You are on page 1of 86

መሠረተ ሃይማኖት

ስድስተኛ ክፍል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት


ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም
አቀፍ) የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተዘጋጀ ፳፲፭ ዓ.ም
ያግኙን

Email
office@eotc-gssu.org
YouTube
https://www.youtube.com/channel/
UC83LE1vp0FBsV2TEfcpSmUg
Facebook
http://facebook.com/EOTC.GSSU
Telegram
https://t.me/EOTCNSSU
Website
https://eotc-gssu.org/a/
Twitter
https://twitter.com/tibeb_felege

Copyright ©
፳፲፭
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት
ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ
አስኪያጅ እና የባህርዳር ሁገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ በሰንበት ትምህርት ቤቶች


ማደራጃ መምርያ የበላይ ሊቀጳጳስና የሰሜን ሸዋ ሀገረ
ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ማወጫ
ምዕራፍ አንድ
የነገረ ቅዱሳን ትምህርት መሠረታዊያን
፩.፩ መግቢያ................................................. ፬
፩.፪ ትርጓሜ................................................. ፭
፩.፫ የባሕርይ እና የጸጋ ቅድስና...................... ፭
፩.፫.፩ የባሕርይ ቅድስና.................................. ፭
፩.፫.፪ የጸጋ ቅድስና........................................ ፮
፩.፬ ቀኖና ቅድስና በቤተክርስቲያን................... ፯
፩.፭ የነገረ ቅዱሳን ትምህርት አስፈላጊነት........................... ፱
፩.፭.፩ የእምነት ጽናትን እንማራለን............................ ፲
፩.፭.፪ በረከትን እናገኛለን........................................... ፲
፩.፭.፫ መንፈሳዊ ሕይወት እንማርባቸዋለን።.............. ፲፩
፩.፫.፬ የተጋድሎ ውሎአቸውን እንድናውቅ ይረዳናል..... ፲፩
፩.፭.፭ በቃል ኪዳናቸው እንድንጠቀም ያደርገናል......... ፲፪
፩.፭.፮ አሰረ ፍኖታቸውን እንድንከተል........................ ፲፪

ምዕራፍ ሁለት
ቅዱሳን እነማን ናቸው?
፪.፩. ቅዱሳን ሰዎች.............................................................. ፲፮
፪.፪. ቅዱሳን መላእክት........................................................ ፲፱
፪.፫. ቅዱሳት መጻሕፍት..................................................... ፳
፪.፬. ቅዱሳት ሥዕላት ......................................................... ፳፩
፪.፭. ንዋያተ ቅድሳት.......................................................... ፳፪
፪.፮. ቅዱሳት መካናት ........................................................ ፳፫
የምዕራፉ ማጠቃለያ


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ምዕራፍ ሦስት
መዓርጋተ ቅዱሳን.................................................... ፳፰
፫.፩ ንጽሐ ሥጋ....................................................... ፴
፫.፪ ንጽሐ ነፍስ........................................................ ፴፬
፫.፫ ንጽሐ ልቡና...................................................... ፴፮

ምዕራፍ አራት
የቅዱሳን ምልጃ
፬.፩. ምልጃ ምንድን ነው?................................................. ፵፪
፬.፪. ምልጃ በአጸደ ሥጋ.................................................... ፵፬
፬.፪.፩. የቅዱሳን ምልጃ በዘመነ ብሉይ ........................ ፵፬
፬.፪.፪. የቅዱሳን ጻድቃን ምልጃ በሐዲስ ኪዳን............ ፵፱
፬.፫ አማላጅነት በዘመነ ሐዋርያት...................................... ፶
፬.፬. ቅዱሳን አማላጅነት በአጸደ ነፍስ (ከሞት በኋላ)........... ፶፪

ምዕራፍ አምስት

፭.፩. የቅዱሳን ክብርና ሥልጣን...................................... ፷


፭.፩.፩. የቅዱሳን ክብር............................................ ፷፩
፭.፩.፪. የቅዱሳን ሥልጣን....................................... ፷፬
፭.፪. ቅዱሳት ሥዕላት................................................... ፷፭
፭.፪.፩. የቅዱሳት ሥዕላት ትርጉም......................... ፷፭
፭.፪.፪. የቅዱሳት ሥዕላት ጥቅም.................................... ፷፮
፭.፪.፫. ቅዱሳት ሥዕላት በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን.......... ፷፰
፭.፪.፬. የቅዱሳት ሥዕላት አሳሳል በኢትዮጵያ............. ፷፰
ዋቢ መጻሕፍት


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ምዕራፍ አንድ
የነገረ ቅዱሳን ትምህርት መሠረታዊያን

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

፩ የነገረ ቅዱሳንን ትርጉም ይገልጻሉ።


፪ የባህርይ እና የጸጋ ቅድስናን ምንነት ያብራራሉ።
፫ የቅዱሳን አሠያየም እንዴት እንደሆነ ይገልጻሉ።
፬ የነገረ ቅዱሳንን ትምህርት አስፈላጊነት ይገልጻሉ።

የመክፈቻ ጥያቄዎች

፩. እስከ ዛሬ ድረስ ከምታዉቋቸው ቅዱሳን መካከል የአንዱን ስም


ጥቀሱና ቅድስናው የተገለጠበትን መንገድ ዘርዝሩ።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

፩.፩ መግቢያ

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ዓለምን ፈጥሮ


የሚገዛ፣የሚመግብ እና የሚጠብቅ፤የሰው ልጅንም ከሁሉ ፍጥረት በላይ
አክብሮ በአርአያውና በአምሳሉ እንደፈጠረ፤ የሰው ልጅም ከእግዚአብሔር
ጋር ተጣልቶ ከገነት ከወጣ ወደ ምድረ ፋይድ ከወረደ በኋላ አምላካችን
ሰውን ያድን ዘንድ ወደ ምድር መጥቶ ለኛ የአርአያ እና የቤዛነት ሥራን
እንደሠራ እርሱን እንድንመስል ፍለጋውንም እንድንከተል ዘወትር
ታስተምራለች። ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው “እኔ ክርስቶስን እንደምመስል
እኔን ምሰሉ።” ፩ኛ ቆሮ ፲፩፥፩

በእግዚአብሔር አነሰሳሽነት ቅዱሳን ሰዎች ተመርጠው መጽሐፍ ቅዱስ


እንዲጻፍ የተደረገውም ይህንን የእግዚአብሔር ሥራ ለሰዎች ለመግለጽ
ነው። ነገር ግን አስቀድሞ እግዚአብሔር ፍጥረትን የፈጠረው፣ ሰውንም
ከሁሉ ያከበረው እንዲሁ በፍቅር ነውና በዚህ የእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ
ሰዎችንም ተሳታፊዎች እንዲሆኑ፣ አብረዉት እንዲሰሩ ይጋብዛል።
እግዚአብሔር ሰዎችን ይመርጣል፣ ይቀድሳል፣ አብረዉት የሠሩትን
ሕጉን የጠበቁትን ደግሞ ይሸልማል፣ አክሊልን ያቀዳጃል። ለዚህ ነው
ቅዱስ ጳውሎስ “ሩጫዬን ጨርሻለሁ፣ ተጋድሎዬን ፈጽሜአለሁ።
ከእንግዲህ ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረከባል።” ያለው።
፪ኛ ጢሞ ፬፥፯

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር እንዲህ አለ፣ እንዲህ አደረገ”


የሚለውን ያህል ቅዱሳንንም እየጠራ “አብርሃም እንዲህ አደረገ፣ ቅዱስ
ጳውሎስ ይሄንሠራ” እያለ የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለው ከእርሱ ጋር
በመተባበር፣ እርሱ እየመራቸው፣ መንገዱን እየነገራቸው፣ ሲደክሙ
እያበረታቸው የሠሩትን ሥራ ይናገራል።
እኛም በዚህ ትምህርት እነዚህ እግዚአብሔርን በሥጋቸው ያከበሩትን፣

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ራሳቸውን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ታቦት ያደረጉትን እና ሰውነታቸውን
ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ ቅዱስ መስዋዕት ያደርጉትን ቅዱሳን
ሰዎች ሕይወታቸውን እንማራለን። በሕይወታቸው እንድንማር፣
በቃል ኪዳናቸው ታምነን ድኅነትን እንድናገኝ አምላካችን ቅዱስ ፈቃዱ
ይሁንልን!

፩.፪ ትርጓሜ
“ነገረ ቅዱሳን” የሚለው ቃል ከሁለት ቃላት የተገኘ ጥምር ቃል ሲሆን
ትርጉሙም፦
. “ነገር” የሚለው ቃል በቤተክርስቲያን አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ወይም
የቤተክርስቲያን የትምህርት ዘርፍ ወይም አይነት አጉልቶ ለማሳየት
የሚውል ቃል ነው። ለምሳሌ፦ ነገረ መለኮት፣ ለገረ ማርያም፣ ነገረ
ቤተክርስቲያን. . .
• “ቅዱስ” የሚለው ቃል “ቀደሰ” ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘነው።
ትርጉሙም ለየ፣አከበረ፣ አመሰገነ፣ አገነነ፣ መረጠ፣ አጠራ፣ አነጻ፣ ባረከ
ወዘተ … ማለት ነው፡፡በመሆኑም ቅዱስ ስንል የተለየ ፣ የተከበረ ፣
የተመረጠ ፣ የተመሰገነ ፣ የገነነ ፣ የጠራ የነጻ ማለት ነው።
. ስለዚህ ነገረ ቅዱሳን የተቀደሰ ሕይወት ስለኖሩ አባቶች እና እናቶች
ከልደታቸው እስከ ዕረፍታቸው ሕይወታቸውን፣ እንዲሁም ሌሎችም
ቅዱሳን ብለን ስለምንጠራቸው መካናት እና ንዋያት የምናጠናበትና
የምንማርበት የትምህርት ክፍል ነው።

፩.፫ የባሕርይ እና የጸጋ ቅድስና


፩.፫.፩ የባሕርይ ቅድስና
ቅዱስ የሚለው ቃል ከሁሉም በላይ ጥቅም ላይ የሚውለው (የሚያገለግለው)
ለሠራዊት ጌታ ለቅዱስ እግዚአብሔር ነው። ቅድስና የባሕርይ
ገንዘብነቱ ለእግዚአብሔር ብቻ ነው።ይህም ማለት ቅድስናው ከእርሱ
የማይለይ ከማንም ያልተቀበለውና የማይቀበለው፣ ማንም ሊወስድበት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

የማይችለው፣ ለሌላ ሲሰጥም የማይጐድልበትና የማይከፈልበት የራሱ


ገንዘብ ብቻ ማለት ነው። ቅድስና እና እግዚአብሔር ተለያይተው ሊነገሩ
አይችሉም፣ አይገባምም። በእግዚአብሔር ዘንድ ከቅድስና በስተቀር ሌላ
ነገር አይታሰብም። በቅድስናው ርኩሰት፣ በጻድቅነቱ (እውነተኛነቱ)
ሐሰት የሌለበት ነውና።

መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ እግዚአብሔርን ስም ሲጠራ ቅዱስ የሚለውን


ቃል ወይ በገላጭነት ወይም ደግሞ ራሱን ችሎ እግዚአብሔር የሚለውን
ስም ይዞ እናገኘዋለን።
ምሳሌ፦
. “እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ ይላል ቅዱሱ።” ኢሳ
፵ ፥ ፳፭
. “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ
የተነሣ ተሞልታለች።” ኢሳ ፮ ፥ ፫
. “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።”
ዘሌ. ፲፱፥፪
ስለዚህ አምላካችን እግዚአብሔር የባሕርይው መገለጫ ሁኖ የሚጠራበት
ስሙም “ቅዱስ” የሚለው ነው።

፩.፫.፪ የጸጋ ቅድስና


ጸጋ ማለት የቃሉ ትርጉም ቸርነት፣ በጎነት፣ ምሕረት፣ ያለ ብድራት
እና ያለ ዋጋ የሚደረግ ሥጦታ ማለት ነው። በመሆኑም ማናቸውም
ከእግዚአብሔር የሚገኝ ሥጦታ ሁሉ ጸጋ ይባላል። ስለዚህ የቨጸጋ
ቅድስና ማለትም ከቅዱስ እግዚአብሔር በስጦታ የተሰጠ የተገኘ ማለት
ነው። በባሕርዩ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ የፍጡራን
ቅድስና መገኛውና ምንጩ እርሱ ብቻ ነው። ሰው ወይም ማናቸውም
ነገር ለእግዚአብሔር አገልግሎት ሲለይ ቅዱስ ይባላል። ስለዚህ ቅዱስ
ብለን የምንጠራቸው ሁሉ ቅዱስ የሚሆነው ከእግዚአብሔር የተነሣና

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ለእግዚአብሔር የተለየ ስለሆነ ነው።እግዚአብሔር ቅዱስ በመሆኑ
ለእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ ቅዱስ መሆን አለበት።

በባሕርይው ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጸጋ የተዋሐዳቸው፣ በረድኤት


ያደረባቸው ሰዎች ቅዱሳን ይባላሉ። ይኸውም በሃይማኖት በመኖር፣ በጎ
ምግባራትን ለመሥራት ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው ለማስገዛት
ከክህደትና ክርክር፣ ከጥፋት ከኃጢአት በመለየታቸው ነው።

ቅዱስ የሚለው ቃል አንድን ነጠላ ነገር የሚያመለክት ሲሆን፣ቅዱሳን


የሚለው ደግሞ ብዛትን የሚያመለክት ነው።
. “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።”
ዘሌ ፲፱፥፪፣
. “የጠራችሁ እግዚአብሔር ቅዱስ እንደሆነ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።”፩ጴጥ
፩፥፲፭
. “ብርና ወርቅ ሁሉ የናስና የብረት ዕቃ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ
ይሁን፤ ወደ እግዚአብሔርም ግምጃ ቤት ይግባ።” ኢያ ፮፥፲፱

፩.፬ ቀኖና ቅድስና በቤተክርስቲያን

ቀኖና ማለት ሕግ፣ ሥርዓት፣ ደንብ፣ ፍርድ፣ ቅጣት፣ መጠን፣ ልክ


ማለት ነው። ይኸውም አንድን ነገር ለመለካት፣ ለመመዘን፣ ትክክል
መኾኑንና አለመኾኑን ለመለየት፣ መጠኑን ለማወቅ የሚያገለግል
መለኪያ ወይም መስፈሪያ ነው፡፡

ስለዚህ ቀኖና ቅዱሳን ሲባል የቅዱሳን አሠያየም ሥርዓት፣ ሕግ ማለት


ነው። በቅድስት ቤተክርስቲያን ቅዱሳን “ቅዱስ “እየተባሉ የሚሰየሙት
በድምጽ ብልጫ አይደለም። ቅዱስ የሚያሰኛቸው ሕይወታቸው ነው።
ስለእኛ ብሎ ሰው የሆነውን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

አብነት አድርገው እርሱን ለመምሰል የተጋደሉ እግዚአብሔርም ራሱ


የመሰከረላቸው ናቸው።

ቅዱስ ጳውሎስ በሐዋርያዊ አግልግሎቱ በብዙ ድካም፣ ርሃብ እና ጥም፣


እንቅልፍ ማጣት፣ እስርና እንግልት ሳይሰለች የክርስቶስን ወንጌል ከሰበከ
በኋላ ወደ አምላካችን ክርስቶስ የመሄጃ ጊዜው ሲደርስ “መልካሙን
ገድል ተጋድያለሁ፥ ሩጫዬን ጨርሻለሁ፤ ሃይማኖቴን ጠብቄ አለሁ፤ወደ
ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል። ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው
ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል” እንዳለው ቅዱሳን የምንላቸው መልካሙን
ገድል ተጋድለው ሩጫቸውን ጨርሰው የድል አክሊላቸውን ክርስቶስ
ያስረከባቸውን ነው። ፪ኛ ጢሞ ፬፥፯፣፰

በተጨማሪም በተጋድሎው ያገኘውን ቅድስና ‘እኔ ክርስቶስን እንደምመስል


እኔን ምሰሉ።’ በማለት ገልጿል። (፩ኛ ቆሮ ፩፥ ፲፩)
በመጽሐፍ ቅዱስ ልዑል እግዚአብሔር ያከበራቸውን ቅዱሳን እናት እና
አባቶችን ክብራቸውን በሚከተለው መልኩ ሲገልጥ ወይም ሲያወድሳቸው
እናገኛለን፦
• “እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ
አልተነሳም።” ማቴ ፲፩፥፲፩
• “ኢዮብ የሚባል ሰው ነበረ፤ ፍጹም ቅንና እግዚአብሔርን የሚፈራ
ከክፋትም የራቀ ነበረ።” ኢዮብ ፩፥፩
• “ሁለቱም በጌታ ሕግጋት እና ትእዛዛት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ
በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ።” ሉቃ ፩፥፮

ቅዱሳንን በቀኖና ወይም በሥርዓት ደረጃ ማክበር የተዠመረው ከኹለተኛው


መቶ ክፍለ ዘመን አንሥቶ ነው፡፡ ነገር ግን ይኽን ያደረገው ቅዱስ
ሲኖዶስ ሳይኾን ሕዝቡ ወይም ምእመኑ ራሱ ነው፡፡ በዚኽም ቀድመው
ይታሰቡና ይከበሩ የነበሩት ቅዱሳን ሰማዕታት ናቸው፡፡ ከአራተኛው

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
መቶ ክፍለ ዘመን ዠምሮ ግን አንዳንድ ሰዎች በራሳቸው እይታ ቅዱስ
እንደኾነ የሚያስቡትን ኹሉ ቅዱስ ለማስባል ስለተነሣሡ ቤተክርስቲያን
በጉባኤ ደረጃ ቀኖና ቅዱሳን ማውጣት ዠመረች፡፡ ቤተክርስቲያን ቀኖና
ቅዱሳን ማውጣት ዠመረች ማለት ግን ለሰዎቹ ቅድስናን ሰጠች ማለት
ሳይኾን ለቅድስናቸው ዕውቅናን ሰጠች ለማለት ነው፡፡ አንድን ቅዱስ
ቅዱስ ለማለትም መስፈርቶች አሉት፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያኽል፡-`

• የቀና ሃይማኖት ሊኖረው ይገባል።


• የቅድስና ሕይወት ሊኖራቸው ይገባል።
• በቤተ ክርስቲያን ጉባኤያት ዕውቅና ወይም ምስክርነት የተሰጣቸው።
(ዜና አበው)

እንዲኽ በቀኖናው መሠረት ቅዱስ የተባለው ታላቅ ሰው ቅድስና ሲሰጠው


የሚከተሉት ነገሮች ይፈጸሙለታል፡-
. በስሙ ቤተክርስቲያን ይታነጽለታል፤
. ገድል ይጻፍለታል፤
. በዓል ይደረግለታል (ሰማእትነት የተቀበለበት ቀን (ለሰማእታት)
የዕረፍት ቀን ወዘተ፤
. ቅድስናውን አጕልቶ የሚያሳይ ሥዕል ይሣልለታል፤
. ዐፅሙ በክብር እንዲያርፍና ምእመናን እንዲያከብሩት ይደረጋል፤
. ምእመናን በስሙ ሊሰየሙና ውሉደ እግዚአብሔር ሊባሉ ይችላሉ።

፩.፭ የነገረ ቅዱሳን ትምህርት አስፈላጊነት

ይኸውም ከትሩፋታቸው ብዙ እንድንማር፣ በቃል ኪዳናቸው እንድንጠቀም፣


አሰረ ፍኖታቸውን እንድንከተል፣ አማላጅነታቸውን እንድንጠይቅ ነው፡፡
አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን
ደግሞ አጸደቃቸው፤ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው። (ሮሜ ፰፥ ፴)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

፩.፭.፩ የእምነት ጽናትን እንማራለን


ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ
የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው፤ ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው
በዚህ ነውና ”በማለት በብሉይ ኪዳን ዘመን በእምነታቸው ታላቅ ሥራ
የሠሩትን ዋና ዋናዎቹን አባቶች እና እናቶች ስማቸውን፣ መዓርጋቸውንና
ግብራቸውን ጽፎ በማስረጃነት ጠቅሷቸዋል። (ዕብ ፲፩፥፩-፵) ከዚህም
በመቀጠል ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን ዋኖቻችሁን
አስቡ፤ የሕይወታቸውንም ፍሬ እያያችሁ በእምነት ምሰሏቸው” እያለ
እነዚህን ቅዱሳን አበው በእምነት ልንመስላቸው እንደነእርሱም መንፈሳዊ
ፍሬ ልናፈራ እንደሚገባ ያሳስባል። ዕብ ፲፫፥፯

በዘመናችን ብዙ ሰው ሕግጋተ እግዚአብሔርን እንደሸክም፣ ዕዳ


ቢቆጥራቸውም እግዚአብሔርን አምኖ አጋዥ አድርጎ በሕጉ ለመኖር
ለወሰኑ ሰዎች ግን ጌታ እንዳለው ሽክሙ ቀላል፣ ቀንበሩም ልዝብ
ነው። ማቴ ፲፩፥፴ በክርስትና ሕይወት ስንኖር በመከራ ሁሉ በመደሰት፣
ለሚሰድበን እና ለሚያበሳጨን ለሚገድለን ሰው እየጸለይን መኖር
እንደሚቻል የጌታን አሰረ ፍኖት የተከተሉ ቅዱሳን ማሳያዎችና እውነተኛ
ምስክሮች ናቸው። የሐዋ ፯፥፶፱

፩.፭.፪ በረከትን እናገኛለን


“በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው፣ የጻድቅም መታሰቢያ ለበረከት ነው።”
(ምሳ፲፥፮) እንደተባለ ቅዱሳኑን በማክበር በረከት እናገኛለን እግዚአብሔር
አብርሃምን “እባርክሃለሁ፣ ስምህንም አከብረዋለሁ፣ ለበረከትም ሁን፣
የሚባርኩህንም እባርካለሁ፣ የሚረግሙህንም እረግማለሁ” (ዘፍ ፲፪፥፪)
በማለት ስሙን የሚያከብሩትን፣ በቃል ኪዳኑ የሚታማመኑትን
እንደሚባረካቸውና አብርሃምን ለበረከት እንዳደርገው እናስተውላለን።
በቅድስናና በተጋድሎ በአገልግሎት በጸጋ አብርሃምን የመሰሉ ቅዱሳን
ሁሉ የበረከት ምንጭ ናቸው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

