You are on page 1of 57

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲ

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር

ህዳር 2014
አዲስ አበባ
ማውጫ
መግቢያ 1
ክፍል አንድ...............................................................................................................................................................3
1.1 የፖሊሲ ማሻሻል አስፈላጊነት...............................................................................................................................3
1.2 ዕሳቤወች............................................................................................................................................................4
1.2.1 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ምንነትና ባህሪው.......................................................................4
1.2.1.1 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ምንነት እና ወሰን.............................................................4
1.2.1.1 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ባህሪያት.........................................................................5
1.2.2 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪና የሃገራችን ልማት.....................................................................6
1.2.3 ለማክሮ ኢኮኖሚ እድገት ያለው እስተዋጾ..............................................................................8
1.2.4 ለሃገራዊ ልማት ስኬት የሚኖረው ፋይዳ.................................................................................9
1.2.5 ዋና ዋና ማነቆዎችና መንስኤዎቻቸው.................................................................................11
1.2.5.1 የሌብነት ተግባርና ኢፍታዊ ተጠቃሚነት የሰፈነ መሆኑ...............................................11
1.2.5.2 የሙያ ብቃቱ የተረጋገጠና ምርታማ የሆን የሰው ኃይል እጥረት ያለ መሆኑ..................13
1.2.5.3 የፕሮጀክቶች ስራ አመራር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የተሳለጠ ያለመሆኑ......................14
1.2.5.4 ተወዳዳሪነትን ሊያጠናክር የሚችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር ያልተቻለ መሆኑ..................18
1.2.5.5 የግብዓቶች ጥራት ተወዳዳሪነትን የሚያሳልጥ እና ቀጣይነት ያለው የአቅርቦት ሰንሰለት
ያልተዘረጋ መሆኑ.....................................................................................................20
1.2.5.6 የፋይናንስና የማሽነሪ አቅርቦት በቂ ያለመሆኑ.........................................................22
1.2.5.7 የዘርፉ ዋና ዋና ባለሚናዎች በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ በጋራ የሚሰሩበት ሁኔታ
ያለመፈጠሩ.............................................................................................................23
1.2.5.8 የባለሙያዎች፣ የኩባኒያዎች፣የህንፃ ግንባታና መጠቀሚያ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር
አገልግሎት የተሳለጠ ያለመሆን..................................................................................26
1.2.5.9 ፈርጀ ብዙ ሥራዎች ተጣጥመው የሚታቀዱበትና የሚተገበሩበት ሥርዓት ያለመዘርጋቱ
27
1.2.5.10 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ፕሮግራም በተሟላና በቀጣይነት ያለመተግበር.....29
1.3 ርዕይ 30
1.4 ተልእኮ....................................................................................................................................30
1.5 ዓላማ...................................................................................................................................31
1.6 ስትራቴጂያዊ ግቦች..............................................................................................................31
ክፍል ሁለት.............................................................................................................................................................33
2 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ጉዳዮችና የአፈጻጸም አቅጣጫዎቻቸው....................................................33
2.1 የሌብነት አረንቋን ማድረቅና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በመፍጠር በጎ ገጽታ መገንባት ፣............33
2.2 ብቃት ያለዉ ፕሮፌሽናልና ባለሙያ የሚበቃበት አቅጣጫ በብቃት መፈጸም......................................34
2.3 በዘርፉ ቀልጣፋና ጠንካራ የገበያ ውድድር የሚያሰፍን አሠራር መዘርጋት................................36

i
2.3.1 ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ ቅልጥፍና እና ወጤታማነት የሚያረጋግጥ አሰራር ማስፈን.................36
2.3.2 ጠንካራ የገበያ ውድድርን የሚያሰፍን አሰራር ማንገስ............................................................42
2.3.3 የመረጃ ልማትና ቋት ማጠናከር............................................................................................44
2.4 የፕሮጀክቶች ሥራ አመራር እና የቴክኖሎጂ ዕድገት ድጋፍ ሰጪ ተቋም በማደራጀት ሽግግሩን
ማቀላጠፍ....................................................................................................................45
2.5 አስተማማኝ ግብዓት አቅርቦት ሠንሠለት እንዲዘረጋ ማድረግ..........................................................47
2.6 ዘመናዊና የተመቻቸ የፋይናንስና የመሣሪያዎች አቅርቦት ድጋፍ የሚሰጥበት ሥርዓት መፍጠር...............48
2.7 የዘርፉ ባለሚናዎች ለዘርፉ የተፋጠነ ዕድገት በጋራ የሚሰሩበትን አቅጣጫ መከተል.............................50
2.8 የባለሙያዎች፣ የኩባኒያዎች፣የህንፃ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥርና መጠቀሚያ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ
ሥርዓት ማጠናከር...........................................................................................................51
2.9 የፈርጀ ብዙ ሥራዎች ተጣጥመው የሚታቀዱበትና የሚተገበሩበት ሥርዓት መዘርጋት..........52
2.9.1 የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ....................................................................................................52
2.9.2 የኮንስትራክሽን ሠራተኞችና ሥራ አካባቢ ጤንነትና ደህንነት መጠበቅ.................................53
2.9.3 የኢንዱስትሪው በአካባቢ ደህንነት ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ መቀነስና መከላከል.................54
2.9.4 የስራ ዕድል ፈጠራን በማሳደግ ድህነትን መዋጋት...................................................................55
2.9.5 በኮንስትራክሽን ፕሮጄክት ሰራተኞችና በአካባቢው ማህበረሰብ የሚደርሰውን የ HIV/AIDS፣
ኮቪድ ስርጭት ጉዳት መቀነስና መከላከል......................................................................56
2.9.6 የህንፃና መሰረተ ልማት ግንባታ ሂደትና ዲዛይን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ፣..............57
5.10 የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ስራዎች ማስፈፀሚያ ዝርዝር የፕሮግራምና የህግ ማዕቀፍ
ወይም ፓኬጅ በመንግስት በማፅደቅ ተግባራዊ ማድረግ.................................................57
3.1 የፖሊሲው የተፈጻሚነት ወሰን.....................................................................................................................60
3.2 ፖሊሲውን የሚስፈጸም ተቋምና የባለድርሻዎች ሚና...............................................................................................60
3.2.1 የፌዴራል መንግስት............................................................................................................60
3.2.2 የክልል መንግስታት...............................................................................................................60
3.2.3 የከተሞች እና የገጠር ወረዳ አስተዳደሮች.............................................................................61
3.2.4 የግሉ ዘርፍ ሚና...................................................................................................................61
3.2.5 የዩኒቨርስቲና የምርምር ተቋማት ሚና.........................................................................................61
3.3 የአፈጻጸም ስልት............................................................................................................................................62
3.4 የፖሊሲ ክትትል፣የግምገማ እና የክለሳ ስርዓት.....................................................................................................62
3.5 የፖሊሲው ስርጭት.........................................................................................................................................62
3.6 ፖሊሲው ተፈጻሚ የሚሆንበት ጊዜ....................................................................................................................62
3.7 ማጠቃለያ..................................................................................................................................................63

ii
iii
መግቢያ
ኢትዮጵያን የመካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ እና የሀገሪቱ እድገት ‘‘የአፍሪካ የብልጽግና
ተምሳሌት” ለማድረግ ሀገራዊ ራዕይ ተሰንቋል፡፡ ከዚህ በመነሳት የኮንስትራክሽን የተሰነቀውን ሀገራዊ ራዕይ
ለማሳካት እና ዘርፉን በረዥም ጊዜ እይታ በመምራት ለሀገራዊ ልማቱ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ለማስቻል
እንዲሁም የኮንስትራክሽን ዘርፍ የአቅም ግንባታና የሬጉላቶሪና አቅም በማሳደግ የባለድርሻ አካላትን
በማስተባበርና በመደገፍ ቀልጣፋ፣ ምርታማ፣ ደህንነቱንና የተጠበቀና በክፍለ አህጉር ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ
የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ለመፍጠር የሚያስችል የተከለሰ የኮንስትራክሽን ፖሊሲ ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የተለያዩ ሀብቶችን ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት አስፈላጊ ወደሆኑ የግንባታ
ውጤቶች የሚለውጥ እና እሴት የሚፈጥር የኢኮኖሚ ዘርፍ ነው፡፡ ኢንዱስትሪው የአንድ አገር የማኅበራዊና
የኢኮኖሚ መሠረተ ልማት አገልግሎቶች፣ የህንጻዎችና ሌሎች የሲቪል ግንባታዎች የሚጠኑበት፣
የሚቀረፁበት፣ የሚታቀዱበት፣ የሚገነቡበትና አገልግሎት ላይ የሚውሉበትን ሂደት ያጠቃልላል፡፡
ኢንዱስትሪው መንግስታዊ፣ የግል ድርጅቶች፣ማህበራትንና ግለሰቦችን በባለቤትነት፣ በተቆጣጣሪነት፣
በአማካሪነት፣ በሥራ ተቋራጭነት፣ በግንባታ ዕቃዎችና መሳሪያዎች አምራችነትና አቅራቢነት፣ በፋይናንስ
አቅራቢነት እና በግብይት ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሚናዎች በሙሉ የሚሳተፉበት ዘርፍ ነው ፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚና የማህበራዊ መሠረተ-ልማት አውታሮችን እንዲሁም ፋብሪካዎችና


መኖሪያ ቤቶችን በማስፋፋት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና ሌሎች ዘርፎች እንዲስፋፉና እንዲለሙ በማድረግ
የአገሪቱን ኢኮኖሚ የሚያሳድግ ከመሆኑም በላይ ብዙ የፈጠራ ስራዎችና ሳይንሳዊ ግኝቶችም የሚከናወኑበት
የኢንዱስትሪ ዘርፍ ከመሆኑም ባሻገር የውጭ ምንዛሪም የማመንጨት ሚናም አለው፡፡ የአገር ውስጥ ሥራ
ተቋራጮችና አማካሪዎች በአግባቡ ከተደራጁ እና ተገቢውን የመወዳደር አቅም ከገነቡ ለውጭ የሥራ
ተቋራጮችና አማካሪዎች የሚከፈለውን የውጭ ምንዛሪ ማዳን እና ደረጃ በደረጃ በፈጠነ መንገድ ከአገር ውጭ
ተወዳድረው ሥራ በመሥራት የውጭ ምንዛሪ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በአማካኝ 45.8 በመቶ ዕድገት ያስመዘገበ ሲሆን
ለአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋፅኦም በ 2001 ከነበረበት 4.0 በመቶ በ 2010 ወደ 19.2 በመቶ
ማሳደግ ችሏል፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ባለፉት ዓመታት ፈጣን ዕድገት እንዲያሳይ በመንግስት በኩል የተለያዩ
እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ በስልጠና፣ በማሽነሪ አቅርቦትና ደጋፊ የአደረጃጀት መመሪያዎች በማውጣትና የስራ
ዕድል በመፍጠር መንግስት ሁኔታዎች ለማመቻቸት ጥረት አድርጓል፡፡ በዚሁ መሠረት መንግስት
በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ ፖሊሲ፤ አዋጆችን፣ ደንቦችን፣
መመሪያዎችን በማውጣት ለግል የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ዕድገትና በመንግስት ለተያዙ መሰል ድርጅቶች
ብቃት መሻሻል አመቺ ሁኔታ እንዲፈጠር ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ኢንዱስትሪው በበርካታ ችግሮች
የተተበተበ በመሆኑ ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ የተወሰዱ እርምጃዎች በቂ ሆነው በኢንዱስትሪው ውስጥ
መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የተጀማመሩ ስራዎች ቢኖሩም በቀጣይ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ በመንገድ

1
ሥራም ሆነ በህንፃ፣ በመጠጥ ውሃ፣ በመስኖ ወይም በሌላ የጠቅላላ ምህንድስና ግንባታ እና ዲዛይን እቅዶች
ለማስፈጸም የሚያስችል አቅም ኢኮኖሚው በሚጠብቀው ደረጃ አልተገነባም፡፡ በዚሁ ጉድለት ምክንያት
ቀጣይ ዕቅዶቻችንና የልማት ግቦቻችንን በወጣላቸው መርሃ ግብር፣ ወጪና የጥራት ደረጃ በማሳካት ፈጣን
የኢኮኖሚ ዕድገት ከማስመዝገብ አኳያ ያለው የማስፈፀም አቅም ጉድለት ዋነኛ እንቅፋት መሆኑ የማይቀር
ነው፡፡ የኢንዱስትሪው የግንባታ አፈፃፀም፣ ጥራት እንዲሁም የጊዜ አጠቃቀምና የወጪ ንረት አሳሳቢነቱ
እንደቀጠለ፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪን የሀገሪቱን የልማት ፖሊሲዎች ለማስፈፀም ዋነኛ መሣሪያ አድርጎ
ለመጠቀምና ለሚካሄደው አገራዊ የልማት ሥራ አጋዥ ዘርፍ ማድረግ እንዲቻል ለኢንዱስትሪው የተመቻቸ
የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ መፍጠር፣ በኢንዱስትሪው የሚሰማራውን የሰው ሃይል ብቃት ማሳደግ፣ አደረጃጀቱን
ማስተካከል፣ እንዲሁም የሌብነት አመለካከትና ተግባር ማስወገድ የሚችል ግልጸኝነትና ተጠያቂነት ያለው
የአሰራር ሥርዓት ዘርግቶ ኢንዱስትሪው በጠንካራ አመራር መምራት ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም በኢንዱስትሪው
መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣትና ሃገራዊ ርእዩን ለማሳካት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ብቁና ተወዳዳሪ
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለመገንባት የሚያስችል ይህ የተከለስ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ
ተዘጋጅቷል፡፡

2
ክፍል አንድ

1.1 የፖሊሲ ማሻሻል አስፈላጊነት

የኮንስትራክሽን ኢንዲስትሪ አገልግሎት ፍላጎት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በከፍተኛ ፍጥነት


እያደገ በመሄድ ላይ ሲሆን የአገር ውስጥ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አቅም ውስንነት ደግሞ
በግልጽ የሚታይ ነው፡፡ ኢንዱስትሪው በሌሎች ክፍለ-ኢኮኖሚዎች ዕድገትና ልማት ውስጥ
ከፍተኛ ሚና የሚጫወትና ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መሰረት ልማቶች ዝርጋታ እና ለሌሎች
ኢንቨስትመንቶች መስፉፉት ወሳኝ ሚና ያለው ነው፡፡ ኢንዲስትሪው ድህነትንና ሥራ አጥነትን
በማጥፋት፣ የውጭ ማንዛሪን በማዳንና በማሳደግ ረገድም የማይናቅ ሚና የሚጫወት እንደሆነ
ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም የሃገራች የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ባሉበት ውስብስብ ችግሮች ምክንያት
የሚጠበቅበትን ሚና በሚፈለገው ደረጃ ለመጫወት አልቻለም፡፡ በመሆኑም የሃገራዊ
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አቅም በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኘውን የኢንዲስትሪውን
ፍላጎት መሸፈን በሚችልበት ሁኔታ ማደራጀት ያስፈልጋል ፡፡

በመሆኑም በኢንዱስትሪው ለሚታዩ ቁልፍ ችግሮች መንስኤ የሆኑት ጉዳዮች ተቀርፈው


ዕድገቱ ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲጓዝ ለማድረግና ከሌሎች ዘርፎች ጋር ያለውን ትስስር
ለማጠናከር የአገሪቱን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የዕድገት አቅጣጫ ማመላከት የሚችል
የፖሊሲ ማዕቀፍ መቅረጽ አስፈላጊና ወቅታዊ ነው፡፡ ኢንዲስትሪው የሚመራት የፖሊሲ
አቅጣጫ መንደፍና መተግበር እየታየ ያለውን ዕድገት በአግባቡ ወደሚፈለገው አቅጣጫ
ለመምራት እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ለማድረግ
ያስችላል፡፡ እስካሁን ድረስ የተሟላ የፖሊሲ ማዕቀፍ ሳይኖር ሲሰሩ የቆዩት የአቅም ግንባታ
ሥራዎች በሚፈለገው የፖሊሲ አቅጣጫ ተቃኝተውና ፈር ይዘው እንዲቀጥሉ ለማድረግ
በመንግስት የታመነበት የፖሊሲ አቅጣጫ መኖሩ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡

እስካሁን ድረስ ባለው አፈጻጸም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ብዙ ያልተቀናጁ


ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ ሂደቱም በመስኩ ያሉ ማነቆዎችን አንጥሮ ለማውጣት እድል
ከመስጠቱም ባሻገር ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ስልቶችን ለመቃኘት መልካም አጋጣሚ
ፈጥሯል፡፡ ይህን የተገኘውን የብዙ ጥረቶች ድምር በተቀናጀ መልኩ በፖሊሲ አቅጣጫ
መምራትና ውጤቱም በሃገራዊ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ እድገት ላይ ዘለቄታዊ ተጽዕኖ
እንዲኖረው ማድረግ ተገቢና አስፈላጊም በመሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም ዘርፋ የሌሎች ክፍለ
ኢኮኖሚ እምብርት እንደመሆኑ መጠን ወጥ የሆነ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትንና ግቦችን
ያማከለ ፖሊሲ እንዲኖረው የግድ ስለሚሆን ነው፡፡ ስለሆነም ይህ የፖሊሲ ማዕቀፍ በመንግስት
ተዘጋጅቶ መውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
1.2 ዕሳቤወች
ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ በመንግስት ቅድሚያ ለተሰጣቸው ዘርፎች ማለትም የትምህርት፣
የጤና፣ የትራንስፖርት፣ የመኖሪያ ቤት፣ አቅርቦት፣የውሃ አቅርቦት፣ የግብርና፣ የማኑፋክቸሪንግ፣ የቱሪዝም፣
የማዕድን፣ የኃይል አቅርቦት፣ የመሬትና መልካም አስተዳደር ዓላማና ግብ ለማሳካት ጠንካራ ብቃት ያለው

3
ተወዳዳሪ ሃገር በቀል የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መኖርና ጥራት ያለው አቅርቦት ለተገልጋዮቹ ማድረስ
መቻል ወሳኝ መሆኑን ከግምት ውስጥ ያስገባል ፡፡ በየአስተዳደር እርከኑ በግልና በመንግስት ተቋማት በኩል
በሚከናወኑ ኢንቨስትመንቶች አዳዲስ ግንባታዎችን እንዲሁም መልሶ የማልማት ሥራ በተጓዳኝ በማከናወን
የሁሉንም ሴክተር እድገት በታቀደዉ መሠረት እንዲሆን ለማድረግ የሃገር በቀል ተቋማት ተሳትፎና የላቀ
አፈጻጸም ወሳኝ ይሆናል፡፡ በዚሁም መሰረት እስከ 2022 ባለው ጊዜ የፖሊሲው አቅጣጫ ሃገር በቀል
የኮንስትራክሽን ተዋናዮች በሰፊው በግንባታ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ተወዳዳሪ
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መገንባት ላይ ያተኩራል፡፡ በመሆኑም የፖሊሲው ርዕይ ና ዓላማዎች ከዚህ በታች
የቀረቡት እንዲሆኑ ተደርጓል ፡፡

1.2.1 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ምንነትና ባህሪው

1.2.1.1 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ምንነት እና ወሰን

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የተለያዩ ሀብቶችን ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት አስፈላጊ ወደሆኑ


የፊዚካልና ኢኮኖሚያዊ መሠረተ ልማቶች እና የግንባታ ውጤቶችን የሚለውጥ እና እሴት የሚፈጥር
የኢኮኖሚ ዘርፍ ነው፡፡ በዚህ ለልማት ወሳኝ የኢንዱስትሪ ዘርፍ የኢኮኖሚና የማህበራዊ የመሠረተ ልማት
አገልግሎቶች እንዲሁም ፋብሪካዎችና መኖሪያ ቤቶች ከተያያዥ ልማቶቹ ጋር የሚጠኑበት፣ የሚታቀዱበት፣
የሚቀረፁበት፣ የሚጠገኑበት፣ ነባር ግንባታዎች ተስተካክለው ሌላ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚቀየሩበት፣
የሚገነቡበትና አገልግሎት ላይ የሚውሉበትን ሂደት ያጠቃልላል፡፡

የሚገነቡ የኢኮኖሚ መሠረተ ልማቶችም የመኖሪያና የመስሪያ ህንፃዎችን፣ ከትራንስፖርት አውታሮች ጋር


የተያያዙ አውራ መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ የባቡር ሐዲዶችንና የገጠር መንገዶችን፣ የኃይል ማመንጫዎችንና
ማስተላለፊያ መስመሮችን፣ የስልክ ማስተላለፊያ መስመሮችን፣ የመስኖ ልማት ግንባታዎችን፣ የግድብ
ግንባታዎችንና የንፁህ ውሃ አቅርቦትን፣ የፍሳሽ ማስወገጃና ማጣሪያ ግንባታዎችን፣ የጤና ተቋማት ግንባታ፣
የትምህርት ተቋማት ግንባታ፣የማረፍያና የመዝናኛ ሕንጻዎች ግንባታን፣ የንግድ ሕንፃዎች ግንባታን፣
የማምረቻና የማከማቻ መጋዘኖች ግንባታን፣ የሐይማኖት ተቋማት እና ማምለኪያ ሕንፃዎች ግንባታን፣
የሕዝብ ደህንነት መቆጣጠሪያ ሕንፃዎች ግንባታን፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ግንባታ እና የመሳሰሉትን
ያካትታል ፡፡

ኢንዱስትሪው መንግስታዊና የግል ድርጅቶችን እንዲሁም ኩባንያዎችን፣ የግንባታ ባለቤቶችን፣ በአማካሪነት


የሚሰሩ ድርጅቶችንና ባለሙያዎችን፣ ሥራ ተቋራጮችን፣ የፋይናንሻል ተቋሞችን፣ የግንባታ ዕቃዎች
አምራቾችን፣ በምህንድስና ዕቃዎችና መሣሪያዎች አቅራቢነት እና በግብይት ሥራ ላይ የተሰማሩ አካላትን፣
የግንባታው ተጠቃሚ ድርጅቶችና ግለሰቦች፣ የግንባታ መሠረት ልማት አቅራቢ ተቋማት፣ የግንባታ ፍቃድ
የሚሰጡና የሚቆጣጠሩ ተቋማት እና ከእነዚህ አካላት ጋር የተያያዙትን ያጠቃልላል ፡፡

የኮንስትራክሽን ዋጋ ብለን የምናሰላው ደግሞ ለግንባታ የዋሉ የግብዓት ዋጋዎችን፣ የመሠረታዊ አገልግሎቶች
አቀርቦት (Utilities) ዋጋዎችን፣ በግንባታው ላይ ለተሰማሩ የጉልበት ሰራተኞች፣ ባለሙያዎችና አመራሩ
የሚከፈለው ክፍያ፣ በኮንስትራክሽን ስራው ላይ ለሚሰማራው ማሽነሪ የሚከፈለው የአገልግሎት ዋጋ፣

4
የአርክቴክቱና የመሃንዲሱ የአገልግሎት ክፍያ፣ የህንጻ ተ s ራጩና የአማካሪው የትርፍ ህዳግ፣ የአስተዳደራዊ
ወጪዎች እና ለኮንስትራክሽን ስራው ለዋለው ብድር የሚከፈለው ወለድና የመንግስት የግብር ክፍያን
ባጠቃላይ በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ በስራ ላይ የዋለ የገንዘብ ድምር መሆን ይኖርበታል ፡፡

1.2.1.1 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ባህሪያት

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በልማት እንቅስቃሴአችን ውስጥ በማደግ ላይ የሚገኝ፣ የመጀመሪያ


ኢንቨስትመንት በመሆን ከፍተኛ የስራ ዕድል የሚፈጥርና ለሃገራችን ኢኮኖሚ ልዩ ሚና የሚጫወት
ጠቀሜታቸውን የጎላ ኢንዱስትሪ ነው፡፡ በተዘጋጀው የአስር አመት እቅድ ከ 2013-2022 ውስጥ
የኮንስትራክሽን ዘርፍ የማይገባበት ስራ የለም ማለት ይቻላል፡፡ እንደ መንገድ፣ የባቡር መስመር፣ የአውሮፕላን
ማረፍያ፣ የወደብ፣ የኃይል ማመንጫና ስርጭት፣ የቴሌኮሙኒኬሽን መስመርና ስርጭት፣ የውሃ ልማት፣ የቆሻሻ
ማስወገጃ መስመር…ወዘተ ያሉ የኢኮኖሚ መሠረተ-ልማቶች መዘርጋት ከተፈለገ የኮንስትራክሽን
ኢንዱስትሪ ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ እንደ ትምህርት ቤቶች፣ የሕክምና ቤቶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ
ቦታዎች እና ቤቶች፣ የመናፈሻና መዝናኛ ቦታዎች እና ቤቶች…ወዘተ ያሉ የማህበራዊ መሠረተ-ልማት
ተቋሞችን እናስፋፋ ከተባለ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ቁልፍ ይሆናል ማለት ነው፡፡ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ
እናስፋፋ፣ እናጠናክር ከተባለ ከፋብሪካዎች ግንባታ ወጪ ከ 30 በመቶ እስከ 60 በመቶ የሚደርሰው
የኮንስትራክሽን ስራው ወጪ በመሆኑ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ቁልፍ ድርሻ ይኖረዋል ማለት ነው ፡፡

በከተማና በገጠር ያለው ሕዝብ ኑሮ ይሻሻል ስንል ለኑሮ መሠረታዊ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ የሆነው የመኖሪያ
ቤቶችን መገንባትና ተደራሽ ማድረግ ስለሚሆን በዚህ ረገድም የኮንስትራክሽን ሚና የላቀ ይሆናል፡፡
በየትኛውም የኢኮኖሚ ዘርፍ ፈጣንና ተከታታይ ዕድገት ለማምጣት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን አቅም
ማጎልበት ወሳኝ ያደርገዋል ፡፡
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለሌሎች ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ሞተርና ማዕከል እንደመሆኑ መጠን
ቀጣይነት ያለው ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት መሳካት የላቀ ሚና ስለሚኖረው የሃገር በቀል ባለሃብቶችና
ባለሙያዎች ተሳትፎ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ከዚህ አንጻርም ቀጥተኛ ያልሆነ ተጽእኖ
በአጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ላይ እንደሚኖረው መገመት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ጠንካራ የኮንስትራክሽን
ኢንዱስትሪ ለመገንባት በሌሎች የማክሮ-ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች መደገፍና የዘርፉን ብቃትና ተወዳዳሪነት
በሚያጎለብት መልኩ መቃኘት ይኖርባቸዋል፡፡

ከሌሎች ሃገሮች ልምድ መረዳት እንደሚቻለው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ እድገት በተገቢው ደረጃ
ለማምጣት እና ከኢንዱስትሪው የሚጠበቀውን ተልዕኮ እንዲወጣ የመንግስት ቁርጠኝነትና ዘለቄታዊነት
ያለው ልማታዊ ድጋፍ እንደሚጠይቅ እንዲሁም ምቹ የሆነ የአሰራር ሥርዓት ማስፈን እና ይህንኑ
የሚያስፈጽም ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር እንደሚያስፈልግ ግንዛቤ ሊወሰድበት የሚገባ ጉዳይ ነው ፡፡

1.2.2 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪና የሃገራችን ልማት

በሃገራዊ ልማት በማፋጠን ድህነትን ለማስወገድና የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታ በቀጣይነት ለማሻሻል ሁሉን አቀፍ
ክፍለ ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽን በማምጣት ሀገራችን ወደ መካከለኛ ገቢ ካላቻዉ አገሮች ለማሰለፍ

