You are on page 1of 8

የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #7

7
www.tlcfan.org 0
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #7

የእግዚአብሔር ፍርድ፣ ምሕረትና ጽድቅ በዳዊት ላይ

“ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ” መዝ.85፥10

“Mercy and truth are met together; righteousness and peace have kissed each other.”KJV

ጽድቅና ሰላም ተስማሙ የሚለውን እንግሊዘኛው ተሳሳሙ ይለናል። መሳሳም ሰውን ፊት


ለፊት ማየትን የሚጠይቅ ነው። ማለትም ልክ እግዚአብሔር ሙሴን አፍ ለአፍ ያነጋግረው እንደነበረው
አይነት ሲሆን ሕብረትን፣ አንድነትን፣ መቀባበልን እና መስማማትን የሚያመለክት ነው። ዘጸ.33፥11
ወይም ደግሞ በአዳምና በእግዚአብሔር ዘንድ በፍጥረት ቀን የሆነውንም የሚያሳይ ነው። የሕይወትን
እስትንፋስ በአፍንጫው እፍ እዳለበት ማለት ነው። ይህ የፍጥረት ክንውን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር
ለሰው ያለውን ፍቅሩን ሕይወቱን በማካፈል የገለጠበት አባት ልጁን ወልዶ የሳመበት ቀን ነው።

ታዲያ ይህ ክንውን በምሕረትና በእውነት በጽድቅና ሰላም መካከል እንዴት ሊሆን ወይም
ሊፈጸም ይችላል? ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን መሳሳም ወይም መስማማት የምናየው በማደሪያው ድንኳን
ውስጥ በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ባለው ታቦት ላይ ነው። የእግዚአብሔር ሕግ እውነት ሲሆን በታቦቱ
ሳጥን ውስጥ ሲቀመጥ ምሕረት ደግሞ ታቦቱ ከድኖ የሚይዘጋው ኪሩቤሎቹ የተሸከመው መክደኛ
ነበር። ምሕረትና እውነት በቅድስተ ቅዱሳን ተሳስመዋል። ያቆብም በያቆ.2፥13 “ ምሕረት በፍርድ ላይ
ይመካል” ብሎ ይህን መሰከረ። ያቆብ ይህን ማለቱ ምሕረት ሕግን ወይም ፍርድን አስወገደ ማለቱ
ነውን? ምሕረት ፍርድን እና ሕግን ያጠፋልን ወይስ ያስወግዳልን?

በፍጹም!! የመሳሳም ወይም የመስማማት ውጤት እንዱን አስወግዶ አንዱና ማቆም


አይደለም። ስሞ ማስወገድ በይሁዳ የተገለጠ የሃሰት ምስክር የሰይጣን ሃሳብ ነው። መሳሳም ወይም
መስማማት በእግዚአብሔር ሃሳብ ዘንድ ሁለቱንም አስማምቶ በፍቅር የማቆም ምልክት ነው። አንድ
ሰው ይሁዳ ላይ እንደገባው የሴጣን ሃሳብ ካልገባበት በቀር ወዳጁን ስሞ አይሸጥም፣ ወዳጁንም እየሳመ
ወደታች አይጨቁንም ወይም አይጫንም። በመኋልየ ላይ በጻፍኩት ከመዝሙር የሚበልጥ መዝሙር
በሚለው መጽሐፌ ላይ በግልጽ ስለ መሳሳም ምን ማለት እንደሆነ አስተምሪያለው። የመሳሳምን
መንፈሳዊ ትርጉም በይበልጥ ለማወቅ ወደ ድረ ገጹ ሄደው መጽሐፉን ያነቡት ዘንድ እጋብዛለሁ።

መሳሳም ወደ ጋብቻና ቃል ኪዳን የሚወስድ ጅማሬ የመግባባት የመስማማት ምሳሌ ነው።


የጽላቱ ላይ የተጻፈው ሕግ እውነትን የሚያመለክትና የያዘ ነው። ከምሕረት መክደኛው ጋር በታቦቱ
ሳጥን ውስጥ ሆኖ ተሳሰሟል። ሌላው ደግሞ ሕጉ እራሱ ጽድቅን የሚያሳይ ሲሆን የምሕረት መክደኛው
ደግሞ ሰላምን ያመለክታል። ስለዚህ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ያለው ታቦት መዝሙር.85፥10 ተስማሙ፣
ተሳሳሙ የሚለውን በደንብ አድርጎ ይገልጠዋል።

