል አማካኝነት ጠፍቶ የነበረውን ዓይኑን እንዴት እንዳበራለት እንዴት እንደረዳቸው እና ጦቢት በስፋት የነበሩ አይሁዳውያን
ይመክራቸው፣ የሞቱትንም ተደብቆ ይቀብራቸው እንደነበር በስፋት ይተነትናል፡፡

የመጽሐፉ አከፋፈል፡- መጽሐፈ ጦቢት 14 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 3 ዓበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡

ጦቢት 1-3፡ በዚህ ክፍል ጦቢት በበጎ ሥራው ስላገኘው መከራና ወደ እግዚአብሔር ያደረገው ምስጋናና ልመና ይገኝበታል፡፡
ጦቢት 4-12፡ ጦቢት በመከራው ጊዜ ልጁን ጦቢያን ወደ ወገኖች ሲልክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በሰው ተመስሎ እንዴት እንዳዳነውና
እንደረዳቸው በዝርዝር ይገልጻል፡፡
ጦቢት 13-14፡ በዚህ ክፍል ጦቢት እግዚአብሔርን ስላደረገለት ነገር ሁሉ ያመሰገነበት ጸሎትና በእርጅናው ጊዜ ልጁንና የልጁን ልጆች ጠርቶ
የሰጣቸውን አባታዊ ምክርና ኑዛዜ ይገኛል፡፡

14. መጽሐፈ ዮዲት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 56


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ዮዲት ማለት ኃያል፣ አሸናፊት ማለት ነው፡፡ መጽሐፉን የጻፉት በስደት የነበሩ አይሁድ ነበሩ፡፡ የተጻፈበት ዘመን
በ 600 ቅ.ል.ክ ሲሆን ቦታውም በኢየሩሳሌም ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
ንጉሥ ናቡከደነፆር እስራኤላውያንን ለመውጋት የተላከው የጦር መሪ ሆሎፎርኒስ የተባለውን እስራኤላዊቷ ዮዲት ገድለው
ወገኖቿን ነፃ ማውጣቷን ይገልጻል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል፡
መጽሐፈ ዮዲት 16 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 3 ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡
ዮዲ 1-4፡ ናቡከደነፆር ጠላቱን ሁሉ የማጥፋት ሥልጣንን ለጦር መሪው ለሆሊፎርኒስ እንደሰጠውና ይህ መሪ
የሠራቸውን ሥራዎች
ዮዲ 5-10፡ የኢየሩሳሌም በናቡከደነፆር ትእዛዝ መከበቧን
ዮዲ 11-16፡ ዮዲት የጦር መሪ የሆነውን ሆሊፎርኒስን እንዴት እንደገደለችውና ይህንን ያደረገላት አምላኳን
እግዚአብሔርን እንዳመሰገነችው እና ዕረፍቷን ይገልጻል፡፡
15. መጽሐፈ አስቴር
ይህ መጽሐፍ ስያሜውን ያገኘው ከመጽሐፉ ባለ ታሪክ አስቴር ነው፡፡ አስቴር ማለት ቃሉ የፋርስ (በአርማይክ) ሲሆን ትርጓሜውም ኮከብ ማለት ነው፤
የዕብራይስጥ ወይም የቀድሞ ስሟ ሀዳሳ ሲሆን ትርጕሙም አዲስ ማለት ነው፡፡

እንደ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን (ጆሴፈስ) እና እንደተለያዩ የአይሁድ ሊቃውንት አስተሳሰብ የመጽሐፉ ጸሐፊ የአስቴር አጎት ልጅ መርዶክዮስ ነው፡፡ ይህም
አመለካከት በአብዛኛዎቹ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት የሚደገፍ ነው፡፡ /አስ 9፡ 20-30/ (Flavius Josephus, The Antiquities of the
Jews, Book 11 Chapter 6:11)
መጽሐፉ የተጻፈበትን ዘመን ለማወቅ ታሪኩ የተፈጸመበትን ዘመን መረዳት ያስፈልገዋል፡፡ በ 536 ቅ.ል.ክ በቂሮስ (539-530 ቅ.ል.ክ)
የእስራኤላውያን የመጀመሪያው ሚጠት(ከምርኮ መመለስ) ሆነ፡፡ በዚህም ቂሮስ ወደ ሀገሩ ለመመለስ የፈለገ ሁሉ እንደሚችል ዓዋጅ አስነገረ (ዕዝ 1፡1) ፡፡
ከቤተ አይሁድ አንዳንዶች ግን በዚሁ ንብረት አፍርተናል፣ አግብተን ወልደናል፣ እርሻን አርሰን ዘር ዘርተናል በማለት ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
ሌሎቹ ግን በዘሩባቤል መሪነት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ አስቴር የምትገኘው እምቢ ብለው ከቀሩት አይሁድ ጋር ነው፡፡ አስቴርን ያገባት ንጉሥ
አሕሳዌሮስ (486-464 ቅ.ል.ክ) (በግእዙ አርጤክስስም) ሲባል ንጉሥ ቂሮስ ከነገሠ በኋላ ሦስተኛው የነገሠ ንጉሥ ነው፡፡ ይህም ማለት ቂሮስ ከሞተ
ከ 90 ዓመት በኋላ ነው፡፡ የመጽሐፉም መጻፍ በዚህ ዘመን እንደ ሆነ ይታመናል፡፡

ይህ መጽሐፍ ከሌሎቹ መጻሕፍት የሚለየው በአንድም ቦታ ላይ የእግዚአብሔርን ስም አለመጥቀሱ ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በወቅቱ የእግዚአብሔርን
ስም መጥራት ወይም ስለ ሃይማኖት አንስቶ መነጋገር ችግር የሚያስከትል ስለ ነበር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መርዶክዮስ የመጽሐፉን ቅጅ ፋርሳውያን
እንደሚፈልጉትና በስመ እግዚአብሔር ፈንታ የጣኦታን ስም እንዲገባላቸው እንደሚጠይቁ ስለ ተረዳ ስመ አምላክን ሳያስገባ ጽፎታል፡፡ ነገር ግን
እግዚአብሔር ለአይሁድ ሕዝብ ያደረገው ጥበቃና ተራዳኢነት በሰፊው ይዘግባል፡፡ የግእዙ ትርጉም ግን ስመ እግዚአብሔርን እያስገባ ይጽፋል፡፡

የመጽሐፉ አጠቃላይ ይዘት በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት በምርኮኝነት ይኖሩ በነበሩ እስራኤላውያን ላይ በሐማ ምክር የደረሰውን ስደት የሞት አደጋ
አስቴር የተባለችው እስራኤላዊት በእግዚአብሔር ሞገስ አክሽፋ ወገኖቿን ማዳኗን ይገልጻል፡፡

የመጽሐፉ አከፋፈል፡- መጽሐፈ አስቴር 10 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 3 ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡

ከምዕ 1-2፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የፋርሱ ንጉሥ አርጤክስስ ሚስቱን አስጢንን ፈትቶ አይሁዳዊቱን አስቴርን ያገባ መሆኑን
ከምዕ 3-5፡ በዚህ ክፍል ሐማ የተባለው ሰው ወደ ከፍተኛ ሹመት ማደጉና ሐማ ሲወጣና ሲገባ መርዶክዮስ የማይሰግድለት መሆኑን በተረዳ ጊዜ
ከቁጣው የተነሳ የአይሁድን ዘር በሙሉ በአንድ ቀን ለማጥፋት ከንጉሡ ፈቃድ መቀበሉ ተገልጽዋል፡፡
ከምዕ 6-10፡ በዚህ ክፍል መርዶክዮስ የአስቴርን እርዳታና ድጋፍ መጠየቁ፣ አይሁድ በጾም፣ በጸሎት በእግዚአብሔር ፊት መቆማቸው፣ አስቴር
ንጉሡንና ሐማን ግብዣ መጥራቷ፣ የመርዶክሰዮስ መሾምና የሐማ መሰቀል እንዲሁም አይሁድ ጠላቶቻቸውን መበቀላቸውንና የፋሪም በአል
አከባበር ይገኙበታል፡፡

16. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ


የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 57
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

መጽሐፈ መቃብያን
መቃቢስ /መቃባ/ ማለት ጸረ ጠላት፣ ቀስት፣ ጀግኖች ማለት ነው፡፡ ጀግኖች የሚለው ትርጉም ቃሉ ሲበዛ (መቃብያን)
ሲሆን ነው፡፡ የመቃብያን ታሪክና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን የያዙ ስምንት መጻሕፍተ መቃብያን መኖራቸው
ታውቋል፡፡ በግእዝና በአማርኛ ተተርጉመው የሚገኙ ሦስቱ የመቃብያን መጻሕፍት ናቸው፡፡ የመቃብያንን መጻሕፍት ማን
እንደጻፋቸው በውል አይታወቅም፡፡
በፍትሐ ነገሥት የተገለጹት መጻሕፍት፡
1. መቃብያን ዘመቃቢስ አልዓዛር
2. መቃብያን ዘመቃቢስ ሞአብ
3. መቃብያን ዘመቃቢስ ዘብንያም
4. መጽሐፈ መቃብያን ራብዕ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን ዜና አይሁድ ዜና ሥርው
ያልተተረጎሙት መጻሕፍተ መቃብያን
አንደኛው መጽሐፈ መቃብያን 16 ምዕራፎች ሲኖሩት ወንድሞቹ የአይሁድን ሃይማኖታዊ ሕግና ሥርዓት ለመጠበቅ ሲባል
ከሌሎች መንግሥታት ጋር ያደረጉትን ተጋድሎ የሚተርክ ነው፡፡ ሁለተኛው መጽሐፈ መቃብያን ደግሞ 15 ምዕራፎች ያሉት
ሲሆን የመጀመሪያው መጽሐፍ ተከታይ ሲሆን በተለይ በግብጽ የሚኖሩ አይሁድ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ላይ ይደርሳል
ብለው ስለሚፈሩት ስደት ዘርዝሮ የሚያስረዳ ነው፡፡ እነዚህ አንደኛና ሁለተኛ መጽሐፈ መቃብያን ተብለው የተጠቀሱት
መጻሕፍት በትልቁ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ መጽሐፈ መቃብያን የተለዩ ናቸው፤
የታሪኩም ይዘት የተለየ ነው፡፡ በሰማንያ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት መጻሕፍተ መቃብያን ደግሞ እንደሚከተለው
ናቸው፡፡
በግእዝና በአማርኛ ተተርጉመው ከሚገኙት ሦስቱ የመቃብያን መጻሕፍት አንዱና ራሱን ችሎ የሚቆጠር መጽሐፍ ነው፡፡
የመጽሐፉ ጸሐፊ አንድ ፍልስጤማዊ /አይሁድ/ ነው፡፡ የተጻፈበት ቋንቋ ዕብራይስጥ ሲሆን ዘመኑ በ 103 ቅ.ል.ክ
በኢየሩሳሌም ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ፡-
የመቃቢስ ዘብንያም ልጆች አብያ፣ ሲላስና ፈንቶስ ለጣዖት አንሰግድም በማለታቸው አመጸኛው ንጉሥ ጺሩዳይዳን
እንዳሰቃያቸውና የተቀበሉትን ሰማዕትነት
ከብሉይ ኪዳን ታሪኮችና ምሳሌዎች እየጠቀሱ ስለ ትንሳኤ ሙታን መናገራቸውን የሰው ልጅ የነፍስና ሥጋ በረከትና
ሕይወት ስለሚያገኝበት መንገድ የመከሩትን ይገልጻል፡፡
ከቀድሞ ጀምሮ የነበሩትን የቅዱሳት አበው ታሪክን በማንሳት በዘመናቸው በአመጽ ምክንያት የጠፉትን የእስራኤል
ሕዝቦች ማለትም በኖኅ ዘመን፣ በሎጥ ዘመንና በግብጽ ተሰደው መከራን የተቀበሉትን ሕዝቦች ታሪክም ይተርካል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል፡-
1 ኛ መቃብያን 36 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 3 ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡
1 ኛ መቃ 1-5፡ ስለ ጺሩዳይዳንና የመቃቢስ ልጆች ሰማዕትነት
1 ኛ መቃ 6-11፡ ስለ ዳግም ምጽአት
1 ኛ መቃ 12-36፡ በብሉይ ኪዳን ስለነበሩ አበውና ስለ እስራኤላውያን ይናገራል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 58


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1. መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ


በግእዝና በአማርኛ ተተረጉመው ከሚገኙት ሦስቱ የመቃብያን መጽሐፍ አንዱ ሲሆን ከመጽሐፈ መቃብያን ሣልስ
ጋር እንደ አንድ ይቈጠራሉ፡፡ የመጽሐፉ ጸሐፊ አንድ እስክንድሪያዊ (አይሁዳዊ) ነው፡፡ የተጻፈበት ቋንቋ በግሪክ (በጽርዕ)
ሲሆን ዘመኑ በ 1 ኛው መ.ክ.ዘ ድ.ል.ክ በኢየሩሳሌም ነው፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል፡-
እስራኤላውያን በድለው ሞአባዊው መቃቢስን እንዳሥነሳባቸው እና እስራኤልን በሰይፍ ገድሎ ሲታበይ እግዚአብሔር
በመቃቢስ ሥራ ተቆጥቶ ነቢይ ልኮ በንስሐ እንዲመለስ ሲነግረው በእግዚአብሔር ፊት ራሱን አዋርዶ ምሕረት እንዳገኘ
ይገልጻል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፋል፡-
2 ኛ መቃብያን 21 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 3 ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡-
2 ኛ መቃ 1-4፡ ይህ ክፍል መቃቢስ የተባለውን የሞአብ ንጉሥ የሞአብ ንጉሥ እስራኤላውያንን ከተዋጋ በኋላ
በኢየሩሳሌም ላይ ያደረሰውን ጥፋት በንስሐ ተመልሶ የሠራውን በጎ ሥራና ዕረፍቱን ይገልጻል፡፡
2 ኛ መቃ 5-12፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የመቃቢስ ዘሞአብ ልጆች በእግዚአብሔር ስላመኑ ጺሩዳይዳን የተባለው
የከለዳውያን ንጉሥ ስላደረሰባቸው መከራ ተጽፎ ይገኛል፡፡
2 ኛ መቃ 13-21፡ በዚህ ክፍል የመቃቢስ ዘሞአብን ልጆች አብነት አድርጎ ትንሳኤ ሙታንን ለሚያምኑ የተሰጠ መልስ
ይገኝበታል፡፡
2. መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ
በግእዝና በአማርኛ ተተርጉመው ከሚገኙ ሦስቱ የመቃብያን መጽሐፍ አንዱ ሲሆን ከመጽሐፈ መቃብያን ካልዕ ጋር
እንደ አንድ ይቆጠራል፡፡ የመጽሐፉ ጸሐፊና የተጻፈበት ቋንቋ አይታወቅም፡፡ የተጻፈበት ዘመን በ 1 ኛ መ/ክ/ዘ ድ.ል.ክ ነው፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል፡-
መጽሐፉ የብሉይ ኪዳንን ታሪኮች እየጠቀሰ የጽድቅ፣የኩነኔ፣ የትንሳኤ ሙታንንና ዲያቢሎስ የሰው ልጆችን
የሚያሰናክልባቸው መረቦችን በዝርዝር የቀረበበት ነው፡፡ ስለ ንስሐ እና ስለ መንግሥተ ሰማያት 3 ኛ መቃ 6፡ 7-9
ይገልጻል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል፡
3 ኛ መቃብያን 10 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 3 ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡
3 ኛ መቃ 1-3፡ ስለ ሰይጣን ሥራና ስለ አዳምና ሔዋን ውድቀት
3 ኛ መቃ 4-6፡ ስለ ሰይጣን ውድቀት፣ ስለ ጌታችን ማዳንና ስለ ጻድቅና ኃጥዕ
3 ኛ መቃ 7-10፡ በእግዚአብሔር ስለማመንና ስለ ኢዮብ ይናገራል፡፡

3. መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን


የኮርዮን ልጅ ዮሴፍ የጻፈው ይህ መጽሐፍ ዜና አይሁድ ወይም መጽሐፈ ሥርው በመባል ይታወቃል፤ በተጨማሪም በፍትሐ ነገሥት መጽሐፋችን
እንደተለጸው አራተኛ የመቃብያን መጽሐፍ በመባል ይታወቃል፡፡ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መጻሕፍት መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ
ኮርዮን ራሱን ችሎ እንደ አንድ መጽሐፍ ይቆጠራል፡፡

የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ የኮርዮን ልጅ ዮሴፍ ሲሆን በ 1 ኛው መ.ክ.ዘ ድ.ል.ክ በኢየሩሳሌም አካባቢ በግሪክ /በጽርዕ/ ቋንቋ ጽፎታል፡፡ ዮሴፍ ማለት
ይጨመር፣ ይደገም ማለት ነው፡፡ ከካህናት ቤተሰብ በ 37 ዓ.ም የተወለደ ታዋቂ የአይሁድ የታሪክ ጸሐፊ ነው፡፡ በልጅነቱ የቤተ እስራኤልን ትምርት ቦኖስ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 59


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ከተባለው ሊቅ ሥር መናኝ ደቀ መዝሙር ሆኖ ለ 3 ዓመታት በበረሃ ኖሯል፡፡ በ 64 ዓ.ም ወደ ሮም በመጓዝ አንዳንድ አይሁድን ለማስፈታት ሞክሮ ነበር፤
በዚያም የኔሮል ቄሳር ሚስት ለእርሱ ቀና አመለካከት ነበራት በዚያም ምንም ችግር ሳይደርስበት ወደ ሀገሩ ተመልሷል፡፡

በ 66 ዓ.ም አይሁድን ከወራሪዎች ነጻ ለማድረግ ጦሩን ከመሩት ሰዎች መካከል አንዱ ነበር፡፡ በ 67 ዓ.ም በቬስፓስያን ወታደሮች ተማረከ፡፡ ዮሴፍ
ኤስፓስያን ንጉሥ እንደሚሆን ትንቢት ተናግሮ ነበርና ይህም ትንቢት በ 69 ዓ.ም ሲፈፀም ንጉሡ ዮሴፍን በነፃ አሰናብቶታል፡፡

በ 70 ዓ.ም ኢየሩሳሌም በጥጦስ ስትከበብ ለሮማውያን አስተርጓሚ ሆኖ አገልግሏል፤ በዚህም የተነሳ በአይሁድ ዘንድ ለመጠላት ምክንያት ሆነው፡፡
ከዚያም በኋላ በሮም በነገሡ ነገሥታት ዘንድ የከበረ ሰው ሆነ የሮምን ዜግነትም አግኝቷል፡፡ በመንግሥት የተፈቀደለት የጡረታ ገንዘብም ሙሉ ጊዜውንም
ወደ ጽሐፍ እንዲያደርግ ረድቶታል፡፡

ይህ መጽሐፍ ከጌታችን ልደት በኋላ የተጻፈ ብቸኛ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ነው፡፡ በይዘቱም ከአዳም ጀምሮ እስከ 70 ዓ.ም በጥጦስ መሪነት
የተፈፀመው የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ መቃጠል ድረስ ያለው የአይሁድን ታሪክ የሚገልጽ መጽሐፍ ነው፡፡ በዚህም ዜና አይሁድ ተብሏል፡፡ ከጌታ ልደት
በኋላ ተጽፎ ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ጋር ያልተካተተበት ምክንያት መጽሐፉ በአብዛኛው በብሉይ የነበሩ ታሪኮችን የሚያነሣ ስለሆነ ነው፡፡ በዓለሙም
እንደታሪክ ማጣቀሻ ከሚጠቀሱ መጻሕፍት መካከል አንዱ ነው፡፡

የመጽሐፉ ዓላማ፡-
ከአዳም ጀምሮ እስከ 70 ዓ.ም በጥጦስ መሪነት የተፈፀመው የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ መቃጠል ድረስ ያለው የአይሁድን
ታሪክ የሚገልጽ መጽሐፍ (ዜና አይሁድ) ነው፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል፡-
መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን 8 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 8 ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡
ስለ አዳም
ስለ ንጉሥ አንጥያኮስ መቄዶናዊ፣ ስለ ዮናናውያንን ንጉሥ
የእስክንድርያ ንግሥት፣ የህርቃሎስና የአስትሮቦሎስ ልጅ
የህርቃሎስ ከፋርስ መግባቱና መንገሡ
ስለ አስቴር ንግሥና እና ስለ አርኬላዎስ ታሪክ
የሄሮድስ ልጅ አርኬላኦስ ታሪክ
ስለ ስምዖን ያርብሃዊ
ስለ ቤተ መቅደስና ሮማውያን ከአይሁድ ጋር መጣላታቸውን

4. የመዝሙር የቅኔ፣የጥበብና የግጥም መጻሕፍት


1. መጽሐፈ ኢዮብ
ኢዮብ ማለት አበባ ማለት ሲሆን እጅግ ባለጸጋና እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነው፡፡ ኢዮብ ይኖር
የነበረው ፆዕ በምትባል ሀገር ውስጥ ነው፡፡ ኢዮብ አብርሃምን የሚመስለው በእንግዳ ተቀባይነቱ ነው፤ ፃዲቁ
ኢዮብ ጥመት የሌለበት ቅን፣ ኃጢአት የሌለበት ንጹህ ነው፣ ሐሰት የሌለበት እውነተኛና እግዚአብሔርን
የሚፈራ፣ ልቡናው ከክፋት የራቀና በሕይወቱ ብዙ መከራና ስቃይ ደርሶበት የነበረ ሰው ነው፡፡
ኢዮብ የአብራኩ ክፋይ የሆኑ ልጆቹ በሞት ቢለዩት፣ ያፈራውን ሀብትና ብረት ቢያጣ፣ ሰውነቱ
በመቁሰል የውስጥ አካሉ ወደ ውጭ የውጭ አካሉ ወደ ውስጥ ሆኖ ብዙ መከራ ቢደርስበትም
‹‹እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ›› ብሎ ሰይጣንን ያሣፈረ ፃዲቅ ሰው ነው፤ የሚመጣበትን መከራ
ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ‹‹እነሆ ቢገድለኝ እንኳ እርሱን በትዕግስት እጠብቃለው›› በማለት አረጋግጧል፡፡
እንደ ኢዮብ ትዕግስተኛ ሰው እንደሌለም እግዚአብሔር አምላክ መሰክሮለታል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 60


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመጽሐፈ ኢዮብ የአጻጻፍ ይዘት ጠቢቡ ሰሎሞን ከጻፋቸው መጻሕፍት ጋር ይመሳሰላል፤ የጥበብ
መጻሕፍት ከሚባሉት ከመጽሐፈ ምሳሌና ከመጽሐፈ መክብብ ጋር አጻጻፉ አንድ አይነት ነው፡፡ ከምዕራፍ
አንድ እስከ ሦስት የተጻፈው በስድ ንባብ ሲሆን ከምዕራፍ አራት እስከ አርባ አንድ ያለው በግጥምና በጥበብ
መልክ ነው የተጻፈው፡፡
መጽሐፈ ኢዮብ 41 ምዕራፎች አሉት፣ መጽሐፉ መቼና በማን እንደተጻፈ በእርግጠኝነት
አይታወቅም፤ በብዙ ሊቃውንት ዘንድ ኢዮብ እስራኤላውያን በግብጽ በነበሩበት ዘመን የኖረ ሰው እንደነበረና
ከአብርሃም ጀምሮ ሲቆጠር አምስተኛ ትውልድ አንደሆነ ይነገራል፤
የመጽሐፉ ዓላማ
ይህ መጽሐፍ አጠቃላይ ይዘቱ እግዚአብሔርን በሚወዱና ለሕጉ በሚታዘዙ ሰዎች ላይ መከራ ሊደርስ
እንደሚችልና በትዕግስት ካሳለፉት ግን መከራው እንደሚወገድና በረከትንም ከእግዚአብሔር በእጥፍ
እንሚያገኙ የሚያስተምር ነው፡፡ቅዱሳን አላውያን የሚያደርሱባቸውን ጽኑ መከራ ችለው መቀበላቸው
ብዙዎችን ወደ እምነት መልሷቸዋል፤ እግዚአብሔር ልጆቹን ያስተምራል፣ እግዚአብሔር ትዕግስተኛ
እንደመሆኑ ልጆቹም ትዕግስተኛ እንዲሆኑ ያስተምራል፡፡ የእግዚአብሔር ትዕግስት ወደ ጭንቀት ሳይሆን
በጸሎት ወደ መትጋት ይመራል፤ እምነትና ትዕግስት በምድርም ምንጊዜም በድል ይጠናቀቃሉ፡፡ ጻዲቁ
ኢዮብም መከራና ችግር በደረሰበት ጊዜ እግዚአብሔር ሰጠ፣ እግዚአብሔር ነሳ በማለት በእምነትና
በትዕግስተኛነቱ ዲያቢሎስን አሳፍሯል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
ኢዮ 1-2፡ የኢዮብ መፈትን
ኢዮ 3፡ ኢዮብ በሕይወቱ በደረሰበት መከራ አምላኩ እግዚአብሔርን የጠየቀው ጥያቄ
ኢዮ 4-31፡ ሦስቱ የኢዮብ ጓደኞች ኢዮብ የደረሰበትን መከራ በመታገሱ መጥተው እንደተከራከሩት
ኢዮ 32-42፡ የእግዚአብሔር መልስና የኢዮብ መጽናናት

2. መዝሙረ ዳዊት
መዝሙረ ዳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ለአገልግሎት ዘወትር ከምትጠቀምባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት መካከል
አንዱ ነው፡፡ ጸሐፊውም ከእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ታላቅና ተወዳጅ የሆነው ንጉሥ ዳዊት ነው፡፡ ጸሐፊም የተባለው
ብዙውን ክፍል እርሱ ስለ ጻፈ ነው፡፡
መዝሙር የሚለው ቃል ዘመረ፣ አመሰገነ ከሚለው ቃል የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም ምሥጋና፣ ማመስገን ማለት ነው፡፡
መዝሙረ ዳዊት በውስጡ 150 መዝሙራት፣ ጸሎት፣ ትምህርት እና ቅኔ በአንድነት ይገኙበታል፡፡ መዝሙረ ዳዊት የዳዊት
መዝሙር የሚባሉት አብዛኛውን 73 መዝሙሮችን እርሱ ስለደረሳቸው ነው፤ በሌሎች ሰዎች የተደረሱ መዝሙራት እንዳሉ
ከመዝሙረ ዳዊት ራሱ መገንዘብ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ፡
 መዝ 90 የሙሴ መዝሙር መሆኑ ተገልጧል፡፡
 መዝ 146፣ 147 እና 148 የሐጌና የዘካርያስ መዝሙሮች ናቸው፡፡
 በቆሬ ልጆች ስም የሚጠሩ 11 መዝሙሮች አሉ (መዝ 2፣ 4፣ 84፣ 86፣ 87….ወዘተ)
 የአሳፍ መዝሙሮች የሚባሉት 12 መዝሙሮች አሉ (መዝ 50፣ 73፣ 79፣ 80፣ 81…. ወዘተ)

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 61


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

 ኤታን በሚባል እስራኤላዊም የተደረሱ መዝሙሮች አሉ፡፡ (ለምሳሌ፡ መዝ 68)/ 1 ኛ ዜና 15፡16-24፣ 1 ኛ ዜና 25-
ፍፃሜ/
መጽሐፈ መዝሙርን (መዝሙረ ዳዊትን) አሁን ባለበት ሁናቴ ያዘጋጀው ካህኑ ዕዝራ ነው፤ መዝሙሮቹም በተለያዩ
ዘመናት እንጂ በአንድ ዘመን ብቻ የተዘጋጁ አይደሉም፡፡ ለምሳሌ፡ መዝ 74፣ 96፣ 137 የተዘጋጁት ከእስራኤላውያን ምርኮ
በኋላ ነው፡፡
መዝሙረ ዳዊት የሰውን የሕይወት ዘመን ሳይለይ ሰው በሕይወቱ የሚያጋጥሙትን ኃዘንና ደስታ፣ መልካሙንና
ክፉውን፣ በመውደቅና በመነሣት፣ ችግርና ምቾት፣ ከእግዚአብሔር መራቅና ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የያዘ መጽሐፍ
ነው፡፡
መዝሙረ ዳዊት ለአራት ነገሮች ይጠቅመናል
 ለሕያዋን ዕቅበት (ጥበቃ)
 ለሙታን ጸሎት ማድረጊያ
 ለሕፃናት ትምህርት
 ለቤተክርስቲያን ስብከት፡ ለቤተክርስቲያናችን የጸሎትና የመዝሙር መጻሕፍት (ምሳሌ፡ መጽሐፈ ደጓ)
መሠረታቸው መዝሙረ ዳዊት ነው፡፡ መዝሙረ ዳዊት መዘምራን በዜማ ስልት የሚገለገሉበት፣ መነኮሳትና ካህናት
በመዓልትና በሌሊት በቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑትን ምእመናን በያሉበት ሆነው እየጸለዩ
መላእክተ ብርሃንን የሚያቀርቡበት ፣ መላእክተ ጽልመትን የሚያርቁበት፣ ሕሙማንን የሚፈውሱበት እጅግ ጠቃሚ
የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡
መዝሙረ ዳዊት በ 5 ክፍሎች የተከፈለ መጽሐፍ ነው፡፡ እነዚህም፡- 1. ከመዝ 1-መዝ 40፤ 2. ከመዝ 41-መዝ 71፤ 3.
ከመዝ 72-መዝ 88፤ 4. ከመዝ 89-መዝ 105፤ 5.ከመዝ 106-መዝ 150 ናቸው፡፡
የእያንዳንዱ ክፍል ፍጻሜ የሚታወቀው ‹‹ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም እግዚአብሔር ይባረክ አሜን አሜን›› የሚሉ
ቃላት ስለተጻፈባቸው ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን ደግሞ ዐሥሩን በአንድነት አንድ በማለት ‹‹አንድ ንጉሥ›› በማለት በዐሥራ
አምስት ይከፈላል፡፡
መዝሙረ ዳዊት ሰዎች በዚህች ዓለም በሚኖሩበት ጊዜ ስለሚያጋጥማቸው ሁኔታዎች በሙሉ ምን መጸለይ
እንደሚገባቸው የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው፡፡ መዝሙራቱ የሃይማኖታዊውን ሥርዓት አብዛኛውን ክፍል ይሸፍናሉ፡፡
የመዝሙራቱን ዓላማ በዝርዝር ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው፤ ሆኖም በዓይነት በዓይነት ለማየት እንሞክራለን፡፡ መዝሙራት
የተለያየ አርዕስት ኖሮአቸው በሁለት ባለቤት ክፍል ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም፡- የማኅበርና የግል ናቸው፡፡
የማኅበር የሚባለው ሕዝቡ በኅብረት እንደሚዘመሩና እንደሚጸለዩ ሲያመለክቱ፤ የግል የሚለው ደግሞ ሕዝቡ እንደ አንደ ሰው
ሆነው መዘመራቸውን ያመለክታል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በቀረበው ሰንጠረዥ አማካኝነት የመጽሐፉን አብዛኛውን ይዘት መረዳት ይቻላል፡፡

የሚጸለይበት /የሚዘመርበት/ ሁኔታ የሚጸለየው /የሚዘመረው/ የመዝሙረ ዳዊት ክፍል


ለእግዚአብሔር ምስጋና ለማቅረብ መዝ 8፣ 29፣ 33፣ 36፣ 89፣ 94፣ 103፣ 104 ፣ 105፣
106፣111፣ 118፣ 138፣ 145
የእግዚአብሔርን የባሕርይ ልዕልና ለመግለጥና መዝ 8፣ 19፣ 29፣ 33፣ 47፣ 65፣ 66፣ 68፣ 76፣ 81፣
ለማወደስ 89፣ 92፣ 95፣ 96፣ 98፣ 135፣ 136፣ 147፣ 148፣ 150

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 62


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

አንድ ኃጢአተኛ ከኃጢአቱ በንስሐ ተመልሶ መዝ 6፣ 31፣ 37፣ 50፣ 85፣ 101፣ 102፣ 142
የእግዚአብሔርን ይቅርታ የሚጠይቅበት

ጭንቀት፣ ፈተና ፣ ውርደት፣ ኃዘን፣ ስደትና ጭቆና መዝ 2፣ 6፣ 13፣ 21፣ 35፣ 41፣ 43፣ 44፣ 52፣ 56፣
በሚያጋጥም ጊዜ 59፣ 64፣ 68፣ 74፣ 77፣ 79፣ 80፣ 83፣ 88፣ 90፣
94፣ 102፣ 109፣ 140፣ 143

ፍርሃት፣ ፈተና ሲያጋጥም በእግዚአብሔር መዝ 11፣ 16፣ 18፣ 20፣ 25፣ 25፣ 27፣ 28፣ 30፣ 32፣
ለመተማመን 37፣ 46፣ 54፣ 57፣ 62፣ 70፣71፣ 91፣ 115፣ 124፣
125፣ 144፣ 146
የእግዚአብሔር ሕጉና ቤቱ በሚናፈቅበት ጊዜ መዝ 16፣17፣18፣40፣41፣44፣63፣72፣
83፣119፣121፣131
ካህናት የቤተመቅደሱን ደረጃዎች ሲወጡና መዝ 102 እና 103
ሲወርዱ የሚዘምሯቸው የማዕረግ መዝሙሮች
ሃሌሉያ ብለው የሚጀምሩ የስብሐት (የምሥጋና) መዝ 148-150
መዝሙሮች

እነዚህን መዝሙራት ሰው በማኅበርም ሆነ በግል የሚጸልይበት /የሚዘምርበት/ የትኛውን የመዝሙረ ዳዊት ክፍል
እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡
ሌሎች ትምህርቶችንና ድርጊቶችን የያዙ የመጽሐፍ ክፍሎች

መሠረተ እምነትንና የእግዚአብሔርን ብቸኛ አምላክነት መዝ 50፣ 86፡8፣ 89፡6፣ 135፡5፣ 139፡7፣33፡
የሚያመለክቱ 13

የሥላሴን በመለኮት አንድነት በአካል ሦስትነት መዝ 2፡7፣ 33፡6፣ 45፡6፣ 110


የሚያመለክቱ

ስለ ትንሣኤ ሙታንና ከዚያ በኋላ ስለሚሆነው ፍርድ መዝ 1፡5፣ 16፡8፣ 116፡15


ስለ ክርስቶስ እና ስለ ክርስቶስ ዘመን የተነገሩ ትንቢቶች መዝ 1፡9፣ 22፣ 68፡1፣ 69፡21፣ 72፣ 107፣ 109፣
110፣ 117፣ 118፡22፣132፡11
ስለ ዳዊት እና ስለ ሕዝቡ ታሪካዊ ድርጊቶች መዝ 78፣105፣106፣135፣136
በቤተክርስቲያን አባቶች ስያሜ መሠረት መዝሙራት ስለ ምሥጢረ ሥላሴ፣ ስለ ነገረ ማርያም ሰፊ ትምህረት አላቸው፤

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 63


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

አባቶች እያንዳንዱ መዝሙር ስለ እመቤታችን እና ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጢርን የያዘ ነው ይላሉ፤ በመቶ
አምሳው መዝሙራት ሁሉ መዝሙረ ድንግልና መዝሙረ ክርስቶስ መዘጋጀቱ ይህን የሚያመለክት ነው፡፡
ከጥንት ኢትዮጲያውያን ሊቃውንት ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው የመዝሙረ ዳዊት የመዝሙረ ዳዊት ንባብና
ትርጓሜ መሠረት ደግሞ መዝሙረ ዳዊት በ 10 አርዕስት እንደሚከፈል ይገልፃል፡፡ እነርሱም፡
1. ተግሣጽ ለኩሉ (ለሁሉም የሚሆን ተግሣጽና ምክር)፡ ‹‹ምስጉን ነው በክፉዎች መንገድ ያልሄደ፣
በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ…›› እንዲል /መዝ 1፡1/
2. ትንቢት በእንተ ክርስቶስ (ስለ ክርስቶስ የተነገረ ትንቢት)፡ ‹‹አሕዛብ ለምን ያጉረመርማሉ? ወገኖችሽ
ለምን በከንቱ ይናገራሉ? በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ . . . እግዚአብሔር አለኝ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ
ወለድሁህ›› /መዝ 2፡1/
3. ትንቢት በእንተ ርእሱ (ስለ ዳዊት የተነገረ ትንቢት)፡ ‹‹አቤቱ የሚያስጨንቁኝ ምነኛ በዙ፤ በእኔ ላይ
የሚቆሙት ብዙ ናቸው፡፡›› /መዝ 3፡1/
4. ትንበት በእንተ ትሩፈን /ስለ ትሩፋት የተነገረ ትንቢት/፡ ‹‹አቤቱ ቃሌን አድምጥ፣ ጩኸቴንም
አስተውል፡፡›› /መዝ 5፡1/
5. ትንቢት በእንተ ሕዝቅያስ ወሰናክሬም /ስለ ሕዝቅያስና ሰናክሬም የተነገረ ትንቢት/፡ ‹‹ሰነፍ በልቡ
አምላክ የለም ይላል፤ በሥራቸው ረከሱ፣ ጎሰቆሉ፣ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፡፡›› /መዝ 13፡1/
6. ትንቢት በእንተ ኤርሚያስ /ስለ ኤርሚያስ የተነገረ ትንቢት/፡ ‹‹አቤቱ የሚበድሉኝን በድላቸው፣
የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው፡፡››
7. ትንቢት በእንተ መቃብያን /ስለ መቃብያን የተነገረ ትንቢት/፡ ‹‹አቤቱ በጆሮአችን ሰማን ፤ አባቶቻችንም
በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን፡፡›› /መዝ 43፡1/
8. ትንቢት ዘለፋ ካህናት /ስለ ካህናት ተግሣጽ/፡ ‹‹የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ከፀሐይም
መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራት፡፡›› /መዝ 49፡1/
9. ትንቢት በእንተ ሰሎሞን ወልዱ /ትንቢት ስለ ሰሎሞን ልጁ/፡ ‹‹አቤቱ ፍርድህን ለንጉሥ ስጥ ጽድቅህንም
ለንጉሥ ልጅ፣ ሕዝብህን በጽድቅ…..ለችግረኞች ሕዝብ በጽድቅ ትፈርዳለህ፡፡›› /መዝ 71፡1/

? ? የተነገሩ ትንቢቶች አሉ የተቀሩት 140 ው ምዕራፎች በእነዚህ ሥር ይካተታሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ መዝሙረ ዳዊት
በውስጡ ሰባት ዓበይት ትምህርቶችን ይዟል፡፡ እነርሱም፡
1. ጠላትን መውደድ፡ ‹‹ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶች ጠበቅሁ›› /መዝ 16፡4/
2. ትህትና፡ ‹‹እኔ ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም፡፡›› /መዝ 21፡6/
3. ሃይማኖት፡ ‹‹ከማህፀን ጀምሮ በአንተ ተጣልሁ ከእናቴ ሆድ ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ፡፡›› /መዝ 21፡6/
4. ተስፋ መንግሥተ ሰማያት፡ ‹‹የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ፡፡›› /መዝ 26፡13/
5. ኃጢአትን ማመን፡ ‹‹ኃጢአቴ በራሴ ላይ ከፍ ከፍ ብሎአልና እንደ ከባድ ሸክምም በላዬ ከብዷልና፡፡›› /መዝ 37፡4/
6. ይቅርታ ስለመለመን፡ /መዝ 50/

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 64


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

7. ስለ ምጽዋት፡ ‹‹በተነ ለችግረኞችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡›› /መዝ 111፡8/ ናቸው፡፡
መዝሙረ ዳዊት በ 6 ተከፋፍሎ ለጸሎት አገልግሎት ይውላል፡፡ ይኸውም፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 65


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

 ከ 1-30 (በእለተ ሰኞ የሚጸለይ)


 ከ 31-60 (በእለተ ማክሰኞ የመጸለይ)
 ከ 61-80 (በእለተ ረቡዕ የሚጸለይ)
 ከ 81-110 (በእለተ ሐሙስ የሚጸለይ)
 ከ 111-130 (በእለተ አርብ የሚጸለይ)
 ከ 131-150 (ከነቢያት ጸሎት ጋር በዕለተ ቀዳሚት
ሰንበት የሚጸለይ)

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 66


በአጠቃላይ በመዝሙረ ዳዊት ከዳዊት በፊትም ሆነ በኋላ የተደረጉት ድርጊቶች መገለፃቸው ያለፈውን አንስቶ ምክር፣
ተግሳጽና ምስጋና ለወደፊቱ ስለሚሆነውም በትንቢት መናገር ነው፡፡ መዝሙረ ዳዊት ከክርስቶስ ልደት 1000 ዓመታት
በፊት በኢየሩሳሌም፤ አብዛኛው ክፍል በንጉሥ ዳዊት የተጻፈ ለኃዘን፣ ለደስታ፣ ለምክር (ተግሳጽ) ለመጽናናት፣ ለምስጋና
ለሁሉም የሚሆን መጽሐፍ ነው፡፡

3. መጽሐፈ ምሳሌ
መጽሐፈ ምሳሌ በጠቢብ ሰሎሞን በ 950 ቅ.ል.ክ የተጻፈ እና 24 ምዕራፎች ያሉት መጽሐፍ ነው፤
መጽሐፉ የተጻፈው በግጥም መልክ ነው፤ ምክንያቱም በግጥም የተሰጠ ትምህርት በልብ ስለሚያዝ ነው፡፡
መጽሐፉ ትምህርትና ምክርን በምሳሌ የሚያስተምር ነው፡፡ መጽሐፉ የተጻፈበት ዘመን በሰሎሞን ዘመነ
መንግሥት በ 950 ዓ.ዓ አካባቢ ነው፡፡
ሰሎሞን እግዚአብሔርን በጸሎት ለምኖ የተቀበለው ነገር ጥበበኛና አስተዋይ ልቡናን ነበር፡፡ ስለዚህም
መጻሕፍቱ የጥበብ መጻሕፍት ናቸው፡፡ በዘመኑ ከነበሩ ጠቢባት ሁሉ የበለጠ ስመጥር ፈላስፋ፣ ሊቀ ሥነ
ፍጥረት (ሳይንቲስት)፣ ርዕሰ ብሔር፣ ሊቀ ሥነልቡና (ሳይኮሎጂስት) ነበር፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ሦስት ሺህ
ምሳሌዎችንና አንድ ሺህ አምስት መዝሙሮችን ተናግሯል፡፡ 1 ነገ 4፣32
የመጽሐፉ አቀማመጥ
በዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፈ ምሳሌ በመዝሙራትና በኢዮብ መካከል ይገኛል፤ በሰባው
ሊቃናትና በግእዝ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ላይ ግን መጽሐፈ ምሳሌ በመዝሙራትና በመጽሐፈ መክብብ
መካከል ይገኛል፡፡
በግእዙ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ላይ መጽሐፈ ምሳሌ ሁለት መጽሐፍ ነው፤ ከምዕራፍ 1-24 ያለው
እንዲሁም ከምዕራፍ 25-31 ያለው ሌላ መጽሐፍ ነው፡፡ የመጀመሪያው ምሳሌ ዘሰሎሞን ሲባል ሁለተኛው
ተግሣጽ ዘሰሎሞን ተብሎ ይጠራል፡፡ የአማርኛውም ሁለተኛው ትርጉም ብሉይ ኪዳን ምዕራፍ ሃያ አምስትን
በግእዙ ‹‹መጽሐፈ ተግሣጽ›› ይባላል በማለት ርዕሱን ይገልጣል፡፡
መጽሐፈ ምሳሌ በዕብራይስጥ ብሉይ ኪዳን 31 ምዕራፎች አሉት፤ የሰባው ሊቃውንት ግን ባለ 29
ምዕራፎች ብቻ ያደርጓቸዋል፤ ይህም ምዕራፍ ሠላሳንና ሠላሳ አንድን በምዕራፍ 24 እና 29 ውስጥ
በማስተባበር ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ፡-
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዴት መኖር እንደሚገባው ያስተምራል፡፡ ይህንንም ‹‹የጥበብ መጀመርያ
እግዚአብሔርን መፍራት ነው›› ምሳ 1፣7 በማለት ገልጾታል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
መጽሐፈ ምሳሌ በ 3 ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፤ እነርሱም፡
ምሳ 1-9፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ስለ ጥበብ ገለጻ የተደረገበትና ጥበብን መማር እንደመጠቅም ፤ አለመማር
እንደሚጎዳ የተነገረበት ነው፡፡
ምሳ 10-22፡ ይህ ክፍል፡ ልብን ማደስ፣ ጠባይን ስለማረም፣ አስተሳሰብን ለማጎልበት፣ በሥነ ምግባር
ለመታነጽ የሚረዱ ትምህርቶችን በተለያዩ ምሳሌዎች የሚገልጽ ነው፡፡
ምሳ 23-24፡ በዚህ ክፍል ውስጥ በቀላል የስብከት መንገድ ጥበብን ለመማር ትእዛዞችን ምክሮችና
መመሪያዎች ቀርበዋል፡፡

4. መጽሐፈ ተግሣጽ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 67


ተግሣጽ ማለት ምክር ማለት ነው፤ ጸሐፊው ጠቢቡ ሰሎሞን ጀምሮት አጎርና ሳሙኤል ጨርሰውታል፡፡ /ተግ 1፡1/ ፤
የተጻፈበት ዘመን በ 700 ቅ.ል.ክ ሲሆን የተጻፈውም በኢየሩሳሌም ነው፡፡ ይዘቱም መንፈሳዊ ምክርን የያዘ ፈሪሃ
እግዚአብሔርን የሚያስተምር መጽሐፍ ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ፡-
የሰውን ልጅ በተግሣጽ ለማስተማር የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል፡-
መጽሐፈ ተግሣጽ 7 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 3 ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡
ተግ 1-5፡ የንጉሥ ሰሎሞን ምሳሌዎች
ተግ 6፡ የማሳ አገር ሰው አጉር ለአትኤልና ለኡካል የተነገረው ምሳሌ
ተግ 7፡ የማሳ ንጉሥ የልሙኤልን ቃል ይገልፅልናል፡፡
ማስታወሻ፡- መጽሐፈ ተግሣጽ በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን ችሎ እንደ አንድ መጽሐፍ የተቀመጠ ሳይሆን ከመጽሐፈ
ምሳሌ ጋር በአንድነት ከምዕራፍ 25-31 ድረስ በመካተት ነው፡፡ በግእዙ መጽሐፍ ቅዱስ ግን መጽሐፈ ተግሳፅ ራሱን ችሎ 7
ምዕራፎች ያሉት መጽሐፍ ነው፡፡

5. መጽሐፈ ጥበብ
መጽሐፈ ጥበብ በሌላ ስሙ ባጎር ይሉታል ጥበብ ማለት በቁሙ ሲፈታ ዕውቀት ማለት ነው፤ ጸሐፊው ንጉሥ
ሰሎሞን ሲሆን የተጻፈበት ዘመን በ 900 ቅ.ል.ክ አካባቢ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በ 1 ኛ ቆሮ 15፡32 ላይ ‹‹ነገ
ስለምንሞት ዛሬ እንብላ እንጠጣ›› ስለሚሉ ሰዎች የጻፈው መልእክት በብሉይ ኪዳንም ከአምስቱ የሰሎሞን መጻሕፍት
አንዱ በሆነው በመጽሐፈ ጥበብ በአስደናቂ ሁኔታ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ይህም በመ.ጥበብ 2፡1-9 ያለው ነው፡፡
በአጠቃላይ ይዘቱም እንደ መጽሐፈ ምሳሌ መንፈሳዊ ምክርና ስለ መነናውያንና አይሁዳውያን ይገልፃል፤ እንዲሁም
ስለ ጥበብ ጥቅም በመምከር ሰው ጥበብን እንዲፈልግ ይመክራል፡፡ መጽሐፈ ጥበብ 19 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 3 ዐበይት
ክፍሎች ይከፈላል፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
ስለ ጥበብ ጥቅም በመምከር ሰው ጥበብን እንዲፈልግ ያስተምራል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
ጥበ 1-6፡ ስለ ነገሥታትና ስለ ክርስቶስ
ጥበ 7-15፡ ስለ ሰው ተፈጥሮና ስለ ጣዖት አምልኮ
ጥበ 16-19፡ ስለ ግብጻውያንና ስለ ኢየሩሳሌም ይናገራል፡፡

6. መጽሐፈ መክብብ
መክብብ ማለት ሰባኪ ማለት ነው፤ በዕብራይስጥ ቁሃልት ሲባል፣ ሰብአ ሊቃናት ኤክሊሲያስተርስ
ብለውታል፣ አባ ኤሮኒሞስ /ጄሮም/ ደግሞ ኮንሲአናቶር ብለውታል፡፡ ጸሐፊው ንጉሥ ሰሎሞን ነው /መክ 1፡1/፤
የተጻፈበት ዘመን በ 900 ቅ.ል.ክ አካባቢ ነው፡፡
ይዘቱም ስለ ሕይወት አስቸጋሪ ነገሮች ሁሉም ከንቱ መሆኑንና ጥበብ ከእግዚአብሔር ዘንድ መሆኑን
በዓለም ስላሉ ተቃራኒ ነገሮች እያነሳ ሁሉም ከንቱ መሆኑን ይገልጻል፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 68


ከፈቃደ እግዚአብሔር ውጭ የሆነ ተድላ፣ ደስታ፣ ሥልጣን፣ ሀብት፣ ንብረት ከንቱ መሆናቸውን ያስተምራል
የመጽሐፉ አከፋፈል
መጽሐፈ መክብብ 12 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 3 ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡
መክ 1-4፡ ሁሉም ከንቱ መሆኑን ለሁሉም ጊዜ እንዳለው
መክ 5-8፡ ፈሪሀ አግዚአብሔር፣ ስለ ጥበብ ክብር
መክ 9-12፡ ስለ ጻድቃንና ኃጥአን ይናገራል፡፡
በአጠቃላይ ስንመለከተው መጽሐፉ ሁሉም ከንቱ ነው ሲል ከፈቃደ እግዚአብሔር ውጪ የሆነ ተድላ፣
ደስታ፣ ስልጣን፣ ሀብት፣ ንብረት፣ ከንቱ መሆናቸውን ለማስተማ ነው፡፡ ከንቱ የሚለው ቃል በመጽሐፈ
መክብብ ውስጥ 37 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን በንጉሥነት ዘመኑ የጣዖት ቤትን በመሥራት ለጣኦዖት
በመስገድ እግዚአብሔርን አስቆጥቷል፤ በሕይወቱ ፍፃሜ ግን የፈፀመው በደል እንዳልጠቀመውና እንዳልረባው
ባወቀ ጊዜ ተጸጽቶ ንስሐ ገብቷል፡፡ ይህንን መጽሐፍም የጻፈው በዚህ ወቅት ነው፡፡ በዚህ ምድር ላይ
ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ ያለው ሥጋዊ ነገር ሁሉ አስፈላጊ እንዳለሆነ ለማሳወቅ በተደጋጋሚ ‹‹ሁሉ
ከንቱ ነው›› በማለት አስተምሯል፡፡
መጽሐፉ እጅግ መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን በማንሣት ምክር የሚያስተላልፍ ነው፡፡ ለምሳሌ፡
የምንሞትበት ቀን ሳይደርስ ሕይወታችንን በንስሐ መምራት እንደሚገባን ‹‹አፈርም ወደነበረበት ምድር
ሳይመለስ፣ ነፍስም ወደሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ፡፡›› መክ 12፡7 በማለት የሰውን
ሥጋ በአፈር መስሎ ምክር አስተላልፏል፡፡

7. መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን


መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ማለት ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር ማለት ነው፡፡ በዕብራይስጥ ሸሪሃ ሸሪም ሲባል ትርጕሙም
ማኅሌተ ማኅልይ ማለት ነው፡፡በግሪክ አዚማ አዝማቶን ይባላል፡፡ በእንግሊዘኛውም (Song of Songs) ሲባል የመዝሙሮች መዝሙር ማለት ነው፡፡
እነዚህ ሁሉ ስያሜዎች የሚያስረዱን ሰሎሞን ከጻፋቸው ብዙ መዝሙሮች (1 ነገ 4፡32) ሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ነው፡፡
የመጽሐፉ ጸሐፊ ጠቢቡ ሰሎሞን ሲሆን መጽሐፉንም በ 900 ዓመት ቅ.ል.ክ ጽፎታል፡፡ ከዕብራይስጥ ወደ አረማይክ በተደረገው ትርጕም 39
መጽሐፍ ላይ ‹‹ የእስራኤል ነቢይና ንጉሥ የሆነው ሰሎሞን በመንፈስ ቅዱስ አነሣሽነት እግዚአብሔርን ለማመስግን የተናገራቸው ዝማሬዎችና ምስጋናዎች 10
ናቸው፤ ከእነርሱም ይህ መዝሙር ይበልጣል ›› ይላል፡፡ ይህ የርሱ ጽሐፊነትንና የመዝሙሩን ክብር ይገልጣል፡፡

ይህ መጽሐፍ በ 500 ዓመት ቅ.ል.ክ ካህኑ ዕዝራ ከሰበሰባቸው መጻሕፍት ውስጥ ይገኛል፡፡ በኋላም በ 300 ዓመት ቅ.ል.ክ ሰባ ሊቃንት ብሉይ
ኪዳንን ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ ሲተረጕሙት ይህን መጽሐፍ በመንፈሳዊ ትርጕሙ በመረዳት አካተው ተርማውታል፡፡ ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በነበረበት ዘመን ልክ እንደ ዘመኑ መናፍቃን መጽሐፉን በሥጋዊ እይታ በማየት ሀካም ሼሜይ (Hakham Shemey) ከብሉይ አውጥቶ ቆጥሮት ነበር፤
ነገር ግን የአይሁድ ባሕላዊ ትምህርት ቤት (Helil School or House of Hellil) የቀኖና መጽሐፍ ነው በማለት ተቃውሞታል፡፡ በ 95 ዓ.ም
የተደረገውም የናሚኒያው የአይሀድ ጉባኤም (council at Jamnia) ይህ አጽንቷል፡፡ በ 135 ዓ.ም የነበሩት የአይሁድ ሊቅ ሀካም አኪባ ስለመጽሐፉ
ታላቅነት ሲናገሩ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱስ መጽሐፍ ነው፤ ነገር ግን መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን የበለጠ የከበረ መጽሐፍ ነው . . . ዓለሙ ሁሉ የዚህን ያህል
ጠቃሚ መጽሐፍ አልሰጠንም፡፡›› ብለዋል፡፡

ይህን መጽሕፍ ጠቢቡ ሰሎሞን ከሌሎች መጻሕፍቱ በተለየ በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን መንፈሳዊ ፍቅር (Agape in Greek)
ለማስረዳት በወንድና ሴት ፍቅር (Eros in Greek) በመመሰል ጽፎታል፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንዶች ምስጢሩን ባለ መረዳት ሰሎሞን የፈርኦንን ልጅ
ሲያገባት የጻፈው ነው በማለት የያዘውን መንፈሳዊ ትርጕም ሊያዛቡ ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን ይህ መጽሐፍ ለሥጋዊ ፍቅር (Carnal Love) ሳይሆን
መንፈሳዊ ፍቅርን ለማስረዳት የተጻፈ፤ እነርሱም ፍጹም የተሳሳቱ መሆኑን የመጽሐፉ መጀመሪያ ያስረዳናል፡፡

ይህም መጽሐፉ ሲጀምር (ቊ 2-7) ያለው ንግግር የመርዓት (የሙሽራዋ) ነው፤ ለሙሽራውም እንዲህም ትለዋች ‹‹በአፉ መሳም ይሳመኝ፥
ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና።›› አገላለጹ እጅግ ያስደንቃል፤ ምክንያቱም ‹‹በአፍህ አሳሳም ሳመኝ›› ሳይሆን ያለቸው ‹‹ በአፉ መሳም
ይሳመኝ›› ነው፡፡ ስለዚህ የሚስማት ሌላ፣ ፍቅሩ ደግሞ የመሽራው መሆኑን ገልጣለች፡፡ ምክንያቱም ‹‹ፍቅሩ›› ሳይሆን ያለቸው ‹‹ፍቅርህ›› ነውና፡፡ ይህ
አገላለጽ ከመንፈሳዊ ትርጕሙ በስተቀር በሌላ ሊተረጎም ፈጽሞ አይችልም ምክንያቱም ሙሽሪት ሌላ ወንድ እንዲስማት ሙሽራዋን ፈጽማ አትጠይቅምና፡፡
39
ይህ ትርጕም ‹‹ኤልታርጉም›› የሚባለው ሲሆን አይሁዳውያን ከባቢሎን ምርኮ ሲመጡ ከመከራው ጽናት የተነሣ ዕብራይስጥን ረስተው ስለነበር በዘመኑ የነበሩት
ሊቃውንት ወደ አረማይክ በቃል በኋላም በጽሑፍ የተረጐሙት ትርጕም ነው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 69


ነገር ግን ይህ አገላለጽ በክርስቶስና በቤተ ክርሰርቲያን መካከል ባለው መንፈሳዊ ፍቅር ይመሰላል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ‹‹ በአፉ መሳም ይሳመኝ›› ያለችው
እግዚአብሔር አብን ነው፤ የሰው ልጅ ይድን ዘንድ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና፡፡ ፍቅርህ ብላ ደግሞ የምትናገርለት ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፤
በመስቀል ሞት የርሱን የአባቱንና የሕይወቱን የመንፈስ ቅዱስን ፍቅር ለዓለም ገልጧልና፡፡

ከዚህ ቀጥሎ ያለውም የሙሽራዋ ንግግር ይህንኑ ያስረዳል ‹‹ ሳበኝ፥ ከአንተም በኋላ እንሮጣለን ንጉሡ ወደ ቤቱ አገባኝ በአንተ ደስ
ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እናስባለን በቅንነት ይወድዱሃል።›› በዚህ አገላለጥ ደግሞ ሙሽራዋ ወደ
ሙሽራው እንድትቀርብ እንዲስባት ስትጠይቀው ነገር ግን ሌሎች ደናግላንን ከርሷ ጋር ይዛ እንደምትመጣ በርሱም በፍቅሩም ደስ እንደሚላቸው ተጽፏል፡፡
ይህም ጠቢቡ ሊያስረዳ የፈለገው ሥጋዊ ፍቅርን አለመሆኑን ያሳየናል፡፡ ምክንያቱም የትኛዋም ሙሽሪት እጮኛዋን ለሌሎች ሴቶች የምትፈቅድ
አይደለችምና፡፡

መጽሐፉ ከቅዱሳት መጻሕፍት የሚመደብ ከሆነ ለምን እንደዚህ ዓይነት አገላለጽ መጠቀም አስፈለገ ብለው ብዙዎች ይጠይቃሉ፡፡ ነገር ግን ይህ
የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕል ነው፡፡ እግዚአብሔር እኛ እንረዳው ዘንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በእኛ አገላለጾች ተናግሯል፡፡ ለምሳሌ እግዚአብሔር
ተናደደ፣ ተጸጸተ ... የሚሉት አገላለጾች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ለእግዚአብሔር ዓይን፣ ጆሮ፣ ቅንድብ፣ ወይም መቀመጥ መቆም ሲነገርለት
እግዚአብሔር ልክ እንደ እኛ ዓይነት ዓይን ጆሮ አለው፤ ወይ መቀመጥ መነሣት ይነገርለታል ማለት ሳይሆን እኛ እንረዳው ዘንድ በእኛ
አገላለጥ ሲገልጸው ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር ለማሳየት ምን ያህል እንደሆነ እኛ እንድንረዳው ጠቢቡ ሰሎሞን
በወንድና በሴት መካከል በሚፈጠረው ፍቀር አስረድቶናል፡፡ መንፈሳዊውን ፍቅር በዚህ መመሰል ደግሞ በሌሎች መጻሕፍት ላያም
እናገኘዋለን፡፡

በብሉይ ኪዳን

 ኢሳ 62፡5 ‹‹ጕልማሳም ድንግሊቱን እንደሚያገባ፥ እንዲሁ ልጆችሽ ያገቡሻል ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ
አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።››
 ኤር 3፡1 ‹‹በሰው ዘንድ ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመለሳለችን?
ያች ሴት እጅግ የረከሰች አይደለችምን? ይባላል። አንቺ ከብዙ ውሽሞች ጋር አመንዝረሻል፥ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል
እግዚአብሔር››
በሐዲስ ኪዳን

 ኤፌ 5፡24-26 ‹‹ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ። ባሎች
ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ
እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ ››
 ዮሐ 3፡ 27-29 ‹‹ ዮሐንስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ ከሰማይ ካልተሰጠው ሰው እንዳች ሊቀበል አይችልም። እናንተ። እኔ ክርስቶስ
አይደለሁም፥ ነገር ግን። ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ እንዳልሁ ራሳችሁ ትመሰክሩልኛላችሁ። ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ
ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ።››
ይህን መጽሐፍ የአይሁድ ሊቃውንት ከነቢያቱ ቃል በመነሣት በእግዚአብሔርና በእስራኤላውያን መካከል ባለ ፍቅር መስለው ያስተምሩታል፡፡
የቤተ ክርስቲያንም አባቶች ይህን መጽሐፍ በሦስት ዓይነት መንገድ ይተረጉሙታል፡፡

ቅዱስ ጄሮም፣ ሊቁ አርጌንስና ሊቁ አውግስጢኖስ የቅዱስ ጳውሎስን ቃል መሠረት በማድረግ በቤተ ክርስቲያንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መካከል
ባለ ፍቅር መስለው ተርጉመውታል፡፡
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ደግሞ በሰው ነፍስና በእግዚአብሔር መካከል ባለው ፍቅር መስሎ አስተምሯል፡፡ ሊቁ አርጌንስም በአንዳንድ አገላለጹ ላይ ይህን
ተጠቅሟል፡፡
40
አንዳንድ አባቶች ሊቃውንት እንዲሁም ኢትዮጲያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የተወሰኑ የመጽሐፉ ክፍሎችን በሥጋዌ ምስጢር ሙሽራዋንም
በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም ቆነጃጂቱን በቅዱሳን መስለው አስተምረዋል፡፡
ይህ መጽሐፍ 8 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን ለአከፋፈል ትንሽ አስቸጋሪ ቢሆንም በሙሽራዋና በሙሽሪቱ ንግግር አንጻር ለ 4 ይከፈላል፡፡