5
የምትችልበት የአስር አመት ዕቅድ ተነድፎ የትግበራ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡ የአንድ ሃገር የእድገት ደረጃ
የሚለካው የማህበራዊ መሠረተ ልማቶችና የኢኮኖሚ መሠረተ ልማቶች መንግስት ለህዝቡ በሚያቀርበው
ጥራትና ተደራሽነት እንዲሁም የሀገሪቱ ዜጋ ምርቶችና አገልግሎቶች ለመግዛት የሚኖረው የገቢ ድርሻ ምጣኔ
ፍትሃዊ ሲሆን መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሠረት ባለፉት ዓመታት ሀገራችን ዕድገት በማስመዝገብ የገጠሩ
ሕዝብ የግብርና ምርታማነቱን በማሻሻል የከተማ ነዋሪው ደግሞ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች
በመሰማራት የህዝቡ ገቢ እንዲሻሻል በተደረገው ጥረት ውጤት ተመዝግቧል፡፡ ሀገራችን የማህበራዊና
የኢኮኖሚ መሠረተ ልማቶች በማስፋፋትና ተደራሽ በማድረግ የምዕተ-ዓመቱን ግቦች ማሳካት በሚቻልበት
ደረጃ ስራ በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡ እነዚህ ውጤቶች የተመዘገቡት መንግስት የሕዝቡን ተሳትፎና
ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ልማታዊ ስትራቴጂዎች በመንደፉና ለተግባራዊነታቸው በቁርጠኝነት በመረባረቡ
ነው፡፡ የእነዚህ የማህበራዊና የኢኮኖሚ የመሠረተ ልማት ዕቅዶች ለማስፈጸም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው
ተልዕኮ ግልጽ ነው፡፡ ይህን ከማስፈጸም አኳያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበትም
ይታመናል፡፡ በአንፃሩ ኢንዱስትሪው ይህን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት በቅድሚያ የራሱን አቅም ማሳደግ
ይጠበቅበታል፡፡

በዚህ ረገድ መንግሥት ሃገራዊውን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አቅም በተለይ በኢንዱስትሪው የተሰማሩ
ተዋናዮችን አቅም ከመገንባት አንጻር ሰፊ ጥረቶችን አድርጓል፡፡ በ 1998 እንዲሁም በ 2003 የኮንስትራክሽን
ሴክተሩን በበላይነት እንዲመራ የቀድሞውን የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የአሁኑን የከተማ ልማት፤
ቤቶችና የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በአዲስ መልክ አደራጅቷል፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የማስፈጸም
አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችና ፕሮግራሞች ነድፎ ተግብሯል፡፡ በ 1994 በወጣው
የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሚና በግልጽ አመላክቷል፡፡ በዚሁ መሠረት
የኮንስትራክሽን ሴክተር አቅም ግንባታ ፕሮግራም (ECBP) ተዘጋጅቶ በተለይ በሰው ኃይል ልማትና
በኢንዱስትሪው ውስጥ ለተሰማሩ ተ s ራጮችና አማካሪዎች በማሽነሪና በስልጠና ድጋፍ በማድረግ
እንዲጠናከሩ ጥረት ተደርጓል፡፡ በኢንዱስትሪው የነበረውን የሰው ኃይል እጥረት በማገናዘብ ባለሙያዎች
ተደራጅተው በኮንትራክተርነትና በአማካሪነት መሳተፍ የሚያስችላቸው የስልጠና፣ የማሽነሪ፣ የመስሪያ
ካፒታልና የገበያ ዕድል እንዲመቻችላቸው ተደርጎ ወደስራ ቢገቡም በአብዛኛዉ ቀጣይነት አልነበራቸዉም፡፡
ወደ ዩኒቨርስቲ ከሚገቡ ተማሪዎች 70 በመቶ ወደ ሳይንስ እና 30 በመቶ ወደ ሶሻል ሳይንስ እንዲመደቡ ግብ
ተጥሎ እና ኢንዱስትሪው በቀጣይነት እንዲያድግ በተፈጥሮ ሳይንስ ከተመደቡት 70 በመቶ ተማሪዎች ውስጥ
4 ዐ ከመቶዎቹ የኢንጅነሪንግ ፕሮፌሽን ቅበላ ስብጥር ፖሊሲ ወጥቶ እንዲተገበር ቢደረግም የሰዉ ኃይሉን
ችግር ከመፍታት ይልቅ በርካታ ስራ አጥ ተመራቂዎችን አፍርቷል ፡፡ በቴክኒክና ሙያ ተቋማትም የመለስተኛ
ሙያ ዘርፎች ተጠንተው ስልጠና በስፋት መስጠት ተጀምሯል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ጥረቶች በመስኩ
በመካሄዳቸው የተሻሉ ለውጦች በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው መታየት ጀምሯል፡፡

ሃገራችን በምትገኝበት የዕድገት ደረጃ ቀላል የማይባሉ የኮንስትራክሽን ልማት ሥራዎች የሚከናወኑት
በመንግስት በጀት እንደሆነ ይገመታል፡፡ የግሉ ዘርፍ ያለመጠናከርና ኢኮኖሚው ያለበት ደረጃ አሁንም በወሳኝ
የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች ማስፋፋት የመንግስትን ልማታዊና የተመረጠ ጣልቃ ገብነት መጠየቁ ግልፅ
ነው፡፡ ስለዚህ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ሞተር በመሆኑ በማስፈፀም አቅም

6
ግንባታ ረገድ የተጀመረውን ጥረት በላቀ ደረጃ ማስቀጠል ወሳኝ የመንግስት ኃላፊነት ሆኖ መቀጠሉ
አያጠያይቅም፡፡

1.2.3 ለማክሮ ኢኮኖሚ እድገት ያለው እስተዋጾ

በሃገራችን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከመንግስትና ከግሉ ዘርፍ ብዙ መዋለ ነዋይ የሚመደብለት አበይት
የኢኮኖሚ ዘርፍ ነው፡፡ በመግቢያው እንደተገለጸው የኮንስትራክሽን ዘርፉ በሀገራችን እየተመዘገበ ባለው
ልማት ምክንያት በየዓመቱ በአማካይ የ 45.8 በመቶ ዕድገት ሲያሳይ ከጠቅላላው የአገር ውስጥ ምርት ያለው
ድርሻም ወደ 19.2 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በኢትዮጵያ
በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት እንዲሁም በሚካሄዱት መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ከፍተኛ ግንባታዎች
አማካኝነት በከፍተኛ ቁጥር ለሚገመት የሠው ኃይል የሥራ እድል በመፍጠር ድህነትን ከመዋጋት አኳያ ከፍተኛ
ሚና እየተጫወተ ነው፡፡

በሌላ በኩል መንግሥት በዘርፉ ግዙፍ የመሰረተ-ልማት ዝርጋታ ግብ በመንደፍ በተለይም ለመንገድ፣ ለባቡር
መስመር፣ ለአውሮኘላን ማረፍያ፣ ለኃይል ማመንጫ፣ ለትምህርትና ለጤና ተቋማት፣ ለመስኖ እና መጠጥ ውሃ
አቅርቦትና ፍሳሽ ማስወገድ ስራ ከፍተኛ የሆነ በጀት በየዓመቱ እየመደበ ይገኛል፡፡ ከዚህ አኳያ በፈጣን እድገት
ላይ ያሉ ሃገሮች ለግንባታ የሚያወጡት አመታዊ ወጪ የዳበረ ኢኮኖሚ ካላቸው ጋር ሲነፃፀር ከእጥፍ በላይ ከፍ
ባለ ተነፃፃሪ ምጣኔ የሚያድግ በመሆኑ ለሃገራዊ ምርት እድገት የሚያበረክተው ድርሻም የዚያኑ ያህል
እየጨመረ እንደሚሄድ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ በዚሁ መሠረት የሀገራችን ኢኮኖሚ ዓመታዊ አጠቃላይ ምርት
እድገት እና በኮንስትራክሽን ምርት መካከል ያለውን ትስስር አብረው በተደማሪነት እያደጉ እንደሚሄዱ
መገንዘብ ይቻላል ፡፡

በመሆኑም የሃገራችን የዘርፉ አወቃቀር ይህንን ተልዕኮ ለመወጣት በሚያስችለው ደረጃ ላይ መገኘቱ መረጋገጥ
ይኖርበታል፡፡ ዕቅዳችን የተነደፉት የልማት ኘሮግራሞች የሀይል ማመንጨት፣ ሠፋፊ የመስኖ ልማት፣ የግድብ
ግንባታዎች፣ የካናል፣ የመኖሪያና የገበያ ማዕከላት፣ የጤና ተቋማት፣ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ግንባታ፣
የትምህርት ተቋማት፣ የመኖሪያ ቤቶች፣ትራንስፖርት አውታሮች (የአስፋልት መንገዶች፣ የባቡር
ሐዲዶች፣አየር መንገድ)፣ የስፖርት ማዘዉተሪያ ተቋማት፣ ኢንደስትሪ ፓርኮች፣ የገጠር መንገዶች እንዲሁም
የከተማና ገጠር ንፁህ ውሃ አቅርቦት የልማት ሥራዎቻችን ምላሽ የሚሰጠው በዚሁ ዘርፍ በመሆኑ
የሚስተዋለውን ከውጤትና ቅልጥፍና እንዲሁም የሚፈጠረው እሴት ዋጋ ተመጣጣኝነት እና ከሚወጣው
ወጪ ጋር የተያያዙ የማስፈፀም አቅም ክፍተት መሙላት የርብርብ ማዕከል ማድረግ የወቅቱ አጀንዳ መሆን
አለበት፡፡
የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዕድገት ከሲሚንቶ ጀምሮ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን እጥረትና የዋጋ መናር
እንደሚፈጥር ይታወቃል፡፡ ይህ እጥረት ከአጭር ጊዜ አንጻር በፕሮጀክት ዋጋዎች ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠረ
ቢሆንም ከረዥም ጊዜ አንጻር ደግሞ ቀጣይ ፍላጎት በመፍጠር ለአቅርቦት መነሳሳትና መስፋት መልካም
አጋጣሚ ፈጥሯል፡፡ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በአገር ዉስጥ ምርቶች አለመተካት በአቅርቦት በኩል

7
የነበረው ችግር አለመቀረፉ ፕሮጀክቶችን አፍጻጸ ከማስተጓጐልም በላይ የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ የዋጋ
አለመረጋጋት እንዲቀጥል የበኩሉን አስተዋጾ አበርክቷል፡፡

የኮንስትራክሽን ዘርፉ ስራ እየሰፋና እያደገ ሲሄድ በዘርፉ የሚሰማራው ዜጋ ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ግልጽ
ነው፡፡ የሚመደበውም በጀት ከስራው ስፋት አንጻር እየጨመረ መሄዱም የማይቀር ነው፡፡ በዚሁ መሠረት
ለኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የምናወጣው ገንዘብ ወደ ሰራተኛው ገብቶ ለፍጆታ በመዋል የዋጋ ግሽበት ጫና
ከሚፈጥር ይልቅ ቢያንስ የተወሰነው ክፍል እንዲቆጠብ ለማድረግ መስራት የሚቻልና ተገቢም ይሆናል፡፡
አብዛኛው የጉልበት ሰራተኛ ወይም የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋሞች አዲሱም ይሁን ነባር የራሳቸው
ኢንተርፕራይዝ ለማቋቋም ብዙም መነሻ ካፒታል ስለማይኖራቸው ብድር ስጡን ማለታቸው አይቀርም፡፡ ይህ
የቁጠባ ባህልን ከመጉዳቱም ባሻገር ያለዋስትና የሚሰጥ ብድር እንዲስፋፋና ያለመመለስ አደጋ እንዲስፋፋ
እያደረገ ነው፡፡ በምትኩ በነዚህ ስራዎች የሚሰማራ ሰው ሁሉ ከሚያገኘው ገቢ ውስጥ የተወሰነውን
እንዲቆጥብ የሚያበረታታ ሥርዓት ብንፈጥር እና በዚህ መልኩ ዜጎች የቆጠቡት ገንዘብ ተቋም ለመፍጠር
ወይም ለማስፋፋት ሲፈልጉ ተጨማሪ ብድር እንደሚያስገኝላቸው ተደርጎ ቢቀረጽ ቁጠባን ለማዳበርና የዋጋ
ግሽበት ጫናን ለመቀነስ እንደሚረዳ ግልጽ መሆን አለበት፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ተ s ራጮችን በዚህ መልኩ ቆጥቡ
በማለት ማስፈጸም ብዙ የማያሠራን ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁንና የማሽነሪ ፍላጎታቸውን ለማርካት በሊዝ ወይም
በብድር የምንሰጣቸው ከሆነ ከገቢያቸው እየተቆረጠ ለክፍያ እንዲውል ቢደረግ ቢያንስ የዋጋ ግሽበት ጫና
(ተዘዋዋሪ ጉዳቱን) መቀነስ ይቻላል፡፡ በዚህ ዓይነት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ወደ መካከለኛና
ትላልቅ ተ s ራጭነት እንዲሸጋገሩ እና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ለአጠቃለይ የኢኮኖሚ ዕድገቱ ተደማሪ
ውጤት እንዲያስመዘግብ የተቀናጀ ስራ መስራት ይጠይቃል፡፡

1.2.4 ለሃገራዊ ልማት ስኬት የሚኖረው ፋይዳ

ኢትዮጵያ በ 2022 ወደ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ በማሰለፍ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት
ለመሆን ላስቀመጠችዉ ርእይ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አጠያያቂ
አይደለም፡፡ ለዚህ ግብ መሳካትም እንደ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠው የመሰረተ ልማቶች እድገትና ጠንካራ
መሰረት ያለውና በእድገት አማካኝነት ሊከሰት የሚችለውን የገበያ መዋዠቅ ሊቋቋም የሚችል ኢኮኖሚ
መፍጠር ስንችል መሆኑ ግልጽ ነው ፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ግዙፍ ዘርፍ ሃገራዊውን ርዕይ ከማሳካት አንጻር ያለውን ድርሻ መወጣት ይችል ዘንድ አሁን
ካለበት የተወሳሰበ ችግር በማላቀቅ የላቀ ሙያዊ ግልጋሎት የሚያበረክትበት፣ ምርታማነቱና ቅልጥፍናው
እያደገ እና እየተሻሻለ እንዲሄድ በማድረግ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ተገቢ ነው፡፡ ከዚሁ ባሻገር ደረጃ በደረጃ
ከአነስተኛ ሙያ ወደ መካከለኛ ደረጃ የስልጠና ክህሎት ባለው ባለሙያ የተገነባ ኢንዱስትሪ እና በሂደትም
የዕውቀት ማዕከል የሆነ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የመገንባት አቅጣጫ መከተል ይኖርብናል፡፡ የተጠናከረ
የሠው ኃይል አቅም እየተገነባ በሄደ ቁጥር በግንባታ ቦታዎች የሚከወኑ ተግባራት እየቀነሱ ከአንድ ማዕከል
የሚሰራጩ የፋብሪካ ውጤቶች ምርት መጠቀም የሚቻልበት ደረጃ ላይ ለመድረስ መሠራት ይኖርበታል፡፡

8
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዉ አቅሙን እየገነባና ልማቱ መሠረታዊ ዓላማ አድርጎ መንቀሳቀስ ያለበት ሲሆን
በሀገራችን ልማት እንዲፋጠንና ከሂደቱም አብዛኛው ዜጋ እንዲጠቀም ማድረግ መሆን ይኖርበታል፡፡ ለዚህም
የተቀናጀና በኢንዱስትሪ የታገዘ ፈጣን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የመገንባት ርዕይ ሰንቆ መንቀሳቀስ
ይጠበቅበታል፡፡ ይህንን ርዕይ ለማሳካት ደግሞ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ በላቀ ፍጥነትና ተከታታይነት ባለው
አኳኋን መኮረጅ፣ የተቀናጀና የተናበበ የኮንስትራክሽን የእሴት ሰንሰለት ሥርዓት የመገንባትና ፈጣን የግንባታ
ቴክኖሎጂም መጠቀም መጀመርና አጠናክሮ መቀጠልንም ታሳቢ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ የግንባታ
ፕሮጀክቶቻችን ማስፈፀም የሚጠበቅብን አሁን በተለምዶና በሀገር ውስጥ ባለው የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና
በገበያ ያለውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሀገሮች የተፈጠሩ ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት
በመኮረጅ፣ በማላመድና ምርጥ ልምዶችን በመቀመር፣ በፍጥነት በመጠቀምና በማስፋት መሆን ይኖርበታል፡፡
ለአፈጻጸሙም የቁጥጥር ሥርዓት ማሻሻልና በቴክኖሎጂው ግኝት መሠረት ግብዓቱን በፍጥነት የሚቀርብበት
ሥርዓት በትይዩ ዝግጅት ማድረግ ይጠይቀናል፡፡ በዚህ ዓይነት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የአቅርቦትና
ፍላጎት ሥርዓቱን አጣጥሞ ተደማሪ እሴት እየፈጠሩ በመሄድ ምርታማነት፣ የግንባታ ጥራት፣ ተለዋጭነት፣
ወጪና ኃይል መቆጠብ እና የተገኙ ተደማሪ እሴቶችን በቀጣይነት ማሻሻል የፖሊሲው ትኩረት አድርጎ
መረባረብ ያስፈልጋል፡፡ በዘርፉ የተሠማሩ ተዋናዮች ተጠቃሚው ዜጋ፣ አማካሪዎች፣ ተቋራጮች፣ አሠሪዎችና
ባለሙያዎች ለዘርፉ ዕድገት የሚኖራቸው አስተዋፅኦ የማይተካ ሲሆን፣ የአማካሪዎችና ተቋራጮች ማህበራት
ሚናም ለዘርፉ እድገትና ሙያዊ ስነ-ምግባር መከበር እጅግ የላቀ እንደሚሆን ይታመናል፡፡ የዘርፉን የመወዳደር
አቅም በመገንባት ሂደት ከእነዚህ አካላት ቀጥተኛ ተሣትፎ ውጭ ሊታሠብ አይችልም፡፡ ስለሆነም
የኮንስትራክሽን ዘርፉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሃገራዊ ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ አሟጦ
ለመጠቀም የሚያስችል ሁሉን አቀፍና የተደራጀ ርብርብ በባለሚናዎች በኩል መደረግ ይኖርበታል፡፡ ከዚህም
በተጨማሪ ይህ በለጋ ዕድሜ ላይ የሚገኘው ዘርፍ የሚያቀርበው አገልግሎት ዋጋ ከ 60 በመቶ በላይ ከውጭ
በሚገቡ ግብአቶችና አገልግሎቶች ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ይህን በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ በሃገራዊ የግንባታ
ግብአቶችና አገልግሎቶች ላይ እንዲመሰረት ማድረግ ተገቢ እና ወቅታዊም ይሆናል፡፡ በዚህ ዓይነት
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ልማታችን መዳበር አንዱ የዕድገት ምንጭ በመሆን ለሀገራችን ህዳሴ
መረጋገጥ የበኩልን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት እሙን ነው፡፡

1.2.5 ዋና ዋና ማነቆዎችና መንስኤዎቻቸው


በሀገራችን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ቀላል የማይባል የአፈጻጸም ችግር ይታይባቸዋል፡፡ የግንባታ
አገልግሎትና አቅርቦቱ የተጣጣመ አይደለም፡፡ ብቃት ያለው እና አመለካከቱ የተስተካከለ ባለሙያ፣ አስፈጻሚ
አካል፣ አማካሪና ተ s ራጭ በብዛት ባለመኖሩ ምክንያት ብዙ ግንባታዎች በታቀደላቸው ጊዜ አይጠናቀቁም፡፡
ፕሮጀክቶቹ በሚጠናቀቁበትም ጊዜ ወጪያቸው ይንራል፡፡ የብዙዎቹ የግንባታ ፕሮጀክቶች ርክክብ
በሚፈጸምበት ጊዜ የሚታይባቸው የጥራት መጓደል በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ በመሆኑም ማነቆዎቹን
አንጥሮ ማስመቀጥ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

1.2.5.1 የሌብነት ተግባርና ኢፍታዊ ተጠቃሚነት የሰፈነ መሆኑ

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የተሰማሩ ብዙ አማካሪዎችና ተቋራጮች በዋጋ፣ በጥራትና በጊዜ ከመወዳደር


ይልቅ ባልተገባ መንገድና በአቋራጭ ለመበልጸግ ሲንቀሳቀሱ ይስተዋላል፡፡ በኮንስራትክሽን ፕሮጀክቶቻችን

9
ከዲዛይን ጥራት፣ ግልጽነት ካለው የጨረታ አወጣጥ፣ ተጠያቂነት በግልጽ ካሰፈነ የኮንትራትና የክፍያ ሥርዓት፣
ተቀባይነት ካለው የኮንስትራክሽን ኮንትራት አስተዳደር እና ወቅቱን በጠበቀ የርክክብ ስርዓት በተሟላ አኳኋን
የተገነባ ባለመሆኑ የግልጸኝነትና ተጠያቂነት አሠራር ጉድለት ይታይበታል፡፡ በዚሁ ምክንያት ለሙስና እና ብልሹ
አሠራር እየተጋለጠ ነው፡፡ ይህ ከዲዛይን፣ ከጨረታ ሂደት፣ ከኮንትራት አስተዳደር እና ከግንባታ አፈጻጸም ጋር
በተያያዘ የሚፈጠረው የሌብነት አመለካከትና ተግባር የሀብት ብክነት ብቻ ሣይሆን የሀገራችንና
የኢንዱስትሪውን የተወዳዳሪነት አቅም መገንባት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ መፍጠሩ የማይቀር ነው፡፡ በዚህ
ምክንያት በብዙዎቹ ፕሮጀክቶች በወጣላቸው መርሃ ግብርና በጀት እንዲሁም ዲዛይን በተደረገው የጥራት
ደረጃ ማስፈጸም አዳጋች እየሆነ ነው፡፡

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲባል ጥራት የሌላቸው ግንባታዎች ሲካሄድ ይስተዋላል፡፡
የዚህ ችግር አንዱ መንስኤው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ጥራታቸው የተጓደለ የግንባታ ዕቃዎች
መቅረባቸው ነው፡፡ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡና በአገር ውስጥ በሚመረቱ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ላይ
አስፈፃሚ የመንግስት አካላት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የተጠናከረና የተቀናጀ የቁጥጥር ሥርዓት
ዘርግተው ተግባራዊ እያደረጉ አይደለም፡፡ ጥራት የሌላቸው ግንባታዎች ቀላል ያልሆነ የገንዘብ ብክነትና በሰው
ሕይወት ላይ አደጋ እያስከተሉ ነው፡፡ ለአብነትም ጥራቱ ባልጠበቀ አኳኋን በተገነቡ መንገዶች ምክንያት
የተሽከርካሪ ባለንብረቶች በዓመት ከፍተኛ ግምት ያለው የጥገና ወጪ ያደርጋሉ፡፡ በዚሁ ምክንያት በሰውና
በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋና የንብረት ብክነት እየተከሰተ ነው፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ለሙስና የተጋለጡ የሥራ ደረጃዎች በሦስት ከፍሎ ማየት
ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው በቅድመ ግንባታ በሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ወቅት የሚፈጸም ነው፡፡ በአዋጪነት
ጥናት፣ በዲዛይን፣ በጨረታ ሠነድ ዝግጅት፣ በጨረታ ግምገማ፣ በውለታ መፈፀምና መከታተል ወቅት
የሚፈጸሙ ናቸው፡፡ በዚህ ወቅት ዲዛይኑን ለተወሰነ ተጫራች በልክ መስራት፣ ግልጽ ያልሆነ ዲዛይንና የተጋነነ
ፍላጎት ማስቀመጥ፣ ግልጽነት የሌለው የጨረታ ማወዳደሪያና መገምገሚያ ሰነድ ማዘጋጀት፣ ተጫራቾች
ግንባር ፈጥረው በጨረታ መወዳደር፣ በተለያዩ ተገቢ ባልሆኑ ምክንያቶች ተጫራቾችን ማስገወገድ እንዲሁም
አንዳንድ ጊዜ የተሣሣተ የውል ማሻሻያ ወዘተ ማድረግ በተወሰነ ደረጃ ሊጠቀሱ የሚችሉ መገለጫዎቹ
ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለይ አንዳንድ የመንግስት አሰሪዎች /procuring entities/ በቅድመ ጨረታ
ወቅት ለውስን ጨረታ ተሳትፎ ኮሚሽን በመጠየቅ፣ የሚፈል Õ ቸው ተወዳዳሪዎች ብቻ እንዲያሸንፉ አመቺ
ሁኔታ በመፍጠር እና የገበያ ተወዳዳሪ ዋጋ በማያመለክት መልኩ በህዝብ ሃብት ላይ ውሳኔ ሲሰጡ ይስተዋላል፡፡
ሁለተኛው በግንባታ ጊዜ በሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ወቅት ነው፡፡ ከላይ እንደተገለፀው ችግር ውስጥ የገባ
ፕሮጀክት ጥራቱን ያልጠበቀ ግንባታ ከማካሄድ ባሻገር የውለታው ሰነድ ከሚያመለክተው የጊዜ ሰሌዳ
ዘግይቶም ቢሆን ካለተጠያቂነት ግንባታዎቹ እንዲቀጥሉ ሲደረግም ይታያል፡፡ ለዚህም በተለይ የመንግስት
አሰሪዎች ለጉዳቱ ካሳ ከመጠየቅ ይልቅ በአጋጣሚ እንኳን ተ s ራጩን ተጠያቂ ለማድረግ ጥረት ቢደረግ
የመጀመሪያው ምክንያት አቅራቢ በመሆን የመከላከል አዝማሚያ የሚያሳዩ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ በአማካሪው
በኩል ፕሮጀክቶቹ በዘገዩ ቁጥር የራሱን የክፍያው መጠን ከመጨመርና ጥቅም ማስገኘት ባለፈ ተጠያቂ
ባለመሆኑ የሙያው ስነምግባር ከሚያስገድዳቸው ጥቂቶች በስተቀር ከተ s ራጩ ባልተናነሰ መልኩ መዘግየቱን
ይፈልገዋል፡፡ በሌላ በኩል የክፍያ ሰነዶች በአማካሪው በኩል ጸድቀው ለአሰሪ መስሪያ ቤቶች ጥያቄው ከቀረበ
በኋላ በየደረጃው ያሉ የተ s ሙ አስፈጻሚዎች የድርሻዬን የሚል ውስጠ ሚስጥር ያለው ጥያቄ ያዘለ

10
አላስፈላጊ ቢሮክራሲ በማብዛት በተ s ራጩ ላይ ጫናዎች መፍጠር፣ የባለቤቱን ጥቅም ያልጠበቁ የለዉጥ ስራ
በመስጠት፣ በስኮፕ መቀየር ምክንያት አዳዲስ ዋጋዎችን በመትከል ያልተገባ ጥቅም ማግኝት፣ የወደቁ
ላብራቶር ዉጤቶቸንና ስፔስፊኬሽን የማያሟሉ የግንበታ እወቃዎችን ማሳለፍ ሚስተዋሉ ናቸዉ ፡፡
ሦስተኛው ደግሞ በድህረ ግንባታ ጊዜ በሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ወቅት ነው፡፡ በውለታው መሠረት
የመጨረሻ ርክክብ ያለመፈፀም፣ የፕሮጀክት ሠነዶችን መሰወር፣ ክፍያ ማዘግየት፣ በግልግል ወቅት ግልጽነትና
ተጠያቂነት ባለው መንገድ ያለማስፈፀም ናቸው፡፡

እነዚህ ከላይ በምሳሌነት የተነሱ የሌብነት አስተሳሰብና ተግባራት የሚገለጹበት መሠረታዊ መንስኤው
ለኢንዱስትሪው ልማት የተቀመጡ አቅጣጫዎችና ዘርፉን ለመምራት የወጡ የሕግ ማዕቀፎች በአግባቡ
ማስተግበር ባለመቻላችን ነው፡፡ የለውጥ ሥራ በአግባቡ ባለመተግበሩ እና ይህንን ተልዕኮ ለመወጣት
ቁርጠኝነት ያለው አመራር በብዛት መፍጠር ባለመቻላችን ነው፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሚመራበት
ፖሊሲና የአፈፃጸም ዝርዝር ስትራቴጂ፣ ለኢንዱስትሪው ስራ ግልጸኝነትንና ተጠያቂነትን ሊያሰፍኑ የሚችሉ
የህግ ማዕቀፎችና ተልዕኮውን ማስፈጸም የሚችል አደረጃጀትና የሰው ኃይል ተሟልተው ወደ ተግባር
ያለመገባቱም የበኩሉን አሉታዊ ተፅዕኖ ነበረው፡፡