፩.፭.፫ መንፈሳዊ ሕይወት እንማርባቸዋለን።


ቅዱሳን ሕይወታቸው በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በትሕትና፣ በተስፋ፣
በትዕግሥት፣እና በአርምሞ (በዝምታ) የተሞላ ነው። ከእግዚአብሔር
ጋር፣ ከበጐና ክፉ ሰዎች ጋር በመከራና በደስታ ጊዜ ሕይወታቸውና
አኗኗራቸው እንዴት እንደነበር መማር እንችላለን።
• “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ
የኑሮአቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሉአቸው” (ዕብ
፲፫፥፯) እንዲል።

እንደ እኛ ሰዎች ሆነው ድንቅ ነገር እንዲያደርጉ ያገዛቸውን እምነታቸውን፣


መንፈሳዊ ሕይወታቸውን አይተን እንደእነርሱ ሕጉን ጠብቀን በጾም፣
በጸሎት፣ መንፈሳዊ ፍሬ በማፍራት ለመኖር ያግዘናል።
ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ ስለ ጸሎት ኃያልነት እና በትክክል ጸሎት
የሚያደርግሰው ድንቅ ነገር ማድረግ እንደሚችል ሲናገር “ኤልያስም
እንደ እኛ ሰው ነበረ፣ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፣ በምድር ላይም
ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም። ሁለተኛም ጸለየ ሰማዩ ዝናብን፣
ምድሪቱም ፍሬን ሰጠች” ይላል። (ያዕ. ፭፥፲፯)

፩.፭.፬ ተጋድሏቸውን እንድናውቅ ይረዳናል


የቅዱሳን ሕይወት በተጋድሎ የተሞላ ነው ጌታችን በወንጌል “በዓለም
ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ”
(ዮሐ ፲፮፥፴፫) በማለት እንደተናገረው በፍጹም እምነትና ትዕግሥት በመከራ
መካከል አልፈዋል፤ በሰይፍ ተመትረዋል፤ በመጋዝ ተሰንጥቀዋል፤ በእሳት
ተቃጥለዋል፤ ተሰደዋል፤ ተርበዋል፤ ተጠምተዋል፤ ታርዘዋል።(ዕብ ፲፩ ፥፴፯)
ነገር ግን ይህንን ሁሉ መከራ በደስታ እየተቀበሉ “ወደ እግዚአብሔር
መንግሥት በብዙ መከራና ድካም እንገባ ዘንድ ያስፈልጋል፥ ይሉ ነበር።”
(የሐዋ. ፲፬ ፥ ፳፪)

፲፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ “ወንድሞች ሆይ የእምነታችሁ መፈተን


ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ
እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት” (ያዕ ፩፥፪) እንዳለ መከራውን ሁሉ በደስታ
ተቀብለውታል የተጋደሉትም እስከሞት ድረስ ነው። በዚህ ጉዞአቸው
ሁሉ በአሸናፊነት የተወጡ የሃይማኖት ጀግኖች ናቸው።

፩.፭.፭ በቃል ኪዳናቸው እንድንጠቀም ያደርገናል


ከዘመነ አበው ጀምሮ የነበሩ ቅዱሳን በእምነታቸውና በአካሄዳቸው
በሕይወታቸው ፍጻሜም እግዚአብሔርን ደስ ስለአሰኙት የተለየ ቃል
ኪዳን ተቀብለዋል። ይህም ቃል ኪዳን የሚጠቅመው በእነርሱ ቅድስናና
ተጋድሎ የሚያምኑትን፣ በምልጃቸውና በጸሎታቸው የሚተማመኑትን
ሰዎች ነው። ስለዚህ በቃልኪዳናቸው ታምነን ልንጠቀም ሰያስፈልጋል።
ጌታችንም በማቴዎስ ወንጌል ደቀመዛሙርቱን ሲያሰማራ እንዲህ ብሏል
“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፣ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።
ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፣ ጻድቅንም በጻድቅ
ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ
ለአንዱ ቀዝቃዛ ውኃ በደቀመዝሙሬ ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም።” ማቴ ፲ ፥፵-፵፪

፩.፭.፮ አሠረ ፍኖታቸውን እንድንከተል


ከእርሻ ሜዳ የተጠራው ነቢዩ ኤልሳዕ እግዚአብሔር ኤልያስን በዐውሎ
ነፋስና በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ሊወስደው በወደደ ጊዜ ኤልያስ
ኤልሳዕን፦ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ልኮኛልና በዚህ ቦታ ቆይ ቢለውም
ኤልሳዕ ግን ሕያው እግዚአብሔርን በሕያው ነፍስህ እምልልሃለሁ
አልለይህም ነበር ያለው። (፪ነገ ፪፥፩) ኤልያስን የተከተለ ኤልሳዕ በረከቱ
እጥፍ ሁኖ ስለአደረበት፦
. በመጐናጸፊያው የዮርዳኖስን ወንዝ ከፈለ
. ሙታንን በአካለ ሥጋ እያለና ከሞተ በኋላ ማስነሣት ችሏል
፲፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
. የመረረውን ውኃ ማጣፈጥ ችሏል
. እህል በጠፋበት ዘመን ማበርከት ችሏል
. በሃይማኖታዊ አቋም ከነገሥታት ጋር ታግሏል
ሌሎችም እነሐዋርያው ቅዱስ አትናቴዎስ፣ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣
ኢትዮጲያዊው ሊቅ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ …ሃይማኖታዊ
ጽናታቸው ፥በመከራ ጊዜ ትዕግስታቸው፥የጸሎት ሕይወታቸው፥ በጥንቃቄ
የተሞላ ስብዕናቸውና ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባራቸው፥የአገልግሎት
ትጋታቸው ዛሬ ላይ ለምናገኘው አቅምና ብርታት ይሆናል፤ የሄዱበትን
ፈለግ እንድንከተል ያደርገናል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦
• ሰይጣን የብርሃን መልአክ መስሎ እንዳያስተን እንጠበቃለን።
• ቤተክርስቲያን መታሰቢያቸውን ለይታ ለመፈጸምና ለእኛ ለማሳወቅ
ያስችላታል።
• ምዕመናን በክርስቶስ የወይን ግንድነት ላይ ቅርንጫፍ በመሆን
ብዙ ፍሬ ያፈሩ የሃይማኖት አባቶቻቸውን አውቀው ከአታላዮች፣
ከአስመሳዮች፣ከሐሳውያን እንድንጠበቅ ይረዱናል፡፡

፲፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

የምዕራፉ ማጠቃለያ ጥያቄዎች


ክፍል ፩፡ ትክክል የሆነውን እውነት ያልሆነውን ሐሰት በማለት መልሱ።
፩ ቅዱሳን ቅድስናቸው የሚወሰነው በድምጽ ብልጫ ነው።
፪ ደግ ሥራ የሚሠራ ሰው ሁሉ ቅዱስ ነው።
፫ ኤልሳዕ በአጽሙ ሙት አስነስቷል።

ክፍል ፪፡ ትክክለኛውን መልስ ምረጡ


፩ ቅዱሳን‘ ቅዱስ’ ተብለው ሲሰየሙ ምን ይደረግላቸዋል?
ሀ. ጽላት ይቀረጽላቸዋል። ሐ. ገድል ይጻፍላቸዋል።
ለ. አጽማቸው በክብር ያርፋል። መ. ሥዕል ይሳልላቸዋል
ሠ. ሁሉም
፪ ከሚከተሉት ውስጥ የባሕርይ ቅድስና ያለው የቱ ነው?
ሀ. ቅዱስ ጳዉሎስ ለ. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐ. ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
መ. እግዚአብሔር

ክፍል ፫ ፡መልስ ስጡ /ዘርዝሩ


፩ ቅዱሳንን መሰየም እንዴት እንደተጀመረ አብራሩ።
፪ ቅዱሳን ‘ቅዱስ’ ተብለው የሚሰየሙ ምንምን ሲያደርጉ ነው?
፫ የነገረቅዱሳንትምህርትንመማርምንጥቅምያስገኝልናል?

፲፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ምዕራፍ ሁለት

ቅዱሳን እነማን ናቸው?

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• ቅዱሳን የምንላቸው እነማን እንደሆኑ ይዘረዝራሉ።

የመክፈቻ ጥያቄዎች

፩ ቅዱሳን ሲባል ከቅዱሳን ሰዎች ውጪ የምታስታዉሱት ወይም


ትዝ የሚላችሁ ምንድን ነው?

፲፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

፪.፩. ቅዱሳን ሰዎች

ቅዱሳን ሰዎች ለተለያየ ተግባር ነገር ግን ለአንድ ዓላማ በእግዚአብሔር


የተጠሩ ሰዎች ናቸው። መጠራት ብቻ ሳይሆን ከተጠሩት መካከል
ተለይተው የተመረጡ ናቸው። “የተጠሩ ብዙ ናቸው የተመረጡ ግን
ጥቂቶች ናቸው” የተባለው ለዚህ ነው። (ማቴ ፳፪፥፲፬) አገልግሎታቸውም፣
ጸጋቸውም ልዩ ልዩ ነው። ይህንን በተመለከተ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ
ይላል።

‘‘እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች


ናችሁ።እግዚአብሔርም በቤተክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን
፥ሁለተኛም ነቢያትን፥ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት
ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥አገዛዝንም፥ የልዩ
ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል። ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ
ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸውን? ሁሉስ ተአምራትን
ይሠራሉን? ሁሉስ የመፈወስ ስጦታ አላቸውን? ሁሉስ በልሳኖች
ይናገራሉን? ሁሉስ ይተረጉማሉን? ነገር ግን የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ
በብርቱ ፈልጉ። ደግሞም ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ አሳያችኋለሁ።” ፩ኛ
ቆሮንቶስ ፲፪፥፳፯-፴፩

ስለዚህ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ከእኔ ተማሩ፣ እኔ


የዋኅ በልቤም ትሁት ነኝና” እንዳለ በሄደበት መንገድ ሄደው እርሱን
የመሰሉት ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ መነኮሳት፣ ሰማዕታት፣ ጻድቃን፣
ነገሥታት፣ ጳጳሳት፣ ሊቃውንት ሁሉ ቅዱሳን ናቸው። ይህ ማለት ግን
እግዚአብሔር ጥቂት ሰዎችን ብቻ ቅዱስ እንዲሆኑ መርጧል፣ ሌላውን
አልመረጠም ማለት አይደለም። ከቤት ውስጥ የጸሐይ ብርሃን የሚገባው
እንደተከፈተው መስኮት እና በር መጠን እንደሆነው ሁሉ ቅዱሳንም
ቅዱስ የሆኑት ሁላችንም እንድንተገብረው፣ እንድንኖርበት የታዘዝነውን
፲፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ሕይወት እነርሱ በትክክል ስለኖሩት እና እግዚአብሔርንን ስላከበሩት፣
እርሱ በረድኤት ስላደረባቸው ነው። ይህን በተመለከተ ጌታችን በወንጌል
“የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፤ ወደ እርሱም
እንመጣለን በእርሱም ዘንድ ማደሪያ እናደርጋለን” ያለውን ነው በትክክል
የተገበሩት እና የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆኑትን ናቸው። (ዮሐ ፲፬፥፳፫)
ስለዚህ እነዚህን ቅዱሳን ጥቂት ጥቂት እነማን እንደሆኑ እንደሚከተለው
እናብራራቸዋለን።

• ቅዱሳን አበው፡- መጻሕፍት ሳይጻፉላቸው ፥መምህራን ሳይላኩላቸው፤በሕገ


ልቡና በቃል ብቻ የተላለፈላቸውን ይዘው፤እንዲሁም በሥነ ፍጥረት
በመመራመር ፈጣሪያቸውን አምነው እርሱ የሚወደውን ሥራ የሠሩና
በጣዖት አምልኮ ራሳቸውን ያላረከሱ አባቶች ቤተክርስቲያናችን ቅዱሳን
ትላቸዋለች፡፡ ለምሣሌ አበ ብዙኃን አብርሃም (ኩፋሌ ፵፪-፵፬፣ ፲፩÷፩) ፣
ይስሐቅ ፣ ያዕቆብ ወዘተ።

• ቅዱሳን ነቢያት፡- እግዚአብሔር ከማኅፀን ጀምሮ ጠርቶ መርጧቸው፥ሀብተ


ትንቢትን አጐናጽፏቸው ያለፈውንና ወደፊት የሚሆነውን በእርግጠኝነት
እየተናገሩ ሕዝቡን ይመክሩትና ይገስጹት የነበሩ ቤተክርስቲያን በቅድስና
ማዕረግ የምትጠራቸው አባቶች ናቸው፡፡
፪ኛ ጴጥ ፩÷፳፭‹‹ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፣ዳሩ ግን
በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው
ተናገሩ›› እንዲል፡፡

• ቅዱሳን ሐዋርያት፡- በነቢያት የተነገረውን ቃለ ትንቢት መድረሱንና


በዘመናቸው መፈጸሙን ለዓለም እንዲያስተምሩ ጌታችን ራሱኑ ተከተሉኝ
ብሎ የጠራቸውና የመረጣቸው ናቸው፡፡
‹‹በእውነት ቀድሳቸው ቃልህ እውነት ነው፡፡ ወደ ዓለም እንደላክኸኝ
እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው፤ እነርሱም ደግሞ በእውነት የተቀደሱ
፲፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

እንደሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ እቀድሳለሁ›› (ዮሐ. ፲፯÷፲፯-፲፱)


• ቅዱሳን ጻድቃን፡- ቅዱሳን ጻድቃን ጌታን አርአያ አድርገው መላ
ዘመናቸውን ከጣዕመ ዓለም ተለይተው ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ
ነፍሳቸው አስገዝተው በጾም፣ በጸሎት፣በስግደት፣ በምናኔ ጸንተው ድምጸ
አራዊትን፣ ጸብአ አጋንንትን፣ግርማ ሌሊትን ሳይሰቀቁ ዳዋ ጥሰው፣
ደንጊያ ተንተርሰው፣ጤዛ ልሰው የኖሩ አባቶችን ቤተክርስቲያን በቅድስና
ማዕረግ ታከብራቸዋለች፡፡
ማቴ ፲÷፵፪ ‹‹ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ያገኛል››
እንዲል፡፡

• ቅዱሳን ሰማዕታት፡- ቅዱሳን ሰማዕታት ጌታችን በጲላጦስ ፊት


‹‹እኔ እውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም
መጥቻለሁ›› ዮሐ ፲፰÷፴፯ ያለውን ምስክርነት በመከተል እግዚአብሔርን
አንክድም፥ለጣዖት አንሰግድም በማለት በዓላውያን ነገሥታት ፊት ሳይፈሩና
ሳያፍሩ ቆመው የመሰከሩትን ቤተክርስቲያን በቅድስና ትጠራቸዋለች፡፡

• ቅዱሳን ነገሥታት፡- እንደ አሕዛብ፣ ዓላማውያን ነገሥታት በሥልጣናቸው


በሀብታቸው በሠራዊታቸው ሳይመኩ ሃይማኖት ይዘው፥ምግባር ሠርተው
የተገኙ እንደዳዊት ያሉ ቅዱሳን አባቶች ናቸው፡፡

• ቅዱሳን ሊቃውንት፡- ቅዱሳን ሊቃውንት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ


ያልተመሰለውን መስለው፥የተመሰለውን ተርጉመው በማስተማር
መጻሕፍትን በመተርጐም መናፍቃንን ጉባኤ ሠርተው የረቱና ያስተማሩ
ቅዱሳን ይባላሉ፡፡
‹‹መልካሙን የምስራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው››
(ሮሜ ፲÷፲፭)

• ቅዱሳን ጳጳሳት፡- ቅዱሳን ጳጳሳት የካህናትና የምዕመናን፣የሰማያውያንና

፲፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
የምድራውያን አንድነት የሆነችውን ቤተክርስቲያን በሃይማኖት
በመምራት መንጋውን ከተኩላ በመጠበቅ የክርስቶስን ትዕዛዝ የፈጸሙ
ቅዱሳን ናቸው፡፡

‘‘በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ


መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና
ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።’’ (የሐዋ ፳፥፳፰)

• ቅዱሳን መነኮሳት (ደናግል)፡- ቅዱሳን መነኮሳት (ደናግል) ከሕገ እንስሳ


ሕገ መላእክት ይበልጣል ብለው ራሳቸውን ለክርስቶስ አጭተው ከሴት
ወይም ከወንድ ርቀው፥ ንጽሕ ጠብቀው ስለ መንግሥተ ሰማያት ብለው
ራሳቸውን ጃንደረቦች ያደረጉናቸው፡፡
‘‘ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ።’’ (ማቴ
፲፱፥ ፲፪)

• ቅዱሳት አንስት፡- ጌታችን መርጦ ካስከተላቸው ፻፳ው ቤተሰብ ፴፮ቱ


ቅዱሳት አንስት የሚባሉ ሲሆን ጌታ ሲሰቀል ሳይሸሹ፣ በመቃብሩም
በመገኘት፣ የትንሳኤው ምስክር የሆኑ ናቸው። ከእነርሱም በተጨማሪ
መከራ በበዛበትና በጸናበት የክርስትና ጐዳና የተጓዙ እናቶች፣ እህቶች
ሁሉ ቅዱሳት አንስት ይባላሉ፡፡

፪.፪. ቅዱሳን መላእክት


ቅዱሳን መላእክት በባሕርዩ ቅዱስ የሆነውን እግዚአብሔርን
ስለሚያመሰግኑ፣ስለ ሚቀድሱ ቅዱሳን ተብለዋል፡፡ ከተፈጠሩባት ዕለት
ጀምሮ እርሱን በማመን ከቅዳሴና ከማኅሌት አልተለዩም። ነቢዩ ኢሳይያስ
በራእይ አይቶ እንዲህ እያሉ ያመሰግናሉ ብሏል። አንዱም ለአንዱ፦
ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ
ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።›› ኢሳ. ፮÷፫
፲፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ቅዱሳን መላእክት ከሰማይ ወደ ምድር ከምድር ወደ ሰማይ እየተላላኩ


ሰው እና እግዚአብሔርን ያገለግላሉ። ‘‘ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ
ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?’’
እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ። (ዕብ ፩፥፲፬)

‘‘መልአኩም አለው። ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት


ለመታሰቢያ እንዲሆን ዐረገ።’’ (የሐዋ ፲፥ ፬)

፪.፫. ቅዱሳት መጻሕፍት


ቅዱሳት መጻሕፍት የሚባሉት የብሉያትና ሐዲሳት፣ የመነኮሳትና
ሊቃውንት፣እንዲሁም አዋልድ መጻሕፍት ናቸው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት
ስንል የተመረጡ፣የተከበሩ የተወደዱና የተመሰገኑ መጻሕፍት ማለት
ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በቤተክርስቲያን ቀኖና የተሰፈሩት የብሉይ እና
የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት “አሥራው መጻሕፍት” ይባላሉ። ቁጥራቸውም
፹፩ ነው። እነዚህም ብዙ ጊዜ “መጽሐፍ ቅዱስ” የሚባሉት ናቸው።
ቅዱሳን መጻሕፍት ቅዱስ መሰኘታቸው የሰውን ልጅ መነሻና መድረሻ
ታሪክ፥በሦስቱም ሕግጋት የተነሱ ቅዱሳን ነቢያትና ቅዱሳን ሐዋርያት
በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው በተለያየ ልሳናት (ቋንቋ) የጻፏቸው፣
ከሐሰትና ኑፋቄ የተለዩ፣ ሰውን ለንጽሕና ለቅድስና የሚያበቁ ክቡራት
መጻሕፍት በመሆናቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ተብለዋል። ያስጻፋቸው
መንፈስ ቅዱስ ነው፣ ቃሉም የራሱ የቅዱስ እግዚአብሔር ነው።‘‘ዳሩ
ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው
ተናገሩ።’’ (፪ኛ ጴጥ ፩፥ ፳፩)

ቅዱስ ጳውሎስ የመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስን ሲመክር “ከሕፃንነትህ


ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ
የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን አውቀሃል። የእግዚአብሔር ሰው
ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት
በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል” ብሏል። ፪ኛ ጢሞ ፫፥፲፭-፲፯
ስለዚህ ቅዱሳን ነቢያት ቅዱሳን ሐዋርያት የጻፏቸው ቅዱሳትን መጻሕፍት
መማር፣ ማንበብ ልቦናን ለማቅናት እና ክርስቲያኖች ፍጹማን፣ ለበጎ
ሥራ ሁሉ የተዘጋጀን እንድንሆን ያደርገናል ማለት ነው።

በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ


የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ እራሱ ሕይወት በመሆኑ ቃሉን ሰምቶ
የሚኖርም የዘላለም ሕይወትን ያገኛል። ጌታ በወንጌል “ቃሌን የሚሰማ
የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ወደ ሕይወት ተሻገረ
እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም” እንዳለ። ዮሐ ፭ ፥ ፳፬

፪.፬. ቅዱሳት ሥዕላት


በቤተክርስቲያናችን እግዚአብሔርን፣ እመቤታችንን፣ ሐዋርያትን፣
ሰማዕታትን፣ ጻድቃንን፣ ሊቃውንትን እና ሌሎችንም ቅዱሳንን
የሚያመለክቱ አያሌ ቅዱሳት ሥዕላት አሉ። እነዚህ ሥዕላት ቅዱሳት
ይባላሉ። ቅዱሳት መባላቸውም፦
• ሥጋዊውን ዓለም ከሚያንጸባርቁ ዓለማውያን ሥዕላት ፈጽመው
የተለዩ በመሆናቸው ነው።
• የቅዱሳኑ ቅድስና ሥዕላትቱንም ቅዱሳት አሰኝቷቸዋል።
• ሥዕላቱ በራሳቸው የሚያደርጉት ገቢረ ተአምራት ቅዱሳት አሰኝቷቸዋል።
ቅዱሳት ሥዕላት በእግዚአብሔር ትእዛዝና ፈቃድ ተስለው የእግዚአብሔር
ስም በሚጠራበት ቦታ የሚቀመጡና ከሥዕሉ ባለቤት ተራዳኢነትና በረከትን
ለማግኘት ለመማጸኛ የሚጠቅሙ የእግዚአብሔር ልዩ ስጦታዎች ናቸው።

በብሉይ ኪዳን ዘመን ሥዕል እንዲሳል ያደረገው ራሱ እግዚአብሔር


ነው። ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ሥዕለ ኪሩብ እንዲሳል ታቦቱ አጠገብ
እንዲያስቀምጥ ነግሮታል። ዘጸ ፳፭፥፳፩
፳፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

እኛም ክርስቲያኖች ቅዱሳት ሥዕላትን ከሥዕሉ ባለቤት በረከት ለማግኘት


ቆመን እንጸልያለን፣ በሥዕሉ ፊት እንሰግዳለን፣ በዚህም እንባረካለን።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የቅዱሳኑ እንኳን ሥዕላቸው በመንገድ ያለፉ
በትጥላቸው በሽተኞችን ይፈዉስ ነበር። ሥለዚህ እኛም በእምነት ሆነን
ከጸለይን፣ ድኅነት ሥጋ ድኅነተ ነፍስን እናገኛለን።

