You are on page 1of 7

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “, [29.05.

19 22:42]

#በጣም_አጭርና አስተማሪ መልእክት ነው አንብቡት

#ልቡናውን_ሰብስቦ_መጸለይ_ያቃተው_ወጣት

#አንድን_አባት እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል፡-

...

#አባቴ_የጸሎት መጽሐፍ ይዤ ስጸልይ ልቡናዬ አይሰበሰብልኝም፤ አፌ ቢያነበውም ልቡናዬ ግን ይበታተናል፡፡

እኔ ደግሞ ዝም ብዬ ሳስበው፦ ቅዱሳን በፍጹም ሐሳባቸው እያሰቡና እያራቀቁ እንባንና ጸጸትን እየጨመሩ የጻፉትን እኔ በልቤ ሌላ
እያሰብኩ በአፌ ብቻ ባነበንበው እንደ ገደል ማሚቶ ፊደሉ አፌ ላይ እየነጠረ ይሄዳል እንጅ ጸሎትም አይሆንልኝም ፡፡

ስለዚህ አባቴ የአፍ ብቻ ጸሎቴ ቅድመ እግዚአብሔር የማይደርስ ከሆነ ጸሎቴን ብተወው ይሻላል ወይስ ባልተወው ይሻላል?" . . .
ብሎ ጠየቃቸው።

አረጋዊው አባትም እንዲህ ሲሉ አስረዱት፡-

“አየህ ልጄ ዐይነ ስውር ሰው በዘንጉ ምድር እየመታ ሲሄድ ከመንገድ ላይ ያለ እባብ ለጊዜው የበትሩን ድምጽ ሰምቶ ይመታኛል ብሎ
ይሸሻል እንጅ ዐይነ ስውር ነው አላየኝም ብሎ ባለበት አይጠብቀውም። ስለዚህ አንተም አስተውለህ ብትጸልይ መልካም ቢሆንም
ለጊዜው ግን ጭራሽ ከምታቆመው በአፍህ ውስጥ ያለው የቃለ እግዚአብሔርን መንኳኳት የሚሰሙ አጋንንት መሸሻቸው አይቀርምና
መቼም ቢሆን ጸሎትህን አትተው፡፡

. . . አጋንንትንም ማባረር አንድ ታላቅ ጥቅም ነውና፡፡

ብዙ ከመጸለይህም አንጻር አንዳንድ ጊዜ ልብህ የሚወድቅባት ቃል ተጠራቅማ ወደ እግዚአብሔር ታደርስሃለች።

እናም ልጄ ልብህ ምንም ዝርው ቢሆንም አፍህም የእግዚአብሔር ፍጥረት ነውና ይህንንም እንዳታቆመው።

...

አሁን አንዱን ይዘህ ወደፊት ደግሞ ሁለቱንም ለማገናኘት መጣር ይኖርብሃል እንጅ አንተው በዳይ አንተው አኵራፊ ሆነህ ጭራሽ
ከአምላክ ርቀህ የጠላት ሰይጣን መጫወቻ እንዳትሆን አሉት።

እኛም እኮ ብዙ መፀለይ ፈልገን በብዙ ሰበብ ሳንፀልይ እንቀራለን

ፈጣሪ ግን የልባችንን ያቃልና ሁሌም ሃሳባችንን ይሞላልናል

እግዚአብሔር ሀሳባችንን ህልማችንን እውን ያርግልን🙏🙏🙏

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “, [19.09.19 10:01]