ዛሬ በዚህ ባለንበት ዘመን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በምትክነት በሞተበት ወቅት


ፍርድን ሁሉ አስወግዷን የሚሉ አሉ። እንዲሁ በግልጽ እግዚአብሔር ሕጉ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከክርስቶስ
ጋር ሰቅሎ አስወግዶታል ይላሉ። የሚደንቀኝ ግን ኢየሱስ ታዲያ ካስወገደው ስለሚመጣ ፍርድ ለምን
ያስተምረናል? ኢየሱስ ሞቶ ከተነሳ በኋላ ሕጉን አስተምሯል። ጳውሎስ ሊመጣ ስላለው የእግዚአብሔር
ፍርድ ያስተምረናል። እንዲሁ በአማኞች ላይ ሳይቀር ስለሚመጣው የእሳት ፍርድ በ1ቆሮ.3:፥15 ላይ
አስተምሯል። ኢየሱስ አስረግጦ ብትወዱኝ ትዕዛዛቴን ጥበቁ ብሏል። ዮሐንስ ሃጢያትን የሚያደርግ
ሕግን ይተላለፋል ይለናል።

www.tlcfan.org 1
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #7

ሊሎች ደግሞ አክርረው ይህ የእግዚአብሔር ፍድር የማያልቅ ለዘላለም እስከ ዘላለም


የሚቆይ ነው ብለው ከቃሉ ውጭ የሆነ ነገርም ያስተምራሉ። ኢየሱስም ሆነ ጳውሎስ እንዲሁ ዮሐንስ
ያስተማሩት በዘመን ስለ ተወሰነው እግዚአብሔር ፍርድ ነው። በግሪኩ “eonian judgment” ይለዋል።
ይህ ፍርድ ዘላለማዊ ወይም በኢንግሊዘኛው እንደተጻፈው “eternal” አይደለም።

የግሪኩ ቃል eonian ማለት “age-abiding” (Rotherham) or “age-during”


(Young) መጽሐፍ ቅዱስ ቀጥታ ተርጉመው በትክክለኛ ትርጉሙ አስቀምጠውታል። በጣም
የሚደንቀኝ ግን ይህን የዘላለም ፍርድ የሚያስተምሩ ደግሞ ሕጉ እደተሻረና ፍርድ በክርስቶስ
እንደተወገደም የሚሰብኩ ናቸው። እንዴት አርገው ሁለቱን እንደሚያስማሙ ይደንቀኛል። እነዚህ ሰዎች
በጊዜው ምርጫ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። እኔ የማምነው የእግዚአብሔር ፍርድ ለዘመናት እንደሚቆይና
ዘላለማዊ እንዳልሆነ ነው። ፍርድ አለ ነገር ግን ለዘላለም እስከ ዘላለም የሚቆይ ፍርድና የፍርድ ቅጣት
በእግዚአብሔር ዘንድና ሕግ ውስጥ የለም። እግዚአብሔር ሕግን ሳይሆን የቀየረው ኪዳንን ነው።

በሙሴ፣ በዳንኤልና በዮሐንስ እንደተነገረው የእሳት ፍርድ ግን በሰው ልጆች ላይ መምጣቱ


የማይቀር ነው። ይሁንና ለዘላለም እስከ ዘላለም የሚቆይ አይደለም። ይህን የሚደግፍ በትርጉም ስህተት
ለዘላለም እስከ ለዘላለም ተብሎ ከተጻፈው በስተቀር የእግዚአብሔር ቃል፣ ሕግና ባሕሪ ይህን የስህተት
ትምሕርት ፈጽሞ አይደግፍም። ኢዬቤልዮ ሕግ ብቻውን ይህንን ለዘላለም እስከ ዘላለም የሚለውን
ፍርድ ውድቅ ያደርገዋል። ኢዬቤልዮን የሚያልፍ ምንም አይነት የሐጢያት ፍርድ የለም። ይህ
የእግዚአብሔር ሕግ የእግዚአብሔር የፀጋው ጣራ ነው።

