You are on page 1of 17

ተዋሕዶን እንወቅ።:

🌀 መራሕያን (ተውላጠ ስም)

ክፍል ፩

✝ ዐሠርቱ መራሕያን (The Ten Pronouns)

- መራሕያን ብሂል "መርሐ" እምዘይብል ግስ ዘተረክበ ውእቱ።


- መራሕያን ማለት "መርሐ" ከሚለው ግስ የተገኘ ነው ሲሆን መርሐ ማለት በአማርኛ መራ ማለት ነው። ሲበዙ
መራሕያን ይባላሉ። በልሳነ ግእዝ መራሕያን ዐሥር ናቸው።

- እሉኒ (እነሱም)፦

🔸ቀዳማይ መደብ

፩ . አነ = እኔ | I
፪ . ንሕነ = እኛ | We

🔸ካልዓይ መደብ

፫ . አንተ = አንተ | You


፬ . አንቲ = አንቺ | You
፭ . አንትሙ = እናንተ | You
፮ . አንትን = እናንተ (ለሴቶች) | You

🔸ሣልሳይ መደብ

፯ . ውእቱ = እሱ | He
፰ . ይእቲ = እሷ | She
፱ . ውእቶሙ = እነሱ | They
፲ . ውእቶን = እነሱ (ለሴቶች) | They
##😂😂#
🌀 መራሕያን (ተውላጠ ስም)

ክፍል ፪

🔶 በጾታ እንዘ ንትከፍሎሙ ለመራሕያን

➩ ዘተባዕታይ ጾታ (ወንድ)
• አንተ
• አንትሙ
• ውእቱ
• ውእቶሙ
➩ ዘአንስታይ ጾታ (ሴት)
• አንቲ
• አንትን
• ይእቲ
• ውእቶን

➩ ዘኲሉ (የወል) ለሁለቱም


• አነ
• ንሕነ

🔶 በኁልቁ (በቁጥር) እንዘ ንትከፍሎሙ ለመራሕያን

➩ ዘዋሕድ (ነጠላ)
• አነ
• አንቲ
• አንተ
• ውእቱ
• ይእቲ

➩ ዘብዙኅ (የብዙ)
• ንሕነ
• አንትሙ
• አንትን
• ውእቶሙ
• ውእቶን

🔶 በግብር እንዘ ንከፍሎሙ ለመራሕያን

➩ ዘቅሩብ (የቅርብ)
• አንተ
• አንቲ
• አንትሙ
• አንትን

➩ ዘርሑቅ (የሩቅ)
• ውእቱ
• ይእቲ
• ውእቶሙ
• ውእቶን

➩ ዘክልዔቱ (የወል)
• አነ
• ንሕነ
######
🌀 መራሕያን (ተውላጠ ስም)

ክፍል ፫

- መራሕያን ከግስ ጋር አብረው ሲመጡ የሚጨምሩአቸው ቅጥያ ፊደላት አሉ። እነርሱም፦

➩ አነ ▹ ( -ኩ)
ንሕነ ▹ ( -ነ)
ይእቲ ▹ ( -ት)

➩ አንተ ▸ ( -ከ)
አንቲ ▸ ( -ኪ)

➩ አንትሙ ▹ ( -ክሙ)
አንትን ▹ ( -ክን)

➩ ውእቱ ▸ (ግዕዝ ፊደል)


➩ ውእቶሙ ▹ (ካዕብ ፊደል)
➩ ውእቶን ▸ (ራብዕ ፊደል)

ምሳሌ፦ ዘመረ (ግስ) ▸ በዐሥሩ መራሕያን

፩ - አነ ዘመርኩ
እኔ አመሰገንኩ።

፪ - ንሕነ ዘመርነ
እኛ አመሰገንን።

፫ - ይእቲ ዘመረት
እሷ አመሰገነች።

፬ - አንተ ዘመርከ
አንተ አመሰገንክ።

፭ - አንቲ ዘመርኪ
አንቺ አመሰገንሽ።

፮ - አንትሙ ዘመርክሙ
እናንተ አመሰገናችሁ።

፯ - አንትን ዘመርክን
እናንተ አመሰገናችሁ።

፰ - ውእቱ ዘመረ (ግዕዝ ፊደል)


እሱ አመሰገነ።

፱ - ውእቶሙ ዘመሩ (ካዕብ ፊደል)