1. ሙሽሪት ለሙሽራው በቅርብ የምታደርገውን ንግግር


2. ሙሽሪት ለሙሽራ በሩቅ የምታደርገውን ንግግር
3. መሽራው ለሙሽሪት በቅርብ የሚያደርገውን ንግግር
4. በሙሽራው በሙሽሪት መካከል ያለ ጥያቄና መልስ

40
ቅዱስ ያሬድ ከዚህ መጽሐፍ አወጣጥቶ በግጥም መልክ ያዘጋጀው መጽሐፍ የሰሎሞን ምቅናይ ይባላል፡፡ ይህም መጽሐፍ ጌታችንን በፍሬ እመቤታችንን በአበባ እየመሰለ
የሚያስተምር ነውና የቤተክርስቲን ሊቃውንት በዘመነ ጽጌ (መስከረም 25- ኅዳር 6) ለምስጋና ይጠቀሙበታል፡፡ በተጨማሪም በሥርዓተ ተክሊል ጊዜ ከመጽሐፈ ተክሊል
ጋር እንደ አንድ ክፍል ተደርጎ ይጸለያል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 70


8. መጽሐፈ ሲራክ
ሲራክ ማለት ጸሐፊ ማለት ነው፤ ጸሐፊው የሲራክ ልጅ ኢያሱ ሲሆን የተጻፈበት ዘመን በአንዳንድ
መጻሕፍት 180 ዓ.ዓ በኢየሩሳሌም ይነገራል፡፡ መጽሐፈ ሲራክ እንደ ሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ
መጽሐፈ ሲራክም በሐዲስ ኪዳን ከይዘቱ ተጠቅሶለት ይገኛል፡፡ ለምሳሌ፡በሲራ 28፡4 ላይ ስለ ይቅርታ
የተነገረው በወንጌል ከተነገረው ጋር አንደ መሆኑን እናያለን ‹‹እንዳንተ ያለውን ሰው ይቅር ሳትል ኃጢአትህነ
ያስተሰርይልህ ዘንድ እንግዲህ እንዴት አምላክህን ትለምነዋለህ›› ማር 11፡25 ‹‹ለጸሎት በቆማችሁ ጊዜ
በሰማያት ያለው አባታችሁን ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ በማንም ላይ አንዳችም ቢኖራችሁ
ይቅር በሉት››፡፡
መጽሐፈ ሲራክ በመጀመሪያ በዕብራይስጥ ተጽፎ ኋላ በልጅ ልጁ ወደ ግሪክ ተተርጉሟል፡፡
መጽሐፉም በአጠቃላይ ለመንፈሳዊና ሥጋዊ ሕይወታችን ጥበብና ምክር የሚሰጥ ነው፡፡
ሲራክ የኢያሱ የግብር ስሙ ሲሆን ወለደ አልአዛር ወልደ ሲራክ ይባላል፡፡ በዘመኑ ድምትርያስ የተባለ
የግሪክ ንጉሥ ጠጅ አሳላፈውን ተጣልቶት አባሮት ነበረ፡፡ እርሱም በሲራክ ቤት ተደብቆ ስለኖረ ጠጅ
አሳላፊውን መደበቁ ንጉሡን ስላስቆጣው ሲራክ ለእስር ተዳርጎ ነበር፤ በዚያ መከራ ውስጥ ሆኖ ነው ጥበብ
መንፈሳዊ ጥበብ ሥጋዊን ግለፅልኝ እያለ ፈጣሪውን ይጠይቅ የነበረው፤ ይመኘው የነበረው ጥበብ መንፈሳዊና
ጥበብ ሥጋዊ ተገልፆለት ይህንን መጽሐፍ ጽፏል፤ መጽሐፉም ከመጽሐፈ ምሳሌ ጋር ተቀራራቢነት አለው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ፡-
የሰው ልጆችን መንፈሳዊና ሥጋዊ ጥበብ በምክር አዘል አቀራረብ ያስረዳል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል፡- ከአዳም ጀምሮ ያሉትን አበው ታሪክ ይገልፃል፤ የሰሎሞንን ምሳሌዎች የሚመስሉ
ለመንፈሳዊና ለሥጋዊ የሚሆን ምክርና ጥበብን ይገልጻል፡፡
መጽሐፈ ሲራክ 51 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 5 ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡
ሲራ 1-10፡ ስለ ጥበብና ፈሪሀ እግዚአብሔር፣ ስለ ቤተሰባዊ ኑሮ፣ ስለ ዝምታና ትዕግስት ይገልፃል፡፡
ሲራ 11-20፡ ስለ ፍርድ፣ ስለ ምፅዋት፣ ስለ ሥነ ፍጥረት ይናገራል፡፡
ሲራ 21-30፡ ስለ ንስሐ፣ ስለ ንጽሕና፣ ስለ ብልህ ሰውና ስለ 5 ቱ አዕማደ ምስጢር
ሲራ 31-40፡ ስለ መባና ገንዘብ፣ ስለ ምክር፣ ስለ ምግባረ ሃይማኖት
ሲራ 41-51፡ ስለ ኃጢኢተኞችና ስለ ሥነ ፍጥረት ይናገራል፡፡

5. የትንቢት ክፍል
ነቢይ ማለት ምን ማለት ነው ?
ነቢይ ማለት አፈ አምላክ /የእግዚአብሔር አፍ/፣ መምህር ማለት ነው፡፡ ቃለ እግዚአበብሔርን
ተቀብሎ ለሕዝቡ የሚናገር ‹‹ነቢይ›› የእግዚአብሔር ሰው ይባላል፡፡ ነቢያት ቃሉ ከእግዚአብሔር እንደመጣ
ቢረዱም እንዴት እንደመጣላቸው ብዙ ጊዜ አይገልጡም፤ ነገር ግን ‹‹እግዚአብሔር እንዲህ አለ›› እያሉ
ትንቢት ይናገሩ ነበር፡፡ አሞ 1፡3፣ 6፡9፤ ሚክ 3፡8 የእግዚአብሔር ቃል አንዳንድ ጊዜ በራዕይ፣ በህልምም፣
በመልአክም ይገለጥላቸው ነበር፡፡ ዘካ 12፡6፣ ዳን 10፡11 ቃሉ በብዙ ዓይነት መንገድ ቢሰጣቸውም (ዕብ 1፡1)
እስኪናገሩት ድረስ እንደሸክም ይከብዳቸው ነበር፡፡ በእግዚአብሔር መንፈስ ስለተጠሩና ስለሚናገሩም (ኢሳ
15፡1፣ 2 ኛ ጴጥ 1፡21) ሕዝቡ በኃጢአት ከመጥፋቱ በፊት ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡና ይቅርታን
እንዲጠይቁ ያደርጉ ነበር፡፡
ነቢያት በሁለት መንገድ ከእግዚአብሔር ተቀብለው ለሕዝቡ ይናገራሉ፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 71


 በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለተፈጸሙ ድርጊቶች ፣ ስለ መንግሥት፣ ስለ ሰዎችና ስለ ኃጢአት ይናገራሉ፡፡
 ወደ ፊት ስለሚከሰቱ ድርጊቶች፡፡ የእነዚህ መጽሐፍ አቀራረብ በዚህ መልክ ስለሆነና ሁሉም በነቢያት
በመጻፋቸው የትንቢት መጻሕፍት ተብለዋል፡፡
ነቢያት በስንት ይከፈላሉ ?
ሀ. ነቢያት ትንቢታቸውን ካስተላለፉበት መንገድ አንጻር በሁለት ይከፈላሉ፡-
1. በቃል ብቻ ትንቢታቸውን የተናገሩ የቃል ነቢያት ይባላሉ፡፡ ለምሳሌ፡ ነቢዩ ጋድ፣ ናታን፣ ራአይ፣ አኪያ፣
ኤልሳዕ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ አጋቦስና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
2. ትንቢታቸውን በጽሑፍ መልክ ያሰፈሩ የጽሑፍ ነቢያት ይባላሉ፡፡ ለምሳሌ፡ ከትንቢተ ኢሳይያስ እስከ
ትንቢተ ሚልኪያስ ያሉ ነቢያት፡፡
ለ. ነቢያት በመጽሐፍቶቻቸው ምዕራፍ ብዛት፣ ቊጥርና እድሜ በሁለት ይከፈላሉ፡፡
1. ዐበይት ነቢያት፡ ኢሳይያስ፣ ኤርሚያስ፣ ሕዝቅኤል እና ዳንኤል ናቸው፡፡
2. ደቂቀ ነቢያት፡ ሆሴዕ፣ አሞፅ፣ ሚክያስ፣ ኢዩኤል፣ አብድዩ፣ ዮናስ፣ ናሆም፣ ዕንባቆም፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣
ዘካርያስና ሚልኪያስ ናቸው፡፡
ሐ. ነቢያት ከኖሩበት ቦታ አንፃር በ 3 ይከፈላሉ፡፡
1. በይሁዳ የነበሩ ነቢያት፡ ኢሳይያስ፣ ኤርሚያስ፣ ሚክያስ፣ ሶፎንያስና ሚልክያስ
2. በሰማርያ የነበሩ ነቢያት፡ ሆሴዕ፣ ዮናስና የመሳሰሉት
3. በባቢሎን የነበሩ ነቢያት፡ ሕዝቅኤልና ዳንኤል
መ. በኖሩበት ዘመን ነብያት በሦስት ይከፈላሉ፡፡
1. ከባቢሎን ምርኮ በፊት (እስራኤላውያን ከመማረካቸው በፊት)፡ ኢሳይያስ፣ ሆሴዕ፣ ኢዩኤል፣ አሞፅና
ሚክያስ ናቸው፡፡
2. በባቢሎን ምርኮ ጊዜ፡ ኤርሚያስ፣ ዕንባቆም፣ ሕዝቅኤልና ዳንኤል ናቸው፡፡
3. ከባቢሎን ምርኮ በኋላ፡ ሐጌ፣ ዘካርያስና ሚልክያስ ከምርኮ በኋላ በ 538 ዓ.ዓ.ቅ.ል.ክርስቶስ ይኖሩ ነበር፡፡
4. በእነዚህ ጊዜያት የተነገሩት ትንቢቶችና መጽሐፍቶች ከ 250-350 ዓመታት ውስጥ ተጠራቅመዋል፡፡
እነዚህ የትንቢት መጻሕፍት በጊዜው ለእስራኤል ዘሥጋ የተነገሩ ቢሆንም ፍጻሜያቸው ግን በዚህ
ዘመን ላለነው ወደፊትም ለሚመጣው ትውልድ ነው፡፡

1. ትንቢተ ኢሳይያስ
ኢሳይያስ ማለት እግዚአብሔር ደህንነት ነው፣ መድኃኒት፣ አዳኝ ማለት ነው፡፡ አባቱ አሞፅ ይባላል፤
ይህም ከነቢዩ አሞፅ የተለየ ነው፡፡ /2 ኛ ነገ 17፡1፣ ኢሳ 1፡1/ ኢሳይያስ ባለትዳር ሲሆን ሚስቱም እንደ እርሱ
ነቢይት ነበረች፤ ሁለት ልጆቹም ነበሯቸው የልጆቹም ስም አንደኛው ማሄር ሻላል ሲባል ሌላኛው ሺያር
ያሼብ ይባላል፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ አገልግሎቱን የጀመረው በዖዝያን መንግሥት መጨረሻ አካባቢ ነው፡፡ /ኢሳ 6፡1-13/ ነቢዩ
ኢሳይያስ በአራት የይሁዳ ነገሥታት (በዖዝያን፣ በኢዩአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ) ዘመን ከክርስቶስ ልደት
በፊት ከ 740-688 ዓመት አካባቢ ትንቢት የተናገረ ነቢይ ነው፡፡ ኢሳይያስ የታወቀ የኦሪት ምሁር ሲሆን
ትንቢቱንም የተናገረው በኢየሩሳሌም ሆኖ ነው፡፡ ትንቢተ ኢሳይያስ የተጻፈው ከምርኮ በፊት በኢየሩሳሌም

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 72


(ሊባኖስ) ሰሜን ፈንቄ ነው፡፡ ኢሳይያስ ከዐሥራ ስድስቱ ነቢያት የመጀመሪያው ነቢይ ሲሆን ከታላላቆቹ
ነቢያት አንዱና መጽሐፉም የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘ ነው፡፡ መጽሐፉ የራዕይና የንግግር ስብስብ ነው፤
መጽሐፉም የተጻፈው ከክርስቶስ ልደት በፊት 700 ዓመት ላይ በነበረው ከዐበይት ነቢያት፣ ከይሁዳ ነቢያትና
ከባቢሎን ምርኮ በፊት ከነበሩት ነቢያት አንዱ በሆነው በነቢዩ ኢሳይያስ ነው፡፡
ስለ ትንቢተ ኢሳይያስ ጸሐፊ ብዙ የተለያዩ አስተያየቶች አሉ፤ አንዳንድ ሊቃውንት ይህ የትንቢት
መጽሐፍ በ 3 ሰዎች ተጽፏል ይላሉ፤ በዚህም መጽሐፉን ቀዳማይ፣ ካልዕና ሣልስ በማለት ይከፋፍሉታል፤
ቀዳማይን ታልሙድ ሕዝቅያስና ሰዎቹ፣ ካልዕን ሙሴ ቤን ሳሙኤል ኢብን ጌካቱላ፣ ሣልስን ቤሮንሀርድ ዱም
በእነዚህ ሰዎች ተጻፈ ይላሉ፤ በእነዚህ ሊቃውንት ዘንድ ኢሳይያስ ቀዳማዊ /1-39/፣ ካልዕ /40-55/፣ ሣልስ /56-
66/ በማለት ሰይመውታል፡፡
ነገር ግን አብዛኛዎቹ የብሉይ ኪዳን ሊቃውንት በተለይም ኦርቶዶክሳዊያን በስሙ የተሰየሙንትነ
መጽሐፍ በሙሉ የጻፈው ኢሳይያስ ወልደ አሞፅ መሆኑን አምነው ይቀበላሉ፡፡ ስለዚሀም የሚያቀርቡት
ምክንያት በሐዲስ ኪዳን ውስጥ ኢሳይያስ ከሁለቱም ነቢያት ይልቅ በብዛት መጠቀሱን ነው፤ /ዮሐ 12፡38-42/
ያሉት ጥቅሶች ከሁለቱም ከቀዳማዊና ከካልዕ ኢሳይያስ የተወሰደ ሲሆን ለአንድ ኢሳይያስ የተሰጡ ናቸው፡፡
/ኢሳ 53፡1፣ 6፡9/ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ 9፡2-33 ከኢሳይያስ ቀዳማዊ 1፡9፣ 8፡14፣ 28፡16 በኋላ
እንደገና በዚሁ በሮሜ መልእክቱ 10፡15-21 ከኢሳይያስ ካልዕ 52፡7፣ 53፡1፣ 65፡1-2 ሲጠቅስም ኢሳይያስ የሚል
ስም ብቻ ተጠቀመ እንጂ ልዩነቱን አላሳየም፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ ስለ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ግልጽ ትንቢቶችን በመናገሩ (ኢሳ 7፡14፣ 5፡31፣ 9፡6) ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፉን ደረቅ
ሐዲስ ሲሉት እርሱን (ኢሳይያስን) ደግማ ወንጌላው ነቢይ ይሉታል፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ ንጉሥ ዖዝያን ክህነት ሳይኖረው ቤተ መቅደስ ገብቶ ሲያጥን አይቶ ባለመገሰጹ
ምክንያት ለ 3 ዓመት ነቢይነቱን ከተነሣ በኋላ በትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 6፡1 ላይ እንደምናገኘው በድጋሚ
የተላከ ታላቅ የእግዚአብሔር ነቢይ ነው፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ የኖረው እስከ ንጉሥ ምናሴ ዘመን ድረስ ሲሆን ንጉሥ ምናሴ በንስሐ ወደ አምላኩ
ከመመለሱ በፊት ኢሳይያስን በመጋዝ ቆርጦት መስከረም 6 ቀን በሰማዕትነት አርፏል፡፡ /ዕብ 11፡37/
የመጽሐፉ ዓላማ
የእስራኤል ቅዱስ በዚህ ዓለም ላይ ነግሦ በአመፀኞች ላይ ለመፍረድ የሚያምኑበትንም በማዳን ኃያል
መሆኑን ያስረዳል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል፡-
ትንቢተ ኢሳይያስ እስራኤል በአንድ አምላክ እንዲድኑ እንዲሁም በእግዚአብሔር ሕግና ሥርዓት እንዲመሩ
ምክርን የያዘ ሲሆን ስለ ጌታችንና ስለ እመቤታችን ትንቢት ይናገራል፡፡
ትንቢተ ኢሳይያስ 66 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን መጽሐፉም በ 6 ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡
ኢሳ 1-5፡ በዚህ ክፍል ውስጥ በዖዝያን ዘመነ መንግሥት የይሁዳ ሕዝብ የሰዶምንና የገሞራን ሕዝብ
ዓይነት ርኩሰት ይፈጽሙ ስለነበር በንስሐ እንዲመለሱ፣ ካልተመለሱ ግን ከእግዚአብሔር ከባድ ቅጣት
እንደሚጠብቃቸው ነቢዩ አስጠንቅቋል፤ እንዲሁም የሕዝቡ መሪዎች ከሌላው ሕዝብ ይበልጥ
ኃላፊነት እንዳለባቸውና መሪዎቹ ሕዝቡን ከሚያሳዝኑባቸውን ኃጢአቶች (ስስታምነት፣ በድሆች ላይ
መጨከን፣ በጉቦ ምክንያት ፍርድን ማጣመም ) እንዲመለሱ ነቢዩ ወቅሷቸዋል፡፡
ኢሳ 6-12፡ በዘህ ክፍል ውስጥ ነቢዩ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ትንቢት ተናግሯል፡- ስለ ኢዩአታምና
አካዝ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ስለ መወለዱ፣ ከድንግል የሚወለደው መድኃኒት ክርስቶስ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 73


አምላክ ስለመሆኑ፣ ጌታ በሥጋ የሚገለጠው (የሚወለደው) ከእሴይ ዘር ከዳዊት ስለ መሆኑ፣ ስለ
ክርስቶስ መምጫ ጊዜ፣ በዛብሎንና በንፍታሌም ነገዶች ምድር የክርስቶስ ብርሃን እንደሚገለጥና ስለ
እስራኤልና ሶርያ መፍረስና ስለ ሕዝቦቻቸው መማረክ
ኢሳ 13-23፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ስለ ባቢሎን፣ አሦር፣ ሞአብ፣ ሶርያ፣ እስራኤል፣ ግብጽና ጢሮስ
የተለያዩ ትንቢቶች ተነግረዋል፡፡
ኢሳ 24-25፡ ስለ ሕዝቡ እምቢተኝነትና እግዚአብሔር ለሕዝቡ ዐመጸኝነት ማስጠንቀቂያ መስጠቱ
እንዲሁም ስለ እግዚአብሔር ዓላማና ፍርድ የተነገረበት ነው ክፍል ነው፡፡
ኢሳ 26-39፡ በዘህ ክፍል ንጉሥ ሰናክሬም ይሁዳን መውረሩ፣ በንጉሥ ሕዝቅያስ ጸሎት አማካኝነት
በእግዚአብሔር እርዳታ ከንጉሥ ሰናክሬም ወታደሮች መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ /185,000/
በተአምር መሞታቸውንና የሕዝቅያስ መታመምና ከሕመሙ መፈወሱ ይገኝበታል፡፡
ኢሳ 40-66፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ነቢዩ ኢሳይያስ በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ ትንቢት ተናግሯል፡
 የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስን መምጣት
 የክርስቶስን አመጣጥና ትህትና
 ክርስቶስ ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙለት ዘንድ ስላቀረበው ጥሪ
 መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ኃጢአት ሕማምን መቀበሉን፣ መሞቱ፣
መቀበሩንና ከሙታን መነሳቱን
 ስለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ
 ነቢዩ ኢሳይያስ በዘህ ክፍል ውስጥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ከወንጌል በረከት ይሳተፉ ዘንድ
እንዲህ ሲል ጋብዟቸል ‹‹የተጠማችሁ ሁሉ ወደ ውኃ ኑ፣ የምትገዙበት የሌላችሁ ኑ፣ ያለ
ገንዘብና ያለ ዋጋ ገዝታችሁ ብሉ፣ ያለ ገንዘብና ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ፡፡››

2. ትንቢተ ኤርሚያስ
ኤርሚያስ ማለት እግዚአብሔር ያሌዕል (ከፍ ያደርጋል) ማለት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት
ግን ‹‹ብርሃነ እግዚአብሔር ማለት ነው›› ብለው ይተረጉማሉ፤ ለዚህም እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት
ኤርምያስ በእናቱ ማህጸን ሳለ የተመረጠና በወጣትነቱ እግዚአብሔር ለአገልግሎት ያዘጋጀው ታላቅ ነቢይ
ነው፡፡
ኤርሚያስ ከእግዚአብሔር የመጣለትን ቃል ሁሉ በቃል እየነገረው ባሮክ ይጽፍለት ነበር /ቁ 4/
ከዓመታት በኋላ በኢዩዋቄም ዘመነ መንግሥት በ 5 ኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር የጻም ዓዋጅ በሚነገርበት
ቀን ባሮክ የኤርምያስን መጽሐፍ በአደባባይ አነበበ፤ ይህንንም ንጉሡ ሰማ መጽሐፉንም አቃጠለው፡፡ ነቢዩ
ኤርሚያስም ባሮክን ጠርቶ በድጋሚ በቃል እየነገረው የቀድሞውን የትንቢት ቃል አጽፏታል፤ አንዳንድ ቃል
ተጨምሯል፤ ለምሳሌ ቁ፡32
ኤርምያስ በ 650 ዓመት ቅ.ል.ክርስቶስ ተወለደ፤ አባቱ ከካህናት ወገን የነበረ ኬልቅያስ የተባለ ሰው
ነበር፡፡ /2 ኛ ነገ 22፡8/ የትውልድ ቦታውም በኢየሩሳሌም ሰሜን አናቶች ትባላለች፤ በዛሬው አጠራር አናታ
ትባላለች፡፡ ኤርምያስ ገና ወጣት የ 20 ዓመት ሳለ ለነቢይነት ተጠራ /ኤር 1፡6/ በጠቅላላ ለ 40 ዓመታት ያህል
በነቢይነት አገልግሏል፤ ሚስትም አላገባም ነበር፡፡ /ኤር 16፡1-4/

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 74


ነቢዩ ኤርምያስ እግዚአብሔር ገልጦለት የኢየሩሳሌም ጥፋት በሰሜናዊው ጠላት እንደሚፈፀም
ያውቅ ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተማረው በአናቶች ሲሆን በእውነተኛ ትምህርቱ ምክንያት የአናቶች
ሰዎች በጥላቻ ተነስተውበት፣ ሊገድሉትም ወሥነው ነበር፤ ብዙ ስቃይም እንዲደርስበት በጉድጓድ ጣሉት፣
በዚህ ጊዜ ኤቤድሚሊክ ረድቷታል፡፡ /ኤር 20፡1-10/ ኤርምያስ ይህ ሁሉ መከራ ቢደርስበትም ንጉሥ ኢዮስያስ
በነበረበት ዘመን ሁሉ መከራውን ታግሶ በደስታ ያስተምር ነበር፤ ኢዮስያስ በሞተ ጊዜ እጅግ አዝኖ ነበር፡፡ /2 ኛ
ዜና 35፡25/
ነቢዩ ዳንኤል በምርኮ በተያዘ ጊዜ የቤተ መቅደስ ንዋያት ሁሉ በተዘረፈ ጊዜ ኤርምያስ ሰብዓው
የፄዋዌ ዓመታት ተነበየ /ኤር 25፡1-4/ ንጉሥ ኢዩአቄም የነቢዩ ኤርምያስ ዋና ተቃዋሚ ነበር፤ ናቡከደነፆር
ኢየሩሳሌምን ለረዥም ጊዜ በከበበ ወቅት ለነብዩ ኤርምያስ እጅግ የስቃይ ጊዜ ነበር፤ ናቡከደነፆር ወደ
ጉድጓድ ሲጠለው ኢትዮጵያዊው አቤማሌክ ከንጉሡ አስፈቅዶ አውጥቶታል፡፡ /ኤር 38፡7-13/
በመጨረሻም ኢየሩሳሌም በወደቀች ጊዜ ባቢሎናውያን ሴዲቅያስን ዓይኑን አጥፍተው ከሕዝቡ ጋር
ማረኩት የባቢሎናውያን ጄነራል ናቡከደነፆር ግን ኤርምያስን በነፃ ለቀቀው በገዛ ሀገሩ እንዲኖርም ፈቀደለት
/ኤር 39፡11-14/ አይሁድ ስለ ልባቸው ክፋትና ስለ ሕግ መተላለፋቸው ይወቅሳቸው ነበር፤ ኋላም በድንጋይ
ወግረው ገደሉት፡፡
የኤርምያስ ዘመነ ትንቢት
የኤርምያስ ዘመነ ትንቢት በ 4 ክፍል ይመደባል፡፡
1. ከተጸውዖ እስከ ተሐድሶ /626-621 ቅ.ል.ክርስቶስ/
2. ከተሐድሶ እስከ ሞተ ኢዮስያስ /622-608 ቅ.ል.ክርስቶስ/
3. ከሞተ ኢዮስያስ እስከ ዳግም ፍልሰት /609-586 ቅ.ል.ክርስቶስ/
4. ከዳግም ፍልሰት እስከ ዕለተ ሞት
የኤርምያስ የትንቢት ጓደኞች
1. ነቢዩ ኤርምያስ በኢየሩሳሌም ሲያስተምር ሕዝቅኤልና ዳንኤል በዚያው ዘመን በባቢሎን ፄውዋያን
ያስተምሩ ነበር፡፡
2. ዕንባቆምና ሶፎንያስ በኢየሩሳሌም ኤርምያስን ይረዱ ነበር፡፡
3. ናሆም በዚያው ዘመን የነነዌን ድቀት ተናግሯል፡፡
4. አብድዩ በተመሳሳይ ዘመን የኤዶምያስን ድምሳሴ ተነበየ፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ፡-
መጽሐፈ ኤርምያስ አይሁድ እግዚአብሔርን ትተው ጣዖት በማምለካቸው፣ ጽድቅን ትተው ኃጢአትን
አብዝተው በመሥራታቸው በባቢሎናውያን ኃይል እንደሚማረኩ፣ በምርኮም 70 ዓመታት እንደሚኖሩ፣
ሀገራቸው ኢየሩሳሌምም ፈጽሞ እንደምትደመሰስ ይገልጣል፤ ይህም ፍትሐ እግዚአብሔር ስለሆነ ሕዝቡ
ለባቢሎናውያን መገዛት እንዳለባቸው መጽሐፉ ያስረዳል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
መጽሐፉ 52 ምዕራፎች አሉት፤ አጠቃላይ የመጽሐፉን ይዘት ከዚህ በታች በቀረቡት 9 ክፍሎች በዝርዝር
መረዳት ይቻላል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 75


ኤር 1 -2፡ በዚህ ክፍል እግዚአብሔር ነቢዩ ኤርምያስን በእናቱ ማህፀን ሳለ እንደቀደሰው እና ለአሕዛብ
ነቢይ እንዳደረገው እናገኛለን፡፡
ኤር 3-20፡ ይህ ክፍል የእስራኤል ሕዝቦች ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ነቢየ ያደረገው ጥሪና
መልእክቶች ይገኙበታል፡፡
ኤር 21-29፡ የይሁዳ ንጉሥ የነበረው ዮአኪን ወደ ባቢሎን ከተማረከ በኋላ ነቢዩ ኤርምያስ ለነገሥታት፣
ለሕዝቡና ለምርኮኞች ያስተላለፈውን ይዟል፡፡
ኤር 30-33፡ ነቢዩ ስለ ሐዲስ ኪዳንና የወንጌል ሕግ መምጣት የተናገረ ሲሆን በተጨማሪም ስለ
ኢየሩሳሌም አዲስ ተስፋ የተናገረበት ነው፡፡
ኤር 34-39፡ ይህ ክፍል ኢየሩሳሌም በጠላቶቿ መከበቧንና ውድቀቷን ይናገራል፡፡
ኤር 40-42፡ ነቢዩ ኤርምያስ ከምርኮ ከተረፉት አይሁድ ጋር በይሁዳ መቅረቱን ይገልፃል፡፡
ኤር 43-44፡ የነቢዩ ኤርምያስን የግብጽ የስደት ኑሮና በዚያ ያከናወናቸውን አገልግሎቶች ያትታል፡፡
ኤር 45-51፡ በዚህ ክፍል ነቢዩ በአሕዛብ ላይ የተናገራቸው የትንቢት ቃላት ይገኝበታል፡፡
ኤር 52፡ በዚያ ዘመን ስለተፈፀመው የኢየሩሳሌም ውድቀት ጥፋትና የሕዝቧ ስደት እንዴት እንደ ነበር
ይናገራል፡፡

2.1 መጽሐፈ ባሮክ


ባሮክ ማለት ቡሩክ ማለት ነው፡፡ ባሮክ የነቢዩ ኤርምያስ ታማኝ ወዳጅና ጸሐፊም ነበር፡፡ ባሮክ በነቢዩ
ኤርምያስ ትእዛዝ እግዚአብሔር ለነቢዩ ኤርምያስ የተነገረውን ቃል በመጽሐፍ ጽፏል፡፡ ኤር 36፣1-32
ኤርምያስ በንጉሥ ሴዴቅያስ ዘመን በታሠረ ጊዜ ባሮክ የንጉሡን ቁጣ ሳይፈራ ነቢዩን ይረዳው ነበር፡፡ ኤር
32፣12-16 ነቢዩ ኤርምያስ ከጥቂት አይሁዶች ጋር ወደ ግብፅ እንዲጓዝ በተገደደ ጊዜ አብሮት ሄዷል፡፡
መጽሐፈ ባሮክ የተጻፈው የነቢዩ ኤርምያስ ደቀመዝሙር በነበረው ባሮክ ነው፡፡ መጽሐፉም ባሮክ በባቢሎን
በምርኮ በነበረበት ጊዜ ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ጽፎ የላከላቸው ነው፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል

ባሮክ 1-3 እስራኤላውያን በምርኮ ሲያዙ በኀጢያታቸው ምክንያት እንደደረሰባቸው አውቀው ስለ


መጸጸታቸው ና ስላቀረቡት የኀጢያት ኑዛዜ፤
ባሮክ 4-5 እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንዳጽናናቸው እና ስለተሰጣቸው ምክር
2.2 ሰቆቃወ ኤርምያስ
ሰቆቃ ማለት ሙሾ ልቅሶ ማለት ነው፡፡ ምንም እንኳን በመጽሐፉ የነቢዩ ኤርምያስ ስም ባይገለጽም
በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደታመነበት የመጽሐፉ ጸሐፊ ነቢዩ ኤርምያስ ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
መጽሐፉ በኢየሩሳሌም በጠላት እጅ አወዳደቋን የአጥሮቿንና የቤተመቅደሷ መፍረስን የንብረቷና የሕዛቧ
መማረክን መነሻ በማድረግ ነቢዩ ኤርምያስ ያቀረበውን ሰቆቃ (የኀዘን እንጉርጉሮ) ይዞ ይገኛል፡፡
መጽሐፉ በዚያን ጊዜ እናቶች ልጆቻቸውን እስከ መብላት ያደረሰውን አስከፊ ረኀብ ኢየሩሳሌም በጠላት
እጅ ስትወድቅ የካህናትና የነቢያት መገደል እንዲሁም ነቢዩ ራሱ በምርኮ የደረሰበትን ችግር በዝርዝር ይዟል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 76


በተጨማሪም ስለ እግዚአብሔር ቁጣና ቅጣት ማዳኑን ተስፋ ስለማድረግና ስለ ምሕረቱም ጭምር
የተገለጠበት መጽሐፍ ነው፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል

ሰ.ኤ 1- ስለ ኢየሩሳሌም መከራና ኀዘን


ሰ.ኤ 2- እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ላይ ስላመጣው ቅጣት
ሰ.ኤ 3- ስለ ቅጣት፤ ንስሓና ተስፋ
ሰ.ኤ 4- ስለ ኢየሩሳሌም ከውድቀት በላ
ሰ.ኤ 5- ምህረትን ለማግኘት ስለቀረበ ጸሎት
2.3 ተረፈ ኤርምያስ
ተረፈ ኤርምያስ ከሰቆቃወ ኤርምያስ ቀጥሎ ምዕራፍ 6 ብሎ የሚጀምር 6 ምዕራፎች ያሉት መጽሐፍ
ነው፡፡ ጸሐፊውም ባሮክ ነው፡፡ ተረ.ኤር 11፣63
መጽሐፉ ስለ ጣዖት አምልኮ ከንቱነት በስፋት ስለሚያትት ‘’አርአያ መጽሐፍ ዘኤርምያስ’’ ተብሎ
ይጠራል፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
መጽሐፉ ስለ ባቢሎን ምርኮና የምርኮውን ዘመን እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ ለባሮክና ለአቤሜሌክ
እንዳሳለፈላቸው እንዲሁም ስለ ኤርምያስ ሰማዕትነት ይገልጻል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
ይህ መጽሐፍ አንድ ምዕራፍ ብቻ ነው ያለው ሲሆን
ምዕራፍ 1፡- ////////////
ማስታወሻ
ሰቆቃወ ኤርምያስ ተረፈ ኤርምያስና መጽሐፈ ባሮክ ተረፈ ባሮክ በተጻፉበት ጊዜና የመጻሕፍቱ ይዘት
ተመሳሳይነት ምክንያት ዐራቱ መጻሕፍት ከትንቢተ ኤርምያስ መጽሐፍ ጋር በመደመር እንደ አንድ መጽሐፍ
ይቈጠራሉ፡፡

2.4 ተረፈ ባሮክ


የአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት እንደሚያስረዳው ተረፈ ባሮክ የመጽሐፈ ባሮክ ቀጣይ
ጽሑፍ በመሆኑ መጽሐፈ ባሮክ ተብሎ ይጠራል፡፡ በብሉይ ኪዳን ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍት ደግሞ ተረፈ
ኤርምያስ በሚለው ተካቶ ይገኛል፡፡ እግዚአብሔር ለባሮክ ለአቤሜሌክና ለኤርምያስ የተናገረው ቃል ነው፡፡
መጽሐፉ አምስት ምዕራፎችን የያዘ ሲሆን የጻፈውም የኤርምያስ ደቀመዝሙር ባሮክ ነው፡፡

3. ትንቢተ ሕዝቅኤል
ሕዝቅኤል ማለት ‹‹እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል›› ማለት ነው፤ አባቱ ቡዝ ይባላል፡፡ ሕዝቅኤል
በ 622 ዓመት ቅ.ል.ክ ክርስቶስ ተወለደ፤ ነገዱ ከቤተ ሌዊ፣ ትውልዱ ከቤተ ሳዶቅ ነው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ
የነቢዩ የኤርምያስ ደቀ መዝሙር እንደ ነበረ ይነገራል፡፡
ከክርስቶስ ልደት በፊት 597 ዓመት በንጉሥ ኢኮንያን ዘመን የእስራኤል ልጆች ወደ ባቢሎን በተማረኩ
ጊዜ ነቢዩ ሕዝቅኤል ከምርኮኞቹ አንዱ ነበር፤ በባቢሎን ምርኮ ይኖርበት የነበረው ቦታ በከበር ወንዝ አጠገብ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 77


ነበር፡፡ ሕዝቅኤል ሚስት፣ ቤትና ንብረት ነበረው፤ ነገር ግን በ 586 ዓመት ቅ.ል.ክ ኢየሩሳሌም ለመጨረሻ ጊዜ
በተወረረች ወቅት ሚስቱ ሞታለች፡፡ /ሕዝ 24፡15-24/
ምርኮ በሆነ በ 5 ኛው ዓመት በ 4 ኛው ወር ለነቢይነት ተጠራ፤ ንጉሥ ኢኮንያን የተማረከው በ 597
ዓመት ቅ.ል.ክርስቶስ ነው፤ በምርኮ ሳሉ ነቢዩ ሕዝቅኤልና ነቢዩ ዳንኤል ይተዋወቁ እንደነበር በትንቢቱ ላይ
ተጠቅሷል፡፡ /ሕዝ 14፡14፣ 28፡3/
ሕዝቅኤል በ 30 ዓመት ዕድሜው እግዚአብሔር በሱራፌልና በኪሩቤል ዙፋን ላይ ተቀምጦ ሳለ በራዕይ
ለመመልከት የበቃ ነው፡፡ /ሕዝ 1/ እግዚአብሔርም ሕዝቅኤል በምርኮ ሳለ ለተማረኩት ሕዝበ እስራኤል ነቢይ
ይሆን ዘንድ ጠራው ፡፡ /ሕዝ 2፡1-4/ ሕዝቅኤል በባቢሎን ሳለ ከ 592-570 ዓመት ቅ.ል.ክርስቶስ ለእስራኤል
ምርኮኞች ነው ትንቢት የተናገረው፤ የነቢዩ የአገልግሎት ዘመን በሁለት የተለያዩ ክፍሎች ሊከፈል ይችላል፡፡
ይኸውም፡-
1 ኛ ከክርስቶስ ልደት በፊት 587 ዓመት ኢየሩሳሌም በጠላት እጅ ከመውደቋ አስቀድሞ በባቢሎን
ምርኮኞች መካከል የፈጸመው የስብከት አገልግሎት /ሕዝ 4-24/
2 ኛ ኢየሩሳሌም በጠላት እጅ ከወደቀች በኋላ በባቢሎን የፈጸመው የስብከት አገልግሎት /ሕዝ 33-48/
ሕዝቅኤል በባቢሎን ለ 20 ዓመታት እያስተማረ ቆይቶ እዚያው በምርኮ ሳለ በሰማዕትነት ያረፈ ታላቅ
ነቢይ ነው፡፡
ይህን መጽሐፍ የጻፈው ከዐበይት ነቢያት የባቢሎን ነቢያትና በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ከነበሩት ነቢያት አንዱ
በሆነው በነቢዩ ሕዝቅኤል ነው፡፡ /ሕዝ 1፡3/፣ /ሕዝ 24፡2/፤ የተጻፈበት ዘመን ከ 592-570 ዓመት ቅ.ል.ክርስቶስ
ሲሆን ቦታውም በኢየሩሳሌም (በባቢሎን ምርኮ) ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ ፡- ስለ ኢየሩሳሌም ውድቀትና ከውድቀት መነሳት ፣ ስለ ምርኮውና ስለ ሕዝቡ፣ ስለ
ጌታችንና ስለ 5 ቱ አዕማደ ምስጢር፣ ስለ እመቤታችን ይናገራል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል፡-
ትንቢተ ሕዝቅኤል 48 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 4 ዋና ዋና ክፍሎችም ይከፈላል፡፡
ሕዝ 1-3፡2- በዚህ ክፍል ውስጥ እግዚአብሔር ለሕዝበ እስራኤል መልእክቱን ለማስተላለፍ ለነቢዩ
ሕዝቅኤል ያደረገለት ጥሪ፣ ሕዝቅኤል ይህን ኃላፊነት በሚገባ ካልተወጣ ስለሚጠብቀው ቅጣት፣ ነቢዩ
ስለተመለከታቸው ስለ ኪሩቤልና ስለ መንኮራኩሮቹ ራዕይ እና በራዕይ ስለተመለከተው የእግዚአብሔር
ግርማና ክብር እናገኛለን፡፡
ሕዝ 3፡3-24፡ ይህ ክፍል ስለ ሕዝቡ ክፉ ሥራና ጣዖት በማምለካቸው ወዮታ እንዳለባቸው በመግለጽ ነቢዩ
ሕዝቅኤል ያሰማው የማስጠንቀቂያ ቃል፣ ነቢዩ የኢየሩሳሌም ካርታ በተሠራበት ጡብ ምሳሌነት ገለጻ
ማድረጉ፣ በባቢሎንና በግብጽ ነገሥታት ተመስለው ነቢዩ ስለተናገራቸው ሁለት ንስሮች፣ ዝገት በበላው
ብረት ድስት ምሳሌ በኢየሩሳሌም ላይ የተሰነዘረው ወቀሳ፣ በመጨረሻም ለነቢዩ ሕዝቅኤል የዐይኑ
ማረፊያ የነበረችው ሚስቱ በቤተመቅደስ ሞት በቤተመቅደስ መፍረስና ለልጆቻቸው ሞት በዚህም
ለሚደርስባቸው ኃዘን ምሳሌ ይሆን ዘንድ የሚስቱ ሞት ተገልጽዋል፡፡
ሕዝ 25-33፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ነቢዩ በይሁዳ አካባቢ ስለነበሩት እንደ አሞን፣ ሞአብ፣ ኤዶም፣
ፍልስጤም፣ ጢሮስ፣ ሲዶናና ግብጽ ላይ የተነገራቸው ትንቢቶች ሰፍረዋል፡፡
ሕዝ 34-48፡ በዚህ ክፍል ውስጥ እግዚአብሔር ለነቢዩ የሰጠው ኃላፊነት በድጋሚ ቀርቧል፤ ለኃጢአተኛ
ሰው የማስጠንቀቂያ ትምህርት የመስጠት ኃላፊነት እንዳለበት ተገልጧለታል፡፡ በተጨማሪም በዚህ ክፍል

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 78


ነቢዩ ሕዝቅኤል ስለ ምስጢረ ጥምቀት፣ስለ ትንሣኤ ሙታን፣ ስለ እመቤታችን ዘለዓለማዊ ድንግልና፣ ስለ
ምስጢረ ሥጋዌ የተናገረው ይገኝበታል፡፡

4. ትንቢተ ዳንኤል
ነቢዩ ዳንኤል ማን ነው?
ነቢዩ ዳንኤል የዮናኪር የልጅ ልጅ ሲሆን በ 618 ዓመት ቅ.ል.ክርስቶስ ተወለደ፤ ዳንኤል የስሙ ትርጉም
እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው፡፡ ዳንኤል ከክርስቶስ ልደት 605 ዓመት በፊት በናቡከደነፆር ተማርኮ
ወደ ባቢሎን የተጓዘ አይሁዳዊ ነው፡፡ ዳንኤል ጠቢብ እና አስተዋይ ለቤተመቅደስም ተልዕኮ ብቁ የሆነ
የሃይማኖቱን ሥርዓት የሚጠብቅ ሰው ነበር፡፡ ዳንኤል በስደት ሀገር ስሙ ብልጣሶር ተባለ፣ የከለዳውያንንም
ትምህርት ተማረ ተምሮም በባቢሎን ተሾመ፡፡ ዳንኤል በምርኮ ሀገር ካገኘው ሹመት ጋር ባለ ትንቢትም
ነበር፤ በፆም፣ በጸሎት የሚተጋ ሰው ነበር፡፡
ዳንኤል በምርኮ ሀገር እያለ አራት የአሕዛብ ነገሥታትን አሳልፏል፡፡ እነርሱም፡ ናቡከደነፆር፣ ብልጣሶር፣
ዳርዮስ እና ቂሮስ ናቸው፡፡ እርሱም እነዚህን ነገሥታት በማስተማር ህልምን በመፍታት እና ጽሑፍን
በመተርጎም አገልግሏል፡፡ ዳንኤል ምንም እንኳ የአሕዛብ የመንግሥት ባለስልጣን ቢሆንም ለእግዚአብሔር
ሕዝብ እየጸለየ ሕዝቡ በአምልኮተ እግዚአብሔር እንዲጸና ያደረገ ነቢይ ነው፡፡ ነቢዩ ዳንኤል በብሉይ ኪዳን
የሚገኘውን ትንቢተ ዳንኤል፣ መጽሐፈ ሶስና፣ ተረፈ ዳንኤል እና ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅን የጻፈልን አባት ነው
፤ የኖረውም ከ 618-534 ዓመት ቅ.ል.ክርስቶስ ሲሆን በመጋቢት 23 እንዳረፈ ስንክሳር ያስረዳል፡፡
ትንቢተ ዳንኤልን ከቅዱሳት መጻሕፍት እና ቀኖና አንፃር ስናየው፡-
1. ነቢዩ ዳንኤል ረበናቱ ያልተቀበሉትን የጌታን ልደት እና ሞት በተመለከተ ዘመኑን ቁልጭ አድርጎ በመግለጡ
2. ሁሉም ነቢያተ እስራኤል ሙሉ ጊዜያቸውን ለነብይነት አገልግሎት ሲያውሉ ነብዩ ዳንኤል ግን በቤተ
መንግሥት በማገልገሉ
3. ነብያተ እስራኤል ሕዝቡን በየጊዜው ስለ ኃጢአታቸው ሲገስፁ ዳንኤል ግን ይህን ሲያደርግ ባለመታየቱ
4. ነብዩ ዳንኤል የትንቢቱ መጽሐፍ በምርኮ ጊዜ በመጻፉ የሚሉ ልዩ ልዩ ሀሳቦች ተሰጥተዋል፡፡
የመጽሐፉ ዓለማ
ዳንኤልና ሠለስቱ ደቂቅ (አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል) በሃይማኖታቸውና በሥርዓታቸው በመጽናት በባዕድ
አገር ለእግዚአብሔር ታማኝ ስለሆኑ መከራ ቢደርስባቸውም እርሱ እንደሚጠብቃቸው፤ እግዚአብሔር የዚህ
ዓለም መንግሥታትን እንደሚቆጣጠርና የራሱ መንግሥት ደግሞ ዘላለማዊ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
ይህ መጽሐፍ ዐሥራ ሁለት ምዕራፍ ሲኖረው ከምዕራፍ አንድ እስከ ስድስት የታሪክ ክፍል ሲሆን ከሰባት
እስከ ዐሥራ ሁለት ያለው የራዕይ ክፍል በመባል ተሰይሟል፡፡
የየምዕራፉ ዐበይት መልእክታትና ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ዳን 1፡ የዳንኤል በባቢሎን መማረክንና በዚያም ዳንኤል በንጉሡ መሾሙን ይገልጣል፡፡
ዳን 2፡ ዳንኤል፣ ናቡከደነፆር የተመለከተውን ታላቅ ህልም የተረጎመበት ክፍል ነው፡፡
ዳን 3፡ በባዕድ ሀገር አናንያ፣ አዛርያ እና ሚሳኤል ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል አንሰግድም
በማለታቸው ወደ እቶን እሳት መጣላቸውና በእግዚአብሔር አዳኝነት በመልአኩ ተራዳኢነት መዳናቸውን
ይገልጻል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 79


ዳን 4፡ ዳንኤል ሁለተኛው የናቡከደነፆር ህልም መተርጎሙን እና የተረጎመው ህልም ፍጻሜም ምን
እንደሆነ ይገልጻል
ዳን 5፡ ዳንኤል በግድግዳ ላይ ስለ ንጉሡ ብልጣሶር የተጻፉትን ‹ማኔ ቴቄል ፋሬስ› የሚሉትን ቃላት
የተረጎመበትና የእግዚአብሔርን ሥራ ያሳየበት ነው፡፡
ዳን 6፡ ዳንኤል በዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ወደ አንበሶች ጎድጓድ መጣሉና በዚያም እግዚአብሔር
መልአኩን ልኮ እንዳዳነው ይገኝበታል፡፡
ዳን 7፡ በምዕራፍ ሁለት ላይ የተገለጡትን አራት መንግሥታት በአራት አራዊት እንደሚመሰሉ ዳንኤል
በራዕይ እንደተመለከተና ግዛት እና መንግሥት ለሰው ልጅ ለሚመስል (ለክርስቶስ) መሰጠቱን ይገልጻል፡፡
ዳን 8፡ ዳንኤል በኩባል ወንዝ አጠገብ ሆኖ የተገለጠለት ራዕይ ምን እንደነበር እና የራዕዩን ምስጢር
የተነተነበት ምዕራፍ ነው፡፡
ዳን 9፡ ዳንኤል ከምርኮ ስለመመለስ መጸለዩና መሲህ እስኪመጣ ሰባ ሱባኤ እንደሚያልፍ ትንቢት መናገሩ
ይገኛል፡፡
ዳን 10-12፡ በዚህ የመጽሐፍ ክፍል ውስጥ ከታላቁ እስክንድር በኋላ በሶርያ እና በግብጽ መንግሥታት
መካከል ስለሚደረገው ጦርነት፣ ስለ እግዚአብሔር ሕዝብ መከራ ትንቢት የተናገረበት ነው፡፡
ከዚህ በመቀጠል በሰማንያ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ ከትንቢተ ዳንኤል መጽሐፍ ጋር ተደምረው
ስለሚቆጠሩት መጽሐፈ ሶስና፣ ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ እና ተረፈ ዳንኤል ስለሚባሉት ቅድሳት መጻሕፍት
ይዘት ይቀርባል፡፡

4.1 መጽሐፈ ሶስና


ሶስና በሚል ርዕስ የምናገኘው ይህ መጽሐፍ በነብዩ ዳንኤል የተጻፈ ባለ አንድ ምዕራፍ መጽሐፍ ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ፡- ሶስና ከነዳንኤል ጋር በፋርስ በስደት የነበረች ሴት ናት፤ ይህች ሴት በዘመኑ ለነበሩ ሁለት
አይሁድ መምህራን /ረበናት/ ፈቃዳቸውን አልፈጽምም በማለቷ በሐሰት በዝሙት ወንጀል የሞት ፍርድ
አስፈረዱባት፤ በዚህን ጊዜ የሞት ፍርዱ በድንጋይ ወገራ ሊፈጽምባት ሲል ነቢዩ ዳንኤል የእግዚአብሔር
ጥበብ በሞላበት ዘዴና ፍርድ እንዴት እንዳዳናት መጽሐፉ ይገልጻል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
ይህ መጽሐፍ አንድ ምዕራፍ ሲኖረው በውስጡም ስድሳ ስድስት ቊጥሮችን ይዟል፡፡ በሦስት ዐበይት
ክፍሎችም ይከፈላል
ሶስ 1፡ 1-14 ፡- የሶስና አስተዳደግና የሁለት መምህራን ተንኮል
ሶስ 1፡ 14-23 ፡- መምህራን ሶስናን በሐሰት መክሰሳቸውና የሶስና ጸሎት
ሶስ 1፡ 44-66 ፡- ነቢዩ ዳንኤል በጥበበ እግዚአብሔር እንዴት እንዳዳናት ሐሰተኞቹ መምህራን
መቀጣታቸው
4.2 ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ
የስሙ ትርጉም የሦስቱ ልጆች መዝሙር/ጸሎት/ ማለት ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ እንደ መጽሐፈ ሶስና ባለ
አንድ ምዕራፍ ሲሆን በነቢዩ ዳንኤል የተጻፈ ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
ይህ መዝሙር ከነብዩ ዳንኤል ጋር ወደ ባቢሎን ተሰደው የነበሩት አናንያ፣ አዛርያ እና ሚሳኤል /ሠለስቱ
ደቂቅ/ ታሥረው ወደ የሚነድ እቶን እሳት በተጣሉ ጊዜ ለልዑል እግዚአብሔር ያቀረቡትን ጸሎት እና
ምሥጋና የሚገልጽ ነው፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 80


ይህ መጽሐፍ አንድ ምዕራፍናስድሳ ስድስት ቊጥሮችን ይዟል፡፡በሁለት ዐበይት ክፍሎችም ይከፈላል
ሠለ.ደቂ 1፡ 1-25፡- የአናንያን ፀሎት እና መልዐኩ እሳቱን ማብረዱ
ሠለ.ደቂ 1፡ 26-66፡- ሦስቱም በህብረት የዘመሩት ዝማሬ
4.3 ተረፈ ዳንኤል
ተረፈ ዳንኤል በነብዩ ዳንኤል የተጻፈ አንድ ምዕራፍ ብቻ ያለው መጽሐፍ ነው፤ በመጽሐፉ በዳንኤል ላይ
ከምናገኘው ታሪክ ጋር ተመሳሳይነት ያለው እና ታሪኩም በስፋት የተነተነበት ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
መጽሐፉ የባቢሎን ሰዎች ያመልኳቸው የነበሩትን ጣዖታት ገብቶ ዳንኤል እንዴት እንዳጠፋ እና ነቢዩ ዳንኤል
እግዚአብሔር ከአንበሶች አፍ እንዳዳነው የሚገልጽ መጽሐፍ ነው፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
ይህ መጽሐፍ አንድ ምዕራፍና 42 ቊጥሮች ሲኖረው በሁለት ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡
ተረ.ዳን. 1፡1-28፡- ነቢዩ ዳንኤል ቤልን እንዳጠፋው
ተረ.ዳን 1፡29-42 ነብዩ ዳንኤል በአንበሳ ጉድጓድ ተጥሎ እንዴት እንዳደገ
ደቂቀ ነቢያት

1. ትንቢተ ሆሴዕ
ይህ መጽሐፍ 14 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን ጸሐፊው ነቢዩ ሆሴዕ ነው፡፡ ሆሴዕ ማለት እግዚአብሔር
ያድናል ማለት ነው፡፡ ሆሴዕ አባቱ ብኤረ ይባላል፡፡ ይህ ነቢይ ዳግማዊ ኢዮርብዓም በሰማርያ ነግሦ በነበረበት
ዘመን በሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት የተነሣ ሲሆን በዘመኑም ዖዝያን፣ ኢዮአታም፣ አካዝና ሕዝቅያስ
የተባሉ የይሁዳ ነገሥታትን አሳልፏል፡፡ ከጌታችን ልደት በፊት 700 ዓመት ቀድሞ እንደነበር መጻሕፍት
ተባብረውበታል፡፡ ከነቢያት መካከል የኢሳይያስ፣ የኢሞጽና የሚክያስ የዘመን ኋደኛ ነበር፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
 ኃጢአተኛ ዐመጸኛና አመንዝራ የሆነው ሕዝበ እስራኤል አለመታመንና ለእነርሱ የእግዚአብሔር ፍቅርና
ጸጋ ምን ያህል እንደሆነ ለመግለጥ
 የእስራኤልን አምልኮተ ጣዖት ለባልዋ ታማኝነት በሌላት በአመንዝራ ሴት በመመሰል ሆሴዕ አመንዝራዋን
ሚስቱን እንዲታረቅ፣ እግዚአብሔርን ትተው ወደ አምልኮተ ጣዖት የሔዱትን ሕዝበ እስራኤል ቢመለሱ
እግዚአብሔር በፍቅር የሚቀበላቸው መሆኑን ለማመልከት
 በግልሙትና ከተመሰለው ኃጢአታቸው እንዲመለሱ ‹‹እስራኤል ሆይ ወደ ፈጣሪህ ወደ እግዚአብሔር
ተመለስ›› በማለት ንስሐን ለማወጅ
 እግዚአብሔር የማይለወጥ አምላክ በመሆኑ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ በመመለስና
ተመልሰውም በመንፈስ እንዲድኑ ጥሪ ለማስተላለፍ ነበር፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል፡-
ይህ መጽሐፍ በ 5 ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡
ሆሴ 1-3፡ የእስራኤል ልጆች እግዚአብሔርን ጣዖት በማምለካቸው ምክንያት ስለማሳዘናቸውና
ስለሚደርስባቸው ቅጣትና ተግሣጽ
 እግዚአብሔር ፍቅሩን ከእስራኤል ሕዝብ ላይ ሙሉ በሙሉ ያላነሣ መሆኑንና ንስሐ ቢገቡ ይቅርታ
እንደሚያደርግላቸው

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 81


 ሕዝበ እስራኤል በኃጢአታቸው ምክንያት ያለ ንጉሥ፣ ያለ መሪ፣ ያለ መሥዋዕት ፣ ያለ ልብሰ
ተክህኖ፣ ያለ ሐውልት፣ ያለ መተንበያ ምስል ለብዙ ዘመን እንደሚኖሩ የተነገረ ትንቢትን አካቶ
ይዟል፡፡
ሆሴ 4-6፣ 3 ፡ ሕዝቡና ካህናቱ እግዚአብሔርን በማሳዘናቸው የተሰነዘረባቸው ወቀሳዎች
 ስለ ኃጢአታቸው ምክንያት ምድሪቷ ደረቅ እንደምትሆን፣ ነዋሪዎቹ፣ እንስሳት፣ አዕዋፍና የባሕር
ዓሣዎች ሁሉ እንደሚያልቁ የተነገረ ትንቢት
 በንስሐ የሚመለሱ ሰዎች ግን ተስፋ እንዳላቸውና እግዚአብሔር ይቅር፡ እንደሚላቸው ተጽፏል፡፡
ሆሴ 6፡4-8፡ እስራኤላውያን የሃይማኖትን የዓለማዊ መሪነት ቦታን ተገቢ ላልሆኑ ሰዎች በመስጠታቸው
በነቢዩ የደረሰባቸው ወቀሳ
ሆሴ 9-13፣ 3 ፡ በሕዝበ እስራኤል ላይ እግዚአብሔር የተናገረውን ወቀሳና በንስሐ እንዲመለሱ የቀረበ
ጥሪ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከግብጽ ስደት መመለስ
ከእስራኤል ልጆች ከግብጽ መውጣት ጋር ምሳሌነት እንዳለው፡፡
ሆሴ 13፣ 14-14፡ መታዘዝን ገንዘብ ያደረጉ ሰዎች በረከት እንደሚያስገኝና የመዳን ተስፋ
እንደሚሰጣቸው ይገልጣል፡፡

2. ትንቢተ አሞጽ
የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ ከበግ እረኝነትና የሾላ ፍሬ ከመጠበቅ ለነቢይነት የተጠራው ነቢዩ አሞጽ ነው፡፡
(አሞ 7፡14) አሞጽ ማለት ኃይል ማለት ነው፡፡ ትውልዱ ከነገደ ስምዖን ሲሆን አባቱ ቴና እናቱ ሚስታ ይባሉ
ነበር፡፡ አሞጽ በዕለታዊ ተግባሩ ተሠማርቶ ሳለ ለሰሜኑ ሕዝብ ነቢይ እንዲሆን እግዚአብሔር ጠራው፡፡ ይህ
ነቢይ ሥራውን የጀመረው በይሁዳ ዖዝያን፣ በእስራኤል ደግሞ ዳግማዊ ኢዮርብዓም ነግሠው በነበረበት
ዘመን ማለትም ከ 793-733 ቅ.ል.ክ ሲሆን ሁለቱን ጨምሮ አካዝ፣ ኢዮአታምና ሕዝቅያስ የተባሉ ነገሥታት
አሳልፏል፡፡ ይህ ነቢይ በ 2 ኛ ነገ 19፡20 ላይ የተገለጸው የነቢዩ ኢሳይያስ አባት የሆነው አሞጽ አይደለም፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
 እግዚአብሔር ለኃጥአን የሚያደርገውን ምህረት ለማስረዳት
 የፍርድ ቀን እንደደረሰና እስራኤላውን ፍርድ እንደሚቀበሉ፣ በመጨረሻም ለእስራኤላውያንም ሆነ
ለአሕዛብ የደኅንነትና የሰላም ጊዜ እንደሚመጣ የሐዲስ ኪዳንን ዘመን በትንቢት ለማመልከት
የመጽሐፉ አከፋፈል፡-
ትንቢተ አሞጽ 9 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 3 ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡
አሞ 1-2፡ በእስራኤላና በአጎራባቾቿ (ሶርያ፣ ፍልስጤም፣ ጢሮስ፣ ኤዶም፣ ቴማን፣ ሞዓብ፣ ይሁዳ)
የእግዚአብሔር ፍርድ እንደደረሰባቸው
አሞ 3-6፡ ሕዘበ እስራኤል የተደረገላቸውን የንስሃ ጥሪ ባለመቀበላቸው የተነገረው የትንቢት ቃል
ተግባራዊ እንደሚሆን በድጋሚ ማስጠንቀቂያ ስለመሰጠቱ
አሞ 7-9፡ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ ስለሚያመጣው ፍርድ በራዕይ ለአሞጽ እንዳሳየው፣
እንዲሁም በፍጻሜው ዘመን (በዘመነ ሐዲስ) ስላለው ተስፋ

3. ትንቢተ ሚክያስ
ይህ መጽሐፍ ከጌታችን ከአምላካችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ከ 700 ዓመታት በፊት
በነበረው በነቢዩ ሚክያስ የተጻፈ ነው፡፡ ሚክያስ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔርን የሚመስል ማን ነው? ማለት
ሲሆን አንድምታዊ ፍቺውም እግዚአብሔርን የሚመስል አዳም (ሰው) ነው የሚል ነው፡፡ ሰውን እንደ
አርአያችንና እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር እንዲል ዘፍ….፤ ይህ ነቢይ በ 1 ኛ ነገ 22፡8 ላይ ከተጠቀሰው በይሁዳ
ንጉሥ በኢዮሳፍጥና በእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ዘመን ከነበረው ነቢዩ ሚክያስ የተለየ ነው፡፡ ይህንን ትንቢት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 82


