You are on page 1of 10

በእናንተ ዘንድ ያለው ክርስቶስ — የእግዚአብሔር ፍቅርና ኀይልን ማስተላለፍያ ነው

መግቢያ

 ሙሉ ትምህርቱን ለማገባደድ የመጨረሻውን የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን ላይ


በአንድነት እንደደረስን ታምናላችሁን!?
 ጌታ መልካሙን ሥራ በእናንተ እንደጀመረ፣ በእናንተ ክርስቶስን የመምሰል
ባሕርይን እየቀረጸ እንደሆነ፣ ይህም የለውጥ ሂደት ቤበተሰባችሁ ውስጥ፣ በሥራ
ቦታችሁ እና በማኅበረሰባችሁ ላይ በጎ ተጽዕኖ ማሳደር እንደጀመረ ተስፋ
አደርጋለሁኝ፡፡
 በፊልጵስዩስ 1፡6 እንዲህ የሚል የተስፋ ቃል አለን፡-"በእናንተ መልካምን ሥራ
የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን
ተረድቼአለሁና፤"
 ትሑታንና እና ለእግዚአብሔር ታዛዦች ከሆናችሁ፣ እንዲሁም መንፈሱ
በቀጣይነት እንዲቀርጻችሁና ዕለት በዕለት እንዲያድሳችሁ ከፈቀዳችሁ፣ የክብርና
የማዕረግ ሰዎች እንደምትሆኑ አስረግጬ እነግራችኋለሁ!

የነገር ሁሉ ፍጻሜ

 መጽሐፍ ቅዱስ የዓለም ታሪክ እንዴት እንደሚፈጸም ይነግረናል፡፡


 ደቀ-መዝሙር ዮሐንስን አንድ ቀን በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ኾኖ ምን
እንደሚከናወን ለቅጽበት ወዳየው ወደ ራእ 7፡9-17 ወዳለው ክፍለ ምንባብ
እንመለስ፡፡ (ጥቅሱ ይነበብ)

 ታላቁ ተልእኮ ስኬታማ እንደሚሆን ግልጽ ነው - ከንቱ ሆኖም አይቀርም!


 እዚህ ላይ ትልቁ ጥያቄ የሚሆነው፣ በዚህ ረገድ የእኛ ሚና ምን ይሆናል?
 ለእንደዚህ ዓይነቱ ታላቅ ትዕይንተ ፍጻሜ በማናቸውም መንገድ አስተዋጽዖ
ማበርከት ትሻላችሁን?
 ቤተሰቦቻችሁ፣ የሥራ ባልደረቦቻችሁ፣ እና ጎረቤቶቻችሁ በእግዚአብሔር ዙፋን
ፊት ከሚሰበሰቡት እልፍአእላፍ ሰዎች መካከል ይሆኑን?
 ሰዎች የዘላለምን ሕይወት የመምረጥ ዕድል እንዲኖራቸው ታደርጋላችሁን?
የክርስቶስ አምባሳደር

 በዮሐንስ 15:16 ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፡-"እኔ መረጥኋችሁ


እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ
እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።"
 ኢየሱስ የእርሱ አምባሳደሮች እንድትሆኑ መርጧችኋል!
 አምባሳደር ምንድን ነው?
 ዊኪፔዲያ እንደገለጸው አምባሳደር ማለት "ሕጋዊ ባለ ሙሉ ሥልጣን ወኪል"
ሆኖ በተለይም ያንዲትን ሉዓላዊት ሀገር፣ ሕዝብንና መንግሥትን በከፍተኛው
የዲፕሎማት ደረጃ የሚወክል/የምትወክል ወይም ልዩ እና ብዙጊዜ ለጊዜያዊ
የዲፕሎማሲ የሥራ ሹመት የሚወከል ነው፡፡ "
የዲፕሎማሲ ሥራ

