You are on page 1of 33

1 ፓስተር ክሪስ

መለኮታዊ ግንኙነት

ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው (1 ኛ ቆሮንቶስ 6፡17)


በጌታ እና በአንድ መንፈስም ከእርሱ ጋር ተጣምረናል። ከጌታ ጋር አንድ እንድንሆን የእግዚአብሔር ምኞት ነበርና ያም በክርስቶስ
እውን ሆነ። ለዚህ አንድነት ሃላፊነት የወሰደው መንፈስ ቅዱስ ነው።ኢየሱስ “እኔና አብ አንድ ነን” ብሏል (ዮሐንስ 10፡30)። ኢየሱስ ከአብ ጋር
እንዴት አንድ ሆነ? ይህ የሆነው በመንፈስ ቅዱስ በኩል ነበር። ዛሬም ከእናንተ ጋር እንዲሁ ነው።
2 ኛ ቆሮንቶስ 6፡16 እንዲህ ይላል፡- “...እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረ ። በእነርሱ
እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።"አሁን፣ እሱ በእናንተ ውስጥ ይኖራል እንዲሁም
በእናንተ ውስጥ ይመላለሳል። እናንተ እግዚአብሔርን የምትሸከሙ ዕቃዎች ናችሁ።
በዮሐንስ 14፡20፣ ኢየሱስ “እኔ በአባቴ እንዳለሁ፣ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ፣ እኔም በእናንተ እንዳለሁ…።” ይህም ማለት እናንተ
በኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ውስጥ ናችሁ እናም እሱ በእናንተ ውስጥ ነው። ያ ነው መለኮታዊ ትስስር!
ስለዚህ፣ ችሎታችሁ ወይም ብቃታችሁ የእርሱ ነው (2 ኛ ቆሮንቶስ 3፡5)። በመንፈስ ቅዱስ በኩል ገደብ ከሌለው የእግዚአብሔር ኃይል
ጋር ወሰን ከሌለው ዕድል እና ማለቂያ ከሌለው ክብር ጋር ተያይዛችኋል። እግዚአብሔር ይባረክ!
የእምነት አዋጅ
መንፈስ ቅዱስ በእኔ ስለሚኖር፣ እኔ ከእግዚአብሔር ጋር የተገናኘሁ ነኝ! የድል አድራጊውን የክርስትና ሕይወት እንድኖርና በማደርገው
ነገር ሁሉ፤ ለአብ ክብር ስኬታማ እንድሆን የሚረዳኝ እርሱ በእኔ ውስጥ ነው። በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት፣ በእኔ ሲሰራ፣ እኔን ሲያንጽ እና
ሌሎችን በእኔ በኩል ሲገነባ በየቀኑ እጅግ አስደናቂ የሆነ የበረከት ህይወትን እኖራለሁ። ክብር ለእግዚአብሔር!
ለተጨማሪ ጥናት
ዮሐንስ 14፡10
ዮሐንስ 14፡16
ቆላስይስ 1፡29
ዘካርያስ 4፡6
2 ፓስተር ክሪስ
በከተማችሁ ውስጥ ያሸንፋል
እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር (የሐዋርያት ሥራ 19፡20)

ሉቃስ፣ ጳውሎስ በእስያ ስላደረገው ሚስዮናዊ ጉዞ፣ በተለይም በኤፌሶን ስላደረጋቸው አንዳንድ ተግባራት ታሪካዊ ዘገባ ሰጥቷል።
የሐዋርያት ሥራ 19፡8 እንዲህ ይላል፡- “ወደ ምኵራብም ገብቶ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየተነጋገረና እያስረዳቸው ሦስት ወር ያህል
በግልጥ ይናገር ነበር።"
ነገር ግን በምኩራብ ወንጌልን ሲሰብክ፣ አንድ ነገር መከሰት ጀመረ፡- ተቃውሞ እየተፈጠረ መጣ። አንዳንድ አይሁዶች አላመኑም
ነበር፤ ይልቁንም፣ የጌታን መንገድ በአደባባይ ያጥላሉ ነበር! ይህንንም ፈጥኖ የተገነዘበው ሐዋርያው ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን ለብቻቸው
ወስዶ በየእለቱ ግን በጢራኖስ የትምህርት አዳራሽ ይሰባሰቡ ነበር (የሐዋርያት ሥራ 19፡9)።
ቁጥር 10 ላይ ይህ ለሁለት ዓመታት ያህል እንደቀጠለ ይነግረናል። ውጤቱም በእስያ ግዛት ይኖሩ የነበሩት አይሁድና ግሪኮች ሁሉ የጌታን
ቃል ሰሙ። የሐዋርያት ሥራ 19፡11-12 እግዚአብሔር በጳውሎስ እጅ ድንቅ ተአምራትን አደረገ፤ ስለዚህም እርሱን የዳሰሱ ጨርቆችና መሃረቦችን
ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፣ ከሕመማቸው ይፈወሱም ርኩሳን መናፍስትም ለቀዋቸው ይሄዱ ነበር። የእግዚአብሔር ቃል ድል ሲያደርግ
የሚሆነው ይህ ነው።
ቃሉን ብትሰብኩና ብታስተምሩ በአገራችሁ፣ በከተማችሁ፣ በወረዳችሁ ወይም በአካባቢያችሁ ማህበረሰብ ተመሳሳይ ነገር ይሆናል።
ጳውሎስ አንድ ከተማ ሙሉ ወንጌልን እስኪሰማ ድረስ ቃሉን ለመስበክና ለማስተማር በቂ ጊዜ ሰጠ። የእግዚአብሔር ቃል የኤፌሶንን ከተማ
ሊቆጣጠር እና ሊለውጥ ከቻለ፣ በእናንተ ህይወትና አለምም ላይ ተመሳሳይ ውጤት ያስገኛል።
በአለማችሁ ያሉትን ነገሮች ለመለወጥ የእግዚአብሔርን ቃል ተጠቀሙ እንዲሁም ተግባር ላይ አውሉት። ያ ቃል በአፋችሁ ውስጥ
ነው እናም ያሸንፋል። አሁንም አፋችሁን ከፍታችሁ በአካባቢያችሁ ማኅበረሰብ፣ በከተማችሁ እና በሕዝብ ላይ ጽድቅን አፍስሱ! አካባቢያችሁን
የወንጌል ዘር ዝሩበት።

ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፣ የጽድቅ ወንጌል በመሰበኩና ትምህርቱም በመሰጠቱ ፣ መንግሥትህ በሁሉም ከተማና ሕዝቦች ላይ ተመስረቷል፣
እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ሁሉ፤ በየትኛውም ቦታ ያሉ ሰዎች፣ እና በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በመልእክቱ ተጽዕኖ ሥር ናቸው፣ ይህም ጌታን
የሚያስደስት ነገር እንዲያደርጉ ያደርጋቸዋል። በመጨረሻዎቹ ቀናት፣በምድር ሁሉ ላይ ነፃነትን ለማወጅ በቤተ ክርስቲያን ላይ ለጨመረው
ጸጋህ እናመሰግንሃለን፣በኢየሱስ ስም። አሜን።
ለተጨማሪ ጥናት
2 ጢሞቴዎስ 4:2
የሐዋርያት ሥራ 28፡30-31
3 ፓስተር ክሪስ
በእሱ ችሎታ ተኩራሩ
እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ
ፍሬ ያፈራል (ዮሐንስ 15፡5)
ጌታ እንዲህ ይላል፣ “...ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም።"በራሳችሁ ሰዋዊ ችሎታ፣ ብልሃት፣ ጥበብ፣ ክህሎት እና ብቃት ምንም
ነገር ማሳካት አትችሉም። ስለዚህ፣ የራሳችሁ በሚመስሉ ችሎታዎች በጭራሽ አትኩራሩ። በጌታ ታመኑ።
ስኬታችሁ ሙሉ በሙሉ የሚወሠነው ከጌታ ጋር ባላችሁ ግንኙነት ላይ ነው። ብቃታችሁ የእርሱ ነው፡- “ለራሳችን ብቁ መሆናችንን
(ብቃታችን እና ችሎታችን) ከኛ የተገኘ ነው ብለን በግላችን ለመፍረድ ወይም የኔ ነው ለማለት ወይም ለመቁጠር ሳይሆን ኃይላችን ችሎታችን
እና ብቃታችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው እንጂ።” (2 ኛ ቆሮንቶስ 3፡5 አምፕሊፋይድ ክላሲክ ትርጉም)
ጳውሎስ “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ”(ፊልጵስዩስ 4፡13) ሲል በጌታ መኩራቱ ምንም አያስደንቅም። እሱ "በጣም
እውቀት ስላለኝ ሁሉንም ነገር ማድረግ እችላለሁ"አላለም፤ ይልቁንስ የተናገረው ስለ ክርስቶስና እሱ በእናንተ ውስጥ ስላለው ማንነት -
በእናንተ እና በእናንተ ውስጥ ስላለው አገልግሎት እንጂ። በ 2 ኛ ዜና 14 ላይ የአሳን ታሪክ ያስታውሰናል። መጽሐፍ ቅዱስ ይሁዳን በአንድ
ሚሊዮን ሰዎችና በሦስት መቶ ሰረገሎች መወረሯን ይነግረናል። ንጉሥ አሳና ሠራዊቱ ሙሉ በሙሉ በቁጥር ተበልጠዋል። አሳ ድል ሊያደርግበት
የሚችለው ብቸኛው መንገድ በጌታ ላይ ሙሉ በሙሉ በመታመን እንደሆነ ተገነዘበ።
በዜና መዋዕል ካልዕ 14፡11 አሳ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ከልብ ጮኸ እንዲህም አለ፡- “... አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን
አይሳንህም፤ አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና እርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤
ሰውም አያሸንፍህ ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።”
እግዚአብሔርም በምላሹ ለይሁዳ አስደናቂ ድልን አጎናጸፈ፡- “እግዚአብሔርም በአሳና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንን መታ።
ኢትዮጵያውያንም ሸሹ”(ዜና መዋዕል ካልዕ 14፡12)። አሁን፣ ስለ አሳ አንድ ልብ ልንለው የሚገባው ነገር አለ፡ “የሚሆነው፣ ይሆናል” ብሎ
በማሰብ ዝም ብሎ አልተቀመጠም፤ እርምጃ ወሰደ።በእምነት የምትወስዱት እርምጃ አስፈላጊ ነው። አሳና ሠራዊቱ ከጸለዩ በኋላ፣ የጠላትን
ኃይል በማጥቃት ድል አደረጉ። ሃሌ ሉያ!

ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፣ በእኔ ውስጥ በብርታት ስለሚሠራው መለኮታዊ ኃይልህ አመሰግንሃለሁ። የእኔ ብቃት፣ችሎታ እና ተፎካካሪነት የእግዚአብሔር
ነው። እኔ ምርጥ ነኝ እንዲሁም ምርጥ የሆነ ሕይወት አለኝ! በውስጤ የሚሠራው ኃይል መለኮታዊ ስለሆነና፣ እንዲሁም ገደብ ስለሌለው
ሁሉንም ነገር ማድረግ እችላለሁ።ስምህ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን። አሜን!
ለተጨማሪ ጥናት
ፊልጵስዩስ 4:13
2 ኛ ቆሮንቶስ 4፡7
ቆላስይስ 1፡10-11
ኤፌሶን 6፡10

4 ፓስተር ክሪስ
“ወደ” ስሙ ተጠምቃችኋል
እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው… (ማቴዎስ 28፡19)
በአዲስ ኪዳን የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ኢየሱስ ነው። ሐዋርያትም ይህንን ተረድተው ሰዎችን በኢየሱስ ስም
አጠመቁ። በሐዋርያት ሥራ 19 ላይ፣ ሉቃስ በኤፌሶን ከነበሩት ከአሥራ ሁለቱ ሰዎች ጋር ጳውሎስ ስለነበረው ግንኙነትና፣ እንደ አጵሎስ፣
የመጥምቁ ዮሐንስን የንስሐ ትምህርት ቀናተኛ ተከታዮች እንደነበሩ ነገር ግን ወደ ኢየሱስ ጥምቀት እንዳልተቀየሩ ያትታል።
ጳውሎስ ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ"... በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ" (ሐዋ. 19፡3-5)ይላል።ይህም የአብ፣ የወልድ
እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ኢየሱስ መሆኑን የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል። ነገር ግን ጳውሎስ በኤፌሶን ከነበሩት ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ጋር
በተገናኘበት ጊዜ ወዲያውኑ ግልጽ ያልሆነው ሌላ ነገር፣ “ታዲያ ወደምን ተጠመቃችሁ?”ብሎ ሲጠይቃቸው ነው።
"ወደ"የሚለውን ቃል አስተውሉ፤ “ወደ…ውስጥ”ከሚለው ተመሳሳይ የግሪክ ቃል የተገኘ ነው። ስለዚህ፣ ስትጠመቁ፣"ወደ"የሆነ ነገር
ነው የምትጠመቁት። በመሠረቱ፣ ጳውሎስ እነዚያን ሰዎች “ታዲያ ወደ ምን ተጠመቃችሁ?” ሲል መጠየቁ ጥምቀት በውኃ ውስጥ ከመነከር
የበለጠ ጥልቅ ነገር መሆኑን ያሳያል።
የዚያ ጥቅስ ትርጉም በአንዳንድ አዳዲስ ትርጉሞች፣ ለምሳሌ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ በተሻለ ሁኔታ ተገልጿል። “ይህን በሰሙ
ጊዜ ወደ ጌታ ኢየሱስ ስም ተጠመቁ” ይላል። በውኃ ስትጠመቁ፣ በስም ብቻ ሳይሆን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ትጠመቃላችሁ። እሱ ነው
የጥምቀት ምንነት።
የጥምቀት አንዱ አካል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ስም እያጠመቃችሁካለው አገልጋይ በተለይ፣ ትልቁ ክፍል ወደ ጌታ ኢየሱስ ስም
መጠመቃችሁ ነው። ስለዚህ የውሃ ጥምቀት ከክርስቶስ ጋር ያላችሁን ህጋዊ ህብረት ያጸናዋል። (ሮሜ 6፡3-4)። እግዚአብሔር ይባረክ!
ጸሎት
አባት ሆይ፣በውስጡና በሱ እንድንኖር የኢየሱስን ስም ስለሰጠኸን እናመሰግንሃለን። ወደ ክርስቶስ ተጠምቄአለሁ፣ እናም ከእርሱ ጋር
ላልለያይ አንድ ሆኛለሁ፤ በእርሱ ውስጥ እኖራለሁ፣ እንቀሳቀሳለሁ ማንነቴንም አገኛለሁ ! የምኖረው በኢየሱስ ስም ነው፣ እናም እኔ ዓለሜን
የምቆጣጠረውና የምገዛው በዚህ ስም ኃይል ነው። ክብር ለእግዚአብሔር!
ለተጨማሪ ጥናት