[ Photo ]

~~~በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን~~~

✍️አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት

"ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ ፣ እንዴት ላድርግ?"

ቅዱሱ አባት መለሰለት

"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው

ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው

ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል

ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው

በል ሒድና ተአምር ሥራ!"

★★★

ለልጆቻችን ክርስቶስ ማን እንደሆነ እኛ ካልነገርናቸው ዓለም ክርስቶስ ያልሆነውን ሁሉ ይነግራቸዋል።

★★★

ኃጢአተኞች በሌላ ኃጢአተኛ ላይ ከእነርሱ ለየት ያለ ኃጢአት ስለ ሠራ ይፈርዱበታል ፣ ወይም ተመሳሳይ ኃጢአት ቢሠራም
ይፈርዱበታል።

★★★

አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?

እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ?

ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ?

ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ?

ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ?

ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ?

መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ?

ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ?

በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ?

የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ?

ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ?

ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ?

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “, [22.09.18 17:36]

ከተሰወረ ኃጢያት አንጻኝ

ከመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ

ከተሰወረ ኃጢያት አንጻኝ ይህንን የተናገረው ክቡር ዳዊት በመዝሙር 19፡12 ላይ የምናገኘው ነው፡፡ ‹‹ከተሰወረ ኃጢአት
አንጻኝ። የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ፤ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፥ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።›› በማለት
ይናገርና ማብቅያው ‹‹አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።›› በሚል ይደመድማል

ብዙ ጊዜ ብዙ የስዉር ህይወት ጎዳና ውስጥ ብዙ ጥፋቶች ይመጣሉ፡፡ ብዙ ነገሮች ይከሰታሉ፡፡ ለብዙ ዘመናት የቆየ የክፉ
መናፍስት አሰራር ውርስ ውስጥ እንደገባን እንኳን አሁን አሁን ጥቂት መባነን ጀምረናል፡፡ ብዙዎቹ እንኳን አሁንም ሊባንኑ ያልቻሉ
በዚሁ በክፉ አሰራር ስዉር መንገድ ውስጣዊው ህይወታቸው አቅጣጫ የጠፋቸው፣ የህይወት መንገድን ያጡ፣ ሠላማዊ የሆነ በረከት
የራቃቸው ብዙ ናቸው፡፡ ያንን እንደ ልማድ ይዘዉት፣ እንደ ጸጋም ቆጥረዉት በተምታታና በረከት አልባ በሆነ ህይወት ራሳቸዉን
መርተው ትውልዳቸው ኪሳራ ውስጥ ጥለው የሚያልፉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ስለዚህ ከተሰወረ ኃጢያት አንጻኝ ሁላችንም ልንል
ይገባናል፡፡

እና ዛሬ ብዙ ሰው ከበረከትና ከእግዚአብሔር አምላክ ጸጋና ተስፋ በመራቅ በዲያብሎስ በኩል የሚኖረዉን ኑሮ እንደ ጣፋጭ
የህይወት አካል አድርጎ ይዞታል፡፡ ከዚሁም ውስጥ አንዱ በግሉ ለመናፈስት መገበር ነው፡፡ በግሉ ለመናፍስት መገበር ማለት
በተሰወረ ሐጥያት በኩል መናፍስቶቹን እንደ ሥራ ባህሪ ማሰማራት ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዳንዱ ሰውነትን ለክፉ መናፍስት