 እንድትሄዱና የዘላለምን ፍሬን እንድታፈሩ ለተለየ ተግባር በኢየሱስ የተሾማችሁ


ሕዝባችሁንም የወከላችሁ የእግዚአብሔር አምባሳደሮች ናችሁ፡፡
 "ከፍተኛ ደረጃ ዲፕሎማት" እንደመሆናችሁ መጠን የትም ስትሄዱና ምንም
ስታደርጉ እርሱንና መንግሥቱን እንድትወክሉ አድርጎ ንጉሣችሁ እውቅና እና
ሙሉ ሥልጣን ሰጥቷችኋል፡፡
 "በመንፈስ ቅዱስ የሆነች ጽድቅ፣ ሰላምና ደስታ" ያለባትን መንግሥትን ነው
የወከላችሁት— ይገርማል ከዚህ ከጎጂውና ከወደቀው ዓለም ጋር ምንኛ ተጻራሪ
ነው!
 ዲፕሎማሲያዊ ሥራችሁ ጊዜያዊ ነው አንድ ቀን ወደ ሀገራችሁ ትመለሳላችሁ፤
ተመልሳችሁም ከንጉሣችሁና ከሁሉም የሰማይ ዜጎች ጋር አብራችሁ ለዘላለም
ትኖራላችሁ፡፡
 ለዚያም ነው በምድር ላይ ያለንን ውሱን ቀሪ ጊዜያችንን በጥበብ መጠቀሙ ወሳኝ
የሆነው፡፡

የንጉሥ ካህናት

 የኢየሱስ ተከታዮች እንደመሆናችን ሰማይን "ከሕዝብ፣ ከነገድ ከቋንቋ በተዋጁ"


ሰዎች ለመሙላት ልንፈጽመው የሚገባን በዓለም አሉ ከሚባሉት ተልዕኮዎች
ሁሉ እጅጉን የላቀ ተልዕኮ አለን፡፡
 ንጉሣችን በማያልቀው ጸጋው ዕጹብ ድንቅ ለሆነው ተልዕኮው እንደምንገባ
አድርጎ ስለቆጠረን በጭራሽ ማፈር አይገባንም፡፡
 1 ጴጥሮስ 2፡9 እንዲህ ይለናል፡-"[እናንተ] ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ
የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥
ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤"

ኦርኬስትራ፡- የሙዚቃ ጓድ ተምሳሌት

 የበለጠ የተከበረና የተሟላ ተልዕኮ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ?


 የንጉሥ ካህናት እንደመሆናችን መጠን፣ ሁላችንም የተጠራነው ምስጋናውን
እንድናስታውቅ ነው፡፡
 ይህም እያንዳንዳችን በተለያየ መንገድ እናደርገዋለን፤ ይሁን እንጂ አንድ ሆነን
እንሠራለን አንደኛችን ለሌላችንም በጣም አስፈላጊዎች ነን፡፡
 እኛ ልክ በአንድ የሙዚቃ ጓድ (ኦርኬስትራ) ውስጥ እንዳሉ የተለያዩ የሙዚቃ
መሣሪያዎች ነን፡፡
ሲምፎኒ፡- በሙዚቃ ጓድ ተሰናስሎ የተሐደ ወይም የተቀነባበረ ረዥም
የኅብረ-ሙዚቃ ፈጠራ፤ (በተርጓሚው የተጨመረ)
 እያንዳንዱ የሙዚቃ መሣሪያ የራሱ የሆነ የተለየ ድምጽ እና ተግባር አለው፤ ነገር
ግን መሣሪያዎቹ ባንድነት ሲሆኑ ነው ግሩም የሆነ የተሰናሰለ፣ የተዋሐደ ወይም
የተቀናበረ ረዥም ኅብረ-ጣዕመ ሙዚቃን የሚፈጥሩት፡፡
ልዩ ጥሪ

 የእርሱ የዘላለማዊው ዓላማው የኅብር ጓዶች ለመሆን በእግዚአብሔር መልክና


አምሳል ተፈጥራችኋል፡፡ (ባንድነት፣ በውሕደት፣ በተሰናስሎ
ለመሥራት/በተርጓሚው የተጨመረ/)
 ሁላችሁም ልዩ ልዩ መሣሪያዎች ናችሁ፡፡ በዓለም ሙሉ እናንተን
(አንተን/አንቺን) የመሰለ የለም፡፡ የእናንተ የድምጽ ውሕደት የሚጎድል ከሆነ
የሙዚቃ ጓዱ የተማላ አይደለም፡፡
 ኤፌሶን 2:10 እንዲህ ይላል፡- "እኛ ፍጥረቱ ነንና እንመላለስበት ዘንድ
እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ
ኢየሱስ ተፈጠርን።"
 እግዚአብሔር ከእናንተ ውጪ ማንም ሊሄድበት የማይቻልበትንና
ለእያንዳንዳችሁ የሚሆን የተለየ መንገድን አዘጋጅቶላችኋል፡፡
 በዚያ መንገድ ላይ የተወሰኑ ተግባሮች አሉ - መልካም ሥራዎች እየጠበቋችሁ
ነው፡፡ እግዚአብሔር ራሱ እነዚህን ሥራዎች አስቀድሞ አዘጋጅቷቸዋል ስለዚህም
አሸናፊዎች ናችሁ፡፡
የእግዚአብሔር ታላቅ ዕቅድ

