You are on page 1of 6

መለከት #5

5
www.tlcfan.org 0
መለከት #5

በሸመገለው ፊት የመነሳት ሕግ
ከአስርቱ ትእዛዛት መካከል አንዱ፦ “አባትህንና እናትህን አክብር እግዚአብሔር አምላክህ
በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።” የሚል ነው። ዘጸ.20፥12 ይህ ሕግ የሚያያዘው ወይም
የሚዛመደው በዘሌዋውያን 19፥32 ላይ ከሚገኘው ጥቅስ ጋር ነው።
“በሽበታሙ ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”

ይህ ሕግ እንዲሁ በቀጥታ ስንመለከተው የሚያወራው የሸመገለውንና በእድሜ ባለጸጋ የሆነውኝ


ሰው ስለማክበር ነው። በእኛም ባሕልም አዋቂ ሲገባ ከተቀመጡበት መነሳት ክብር መስጠትን ለማሳየት
የምንጠቀምበት ልምድ ነው። ይህንንም ሁላችን እንደሚንስማማበት መልካም ልምድና የእግዚአብሔር
ሕግ ነው። ይሁንና ይህ ሕግ እንደሌሎቹ የሚፈቱትና የሚተረጎሙት ወይም ትንቢታዊ እንደሆኑት
የእግዚአብሔር ሕጎች የሚፈታ ነው። ዛሬም ለዚህ ዘመን ኑሮና ዝግጅት የጠለቀ ሚስጥርን፣ መርህና
መልክትን የያዘ ሕግ ነው።

ይህ በሽበታሙና በሸመገለው ፊት የመነሳት ሕግ የሚያወራው ወይም የሚተነብየው ስለ


ሙታን ትንሳኤ ነው። ዳንኤል በራእዮ ላይ በዘመናት የሸመገለውን በዙፋ ላይ ተቀምጦ ተመልክቶታል።
ዳንኤል.7:፥9-10 “ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ ልብሱም
እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥
መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ። 10 የእሳትም ፈሳሽ ከፊቱ ይፈልቅና ይወጣ ነበር ሺህ ጊዜ ሺህ
ያገለግሉት ነበር፥ እልፍ አእላፋትም በፊቱ ቆመው ነበር ፍርድም ሆነ፥ መጻሕፍትም ተገለጡ።” ይላል።

ይህ የዳንኤል ራእይ ሰለሙታን ትንሳኤ ያየው ወደፊት የሚፈጸም ራእይና ትንቢት ነው። የተለያዮ
የእንግሊዘኛ ትርጉሞች ላይ ቃሉን ብናይ የበለጠ ቃሉን ግልጽ ያደርገዋል። Young's Literal
Translation “myriads of myriads do RISE UP.” The concordant Literal Translation “ a
thousand touseands are irradiating Him, and ten thousand ten thousands are RISING
before Him.” ብሎ ያስቀምጠዋል።

ስለዚህ በዘሌዋውያን ላይ የምናየው በሸመገለው ፊት ተነስ የሚለው ሕግ ከምክር እና ከመልካም


ምግባርም ያለፈ ትዕዛዝ ነው። በዚህ ባለንበት ዘመን በንግስትና ንጉስ ስር ያሉ ሃገሮች በፍርድ ቤቶች
ሲያደርጉ የምናየው ጥላ ይህን በግልጽ የሚያሳይም ነው። ዳኛ ፍርድን ሊያወጣ ሲገባ አርተፊሻል ነጭ
ጸጉር በራሱ ላይ ያደርጋል። ከውጭ ወደ ውስጥ ገብቶ በዙፋኑ ላይ እስኪቀመጥ ሁሉ በፊቱ እንደሚነሱ
ሁሉ የነገስታት ንጉስ በሸመገለው እግዚአብሔር ፊት ሁሉ በነጩ ዙፋን ፍርድ ቀን ይነሳሉ። መልካምና
ክፉ ያደረጉ የሁለተኛው የሙታን ትንሳኤ የዚህ የእግዚአብሔር ሕግ ትንቢታዊ ውጤት ወይም ፍጻሜ
ነው።