ኢዮቤልዮ የሚያሳየው ያቆብ እዳለው ምሕረት በፍርድ ላይ መመካቱን ነው።


የእግዚአብሔር ሕግ ሃጢያተኛውን ከሃጢያቱ መጠን በላይ እንዳትገርፈው ደግሞም ቢበዛ ከ40 ጅራፍ
በላይ እንዳትገርፈው ብሎ ያስተምራል። የእግዚአብሔር ጽድቅና ሰላም የሚመጣው እውነትና ምሕረት
ሲስማሙ ነው ብሎ ያስተምረናል። ይህም ሃጢያተኛው በሚመልስ በሚያርም በሕግ ፍርድን በማድረግ
በምሕረት ደግሞ ጽድቅንና ሰላምን በማቆም የሚፈጸም ነው። ስለዚህም እግዚአብሔር ልጆቹን
ትክክለኛ ስፍራ ላይ ለማምጣት ልጆቹን ሕጉን በልባቸው ላይ በመጻፍ፣ ይቀጣል፣ ያርማል
ይገርፋቸውማል ደግሞም ወደ እርሱ ይመልሳቸዋል። ዕብ.12

“እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር፦ ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ


አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ
የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል። ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች
ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?” ዕብ.12

እግዚአብሔር ልጆቹ ያለ ምክንያት አይቀጣም ወይም አይፈልድባቸውም። ካልበሰለ


ቤተሰብና ሰው የሚወጣ ቅጣትና ፍርድ ምሬትን ያበቅላል። ሌሎች ደግሞ ልጆቻቸው አይቀጡም ወይም
ስርዓት አያስይዙም ይህ ደግሞ ሕግ የለሽ ኑሮ የሚኖሩ መረን የወጡ ልጆን እንዲያሳድጉ ያደርጋቸዋል።
እግዚአብሔር ግን እንደ ሰው አይቀጣም ወይም አይፈርድም። እግዚአብሔር ሁሉን እኩል ሚዛን ባለው
መልኩ ይፈጽማል። ይህንን እኛም እንድናደርገው ይጠብቅብናል። ማክረር ወይም ጭራሽ የለም ብሎ
መረን ማውጣት ሳይሆን በእኩል ሚዛን ምሕረትንና እውነትን አገናኝተን ጽድቅንና ሰላምን ልናሳስም
የገባል። ስለዚህ በጥቅሉ ፍርድ የለም የሚሉ የእግዚአብሔር አባትነት የሚቃወሙና የረሱ ናቸው ብል
ከእውነት የሚያርቀኝ አይመስለኝም።

www.tlcfan.org 2
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #7

እግዚአብሔር ታዲያ ልጆቹን እንዴት ይቀጣል እንዴትስ ይፈርድባቸዋል? ብሎ ማሰብ ወሳኝ


የሆነ እራሳችንን ልንጠይቅ የሚገባው ጥያቄ ነው። እግዚአብሔር የሚቀጣውም ሆነ የሚፈርደው ፍቅርን
ምህረትን መሰረቱ አድርጎ ነው። በመዝሙር ላይ “ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ”
የሚለውን ቃል የሚፈታልን ሌላ ቃል የምናገኘው ሰለሞን የእግዚአብሔር መቅደስ በመረቀ ቀን የጸለየው
ጸሎት ላይ ነው። 2.ዜና.6፥36-39

“የማይበድል ሰው የለምና አንተን ቢበድሉ፥ ተቈጥተህም ለጠላት አሳልፈህ


ብትሰጣቸው፥ ሩቅም ወይም ቅርብ ወደ ሆነ አገር ቢማርኩአቸው፥
በተማረኩበትም አገር ሆነው በልባቸው ንስሐ ቢገቡ፥ በምርኮአቸውም አገር ሳሉ
ተመልሰው፦ ኃጢአት ሠርተናል፥ በድለንማል፥ ክፉም አድርገናል ብለው
ቢለምኑህ፥በተማረኩበትም በምርኮአቸው አገር ሳሉ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም
ነፍሳቸው ወደ አንተ ቢመለሱ፥ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃት ወደ ምድራቸው
ወደ መረጥሃትም ከተማ ለስምህም ወደ ሠራሁት ቤት ቢጸልዩ፥ጸሎታቸውንና
ልመናቸውን በማደሪያህ በሰማይ ስማ፥ ፍርድንም አድርግላቸው አንተንም
የበደሉህን ሕዝብህን ይቅር በል።”

