You are on page 1of 3

የመጨረሻ የተሻሻለበት ቀን: 2012-11-07

መግቢያ

እንኳን ወደ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኦንላየን የንግድ ምዝገባ እና ፍቃድ አገልግሎት መስጫ ሲስተም
በሰላም መጡ! !

ይህ ደንብና ግዴታ (“ሕግ “፣ የአገልግሎት አጠቃቀም“) የወጣው በንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለተዘጋጀው
እና eTrade.gov.et ላይ ያለውን ሲስተም (በተናጠልም ሆነ በጋራ ለመጠቀም) ለማስተዳደር ነው።.

ይህ የሚስጥራዊነት ፖሊሲ እና ደንብና ግዴታ የእርስዎን የአገልግሎት አጠቃቀም ለማስተዳደር፣ መ/ቤቱ


መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ፣ እንደሚጠብቅ እና እንደሚቆጣጠር የተዘጋጀ ኤልክትሮኒክስ የስምምነት ሰነድ
ነው፡፡

በዚህ የኤሌክትሮኒክስ-ስምምነት ሰነድ ተስማምተዋል ማለት በሰነዱ ላይ በተጠቀሱት መመሪያና ደንብ


ለመገዛት አንበበውና ተረድተው፣ በሕጉ ለመገዛት ተስማምተዋል ማለት ነው። በዚህ ደንብና ግዴታ
ካልተስማሙ (ለመፈጸም ካልፈለጉ)፣ በሲስተሙ አገልግሎት ማግኝት አይችሉም። ቢሆንም ለምን መስማማት
እንዳልፈልጉ በ support@etrade.gov.et ላይ ኢሜይል ልከው ቢያሳውቁን ለማስተካከል እና መልስ ለመስጠት
ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን።

ይዘት

ይህ የኦንላየን አገልግሎት በንግድ ምዝገባና ፈቃድ የሚሰጡ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ይረዳዎታል። በዚህ
ሲስተም ዳታ ማስገባት፣ ማስተካከል እና አስፈላጊ ሰነዶችን ማያያዝ ይፈቅድሎታል። ወደዚህ ሲስተም
ለሚያስገቡት ማናቸውም መረጃዎች ሕጋዊነት እና ትክክለኝነት ሃላፊነቱን ይወስዳሉ። የንግድ እና ኢንዱስትሪ
ሚኔስቴር መረጃዎቹን የመቆጣጠር፣ የማስተካከል እና ሕጋዊነታቸውን በራሱ መንገድ የመፈተሽ እና የማጣራት
መብት አለው።

የተከለከሉ ተግባራት

ማንኛውም የሲስተም ተጠቃሚ እራሱም ሆነ ውክልና የሰጠው ሰው ከታች ከተጠቀሱት አንዱን ወይም
በጣምራ የፈጸመ እንደሆነ በኮሚፒዩተር አዋጅ ቁጥር 958/2008 እና የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ 980/2016
ከ 3 አመት እስከ 20 አመት እስራትና እንዲሁም ከብር 30,000.00 እስከ 300,000.00 ይቀጣል።
• ማንኛውም ተጠቃሚ ሆን ብሎ፣ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ስርአት፣
የኮሚፒዩተር ዳታ ወይም ኔትዎርክ ደራሽነት በከፊልም ሆነ በሙሉ ያገኘ እንደሆነ፣

• ማንኛውም ተጠቃሚ ሆን ብሎ፣ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ስርአት፣


የኮሚፒዩተር ዳታ ወይም ኔትዎርክ ደራሽነት በከፊልም ሆነ በሙሉ ያገኘ እንደሆነ፣

• ማንኛውም ተጠቃሚ ሆን ብሎ ሃሰተኛ ሰነድ ያያያዘ፣ የተሳሳተ የስራ አድራሻ ያስገባ ወይም ትክክለኛ ያልሆነ
ስራ አስኪያጅ ካስመዘገበ ከሆነ፣

• ማንኛውም ተጠቃሚ ሆን ብሎ፣ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፍቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ዳታን በማስገባት፣
በማሰራጨት፣ በማጥፋት ወይም በመለወጥ የኮምፒዩተር ስራአትን ወይም የኔትዎርክን መደበኛ ተግባር
በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ ያደናቀፈ፣ ያወከ፣ ያወደመ ወይም እንዲቋረጥ ያደረገ ከሆነ፣

• ሐሰተኛ መረጃ በማቅረብ በንግድ መዝገብ የተመዘገበ ወይም የንግድ ስሙን ያስመዘገበ ወይም የንግድ ሥራ
ፍቃድ ወይም የንግድ እንደራሴ ልዩ የምስክር ወረቀት ያወጣ ወይም የንግድ ሥራ ፍቃዱን ወይም የንግድ
እንደራሴ ልዩ የምስክር ወረቀቱን በሐሰተኛ መረጃ ያሳደሰ ወይም ለማውጣት ወይም ለማሳደስ ሙከራ ያደረገ
ከሆነ፣