እነሱ አመሰገኑ።

፲ - ውእቶን ዘመራ (ራብዕ ፊደል)


እነሱ አመሰገኑ
######

🌀 መራሕያን (ተውላጠ ስም)

ክፍል ፬

ግስ፦ ሖረ ➛ ሄደ

◍ አነ ኀበ ቤተ ትምህርት ሖርኩ
እኔ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ።

◍ ንሕነ ኀበ ቤተ ትምህርት ሖርነ


እኛ ወደ ትምህርት ቤት ሄድን።

◍ አንተ ኀበ ቤተ ትምህርት ሖርከ


አንተ ወደ ትምህርት ቤት ሄድክ።

◍ አንቲ ኀበ ቤተ ትምህርት ሖርኪ


አንቺ ወደ ትምህርት ቤት ሄድሽ።

◍ አንትሙ ኀበ ቤተ ትምህርት ሖርክሙ


እናንተ ወደ ትምህርት ቤት ሄዳችሁ።

◍ አንትን ኀበ ቤተ ትምህርት ሖርክን (ለሴቶች)


እናንተ ወደ ትምህርት ቤት ሄዳችሁ።

◍ ይእቲ ኀበ ቤተ ትምህርት ሖረት


እሷ ወደ ትምህርት ቤት ሄደች።

◍ ውእቱ ኀበ ቤተ ትምህርት ሖረ
እሱ ወደ ትምህርት ቤት ሄደ።

◍ ውእቶሙ ኀበ ቤተ ትምህርት ሖሩ
አነሱ ወደ ትምህርት ቤት ሄዱ።
◍ ውእቶን ኀበ ቤተ ትምህርት ሖራ (ለሴቶች)
እነሱ ወደ ትምህርት ቤት ሄዱ።
########
መጠይቃዊ ቃላት ( WH-words )

ክፍል ፩

መጠይቃን ቃላት የምንላቸው ነገሮችን በፈለግነው መንገድ እንድንጠይቅ የሚያረጉን ናቸው። እነሱም (እሉኒ)
የሚከተሉት ናቸው።

• መኑ ➾ ማን | Who

• ምንት ➾ ምን | What

• ማእዜ ➾ መቼ | When

• አይቴ ➾ የት | Where

• አይ ➾ የቱ | Which

• እፎ ➾ እንዴት | How

• እስፍንቱ ➾ ስንት | How much


#############
መጠይቃዊ ቃላት ( WH-words )

ክፍል ፫

፪ . ለጠይቆተ ነገራት
(What - Asking things)

• ምንት ➾ ምን
• ምንተ ➾ ምንን

ምሳሌ

➛ ምንት መጽአ ናሁ?


(አሁን ምን መጣ?)
• ከልብ መጽአ።
(ውሻ መጣ። )

➛ ምንተ ታፈቅር ?
(ምንን ትወዳለህ?).
• አነ አፈቅር ግብር።
(እኔ ሥራ እወዳለሁ። )
➛ ምንት ገበርከ ናሁ ?
(አሁን ምን ሠራኸ?)
• ግብረ ቤት ገበርኩ።
(የቤት ሥራ ሠራሁ። )
➛ ምንት ገበርኪ ትማልም ?
(ትናንት ምን ሰራሽ?)
• አንበብኩ መጽሐፍ ትማልም።
(ትናንት መጽሐፍ አነበብኩ። )
➛ ምንት ተመሀርክሙ ትማልም?
(ትናንት ምን ተማራችሁ?)
• በእንተ አድዋ ተማሀርነ ትማልም።
(ትናንት ስለ አድዋ ተማርን። )
➛ ምንተ ታፈቅሩ አርድእት ?
(ተማሪዎች ምንን ትወዳላችሁ?)
• ንሕነ ናፈቅር ተውኔት።
(እኛ ጨዋታ እንወዳለን። )

መጠይቃዊ ቃላት ( WH-words )