ስለሞን በጸሎቱ ፍርድ ሃጢያተኛው በንስሃ እስኪመለስ ድረስ የሚቀጥል እንደሆነ


ያስረዳል። የፍርድ አላማ ሰውን ወደ ምሕረትና ወደ ጽድቅ ለመለስ ነው። በፍጥረታዊ አለምም ቢሆን
ሰው ፍርድ ቤት የሚፈርድበ ቅጣት ሰጥቶ ከቅጣቱ በኋላ በደለኛውን ወደ ሕብረተሰቡ በእርማትና
በታደስ ማንነት ሕብረተሰቡን የሚጠቅም አድርጎ ለመመለስ ነው። የእግዚአብሔር ፍርድም ሲፈጸም
ያን ጊዜ እውነትና ምሕረት ይስማማሉ ጽድቅና ሰላምም ይሳሳማሉ።

የንጉስ ዳዊት ሕይወት ምሳሌነት፦

ሳኦል የእግዚአብሔር ሕግን በመተላለፉ ንጉስ እንዳይሆን እግዚአብሔር ናቀው። በሌላ


አባባል እንዳይገዛ አደረገው በእርሱ ፋንታም እግዚአብሔር ዳዊትን ንጉስ አድርጎ ቀባው። 1.ሳሙ.13፥14
“አሁንም መንግሥትህ አይጸናም፤ እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መርጦአል፤ እግዚአብሔርም
ያዘዘህን አልጠበቅህምና እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ አዝዞታል አለው።’’ አስተውሉ
እግዚአብሔር ፍጹም የሆነ ሰው ወይም ጻድቅ የሆነ ሰው መርጧል አላለም። ይልቁኑ እግዚአብሔር እንደ
ልቡ ማለት በራሱ ፍቃድና ውሳኔ ዳዊትን ተክቷል ይለናል።

ዳዊት ፍጹምና ጻድቅ የነበረ ሰው አይደለም። ዳዊት ለንግስና የተመረጠው እግዚአብሔር


ለማወቅ ለማግኘት ከመፈለጉ ብቻ የተነሳ እግዚአብሔር ስለሳበው እንጂ በራሱ የነበረው ጽድቅና
ፍጽምና ሥራ አልነበረውም። በተቃራኒው ደግሞ ሳኦልን ስናየው እግዚአብሔርን እንደ ልቡ ፍቃድ
እንዲሆንለት የሚፈልግ፣ እግዚአብሔር በራሱ መንገድ ሊያስኬድ የሚፈልግ ሰው ነበር። እግዚአብሔርን
በመስዋዕት ብዛት በራሱ መንገድ ሊያስኬድ ደጋግሞ የሞከረ ሰው ነው። ነብዮ ሚኪያስ የእግዚአብሔር
ልብና ፍላጎት ምን እንደሆነ ይገልጥልናል። “ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ
ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር
በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?” ይላል። ትሕትና የፀጋ ሥርና መሰረት ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር
መለኮታዊ ፍርድ ለማወቅ የእግዚአብሔር ልብና ፍላጎት ማወቅ ወሳኝ ነው። ጴጥሮስም ይህን እውነት
ይገልጥልናል። በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ ሰዓት ትልቅ ቁልፍ ስፍራ እንዳለው ይጠቁመናል።

www.tlcfan.org 3
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #7

“እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ


ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ። ለአንዳንዶች
የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ
ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።”
2.ጴጥ.3፥9

ንጉስ ዳዊት በንግሥናው ዘመን ወደ ፍርድ ውስጥ ያስገባውን ሃጢያት ሰራ። ይህም ሃጢያት
ሁላችን እንደምናውቀው ከኦሪዮን ሚስት ከቤርሳቤ ጋር የሰራው የዝሙት ሃጢያት ነው። ዳዊት በዝሙት
አላበቃም። በመቀጠልም ሃጢያቱን ለመደበቅ በሄደበት መንገድ ባሏን በማስገደል አውቆና አሰላስሎ
የሰው ነፍስ በማጥፋቱ ነፍሰ ገዳይም ሆኗል። 2.ሳሙ.11 እንደ እግዚአብሔር ሕግና እውነት መሰረት
ዝሙት ያደረገም ሆነ ነፍስ የገደለ ቅጣቱ ወይም ፍርዱ ሞት ነው። ዘጸ. 21፥12-14, ዘዳ.22፥22

“ሰው ሰውን ቢመታ ቢሞትም፥ እርሱ ፈጽሞ ይገደል።”

“ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አመንዝራውና አመንዝራይቱ


ሁለታቸው ይሙቱ፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከእስራኤል ታስወግዳለህ።”

