You are on page 1of 10

የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #8

#8
www.tlcfan.org 0
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #8

የእግዚአብሔር ቅባት ሕግ

የእግዚአብሔር ቅባት ዘይት አስራር ሕግና ሥርዓቱ በዘጸ.30፥23-25 ላይ በዝርዝር ተጽፏል።

በማደሪያው ድንኳን ውስጥ ያሉ እቃዎች በሙሉ ለእግዚአብሔር የተለዮ ይሆኑ ዘንድ በቅባ ዘይቱ

ይቀቡና ለእግዚአብሔር ሥራ ብቻ ይለዩ ነበር። (ቁ. 26-28). ዘጸ. 30፥30 - 31 እንዲህ ይለናል፦

“በክህነትም ያገለግሉኝ ዘንድ አሮንንና ልጆቹን ቅባቸው፥ ቀድሳቸውም።አንተም ለእስራኤል

ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ይህ ለልጅ ልጃችሁ የተቀደሰ የቅብዓት ዘይት ይሁንልኝ።”

አሮንና ልጆቹ የሚያሳዩት በመልከ ጸዲቅ ክህነት ተስፋ የተገባልን እኛንና ኢየሱስ ክርስቶስን

ነው። በራእይ.20 መሰረት የመንግሥቱ ካህናት የመሆን ተስፋ ስለተገባልን ይህ የካህናት መቀባት ሕግ

ጥናት ለእኛም አሁን የሚሰራና ሕያው ነው። ሕጉ እንደሚያሳየው ደግሞ የሚቀባው ካህኑ ብቻ ሳይሆን

ማደሪያው ድንኳን ጭምር ነው። የማደሪያውን ድንኳን ደግሞ በሦስት ከፍለን ማየት እንችላለን።

ቅድስተ ቅዱሳን፣ ቅድስት እና አደባባይ // ከዳስ በዓል፣ ከበዓለ አምሣ እና ከፋሲካ ጋርም ይገናኛል። ይህን

ደግሞ ወደ ግል ማንነታችን ስናመጣው ደግሞ ቅርስተ ቅዱሳንና ፋሲካ ከመንፈሳችን ጋር፣ ቅድስትና

በዓለ አምሳ ከነፍሳችን ጋር እንዲሁም የዳስ በዓል እና አደባባዮ ከሥጋችን ጋር የተያያዘ መሆኑን

እንመለከታለን። ስለዚህም የእግዚአብሔር ቅባት በሕይወታችን ትልቅ ስፍራን ይይዛል። ማደሪያው

ለእግዚአብሔር የተለየው በመቀባት ነው። እኛ ደግሞ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና ማደሪያዎች ነን።

ስለዚህም መቀባት ለማደሪያዎች ወሳኝና የማይቀር ነው። (ዮሐ.1፥14,1 ቆሮ. 3፥16 ፣ 1.ተሰሎ. 5፥23 )