፪.፭.ንዋያተ ቅድሳት

የእግዚአሔር ቤት በሆነው በቅዱስ ቤተመቅዱስ ለመንፈሳዊ አገልግሎት


የሚውሉ ንዋያት /ዕቃዎች ሁሉ የተቀደሱ ናቸው፡፡ ምክንያቱም
አገልግሎቱ የሚፈፀመው ቅድስና የባሕርይ ገንዘቡ ለሆነ ለእግዚአብሔር
ነውና፡፡ ለቤተመቅደስ አገልግሎት የሚዉሉትን ንዋያት የቅድስት
ቤተክርስቲያን ሥርዓትና ሕግን ጠብቀው ከተዘጋጁ በኋላ በሊቃነ ጳጳሳት
ጸሎት (ተጸልዮባቸው) እና ቅብዓ ሜሮን ተቀብተው ቅዱስ ይሆናሉ።
እነዚህ (ንዋያት) ምን አልባት ከምናውቀው ነገር ሊዘጋጁ ይችላሉ፣ ነገር
ግን በአባቶች ጸሎት ተባርከውና ተቀድሰው ለእግዚአብሔር አገልግሎት
ከዋሉ በኋላ ቅዱሳት ናቸው። “ከሰው መርጦ ለሹመት ከእንጨት መርጦ
ለታቦት” እንደሚባለው ተለይተው የከበሩ ናቸው። ከእነዚህም መካከል
የተወሰኑትን ጠቅሰን አገልግሎታቸውን እንደሚከተው እናብራራለን።

• ቅዱስ መስቀል፡- የጌታችን ቅዱስ መስቀል ሕያው፣ አማናዊ በሆነው


በክርስቶስ ደም ከመክበሩ የተነሳ ቅዱስ ተብሏል፡፡
ቅዱስ ያሬድ ስለመስቀሉ በድጓ ዘክረምት ላይ እንዲህ ብሏል። ‹‹የቅዱሳን
ክብራቸው የጻድቃን ሞገሳቸው የዕውራን ብርሃናቸው እነሆ ይህ መስቀል
ነው›› ፡፡
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎበት፣ በሞቱ
ሕይወትን ስለሰጠን፣ ዲያብሎስን ስለቀጠቀጠበት እና ቅዱስ ደሙንም
ስላፈሰሰበት መስቀል የቤተክርሲያን ቅዱስ ንዋይ ነው። እኛም ክርስቲያኖች
፳፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
መስቀል በመሳለም፣ በትእምርተ መስቀል በማማተብ ርኩስ መንፈስን
ከሕይወታችን እያራቅን ሰውነታችንን እንባረክበታለን።
• ታቦት፡- ቤተክርስቲያን ቅዱስ ብላ ከምታከብራቸው አንዱ ታቦተ
ሕጉን ነው፡፡
ታቦት ማለት የግእዝ ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙም ማደሪያ ማለት ነው።
ታቦት እግዚአብሔር የሚያድርበትና የሚገለጥበት የጽላተ ሕጉ ማደሪያ
ነው፡፡ ዘፀ. ፳፭÷፳፪
ይህንን ታቦት በመጀመሪያ ያዘጋጀው ቅዱስ ሙሴ ሲሆን ያዘዘውና
የሚዘጋጅበት ልኩን እና ሥርዓቱን የሰጠው ቅዱስ እግዚአብሔር ነው።
እግዚአብሔርም በቸርነቱ በታቦት ላይ ያድራል፣ ይገለጣል።

፪.፮. ቅዱሳት መካናት

ቅዱሳት መካናት፡- ማለት የተለዩ፣ የተከበሩ ሥፍራዎች፣ ቦታዎች


ናቸው። እግዚአብሔር በመዝሙር፣ በቅዳሴ፣ በማኅሌት፣ በምስጋና፣
በጸሎት ይገለገልባቸው ዘንድ የመረጣቸው ገዳማትና አድባራት ቅዱሳት
መካናት ይባላሉ፡፡

አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር በደብረ ሲና ለሙሴ በእሳት ነበልባል


አምሳል ሐመልማሏን ተዋህዶ በተገለጠለት ጊዜ ሙሴ ነገሩን
ለመመርመር ወደ ሐመልማሏ ሲጠጋ “ሙሴ ሙሴ ሆይ! ወደዚህ
አትቅረብ፣ አንተ የቆምክባት መሬት የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ
አውልቅ” ብሎታል። ዳግመኛም ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴን ተክቶ
እስራኤላውያንን ከነዓን መርቶ ያገባቸው ኢያሱን መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል
“አንተ የቆምክባት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግር አውልቅ”
ብሎታል። ኢያሱ ፭÷፲፭ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም የእግዚአብሔር
ስሙ የሚቀደስባት ክብር ሥጋው እና ቅዱስ ደሙ የሚፈተትባት ናትና
ወደ ቤተመቅደስ ስንገባ ጫማችንን እንድናወልቅ ታዝዛለች።
፳፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ቅዱስ ጴጥሮስም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ


ታቦር ተራራ መለኮታዊ ክብሩን የገለጠበትን እና አብም ስለ ልጁ
የመሰከረበትን ነገር ሲያብራራ ቆይቶ “ እኛም በቅዱሱ ተራራ ሳለን
ይህንን ድምጽ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን” በማለት የታቦርን ተራራ ቅዱስ
ብሎ ጠርቶታል።

ቅዱሳን መካናትን የመረጠና ያከበረ እርሱ እግዚአብሔር ነው። ጠቢቡ


ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሠርቶ በጨረሰ ጊዜ እግዚአብሔር
በዚህ ቤተ መቅደስ የሚጸለየውን ጸሎት ሁሉ እንዲሰማ፣ እንዲቀበል
እና እንዲፈጽም፣ ምሕረትንም እንዲያደርግ በጸሎት ሲለምነው
እግዚአብሔርም እንዴት እሺ እንዳለው በሚያስደንቅ መልኩ በመጽሐፈ
ዜና መዋእል ሁለተኛ ተተርኳል። ፪ኛ ዜና ፮፥፲፰-፵፪ እና ፪ኛ ዜና ፯፥፲፩-፳፪

፪.፯. የምዕራፉ ማጠቃለያ


በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እግዚብሔርን ስላከበሩ እና ሕጉን ጠብቀው
በንጽሕና ስለኖሩት ቅዱሳን እንዲሁም ስለቅዱሳን መላእክት፣
እና እግዚአብሔር ከቦታም ከሌላ ነዋይ መርጦ ለአገልግሎት
ስላከበራቸውና በረድኤት ስለሚገለጥባቸው ቅዱሳት መካናት፣
ነዋያተ ቅድሳት፣ እንዲሁም ቅዱሳት ሥዕላት አይተናል።

፳፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
የማጠቃለያ ጥያቄዎች
ክፍለ አንድ - እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ።
፩ ቅዱሳን ተብለው የሚጠሩት ሰዎች ብቻ ናቸው።
፪ እግዚአብሔር ቅድስናን ለሁሉም ይሰጣል።
፫ ቅዱሳን መላእክት መልእክት ከእግዚአብሔር ወደ ሰው እንጂ
ከሰው ወደ እግዚአብሔር አይወስዱም።

ክፍል ሁለት - አዛምዱ


ረድፍ ሀ ረድፍ ለ
፩ ቅዱሳን አበው ሀ. በማያምኑ ነገሥታት ፊት ለእግዚአብሔር
በእውነት የመሰከሩና ደማቸውን ያፈሰሱ
፪ ቅዱሳን ሰማእታት ለ. የነቢያትና ሐዋርያትን መጻሕፍት፣
የተረጎሙ፣ ያስተማሩ፤ መናፍቃንን በጉባኤ የረቱ
፫ ቅዱሳን ሐዋርያት ሐ. በሕገ ልቡና ብቻ ተመርተው
እግዚአብሔርን ያመለኩ፣ ከጣዖት እና ርኩሰት የራቁ
፬ ቅዱሳን ነቢያት መ. ያለፈውንና የሚመጣውን እየተናገሩ
ሕዝቡን ያስተማሩ፣ የገሰጹ
፭ ቅዱሳን ሊቃውንት ሠ. በነቢያት የተነገረው ትንቢት
መድረሱንና መፈጸሙን፣ አምላክ ሰው ሆኖ ማዳኑን በዓለም ዞረው
ያስተማሩ
፮ ቅዱሳን ደናግላን ረ. ራሳቸውን የክርስቶስ እጮኞች
አድርገው ከሴት ወይም ወንድ ርቀው በንጽሕና የኖሩ
ክፍል ሁለት - አዛምዱ

ክፍል ሦስት - ትክክለኛውን መልስ ምረጡ


፩ ቅዱሳት ሥዕላት ለምን ቅዱስ ይባላሉ?
ሀ. ከዓለማውያት ሥዕላት ስለሚለዩ ሐ. በሚያደርጉት
ገቢረ ተአምራት
፳፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ለ. የቅዱሳኑ ቅድስና ቅዱስ ስለሚያደርጋቸው መ. ሁሉም


፪ ከሚከተሉት ውስጥ ቅዱስ ነዋይ ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ታቦት ለ. ቅዱስ መስቀል
ሐ. ጽዋ መ. ጻሕል ሠ. መልስ የለም

ክፍል አራት - መልስ ስጡ ወይም አብራሩ


፩ እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ ያለና የሚገኝ አምላክ ሆኖ እያለ የተለዩ
ቦታዎችን በረድኤት እንደሚገለጥባቸው፣ ከእነዚያ የተቀደሱ ቦታዎች
የሚጸለይን ጸሎትም ሁሉ እንደሚሰማ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃዎች
ጨምራችሁ አብራሩ።

፳፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ምዕራፍ ሦስት

መዓርጋተ ቅዱሳን

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ
• ቅድስና በአንድ ግዜ የሚገኝ እና የሚደረስበት ሳይሆን የዕድሜ ዘመንን
ተጋድሎ እንደሚጠይቅ ይረዳሉ።
• ሦስቱን ዋና ዋና የቅድስና መዓርጋት ይዘረዝራሉ።
• አሥሩን መዓርገ ቅዱሳን ይዘረዝራሉ።
• ቅዱሳንን አብነት አድርገው ራሳቸውን ለቅድስና ሕይወት ያለማምዳሉ።

የመክፈቻ ጥያቄዎች

፩ .ቅዱሳን ወደ ቅድስና መዓረግ ሲሄዱ ወይም የቅድስና ሕይወትን


ሲኖሩ ከሚኖራቸው መገለጫዎችን መካከል ዘርዝሩ።
፪ ለዘረዘራችኋቸው መገለጫዎች ምሳሌ የሆኑ ቅዱሳንን ጥቀሱ።

፳፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

መዓርጋተ ቅዱሳን

የቅድስና ሕይወት ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ የተሰጠ ሳይሆን ሁላችንም


ክርስቲያኖች ልንኖረው የሚገባ ሕይወት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ “ትቀደሱ
ዘንድ ፈልጉ፣ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።” በማለት
እንደተናገረው ያለ ቅድስና ሕይወት እግዚአብሔርን ማየትና መንግሥተ
ሰማያትን መውረስ አይቻልም። ዕብ ፲፪፥፲፬

ይህ የቅድስና ሕይወት ደግሞ በቅጽበት ወይም በተወሰነ ትምህርት


በመማር የሚገኝ ሳይሆን ብዙ ድካምና ተጋድሎን የሚጠይቅ ነው።
ክርስቲያኖች እነርሱን ሊያጠቃ ወይም መንፈሳዊ ሕይወታቸውን
እንዳይኖሩ፣ ከክርስቶስ ጋር ሕብረት እንዳይፈጥሩ የሚያደርግ እረፍት
የሌለው ጠላት አለባቸው። እርሱም ጥንተ ጠላታቸው ዲያብሎስ
እንደሆነ ቅዱስ ጴጥሮስ “በመጠን ኑሩ ንቁም፣ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ
የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና” በማለት ይናገራል።
(፩ኛ ጴጥ ፭፥፰) ይህንን የጠላት ፈተና ለማሸነፍ ደግሞ ሁልጊዜ መንቃት፣
በመጠን መኖር፣ መትጋት ያስፈልጋል። ቅዱስ ጴጥሮስ በሁለተኛይቱ
መልእክቱም እንዲህ ይላል።

“ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነት ላይ


በጎነትን፣ በበጎነት እውቀትን፣ በእውቀት ራስን መግዛትን፣ ራስን
በመግዛት መጽናትን፣ በመጽናት እግዚአብሔርን መምሰልን፣ በዚህም
የወንድማማችን መዋደድ እና ፍቅርን ጨምሩ” ፪ኛ ጴጥ ፩፥ ፭-፰

ስለዚህ ቅዱሳንም በዚህ መንገድ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ በጥምቀት


ከተወለዱበት እና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ ተግተው፣
መንፈሳዊ ገድልን ተጋድለው፣ እያንዳንዷን ሰዓት እና ደቂቃ ከክርስቶስ ጋር
ስለኖሩባት ቅዱሳን ተብለዋል። በዚህ ሕይወታቸው ብዙ መከራ፣ ፈተና፣
፳፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ስቃይ፣ ርሀብና ጥም ይደርስባቸዋል። እነርሱ እግዚአብሔርን ብለው
መከራውን ሲቀበሉ እርሱ ደግሞ ይረዳቸዋል፤ከክብር ወደ ክብርም ከፍ
ከፍ ያደርጋቸዋል። ቅዱስ መጽሐፍ “ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ
በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል፣ ያጸናችኋል፣ ያበረታችሁማል”
እንዲል። (፩ኛ ጴጥ ፭፥፲)

ስለዚህ በዚህ ምዕራፍ ቅዱሳን እንዴት እንደኛ ሰው ሆነው ወደዚያ


የፍጹምነት ደረጃ እንደሚደርሱ፣ ከክብር ወደ ክብር እንደሚያድጉ
የምንማር ይሆናል።

መዓርግ ማለት ክብር፣ ሥልጣን ማለት ነው፡፡ ቅዱሳን በገድልና በትሩፋት


ብዛት የሚያገኟቸው መዓርጋት አሉ። እኒህም የቅዱሳን የመንፈሳዊ
ሕይወታቸው የዕድገት ደረጃዎች በቁጥር ሦስት ሲሆኑ እነርሱም
ወጣኒነት (ንጽሐ ሥጋ)፣ ማዕከላዊነት (ንጽሐ ነፍስ) እና ፍጹምነት
(ንጽሐ ልቡና) ናቸው። በእነዚህ በእያንዳንዳቸው ውስጥ ደግሞ የተለያዩ
መዓርጋት ወይም የዕድገት ደረጃዎች አሉ። በንጽሐ ሥጋ ሦስት፣
በንጽሐ ነፍስ አራት፣ በንጽሐ ልቡና ደግሞ ሦስት መዓርጋት ሲኖሩ
በጠቅላላው ዐሥሩ መዓርጋተ ቅዱሳን በመባል ይታወቃሉ።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በ፩ኛቆሮ. ፲፭፥፴፩ ላይ “በክብር አንዱ ኮከብ


ከሌላው ኮከብ ይለያል” በማለት እንደተናገረው በመልካም ሥራቸው
ለዘለዓለም እንደ ከዋክብት ደምቀው የሚኖሩ ቅዱሳን በሠሩት ገድልና
ትሩፋት መጠን የአንዳቸው ክብርና ሥልጣን ከሌላው ይለያል፡፡ (ዳን
፲፪፥፫፤ ራእ፲፪፥፩-፪) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባስተማረው
የገበሬና የዘር ምሳሌ ላይ “ሌላውም ዘር በመልካም መሬት ወደቀ አንዱም
መቶ፣ አንዱም ስድሳ፣ አንዱም ሰላሳ ፍሬ ሰጠ” ብሏል፡፡ /ማቴ ፲፫፥፰/
ዘር የተባለው ቃለ እግዚአብሔር ሲሆን መልካም መሬት የተባሉት ደግሞ
የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው ፍሬ ሃይማኖትና ፍሬ ምግባር የሚያፈሩ
፳፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ እነርሱም እንደሥራቸው መጠን ፴፣ ፷፣ ፻ /


ሠላሣ፣ ስልሣ፣ መቶ/ ፍሬ ያፈራሉ ወይም የተለያየ ክብርና ሥልጣን
ያገኛሉ ማለት ነው፡፡ የቅዱሳን መዓርጋትን የሚወሰኑት በቅድስና
ሕይወት በፈጸሙት ገድልና ትሩፋት መጠን ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በ፩ኛ
ተሰ ፭፥፲፪-፲፬ ላይ “የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤
መንፈሳችሁም፣ ነፍሳችሁም፣ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በመጣ ጊዜ ያለነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።” ማለቱ ንጽሐ ሥጋ፣ ንጽሐ
ልቡና፣ ንጽሐ ነፍስ ይኑራችሁ፤ ከኃጢአት ከነቀፋ የተጠበቃችሁ ሁኑ
ማለት ነው፡፡ እነዚህም እያንዳንዳቸው መዓርጋት ምን እንደሚመስሉ
እንመለከታቸዋለን።

፫.፪ ንጽሐ ሥጋ
ይህ ደረጃ ወጣንያን በባሕርዩ ፍጹም ከሆነው እግዚአብሔር ፍጹም
ጸጋን ተቀብለው ለመክበር ቁርጥ ተጋድሎ የሚጀምሩበት ሕይወት
ነው። በዚህም ጊዜ ጠላት የተባለ ሰይጣን የተጋድሎ ሕይወታቸውን
የሚያቀጭጭ ፈተና ያመጣባቸዋል። እነርሱ ግን በፍጹም ተጋድሎ
በእግዚአብሔር ጸጋ ከአንዱ መዓርግ ወደ ሌላ መዓርግ ይሸጋገራሉ።
የንጽሐ ሥጋ መዓርጋት ሦስት ናቸው። እነሱም ጽማዌ፣ ልባዌ፣
ጣዕመ ዝማሬ ሲሆኑ፤እነዚህ መዓርጋት ላይ የደረሱ ቅዱሳን ሠላሳ ፍሬ
በሚያፈራው ዘር የተመሰሉት ናቸው፡፡

ሀ. ጽማዌ
ጽማዌ ማለት ዝምታ ጸጥታ ማለት ነው፡፡ቅዱሳን ይሄን የሚያደርጉት
በመናገር በማውራት ብዙ ኃጢአት፣ ብዙ ሰው ማስቀየም እና ማቁሰል
ስላለ፣ ራሳቸው አንደበታቸውን በመግዛት ከእግዚአብሔር እና ቅዱሳን
መላእክት እንዲሁም ቅዱሳን ሰዎች ጋር ብቻ በልቡናቸው የሚነጋገሩበት
ሕይወት ነው። አባ አርሳኔዎስ የሚባሉ አባት “ብዙ በተናገርኩ ቁጥር
እጸጸታለሁ፣ ዝም ስል ግን ጸጽቶኝ አያዉቅም” ብለዋል። ሰው በተናገረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ቁጥር አስቦበት ሰውን ለማስቀየምም ይሁን ሳያስበው ለመልካም
የተናገረው ሰዎችን ያስከፋል። ሰውን ተናግሮ ማስከፋት ደግሞ ኃጢአት
ነው። ዝም ማለት ግን ምንም አያስጸጽትም።
ቅዱስ ያዕቆብም በመልእክቱ እንዲህ ይላል። “አንደበት እሳት ነው።
አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመጸኛ ዓለም ሆኗል፣ ሥጋን ሁሉ
ያሳድፋልና፣ የፍጥረትንም ሁሉ ሩጫ ያቃጥላል፣ በገሃነምም ይቃጠላል።”
(ያዕ ፫፥፮)

መጽሐፍ ቅዱስ አንደበትን መግራት፣ ዝምታን መለማመድ፣ ክፉን ነገር


ሁሉ ከአንደበት ማራቅ እንደሚያስፈልግ በስፋት ይናገራል።
• “በቃል ብዛት ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፤ ከንፈሩን የሚገታ
ግን አስተዋይ ነው።” ምሳ ፲፥፲፱
• “በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ
በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ። ከዝምታ የተነሳ እንደዲዳ
ሆንሁ፣ ለበጎ ነገር እንኳን ዝም አልኩ።” መዝ ፴፰ ፥ ፩፣፪

በጽማዌ ማዕረግ ላይ የደረሱ ቅዱሳን በዓለም ላይ እያሉ የዓለምን


ማንኛውንም ነገር ለመስማት አይፈልጉም፡፡ ነገር ግን በሕሊናቸው ነገረ
እግዚአብሔርን ያስባሉ፣በአፍንጫቸው መዓዛ ገነትን ያሸታሉ፡፡ እዚህ
ማዕረግ ላይ ሲደርሱ በዐይናቸው ሥውራን፣ ዓለማትን፣ ግሩማን
አራዊትን፣ከሥጋዋ የተለየች ነፍስን፣ አጋንንትን ለመለየት ይችላሉ፡
፡ እንዲሁም በዚህ ዓለም ለተልእኮ የሚመላለሱ መላእክትን የማየት
ደረጃ ላይ ይደርሳሉ፡፡ ነገር ግን የተገለጡላቸው መላእክት የሚሠሩትን፣
የሚናገሩትን እንዲሁም እነማን እንደሆኑ ስማቸውን ለይተው አያውቁም፡፡

እዚህ ማዕረግ ላይ የደረሱ አባቶች/ እናቶች በመንፈስ ቅዱስ መግቦት


ይኖራሉ እንጂ፤ራሳቸው ጥረው ግረው አይመገቡም፡፡ እናነባለን፤
እንዘምራለን፤ ከሰው ጋር እንነጋገራለን አይሉም፡፡ዓለምን ከማሰብ
፴፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ይለያሉ፡፡ ቀንና ሌሊት ምንም ሳይበሉና ሳይጠጡ መጾምና መጸለይ


ይችላሉ፡፡ለዚህም አብነት የምናደርገው ሊቀ ነቢያት ሙሴን ነው፡፡ ሙሴ
ቀንና ሌሊት ምግብ ሳይመገብ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለ ፵ መዓልትና
ሌሊት ቆይቶ ዐሥርቱ ትእዛዛትን ከእግዚአብሔር ተቀብሏል፡፡