የኮንስትራክሽን ግዢ ጨረታ አገልግሎትና አመራር የቴክኒክ ብቃቱም ቢሆን ደረጃውን በጠበቀ የኮንስትራክሽን
ኢንዱስትሪ ክህሎት የታገዘ አልሆነም፡፡ የኮንስትራክሽን አገልግሎት የግዥ አሰራር ሥርዓቱ የኢንዱስትሪው
ዕድገት ከሚጠይቀው ሙያና መሻሻል አንጻር በየጊዜው እየተፈተሸ እንዲሻሻል እየተደረገ አልቆየም፡፡
ለኮንስትራክሽን አገልግሎት ግዢና ቁጥጥር የሚያመች የሰው ኃይል፣ አሰራርና ተገቢው አደረጃጀት ከመፍጠር
አንጻር ክፍተቶች አሉ፡፡ ግንባታዎች የዘርፉ የሙያ ስነ-ምግባር ጠብቀው መከናወናቸው፣ የጥራት ደረጃቸው
ያሟሉ ስለመሆናቸው፣ የወጣው ወጪና የተከናወነው ግንባታ ተመጣጣኝ ስለመሆኑ በክትትልና ቁጥጥር
የሚረጋግጥበት የተጠናከረ ሥርዓት እለመዘርጋትና አለመተግበር፡፡ በኮንስትራክሽን ሂደቱ በተጨባጭ
የሚፈጠሩ የዋጋዎች ውጣ ውረድ የሚስተካከልበትና የሚጣጣምበት ቀመር በመመሪያ ደረጃ ቢኖርም
ተአማኒነት ያለው መረጃ ማደራጀት ባለመቻሉ ምክንያት በተግባር እየተሰራበት አይደለም፡፡ በእነዚህና
ተያይዘው በሚታዩት ምክንያቶች የግንባታ ፕሮጀክቶች ጥራትና ደረጃቸው እንዲሁም ዋጋቸውና የግንባታ
መርሃ-ግብራቸው የተጠበቀ እንዳይሆን እና የኢንዱስትሪው ዕድገትና ተወዳዳሪነት የሚፈለገውን ያህል
እንዳይደርስ አድርጎታል፡፡

1.2.5.2 የሙያ ብቃቱ የተረጋገጠና ምርታማ የሆን የሰው ኃይል እጥረት ያለ መሆኑ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሰለጠነ እና የሙያ ደረጃው የተረጋገጠ የሰው ኃይል እጥረት ያለበት ነው፡፡
መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራምና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ሥርዓት ዘርግቶ ብዛት ያለውና ዘርፉን
መቀየር የሚችል የሰው ኃይል እያሰለጠነ በማስመረቅ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በአርክቴክቸር፣ በሲቪል
ምህንድስና፣ በኤሌክትሪካል ምህንድስና፣ በህንጻ ምህንድስና ወዘተ የሚመረቁ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ
ያሉ ፕሮፌሽናሎች ብዛት በየጊዜው እየጨመረ የመጣ ቢሆንም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ከሚፈልገው
የሰው ኃይል ብቃት አንጻር ሲታይ አሁንም ክፍተት ችግር ያለበት ነው፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው
የሚያስፈልገውን የሰው ሃይል ከማፍራት አንጻር በከፍተኛ ትምህርትና በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መካከል

11
የመረጃ ኔትዎርክ በመፍጠር የኢንዱስትሪውን ፍላጎትና አቅርቦት ለማጣጣም የሚያግዝ ስርዓት
አልተዘረጋም፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚህ በላይ ተመርቀው የሚወጡ ፕሮፌሽኖሎችም በተግባር ተፈትነው
ፕሮፌሽናል ሠርተፊኬሽን የሚያገኙበትና ብቃታቸው በተግባር የሚረጋገጥበት ሥርዓትም መዘርጋት
ይኖርበታል፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ የኮንስትራክሽን ስነ-ምግባር (Construction Ethics)
ትምህርት ባለመካተቱ በመስኩ እየታየ ያለውን ሌብነት ከመከላከሉ እና የተዛባውን አመለካከት ከማስተካከል
አንጻር የሚኖረው ፋይዳ መጠቀም አልተቻለም፡፡

በተመሳሳይ መንገድ ኢንዱስትሪው ከፍተኛ መጠን ያለው መለስተኛ ባለሙያና የጉልበት ሠራተኛን በስፋት
የሚጠቀም እንደመሆኑ እነዚህ ሠራተኞች ምርታማነታቸውና የኮንስትራክሽን አገልግሎት የሙያ ብቃታቸው
በምዘና ተረጋግጦ የሚሰማሩበት ሥርዓት ቢዘረጋም አፈጻጸም ላይ መዘግየት አለ፡፡ ተመዝነው በገበያ ውስጥ
የሚገኙት ብዛታቸውም ገበያው በሚፈልገው ደረጃ አይደለም፡፡ የእነዚህ መለስተኛ ባለሙያዎች እጥረት
ለማቃለል በመንግስት በኩል በቴክኒክና ሙያ ተቋማት አማካይነት ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ሆኖም የሚዘጋጀው የሰው ኃይል ከገበያው ፍላጎት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ክፍተት የሚስተዋልበት ነው፡፡
በኢንዱስትሪው የሚሰማራው መለስተኛ ባለሙያ እየተመዘነና የሙያ ብቃቱ እየተረጋገጠ ብዛት ኖሮት
በውድድር የሚሰማራ ባለመሆኑ በስራው ላይ ያለው ምርታማነት አናሳ ከመሆኑም ሌላ ግብዓትን በማባከን
በኩል እየፈጠረ ያለው ጫና ከፍተኛ ነው፡፡ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ተገዝተው የሚመጡ የኮንስትራክሽን
መሣሪያዎች በአጠቃቀም ክህሎት ማነስ ምክንያት ተገቢውን አገልግሎት ሳይሰጡ ለጉዳት በመዳረጋቸው
ለከፍተኛ የመለዋወጫ ግዢ ወጪ ይዳረጋሉ፡፡ በመሆኑም የሰው ኃይል እጥረቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ
አቅምና ተወዳዳሪነት አናሳ እንዲሆን በማድረግ ፕሮጀክቶቻችን በሚፈለገው ጊዜ፣ የጥራት ደረጃና የወጪ
መጠን እንዳይፈጸሙ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው፡፡

1.2.5.3 የፕሮጀክቶች ስራ አመራር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የተሳለጠ ያለመሆኑ

በሀገራችን ለተፈጠረው ፈጣን ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርገው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ


በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ሳይሆን ከተለያዩ ተቋማት ጋር እየተዋቀረ በመሄዱ ቀጣይነት ባለውና ተቋማዊ
ዕውቀት እየገነባ አልሄደም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስት ክፍተቱን በማጤን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት
ማኔጅመንት ኢንስቲቲዉት በአዲስ መልክ አደራጅቶ የዘርፉን አቅም ለመገንባት ጥረት ቢደረግም
የኮንስትራክሽን ዘርፉ አሁንም ከተልዕኮው ስፋት አንጻር ለስራው ተገቢ የሆኑ አደረጃጀቶች በተሟላ መልኩ
ተፈጥሯል ማለት አይቻልም፡፡ የተቋራጮች፣ የአማካሪዎች፣ የባለሙያዎች፣ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች
አቅራቢዎችና አስመጪዎች በአግባቡ የሚመዘግብና የሚቆጣጠር ተቋም መፍጠር የነበረብንና የዘገየ ስራ ነው፡፡

በሀገራችን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚሠራባቸው ህጎችና ኮዶች፣የሕንጻ አዋጁ ተዘጋጅተው በሥራ ላይ


የዋሉ ቢሆንም በአተገባበር ላይ መዘግየት ይታያል፡፡ በሥራ ላይ ያለው የኮንስትራክሽን የጨረታ አሠራር እና
የቁጥጥር ሥርዓት የኢንዱስትሪውን የዕድገት ደረጃ ባገናዘበ መልኩ ተፈትሾ በቀጣይነት መሻሻል የሚጠይቅ
ነው፡፡ የግንባታ ቁሳቁሶችና ግብዓቶች ጥራትና ደረጃቸው ስልታዊና አንጻራዊ በሆነ ዘዴ የተጠናከረ የቁጥጥር
ስርዓትና ባለቤት ሊሰየምለት የሚገባ ነው፡፡ ግንባታዎች የኢንዱስትሪውን ስነ-ምግባር ጠብቀው እንዲከናወኑ
የሚያስችለው የህንጻ አዋጅ በተሟላ መንገድ መተግበር ነበረበት፡፡

12
የሥራ ተቋራጮች፣ የአማካሪ ድርጅቶች፣ የግንባታ ግብዓት አቅራቢዎች እንዲሁም የሙያና የባለሙያዎቹ
ማህበራት የራሳቸውን ፍላጎትና የኢንዱስትሪውን ጥቅምና ዕድገት የሚያረጋግጥ አደረጃጀት በመፍጠር ርዕይ
ሰንቀው መስራት ላይ ክፍተት ይስተዋልባቸዋል፡፡ ማህበራቱ በአባላት ብዛትና በተጠናከረ አሠራር ያልተደራጁ
በመሆኑ ለዘርፉ ዕድገት መጫወት የሚገባቸውን ሚና መጫወት አልቻሉም፡፡ እነዚህ ማህበራት
በኢንዱስትሪው ውስጥ ሊኖር የሚገባው የአገልግሎት ጥራት ከማረጋገጥ፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት
የጎደለውንና ለሙስና ተጋላጭ የሆነውን አሠራር እንዲስተካከል ከማድረግ እና የኢንዱስትሪውን ገጽታ
አስተካክሎ ከመገንባት አንጻር የአቅም ውስንነት ስላለባቸው የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ አላደረጉም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት አቅማችን አሁን ያለው ልማታችን ከሚጠይቀው አኳያ
የተጠናከረ አይደለም፡፡ በሃገራችን የኮንስትራክሽን ስራ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ በፍጥነት እያደገ የመጣ
ቢሆንም ይህንን ተከትሎ የዘርፉ ባለሚናዎች በሆኑት የባለቤቱ፣ የተቋራጩ፣ የአማካሪው፣ የምህንድስና
ባለሙያው፣ የግንባታ ግብዓት አምራቾችና አቅራቢዎች፣ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎቹ አስመጪዎችና
አቅራቢዎች እንዲሁም የተቆጣጣሪ ባለሥልጣኑ የማስፈጸም አቅም በተመጣጣኝና በሚፈለገው ደረጃ በትይዩ
አላደገም፡፡ መንግስት ያቀዳቸውን ትላልቅ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የመሠረተ ልማት አውታሮች በወቅቱ
ለማስፈጸም ብቃት እና የባለቤትነት ስሜት ያለው አመራርና ፈጻሚ፣ ተቀባይነት ያለው የቁጥጥርና ክትትል
ሥርዓት፣ የተሻለ ክህሎትና አደረጃጀት ይፈልጋሉ፡፡ እነዚህ ጉዳዮች ከማሟላት አንጻር ብዙ መስራት
ይጠበቅብናል፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሚገኝበትን ነባራዊ ሁኔታ በትክክል ተንትኖ በማወቅ የዕድገት አቅጣጫውን
ለመቀየስና መንግስትና በኢንዱስትሪው የተሰማሩ ባለሚናዎች የተቀናጀ ዕቅድ አዘጋጅተው ለመተግበር
የመረጃ አስፈላጊነት አጠያያቂ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ገጽታ ለማወቅ
የተጀመረው የመረጃ ማደራጀት እንቅስቃሴ የባለሚናዎችን ተገቢ ድጋፍ እያገኘ አይደለም፡፡ ለዚህም
መሠረታዊ መንስኤው በባለሚናዎቹ በኩል ስለመረጃው አስፈላጊነት ያለው ግንዛቤ አናሳ በመሆኑ ነው፡፡ ይህም
ለኢንዱስትሪው ችግሮች የሚቀመጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎች በተሟላ መረጃ ላይ ያልተመሰረቱ እንዲሆኑ
ያደርጋቸዋል፡፡
በአገራችን አሁን ያለው ዝቅተኛ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በዘርፉ አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ
እያሳደረ ይገኛል፡፡ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን ለማምረትና እንዲሁም በግንባታ እንቅስቃሴዎች ላይ በሰፊው
ለመሰማራት ወቅቱ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ መጠቀም ግድ የሚልበት ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡

በኢንዱስትሪው ውስጥ ቁጥራቸው የበዛ በግብዓት አምራችነት የተሰማሩ ድርጅቶች መስፋፋት፣ ያልተቀናጁ
አካላት መኖራቸውና ለዚህም የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓትና አደረጃጀት
ባለመጠናከሩ ምክንያት በጥራት ላይ ከፍተኛ ግድፈት እየተስተዋለ ይገኛል፡፡

በሀገራችን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በጥቅሉ ሲታይ በኮንስትራክሽን ሴክተር ዝቅተኛ ቴክኖሎጂ


አጠቃቀም፣ የእሴት ጭማሪውን አነስተኛ ከማድረጉም በላይ የዘርፉን ምርታማነትም በመቀነስ ጥራትን

13
የሚያጓድልና በፕሮጀክት አፈጻጸም ሂደት የጊዜ ሰሌዳን የሚያራዝም መሆኑ በግልጽ የሚታይ ብቻም ሳይሆን
ተደጋግሞ እየተነሳ ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ቴክኖሎጂ ከዘመኑ ጋር ራሱን ያላስኬደ እንደ አርማታ ማቀናበሪያና
ፕሪካስት ምርቶችን እንኳን በብዛት የማይጠቀም ኋላቀር ነው፡፡ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዙሪያ የሚበጁ
ቴክኖሎጂዎችን አፈላልጎ ከሁኔታው ጋር የማጣጣም የተወሰነ ሥራ በመስራት በግንባታ ፕሮጀክቶች ሂደት
የሚያጋጥሙትን ችግሮች የሚፈታ ቴክኖሎጂ ለሁሉም ለማዳረስ እና በአሠራር፣ በዲዛይንና በህግ ማዕቀፎቹ
ውስጥ እንዲካተት በማድረግ የቴክኖሎጂ ዕድገቱን የሚያፋጥን ተቋም በሚፈለገዉ መልኩ አልተደራጀም፡፡
በግንባታ ስራዎች ወጪ ቆጣቢ ግብዓትን እና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ልማትን ለማፋጠን ካለው ጉልህ ድርሻ
አንጻር የተሠራው ሥራ መልካም ጅምር ቢኖረንም ብዙ ሥራ የሚጠብቀን ነው፡፡ በመኖሪያ ቤቶች፣
በመንገዶች፣ በጤና ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች፣ በመስኖ፣ በግድቦች ወዘተ ቴክኖሎጂዎችን ከወጪ፣
ከጥራትና ከጊዜ አንጻር ገምግሞ ምርጥ ተሞክሮን በፍጥነት ለማሸጋገር የተደረገው ጥረት በቂ አይደለም ፡፡

የኮንስትራክሽን ግብዓት ጥራት መቆጣጠሪያ ማዕከላዊ ላቦራቶሪ እንዲሁም ኢንዱስትሪው በዘርፉ የተፈጠሩ
አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የሚቀዳበትና የሚያላምድበት ፈጣን የመረጃ ምንጭ አለመኖሩና ስርዓትም አለመዘርጋቱ
ሌላው የዘርፉ ተግዳሮት እንደሆነ ተለይቷል፡፡ ከዚህ አኳያ የዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማጎልበት ስርዓት መዘርጋትና
የመረጃ ተደራሽነትን ከማስፋት ባሻገር የመጠቀሚያ መሳሪዎችንም ማሟላት አስፈላጊ ይሆናል፡፡ የዓለም አቀፉን
ተጨባጭ ሁኔታ ስንመለከት ከግንባታ መስኮች (Construction Site) ይልቅ በፋብሪካ ተመርተው
የሚገጣጠሙ አካላት (Off-site production) ላይ ትኩረት የሰጠበት ወቅት እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

በአጠቃላይ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ለመንግስትንና ለህብረተሰቡ የልማት ፍላጎት የተሳካ ምላሽ ለመስጠት
እንዲችል ቴክኖሎጂን በላቀ ሁኔታ መጠቀም ግዴታ እንጂ አማራጭ የማይሆንበት የዕድገት ምዕራፍ ላይ
መድረሳችንን ከግምት ያስገባ ስትራቴጂካዊ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡

የቴክኖሎጂ ሽግግር፡-የቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደት ማለት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ግኝቶችን ከግለሰብ፣
ከካምፓኒ ወይም ከሃገር ወደ ሃገር የሚቀዳበትና ፍሰቱ ስርዓት ባለው አደረጃጀት የሚፈጸምበት ክንውን ነው፡፡
በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ብዙ የተሻሻሉ አሰራሮችና የቴክኖሎጂ ግብዓቶች ያሉ ቢሆንም በዓለም አቀፍ ደረጃ
በመስኩ ተዋናዮች ዘንድ በፍጥነት ተቀብሎ የማስረጽ ሁኔታ ዘገምተኛ መሆኑን የዘርፉ ተንታኞች ይገልጻሉ፡፡
ከዚህ አንጻር የሃገራችንን ሁኔታ ስንገመግም በአብዛኛው ኋላ ቀርና አላስፈላጊ የጉልበት ብክነት፤ በአንጻሩ ደግሞ
የምርታማነቱ ዝቅተኛነት የሚጎላበት አሰራር የሚከተልና በሌሎች ሃገሮች የየእለት የግንባታ ክንውን ባለበት
ነባራዊ ሁኔታ የተለመዱ ቴክኖሎጂዎች እንኳን በአግባቡ ማላመድ ያልተቻለበት ሁኔታ መኖሩ ይስተዋላል፡፡
በመሆኑም ካለንበት ዝቅተኛ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ደረጃ በአፋጣኝ ማንሰራራት እንደሚኖርብን በማጤን
በጥናት ላይ የተመሰረተ የቴክኖሎጂ ግብዓት በሁሉም የግንባታ መስኮች ማስረጽ አማራጭ የሌለው ወሳኝ ተግባር
መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

የግንባታውን ዘርፍ ትራንስፎርም ለማድረግ ከቁልፍ ተግባራት ውስጥ የቴክኖሎጂ ድጋፍ አንዱ ሲሆን ይህም
መንግስት የሚያቅዳቸው የልማት ፕሮጀክቶች በወቅቱና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማጠናቀቅ ከማስቻሉም በላይ በዓለም
አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘትም የሌሎችን የመፈጸም አቅም መነሻ (ቤንች ማርክ) አድርጎ በዚሁ አቅጣጫ
መንቀሳቀስ ተገቢና አስፈላጊ ይሆናል፡፡

14
በኮንስትራክሽን እንደስትሪዉ ባለፉት አመታት የቴክኖሎጂ ሽግግሮችን ለማሳለጥ የተለያዩ ስራዎች እየተከናዎኑ
ቢሆንም ሽግግሩ በተቀናጀ፤ ሁሉን ባሳተፈና ቁልፍ ችግሮች ላይ ትኩረት ባደረገ መልኩ ባለመከናወኑ በሚፈለገው
ፍጥነትና ልክ ለዉጥ ሊመጣ አልቻለም፡፡

በጥቅሉ የምንጠቀምባቸዉ ቴክኖሎጂዎች በአብዛኛዉ የገቢ ንግድ ላይ ጥገኛ በመሆናቸዉና አስተማማመኝ


የአቅርቦት ሰንሰለት ያልተዘረጋለት በመሆኑ ግንባታዉ በተለመደዉ አሰራርና ቴክኖሎጂ በሚገነባበት ወቅት
እንኳን የአቅርቦት እጥረት መቆራረጥ ስለሚስተዋል በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪዉ ተወዳዳሪነት ላይ የራሱን ጥላ
አጥልቷል፡፡

1.2.5.4 ተወዳዳሪነትን ሊያጠናክር የሚችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር ያልተቻለ መሆኑ

በሀገራችን ባለፉት አመታት እየተመዘገበ ባለው የኢኮኖሚ ዕድገት ምክንያት ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው
ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ቀደም ሲል በነበረው አገራዊ ጥቅምን ያላስቀደመ አግላይ ቡድንተኛ ሥርዓት ከጥቂት
የቡድኑ ድርጅቶች ቁጥጥር ሥር ወጥቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ተ s ራጮችና በመቶዎች የሚቆጠሩ አማካሪዎች
እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ውስጥ በፍትሃዊንት መሳተፍ ባለመቻላቸዉ
የሀገራችን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከሚፈልገው አንጻር ሲታይ ክፍተት ያለበትና የማስፈጸም
ብቃታቸው አነስተኛ ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በደረጃ አንድና ሁለት የተመዘገቡት ከ 3 በመቶ አይበልጡም፡፡
በሥራ ተቋራጮችና አማካሪዎች በማስፈጸም አቅማቸው ውስንነት ምክንያት የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች
የጊዜ መዘግየትና የወጪ መናር አደጋ እያጋጠማቸው ነው፡፡ ባለሚናዎቹ በኢንዱስትሪው እሴት ሰንሰለት ላይ
በመመርኮዝ ጥራትና ምርታማነትን የማረጋገጥ አሠራሮች ላይ ተመስርቶ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን ስራ
ማከናወን ላይ ውስንነቶች ይታያሉ፡፡ በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች የዲዛይን ጥናቶች፣ የግንባታዎች ጥራት፣
የግንባታዎች የዋጋና የሥራ ዝርዝር፣ የግንባታዎች የቁጥጥርና ድጋፍ ሥርዓት ወጥነት ባለውና ስታንዳርድ
ተዘርግቶለት በተሟላ መንገድ በመተግበር ላይ አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት የኮንስትራክሽን አገልግሎቶች
ከውጤት አንጻር ሲመዘኑ ቀላል የማይባል ብክነት የሚታይባቸውና የመወዳደር አቅማቸው ውስንነት
የሚስተዋልበት ነው፡፡

በሀገራችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየተፈጠረ ባለው የኢኮኖሚ ዕድገት ምክንያት የተፈጠረውን የግንባታ
አገልግሎት ፍላጎት የሚመልስ የኢንዱስትሪ አቅም ለመገንባት ተጨማሪ ጥረት ይጠብቀናል፡፡ አንዳንድ ጊዜም
የተሟላ ግንባታ አገልግሎት ባለመቅረቡ ምክንያት የተያዙ ፕሮጀክቶች በወቅቱ ሳይፈጸሙ የሚቀሩበት ሁኔታ
እየተፈጠረ ነው፡፡ ለዚህም ለገበያ ክፍተት እንደመንስኤ ከሚነሱ ጉዳዮች የመጀመሪያው ምክንያት በዘርፉ
የተሰማሩ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች እና ባለሙያዎች ብቁ አለመሆን ሲሆን ሌላው ማነቆ ደግሞ
ኢንዱስትሪው ለመግባት የሚጠየቁ የፋይናንስና የማሽነሪ አቅም ከፍተኛ መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
ዘርፉን የተቀላቀሉ አማካሪዎችና ተቋራጮች አቅማቸው የሚገነባበት፣ የሙያና የማስፈጸም አቅም
ብቃታቸው በተከታታይ በየዓመቱ እየተመዘነ የሚረጋገጥበት ሥርዓት ወጥ በሆነ አኳኋን አልተዘረጋም ፡፡

በመሆኑም በቀላል ቁጥር የማይገመቱ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የግንባታ አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ ነው፡፡
ፕሮጀክቶቹ በታቀደላቸው ጊዜ እየተጠናቀቁ አይደለም፡፡ ከዚህ አንጻር አንዱ ማነቆ ተብሎ የተለየው ከውለታ

15
አንጻር የተጣጣመ አፋጣኝ ምላሽ ያለመሰጠቱና ግልጽ የሆነ የግንባታ ሂደትን ለመምራት የሚያስችልና
ተገቢው የማስተካከያ እርምጃዎች ለመውሰድ የሚያግዝ ሥርዓት ያለመዘርጋቱ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት
ፕሮጀክቶች በወጣላቸው መርሃ-ግብር መሠረት ባለመጠናቀቃቸው የዋጋ መጨመር እና የአገልግሎት አቅርቦት
መስተጓጎልና መዘግየት ላይ የራሱ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ ለእነዚህ ማነቆዎች መሠረታዊ መንሰኤ ተብለው
ከተለዩት ሁለተኛው ምክንያት ለፕሮጀክት ግንባታ የሚደረገው የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጓደል አንዱ ነው፡፡
የፕሮጀክት ጥናት፣ የዲዛይንና የሥራ ተአማኒነት ያለው ዝርዝር እንዲሁም የጠራ ኘሮጀክት ሠነድ ሳይያዝ ወደ
ተግባር መግባት በብዙ ፕሮጀክቶች ይስተዋላል፡፡ ለአማካሪዎች ፕሮጀክቱ ባልተንቀሳቀሰበት ወቅት
የሚፈጸመው የክፍያ አሠራራችን መፈተሸ ያለበት ነው፡፡ ተቋራጮችም የሚጠየቁበት ሥርዓት የለም፤
ቢኖርም ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም፡፡ በተሻለ ሁኔታ በሰራውና ባልሰራው መካከል ልዩነት የሚፈጥር
አሠራር ተዘርግቶ ተግባራዊ አልሆነም፡፡ በፕሮጀክት ግንባታና ውለታ አስተዳደር በኩል የሚስተዋለው የብቃትና
የተነሳሽነት ማነስ ከግልጽነትና ተጠያቂነት መጓደል ጋር ተዳምሮ ሶስተኛው እና ዋናው ችግር አድርጎ
ማስቀመጥ ይቻላል፡፡

በፕሮጀክቶቹ ወጪም በኩል ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች እና በግንባታ ግብዓትና አቅርቦት ብክነት የግንባታ
ወጪው ይንራል፡፡ የግንባታ ዲዛይኖች መለዋወጥ፣ በፕሮጄክት አመራር አቅም ማነስ እና ተወዳዳሪነትን
የሚያረጋግጥ የጨረታ ሥርዓት ባለመረጋገጡ የወጪ መጨመሩ እንደ አራተኛ ምክንያት መወሰድ ይችላል፡፡
የኮንስትራክሽን ሥራ ጥራትና ደረጃ መጓደል የገበያው ተወዳዳሪነት ያለመረጋገጥ አንዱ መገለጫ አድርጎታል፡፡
ብዙ ፕሮጀክቶች ከተቀመጠላቸው የአገልግሎት ዘመን በፊት ተጎድተው በሚፈለገውና በሚጠበቀው
የአገልግሎት ደረጃ አገልግሎት እንዳይሰጡ መሆናቸው የጥራት መጓደል ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል፡፡
በዚህም ምክንያት ከአገልግሎት መስተጓጎል በተጨማሪ ለዕድሳትና ጥገና ከፍተኛ ወጪ በመጠየቁ የሀብት
ብክነት ማምጣቱ አልቀረም፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የጥገና በጀት መያዝና ይህንኑ የሚያስፈጽም የሥራ ክፍል
ፈጥሮ በፕሮግራም ጥገና የሚያስፈልጋቸው ቋሚ ንብረቶች በወቅቱ ጥገና መስጠት በሀገራችን ክፍተት
የሚስተዋልበትና ያለውም አሠራር ቢሆን ማጠናከር የሚፈልግ ነው፡፡ ሲመች የሚሠራ ተጨማሪ ተግባር
ተደርጎ ስለሚወሰድ የሕዝብና የመንግስት ቋሚ ንብረቶች በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎሳቆሉ የሚገኙበት
ሁኔታዎች ይስተዋላሉ፡፡

1.2.5.5 የግብዓቶች ጥራት ተወዳዳሪነትን የሚያሳልጥ እና ቀጣይነት ያለው የአቅርቦት ሰንሰለት


ያልተዘረጋ መሆኑ

ባለፉት ዓመታት ሀገራችን ዕድገት ሂደት የሚመነጩና ቀጣይ የሀገሪቱን ዕድገት ሊፈታተኑ ከሚችሉ
አዝማሚዎች አንዱ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ያለው የቅልጥፍና እና ምርታማነት መጓደል መሆኑ
ተለይቷል፡፡ ለዚህ ችግር ተጠቃሽ ከሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ ደግሞ የተሳለጠ የግብዓት አቅርቦት ሰንሰለት
ያለመኖር መሆኑ ግልፅ ሆኗል፡፡