“ በሽበታሙ ፊት ተነሳ” በብሉይ ኪዳን ይህ ሕግ በሰዎች የመታዘን ወይም ያለመታዘዝ ብቃት


ምክንያት ይህ ሕግ ሊጣስና ሊናቅ ይችላል። ነገር ግን በአዲሱ ኪዳን ሕጉ በእግዚአብሔር ፍቃድና ችሎታ
የሚፈጸም ነው። ምክንያቱም እርሱ ሕጉን በልባችን ጽፎ በትዕዛዛቱ ስለሚያስኬደን ነው። ኤፌ.1፥11
“እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን
ተቀበልን።” በብሉይ ኪዳን ሕጉ አትስረቅ ሲል። አማኙ ወይም ሕግን የተቀበልው ሕዝብ ላለመስረቅ ብዙ
ትግልን ያደርጋል ነገር ግን ዞር ሲሰርቅ ራሱን ያገኛል። በአዲሱ ኪዳን ግን ሕጉ አትስረቅ ሲለን ሕጉ ትእዛዝ
ብቻ ሳይሆን የተስፋም ቃል ወይም ሕይወትንና ብቃትን የሚሰጥ ነው። ይህም ከዚህ በኋላ እንዳንሰርቅ
ሕጉን በልባችን ላይ በመጻፍ ይፈጽመዋል። ቃሉም ሕይወታችን ይሆናል ወይም ከእኛ ጋር ይዋሃዳል።

www.tlcfan.org 1
መለከት #5

ስለዚህ አለመስረቅ ባሕሪያችን የእለት ተእለት ኑሯችን ይሆናል። መስረቅ ደግሞ ተፈጥሯችን
መሆኑ ያከትማል። በአዲስ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕግንና ትዕዛዛቱን አጠባበቅ እንደ ብሉይ ኪዳን
ሃላፊነቱን በሰዎች ላይ የሚጭን ሳይሆን እግዚአብሔር ሕጉን እንድንጠብቅ ሕጉን ባሕሪያችን አድርጎ
በውስጣችን ሊቀርጽ የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ሊሰጠን ሃላፊነቱን በራሱ በእግዚአብሔር ላይ ይጭናል።
ለዚህ ነው ሕጉ ከትእዛዝ ባለፈ መልኩ ትንቢታዊነቱ በአዲስ ኪዳን በይበልጥ የተገለጠው። ትእዛዝ ሊጣስ
ወይም ሊሰበር ይችላል። ይህም ፍርድን ያስከትላል። ትንቢት ግን ፈጽሞ የሚጣስ ወይም የሚሰበር
አይደለም። ምክንያቱም ትንቢቱ እውን እንዲሆን የተናገረው እግዚአብሔር ለማጽናትና ለመፈጸም ከቃሉ
ጀርባ ስለሚተጋ ነው። እንዳለውና እንዳሰበው እንደተናገረውም የሚጸናለት ብቸኛ አምላክ እግዚአብሔር
ብቻ ነው።

ትንቢትም ሆነ በልባችን የሚጻፍ ሕግ እግዚአብሔር እንዳለው ጊዜን ጠብቆ የሚፈጸም ወይም


ሕይወታችን የሚሆን ነው፡። የእግዚአብሔር ሕግጋት ለመፈጸም በራሳችን ስንጥር ገና በአሮጌው ኪዳን
ውስጥ እንዳለንና እንደምንኖር እራሳችንን እናጋልጣለን። ነገር ግን በመንፈስ ስንመራ እግዚአብሔር
ሕግጋቶቹን በሕይወታችን እንዲፈጽምና በልባች እንዲጽፈው እንፈቅድለታለን። በሰው ሃይልና ጥረት
የማይቻለውን በእግዚአብሔር ብቃትና ችሎታ ይችላልና ነው። በመንፈስ እንጂ በሃይልና በብርታት
አይደለም።
“4. . .እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በባንመላለስ
በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ።. . .ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥
ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤
ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤ በሥጋ ያሉትም
እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም። እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ
በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም።
የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም።”
ሮሜ.8፥4-12

ይህ ሙሴ ከዘፍጥረት ጀምሮ ያሰቀመጠው እውነት ነው። ዘፍጥረት አንድ አንድ ላይ


የዕብራይስጡ ቃል “ዬድ” የሚለው ቃልን እናገኛለን። ይህን በዕብራይስጡ መጽሐፍ ቅዱስ ቃሉን
ስናጠናው በየ512ኛው ፍደል ላይ እናገኘዋለን ይህም “ያሽዋ ብቁ ነው” የሚለውን ቃል ነው። ይህ
የኢየሱስ የዕብራውያን ስሙ ነው ወይም እያሱ ማለት ነው። እውነት ነው በአሁን ዘመን ይህ እውነት
የሚደንቅ አይደለም። አብዛኞቻችን ዛሬ ኢየሱስ ሁሉን ማድረግ እንደሚችልና ብቁ እንደሆነ እናምናለን።
ነገር ግን ልናውቅ የሚገባው በእርግጥ እንዳለው ሁሉ ማድረግ መቻሉን ነው ማመናችንን እራሳችንን
መፈተን ነው። የጀመረውን ስራ ሊፈጽም እግዚአብሔር ብቁ ነው። የጠፋውን ሊያድን ብቁ ነው። እንደ
ሕዝበ እስራኤል እንቢ ብንል እንኳን ወደ ተስፋይቱ ምድር ሊያስገባን ብቁ ነው። የእኛ አለማመን
የእግዚአብሔርን ታማኝነት አያስቀርም። ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።