በኢየሱስ ክርስቶስ በፋሲካው በግ ስናምን በእምነት እንጸድቃለን (Justified) እንሆናለን።

ይህ ደግሞ የአንድ አማኝ የፋሲካን በዓልን የማድረግ ልምምዱ ነው። ነገር ግን ይህን ማድረግ

የመጀመሪያው እርምጃ እንጂ የመጨረሻው አይደለም። አማኙ ከፀደቀ በኋላ ከዛም በመቀጠል የበዓለ

አምሣን በዓል በማድረግ ደግሞ ሊቀደስ፣ ቃሉን ሰምቶ ወደ መታዘዝ ሊመጣ ወይም ለጌታ ሊለይ

ይገባዋል። ያኔም ተለየ፣ ተቀደሰ (Sanctified) ሆነ ይገባል። ይህም ሁለተኛው ደረጃ ነው። አማኙ በሩጫው

ፍጻሜ ወይም የመጨረሻው የመንፈሳዊ ዕድገቱ ፍጻሜ በሆነውን የዳስ በዓል ነው። ይህን በዓል

በማድረግ ደግሞ አማኙ ይከብራል። ያኔም አማኙ ከበረ ወይም (Glorified) ሆነ ይባላል። ነገር ግን ይህ

በሥጋ መክበር ከመንፈሳዊ ልምምድ ባሻገር የሚሞተው የማይሞተውን በመልበስ የሚፈጸም ታላቅ

በሩጫው ላሸነፉ የሚሰጥ የኢየሱስ ክርስቶስ አይነት የትንሣኤ አካል ነው። ሮሜ.6፥5

www.tlcfan.org 1
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #8

እነዚህን የእግዚአብሔር በዓላትና ከማደሪያው ጀርባ ያለውን ሚስጥር እና መንፈሱን

ለማግኘት ከሁለት አቅጣጫ ማደሪያውን ልንመለከተው ይገባል። ይህም ከውጭ ወደ ውስጥ ስንገባና

እና ከውስጥ ወደ ውጭ ስንወጣ ነው። በሌላ አባባል በእግዚአብሔር እይታና በሰው እይታ በማየት ነው።

የስው እይታና ሩጫ ( ከውጭ ወደ ውስጥ)