የጻፈው ነቢይ ከይሁዳ ግዛት ሲሆን ያኛው ሚክያስ ግን ነዋሪነቱ በእስራኤል ግዛት ውስጥ ነበር፤ የኖረውም
የይሁዳ ነገሥታት ኢዮኣታም፣ አካዝና ሕዝቅያስ በተከታታይ በነገሡበትና ፣ በእስራኤል ደግሞ ፋቁሔና
ሆሴዕ በነገሡበት ዘመን ነው፡፡
በዘመኑም ኢሳይያስ፣ ሆሴዕና አሞጽ ትንቢት ይናገሩ ነበር፡፡ ሚክያስን ከነቢያት ሁሉ የተለየ ብቸኛ
የሚያደርገው ስለ ሁለቱም መንግሥታት (ስለ ሰሜኑና ደቡብ) በአንድነት ስለጻፈና ስለተናገረ ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
 ነቢዩ ትንቢት የተናገረው ከሰማርያ ውድቀት በፊት ስለነበር ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም መፍረስ
ትንቢት ለመናገር
 ሕዝቡ ፍቅር፣ ርኅራኄ፣ ትሕትና፣ መታዘዝ ሳይኖራቸው ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ስጦታ ሁሉ
በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው በማስረዳት በዚህ ፈንታ ሊያቀርቡት የሚገባቸውን
ለመንገር
 ስለ መሲሕ መምጣትና ስለ አድኅኖቱ ለመናገር
 ኢሳይያስ ክርስቶስ ከማን እንደሚወለድ ገልጦ እንደተናገረ ፤ሚክያስ ደግሞ በየት እንደሚወለድ
ለመግለጥ
የመጽሐፉ አከፋፈል
መጽሐፉ 7 ምዕራፎች ሲኖሩት አጠቃላይ ይዘታቸው እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ሚክ 1፡ በሰማርያና በኢየሩሳሌም የነበሩ ሕዝቦች ስለበደላቸው ምክንያት የተላለፈባቸውን ፍርድ
በትንቢት መልክ ይነግረናል፡፡
ሚክ 2፡ በተፈፀሙት በደሎች ምክንያት የቀረቡት ወዮታዎች ተዘርዝረውበታል
ሚክ 3፡ ለያዕቆብ ልጆች መሪዎች የተደረገ ጥሪ፣ መሪዎች በሕዝቡ ላይ ለፈጸሙት በደል ወቀሳ
እንደደረሰባቸውና እንዲያቆሙ ስለተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ
ሚክ 4፡ የእግዚአብሔር ቤት (ቤተ ክርስቲያን) በተራራው ጫፍ ላይ ስለሚሠራበት ሁናቴ፣
እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ላይ ንጉሥ ስለ መሆኑ
ሚክ 5፡ የእስራኤል ገዥ በኢየሩሳሌም እንደሚወለድ በዚህም ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ መምጣት ቀዳማዊነቱን፣ ዘላለማዊነቱን በግልፅ ትንቢት የተናገረበት ክፍል ነው፡፡
ሚክ 6፡ ሕዝበ እስራኤል የእግዚአብሔርን ሕግ ስለመተላለፋቸው ይነግረንና በዚህም እግዚአብሔር
አምላክ ‹‹ምን በደልኳችሁ?›› ‹‹ምን ያላደረግሁላችሁ ነገር አለ?›› እያለ እንደሚፈርድባቸው ነቢዩ
የተናገረው ቃል ይገኝበታል፡፡
ሚክ 7፡ ምንም እንኳ ሕጉን ባይጠብቁም ለያዕቆብ በገባው ቃል መሠረት ለልጆች እንደሚፈርድላቸው የተናገረውን
የተስፋ ቃል ይዟል፡፡

4. ትንቢተ ኢዩኤል
ትንቢተ ኢዩኤል በነቢዩ ኢዩኤል ከጌታ ልደት 600 ዓመታት በፊት የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ ኢዩኤል
ማለት እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው፤ ነገዱ ከነገደ ሮቤል ሲሆን አባቱ ባቱኤል እናቱ መርሱስ
ይባላሉ፡፡ ይህ ነቢይ ከነቢይነቱ በተጨማሪ ካህን እንደ ነበር ይነገራል፤ ኢዩኤል አገልግሎቱ በይሁዳ መንግሥት
ሲሆን በመጀመሪያ ለአገልግሎት የተጠራበት ምክንያት በሕዝቡ ላይ ሊወርድ ስላለው የአንበጣ መንጋ ጾምና
ጸሎት ይደረግ ዘንድ ሕዝቡን እንዲያስጠነቅቅ ነው፡፡ በኢዩኤል ትንቢት በጣም የሚታወቀው ክፍል
እግዚአብሔር በመጨረሻው ክፍለ ዘመን (በዘመነ ሐዲስ) በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ
ለማፍሰስ የሰጠው ተስፋ ነው፡፡ (ኢዩ 2፡ 28-30)
የመጽሐፉ ዓላማ
 ሕዘቡ ከእግዚአብሔር መአትና ቁጣ እንዲድኑ የሚመጣውን የእግዚአብሔር ፍርድ በመግለጥ ንስሐ
እንዲገቡና እንዲጾሙ ለማስጠንቀቅ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 83


 የሚመጣውን ድኅነትና የጠላቶቻቸውን ድምሳሴ በማስታወስ እግዚአብሔር ለሚሰጠው ተስፋ
የሕዝቡ ልብ እንዲሆን ለማድረግ
 በኋለኛው ዘመን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለሰው ሁሉ እንደሚታደል ለመግለጥ
የመጽሐፉ አከፋፈል
መጽሐፉ 3 ምዕራፎች ሲኖሩት የየምዕራፉ አጠቃላይ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ኢዩ 1፡ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁናቴ ከፍተኛ የአንበጣ መንጋ መጥቶ ሰብልንና ዛፎችን ሁሉ
ስለሚያጠፋ ሕዝቡ ሁሉ በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ይጮኹ ዘንድ ያሳስባል፡፡
ኢዩ 2፡ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ እንዴት ንስሐ እንደሚገባ የውሳኔ ሀሳብ ተይዞ ወደ ንስሐ
አባት እንደማይቀረብ፣ ከንስሐ በኋላ ድኅነትን ስለመታደል፣ ቁሳዊና መንፈሳዊ በረከቶችን
ስለማግኘት፣ በኋለኛው ዘመን (በዘመነ ሐዲስ) ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እንደሚታደል የተነገረበት ክፍል
ነው፡፡
ኢዩ 3፡ የማይታዘዙ ሰዎች ከእግዚአብሔር ዘንድ ቅጣት እንደሚቀበሉና ለሚታዘዙት ደግሞ በረከት
እንደሚሰጣቸው ተነግሯል፡፡

5. ትንቢተ አብድዩ
አብድዩ ማለተ የጌታ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ከጌታ ልደት 600 ዓመታት በፊት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ይህ
ነቢይ ኤልዛቤል የእገዚአብሔር ነቢያትን ባስገደለበችበት ወቅት መቶውን ነቢያት ወስዶ ወደ ዋሻ በመሸሸግ
ያዳነ ነቢይ ነው፡፡ ነቢዩ አብድዩ በኤዶማውያን (የዔሳው ዘሮች) ትዕቢትና ትምክህት ስለሚመጣው ፍርድ
ተንብይዋል፣ ጽፏል፡፡ ትንቢቱን የተናገረው በይሁዳ ንጉሥ በአክዓብ ዘመን እንደሆነ ይነገራል፤ ይህ ትንቢት 21
ቁጥሮች ያሉት ባለ 1 ምዕራች መጽሐፍ ነው፡፡

የመጽሐፉ ዓላማ
 የኤዶማውያንን በአይሁድ ላይ ማመጽ፣ ትዕቢትና ውርደት ለመግለጥ
 በሚመጣው የእግዚአብሔር ቀን ኤዶማውያን በኃጢአታቸው ምክንያት እንደሚቀጡ ለማስረዳት
 በመጨረሻ ድኅነት ለእስራኤል፣ መንግሥትም ለእግዚአብሔር እንደሆነ ለማስረዳት
የመጽሐፉ አከፋፈል
ይህን መጽሐፍ በሦስት ክፍል በመክፈል ማጥናት ይቻላል፡፡
አብ 1፡1-9- በኤዶማውያን ላይ ስለሚፈጸመው ፍርድ ይናገራል፡፡
አብ 1፡10-14- በኤዶማውያን በእስኤላወያን ላይ ስለፈጸሙት በደል ያትታል፡፡
አብ 1፡15-21- ኤዶማውያነና አሕዛብ ስለሠሩት በደል ፍርድ እንደሚያገኙና እስራኤላውያን ነጻ
ወጥተው ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ይገልጽልናል፡፡

6. ትንቢተ ዮናስ
ዮናስ ማለት ርግብ ማለት ነው፡፡ በገሊላ ውስጥ የምትገኘው የጋትሔፈር ሰው የአማቴ /አሚቴ/ ልጅ
ነው ፤ የነቢዩ ኤልያስ ደቀመዝሙርም ነበረ፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመን በሰሜን የእስራኤል መንግሥት
የተነሣ ነቢይ ሲሆን ከኤልያስ ጋር ሳለም ሀብተ ትንቢት ተሰጥቶት ነበርና ባለ 4 ምዕራፍ የሆነው ትንቢትን
ተንብየዋል፡፡ ይህም ዘመን ከጌታ ልደት በፊት 400 ዓመታት ገደማ ነው፡፡ በአይሁዳውያን ልማድ
እንደሚጠቀሰው በሰራጵታ ትኖር የነበረችው ባልቴት ከሞትም ኤልያስ ያሥነሳላት ልጅ ነው ይባላል፡፡
መጽሐፉ ነቢዩ ዮናስ ወደ አሕዛብ ሀገር ነነዌ ወደ ተባለችው ከተማ በመሔደ በሕዝቡ ላይ
የተቃጣውን ፍርድ ለነነዌ ሰዎች በመንገር በንስሐ እንዲመለሱና ከእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደደረሰው
ይገልጣል፡፡ ነገር ግን ዮናስ ትእዛዘ እግዚአብሔርን ባለ ማክበር ወደ ተርሴስ እንደተጓዘና በጉዞው ወቅት
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 84
በተነሣው ማዕበል ምክንያት እግዚአብሔር ባወቀ በባለመርከበኞች ወደ ባሕር ተጥሎ በዓሣ አንበሪ ሆድ 3
ቀንና ሌሊት አድሮ በመጨረሻም ነነዌ ደርሶ የንስሐ ስብከት በማሰማት ሕዘቡን ከጥፋት እንዳዳነ ይገልጻል፡፡
የዮናስን ትንቢት የሰሙት የነነዌ ሰዎች ዛሬ ቃሉን ሰምተው ንስሐ ለሚገቡት ምዕመናን ምሳሌዎች ናቸው፡፡
ነቢዩ ዮናስ በትንቢቱ በአንድምታዊ ፍቺ የጌታቸንን ሞትና ትንሣኤ መስሎ አስረድቶናል፡፡

ይህ መጽሐፍ ከሎሎች ለየት የሚያደርገው ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ምዕራፍ ስለ ጸሐፊው


ነቢይ ታሪክ የሚተርክ በመሆኑ ነው፡፡

የመጽሐፉ ዓላማ
 ዮናስ ከእስራኤል ወደ አሕዛብ የተላከ ነቢይ በመሆኑ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ያለውን ፍቅር ለመግለጥ
 ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ፣ በጠቅላላ በዓለም ላይ እንደሚፈርድና ጸጋውና
ክብሩም በሚከተሉት ላይ እንደሆነች ለማመልከት ሲሆን፤ እግዚአብሔር የእስራኤል ብቻ ሳይሆን
የአሕዛብም አምላክ እንደሆነና እስራኤላውያንም ለአሕዛብ ብርሃን እንጂ ጠላት መሆን
እንደሌለባቸው፣ የእግዚአብሔርን ቸርነት ለማመልከትና እግዚአብሔር አሕዛብ እንዲጠፉና
የማይፈልግ ርኅሩኅ አምላክ በመሆኑ በንስሐ ወደ እርሱ የተመለሱነትን ሁሉ በምሕረት እንዲጎበኝ
ለማሳየት ነው፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
ይህ መጽሐፍ በ 4 ክፍሎች የሚከፈል ሲሆን እነርሱም፡
ዮና 1- ወደ ነነዌ እንዲሄድ የቀረበለትን ጥሪና አሻፈረኝ በማለቱ የገጠመውን ችግር እንመለከታለን፡፡
ዮና 2- ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ሳለ ያሰማው ጸሎትና ጸሎቱም ተሰምቶ ወደ ቀድሞ ግብሩ
(ሥራው) መመለሱ
ዮና 3- ለነነዌ ሕዝብ የሚድኑበትን መንገድ መንገሩና እርሱን በመተግበራቸው ከመአቱ እንዳመለጡ
ምሕረት እንደተደረገላቸው
ዮና 4- ነቢዩ በከተማይቱ መዳን እንዳልተደሰተና እግዚአብሔርም ቅልን ምሳሌ በማድረግ ምሕረት
መልካም መሆኑን እንዳስተማረው ይነግረናል፡፡

7. ትንቢተ ናሆም
ናሆም ማለት መጽናናት ማለት ነው፤ ነገዱ ከነገደ ይሁዳ ሲሆን ከጌታ ልደት 700 ዓመታት በፊት
የተነሣ ነቢይ ነው፡፡ ከነቢያት መካከል የሆሴዕ፣ የሶፎንያስ፣ የዕምባቆምና የኤርምያስ የዘምን ጓደኛ ነበር፤
ከአነጋገሩ እንደሚታየው በነቢዩ ኢሳይያስ ዘመንና በንጉሥ ሕዝቅያስ ዘመን እንደነበር ይገመታል፡፡
መጽሐፉ የእስራኤልን መጽናናትና የነነዌን ፍርድ በአንድነት የያዘ ነው፤ ስለ ይሁዳ ሕዝብ
ከአሶራውያን ነጻ መውጣትና ስለ ነነዌ ዳግም መጥፋት የተነበየ ነቢይ ነው፡፡ ነነዌ በዮናስ ንስሐ ብትገባ
እንደምታመልጥ ሲነገር በናሆም ጊዜ ግን በቀጥታ ስለ ውድቀቷ ብቻ ነበር የተናገረው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
 ስለ ይሁዳ መጽናናትና ሁሉን ቻይ ስለሆነው እግዚአብሔር ትእግስት ለመናገር
 በቀል የእኔ ነው በሚለው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት የእስራኤል ሕዝብ ጠላት የነበረቸውን ነነዌን
ከጥፋት ከተመለሰች በኋላ ባሳየቸው ጭካኔ እግዚአብሔር የሚበቀላት መሆኑን ለመግለፅ
 ነነዌና አሦር ምን ታላቅ ከተማና ገናና መንግሥት ቢሆኑም በእግዚአብሔር ኃይል ስላልነበሩ
መጥፋታቸውን ለማሳወቅ
የመጽሐፉ አከፋፈል
መጽሐፉ 3 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን አከፋፈሉም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ናሆ 1- እግዚአብሔር የፍርድና የበቀል አምላክ እንደሆነ ፍርዱም እንደማይዛባና ሰው ደግሞ ስለ
ሠራው በደል ዋጋውን እንደሚቀበል፤

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 85


ናሆ 2- በጭካኔ በድፍረት እስራኤላውያንን የሚያስጨንቁትን እግዚአብሔር በጠላትነት
እንደሚነሳባቸው እንዲሁም ስለ ነነዌ ዳግም ጥፋትና ወደ ቀደመ ግብሯ (ሥራዋ) መመለሷን
ያትታል፡፡
ናሆ 3- ነነዌ የጠፋችበትን ምክንያት ይዘረዝርልናል፡፡

8. ትንቢተ ዕንባቆም
ትንቢተ ዕንባቆም ከጌታ ልደት 600 ዓመታት በፊት የተጻፈ መጽሐፍ ሲሆን ጸሐፊው ዕንባቆም
ይባላል፡፡ ዕንባቆም ማለት እቅፍ ማለት ነው፤ ነገዱ ከነገደ ሌዊ ሲሆን አባቱ ኢያሱ በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ
ነቢይ ያላገባ ድንግል፣ ካህንና የቤተመቅደስ ዘማሪ የነበረ እንደሆነ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ በሌላ ታሪክ ደግሞ
ዳንኤል በባቢሎን ተማርኮ ሳለ ዕንባቆም ለአጫጆች ምሳ ይዞ ሲሄድ የእግዚአብሔር መልአክ በራሱ ጠጉር
አንጠልጥሎ ወደ ባቢሎን ወስዶ ለዳንኤል ምግብ እንዳቀበለው ተተርኳል፡፡
መጽሐፉ የአይሁድ ሕዝብ በኃጢአት ስለሚደርስበት መከራ፣ ከለዳውያን በሚገዟቸው ሕዝቦች
ባደረሱት ግፍ የሚደርስባቸውን ቅጣትና ነቢዩ የጸለየውን ጸሎት የያዘ ነው፤ ዕንባቆም ብዙ በደልና ክፋትን
ስለተመለከተ እግዚአብሔር እንደቸርነቱ ብዛት የማይፈርድ መስሎት ደጋግሞ ጠይቆታል፡፡ ይህ ነቢይ
ትንቢቱን የተናገረው በይሁዳ ኢዩአቄም በነገሠበትና ነቢዩ ኤርምያስ በነበረበት ዘመን ነው፡፡

የመጽሐፉ ዓላማ
 የእግዚአብሔር ፍርድ ፣ የኢየሩሳሌም መደምሰስና በእግዚአብሔር ኃይል የሚያምነውን ሀገረ
ባቢሎንን ለማሳየት
 ጻድቅን ደግሞ ስለ እምነቱ የሚያድነው መሆኑም ለማሳወቅ
የመጽሐፉ አከፋፈል
መጽሐፉ ሦስት ምዕራፎች ሲኖሩት የየምዕራፉ መልእክትም የሚከተለው ነው፡
ዕን 1- ዕንባቆም ኃጢአት ሲበዛ የጸለየውን ጸሎትና ጸሎቱ እንደተሰማ፤ እግዚአብሔርም በሰጠው
መልስ በባቢሎናውያን መሣሪያነት ቅጣት እንደሚያመጣና ጊዜው ሲደርስም ነቢዩ ትንቢት
እንዲናገር ማዘዙ
ዕን 2- ከለዳውያን (ባቢሎናውያን) በትዕቢታቸው፣ በግፍ ሥራቸው፣ ሌሎች ሀገራትን በግድ
በማስገበራቸው፣ በዝርፊያቸውና ጣዖትን በማምለካቸው ምክንያት ስለሚያገኛቸው ችግርና ቅጣት
የተተነበየበት ክፍል ነው፡፡
ዕን 3- ነቢዩ እግዚአብሔር ለሕዝብ ያደረገውን ጥበቃ በማሰብ የጸለየውን የምሥጋና ጸሎት፣ ወደ
ፊትም እስኤራላውያን መልካም ሥራቸውን እንዲጠብቁ፣ የእግዚአብሔር ርዳታና ጥበቃ
እንዳይለያቸው ያቀረበው ተማጽኖ ይገኝበታል፡፡

9. ትንቢተ ሶፎንያስ
ይህ የትንቢት መጽሐፍ ከጌታ ልደት 700 ዓመታት በፊት በይሁዳ በነበረው ነቢይ ሶፎንያስ የተጻፈ
ነው፤ ሶፎንያስ የስሙ ትርጓሜ እግዚአብሔር ሰውሯል (ጠብቋል) ማለት ነው፤ ነገዱ ከነገደ ንፍታሌም ሲሆን
እናቱ ንሠባ ትባላለች፡፡ በሶፎ 3 ላይ የተጠቀሰው ሕዝቅያስ አያቱ ሲሆን የኢዮስያስ የአጎት ልጅ እንደነበረም
ይተረካል፡፡
ካህናትና ነቢያት በዘመኑ በብልጽግና ሥራ፣ በጣዖት የአምላክን ቤተመቅደስን በማርከስና
የእግዚአብሔርን ሕግ በመጣስ የታወቁ ነበሩ፡፡ የሶፎንያስ ትንቢት በይሁዳ ላይ ብቻ ሳይሆን በምድር ሁሉ ላይ
ስለሚመጣው የእግዚአብሔር የፍርድ ቀን ጭምር የተነገረ ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈሩት ትሑታን ሁሉ
ግን ፍጽም የሆነ ተስፋ እንዳላቸው ተንብዮላቸዋል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 86


የመጽሐፉ ዓላማ
 አይሁዳውያን የሆኑ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር እንደሚመለሱና በጊዜው ስለ እግዚአብሔር ፍርድ ወደ
እርሱ እንዲማጸኑ ለማድረግ
 ክፉ አድራጊ ሰዎችን ለማስጠንቀቅ
 ስለ እግዚአብሔር የቁጣ ቀን ለመናገር
የመጽሐፉ አከፋፈል
ትንቢተ ሶፎንያስ ሦስት ምዕራፎች ሲኖሩት በ 4 ዐበይት ክፍላት በመክፈል ይጠናል፡
ሶፎ 1- በኃጢአታቸው ምክንያት ሕዝቡ ላይ ስለሚመጣው መቅሰፍትና ቁጣ፤ ነገር ግን ከተጸጸቱ
እግዚአብሔር አምላክ መሐሪ ይቅር ባይ ነውና ይቅር እንደሚላቸው ይገልጻል፡፡
ሶፎ 2፡ 1-3- አይሁዳውያን ሕግ በመተላለፋቸው ተጸጽተው ንስሐ እንዲገቡ የቀረበላቸውን ጥሪ
ይዟል፡፡
ሶፎ 2፡4- 15- የአይሁዳውያን ጎረቤቶች ስላጠፉት ጥፋትና በአይሁድ ላይ ባደረሱት በደል
ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚደርስባቸውን ቅጣት ነቢዩ ነግሯቸዋል፡፡
ሶፎ 3፡ በኋለኛው ዘመን (በዘመነ ሐዲስ) አረማውያን ወደ ክርስትና ሕይወት እንደሚመለሱና
በተመለሱም ጊዜ ከነባሮቹ የተሻለ ትጋትና ጥሩ ክርስቲያናዊ ሕይወት እንደሚኖራቸው የተናገረውን
የትንቢት ቃል ይዟል፡፡

10. ትንቢተ ሐጌ
ትንቢተ ሐጌ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 520 ዓመታት በፊት በኢየሩሳሌም
ይኖሩ ለነበሩ አይሁድ የተነገረ ትንቢት ነው፡፡ የመጽሐፉ ጸሐፊም ነቢዩ ሐጌ ነው፡፡ ሐጌ ማለት በዕብራይስጠተ
‹‹በዓላዊ›› ማለት ነው፤ ይህም በበዓል ቀን ተወለደ እንደማለት ነው፡፡ በቤተክርስያናችን ትውፊት ነቢዩ
ሐጌ ካህን እንደነበር ይነገራል፤ ይህ አስተሳሰብ የተመሠረተው በሰብዓ ሊቃናት ትርጉም በመዝሙረ ዳዊት
ውስጥ በሐጌና በዘካርያስ ስም የተሰየመ መዝሙር (መዝ 145-148) ስለሚገኝ ነው፡፡ ይህም ሐጌ በክህነት
አገልግሎት ጊዜ የዘመረው መዝሙር ነው ለማለት ነው፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
 ሕዝቡ የተጀመረውን ቤተ እግዚአብሔር እንዲሠሩ በማበረታታት ለእግዚአብሔር ሊያደርጉት
የሚገባቸውን ሳያስቀድሙ የራሳቸውን ቢሠሩ በረከተ እግዚአብሔርን ማግኘት እንደማይችሉ
ለማስገንዘብ፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
ትንቢተ ሐጌ ባለ 2 ምዕራፍ መጽሐፍ ሲሆን በ 4 ክፍሎች ተከፍሎ ሊጠና ይችላል፡፡
ሐጌ 1- የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ለመሥራት ተነሡ የሚል የነቢዩ መልእክት የቀረበበት ነው፡፡
ሐጌ 2፡1-9- አዲሱን ቤተመቅደስ ምንም እንኳ ሰዎች ቢሠሩትም በእነርሱ ላይ አድሮ የሚሠራውእግዚአብሔር
እንደሆነና ይሄኛው ቤተ መቅደስ በወርቁና በውበቱ ከበፊተኛው ቢያንስ በመንፈሳዊ ጌጡ እጅግ የተዋበ እንደሆነ
ነቢዩ የገለጠበት ክፍል ነው፡፡
ሐጌ 2፡10-19- በጎ ነገርን ለሚያደርጉና የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስን ለሚሠሩ እግዚአብሔር ‹‹እባርካችኋለሁ››
እያለ የነገራቸውን የተስፋ ቃል ይዟል፡፡
ሐጌ 2፡20-23- የይሁዳ አለቃ የነበረው ዘሩባቤልን እግዚአብሔር የጠላቶቹን ኃይል በማደስም እርሱን ከፍ ከፍ
እንደሚያረገው የተነገረውን የትንቢት ቃል ይዟል፡፡

11. ትንቢተ ዘካርያስ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 87


ዘካርያስ ማለት እግዚአብሔር ያስታውሳል ማለት ነው፤ ከነገደ ሌዊ የሆነው ይህ ነቢይ ከጌታ ልደት 500 ዓመታት
በፊት ይህን የትንቢት መጽሐፍ ጽፏል፡፡ ዘካርያስ ነቢይና ካህን እንደነበር መጻሕፍት ተባብረውበታል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ
በዚህ ስም የተጠሩ 33 ያህል ሰዎች ይገኛሉ፡፡ የዚህ መጽሐፍ ባለቤት ግን የበራክዩ(ዮ) ልጅና የዒዶ የልጅ ልጅ የነበረው
ካህኑ ዘካርያስ ነው፡፡
ዘካርያስ የሐጌን ትምህርታዊ ማስጠንቀቂያና የራሱንም መልእክት በሰፊው ያቀረበ እንዲሁም ሐጌ የዘረዘራቸው
በሕዝቡ ላይ የደረሱ ችግሮች የሚወገዱት ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ሲመለስ እንደሆነ የገለጠ ነቢይ ነው፡፡ ከዚህ በፊት
የነበሩትን ነቢያት መልእክት በአንድነት አጠቃሎና ወደ ፊት የሚሆነውንና የሚመጣውን በሩቅ ተናግሯል፣ ጽፏልም፡፡
ዘካርያስ አገልግሎቱን የጀመረው ከሐጌ ሁለት ወር ዘግይቶ ነበር በመሆኑም የሐጌ የዘመን ጓደኛ እንደነበር ከዚህ መረዳት
እንችላለን፡፡

የመጽሐፉ ዓላማ
 የቀረውንና ተጀምሮ የተቋረጠውን የቤተመቅደስ ሥራ መፈጸም ታሪካዊ ግዴታ እንደሆነ ለማሳወቅ
 ሁለተኛውን ቤተመቅደስ በመሥራት ላይ ያሉ ሕዝቦችን ለማጽናናተ፣ ኢየሩሳሌም እንደምትበለጽግና አሕዛብ
አንደሚወድቁ ለማጠየቅ
 የሚመጣው በረከትም በመሲሑ በኩል መሆኑን ለማስገንዘብ
የመጽሐፉ አከፋፈል
መጽሐፉ 14 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 3 ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡
ዘካ 1-6፡ በዚህ ክፍል ነቢዩ ዘካርያስ ያያቸው የተለያዩ ራእዮች ተገልጸዋል፤ ከእነዚህም ውስጥ፡ ከምርኮ የተመለሱ
ሰዎች ታዛዥነት እንደሚጠበቅባቸው፣ ስለ ቤተመቅደሱ አሠራር፣ ስለ ካህኑ ዘውድ መጫን፣ ስለ ክህነት ሥራዎች፣
ሕግጋቱን በተዳፈሩትና በሚያፈርሱት ላይ ስለሚደረሰው ርግማን፣ ስለ ጌታ መምጣትና ስለ መለኮታዊ ክብሩ
ዘካ 7-8፡ በኢየሩሳሌም መፍረስ ጊዜ አረማውያን ሕግን አፍርሰው የጾም ቀናትን በዓላት የበዓል ቀናተን አጽዋማት
አድርገዋቸው ነበርና እነርሱ ተለውጠው ሥርዓቱ እንደቀድሞው እንዲሆን የተሰጠውን ትእዛዝ ይዟል፡፡
ዘካ 9-14፡ በዚህ ክፍለ ወስጥ ስለ ጌታችን የተነገሩ ትንቢቶች ይገኙበታል፡፡ እነዚህም፡-
 ወንጌል ስለሚሰበክበተ ዘመን፣ ስለ ወንጌል መስፋፋተና ያመኑ ሰዎች ስለሚወረድላቸው በረከት
 ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ስለ መግባቱ
 አይሁድ የጌታን ሕይወት ለማጥፋት የከፈሉትን የገንዘብ መጠን
 ስለ ጌታችን ጎን መወጋትና ከጎኑ ደምና ውኃ (ማየ ገቦ) ስለመፍሰሱ፣ አይሁድም ወደ ክርስቶስ ሲመለሱ
አባቶቻቸው ያደረሱነትን ሕማም በማስታወስ የሚያዝኑ ስለ መሆናቸው
 በጌታችን ሕማም ወቅት ደቀመዛሙርቱ ጥለውት እንደሚሸሹ
 የቤተክርስቲያን አባላት አይሁድ፣ አረማውያንና ሌሎች ሕዝቦች እንደሚሆኑ የተነገረ ትንቢትን አካትቶ
ይዟል፡፡

12. ትንቢተ ሚልክያስ


ይህ የትንቢት መጽሐፍ የተጻፈው በነቢዩ ሚልክያስ በ 490-430 ቅ.ል.ክ ነው፡፡ ሚልክያስ ማለት መልእክተኛዬ
ማለት ነው፡፡ ሚልክያስ የእግዚአብሔርን ቃል ተቀብሎ ትንቢት መናገሩን ሚልክያስ የሚለው ስምም የነቢያት መጠሪያ ስም
እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህ ነቢይ ከሐጌና ከዘካርያስ ጋር በመሆን ሕዝቡ ለቤተመቅደሱ ሥራ እንዲተባበሩ ያደርግ ነበር፡፡
ሕዝቡ ግን በዚህ ቅር ስለተሰኘ ለእግዚአብሔር አገልግሎትና የእግዚአብሔርን ሕግ በመጠበቅ የሚጠቀሙት እጅግ
በጣም ጥቂት ስለነበሩ በዚህ ሁናቴ ላይ ሚልክያስ የእግዚአብሔርን ቃል መናገርና ለሕዝቡም ግልጽ ማድረግ ጀመረ፡፡ ነቢዩ
ሚልክያስ ካህን እንደነበረም መጻሕፍት ይተርካሉ፡፡

የመጽሐፉ ዓላማ
 የእግዚአብሔር እስራኤልን መክሰስና በንስሐ በኩል ወደ እርሱ እንዲመለሱ ወይም እንዲቀርቡ ለማድረግ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 88


 እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለውን ፍቅርና የእነርሱን ደንዳናነት በአጠቃላይ እርሱን በመናቅ ያጠፉ እንደነበር፣ በዚህም
ላይ እግዚአብሔር እንደሚፈርድ ለመግለጥ
 ከክፋታቸው በንስሐ የተመለሱትን እንደሚባርክ፣ ጌታም ወደ መቅደሱ እንደሚመጣ እግዚአብሔርም
መልእክተኛውን ቀኑ ሳይደርስ ኤልያስን እንደሚልክ ለመናገር፡፡ ሚልክያስ ይህን ከተናገረ ከ 500 ዓመታት በኋላ
መጥምቁ ዮሐንስ ስለመጣ የተናገረው ትንቢት ተፈጽሟል፡፡
የመጽሐፉ አከፋፈል
ይህ መጽሐፍ 4 ምዕራፎች ሲኖሩት በ 2 ዐበይት ከፍሎች ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡-
ሚል 1-2፡ አይሁዳውያን ካህናትና ምዕመኑ ማድረግ ያለባቸውን በማጉደላቸው ይወቅሳቸዋል፡፡ ካህናት ልብሰ
ተክህኖአቸውን ከቤተመቅደስ ውጪ በመልበሳቸው፣ ከሃይማኖት አገልግሎታቸው በስተኋላ ትርፍ በመጋበሳቸው
የደረሰባቸው ወቀሳ እናገኛለን፡፡ ካህናት ከሕዝብ፣ ሕዝብም ከካህናት እንደሚለያዩም ይነግረናል፡፡
ሚል 3-4፡ ስለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ መምጣት፣ አይሁድ አሥራታቸውን በማስታጎላቸው
የደረሰባቸውን ወቀሳና ስለ ጌታ መምጫ ቀን መቃረብ፣ ምልክቱና የተነገሩ የትንቢት ቃላትን እናገኛለን፡፡

ምዕራፍ ፫
የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት
ኪዳን በሁለት ወገኖች መካከል የሚመሠረት፣ በመሐላ የሚጸና ከተመሠረተ በኋላ በሁለቱ ወገኖች መካከል እንደ ሕግ
ኾኖ የሚሠራ ስምምነት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኪዳን ሲባል ከእግዚአብሔር ለሰዎች የተሰጠ እና ሰዎች በእምነት
የተቀበሉት ውል ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ለሰዎች የተሰጠ የደኅንነት ኪዳን ነው፡፡ ይኸውም በወልደ እግዚአብሔር በኢየሱስ
ክርስቶስ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንደሚያገኝ የሚያረጋግጥ ኪዳን ነው፡፡ የዚህ የደኅንነት ኪዳን ቃላትም፡-
‹‹ያመነ የተጠመቀ ይድናል፡፡›› (ማር 6፤16)
‹‹በልጁ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፡፡›› (ዮሐ 3፤16)
‹‹እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በእኔ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፡፡›› (ዮሐ 6፤47)
‹‹ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል፤ በአፉም መስክሮ ይድናል፡፡›› (ሮሜ 10፤131 ዮሐ 2፤21) የሚሉትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ሐዲስ ኪዳን ሲባል ፊተኛ ኪዳን እንዳለ ያመለክታል፡፡ ይህም ፊተኛ ኪዳን ብሉይ ኪዳን ነው፡፡ ብሉይ ኪዳንን “ብሉይ”
ያሰኘው የሐዲስ ኪዳን መምጣት ነው፤ ‹‹አዲስ በማለት ፊተኛውን አስረጅቷል›› እንዲል (ዕብ 8፤13)፡፡ ‹‹ያረጀ›› የሚለው
ቃል ያለፈበት መሆኑን አያመለክትም፡፡ እርጅናው የዕድሜ ባዕለጸግነቱም የሚገልጽ ብሉይነቱም በዘመን ብዛት ነው
እንጂ፡፡ የምሥጢራት አፈጻጸም ሁኔታ ተለወጠ እንጂ ቃሉ አይሠረዝም ወይም አይሻርም፡፡ ማቴ 5፣17-20

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 89


ሐዲስ ኪዳን በቀለም ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ተጻፈ የኵነኔ ሳይሆን የጽድቅ አገልግሎት ፍሬ አለው፡፡ ለጊዜው ሳይሆን
ለዘለዓለሙ ጸንቶ ይኖራል፡፡ ፍጹም ነጻነት ስላለው የሚቀበሉት ሁሉ ወደ ጌታችን ይቀርባሉ፡፡ በመሆኑም ክብሩ ከፍ ያለ
ነው፡፡ (2 ቆሮ 3፣4-17)
ዐርባዕቱ ወንጌላት

1. የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል


ቅዱስ ማቴዎስ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት (ሐዋርያት) እና ከአራቱ ወንጌላውያን አንዱ ነው፡፡
በመቅድመ ወንጌል በተመዘገበው ታሪክ መሠረት ነገዱ ከነገደ ይሳኮር፣ ትውልዱ አይሁዳዊ፣ ሀገሩ ናዝሬት፣
አባቱ ዲቁ፣ እናቱ ክሩትስያ እንደምትባል ተገልጧል፡፡ ጌታችንም ይህን ሐዋርያ ከቀራጭነት ግብር
እንደጠራው በወንጌሉ ተጠቅሷል፡፡ ማቴዎስም የቀደመ ሥራውን ትቶ ተከትሎታል፡፡

የማቴዎስ ወንጌል 28 ምዕራፎች በመያዙ በምዕራፎች ብዛት የመጀመሪያው ወንጌል ሲሆን 1068
ቁጥሮችን በመያዝ በቁጥሮች ብዛት ከማርቆስ ወንጌል ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡ ከአንድ ሺህ
ስድሳ ስምንት ቁጥሮች መካከል ስድስት መቶ አርባ አራቱ የጌታን ትምህርቶች የያዙ በመሆናቸው ከሌሎቹ
ወንጌላት በተለየ መልኩ ከዮሐንስ ወንጌል ጋር ይበልጥ ይዛመዳል፡፡ ወንጌሉን የጻፈው ለአይሁድ በመሆኑ ከ 150
በላይ ጥቅሶችን ከብሉይ ኪዳን አቅርቧል፡፡ በዚህ የተነሣ ብሉይ ኪዳንን አብዝቶ በመጥቀስ ከሌሎች
ወንጌሎች ይበልጣል፡፡ ወንጌላዊው ይህንን ወንጌል ሲጽፍ ትውፊትን በብዛት ተጠቅሟል፡፡ ይህንንም
ያደረገው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሲስ ክርስቶስ ቀድሞ በነቢያት የተነገረለት መሲሕ መሆኑን
ለማረጋገጥ ነው፤ ስለዚህም አንድን ታሪክ ከጻፈ በኋላ በነቢዩ የተጻፈው ተፈጸመ ብሎ ይመሰክራል፡፡

የማቴዎስ ወንጌል ከማርቆስ ወንጌል ቀጥሎ በሁለተኛነት ተጽፎ እያለ የመጀመርያውን ተርታ ያገኘበት
ዋናው ምክንያት አቀራረቡ ለብለይና ለሐዲስ ኪዳን ድልድይ ስለሆነና የብሉይ ኪዳን ትንቢትና ምሳሌ
በሐዲስ ኪዳን መፈጸሙን ስለሚያሳይ ነው፡፡
ወንጌሉ የተጻፈላቸው ሰዎች
ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌሉን የጻፈው ከዕብራውያን /ከአይሁድ/ ወደ ክርስትና ለተመለሱ ሰዎች ነው፡፡ በወንጌል
ትርጓሜ እንደተገለጠው ‹‹ ምድረ ፍልስጥኤም ለማቴዎስ በዕጣ ደረሰችው፣ ከዚያ ገብቶ ጌታ ከጽንስ
ጀምሮ ያደረገውን ተአምራት፣ ያስተማረውን ትምህርት የሠራውን ትሩፋት ቢነግራቸው በወንጌል አምነው
ተጠመቁ፡፡ ትምህርት ካልደረሰበት ለማዳረስ ወጥቶ በሚሄድበት ጊዜ በቃል ያለ ይረሳል፤ በመጽሐፍ ያለ
ይወረሳል ብለውት ጽፎላቸዋል፡፡›› ማቴዎስ ወንጌሉን የጻፈው ለዕብራውያን መሆኑ ከጥንት የቤተክርስቲያን
አባቶች መካከል ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ የቅዱሳት መጻሕፍትን ቀኖና በገለጸበት ጽሑፉ ‹‹ማቴዎስ
ለዕብራውያን ተአምራተ ኢየሱስን ጻፈ›› ብሏል፡፡ የመጽሐፉም አጠቃላይ ይዘት ለዕብራውያን ክርስቲያኖች
የተጻፈ መሆኑን ያሳየናል፡፡

የመጽሐፉ ዓላማ
 አይሁድ ጌታ በድንግልና አልተወለደም ብለው ስለነበር ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት
መወለዱን ለመመስከር
 ኦሪትን ሊሽር መጣ ብለውት ነበርና ኦሪትን ሊፈጽም እንጂ ሊሽር አለመምጣቱን ለመግለጥ
 ጌታችን ከአብርሃምና ከዳዊት ዘር የተወለደ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማስረዳት
 በሰዎች ዘንድ ጌታ ከነቢያት አንዱ ነው ቢባልም ከነቢያት አንዱ እንዳልሆነና የእግዚአብሔር ልጅ
እግዚአብሔር መሆኑን ለመግለጥ
 በዘመነ ብሉይ የተነገረለት፣ ሱባኤ የተቆጠረለት መሲሕ፣ የዓለም ጌታ፣ የአይሁድና የአሕዛብ መድኃኒት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ለማስረዳት
 በሕግና በነቢያት መጻሕፍት ስለ ጌታ የተነገረለትን ትንቢታዊ ቃላት በመጥቀስ ፍጻሜያቸውን
ለማስረዳት
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 90
የመጽሐፉ አከፋፈል
ወንጌሉ 28 ምዕራፎች ሲኖሩት እያንዳንዱን ከፍለን እናያቸዋለን፡፡

ማቴ 1 ፡ ስለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዘር ሐረግና ልደት፡፡


ማቴ 2 ፡ ሰብአ ሰገል ስጦታ እንዳመጡለት እና የጌታችን፣ የእመቤታችንና የዮሴፍ ወደ ግብጽ መሰደድ
ማቴ 3 ፡ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ስብከትና የጌታችን ጥምቀት
ማቴ 4፡ ስለ ጌታችን 40 ቀን መጾምና መፈተን፣ ለሐዋርያት ስለሰጣቸው ሥልጣንና ትእዛዝ
ማቴ 5-7፡ የተራራው ስብከት
ማቴ 8-9፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰለሠራቸው ተአምራት
ማቴ 10፡ ጌታ 12 ቱን ሐዋርያት ስለመላኩ
ማቴ 11፡ ከመጥምቁ ዮሐንስ ስለተላኩ መልእክተኞች
ማቴ 12፡ ስለ ሰንበት በዓል አከባበር
ማቴ 13፡ ጌታችን በምሳሌ ስላስተማራቸው ትምህርቶች
ማቴ 14-15፡ ትምህርቱን በመስማት የተሰበከውን ሕዝብ ስለመመገቡ
ማቴ 16፡ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደተገለጠለትና እንደመሰከረ
ማቴ 17፡ በደብረ ታቦር አምላካችን ብርሃነ መለኮቱን ስለመግለጡ
ማቴ 18-20፡ ጌታችን ስላስተማራቸው ዐበይት ትምህርቶች፣ በኢያርኮ ያደረገው ተአምር
ማቴ 21፡ ጌታችን በክብር ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱ
ማቴ 22፡ ፈሪሳውያን ጌታችንን ሰለመፈተነቸው
ማቴ 23፡ ስለ ሙሴ ሕግ፣ ስለ መምህራንና ስለፈሪሳውያን ተንኮል
ማቴ 24-25፡ ስለ ዳግም ምጽአት
ማቴ 26፡ ይሁዳ አምላካችንን ስለመካዱ፣ ጌታችን በመስቀል ስለመሰቀሉ፣ በአዲስ መቃብር ስለ መቀበሩና
አይሁድ መቃብሩን እንዳስጠበቁት
ማቴ 27፡ ስለ ጌታችን ስቅለት
ማቴ 28፡ ስለ ጌታችን ትንሣኤና መገለጥ፣ ለማርያም መግደላዊትና ለሁለተኛዋ ማርያም እንደ ታየ፣
ጠባቂዎቹ ገንዘብ ተቀብለው ስለ ትንሣኤው የሐሰት ወሬ እንዳወሩ፣ ጌታ ለደቀመዛሙርቱ የሰጠው
የመጨረሻ ትእዛዝ

2. የቅዱስ ማርቆስ ወንጌል


የቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ
ቅዱስ ማርቆስ ከሌዊ ወገን የሆነ አይሁዳዊ ነው፡፡ ለአይሁድም ለአሕዛብም ወንጌልን ያስተማረ ሐዋርያ ቢሆንም
በዋነኝነት ግን አሕዛብን ሰብኳል፡፡ ቅዱስ ማርቆስ በአፍሪካ አህጉር የተወለደ አይሁዳዊ በመሆኑ የአፍሪካ ተወላጅ ሐዋርያ
ነው፡፡ የተወለደውም በአፍሪካ በምትገኝው ሊቢያ ሀገር ሲረናይካ (ቀሬና) በተባለ ቦታ ልዩ ስሙ አብርያጦሎስ በተባለ
አካባቢ ነው፡፡ ቅዱስ ማርቆስ ቁጥሩ ከጌታ መቶ ሀያ ቤተሰቦች መካከል ከ 72 ቱ አርድዕት እና ከአራቱ ወንጌላውያን አንዱ
ነው፡፡
ቤተሰቡ፡ - የቅዱስ ማርቆስ አባቱ አርስጦቡሎስ እናቱ ደግሞ ማርያም ባውፍልያ ይባላሉ፡፡ አጎቱም ማለትም የአባቱ
ወንድም በርናባስ ይባላል፡፡ አባቱ አርስጦቡሎስና አጎቱ በርናባስ በእናት የሚገናኙ ወንድማማቾች ሲሆኑ እህታቸው ደግሞ
የቅዱስ ጴጥሮስ ሚስት ናት፡፡ ቅዱስ ማርቆስ ከሀብታም ቤተሰብ ነው የተወለደው፡፡ ቤተሰቦቹ ኢየሩሳሌም ከመምጣታቸው
በፊት ቅዱስ ማርቆስ የተወለደበት ቦታ በዛሬዋ ሊቢያ ምዕራባዊ ጠረፍ በተቆረቆረችው ደማቅ ከተማ ነበር፡፡ ነገር ግን
የሰሜን አፍሪካ ዘላን ጎሳዎች የሆኑት በርበሮች በየጊዜው በከተማዋ ጥቃት እየሰነዘሩ ሀብት ንብረታቸውን እየዘረፉ
ስላስቸገሯቸው በአውግስጦስ ቄሳር ዘመን እናቱና አባቱ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ኢየሩሳሌም በመመለስ ቤት ሠርተው
ተቀመጡ፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እየተዘዋወረ ማስተማር በጀመረበት ጊዜ የማርቆስ ቤተሰብ በዚያ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 91


ከትመው ነበር፡፡ የቅዱስ ማርቆስ እናት የግሪክ /ጽርእ/፣ ላቲንና የዕብራዊያን ቋንቋን ጠንቅቃ ታውቅ ነበር ለቅዱስ ማርቆስም
እነዚህን ቋንቋ አስተምራዋለች፡፡ ቅዱስ ማርቆስም ቋንቋዎቹን አሳምሮ ያውቃል፡፡ የላቀ መንፈሳዊ ትምህርትም ነበረው፡፡
የሕግና የነብያት መጻሕፍትን በሚገባ አጥንቷል፡፡
ቅዱስ ማርቆስ ብዙ የክርስቶስ ተከታዮች ከነበሩት ቤተሰቦች መካከል ያደገ ነው፡፡ እናቱ ማርያም ባውፍልያ
ጌታችንን ካገለገሉት ቅዱሳን ሴቶች መካከል አንዷ የሆነች ቤቷንም ለክርስቲያኖች መታሰቢያነትና መሰብሰቢያነት የሰጠች
ደግ ሴት ነበረች በሐዋ. 12፡12 ላይ ጌታም የመጀመሪያውን የሐዲስ ኪዳን ቁርባን ለሐዋርያት ያቆርባቸው የመጨረሻው
የሚባለውን እራት ያደረገበት ቤት፤ በበዓለ ሀምሳም መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደላቸው በእርሷ ቤት ተሰብስበው
ሲጸልዩ ነው፡፡ የቤቱ ባለቤት ሆና የተጠቀሰችው የማርቆስ እናት ማርያም ነች፤ ከዚህም አንፃር ምናልባት ያን ጊዜ የማርቆስ
አባት መቶ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ የማርቆስ አባት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሙ ባይነገርም የበርናባስ ወንድም
እንደሆነ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማወቅ ይቻላል፡፡ ምክንያቱን ማርቆስ የበርናባስ የወንድም ልጅ እንደሆነ ተገልጧልና ነው
/ቆላ. 4፡10/ በስንክሳርና በገድለ ሐዋርያት ላይ ግን የማርቆስ አባት ስሙ አርስጦቦሎስ እንደሆነም ይነገራል፡፡
ማርቆስ የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ ለመሆን የበቃው ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ እዚያ
በማደጉ ነው፡፡ በእርግጥ ጌታችን በሚያስተምርበት ወቅት ቅዱስ ማርቆስ ገና ሕፃን ነበር፡፡ ቅዱስ ማርቆስ ጌታችን በቃና
ገሊላ ውኃውን ወደ ወይን ለውጦ የመጀመሪያውን ተአምር ባደረገ ጊዜ በዚያ እንደነበረና ወይኑንም ከቀመሱት ሰዎች አንዱ
እንደሆነ ይነገራል (ዮሐ. 2)፡፡እንዲሁም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በይሁዳ አውራጃዎች እየተዘዋወረ
ሲያስተምረ ማርቆስ ገና ሕፃን ነበር፡፡ በምሴተ ሐሙስ ለሐዋርያት ‹‹ወደ ከተማ ሂዱ በማድጋ ውኃ ተሸከመ ሰው
ታገኛላችሁ ተከተሉትም›› በማለት ፋሲካን ሊያዘጋጁለት የመረጠውን ቤት እንዲያሳያቸው የጠቆማቸው ወጣት ቅዱስ
ማርቆስ መሆኑን የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ይመሰክራሉ /ማር. 14፡13/፡፡
የቅዱስ ማርቆስ ወንጌል
ወንጌሉ የተጻፈበት ቋንቋ፣ዘመንና ቦታ
ከወንጌላዊያን መካከል የመጀመሪያውን ወንጌል የጻፈው ቅዱስ ማርቆስ ነው፡፡ ስለተጻፈበትም ጊዜ የተለያይ
ሊቃውንት የተለያየ ሃሳብ ያነሣሉ፡፡ የማርቆስ ወንጌል የተጻፈበት ቦታ ሮሜ ሲሆን የተጻፈበትም ቋንቋ
ሮማይስጥ/ላቲን/ነው፡፡ ዘመኑም በእኛ ትውፊት እንደተገለጸው ጌታ ባረገ 11 ኛው ዓመት ተፈጽሞ 12 ኛው
ዓመት ሲጀምር ቀላውዲዎስ ቄሳር በነገሠ በዓራተኛው ዓመት ነው፡፡ ይህም በዓመተ ምህረት ሲታሰብ፡-
ከጌታ ዕርገት በፊት፡34 ዓመት + ከጌታ ዕርገት በኋላ/11 ዓመት ስለዚህ በ 45 ዓ.ም ተጽፏል ማለት ነው፡፡
ወንጌሉ የተጻፈላቸው ሰዎች
ማርቆስ ወንጌሉን የጻፈው ለሮማውያን በመሆኑ ከሌሎች ወንጌላዊያን (ቅዱስ ማቴዎስና ቅዱስ
ዮሐንስ) የተለየ አገላለጽና አጻጻፍ ተጠቅሟል፡፡ የተጻፈበት ቋንቋ ሮማይስጥ ነው፡፡ ሮማውያን በዘመናቸው
ኃያልነን ብለው ይታበይ ስለነበርና ያለ እኛ ማን አለ? የሚል ኩራት ስለነበራቸው የወንጌሉ አጻጻፍ ከእነርሱ
በላይ ኃያል መኖሩን ለመግለጥ ነው፡፡ ገና ወንጌሉን ሲጀምር የጌታን ሥልጣን በአጋንንት ላይ (ማር 1፡27)፣
በበሽታ ላይ (ማር 1፡34) የማስተማር ስልጣኑን (ማር 1፡22) በመግለጥ የጌታችንን ኃያልነት አሳይቷል፡፡
በሮማውያን ባሕል መሠረት አንድ ንጉሥ ሲመጣ አጋፋሪው ከፊቱ በፈረስ ይቀድማል፡፡ እርሱም የንጉሥን
መምጣት እያወጀ ያልፋል፡፡ በዚህ ባሕል መሠረትም ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ የዮሐንስ መጥምቅን ታሪክ
አስቀድሞ ጽፏል፡፡
ቅዱስ ማርቆስ በሮም ውስጥ ሆኖ ወንጌሉን የጻፈላቸው ለራሳቸው ለሮማውያን ነው፡፡

 በመሆኑም የአረማይክን ቃላትና የዕብራውያንን ባሕል ሊያውቁት ስለማይችሉ ትርጉም


አስቀምጦላቸዋል፡፡ ለምሳሌ፡-
 ቦኤኔርጌስ፡ - የነጎድጓድ ልጆች (ማር 3፡17)
 ቁርባን፡ - መባዕ (7፡11)

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 92


 አባ፡ - አባት (14-፡36)
 ገሀነም፡ - እሳቱ የማይጠፋበት፣ ትሉ የማያንቀላፋበት ሲል ገልጾታል (9፡47)
 ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሳበቅታኒ፡ - አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ? (15፡34)
 ጣቢታ ቁሚ፡ - አንቺ ብላቴና ተነሽ (ማር 5፡41)
 ኤፍታህ፡ - ተከፈተ (7፡34)
 ጎሎጎታ፡ - የራስ ቅል (15፡22)

ነገር ግን ሌሎች የላቲን ቃላትን አልተረጎመም፡፡ ለምሳሌ፡ - ጴጥሮስ የሚለውን ዓለት ማለት ነው ብሎ
አይተረጉመውም፡፡

 የአይሁድን ባሕል (ሥርዓት) እና የቦታ ስሞችን አብራርቶላቸዋል፡፡ ለምሳሌ፡-


 የመታጠብ ባሕል (7፡1-4)
 ፋሲካን በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን በማለት ስለበዓሉ ዘርዝሯል፡፡ (14፡12)
 በመሸ ጊዜ የሰንበት ዋዜማ የሆነ የማዘጋጀት ቀን ነበር፡ የጻፈው ለአይሁዳውያን ቢሆን ኖሮ የማዘጋጀት
ቀን የሚለው ብቻ በቂ ነበር፡፡ ምክንያቱም ቀን በሰንበት ዋዜማ መሆኑን ያውቃሉና፡፡ ዲናር ግን የሮማ
ገንዘብ ስለነበር አልተረጎመውም፡፡ (6፡37)
 ሰዱቃውያን፡ - ትንሣኤ ሙታን የለም ብለው የሚያምኑ (12፡18) በማለት እምነታቸውን ገልጧል፡፡
 ስለ ሰሮኒፊቃዊቷም ሴት ሲገልጽ በሮማውያን ያነጋገረ (ያገላለጽ) ዘይቤ ዜግነቷን ተናግሯል፡፡ (7፡26)
 ለዮርዳኖስ፡ - ወንዝ የሚል ቅጽል አስቀጧል (1፡5)
 ደብረዘይትን ተራራ በመቅደሱ ትይዩ ብሎ ቦታውን ገልጦታል (ሮማውያኑ ስለማያውቁት)
 ወደ ኢየሩሳሌምም ከደብረዘይት አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ ብሎ መልክአምድራዊ ገለጣ
ጨምሮላቸዋል፡፡ (11፡1)ለአይሁዳውያን ቢሆን ግን ለመረዳት ምንም ስለማያስቸግራቸው ቦታዎቹን እየዘረዘረ
አይጽፍም ነበር፡፡
 ጌታን ሲሰቅሉት በወሰዱት ጊዜ በመንገድ ላይ አግኝተውት መስቀሉን እንዲሸከም ያስገደዱት ስምኦን ቀሬናዊ
የአሌክሳንድሮስና የሩፎስ አባት መሆኑን ይገልጣል፡፡ /15፡21/፡፡ ከእነዚህ ልጆች አንዱ ሩፎስ የተባለው በሮሜ
እንደነበር ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ ውስጥ ባቀረበለት ሰላምታ ይታወቃል(ሮሜ 16፡13) ስለዚህ ማርቆስ እና
ሩፎስን አንባቢያን እንደሚያውቋቸው አድርጎ መግለጡ የተጻፈው ለሮማውያን መሆኑን እንገነዘባለን፡፡
 ከብሉይ ኪዳይ በብዛት አለመንቀሉ፡- ቅዱስ ማሬዎስ ወንጌሉን ለአይሁዳውያን ስለጻፈ ከብሉይ ኪዳን መጻህፍት
በብዛት ጠቅሷል፡፡ ቅዱስ ማርቆስ ግን ወንጌሉን ለአሕዛብ/አርማውያን/ ስለጻፈ ከብሉይ ኪዳን የጠቀሳቸው አሳቦች
ከቅዱስ ማቴዎስና ከቅዱስ ሱቃስ ጋር ሲነጻጸር በጣም ትንሽ ነው፡፡
 ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ የጌታን ሥራ ሲገልጥ ከትህትና ሥራው ጎን ሁልጊዜ የኃይል ሥራውን አብሮ ያቀርባል፡፡
ምክንያቱም ሮማውያኑ አማልክቶቻቸውን የሚያውቋቸው በኃይላቸው ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስን አሳንሰው
እንዳይመለክቱትና የአምላኮች አምላክ የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ እንደሆነ ለማስረዳት ነው፡፡ ለምሳሌ፡-በዚህ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንመለከት (4፡41፣6፡48-54፣15፡3፣11፡12-20/ በእነዚህ ጥቅሶች አስረድቷል፡፡

የማርቆስ ወንጌል መገለጫዎቹ/ይዘቱ/


የቅዱስ ማርቆስ ወንጌል ከወንጌላት ሁሉ አጭር ወንጌል ነው፡፡ 16 ምእራፎች እና 678 ቁጥሮችን ይዟል፡፡
አስቀድመን እንደገለጥነው ወንጌሉን የጻፈው ለሮማውያን /ለአረማውያን/ ነውና ይህ መሆኑ የወንጌሉን አብዛኘውን ጠባይ
ወስኖታል፡፡ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌሉን በእግዚአብሔር ለሚያምኑ ለአይሁድ ወይም ደግሞ የፍልስፍና አስተሳሰብ ላላቸው
ሰዎች ለሆኑት ግሪካውያን ያይደለ የድርጊት ሰዎች ለሆኑ ለሮማውያን ጽፎአልና መጽሐፉ በመጠኑ ትንሽ የሆነና መግቢያ
የሌለው ነው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 93


ሮማውያኑ በወቅቱ የዓለምን አብዛኛው ክፍል የሚገዙ ኃያላን የነበሩን በኃይልና በሥልጣን የሚያምኑ ጦረኞች ነበሩ፡፡ ያለ
እኛ ማን አለ? እያሉም ይኩራሩ ነበርና የወንጌሉ አጻጻፍ ከነርሱ በላይ ኃይል እንዳለ ለመግለጥ ነው፡፡ በዚህም መሠረት
ቅዱስ ማርቆስ ክርስቶስን ለሮማውያን ያስተዋወቀው በሥራውና በኃይሉ ነው፡፡ ሮማውያን መንገድ የሚያበዙ ሰዎች ነበሩ፤
ይጓዛሉ፣ ይነግዳሉ፣ ጦርነት ይሄዳሉ፡፡ ስለዚህ የቅዱስ ማርቆስ ወንጌል መግቢያ የለውም፤ የክርስቶስን መምጣት የሚያስረዱ
ቅድመ ዝግጅቶችን፡፡ ብሥራቱን እመቤታችን ኤልሳቤጥን፤ እንደጎበኘቻት፣ የእርሱ መጸነስ፣ መወለድ ሁሉ አልጠቀሰም፡፡
የክርስቶስን የዘር ሐረግ በመጥቀስ ከጀመረው ከቅዱስ ማቴዎስ በተለየ ‹‹ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ ይህ ነው›› በማለት ይጀምራል፡፡ ከዚያም በሮማውያኑ ባሕል መሠረት አንድ ንጉሥ
ሲመጣ አጋፋሪው በፈረስ ከፊቱ ይቀድማል፡፡ እርሱም የንጉሡን መምጣት እያወጀ ያልፋል፡፡ በዚህ ባሕል መሠረትም
ቅዱስ ማርቆስ የዮሐንስ መጥመቅን ታሪክ በማስቀደም ይጽፋል፡፡
የማርቆስ ወንጌል ዋና አላማ
የወንጌሉ ትምህርት ዋና መልእክቱ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ /አምላክ/ መሆኑን
መግለጥ ነውና ሲጀምር ያስተላለፈውን ይህን መልእክት /ማር 1፡1/ በወንጌሉ ማጠናቀቂያ ላይም በሮማዊ መኮንን ምስክርነት
ደምድሞታል /ማር 15፡39/ በሌሎች ብዙ አንቀጾችም ይህንን እውነት አስቀምጧል፡፡ /ማር፡- 1፡11፣3፡11፣5፡6፣9፡7፣13፡
32፣14፡61/ ከዚህም ሌላ የአምላክ ልጅ ሳለ የሰው ልጅም ደግሞ ስለመሆኑ /በማር 2፡28፣14፡62፣13፡26/ ላይ ገልጧል፡፡
ቅዱስ ማርቆስ ገና በመጀመሪያ ምዕራፍ ጌታ ያደረጋቸውን ተአምራት በመጻፍ የክርስቶስን ሥልጣን ገልጧል፡፡
በአጋንንት /በርኩሳን መናፍስት/ ላይ ስላለው ሥልጣን አጋንንትን ከሰዎች ላይ ያርቅ እንደነበር /ማር 1፡29፣1፡
34፣3፡11፣5፡6፣/ድውያኑን ሳያይ ይፈውስ እንደነበር/ /7፡24-30/ ለደቀ መዛሙርቱ በአጋንንት ላይ ኃይልን
እንደሰጣቸው/ /3፡15፣6፡7፣9፡39/
በደዌ በበሽታ ላይ ስላለው ሥልጣን
 በእውራን /8፡22-28፣10፡46-52/
 በዲዳና በድንቆሮ /7፡31-37/
 ሥጋ ደዌ /1፡42/
 ሽባ /2፡11/
 እጁ የሰለለለት /3፡5/
 ደም ሲፈሳት የነበረች ሴት /5፡25-34/
 ሰዎች ይህን ዓይነት ከቶ አይተው እንደማያውቁ ተናግረው ፈጽመው አደነቁ /2፡12/
በተፈጥሮ (በሥነ-ሥርዓት) እና በሞት ላይ ስላለው ሥልጣን
 ነፍሳትንና ባሕርን የመገሰጽ ሥልጣን /4፡39-41፣ 6፡48-54/
 በተክሎች ላይ /በለሲቱን መርገሙ/ 11፡12-20/
 በሞት ላይ /5፡22-43፣ 16፡6፣ 15፡33-38/