የሐዋርያት ሥራ 2፡38
የሐዋርያት ሥራ 8፡16
የሐዋርያት ሥራ 10፡47-48

5 ፓስተር ክሪስ
ያው አምላክ - ያው ምስክርነቶች
ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው
በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር (የሐዋርያት ሥራ 5:15)
መጽሐፍ ቅዱስ በዕብራውያን 13:8 ላይ እንዲህ ይላል "ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው። "
አንዳንዶች በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ ስለ ጴጥሮስ ያነበብነው ነገር በዘመናችን መሆን ይችላል እንዴ ብለው ይጠይቃሉ። በሚገባ!
ዛሬም ተመሳሳይ ተአምራቶችን እና ምስክርነቶችን እናያለን ምክንያቱም እግዚአብሔር ያው ነውና።
የጳውሎስን ሰውነት የነኩ መሀረብ እና ጨርቆች በህመምተኞች ላይ ሲደረጉ ደዌአቸው ይለቃቸው እና ክፉ መናፍስትም ይወጡ
እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።
በተመሳሳይ ይህን የምታነቡት ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ መጽሐፍ በታመሙ እና በሞቱ ሰዎች ላይ ሲቀመጡ ተዓምራቶች
እንደነበሩ፤ህመምተኞች እንደ ተፈወሱ እንዲሁም የሞቱ ወደ ሕይወት እንደ መጡ በብዙ የሚቆጠሩ ምስክርነቶችን ሰምተናል ። ይህ በተለያዩ
የዓለም ክፍሎች ብዙ ጊዜ ሆኗል ምክንያቱም ይህ መጽሐፍ ከእግዚአብሔር ነውና።
ባሏ የሞተባትን ሴት ታሪክ አስቡ። ለአንዲት ሴት እንዲህ አለች "ሰዎች ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ ተጠቅመው በቤተ ክርስቲያንሽ
ውስጥ ሙታንን ሲያስነሱ ሰምቻለሁ። እባክሽን አንድ ቅጂ ይዘሽ ወደ ሆስፒታል ነይ ባለቤቴ ሞቷል"። የደወለችላትም ሴት የራፕሶዲ
ኦፍ ሪያሊቲስ ቅጂ ይዛ በመሄድ በሞተው ሰው ላይ አደረገች እናም ሰውየው ወደ ሕይወት ተመለሰ! ሃሌሉያ!
የዚህን ታሪክ እና በሉቃስ 8:43-48 ላይ ደም ሲፈሳት የነበረችው ሴት ታሪክ ተመሳሳይነት ወዲያውኑ ማየት
ትችላላችሁ: "ሰማች" እናም ስለ ሰማች የኢየሱስን የልብስ ጫፍ ለመዳሰስ በብዙ ሰዎች መካከል ገፍታ ሄደች እናም ወዲያውኑ
ተፈወሰች።
ልዩነቱ ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ መጽሐፍ ምንም ካልተጻፈባቸው መሀረቦች እና ጨርቆች በበለጠ የእግዚአብሔርን ኃይል ተሸካሚ
የሆነው ደጋግማችሁ ልታጠኑት የምትችሉትን የእግዚአብሔርን ቃል ስለያዘ ነው። ክብር ለእግዚአብሔር!
የእምነት አዋጅ
እኔ የበረከቱ ተሸካሚ ነኝ፤ ከእኔ ጋር የተገናኘ ነገር ሁሉ የተባረከ፣ የሚያድግ እና የሚበዛ ነው። እኔ የጌታን መልካምነት
ለዓለሜ ሁሉ የማከፋፍል፣ ዛሬ ለምገናኛቸው ሁሉ የእርሱን የሞላ ጸጋ የማሳይ እና የምገልጽ ነኝ፣ በኢየሱስ ስም።አሜን።
ለተጨማሪ ጥናት፡-

የሐዋርያት ሥራ 19፡11-12
የሐዋርያት ሥራ 5:15
የማቴዎስ ወንጌል 14፡35-36

6 ፓስተር ክሪስ
በእኛ በኩል ይነግሣል
አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው (ቆላስይስ 2:15)
በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ ኢየሱስ በሲኦል ሰይጣንንና ጭፍራዎቹን ድል ነስቶ በግልጽ እንዳሳያቸው እንመለከታለን።
አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ በግልጽ አዋረዳቸው። ሁሉም የጨለማ መናፍስት ይህንን ተመለከቱ። የኮንይቤር ትርጉም
ትጥቃቸውን አስፈታቸው ይላል። ሃሌ ሉያ! አሁን በእነርሱ እና በነገር ሁሉ ላይ እርሱ እየገዛ ነው።
1 ኛ ቆሮንቶስ 15:25 እንዲህ ይላል "ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።" ኢየሱስ
በእግዚአብሔር ቀኝ በሰማይ ተቀምጧል፤ በኃይል ስፍራ። ስለዚህ ታዲያ እንዴት ነው እየገዛ ያለው? በጠላቶቹ ላይ የሚነግሰው
እንዴት ነው? ሮሜ 5:17 አንድ ሀሳብ ይሰጠናል፤ እንዲህ ይላል"በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና
የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ።" በእኛ ይነግሣል!
እኛ ስንነግስ፥እርሱ ይነግሳል። አስታውሱ መጽሐፍ ቅዱስ ጸጋ በጽድቅ እንደሚነግሥ ይነግረናል "…ኃጢአት በሞት
እንደነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ…"
(ሮሜ 5: 20-21)። ስለዚህ የእርሱ ብርሃን ሆነን ለእርሱ ስንኖር ጸጋው በእኛ ላይ እና በእኛ ውስጥ ይሰራል፤ ለመንገሥ የሚሆን
የእርሱ ጸጋ። ሃሌ ሉያ!
ሥራችን በግልጽ ተቀምጦልናል፥ ሥራችንም በሕይወት እንድነግሥ እና የክርስቶስን በጎነት እና ፍጹምነት ለማሳየት
ነው: - "እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ እና ደግነት እና ፍጹምነት እንድታሳዩ
የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ በእግዚአብሔር የተገዛችሁ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ " (1 ኛ ጴጥሮስ
2:9 አምፓሊፋይድ ትርጉም)።
ቃሉን እንድንማር እና እንድናድግ እንዲሁም ቃሉን እንድናደርግ የሚፈልገው ለዚህ ነው ። የኢየሱስን ስም ተጠቅመን ይህንን
ዓለም እንድንገዛ ይፈልጋል። እኛ የዓለም ብርሃን ነን እናም ተቃዋሚዎችን እና ተግዳሮቶችን ሁሉ አሸንፈናል፤ በተባረከው በጌታ
በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሸንፈናል። ሃሌ ሉያ!
የእምነት አዋጅ
እንደ ንጉስ በሕይወት ለመንገስ እና ለመግዛት ጸጋን አግኝቻለሁ። ስለዚህ በሁኔታዎች ላይ፥ በዲያብሎስና በጭፍሮቹ ላይ
እገዛለሁ። አሁን በኢየሱስ ስም በሀገራት፣ በሕዝቦች፣ በመሪዎች፣ በዓለም ዙሪያ ባሉ ወጣቶች ሁሉ ላይ ያለውን የሰይጣንን
ተጽዕኖ እሰብራለሁ! ክርስቶስ በሀገራት ላይ ነግሷል እንዲሁም ጽድቁ ምድርን ሞልቶታል እናም የሰውን ልብ ሽፍኖል። ነፍስ
ሁሉ የእርሱ ናትና። ሃሌ ሉያ!
ለተጨማሪ ጥናት፡-

ትንቢተ ዳንኤል 7፡18


የዮሐንስ ራእይ 11:15
የዮሐንስ ራእይ 20፡6
 

7 ፓስተር ክሪስ
ሰላም ከእግዚአብሔር ጋር
ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ
አይፍራም (ዮሐንስ 14:27)
የኢየሱስ ክርስቶስ የሞቱን፣የመቀበሩን እና የመነሳቱን ትልቅነት እና አስፈላጊነት በዓለም ላይ ያለ ሰው ሁሉ እንዲረዳው እግዚአብሔር
ይወዳል! በእኛ ፈንታ ከመሰዋቱ በፊት መጽሐፍ ቅዱስ እኛን"በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን
እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ "ይለናል (ኤፌሶን
2:12)።የእግዚአብሔር ጠላቶች ነበርን።
ነገር ግን እግዚአብሔር ይባረክ! ሮሜ 5:10 በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ከራሱ ጋር አስታረቀን ይላል። ኤፌሶን 2:13-18 "አሁን ግን
እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን
ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው
አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል
ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን
የምስራች ብሎ ሰበከ፤ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።" ሃሌ ሉያ! 
ኢየሱስ ዋጋ ከፍሎ ከአብ ጋር ወዳለ ሰላም እና አንድነት አመጣን ። ጳውሎስ በሮሜ 5:1 ላይ እንዲህ ማለቱ አያስገርምም
"እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ። " "ሰላም" የሚለው ቃል
ከግሪኩ "ኤይረን" ከሚለው ቃል ነው። ይህ የጥልን መጨረሻ ያሳየናል። አንድ መሆን ማለት ነው።
በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ሆናችኋል ፤ በእርሱ ወደ ቤት መጥታችኋል! ፍርድን በመፍራት መኖር
አያስፈልግም፤ ኢየሱስ ለኃጢአታችሁ ቅጣትን ወስዷል። ኢሳይያስ 53:3 እንዲህ ይላል"…የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ
ነበረ…" (ኢሳይያስ 53:3)። ሃሌ ሉያ!
ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፣ ስለተሰጠኝ የማስታረቅ መልዕክት አመሰግንሃለሁ።በእኔ በዓለሜ ያሉ እና ከዛም ያለፉ ብዙ ሰዎች
እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ እና በክርስቶስ ወዳላቸው ርስት ይመጣሉ፤ከኩነኔ ነጻ ወደ ሆነ ከአብ ጋር ያለ የሰላም እና የህብረት
ሕይወት እየመጡ ነው፣በኢየሱስ ስም። አሜን።
ለተጨማሪ ጥናት፡-

1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡1


ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3፡8-9

 
 
 
 
 
 

 
8 ፓስተር ክሪስ
ቃሉ በልባችሁ ውስጥ
ዘሪው ቃሉን ይዘራል። ቃልም በተዘራበት በመንገድ ዳር የሆኑት እነዚህ ናቸው፥ በሰሙት ጊዜም ሰይጣን ወዲያው
መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል (ማርቆስ 4:14-15)
የእግዚአብሔር ቃል በልባችሁ በተቀበላችሁ ጊዜ፤ቃሉ ያለውን ኃይል በማወቅ የጨለማው ኃይላት ቃሉን ከልባችሁ
ለመስረቅ ፈጥነው ይመጣሉ።ጌታ ኢየሱስ በዘሪው ምሳሌ ላይ ያሳየን ይህንን ነው።
አንዳንድ ሰዎች ቃሉን ሰምተው የማያስተውሉት ለዚህ እንደሆነ ያሳየናል። ታላቅ ትንቢት ከተቀበሉ በኋላ ሁኔታ ሁሉ
በእነርሱ ላይ የተነሳ የሚመስለው ለምን እንደሆነ ማስረዳት ይከብዳቸዋል። ሰይጣን ቃሉን ከልባቸው ለመስረቅ ማንኛውንም
ነገር ስለሚያደርግ ነው፤ ቃሉን ከልባችሁ ውስጥ ለመስረቅ ያለውን ሁሉ ፍላጻ እና ክስ ይወረውራል። ስለ እርሱ የተነገረውን ቃል
በመጠራጠር እንዲያረጋግጥለት ጌታ ኢየሱስን እንኳን በዚህ መንገድ ፈትኖታል (ሉቃስ 4:3)። በእርግጥ ጌታ ጠላትን በሚገባ
ተቃውሞታል ምክንያቱም ቃሉ በልቡ ውስጥ ስር ሰዷልና።
ሆን ብላችሁ በልባችሁ ውስጥ ቃሉን ልትጠብቁት ይገባል። ቆላስይስ 3:16 እንዲህ ይላል"የእግዚአብሔር ቃል በሙላት
ይኑርባችሁ…"ይህ ማለት ቃሉ ይሙላባችሁ እና በልባችሁ ውስጥ ስር ይስደድ ማለት ነው። በዚህ መንገድ ምንም ያህል ጠላት
ከልባችሁ ውስጥ ሊሰርቅ ቢሞክር፥ አይሳካም።
ሰይጣን ከሕይወታችሁ ውስጥ ሊወስደው የሚፈልገው እጅግ ዋጋ ያለው ነገር በልባችሁ ያለውን የእግዚአብሔርን ቃል
ነው። ለዚህ ነው ቃሉን በልባችሁ ውስጥ መጠበቅ ያለባችሁ። ጠላት ሊደርስበት በሚችልበት እና ሊነቅለው በሚችለው ሁኔታ
ቃሉ በልባችሁ ሳይተከል ከላይ እንዲቀመጥ አትፍቀዱ። በማሰላሰል እና በልሳን በመጸለይ ወደ መንፈሳችሁ ውስጥ እንዲገባ
አድርጉ። በዚህ መንገድ ቃሉ በልባችሁ ውስጥ ስር ይሰድና ፍሬ ያፈራል። ሃሌ ሉያ!
ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፣ ስለ ቃልህ ክብር እና አሁን እንኳን ቃልህ በመንፈሴ ውስጥ ሲተከልና የጽድቅን ፍሬ ሲያፈራ
ስለምለማመደው መለወጥ አመሰግንሃለሁ። ቃልህን እንድኖርበት፣ በሕይወት ውስጥ ያሉ ሁኔታዎችን እንድቀይርበት እና ከአንተ
ፍጹም ፍቃድና ለእኔ ካለህ ዓላማ ጋር እንዳጣጥምበት ስለ ሰጠኸኝ አመሰግናለሁ፣በኢየሱስ ስም። አሜን።
ለተጨማሪ ጥናት

የሉቃስ ወንጌል 8፡14-15


ወደ ዕብራውያን 2፡1
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡16

9 ፓስተር ክሪስ
ከሰይጣን ግዛት ውጪ

...በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ፥... እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥... ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት
አፈለሰን (ቆላስይስ 1፥12-14)