አሰራር መስጠት ነው፡፡ በዚህ ዘመን፣ በዚህ ግዜ፣ በዚህ በእውቀት፣ በዚህ በቴክኖሎጂ ዘመን ውስጥ ሰዎች የተሰወረ ስዉር የሆነ
የሐጥያት አሰራር ውስጥ ይገባሉ፡፡ ከዚህም ውስጥ አንዱ መናፍስቱን የሚፈልጉትን ነገሮች ያሟላሉ፡፡

ከሚጠይቅዋቸው ነገሮች አንዱ በፈርስ፣ በእንስሳት ደም፣ በሌሎች የደም አይነቶች መታጠብ፡፡ ሰውነትን፣ ገላን እነዚህ እነዚህን
የመሳሰሉት ነገሮች በመናፍስት ግብር ውስጥ ሰውነትን ማሳለፍ ማለት ነው፡፡ በፈርስና በደም መታጠብ በዘመናችን በጣም ትልልቆቹ
ወይዘራዝርትና ልዩ ሆኑ የሚባሉ ሰዎች ሁሉ ጭምር ለተሰሚነት፣ ለግርማ ሞጎስ አንዳንድ ነገሮችን ፍፃሜ እንዲመጣላቸው ወይም
በመናፍስት እንዲጠበቁ አልያም በመናፍስት አሰራር ውስጥ ገበያው እንዲቃጠል፣ የሃብት ኃይሉ እንዲጨምር እነዚህ የመሳሰሉ
ነገሮች በዚህ በተሰወረው የሐጥያት ኃይል ውስጥ የሚከናወን ነው፡፡ ለዚህ ነው ክቡር ዳዊት ከተሰወረ ኃጢያት አንጻኝ በማለት
ይህንን የጸሎት ኃይል ሲገልፅ የምናገኘው፡፡

ዛሬ በዚህ አይነት የተጠላለፉና በዚህ በመናፍስት ጎዳና ውስጥም ዘግጠው የገቡ እንደ አንዱ ራሱን የቻለ ኑሮ አድርገው የያዙት
ብዙዎች ናቸው፡፡ እንደዚህ አይነቶቹ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንፈሳዊ ክብር ቢጠሩ እንኳን የማድመጥም፣ የመስራትም፣
የመለወጥም ፍቃድ የላቸዉም፡፡ ለምን? በተሰወረ ኃጢያት በኩል ልቦናቸው የሚያውቀዉና በአኗኗራቸው ውስጥ የክፉዉን አሰራር
በህይወታቸው ዙርያ የለመዱት ነገር ሆኖው ስለሚገኙ፡፡

ኃጢያት በራሱ ከመናፍስት ውጪ ተሰዉሮ የሚኖር ጉዳትም ጭምር ነው፡፡ አሁን ይህንን በዝርዝር ለመመልከት እስቲ በመጀመርያ
ስዉር ሐጥያት ሲባል ምንድነው? የሚለዉን ነገር ላይ ትኩረት ለመስጠት እንሞክር፡፡

የተሰወረ ኃጢያት የሚነሳው ከልብ፣ ሕሊናና ከአዕምሮ ውስጥ ነው፡፡ ከሕሊናና ከአዕምሮ ውስጥ ከመሰወሩ ባሻገር ደግሞ
የመናፍስት ግፊቶች ከነዚህ ካሉት ሦስት ቦታዎች ላይ መነሳት ሲጀምር የተጠናከረ የክፉ አሰራር ኃይል ወደ ዉጪ እንዲወጣ
ያደርገዋል፡፡ ያ በሐሳብ፣ በዕቅድ፣ በፕሮግራም፣ በአነጋገርና በአፈፃፀም የሚገለጥ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ከተሰወረ ኃጢያት አንጻኝ
በማለት ክቡር ዳዊት ይህንን ወደ ሰማይ አምላክ ኃይልና ወደ ሰማይ አምላክ መንፈሳዊ ተስፋ እንዲገባ ራሱን አዘጋጅቶ
እናገኘዋለን፡፡

የተሰወረ ኃጢያት ምንጩ በምኞት ውስጥ የተካተተ ነው፡፡ የሰው ኑሮን መመልከት፣ የሰው ህይወትን ማየት፡፡ የሰው ህይወትን
አይቶ ደግሞ በክፉ መከጀል፣ በክፉ ነገር ላይ ማሰብ፣ ተንኮል መፈፀም፣ ግፍ መስራት፣ በምቀኝነት ማየት፣ ኪሳራዉን መመኘት፣
ውድቀቱን መመኘት እና ደግሞ ከዛም በተግባር አልፎ ተርፎ በምትሐት ዓለም መሄድ የተሰወረ ሐጥያት ክፍል ነው፡፡

ኃጢያት በራሱ ከመናፍስት ተሰዉሮ የቱን ያህል ጊዜ ፣ ዘመን፣ ወቅትን እንደሚጎዳ ለማረጋገጥ አሁን ብዙ አትቸገሩም፡፡ ከቁጥር 1
ጀምሮ እስከ ቁጥር 54 ድረስ ያሉትን። ቪሲዲ ( VCD )የሚታዩትን በሰው ህይወት ውስጥ ያሉትን የጉዳት መንገዶችን መገንዘብ
አያስቸግረንም፡፡ ስለዚህ ይሄ የተሰወረ አሰራር ነው፡፡ የመናፍስት አሰራር ነው፡፡ ዓለማችን ይህንን በግልፅም በስዉርም የመሄጃ
መንገድና የመኖርያም አካል አድርጎት እየተገነዘብን ነው ያለነው፡፡ ስለዚህ የመጀመርያው ኃጢያት ለክፉ መንፈስ ከመዳረግ በፊት
ክፉዉን ሐሳብ በህይወታችን ውስጥ እንደ አንድ ራሱን የቻለ ጊዜ፣ ዘመን፣ ወቅትን ማምለጫ አድርገን ከተጠቀምንበት የተሰወረ
ኃጢያት ከውስጣችን ጀምረዋል ማለት ነው፡፡

ከመንፈሳዊ እስከ ዓለማዊ ድረስ ያለዉ ውድቀት ተጠናክሮ አንዱ ላንዱ የጠላትነት ስሜትን በፍቅር ምትክ ጠብን፣ በሠላም ምትክ
ጦርነትን፣ በቦጎነትን ምትክ አረመኔነትን ለሰው ልጅ እየሰጠን ያለን ፍጡሮች ሆነናል፡፡ ስለዚህ‹‹ከተሰወረ ኃጢያት አንጻኝ።
የድፍረት ኃጢያት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ፤ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፥ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ። አቤቱ፥ ረድኤቴ
መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።›› በእውነት እንዲህ እያልን ልንጸልይ ያስፈልጋል፡፡

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “, [29.05.19 22:42]

#በጣም_አጭርና አስተማሪ መልእክት ነው አንብቡት

