You are on page 1of 4

እግዚአብሔር የረሳን ለምን ይመስለናል?

1. እኛ ስለምንረሳው
የመከራ ጽናት የዘመን ብዛት እግዚአብሔር ረስቶኛል ብቻ ሳይሆን (ሎቱ ስብሐት) እግዚአብሔር የለምም
ያስብላል። የሰው ልጅ መከራው ጽኑ በሆነ ጊዜ፣ ዘመን በራቀበት ጊዜ፣ ለጥያቄው መልስ ባጣ ጊዜ በእነዚህ በሦስቱ
በሃይማኖት እንቅፋት ይገጥመዋል። ስለዚህ እግዚአብሔር ረስቶኛል፣ አይወደኝም ይልና ቀቢጸ ተስፋ ላይ ሲደርስ
ደግሞ እግዚአብሔር ባይኖር ነው እንጂ ቢኖርማ ማለት ይጀምራል። በመጨረሻም የለም ብሎ ይክዳል።
ሰይጣን ሰውን ወደ ምንፍቅና ወደ ክህደት የሚወስድባቸው 3 ቱን መንገዶች መጠንቀቅ ይገባል። ይህንን ይበልጥ
ለመረዳትም የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሀሳቦችን እንመልከት:-
👉ሀ. "ስለምን ጦምን? አንተም አልተመለከትከንም? ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን? አንተን አላወቅህም?"
(ኢሳ 58÷3)
እዚህ ላይ ጹመው ለጥያቄያቸው ምላሽ በማጣታቸው እግዚአብሔርን አልተመለከትከንም፣ አላወቅኸንም
እስከማለት ደርሰው ነበር። "የእግዚአብሔር ዓይኖች ምን ሆነው አልተመለከቱም?፣ አይወሰኑ ምሉዓን፣ አይሞቱ
ሕያዋን፣ አያዳሉ ጻድቃን ናቸው። ታዲያ ለምን አልተመለከትከንም አሉ?" ብንል መልሱ "ጥያቄያቸው ባለመመለሱ
እግዚአብሔር የተዋቸው የገፋቸው የረሳቸው መስሏቸዋል" የሚል ይሆናል።
የፈለጉትን በማጣታቸው በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት እግዚአብሔር የሌለ እየመሰላቸው ወዲያ ወዲህ
የሚቅበዘበዙ ወገኖች በዚህ ዘመንም አይታጡም። ግን እግዚአብሔር አላይ ብሎ ሳይሆን እኛ አንታይም አትየን
ብለነው ነው። "ገዳም ሄድኩ፣ ንስሐ ገባሁ፣ እጸልያለሁ፣ እጦማለሁ፣ በቅዱሳን አምናለሁ፣ እቆርባለሁ ነገር ግን
እስከዛሬ ከነበርኩበት ነኝ ምን ይሻለኛል?" የሚሉ ብዙዎች ናቸው። መልሱን ለእነዚህ ጦመኞች የመለሰውን እንስማ!
"በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትቾላለችን? አዎ እርስዋ
ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም" ይላል (ኢሳ 49÷15)። እናት 9 ወር ፀንሳ፣ ከደምዋ ተከፍሎ፣ በምጥ በፃዕር
በጭንቅ የወለደችውን፣ 3 ዓመት ያጠባችውን፣ ሁሉን ታግሳ በንጽሕና ያሳደገችውን ልጇን ትረሳለችን? አትረሳም።
ዳሩ ግን ቢያንስ ሙቶ እንኳን አልቅሳ አልቅሳ ስታንቀላፋ በዕለቱም ቢሆን ትረሳለች። እግዚአብሔር ግን ይህ ሁሉ
በባሕርዩ የለበትምና አይረሳም። "እንግዲያውስ ስለምን አልተመለከትከንም ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን?
አንተም አላወቅኸንም?

ጥያቄ:- ስለምን ጦምን? አንተም አልተመለከትከንም ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን? አንተም አላወቅኸንም?

መልስ.......
ይቀጥላል
ከጸያሔ ፍኖት (በአባ ገብረ ኪዳን) ከገጽ 68-69 የተወሰደ
።።።።።።።
"ኹሌም በሄድኩበት የምናገረው አንድ ነገር አለኝ"!

ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም

ትዳር፣
ምልኩስና
፣ክህነት ናቸው።
እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው።
ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም።እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን
ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር ፣በተከበረ ምንኩስና፣በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ እንዴት ካልን፦

የተከበረ ትዳር" የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት: የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል። የተከበረው ትዳር መለሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል
።በዚህ ኡደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አኹን ግን ምንጩ ደፍርሷል። ለዚህም ኹላችንም
መስተካከል አለብን" አሁን እኔ ኹሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ!ተምረን ማግባትና፣ተምረን
መመንኮስም ሆነ ክህነት መያዝ ማስቀጠል አለብን።

ር/ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን

የቴሌግራም ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ
https://t.me/tsidq
###########
የርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች:
እግዚአብሔር የረሳን ለምን ይመስለናል?
1. እኛ ስለምንረሳው
የመከራ ጽናት የዘመን ብዛት እግዚአብሔር ረስቶኛል ብቻ ሳይሆን (ሎቱ ስብሐት) እግዚአብሔር የለምም
ያስብላል። የሰው ልጅ መከራው ጽኑ በሆነ ጊዜ፣ ዘመን በራቀበት ጊዜ፣ ለጥያቄው መልስ ባጣ ጊዜ በእነዚህ በሦስቱ
በሃይማኖት እንቅፋት ይገጥመዋል። ስለዚህ እግዚአብሔር ረስቶኛል፣ አይወደኝም ይልና ቀቢጸ ተስፋ ላይ ሲደርስ
ደግሞ እግዚአብሔር ባይኖር ነው እንጂ ቢኖርማ ማለት ይጀምራል። በመጨረሻም የለም ብሎ ይክዳል።
ሰይጣን ሰውን ወደ ምንፍቅና ወደ ክህደት የሚወስድባቸው 3 ቱን መንገዶች መጠንቀቅ ይገባል። ይህንን ይበልጥ
ለመረዳትም የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሀሳቦችን እንመልከት:-
👉ሀ. "ስለምን ጦምን? አንተም አልተመለከትከንም? ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን? አንተን አላወቅህም?"
(ኢሳ 58÷3)
እዚህ ላይ ጹመው ለጥያቄያቸው ምላሽ በማጣታቸው እግዚአብሔርን አልተመለከትከንም፣ አላወቅኸንም
እስከማለት ደርሰው ነበር። "የእግዚአብሔር ዓይኖች ምን ሆነው አልተመለከቱም?፣ አይወሰኑ ምሉዓን፣ አይሞቱ
ሕያዋን፣ አያዳሉ ጻድቃን ናቸው። ታዲያ ለምን አልተመለከትከንም አሉ?" ብንል መልሱ "ጥያቄያቸው ባለመመለሱ
እግዚአብሔር የተዋቸው የገፋቸው የረሳቸው መስሏቸዋል" የሚል ይሆናል።
የፈለጉትን በማጣታቸው በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት እግዚአብሔር የሌለ እየመሰላቸው ወዲያ ወዲህ
የሚቅበዘበዙ ወገኖች በዚህ ዘመንም አይታጡም። ግን እግዚአብሔር አላይ ብሎ ሳይሆን እኛ አንታይም አትየን
ብለነው ነው። "ገዳም ሄድኩ፣ ንስሐ ገባሁ፣ እጸልያለሁ፣ እጦማለሁ፣ በቅዱሳን አምናለሁ፣ እቆርባለሁ ነገር ግን
እስከዛሬ ከነበርኩበት ነኝ ምን ይሻለኛል?" የሚሉ ብዙዎች ናቸው። መልሱን ለእነዚህ ጦመኞች የመለሰውን እንስማ!
"በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትቾላለችን? አዎ እርስዋ
ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም" ይላል (ኢሳ 49÷15)። እናት 9 ወር ፀንሳ፣ ከደምዋ ተከፍሎ፣ በምጥ በፃዕር
በጭንቅ የወለደችውን፣ 3 ዓመት ያጠባችውን፣ ሁሉን ታግሳ በንጽሕና ያሳደገችውን ልጇን ትረሳለችን? አትረሳም።
ዳሩ ግን ቢያንስ ሙቶ እንኳን አልቅሳ አልቅሳ ስታንቀላፋ በዕለቱም ቢሆን ትረሳለች። እግዚአብሔር ግን ይህ ሁሉ
በባሕርዩ የለበትምና አይረሳም። "እንግዲያውስ ስለምን አልተመለከትከንም ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን?
አንተም አላወቅኸንም?

ጥያቄ:- ስለምን ጦምን? አንተም አልተመለከትከንም ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን? አንተም አላወቅኸንም?