ሕዝበ እስራኤል ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት እንቢ ሲል። እግዚአብሔር ሙሴን ፈተነው።
ይህንንም ፈተና ለሙሴ አዲስ የስራ እድል በመክፈት ነው። ሙሴ ግን እንቢ አለ። ዘሁ.13‐14
እግዚአብሔር ሕዝበ እስራኤል ሁሉ ሊያጠፋና ከሙሴና ከእርሱ ዘር ጋር ብቻ ሊቀጥልና ለእርሱ ሌላ
ትውልድ ሊሰጠው እንደሚፈልግ ለሙሴ ነገረው። ሙሴ ግን ለእርሱ እንዲህ አለው፦ “እግዚአብሔር
ይህን ሕዝብ ወደ ማለላቸው ምድር ያገባቸው ዘንድ አልቻለምና በምድረ በዳ ገደላቸው ብለው
ይናገራሉ።’’ አለው። እግዚአብሔር ሙሴን ከሰማ በኋላ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔርም አለ፦ እንደ ቃልህ
ይቅር አልሁ 21. ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝና በእውነት የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል።’’ ታላቅ
የተስፋ ቃል ገባ።

www.tlcfan.org 2
መለከት #5

እኔ ሕያው ነኝና የሚለው ቃል እግዚአብሔር አንድ ነገር ሊያደርግ እንደወሰነ ከማሳየት አልፎ
በማንነቱ ላይም ጭምር ያተኮረ ተስፋ እንደሆነ ይሳያል። እግዚአብሔር እሞክራለሁ አላለም፣ ከቻልኩ
አላለም ወይም ሰዎች የምላቸው ከሰሙኝ አላለም። ነገር ግን በእራሱ ማንነት ታምኖ ይህን ሊፈጽም
ወሰነ፣ ቃል ገባ፣ ተነበየ። ምድር በክብሩ ካልተሞላች እኛ የሚገባውን ስላላደረግን ሳይሆን እግዚአብሔር
የገባውን ተስፋ ስላልፈጸመ ወይም ስላላደረገ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ግን ሕዝበ እስራኤልን ወደ
ተስፋይቱ ምድር በማስገባት ቃሉ እንደሚፈጸመው እንዳሳየ ምድርንም በክብሩ በመሙላት የተስፋ
ቃሉን ይፈጽማል።

ይህ የእስራኤል ሕዝብ ከንዓንን መውረስ ምሳሌ ግን የቃሉ ፍጻሜ አልነበረም። ይልቁኑ ወደፊት
ለሚፈጸመው ለእግዚአብሔር ታላቁ ሰራው መለኮታዊ ትንቢታዊ ጥላም ነበር። በእርግጥ ገና ምድር
በክብሩ ትሞላለች። መሃላው አንድ ከንዓንን ብቻ በክብሩ መሙላት ሳይሆን ምድርና ሞላዋን ውሃ
የባሕርን ፊት እንደሚሸፍን ምድርን በእግዚአብሔር ክብር መሙላት ነው። ይህ ደግሞ በውስጧ ያለውን
ፍጥረት ሁሉ የሚጨምር ነው።

ይህ የሕዝበ እስራኤል ታሪክ ግን የዳስ በዓልን ዮርዳኖስ ተሻግረው ማድረግን እንቢ ያሉትን
ፍቃዳቸውን በፍቃዱ ጥሎ ራሱን በእነርሱ አከበረ ከንዓን ስለ ስሙና ማንነቱ አወረሳቸው። በሌላ አባባል
እግዚአብሔር እንቢ ብንልም እሺ እንድንል ያደርገናል። ይህም የደነቆረውን ጆሮና የታወረውን አይን
በመክፈት ነው። ዘጸ.4፥11 የሰው ፍቃድ ወይም ምርጫ ሁል ጊዜ በእግዚአብሔር ፍቃድና ምርጫ ስር
ነው። ይህም ማለት ሰው በሚያደርገው ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቃድና ሃሳብ መፈጸሙን ፈጽሞ
አያግድም ማለት ነው። እግዚአብሔር ሁሉን አዲስ ያደርጋል። እግዚአብሔር ሁሉን ይለውጣል።
እግዚአብሔር ሁሉን ያድናል። 1.ጢሞ.4፥10 ይህ ማለት ግን ሰዎች ባለመታዘዝ ሕይወት እንዳሉ ያድናቸል
ማለት አይደለም። ሁሉን ያድናል ማለት ልባቸውን በፍቅሩና ምሕረት በተሞላው ፍርዱ በመቀየር
ባሕሪውና ማነቱን በማይቃረን ስርዓቱ ሁሉን በማይጥስ መልኩ ሁሉን አዲስ በማድረግ ነው። ይህም
ተሃድሶ ደህንነት በእሳት የሚገለጥ ተሃድሶ ነው። ሚል.3 ስለ ነጻ ፍቃድ በበለጠ ለማወቅ ነጻ ፍቃድ
የሚለውን መጽሐፍ ያንብቡ።