እኛም በሕይወታችን እንደ እነርሱ አንደበታችንን ዘግተን መኖር ባንችል


እንኳን ንግግርን መቀነስ፣ አስፈላጊ ካልሆነ አለማውራት፣ የስድብን ቃል
ፈጽሞ ከእኛ ማራቅ አለብን። በሕይወታችን ለተናገርናት እያንዳንዷ
ቃል በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ እንቀበልበታለን። ሰዎችን የሚያንጽ፣
ያዘኑትን የሚያጽናና ከሆነ መልካም ዋጋ እናገኝበታልን፣ ለተሳደብነው፣
ሰዎችን ላስቀየምነው ነገር ሁሉ ደግሞ እንቀጣበታለን። ‘‘ወንድሙንም
ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም
ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።’’ እንዲል (ማቴ ፭፥ ፳፪)

ለ. ልባዌ
ልባዌ ማለት ልብ ማድረግ፣ ማስተዋል፣ ዕውቀት፣ ማለት ነው፡፡
ከዚህ መዓርግ ላይ የደረሱ ቅዱሳን የሕሊና ጾር በተነሣባቸው ጊዜ
(ክፋ ምኞት ሲመጣባቸው) መስቀል ተክለው ይሰግዳሉ፡፡ሥጋዊ ነገርን
በማሰብ ጸጋቸው እንዳይነሣ ሕሊናቸው ነገረ መስቀልን ከማሰብ
እንዲለይ አይፈልጉም፡፡ በበአታቸው ጸንተው ቢኖሩም የሚፈልጉትን
ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ፈጥኖ ይሰጣቸዋል፡፡ እንዲሁም ነፍስ ከሥጋ
ተለይታ ወዴት እንደምትሔድ ያያሉ፤መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ፣
ተልእኳቸውንና እነማን እንደሆኑም ጭምር ስማቸውን ለይተው ያውቃሉ፡
፡አጋንንትንም የማየትና ለምን እንደተላኩ የማወቅ ጸጋ ይሰጣቸዋል፡፡
እግዚአብሔር ከሚሰውራቸው አንዳንድ ነገሮች በስተቀር ከጠፈር በታች
ያለውን ማናቸውንም ነገር ሳይጠይቁ ይረዳሉ፡፡ /፪ኛቆሮ ፲፪፥፩-፯/፡፡

፴፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ሐ. ጣዕመ ዝማሬ
አባቶች እዚህ ማዕረግ ላይ ሲደርሱ የሚጸልዩትን ጸሎት አንድ በአንድ
ምስጢሩን ያውቃሉ፡፡የሚጸልዩትን ጸሎት ምሥጢሩን ተረድተው
በልቡናቸው እያመላለሱ ያለማቋረጥ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፣
ይጸልያሉ። እያንዳንዷን ቃል ጣዕሟን አይጠግቧትም። የአቡነ ዘበሰማያት
ምስጢር አላልቅ ብሏቸው ለ፴ ዓመት የሚቆዩ አሉ፡፡

አንድ አባት በገዳም “አባታችን ሆይ፣ አባታችን ሆይ፣ አባታችን ሆይ፣


አባታችን ሆይ ... እያሉ ለብዙ ዘመን ያለማቋረጥ ሲጸልዩ ራሱ እግዚአብሔር
ተገልጦ ‘ለምን ይሄን ብቻ? በሰማያት የምትኖር ብለህ አትጨርሰውም?’
ሲላቸው አባቴ ሆይ መች የአባትነት ፍቅርህን ጠገብኩት” ብለዋል።

ስለዚህ ከዚህ ደረጃ የደረሱ አባቶች ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ ቁመት


አይሰለቻቸውም ሲዘምሩ ድምፃቸው እንደ መላእክት ይሆናል፤ ቀንና
ሌሊት ያለ ዕረፍት ያመሰግናሉ፡፡ የራሳቸውም ድምፅ እንደ መላእክት
ዝማሬ አይሰለቻቸውም፡፡ ክብራቸውን ለመሰወር ካልፈለጉ በስተቀር
ሥጋዊ ምግብ አይመገቡም፤ አያንቀላፉም፡፡ እዚህ ማዕረግ ላይ በደረሱ
አባቶች ሰይጣናት ‘ከዚህ ዋሻ ውስጥ እንደሽኮኮ ተሸጉጠህ ትኖራለህን
ከተማ ገብተህ ቀድሰህ፣ ዘምረህ፣ አስተምረህ አትኖርምን? ’የሚል
የኅሊና ፈተና ያመጡባቸዋል፡፡ ይህን ጊዜ ልቡናቸው ከውዳሴ ከንቱ
ተለይቶ በአጽንዖ በአት /በበዓት ጸንቶ መቆየት/ የጸና እንደሆነ የንጽሐ
ነፍስ መዓርጋት ይሰጣቸዋል፡፡

ቅዱስ ያሬድም እግዚአብሔር የገለጠለትን ሰማያዊ ዜማ በንጉሡ አጼ


ገብረ መስቀል ፊት በሚያዜምበትና በመቋሚያ በሚዘምበት ጊዜ ንጉሡ
በተመስጦ ይሰሙት ነበር። ሳያውቁትም እንደ ዘንግ በሚይዙት በትረ
መስቀላቸው እግሩን ወግተውታል፤ይህ ሁሉ ሲሆን ደሙም ሲፈስ ግን
ቅዱስ ያሬድ አልተሰማውም ነበር።
፴፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

፫.፫ ንጽሐ ነፍስ


የንጽሐ ነፍስ መዓርግ ሥጋ የሚረሳበት፣ የነፍስ ኃጢአት የሌለበት
ጊዜ ነው፡፡ በንጽሐ ነፍስ ጊዜ በተባሕትዎ ጸንቶ በኖረ ሰው ጸጋ
እግዚአብሔር ያድርበታል፡፡በዚህ ዓለም ያሉ ሰዎች በዐይነ ሥጋ ለማየት
የማይችሉትን የእግዚአብሔርን ምሥጢር ያያሉ ነገር ግን ልዩ ጾር
(ፈተና) ይታዘዝባቸዋል፡፡ ትሩፋትን መተው፣ ተስፋ መቁረጥ፣ በአቴን
ጥዬ ልውጣ ማለት መጠራጠር፣ አይምረኝም፣ አያድነኝም የማለት
ሐሳብ ይመጣበቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጾሩ ብዛት የተነሣ ከጽናታቸው
ሳይናወጹ፣ እግዚአብሔር ያድነናል በማለት በሃይማኖት ከጸኑ ክብሩ
(ጸጋው) አይለያቸውም፡፡ በንጽሐ ነፍስ መዓርግ ላይ ያሉት ስድሣ ፍሬ
ባፈራው ዘር የተመሰሉ ናቸው፡፡ የንጽሐ ነፍስ መዓርጋት የሚባሉት
አንብዕ (አንብዐ ንስሐ)፣ ኩነኔ፣ፍቅርና ሑሰት ናቸው፡፡

ሀ. አንብዕ
እዚህ መዓርግ ላይ የደረሱ ቅዱሳን የዕንባ ሀብት (አንብዐ ንስሐ) ይሰጣቸዋል፡
፡ ሳያቋርጡ ያነባሉ፤ ዐይናቸው ግን አይጠፋም፤ ዕንባቸው ሌሊትና ቀን
አያቋርጥም፤ አንብዐ ንስሐ መዓርግ ላይ የሚደርሱ ቅዱሳን አብዛኛውን
ጊዜ የሚጸልዩት በሕሊና ነው። ይኽም በሕሊናቸው የሚመላለስ ረቂቅ
ጸጋ ስለኾነ ኃጢአትን ያስወግድላቸዋል፡፡ እርጥብ እንጨትን በእሳት ላይ
ቢጥሉት እየነደደ ውኃ እንደሚወጣው ሁሉ በሀብተ አንብዕ ደረጃ ላይ
ያሉ ቅዱሳንም ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን፣ ግፍዐ ሰማዕታትትን፣ምረረ
ገሃነመ እሳትን እያሰቡ በልቡናቸው ከሚቀጣጠለው መንፈሳዊ ጸጋ እሳት
የተነሣ የጸጋን ዕንባ ያነባሉ (ያፈሳሉ)፡፡ ማቴ ፭፥፬፡፡

ለ. ኩነኔ
ኩነኔ ማለት አገዛዝ፣ ግዛት ማለት ነው፡፡ እዚህ መዓርግ ላይ የደረሱ
ቅዱሳን የነፍስ ፈቃዳቸው የሥጋ ፈቃዳቸውን ይገዛል፤ ያሸንፋል፡፡ ገላ
፭፥፲፮ በሰው ሕይወት የሥጋና የነፍስ ፈቃዳት ሁልጊዜ ይቃረናሉ፡፡ ገላ
፴፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
፭፥፲፯ የነፍስ ፈቃድ እያሸነፈ ሔዶ ሥጋን በቁጥጥር ሥር የሚያውልበት፣
ነፍስ የመንፈስን ፈቃድ ብቻ መፈጸም የምትጀምርበት መዓርግ ኩነኔ
ነው፡፡የሥጋቸው ፈቃድ በፈቃደ ነፍሳቸው ላይ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ
አይኖረውም፡፡በሐሳብም ከመበደል ይጠበቃሉ፡፡ የሲዖልንና የገሃነመ
እሳትን ኩነኔ እያሰቡ ያዝናሉ፡፡

ሐ. ፍቅር
እዚህ መዓርግ ላይ የሚደርሱ አባቶች ሁሉን የመውደድ ሀብት
ይሰጣቸዋል፡፡እነርሱንም ሁሉ ይወዳቸዋል፡፡ በእነዚህ አባቶች ዘንድ ይህ
ጌታ ነው፣ ይህ ባሪያ ነው፣ ይህ ወንድ ነው፣ይህች ሴት ናት፣ ይህ ደግ
ነው፣ ይህ ክፉ ነው፣ ይህ መልከ ቀና ነው፣ ይህ መልከ ክፉ ነው ማለት
የለም፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ክርስቶስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷል ብለው ሰውን
ሁሉ አስተካክለው ይወዳሉ፤ ለሁሉም ይራራሉ፤ የወጡትን በደኅና
አግባቸው፤ የሰው ልጆችን ከክህደት ወደ ሃይማኖት፣ ከገቢረ ኃጢአት
ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሳቸው እያሉ ይጸልያሉ፡፡ ፩ኛ ቆሮ ፲፫፥፩-፲፫፣
ማቴ. ፭፥፵፬ አዕዋፋት እንስሳትና አራዊት አይጣሏቸውም፡፡ ዓመፀኞች
አጋንንት ጭምር ይታዘዙላቸዋል፡፡ መዝ. ፺(፺፩)፥፲፫፤፡

መ. ሑሰት
ሑሰት ማለት እንደ ፀሐይ ብርሃን ካሰቡበት ሁሉ መገኘት፤ በሌላ
ቦታ የሚሠራውን ባንድ ቦታ ሆኖ ማየት መቻል ሲሆን የሚደረገው
ሁሉ አይሰወራቸውም፡፡ ሁሉንም አንድ ቦታ ሆነው ማየት ይችላሉ።
ለምሳሌ በአንድ ተመሳሳይ ሰዓት በመላው ዓለም ቅዳሴ ቢቀደስ እነማን
እንደቀደሱ እነማን እንደቆረቡ በቅጽበት ያውቃሉ፡፡ በዚህ መዓርግ ሳሉ
ረቂቅ መንፈስ ቅዱስ ስለሚዋሐዳቸው ረቂቃን ይሆናሉ፡፡ በሥጋ ግዙፋን
ቢሆኑም ጠፈር፥ ደፈር ሳይከለክላቸው በመስተዋት ብርሃን እንደሚያልፍ
ማለፍ ይችላሉ፡፡ ፪ኛነገ. ፮፥፰-፲፫፤የሐዋ. ፭፥፩-፲፩፡፡

፴፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

እነዚህ ቅዱሳን ዓለመ መላእክትን፣ ገነትን፣ ብሔረ ሕያዋንን፣ ብሔረ


ብፁዓንን ጎብኝተው መምጣት ይችላሉ፡፡ የብርሃን መንኮራኩር (ሰረገላ)
እና ክንፈ ጸጋ ይሰጣቸዋል፡፡

፫.፬ ንጽሐ ልቡና


አንድ ሰው ንጽሐ ልቡና ላይ ሲደርስ ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ ወደ
መላእክት ዓለም ትሔዳለች ነገር ግን ዐይኑ እንደ ማንኛውም ሰው
ያያል ሰውነቱም ይሞቃል፤እንደሞተ ሰው ዐይኑ አይጨፈንም፡፡ ነፍሱ
ግን ለተወሰነ ጊዜ ከመላእክት ጋር እግዚአብሔርን እያመሰገነች በጣዕመ
ዝማሬ ተመስጣና ተደስታ ከቆየች በኋላ ትመለሳለች፡፡ እነዚህም ፻
(መቶ) ፍሬ በሚያፈራው ዘር የተመሰሉ ናቸው፡፡ ይህም የፍጹማን
መዓርግ ነው፡፡ የንጽሐ ልቡና መዓርጋት የሚባሉት ንጻሬ መላእክት፣
ተሰጥሞ ብርሃን እና ከዊነ እሳት ናቸው፡፡

ሀ. ንጻሬ መላእክት
ንጻሬ ማየት ማለት ነው፡፡ ንጻሬ መላእክት ማለት መላእክትን ማየት
ማለት ነው፡፡ ወጣንያንስ መላእክትን ያዩ የለምን፣ የልባዌ መዓርግ ላይ
የደረሱስ መላእክትን እያዩ እነማን እንደሆኑ ለምን እንደመጡ ያውቁ
የለምን? ቢሉ እነዚያ መላእክትን የሚያዩት በዚህ ዓለም ሆነው ነው፡፡
ንጻሬ መላእክት ላይ የደረሱ ግን መላእክትን በዓለማቸው እየገቡ፣ በዚህም
ዓለም ሆነው በተመስጦ እላይ የመላእክት ዓለም እየገቡ ነው፡፡ እነዚህ
ቅዱሳን ነፍሳቸው ብቻ ወይም ከነሥጋቸው ወደ መላእክት ዓለም ሂደው
እያንዳንዱን ከተማይ ጎበኛሉ፤ ዜማቸውንም ይሰማሉ፤ ምስጋናቸውም
ከመላእክት ጋር አንድ ሆኖ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እያሉ አብረው
ያመሰግናሉ፡፡ ረቂቃን የሆኑት መላእክት አካል ገዝተው ዳመና ዳመና
አክለው ይታዩዋቸዋል፡፡ከመላእክት መዓርግ ላይ ይደርሳሉ፤ የመላእክትን
መኖሪያና ክብር እያዩ ያደንቃሉ፤ በመላእክት ቋንቋ ይናገራሉ፡፡ ቅዱስ
ያሬድ በአካለ ሥጋ በምድር ሆኖ በአካለ ነፍስ የመላዕክትን ዜማ ከሰማይ
፴፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ሰምቶ እንደመጣው እና ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ
እንደተነጠቀው ማለት ነው፡፡ ‘‘ወደ ገነት ተነጠቀ፥ ሰውም ሊናገር
የማይገባውን የማይነገረውን ቃል ሰማ።’’ እንዳለ (፪ኛቆሮ.፲፪፥፪)፡፡ ከዚህ
መዓርግ በታች ያሉ ወጣንያን እንኳን በጸጋ በመላእክት ቋንቋ መናገር
ይችሉ የለምን? ቢሉ ልዩነቱ ወጣንያን ከፍቅር መዓርግ ላይ ሳይደርሱ
ነው፡፡ እነዚህ ግን ከፍቅር መዓርግ ደርሰው ነው፡፡ ይህ መዓርግ ከሑሰት
ይበልጣል፡፡ እዚህ መዓርግ ላይ የሚደርሱ ቅዱሳን ከጠላቶቻቸው
ከአጋንንት ይሰወራሉ፤ የመንግሥተ ሰማያትን ምስጢር ያውቃሉ፡፡

ለ. ተሰጥሞ ብርሃን
ዓሣ በባሕር ውስጥ ተሰጥሞ (ጠልቆ) እንደ ሚኖር፤ እዚህ መዓርግ ላይ
የሚደርሱ አባቶች ኅሊናቸው ጸጥ ይላል፤ ልዑል፣ ስፉሕ፣ ረቂቅ በሚሆን
ብርሃን ይሰጥማሉ (ይዋኛሉ)፤ሕይወታቸው ብሩህ ይሆናል፤ ሙሉ በሙሉ
ደስተኞች ይሆናሉ፡፡ ፪ኛ/ቆሮ ፮፥፲ ፣ ፊልጵ ፫፥፩/ አሞራዎችና ንስሮች
በአየር ባሕር ውስጥ እንደሚበሩ፣ዓሣዎች በባሕር ውስጥ እንደሚዋኙ
ተሰጥሞ መዓርግ ላይ የደረሱ ቅዱሳንም በላይ ባለ የብርሃን ውቅያኖስ
ውስጥ ይዋኛሉ፤ይንሳፈፋሉ፡፡ ይሄም የብርሃን ውቅያኖስ የእግዚአብሔር
ጸጋ ነው፡፡ በዚያ ብርሃን ልቦናቸው ይታጠባል፤ ፍጹም ሆነው የልብ
ንጽሕና ላይ ይደርሳሉ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌ ፭፥፲፫“ ሁሉ ግን በብርሃን
ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና።” እንዲል።

ሐ. ከዊነእሳት (ነጽሮተሥሉስ ቅዱስ)


ከዊነ እሳት ማለት እሳትን መሆን ማለት ነው፡፡ ይህ የመጨረሻው የብቃት
ደረጃ ነው፡፡ ቅዱሳን ከከዊነ እሳት መዓርግ ሲደርሱ እንደ እሳት ይሆናሉ
ሰውነታቸው በብርሃን ይከበባል፤ ከእግር እስከራሳቸው ድረስ እሳት
ይመስላሉ፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ከከዊነ እሳት መዓርግ ላይ
ደርሶ ስለነበር ተሐዋስያን /ነፍሳት/ እላዩ ላይ ሲያርፉ ይቃጠሉ /ይሞቱ/
ነበር፡፡ በዚህ መዓርግ ያሉ ቅዱሳን የራሳቸውን አኗኗር ይዘነጋሉ፡፡
፴፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ነፍሳቸውም በተመስጦ ለብዙ ቀናት መቆየት ትችላለች፡፡ እዚህ መዓርግ


ላይ የደረሱ ቅዱሳን ንጽሐ ልቡና ስለተሰጣቸው እግዚአብሔር (ቅድስት
ሥላሴን) በተለያየ አርአያና ምሳሌ የማየት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ፡፡ጌታችን፣
“ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው እግዚአብሔርን ያዩታልና” እንዳለ /ማቴ
፭፥፰/፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ እስጢፋኖስ አይሁድ በዲንጋይ ሲወግሩት በሰማይ
ላይ እግዚአብሔርን አይቷል (ሐዋ.፯፥፷)፡፡ ፈጣሪን ከማየት የበለጠ ክብር
እና ዕውቀት ስለ ሌለ እግዚአብሔርን ሊረዱት በሚችሉበት መጠን
(በዘፈቀደ) ይገልጽላቸዋል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን በባሕርዩ ማየት
የሚቻለው የለም፡፡ ዮሐ ፩፥፲፰፡፡ እርሱ በፈቀደ ግን ነቢዩ ኢሳይያስና
ቅዱስ ዮሐንስ እግዚአብሔርን በንጉሥ አምሳል አይተውታል፡፡ ኢሳ.፮፥፩
ራእ.፬፥፩-፲፩፡፡

፴፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ማጠቃለያ ጥያቄዎች
ክፍል ፩፦ እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ።
፩ ቅድስና ምንም ዓይነት ደረጃ የለውም።
፪ የቅድስና የመጀምሪያው ደረጃ ዝምታ ወይም አርምሞ ነው።
፫ ቅዱሳን የንጽሓ ልቦና መዓርግ ላይ ሲደርሱ ወደ ንጽሓ ሥጋ
መዓርግ ይሸጋገራሉ።

ክፍል ፪፦ አዛምድ/ጅ
ረድፍ ሀ ገድፍ ለ.
፩ ከዊነ እሳት ሀ. ካሉበት ቦታ ሆኖ ሌላ ቦታ
የሚደረገውንየ ፈለጉትን ነገር ሁሉ ማወቅ
፪ ተሰጥሞ ብርሃን ለ. በተጋድሎ ፈቃድ ሥጋቸውን
ለፈቃደ ነፍሳቸው ማስገዛት
፫ ንጻሬ መላእክት ሐ.ዝምታ
፬ ሑሰት መ.የሚያገለግሏቸውን መላእክትን
በዓይነ ሥጋ ማየትና መስማት
፭ ፍቅር ሠ. በሚያስደንቀው የእግዚአብሔር
ብርሃን ውስጥ መዋኘት
፮ ኩነኔ ረ.ሁሉንም አስተካክሎ መውደድ
፯ አንብዕ ሰ. ያለ ማቋረጥ እንባቸውን የሚያፈሱ
፰ ጣዕመ ዝማሬ ሸ. ማስተዋል ልብ ማድረግ
፱ ልባዌ ቀ. ሳይሰለቹና ሳይቸኩሉ በንቁ ሕሊና
ማመስገን እና መጸለይ
፲ አርምሞ በ. ለአጋንንት የማያስቀርብና የሚያቃጥል
ሰውነት ይኖራቸዋል

፴፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ምዕራፍ አራት

የቅዱሳን ምልጃ

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• የምልጃን አስፈላጊነት ይገነዘባሉ፣ ያብራራሉ።


• የቅዱሳን ምልጃ በብሉይ እና ሐዲስ ኪዳን እንዴት እንደ ነብር
ያብራርሉ።
• ቅዱሳን በአጸደ ሥጋ በአጸደ ነፍስም እንደሚያማልዱ አምነው
ከምልጃ ተጠቃሚ ለመሆን ይጥራሉ።

የመክፈቻ ጥያቄዎች

፩ አንተ ወይም አንቺስ ከሌሎች ቅዱሳን በተለየ የምታስበው፣


የምትለምነው ቅዱስ አለ?
፪ የቅዱሳን አማላጅነት ለምን ይጠቅማል?
፫ የቅዱሳን ምልጃ እስከመቼ ድረስ ነው?

፵፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

፬.፩. ምልጃ ምንድን ነው?

