You are on page 1of 3

‘’ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።’’ ሮሜ 8፡1

ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፡፡ ሰይጣን በባለፈው ኃጠአታችን በብዙ መንገድ ሊከሰን ይሞክራል፤
ምክንያቱም የወንድሞች ከሳሽ ስለሆነ፣ ግን በአብ ዘንድ ደግሞ ቆሞ የሚከራከርልን ጠበቃችን ኢየሱስ አለን፡፡ ስለዚህ
የከሳሻችንን ድምጽ ባለ መስማት የሞተልንን ጠበቃችንን ኢየሱስን እያየን በፊታችን ያለውን ሩጫችንን በእምነትና
በትዕግስት እንሩጥ፡፡

ተባረኩ 😍 😍 😍
‘’in locum domini’’ means ‘’in the site of the lord’’
ይህ ከላይ የምታዩት መፈክር በተሀድሶ(reformation) እንቅስቃሴ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች መለያ ነበር፡፡ በተሀድሶ ዘመን
ከተፈበረኩ ፈጠራዎች 65% የሚሆነው የተፈጠረው በክርስቲያኖች ነበር፡፡ ምክንያቱም የሚያደርጉትን ሁሉ
የሚያደርጉት ለክርስቶስ ስለሆነ፡፡ ቢማሩ፣ ቢሰሩ፤ ቢነግዱ፣ ቢያገለግሉ ለክርስቶስ ብለው ስለሚያደርጉት ውጤታማ
ነበሩ፡፡ እኛም የምናደርገውን ነገር ሁሉ ’’ክርስቶስ በእኔ ቦታ ቢሆነ ኖሮ ምን ነበር የሚያደርገው‘’ ብለን በማሰብ
የምናደርገውን ነገር ሁሉ በትጋትና በመሰጠት አናድርግ፡፡
’’እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።’’
1 ኛ ቆሮ 10፡31
ተባረኩ
Hi family endet nachu, tilant beneberen meeting 2 negerochin lemadireg tesmamtenal:
1. bible beyekenu lemanbeb silezih kenege(SATURDAY) jemiro (የዘፍጥረት መፅሐፍን) manbeb enjemiralen......
beyekenu 1 miraf enanebalen

hamus sinigenagn hulachinim eske miraf 6 cherisen memtat alebin 📖


2. beyekenu tselot metseley

BE BLESSED!!! 😍

‘’እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል።’’
ት.ናሆም 1፡7
እግዚአብሔር በሕይወታችን ሁሌ መልካም ነው፡፡ መልካምነቱም ለአንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለዘላለም ነው፡፡ መልካምነቱን ከእኛ ያላራቀ
አምላክ ዘላለም የተመሰገነ ይሁን፡፡
ተባረኩ
እግዚአብሔርም ዓይንዋን ከፈተላት የውኃ ጉድጓድንም አየች፤ ሄዳም አቁማዳውን በውኃ ሞላች ብላቴናውንም አጠጣች፡፡
ዘፍጥረት 21፡19
አጋር ከአብርሀም ቤት ኮብልላ በምድረ በዳ እየተቅበዘበዘች ስታለቅስ እግዚዘብሔር ተገልጦላት፣ ዓይንዋን ከፍቶላት የውኃ ምንጭ
እንድታይ አድርጓታል፡፡ እኛም በሚያጥመን የሕይወታችን ምድረበዳ ውስጥ ካለንበት ችግር ይልቅ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ማዳን
እንድናይ እግዚአብሔር አይናችንን እንደ አጋር ይክፈትልን ስል እባርካችኋለው፡፡

በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው። በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን? አሉት።

ሕፃንም ጠርቶ በመካከላቸው አቆመ

እንዲህም አለ። እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።

እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፥ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው።
ማቴዎስ 18፡1-4

በክርስትና ሕይወት ውስጥ ለክርስቲያን አንዱና ዋነኛው ጠንቅ ራስን ከሌሎች ከፍ ከፍ አድርጎ መመልከት(በአጭሩ ትዕቢት) ነው፡፡
ደቀ መዛሙርቱ እርስ በርስ የመበላለጥ ፍቅር አድሮባቸው ማነው የበላይ ብለው ሲጠይቁ ኢየሱስ ግን ራሳቸውን በትህትና ዝቅ
እንዲያደርጉ ይነግራቸዋል፡፡ ትህትና ሁሌ ክብረትን ትቀድማለች(ምሳሌ 15፡33)፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር የትዕቢትን ልብ ከላያችን ላይ
ሰብሮልን የትሕትናን ልብ ይስጠን፡፡ ……….. አሜን ………

ቃለሕይወት ያሰማልን ያነበብነውን በልቦናችን ያኑርልን

እወዳቹሃለው ተባረኩልኝ

‘’ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።


 
ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?‘’

መዝሙረ ዳዊት 42፡1-2

ነፍስ ሁሌ የምትረካው ከምንጯ ጋር ስትገናኝ ብቻ ነው፡፡ ምንጯ ደግሞ የፈጠራት እግዚአብሔር ነው፡፡ ነፍሳችንን
በእግዚአብሔር ቃል እየመገብን፣ በፀሎት እያተጋናት ካልያዝናት ታስቸግረናለች፡፡ ምክንየቱም ፈቃዳችን በእርሷ ውስጥ
ስለሚገኝ፡፡ የነፍሳችንን ፈቃድ ደግሞ ለእግዚአብሔር የምናስገዛው በፀሎትና በቃሉ ከያዝናት ብቻ ነው፡፡

የነፍሳችንን ፈቃድ ለእግዚአብሔር ማስገዛት ይሁንልን፡፡

ተባረኩ
16 
፤ ስለዚህ፥ እነሆ፥ አባብላታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳም አመጣታለሁ፥ ለልብዋም እናገራለሁ።’’ ሆሴ 2፤16

እግዚአብሔር እኛን ወደራሱ መስመር ማስገባት ሲፈልግ መጀመሪያ እኛን ይሰብረናል፡፡ ዛሬ ምን አመጣህብን እንዳትሉ፤ ማለትም
በውስጣችን ያለውን አልነካ ያለውን ራስ ወዳድ የሆነውን ማንነታችንን ይሰብረዋል፡፡ ለዚህ ነው እስራኤልን ወደ ራሱ ሊወስዳት
ሲፈልግ ወደ ምድረ በዳ እወስዳታለው፤ ለልብዋም እናገራታለው የሚለን፡፡

በምድረ በዳ ውስጥ እያባበለን እኛን የሚቀርፀን አምላክ ስሙ የተባረከ ይሁን፡፡ አሜን

ሊያባብለኝ በምድረ በዳ ወሰደኝ

አስተምሮ አስተካክሎ ሊቀርፀኝ

በውዴ ላይ በእርሱ ብቻ ተደግፌ

ይህች ማናት የሚሉኝን እንዳይ አልፌ

ያለኝን በሙሉ ወደማዶ

አሻገረው ብቻዬን ሊያይ ወዶ

ሲታገለኝ ውሎ በጨለማው

አስቸጋሪው ልቤን እስኪረታው

You might also like