ክፍል ፬
፫ . ለጠይቆተ ጊዜ
(When - Asking times)
• ማዕዜ - መቼ
• እስከ ማዕዜ - እስከ መቼ
ምሳሌ
➛ ማዕዜ ተወለድከ ?
(መቼ ተወለድክ)
• በወርኃ መስከረም።
(በመስከረም ወር)
➛ ማዕዜ ማዕዜ ውእቱ ትምህርተ ግእዝ?
(የግእዝ ትምህርት መቼ መቼ ነው)
• ዕለተ ሐሙስ ወ ዕለተ ዓርብ።
(ዕለተ ሐሙስ ና ዕለተ ዓርብ)
➛ ማዕዜ ውእቱ ፈተና ?
(ፈተና መቼ ነው)
• ጌሠም ውእቱ ፈተና።
(ፈተና ነገ ነው)
➛ ማዕዜ ተሐውሪ ኀበ ቤተ ክርስቲያን ?
(ወደ ቤተ ክርስቲያን መቼ ትሄጂያለሽ)
• በዕለተ ሰንበት።
(በዕለተ እሑድ)
➛ ማዕዜ ይመጽእ መምህር ?
(መምህር መቼ ይመጣል)
• ጌሠም ይመጽእ መምህር።
(መምህር ነገ ይመጣል)
➛ እስከ ማዕዜ ውእቱ ዘትመጽእ ?
(እስከ መቼ ነው የምትመጣው)
• እስከ ዘይመጽእ ወርኀ።
(እስከ ሚመጣው ወር)

መጠይቃዊ ቃላት ( WH-words )


ክፍል ፭

፬ . ለጠይቆተ መካን (ቦታ)


(Where - Asking place)
• አይቴ ➾ የት
• ኅበ አይቴ ➾ ወዴት
• እም አይቴ ➾ ከየት
ምሳሌ
➛ አይቴ ውእቱ ቤተ ትምህርትከ ?
(ትምህርት ቤትህ የት ነው)
• ጎንደር ውእቱ።
(ጎንደር ነው)
➛ አይቴ ይእቲ እምኪ ?
(እናትሽ የት ናት)
• አክሱም ይእቲ እምየ።
(እናቴ አክሱም ናት)
➛ አይቴ ተወለድኪ ?
(የት ተወለድሽ)
• አነ አዲስ አበባ ተወለድኩ።
(እኔ አዲስ አበባ ተወልድኩ። )
➛ ኅበ አይቴ ተሐውሪ ?
(ወዴት ትሄጂያለሽ)
• ኅበ ቤተ ትምህርት።
(ወደ ትምህርት ቤት)
➛ እም አይቴ መጻእከ ?
(ከየት መጣኸ)
• እም ቤትየ መጻእኩ።
(ከቤቴ መጣኹ)
➛ ኅበ አይቴ ተሐውር መርድእ ?
(ወዴት ትሄዳለህ ተማሪ)
• ኅበ ቤተ ትምህርት።
(ወደ ትምህርት ቤት)
ተዋሕዶን እንወቅ።:
መጠይቃዊ ቃላት ( WH-words )

ክፍል ፮
፭ . ለጠይቆተ ኲነት
(How - Asking process)

• እፎ ➾ እንዴት
ምሳሌ
➛ እፎ ኃደርከ ?
(እንዴት አደርክ)
• እግዚአብሔር ይሰባሕ።
(እግዚአብሔር ይመስገን፡)
➛ እፎ ወአልክሙ አርድእት ?
(እንዴት ዋላችሁ ተማሪዎች)
• እግዚአብሔር ይሰባሕ መምህር።
(እግዚአብሔር ይመስገን መምህር፡)
➛ እፎ ኀደርኪ ኦ እምየ ?
(እናቴ ሆይ እንዴት አደርሽ)
➛ ትምህርት እፎ ውእቱ ?
(ትምህርት እንዴት ነው)
• ሠናይ ውእቱ።
(ጥሩ ነው)
➛ ግብር እፎ ውእቱ ?
(ሥራ እንዴት ነው)
• ጥቀ ሠናይ ውእቱ።
(በጣም ጥሩ ነው፡)
➛ እፎ አንተ ?
(እንዴት ነኽ)
• ዳኅና አነ።
(ደኅና ነኝ)
➛ ሕይወት እፎ ውእቱ ወልድየ ?
(ሕይወት እንዴት ነው ልጄ)
• አኮ ሠናይ አቡየ።
(መልካም አይደለም አባቴ)

መጠይቃዊ ቃላት ( WH-words )


ክፍል ፯

፮ . ለጠይቆተ ኁልቁ
(How Many - asking quantity)
• ስፍን ➾ ስንት
• እስፍንቱ ➾ ስንት
• እስፍንተ ➾ ስንትን