 ራሳችን ከምንወጥነው ከማንኛውም ዕቅድ ይልቅ እግዚአብሔር ለኛ ያለው ልዩ


ዕቅድ ይበልጣል፡፡(ኢሳያስ 55: 8-9ን ይነበብ.)
 ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏል፡-"እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ
የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ
ያደርጋል፥"(ዮሐንስ 14፡12).
 ኢየሱስ ካደረጋቸው የበለጡ ታላላቅ ነገሮችን! ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?
 በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ብቻ ነው የሚቻለው!
 እግዚአብሔር እንድትሠሩ ከጠራችሁ ማንኛውም ነገር በራሳችሁ ጥንካሬና ኀይል
መሥራት ፈጽሞ አይቻላችሁም፡፡ ነገር ግን "…በሰው ዘንድ አይቻልም
በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል!" (ማቴዎስ 19:26)

የነገረ ትሥጉት መርሆ


ትሥጉት የግእዝ ቃል ሲሆን፣ ሥጋ የመልበስ፣ ሰው የመሆን ምስጢር ማለት ነው፡፡

 እግዚአብሔር በሰጣችሁ ጥሪ ውስጥ ስኬታማ ለመሆን ቊልፍ ነገር ሥጋዌ/


ትሥጉት ነው፡፡
 ልክ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ፣ ሰው እንደሆነ ሁሉ መለኮታዊ
ሐሳቡ—የተልዕኮ ጥሪው በእኔ እናንተ ውስጥም ሥጋ ሊለብስ ይገባዋል፡፡
 "ከመንፈስ መወለድ" ይገባናል(ዮሐንስ 3፡8)፤ እንዲሁም በመለኮታዊ ፍቅሩና
ኀይሉ መሞላት ይኖርብናል፡፡
 የነገረ ትሥጉትን መርሆ በግጽና ባጭሩ ከጳውሎስ የበለጠ ሊያብራራልን የሚችል
ማንም ሰው የለም፤ በገላትያ 2፡20 እንዲህ በማለት አስፍሮልናል፡-"ከክርስቶስ
ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ
ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው
በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።"
 ይህ ጥቅስ ክፉም የምስራች ዜናንም በአንድ ላይ አጣምሮ ይዞኣል፡፡
ክፉ ዜና እና የምሥራች

 መጥፎ ዜናው፤ ሞተናል —ከክርስቶስም ጋር ተሰቅለናል!


 ግን ያን ያህል መጥፎ ነገር ነውን? የሞቱ ሰዎች ...

... በወንጌል አያፍሩም

... ሌሎች ስለ እነሱ በሚያስቡት ነገር ግድ አይላቸውም፡፡

... ዓለማዊ ሀብትን አያሳድዱም፣ ሥጋዊ የደስታ ምኞታቸውንም


አይከተሉም፡፡

 ቀጥሎም መልካሙ ዜና ይሆናል፤ ክርስቶስ በእኛ ይኖራል!


 ክርስቶስ በእኛ የሚኖር ከኾነ…

… ማንኛውንም ሰው ለመቀየር ምንም ዓይነት ጫና አይኖርብንም፤ ምክንያቱም በእኛ


የሚኖረው እርሱ ክርስቶስ ራሱ በእኛና በእኛ በኩል ሥራውን ይሠራል፡፡

… እንዲሁም በሰማይና በምድር ያለው ሥልጣን ሁሉ አለን!