ዳግመኛ በመወለዳችሁ፣ ከጨለማ ግዛት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ፈልሳችኋል ወይም ተዛውራቸዋል። የህይወት፣ የብርሃን እና የታላቅ ክብር
ግዛት ነው። ሰይጣን በእናንተ ላይ ወይም ከእናንተ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ነገር ላይ የይገባኛል ጥያቄ የለውም ምክንያቱም እናንተ በእሱ
ስልጣን ውስጥ አይደላችሁም።

ከሰይጣን ግዛት ወጥታችሁ ወደሚደነቅ ወደ እግዚአብሔር ብርሃን ተጠርታችኋል፦ “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን
የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤”(1 ኛ ጴጥሮስ 2፥9)

ዳግመኛ ያልተወለዱት ግን በተፈጥሯቸው በሰይጣን ባርነት ውስጥ ናቸው፣ በመከራ እና በህይወት ፍርሃት ተንገላተዋል፣ እራሳቸውን ነጻ
ማውጣት አይችሉም። እነሱ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ናቸው፣ ለመውጣት ምንም ተስፋ የላቸውም፣ ምክንያቱም ያለ እግዚአብሔር እየኖሩ
ነው። ተስፋቸው በክርስቶስ ኢየሱስ መዳንን ማግኘት ብቻ ነው።

ይህ ወዲያውኑ ጌታን ስለማያውቁት የቤተሰብ አባላት፣ ጓደኞቻችሁ፣ የስራ ባልደረቦቻችሁ እና ጎረቤቶቻችሁ እንድታስቡ ሊያደርጋችሁ ይገባል።
በክርስቶስ ወዳለው መዳን የምታመጧቸው፣ ከጨለማ እና ከሰይጣን ግዛት ወደ ብርሃን እና ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን የከበረ ነፃነት
የምታመጧቸው የእግዚአብሔር መጠቀሚያ ዕቃ እናንተ ናችሁ።

2 ኛ ቆሮንቶስ 5፥19 እንዲህ ይላል፣ “እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤
በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።” ማንም ሰው ራሱን ማዳን አይችልም፣ እኛ በራሳችን ማድረግ አንችልም ነበር፣ ለዚህም ነው ኢየሱስ የመጣው።

በእርሱ የምትክ ሞት መዳን ተቻለ፣ በእርሱ የክብር ትንሳኤም፣ የዘላለም ህይወት ቀርቧል። ሃሌ ሉያ! ከሰይጣን እንድንበልጥ የሚያደርገን እና
አሁን ካለው ከጨለማው ዓለም አካላት በላይ እንድንሆን የሚያደርገን፦ የዘላለም ሕይወት - የእግዚአብሔር ተፈጥሮ! አለን።ሃሌ ሉያ!

ጸሎት

ውድ አባት ሆይ፣ በክርስቶስ የምትክ መስዋዕትነት እና በክብር ትንሳኤው አማካኝነት ስላመጣኽልኝ የመዳን ጥቅሞች እና የጽድቅ ህይወት
አመሰግንሃለሁ። ሙሉ በሙሉ በእምነት እንደጸደቅኩ፣ እና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከአንተ ጋር ሰላም እንዳለኝ በመገንዘብ፣ በክርስቶስ
ባለኝ በአዲሱ ሕይወቴ እውነት እመላለሳለሁ። አሜን ።

ለተጨማሪ ጥናት፦
ዕብራውያን 13፥5
2 ቆሮንቶስ 4፥13

10 ፓስተር ክሪስ
ቃሉን የማጥናት ልማድ አዳብሩ

ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ (1 ኛ
ጴጥሮስ 2፥2-3)

ለትክክለኛ አካላዊ እድገት ጥሩ አመጋገብ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ የእግዚአብሔር ቃልም ለመንፈሳዊ እድገት አስፈላጊው ምግብ ነው።
አንድ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል ቸል ሲል፣ ከዲያብሎስ ለሚሰነዘር ጥቃት የተጋለጠ እና ለዚህ ዓለም አካላት እና ጎጂ ተጽዕኖዎች ይገዛል።
አስታውሱ፣ በቃሉ በኩል፣ አእምሮአችንን እናድሳለን፣ እምነት እና ባህሪን እንገነባለን። ስለዚህም ቃሉን ያለማቋረጥ መመገብ አለብን።

2 ኛ ጴጥሮስ 3፡18 እንዲህ ይላል፣“ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም
ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።” ከዚያም በምዕራፍ አንድ ቁጥር ሦስት ላይ የእግዚአብሔርን ቃል እውቀት አስፈላጊነት በድጋሚ ያጎላል። እንዲህ
ይላል፣ “የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥
በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ...”

እግዚአብሔር አስቀድሞ ለእናንተ አድርጎላችኋል እናም ለላቀ የክብር እና የጽድቅ ህይወት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ሰጥቶአችኋል። ነገር ግን፣
ለእናንተ የወሰነውን የበላይነት፣ የስኬት እና የብልጽግና ህይወት መኖር የሚወሰነው ባላችሁ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት እና በህይወታችሁ
ውስጥ በስራ ላይ ባዋላችሁት መጠን ላይ ነው። የእናንተ ቃሉን የማወቅና የመተግበር ጉዳይ ነው።

ስለዚህ ቃሉን እወቁ። ኢየሱስ እውነትን ታውቃላችሁ እውነትም አርነት እንድትወጡ ያደርጋችኋል ብሏል። የእግዚአብሔርን እውነት ለማወቅ፤
በቃሉ ለማደግ የሚገፋፋ ፍላጎት ይኑራችሁ። 1 ኛ ጴጥሮስ 2፡2 እንዲህ ይላል፣ “ ...በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል
የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።”

የእግዚአብሔርን ቃል ሆን ብላችሁ ተማሩ፤ ቃሉን በማጥናትና በማሰላሰል ብቻ ጊዜ የምትወስዱበት የጊዜ ሰሌዳ ይኑራችሁ። እምነት የሚገነቡ
መልዕክቶችን በየቀኑ ለመመልከት እና ለማዳመጥ ወደ ፓስተር ክሪስ ዲጂታል ላይብረሪ (PCDL) ይምጡ፣ ይህም ህይወታችሁን ይገነባል
ደግሞም ይለውጣል።

ለማጥናት ቅዱሳት መጻሕፍትን በከፈታችሁ ቁጥር አዲስ ነገር መማር ትችላላችሁ፣ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ ወደ አዕምሮአችሁ በሚያመጣቸው
በተወሰኑ ነገሮች ላይ ማሰላሰል ትችላላችሁ። ስለዚህ ቃሉን ለራሳችሁ የማጥናትን ልማድ አዳብሩ።

ጸሎት

ውድ አባት ሆይ፣ ከቃልህ ጋር ህብረት በማድረግ አንተን እንዳውቅ ጥልቅ ፍላጎት በልቤ ስላደረክ አመሰግንሃለሁ። በጠንካራ እምነት በክርስቶስ
ያለኝን ፍፃሜ ለመጨረስ በመንፈሳዊ ነገሮች ለመነሳሳት፣ ለመማር እና ለመለማመድ ራሴን አሳልፌ እሰጣለሁ፣ በኢየሱስ ስም። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት፦

ዕብራውያን 10፥25
1 ኛ ጢሞቴዎስ 3፥15

11 ፓስተር ክሪስ

ሙሉ በሙሉ ለወንጌል የተሰጠ


በውትድርና አገልግሎት ውስጥ ያለ ማንም ሰው በዕለት ተዕለት ኑሮው ውስጥ ጣልቃ አይገባም፤ ያለዚያ ለጦር የመለመለውን ደስ አያሰኝም።
(2 ኛ ጢሞቴዎስ 2፥4 ኤንኢቲ ትርጉም )

በማርቆስ 16፥15 ላይ  ኢየሱስ፣“... ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።” ብሎ ሲናገር ለእያንዳንዱ ክርስቲያን የተሰጠ ኃላፊነት
ነበር። ወንጌሉን ወደ አለማችሁ አልፎም ወደ ሌላው አለም የምትወስዱት እናንተ ናችሁ። በመናፈሻ ቦታ ውስጥ የምታደርጉት የጉዞ አይነት ብቻ
እንዳልሆነም አሳውቆናል።

በ 1 ኛ ቆሮንቶስ 16፥9፣ ጳውሎስ ለወንጌል መስፋፋት ታላቅ እና ውጤታማ በር ተከፍቶለት እንደነበር ነገር ግን ብዙ ተቃዋሚዎች እንደነበሩ
ተናግሯል። በ 2 ኛ ጢሞቴዎስ 3፥12 ላይ እንዲህ አለ፣“በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ
ይሰደዳሉ።”(2 ኛ ጢሞቴዎስ 3፥12):: ይሁን እንጂ አንዳቸውም ቢሆኑ ቅንዓቱን አላጠፉበትም ወይም ወንጌልን የመስበክ ፍላጎቱን አላቆመውም።

እናንተም እንዲሁ መሆን ነው ያለባችሁ። ወንጌልን መስበክ ምንም ቢመጣ ልንሰራው የሚገባ ስራ ነው። ለዚያም ነው ጳውሎስ በሐዋርያት ሥራ
20፥24 እንዲህ ያለው፣ “ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር
እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።”

ይህ የጳውሎስ ውሳኔ ነበር። ይህ መግለጫ ሊደርስበት ባለው ስደት ምክንያት ወደ እየሩሳሌም ሄዶ እንዳይሰብክ ሊከለክሉት ለሞከሩት ሰዎች
የሰጠው ምላሽ ነው። ከዚህ በፊት ባለው ቁጥር 22-23 ላይ፣ “አሁንም፥ እነሆ፥ እኔ በመንፈስ ታስሬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ፥ በዚያም
የሚያገኘኝ ምን እንደ ሆነ አላውቅም፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ፦ እስራትና መከራ ይቆይሃል ብሎ በየከተማው ሁሉ ይመሰክርልኛል።” ሆኖም ወደ
ኋላ አላለም።

በምዕራፍ 21 ከቁጥር 10-11 አጋቦስ የሚባል አንድ ነቢይ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም እንዴት እንደሚታሰር እና ለአሕዛብ አሳልፎ እንደሚሰጥ
ተንብዮአል። ከዚህም የተነሳ ሌሎች ደቀ መዛሙርት ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ለመኑት፤ እንደውም አለቀሱ። ነገር ግን የጳውሎስ
አነቃቂ ምላሽ ይህ ነበር፡-“... እያለቀሳችሁ ልቤንም እየሰበራችሁ ምን ማድረጋችሁ ነው? እኔ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት
እንኳ ተሰናድቼአለሁ እንጂ ለእስራት ብቻ አይደለም አለ።”

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማስፋፋት ምን ያህል ቁርጠኝነት አላችሁ? ይህ ጨዋታ አይደለም! ግድ ከሆነ ህይወታችንን አሳልፎ መስጠትን
ጨምሮ ሁሉም ነገር ውስጥ ብንገባ ይገባዋል ደግሞም ይጠይቀናል። ክርስቶስ ሁሉ ይገባዋል። ስለዚህ፣ ወንጌልን በምትሰብኩበት ፍጥነት፣
በጥልቅ ስሜታችሁ እና በፅናታችሁ ሌሎች ይነሳሱ።

የእምነት አዋጅ

እኔ ትጉ ነፍስን የምማርክ ነኝ፤ ለጌታ እና ለወንጌል ስርጭት ያለኝ ፍቅር ተወዳዳሪ የለውም። በምኖርበት እና ወንጌልን በምሰብክበት ጥልቅ
ፍቅር፣ ፍጥነት እና ፅናት ሌሎችን አነሳሳለሁ። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት፦
2 ኛ ጢሞቴዎስ 2፥3-4
ኤፌሶን 6፥13-17
12 ፓስተር ክሪስ
በጸሎት ለአገራት መጋደል

ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ (መዝሙር 2፡8)

መልእክት የተሰኘው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መሪ ጥቅሳችንን እንዲህ ያስቀምጠዋል፣“ምን ትፈልጋለህ? ንገረኝ፦ አገራትን እንደ ስጦታ?
አህጉራትን እንደ ሽልማት?" ይህን ጥቅስ ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘሁት በ 15 ዓመቴ ነው፣ እናም በዚህ ጥቅስ መሰረት ወደ ጌታ ጸለይኩ። በምላሹ፣
የጌታ መንፈስ፣ “አገራትን ሰጥቼሀለሁ!” አለኝ።

በዚያ ለጋ ዕድሜ፣ በዓለም አገራት ውስጥ ስላሉት የማያምኑ ሰዎች እና ስላሉበት አስከፊ ሁኔታ ያሳስበኝ ነበር። በመንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ ናቸው
እንዲሁም ከእግዚአብሔር ሕይወት የራቁ ናቸው። በዓለም ውስጥ ተስፋ የሌላቸው እና ያለ እግዚአብሔር ናቸው። ስለዚህ፣ የአለም
ካርታ፣የተለያዩ ካርታዎች ያሉበት መጽሐፍ አገኘሁ፣ ብዙ ጊዜ እጆቼን በእሱ ላይ አድርጌ፣ በአለም መንግስታት እና በሰዎች ህይወት ላይ
እናገራለሁ እንዲሁም እተነብያለሁ።

በአለም ላይ ላሉ ለችግረኞች በጸሎት ተጋድያለሁ። በጌታ ፊት እራሴን ዝቅ አድርጌ ጸልያለሁ፣ አልቅሻለሁ። አቤት፣ ለዓለም አገራት በጸሎት
እንዴት እንዳለቀስኩ! ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አንድም አገር በእኔ ላይ በሩን ሊዘጋ እንደማይችል አውቃለሁ። ዛሬ፣ ጌታ በእኛ በኩል በአለም አገራት
ውስጥ ብዙ ታላላቅ ስራዎችን እየሰራ ነው።

“ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ...እሰጥሃለሁ” ብሎ ሲናገር፣ እሱ ስለ ሰዎች ነፍሳት እየተናገረ ነው፣ በወንጌል እና በእግዚአብሔር ጽድቅ በእነርሱ
ላይ ተፅዕኖ ስለማድረግ ነው። ሐዋርያት ያደረጉት ያንን ነው፣ እኛም ዛሬ ማድረግ ያለብን ነገር ይህ ነው፣ ምንም ነገር ሊያግደን አይችልም።

ጳውሎስ በኤፌሶን ቃሉን ሲሰብክ፣ በእርግጥ ብዙ ተቃውሞዎች ነበሩ፣ ነገር ግን የወንጌልን ሥራ ማቆም ለወንጌል የሚፈለገውን ያህል እርቀት
አለመሄድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፣“እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር።”(የሐዋርያት ሥራ 19፥20):: የዚህ አይነት
ውጤት ቁልፉ በጸሎት መጋደል ነው። ለሀገራችሁ፣ ለከተማችሁ፣ ለትምህርት ቤታችሁ፣ ለስራ ቦታችሁ፣ ወዘተ በጸሎት ተጋደሉ፣ በእርግጥም፣
የእግዚአብሔር ቃል በዚያ በኃይል ያድጋል፣ ያሸንፋልም። ሃሌ ሉያ!