ሌሎች ሥልጣናት
 ሳይነግሩት እንደሚያውቅ /2፡8/
 የአምስት ገበያ ሕዝብ ስለመመገቡ /6፡23-44፣ 8፡1-9/
 የሰንበት ጌታዋ ስለመሆኑ /2፡28/
 በቤተመቅደሱ ካህናቱ እንኳ ሊገፉት ያሰተቻላቸው ታላቅ ሥልጣን እንደነበረው /11፡33/
 ጌታ መሆኑንና ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው /11፡3፤ 2፡10/
 ወደፊት ስለሚሆነው እንደሚያውቅ(ትንቢት)/8፡3-38/
 ብዙ ሕዝብ ይከተለው እንደነበር /1፡28-33፣ 3፡7-9፣ 4፡1-2፣ 6፡32-34፣ 5፡24፣ 9፡15፣ 7፡24
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 94
በአጠቃላይ የማርቆስ ወንጌል ምንም እንኳ አጭር ቢሆንም ለአጠናን ይመቸን ዘንድ 16 ቱን የማርቆስ
ወንጌላት ምዕራፍ በ 15 ዐበይት ክፍሎችና የመጽሐፉ አከፋፈል እንከፍላቸዋለን፡፡
ምዕራፍ 1፡- የመጥምቁ ዮሐንስ ስብከትና የኢየሱስ ክርስቶስ መጠመቅ
ምዕራፍ 2፡- ሽባውን ሰለመፈወሱ እንዲሁም ስለጾምና ሰንበት የቀረበ ጥያቄ
ምዕራፍ 3፡- ጌታ በገሊላ ስላደረገው ስብከት
ምዕራፍ 4፡- በምሳሌ ስለማስተማሩ
ምዕራፍ 5 ና 6፡- ሕሙማንን ስለመፈወሱና ሐዋሪያትን ስለመላኩ
ምዕራፍ 7፡- ሰውን ሰለሚያረክሱ ነገሮች
ምዕራፍ 8፡- እንጀራውን አበርክቶ ስለመመገቡ
ምዕራፍ 9፡- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደብረ ጣቦር ብርሐን መለኮቱን፤ክብሩን ስለመግለጡ
ምዕራፍ 10፡- በይሁዳ ስለማስተማሩና በኢሪኮ ዓይነ ስውሩን ስለመፈወሱ
ምዕራፍ 11፡- በክብር ወደ ኢየሩሳሌም እንደገባ
ምዕራፍ 12፡- ስለ ወይን ቦታ ሰራተኞች
ምዕራፍ 13፡- ስለ ዓለም ፍፃሜ ማስተማሩ
ምዕራፍ 14፡- ስለጌታ እራትና ስለጌቴ ሴማኒ ጸሎት
ምዕራፍ 15፡- ስለጌታ መያዝ፣ስለጌታ መሰቀል፣መሞትና መቀበር
ምዕራፍ 16፡- ስለጌታ ትንሣኤና ስለ ሐዋርያት መላክ

3. የቅዱስ ሉቃስ ወንጌል


ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ ሀገሩ አንጾኪያ ሲሆን በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከተነሡት ቅዱሳን አንዱ ነው፡፡ ከ 72 ቱ
አርድዕት መካከል አንዱ ሲሆን ከጰራቅሊጦስ በኋላ ወደ አንጾኪያ ሄዶ ሰብኳል፡፡ ከሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጋር
የተገናኘውም በዚህ ነው፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ሐኪም ሲሆን የሕክምና ሙያውን ያጠናው ከአቴናና ከእስክንድርያ ነው (ቆላ 4፡
14)፡፡ የሥነ ሥዕል ችሎታም ነበረው፡፡ ይ የሥዕል ችሎታውም በመጻሕፍቱ ላይ በሥዕላዊ ሁኔታ ገልጾታል፡፡
ቅዱስ ሉቃስ እመቤታችን ጌታን ታቅፋ (ምስለ ፍቁር ወለዳን) የሣለው እርሱ ሲሆን እነዚህም ሥዕላት በኢትዮጵያ
በተለያዩ ገዳማትና በስፔን ቅድስት ማርያም ካቴድራል ይገኛል፡፡ ይህ ሐዋርያ በሰማዕትነት እስካረፈበት ጊዜ ድረስ የቅዱስ
ጳውሎስ ደቀ መዝሙር ነበር(2 ኛ ጢሞ 4፡11)፡፡
ሉቃስ ወንጌልን ያስተማረበት ሀገር
ሉቃስ ስላስተማረበት ሀገር የምንረዳው ስትውፈታውያን መጽሐፍት በምናገኘው ታሪክ ነው፡፡ እነዚህም ታሪኮች
ሉቃስ ጳውሎስን ከመስቀሉ በፊትና ከጳውሎስ ዕረፍት በኋላ በየትኞቹ ሀገሮች እንዳስተማረ ይነግሩናል፡፡
በሉቃስ ወንጌል ትርጓሜ መግቢያ ላይ ሐዋርያት ያለምን ዕጣ በዕጣ ብለው ተካፍለው ለማስተማር በሚወጡበት
ጊዜ ሉቃስ ዮሐንስን ተከትሎ በመሄድ ዮሐንስ በዕጣ ከደረሳቸው ከምድር ድርዕ ክድሉ በሰጠው በመቄዶንያ ገብቶ ስለ
ክርስቶስ እንዳስተማረ ይነገራል፡፡ ይህም ቅዱስ ጳውሎስን ከመከተሉ በፊት መሆኑ ነው፡፡
ገድለ ሐዋርያት ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት ከሞተ በኋላ ሉቃስ ከሞት ተርፌ በሮሜ ዳርቻ ባሉ ሀገሮች
ያስተምር እንደነበረ ሲገልጥ «ወኔሮንኒ ንጉሥ ዘይስመይቄሳር አኃዘ ጳውሎስ መመተሮ ርዕስ ሀገረ ሮምያ ወሉቃስ ቅዱስ
ተረፈ እምገደ ንጉሥ ወተሰወረ ወኮነ ይስበክ ወስተ ኮሎ በሐውርተ አህጉር ዘውስተ ይዕቲ አጽናፍ» ይላል፡፡ ስንክሳር ደግሞ
በበኩሉ «ወይሰስክ ሉቃስ በሀገሮ ሮሜ» ይላል፡፡ ስንክሳር ቅዱስ ሉቃስ በፉት በመቅዶኒያ፣ በኋላም በሮምና በዳርቻዎች
እየተዘዋወረ የክርስቶስን ወንጌል አስተምሮ እንደነበረ እንገነዘባለን፡፡
የቅዱስ ሉቃስ ዕረፍት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 95


ኔሮን ቄሳር ባስነሳው ስደትና መከራ ቅዱ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ በሞተ ጊዜ የብዙ ክርስትያኖች እልቂት ተፈጽሞ
ነበር፡፡ ሉቃስ ግን ሰኔሮን ሉቃስ ተሰውሮ ወንጌልን በመስበክ ላይ ነበር፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተለያዩ ተአምራቶችን
እያደረገ ብዙ ህዝብ ሲያሳምን ያዩ ናህናተ ጣዖት ወደ ኔሮን ቄሳር ሄደው «በስራው ብዙ ህዝብ እየተሳሳተ ነው» ብለው
ከሰሱት፡፡ ከዚያም ተይዞ በኔሮን ቄሳር ፊት ቀረበ፡፡ ንጉሥ ኔሮንም «እስከመቼ አንተ ሰዎችን በስራህ ታስታለህ?» ባለው ጊዜ
«እኔ መሰርይ አይደለሁም የህያው የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ መልዕክተኛ እንጂ» ብሎ መለሰለት በዚህን ጊዜ
ኔሮን ተቆጥቶ እጁን እንዲቆርጡት አዘዘና መጽሐፍት የሚጽፍበትን ቀኝ እጁን አስቆረጠው፡፡ ሉቃስ ግን ፀሎት እያደረገና
የተቆረጠጭውን እጁን ቀጥሎ የኢየሱስ ክርስቶስን ሀይል አሳየው፡፡ የጭፍሮቹን አለቆች ጨምሮ 270 ነፍሳት ይህን አይተው
በክርስቶስ አመኑ፡፡ በዚህን ጊዜ ኔሮን በጣም ተቆጣና እነዚህን ሰዎችና ቅዱስ ሉቃስን በሰይፍ አስገደላቸው፡፡ ሉቃስን
በሰይፍ ሊገድሉት ከመጡት ጭፍሮች አንዱ አንድ አይኑን ታውሮ ነበር፡፡ ገና ወደ ሉቃስ ሲቀርብ የታወረ አይኑ በራለት፡፡
በዚህ ተገርሞ በእግሩ ስር ወድቆ ሉቃስን ይቅርታ ጠየቀውና ንስሀ ገባ፡፡ ሌላው ጭፍራ ግን ይህን ያመነውን ሰው በድኑን
ወደ ባህር ጣሉት፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ሞገድን አስነስቶ ወደ አንዲት ደሴት አደረሰው አንድ አማኝም አግኝቶ ገነዘውና
ቀበረው፡፡ በማለት ገድለ ሐዋርያትን ስንክሳር ይተርካሉ፡፡ ስንክ ጥቅ 12
ሉቃስ የሞተው በ 84 ዓመቱ ሲሆን እስከ 84 ዓመቱ ድረስ ግን ሚስት ያላገባ ሰው እንደነበር ጥንታዊያን መረጃዎች
ይገልጣሉ፡፡
ወንጌሉ የተጻፈበት ቦታ ቋንቋና ዘመን
ወንጌሉ የተጻፈበት ቦታ ቋንቋና ዘመን የተለያየ አመለካከት አለ፡፡ ይኸውም ዘመናውያን የሆኑ ሊቃውንት የሉቃስ ወንጌል
ከሐዋርያት ስራ አስቀድሞ የተጻፈ መሆኑ በሐ.ሥ 1 2 ስለተገለጠ የሐዋርያት ሥራ የተጻፈው ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ በሮም
ለሁለት ዓመት ታስሮ ከነበረበት ጊዜ /62-64/ ዓ.ም በኋላ ወዲያውኑ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ መቅድመ ወንጌልና የትርጓሜ
ወንጌል የታሪክ አምድ ደግሞ ሉቃስ ወንጌሉን የጻፈበት ሀገር መቄዶኒያ የጻፈበት ቋንቋ /ልሳን/ ዮኒና የተጻፈበት ዘመን ደግሞ
ጌታ ካረገ ሀያ አንድ አመት ተፈፅሞ ሃያ ሁለተኛው ሲጀመር ቀላውዲዎስ ቄሳር በነገሰበት በዐሥራ አራተኛው ዘመን እነደሆነ
ይገልጣሉ፡፡ ዘመናት ወደ ዓመተ ምህረት ስንለውጠው ከጌታ ዕርገት በፊት 33 ዓመትከጌታ ዕርገት በኋላ 21 ዓመት ድምር
54 ዓ.ም ይሆናል፡፡
ስለተጻፈበት ቦታ፣ቋንቋና ዘመን ይህን ሁሉ አጠቃሎ የሚናገረው በሉቃስ ወንጌል ትርጓሜ መደምደሚያ ላይ
የሚገኘው ቃል ነው፡፡ እርሱም በግእዝ እንዲህ ይላል፡፡
«መልዓ ፅሕፈተ ብሥራቱ ለሉቃስ ወንጌላዊ አሐዱ እምስብአ ወክልኤቱ እርድእት ዘጸሐፎ በልሳነ ዮናኒ ላሰብእ ሀገረ
መቄዶኒያ እምድኀረ ዕረገቱ ለእግዚእነ ወስተ ሰማይ በእሥራ ወአሐዱ ዓመት ወበዐባርቱ ዓመት መንግስቱ ለአቅሌን ጽዮን
ቄሳር»
ከነዚህ መረጃዎች እንደተመለከትነው የተጻፈበትን ቦታና ዘመን በተመለከተ በኛ ትውፊት የተገለጠውና በሌሎች ሊቃውንት
የተነገረው አመለካከት የተለያየ ቢሆንም የተጻፈበትን ቋንቋ በተመለከተ ያለው አመለካከት ግን ተመሳሳይ ነው፡፡
ምክንያቱም በኛ ትውፊት «ዩናኒ» የተባለው ቃል «ኪኒ» የተባለው የግሪክኛ /የድርዕ/ ዲያሌክት ስለሆነ ነው፡፡
የተጻፈለት ሰው
የሉቃስ ወንጌል የተጻፈለት ሰው «ቴዎፍሎስ» የተባለ በሮም ግዛት ስር ያለ አንድ ባለስልጣን ነበር ይህም በወንጌሉ መግቢያ
ላይ ተገልጧል /1 1/ ቴዎፍሎስ ማለት መፍቀሬ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ሉቃስ በስብከቱ አስተምሮ ያሳመነው
ባለስልጣን እንደሆነ በወንጌሉ መጀመሪያ ላይ ካሉት የመግቢያ ቃላት እንገነዘባለን፡፡
አንዳንዶች ግን «ቴዎፍሎስ» የሚለው ይህ ስም የሚመለከተው አንድን የታወቀ ሰውን ሳይሆን መፅሐፉን እንዲያነቡ
የተጻፈላቸውን የእግዚአብሔር ወዳጆች ሁሉ ነው በማለት ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን አንድ የታወቀ ሰው መሆኑን የሚከተሉት
ማስረጃዎች ያገልጣሉ፡፡
 «ቴዎፍሎስ» የሚባለው ስም በዚያን ዘመን በግሪኮችና በአይሁዳውያን ዘንድ የግለሰቦች መጠሪያ ስም /የተጾውኦ ስም/
ሆኖ የተለመደ ስም ነበር ስለዚህ «ቴዎፍሎስ» የአንድ ሰው የተጾውኦ ስም መሆኑን እንረዳለን፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 96


 ሉቃስ ይህን ሰው ሲጠራው «ኦ-አዚዝ ታአፈላ- የተከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ/most excellent/most noblel/» ብሎ
ይጠራዋል፡፡ ስለዚህም አያይዞ የሚናገራቸው ቃላት ሁለተኛ መደብ ነጠላ ቊጥር የሆኑ ቃላት ስለሆኑ ቴዎፍሎስ በሮም
ግዛት ውስጥ አንድ የታወቀ ባለስልጣን የነበረ ሰው መሆኑን እንገነዘባለን /11-4/
 የሉቃስ ወንጌል ትርጓሜ /አንድምታ/ በመግቢያው ላይ ቴዎፍሎስ /ታኦፈላ/ በመቄዶንያ አጠገብ ያለችው የእስክንድርያ
መኮንን /ሀገረ-ገዥ/ እንደነበርና በሉቃስ ስብከት ክርስትናን የተቀበለ ሰው እንደሆነ ገልጦ ይናገራል፡፡
ወንጌሉ የመጽሐፉ ዓላማ
የሉቃስ ወንጌል 24 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን የመጽሐፉ ዓላማ በዋናነት
 «ቴዎፍሎስ» ለተባለ በሮም ግዛት ስር ላለ አንድ ባለስልጣን ነው፡፡
 በሮም ግዛት ውስጥ የሚኖሩትን ወደ ክርስትና የተመለሱትን ለማጽናት ያልተመለሱትን ደግሞ ለመመለስ ነው፡፡
 ከሁሉም መፅሐፍት በበለጠ ሁኔታ የእመቤታችንን ፍቅርና እናትነት ለመግለፅ ፅፏል
 ስለፀሎት አስፋፍቶ ለመፃፍ
የወንጌሉ ዝርዝር አሰፋፈር
በአጠቃላይ የሉቃስ ወንጌል 24 ምዕራፎች አሉት
መግቢያ /ለምን? ለማን? እንዴት እንደጻፈው ይገልጣል /11-4/
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ የሕፃንነት ታሪክ /15-252/
 መልአኩ ገብርኤል ወደ ዘካሪያስ በተላከ በ 6 ኛው ወር ወደ ድንግል ማርያም ተልኮ ጌታን እንደምትወልድ
ማብሰሩ፡፡
 ድንግል ማርያም በኤልሳቤጥ ቤት /139-59/
 የመጥምቁ ዮሐንስ መወለድ መገረዝና ማደግ /157-80/
 ጌታ ሲወለድ እረኞች በቤተልሄም በግርግም እንደተወለደ /21-20/
 ሊገርዙት 8 ቀን ሲሞላ ጊዜ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ እንደተጠራ /221/
 መሥዋዕት ሊያቀርብ ወደ ኢየሩሳሌም እንደወሰዱት
 በ 12 ዓመቱ ለፋሲካ በአል ወደ ኢየሩሳሌም እንደወጣ /140-51/
 በጥበብ በቁመትና በሞገስ ማደጉ /252/
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሊጀምር ሲዘጋጅ የተደረጉ ነገሮች /31-413/
 የመጥምቁ ዮሐንስ ጥምቀትና ስብከት
 የጌታ መጠመቅ /321፡22/
 እስከ አዳም የተቆጠረው የጌታ ሐረገ-ትውልድ/323-283/
 በምድረ በዳ 40 ቀን በዲያቢሎስ እንደተፈተነ /41-13/
ጌታ በገሊላና ባጠገቧ ባሉ አገሮች ያደረገውና ያስተማረው ነገር /414-950/
 በናዝሬት ምኩራብ ያስተማረው ት/ት /414-30/
 በቅፍርናሆም ያረጋቸው ተአምራት /431-48/
 በጌንሳሬጥ ባህር ዳር ስምዖንና የዘብዴዎስን ልጆች መጥራቱ /51-11/
 በቅፍርናሆም ውስጥ በቤት፤ በምኩራብና፣ በከተማዋ ዙሪያ ያደረጋቸው ነገሮች /512-616/
 በተካከለ ስፍራ የሰጠው ሰፊ ት/ት /617-49/
 በምድረ በዳና በፈሪሳውያን ቤት ያደረገውና ያስተማረው /718-50/
 እየተዘዋወረ ሲያስተምር በምሳሌዎች ያስተማረው ት/ት /81-21/
 ከገሊላ ወደ ጌንሳሬጥ ተሻግሮ እንዲሁም ወደ ገሊላ ለመልሶ ያደረጋቸው ታምራት /822-56/
 በገሊላ ውስጥ ለመጨረሻ ጊዜ ለሐዋርያት የተናገረውና ያሳያቸው ነገሮች /91-50/
ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም በመጓዝ ላይ ሳለ ይሁዳ ውስጥ ሳይገባ ያደረጋቸው ነገሮች /951-1037/
 በሰማያት ሊያልፍ ሲል ስላልተቀበሉት ወደ ሌላ መንደር መሄዱ /951-56/
 በትክክለኛ አሳብ ሳይሆን በጉዞው ሲከተለው የጠየቀውን እንዳልተቀበለው /957-62/

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 97


 ሰገ አርድእትን ሹም በፊቱ ወዳሉ ከተሞች እንደላካቸው /101-24/
 በጉዞ ላይ ሳለ ሊፈትነው ለጠየቀው ሕግ አዋቂ የሰጠው መልስ /1025-37/
ወደ ኢየሩሳሌም በመውጣት ላይ ሳለ በይሁዳ ውስጥ ያደረጋቸው ነገሮች /1038-1927/
 በቢታንያ ማርታ በቤትዋ እንደተቀበለችው /1038-42/
 በጉዞ ላይ በተለያዩ ስፍራዎች ለሕዝብና ለደቀመዛሙርቱ ያስተማራቸው ተለያዩ ት/ቶች /111-1834/
ወደ ኢየሩሳሌም ከገባ በኋላ /በመጨረሻው ሳምንት/ ያደረጋቸውና ያስተማራቸው ነገሮች /1928-2246/
 ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ህዝቡ እየዘመሩ እንደተቀበሉት /1928-46/
 በዚህ ሳምንት በመቅደስ ዕለት ዕለት ያስተማረው ት/ት /1947-2138/
 በፋሲካ ምሽት ያደረጋቸውና የነገራቸው ነገሮች/221-46/
የጌታ የስቅለቱ ታሪክ
 ተይዞ ለሊቀካህናቱ፣ በጲላጦስና በሄድሮስ እንደተመረመረ /2247-2325/
 በብዙ መከራ አሰቃይተው በመስቀል እንደሰቀሉት /2326-49/
 ዮሴፍ ዘአርማትያስ ከዓለት የተወቀረ አዲስ መቃብር ውስጥ እንዳኖረው /2350-56/
የጌታ ትንሳኤውና እርገቱ /241-53/
 ከተነሣ በኋላ ለተከታዮቹ በተለያዩ ቦታዎች መታየቱ /241-43/
 ለሐዋርያት የተናገራቸው የመጨረሻዎቹ ቃላት /2444-49/

4. የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል


ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ

ቅዱስ ዮሐንስ አባቱ ዘብዴዎስ፣ እናቱ ደግሞ ሰሎሜ (ማርያም ባውፍልያ) ይባላሉ፡፡ በአባቱ ከነገደ ይሁዳ ሲሆን በእናቱ ደግሞ ከነገደ
ሌዊ ነው፡፡ ሀገሩም የገሊላ ክፍል በምትሆን በሲዶና ነው፡፡ ታላቅ ወንድሙም ያዕቆብ ይባላል፤ ርሱም በሄሮድስ አግሪጳ ዘመን በ 44 ዓ.ም
በሰማዕትነት ያረፈው ነው፡፡ እናቱ ቅድስት ሰሎሜም ከ 36 ቱ ቅዱሳት አንስት መካከል አንዷ ስትሆን ጌታ በገሊላ ሳለ ያገለግሉት ከነበሩት
ቅዱሳት አንስትም አንዷ ነበረች፤ ጌታችን በተነሣባት ማለዳ ሽቱ ለመቀባት ከሔዱት ሴቶችም መካከል አንዷ ነች፡፡ (ማር 16፤1) እጅግ
መልካምና ጻድቅ ሴት እንደ ነበረችም አባቶች መስክረውላታል፡፡ (ማቴ 27፤56)

ወንጌላዊው ዮሐንስ ከሦስቱ አዕማደ ሐዋርያት (ምስጢረ ሐዋርያት፤ መዝገበ ሐዋርያት) መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህንንም ቅዱስ
ጳውሎስ በገላትያ መልእክቱ ላይ፣ “አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ኬፋ ዮሐንስም. . .” በማለት ገልጦታል፡፡ ገላ 2፤9፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ
አዕማድ ሐዋርያ መባሉም ለጌታ ፍቅር ስለሚቀና ነው፡፡ ከጽኑ ፍቅሩም የተነሣ አይሁድን ሳይፈራ እስከ እግረ መስቀል የደረሰ ሐዋርያ ነው፡፡
በዚህም ምክንያት ጌታችን በመስቀል ሥር የተገኘችውን እናቱን በመስጠት ለርሱ ያለውን ፍቅር ገልጾለታል፤ ምክንያቱም አባት ለሞት በተቃረበ
ጊዜ ያለውን ሃብቱን የሚናዘዘው ለሚወደው ልጁ እንደሆነ ሁሉ ጌታችንም ምድራዊ ሃብት ባይኖረውም የዕውቀት ማኅደር፣ መዝገበ ምስጢር
የሆነችውን የቀረችውን አንድ ሃብቱን እመቤታችንን የሰጠው ለሚወደው ደቀመዝሙሩ ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ
እመቤታችንን ከተረከበ በኋላ እስካረፈችበት ጊዜ ድረስ ለ 15 ዓመታት በቤቱ አኑሯታል፡፡

ከበዓለ ጰራቅሊጦስ በኋላ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በመሆን በኢየሩሳሌም፣ በአንጾኪያ፣ በሎዶቅያ፣ በእስያ ከተሞች በተለይም በኤፌሶን
አስተምሯል፡፡(ዮሐ 19፡27) በኤፌሶን በሚያስተምርበት ጊዜ ንጉሥ ድምጥያኖስ ለራሱ ምስል እንዲሰግድ ባዘዘበት ወቅት ዮሐንስ ይህን
በመቃወም ወደ ፍጥሞ ደሴት ተግዟል፡፡ በወጣትነቱ ተጠርቶ በዕለተ ዓርብ ያየውን የጌታች መከራ እያሰበ ያነባ የነበረ የተጠራበት የአገልግሎት
ጊዜው ጀምሮ በፍቅር በታማኝነት እስከመጨረሻው ድረስ የጸና ከጌታው ያልተለየ ሐዋርያ ነው፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል

የቅዱስ ወንጌል የተጻፈው ከፍጥሞ ደሴት ግዞቱ ሲመለስ በኤጂያን ባሕር ወደብ በ 96 ዓ.ም አካባቢ ነው፡፡ ወንጌሉ ከትረካ ይልቅ ነገረ መለኮታዊ
(theological) ይዘት ስላለው ከሌሎቹ ወንጌላት(Synoptic Gospels) ይለያል፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስ ወንጌላትን ሲጽፍ ዋና ሐሳቡ የወልደ
እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት መመስከር ነው፡፡ (ዮሐ 20፡21) በመደጋገምም ‹‹የዘለዓለም ሕይወት የሚሰጥ የእግዚአብሔር ልጅ››
ይለዋል፡፡ ተአምራቱም አምላክነቱን የሚገልጡ ናቸው፡፡ (ዮሐ 2፡11) ኢየሱስ ክርስቶስ በሚጸልዩበት ጊዜ የእግዚአብሔር አብ ልጅ መሆኑን በዚሁ ወንጌል
ላይ ገልጧል፡፡ (ዮሐ 17፡1-5) በዚህ ወንጌል ሰባት ጊዜ “እኔ ነኝ” በማለት ማንነቱን ገልጧል፡፡ (ዮሐ 6፡35) ቅዱስ ቶማስም በዚህ ወንጌል ‹‹ጌታዬ
አምላኬም›› በማለት ጌትነቱንና አምላክነቱን መስክሯል፡፡ (ዮሐ 20፡28)

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 98


ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን የጻፈበት ምክንያት

መጽሐፍ በአጠቃላይ የጌታችንን ታሪክ፣ ትምህርትና ተአምራት በጥልቀት የሚመረምር ቢሆንም ወንጌሉ የተጻፈበት ሌሎች ዝርዘር ምክንያቶች
አሉት፡፡ ከእነርሱም በጥቂቱ

 ከሦስቱ ወንጌላት ከማቴዎስ፣ ማርቆስና ሉቃስ የጎደለውን በመንፈስቅዱስ መሪነት ለመሙላት


 ቅድመ ዓለም የነበረው፣ ሥጋን የተዋሐደው ትንቢት የተነገረለትና ሱበኤ የተቆጠረለት መሲሕ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ማስረዳት
 የእነ ሄራቅሎጦስ የሎጎስ(Logos) አመለካከት ከአይሁዳውያ አመለካከት ጋር ቀላቅለው የሚያስተምሩ ነበሩ ቅዱስ ዮሐንስ የሎጎስን (የቃልን)
እውነተኛ ትርጓሜ ‹‹ቃለ እግዚአብሔር ወልደ እግዚአብሔር ነው›› በማለት ጽፎላቸዋል፡፡
 የሰው ልጆች ሁሉ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ መሆኑን አምነው የዘለዓለም ሕይወት የማይገኙ መሆኑን ጽፏል፡፡
 የሕይወት እንጀራ፣ የዓለም ብርሃን፣ የበጎች በር፣ መልካም እረኛ፣ ትንሣኤና ሕይወት፣ መንገድ እውነትና ሕይወት ‹‹እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ››
የሚለውን የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነትና አምላክነትን የማይገልጽ መሆኑን ለማስረዳት ጽፏል፡፡
የዮሐንስ ወንጌል የመጽሐፉ አከፋፈል

ምዕ 1፡- ስለ ጌታ ቅድመ ዓለም ህልውናና በሥጋ መገለጥ


ምዕ 2፡- ስለ ቃና ዘገሊላ ተአምር
ምዕ 3፡- ስለ ኒቆዲሞስና ስለ ዳግም ልደት
ምዕ 4፡- ስለ ሳምራዊቷ ሴት
ምዕ 5፡- የመጻጉዕ መፈውስና ለአይሁድ ስለተሰጡ ትምህርቶች
ምዕ 6፡- ስለ ምስጢረ ቊርባን
ምዕ 7፡- አምስት ሺህ ሕዝብ ስ፤መመገቡና በባሕር ላይ ስለመጓዙ እንዲሁም ስለተቃዋሚዎቹ
ምዕ 8፡- ለአይሁድ ስለተሰጠው ትምህርት
ምዕ 9፡- ዕውር ሆኖ ስለተወለደው ልጅ
ምዕ 10፡- ጌታችን ራሱን በበጎች እረኛ መመሰሉን
ምዕ 11፡- ስለ አልዓዛር ትንሣኤና የአይሁድ ተቃውሞ
ምዕ 12፡- ወደ ኢየሩሳሌም ስለመግባቱና የአይሁድ ተቃውሞ
ምዕ 13፡- ስለ ሕጽበተ እግርና ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች
ምዕ 14፡- በዕለተ ሐሙስ ስለተፈፀመው የጌታ ራት
ምዕ 15 – ምዕ 16፡- ስለ ጌታ ሰማኒ
ምዕ 17፡- ስለ እግዚአብሔር አብ
ምዕ 18፡- ስለ ጌታ መያዝና ስለ ጲላጦስ ፍርድ
ምዕ 19፡- ስለ ጌታ መስቀል፣ መሞትና መቀበር
ምዕ 20፡- ለማርያም መግደላዊትና ለሐዋርያው ቶማስ ስለተሰጡ ትምህርቶችና ስለ ሥልጣነ ክህነት
ምዕ 21፡- አንቀጸ ኖላዊ
የታሪክ ክፍል

1. የሐዋርያት ሥራ
መጀመሪያ ክቡራን ቅዱሳን ሐዋርያት ለተልእኮ የተመረጡተት በራሱ በጌታችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
መሆኑን እንጠቅሳለን፡፡ ሐዋርያት የሚለው ቃል የሐዋርያ ብዙ ቊጥር ሲሆን ሐዋርያ ማለትም ‹‹ሖረ›› ‹‹ሔደ›› ካለው
የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደጃዝማች ፣የተላከ፣ሔያጅ፣ለዑክ ማለት ነው፡፡(ማቴ ትርጓሜ 10፡2)፡፡
የሐዋርያት ሥራ የ 12 ቱን የመላውን ታሪክ በመጠኑ ይናገራል፡፡ይህም በኢየሩሳሌም ውስጥ 12 ቱም ሐዋርያት
የሠሩትን ሥራ የሚገልጽ ክፍል ነው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 99


ስያሜው፡- የሐዋርያት ሥራ በግእዙ ‹‹ግብረ ሐዋሪት››ተብሎ ይጠራል፡፡ለመጽሐፉ በተሰጠው ርእስ ውስጥ “መጽሐፈ ግብረ
ልኡካን ዜና ሐዋርያት” ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሐዋርያት መጽሐፍ 41፣ አምስተኛው ወንጌል፣ የመንፈስ ቅዱስ
ወንጌል፣ የትንሣኤ ማረጋገጫ42 እየተባለ በጥንታውያን መጽሐፍት ውስጥ ተጠቅሷል፡፡
የሐዋርያት ሥራ ስያሜ ሐዋርያት በመንፈረስ ቅዱስ መሪነት ቤተክርስትን መስራታቸውን ወንጌል መስበካቸውን ታምራት
ማድረጋቸውን ለክርስትና እምነት መስፋፋት ያደረጉትን ሥራ የሚገልጽ ስያሜ ነው፡፡
የሐዋርያት ሥራን ማን ጻፈው
የሐዋርያት ሥራ ጸሐፊ ወንጌላዊ ሉቃስ ነው፡፡ ይህን ከሚያረጋግጡልን ነገሮች መካከል ጥቂቱን እንመለከታለን፡-
 የቅዱስ ጳውሎስን ሐዋርያዊ ጉዞ እስከ ሮም ድረስ አብሮ መሳተፉን ጸሐፊው በተለያየ የመጽሐፉ ክፍል መጥቀሱ
(ሐዋ.16፡10-40, 20፡5-6, 21፡1-8, 27፡1-28)
 በሉቃስ ወንጌል 1፡1 ላይ ወንጌሉ ለቴዎፍሎስ እንደተጻፈ እንደሚገልጽ ሁሉ በሐዋርያት ሥራ 1፡1 ላይም እንዲሁ
የቴዎፍሎስን ስም በመጥቀስ መጽሐፉን መጀመሩ፡፡
 በሁለቱም መጻሕፍት መካከል የአጻጻፍ ዘዴ እና የቋንቋ አጠቃቀም ተመሳሳይነት መኖሩ፡፡
 ተመሳሳይ የሆኑ ሀሳቦች በሁለቱም መጻሕፍት ውስጥ መገኘታቸው፡፡ ለምሳሌ፡-
 ስለ ዓለም ሁሉ ድኅነት (ሉቃ. 2፡32; ሐዋ. 10፡34)
 ስለሴቶች አገልግሎት (ሉቃ.7፡37-38; ሐዋ.9፡36)
 ስለጸሎት (ሉቃ. 11፡13; ሐዋ. 1፡24)
 ኃጢአትን ይቅር ስለማለት (ሉቃ. 38፡2; ሥራ. 5፡31)
 ሁለቱም መጻሕፍት በውጭ መንግሥት ላይ ጉዳት ከማድረስ የተቆጠቡ ናቸው፡፡ (ሉቃ. 20፡20-26; ሐዋ. 16፡36-
39)
 በሁለቱም መጻሕፍት ውስጥ ጸጋ የሚለው ቃል ተደጋግሞ የተጠቀሰ ሲሆን በአንጻሩ ግን ማቴዎስ እና ማርቆስ
አንድም ጊዜ ቃሉን አልተጠቀሰም፡፡
 የተለያዩ የህክምና ቃላትን መጠቀሙ፣ ስለህመምተኞች ክብካቤ እና ስለማዳን የተነገሩ ተአምራትንና ምልክቶችን
መጥቀሱ፤ ቅዱስ ሉቃስ ሀኪም ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሐዋርያት ሥራን እርሱ እንደጻፈ ያረጋግጥልናል፡፡
መጽሐፉ ለማን ተጻፈ
ከላይ እንደተገለጸው የሐዋርያት ሥራ የተጻፈው ለቴዎፍሎስ ነው፡፡ /ሐዋ 1፡1/ ቴዎፍሎስ የታወቀ የእስክንድሪያ ሰው
እንደሆነ ይታመናል፡፡ መጽሐፈ ስንክሳርም ስለ ሉቃስ ታሪክ የሚተረክ ክፍል መጽሐፉ ለቴዎፍሎስ መጻፉን ሲያስረዳ
‹‹ወዝንቱ ቅዱስ ጸሐፈ ወንጌሉ ለቴዎፍሎስ ወኮነ እምነ አሕዛብ ወካዕበ ጸሐፈ ሎቱ ግብረ ሐዋርያት ›› በማለት
ነው፡፡/ጥቅምት 22 ስንክሳር/
የተጻፈበት ዘመን፣ ቦታና ቋንቋ
የሐዋርያት ሥራ የተጻፈው በ 63 ዓ.ም እንደሆነ ይታመናል፡፡ ለዚህም የሚቀርበው ምክንያት የሐዋርያት ሥራ
የመጨረሻው ቃል “ጳውሎስም በገንዘቡ በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ተቀመጠ ወደ እርሱ የሚመጣውንም ሁሉ ይቀበል
ነበር፤ ማንም ሳይከለክለው የእግዚአብሔርን መንግሥት ይሰብክ ነበር ስለ ጌታቸን ስለኢየሱስ ክርስቶስ እጅግ ገልጦ
ያስተምር ነበር” ይላል፡፡ (የሐዋ 28፡30-31)፡፡ ይህም አጨራረሱ ሉቃስ የሐዋርያት ሥራን የጻፈው ጳውሎስ በሮም
በቆየባቸው ጊዜያት ውስጥ እንደሆነ ፍንጭ ይሰጠናል፡፡ ነገር ግን ጳውሎስና ጴጥሮስ በኔሮን ቄሳር ሰማእትነትን
ከተቀበሉበት ከ 64 ዓ.ም በፊት መጻፉ እርግጥ ነው፤ ምክንያቱም ከ 63 ዓ.ም በኋላ ተጽፎ ቢሆን ኖሮ የሰማእትነታቸው
ነገር ይካተት ነበር፡፡
የሐዋርያት ሥራ የተጻፈበት ቦታ በሮም ሲሆን የተጻፈበት ቋንቋ ደግሞ በፅርእ /ግሪክኛ/ ነው፡፡

41
የግሪክና የላቲን አባቶች እና ሌሎች የአሌክሳንድሪያ ጽሑፎች ላይ ተጠቅመውበታል፡፡
42
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 100


የመጽሐፉ መገለጫዎች
 እርግጥ/accurate/ የሆኑ ታሪካዊ ክስተቶችን እና ዝርዝር የሆኑ ትረካዊ አጻጻፎችን ተጠቅሟል፡፡
 ሥነ-ጽሑፋዊ እና ማራኪ የሆነ የአጻጻፍ ዘዴ ይንፀባረቅበታል፡፡
 በደካማው በሰው ልጅ (የቤተክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ) ውስጥ የታየውን የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ማስረዳት
(ሐዋ 15፡39)
 ምስክርነት፣ መመስከር የሚሉ ቃላትን አብዝቶ ተጠቅሟል፡፡
 በሐዋ. 1፡8 ላይ “መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችው” እንዳለ መጽሐፉ የኃይል መጽሐፍ
ነው፡፡
የተጻፈበት ዓላማ
 የቅድስት ቤትክርስትያን አመሰራረት ዕድገት ለመግለጽ
 የርደተ መንፈስ ቅዱስን ሁኔታ ለማስረዳት
 ይህ የተለያየ የክርስትና መጽሐፍ እውነተኛ የክርስትና ጠባይን ለማሳወቅ
 ቅዱሳን ሐዋርያት የኢየሱስ ክርስቶሰን ወንጌል በሐዋሪያት አማካኝነት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በቅርብም በሩቅም ባሉ
ሀገሮች ትእዛዝ በመፈጸም ወንጌልን እንዳዳረሱ በመግለጥ ተጽፏል፡፡ይህን ዓላማውን በግለጽ የሚጠቁመው ቃል(በሐዋ
ሥራ 1፡8)ላይ ያለው ቃል ነው፡፡
 የቅዱሳን ሐዋርያትና ሃይማኖትና ተግባር(ሥራ) እንድንከተል ተጽፏል፡፡
ወንጌል ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም ድረስ በየሀገሮቹ እንዴት እንደተዳረሱ እና የተዳረሰባቸውን ቦታዎችን በሐዋሪያት ሥራ
ላይ የሚገልጹልን ጥቅሶች አሉ አነርሱም፡፡
1. በምድር እስራኤል
 በይሁዳ ኢየሩሳሌም 1፡1-7፡60፤11፡1-18፤12፡1-25
 ልዳ(9፡32-35)
 ኢዮጴ(9፡36-43)
 በሰማርያ ሰማርያ (8፡1-25)
 ቂሣርያ (10፡1-48፤18፡22፤21፡8-16፤23፡32-26፡32)
 በገሊላ ገሊላ(9፡31)
2. በፍልስጥኤም
 ጋዛ (ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ(8፡26-39)
 አዛጦን(8፡40)
3. በፊንቄ(11፡19፤21፡1-7፤27፡3)
4. በቆጵሮስ (11፡19፤13፡4-12፤15፡39)
5. በሶርያ ደማስቆ (9፡1-25)
 አንጾኪያ (11፡19-30፤13፡1-3)
6. ታናሿ እስያ ገላትያ (13፡13-14፡28፤16፡6፤18፡23)
 እስያ (18፡24-41፤20፡7-38)
7. ግሪክ ፊልጵስዮስ (16፡9-40፤20፤1-6)
 ተሰሎንቄ (17፡1-9)
 ቤርያ (17፡10-15)
 አቴና (17፡16-34)
 ቆሮንቶስ (18፡1-17፤18፡26-19፡1፤20፡2)
8. ሮም (27፡1-28፡31)
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ጥቅሶች እያወጣን በነዚህ ሀገሮች ያደረጉት ተአምራት መመልክት እንችላለን፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 101


የሐዋሪያት ሥራ አከፋፈል
የሐዋርያት ሥራ 28 ምዕራፎቹ ሲኖሩት በሦስት ዐበይት ክፍሎች ተከፍሏል አከፋፈሉም እንደሚከተለው ነው፡፡
1. መግቢያ
ለቴዎፍሎስ በመጀመሪያ ከተጻፈለት መጽሐፍ ቀጥሎ እንደተጻፈ /1፡1-5/
ከእርሱ የሰሙትን አብን ተስፋ እንዲጠብቁና ስለጥምቀት/ 1፡4/
ጌታ ሐዋርያት እያዩት ወደ ሰማይ እንዳረገ /1፡9-12/
11 ዱ ሐዋርያትና ሌሎች ደቀመዛሙርት ከጌታ እናት ጋር ለጸሎት ይተጉ እነንደነበር /1፡13-14/
2. በኢየሩሳሌምና በአካባቢዋ በቀደሙት ሐዋርያት የተሠሩ ሥራዎች
ስለ ሐዋሪያት ምርጫና በአስቆሮቱ ይሁዳ ምትክ ማቲያስን በዕጣ እንደተኩ/1፡15-26/
ኀምሳው ቀንም በተፈጸመ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት መውረዱ/2፡1-13/
የጴጥሮስ ምስክርነት/2፡14-20/
ቅዱስ ጴጥሮስ ከዐሥራ አንዱ ጋር ቆሞ በሰበከው ስብከት በዚያች ዕለት ሦስት ሺ ያህል ሕዝብ እንዳመኑ /2፡20-
47/
ጴጥሮስና ዮሐንስ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለ 40 ዓመታት ያህል ሽባ የነበረውን እንደፈወሱ/3፡1-11/
ጴጥሮስና ዮሐንስም ይዘውት ወደ መቅደስ ሲገቡ የጴጥሮስ ንግግር በቤተ መቅደስ/3፡12-26/
ጴጥሮስን የሐንስ በካህናት ሸንጎ ፊት በእግዚአብሔር እርዳታ እንደሆነ ሽባውን የፈውሱት ያስተማሩበት/4፡1-31/
ስለ ምዕመናን አንድነትና ዮሴፍ የሚባል የቆጵሮስ ሰው እርሻውን በሐዋርያ እግር አጠገብ እንዳኖሩት/4፡32-37/
ሐናኒያና ሚስቱ መሬቱን እንደሸጡትና የሸጡበትን እኩሌታ ቀንሰው ሲሰጡ እግዚአብሔር እንደቀጣቸው/5፡1-14/
ድውያንና ክፉዎች አጋንንት የያዛቸውን ስለመፈወሳቸው/5፡15-16/
ሐዋርያት በአንድነት መከራ እንደተቀበሉ ሊቃነ ካህናትና ሰዱቃዊያን ሐዋርያትን እንዳሳደዱዋቸው/5፡17-42/
የሰባቱ ዲያቆናት ምርጫ እንዲሁም የእስጢፋኖስና የፊልጶስ አገልግሎት/6፡1-8/
የእስጢፋኖስ ምስክርነት ስለ አብርሃም/7፡1-8/
ስለዮሴፍ ወደ ግብጽ መሸጥና ያዕቆብ ወደ ግብጽ ስለ መውረዱ/7፡9-19/
ስለ ሙሴ ታሪክና ወደ ግብጽ ስለመላኩ/7፡20-50/
የእስጢፋኖስ የመጨረሻ ንግግርና በድንጋይ መገደል/7፡51-60/
በቤተክርስትያን ስለደረሰው ስደትና ሳውል ቤተክርስትያንን እንዳሳደደ/8፡1-25/
የሳውል መጠራትና የመጀመሪያ ሥራው/9፡1-30/
ጴጥሮስ በልዳ፣ በኢያጲርና፣ በቂሳርያ ስለሠራው ሥራ /9፡31-11፡18/
የአንጾኪያ ቤተክርስትያን መመስረትና ማደግ/11፡19-30/
በሄሮድስ እጅ የያዕቆብ መሞትና የጴጥሮስ መታሰር/12፡1/
መልአክ ጴጥሮስን ከወኅኒ ቤት እንዳወጣና የሄሮድስ ተልቶ መሞት/12፡6-25/
3. በቅዱስ ጳውሎስ አማካኝነት በአሕዛብ ሀገር የተሠሩ ሥራዎች
ጳውሎስ በአንደኛው ሐዋርያ ጉዞው የሠራቸው ሥራዎች/13፡1-14/
አሕዛብን በሚመለከት በኢየሩሳሌም የተደረገው የመጀመሪያው ጉባኤ/15፡1-35/
ጳውሎስ በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው የሠራቸው ሥራዎች/15፡36-18፡22/
ጳውሎስ በሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው የሠራቸው ሥራዎች /18፡23-21፡16/
ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ከተያዘ በኋላ በቂሳሪያ ታስሮ ለሁለት ዓመት መቀመጡ/21፡17-26፡37/
ጳውሎስ ታስሮ ሳለ ይግባኝ በጠየቀው መሠረት ወደ ሮም መወሰዱ/27፡1-28፡16/
ጳውሎስ በሮማ በነጻነት ስለ ክርስቶስ ማስተማሩ/28፡17-33/

የመልእክታት ክፍል

የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት አጠቃላይ እይታ

የቅዱስ ጳውሎስ ልደት፣ መጠራትና ጥምቀት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 102


ቅዱስ ጳውሎስ የተወለደበት ሀገር በኪልቂያ አውራጃ ጠርሴስ ከተማ ሲሆን በሃይማኖት የፈሪሳውያን ወገን ነበር። ከነገደ ብንያም እንደተወለደ ራሱ
መስክሯል። (ሮሜ 11፣1 ሐዋ 21፣39 ሐዋ 22፣3) ሮማዊ ዜግነት እንደነበረውም ተገልጧል። (ሐዋ 9፣11 ፊል 3፣5)

የቅዱስ ጳውሎስ የቀድሞ ስሙ ሳውል ሲሆን ትርጉሙም የእግዚአብሔር ጥያቄ ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ታላቅ አእምሮ የነበረው የማስተዋል
ኃይል የተሰጠው መንፈሳዊ ፍላጎትም የነበረው ሰው ነው። ወላጆቹ በልጅነት ወደ ኢየሩሳሌም ወስደው ለታላቁ የሕግ መምህር ለገማልያ ሰጡት።
በአይሁድም የአስተዳደግ ሥርዓት አሳደጉት። ሐዋ 5፣34 ዕብራውያን ከትምህርትም በተጨማረ ጥበብ ዕድ አብረው ስለሚያስተምሩ ጳውሎስም ድንኳን
መስፋት ተምሮ ነበር። ሐዋ 22፣3 ቅዱስ ጳውሎስ የሕግና የፍልስፍና ትምህርት ቤቶች መናኽሪያ በሆነችው ስመ ጥር የጠርሴስ ከተማ የኖረና በዘመኑ
የነበረውን የሕግ ትምህርት እንደተማረ ይታወቃል።

ቅዱስ ጳውሎስ ለአባቶቹ ሕግ ቀናተኛ በነበረ ጊዜ የክርስትናን ትምህርት በበኩሉ ይቃወም ነበር። ስለዚህ ጳውሎስ ለአባቶች ሕግ ቀናተኛ ሆኖ
ክርስቲያኖችን ከሚያስተምሩበት ሀገር አስወጥቶ ለማሳደድ ተነሣ፣ ክርስቲያኖችም ከጳውሎስና ከሌሎች አይሁድ ፍራቻ የተነሣ ከኢየሩሳሌም እየወጡ ወደ
ተለያዩ ቦታዎች ይሰደዱ ነበር። ገላ 1፣13-14

የቅዱስ ጳውሎስ መጠራት ከቀዳሜ ሰማዕት ከቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት የተነሣ ነበር፡፡ በተለይ ወደ ሶርያ፣ ወደ ደማስቆ ክርስቲያኖች ገብተው ብዙ
አይሁዶችን አጠመቁ፤ ሳውልም በዚህ ብስጭት ክርስቲያኖችን ከኢየሩሳሌም ለማሳደድ ከሊቀ ካህናቱ ፈቃድ ወስዶ አብረው ከሚጓዙት ጋር ከደማስቆ በር
ሲደርስ ድንገት ከሰማይ መብረቅ ወረደና መታው፡፡ ወደቀም፣ ዓይኖቹም ታወሩ፡፡ (ሐዋ 9፡4-28፣ ሐዋ 22፡1-12) ከሰማይም “ሳውል ሳውል ለምን
ታሳድደኛለህ” የሚል ድምጽ ሰማ፡፡ ሳውልም “አንተ ማን ነህ አቤቱ” አለው፡፡ ጌታም “የምታሰድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ” አለው፡፡ ጌታም የምትድነበትን
ታገኛለኛህና ወደ ከተማው ሂድ ብሎ አጽናናው፡፡ ተነስቶ አብረውት ከነበሩት ተጓዦቹ ጋር ገባ፡፡ አብረውት የነበሩት ሰዎች ጳውሎስን ድምጽ ይሰሙ ነበር
እንጂ የሚያናግረውን ሰው አያዩም ነበር፡፡ ወደ ከተማውም ገብቶ ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ሳይበላ ሰነበተ፡፡ በዚያ ከተማ ከ 72 አርድዕት ወገን ለሚሆን
ለሐናንያ ጌታ በሕልም ሳውልን እንዲያጠምቀው ነገረው፡፡ ሳውልን ካለበት ቤት ሲያጠምቀው ዓይኑ በራለት፣ መንፈስ ቅዱስ አደረበት ምስጢርም
ተገለጠለት፣ ማን ያሳድድ እንደነበርም ተረዳ ወዴት መጓዝ እንደነበረበትም ወሰነ፡፡ ለአዲሱ የክርስትና ሃይማኖቱም ቀናተኛ ሆኖ ሳይውል ሳያድር ዕለቱኑ
ማስተማር ጀመረ፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ጥቂት ቀን በደማስቆ ቆይቶ በዓረቢያ ምድረ በዳ ሦስት ዓመት ተቀመጠ፡፡ ሱባኤውንም ፈጸመ (ገላ 1፡17)፡፡ ከዚያም በኋላ ወደ
ደማስቆ ተመልሶ ብዙ አይሁድንና አሕዛብን በማሳመኑና በማጥመቁ ብዙዎች አይሁድ ተቆጥተው ሊገድሉት የደማስቆን በር ቀንና ሌሊት ሲጠብቁ የሰሙ
ክርስቲያኖች በመስኮት አስወጥተው በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት፡፡

ቅዱስ ጳውለስ በሦስት ሐዋርያዊ ጉዞዎቹ በተለያዩ ሀገራት አስተምሯል፡፡ ሲያስተምርም የተመቸ ጊዜና ቦታ እየጠበቀ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ
በምኩራብ፣ በአደባባይ፣ በገቢያ፣ በትያትር ቦታ፣ በደስታም በኃዘንም ጊዜ ያስተምር ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በቃል ካስተማራቸውና ካሳመናቸው ሰዎች ይልቅ
በመልእክቱ ያስተማራቸውና ያሳመናቸው ሰዎች እጅግ ብዙ ነበሩ፡፡ ራሱም ድንኳን በመስፋት እየሠራ ራሱንና ሰውንም ይረዳ እንደነበር ተጽፏል (1 ኛ ቆሮ
4፡12፣ 9፡6፣ 2 ኛ ቆሮ 11፡17፣ 1 ኛተሰ 2፡9፣ ሐዋ 20፡34)፡፡ አንዲህ ዓይነቱ የውሸት ያይደለ የእውነት፣ በቃል ብቻ ተነግሮ ያልቀረ በሥራ የተተረጎመ፣
የሐውልት ጥቅስ ብቻ ያይደለ የሕይወት ተልዕኮውን ሲፈጽም ‹‹ መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ
ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ
አይደለም።›› ሲል መስክሯል (2 ኛ ጢሞ 4፡7-8)፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞዎች

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረዳን ቅዱስ ጳውሎስ በተለያዩ ዓመታት በብዙ ቦታዎች ሦስት የተላያዩ ሐዋርያዊ ጉዞዎችን አድርጓል።

ሀ. የመጀመሪያው ሐዋርያዊ ጉዞ

ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ 45 ዓ.ም በርናባስንና ማርቆስን አስከትሎ ከአንፆኪያ ወደ ቆጰረሮስ ወረዳ ጳፋ፣ ስልማና በሚባሉ የቆጵሮስ ከተማዎች
ትምህርት ሲያስተምር ተአምራት ሲያደርግ ቆይቷል። “ጳውሎስ” የሚለውን ስምም በዚሁ እንረዳገኘ ይነገራል። ከዚህም ጳውሎስ እንጂ ሳውል ሲባል
አናገኝም። ከዚያም ወደ ታናሿ እስያ ሲደርስ ማርቆስ መከራውን ተሰቅቆ ስለተመለሰ በርናባስን አስከትሎ ዛሬ ቱርክ የተባለውን ሀገር ፍርግያ፣ ጵንፍልያ፣
ጵስድያ፣ አንፆኪያን፣ ልስጥራን፣ ደርቤን እያስተማረ ከሔደ በኋላ እንደገና በእነዚሁ ሀገሮች እያስተማረ ወደ አንፆኪያ ተመለሰ። (ሐዋ 13፣1-3 ፤14)
አንፆኪያ እንደደረሰ ከአይሁድና ከአረማውያን ወገን ክርስቲያን የሆኑት ተጣልተው ነበር። ምክንያቱም አይሁድ አረማውያንን በክርስቶስ ብታምኑና
ብትጠመቁ ነገር ግን ካልተገረዛችሁ ምን ይረባችኋል ? ምን ይጠቅማችኋል? እያሉ ያዳክሟቸው ነበርና ቅዱስ ጳውሎስ ሁከቱን ለማረጋጋት ድካማቸውንም
ለማበረታት ሲል ሐዋርያት ወዳለቡት ወደ ኢየሩሳሌም ወረደና ሁኔታውን አስረዳ። ሐዋርያትም ተሰብስበው የመጀመሪያውን ሲኖዶስ ከክርስቶስ ልደት በኋላ
በ 5 ኛው ዓመት አድርገው ነበርና በዚህ ጊዜ በመጨረሻ ውሳኔያቸው ከዝሙት፣ ከርኩሰት፣ ጣዖት ከማምለክ የተለያዩ ፀያፍ ነገሮች ከመሥራት ግርዘትም
በብሉይ ኪዳን ኃይል ቢኖረውም በሐዲስ ኪዳን ሕግ ቦታ እንደሌለው ወሰኑ። ቅዱስ ጳውሎስም ይህንን ውሳኔ ለአንፆኪያ ምዕመናን አደረሰ። ሐዋ 15

ለ. ሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 103


በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ቅዱስ ጳውሎስ ሲላስን ይዞ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ 50 ዓ.ም ፍርግያ፣ ቢጣንያ፣ ሳሞትራቄ፣ ናፑሊ፣ በፊልጵስዩስ፣
በተሰሎንቄ፣ በቤርያ፣ በአቴና፣ በቆሮንቶስ አሳንጾ በታናሿ እስያ አድርጎ ኤፌሶንን እየሰበከ ወደ አንፆኪያ ተመልሷል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመንፈስ ልጁ
ጢሞቴዎስ ያገኘው በዚሁ መንፈሳዊ ጉዞው በልስጥራ ከተማ ነው።

ሐ. ሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞ

በ 54 ዓ.ም በሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞ ሉቃስን፣ ጢሞቴዎስን፣ ቲቶን አስከትሎ ከአንፆኪያ ተነሥቶ ገላትያን፣ ፍርግያን፣ ኤፌሶንን፣ መቄዶንያን፣
ፊልጵስዩስን፣ ቆሮንቶስ፣ ጢሮአዳን፣ አሶንን፣ ሚሊጢኒን፣ አንጠቀከስዩን፣ ትርጊልዩም፣ መስጡን፣ ቆስን፣ ጳጥርን፣ ጢሮስን፣ ጵቶልማስን፣ ቂሳርያን፣
ኢየሩሳሌምን ወዘተ የተለያዩ ሀገሮችን የሃይማኖት ልጆቹን በማበረታታት ተዘዋውሮ በቀደሙ ሐዋርያዊ ጉዞዎቹ ያቋቋማቸውን አብያተ ክርስቲያናት
እያስተማረ እልኮሪቆን የተባለው ሀገርም እንደጎበኘ ተገልጿል። ሮሜ 16፣3

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከተለያዩ ሀገሮችና ክርስቲያኖች የሰበሰበውን ርዳታ ለኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን በመያዝ ሦስተኛውን ሐዋርያዊ ጉዞ
አጠናቆ ኢየሩሳሌም ሲገባ የፋሲካ በዓል ስለነበር ከልዩ ልዩ ሀገሮች የተሰበሰቡ በዝርወት የሚኖሩ አይሁድ ቅዱስ ጳውሎስን ቀድሞም በየሀገራቸው
በትምህርቱና በተአምራቱ ሲቃወሙት የነበሩ በኢየሩሳሌም ሲያዩት ታላቅ ተቃውሞ ሲያስነሱ ተቃውሞዋቸውን ለመግታት እንደ አይሁድ ሕግ በቤተመቅደስ
የመንጻት ሥርዓት መፈጸም ጀመረ። ነገር ግን ከኤፌሶን የተከተለውን ፕሮፈምስን ወደ መቅደስ ያስገባው ስለመሰላቸው ተቃውሞአቸው በረታ፤ ሐዋ 22፣29
ከተማውንም አወኩት። ይህ ነበር ቅዱስ ጳውሎስን በ 58 ዓ.ም ለሮም እስር የዳረገው ከብዙ መከራና ሥቃይ በኋላ ታስሮ ሮም ገባ። በዚያም በቁም እስር
ሆኖ ለሁለት ዓመታት ያህል ወንጌልን ሳይፈራና ሳያፍር መከራውን እየታገሰ ሰበከ። የሁለቱን ዓመት የቁም እስራት እንደጨረሰ ወደ ኔሮን ፍርድ ቤት ቀረበ።
በፍርድ ቤቱ በተደረገው ምርመራ የሮሜን ሕግ የሚቃወም ምንም ዓይነት ወንጀል ስላልተገኘበት በነጻ ተለቀቀ። ከዚህ በኋላ ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ያልመዘገበውን ተጨማሪ ዐራተኛ መንፈሳዊ ሐዋርያዊ ጉዞውን ያደረገው። ይህ ጉዞው ኢየሩሳሌምን፣ ኤፌሶንን፣ ሎዶቅያን፣
መቄዶንያን፣ ቀርጤስን፣ ጢሮአዳን፣ ድልማጥያን፣ እልዋሬቆን፣ ኒቀጵልዮን፣ ብረንዲስን ጎብኝቷል። በዚህ የመጨረሻው የስብከት ጉዞ ለዐራት ዓመታት ያህል
ቆይቷል።

ከዚያም በ 64 ዓ.ም ኔሮን በጥጋቡ የሮም ከተማ ስትቃጠል ምን እንደምትመስል ማየት እፈልጋለሁ ብሎ አቃጠላት። የሮም ሕዝብ በከተማው
መቃጠል በማዘኑና በማመፁ ነገሩን ሁሉ በክርስቲያኖች ላይ አሳበበ። በዚህም የተነሣ ክርስቲያን የተባለ ሁሉ መሰደድ፣ መሰየፍ፣ መታረድ ዕጣ ፈንታው ሆነ።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በኒቆጵልዮን ከተማ ሲያስተምር በ 65 ዓ.ም ተይዞ ወደ ወህኒ ቤት ገባ። ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር በጨለማ የግዞት ቤት
ታስሮ ከቆየ በኋላ በ 74 ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትርያ መንገድ አንገቱን ተሰይፎ በ 67 ዓ.ም ሐምሌ 5 ቀን በሰማዕትነት አረፈ።

የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት ዘመናቸውንና ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው ባይጠረዙም የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት 14 ናቸው። የጥራዙ
ሁኔታም የሚለያየው እንደመልእክቱ ከባድነትና እንደየሀገሩ የቤተክርስቲያን ታላቅነት ነው። መልእክታቱንም በክፍል እንደሚከተለው እንከፍላቸዋለን።

የመጀመሪያው ክፍል ሁለቱ ወደ ተሰሎንቄ የተጻፉትን ይይዛል። እነዚህም በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞ በ 52 እና በ 53 ዓ.ም እንደተጻፉ
ይነገራል። እነዚህ መልእክታት ምስጢረ ምጽአትን በሚመለከት የሚናገሩ ናቸው።

ሁለተኛው ክፍል ሁለቱን የቆሮንቶስ መልእክታትና የገላትያን፣ የሮሜን መልእክታት ይይዛል። እነዚህ በ 3 ኛው የሐዋርያው ጉዞው በ 56 እና
በ 58 ዓ.ም መካከል የተጻፉ ናቸው። በዚህም ጊዜ አይሁድ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ቤተክርስቲያንን የተቃወሙበት፣ የጳውሎስንም ዝና ሆን ብለው
ያበላሹበት ጊዜ ነበር። እርሱ እነርሱን ይዘልፍበት ሕጋቸውን ይቃወምበት የነበረበት ጊዜ ነበር። በተለይም የገላትያ መልእክቱን ስንመለከት የክርስቶስን
ትምህርት አስፋፍቶ የአይሁድን ጥፋት ገልጦ የጻፈበት ነው።

ሦስተኛው ክፍል ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያው የሮም እስራት ጊዜ በ 62 እና በ 63 ዓ.ም የተጻፉ ናቸው። እነዚህም ወደ ፊልጵስዩስ፣ ወደ
ኤፌሶን፣ ወደ ቆላስይስና ወደ ፊልሞና የተጻፉ መልእክታት ናቸው። እነዚህ ስለ ክርስቶስ ማንነት አስፋፍተው የሚናገሩ ናቸው።

ዐራተኛው ክፍል በመጀመሪያ ከእስራት የተፈታበት ከ 63-68 ዓ.ም የተጻፉት 1 ኛ እና 2 ኛ ጢሞቴዎስና ቲቶን ይይዛል። እነዚህ መልእክታት
የካህናትን ተግባር የጠባቂዎችንም ሓላፊነት ስለሚገልጡ የጠባቂነት መልእክታት ይባላሉ። የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት የይዘት ተመሳሳይነት አላቸው።
ይኸውም የሚያመለክተው በአንድ መንፈስ ገላጭነት መጻፋቸው ነው። የመልእክታቱ ክፍል ጠባይ አጠቃላይ 6 ክፍል አለው።