በሀገራችን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ሲመዘገብ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውም ዕድገት በትይዩ እያደገ ነው፡፡
በመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ በትላልቅ መሠረተ ልማቶች ግንባታ መስፋፋት፣ በማኅበራዊ መሠረተ ልማቶች
መስፋፋት… ወዘተ ምክንያት የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ፍላጎት እጨመረ ሄዷል፡፡ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ

16
ውስጥ የሚካሄዱ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች 60 በመቶ የሚሆነው የስራቸው ክፍል የግብዓት አቅርቦት
ማረጋገጥ ነው፡፡ ከሀገር ውስጥና ከውጭ የሚቀርቡ የፋብሪካ ውጤት የሆኑ ግብዓቶችን የማቅረብ ስራ ነው፡፡
በአካባቢ የሚመረቱ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን አቅርቦት የማረጋገጥ ስራ ነው ፡፡

በሃገራችን እየተካሄዱ ባሉ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የአካባቢና የፋብሪካ ውጤት የሆኑ በብዙዎቹ ግብዓቶች
ከፍተኛ በሚባል ደረጃ እጥረት አለ፡፡ በአካባቢና በፋብሪካ የሚመረቱ ግብዓቶች በሚፈለገው መጠን፣ ጥራትና
ጊዜ ማቅረብ ከፍተኛ ችግር አለ፡፡ የፋብሪካ ምርት ሆነው ከውጭ የሚቀርቡ የግንባታ ዕቃዎችና መሳሪያዎች፣
የማጠናቀቂያ ዕቃዎች፣ የአስፋልት፣የሳኒተሪ፣ የኤሌክትሪክ፣ የኬሚካል፣ የብረታ ብረት…ወዘተ ግብዓቶች
በሚፈለጉበት ወቅት ተወዳዳሪነትን ባረጋገጠ ዋጋ እንዲሁም የጥራት ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ማግኘት
ከፍተኛ ፈተና ሆኗል፡፡ በአካባቢ የሚመረቱ የግንባታ ግብዓት የሆኑ ጠጠር፣ አሸዋ፣ ድንጋይና ምርጥ አፈር
አቅርቦትና ፍላጎቱ የማይጣጣም ሆኗል፡፡ በዚህም ምክንያት በግብዓት አቅርቦቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጥራት
መጓደልና መቆሚያ የሌለው የዋጋ ንረት እየተስተዋለበት ነው፡፡

ለእነዚህ የግብዓት አቅርቦትና ፍላጎት ክፍተት አንዱ ምክንያት የተዋናዮቹ አቅም ማነስ ነው፡፡ ከኮንስትራክሽን
ኢንዱስትሪው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የመሳሪያዎች አቅርቦት በቀጣይነት አልተረጋገጠም፡፡ ከኮንስትራክሽን
መሣሪያዎች ውስጥ የግሬደር፣ የሎደር፣ የኤክካቨተር፣የዶዘር፣ፔቨር፣ክረሸር፣ የውሃ ጉድጓድ መቆፈሪያ ሪግ፣
የኮንክሪት፣ የአስፋልትና ጠጠር ማቀነባበሪያ መሣሪያ…ወዘተ ፍላጎትና አቅርቦቱ ክፍተት ያለበት ነው፡፡
የግብዓት ማጓጓዣ የሆኑ የገልባጭ ተሽከርካሪዎች፣ የኮንክሪት ማጓጓዣ ፍላጎትና አቅርቦቱ ክፍተት ያለበት
ነው፡፡ የፋብሪካ ውጤት የሆኑት የግንባታ ግብዓቶች ብረታ ብረት፣ የሴራሚክስ፣የሳኒተሪ፣ የፕላስቲክና
የኤሌክትሪክ ዕቃዎችም የአቅርቦትና ፍላጎት ክፍተት ያለባቸው ናቸው፡፡ የብረታ ብረት የሀገር ውስጥ ምርት
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ከሚፈልገው 50 በመቶ አይበልጥም፡፡ በሀገር ውስጥ የሚመረተው የሴራሚክስ
ውጤት ከቅርብ ግዜ ወዲህ ጥሩ መሻሻልን እያሳየ ቢመጠም በእነዚህ ግብዓቶች የአቅርቦትና ፍላጎት
ያለመጣጣም በመኖሩ የዋጋ ንረት ተጠቂ ሆነዋል ፡፡
ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ የፕላስቲክ ውጤቶችን በተመለከተ በሀገራችን ከ 30 በላይ
የሚሆኑ የተለያዩ የፕላስቲክ ምርት የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ፋብሪካዎቹ የሚያመርቷቸው
የፕላስቲክ ምርቶች የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ከሚፈልገው ምርት አንጻር ሲወዳደር በጣም አነስተኛ
ነው፡፡ በመሆኑም ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶች ከውጭ ሀገር በየዓመቱ በከፍተኛ
መጠን በመግባት ላይ ናቸው፡፡ ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በግብዓትነት ከሚያገለግሉ የአሌክትሪክ ዕቃዎች
ውሰጥ የኤሌክትሪክ ገመድ፣ የኤሌክትሪክ ሽቦ፣ ሶኬት፣ ማብሪያና ማጥፍያ፣አንፖል፣ማሞቂያ፣ሊፍት እና
የኤሌክትሪክ ቱቦ ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ዕቃዎች የተወሰነዉን በሀገር ውስጥ ምርት ፍላጎቱን ማሟላት
የተቻለበት ሁኔታ እንዳለ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ መሠረታዊ ችግሩ ከውጭ የሚገቡ የጥራት ደረጃቸውን
ያልጠበቁ ተመሳሳይ ምርቶች የገበያ ውድድሩን ጤነኛ እንዳይሆን እያደረጉት መሆኑ ነው፡፡

ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በግብዓትነት ከሚወሰዱ ዋና ምርቶች አንዱ ሲሚንቶ ነው፡፡ እስከ ቅርብ ግዜ
ድረስ የሲሚንቶ ፍላጎት በአገር ዉስጥ ምርት የተሙዋላ ሁኔታ የነበረ ቢሆንም ባለፉት ሁለት አመታት ዉስጥ
በገበያዉ የምረቱ እጥረት በስፋት መከሰትና የዋጋዉ መናር ግንባታዎችን እያሰተጉዋጎለ ይገኛል ለዚህም ዋነዉ

17
ምክንያት ፋብሪካዎች በዉጭ ምንዛሪና በሃይል እጥሪት መክንት በሙሉ አቅማቸዉ ማምርት አለመቻል ነዉ
፡፡
የኮንስትራክሽን የአካባቢ የግንባታ ግብዓቶች በሆኑት ጠጠር፣ አሸዋ፣ ድንጋይና ምርጥ አፈር አስተማማኝ
የአቅርቦት ሥርዓት እንዲኖረው ማድረግ አልተቻለም፡፡ የኢንዱስትሪው ፍላጎትና የአቅርቦት አቅም ክፍተት
ይስተዋልበታል፡፡ የጠጠር አቅርቦቱን እንዳይሻሻል በመለዋወጫ እና የኤለክትር እጥረት ምክንያቶች
ክሬሸሮች በተሟላ አቅማቸው አምርተው እያቀረቡ አይደለም፡፡ አሁንም የኮንክሪት ምርት በስፋት ለማምረት
የሜካናይዜሽን ሥራ ለማስፋፋት ምቹ ሁኔታ አልተፈጠረም፡፡ የእነዚህ ክሬሸሮች የኤሌክትሪክና የካባ ጣቢያ
ችግር ተፈትቶ በተሟላ አቅማቸው ቢያመርቱ እንኳ የኢንዱስትሪው ፍላጎት ማሟላት በሚችሉበት ደረጃ
ላይ አይደሉም፡፡ የምርቶቹ ማቅረቢያ ተሽከርካሪዎች እና አጋዥ ማሽነሪዎች እጥረትም ሌላው ችግር ነው፡፡
በዚህም ምክንያት በኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የዋጋ መናር፣ የጊዜ መጓተትና የጥራት መጓደል ላይ የበኩልን
አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳረፈ ነው፡፡

የእነዚህ ችግሮች መንስኤ ዋና ዋናዎቹ በመለየት ዘላቂ መፍትሔ አስቀምጦ ለአፈጻጸሙ መረባረብ
ያስፈልጋል፡፡ ለኢንዱስትሪው ግብዓት ከሆኑ ምርቶች አንዱ የብረታ ብረት አቅርቦት ክፍተት መሆኑን
ለይተናል፡፡ ለአቅርቦቱ ማነስ መንስኤው ደግሞ የመጀመሪያው በሀገር ውስጥ ያሉ ፋብሪካዎች በሙሉ
አቅማቸው ማምረት እንዳይችሉ የኃይል እጥረት ሲሆን ሁለተኛው ለብረታ ብረት አቅርቦት ችግር መንስኤ
የጠገራ ብረት አቅርቦት ችግር ነው፡፡ የውድቅዳቂ ብረትም ቢሆን የማሰባሰቢያ ሰንሰለቱ ግልጽ ሥርዓት
ተዘርግቶለት እየተፈጸመ ባለመሆኑ በበቂ መጠን ማግኘት አይቻልም፡፡ ጠገራ ብረት አቅርቦትና በኃይል እጥረት
ምክንያት ፋብሪካዎቹ የሚያመርቱት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ከሚፈልገው ከ 50 በመቶ ያልበለጠ ነው፡፡
ለሴራሚክስም ምርት ማነስ ተጠቃሽ መንስኤ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ለብረታ ብረትም እንደተጠቀሰው የኃይል
አቅርቦት ማነስና መቆራረጥ ነው፡፡ የፕላስቲክ ምርቶች የአቅርቦቱ ማነስ መንስኤ ከ 90 በመቶ በላይ የሚሆኑ
ግብዓቶቹ ከውጭ ሀገር የሚገቡ በመሆኑ ነው፡፡ ከኃይል እጥረት በተጨማሪ ለሁሉም የጋራ የሚሆነው
ተመሳሳይ የችግሩ መንስኤ ደግሞ የምርቶቻቸው ጥራት መፈተሸያና ማረጋገጫ ዘመናዊ ላቦራቶሪ የሌላቸው
መሆኑ ነው፡፡

1.2.5.6 የፋይናንስና የማሽነሪ አቅርቦት በቂ ያለመሆኑ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከፍተኛ የካፒታልና የመሳሪያዎች አቅም የሚጠይቅ የሥራ ዘርፍ ነው፡፡
በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለመሰማራት ዜጎች ፍቃድ ለማውጣት ሲንቀሳቀሱ የሚጠየቁት የካፒታል መጠን
ቀላል ባለመሆኑ ከጥረቱ ይገታሉ፡፡ ኢንተርፕራይዞቹ የፋይናንስ ችግራቸውን ለመፍታት ተብሎ የተቀመጠው
የቅድሚያ ክፍያ ውጤታማ በሆነ መንገድ የመጠቀም ልምድና ባህሉ የለም፡፡ በአሰሪዎችም በኩል ውጤታማነቱ
ተከታትለው የሚያረጋግጡበትና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ግልጽ አሰራር አልተዘረጋም፡፡ ብዙ ፕሮጀክቶች
በተቀመጠው መርሃ-ግብርና የጥራት ደረጃ ለማስፈጸም በሚደረገው ጥረት ማነቆ ሆነው ከተለዩ ጉዳዮች
አንዱ ከፋይናንስ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ችግር ነው፡፡

18
ለእነዚህ ችግሮች መሠረታዊ መንስኤ ከሚባሉት አንዱ በኢንዱስትሪው ያለው የመረጃ አደረጃጀትና ሀቀኝነት
ነው፡፡ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚሰማሩ ባለሚናዎች ወቅታዊና ሀቀኛ መረጃ ቢኖራቸው ኖሮ ለብዙ
ችግሮች መፍትሔ መሆን በቻለም ነበር፡፡ ለአሰሪዎች ተጨማሪ ክፍያ ለመፈጸም ተጨባጭ ማስረጃ
ሊሆናቸው ይችል ነበር፡፡ እንደዚህ ዓይነት መረጃ ሲኖር ባንኮች ከኢንዱስትሪው ባለሚናዎች የሚቀርብላቸው
የብድር ጥያቄ በአግባቡ ገምግመው፣ የፕሮጀክቶቹን አዋጪነትና አስተማማኘነት መሠረት ያደረገ የብድር
መጠን መፍቀድ የሚችሉበት ሰፊ ዕድል ይከፍትላቸው ነበር፡፡ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው እንደዚህ ዓይነት
የተሟላ፣ ሀቀኛና ወቅታዊ መረጃዎች ስለሌሉ ባንኮች የሚያበድሩት ገንዘብ መጠን ለመወሰን መቸገራቸው
አልቀረም፡፡ ይህ ችግር በመሠረታዊነት ካልተስተካከለ ኢንዱስትሪው በፋይናንስ እጥረት በቀጣይነት መቸገሩ
የማይቀር ይሆናል፡፡ በፋይናንስ ረገድ ሁለተኛ የችግሩ መንስኤ ደግሞ በኮንስትራክሽን ኢንዲስትሪ የሚሰማሩ
ባለሞያዎች የቁጠባ ባህል ያለማዳበራቸው ነው፡፡ ባለሀብቱና አማካሪዎች የሚያገኙትን የስራ ክፍያ በፍጆታና
ለስራው ብዙም በማይደግፏቸው ጉዳዮች ላይ ገንዘቡን ሲያውሉት ይታያል፡፡ በተዋናዮቹ በኩል አስተማማኝ
ተበዳሪ ለመሆን ሀቀኛና ወቅታዊ መረጃ ከማቅረብ በተጨማሪ የቁጠባ ባህል ያለው ተበዳሪ መሆን
ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ ረገድም የቁጠባ ባህሉ በጣም ደካማ ነው፡፡ ሶስተኛው መንስኤ ደግሞ ሥራውን በመድን
ዋስትና ለመደገፍ ያለው የዝግጁነት መጓደል ነው፡፡ ኢንሹራንስ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የተሰማራ አንድ
ተቋም ሊሸከመው የሚከብደውን አደጋ (Risk) በጋራ በመሸከም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቱን በተረጋጋ ሁኔታ
እንዲቀጥል አቅም የሚፈጥር አሰራር ነው፡፡ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የተሰማሩ ተቋማት
ሊያጋጥማቸው የሚችለውን አደጋ ለመቋቋም የሚያስችላቸውን ከስራው ጋር የተያያዙና ዋስትና የሚፈልጉ
ጉዳዮች በቅድሚያ ውል ገብቶ መፈጸም ላይ የግንዛቤ ክፍተት በስፋት ይስተዋላል፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የፋይናንስ እጥረት ካባባሱት ከላይ ከተጠቀሱት ጉዳዮች በተጨማሪ ሌላው
ምክንያት የኮንስትራሽን መሳሪያዎች አቅርቦት እና ፍላጎት ያለመጣጣሙ ነው፡፡ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ
ከሚካሄዱ ፕሮጀክቶች የመንገድ፣ የባቡር፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የግድብ… ወዘተ ሥራዎች ዘመናዊ የሆኑ
ማሽነሪዎች ይፈልጋሉ፡፡ ማሽኖቹም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ ስለሆነ የሚጠይቁት ካፒታል ከፍተኛ ነው፡፡
ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው የፋይናንስ እጥረቱ ደግሞ ዙሪያ መለስ ችግር መሆኑ ተብራርቷል፡፡ በዚህ ዓይነት
በኮንስትራክሽን ኢንዲስትሪ የሚሰማሩ ኩባንያዎች የመነሻ ካፒታል ሲያጥራቸው የማምረቻ መሳሪዎቹና
ማሽነሪዎቹን ከመሳሪያ ሊዝ ኩባንያ ተከራይተው የሚሰሩበት ሁኔታ ቢኖርም በቂ አይደለም፡፡ እነዚህ የሊዝ
ኩባንያዎች ለኮንስትራክሽን ኩባንያዎች የኢንቨስትመንት ፋይናንስን በማምረቻ መሳሪያዎችና ማሽነሪዎች
ኪራይ መልክ በማቅረብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረግ ሲችሉ ይህንን ሚናቸውን በአግባቡ የሚወጡ ኩባንያዎች
አልተደራጁም፡፡ የመሳሪያ ሊዝ ኩባንያዎች ለማቋቋም የሚያስችል አዋጅ በመንግስት የወጣ ቢሆንም ከአዋጁ
ተከትለው መውጣት የሚገባቸው ደንብና መመሪያ በወቅቱ ባለመውጣታቸው አጥጋቢ ውጤት ያለው ስራ
ሣይከናወን ቆይቷል፡፡ በመሆኑም በዚህ ረገድ ያሉትን ችግሮች ፈትሾ በፍጥነት ተግባራዊ በማድረግ የመሳሪያና
የማሽነሪ ሊዝ ኩባንያዎች ተገቢ ድርሻቸውን እንዲጫወቱ የማድረጉ ስራ መዘግየቱን መግባባት ያስፈልጋል፡፡

1.2.5.7 የዘርፉ ዋና ዋና ባለሚናዎች በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ በጋራ የሚሰሩበት ሁኔታ


ያለመፈጠሩ

19
አንዳንድ የመንግስት ፕሮጀክቶች በቅድሚያ የተደራጀ የአዋጪነት ጥናት እና የተሟላ ዲዛይን እስከነዋጋው
ድረስ አይዘጋጅላቸውም፡፡ የፕሮጀክቶቹ የዋጋ፣ የጥራትና የዲዛይን ትክክለኛነት በሚመለከተው ተቋም
የሚፀድቅበት አሰራር የተጠናክ አይደለም ፡፡ ፕሮጀክቶቹንም በወጣላቸው መርሃ-ግብር መሠረት ለማጠናቀቅ
የሚያስችል የተሟላ የቅድመ ዝግጅት ስራ በአግባቡ አይከናወንም፡፡ የግብዓት አቅርቦት በተሟላ መንገድ
የሚቀርብበት ሥርዓት በውል አልተዘረጋም፡፡ ለግንባታ የሚያስፈልገው መሬት ከማንኛውም ዓይነት የይገባኛል
ጥያቄ ፀድቶ ለግንባታ ዝግጁ እየተደረገ አይደለም፡፡ በተለይ በመንገድ ፕሮጀክቶች እንደ ዉሃ፣ መብራት፣ አና
የስልክ መስመሮች መሰረት ልማቶች በግዜዉ አለመነሳት የግንባታ ግብአት ማምረቻ ቦታ አለማግኝት፣ ለብዙ
ፕሮጀክቶች መጓተት እንዱ መክንያት ሆኑዋል ፡፡ ወደ ግንባታ ኮንትራት ከተገባም በኋላ የግንባታ መርሃ-ግብሩ
ተጠብቆ እንዲፈጸም በማድረግ በኩል ከፍተኛ ክፍተት ይታያል፡፡ አማካሪው በፕሮጀክቱ ዋጋ መናር፣ የጥራት
መጓደልና በወቅቱ ባለማለቁ ላይ ተጠያቂ የሚያደርግ ሥርዓት አልተዘረጋም፡፡ ለግንባታ ፕሮጀክቱ የወጣው
ወጪና የስራው ዋጋ (Value for Money) ተመጣጣኝ መሆናቸው የሚገናዘብበት ተቋማዊ አሰራር የለም፡፡
የመንግስት አስፈጻሚ ተቋማት የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶቻቸው በአግባቡ ማስፈጸማቸውን የሚረጋገጥበትና
ጉድለት ካለም የማስተካከያ ምክር የሚሰጥበት ሥርዓት በሀገራችን አልተፈጠረም፡፡ በሀገራችን በከፍተኛ
መጠን ኮንስትራክሽን እየተካሄደባቸው ያሉ የመንገድ፣ የባቡር፣ የአየር ማረፍያ፣ የውሃና ፍሳሽ፣
የቴሌኮሙኒኬሽን፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የህንፃዎችና ቤት…ወዘተ የመንግስት ፕሮጀክቶች አሰሪ ተቋማት
የግልጽነት መርህን ለማስተግበር የሚያስችል ሥርዓት በመዘርጋትና የተጠያቂነት መርህንም በጣምራ
የሚያስፈጽም የሥራ ክፍል በመሰየም ሲያስተገብሩ አይስተዋልም፡፡ ተጠያቂነትና ግልጽነት እርስ በእርሳቸው
ተሳስረውና ተመጋግበው በተቀናጀ አኳኋን ለመተግበር የሚያደርገው ጥረት ሥርዓት አድርጎ መገንባት ላይ
ጉድለት ይታያል፡፡

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ በመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ የሆኑ ፕሮፌሽናሎች የእየራሳቸው ፕሮፋይል
ኖሯቸው ፕሮፌሽናል ብቃታቸው በተግባር ተመዝኖ እየተረጋገጠ የብቃት የምስክር ወረቀት የሚያገኙበት
ሥርዓት አልተዘረጋም፡፡ በመሆኑም በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የተሰማሩ ባለሀብቶች ብቃት ያለውና
የሌለውን ለይተው የሚቀጥሩበት ሥርዓት የለም፡፡ ከትምህርትና ስልጠና ተቋሞች ሰልጥነው የሚወጡ
ወጣቶች የመለማመጃ ዕድል እንዲያገኙ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች በተነሳሽነት የሚሰሩበት ሁኔታ
የተለመደ አይደለም፡፡ የኢንዱስትሪው አስተባባሪ ወይም ተቆጣጣሪ አካል በዘርፉ የሚስተዋለውን የብቃት
ጉድለት አጥንቶ ከትምህርትና ስልጠና ተቋማቱ እንዲሁም ከባለሀብቶቹ ጋር የትብብር መድረክ በመፍጠር
የፕሮፌሽናሎቹና መለስተኛ ባለሙያዎቹ ብቃት የሚረጋገጥበትና ስምሪታቸውም ከዚህ አንጻር እንዲሆን
የተደረገው ጥረት መዘግየት የሚስተዋልበት ነው፡፡

በኮንስትራክሽን ዘርፍ እጅግ ብዙ የጥቃቅንና አነስተኛ ኩባንያዎች ሊቋቋሙ እንደሚችሉና እንደሚገባ


ይታወቃል፡፡ በዚህ ረገድ በሀገራችን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም ይህ እንቅስቃሴ ሥርዓት በማስያዝ
ረገድ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ የጥቃቅንና አነስተኛ ኩባንያዎች ከመካከለኛና ትላልቅ ኩባንያዎች ጋር
በንዑስ-ኮንትራት ከወሰዱት ፕሮጀክት የተወሰነ ድርሻ ወስደው የሚሰሩበት ሁኔታ በስፋት መፍጠር ላይ
ክፍተት ይታያል፡፡ በዚህ ሁኔታ መስራት ብንጀምር ኖሮ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞቹ የስራ ዕድል
ማግኘት ብቻ ሳይሆን ስለኢንዱስትሪው በፍጥነት ልምድ እያገኙ ብክነት የሚቀንሱበትና ፍጥነት
የሚጨምሩበት ሁኔታ በብዛት መፍጠር የሚቻልበት ዕድል እያመለጠን ነው፡፡ የመካከለኛና ትላልቅ ኩባንያዎች

20
በፕሮጀክት አፈጻጸም መዘግየት ምክንያት የሚያጋጥማቸው ኪሳራ ቀላል ባልሆነ መጠን መቀነስ በቻሉም
ነበር፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በሚስፋፋበት ወቅት ኢንዱስትሪውን የሚመግቡ የተለያዩ ግብዓቶችን
የሚያቀርቡ ሌሎች ኢንዱስትሪዎች አብረው እንዲያድጉ የተያዙ ዕቅዶች በፍጥነት መፈጸም ያለባቸው
ናቸው፡፡

በዘርፎቹም መካከል ቀልጣፋ የግብይትና የመመጋገብ ሥርዓት በአጣዳፊነት ካላስፈጸምን በአንድ በኩል
የኮንስትራክሽን ኢንዲስትሪ ዕድገት ለሌሎች ዘርፎች የሚፈጥረውን ተጨማሪ ዕድገት ዕድል አሟጠን
ሳንጠቀም እንድንቀር የሚያደርግ በመሆኑ የጀመርነው የዕድገት ጉዞ በሚገባው ደረጃ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው
እንዳይሆን ማድረጉ የማይቀር ነው፡፡ በዚህ ረገድ ያለንን ምቹ ሁኔታ በአግባቡ ካልተጠቀምን ለማኑፋክቸሪንግ
ዘርፍ ዕድገት ማበርከት ይቻል የነበረው አስተዋፅኦ በአግባቡ ስራ ላይ አይውልም፡፡

የኮንስትራክሽን ዘርፍ እንደሌሎቹ ኢንዱስትሪዎች ሁሉ ከፍተኛ የመነሻ ካፒታል እጥረት እንዳለበት


ይታወቃል፡፡ ይህ ዘርፍ መካከለኛና ትላልቅ እንዲሁም እጅግ በጣም ብዙ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች
የሚሰማሩበት እና በኢንዱስትሪው የሚፈለጉ ኢንቨስትመንቶች የራሳቸው ባህሪ ቢኖራቸውም ከዚህ ጋር
አብሮ የሚሄድ የካፒታል አቅርቦት ሥርዓት አላደገም፡፡ ዘርፉን የሚያስተባብረውና የሚቆጣጠረው ተቋምም
በዚህ ረገድ ያደረገው እንቅስቃሴ በጣም የተወሰነ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ እንደሌሎቹ ልዩ ትኩረት
የሚሹ ኢንዱስትሪዎች ሁሉ በኮንስትራክሽን ዘርፍም ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ለይቶ
ለመንግስት በማቅረብ ማስወሰን፣ በዘርፉ ተዋናይ የሆኑ ክፍሎችን ያሳተፈና በአግባቡ የተደራጀ የጋራ መድረክ
መፍጠር፣ የዘርፉን ችግሮች በማጥናት እነዚህን ለመፍታት የሚያስችልና የእያንዳንዱን ተዋናይ ሚና በትክክል
የሚያስቀምጥ ዕቅድ በማዘጋጀትና በጋራ ጥረት የሚደረግበት ሥርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆን
መቻል የነበረበት ቢሆንም በዘርፉ በተስተዋለው የማስፈጸም አቅም ክፍተት ምክንያት እነዚህ ጉዳዮች
ሳይፈጸሙ ቆይተዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት መድረክ በመፍጠር የዘርፉን ችግሮች በመለየትና የመፍትሔ ዕቅድ
በማዘጋጀት የጋራ አመለካከትና ተልዕኮ በመገንባት ለኢንዱስትሪው ቀጣይ ዕድገትና መሠረት ለመጣል
የተደረገው ጥረትና ርብርብ ውስንነት ያለው መሆኑን ተገንዝቦ ይህንን የሚያስተካክል ዕቅድ አዘጋጅቶ
ለውጤታማነቱ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡

1.2.5.8 የባለሙያዎች፣ የኩባኒያዎች፣የህንፃ ግንባታና መጠቀሚያ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር አገልግሎት


የተሳለጠ ያለመሆን

ህንፃ ግንባታና የከተማ ፕላን እጅግ የተቆራኙ በመሆናቸው ሁለቱንም አስተሳስሮ ማየት ለልማታዊ ፖለቲካል
ኢኮኖሚ ሥርዓት ግንባታችን መሠረታዊ ሆኖ ይታያል፡፡ ከዚህ አንፃር የከተማ መሬት አጠቃቀማችን እና በህንፃ
ግንባታ ሂደት የምንከተላቸው አሰራሮች በይዘትም ሆነ በአቅጣጫ የሃገራችንን የኢኮኖሚ አቅም ከግምት
ያስገቡ፣ መሬትን በቁጠባ መጠቀም የሚያስችሉ እና መሠረታዊና ተቀባይነት ያላቸው የከተማ ፕላንና የህንፃ
አዋጆችንና መስፈርቶች ላይ የተመሠረቱ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ለዚህም ደረጃውን ለጠበቀ ህንፃ ግንባታና
ዲዛይን በጥናትና በምርምር የተደገፈ የከተማ ኘላን አቅም መገንባት ወሳኝ ይሆናል፡፡ መሪ ኘላን፣ የአካባቢ
ልማት ኘላንና ዝርዝር ኘላን ያላቸው ከተሞች መኖር የህንፃ ግንባታ ልማቱን ለማከናወን መሠረት ቢሆንም
በሃገራችን እነዚህ ተሟልተው ወደ ህንፃ ግንባታ የሚገባበት ሁኔታ ውስንነት የሚስተዋልበት ነው፡፡