ጸሎት

ውድ አባት ሆይ፣ ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃንህ እንዲመጡ፣ ከልብ በመነጨ ጸሎት እንድማልድ እና ለጠፉት ወንጌልን እንድሰብክ ፍቅርህ ግድ
ይለኛል። ቃሉ በከተማዬና በአገሬ፣ በዓለምም ዙሪያ ያሸንፋል፣ የጌታም ስም ይከበራል። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት፦
ማቴዎስ 28፥19-20
ሮሜ 10፥14
2 ኛ ጢሞቴዎስ 4፥2 
13 ፓስተር ክሪስ
በመታዘዝ ውስጥ ያለው ትምህርት

በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ (ፊልጵስዮስ 2፡8)
በሉቃስ 3፡38 ላይ ስለ አዳም ስታጠኑ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ ተጠርቷል።ስለዚህ የመጀመሪያው አዳም የእግዚአብሔር ልጅ
ከሆነ እና ሁለተኛው አዳም ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፣በሁለቱ የእግዚአብሔር ልጆች መካከል ያለው ልዩነት
ምንድነው?
መልሱ ያለው በማቴዎስ ወንጌል 21፡28-31 ላይ ኢየሱስ በሰጠው በሁለቱ ልጆች ምሳሌ ውስጥ ነው።አባታቸው ወደ ወይን እርሻ
እንዲሄዱ ነገራቸው። የመጀመሪያው ልጅ ለአባቱ እንደሚሄድ አረጋግጦለት ነበር፤ ነገር ግን አልሄደም፤ አልታዘዘም። ሁለተኛው
ልጅ ለአባቱ እንደማይሄድ ነገረ፤ ነገር ግን ሄደ።ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ጠየቀ “ከሁለቱ ልጆች የትኛው አባቱን ታዘዘ?”

አስቀድሞ ለማድረግ እምቢ ቢልም፦በግልጽ፣ታዛዡ በትክክል የአባቱን ፈቃድ የፈጸመው ነው ።አሁን፣ በጌቴሰማኒ በአትክልት
እርሻ ውስጥ፣ ኢየሱስ ለመሰቀል ከመያዙ በፊት በመጨረሻዎቹ ጊዜያት ለአባቱ እንዲህ ብሎ ተግቶ ጸለየ፤ “ብትፈቅድ ይህችን
ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር” (ሉቃስ 22፡42)።
ኢየሱስ ያንን ለማድረግ አልሄደም ነበር ነገር ግን በምንም መንገድ ይሁን አደረገ! ስለዚህ የመክፈቻ ጥቅሳችን ስለ ኢየሱስ እንዲህ
ይላል፤ “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።”የኢየሱስ ከፍ
ማለት የመጣበት ምክንያቱ እስከ መስቀል ሞት ድረስ ስለታዘዘ ነበር። እንዲሁም የመጀመሪያው አዳም የመውደቁ ምክንያት
አለመታዘዙ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ “በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደሆኑ፥እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ
ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።”(ሮሜ 5፡19)።የመጀመሪያው አዳም ታዝዞ ቢሆን የሁለተኛው አዳም መታዘዝ አያስፈልግም ነበር።
ስለዚህ፣ በመጀመሪያው አዳም እና በሁለተኛው አዳም መካከል ያለው ልዩነት የመታዘዝ ነበር።

መታዘዝ በጣም አስፈላጊ ነው፤ እግዚአብሔርን መስማትና የእርሱን መንገዶች መከተል ነው። በዳግም በመወለድ የተወለድነው
በሁለተኛው አዳም በኢየሱስ ክርስቶስ ተፈጥሮ ነው፤ እናም የእርሱ የመታዘዝ መንፈስ አለን። ከዚያ ጀምሮ በ 1 ኛ ጴጥሮስ 1፡14
ላይ የእርሱ የሚታዘዙ ልጆች ተብለን ተጠርተናል። ስለዚህ በእናንተ ባለው በክርስቶስ ተፈጥሮ ተመላለሱ፤ ሁል ጊዜ አብን
አስደስቱ።
ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፣ ጥበብህን የተሸከሙ፣ መንፈሳዊ ትዕዛዛትን እንድቀበል እድሉን ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ። ነገሮችን በአንተ
መንገድ በማድረግ ልቤ መንፈሳዊ ትዕዛዛትን እንዲተገብር እና በህይወት ዋስትና ላለው ለውጥ ትክክለኛ መለኪያ ወደ ሆነው ወደ
ቃልህ ዕውቀት ጆሮዎቼን እንዳዘነብል መንፈስህ በዘላቂነት ይመራኛል።ለቃልህ መታዘዝን ሳሳይ በስኬት፣ በድል፣ በልህቀት እና
በክብር እመላለሳለሁ፣በኢየሱስ ስም።አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት

1 ኛ ሳሙኤል 15፡22
1 ኛ ጴጥሮስ 1፡13-14
ምሳሌ 8፡10
14 ፓስተር ክሪስ
መንፈሱ እና ቃሉ
ምድርም ባዶ ነበረች፥አንዳችም አልነበረባትም፤ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።
እግዚአብሔርም፦ብርሃን ይሁን አለ፤ብርሃንም ሆነ። (ዘፍጥረት 1፡2-3)
የመዝሙር መጽሐፍን ስታነቡ፣ ዳዊት የቃላትን ዋጋ ማወቁን እና የቃላትን ዋጋ ልጁን ሰለሞንን ማስተማሩን ትገነዘባላችሁ።
ምሳሌ 18፡21 ላይ “ሞትና ህይወት በምላስ እጅ ናቸው…” ያለው ሰለሞን ራሱ ነው።ያንን ያስተማረው አባቱ ዳዊት ነበር። ሞትና
ህይወት በሰይፍ ኃይል ላይ እንዳይደሉ፣ በምላስ እጅ እንዳሉ ዳዊት ያውቅ ነበር።የጌትን ሰው ጎልያድን ሲገናኘው ይሄንን
አሳየ።ጎልያድን እንዴት እንደረታው መረዳት አለባችሁ።
ጎልያድን በለስላሳ ድንጋይ እና ወንጭፍ መርታቱን መረዳት ቀላል ነው። ነገር ግን አይደለም፤ በቃሎች ነበር! በ 1 ኛ ሳሙኤል 17 ላይ
ሀሳቡን አጥኑት። እምነቱን በቃሎች ላይ ስላደረገ፣ ጎልያድን ስለ ማሸነፉ እርግጠኛ ነበር። በእግዚአብሔር ጥበብ እንደተመራ
መሳሪያዎችን ተጠቀመ። ድንጋዩንና ወንጭፍ ያዘ፤ እንዲሁም ከአፉ የሚወጡ ቃሎች ነበሩ። ጎልያድን በድንጋይ እንዳልጣለ
ያውቅ ነበር፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በእሱ ላይ ነበር፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ቃላትን ይጠቀማል።

ቃላት የመንፈስ ሃይልን ይለቃሉ። ያለ ቃሎች መንፈስ ምንም አያሰራም። የመክፈቻ ጥቅሳችንን በድጋሚ አንብቡ። መንፈሱ
በዓለም ሁሉ ላይ ነበር፤ ነገር ግን ምንም አልተቀየረም። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ “እግዚአብሔርም አለ፤”በቅጽበት
መንፈስ ሰራ፤ እግዚአብሔርም ያለው ሁሉ ሆነ! ሃሌ ሉያ!

በኢየሱስ ዳግም መምጫ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ የክርስቶስ ተቃዋሚውን ይረታዋል፤ “በአፉ መንፈስ የሚያጠፋው”
(2 ኛ ተሰሎንቄ 2፡8)ይሄም የሚያመላክተው የመንፈስን ሰይፍ፣ ያም የእግዚአብሔርን “ሬማ”- ከአፉ የሚወጣውን ቃል ነው
(ራዕይ 19፡15, ኤፌሶን 6፡17)።

ቃሉን ስትናገሩ፣ በእናንተ በኩል የእግዚአብሔርን ኃይል ወደ ስራ ትለቁታላችሁ። ስለዚህ በህይወት ቀውሶች ሲያጋጥሟችሁ፣
አትደንግጡ።ቃሉን ተናገሩ! ተናገሩና ለውጥን አድርጉ። ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ የምትናገሩት ነገር ሁሉ አላችሁ (ማርቆስ 11፡23)።
አስታውሱ፣ ቃላት ኃይለኛ ናቸው፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ከሁሉ በላይ ኃይለኛ ነው። ለዘላለም ክብር ለስሙ ይሁን!
የእምነት አዋጅ

ቃሎቼ ለእኔ ስኬትን፣ ድልን እና መሻሻልን ለመገንባትና ለማቀናጀት የመንፈስን ኃይል ይለቃሉ። የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናት
እና በማሰላሰል በውስጤ በሙላት ስኖር፣ በእኔ በኩል የእግዚአብሔርን ኃይል ወደ ተግባር እየለቀኩ፣የህይወት መንገዴን ትክክል
እያደረኩ በእምነት የተሞሉ ቃሎችን እናገራለሁ። ክብር ለጌታ ይሁን!

ለተጨማሪ ጥናት
ማርቆስ 11፡23
ማቴዎስ 12፡37
ኢያሱ 1፡8
15 ፓስተር ክሪስ
የአካሉ አንድነት

ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥የክርስቶስም ሙላቱ


ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥… (ኤፌሶን 4፡13)
ዛሬ በእግዚአብሔር ሰዎች መካከል በታሪክ ከየትኛውም ጊዜ የበለጠ ጠንካራ አንድነት አለ።ለምሳሌ ያህል፣ በዚህ አመት በአለም
አቀፍ የአገልጋዮች ትምህርት ክፍል ውስጥ በኦንላይን ከአለም ዙሪያ ሁሉ ከሰባ ሚሊዮን በላይ አገልጋዮች ተሳታፊ ነበሩ፤ እናም
ይሄ በመንፈስ ቅዱስ ታላቅ በረከት ነበር።
በአለም አቀፍ የጸሎት ቀናችን ላይም በተመሳሳይ ከሁሉም ሀገራትና አካባቢ ከአለም ዙሪያ ብዙ ቢሊዮን የእግዚአብሔር ሰዎች፣
የክርስቶስን ፈቃድና አላማ በምድር ላይ ለማጽናት አብረን እየጸለይን ነበር። ሃሌ ሉያ!
ከእኛ ጀርባ በአንድነት የሚገነቡን ሁለት ኃይለኛ አቅሞች አሉ፤ አንደኛው የእግዚአብሔር ቃል፣ ልባችንን አንድ የሚያደርግ
የእግዚአብሔር የቃሉ ኃይል። ሁለተኛው አቅም ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ነው። እነዚህ ሁለቱ ዛሬ በአለም ዙሪያ ሁሉ
በአንድነት እንድንቆም አጠንክረውናል።
በእርግጥ ብዙዎቻችን የተለያየ የአገልግሎት አመጣጥ መነሻዎችና የተለየዩ ስልጠናዎች እንዳሉን አውቃለሁ። ነገር ግን
በማንኛውም ጊዜ ካለን ልዩነት ይበልጥ በዚህ ላይ የምንስማማባቸው ዋና ዋና ነገሮች አሉ።
‹‹በማንኛውም ጊዜ›› አልኩት፤ምክንያቱም በቂ ጊዜ ሲሰጠን ብዙዎቻችን በዚሁ ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን፤በተለይም አንድ
አይነት መረጃ ሲኖረን። እናም ጌታ ማየት የሚፈልገው ነገር ይሄ ነው።

ኤፌሶን 4፡11-12 እንዲህ ይላል፤”እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ሌሎቹም ነቢያት፥ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ሌሎቹም


እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤…ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ
ዘንድ።”ቤተ ክርስቲያንን የሚያስታጠቅበት አላማው ምንድነው? የሚቀጥለው ቁጥር ያሳየናል፤ “ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ
በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ
ድረስ፥” ይሄ የክርስቶስን አካል ወደ አንድነት ያመጣል። አሜን።
መጽሐፍ ቅዱስ የሚያሳየን፣ የእኛ አንድነት እግዚአብሔር ኢየሱስን እንደላከ ለአለም ማሳያ ምልክት መሆኑን ነው (ዮሐንስ 17፡
21)።በዚህ በመጨረሻው ቤተ ክርስቲያን ጊዜ፣ይህ ዓለም ከዚህ በፊት ከሚያውቀው በላይ፣ የእግዚአብሔር ሰዎች ለጌታ አስገራሚ
ተፅእኖ ለማድረግ በአንድነት ሊሰበሰቡ ነው። ጌታ ይባረክ!
ጸሎት

ውድ አባት ሆይ፣ በአለም ዙሪያ ላለው የክርስቶስ አካል እድገት፣ ለውጥ፣ አንድነት እና መሻሻል እጸልያለሁ። ውኃ ባሕርን
እንደሚሸፍን፣ ምድር ሁሉ በቃልህ ዕውቀት እንዲሸፈን በአንድነት እየተጋን፣ የአንተን አንድ የማድረግ ራዕይ አላማውን
እየፈጸምን፣በአንድ መንፈስ በመቆም፣ በአንድ አእምሮ ለወንጌልም እምነት ተባብረን እንተጋለን፣በኢየሱስ ስም። አሜን።
ለተጨማሪ ጥናት
1 ኛ ቆሮንቶስ 1፡10
1 ኛ ቆሮንቶስ 12፡12
ዮሐንስ 17፡21
ዮሐንስ 13፡34-35