የማይቻል ነገር የለም

 በእናንተ ውስጥ በሚኖረው በክርስቶስ ሁሉን ትችላላችሁ፣ ተአምራቱንም


በእናንተ ያደርጋል!
 ለዚህም ነው ጳውሎስ በፊል. 4፡13 "ኀይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን
እችላለሁ።" በማለት ያወጀው፡፡

 ችግሮች በሚከሰቱበት ጊዜ፣ አስቸጋሪ እንቅፋቶች በሚያጋጥሟችሁ ጊዜ፣ ነውጥ


እንደ ደመና ሲከባችሁ - አትሸበሩ! ተስፋም አትቊረጡ!
 "የጠራችሁ የታመነነ፣ ያደርገዋልም፡፡"
 እምነት ሁኔታዎችን በማየትና ስሜቶቻችሁን በማዳመጥም የሚመጣ ነገር
ኣይደለም፡፡
 እምነት የሚመጣው "የእምነታችን ራስና ፈጻሚ" በሆነው በኢየሱስ ላይ
ዐይናችንን ስናደርግ ብቻ ነው፡፡ (ዕብራውያን 12፡2) እርሱ ያደርገዋል!
የእግዚአብሔር አጠቃላይ እና ፍጹም ክብካቤ

 የእግዚአብሔር ሙሉ እና ፍጹም ክብካቤ ኣስተዋላችሁን? እንደ ሰማይ


አባታችሁ መጠን፣ ዓላማችሁ ሁሉ እንዲፈጸም የሚያግዙ ነገሮችን ሁሉ
አድርጓል፡፡ (ቃላቶቹን በሙሉ በተንጋደደ የፊደል አጣጣል አድርገህ በሰሌዳው
ላይ ጻፍ)

➢ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌላችሁ በፍቅር ትሆኑ ዘንድ በክርስቶስ
መረጣችሁ። (ኤፌሶን 1፡4)

➢ አስቀድሞ መልካም ሥራዎችን አዘጋጅቶላችኋል፡፡ (ኤፌ 2:10)

➢ ያልተሠራ ኣካላችሁና የተፈጠሩ ቀኖቻችሁ አንድስ'ንኳ ሳይኖሩ አስቀድሞ ሁሉንም


በመጽሐፉ ውስጥ ጻፈ፡፡ (መዝሙር 139፡16)

➢ እንደ ጥልፍ ሠራተኛ አንድ ላይ አያይዞ እናተን ፈጥሯል፡፡ (መዝሙር 139:13)

➢ እንድትከተሉትና እንድታገለግሉት ጠርቷችኋል፡፡ (ማቴ4:19)

የእግዚአብሔር አጠቃላይ እና ፍጹም ክብካቤ

➢ኀጢኣታችሁን ሁሉ ይቅር ብሎ አዲስ ሕይወትንና ባሕርይን ሰጣችሁ፡፡(ሮሜ 3፡23-


24፣ 2 ቆሮንቶስ 5፡17)

➢ለእናተ ያለውን በጎ ዓላማዎች እንዲፈጸም መንፈስ ቅዱስን ረዳትና መሪያችሁ አድርጎ


አስታጥቋችኋል፡፡(ሐዋ. 1፡8)

➢ በፍጹም አይጥላችሁም፣ እስከ ዓለም ፍጻሜም ከእናንተ ጋር ይሆናል፡፡(ኢያሱ 1፡5፣


ማቴዎስ 28፡20)

➢ በዚህ ዓለም ያለው ኑሮኣችሁ ሲያበቃም፣ ከሁሉም የላቀ ክብርና ውበት ያለው
ብሎም በሰው ልብና አእምሮ ያልታሰበ የዘላለም ሥፍራ አዘጋጅቶላችኋል፡፡(ራዕይ
ምዕራፍ 22፡1-5)

 ይሄን ያህል ነው እንግዲህ ለእናንተ ሕይወት ያለውን ፍጹም በጎ ሐሳብ


እንዲፈጽም እግዚአብሔር ዝግጁ የሆነው!
መኾን እና ማድረግ

 የእግዚአብሔር ዕቅድ ስለምታደርጉት ብቻ ሳይኾን ስለማንነታችሁም ጭምር


ነው፡፡
 እውነታው ግን በእግዚአብሔር መንግሥት መኾንና ማድረግ ሁሌም አብረው
የሚሄዱ ናቸው፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ለጠራችሁ ጥሪ ተግባራውያን
ሆናችሁ ለመገኘት የተፈጠራችሁበትን ዓለማ ልትኾኑትና ልታደርጉት
ይገባችኋል፡፡
 እግዚአብሔር እንድትሠሩት ለጠራችሁ ዓላማ ሁሉ በቀዝቃዛና ደንዳና ልብ
የምታደርጉት ከሆነ ጥረታችሁ ሁሉ ያለፍሬና መና ይኾናል፡፡
 ይሁን እንጂ፣ ልባችሁን እንዲለውጥና ክርስቶስን እንድትመስሉ አድርጎ
እንዲቀርጻችሁ ለመንፈስ ቅዱስ ብትፈቅዱለት፣ የምታደርጉት ነገር ሁሉ ፍሬያማ
ይኾናል፡፡
 ለዚህም ነው በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ለእያንዳንዱ አስፈላጊ ተግባር
ሁሉ ቀደም ብሎ በዝግጅት ጊዜ የሚጀምረው፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊ የዝግጅት ምሳሌዎች