21
ከመሬት አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የህንፃዎች ግንባታ በፌዴራል፣ በክልል ወይም በከተማ አስተዳደር በጸደቁ
ሃገራዊ ወይም ክልላዊ ወይም ከተማ ነክ አጠቃላይ የፕላን ድንጋጌዎች እንዲመራ፣ የህንፃ አዋጅ ወጥቶ
እየተተገበረ ነዉ ፡፡ በህንፃ ግንባታዎች ኢንዱስትሪ ለነዋሪውና ለህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ
አገልግሎቶችን የሚሰጡ ህንፃዎች በከተማው መሪ ፕላን የተቀመጡ የህንፃ አጠቃቀሞችን፣ ከፍታዎችንና
የሰፈር ወይም የአካባቢ ፕላን ገጽታዎችን መሠረት ያደረገ የፕላን ስምምነት እየተዘጋጀላቸው፣
ዲዛይኖቻቸውን በመመርመር፣ የግንባታ ክትትል በማድረግና የመጠቀሚያ ፈቃድ እየተሰጣቸው ወደ
አገልግሎት እንዲገቡ መደረግ ሲኖርበት በሃገራችን በብዙ ከተሞች አዲስ አበባን ጨምሮ በርካታ ግንባታዎች
ከዚህ አሠራር ውጭ ሲካሄዱ ይታያል፡፡ በአዋጁ በግልጽ እንደተደነገገው ለአካል ጉዳተኞችና ለአረጋውያን
የተመቹ ወይም የእነሱን ፍላጎት ከግምት ውስጥ ያስገቡ ግንባታዎች መካሄድ አለባቸው፡፡ ይህን በወቅቱ
ማስተካከል ካልቻልን ግንባታዎች እየፈረሱ አደጋ የሚያደርሱበትና ብክነት የገነገነበት ሀገር መሆናችን
የማይቀር ነው፡፡ በመሆኑም ከወጣው ሕግ ውጭ የሚያስፈጽሙ አካላት ለሚፈጠረው የአሰራር ዝንፈት
ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ሥርዓት በፍጥነት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ በሕጉ መሰረት
ባለቤት፣ ተቋራጭና አማካሪ እንዲሁም ተቆጣጣሪ በጥብቅ የሚጠየቁበት ሁኔታ መፍጠር መቻል አለብን፡፡

አንዳንድ ተገልጋዮች የሚያቀርቧቸው የትምህርትም ሆነ የተሽከርካሪ ማስረጃዎች (ሊብሬ)

የተጭበረበሩ መሆናቸውን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች ይስተዋላሉ፡፡ መሰል ችግሮችን መቅረፍ

የሚያስችል የተቀናጀ የአሰራር ስርአት ባለመዘርጋቱና ከሌሎች መስሪያ ቤቶች ጋር ያለው የመረጃ

ልውውጥ ዘዴ የተሳለጠ ባለመሆኑ ምክንያት ሰነዶችን ማጣራት ቢያስፈልግ የማጣራት ሂደቱ ረጅም

ጊዜ የሚወስድ መሆኑ የስራ መጓተት እና ግለሰቦች በተጭበረበረ ማስረጃ ፈቃድ እንዲያገኙ

በማድረግ ህገ-ወጥ አሰራር እንዲሰፍንና በአጠቃላይ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ላይ አሉታዊ

ተጽዕኖ እንዲፈጠር እያደረገ የሚገኝ ጉዳይ ነው፡፡

ከምዝገባ አገልግሎት አሰጣጡ ጋር የሚታየው ሌላው ችግር የመረጃ አያያዝ እና አስተዳደር ችግር

ነው፡፡ የመዝገብ ቤቱ አደረጃጀት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ አለመሆን፤ መረጃዎች በአንድ

ወጥ የመረጃ ቋት (database) የማይያዙ በመሆኑ፤ በምዝገባ አገልግሎቱ ውስጥ ያሉ ሰነዶች

(ፋይሎች) ለረጅም ጊዜ የተጠራቀሙ በመሆኑ፣ አገልግሎት የማይሰጡ ፋይሎች የሚወገዱበት

አሰራር አለመኖሩ እና አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለው የሰው ኃይል አደረጃጀት ውስንነት በስፋት

የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸው፡፡ በተከማቹ ፋይሎች ምክንያት የፋይሎችን የኋላ ታሪክ ማየት እና

ማጥራት እንዲሁም ችግር ያለበትን መለየት አስቸጋሪ ከማድረጉም ባለፈ ቦታ በማጣበብ የፋይል

አያያዝ ስርዓቱን ውስብስብ በማድረግ የፋይል መጥፋትና በቀላሉ አለመገኘትና ሌሎች ችግሮች

እንዲከሰቱ ምክንያት ሆኗል፡፡

22
የምዝገባ ስርአታችን ጠቀሜታና አስፈላጊነት በቀጣይ በአግባቡ ተፈትሾ የተሳለጠ የአሰራር ስርአት

(Ease of Doing Business) ከማስፈን አንጻር አንድ የትኩረት አቅጣጫ ሊቀመጥለት የሚገባ ጉዳይ

ይሆናል፡፡

1.2.5.9 ፈርጀ ብዙ ሥራዎች ተጣጥመው የሚታቀዱበትና የሚተገበሩበት ሥርዓት ያለመዘርጋቱ

ሀገራችን እያስመዘገበች ባለችው የኢኮኖሚ ዕድገት ምክንያት በኢኮኖሚው ውስጥ የኮንስትራክሽን


ኢንዱስትሪ ያለው ድርሻ በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ ላይ ነው፡፡ ብዛት ያለው የስራ ዕድልም በመፈጠር ላይ
ይገኛል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮች አሉ፡፡

የሴቶች ድርሻ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በሚጠበቀው ደረጃ አይደለም፡፡ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ


የሚሰማሩ ሴቶች ከወንዶች እኩል ስራ ቢሰሩም በክፍያ ረገድ በአንዳንድ የፕሮጀክት ማሳያዎች እኩል
እየተከፈላቸው አይደለም፡፡ ይህም ክትትል ተደርጐ ተገቢው የግልጸኝነትና ተጠያቂነት ሥርዓት ሊዘረጋበት
የሚገባ ጉዳይ መሆን መቻል ነበረበት፡፡ ሴቶች ባበረከቱት የስራ አስተዋፅኦ ልክ እንዲከፈላቸው ማድረግ ሕገ-
መንግስቱና ሥርዓቱ ያጎናፀፋቸው መብት በመሆኑ በፍጥነት መፈታት ያለበት ችግር ነው፡፡ በኢንዱስትሪው
የሚሰማሩ ሴቶች ቁጥርም በሚጠበቀው ደረጃ ለማሳደግ የራሱ ዕቅድ ወጥቶ ከትምህርት ቤት ጀምሮ
መሰራት እና የዘገየ ስራ ተደርጎ መወሰድ ያለበት ነው፡፡

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከሚታዩት ችግሮች ውስጥ በግንባታ ሂደት እና በግንባታ አካባቢ በሰራተኞች
ደህንነት አጠባበቅ ዙሪያ የህብረተሰቡ ጤናና ደህንነት በተመለከተ በሚፈለገው ደረጃ መሟላት አለመቻሉ
አንዱ ነው፡፡ በሀገራችን በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሚሰማራው የሰው ኃይል የሥራ አካባቢ ጤና እና
ደህንነት በተመለከተ ለመከታተል፣ ለመቆጣጠር እንዲሁም ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ሥርዓት ባለመዘርጋቱ
ግንባታዎች ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ ሲከናወኑና ጉዳት ሲደርስ ይስተዋላል፡፡ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው
በተሰማሩ አካላት በሚካሄዱ የግንባታ ፕሮጀክቶች በዘልማድ ከሚደረጉ ዝግጅቶችና ጥንቃቄዎች በስተቀር
በሰው ኃይሉ ጤንነትና ደህንነት አጠባበቅ ረገድ በተገቢው እንዲፈጸም የሚያስገድዱ ደንቦችና መመሪያዎች
ያሉ ቢሆንም በግንባታዎች አካባቢ ከመለስተኛ የጤና እና የአካል ጉዳት እስከ ሞት የሚያደርሱ አደጋዎች
እየተከሰቱ ነው፡፡ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለሚታዩት የጤና እና የደህንነት አደጋዎች እንደመንስኤ
ከሚጠቀሱት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የግንባታ መሳሪያዎች፣ እና መከላከያ ልብሶች ያለመሟላት እና የሥራ ላይ
ደህንነት አጠባበቅ ያለው ግንዛቤ እና ቁርጠኝነት አናሳ መሆኑ ነው፡፡ በስራ ቦታ ሊደርሱ ከሚችሉ አደጋዎች
ለመከላከል የሚያስችሉ ቅድመ ጥንቃቄዎች በአግባቡ አይደረጉም፡፡ ለሰራተኛውም ተገቢው ስልጠና
አይሰጠውም ፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሰራተኞችን ከስራቸው ባህሪ የተነሳ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቃሽ በመሆናቸው


ለኤች.አየ.ቪ./ለኮቪድ … ጉዳት የተጋለጡ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይታመናል፡፡ ይህንን በተመለከተ አሰሪውም ሆነ
ተቀጣሪው በቫይረሱ ምክንያት የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የጋራ ጥረት የሚያደርጉበት ግንዛቤ እንዲኖር

23
ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ በአብዛኛው የጉልበት ሰራተኞች ልቅ የሆነ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ለቫይረሱ መተላለፍ
ምክንያት መሆኑን ጠንቅቀው በማወቅ የዕለት ተዕለት ጥንቃቄ ስለማያደርጉ ለችግሩ ሰለባ ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡
በመሆኑም ቫይረሱ የሚተላለፍበትን መንገድ እንዲገነዘቡና የመከላከያ አማራጮችንም ጠንቅቀው እንዲያውቁ
ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በግንባታ ተጓዳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ የማህበረሰቡ አካላት
በተመሳሳይ ስለ ኤች.አየ.ቪ. ግንዛቤ እንዲኖራቸው በስልጠና መደገፍ ይኖርባቸዋል፡፡

ሌላው ጉዳይ ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከተፈጥሮ ሀብት
ውጤቶችና ከአካባቢ ምርቶች አጠቃቀም ጋር በቀጥታ የተያያዘ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኮንስትራክሽን
ኢንዱስትሪ የደን ውጤቶችን፣ ውሃን፣ ምርጥ አፈርና ድንጋይን እንደሚጠቀም ግልጽ ነው፡፡ እነዚህ ምርቶች
በአግባቡ ጥቅም ላይ የሚውሉበት ሥርዓት ካልተፈጠረ ለአካባቢ ብክለት የራሱ አስተዋፅኦ ሊያበረክት
ይችላል፡፡ በመሆኑም በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚከናወኑ ተግባራት ለተፈጥሮ ሀብትና ለአካባቢ ጥበቃ
ተገቢው ትኩረት እንዲሰጥና በመልካ ምድራዊም ሆነ በሥነ-ሕይወታዊ ሁኔታዎች እንዲሁም በማኀበራዊ፣
ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ እሴቶች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ምን ሊሆን እንደሚችል በጥናት እየተለየ የመፍትሔ
ሥርዓት ሊዘረጋለት ይገባል፡፡ ለእነዚህ የተፈጥሮና የአካባቢ ሀብት በአግባቡ ያለመጠቀም መንስኤዎች
የተወሰኑትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ግንባታ ኮንትራት ወቅት ስለአካባቢ ጥበቃ
ተገቢው ግንዛቤና ትኩረት እየተሰጠው አይደለም፡፡ የግንባታ ስራውና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃውን የየራሳቸው
የክብደት ሚዛን በመስጠት ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል ስልት በመቅረጽ ለማስተግበር የሚደረገው ጥረት
በሚፈለገው ደረጃ ያለመሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የሚደረገው ቁጥጥር አናሳ ከመሆኑም በተጨማሪ
የአስፈጻሚው አካል አቅምና የማስተግበር ችሎታው አነስተኛ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት በፖሊሲው በተቀመጠው
አቅጣጫ መሰረት ለማስፈጸም የሚያስችል ዕቅድ ወጥቶ መተግበር ይኖርበታል፡፡

1.2.5.10የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ፕሮግራም በተሟላና በቀጣይነት ያለመተግበር

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፕሮግራም ወይም ማዕቀፍ ስንል ሀገራዊ የኮንስትራክሽን


ኢንዱስትሪ የሚመራበት ሲሆን በውስጡም ፖሊሲ፣ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣
ስታንዳርዶችና ማንዋሎችን እንዲሁም ተያያዥነት ያላቸውን የዘርፉ የዕውቀት፣ የክህሎትና
የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ለማለት ነው፡፡ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ከሚያንቀሳቅሰው ሰፊ የሰው
ኃይል እና የፋይናንስ አቅም አንፃር ወጥ የሆነ ሀገራዊ ማዕቀፍ መኖሩ የግድ ይሆናል፡፡
በመሆኑም ይህ ሰፊ ክፍተት ታይቶ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ማዕቀፎች ተዘጋጅተው
ባለመገኘታቸው የተጠያቂነትና ግልጽ አሰራር ለማስፈን አልተቻለም፡፡ ዘርፉ በዋናነት ሙያዊ
አገልግሎቶች የሚሰጡበት እንደመሆኑ መጠን ደረጃቸውን የጠበቁ የፕሮጀክት አፈጻጸም
መለኪያ ስርዓቶች በየንዑስ ዘርፉ ሊኖሩ ይገባል፡፡ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ደረጃዎችን ማዕከል
ያደረገ ከፕሮጀክት ጽንሰ ሃሳባዊ ማዕቀፍ ጀምሮ እስከ ኦፕሬሽንና ጥገና ሂደቶች ድረስ
የአሰራር እና ዝርዝር የፖሊሲ ማስፈጸሚያ ፕሮግራሞች አዘጋጅቶ መተግበር ወሳኝ ይሆናል፡፡

የሕንፃ፣ የመንገድ፣ የውኃ፣ የመስኖ፣ የግድብና የኃይል ማመንጫ ልማታችን የተሳካ እና


ውጤታማ እንዲሆን የሚያግዙን የሠራነው ወይም በስርዓት የተዋስነው መሠረታዊ የቴክኒክ

24
ሰነዶች የሚያሳዩ ማዕቀፎች የሉንም፡፡ የስታንዳርድ ስፔስፊኬሽን ዲዛይን ማንዋል፣
የኮንስትራክሽን ጥራት ቁጥጥር፣ የኮንስትራክሽን ዋጋ ትንታኔ መመሪያ፣ የኮንስትራክሽን
ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር አገልግሎት ግዥና አፈጻጸም ማንዋል፣ የኮንስትራክሽን ሳይት
ማኔጅመንት ጋይድ ላይን እንዲሁም በርካታ ኮዶች ወዘተ… የመሳሰሉት በተሟላ አኳኋን ስራ
ላይ አሟልቶ መተግበር ላይ ዘግይቷል፡፡ በሌላ በኩል የኮንስትራክሽን ዘርፉን አቅም ለመገንባት
የሚያስችል የኢንቬስትሜንት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የሰው ኃይል ልማት፣ የፋይናንሲንግና
የዋስትና አሰጣጥ ፖሊሲና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ጉድለትም ይስተዋላል፡፡ ስለዚህ
እነዚህንና መሰል ቴክኒካዊ ሰነዶች በሀገራችን ልማታዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ግንባታ ሂደት
ተመጋጋቢ ሆነው በሁሉም ዘርፍ መዘጋጀታቸው በሁለት አብይ ምክንያቶች ተፈላጊ ይሆናሉ፡፡
አንደኛው የምንገነባቸው ፕሮጀክቶች ወጪ ቆጣቢነት፣ ጥራትና የፕሮጀክቶችን ደህንነትና
ቀጣይነት ማስጠበቅ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ ሁለተኛው ደግሞ ግልጽነትና ተጠያቂነትን
በማስፈን ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለመገንባት የሚያስችል ምቹ ሁኔታን መፍጠር
ስለሚያስችል ነው፡፡ ይህም ልማታዊ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ባለሀብትና ኢንተርፕራይዝ
እንዲፈጠር መሰረት የሚጥል ይሆናል፡፡

በአጠቃላይ በሁሉም ዘርፎቻችን የሚካሄዱ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ተወዳዳሪነትን


አረጋግጠው እንዲጠናቀቁና በሂደትም የሚገነባው ሀገራዊ አቅም ዘላቂ እንዲሆን ለማስቻል
በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ፕሮግራም እና የተሟላ
የሕግ ማዕቀፍ መፍጠር ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት፡፡

1.3 ርዕይ

በሐገር ዉስጥና በክፍለ አህጉራዊ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በ 2022 በመገንባት
ለሐገሪቱን የብሌጽግና ራእይ ስኬት አስተዋጽኦ ማበርከት ፡፡

1.4 ተልእኮ
“የኮንስትራክሽን ዘርፍ የአቅም ግንባታና የሬጉላቶሪና አቅም በማሳደግ የባለድርሻ አካላትን በማስተባበርና
በመደገፍ ቀልጣፋ፣ ምርታማ፣ ደህንነቱንና የተጠበቀና በክፍለ አህጉር ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የኮንስትራክሽን
ኢንደስትሪ መፍጠር ፡፡

1.5 ዓላማ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲን ተከትሎ አቅምን መገንባት፣ ምርታማነትን መጨመር ብሎም
ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው ሥርዓት የሚከተሉ ተቋማትን በመፍጠርና የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት

25
ተልዕኮዎቻቸውን እንዲወጡ መደገፍን ያካትታል፡፡ ይህንን ተልዕኮ ለማሳካት የሚከተሉትን አራት ጉዳዮችን
ማረጋገጥ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

1) ለሚከፈለው ዋጋ ተመጣጣኝ እሴት እና ጥራት መፍጠርና የአካባቢን ደህንነት ከግምት ውስጥ ያስገባ
ቀልጣፋ አገልግሎት መቅረቡን ማረጋገጥ፣

2) የዘርፉን የመፈጸም አቅም በማሳደግ ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መገንባቱን

ማረጋገጥ፤

3) ዘርፉ ለዜጎች ምርታማ፣ ምቹና አዳጊ የሥራ ዕድል መፍጠሩን ማረጋገጥ

4) የኮንስትራክሽን ዘርፉ ለሀገራዊ ምርት የሚኖረውን አስተዋጽኦ ማጎልበትና ለሃገራዊ እድገት

መሠረት እየጣለ እንዲሄድ ማድረግ

1.6 ስትራቴጂያዊ ግቦች

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ርዕይ ለማሳካት የተቀመጡ አቅጣጫዎችና ስትራቴጂዎች በተሟላ መልክ
በመፈጸም በ 2022 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዋና ዋና ግቦች እናሳካለን፡፡
1) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን በብቃት የሚመራ፣ የሚያስተባብርና የሚደግፍ ተቋማዊ አቅም
ይፈጠራል፡፡
2) በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ መሠረታዊ የአመለካከት ለውጥ በማምጣት ለሙስናና ብልሹ
አሠራር የሚዳርጉ አሠራሮችን በማስወገድ ለልማታዊ የዘርፉ ባለሃብቶች የተመቻቸ ሁኔታ
ይፈጠራል፡፡
3) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን የሚፈልገው የሰው ኃይል በማልማት የኢንዱስትሪው የሰለጠነ
የሰው ኃይል ችግር በመሠረታዊነት /በዘላቂነት/ ይቀረፋል፡፡
4) የዘርፉን ችግር ለመፍታት በሌሎች ሀገሮች የተፈጠሩ ቴክኖሎጂዎችን በላቀ ፍጥነትና ተከታታይነት
ባለው አኳኋን በመኮረጅ ባጠረ ጊዜና ወጪ ወደ ሀገራችን አምጥቶ በመጠቀም የኢንዱስትሪው
ተወዳዳሪ ይገነባል፡፡
5) ሀገር በቀል የኢንዱስትሪው ተዋናዮችን የማስፈጸም አቅም በመገንባት በጊዜ፣ በዋጋ እና በጥራት
ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማብቃት በሃገር ውስጥ ገበያ ያላቸው ተሳትፎ እንዲያድግና ምርትና
አገልግሎታቸው ወደ ክፍለ አህጉር እንዲደርስ ይደረጋል
6) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ምርታማነት እንዲያድግ የሚያስችል ልዩ ድጋፍና ክትትል በማድረግ
የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች አቅርቦት አጠቃቀም እንዲያድግ እና የኮንስትራክሽን መለዋወጫ
በሀገር ውስጥ ኩባንያዎች የማምረት አቅም እንዲፈጠር ይደረጋል፡፡
7) ድጋፍ በማድግ፣ቴክኖሎጂዎችን በመኮረጅ እንዲሁም ፈጠራን በማበረታታት አብዛኛዉን
የኮንስትራክሽን ግብአት አገር ዉስጥ በማምረት እና አቅምን ያገናዘቡ ግብአቶችን ከዉጭ በማስገባት
አስተማማኝ አቅርቦት ሰንሰለት ይዘረጋል ፡፡

26
8) መንግስታዊና የግል ባለሀብቱ እንዲሁም የሌሎች ተዋናዮችን አቅም በመገንባት ቀልጣፋ፣ ግልጸኝነት
እና ተጠያቂነትን ያነገሠ አሠራር በመዘርጋት የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ዋጋ፣
ጥራት ደረጃና ጊዜ የሚጠናቀቁበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡
9) የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን የሚያፋጥኑ የመሰረተ-ልማት አውታሮችን እንደ መንገድ፣ ውሃ
አቅርቦት፣ግድብ፤ መኖሪያ ቤት የመሳሰሉትን በተቀላጠፈ አኳኋን የመገንባት ደረጃ ይደረሳል፡፡
10) በኢንዱስትሪው ባለሚናዎች መካከል ቅንጅታዊ አሠራር በማጐልበት፣ አለም ዓቀፋዊና ክፍለ
አህጉራዊ ትብብር በማጠናከር፣ የኢንዱስትሪው ብቃትና ተወዳዳሪነት ይጐለብታል፡፡
11) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሰፊ የስራ ዕድል ፈጣሪና እያደገ እንዲሄድ በማስቻል ለሀገራዊ ምርትና
ገቢ ከኢንዱስትሪው የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ይደረጋል፡፡

27
ክፍል ሁለት
2 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ጉዳዮችና የአፈጻጸም
አቅጣጫዎቻቸው

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዲስትሪ ልማት ፖሊሲ የኮንስትራክሽን ኢንዲስትሪው በዋና ዋና ርዕሶች ሥር


የተመደቡ የፖሊሲ አቅጣጫዎች እንዲኖሩት ተደርጐ ተዘጋጅቷል፡፡ የእነዚህ የፖሊሲ አቅጣጫዎች በተሟላ
መልኩ መተግበር ኢንዲስትሪው የመሠረተ-ልማትና ሌሎች አገልግሎቶች እንዲሟሉ እና ለልማቱ ቀጥተኛ
ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ለሃገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ በመሆን የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጐላ እንዲሆን
ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም የተጠናከረ የማስፈፀም አቅም በመገንባትና ባለሚናዎች ለዘርፉ ዕድገት በጋራ
የሚሰሩበትን ሁኔታ በማመቻቸት ፖሊሲው የልማታችን ማፋጠኛ መሣሪያ እንዲሆን ርብርብ ማድረግ
ያስፈልጋል ፡፡

2.1 የሌብነት አረንቋን ማድረቅና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በመፍጠር በጎ ገጽታ መገንባት ፣

ሀ) ዓላማ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ሙስናን እና ብልሹ አሠራር የሚጸየፍና የሚከላከል ኃይል ለመፍጠር ፍትሃዊ
ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥና በጎ ገጽታ ለመገንባት ነው ፡፡

ለ) ፖሊሲ

1) በዘርፉ የሚሰማሩ አስፈጻሚዎች፣ አማካሪዎችና ተቋራ à ች በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው


የሚኖራቸው ሚና በልማታዊነትና በተወዳዳሪነት መንፈስ እንዲገነባ የሚያስችል ሠፊ የአመለካከት
ማቅናት ሥራ ይካሄዳል፡፡
2) የዲዛይንና ኮንስትራክሽን አገልግሎተ አሰጣጥ በግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ውጤታማነትን ባረጋገጠ
የአሠራር ሥርዓት ተደግፎ መተግበሩ ይረጋገጣል፡፡
3) በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚሳተፉ ባለድርሻ አካላት የስነ-ምግባር መርሆዎችና ኮድ እንዲተገብሩ
ይደረጋል፡፡
4) በኢንዱስትሪው የሚሣተፉ ባለሙያዎች የሙያ ማህበራት እንዲያቋቁሙ በማድረግ፣
ለዩኒቨርስቲዎች በቂ ግንዛቤ በመፍጠር እና ለሙያዊ ሥነ-ምግባር መጐልበት ጠንክረው እንዲሠሩ
ይበረታታሉ፡፡
5) በከፍተኛ ወጪ የሚገነቡ ግንባታዎችን የአፈጻጸም ደረጃና ወጪ እንዲመረመርና እንዲጠና ይደረጋል፡፡
ችግሮች ሲኖሩ በመደበኛ አኳኋን እየተጠኑ አዳዲስ ሃሳቦችና መመሪያዎች ለሚመለከታቸው አካላት
አቅርቦ እንዲፀድቅና እንዲተገበር ያደርጋል፡፡
6) የኮንስትራክሽን ኮንትራት ህጎችና አሠራሮች እንዲተገበሩና አፈፃጸማቸውንም ክትትል ይደረግበታል፡፡
የግዢ አስፈጻሚ አካላትንም አቅም በተከታታይ እንዲገነባ ይደረጋል፡፡

28
ሐ) የማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች

1) በኮንስትራክሽን ሂደት በቅድመ ግንባታ ጊዜ፣ በግንባታ ጊዜ እና በድህረ ግንባታ ጊዜ የሚኖሩ


መረጃዎችና መመሪያዎች ለህዝቡና ለተዋናዮች ግልጽ የሚደረግበት ሥርዓት ገንብቶ በመተግባር
እንዲሁም ሥርዓቱን የማይከተል ሲኖር ተጠያቂ በማድረግ፣
2) የመንግስትና ለህዝብ አገልግሎት የሚውሉ ግንባታዎች ከተጠናቀቁና የመጨረሻ ርክክብ ከተፈፀመ
በኋላ ለግንባታው የተፈጸመውን ክፍያና በክዋኔ ኦዲት የተረጋገጠውን ግምት በማነፃጸር ትምህርት
የሚወሰድበት ሥርዓት በመዘርጋት፣
3) የኮንስትራክሽን አገልግሎት ግዥ የውስብስብነት ባህሪ ሙያ የሚጠይቅ በመሆኑ በግዥው ላይ
የሚሳተፉ ባለሙያዎች የሙያ ብቃታቸው እና ስብጥራቸው የሚረጋገጥበት /certification/ ሥርዓት
ዘርግቶ ተግባራዊ በማድረግ፣
4) በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለሚሠማሩ አካላት የስነ-ምግባር መርሆ መተግበር የሚኖረው ሃገራዊ
ፋይዳ ላይ ሰፊ የግንዛቤና የህዝብ ግንኙነት ሥራ በቀጣይነት በመስራት፣
5) ኢንዱስትሪውን የሚመሩ አካላት በመሰረተ-ልማት አቅርቦት፣ በፕሮጄክቶች አፈጻጸም፣
በሙያተኞች ክህሎትና ምርታማነት አጠቃላይ የውጤታማነት መለኪያ መስፈርቶችን በማዘጋጀትና
በመለካት ዘለቄታዊነቱን በማረጋገጥ፣