1. ሰላምታ፡- በሰላምታ አገላለጡ ሰፊ ትምህርት ስለሚገኝበት የመሳብ፣ የማቅረብ፣ ወገንም የማድረግ ኃይል አለውና በሰላምታ መጀመርን ተግባር
አደረገው። የሰላምታ አሰጣጡም “ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን” የሚል ነው። ይኸውም የዕብራውያንን ሰላምታ በክርስቶስ የሚሰጠውን ጸጋ
እንደሚያገኙ የሚያነቃቃ ነው።
2. ምስጋና፡- ወደ ዋናው ርዕሱ ከመግባቱ በፊት ስለ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስጦታው እግዚአብሔርን አመስግኖ ጽሑፉን ይቀጥላል።
3. መሠረተ ሃይማኖትን ማሳወቅ፡- እንደሚጽፍበት ምክንያት ይለያይ እንጂ የያዘውን ርዕስ አተኩሮ የርዕሱን ዓላማ አስፋፍቶ ይገልጣል። እንዲሁም
መልእክቱን ለመጻፍ የተነሣሣበትን ምክንያት በመከተል ሰፊ ትምህርተ ሃይማኖትን ይሰጣል።
4. ተግባራዊ ትምህርት፡- የክርስትና ምግባር እንዴት መሆን እንደሚገባው በግልጥ ይጽፋል። ሃይማኖትና ምግባርን በማዋሐድ ያስተምራል።
5. ለግል ሰዎች፡- ለጳውሎስ የፍቅሩ መገለጫ ለእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን አባል የሚሰጠው አክብሮትና አገላለጥ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን እንዴት
የሁሉ እናት እንደሆነች የሚያስረዱ ምልክቶች ናቸው።

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 104


6. የራሱ መሆኑን ማረጋገጥ፡- በዚያን ዘመን ይተላለፉ ከነበሩት የሐሰት መልእክታት ለመለየት የሚገልጥበት መንገዱ ነው። ይኸውም “ይህን ሰላምታ
በገዛ እጄ የጻፍሁት እኔ ነኝ። ከእኔ መልእክት ሁሉ የሚገኘው መልእክት ይህ ነው። የምጽፈውም እንዲህ ነው፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ
ከእናንተ ጋር ይሁን” በማለት መልእክቱ የራሱ መሆኑን በግልጥ ያስረዳ ነበር። 2 ተሰ 3፣ 17-18
1. ወደ ሮሜ ሰዎች

ሮም ስያሜዋን ያገኘችው ከመስራቿ ከንጉሥ ሮሙለስ (Romulus) እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከተማዋም በ 753 ቅ.ል.ክ ተመሥርታለች፡፡ ከተማዋ
ከፍ ባለ ቦታ ላይ የተሠራች በመሆኗና በታላቅነቷ የተነሣ ለሮማውያን ግዛት (Roman Empire) ዋና ከተማ ሆናለች፤ እጅግ እያደገች በመምጣቷም
የተነሣ ለዓለም ገዥዎች መሰባሰቢያ እንዲሁም የሳይንስ፣ ሥዕልና የፍልስፍና መማሪያ ማዕከል ለመሆን በቅታለች፡፡ በዚህም ምክንያት ለተለያዩ ሀገራት
ሕዝቦች መሰባሰቢያ ሆናለች፡፡ ይህም ሐዋርያው በመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ለሚነግረን ክፉ ምግባርና ጣዖት አምልኮ ማዕከል እንድትሆን አድርጓታል፡፡

የሮም ከተማ አንድ ሦስተኛ ሕዝብ በክፉና አጸያፊ ምግባር የሚኖር ሕዝብ ነበር፡፡ (ሮሜ 1፡20-32) እንዲሁም በ 63 ቅ.ል.ክ ፖምፔይ የተባለው
የሮም ገዥ ሶርያን በወረረበት ወቅት የማረካቸው ብዙ አይሁዳውያን ነበሩ፡፡ እነዚህም በኋላ ነጻነታቸውን አግኝተው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክቱን በሚጽፍበት
ወቅት እስከ 16 ሺህ ደርሰው ነው፡፡ እነዚህም አይሁዳውያን በ 14 ዓ.ም ጢባርዮስ ቄሳር እንዲሁም በ 34 ዓ.ም ቀላውዴዎስ ቄሳር ሮምን ለቀው
እንዲወጡ እስካዘዙበት ጊዜ ድረስ በሰላም በዚህ ከተማ ውስጥ ይኖሩ ነበር (ሐዋ 18፡2)፡፡

ክርስትና በሮም ከተማ


43
ክርስትናን ለሮም ያስተዋወቀው ሐዋርያ ማን እንደሆነ በግልጥ ባይታወቅም ነገር ግን እንዴት ሊገባ እንደቻለ በሚከተሉት ነጥቦች መመልከት
እንችላለን፡፡

1. በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተገለጠው ለእምነታቸው ቀናኢ የሆኑ አይሁዳውያን ከተለያዩ ሀገራት በዓለ ጰንጠቆስጤን(በዓለ ሰዊት(ኀምሳ)) ለማክበር
ተሰባስበው ነበር፡፡ ከእነዚህም መካከል በሮም የነበሩ አይሁዳውያንም ሆነ ወደ አይሁድ እምነት የተቀየሩ አሕዛብ እንደነበሩ ተገልጧል (ሐዋ 2 )፡፡
እነዚህም በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት አምነው ተጠምቀው ወደ ሀገራቸው ወደ ሮም ተመልሰዋል፡፡ እነዚህም አይሁዳውያን በሮም ለነበሩት አይሁድ
የክረስትናን እምነት ሰብከውላቸዋል፡፡
2. የሮማውያን ግዛት (Roman Empire) ከሚታወቅበት ነገር አንዱ ከአንድ ግዛት ወደሌላው በተለይ ደግሞ ወደ ዋና ከተማው ለመጓጓዝ ቀላልና
ሙሉ ነጻነት ያለው በመሆኑ ነው፡፡ ይህም የሮምን ከተማ ለተለያዩ ነጋዴዎች፣ መምህራንና መሪዎች ምቹ አድርጓታል፡፡ ከእነዚህም መካከል ደግሞ
ከአጂያን ከተሞች፣ ከመቄዶንያ፣ ከግሪክ አንዳንድ ከተሞች እና ከታናሿ እስያ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆነ ከሌሎች ሐዋርያት ክርስትናን የተቀበሉ ክርስቲያኖች
ይገኙባቸዋል፡፡ ስለዚህ በእነዚህ አማካኝነት ወደ ሮም ሊገባ ችሏል፡፡ የሮሜ መልእክት የመጨረሻው ምዕራፍም ይህን ያሳየናል፤ ምክንያቱም ቅዱስ
ጳውሎስ በሮም ለነበሩ ለብዙ ክርስቲያኖች ሰላምታ ያቀርባልና፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ገና ወደ ሮም ሳይሄድ እነዚህን ሁሉ ክርስቲያኖች ማወቁ ደግሞ
አስቀድመው ከርሱ በሌላ ሀገራት የተማሩ ደቀ መዛሙርቱ እንደሆኑ ያስረዳናል(ሮሜ 16)፡፡
3. ቀላውዴዎስ ቄሳር፣ አይሁዳውያን ሮምን ለቀው እንዲወጡ ባዘዘ ጊዜ እነዚህ አይሁዳውያን ወደ ሌሎች ከተሞች ተፈናቅለው ሄደው ነበር፡፡ ብዙም
አልቆዩም ተመልሰው ወደ ሮም መጥተዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል አንዳንዶች ክርስትናን የተቀበሉ ነበሩ፡፡ በእነርሱ አማካኝነት ክርስትና ወደ ሮም ሊገባ
ችሏል፡፡ ለዚህም እንደምሳሌ የሚሆኑን አቂላና ጵርስቅላ ናቸው፤ ቅዱስ ጳውሎስን በቆሮንቶስ ያገኙት ሲሆን አስቀድመው በሮም ይኖሩ ነበር (ሐዋ
18)፡፡
የተጻፈበት ጊዜና ቦታ

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው ወደ ሮም ለመሄድ ባሰበ ጊዜ ነበር፡፡ ወደ እስፔን ሲሄድ ሮምን ሊያይ እንደወደደም በመልእክቱ
ጽፏል(ሮሜ 15፡23-24)፡፡ መልእክቱንም የታጻፈው ከመቄዶንያና ከአካይያ ክርስቲያኖች የሰበሰበውን ገንዘብ በኢየሩሳሌም ለነበሩት ድሆች ከመስጠቱ
በፊት ነው(ሮሜ 15፡25-26፣1 ኛ ቆሮ 16፡1-16፣2 ኛ ቆሮ 8፡1-4)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም የሄደው ደግሞ በ 58 ዓ.ም መጀመሪያ ስለሆነ
መልእክቱን የጻፈው ከ 55-58 ዓ.ም መካከል(ከ 58 ዓ.ም በፊት) ነው፡፡ ስለዚህም መልእክቱ የተጻፈ በሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው በቆሮንቶስ ለሦስት
ወራት ያህል በተቀመጠ ጊዜ ነው ፡፡

የተጻፈበት ቦታ ደግሞ በቆሮንቶስ በጋይዮስ ቤት ሲሆን ጋይዮስንም ‹‹የእኔና የቤተ ክርስቲያን ሁሉ አስተናጋጅ›› (ሮሜ 16፡23) ይለዋል፡፡
መልእክቱን ከቅዱስ ጳውሎስ አፍ ተቀብሎ የጻፈው ጤርጥዮስ ሲሆን መልእክቱን ወደ ሮም የወሰደችው ደግሞ ዲያቆናዊቷ ፌቤን ናት፡፡ እርሷም ከቆሮንቶስ
በስተምዕራብ በሆነችው በክንክራኦስ ባለች ቤተክርስቲያን አገልጋይ ነበረች(ሮሜ 16፡1)፡፡ የተጻፈበትም ቋንቋ በአብዛኛው በሕዝቡ ዘንድ ይነገር በነበረው
በግሪክ ቋንቋ ነው፡፡

43
ክርስትናን በሮም የሰበከው ቅዱስ ጴጥሮስ እንደሆነና ለ 25 ዓመታት በጳጳስነት ቤተክርስቲያኒቱን እንደመራት ብዙ ጊዜ ቢነገርም ይህን ሀሳብ የምስራቅም ሆነ የምዕራብ
አብያተ ክርስቲያናት ሊቃውንት አይስማሙበትም፡፡ ለዚህም እንደምክንያት የሚያቅርቡት ቅዱስ ጴጥሮስ የሐዋርያት ሲኖዶስ (በ 50 ዓ.ም) እስከሚደረግበት ጊዜ ድረስ
በኢየሩሳሌም ነበር(ሐዋ 15)፡፡ በ 55 ዓ.ም ደግሞ በአንጾኪያ ነበር፣ በዚህም ጊዜ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ተገናኝቷል (ገላ 2፡11)፡፡ በ 60 ዓ.ም ደግሞ በባቢሎን የመጀመሪያ
መልዕክቱን እየጻፈ ነበር፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት ቅዱስ ጴጥሮስ በ 41 ዓ.ም የሮምን ቤተ ክርስቲያንን የመሠረታት ቢሆን ኖሮ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሮም መልእክትን ባላከ
ነበር፡፡ ቢልክ እንኳን ‹‹በሌላው ሰው መሠረት ላይ እንዳልሠራ የክርስቶስ ስም በተጠራበት ስፍራ ሳይሆን ወንጌልን ለመስበክ ተጣጣርሁ፤›› (ሮሜ 15፡20) ባላለን ነበር፤
ወይም ቅዱስ ጴጥሮስን በስም በጠቀሰው ነበር፤ ወይም ሰላምታን ባቀረበለት ነበር፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 105


የሮም ቤተክርስቲያን አባላት እነማን ነበሩ?

ይህ ጥያቄ መልእክቱን እንድነረዳው ታላቅ እገዛ ያደርግልናል፡፡ ተቀባዮቹን ማወቅ ሐዋርያው የጻፈበትን ዓላማ ለማወቅ እጅግ ይጠቅማልና፡፡
በሮም ስለነበሩት ክርስቲያኖች ሦስት ዓይነት አመለካከት አለ፡፡ የመጀመሪያው አብዛኞቹ አይሁዳውያን ናቸው የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አብዛኞቹ
አሕዛብ ናቸው ሲል ሦስተኛው አመለካከት ደግሞ የእነርሱ ድብልቅ ነው የሚል ነው፡፡ ብዙ ሊቃውንት የሚስማሙበት አሳብ ግን የመጀመሪያውን ሲሆን፤
ይህም ከአይሁድ ወደ ክርስትና የተቀየሩት በቁጥር ከአሕዛብ ወደ ክርስትና ከተቀየሩት እንደሚበዙ ነው፡፡ ይህም የቅዱስ ጳውሎስ አጻጻፍ ያረዳናል፡፡ ቅዱስ
ጳውሎስ በዚህ መልእክቱ ከብሉይ ኪዳን ብዙ የጠቀሰ ሲሆን የአብርሃምንም ታሪክ ይተርካል፡፡ አብርሃምንም አባታችን በማለት ይጠራዋል፤ ይህም አብዛኞቹ
አይሁዳውያን ያስረዳናል፡፡ ይህ ማለት ግን ለአይሁዳውያን ብቻ ነው የተጻፈው ማለት አይደለም፤ ቅዱስ ጳውሎስ ራሱ ‹‹ለእናንተ ለአሕዛብም
እናገራለሁ››(ሮሜ 11፡13) በማለት ለአሕዛብም እንደላከው ያሳየናል፡፡

የመልእክቱ ጥቅም እና ዓላማ

ይህ በጥንት ክርስቲያኖች ዘንድ ትልቅ ጠቀሜታ ነበረው፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህንን መልእክት በሳምንት ሁለት ጊዜ ያነበው ነበር፡፡
ይህን መልእክት ማጥናትም አሁን ላለነው ክርስቲያኖች ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ በመጀመሪያም ቅዱስ ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈበትን ዓላማ
እንመልከት፡፡

በቁጥር እጅግ ብዙ የሆኑ በሮም የሚኖሩ አይሁዳውያን በክርስቶስ አመኑ፡፡ እነዚህም በትውልድ አይሁዳውያን የሆኑ ወይም መጀመሪያ አሕዛብ
የነበሩ በኋላ ይሁዲነትን የተቀበሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ክርስትናን እንደ ተቀበሉ ሁሉ የተማሩ አሕዛብ፣ የግሪክ ፈላስፎችም በክርስቶስ አመኑ፡፡
ስለዚህም ሁሉም አንድ መንፈስና አንድ አካል ሆነው ማገልገል መቻል ነበረባቸው፡፡ ነገር ግን አይሁዳውያኑ ክርስቲያኖች፣ ከአሕዛብ ወደ
ክርስትና ከመጡት እንበልጣለን ማለት ጀመሩ፡፡ አይሁዳዊ ዘር ባሕልና አስተምህሮ ከሁሉም ይበልጣል እያሉ ከአሕዛብ ወደ ክርስትና
የመጡት ይንቋቸው ጀመር፡፡ እንበልጣለን ያሉት ስለነዚህ ሦስት ምክንያቶች ነበር፡፡

1. እኛ የአብርሃም ልጆች ነን ስለዚህ እግዚአብሔር የገባለት ቃልኪዳን ለእርሱና ለልጆቹ ብቻ ነውና በማለት
2. ከሁሉም ሕዝብ ተለይተው ሕግ በሙሴ አማካኝነት የተሰጠን እኛ ነን በማለት
3. እግዚአብሔር የመረጠን ሕዝብ እኛ ነን በማለት ነበር፡፡

ከቀደመ አይሁዳዊ ማንነታቸው የወሰዱት ይህ አስተሳሰብ ወደ ከፋ ትዕቢትም መራቸው፡፡ ይህም ትዕቢትም የአብርሃም ልጅ መባል ምን ማለት
መሆኑን፣ ሕግ የመሰጠቱን ዓቢይ ዓላማ እና ለምን እግዚአብሔር ሕዝቡን አንደመረጠ እንዳይረዱ እንቅፋት ሆነባቸው፡፡ ምንም እንኳን በክርስቶስ አዳኝነት
ቢያምኑም እንኳ ራሳቸውን ከሌላው አማኝ በላይ አድርገው ያስቡ ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በመልዕክቱ ላይ ስለነዚህ በሰፊው እያነሳ ያስተማረው ስለዚህ
ነው፡፡

በተቃራኒው ደግሞ ይህን የአይሁዳውያንን አስተሳሰብ በመቃወም አሕዛብ የራሳቸውን ተቃራኒ ጽንፍ ያዙ፡፡ አይሁዳያውን የተዋረዱ እንደሆኑና
እግዚአብሔርም የመዳንን ደጅ በእነርሱ ላይ ዘግቶ ለአሕዛብ እንደከፈተላቸው አድርገው ያስቡ ጀመር፡፡ ይህም ልክ ከትዕቢተኞቹ አይሁዳውያን እኩል
ጥፋተኞች አደረጋቸው፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሳሉ ነው ቅዱስ ጳውሎስ ለሁለቱም ወገኖች ይህን መልእክት የጻፈው፡፡ በመልእክቱ ውስጥም የእምነትን ተግባራዊነትና በዕለት
ተዕለት ኑሯችን ሊኖረን የሚገባውን መንፈሳዊ ጠባይን ያነሣል፡፡ ስለመዳንም በሰፊው ያነሣል፡፡ መዳንም የሚሆነው በፍቅር በሚሠራ ምግባር የተገለጠ፣
ሕይወት ባለው እምነት ለሁሉም ሕዝብ ነው ይለናል፡፡ (He proclaims that the door has been opened to all nations through
a living faith that is evident in deeds of love.)
በመንፈስ ቅዱስም መሪነት በእምነትና በመዳን መካከል ያለውን ጥብቅ ግንኙነት በሰፊው
ያትታል፡፡ ለክርስቶስና እርሱ ለተሰቀለላት ለዓለም ሁሉ ያለውን ፍቅርም ይገልጥልናል፡፡ በተመሳሳይ በአይሁዳውያኑና በአሕዛቡ ዘንድ ስላለው ትዕቢትም
ያነሣል፡፡ ስለ ቅድስና፣ በክርስቲያኖች ዘንድ ስላለው ግንኙነትና ከማኅበረሰቡ ጋር ሊኖራቸው ስለሚገባው ግንኙነት ይናገራል፡፡

የሮሜ መልእክታት አከፋፈል

የሮሜ መልእክት 16 ምዕራፎች አሉት፤ 16 ቱንም ምዕራፎች በስምንት ዐበይት ክፍሎች ከፍለን
እናጠናለን፡፡

ሮሜ 1፡1-17፡ የመግቢያ ሰላምታ

ሮሜ 1፡18 - ምዕ 3፡ ስለ አረማውያን፣ ስለ አይሁዳውያንና ስለ እግዚአብሔር ጽድቅ አስፈላጊነት፤


ሳይገረዝ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ የተቆጠረለት አብርሐም ለአይሁድም ለአሕዛብም አባት እንደሆነ

ሮሜ 4-5፡ የእግዚአብሔር ጽድቅ ለሰው በእምነት የሚገኝ ስለመሆኑ

ሮሜ 6-8፡ ሰው በጽድቅ ሕይወት የሚኖር ከሆነ ከኃጢአት ከሕግና ከሞት ነጻ ስለመሆኑ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 106


ሮሜ 9-11፡ ስለ እስራኤል መመረጥና ተስፋ፤ አሕዛብ የትዕቢትን ነገር ማሰብ እንደሌለባቸው
ልዩነት ሳይኖር የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ እንደሚድን

ሮሜ 12-15፡1-10፡- ስለ ክርስቲያኖች በዓለም በግልና በቤተክርስቲያን አኗኗር

ሮሜ 15፡11-33፡- ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ስብከት

ሮሜ 16፡ የቅዱስ ጳውሎስ ሰላምታ የአደራ ምሥጋናና ጸሎት፣ የጳውሎስ ያለፈው አገልግሎቱና
የአሁኑ ዕቅድ

2. የመጀመሪያይቱ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች

ቆሮንቶስ የአካይያ ግዛት ዋና ከተማ ስትሆን የምትገኘውም ግሪክ ውስጥ ነው፤ የመጀመሪያይቱ
የቆሮንቶስ መልእክት የተጻፈችው በኤፌሶን ነው፡፡ ዘመኑም በ 3 ኛው ሐዋርያዊ ጉዞ ሳለ በኤፌሶን ለሁለት
ዓመት በቆየበት ጊዜ ነው፡፡ ይህም በ 55 ዓ.ም ገደማ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህቺ መልእክት ከኤፌሶን
እንደተለከች የሚያስረዳ ቃል በውስጧ ይገኛል፡፡ ይህም ቅዱስ ጳውሎስ እስከ በዓለ ሃምሳ ድረስ በኤፌሶን
እሰናበታለሁ ብሎ የጻፈው ቃል ነው፡፡ /1 ኛ ቆሮ 16፡8/ ይህም ቃል ቅዱስ ጳውሎስ መልእክታቱን በጻፈ ጊዜ
በኤፌሶን እንደነበር ያስረዳል፡፡

ይህች ከተማ ስመጥርና ታላቅ በንግድም የታወቀች የሀብታሞች መናኸሪያ ነበረች፤ በምስራቁና
በምዕራቡ ዓለም ለንግድ ቅርብ ስለሆነች የበለፀገች ሀገር ነበረች፡፡ ከስድስት መቶ እስከ ሰባት መቶ ሺህ
ከሚሆነው ሕዝቧ ውስጥ አይሁዶች፣ ሮሜዎች፣ ግሪኮች ይገኙበታል፤ በቆሮንቶስ ብዙ ዓይነት ኃጢአት
በተለይም ዝሙት ይሠራ ነበር፤ እንዲህ በሆነበት ዘመን ቅዱስ ጳውሎስ ከአቴና ወደ ቆርንቶስ መጣ /ሐዋ 18፡
1/ እርሱም ይህን ያህል ኃጢአት በመሥራታቸው ብዙ ሰዎች ተጸጽተው ሰማዕያነ ወንጌል በዝተው ሲመለከት
በዚሁ ብዙ ጊዜ ቆየ፤ ለአንድ ወር ያህል ቆይቶ ሐዋርያዊ ጉዞውን ለመቀጠል ተነሣ፡፡ /ሐዋ 18፡9/ ቅዱስ
ጳውሎስ ቆርንቶስን ለቆ ኢየሩሳሌም ገብቶ ሁለት ዓመት ያህል ቆይቶ እንደገና 3 ኛ ሐዋርያዊ ጉዞውን
ቀጥሎ እያስማተረ ኤፌሶን ደረሰ፤ ከዚያም በጠዋት በማታ በሚያደርገው ስብከት ስብከት የእስክንድርያው
ሰው አጵሎስ የተባለው አይሁዳዊ አምኖ ተጠመቀ፡፡

በኋላ የቅዱስ ጳውሎስ ረዳት ሆኖ ቆርንቶስን ለመጎብኘት ሄደ፤ ከዚያም እንደደረሰ የተማረውን ሁሉ
ያስተምር፣ ይመሰክር ጀመረ፡፡ መሠረታዊና ጠለቅ ያለ ትምህርት ያስተምር ስለነበር ብዙ ሰዎች አምነው
ተጠመቁ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በሁለተኛ ጉዞው በ 54 ዓ.ም ደግሞ በኤፌሶን እያለ ልጁ ጢሞቴዎስ
ቤተክርስቲያኗ ውስጥ በምዕመናን መካከል መለያየትና መከፋፈል እንዳለ ይነግረው ነበር፡፡

መልእክቱን የጻፈበት ምክንያት

 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አስተምሮ ከሄደ በኋላ ከእስክንድርያ የመጣው አይሁዳዊ አጵሎስ ተጠምቆ
ለአይሁድ ብሉይን ከሐዲስ እያስማማ ጥልቅና ጠንካራ ምስጢራዊ ትምህርቱን ሲያስተምር ብዙ ሰዎች
ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣት ጀምረው ነበር፡፡ እነዚህ በልዩ ልዩ ምክንያት ያመኑ ክርስቲያኖች የሐሳብ
መለያየትና የወገንተኝነት ስሜት ስለጠናባቸው ከዚያም “እኔ የጳውሎስ ነኝ፣ እኔ የአጵሎስ ነኝ” እያሉ
ሲከፋፈሉና ሲለያዩ ክርስቶስ ተከፋፍሏልን፣ ጳውሎስ ስለ እናንተ ተሰቀለን ወይስ በጳውሎስ ስም
ተጠምቃችኋል በመካከላችሁ መለያየት እንዳለ እሰማለው፡፡ መለያየት ለአንዲት ቤተክርስቲያን የማይበጅ
ነው በማለት ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ችግር ከቀለዮጳ ቤተ ሰዎች ሲሰማ ይህችን የመጀመሪያ መልእክቱን
ጻፈላቸው፡፡ /1 ኛ ቆሮ 1፡12/

 ከአምልኮ ጣዖት ከተመለሱ በኋላ የቆርንቶስ ሰዎች የቀድሞ የአምልኮ ጣዖት ባህላቸውን ወደ
ቤተክርስቲያን እምነት ሥርዓትና ትውፊት በመቀላቀል ይኖሩ ነበር፤ ለምሳሌ ወደ ቅዳሴ ሲመጡ ሁሉም
ለየግሉ ወይንና ኅብስት ይዘው ይመጡና እስኪጠግቡ በልተው እስኪሰክሩ ጠጥተው እየተጨቃጨቁና
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 107
እየተደባደቡ ቊርባን እንደፈጸሙ ይሰማቸው ነበር፤ ይባስም ብለው ወይንና ኅብስት ማምጣት ያልቻሉ
ድሆችን እንደ እነርሱ ሐሳብ እንዳይቆርቡ ይከለክሏቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከጌታና ከቅዱሳን
ሐዋርያት ያገኘውን ሃይማኖት ሥርዓትና ትውፊት አብራርቶ ይመክራቸው ዘንድ ይህችን መልእክት
ጻፈላቸው፡፡

 የቆሮንቶስ ሴቶች ወደ ፍርድ ሸንጎ ገብተው ሳይከናነቡ ያለ ሥርዓታቸው፣ ያለ ባህላቸው ለባሎቻቸው


እያገዙ መሟገትን አዲስ ወግና ሥርዓት አድርገው ከካህናቱ ፈቃድ እየወጡ ቤተ ክርስቲያን ካልሰበክን
ካልቀደስን እያሉ ሲያስቸግሩ በዚህም የተነሣ “ቤተክርስቲያኒቱ ነውረኛ ሴቶች የተሰበሰቡባትና ሥርዓት
የሌላት ናት” እየተባለች በዓለማውያን ዘንድ እንዳትነቀፍ ቅዱስ ጳውሎስ ፀጉራቸውን እንዲከናነቡ
ሥርዓቱን ትውፊቱን ጠብቀው እንዲኖሩ ሲል ይህን መልእክት ጻፈላቸው፡፡

 የቆሮንቶስ ሰዎች በዝሙት ኃጢአት የታወቁ ነበሩ፤ በዚያ “ቆርንቶሳዊ” ማለት ዘማዊ የሚለውን
ትርጉም ይዞ ነበር፤ ቅዱስ ጳውሎስም በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል፣ የዚህን ዓይነት ዝሙት
በአሕዛብ እንኳ የማይገኝ ነው እያለ የተማረውን የወንጌሉን ቃል መሠረት በማድረግ ይህን መልእክት
ከዝሙት ጠንቅ እንዲጠበቁ ጻፈላቸው፡፡ /1 ኛ ቆሮ 5፡1/

 የቆርንቶስ ሰዎች ችግር በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች እርስ በእርስ መቀናናታቸው ነበር “እኔስ ከማን
አንሳለው” እያሉ ሁሉም ትንቢት ተናጋሪ፣ ሁሉም ተርጓሚዎች፣ ሁሉም በልሳን ተናጋሪዎች ስለሆኑ
ሁሉም ራሳቸውን ከፍ በማድረጋቸው ጭቅጭቅ ነበር፡፡ ለእነዚሁ ሁሉ ችግሮች ክርስቲያናዊ መልሶችን
ጽፎ አዘጋጅቶ በጢሞቴዎስ፣ በእስጢፋኖስ፣ በፈርዶናጥስና በአካያቆስ እጅ ይህችን መልእክት በ 54 ዓ.ም
ገደማ ላከላቸው ፡፡ /1 ኛ ቆሮ 15፡2-58፣ 16፡1-24/

 በመጨረሻ ቅዱስ ጳውሎስ ጥያቄ አዘል ደብዳቤዎችን ጽፈውለት ነበርና የተለያዩ ችግሮቻቸውን
በመጠየቅና መልስ በማዘጋጀት ለሃይማኖት ይጸኑ፣ በምግባር ያድጉ ዘንድ ይህን መልእክት ጻፈላቸው፡፡ /1 ኛ
ቆሮ 7፡1፣ 8፡1፣12፡1፣16፡1/

የመልእክቱ ይዘት

የአንደኛው የቆሮንቶስ መልእክት ይዘት የተግሳፅ ትምህርት ነው፡፡ /1 ኛ የቆሮ 4፡14/ ቅዱስ ጳውሎስ
በዚህች መልእክት ውስጥ ለጊዜው በቆሮንቶስ ክርስቲያኖች መካከል ተፈጥረው የነበሩ ስህተቶች እንዲወገዱ
የሚያደርጉ ትምህርቶችን ጽፏል፤ ትምህርቱንም ሥነ ምግባርን፣ ሥርዓትንና ሃይማኖትን የሚመለከቱ
ናቸው፡፡

የመልእክቱ አከፋፈል

1 ኛ የቆሮንቶስ መልእክት 15 ምዕራፎች አሉት እነዚህም በሰባት ዐበይት ክፍሎች ከፍለን እናጠናለን፡፡

1 ኛ ቆሮ 1-4፡ ስለ ቤተክርስቲያንና በመካከለኛ ዘመን ስለተነሣው ችግር

1 ኛ የቆሮ 5-6፡ የቆርንቶስ ሰዎች ስለ ፈጸሙት የዝሙት ኃጢአት

1 ኛ የቆሮ 7፡ ስለ መጋባት

1 ኛ የቆሮ 8-10፡ ለጣዖት ስለተሠዋ ሥጋ፣ ጳውሎስ ስለ ወንጌል ራሱን ምን ያህል እንዳስገዛ

1 ኛ የቆሮ 11፡ ስለ ቅዱስ ቊርባን፣ በጸሎትና ትንቢት ለመናገር ወንድ ራሱን እንዳይከናነብ ሴት ግን
ራስዋን እንድትሸፍን፣ ከሁሉም የጸጋ ስጦታዎች ፍቅር እንደሚበልጥ

1 ኛ የቆሮ 12-14፡ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 108


1 ኛ የቆሮ 15፡ ስለ ዳግም ምጽአት

3. ሁለተኛይቱ መልእክት ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ምዕመናን በሃይማኖት ልጁ በጢሞቴዎስ እጅ የመጀመሪያይቱን


መልእክት ጽፎ ቢልክላቸውም ከኃጢአት ርቀው ንጽሕ ጠብቀው መኖር አልተቻላቸውም ነበር፤ ክፉ
ግብራቸውንም ቀጠሉ፡፡ ይህን በልጁ የላከውን መልእክት እንዳልተቀበሉት፣ ተግባራዊ እንደማያደርጉት በሰማ
ጊዜ እንዳሳዘኑት በዚህ መልዕከቱ ገልጽዋል፡፡ 2 ኛ ቆሮ 2፡5-11፣ 12፡2

የመጀመሪያውን መልእክት ምን ያህል ተግባራዊ እንዳደረጉት ለመረዳት ቲቶን ላከ፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስ
ጋርም በመቄዶንያ ተገኝተው ሲጠይቀው፤ የላከላቸውን መልእክት ብዙዎችን በክፉ ሥራቸው እንዲጸጸቱ
ንስሐም እንዲገቡ እንዲያውም የአባቱን ሚስት ያገባ እንዲለይ አድርገዋል በማለት ደስ የሚያሰኘውን ወሬ
ነገረው /2 ኛ ቆሮ 7፡5-16/፤ የቲቶን ወሬ ሲሰማ ቅዱስ ጳውሎስ እዚያው በመቄዶንያ እያለ ይህችን
“ሁለተኛይቱ” የተባለችውን መልእክት ጻፈላቸው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ሁለተኛይቱን መልእክት የጻፈበት ምክንያት

 ንስሐ ገብተው በመመለሳቸው ለማመስገንና ለማጽናት

 ከአይሁድ ወገን የሆኑ ሐሳውያን መምህራን ወደ ወጋቸውና ልማዳቸው ለመለወጥ በመሞከራቸው


ብዙዎች ተታለው በትምህርታቸውም ተስበው ስለነበረ የሐሰተኞችን መምህራን ትምህርት ወግና
ሥርዓት እንዳይከተሉ ለመምከር ጻፈላቸው፡፡

 ቀድሞ በጻፈላቸው መልእክት፣ ተግሣጽና ምክር ተደናግጠው ሀዘናቸውም ከልክ ያለፈ ነበር፡፡ ከልክ ያለፈ
ሀዘናቸውን ለማስታገስ የመልእክቱን፣ የተግሳጹንና የምክሩን ጠቃሚነት አብራርቶ ጻፈላቸው፡፡

 ይህች በ 55 ዓ.ም አካባቢ በቲቶና በሉቃስ እጅ የተላከችበት ምክንያትም ስለ መልእክቷ እውነተኛነትና


ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ሕይወት መመስከር የሚችሉ በመሆኑ ሲሆን በመጀመሪያዋ መልእክትም
እንዳያቃልሉ ሁለተኛይቱን የምስጋና ምክር አዘል አድርጓ ጽፎላቸዋል፡፡

 የእርሱም ሥልጣን ከእግዚአብሔር እንደሆነ ለማስረዳት አብራርቶ ጻፈ፡፡

የመልእክቱ አጠቃላይ ይዘት

2 ኛው የቆርንቶስ መልእክት ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ራሱ በመግለጥ የጻፈላቸውን ትምህርት ይዛላች፤ ቅዱስ


ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች የነበረውን ስሜትና የአገልግሎት ቅን ባሕርይ የምትገልጥልን መልእክት ናት፤
በዚህ አገላለጡ ውስጥ በመልእክታቱ ሁሉ እንደሚያደርገው የሥነ ምግባርና የሃይማኖት ትምህርት ይሰጣል፡፡

የመልእክቱ አከፋፈል

ሁለተኛይቱ የቆሮንቶስ መልእክት 13 ምዕራፎች አሏት እነርሱንም ለአራት ከፍለን እናጠናቸዋለን፡፡


እነርሱም፡-

2 ኛ ቆሮ 1-2፡ በቆሮንቶስ ምክንያት ቅዱስ ጳውሎስ ስለደረሰበት መከራ፣ በአካይያ ሁሉ ካሉት ጋር


ለቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን የቀረበ ሰላምታ

2 ኛ ቆሮ 3-7፡ ስለ አገልግሎቱ፣ በእስያ ከደረሰባቸው መከራ እግዚአብሔር እንዴት እንዳዳናቸው

2 ኛ ቆሮ 8-9፡ ስለ ኢየሩሳሌም ምዕመናን ዝግጅት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 109


2 ኛ ቆሮ 10-13፡ እውነተኛ ሐዋርያ ስለመሆኑ፣ ራሳቸውን እንዲመረምሩ የጻፈው ምክር፣ ስለ
እነርሱ የሚጸልየው ጸሎት፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

4. ወደ ገላትያ ሰዎች

ይህች ገላትያ የተባለች ሀገር በታናሿ እስያ አጋርያስና አሊያስ በተባሉ ሁለት ወንዞች መካካል
የምትገኝ አውራጃ ስትሆን ዛሬ የቱርክ መናገሻ ናት፡፡ አውራጃው ውስጥ ጵስድያ፣ አንጾኪያ፣ ኢቆንዮስ፣
ልስጥራንና ደርቤን የተባሉ ከተማዎች ይገኛሉ፡፡ አውራጃዋ በምስራቅ ከጳንጦስና ከቀጰዶቅያ፣ በምዕራብ
ከፍርግያ፣ በሰሜን ከቢታንያ፣ በደቡብ ደግሞ ከሊቃኦንያ ትዋሰናለች፡፡

የገላትያ አብያተ ክርስቲያናት የተመሠረቱት በቅዱስ ጳውሎስ ነው፡፡ ክርስቲያኖች በእግዚአብሔር


የባሕርይ ልጅ በኢየሱስ ክርስቶሰ ሞትና ትንሣኤ ያገኘነውን ጸጋና ክብር፣ ከኃጢአት ባርነት እንዴት
እንደወጣንም የምትናገር፣ የምታስረዳ በመሆኗ “የነጻነት መልእክት” በመባል ትጠራለች፡፡

ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት የገባው በሥጋ ድካም ነበር፤ ይህንን የሥጋ ድካም ዘመናውያን
የሆኑት ሊቃውንት ጳውሎስ በአንደኛው ሐዋርያው ጉዞ ወቅት ወደ ገላትያ ከመግባቱ በፊት በቆላማዋ
ሥፍራ በጰርጌን ዘጵንፍልያ ደርሶበት የነበረው የወባ ሕመም እንደነበር ይነገራሉ፡፡ “በሥጋ ድካም እንኳን
ሆኖ አልተጸየፉትም፣ አልናቁትም” ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ፣ እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ
ተቀበሉት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰበከላቸው ወቅት አክብረው በደስታ ተቀብለውት ነበር፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመጀመሪያውን ሐዋርያዊ ጉዞውን ባደረገ ጊዜ በ 47 ዓ.ም በሦስተኛ


ጉዞው በፍርግያ አልፎ ገላትያ በመግባት በሃይማኖታቸው እንደጸኑ በምግባር እንዲኖሩ አስተምሯቸዋል፡፡ ነገር
ግን እርሱ የመጀመሪያውን ጉዞ ፈጽሞ ከተመለሰ በኋላ ሐሰተኛ የአይሁድ መምህራን እውነተኛውን
የሐዋርያትን ትምህርት እየነቀፉ ካልተገዛችሁ የአይሁድን ወግ ሥርዓት ካልጠበቃችሁ ማመናችሁ ከንቱ ነው
በማለት የሚያስተምሩትን የክህደት ትምህርት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሰምቶ ይህችን መልእክት
ጻፈላቸው፡፡

ይህች የገላትያ ሰዎች መልእክት የተጻፈላቸው በ 48 ዓ.ም ሲሆን የተላከቸውም በቲቶ እጅ ነው፡፡

የመልእክቱ ዓላማ

 የአይሁድ መምህራንን የሐሰት ትምህርት፣ ወጋቸውን፣ ሥርዓታቸውን የገላትያ ሰዎች እንዳይቀበሉ


የተማሩትን የሐዋርያት ትምህርት እንዲጠብቁ፣ እንዲያጸኑ

 የአይሁድ መምህራን ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን አላየም በማለት ከቅዱሳን ሐዋርያት
እኩል አይቆጠርም ይሉት ስለነበር ይህንን የእነርሱን ሐዋርያነትና ሥልጣኑን ያውቁ ዘንድ

 ቅዱስ ጳውሎስ ከሐዋርያት እንጂ ከጌታ ስላልተማረ ክብሩ ያነሰ ነው እያሉ የአይሁድ ካህናት የገላትያን
ሰዎች ያወናብዱ፣ ያስጨንቁ ስለነበር ይህን ለማስረዳት

 መገረዝ ጽድቅን ያስገኛል ጳውሎስ ራሱ ተገርዟል፤ እናንተ ግን ጽድቅ እንዳታገኙ “መገረዝ


አይጠቅምም” ይላችኋል እያሉ ከእውነተኛዋ ሃይማኖት ሕግና ሥርዓት ያስወጧቸው ስለነበር ይህን
ለማስረዳት

 ሐዋርያት ከአይሁድ ተፋቅረው ሕገ ኦሪትን ጠብቀው ሥርዓተ አይሁድን አክብረው በኢየሩሳሌም እየኖሩ
እርሱ ግን እናንተን አላዋቂ አድርጎ የሐሰት ትምህርት ያስተምራችኋል በማለት የሚናገሩትን ለማስተማር
ጽፎላቸዋል፡፡

የመልእክቱ አከፋፈል
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 110
የገላትያ መልእክት ስድስት ምዕራፎች አሉት፡፡ በአምስትም ከፍለን እናጠናዋለን

ገላ 1፡1-5፡- መንፈሳዊ ሰላምታና ለእግዚአብሔር የቀረበ ምስጋና

ገላ 1፡6 – 2፡21፡- ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያነቱን እያስረዳ ሐሰተኞችን እየተቃወመ ስለ ጽድቅ የጻፈላቸው
ትምህርት

ገላ 3-4፡- ስለሕግና ስለ ክርስቶስ ያቀረበው ትምህርት

ገላ 5-6፡10፡- ስለ ክረስቲያናዊ ምግባር የጻፈው ትምህርት

ገላ 6፡11-18፡- የሐሰተኞች ዓለማ፣ የቅዱስ ጳውሎስ ትምህርትና ቡራኬ

5. ወደ ኤፌሶን ሰዎች

ኤፌሶን በታናሽ እስያ ውስጥ በምዕራብ በኩል በኤጅያን ባሕር አጠገብ የምትገኘው የእስያ አውራጃ ዋና
ከተማ ነበረች፡፡ ብዙ ነጋዴዎችም ይገኙባት ነበር፡፡ የታወቀው የአርጤምስ (በላቲኑ አጠራር) “ዲያና” ቤተ
ጣዖት እንዲሁም በስደትና በምርኮ የተሰበሰቡ አይሁዳውያን ምኩራብ ሠርተው ይኖሩባት ነበር፡፡ የፋርስ ግዛት
ሆና ስትኖር ታላቁ እስክንድር ፋርሱን ንጉሥ ዳርዮስን ድል አድርጎ ከተማዋን የግሪክ ግዛት አድርጓታል፡፡

ወንጌልን እየሰበከ የኤፌሶንን ቤተክርስቲያን የመሠረተው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነው፤


የመሠረታትም በ 3 ኛው ሐዋርያዊ ጉዞ ነው፡፡ በ 2 ኛው ሐዋርያዊ ጉዞው መጨረሻ ጎብኝቷት ነበር፤ በ 3 ኛው
ሐዋርያዊ ጉዞ ግን ለሦስት ዓመት ያህልም አስተምሯል፡፡ /ሐዋ 19፡8፣ 20፡31/ በወቅቱ በተፈጠረው ሁከት
ምክንያት ከተማይቱን ከለቀቀ በኃላ 3 ኛውን ጉዞ ጨርሶ ወደ ኢየሩሳሌም ሊሄድ ሲል ለኤፌሶን ቅርብ
በነበረችው በሚሉጣን የኤፌሶንን ሽማግሌዎች (ቀሳውስት) አስጠርቶ ምክርና አደራ እንደሰጣቸው
ተመዝግቧል፡፡ ሐዋ 20፡17-18

መልእክቲቱ የተጻፈችበት ቦታ እና ዘመን

የኤፌሶን መልእክት ቅዱስ ጳውሎስ በ 1 ኛው እስራቱ ወቅት በሮም እስር ቤት ሆኖ ከጻፋቸው የጳውሎስ
መልእክታት አንዷ ናት፡፡ /ኤፌ 3፡1፣ 4፡1-20/ የተላከችውም ከቆላስያስና ከፊልሞና መልእክታት ጋር
በተመሳሳይ ጊዜ ነው፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ የመጀመሪያ የሮም እስራቱ ከ 62-64 ዓ.ም ስለሆነ በ 62 ዓ.ም ገደማ
እንደተጻፈች ይነገራል፡፡ መልእክቷን ይዟት የሄደው ቲኪቆስ የተባለው የጳውሎስ ደቀመዝሙር ነው፡፡ ኤፌ 6፡
21

መልእክቱ የመጽሐፉ ዓላማ

 የኤፌሶን ክርስቲያኖች አሕዛብ ወገን ቢሆኑም ከእስራኤል ጋር አንድ ሆነው በክርስቶስ ጸጋ መዳናቸውንና
ሰማያዊ ክብር ማግኘታቸውን አውቀው በእምነታቸው እንዲጠነክሩ ለማድረግ፡፡

 በክርስትና ሕይወታቸው እንዲያድጉ እንጂ በፊተኛ ኑሯቸው እንዳይመላለሱ ከጨለማ ሥራ


እንዳይተባበሩ ሲያሳስባቸው ነው፡፡

የመልእክቱ አጠቃላይ ይዘት

የኤፌሶን መልእክት ከወቀሳና ከተግሣጽ ነጻ የሆነ ትምህርትን ይዛለች፤ ትምህርቱም የሃይማኖት፣ የሥነ
ምግባር ትምህርት ነው፡፡

የኤፌሶን መልእክት አከፋፈል

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 111


የኤፌሶን መልእክት ስድስት ምዕራፎች ሲኖሩት በሦስት ከፍለን እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

ኤፌ 1፡- ሰላምታና ምክር

ኤፌ 2-3፡- ስለ ሰው ልጆች ዘላለማዊ ሕይወት

ኤፌ 4-6፡- ስለ ሥነ ምግባራዊ ትምህርቶች፣ በእስር ላይ ሳለ ስለሚሰብከው ወንጌል


እንዲጸልዩለት ያቀረበው ማሳሰቢያ፣ ስለ ኑሮው ቲኪቆስ እንደሚያስታውቃቸው እና ጸሎትና
ቡራኬ ይገኝበታል፡፡

6. ወደ ፊልጵስዮስ ሰዎች

ፊልጵስዩስ በቀድሞ ዘመን ኣሌኒደስ ትባላለች፤ ፊልጵስዩስ የሮሜ ቅኝ ግዛት የሆነች በመቄዶንያ
አውራጃ ውስጥ የምትገኝ የአንድ ወረዳ ዋና ከተማ ነበረች፡፡ ቀደም ሲል ቅዱስ ጳውሎስ በዚህች ከተማ
ልድያ የተባለችውን ሴትና የእስር ቤቱን ኃላፊ ከእነ ቤተሰቦቻቸው አስተምሮ ወደ ክርስትና መልሷቸዋል፡፡
(የሐዋ ሥራ 16፡9-40)

በ 60 ዓ.ም በሮም ታስሮ ሳለ የጻፋት መልእክት ስለ ክርስቶስ አምላክነትና ሰው መሆን የምታስረዳ


የሃይማኖት ትምህርት ናት፡፡ በተጨማሪም ክርስቶስ መጥቶም ይህን ዓለም እንዲያሳልፍ ያለውን የዳግም
ምጽአቱን ነገር ትናገራለች፡፡ በመጀመሪያው ሐዋርያዊ ጉዞው በ 51 ዓ.ም ወደ ኢየሩሳሌም የተጓዘው
በፊልጵስዮስ አልፎ በጢሮአን በኩል ስለነበር በከተማዋ አስተምሯል፡፡ የፊልጵስዮስ ክርስቲያኖች በሮም
የመጀመሪያ እስራቱ ለቅዱስ ጳውሎስ በአፍሮደጡ እጅ ስጦታ ላኩለት በመከራው የማይዘነጉት ክርስቲያኖች
ስላገኘ ሁልጊዜ ይደሰትባቸውም ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት መልእክቱ በደስታ የተሞላች ናት፤ ለዚህም ደጋግሞ
“ደስ ይበላችሁ” ይላቸዋል፡፡ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በፊልጵስዩስ እንደተጀመረ በ 22 ኛው ተአምሩ
ደስቅስዮስ ተናግሯል፡፡

መልእክቱ የተጻፈችበት ምክንያት

 ቅዱስ ጳውሎስ በሮም እስር ቤት በመሰቃየት ላይ መሆኑን የተረዱ የፊልጵስዩስ ምዕመናን አፍሮዲጡ
በተባለው ወኪላቸው ያዋጡትን አስተዋጽኦ አስይዘው ላኩለት፡፡ እርሱም መከራው የማይዘነጉት፣
በሃይማኖታቸው ጽኑ መሆናቸውን አይቶ የሚያበረታታ ምስጋና፣ ምክርና ትምህርት ላከላቸው፡፡ /ፊል 4፡
14-20/
 ራሳቸውን ከፍ ከፍ ያደርጉ ይመኩም ስለነበር የክርስቶስ አርአያነት ይኑራችሁ እያለ በመምከር
ጽፎላቸዋል፡፡
 መታሰሩን የሰሙ ቢጽ ሐሳውያን እኛም መምህራን ነን እያሉ በፊልጵስዩስ ክርስቲያኖች ላይ ችግር
ፈጥረውባው ነበርና መልስ ለመስጠት
 በተጨማሪም በከተማዋ የነበሩት አይሁድ እኛ የአብርሃም ዘር ነን እያሉ በአሕዛብ ላይ ይመኩባቸው
ስለነበር ከንቱ የሆነ ትምክህታቸውን እኔም እኮ የብንያም ዘር ነኝ በማለት ለሁሉም መልስ በመስጠት
ጽፎላቸዋል፡፡

መልእክቱቲ የተጻፈችበት ቦታና ዘመን

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የፊልጵስዩስን መልእክት የጻፋት በሮም በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ እንደ ነበር
ከመልእክቲቱ እንረዳለን፡፡ (ፊል 1፡7፣ 13፡14) ጊዜውም ከእስራቱ ሊፈታ አካባቢ እንደሆነ ይታመናል፡፡ (ፊል 2፡
19፣ 23፡24)

የፊልጵስዩስ ሰዎች መልእክት አከፋፈል

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 112


የፊልጵስዩስ መልእክት ዓራት ምዕራፎች የያዘች ናት፤ ይህንንም በ 5 ክፍል ከፍለን እንመለከተዋለን፡፡

ፊል 1፡1-11፡- ሰላምታ
ፊል 1፡12-26፡- በሮም እስራቱ ጊዜ ስለ ወንጌል መስፋፋትና አንድነታቸው
ፊል 1፡27-2፡18፡- ስለ ፊልጵስዩስ ምዕመናንና ክርስቲያኖች ኑሮ
ፊል 2፡19-30፡- ስለ ጢሞቲዎስና አፍሮዲጡ መላክ
ፊል 3፡1-21፡- ስለ ሐሰተኞች መምህራን
7. ወደ ቆላስይስ ሰዎች

ቆላስይስ ከኤፌሶን 100 ማይል ወደ ምስራቅ ርቃ በፍርግያ ውስጥ የምትገኝ ከፍርግያ ዋና ከተማ ከሎዶቅያ ደግሞ 13 ማይል የምትርቅ ከተማ ናት፡፡ ዛሬ
ቱርክ በሚባለው ሀገር ትገኛለች፡፡ ከምዕራቡ ዓለም ወደ ምስራቁ በሚወስደው መንገድ ዳር ስለምትገኝ ዋና የንግድ ማዕከል ናት፡፡ በእንጨትና በበግ ጠጉር
ምርቷ ትታወቃለች፡፡

የቆላስይስ ከተማ ምዕመናን ወንጌልን የተማሩት ኤጳፍራ ከተባለው ታማኝ የክርስቶስ አገልጋይ ነው፡፡ (ቆላ 1፣7) ኤጳፋራ የቆላስይስ ተወላጅ ሲሆን ቅዱስ
ጳውሎስ በ 3 ኛው ጉዞ ወቅት በኤፌሶን እያስተማረ ሁለት ዓመት በቆየ ጊዜ ያመነ ሰው ነበር፡፡ ኤጳፋራ ክርስቶስን ካመነ በኋላ ከጳውሎስ ጋር የክርስቶስ
አገልጋይ ሆኗል፡፡ በሀገሩ ቆላስይስ ወንጌልን ሰብኮ ቤተክርስቲያኒቱን መሥርቷል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በሮም መጀመሪያው እስራት ጊዜ ከቆላስይስ መጥቶ ስለ
ቤተክርስቲያኒቱ ነግሮት ነበር፡፡ በዚያም ከጳውሎስ ጋር አብሮ ታስሮ እንደነበረ ተገልጦአል (ፊልሞ 1፣23)፡፡ ስለ አመኑት ምዕመናን ኤጳፋራ ሁልጊዜ
አብዝቶ ይጸልይ ነበር፡፡ (ቆላ 4፣12) በዚህም ወቅት የቆላስይስ ቤተክርስቲያን መሪ የነበረው የባለጸጋው የእግዚአብሔር ወዳጅ የፊልሞና ልጅ አክሪጳ ነው
(ቆላ 4፣17 ፊልሞ 1፣2)፡፡ በቆላስይስ ከኤጳፋራ በተጨማሪ ፊልሞናና ልጁ አክሪጳ ወንጌልን አስተምረውባታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ስለ እነርሱ ታላቅ
ተጋድሎ ነበረው፡፡ (ቆላ 2፣1)

የቆላስይስ መልእክት ጸሐፊ


የቤተክርስቲያን አባቶች የሆኑት ቀሌምንጦስና ቴዎፍሎስ እንደመሰከሩት የቆላስይስን መልእክት የጻፈው ራሱ ቅዱስ ጳውሎስ ነው፡፡ በተጨማሪ ራሱ ቅዱስ
ጳውሎስ ቆላ 1፣1 በእጁ ራሱ እንደጻፈው ይመሰክራል፡፡ አጻጻፉም ከፊልሞና መልእክት ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡

መልእክቷ የተጻፈችበት ቦታና ዘመን


ቅዱስ ጳውሎስ ይህችን መልእክት በእስር ቤት ሳለ ነው የጻፉት፡፡ በእስር ቤት እንደነበረም የሚያስረዱ ቃላት በውስጧ ይገኛሉ፡፡ (ቆላ 4፣3-11)
አብዛኛው የቤተክርስቲያናችን ጥንታዊ ትውፊት እንደሚያስረዳው በሮም የመጀመሪያ እስራት ሐዋ 28 ጊዜ ከ 61-63 ዓ.ም መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ
ተጽፏል ይላል፡፡ የላካትም በቴኪቆስ እጅ ከኤፌሶንና ከፊልሞና መልእክት ጋር ነው፡፡ ቆላ 4፣7

የቆላስይስ መልእክት የተጻፈችበት ምክንያት

1. ኤጳፋራ ቅዱስ ጳውሎስን ሊጠይቀው በመጣ ጊዜ በመንፈስ ስለሚሆን ፍቅራቸው ስለነገረው ሊያመሰግናቸውና ሊያበረታታቸው ስለወደደ ቆላ 1፣3-
7
2. የፊልሞና አገልጋይ አናሲሞስ የቆላስይስን የኑሮ ሁኔታ ስለነገረው ስለ ክርስቲያናዊ የኑሮ ሁኔታ አብራርቶ አስረድቷል፡፡
3. በተጨማሪም በፍልስፍና የተመሠረቱ የተለያዩ የሐሰት ትምህርቶች መግባታቸውን ነግሮት ስለነበር ከእነዚህ ይጠበቁ ዘንድ ነው፡፡

በቆላስይስ የነበሩ መናፍቃንና ትምህርቶቻቸው

ሀ. ግኖስቲኮች፡- ግኖሲስ (እውቀት) ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም አዋቂዎች ማለት ነው፡፡ እምነታቸውም ግኖስቲዝም (Gnostism)
ይባላል፡፡ እነዚህም ሰው የሚድነው ካለው እውቀት ብዛት ነው እንጂ በምግባር አይደለም የሚሉ ናቸው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስም ለእነዚህ መልስ ሲሠጥ እውቀት ለሰው ልጅ እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊ መሆኑን ካስረዳ በኋላ ነገር ግን ከምግባር ፈጽሞ መለየት
እንደሌለበት ይናገራል፡፡ ምክንያቱም እውቀቱ ተግባራዊ መሆን አለበትና፤ ያለዚያ ግን ረብ ወይም ጥቅም የለውም፡፡ ሐዋርያውም በመልእክቱ “እውቀት”
የሚለው መንፈሳዊውን እውቀት ወይም ስለእግዚአብሔር ምስጢራት ማወቅን ነው፡፡ በዚህ መልእክት ላይም እንዲህ ብሏል “… የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ
ጥበብና አእምሮ ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን፣ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም፡፡ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔር እውቀት እያደጋችሁ
…” ቆላ 1፣8-10 በማለት እውቀት ብቻ ሳይሆን በበጎ ሥራ ፍሬ እንዲያፈሩ አስተምሯል፡፡

በተጨማሪ እነዚህ መናፍቃን ‹‹ሥጋ ኃጢኣተኛ ስለሆነ እግዚአብሔርን ማወቅና ማምለክ አይቻልም፣ እግዚአብሔርም ሰውን የራሱ ማድረግ አይቻልም፡፡
ሰውና እግዚአብሔርም በጣም የተራራቁ ናቸው ይላሉ፡፡ ስለዚህ ሰዎች አምልኮ ማቅረብ የሚችሉት ከእነርሱ በላይ ከእግዚአብሔር በታች ለሆኑት ለመላእክት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 113


ነው ይላሉ፡፡›› ይህም በጣም የተሳሳተ ትምህርት ነው፡፡ ምክንያቱም ሥጋ በራሱ ኃጢኣተኛና ርኩስ አይደለም፡፡ ቢሆን ኖሮማ እግዚአብሔር ባልፈጠረው
ነበር፡፡ በተጨማሪም አምልኮን ማቅረብ የሚገባው ለፈጣሪያችን ለእግዚአብሔር ብቻ ሆኖ ሳለ ለመላእክት አቅርቡ ማለት የተሳሳተ ትምህርት ነው፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በምዕራፍ 2 ቁጥር 18 ላይ ‹‹ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ አየወደደ፣ ላላየውም ያለ ፍቃድ እየገባ፣ በሥጋዊም አእምሮ
በከንቱ እየታበየ ማንም አይፈረድባችሁ፡፡›› በማለት ከእነዚህ ይጠበቁ ዘንድ ጽፎላቸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ መናፍቃን ነፍሳችንን ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ ከፈለግን በሥጋችን ላይ ጨካኝ መሆን አለብን በማለት “ አትያዝ፣ አትንካ፣
አትቅመስ” የሚሉ ትምህርቶችን ያስተምሩ ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ ብሏል “እንደሰው ሥርዓትና ትምህርት አትያዝ፣ አትቅመስ፣ አትንካ ለሚሉት
ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በማድረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና፡፡…” በማለት ለእርሱ ትእዛዝ እንዳይገዙ አስጠንቅቋል፡፡ ቆላ
2፣22-23
ለ. የአይሁድ እምነትና ሥርዓት፡- አይሁዳውያን ለሁለት መቶ ዓመታት ያህል በፍርግያ ውስጥ ተቀምጦአል፡፡ ስለዚህም ግዝረትንና የኦሪትን በዓላት
ክርስቲያኖችን ያስገድዱ ነበር፡፡ አንድ ሰውም ክርስቲያን ለመሆን መጀመሪያ አይሁዳዊ መሆን አለበት በማለት ያስተምሩ ነበር፡፡ ስለዚህም ወንጌል ያለ ኦሪት
፣ ክርስቶስ ያለ ሙሴ፣ ጥምቀት ያለ ግዝረት ጥቅም የለውም ይሉ ነበር፡፡ እነዚህ መናቅቃን ጁዲያይዘር ሲባሉ በሮምና በገላትያም በብዛት ነበሩ፡፡
ሐዋርያውም ስለዚህ ሲናገር “እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ፡፡” ቆላ
2፣16-17 በማለት አስተምሯቸዋል፡፡
ሐ. እግዚአብሔር አብ ብቻ ፍጥረታትን ፈጠረ፡- ፍጥረታትን አብ ብቻውን ፈጠረ በኋላም የሰው ልጅ ሲበድል ሊያድነው ኢየሱስ ክርስቶስ መጣ ነገር ግን
እርሱ አስቀድሞ አልፈጠረውም የሚሉ መናፍቃን ነበሩና ለእነርሱ መልስ ይሆን ዘንድ ጽፎታል፡፡ ሐዋርያውም “…እርሱ የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፡፡
የሚታዩትንና የማይታዩትን … ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል፡፡ … ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፡፡” በማለት ከአብ ጋር የሚተካከል የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ
መሆኑን አስረድቷል፡፡ ቆላ 1፣14-15

የመልእክቱ አጠቃላይ ይዘት


የቆላስይስ መልእክት የሐሰት አስተማሪዎች ለሚያስተምሩት ትምህርት በጥንቃቄ የተሰጠ መልስ ነው፡፡ ይህም ማለት ከሥር መሠረቱ ጀምሮ ደረጃ በደረጃ
ትምህርቱን ግልጽ የሚያደርግ አቀራረብ አለው ማለት ነው፡፡ በአጠቃላይ ይህ መልእክት የያዘው ትምህርት እንደ ሌሎቹ የጳውሎስ መልእክታት ሁሉ
የሃይማኖትና የሥነ ምግባር ትምህርት ነው፡፡

የመልእክቱ አከፋፈል

የቆላስይስ መልእክት አራት ምዕራፎች አሉት፤ እነርሱም በአምስት ይከፈላሉ፡፡

ቆላ 1፡1-8 (መግቢያ)፡- ላኪው ለተተቀባዮች ያቀረበው ሰላምታ፣ ስለ ቆላስይስ ክርስትያኖች እምነትና ፍቅር
ሰምቶ ለእግዚአብሔር ያቀረበው ምስጋና

ቆላ 1፡9-2፡7፡- ይህ ክፍል በክርስቶስ ሰው መሆን የተሰወረው የእግዚአብሔር ምስጢር ስለመገለጡ የጻፈው


ትምህርት፣ በእግዚአብሔር ዕውቀት እንዲያድጉ ይጸልይላቸው እንደነበር እንዲሁም በወንጌል የሚሰብከው
ክርስቶስ የእግዚአብሔር ምስጢር የታወቀለት መሆኑ ተገልጾበታል፡፡