ምልጃ የሚለው ቃል በግእዙ “ተንበለ /ለመነ/ ማለደ” ከሚለው ግስ


የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ልመና ማለት ነው። መማለድ/ ማማለድ
ማለት መለመን ሲሆን አማላጅ ደግሞ ይህን ተግባር የሚያከናውነው
ነው። ተግባሩ ደግሞ ምልጃ ይባላል።

በምልጃ ውስጥ ሦስት አካላት አሉ። እነርሱም፥- አማላጅ፣ ተማላጅ እና


የሚማለድለት አካል ወይም ሰው ናቸው።
ሀ. አማላጅ፥ የማማለድን ተግባር የሚከውነው አካል ሲሆን ማማለድ
ለፍጡራን ባሕርይ የሚስማማ የትህትና ሥራ ነው። “የጻድቃን ጸሎት
ኃይልን ታደርጋለች” እንዳለ ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ (ያዕ ፭፥፲፮)

ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ፣ ክብር መወደድ አላቸው። ጌታ


“ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” እንዳለ ትእዛዙን ጠብቀው እግዚአብሔርን
መውደዳቸውን በተግባር ያሳዩ ስለሆኑ እግዚአብሔርም ይወዳቸዋል፤
ልመናቸውንም ይሰማል። ቅዱሳን ሁልጊዜም ስለ ኃጥአን ይማልዳሉ።
የሚማልዱትም ስለ ኃጥአን ራሳቸውን አሳልፈው እስከ መስጠት ነው።
ሊቀ ነቢያት ሙሴ ‘‘አሁንም ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው ያለዚያ
ግን ከጻፍኸው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ’’ እንዲል (ዘጸ ፴፪ ፥፴፪) ነዋይ
ኅሩይ ቅዱስ ጳውሎስም “ብዙ ኀዘን የማያቋርጥ ጭንቀት አለብኝ ስል
በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ አልዋሽም፣ ሕሊናዬም በመንፈስ
ቅዱስ ይመሰክርልኛል። በሥጋ ዘመዶቼ ስለሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ
ተለይቼ እኔ የተረገምሁ እንድሆን እጸልይ ነበርና” በማለት ይናገራል።
(ሮሜ ፱ ፥ ፩-፫) አማላጅ የሚባሉትም ቅዱሳን፣ ጻድቃን፣ ሰማእታት፣
ቅዱሳን መላእክትና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናቸው።

፵፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ለ. ተማላጅ፥- ተማላጅ ማለት ምልጃ ተቀባይ ማለት ነው። የጸሎት ሁሉ
መድረሻ፣ ተቀባይ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው። ቅዱስ እግዚአብሔር
ስንልም አብ ወልድ መንፈስቅዱስን ማለታችን ነው። ሦስቱ አካላት
ባንዲት ጌትነት፣ ሥልጣን፣ መለኮት፣ ፈቃድ በሰማይና በምድር የሚገኙ
ፍጥረታትን ሁሉ ልመና ተቀብለው የፈቃዳቸውን የቸርነታቸውን ሥራ
ይሠራሉ።

ሐ. የሚማለድለት፥- አማላጆች ወደ እግዚአብሔር ምልጃ የሚያቀርቡት


ለኃጥአን ሲሆን ዓላማውም - ምሕረት ቸርነት እንዲያገኙ ነው።
የሚጸለይለት ወይም የሚማለድለት ሰው ወይም ሕዝብ ደግሞ
በአማላጅነት ሥራ ውስጥ የራሱ ድርሻ አለው። ከኃጢአቱ በመመለስ
ንስሐ መግባት ወደ መልካም ሥራ መምጣት አለበት። ለዚህም ነው
እስራኤላዊያን ባቢሎን በምርኮ በነበሩበት ጊዜ አማላጃቸውን ነቢዩ
ኤርምያስን “አምላክህ እግዚአብሔር በአንተ እጅ ወደ እኛ የላከውን ሁሉ
ባናደርግ እግዚአብሔር በመካከላችን እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁን።
የአምላካችን የእግዚአብሔርን ቃል በመስማታችን መልካም እንዲሆንልን
መልካም ወይም ክፉ ቢሆን አንተን ወደ እርሱ የምንልክህ የአምላካችንን
እግዚአብሔርን ቃል እንሰማለን።” ነበር ያሉት (ኤር ፵፪ ፥ ፭-፮)

• ምልጃ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። እግዚአብሔር ለእኛ ለኃጥአን


ምሕረት እንዲያስገኙልን እና እንዲለምኑ አማላጆችን ሰጥቶናል። ለምሳሌ
እግዚአብሔር አቤሜሌክን በአብርሃም አማላጅነት ምሕረትን እንዲያገኝ
“ነቢይ ነውና ስለ አንተም ይጸልያል ትድናለህም።”ብሎ ልኮታል። (ዘፍ
፳፥፯) አምላካችን እግዚአብሔር የጻድቃንን ጸሎት የበለጠ እንደሚሰማ
መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ይናገራል። መዝ ፴፭ ፥ ፲፭ ምሳ ፲፭ ፥ ፳፱
ዮሐ ፲፭ ፥ ፯

፵፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

፬.፪. ምልጃ በአጸደ ሥጋ


ቅዱሳን ተጋድሏቸውን ሳይጨርሱ በአጸደ ሥጋ (በምድር ላይ በሕይወት
እያሉ) እንደሚያማልዱ ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ።

፬.፪.፩. የቅዱሳን ምልጃ በዘመነ ብሉይ


፩ኛ. የጻድቁ አብርሃም ምልጃ
አባታችን አብርሃም ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ቅርበት፣ እምነቱ
ባጠቃላይ ሁለንተናዊ ሕይወቱ ሥርወ ሃይማኖት (የሃይማኖት ጀማሪ)
እንድንለው አድርጎናል። በዚህም በእምነት የሁላችን አባት ተብሏል።
ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ እንዳለ፦“ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም
እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ
ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ
ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ
አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው።” ሮሜ
፬፥፲፮-፲፯

ስለዚህ አባታችን አብርሃም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስና ክብር ያለው


ስለሆነ ለጻድቃን በተደጋጋሚ ሲለምን እናገኘዋለን። ለምሳሌ እግዚአብሔር
ሰዶምና ገሞራን ሊያጠፋ ሲል አባታችን አብርሃም እንዳያጠፋ
ለምኖታል። ነገር ግን በመካከላቸው ቢያንስ ፲ ጻድቃን እንኳን ሊገኝ
ስላልቻለ ጠፍተዋል።

ዘፍ ፲፰፥፳፫ –፴፪ “አብርሃምም ቀረበ አለም፥ በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ


ጋር ታጠፋለህን? አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን
ታጠፋለህን? ከተማይቱንስ በእርስዋ ለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን?
ይህ ከአንተ ይራቅ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም
እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ።
የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን? እግዚአብሔርም፦
፵፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ አምሳ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ
ስለእነርሱ እምራለሁ አለ።

የጌራራውን ንጉሥ አቤሜሌክ ሚስቱ ሣራን ሊወስድ ፈልጎ እግዚአብሔር


እንዴት እንደከለከለው እና አብርሃምም ለአቤሜሌክ እንደጸለየለትም
በዚሁ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንደዚህ ቀርቧል።
ዘፍጥረት ፳ ፥ ፩- ፲፰ ‹‹አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ አዜብ ምድር ሄደ፥
በቃዴስና በሱር መካከልም ተቀመጠ በጌራራም በእንግድነት ተቀመጠ።
አብርሃምም ሚስቱን ሣራን፦ እኅቴ ናት አለ የጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክም
ላከና ሣራን ወሰዳት።

እግዚአብሔርም ሌሊት በሕልም ወደ አቢሜሌክ መጣ፥ እንዲህም አለው፦


እነሆ፥ አንተ ስለወሰድሃት ሴት ምውት ነህ እርስዋ ባለ ባል ናትና።
አቢሜሌክ ግን አልቀረባትም ነበር፤እንዲህም አለ፦ አቤቱ፥ ጻድቁን ሕዝብ
ደግሞ ታጠፋለህን? እኅቴ ናት ያለኝ እርሱ አይደለምን? እርስዋም
ደግሞ ራስዋ፦ ወንድሜ ነው አለች በልቤ ቅንነትና በእጄ ንጹሕነት
ይህንን አደረግሁ።

እግዚአብሔርም በሕልም አለው፦ ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ


እኔ አወቅሁ፥እኔም ደግሞ በፊቴ ኃጢአትን እንዳትሠራ ከለከልሁህ፤
ስለዚህም ትነካት ዘንድ አልተውሁም። አሁንም የሰውዬውን ሚስት
መልስ ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፥ ትድናለህም። ባትመልሳት
ግን አንተ እንድትሞት ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንዲሞት በእርግጥ
እወቅ።

አቢሜሌክም በነገታው ማለደ ፥ባሪያዎቹንም ሁሉ ጠራ፥ ይህንም ነገር


ሁሉ በጆሮአቸው ተናገረ ሰዎቹም እጅግ ፈሩ። አቢሜሌክም አብርሃምን
ጠርቶ አለው፦ ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው? ምንስ ክፉ ሠራሁብህ?
፵፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

በእኔና በመንግሥቴ ላይ ትልቅ ኃጢአት አውርደሃልና የማይገባ ሥራ


በእኔ ሠራህብኝ።

አቢሜሌክም አብርሃምን አለው፦ ይህን ማድረግህ ምን አይተህ ነው?


አብርሃምም አለ፦ በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት በእውነት
እንደሌለ፥ ለሚስቴም ሲሉ እንደሚገድሉኝ ስላሰብሁ ነው። እርስዋም
ደግሞ በእውነት እኅቴ ናት፤ የእናቴ ልጅ አይደለችም እንጂ የአባቴ ልጅ
ናት፤ ለእኔም ሚስት ሆነች። እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ
አልኋት፦ በገባንበት አገር ሁሉ ለእኔ የምታደርጊው ወሮታ ይህ ነው፦
ወንድሜ ነው ብለሽ ስለ እኔ ተናገሪ።

አቢሜሌክም በጎችንና ላሞችን ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችን አመጣ፥


ለአብርሃምም ሰጠው፥ሚስቱን ሣራንም መለሰለት። አቢሜሌክም፦ እነሆ፥
ምድሬ በፊትህ ናት፤በወደድኸው ተቀመጥ አለ። ሣራንም አላት፦ እነሆ፥
ለወንድምሽ ሺህ ሚዛን ብር ሰጠሁት፤ያም እነሆ ከአንቺ ጋር ባሉት ሁሉ
ፊት የዓይኖች መሸፈኛ ይሁንሽ፤ ጽድቅሽ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና።
አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤እግዚአብሔርም አቢሜሌክን
ሚስቱንም ባሪያዎቹንም ፈወሳቸው፥ እነርሱም ወለዱ፤እግዚአብሔር
በአብርሃም ሚስት በሣራ ምክንያት በአቢሜሌክ ቤት ማኅፀኖችን ሁሉ
በፍጹም ዘግቶ ነበርና።››

፪ኛ. የጻድቁ ኢዮብ ምልጃ


ኢዮ ፵፪፥፯-፲፩ “እግዚአብሔርም ይህን ቃል ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ
እግዚአብሔር ቴማናዊውን ኤልፋዝን፦እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ ቅንን
ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና ቍጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ
ላይ ነድዶአል። አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች
ይዛችሁ ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ፥ የሚቃጠልንም መሥዋዕት
ስለራሳችሁ አሳርጉ ባሪያዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፥ እኔም እንደ
፵፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ስንፍናችሁ እንዳላደርግባችሁ ፊቱን እቀበላለሁ እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ
ቅን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና።

፫ኛ. የነቢዩ ሙሴ ምልጃ


. የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባለመስማቱ
እግዚአብሔር ግብፅን በዕንቁራሪት (ጓጉንቸር) አስወረራት፣ መላዋ የግብፅ
አገር በእንቁራሪት ተሸፈነች፣ፈርዖንም ይህን አስደንጋጭ መቅሰፍት
አይቶ ሙሴና አሮንን ጠርቶ (ጓጉንቸሮቹ) ከእኔና ከሕዝቤም እንዲርቁ
ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ አላቸው፡፡ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ
(አማለደ) እግዚአብሔርም በሙሴ ምልጃ ጓጉንቸሮቹን በሙሉ ገደለ፣
ዘጸ. ፰፥፰-፲፭፡፡

እስራኤላውያን ጣዖትን በማምለክ ከባድ ኃጢአት በፈጸሙ ጊዜ


እግዚአብሔር ሙሴን ጠርቶ ይህን ሕዝብ አጠፋለሁ (እደ መስሳለሁ)
አንተም በታላቅ ሕዝብ ላይ እሾምሃለሁ ባለው ጊዜ ሙሴ ወደ ፈጣሪው
ወደ እግዚአብሔር አጥብቆ ጸለየ (አማለደ) በዚህ ጊዜ መሐሪ እግዚአብሔር
በሙሴ ምልጃ ሊያደርገው ካሰበው መቅሰፍት በራሱ መሐሪነት ተመልሶ
መቅሰፍቱን አስቀረ ሕዝቡንም በሙሉ ጸሎት ምልጃ ይቅር አለ ዘጸ.
፴፪፥፲፩-፲፬፣ መዝ.፻፮፥፳፫፡፡

.ሙሴ ኢትዮጵያዊትዋን ሴት ልጅ በማግባቱ ወንድሞቹ አሮንና ማርያም


ሙሴን በመቃወም አሙት በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር የነገሩ
ቆስቋሽና ጀማሪ የነበረችውን ማርያምን በለምጽ በሽታ መታት /በረዶ
መሰለች/ ነገር ግን ሙሴ ሰባት ቀን ወደ እግዚአብሔር ጸለየላት /
ማለደላት/ እግዚአብሔርም በሙሴ ጸሎት /ምልጃ/ ፈወሳት ዘኁል.፲፪፥፩-፯፡፡

፵፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

፬ኛ. የነቢዩ የኤልያስ ምልጃ


ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ በምልጃው /በጸሎቱ/ ብዙ አስደናቂ ተአምራቶች
ፈጽሞአል፡፡ ከእነርሱም መካከል፡፡
. ሕገ እግዚአብሔርን የተው ወገኖችን ለመቅጣትና ለማሳፈር የሰማይ
ዝናብ እንዳይዘንብ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ የሰማይ ዝናብም በኤልያስ
ቃል ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ሳይዘንብ ቀጥ አለ፡፡ ከእነዚህ ዓመታት
በኋላ ግን ነቢዩ ኤልያስ ዝናብ እንዲዘንብ ወደ ፈጣሪው ጸሎት /ምልጃ/
አቀረበ፡፡ ዝናብም በሚገባ ዘነበ ፩ኛነገ. ፲፯፥፩-፯ እንደገና ፩ኛነገ. ፲፰፥፴-፵፮
በጸሎቱ መሥዋዕቱን ከሰማይ እሳት ወርዶ በላለት፡፡
. ለሞተው ሕፃን ልጅ ስለ እናቱ ሲል ኤልያስ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮ
(ምልጃ አቅርቦ) የልጁም ነፍስ ተመልሳ ልጁም ከሞት ተነሳ ፩ኛነገ.
፲፯፥፲፯-፳፬፡፡

፭ኛ. የነቢዩ ኤልሳዕ አማላጅነት


ገቢረ ተአምር ኤልሳዕም በጸሎቱ /በምልጃው/ ብዙ ተአምራቶች
አድርጎአል፡፡ከተአምራቶቹም መካከል አንደኛው የሞተውን ልጅ ጸልዮ
ማስነሳቱ ነው። (፪ኛነገ. ፬ ፥ ፲፰-፴፯ )

፮ኛ.የቅዱስ ዳዊት አማላጅነት


ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም ‘‘ሕዝቡን የሚመታውን መልእክ ባየ ጊዜ
እግዚአብሔርን፦ እነሆ፥ እኔ በድያለሁ ጠማማም ሥራ እኔ አድርጌአለሁ
እነዚህ በጎች ግን እነርሱ ምን አደረጉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ
እንድትሆን እለምንሃለሁ ብሎ ተናገረው።” በማለት በአቀረበው ጸሎት /
ምልጃ/ መቅሰፍቱ በፈጣሪ ቸርነት ተገታ። (፪ሳሙ. ፳፬ ፥ ፲፭-፳፭)
. ፪ኛነገ ፲፱፥፴፬ “ስለባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ
እጋርዳታለሁ።”
. ፪ኛነገ ፳፥፮ “በዕድሜህም ላይ አሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ
አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ ስለ እኔም
፵፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ስለባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ እጋርዳታለሁ።
. መዝ ፹፰፥፫ “ከመረጥሁት ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ፥ ለባሪያዬም
ለዳዊት ማልሁ።ዘርህን ለዘላለም አዘጋጃለሁ፥ ዙፋንህንም ለልጅ ልጅ
እመሠርታለሁ።

፯ኛ.የነቢዩ ኤርምያስ ምልጃ


በአሥር ቀን ጸሎት (ምልጃ) በእስራኤላውያን ታስቦ የነበረውን መቅሰፍት
አንደተገታ ተገልጾአል፡፡ (ኤር. ፵፪፥፩-፲፯)

፬.፪.፪. የቅዱሳን ጻድቃን ምልጃ በሐዲስ ኪዳን


የሐዲስ ኪዳን ዘመን የጠብ ግድግዳ የፈረሰበት፣ ኃጢአት መጋረጃ
የተቀደደበት ዘመን ነው። በመሆኑም ቅዱሳን ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር
የቀረቡበት ጊዜ ነው። በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላቸው ይበልጥ ከብረዋል።
ይህንንም ጌታችንንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነት
እውነት እላችኋለሁ የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህን
ተራራ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል የሚሳናችሁም ነገር የለም”፤
“እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ
ደግሞ ያደርጋል፣ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።” በማለት ተናግሯል።
(ማቴ ፲፮ ፥ ፳ ፣ ዮሐ ፲፬ ፥ ፲፪)

ስለዚህ የአማላጅነት አገልግሎት ሳይቋረጥ በዘመነ ሐዲስም ማለት ጌታችን


ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ዘመንና በዘመነ ሐዋርያትም
ይፈጸም እንደነበረ ከዚህ ቀጥለን እንመለከታለን፡፡ በወንጌል እንደተጻፈው
ወላጆች” ልጄ ታሞ ለሞት ተቃርቦአልና ፈውስልኝ” በማለት ስለ ታመሙ
ሰዎች ወጥተው ባቀረቡት ምልጃ እንኳን ሲታመሙ ሲሞቱ ጭምር
ከሞት እንዳስነሳላቸው ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡ በዚህ ዓይነት
ጌታችንን እየለመኑ ልጆቻቸውን ያዳኑና ከሞት እንዲነሳላቸው ያደረጉ
ብዙ ናቸው፡፡ ይህ የአማላጅነት ሥራ ነው፡፡ ይልቁን እርሱ ያከበራቸውና
፵፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

የመረጣቸው ቅዱሳን አብልጠው የአማላጅነት ሥራ እንደምን አይሠሩ?


(ማቴ. ፱ ፥ ፲፰-፳ ፤ ፲፭ ፥ ፳፩፣ማቴ. ፲፯ ፥ ፲፬፣ ማር.፭ ፥ ፳፪-፵፬፣
ሉቃ. ፯ ፥ ፩-፲ )

ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንዳንድ ጊዜ በሽተኞች በቀጥታ


ሲለምኑት ይፈውሳቸው እንደነበረ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከዚህ በላይ
እንዳየነው ስለበሽተኞቹ ሌሎች ሰዎች በማለዱላቸው ጊዜ ይፈውሳቸው
ነበር፡፡ በዚህ መሠረት አማላጅነት ማለት አንዱ ስለሌላው መጸለይና
መለመን፣ ማማለድ ማለት ነው፡፡

፬.፫ አማላጅነት በዘመነ ሐዋርያት


ሐዋርያት በተሰጣቸው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ መሠረት በሐዲስ
አማንያንና በበሽተኞች ላይ እጃቸውን እያኖሩ መንፈስ ቅዱስን ሲያሰጡና
ሕመምተኞች ሲፈውሱ ያየ ሲሞን ይህን ታላቅ የመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን
እንዲሰጠው ገንዘብ ይዞ ወደ ሐዋርያት ቀረበና ‘‘እጄን በምጭንበት ሁሉ
መንፈስ ቅዱስን ይቀበል ዘንድ ለእኔ ደግሞ ይህን ሥልጣን ስጡኝ’’ አለ፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ ይህንን ሰምቶ ሲሞንን አጥብቆ ገሰጸው ንስሐም እንዲገባ
መከረው፡፡ ሲሞን የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ /ጸጋ/ በገንዘብ መግዛት /
መለወጥ/ ታላቅ ስሕተት መሆኑን ከተገነዘበ በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስን‘‘
ካላችሁት ማለትም ከተናገራችሁት አንዳች እንዳይደርስብኝ እናንተው
ወደ ጌታ ለምኑልኝ አማልዱኝ አላቸው’’ ይላል። (ሐዋ. ፰፥ ፲፬-፳፭)

ከዚህ ላይ ከሲሞን አባባል የምንረዳው ዓቢይ ቁም ነገር አለ ይኸውም


አንዳች ክፉ ነገር እንዳይደርስብኝ እናንተ ወደ እግዚአብሔር አማልዱልኝ
/ለምኑልኝ/ ማለቱ በዚያን ጊዜ ሐዋርያት ስለ በደሉ ሰዎች ወደ
እግዚአብሔር ይጸልዩና ምልጃንም ያቀርቡ እንደነበረ ይረጋገጣል፡፡


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
. ማቴ ፲፥፵-፵፪ “እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል
የላከኝን ይቀበላል።ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ
ይወስዳል፥ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።”
. ዮሐ. ፳፥፳፫ “ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤
የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል አላቸው።”
ሐዋ. ፯፥፷ እስጢፋኖስም ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ
ሲጠራ ይወግሩት ነበር።ተንበርክኮም። “ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት
አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።”

. ሐዋ ፱፥፴፮-፵ “በኢዮጴም ጣቢታ የሚሏት አንዲት ደቀመዝሙር


ነበረች፥በዚያም ወራት ታመመችና ሞተች፤ አጥበውም በሰገነት አኖሯት።
ልዳም ለኢዮጴ ቅርብ ናትና ደቀመዛሙርት ጴጥሮስ በዚያ እንዳለ
ሰምተው፥ ወደ እነርሱ ከመምጣት እንዳይዘገይ እየለመኑ ሁለት ሰዎች
ወደ እርሱ ላኩ። ጴጥሮስም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር መጣ፤በደረሰም
ጊዜ በሰገነት አወጡት መበለቶችም ሁሉ እያለቀሱ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር
ሳለች ያደረገቻቸውን ቀሚሶችንና ልብሶችን ሁሉ እያሳዩት በፊቱ ቆሙ።
ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ ወደ ሬሳውም
ዘወር ብሎ፡- ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ አላት።እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች
ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች።

. ፩ኛ ቆሮ. ፮፥፩ “ከእናንተ አንዱ ከባልንጀራው ጋር ሙግት ቢኖረው


በቅዱሳን ፊት በመፋረድ ፋንታ በዓመፀኞች ፊት ሊፋረድ ይደፍራልን?
ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? በዓለምስ ላይ ብትፈርዱ
ከሁሉ ይልቅ ትንሽ ስለሚሆን ነገር ልትፈርዱ አትበቁምን? የትዳር
ጉዳይ ይቅርና በመላእክት እንኳ እንድንፈርድ አታውቁምን? ስለዚህ
ቅዱሳን ማማለድ ይቅርና በተሰጣቸው ጸጋ ይፈርዳሉ፡፡

፶፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

. ፪ኛቆሮ. ፭፥፳ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር


ያስታርቅ ነበርና፥በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ
ቃል አኖረ። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ
መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ
እንለምናለን።
. ያዕ ፭፥፲፬ “ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተክርስቲያንን
ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው
ይጸልዩለት።”

፬.፬. የቅዱሳን አማላጅነት በአጸደ ነፍስ (ከሞት በኋላ)


ከላይ ስለምልጃ ባብራራነው መሠረት እና ባነሳናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ
ክፍሎች ውስጥ ምልጃን የሠጠ፣ ለቅዱሳን የፈቀደ እርሱ እግዚአብሔር
መሆኑን ሲረዱ ደግሞ “ይሄማ በአጸደ ሥጋ ያሉ ሰዎችን ብቻ
የሚመለከት ነው እንጂ በሥጋ ከእኛ ተለይተው በአጸደ ነፍስ ያሉትን
ቅዱሳን አይመለከትም” የሚኖሩ ይኖራሉ። ቅዱሳን በአጸደ ሥጋ ነው
እንጂ በአጸደ ነፍስ ወይም ከዚህ ዓለም ድካም ካረፉ በኋላ በገነት
እያሉ አያማልዱም ማለት መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ካለመረዳት
የሚመጣነው።
ስለዚህ ቅዱሳን ካረፉ በኋላ ያማልዳሉ የምንለው በሚከተሉት ዋና ዋና
ምክንያቶች ነው።

፩ ሕያዋን ናቸው እንጂ ሙታን አይደሉም!