16 ፓስተር ክሪስ
ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉም ፈራጅ ነው
…ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው…(ሐዋርያት ስራ 17፡31
ከላይ ያለው ጥቅስ ኢየሱስ አለምን በጽድቅ እንደሚፈርድ ይናገራል።ፈራጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።አብ ማንም ሰው
ላይ አይፈርድም።ፍርድን ሁሉ ለኢየሱስ ሰጠው።“ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም።”
(ዮሐንስ 5፡22)።
እንዲሁም በሐዋርያት ስራ 10፡42 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም) ላይ ኢየሱስ በሰዎች ሁሉ ላይ ለመፍረድ በእግዚአብሔር
የተሾመ እንደሆነ እንመለከታለን፡ “ለሕዝቡ እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታንም ላይ እንዲፈርድ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ
መሆኑን እንድንመሰክር እርሱ ራሱ አዘዘን…”
በ 2 ኛ ጢሞቴዎስ 4፡1 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)ላይ ተመሳሳይ ሃሳብ በሐዋርያው ጳውሎስ በኩል በመንፈስ ቅዱስ
ተላልፏል፡፡ “በእግዚአብሔር ፊት እንዲሁም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ባለው በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት፣ መገለጡንና
መንግሥቱን በማሰብ ይህን ዐደራ እልሃለሁ”
የክርስቶስ የፍርድ ወንበር በ 2 ኛ ቆሮንቶስ 5፡10 ላይ ተገልጧል፡ “መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ
በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና።” የክርስቶስ የፍርድ
ወንበር የእግዚአብሔር ህዝብ የሆኑት የክርስቲያኖች ፍርድ ነው።በዚያም እኛ እያንዳንዳችን ከጌታ ዘንድ ብድራትን
የምንቀበልበት ነው። ሁሉም ይመሰገናል (1 ቆሮንቶስ 4፡5)።
ኢየሱስ ወደ ምድር በሚመለስበት ጊዜ በሃገራት ሁሉ ላይ ይፈርዳል።“የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም
ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች
እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል” (ማቴዎስ 25፡31-32)።
በመቀጠል ደግሞ በዮሐንስ ራዕይ 20 ላይ ኢየሱስ ለኃጢአተኞች የተጠበቀውን ከሀሉም ፍርዶች እጅግ የሚያስፈራውን
ፍርድ ሲፈፅም እናገኛለን።የታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ ተብሎ ይጠራል፡ “ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፥
ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ ስፍራም አልተገኘላቸውም።” (ራዕይ 20፡11)።
እነዚህ ፍርዶች ሩቅ አይደሉም። ስለዚህ ጌታን በእውነት አገልግሉት፤ በቅርብ ጊዜ የሚሆነውን የእርሱን መመለስ
እየጠበቃችሁ በእያንዳንዱ ቀን ለእርሱ ኑሩለት።
ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፤ የከበረውን የጌታዬንና አዳኜን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ እየተጠባበኩኝ በመንግስትህ ውስጥ ስላለኝ
የአገልግሎት እድልና በአለሜ ላይ በደህንነት ወንጌል ተፅዕኖ ለመፍጠር ስለሰጠኸኝ መብት አመሰግንሃለሁ። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት

1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡58


የዮሐንስ ራዕይ 22፡12
የዮሐንስ ራዕይ 20፡11-12
17 ፓስተር ክሪስ
በእርሱ ሁሉም ነገር አላችሁ

ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥
ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው (ቆላስይስ 1፡27)
የክርስትና መሰረት፣ ኢየሱስ ሊያደርገው የመጣው ሁሉ ደስታና ክብሩ ክርስቶስ እናንተ ውስጥ መሆኑ ነው። ክርስቶስ
በእናንተ ውስጥ መሆኑ ሁሉም ነገር ነው። ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ማለት ሰማይ በእናንተ ውስጥ ማለት ነው፤ መለኮት በእናንተ
ውስጥ ማለት ነው። አሁን ክርስቶስ ስላላችሁ ሁሉም ነገር አላችሁ። ከዚህ የተነሳ ጳውሎስ እንዲህ ማለቱ ተገቢ ነው፡
“ስለዚህም ማንም በሰው አይመካ። ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና” (1 ቆሮንቶሰ 3፡21)። ሃሌሉያ!
ልናሰላስለው የሚገባ አስፈላጊ ነገር አለ፣ ሮሜ 6፡23 እንዲህ ይላል “…የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ
ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” ይሄ የወንጌል መሰረታዊ እውነት ነው። ነገር ግን በወንጌል መረዳታችሁ
እየጨመራችሁ ስትመጡ ኢየሱስ ከውጪ ቆሞ የዘላለምን ህይወት እንዳልሰጣችሁ ታውቃላችሁ። የዘላለም ህይወት እሱ ራሱ
ነው። የዘላለም ህይወት ሲሰጣችሁ በእርግጥ ራሱን ነው የሰጣችሁ። ሃሌ ሉያ።
ከዚህ እውነታ ጋር በተስማማችሁ ቅፅበት አስተሳሰባችሁንና የጸሎት ህይወታችሁን ይለውጣል። ነገሮችን
ከእግዚአብሔር መጠየቅ ታቆማላችሁ። ክርስቶስ ካላችሁና ይህም እውነት ከሆነ (ደግሞም እውነት ነው እግዚአብሔር
ይመስገን)፤ ምን ሊያስፈልጋችሁ ይችላል? ክርስቶስ ሁሉም ነው። ሁሉም ነገር በክርስቶስ ነው።
በክርስቶስ ያገኛችሁትን ነገር እግዚአብሔርን መጠየቅ አቁሙ። ለምሳሌ እግዚአብሔርን ፈውስ አትጠይቁት፤
መለኮታዊ ጤንነትን ውሰዱ፤ ምክንያቱም ይህ በክርስቶስ ያላችሁ ተፈጥሮ ነው።በድል የተሞላው ህይወት በክርስቶስ የእናንተ
ነው። ክብርና ጽድቅ ለሞላበት አስደናቂ ህይወት የሚያስፈልጋችሁ ሁሉ በክርስቶስ የእናንተ ነው (2 ጴጥሮስ 1፡3)።
አሁን ኢየሱስ በሉቃስ 12፡22 ላይ ለምን እንደዚህ እንዳለ መረዳት ትችላላችሁ፡ “ለነፍሳችሁ በምትበሉት ወይም
ለሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ።” እሱ አቅርቦታችሁ ነው፤ በእርሱ ሁሉም ነገሮች አሏችሁ። ሃሌ ሉያ!
ጸሎት
የተባረክ አባት ሆይ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ሁሉንም ነገሮች ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። ክርስቶስ ሁሉ ነገሬ ነው፤ በክርስቶስ
ለህይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚያስፈልገኝ ሁሉ አለኝ፤ በአሸናፊነት ለመኖርና በነገር ሁሉ አንተን ለማስደሰት
የሚያስፈልገኝ ሁሉ አለኝ። ሃሌ ሉያ!

ለተጨማሪ ጥናት
2 ኛ የጴጥሮስ መልዕክት 1፡3
1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡21-22
18 ፓስተር ክሪስ
የመጨረሻዎቹ ቀናት
በቅድሚያ በመጨረሻዎቹ ቀናት የሚያስቡትን እያንዳንዱን ስህተት የሆነ ነገር የሚያደርጉና እውነት ላይ የሚስቁ ዘባቾች
እንደሚመጡ ላስታውሳችሁ እፈልጋለሁ። የሚያቀርቡት የመከራከሪያ ነጥብ ይሄ ይሆናል፡ “ኢየሱስ ተመልሶ ለመምጣት ቃል
ገብቷል። አይደል? ታዲያ የት አለ? በጭራሽ አይመጣም…”(2 ኛ ጴጥሮስ 3፡3-4 የህያው ቃል ትርጉም )
“የመጨረሻዎቹ ቀናት” የሚለውን አባባል በሚሰሙ ጊዜ ጥቂት ሰዎች ሲዘብቱ መስማት ያልተለመደ ነገር
አይደለም።እርግጠኝነቱን ይጠራጠራሉ። ምክንያቱም እጅግ ለረዘመ ጊዜ ስለ ጉዳዩ እንደሰሙ ያስባሉ።ስለ መጨረሻዎቹ ቀናት
መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ለመረዳት በመጀመሪያ ደረጃ አባባሉ በትንቢት ለብዙ አገላለጽ ጥቅም ላይ እንደዋለ ማወቅ
ያስፈልጋችኋል።በሁለተኛ ደረጃ ነቢዩ ወይም ፀሃፊው አባባሉን ተጠቅሞ ለማን እንደፃፈ ማወቅ ያስፈልጋችኋል።
ለምሳሌ ለአይሁዳውያን በሚነገርበት ጊዜ፤ የሐዋርያው ጴጥሮስ “የመጨረሻዎቹ ቀናት” የሚለው አባባል አጠቃቀም
እጅግ ትክክል ነበር። ምክንያቱም እያብራራ የነበረው የእስራኤልን የመጨረሻዎቹን ቀናት እንጂ የቤተ ክርስቲያንን
የመጨረሻዎቹን ቀናት አልነበረም። እነሱ በራሳቸው መጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ ነበሩ። ነገር ግን ምን ያህል እንደቀረቡ አላወቁም
ነበር። የሆነ ሰው እንዲህ ብሎ ሊጠይቅ ይችላል “ነገር ግን ጴጥሮስ እነዚህን ነገሮች የተናገረው ከሁለት ሺህ አመታት በፊት ነው።
ታዲያ ምን ያህል ቀርበው ነበር?”
የጊዜ ሰሌዳቸው መጨረሻ እጅግ ቀርቦ መጥቶ ነበር።የዳንኤል ትንቢታዊ ፅሁፍ የ 70 ሱባኤ አመታት ለእስራኤል እንደ
ተቀጠረ ይናገራል።በአመቱ ፍፃሜም የመሲሁ የሺህ አመት ግዛት መመስረት ይሆናል። በ 69 ኛው ሱባኤ እስከ ሆነው የመሲሁ
መገደል ድረስ እግዚአብሔር ይሄን ሰሌዳ ያስፈጽም ነበር።
በ 69 ኛውና በ 70 ኛው ሱባኤ የቤተ ክርስቲያን ዘመን መጣ። ስለዚህ ጴጥሮስ በዚያን ጊዜ ለእስራኤል ልጆች
በመጨረሻዎቹ ቀናት መሆናቸውን መንገሩ ትክክል ነበር። ምክንያቱም የነበሩት በ 69 ኛው ሱባኤ ውስጥ ነበር።
ዛሬ እስራኤል በመጨረሻዎቹ ቀናት መሆኗ ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያን ዘመንም እየተገባደደ ነው።የዘመናቱ ውጊያ
ብርቱ ክፍል ተብሎ በሚወሰደው ወቅት ላይ እንገኛለን። ነገር ግን ለነዚህ ጊዜዎች ሰልጥነናል ታጥቀናል።በየሀገራቱ ያሉ ወንዶችና
ሴቶችን በቅርቡ ለሚሆነው ለጌታችን መመለስ እያዘጋጀናቸው በጨለማ ኃይላትም ላይ ታላቅ ጥቃት እያደረሰን እንገኛለን።
በዚህ ታላቅ ስራ ላይ ተካፋይ መሆናችሁን አረጋግጡ፤ ነፍሳትን ለክርስቶስ ማርኩ። ሉቃስ 12፡39-46፡ “ይህን ግን እወቁ ባለቤት
በምን ሰዓት ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ፥ ቤቱም እንዲቆፈር ባልፈቀደም ነበር። እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥
የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና። ጴጥሮስም። ጌታ ሆይ፥ ይህን ምሳሌ ለእኛ ወይስ ደግሞ ለሁሉ ትናገራለህን?
አለው። ጌታም አለ። እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ልባም
መጋቢ ማን ነው? ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው። እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ
ይሾመዋል። ያ ባሪያ ግን። ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ ሎሌዎችንና ገረዶችንም ይመታ ይበላም ይጠጣም
ይሰክርም ዘንድ ቢጀምር፥ የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፥ ከሁለትም ይሰነጥቀዋል እድሉንም
ከማይታመኑ ጋር ያደርጋል።”
ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፤ በነዚህ የመጨረሻዎቹ ቀናት ወንጌልን ወደ አለሜ ለማድረስ እኔን የከበረ እቃ አድርገህ ስለመረጥከኝ
አመሰግንሃለሁ። ሰዎችን ከእስራት ነፃ አውጥቼ የእግዚአብሔር ልጆች ወደሆነው የከበረ ነፃነት እንዳመጣቸው
ቀብተኸኛል።መንግስትህንና ጽድቅህን በሰዎች ልብ ውስጥ ስመሰርት ውድ የሆነው የአንተ መንፈስ ታላላቅ ነገሮችን እንዳሳካ
ይመራኛል፣በኢየሱስ ስም። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት

1 ኛ የዮሐንስ መልዕክት 2፡18


ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡15-16
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡5
19 ፓስተር ክሪስ
የአንድ ጊዜ መስዋዕት

ነገር ግን ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ፥ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች
ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን፥ የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ
በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም(ዕብራውያን 9፡11-12)
በብሉይ ኪዳን፤ መጽሀፍ ቅዱስ የመጀመሪያውን ድንኳን እንዲህ ብሎ ይገልፀዋል“ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ነው፥
እንደዚህም መባና መስዋዕት ይቀርባሉ… የሚያመልከውን በህሊና ፍጹም ሊያደርጉት አይችሉም…” (ዕብራውያን 9፡9)።የብሉይ
ኪዳን ካህናት ለእግዚአብሔር የተለያዩ መባና መስዕዋትን ያቀርባሉ። ለምሳሌ “ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ
መታጠብም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዓቶች…” (ዕብራውያን 9፡10)።
ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ የእርሱ መስዋዕት የራሱ ደም ነበር፤ ራሱን መስዋዕት አድርጎ አቀረበ። ነገር ግን
የብሉይ ኪዳን ካህናት በየአመቱ አመታዊ የኃጢአት ማስተስሪያ መስዋዕት ማቅረብ ነበረባቸው። ኢየሱስ አንድ ጊዜ ፈፅሞ ለሰው
ልጆች የዘላለም መቤዠትን አግኝቷል።የቀድሞው የእንስሳት ደም ለእግዚአብሔር ምርጡ አልነበረም፤ እርሱም የሚፈልገው
አልነበረም። ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- “እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ
መጥቼአለሁ” (ዕብራውያን 10፡7)።
መጽሐፍ ቅዱስ የብሉይ ኪዳን ካህናት እንዲህ እንደሆኑ ይናገራል፡ “ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን
ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፤ እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት
ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ” (ዕብራውያን 10፡11-12)።
ሐዋርያ ጳውሎስ በአንፆኪያ ላልዳኑት አይሁዶች በሚያገለግልበት ጊዜ እጅግ አስደናቂ እውነትን ገልጦ እንዲህ መናገሩ
ተገቢ ነው “…በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ
በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን” (ሐዋርያት ስራ 13፡38-39)።እግዚአብሔር ይባረክ።
ይሄን በስፍራ ሁሉ እና ለሁሉም ሰው ተናገሩ፤ ክርስቶስ ኢየሱስ የሰዎችን የዘላለም መቤዠት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ
ፈፅሟል። ሃሌ ሉያ!
የእምነት አዋጅ
ጌታ ሆይ አንተ ክቡርና ጻድቅ ነህ፤ ምክንያቱም ኃጢአታችንን ተሸክመሃል፤ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜም በደምህ አጥበህ
አስወግደሃቸዋል። ሰው መክፈል ሳይችል የገባበትን ለኃጢአት የሚከፈለውን ዕዳ የመጨረሻ ዋጋ ከፍለሃል።አሁን ታጥበናል፣
ተቀድሰናል እንዲሁም ጸድቀናል፤ ከኃጢአት፣ ከሞትና ከጥፋት ነፃ ነን። ሃሌ ሉያ!