ቆላ 2፡8-23፡- በዚህ ክፍል ቅዱስ ጳውሎስ ሐሰተኞች እንዳይማርኳቸው የጻፈው ማሳሰቢያ፣ በጥምቀት
የክርስቶስ የመለኮት ምስጢር እንዳወቁ፣ ስለ ኦሪት በዓላትና ስለ መላዕክት አምልኮ እንዲፈርድባቸው፣ አትያዝ
አትቅመስ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት እንዲገዙ ያስተማራቸው ትምህርት ይገኝበታል፡፡

ቆላ 3፡- ስለ ሥነ ምግባር የጻፈላቸው ትምህርት፣ በምድር ያለውን ሳይሆን በላይ ያለውን እንዲሹ፣
ሊያስወግዷቸው ሊሽሯቸው ስለሚገቡ ነገሮች፣ ስለ ቤተሰብ ኑሮ ስለባሪያዎችና ስለጌቶች የጻፋላቸው ትእዛዛት
እንዲሁም እንዲጸልዩና በጥበብ እንዲመላለሱ የጻፈው ማሳሰቢያ ይገኝበታል፡፡

ቆላ 4 (ማጠቃለያ)፡- ቲኪቆስን ከሰናሲሞስ ጋር የላከበት ምክንያት፣ ሰላምታ ያቀርቡላቸው ሰዎች እና ላኪው


ሰላምታ ያቀረበላቸው ሰዎች፣ የጳውሎስ የስንብት ሰላምታ እና ቡራኬ

ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች የተላኩ መልእክታት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 114


ተሰሎንቄ ቀድሞ የመቄዶንያ ዋና ከተማ ስትሆን ዛሬ የግሪክ ከተማ ናት፡፡ ቀድሞ ቴርማ ትባል ነበር፤ ትርጉሙም
“ፍል ውኃ” ማለት ነው፡፡ ከሳገደር የተባለ ገዢ ከተማዋን በሚስቱ ስም ተሰሎንቄ ብሎ ሰይሟታል፡፡ የንግድ ወደብ
ስለሆነች የዘመኑ ነጋዴዎች ከእርሷ ወደ ኤፌሶንና ቆሮንቶስ ታላቅ ንግድ ነበራቸው፡፡ በ 50 ዓ.ም ቅዱስ ጳውሎስ ሲላስንና
ጢሞቴዎስን አስከትሎ በመምጣት ለ 3 ሳምንት ያህል ትምህርተ ወንጌልን አስተምሯቸዋል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በተሰሎንቄ
ሳሉ አይሁድ ስለተቃወሙት ወደ ቤሪያ ሄዶ ነበር፤ በዚያ ያሉ አይሁዶች ትምህርታቸውን በትክክል ይማሩ ስለነበር፤ በዚህ
የተነሣ በተሰሎንቄ ያሉ አይሁዶች መጥተው ዳግም ተቃወሙት በዚህ ምክንያት ምዕመናኑ ወደ አቴና ላኩት፡፡ በአቴና
በኩል አድርጎ ቆሮንቶስ ሲገባ ከሲላስና ከጢሞቴዎስ ጋር ተገናኝቷል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ እናትና አባት ልጆቻቸውን እንደሚመክሩ በትህትና ቃል ሲሰብክላቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ
አክብረው ተቀበሉት (1 ኛ ተሰ 2፡13) ለምቀኝነት የተነሣሱ አይሁድ ደበደቡት በገበያ ቦታም እየጎተቱ ያሰቃዩት ነበር፤
እንዲህ አድርጎ በትዕግስትና በታማኝነት ያቋቋማትን ቤተክርስቲያን መከራውን ሳይፈራ በየጊዜው እየተመላለሰ ይጎበኛት
እነርሱንም ይጠይቃቸው ይመክራቸው ነበር፡፡ ሐዋ 20፡6፣ 1 ኛ ጢሞ 1፡3

ቅዱስ ጳውሎስ ይህችን የመጀመሪያቱን መልእክት የጻፋት በአቴና ውስጥ ነው፡፡ የተሰሎንቄ ሰዎች ያለን ይበቃናል
እያሉ ሥራ መሥራት ማቆማቸውን አይሁድም ደግሞ መከራ ዝላበዙባቸውና የገዛ ወጋቸውንና ሥርዓታቸውን
ስለጫኑባቸው ጽድቅ በዚህ የሚገኝ ከሆነማ እያሉ በክርስትና ሕይወታቸው ተስፋ የቆረጡ ነበሩ፡፡ ሁሉንም መንፈሳዊ
ችግራቸውን እንደሰማ አስቀድመው በያዙት እምነት ይጸኑ ዘንድ ትክክለኛውንም የክርስትና ሕይወትና ትምህርት ያውቁ
ዘንድ ይህችን መልእክት በ 50 ዓ.ም አካባቢ ጽፎ በስልዋኖስ (በዕብራይስጥ ሲላስ የተባለው) እና በጢሞቴዎስ እጅ
ለላከላቸው፡፡

8. የመጀመሪያይቱ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች

መልእክቱ የተጻፈበት ዐበይት ምክንያቶች፡

 ቀድሞ በብጥብጥ ምክንያት በድንገት ስለወጣ የተሰሎንቄ ክርስቲያኖችን ለማጽናናት፣ ጠላት ሰይጣን
እንዳይቃወማቸው የእርሱም ድካም ከንቱ እንዳይሆን የመንፈስ ልጁን ጢሞቲዎስን አስይዞ ላከላቸው፡፡

 ምንም እንኳ መከራና ስደት ቢበዛባቸውም ከሃይማኖት ያለመናወጣቸውን፣ እርስ በእርስም በፍቅር መኖራቸውን፣
ቅዱስ ጳውሎስንም ያልረሱ መሆኑንና ሌሎችንም አስደሳች ዜና ነገሮች ስለነበር በዚህ ምክንያት ጻፈላቸው፡፡ 1 ኛ
ተሰ 1፡6

 የተሰሎንቄ ምዕመናን መከራከር ያበዙ ስለነበር የተማሩትን ትምህርትና ሃይማኖት መጠበቅ እንጂ ክርክርን
እንዳያበዙ ሊያስተምራቸው

 አንዳንድ ያልበሰሉ ምዕመናን ከጌታ መምጣት በፊት የሞቱ ሰዎች እንደገና ተነሥተው ጌታን የሚገናኙ
አይመስላቸውም ነበርና ኃዘን ያበዙ ነበር፤ ስለሆነም ከጌታ መምጣት በፊት ትንሣኤ ሙታን እንዳለ በመግለጥ
ሊያጽናናቸው

 እርስ በእርሳቸው የተፈቃቀሩ እየመሰላቸው አንዱ ሚስቱን ለሌላው በመስጠት የማይገባ ሥራ ይሠሩ ስለነበር፤
እነርሱን ለመገሰጽ

 በአጠቃላይ ፍጹማኑን የበለጠ ለማበረታት፣ ተከፍሎ ልብ ያላቸውን ለማጽናት አንዳንዶችንም ለመገሰጽ


ጽፎላቸዋል፡፡

የመልእክቲቱ አከፋፈል

መልእክቱ 5 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን ለ 6 ከፍለን እናጠናዋለን፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 115


1 ኛ ተሰ 1፡ የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ ምስጋና

1 ኛ ተሰ 2፡ 1-16፡ የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ ገድል በተሰሎንቄ ቤተክርስቲያን

1 ኛ ተሰ 2፡17-3፡17፡ ስለ ተሰሎንቄ ቤተክርስቲያን የሐዋርያው ሥጋት

1 ኛ ተሰ 4፡ 1-12፡ ስለ ምዕመናን ቅድስናና ፍቅር

1 ኛ ተሰ 4፡13-5፡11፡ ስለ ዳግም ምጽአት የተሰጠ ትምህርት

1 ኛ ተሰ 5፡12-2፡ ስለ ምዕመናን በሕብረት መኖር

9. ሁለንተኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች

ይህች ሁለተኛይቱ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች የተጻፈች የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት የተጻፈችው የመጀመሪያይቱ
መልእክት ከተጻፈች ከጥቂት ጊዜ በኋላ በቆሮንቶስ ሳለ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ስለ ዳግም ምጽአት ብዙ መናፍቃን
እንደሚያስቸግሯቸው በሰማ ጊዜ ፈጥኖ ይህቺን መልእክት ጻፈላቸው፡፡ በተሰሎንቄ የሚገኙ አይሁድ ራሱ ቅዱስ ጳውሎስን
ሲያስጨንቁት እንደነበር የተሰሎንቄ ክርስቲያኖችንም ያስጨንቋቸው ነበርና የሚያጽናና መልእክቱን በ 51 ዓ.ም
በጢሞቲዎስና በሲላስ እጅ ልኮላቸዋል፡፡

ሁለተኛይቱ የተሰሎንቄ መልእክት በ 2 ኛው ሐዋርያዊ ጉዞ ወቅት አንደኛይቱ መልእክት ከተጻፈች ከጥቂት ጊዜ


በኋላ በዚያው ዓመት ውስጥ በቆርንቶስ እንደተጻፈች ሊቃውንት ይገልጻሉ፤ ዘመኑም 51 ዓ.ም ገደማ ነው፡፡

መልእክቱ የመጽሐፉ ዓላማ

 በነገረ ምጽአት ዙሪያ ብዙዎች መናፍቃን ያስቸግራቸው ስለነበር በሰማ ጊዜ ይህችን መልእክት ጽፎላቸዋል፡፡

 ከመጠን በላይ እርሱን ያስጨንቁት እንደነበር እነርሱንም ሲያስጨንቋቸው ምን ማድረግ እንደሚገባቸው በመምከር
ጽፎላቸዋል፡፡

 የእርሱ መልእክት መሆኗን ስሙን በመጥቀስ እንዲቀበሉት አረጋግጦ ጽፎላቸዋል፡፡

ሁለተኛይቱ የተሰሎንቄ ሰዎች መልእክት ዝርዝር ይዘት

የሁለተኛይቱ የተሰሎንቄ መልእክት ይዘት ከመጀመሪያይቱ መልእክት ይዘት ጋር ተመሳሳይ ነው፤ በውስጡ
የሚገኘው የሃይማኖት እና የሥርዓት ትምህርት ነው፡፡ 3 ምዕራፍ ሲኖሩት በሦስት ፍለን እናጠናዋለን፡፡

2 ኛ ተሰ 1፡ ክርስቲያንና መከራው

2 ኛ ተሰ 2፡ ክርስትያንና ዳግም ምጽአት

2 ኛ ተሰ 3፡ ክርስትያንና ዕለታዊ ተግባሩ

10. ወደ ዕብራውያን ሰዎች


ዕብራውያን በአባታቸው በኔቦር (በአብርሃም ቅድመ አያት) ዕብራውያን የተባሉት በኢየሩሳሌም ያሉ
ምዕመናን አይሁድ ናቸው፡፡ በአዲስ ኪዳን ዘመንም ወንጌል መጀመሪያ የተሰበከው በዕብራውያን ነው፤ ይህች
መልእክት የተጻፈቸው ሮማውያን የኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ካፈሰሩበት ከ 70 ዓ.ም በፊት ነው፡፡ ዕብ 13፡10
መልእክቱም የሙሴ ሕግ፣ የቤተመቅደሱን አገልግሎት የነገሥታቱንና የመሳፍንቱን ታሪክ፣ ትውፊትና

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 116


ሥርዓት ጠንቅቀው የሚያውቁ አይሁዶች የሚበዙባቸው ሀገሮች በኢየሩሳሌም፣ በኢጣልያና በእስክንድርያ
ለሚኖሩ ክርስቲያኖች ነው፡፡

የዚህች መልእክት ጸሐፊ ማን ነው? የሚለው ጥያቄ እጅግ አነጋጋሪ ነበር፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ጸሐፊነት ለብዙ
ጊዜያት አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ብዙዎች ይህ መልእክት የቅዱስ ጳውሎስ አይደለም ለማለት የሚገልጧቸው
ምክንያቶች፡-

 አጻጻፉ ከቅዱስ ጳውሎስ የአጻጻፍ ባሕርይ የተለየ ነው፡፡

 መልእክቱ የተላከው ለዕብራውያን እንደመሆኑ መዘጋጀት የነበረበት በዕብራይስጥ ቋንቋ ነበር ግን


የተዘጋጀው በግሪክ ቋንቋ ነው

 በመልእክቱ መጀመሪያ ላይ በሌሎች መልእክቶች የተለመደውን የሰላምታ አሰጣጥ አልተጠቀመም

 የእርሱ ቢሆን ሊገልጽ ይችል ነበር፤ የሚሉት ናቸው፡፡

ከ 185-254 ዓ.ም የነበረው አርጌንስ (origen)፣ ከ 150-215 ዓ.ም የነበረው ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ ፣
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቅዱስ አትናቴዎስና ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስም የዕብራውያንን መልእክት
ከቅዱስ ጳውሎስ መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ አካተውታል፡፡ ሌሎች አባቶችም የቤተክርስቲያን ትውፊትን
መሠረት በማድረግ ቅዱስ ጳውሎስ እንደጻፈው ተናግረዋል፡፡

በ 397 ዓ.ም በቅርጣግና (chartage) ላይ የተደረገው የቤተክርስቲያን ጉባኤም የቅዱስ ጳውሎስ


መልእክት በማለት ደንግጎ አስቀምጦታል፤ እነዚህ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት መልእክቱ የቅዱስ ጳውሎስ
ነው ሲሉ በመረጃና ከላይ ያልተቀበሉትን ሰዎች ጥያቄ መልስ እንደሚከተለው ነው፡፡

 የአጻጻፉ ባሕርይ የተለየው ቅዱስ ጳውሎስ ጥልቅ የኦሪት ዕውቀት ስላለው መልእክቱ ተቀባይነት
እንዲኖረው ከሌሎቹ መልእክታት በአቀራረቡ ለየት አድርጎታል፡፡
 ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራይስጥ ቋንቋ ከጻፈው በኋላ ወደ ግሪክ ቋንቋ የተረጎመው ወንጌላዊው ቅዱስ
ሉቃስ ነው፡፡
 ቅዱስ ጳውሎስ በሌሎቹ መልእክቶቹ ሁሉ በእርሱ እንደተጻፈ ማረጋገጫ አድርጎ የተናገረው የሰላምታ
ቃል በዚሁ መልእክት ላይም ተገልጧል፡፡ ዕብ 13፡5
 ጥልቅ ዕውቀት ያለው ለአቀራረቡ ምንም ችግር የሌለበት ቅዱስ ጳውሎስ የዕብራውያን ሰዎች
ከእግዚአብሔር ተለይተው እንዳይቀሩ ሕጉን ሥርዓቱን፣ ትውፊቱን እንዲጠብቁ በሚገባቸው ኦሪታዊ
አገላለጽ እንዲመለሱ ለማድረግ የተጻፈላቸው በመሆኑ ነው፡፡

ስሙን በመልእክቱ ውስጥ ያልገለጸበት ምክንያት፡-

 አስቀድሞ የእነርሱ ተማሪና ለወጋቸው ቀናተኛ ስለነበር ስሙን ቢያዩ ኖሮ በበቀል ስሜት መልእክቱን
ስለማይቀበሉት

 ዘመኑ አይሁድ በሮማውያን ላይ ለማመጽ የተዘጋጁበት ጊዜ ስለነበር በሮም መንግሥት የቁም እስረኛ
የነበረ በመሆኑ በግዞትና በጦርነት ጊዜ መተማመን ስለማይኖር ሮማውያን ካወቁ ወገኖቹን ያነሳሳብናል
ብለው እንዳይቃወሙትና ምክንያት አግኝተው እስራቱን ወደ ፓለቲካ እንዳያዞሩበት፡፡

 ቀድሞውንም ያሳሰሩት እነርሱ ናቸውና ገና ስሙን ሲያዩ ኦሪት አለፈች ሊለን ይሆናል ብለው ከማንበብ
እንዳይሰናከሉ፣ ነጻ ሆነው መልእክቱን አንብበው ፣እንዲረዱ ወደ ክርስትና ያልመጡትን ለማምጣት፤
የመጡትን ደግሞ ለማጽናት ጽፎላቸዋል፡፡ ይህችን መልእክት በመጀመሪያዋ እስራቱ በሮሜ እያለ በ 60
ዓ.ም አካባቢ ጽፎ በጢሞቴዎስ እጅ ልኮላቸዋል፡፡
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 117
መልእክቱ የመጽሐፉ ዓላማ

 የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እዚህ ምድር መምጣት ሱባኤ የተቆጠረለት፣ ትንቢት
የተነገረለት እንጂ እንደ እንግዳ ደራሽ እነደ ውኃ ፈሳሽ አለመሆኑን ለማስረዳት

 ኢየሱስ ክርስቶስ ከነቢያት፣ ከመላዕክት እንዲሁም በክህነቱ በመሥዋዕቱ፣ በሕጉ፣ በኪዳኑ በሚያወርሰን
መካነ ዕረፍት . . . ወዘተ የሚበልጥ መሆኑን ለማስረዳት

 በወቅቱ ክርስትናን በተቀበሉ ግሪክኛ ተናጋሪ በነበሩ አይሁድ ላይ ስደትና መከራ ስለጸናባቸው
በእምነታቸው ጸንተው መከራውን ታግሰው የጽድቅ አክሊል ተካፋዮች እንዲሆኑ ለመምከርና
ለማጽናት፡፡

 በኦሪት ሕግ ብቻ ይኖሩ የነበሩ ወደ ክርስትና ሃይማኖት ያልተመለሱ ብዙ አይሁዳውያን መልእክቱን


አንብበው ይመለሱ ዘንድ ጽፎላቸዋል፡፡ እንዲሁም ክርስቲያኖችንም ወንጌል እንበለ ኦሪት (ወንጌል ያለ
ኦሪት) ጥምቀት ያለ ግዝረት፣ ክርስቶስ እንበለ ሙሴ (ክርስትና ያለ ሙሴ) ምንም አይረባም በማለት
ያሳስቷቸው ነበር፤ ብዙዎቹም በዚህ ትምህርት ተደናግጠው ወደ ኦሪት ለመመለስ እያፈገፍጉ ስለነበር
መልስ ለመስጠት ነው፡፡

መልእክቲቱ የተጻፈችበት ቦታና ዘመን በዕብ 13፡24 ላይ “ከኢጣልያ የሆኑ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል”
የሚል ቃል ይገኛል፤ ስለዚህ ጸሐፊው ቅዱስ ጳውሎስ ታስሮ ከተፈታ በኋላ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የተጻፈው
በኢጣሊያ ውስጥ ስለሆነ ጊዜው ከተፈታ በኋላ ከኢጣሊያ ሳይወጣ ነው ማለት ነው፤ ይህም በኢጣሊያ
ተጽፎ በጢሞቴዎስ እጅ መላኳን ይገልጣል፡፡

የመልእክቱ አጠቃላይ ይዘት

እንደሌሎቹ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት ሁሉ የዕብራውያን መልእክትና የሥነ ምግባር ትምህርት ነው፡፡

የመልእክቱ አከፋፈል

ይህች መልእክት 13 ምዕራፎች ሲኖሯት በ 6 ክፍል ከፍለን እንመለከተዋለን፡፡

ዕብ 1-2፡- ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነትና የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅነት


ዕብ 3-4፡- ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙሴ ስለመብለጡ
ዕብ 5-7፡- የሰው ልጆችን ከኃጢአት ለማዳን ራሱን መስዋዕት ያደረገው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ
በብሉይ ኪዳን በዓመት አንድ ጊዜ ለኃጢአት ማስተስርያ መስዋዕት ከሚያቀርቡት ሌዋውያን ሊቃነ
ካህናት ስለመብለጡ
ዕብ 8-9፡- እግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት በብሉይ ለእስራኤላውያን ካደረገው ቃልኪዳን በሐዲስ
ያደረገው የላቀ ስለመሆኑ
ዕብ 10፡- ስለ ኦሪት መሥዋዕት መሻርና ካመኑ በኋላ ወደ ጥፋት ማፈግፈግ እንደማይገባ
ዕብ 11-13፡- ስለ ክርስትና ሕይወት አስፈላጊነት

የኖላዊነት መልእክታት

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለግለሰብ የላካቸው መልእክታት የኖላዊነት መልእክታት በመባል ይታወቃሉ፡፡
እነርሱም 1 ኛና 2 ኛ ጢሞቴዎስ፣ ቲቶ እና ፊልሞና ናቸው፡፡ ለመልእክታቱ ይህ ሥያሜ የተሰጣቸው
በውስጣቸው ትምህርተ ኖሎትን (አገልግሎትን) በስፋት ስለሚያነሡ ስለሆነ ነው፡፡ እነዚህንም መልእክታት
እያንዳንዳቸውን ቀጥሎ እንመለከታለን፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 118


1. መጀመሪያው የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ጢሞቴዎስ
ቅዱስ ጢሞቴዎስ ማነው?

የቅዱስ ጢሞቴዎስ የትውልድ ሀገር በሊቃኦንያ በምትገኘው የልስጥራን ከተማ ነው፡፡ አባቱ ግሪካዊ
ሲሆን ስሙ በታሪክ ተመዝግቦ አይገኝም፤ እናቱ አውንቄ የምትባል አይሁዳዊት ነች፡፡ /ሐዋ 16፡1-3/ በሐዋርያት
ሥራ ላይ እንደተገለጸው የቅዱስ ጢሞቴዎስ እናት ያመነች አይሁዳዊት ተብላ ተጠርታለች፡፡ /ሐዋ 16፣1/
ሴት አያቱ ሎይድ ትባላለች፡፡ ምንም እንኳን ባይገዘርም እናቱና አያቱ ክርስቲያኖች በመሆናቸው ጢሞቴዎስ
ስለ እምነቱ የተማረና ከሕፃንነቱ ጀምሮ ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያውቅ ነበር፡፡ /2 ጢሞ 3፣15 2 ጢሞ 1፣5/

ቅዱስ ጢሞቴዎስ በዕድሜው ወጣት ቢሆንም በሃይማኖትና በምግባር የጸና እንዲሁም መንፈሳዊ ቅናት ያለበት
ነበር፡፡ ጾም በጣም ይወድ ስለነበር ሥጋ፣ ቅቤ፣ ወይን ወዘተ... በአጠቃላይ የላመ የጣመ አይቀምስም ነበር፡፡ በዚህ የተነሣ
ሰውነቱ የመነመነ ሥራው ግን የፈጠነ ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ስለሆድህና ስለ በሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ
እንጂ ወደፊት ውኃ ብቻ አትጠጣ” በማለት የመከረው ሰውነቱ በበሽታ እንዳይጠቃ መድኃኒት ይሆነው ዘንድ ነበር፡፡ /1
ጢሞ 5.23/

ቅዱስ ጳውሎስ ጢሞቴዎስን በ 2 ኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ነው በልስጥራን ያገኘው፤ በልስጥራን፣ በመቄዶንያ


(በኢቆንዮን) ያሉ ወንድሞች ስለ ጢሞቴዎስ ቢመሰክሩ ቅዱስ ጳውሎስ አብሮት ያገለግል ዘንድ ወደደ፡፡ በዙሪያው የነበሩ
አይሁድን ለማስደሰት ሲል ገዝሮ አስከተለው፡፡ በዚያን ጊዜ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዕድሜው 15 እንደነበር ይነገራል፡፡

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ጢሞቴዎስ የቅዱስ ጳውሎስ ደቀመዝሙር ሆነ የመንፈስ ቅዱስ አባቱ ከሆነው ከቅዱስ ጳውሎስ
በዋለበት እየዋለ ባደረበት እያደረ ክርስትናን በሚገባ ተማረ፡፡ ለቅዱስ ጳውሎስ የሥራ ረዳቱ፣ የመከራ አጋር ሆኖት
በሄደበት ሀገር አብሮ እየዞረ ቆይቷል፤ በልዩ ልዩ ሀገሮችም ብዙ መልእክታትን ሳይደክም እየተላከ መንፈሳዊ ግዳጁን
ፈጽሟል፡፡ እነዚህ ቦታዎች በእግር፣ በባሕር፣ በከብት የሚኬድባቸው ከመሆናቸው ባሻገር ሌትተቀን መጓዝን ይጠይቃሉ፤
ነገር ግን ቅዱስ ጢሞቴዎስ የመንፈስ አባቱን መልእክት ያለመታከት ያደርስ ነበር፡፡

በ 2 ኛው ሐዋርያዊ ጉዞዎቹ ወቅት በፊልጵስዩስ፣ በተሰሎንቄ፣ በቤሪያ እንዲሁም በቆሮንቶስ ከጳውሎስ ጋር


የወንጌልን ሥራ አብሮ ሠርቷል፡፡ ጳውሎስ ከተሰሎንቄ ከወጣ በኋላ ስለ እምነታቸው ለማወቅና በእምነታቸው
እንዲያጸናቸው እንዲመክራቸውም ልኮት ነበር፡፡ /1 ተሰ 3፣2 5፣6/ በሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞ ወቅትም በኤፌሶን አብሮት
ነበር፡፡ /የሐዋ 19፣22/፡፡ ሦስተኛውን ጉዞ ጨርሶ ወደ ኢየሩሳሌም በመመለስ ላይ ሳለ ጢሞቴዎስ አብሮት ነበር /ሐዋ
20፣4/፡፡ በመጀመሪያው የሮም እስራቱም ጊዜ አብሮት እንደነበር በዚያን ጊዜ ከእስር ቤት በጻፋቸው መልእክታት ውስጥ
በላኪው አድራሻ ላይ ከርሱ ቀጥሎ ጢሞቴዎስን በማንሣቱ ይታወቃል /ፊል 1፣1 ፤ 2፣19 ፤ ቈላ 1፣1/

ጢሞቴዎስ የቅዱስ ጳውሎስ በሃይማኖትና በትምህርት የወለደው የበኵር ልጁ ነው፡፡ /1 ኛ ጢሞ 1፡2፣ 2 ኛ ጢሞ 1፡


2፣ 1 ኛ ቆሮ 4፡17/ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ደቀመዝሙሩ ስለ ጢሞቴዎስ ሲመሰክር “በእምነት እውነተኛ ልጅ” ብሎ
ጠርቶታል፡፡ /1 ጢሞ 1፣2-18 2 ጢሞ 1፣1 ፤ 2፣1/ በዚህም የተነሣ ቅዱስ ጳውሎስ ዲቁና ሰጠው፤ ደግሞም ተስማሚ የሆነ
ትምህርት፣ ምክር ይጽፍለት ነበር፡፡ (1 ኛ ጢሞ 4፡14)

ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ ጢሞቴዎስን ለኤፌሶን ቤተክርስቲያን ጳጳስ አድርጎ ሹሞታል፡፡ /1 ጢሞ 1፣3/ የቤተክርስቲያን
ታሪክ ጸሐፊ የሆነው አውሳብዮስ የኤፌሶን ሀገረ ስብከት የመጀመሪያው ሊቀጳጳስ ቅዱስ ጢሞቴዎስ መሆኑን መስክሯል፡፡
በዚህ መንበሩ ቅዱስ ጳውሎስ እስካረፈበት 67 ዓ.ም ድረስ አብያተ ክርስቲያናትን እየመሠረተ ትምህርተ ወንጌልን እያስፋፋ
አገልግሏል፡፡ ከሀገረ ስብከቱ ሥራ በተጨማሪ ቅዱስ ጳውሎስንም በየጊዜው ያገለግለው ነበር፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስ ዕረፍት
በኋላ ግን ወደ መንበሩ ተመልሶ ለ 33 ዓመታት ያህል ከኤፌሶን ሳይወጣ ቤተክርስቲያኒቱን አገልግሏል፡፡

የኤፌሶን ሰዎች በዓመት አንድ ጊዜ አርጤምስ የተባለ ጣዖታቸውን በዓል ያከብሩ ነበር፡፡ የበዓሉ አከባበር
እያንዳንዱ ሰው ፊቱን በጨርቅ ተሸፍኖ ከቤቱ በመውጣት ያገኘውን ሰው ሁሉ እያፈሰ ከፍ ዝቅ በማድረግና አናት አናቱን

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 119


በዱላ በመደብደብ ነበር፡፡ እንደተለመደው ሁሉ በ 97 ዓ.ም በዓላቸውን ሲያከብሩ ድርጊታቸው የጢሞቴዎስን ልብ
ስለነካው ሊያስተምራቸው ወደ ውጭ ቢወጣ ርሱንም ተሸክመው በመደብደብ በሞትና በሕይወት መካከል ሳለ በመንገድ
ላይ ጥለውት ሄዱ፡፡ ተማሪዎቹም ወድቆ ሲያገኙት ጥቂት ብቻ ይተነፍስ ነበር፡፡ በአጥር አሾልከው በከተማዋ አጠገብ
ወደሚገኝ መንደር ወስደው አስተኙት፡፡ ለ 30 ቀናት ያህልም በሕመም ተሰቃይቶ ዐረፈ፡፡ ደቀመዛሙርቱም ሥጋውን ግዮን
በተባለው ተራራ ቀበሩት፡፡ በ 356 ዓ.ም ዐፅሙ ወደ ቁስጥንጥንያ ተወስዶ በክብር ተቀመጠ፡፡

ከኖላዊነት መልእክታት ውስጥ የመጀመሪያ የሆነችው መልእክት (1 ኛ ጢሞቴዎስ) ሐዋርያው ቅዱስ


ጳውሎስ ለቅዱስ ጢሞቴዎስ እንደጻፈለት ከርዕሱ መረዳት ይቻላል፡፡ ዘመኑን በተመለከተ ያለው አስተሳሰብ
የተለያየ ቢሆንም በ 66 ዓ.ም ገደማ የሚለው ብዙ ተቀባይነት ይኖረዋል፤ ምክንያቱም መልእክቲቱ ስትነበብ ጳውሎስ
ጢሞቴዎስን በኤፌሶን ከሾመው በኋላ ብዙ ሳይቆይ የጻፋት ስለሆነ ነው፡፡ ይህች ለጢሞቴዎስ የተላከች የመጀመሪያይቱ
መልእክት የተጻፈቸው በአቴና ከተማ በቲቶ እጅ ነው፡፡ አንደኛይቱ የጢሞቲዎስ መልእክት የተጻፈችበት ቦታ ሎዶቂያ
እንደሆነ የሚገልጽ ትውፊት አለ፡፡ እርሱም እንዲህ ይላል፡- “ተፈጸመ መልእክቱ ቀዳማዊ ኃበ ጢሞቴዎስ ወተጽሕፈ
በሎዶቂያ ወተፈነወ በእደ ቲቶ፡፡” በዚህ አስተሳሰብ መሠረት ጳውሎስ ጢሞቲዎስን በኤፌሶን ሾሞት እንደወጣ ወደ
መቄዶንያ ሲሄድ በፊት ሎዶቅያ ደርሶ ስለነበር በዚያ ሆኖ ጽፎታል ማለት ነው፡፡

መልእክቱ የመጽሐፉ ዓላማ

 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጢሞቴዎስን የኤፌሶን ሊቀጳጳስ አድርጎ ሹሞት ነበር፤ ነገር ግን የሥርዓተ ኖላዊን (ሥርዓተ
ክህነትን) ትምህርት የሚያሰተምርበት ጊዜ ስላላገኘ የሁለት ዓመቱን የቁም እስር ጨርሶ ከሮም ሲወጣ በ 80 ዓ.ም
አካባቢ በሎዶቂያ ጥቂት የእረፍት ጊዜ በማግኘቱ ለልጁ ለጢሞቴዎስ ስለ ሊቀጵጵስናው ሥራ አጠቃላይ ሁኔታ
ጻፈለት፡፡ /1 ጢሞ 3፣4-15/
 በኤፌሶን ከተማና በአካባቢዋ ባሉት ሀገሮች የተስፋፋውን የግኖስቲኮችን ፍልስፍና አጠቃላይ ሁኔታ ክርስቲያናዊ
ምላሽ በመስጠት ጻፈለት፡፡
 ጢሞቴዎስ ወጣት በመሆኑ ማንም እንዳይንቀው ለራሱና ለትምህርቱ እንዲጠነቀቅ ሊመክረው ጽፎለታል /1 ጢሞ
4፣16-20 ፤ 20-21/
 በኤፌሶን ገብተው ከነበሩት የሐሰት አስተማሪዎች ምእመናንን እንዲጠብቅ ሊያሳስበው ነው፡፡ /1 ጢሞ 1፣18-20 ፤ 4፣1-
4 ፤ 6-3/
 ጢሞቴዎስን ለመምክርና ለማበርታት ጽፎለታል፡፡

የመልእክቱ ዝርዝር ይዘት

1 ኛ ጢሞ 1፡- ላኪው ለተቀባዩ ያቀረበው ሰላምታ፣ ለጢሞቴዎስ ምክርና መመሪያ ለመስጠት፣ ስለ ቤተክርስቲያን
አገልግሎት የጻፈለት ትምህርህተ ጸሎትቅዱስ ጳወሎስ ስለመጠራቱ ያቀረበው ምስጋና፣ የሕግ አስተማሪ ሊሆኑ
ወደው ልዩ ትምህርትን ስለሚያስተምሩ ሐሰተኞች፣ምእመናን የሐሰተኞችን ትምህርት ከማዳመጥና ከክርክር
እንዲቆጠቡ እንዲመክራቸው
1 ኛ ጢሞ 2፣1-7፡- ስለ ጸሎትና ምልጃ፣ ስለ ሥርዓተ ጸሎት፣ ለሰዎች ሁሉ መጸለይ እንዲገባ
1 ኛ ጢሞ 2፣8-15፡- ስለ ሴቶች የአለባበስ ሁኔታ፣ ሴቶች በጉባኤ ማስተማር እንደማይገባቸው
1 ኛ ጢሞ 3-4፡- ስለ ዲያቆናትና ሊቀጳጳሳት ሹመትና ስለ ግዴታዎቻቸው ዝርዝር፣ የአጋንንትን ትምህርት
ስለሚያዳምጡ ሐሰተኞች፣ ስለ ጢሞቴዎስ የግል ሕይወት
1 ኛ ጢሞ 5-6፡- ስለ ምእመናን ከሐሰተኞች መምራን እንዲጠበቁ ትምህርት፣ ደንቦች እንዲሁም ለጢሞቴዎስ
ምክር ፣ በተለያየ ዕድሜ ስላሉ ሰዎች /ስለ ባልቴቶች፤ ስለ ሽማግሌ /ቀሳውስት/ስላመኑ ባሪያዎች፣ ጢሞቴዎስ የተጻ
ፈለትን አደራ እንዲጠብቅ የጻፈለት ማሳሰቢያ /1 ጢሞ 6፣3-16/ ፣ቃለ ቡራኬ
2. ሁለተኛው የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ጢሞቴዎስ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 120


ይህች መልእክት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ 68 ዓ.ም በሁለተኛው እስራቱ በሮም ወይኒ ቤት እያለ ለደቀመዝሙሩ
ለጢሞቴዎስ የጻፋት የመሰነባበቻ መልእክቱ ናት፡፡ መልእክቲቱን በሰማዕትነት ከመሞቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ጽፎ
በአንክሮሎስ እጅ ልኮለታል፡፡ የተላከችው ከእስር ቤት መሆኑ ከራሷ ከመልእክቲቱ መረዳት ይቻላል፡፡

መልእክቱ የመጽሐፉ ዓላማ

 ጳውሎስ በመከራ ላይ እንደሆነ ሁሉ ጢሞቴዎስም በመከራ ውስጥ ስለነበር በእስረኛው በጳውሎስ ሳያፍር በጊዜውም
አለጊዜውም በተማረውና በተረዳው ነገር ጸንቶ እንዲኖርና መከራ እየተቀበለ የወንጌል አገልግሎቱን እንዲፈጽም
ለመምከር ነው፡፡ /2 ኛ ጢሞ 1፡8፣ 3፡10-14፣ ፣ 1-5/
 ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ከመሞቱ በፊት ሊያየው ስለናፈቀ ማርቆስን አንዳንድ ዕቃዎችን ይዞ በቶሎ እንዲመጣለት
ለማድረግ ነው፡፡ /2 ኛ ጢሞ 1፣4 ፤ 4፣9-11 ፤ 13፣21 /
 ለጢሞቴዎስ መሰነባበቻ መልእክት ጽፎለታል
 የመከረውን ምክር በድጋሚ ለማጽናት ጽፎለታል
 ከሐሰተኞች መምህራን ሕዝቡን እንዲጠብቅ ለማሳሰብና ለመምከር ጽፎለታል፡፡
 ቅዱስ ጢሞቴዎስ በኤፌሶን እየተዘዋወረ ሲያስተምር ግማሹ አምኖ እየካደ የቀረው በፍልስፍና እየተራቀቀ ሌላው
በአምልኮ ጣዖት እየተወሰደ ቢያስቸግረው እየተዘዋወረ መስበኩን አቁሞ በረሃ ገብቶ በብህትውና መኖርን መርጦ
ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ቅዱስ ጳውሎስ የተቀበለውን አደራ እንዲጠብቅ የደረሰበትን ፈተና እንዲታገስ በተማረው
ትምህርት ጸንቶ እንዲኖር ለማበረታታትና ለመምከር ጻፈለት
 ጢሞቴዎስና ማርቆስ ለአገልግሎት የሚረዱትን ዕቃዎች ይዘው ቶሎ ወደ ርሱ እንዲመጡ በማሳሰብ ጻፈላቸው፡፡
/ሐዋ 25፣12 ፤ 27፣1፤ 28፣16 ና 30 2 ጢሞ 1፣6-14፤ 2፣1፤ 3፣10-17፤ 4፣6-8 16 ና 17/

የመልእክቱ ዝርዝር ይዘት

2 ኛ ጢሞ 1፡- ሰላምታ፣ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ያለው ናፍቆትና ሐሳብ፣ ስለተሰጠው ቃልኪዳን፣ ቅዱስ
ጳውሎስ ቅዱስ ጢሞቴዎስን እንዳበረታው
2 ኛ ጢሞ 2፡- ስለ ቤተክርስቲያን፣ በጌታችን ምስክርነትና በእሥረኛው በጳውሎስ እንዳያፍር፣ መልካም
ውጤትን ለማግኘት በመከራ እንዲጋደል፣ ከሐሰት አስተማሪዎች እንዲርቅ
2 ኛ ጢሞ 3፡- ስለሚመጣው አስጨናቂ ዘመን፣ በመጨረሻው ዘመን ካለው ክፋትና ስህተት ርቆ በተማረውና
በተረዳው ነገር እንዲጸና፣ በጊዜውም አለጊዜውም የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ እንዲያደርግ፣
2 ኛ ጢሞ 4፡- ከመሞቱ በፊት እንዲመጣለት የጻፈለት ቃል፣ ሕይወቱ እንደሚሰዋ ሲመጣ ማርቆስንና
በጢሮአዳ የተዋቸውን በርኖሱንና መጻሕፍትን እንዲያመጣለት፣ ፊተኛው ሙግቱ፣ ጳውሎስ ለሌሎች ሰዎች
ያቀረበው ሰላምታ፣ ስለ አርስጦስና ስለ ጥሮፊሞስ፣ ስማቸው የተጠራ አራት ሰዎች ለጢሞቴዎስ ያቀረቡት
ሰላምታ፣ የጳውሎስ ቃለ ቡራኬ፣ ስለ ወንጌል አገልግሎትና ስለመሞቱ
3. የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ቲቶ
ቅዱስ ጳውሎስ ከሚወዳቸውና የወንጌል አገልግሎት የሥራ ረዳቱ ከሆኑት አንዱ ቲቶ ነው፡፡ ቲቶ የተወለደው
ከአሕዛብ ወገን ከግሪክ /የአንጾኪያ/ ሰዎች ነው፡፡ /ገላ 2፣3/ ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ መልእክቱ ውስጥ “ከዚያ ወዲያ
ከዐሥራ አራት ዓመት በኋላ ከበርናባስ ጋር ቲቶን ይዤ ወጣሁ” በማለት ለአገልግሎት የተጠራበትን ጊዜ ይነግረናል፡፡ ይህም
ጊዜ በሐዋርያት ሥራ ላይ ለተመዘገበው ለኢየሩሳሌም ጉባኤ በሄደ ጊዜ መሆኑን ብዙ መምራኖች ይናገራሉ፡፡ /የሐዋ 15፣2/

የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ጢሞቴዎስ አብሮት አገልግሏል፡፡ በ 3 ኛው የቅዱስ
ጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞ ወቅት ወደ ቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን ተልኮ እንዳገለገለ ከ 2 ኛው የቆሮንቶስ መልእክት እንረዳለን፡፡
/2 ቆሮ 2፣13 ፤ 2 ቆሮ 8፣6 ፤ 2 ቆሮ 8፣16-24/ ከዚህ በተጨማሪም ቲቶ ከቅዱስ ጳውሎስ እና ከበርናባስ ጋር ከአንጾኪያ ወደ
ኢየሩሳሌም በመመላለስ በገላትያና በቆሮንቶስ እንዲሁም በተለያዩ አብያተ ክርሰቲያናት ብዙ አገልግሎት እንዳበረከተ ቅዱስ
ጳውሎስ ተናግሯል፡፡ (ገላ 2፣ 2 ኛ ቆሮ 8፡18) በአይሁድ ክርክር የተነሣ የአንጾኪያ ቤተክርስቲያን ጳውሎስንና በርናባስን

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 121


ወደ ኢየሩሳሌም ስትልክ ቲቶም አብሮ ሄዷል፡፡ /ገላ 2፣1-3/ ድሆች ለሆኑ ምእመናን ገንዘብ ለመሰብሰብ ጢሞቴዎስ ተልኮ
ሳይሳካለት በመቅረቱ ቲቶ ተልኳል፡፡ ቲቶ ትጉህና ተወዳጅ አገልጋይ ነበር፡፡ /2 ቆሮ 7፣5-7 ፤ 8፣6/

ቲቶ ክርስትና የተቀበለው በቅዱስ ጳውሎስ አስተማሪነት በመሆኑ የመንፈስ ቅዱስ ልጁ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ
ጳውሎስም ስለ ቲቶ ሲመሰክር “በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ” በማለት ጠርቶታል፡፡ /ቲቶ 1፣1/ በቅዱስ ጳውሎስ
ስብከት ስላመነ በሃይማኖት የወለደው ልጁ ነው፡፡ /ቲቶ 1፣4/

ይህን ሐዋርያዊ ተልእኮውንና መንፈሳዊ ትጋቱን ተረድቶ ቅዱስ ጳውሎስ በሜዲትራንያን ባሕር አጠገብ በምትገኝ
የቀርጤስ ቤተክርስቲያንን እንዲያደራጅና እንዲያስተዳድር በውስጧ አይሁድ በሚኖርበት ሀገር ሊቀጳጰስ አድርጎ ዲያቆናትን
ቀሳውስትን እንዲሾም እንዲያስተምር ሾሞታል፡፡ (ቲቶ 1፡5)

ቅዱስ ጳውሎስ እስከሚያርፍበት ጊዜ ድረስ እንደ ጢሞቴዎስ ሁሉ ቲቶ እየተመላለሰ ሲያገለግለው ከቆየ በኋላ
ቅዱስ ጳውሎስ ሲያርፍ ከእነ ቅዱስ ሉቃስ ጋር በመሆን ከቀበረው በኋላ ወደ ሀገረ ስብከቱ ተመልሶ በቀርጤስ ዋና ከተማ
በጎርቲና ሲያገለግል ቆይቶ በ 94 ዓመቱ ዐረፈ፡፡

መልእክቲቱ የተጻፈችው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከቀርጤስ ወደ ኤፌሶን ጢሮአዳና መቄዶንያ ቆይቶ ወደ
ድልማጥያና እልዋሪቆን በመግባት ካስተማረ በኋላ መቄዶንያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሂቆጵልዮን ገብቶ ጥቂት ዕረፍት አድርጎ
ለቀርጤሱ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ለቲቶ በ 63 (1 ኛ ጢሞቴዎስ በተጻፈበት ዘመን ነው) ዓ.ም አካባቢ ስለ ሥርዓተ ኖሎት፣
ስለ ወንጌል አገልግሎት እና ክብር አርጣ በተባለው ደቀመዝሙር አጽፏታል፡፡ /ቲቶ 3፣12/

መልእክቱ የጻፈበት ምክንያት

 የቀርጤስ አብያተ ክርስቲያናት በቁጥር በዝተው ስለነበር ወንጌል እንዲስፋፋባቸው በአስተዳደርም በኩል መመሪያ
ለመስጠት ይህችን መልእክት ጻፈለት፡፡
 ለቲቶ ሥርዓተ ኖሎትን የእረኝነትን ሥርዓት ለማስተማር፤ የቀርጤስ ሰዎችን ሊገሥጻቸውና ሊመክራቸው ስለፈለገ
መልእክቱን ጽፎለታል
 ኤጵስ ቆጶሳትና ቀሳውስት ሆነው ለመሾም የሚችሉት ምግባራቸው ምን መምሰል እንዳለበት ይጽፍለታል
 ለሌሎች አርአያ በመሆን ቤተክርስቲያኒቱን እንዲመራ ጽፎለታል
 ሕዝቡን የሚጠራበትን ሥርዓት ሊጽፍለት ስለፈለገ
 የቀርጤስ ሰዎች ጠባያቸው የከፋ ሰማቸው የጠፋ ነበርና መከራ እንዳይበዛበት፣ መከራ ቢመጣበትም እንዲታገስ
አስቀድሞ የሰዎቹን ጠባይ በማስገንዘብ አገልግሎቱም እንዳይጎዳ ጽፎለታል፡፡ /ቲቶ 1፡12/
 በሀገሪቱ ብዙ ዓለማውያን ሰዎችና መናፍቃን ስለነበሩ ከእነርሱ እንዲርቅ ምዕመናኑም ግንኙነት እንዳይኖራቸውና በከፋ
ትምህርታቸው እንዳይስቡ ክህደታቸውንና ክፋታቸውን እየገለጠ ጽፎለታል፡፡ /ቲቶ 1፡9-11/
 ለድሆች ርዳታ የሚሆን የልግስና ስጦታን ለማሳሰብ፡፡
 ወደ ርሱ እንዲመጣ ሊጠራው ስለፈለገ
 በመጨረሻም በትምህርትና በግብረገብነት የታወቁ ሰዎችን በመምረጥ የቤተክርስቲያን ጠባቂ የሚሆኑትን እንዲሾም
እርሱም በትጋት እንዲያገለግልና እንዲጸና ለሌሎች አርአያ በመሆን ቤተክርስቲያኒቱን እንዲመራ ጽፎለታል ፡፤/ቲቶ 1፡5-
10/

የመልእክቱ ዝርዝር ይዘት

ቲቶ 1፡- ላኪው ጳውሎስና ማንነት፣ ተቀባዩ ቲቶና ከጳውሎስ የቀረበለት ሰላምታ፣ ስለ ቀርጤስ ቤተክርስቲያን
አስተዳደር፣ ስለ ቀሳውስትና ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት፣ ከተገረዙት ወገን ስለሆነ የሐሰት አስተማሪዎች
ቲቶ 2፡- ስለ ቤተክርስቲያን መሪዎች አርአያነት፣ በተለያየ ዕድሜና ደረጃ ስለሚገኙ ምእመናን ሕይወት፣ ሰዎችን
የሚያድነው የእግዚአብሔር ጸጋ መገለጡና ጥቅሙ፣ ስለ ቤተክርስቲያን መሪዎች አርአያነት
ቲቶ 3፡- ስለ ሐዋርያት ግብረ ገብነትና መንፈሳዊ ተልዕኮ፣ ድኅነት በእግዚአብሔር ቸርነት ስለመሆኑ፣
እግዚአብሔርን የሚያምኑ መልካም ሥራ መሥራት እንዳለባቸው፣ የመጨረሻ ቃላት፣ ሰላምታና ቡራኬ
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 122
4. የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ፊልሞና
ሀገሩ ቆላስይስ የሆነው ፊልሞና ደግ ባለጸጋ ሲሆን አፉብያ የተባለች ሚስትና የቈላስይስ ቤተክርስቲያን ኤጲስቆጶስ
የነበረው አክርጳ የተባለ ልጅ ነበረው፡፡ ወደ ኤፌሶን ለሥራ በሄደ ጊዜ የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስን ስብከት ሰምቶ
ከነቤተሰቡ አምኖ ተጠምቋል፡፡

ይህ ሰው አብርሃማዊ ሕይወት የነበረው ሲሆን እንግዶችን በቤቱ እየተቀበለ ያበላ፣ ያጠጣ፣ ያሳድርም ነበር፡፡
በቤቱም ክርስቲያኖች ይሰበሰቡ እንደነበርም ተገልጧል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስን ይንከባከበው፣ በአገልግሎቱም የሚያስፈልገውን
ያደርግለት ነበር፡፡ በመልእክቲቱ ውስጥም ጳውሎስ እንደ ወንድም እንደ ልብ ወዳጅ ወይም እንደ ባልንጀራ አድርጎ
እያቀረበ “የማስተናገጃ ቤት አዘጋጅልኝ” እያለ በመልእክቱ ይጽፍለታል፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክቲቱን የጻፈው ለፊልሞና ቢሆንም ከርሱ ጋር ላሉ ክርስቲያኖችም ጭምር መሆኑን
የሚገልጹ ቃላት አሉ፡፡ /ፊል 1፣1-25/ መልእክቱንም በ 62 ዓ.ም (የቈላስይስ መልእክት በተጻፈበት ጊዜ) ነው በሮም እስር
ቤት የጻፈው፡፡ /ቲቶ 1፡1-23/ በኋላም ከቲኪቆስ ጋር አናሲሞስን አስከትሎ ለርሱና ለቤተሰቡ ላከላቸው፡፡

መልእክቱ የመጽሐፉ ዓላማ

 ፊልሞና አናሲሞስ የተባለ አገልግጋይ ነበረው፤ ይህ አገልጋዩ የሚጠብቃቸው የፊልሞና ከብቶች ሲጠፉበት ሀገሩን ትቶ
ሄደ፡፡ “ማን ባስታረቀኝ” እያለ ሲያዝን ቅዱስ ጳውሎስን ስለጠቆሙት ወደ ሮሜ ሲገባ ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያ
እስራቱ ላይ አግኝቶት ትምህርቱንም ሰምቶ አምኖ ተጠመቀ፡፡ ወደ ሮሜ ለምን እንደመጣም የደረሰበትንም ሁኔታ
ሲነግረው ይህቺን የማስታረቂያ መልእክት ለፊልሞናና ለቤተሰቦቹ ጻፈ፡፡
 ቅዱስ ጳውሎስ የፊልሞናን አገልጋይ አናሲሞስን ለራሱ ሊያስቀር ፈልጎ ነበር፤ ነገር ግን ከፊልሞና ሳይማከር ሊያደርግ
ስላልወደደ በመልእክቱ ለመነው፡፡ በዚህም ቅዱስ ጳውሎስ አናሲሞስን “በእሥራት የወለድሁት ልጄ “ ብሎ
ጠርቶታል፡፡ /ፊል 1፣11/
 ፊልሞናና አፍብያ በአናሲሞስ መጥፋት እንዳያዝኑ፣ መንፈሳዊዉ አገልግሎታቸውን ከመወጣት ወደ ኋላ እንዳይሉ፣
ከብቶችን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የተጠመቁ ክርስቲያን ወገኖቹን ሁሉ እያስተማረ ከእነርሱ ጋር ሆኖ ያበረታታቸው
ዘንድ መልእክቷን በእጅ አስይዞ ልኮላቸዋል፡፡
 ስለጠፋው የፊልሞና ንብረትና በዚህ ምክንያት በክርስቲያኖች መካከል ልዩነት እንዳይኖር አጠቃላይ ሁኔታ
ጽፎለታል፡፡
 አናሲሞስን ከጌታው ከፊልሞና ጋር ለማስታረቅ፤ “ያለበትን ብድር እኔ እመልሳለው ብዬ በእጄ እጽፋለው፡፡” እያለ ቃል
በመግባት እንደ ባርያ ሳይሆን እንደ ወንድም እንዲቀበለው ሊማልደው ጻፈለት፡፡ /ፊል 1፡11-20/
 በእነ ፊልሞና ጸሎት ወደ እነርሱ የመሄድ ተስፋ ነበረውና ሲሄድ በፊልሞና ቤት ለማረፍና ለማገልገል ስለፈለገ
የማስተናገጃ ቤት እንዲያዘጋጅለት ሊለምነው ይህችን መልእክት ላከ

የመልእክቱ ዝርዝር ይዘት

ፊል 1፣1-7፡- ሰላምታና ምስጋና፣ በላኪው እሥር ላይ ያለው ጳውሎስና ተቀባዩ ፊልሞና ከነቤተሰቡ፣ ጳውሎስ
በፊልሞና እምነትና ፍቅር ለአምላኩ ያቀረበው ልመና
ፊል 1፣8-21፡- ስለ አናሲሞስ የቀረበ ምልጃ፣ ክርስቲያን ስላደረገው እንደ ወንድሙ እንዲቀበለው ስለማድረጉ፣
ስለ አናሲሞስ በደል ጳውሎስ የወሰደው ኃላፊነት፣ ጳውሎስ በፊልሞና ላይ ያለው መታመን
ፊል 1፣22-25፡- ከጳውሎስ ጋር ካሉት ሰዎች ለፊልሞና የቀረበ ሰላምታ፣ የአደራ ሰላምታ እንዲሁም ቡራኬ

ሰባቱ መልእክታት

የቅዱስ ጴጥሮስ 1 ኛና 2 ኛ፣ የያዕቆብ፣ የዮሐንስ 1 ኛ 2 ኛ ና 3 ኛና የይሁዳን ጨምሮ እነዚህ ሰባቱ መልእክታት


ሁሉን አቀፍ ወይም ዓለም አቀፍ መልዕክታት (Universal Epistels) በመባል ይታወቃሉ፡፡ ይህ ስያሜም የተሰጣቸው

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 123


ለግለሰብ ወይም ለአንድ ቤተክርስቲያን ብቻ ስላልተጻፉ ነው፤ ማለትም ለአብያተ ክርስቲያናት ስብስቦች የተላኩ
መልእክታት በመሆናቸው ነው፡፡

መልእክታቱም ሲላኩ ከአንዱ ቤተክርስቲያን ይደርስና ለምእመኑ ከተነበበና ከተረዱ በኋላ ሀብት ያላቸው አጽፈው
ቅጅ ያስቀሩና ዋናውን ለአዋሳቸው ወይም ለሌላ ቤተክርስቲያን እንዲዳረስ በማሰብ ያስተላልፉና ይጠቀሙበት ነበር፡፡

የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ መልእክታት

ቅዱስ ጴጥሮስ የቀድሞ ሰሙ ስምዖን ይባል ነበር፡፡ /ሉቃ 5፡34/ ስምዖን ማለት “ስምኦኒ እግዚአብሔር-
እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት እንደሆነ የትርጓሜ መምህራን ይናገራሉ፡፡ እናቱ ትወደው ስለነበር በነገድዋ ስም ስምዖን
ብላ ጠርታዋለች፡፡ በኋላ ግን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ኬፋ ብሎ ሰየመው፤ ኬፋ በአርማይክ
ቋንቋ ሲሆን በግሪክ እና በላቲን ቋንቋ ጴጥሮስ ማለት ነው፡፡ ጴጥሮስ ማለት ዐለት ማለት ነው፡፡ /ናቴ 16፡18፣ ዮሐ 1፡43/
ጴጥሮስ ተብሎ ከተሰየመ በኋላ ስምዖን በሚለው ሰሙ የተጠራበት ጊዜ አለ፡፡ /ዮሐ 21፡15-16/ በአንዳንድ ንባቦችም ስምኦን
ጴጥሮስ እየተባለ ይጠራል፡፡ /2 ኛ ጴጥ 1፡1/

የጴጥሮስ አባት “ዮና” ሲባል እናቱ ግን ስሟ አልተዘገበም፡፡ እንድርያስ የተባለ ወንድም አለው፤ ሚስት እንደነበረችውም
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተገልጧል፡፡ /1 ኛ ቆሮ 9፡5/ ስሟ ግን አልተገለጠም፤ አንዳንድ ትውፊቶች “ጴርጴተዌ” ትባል
እንደነበር ይገልጻሉ፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ያደገበት ሀገር ከገሊላ ባሕር በስተሰሜን ዮርዳኖስ አቅራቢያ በምትገኘው
“ቤተሳይዳ” ተብላ በምትጠራ ቦታ ነበር፡፡ /ዮሐ 1፡45/ ይህቺ ከተማ የወላጆቹ ሀገር ናት፡፡ በትዳር ሳለ ግን ከወንድሙ
ከእንድርያስ ጋር የዓሣ ማጥመድ ሥራ እየሠራ በቅፍርናሆም ከተማ ይኖር እንደነበር በማር 1፣21 ላይ ተገልጧል፡፡

ከጴጥሮስ በፊት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የተዋወቀው ወንድሙ እንድርያስ ነው፤ እንድርያስም “መሲህን
አግኝተናል” ብሎ ከነገረው በኋላ ነው ጴጥሮስ ወደ ጌታችን ሄዶ ኬፋ /ጴጥሮስ/ ትባላለህ ብሎ የሰየመው፡፡ /ዮሐ 1፡41-43/

ብዙም ሳይቆይ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገሊላ ሀገር አጠገብ ሲመላለስ ጴጥሮስና እንድርያስ
መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ በስምዖን ጴጥሮስ ታንኳ ውስጥ ሆኖ ለሕዝቡ ትምህርት ከሰጠ በኋላ ብዙ ዓሣ
እንዲያጠምዱ አደረጋቸው፡፡ ጴጥሮስ ግን “ኃጢአተኛ ነኝና ከእኔ ተለይ” ብሎት ነበር፤ ጌታችን ግን “አትፍራ ከእንግዲህ
ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ” ብሎ ጠራው፤ ያን ጊዜም ሁሉን ትቶ ተከተለው፡፡ /ማቴ 4፡18-22/

ክርስቶስም ቅዱስ ጴጥሮስን ዐለት ብሎ ከሰየመው በኋላ በዚህ ዐለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሠራለው
የገሀነም ደጆችም አይችሏትም ብሏል፡፡ /ማቴ 16፡18/ ቅዱስ ጴጥሮስ ይህንን ለመባል ያበቃው የክርስትና
እምነት መሠረት የሆነውን ምሥጢረ ሥጋዌ /ምሥጢረ ተዋሕዶን/ በመመስከሩ ነው፡፡ አይሁድ አንዶቹ
የዮሴፍ ልጅ ነው፣ ሌሎቹ ደግሞ ከነቢያት አንዱ ነው ሲሉ የክርስቶስን አምላክነት ቁልጭ አድርጎ
በመመስከሩ ምስክርነቱ የእምነት መሠረት ነውና “ዐለት” ተባለ፡፡ ከሦስቱ ምስጢር ሐዋርያትም
ተቈጠረ፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ በሰማዕትነት ያረፈው በኔሮን ቄሳር (54-68 ዓ.ም) ዘመን ነው፤ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር
በአንድ ቀን እንደሆነና ቀኑም ሐምሌ 5 ቀን 68 ዓ.ም ነው፡፡ ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ በአንድ ቀን ይሁን እንጂ
የተሰዉት በአንድ ዓመት አይደለም ይላሉ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ሁለት መልእክታትን ጽፎልናል፡፡ እነዚህን
እያንዳንዳቸውንም ቀጥሎ እንመለከታለን፡፡

1. መጀመሪያው የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት


የመጀመሪያይቱ የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት የተጻፈላቸውን ሰዎች ቅዱስ ጴጥሮስ
በመጀመሪያይቱ መልእክት ጴጥ 1፣2 ላይ ገልጧቸዋል፡፡ እነርሱም በጰንጦስና በገላትያ፣ በቀጶዶትያ፣ በእስያ፣
በቢታንያ የተበተኑ መጻተኞች ናቸው፤ እነዚህን ሰዎች “ኅሩያን/ የተመረጡ” ብሎ ስለሚጠራቸው

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 124


አማኞች ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ እነዚህም አምስት ሀገሮች በታናሽ እስያ ውስጥ የሚገኙ አውራጃዎች
ናቸው፤ የመልእክቱ ተቀባዮች የሆኑት በእነዚህ ሀገሮች የሚገኙት ምዕመናን “የተበተኑ ምጽአተኞች”
ተብለዋል፡፡ በቤተክርስቲያናችን ያለው የ 1 ኛ ጴጥሮስ ትርጓሜ እነዚህን ሰዎች በጴጥሮስ በስብከተ ቃሉ
ያመኑ፣ በሞተ እስጢፋኖስ የተበተኑ ሰዎች መሆናቸው ይገለጣል፡፡ /ስብከተ ሐዲስ ገጽ 197/

ቅዱስ ጴጥሮስ ይህቺን መልእክት የጻፈው በ 60 ዓ.ም በርሱ ተናጋሪነት በስልዋኖስ እጅ ሲሆን
የጻፈበት ቦታው “ባቢሎን” መሆኗን ከራሷ ከመልእክቲቱ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህንንም መረዳት
የሚቻለው “ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ
ያቀርብላችኋል” ብሎ በጻፈው ቃል ነው፡፡ /1 ኛ ጴጥ 5፡13/ ስለዚህ ጴጥሮስ ያን ጊዜ በባቢሎን ነበር ማለት
ነው፡፡