 ሙሴ እስራኤልን ከግብፅ ባርነት እንዲታደግ እግዚአብሔር ሲጠራው እድሜው


80 ዓመት ነበር፡፡
 ኢየሱስ ሦስት ዓመት ተኩል ብቻ የቈየውን ይፋዊ አገልግሎቱን ለመጀመር የ 30
ዓመታት የሕይወት ዝግጅትን አድርጎኣል፡፡
 በሌላ አባባል፣ ብዙ ጊዜ ጾማችሁና ጸልያችሁ እግዚአብሔር ያሳያችሁ ኅልሞችና
ራዕዮች ከመፈጸም የዘገዩ ሲመስላችሁ— ተስፋን አትቊረጡ!
 ምንም ዓይነት የተከፈቱ በሮች የሌሉ ቢመስሉም፣ ብዙ ጥረቶችን እያደረጋችሁ
ቢሆንም፣ በዚህ ሁሉ እናንተ ባታዩትም እንኳ እግዚአብሔር በሥራ ላይ ነው
ያለው! ምናልባትም እግዚአብሔር እናንተንና ወደ ፊታችሁ ስለሚጠብቃችሁ
መንፈሳዊ ተልዕኮ በር በማዘጋጀት መለኮታዊ ሐሳብ ላይ ተጠምዶ ሊሆን
ይችላል፡፡
በክርስቶስ መኖር

 እስከዚያ ድረስ አንድ ከሁሉም በላይ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ማድረግ
ትችላላችሁ፡፡ ዮሐንስ 15: 4-5 እናንብብ. (ጥቅሱ ይነበብ)
 ኢየሱስ በርሱ እንድትኖሩ ይጠይቃችኋል፡፡ ያለ ኢየሱስ ምንም ልታደርጉ
አትችሉም፤ ምንም ዓይነት ዘላቂ ፍሬ ሊያፈራ የሚችል ነገርን ኣታደርጉም፡፡
 ኢየሱስ የወይን ግንድ ነው፤ እናንተ ቅርጫፎች ብቻ ናቸው፡፡
 ፍሬውን የሚያፈራ ቅርንጫፍ አይደለም፤ ቅርንጫፍ ከግንዱ ውስጥ
የሚመጣውን የወይን ዕፅ ፈሳሽ ምግብ የሚተላለፍበት ነው!
 የክርስትና ሕይወት የሚሠራው እንዲህ ነው፤ ራሳችን ፍሬን ማመንጨት
(ልንሰጥ) አንችልም፣ በእኛ ውስጥ የሚፈሰው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው ፍሬን
የሚያፈራው!
 መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ እንዲፈስላችሁ በክርስቶስ ኑሩ!

በእናንተ ዘንድ ያለው ክርስቶስ የዓለም ተስፋዋ ነው

 በእናንተ ዘንድ ያለው ክርስቶስ የዓለም ተስፋዋ ነው! በክርስቶስ በመኖር፣


በዙሪያችሁ ላሉት ሰዎች ሁሉ የእርሱ ፍቅርና ኀይል ማስተላለፊያ (አሸንዳ)
ትሆናላችሁ፡፡
 በሄዳችሁበት ሁሉ፣ የተትረፈረፈው የርሱ ሕይወት በእናንተ በኩል ወደሚወደው
ፍጥረቱ ሁሉ ይፈሳል፡፡
 ስታናግሯቸው፣ ኢየሱስ ነው በእናንተ በኩል የሚናገራቸው፡፡
 እጆቻችሁን በእነሱ ላይ ስትጭኑ፣ የኢየሱስ እጆች ናቸው በነሱ ላይ የተጫኑት፡፡
 በእናንተ ዘንድ ያለው ክርስቶስ ልብንና አእምሮን ሊለውጥ ይችላል፡፡
 በእናንተ ዘንድ ያለው ክርስቶስ ሊያድን፣ ሊፈውስና ነፃ ሊያወጣ ይችላል፡፡
 በእናንተ ዘንድ ያለው ክርስቶስ ለእግዚአብሔር መንግሥት ክብር ተራሮችን
ማንቀሳቀስና ትላልቅ ገቢረ ታአምራትን ማከናወን ይችላል፡፡
እኔና እናንተስ?