ለተጨማሪ ጥናት
ወደ ዕብራውያን ሰዎች 9፡11-14
የዮሐንስ ወንጌል 3፡16
20 ፓስተር ክሪስ
እኛ የማስታረቅ አገልጋዮች ነን
ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ከእግዚአብሔር ነው (2 ኛ ቆሮንቶስ 5፡18)

በአዲስ ኪዳን፣ “አገልጋይ” የሚለው ቃል በግልባጭ ጥቅም ላይ እንደዋለ ትመለከታላችሁ።ሆኖም የተተረጎመባቸው ሦስት የግሪክ ቃላት እንዳሉ
ልብ ማለት ያስፈልጋል።የመጀመሪያው "ዱሎስ" ነው፤እሱም እንደ አገልጋይ ወይም ባሪያ ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ጳውሎስ ራሱን “ዱሎስ” (ባሪያ)
ብሎ ይጠራዋል—የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ወይም አገልጋይ(ሮሜ 1:1)።
ከዚህም ሌላ “አገልጋይ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል “ሁፐረተስ” ሲሆን እሱም የአገልግሎት ቢሮን የሚያመለክት ሲሆን ይህም
የሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ደማስቆ ሲሄድ በነበረው የንግግር ታሪክ እንደምናገኘው ነው።በዚያ ንግግር ወቅት፣ኢየሱስ ለጳውሎስ እንዲህ አለው፡-
“...ስለዚህ እኔን ባየህበት ነገር ለአንተም በምታይበት ነገር አገልጋይና ምስክር ትሆን ዘንድ ልሾምህ ታይቼልሃለሁና…” (የሐዋርያት ሥራ 26፡15)።

ኢየሱስ ለጳውሎስ ተገለጠለት እና ወደ አገልግሎት ቢሮ ጠራው።በ 1 ኛ ቆሮንቶስ 4፡1 ላይ “እንዲሁ ሰው እኛን እንደ ክርስቶስ ሎሌዎችና
(ሁፐረተስ)እንደ እግዚአብሔር ምሥጢር መጋቢዎች ይቍጠረን።”
እንዲሁም “አገልጋይ” የሚለው ቃል ሦስተኛው ፍቺ እያንዳንዱ ክርስቲያን የተጠራበት ነው፡“ዲያኮኒያ” (ግሪክ) እሱም የሚያገለግልን ሰው
ያመለክታል፣አስተናጋጅ እንደሆነ ሰው ነው።እንዲያውም የዲያቆንን ቢሮ ይገልፃል።በሐዋርያት 6:4 ላይ የቃል አገልግሎትን ለመግለጥ
ተጠቅሟል፣“እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን።”
ሁላችንም የክርስቶስ አገልጋዮች የመሆን ኃላፊነት አለብን፣የመልእክቱ ና የእርስ በርሳችን አገልጋዮች።የክርስቶስ ምስክር የመሆን፣ወንጌልን
ለሌሎች ሰዎች የማድረስ ኃላፊነት አለባችሁ።

የመክፈቻ ጥቅሳችን እግዚአብሔር “የማስታረቅን አገልግሎት ሰጠን” ይላል።እግዚአብሔር ብቁ የማስታረቅ አገልጋይ አድርጎናል (2 ኛ ቆሮንቶስ
3፡6)።ስለዚህ፣ለጌታ ጨካኝ ሁኑ! አፋችሁን ክፈቱ እና እራሳችሁን ባገኛችሁበት ቦታ ሁሉ የማዳን ቃሉን በድፍረት አውጅ።እሱ በእናንተ
እየተማመነ ነው።
ጸሎት
አባት ሆይ፣ኃጢአተኛውን የሚያድነው እና ከጨለማ ወደ ከበረው የጽድቅ ህይወት የሚያመጣው ብቸኛው መልእክት ወንጌል ነውና
አመሰግናለሁ! የማስታረቅ አገልጋይ እንድሆን ታማኝ እና ብቁ አድርገህ ስለ ቆጠርከኝ አመሰግንሃለሁ።ለወንጌል የተነሣሣሁ ነኝ፣እናም
ኃጢአተኞችን ከጨለማ ግዛት ወደ አንተ የብርሃን መንግስት እያመጣሁ፣በአለሜ ላይ ላሉ ሰዎች ሁሉ በድፍረት እሰብከዋለሁ፣በኢየሱስ
ስም።አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት
2 ጢሞቴዎስ 4:1-2
1 ኛ ቆሮንቶስ 9፡16
2 ኛ ቆሮንቶስ 3፡6
21 ፓስተር ክሪስ
የእግዚአብሔርን ቋንቋ ተናገሩ
መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ
በሚያስተምረን ቃል አይደለም (1 ኛ ቆሮንቶስ 2፡13)

በገላትያ 4፡1-2 መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፣ “ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ
አይለይም፥ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው።”ወራሽ ማለት በውርስ የተረከበው ርስት
ያለው፣ህጋዊ የቦታ ወይም የከፍተኛ ሥልጣንና ሀብት ወራሽ የሆነ ነው።
ይሁን እንጂ ወራሹ ልጅ እስከሆነ ድረስ ከአገልጋይ አይለይም።"ልጅ" ተብሎ የተተረጎመው ቃል "ኔፒዮስ" ነው፣በትክክል መናገር ወይም
በጥበብ መነጋገር የማይችል።አንድ ሰው በክርስትና ውስጥ አርባ አመት ሊሆን ይችላል ሆኖም አሁንም "ኔፒዮስ" ሊሆን ይችላል፤ በመንፈስ ግዛት
ውስጥ ትክክለኛ ቃላትን መናገር አይችልም።
አዎን፣ቃሉ እኛ የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፣እና ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን ይላል፣ነገር ግን “ኔፒዮስ” የወራሽን ሕይወት መኖር
አይችልም። 1 ኛ ቆሮንቶስ 3፡21 “…ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና” ይላል።ነገር ግን በመንፈሳዊነት ስላላደጉ በህይወት እየተሰቃዩ ነው።የእግዚአብሔርን
ቋንቋ ፈጽሞ ስላልተማሩ የተሳሳቱ ቃላትን ይጠቀማሉ።

የእግዚአብሔርን ቋንቋ የመማር እና የመናገር መንገድ ቃሉን ማጥናት እና ማሰላሰል ነው።የኛ መክፈቻ ጥቅስ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረንን
ቃል እንናገራለን ይላል- ከመንፈስ እና በመንፈስ የተገኘ የጥበብ ቃል።ስለዚህ፣ሁኔታው ምንም ይሁን ምን እራሳችሁን በእግዚአብሔር ቃል
አሰልጥኑ እና ቃሉ በልባችሁ እና በከንፈሮቻችሁ ይኑሩ።
የእምነት አዋጅ

የእግዚአብሔርን ጥበብ በተጨባጭ ቋንቋ እናገራለሁ።በክርስቶስ ኢየሱስ፣በሁኔታዎች ላይ ስልጣን ተሰጥቶኛል፣እናም ከሰይጣን እና ከጨለማ
ኃይሎች እበልጣለሁ።እግዚአብሔር በክርስቶስ የሰጠኝ ሕይወት የታላቅ ክብር እና የልቀት ነው፣በቃሉ በነገር ሁሉ የምበለጽግበት ነው !
በጥበብ፣በክብር እና በጥንካሬ ተሞልቻለሁ።ሃሌ ሉያ!

ለተጨማሪ ጥናት
1 ኛ ቆሮንቶስ 2፡7
1 ኛ ቆሮንቶስ 2፡12-13
ዕብራውያን 13፡5-6
22 ፓስተር ክሪስ
እሱ ፊተኛውና መጨረሻው ነው

ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል (ራዕይ 1፡8)

በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ ስለ ኢየሱስ ስታጠኑ ወደ አንድ የማያሻማ መደምደሚያ ትደርሳላችሁ፡እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ነው! እርሱ
ፊተኛውና መጨረሻው፣የነበረውና የሚመጣውም ነው።በዘመናት የሸመገለው ተብሎ በዳንኤል የተገለጸው እርሱ ነው።
ሐዋርያው ዮሐንስ፣በፍጥሞ ደሴት በግዞት ሳለ፣ከጌታ መገለጦችን ተቀበለ።እንዲህ አለ፡- “በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥በኋላዬም የመለከትን
ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፥እንዲሁም፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ፣ፊተኛውና መጨረሻው…” (ራዕይ 1፡10-11)።ያ ኢየሱስ ነው!
ጌታም በተጨማሪ በቁጥር 17-18 ላይ እንዲ አለው“...አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም
እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ …” (ራዕይ 1፡17-18)።ለዚህ መግለጫ የሚስማማው ኢየሱስ ብቻ ነው።እርሱ የሞተው ግን ከዘላለም እስከ
ዘላለም ሕያው ነው።ሃሌ ሉያ!
አሁን፣እሱ ፊተኛውና መጨረሻው ከሆነ፣ይህ ማለት በስኬት ጉዞዋችሁ ውስጥ ምንም የሚያስፈራችሁ ወይም የሚያስጨንቃችሁ ነገር የለም።እሱ
ከእናንተ ጋር ነው፣እና በእናንተ ውስጥ ነው።ስትጀምሩ እሱ እዚያ አለ።በመንገዳችሁ ላይ እሱ እዚያ አለ።መጨረሻ ላይም እሱ እዚያ አለ።ሙሉ
በሙሉ ሸፍኗችኋል።እሱ በእያንዳንዱ የጉዞአችሁ ደረጃ ከእናንተ ጋር ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ በዕብራውያን 12፡2 ላይ “…የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን…” ያለው ምንም አያስገርምም።ያም ማለት
ስለ ወደፊቱ መጨነቅ አያስፈልጋችሁም፣ገና ከመጀመሪያው፣እርሱ ፍጻሜውን አስቀድሞ ያውቃል፣እናም “አትፍራ” ይላል።

ስለዚህ እናንተ በክርስቶስ እንደሆናችሁ እና እርሱ በእናንተ እንዳለ እና የሚመለከታችሁን ሁሉ ፍፁም ማድረጉን በማወቅ ሁል ጊዜ ደፋር እና
የምትተማመኑ ሁኑ።እሱ የሁሉም ነገር ደራሲ (ፊተኛው) እና ፈጻሚው(መጨረሻው) ነው።እግዚአብሔር ይባረክ!
ጸሎት
ውድ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣የከበርህ ነህ፣ታላቅና ኃያል ነህ፤ ጻድቅ ነህ፣ቅዱስ፣ንጹሕ እና እውነተኛ ነህ።አንተ አልፋና ኦሜጋ ነህ፤የሁሉም ነገር ደራሲ
እና ፈጻሚው! ፍፁም ፈቃድህን ለመፈጸም ሁል ጊዜም በእኔ ውስጥ እና ከእኔ ጋር እንዳለህ፣በህይወት መንገድ እንደምትመራኝ በማወቅ፣ሁሌም
ደስ ይለኛል።አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት
ቆላስይስ 1፡16-17
1 ኛ ጢሞቴዎስ 6፡14-16
ቆላስይስ 2፡9-10
23 ፓስተር ክሪስ
የኛ ዘላለማዊ ጠበቃ