ምሳሌ
➛ እስፍንቱ ውእቱ ዕድሜኪ ?
(ዕድሜሽ ስንት ነው)
• እስራ ውእቱ ዕድሜየ።
(ዕድሜዬ ሃያ ነው)
➛ እስፍንቱ ውእቶሙ አኀዊከ ?
(ወንድሞችህ ስንት ናቸው ?)
• ክልዔቱ ውእቶሙ።
(ሁለት ናቸው። )
➛ እስፍንቱ ሰዓት ውእቱ ናሁ ?
(አሁን ስንት ሰዓት ነው ?)
• ተስዓቱ ሰዓት ውእቱ ናሁ።
(አሁን ዘጠኝ ሰዓት ነው። )
➛ ስፍን ውእቱ ዝንቱ ?
(ይኸ ስንተ ነው ?)
• ዐሠርቱ ብር ውእቱ።
(ዐሥር ብር ነው። )
➛ እስፍንቱ አርድእት መጽኡ ዮም ?
(ዛሬ ስንቱ ተማሪዎች መጡ)
• ብዙኀኑ መጽኡ።
(ብዙዎቹ መጡ)
➛ እስፍንተ ሐዋርያተ ኀረየ ክርስቶስ ?
(ክርስቶስ ስንት ሐዋርያትን መረጠ)
• ዐሠርተ ወክልዔተ ሐዋርያተ።
(አሥራ ሁለት ሐዋርያትን፡)

ግስ ( Verb )
ክፍል ፫
✝ አርእስተ ግስ (Root Verbs)
፪. ቀደሰ ➾ አመሰገነ
- በመሀከል ያለው ፊደል ጠብቆ ይነበባል።
- ሦስት እና አራት ፈደላት አሉት።
- መነሻው ፊደል ግዕዝ ነው።
- መሀከል ላይ ያለው ፊደል ግዕዝም ሳድስም ይሆናል።

ቀ = ግዕዝ
ደ = ግዕዝ
ሰ = ግዕዝ
➜ የቀደሰ ቤት ለምሳሌ

• ➾ ፈጸመ = ጨረሰ
• ➾ ሐወጸ = ጎበኘ
• ➾ ሰብሐ = አመሰገነ
• ➾ ነጸረ = አየ
• ➾ አደመ = አማረ
• ➾ ዘሠረ = አመሰገነ
• ➾ ፈወሰ = አዳነ
• ➾ ኀለየ = አሰበ
• ➾ ተነበየ = ተናገረ
• ➾ ተመነየ = ተመኘ
• ➾ ተመገበ = በላ
• ➾ ተመክሐ = ተመካ
• ➾ ወለጠ = ለወጠ
• ➾ ወደሰ = አመሰገነ
• ➾ ከለለ = ጋረደ
• ➾ ጸውዐ = ጠራ
ግስ ( Verb )

ክፍል ፬

✝ አርእስተ ግስ (Root Verbs)

፫. ገብረ ➾ ሠራ

- ላልቶ ይነበባል።
- ሦስት ፈደላት ብቻ አሉት።
- መነሻው ፊደል ግእዝ ነው።
- መሀከል ያለው ፊደል ሳድስ ነው።

ገ = ግእዝ
ብ = ሳድስ
ረ = ግእዝ

➜ የገብረ ቤት ለምሳሌ
• ➾ ከብረ = ከበረ
• ➾ አምነ = አመነ
• ➾ መጽአ = መጣ
• ➾ ሰምዐ = ሰማ
• ➾ ወድቀ = ወደቀ
• ➾ ሰክረ = ሰከረ
• ➾ ለብሰ = ለበሰ
• ➾ መስየ = መሸ
• ➾ ከርመ = ከረመ

• ➾ ደክመ = ደከመ
• ➾ ቀርበ = ቀረበ
• ➾ ቀድሐ = ቀዳ
• ➾ ነግሠ = ነገሠ
• ➾ ሰፍሐ = ሰፋ
ተዋሕዶን እንወቅ።:
ግስ ( Verb )

ክፍል ፭

✝ አርእስተ ግስ (Root Verbs)