በሃይማኖት፣ በምግባር ጸንቶ የኖረ ሰው ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ
ቢለይ እንኳን ሞተ ሳይሆን ከዚህ ዓለም ድካም አረፈ፣ ወደ ዘለዓለማዊ
ሕይወት ተሻገረ ይባላል እንጂ ተስፋ ትንሳኤ እንደሌላቸው አሕዛብ
እንደ ሞተ የሚቀር፣ የሚበሰብስ አይደለም። ይህንንም ጌታ በወንጌል
በተደጋጋሚ ተናግሯል።

፶፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
• “ሙታንስ በሚነሡበት ጊዜ በሰማያት እንደ እግዚአብሔር መላእክት
ሆነው ይኖራሉ እንጂ አያገቡም፣ አይጋቡምም። ስለ ሙታን መነሣት
ግን ስለ እናንተ ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም
አምላክ ነኝ’ የሚልከ እግዚአብሔር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን
አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም”
እንዲል፡፡ (ማቴ ፳፪ ፥ ፴፪)

• “ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። ሥጋዬን


የሚበላ ደሜን የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ።
ሕያው አብ እንደላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን እንዲሁ
የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሳ ሕያው ይሆናል።”፤ “ ትንሳኤና ሕይወት
እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳን ሕያው ይሆናል፤ ሕያው የሆነም
የሚያምነኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም።” (ዮሐ ፰ ፥ ፶፭-፶፯፤ ዮሐ ፲፩
፥ ፳፭ -፳፮)

ቅዱስ ጳውሎስም “ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት


ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና። መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ
ለኃጢአት ሞቶአልና፤ በሕይወት መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል።
እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደሞታችሁ ግን በጌታችን በኢየሱስ
ክርስቶስ ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደሆናችሁ ቁጠሩ።” (ሮሜ
፮ ፥ ፱-፲፩)

ስለዚህ እኛም በዚህ የሙታን ትንሳኤ ሕይወት እና የቅዱሳን ቃል ኪዳን


የምናምን እኛ ስለባለሟልህ ብለህ እያልን ቅዱሳንን እንጠራለን።
• “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር፤ ...ቃል ኪዳንህንም
አትለውጥብን ፤ ይቅርታህንም አታርቅብን። ስለ ወዳጅህ ስለ አብርሃም
፥ ስለ ባለሟልህ ስለ ይስሐቅ ፣ ስለ ቅዱስህ ስለ እስራኤል።” (ትንቢተ
ዳንኤል ፦ ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ ቁ. ፲፩ ፥ ፲፫ )
፶፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

• በተመሳሳይ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር ለልጁ


ሰሎሞን እንዲህ ብሏል። “ይህን ሠርተሃልና፣ ያዘዝሁትንም ትእዛዜን
አልጠበቅህምና መንግሥትህን ካንተ ከፍዬ ለባርያህ እሰጠዋለሁ። ነገር
ግን ከልጅህ እጅ እከፍለዋለሁ እንጂ ስለ አባትህ ስለ ዳዊት ይህን
በዘመንህ አላደርግም። ነገር ግን ስለባርያዬ ስለ ዳዊትና ስለ መረጥኋት
ሀገሬ ስለ ኢየሩሳሌም ለልጅህ አንድ ነገድ እሰጣለሁ እንጂ መንግሥቱን
ሁሉ አልከፍልም።” (፩ኛ ነገ ፲፩ ፥ ፲፩-፲፬ )

፪ አዋቂዎች ናቸው - ያውም በምድር እያሉ ከነበራቸው እውቀት የተሻለ!

ከሞት በኋላ ሕይወት ካለ ደግሞ ዓዋቂነትም መኖሩ የማይጠረጠር ነገር


ነው። ይሄውም ዕወቀት በዚህ ዓለም ከነበረው የተከፈለ እና ድንግዝግዝ
ያለ ዕውቀት ይልቅ ግልጥ እንደሆነ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል። “ዛሬስ
በመስታወት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት
እናያለን ዛሬስ በዕውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ
እንደታወቅሁ አውቃለሁ” በማለት የቅዱሳን ዕውቀት በአጸደ ነፍስ ታላቅ
እንደሆነ ተናግሯል።” (፩ኛ ቆሮ ፲፫ ፥ ፲፪) ስለዚህ ቅዱሳን ሕያዋን፣
አዋቂዎች በመሆናቸው እዚህ ምድር ላይ ሆነን የምንለምናቸውን
ይሰማሉ፣ ለእግዚአብሔርም ምህረትን ይለምኑልናል።

በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፮ ላይ የሚገኘው የነዌ እና አልዓዛር እንዲሁም


አብርሃም ታሪክ የምልጃን ምንነት እና የቅዱሳንን ዕውቀት፣ ሕያውነት
በደንብ ስለሚያስረዳልን በስፋት እንየው።

ሉቃስ ፲፮ ፥ ፲፱ - መጨረሻ
<<ቀይ ልብስና ቀጭን የተልባ እግር የለበሰ አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፥
ዕለት ዕለትም እየተመቸው በደስታ ይኖር ነበር። አልዓዛርም የሚባል
አንድ ድሀ በቍስል ተወርሶ በደጁ ተኝቶ ነበር፥ ከባለ ጠጋውም ማዕድ
፶፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ከሚወድቀው ፍርፋሪ ሊጠግብ ይመኝ ነበር፤ ውሾች እንኳ መጥተው
ቍስሎቹን ይልሱ ነበር። ድሀውም ሞተ፥ መላእክትም ወደ አብርሃም
እቅፍ ወሰዱት፤ ባለጠጋው ደግሞ ሞተና ተቀበረ። በሲኦልም በሥቃይ
ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ። እርሱም እየጮኸ፦
አብርሃም አባት ሆይ፥ ማረኝ፥ በዚህ ነበልባል እሰቀያለሁና የጣቱን ጫፍ
በውኃ ነክሮ መላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ስደድልኝ አለ።

አብርሃም ግን፦ ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም እንደተቀበልህ


አስብ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል
አንተም ትሰቃያለህ። ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ
የሚፈልጉ እንዳይችሉ፥ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና
በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጓል አለ።

እርሱም፦ እንኪያስ፥ አባት ሆይ፥ ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው


እለምንሃለሁ፤ አምስት ወንድሞች አሉኝና፤ እነርሱ ደግሞ ወደዚህ
ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው አለ።
አብርሃም ግን፦ ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ አለው።
እርሱም፦ አይደለም፥ አብርሃም አባት ሆይ፥ ነገር ግን ከሙታን አንዱ
ቢሄድላቸው ንስሐ ይገባሉ አለ።
ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ
አያምኑም አለው።>>

ከዚህ ታሪክ ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን።


፩ ኃጥኡ ነዌ እንኳን ሲዖል ሆኖ የአብርሃምንና አልዓዛርን ማንነት
ማወቁና በትክክለኛ ጊዜም ባይሆን አብርሃምን ያድነው ዘንድ መለመኑ
፪ አባታችን አብርሃም አልዓዛር እና ነዌ መሬት ላይ የኖሩትን የተራራቀ
ሕይወት ማወቁ፣
፫ ምንም እንኳን የኃጥአን ጸሎት ያውም የንስሐ ዕድል በሌለበት ሲዖል
፶፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ውስጥ ሆኖ (ሆኖ) በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ባይኖረውም፣ ነዌ


እንኳን በምድር ላሉት ወንድሞቹ ድኅነት እንዲያገኙ መለመኑ፣
፬ አባታችን አብርሃም የነበረበት ዘመን ከሙሴና ከሌሎች በርካታ
ነቢያት መነሣት እጅግ ብዙ ዓመታት በፊት /የራቀ/ ቢሆንም፤ በዚህች
ምድር ላይ በነዌ እና በአልዓዛር ዘመን የሙሴ መጻሕፍት እና በወንበሩ
የተተኩ ካህናት፣ መምህራንና ነቢያት መኖራቸውንና ማስተማራቸውን
ዐውቆ መናገሩ የቅዱሳንን ሁሉ ክብር፣ ዕውቀት፣ ሥልጣንና ታላቅነት
የሚያሳይ አምላካዊ ምስክርነት ነው።

ቅዱሳን በአካለ ነፍስ ሆነው በምድር የሚሠራውን ነገር ማወቅ እስከቻሉ


ድረስ የኛን ልመና ሰምተው መግለጽ አይሳናቸውም፡፡ ምክንያቱም ሥጋ
ወደ መቃብር ቢወርድም ነፍስ ሕያዊት ናትና አትሞትም፡፡

በአካለ ነፍስ ያሉ ቅዱሳን “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ እስከ መቼ ድረስ


አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትቀበልም?”
በማለት በአካለ ነፍስ እንደሚከሱ ተገልጿል፡፡ (ራእ. ፮፥፱-፲፩) ቅዱሳን
በአካለ ነፍስ ደማችንን በምድር ተበቀልልን ብለው ከለመኑ ለበጎ ነገር
አማልዱን ስንላቸው ምን ያህል አብዝተው ይለምኑልን?

ቅዱስ ጴጥሮስም በመልእክቱ ከዚህ ዓለም መሄጃ ጊዜ የስለደረሰ


እየተጋችሁ በጸጋ ላይ ጸጋ እየጨመራችሁ በመንፈሳዊ ሕይወት
ጠንክራችሁ የምንፈስ ፍሬን ልታፈሩ እንደሚገባ ላሳስባችሁ እፈልጋለሁ
ሲል ይቆይና “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ ማደሪያዬ
መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁና። ከመውጣቴም በኋላ እነዚህን
ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ። “በማለት ቅዱስ
ጴጥሮስ ከመውጣቴም በኋላ ወይም ከሞት በኋላ ስለናንተ እተጋለሁ
(እለምናለሁ) በማለት ያስረዳል፡፡ (፪ኛ ጴጥ. ፩፥፲፭)

፶፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሐዋርያትን “አንትሙ ውእቱ ብርሃኑ
ለዓለም - እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ” ያላቸው ብርሃንነታቸው በዚህ
በኃላፊው ዓለም ብቻ ተወስኖ እንዲቀር አይደለም፣አማላጅነታቸውም
በአጸደ ነፍስ ሳሉ ጭምር ነው እንጂ ከሞቱስ በኋላ ማማለድ የለባቸውም
እንዳይባል የሰው ልጅ በግርማ መንግሥት በክበበ ትስብዕት መጥቶ
በጌትነቱ በተገኘ ጊዜ እናንተም በ፲፪ መንበሮች ተቀምጣችሁ በ፲፪ቱ ነገደ
እስራኤል ላይ ትፈርዳላችሁ ብሎአቸዋል ማቴ. ፲፱፥፳፰፡፡ ከማማለድና
ከመፍረድስ የቱ ይቀላል?

ማጠቃለያ
በሥጋ የተለዩ፣ በነፍስ ግን ሕያዋን የኾኑ ቅዱሳን በሥጋ ለሞቱት ሰዎች
ያማልዳሉ፤በሥጋ ያልሞቱት ደግሞ በሥጋ ለሞቱት ‹‹አማልዱን›› እያሉ
ይጸልያሉ፡፡ ‹‹በዚያ ወራት የወዳጆቼ የጻድቃን ልመናቸው ወደ ሰማይ
ወጣች፤ከዚህ ዓለም በግፍ የፈሰሰ የጻድቁም ደም በመላእክት ጌታ ፊት
ተወደደ፡፡ በእነዚህ ወራቶች በሰማይ የሚኖሩ ጻድቃን በአንድ ቃል ኾነው
ተባብረው ያመሰግናሉ፤ ለሰው ፈጽመው ይለምናሉ፡፡ ፈጣሪያቸውን
ያመሰግናሉ፤›› ተብሎ እንደተጻፈ (ሄኖክ ፲፪፥፴፫)፡፡ ሙታን ለሕያዋን፣
ሕያዋን ለሙታን ይጸልያሉ ማለትም ይኸው ነው፡፡እግዚአብሔር
አምላካችን በቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ይጠብቀን፡፡

፶፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

የማጠቃለያ ጥያቄዎች
ክፍል ፩ - እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ
፩ ቅዱሳን በዚህ ዓለም በሥጋ እያሉ ብቻ ሳይሆን ካረፉ በኋላ በአጸደ
ነፍስም ያማልዳሉ።
፪ ቅዱሳን ሕያዋን እንጂ ሙታን አይደሉም።
፫ አምላካችን እግዚአብሔር ስለ ቅዱሳን ጸሎት እና ቃልኪዳን ሲል
ቅጣትን ያስወግዳል።
፬ አባታችን አብርሃም እየለመነው እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን
ያጠፋቸው ምልጃውን አልቀበል ብሎ ነው።
፬ ቅዱሳን ከሞቱ እና ወደ ገነት ከሄዱ በኋላ እዚህ ዓለም ስለሚሆነው
ነገር አያውቁም።

ክፍል ፪ -የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ ወይም አብራሩ


፩ ቅዱሳን በበሉይ ኪዳን ያማልዱ እንደነበር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ
ጨምራችሁ አብራሩ።
፪ በዘመነ ሐዋርያት ከነበሩ ምልጃዎች የተወስኑትን ጥቀሱ።
፫ ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ ስለምልጃ የተናገረውን ቃል ጠቅሳችሁ
አብራሩ።

፶፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ምዕራፍ አምስት

የቅዱሳን ክብርና ሥልጣን

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

፩ የቅዱሳንን ክብር ይረዳሉ


፪ ቅዱሳን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጣቸውን ሥልጣን ይረዳሉ

የመክፈቻ ጥያቄዎች

፩ ለቅዱሳን እናቶቻችንና አባቶቻችን እግዚአብሔር የሰጣቸውን


ክብር ተናገሩ?
፪ እኛ ለቅዱሳን ምን አይነት ክብርን መስጠት ይገባናል?

፶፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

፭.፩. የቅዱሳን ክብርና ሥልጣን

እግዚአብሔር ከ፳፪ቱ ሥነፍጥረት በቅድስና መዓርግ ስሙን ቀድሰው


ክብሩን እንዲወርሱ አድርገው የፈጠራቸው ቅዱሳን መላእክትንና፣ የሰው
ልጅን ነው፡፡ ቤተክርስቲያን የቅዱሳንን ውለታ አትረሳም፡፡ በአጸደ ሥጋ
ያሉትን በማገልገል ያረፉትን ቅዱሳንን ደግሞ በማክበር ገድላቸውን
በመጻፍ መታሰቢያቸውን ታደርጋለች፡፡ “እግዚአብሔር
ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው ያደረጋችሁትን
ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ አመጸኛ አይደለምና፡
፡” (ዕብ. ፮÷፲ ) ቤተክርስቲያን ቅዱሳንን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ
በጸበል፣ ቤተ ክርስቲያን በማነጽ፣ ጽላት በመቅረጽ ታስባቸዋለች፡፡
እግዚአብሔርም በነቢዩ አንደበት “በቤቴና በቅጽሬ ውስጥ ከወንዶችና
ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋልሁ
የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ፡፡” ብሎ ቃል ገብቶላቸዋል።
(ኢሳ.፶፮÷፭) ቤተክርስቲያን በቅዱሳን የልደትና የእረፍት ዕለታት
የመታሰቢያ በዓል በማድረግ በቅዳሴና በማኅሌት በማክበር በዓለ ንግሥ
ታደርጋለች፡፡ በስማቸው ጠበል ጻዲቅ ታደርጋለች፡፡ ጻድቅን በጻድቅ ስም
የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይቀበላል እንዲል፡፡ (ማቴ ፲÷፵-፵፪)

ሌላው ቤተክርስቲያን ቅዱሳንን የምታስበው የተጋደሉትን ተጋድሎ፣


የደረሰባቸውን ፈተና፣ያደረጉትን ውጊያ፣ ጦርነት ድልና አክሊል
እስካገኙበት ድረስ ያሉትን ገድላቸውን በመጻፍ ታስባቸዋለች፡፡ (፪ኛጢሞ.
፮÷፲፪፣ ይሁዳ ቁጥር ፫) እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ የሰጠውን ክብርና ጸጋ
የሚገልጽባቸው ብዙ መንገዶች አሉ:: እነዚህም የቅዱሳኑን ማንነት
መግለጫና ለሰው ጥቅም የተሰጡ ናቸው:: የቅዱሳን ክብር የመላዕክትንም
ጭምር የሚያካትት ሲሆን በዚህ ንዑስ ርእስ ስር ግን የቅዱሳን ሰዎች
ብቻ ቀርቧል፡፡


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

፭.፩.፩. የቅዱሳን ክብር

፩ በስማቸው ቤተክርስቲያን ማነጽ


ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ስም በማኅበር የሚጠራባት እግዚአብሔርም
ጸጋውንና በረከቱን የሚያድልባት የምህረት ግምጃ ቤት ናት። (ኢሳ.
፩፥፳፮) መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም በቤተ መቅደስ እየተገኘ
ያስተምር ነበር:: ቤተክርስቲያንን “የአባቴ ቤት” ብሎታል። (ሉቃ ፪፥፵፱)
እግዚአብሔር አምላክ በቤቱ ወዳጆቹ ቅዱሳን እንዲታሰቡበት እንዲህ
ሲል አዞአል::

ኢሳ. ፶፮፥፬-፯ “እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም


ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ
ይላልና። በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ
የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ የማይጠፋም የዘላለም ስም
እሰጣቸዋለሁ። ያገለግሉት ዘንድ የእግዚአብሔርንም ስም ይወድዱ ዘንድ
ባሪያዎቹም ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚጠጉትንም መጻተኞች፥
እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን ቃል ኪዳኔንም የሚይዙትን ሁሉ፥
ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ”
እግዚአብሔር ይህንን ቃል ኪዳን የገባው ለጃንደረቦች ነው:: ጃንደረባ
የሚለውን ደግሞ ሲፈታው ማቴ ፲፱፥፲-፲፪ “ይህ ነገር ለተሰጣቸው
ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም፤ በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ
አሉ፥ ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ፥ስለ መንግሥተ ሰማያትም
ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ። ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው።
ቅዱሳን ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ሲሉ እራሳቸውን ጃንደረባ ያደረጉ
ናቸውና ቅዱሳን ስማቸው የማያልፍ: ሁልጊዜ የሚዘከርና የማይጠፋ
እንደሆነ በማይታበል ቃሉ ተናገረ::

፷፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

“በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ” ማለቱም ስማቸው የሚዘክረውና


የሚጠራው በቤቱና በቅጥሩ ውስጥ በመሆኑ ነው:: ራሳቸውን ስለ
እርሱ ፍቅር ሲሉ ጃንደረቦች ያደረጉት የወዳጆቹ የቅዱሳን ስም በራሱ
ቤት ማለትም በቤተክርስቲያን እንዲጠራ ቅዱስ ፈቃዱ መሆኑን ራሱ
እግዚአብሔር ነግሮናል::

ስለዚህ ቅድስትና ሐዋርያዊት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን


የእግዚአብሔርን ቤት በቅዱሳን ስም የምትሰይመው ይህን የፈጣሪዋን
ትእዛዝ ይዛ እንጂ በልብ ወለድ ተረት አይደለም:: የቅዱሳኑ ስምና ክብር
የማይጠፋና የማያልፍ ዘለዓለማዊ በመሆኑ ከብዙ ጊዜ በፊት ገድላቸውን
ፈጽመው ባረፉ ቅዱሳን ስም ቢሰየምም በውስጡ የሚሠራው ሥራ፡
- ማኅሌቱ፣ ቅዳሴው፣ መሥዋዕቱ፣ አገልግሎቱ ሁሉ አንድ ነው፤
የሚመሰገነው እግዚአብሔር ሲሆን የሚሰዋውም አንድ የክርስቶስ
ሥጋና ደም ነው:: መታሰቢያነቱ ለቅዱሳን እንዲሆን ያዘዘ የቤቱ
ባለቤት እግዚአብሔር ነው:: ይህንን እግዚአብሔር ለወዳጆቹ የሰጠውን
ክብር የሚቃወም ካለባለቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴ. ፳፥፲፭ “በገንዘቤ
የወደድሁትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን? ወይስ እኔ መልካም
ስለሆንሁ ዓይንህ ምቀኛ ናትን?” ይለዋል።

፪. በስማቸው ጸበልን: ጽላትን እና ሌሎችንም የተቀደሱ ነገሮች


መሰየም
በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጸበል ብለን የምንጠራው
በእግዚአብሔር ኃይል ሕሙማን የሚፈወሱበትና ልዩ ልዩ ተአምራትን
የሚደረግበት የተለየ (የተቀደሰ) ውኃ ነው:: የተለየ (የተቀደሰ) መባሉም
በዓይነ ሥጋ ሲያዩት እንደማንኛውም ውኃ ሲሆን ነገር ግን እግዚአብሔር
አምላክ ቸርነቱን የሚገልጽበትና ኃይሉን የሚያሳይበት ልዩ ውኃ ስለሆነ
ነው::