2.2 ብቃት ያለዉ ፕሮፌሽናልና ባለሙያ የሚበቃበት አቅጣጫ በብቃት መፈጸም

ሀ) ዓላማ

ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በምህንድስና፣ በአርክቴክና በተያያዥ የሙያ ዓይነቶች መርታማና ብቃት


ያለዉ ባለሙያ በማልማት የኢንዱስትሪውን ችግር በመሠረታዊነት ለመቅረፍ ነው፡፡
ለ) ፖሊሲ

1) በየትኛውም ደረጃ የሚመደብ የሰው ኃይል ለተመደበበት ቦታ የተሟላ ዕውቀት እና ክህሎት ያለው እንዲሆን
ይደረጋል፤ የሰው ኃይል ክምችት ለማወቅም በምዘናና ምዝገባ የታገዘ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ የቴክኒክና ሙያ
ማሰልጠኛ ተቋማትን በማጠናከርና በማደራጀት በቂ ቁጥርና የሙያ ብቃት ያላቸው መካከለኛ እና መለስተኛ
ባለሙያዎች እንዲሰለጥኑ፣ በምዘናና ምዝገባ ሥርዓት ውስጥ እንዲያልፉ ይደረጋል፡፡
2) በኢንዱስትሪው በፕሮፌሽናል፣ በመካከለኛ ደረጃ እና በተግባር የሰለጠነው የሰው ኃይል በምዝገባ እና በምዘና
ከተለየ በኋላ በየዘርፉ የሚጐለውን በዩኒቨርስቲ፣ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ማዕከላት አማካይነት ከአስፈፃሚ
ተቋማት ጋር በተሳሰሩ ሥልጠናዎች እንዲሟሉ ይደረጋል፣
3) ትላልቅ ኩባንያዎች በሥራቸው የሥልጠና ማዕከላት እንዲኖሯቸው በማድረግ የሚያሰለጥኗቸውን ባለሙያዎች
በቅድሚያ በሚያደርጉት ስምምነት መሠረት የሚያቆዩበት ሥርዓት ይዘረጋል፡፡

29
4) ለየሴክተሩ የተዘጋጁትን የተለያዩ የብቃት ደረጃዎች በመጠቀም፣ ተጨማሪ ደረጃዎችን በመለየት እና የሙያ
እድገት መሠላል በመፍጠር የሚሰጡ የሥራ ላይ ሥልጠናዎች በበቂ እውቀት እና ክህሎት በፖኬጅ መልክ
እንዲዘጋጁ በማድረግ ባለሙያዎች ደረጃ በደረጃ ከፍ ወዳለ ዕርከን እንዲያድጉ ይደረጋል፡፡
5) የሥራ ተከታታይነት እና ቅልጥፍና ለማረጋገጥም የአንድ የኮንስትራክሽን የስራ ቡድን ቁጥር ከታቀደው የሥራ
መጠን ጋር አጣጥሞ በመገመት አደረጃጀቱ ከተዛማጅ ሥራዎች ጋር ተያይዞ የሙያ ብቃትና ውጤታማነት
የሚያሳልጥ ስታንዳርድ የግንባታ ቡድን (Specialized Crew/ Team) ሆነው እንዲደራጁ ይደረጋል ፡፡

ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

1) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚፈለገውን የሠለጠነ ባለሙያ ለማልማት የሚያስችል
የሥልጠና መርሀ-ግብር ቀርፀው እንዲተገብሩ በማድረግ፣ ተማሪዎቻቸውም ከንድፈ ሃሳብ ትምህርት ትይዩ
የተግባር ልምምድና ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ፤ የትምህርት ሥርዓቱንም ከተቋማቱ የሚወጡት በቀጥታ
ኢንዱስትሪውን በሚያገለግሉበት ደረጃ በመቅረፅ፣
2) የኢንዱስትሪውን ባለሙያ የሥልጠና ዕቅድ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ሁኔታ እንዲመራ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ
ምክር ቤት የማማከር ኃላፊነት እንዲወጣ በማድረግ፤
3) ለኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ሥልጠና አገልግሎት ቀጣይነት ያለው የስልጠና ፋይናንስ በመንግስትና
በኢንዱስትሪው ትብብር በመመደብ፣
4) የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ለማስፈፀም የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል በየሙያውና ደረጃው
በሚመለከታቸው አካላት በማሰባሰብ፤ ፕሮጀክቶችን የባለሙያዎች የብቃት መመዘኛ ማዕከል አድርጎ በመጠቀም፤
በምዘናና ምዝገባ ሥርዓት ያለውን የሰው ኃይል መረጃ በመያዝ ፤
5) በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት አቅም ግንባታ ረገድ፡-
i) በሀገሪቱ የተገነቡ ልዩ ልዩ የቴክኒክና ሙያ ማዕከላት የሚሰጡ የሙያና ክህሎት ምዘና ስራዎችን
በመደገፍ፣
ii) ለምዘናና ስልጠና የሚያስፈልጉ ወጪዎችን በመጋራት፣
iii) ከኢንዱስትሪው ፍላጎት አንጻር ለሚፈጠሩ አዳዲስ ዘርፎች ስልጠናና ብቃት ማረጋገጥ
የሚያስችል የአቅም ግንባታ ዝግጅት በማድረግ፣
6) በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አቅም ግንባታ ረገድ፡-
i) በዘርፉ ልማት ላይ የተመሰረተ ጥናትና ምርምር በማካሄድ፣
ii) የትምህርት ካሪኩለሞች በተጨባጭ ከልማት አጀንዳዎች ጋር እንዲተሳሰሩ በማድረግ፣
iii) በስታንዳርድ ዝግጅት ላይ የቴክኖሎጂ ፋኩልቲዎችን አቅም በማሳደግ፣
7) የምህንድስና ሙያዎችን ማዕከል ያደረጉ በአጭር ጊዜ የማበረታቻና የማቆያ ጥቅማ ጥቅሞች ሥርዓት በመዘርጋት፣
ከረዥም ጊዜ አንጻር ደግሞ በመስኩ በብዛትና በጥራት አቅርቦቱ እንዲያድግ በማድረግ፣
8) በሰራተኞች ማህበራትና በፕሮጄክት ኮርፖሬት ማናጅመነት መካከል በሚደረጉ የህብረት ስምምነቶች የክህሎት
ስልጠና እና የክፍያ ተመጣጣኝነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር፣

2.3 በዘርፉ ቀልጣፋና ጠንካራ የገበያ ውድድር የሚያሰፍን አሠራር መዘርጋት

2.3.1 ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ ቅልጥፍና እና ወጤታማነት የሚያረጋግጥ አሰራር ማስፈን

30
ሀ) ዓላማ

በኮንስትራክሽን አገልግሎትና የግብዓት ግዥ ሂደት ተሳታፊ የሚሆኑ የአገልግሎቱ ገዢ፣ አማካሪዎች፣ የሥራ
ተቋራጮች፣ የኮንስትራክሽን ግብአት አቅራቢዎች፣ ንዑስ ተቋራጮች እንዲሁም ከሥራው ጋር በተዘዋዋሪ
ግንኙነት ያላቸው ሌሎች ባለሚናዎች የሚኖራቸው ኮንትራት ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለውና ሥራውን
በሚፈለገው ጊዜ፣ በተገመተው ዋጋና ጥራት ደረጃ ለማስፈጸም የሚያስችላቸው አቅም ኖሯቸው
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በቅልጥፍና እንዲጠናቀቁ ማድረግ የሚያስችል አቅም ለመፍጠር ነው፡፡
በአንጻሩም ይህንን ፖሊሲ መሰረት በማድረግ የአስገዳጅነት አቅም እንዲኖረው የሕግ ማዕቀፍም
ለማዘጋጀት እንዲያግዝ ጭምር ነው፡፡

ለ) ፖሊሲ

1) በህንጻ፣ በትራንስፖርት መሠረተ ልማት እና በውሃ ሥራዎች ልማት ሥራ ላይ ግልፅ ተልዕኮ የወሰዱ
ተቋማት ብቁ አደረጃጀት እንዲኖራቸው ይደረጋል ፡፡
2) ሰፊ የገበያ ጉድለት በሚታይባቸው ግዙፍ እና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ የሚጠይቁ ፕሮጀክቶችን መፈፀም የሚችል
የሲቪል ኢንጅነሪንግ ሥራዎች የጥናትና ዲዛይን ተቋም ግንባታ ይካሄዳል፡፡ አሠራራቸውም ግልጽነትና
ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ እንዲሆን ይደረጋል ፡፡
3) በኮንስትራክሽን ልማት ኦፕሬሽናል ሥራዎች ትይዩ የአቅም ግንባታ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ የሚችልና የተለያዩ ተልዕኮ የሚወስድ የስልጠና ሥርዓት ይዘረጋል ፡፡
4) የባለሙያዎች የአማካሪዎች፣ የተቋራጮችና የአቅራቢዎች ብቃት ለማረጋገጥ የሚያስችል የባለሙያዎች መብትና
ግዴታ ግልጽነትና ተጠያቂነትን በሚያረጋግጥ አኳኋን የምዝገባ አዋጅ በማዘጋጀት ይተገበራል ፡፡
5) የፌዴራል፣ የክልልና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተወካዮች የሚገኙበትና ለኢንዱስትሪው ምክር የሚሰጥ ሀገራዊ
የኮንስትራክሽን ምክር ቤት ሃላፊነቱን እንዲወጣ በማድረግ ፡፡
6) የኮንስትራክሽን አገልግሎት ሰጪዎችና ግብዓት አቅራቢዎች ያላቸውን ብቃት የሚያሳዩበትና አዳዲስ
ቴክኖሎጂዎችን የሚያስተዋውቁበት ዓመታዊ የኮንስትራክሽን አውደ ርዕይ ቀን አለም ዓቀፍ ይዘት
ባለው አግባብ እንዲዘጋጅ ይደረጋል፡፡
7) የዲዛይንና ኮንስትራክሽን ጥራት እንዲሁም ግልፅነትና ተጠያቂነት የሚያግዙ አስገዳጅ ስታንዳርዶች
ተዘጋጅተው ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
8) ለየግንባታ ዓይነቶች የተቋቋሙ የጥራት መፈተሻ ማዕከላት ብቃት ባለው የሰው ኃይልና በዘመናዊ
የላቦራቶሪ መቆጣጠሪያ ቁሳቁሶች የተሟሉ እንዲሆኑ ድጋፎች ይደረጋሉ፡፡

ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

የግልፅነት፣ ውጤታማነት፣ ተጠያቂነትና ቅልጥፍና ያለው አሠራር ለመዘርጋት ተልዕኮ የሚወስዱ ተቋማት ኃላፊነታቸውና
የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎቻቸው እንደሚከተለው ቀርቧል፤

31
1) የመንግስት አስፈፃሚዎች በኮንስትራክሽን ኢንዱስሪው የተፈጠረውን ጉድለት በፍጥነት
ከማስተካከል አኳያ፡-

i) በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚመለከታቸውና ግንባር ቀደም አስፈፃሚ የሆኑትን የመንግስት መ/ቤቶች


በኮንስትራክሽን ዘርፍ ባለቤትነትና አስተባባሪነት የኮንስትራክሽን ስራዎች አፈፃፀም በጠንካራ
ቅንጅት በማስፈፀም፣
ii) በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የገበያ ጉድለት ባለባቸው መስኮች በተመረጠ አኳኋን ጣልቃ
መግባት እና በቀጣይ ለግሉ ዘርፍ ዕድገትና ልማት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር፣
iii) የመንግስት መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ማዕከል በማድረግ ዩኒቨርስቲዎች በጥናት፣ ዲዛይንና
ማማከር አገልግሎት በማሳተፍ የቴክኖሎጂ አቅም እንዲዳብር በማድረግ፣
iv) ኢንዱስትሪው በየደረጃው የሚመራበትን ግልጽና ተጠያቂነት ያለው የአሠራር ሥርዓት
በመተግበር፣ ተጠያቂነትን በማስፈን፣ የኮንስትራክሽን ጥራት ቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት፣
ውጤታማ ማድረግ ይቻላል፡፡

2) በምዝገባ ተቋማት ተግባርና ኃላፊነት ስር የሚወድቁና ለኢንዱስትሪው ማዘመን ወቅታዊ


የሆኑ ተግባራት ከማስፈጸም አኳያ፡-

i) የፕሮጀክት አገልግሎት አሠጣጥ አማራጮችን ያገናዘበ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተናባቢና


በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ የምዝገባ ሥርዓት በመገንባት እና የሀገር በቀል ኩባንያዎች እና
ባለሙያዎች ወደ ኢንዱስትሪው ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው አሠራር ገብተው እንዲሠሩ
በመደገፍ፣
ii) በኢንዱስትሪው የተሠማሩ የምህንድስናና ኮንስትራክሽን ባለሙያዎች እና ድርጅቶች ተፈላጊውን
ብቃት አሟልተው መሠማራታቸውን በማረጋገጥ ፣
iii) የተመዘገቡ ባለሙያዎች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን የሙያ ሥነ-ምግባር መርሆዎች /Code of Ethics/
አዘጋጅቶ ተግባራዊ በማድረግ እና ለኢንዱስትሪው ተዋናዮች ያሉባቸውን ክፍተቶች የሚሞላ
የሥልጠና ፕሮግራም እና የብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት በመንደፍና በመተግበር ውጤት ማስመዝገብ
ይቻላል ፡፡

3) በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ምክር ቤት መሰራትና መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች በማስተግበር

በህግ የተቋቋመው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ምክር ቤት በዘርፉ የሚታየውን የላላ አደረጃጀት ለማጠናከር
እንዲቻል፡-
i) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በለውጥ ጐዳና እንዲጓዝ የሁሉንም ተዋናዮች አቅምና ተሣትፎ
ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የጋራ አመራር እና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በመስጠት፣

32
ii) ምክር ቤቱን ለቅንጅት እና ለማስተዋወቅ ጤናማ የመወዳደር አቅም ለመገንባት እንደ አንድ የጋራ
ማዕከል በመጠቀም፣
iii) ኢንዱስትሪ አቀፍ ፎረሞችን በመፍጠር እና በማበረታታት ቅንጅትና ትብብርን በማጐልበት፣
iv) የኮንስትራከሽን ንዑስ ዘርፎች በማህበር እንዲደራጁ በማበረታታት ማጠናከር ይቻላል፡፡

4) በሙያ ማህበራት አማካይነት መተግበር ያለባቸው ተግባራትን በማስፈጸም

በኢንዱስትሪው ያሉ ኃይሎች እንደ አገልግሎታቸውና በየተሠማሩበት መስክ ተቀራራቢነት መደራጀት


ለኢንዱስትሪው ልማትና ጠንካራ አደረጃጀት መፈጠር ጉልህ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም፡-
i) ማህበራት በአባሎቻቸው ለሚበረከቱ ተግባራት ሙያዊና ተቋማዊ አገልግሎቶች ጥራት
ለማስጠበቅ፣ ተወዳዳሪ የሆነ ኢንዱስትሪ ግንባታ ሂደት አፈፃፀም፣ ለሙስናና ብልሹ አሠራር
የሚቋቋም ሥርዓት በመዘርጋትና በመሳተፍ የማይተካ ሚና እንዲጫወቱ በማድረግ፣
ii) የሙያ ማህበራት ለአዳዲስ ግኝቶች እና ችግር ፈቺ የሆኑ የምርምር ውጤቶችን መሠረት
በማድረግ የአባሎቻቸውን ዕውቀትና ክህሎት እንዲገነቡ በመደገፍ፣
iii) ማህበራት የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና በተለይም ወጪ ቆጣቢ፣ አዋጪ፣ አካባቢን የማይበክሉ፣
የህዝብን ደህንነትና ጤንነት የማይጐዱ እና የአካባቢን የአደጋ ተጋላጭነት በመቀነስ ትኩረት የሠጠ
አመለካከት ያላቸው እንዲሆኑ በማድረግ፣
iv) የሙያ ማህበራት በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ አቅማቸውንና
አፈጻጸማቸውን በማሻሻል የሙያና አገልግሎታቸውን ደረጃ በማሳደግ የመወዳደር አቅም በማሳደግ
ተሳትፎአቸውን ማጎልበት ይቻላል፡፡

5) በኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች በፍጥነት መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ከማስተካከል አኳያ፡-

i) በተቋራጭነት የሚይዟቸውን የኮንስትራክሽን ውሎች በገበያ ዋጋ፣ የጥራት ደረጃና የጊዜ ገደብ
ለማስረከብ በሚያስችል መንገድ በማቀድና በማስተዳደር እንዲሁም ሥራቸውንና
ሠራተኞቻቸውን በአግባቡ በመቆጣጠር ካልሆነም ተጠያቂነት እንደሚኖር በማድረግ፣
ii) የሠራተኞቻቸው ብቃት ደረጃ ከሚሠጣቸው ተግባር ጋር ተመጣጣኝ መሆኑን
በማረጋገጥና ተገቢነት ያለውን ተግባር ተኮር ሥልጠና በመስጠት፣
iii) ስለኘሮጀክቶቻቸው ተገቢ የሆነ መረጃ ለሠራተኞቻቸው በማቅረብ፣
iv) የግንባታ ቦታ ደህንነት በማስጠበቅ እና የአደጋ ተጋላጭነት በመቀነስ፣
v) በሁሉም አቅጣጫ፣ ጥራትን የሚቀንሱ፣ ተወዳዳሪነትን የሚያዳክሙ የሙያ ክብርን
የሚያዋርዱ ተግባራትን በመከላከል፣ ሥነ ምግባርን በማጐልበት፣ ሙያዊ ግንኙነት
ከአማካሪውና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በማስፈጸም የሴክተሩን እሴቶች ማስጠበቅ
ይቻላል ፡፡

6) በአማካሪ ድርጅቶች አማካይነት ኃላፊነት ወስደው መስተካከል ያለባቸው ስራዎች ከማስፈጸም አኳያ፡-

33
i) ለኘሮጀክቶች ጥናት ተመጣጣኝ ብቃት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል
አደረጃጀት መፈጠሩን በማረጋገጥ፣
ii) በዲዛይን ዝርዝር ዝግጅቶች፣ ተቀባይነት ያላቸው ስታንዳርዶችን በተሟላ አኳኋን ሥራ
ላይ በማዋል፣
iii) ለኘሮጀክት ባለቤቶች በውሉ መሠረት ተገቢ የሆነ ግንባታ መከናወኑን ለማረጋገጥ ጠንካራ
ሙያዊ ክትትል በማድረግና በወቅቱ ፕሮጀክቱ ባይጠናቀቅና ከውሉ ውጭ ሆኖ ቢገነባ
ተጠያቂነት እንዲኖር በማድረግ፣
iv) በኘሮጀክት ትግበራ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በኃላፊነት ሥሜት በፍጥነት
በመፍታት፣
v) የኢንዱስትሪውን ዕድገት ከሚገቱ አሠራሮች በመራቅ ሥነ ምግባሩን የሚያሣድግ ባለሙያ
እንዲፈራ በማድረግ፣
vi) ተወዳዳሪ ያልሆነ ዋጋ ከመስጠት መቆጠብና ሌላውም እንዳይሰጥ ጠንክሮ በመስራት፣
vii) ጥራትን የሚያረጋግጡ የአሠራር ዘይቤዎችን በማላመድ የቁጥጥር ሥራዎች እንዲጠናከሩ
በማድረግ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ፡፡

7) በአርክቴክትና ምህንድስና ባለሙያዎች አማካይነት መሠራት ያለባቸው ተግባራት ከማስፈጸም አኳያ፡-

i) ሙያዊ ሥነ ምግባርን በመላበስ ለሕዝብ ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት ባለሙያው


የተሠማራበት መስክ እንዲያድግ አስተዋፅኦ በማበርከት፣
ii) ጥራትንና ተወዳዳሪነትን ከሚገቱ ተግባራት ራስን በማራቅና በዚህ ተግባር ተሠማርተው የሚገኙ
ካሉም እንዲታረሙ በማድረግ፣
iii) ተዓማኒነት ያለው ሙያዊ አገልግሎት እንዲስፋፋ በሙያ ማኀበሩ ተደራጅቶ እንዲንቀሣቀስ
በማድረግ፣
iv) የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን ሥራዎች እንዲስፋፋ ራስን ከወቅታዊ
ቴክኖሎጂዎችና ሀገራዊ ስታንዳርዶች ጋር በማስተዋወቅ፣
v) ለኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር የሚያጋልጡ መንገዶችን በመዝጋት በልማታዊ መንገድ
ለህዝብ አገልግሎት በመስጠት፣
vi) በተመዘገቡበት የሙያ መስክ ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲመጣና ኘሮጀክቶችም የተሣኩ እንዲሆኑ
ተገቢ የሆነ አገልግሎት በተማሩበት እንዲሠጡ በማድረግ እና በተሰማሩበት ፕሮፌሽን ወይም ሙያ
የብቃት ማረጋገጫ ምዘና በመውሰድ ሰርቲፋይድ በማድረግ የሙያ ማብቃት ማሳደግ ይቻላል፡፡

8) በግብዓት አቅራቢዎች አማካይነት ተልዕኮ ተወስዶ መፈጸም ያለባቸውን ስራዎች ከማስፈጸም አኳያ፡-

34
i) የኮንስትራክሽን ጥራትን የሚቀንሱ ግብዓቶች ወደ ገበያው እንዳይገቡ ጥብቅ ቁጥጥር
በማድረግ፣
ii) የአካባቢ ብክለት የሚያስከትሉ፣ በህዝብ ደህንነት አደጋ የሚያስከትሉ የኮንስትራክሽን
ዕቃዎች ሥራ ላይ እንዳይውሉ በማድረግ፣
iii) ከደረጃ በታች ወይም የዋናው ግልባጭ (forged) የሆኑ ግብዓቶች በገበያ ገብተው ህዝቡ
እንዳይጭበረበር በማድረግ ጥራትን በማስጠበቅ፣
iv) ተወዳዳሪ የሆነ ዋጋ፣ የጥራት ደረጃ እና የተሻለ ጊዜ በመስጠት ቀጣይነት ያለው ዕድገት
እንዲመጣ በመስራት ማስተካከል ይቻላል፡፡

9) የኮንስትራክሽን አመራር ብቃት ለማሳደግ የሚያስችል አሠራርና አደረጃጀት ከመፍጠር አኳያ፡-

i) የኮንስትራክሽን ሂደቶች ውጤታማ እንዲሆኑና በላቀ የጥራት፣ የዋጋና የጊዜ ደረጃ እንዲከናወኑ
የሚያግዝ ወጥነት ያለው የኮንስትራክሽን አገልግሎትና ሥራዎች ግዥ ሥርዓት እንዲዘረጋ
በማድረግ፣
ii) በመንግሥትና በግሉ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተዋናዮች አጋርነት ችግር ፈች የሆኑ የሥልጠና፣
ጥናትና ምርምር፣ ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት በመዘርጋት (Service Level Agreement)፣
ምርጥ የፈጠራ ውጤቶችን እንዲተገብሩ በማበረታታት፣
iii) የዘርፉ ተዋናዮች ዘመናዊ የፕሮጀክት አስተዳደር እና አመራር እንዲሁም የኮንትራት አስተዳደር
አቅም እንዲገነቡ በመደገፍ፣
iv) ለኢንዱስትሪው መበልጸግ አጋዥ የሆኑ ኮንስትራክሽን ነክ የሆኑ ስታንዳርድ የፕሮጀክት ትግበራ
መመሪያዎች በማዘጋጀትና በማስተግበር፣
v) የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያመች ዘንድ ያልተማከለ አሰራር በማጎልበት የክልሎችና ከተማ
አስተዳደሮችን አቅም በመገንባት አገልግሎቶች ወደ ታች እንዲወርዱ እና በተቀላጠፈ አኳኋን
እንዲቀርቡ በማድረግ ውጤታማ ማድረግ ይቻላል፡፡

10) የኮንስትራክሽን ምርታማነት ፣ ጥራት እና ቅልጥፍና ለማሳደግ የሚያስችል አሠራርና አደረጃጀት


ከመፍጠር አኳያ ፡-
i) በኮንስትራክሽን ሥራዎችና ምህንድስና አገልግሎት የምርታማነትና ጥራት ቁጥጥር ፕሮጀክት
ማኔጅመንት ምርጥ ልምድ በመቀመር እና እንዲስፋፋ በማድረግ፣
ii) ምርታማነትን የሚጨምሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና መሣሪያዎች የሚቀርቡበት ሥርዓት ዘርግቶ ስራ
ላይ በማዋልና የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችና ዕቃዎች በዘላቂነት ለኢንዱስትሪው የሚቀርብበት መንገድ
በመቀየስ፣
iii) በሁሉም የኮንስትራክሽን ሥራዎቻችን ብቃት ያለው የቁጥጥር አገልግሎት መኖሩንና መሠጠቱ እና
በኮንስትራክሽን አገልግሎት ሥራዎች፣ በዲዛይን ዝግጅት እንዲሁም በኮንትራት አስተዳደር ቀልጣፋና
ውጤታማ የግዥ ሥርዓት እንዲኖር በማድረግ፣

35
iv) ኢንዱስትሪው ራሱን በራሱ የሚቆጣጠርበት እና ክፍተቶችን የሚያርምበት የአሠራር ዘዴ በመቀየስ
የሴክተሩን አቅም ማጎልበት ይቻላል፡፡

2.3.2 ጠንካራ የገበያ ውድድርን የሚያሰፍን አሰራር ማንገስ

ሀ) ዓላማ

በሃገራችን ያሉ አማካሪዎችንና ሥራ ተቋራጭ ኩባንያዎችን የማስፈፀም አቅም በመገንባት በሀገራዊ የኮንስትራክሽን


ልማት ሂደት ከሙስናና ከሌብነት ተግባር በፀዳ አኳኋን በጊዜ፣ በዋጋ እና በጥራት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ
በማብቃት በሃገር ውስጥ ገበያ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግና ምርትና አገልግሎታቸው ተወዳዳሪ እንዲሆን
በማስቻል ኢንዱስትሪው በመልካም ስነ-ምግባር የሚታወቅ እንዲሆን ለማድረግ ነው፡፡

ለ) ፖሊሲ

1) በመካከለኛ ደረጃ አዳዲስ የስራ ተቋራጮችን በማቋቋም፣ መካከለኛና ከፍተኛ ደረጃ ያሉ ነባር የሥራ
ተቋራጮች ደረጃቸውን እንዲያሳድጉ በማመቻቸት የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች ቁጥር በብዛት
እና በብቃት እንዲያድግ ይደረጋል፡፡ በየሥራ ዲሲፕሊኑ ልዩ የሥራ ተቋራጮች (Special
Contractors) በዓይነትና በብዛት እንዲደራጁ የተመቻቸ ሁኔታ ይፈጠራል፤ የንዑስ ሥራ ተቋራጭነት
አሠራርም ይጠናከራል፡፡
2) በመካከለኛ ደረጃ አዳዲስ አማካሪ ድርጅቶችን በማቋቋም፣ መካከለኛና ከፍተኛ ደረጃ ያሉ ነባር
አማካሪዎች ደረጃቸውን እንዲያሳድጉ በማመቻቸት እና የመግቢያ መስፈርቶችን በማስተካከል
የአገር ውስጥ አማካሪ ድርጅቶች ቁጥር በብዛትና በብቃት እንዲያድግ ይደረጋል፡፡ በሥራ ላይ ለሚገኙ
አማካሪ ድርጅቶች ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ የደረጃ መሻሻል እንዲያመጡ ይደረጋል ፡፡
3) የአገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮችና አማካሪዎች የፋይናንስ እና የመሣሪያ አቅም አጎልብተው የአገር
ውስጥ የገበያ ፍላጎት እንዲሸፍኑ ይደረጋል፡፡
4) በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች ዘመናዊ የኮንስትራክሽን አመራርና አደረጃጀት
እንዲኖራቸው ስልጠና በመስጠት የክህሎት ብቃታቸው እንዲረጋገጥ ይደረጋል፡፡
5) ከውጭ ሃገር ለሚፈፀሙ የምክር አገልግሎቶች ግዢ የአገር ውስጥ አማካሪ ድርጅቶች በፕሮጀክት
ትግበራው ላይ ተባባሪና አጋዥ (Counter part) ሆነው እንዲሰሩ የሚያደርግ አሠራር ይዘረጋል ፡፡
6) ፕሮጀክቶችን ማዕከል በማድረግ በአማካሪ ድርጅቶች ውስጥ የሚያገለግሉ ባለሙያዎች ያለባቸውን
የዕውቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት ችግሮች ለመቅረፍ እና ከነባር እና አዳዲስ ቴክኖሎጂ ጋር በአግባቡ
ለማስተዋወቅ ተከታታይነት ያለው የሥራ ላይ ሥልጠና በሙያው የዳበረ ዕውቀት ባላቸው የውጭ
ሀገር እና የሀገር ውስጥ ባለሙያዎች እንዲሰጥ ይደረጋል ፡፡
7) በምክር አገልግሎት ዘርፍ የምህንድስና የትምህርት ክፍሎች ያሏቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት
ምሩቃኖቻቸውን ከሚቀበሉ አስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች ጋር ስምምነት በማድረግ በምርምር
ሥራዎች፣ በአዋጪነት ጥናቶች፣ እና በዲዛይን ሥራዎች ላይ በመሣተፍ ዘርፉን አግዘው
የተቋማቸውን አቅም እንዲገነቡ ይደረጋል ፡፡