መልእክቱ የመጽሐፉ ዓላማ

 የመልእክቲቱ ተቀባዮች በልዩ ልዩ ፈተና አዝነው ነበርና ለጥቂት ጊዜ መከራ ቢቀበሉም ታላቅ ክብርና ጸጋ
እንደሚያገኙበት እየመሰከረ ሊያጽናናቸው ጽፎታል፡፡ /1 ኛ ጴጥ 2፡20፣ 4፡12-14/
 በአሕዛብ መካከል ሲመላለሱ ከቀድሞ ሥራቸው ተለይተው ኑሯቸው መልካም እንዲሆን ሊመክራቸው
ጽፎታል፡፡ /1 ኛ ጴጥ 2፡12/
 ያለምንም ምክንያት ሊደርስ ከሚችል ፈተናና ችግር ጌታችን እንደታገሠ እንዲታገሡ ለመምከር
 በንጹሕ ደም የተዋጁ ስለሆነ በንጽሕና እንዲኖሩ በክርስቶስ ላይ እንደተመሠረቱት ካህናትና ቤተመቅደስ
እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ
 የዘለዓለም ሕይወት እንዳላቸው ያውቁ ዘንድ
 ከሥጋ ምኞት እንዲጠበቁ
 ከምእመናን ሁሉ ጋር ባላቸው የሚገባ ግንኙነት ትሑታን እንዲሆኑ ጽፎላቸዋል

የመልእክቱ ዝርዝር ይዘት

1 ኛ ጴጥ 1፡1-2፡- ላኪው ቅዱስ ጴጥሮስ ለተቀባዮቹ የላከው ሰላምታ


1 ኛ ጴጥ 1፡3-12፡- መከራ ስለመቀበልና ስለ መዳን የጻፈላቸውን ትምህርት፣ ነቢያት ስለዚህ መዳን
ተግተው እየፈለጉ ይመራመሩ እንደነበር፣ ይህን መዳን ለማግኘት አማኞች ሊኖሩት ስለሚገባ
የቅድስና ኑሮ
1 ኛ ጴጥ 1፡13 – 2፡22፡- በአሕዛብ መካከል ሲኖሩ ሊያሳዩት ስለሚገባ መልካም ኑሮ፣ ስለጌታ ብለው
ለሰው ሥርዓት ሁሉ መገዛት እንደሚገባ፣ ስለ ተጠራንለት ቅድስና፣ ሊያስወግዷቸውና ሊያቀርቧቸው
የሚገቡ ነገሮች፣ ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ ክርስቶስ እንዲቀርቡ፣ የቀድሞውንና የአሁኑን ሕይወት
እያነጻጸረ ከሥጋዊ ምኞት ርቀው መልካም ሥራ እንዲሠሩ የጻፈው ትምህርት
1 ኛጴጥ 3፡- ሰው ከክፉ ነገር መራቅ እንዳለበት፣ ስለ ጋብቻ፣ በጎ ለማድረግ እንዲቀኑ
1 ኛ ጴጥ 4፡- በሚቀበሉት መከራ ክብር እንደሚያገኙበትና መከራ መቀበል ያለባቸው በክፉ ሥራ
ሳይሆን በክርስትና ምክንያት መሆን እንዳለበት፣ በመከራ ወቅት ደስታ ስለመኖሩ፣ የክርስቶስን መከራ
እያሰቡ የአሕዛብን ፈቃድ ትተው የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲያደርጉ፣ ክብሩን እያዩ በመከራው ልክ
ደስ እንዲላቸው እንጂ በመከራው እንዳይደነቁ
1 ኛ ጴጥ 5፡- ለቤተክርስቲያን ካህናትና አባላት የተሰጠ ማጽናናትና የሚገባ ማኅበራዊ ትጋት፣
ሽማግሌዎች በአገልግሎታቸው ስለሚያገኙት ክብር፣ በትሕትና የሚኖር ለጥቂት ጊዜ መከራ ውስጥ
ያሉ ምእመናን ከጌታ የሚያገኙት ክብርና ጸጋ፣ በሰልዋኖስ እጅ እንደጻፈው፣ የመጨረሻው ሰላምታ
2. ሁለተኛዪቱ የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት
ሁለተኛይቱ የጴጥሮስ መልእክት የተጻፈላቸው ሰዎች “በጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ
ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ” ተብለው ተገልጠዋል፡፡ /2 ኛ ጴጥ 1፣1/ ነገር ግን እነዚህ አማኞች

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 125


የመጀመሪያይቱ መልእክት የተጻፈላቸው አማኞች እንደሆኑ በ 2 ኛ ጴጥ 3፡1 ላይ “ወዳጆች ሆይ አሁን የምጽፍላችሁ
ይህቺ ሁለተኛይቱ ናት” በሚለው ቃል መረዳት ይቻላል፡፡ እነዚህ ሰዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ብቻ ሳይሆን
በተለያዩ ሐዋርያት ያመኑ ክርስቲያኖች እንደሆኑ መልእክቲቱ ትጠቁማለች፡፡ /2 ኛ ጴጥ 3፡2/ የጻፈላቸውም
በ 67 ዓ.ም አካባቢ በኔሮን አዋጅ ተይዞ በእሥራት እያለ ነው፡፡

መልእክቱ የመጽሐፉ ዓላማ

 በክርስትና ሕይወታቸው የጸኑ ቢሆኑም ከፊት ይልቅ እንዲተጉ ስለፈለገ ጻፈላቸው፡፡ /2 ኛ ጴጥ 1፡10 /
 ኑፋቄን አሾልከው ከሚያገቡ ሐሰተኛ አስተማሪዎች እንዲጠበቁ /2 ኛ ጴጥ 2፡1/
 የመልእክቲቱ ተቀባዮች እውነትን ቢያውቁም በእውነት ቢጸኑም የሚያነቃቃቸው አድርጎ ጽፎላቸዋል፡፡
 ሐሰተኞች ነቢያትና መምራን ለዚህ ዓለም ሠራኢ መጋቢ የለውም፣ ትንሣኤ ሙታን የለም፣ ኅልፈተ ሰማይ ወምድር
የለም፣ አንድ ጊዜ ካመኑ ምግባር አይጠቅምም እያሉ የክህደት ትምህርታቸው ያላመኑትን ምግባር ያላቸውን
ክርስቲያኖች ያውኳቸው ስለነበር ለእነዚህ ሰዎችና ለጥያቄዎቻቸው መልስ በመስጠት ይህን መልእከት ጽፎላቸዋል፡፡
 የሚገባውን የክርስቲያን አኗኗር ሕይወትና መሠረቱ፣ የቤተክርስቲያን መሥራች የቅዱሳን ሁሉ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ
መሆኑን ያውቁና በክርስትና እምነት ይጸኑ ዘንድ ጽፎላቸዋል፡፡
 ያመኑት ሰዎች ይህን መልእክት ተረድተው በሃይማኖት በምግባር እንዲኖሩ ሌላዎቹ ምግባር ሃይማኖት የሌላቸው
አንብበው ተረድተው ይመለሱ ዘንድ ይህን መልእክት ጽፏል፡፡

የመልእክቱ ዝርዝር ይዘት

2 ኛ ጴጥ 1፡- ላኪው ቅዱስ ጴጥሮስ ለተቀባዮቹ ያቀረበው ሰላምታ፣ የተሰበከላቸው ትምህርት


እውነተኛ እንደሆነ፣ ከፊት ይልቅ ትጋትን እንዲያስቡ የላከላቸው መነቃቂያ፣ የጌታን ግርማ ዐይቶ
የአብን ድምፅ ሰምቶ የጸና የትንቢት ቃል ይዞ እንዳስተማራቸው
2 ኛ ጴጥ 2፡- በመካከላቸው ስለነበሩ የሐሰተኛ አስተማሪዎች ማንነትና ትምህርታቸው፣
በኑፋቄያቸውና በኃጢኣታቸው ምክንያት ስለሚጠብቃቸው ፍርድ፣ መጥፎ ባሕርያቸውና ክፉ
ሥራቸው፣ ዓለም ያሸነፈቻቸው ስለመሆናቸው
2 ኛ ጴጥ 3፡- ስለ ዳግም ምጽአት የጻፈው ትምህርት፣ ከነቢያትና ከሐዋርያት ያገኙትን የጌታን
ትእዛዝ እንዲያስቡ፣ የጌታን ዳግመኛ መምጣት የሚክዱ ዘባቾች አባባልና ለነርሱ የሰጣቸው መልስ፣
ክርስቲያኖች የጌታን ቀን ያለ ነቀፋ ሆነው እንዲጠብቁ፣ ጳውሎስ በጻፈላቸው ትምህርት ስለእነዚህ
ነገሮች የሚናገሩ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስለመጠበቅ፣ በአመፀኞች እንዳይሰናከሉ የጻፈው ማሳሰቢያና
ለጌታ ያቀረበው ምስጋና ይገኝበታል፡፡

የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ መልአክታት

በሐዲስ ኪዳን ውስጥ የዮሐንስ መልእክታት የሚባሉት ሦስት ናቸው፡፡ ነገር ግን በሦስቱም መልእክታት መጀመሪያ
ላይም ሆነ በውስጣቸው የዮሐንስ ስም አይገኝም፤ ይሁን እንጂ አራተኛውን ወንጌል የጻፈው ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ
እንደሆነ ከጥንት ጀምሮ የታመነ ነው፡፡ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ ደቀመዝሙር እንደሆነ የሚነገርለት ፖሊካርፕ የተባለው
የቤተክርስቲያን አባት ወደ ፊልጵስዮስ በጻፈው ጽሑፍ ውስጥ እነዚህን ሦስቱን መልእክታት ዮሐንስ እንደጻፋቸው
መስክሯል፡፡

ከዚህም ሌላ ፓፒያስ፣ አውሳብዮስ፣ ሄሬኒዎስ፣ የእስክንድርያው ቀሌምንጦስ እነዚህ መልእክታት የሐዋርያው


የቅዱስ ዮሐንስ ጽሑፎች መሆናቸውን በየጽሐፋቸው ገልጸው ተናግረዋል፡፡ የመልእክታቱ ይዘትና በውስጣቸው የሚገኙት
ኃይለ ቃላት ቋንቋቸውም ከዮሐንስ ወንጌል ጋር ስለሚመሳሰል ጸሐፊያቸው ወንጌላዊው ዮሐንስ መሆኑን ያሳያል፡፡ ዮሐንስ
እነዚህን መልእክታት በ 90 ዓ.ም የጻፋቸው ሲሆን በኤፌሶን እንደጻፋቸውም ይነገራል፡፡

3. መጀመሪያው የዘብዴዎስ ልጅ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ መልእክት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 126


አንደኛይቱ የዮሐንስ መልእክት ለማን እንደተጻፈች የሚገልጽ ቃል በውስጧ አልተመዘገበም፤ ነገር ግን ዮሐንስ
ያስተማራቸው ክርስቲያኖች ስለመሆናቸው “ልጆቼ ሆይ” እያለ በጻፈው ቃል መረዳት ይቻላል፡፡ /1 ኛ ዮሐ 2፡1፣ 3፡18/

ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ይህንን መልእክት የጻፈው ለሰባት ዓመታት በፍጥሞ ደሴት ታሥሮ ከተፈታ በኋላ በ 96
ዓ.ም አካባቢ ነው፡፡

መልእክቲቱ የተጻፈችበት ምክንያት

 በዚያ ዘመን ከተነሡት የሐሰት መምህራን እንዲጠበቁ ምዕመናን ለማሳሰብ ነው፡፡ /1 ኛ ዮሐ 2፡26/ እነዚህን ሰዎች
ቅዱስ ዮሐንስ “የክርስቶስ ተቃዋሚዎች” በማለት ይጠራቸዋል፡፡ /1 ኛ ዮሐ 2፡18/ የመልእክቲቱንም አጠቃላይ ይዘት
ቅዱስ ዮሐንስ “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” በማለት ይናገራል፡፡ /1 ኛ ዮሐ 4፡9-16/
 ትንሣኤ ሙታን የለም፤ በመናገርና መሥራት እንጂ በማሰብ የሚሠራውን ኃጢኣት እግዚአብሔር አያውቅም፤ ኢየሱስ
ክርስቶስ በሥጋ አልተገለጠም ከጥምቀት በኋላ ምግባር መሥራት ጥቅም የለውም ዋጋም አያሰጥም፤ አዋቂዎች
“ግኖስቲኮች” ነን በማለት ያለ እነርሱ እውነተኛ ክርስቲያን እንደሌለ በማሰብ ለእኛ የመጨረሻ ዕውቀት ተገልጦልናል
ስለዚህ ያለ ሕግ ልንኖር እንችላለን ብለው ላስተማሩ ከሀድያን መልስ ይሆን ዘንድ

የመልእክቱ ዝርዝር ይዘት

1 ኛ ዮሐ 1፣1-4፡- ስላየውና ስለሰማው የክርስቶስ መገለጥ


1 ኛ ዮሐ 1፣5- 2፣17፡- ክርስቲያኖች በሃይማኖትና በምግባር መጽናት እንዳለባቸው፣ ሰው
ኃጢኣቱን አምኖ ቢናዘዝ ይቅርታ እንደሚያገኝ፣ ከኃጢኣትና ከዓለም ምኞቶች ተለይተው በብርሃን እንዲኖሩ
የጻፈው ትምህርት፣ በጨለማ የሚመላለስ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት እንደሌለው፣ ኃጢኣትን አምነው ቢናዘዙ
ይቅርታ እንደሚገኝ፣ የጌታን ትእዛዛት መፈጸም እንጂ ኃጢኣትን ማድረግ እንደማይገባ፣ ዓለምንና በዓለም ያለውን
እንዳይወዱ በየዕድሜያቸው የጻፈላቸው ምክር
1 ኛ ዮሐ 2፣18-29፡- ስለሚነሡት የክርስቶስ ተቃዋሚዎች፣ የሐሰኞቹን ማንነት ተገንዝበው በተማሩት ጸንተው
እንዲኖሩ
1 ኛ ዮሐ 3፣1- 4፣6፡- የእግዚአብሔር ልጆች ስለመሆናቸው፣ በክርስቶስ የሚኖሩ የእግዚአብሔር ልጆች ኃጢኣት
እንደማያደርጉ፣ ፍቅርን እንዴት እንዳወቅነው፣ የእውነትና የሐሰት መንፈስ በምን እንደሚለይ
1 ኛ ዮሐ 4፣7- 5፣5፡- እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለው ፍቅርና ሰዎች ርስ በርሳቸው ሊያደርጉት ስለሚገባ
ፍቅር፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ የሚያምን ከእግዚአብሔር እንደሚወለድ
1 ኛ ዮሐ 5፣6-21፡- ስለ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክነት እና ዘለዓለማዊ ሕይወት ይነግረናል፡፡
4. ሁለተኛዪቱ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ መልእክት
ቅዱስ ዮሐንስ ሁለተኛይቱን መልእክት የጻፈው ለአንዲት ለተመረጠች እመቤትና ለልጆችዋ ነው፡፡ የእኛ
ቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስረዳው ይህቺ ሴት በአንዲት ደሴት የምትኖር የነገሥታትን፣ የመኳንንቱን ልጆች የምታሳድግ
እመቤት ነበረች፡፡ ዮሐንስ ከደቀመዝሙሩ ከአብሮኮስ ጋር በቤርያ ገብቶ በክርስቶስ አሳምኗት ከዚያ ወጥቶ ከሄደ በኋላ
ይህንን መልእክት ጽፎላታል፡፡

በቤተክርስቲያናችን ባለው የዚህች መልእክት ትርጓሜ መግቢያ ላይ የተመረጠችው እመቤት ስሟ “ሮምና” እንደምትባል
ተገልጧል፡፡ ዮሐንስ በዚህች መልእክቱ ራሱን እኔ “ሽማግሌው (ቀሲስ)” ብሎ ይጠራል፡፡

መልእክቱ የጻፈበት ምክንያት

 በመጀመሪያው መልእክት የተገለጹት መናፍቃን ምዕመናንን ለማስካድ ይጣደፉ ስለነበር የሐሰት ትምህርታቸውን
በመቃወም እውነተኛዋን የክርስትና ትምህርት እንዲያጸኑ ነው፡፡
 በአጠቃላይ ቅዱስ ዮሐንስ በፍጥሞ ደሴት በታሠረ ጊዜ በመናፍቃን የክህደት ትምህርት የተነሣ በቤቷ ያለው
የክርስቲያኖች ጉባኤ መከፋፈል ደረሰበት፤ ጠብ ክርክር ተነሣ፡፡ ይህን የሰማው ቅዱስ ዮሐንስ የቀድሞ ኑሮዋን ወይም

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 127


ሕይወቷን አስታውሳ ያሁኑን መከራ እንድትረሳ እመምኔቷም ለትዕቢት እንዳይሆንባት ታላቁ ሐዋርያ በድሮ ስሟ
“እመቤቴ” እያለ በትህትና በመጥራት አጠቃላይ ሁኔታውን ጽፎላታል፡፡
 በዚያን ጊዜ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደሚገለጥ የማያምኑ ብዙ አሳቾች ስለነበሩ
እነዚህም እንዳይቀበሉ ለማሳሰብ ጽፎታል

የመልእክቱ ዝርዝር ይዘት

2 ኛ ዮሐ 1፣1-3፡- ሰላምታ፣ የጸሐፊው ፍቅር


2 ኛ ዮሐ 1፣4-6፡- የምዕመናን አንድነትና ጸንቶ የመኖር ትምህርት፣ ርስ በርሳቸው በመዋደድ ትእዛዝ እንዲሄዱ፣
በእውነት በሚሄዱት ልጆች የተሰጠው ደስታ
2 ኛ ዮሐ 1፣7-11፡- የሐሰተኞችን ትምህርት ስለመቃወምና እንዳይቀበሏቸው ስለማስጠንቀቅ
2 ኛ ዮሐ 1፣12-13፡- ወደ ተቀባዮቹ ለመሄድ ያለው ታሪክ፣ ብዙ ያልተጻፈ መኖሩ፣ ለሰዎች የሚቀርብ ሰላምታ
5. ሦስተኛዪቱ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ መልእክት
ይህቺ መልእክት የተላከችው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋይዮስ ለተባለ ሰው ነው፡፡ በሐዲስ ኪዳን ውስጥ ጋይዮስ በመባል
የሚጠሩ ሦስት ሰዎች አሉ፡፡ /ሐዋ 20፣4፤ ሮሜ 16፣23፤ 1 ኛ ቆሮ 1፣14/ ከእነዚህም መካከል ይህቺን መልእክት
እንድትጻፍለት የታደለው በሮሜ መልእክት /ሮሜ 16፣23/ ላይ ለተጠቀሰው የአብርሃማዊ እንግዳ መቀበል በረከት የደረሰው
ጋይዮስ ነው፡፡ ዮሐንስም ለዚህ የቤተክርስቲያን አባልና ተቆርቋሪ ለሆነው ሰው ምስጋና አቅርቧል፡፡

መልእክቲቱ የተጻፈችበት ምክንያት

 ጉባኤው ይሰፋ ዘንድ እንግዳ እየተቀበለ የሚያገለግለውን ጋይዮስን ለማመስገን


 በጎ የሆነውን እንጂ ክፉ የሆነውን እንዳይመስል ሊያሳስበው
 በቤተክርስቲያን ውስጥ መለያየት እንዳይኖር ለመምከር
 ዲዮጥራጢስን ለመገሰጽ

የመልእክቱ ዝርዝር ይዘት

3 ኛ ዮሐ 1፣1-4፡- ስለ እምነቱ ጠንካራነት ለጋይዮስ የቀረበ ምስጋናና ጸሎት፣ ስለ ጋይዮስ እውነተኛነት የወንድሞች
ምስክርነት
3 ኛ ዮሐ 1፣5-8፡- ስለ እንግዳ ተቀባይነቱ ለጋይዮስ የቀረበ ምስጋና ስለ ጌታም ከአሕዛብ የወጡ ወንድሞችን
በእንግድነት ተቀብሎ ያሳየው የፍቅር ሥራና እንዲህ ያሉትን በእንግድነት መቀበል በሃይማኖት እንደሚገባ
3 ኛ ዮሐ 1፣9-11፡- በትዕቢታቸው ዲዮጥራጢስ ላይ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ
3 ኛ ዮሐ 1፣12-14፡- ስለ ድሜጥሮስ የተሰጠ ምስክርነት፣ ጋይዮስን ሄዶ ሊያየው እንደነበር የሰጠው ተስፋ
3 ኛ ዮሐ 1፣15፡- የጋይዮስና ለወገኖቹ የቀረበ ሰላምታ
6. የሐዋርያው የቅዱስ ያዕቆብ መልእክት
የመልእክቱ ጸሐፊ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያዕቆብ ተብለው የተጠሩና በተቀራራቢ ዘመን የኖሩ ከሦስት በላይ ሰዎች አሉ፡፡ ከእነዚህም
መኸከል፡-

 ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ፡

ይህ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱና የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወንድም ነው፡፡ (ማቴ. 10-2 ፣ 4-21) በሄሮድስ
አግሪጳ ዘመን በ 44 ዓ.ም ሰማዕትነትን የተቀበለ ነውና የዚህ መልእክት ጸሐፊ እርሱ ሊሆን አይችልም፡፡ (ሐዋ. 12-2)

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 128


ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ዘመን የቤተክርስቲያን መሠረት ገና አልሰፋም ነበርና፤ ኑፋቄም ገና አልጀመረምና መልእክት
የሚጻፍለት አካል አልነበረም፡፡

 ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ፡

ይህ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ከቊጥር 3 ላይ ስሙ የተጠቀሰ ሐዋርያ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የጌታችን ወንድም
የተባሉት የእልፍስ ልጆች ናቸው፤ ስለዚህም የዚህ መልእክት ጸሐፊ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ ነው ይላሉ፡፡ ሆኖም ግን
መልእክቱን እርሱ አልጻፈውም፡፡ ይሄን ከሚያረጋግጡልን ነገሮች አንዱ በዮሐ 7-5 ላይ“ወንደሞቹ ስንኳ አላመኑትም”
ተብሎ እንደተጻፈ የጌታ ወንድም ያዕቆብ በጊዜው ገና በኢየሱስ ክርስቶስ የማያምን መሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን የእልፍዮስ ልጅ
ያዕቆብ የጌታችን ሐዋርያ እንደመሆኑ መጠን በጌታ አላመነም ሊባል አይችልም፡፡44

 ያዕቆብ ወልደ ዮሴፍ፡

በመጽሐፈ ስንክሳር ላይ “ይህም ቅዱስ የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ ነው፡፡ እርሱም ከልጆቹ ሁሉ የሚያንስ ነው፡፡
እርሱም ንጹሕ ድንግል የሚሆን ከጌታችን ጋር አደገ ስለዚህም ክብር ይግባውና የጌታችን ወንድም ተባለ” 45 በማለት
እንደሚነግረን የመልእክቱ ጸሐፊ የጌታ ወንድም ቅዱስ ያዕቆብ ይህ ነው፡፡ ቅዱስ ጄሮም እንደገለጸው ቅዱስ ያዕቆብ
በኢየሩሳሌም ጳጳስ ሆኖ የተሾመ እና እስከ ዕለተ ዕረፍቱም በዚያው ስፍራ የነበረ ነው፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስና ታሪክ ጸሐፊው
አውሳብዮስ እንደሚሉት ያዕቆብ ለጌታ የተለየ ናዝራዊ ነበር፡፡ ከእናቱ ማኅፀንም የተመረጠ ነው፡፡ ወይንና የሚያሰክር
መጠጥን አልጠጣም በፀጉሩም ላይ ምላጭ አላረፈበትም፡፡

መልእክቱ ለማን እና መች ተጻፈ

መልእክቱ የተጻፈው ለተበተኑት ዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ነው፡፡ /ያዕ.1፡1/ ይህንን በተመለከተ የተለያዩ ሀሳቦች አሉ፡፡
ዋና ዋናዎቹን እንደሚከተለው አስቀምጠናቸዋል፡፡

-መልእክቱ የተጻፈው አስቀድሞ አይሁድ ለነበሩ ከክርስትና መነሣት በፊት በተለያየ ሀገር ተበትነው ላሉ አይሁድ
ነው፡፡ እግዚአብሔር የአይሁድን መበተን ለክርስትና መሰበክና መስፋፋት ተጠቅሞበታል፡፡

ከእነዚህ አይሁድ መካከል በበዓለ ኀምሳ በኢየሩሳሌም የነበሩ ብዙዎች ወደ ክርስትና ተመልሰዋል፡፡ አስቀድሞ አይሁድ
የነበሩ በክርስቶስም ያመኑ ወገኖች ከአይሁድ ወንድሞቻቸው ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል፡፡ ይኸውም አይሁድ በክርስቶስ
ባለማመናቸው ምክንያት ነው፡፡

አንዳንድ ወገኖች ደግሞ 12 ቱ ነገዶች መጠቀሳቸው ከአይሁድ የነበሩ ናቸው ለማለት አይደለም ይልቁንም ይህ
የሚያመለክተው ቤተ-ክርስቲያንን ነው ይላሉ፡፡ ቤተ-ክርስቲያን አማኞቿ ሰማያውያንም ይሁኑ ምድራውያን፤ መንፈሳዊ
የሆኑ አካላት ያሉባት ናት፡፡ እሥራኤል የሚለው ቃልም ለእሥራኤል ዘሥጋ የተሰጠ ሳይሆን ለእሥራኤል ዘነፍስ ነው፡፡
ስለዚህ አይሁድ አዲሲቱ እሥራኤል መሆናቸውን ማስረገጥ ከፈለጉ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን
ነበረባቸው፡፡ ምክንያቱም አዲሲቱ እሥራኤል በአዲስ ኪዳን በመድኃኒታችን ያመኑት ወገኖችን የያዘች የቅድስት ቤተ-
ክርስቲያን ጉባኤ ናትና በማለት ይናገራሉ፡፡

መልእክቱ የተጻፈበትም ጊዜ ደግሞ ከኢየሩሳሌም መውደቅ አስቀድሞ ማለትም ኢየሩሳሌም ከተበታተነችበት ከ 70


ዓ.ም አስቀድሞ በ 60 ወይም በ 61 ዓ.ም እንደሆነ ይታመናል፡፡

የመልእክቱ አላማ

44
ከጌታችን ትንሣኤ በኋላ ግን በጌችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም የሚያምን ሆኗል፡፡ በሐዋርያት ሥራ ላይም እንዲ ተብሎ ትጽፏል፡- “እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ
እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር፡፡” ሐዋ. 1-14፡፡
45
ስንክሳር፤ ሐምሌ 18

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 129


 ክርስቲያኖች መከራን በጽናት ይቀበሉ ዘንድ ለማደፋፈር፤ የፈተናን ትርጉም ለማስረዳትና በመስቀል ላይ ስለሰው
ልጆች መከራ የተቀበለውን መድኃኒታችንን አብነት እንዲያደርጉ ማመልከት ነው፡፡
 በእምነታቸው ጸንተው እንዲቆሙ ተግባራዊ የሆነ ክርስቲያናዊ ሕይወትን እንዲመሩ ማድረግ
 ሕያው የሆነ እምነትን ከሥራ ጋር ያለውን መንፈሳዊ አንድነት ማሳየት፡፡
 የአንዳንድ ኃጢአቶችን አደገኛነት መግለጥ፤ አንዳንዶች ቀለል አድርገው ተመልክተዋቸው እንዳይጠፉባቸው ማድረግ፡፡

ከቀኖና መጽሐፍት መቆጠሩ

ቊጥሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ የቀኖና መጽሐፍት ለመቆጠሩ ከሚያረጋግጡል ማስረጃዎች መካከል አንዱ በ 2 ተኛው
መቶ ክፍለ ዘመን ኦሪገን የቅዱስ ያዕቆብ መልእክት በማለት መጥቀሱ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ጸሐፊው ቅዱስ ያዕቆብ
እንደሆነ ከሚያረጋግጡልን ነገሮች መካከል፡-

የመልእክቱ አከፋፈል

ምዕራፍ 1፡- እምነት እና ፈተና


ምዕራፍ 2፡- እምነት እና ሥራ
ምዕራፍ 3፡- እምነት እና አንደበት
ምዕራፍ 4፡- እምነት እና የሥጋ ፍላጎት
ምዕራፍ 5:1-11፡- እምነት እና በሀብት ውስጥ ስለመዋጥ
ምዕራፍ 5:12-20፡- እምነትና አጠቃላይ ልንይዘው ስለሚገባን ነገሮች
7. የይሁዳ መልዕክት
የመልእክቱ ጸሐፊ

የመልእክቱ ጸሐፊ ቅዱስ ይሁዳ ሲሆን የቅዱስ ያዕቆብ ወንድም ነው፡፡ ይህ ያዕቆብ የኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ የነበረና የያዕቆብ መልእክትን የጻፈልን
ነው፡፡ የይሁዳ የጌታ ወንድም ተብሏል፡፡ የተባለበትም ምክንያት የእመቤታችን ጠባቂ የሆነው ቅዱስ ዮሴፍ ከሟች ሚስቱ የወለደው ስለሆነና እመቤታችን
ከጌታ ጋር ስላሳደገችው ነው፡፡ ይሁዳ መጀመሪያበጌታ አያምንም ነበር (ዮሐ 7፡3-5)፡፡ ነገር ግን ከጌታችን ትንሣኤ በኋላ የክርስቶስ ተከታይ ሆኗል፡፡ (ሰኔ
25 ስንክሳርን ተመለከት)
የተጻፈላቸው ሰዎች

በመልእክቱ መጀመሪያ ላይ ተቀባዮቹ ‹‹በእግዚአብሔር አብ ተወደው በኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ›› ስለሚል በየትኛውም ቦታ
ለሚገኙ ክርስቲያኖች እንዲያነቡአት የተጻፈች አጠቃላይ መልእክት ናት፡፡

የተጻፈበት ቦታና ዘመን

የይሁዳ መልእክት የተጻፈበት የት እንደሆነ የተመዘገበ ነገር የለም፡፡ የተጻፈበት ዘመንም የሁለተኛይቱ ጴጥሮስ መልእክት ከተጻፈች በኋላ ብዚም
46
ሳይቆይ እንደሆነ ብዙ ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ስለዚህም መልእክቱ በ 68 ዓ.ም ገደማ ተጽፋለች፡፡

የመልእክቱ ዓላማ

ሐሰተኞች መምህራን እየበዙ መሄዳቸውን፣ ስለዚህም ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንዲጋደሉ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የእነዚህ
ሐሰት መምህራን መገለጫዎች በናገር ከእነርሱ እንዲጠበቁ ነው፡፡

የመልእክቱ አከፋፈል

መልእክቱ አንድ ምዕራፍ ያለው ሲሆን ለ 7 ከፍለን እናጠናዋለን፡፡

ሰላምታ (ከቁጥር 1-2)


ስለ እምነት መጋደል እንደሚገባ (ከቁጥር 3-4)
ሐሰተኞች ስለሚደርስባቸው ቅጣት የተሰጠ ምሳሌ (ከቁጥር 5-7)

46
ይህም የተባለበት ምክንያት ቅዱስ ይሁዳ ሲጽፍ ከሁለተኛው የጴጥሮስ መልእክት ይጠቅሳልና ነው፡፡ (ይሁ 1፡18 እና 2 ኛ ጴጥ 3፡21)

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 130


የሐሰተኞች መምህራን መገለጫዎች (ከቁጥር 8-13)
ስለነዚህ የሐሰት መምህራን የተነገረ ትንቢት (ከቁጥር 13-20)
ስለ መንፈሳዊ ሕይወት የተሰጠ ትምህርትና ሌሎችን ከሐሰት ትምህርት እንዲጠብቁ (ከቁጥር 20-24)
ይሁዳ ለእግዚአብሔር ያቀረበው ሰላምታ (ቁጥር 25 )
የትንቢት ክፍል

የቅዱስ ዮሐንስ ራእይ


በግእዝ ራእዩ ለዮሐንስ አቡቀለምሲሰ በአማርኛ የዮሐንስ ራእይ በግሪኩ አፖካሊፕሲስ በእንግሊዝኛ ሪቨሌሽን ተብሎ
ይጠራል የግሪኩ ቃል ትርጉም መግልጥ፣ትሸሸገውን ማሳወቅ ማለት ነው፡፡ይህ መጽሐፍ የዮሐንስ ራዕይ ተብሎ ሊጠራ
የቻለው ዮሐንስ ስለ መጨረሻው ዘመን ያያቸውን ራዕይ ስለያዘ ነው፡፡
ዮሐንስ ለቄሳር ድምጥያኖስ ሀውልት የሚሰግዱትን በመቃወሙ በንጉሡ ትእዛዝ ወደ ፍጥሞ ደሴት ተጋዘ፡፡ ፍጥሞ
ከታናሿ እስያ አምስት ማይል ርቀት ላይ የምትገኝ የኤጅያን ባህር ደሴት ናት፤ በሮማውያን ዘመን ደሴቷ አምልኮ ጣዖትን
አንቀበልም ያሉ ሁሉ የሚጋዙበት ቦታ ነበረች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በፍጥሞ ደሴት በጠባብ ዋሻ ውስጥ ለሰባት ዓመታት
(ከ 98-96) ዓ.ም ያህል ለግዞት ተቀምጦ ራዕዩን ባየበት ጊዜ እንዲህ ብለህ ጻፍ አለኝ እያለ ያየውን ራዕይ ጽፎታል፡፡
አረማውያን በዮሐንስ ላይ ጥላቻ አድሮባቸው ነበር፤ ንጉሡ ታማኝ የጦር አለቃው በከዳው ጊዜ በዮሐንስ ላይ
ያላቸውን ጥላቻ ለመወጣት መንገድ አገኙ በትምህርቱ የተነሣ በአረማውያን ተከሶ በድምጥያኖስ ፊት ቀረበ፤ እርሱም በፈላ
ውኃ ከተሞላ በርሜል ውስጥ ካሰቃየው በኋላ በፍጥሞ ደሴት አጋዘው፡፡
የዮሐንስ ራዕይ ጸሐፊ አራተኛውን ወንጌል የጻፈው ዮሐንስ ወንጌላዊ ነው፤ ለዚህም ማስረጃ
የሚሆነው በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሔር በግ እና የእግዚአብሔር ቃል
ብሎ ጠርቶታል፡፡ /ዮሐ 1፡ 1፣ ዮሐ 14፡29/ በዮሐንስ ራዕይ ውስጥም ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ቃል
ተብሎ ተጠርቷል፡፡ /ራዕ 15፡6፣ 12፡7፣ 10፡17፣ 14፡1፣ 19፡13/ ፡፡
የመጽሐፉ ዓላማ
 ወደ ፊት ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር እግዚአብሔር ለባርያዎቹ ያሳውቅ ዘንድ ስለፈቀደ ነው፡፡ /ራዕ 1፡
1፣22፡6-7/
 ብዙዎች የፋርስ ነገሥታት የሰሩትን የአርጤም ጣዖት በማምለካቸው ሁሉንም ሊያስተምር
 መላዕክት (አለቃዎቹ) ተብለው ለተጠሩ በታናሿ እስያ ከተሞች ለሾማቸው ሰባት ሊቃነ ጳጳሳት
በቤተክርስቲያን መልካም አስተዳደርና ሕይወት ዙሪያ ለመምከር
 የክርስቲያኖችን ሰማያዊ ሕይወትና የመላዕክትን፣ የጻድቃንና የሰማዕታትን ክብር ለማሳየት ጽፏል፡፡
 የጥጦስን፣ የሐሳዊ መሲህን፣ የምጽዋትን፣ የመንግስተ ሰማያትን ነገር የገለጸለት እግዚአብሔር ጻፍ ብሎት
መሆኑን ለማስረዳት ጽፏል፡፡
ዮሐንስ ራዕይ የተጻፈበት ቦታ በፍጥሞ ደሴት ነው፤ ይህቺ ቦታ በሮማ መንግስት ላይ ያመፁ ሰዎች
የሚታሰሩባት ልምላሜ የማይታይባት ደረቅና ድንጋያማ የሆነች ምድረ በዳ ቦታ ነበረች፡፡ ዮሐንስ ከ 81-96
ዓ.ም በነገሠው በድምጥያኖስ (በዶምታያን) ዘመን ንጉሡ እንዲሰግድለት በኤፌሶን ያቆመውን ምስል
በመቃወም በዚህች ደሴት ታስሯል፤ ስለዚህ ዮሐንስ ራዕይ የተጻፈበት ዘመን ጌታ ባረገ በ 9 ኛው ዓመት
ወይም በ 96 ዓ.ም ገደማ እንደሆነ ይነገራል፡፡
የዮሐንስ ራዕይ አጠቃላይ የመጽሐፉ አከፋፈል እና አከፋፈል
የዮሐንስ ራዕይ ይዘቱም ትንቢት ነው፤ ትንቢቶቹም በዮሐንስ ዘመን ስላለውና ወደፊት ስለሚሆነው ነገር
የሚገልጡ ናቸው፤ ትንቢቶቹም የተገለጡት በራዕይ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ 22 ምዕራፍ ሲኖረው በ 8 ዓበይት
ክፍል ከፍለን እናየዋለን፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 131


ራዕ 1-3፡ ለሰባቱ አብያተ ክርስትያናት ስለተጻፉት መልእክታት እንዲሁም ትንቢቱን ከማን እንደተቀበለ
ይገልጣል፡፡
ራዕ 4-5፡ በሰማያት ስለሚሆኑ ነገሮች የመጀመሪያ ገለፃ፣ ዮሐንስ በሰማይ በተከፈተ ደጅ ውስጥ ያየው
ራዕይ
ራዕ 6-11፡ ስለ ሰባቱ ማህተሞችና ሰባቱ መልእክቶች
ራዕ 12-13፡ ስለ ዘንዶው፣ ስለ አውሬውና ስለ ሐሰተኛ ነቢያት
ራዕ 14፡ በሰማያት ስለሚሆኑ ነገሮች ሁለተኛ ገለፃ
ራዕ 15-16፡ ስለ ሰባቱ ጽዋዎች ራዕይ
ራዕ 17-19፡ ስለ ባቢሎን መፍረስ
ራዕ 20-22፡ የክርስቶስን መምጣት የሚገልጽ ራዕይ፣ ስለ እግዚአብሔር መንግስት፣ በራዕይ ውስጥ ያሉት
ቃሎች የታመኑና እውነተኛ እንደሆኑ፣ ራዕዩን ያየውና የሰማው ዮሐንስ መሆኑን፣ ጌታ በቶሎ
እንደሚመጣ የዮሐንስ ናፍቆት፣ የዮሐንስ ቃለ ቡራኬ /ራዕ 22፡21/
የሥርዓት መጻሕፍት
ሥርዓት የሚለው ቃል ሠርዐ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም አሠራር፣ ሕግ፣ ደንብ፣
መርሐ ግብር ማለት ነው፡፡ ይህ ሲባል የመንፈሳዊው አገልግሎት ሕግና ደንብ ወጥቶለት የአሠራር ሒደቱ
የተስተካከለ መነሻና መድረሻ ያለው እንዲሁም ሊጠበቅ እንክብካቤ ሊደረግለት፣ ለትውልድም ሊተላለፍ
የሚችል የሥራ መመርያ ማለት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሥርዓት መናገር ወይም ማስተማር የጀመረው በዘመነ ሐዲስ የሥርዓት መጻሕፍት
ሲጻፍ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም መላው የብሉይና የሐዲስ ቅዱሳት መጻሕፍት አስፍተው አምልተው
ተናግረውታል እንጂ፡፡ ከሌሎች ሕጎችና ደንቦች የሚለየው በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም
የተመሠረተች ቅድስት ቤተክርስቲያን አምልኮቷን የምትፈጽምበት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ራሱ የተቀደሰና
የተከበረ፤ ሌላውንም ፈጻሚውን አካል የሚያከብር፣ የሚቀድስ፣ ጸጋ መንፈስ ቅዱስም የሚያሰጥ ቅዱስ
ሥርዓት መሆኑ ነው፡፡
አምላካችን እግዚአብሔርም ያለ ሥርዓት እንዲሁ የፈጠረውና የሠራው ሥራ የለም፡፡ የሥነ ፍጥረትን
የአፈጣጠር ታሪክ እንኳን ብንመለከት በነቢብ፣ በገቢር፣ በሐሊዮ የተፈጠሩት ሁሉ ሥርዓት፣ ልክና መጠን፣
መርሐ ግብር፣ የአሠራር ዓይነትና ቅርጽ፣ የጊዜ ቅደም ተከተል፣…ወዘተ አላቸው፡፡
ሐዋርያው ቅዱሰ ጳውሎስም ለተሰሎንቄ ምዕመናን በላከው መልእክቱ ‹‹ያለ ሥርዓት የሚሔዱትን
ገስ...ቸው፡፡›› /1 ኛ ተሰ 5፡14/ ‹‹ወንድሞች ሆይ፣ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ
ወንድም ትለዩ ዘንድ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እለምናችኋለው›› 2 ኛ ተሰ 3፡6 በማለት
አጥብቆ ለምኖናል አዞናልም፡፡
የሥርዓት ዓላማ
የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ዋና ዓላማ ቤተክርስቲያን በሰላም እንድትጓዝ ማድረግ በመሆኑ በየጊዜው
ለሚነሱ የቤተክርስቲያን ጉዳዮችና ችግሮች እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ላይ አድሮ በሠራው
ሥርዓት እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የቤተክርስቲያን አካላት በመጠቀም ትእዛዘ እግዚአብሔርን ማክበር ነው፡፡
ሥርዓትን ማን መሠረታት?

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 132


በዘመነ ኦሪት እግዚአብሔር አምላክ በሙሴ ላይ አድሮ ሥርዓትን ሠርቶልናል፡፡ በሐዲስ ኪዳንም ራሱ
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ አልዓዛር ሥርዓተ ቊርባንን፣ በጌቴሴማኒና
በተራራው ስብከቱ ላይነ ሥርዓተ ጸሎትን፣ ስግደትን፣ ጾምን፣ ምጽዋትን አስተምሮ መሥርቶልናል፡፡
የሥርዓት አስፈላጊነት
 ‹‹ሁሉ በአግባብ እና በሥርዓት ይሁን›› 1 ኛ ቆሮ 14፡40 እንደ ተባለ ለዓለማዊውም ሆነ ለመንፈሳዊ
ሕይወታችን ክንውን ሥርዓት ያስፈልጋል፡፡
 ለእግዚአብሔር ተገዢ መሆናችንን ለመግለጽ /ሚል 3፡7-10/
 አንድ አሳቢና አንድ ልብ ለመሆን አንድ ዓይነት ሥርዓት ያስፈልጋል፡፡ ኤፌ 4፡13፣ ሐዋ 4፡32፣ ሮሜ 15፡
5-6
 ቤተክርስቲያን በሰላም እንድትጓዝ ለማድረግ
 የሃይማኖት ምስጢራትን በአግባቡ ለመፈጸም
ሥርዓትን ባንጠብቅ ምን እንሆናለን ?
ሥርዓትን መጠበቅና በሥርዓት መኖር አስፈላጊ እንደሆነና መንፈሳዊ ግዴታም እንዳለብን ዋነኛው
የሥርዓት ምንጭ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡
 ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ‹‹ከሥርዓትህ የሚርቁትን አጎሳቆልካቸው›› በማለት ከሥርዓት የተለየ
ሰው ማንኛውም ሕይወቱ የተጎሳቆለ እንደሆነ ነግሮናል፡፡ መዝ 118፡118
 ነቢየ እግዚአብሔርረ ኢሳይያስም ‹‹…..ምድርም ከሚቀመጡባት በታች ረክሳለች ሕጉን
ተላልፈዋልና ሥርዓቱንም ለውጠዋልና የዘላለሙንም ቃልኪዳን አፍርሰዋልና፡፡ ስለዚህ መርገም
ምድርን ትበላለች በእርስዋም የተቀመጡ ይቀጣሉ፤ስለዚህ የምድር ሰዎች ይቃጠላሉ፣ ጥቂት
ሰዎችም ይቀራሉ፡፡›› ኢሳ 24፡5-6 በማለት ሕግና ሥርዓትን ባንጠብቅ የሚመጣብንን በማስረዳት
ከዚያ እንድንጠነቀቅ ይመክረናል፡፡
የሥርዓት መጻሕፍት
የቅድስት ቤተክርስቲያናችን የሥርዓት መጻሕፍት በሐዋርያት ቅዱስ ሲኖዶስ የተደነገጉ ናቸው፡፡ ሲኖዶስ
ማለት ስብሰባ ማለት ነው፤ ይህም ሐዋርያት ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገትና ርደተ
ጸጋ መንፈስ ቅዱስ በኋላ ተሰብስበው የሠሯቸው የደነገጓቸው ቀኖናት ናቸው፡፡
በመጻሕፍት ጥራዝ ራሳቸውን ችለው ከ 81 ቀኖና ቅዱሳት መጻሕፍት የተመዘገቡ የሥርዓት መጻሕፍት
ስምንት ሲሆኑ ከምንጠቀምበት መጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ራሳቸውን ችለው በተለያዩ አድባራትና ታላላቅ
ገዳማት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ምንጮች
የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዕለት ተዕለት መንፈሳዊ አገልግሎት የምትፈጽምበት
የሥርዓተ ቤተክርስቲያን መጻሕፍት እንዳሏት ከላይ ተገልጧል፤ የእነዚህም መጻሕፍት ምንጮች 6 ሲሆኑ
ዝርዝራቸው እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
1. የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት
2. የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 133


3. የሊቃውንት መጻሕፍት
4. ቀኖናተ አበው
5. የሥርዓት መጻሕፍት
6. የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ
መጻሕፍቱ የተጻፉበት ቋንቋ
ስምንቱ የሥርዓት መጻሕፍት የተጻፉበት ቋንቋ ሱርስት (የሶርያ ቋንቋ) ሲሆን አንዳንድ ሊቃውንት ደግሞ
በጽርዕ (የግሪክ ቋንቋ) እንደተጻፉ ይናገራሉ፡፡ በኋላ የተነሱ ሊቃውንት የሱርስቱና የጽርዑን ቋንቋ መሠረት
በማድረግ ወደ ላቲን፣ ግእዝ፣ አማርኛ፣ እንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ፣… ወዘተ ቋንቋዎች ተርጉመውታል፡፡
ስምንቱ የሥርዓት መጻሕፍት በሰማንያ አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተካተው ያልተጠረዙት ስለምንድነው?
አንደኛ መጠናቸው ተለቅ ያለ በመሆኑ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ ለአያያዝ አመቺ
ባለመሆናቸው
ምዕመናን ሊረዱት የማይችሉትን ሊያዩት የማይገባ ክህነት ላላቸው ሰዎች ብቻ የሚረዳ
ጥልቅ ምስጢርን በመያዙ ከቤተመቅደስ ውጪ በሁሉም ሰው ዘንድ እንዳይገቡ ሆነዋል፡፡
የሥርዓት መጻሕፍት አከፋፈል
ከሠላሳ አምስቱ የሐዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት ሐዋርያት ለቀለሜንጦስ ስምንት ያህሉን ቆጥረውና
መርጠው ለቅዱስ ቀለሜንጦስ እንዳስረከቡት መጻሕፍት ተባብረውበታል፡፡ እነዚህ መጻሕፍትም በ 3 ዐበይት
ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም፡
1. መጽሐፈ ድድስቅልያና አራቱ መጻሕፍተ ሲኖዶሳት /ትእዛዝ፣ ግፅው፣ አብጥሊስ፣ ሥርዓተ ጽዮን/
 እነዚህ መጻሕፍት በቤተክርስቲያን አመሠራረት፣ አወቃቀር፣ አጠቃላይ የአገልግሎት ሥርዓትና
ትምህርት ክፍል የሚያተኩሩ ናቸው፡፡ ሐዋርያት በየጊዜው በመንፈስቅዱስ መሪነት እየተሰበሰቡ
የሠሯቸው፣ የደነገጓቸው፣ ያዘጋጇቸው እጅግ ጠቃሚ የሆኑ መጻሕፍት ናቸው፡፡
2. ሁለቱ ኪዳናት /መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊና ካልዕ/
 ጌታ ከትንሣኤው በፊት የሠራቸው ሥራዎች፣ ያደረጋቸው ተአምራት እንዲሁም ልዩ ልዩ ተግባራት
ወንጌል ሲባል ከትንሣኤው እስከ ዕርገቱ ባሉት 40 ቀናት ያደረገው ሁሉ ደግሞ ኪዳን ይባላል፡፡ ይህም
በሁለት የኪዳን መጻሕፍት ተዘጋጅቶ ቤተክርስቲያን በጧት፣ በሰርክ፣ በሌሊት፣ በሁሉም ሰዓታት
ለአገልግሎት እግዚአብሔርን በማመስገን እየተጠቀመችባቸው ይገኛሉ፡፡
3. መጽሐፈ ቀለሜንጦስ
 በሮም ኤጲስቆጶሥነት ተሹሞ የነበረው የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀመዝሙር የሆነው ቅዱስ ቀለሜንጦስ
የጻፈው መጽሐፍ ሲሆን ፊሊ 4፡3፤ ስለ ራሱና ስለ ምዕመናን በሥርዓት መጓዝ እንዳለባቸው በሰፊው
ይተነትናል፡፡ በአጠቃላይ አገልጋዮች አበው ነቢያትን፣ ሐዋርያትንና አርድዕትን… ወዘተ የሚመለከት
ክፍል ነው፡፡
የእነዚህን የሥርዓት መጻሕፍት አከፋፈል ከተመለከትን ስለ መጻሕፍቱ ምንነትና ዝርዝር ይዘታቸው ቀጥለን
እንመለከታለን፡፡
1. መጽሐፈ ትእዛዝ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 134


ትእዛዝ ማለት በቁሙ ከሥራ አስቀድሞ የሚሰጥ፣ የሚጸናና የሚነገር ሕግ፣ ሥርዓት ወይም አድርግ
አታድርግ የሚል ፈቃድና ደንብ ነው፡፡
መጽሐፉን ቅዱሳን ሐዋርያት በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢየሩሳሌም ጽፈውታል፤ ይኸውም ቅዱሳን
ሐዋርያት በቀለሜንጦስ እጅ ለአሕዛብ ሕገ ቤተክርስቲያንን ለማሳወቅ እንደጻፉት ይነገራል፡፡ የዚህ መጽሐፍ
ልዩ ምልክቱ ወይም በአሕፅሮተ ቃል ልዩ መጠሪያው ‹‹ረሰጠብ›› በመባል ይታወታል፡፡
ትእዛዝ ሲኖዶስ 82 አንቀጾች ሲኖሩት እነዚህም ስለ ሲመተ መላእክት፣ ስለ ሊቃነ ጳጳሳት ሥርዓተ
ሲመት አተገባበር፣ ስለ መሥዋዕት አቀራረብ፣ ስለ ዐሥራት፣ መባዕ፣ ሥርዓተ ቊርባን፣ ሥርዓተ ጥምቀት፣
ጸሎት፣ የሰንበት አከባበር፣ ስለ ንዋየ ቅድሳት ክብር የሚናገር መጽሐፍ ነው፡፡
የመጽሐፈ ትእዛዝ አንቀጾች የመጽሐፉ አከፋፈል

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 135


ረስጠብ 1፣2፡- ስለ ሊቃነ ጳጳሳት አጠቃላይ ረስጠብ 51፡- የካህናትን አርአያነትና አንዱ ካህን
ሥርዓት ያወገዘውን ሌላው ካህን መፍታት
ረስጠብ 3፡- ስለ መሥዋዕትና የመሥዋዕት እንደማይችል
አቀራረብ ሥርዓት ረስጠብ 53፡- ተሹሞ የማያስተምርና
ረስጠብ 4፡- ስለ ምስጢረ ጥምቀትና ሥርዓተ የማያስተዳድር ካህን ስለሚሰጠው ትምህርት፣
ጥምቀት በተለይም ማንኛውም ተጠማቂ ምክርና ተግሣጽ
በሃይማኖት ከተለዩ ከተወገዙ ሰዎች ቢጠመቅ ረስጠብ 54፡- የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ
ክርስቲያን ሊሆን እንደማይችል የተቸገሩትን መርዳት እንደሚገባው
ረስጠብ 7፡- ጸሎተ ፍትሐት እንዲገባ ረስጠብ 57፡- ወላጆች ልጆቻቸውን በሃይማኖት
ረስጠብ 8፡- ስለ ሊቃነ ጳጳሳት ሥርዓተ ሲመት ለማይመስሏቸው ማጋባት
ረስጠብ 9፡- ሥልጣነ ክህነትን ስለ መጠበቅ እንደሌለባቸው
ረስጠብ 10፡- ካህናትን ማቃለልና መሳደብ ረስጠብ 61፡- በአውሬ የተበላውንና የሞተውን
እንደማይገባ የእንስሳ ሥጋ መብላት እንደማይገባ
ረስጠብ 11፡- የዲያቆናትና የቀሳውስት የሥልጣነ ረስጠብ 62፡- ከቀዳም ሥዑር በስተቀር
ክህነት መቀበያ ጊዜ ቅዳሜና እሑድን መጾም እንደማይገባ
ረስጠብ 13፡-ሁለት ያገባ ካህን ሆኖ መሾም ረስጠብ 68፡- በቤተክርስቲያን የጸሎት ጊዜ
እንደማይገባው የሊቀ ጳጳሳትን ስም መጥራት እንደሚገባ
ረስጠብ 17፡- ጠጉራቸውን ስለሚላጩ ሴቶች ረስጠብ 69፡- ስለ ሊቃነ ጳጳሳት ሥርዓተ ቀብር
የተሰጠ ምክር አፈጻጸም
ረስጠብ 18፡- ወደ ዓለም ስለሚገቡ መነኮሳት ረስጠብ 73፡- ያለ ራሳቸው ፈቃድ ልጆችን
ንስሐ፣ ምክርና ተግሣጽ ማጋባት እንደማይገባ
ረስጠብ 19፡- ግብረ ሰዶም ስለሚፈጽሙ ሰዎች ረስጠብ 81፡- ስለ መነኮሳትና ካህናት የአለባበስ
ንስሐ ስለመስጠት ሥርዓት
ረስጠብ 20፡- መናፍቃን ወደ ቤተክርስቲያን ረስጠብ 82፡- በዝሙት የወደቀ ካህን ከሥልጣኑ
ከመመለሳቸው በፊት ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደሚሻር
ማንበብና መማር እንደሚገባቸው
ረስጠብ 21፡- ለቅዱሳን ሰማዕታት መታሰቢያ
እንደሚገባቸው
ረስጠብ 22፡- ምዕመናን ከጠንቋዮችና
ከአስማተኞች ጋር መተባበር እንደማይገባቸው
ረስጠብ 25፡- ልጅ ወልደው በድብቅ
ስለሚገድሉ ዘማውያን ሴቶች
ረስጠብ 28፡- ወደ ቤተክርስቲያን የገባውንና
የተቀደሰውን ንዋየ ቅዱሳት እንደገና ወደ
ውጪ አውጥቶ ለሥጋዊ አገልግሎት ማዋል
እንደማይገባ
ረስጠብ 30፡- ስለ ምስጢረ ቊርባን
ረስጠብ 33፡- ክርስቲያን ከጣዖት አምልኮ
የተለየ መሆን እንደሚገባው
ረስጠብ 34-36፡- አንድ መናፍቅ ወደ እምነቱ
ሲመለስ ስለሚፈጸምለት ሥርዓት
ረስጠብ 42፡- በስካርና በዘፈን ለሚገኝ ካህን
ስለሚሰጠው ምክርና ስንብት
ረስጠብ 45፡- ስለ ሥጋወደሙ ክብርና
አስፈላጊነት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 136


2. መጽሐፈ ግጽው
ግጽው ማለት በቁሙ የታየ፣ የተገለጠ፣ ጉልሕ ማለት ነው፡፡ ሐዋርያት ለቀለሜንጦስ የሰጡት ሁለተኛ
መጽሐፍ ነው፡፡ የዚህ መጽሐፍ መሪ ምልክት ‹‹ረሰጠጅ›› በመባል እንደሚታወቅ ፍትሐ ነገሥት ይናገራል፡፡
መጽሐፉ የእግዚአብሔርን ሕልውና በማስረዳት ጀምሮ ስለ ምስጢረ ሥጋዌ፣ ጌታችን በኢየሩሳሌም
ስለማስተማሩና ስለሠራቸው ሥራዎች፣ ስለ ሲመተ ክህነትና ስለ ሕዝባውያን ተልዕኮ፣ ስለ ትሕትና፣ ስለ
10 ቱ ቃላት፣ ስለ ዐሥራት፣ ስለ ሰንበት፣ ስለ ሙታን ተዝካር፣ ስለ ቊርባን እና ጋብቻ በዝርዝር ያስረዳል፡፡
መጽሐፉ 57 አንቀጾች ሲኖሩት ከዚህ በመቀጠል የከፊል አንቀጾቹን የመጽሐፉ አከፋፈል እንመለከታለን፡፡
የመጽሐፈ ግጽው ከፊል አንቀጾች ዝርዝር
ረስጠጅ 30፡ ስለ መሥዋዕትና አቀራረቡ ይዘረዝራል፡፡
ረስጠጅ 34፡ ጥምቀት በውኃ የሆነበትን ምስጢር፣ የሐዲስ አማንያንን አጠማመቅ ሥርዓት፣
በተጨማሪም ወንድ ሴትን፣ ሴት ወንድን ክርስትና የማያነሳ መሆኑን በሰፈው ያስተምራል፡፡
ረስጠጅ 44፡ ያላመኑ ሰዎች (ለጥምቀት ያልደረሱ አረማውያን ወይም ንዑሰ ክርስቲያን) ሥጋወደሙ
እንዳይቀበሉ ያዛል፡፡
ረስጠጅ 46፡ ሥጋ ወደሙን ለመቀበል 18 ሰዓት ከምግብ መከልከል ወይም መጾም እንዲገባ ያስረዳል፡፡
3. መጽሐፈ አብጥሊስ
አብጥሊስ ማለት ሐዋርያውያን ቀኖናት ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ቀለሜንጦስ በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን
ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት የቅዱስ ሲኖዶስ ድንጋጌዎችን እንደጻፈ ይነገራል፡፡ ይህ መጽሐፍ ሰማንያ አንዱን
ቅዱሳት መጻሕፍት በዝርዝር ይገልጣል፡፡ የአብጥሊስ መለያ መጠሪያው ወይም መሪ ምልክቱ ‹‹ረሰጠአ››
ወይም ‹‹ረሰጠ›› በመባል ይታወቃል፡፡ መጽሐፉ ስለ ኤጲስ ቆጶሳት፣ ስለ ካህናት፣ ስለ ዲያቆናትና ምዕመናን
አጠቃላይ የሥራ ድርሻና መንፈሳዊ ሕይወት፣ በስፋትም ስለ ምስጢረ ንስሐ አስጣጥና አተገባበር
የሚያስረዳና የትምህርተ ሃይማኖትን እና የሥርዓተ ቤተክርስቲያንን አስፈላጊነትና ምንነት የሚያትት ነው፡፡
የመጽሐፈ አብጥሊስ የመጽሐፉ አከፋፈል

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 137


ረስጠ 3፡- ለእግዚአብሔር ንጹሕና የተለየ ረስጠ 54፡- ኤጲስ ቆጰስ ድሆችን መርዳት
መሥዋዕት ማቅረብ እንደሚገባ እንዳለበት
ረስጠ 4፡- ዐሥራት በኩራት፣ ቀዳማይት ረስጠ 57፡- ከሥጋዊ ፍርሃትና ጊዜያዊ
ማውጣት እንደሚገባ ጥቅም የተነሣ ሃይማኖትን መካድ
ረስጠ 7፡- ቀዳስያን ካህናት ሥጋ ወደሙን እንደማይገባ
ሳይቀበሉ ማቀበል እንደማይገባቸው ረስጠ 58፡- ካህናት አውሬ የነከሰውንና
ረስጠ 8፡- ምዕመናን ቤተክርስቲያን የሞተውን እንስሳ ሥጋ መብላት
ገብተው ሥርዓተ ቅዳሴውን መከታተል እንደሌለባቸው
እንደሚገባቸው ረስጠ 59፡- በዕለተ ሰንበት ጾም መጾምም
ረስጠ 9-10፡- ምዕመናን በካህናት ተወግዘው ማጾምም እንደማይገባ
ከተለዩ ሰዎች ጋር መነጋገር ረስጠ 64፡- በቤተክርስቲያን የተደነገጉ
እንደሌለባቸው ዐበይት አጽዋማትን መጾም እንደሚገባ
ረስጠ 13፡- ካህናት የቤተክርስቲያንን ረስጠ 66፡- ከቤተክርስቲያን ውጪ ለሆኑ
አገልግሎት ትተው ለሥጋዊ ጥቅም ሌላ የማምለኪያ ቦታዎች መባዕ መላክ
ቦታ መሄድ እንደሌለባቸው እንደማይገባ
ረስጠ 20፡- አንድ ሰው በፈቃዱ ራሱን ረስጠ 71፡- አንድ ካህን ሹመቱን (ሥልጣኑን)
ጃንደረባ ቢያደርግ ራሱን ገድሏልና ሊሾም ለማንም ማውረስ እንደማይችል
እንደማይገባው ረስጠ 72፡- የአካል ጉድለት (አንካሳነት፣
ረስጠ 27፡- ሥልጣነ ክህነትን በገንዘብ ዓይነ ሥውርነት) ከሹመት
መቀበል እንደማይገባ እንደማያስከለክል
ረስጠ 30፡- አንዱ ኤጲስ ቆጶስ የሻረውን ረስጠ 73-74፡- ዕብድ፣ ጋኔን ያለበት፣
ካህን ሌላው ኤጲስ ቆጶስ መመለስ የማይሰማ ሰው ለሹመት እንደማይበቃ
እንደማይችል ረስጠ 75፡- አንድ ሰው ከአረማዊነት ወደ
ረስጠ 33፡- ኤጲስ ቆጶስ በመማለጃ ሥልጣነ ክርስትና ከተመለሰ በኋላ ሥነ ምግባሩ
ክህነትን መስጥ እንደማይገባው መልካም ካልሆነ ሥልጣነ ክህነት
ረስጠ 35፡- ስለ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደማይሰጠው
ረስጠ 38-39፡- የኤጲስ ቆጰስ ሀብት ረስጠ 80፡- የቅዱሳት መጻሕፍት ቊጥር 81
ከቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድሳት ጋር ስለመሆናቸው … ወዘተ የሚሉትን ዐበይት
መደባለቅ እንደማይገባ ነገሮች ያስገነዝባል፡፡
ረስጠ 40፡- በሥርዓተ ቊርባን ከመናፍቃን
ጋር ኅብረት እንደሌለን
ረስጠ 43፡- ባልን ወይም ሚስትን መፍታት
በማያስችል ምክንያት መፍታት
እንደማይገባ
ረስጠ 44-45፡- ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ
እንደማይገባ
ረስጠ 48፡- ምዕመናን ከአመንዝሮችና
ከዘማውያን ኅብረት ስለመለየታቸው
ረስጠ 49-50፡- ካህናት በበደሉ ብዛት
የተለዩት ሰው ከቤተክርስቲያን እንደሚለይ
ረስጠ 51፡- መርዳት እነጂ በደካሞችና
በበሽተኞች መሳቅና መሳለቅ እንደማይገባ
ረስጠ 53፡- ኤጲስ ቆጶስ ሕዝቡን በሥርዓት
ማስተዳደር እንደሚጠበቅበት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 138