፷፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ሲፈጠር ጀምሮ ዕውር የነበርውን ሰው አምላክችን ኢየሱስ ክርስቶስ
መለኮት የተዋሐደውን ቅዱስ ምራቁን እንትፍ ብሎ በምራቁ ጭቃ
አደረገና የዚያን ዕውር ዓይኑን ቀባው:: ከቀባውም በኋላ “ሒድና
በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ” አለው ዮሐ.፱፥፩:: ዕውሩም ሄዶ ታጠበና
እያየ ተመለሰ:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕውሩን ጭቃ ከቀባው በኋላ
ለምን በሰሊሆም መጠመቂያ እንዲጠመቅ አዘዘው? ያዳነው ራሱ ነው::
እርሱ ራሱ አግኝቶትና ፈውሶት ሳለ ሄደህ ታጠብ ለምን አለው?
ጌታችን ይህንን ያደረገው ኃይሉን በጸበል ላይ ማሳደሩን ለመግለጽ ነው::
እግዚአብሔር ፈውስ የሚሰጥበት ቅዱስ ውኃ “ጸበል” መባሉም ጌታችን
የዚህን ዕውር ዓይን የፈጠረው መለኮት በተዋሐደው ቅዱስ ምራቁ
ለውሶ ጭቃ ባደረገው መሬትና ከሰሊሆም መጠመቂያ ከተገኘው ቅዱስ
ውኃ ድብልቅ በመሆኑ ነው:: እንዲሁም በጭቃ በተዋሐደ ቅዱስ ምራቁ
አማካይነት ኃይሉን ስላሳደረበት ነው::

ወደ መጠመቂያ ጸበል ሄዶ መጠመቅ ራሱ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ


ያዘዘው መለኮታዊት እዛዝ እንጂ የፍጡር ትእዛዝ አይደለም:: ስለዚህ
ጸበል መጠመቅ የእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደሆነ በዚህ እንረዳለን፡
፡ ቤተክርሰቲያን በስማቸው ከተሰየመ የጸበል ቦታ በስማቸው ቢሰየም
አይደንቅም፡፡ ጽላትም በስማቸው የሚሰየመው ጽላት በቤተክርሰቲያን
ይገኛልና፡፡ ጽላት ያለ ቤተመቅደስ አይገለገሉበትምና በስማቸው
ጽላት ይቀረጽላቸዋል፡፡ በስማቸው ቤተክርስቲያን ቢሰየም፣ ጽላት
ቢቀረጽላቸውም የአንዱ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ ለምዕመናን
የሚሰጥ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ይህን ክብር
ለቅዱሳኑ ሰጥቷቸው እያለ “ለምን በስማቸው ቤተክርስቲያን እና ጸበል
እንዲሁም ጽላት ይፈቀድላቸዋል? ብሎ መከራከር እግዚአብሔርን
መቃወም እንደሆነ መረዳት ይገባል፡፡”

፷፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

፭.፩.፪. የቅዱሳን ሥልጣን


የጸጋ ስግደት መስገድ
ስግደት የአክብሮት የተገዢነት እንዲሁም የትሕትና መግለጫ
ነው:: ዓላማው የሚወሰነውም እንደሚሰገድለት አካል ማንነት ነው::
ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ስግደት የአምልኮ መግለጫ ሲሆን ይህም
ፈጣሪነቱን ከሃሊነቱንና ገናንነቱን እያሰቡ የሚፈጸም ስግደት ነው:: ይህ
የአምልኮት ስግደት ለሌላ ለማንም አይቀርብም ነገር ግን እግዚአብሔር
ለወዳጆቹ ለቅዱሳን የአክብሮት ስግደት እንዲሰገድላቸው ፈቅዶአል::
ይኽውም ስግደቱን የሚያቀርበው ሰው ለቅዱሳኑ ያለውን አክብሮት
በተግባር ከሚገልጽባቸው መንገዶች አንዱ ነው:: የጸጋ እና የአክብሮት
ስግደትን የሚያመልክቱ ጥቅሶች እንደሚከተለው ቀርቧል፡

. “ሳኦልም ሳሙኤል እንደሆነ አወቀ፥ በፊቱም ተጐነበሰ፥ በምድርም ላይ


እጅ ነሣ።” ፩ኛ ሳሙ.፳፰፥፲፬፡፡
. “ከኢያሪኮም መጥተው በአንጻሩ የነበሩት የነቢያት ልጆች ባዩት ጊዜ።
የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ ዐርፎአል አሉ። ሊገናኙትም መጥተው
በፊቱ ወደ ምድር ተደፉ።” ፪ኛ ነገ.፪፥፲፭፡፡
. “ዳዊትም ወደ ኦርና መጣ ኦርናም ከአውድማውም ወጥቶ ዳዊትን
ተቀበለው፡፡ በምድር ላይ ወድቆ ሰገደለት።” ፩ኛዜና. ፳፩፥፳፩፡፡
. “የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር በግምባሩ ተደፍቶ ለዳንኤል
ሰገደለት፥” ዳን ፪፥፵፮
. “በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ከሳኦል ሰፈር አንድ ሰው ልብሱን ቀድዶ
በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ መጣ ወደ ዳዊትም በመጣ ጊዜ በግምባሩ
ተደፍቶ እጅ ነሣ።” ፪ኛሳሙ ፩፥፩
. “ያዕቆብም ዓይኑን አነሣ፥ እነሆም ዔሳውን ሲመጣ አየው፥ ... ሴቶች
ባሪያዎችም ከልጆቻቸው ጋር ቀርበው ሰገዱ ደግሞም ልያና ልጆችዋ
ቀርበው ሰገዱ ከዚያም በኋላ ዮሴፍና ራሔል ቀርበው ሰገዱ።” ዘፍ
፴፫፥፩-፰፡፡
፷፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
. “ጴጥሮስም በገባ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ተገናኝቶ ከእግሩ በታች ወደቀና
ሰገደለት።” ሐዋ ፲፥፳፭፡፡

፭.፪. ቅዱሳት ሥዕላት


፭.፪.፩. የቅዱሳትሥዕላት ትርጉም
ቅዱሳት ሥዕላት “ቅዱስ” እና “ሥዕላት” ከሚሉት ቃላት የተገናኘ ወይም
የተሰናሰለ ቃል ሲሆን፤ ሥዕል በቁሙ፣ መለክ፣ የመልክ ጥላ፣ ንድፍ፣
አምሳል፣ ንድፍ ውኃ፣ በመጽሔት፣በጥልፍ፣ በስፌት ወይም በቀለም
በወረቀት ገዝፎ ተጽፎ፤ ከእብን ከእፅ ከማዕድን ታንጦ፡ተቀርጦ ተሸልሞ
አጊጦ የሚታይ የሚዳሰስ ነገር ነው።

ሥዕል ነጠላ ሲሆን ሥዕላት ደግሞ ብዛትን ያመለክታል። ቅዱሳት


የሚለው ቃል ደግሞ “ቀደሰ” ከሚለው የግእዝ ግሥ የተወሰደ ሲሆን
ትርጉሙም ለየ፣ አከበረ፣ መረጠ ማለት ነው።ከዚህ በመነሳት ቅዱሳት
ሥዕላት ለእግዚአብሔር የተለዩ፣ የተቀደሱ፣ ልዩ፣ ምርጥ፣ ንጹህና
ጽሩይ የሆኑ የቤተመቅደሱ መገልገያ ንዋያተ ቅድሳት በመሆናቸው
ቅዱሳት ተብለው ይጠራሉ። ዳግመኛም የቅዱሳንን ታሪክና ማንነት
በጊዜው ላልነበርን በመንፈስ ዓይን እንድናይ ስለሚያደርጉን፣
ሥጋዊውን ዓለም ከሚያንጸባርቁ ዓለማውያን ሥዕላት ፈጽመው የተለዩ
በመሆናቸው፣ የቅዱሳኑ ቅድስና ሥዕላቱን ቅዱስ ስላሰኛቸው እና
በሥዕላቱ አድሮ እግዚአብሔር ስለሚፈጽማቸው ገቢረ ተዓምራት የተነሳ
ሥዕላቱ “ቅዱሳት ሥዕላት” ተብለው ይጠራሉ። በአጠቃላይ በኢትዮዽያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን “ቅዱሳት ሥዕላት” ተብለው
የሚጠሩት የቅዱስ እግዚአብሔር፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል
ማርያም፣ የቅዱሳን መላእክት፣ የቅዱሳን ነቢያት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣
ቅዱሳን ጻድቃን እና ሌሎች ቅዱሳን ማንነት ሕይወትና ታሪክ የሚያሳዩ
ሥዕሎች ናቸው። ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊት እንደመሆኗ መጠን
የምትፈጽማቸው አገልግሎቶችና ሥርዓቶች ዶግማና ቀኖናን እንዲሁም
፷፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ትውፊትን መሰረት ያደረጉ ናቸው። ይህ ደግሞ ኦርቶዶክሳዊያን ቅዱሳት


ሥዕላት በእግዚአብሔር ፈቃድ ሐዋርያዊ ቀኖናን ተከትለው የሚሳሉ
የቤትክርስቲያን ንዋያተ ቅዱሳት ናቸው እንጂ እንዴው በዘፈቀደ
የሚዘጋጁ የኪነ ጥበብ ሥራዎች አለመሆናቸውን ያስገነዝባል፡፡

፭.፪.፪. የቅዱሳት ሥዕላት ጥቅም


ለሥርዓተ አምልኮ፡- ቅዱሳት ሥዕላት ሰውንና እግዚአብሔርን የሚያገናኙ
መንፈሳዊ ሀብቶች ናቸው። በሥዕል ፊት ቆሞ መጸለይ ወይንም መስገድ
ሥዕሉን አምላክ ማድረግ አይደለም። ነገር ግን የሥዕሉን ባለቤት
በሥዕሉ ፊት ሆኖ በመማጸን በረከቱን ለማግኘት የሚፈጸም ሥርዓት
ነው። ሥዕሉ ለባለቤቱ መታሰቢያ ነው። “የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት
ነው ተብሎ እንደተጻፈ” (ምሳ. ፲፥፯) የሥዕሉን ባለቤት አቅርቦ ያሳየናል።
ገድሉን፣ ተአምራቱንና ቃልኪዳኑን ያስታውሰናል። በመንፈስም ድልድይ
ሆኖ ከሥዕሉ ባለቤት ያገናኘናል። ሙሴና አሮን ወደ ደብተራ ኦሪት
ገብተው በታቦቱና ሥዕለ ኪሩብ ፊት እየሰገዱ ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ
ይቀበሉ እንደነበረው። (ዘኁ. ፲፮ ፥ ፵፭)

ለትምህርት፡- ቅዱሳት ሥዕላት ሲሳሉ የሥዕሉን ባለቤት ዐቢይ ገድልና


ተአምራት በሚያጎላ መልኩ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ምዕመን
ሥዕሉን ባለቤት መንፈሳዊ ተጋድሎ በቀላሉ እንዲረዳ ያደርገዋል፡
፡ ለምሳሌ የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥዕል ሲሣል
ለ፳፪ ዓመታት ፰ ጦሮችን ከግራ ከቀኝ ከፊት ከኋላ ተክለው ሲጸልዩ
አንድ እግራቸው በቁመት ብዛት መቆረጡን እንዲሁም ስለ ቅድስናቸው
ከተሰጣቸው ስድስት የብርሃን ክንፎች ጋር ተደርጎ ይሣላል። ክህነታቸውን
ለመግለጽም የእርፍ መስቀልና ጽና ይዘው ይሣላል። የሥዕሉ ባለቤት
እንዲታወቅም በሥዕሉ ላይ አጭር የጽሑፍ መግለጫ ይቀመጣል።
”ዘከመ ጸለየ አቡነ ተክለሃይማኖት” እንዲል። በዚህ ሥዕል ምእመናን
የጻድቁን ተጋድሎ ይማሩበታል፤አርአያም ያደርጉታል።
፷፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ሌላው ምሳሌ ቅድስት ሥልሴ ሲሳሉ አንድነታቸውና ሦስትነታቸው
በሥዕል ይገለጣል።አንድነታቸውን ለመግለጽ ነደ እሳት የሚሆኑ ኪሩቤል
በተሸከሙት አንድ መንበር እንደተቀመጡ ልብሳቸው ሳይነጣጠል፤
ሦስትነታቸውን ዓለምን በቀኝ እጃቸው እንደ ያዙ፣የሦስቱም ፊት ወደ
አንድ አቅጣጫ እየተመለከቱ አካላቸው ገጽታቸው በተመጣጣኝ ሁኔታ
ይሣላል። የጌታ ትንሳኤ ሲሳል መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ
አለማለቱን ለመግለፅ የተዘጋ መቃብር ይታያል።በትንሳኤው ብርሃን
ዓለምን የቀደሰ ነውና ብርሃን ጨለማውን ሲገልጥ የሚያሳይ ተደርጎ
ይሳላል። ሆኖም ግን በአንዳንድ የምዕራባውያን አብያተ ክርስቲያናት
ሥዕላት ላይ የምንመለከተው የተከፈተ መቃብር ወይም መላእክት
የመቃብሩን በር ለጌታችን ሲከፍቱለት የሚያሳይ ሥዕል ነው። ይህም
በስልጣኑ አልተነሳም የሚል ትርጓሜን ይሰጣል። ይህ ደግሞ ትምህርተ
ሃይማኖትን ስለሚፋልስ ቤተክርስቲያን አትቀበለውም።

ቅዱሳት ሥዕላት እምነትን፣ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን እና መጽሐፍ


ቅዱሳዊ ታሪኮችን የምናስተምርባቸው አንዱ መሣሪያዎች ሲሆኑ፤በተለይ
ማንበብ እና መጻፍ ለማይችሉ አማኞች ትልቅ ጥቅም ሲሰጡ ይገኛሉ፡፡
ቅዱሳት ሥዕላትን ለማስተማሪያነት ብቻ የምንጠቀም ከሆነ በሥዕሉ ፊት
እጣን የማይታጠን፣ጸሎት የማይደርስ ስግደት የማይቀርብ ከሆነ፤ ልክ
መናፍቃኑ ለትምህርቶቻቸው በሚጠቀሙባቸው ፊልሞች፣ መዝሙሮች
እና መጽሐፍቶች ላይ እንደሚገቡት ሥዕሎች ይሆናሉ፡፡

ፍቅራችንን ለመግለጽ፡- አንድ ሰው የሚወደውን የቤተሰቡን ፎቶ በተለያዩ


ቦታዎች በማስቀመጥ ናፍቆቱን እንደሚወጣ እኛም ‹‹የገነት መስኮቶች››
ብሎ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የጠራቸውን ቅዱሳት ሥዕላትን እንደ
መስኮት በመጠቀም ቤተሰቦቻችን ቅዱሳንን እናይባቸዋለን፡፡ናፍቆታችንንም
እንወጣባቸዋለን፡፡ ሐዋርያው ሀገራችን በሰማይ ነው እንዳለ እኛም
ሰማያዊቷን ኢየሩሳሌምን የምናይባቸው መብራቶች ቅዱሳት ሥዕላት
፷፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ፍቅራችን ለመግለጽ እንጠቀምባቸዋለን፡፡

ድኅነት ለማግኘት፡- ቅዱሳት ሥዕላት ቅዱስ በመሆናቸው እግዚአብሔር


በእነርሱ ላይ አድሮ ድንቅ ተአምራት ይሠራል፡፡ ከእነዚህ መካከል
የታመሙ ሰዎች በቅዱሳት ሥዕላት አማካኝነት እንዲድኑ ያደርጋል፡
፡ ከታሪክም እንደምንረዳው ብዙ ሰዎች ቅዱሳት ሥዕላትን ዳስሰው፣
ከፊታቸው ቆመው ጸሎት አድርሰው ተፈውሰዋል፡፡ እንዲሁም ቅዱሳት
ሥዕላት በቤት ዉስጥ ካሉ እና በክብር ከያዝናቸው እርኩሳን መናፍስትን
ያርቃሉ፡፡

፭.፪.፫. ቅዱሳት ሥዕላት በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራሷ የሆነ ፊደል፣
ሥነ ጽሑፍ፣ ዜማ፣ ኪነ ሕንጻ…ወዘተ እንዳሏት ሁሉ የራሷ የሆነ
የሥነ ሥዕል ጥበብም ያላት ስንዱ እመቤት ናት፡፡ ከጥንተ ክርስትና
የአክሱማዊያን ዘመን ጀምሮ ሥዕል በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቦታ እንደ
ነበረው የአርኪዮሎጂ ግኝቶችና የጥንት አብያተ ክርስቲያናት ፍርስራሾች
ያመለክታሉ፡፡ በተለይ በዘመነ አክሱም ተሰርተው በከፊል የፈረሱ
እና ከመፍረስ የተረፉ እንደ አብርሃ አጽብሐ፣ ውቅሮ ቅዱስ ቂርቆስ፣
ደብረ ዳሞ ገዳም፣ መርጡ ለማርያም የመሳሰሉት አብያተ ክርስቲያናት
የያዟቸው ቅዱሳት ሥዕላት የዘመኑን የሥዕል ጥበብ አሻራ ያሳያሉ፡፡
በተለይ በመካከለኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስቲያን የቅዱሳት ሥዕላት ጥበብ ያደገበት ዘመን ነው፡፡ በአሁኑ
ወቅት በአብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት የምናገኛቸው ሥዕላት በዚህ
ዘመን የተሠሩ ናቸው፡፡

፭.፪.፬. የቅዱሳት ሥዕላት አሳሳል በኢትዮጵያ


በኢትዮጵያ የአሣሣል ዘዴ ሥዕላቱ የሚሣሉበት ጥበብ ከሌሎች አገራት
የአሣሣል ትውፊት ይለያል፡፡ በኢትዮጵያ አሣሣል ጥበብ የፊት ቅርጻቸው
፷፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
ጎልቶ ይሣላል፡፡በራሳቸው ላይም የብርሃን አክሊል ይሣላል፡፡ የጎላች
የተራዳችው ሃይማኖት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ባለቤቶችም ናቸውና
ዓይናቸው ጎላ ተደርጎ ይሣላል፡፡ ዓይናቸው የሚመጣውን ያለፈውንም
ዓለም በትንቢት መነጽርነት ይመለከታሉና የጎላ ዓይን ሁሉን የሚመለከት
ንጹህ ዓይን እንዳላቸው ለማሳየት ዓይናቸው ጎልቶ ይሳላል፡፡ እውነተኛ
ኢትዮጵያዊ ሥዕሎች ምን መሥፈርት ተከትለው እንደሚሣሉ ለማየት
ያህል፡፡

ሀ. የቅድስት ሥላሴ ሥዕል፡- ሦስቱ በአንድ መንበር ተቀምጠው፣


ዓለምን በመሃል እጃቸው (በመዳፋቸው) ይዘው፣ በአንድ አቅጣጫ
እየተመለከቱ፣ ፍጹም በተመጣጠነ መንገድ ሽማግሌ መስለው ይሣላሉ፡፡
የዚህም ዋና ትርጉሙ አንድነትን ከሦስትነት ማስተባበራቸውን ለማሳየት
ነው፡፡ በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በአገዛዝ፣ በመፍጠር፣ ዓለምን በማሳለፍ
እና በመሳሰለው አንድ በአካል፣ በግብር፣ በስም ሦስት መሆናቸውን
ለማሳየት ነው፡፡

ለ. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል፡-


፩ የሥነ ልደቱ፡- ከታሪኩ እንደምንረዳው የጌታ ልደት በከብቶች በረት
ውስጥ ነው፡፡አንዳንዶች ግን በተመቻቸ አልጋ ላይ አበባ ተነስንሶ በዚያ
እንደተወለደ አድርገው የሚሥሉ አሉ፡፡ ከጎን አብሮ የሚሣለው ቅዱስ
ዮሴፍም አረጋዊ (ሽማግሌ) በመሆኑ ከሌሎች ሁሉ ሽማግሌ ሆኖ
ይሣላል፡፡ አንዳንድ መናፍቃን ግን በእድሜ ከእመቤታችን ጋር እኩል
እንደሆነ አድርገው እጅግ በጣም ወጣት አድርገው ይስሉታል፡፡ ይኸውም
“እጮኛዋ” የሚለውን ቃል ለጋብቻ አድርገው ቅዱስ ዮሴፍ የእመቤታችን
የትዳር ጓደኛ ነበር የሚለውን ኑፋቄ ለመዝራት የተጠቀሙበት ነው፡፡

፪ የሥነ ስቅለቱ፡- የተቸነከረባቸው አምስት ችንካሮች (ማለትም ሳዶር፣


አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ)፣ በራሱ ላይ የእሾህ አክሊል ደፍቶ፣
፷፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ጎኑን በጦር ተወግቶ፣ በ “ለ” ቅርጽ ደምና ውኃ እየፈሰሰ፣ ራሱን ወደ


ቀኝ አዘንብሎ፣ በቀኝና በግራ እመቤታችንና ወንጌላዊው ዮሐንስ ቆመው፣
በቀኝና በግራ ሁለት ወንበዴዎች ተሰቅለው ይሳላል፡፡

፫ የብርሃነ ትንሣኤው፡- የጌታ ትንሣኤ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ


ሳይል ስለሆነ መቃብሩ እንደተዘጋ፣ ሲነሣ ለማስቀረት የተመደቡት ፬
ወታደሮች ተኝተው፣ የተቸነከረ እጅና እግሩ እየታየ አካባቢው ብርሃን
ለብሶ ይሳላል፡፡ አንዳንዴም ወታደሮቹ የጌታን የትንሣኤ ብርሃን ማየት
እንደተሣናቸው መብረቃዊ ድምጹንም መስማት እንደተሳናቸው ሆኖ፣
መልአኩም ድንጋዩን እንዳገላበጠው ሆኖ ይሣላል፡፡ /ማቴ ፳፰፥፩- መጨ/
ያለውን ታሪክ ይመልከቱ፡፡