ከእግዚአብሔር ሕግ ተነስተን የምንጠይቀው ታዲያ ለምን ዳዊት አልተገደለም? የሚል


ጥያቄ ነው። ዳዊት ለምን ከዚህ ፍርድ አመለጠ? ለምን ብሎ መጠየቅ የሚገባ ነው። እውነት
ከእግዚአብሔር ሊማር የሚወድ ሁሉን ነገር ኢየሱስ በ12 ዓመቱ እንዳደረገው የሚጠይቅ ሰው ነው።
እግዚአብሔር ሕጉን ከመስቀሉ በፊትም አስወግዶት ይሆንን? በፍጹም! ከላይ ቀደም ብለን እንዳየነው
ታቦቱ የሕግና እውነት ማደሪያ ብቻ ሳይሆን እርሱን ሸፍኖ የሚይዝ የምሕረት መክደኛ ነበረው።
ስለዚህም ዳዊት በጣም ወሳኝ የሆነ እንዴት እግዚአብሔር ሕጉን ሳይሽር ወይም ሳያስወግድ ምሕረትን
በእኩል ሚዛን ሕጉ እንዴት እንደሚያስተላልፍ እንደሚፈርድና ጽድቅንና ሰላምን እንደሚያሳስም
እንመለከታለን።

በመጀመሪያ የምንመልከተው ዳዊት የሰራው ሥራ በአምላኩ ፊት ክፉ መሆኑን ነው።


“የልቅሶዋም ወራት ሲፈጸም ዳዊት ልኮ ወደ ቤቱ አስመጣት፥ ሚስትም ሆነችው፥ ወንድ ልጅም
ወለደችለት ነገር ግን ዳዊት ያደረገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሆነ።” ይህ የሚያሳየው
እግዚአብሔር ዳዊትን እንደማይለቀውና እስከ ሃጢያቱ እንደማይተወው ያሳያል። ንጉስ ዳዊት ያለ
ምንም እርማትና ቅጣት እግዚአብሔር ቢተወው ኖሮ ዳዊት ሌላም ሌልእም ሃጢያቶችን ለመስራት
ይገፋፋ ወይም የእስራኤል ንጉስ የሆነ ምንም ስለ ሃጢያት ተጠያቂ አይደለም የሚል ድምዳሜ ላይ አዲስ
ስርዓትንና ትምህርትን ወደ ማስተላለፍ ይደርስ ነበር። ይሁንና እግዚአብሔር ዳዊትን እንዲሁ ያለ ፍርድ
አልተወውም እንዲያውም አስቀድሞ በራሱ ላይ በእኩል ሚዛን ሕግ እንዲፈርድ እድልን ሰጠው። ይህም
እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለጠጋ ስለሆን ነው። ይህ ኢየሱስ ለአመንዝራይቱ ሴት በአመንዝራው ሕግ
ሳይሆን በቅናት ሕግ ፍርድን ፈርዶ በምሕረት እንደመለሳት አይነት እርምጃ ነው።

“እግዚአብሔርም ናታንን ወደ ዳዊት ላከ፥ ወደ እርሱም መጥቶ አለው፦ በአንድ ከተማ


አንዱ ባለጠጋ አንዱም ድሀ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ። ባለጠጋውም እጅግ ብዙ በግና ላም
ነበረው። ለድሀው ግን ከገዛት አንዲት ታናሽ በግ በቀር አንዳች አልነበረውም፤ አሳደጋትም፥

www.tlcfan.org 4
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #7

ከልጆቹም ጋር በእርሱ ዘንድ አደገች፤ እንጀራውንም ትበላ፥ ከዋንጫውም ትጠጣ፥


በብብቱም ትተኛ ነበር፥ እንደ ልጁም ነበረች። ወደ ባለጠጋውም እንግዳ በመጣ ጊዜ ከበጉና
ከላሙ ወስዶ ለዚያ ወደ እርሱ ለመጣው እንግዳ ያዘጋጅለት ዘንድ ሳሳ፤ የዚያንም የድሀውን
ሰው በግ ወስዶ ለዚያ ለመጣው ሰው አዘጋጀ። ዳዊትም በዚያ ሰው ላይ እጅግ ተቈጥቶ
ናታንን፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ይህን ያደረገ ሰው የሞት ልጅ ነው። ይህን አድርጎአልና፥
አላዘነምና ስለ አንዲቱ በግ አራት ይመልስ አለው።”2.ሳሙ.12፥1-6