አንድ ሰው መዳኑን ሲጀምር እንደ ማንኛው አማኝ ሰው ከውጭ ወደ ውስጥ ማለትም

ከአለምና ከግብፅ ኑሮ ወደ እግዚአብሔር መገኘት በመግባትና በማደግ የሚጀምር ነው። ይህም አንድ

ሰው በእምነት ሲጸድቅ/justified ሲሆን። በመንፈሳዊ ሕይወቱ ወደ አደባባይ ሕይወት ልምምድ ወይም

ወደ ፋሲካ በዓል ልምምድ ገባ ማለት ነው። ይህም የኢየሱስን ደምና ሥጋ እንዲሁ የውሃ ጥምቀትን

የምናውቅበት በሕይወታችንም የምንለማመድበት የእድገት ሥፍራ ነው። በማደሪያው ድንኳን አደባባይ

ያለው መሰዊያው ከደምና ሥጋ ጋር ሲያያዝ። የመታጠቢያው ሰሃንና በውስጡ ያለው ውሃ ደግሞ

የመታጠብበን ወይም የጥምቀት ምሳሌ ነው።

ስለዚህ አደባባይ የገባ ወይም ፋሲካ በዓል በሙላት ያደረገ በእግዚአብሔር ፊት

የመጀመሪያውን የሕይወት ወይም የመንፈሳዊ እድገት ደረጃውን እየፈጸመ ነው ማለት እንችላለን። ነገር

ግን አደባባይ የገባ ሁሉ የአደባባይን ሕይወት ኑሮ ፈጽሟን ማለት አይቻልም። ምክንያቱም መግባት

ሳይሆን ወደ አደባባይ ገብቶ በአደባባዮ ሊያደርግ ከአማኙ የሚጠበቀውን በሙሉ ማድረግ አለበትና

ነው። ይህ ሲሆን ወደ ሁለተኛው እድገቱ መሻገር ይችላል። ደግሞም ሁሉ እንደ ቃሉ ሲፈስም ወይም ታዞ

ሲያደርግ የአደባባይ ልምምዱን በሚገባ ጨርሷል ማለት እንችላለን።

ስለዚህ አንድ አማኝ የመጀመሪያውን የአደባባይ እድገቱን ሲፈጽም በዚህ በአደባባይ ብቻ

መቆየት የለበትም። አማኙ ወደ ውስጥ ለመግባት ከአደባባይ ሁለተኛውን መጋረጃ አልፎ ወደ ቅድስት

መግባት ይጠበቅበታል። ይህ ደግሞ ከፋሲካ በዓል በመቀጠል የሚገለጠው የበዓለ አምሣ በዓል ልምምድ

ነው። በዓለ አምሣን ሰዎች በዚህ ዘመን በተለያየ መልኩ ሲመለከቱት ማየት የተለመደ ነው። ይሁንና

ትክክለኛው የዚህ በዓል መደረግ ምክንያትና ከእግዚአብሔር ሕግ በሲና ከመሰጠቱ ጋር የተያያዘ ነው።

እግዚአብሔር በእሳት በሲና ተራራ ላይ በወረደ ወቅት ሁሉም በገዛ ቋንቋቸው ድምፁ ሰምተዋል።

የተከፋፈሉ እሳትን አይተዋል። የዕብራይስጡ ቃል በሲና የሆነውን በትክክል የሚደግመው ልክ እንደ

ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ሁለት ታሪክ ነው።

www.tlcfan.org 2
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #8

ከሰሙ በኋላ የሰሙትን እንደተናገሩ ይህ ለእኛም በአሁን ዘመን እንዲሁ ነው። የሰማነውን

እንጂ ያልሰማነውን አንናገርም። ስለዚህ የበዓለ አምሣን አንድ ሰው በሕይወቱ መፈጸሙ የሚታወቀው

በልሳን ስለተናገረ ሳይሆን እግዚአብሔር ሰምቶ የሚታዘዝና የሚናገር ከሆነ ብቻ ነው። መንፈስ ቅዱስም

በአማኙ ላይ የሚመጣበት ቅባቱ የሚፈስበት ዋንኛው ምክንያት ስምተን እንድንታዘዝ ነው። ቅባት

ማለት አንድን ሥራ ለመስራት የሚያስችል ብቃት ወይም ችሎታ ነው። ሐዋርያትም ይህ መንፈስ

ሲወርድባቸው ያደረጉት ይህን ነው። እርሱ የተናገራቸውን ብቻ ተናገሩ። ደግሞ እግዚአብሔርን እና

የእርሱን ትዕዛዝ በዘመናቸው ፈጸሙ። በመንፈስ የመመራት ዋንኛው ምክንያትና ቁልፍ ለመታዘዝ

ወይም ትዕዛዛቱን ለመፈጸም ነው።

“. . . እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በማንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ

ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ።እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ

የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን

ሕይወትና ሰላም ነው። ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ

አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም።”

ሮሜ.8፥3-8

በብሉይ የሚቀቡ ካህናትም ቢሆኑ እግዚአብሔር በመቅደሱ ይሰሙታል የሰሙትን ደግሞ

ለሕዝቡ ይነግራሉ፣ይተነብያሉ ወይም በትምህርት መልኩ ያስተምራሉ። ሌላ ካህናቱ የተሰጣቸው ሥራ

ደግሞ ምልጃ ነው። ይህን ሃሳብ በልባችን አኑረን ትምህርታችንን እንቀጥል።

በመጨረሻም አማኞች ከውጭ ወደ ውስጥ ስንገባ የሩጫችን ማጠናቀቂያ የሚሆነው

ቅድስተ ቅዱሳን ወይም የዳስ በዓል እናደርጋለን። ይህም ወደ እግዚአብሔር ሙላት፣ ክብርና መገኘት

መግባት ነው። ይህ ሥፍራ ሁሉ አማኞችና ካህናት የሚገቡበት ሥፍራ አይደለም። ይልቁኑ ለሊቀ ካሕኑ

ብቻ የተወሰነ ነው። ሁሉ ካሕን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ሊገቡ አይችሉም። ስለዚህም የግድ አንድ ሰው ወደ

ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት የግድ ከሊቀ ካህኑ ጋር አንድ ሊሆን ወይም የእርሱ አካል ክፍል ሊሆን

ይገባዋል። ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በሁሉ አንድ መሆን የድል ነሺ ሕይወት መኖር ይህን ወደ ውስጥ