ሐ. የእመቤታችን ሥዕል፡- የእመቤታችን ሥዕል ሲሳል እመቤታችን


በቀኝ ጌታችንን በግራ እጇ ታቅፋ ነው፡፡ ይህ ያለ ምክንያት አይደለም
የሆነው መዝ ፵፬÷፱ “የንጉሦች ልጆች ለክብርህ ናቸው፡፡ በወርቅ ልብስ
ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” የሚለውን ቃል
መነሻ በማድረግ ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በቀኝ ሰይፍ ይዞ ቅዱስ ገብርኤል
በግራ መስቀል ይዞ ይሣላሉ፡፡ ዘላለማዊ ድንግል ናትና ጸጉሯ ሙሉ
በሙሉ በአጽፍ ተሸፍኖ መሣል አለበት፡፡የልብሷ ቀለም አቀባብም ከላይ
ሰማያዊ ከውስጥ ደግሞ ቀይ ሆኖ ይሣላል፡፡ ቀይ ከውስጥ መሆኑ
እሳተ መለኮትን በማኅጸኗ መሸከሟን ለማስረዳት ነው፡፡ ሰማያዊት ናትና
ከላይ ያለው ሰማያዊ ቀለም ይደረጋል፡፡ አንድም ከላይ ሰማያዊ ከውስጥ
ቀይ መሆኑ ክብሯ ሰማያዊያውም መልዕልተ ፍጡራን መትሕተ ፈጣሪ
ከፍጡራን ሁሉ በላይ ከፈጣሪ በታች የሆነ ቢሆንም በመከራና በስደት
እንጅ በተድላና በደስታ እንዳልኖረች ያስረዳል፡፡ እዚህ ላይ ጌታ አውራ
ጣቷን የሚይዛት ሆኖ የሚሣልበትም አለ፡፡ ጣጦች ሁሉ ካለ አውራ ጣት
ምንም ሊሠሩ አይችሉም፡፡ ያለ አውራ ጣት ይዞ ማስቀረት አስሮ ማጥበቅ
አይቻልም፡፡ እርሷም እንዲሁ ከሁሉ በላይ ናት ካለ እርሷ ምልጃ ዓለም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ድኅነትን አያገኝምና፡፡ መናፍቃን ግን በብዙ መንገድ ሥዕሏን ይሥላሉ፡፡


አንደኛ ጸጉሯን በአጽፍ አይሸፍኑም ምክንያቱም ጸጉር ማሳየት ድንግልና
የሌላት ሴት የምታደርገው ነውና ዘላለማዊ ድንግልናዋን ለመካድ፡፡
ሁለተኛም ቀዩን ከላይ ሰማያዊውን ከውስጥ አድርገው የሚሥሉም አሉ
እሳተ መለኮት በውስጧ አላደረም ለማለት፡፡ የእመቤታችን ሥዕል ከዚህ
በተጨማሪም እመቤታችን በቤተ መቅደስ ሐርና ወርቅን እያስማማች
ስትፈትል በቅዱስ ገብርኤል ስትበሰር፣ጌታን ይዛ በአህያ ተቀምጣ ከቅዱስ
ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ስትሰደድ ትሣላለች፡፡

መ. የቅዱሳን መላእክት ሥዕል፡- ቅዱሳን መላእክት በሁለት መልኩ


ይሣላሉ፡፡ ሊቃነ መላእክት ብቻቸውን ከሆነ በሰው ሙሉ አካል መልክ
መስቀልና ሰይፍ እንደያዙ ልብሰ ተክህኖ ለብሰው ይሣላሉ፡፡ መስቀልና
ሰይፍ መያዛቸው ለምሕረትም ለመቅሰፍትም እንደሚላኩ ለማስረዳት
ነው፡፡ ዘፍ፵፰ን ይመልከቱ፡፡ ልብሰ ተክህኖ መልበቸው ደግሞ ዕጣን
በማጠን የሰውን ጸሎት ቅድመ እግዚአብሔር የሚያደርሱ ናቸውና ነው፡
፡ ራዕ ፰÷፬-፭ “የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋራ ከመልአኩ እጅ
በእግዚአብሔር ፊት ወጣ፡፡ መልአኩም ጥናውን ይዞ የመሰዊያውን እሳት
ሞላበት ወደ ምድርም ጣለው ነጎድጓድና ድንጽም መብረቅም መናወጥም
ሆነ” እንዲል፡፡ሠራዊተ መላእክት የሆኑ እንደሆነ ግን ከአንገት በላይ እና
በክንፍ በክንፎቻቸውም ላይ ብዙ ነጠብጣቦች ይሣሉባቸዋል ዓይናቸው
ብዙ መሆኑን ለማሣየት፡፡አንድም ያለፈውንና የሚመጣውን ያውቃሉና፡፡

ሰ. የቅዱሳን፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት ሥዕላት፡- መስቀልና መጻሕፍት


ይዘው ልብሰ ተክህኖ ለብሰው ዓይናቸው ጎላ ጎላ ብሎ በጸሎት
የተጋደሉ፣ ወንጌልን ዞረው ያስተማሩ፣ በክህነታቸው እግዚአብሔርንና
ሰውን ያገለገሉ፣ በተሰጣቸው ልዩ ልዩ ጸጋ መሠረት ሁሉን የሚያውቁ
መሆናቸውን የሚገልጽ ሆኖ ይሣላል፡፡ በተጨማሪም በምድር እያሉ
የተጋደሉትን ተጋድሎ ዓይነትና የደረሰባቸውን ስቃይና መከራ በዚህም
፸፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ትእግስታቸው ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን አክሊል እንዲያሳይ ሆኖ


ይሣላል፡፡

ረ. የመምህራን የሊቃውንንት ሥዕል፡- መምህራንና ሊቃውንንት ካባ


ለብሰው ወንጌል ይዘው ይሣላሉ፡፡ ይህም ክብራቸውን ለማሳየት ነው፡፡
በዚህ ዓለም ዞረው ወንጌልን ለማስተማራቸው መናፍቃንን ተከራክረው
ስለመርታታቸው እውነተኛዋን እምነት ስለማስተማራቸው ነው፡፡

ሠ. የርኩሳን መናፍስትና የአፅራረ ቤተክርስቲያን ሥዕል፡- ሌላው


በቤተክርስቲያናችን የአሣሣል ዘዴ ልዩ የሆነው የርኩሳን መናፍስት
አሣሣል ነው፡፡ እነዚህ ሲሣሉ የብዙ ቀለሞች ድብልቅ ሆነው፣ በዓይን
በማይታይ መልኩ የሰውም የአውሬም ቅርጽ ይዘው፣በግማሽ ፊት
አንድ ዓይናቸው ብቻ እየታየ ይሣላሉ፡፡ ምክንያቱም የሃይማኖት ሕጸጽ
አለባቸውና፣ ሁሉንም መርምረው አያቁምና ነው፡፡

እያንዳንዱ ምዕመንም የራሱ የሆነውን ትምህርተ ሃይማኖትን ታሪክንና


ትውፊትን የጠበቁትን ሥዕላት ማወቅና መረዳት ይኖርበታል። እንዲሁም
ቅዱሳት ሥዕላት ሲገዙ ተገቢዉን ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቃል፡፡ ያወቀውን
ደግሞ ላላወቁት በማሳወቅ አባቶች ያስቀመጡት ድንበር እንዳይደፈርስ
መጠበቅ ይኖርበታል። የቀደሙት አባቶች የሰሩትን ድንበር አታፍርስ
እንዲል ምሳ ፳፥፳፰።

ቅዱሳት ሥዕላት ይህን መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡን ከሆነ በጥንቃቄ


በመያዝ መገልገል እንደሚገባና ዘወትር በጸሎት ሰዓት ከፊት ለፊታችን
በማስቀመጥ ልንጸልይ እንደሚገባ ቅድስት ቤተክርስቲያን መልዕክቷን
ታስተላልፋለች።

፸፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
የቅዱሳን ክብርና ቃልኪዳን
እግዚአብሔር አምላክ ቅዱሳን በሚፈጽሙት መንፈሳዊ ተጋድሎ
ምክንያት ስለሚደሰት የክብራቸው መገለጫ እንዲሆን እና ኃጥአን
በቅዱሳን ተማጽነው መልካም ሥራ ሠርተው መንግሥቱን እንዲወርሱ
፥በቅዱሳን ቃል ኪዳን ተጠቃሚ እንዲሆኑና የቅዱሳን ክብር ይገለጽ
ዘንድ ለቅዱሳኑ ቃል ኪዳን ይሰጣቸዋል፡፡ ‘‘ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል
የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ
ይወስዳል። (ማቴ ፲ ፥ ፵፩) እንዲል

እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ለቅዱሳን ያለው ፍቅር ጊዜያዊና በዚህ ዓለም


ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን ዘለዓለማዊ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ፡
- “በዚህ ዓለም ያሉቱን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ድረስ
ወደዳቸው” በማለት የክርስቶስ ፍቅር ፍጻሜ የሌለው መሆኑን ተናግሯል፡
፡ (ዮሐ. ፲፫፥፩) ስለሆነም በሥጋ ሳሉ ያገለገሉትንና ያስደሰቱትን
ባለሟሎቹን ከዕለተ ሞታቸው በኋላ የሚያገለግል ቃል ኪዳን ይሰጣቸዋል፡
፡ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ለቅዱሳኑ ቃልኪዳን መግባቱን ሲናገር፡-
“ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ- ከመረጥኳቸው ጋር ቃልኪዳን አደረግሁ”
ብሏል፡፡ (መዝ. ፹፰(፹፱)፥፫) ቃልኪዳኑን የሰጠው እግዚአብሔር ሲሆን
ቃል ኪዳኑ የሚሰጣቸው ደግሞ ቅዱሳን ናቸው፡፡

በዚህ ቃል ኪዳን ለመጠቀም የሚፈልጉ ሰዎች እግዚአብሔር ያዘዛቸውን


ነገር ማሟላት ይገባቸዋል፡፡ ማሟላት ከሚገባቸው ነገሮች መካከል
እግዚአብሔር ለቅዱሳን ቃል ኪዳን እንደሰጣቸው ማመን፣ በስማቸው
መማጸን እና ቃልኪዳኑን መጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህም በኋላ
እግዚአብሔር ለወዳጆቹ የገባውን ቃል ኪዳን እያሰቡ የሚለምኑትን
ይቅር ሲላቸውና ሲምራቸው ይኖራል፡፡ “ የእግዚአብሔር ምሕረት ግን
ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚፈሩት ላይ ጽድቁም በልጅ ልጆቹ ላይ
ነው፣ ቃል ኪዳኑን በሚጠብቁ ትእዛዙንም ያደርጉት ዘንድ በሚያስቡ ላይ
፸፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ነው” እንዲል (መዝ. ፻፪ (፻፫)፡ ፲፯-፲፰)፡፡ እግዚአብሔር ለእሥራኤላዊያን


ትእዛዙንና ሕጉን ሲሰጣቸው በቃል ኪዳን ነበር፡፡ ይኸውም ቃል ኪዳኑን
ቢጠብቁት ሊጠብቃቸው ባይጠብቁት ደግሞ ሊፈርድባቸው ነው፡፡ ዘዳ.
፳፰ ፥፩- መጨረሻ::

፪.፯.፩ እግዚአብሔር ቃልኪዳን ከገባላቸው ቅዱሳን መካከል የተወሰኑት

እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከገባላቸው ቅዱሳን መካከል አንዱ አበ


ብዙኀን አብርሃም ሲሆን እንዲህ በማለትም ቃል ኪዳን ገብቶለታል፡
- “በእንግድነትህ የምትኖርበትን የከነዓን ምድር ሁሉ ለዘላለም ግዛት
ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ፡፡ ከአንተ ወንድ ሁሉ ይገረዝ
በእኔና በአንተ መካከል ሳለሁም ቃልኪዳን ምልክት ይሆናል” ዘፍ.
፲፯፥፲፰፡፡ ይህ የሚያመለክተን እግዚአብሔር ለእሥራኤላዊያን ቃል ኪዳን
በአብርሃም በኩል እንደገባላቸው ነው፡፡ ቃል ኪዳን ሲገባላቸውም ከቃል
ኪዳኑ ተጠቃሚ ለመሆን ከእነርሱ መወጣት የሚጠበቅባቸው ድርሻ
እንዳለ የሚያሳይ ነው፡፡

እንዲሁም ለዳዊት ቃል ኪዳን ሲሰጠው “ምዕረ መሐልኩ በቅዱስየ


ከመ ለዳዊት ኢይሔስዎ - ኪዳኔን አላረክስም ከከንፈሬም የወጣውን
አልለውጥም ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ ማልሁ” ብሏል፡
፡ (መዝ. ፹፰፥፴፬) ልበ አምላክ ዳዊት ቢያልፍም በልዑል እግዚአብሔር
የተሰጠው ቃል ኪዳን የማያልፍ ዘላለማዊ ነው፡፡ ራእ. ፮፥፱ ላይ አቤቱ
ስለፈሰሰው ደማችን ፍረድልን ብለው ቅዱሳን ከተማጸኑ ስማቸውን
በመጥራት የተሰጣቸውን ቃል ኪዳን በማዘከር ከፈጣሪያቸው ምህረትና
ይቅርታ እንዲያሰጧቸው ለሚለምኑ ሰዎችማ እንደምን አብልጠው
አይጸልዩላቸው? ምክንያቱም ጻድቃን ከመዓት ይልቅ ምህረትን
ይለምናሉና፡፡ ቅዱሳን እንኳን ጸሎታቸው እና ቃል ኪዳናቸው፣ ዐጽማቸው
ሙት እስኪያነሳ ድረስ እግዚአብሔር ጸጋውን አብዝቶላቸዋል፡፡ ለምሳሌ
፸፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
፪ኛ ነገ. ፲፫፥፳-፳፩ ላይ እንደተገለጸው የኤሊያስ ደቀ መዝሙር የነበረ
ነቢዩ ኤልሳዕ በአጽሙ ሙት አስነስቷል፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አምላካችን መድኃኒታችን


ኢየሱስ ክርስቶስ በተቀበረበት በጎለጎታ መቃብር ስፍራ ሆና ባቀረበቸው
ጸሎት ምክንያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መጥቶ በስሟ
ለሚማጸኑ እንደሚምራቸው፣ በስሟ ለተቸገሩት (ለነዳያን) ቢያበሉ
ቢያጠጡ፣ መጽሐፏን ቢያጽፉ፣ የተጻፈውን ቢያነቡ …. ወዘተ ኃጥአንን
እንደሚምራቸው ቃል ኪዳን ገብቶላት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ ይህም ኪዳነ
ምሕረት እያልን የምንጠራው ነው፡፡ ኪዳን ማለት ውል ስምምነት ማለት
ነው፡፡ ምሕረት ደግሞ ይቅርታ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት
ማለት የምሕረት ወይም የይቅርታ ውል ስምምነት ማለት ነው፡፡ ይህም
በእመቤታችን በኩል ዓለምን ይቅር እንደሚል የሚያስረዳ ነው፡፡ እኛም
ልጆቿ በተሰጣት ቃል ኪዳን መሠረት በአማላጅነቷ በመታገዝ ከጥፋት
(ከዘለዓለም ሞት) እንድናለን፡፡

፪.፯.፪ ለቅዱሳን የሚሰጥ ቃል ኪዳን ጊዜያዊ ሳይሆን ዘለዓለማዊ ነው

ለቅዱሳን የሚሰጥ ቃል ኪዳን እስከ ሺህ ትውልድና ዘርንም በሙሉ


እንደሚያስባርክ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ እያለ [መናፍቃን ግን
ይህንን ሳያስተውሉ በተለያዩ የቅዱሳን ገድሎች ውስጥ እስከእዚህ ትወልድ
እምርልሃለው ወይም እምርልሻለሁ ተብሎ የተነገሩትን የቅዱሳን ቃል
ኪዳን ይቃወማሉ፡፡ ]መጽሐፍ ግን ‹‹ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ
እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ
ቀናተኛ አምላክ ነኝና።›› እንዲል እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ ቅርብ ስለሆነ
ትውልድን የሚያድን ቃል ኪዳን ይገባላቸዋል ጸሎታቸውንም ሰምቶ
ምህረትን ያደርጋል፡፡ ዘጸ.፳፥፮ ላይ “የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ
ይባረካሉ፥ ቃሌን ሰምተሃልና።›› በማለት እግዚአብሔር ለአብርሃም
፸፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

በገባለት ቃል ኪዳን ሌሎችም እንደሚባረኩ ተናግሯል እንጂ አብርሃም


ብቻ እንደሚጠቀም አልተናገረም፡፡ ዘጸ.፫፥፲፮ ላይ ‹‹ሂድ የእስራኤልንም
ሽማግሌዎች ሰብስብ። እግዚአብሔር የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም
የይስሐቅም የያዕቆብም አምላክ። መጐብኘትን እጐበኛችኋለሁ፥ በግብፅም
የሚደረግባችሁን አየሁ›› ተብሎ እንደተጻፈው እግዚአብሔር የደጋግ
አባቶችን ቃል ኪዳን እያሰበ ከመከራ ያድናል፡፡ እንዲሁም በመዝ. ፻፲፩፥፮
ላይ “ዝክረ ቅዱሳን ለዓለም ይኼሉ- የቅዱሳን መታሰቢያ ለዘለዓለም
ይኖራል” ተብሎ እንደተነገረው፣ ቃል ኪዳናቸው መታሰቢያቸውን
የሚጠቁም ነውና የቅዱሳን ቃል ኪዳን ለዘለዓለም ይኖራል ማለት ነው፡
፡ እግዚአብሔር እንደ ሰው በገባው ቃል ኪዳን የሚጸጸት አይደለምና
በቃል ኪዳኑ መሠረት ቃሉ ሳይለወጥ ሰዎችን ይምራል “ለአባቶቻችን
እንደተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘለዓለም ምሕረቱ ትዝ እያለው
እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።›› እንዲል ሉቃ ፩፥፶፬-፶፭፣ ምሕረቱ
ዘለዓለማዊ እንደሆነ ይጠቁማል፡፡

፪.፯.፫ በቅዱሳን ቃል ኪዳን ተጠቃሚ ለመሆን


እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ በገባላቸው ቃል ኪዳን ተጠቃሚ ለመሆን
በእግዚአብሔር ስናምን ለቅዱሳኑም በተሰጣቸው ቃል ኪዳን ማመን
ይገባል፡፡ በተሰጣቸው ቃል ኪዳን የሚጠራጠሩ ከቃል ኪዳኑ ተካፋይ
አይሆኑም፤ በመንገዱ ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ አንዳች
እንዲያገኝ አይምሰለው እንዲል፣ ያዕ. ፩፥፰፡፡ እግዚአብሔር ሕዝበ
እስራኤልን ከግብፅ ለማውጣት ቃል ኪዳን በገባ ጊዜ እግዚአብሔር
በሙሴ አማካይነት እንደሚያወጣቸው ሕዝቡ አምኗል፡፡ “እስራኤልም
እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፥ሕዝቡም
እግዚአብሔርን ፈሩ፥ በእግዚአብሔርም በባሪያውም በሙሴ አመኑ።”
እንዲል፡፡ ዘጸ. ፲፬፥፴፩፡፡ ሌላው በቅዱሳን ቃል ኪዳን ለመጠቀም
ከሚያስፈልጉ ነገሮች አንዱ ትዕዛዙን መፈጸም ነው፡፡ እግዚአብሔር
ለአብርሃም በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ተጠቃሚ ለመሆን ግዝረትን
፸፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል
መፈጸም የግድ አስፈላጊ ነበር፡፡ ዛሬም በቅዱሳን ቃል ኪዳን ለመጠቀም
ቃሉን ሰምቶ መፈጸም ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ከቃል ኪዳኑ ተጠቃሚ
ለመሆን ከሚያስፈልጉ ነገሮች አንዱ ንስሐ ለመግባት የተዘጋጀ ልብ ነው፡
፡ ኃጥኡ በቅዱሳን ቃል ኪዳን ተማጽኖ የንስሐ ጊዜ በማግኘት ከክፋቱ
ተመልሶ ተዘጋጅቶ ለመሞት ይጠብቃል፡፡ አሁንም በዘመናችን እስራኤል
ዘነፍስ የሆንን እኛን ለቅዱሳኑ ስለገባላቸው ቃል ኪዳን ድንቅ ሥራውን
ሲያደርግልን ሲምረን ይኖራል፡፡

በቅዱሳን ቃል ኪዳን ለመጠቀም እያንዳንዱ ክርስቲያን የራሱ ድርሻ


አለው፡፡ በኃጢአት ውስጥ ያለ ሰው ከቅዱሳኑ ቃል ኪዳን ተጠቃሚ
ለመሆን በቅዱሳኑ ጸሎትና ቃል ኪዳን ማመን አለበት፣ ከኃጢአት መራቅና
በንስሐ ሕይወት መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ከኃጢአት ሕይወት ለመውጣት
ያልፈቀደ፣ በኃጢአቱ የሚገፋ፣ የማይጸጸት፣ ኃጢአቱን የሚወድ ሰው
እንደፈለገ ኃጢአት እየሰራ ከቅዱሳኑ ቃል ኪዳን ለመጠቀም አይችልም፡፡
ነገር ግን ምንም እንኳ በኃጢአት ውስጥ ያለ ሰው ቢሆንም ለመልካም
ሥራ ከተጋ እና በቅዱሳኑ ቃል ኪዳን ከተማጸነ የእግዚአብሔር ቸርነት
ተጨምሮበት ለንስሐ ሞት ይበቃል፣ ከሞት ወደ ሕይወት ይሸጋገራል፡፡
እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ በሚገባው ቃል ኪዳን የሰው ልጆች ተጠቃሚዎች
ናቸው፡፡ በኖኅ ዘመን ዳግመኛ ዓለምን በንፍር ውኃ አላጠፋም በማለት
ለኖኅ በሰማይ ላይ የቀስተ ደመና ምልክትን በማኖር ቃል ኪዳን ገብቷል፡
፡ ዛሬም ይህ በቤተክርስቲያን፣ በቤታችን፣ በመሥሪያ ቤት መጠቀማችን
ትርጉሙ ይህ ነው እንጂ በዘፈቀደ ቀለማቱ የተመረጡ አይደሉም፡፡
ቀስተ ደመና የተለያዩ ሕብረ ቀለማት ቢኖሩትም በሰማይ ላይ ጎልተው
የሚታዩት አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ በመሆናቸው፣ ለባንዲራችን እነዚህን
ቀለማት እንጠቀማለን፡፡

፸፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ስድስተኛ ክፍል

ዋቢ መጻሕፍት
መጽሐፍ ቅዱስ ሰማንያ ወአሐዱ
ነገረ ቅዱሳን -፩፣ 2004 ዓ.ም፣ ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው
ነገረ ቅዱሳን ፣ መምህር ፈቃዱ ሳህሌ ፣ 2011 ዓ.ም. ፣ ማኅበረ
ቅዱሳን

፸፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
የሰንበት ት/ቤት አመራር እና መምህራን እንዲሁም
ተማሪዎችና ወላጆች በመጽሐፉ ላይ ያላችሁን
ማንኛውም አስተያየት እና ግብዓት በሚከተለው
አድራሻ ላኩልን

office@eotc-gssu.org
https://t.me/GSSUCurriculum_bot

You might also like