መልስ.......
ይቀጥላል
ከጸያሔ ፍኖት (በአባ ገብረ ኪዳን) ከገጽ 68-69 የተወሰደ
እግዚአብሔር የረሳን ለምን ይመስለናል?
....እኛ ስለምንረሳው...

.... ከላይኛው የቀጠለ

ጥያቄ:- ስለ ምን ጦምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም?
መልስ:- እነሆ፥ በጦማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ። እነሆ፥
ለጥልና ለክርክር ትጦማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ
እንደምትጾሙት አትጾሙም።
እኔ የመረጥሁት ጦም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ
ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን ? በውኑ ይህን ጦም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ
የተወደደ ቀን ትለዋለህን?
እኔስ የመረጥሁት ጦም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥
የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው
ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥
የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።
የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። (ኢሳ 58÷3-8)

እግዚአብሔር ፍጥረቱን ዘንግቶ ሳይሆን ፍጥረት እግዚአብሔርን ሲዘነጋው እግዚአብሔር ረሳኝ ይላል።
እግዚአብሔርን ማግኘት ማለት ፈቃዱን ማግኘት ማለት ነው። እግዚአብሔርን ማግኘት ማለት ፈቃዱን ማግኘት
ከሆነ ፈቃዱን ለማግኘት መጀመሪያ የማይፈቅደውን ለይቶ መተው ይገባል። እግዚአብሔር የሚፈቅደውን ነገር
በማይፈቅደው መንገድ የቀረበ እንደሆነ አሁንም ረስተናል ማለት ነው።

አንድ ሰው ማር ይወዳል እንበል የሚወደውን ማር በሬት ለውሰን ከሰጠነው የሚወደውን በማይወደው መንገድ
ሰጠነው ማለት ነው። ይደሰት ዘንድ ወይን ለሚወድ ሰው በመርዝ ዕቃ የሰጠነው እንደሆነ ደስታውን ብቻ ሳይሆን
ሕይወቱንም ነጠቅነው ማለት ነው።
ለፍጡር እንዲህ ማድረግ መልካም ካልሆነ ለፈጣሪማ እንዴት?

እግዚአብሔር ጦም ይወዳል፤ ጦሙ ግን ግፍ፣ ዓመጻ፣ ዝርፊያ፣ ዝሙት፣ ደም ማፍሰስ፣ ዘፈን፣ ድልቂያ፣ ግፍን በተመላ
ሥጋ ካቀረብነው ፈቃዱን በማይፈቅደው ተቃወምነው ማለት ነው። እግዚአብሔር ምጽዋት ይወዳል፤ ምጽዋቱ ግን
ተዘርፎ የተሰጠ ከሆነ ማሩን በሬት አቀረብነው ማለት ነው። እግዚአብሔር ጸሎት ይወዳል፤ ጸሎቱ ቂም ቋጥሮ ከሆነ
መድኃኒቱን በመርዝ አቀረብነው ማለት ነው። እየቀማ ቢጦም ቆጠበ እንጂ ጦመ አይባልም ስለዚህ ፈቃደ
እግዚአብሔር ኂሩት፣ ቸርነት፣ ምሕረት፣ ፍቅር፣ ሰላም፣ ምጽዋት፣ ልግስና፣ ሃይማኖት፣ ጽድቅ ማለት ነው።

"ለምን ረሳኸኝ?" ላሉት እርሱ የመለሰው "መቼ ጠራችሁኝ?" ነው ያላቸው። ከላይ የዘረዘርናቸውን የጽድቅ
ተግባራት ከዘረዘረ በኋላ "ያንጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል" ነበር ያለው። ይህ ማለት እግዚአብሔርን
የምንጠራባቸው ሁለቱ አንደበቶች ንጽሕናና ምግባረ ሠናይ ናቸው ማለት ነው።

ስለዚህ ወዳጄ ሆይ! አንተ የረሳኸውን አስታውስ እንጂ እግዚአብሔር ረሳኝ አትበል። ስትጸልይ ቂም መያዝህን ረስተህ
እንደሆነ፣ ስትሰጥ ሰርቀህ እንደሆነ፣ ስትጦም ደም አፍስሰህ፣ ስትዘምር እየዘፈንህ እንደሆነ የረሳኸውን አስታውስ።
ለ. መከራ ሲጸና እግዚአብሔር የረሳቸው የሚመስላቸው እንዳሉ ቅዱስ ጳውሎስ በራሱ አስመስሎ እንዲህ ሲል
ገልጦታል:-
ይቀጥላል....
ከጸያሔ ፍኖት (በአባ ገብረ ኪዳን) ገጽ 70-71

You might also like