፬. ተንበለ ➾ ለመነ

- ላልቶ ይነበባል።
- አራትና ከዚያ በላይ ፈደላት አሉት።
- መነሻው ፊደል ግእዝ ነው።
- መኸከለኛው ፊደሉ ሳድስ ና ግእዝ አሉት።

ተ = ግእዝ
ን = ሳድስ
በ = ግእዝ
ለ = ግእዝ

➜ የተንበለ ቤት ለምሳሌ

• ➾ ሐንከሰ = አከማቸ
• ➾ አድለወ = አደላ
• ➾ ሰንበተ = አከበረ

• ➾ አመድበለ = አከማቸ
• ➾ አመስጠረ = አራቀቀ
• ➾ ገልገለ = ገላገለ
• ➾ ደምሰሰ = አጠፋ

፭. ባረከ ➾ ባረከ

- ሦስትና ከዚያ በላይ ፊደላት አሉት


- ላልቶ ይነበባል።
- መነሻ ፊደሉ ራብዕ ነው።

ባ = ራብዕ
ረ = ግእዝ
ከ = ግእዝ

የባረከ ቤት ለምሳሌ

• ➾ ሣረረ = ሠራ
• ➾ ፃመወ = ደከመ
• ➾ ማህረከ = ማረከ
• ➾ ባረወ = ቆፈረ
• ➾ ቃነየ = ደረደረ
• ➾ ሣቀየ = አናወጠ

፮. ክህለ ➾ ቻለ

- ሦስትና ፊደላት አሉት


- ላልቶ ይነበባል።
- መነሻ ፊደሉ ሳድስ ነው።

የክህለ ቤት ለምሳሌ

• ➾ ርእየ = አየ
• ➾ ልህቀ = አደገ
• ➾ ብህለ = አለ
• ➾ ርሕቀ = ራቀ
• ➾ ጥዕመ = ቀመሰ
• ➾ ንዕደ = አማረ

ግስ ( Verb )

ክፍል ፮

✝ አርእስተ ግስ (Root Verbs)

፯. ዴገነ ➾ ተከተለ

- ላልቶ ይነበባል።
- ሦስትና ከዚያ በላይ ፈደላት አሉት።
- መነሻው ፊደል ኃምስ ነው።

ዴ = ኃምስ
ገ = ሳድስ
ነ = ግእዝ

➜ የዴገነ ቤት ለምሳሌ

• ➾ ዜነወ = ነገረ
• ➾ ጼነወ = ሸተተ
• ➾ ሌወወ = ጠመጠመ
• ➾ ጤገነ = ጣደ
• ➾ ፄወወ = ማረከ
• ➾ ቴፈነ = ገረፈ
፰. ጦመረ ➾ ጻፈ

- ላልቶ ይነበባል።
- ሦስትና ከዚያ በላይ ፈደላት አሉት።
- መነሻው ፊደል (ሳብዕ) መጨረሻ ፊደል ነው።

ጦ = ሳብዕ
መ = ግእዝ
ረ = ግእዝ

➜ የጦመረ ቤት ለምሳሌ

• ➾ ሞጥሐ = ለበሰ
• ➾ ሞቅሐ = አሰረ
• ➾ ሎለወ = ጠበሰ
• ➾ ኖተወ = ዋጠ
• ➾ ሞፈደ = ጫረ
• ➾ ሞገደ = አወከ

📜 የግስ ጥናት 📜

•ክፍል (፩ )•

ከዚኽ በታች ያሉ ግሶች ሁሉም ላልተው እና ተነሥተው ይነበባሉ።

► መራ - መርሐ
► ደረሰ - በጽሐ
► አቀረበ - አውጽሐ
► ፈላ - ፈልሐ

► መዘነ - ጠፍልሐ
► አጨበጨበ - ጠፍሐ
► ፈታ - ፈትሐ
► ጮኸ - ጸርሐ

► አመሰቃቀለ - አመልትሐ
► ቆየ - ጸንሐ
► ረዘመ - ኖኀ
► ዘረጋ - ሰጥሐ
📜 የግስ ጥናት 📜

•ክፍል (፪)•
ከዚኽ በታች ያሉ ግሶች ሁሉም ጠብቀው እና ተነሥተው ይነበባሉ።

► ቀሰመ - አጣፈጠ
► ጸለለ - ጋረደ
► ቀበለ - ሸኘ
► ሐቀለ - ቀማ

► መከለ - ቆረጠ
► ኀየለ - በረታ
► የውሐ - አታለለ
► አምኀ - እጅ ነሣ

► ተፈሥሐ - ደስ ተሰኘ
► ነስሐ - ተጸጸተ
► ረውሐ - ቀደደ
► ለቅሐ - አበደረ
############
ተዋሕዶን እንወቅ።:
📜 የግስ ጥናት 📜 ክፍል ፲፩