ይህም ትንቢት የሚፈጸመው በሸመገለው ፊት ሁሉ በነጩ ዙፋን ፊት ሲነሱ ነው። ዳንኤል በራእዮ
እንዳየው ዙፋኑ ራሱ ነበልባልና መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ። ዙፋን ሁል ጊዜ የእግዚአብሔር
የሕግ ምሳሌ ነው። ንጉስ ሁል ጊዜ ዙፋን ላይ ሲቀመጥ ትእዛዝ እንደሚወጣ በሰው ልጆች ታሪንና
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠ እውነት ነው። የእሳትም ፈሳሽ ከፊቱ ይፈልቅና ይወጣ ነበር የሚለው
ቃል ከእርሱ የሚወጣውን ሕግ የሚያመለክት ነው። “ሺህ ጊዜ ሺህ ያገለግሉት ነበር፥ እልፍ አእላፋትም
በፊቱ ቆመው ነበር ፍርድም ሆነ፥ መጻሕፍትም ተገለጡ።” ዳኤ.7 ይህ ደግሞ የሚያሳየው በፊቱ በትንሳኤ
የተነሱት መልካምና ክፉ ያደረጉትን በጠቅላላው ወይም በሁለተኛው ትንሳኤ የተነሱትን ሰዎችን ሁሉ
የሚፈድበትን ሕጉን የሚያሳይ ነው።

ራእይ 20 ደግሞ ይህንኑ ታሪክ በሌላ መልኩ ይገልጥልናል። ድል ነሺዎች ከነጩ ዝፋን ፍርድ
በፊት በመጀመሪያው ትንሳኤን እንደሚቀበሉና የቀሩት ሙታን ግን በመጀመሪያውና ለጻድቃንና ለድል
ነሺዎች ብቻ በተወሰነው ትንሳኤ እንደማይነሱ ይነግረናል። ነገር ግን በሁለተኛው ትንሳኤ በነጩ ዙፋን
ፊት በዘመናት በሸመግለው ፊት ለፍርድ እንደሚነሱ ይነግረናል። ከሚነሱትም ክፉ ያደጉ ማለትም
በሕይወት መጽሐፍ ስማቸው ተጽፎ ያልተገኘ ሁሉ በእሳት ባሕር ውስጥ ፍርዳቸውን እንደሚቀበሉ
ይነግረናል። ይህ እሳት እኛ እንደምናውቀው ምግን እንደምናበስልበት አይነት ፍጥረታዊ እሳት አይደለም።
ይህ እሳት ደግሜ እላለሁ የእግዚአብሔር ሕግ ምሳሌ ነው።

www.tlcfan.org 3
መለከት #5

“እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ከሲና መጣ፥ በሴይርም ተገለጠ፤ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥
ከአእላፋትም ቅዱሳኑ መጣ፤ በስተ ቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው።”
ዘዳ.33፥2
“በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድንጋዩንም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን?
ይላል እግዚአብሔር፦’’ ኤር.23:፥29

የእግዚአብሔር ሕግ እንደ ቃሉ ያጠና ሁሉ የሚያውቀው እውነት አለ ይህም የእግዚአብሔር እሳት


ሕግ ሃጢያተኛውን ለማሰቃየት ወይም ለማቃጠል የሚመጣ አለመሆኑ ነው። እሳት በፍጥረታዊ አለምም
ስራው ይለያያል። ለጥቅምም ለጥፋትም ይውላል። የእግዚአብሔር እሳትም እንዲሁ ነው። እግዚአብሔር
የሕጉ እሳት የሚጠቀመው ሃጢያተኛውን እንደ ሳሙና አጣቢ በማጠብ ለማንጻትና ለማጥራት ነው።
በጻድቁና በቅዱሱ እግዚአብሔር ፊት መቆም እንዲችል ያነጻዋል። ነገር ግን ሁሉ የፍርድ ተካፋይ ይሆናል።
ፍርድ ማለት ደግሞ የተበላሸውን የሚገባውን ቅጣት ቀጥቶ ማስተካከል ወይም ማረም ማለት ነው።