ልጆቼ ሆይ፥ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ።ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ
ክርስቶስ ነው (1 ኛ ዮሐንስ 2፡1)
አብ ለእኛ ያለው የፍቅሩ ታላቅነት በእርግጥም ከሰው መረዳት በላይ ነው።ቤተ ክርስቲያን ለእኛ ያለውን የአብ ጥልቅ፣ታላቅ እና ቅድመ ሁኔታ
የለሽ ፍቅር ወደ መረዳት እንድትመጣ መንፈስ በጳውሎስ በኩል መጸለይ ነበረበት (ኤፌሶን 3፡18-19)።ኢየሱስን ስለ እኛ እንዲሞት ላከው፤
እርሱን ከሙታን አስነስቶ የዘላለም ጠበቃ አድርጎ ሾመው።ሃሌ ሉያ!
በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ “ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” ብሏል።በእኛ ቦታ
ከሞተው በቀር ማንም የእኛን ጉዳይ ለማስፈፀም ብቁ አይደለም፤እርሱ የኃጢአተኛው ምትክ ሆነ እናም ጽድቁን ሰጠን።ማንም በአብ ፊት
ሊፈርድብን አይችልም።በቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ሰዎች ከሳሽ ተብሎ የተገለፀው ሰይጣን፣ሲከሰን እና ለእግዚአብሔር በረከቶች
የማይገባን ሊያደርገን ሲሞክር፤ጠበቃችን የሆነው ጌታ ኢየሱስ ሊከላከልልን ይቆማል።ለእኛ ጉዳይ ጥብቅና ይቆማል።መጽሐፍ ቅዱስ ለወደደን
ከኃጢአታችንም በደሙ ያጠበን ይላል (ራዕይ 1፡5-6)።
ደሙ ስለ እኛ ያለ ማቋረጥ ይናገራል ከዓመፅም ሁሉ ከኃጢአትም እድፍ ሁሉ ያነጻችኋል (1 ኛ ዮሐንስ 1፡7-9)።ኢየሱስ እኛን በእግዚአብሔር
ፊት ቅዱሳን፣ ነውር እና ነቀፋ የሌለን አድርጎ ያቀርበን ዘንድ (ቆላስይስ 1፡22)።በሰማይ፣ኢየሱስ ከአብ ቁጣ ሊከላከልላችሁ እየሞከረ
አይደለም፣አብ ራሱ ይወዳችኋልና (ዮሐንስ 16፡27)።አብ ኢየሱስን ለእናንተ ጠበቃ አድርጎ ሾሞታል - የሚከላከልላችሁ ጠበቃ።እሱ ከጎናችን ሆኖ
ለመሸነፍ ወይም ለመጎዳት የማይቻል ነው፡፡ ሃሌ ሉያ!
ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፣ከኃጢአት፣ከጥፋተኝነትና ከኩነኔ ነፃ የሆነ የክብር ሕይወት የምኖርበት ስለ ጸጋህ፣ምሕረትህና ፍቅርህ አመሰግንሃለሁ።ከዓመፃ
ሁሉ የሚያነጻኝ፣በአንተ ፊት ነቀፌታ የሌለኝና ቅዱስ ስለሚያደርገኝ የኢየሱስ ደም አመሰግናለው፣በኢየሱስ ስም።አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት
1 ኛ ጢሞቴዎስ 2፡5-6
ዕብራውያን 12:24
24 ፓስተር ክሪስ
መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉንም ያብራራል
ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደተዘጋጁ፥ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እንረዳለን (ዕብራውያን 11፡3)
ከላይ ያለው መልእክት በጣም ኃይለኛ ነው፡፡ የዚህ ዓለም የሚታየው ነገር ከማይታዩ ነገሮች እንደ ተፈጠሩ እንድናውቅ ያደርገናል።ዘመናዊው
ፊዚክስ የተመሰረተበትን ዋና መሰረታዊ መርሆ ወደ አእምሮአችን ያመጣል፡፤የቅንጣተ-ሞገድ ሁለትነት።የሰብ አቶሚክ ቅንጣቶች (እነሱ
ቅንጣቶች፣ኤሌክትሮኖች ወይም ፕሮቶን ተብለው መጠራት ካለባቸው) በቤተ-ሙከራዎቻቸው ከተገኘው አስደናቂ ውጤት የተነሳ ሞገዶች
ወይም ቅንጣቶች መሆናቸውን ግራ መጋባት አለ።
በኤሌክትሮን ሙከራቸው ሰዎቹ በማይመለከቱበት ጊዜ የሞገድነት ባህሪያት እንዳሉት አወቁ።በሌላ አነጋገር ተመልካቹ ወይም ሙከራውን
የሚያካሂደው ሰው ኤሌክትሮኑን የማይመለከት ከሆነ ሞገዶችን ያመጣል።በዚህም ኤሌክትሮን ሞገድ ነው ብለው ደምድመዋል።ነገር ግን፣ዞር
ብለው ለማየት በሄዱበት ቅጽበት፣እየተመለከቱት እንደሆነ የሚያውቅ ይመስላል፣እናም ከመታየቱ በፊት፣ቅንጣት ሆነ።
እንዴት እንዲህ አይነት ንድፎችን እና የሞገድ ባህርያትን ሊይዝ ይችላል? እንዴት ይህን ያህል አስተዋይ ሊሆን ይችላል? አሁን እዚህ ላይ አንድ
በጣም አስደሳች ነገር አለ፡፡ይህ ነገር ሞገድ ከሆነ ኢነርጅ አለዉ፣ እና ኢነርጅ ደግሞ ቁስ አካል አይደለም፤ ቅንጣት ከሆነ ደግሞ፣ ሞገድ
አይደለም ማለት ነው፡፡ ከሁለቱ አንዱን ነው፣ ግን በሚገርም ሁኔታ ሁለቱም ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ይህ ሳይንቲስቶች ካካሄዷቸው በጣም አስደናቂ ሙከራዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እናም ለብዙ አመታት ምንም ማብራሪያ አላገኙም፡፡ ግን
ማብራሪያው ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው።በጣም ቀላል ነው።እስኪ አስቡት በማትመለከቱበት ጊዜ ኢነርጅ ነው፤ ለማየት ዘወር ስትሉ
ቅንጣት ነው!
መጽሐፍ ቅዱስስ ምን ይላል? “እንግዲህ እምነት በተስፋ ውስጥ ያለው ነገር ማስረገጫ ነው” ይላል።በሥጋዊ ዓይኖቻችሁ ባትመለከቱም፣ነገሩ
በመንፈሳችሁ ውስጥ እውነተኛ ነው፤ንጥረ ነገር ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔር ቃል አለ! እምነት የተስፋ “ቁስ” ስለሆነ ኢነርጂ አለው ማለት
ነው፤በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሰረተ ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ድምጽ ነው፤ እግዚአብሔር ሲናገር ፍጥረት ሆነ።ኢነርጅ ያለው በድምጽ ሞገድ ውስጥ ነው ፡፡ ስለዚህ ሳይንቲስቶች እነዚህን
ነገሮች ለመረዳት ከፈለጉ፣ ከኒው ኤጅ አስተሳሰብ ወጥተው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መድረስ አለባቸው፡፡ መጽሐፉ ሁሉንም ያብራራል።ሃሌ ሉያ።
ጸሎት
ውድ የሰማይ አባት ሆይ፣ፍጥረትን ወደ መሆን እንደተናገርክ፣የአንተን ፍፁም ፈቃድ፣እቅድ እና አላማ በዝርዝር በሚገልጽ ቃልህ የህይወቴን
ጎዳና እቀርጻለሁ።አሁን እንኳን ብልጽግናን እፈጥራለሁ የከፍታ ቃላትንም በህይወቴ ውስጥ እለቅቃለሁ።በጠላት እና በህይወት ሁኔታዎች ላይ
በድል አድራጊነት እኖራለሁ፤ በከንፈሮቼ ያለው ቃል ከፍ ያደርገኛል፡፡ በሁኔታዎች ላይ በገዢነት እመላለሳለሁ፣በኢየሱስ ስም።አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት፡-
መዝሙረ ዳዊት 33፡6
ማርቆስ 11፡23
ዕብራውያን 11:3
25 ፓስተር ክሪስ
እምነት የማስረጃ እውቀት ነው

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው (ዕብራውያን 11፡1)


ከላይ ያለው የእምነት ትርጉም በቀላሉ እምነት የማስረጃ ዕውቀት ነው ማለት ነው።በሥጋዊው ዓለም የማይታይ ቢሆንም፣ተስፋ ያደረጉት ነገር
እውን እንደሆነ እርግጠኛ ነን:: እምነት ንጥረ ነገር ነው፣የማይታዩ እውነታዎች ማስረጃ ነው፡፡

ማስረጃ የአንድ ነገር ማረጋገጫ ነው፤ እንዲገኝ ማድረግ ይቻላል። ስለዚህ እምነት ማስረጃ ከሆነ የሚወክለው ነገር አለ ማለት ነው፡፡ የንብረት
ባለቤት ሲሆኑ ነው የዚያ ንብረት የባለቤትነት ደብተር የእናንተ ማስረጃ የሚሆነዉ::ንብረቱ የእናንተ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ
ነው።በንብረቱ ላይ ያላችሁ መብት ጥያቄ ውስጥ ሲገባ በቀላሉ የይዞታ ማረጋገጫ የሆነውን ማስረጃ ታቀርባላችሁ።
እንደዚሁም፣በማንኛውም ጊዜ ዲያብሎስ በክርስቶስ ውስጥ ያላችሁን በረከቶች፣መብቶች እና ርስት የማግኘት መብታችሁን ሊጠይቅ
ከሞከረ፣ማስረጃችሁን አቅርቡ፣እሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።ቃሉ ስለ እናንተ የሚናገረውን በልበ ሙሉነት ተናገሩ።
ለምሳሌ ሮሜ 8፡10-11 እና 3 ኛ ዮሐንስ 1፡2 ለመለኮታዊ ጤንነት ማስረጃችሁ አድርጋችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ሮሜ 8፡10-11 “ክርስቶስ በእናንተ
ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፣መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው።ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን
ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ ለሚሞተው
ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።” 3 ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:2 “ወዳጆች ሆይ፣ነፍስህ እንደሚከናወን በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና
እንዲኖርህ እመኛለሁ።”እነዚህን ቅዱሳት መጻህፍት በማስረጃነት በማቅረብ፣ማስረጃችሁን በስራ ላይ እያዋላችሁት ነው።ሃሌ ሉያ!

የእምነት አዋጅ
በእግዚአብሔር ቃል ሙሉ በሙሉ አምኛለሁ! ሕይወቴን በአምላክ ቃል ላይ እመሰርታለሁ፣እናም በተቃራኒ ነፋሶች ወይም ሁኔታዎች መመራትን
አልፈልግም፣ምክንያቱም እምነቴ ለማይታዩ እውነታዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃዬ ነው።በመለኮታዊ ጤንነትና ከተፈጥሮ በላይ በሆነ
ብልጽግና እየኖርኩ በክርስቶስ ባለው ርስቴ ብርሃን በኃይል እና በጸጋ እመላለሳለሁ።በቃሉ ውስጥ እና በቃሉ ስለምኖር ሁል ጊዜም አሸናፊ
ነኝ።አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት

ዕብራውያን 11፡6
ማቴዎስ 15፡28
26
ፓስተር ክሪስ
በሞት እና በሲኦል ላይ ግዛት

ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ (ራዕይ 1፡18)

የአዳምን አለመታዘዝ ተከትሎ፤መጽሐፍ ቅዱስ ሞት በሰው ልጅ ላይ ሁሉ ወረደ ይለናል፡፡ “ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ
ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤” (ሮሜ 5፡12)፡፡ሞት
ከኃጢአት ጋር የተያያዘ ነው፤ስለዚህ አዳም በዚያ በኤደን ገነት ውስጥ ሰይጣንን ታዞ ከፍተኛ የሆነ ክህደት ሲፈፅም፤ሞት
በሁሉም ሰው ላይ መስራት ጀመረ፡፡ሰይጣን ሰዎችን በህመም፣በበሽታ፣በጥፋት እና በስተመጨረሻም በሞት ሊያሰቃይ ይችል
ዘንድ ነፃነትን አገኘ፡፡

ነገር ግን ኢየሱስ ሲመጣ፤ነገሮች ተቀየሩ፡፡ዘመናቸውን ሁሉ በሞት ፍርሀት እስራት ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ
በሞት እና በመቃብር ላይ ድል በነሳበት እነርሱ ነፃነትን አገኙ፡፡ “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥እርሱ ደግሞ በሞት
ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ
የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።” (ዕብራውያን 2፡14-15)፡፡
ዛሬ ማንም ዳግም ቢወለድ ሞትን መፍራት አይኖርበትም፤ሞት በኢየሱስ ተሸንፏል፡፡መጽሐፍ ቅዱስ በ 1 ቆሮንቶስ 15፡54-57
“ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥በዚያን ጊዜ።ሞት ድል
በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።ሞት ሆይ፥መውጊያህ የት አለ ?ሲኦል ሆይ፥ድል መንሣትህ የት አለ? የሞት
መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው፤ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።” ማለቱ አያስደንቅም፡፡

በሞት እና በመቃብር ላይ ድልን ሰቶናል፡፡ዛሬ ሰይጣን የማንንም ህይወት በፈቃዱ መውሰድ አይችልም ምክንያቱም በሞት ላይ
ኃይል የለውም፡፡ክርስቶስ ህይወትን በሙላት እንድንኖር ሰጥቶናል፡፡ከፊቱ ጋር ደስታን አጠገበን፥ በቀኙም የዘላለም ፍሥሐ አለ።
“ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም (ሙሉ
እስኪሆንላችሁ) መጣሁ።”(ዮሐንስ 10፡10 አምፕሊፋይድ ክላሲክ ትርጉም)
የእምነት አዋጅ
ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ እናም እኖራለሁ ነገር ግን እኔ ሳልሆን ክርስቶስ በእኔ ውስጥ ይኖራል እንጂ፤አሁን በሥጋ የምኖረው
ሕይወት በእግዚአብሔር ልጅ እምነት እኖራለሁ! ወደ ሕይወት እና ወደ ሞት አልባነት መጥቻለሁ።እኔ ደፋር ነኝ፣ሞት ሽባ
ሆኗል፣በኢየሱስ ተሸንፏል፣ኢየሱስም ይህን ሲያደርግ በእርሱ ውስጥ ነበርኩ! ሃሌ ሉያ!

ለተጨማሪ ጥናት

ሮሜ 6፡9-11
2 ጢሞቴዎስ 1፡10
27 ፓስተር ክሪስ

ቃሉ እምነትን ይጨምራል

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው (ሮሜ 10፡17)

የእግዚአብሔር ቃል እምነትን ይጨምራል፡፡ምናልባት አስተውላችሁት ይሆናል፤ተቀምጣችሁ ቃሉን እየሰማችሁ ወይም


የእግዚአብሔርን ቃል እያጠናችሁ፤መንፈሳችሁ በብርታት ይሞላል፡፡በእንደዚህ ያሉ ጊዜያት፤ያጋጠሟችሁ ተግዳሮቶች ሁሉ
ድንገት ምንም ይሆናሉ፡፡ምክንያቱም በዚያ ሰአት ላይ የምትቀበሉት ቃል እምነት በውስጣችሁ ያነሳሳል፡፡
የእግዚአብሔር ቃል መንፈሳዊ ነው፤ስለዚህ ስጋዊ ስሜታችሁ መቀበል ከሚችሉት በላይ እውነተኛ ነው፡፡ለዛም ነው ቃሉን ወደ
መንፈሳችሁ ስትቀበሉ፤በሁኔታዎች ላይ እንድትገዙ የሚያስችላችሁ መንፈሳዊ ምላሽ ከመንፈሳችሁ እና ከእግዚአብሔር ቃል
ጋር ይነሳሳል፡፡ያ ምላሽ ሲመጣ፤እምነት በውስጣችሁ ይገዝፋል እናም የድል ማረጋገጫችሁን ታገኛላችሁ፡፡

ምንም ያህል እምነታችሁ ትንሽ እና ያነሰ ቢመስላችሁ፤ኢየሱስ ያ ትንሽ እምነት ትልቅ ነገሮችን ማድረግ ይችላል
ብሏል፤ተራሮችን ማንቀሳቀስ ይችላል፡፡ (ሉቃስ 17፡6)፡፡ምናልባት “እምነት የለኝም” ብላችሁ እያሰባችሁ ይሆናል ፤የመክፈቻ
ጥቅሳችን እንዴት እንደምናገኘው ነግሮናል፤እምነት ከመስማት ነው፤መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡

ምን ጊዜም በቂ እምነት የለኝም ብላችሁ ካሰባችሁ፤ያ ማለት በይበልጥ የእግዚአብሔርን ቃል የምትሰሙበት ሰአት ነው ማለት
ነው፡፡ቃሉ በፈቃዱ እና በአስፈላጊነት እምነትን ይሰጣችኋል፤የእግዚአብሔር መንግስት መርህ ነው፡፡ይሆን ዘንድ መታገል
አያስፈልጋችሁም፤ለእግዚአብሔር ቃል ትኩረትን ከሰጣችሁ፤እምነት ወደ እናንተ ይመጣል፡፡

ከአመታት በፊት ወደ አንድ ጉባኤያችን ሊካፈል ወደ መጣው አንድ ወጣት ያስታውሰኛል፡፡እያካፈልነው የነበረውን መልእክት
እንደማያምን ነገረን፡፡ነገር ግን ጓደኞቹ እንዲመጣ እንዳሳመኑት ነገረን፡፡ስለዚህ በጉባኤው ውስጥ ተቀመጠ፤ላለማመን ጥረት
እያደረገ ነበር፡፡ነገር ግን መልእክቱን “እየሰማ” ነበር (አስታውሱ እምነት ከመስማት ነው)፡፡

ከዛም ከእሱ ጋር በነበረኝ ውይይት “ድንገት፤ያካፈልከውን መልእክት ስቀበለው እራሴን አገኘሁት፤ያልከውን ሁሉ አምናለሁ”፡፡
ሊያመልጥ አልቻለም ምክንያቱም እምነት ቃሉን ከመስማት ይመጣል፡፡ሃሌ ሉያ!
ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፣ቃልህን ሳጠናና ሳሰላስል፣በክርስቶስ ያለኝን ርስቴን አገኝቻለሁ፤እናም እንድገናኝ የሚያደርገኝን እምነት ደግሞ
እቀበላለሁ፣እናም በክርስቶስ በቀረቡሉኝ አቅራቦቶች ሁሉ እደሰታለሁ።እምነቴ ሁል ጊዜ ያሸንፋል፤በሁኔታዎች ላይ በእምነቴ
አዋጆቼ እገዛለሁ፣በክርስቶስ ወንጌል ሙሉ በረከቶች ስራመድ አለሜን እቆጣጠራለሁ፣በኢየሱስ ስም፡፡አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት
ዕብራውያን 11፡6
ሮሜ 4፡19-20
2 ቆሮንቶስ 4፡13

28 ፓስተር ክሪስ

“ፍላጎታችሁ” እምነታችሁን ያነሳሳዋል

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው።በእግዚአብሔር እመኑ።እውነት እላችኋለሁ፥ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን
በልቡ ሳይጠራጠር፥ይህን ተራራ:-ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል (ማርቆስ 11፡22-23)

አንድ ሰው በአንድ ወቅት እንዲህ አለ “አንድም ሰው ተራራን በእምነት ሲያንቀሳቅስ አላየሁም፤ኢየሱስ ምሳሌን ብቻ
እየተጠቀመ ብቻ ነበር ወይስ ያለው እውነት ነው?እውነት ተራራን ማዘዝ ትችላላችሁ?”