ገብረ ላልቶ ይነበባል።

🔻 ግሱ ሲገሰስ

• ገብረ ➜ ሠራ፥ አደረገ

• ይገብር ➜ ያሠራል

• ይግበር ➜ ይሠራ ዘንድ

• ይግበር ➜ ይሥራ

• ገቢር /ገቢሮት/ ➜ መሥራት

• ገባሪ ➜ የሠራ

• ገባርያን ➜ የሠሩ ለወንዶች

• ገባሪት ➜ የሠራች

• ገባርያት ➜ የሠሩ ለሴቶች

• ግቡር ➜ የተሠራ
• ግብር ➜ ሥራ

• ግብረት ➜ አሠራር /አደራረግ/

• ምግባር ➜ በጎ ሥራ

• ተግባር ➜ ሥራ

📜 የግስ ጥናት 📜 ክፍል ፲፪

አእመረ ላልቶ ይነበባል።

➖ አእመረ ➜ አወቀ

• አእመረ ➜ አወቀ

• የአምር ➜ ያውቃል

• ያእምር ➜ ያውቅ ዘንድ

• ያእምር ➜ ይወቅ

• አእምሮ /አእምሮት/ ➜ ማወቅ

• አእማሪ ➜ አዋቂ

• አእማርያን ➜ አዋቂዎች ለወንዶች

• አእማሪት ➜ አዋቂ

• አእማሪያት ➜ አዋቂዎች ለሴቶች

• እሙር ➜ የታወቀ

• እምርት ➜ የታወቀች ለሴት

• እሙራት ➜ የታወቁ ለሴቶች

• ማእምር ➜ አዋቂ አሳዋቂ

• ማእምራን ➜ አሳዋቂዎች ለወንዶች

• ማእምርት ➜ አዋቂ ሴት
• ማእመራት ➜ አሳዋቂዎች ለሴት
########
📜 የግስ ጥናት 📜 ክፍል ፲፫

ባረከ ላልቶ ይነበባል።

➖ ባረከ ➜ ባረከ

• ባረከ ➜ ባረከ

• ይባርክ ➜ ይባርካል

• ይባርክ ➜ ይባርክ ዘንድ

• ይባርክ ➜ ይባርክ

• ባርኮ/ባርኮት/ ➜ መባረክ

• ባራኪ ➜ የባረከ

• ባራክያን ➜ የባረኩ

• ባራኪት ➜ የባረከች

• ባራክያት ➜ የባረኩ ለሴቶች

• ባራኪ ➜ የሚባርክ

• ቡራኬ ➜ ቡራኬ

• በረከት ➜ በረከት
######
📜 የግስ ጥናት 📜 ክፍል ፲፬

- ብህለ ከስምንቱ አርእስተ ግስ አንዱ ሲሆን ላልቶ ይነበባል።


- ብህለ በሳድስ ፊደል ተነስቶ በግእዝ ፊደል ይጨርሳል።
- የብህለ ቤቶች ሁሉ ከታች በተዘረዘረው ይወርዳሉ ይገሰሳሉ። ለምሳሌ፦ ስህወ፥ ጥዕየ፥ ምዕዘ፥

➖ ብህለ ➜ አለ

• ብህለ ➜ አለ

• ይብህል ➜ ይላል
• ይብሃል ➜ ይል ዘንድ

• ይብሃል ➜ ይበል

• ብሂል /ብሂሎት/ ➜ ማለት

• በሃሊ ➜ ያለ

• በሃልያን ➜ ያሉ

• በሃሊት ➜ ያለች

• በሃልያት ➜ ያሉ ለሴቶች

• ብሁል ➜ የተባለ

• በሃሊ ➜ የሚል

• ባህል ➜ አባባል

ከላይ በተሰጠው ምሳሌ መሠረት የብህለ ቤት የሆነውን ምዕዘ = ሸተተ የሚለውን ግስ ዘርዝሩ።

You might also like