የመግባት እድል ያጎናጽፈናል። ሌላው ደግሞ በቅድስተ ቅዱሳን የሚገኘው በምህረት መክደኛው ላይ

ያለው ሁለንተናው ወርቅ የሆነው ኩሩብ ነው። ስለዚህ ሊቀ ካህን ወይም ሁለንተናው ወርቅ የሆነ ኪሩብ

መሆን በቅድስት መግባትንና መኖርን ይሰጣል።

www.tlcfan.org 3
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #8

የወርቅ ኪሩብ መሆን ራሱን የቻለ ትምህርት ነው። በዚህ ላይ የሚናተኩረው በካህናቱ ላይ

ነው። ስለዚህ አንድ አማኝ የቅድስተ ቅዱሳን መጋረጃ አልፎ ወደ ውስጥ ገብቶ በምሕረት መክደኛው ላይ

የተቀመጠውን ወይም ያደረውን እግዚአብሔርን የማየትና የመስማት ሕይወት፦ የእርሱን ሙሉ ባህሪና

መገለጥ መቀበል፣ ፍቃዱን መረዳት፣ እቅዱንና አላማውን ከማወቅ ጋር ይያያዛል። ይህ ከማወቅ

የሚመጣው ብቃት ከእርሱ ጋር በዙፋኑ በምሕረት መክደኛው ላይ መቀመጥና ከእርሱ ጋር ጽድቅን

ፍርድ በሚያመጣው በምሕረት ሕግ ላይ በመሆን መግዛትን የሚሰጥና የሚያጎናጽፍ ነው።

“ዙፋኖችንም አየሁ፥ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም

ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ ለአውሬውና

ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤

ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ። የቀሩቱ ሙታን ግን ይህ ሺህ ዓመት እስኪፈጸም

ድረስ በሕይወት አልኖሩም። ይህ የፊተኛው ትንሣኤ ነው። በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው

ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፥ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና

የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።” ራእይ.20

ይህ ሁላችን አማኞች ከውጭ ከደባባይ ተነስተን ወደ ውስጥ የምናደርገው መንፈስዊ ጉዞ፣

ከጌታ የሚጠበቅብን የእኛ የአማኞች እሩጫ ነው። እሩጫችሁን ጨርሳችኋል? በሩጫችን ውስጥ

የትኛው ክፍል ላይ እንገኛለን? የት ክፍል ላይ እንዳለን ዛሬ በቃሉ ራሳችንን በማየትና በትክክል

እሩጫችንን በሚገባ መልኩ የተባልነውንና ማድረግ ያለብንን እያደረግን መሮጥ እንችላለን። ዕብ.12፥1

የእግዚአብሔር እይታ ከውስጥ ወደ ውጭ፦ (ከመንፈስ ወደ ነፍስ ከዛም ወደ ሥጋ)