ንጉስ ዳዊት እረኛ ነበርና በበግ በኩል ይግባኙ ግልጽ ሆኖ ሲቀርብለት ፍርድን በራሱ ላይ
እየፈረደ እንደሆነ ሳያውቅ ፈረደ። ነብዮ ናታንም ያ ሰው አንተ ነህ ብሎ ፍርዱን በገዛ አንደበቱ እንደበየነ
አበሰረለት። ይህ ለንጉስ ዳዊት ትልቅ በፍርድ የሆነ የምሕረትና ስለላም የሚቀበልበት ጅማሬ የሆነና ወደ
ንስሃ ያመጣው ነበር። ቃሉ እንደሚል በራሳችን ብንፈርድ ባልተፈረደብንም እንደሚል። ለንጉስ ዳዊት
በራሱ ላይ ፈረደ። ፍርዱ የሚያመጣበትንም ስላወቀ ወዲያው እልፍኙን ዘግቶ ወደ እግዚአብሔር በንስሃ
ቀረበ።

እግዚአብሔር ለምን ናታንን ይህን ቃል አስይዞ ወደ ዳዊት የላከው ዳዊትን ወደ እርሱ


በፍርዱና ምሕረቱ ይመልሰውና ጽድቅንና ስለማንን ያስማማ ዘንድ ነው። ዛሬም ብዙዎቻችን እኛ
ራሳችን በወደቅንበት ሃጢያት ያሉትን ወይም የወደቁትን ሰዎች እንደ ንግስ ዳዊት ይቅር ማለት ስንቸገር
ፍርድን ስናወጣ አያለሁ። እግዚአብሔር በራሳችን ላይ እያስፈረደን ይሆንን? ብሎ ከመፍረድ በፊት ራስን
መመርመር ልባምነት ነው።“እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥
በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።” ማቴ.7፥1-2 ሰው ይቅር ማለት የሚችለው ምን
ያሕል ይቅር እንደተባለ ሲገባው ብቻ ነው። በሃጢያተኛ ሕይወትና በፍርድ ስር ሆኖ ለሌሎች ምሕረትን
ማድረግ በጣም አስቸጋሪ ነው። ይሁንና በሌሎች ከመፍረድ በፊት ራስን ማየት ተገቢ ነው።

“በከረጢትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ የሆነ ሁለት ዓይነት ሚዛን አይኑርልህ። በቤትህ ውስጥ
ታላቅና ታናሽ የሆነ ሁለት ዓይነት መስፈሪያ አይኑርልህ። ይህን የሚያደርግ ሁሉ
ክፋትንም የሚያደርግ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና አምላክህ
እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እውነተኛና ፍጹም ሚዛን
ይሁንልህ፤ እውነተኛና ፍጹም መስፈሪያም ይሁንልህ።” ዘዳ.25፥13-16

ንጉስ ዳዊትን እግዚአብሔር በእኩል ሚዛን ሕግ ሊፈርደው ተነሳ። ፍርዱንም እራሱ በራሱ
ላይ በራሱ አንደበት እንዲፈርድ ወይም እንዲሰፍር አደረገው። እግዚአብሔር ለሌሎች ባለን የምሕረት
ልክ እኛንም ይፈርዳል ወይም የበይናል። ለዚህ ነው ጌታ በጸሎቱ የበደሉንን ይቅር እንደምንል እኛንም
ይቅር በለን ብለን ወደ እግዚአብሔር እንድንጸልይ ያስተማረን። ለንጉስ ዳዊት ምሕረትን ሊያበዛለት
ወደደ ነገር ግን ምሕረቱን እርሱ በሰፈረውና በፈረደው ፍርድ ልክ አደረገበት። ዳዊት በዚያች እለት
ትሕትናንና ንስሃን ተማረ። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሕግ ዋናው አላማው ሃጢያት ምን እንደሆነ
ማሳየትና ወደ ንስሃ እንድንመጣ ማድረግ ነው። እግዚአብሔር ከምሕረት መክደኛው ሆነ ሁሉን ሸፍኖ
እንደ ንጉስ ዳዊት የአፉ ቃል ሊፈርድበት ተነሳ። ዳዊት ያ ሰው እርሱ መሆኑን ሲያውቅ ወደ መለኮታዊው
የእግዚአብሔር ፍርድ ቤት በንስሃ ጸሎት የምሕረት ጥያቄን አስገባ። ነገ ግን ፍርዱን እራሱ አውጥቶ
ነበርና እንዳለውና እንደፈረደው ተፈጸመበት። በሰማዩ በእግዚአብሔር ፍርድ ቤት እውነትን (ሕጉን) እና
ምሕረን አስማምቶ ጽድቅንማ ስላምን ማድረግ ይችላል። በምድር ያሉ ፍርድ ቤቶች ግን ጽድቅንና
ሰላምን ላድርግ ቢሉም ለማድረግ ሰርዓትና ሕጋቸው ፈጽሞ ራሳቸውን እጃቸውን ያስራል።