 በዚህች ሀገር ውስጥ ሁላችሁም የምትነሡበትና የምታበሩበት ጊዜ ነው!


 ክርስቶስ በእናንተ በኩል ሆኖ ያበራል፣ ብሎም ቤተሰቦቻችሁን፣ የሥራ
ቦታችሁንና ማኅበረሰባችሁን ደግሞ በኀይሉና በፍቅሩ ይነካል፡፡
 ሁል ጊዜ የክብር የማዕረግ ሰዎች፣ ክርስቶስን-ማዕክል ያደረገ ሕይወት፣ ፍቅር፣
ጸጋ፣ ሐቀኝነትና አክብሮት ያላችሁ ሰዎች መሆን እንደሚገባችሁ አትዘንጉ፡፡
 ሁላችንም ጳውሎስ በ2ኛጢሞቴዎስ 4፡7-8 በተናገረው ቃል መሠረት የሕይወት
መንገዳችን ፍጻሜ ይሁንልን፡፡(ጥቅሱ ይነበብ)
 አሁን ወደ ፊት እየመጣችሁ ዲፕሎፕሎማችሁን እንድትቀበሉ እጋብዛችኋለሁ፡፡
(የእያንዳንዳቸውን ተሳታፊ ስም እያነበብክ ዲፕሎማቸው ን ስጥ፡፡)

ለቡድን ውይይት የቀርቡ ጥያቄዎች

 ከክፍለ ትምህርቱ ምን ገንቢና ጠቃሚ ሐሳቦችን አገኛችሁ?


 ይህ የትምህርት-መርሐ-ግብር ከተጀረ ጀምሮ ያስተዋላችሁት የኾነ ለውጥ
አለን፡-
 በሕይወታችሁ? በምን መንገድ?
 በቤተሰባችሁ ውስጥ? በሥራ ቦታችሁ? በማኅበረሰባችሁ ውስጥ?
 እንደ እግዚአብሔር አምባሳደሮች መጠን የተሰጣችሁ የተልዕኮ ድርሻ በዕለት
ተዕለት ሕይወታችሁ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል? ራስሳችሁንስ እንደ "ንጉሥ
ካህናት" ትመለከታላችሁን?
 ልዩ ጥሪያችሁ ምን እንደሆነ ለይታችሁ ኣውቃችኋልን? ምንድን ነው?
 …ሀ)…ለ)………. ለእናንተ ምን ትርጒም ኣለው?

ሀ) "ከክርስቶስ ጋር መሰቀል"?

ለ) ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ መኖሩ?

 በእናንተ ውስጥ ላለው የእግዚአብሔር ፍቅር እና ኀይል እንዴት ነው


ለቤተሰቦቻችሁ፣ለሥራ ቦታችሁ ና፣ ለማኅበረሰባችሁ ማስተላለፊያ-አሸንዳ
የምትሆኑት?
ጸሎት (በትናንሽ ቡድኖች የሚደረግ)

 ክርስቶስ በእናንተ እንዲኖርና በእናንተ በኩል እንዲሠራ ራሳችሁን በመስቀሉ


ሥር አኑሩ፡፡
 ልዕለፍጥረታዊው የእግዚአብሔር ፍቅርና ኀይል እንዲሞላባችሁ መንፈስ ቅዱስን
ጋብዙት፡፡ (supernatural = ልዕለፍጥረት/ከሰው ፍጥረተ -ጠባይ/ባሕርይ
ከፍ ያለ፣ውጭ የሆነ)
 ይህን ፍቅርና ኀይል ለቤተሰቦቻችሁ፣ ለሥራ ገበታችሁና ለማኅበረሰባችሁ
ማስተላለፊያ-አሸንዳ መሆን እንድትችሉ ጸጋና ጥበብ እንዲያድላችሁ በጸሎት
ጠይቁ፡፡
 እግዚአብሔር በሕይወታችሁ የጀመረውን መልካሙን ሥራውን እንዲቀጥልና
ፍጻሜንም እንዲያደርግለት ጸልዩ!

You might also like