ከሰው የሚጠበቀውን መንፈሳዊ የእድገት ጉዞና ሩጫ እንዳየነው ከውጭ ወደ ውስጥ

እንገባለን ወይም እንሮጣለን። የእግዚአብሔር እይታ ወይም በሕይወታችን እርሱ በእኛ የሚሰራው ሥራ

ደግሞ ከውስጥ ወደ ውጭ ነው። ከቅድስተ ቅዱሳን በመጀመር በደባባይ ላይ ሥራውን በሕይወታችን

ይፈጽማል። በመንፈሳችን ጀምሮ ሥጋን በመለወጥ ይጨርሳል። በሌላ መልኩ ብናየው የእግዚአብሔር

ሥራ በሕይወታችን ከእኛ እይታና ሩጫ ተገላቢጦሽ ነው። የእኛ አደባባይ ልምምድ እርሱ በሕይወታችን

የሚሰራው መንፈሳችን ነው። በበዓለ አምሳ ልምምዳችን የሚሰራው ነፍሳችንን ነው። በእኛ የቅድስተ

ቅዱሳን ልምምዳችን የሚሰራው አካላችንን ወይም ሥጋችንን ነው።

www.tlcfan.org 4
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #8

አንድ አማኝ በፋሲካ በዓል፣ ዳግም ውልደትን ወይም ጽድቅን ሲለማመድ መንፈስ ቅዱስ

በመንፈሱ ውስጥ ያድርራል። የአማኙም መንፈስ ከሞት ወደ ሕይወት ይሸጋገራል፣ ይነቃል ወይም

ሕያው ይሆናል። አዳም ያመጣው የመንፈስ ሞት ይወገድለታል። ይህም ቅድስተ ቅዱስን ነው። ያን ጊዜ

አማኙ ጸድቋል / Justified ሆኗል እንላለን።

ከዚያም በመቀጠል አንድ አማኝ በዓለ አምሣን ሲለማመድ ተለየ ወይም ተቀደሰ /

Sanctified ሆነ እንላለን። ይህ ከላይ በመግቢያው ላይ እንደ ሕጉ ሙሴን እግዚአብሔር ካሕኑን በመቀባት

ለይልኝ ከሚለው የእግዚአብሔር የቅባት ሕግ ጋር እንደሚያያዝ በዚህ እንመለከታለን። ይህ ደግሞ በግል

ከነፍሳችን ጋር የሚያያዝ ነው። ስለዚህ የቅባት ትኩረት በነፍስ ላይ ነው ብንል አንሳሳትም። ነገር ግን

ቅባት ከዚያም አልፎ ይሰራል። ዋናው የቅባት ትኩረት ነፍስ ላይና መለየት ላይ ነው። እግዚአብሔር

ነፍሳችንን ለመመለስ የሚጠቀመው ሕጉን ነው። ሕጉን መታዘዝ ደግም ያለ መንፈስ ቅዱስ ፈጽሞ

የማይቻል ነው። ስለዚህም የመንፈስ ቅዱስ ቅባት በላያችን ላይ መምጣት ይህን መታዘዝ በእኛ ላይ

ለማምጣት ነው። እርሱ ሕጉን በልባችን ጽፎ በትእዛዛቱ ሊያስኬደን ቃል ገብቶልናል።

“የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ

ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።” መዝ.19:፥7

“ሕግህን ለሚወድዱ ብዙ ሰላም ነው፥ ዕንቅፋትም የለባቸውም።” መዝ.119:፥165

በመጨረሻም እግዚአብሔር የዳስ በዓልንን እንድንለማመድ ሲያደርገን አሮጌውን ድንኳን

አስወግዶ አዲሱን ድንኳን የማይሞተውንና የማይበሰብሰውን የክርስቶስ አይነቱ የትንሳኤ አካል

ይሰጠናል። ይህም እግዚአብሔር በሕይወታችንን የሚሰራው የአደባባዮ ሥራው ነው። እግዚአብሔር

በእኛ የጀመረውን መልካሙን ሥራ ከውስጥ ወደ ውጭ መፈጸሙ ፈጽሞ የማይቀር እቅዱ ነው።

ስለዚህም የማደሪያውን ድንኳን ሆነ፣ ሦስቱን በዓለትን በግል ደግሞ የማንነታችንን

ሁለንተና ስናጠና ግራ እንዳንጋባ ሁለቱን እይታዎች ለይተን ማወቅ ይጠበቅብናል። ይህ በመንፈሳዊ ጉዞ

ውስጥ ከግራ መጋባት የሚያድን ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ የሆነ መንፈሳዊ ሩጫና እድገት እንዲኖረን ነው።

ደግሞም ውጤታማ ድል ነሺ አማኞች እንድንሆን ይረዳናል። እግዚአብሔር ሙሴን አሮንና ልጆቹን

እንዲቀባለት ሲጠይቀው ለእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥራ እንዲለይለት ነው።

www.tlcfan.org 5
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #8

Sanctification / መለየት፣ መቀደስ ፍጽምና በዚህ ዘመን በብዙዎች እንደምንገምተው

አይነት ፍጽምና ላይ መምጣት የሚያሳይ አይደለም። ለምሳሌ አሮንና ልጆቹ የተቀቡት የተለየውን

የእግዚአብሔር ሥራ ለመስራት የሚያስችል ስልጣንንና እውቀትን ሃይል ለመቀበል ነው። ሥጋችን

እግዚአብሔር ወደ ክብር ሳይለውጠው ወይም የመጀመሪያው ትንሣኤ ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ ፍጽምና

ክብር በአካል አይገለጥም። ይህ ማለት ግን እንደ ፈለግን እንኖራለን ማለት አይደለም!!!!