• ማንኛውም ተጠቃሚ ሆን ብሎ ያለፍቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮሚፒዩተር ስርአትን፣


የኮምፒዩተር ዳታ ወይም ኔትዎርክ ደራሽነትን ማግኝት የሚያስችል የኮምፒዩተር ፕሮግራም፣ የሚስጥር ቁልፍ
የወሰደ ወይም የፈጠረ ከሆነ፣

• የሌላ ነጋዴን ወይም ሲስተም ተጠቃሚን መብት ወይም ጥቅም ለመጉዳት ወይም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው
ተገቢ ያልሆነ ማንኛውም መብት ወይም ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ የኮምፒዩተር ዳታ ወደ ሃሰት የለወጠ
ወይም ሃሰተኛ የኮምፒዩተር ዳታ ያዘጋጀ ከሆነ፣

• የንግድ ሥራ አድራሻ ለውጥ በአዋጁ መሠረት በወጣው ደንብ በተመለከተዉ የጊዜ ወሰን ውስጥ ለመዝጋቢው
መስሪያ ቤት ያላሳወቀ ከሆነ፣

• የሌላን ድርጅት፣ ግለሰብ ነጋዴ ወይም የድርጅቱ ሰራተኛ ወይም ሌላ መስሎ ሲስተም መጠቀም ወይም
ለመጠቀም የሞከረ ከሆነ፣

ማንኛውም ተጠቃሚ ከላይ ከተጠቀሱት አንዱን ወይም በጣምራ ሲፈፅም የተገኘ ማንኛውም ሰው የንግድ
ሥራ ሲያካሂድባቸው የነበሩ የንግድ ዕቃዎች፣ የአገልግሎት መስጫ ወይም የማምረቻ መሣሪያዎች መወረሳቸው
እንደ ተጠበቀ ሆኖ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የንግድ ምዝገባውን እና የንግድ ፍቃዱን ያግዳል ወይም ይሰርዛል።
የመጠቀሚያ ስም እና የይለፍ ቃል አጠቃቀም

በሲስተም ላይ የመጠቀሚያ ስም ሲፈጥሩ እድሜዎ 18 ዓመት እና ከዚህ በላይ መሆኑን፣ እንዲሁም የሚሰጡት
መረጃ ትክክለኛ፣ የተሟላ እና በጊዜው የቀረበ መሆኑን እርግጠኛ መሆን አልብዎት። ትክክለኛ ያልሆነ፣
ያልተሟላ ወይም ጊዜው ያለፈበት ከሆነ የይለፍ ቃልዎን እንዲሁም ጥያቄዎት ወዲያውኑ ይሰረዛል።

በዚህ ደንብና ግዴታ ተስማምተዋል ማለት በእርስዎ የመጠቀሚያ ስም እና የይለፍ ቃል በእርሶም ሆነ


በማንኛውም ሰው ለሚፈጸሙ ተግባራት ተጠያቂ ለመሆን ተስማምተዋል ማለት ነው። የይለፍ ቃልዎትን
በየጊዜው የመቀየር፣ ሰው እንዳያገኝው የመጥበቅ እንዲሁም የሚጠቀሙበትን ኮምፒዩተር ወይም የመጠቀሚያ
ስም የመጠበቅ ሃላፊነቱ የእርሶ ነው። የይለፍ ቃልዎ ከእርሶ እውቅና ውጪ እንደተቀየረ ካወቁ በፍጥነት
ለሚኒስቴር መ/ቤቱ በማሳወቅ እንዲቀየርሎት ያድርጉ።

የመጠቀሚያ ስም ሲፈጥሩ የሌላ ሰው ስም፣ የሌላ ድርጅት የንግድ ስም፣ የድርጅት ስም፣ በሕግ ያልተፈቀደ
ስም ወይም የሌላውን ሕጋዊ ሰው ስም የሚጻረር ስም አይጠቀሙ። በተጨማሪም ሌላውን የሚያስቀይም፣
የሚያናድድ ወይም የሚያስከፋ ስም አይጠቀሙ። ተገቢ ያልሆነ የመጠቀሚያ ስም ተጠቅመው ከተገኙ
ሚኒስቴር መ/ቤቱ አገልግሎቱን የመከልከል፣ የመጠቀሚያ ስሙን የመዝጋት እና የመሰርዝ መብቱ በሕግ
የተጠበቀ ነው።

You might also like