4. መጽሐፈ ሥርዓተ ጽዮን
ጽዮን ማለት አንባ፣ መጠጊያ ማለት ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ለቤተክርስቲያን ሥርዓት በማርቆስ እናት ቤት
ጽርሐ ጽዮን በተባለው ስፍራ በመጻፉ ምክንያት የተሰጠው ስያሜ ነው፡፡ የሥርዓተ ጽዮን መጽሐፍ
መጀመርያ የተጻፈበት ቋንቋ ጽርዕ ሲሆን በኋላ ወደ ዐረብኛና ወደ ግሪክ ቋንቋዎች ተተርጉሟል፡፡ የሥርዓተ
ጽዮን መሪ ምልክቱ ‹‹ዓይን›› ነው፡፡ መጽሐፉ ስለ ሥርዓተ ክህነት አገልግሎትና ምግባር፣ ስለ በዓለ
አስተርእዮ (ኤጲፋንያ)፣ ስለ በዓላትና ስለ አጽዋማት፣ ስለ ሰንበተ ክርስቲያን አከባበር፣ ስለ ገሃድ ፆም፣ ስለ
ቅዱሳን ክብር በሰፊው ይተነትናል፡፡
የሥርዓተ ጽዮን ቀኖናት የመጽሐፉ አከፋፈል
የሥርዓተ ጽዮን ቀኖናት የመጽሐፉ አከፋፈል በሦስት ልንከፍለው እንችላለን፡፡
1. የሥርዓተ ቅዳሴ ይዘት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 139


ቀኖና 1፡- ፊትን ወደ ምስራቅ አዙሮ ስለ
መጸለይ
ቀኖና 2-4፡- በዕለተ እሑድ፣ ረቡዕና ዓርብ
ስለሚደረግ ጸሎት
ቀኖና 8-9፡- ስለ በዓለ ልደትና በዓለ
ጥምቀት
ቀኖና 10፡- ስለ ዓቢይ ፆም
ቀኖና 11፡- ስለ በዓለ ዕርገት
ቀኖና 12፡- ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት
ቀኖና 21፡- ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት
መታሰቢያ
ቀኖና 22፡- ስለ ዘወትር ጸሎት
ቀኖና 30፡- ስለ ቅዱስ ቊርባን

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 140


2. የቤተክርስቲያን የአገልግሎት ሥርዓት ድንጋጌዎች
ቀኖና 5፡- ስለ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች መዓረጋት
ቀኖና 6፣13፡- ስለ ዲያቆናትና ካህናት አስፈላጊነት
3. የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ሥነ ጠባይዓት
ቀኖና 13፡- ስለ ሐሰተኛ ካህን የተሰጠ ትእዛዝ
ቀኖና 15፡- ስለ ካህናትና ምዕመናን ኮከብ ቆጠራ መከልከል
ቀኖና 14፣20፣23፣26፣29፡- ስለ ቤተክርስቲያን አባላት ሥነ ጠባይዓት
ቀኖና 27፣28፡- የቤተክርስቲያን መሪዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ክብርና የተለየ ቦታ
ይናገራል፡፡
5. መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ
ኪዳን ማለት በቁሙ ውል፣ ስምምነት፣ የፍቅር፣ የአንድነት መሐላ፣ ሰላማዊ ሕግ፣ ትምህርት፣
ምሥጋና፣ ሁለቱን ወገን አንድ የሚያደርግ ማለት ነው፡፡ ይህን የኪዳን ቃል የጠበቀ እንደ መላእክት ይኖራል፡፡
ከትንሣኤ በኋላ ስለምን ኪዳንን አስተማረ ቢሉ በመዋዕለ ሥጋዌው በፈቃዱ ለሰው ልጅ ድኅነት ወንጌልን
እንዳስተማረ ከተነሣ በኋላም በፈቃዱ ለሰው ልጅ ሕይወት ኪዳንን አስተምሯል፡፡
ይህን የመጀመሪያውን የጌታችንን የኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ፣ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ማቴዎስ
እንደጻፉት ይነገራል፡፡ መጽሐፉ ስለ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ የዘወትር ኪዳናት ፣ ትምህርተ ኅቡአት፣
እግዚአብሔር ብርሃናት፣ ቅዳሴ እግዚእ፣ በእንተ (ስለ) ቅድሳት የሚናገር መጽሐፍ ነው፡፡
የመጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ ይዘት ሥርዓተ ጸሎትና ሥርዓተ ቅዳሴ ነው፡፡ ይህም ጸሎተ ኪዳን ዘእግዚእ
እንዲጸለዩባቸው በተመደቡ ሦስት የኪዳን ጊዜያት /ጸሎተ ኪዳን ዘሠለስቱ ጊዜያት/ ተከፍለው የሚገኙ
ዘጠኝ ሥርዓታተ ጸሎታትን (ዘጠኙ ኪዳናት የሚባሉትን) ይዟል፡፡ እነርሱም፡-

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 141


1. ኪዳን ዘመንፈቀ ሌሊት (ሌሊት የሚደርስ
ኪዳን)
 ለከ እግዚኦ ለገባሬ ኩሉ
 አምላከ ብርሃን ወላዴ ሕይወት
 ንሤልስ ለከ ዘንተ ስብሐተ
2. ኪዳን ዘነግዕ (ጠዋት የሚደርስ ኪዳን)
 እግዚአብሔር አብ ወሀቤ ብርሃን
 እግዚኦ ኢየሱስ ክርስቶስ ስምዓነ ቅዱስ
 ንሤልስ ለከ ቅዱስ ስብሐተ
3. ኪዳን ዘሠርክ (ከምሽቱ 11 የሚደርስ ኪዳን)
 ለከ ለአብ ዘኢይማስን መድኃኔ ነፍሥነ
 ንዌድሰከ እግዚኦ
 ለከ ዘእምልብነ ናቸው፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 142


መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ 59 አንቀጾች ያሉት መጽሐፍ ሲሆን ዝርዝር ይዘታቸውንም እንደሚከተለው
ቀርቧል፡፡
የመጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ ዝርዝር አንቀጾች

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 143


አንቀጽ 1፡- ስለ መንፈስ ቅዱስ አንቀጽ 34-36፡- ስለ ምዕመናን ሹመትና
አንቀጽ 2፡- ስለ ኋለኛው ዘመን ሊደረግላቸው ስለሚገባ ጸሎት
አንቀጽ 3፡- በሰማያት ስላለው ነገር አንቀጽ 37፡- ስለ ጠዋት አገልግሎት
አንቀጽ 4፡- ስለተመረጡ ሰዎች አንቀጽ 38፡- ስለ ንፍቅ ዲያቆናት ሹመት
አንቀጽ 5፡- በሀገሮች ላይ ስለተነገረ ትንቢት አንቀጽ 40፡- መሾም ስለማይገባው ሰው
አንቀጽ 6፡- ስለ ሐሳዊ መሲሕ ትንቢት አንቀጽ 41፡- ስለ ሕዝባውያን
አንቀጽ 7፡- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ አንቀጽ 42፡- አገልጋዮችን ስለመቀበል
ክርስቶስ ለሐዋርያት ስላስተማራቸው አንቀጽ 43፡- ስለ ዘማውያን ስርዓተ ጥምቀት
ትምህርት አንቀጽ 44፡- ሰላምን ስለመቀበል
አንቀጽ 8፡- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ አንቀጽ 45፡- ሴቶች ራሳቸውን
ክርስቶስ ለማርያም፣ ለማርታና ለሰሎሜ ስለመከናነባቸው
ስለመ…….. አንቀጽ 46፡- ንዑሰ ክርስቲያንን ስለመባረክ
አንቀጽ 9፡- በሃይማኖትና በምግባር ስለሚጸኑ አንቀጽ 47-48፡- ንዑሰ ክርስቲያንን
ሰዎች በመከራቸው ጊዜ ስለመቀበል
አንቀጽ 10፡- ስለ ቤተክርስቲያን ቀኖና አንቀጽ 49፡- ስለ ሥርዓተ ጥምቀት
አንቀጽ 11፡- ስለ ጳጳሳት ሹመት አንቀጽ 50፡- ስለ ሜሮን አቀባብ
አንቀጽ 12፡- ስለ ጳጳሳት ሹመት የሚደረግ አንቀጽ 51፡- ስለ ምስጢረ ቊርባን
ሥርዓተ ጸሎት አንቀጽ 52፡- በበዓለ ሃምሳ ጾምና ስግደት
አንቀጽ 13፡- ኤጲስ ቆጶሳት ለጸሎትና እንደማይገባ
ለመሥዋዕት ስለሚያደርጉት ዝግጅት አንቀጽ 53፡- ከኤጲስ ቆጶሳት ጋር ስለሚጠሩ
አንቀጽ 14፡- በቤተክርስቲያን ስለሚያስተምሩ ሰዎች
ሰዎች አንቀጽ 54፡- ለቤተክርስቲያን መባ
አንቀጽ 15፡- በቤተክርስቲያን የተለያየ ስለሚያስገቡ ሰዎች
መቆሚያ ቦታ ስለመኖሩ አንቀጽ 55፡- ስለ ሙሽሮች ሥርዓት
አንቀጽ 16፡- ስለ ሥርዓተ ቊርባን አንቀጽ 56፡- ለበሽተኞች ስለሚፈጸም
አንቀጽ 17፡- ስለ ሥርዓተ ቅዳሴ ተግባር
አንቀጽ 18፡- ለበሽተኞች ስለሚደረግ ቅብዕ አንቀጽ 57፡- ስለ ሞተ ደሀ ሰው የሚደረግ
አንቀጽ 19፡- ስለ ማኅበር ምሥጋና ሥርዓተ ጸሎት
አንቀጽ 20፡- ስለ ትምህርተ ኅቡዓትና ኪዳን አንቀጽ 58፡- ሁልጊዜ ስለሚጸልዩ ሰዎች
አንቀጽ 21-24፡- ስለ ቀሳውስት ሹመትና ስለ አንቀጽ 59፡- ስለ ሥርዓተ ቊርባን
ሥርዓተ ጸሎት
አንቀጽ 25፡- የካህናትን ቃል ስለሚሰሙ
ሰዎች
አንቀጽ 26፡- ስለ ድኅነትና ስለ ጥፋት
አንቀጽ 27፡- በሽተኞች ስለሚጎበኙ ካህናት
አንቀጽ 28፡- ስለ ዲያቆናት ሹመት
አንቀጽ 29፡- ስለ ዲያቆናት መላላክና እንግዳ
መቀበል
አንቀጽ 30፡- ካህናት በቤተክርስቲያን ውስጥ
እንዴት መቆም እንዲገባቸው
አንቀጽ 31፡- ስለ ቤተክርስቲያን አገልግሎት
አንቀጽ 32፡- ከቤተክርስቲያን ውጪ
ስለሚቆሙ ሰዎች
አንቀጽ 33፡- ስለ ዲያቆናት አገልግሎት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 144


6. መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ
ይህ መጽሐፍ ሁለተኛው የጌታችን የኪዳን መጽሐፍ ሲሆን በአንቀጾች ያልተከፋፈለ ወጥ ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡
መጽሐፉ ከዮሐንስ ራእይ ጋር ብዙ ተመሳሳይነት አለው፡፡ ስለ ካህናት ሹመትና አገልግሎት፣ ስለ ንዑሰ ክርስቲያን ጥምቀትና
ምስጢረ ቊርባን እንዲሁም ስለ ሐሳዊ መሲህ (እኔ ክርስቶስ ነኝ ስለሚለው)፣ ስለ ጥጦስ የዘር ግንድ (አባቱ ከነገደ ኤሳው
እናቱ ከነገደ ዳን እንደሆነ ስለሚነገርለት)፣ ስለ ጌታችን ዳግም ምጽአት የሚናገር መጽሐፍ ነው፡፡
7. መጽሐፈ ዲድስቅልያ
ድድስቅልያ ማለት ትምህርት ማለት ሲሆን ሥያሜውንም ያገኘው ከያዘው ይዘት የተነሣ ነው፡፡ መጽሐፉ
ድድስቅልያ ዘቅዱሳን ሐዋርያት እየተባለም ይጠራል፡፡ ይህ መጽሐፍ 45 አንቀጾች የያዘ ሲሆን ብዙ ትምህርትና ተግሳጾችን
አካቶ ይዟል፡፡ እነዚህም፡ ስለ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሚፈጸሙ ልዩ ልዩ ምስጢራት፣
ስለ ሰው ልጅ ሕይወትና ሞት፣ ስለ ፍቅረ ሰብእና ፍቅረ እግዚአብሔር፣ ስለ ምስጢረ ጥምቀት፣ ስለ ጾምና ጸሎት፣ ስለ
ምስጢረ ቊርባን፣ ስለ ካህናት ክብርና አገልግሎት….ወዘተ ያትታል፡፡
መጽሐፈ ድድስቅልያ ዐበይትና ንዑሳን አንቀጾች አሉት፤ በእያንዳንዱ ዐቢይ አንቀጽ ብዙ የተለያዩ ንዑሳን ክፍሎች ይገኛሉ፡፡
የመጽሐፈ ድድስቅልያ ዐበይት አንቀጾች ዝርዝር

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 145


አንቀጽ 1፡- ስለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን አንቀጽ 26፡- ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን ዘፈን
ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ሳይሆን መዝሙር ማቅረብ እንደሚገባቸው
አንቀጽ 2፡- ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብና አንቀጽ 27፡- ክርስቲያን በጣዖትና በአጋንንት
መረዳት እንደሚገባ ስማቸውን ይጠሩና ይምሉ ዘንድ እንደማይገባ
አንቀጽ 3፡- የትዳር ጓደኞች መከባበር አንቀጽ 28፡- የበዓላትን ቀን በመንፈሳዊ ደስታ
እንዲገባቸው ማክበርና መጠበቅ እንዲገባ
አንቀጽ 4፡- የካህናት ክብርና አገልግሎት አንቀጽ 29፡- ሰሙነ ሕማማትንና የፋሲካ
አንቀጽ 5፡- ኤጲስ ቆጶሳት ነገረ ሠሪን መስማት በዓላትን ማክበር እንዲገባ
እንዳይገባቸው አንቀጽ 30፡- ወንጀለኞችና መናፍቃን
አንቀጽ 6፡- ካህናት በፍቅር በየውሃት ሆነው ካልተመለሱ መለየት እንዲገባ
ከኃጢአት ወደ ጽድቅ የሚመለሱትን ሰዎች አንቀጽ 31፡- ጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ
ንስሐቸውን መቀበል እንደሚገባቸው በቤተክርስቲያን ክርክርንና መለያየትን
አንቀጽ 7፡- አንድን ሰው መበደሉን ሳያረጋግጡ እንደሚፈጥር
መቅጣት እንደማይገባ አንቀጽ 32፡- ሐዋርያት ያስተማሩትን የአንድነት
አንቀጽ 8፡- ምዕመናን ለቤተክርስቲያን መባ የሦስትነት ትምህርተ ሃይማኖት መማር
ማቅረብ እንዲገባቸው እንደሚገባ
አንቀጽ 9፡- ዲያቆናት ለካህናትና ለኤጲስ ቆጶሳት አንቀጽ 33፡- ለሞቱ ሰዎች መጸለይ እንደሚገባ
መታዘዝ እንዲገባቸው አንቀጽ 34፡- የሞትና የሕይወትን ጎዳና መለየት
አንቀጽ 10፡- ኤጲስ ቆጶሳት መንፈሳዊ ዕውቀትና እንዲገባ
ጥበብ ሊኖራቸው እንዲገባ አንቀጽ 35፡- ስለ ሜሮን አስፈላጊነት
አንቀጽ 11፡- ቂም በቀል መያዝ እንዲገባ አንቀጽ 36፡- ስለ ቤተክርስቲያንና ስለ ሠራዊተ
አንቀጽ 12፡- ክርስቲያን መዝፈንና ወደ ዘፈን ቦታ መላዕክት አገልግሎት
መሄድ እንዳይገባው አንቀጽ 37፡- ሰንበትን ሲያከብሩ ቅዱሳት
አንቀጽ 13፡- ባል የሌላቸው ባልቴቶች መጻሕፍትን ማንበብ እንደሚገባ
ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ማበርከት አንቀጽ 38፡- ይጠመቁ ዘንድ ስለሚወዱ ንዑስ
እንዳለባቸው ክርስቲየን
አንቀጽ 14፡- ሴቶች ማጥመቅ እንዳይገባቸው አንቀጽ 39፡- በውኃ ላይ ስለሚደረገው ጸሎት
አንቀጽ 15፡- ሥልጣነ ክህነት የሌላቸው የክህነትን አንቀጽ 41፡- አዲስ አማንያን ሲጠመቁ ጸሎት
ሥራ እንደማይሠሩ እንደሚገባ
አንቀጽ 16፡- ባልን ወይም ሚስትን ያለ ምክንያት አንቀጽ 42፡- በሐዋርያትሥልጣን ስለተሾሙ
መፍታት እንደማይገባ ኤጲስ ቆጶሳት
አንቀጽ 17፡- አባትና እናት ስለሞቱባቸው ሰዎች
አንቀጽ 18፡- ኤጲስ ቆጶሳት አባት እናት
ስለሞቱባቸው ልጆች ማዘንና መርዳት
እንደሚገባቸው
አንቀጽ 19፡- ባል የሞተባት ሴት በሃይማኖትና
በትዕግስት መቀበል እንደሚገባት
አንቀጽ 20፡- ኤጲስ ቆጶስ መባ ከማን መቀበል
እንደሚገባው ስለመረዳቱ
አንቀጽ 21፡- ወላጆች ልጆቻቸውን መምከርና
መገሰጽ እንዲገባቸው
አንቀጽ 22፡- ስለ ፋሲካ አከባበርና ስለ ዐበይት
በዓላት ክብር እንደሚገባ
አንቀጽ 25፡- ለቅዱሳን ሰማዕታት ክብር እንዲገባ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 146


8. መጽሐፈ ቀለሜንጦስ
ይህ መጽሐፍ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውና ቅዱስ
ቀለሜንጦስ ከእርሱ አግኝቶ የጻፈው ነው፡፡ የመጽሐፉ አከፋፈል ሥርዓተ ቅዳሴያዊና ቀኖናዊ ቅርጽ ያለው ሲሆን፤ ሥርዓተ
ቅዳሴያዊ ቅርጹን አስመልክቶ ስለ ጽላተ ኪዳን ቡራኬ ማለትም በኤጲስ ቆጶስ አዲስ ቤተመቅደስ የሚባረክበትን ሥርዓት፣
ሥርዓተ ጥምቀትንና በእጅ መንሻ ጥምቀት እንደማይፈቀድ፣ ስለ ሥርዓተ ቊርባን፣ …. ወዘተ ይናገራል፡፡ በቀኖናዊ ክፍሉም
ስለ ሰማዕታትና ስለ ክብረ በዓላት፣ ስለ ሰንበተ ክርስቲያን የዕረፍት ቀን መሆንና በሰሙነ ሕማማት ምዕመናን ከተግባረ ሥጋ
ማረፍ ግዴታ ስለመሆኑ ያትታል፡፡
የቅዱስ ቀሌምንጦስ መጽሐፍ በአሕጽሮተ ቃል ልዩ መጠሪያው ‹‹ጴጥ›› ሱሆን ትርጉሙም ጴጥሮስ ማለት ነው፡፡
የዚህ ቅዱስ አባት ስሙ በሕይወት መጽሐፍ እንደጻፈ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ገልጽዋል፡፡ (ፊል 4፡3)
መጽሐፉ ከአዳም ጀምሮ ያሉትን ታላላቅ አባቶች በመዘርዘር ስለ ገነትና ከገነት መጥተው ደብር ቅዱስ ስለገቡ ሰዎች
ሁናቴ፣ ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ ስለሚደረገው የቤተክርስቲያን ሥርዓት በማተት እንዲሁም ቅዱስ ቀሌምንጦስ ስላየው
ራዕይና አጠቃላይ አገልግሎት ይናገራል፡፡ በትውፊት ቅዱስ ቀሌምንጦስ የሮማ 3 ኛ ጳጳስ መሆኑ ይነገራል፡፡
መጽሐፈ ቀሌምንጦስ በስምንት ዐበይት ክፍሎች የሚከፈል ሲሆን ክፍሎቹ በከፊል እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 147


ክፍል 1፡- ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ደግሞ ለቀሌምንጦስ ይህን ሰማያዊ ሥርዓት
ክርስቶስ ካረገ በኋላ ሐዋርያትን እስከ ዓለም ዳርቻ እንዳስተማረው
ድረስ እንዲያስተምሩ እንደላካቸው
ሙሴ እንደ ሊቀ ጳጳሳት ሆኖ አሮንና ልጆቹን
ቤተክርስቲያን በሐዋርያት ትምህርት ላይ ስለመሾሙ
እንደተመሠረተች
ቅዱስ ጴጥሮስ ለቀሌምንጦስ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን
ከአዳም ጀምሮ ስላለው አጠቃላይ የዘር ሐረግ እንዳስተማረው
ስለገነትና ስለ ታላላቅ አባቶች የቀረበ ሰላምታ ስለሙሴና ስለጴጥሮስ ንጽጽራዊ ትምህርት
(ምሥጋና)
በክርስቶስ የሚያምን የክርስቶስን ሥራ እንደሚሠራ
ከገነት ወጥተው ወደ ደብር ቅዱስ ስለገቡ ሰዎች ሁናቴ
ቅዱሳን ሐዋርያት ድውያንን ስለመፈወሳቸው
ክፍል 2፡- ቅዱስ ቀሌምንጦስ የቅዱስ ጴጥሮስ
ደቀመዝሙር ሆኖ ስለመመረጡ ንጽሕና በረከት ለመቀበልም ለመስጠትም አስፈላጊ
እንደሆነ
ስለ ቀሌምንጦስ ሕይወትና አጠቃላይ ኑሮው
ጌታችን ራሱን ለቤተክርስቲያን መሥዋዕት አድርጎ
የቀሌምንጦስ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳቀረበ ይናገራል፡፡
ክፍል 3፡- ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የጌታችንን ክፍል 7፡- ስለ ክርስቶስ አምላክነትና አዳኝነት
ማንነትና ለሐዋርያት ያደረገውንና ያስተማረውን ሁሉ
በቀሌምንጦስ እንደነገረው ስለ ዲያቢሎስ ክፋትና ሽንፈቱ

በአገልግሎት እንዲጸና እንደመከረው ስለ ሙሴ በትርና ስለ ክርስቶስ መስቀል ምሳሌነት

ክፍል 4፡- እግዚአብሔር ለቅዱስ ጴጥሮስ ስላሳየው ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት አስተምህሮት


ራዕይና ተአምራት ኖኅ መርከብ እንዲሠራ ስለመታዘዙ ይናገራል፡፡
ስለ ሥልጣነ ክህነት ከጳጳሳት እስከ ዲያቆናት ክፍል 8፡- ቅዱስ ጴጥሮስ ስለ ንስሐ አስፈላጊነት ያየውና
አጀማመርና አሰጣጥ ያስተማረው
ስለ ዓለም አፈጣጠርና ሁናቴ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ብፁዕ ስለመባሉ
ስለ ዳግም ምጽአት እንዲሁም ስለጻድቃንና ኃጥአን ቤተክርስቲያን በቅዱስ ጴጥሮስ የቃል መሠረትነት
ሁናቴ እንደምትሠራ
ስለ መንፈስ ቅዱስ ጸጋ መውረድና ሁሉን ቅዱስ ጴጥሮስ የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ ስለመቀበሉ
እንደሚገልጥላቸው ይናገራል፡፡ ….ወዘተ ይናገራል፡፡
ክፍል 5፡- በሰው ልጆች፣ በሰማይና በምድር ላይ
ስለሚሆነው ነገር ሁሉ ቅዱስ ጴጥሮስ ለቀሌምንጦስ
እንደነገረው
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም
ስለመወለዱ፣ ወደ ግብጽ ስለመሰደዱ፣ ግብጽንና
በዙሪያዋ ያሉ አውራጃዎችን ከአምልኮ ጣዓታት ነጻ
ስለማድረጉ፣ ወደ ገሊላ ስለመግባቱ ይናገራሉ፡፡
ክፍል 6፡- እግዚአብሔር ለሙሴ የነገረው ሥርዓተ
ደብተራ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንደተነገረው ቅዱስ ጴጥሮስ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 148


ማጠቃለያ
በአጠቃላይ ስምንቱ የሐዲስ ኪዳን የሥርዓት መጻሕፍት ይዘታቸው በትምህርት፣ በትንቢት በይበልጥም በሥርዓተ
ቤተክርስቲያን ላይ ያተኩራል፡፡ እነዚህ የሥርዓት መጻሕፍት በተለያዩ ሀገሮች በተለያዩ ቋንቋዎች ተጽፈው የሚገኙ ቢሆንም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብዙዎቹ ተጽፈው የሚገኙት በግእዝ ቋንቋ ነው፤ የሚገኙትም በታላላቅ
ገዳማትና ጥንታዊያን አድባራት ነው፡፡ በጽሑፉ እንደተገለጠው የሁሉም የሥርዓት መጻሕፍት አጠቃላይ ዝርዝር ይዘታቸው
አልተሟላም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት መጽሐፍቱ የሚገኙባቸው ቦታዎች ውስንነት የቦታ ርቀትና ምስጢር አዘል
መሆናቸው ነው፡፡
ከመጻሕፍቱ ብዙዎቹ በአንቀጾች የተከፋፈሉና ለእያንዳንዳቸው መሪ ምልክት ወይም ልዩ መጠሪያ እንዳላቸው ሊቃውንት
ይናገራሉ፤ መጻሕፍትም ያረጋግጣሉ፡፡ ከዚህ በመቀጠል ለመጻሕፍቱ ልዩ መጠሪያ ስለሆኑት ቃላት ትርጉምና አንቀጽ በሰንጠረዥ
እንመለከታለን፡፡

ተ. የመጽሐፉ ስም መሪ ምልክት

የመሪ ምልክቱ ትርጉም አንቀጽ
1 ትእዛዝ ረስጠብ ‹‹ረስ››- ሩሱል ከሚለው ዐረብኛ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም 72
ሐዋርያት ማለት ነው፡፡
‹‹ጠ››- የቅዱስ ቀሌምንጦስን ስም በማሳጠር የመጣ ነው፡፡
አንድም ተጥላሳት የሚለውን የዐረብኛ ቃል በማሳጠር
የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም ቀኖናተ ትእዛዛት ማለት ነው፡፡
‹‹አ››- በግብጻውያን የአኃዝ (ቊጥር) የአቆጣጠር ሥርዓት
አንደኛ፣ ቀዳማዊ ማለት ነው፡፡
2 ግጽው ረስጠጅ ‹‹ረስጠ›› የሚለው ከላይ ተገልጧል፤ ‹‹ጅ›› ደግሞ በግብጻውያን 57
የአኃዝ አቆጣጠር ‹‹ሦስተኛ›› ማለት ነው፡፡
3 አብጥሊስ ረስጠብ ‹‹ብ›› በግብጻውያን የአኃዝ አቆጣጠር ‹‹ሁለተኛ›› ማለት ነው፡፡ 82
4 ሥርዓተ ጽዮን ዓይን ‹‹ዓ››- የሚለው ቃል ከጽርሕ ‹‹ይን›› ደግሞ ከጽዮን ከጽርሐ 30
ጽዮን ሥርዓተ ጽዮን (ዓይን) እንደተገኘ ይነገራል፡፡ በሌላም
በኩል ዓይን ሐዋርያት ከተሰበሰቡበት ቦታ የጽርሐ ጽዮን ሰገነት
የመጀመሪያው ፊደል ነው ይባላል፡፡
5 መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ -/…. ኪዳን 59

6 መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ -/….. ኪዳን የለውም


7 ድድስቅልያ ድስቅ 43
8 ቀሌምንጦስ ቀሌ/ጴጥ ‹‹ቀሌ››- የቀሌምንጦስን ‹‹ጴጥ››- የጴጥሮስን ስም በመውሰድ 8 ክፍል
ቅዱስ ጴጥሮስ ለቀሌምንጦስ እየነገረው የጻፈው መሆኑን
ያስረዳል
ምዕራፍ ዐራት

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 149


የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን ግንኙነት (ተወራራሽነት)

ቀደም ባሉት ክፍሎች እንደተማርነው ኪዳን ማለት በተለያዩ ወገኖች መካከል የሚደረግ ውል፣
ስምምነትና መሐላ እንደሆነ ተገንዝበናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ ከፈጠረው በኋላ አስቀድሞ
ሕግ በመስጠት ኋላም ምንም እንኳን ሕጉን ቢያፈርስ የሰውን ኃጢአትና በደል ሳይመለከት እንደ ቸርነቱ
ብዛት እንደገና ውሉን በማደስ ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሣ መሐላ እንደሚምልልን፣ ቃል እንደሚገባልን፣
በተለያየ ዘመንም የተለያዩ ቃልኪዳን እንደሰጠን ተመልክተናል፡፡
ነገር ግን በዘመናችን አንዳንድ መናፍቃን ቅዱሳት መጻሕፍት እርስ በእርስ ይጣላሉ፣ ይጣረሳሉ
በማለት ያላዋቂ ሲናገሩ ይደመጣሉ፤ ይህ ችግር ከምን እንደሚመጣ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በወንጌል ‹‹መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል ባለማወቃችሁ ትስታላችሁ›› በማለት
አስረድቷል፡፡
ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም መጻሕፍትን ባለማወቃቸው እንደሚስቱ እየተናገረች ትክክለኛውን
ርቱዕ የሆነውን መንገድ በማሳየት ምዕመኗን በተገቢው መንገድ ታስተምራለች፡፡ በመሆኑም ከዚህ በመቀጠል
እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ቅዱሳት መጻሕፍት እርስ በእርሳቸው የማይጣሉና የማይጣረሱ
ይልቁንም ተወራራሽና ተዛማጅ መሆናቸውን እንመለከታለን፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት እርስ በእርሳቸው ይጣላሉን?


መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በተለያዩ ቅዱሳት አባቶች፣ በተለያየ ዘመንና ቦታ እንደሆነ ቀደም ብለን
ተመልክተናል፡፡ ይሁንና ሁሉም በውስጡ የተካተቱ መጻሕፍት ሲጻፉ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለጸሐፍቱ
ምስጢሩን ጥበቡን ገልጦላቸው፣ በመንፈስ ቅዱስ ድህንፃም እየተቃኙ በመሆኑ እርስ በእርሳቸው የተሳሰሩና
አንድ እውነታን ብቻ የሚገልጹ ናቸው፡፡
የሁለቱም ኪዳናት አስገኝ እግዚአብሔር በመሆኑ ዓላማቸው አንድ ነው፡፡ መጽሐፉም ከሌሎች
መጻሕፍት በተለየ ቅዱስ የተባለውን ቅጥያ ያገኘው የተለያዩ መጻሕፍት ስብስብ ቢሆንም መልእክቱ ግን
ያልተዛባ ቀጥተኛና የአንዱ አሳብ ከሌላው ጋር የሚስማማና የሚገናኝ በመሆኑ ነው፡፡
ጌታችንም በዮሐንስ ወንጌል ‹‹እናንተ በመጻሕፍት የዘለዓለም ሕይወት ያላችሁ ይመስላችኋልና
እነርሱን ትመረምራላችሁ፡፡ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፡፡ ሙሴንም ብታምኑ እኔን ባመናችሁ
ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፏልና መጽሐፉን ካላመናችሁ ግን ቃሌን እንዴት ታምናላችሁ›› በማለት ዘለዓለማዊ
አንድነትና ግንኙነት እንዳላቸው ገልጧል፡፡ ከትንቢተ ኢሳይያስ ስለሠራው አስቀድሞ የተጻፈውን
ከሚያምኑት መጽሐፍ ገልጾ ካነበበ በኋላ በናዝሬት ሌላ ምኩራብ ለተሰበሰቡት ‹‹ዛሬ ይህ መጽሐፍ
በጆሮአችሁ ተፈጸመ፡፡›› በማለት ብሉይ ኪዳን የሐዲስ ኪዳን ትንቢት፣ ጥሬ ንባብ፣ አማናዊ ምሳሌ፣ መነሻ
ሐዲስ ኪዳን ደግሞ ፍጻሜ፣ ትርጓሜ፣ መድረሻ መሆኑን አስረድቷቸዋል፡፡
ሐዋርያትም ጌታችንን አብነት በማድረግ ከብሉይ ኪዳን እየጠቀሱ አስተምረዋል፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ
መልእክታት በተለይም ወደ ሮሜ ሰዎችና ወደ ዕብራውያን ሰዎች በጻፈው መልእክቱ በብዛት ብሉይ ኪዳንን
እየጠቀሰ ሐዲስ ኪዳንን አስተምሯል፡፡ ስለዚህ የሐዋርያት ትምህርት የብሉይ ኪዳን ትርጓሜ ነው፡፡
በመሆኑም በብሉይም በሐዲስም የተገለጸው የእግዚአብሔር ቃል የማይወለጥ የማይሻር መሆኑን
በአምላካዊ ቃሉ መስክሯል፡፡ ሉቃ 16፡17፣ ዮሐ 10፡35 ብሉይን ከሐዲስ ሐዲስን ከብሉይ ብናመሰክር የሚጋጭ፣
የሚጣረስ ቃል ፈጽሞ የለውም፡፡ የተለያዩና የተቃረኑ ቢሆኑ ኖሮ ኦሪቱን መጀመሪያውኑ አይሠራውም ነበር፤
ኋላም ኦሪትን የሠራው ራሱ እግዚአብሔር ሆኖ በምድር ሲገለጥ አይፈጽመውም ነበር፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 150


ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በእርሱ ይጣላል የሚሉ ሰዎች በመንፈስቅዱስ ምስጢር ገላጭነት
ሳይሆን እንደራሳቸው ፈቃድ የሚተረጉሙ ግብዞች ደፋሮችና አላዋቂዎች ናቸው እንጂ ቅዱሳት መጻሕፍት
ፈጽሞ የማይጣሉ ወጥ የሆኑ የሕያው የእግዚአብሔር ቃል የያዙ ክቡራን መጻሕፍት ናቸው፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት እርስ በእርስ የማይጣሉ ስለ መሆናቸው ከዚህ በመቀጠል ብሉያት ከብሉያት፣
ከሐዲሳት ሐዲሳት እንዲሁም በንባብ የተጣሉ የሚመስሉ ትርጓሜያቸው አንድ እንደሆነና ሁሉም
የተስማሙ መሆናቸውን አንድ በአንድ ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
1. የብሉያት መጻሕፍት እርስ በእርሳቸው የማይጣሉ ስለመሆናቸው
መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ሰዎች ሊረዱትና ሊገባቸው በሚችለው በሰዎች አእምሯዊ አቅም መጠን
ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህንን እንኳን ለመረዳት ገጸ ንባቡን ብቻ ይዘን መጓዝ እንደሌለብን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
ስለሆነም አገናዝቦና አስተውሎ አመሳክሮ ባይሆንም ሊቃውንትን ጠይቆ በትሕትና መረዳት ይገባል፡፡ በንባብ
የተጣሉ የሚመስሉትን በትርጓሜ ማስታረቅ እንደሚገባም ለመረጃ ያህል የተወሰኑትን እንመልከት፡-
እግዚአብሔር ሰውን በምድርላይ በመፍጠሩ ሀሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፣
ተጸጸተ፡፡ ዘፍ 6፡7 ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅአይደለም ዘኁ 23፡19

ዕጣናችሁ በእኔ ፊት አጸያፊ ነው፡፡ ኢሳ 58 ጸሎቴን እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ፡፡ መዝ 140፡2

በሰው እጅ ከምንወድቅ በእግዚአብሔር እጅ ሰውን ፈርተን በገሀነም ከምንወድቅ እግዚአብሔር


ብንወድቅ ይሻለናል፡፡ ሲራ 2፡18 ፈርተን /በዓላውያን በሰው እጅ/ ብንወድቅ ይሻለናል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ገጸ ንባባቸው የተጣላ ቢመስልም ዓይነ ልቡናውን
እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ያበራለት ሰው ትርጉማቸው አንድ እንደሆነ በእርግጠኝነት ይረዳል፡፡
የመጀመሪያውን ጥቅስ ስንመለከት ሁለቱም የብሉይ ኪዳን ጥቅሶች የሚሳማሙበት ምስጢር ወይም ቁም
ነገር እግዚአብሔር አይጸጸትም በሚለው ነው፡፡ ነገር ግን ለእኛ በሚገባን መንገድ የሰዎችን ኃጢአትና የበደል
ክብደት መጠኑ ከልክ ያለፈ መሆኑንና እግዚአብሔር የሚጸጸት አምላክ ቢሆን ኖሮ ሥራችን የሚያጸጽት
መሆኑን ለማሳየት ሲል ‹‹ተጸጸተ›› ብሏል፤ እንጂ አምላካችን እግዚአብሔር በባሕርይ የነበረውን፣ ያለውን፣
ወደ ፊት የሚሆነውን የሚያውቅ ስለሆነ በሥራው አይጸጸትም፡፡
ወደ ሁለተኛውም ስንመጣ በአንድ በኩል ዕጣንን በንጽጽር አቅርቦ ‹‹ጸሎቴን እንደ ዕጣን
ተቀበለልኝ›› በሌላም በኩል ‹‹ዕጣናችሁ በእኔ ፊት አጸያፊ ነው›› ሲል ተናግሯል፡፡ የዚህ ምስጢሩና ችግሩ
ከዕጣኑ ንጽሕናና ርኩሰት ጋር የተያያዘ ሳይሆን ከአቅራቢዎቹ ሕይወት ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ችግሩ የዕጣኑ ሆኖ
ቢሆን ኖሮ ጸሎቴን እንደ ዕጣን ተቀበለልኝ ብሎ ነቢዩ ባልጸለየም ነበር፡፡ ሰብአ ሰገልም ከአመኃዎቻቸው
መካካል ዕጣን ይዘው ወደ አምላካቸው ባልቀረቡ ነበር፡፡ ስለዚህ የአድራጊውን ሕይወት ከተደራጊው፣
መሥዋዕቱን ከመሥዋዕት አቅራቢው ሕይወት ለይቶ ማየት እንጂ በጭፍኑ መሥዋዕቱንም መሥዋዕት
አቅራቢውንም ከተነገረለት የመልእክቱ ይዘት ውጪ መተርጎም ተገቢ አይደለም፡፡
እንደዚሁም ሦስተኛው ላይ የተጠቀሱት ኃይለ ቃሎች በትርጓሜ ሲፈቱ የመጀመሪያው በዚህ ዓለም
ሎሌ ሆኖ ለሰው ሲገዙ ከመኖር በገዳም ውስጥ ለእግዚአብሔር በመገዛት ብዙ ትርፍ ማትረፍ እንደሚችል

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 151


ሲናገር በአንጻሩ ደግሞ ሰውን ፈርተን በገሀነም ከምንወድቅ እግዚአብሔርን ፈርተን በዓላውያን እጅ
ብንወድቅ እንደሚሻል ለማጠየቅ ነው፡፡
2. ብሉይና ሐዲስ እርስ በእርስ የማይጣሉ ስለ መሆናቸው
ብሉይ ሐዲስ

እስራኤል ሆይ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ


እግዚአብሔር ነው፡፡ ዘዳ 6፡4 ደቀመዛሙርቴ አድርጓቸው፡፡ ማቴ 28፡19

ሰማይ ዙፋኔ ነው…ምን ዓይነት ቤት ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፡፡ ማቴ 21፡13


ትሠሩልኛላችሁ? ኢሳ 66፡1

እንደቀደሙት ምንባባት ሁሉ በዚህ ክፍል ያሉት የብሉይና የሐዲስ ኪዳን ጥቅሶች በደፈናው
ስንመለከታቸው ልዩነት ያላቸው ይመስላል፡፡ ነገር ግን በምስጢረ እግዚአብሔር አንድ ናቸው፡፡
የመጀመሪያውን ብንመለከት ዘመነ ብለይ ዕውቀት ያልሰፋበት፣ ኃጢአት የበዛበት ዘመን በመሆኑ
ሕዝቡ ሊሰማው የሚገባው ስም አንድ እግዚአብሔር የሚል መሆን ነበረበት፤ ምክንያቱም የብዙ ጣዖታት
አምልኮዎችን ለመከላከል እና የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት ስም ለእስራኤላውያን የመገለጫ ጊዜው
ስላልነበረ (ገና ስላልጸኑ) ‹‹አምላክህ እግዚአብሔር አንድ ነው›› በሚል ተቀምጧል፡፡
ወደ ዘመነ ሐዲስ ስንመጣ ደግሞ አምልኮ ጣዖታት የጠፋበት፣ ስመ እግዚአብሔር በአንድነትና
በሦስትነት በግልጥ የታየበት፣ ለሰዎች የታወቀበትና የተገለጠበት ዘመን በመሆኑ አንድ እግዚአብሔር
የሚለው ምስጢር ሳይፋለስ፣ ሳይጨመርና ሳይከለስ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በሚለው ተገልጧል፡፡
በመሆኑም እግዚአብሔር የሚለው ስም ቀድሞም አሁንም ወደፊትም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ
እግዚአብሔር ተብሎ ይታመናል፡፡ /ዮሐ 1፡1/
ሁለተኛው ጋር ስንመጣ ‹‹ሰማይ ዙፋኔ ፣ ምድር የእግሬ መረገጫ ናት፣ ምን አይነት ቤት
ትሠሩልኛላችሁ›› ብሉ የተናገረ እግዚአብሔር በሐዲስ ኪዳን በመዋዕለ ሥጋዌው ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት
ትባላለች፣ እናንተ ግን የሽፍቶች ቤት አደረጋችኋት›› እያለ ቤተ መቅደሱን ሲያጸዳና ሲባርክ ፈቅዶም
ሲቀበል እናገኛለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ በመለኮታዊ ባሕርዩ የማይጠቀለል፣ የማይወሰን፣ የማይገደብ መሆኑን
ሲያስተምር፤ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ደግሞ ምእመናን ተሰባስበው ቃለ እግዚአብሔርን የሚማማሩበት
ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ የሚፈተትበት የሚቀዳበት እርሱም በረድኤት የሚገኝበት ቤተመቅደስ
እንደሚያስፈልጋቸው ያስተምራል፡፡ በመሆኑም የባሕርይ መለኮቱን ርቀትና ጥልቀት እየተረዳን ነገር ግን
ስሙን የምንቀድስበትና የምንጠራበት የተለየና የተቀደሰ ቦታ እንደሚያሰፈልግ መገንዘብ ያሻል፡፡
3. የሐዲሳት መጻሕፍት እርስ በእርስ የማይጣሉ ስለመሆናቸው
ሐዲስ ሐዲስ
እኔና አብ አንድ ነን፡፡ ዮሐ 10፣ 30 ከእኔ አብ ይበልጣል ዮሐ 14፣28

ቃልም እግዚአብሔር ነበር፡፡ (ዮሐ 1፡1) የሐዲስ ኪዳን መካካለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ
ክርስቶስ (ዕብ 12፡24)
እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 152


ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር
አልቆጠረውም፡፡ (ፊሊ 2፡6)
እኔ ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ ስለ እርሱም ሊያማልድ በሕይወት ይናራልና፡፡
አይደለሁም፡፡ ዮሐ 16፡26 ዕብ 7፡25

ከእኔ ጋር የነበሩትም ብርሃኑን አይተው ደነገጡ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሰዎች ድምፅ እየሰሙ
የሚናገረኝን አልሰሙም (ሐዋ 22፡9-7) ማንንም ሳያዩ ተደንቀው ቆሙ፡፡ ሐዋ 9፡7

በመጀመሪያው የወንጌል ክፍል ‹‹እኔና አብ አንድ ነን›› ሲል በመለኮት፣ በአገዛዝ፣ በሥልጣን፣ ይህን
ዓለም በመፍጠር በመመገብ በማሳለፍ በእግዚአብሔርነት አንድ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ ‹‹አብ ከእኔ
ይበልጣል›› ሲል ደግሞ የአብና የመንፈስ ቅዱስ ቃል ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በምስጢረ ሥጋዌው ሥጋን በመዋሐዱ በመራቡ፣ በመጠማቱ፣ በመሞቱ፣ በመነሣቱ አብን ከእኔ ይበልጣል
ብሏል፤ ምክንያቱም ወልድ በምስጢረ ሥጋዌው የተቀበላቸው የማዳን ሥራዎች እግዚአብሔር አብ
በመለኮታዊ ባሕርዩ ሊቀበላቸው አይችልምና አብ ከእኔ ይበልጣል አለ እንጂ ክብር ይግባውና ጌታችን
በመለኮት ከአብ ያነሰ ሆኖ አይደለም፤ ስለዚህ በመለኮት አንድ ሲሆን በምስጢረ ሥጋዌ ወልድ በተለየ አካሉ
በለበሰው (በተዋሐደው) ሥጋ ‹‹ከመላዕክት እንኳ ጥቂት አሳነስከው›› እንደተባለ ከተዋረደ አብ ከእኔ
ይበልጣል ቢል የንባብ እንጂ የምስጢር ተፋልሶ የለውም፡፡
በሌላ ምስጢር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ቃልም እግዚአብሔር ነበረ›› ብሎ ጽፏል፡፡ ሐዋርያው
ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መስተካከልን መቀማት
እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም ካለ በኋላ በሌላው መጽሐፉ የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ ጽፏል፡፡ ይህም
ትርጓሜው ከላይ ከተገለጠው ጋር አንድ ነው፡፡ ምክንያቱም በመጀመሪያ እግዚአብሔር ነበረ ሲል መለኮታዊ
ባሕሪውን፣ የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ ሲል ደግሞ ፍጽም ሰው ፍጽም አምላክ ከማለቱ በስተቀር
በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል ያለ ትንሽ (ዝቅተኛ) አምላክ ነው ማለት አይደለም፤ ይህ ፍፁም የተሳሳተ
አስተሳሰብና ክህደት ነው፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን እንደ አምላክነቱ ሥጋዌን እነደ ምሥጢረ ሥጋዌ
አምኖ መቀበል ያስፈልጋል፡፡
ሦስተኛው ጥቅስ ጋር ስንመጣ እግዚአብሔር ወልድ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ከሐዋርያት ሊለይ ሲል የነገራቸው ምስጢር ‹‹ከእንግዲህ ስለ እናንተ
አብን የምለምን አይደለሁም›› የሚል ሲሆን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ‹‹ስለ እኛ ዘወትር
ሊያማልድ ይኖራ›› ብሎ ጽፏል፤ ጌታችን ለሐዋርያት የገለጠው በነቢያት የተናገረው፣ በሱባኤ የተቆጠረው
የማዳን ሥራ የተፈጸመ መሆኑን ነው፤ ሐዋርያው የገለጠው ደግሞ ይህ የድህነት ሥራ በሌላ ዘመን በሌላ
ኪዳን የማይተካና የማይሻሻል ለዘለዓለም የድኅነት በር የመንግሥተ ሰማያት መንገድ ሆኖ እስከ ዕለተ
ምጽአት ድረስ እንደሚቀጥልና እንደ ኦሪት ሥርዓት የማይሻሻል የማይለወጥ ኪዳን መሆኑን አረጋግጦ ጻፈልን
እንጂ ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ነው ለማለት ተፈልጎ
አይደለም፡፡ ይህንን በምሳሌ ለመረዳት አንድ ካህን በቅዳሴ ሰዓት ቀዳሲ ዲያቆን ጠፍቶ ለዚያን ዕለት እንደ
ቢያገለግሉ ከቅዳሴ ሲወጡ ካህንነታቸው ተሽሮ ዲያቆን እገሌ አይባሉም፡፡ ጌታችንም ሰው ሁሉ በበደለ እና
ሁሉም በኃጢአት ተይዞ በነበረበት ጊዜ ሰው ሆኖ መጥቶ በሥጋው በፈፀመው የቤዛነት ሥራ ከራሱ ጋር
አስታርቆናል፤ ይህ ማለት ግን ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታቸን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁልጊዜ አማላጅ ነው
ማለት አይደለም፡፡ እርሱም ቢሆን በገዛ ቃሉ ‹‹ተፈፀመ›› በማለት በመስቀል ተሰቅሎ የቤዛነቱን ሥራ
አስታውቆናል፡፡ ‹‹እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም›› በማለትም አስረግጦ
ገልጦልናል፡፡ ዮሐ 16፡26

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 153


በመሆኑም ቃለ እግዚአብሔርን በእግዚአብሔር መንፈስ እንጂ ንባቡን እንደገዛ ፈቃዳችን በመተርጎም
ወደ ስሕተት ጎዳና ማምራት የለብንም፤ በተገቢው መልኩ ብንረዳው፣ ብናውቀውና ብናምንበትም
እንጠቀምበታለን እንድንበታለንም፡፡
4. የብለይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን ተወራራሽነት
ሁለቱ ኪዳናት ምግብና (ተመጋጋቢነት)፣ ሽግግር አላቸው፤ ይህም ማለት እግዚአብሔር በዘመነ ብሉይ
የተሰጡ ሕግጋትንና ትእዛዛትን እንዲሁም ሥርዓቶችን የሠራው በዚያን ዘመን ከነበሩ ሰዎች የመረዳትና
የመፈፀም አቅም አንጻር ነው፡፡ ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ዘመን የተሠሩት ለሐዲስ ኪዳን እንደ መድረሻ ናቸው፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ገላትያ ምዕመናን በላከው መልእክቱ ‹‹ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ
ሞግዚታችን ሆኗል›› በማለት ገላ 3፡24 ላይ ገልጽዋል፡፡ ሕፃን ልጅ እስኪያድግ ድረስ ሞግዚት ያስፈልገዋል፤
ካደገ በኋላ ግን ሞግዚት አይፈልግም፡፡ የኦሪት ሕግም አስቀድም ሕዝቡን ለማጽናናት አምልኮ እግዚአብሔርን
ለማለማመድ የተሰጠ፣ የተዘጋጀ ነው፤ ከመጀመሪያው ወንጌል ቢሠራና ቢነገር ኖሮ ለመፈጸም ይከብደና
ያዳግት ስለነበር አይፈጽሙትም ነበር፡፡ በብሉይ የተነገረውና የተሠራው ኋላ በወንጌል ለሚታዘዘውና
ለሚሠራው ሕሊናዊና አምልኮታዊ ዝግጅትና ልምምድ ነበር፡፡ ለምሳሌ፡ በወንጌል ‹‹ጠላትህን ውደድ››
ተብሏል፤ ጠላትን መውደድ ከመጀመር በፊት ግን ወዳጅን መውደድ ያስፈልጋል፡፡ ጌታችንም ‹‹ባልንጀራህን
ውደድ ጠላትህን ጥላ እንደተባለ ሰምታችኋል፣ እኔ ግን እላችኋለው ጠላቶቻችሁን ውደዱ›› በማለት ያ
ዘመን አልፏል ብሎ ሌላ የበለጠ የፍጽምነት ዘመን መምጣቱን ያሳያል፡፡
በሌላ በኩል አስቀድሞ በትንቢትና በተምሳሌት ሳይናገር እንዲሁ ዘመኑ ሲደርስ በሐዲስ ኪዳን
ቢፈጽመው ኖሮ አማናዊነቱን (እውነተኛነቱን) ለመቀበል በከበደ ነበር፡፡ ለሌሎች ሐሳውያንም በር ይከፍት
ነበር፡፡ ጌታችን የተወለደበት ቦታ፣ መጠመቁ፣ ማስተማሩ፣ የሚያደርገው ተአምር …. ወዘተ ከመነሻ እስከ
መድረሻ በብዙ ነቢያት በተለያየ መልኩ በትንቢትና በምሳሌ ሲነገር ቆይቷል፡፡ እንዲያ ባይናገር ኖሮ እውነት
የአምላክን ሰው መሆን ከመሬት ተነስቶ ለማመን ይከብድ ነበር፡፡
በመሆኑም ብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በሐዲስ ኪዳን ጊዜው ደርሶ ከመፈጸሙ በፊት በትንቢት
አናግሮ ሳለ ሲፈጸም እውነት መሆኑ በሚታመን መልኩ ለሐሳውያንም መንገድ እንዳይከፍት ተደርጎ ሲያናግ
ኖሯል፤ ይህንንም ያደረገበት ዋናው ምክንያት እግዚአብሔር ሥራውን የሚሠራው ለሠው ሕሊና ቢመችና
በሚረዳ መልኩ በመሆኑ ነው፡፡
ስለዚህ የብሉይና የሐዲስ ኪዳንን ምግብና (ተመጋጋቢነት) የምንረዳው በሽግግር ሒደት የተገለጡ
ሁሉ በሐዲስ ኪዳን ተፈፅመው ያሉ መሆናቸውን ነው፡፡ ወንጌል የብሉይ ኪዳን ክብሩ ነው፡፡ ጌታም
ልፈጽማቸው ነው የመጣሁት ያለው ከዚሁ የተነሣ ነው፤ በመሆኑም ሁለቱ ኪዳናት ተመጋጋቢ የሆኑ ፈጽሞ
የማይጣረሱ ሙሉ በሙሉ የሚስማሙ መሆናቸውን መረዳት ያስፈልጋል፡፡
የሁለቱ ኪዳናት አንድነት
ከላይ በተጠቀሱት ንዑሳን ክፍሎች ሁለቱ ኪዳናት እንደማይለያዩ ተረድተናል፤ ከዚህ በመቀጠል
አንድነታቸውን በጥቂቱ በምሳሌ ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
1. ሁለቱም መጻሕፍትን ዘመን አይሽራቸውም፡፡
2. ሁለቱም የተጻፉት በአንድ በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት በተለያዩ ዘመናት ባሥነሳቸው ቅዱሳን
አባቶች ላይ በጸጋ አድሮ የሚጽፉትን እያመላከታቸው ነው፡፡
3. የሚታየውንና የማይታየውን ፍጥረት የፈጠረ እግዚአብሔር እንደሆነ ዓለምን ከመፍጠሩ በፊትም
በኋላም በክብር በአንድነት በሦስትነት እንዳለ ይገልጣሉ፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 154


4. ሁለቱም ኪዳናት የእግዚአብሔርን ባሕርይና ዘለዓለማዊነት ፈቃዱን ተረድተን እንደ ፈቃዱ
እንድንመራ ያደርጋሉ፡፡
5. የሰው ልጅ ትእዛዙን በመጠበቅ በሃይማኖትና በምግባር ሲኖር የእግዚአብሔርን ርስት የመውረስ ተስፋ
እንዳለው ያስረዳሉ፡፡
6. ብሉይና ሐዲስ ኪዳን የተቀደሱ መጻሕፍት እንደመሆናቸው መጠን የሚያነቡትንና የሚሰሙትን
ይቀድሳሉ ወደ ቅድስናም ያመራሉና ዓላማቸው አንድ ነው፡፡
ከዚህ በታች የምንመለከተው የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳንን አለመለያየት ወይም አንድነት ነው፡፡
ብሉይ ኪዳን ሐዲስ ኪዳን
አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በዕምነት ተወሰደ፣
እግዚአብሔር ወስዶታልና ዘፍ 5፡19 እግዚአብሔርም ስለወሰደው አልተገኘም፡፡ ዕብ 11፡5
እግዚአብሔር ሙሴን ያለነ የሚኖር እኔ ነኝ አለው፡፡ ዘጸ ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ
3፡14 ጌታ አምላክ አልፋና ኦሜጋ እኔ ነኝ፡፡ ራዕ 1፡8
እግዚአብሔር አለኝ አንተ ልጄ ነህ ዛሬ ወለድሁህ፡፡ መዝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፡፡ ማቴ 3፡17
2፡7
እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ፡፡ መዝ 46፡5 ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ፡፡
ሉቃ 24፡51
እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ የወይን ጌታችን መድኃኒታችን ከሙታን ተነሣ፡፡ ማቴ 28፡1
ስካር እንደተወው እንደ ኃያል ሰው ጠላቶቹንም
በኋላው መታ፡፡ መዝ 77፡5
ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ልጅም ትወልዳለች እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው
ትጠራዋለች፡፡ ኢሳ 7፡14 ያጽናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ፡፡ ማቴ……….
የእስራኤል ልጆች የተስማሙበት የክርስቶስን ዋጋ በዚያን ጊዜ በነቢዩ ኤርምያስ የተባለው ከእስራኤል
ሠላሳውን ብር ይቀበሉታል፤ ይህንንም ብር በሸክላ ሠሪ ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን የገመተውን ሠላሳ
ቦታ ዋጋ አድርገው ይሰጡታል፡፡ ተረ ኤር 7፡3 ብር ያዙ ጌተም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት
ሰጡት የሚለው ተፈፀመ፡፡ ማቴ 27፡9
አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ አንቺ በይሁዳ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ ምድር ከይሁዳ ገዥዎች
አእላፋት መካከል ትሆኝ ዘንድ ታናሽ ነሽ፡፡ ሚክ 5፡2 ከቶ አታንሺም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ
መስፍን ከአንቺ ይወጣልና፡፡ ማቴ 2፡5
በራስህ ላይ ሊደረግብህ የማትፈልገውን በማንም ላይ ሰዎች ቢያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ እንዲሁ
አታድርግ፡፡ ጦቢት 4፡15 እናንተም አድርጉላቸው፡፡ ማቴ 7፡12
እግዚአብሔርን ትፈትን ዘንድ አንተ ማን ነህ? ዮዲት 8፡ እግዚአብሔር አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ
12 ተጽፏል፡፡ ማቴ 4፡7

ሰዱቃውያን ግን ነፍሳችን ከሥጋችን ከወጣች በኋላ ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዱቃውያን…ማቴ
ከሞቱ ሰዎች ጋር አንነሣም ለሥጋና ለነፍስም ከሞቱ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 155


በኋላ መነሣት የላቸውም ከሞትንም በኋላ አንነሳም 22፡23-33፣ ማቴ 16፡6-12
ይላሉ፡፡ 2 ኛ መቃ 14፡7
የስንዴ ቅንጣት ካልፈረሰች አትበቅልም፣ አታፈራም፡፡ …. በመበስበስ ይዘራል፣ ባለመበስበስ ይነሣል፡፡ 1 ኛ ቆሮ
2 ኛ መቃ 17፡1 15፡35-42
ስማችን በምንሞትበት ወራት ይዘነጋልና …. ኑ ተድላ ነገ ስለምንሞት ዛሬ እንብላ እንጠጣም፡፡ 1 ኛ ቆሮ 15፡32
ደስታ እናድርግ፡፡ ጥበ 2፡1-6
ጌታ ሆይ ተወዳጅ ልጆችህ ይማሩ ዘንድ የሰውን ልጅ ሰው የሚኖረው እግዚአብሔር በሚናገረው ቃል ሁሉ
የሚመግበው ልዩ ልዩ እህል ብቻ ሳይሆን በአንተ ላይ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም፡፡ ማቴ 4፡4
የሚታመኑትን ሁሉ የሚጠብቀው ቃልህ ነው፡፡ ጥበ 16፡
26፣ ዘዳ 8፡3

እንዳንተ ያለውን ሰው ይቅር ሳትል ኃጢአትህን ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ በሰማያት ያለው


ያስተሰርይልህ ዘንድ እንግዲህ እንዴት ትለምነዋለህ? አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ
ሲራ 28፡4 በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት፡፡ ማር
11፡25፣ ሉቃ 6፡37
ለወዳጆቹ ይፈርድላቸው ዘንድ እነሆ ከብዙ መላዕክት ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ እነሆ ጌታ በሁሉ
ጋር ይመጣል፡፡ ሕገ እግዚአብሔርንም የዘነጉ ሰዎችን ላይ እንዲፈርድ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ
ያጠፋቸዋል፡፡ ሕገ እግዚአብሔርን የዘነጉ ሰዎችና ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ አመጸኞችም በእርሱ ላይ
ኃጥአን በእርሱ ፈጽመው ስላደረጉት ነገር ሁሉ ሥጋዊ ስለተናገሩት ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ
ደማዊን ሁሉ ይወቅሳል፡፡ ሄኖ 1፡9 እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳት ጋር መጥቷል ብሎ
ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ፡፡ ይሁ 1፡14-15

ከላይ በተዘረዘሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የብሉይ ኪዳንንና የሐዲስ ኪዳንን አንድነት፣ አንድ ዓላማ
ያላቸው መሆኑን፣ የማይለወጡ፣ የማይሻሩ የእግዚአብሔር ቃል መሆናቸውን ተመልክተናል፤ በመሆኑም
ቅዱስ ሉቃስ ‹‹ከኦሪትና ከነቢያት አንዲት ቃል ከምትወድቅ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል›› ሉቃ 16፡17
እንዳለ ተገንዝበን እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ ምስጢር ገላጭነት ተመርተን ቅዱሳት መጻሕፍትን
አንብበን ሕይወት እንድናገኝባቸው እግዚአብሔር አምላካችን ይርዳን፡፡

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 156


የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 157
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 158
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 159
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 160
የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ 161

You might also like