እርግጥ ነው እኛ ከምንገምተው አይነት ቅድስና ይልቅ ይህን የእግዚአብሔር የቅድስና

ሕይወትና እውቀት ከእግዚአብሔር ከራሱና ከአፉ ቃል የተማርነው ሊሆን ይገባናል። በሰው እውቀትና

በአዳማዊ የራስን ጽድቅ ማቆም እና በራስ ጥረት የሚደረግ ሥራ አይደለም። በእግዚአብሔር ሕግ

የሚደረግ ሥራ እንጂ በወግና ሥርዓት፣ በአሮጌቶች ተረት መጻፎችና ፈሪሳዊያን ትምህርት የሚደረግ

አይደልም። ኢየሱስ በምድር በነበረበት ወቅት የነበሩ ካህናቶችም ችግራቸው ይህ ነበር። እግዚአብሔርን

ከመስማት ይልቅ ወግና ሥርዓታቸው ላይ ያተኮሩና የእግዚአብሔርን ሕግ ሃይል ያሳጡት ነበሩ።

“ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል

ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።” “Making the word of God of none effect through your tradition,

which ye have delivered: and many such like things do ye. ” ማር.7፥13

ስለዚህም በሌዊና በአሮን ክህነት ሥር ተከትለው ክህነታቸውን ያቀለሉና የእግዚአብሔር

ሕግ ጉልበት አልባ፣ ውጤት አልባ፣ ፍሬ ቢስ ያደርጉ ካህናት ከክህነቱ ቢሮ ሥራ ወድቀዋል። ደግሞም ወደ

ቅድስተ ቅዱስንም እዳይገቡ ተደርገዋል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቅባትን፣ ስልጣንንና ሕግን

ለራሳቸው ጥቅምና ለወግ ስርዓታቸው ስለተጠቀሙበት ነው። ስለዚህም እግዚአብሔር በመልከ ጸዲቅ

ክህነት ተካቸው። ኢየሱስ ደግሞ በመልከ ጸዲቅ ክህንት የሆነ ሊቀ ካህናችን ነው። ይህ የመልከ ጸዲቅ

ክህነት ደግሞ ትክክለኛውን የእግዚአብሔር ቅባት የተቀበለው ሲሆን በሰማያዊው መቅደስ የምልጃን

ሥራ ለመስራት ወደ ቅስተ ቅዱሳን ለመግባት ብቃትን አግኝቷል።

“ዚያም ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው፥ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ

ገባ።”ዕብ.6፥2 “እነርሱም ያለ መሐላ ካህናት ሆነዋልና፤ እርሱ ግን፦ ጌታ፦ አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት

ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ ማለ አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት ከመሐላ ጋር ካህን ሆኖአልና ያለ መሐላ ካህን

እንዳልሆነ መጠን፥ እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።”ዕብ.7:፥20-22

www.tlcfan.org 6
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #8

መልከ ጸዲቅ ማለት የጽድቅ ንጉስ "King of Righteousness" ማለት ነው። ይህ ሥም የሳሌም

ንጉስ ከሚለው ጋርም ይያያዛል። በመልከ ጸዲቅ ክህነት ሥር ያሉ ካህናትም እንደ ስማቸው ከኖሩ እንደ

ኢየሱስ አካልነታቸው ከዚህ ክህነት ተካፋይና ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የመግባትን ፍቃድ ያገኛሉ። ራእይ 20

እንደሚናገረው ሁሉ ካህናት ለዚህ የታደሉ አይደሉም። ምክንያቱም የሚገባቸው ሩጫና የእነርሱን ድርሻ

ስለማይፈጽሙ ድል ስለማይነሱ ነው።

“እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን

ሃይማኖታችንን እንጠብቅ። ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥

በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም። እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል

በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።”

ዕብ. 4፥14-16

እነዚህ ጽድቅ፣ ሰላም፣ ፍትህና ምህረት ደግሞም ጸጋና ሕግ ተስማምተው ሲገለጡ ማየት

የእግዚአብሔር ናፍቆት ነው። ከዚህ በፊት በቀደሙት የትምህርት ክፍሎች እንዳየን ማለት ነው። መዝ.

85፥10,

"Mercy and truth have met together; righteousness and peace have kissed each other."

“ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ።”

ይህ ባለፈው በቁጥር ስባት ትምህርታችን እንደተመለከትለው የምሕረት መክደኛውና ሕጉ

በቅድስተ ቅዱሳን በታቦቱ ላይ እንዴት እንደ ተሳሳሙ ተመልክተናል። ስለዚህ በድንጋይ ላይ የተጻፈውን

የእግዚአብሔር ሕግ ማወቅ ብቻ በቂ አይደለም። ማንኛውም ንጉሥ በቁጣ በጭካኔ በሕጉ ዙፋን ላይ

ሊቀመጥ ይችላል። ነገር ግን እንደ መልከ ጸዲቅ ያለ የሰላም ንጉሥ ግን ከሁሉ የሚበልጥ ነው። የሰላም

ንጉሥ በምህረት በእግዚአብሔር ሕግ በእውነትና በጽድቅ ይገዛል። ሕጉንም ለምህረትና ለሰላም እንዴት

እንደሚውል በትክክል ያውቃል። ሲፈርድም አይኑ እንዳየች ጆሮውም እንደስማች አይፈርጽም፤ በጽድቅ

ይፈርዳል። ፍርድንም በጽድቅ ሲያደርግ ሁሉ ሕዝቦች ጽድቅን በፍቅርና በምህረቱ ይማራሉ።

“ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥

መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች።”ኢሳ.26፥9

www.tlcfan.org 7
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #8

የጃሻርን መጽሐፍ ያነበባችሁ። መልከ ጸዲቅ የሰላም ንጉስ ከመሆኑ ባሻገር ኢየሩሳሌምን

የመሰረታት እርሱ እንደሆን ይናገራል። የመጀመሪያዋ የሳሌም ወይም የኢየሩሳሌም ንጉስ የነበረው የኖሕ

ልጅ ሴም ነው። ሴም የልጅነትን ሥልጣን ይዞ እስከ ይሳቅ ዘመን የኖረ የእግዚአብሔር ባሪያ ነው።

ለዚህም ነው አብርሃም ልጅነትን ሥልጣን ሳይቀበል ወደ ልጁ ወደ ይሳቅ የተላለፈው። ምክንያቱም ሴም

ገና በሕይወት ስለበር ነው። ዕብራውያን ጸሐፊ ጃሻርን ያነበበ ይመስላ። ለትውልዱ ቁጥር የለውም

የሚለው ቃል ሃሳብ የሴምን የእድሜ ባለጠግነት የሚገልጥ ነው።

ይህ ለጠቅላላ እውቀታችን ያህል ነው። ዋናው ቁም ነገር ግን ኢየሱስ የእኛ በእግዚአብሔር

የተቀባ ሊቀ ካህናች ነው። “በጌታም የተቀባውን ሳያይ ሞትን እንዳያይ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ነበር።”

ሉቃ.2፥26 “የምድር ነገሥታት ተነሡ አለቆችም በጌታና በተቀባው ላይ አብረው ተከማቹ ብለህ

የተናገርህ አምላክ ነህ።” ሐዋ.4፥26 “እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም

ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ

ጋር ነበረና፤”ሐዋ.10፥38 የእርሱ አካል የሆንን ከእርሱ ጋር በሁሉ የምንተባበርና የምንካፈል የዚህ

ቅባትም ተካፋዬች እንሆናልን ማለት ነው። ከቅዱሱ ቅባትም እንቀበላለን።

ክርስቶስ የሚለው ቃል ከግሪኩ በቀጥታ ሳይተረጎም የተወሰደ ሲሆን በዕብራይስጡ ደግሞ

መሲህ የሚለውን ቃል ይዛል። መሲሁ ወይም ክርስቶስ ማለት የተቀባ ማለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ

እንደ ካህናቶቹ የትም ሥፍራ ላይ በፍጥረታዊ ዘይት ሲቀባ አናየውም። መጥምቁ ዮሐንስም ቢሆን

ያጠመቀው በውሃ እንጂ በዘይት አልነበነም። ታዲያ ለምን እና እንዴት ክርስቶስ የተቀባ ተባለ?

ይቀጥላል …………………….

www.tlcfan.org 8
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #8

www.tlcfan.org 9

You might also like