You are on page 1of 1

የምቀበለውን እመርጣለሁ I Receive Selectively

በዚህ ፅሁፍ ውስጥ "እኔ" የሚለው ሃሳብና ቃል የሚወክለው አንባቢውን ነው፡፡

የወሰንኩት አንድ ውሳኔ አለ፡፡ በዚህ አለም ብዙ መረጃዎች (Information) አሉ፡፡ ብዙ መፅሀፎች፣ ብዙ ቪዲዮዎች፣
ብዙ ሰባኪዎች፣ ብዙ ሳይኮሎጂስቶች፣ ብዙ ተናጋሪዎች፣ ብዙ አማካሪዎች፡፡ እነዚህ ሁሉ መረጃ ሊሰጡኝ የሚታገሉ
ናቸው፡፡ ስለእራሴ ማንነት ይነግሩኛል፣ ስለህይወት፣ ስለሰዎች yadi yadi ya. እውነት መሆናቸውን በምንድነው
የማውቀው?? እራሳቸውም እኮ ዛሬ የተናገሩትን ተቃራኒ በሚቀጥለው ጊዜ ሲናገሩ ሰምቻቸዋለሁ፡፡ ላምናቸው
የምችልበት ደረጃ ውስን ነው፡፡ እነሱ የሚሉት ሁሉ ስለእኔ ሊነገር የሚችል መሆኑን ወይም አለመሆኑን እለያለሁ፡፡
ምክንያቱም እኔ ዳግመኛ የተወለድኩ የእግዚአብሔር ልጅ እንጂ ሰው ብቻ አይደለሁም፡፡ ማን ነው እኔን ሰው ብቻ
መሆኔን የነገረኝ?? ሰው በሚቸገርበት ነገር እኔ ልቸገር አልችልም፡፡ ሰው የሚደርስበት ሁሉ እኔ ላይ ሊደርስ
አይችልም፡፡ እንዴት ይችላል?? እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ (1ዮሐ 5)፡፡ ሃሌሉያ!

አንዳንድ ሰዎች ለክርስቲያን ከአጋንንትና ከእርግማን ነፃ ስለመውጠት እድሜያቸውን ሁሉ ያስተምራሉ፣ ስላሉብኝ


ችግሮች መረጃ ይሰጡኛል፡፡ እንዴ! ጌታ ያለውን አልሰሙትም እንዴ?? "እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም
እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።" (ቆላ 1) ያለው ጌታ ውሸቱን ነው
ማለት ነው?? ገና አላዳነንም ከጨለማ ስልጣን ማለት ነው?? ከእርግማንና ከሰይጣን ገና አልዳንንም ማለት ነው??
ወደ መንግስቱ ከገባሁ በኋላ እነርሱ የሚሉትን ሰምቼ እንዴት ስለነዚህ ነገሮች ልጨነቅ እችላለሁ??

እስካሁን የሰማሁት፤ ሰው ጥሩ ጎን አለው መጥፎ ጎን ደግሞ አለው፤ ጥሩ ባህሪ አለው መጥፎ ባህሪ ደግሞ አለው
ሲባል ነው፡፡ ሀጢያት፣ ንዴት፣ ጥላቻ፣ ክፋት የመሳሰሉ መጥፎ ባህሪዎችን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል በስፋት
በማስተማር ነው ሰባኪዎች የተጠመዱት፡፡ ይህ ሁሉ ሰው ብቻ ለሆኑት ሰዎች ይጠቅማቸዋል፡፡ ለእኔ ግን አይሰራም፡፡
እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፡፡ ፍፁም የእግዚአብሔር ልጅ፡፡ ጌታ ያለኝ "እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን
አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል" ነው (ቆላ 3)፡፡ አንዳንዶች ህይወት ውጣ ውረድ ነው ብለው በውጣ ውረድ ውስጥ
ስለመፅናት ያስተምራሉ፡፡ ጥሩ ይመስላል፡፡ የሰው ልጆች ሁኔታም የሚያስረዳው ያንን ነው፡፡ ጌታ ግን ያለኝ "ነገር ግን
በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ
ምስጋና ይሁን" ነው (2ቆሮ 2)፡፡ ሁልጊዜ! ሁልጊዜ እንጂ አንዳንድ ጊዜ አላለኝም፡፡ የቱ ነው ታዲያ እውነት?? ብዙ
ሰዎች የምችለውን እንዳደርግ፤ ከዛ ካለፈ ግን በቃ ለእግዚአብሔር ሰጥቼ እንድተወው ነው የነገሩኝ፡፡ ጌታ ያለኝ ግን
"ለሚያምን ሁሉ ይቻላል" ነው (ማር 11)፡፡ የቱ ነው ትክክል??

የሰዎች መረጃ ሁሌም በነበራቸው ልምድ፣ አሁን ባለው ሁኔታ፣ በሚያውቁት እውቀት መጠን፣ በሃይማኖትና ሰው
በመሆናቸው ምክንያት የተገደበና እውነትን ለማወቅ የራቀ ነው፡፡ ነገር ግን "ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው
አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም።" ሃሌሉያ! የኔ አምላክ! የማምነው አንተን ነው፡፡ በቃ ምንም
ይሁን ምን፤ ጌታ ያለኝ ሁሉ እውነት ነው፡፡ ሌላው መረጃ ሁሉ ምንም ይሁን ምን ውሸት ነው፡፡ የሰማሁትን ሁሉ
ልቀበል አልችልም፡፡ መረጃ የምቀበለው መርጬ ነው፡፡ ሃሌሉያ!

Love by sharing
ቴሌግራም ለመቀላቀል t.me/Lovedface

እወዳችኋለሁ አከብራችኋለሁ, አማኑኤል ከበደ(@emanuellf) ከLovedface

ከእግዚአብሔር ጋር ጥልቅ ፍቅር ዲቮሽናል በየእለቱ

በየእለቱ አማርኛና እንግሊዝኛ ዲቮሽናል ቪዲዮዎች በዩቱዩብና ፌስቡክ እንዲሁም የፅሁፍ ዲቮሽናል በፌስቡክና
ቴሌግራም

You might also like