#ልቡናውን_ሰብስቦ_መጸለይ_ያቃተው_ወጣት

#አንድን_አባት እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል፡-

...

#አባቴ_የጸሎት መጽሐፍ ይዤ ስጸልይ ልቡናዬ አይሰበሰብልኝም፤ አፌ ቢያነበውም ልቡናዬ ግን ይበታተናል፡፡

እኔ ደግሞ ዝም ብዬ ሳስበው፦ ቅዱሳን በፍጹም ሐሳባቸው እያሰቡና እያራቀቁ እንባንና ጸጸትን እየጨመሩ የጻፉትን እኔ በልቤ ሌላ
እያሰብኩ በአፌ ብቻ ባነበንበው እንደ ገደል ማሚቶ ፊደሉ አፌ ላይ እየነጠረ ይሄዳል እንጅ ጸሎትም አይሆንልኝም ፡፡

ስለዚህ አባቴ የአፍ ብቻ ጸሎቴ ቅድመ እግዚአብሔር የማይደርስ ከሆነ ጸሎቴን ብተወው ይሻላል ወይስ ባልተወው ይሻላል?" . . .
ብሎ ጠየቃቸው።

አረጋዊው አባትም እንዲህ ሲሉ አስረዱት፡-

“አየህ ልጄ ዐይነ ስውር ሰው በዘንጉ ምድር እየመታ ሲሄድ ከመንገድ ላይ ያለ እባብ ለጊዜው የበትሩን ድምጽ ሰምቶ ይመታኛል ብሎ
ይሸሻል እንጅ ዐይነ ስውር ነው አላየኝም ብሎ ባለበት አይጠብቀውም። ስለዚህ አንተም አስተውለህ ብትጸልይ መልካም ቢሆንም
ለጊዜው ግን ጭራሽ ከምታቆመው በአፍህ ውስጥ ያለው የቃለ እግዚአብሔርን መንኳኳት የሚሰሙ አጋንንት መሸሻቸው አይቀርምና
መቼም ቢሆን ጸሎትህን አትተው፡፡

. . . አጋንንትንም ማባረር አንድ ታላቅ ጥቅም ነውና፡፡

ብዙ ከመጸለይህም አንጻር አንዳንድ ጊዜ ልብህ የሚወድቅባት ቃል ተጠራቅማ ወደ እግዚአብሔር ታደርስሃለች።

እናም ልጄ ልብህ ምንም ዝርው ቢሆንም አፍህም የእግዚአብሔር ፍጥረት ነውና ይህንንም እንዳታቆመው።

...

አሁን አንዱን ይዘህ ወደፊት ደግሞ ሁለቱንም ለማገናኘት መጣር ይኖርብሃል እንጅ አንተው በዳይ አንተው አኵራፊ ሆነህ ጭራሽ
ከአምላክ ርቀህ የጠላት ሰይጣን መጫወቻ እንዳትሆን አሉት።

እኛም እኮ ብዙ መፀለይ ፈልገን በብዙ ሰበብ ሳንፀልይ እንቀራለን

ፈጣሪ ግን የልባችንን ያቃልና ሁሌም ሃሳባችንን ይሞላልናል

እግዚአብሔር ሀሳባችንን ህልማችንን እውን ያርግልን🙏🙏🙏

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “, [19.09.19 10:01]

[ Photo ]

~~~በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን~~~

✍️አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት

"ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ ፣ እንዴት ላድርግ?"

ቅዱሱ አባት መለሰለት

"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው

ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው

ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል

ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው

በል ሒድና ተአምር ሥራ!"

★★★

ለልጆቻችን ክርስቶስ ማን እንደሆነ እኛ ካልነገርናቸው ዓለም ክርስቶስ ያልሆነውን ሁሉ ይነግራቸዋል።

★★★

ኃጢአተኞች በሌላ ኃጢአተኛ ላይ ከእነርሱ ለየት ያለ ኃጢአት ስለ ሠራ ይፈርዱበታል ፣ ወይም ተመሳሳይ ኃጢአት ቢሠራም
ይፈርዱበታል።

★★★

አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?

እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ?

ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ?

ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ?

ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ?

ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ?

መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ?

ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ?

በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ?

የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ?

ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ?

ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ?

You might also like