የእሳት ባሕር ራሱን የቻለ ፍርዱ የሚፈጸምበት ዘመን አለው። የእሳት ባሕር ፍርድ ለዘለዓለም
የሚቀጥል ፍርድ አይደለም። ሁሉ ነገር ጅማሬ እንዳለሁ ሁሉ ፍጻሜም አለው። ደግሞ ከዘላለም እስከ
ዘለዓለም የሚለው ቃል ትክክለኛ ትርጉም አይደለም። ማንኛውም ቃሉን በዋናው ትርጉም የሚያጠና
ዘላለም ተብሎ በአማርኛና በእንግሊዘኛ የተረጎመውን ቃል ትክክለኛ ትርጉም እንዳልሆነ ይረዳል። ዘላለም
የሚለውን ቃል ግሪኩ የሚለው “ኢዬን” ነው። ይህ ደግሞ ዘመን ማለት ነው። (eon, or age/ age-
during) ስለዚህ የዚህ የእሳት ባሕር ዘመን ሲፈጸም ያኔ የኢዮቤልዮ ሕግ ፍጻሜ ዘመን ይሆናል። የፍርድ
ሁሉ ፍጻሜ ኢዮቤልዮ ነው። ምሕረት በፍርድ ላይ ይመካል። ይህም የሁሉ እዳ ፈጽሞ ከሁሉ ላይ
ሲደመሰስ የሚፈጸም ነው።

ኢዮቤልዮ ሕግ ፍጻሜ ውጤቱ ሁሉ ወደ ቀድሞውና ወደ ጠፋው ርስቱ እንደገና እንዲመለስ


ማድረግ ነው። ኢዮቤልዮ ሕግ የሃጢያት የፍርድ ገደብ ነው። እዳ ማለት ሃጢያት ማለት ነው። እዳው
ደግሞ የሚደመሰስበት ዘመንና ገደብና የተወሰነለት ዘመን አለው። ዳንኤልም ይህንን በትንቢቱ
ተናግሯል። በሉቃስ 12 መሰረትም በመጨረሻው ዘመን ግርፊያ ወይም ፍርድ እንደሚኖር ይናገርና። ይህ
ግርፊያ ግን ለዘላለም እንዳልሆነ ሕጉን ያጠና ያውቀዋል።

“በሰዎች መካከል ጠብ ቢሆን፥ ወደ ፍርድም ቢመጡ፥ ፈራጆችም ቢፈርዱባቸው፥


ጻድቁን፦ ደኅና ነህ፥ የበደለውንም፦ በደለኛ ነህ ይበሉአቸው። በደለኛውም መገረፍ
ቢገባው እንዲገረፍ ፈራጁ በፊቱ በምድር ላይ ያጋድመው፤ የግርፋቱም ቍጥር እንደ
ኃጢአቱ መጠን ይሁን። ግርፋቱም አርባ ይሁን፤ ከዚህ በላይ ጨምሮ ብዙ ግርፋት
ቢገርፈው ወንድምህ በፊትህ ነውረኛ ይሆናልና ከዚህ በላይ አይጨመርበት።”
ዘዳግም 25፥1‐3

ቃሉና ዘላለማዊ የሆነው የማይሻረው የእግዚአብሔር ሕግ እንደሚናገር ግሪፊያው የሃጢያቱን


ልክ ያህልና ቢበዛ ደግሞ 40 ብቻ ነው። ከዚህ በኋላ መግረፍን ወይም ያለማቋረጥ ማስቃየትን
በእግዚአብሔር ሕግና ቃል ውስጥ የትም ቦታ ተጽፎ አናገኝም። እንግዲህ ድል የማንነሳ ቅማኞች ሁሉና
ክፉ እያደረግን በአመጸኛ ሕይወት የምንቀጥል በሸመገለው ፊት ፍርድን ልንቀበል በትንሳኤ መነሳታችን
የማይቀር የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው። ነገር ግን በመጀመሪያው ትንሳኤ እንድንነሳ ደግሞም ከእሳት
ባሕር ፍርድ ለመዳን ድል ነሺ አማኝ ለመሆን የምንወድ ሁሉ በመንፈስ እየተመራን እግዚአብሔር
ትዕዛዛት እንታዘዝ።
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።
ድል የነሣው በሁለተኛው ሞት አይጐዳም።” ራእይ.2፥11

www.tlcfan.org 4
መለከት #5

www.tlcfan.org 5

You might also like