www.tlcfan.org 5
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #7

ዳዊት በራሱ ላይ አራት እጥፍ ብሎ ፈረደ። “ይህን አድርጎአልና፥ አላዘነምና ስለ አንዲቱ


በግ አራት ይመልስ አለው።” ፍርዱም እንዳስተላለፈው ተፈጸመ። አራቱ ልጆቹ ስለ ዳዊት ሃጢያት
በየተራ ሞቱ። 2.ሳሙ.11፥5-6 ንጉስ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ከልቡ ንስሃ ስለገባ ምሕረትንም
አድርጎለታል። ይህም በሃጢያቱ ምክንያት በዝሙት ሕግ ተፈርዶበት እንዳይሞት በእኩል ሚዛን ሕግ
በርዶበት ጽድቅንና ሰላምን በማምጣት ወደ እርሱ መለሰው።

በእግዚአብሔር ምሕረት ባለጠገነት ብዛት እርሱ ከሞት ተረፈ። ነገር ግን የጥፋቱን ቅጣት
ሳይቀበል አልቀረም። ምንም እንኳን ዳዊት ሌሊቱን ሙሉ ቢጸልይና ቢጾም ከቤርሳቤ የጸነሰው ልጅ ሞተ።
2.ሳሙ.12፥15-17 “ናታንም ወደ ቤቱ ተመለሰ። እግዚአብሔርም የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችውን
ሕፃን ቀሠፈ፥ እጅግም ታምሞ ነበር።” በመንፈሳዊ ትርጉሙ ካየነው ልጁ የክርስቶስ ኢየሱስም ጥላ ነው።
ሃጢያት ያላወቀው በኩር በመሞቱ ዳዊት ከሞት ተረፈ። ኢየሱስ ስለ አባቱ አዳም እንደሞተ ወንጌል
እንደሚናገር ማለት ነው። ዮሐ.11፥50 የሆነው ሆኖ ይህ የመጀመሪያው ልጅ ፍርድ ውጤት ከአራቱ
ፍርዶች ዳዊት እንደ ወሰነው የመጀመሪያው ነበር። የበኩር ልጁ ከሞተ በኋላ የንጉስ ዳዊት ሕይወት
የነበረው የቀሩትን ፍርዶች በየተራ መቀበል ነው። ይህም የእግዚአብሔር ቅጣትና ፍርድ ንጉስ ዳዊትን
ወደ ትሕትና ሕይወት ወደ ጽድቅና ሰላም በመጨረሻ አስገባው። ጽድቅና ሰላም ተሳሳሙ ወይም
ተስማሙ።

 የእግዚአብሔር ሕግ አልተሻረም!
 ሃጢያትን የሰራ ሰው ሁሉ የሃጢያቱን ቅጣት ልክ እንደ ሃጢያቱ መጠን ሳይቀበል አይቀርም!
 እግዚአብሔር በሃጢያት ሳይፈርድ ምሕረትን አያመጣም!
 እውነትና ምሕረት ሳይስማሙ ጽድቅና ሰላም አይመጣም።
 ከንጉስ ዳዊት ሕይወት እንዳየነውና እንደተማርነው በሰዎች ላይ ከመስፈርና ከመፍረዳችን
በፊት ራሳችንን ዞር ብለን መመልከት እንዳለብን ነው።

“ስለዚህ በእናንተ ዘንድ የደከሙና የታመሙ ብዙዎች አሉ አያሌዎችም


አንቀላፍተዋል። ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር፤ነገር ግን
በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን።”
1.ቆሮ.11፥32

www.tlcfan.org 6
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #7

www.tlcfan.org 7

You might also like