36
8) በየደረጃው የሚደረጉ የአቅም ግንባታ ድጋፎች በምቹ የውስጥ አደረጃጀት የታገዙ እንዲሆኑ የሥራ
ተ s ራ à ች እና የአማካሪ ድርጅቶች በሙያ ደረጃ ማረጋገጥ፣ የ ISO ወይንም ሌሎች አለም አቀፍ
መስፈርቶችን ያሟላ ውስጣዊ ይዘት እንዲኖራቸው ይደረጋል፡፡

ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

1) በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ትብብር በኮንስትራክሽን አመራርና አስተዳደር አቅም ለማሳደግ


በኮንስትራክሽን አገልግሎት አሠጣጥ ምርታማነት ለማሳደግ፣ የጥራት ቁጥጥር አስተዳዳር ለማጎልበት
የሚያስችሉ በጊዜ፣ በዋጋና በጥራት የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው ሀገሮችን ምርጥ ተሞክሮዎች ቀምሮ
ተግባራዊ በማድረግ፣
2) የኮንስትራክሽን ዘርፍ ኩባንያዎችን የሚደግፍና ለፋይናንስ ተደራሽነታቸውን የሚያሳድግ የብድር
ቦንድ፣ ዋስትና፣ የሥልጠና ፋይናንስ እና የመሳሪያና ግብዓቶች አቅርቦት የሚደግፍ ሥርዓት በመገንባት
እና የብድርና ዋስትና አሰጣጥ ሥርዓት ከፕሮጀክት የሥራ እንቅስቃሴ ጋር የተናበበ እንዲሆን በማድረግ፤
3) ለሀገራዊ ኮንስትራክሽን ኩባንያዎች መስፋፋትና ቀጣይ እድገት የአለም አቀፍ የግዥና ኮንትራት
አስተዳደር ማዕቀፎችን በማመቻቸት፣
4) በመንግስት ፋይናንስ ድጋፍ የሚገነቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የውጭ ኩባንያዎች ከሀገር ውስጥ ኩባንያዎች
ጋር በትብብር እንዲገቡ በማመቻቸት እና የሀገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች እና አማካሪ ድርጅቶች
ፕሮጀክት የመያዝ አቅም ሥርዓት በመዘርጋት እንዲሁም ሥራዎች በተሻለ ጥራትና ምርታማነት
እንዲሠሩ ንዑስ የሥራ ተቋራጭነትን በማበረታታት፤
5) የሥራ ተቋራጮች እና አማካሪ ድርጅቶች የተሟላ አቋም እንዲኖራቸው የ ISO ወይንም የሌሎች
ዓለም አቀፍ ደረጃ ሰጪዎች ያላቸውን የአሠራርና የአደረጃጀት ብቃት እንዲያስመዝኑ የውዴታ ግዴታ
እንዲገቡ፣ በእነዚሁ ፕሮጀክቶች አማካይነት የብቃት ደረጃቸው የተረጋገጠ ባለሙያዎችን
እንዲያሰማሩ በማድረግ፣

2.3.3 የመረጃ ልማትና ቋት ማጠናከር

ሀ) ዓላማ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ገጽታ የሚያሳይ ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓት በመፍጠር ኢንዱስትሪውን ለመለወጥ
የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ የሚያስችል የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ታዕማኒነት ያለው የመረጃ ቋት ወይም ዳታ ቤዝ
ለማደራጀት ነው፡፡

ለ) ፖሊሲ

37
1) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ገጽታ የሚያሳዩ መረጃዎች በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲሰበሰቡ ይደረጋል፡፡
የሚመለከታቸው ባለሚናዎችም በቅድመ ግንባታ ጊዜ፣ በግንባታ ጊዜና በድህረ ግንባታ ጊዜ
የሚጠበቅባቸውን መረጃ ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሚያደርጉበት ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
2) ለፖሊሲዎች፣ ኘሮግራሞች፣ የህግ ማዕቀፎች፣ ዕቅዶችና ለሌሎች የጥናት ሰነዶች ዝግጅት የሚውሉ
የኢንዲስትሪውን መረጃ የሚሰበስብ፣ የሚያደራጅና የሚተነትን አቅም በከተማ ልማት፣ ቤቶችና
ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና እንደየአስፈላጊነቱም በየደረጃው ይፈጠራል፡፡
3) መረጃዎችን የሚሰበስበውና የሚያደራጀው አካል የተቀላጠፈና ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያቀርቡበት
ሥርዓት (Service Level Agreement) በመዘርጋት እና የሕግ አስገዳጅነት እንዲኖረው በማድረግ
በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎት መስጠት እንዲችል በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ
ይደረጋል፡፡
ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

1) የዘርፉን ገጽታ የሚያሳዩ መረጃዎችን ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በአገር አቀፍ
ደረጃ እንዲሰባሰቡ በማድረግና ባለድርሻዎችም ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሚያደርጉበት ህግ አውጥቶ
በማስፈፀም፣
2) በፌዴራልና እንደ አስፈላጊነቱም በክልሎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ መረጃ የሚሰበስብና የሚያደራጅ
አቅም በመፍጠር፣
3) መረጃ የመሰብሰብ፣ የማደራጀትና የማቅረብ ሥራ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እንዲታገዝና የሚናበብ
በማድረግ፡፡

2.4 የፕሮጀክቶች ሥራ አመራር እና የቴክኖሎጂ ዕድገት ድጋፍ ሰጪ ተቋም በማደራጀት ሽግግሩን


ማቀላጠፍ

ሀ) ዓላማ

በመንግሥት የሚነደፉ የአጭርና ረዥም ጊዜ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች እንዲሁም በባለሃብቱ ለሚፈጸሙ


ልዩ ልዩ የኮንስትራክሽን ኢንቨስትመንቶች አፈፃፀም በጊዜ፣ በፋይናንስና በውጤት የላቁ እንዲሆኑ ለማድረግ
እና በመንግስት አስፈፃሚ ተቋማት፣ ዋና ዋና የፕሮጀክት ተዋናዮች የፕሮግራምና ፕሮጀክት ማኔጅመንት
አቅም በመገንባት የፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ለማሻሻልና በሃገራችን የተጀመረውን ፈጣን ልማት በላቀ ደረጃ
ለማስቀጠል ነው፡፡

ለ) ፖሊሲ

1) በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ስራዎች በተለያየ ደረጃ የሚሳተፉ የኘሮጀክት ኘሮፌሽናሎች የብቃት


ማረጋገጫ /certification/ የሚያገኙበትና ስራ ላይ የሚሰማሩበት አሰራር ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

38
በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ፕሮፌሽናል ሃገራዊ አቅም በመገንባት
የሰው ሃይል ካፒታል አቅም እንዲፈጠር ይደረጋል፡፡
2) የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅሜንት ኘሮፌሽናሎች አገር አቀፍ ማህበር እንዲቋቋም በመደገፍ
ከዓለም አቀፍ መሰል የሙያ ማህበራት ጋር ትስስር እንዲፈጥሩ ይደረጋል፣
3) ከትምህርትና ምርምር ተቋማት፣ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች እና ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲዎች ጋር
በመሆን ዓለም አቀፍ የተሻሻሉ ወጪ ቆጣቢ አማራጭ የግንባታ ስታንዳርዶችንና ቴክኖሎጂዎችን
እንዲሁም የዲዛይንና ፕላን አጋዥ የሆኑ ሶፍትዌሮችን በመምረጥ ከአገራችን ጋር በሚጣጣም
መልኩ እንዲዘጋጁ ይደረጋል፡፡ የአካባቢ ግብዓቶችን፣ ቴክኖሎጂዎችንና ምርጥ ተሞክሮዎችን በላቀ
ደረጃ መጠቀምና ሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችሉ የአሠራርና የአደረጃጀት ስታንዳርዶችና
መመሪያዎች በመንግስትና በግሉ ዘርፍ በኩል ተዘጋጅተው ተግባራዊ ይደረጋሉ፣
4) በሌሎች ሀገሮች የተፈጠሩ ቴክኖሎጂዎችን በላቀ ፍጥነትና ተከታታይነት ባለው አኳኋን በብቃት
የመምረጥ፣ ባጠረ ጊዜና ወጪ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት፣ በላቀ ውጤታማነት መጠቀም በዋጋና
በጥራት ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ እንዲገነባ የሚሰራ የሰው ኃይል በብዛትና በሚፈለገው
ጥራት ደረጃ ማፍራትና ይህንኑ በቀጣይነት እያሻሻሉ የሚኬድበት ሥርዓት ይዘረጋል፡፡ የኮንስትራክሽን
ቴክኖሎጂ ልማት መረጃ ማዕከል በማደራጀት ቴክኖሎጂ የማባዛት/ማራባት እንዲሁም የጥናትና
ምርምር ውጤቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ተሳታፊ የሚሆኑ ተዋናዮች
ለኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ልማት ዕድገት አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ይደረጋል፡፡

ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

1) የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዪት እንዲጠናከር በማድረግና ከኢንዱስትሪው ጋር


የሚኖረውን ትስስር በማጐልበት የፕሮጀክት ማኔጅመንት ልህቀት ማዕከል እንዲሆን በማድረግ እና
የዓለም አቀፍ ምርጥ አሠራሮችንና ልምዶችን መሠረት በማድረግ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች
በጊዜ፣ በዋጋና በጥራት ውጤታማ አፈጻጸም የፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮፌሽናል አቅም በመገንባት፣
2) በግንባታ ጥራት መቆጣጠሪያ ማዕከላት አቅም ግንባታ ረገድ፡-
i) የዘመናዊ የላቦራቶሪ መቆጣጠሪያ ቁሳቁሶች በግዥ በማሟላት፣
ii) የስራ ላይ እና የውጭ ሃገር ስልጠናዎችን በመስጠት፣
iii) ብቃት ያለው የሰው ኃይል በመለስተኛ ባለሙያነትና በፕሮፌሽናል ደረጃ ተመዝኖ፣ በዝርዝር
ታውቆና መረጃውም እንዲደራጅ በማድረግ፣

2.5 አስተማማኝ ግብዓት አቅርቦት ሠንሠለት እንዲዘረጋ ማድረግ

ሀ) ዓላማ

የኮንስትራክሽን ግብአቶች አምራቾችንና አገልግሎቶች አቅራቢዎችን በማበረታታት ዓለም አቀፍ የጥራት


ደረጃቸውን ጠብቀው በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ በማድረግ ገቢ ምርት መተካት የሚያስችል እና በሂደትም

39
ለውጭ ገበያ የሚሆን አቅም እንዲፈጠር እና የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ፣ በተበጀተው
ወጪና በሚፈልገው የጥራት ደረጃ ለማጠናቀቅ ግብዓት ማነቆ በማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ ነው ፡፡

ለ) ፖሊሲ

1) የሀገራችን የኮንስትራክሽን ግብዓቶች የሚገኙበት ቦታና ዕምቅ አቀማቸው በግልጽ እንዲታወቁ


በማድረግ፣ የአጭርና የረዥም ጊዜ ዕቅዶችን በማስቀመጥ የኢንዱስትሪው ዘላቂ ልማት እንዲረጋገጥ
ይደረጋል፡፡
2) የሀገር ውስጥ የኮንስትራክሽን ግብዓት የሚመረትበትና የሚቀርብበት ሠንሠለት አስተማማኝና
ቀጣይ እንዲሆን የሚያስችል ሥርዓት ለመዘርጋት ጥናት ተደርጎ ውጤቱም ይተገበራል፡፡
3) የግንባታ ዕቃዎችን በሚፈለገው መጠን፣ ዓይነትና ጥራት በሀገር ውስጥ ምርት ለማቅረብ የሚያስችል
አቅም ይፈጠራል፡፡ የተጀመሩት እንዲጠናከሩ ይደረጋል፡፡ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላቸው
ግብዓቶችን የሚያመርቱ ድርጅቶችን በመለየት በአብዛኛው የሚደገፉበት ሁኔታ ይመቻቻል፡፡ በዚህ
ሂደት በሀገር ውስጥ መተካት እስከሚቻል ድረስ የሚያስፈልጉን ግብዓቶች የጥራት ደረጃቸው
እየተረጋገጠ ከውጭ የሚገቡበት ሁኔታ ይመቻቻል፡፡
4) ከፍተኛ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ዕጥረት በሚታይባቸው የብረትና ማጠናቀቂያ የግንባታ ዕቃዎች በጋራ
ግዥ ሥርዓትና ጥብቅ የጥራት ቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡና የጥራት
ደረጃን ጠብቀው እንዲመረቱ ይደረጋል፡፡

ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

1) የኮንስትራክሽን ግብአቶችን ጥራት እና የአገልግሎት አሠጣጥ ምርታማነትን የሚያሳድግ የአቅርቦት


ሠንሠለት በማጥናትና ውጤቱን በመተግበር እንዲሁም የሀገራችን የኮንስትራክሽን ግብዓት ዕምቅ
አቅም በማጥናትና በማልማት፣
2) ለዘርፋ ልማት የሚያግዙ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶችን በመፍጠር፣

2.6 ዘመናዊና የተመቻቸ የፋይናንስና የመሣሪያዎች አቅርቦት ድጋፍ የሚሰጥበት ሥርዓት መፍጠር

ሀ) ዓላማ

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ተፈላጊ የሆኑ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና መሣሪያዎች አቅርቦት ከገበያው


ፍላጐት ጋር እንዲጣጣም ለማድረግ የሚያስችል የፋይናንስ አቅርቦት ሥርዓት በመዘርጋት የኮንስትራክሽን
ዕቅዶቻችን በተቀላጠፈ አኳኋን ለማስፈፀም ነው፡፡

40
ለ) ፖሊሲ

1) ለፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያና ፋይናንስ የፕሮጀክት ኮንትራትን መሠረት ያደረገ የባለቤት፣ ተቋራጭና


ባንክ የሶስትዮሽ የብድር አቅርቦት አሠራር ሥርዓት በባንኮች ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ የአገር ውስጥ ሥራ
ተቋራጮችና አማካሪዎች የፋይናንስ አቅም አጎልብተው የአገር ውስጥ የገበያ ፍላጎት እንዲሸፍኑ ይደረጋል፡፡
ከውጭ የምናስገባቸው መሣሪያዎች በመንግስት ላይ የሚያስከትሉትን የወጪ ጫና ለመቀነስ እና
የቁጠባ ባህል እንዲዳብር ለማድረግ የፋይናንስ አቅርቦቱን ለመካከለኛና ለትላልቆቹ እና ለጥቃቅንና
አነስተኛ ኩባንያዎች ከባንክ የብድር ፖሊሲ ጋር በማስተሳሰር እንዲሰራ ይደረጋል፡፡
2) የፕሮጀክት ሥራ አፈፃፀም ዋስትና አሠጣጥ ሥርዓት ወጥ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
3) በሥራ ላይ የሚገኙት የኮንስትራክሽን መሣሪያና ማሽነሪ አከራይ ድርጅቶች አቅማቸው እንዲያድግና
ፍትሀዊ የግብይት ሥርዓት እንዲፈጠር ይደረጋል፡፡ ባለሀብቶችና አቅም ያላቸው ተቋማት ያላቸውን መሣሪያ
ወይም አዳዲስ በማስመጣት ለኪራይ አገልግሎት እንዲያውሉ የመሣሪያ አቅርቦት ሊዝ ሥርዓቱ ተጠናክሮ
ይቀጥላል፡፡
4) በባንኮችና ለዚሁ ሥራ በተደራጁ የፋይናንስ ተቋማት አማካይነት ደግሞ የፋይናሻል ሊዝ ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
ይህም ተበዳሪው የሚከፍለው መደበኛ ክፍያ ሲያጠናቅቅ መሣሪያውን የራሱ የሚያደርግበት ሥርዓት ይሆናል፡፡
5) የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን በሃገር አቅም ደረጃ በደረጃ ለመስራት የሚያስችል የፋይናንስ፣ የሰው ኃይልና
የግብዓት አቅርቦት ይመቻቻል፡፡ የድህረ ሽያጭ አገልግሎትን እና የጥገና ማዕከላት ማስፋፋትን ጨምሮ
ለምናደርገው ግዥ የሚመጥን የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አቅም እርሾ ሆኖ ያገለግላል፡፡
6) ከኮንስትራክሽን መሣሪያዎች አቅርቦት ጋር የተያያዙት ችግሮቻችን ያሉንን በአግባቡ መጠቀም
ካለመቻል የሚጀምር በመሆኑ የመሣሪያ አንቀሳቃሾች በሥልጠና እና በምዘና ሥርዓት እንዲያልፉ
ይደረጋል፡፡
7) ከባድ እና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ከሚጠይቁ መሣሪያዎች ጎን ለጎን መካከለኛ እና ቀላል የኮንስትራክሽን
መሣሪያዎችን በመጠቀም መጀመር ስለሚገባን የመካከለኛና ቀላል መሳሪያዎች እና የተመጣጠነ
የጉልበት አጠቃቀም እንዲበረታታ ማስቻል፤ ለዚህም በብቃት ማረጋገጫ መስፈርቶቻችን ውስጥ
መካከለኛ መሣሪያዎች በአቻ ግምት እንዲካተቱ በማድረግ በቀጣይ መሣሪያዎቹ ደረጃ በደረጃ በአገር
ውስጥ እንዲመረቱ ይደረጋል፡፡
8) አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በመሳሪያዎች እና ሌሎች የመገልገያ ቁሳቁስ ግዥ ወቅትም ማሳተፍ እና
የሚገዙት መሳሪያዎች እና ቁሳቁሶች ጥራት፣ በቂ የመለዋወጫ እና የድህረ ሽያጭ አገልግሎት
እንዲኖር ይደረጋል፡፡

ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

1) ለሀገራዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት የግሉ ዘርፍ እና መንግስት በጣምራና በተናጠል የመሣሪያ
ሊዝ ኩባንያ አቋቁመው ግልጽነት፣ ተጠያቂነት እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸውን
አቅም በመገንባት እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራይ ድርጅቶች እንዲስፋፋ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር
እና በመደገፍ፣

41
2) የኮንስትራክሽን ኮንትራት ማስፈጸሚያ ፋይናንስና ኢንሹራንስ አቅርቦት ሥርዓቱን የተቀላጠፈ
በማድረግ፣
3) የኮንስትራክሽን ኮንትራት ማስፈጸሚያ ዋስትና አጠቃቀም፣ ብድርና የድጋፍ አጠቃቀም ፍትሃዊ
መሆኑን በማረጋገጥና የግሉን ዘርፍና የመንግሥትን አጋርነት የሚያጠናክሩ አዳዲስና የተለያዩ
የፕሮጀክት ቀረፃ አማራጮችንና አሠራሮችን በማስተዋወቅ፣
4) በተለያዩ የኮንስትራክሽን ሥራዎች፤ በግንባታና በጥገና ሥራ ፋይናንስ ፍላጎት የመንግስትና የግሉን ዘርፍ
አጋርነት በማጠናከርና በጥገና ላይ የተሰማሩ አካላት በየጊዜው አቅማቸውንና ደረጃቸውን እንዲያሳድጉ
የብድር ሥርዓት በማመቻቸት፤
5) በሃገር አቅም በመስራት የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን የመተካት አቅጣጫ ተግባራዊ ለማድረግ
የሚያስችል የፋይናንስ፣ የሰው ኃይል፣ የግብዓት አቅርቦትና የገበያ ዕድል በመፍጠር፣
6) በዓለም የታወቁ መሣሪያ አምራቾች ለሀገራችን ገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ ማበረታቻ
በመስጠትና ለመለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ ብድር በማቅረብ፣
7) የመሣሪያና ማሽን አጠቃቀም የቴክኒክና አስተዳደር ክህሎትና ብቃት ለማሳደግ የቴክኒሺያኖችን
ብቃት በምዘና በማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው ሥልጠና በመስጠት፣

2.7 የዘርፉ ባለሚናዎች ለዘርፉ የተፋጠነ ዕድገት በጋራ የሚሰሩበትን አቅጣጫ መከተል

ሀ) ዓላማ

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ተዋናዮች መካከል ውጤታማ የሆነ ቅንጅታዊ አሠራር በማጎልበት የልማት ኃይል ሆነው
እንዲንቀሳቀሱ ለማስቻል ነው ፡፡

ለ) ፖሊሲ

1) የመንግስትንና የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ አጋርነት በማጠናከር ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ


አስፈጻሚዎችና ተዋናዮች የስነ ምግባር ደንብ በማዘጋጀት፣ በኢንዱስትሪው የተደራጁ የሙያ
ማኀበራት ለዘርፉ ሊያበረክቱ የሚችሉትን አስተዋጽኦ እንዲያሳድጉ የማስፈፀም አቅም ግንባታ
ፕሮጀክት ተነድፎ ሰፊ ስልጠና በተከታታይ ይሰጣል፡፡
2) ዕቅዶቻችንን የጋራ ለማድረግ እና ትግበራውም የባለድርሻ አካላትን በአግባቡ ባሳተፈ መልኩ
እየተፈጸመ መሆኑን ለመከታተል እንዲቻል የመንግስትን አወቃቀር እና አሰራር ከግምት ውስጥ ያስገባ
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ምክር ቤቱ የማማከር ኃላፊነቱን የሚወጣበት ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
3) የሙያ ማህበራት የላቀ ተሞክሮ ካላቸው የውጭ የሙያ ማህበራት የክህሎት ሽግግር የሚያደርጉበት ሁኔታ
ይመቻቻል ፡፡
4) በኢንዱስትሪው የሚፈለገውን የግንባታ አገልግሎትና አቅርቦት በአጭርና በመካከለኛ ጊዜ ከፍላጎቱ
ጋር እየተጣጣመ መሄዱ የሚረጋገጥበት፣ በአቅራቢዎችና ልማቱን በአቀዱት ሴክተር መሥሪያ ቤቶች
መካከል የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የተቀናጀ የዕቅድና የአፈፃፀም ቅንጅት እንዲፈጠር እና ማነቆዎቹ ተለይተው

42
የሚፈቱበት ሥርዓት ይዘረጋል፡፡ ፕሮጀክቶችም በጊዜ፣ በዋጋና በጥራት የሚፈፀሙበት ነባራዊ ሁኔታ መኖሩን
የዝንባሌ ጥናት በየዓመቱ እንዲካሄድ ይደረጋል፡፡
5) ሁሉም ባለሚናዎች በእያንዳንዱ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት በቅድመ ግንባታ፣ በግንባታ እና በድህረ ግንባታ ጊዜ
የሚኖሩ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለህዝቡ በተለይ ደግሞ ለተገልጋዩ ግልጽነት በሚፈጥር መንገድ ተደራሽ
እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ሥርዓት ይዘረጋል፡፡

ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

1) በሚወጡ ህጎች ቀረፃ የሚመለከታቸውን መንግስታዊ አካላት፣ የሙያ ማህበራትንና የግሉን ዘርፍ
በማሳተፍ፤
2) ከሙያ ማህበራት ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን በማመቻቸት እና በዘርፉ
የተሻለ እንቅስቃሴ ለሚያደርጉ አደረጃጀቶች ማበረታቻና ዕውቅና እንዲያገኙ በማድረግ፤
3) ኮንስትራክሽን ሴክተር አቀፍ ኘሮግራምና የጋራ ዕቅድ አዘጋጅቶ በመተግበር እንዲሁም የጥናትና
ዲዛይን ምህንድስና ሥራዎች እና የግንባታ ሥራዎች አፈፃፀም የሚመራበት ስታንዳርዳይዝድ የሆነ
የውለታ አሠራር በመተግበር፣
4) መረጃ የሚደራጅበትና ተደራሽ የሚደረግበት ወጥ የሆነ አሠራርና ደረጃ አዘጋጅቶ አቅም ፈጥሮና
ተግባብቶ ስራ ላይ ለማዋል ካልሆነም የተጠያቂነት ሥርዓቱን በማስፈጸም የመረጃ አቅርቦት
ሥርዓቱን እውን ማድረግ፡፡

2.8 የባለሙያዎች፣ የኩባኒያዎች፣የህንፃ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥርና መጠቀሚያ ፈቃድ አገልግሎት


አሰጣጥ ሥርዓት ማጠናከር

ሀ) ዓላማ

የባለሙያዎች፣ የኩባኒያዎች፣ የህንፃ ዲዛይን፣ ግንባታና ፍቃድና አጠቃቀም ሥርዓት በማዘመን የህዝብ
ጤንነትና ደህንነት እንዲጠበቅና የግንባታ ሂደት ፈጣን፣ ውጤታማ እና ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል
ነው፡፡

ለ) ፖሊሲ

1) የህንፃ ግንባታ ሥራዎችን የግንባታ ፈቃድ፣ የግንባታ ቁጥጥር እና የመጠቀሚያ ፈቃድ አሠጣጥ
ሥርዓት በሕጉ መሠረት በተሟላ መንገድ እንዲተገበር እና እንዲጠናከር ይደረጋል፡፡ የተጠያቂነት
ሥርዓቱም ተግባራዊ ይሆናል፡፡
2) በህንፃ ግንባታ የሚሣተፉ ባለሙያዎች፣ ተቋራጮችና አማካሪዎች አቅም ግንባታ ሥራ ይሠራል፡፡
3) በከተሞች ያሉ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፈፃሚ አደረጃጀቶች በሠው ኃይል፣ በአሠራር እና በግብዓት
አቅርቦት በተደራጀ መንገድ በማጠናከር ስታንዳርዳይዝ ይደረጋሉ፡፡ የህንፃ ኮድ አተገባበር ምርጥ
ተሞክሮም ተቀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

43
4) የህንፃ ኮድ ተግባራዊ ለማድረግ አጋዥ የሆኑ ስታንዳርዶችን በማዘጋጀት ሥራ ላይ እንዲውሉ
ይደረጋል፡፡ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ዘመናዊ አገልግሎት መስጫና ደጋፊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
በተጠናከረ መልኩ ይተገበራል፡፡
5) የህንፃ ግንባታ ዲዛይኖቻችን ለአካል ጉዳተኛ ተደራሽ መሆናቸው ይረጋገጣል፡፡
6) በህንጻ ግንባታ ብቃት ያለው አመራር ለመስጠት ከሚያስችሉ የአሰራር ሥርዓቶች /ከዲዛይን፣
ከቁጥጥር እና ፕሮጀክት አስተዳደር/ ጋር ተያይዞ ያሉትን ክፍተቶች በመፈተሽ እንዲስተካከሉ
ይደረጋል፡፡ የህንጻ ግንባታዎች አፈፃፀም መሠረታዊ የሆኑትን ዲዛይንና ግንባታ ጊዜ አጠቃቀም ልዩ
ትኩረት በመስጠት የጥራት ቁጥጥር ስርዓት ይዘረጋል፡፡

ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

1) የህንፃ አዋጁ ተግባራዊ በሚደረግባቸው ከተሞች አፈፃፀሙን ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው አሠራር መገንባቱን
በማረጋገጥ፤ በጥብቅ ክትትል ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ እና የህንፃ አዋጅ ትግበራ አፈፃፀም ዝርዝር
ኢንስፔክሽን በማድረግ የአዋጁ ጥሰት በሚታይባቸው ከተሞች አስተማሪ የሆኑ የተጠያቂነት እርምጃዎች
በመውሰድ፣
2) የግንባታ ስራዎቻችን ዕድገት እያሳዩ ከመሄድ ጋር ተከትሎ የመጣውን የግንባታ ዋጋ ንረት፣ የጥራትና
ያልተስተካከለ የማጠናቀቂያ ጊዜን መቆጣጠር የሚያስችል አሰራር በመፍጠር፣

2.9 የፈርጀ ብዙ ሥራዎች ተጣጥመው የሚታቀዱበትና የሚተገበሩበት ሥርዓት መዘርጋት

2.9.1 የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ

ሀ) ዓላማ

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ልማትና ዕድገት የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግ ተጠቃሚነታቸውን


ለማረጋገጥ እና ለሀገራችን ህዳሴ የበኩላቸውን የላቀ አስተዋፅኦ ማበርከት የሚችሉበት ሁኔታ ለማመቻቸት
ነው፡፡

ለ) ፖሊሲ

1) መንግስትና የኢንዱስትሪው ባለድርሻዎች የሴቶችን የቴክኒክ ብቃትና ክህሎት በማሳደግ ተሳትፎአቸው


እንዲጨምር እና ከሚፈጠረው የሥራ ዕድል ሃብት እንዲያፈሩ የሚያስችል መርሃ-ግብር ወጥቶ ተግባራዊ
ይደረጋል፡፡
2) በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሴቶች ተሣትፎ በክህሎት ግንባታና የአመራር አቅም ለመፍጠር የተለየ ፕሮጀክት
ተቀርጾ ተግባራዊ የሚደረግበት ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
3) የሴቶችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በአስተዋፅኦቸው ልክ መሆኑን የሚያረጋግጥ የሥራ ሥምሪት እንዲኖር ይደረጋል፡፡

44
ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

1) በኢንዱስትሪው የሴቶችን ተሣትፎ ለማጎልበት የቅድሚያ ትኩረት በመስጠትና ተቀናጅቶ በመፈጸም፣


2) በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሴቶችን የሙያና የአመራር ተሳትፎ ለማሣደግ በልዩ ሁኔታ በመደገፍ፣

2.9.2 የኮንስትራክሽን ሠራተኞችና ሥራ አካባቢ ጤንነትና ደህንነት መጠበቅ

ሀ) ዓላማ

በሃገራችን ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሰራተኛውን ጤንነትና ደህንነት የሚጠብቁ ዘላቂ የኮንስትራክሽን ልምዶች እንዲስፋፉ
ለማድረግ ነው፡፡

ለ) ፖሊሲ

1) በኮንስትራክሽን ሥራ አካባቢ በሰዎች ጤናና ደህንነት ላይ አደጋ የማይጥሉ የመሳሪያዎች


እንቅስቃሴና ሥራ አካባቢ እንዲፈጠር ይደረጋል፡፡
2) በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ዲዛይንና ግንባታ ሂደቶች አስገዳጅ የስራ ላይ ደህንነት ማረጋገጫ
ስርዓት ይዘረጋል፡፡
3) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚሠማራውን የሰው ኃይል መብት፣ ግዴታ እና ጥቅም ለመጠበቅና
ለማስጠበቅ የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
4) በኮንስትራክሽን ወቅት የሚለቀቁ መርዛማ ውህዶች (ለምሳሌ ሙቀት፣ ጨረር፣ ድምፅ፣ ተረፈ-ምርት፣ የመሬት
መንቀጥቀጥ) ቁጥጥር ይደረጋል፡፡
ሐ) የማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች

1) የሥራ ላይ ጤንነትና ደህንነት ቁጥጥር ሥርዓት አስገዳጅ እንዲሆን የሚያደርግ እና የደህንነት መጠበቂያ
አልባሳትንና መሣሪያዎች አቅርቦት እንዲቀላጠፍ የሚያስገድድ የግንባታ አካባቢ ስራተኞችን ጤንነትና
ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ አዘጋጅቶ በመተግበር፣
2) ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተቀናጅቶ በጋራ በመስራት፣
3) በግንባታ ላይ የሚሰማሩ ሰራተኞች የደህንነት መጠበቂያ አልባሳትና መሣሪያዎች አስፈላጊነትን
በተመለከተ ግንዛቤ እንዲያገኙ ስልጠና በመስጠት ይሆናል፡፡

2.9.3 የኢንዱስትሪው በአካባቢ ደህንነት ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ መቀነስና መከላከል

ሀ) ዓላማ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የልማት አቅጣጫ ለአካባቢ ጥበቃ ሚዛናዊ ትኩረት የሰጠ እንዲሆን ለማድረግ ነው፡፡

45
ለ) ፖሊሲ

1) በኮንስትራክሽን ግንባታ ሂደት ፈንጂና ተቀጽላዎች፣ ጎጂ ጨረር አመንጪ የሆኑ የግብዓት ተረፈ
ምርቶች፣ ለአየር ብክለት መንስኤ የሆኑ የተሽከርካሪና የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ጭስ እንዲሁም
ሌሎች ኬሚካሎች በአካባቢ ላይ የሚያደርሱትን የጉዳት ደረጃ ክትትል በማድረግ ተቀባይነት ባለው
ደረጃ መሆኑ ይረጋገጣል፡፡
2) የደን መራቆት ለአየር ንብረት መዛባትና ለግድቦች በደለል መሞላት መንስኤ መሆኑን በመገንዘብ
አረንጓዴ ልማት እንዲከናወን ይደረጋል፡፡
3) የሲሚንቶ ኖራ ልማት እና የአስፋልት ግብዓቶችና ምርቶቻቸው በአየር ላይ የሚያደርሱትን ብክለት
የመቀነስ አሠራር ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
4) በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ልማት ለተፈጥሮ አካባቢ ደህንነት በተለይ ለካባ ጣቢያዎች ተገቢው
ትኩረት የሚሰጥ አሰራር ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ድንጋይ፣ ጠጠርና አሸዋ ለማምረት የሚቆፈሩ
አካባቢዎች እንዲሁም ረግረጋማ ቦታዎች መልሰው የሚለሙበት አሠራር ይዘረጋል፡፡ ኮንስትራክሽን ነክ
ጥናቶችና ኮንስትራክሽን ሂደቶች በተፈጥሮ ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት የሚቀንስ የአሰራር ዘዴ
ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
5) ግዙፍ የመሰረተ ልማትና የኢንዱስትሪ ልማት ፕሮጀክቶች ሲወጠኑ የአካባቢ እና ስትራቴጅክ ተጽዕኖ
ግምገማ እንዲካሄድላቸው ይደረጋል፡፡
ሐ) የማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች

1) ከአካባቢ እና የደን ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት የሚሰራበትን አሰራር በመፍጠር፣


2) የግንባታ ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ አካባቢ ተጽዕኖ ሁኔታ ጥናት በማድረግ፣ ሕግ በማውጣትና በአፈጻጸሙ ላይ
የኢንስፔክሽን ስርዓት እንዲኖር በማድረግ፣

2.9.4 የስራ ዕድል ፈጠራን በማሳደግ ድህነትን መዋጋት

ሀ) ዓላማ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሚፈጥረውን የሥራ ዕድል በመጠቀም ዜጎች ከድህነት እንዲላቀቁ ለማድረግ እና
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ዋጋ፣ ጊዜና ጥራት ተጠናቀው ፈጣን ልማታችን ቀጣይ እንዲሆን ለማድረግ
ነው፡፡

ለ) ፖሊሲ

1) በኮንስትራክሽን ዘርፍ ልማት ፕሮግራሞች ጉልበት ተኮር ሥራዎች እንዲሠፉ መለስተኛ ክህሎት
እንዲኖራቸው በማድረግ ሠፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ይደረጋል፡፡
2) ከአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ጋር የንዑስ-ሥራ ተቋራጭነት ትስስር የሚፈጠርበትና አሠራሩ ተጠናክሮ
እንዲቀጥል የሚያስችል የማበረታቻ ሥርዓት ተጠንቶ ይተገበራል፡፡

46
ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

1) የግልና የመንግስት ተቋማት ኮንስትራክሽን ነክ በሆኑ ሥራዎች ላይ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና ሂደቱን
ለማበረታታት ጠንካራ ትብብርና ቅንጅት በመፍጠር ምርታማነቱን የሚያሳድግ አሠራር በመዘርጋት፣
2) በህዝብ ተሣትፎና ጉልበት ለሚሠሩ የኮንስትራክሽን ልማት ሥራዎች የግሉ ዘርፍና መንግስት
ለአማካሪዎች፣ ተቋራጮችና ባለቤቶች የቴክኒክና አመራር ክህሎት ሽግግር በማድረግ፣
3) በጉልበት ተኮርና ጉልበት በስፋት በሚጠቀሙ ፕሮጀክቶች የአማካሪ፣ የስራ ተቋራጮች እንዲሁም
የባለቤቶችን አቅም ለመገንባት የቴክኒክና የአስተዳደር ብቃት ዕውቀት፣ የአሠራርና አደረጃጀት
እንዲሁም የክትትልና ቁጥጥር ስታንዳርዶች አዘጋጅቶ በመተግበር፣ ምርጥ ተሞክሮም ቀምሮ
በማስፋፋት፣
4) ጉልበት ተኮር እና ህብረተስብ ተኮር የኮንስትራክሽን ሥራዎች አመራርና አስተዳደር እንዲሁም
ተጠቃሚነት ግንዛቤ በመፍጠር ፡፡

2.9.5 በኮንስትራክሽን ፕሮጄክት ሰራተኞችና በአካባቢው ማህበረሰብ የሚደርሰውን የ HIV/AIDS፣ ኮቪድ ስርጭት
ጉዳት መቀነስና መከላከል

ሀ) ዓላማ

በግንባታ ተሳታፊ የሆኑ ሰራተኞችና በስፍራው የሚገኙ ዜጎች ስለ HIV/AIDS በቂ እውቀት ኖሯቸው
በቫይረሱ እንዳይጠቁ የ HIV/AIDS መመሪያን መሠረት ባደረገ አኳኋን ግንዛቤ በመፍጠር እራሳቸውንና
ሌላውን እንዲከላከሉ ለማድረግ ነው፡፡

ለ) ፖሊሲ

1) አሰሪዎች የብሄራዊ HIV/AIDS ምክር ቤት በሚደነግገው መሰረት ለሰራተኛውና በግንባታው ተጽዕኖ


ክልል ውስጥ ለሚኖሩ የአካባቢ ማህበረሰብ አካላት በቂ ግንዛቤ እንዲፈጥሩና የኮንዶም ተደራሽነትን
እንዲያረጋግጡ ይደረጋል፡፡
2) ስለ HIV/AIDS ግንዛቤ ከመፍጠር አንጻር አብዛኛው ሰራተኛ በሚግባባበት ቋንቋ ተዘጋጅቶ በ A1 መጠን
የተዘጋጁ ፖስተሮች የግንባታ ሰራተኞች በሚንቀሳቀሱበት ስፍራ እንዲለጠፍ ይደረጋል፡፡
3) ሰራተኛው በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የ HIV/AIDS ምርመራ እንዲያደርግ ይበረታታል፡፡
4) በቫይረሱ የተያዙ በቂ የሆነ የምክር እና የመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት፣ እንክብካቤና ድጋፍ ማግኘታቸው
ይረጋገጣል፡፡

ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

47
1) በ HIV/AIDS ዙሪያ ያለው ግንዛቤ በስልጠና፣ ፖስተሮችና በራሪ ወረቀቶች አማካኝነት እንዲዳብር
በማድረግ፣
2) ለግንባታ ሰራተኞች ኮንዶም በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆን በማስቻል፣
3) የ HIV/AIDS ምክር፣ ምርመራና የመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት በግንባታ ጣቢያዎች እንዲኖር
ምቹ ሁኔታ በመፍጠር፡፡

2.9.6 የህንፃና መሰረተ ልማት ግንባታ ሂደትና ዲዛይን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ፣

ሀ) ዓላማ

በሀገራችን የሚገነቡ ህንጻዎችና መሰረተ ልማቶች ለሁሉም ዜጎች በተለይ ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ መሆናቸውን፣ ፍትሃዊ
ተጠቃሚነታቸውን እና ተሳትፎአቸውን በማረጋገጥ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ
ለመገንባት ነው፡፡

ለ) ፖሊሲ

5) በሀገራችን የሚገነቡ ህንጻዎችና የመሰረተ ልማቶች ዲዛይኖች እና ግንባታዎች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲሆን
ይደረጋል፡፡
6) በአገልግሎት ላይ ያሉ ነባር የህዝብ አገልግሎት ተቋማቶችና መሰረተ ልማቶች በጥገና ወቅት ለአካል ጉዳተኞች
ምቾትና ደህንነት ታሳቢ ያደረጉ እነዲሆኑ ጥረት ይደረጋል፡፡

ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

4) የሚዘጋጁ የዲዛይን ጥናቶች እና ግንባታዎች ለአካል ጉዳተኞችና ለሌላው ዜጋ እኩል አገልግሎት የሚሰጡበት
የዲዛይን አዘገጃጀት ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ በማድረግ፣
5) ለህዝብ መገልገያ ተቋማቶችና መሰረተ ልማት ግንባታ ዲዛይኖችና ግንባታዎች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ
እንዲሆኑ አስገዳጅ ዲዛይን ስታንዳርድ በመተግበር፣
6) ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ዲዛይን (accessible design) እንዲሁም ሁሉን አቀፍ ዲዛይን ( universal
design ) አጣምሮ ተግባራዊ በማድረግ፣

5.10 የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ስራዎች ማስፈፀሚያ ዝርዝር የፕሮግራምና የህግ ማዕቀፍ


ወይም ፓኬጅ በመንግስት በማፅደቅ ተግባራዊ ማድረግ

ሀ ዓላማ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በሥርዓት እንዲመራ፣ ሥርዓቶችን በአግባቡ ለመተግበር እንዲበቃ በማድረግ ላይ


የተመሠረተና ኢንዱስትሪው ፈጣን ዕድገት ለማምጣት የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት ለመፍጠር ነው፡፡

48
ለ ፖሊሲ

1) በሀገሪቱ ኮንስትራክሽን የምቾት፣ የደህንነትና የጤና አጠባበቅ ሂደቶች፤ የኮንስትራክሽን ጨረታ፣ ውለታ፣ ዋስትና፣
ግጭት አፈታትና ይግባኝ ሥርዓቶች እንዲሁም በውስጡ የሚሳተፉ አካላት የሚመሩበት የዲዛይን፣ የግንባታ፣
የምክር፣ የቁጥጥር እና የማኔጅመንት ሁኔታዎችን የያዘ የተሟላና ሁሉን አቀፍ የኮንስትራክሽን የህግ ማዕቀፍ
ተዘጋጅቶ ስራ ላይ እንዲውል ይደረጋል፡፡
2) ለመንገድ፣ ለህንጻ፣ ለመስኖ፣ ለመጠጥ ውሃ ቁፋሮ፣ ለኃይል ማመንጫና ለባቡር መሠረተ ልማት ዲዛይኖችና
ግንባታዎች ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ የአሰራር ማንዋሎች እና ስታንዳርዶች እንዲዘጋጁ፣ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት
እንዲዳረሱና ተግባራዊነታቸው እንዲረጋግጥ የሚያደርግ ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
3) በጥናትና ምርምር የሚገኙ አዳዲስና የተሻሻሉ አማራጭ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችና የአገነባብ ዘዴዎች ስታንዳርድ
እንዲወጣላቸውና ለምናዘጋጃቸው ህጎች ግብዓት ሆነው እንዲያገለግሉ ይደረጋል፡፡
4) የአማካሪና ሥራ ተቋራጭ ድርጅቶች ለሠሯቸው ሥራዎች ተጠያቂ የሚሆኑባቸው የህግ አግባቦች ቢኖሩም ከዚህ
አንፃር ለፕሮጀክት በተያዘበት ጊዜ እና ወጪ መጠናቀቅ እንዲተጉ የሚያደርግ የአሠራር ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
5) የሥራ ተቋራጮችን አቅም ለመገንባት ፕሮጀክቶችን በንኡስ በንኡስ በመክፈል ወደ አብዛኛው ሥራ ተቋራጭ
አቅም ማምጣት እና የመግቢያ መስፈርቶችን ለማመጣጠን የሚያስችል የተቋራጮች ምዝገባ ህግ ይዘጋጃል፡፡
6) የፕሮጀክቶቹን አጣዳፊነት፣ ልዩ ባህሪያት እና የአገር በቀሉን አቅም መገንባትን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በመያዝ
ለአቅም ግንባታ የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን በመለየት፣ በውጭ ሀገር ሥራ ተቋራጮች እና አገር በቀል ሥራ ተቋራጮች
መካከል፣ በአገር በቀል ሥራ ተቋራጮችም መካከል እርስ በእርስ የንኡስ ስራ ተቋራጭነት አሰራር እንዲኖር
ይደረጋል፡፡
7) የእሽሙር (joint venture) አሰራርን ጨምሮ ሌሎች ከኮንስትራክሽን ጋር ተያያዥነት ያላቸውን አሰራሮች እና
ህጎች በመከለስ ማስተካከያዎች ይደረጋሉ፡፡
8) የሥራ ተቋራጮችን የገንዘብ ፍሰት ችግር ለማቃለል መተዋወቅ ያለበት አሰራር በአሰሪ፣ በተቋራጭ እና
በፋይናንስ ተቋማት መካከል የብድር አሰጣጥ እና የአመላለስ የሶስትዮሽ ስምምነት አሰራር ለጥቃቅን እና አነስተኛ
ተቋማት አቅም ግንባታ በሰፊው የምንጠቀመው እና ውጤት ያስገኘ አሰራር እንደመሆኑ ለመካከለኛ እና ከፍተኛ
ሥራ ተቋራጮችም በሚመጥን መልኩ ተቀርፆ ስራ ላይ ይውላል፡፡
9) አንድ ተቋራጭ ሊይዘው የሚገባው የፕሮጀክት መጠን ካለው አቅም ጋር እንዲመጣጠን በማድረግ ያልተመጣጠኑ
ፕሮጀክቶችን ከመያዝ ጋር የተገናኙ የአፈፃፀም ችግሮች ለመቀነስ፣ የአገራችን ሥራ ተቋራጮች ዓመታዊ የሥራ
አፈጻጸማቸው (annual turnover) ለማሻሻል ትላልቅ እና በርካታ ፕሮጀክቶችን እንዲያገኙ በማድረግ አካሄዱም
ከድርጅቶቹ ውስጣዊ ጥንካሬ እና ከተመጣጠነ ውድድር ጋር እንዲሆን ይደረጋል፡፡
10) የኮንስትራክሽን ሥራዎች በጥራት፣ በጊዜ፣ በወጪ፣ በምቾት እና በደህንነት በላቀ ደረጃ የሚያስጠብቅና
በሚፈለገው ደረጃ መፈፀማቸውን የሚያረጋግጥ የቁጥጥር ሥርዓት ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ ይውላል፡፡
11) የአማካሪዎች የአገልግሎት ክፍያ በውጤትና የፕሮጀክት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

ሐ) የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች

1) በኢንዱስትሪው የሚያስፈልጉ የሬጉላቶሪ ኮዶችና ስታንዳርዶችን በመዘርዝር፣ ከሚመለከታቸው


አካላት ጋር ማሰባሰብ፣ በየዲሲፕሊኑ በመከፋፈልና እንዳስፈላጊነታቸው በቅደም ተከተል

49
በማስቀመጥ የዘርፉንና የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርን የጋራ ዕቅድ አዘጋጅቶ
በመምራት፤
2) የኮንስትራክሽን ማቴሪያል ምርምር ሥራ በስፋት በመስራት ፡-
i) የየንዑስ ዘርፉን ማኔጅሜንት ብቃት በማሳደግ፣
ii) በንዑስ ዘርፉ ዕቅዶች ከዲዛይን አገልግሎት ዘመን ጋር ያላቸውን ቁርኝት በማየት በጥገና፣
በክብካቤና አጠቃቀም እንዲሁም ማሻሻል ላይ የተመሰረተ አቅጣጫ እንዲከተሉ የማስቻል
አቅምን በመገንባት፣
iii) በስራ ሂደት የተለዩ የውጭ ሃገር ተሞክሮዎችን በመቀመር በሃገር ውስጥ የመተካት አቅጣጫ
በመከተል አቅም መገንባት፣
3) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ፋይናንሲንግና ኢንሹራንስ አቅርቦት ስትራቴጂ በማዘጋጀትና
በማስተግበር፡፡

50
ክፍል ሶስት
3 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትግበራ እና ማጠቃለያ

3.1 የፖሊሲው የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ ፖሊሲ ሀገር አቀፍ ተፈፃሚነት ያለው ሆኖ የፌዴራልና የክልል መንግስታት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ
አካላት በተናጠልና በቅንጅት ለልማታችን ወሳኝ የሆነውንና የኮንስትራክሽን ልማትን ለማፋጠን የወጣውን
ፖሊሲ በየስራ ዘርፎቻቸው በኃላፊነት መፈጸም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የኢንዱስትሪውን
ብቃትና ተወዳዳሪነት ለማፋጠን የሚቀረጸውን የአቅም ግንባታ ፕሮግራምና የሕግ ማዕቀፍ በባለቤትነት
በማስፈጸም የተቋሞቻቸውን/ የድርጅቶቻቸውን ብቃት ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡

3.2 ፖሊሲውን የሚስፈጸም ተቋምና የባለድርሻዎች ሚና

3.2.1 የፌዴራል መንግስት

1) በኮንስትራክሽን ዘርፍ ባለቤትነትና አስተባባሪነት የሚመለከታቸውን ባለሚናዎችና ባለድርሻዎች


በማሳተፍ ፖሊሲውን አቀናጅቶ ያስፈጽማል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ አስፈላጊ ሆኖ
ሲገኝ በሚኒስትሮች ም/ቤት አማካይነት ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ያደርጋል፣
2) ፖሊሲውን ለማስፈፀም የሚረዱ በፌዴራል ደረጃ መዘጋጀት ያለባቸውን ሕጎች፣ ደንቦች፣
ፕሮግራሞች፣ ስትራቴጂዎች፣ ወዘተ… የሚመለከታቸው አካላት በመቀናጀት ያዘጋጃል፣
3) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚቀረጸውን የአቅም ግንባታ ፕሮግራም
የሚመለከታቸው አካላት በባለቤትነትና ተነሳሽነት በመጠቀም ተቋሞቻቸውን ብቁና ተወዳዳሪ
የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
4) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በፖሊሲው የተጠቀሱ የማስተባበር ተግባራትን
ያከናውናል፡፡

3.2.2 የክልል መንግስታት


1) ፖሊሲው በክልላቸው እንዲፈፀም የማድረግ ኃላፊነታቸውን ይወጣሉ፣
2) ፖሊሲውን ለማስፈፀም የሚያግዙ ፕሮግራሞች፣ ሕጎችና ደንቦችን ያወጣሉ፣
3) በክልላቸው ለሚገኙና በኢንዱስትሪው ለተሰማሩ አካላት የአቅም ግንባታ ድጋፍ ይሰጣሉ፣

3.2.3 የከተሞች እና የገጠር ወረዳ አስተዳደሮች

1) ፖሊሲውን በከተሞቻቸው/በወረዳቸው ያስፈጽማሉ፣


2) በክልል መንግስታት ፀድቀው የሚወጡትን ፕሮግራሞችና ህጎች ከየከተሞቻቸው እና ከየወረዳቸው
ሁኔታ ጋር በማገናዘብ በሥራ ላይ ያውላሉ፣
3) በየከተሞቻቸው/በየወረዳቸው ለተደራጁ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት እና ለሌሎች በዘርፉ
ለተሰማሩ አካላት ሁለገብ ድጋፍ ያደርጋሉ፣

51
3.2.4 የግሉ ዘርፍ ሚና

1) ፖሊሲውን በየሥራ ዘርፎቻቸው በማስፈጸም ተቋሞቻቸውን ተወዳዳሪ ያደርጋሉ፣ ለሀገራችን


ትራንስፎርሜሽን ይተጋሉ፡፡
2) በፖሊሲው አፈፃፀም ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ከመንግስት ጋር በጋራ ይሰራሉ፣
3) ፖሊሲውን ለማስፈፀም በሚወጡ ሠነዶች ላይ አስተያየት በመስጠት ሠነዶቹን ያዳብራሉ፣
4) በየደረጃው ለሚሰሩ የአቅም ግንባታ ሥራዎች ድጋፍ ይሰጣሉ፣
5) በኢንዱስትሪው ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት አሠራር እንዲዘረጋና ሙስናና ብልሹ አሰራር
እንዳይኖር በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ሃላፊነት ይወጣሉ፣

3.2.5 የዩኒቨርስቲና የምርምር ተቋማት ሚና

1) ፖሊሲውን ለመፈፀም የሚያስችሉ የምርምርና ሥርፀት ሥራዎች ያከናውናሉ፡፡


2) ኢንዱስትሪውን ለማሳደግና ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል ከመንግስት ጋር በጋራ ይሰራሉ፣
3) በዘርፉ የተሰማሩ የትምህርትና የሥልጠና ተቋማት የሰለጠነ የሰው ኃይልን በብዛትና በዓይነት
ለማፍራት ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋሉ፣

3.3 የአፈጻጸም ስልት

ይህ ፖሊሲ በተገቢው ደረጃ ተፈፃሚ እንዲሆን የሚከተሉትን የአፈፃፀም ስልቶች መከተል ይገባል፡፡
1) ፖሊሲው በሚመለከታቸው ፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ዘንድ እንዲሰርጽና እንዲታወቅ ማድረግ፣
2) ፖሊሲውን ለማስፈፀም የሚያስችሉ ዝርዝር ፕሮግራሞች ቀርፆ ተግባራዊ ማድረግ፣
3) ፖሊሲውንና የሚቀረጹትን ፕሮግራሞች የሚፈፅም አደረጃጀት እንደአስፈላጊነቱ በየደረጃው
መፍጠር፣
4) ፖሊሲውን ለማስፈጸም በየደረጃው በሚደረግ ክትትልና ግምገማ ማረጋገጥ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም
ከግምገማው በመነሳት ውጤታማነታቸውን የሚያሳድጉ ማሻሻያዎችን ማድረግ፣
5) የፖሊሲው አፈጻጸም የሕዝቡና የተጠቃሚውን ተሳትፎና ባለቤትነት በሚያረጋግጥ አኳኋን
በማስተግበር፤

3.4 የፖሊሲ ክትትል፣የግምገማ እና የክለሳ ስርዓት

የፖሊሲዉ አጠቃላይ የአፈጻጸም ሪፖርት ከአስር አመቱ የሴክተር እቅድ ጋር በተጣጣመ መለኩ በየአመቱ በሚ /መስያ ቤቱ ሚቀርብ ይሆናል ፡፡

52
3.5 የፖሊሲው ስርጭት

ፖሊሲ እንደጸደቀ ለባለድርሻ አካለት የግንዛቤ መስጫ በድረኮች በፌደራል እና በክልል ደረጃ የሚዘጋጅ ሲሆን የፖሊሲዉም ሰነድ አሃርድ ኮፒና

በሚ/መስሪያ ቤቱ ድህረ ገጽ ላይ ተደራሽ ይደረጋል ፡፡

3.6 ፖሊሲው ተፈጻሚ የሚሆንበት ጊዜ

ፖሊሲዉ ከሴክተሩን አስር አመት እቅድ መጨረሻ ድረሽ እስከ 2022 ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን በአምስት አመቱ እንደአስፈላጊነቱ ሊከለስ ይችላል ፡፡

53

You might also like