አዎ፣ኢየሱስ የተናገረው እውነት ነው፡፡ነገር ግን ኢየሱስ ጨዋታ አልነበረም የተናገረው፡፡እያለ የነበረው ወደ ጎዳና ወጥተን
“ተመልከቱ ምን ያህል ኃያል እንደሆንኩኝ” እንድትሉ አይደለም፤ከዛም ተራሮችንና ህንፃዎችን እንዲንቀሳቀሱ እንድታዙ
አይደለም፡፡እንደዚያ አይደለም!

ጥያቄው፤ለምን ተራራን ማንቀሳቀስ ትፈልጋላችሁ፤አላማችሁ እና ፍላጎታችሁ ምንድን ነው?እምነታችሁ ሁልጊዜም


ከፍላጎታችሁ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ፍላጎት ከሌለ፤ለዛም የሚሆን እምነት አይኖርም፡፡ስለዚህ እራሳችሁን ሊሆን የማይችልን ነገር
ለማድረግ ስትሞክሩ ልታገኙ ትትችላላችሁ ምክንያቱም ቅድሚያ እምነትን ለማነሳሳት የሚሆን ፍላጎት የለም፡፡

እምነት ሁሌም ለመነሳሳት የሚያስፈልገው ነገር ሲኖር ነው የሚነሳሳው፡፡እራሳችሁን በፍላጎት ቦታ ላይ ስታገኙት አትረበሹ፤ያ
ፍላጎት እምነትን በውስጣችሁ ያነሳሳል፡፡መቼም ልታረግዝ እንደማትችል እንደ ተነገራት ሴት ነው፡፡ያ ዜና እምነቷን
አነሳሳው፤እናም ብዙም ሳትቆይ ልጇን ወለደች፡፡ልጅ መቼም መውለድ እንደማትችል እስኪነገራት ድረስ በእምነቷ መውለድ
እንደምትችል አታውቅም፡፡
ተመሳሳይ ነገር ከካንሰር ስለተፈወሰው ሰው መናገር ይቻላል፤ለመኖር አንድ ወር ነው የቀረህ እስኪባል ድረስ ማድረግ
እንደሚችል አላወቀም ነበር፡፡ይህ ዜና እምነቱን አነቃቃው፤እናም ማወጅ ጀመረ፤ “በህይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም” እናም
በርግጥ ተፈወሰ፡፡ሃሌ ሉያ!

በፍላጎታችሁ አትወሰዱ ይልቁንም ፍላጎታችሁ ከእምነታችሁ ጋር ይገናኝ፡፡ፍላጎታችሁ ያነቃቃችሁ፡፡አንዴ ፍላጎታችሁን


ካገናኛችሁ፤ያ ፍላጎታችሁን ለእምነታችሁ የምትጠቀሙበት እድላችሁ ነው፡፡እግዚአብሔር ይባረክ፡፡

የእምነት አዋጅ
በክርስቶስ እራሴን የቻልኩኝ ነኝ፡፡የተወለድኩት ከማይጠፋ ውርስ ነው።እምነቴ ዓለምን የሚያሸንፈው ድሌ ነው ! ዓለምን እና
ስርዓቶቹን እና መዋቅሮቹን አሸንፋለሁ።መንገዴ እግዚአብሔር ለእኔ ያዘጋጀልኝ የክብርና የልቀት
የመልካምነት፣የድል፣የስኬት፣የደስታ፣የጤና እና የብልፅግና መንገድ ነው።በግዛት እመላለሳለሁ።ሃሌ ሉያ!

ለተጨማሪ ጥናት
ሮሜ 4፡19-20
2 ቆሮንቶስ 4፡17-18
ፊልሞና 1፡6

29 ፓስተር ክሪስ
በመንገዳችሁ ላይ የሆነ ነገር አለ
እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀልንን መልካምን ሥራ እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ እንደገና የተፈጠርን የእግዚአብሔር የእጅ
ሥራዎች (አሠራሩ) ነንና። በእነርሱ ልንመላለስ ይገባናል (እርሱ አስቀድሞ ያዘጋጀውንና እንድንኖር የወሰነውን መልካም ሕይወት
በመምራት) (ኤፌሶን 2፡10 አምፕሊፋይድ ክላሲክ ትርጉም)

እያንዳንዳችን በህይወት እንድንመላለስ በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተዘጋጀ መንገድ አለን። የስኬት እና የታላቅነት መንገድ ነው።
ነገር ግን፣ በምትጓዙበት ጊዜ፣ እምነታችሁን ከሚፈትኑ ኃይሎች ወይም ሁኔታዎች ጋር ትጋጫላችሁ። ለዳዊት፤ ድብና አንበሳ
ነበሩ። ከዚያ በኋላም፣ ጎልያድና የፍልስጥኤማውያን ሠራዊት፣ ከዚያም ሌሎች ብዙ ሠራዊት ነበሩ። እርሱ ግን ሁሉንም
አሸነፋቸው። ሃሌ ሉያ!
በመንገዳችሁ ላይ ምን እንዳለ እርግጠኛ አይደለሁም፣ ግን በእርግጥ በመንገዳችሁ ላይ የሆነ ነገር አለ። ግን አንድ ነገር እርግጠኛ
ነው፤አስቀድማችሁ አሸንፋችኋል። ለዛም ነው መጽሐፍ ቅዱስ “ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ
ቍጠሩት፤”(ያዕቆብ 1፡2)የሚለው።
በመንገዳችሁ ላይ ያሉ ፈተናዎች ወይም እንቅፋቶች ከእውነታ ያልሆኑ ናቸው። ወደ እነርሱ ስትደርሱ አታልቅሱ።እግዚአብሔር
አንድ ነገር እንዲያደርግ መለመንም አትጀምሩ። አትብረክረኩ ። ያንን "ጭንብል የለበሰውን ሰይጣን"ስታገኙት፣ ይህም ማለት
በንግዳችሁ ወይም በስራችሁ ላይ መሰናከል፣ ነፍሳትን በማዳን ወይም በወንጌል ስርጭት ጥረታችሁ ላይ ገደብ ወይም መሰናክል፤
ወይም አንዳንድ የጤና ችግሮች ማለት ሊሆን ይችላል፣ "በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከመንገዴ ላይ ዘወር በል!"ትሉታላችሁ።
ይህን ስትሉ፣ አንዳንድ መሰናክሎች አሁንም ያሉ ሊመስሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን እውቅና ለመስጠት እምቢ ብላችሁጉዞአችሁን
ቀጥሉ። አትመልከቱት፤ ይልቁንስ አይናችሁን ጨፍኑበት እና በልሳን በመጸለይ፣በመንፈስ መቃተት ተናገሩ፤ ከዚያም፣ ዳዊት ወደ
ጎልያድ እንደሮጠ፣ ወደዛ መሰናክሉ ሂዱ እና መንፈስ እንዳነሳሳችሁ በኢየሱስ ስም አቋርጣችሁት እለፉ።
እዛ ከመድረሳችሁ በፊት እግዚአብሔር ጨርሶታል። አሁን አትጨነቁ የሚልበትን ምክንያት ይገባችኋል። ምክንያቱም ትልቅ
ችግር ሲያጋጥማችሁ፤ እሱ ጣልቃ ስለሚገባ ነው። መጮህ አያስፈልጋችሁም። መምታትም አያስፈልጋችሁም። መግፋትም
አያስፈልጋችሁም። ዝም ብላችሁ ቀጥሉ፤ ዝም ብላችሁ አቋርጣችሁ እለፉ! ሃሌ ሉያ!
የእምነት አዋጅ
አባት ሆይ፣ አስቀድመህ ባዘጋጀኸልኝ መንገድ ብቻ ስለምመላለስ አመሰግናለሁ፣ እሱም ደግሞ የጽድቅ፣ የታላቅ ክብር፣
የታላቅነት እና የማያቋርጥ ድሎች መንገድ ነው። ለመንፈስ ቅዱስ፣ ለእርሱ ምሪት፣ ምክር እና ጥበብ፣ ተሰጥቻለሁ፣በኢየሱስ
ስም ።አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት
ሮሜ 8፡14
ኢሳይያስ 30፡21
መዝሙረ ዳዊት 16:11

30 ፓስተር ክሪስ
የጸናው መሠረት

ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥
መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ የሚያምን አያፍርም (ኢሳይያስ 28፥16)
ህይወታችሁ የተመሰረተበት መሠረት አስፈላጊ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ
መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”( 1 ኛ ቆሮንቶስ 3፥11)። ብቸኛው የጸናው መሠረት ክርስቶስ
ነው። እሱ የስኬታችሁ መሰረት መሆን አለበት። በዚህም መንገድ፣ የሕይወትን መከራ ስትጋፈጡ፣ ቆማችሁ ትቆያላችሁ፣
ምክንያቱም በዓለቱ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ተመስታችኋል!
ነቢዩ ኢሳይያስ ፣ በመክፈቻ ጥቅሳችን ፣ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ስለሚያስቀምጠው "ድንጋይ" በትንቢት ተናግሯል፣ እናም ይህ
"ድንጋይ" የተገለጸበትን መንገድ እንድትመለከቱት እፈልጋለሁ። በመጀመሪያ"የተፈተነ ድንጋይ"ብሎ ይጠራዋል፤ ከዚያም "የከበረ
የማዕዘን ድንጋይ" ብሎ ይጠራዋል። በሶስተኛ ደረጃ፣ "የጸና መሠረት"ብሎ ይጠራዋል።

"የተፈተነ ድንጋይ" ማለት ተፈትኗል እና ተረጋግጧል ማለት ነው። እንደ "የከበረ የማዕዘን ድንጋይ"ማለት ለህንፃው ፅናት በጣም
አስፈላጊው ድንጋይ ነው ማለት ነው። እንደ "የጸናው መሠረት"ማለት ህይወታችሁን በእርሱ ላይ በእርግጠኝነት መመሥረት
ትችላላችሁ ማለት ነው። ጌታ ኢየሱስ ማለት ይህ ነው፣ ህይወታቻችሁን መመሥረት ያለባችሁ ብቸኛው እውነተኛ መሠረት
እርሱ ነው።
ለዚህም ነው በሉቃስ 6፡47-49 ላይ"ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ ቃሌንም ሰምቶ የሚያደርገው፥ ማንን እንዲመስል አሳያችኋለሁ።
ቤት ሲሠራ አጥልቆ የቆፈረ በዓለት ላይም የመሠረተ ሰውን ይመስላል፤ ጐርፍም በመጣ ጊዜ ጎርፍም ያን ቤት ገፋው፥ በዓለት
ላይም ስለ ተመሠረተ ሊያናውጠው አልቻለም።ሰምቶ የማያደርገው ግን ያለ መሠረት በአሸዋ ላይ ቤቱን የሠራ ሰውን
ይመስላል፤ ወንዙም ገፋው ወዲያውም ወደቀ የዚያ ቤት አወዳደቅም ታላቅ ሆነ።" በማለት ተናግሯል።
አስታውሱ፣ልዩነቱን የሚያመጣው መሠረቱ ነው። ኢየሱስ ከላይ በተናገረው ምሳሌ ውስጥ ያሉት ሁለቱም ቤቶች አንድ ዓይነት
ጐርፍ ያጋጠማቸው ቢሆንም፣ መሠረት የሌለው ቤት ፈርሷል። ክርስቶስ፣ ጠንካራው ዓለት፣ የሕይወታችሁ መልህቅ ይሁን!
የእግዚአብሔርን ቃል አድራጊ ሁኑ፣ ምክንያቱም ህይወታችሁን በዓለት ላይ መገንባት የምትችሉት በዚህ ስለሆነ። ሁሉም ነገር
ሲወድቅ እንድትቆሙ የሚያደርጋችሁ ይህ ነው። ህይወታችሁ በሙሉ ስኬት እና ብልጽግናን እንዲሆን የሚያደርገው ይህ ነው።

ጸሎት

ውድ አባት ሆይ፣ ስለ ቃልህ አመሰግንሃለሁ፣ እርሱም አስተማማኝና ጽኑ መሠረቴ ነው። በእርሱ ላይም አስተማማኝ እና
የማይነቃነቅ፣ የተጠናከረ፣ ሥር የሰደደ እና የተመሰረትኩ ሆኜ እቆማለሁ።ቃልህ የሚይዘኝ ዓለት ነው፤ ምክንያቱም የሚታመን፣
አስተማማኝ እና እውነት ነው። ጌታ ሆይ፣በቃልህ ስላለኝ የድል አድራጊነት ህይወት አመሰግንሃለሁ፣በኢየሱስ ስም፣ አሜን።
ለተጨማሪ ጥናት

የሐዋርያት ሥራ 20፡32
ማርቆስ 13፡31

You might also like